47ኛ እና 48ኛ ዙር የግራፊክ ዲዛይን፣ ቪዲዮ ኤዲቲንግ፣ ሞሽን ግራፊክ እና ዲጂታል ማርኬቲንግ ስልጠና በፒያሣ እና በመገናኛ ካምፓስ የፊታችን ሰኞ ግንቦት 11/2017 ዓ.ም ይጀምራል።
👉 ተግባርን ከንድፈ ሀሳብ ያስተሳሰረ ስልጠና
👉 Advanced Graphic + Video Editing + Motion Graphic + Digital Marketing በአንድ ላይ
👉 ከ50 በላይ ፕሮጀክቶች ያሉት
👉 የሥራ ላይ ስልጠና (Internship) የተመቻቸለት
☎️ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ
ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ
ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ
Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
9ኛው ሀገር አቀፍ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሕግ ተማሪዎች የምስለ ችሎት (Moot Court) ውድድር በሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ እየተካሔደ ነው።
ውድድሩ በፌደራል የህግና ፍትህ ኢንስቲትዩት እና በሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ትብብር የተዘጋጀ ሲሆን፤ እስከ እሑድ ግንቦት 10 ቀን 2017 ዓ.ም ይካሔዳል።
አሸናፊ የሚሆኑ ዩኒቨርሲቲዎች የሰርተፍኬት፣ የሜዳሊያ እና የዋንጫ ስልማት ይበረከትላቸዋል ተብሏል።
በዘንድሮው ውድድር ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ 12 ዩኒቨርሲቲዎች ማለትም አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ፣ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ፣ ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ፣ ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ፣ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ፣ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ፣ ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ፣ ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ፣ ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ፣ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ እና ወሎ ዩኒቨርሲቲ በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።
@tikvahuniversity
ለ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ይዘጋጁ!
የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከሰኔ 23 እስከ ሐምሌ 8/2017 ዓ.ም እንደሚሰጥ መገለፁ ይታወቃል፡፡
ለሀገር አቀፍ ፈተናው እየተዘጋጁ ነው?
ተፈታኝ ተማሪ ከሆኑ ከታች የተቀመጠውን ሊንክ በመጫን ለፈተናው በቂ ዝግጅት ለማድረግ የሚያስችሉ ትምህርቶችን ማግኘት ይችላሉ።
በትምህርት ሚኒስቴር የተዘጋጁ የቲቶርያል ቪዲዮዎችን ለማግኘት 👇
https://examinfo.moe.gov.et/guides
@tikvahuniversity
27ኛ ዙር ሙሉ የሒሳብ መዝገብ አያያዝ (Modern Accountancy) ስልጠና በፒያሣ እና በመገናኛ ካምፓስ ምዝገባ ላይ ነን።
👉 ተግባርን ከንድፈ ሀሳብ ያስተሳሰረ ስልጠና
👉 መሠረታዊ የአካውንቲንግ እና ኦዲት አሰራር፣ ሙሉ የአካውንቲንግ ሒሳብ አሰራር በፒስቺሪ ተደግፎ እና የግብር አያያዝ ትምህርቶችን አካቶ የሚሰጥ
👉 የሥራ ላይ ስልጠና (Internship) የተመቻቸለት
☎️ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ
ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ
ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ
Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
አስደሳች ዜና!
የ500 ብር የአየር ሰዓት ገዝተው ተመሳሳይ የ 0911 ቁጥርዎን በ 0711 አግኝተው በስጦታዎች ይንበሽበሹ!
📲 500 ብር የአየር ሰዓት
📞 ያልተገደበ ከሳፋሪኮም ወደ ሳፋሪኮም ስልክ
🌐 6 ጊባ ዳታ ያግኙ
🤳 1000 ደቂቃ ወደ ቴሌ መስመር
ፈጣኑን ኔትወርክ ይቀላቀሉ!
#SafaricomEthiopia
#ModelExitExam
ዩኒቨርሲቲዎች በ2017 ዓ.ም ለሚያስመርቋቸው እጩ ተመራቂዎች #ሞዴል የመውጫ ፈተና መስጠት ጀምረዋል፡፡
ሞዴል ፈተናው እጩ ተመራቂዎቹን ለመውጫ ፈተና (Exit Exam) ለማብቃት እና ለበይነ-መረብ (Online) ፈተና ለማዘጋጀት መሆኑ ተገልጿል፡፡
ትምህርት ሚኒስቴር ከዘንድሮ ጀምሮ ማለትም በሰኔ 2017 ዓ.ም ከሚሰጠው የመውጫ ፈተና አስቀድሞ ሁሉም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት #ሞዴል የመውጫ ፈተና በአስገዳጅነት ለተማሪዎቻቸው እንዲሰጡ ይደረጋል ማለቱ አይዘነጋም።
ምስል፦ ወልድያ ዩኒቨርሲቲ
@tikvahuniversity
#ETA
ሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በሰኔ 2017 ዓ.ም ለሚሰጠው የመውጫ ፈተና የሚፈተኑ ብቁ እጩ ተፈታኞች መረጃን በሶፍትዌር ቴምፕሌት እንዲያስገቡ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን አሳስቧል፡፡
በሰኔ ወር 2017 ዓ.ም ለሚሰጠው የመውጫ ፈተና ብቁ እጩ ተፈታኞችን ለማጣራት የተፈታኞችን መረጃ በሶፍት እና በሃርድ ኮፒ እንዲልኩ ባለስልጣኑ ለተቋማቱ ጥያቄ ማቅረቡ ይታወቃል፡፡
በዚህም በሶፍት እና በሃርድ ኮፒ የላካችሁ ተቋማት ብቻ በትምህርት ሚኒስቴር ሶፍትዌር ቴምፕሌት እስከ ግንቦት 12/2017 ዓ.ም ድረስ እድታስገቡ ተብሏል፡፡
@tikvahuniversity
የዲጂታል ማርኬቲንግ ስልጠና በፒያሣ ካምፓስ በቅዳሜ እና እሑድ መርሐግብር የፊታችን ቅዳሜ ግንቦት 09/2017 ዓ.ም ይጀምራል።
👉 በሁለት ወር ምርጥ የዲጂታል ማርኬቲንግ ባለሙያ የሚያደርግዎት
👉 ንድፈ ሀሳብን ከተግባር ጋር ያስተሳሰረ ስልጠና
የበለጠ ይጠብቁ ...
ሴጅ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት
☎️ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ
ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ
ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ
Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
#NationalIDEthiopia
ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመውጫ ፈተና ለመውሰድ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ቅደመ ሁኔታ መደረጉ ይታወቃል።
ዕጩ ተመራቂዎች ሊያውቋቸው የሚገቡ አስፈላጊ የፋይዳ አገልግሎቶች፦
➫ የፋይዳ ቁጥር ከጠፋባችሁ ወይም ካልደረሳችሁ *9779# በመደወል በድጋሚ ማስላክ ትችላላችሁ።
➫ በምዝገባ ወቅት የተሳሳተ መረጃን ለማደስ በ National ID Ethiopia ድረ-ገፅ id.gov.et/update ላይ በመግባት ወይም የፋይዳ "Fayda ID" ሞባይል መተግበሪያ ላይ በመግባት በቀላሉ ማደስ ትችላላችሁ።
➫ በተጨማሪ ለማንኛውም ጥያቄ ይህን /channel/+RJ5TcWZ_HvUzMzQ0 የቴሌግራም ግሩፕ ይቀላቀሉ።
@tikvahuniversity
#ETQRA
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ8ኛ ክፍል የመማር ብቃት ምዘና ጥናት ሊካሔድ ነው፡፡
የብቃት ምዘና ጥናቱ በከተማዋ የ8ኛ ክፍል የተማሪዎችን ዝቅተኛ የመማር ብቃት ያለበት ደረጃን ለመለየት እንደሚያስችል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ገልጿል፡፡
በዚህም በሚገኙ ክፍተቶች ላይ ተገቢው ምክረ-ሃሳብ ለሚመለከታቸው አካላት እንደሚቀርብ ተገልጿል፡፡
በጥናቱ መረጃዎችን ለሚሰበስቡ አስተባባሪዎች እና የትምህርት ቤት ርዕሳነ መምህራን በባለስልጣኑ ኦረንቴሽን ተሰጥቷል፡፡
በከተማዋ በተመረጡ 110 የትምህርት ተቋማት፥ በአራት የትምህርት አይነቶች ላይ የመማር ብቃት ምዘና ጥናቱ ይካሔዳል ተብሏል፡፡
@tikvahuniversity
Artificial Intelligence and Data Science ስልጠና በፒያሣ እና በመገናኛ ካምፓስ ምዝገባ ላይ ነን!
👉 ከፍተኛ ልምድ ባላቸው መምህራን የሚሰጥ ስልጠና
👉 ንድፈ ሀሳብን ከተግባር ጋር በማዛመድ የሚሰጥ ስልጠና
☎️ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ
ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ
ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ
Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
#AAEB
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2017 ዓ.ም የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተናዎች የሚሰጡበትን ጊዜ ይፋ አድርጓል።
በዚህም የ6ኛ ክፍል ፈተና ከሰኔ 10-12/2017 ዓ.ም የሚሰጥ ሲሆን፤ የ8ኛ ክፍል ፈተና ሰኔ 3 እና 4/2017 ዓ.ም ይሰጣል፡፡
በከተማዋ ከ80 ሺህ በላይ የ6ኛ ክፍል ተማሪዎች እንዲሁም ከ71 ሺህ በላይ የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ፈተናቸውን እንደሚወስዱ ይጠበቃል።
@tikvahuniversity
ጂንካ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ተመድቦለታል፡፡
ዮሐንስ ይትባረክ (ዶ/ር) ከግንቦት 01/2017 ዓ.ም ጀምሮ የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ሆነው እንዲሠሩ የተወከሉ መሆኑን በትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በቀን ሚያዝያ 29/2017 ዓ.ም ተፈርሞ የወጣ ደብዳቤ ያሳያል።
ዶ/ር ኩሴ ጉዲሼ ከህዳር 2013 ዓ.ም ጀምሮ የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት በመሆን ሲያገለግሉ መቆየታቸው ይታወቃል፡፡
አዲሱ ተጠባባዊ ፕሬዝዳንት ዮሐንስ ይትባረክ (ዶ/ር) በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የሶሻል አንትሮፖሎጂ ረዳት ፕሮፌሰር ሲሆኑ፤ በጀርመኑ Max Planck Institute የሶሻል አንትሮፖሎጂ ተባባሪ ተመራማሪ እንደነበሩ ማህደራቸው ያሳያል፡፡
@tikvahuniversity
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አሻሽሎ ባወጣው የአካዳሚክ ካላንደር የ2017 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ከሰኔ 2-10/2017 ዓ.ም መሆኑን ያሳያል።
ዩኒቨርሲቲው የ2017 ትምህርት ዘመን የተማሪዎች የምረቃ ስነ-ስርዓት ሰኔ 21/2017 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል።
(የተሻሻለው የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ካላንደር ከላይ ተያይዟል፡፡)
@tikvahuniversity
#WoldiaUniversity
ወልድያ ዩኒቨርሲቲ ባለፉት ዓመታት ከተቋሙ ለተመረቁ ተማሪዎች የኦሪጅናል ዲግሪ ህትመት ለመስጠት መዘጋጀቱን ገልጿል።
የዩኒቨርሲቲው ተመራቂ ከሆኑ ከግንቦት 04/2017 ዓ.ም ጀምሮ በማመልከት ኦሪጂናል ዲግሪ መውሰድ ትችላላችሁ ተብሏል።
(ተጨማሪ መረጃ ከላይ ተያይዟል።)
@tikvahuniversity
#MoH
የተግባር ምዘና ፈተና ለመውሰድ በመጠባበቅ ላይ የምትገኙ የአንስቴዥያ ተመዛኞች፥ ፈተናውን ለመውሰድ ምዝገባ ከግንቦት 8-13/2017 ዓ.ም እንደሚከናወን ጤና ሚኒስቴር አሳውቋል።
በመሆኑም የመንግሥት እንዲሁም የግል ተቋማት ተመዛኞች hple.moh.gov.et/hple ላይ በመግባት በተጠቀሱት ቀናት ብቻ ምዝገባ እንድታደርጉ ተብሏል።
ምዝገባ ካደረጋችሁ በኋላ ሲስተሙ የሚሰጣችሁን የፈተና መለያ ቁጥር (Registration No) የያዘ ስሊፕ Print አድርጋችሁ በመያዝ ስትመዘገቡ በመረጣችሁት የፈተና ጣቢያ በፈተናው ወቅት እንድትገኙ ሚኒስቴሩ አሳስቧል።
ጤና ሚኒስቴር የአንስቴዥያ ተመዛኞች የተግባር ምዘና ፈተናን በግንቦት ወር 2017 ዓ.ም ለመስጠት በዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡
@tikvahuniversity
🤙🏽 ከሳፋሪኮም ወደ የቴሌ የሚያስደውሉ የድምፅ ጥቅሎች በመጠቀም ከ07 ➡️ 09 መስመር በእጥፍ ጉርሻ በሽበሽ ብለን እንደዋወል! ከሳፋሪኮም ጋር በአብሮነት አንድ ወደፊት⚡️
🔗 የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያን በዚህ ሊንክ እናውርድ 👇
https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle
#MPESASafaricom
#SafaricomEthiopia
#1Wedefit
#Furtheraheadtogether
#ጥቆማ
የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ሞጆ በሚገኘው የቢዝነስና ማህበራዊ ጥናት ኮሌጁ ለ2018 የትምህርት ዘመን በተለያዩ ፕሮግራሞች የመከላከያ ሰራዊቱን ተቀላቅለው መማር የሚፈልጉ ተማሪዎችን ተቀብሎ በመደበኛ ፕሮግራም ለማስተማር ይፈልጋል፡፡
በመጀመሪያ ዲግሪ ለማመልከት የሚያስፈልጉ፦
➫ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ከ2014-2016 ዓ.ም የወሰዳችሁ
➫ በትምህርት ሚኒስቴር በዓመቱ የተቀመጠውን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመግቢያ ነጥብ የምታሟሉ
በቴክኒክ እና ሙያ ላጠናቀቃችሁ የሚያስፈልጉ፦
➫ የደረጃ 4 የብቃት ማረጋገጫ
➫ የሁለት ዓመት የሥራ ልምድ
➫ የመግቢያ ፈተና የሚያልፍ/የምታልፍ
በሁለተኛ ዲግሪ ለማመልከት የሚያስፈልጉ፦
➫ የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራም መግቢያ ፈተና (NGAT) ያለፈ/ያለፈች
➫ የመጀመሪያ ዲግሪ ኦፊሺያል ትራንስክሪፕት ማቅረብ የሚችል/የምትችል
የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በመገኘት ምልመላ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል።
@tikvahuniversity
በተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና በተከታታይ ሦስት ጊዜ ከ25 በመቶ በታች በሚያስመዘግቡ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ ዕርምጃ እንዲወሰድባቸው የሚፈቅደው መመሪያ ቅሬታ ቀረበበት፡፡
መመሪያው ግልፅ እና ያልተብራራ ነው ሲል የኢትዮጵያ የግል ከፍተኛ ትምህርትና ቴክኒክና ሙያ ተቋማት ማኅበር ቅሬታውን አሰምቷል፡፡
የማኅበሩ ዋና ሥራ አስኪያጅ ተፈራ ገበየሁ፣ ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ ገቢራዊ የሆነው የቅድመ-ምረቃ እጩ ተመራቂዎች የመውጫ ፈተና አወጣጥ በትክክለኛ መንገድ ግምገማ ሳይደረግበት ዕርምጃ የሚያስወስድ መመሪያ ማውጣት አግባብ አይደለም ብለዋል፡፡
በተለይ ከታች ጀምሮ የሚሰጠው ትምህርት ጥራቱ ምን ይመስላል የሚለው መሠረታዊ ጉዳይ ሳይፈተሽ ወደ ዕርምጃ መገባቱ፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ከማቀጨጭና ከዘርፉ ከማስወጣት የዘለለ ምንም ዓይነት ሚና እንደማይኖረው ዋና ሥራ አስኪያጁ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡
መመሪያው የተብራራ ስላልሆነ በድጋሚ እንዲታይ ማኅበሩ ለትምህርት ሚኒስቴር ጥያቄ ማቅረቡን ገልፀዋል፡፡
መመሪያውን በተመለከተም ሆነ ለሌሎች ጥያቄዎች ማኅበሩ ለትምህርት ሚኒስቴር በተደጋጋሚ ጥያቄዎች ቢያቀርብም ምላሽ አለማግኘቱን ዋና ሥራ አስኪያጁ አስረድተዋል፡፡
"በተከታታይ ሦስት ጊዜ በመውጫ ፈተና ከ25 በመቶ በታች ካስመዘገቡ ዕርምጃ ይወሰዳል" የሚለው በተቋም ደረጃ ነው ወይስ በፕሮግራም (በዲፓርትመንት) ያስመዘገቡ ናቸው ለሚለው ጥያቄ መመሪያው ውስጥ እንደሌለ ተናግረዋል፡፡
"የከፍተኛ ትምህርት የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ፈቃድና ፈቃድ እድሳት አሰጣጥ" የሚል ስያሜ የተሰጠው መመሪያው፣ ማንኛውም የከፍተኛ ትምህርት ተቋም ፈቃድ እንዲታደስለት ትምህርት ካጠናቀቁት ውስጥ የወቅቱ ተመራቂዎች ቢያንስ 25 በመቶ የሚሆኑት የመውጫ ምዘናን ፈተና ማሳለፍ ይኖርባቸዋል ይላል፡፡
በኢትዮጵያ የመውጫ ፈተና መስጠት ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ቅበላ በተደረገላቸው ተማሪዎች ላይ ተፈጻሚ እንደሚሆን በመመሪያው ተካቷል፡፡ #ሪፖርተር
@tikvahuniversity
#TVTI
የድኅረ-ምረቃ መግቢያ ፈተና ያለፉ የሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራም ተማሪዎች ትምህርት ግንቦት 11/2017 ዓ.ም እንደሚጀምር የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ገልጿል፡፡
በተገለፀው ቀን ትምህርት መስጠት የሚጀምሩ የሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራሞች፦
➫ ኮንስትራክሽን ቴክኖሎጂና ማኔጅመንት፣
➫ ኤሌክትሪካል አውቶሜሽንና ቁጥጥር ቴክኖሎጂ፣
➫ ኤሌክትሪካል ኮሚዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ፣
➫ የእንጨት ሳይንስ ቴክኖሎጂ።
@tikvahuniversity
2ኛ ዙር የዓለም አቀፍ ግብይት (Import and Export Business) ስልጠና በፒያሣ እና በመገናኛ ካምፓስ ምዝገባ ላይ ነን!
🔔 ፈጥነው ይመዝገቡ!
👉 ተግባርን ከንድፈ ሀሳብ ያስተሳሰረ ስልጠና
👉 ሀገራዊ እና ዓለም አቀፋዊ አሰራሮች የሚተነተኑበት
👉 በዘርፉ ከፍተኛ ልምድ ባላቸው አሰልጣኞች የሚሰጥ
የበለጠ ይጠብቁ ...
ሴጅ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት
☎️ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ
ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ
ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ
Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
#TVTI
#ExitExamRegistration
በቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት በዋና ግቢ እና በሥሩ በሚገኙ የሳተላይት ተቋማት በ2017 ዓ.ም ለምትመረቁ የመደበኛ እና የተከታታይ ፕሮግራም ተማሪዎች እንዲሁም በ2015፣ 2016 እና በ2017 (1ኛ ሴሚስተር) የመውጫ ፈተና ተፈትናችሁ የማለፊያ ውጤት ያላመጣችሁ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ለመውሰድ ምዝገባ ጊዜ ከግንቦት 09-17/2017 ዓ.ም መሆኑን ኢንስቲትዩቱ አሳውቋል።
የምዝገባ ቦታ፦
➫ በ2017 ዓ.ም ሁለተኛ ሴሚስተር ለምትጨርሱ መደበኛ እና ተከታታይ ፕሮግራም ተመራቂዎች ምዝገባው በምትማሩበት ግቢ በየትምህርት ክፍላችሁ ይሆናል፡፡
➫ በሳተላይት ተቋማት ለምትጨርሱ መደበኛ እና ተከታታይ ፕሮግራም ተመራቂዎች በሳተላይት አስተባባሪዎች አማካኝነት በየሳተላይቱ ይሆናል፡፡
➫ በ2015፣ 2016 እና በ2017 አንደኛ ሴሚስተር በተሰጠው የመውጫ ፈተና ተፈትናችሁ የማለፊያ ውጤት ያላመጣችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ቦታ በዋናው ግቢ ICT ትምህርት ክፍል ህንጻ 2 አንደኛ ፎቅ ይሆናል፡፡ በአቅራቢያው የሳተላይት ተቋም ያለ ተፈታኝ በሳተላይት ተቋሙ መመዝገብ ይችላል፡፡
(ተጨማሪ መረጃ ከላይ ተያይዟል።)
@tikvahuniversity
#MoE
በሰኔ 2017 ዓ.ም የሚሰጠው የመውጫ ፈተና መመዝገቢያ ጊዜ እስከ ግንቦት 14/2017 ዓ.ም ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ብቻ መራዘሙን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡
እስካሁን ያልተመዘገባችሁ የድጋሚ ተፈታኞች (Re-sitters) ከዚህ በፊት ለምዝገባ በተከፈተው የመመዝገቢያ ፕላትፎርም (https://exam.ethernet.edu.et) ገብታችሁ ምዝገባችሁን እንድታጠናቅቁ ተብሏል።
ለመጀመሪያ ጊዜ ለመውጫ ፈተና የምትቀመጡ ተፈታኞች በተቋሞቻችሁ በኩል መመዝገባችሁን እንድታረጋግጡ ሚኒስቴሩ አሳስቧል።
የመውጫ ፈተናው ከሰኔ 2-10/2017 ዓ.ም የሚሰጥ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አረጋግጧል።
ለፈተናው የምታመለክቱ አመልካቾች ለመመዝገብ የብሔራዊ መታወቂያ ካርድ (ፋይዳ) ሊኖራችሁ ይገባል፡፡
@tikvahuniversity
⚡️ በዕለታዊ የዳታ ጥቅሎች ቀኑን ሙሉ ፈታ እንበል! 🥳
በM-PESA ላይ ስንገዛ ሁሉም ቅናሽ አላቸው! በልዩ ልዩ አማራጮች የቀረበልንን የሳፋሪኮም የኢንተርኔት ጥቅል የM-PESA Appን በመጠቀም አሁኑኑ እንግዛ! በፈጣን ዳታ እንንበሽበሽ!
🔗 የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናውርድ፦ https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle
የቴሌግራም ቦት /channel/official_safaricomet_bot በመጠቀም የአየር ሰዓት ወይም ልዩ ልዩ ጥቅሎችን እንግዛ!
#MPESASafaricom
#SafaricomEthiopia
#1wedefit
#Furtheraheadtogether
#MoE
የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) አዳዲስ የዩኒቨርሲቲ ሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢዎች ምደባ እየሰጡ ነው።
የገቢዎች ሚኒስትር ዴኤታ የሆኑት አቶ አብዱርህማን ኢድጣሂር ከሚያዝያ 22/2017 ዓ.ም ጀምሮ የወለጋ ዩኒቨርሲቲ ሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው እንዲሠሩ ተመድበዋል።
ወለጋ ዩኒቨርሲቲ ከሚያዝያ 2014 ዓ.ም እስከ ሚያዝያ 2017 ዓ.ም ድረስ ለሦስት ተከታታይ ዓመታት የዩኒቨርሲቲው ሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ላገለገሉት የማዕድን ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሚሊዮን ማቴዎስ አሸኛኘት አድርጓል።
በተመሳሳይ የፍትህ ሚኒስትር ዴኤታ የሆኑት አቶ በላይሁን ይርጋ ከሚያዝያ 22/2017 ዓ.ም ጀምሮ የደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው እንዲሠሩ ተመድበዋል።
@tikvahuniversity
#ETA
የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በሰኔ ወር 2017 ዓ.ም የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና የሚወስዱ ብቁ ዕጩ ተፈታኞችን ዝርዝር በሶፍት እና በሃርድ ኮፒ እስከ ግንቦት 06/2017 ዓ.ም እንዲልኩ በጥብቅ አሳስቧል።
@tikvahuniversity
"በድጋሜ የመውጫ ፈተና የሚወስዱ ተፈታኞች የመፈተኛ ጊዜ አልተራዘመም፡፡" - ትምህርት ሚኒስቴር
የመውጫ ፈተና በድጋሜ ተፈታኞች የፈተና ጊዜን በተመለከተ ትምህርት ሚኒስቴርን ጠይቀናል፡፡
አሁን ላይ የመወጫ ፈተናውን በድጋሜ የሚወስዱ ተፈታኞችን የምዝገባ ሁኔታ እየገመገመ እንደሚገኝ ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡
በድጋሜ የመውጫ ፈተናውን የሚወስዱ ተፈታኞች፥ ለመጀመሪያ ጊዜ ከሚፈተኑት ጋር አብረው ፈተናውን እንደሚወስዱ ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡
ከሚያዝያ 14/2017 ዓ.ም ጀምሮ ሲከናወን የቆየው የቅድመ-ምረቃ ፕሮግራሞች የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ዳግም ተፈታኞች ምዝገባ ነገ ግንቦት 05/2017 ዓ.ም እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል፡፡
በቀሩት ሰዓታት ይመዝገቡ 👇
https://exam.ethernet.edu.et
Note:
በዲሲፕሊን ምክንያት የመውጫ ፈተና ውጤታችሁ የተሰረዘባችሁ የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ የመውጫ ፈተና ማዕከል ድጋሚ ተፈታኞች፤ ፈተናውን በድጋሚ ለመውሰድ ምዝገባ ማድረግ የምትችሉ መሆኑ በሚኒስቴሩ መገለፁ ይታወሳል፡፡
@tikvahuniversity
7ኛ ዙር የኢንቴሪየር ዲዛይን (Interior Design) ስልጠና በመገናኛ ካምፓስ ነገ ማክሰኞ ግንቦት 05/2017 ዓ.ም ይጀምራል።
👉 Sketch-Up, Revit, Rhino, 3D Max እና Lumion ሶፍትዌሮችን በአንድ ላይ
👉 ከንድፈ ሀሳብ እና ሶፍትዌር ስልጠና በተጨማሪ በተግባር በወርክሾፕም የሚሰጥ በመሆኑ ነው።
የበለጠ ይጠብቁ ...
ሴጅ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት
☎️ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ
ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ
ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ
Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
ሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመውጫ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎችን መረጃ ለትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን እንዲልኩ ትምህርት ሚኒስቴር አሳስቧል።
ተቋማቱ የመጨረሻውን ቀን ሳይጠብቁ የተጠየቁትን መረጃ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ እንዲያስገቡ በትምህርት ሚኒስቴር የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አገልግሎት ዴስክ አስገንዝቧል።
ተቋማቱ በሰኔ ወር 2017 ዓ.ም ለሚሰጠው የመውጫ ፈተና ለመጀመሪያ ጊዜ የሚፈተኑ ዕጩ ምሩቃንን ዝርዝር መረጃ እስከ ግንቦት 10/2017 ዓ.ም በሶፍት እና በሃርድ ኮፒ እንዲልኩ መጠየቁ ይታወሳል።
@tikvahuniversity
ለ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ይዘጋጁ!
የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከሰኔ 23 እስከ ሐምሌ 8/2017 ዓ.ም እንደሚሰጥ መገለፁ ይታወቃል፡፡
ለሀገር አቀፍ ፈተናው እየተዘጋጁ ነው?
ተፈታኝ ተማሪ ከሆኑ ከታች የተቀመጠውን ሊንክ በመጫን ለፈተናው በቂ ዝግጅት ለማድረግ የሚያስችሉ ትምህርቶችን ማግኘት ይችላሉ።
በትምህርት ሚኒስቴር የተዘጋጁ የቲቶርያል ቪዲዮዎችን ለማግኘት 👇
https://examinfo.moe.gov.et/guides
@tikvahuniversity