#WolloUniversity
ወሎ ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያ፣ በሁለተኛ እና በሦስተኛ ዲግሪ ያስተማራቸውን 1113 ተማሪዎች አስመርቋል።
ከተመራቂዎቹ 5 በሦስተኛ ዲግሪ እንዲሁም 211 በሁለተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው።
@tikvahuniversity
በሦስቱም ቅርንጫፎቻችን (መገናኛ፣ ሜክሲኮ እና ጀሞ) እንዲሁም በኦንላይን በምንሰጣቸው ስልጠናዎች በ Advanced Level እና 90% Practical በሆነ ካሪኩለምና ዘመኑ ያፈራቸውን ሙሉ የስቱዲዮ እቃዎችን በማሟላት የምንሰጠውን ስልጠና ይውሰዱ።
ከሁሉም ስልጠናዎቻችን ላይ ታላቅ የዋጋ ቅናሽ አድርገናል! አሁኑኑ ይመዝገቡና ትልቅ ለውጥ ወደሚያመጡበት ተቋም ይቀላቀሉ!
ከትምህርትና ስልጠና ጥራትና ቁጥጥር ባለስልጣን ሙሉ ዕውቅና ካለው ሰርተፊኬት ጋር! የብዙ ዓመት ልምድና ብቃት ባላቸው አሰልጣኞች!
🎯 Graphics Design
🎯 Video Editing
🎯 Digital Marketing
🎯 Photography
🎯 Videography
🎯 Cinematography
🎯 Adobe photoshop
🎯 Fullstack Webapp Development
🎯 Programming Language
🎯 Interior Design
🎯 English Language
🎯 Database
🎯 Basic Computer
🎯 Accounting Softwares
🎯 Engineering Softwares
🎯 SPSS & STATA
🎯 MS-Project
🎯 Foreign & Local Languages
አድራሻ
1. መገናኛ መተባበር ህንጻ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁ. 419 (ሊፍት ይጠቀሙ) ☎️ 0991929303
2. ሜክሲኮ ኬኬር ህንጻ 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁ. 639 (ሊፍት ይጠቀሙ) ☎️ 0991929304
3. ጀሞ 1 አንደኛ በር ካኩ ቢዝነስ ሴንተር 3ኛ ፎቅ ☎️ 0991926707
Telegram: /channel/topinstitutes
TikTok: topinstitute" rel="nofollow">https://Tiktok.com/@topinstitute
Facebook: https://www.facebook.com/Topinstitutes
42 A+ ያመጣው ተመራቂ
ደሲ መሀመድ ይባላል። በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በኬሚካል ኢንጂነሪንግ ትምህርት ክፍል እጅግ ከፍተኛ ውጤት በማምጣት የሜዳሊያ እና የዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል።
ቤተሰቦቹ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ቢሆንም የሚችሉትን ያህል ደግፈውታል። ወደ ዩኒቨርሲቲ ከገባ በኋላ ጎን ከትምህርቱ ጎን ለጎን ልጆችን በማስጠናት በሚያገኘው ገቢ ራሱን ደጉሟል። ከሚያስጠናቸው ልጆች ቤተሰብ ጋርም የጠበቀ ወዳጅነት መፍጠሩን ተናግሯል።
ደሲ አጠቃላይ ውጤት (CGPA) 3.94 ከፍተኛ ውጤት በማምጣት የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የ2017 ዓ.ም የማዕረግ ተመራቂ ሆኗል።
ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች በመጀመሪያ እና ሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራም ያስተማራቸውን 596 ተማሪዎች አስመርቋል።
@tikvahuniversity
#DillaUniversity
#ClassOf2025
#CommencementPhotos
ዲላ ዩኒቨርሲቲ የመውጫ ፈተና ከወሰዱ የ2017 ዓ.ም የቅድመ-ምረቃ አጠቃላይ ተማሪዎች ውስጥ ከ75 በመቶ በላይ የሚሆኑት ማለፋቸውን ገልጿል።
ዩኒቨርሲቲው በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን 1,576 ተማሪዎች አስመርቋል። ከተመራቂዎቹ ሁለት ተማሪዎች በሦስተኛ ዲግሪ እና 100 ተማሪዎች በሁለተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ናቸው።
በመጀመሪያ ዲግሪ ከተመራቂ ተማሪዎች መካከል የማኔጅመንት ትምህርት ክፍል ምሩቅ የሆነው ዳንኤል ግርማ አጠቃላይ ውጤት (CGPA) 3.96 በማምጣት የዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል።
@tikvahuniversity
#JimmaUniversity
#ClassOf2025 #CommencementPhotos
ጅማ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 3,045 የቅድመ እና የድኅረ-ምረቃ ተማሪዎች ዛሬ አስመርቋል። ከተመራቂዎቹ 61 በሦስተኛ ዲግሪ፣ 992 በሁለተኛ ዲግሪ እንዲሁም ሁለት ተማሪዎች በሰብ ስፔሻሊስት ፕሮግራም ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው።
@tikvahuniversity
ሁለት የወርቅ ሜዳሊያዎች እና የዋንጫ ተሸላሚዋ
ፌቨን ጉርጁ አውግቸው በ2017 ዓ.ም ከባህርዳር ዩኒቨርሲቲ አጠቃላይ የመጀመሪያ ዲግሪ ተመራቂዎች እጅግ ከፍተኛውን ውጤት በማምጣት ሁለት የወርቅ ሜዳሊያዎች እና የዋንጫ ተሸላሚ ሆናለች፡፡
የሳይበር ደህንነት የትምህርት መስክ ተማሪዋ ፌቨን፤ አጠቃላይ ውጤት (CGPA) 4.00 በማምጣት ከትምህርት ክፍሏ፣ ከፋኩልቲዋ፣ ከኮሌጇ እንዲሁም ከአጠቃላይ የዩኒቨርሲቲው ተመራቂዎች ከፍተኛ የሆነውን ውጤት አስመዝግባለች፡፡
ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ በዛሬው ዕለት ከ6 ሺህ በላይ ተማሪዎች ያስመረቀ ሲሆን፤ ከተመራቂዎቹ መካከል 111ዱ የሦስተኛ ዲግሪ (PhD) ተመራቂዎች ናቸው፡፡ ዩኒቨርሲቲው በሳይበር ደህንነት የትምህርት መስክ ለመጀመሪያ ጊዜ ተማሪዎችን አስመርቋል፡፡
@tikvahuniversity
የሁለት ወር የክረምት ስልጠና
25% ቅናሽ እስከ ሰኔ 21/2017 ዓ.ም.
የቤት እና የቢሮ ዕቃዎች ጥገና ስልጠና በፒያሣ እና በመገናኛ ካምፓስ ምዝገባ ላይ ነን።
👉 ፍሪጅ፣ ስቶቭ፣ ስማርት ቴሌቪዥን፣ ኦቭን እና ሌሎች የቤት ዕቃዎች ጥገና በተግባር በአንድ ላይ አካቶ የሚሰጥ
👉 የኮፒ ማሽን፣ ፕሪንተር እና ሌሎችም የቢሮ ዕቃዎች ጥገናን አካቶ የሚሰጥ
👉 በሁለት ወር ስልጠና የራስዎን ሥራ ለመስራት የሚያስችልዎት
👉 ስልጠናው ሰኔ 30/2017 ዓ.ም ይጀመራል።
☎️ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ
ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ
ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ
Instagram: https://www.instagram.com/sage_training_institute/
Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
#WolloUniversity
ወሎ ዩኒቨርሲቲ በእፅዋት ሳይንስ እና ብዘሀ-ህይወት ጥበቃ የ3ኛ ዲግሪ ትምህርት መስጠት ሊጀምር ነው።
ዩኒቨርሲቲው በትምህርት መስኩ የሦስተኛ ዲግሪ (ፒኤች.ዲ.) ፕሮግራም ለመክፈት የስርዓተ ትምህርት የውስጥ እና የውጭ ግምገማዎች አካሒዷል።
ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ ከሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ እና ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የተጋበዙ ምሁራን በውጭ የስርዓተ ትምህርት ግምገማው ላይ ተሳተፈዋል።
ወሎ ዩኒቨርሲቲ የሚገኝበት አካባቢ የበርካታ ብዘሀ-ህይወት እና ተፈጥሮ ሀብት መገኛ መሆኑ ፕሮግራሙን ለመከፈት ምክንያት እንደሆ ተገልጿል።
@tikvahuniversity
#BahirDarUniversity
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በ Cyber Security እንዲሁም በ Data Science ትምህርት ክፍሎች ትምህርታቸውን የተከታተሉ ተማሪዎችን ለመጀመሪያ ጊዜ ነገ ያስመርቃል።
በሁለቱም የትምህርት መስኮች ተማሪዎች ሲመረቁ በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደሆነ ነው የተገለፀው።
በሁለቱም የትምህርት ክፍሎች የመውጫ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች በሙሉ ማለፋቸውን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።
@tikvahuniversity
🌐 ቅመም ማይፋይ በአዲስ ዋጋ መጥቷል!
💨⚡ እስከ 7 ሰዓት የሚቆይ የባትሪ አቅም ያለውና አዳዲስ የቴክኖሎጂ ትሩፋቶችን ይዞ በአንዴ እስከ 8 ሰው ድረስ የሚያስጠቅመውን ልዩ ቅመም MIFIን ገዝተን ፈጣን 4G ኢንተርኔት እንጠቀም!
🍰 ለ30 ቀን ከሚቆይ ነጻ 30ጊባ ዳታ ጉርሻ ጋር 😊
ከሳፋሪኮም ጋር አንድ ወደፊት⚡
#SafaricomEthiopia
#EthiopianDefenceUniversity
የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ በ2017 ዓ.ም በ16 ፕሮግራሞች በመደበኛ መርሐግብር ሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ካስፈተናቸው ዕጩ ተመራቂ ተማሪዎች መካከል 88% ያህሉ ማለፋቸውን ገልጿል።
@tikvahuniversity
የሁለት ወር የልጆች የክረምት ስልጠና!
25% ቅናሽ እስከ ሰኔ 21/2017 ዓ.ም.
👉 ስልጠናው ዕድሜያቸው ከ 5-18 ዓመት ላሉ ልጆች የሚሰጥ
👉 ልጆች ፕሮጀክቶች እየሰሩ የሚሰለጥኑበት
👉 ስልጠናው ሰኔ 30/2017 ዓ.ም ይጀመራል።
የስልጠናዎች አይነት፦
👉 Computer Programming and Website Development
👉 AI and Robotics
👉 Graphic Design, Video Editing and Animation
👉 Art (Film Acting, Writing and Modeling)
👉 Painting, Drawing and Sculpture
👉 Language and Basic Computer
☎️ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ
ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ
ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ
Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
#BahirDarUniversity
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በመደበኛው መርሐግብር ለመጀመሪያ ጊዜ የመውጫ ፈተና ካስፈተናቸው ተማሪዎች 96.11% ተፈታኞች የማለፊያ ውጤት ማምጣታቸውን አሳውቋል።
በሁሉም መርሐግብሮች ማለትም በመደበኛ፣ በተከታታይ፣ በክረምት እና በርቀት መርሐግብሮች ለመጀመሪያ ጊዜ ከተፈተኑት ውስጥ 94.4% ተፈታኞች ማለፋቸው ተገልጿል።
ዩኒቨርሲቲው የመውጫ ፈተና ለመጀመሪያ ጊዜ በሰጠባቸው 46 ትምህርት ክፍሎች 100% ተማሪዎችን ማሳለፍ መቻሉን ነው የገለፀው፡፡
የባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ካስፈተናቸው ተማሪዎች ውስጥ ከሦስት ተማሪዎች በስተቀር ሁሉም ተማሪዎች ማለፋቸውም ተገልጿል።
@tikvahuniversity
#TVTI #ExitExam
የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ለ2017 ዓ.ም ዕጩ ተመራቂ ተማሪዎቹ የመውጫ ፈተና በ10 የፈተና ማዕከላት በመሰጠት ላይ ይገኛል።
2,455 ሰልጣኞች በ46 ፕሮግራሞች በኢንስቲትዩቱ ዋና ግቢ እና በ15 ሳተላይት ተቋማት የመውጫ ፈተና እየወሰዱ መሆናቸው ተገልጿል።
@tikvahuniversity
የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት በቅድመ-ምረቃ እና በድኅረ-ምረቃ መርሐግብር ያሰለጠናቸውን ከ1050 በላይ ተማሪዎች እሑድ ሰኔ 15/2017 ዓ.ም ያስመርቃል።
ተመራቂዎቹ በኢንስቲትዩቱ ዋናው ግቢ እና በሳተላይት ካምፓሶች በቀን፣ በማታ እና በቅዳሜና እሑድ ፕሮግራሞች ስልጠናቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው።
@tikvahuniversity
#WachemoUniversity
#ClassOf2025
#CommencementPhotos
ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራሞች ያሰለጠናቸውን 1,255 ተማሪዎችን አስመርቋል።
የሶፍትዌር ኢንጅነሪንግ ተማሪ የሆነው መብራቱ ደጀኔ ከአጠቃላይ የ2017 ዓ.ም ተመራቂ ተማሪዎች አጠቃላይ ውጤት (CGPA) 3.90 ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ የዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል።
የአንስቴዥያ ትምህርት ክፍል ተማሪ የሆነችው ብሌን ስዩም ከአጠቃላይ የ2017 ዓ.ም ሴት ተመራቂ ተማሪዎች አጠቃላይ ውጤት (CGPA) 3.84 ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ ልዩ ተሸላሚ ሆኗለች።
@tikvahuniversity
#KotebeUniversityOfEducation
ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 1,989 ተማሪዎች በዛሬው ዕለት አስመርቋል።
ተመራቂ በመጀመሪያ ዲግሪ፣ በሁለተኛ ዲግሪ እና በፒ.ኤች.ዲ. ፕሮግራሞች ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው።
@tikvahuniversity
የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተፈታኞች የመውጫ ፈተና ውጤት ተለቋል። - ትምህርት ሚኒስቴር
የፈተና አገልግሎት ክፍያ (Exam Service Payment) የከፈሉ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውጤት ዛሬ ሰኔ 14/2017 ዓ.ም የተለቀቀ መሆኑን ከትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራር አረጋግጠናል።
በዚህም የፈተና አገልግሎት ክፍያ የከፈሉ ተቋማት የተፈታኞቻቸውን ውጤት እንዲያውቁት የተደረገ ሲሆን፤ የግል ተፈታኞች ወደ ተማሩበት ተቋም በመሔድ ውጤታቸውን ማየት ይችላሉ ተብሏል።
@tikvahuniversity
መንትዮች ተመራቂዎች 🎉
ዮሐንስ ደረጀ እና ያዕቆብ ደረጀ ከጅማ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በሶፍትዌር ምህንድስና ዛሬ ተመርቀዋል።
መንትዮቹ ከልጅነታቸው ጀምረው በአንድ ክፍል ፊደል ቆጥረው፣ በአንድ ሁለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመረው በጅማ ዩኒቨርሲቲ ዩኒቨርሲቲ ተምረው በተመሳሳይ ውጤት እና ደረጃ ለማጠናቀቅ ችለዋል። #JiT
@tikvahUniversity
ጂንካ ዩኒቨርሲቲ በ29 የትምህርት መስኮች የመውጫ ፈተና ከወሰዱ 1,117 ዕጩ ተመራቂዎች መካከል 780 ተማሪዎች (69.8%) የሚሆኑት ፈተናውን ማለፋቸውን ገልጿል።
ዩኒቨርሲቲው በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 851 የቅድመ እና የድኅረ-ምረቃ ተማሪዎችን አስመርቋል።
@tikvahuniversity
Class of 2025 Commencement!
በርካታ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች በልዩ ልዩ የሙያ መስኮች ያሰለጠኗቸውን ተማሪዎች እያስመረቁ ነው።
ከ25 በላይ ዩኒቨርሲቲዎች በዛሬው ዕለት ተማሪዎቻቸውን እያስመረቁ ይገኛሉ፡፡
ተመራቂዎቹ በተለያዩ ፕሮግራሞች ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁና የመውጫ ፈተና ወስደው ያለፉ የቅድመ-ምረቃ መርሐግብር ተማሪዎች እንዲሁም የድኅረ-ምረቃ እና የስፔሻሊቲ ፕሮግራም ሰልጣኞች ናቸው፡፡
እንኳን ደስ አላችሁ!
ምስል፦ ጅማ፣ ባህርዳር፣ ደምቢ ዶሎ እና አሶሳ ዩኒቨርሲቲዎች
@tikvahuniversity
የግል ተፈታኞች የመውጫ ፈተና ውጤት ነገ ሰኔ 14/2017 ዓ.ም ይለቀቃል። - ትምህርት ሚኒስቴር
የግል ተፈታኞች ውጤት አለመለቀቁን ተከትሎ፥ በርካታ የግል ተፈታኞች ጥያቄያቸውን ለቲክቫህ አድርሰዋል። እኛም በጉዳዩ ዙሪያ የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራርን ጠይቀናል።
"ያልተጣሩ ጉዳዮች በመኖራቸው የግል ተፈታኞች ውጤት መዘግየቱን" ከፍተኛ አመራሩ ገልፀዋል።
የፈተና አገልግሎት ክፍያ (Service Payment) ያልከፈሉ ተቋማት መኖራቸውን የጠቆሙት ኃላፊው፤ ክፍያቸውን የፈፀሙ ተቋማት የተፈታኞቻቸው ውጤት ነገ ሰኔ 14/2017 ዓ.ም ይገለጽላቸዋል ብለዋል።
በዚህም የፈተና አገልግሎት ክፍያ የከፈሉ ተቋማት ተወካዮች የተፈታኞቻቸውን ውጤት እንዲያውቁት እንደሚደረግ ተናግረዋል።
@tikvahuniversity
እስከ ሰኔ 15/2017 ዓ.ም ብቻ!
በሦስቱም ቅርንጫፎቻችን (መገናኛ፣ ሜክሲኮ እና ጀሞ) እንዲሁም በኦንላይን በምንሰጣቸው ስልጠናዎች በ Advanced Level እና 90% Practical በሆነ ካሪኩለምና ዘመኑ ያፈራቸውን ሙሉ የስቱዲዮ እቃዎችን በማሟላት የምንሰጠውን ስልጠና ይውሰዱ።
ከሁሉም ስልጠናዎቻችን ላይ ታላቅ የዋጋ ቅናሽ አድርገናል! አሁኑኑ ይመዝገቡና ትልቅ ለውጥ ወደሚያመጡበት ተቋም ይቀላቀሉ!
ከትምህርትና ስልጠና ጥራትና ቁጥጥር ባለስልጣን ሙሉ ዕውቅና ካለው ሰርተፊኬት ጋር! የብዙ ዓመት ልምድና ብቃት ባላቸው አሰልጣኞች!
🎯 Graphics Design
🎯 Video Editing
🎯 Digital Marketing
🎯 Photography
🎯 Videography
🎯 Cinematography
🎯 Adobe photoshop
🎯 Fullstack Webapp Development
🎯 Programming Language
🎯 Interior Design
🎯 English Language
🎯 Database
🎯 Basic Computer
🎯 Accounting Softwares
🎯 Engineering Softwares
🎯 SPSS & STATA
🎯 MS-Project
🎯 Foreign & Local Languages
አድራሻ
1. መገናኛ መተባበር ህንጻ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁ. 419 (ሊፍት ይጠቀሙ) ☎️ 0991929303
2. ሜክሲኮ ኬኬር ህንጻ 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁ. 639 (ሊፍት ይጠቀሙ) ☎️ 0991929304
3. ጀሞ 1 አንደኛ በር ካኩ ቢዝነስ ሴንተር 3ኛ ፎቅ ☎️ 0991926707
Telegram: /channel/topinstitutes
TikTok: topinstitute" rel="nofollow">https://Tiktok.com/@topinstitute
Facebook: https://www.facebook.com/Topinstitutes
🎓 Congratulations! 🎉
ከ30 በላይ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማሯቸውን ተማሪዎች በሳምንቱ መጨረሻ ማለትም ሰኔ 14 እና 15/2017 ዓ.ም ያስመርቃሉ።
🎓 ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ
🎓 አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
🎓 ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ
🎓 ጅማ ዩኒቨርሲቲ
🎓 ዲላ ዩኒቨርሲቲ
🎓 አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ
🎓 አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ
🎓 አምቦ ዩኒቨርሲቲ
🎓 መቐለ ዩኒቨርሲቲ
🎓 ወልድያ ዩኒቨርሲቲ
🎓 ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ
🎓 ራያ ዩኒቨርሲቲ
🎓 አክሱም ዩኒቨርሲቲ
🎓 ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ
🎓 ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ
🎓 ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ
🎓 እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ
🎓 ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ
🎓 ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ
🎓 አሶሳ ዩኒቨርሲቲ
🎓 ሰመራ ዩኒቨርሲቲ
🎓 ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ
🎓 ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ
🎓 ወራቤ ዩኒቨርሲቲ
🎓 ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ
🎓 ጂንካ ዩኒቨርሲቲ
🎓 ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ
🎓 መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ
🎓 ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ
🎓 ቦረና ዩኒቨርሲቲ
🎓 አርሲ ዩኒቨርሲቲ
🎓 ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ
🎓 መቱ ዩኒቨርሲቲ
🎓 የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ
@tikvahuniversity
#BongaUniversity
ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በ2017 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ካስፈተናቸው 902 የቅድመ-ምረቃ መርሐግብር ተማሪዎች መካከል 741 ተማሪዎች ወይም 82.1% ያህሉ የማለፊያ ውጤት ማምጣቸውን አሳውቋል።
@tikvahuniversity
#WerabeUniversity
ወራቤ ዩኒቨርሲቲ በ2017 የመውጫ ፈተና ካስፈተናቸው ተማሪዎች መካከል 90% ያህሉ ማለፍ መቻላቸውን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።
በሌላ በኩል የHotel and Tourism Management ትምህርት ክፍል በዩኒቨርሲቲው እንዲከፈት የሚያስችል የተገመገመ ስርዓተ-ትምህርት በዩኒቨርሲቲው ሴኔት ፀድቋል።
@tikvahuniversity
#DebreTaborUniversity
ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ በመደበኛ መርሐግብሮች በ10 ፕሮግራሞች የመውጫ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች ውስጥ 86.85% የማለፊያ ውጤት ማምጣታቸውን አሳውቋል።
ከነዚህ ውስጥ በሰባት ፕሮግራሞች የመውጫ ፈተና የወሰዱ ተፈታኞች 100% ማለፋቸው ተገልጿል፡፡
በደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ በሦስት የትምህርት ክፍሎች ማለትም ሜዲካል ላብራቶሪ፣ ኮምፕርሄንሲቭ ነርሲንግ እና ሚድዋይፈሪ የመውጫ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ሁሉም የመውጫ ፈተናውን አልፈዋል ተብሏል።
@tikvahuniversity
በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የአስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ በ2017 ዓ.ም የመውጫ ፈተና የወሰዱ 188 ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ (100%) ማለፋቸውን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡
ዕጩ ተመራቂዎቹ በአምስት ፕሮግራሞች ማለትም በህክምና፣ በህክምና ላቦራቶሪ ሳይንስ፣ በአጠቃላይ ነርሲንግ፣ በማህበረሰብ ጤና እና በሚድዋይፈሪ መስኮች ለፈተና የተቀመጡ እንደነበሩ ተገልጿል።
@tikvahuniversity
#InjibaraUniversity
እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ በ2017 ዓ.ም በመደበኛ መርሐግብር በ48 ፕሮግራሞች የመውጫ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች ውስጥ 92% የሚሆኑት የማለፊያ ውጤት ማስመዝገባቸውን አሳውቋል፡፡
ተፈታኞች በ48 ፕሮግራሞች ፈተና የወሰዱ ሲሆን፤ በ32 ፕሮግራሞች 100% ተፈታኞች ማለፋቸው ተገልጿል፡፡
@tikvahuniversity
🚀 ቤት-ዋይፋይ መጥቷል!
እጅግ ፈጣኑ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ቤት ዋይፋይ አገልግሎት በኮዬ ፈቼ፣ ቡልቡላ እና አያት ኮንዶሚኒየሞች ተጀምሯል! በቀጣይም ወደ ሁላችሁም ሰፈር እየመጣን ስለሆነ በትዕግስት ይጠብቁን!
#SafaricomEthiopia