ሮማ በይፋ ተጨዋች አስፈርሟል !
የጣልያን ሴርያው ክለብ ሮማ ብራዚላዊውን የቀኝ መስመር ተጨዋች ዌስሌይ ከፍላሚንጎ ማስፈረማቸውን ይፋ አድርገዋል።
ሮማ ለተጨዋቹ ዝውውር አጠቃላይ 30 ሚልዮን ዩሮ ለብራዚሉ ክለብ ፍላሚንጎ እንደሚከፍሉ ተገልጿል።
ለብራዚል ዋናው ብሔራዊ ቡድን ሁለት ጨዋታዎች ያደረገው ዌስሌይ በቀጣይ የአሰልጣኝ ጂያን ፔሮ ጋስፔሪኒ የመጀመሪያ ተመራጭ እንደሚሆን ይጠበቃል።
የ 21ዓመቱ የቀኝ መስመር ተጨዋች ዌስሌይ በዚህ ክረምት በማንችስተር ሲቲ ሲፈለግ እንደነበር ይታወሳል።
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
በላሊጋ በቀጣይ ምን ህግ ሊተገበር ነው ?
የስፔን ላሊጋ በሚቀጥለው የውድድር አመት አዲስ ህግ ለመተግበር ማሰቡን የስፔን መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
በቀጣይ በስፔን ላሊጋ ጨዋታዎች አሰልጣኞች ቫር ጣልቃ ገብቶ እንዲመለከት የመጠየቅ መብት እንደሚሰጣቸው ተገልጿል።
ሁሉም አሰልጣኞች በአንድ ጨዋታ ሁለት ጊዜ ቫር እንዲመለከት ዳኞችን መጠየቅ እንደሚችሉ ተነግሯል።
የቀረበው የቫር ጣልቃገብነት ትክክለኛ ከሆነ የአሰልጣኞቹ ሁለት እድል እንደማይቃጠል ተገልጿል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe
“ ከክለብ ጋር መጫወት አዲስ አይደለም “ አቶ ባህሩ ጥላሁን
የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ባህሩ ጥላሁን የዋልያዎቹ የአሜሪካ ጉዞ " የቢዝነስ ስምምነት ነው “ ሲሉ ገልጸዋል።
“ ፌዴሬሽኑ ያደረገው ስምምነት የቢዝነስ ስምምነት መሆኑ ልናውቅ ይገባል “ ያሉት አቶ ባህሩ “ እኛን የሚያሶጣን ምንም የለም “ብለዋል ።
አክለውም “ ቡድኑ አሜሪካ ሲደርስ 25ሺህ ዶላር ጨዋታውን ካሸነፈ ደግሞ ተጨማሪ 50ሺህ ድላር ያገኛል “ ያሉ ሲሆን “ ፌዴሬሽኑ እያወረሰ ያለው እዳ አይደለም የተሻለ ነገር ነው ትርፍ ነው “ ብለዋል።
“ ከክለብ ጋር መጫወት አዲስ ነገር አይደለም በርካታ ታላላቅ የአውሮፓ ክለቦች እና ብሔራዊ ቡድኖች እያደረጉት ይገኛሉ።“ አቶ ባህሩ ጥላሁን
አቶ ባህሩ ጥላሁን ለማሳያነትም
- ሜክሲኮ ከ ሪቨር ፕሌት
- ዩክሬን ከ ሞንቻግላድባህ እና
- ዮኮሀማ ከ ማሪኖስ ጋር ያደረጓቸውን ጨዋታዎች ጠቅሰዋል።
አቶ ባህሩ ጥላሁን አክለውም " ከዲሲ ዩናይትድ ጋር የምናደርገው ጨዋታ ከግብፅ ጋር ላለብን የአለም ዋንጫ ጨዋታ በነሐሴ ወር መዘጋጃ ይሆናል " ብለዋል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe
#wanawsportswear✔️
መርካቶ ጤና ካፕ 2017 የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር ሊጀመር ነው።
🏆 የመርካቶ አካባቢ ወንድማማቾች ጤና ስፖርት ማህበር የስፖርታዊ ውድድር ብቻ ታስቦ የሚዘጋጅ አይደለም በመርካቶና አካባቢዋ ለ41 አመታት በጽናት የኖረውን የማህበረሰብ ጤና፣ባአብሮነት እና ታሪክ አንድነትን በሚያጎናጸፉ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች እና ትጥቆች ከአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ስፖርት ጵ/ቤት ጋር በመተባበር አንደነት ማበልጸግ ነው ዋና አላማው።
📅ማክሰኞ 7፡30
📍አበበ ቢቂላ ስታዲየም
💪🏿 ይፋዊ የስፖርት ትጥቅ አቅራቢ እንደመሆናችን ዋናው ስፖርት እያንዳንዱን በዚህ ዝግጅት ላይ የሚገኙ ታዳሚዎችን እና የእግር ኳስ ባለታሪኮችን የስፖርት ትጥቁ ሲያጎናጽፋቸው ኩራት ይሰማዋል!
⭐️ ዋናው ወደፊት»»» | ውድድር ካለ ዋናው አለ!
“ ፌዴሬሽኑ በአሜሪካ ጉዞ ምንም አይነት ወጪ አያወጣም “
" 31 የቡድን አባላት ወደ አሜሪካ ያቀናሉ " አቶ ባህሩ ጥላሁን
ዋልያዎቹ ወደ አሜሪካ የሚያደርጉትን ጉዞ ተከትሎ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በአሁኑ ሰዓት መግለጫ እየሰጠ ይገኛል።
በመግለጫው አስተያየታቸውን የሰጡት የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ባህሩ ጥላሁን ስለ ጉዞው አብራርተዋል።
1️⃣5️⃣ የቡድኑ አባላት አዲስ ቪዛ ያስፈልጋቸው እንደነበር የገለፁት አቶ ባህሩ ጥላሁን 7️⃣ አግኝተዋል እንዲሁም 8️⃣ ደግሞ ተከልክለዋል ብለዋል።
አቶ ባህሩ ጥላሁን አያይዘውም ቪዛው ያልተፈቀደው ከኤምባሲው ፖሊሲ ጋር የተያያዘ ነው ብለዋል።
በሌላ በኩል :-
- ቪዛ ከጠየቁ 6️⃣ የስራ አስፈፃሚ አባላት መካከል 3️⃣ አግኝተዋል።
- ከአሰልጣኝ አባላት 4️⃣ ጠይቀው 2️⃣ ሲያገኙ 2️⃣ አላገኙም “ ሲሉ አቶ ባህሩ ጥላሁን ተናግረዋል።
ይህንንም ተከትሎ 3️⃣5️⃣ አባላት ይዞ ለመሄድ ስምምነት የነበረው ብሔራዊ ቡድኑ 3️⃣1️⃣ አባላት በመያዝ ነገ ምሽት ወደ አሜሪካ እንደሚያቀና ተገልጿል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe
" እረፍት ያስፈልገኛል " ፔፕ ጋርዲዮላ
ስፔናዊው አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ በማንችስተር ሲቲ ያላቸው ውል ሲያበቃ እረፍት ማድረግ እንደሚፈልጉ ገልጸዋል።
“ በማንችስተር ሲቲ ያለኝ ቆይታ ሲያበቃ ስራዬን ማቆም እፈልጋለሁ " ሲሉ አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ተናግረዋል።
“ ለምን ያህል ጊዜ እንደሆነ አላውቅም " ያሉት አሰልጣኙ ለአንድ ፣ አምስት ወይም አስራ አምስት መሆኑን ግን አላውቅም ብለዋል።
" እረፍት ማድረግ ያስፈልገኛል ራሴ ላይ ማተኮር አለብኝ " ፔፕ ጋርዲዮላ
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
ቼልሲ ተጨዋች ለማስፈረም ተቃርቧል !
የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ የአያክሱን የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ጆሬል ሀቶ ለማስፈረም መቃረባቸው ተገልጿል።
ቼልሲ ተጫዋቹን ከ 40 ሚልዮን ዩሮ በላይ በማውጣት ለማስፈረም ከአያክስ ጋር ለስምምነት መቃረባቸውን ዘ አትሌቲክ አስነብቧል።
የ 19ዓመቱ ተከላካይ ጆሬል ሀቶ ቼልሲን ለመቀላቀል በግል ጥቅማጥቅም ከስምምነት መድረሱ ተገልጿል።
ኔዘርላንዳዊው ተከላካይ ጆሬል ሀቶ ለአያክስ ዋናው ቡድን 111 ጨዋታዎች ማድረግ ችሏል።
ተጨዋቹ በግራ መሐል ተከላካይ ቦታ መጫወት የሚያዘወትር ሲሆን በግራ መስመር ተጨዋችነትም ቡድኑን ማገልገል ይችላል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe
ሊሳንድሮ ማርቲኔዝ መቼ ይመለሳል ?
ከረጅም ጊዜ ጉዳት የተመለሰው የማንችስተር ዩናይትዱ ተከላካይ ሊሳንድሮ ማርቲኔዝ በአሁን ሰዓት ከቡድኑ ጋር በአሜሪካ ይገኛል።
ሊሳንድሮ ማርቴኔዝ የቡድኑ ሀኪም ፍቃድ ከሰጡ በታክቲካል ልምምዶች ላይ እንደሚካፈል ተነግሮ ነበር።
ሊሳንድሮ ማርቲኔዝ በቀጣይ ቢያንስ የመጀመሪያ ሶስት የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ጨዋታዎች ያመልጡታል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተገልጿል።
ማንችስተር ዩናይትድ ሊሳንድሮ ማርቲኔዝን ወደ ውድድር ለመመለስ ጥንቃቄ እንደሚያደርግ ተዘግቧል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe
ከየትም፣በማንኛውም ጊዜ ያሸንፉ!
የሩጫ ፣የኳስ እና ሌሎችም ቨርቹዋል ጨዋታዎች የሚጨበጡ ድሎች!
በሰከንዶች ውስጥ ድል በድል መሆን ከፈለጉ https://betika.et/et/mobile/#/betika-super-league እዚህ ይጭወቱ!
ቤቲካ - የአሸናፊዎች ቤት!
እንግሊዝ ሻምፒዮን ሆናለች !
በሴቶች የአውሮፓ ዋንጫ ውድድር ፍፃሜ እንግሊዝ ስፔንን በመለያ ምት 3ለ1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ሻምፒዮን ሆናለች።
ሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች መደበኛውን የጨዋታ ክፍለጊዜ 1ለ1 ማጠናቀቃቸውን ተከትሎ በተሰጠው መለያ ምት እንግሊዝ ልታሸንፍ ችላለች።
የእንግሊዝ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ለሁለተኛ ተከታታይ አመት የአውሮፓ ዋንጫ አሸናፊ መሆን ችሏል።
የእንግሊዝ አሰልጣኝ ሳሪና ዌግማን በተከታታይ ሶስት የአውሮፓ ዋንጫዎችን በማሸነፍ በታሪክ ሁለተኛዋ አሰልጣኝ ሆነዋል።
ስፔናዊቷ የመሐል ሜዳ ተጨዋች አይታና ቦንማቲ የአውሮፓ ዋንጫው ምርጥ ተጨዋች በመባል መመረጥ ችላለች።
@tikvahethsport @kidusyoftahe
" ሁሉንም ዋንጫ ለማሸነፍ እንሰራለን " ዊሊያም ሳሊባ
የለንደኑ ክለብ አርሰናል ተከላካይ ዊሊያም ሳሊባ ቡድናቸው በዚህ የውድድር አመት ለሁሉም ነገር እንደሚፎካከር ገልጿል።
“ በዚህ የውድድር አመት ሁሉንም ዋንጫዎች ለማሸነፍ የተቻለንን እናደርጋለን “ ሲል ዊሊያም ሳሊባ ተናግሯል።
ስለ ኮንትራት ማራዘም የተጠየቀው ዊሊያም ሳሊባ " በቅርቡ ውሌን አራዝማለሁ “ ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe
ባየር ሙኒክ ተጨዋች ለማስፈረም ተስማማ !
የጀርመን ቡንደስሊጋው ክለብ ባየር ሙኒክ የሊቨርፑልን የፊት መስመር ተጫዋች ሉዊስ ዲያዝ ለማስፈረም ሙሉ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ዘ አትሌቲክ አረጋግጧል።
ባየር ሙኒክ ሉዊስ ዲያዝን በ 75 ሚልዮን ዩሮ የዝውውር ሒሳብ ለማስፈረም ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል።
ከቡድኑ ጋር ቶኪዮ የሚገኘው የ 28ዓመቱ ተጨዋች ሉዊስ ዲያዝ የጤና ምርመራውን እንዲያደርግ ከሊቨርፑል ፍቃድ ማግኘቱ ተነግሯል።
ሉዊስ ዲያዝ በባየር ሙኒክ ቤት ለአንድ አመት የመቆየት አማራጭ ያካተተ የአራት አመት ኮንትራት እንደሚፈርም ተዘግቧል።
ባየር ሙኒክ ሉዊስ ዲያዝ በተለያዩ የፊት መስመር ቦታዎች መጫወት የሚችል ሁልገብ ተጨዋች አድርገው እንደሚመለከቱት ተገልጿል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe
አሌክሳንደር አይሳክ ቡድኑን አይቀላቀልም !
ስዊድናዊው አጥቂ አሌክሳንደር አይሳክ የኒውካስል ዩናይትድን የቅድመ ውድድር ዝግጅት እንደማይቀላቀል ተገልጿል።
አሌክሳንደር አይሳክ ክለቡን ለመልቀቅ ማሰቡን ተከትሎ ከቡድኑ ጋር ለቅድመ ውድድር ዝግጅት ወደ እስያ አለማምራቱ ይታወሳል።
የኒውካስሉ አሰልጣኝ ኤዲ ሀው ተጨዋቹ በቀጣይ ወደ ደቡብ ኮርያ የሚያቀናውን የቡድኑን ስብስብም እንደማይቀላቀል አረጋግጠዋል።
አሰልጣኝ ኤዲ ሀው አክለውም " በዚህ ሰዓት የተቀየረ አዲስ ነገር የለም " ብለዋል።
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
አል ነስር ተጨዋች ለማስፈረም ተስማማ !
የሳውዲ አረቢያው ክለብ አል ነስር ፖርቹጋላዊውን የፊት መስመር ተጨዋች ጇ ፊሊክስን ለማስፈረም ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል።
አል ነስር ተጫዋቹን 50 ሚልዮን ዩሮ በሚደርስ የዝውውር ሒሳብ ለማስፈረም ከቼልሲ ጋር ከስምምነት መድረሳቸውን ዘ አትሌቲክ ዘግቧል።
ቼልሲ 30 ሚልዮን ዩሮ በቀጥታ የሚቀበሉ ሲሆን ቀሪ 20 ሚልዮን ዩሮውን በተጨማሪ ክፍያ መልክ ያገኛሉ።
ፖርቹጋላዊው የፊት መስመር ተጨዋች ጇ ፊሊክስ ባለፈው የውድድር አመት ግማሽ በውሰት በኤሲ ማላን ማሳለፉ ይታወሳል።
ቼልሲ ከአመት በፊት ጇ ፊሊክስን በ 44.5 ሚልዮን ፓውንድ ያስፈረሙ ሲሆን ኤሲ ሚላንን ከመቀላቀሉ በፊት በሶስት ጨዋታዎች ነው በቋሚነት የተጫወተው።
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
ባርሴሎና የወዳጅነት ጨዋታውን አሸንፏል !
በጃፓን የቅድመ ውድድር ዝግጅቱን በማድረግ ላይ የሚገኘው ባርሴሎና ከቪሴል ኮቤ ጋር ያደረገውን የወዳጅነት ጨዋታ 3ለ1 ማሸነፍ ችሏል።
የባርሴሎናን ግቦች ኤሪክ ጋርሺያ ፣ ፔድሮ ፈርናንዴዝ እና ሩኒ ባርግዬ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።
እንግሊዛዊው የፊት መስመር ተጨዋች ማርከስ ራሽፎርድ ተቀይሮ በመግባት የባርሴሎና የመጀመሪያ ጨዋታውን አድርጓል።
የ 19ዓመቱ የፊት መስመር ተጨዋች ሩኒ ባርግዬ ለባርሴሎና ባደረገው የመጀመሪያ ጨዋታ ግብ አስቆጥሯል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe
የናይጄሪያ ብሔራዊ ቡድን ሽልማት ተበረከተለት !
የ 2024 ሴቶች አፍሪካ ዋንጫ ውድድር ያሸነፈው የናይጄሪያ ሴት ብሔራዊ ቡድን ሽልማት ተበርክቶለታል።
የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ቦላ አህመድ ቲኑቡ ለብሔራዊ ቡድኑ ተጨዋቾች ለእያንዳንዳቸው 100,000 ዶላር ሽልማት ሰጥተዋል።
በተጨማሪም ለሁሉም የቡድኑ አባላት ባለሶስት መኝታ አፓርትመንት የመኖሪያ ቤት እንደተሰጣቸው ተገልጿል።
የቡድኑ ቴክኒካል ስታፍ እንዲሁ የ 50,000 ዶላር ሽልማት እንዳገኙ ተነግሯል።
ናይጄሪያ ሞሮኮን 3ለ2 በሆነ ውጤት በማሸነፍ የአፍሪካ ዋንጫን ለአስረኛ ጊዜ አሸናፊ መሆኗ አይዘነጋም።
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
አሮን ራምስዴል ወደ ኒውካስል ዩናይትድ ?
የበርንሌዩን ግብ ጠባቂ ጄምስ ትራፎርድ በማንችስተር ሲቲ የተቀማው ኒውካስል ዩናይትድ አሮን ራምስዴልን ለማስፈረም ማሰባቸው ተገልጿል።
ኒውካስል ዩናይትድ የቀድሞውን የአርሰናል ግብ ጠባቂ አሮን ራምስዴል የመግዛት አማራጭ ባካተተ የውሰት ውል ለማስፈረም ንግግር ላይ መሆናቸው ተነግሯል።
ሳውዝሀምፕተን ግብ ጠባቂውን ከሸጠ በቋሚነት መሸጥ እንደሚፈልግ ሲገለፅ ካልሆነ የክፍያ የውሰት ውል እንደሚፈልጉ ተገልጿል።
ባለፈው አመት በ 25ሚልዮን ፓውንድ ከአርሰናል ሳውዝሀምፕተንን የተቀላቀለው ራምስዴል በክለቡ ያለው ውል በ እስከ 2027 ይዘልቃል።
አሮን ራምስዴል ባለፈው አመት ለሳውዝሀሞፕተን በሁሉም ውድድሮች 32 ጨዋታዎች ማድረግ ችሏል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe
ከቀኑ 7:00 - 8:00 ሰዓት ባለው የእረፍት ሰዓታችን በማይቆራረጠው እና ፈጣኑ ኢንተርኔት በክረመት ምጥን የዳታ ጥቅል ፈታ እንበል! 1ጊባ በ5 ብር ብቻ!
#SafaricomEthiopia
#1Wedefit
#Furtheraheadtogether
" ምርጫው ቪዛን ያማከለ አይደለም “ አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ
የዋልያዎቹ ዋና አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ ወደ አሜሪካ የሚያቀኑ የብሔራዊ ቡድኑ ተጨዋቾች ምርጫ አቅም ላይ መሰረት ያደረገ መሆኑን ገልጸዋል።
" ምርጫው ቪዛን ያማከለ ሳይሆን ብቃትን ነው “ ያሉት አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ “ የመረጥናቸው ልጆች አቅማቸውን አይተን ነው “ ብለዋል።
ስለ ዝግጅት ያነሱት አሰልጣኙ " ማድረግ የሚገቡን ታክቲካዊ ዝግጅቶች አድርገናለል “ ሲሉ ተናግረዋል።
በቀጣይ ከ/ሊጉ ውጪ ጥሩ የሰሩ ተጨዋቾች ለመምረጥ ያስቡ እንደሆነ የተጠየቁት አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ “ አንዳንድ ተጨዋቾች ለማየት ሞክሪያለሁ በቀጣይም እንመለከታለን። " ብለዋል።
በአሜሪካ ስለሚገኘው ሱራፌል ዳኛቸውን በተመለከተ “ ያለበትን ሁኔታ አጣርተን ነው የመረጥነው “ ሲሉ አሰልጣኙ ምላሽ ሰጥተዋል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe
" ዮኬሬሽን መጋፈጥ አስፈሪ ነው " ዊሊያም ሳሊባ
የመድፈኞቹ ተከላካይ ዊሊያም ሳሊባ አዲሱ የቡድናቸው አጥቂ ቪክቶር ዮኬሬሽ ለመግጠም አስፈሪ አጥቂ መሆኑን ተናግሯል።
" ቪክቶር ዮኬሬሽ ምን ያህል ምርጥ እንደሆነ እናውቃለን የሚለው ዊሊያም ሳሊባ ከእሱ በተቃራኒ መጫወት አስፈሪ ነው ብሏል።
“ እሱ በቡድናችን ስላለ ደስተኛ ነኝ ጨዋታዎች እንድናሸንፍ እና ዋንጫ እንድናነሳ እንደሚረዳን እርግጠኛ ነኝ።“ ብሏል።
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
ሰንደርላንድ ዣካን ለማስፈረም ተስማማ !
አዲስ አዳጊው ክለብ ሰንደርላንድ ስዊዘርላንዳዊውን አማካይ ግራኒት ዣካ ለማስፈረም ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል።
ሰንደርላንድ ተጫዋቹን 20 ሚልዮን ዩሮ በማውጣት በሁለት አመት ኮንትራት ለማስፈረም ከባየር ሌቨርኩሰን ጋር ከስምምነት ደርሰዋል።
የ 32ዓመቱ የቀድሞ የአርሰናል አማካይ ግራኒት ዣካ ሰንደርላንድን ለመቀላቀል ጉዞ እንዲያደርግ ፍቃድ ማግኘቱ ተዘግቧል።
የባየር ሌቨርኩሰኑ ዋና አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ወሳኝ ተጨዋቾቹን ያጣው ቡድናቸው ግራኒት ዣካን መልቀቅ እእንደማይፈልግ ሲገልፁ ነበር።
ባለፉት ሁለት አመታት በባየር ሌቨርኩሰን ያሳለፈው ተጨዋቹ ለክለቡ 99 ጨዋታዎች ሲያደርግ ቡድኑ ቡንደስሊጋውን እንዲያሸንፍ ረድቷል።
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
አንድሬ ኦናና ለአርሰናል ጨዋታ ይደርሳል ?
የማንችስተር ዩናይትዱ ቁጥር አንድ ግብ ጠባቂ አንድሬ ኦናና የጡንቻ ጉዳት እንዳጋጠመው አይዘነጋም።
ተጨዋቹ ከጉዳቱ አገግሞ ወደ ሜዳ ለመመለስ እስከ ስድስት ሳምንት ጊዜ ሊያስፈልገው እንደሚችል መነገሩም አይዘነጋም።
አንድሬ ኦናና አሁን ላይ በፕርሚየር ሊጉ ከአርሰናል ጋር ለሚደረገው መርሐግብር ወደ ሜዳ ለመመለስ ተስፋ ማድረጉ ተገልጿል።
ማንችስተር ዩናይትድ የሊጉን መክፈቻ ጨዋታ በኦልድትራፎርድ ከአርሰናል ጋር እንደሚያደርግ ይታወቃል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe
የጆሬል ሀቶ የቼልሲ ዝውውር ከምን ደረሰ ?
የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ በጆሬል ሀቶ ዝውውር ዙሪያ በዚህ ሳምንት ከአያክስ ጋር ቀጥተኛ ድርድር እንደሚጀምሩ ተገልጿል።
ኔዘርላንዳዊው ተከላካይ ጆሬል ሀቶ ለክለቡ አያክስ ቼልሲን መቀላቀል እንደሚፈልግ ማሳወቁ ተነግሯል።
በሌላ በኩል ሰማያዊዎቹ የዣቪ ሲሞንስን ዝውውር ለማጠናቀቅ ከጫፍ እንደደረሱ ፋብሪዝዮ ሮማኖ ዘግቧል።
ተጨዋቹ በእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ መጫወት እንደሚፈልግ ሲገለፅ ወደ ጣልያን ሴርያ የማምራት እቅድ እንደሌለው ተነግሯል።
ኢንተር ሚላን ስሙ ከዣቪ ሲሞንስ ጋር ቢያያዝም አሁን ላይ የተጀመረ የዝውውር ሂደት እንደሌለ ተዘግቧል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe
የባርሴሎናው ምክትል ፕሬዝዳንት ወደ አል ነስር ?
የባርሴሎናው ምክትል ፕሬዝዳንት ራፋ ዩስቴ ከሳውዲ አረቢያው ክለብ አል ነስር የዝውውር ጥያቄ እንደቀረበላቸው ተገልጿል።
አል ነስር የባርሴሎናው ምክትል ፕሬዝዳንት ራፋ ዩስቴን የክለቡ ዋና ስራ አስፈፃሚ ለማድረግ መጠየቁን ሙንዶዴፖርቲቮ ዘግቧል።
ምክትል ፕሬዝዳንት ራፋ ዩስቴ ነገ ከጃፓን ወደ ስፔን ሊመለሱ መሆኑ ሲገለፅ አል ነስር ከፍተኛ ክፍያ እንዳቀረበላቸው ተጠቁሟል።
የባርሴሎናው ፕሬዝዳንት ሁዋን ላፖርታ ስለጉዳዩ እንደሚያውቁ ነገርግን በመንገዳቸው ለመቆም እንዳላሰቡ ተገልጿል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe
" ከሜሲ ጋር መጫወት ህልም ነው " ማህሬዝ
አልጄሪያዊው የፊት መስመር ተጨዋች ሪያድ ማህሬዝ ከአል አህሊ ጋር ስሙ የተያያዘው ሊዮኔል ሜሲ ቡድናቸውን ቢቀላቀል እንደሚመኝ ተናግሯል።
" ሊዮኔል ሜሲ ወደ አል አህሊ ይመጣል የሚሉ ዘገባዎች ከሚዲያዎች እየሰማን እውነት ከሆነ ከእሱ ጋር መጫወት ህልም ይሆናል ሲል ተደምጧል።
“ ሳውዲ ሊግ ኳስ ይዘው ለሚጫወቱ ተጨዋቾች ጥበቃ አይደረግም ሊዮኔል ሜሲ ከመጣ የተለየ ጥበቃ ያስፈልገዋል “ ማህሬዝ
@tikvahethsport @kidusyoftahe
ሊቨርፑል ከዲያዝ ሽያጭ ትርፍ ያገኛሉ !
ኮሎምቢያዊው የፊት መስመር ተጨዋች ሉዊስ ሊቨርፑልን ለመልቀቅ ጥያቄ ያቀረበው ያለፈው ክረምት እንደነበር ተገልጿል።
ሊቨርፑል ለተጨዋቹ ሁለት ጊዜ የኮንትራት ማራዘሚያ ጥያቄ ቢያቀርቡም ውድቅ እንዳደረገባቸው ዘ አትሌቲክ አስነብቧል።
የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ከሉዊስ ዲያዝ ሽያጭ 26 ሚልዮን ዩሮ ትርፍ እንደሚያገኙ ተገልጿል።
ሊቨርፑል ሪቻርድ ሂውዝን በስፖርቲንግ ዳይሬክተርነት ከሾመ ወዲህ ከተጨዋቾች ሽያጭ 190 ሚልዮን ፓውንድ ገቢ ማግኘቱ ተነግሯል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe
" ተጨዋች አስፈርመን አልጨረስንም “ አርቴታ
የመድፈኞቹ ዋና አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ቡድናቸው በዝውውር ገበያው ገና ስራውን እንዳልጨረሰ ተናግረዋል።
" የዝውውር ገባያው ገና አልተጠናቀቀም " ያሉት ሚኬል አርቴታ አሁንም እየሰራን ነው ጥሩ አማራጮችን እየፈተሽን ነው ብለዋል።
አክለውም “ በዝውውር መስኮቱ የቡድኑን ሚዛን መጠበቅ አለብን “ ሲሉ ተደምጠዋል።
ቪክቶር ዮኬሬሽ በቶተንሀም ጨዋታ ይሳተፍ እንደሆነ የተጠየቁት አሰልጣኙ “ ነገ እንመዝነዋለን በተሻለ ፍጥነት ዝግጁ እንዲሆን እንፈልጋለን " ብለዋል።
ጥሩ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ስለሚገኘው ማክስ ዶውማን ያነሱት አርቴታ “ ከ 15ዓመት ተጨዋች ይህንን ብቃት ማየት የተለመደ አይደለም “ ሲሉ ገልፀዋል።
" ካላፊዮሪ የሆነ ነገር ተሰምቶታል የጉዳት መጠኑን ላውቅ አልቻልኩም “ ሚኬል አርቴታ
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
አርሰናል ኒውካስል ዩናይትድን አሸንፏል !
በወዳጅነት መርሐ ግብር አርሰናል ከኒውካስል ዩናይትድ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 3ለ2 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።
የአርሰናልን የማሸነፊያ ግቦች ማርቲን ኦዴጋርድ ፣ ሚኬል ሜሪኖ እና ሙርፊ በራሱ መረብ ላይ አስቆጥረዋል።
ለኒውካስል ዩናይትድ አንቶኒ ኢላንጋ እና ጃኮብ ሙርፊ አስቆጥረዋል።
መድፈኞቹ ከጨዋታው በፊት አዲሱን ፈራሚ ቪክቶር ዮኬሬሽ ከደጋፊዎቻቸው ጋር አስተዋውቀዋል።
አርሰናል የፊታችን ሐሙስ ከቶተንሀም ጋር በ ሆንግ ኮንግ ካይ ታክ ስፖርትስ ስታዲየም የሚጫወቱ ይሆናል።
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
ባየር ሙኒክ ዲያዝን ለማስፈረም ተቃርቧል !
የቡንደስሊጋው ክለብ ባየር ሙኒክ የሊቨርፑልን የፊት መስመር ተጫዋች ሉዊስ ዲያዝ ለማስፈረም የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል።
ሊቨርፑል ተጫዋቹን ተጨማሪ ክፍያን ጨምሮ በ 75 ሚልዮን ዩሮ የዝውውር ሒሳብ ለማስፈረም ከባየር ሙኒክ ጋር መስማማታቸው ተነግሯል።
ሁለቱ ክለቦች አሁን ላይ በተጨማሪ ክፍያው አከፋፈል ዙሪያ ንግግር ላይ መሆናቸው ተዘግቧል
የ 28ዓመቱ ኮሎምቢያዊ ሉዊስ ዲያዝ ሊቨርፑልን በመልቀቅ አዲስ ነገር መሞከር እንደሚፈልግ ማሳወቁ አይዘነጋም።
ሉዊስ ዲያዝ በቀጣይ በባየር ሙኒክ ቤት የአራት አመት ኮንትራት እንደሚፈርም ስካይ ስፖርት ዘግቧል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe
🔉 ጎልልልልልል- የኳስ መረጃዎችን በየቀኑ በስልካችን!
ከሳፋሪኮም ቁጥራችን 'A’ ብለን ወደ 30002 SMS በመላክ ወይም ወደ *799# በመደወል አሁኑኑ ቴስታ ጎል እንቀላቀል! በቀን 1 ብር ብቻ!
በቴስታ ጎል ትኩስ ስፖርታዊ መረጃዎች በሽ በሽ ነው!⚡️
#SafaricomEthiopia
#1Wedefit
#Furtheraheadtogether