tikvahethsport | Unsorted

Telegram-канал tikvahethsport - TIKVAH-SPORT

256797

Subscribe to a channel

TIKVAH-SPORT

“ አላማችን ሊጉን ማሸነፍ ነው “ ሉክ ሾው

እንግሊዛዊው የማንችስተር ዩናይትድ የመስመር ተጨዋች ሉክ ሾው በቀጣዩ የውድድር አመት የቡድናቸው አላማ ሊጉን ማሸነፍ መሆኑን ተናግሯል።

" የፕርሚየር ሊጉን ዋንጫ ማሸነፍ ማለም አለብን " ያለው ሉክ ሾው “ እኔ ብቻ አይደለሁም ቡድኑ ውስጥ ሁሉም እንደዚህ እንደሚያስቡ እርግጠኛ ነኝ " ብሏል።

" አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም መገናኛ ብዙሀን ፊት ይህንን ባይናገሩትም ሁላችንም ሊጉን የማሸነፍ ህልም እና እምነት እንጋራዋለን።" ሉክ ሾው

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

Читать полностью…

TIKVAH-SPORT

የሊቨርፑል ባለቤቶች አዲስ ክለብ ሊገዙ ነው !

የመርሲሳይዱን ክለብ ሊቨርፑል በባለቤትነት የያዘው " FSG " የስፔኑን ክለብ ሄታፌ ለመግዛት በንግግር ላይ መሆናቸው ተገልጿል።

የስፔን ላሊጋው ክለብ ሄታፌ የሽያጭ ገንዘብ 100 ሚልዮን ፓውንድ ሊሆን እንደሚችል ተዘግቧል።

የሊቨርፑል ባለቤት " FSG " አሁን ላይ ከሄታፌ ባለቤት ጋር በሽያጩ ዙሪያ ንግግር በማድረግ ላይ መሆናቸው ተገልጿል።

ሄታፌ ባለፈው የውድድር አመት በስፔን ላሊጋ 13ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቋል።

ክለቡ ባለፉት ሀያ ሁለት የውድድር አመታት በሀያ አንዱ በስፔን የመጀመሪያ ሊግ ላሊጋ መወዳደር ችለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

Читать полностью…

TIKVAH-SPORT

ጆሬል ሀቶ በቼልሲ ምን አይነት ሚና ይኖረዋል ?

ስፔናዊው ተከላካይ ማርክ ኩኩሬላ ባለፈው የውድድር አመት የቡድኑን የግራ መስመር በብቸኝነት ነበር የመራው።

ተጨዋቹን የሚያግዝ ተፈጥሯዊ የግራ መስመር ተጨዋች አለመኖሩ የአሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካን ቡድን በቦታው ላይ አሳስቶታል።

ባለፈው አመት ማሎ ጉስቶ በግራ መስመር ቦታ ተሰልፎ በመጫወት ቢያገለግልም ለእሱ የበለጠ ምቹ ቦታ የቀኝ መስመር እንደሆነ ይታወቃል።

በሌላ በኩል የማርክ ኩኩሬላ አጋዥ ይሆናል ተብሎ ታስቦ የነበረው ሬናቶ ቬጋ የኢንዞ ማሬስካን እምነት ማግኘት ሳይችል ባለፈው ጥር ወር በውሰት አቅንቷል።

ፖርቹጋላዊው ተጨዋች ሬናቶ ቬጋ በዚህ ክረምት ቼልሲን በቋሚነት ይለቃል ተብሎ ይጠበቃል።

ጆሬል ሀቶ ከማርክ ኩኩሬላ የተለየ ተክለሰውነት ቢኖረውም ተመሳሳይ አስደናቂ ብቃቶች መያዙ ይነገራል።

ተጨዋቹ ኳስ ይዞ ወደ ተቃራኒ ግብ ክልል መሄድ እና ለቡድን አጋሮቹ ማቀበል እንዲሁም ወደ መሐል ሜዳው በመውጣት የቡድን አጋሮቹን ማገዝ ይችላል።

ጆሬል ሀቶ ከአብዛኞቹ ተከላካዮች አንፃር ሲታይ በግብ አስቆጣሪነት ረገድ የተሻለ ተጨዋች መሆኑ ተገልጿል።

ተጨዋቹ በመሐል ተከላካይ ቦታ ተሰልፎ መጫወት መቻሉ ለቼልሲ ተጨማሪ አማራጭ በመሆን ሌላ እድል ይሰጣል።

ከወራት በፊት 19ዓመቱን የያዘው ጆሬል ሀቶ በትንሽ እድሜው ከወዲሁ 100 ፕሮፌሽናል ጨዋታዎች አድርጓል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

Читать полностью…

TIKVAH-SPORT

የኪሊያን ምባፔ አዲስ ማልያ ቁጥር !

በሪያል ማድሪድ ቤት ይበልጥ የሚከበረው ቁጥር 7️⃣ ቢሆንም ከእሱ ቀጥሎ 1️⃣0️⃣ ቁጥር ማልያ የተለየ ቦታ ይሰጠዋል።

ከዚህ በፊት የክለቡ ታሪካዊ ተጨዋቾች ማልያውን ለብሰው ደማቅ ታሪክ በመፃፍ በክለቡ አሻራቸውን ያኖሩበት ቁጥርም ነው።

ከእነዚህ መካከልም :-
- ሉካ ሞድሪች
- ሉዊስ ፊጎ
- ዌስሌይ ሽናይደር
- ሲዶርፍ
- ሜሱት ኦዚል እና
- ሚኬል ላውድሩፕ ይጠቀሳሉ።

ኪሊያን ምባፔ በበኩሉ በልጅነቱ ከቁጥሩ ጋር የግል ግንኙነት እንዳለው ከዚህ በፊት ታይቷል።

ምባፔ በታዳጊነቱ ለመጫወት የሚያልመውን ሪያል ማድሪድ ማልያ ለብሶ በሚታየው ምስል የለበሰው የ 1️⃣0️⃣ ቁጥር ማልያ ነበር።

ቁጥሩን ለመውሰድ የክለቡ ነባር ተጨዋቾች ጓጉተውለት የነበረ ቢሆንም ሪያል ማድሪድ “ በጣም ልዩ ለሆነ ተጨዋች ልዩ ቁጥር " በሚለው አቋሙ ለምባፔ ሰጥቷል።

በክለቡ ውስጥ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው የ 7️⃣ ቁጥር ማልያ በቪንሰስ ጁኒየር መያዙ ይታወቃል።

በሌላ በኩል ሪያል ማድሪድ ከምባፔ ማልያ መቀየር ትልቅ የንግድ ተፅዕኖ ይፈጥራል ብለው እንደሚጠብቁ ተገልጿል።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe

Читать полностью…

TIKVAH-SPORT

" ፈተና የምወድ አይነት ተጨዋች ነኝ " ምቤሞ

የቀያይ ሴጣኖቹ የፊት መስመር ተጨዋች ብሪያን ምቤሞ ማንችስተር ዩናይትድ ለእሱ የሚስማማ ክለብ ሆኖ እንዳገኘው ገልጿል።

" ማንችስተር ዩናይትድ ትልቅ ክለብ ነው " ያለው ብሪያን ምቤሞ " ለእኔ ትልቅ እድል ይመስለኛል ፤ ፈተናን የሚወድ አይነት ሰው ነኝ ብሏል።

አክሎም " ማንችስተር ዩናይትድ ጥሩ የወደፊት እቅድ አለው የዛ አካል መሆን ፈልጌ ነበር “ ሲል ተደምጧል።

“ ከብዙ አሰልጣኞች ጋር ተነጋግሪያለሁ ነገርግን ለእኔ የተስማማው የማንችስተር ዩናይትድ ነው ፤ ከአሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ጋርም ተነጋግሬያለሁ።" ብሪያን ምቤሞ

" ሩበን አሞሪም እኛ ማሸነፍ እና ምርጥ ቡድን መሆን እንፈልጋለን ብሎ ነግሮኛል አሁንም ለማድረግ እየሞከርን ያለነው ይህንኑ ነው " ሲል ምቤሞ ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

Читать полностью…

TIKVAH-SPORT

የአል ነስር የጨዋታ ትኬቶች ተጠናቀዋል !

የሳውዲ አረቢያው ክለብ አል ነስር ነገ ከፈረንሳዩ ክለብ ቱሉስ ጋር ኦስትሪያ ውስጥ የወዳጅነት ጨዋታ ያደርጋሉ።

ለወዳጅነት ጨዋታው የተዘጋጁ የስታዲየም መግቢያ ትኬቶች በደቂቃዎች ውስጥ ተሸጠው መጠናቀቃቸውን የኦስትሪያ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

የጨዋታ መመልከቻ ትኬቶች 500 ዩሮ የሚያስወጡ መሆናቸው ተዘግቧል።

ጨዋታውን ያዘጋጀው ተቋሙ ከስታዲየሙ መግቢያ ትኬቶች 2.3 ሚልዮን ዩሮ ገቢ ማግኘቱ ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

Читать полностью…

TIKVAH-SPORT

#wanawsportswear

⭐️|🇪🇹|🇸🇳
"ኢትዩጵያ ውስጥ እንደዚህ አይነት አካዳሚ ይኖራል ብዬ አልገመትኩም ከጠበኩት በላይ ነው👏" የአፍሪካ እግር ኳስ ታሪክ ሲነሳ ሁሌም የሚወሳው ኤል ሀጂ ዲዩፍ ሀምሌ/15/2017 የኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ሲጎበኝ ይህን ነበር የተናገረው!

🌍በአውሮፓ ሊጎች ላይ በመጫወት እውቅናን ያተረፈው እና አሁን ደግሞ የዋናው ስፖርት ብራንድ አምባሳደር የሆነው ኤል ሀጂ ለአካዳሚው በራሱ እጅ የተፈረመበትን ቲሸርት የነገዎቹን እግር ኳስ ተስፈኞች ለማነቃቃት ይረዳ ዘንድ በስጦታ መልክ አበርክቶ ነው የሄደው።

በዚህ የጉብኝት ስነስረአት ላይ ኤል ሀጂ ዲዩፍ በተጨማሪ የላይቤሪያ እና ብሩንዲ እግር ኳስ ፌደሬሽን ባለድርሻዎች፣የዋናው ስፖርት መስራች እና ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆኑት አቶ ኀብተስላሴ ገ/ክርስቶስ (ሀብቴ) ተግኝተው ነበር።

⭐️ |ይሄ ነው ዋናው!


ለበለጠ መረጃ
8️⃣2️⃣8️⃣9️⃣

🔗 ማህበራዊ ገጾቻችን🔗
Instagram|Facebook |TikTok |X|wanawsportswear?si=TSJ9HZINs4MzMPj2">Youtube
🔥🔥🔥🔥በኢትዮጵያ የተመረተ🔥🔥🔥🔥

Читать полностью…

TIKVAH-SPORT

ሊቨርፑል ተጨዋች ለማስፈረም ተስማማ !

ሊቨርፑል አርሰናልን ለመቀላቀል ተቃርቦ የነበረውን የሳልፎርድ ወጣት ተጨዋች ዊል ራይት ለማስፈረም ከስምምነት መድረሳቸውን ዘ አትሌቲክ አስነብቧል።

መድፈኞቹ የ 17ዓመቱን አጥቂ ዊል ራይት በ 200,000 ፓውንድ እና ተጨማሪ ክፍያ ለማስፈረም ተስማምተው ነበር።

ይሁን እንጂ አርሰናሎች ከተጨዋቹ ጋር በግል ከስምምነት መድረስ እንዳልቻሉ ተገልጿል።

ሊቨርፑል በበኩሉ ተጫዋቹን ለማስፈረም ከክለቡም ከተጨዋቹም ጋር ሙሉ ስምምነት ላይ መድረሳቸው ተነግሯል።

ዊል ራይት በቀጣይ ከሊቨርፑል ከ 21ዓመት በታች ቡድን ጋር መስራት እንደሚጀምር ተገልጿል።

ሊቨርፑል ለተጨዋቹ ዝውውር አርሰናል ካቀረበው ጋር ተመሳሳይ ክፍያ እንደሚከፍሉ ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

Читать полностью…

TIKVAH-SPORT

የሪያል ማድሪድ የዝውውር ሁኔታ ?

ብራዚላዊው የፊት መስመር ተጨዋች ቪንሰሰ ጁኒየር በዚህ ክረምት በሪያል ማድሪድ ቤት እንደሚቆይ ተገልጿል።

ተጨዋቹ በአሁኑ ሰዓት ከሳውዲ አረቢያ ሊግ ክለቦች የቀረበለት የዝውውር ጥያቄ እንደሌለ ተነግሯል።

ሪያል ማድሪድ ዳኒ ሴባዮስን ከጠየቁት የዝውውር ሒሳብ በታች መልቀቅ እንደማይፈልግ ተገልጿል።

ይህንንም ተከትሎ ተጨዋቹ በሚቀጥለው የውድድር አመት በክለቡ የሚቆይበት እድል ሰፊ እንደሚሆን ተዘግቧል።

ሎስ ብላንኮዎቹ ዴቪድ አላባ እና ፌርላንድ ሜንዲን መልቀቅ ቢፈልጉም ሁለቱም ተጨዋቾች ከክለቡ ለመውጣት ዝግጁ አለመሆናቸው ተነግሯል።

ፌርላንድ ሜንዲ በክለቡ በመቆየት ለቦታው ከካሬራስ ጋር መፎካከር እንደሚፈልግ እና እንደማያስፈራው ተዘግቧል።

በሌላ በኩል ሪያል ማድሪድ ስፔናዊውን አማካይ ሮድሪን ለማስፈረም እየሰራ #አለመሆኑን ዘ አትሌቲክ በዘገባዉ አረጋግጧል።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe

Читать полностью…

TIKVAH-SPORT

🌐 ለክረምቱ ፍቱን ቅመም 🔥

💨⚡️እስከ 7 ሰዓት የሚቆይ የባትሪ አቅም ያለውና አዳዲስ የቴክኖሎጂ ትሩፋቶችን ይዞ በአንዴ እስከ 8 ሰው ድረስ የሚያስጠቅመውን ልዩ ቅመም MIFIን ገዝተን ፈጣን 4G ኢንተርኔት እንጠቀም!

🍰  ለ30 ቀን ከሚቆይ ነጻ 30ጊባ ዳታ ጉርሻ ጋር 😊

ከሳፋሪኮም ጋር አንድ ወደፊት⚡️

#SafaricomEthiopia

Читать полностью…

TIKVAH-SPORT

አሌሀንድሮ ጋርናቾ ቼልሲን እየጠበቀ ነው !

በዝውውር መስኮቱ ንቁ ተሳትፎ እያደረጉ የሚገኙት ሰማያዊዎቹ አሁንም የፊት መስመሩን ለማጠናከር እየሰሩ መሆኑ ተገልጿል።

ቼልሲዎች አሁን ላይ ለማስፈረም የያዙት ዝርዝር አሌሀንድሮ ጋርናቾ እና ሞርጋን ሮጀርስ መሆናቸው ተነግሯል።

ማንችስተር ዩናይትድ አሌሀንድሮ ጋርናቾን ለመሸጥ መፈለጉን ተከትሎ ለቼልሲ ቀላሉ ዝውውር ሊሆን እንደሚችል ተዘግቧል።

እንደ ዘ አትሌቲክ ዘገባ አስቶን ቪላ በበኩሉ ለሞርጋን ሮጀርስ አዲስ ኮንትራት በማቅረብ በክለቡ ለማቆየት ማሰባቸው ተነግሯል።

ይህንንም ተከትሎ ከሁለቱ የተጨዋቾች ሁኔታ ለሰማያዊዎቹ አሌሀንድሮ ጋርናቾ ለመግዛት ርካሽ እንደሚሆን ተገልጿል።

አሌሀንድሮ ጋርናቾ በበኩሉ በሌሎች ክለቦች ቢፈለግም ቼልሲ እንዲያስፈርመው በመጠበቅ ላይ መሆኑ ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

Читать полностью…

TIKVAH-SPORT

አርሰናል እነማንን ሊሸጥ ይችላል ?

ስድስት አዲስ ተጨዋቾች ወደ ቡድናቸው የቀላቀሉት መድፈኞቹ በቀጣይ የተጨዋቾች ሽያጭ ላይ ለማተኮር ማሰባቸው ተገልጿል።

መድፈኞቹ በቀጣይ የመስመር አጥቂ ካስፈረሙ ጋብሬል ማርቲኔሊ ወይም ሊያንድሮ ትሮሳርድን ሊሸጡ እንደሚችሉ ዘ አትሌቲክ ዘግቧል።

በአርሰናል እስካሁን ውሉን ያላራዘመው ሊያንድሮ ትሮሳርድ ባለፈው አመት ከአል ኢቲሀድ ጥያቄ ቀርቦለት እንደነበር ይታወሳል።

በወቅቱ የዝውውር ጥያቄው የቀረበው በመጨረሻ ሰዓት በመሆኑ አርሰናል ሌላ ተጨዋች መተካት ስለማይችል ውድቅ ማድረጉ ተዘግቦ ነበር።

በሌላ በኩል ክሪስታል ፓላስ በቀጣይ ጨዋታዎች የኢዜን ገንዘብ የሚቀንሱ ከሆነ አርሰናል ለማስፈረም እንደሚንቀሳቀስ ተዘግቧል።

ሮድሪጎን በተመለከተ አርሰናል ወደ ዝውውሩ ከመግባቱ በፊት የተጨዋቾች ሽያጭ መፈፀም እንደሚፈልግ ተነግሯል።

ስሙ ከሮድሪጎ ጋር እየተያያዘ የሚገኘው ቶተንሀም በዝውውሩ እየሰራ እንዳልሆነ ተጠቁሟል።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe

Читать полностью…

TIKVAH-SPORT

“ ቨርትዝ በየትኛውም ክለብ መድመቅ ይችላል “ ቶማስ ሙለር

ጀርመናዊው የቀድሞ የባየር ሙኒክ ተጨዋች ቶማስ ሙለር ፍሎሪያን ቨርትዝ በሊቨርፑል ቤት መድመቅ እንደሚችል ገልጿል።

" ቨርትዝ ባለተሰጥኦ ተጨዋች ብቻ አይደለም ጠንካራ አስተሳሰብም አለው በየትኛውም ክለብ መድመቅ ይችላል “ ሲል ቶማስ ሙለር ተናግሯል።

“ 150 ሚልዮን በክለቦች መካከል ያለ ቁጥር ነው ተጫዋችን በወጣበት ዋጋ አትመዝነውም ፤ በዚህ ገንዘብ ኔይማርን አትገዛም ነገርግን በሺዎች የሚቆጠሩ ዛፎችን መትከል ትችላለህ።"ቶማስ ሙለር

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe

Читать полностью…

TIKVAH-SPORT

ኦዶች ዛሬም ከፍ ብለዋል!
ታዲያ ምን ይጠብቃሉ? ለማሸነፍ በተመቻቹ ኦዶች ይወራረዱ!
አሁኑኑ Betika.et ላይ ብቻ!
ቤቲካ የአሸናፊዎች ቤት!

Читать полностью…

TIKVAH-SPORT

አሌክሳንደር አይሳክ ወደ ሊቨርፑል ?

የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል አሌክሳንደር አይሳክን ለማስፈረም ሪከርድ የሆነ ሒሳብ ለመክፈል ፍቃደኛ መሆናቸው ተገልጿል።

ሊቨርፑል ተጫዋቹን በእንግሊዝ እግርኳስ ታሪክ ከፍተኛ ገንዘብ የወጣበት ተጨዋች ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን ፋብሪዝዮ ሮማኖ ተናግሯል።

አሌክሳንደር አይሳክ በበኩሉ ሊቨርፑልን የመቀላቀል ሀሳብ ሲያልመው የኖረው ህልም አድርጎ ማሰቡ ተዘግቧል።

ተጨዋቹ ሊቨርፑልን መቀላቀል እንደሚፈልግ ለኒውካስል ዩናይትድ በግልጽ ማሳወቁ ተገልጿል።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe

Читать полностью…

TIKVAH-SPORT

ላሚን ያማል ባለ ልዩ ተሰጥኦ ነው “

የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና ዋና አሰልጣኝ ሀንስ ፍሊክ በቅድመ ውድድር ዝግጅት ከሲዮል ጋር ከሚያደርጉት ጨዋታ አስቀድሞ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

ሀንስ ፍሊክ ቡድናቸው በቅድመ ውድድር ዝግጅት ወቅት እያሳየ ባለው አቋም ደስተኛ መሆናቸውን ሲገልፁ “ በቡድኔ ደስተኛ ነኝ “ ብለዋል።

አሰልጣኙ ላሚን ያማል ሲያወድሱ “ ባለ ልዩ ተሰጥኦ እና ጨዋታዎችን ለማሸነፍ የመወሰን አቅም ያለው ተጫዋች “ ሲሉ አወድሰውታል።

የክለቡ ዋና አምበል ማን እንደሚሆን ከሊጉ ጅማሮ ሁለት ሳምንት በፊት እንደሚያሳውቁም አሰልጣኙ ገልፀዋል።

ስለ ቀጣይ አመት የቡድኑ እቅድ የተናገሩት ሀንስ ፍሊክ “ እንደ ባርሴሎና ያለ ታላቅ ክለብ ዋንጫዎችን ማሸነፍ ይፈልጋል ፣ የቀጣይ አመት ፍላጎታችን ይሄ ነው “ በማለት ተናግረዋል።

ባርሴሎና በነገው ዕለት ከ ጄሲ ሊንጋርድ ክለብ ሲዮል ጋር የአቋም መፈተሻ ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ይሆናል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe

Читать полностью…

TIKVAH-SPORT

ኒውካስል ራምስዴልን ለማስፈረም ተስማማ !

ኒውካስል ዩናይትድ የሳውዝሀምፕተኑን ግብ ጠባቂ አሮን ራምስዴል ለማስፈረም ከስምምነት መድረሳቸውን ዘ አትሌቲክ አስነብቧል።

ኒውካስል ዩናይትድ አሮን ራምስዴልን የመግዛት አማራጭ ባካተተ የውሰት ውል ለማስፈረም መስማማታቸው ተገልጿል።

የቀድሞው የአርሰናል ግብ ጠባቂ አሮን ራምስዴል አሁን ላይ የህክምና ምርመራውን እንዲያደርግ ፍቃድ ማግኘቱ ተነግሯል።

የ 27ዓመቱ ግብ ጠባቂ አሮን ራምስዴል ባለፈው አመት ለሳውዝሀሞፕተን በሁሉም ውድድሮች 32 ጨዋታዎች ማድረግ ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

Читать полностью…

TIKVAH-SPORT

ማንችስተር ሲቲ ግብ ጠባቂ አስፈረመ !

ማንችስተር ሲቲዎች የበርንሌዩን ግብ ጠባቂ ጄምስ ትራፎርድ ማስፈረማቸውን በይፋ አስታውቀዋል።

ጄምስ ትራፎርድ በማንችስተር ሲቲ ቤት ለአንድ ተጨማሪ አመት የመቆየት አማራጭ ያካተተ የአምስት አመት ውል ፈርሟል።

ማንችስተር ሲቲ ግብ ጠባቂውን በ 27 ሚልዮን ፓውንድ እንዳስፈረሙት ተዘግቧል።

ጄምስ ትራፎርድ በማንችስተር ሲቲ ቤት የ 1️⃣ ቁጥር ማልያ የሚለብስ ይሆናል።

ግብ ጠባቂው  ከፊርማው በኋላ “ ወደ ማንችስተር ሲቲ መመለስ የተለየ ቅፅበት ነው ለእኔ እና ቤተሰቤ ኩራት ነው " ብሏል።

አክሎም “ አንድ ቀን ወደ ማንችስተር ሲቲ እንደምመለስ ሁልጊዜም ሳልም ነበር " ሲል ተደምጧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

Читать полностью…

TIKVAH-SPORT

ኪሊያን ምባፔ 1️⃣0️⃣ ቁጥር ተሰጠው !

ሪያል ማድሪዶች ፈረንሳዊው የፊት መስመር ተጨዋች ኪሊያን ምባፔ የ 1️⃣0️⃣ ቁጥር ማልያ እንደተሰጠው በይፋ አስታውቀዋል።

የክለቡ ታሪካዊ ተጨዋች ሉካ ሞድሪችን መልቀቅ ተከትሎ ኪሊያን ምባፔ የማልያ ቁጥሩን ወስዷል።

ኪሊያን ምባፔ በሪያል ማድሪድ ቤት 1️⃣0️⃣ ቁጥር የለበሰ አራተኛው ፈረንሳዊ ተጨዋች መሆን ችሏል።

የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን አምበል ኪሊያን ምባፔ በብሔራዊ ቡድኑም የ 1️⃣0️⃣ ቁጥር ማልያ ይለብሳል።

ቁጥሩ ሪያል ማድሪድ ቤት ከ 7️⃣ ቁጥር ማልያ በመቀጠል ትልቅ ቦታ የሚሰጠው እንደሆነ ይታወቃል።

ከዚህ በፊት ከሞድሪች በተጨማሪ ሜሱት ኦዚል ፣ ሀሜስ ሮድሪጌዝ ፣ ዌስሌይ ሽናይደር ፣ ሉዊስ ፊጎ እና ሲዶርፍ የመሳሰሉ ኮከቦች ቁጥሩን ለብሰው ተጫውተዋል።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe

Читать полностью…

TIKVAH-SPORT

የቪክቶር ዮኬሬሽ ማልያ ሽያጭ ሪከርድ ሰበረ !

አዲሱ የአርሰናል የፊት መስመር አጥቂ ቪክቶር ዮኬሬሽ 1️⃣4️⃣ ቁጥር ማልያ የክለቡን ከፍተኛ ማልያ ሽያጭ ሪከርድ መስበሩ ተገልጿል።

የተጨዋቹ ማልያ ሽያጭ በአርሰናል ታሪክ ከፍተኛ ሽያጭ ያስመዘገበ ማልያ በመሆን ሪከር መያዙ ተነግሯል።

ከቪክቶር ዮኬሬሽ በፊት ቡካዩ ሳካ ፣ ዴክላን ራይስ እና ማርቲን ኦዴጋርድ በአርሰናል ማልያ ሽያጭ ተፅዕኖ የፈጠሩ ተጨዋቾች ነበሩ።

በተጨማሪም የሉዊስ ስኬሊ 49 ቀጥር ማልያ በክለቡ ውስጥ ከፍተኛ ፈላጊ ያለው ማልያ እንደነበር ተገልጿል።

የሉዊስ ስኬሊ 49 ቀጥር ማልያ በአሰልጣኝ አርሴን ቬንገር የሚመራው " Invincibles " የአርሰናል ቡድን ሳይሸነፍ የተጓዘው የጨዋታ ቁጥር በመሆኑ በክለቡ ደጋፊዎች ይወደዳል።

ቪክቶር ዮኬሬሽ ከስፖርቲንግ ሊዝበን አርሰናልን ከተቀላቀለ ወዲህ የሁሉም ሪከርድ በመስበር የግሉ አድርጓል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

Читать полностью…

TIKVAH-SPORT

ቼልሲ ኩኩሬላን መሸጥ አይፈልግም !

የለንደኑ ክለብ ቼልሲ ስፔናዊውን የመስመር ተጨዋች ማርክ ኩኩሬላ ኮንትራት ለማራዘም ማሰባቸው ተገልጿል።

ማርክ ኩኩሬል በቼልሲ የወደፊት እቅድ ውስጥ መሆኑ ሲገለፅ ሰማያዊዎቹ እሱን የመሸጥ ፍላጎት እንደሌላቸው ተነግሯል።

ማርክ ኩኩሬላ ስሙ እየተያያዘ ከሚገኘው የሳውዲ አረቢያው ክለብ አል ነስር ጋር ምንም ግንኙነት እንደሌለው ፋብሪዝዮ ሮማኖ ተናግሯል።

ሰማያዊዎቹ በሚቀጥለው ወር የማርክ ኩኩሬላን ኮንትራት ሊያራዝሙ እንደሚችሉ ተጠቁሟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

Читать полностью…

TIKVAH-SPORT

“ አል ነስርን በመቀላቀሌ ደስተኛ ነኝ “ ጇ ፊሊክስ

የሳውዲ አረቢያውን ክለብ አል ነስር የተቀላቀለው ጇ ፊሊክስ በዝውውሩ ደስተኛ መሆኑን ተናግሯል።

“ ለአል ነስር ልጫወት በመሆኑ ደስተኛ ነኝ “ ያለው ጇ ፊሊክስ በመጨረሻም በአሰልጣኝ ጆርጅ ጄሱስ ስር ልሰለጥን በመሆኑ ተደስቻለሁ ብሏል።

አክሎም " አሰልጣኝ ጆርጅ ጄሱስ እንደሚወዱኝ አውቃለሁ " ሰል ተደምጧል።

ፖርቹጋላዊው የፊት መስመር ተጨዋች ጇ ፊሊክስ ባለፉት አምስት አመታት ስድስተኛ ክለቡን ተቀላቅሏል።

ጇ ፊሊክስ በነገው የአል ነስር እና ቱሉስ የወዳጅነት ጨዋታ ሊሳተፍ እንደሚችል ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

Читать полностью…

TIKVAH-SPORT

" አርሰናል ከአለም ምርጥ ቡድኖች አንዱ ነው “ ቶማስ ፍራንክ

የቶተንሀሙ ዋና አሰልጣኝ ቶማስ ፍራንክ ከአርሰናል ጋር የሚያደርጉት የሰሜን ለንደን ደርቢ ጨዋታ ጠንካራ እንደሚሆን ገልፀዋል።

“ ከታሪካዊ የሀገር ውስጥ ተቀናቃኛችን ጋር የምናደርገው ትልቅ ፈተና ነው “ ሲሉ አሰልጣኝ ቶማስ ፍራንክ ተናግረዋል።

አክለውም “ እውነት መነጋገር አለብን እንዳለመታደል ሆኖ አርሰናል ከአለም ምርጥ ቡድኖች አንዱ ነው “ ሲሉ ተደምጠዋል።

" ጨዋታው ራስን ከመፈተሽም በላይ ነው ምክንያቱም ከአርሰናል ጋር መጫወት ከወዳጅነት ጨዋታ በላይ ነው ፤ ለማሸነፍ ያለንን ሀይል ሁሉ እንጠቀማለን።" ቶማስ ፍራንክ

አርሰናል እና ቶተንሀም ሐሙስ ከቀኑ 8:30 የወዳጅነት ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe

Читать полностью…

TIKVAH-SPORT

የሰሜን ለንደን ደርቢ🔥

⚽️ Arsenal vs Tottenham
🗓 ሐሙስ ሐምሌ 24
⏰ ከሰዓት 08፡30

መድፈኞቹ ከስፐርስ ጋር ፣ ሁሉም አይኖች በሜዳው ላይ ናቸው፣ አዳዲስ ፈራሚዎች ደረቢውን ለመጀመሪያ ጊዜ ለመሳተፍ ዝግጁ ናቸው?

ዮኬሬሽ ለመድፈኞቹ የመጀመሪያውን ጨዋታ ያደርጋል?

👉 ጨዋታውን በ SS Premier League CH 223 በሜዳ ፓኬጅ ይከታተሉ

⚽️ ጨዋታው አመለጠን ብለው አያስቡ! ዲኤስቲቪ ስትሪም መተግበሪያን በመጠቀም የጨዋታውን በላቀ ጥራት በስልክዎ ይከታተሉ!

ዛሬውኑ ዲኤስቲቪ ያስገቡ ፣ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ!
⬇️
https://mydstv.onelink.me/vGln/xepsjmo7

ደንብና ሁኔታዎች ተፈፃሚነት አላቸው!

#እናያለንገና👀 #ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia

Читать полностью…

TIKVAH-SPORT

ቼልሲ ለተጨዋቾቹ ስንት ይፈልጋል ?

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ በክረምቱ የዝውውር መስኮት በርካታ ተጨዋቾቹን ለመሸጥ እየሰራ ይገኛል።

ሰማያዊዎቹ በበርካታ ክለቦች እየተፈለገ የሚገኘውን ዴውስቡሪ ሀል ከሌስተር ሲቲ በገዙበት 30 ሚልዮን ፓውንድ መሸጥ እንደሚፈልጉ ተገልጿል።

ፉልሀም በበኩሉ እንግሊዛዊውን ተጨዋች ራሂም ስተርሊንግ ለማስፈረም በማሰብ ላይ መሆናቸው ተነግሯል።

ቼልሲ በበኩሉ ራሂም ስተርሊንግን በውሰት መስጠት እንደማይፈልግ ሲገለፅ ለተጨዋቹ 20 ሚልዮን ፓውንድ እንደሚፈልጉ ተዘግቧል።

ሰማያዊዎቹ ኒኮላስ ጃክሰንን ከሚሸጡ ተጨዋቾች ዝርዝር ውስጥ ባያካትቱትም ጥሩ ሒሳብ ከቀረበ ለመሸጥ ፍቃደኛ ናቸው።

በተጨማሪም ቼልሲዎች

- ክርስፈር ንኩንኩን በ 50 ሚልዮን ዩሮ
- ሬናቶ ቬይጋን በ 40 ሚልዮን ዩሮ
- አርማንዶ ብሮሀን በ 25 ሚልዮን ፓውንድ ለመሸጥ ዋጋ ማውጣቸውን ዘ አትሌቲክ አስነብቧል።

በሌላ በኩል እንግሊዛዊው ተጨዋች ቤን ቺልዌል ፈላጊ ክለብ እንዳልተገኘለት ተዘግቧል።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe

Читать полностью…

TIKVAH-SPORT

ዲያዝ ቡድኑን ተሰናብቶ ወደ ጀርመን አቅንቷል !

ባየር ሙኒክን ለመቀላቀል ከስምምነት የደረሰው ሉዊስ ዲያዝ ትላንት ምሽት የሊቨርፑል የቡድን አጋሮቹን እና አሰልጣኞች ተሰናብቶ መውጣቱ ተገልጿል።

ሉዊስ ዲያዝ የጤና ምርመራውን ለማድረግ ትላንት ሌሊት ከጃፓን ቶኪዮ ወደ ጀርመን መጓዙ ተነግሯል።

ተጨዋቹ ዛሬ ጠዋት ጀርመን የደረሰ ሲሆን በቀጣይ ወደ ባየር ሙኒክ የሚያደርገውን ዝውውር ያጠናቅቃል።

በሊቨርፑል የሁለት አመት ውል ያለው ሉዊስ ዲያዝ ክለቡን ለመልቀቅ ጠይቆ በ 75 ሚልዮን ዩሮ ባየር ሙኒክን ለመቀላቀል ከስምምነት ተደርሷል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

Читать полностью…

TIKVAH-SPORT

ዩናይትድ ሁለት አጥቂዎች መለየቱ ተገለጸ !

የፊት መስመር አጥቂ ለማስፈረም በማፈላለግ ላይ የሚገኘው ማንችስተር ዩናይትድ አሁን ላይ ሁለት ተጨዋቾች መለየታቸው ተገልጿል።

ማንችስተር ዩናይትድ በአሁኑ ሰዓት ለመመልከት የያዛቸው አጥቂዎች ቤንጃሚን ሴስኮ እና ኦሊ ዋትኪንስ መሆናቸውን ዘ አትሌቲክ አስነብቧል።

ስማቸው ከቼልሲው ኒኮላስ ጃክሰን ጋር ሲያያዝ የነበረው ቀያዮቹ ሴጣኖች በዋጋው ምክንያት ከዝውውሩ መውጣታቸው ተገልጿል።

ማንችስተር ዩናይትድ ሴስኮ የሚያስወጣውን ክፍያ ተከትሎ ከዝውውሩ አፈግፍገው የነበረ ቢሆንም አሁን ላይ ንግግሮች ማድረግ መጀመራቸው ተነግሯል።

በሌላ በኩል ማንችስተር ዩናይትድ በኦሊ ዋትኪንስ ዝውውር ላይ ተመሳሳይ ንግግር ማድረጋቸው ተዘግቧል።

ክለቡ እስካሁን ከውሳኔ ባይደርስም ሁለቱ ተጨዋቾች የሚያስወጡትን ክፍያ ለማወቅ እየተነጋገሩ መሆኑ ተገልጿል።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe

Читать полностью…

TIKVAH-SPORT

“ ለአይሳክ ጥያቄ አልቀረበልንም “ ኤዲ ሀው

የኒውካስል ዩናይትዱ አሰልጣኝ ኤዲ ሀው ለአሌክሳንደር አይሳክ እስካሁን ይፋዊ የዝውውር ጥያቄ እንዳልቀረበ ገልጸዋል።

“ አይሳክ አሁንም የእኛ ተጨዋች ነው ውል አለው በእሱ ዙሪያ የሚፈጠሩ ነገሮችን በተወሰነ እንቆጣጠራለን “ ሲሉ ኤዲ ሀው ተናግረዋል።

አክለውም " ሁሉም አማራጮች ለእኛ ክፍት ናቸው ለእሱ የምመኘው እንዲቆይ ነው ፤ ነገርግን ሁኔታው ሙሉ ለሙሉ በእኔ ቁጥጥር ስር አይደለም " ብለዋል።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe

Читать полностью…

TIKVAH-SPORT

አል ነስር በሮናልዶ እየተመራ መሆኑ ተገለጸ !

የሳውዲ አረቢያው ክለብ አል ነስር በአሁኑ ሰዓት በቡድኑ አምበል ክርስቲያኖ ሮናልዶ ሀሳብ እየተመራ መሆኑ ተገልጿል።

ፖርቹጋላዊው ተጨዋች ክርስቲያኖ ሮናልዶ አሁን ላይ በክለቡ የወደፊት እቅድ ዙሪያ እያማከረ እና ሀሳቡን እያጋራ መሆኑ ተነግሯል።

ክርስቲያኖ ሮናልዶ ፖርቹጋላዊውን ተጨዋች ጇ ፊሊክስ ሀሳብ በማስቀየር ለአል ነስር እንዲፈርም ማሳመኑ ተገልጿል።

ጇ ፊሊክስ ቤኔፊካን ለመቀላቀል ተስማምቶ የነበረ ቢሆንም ክርስቲያኖ ሮናልዶ ስልክ ደውሎ ሀሳቡን እንዳስቀረው ተነግሯል።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe

Читать полностью…

TIKVAH-SPORT

ዩናይትድ በቀጣይ ምን ያስፈርማል ?

ማንችስተር ዩናይትድ በቀጣይ የዝውውር መስኮቱ ከመጠናቀቁ በፊት ሁለት ወይም ሶስት ተጨዋቾች ሊያስፈርም እንደሚችል ተገልጿል።

ቀያዮቹ ሴጣኖች በቅድሚያ አጥቂ ለማስፈረም ያሰቡ ሲሆን ግብ ጠባቂ እና የመሐል ሜዳ ተጨዋች በእቅዳቸው እንዳሉ ተነግሯል።

በአጥቂ ረገድ ማንችስተር ዩናይትድ ቤንጃሚን ሴስኮን እያነጋገሩ መሆኑን ፋብሪዝዮ ሮማኖ ዘግቧል።

በሌላ በኩል ቀያዮቹ ሴጣኖች ባለፈው ሳምንት የአስቶን ቪላውን ግብ ጠባቂ ማርቲኔዝ በውሰት ለማስፈረም ጠይቀው እንደነበር ተገልጿል።

ይሁን እንጂ አስቶን ቪላ አንቀበልም በማለት ለመግዛት እስከ 40 ሚልዮን ፓውንድ ይከፈለን በማለት መጠየቃቸው ተነግሯል።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe

Читать полностью…
Subscribe to a channel