tikvahuniversity | Unsorted

Telegram-канал tikvahuniversity - Tikvah-University

308824

Subscribe to a channel

Tikvah-University

#MoE

ከግንቦት 25-30/2017 ዓ.ም በተሰጠው የሪሚዲያል ተማሪዎች የማጠቃለያ ፈተና የተከለከሉ ነገሮችን ይዘው በተገኙ የተወሰኑ ተፈታኞች ላይ የዲሲፕሊን እርምጃ ተወስዷል። - ትምህርት ሚኒስቴር

የሪሚዲያል ፈተናውን ደኅንነት ለማስጠበቅ ሲባል የተወሰኑ ተፈታኖች ከፈተናው እንዲሰናበቱ መደረጉን በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚ ኤባ ሚጀና (ዶ/ር) ገልፀዋል፡፡

76,790 የሪሚዲያል ተማሪዎች ለማጠቃለያ ፈተናው መቀመጣቸውን መሪ ስራ አስፈጻሚው ተናግረዋል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

የ8ኛ ክፍል ክልላዊ እና ከተማ አቀፍ ፈተና ዛሬ መሰጠት ጀምሯል።

ክልላዊ ፈተናው ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ቀናት በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ይሰጣል።

ምስል፦ የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ ትምህርት ቢሮዎች

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

🔔 የመውጫ ፈተና የመጀመሪያ ቀን የኦንላይን ፈተና ውሎን ተከትሎ ከትምህርት ሚኒስቴር የተሰጠ ማሳሰቢያ፦

✅ ማንኛውም ተፈታኝ ፈተናውን ሲጨርስ Finish and Submit ሳያደርግ መውጣት የለበትም። ተፈታኙ ይህንን ማድረጉንም በፈተና ክፍሉ የተመደበ ባለሙያ ማረጋገጫ ሳይሰጠው እና ተፈታኙም ፈተናውን መጨረሱን በፊርማው ሳያረጋግጥ ከመፈተኛ ክፍል መውጣት አይኖርበትም።

✅ በተለያየ ምክንያት ሲስተም ዘጋብን በማለት ፈተና ክፍል ውስጥ የሚቀመጡ ተፈታኞችን በተለያዩ መንገዶች የማጣራት ሥራ በመስራት አስፈለጊውን የእርምት ወይም አስተዳደራዊ እርምጃ መወሰድ ይኖርበታል።

(ሚኒስቴሩ ለዩኒቨርሲቲዎች ያስተላለፈው ሙሉ መረጃ ከላይ ተያይዟል።)

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

#SouthEthiopiaEducationBureau

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ከነገ ሰኔ 3/2017 ዓ.ም ጀምሮ ለሁለት ቀናት ይሰጣል።

በክልሉ ከ114 ሺህ በላይ የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ፈተናውን ለመውሰድ መመዝገባቸው ተገልጿል።

በተመሳሳይም ከ120 ሺህ በላይ የ6ኛ ክፍል ተማሪዎች ሰኔ 10 እና 11/2017 ዓ.ም ለፈተና እንደሚቀመጡ የክልሉ ትምህርት ቢሮ አሳውቋል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

#AmharaEducationBureau

በአማራ ክልል የ8ኛ እና የ6ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ከሰኔ 3-6/2017 ዓ.ም ይሰጣል።

በድምሩ ከ302 ሺህ በላይ የ8ኛ እና የ6ኛ ክፍል ተማሪዎች ክልላዊ ፈተናዎቹን እንደሚወስዱ የክልሉ ትምህርት ቢሮ አሳውቋል።

በክልሉ ሰኔ 3 እና 4/2017 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና በ2,642 ትምህርት ቤቶች የሚሰጥ ሲሆን 148,256 ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ ይጠበቃል።

በተመሳሳይ ሰኔ 5 እና 6/2017 ዓ.ም የ6ኛ ክፍል ፈተና በ3,551 ትምህርት ቤቶች ለ154,260 ተማሪዎች ይሰጣል።

በክልል ደረጃ የተቋቋመ የፈተና ግብረ ኃይል አስፈላጊ የዝግጅት ሥራዎችን ማጠናቀቁ ተገልጿል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

የሁለት ወር የክረምት ስልጠና (25% ቅናሽ እስከ ሰኔ 21/2017 ዓ.ም)

IFRS and Asset Valuation ስልጠና በፒያሣ እና በመገናኛ ካምፓስ ምዝገባ ላይ ነን።

👉 IFRS + Peachtree + Asset Valuation + IFRS Conversion + IPSAS + Quick Book በአንድ ላይ 
👉 ስልጠናው ሙሉ በሙሉ በተግባር የተደገፈና ፒስትሪ (Peachtree Software) ላይ የሚሰጥ ነው።
👉 ስልጠናው ሰኔ 30/2017 ዓ.ም ይጀመራል።

☎️  0906777799 / 0906777755
አድራሻ
ቁ.1:
ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ
ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ

Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute

Читать полностью…

Tikvah-University

#AAU #ExitExam

በርካታ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመውጫ ፈተና ተፈታኞች ፈተናቸውን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ይወስዳሉ።

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመውጫ ፈተና በየቀኑ በሦስት ፈረቃ መርሐግብር እንደሚሰጥ ተገልጿል።

ተፈታኞች በተመደቡበት ካምፓስ እና የፈተና ክፍል ብቻ ፈተናቸውን መውሰድ ይጠበቅባቸዋል።

(የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ቀን የ Management ፈተና መርሐግብር ከላይ ተያይዟል)

✅ ፈረቃ 1: ጠዋት 2:30-5:00 ሰዓት
✅ ፈረቃ 2: ረፋድ ከ 5:30-8:00 ሰዓት
✅ ፈረቃ 3: ከሰዓት 8:00-9:30 ሰዓት

ተፈታኞች ከፈተናው ከሚጀመርበት ሰዓት 30 ደቂቃ አስቀድመው በመፈተኛ ክፍል መገኘት ይጠበቅባቸዋል።

ፈተናውን ለመውሰድ ወደተመደቡበት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ካምፓስ ሲሔዱ የፋይዳ መታወቂያዎን መያዝ ይኖርብዎታል። ስልክ እና ሌሎች የተከለከሉ ነገሮችን የያዘ/የያዘች ተፈታኝ ወደ ግቢው እንዲገባ/እንድትገባ አይፈቀድላቸውም።

🔔 ስምዎ ከላይ በተያያዘው ዝርዝር ውስጥ ከሌለ የ Management and Business Management ተፈታኞች ሰኔ 5/2017 ዓ.ም በፈረቃ 3 ተፈታኞች ዝርዝር ላይ ተካተዋል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

#ExitExam

የቅድመ-ምረቃ መርሐግብር ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ከነገ ሰኔ 2/2017 ዓ.ም ጀምሮ ለዘጠኝ ተከታታይ ቀናት ይሰጣል።

ከ190 ሺህ በላይ ተፈታኞች የመውጫ ፈተናውን በ51 ዩኒቨርሲቲዎች በተዘጋጁ 87 የፈተና ማዕከላት ይወስዳሉ፡፡ ከእነዚህ ውስጥ 88 ሺህ የሚሆኑት ዳግም የመውጫ ፈተናውን የሚወስዱ ናቸው።

የመውጫ ፈተናው በ238 የትምህርት መርሐግብሮች በበይነ መረብ ይሰጣል።

በፈተና ወቅት የተከለከሉ ነገሮ፦

➻ ተንቀሳቃሽ ስልክ፣
➻ ሜሞሪ ያለው የእጅ ሰዓት፣
➻ የተጭበረበሩ ሰነዶች፣
➻ የራስ ያልሆነ መታወቂያ፣
➻ ያልተፈቀዱ የሂሳብ ማሽኖች።

➡️ የማይፈቀዱ የሂሳብ ማሽኖች
በአንዳንድ ፕሮግራሞች #ካልኩሌተር ማምጣት ይፈቀዳል፡፡ ሆኖም ግን ስልክ፣ ስማርት ዋች፤ ታብሌትና ተመሳሳይ ቁሶችን እንደ ካልኩሌተር መጠቀም ፈፅሞ አይፈቀደም። ሥራ ላይ የሚውሉ ካልኩሌተሮች የተራቀቁ እንዲሁም ፕሮግራሜብል መሆን የለባቸውም ተብሏል።

ተፈታኝ ተማሪዎች ፈተናው ከመጀመሩ ከ30 ደቂቃ ቀድመው በተመደቡበት የፈተና ክፍል መገኘት የሚኖርባቸው ሲሆን፤ ከተመደቡበት ክፍል ውጪ መፈተን ውጤት ያሰርዛል።

✅ ተፈታኞች የፋይዳ መታወቂያ (ኮፒ) መያዝ ይኖርባችኋል።

✅ በሌላ ሰው ስም፣ User Name እና Pasword መፈተን አይቻልም፡፡

✅ ከላይ የተዘረዘሩ የፈተና ስርአቶችን የጣሰ ተፈታኝ ውጤቱ ተሰርዞ በዲሲፒሊን ጥሰት የሚጠየቅ መሆኑ ተገልጿል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

ለአምስት ቀናት የተሰጠው የ2017 ዓ.ም የሪሚዲያል ተማሪዎች ፈተና ዛሬ ተጠናቋል።

ከአራት ወራት በላይ የአቅም ማሻሻያ ትምህርት የወሰዱ 77 ሺህ የሚሆኑ ተማሪዎች፥ የሪሚዲያል ፈተና እንደሚወስዱ ትምህርት ሚኒስቴር መግለፁ ይታወሳል።

የሪሚዲያል ፈተናው በ41 ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ በተዘጋጁ 64 የፈተና ማዕከላት መሠጠቱ ተገልጿል።

ምስል፦ ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

የሁለት ወር የክረምት ስልጠና (25% ቅናሽ እስከ ሰኔ 21/2017 ዓ.ም)

የህንጻ ኤሌክትሪክ እና የዲሽ መስመር ዝርጋታ ስልጠና በፒያሣ እና በመገናኛ ካምፓስ በምዝገባ ላይ ነን።

🔔 ፈጥነው ይመዝገቡ!

👉 ተግባርን ከንድፈ ሀሳብ ያስተሳሰረ ስልጠና
👉 የሳተላይት ዲሽ መስመር ዝርጋታ በተጨማሪነት የሚሰጥበት 
👉 ከትምህርት ቢሮ የCOC ምዘና የተዘጋጀለት
👉 ስልጠናው ሰኔ 30/2017 ዓ.ም ይጀመራል።

☎️  0906777799 / 0906777755
አድራሻ
ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ
ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ

Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute

Читать полностью…

Tikvah-University

የ2017 ዓ.ም የሪሚዲያል ተማሪዎች የማጠቃለያ ፈተና አራተኛ ቀኑ ላይ ይገኛል፡፡ ፈተናው በጥብቅ ዲሲፕሊን እና የፈተና ስነ-ምግባር እየተሰጠ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በወለጋ ዩኒቨርሲቲ ሻምቡ ካምፓስ ባለፉት ሦስት የፈተና ቀናት ተንቀሳቃሽ ስልክ ሲጠቀሙ የተገኙ ተማሪዎች ከመፈተኛ ክፍል እንዲሰናበቱና የትምህርት ዓይነቱ የፈተና ውጤታቸዉ እንዲሰረዝ መደረጉን ከዩኒቨርሲቲው የተገኘ መረጃ ያሳያል።

77 ሺህ የሚሆኑ የሪሚዲያል ተማሪዎች በ41 ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ በተዘጋጁ 64 የፈተና ማዕከላት የሪሚዲያል ፈተና እየወሰዱ እንደሚገኙ ትምህርት ሚኒስቴር መግለፁ ይታወቃል፡፡

የሪሚዲያል ተማሪዎች ፈተና ነገ በአረፋ በዓል ምክንያት የማይሰጥ ሲሆን፤ ቅዳሜ ግንቦት 30/2017 ዓ.ም ይጠናቀቃል፡፡ ምስል፦ ወለጋ ዩኒቨርሲቲ

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመውጫ ፈተና ለመውሰድ ዕጩ ተመራቂዎች የፋይዳ መታወቂያ (ብሔራዊ መታወቂያ) ሊኖራቸው እንደሚገባ መገለጹ ይታወቃል።

ተፈታኞች ሊይዟቸው የሚችሉ የፋይዳ መታወቂያ አማራጮች፦

➻ በኢትዮ ቴሌኮም ወይም በኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት አማካኝነት የታተሙ የፋይዳ መታወቂያዎች፣

➻ ከ "Fayda ID" ሞባይል መተግበሪያ፣ ከቴሌብር ሱፐር አፕ፣ እንዲሁም ሲቢኢ ብር ሞባይል መተግበሪያ ላይ QR ኮድ በማውረድ እና በወረቀት በማሳተም መያዝ ይችላሉ።

📵 ዲጂታል ኮፒ (በስልክ ይዞ መገኘት) እንደማይቻል ብሔራዊ መታወቂያ አገልግሎት ጽ/ቤት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቋል።

የፋይዳ ቁጥር ከጠፋብዎ ወይም ካልደረስዎ *9779# ላይ በመደወል በድጋሚ ማስላክ ይችላሉ።

ፎቶ፦ ተማሪዎች ሊይዟቸው የሚችሉ የፋይዳ አማራጮች

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ


@tikvahethiopia

Читать полностью…

Tikvah-University

ከ190 ሺህ በላይ የሚሆኑ የቅድመ-ምረቃ መርሐግብር ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ይወስዳሉ። - ትምህርት ሚኒስቴር

የመውጫ ፈተናው ከሰኔ 02-10/2017 ዓ.ም በ51 ዩኒቨርሲቲዎች በተዘጋጁ 87 የፈተና ማዕከላት ይሰጣል፡፡

ፈተናውን በ238 የትምህርት መርሐግብሮች ለ190,787 የቅድመ ምረቃ ዕጩ ተመራቂዎች በበይነ መረብ ለመስጠት አስፈላጊው ዝግጅት መጠናቀቁን በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚ ኤባ ሚጀና (ዶ/ር) ተናግረዋል።

102,360 ተማሪዎች ለመጀመሪያ ጊዜ እንዲሁም 88,422 ተማሪዎች ደግሞ ዳግም የመውጫ ፈተናውን የሚወስዱ መሆናቸውን መሪ ስራ አስፈጻሚው ገልፀዋል።

ተፈታኞች ወደ ፈተና ማዕከላት ሲሔዱ ብሔራዊ የዲጂታል መታወቂያ (ፋይዳ) መያዝ እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል፡፡

ተንቀሳቃሽ ስልክ፣ ሜሞሪ ያለው የእጅ ሰዓት፣ የራስ ያልሆነ መታወቂያ፣ ያልተፈቀዱ ካልኩሌተሮችና መሰል የተከለከሉ ነገሮች ይዞ ወደ ፈተና ማዕከል መምጣት እንደማይቻል አስረድተዋል፡፡

የመውጫ ፈተናውን ለመስጠት 4,017 ፈተና አስፈጻሚዎች እንደሚሳተፉ ተገልጿል። #MoE

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተናን የሚሰጡ ከ28 ሺህ በላይ #ፈታኞች መመልመላቸው ተገለፀ፡፡

ፈታኞቹ በወረቀት እና በበይነ መረብ የሚሰጠውን ፈተና በብቃት ለመስጠት ዝግጅት ያደረጉ መሆናቸውን የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ለኢቲቪ ተናግረዋል፡፡

ዘንድሮ መልቀቂያ ፈተናውን በበይነመረብ የሚፈተኑ 150 ሺህ ተማሪዎች አስፈላጊውን ልምምድ እያደረጉ እንደሆነ ጠቅሰዋል።

በፈተናው ወቅት የኢንተርኔት እና የመብራት መቆራረጥ እንዲሁም ሌሎች ችግሮች እንዳይፈጠሩ፤ ከ10 ተቋማት የተወጣጣ ግብረ-ኃይል ተቋቁሞ እየሠራ እንደሚገኝ ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

የሁለት ወር የክረምት ስልጠና (25% ቅናሽ እስከ ሰኔ 21/2017 ዓ.ም)

የኢንቴሪየር ዲዛይን (Interior Design) ስልጠና በፒያሣ እና በመገናኛ ካምፓስ ምዝገባ ላይ ነን ። 

👉 Sketch-Up, Revit, Rhino, 3D Max እና Lumion ሶፍትዌሮችን በአንድ ላይ
👉 ከንድፈ ሀሳብ እና ሶፍትዌር ስልጠና በተጨማሪ በተግባር በወርክሾፕ  የሚሰጥ
👉 ስልጠናው ሰኔ 30/2017 ዓ.ም ይጀመራል።

የበለጠ ይጠብቁ ...
💥 ሴጅ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት 💥

☎️   0906777799 / 0906777755
አድራሻ
ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ
ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ

Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute

Читать полностью…

Tikvah-University

#ExitExam

የ2017 ዓ.ም የቅድመ-ምረቃ መርሐግብር ተማሪዎች የመውጫ ፈተና የሁለተኛ ቀን ፈተናዎች እየተሰጡ ነው።

የመውጫ ፈተናው እስከ ሰኔ 10/2017 ዓ.ም በኦንላይን ይሰጣል።

በ51 ዩኒቨርስቲዎች የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና ከ190 ሺህ የሚሆኑ ተፈታኞች እንደሚወስዱ ይጠበቃል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

የሁለት ወር የክረምት ስልጠና (25% ቅናሽ እስከ ሰኔ 21/2017 ዓ.ም.)

Artificial Intelligence and Data Science ስልጠና በፒያሣ እና በመገናኛ ካምፓስ ምዝገባ ላይ ነን።

👉 ከፍተኛ ልምድ ባላቸው መምህራን የሚሰጥ
👉 ንድፈ ሀሳብን ከተግባር ጋር በማዛመድ የሚሰጥ ስልጠና
👉 ስልጠናው ሰኔ 30/2017 ዓ.ም ይጀመራል።

☎️   0906777799 / 0906777755
አድራሻ
ቁ.1:
ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ
ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ

Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute

Читать полностью…

Tikvah-University

#HarariEducationBureau

በሀረሪ ክልል የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ከነገ ሰኔ 3/2017 ዓ.ም ጀምሮ ለሁለት ቀናት ይሰጣል።

በክልሉ 5,250 የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ የክልሉ ትምህርት ቢሮ አሳውቋል።

በተመሳሳይ ከ5,800 በላይ ለሚሆኑ የ6ኛ ክፍል ተማሪዎች ክልላዊ የ6ኛ ክፍል ፈተና ከሰኔ 10-12/2017 ዓ.ም የሚሰጥ መሆኑ ተገልጿል።

የፈተናዎቹን አሰጣጥ ስኬታማ ለማድረግ በቂ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች መከናወናቸውን የሀረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ዘከሪያእ አብዱልአዚዝ ተናግረዋል፡፡

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

#DireDawaEducationBureau

በድሬዳዋ አስተዳደር የ2017 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል አስተዳደር አቀፍ ፈተና ከነገ ሰኔ 3/2017 ዓ.ም ጀምሮ ለሁለት ቀናት ይሰጣል።

በአስተዳደሩ 8,891 የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች በ61 የፈተና ማዕከላት ፈተናቸውን ይወስዳሉ ተብሏል። 

የ6ኛ ክፍል ፈተና በሚቀጥለው ሳምንት እንደሚሰጥ የአስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ አሳውቋል።

የፈተናው አሰጣቱን ስኬታማ ለማድረግ 328 ፈታኝ መምህራን፣ 42 ሱፐርቫይዘሮች እና 65 የጣቢያ ኃላፊዎች መመደባቸውን የቢሮው ኃላፊ ሱልጣን አልይ ገልፀዋል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

#ExitExam

የ2017 ዓ.ም የቅድመ-ምረቃ መርሐግብር ተማሪዎች የመውጫ ፈተና መሰጠት ጀምሯል።

የመውጫ ፈተናው ከዛሬ ሰኔ 2/2017 ዓ.ም ጀምሮ ለዘጠኝ ተከታታይ ቀናት ይሰጣል።

190 ሺህ የሚሆኑ ተፈታኞች በኦንላይን የሚሰጠውን ፈተና እንደሚወስዱ ይጠበቃል።

ምስል፦ ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

#AAU #ExitExam

የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ዕጩ ተመራቂና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የ Management መውጫ ፈተና ተፈታኝ ሆነው ነገ ሰኔ 2/2017 ዓ.ም የሚወስዱ ተፈታኞች ዝርዝር ላይ ስምዎ ከሌለ ሰኔ 5/2017 ዓ.ም በፈረቃ 3 ተፈታኞች ዝርዝር ላይ ስምዎን ይፈልጉ።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

ዩኒቨርሲቲዎች ከነገ ሰኔ 2/2017 ዓ.ም ጀምሮ በሚሰጠው ሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ዙሪያ ለተፈታኝ ተማሪዎች ገለጻ ሰጥተዋል።

በኦንላይን የሚሰጠው የመውጫ ፈተናው  በጥብቅ የፈተና ዲሲፕሊን እንደሚከናወን ተገልጿል።

ከተፈታኞች በተጨማሪ ፈታኝ መምህራን፣ አስተባባሪዎች፣ የፀጥታና ደህንነት አካላት በገለጻው ተሳትፈዋል።

ተፈታኝ ተማሪዎች በፈተና ወቅት ሊከተሏቸው የሚገቡ የፈተና ዲሲፕሊን፣ ወደ ፈተና ማዕከል ይዞ ለመግባት የሚፈቀዱ ነገሮች እና በሌሎች ተያያዥ ደንቦች ላይ ገለጻ ተሰጥቷቸዋል።

ከ190 ሺህ በላይ ተፈታኞች ከነገ ሰኔ 2/2017 ዓ.ም ጀምሮ ለዘጠኝ ተከታታይ ቀናት የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና ይወስዳሉ።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

የሁለት ወር የልጆች የክረምት ስልጠና (25% ቅናሽ እስከ ሰኔ 21/2017 ዓ.ም.)

👉 ስልጠናው ዕድሜያቸው ከ 7-18  ዓመት ላሉ ልጆች የሚሰጥ
👉 ልጆች ፕሮጀክቶች እየሠሩ የሚሰለጥኑበት
👉 ስልጠናው ሰኔ 30/2017 ዓ.ም ይጀመራል።

የስልጠና ዓይነቶች፦
👉 Computer Programming and Website Development
👉 AI and Robotics
👉 Graphic Design, Video Editing and Animation
👉 Art (Film Acting, Writing and Modeling)
👉 Painting, Drawing and Sculpture
👉 Language and Basic Computer

☎️  0906777799 / 0906777755
አድራሻ
ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ
ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ

Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute

Читать полностью…

Tikvah-University

#MoE

በተለያዩ የትምህርት መስኮች የሰለጠኑና ወደ መምህርነት ሙያ መግባት ለሚፈልጉ ምሩቃን አዲስ የአሠራር ስርዓት ገቢራዊ ሊሆን ነው።

እነዚህ ባለሙያዎች ተጨማሪ ስልጠና ወስደው መምህር መሆን የሚችሉበት የሰልጠና ማዕቀፍ ማዘጋጀቱን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

ይህም በሀገሪቱ የሚታየውን የመምህራን እጥረት ለመቅረፍ እንደሚያስችል በሚኒስቴሩ የመምህራንና የትምህርት አመራር ልማት መሪ ሥራ አስፈፃሚ ሙሉቀን ንጋቱ (ዶ/ር) ገልፀዋል።

በዚህም መምህር ሆነው መስራት ለሚፈልጉ ምሩቃን በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ገብተው ተጨማሪ የመምህርነት ሙያ፣ የማስተማር ዘዴ፣ የትምህርት ቴክኖሎጂ እና የጋራ ኮርሶችን ስልጠና እንዲወስዱ ይደረጋል ብለዋል።

በተለያዩ የትምህርት መስኮች የተመረቁ ባለሙያዎች፥ ተጨማሪ የማስተማር ሙያ ስልጠና ቢሰጣቸው ወደ ሙያው የመግባት ፍላጎት እንዳላቸው በተደረገ የዳሰሳ ጥናት ለማረጋገጥ መቻሉን በሚኒስቴሩ የመምህራንና የትምህርት አመራር ልማት ዴስክ ኃላፊ አሰገድ ምሬሳ ገልፀዋል።

አዲሱን የስልጠና ማዕቀፍ ወደ ሥራ ለማስገባት ከአሰልጣኝ የትምህርት ተቋማት፣ ከክልል ትምህርት ቢሮዎች እና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር የምክክር መድረክ እየተካሔደ ይገኛል።

አዲስ የተዘጋጀው አማራጭ የመምህራን ማሰልጠኛ ማዕቀፍ ከቀጣይ ዓመት ጀሞሮ ገቢራዊ ይሆናል ተብሏል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

እንኳን ለኢድ-አል አደሃ (አረፋ) በዓል አደረሳችሁ!

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምትገኙ የእስልምና ዕምነት ተከታይ ተማሪዎች መልካም በዓል እንዲሆንላችሁ እንመኛለን!

ኢድ ሙባረክ!! Eid Mubarak!!

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

#ጥቆማ

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (INSA) የ2017 ዓ.ም የሳይበር ታለንት ቻሌንጅ ሰመር ካምፕ ፕሮግራም ምዝገባ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡

አስተዳደሩ በመላ ሀገሪቱ ከአንደኛ ደረጃ እስከ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ የሆኑ ልዩ ታለንት ያላቸውን በመመልመል ለማሰልጠን ተዘጋጅቷል።

በመሆኑም በሳይበር ደህንነት፣ በዴቨሎፕመንት፣ በኢምቤድድ ሲስተም እና በኤሮስፔስ መስኮች ልዩ ተሰጥኦ እና ፍላጎት ያላችሁ በተከታዩ ሊንክ አማካኝነት ኦንላይን መመዝገብ ትችላላችሁ፡፡

🔔 ምዝገባው ግንቦት 24/2017 ዓ.ም ያበቃል ተብሎ የነበረ ቢሆንም፤ የኦንላይን ምዝገባው አሁንም ክፍት መሆኑን ለማወቅ ችለናል፡፡

ለመመዝገብ 👇
https://talent.insa.gov.et

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ባለፉት ሦስት ተከታታይ ዓመታት በሳይበር ደህንነት ዘርፍ ልዩ ተሰጥኦ ያላቸውን ታዳጊዎች በመመለመለና በማሰልጠን ወደ ተቋሙ እና ወደ ሳይበር ኢንዱስትሪው እንዲቀላቀሉ ሲያደርግ ቆይቷል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

የሁለት ወር የክረምት ስልጠና (25% ቅናሽ እስከ ሰኔ 21/2017 ዓ.ም)

የጥናታዊ ጽሑፍ አሰራር እና አቀራረብ (Research Methods and Analysis) ስልጠና በፒያሣ እና በመገናኛ ካምፓስ ምዝገባ ላይ ነን።

👉 Stata, SPSS, E-View,  R, Atlas እና  Nivivo ሶፍትዌሮችን በመጠቀም Quantitative እና Qualitaitive ሪሰርቾችን መስራትን በአንድ ላይ አካቶ የሚሰለጥኑበት
👉 ከፕሮፖዛል ቀረጻ ጀምሮ ሪሰርች አሰራር ቴክኒኮችን አካቶ እስከ ሪሰርች ሪፖርት አቀራረብ ያለውን አሰራር የሚሰለጥኑበት
👉 ልምድ ባላቸው የጥናታዊ ፅሑፍ ባለሙያዎች የሚሰጥ ስልጠና
👉 ስልጠናው ሰኔ 30/2017 ዓ.ም ይጀመራል።

☎️   0906777799 / 0906777755
አድራሻ
ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ
ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ

Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute

Читать полностью…

Tikvah-University

በአዲስ አበባ ከ7500 በላይ መምህራን እና የትምህርት አመራሮች የጽሁፍ የሙያ ብቃት ምዘና መውሰዳቸው ተገለጸ፡፡

ለመምህራን ባለፈው ቅዳሜ የተሰጠው የሙያ ፍቃድ ምዘና በተያዘለት ጊዜ ያለምንም ችግር በስኬት መጠናቀቁን በከተማ አስተዳደሩ የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ምክትል ስራ አስኪያጅ ታጋይቱ አባቡ ገልፀዋል፡፡

7549 ተመዛኞች በ10 መመዘኛ ጣቢያዎች ላይ መውሰዳቸውን የጠቆሙት ኃላፊዋ፤ በተለያዩ ምክንያቶች ምዘናውን ያልወሰዱ ተመዛኞች በሚቀጥለው ዓመት መመዘን ይችላሉ ብለዋል፡፡

ምዘናው አሰገዳጅ እንደሚሆንና ተመዝነው ሁለት ዓመት የሞላቸው መምህራን እና የትምህርት አመራሮች ደግሞ ማደስ እንደሚያስፈልጋቸው ጠቁመዋል፡፡

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

#DigitalID

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዕጩ ተመራቂዎች የመውጫ ፈተና ለመውሰድ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ሊያወጡ እንደሚገባ መገለፁ ይታወቃል።

ጊዚያዊ ስሊፕ ወይም የተማሪነት መታወቂያ ተቀባይነት እንደማይኖራቸው ተገልጿል።

በመሆኑም ፈተናውን ለመውሰድ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያዎ መያዝ እንዳይዘነጉ።

የፋይዳ ቁጥር ከጠፋብዎ ወይም ካልደረስዎ *9779# ላይ በመደወል በድጋሚ ማስላክ ይችላሉ።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

#ExitExamSchedule

የቅድመ-ምረቃ ፕሮግራም ዕጩ ተመራቂዎች በመውጫ ፈተናው መርሐግብር ላይ ለውጥ ተደርጓል ወይ ሲሉ ጠይቀውናል።

የ2017 ዓ.ም የቅድመ-ምረቃ ዕጬ ተመራቂዎች የመውጫ ፈተና ከሰኔ 02-10/2017 ዓ.ም የሚሰጥ መሆኑንና ለውጥ አለመኖሩን ለማረጋገጥ ችለናል።

በዚህም የመውጫ ፈተናው ከሰኔ 02/207 ዓ.ም ጀምሮ ለዘጠኝ ተከታታይ ቀናት ይሰጣል።

(የፈተናው ጊዚያዊ መርሐግብር ከላይ ተያይዟል።)

@tikvahuniversity

Читать полностью…
Subscribe to a channel