የሁለት ወር የክረምት ስልጠና!
25% ቅናሽ እስከ ሰኔ 21/2017 ዓ.ም.
የሞባይል ጥገና (Advanced Mobile Maintenance) ስልጠና በፒያሣ እና በመገናኛ ካምፓስ ምዝገባ ላይ ነን።
👉 ንድፈ ሀሳብን ከተግባር ጋር በማዛመድ የሚሰጥ ስልጠና
👉 Hardware እና Software ጥገና በከፍተኛ ደረጃ (Advanced Level) የሚሰጥበት
👉 ስልጠናው ሰኔ 30/2017 ዓ.ም ይጀመራል።
☎️ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ
ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ
ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ
Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
#DebreMarkosUniversity
ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የ2017 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ከተፈተኑት መደበኛ ተማሪዎቹ መካከል ከ88% በላይ የሚሆኑት የማለፊያ ውጤት ማስመዝገባቸውን አሳውቋል።
@tikvahuniversity
የ2017 ዓ.ም የቅድመ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመውጫ ፈተና ውጤት ተለቋል ወይ የሚሉ በርካታ ጥያቄዎች ደረሰውናል።
የመውጫ ፈተና ውጤትን በተመለከተ ትምህርት ሚኒስቴርን የጠየቅን ቢሆንም፥ ምላሽ ማግኘት አልቻልንም።
ይሁን እንጂ እስካሁን ባደረግነው ማጣራት የመውጫ ፈተና ውጤት በዌብሳይት በይፋ አለመለቀቁን ለማወቅ ችለናል።
ከዚህ በፊት ውጤት በ https://result.ethernet.edu.et በኦንላይን ይለቀቅ እንደነበር አይዘነጋም።
አሁን ላይ ወደ አንዳንድ ትምህርት ተቋማት ውጤት እየተላከ ይገኛል። ተማሪዎችም በዛው በግቢያቸው ማየት ይችላሉ።
ከመውጫ ፈተና ውጤት ጋር የሚወጡ መረጃዎችን ተከታትለን የምናደርሳችሁ ይሆናል።
@tikvahuniversity
የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ለመስጠት አስፈላጊው ዝግጅት መጠናቀቁን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ገልጿል።
መንግሥት ከክልል ትምህርት ቢሮዎች፣ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ ከጸጥታ አካላት እና ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በትብብር እየሠራ መሆኑን የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) ለፋና ሚዲያ ተናግረዋል።
የፈተና ጥያቄዎች እና የመሰረተ ልማት ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውን የገለፁት ዋና ዳይሬክተሩ፤ ኩረጃን ለማስቀረት ፈተናዎች በከፍተኛ ስብጥር እንዲዘጋጁ መደረጉን ገልፀዋል።
በፈተና ወቅት ስልክን ጨምሮ ኤሌክትሮኒክስ ነገሮችን መያዝ መከልከሉንና ይዘው የተገኙ ተፈታኞች ውጤታቸው እንደሚሰረዝ አስገንዝበዋል።
የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ከሰኔ 23/2017 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 8/2017 ዓ.ም ይሰጣል። ፈተናውን ለመውሰድ 608 ሺህ ተማሪዎች የተመዘገቡ ሲሆን፤ 150 ሺህ የሚሆኑት በበይነ መረብ የሚፈተኑ ናቸው።
@tikvahuniversity
እስከ ሰኔ 15/2017 ዓ.ም ብቻ!
በሦስቱም ቅርንጫፎቻችን (መገናኛ፣ ሜክሲኮ እና ጀሞ) እንዲሁም በኦንላይን በምንሰጣቸው ስልጠናዎች በ Advanced Level እና 90% Practical በሆነ ካሪኩለምና ዘመኑ ያፈራቸውን ሙሉ የስቱዲዮ እቃዎችን በማሟላት የምንሰጠውን ስልጠና ይውሰዱ።
ከሁሉም ስልጠናዎቻችን ላይ ታላቅ የዋጋ ቅናሽ አድርገናል! አሁኑኑ ይመዝገቡና ትልቅ ለውጥ ወደሚያመጡበት ተቋም ይቀላቀሉ!
ከትምህርትና ስልጠና ጥራትና ቁጥጥር ባለስልጣን ሙሉ ዕውቅና ካለው ሰርተፊኬት ጋር! የብዙ ዓመት ልምድና ብቃት ባላቸው አሰልጣኞች!
🎯 Graphics Design
🎯 Video Editing
🎯 Digital Marketing
🎯 Photography
🎯 Videography
🎯 Cinematography
🎯 Adobe photoshop
🎯 Fullstack Webapp Development
🎯 Programming Language
🎯 Interior Design
🎯 English Language
🎯 Database
🎯 Basic Computer
🎯 Accounting Softwares
🎯 Engineering Softwares
🎯 SPSS & STATA
🎯 MS-Project
🎯 Foreign & Local Languages
አድራሻ
1. መገናኛ መተባበር ህንጻ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁ. 419 (ሊፍት ይጠቀሙ) ☎️ 0991929303
2. ሜክሲኮ ኬኬር ህንጻ 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁ. 639 (ሊፍት ይጠቀሙ) ☎️ 0991929304
3. ጀሞ 1 አንደኛ በር ካኩ ቢዝነስ ሴንተር 3ኛ ፎቅ ☎️ 0991926707
Telegram: /channel/topinstitutes
TikTok: topinstitute" rel="nofollow">https://Tiktok.com/@topinstitute
Facebook: https://www.facebook.com/Topinstitutes
በርካታ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማሯቸውን ተማሪዎች በሳምንቱ መጨረሻ ያስመርቃሉ።
ከ15 በላይ ዩኒቨርሲቲዎች የ2017 ዓ.ም የተማሪዎች የምረቃ ስነ-ስርዓት ቅዳሜ ሰኔ 14/2017 ዓ.ም የሚያከናውኑ ሲሆን፤ የተወሰኑ ዩኒቨርሲቲዎች እሑድ ሰኔ 15/2017 ዓ.ም ያካሒዳሉ።
🎓 አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ፣
🎓 ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ፣
🎓 ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ፣
🎓 አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ፣
🎓 አምቦ ዩኒቨርሲቲ፣
🎓 ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ፣
🎓 እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ፣
🎓 ራያ ዩኒቨርሲቲ፣
🎓 ሰመራ ዩኒቨርሲቲ፣
🎓 ወልድያ ዩኒቨርሲቲ፣
🎓 ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ፣
🎓 ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ፣
🎓 አክሱም ዩኒቨርሲቲ፣
🎓 ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ፣
🎓 መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ፣
🎓 ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ፣
🎓 መቱ ዩኒቨርሲቲ እና
🎓 የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ በሳምንቱ መጨረሻ ተማሪዎቻቸውን ከሚያስመርቁ ዩኒቨርሲቲዎች መካከል ይጠቀሳሉ።
@tikvahuniversity
የሁለት ወር የክረምት ስልጠና
25% ቅናሽ እስከ ሰኔ 21/2017 ዓ.ም.
መሰረታዊ የኮምፒውተር (Basic Computer) ስልጠና በፒያሣ እና በመገናኛ ካምፓስ ምዝገባ ላይ ነን!
👉 Microsoft Word, Excel, Access, Powerpoint, Publisher እና ሌሎች የኮምፒውተር አጠቃቀሞችን አካቶ የሚሰጥ ስልጠና
👉 ስልጠናው ሰኔ 30/2017 ዓ.ም ይጀመራል።
☎️ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ
ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ
ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ
Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
#ExitExam
ከሰኔ 2/2017 ዓ.ም ጀምሮ ሲሰጥ የቆየው የመውጫ ፈተና ዛሬ ተጠናቋል።
በዛሬ ዕለት በተጨማሪም በክረምት የመምህራን ስልጠና መርሐግብር ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ለቆዩ ከ5 ሺህ በላይ መምህራን የመውጫ ፈተና ተሰጥቷል።
ከ190 ሺህ በላይ ተፈታኞች በ51 ዩኒቨርሲቲዎች በተዘጋጁ 87 የፈተና ማዕከላት የመውጫ ፈተናውን እንደወሰዱ ይጠበቃል። ከእነዚህ ውስጥ 88 ሺህ የሚሆኑት ዳግም የመውጫ ፈተና ተፈታኞች ናቸው።
@tikvahuniversity
ስትጠብቁት የነበረው የ12ኛ ክፍል ማትሪክ ፈተና አጋዥ አፕሊኬሽናችን አሁን playstore ላይ ይገኛል። ዳውንሎድ አድርገው ይጠቀሙ!
✅ በነጻ
✅ አዲሱን ስርዓተ ትምህርት ያካተተ
✅ አጫጭር ኖቶችና አጋዥ ቪድዮዎች የያዘ
አሁኑኑ ይሞክሩት!!
መተግበሪያውን ለማግኘት 👇
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.exam_time.exam
ለተጨማሪ መረጃ የTelegram ቻናላችንን ይቀላቀሉ፦ @thinkhub
#ethiopia #ethiopian #ትምህርት #grade12 #Ethiopians #entranceexam #examtime #matric #education #Ethiopians
#AASTU
የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በ Bioprocess Engineering የማስተርስ እና የሦስተኛ ዲግሪ ትምህርት መስጠት ሊጀምር ነው።
በዩኒቨርሲቲው የባዮቴክኖሎጂ እና የባዮፕሮሰስ የልህቀት ማዕከል በ Bioprocess Engineering የማስተርስ እና የሦስተኛ ዲግሪ ፕሮግራሞች ለመጀመር የስርዓተ ትምህርት የውጭ ግምገማ አድርጓል።
የሁለቱ የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች መጀመር የልህቀት ማዕከሉን የምርምርና ልማት አቅም እንደሚያጎለብተው ተገልጿል
@tikvahuniversity
የሁለት ወር የክረምት ስልጠና
25% ቅናሽ እስከ ሰኔ 21/2017 ዓ.ም.
የፋይናንስ እና ካፒታል ማርኬት ስልጠና በፒያሣ እና በመገናኛ ካምፓስ ምዝገባ ላይ ነን።
👉 ፈጥነው ይመዝገቡ!
ብቁ በሆኑ መምህራን የሚሰጠው ስልጠናው፤ ከመሰረታዊ የካፒታል ገበያ ምንነት አንስቶ፣ እንዴት አንድ ግለሰብ ወይም ተቋም ከስጋት ነጻ በሆነ መንገድ በገበያው ላይ መሳተፍ እንደሚችል ግልፅ ያደርጋል።
ስልጠናው ሰኔ 30/2017 ዓ.ም ይጀመራል።
☎️ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ
ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ
ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ
Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2017 ዓ.ም የ6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ከነገ ሰኔ 10/2017 ዓ.ም ጀምሮ ለሦስት ተከታታይ ቀናት ይሰጣል።
በአምስት የትምህርት ዓይነቶች የሚሰጠውን ፈተና ከ80 ሺህ በላይ ተማሪዎች እንደሚወስዱ ይጠበቃል።
በ192 የመፈተኛ ጣቢያዎች የሚሰጠውን ፈተና ለመቆጣጠር 2,160 ፈታኞች፣ 697 ሱፐርቫይዘሮች እና 192 የፈተና ጣቢያ ኃላፊዎች መመደባቸውን የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ ገልጿል።
@tikvahuniversity
በሀረሪ ክልል የ6ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ከነገ ሰኔ 10/2017 ዓ.ም ጀምሮ ለሦስት ተከታታይ ቀናት ይሰጣል።
ከ5,800 በላይ የ6ኛ ክፍል ተማሪዎች ለፈተና እንደሚቀመጡ ይጠበቃል።
በዛሬው ዕለት በፈተናው አሰጣጥ እንዲሁም በፈተናው ደንብና መመሪያዎች ዙሪያ ለተፈታኝ ተማሪዎች ገለጻ ተሰጥቷል፡፡
@tikvahuniversity
ስትጠብቁት የነበረው የ12ኛ ክፍል ማትሪክ ፈተና አጋዥ አፕሊኬሽናችን አሁን playstore ላይ ይገኛል። ዳውንሎድ አድርገው ይጠቀሙ!
✅ በነጻ
✅ አዲሱን ስርዓተ ትምህርት ያካተተ
✅ አጫጭር ኖቶችና አጋዥ ቪድዮዎች የያዘ
አሁኑኑ ይሞክሩት!!
መተግበሪያውን ለማግኘት 👇
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.exam_time.exam
ለተጨማሪ መረጃ የTelegram ቻናላችንን ይቀላቀሉ፦ @thinkhub
#ethiopia #ethiopian #ትምህርት #grade12 #Ethiopians #entranceexam #examtime #matric #education #Ethiopians
#UniversityOfGondar
ጎንደር ዩኒቨርሲቲ አራት ቢሊዮን ብር በሚሆን ወጭ ያስገነባቸውን 22 ፕሮጀክቶች ማስመረቁ ይታወቃል። ሦስቱ ፕሮጀክቶች የሚከተሉት ናቸው።
የካንሰር ጨረር ሕክምና ማዕከል
- በዩኒቨርሲቲው ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ውስጥ ይገኛል።
- 51ዐ ሚሊዮን ብር ወጭ ተደርጎበታል።
- በአማራ ክልል የመጀመሪያው ማዕከል ነው።
- በአገር አቀፍ ደረጃ አምስተኛ ማዕከል ነው።
- ከተለያዩ የአማራ ክልል አካባቢዎች፣ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና ከትግራይ ክልሎች እንዲሁም በከፊል ከሱዳን እና ደቡብ ሱዳን የሚመጡ ታካሚዎችን ተጠቃሚ ያደርጋል ተብሏል።
የኦክስጅን ማምረቻ ማዕከል
- በጎንደር ዩኒቨርሲቲ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ውስጥ ይገኛል።
- ፋብሪካው በቀን 200 ሲሊንደር ኦክስጅን የማምረት አቅም አለው።
- ባለፉት ወራት ለተለያዩ ታካሚዎች አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡
ሰው ሰራሽ እግር ማምረቻ ማዕከል
ሰው ሰራሽ እግር የሚያመርት ማዕከል ለ80 ተጎጂዎች ሰው ሰራሽ እግር በማምረት ታካሚዎችን ተጠቃሚ አድርጓል። ማዕከሉ ከአማራ ክልል ባለፈ ለአጎራባች ክልሎች አገልግሎት ይሰጣል ተብሏል።
የማኅበረሰብ ትምህርት ቤቶች፣ የቅድመ ሕክምና ቤተ-ሙከራ፣ ማራኪና አረንጓዴ የግቢ ልማት እንዲሁም የዲጂታላዜሽንና ሲስተም አውቶሜሽን ሥራዎች ከተመረቁት ፕሮጀክቶች መካከል ይጠቀሳሉ።
@tikvahuniversity
የ2017 ዓ/ም የመውጫ ፈተና የወሰዱ የአምቦ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ውጤታቸውን በዩኒቨርሲቲው የሬጅስትራር ፖርታል ይህን ሊንክ estudent.ambou.edu.et በመጠቀም ማየት እንደሚችሉ ተገልጿል።
#AmboUniversity
@tikvahuniversity
የመውጫ ፈተና ውጤት ለተቋማት እየተላከ ነው።
የ2017 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ውጤት እስካሁን ሁሉም ተማሪ ባለበት ሆኖ እንዲያይ በድረ-ገጽ ይፋ ባይደርገም፤ ትምህርት ሚኒስቴር ውጤት ለዩኒቨርሲቲዎች እየላከ ይገኛል።
ተቋማትም ዘንድሮ ምን ያህል ተማሪዎቻቸው እንዳለፉ ይፋ ማድረግ ጀምረዋል።
ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛ መርሐግብር በ46 ፕሮግራሞች የመውጫ ፈተና ከወሰዱ 1108 ተማሪዎቹ ውስጥ 1008 ማለትም 91% እንዳለፉ ይፋ አድርጓል።
ከ46 ፕሮግራሞች በ17 ፕሮግራሞች 100% ተፈታኞች እንዳለፉም ገልጿል።
@tikvahuniversity
#TVTI #ExitExam
የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ሠልጣኞች የ2017 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ከነገ ሰኔ 12/2017 ዓ.ም ጀምሮ ለሁለት ቀናት ይሰጣል።
የመውጫ ፈተና ተፈታኞች የሆናችሁ የተቋሙ ሠልጣኞች የመፈተኛ ቦታ እንዲሁም Username and Password በማረጋገጥ በተመደባችሁበት ቦታ በሰዓቱ እንድትገኙ ኢንስቲትዩት አሳስቧል።
(የመፈተኛ ቦታ ለማወቅ እና የመለያ ስም እና የይለፍ ቃል ለማረጋገጥ የምትጠቀሙት ሊንክ በኢንስቲትዩቱ ማኅበራዊ ትስስር ገጾች ላይ ይገኛል።)
@tikvahuniversity
#UniversityOfGondar
ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመቀጠል ሁለተኛው ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ ለመሆን የሚያስችሉ ቅድመ ዝግጅቶችን አጠናቋል፡፡ - የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት
ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ወደራስገዝነት የሚያደርገውን ሽግግር የሚያስችሉ ከ40 በላይ ፖሊሲዎች እና መመሪያዎች መዘጋጀታቸውን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት አሥራት አፀደወይን (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡
ራስ ገዝ ለመሆን ዓለም አቀፍ እና አገር አቀፍ ተሞከሮዎች መወሰዳቸውን የተናገሩት ፕሬዝዳንቱ፤ ከአገር ውስጥ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እንዲሁም ከውጭ ከተለያዩ የአሜሪካ ዩኒቨርሲቲዎች አሉበት ብለዋል፡፡
ራስ ገዝ ለመሆን የሚያስችሉ የሀብት መፍጠሪያ ተቋማት መገንባታቸውን የተናገሩት ፕሬዝዳንቱ፣ የአካባቢው ማኅበረሰብ በአተገባበሩ ላይ ተሳታፊ እንዲሆን የግንዛቤ ማስጨበጥ ሥራ መከናወኑን አስረድተዋል፡፡
የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ራስ ገዝ እንዲሆኑ በ2015 ዓ.ም የራስ ገዝ አስተዳደር አዋጅ መውጣቱ ይታወሳል፡፡ አዋጁ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አካዳሚያዊ፣ አስተዳደራዊ እና የገንዘብ ነፃነት እንዲኖራቸው የሚያስችል ነው፡፡
በአዋጁ መሠረት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያው ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ በመሆን የተመዘገበ ሲሆን፤ ጎንደር ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ ሌሎች ዘጠኝ ዩኒቨርሲቲዎች ራስ ገዝ ለመሆን በእንቅስቃሴ ላይ ናቸው ተብሏል፡፡ #ሪፖርተር
@tikvahuniversity
የ2017 ዓ.ም የቅድመ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመውጫ ፈተና ከሰኔ 2-10/2017 ዓ.ም ለሰባት ቀናት መሰጠቱ ይታወቃል።
ውጤት መቼ ይፋ እንደሚደረግ የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮችን እየጠየቅን ሲሆን፤ ምላሽ እንዳገኘን መረጃውን የምናደርሳችሁ ይሆናል።
ይሁን እንጂ በርካታ ዩኒቨርሲቲዎች የ2017 ዓ.ም ዕጩ ተመራቂዎቻቸውን የፊታችን ቅዳሜ እና እሑድ ያስመርቃሉ። በመሆኑም የመውጫ ፈተና ውጤት በቀጣይ ጥቂት ቀናት፥ ቢዘገይ እስከ አርብ ድረስ ይፋ እንደሚደረግ ይጠበቃል።
እስካሁን በነበረው ሁኔታ ውጤት የሚገለፀው በኦንላይን በ https://result.ethernet.edu.et ላይ እንደነበር አይዘነጋም።
@tikvahuniversity
በአማራ ክልል የግዕዝ ትምህርት ከ3ኛ-5ኛ ክፍል ለሚገኙ የአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች እየተሰጠ ነው። - የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ
አዲሱ ስርዓተ ትምህርት ትኩረት ከሚሰጥባቸው ጉዳዮች መካከል አገር በቀል እውቀትን ማጎልበት አንዱ ነው።
በዚህም የግእዝ ትምህርትን በአማራ ክልል በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች (ከ3ኛ-8ኛ ክፍል) ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ገልጿል።
ከ3ኛ እስከ 5ኛ ክፍል ለሚማሩ ተማሪዎች የግዕዝ የመማሪያ እና የማስተማሪያ መጽሐፍት ተዘጋጅተው ለዞን እና ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያዎች በሶፍትኮፒ መላካቸውን የቢሮው የቋንቋ እና ማኅበራዊ ሳይንስ ቡድን መሪ ውባለ ሙሄ ገልጸፀል፡፡
በዚህ ዓመት በ276 ትምህርት ቤቶች ከ3ኛ-5ኛ ክፍል ለሚገኙ ከ35 ሺህ በላይ ተማሪዎች የግዕዝ ትምህርት መሰጠቱን አንስተዋል።
በቀጣይ ዓመት የ6ኛ ክፍል የግዕዝ ትምህርት ለማስጀመር የመማሪያ እና የማስተማሪያ መጽሐፍት ዝግጅት ተጠናቋል ያሉት ኃላፊው፤ ለ2018 የትምህርት ዘመን ከ3ኛ-6ኛ ክፍል 500 ሺህ የሚጠጋ የተማሪዎች መማሪያ እና ከ16 ሺህ በላይ የማስተማሪያ መጽሐፍት ለማሳተም ዝግጅት እየተደረገ ነው ብለዋል።
የ7ኛ እና የ8ኛ ክፍል የግዕዝ ትምህርት ለማስጀመር በቀጣይ ዓመት የስርዓተ ትምህርት ዝግጅት እንደሚደረግ ከክልሉ ትምህርት ቢሮ የተገኘ መረጃ ያሳያል።
@tikvahuniversity
የ65 ዓመቱ የ6ኛ ክፍል ፈተና ተፈታኝ
የዕድሜ ባለፀጋው አቶ ኑር አሊ አርባ በአፋር ክልል፣ በራህሌ ወረዳ፣ የበራህሌ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ6ኛ ክፍል ተማሪ ናቸው።
የአራት ልጆች አባት የሆኑት አቶ ኑር አሊ አርባ ለትምህርት ልዩ ፍላጎት እንዳላቸው ይናገራሉ።
ልጆቻቸውን ከማስተማርና ቤተሳባቸውን ከመምራት ጎን ለጎን፤ ራሳቸውም ትምህርታቸውን በመከታተል የ6ኛ ክፍል ፈተና ወስደዋል። ትምህርት በዕድሜ እንደማይገደብም ምሳሌ ሆነዋል።
በአፋር ክልል የ6ኛ ክፍል ፈተና ሰኔ 9 እና 10/2017 ዓ.ም ተሰጥቷል። #ARSEB
@tikvahuniversity
#ጥቆማ
5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደርስ ኢንሼቲቭ ነፃ ስልጠናን ለመከታተል ይመዝገቡ።
ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው ሰርትፍኬት ማግኘት የሚያስችልዎትን ስልጠና ባሉበት ሆነው ይውሰዱ።
የስልጠና ዘርፎች፦
► ዌብ ፕሮግራሚንግ
► አንድሮይድ ማበልፀግ
► ዳታ ሳይንስ
► አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ፋንዳሜንታልስ
ለመመዝገብ 👇
https://www.ethiocoders.et/
በተሰጠው ስምንታት ሳምንት ስልጠናውን ሲያጠናቅቁ፥ ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው ሰርተፊኬት ይበረከትልዎታል።
@tikvahuniversity
አሁንም በSMS ጨዋታ ፈታ 💬🎊 እያልን በየቀኑ እንሸለም! 🎁
ከሳፋሪኮም ቁጥራችን 'START’ ብለን ወደ 34000 በመላክ ወይም ወደ *799# በመደወል እንወዳደር! እናሸንፍ! በአንድ መልስ 1ብር ብቻ!
🔗 የ M-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያን በዚህ ሊንክ እናውርድ፦
https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle
#MPESASafaricom
#SafaricomEthiopia
#1Wedefit
#Furtheraheadtogether
የ6ኛ ክፍል ክልላዊ እና ከተማ አቀፍ ፈተና በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች እየተሰጠ ነው።
ፈተናው ከዛሬ ሰኔ 10/2017 ዓ.ም ጀምሮ ለሦስት ተከታታይ ቀናት ይሰጣል።
@tikvahuniversity
#MoE
የመውጫ ፈተና የሰባተኛ እና የመጨረሻ ቀን መርሐግብር (ሰኔ 10/2017 ዓ.ም)
ፈተናው በ31 የትምህርት ፕሮግራምች በሁለት ክፍለ-ጊዜ ይሰጣል፦
✅ ፈረቃ 1: ጠዋት ከ2:30-6:00 ሰዓት
✅ ፈረቃ 2: ከሰዓት ከ9:00-12:00 ሰዓት
@tikvahuniversity
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የ2017 ዓ.ም ክልላዊ የ6ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ሰኔ 10 እና 11/2017 ዓ.ም ይሰጣል።
ከ120 ሺህ በላይ ተማሪዎች ክልላዊ ፈተናው እንደሚወስዱ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ገልጿል።
ለተፈታኝ ተማሪዎች በአጠቃላይ የፈተናው አሰጣጥና ተማሪዎቹ ሊከተሏቸው በሚገቡ ስነ-ምግባር ላይ ገለጻ ተሰጥቷል።
@tikvahuniversity
በድሬዳዋ አስተዳደር የ6ኛ ክፍል ፈተና ከነገ ሰኔ 10/2017 ዓ.ም ጀምሮ ለሦስት ቀናት ይሰጣል።
8,276 ተማሪዎች በ114 የመፈተኛ ጣቢያዎች የሚሰጠውን ፈተና እንደሚወስዱ የአስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ ገልጿል።
@tikvahuniversity
የመውጫ ፈተና የስድስተኛ ቀን ፈተናዎች እየተሰጡ ነው።
የዛሬ ሰኔ 9/2017 ዓ.ም ፈተናዎች ጠዋት እና ከሰዓት በሁለት ክፍለ-ጊዜ እንደሚሰጡ የወጣው መርሐግብር ያሳያል።
ነገ ማክሰኞ ሰኔ 10/2017 ዓ.ም ቀሪ ፈተናዎች እንዲሁም በክረምት የመምህራን ስልጠና መርሐግብር ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ለቆዩ ከ5 ሺህ በላይ መምህራን የመውጫ ፈተና ይሰጣል።
መምህራኑ የመውጫ ፈተናውን በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ በተዘጋጁ 35 የፈተና ማዕከላት ስልጠና በወሰዱባቸው 24 የትምህርት ፕሮግራሞች እንደሚወስዱ ተገልጿል።
ተፈታኞች በዛሬው ዕለት ፈተና ለመውሰድ የሚያስችላቸውን User Name እና Password ከሚፈተኑባቸው ተቋማት እየወሰዱ ይገኛሉ።
@tikvahuniversity
የሁለት ወር የክረምት ስልጠና
25% ቅናሽ እስከ ሰኔ 21/2017 ዓ.ም.
Entrepreneurship, Leadership & Marketing ስልጠና በፒያሣ እና በመገናኛ ካምፓስ ምዝገባ ላይ ነን!
👉 የሽያጭ መንገዶች እና ቢዝነስ ፕሮፖዛል አዘገጃጀት ብቃትን የሚያገኙበት
👉 ዲጂታል ማርኬቲንግ በተግባር የሚሰጥበት
👉 በተጨማሪነት የቢዝነስ አመራር እና ሥራ ፈጠራ ስልጠናን አካቷል
👉 ለመክፈት የሚያስቡትን ቢዝነስ ከስልጠና እስከ ማማከር አካቶ የሚሰጥ
👉 ስልጠናው ሰኔ 30/2017 ዓ.ም ይጀመራል።
☎️ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ
ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ
ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ
Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute