#MoE
የመውጫ ፈተና የስድስተኛ ቀን መርሐግብር (ሰኔ 9/2017 ዓ.ም)
ፈተናው በተለያዩ የትምህርት ፕሮግራምች በሁለት ክፍለ-ጊዜ ይሰጣል፦
✅ ፈረቃ 1: ጠዋት ከ2:30-6:00 ሰዓት
✅ ፈረቃ 2: ከሰዓት ከ9:00-12:00 ሰዓት
@tikvahuniversity
ስትጠብቁት የነበረው የ12ኛ ክፍል ማትሪክ ፈተና አጋዥ አፕሊኬሽናችን አሁን playstore ላይ ይገኛል። ዳውንሎድ አድርገው ይጠቀሙ!
✅ በነጻ
✅ አዲሱን ስርዓተ ትምህርት ያካተተ
✅ አጫጭር ኖቶችና አጋዥ ቪድዮዎች የያዘ
አሁኑኑ ይሞክሩት!!
መተግበሪያውን ለማግኘት 👇
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.exam_time.exam
ለተጨማሪ መረጃ የTelegram ቻናላችንን ይቀላቀሉ፦ @thinkhub
#ethiopia #ethiopian #ትምህርት #grade12 #Ethiopians #entranceexam #examtime #matric #education #Ethiopians
#UniversitiesBudget
የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ከፍተኛ በጀት የሚመደብላቸው ቢሆንም፥ በጀቱን እጅግ አስፈላጊ ላልሆኑ ፕሮጀክቶች እያዋሉ ይገኛሉ ሲል መንግሥት ወቀሰ።
እያንዳንዱ ዩኒቨርሲቲ የሚመደብለት በጀት ቢደመር ከየትኛውም የሀገሪቱ ተቋም የበለጠ እንደሆነ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከመመህራን ተወካዮች ጋር ባደረጉት የውይይት መድረክ ላይ ገልፀዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምን አሉ?
"አንድ ዩኒቨርሲቲ ያለው በጀት ከራሱ ከትምህርት ሚኒስቴር ይበልጣል። በቢሊየኖች እኮ ነው የሚመደበው። ከዛ ዩኒቨርሲቲው ምን ያደርጋል? ስታዲየም፣ ሆቴል፣ አጥር፣ (ይገነባል) ለዚህ እኮ ነው ዩኒቨርሲቲ (ግንባታ) ይቁም ያልነው። ዩኒቨርሲቲ ማለት የኮንዶሚኒየም ግንባታ ማኅበር አይደለም። ለምሳሌ ጅማ ዩኒቨርሲቲ ጤና ላይ የሚሠራ ከሆነ ይሁን ሆስፒታል ይገንባ። ሌላ ደግሞ አዳማ ዩኒቨርሲቲ ሳይንስ ላይ የሚሠራ ከሆነ የሳይንስ ላብ ይገንባ። ፋሽን እኮ ነው ሁሉም ሆስፒታል (መገንባት) ይጥቀመው አይጥቀመው። ሁሉ ስታዲየም፣ ሁሉ አጥር ፓላስ ይመስል። ይሄ ሁሉ ብር ይወጣበታል። እያንዳንዱ ዩኒቨርሲቲ የሚወስደውን ገንዘብ ብትደምሩት የትኛውም ተቋም ኢትዮጵያ ውስጥ ያን የሚያክል በጀት የሚወስድ የለም።"
@tikvahuniversity
ስትጠብቁት የነበረው የ12ኛ ክፍል ማትሪክ ፈተና አጋዥ አፕሊኬሽናችን አሁን playstore ላይ ይገኛል። ዳውንሎድ አድርገው ይጠቀሙ!
✅ በነጻ
✅ አዲሱን ስርዓተ ትምህርት ያካተተ
✅ አጫጭር ኖቶችና አጋዥ ቪድዮዎች የያዘ
አሁኑኑ ይሞክሩት!!
መተግበሪያውን ለማግኘት 👇
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.exam_time.exam
ለተጨማሪ መረጃ የTelegram ቻናላችንን ይቀላቀሉ፦ @thinkhub
#ethiopia #ethiopian #ትምህርት #grade12 #Ethiopians #entranceexam #examtime #matric #education #Ethiopians
የሁለት ወር የልጆች የክረምት ስልጠና 25% ቅናሽ እስከ ሰኔ 21/2017 ዓ.ም.
👉 ስልጠናው ዕድሜያቸው ከ 7-18 ዓመት ላሉ ልጆች የሚሰጥ ነው።
👉 ልጆች ፕሮጀክቶች እየሰሩ የሚሰለጥኑበት።
👉 ስልጠናው ሰኔ 30/2017 ዓ.ም ይጀመራል።
የስልጠናዎቹ ዓይነት፦
👉 Computer Programming and Website Development
👉 AI and Robotics
👉 Graphic Design, Video Editing and Animation
👉 Art (Film Acting, Writing and Modeling)
👉 Painting, Drawing and Sculpture
👉 Language and Basic Computer
☎️ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ
ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ
ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ
Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
ለ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ይዘጋጁ!
የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከሰኔ 23/2017 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 8/2017 ዓ.ም ይሰጣል፡፡
ለሀገር አቀፍ ፈተናው እየተዘጋጁ ነው?
ተፈታኝ ተማሪ ከሆኑ ከታች የተቀመጠውን ሊንክ በመጫን ለፈተናው በቂ ዝግጅት ለማድረግ የሚያስችሉ ትምህርቶችን ማግኘት ይችላሉ።
በትምህርት ሚኒስቴር የተዘጋጁ የቲቶርያል ቪዲዮዎችን ለማግኘት 👇
https://examinfo.moe.gov.et/guides
@tikvahuniversity
ሰላም ሚኒስቴር በአምስት ዩኒቨርሲቲዎች ሲሰጥ የቆየው 13ኛ ዙር የብሔራዊ በጎ ፈቃድ ማኅበረሰብ አገልግሎት ስለጠና ተጠናቋል።
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ፣ ወሎ ዩኒቨርሲቲ፣ መቱ ዩኒቨርሲቲ፣ አሶሳ ዩኒቨርሲቲ እና ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ 13ኛው ዙር ስልጠና የተሰጥባቸው ዩኒቨርሲቲዎች ናቸው።
5 ሺህ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ለ22 ቀናት በተሰጠው ስልጠና ተሳትፈዋል።
ሰላም ሚኒስቴር ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶችን በማሳተፍ፤ በስነ-ምግባር፣ በክህሎት እና በሥራ ፈጠራ ግንዛቤ የሚያዳብር ስልጠና ሲሰቆይቷል፡፡
@tikvahuniversity
የሁለት ወር የክረምት ስልጠና
25% ቅናሽ እስከ ሰኔ 21/2017 ዓ.ም.
ፒስቺሪ አካውንቲንግ ስልጠና በፒያሣ እና በመገናኛ ካምፓስ ምዝገባ ላይ ነን!
👉 ንድፈ ሀሳብን ከተግባር ያስተሳሰረ ስልጠና
👉 በፒስቺሪ ላይ የኢትዮጵያ ግብር ህግን፣ ሒሳብ አያያዝ እና ሪፖርት አቀራረብን አካቶ የሚሰጥ
👉 ስልጠናው ሰኔ 30/2017 ዓ.ም ይጀመራል።
የበለጠ ይጠብቁ ...
💥 ሴጅ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት 💥
☎️ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ
ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ
ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ
Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
#ETA
የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን የትምህርት ማስረጃ ማረጋገጫ አገልግሎት ለማግኘት የሚፈልጉ ተገልጋዮችን በቀጠሮ እንደሚያስተናግድ ገልጿል።
ለነገ ሰኔ 6/2017 ዓ.ም የተቀጠሩ የትምህርት ማስረጃ ማረጋገጫ ተገልጋዮችን ስም ዝርዝር በተቋሙ የማኅበራዊ ትስስር ገፆች ለጥፏል።
በቀጣይ ተገልጋዮችን ከቀጠሮ ውጪ የማያስተናግድ መሆኑን ተቋሙ አሳውቋል።
@tikvahuniversity
#TVTI #ExitExam
የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ሠልጣኞች የ2017 ዓ.ም የመውጫ ፈተና የሚሰጠው ሰኔ 12 እና 13/2017 ዓ.ም መሆኑን ተቋሙ አሳውቋል።
(የመፈተኛ ቦታ እና የፈተና ፕሮግራም ከላይ ተያይዟል።)
@tikvahuniversity
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ የ6ኛ ክፍል መሰጠት ተጀምሯል።
ከ48 ሺህ በላይ የ6ኛ ክፍል ተማሪዎች የአንደኛ ደረጃ ትምህርት መልቀቂያ ፈተና እንደሚወስዱ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ገልጿል።
@tikvahuniversity
#MoE
የመውጫ ፈተና የአራተኛ ቀን መርሐግብር
(ሰኔ 5/2017 ዓ.ም)
ፈተናው በ58 የትምህርት ፕሮግራምች በሦስት ክፍለ-ጊዜ ይሰጣል፦
✅ ፈረቃ 1: ጠዋት ከ2:30-5:00 ሰዓት
✅ ፈረቃ 2: ረፋድ ከ5:30-8:00 ሰዓት
✅ ፈረቃ 3: ከሰዓት ከ8:30-11:00 ሰዓት
@tikvahuniversity
የመምህራን መውጫ ፈተና!
በክረምት የመምህራን ስልጠና መርሐግብር ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ለቆዩ 5,521 መምህራን የመውጫ ፈተና ይሰጣል። - ትምህርት ሚኒስቴር
በክረምት የመምህራን ስልጠና መርሐግብር ትምህርታቸውን በተለያዩ የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሲከታተሉ የነበሩ 5,521 መምህራን የመውጫ ፈተና እንደሚወስዱ ተገልጿል።
መምህራኑ የመውጫ ፈተናውን በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ በተዘጋጁ 35 የፈተና ማዕከላት ሰኔ 10/2017 ዓ.ም እንደሚወስዱ በሚኒስቴሩ የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚ ኤባ ሚጀና (ዶ/ር) ተናግረዋል።
መምህራኑ የመውጫ ፈተናውን ስልጠና በተከታተሉባቸው 24 የትምህርት ፕሮግራሞች እንደሚወሰዱ መሪ ስራ አስፈጻሚው ገልፀዋል።
ተፈታኞቹ ወደ ፈተና ማዕከላት ሲሔዱ ብሄራዊ መታወቂያ (ፋይዳ) መያዝና በትምህርት ሚኒስቴር የተዘጋጀውን የፈተና ፕሮቶኮል ማክበር ይገባቸዋል ብለዋል፡፡
@tikvahuniversity
አስር የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ምክትል ፕሬዝዳንቶች እና የምርምር ዳይሬክተሮች በዩናይትድ ስቴትስ ጉብኝት በማድረግ ላይ ይገኛሉ።
የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች እና የአስር ዩኒቨርሲቲዎች ኃላፊዎች በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በተዘጋጀ የዩኒቨርሲቲ ምርምር አስተዳደር ዓለም አቀፍ የጎብኚዎች የአመራር ፕሮግራም ላይ እየተሳተፉ መሆናቸው ታውቋል።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ፣ አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ፣ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ፣ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ፣ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ፣ ጅማ ዩኒቨርሲቲ፣ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ፣ መቐለ ዩኒቨርሲቲ እና ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተወካዮች እየተሳተፉ ነው።
ለሁለት ሳምንት በሚቆየው ጉብኝት፤ ተሳታፊዎች የዩናይትድ ስቴትስ ዩኒቨርሲቲ ምርምር አስተዳደር ጽ/ቤቶችን የተለያዩ ዘመናዊ አሰራሮች እየተመለከቱ መሆናቸው ተገልጿል።
@tikvahuniversity
#MoE
የመውጫ ፈተና የሦስተኛ ቀን መርሐግብር
(ሰኔ 4/2017 ዓ.ም)
ፈተናው በ23 የትምህርት ፕሮግራምች በሦስት ክፍለ-ጊዜ ይሰጣል፦
✅ ፈረቃ 1: ጠዋት ከ2:30-5:00 ሰዓት
✅ ፈረቃ 2: ረፋድ ከ5:30-8:00 ሰዓት
✅ ፈረቃ 3: ከሰዓት ከ8:30-11:00 ሰዓት
@tikvahuniversity
#AASTU
በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የፈተና ማዕከላት ተመድባችሁ አርብ ሰኔ 6/2017 ዓ.ም በጠዋቱ የፈተና ክፍለ ጊዜ በተፈጠረ የኢንተርኔት ችግር ምክንያት የመውጫ ፈተናችሁን ያልትፈተናችሁ ተፈታኞች፤ ፈተናው ማክሰኞ ሰኔ 10/2017 ዓ.ም ጠዋት እንደሚሰጥ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።
(ሙሉ መልዕክቱ ከላይ ተያይዟል።)
@tikvahuniversity
ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ግንባታቸው የተጠናቀቁ 22 ፕሮጀክቶችን አስመረቀ።
ፕሮጀክቶቹን የማስመረቅ መርሐግብሩ፥ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ 70ኛ ዓመት እና የዩኒቨርሲቲ ሆስፒታሉ 100ኛ ዓመት ምስረታ በዓል አከባበር አካል እንደሆነ ተገልጿል።
ከተመረቁት ፕሮጀክቶች ሀያዎቹ በመንግሥት በጀት የተገነቡ ሲሆን፤ ሁለቱ ደግሞ በአጋር አካላት ድጋፍ በአጠቃላይ 4 ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ገንዘብ ወጪ የተደረገባቸው መሆናቸውን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት አስራት አፀደወይን (ዶ/ር) ተናግረዋል።
ከፕሮጀክቶቹ መካከል የካንሰር ሕክምና ማዕከል አንዱ ሲሆን፤ ይህም ጎንደርና አካባቢው የሜዲካል ቱሪዝም ማዕከል እንዲሆን ያስችላል ብለዋል።
ሌላው የተመረቀው ፕሮጀክት የኦክስጅን ማምረቻ ፋብሪካ ሲሆን ትልቅ አቅም የፈጠረና ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል አልፎ ለሌሎች እንደሚተርፍ ገልፀዋል።
ለምረቃ የበቁት ፕሮጀክቶች በትምህርት፣ በጤና፣ በምርምር እና በሌሎችም ዘርፎች የተሠሩና የዩኒቨርሲቲውን እንዲሁም የማኅበረሰቡን ተጠቃሚነት ከፍ የሚያደርጉ ናቸው ተብሏል።
@tikvahuniversity
ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ያስገነባቸውን 22 ፕሮጀክቶች ነገ ያስመርቃል።
የተመሰረተበትን 70ኛ ዓመት እያከበረ የሚገኘው ዩኒቨርሲቲው፤ በጎንደር ከተማ እና ባሉት ካምፓሶች ውስጥ ያስገነባቸውን 22 ፕሮጀክቶች በነገው ዕለት እንደሚያስመርቅ የተቋሙ ፕሬዝዳንት አስራት አፀደወይን (ዶ/ር) ተናግረዋል።
ለምረቃ የሚበቁት ፕሮጀክቶች የዩኒቨርሲቲውን ተልዕኮ ከማሳካት አኳያ የመማር ማስተማር፣ የምርምር እና የማኅበረሰብ አገልግሎት ሥራን የሚያግዙ ናቸው ተብሏል። #ኢፕድ
@tikvahuniversity
#ጥቆማ
የእንግሊዘኛ ቋንቋ ምዘና ፈተና (IELTS) በጅማ ዩኒቨርሲቲ ይውሰዱ!
ብሪቲሽ ካውንስል ከጅማ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር የ'IELTS' ፈተና ሐምሌ 19/2017 ዓ.ም በጅማ ዩኒቨርሲቲ ይሰጣል፡፡
በጅማ ዩኒቨርሲቲ ፈተናውን ለመውሰድ ፍላጎት ያላችሁ በአካባቢው የምትገኙ ምህራን፣ ተማሪዎች እና ባለሙያዎች እስከ ሐምሌ 13/2017 ዓ.ም ምዝገባ ማድረግ ይችላሉ።
ለመመዝገብ፦ www.ieltsregitration.britishcouncil.org ላይ ይግቡ፣
- IELTS Academics የሚለውን ይምረጡ፣
- 'Choose Country/Territory' የሚለውን ይጫኑ፣
- Ethiopia የሚለውን ይምረጡ/ይጻፉ፣
- ጅማ የሚለውን የመፈተኛ ቦታ ይምረጡ፣
- July 26, 2025 የሚል የመፈተኛ ቀን ይምረጡ፣
- 'Search for Tests' የሚለውን በመጫን 'Book Test' የሚለውን ይምረጡ፣
- አስፈላጊ ሰነዶች እና ክፍያ ይፈጽሙ።
ለተጨማሪ መረጃ 👉 0911769560
@tikvahuniversity
#ExitExam
የ2017 ዓ.ም የቅድመ-ምረቃ መርሐግብር ተማሪዎች የመውጫ ፈተና የአምስተኛ ቀን ፈተናዎች ዛሬ ተጠናቀዋል።
ፈተናው ላለፉት አምስት ቀናት የተሰጠ ሲሆን፤ ለቀጣይ ሁለት ቀናት (ቅዳሜ እና እሑድ) እንደማይሰጥ የወጣው መርሐግብር ያሳያል።
ከሰኔ 2/2017 ዓ.ም ጀምሮ እየተሰጠ የሚገኘው ፈተናው፤ ማክሰኞ ሰኔ 10/2017 ዓ.ም ይጠናቀቃል።
190 ሺህ የሚሆኑ ተፈታኞች በኦንላይን የሚሰጠውን ፈተና እየወሰዱ እንደሆነ ይጠበቃል።
ምስል፦ ደምቢ ዶሎ፣ ዓዲግራት እና ወለጋ ዩኒቨርሲቲዎች
@tikvahuniversity
በአማራ ክልል የ6ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና በአስፈታኝ ትምህርት ቤቶች እየተሰጠ ነው፡፡
በክልሉ የ6ኛ ክፍል ፈተና ሰኔ 5 እና 6/2017 ዓ.ም በ3,551 ትምህርት ቤቶች እንደሚሰጥ የክልሉ ትምህርት ቢሮ መግለፁ ይታወቃል።
በክልሉ የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ሰኔ 3 እና 4/2017 ዓ.ም ተሰጥቷል።
@tikvahuniversity
ስትጠብቁት የነበረው የ12ኛ ክፍል ማትሪክ ፈተና አጋዥ አፕሊኬሽናችን አሁን playstore ላይ ይገኛል። አሁኑኑ አድርገው መጠቀም ይጀምሩ!
✅ በነጻ
✅ አዲሱን ስርዓተ ትምህርት ያካተተ
✅ አጫጭር ኖቶችና አጋዥ ቪድዮዎችን የያዘ
አሁኑኑ ይሞክሩት!!
መተግበሪያውን ለማግኘት 👇
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.exam_time.exam
ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 @thinkhub
#ethiopia #ethiopian #ትምህርት #grade12 #Ethiopians #entranceexam #examtime #education #matric #Ethiopians
#MoE
የመውጫ ፈተና የአምስተኛ ቀን መርሐግብር (ሰኔ 6/2017 ዓ.ም)
ፈተናው በተለያዩ የትምህርት ፕሮግራምች በሁለት ክፍለ-ጊዜ ይሰጣል፦
✅ ፈረቃ 1: ጠዋት ከ2:00-5:00 ሰዓት
✅ ፈረቃ 2: ከሰዓት ከ9:00-12:00 ሰዓት
@tikvahuniversity
🤙🏽 ማንኛውም የድምጽ ወይም የዳታ ጥቅል እየገዛን በጉርሻ ደቂቃዎች እንንበሽበሽ! ከሳፋሪኮም ጋር በአብሮነት አንድ ወደፊት⚡️
🔗 የ M-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያን በዚህ ሊንክ እናውርድ 👇
https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle
#MPESASafaricom
#SafaricomEthiopia
#1Wedefit
#Furtheraheadtogether
በድሬዳዋ አስተዳደር የ2017 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል አስተዳደር አቀፍ ፈተና ሰኔ 3 እና 4/2017 ዓ.ም ተሰጥቷል።
ከ8 ሺህ በላይ የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች በ61 የፈተና ማዕከላት ፈተናቸውን የወሰዱ ሲሆን፤ ከነዚህ ውስጥ በድሬዳዋ ፌደራል ማረሚያ ቤት በህግ ታራሚነት የሚገኙ የ8ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች ፈተናቸውን መውሰዳቸው ተገልጿል።
@tikvahuniversity
የሁለት ወር የክረምት ስልጠና
25% ቅናሽ እስከ ሰኔ 21/2017 ዓ.ም.
የዲጂታል ማርኬቲንግ ስልጠና በፒያሣ እና በመገናኛ ካምፓስ ምዝገባ ላይ ነን!
👉 በሁለት ወር ምርጥ የዲጂታል ማርኬቲንግ ባለሙያ የሚያደርግዎት
👉 ንድፈ ሀሳብን ከተግባር ጋር ያስተሳሰረ ስልጠና
👉 ስልጠናው ሰኔ 30/2017 ዓ.ም ይጀመራል።
የበለጠ ይጠብቁ ...
💥 ሴጅ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት 💥
☎️ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ
ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ
ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ
Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
#AASTU
አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጄ ዩኒቨርሲቲ Virtual Desktop Infrastructure (VDI) የተሰኘ የማስተማሪያ ዲጂታል ላይብረሪ አስመርቋል።
ዲጂታል ላይብረሪው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን በበይነ መረብ ለመስጠት የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል።
ላይብረሪው ዘመኑ የሚጠይቀው የቴክኖሎጂ ከፍታ ያሟላና ከአንድ ማዕከል በተመሳሳይ ሰዓት የተለያዩ ፈተናዎችን ለመስጠት፣ ትምህርት ለማስተማር እንዲሁም ተማሪዎች ከአንድ ማዕከል የተለያዩ ሶፍትዌሮችን እንዲያገኙ የሚያስችል ነው ተብሏል።
@tikvahuniversity
#MoH
ግንቦት 22/2017 ዓ.ም የተሰጠውን የተግባር ምዘና ፈተና (OSCE) የወሰዳችሁ የአንስቴዥያ ተመዛኞች ውጤታችሁን ኦንላይን መመልከት ትችላላችሁ። - ጤና ሚኒስቴር
የአንስቴዥያ ተመዛኞች http://hple.moh.gov.et/hple ላይ በመግባት ሙሉ ስም እና የፈተና መለያ ቁጥራችሁን በማስገባት የፈተና ውጤታችሁን መመልከት የምትችሉ መሆኑን ጤና ሚኒስቴር አሳውቋል።
በውጤታችሁ ላይ ቅሬታ ያላችሁ ተመዛኞች ከሰኔ 3/2017 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት አስር (10) ተከታታይ የሥራ ቀናት በስልክ ቁጥሮች 0115186275 / 0115186276 በመደወል ጥያቄዎቻችሁን ማቅረብ ትችላላችሁ ተብሏል።
ፈተናውን ያለፋችሁ ተመዛኞች ዛሬ ሰኔ 4/2017 ዓ.ም ስም ዝርዝራችሁ ወደ ክልል ተቆጣጣሪ አካላት የሚላክ በመሆኑ፥ ሌሎች ቅድመ ሁኔታዎችን በማሟላት የሙያ ፍቃድ ማውጣት የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል።
@tikvahuniversity
የሁለት ወር የክረምት ስልጠና (25% ቅናሽ እስከ ሰኔ 21/2017 ዓ.ም.)
የፎቶግራፊ፣ ቪዲዮግራፊ፣ ግራፊክ ዲዛይን እና ቪዲዮ ኤዲቲንግ ስልጠና በፒያሣ እና በመገናኛ ካምፓስ ምዝገባ ላይ ነን።
👉 ተግባርን ከንድፈ ሀሳብ ያስተሳሰረ ስልጠና
👉 Photography, Videography, Cinematography, Graphic Design & Video Editong በአንድ ላይ
👉 ፕሮጀክቶችን በስቱዲዮ እና በመስክ በመስራት የሚሰጥ
👉 ስልጠናው ሰኔ 30/2017 ዓ.ም ይጀመራል።
☎️ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ
ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ
ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ
Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
#MoE
የ2017 ዓ.ም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመውጫ ፈተና በጥብቅ ዲሲፕሊን እየተሠ ነው። - ትምህርት ሚኒስቴር
ከሰኔ 2/2017 ዓ.ም ጀምሮ እየተሰጠ ለሚገኘው የመውጫ ፈተና የሚያገለግል የፈተና ፕሮቶኮል ተዘጋጅቶ ተፈታኞች እና ፈታኞች እንዲያውቁት መደረጉ ተገልጿል።
የፈተና ፕሮቶኮል ሰነዱ በመውጫ ፈተና የተከለከሉ ነገሮች፣ ተፈታኝ ሊከተሏቸው የሚገቡ የፈተና ዲሲፕሊን እንዲሁም ጥፋት ከተገኘ የሚወሰደው እርምጃን የሚገልጽ መሆኑን በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚ ኤባ ሚጀና (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡
ፈተናው ከሌሎች ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተመድበው በመጡ ፈታኞች እየተሰጠ እንደሆነም መሪ ስራ አስፈጻሚው ገልፀዋል፡፡
በዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንቶች የሚመራ ግብረኃይል የፈተና አሰጣጡን በቅርብ ክትትል እንደሚያደርግ ተናግረዋል።
190,787 ተማሪዎች እስከ ሰኔ 10/2017 ዓ.ም የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና በመውሰድ ላይ ይገኛሉ።
@tikvahuniversity