tikvahuniversity | Unsorted

Telegram-канал tikvahuniversity - Tikvah-University

308824

Subscribe to a channel

Tikvah-University

#ጥቆማ

5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደሮች ኢንሼቲቭ ነፃ ስልጠናን ለመከታተል ይመዝገቡ።

ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው ሰርትፍኬት ማግኘት የሚያስችልዎትን ስልጠና ባሉበት ሆነው ይውሰዱ።

የስልጠና ዘርፎች፦

► ዌብ ፕሮግራሚንግ
► አንድሮይድ ማበልፀግ
► ዳታ ሳይንስ
► አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ፋንዳሜንታልስ

ለመመዝገብ 👇
https://www.ethiocoders.et/

በስምንት ሳምንት ስልጠናውን ሲያጠናቅቁ፥ ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው ሰርተፊኬት ይበረከትልዎታል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው አደረሳችሁ!

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምትገኙና በዓሉን ከቤተሰቦቻችሁ ርቃችሁ እያከበራችሁ ላላችሁ ተማሪዎች መልካም በዓል እንመኛለን።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

#BongaUniversity

ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ተመድቦለታል።

ደገላ ኤርገና (ዶ/ር) ከሚያዝያ 07/2017 ዓ.ም ጀምሮ የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ሆነው እንዲሠሩ የተወከሉ መሆኑን በትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በቀን ሚያዝያ 01/2017 ዓ.ም ተፈርሞ የወጣ ደብዳቤ ያሳያል።

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት በመሆን ላለፉት ዓመታት ሲያገለግሉ የቆዩት ጴጥሮስ ወ/ጊዮርጊስ (ዶ/ር) ከኃላፊነታቸው የተነሱበት ምክንያት አልተገለፀም።

ጴጥሮስ ወ/ጊዮርጊስ (ዶ/ር) ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ከምስረታው ጀምሮ አሁን ለደረሰበት ስኬት በርካታ አበርክቶ እንደነበራቸው በመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጭምር ከዚህ ቀደም ሲገለፅ እንደነበር አይዘነጋም።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

M-PESA ታላቅ የበዓል ቅናሽ!

የበዓል ግብይታችንን በ M-PESA እንክፈል፣ 10% ተመላሽ እናግኝ!

እና ምን እንጠብቃለን ሸመት ሸመት እናድርግ!

#MPESAEthiopia #MPESASafaricom

Читать полностью…

Tikvah-University

✝ እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት መታሰቢያ በዓል አደረሳችሁ!!

ዕለቱ መልካም የምናደርግበት፥ የተቸገሩን የምንረዳበት እና አምላካችንን የምናስብበት እንዲሆን ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ይመኛል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

🌐 እጅግ ፈጣን ዋይፋይ በአዲስ ቅመም! ሊያውም ከጉርሻ ጋር!

💨⚡️ እስከ 6 ሰዓት የሚቆይ የባትሪ አቅም ያለውና አዳዲስ የቴክኖሎጂ ትሩፋቶችን ይዞ በአንዴ እስከ 8 ሰው የሚያስጠቅመውን ልዩ ቅመም MIFI ን ገዝተን ፈጣን 4G ኢንተርኔት እንጠቀም!

🍰 ለ30 ቀን ከሚቆይ ነጻ 30ጊባ ዳታ ጉርሻ ጋር!

ከሳፋሪኮም ጋር አንድ ወደፊት⚡️

#SafaricomEthiopia

Читать полностью…

Tikvah-University

የሙስሊም ሴት ተማሪዎች ሂጃብ ጉዳይ

የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) በትምህርት ዘርፍ የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጻም ላይ በሕ/ተ/ም/ቤት ተገኝተው ማብራሪያ መስጠታቸው ይታወቃል፡፡

የምክር ቤቱ አባላት ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ከሂጃብ ጉዳይ ጋር በተያያዘ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ችግር እየገጠማቸው መሆኑን አንስተዋል፡፡

በጉራጌ ዞን ጉንችሬ ከተማ፣ በትግራይ ክልል አክሱም ከተማ አንዲሁም በዲላ ዩኒቨርሲቲ ከሂጃብ ጋር በተያያዘ ችግሮች መከሰታቸውን ያነሱት አባላቱ፤ በጉዳዩ ላይ መንግሥት ዘላቂ መፍትሔ እንዲያስቀምጥ ጠይቀዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) ምን አሉ?

"የኢትዮጵያ ሕግና ደንቦች፥ በዚህ ጉዳይ ላይ የወጡት ደንቦች ሂጃብ ለብሶ ትምህርት መማርን የሚከለክል የኢትዮጵያ ሕግ የለም፡፡ በሂጃብ ምክንያት፥ ማንም ሂጃብ ለበሰ ተብሎ ትምህርት ቤት መከልከል አይችልም፡፡"

"ኒቃብ ግን የተለየ ነው፡፡ ህጻናቶች፣ ልጆች ባሉበት ትምህርት ቤት የአንድ ሰው ፊት ተሸፍኖ በሚገባ ጊዜ የsecurity risk (የደኅንነት ስጋት) አለው፡፡"

"ከመጅሊስ ሰዎች ጋር ተሰብስበን፣ ተወያይተን፣ ተማምነናል፡፡ በኒቃብ ላይ ሕግ ማስቀየር ካለባችሁ እዚሁ ፓርላማ በማምጣት ማስቀር ነው እንጂ፣ በየጊዜው Issue እየሆነ የግጭት ምክንያት መሆን የለበትም፡፡" "አሁን ያለው ሕግ ግን ሂጃብ በምንም ምክንያት የትም ቦታ መከልከል የለበትም፡፡"

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

4ኛ ዙር የፋይናንስ እና ካፒታል ማርኬት ስልጠና በፒያሣ እና በመገናኛ ካምፓስ ምዝገባ ላይ ነን።

🔔 ፈጥነው ይመዝገቡ!

የካፒታል ማርኬት ገበያ በኢትዮጵያ ተጀምሯል። እርስዎም በሴጅ ኢንስቲትዩት የሚሰጠውን የፋይናንስና ካፒታል ማርኬት ስልጠና በመውሰድ በገበያው ለመሳተፍ ራስዎን ያዘጋጁ።

ብቁ በሆኑ መምህራን የሚሰጠውን ስልጠና ይውሰዱና ትግበራውን ይጠባበቁ!

☎️   0906777799 / 0906777755
አድራሻ
ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ
ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ

Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute

Читать полностью…

Tikvah-University

#BongaUniversity

ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በተፈጥሮ ሃብት አያያዝ እና አጠባበቅ ላይ ትኩረት የሚያደርጉ የጥናት ውጤቶች የሚወጡበት ማኪራ ጆርናል (Makira Journal of Natural Resource Management) ህትመት አስጀመረ።

የጆርናሉ ህትመቱ ይፋዊ የማስጀመሪያ ስነ-ስርዓት በዛሬው ዕለት ተካሒዷል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

#JigjigaUniversity

በ2017 ዓ.ም ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ ሬዚደንት ሐኪሞች የምዝገባ ጊዜ ሚያዝያ 13 እና 14/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ለምዝገባ የሚያስፈልጉ፦
➫ ዲግሪ እና ስቱደንት ኮፒ ዋናውና ኮፒው
➫ ኦፊሺያል ትራንስክሪፕት ለዩኒቨርሲቲው ሬጅስትራር በፖ.ሳ.ቁ. 1020 ማስላክ
➫ የ 'NGAT' ውጤት
➫ የስፖንሰርሺፕ ደብዳቤ
➫ የሥራ መልቀቂያ ይሰሩበት ከነበረ ተቋም
➫ ሁለት ፓስፖርት መጠን ፎቶግራፍ

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

#HaramayaUniversity

በ2017 ዓ.ም ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ሕክምና ትምህርት ቤት አዲስ የተመደባችሁ ሬዚደንት ሐኪሞች የምዝገባ ጊዜ ከሚያዝያ 16-18/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ለምዝገባ የሚያስፈልጉ፦

➫ ከ8-12ኛ ክፍል የትምህርት ማስረጃዎች
➫ አራት ፓስፖርት መጠን ፎቶግራፍ
➫ ዲግሪ እና ስቱደንት ኮፒ ዋናውና ኮፒው
➫ የሥራ መልቀቂያ ይሰሩበት ከነበረ ተቋም
➫ የስፖንሰርሺፕ ደብዳቤ (በጤና ሚኒስቴር ስፖንሰር ከተደረጉ ውጪ)
➫ የ 'NGAT' ውጤት
➫ ኦፊሺያል ትራንስክሪፕት ለሬጅስትራር ጽ/ቤት በፖ.ሳ.ቁ. 235 ማስላክ

ገለጻ (Orientation) ሚያዝያ 19/2017 ዓ.ም የሚሰጥ ሲሆን፤ ሚያዚያ 23/2017 ዓ.ም ትምህርት ይጀመራል ተብሏል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) በትምህርት ዘርፍ የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጻምና የቀጣይ ሦስት ወራት ዕቅዶች ላይ በሰጡት ማብራሪያ ካነሷቸው ነጥቦች፦

◉ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ከአንድ ወር ተኩል በኋላ ይሰጣል፣

◉ ዘንድሮ ለ150 ሺህ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ፈተናውን በኦንላይን ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል፣

◉ 84 ሺህ መምህራንን በመጪው ክረምት ለማሰልጠን ዕቅድ ተይዟል፣

◉ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የሚማሩ 3ኛ ዓመት የጨረሱ ተማሪዎች፥ ከ2019 ዓ.ም ጀምሮ 4ኛ ዓመት ከመግባታቸው በፊት የአንድ ዓመት አገልግሎት እንዲሰጡ ይደረጋል፣

◉ የኮምፒውተር መገጣጠሚያ ፋብሪካ ለማቋቋም ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጋር በጋራ እየሠራን ነው፡፡ ከመስከረም 2018 ዓ.ም ጀምሮ ማምረት ይጀምራል፡፡

@tikvauniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

📍የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መንደር ፕሮጀክት

ፕሮጀክቱ በአዲስ አበባ ከተማ ፕላንና ልማት ቢሮ እና በትምህርት ሚኒስቴር በጋራ የተጠና ነው።

የዩኒቨርሲቲ መንደሩ የኃይማኖት ተቋማት፣ ሙዝየም፣ የምርምር ተቋማት፣ የገበያ ማዕከላት፣ ትምህርት ቤቶች እና የመኖሪያ መንደር ይኖረዋል።

የዩኒቨርሲቲ መንደሩ በሰሜን የሽሮ ሜዳ የገበያ ማዕከልን፣ በደቡብ የአብርሆት ቤተ መፃሕፍትን፣ በምስራቅ የግንፍሌ እና የቀበና ወንዝን፣ በምዕራብ የቀጨኔ ወንዝ ዳርቻን ያካልላል ተብሏል።

የመንደር ግንባታውን በተለያየ ምዕራፍ በአስር ዓመት ለማጠናቀቅ ዕቅድ ተይዟል። #ኢፕድ

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ከተቋሙ መምህራን ጋር በመተባበር ያበለፀጋቸው አራት ሶፍትዌሮች ከኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለስልጣን የቅጅና ተዛማጅ መብቶች ሥራ የምዝገባ የምስክር ወረቀት አጊኝተዋል።

የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያገኙ የተቋሙ ሶፍትዌሮች፦

➫ የለሊት ትራንስፖርት ስምሪት መከታተያ እና ማስተዳደሪያ ስርዓት (Night Transport Dispatching and Management System)
➫ የደብዳቤ እና ማህደር አስተዳደር ስርዓት (Letter Management and Archival System)
➫ የወንጀሎች መዝገብ እና የመረጃ አስተዳደር ስርዓት (Crime Record Information and Managment System)
➫ የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና የሮስተር ማስተዳደሪያ፣ ፈተና ማረሚያ፣ ውጤት ማደራጃና ማስተዳደሪያ ስርዓት (Web Based Ministry Exam Scoring, Rostering, and Record Management System)

መተግበሪያዎቹን ያበለፀጉት ጋዲሳ ኦላኒ (ዶ/ር)፣ መ/ር ዳመና ደስታ፣ መ/ር አንድነት አሰፋ እና መ/ር ጌትነት ቶሎሳ የተባሉ የዩኒቨርሲቲው መምህራንና ተመራማሪ መሆናቸው ተገልጿል።

ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በአጠቃላይ ስምንት የሶፍትዌር የምዝገባ ምስክር ወረቀቶች ማግኘቱን ገልጿል፡፡

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

#ጥቆማ

5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደሮች ኢንሼቲቭ ነፃ ስልጠናን ለመከታተል ይመዝገቡ።

ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው ሰርትፍኬት ማግኘት የሚያስችልዎትን ስልጠና ባሉበት ሆነው ይውሰዱ።

የስልጠና ዘርፎች፦

► ዌብ ፕሮግራሚንግ
► አንድሮይድ ማበልፀግ
► ዳታ ሳይንስ
► አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ፋንዳሜንታልስ

ለመመዝገብ 👇
https://www.ethiocoders.et/

በስምንት ሳምንት ስልጠናውን ሲያጠናቅቁ፥ ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው ሰርተፊኬት ይበረከትልዎታል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

እንኳን ለጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳዔ በዓል አደረሳችሁ!

ለክርስትና ዕምነት ተከታዮች በሙሉ መልካም የብርሃነ ትንሣኤ በዓል እንመኛለን። በዓሉ የሰላም፣ የደስታ፣ የፍቅር እና የመተሳሰብ ይሁንልዎ።

የበለጠ ይጠብቁ ...
ሴጅ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት

☎️   0906777799 / 0906777755
አድራሻ
ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ
ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ

Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute

Читать полностью…

Tikvah-University

በፌዴራል ተቋማት ላይ በተደረገ ፍተሻ የ129 የመንግሥት ሠራተኞች የትምህርት ማስረጃ ሐሰተኛ ሆኖ ተገኘ።

የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) የተቋማቸውን የዘጠኝ ወር ሪፖርተር ለህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ባቀረቡት ወቅት እንደገለፁት፥ ትምህርት ሚኒስቴር የፌዴራል መስሪያ ቤት ሠራተኞችን የትምህርት ማስረጃ የማጣራት ሥራ እያከናወነ ይገኛል።

በመጀመሪያ ዙር ከ280 የፌዴራል እና ተጠሪ ተቋማት መስሪያ ቤቶች ከሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የተላከ መረጃን መሠረት በማድረግ የ32,815 ሰራተኞች የትምህርት ማስረጃ ትክክለኛነት መጣራቱን አብራርተዋል።

በዚህም 129 ሐሰተኛ የትምህርት ማሰረጃ የተገኘ ሲሆን፤ የ469 ሰራተኞች መረጃ ያልተሟላ በመሆኑ ለሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ተመላሽ ተደርጓል ብለዋል።

ከ2017 ዓ.ም ጀምሮ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተመራቂዎች የዲግሪ ሰርተፊኬት ህትመት በአንድ ማዕከል ማለትም በትምህርት ሚኒስቴር እንደሚታተም መገለፁ ይታወቃል። #ኢፕድ #GazettePlus

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

ዲላ ዩኒቨርሲቲ ለ2017 ዓ.ም ዕጩ ተመራቂዎች #ሞዴል የመውጫ ፈተና ሰጥቷል።

በዩኒቨርሲቲው የትምህርትና ስነ-ባህሪ ኮሌጅ እና የኢንጂነሪንግና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ ዕጩ ተመራቂዎች ሞዴል የመውጫ ፈተና መውሰዳቸወሰ ተገልጿል።

በቀጣይ የዩኒቨርሲቲው ሌሎች ኮሌጆች ለዕጩ ተመራቂዎቻቸው ሞዴል የመውጫ ፈተና ይሰጣሉ ተብሏል።

ቀጣዩ ሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና በሰኔ 2017 ዓ.ም ለሁሉም የመንግሥት እና የግል ዕጩ ተመራቂዎች እንደሚሰጥ ይታወቃል።

ፈተናውን ለመውሰድ ብሔራዊ የዲጂታል መታወቂያ (ፋይዳ) ማውጣት የግድ እንደሆነ መገለፁ አይዘነጋም።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

ዛሬ በክርስትና ኃይማኖት ተከታዮች ዘንድ ልዮ ቀን ነው። መልካም የጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት መታሰቢያ በዓል ይሁንላችሁ።

መልካም በዓል! 

የበለጠ ይጠብቁ ...
ሴጅ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት

☎️   0906777799 / 0906777755
አድራሻ
ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ
ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ

Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute

Читать полностью…

Tikvah-University

#HaramayaUniversity

ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በኢትዮጵያና የአፍሪካ ቀንድ ታሪክ የዶክትሬት ዲግሪ ትምህርት መስጠት ሊጀምር ነው።

በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የኅብረተሰብ ሳይንስና ስነ-ሰብ ትምህርት ኮሌጅ ሦስት አዳዲስ ፕሮግራሞችን ለመጀመር የስርዓተ ትምህርት የውስጥ ክለሳ አካሒዷል።

አዲስ የሚጀመሩ የትምህርት ፕሮግራሞች፦

➫ የኢትዮጵያና የአፍሪካ ቀንድ ታሪክ በዶክትሬት ዲግሪ
➫ የባህልና ቅርስ ጥናት በማስተርስ ዲግሪ
➫ ፖለቲካል ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት በመጀመሪያ ዲግሪ

በቀጣይ የውጭ ክለሳ በማድረግ በ2018 የትምህርት ዘመን በፕሮግራሞቹ ትምህርት ለማስጀመር እየተሠራ መሆኑ ተገልጿል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

“ እንዳንማር ነው እንዴ የተፈለገው? ውጤቱ የማይያዝልን ከሆነ ለምን ሪሚዲያል ተፈተንን ?” - የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች

“ ከትምህርት ሚኒስቴር የመጣ መመሪያ ነው” - የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ኅብረት
 

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ አንደኛ ዓመት ጀማሪ የሕግ ተማሪዎች ፊልድ ለመምረጥ የሪሚዲያል ውጤታቸው ብቻ አለመያዙን፣ ሪሚዲያል ከተፈተኑ ከ90 በላይ ተማሪዎች 40 የሚሆኑት ውጤታቸውን ባለማወቃቸው ቅሬታ አሰሙ።

የኢንትራንስ ውጤታቸው ከሪሚዲያል ጋር ተደምሮ ፊልድ ለመምረጥ እንደ መስፈርት መያዙን፣ የሪሚዲል ፈተና ውጤታቸው ከፍተኛ ቢሆንም የኢንትራንሱ በመያዙ ዝቅ ስለሚያደርገው የሚፈልጉትን ፊልድ መምረጥ እንዳልቻሉ ተማሪዎቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

በሌላ በኩል፣ ሪሚዲያል ከተፈተኑት 96 የሕግ ተማሪዎች መካከል ውጤት የተለቀቀላቸው የ40ዎቹ ብቻ እንደሆነ፣ ቀሪዎቹ ውጤታቸውን እንዳላወቁ ገልጸዋል።

ተማሪዎቹ አክለው ምን አሉ?

“ለፊልድ መረጣ በ12ኛ ክፍል ውጤት ወይም በሪዛልቱ ሳይሆን መያዝ የነበረበት በሪሚድያሉ ብቻ ነበረበት። በተጨማሪ ውጤቱ የሁላችንም ተማሪዎች ሙሉ መለቀቅ ነበረበት። 96 ተማሪዎች ተፈትነዋል የተለቀቀው የ40ዎቹ ነው። ለምን የሁሉም አልተለቀቀም?።

ማለፍ ወይም መውደቃችንን ለማወቅ ግዴታ የሁሉም ተማሪዎች ውጤት መለቀቅ ይኖርበታል። ባለመለቀቁ ብዙ ተማሪ ችግር ሊያጋጥመው ይችላል። ውጤታችን ሳይለቀቅ ፈተናውን ራሱ በትክክል እንዳረሙትና እንዳላረሙት በምን ልናቀው እችላለን? 

እንዳንማር ነው እንዴ የተፈለገው? ውጤቱ የማይያዝልን ከሆነ ለምን ሪሚዲያል ተፈተንን?” ሲሉ ጠይቀዋል።

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ኀብረት ምን አለ?

ለተማሪዎቹ ቅሬታ የጠየቅነው የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ኀብረት፣ “ጥያቄው አግባብነት ያለው ጥያቄ ነው ብለንም አናስብም” የሚል ምላሽ ሰጥቷል።

“ምክንያቱም መመሪያ ላይ የነበረ ነገርን ነው እየተገበረ ያለው ሪጅስትራር ስናወራ ያገኘነው ነው። 20% የኢንትራስ ውጤትን 30% ትምርት ክፍል ያዘጋጀው ሲኦሲና 50% ኮምሌቲቭ ጂፒያቸው መሰረት ነው የተወዳደሩት።

ያ ደግሞ ከትምህርት ሚኒስቴር የመጣ መመሪያ ነው በዛ መመሪያ መሰረት ነው ሪጅስትራሉ እየሰራ ያለው” ብሏል።

የ40ዎቹ ውጤት ተለቆ የሌሎቹ ያልተለቀቀውስ ለምንድን ነው? ስንል ላቀረብንለት ጥያቄ በሰጠን ምላሽ፣ “ያለፉት ተማሪዎች ውጤት ነው የሚለቀቀው። እነዚህን ተማሪዎች ተቀብለናል እነዚህ ተማሪዎች አልፈዋል፣ ተብሎ ነው የሚለቀቀው” የሚል ምላሽ ሰጥቷል።

የተፈተኑ ተማሪዎች ወጤቱ ተለቆ ማለፍ/አለማለፋቸው መነገር አልነበረባቸውም? የሚለውን ጥያቄም፣ “ውጤቱን ማየት የሚፈልግ ሪጅስትራል መጥቶ ማየት ይችላል። ያለፉት ተማሪዎች ስማቸው ወደ ኮሌጅ ስለሚተላለፍ ወደምዝገባው ነው የሚቀጥሉት” ሲል መልሷል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

Tikvah-University

በደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ በ2017 ዓ.ም ሁለተኛ ሴሚስተር በሕግ እና በአይቲ የድኅረ-ምረቃ ትምህርት ለመከታተል ያመለከታችሁ ተማሪዎች ምዝገባ ማክሰኞ ሚያዝያ 14/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

የአይቲ የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራም ትምህርት ሚያዝያ 15/2017 ዓ.ም፤ የሕግ ደግሞ ሚያዝያ 18/2017 ዓ.ም ይጀምራል ተብሏል፡፡

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

#DireDawaUniversity

ዘመናዊ የመልቲ ሚዲያ ስቱዲዮ ግንባታ በተመረጡ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች እየተከናወነ እንደሚገኝ ይታወቃል።

ስቱዲዮዎቹ የዲጂታል ትምህርትን ለማጠናከር ትልቅ ፋይዳ እንደሚኖራቸው ይታመናል።

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ መልቲ ሚዲያ ዲጂታል ስቱዲዮ (ምስል ተያይዟል) የምስራቅ ኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች የበይነ መረብ ትምህርት (E-Learning) ሪሶርስ ማዕከል በመሆን ያገለግላል ተብሏል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

#HawassaUniversity

በ2017 ዓ.ም ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ ሬዚደንት ሐኪሞች የምዝገባ ጊዜ ሚያዝያ 14 እና 15/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ለምዝገባ የሚያስፈልጉ፦
➫ ዲግሪ እና ስቱደንት ኮፒ ዋናውና ኮፒው
➫ ሁለት ፓስፖርት መጠን ፎቶግራፍ
➫ የስፖንሰርሺፕ ደብዳቤ (በጤና ሚኒስቴር ስፖንሰር ከተደረጉት ውጪ)
➫ የ 'NGAT' ውጤት
➫ የሥራ መልቀቂያ (Clearance) ይሰሩበት ከነበረ ተቋም

ምዝገባውን ለማድረግ ኦፊሺያል ትራንስክሪፕት በኢሜል (registrar@hu.edu.et) ወይም በፖ.ሳ.ቁ. 05 አስቀድሞ ማስላክ ያስፈልጋል።

ምዝገባው በዩኒቨርሲቲው የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ሬጅስትራር ቢሮ የሚከናወን ሲሆን፤ ከዋናው ግቢ ሬጅስትራር እና ከድኅረ-ምረቃ ትምህርት ቤት የ “Admission” እና የ “Acceptance” ደብዳቤ መያዝ ይጠበቅባችኋል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

5ኛ ዙር የፎቶግራፊ፣ ቪዲዮግራፊ፣ ግራፊክ ዲዛይን እና ቪዲዮ ኤዲቲንግ ስልጠና በፒያሣ እና በመገናኛ ካምፓስ ምዝገባ ላይ ነን። 

👉 ተግባርን ከንድፈ ሀሳብ ያስተሳሰረ ስልጠና
👉 Photography, Videography, Cinematography, Graphic Design and Video Editing በአንድ ላይ
👉 ፕሮጀክቶችን በስቱዲዮ እና በመስክ በመስራት የሚሰጥ

☎️   0906777799 / 0906777755
አድራሻ
ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ
ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ

Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute

Читать полностью…

Tikvah-University

#Phones_Ban_In_Schools

ተማሪዎች ሞባይል ስልክ ይዘው ወደ ትምህርት ቤት እንዳይሔዱ ክልከላ ሊቀመጥ ነው።

ተማሪዎች ሞባይል ስልክ ይዘው ወደ ትምህርት ቤት እንዳይገቡ ለማድረግ እንቅስቃሴ መጀመሩን የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ተናግረዋል።

ሚኒስትሩ በትምህርት ዘርፍ የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጻምና የቀጣይ ሦስት ወራት ዕቅዶች ላይ ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት እንደገለፁት፤ በቀጣይ ሳምንት ከክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች ጋር በስልክ ክልከላው ላይ ውይይት እንደሚካሔድ ገልፀዋል።

የጋራ ስምምነት ላይ ከደረስን ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ ተማሪዎች ስልክ ወደ ትምህርት ቤት ይዘው እንዳይሔዱ ይደረጋል ብለዋል።

@tikvauniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

የኮምፒውተር ፕሮግራሚንግ እና ዳታቤዝ (Computer Programming and Database) ስልጠና በፒያሣ እና በመገናኛ ካምፓስ ምዝገባ ላይ ነን።

🔔 ፈጥነው ይመዝገቡ!

👉 ተግባርን ከንድፈ ሀሳብ ያስተሳሰረ ስልጠና
👉 C++, Java እና Python ፕሮግራሞች በ Advanced Level በጋራ የሚሰጡበት
👉 ፕሮጀክቶችን እየሠሩ የሚሰለጥኑበት

☎️   0906777799 / 0906777755
አድራሻ
ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ
ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ

Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute

Читать полностью…

Tikvah-University

#BahirDarUniversity

ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የ TOEFL ምዘና ፈተና መስጠት ሊጀምር ነው፡፡

ዩኒቨርሲቲው በዓለም አቀፍ ደረጃ የተረጋገጠ የፈተና አስተዳደር አገልግሎቶች በመሰጠት ከሚታወቀው የትምህርት ፈተና አገልግሎት (ETS) ተቋም የ TOEFL iBT ፈተና ማዕከል ሆኖ ፈቃድ አጊኝቷል፡፡

ኢንተርኔትን መሰረት ያደረገ የ TOEFL የእንግሊዘኛ ቋንቋ ምዘና፤ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለመቀላቀል፣ ለሙያ እድገት እንዲሁም ለስኮላርሺፕ ዕድሎች አስፈላጊ መሆኑ ይታወቃል፡፡

በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የ TOEFL ፈተና ማዕከል ፔዳ ግቢ፣ ፈተናውን ለመውሰድ የአመልካቾች የኦንላይን ምዝገባ በቅርቡ እንደሚጀምር ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ለበለጠ መረጃ፦
☎️ +251911816361
📧 toefl.center@bdu.edu.et

@tikvahuniveristy

Читать полностью…

Tikvah-University

7ኛ ዙር IFRS and Asset Valuation ስልጠና በፒያሣ እና በመገናኛ ካምፓስ በምዝገባ ላይ ነን።

👉 IFRS + Peachtree + Asset Valuation + IFRS Conversion + IPSAS + Quick Book በአንድ ላይ 
👉 ስልጠናው ሙሉ በሙሉ በተግባር የተደገፈና ፒስትሪ (Peachtree Software) ላይ የሚሰጥ ነው።

☎️   0906777799 / 0906777755
አድራሻ
ቁ.1:
ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ
ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ

Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute

Читать полностью…

Tikvah-University

#SPHMMC

በ2017 ዓ.ም በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሕክምና ኮሌጅ የተመደባችሁ ሬዚደንት ሐኪሞች የምዝገባ ጊዜ ሚያዝያ 14 እና 15/2017 ዓ.ም መሆኑን ኮሌጁ አሳውቋል።

ገለጻ (Orientation) ሚያዝያ 16 እና 17/2017 ዓ.ም የሚሰጥ ሲሆን፤ ሚያዚያ 20/2017 ዓ.ም ትምህርት ይጀመራል ተብሏል።

ለምዝገባ የሚያስፈልጉ፦

➫ የስፖንሰርሺፕ ደብዳቤ
➫ የመጀመሪያ ዲግሪ እና ስቱደንት ኮፒ
➫ የሥራ መልቀቂያ
➫ ሁለት ጉርድ ፎቶግራፍ
➫ ኦፊሺያል ትራንስክሪፕት ለኮሌጁ ማስላክ
➫ የ 'NGAT' ያለፉበት ሰርተፍኬት

የምዝገባ ቦታ፦ በኮሌጁ የሬጅስትራር ጽ/ቤት፣ የሰው ሀብት ልማት አስተዳደር

በተጨማሪም የቅጥር ውል ለመግባት መሟላት ያለባቸው፦

➫ የጤና ሚኒስቴር ውል የገቡበት ሰነድ
➫ የመጀመሪያ ዲግሪ እና ስቱደንት ኮፒ
➫ የሥራ መልቀቂያ
➫ ሁለት ጉርድ ፎቶግራፍ

ለበለጠ መረጃ፦ 0118965125

@tikvahuniversity

Читать полностью…
Subscribe to a channel