tikvahethiopia | Unsorted

Telegram-канал tikvahethiopia - TIKVAH-ETHIOPIA

1532594

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። @tikvahuniversity @tikvahethAfaanOromoo @tikvahethmagazine @tikvahethsport @tikvahethiopiatigrigna #ኢትዮጵያ

Subscribe to a channel

TIKVAH-ETHIOPIA

#NewsAlert
#Tigray #Afar

" ኃላቀሩ ቡድን የፌደራል መንግስትን ወደ ግጭት ለማስገባት በዓፋር በኩል ትንኮሳዎች ፈፅሟል ይህንንም የአዛዡና ጌታውን ሻዕብያ አጀንዳ ለማስፈፀም የተደረገ ነው " - አቶ ጌታቸው ረዳ

ጥቂት የትግራይ ኃይል አመራሮች በሻዕብያ ትእዛዝ ሰጪነት በፌደራል መንግስት ላይ ትንኮሳ እንደጀመሩና ይህን ትንኮሳ እንዲያቆሙ አቶ ጌታቸው ረዳ አሳሰቡ።

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚንስትር የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚንስትር አቶ ጌታቸው ረዳ  ፤ " ፍስሃ ማንጁስና ዮሃንስ መዲድ የተባለችሁ የትግራይ ሰራዊት አመራሮች የጀመራችሁትን የግጭት ቀስቃስ እንቅስቃሴ አቁሙ " ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

ሚንስትሩ " ኃላቀር ቡድን " ሲሉ የጠቀሱት የህወሓት አመራር የፕሪቶሪያ ስምምነት ለመቅደድ ሁሉም ዓይነት ትንኮሳ ቢፈፅምም የፌደራል መንግስት የአፀፋ ምላሽ ከመስጠት ተቆጥቧል ብለዋል።

" ኃላቀር " ያሉት የህወሓት አመራር ቡድን የፌደራል መንግስትን ወደ ግጭት ለማስገባት " በዓፋር በኩል ትንኮሳዎች ፈፅሟል ይህንንም የአዛዡና ጌታውን ሻዕብያ አጀንዳ ለማስፈፀም የተደረገ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

በዓፋር ክልል በኩል በፌደራል መንግስት ላይ የተደረገው ትንኮሳ " ጀነራል ፍስሃ ማንጁስና  ጀነራል ዮሃንስ መዲድ ናቸው የመሩት ማቆም ያለባቸው እነሱ ናቸው " ሲሉ አሳስበዋል።

" ጦር አውርድ በሚል ፀሎት በራስ ህዝብ ላይ መከራና ጭፍጨፋ መጋበዝ ክህደት ነው " ያሉት ሚንስተር ጌታቸው " በትግራይና በዓፋር በኩል ያላችሁት የትግራይ ሰራዊት (TDF ) እና የትግራይ የሰላም ሃይል (TPF) የሻዕብያን ፍላጎት ለማሳካት ወደ እርስ በርስ ግጭት መግባት የለባችሁም " ብለዋል።

" ለትግራይ የሚያስብና እርባና ያለው ሰው ሦስተኛ ዓመቱ ያስቆጠረውን የፕሪቶሪያ ውል ከወዴት ደረሰ ? ብሎ መጠየቅ ብቻ ነው የሚያዋጣው " ሲሉ አቶ ጌታቸው ረዳ ገልጸዋል።

ትላንት ማክሰኞ ጥቅምት 25 /2018 ዓ.ም ከሰዓት በኃላ በትግራይ ኃይሎች እና በትግራይና ዓፋር ክልል አዋሳኝ በሚገኙት ራሳቸውን " የትግራይ የሰላም ኃይል ታጣቂዎች (TPF) " ብለው በሚጠሩት መካካል ግጭት መቀስቀሱ በማህበራዊ የትስስር ገፆች በስፋት ተነግሯል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" ያለኝ ሕይወት የኔ አይደለም። የእግዚአብሔር ነው። የምኖረው እሱ የሰጠኝን ነው !! " - ሌሊሴ ዱጋ

🙏 " የካንሰር አራተኛ ደረጃ ላይ ነው ያለሁት። የሚጎዳኝ ነገር ቢሆንም በፈጣሪ አምናለሁ። ፈጣሪን አስቀድማለሁ። እፀልያለሁ !! "

የኦሮሚያ የቱሪዝም ኮሚሽን ኮሚሽነር ሌሊሴ ዱጋ የካንሰር ሕክምና እየተከታተሉ መሆናቸውን በመግለጽ ፎቷቸውን ጭምር አያይዘው በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ከቀናት በፊት አጋርተው ነበር።

ሌሊሴ ፀጉራቸውን አጥተው ከሚሠሩበት ላፕቶፕ ፊት ለፊት በፈገግታ የተሞላ ፎቶ ግራፋቸውን " እየሠራሁ፣ እየታገልኩ፣ እያሳካሁ " ከሚል የእንግሊዝኛ ጽሑፍ ጋር አጋርተዋል።

ኮሚሽነሯ ይህንን ፎቶ እና መልዕክት ካስተላለፉ በኋላ በርካታ ሰዎች እንዲፈወሱ መልካም ምኞታቸውን በመግለጽ ፎቷቸውን እያጋሩት ነው።

እንዲህ ያለውን የጤና ሁኔታ ለሕዝብ ማጋራት ባልተለመደበት ማኅበረሰብ ውስጥ ኮሚሽነር ሌሊሴ ይህንን ማድረጋቸው በብዙዎች ዘንድ መነጋጋሪያ ከመሆኑ በላይ አድናቆት እንዲቸራቸው አድርጓል።

ሌሊሴ ሕክምና እየተከታተሉ የሚገኙበት በመካከለኛው ምሥራቋ ዮርዳኖስ ውስጥ ነው።

ስላሉበት ሁኔታ ለቢቢሲ አማርኛ ቃላቸውን ሰጥተዋል።

ሌሊሴ ዱጋ ምን አሉ ?

" ሊምፎሚያ በተባለው የካንሰር ዓይነት መያዜን ያወቁት ከአራት ወራት በፊት ለሌላ ምርመራ ወደ ጤና ተቋም በሄድኩበት ወቅት ነው።

ይህ የካንሰር ዓይነት ነጭ የደም ሕዋስን የሚያጠቃ ነው።

የጋስትሮኢንተስታይን ችግር / ሰውነት ምግብ የሚያብላላበት ሆድ ዕቃ ሕመም / መስሎኝ ወደ ሆስፒታል ሄድኩ። ካንሰር እንደሆነ ተነገረኝ።

ቀላል አይደለም። የካንሰር አራተኛ ደረጃ ላይ ነው ያለሁት። የሚጎዳኝ ነገር ቢሆንም በፈጣሪ አምናለሁ። ፈጣሪን አስቀድማለሁ። እፀልያለሁ።

ባለቤቴ፣ ልጆቼ፣ ቤተሰቦቼ እና ጓደኞቼ ከጎኔ ናቸው። ይፀልዩልኛል። ያበረታቱኛል። ሕልም ስላለኝ ብታመምም መኖር፣ መታገል እና ታትሮ መሥራት አላቋርጥም።

አሁን ላይ የኬሞቴራፒ ሕክምና እያገኘው ነው። ብዙ የጎንዮሽ ጉዳት አልደረሰብኝም።

ፀጉሬን አጥቻለሁ። ቆንጆ ፀጉር ነበረኝ። ፀጉር ማጣት ለሴት ልጅ ከባድ ነው። ፀጉርን ማጣት የተለየ ዝግጅት ይጠይቃል።

ፈጣሪ ረድቶኝ ወደ አገሬ ከተመለስኩ ለሕክምና ገንዘብ የሌላቸውን የካንሰር ሕሙማን የሚደግፍ ማዕከል ማቋቋም እፈልጋለሁ።

በባለቤቴ በኩል የተባበሩት መንግሥታት የጤና መድኅን አለኝ፤ መንግሥትም እያሳከመኝ ነው። የገንዘብ ችግር ስለሌለብኝ ነው እየታከምኩ ያለሁት። እርዳታ የሚያሻቸው ብዙ ሰዎች አሉ። ሲሻለኝ እነዚህ ሰዎች ለመርዳት ማዕከል አቋቁማለሁ።

አሁን ላይ ብርታት የሰጠኝ የሕይወት ፍልስፍናዬ ነው።

የሕይወት ፍልስፍናዬ ቀላል ነው። በየቀኑ የምችለውን ማድረግ፣ ዋጋ ያለው ነገር ማድረግ እና ጥሩ መሆን። ፈጣሪ ያስተማረን ይሄንን ነው። ምድር ላይ እስካለን ድረስ ጥሩ ነገር ብናደርግ መልካም ነው።

ያለኝ ሕይወት የኔ አይደለም። የእግዚአብሔር ነው። የምኖረው እሱ የሰጠኝን ነው። ያለ ፀፀት መኖር ነው የምሻው። ለመኖር የሚያበረታኝ እና ወደፊት የምቀጥለው በዚህ ነው።

በየዕለቱ ጥሩ እንዳደረኩ ለራሴ እየነገርኩት  ከፈጣሪ ምሕረትን ጠይቄ ነው የምተኛው።

ሕክምናውን ለመጨረስ ከአራት እስከ አምስት ወራት ይወስዳል " ብለዋል።

ሌሊሴ ዱጋ አሁን ላይ ካሉበት ዮርዳኖስ ሆነው ስራቸውን ቀጥለዋል።

ከሚከታተሉት ሕክምናቸው ጎን ለጎን ሥራቸውን የሚያከናውኑበት ቢሮ አላቸው። አንድም ቀን " ታምሜያለሁ " ብለው እያሰቡ እንደማያድሩ ተናግረዋል።

የኦሮሚያ የቱሪዝም ኮሚሽን የአምስት ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድን እያወጡ ሲሆን በቀጣይ አምስት ዓመታት ምን መሠራት አለበት የሚለውን እየሰሩበት እንዳለ ገልጸዋል።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የቢቢሲ አማርኛ አገልግሎት ነው።

🙏 ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለብርቱዋ ሴት ሌሊሴ ዱጋ ህክምናቸው እንዲሳካ ፤ ሙሉ ጤንነታቸውም እንዲመለስ ዘንድ ይመኛል። ሙሉ ጤንነትን ከረጅም እድሜ ጋር እንመኝላቸዋለን። የሚያምኑት ፈጣሪ ከዚህ በሽታ ይፈውሳቸው ዘንድም እንማጸናለን።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#SafaricomEthiopia

እንኳን ደስ አላችሁ! 🎉💵

ሰኞ ጥቅምት 24/2018 የአስረኛው ዙር ዕድለኞች ዕጣ አወጣጥ በቲክቶክ እና ፌስቡክ ገፃችን ላይ በቀጥታ ስናስተላልፍ በነበረዉ መሰረት የ100,000 ብር ዕድለኛ ከደቡብ ጎንደር ሆኑዋል።

ማን ያውቃል ቀጣይ እርስዎ ሊሆኑ ይችላሉ! የበሽ ጥቅል እየገዛን እንንበሽበሽ! 🥳🎉🎉

📲 የM-PESA መተግበሪያን አሁኑኑ ያውርዱ፡ https://onelink.to/ewsb22

የቴሌግራም ቦታችን👉🏽 /channel/official_safaricomet_bot

ወደ *777*0# ይደውሉ ወይም በM-PESA የበሽ ጥቅል ይግዙ!

#MPESASafaricom
#furtheraheadtogether
#Besh100Winner

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" ኢትዮጵያ 🇪🇹 የባህር በር ማግኘቷ አይቀርም ! "

ጄነራል ዓለምሸት ደግፌ ፦

" የባህር በር የማግኘት ጉዳይ ጥያቄው ቀርቧል ፤ ተነስቷል። ብዙዎቹ ሀገሮችም አምነውበታል።

አፈጻጸሙ ላይ ችግር ሊኖረው ይችላል ፤ ሊያንገታግተን ይችላል ፤ ጊዜ ሊወስድ ይችላል ግን ኢትዮጵያ የባህር በር የማግኘቷ ጉዳይ የግድ ነው ፤ ማግኘቷም አይቀርም።

ይሄ ትልቅ ህዝብ ፣ ይሄ ትልቅ ሀገር በፍጹም ታፍኖ ሊኖር አይችልም። የባህር በር እናገኛለን ይሄን የምናገኝበት መንገድ በዋናነት በሰላማዊ መንገድ ነው ብለን ነው የምናስበው።

ይሄ ከተረጋገጠ ደግሞ እኛም ባህር ኃይላችንን እዛ ላይ አጠናክረን እናዘጋጃለን። ስለዚህ የባህር ኃይል መደራጀቱ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ለማስከበር ነው።

የባህር በር ካገኘን በኃላ ' ቀስ ብለን እንደርስበታለን ' የሚባል ጉዳይ አይደለም። እያዘጋጀን እንቆያለን፣ እናሰለጥናለን ፣ ትጥቆቻችንን እናዘጋጃለን የባህር በሩ በተገኘ ሰዓት ኃይላችንን እናሰፍራለን። የራሳችንን ብሔራዊ ጥቅም እናስከብራለን። "

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#AmazonFashion

ኳሊቲ አዳዲስ ሙሉ ልብሶች አስገብተናል። ከ10ሺ እስከ 16ሺ የተለያዩ ሱፎች ገብተዋል።ዛሬዉኑ መተዉ የእርሶን ድርሻ ይዉሰዱ።ሱፍ መግዣ ጊዜዉ አሁን ነዉ።ሳይመረጥበት እና ሳያልቅቦት ይምጡ።

ቴሌግራም ቻናላችን ላይ ፎቶዋቸው ተለቀዋል። follow ያድርጉ ከፎቶቹ ላይ ይምረጡ።

በተጨማሪም 100% cotton ሸሚዝ high quality ፤በጅንስም በሱፍም የሚለበስ በ2900 ብር ብቻ፤በ1 ሺ 500ም ኳሊቲ ሸሚዞች አለን፤ አሪፍ ኮቶችንም  አስመጥተናል፤ በርካታ አማራጭ ስላለን ለብዛት ፈላጊዎች በብዙ አማራጭ አለን።   
   👉በተጨማሪም የሙሉ ልብስ ኪራይም  በሌላኛው ብራንቻችን አለን።
አድራሻ ፒያሳ downtown ህንፃ ምድር ላይ 
    ☎️0911072936 /0919339250
https://t.me/joinchat/AAAAAEc8iQJX1Zjgepjq1w

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን " ትላንትም 5 ምእመኖቼ ተገድለውብኛል " አለች።

" በአርሲ መርቲ ወረዳ የሚኖሩ 5 ኦርቶዶክሳውያን ተገድለው ፤ 3 ምዕመኖቼ ታግተው ተወስደዋል " ነው ያለችው።

" ግድያው እና እገታው የተፈጸመው በትናንትናው ዕለት ጥቅምት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ጋዶ ቀበሌ ነው " ብላለች።

" 5 ምእመናን የእርሻ ሥራቸውን አጠናቀው ምሳቸውን እየበሉ ባሉበት ጊዜ ነው በታጠቂዎች በተከፈተባቸው የተኩስ የተገደሉት " ስትል አክላለች።

ሥርዓተ ቀብራቸው በአቦምሳ ከተማ በሚገኘው በደብረ ገነት ትንሣኤ ብርሃን መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን እንደተፈጸመ ገልጻለች።

የታገቱት 3 ምእመናን እስከ አሁን የደረሰቡት እንዲሁም ያሉበት ሁኔታ አይታወቅም ብላለች።

" ይህን የምእመናኑ የግድያ እና የአፈና ተግባር ከሰሞኑ በሀገረ ስብከቱ እንደነበረው ሁሉ ተባብሶ የቀጠለ ነው " ያለችው ቤተክርስቲያኗ " በተለይም ላለፉት ሁለት ዓመታት የገጠር ቀበሌው እና በውስጡ የሚኖሩ ምእመናን ከስጋት ነጻ ሆነው ኖረው አያውቁም " ስትል አሳውቃለች።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" አጨዳ ላይ ቆይተው ምሳ ሊበሉ ጥላ ሥር አርፈው እየበሉ ባሉበት አምስት ሰዎች ተገድለዋል " - የአካባቢው ቤተክህነት አመራር

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በዚሁ ወር 25 ምዕመናን እንደተገደሉባት በገለጸችበት አርሲ ዞን ታጣቂዎች ትናንት በድጋሚ በተፈናቃይ አርሶ አደሮች ላይ ግድያ መፈጸማቸውን የአካባቢው ቤተ ክህነት አመራር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ለደኀንነታቸው ሲባል ስማቸው እንዲነገር ያልፈለጉት አመራሩ በሰጡን ቃል፣ ትናንት መርቲ ወረዳ ጋዶ የሚባል ቦታ ላይ " የሚሊሻ የጤፍ አጨዳ ውጡ ተብለው ታዘው አጨዳ ላይ ቆይተው ምሳ ሊበሉ ጥላ ሥር አርፈው እየበሉ ባሉበት አምስት ሰዎች ተገድተዋል " ብለዋል።

" ሸሽተውም ይሁን ተይዘው ያልታወቀና ያልተገኙ የጠፉ ሰዎችም አሉ። ሸሽተው የተጠፉ ናቸው። ቁጥራቸው በትክክል አልታወቀም ግን ብዙ ናቸው " ሲሉም አክለዋል።

የሟች አርሶ አደሮች አስከሬን ትላንት ምሽት ወደ ከተማ መግባቱን፣ የቀብር ሥነ ስርዓቱ ዛሬ በመርቲ ወረዳ አቦምሳ መድኃኒዓለም ቤተክርስቲያን እንደተፈጸመ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

በወረዳው በዚሁ ወር የተፈጸመውን ግድያ በማስታወስ የአሁኑም ግድያ በዚያው አቅራቢያ መፈጸሙን የገለጹት እኝሁ አካል፣ ሟቾቹን " ከዚህ በፊት አፈናቅለዋቸው ነበር " ሲሉ ገልጸዋል።

ጥቃቱ ተደጋጋሚ መሆኑንና አራት አመት እንዳስቆጠረ፣ በዚህ አራት አመት ውስጥ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እንደተገደሉ አስረድተዋል።

" የትላንቱ ግድያ በተፈጸመበት ቦታ አጠገብ ህብረተሰቡ ተፈናቅሏል። ታጣቂዎች በቤታቸው እየገቡ ይገድሏቸዋል፤ ያንን እያየ  ሰው ተፈናቅሏል፤ ከዚህ ሸሽተው የነበሩ ሰዎች ናቸው 'ሚሊሻ አገርን እየጠበቀ ነው፤ ኑ ለአጨዳ ውጡ' በተባሉበት ነው የተገደሉት፤ ደኀና ተደብቀው የነበሩት ናቸው የተገደሉት " ነው ያሉት።

" ከዚህ ቀደምም ለአባቶች መልዕክት አስተላልፈናል። ሰሚ አካል ካለ ይህንን ሰምቶ መንግስት እንዲህ አይነቱን ወንጀለኛ አውጥቶ ህዝቡ በሰላም የሚኖርበትን ነገር ቢመቻችልን። እየሆነ ያለው ነገር በጣም ከባድ ነው " ብለዋል።

በጥቅምት 2018 ዓ/ም በአርሲ ዞን የተለያዩ ወረዳዎች 25 የኦሮቶዶክስ እምነት ተከታዮች መገደላቸውን ቤተ ክርስቲያኗ ጭምር ማሳወቋ የሚታወስ ሲሆን፣ የትናንቱን የአርሶ አደሮች ግድያ ጨምሮ በዚሁ ወር የሟቾች ቁጥር 30 ደርሷል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የአካባቢውን አካላት ምላሽ ለማካተት ሙከራ ቢያደርግም ለጊዜው አልተሳካም። የቅርቡን የዞኑ ግድያ በተመለከተ ምላሽ የጠየቅናቸው የዞኑና የክልሉ አካላት ፈቃደኛ ሳይሆኑ መቅረታቸው ይታወሳል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" ድጋፍ ማድረግ በምትፈልጉበት ወቅት ተገቢውን ማጣራት አድርጉ " - ፖሊስ

ያልታመመ ሰው ታማሚ በማስመሰል ተሽከርካሪ ውስጥ አስተኝተው ከህብረተሰቡ ገንዘብ ሲለምኑ የነበሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ማዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ።

አንድን ወጣት የኩላሊት ታማሚ በማስመሰል በተከራዩት የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3- 26734 ኦሮ የሆነ ሚኒባስ ውስጥ አስተኝተው በእርዳታ ስም ከህብረተሰቡ ገንዘብ ሲሰበስቡ የነበሩት ተጠርጣሪዎች ሊያዙ የቻሉት አያት አደባባይ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ባደረገው ክትትል እንደሆነ ገልጿል።             

በተሽከርካሪው ውስጥ በተደረገ ፍተሻ ፦
- በዕርዳታ ስም የተሰበሰበ 23 ሺህ 325 ብር
- በሃሰት የተዘጋጀ የህክምና ሰነድ እና የድጋፍ ደብዳቤ ተገኝቷል።

በሰነዶቹ ላይ በተደረገው ማጣራት ሃሰተኛ መሆናቸው እንደተረጋገጠ ፖሊስ ገልጿል፡፡

ገንዘብ በመሰብሰብ ስራ ላይ ለተሰማሩት ግለሰቦች በቀን 300 ብር የሚከፈላቸው ሲሆን ተሽከርካሪውን በቀን 3000 ሺህ ብር እንደተከራዩት እና ለአሽከርካሪው 1 ሺህ ብር እንደሚከፈለውም አረጋግጫለሁ ብሏል።             

በወንጀሉ በቀጥታ የተሳተፉ እና የተባበሩ በአጠቃላይ 9 ተጠርጣሪዎች ላይ ምርመራ እየተጣራ እንደሚገኝም አሳውቋል።

ህብረተሰቡ በየመንገዱ የሚካሄዱ እንዲህ አይነት ህገ ወጥ ተግባራትን በመከላከል ረገድ የድርሻውን እንዲወጣ ፤ ድጋፍ ማድረግ በሚፈልግበት ወቅት ተገቢውን ማጣራት እንዲያደርግና አጠራጣሪ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙ ለሚመለከተው አካል ጥቆማ እንዲሰጥ ፖሊስ ጥሪውን አቅርቧል፡፡

#AddisAbabaPolice

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" ጦርነት ብታሸንፍም ባታሸንፍም ጣፋጭ ሆኖ አያውቅም " - ጀነራል ሳሞራ የኑስ

➡️ " ህዝቡ እስካሁን ድረስ የጦርነቱን ጦስ በጫንቃው ተሸክሟል፡፡ እንደዚህ ዓይነት  ከባድ ስህተት  መደገም የለበትም ! "

" በትግራይ ክልል የሀሳብ ልዩነት ሲፈጠር በጦርነት ብቻ ለመፍታት የሚደረግ ሩጫ መቆም አለበት " ሲሉ የቀድሞው  የመከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀነራል ሳሞራ ዩኑስ ተናገሩ።

ጀነራል ሳሞራ ይህን ያሉት ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ በሰጡት ቃል ነው።

ጀነራል ሳሞራ የኑስ ምን አሉ ?

" ከዚህ ቀደም  የተፈፀመው ከባድ ስህተት የትግራይን ህዝብ ዋጋ አስከፍሏል፡፡  አሁን የትግራይ ህዝብ ጦርነት በቃኝ ብሏል፡፡  በሆነ አጋጣሚ የጦርነት አዝማሚያ ቢፈጠር እንኳ ህዝቡ ይህንን የመደገፍ ሀሳብ የለውም።

ከዚህ ቀደም ችግሮችን በውይይት መፍታት ባለመቻሉ የተቀሰቀሰው ጦርነት የትግራይን ህዝብ ከባድ ጉዳት አድርሶበታል፡፡ ህዝቡ እስካሁን ድረስ የጦርነቱን ጦስ በጫንቃው ተሸክሟል፡፡ እንደዚህ ዓይነት  ከባድ ስህተት  መደገም የለበትም።

ጦርነት ብታሸንፍም ባታሸንፍም ጣፋጭ ሆኖ አያውቅም። በክልሉ በርካታ ወጣት ህይወቱን አጥቷል፣ እናቶችም በሀዘን ተጎድተዋል፣ ተቸግረዋልም፤ በመሆኑም ህዝቡ በተደጋጋሚ ውጊያ ውስጥ ሊማገድ አይገባውም።

በትግራይ ውስጥ ማንኛውም ችግር ወይም የሀሳብ ልዩነት ሲፈጠር በጦርነት ብቻ ለመፍታት የሚደረግ ሩጫ መቆም አለበት። ልዩነቶች በሰላምና በሰላም ብቻ መፈታት አለባቸው በሚል እምነት መፅናት ያስፈልጋል።

በክልሉ የጦርነት ችግር ይመጣል እያሉ ያልተጨበጠ ወሬ የሚለፍፉ የጦር ጀነራሎችን እሰማለሁ። ይህ የግል ሀሳባቸው ሊሆን ይችላል፤ እኔ የምላቸው ግን የእውነት የህዝብ አገልጋይ ከሆኑ በትግራይ ክልል ያለውን የፀጥታ ችግር መፍታት የመጀመሪያው ጉዳያቸው ሊያደርጉት ይገባል። " ብለዋል።

#ኢፕድ

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" ባለፉት ሦስት ወራት በአዲስ አበባ በወቅቱ የተመዘገበ ፍቺ ቁጥር 853 ነው " - የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት

የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ በመዲናዋ የወሳኝ ኩነት ምዝገባ የሚያከናውንባቸው አምስት ኩነቶች ማለትም በልደት፣ ሞት፣ ጋብቻ፣ ፍቺ እና ጉዲፈቻ በአጠቃላይ በሩብ አመቱ በወቅቱ፣ በዘገየ እና ጊዜ ገደብ ባለፈበት 172 ሺ 11 ኩነቶችን ምዝገባ ማከናወኑን ገልጿል።

ኤጀንሲው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደገለጸው በሩብ አመቱ በአዲስ አበባ በወቅቱ፣ በዘገየ እና ጊዜ ገደብ ባለፈበት የተመዘገበ ፍቺ ቁጥር 3 ሺ 32 መሆኑን አሳውቋል።

ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ጥጋቡ ሹመይ"ፍቺን በተመለከተ የሚዘዋወረው መረጃ በሩብ አመቱ 3 ሺ 32 ተብሎ ነው ነገር ግን አብዛኛው ተመዝጋቢ ጊዜ ገደቡ ያለፈበት ተመዝጋቢ ነው"ብለዋል።

እንደ ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ገለጻ ባለፉት ሦስት ወራት በወቅቱ ወይም ፍቺው በተፈጠረ በ 30 ቀናት ውስጥ ምዝገባ ያከናወኑ ነዋሪዎች ቁጥር 853 ነው።

የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር እና የኩነት እና የነዋሪዎች ዘርፍ ኃላፊ አቶ ጥጋቡ ሹመይ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ምን አሉ?

" ወሳኝ ኩነቶች በሦስት ደረጃ ይመዘገባሉ የመጀመሪያው በወቅታዊ ሲሆን ልደት እንደተከሰተ በ90 ቀናት ውስጥ መመዝገብ አለበት የቀሩት ኩነቶች ደግሞ በ 30 ቀናት መመዝገብ ይኖርባቸዋል።

ሁለተኛው በዘገየ ተብለው የሚመዘገቡ ናችው የዘገየ ተብለው የሚመዘገቡ ኩነቶች በተከሰተ በአንድ አመት ውስጥ ምዝገባ ሲከናወን ማለት ነው።

ሦስተኛው ጊዜ ገደቡ ያለፈበት ምዝገባ የሚባለው ነው እነዚህ ኩነቶች በተከሰቱ ከአንድ አመት በላይ ጊዜ ገደብ ካሳለፉ በኋላ የሚመዘገቡ ከሆነ ጊዜ ገደቡ ያለፈበት ምዝገባ ይባላሉ።

የወሳኝ ኩነት ምዝገባዎች በሃገር አቀፍ ደረጃ እና በአዲስ አበባ እየተከናወነ ያለው በሦስቱም መንገዶች ነው ።

በሩብ አመቱ በልደት፣ በጋብቻ ፣ ፍቺ፣ ሞት እና ጉዲፈቻ በወቅቱ መመዝገብ የቻልነው 30 ሺ 571 ናቸው።

ልደት 25 ሺ 876 ፣ ጋብቻ 2536፣ ፍቺ 853  ፣ ሞት 1258 ፣ ጉዲፈቻ 58 በወቅቱ ተመዝግበዋል።

ከእቅዳችን አንጻር ሁሉም ኩነቶች ላይ የተሻለ አፈጻጸም ቢኖረንም የሞት ምዝገባ ግን ከእቅዳችን አንጻር ዝቅተኛ ነው ይህ የሆነበት ምክንያት ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር (እድር) በቅንጅት መስራት እንዳለብን ያሳያል።

በዘገየ ምዝገባ ማለትም ከተከሰተ ከ 30 ቀን እስከ አንድ አመት ባለው ጊዜ የተመዘገበ ልደት 4,194 ፣ ጋብቻ 844  ፣ፍቺ 416 ፣ ሞት 818 ጉዲፈቻ 12 መዝግበናል።

ጊዜ ገደብ ባለፈበት የተመዘገቡ ኩነቶች ልደት 123 ሺ 717 ፣ ጋብቻ 7326፣ ፍቺ 1763 ፣2320 ሞት ፣ጉዲፈቻ 30 ናቸው።

በአጠቃላይ በሩብ አመቱ በአምስት ኩነቶች በወቅቱ፣ በዘገየ እና ጊዜ ገደብ ባለፈበት ብለን የመዘገብናቸው ኩነቶች 172 ሺ 11 ኩነቶችን ናቸው።

ከእዚህ ውስጥ ልደት 153 ሺ 787፣ ጋብቻ 10 ሺ 696፣ ፍቺ 3,032 ፣ ሞት 4 ሺ 396፣ ጉዲፈቻ 100 ተመዝጋቢዎችን ይይዛሉ።

ፍቺን በተመለከተ የሚዘዋወረው መረጃ በሩብ አመቱ 3 ሺ 32 ተብሎ ነው ነገር ግን አብዛኛው ተመዝጋቢ ጊዜ ገደቡ ያለፈበት ተመዝጋቢ ነው።

ጊዜ ገደቡ ያለፈበት ምዝገባ ማለት ከእዚህ በፊት ፍቺው ተከስቶ ሳያስመዘግቡት ቀርተው የፍቺ ምስክር ወረቀቱን ያላገባ ለማውጣት እና ለተለያዩ አስተዳደራዊ ጉዳዮች በሚጠየቁበት ወቅት መጥተው የተመዘገቡ ናቸው።

ወሳኝ ኩነት ምዝገባውን ለማሳደግ ለምሳሌ ልደትን በተመለከተ ከ 143 ጤና ተቋማት ጋር በቅንጅት ነው የምንሰራው።

ፍቺም በወቅቱ እንዲመዘገብ ለማድረግ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት 11 ምድብ ችሎቶች አሉት በሁሉም ምድብ ችሎቶች የሚፈጸሙ ፍቺዎችን በወቅቱ ለመመዝገብ ባለሞያዎቻችን ገብተው የመመዝገብ ስራ እየሰራን እንገኛለን የጉዲፈቻም በተመሳሳይ።

ከሞት ምዝገባ ጋር ተያይዞም የሞት መረጃ የምናገኘው በጤና ተቋማት እና በማህበረሰብ በኩል ነው በማህበረሰቡ ውስጥ የሚከሰቱ የሞት መረጃዎች የሚገኙት በእድሮች በኩል በመሆኑ የእኛ ወረዳዎች ከእድር አመራሮች ጋር በመስራት ላይ እንገኛለን።

በቅርቡ አዲስ ሲስተም አልምተናል ለምረቃ ዝግጅት ላይ እንገኛለን ወደ ተግባር ሲገባ ወደ እድሮች ተደራሽ አድርገን በእድር አባሎች ላይ የሚከሰት ሞት እዛው ተመዝግቦ የምዝገባ መረጃው በሲስተሙ ወደ እኛ የሚገባ ይሆናል።

በጤና ተቋማትም ሲስትሙ ተደራሽ ይሆናል ስልጠና ሰጥተን አስፈላጊውን ግብአት አሟልተን በሙከራ ደረጃም እየወሰድን ወደ ተሟላ የምዝገባ ስርአት እንዲገቡ እናደርጋለን " ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" የልጄ ሊዛ ደም ባክኖ ሊቀር ነው፤ ፍትህ ልናጣ ነው ተቸግረናል " - የሟች ተማሪ ሊዛ አባት

" ባለቅስም እንባ ነው ሊዛን አላገኘኋትም፥ የልጄን ገዳይ ግን አያይዙኝ " - እናት


ከሳምንታት በፊት በደሴ ከተማ ተደፍራና ተገድላ የተገኘቸው ዘንድሮ ትመረቃለች ተብላ ስትጠበቅ የነበረችው የፋርማሲ ተማሪዋ ሊዛ ደሳለ ወላጆች እስካሁን የልጃቸው ገዳይ መያዝና አለመያዙን ባለማወቃቸው ፍትህ እንዲሰጣቸው ጠየቁ።

የተማሪ ሊዛ አባት መምህር ደሳለ ሞላ፣ ከሚያገኙት ትንሽ የመምህር ደመወዝ እየከፈሉ ልጃቸውን እያስተማሩ እያለ የሞት ዱብ እዳ እንደሰሙ፣ በጉዳዩ ላይ በሳምንት ፍትህ እንደሚሰጣቸው ቢነገራቸውም እሳከሁን ምንም እንዳልተባሉ ዛሬ ምሽት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

የተማሪዋ አባት መምህር ደሳለ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን አሉ ?

" እኔ ሀዘን ላይ በመሆኔ የሊዛ እክስት አጎቶች 'ለሕግ አመልክተን እንምጣ' ብለው ሂደው ነበር። በዚህም 'የህግ ጉዳዩን ባጭር ጊዜ እንጨርሳልን፣ በጣም ቢበዛ ሳምንት ነው የሚፈጀብን ከዚያ ውጭ አይሄድም' እንዳሏቸው ነበር የነገሩኝ።

እኔም የተጨበጣቸው ነገር ይኖራል በሚል በተስፋ ነበር የቆየሁት። ነገር ግን አንድ ሳምንት አልፎ አሁን ወደ ሶስተኛ ሳምንት ሆነ። የፍትህ ሂደቱ እንዳውም እየተዳከመ መጥቷል። ነገሩ እየቀዘቀዘ ነው። ለውጥ አላየሁም።

ቤተሰቡ ተበሳጭቷል፥ 'ሶስትም ሆነ አራት  ኮንትራት መኪና ይዘን ደሴ ፖሊስ ጣቢያ ገብተን ምርመራው ከምን ደረሰ? ብለን ጮኸን፥ ልጃችንም የወደቀችበት ቦታ ላይ አልቅሰን እንመጣለን' በሚል አዲስ አቋም ተይዟል። እኔ ቆይ እያልኩ ነው። መሄዳችን አይቀርም።

እኔ በቶሎ ፍትህ እንደሚሰጠኝ እርግጠኛ ነበርኩ፤ ምክንያቱም ልጄ ከጓደኞቿ ቤት 10 ሜርት ባልራቀ ቦታ ነው ተደብድባ ህይወቷ ያለፈው። የጠሩዋት ሰዎች ሲጯጯሁ ሳይሰሙ አይቀሩም ግን 'አንሄድም' ብለዋል። እነዛ ሰዎች ማዳን ይችሉ ነበር። ያ የሆነው ሆኖ አልፏል።

ግን አንድ ሰሞን ሆሆ ተብሎ ጉዳዩ አሁን ግራ እያጋባኝ መጥቷል። የልጄ ሊዛ ደም ባክኖ ሊቀር ነው፣ ፍትህ ልናጣ ነው ተቸግረናል። የህግ ክፍተት ያሳያል። ምናልባት ሂደቱ ውስብስብ ሊሆን ይችላል፥ እኛ ግን እምነታችን እየተሸረሸረ መጥቷል።

በሰባት ቀን ብለውን አሁን ሶስተኛ ሳምንት ባንገባ ተስፋችን አይሟጠጥም ነበር፣ ገና ነው ቢሉን ኑሮ። ተቃርበናል ካሉ በኋላ ይህን ብሎን የነበረው ደሴ ፖሊስ ምርመራ ቡድን ነው። መራቅና መቀዝቀዝ ምን ማለት ነው ?

ሕጉ እየላላ ነው መጣው፤ ምን አይነት ጥርጣሬና ሀሳብ አለ? በሚል እንኳ ደውለው አልጠየቁንም። መረጃም ከመሰብሰብ አኳያ ክፍተት አለባቸው። ወይ ገዳዩን ይዘዋል፥ አለበለዚያ ግን እኛን ባለመጠየቃቸው ራሱ ለምን? የሚል ጥያቄ እያስነሳብኝ ነው" ብለዋል።

መምህር ደሳለ፥ " ካልተረጋገጠ እኮ የልጀ ገዳይ ተይዟል ሊባል አይችልም። ተጠርጣሪ የተያዙ ሰዎች አሉ። ያንም እርግጠኛ አይደለሁም። መርማሪ እንደሚለው ግን ወደ 9፣ 10 ተጠርጣሪዎች ታስረው ነበር ወደ 3፣ 4 የተፈቱ አሉ " ሲሉም ተናግረዋል።

የተማሪ ሊዛ እናት ወ/ሮ የንጉሴ ጌጤ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን አሉ ?

" ፍትህ እንዲሰጠኝ እፈልጋለሁ። እስካሁን ፍትህ የምናገኝ ነው መስሎኝ የነበረው። አሁን ላይ ግን ዝም ብሎ ነው ያለው። ውስጤ ቆስሏል። ቤተሰቦቼ 'ደሴ ሄደን እንጩህ' እያሉ ነው። የሚለቀስበት ጠፍቶን ነው እንጅ ፍትህ እንፈልጋለን።

በእርግጥ የኢትዮጵያ ህዝብ ነው በሊዛ ሞት ያስተዛዘነኝ። ግን ደግሞ ልጄ የደሴ ህዝብ በሚኖርበት 10 ሜትር ላይ ስትወድቅ/ስትሞት ምንም ሳይሰሙና ጩኸት ሳይኖር አይቀርም ነበር። ቢያንስ የልጄን ገዳይ ማወቅ አለብኝ። ባለቅስም እንባ ነው ሊዛን አላገኘኋትም፣ የልጄን ገዳይ ግን አያይዙኝ " ሲሉ ጠይቀዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም ጉዳዩን ይዘውታል የተባሉትን ኢንስፔክተር ማብራሪያ ቢጠይቀም ጉዳዩ በምርመራ ሂደት መሆኑን ጠቁመው ዝርዝር ማብራሪያ ከመስጠት ተቆጥበዋል። የደሴ ከተማ ፓሊስን ለማግኘት ዛሬ ምሽት ያደረግነው ጥረት ደግሞ ያልተሳካ ሲሆን፣ በድጋሚ የምንጠይቅ ይሆናል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamiliyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

ከአትላስ - ቦሌ መድኃኒዓለም - ብራስ ኮሪደር !

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ከአትላስ - ቦሌ መድኃኒዓለም - ብራስ የሚዘልቀውን ኮሪደር በራስ ኃይል እና በማህበራት ተሣትፎ እየገነባ ይገኛል፡፡

ይህ ኮሪደር በአጠቃላይ 2 ነጥብ 34 ኪሎ ሜትር ርዝመት የሚሸፍን ሲሆን፣ ከ42 እስከ 50 ሜትር የጎን ስፋት አንዲኖረው ተደረጎ እየተገነባ ነው፡፡

ከቦሌ መደኃኒዓለም እስከ ብራስ ያለው የመንገዱ ክፍል፦
➡️ 1 ነጥብ 4 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን የሳይክል እና ምቹ የእግረኛ መንገድ፣
➡️ የህፃናት መጫዎቻ ሥፍራ፣
➡️ የህዝብ መፀዳጃ ቤቶች፣
➡️ የመኪና ማቆሚያና ተርሚናል፣
➡️ አረንጓዴ ስፍራዎች እንዲሁም ሌሎች የልማት ስራዎችን ያካትታል፡፡

በእስከ አሁኑ የግንባታ ሂደት፦
° የድሬኔጅ መስመር፣
° የውሃ፣
° የቴሌና የመብራት መስመሮች ዝርጋት፣ እንዲሁም ሌሎች ተያያዥ ስራዎች በባለድርሻ አካላት ቅንጅት በመከናወን ላይ ይገኛል፡፡

የኮሪደሩ ግንባታ አፈፃፀም በየዕለቱ ክትትልና ድጋፍ እየተደረገለት ሲሆን፣ በጥራት እና በአጭር ጊዜ ውስጥ በማጠናቀቅ ለአገልግሎት ለማብቃት በቀንና በለሊት ክፍለ ጊዜ በትጋት በመሰራት ላይ ነው።

(የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን)

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" ሀገራችንን አላህ ሰላም ያድርግልን። ሀገራችንን አላህ አማን ያድርግልን።

እኛም የምንዋደድ አላህ ያድርገን። የምንከባብር አላህ ያድርገን። የምንረዳዳ አላህ ያድርገን። የምንመካከር አላህ ያድርገን።

ጥላቻን ከውስጣችን አላህ ያጥፋው።

በሃይማኖትም ሆነ በፖለቲካ መገዳደልን፣ መጋጨትን፣ መለያየትን ከሀገራችን ከውስጣችን አላህ ያንሳልን።

እንደ አባቶቻችን ከዛም በበለጠ የምንተባበር ፣ የምንከባበር፣ የምንዋደድ ፣ የምንረዳዳ አላህ ያድረገን። " - ታላቁ አባት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" እርቦናል፤ ጠምቶናል ፣ የ8 ወር ደመወዝ አልተከፈለንም። ... በመጠጥ ውሃም ችግር ላይ ወድቀናል፣ እኛ ማንን እንጠይቅ፣ በየጊዜው አመራሮች ይቀያየራሉ፣ ህዝቡ ተቸግሯል " - ሰልፈኞቹ

➡️ " የሀገር ሽማግሌዎች መጥተው ' ለ3 ቀን ታገሱን ' ሲሉ ጠየቁን፣ እኛም አባቶቻችንን ማስከፋት ስላልፈለግን እሺ ብለናቸዋል "

በአፋር ክልል የገዋኔ ወረዳ ዞን 3 ነዋሪዎች ከደመወዝ ጥያቄ እና ከመጠጥ ውሃ ችግር ጋር በተገናኘ በዛሬው እለት ጥቅምት 10/2018 ዓ/ም ከጠዋቱ ሶስት ሰአት አካባቢ ህዝባዊ ተቃውሞ ሰልፍ መንገድ በመዝጋት አካሂደዋል።

ሰልፈኞቹ በሰልፉ ላይ ፦
- " ካልተከፈለን አናስተምርም "
- " እኛ የገዋኔ ነዋሪዎች እርቦናል ፤ ጠምቶናል "
- " ለወላጅ አልባ ህጻናት የ8 ወር ደመዝ ይሰጠን " የሚሉ እና ሌሎችም ደምጾችን አሰምተዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም በሰልፉ ላይ የነበሩ የወረዳ ነዋሪዎችን ስለጉዳዩ ጠይቋል።

ነዋሪዎቹ በዝርዝር ምን አሉ ?

" የገዋኔ ወረዳ ሁሉም የመንግስት ሰራተኞች በ2017 ዓ.ም የ5 ወር ደመወዝ አልተከፈለንም፣ በ2018 ዓ.ም በጀት አመት ደግሞ የሀምሌ፣ የነሀሴ እና የመስከረም ወር አልተከፈለንም። በአጠቃላይ የ8 ወር ማለት ነው።

ይህ የሆነው በወረዳው የፋይናንስ ጽህፈት ቤት ሃለፊ ነው። ሃላፊው ወረዳው ላይ አይኖርም፣ አዲስ አበባ እና አዋሽ እንደሚኖር ነው የሰማነው። ቢሮ ስንሄድ አናገኘውም። ችግሩ የማን እንደሆነም እንኳ ማወቅ አልቻልንም።

ክልሉ እራሱ ጥያቄያችንን ሰምቷል፣ በባለፈው አመት ሲከፍሉን የመቼ፣ የመቼ ወር እንኳ እንደከፈሉ አልነገሩንም።

አልፎ አልፎ ይከፍላሉ፣ እኛን እያዘናጉን ነው፣ በዘንድሮው አመት ችግሮች ይስተካከላሉ ብለን ስንጠብቅ ይሄው መስከረም አልቆ ጥቅምት ላይ ነን፣ እስካሁን ግን የተስተካከለ ነገር የለም።

የመጠጥ ውሃ ችግር በክልሉ እንደአጠቃላይ እንዳለ እናውቃለን፣ ነገር ግን የእኛ የተለየ ነው፣ ይህን የውሃ ችግር ለመቅረፍ በ2012 ዓ.ም ከወረዳዋ 30 ኪሎሜትር እርቀት ላይ ከሚገኝ ቦታ ተቆፍሮ ተሰርቶ ነበር። ነገር ግን ብዙም ሳይቆይ ተበላሽቷል፣ ከዛም በኋላ ችግሩ ተበብሶ ቀጥሏል።

አሁን ላይ አንዱን የሮቶ ውሃው ከ250 እስከ 350 ብር እየገዛን ነው፣ ይህንን ራሱ ለመግዛት እንኳ ደመወዛችን እየተሰጠን አይደለም። የገዋኔ ነዋሪ እያየው ያለው ሰቆቃ በጣም ያሳዝናል።

የወረዳዋ ነዋሪዎች አብዛኞቹ ወላጅ አልባ ህፃናት ናቸው። እርዳታ አያገኙም፣ በጣም ችግር ላይ ናቸው፣ ደመወዝ በአግባቡ ቢሰጥ ኖሮ በቤተሰቦቻቹው የጡረታ ገንዘብ ይተዳደሩ ነበር። ይህ ግን አልሆነም።

ከሌላ አካባቢ መጥተው በወረዳዋ በመምህርነት የሚያገለግሉ መምህራኖች ስራቸውን ለቀው ወጥተዋል። በዛሬው እለትም ከትምህርት ቤት ተማሪዎች ተመልሰዋል።

መብላት እና መጠጣት ያልቻለ መምህር እንደት አድርጎ ያስተምራል ? እኛ ማንን እንጠይቅ፣ በየጊዜው አመራሮች ይቀያየራሉ፣ ህዝቡ ተቸግሯል።

ይህን ተከትሎ በዛሬው እለት የወረዳው ነዋሪ ሰላማዊ ሰልፍ ወጥተን ነበር። ሰልፍ የወጡት ወጣቶች በመሃል መንገድ ላይ ደረቅ እንጨት እሳት በመለኮስ ተቃውሞ አሰምተናል። ለተወሰነ ደቂቃም የትኛውም ተሽከርካሪ እንዳይንቀሳቀስ አግደን ነበር። ሰልፍ ላይ እያለን የሀገር ሽማግሌዎች መጥተው ' ለ3 ቀን ታገሱን ' ሲሉ ጠየቁን፣ እኛም አባቶቻችንን ማስከፋት ስላልፈለግን እሺ ብለናቸዋል።

አባቶች በስአቱ ያሉን ' መንገዱን ክፈቱት መኪኖች ይሒዱ፣ ለእኛ ደግሞ የሶስት ቀን እድሜ ስጡን፣ ችግሩን ለመቅረፍ በዚህ ሶስት ቀን እኛ የወረዳውን አስተዳደር እንጠይቅ፣ መፍትሔ ከሌለው ግን ለእናንተ እናሳውቃለን ' ነው ያሉት፣ እነሱን የላካቸው የወረዳው አስተዳደር እንደሆነም ሰምተናል።

ሰልፍ የወጣንበት ዋነኛ ምክንያት ለ8 አመት በመጠጥ ውሃ ችግር ላይ በመሆናችን፣ የመንግስት ሰራተኛው ደግሞ የ8 ወር ደመወዝ ስላልተከፈለው ነው። የጡረታ ደመወዝ የሚያገኙ ህፃናት በርሃብ ውስጥ ስለሆኑ ነው።

ውሃ የምንገዛው በየወሩ ነው። ይህንንም የምናገኘው በመከራ ነው። ውሃውን የሚያመጡት የመንግስት መኪኖች ናቸው። በየጊዜው ጥያቄ ስንጠይቅ መፍትሔ እናመጣለን ነው ወረዳው ምላሹ፣ ዛሬ ደግሞ የሀገር ሽማግሌዎች ሰልፍ ላይ እያለን ለሶስት ቀን እንዲንታገስ ጠይቀውናል፣ ነገር ግን አስቡት እስኪ 8 አመት ለተጠየቀ ጥያቄ በ8 አመት መመለስ ሳይችሉ በሶስት ቀን ይመለሳል ብሎ ማሰብ ከባድ ነው " ብለዋል።

ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቃላቸውን ከሰጡ መካከል በወረዳው የአመራርነት የስራ ሃላፊነት ያላቸው አንድ አካል ጉዳዩ በቀላሉ እንደማይፈታ እና የፌደራል መንግስት የማህበረሰቡን ችግር ተገንዝቦ መፍትሔ ቢሰጥ የተሻለ እንደሚሆን ተናግረዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

የታላቁ የሃይማኖት አባት የቀድሞው የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝደንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ ሥርዓተ ቀብር ተፈጽሟል።

ከስርዓተ ቀብራቸው ቀደም ብሎ በሚሊኒየም አዳራሽ ሽኝት ተደርጓል።

ታላቁ የሃይማኖት አባት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር በታላቁ አንዋር እና በኑር (በኒ) መስጂዶች ከአራት አስትርት ዓመታት በላይ ኢስላማዊ ሃይማኖታዊ ትምህርት አስተምረዋል።

ከ50 በላይ ሃይማኖታዊ መጽሐፍትንም ጽፈዋል፡፡

ቅዱስ ቁርአንንም ተርጉመዋል፡፡ የቁርአን ትርጉም ሥራቸውን በሲዲ በማሳተም አሰራጭተዋል፡፡

ከ50 ዓመታት በላይ በዘለቀ የአዲስ አበባ ቆይታ ቅዱስ ቁርአንን ከ300 ጊዜ በላይ በትርጉም (ተፍሲር) አስተምረዋል፡፡

ተቀዳሚ ሙፍቲ በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች የተፈጠሩ ሃይማኖታዊ አለመግባባቶችን በመፍታት የሃይማኖታዊ አባትነታቸውን ሚና ተወጥተዋል።

በ1967 ዓ.ም የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ሲመሰረት የምክር ቤቱ አባልና የዑለማ ሊቀመንበር በመሆን አገልግለዋል።

ከ2010 መጋቢት እስከ ግንቦት ወር 2014 ዓ.ል ድረስ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤትን በፕሬዚዳንትነት እንዲሁም የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የበላይ ጠባቂ በመሆን አገልግለዋል፡፡

ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ ባለትዳርና የአምስት ወንዶችና የአራት ሴቶች አባት እንደነበሩ ከጠቅላይ ምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#NewsAlert

" ህወሓት የፕሪቶሪያውን ስምምነት በግልጽ አፍርሷል " - የአፋር ክልል መንግስት

" የህወሓት ቡድን በዛሬው ዕለት በአፋር ክልል ወሰን ውስጥ በማግባት 6 መንደሮችን በጉልበት በመቆጣጠር ንጹሃንን በሞርታርና በዙ-23 ደብድቧል " ሲል የአፋር ክልል መንግሥት አስታወቀ።

ክልሉ " ቡድኑ የተለመደውን የሽብር ተግባሩን በግልጽ ጀምሯል " ሲል ከሷል።

" በዛሬው ዕለት ማለትም በቀን 26/02/2018 ዓ/ም የአዛውንቶች የህወሓት ጉጅሌ /ቡድን/ በአፋር ክልል በዞን ሁለት በመጋሌ ወረዳ ቶንሳ ቀበሌ ዋራዓ እና ሚልኪ በሚባሉ ልዩ አካባቢዎች ወሰን ተሻግሮ በመግባት ከምሽቱ አንድ ሰአት አካባቢ በንጹሐን የአፋር አርብቶ-አደሮች ላይ የከባድ መሳሪያ ተኩስ በመክፈት የፕሪቶሪያ ስምምነትን በግጭት አዋጅ በግልጽ አፍርሷል " ሲል አሳውቋል።

" ይህ የህወሓት ጣብ-ጫሪ ቡድን በቶንሳ ቀበሌ ላይ ተኩስ በሚከፈትበት ወቅት ሰላም ወዳድ የአፋር ሽማግሌዎች እንድመለሱ ቢማፀኗቸውም የህወሓት ቡድን ግን አሻፈረኝ በማለት ግጭቱን አስከትሏል " ብሏል።

" ይህ ከትናንት ጥፋቱ የማይማረው ተስፋ ቢሱ የህወሓት ቡድን ከድርጊቱ በአስቸኳይ ካልተቆጠበ የዜጎች ደህንነትና የወሰናችንን ክብር የማስጠበቅ፣ እንዲሁም ራሳችንን ከማንኛውም ውጫዊ ጥቃት የመከላከል ኃላፊነታችን እንደምንወጣ እንገልፃለን " ሲል የአፋር ክልል መንግሥት አስጠንቅቋል።

#Afar #Tigray

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#WolaitaSodo

‎የሶስት ዓመት ታዳጊ ላይ የግብረ ስጋ ድፍረት ወንጀል የፈፀመው ግለሰብ በ17 ዓመት ፅኑ እስራት እንደተቀጠ ተሰምቷል።

‎በወላይታ ዞን ሶዶ ከተማ አስተዳደር ድል በጌሬራ ቀበሌ ቆንቶ መንደር አቶ ቴዎድሮስ ያዕቆብ የተባለ ግለሰብ መስከረም 2018 ዓ/ም የ3 ዓመት ህፃን እናቷ ገበያ በሄደችበት የግብረ ስጋ ድፍረት ወንጀል መፈፀሙን የሶዶ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ሀብታሙ አሰፋ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ  ተነግረዋል።

በወቅቱ መረጃው የደረሰው ፖሊስ መረጃ በማሰባሰብ በአጭር ጊዜ ዉስጥ ምርመራ በማጠናቀቅ መዝገቡን ለዐቃቤ ሕግ ማቅረቡን ገልፀዋል።

‎ዐቃቤ ሕግ አስፈላጊዉን ሂደት በማሟላት ለሶዶ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ማቅረቡንና ፍርድ ቤቱም ራሷን መከላከል በማትችል እና ልዩ ጥበቃና እንክብካቤ በሚያስፈልጋት ህፃን ላይ ይህ አስነዋሪ ድርጊት መፈፀሙን በሰዉና በሕክምና ማስረጃ በማረጋገጥ የጥፋተኝነት ዉሳኔ አስተላልፎበታል።

‎ፍርድ ቤቱም ዛሬ በ26/02/2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት ግለሰቡ በፖሊስ እጁ ከተያዘበት ቀን ጀምሮ በሚታሰብ በ17 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ዉሳኔ ማስተላለፉንም ኮማንደር ሀብታሙ አሰፋ አስረድተዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#China

የቻይና ፍርድ ቤት ምያንማር ውስጥ የኦንላይን ማጭበርበር ተግባር ላይ ተሰማርተው በነበሩ 5 ዋና የውንብድና ቡድን አባላት ላይ የሞት ፍርድ አስተላለፈ።

ባይ የተባለው ቤተሰብ አባላት እና አጋሮች የሆኑ 21 ሰዎች ፦
- በማጭበርባር፣
- በነፍስ ማጥፋት፣
- በሰዎች ላይ ጉዳት በማድረስ እና በሌሎች ወንጀሎች የጥፋተኝት ውሳኔ ተላልፎባቸዋል።

ይህ ቤተሰብ በእኤአ 2000ዎቹ ላይ ኃይሉ እየጎለበት የመጣ ነው።

በድህነት እና ኋላ ቀርነት ትታወቅ የነበረችውን የምያንማሯን ላውካኢንግ ዞንን ዋነኛ የቁማር እና የወሲብ ንግድ መናኸርያ አድርጓታል።

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ደግሞ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በሕገ ወጥ መንገድ ከተዘዋወሩ በኋላ በኦንላይን የማጭበርበር ተግባር ላይ እንዲሰማሩ ተገድደዋል።

ቤተሰቡ በዚህ የማጭበርበር ስራ በቢሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር ያገኝ ነበር።

የፍርድ ውሳኔ ከተላለፈባቸው 5 ዋነኛ ሰዎች መካከል የውንብድና ቡድኑ አለቃ ባይ ሱቸንግ እና ልጁ ባይ ዩንግካንግ ይገኙበታል።

ያንግ ሊ ቺያን፣ ሁ ሲያውጃንግ እና ቼን ግዋንዩ ቀሪዎቹ ፍርደኞች ናቸው።

የባይ ቤተሰብ ፦
- የራሱ ታጣቂ ሚሊሻ ያለው።
- ለሳይበር ማጭበርበር ተግባር እና ለቁማር የሚውሉ 41 ካምፖችን ያለው።
- የወንጀሉ እንቅስቃሴ 4.1 ቢሊዮን ዶላር የሚዘዋወርበት እንደሆነም ተገልጿል።

ባለፈው መስከረም ላይ በተመሳሳይ የቻይና ፍርድ ቤት ላውካኢንግ ዞን በዚሁ ተግባር ላይ በተሰማራ ' ሚንግ ' የተባለ ቤተሰብ አባላት ላይ የሞት ፍርድ አስተላልፏል።

መረጃው የቢቢሲ ነው።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

ፓስፖርት !

ሙሀባው የሱፍ የተባሉ ወንድማችን ትላንት ምሽት ቦሌ ኤርፖርት ፓስፖርትዎት  ወድቆ ተገኝቷል።

እራሶ መሆንዎን የሚያረጋግጥ ማስረጃ በመላክ ፓስፖርቶን ካገኘው ሰው መውሰድ ይችላሉ።

ካታች ባለው የመልዕክት መቀበያ መልዕክት ያስቀምጡ።

የምታውቋቸው ካላችሁም መልዕክቱን ላኩላቸው።

* አንደኛ ወንድማችን ፓስፖርቱን ተቀብሏል (8:40)

(ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት አዲስ አበባ)

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

የቤንዚን ወይም የናፍጣ መኪናን ወደ ጋዝ መቀየር ምን ያህል ያዋጣል ?

የገንዘብ ሚኒስቴር በተፈጥሮ ጋዝ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ከቀረጥ ነጻ ወደ ሀገር እንዲገቡ መፍቀዱ ይታወሳል።

ይህም በሶማሌ ክልል ካሉብ በዓመት 111 ሚሊዮን ሊትር ማምረት የሚችለውን የኦጋዴን ፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ ፕሮጀክት የመጀመሪያ ዙር መመረቁ ከተገለፀ ከቀናት በኃላ ነበር።

ለመሆኑ በቤንዚን ወይም ናፍጣ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን የተፈጥሮ ጋዝን ወደሚጠቀሙ መቀየር ይቻላል ?


ቲክቫህ ኢትዮጵያ ያነጋገራቸው ባለሞያዎች “አዎን” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

ሦስተኛ ዲግሪያቸውን በታዳሽና አማራጭ ኃይል የሰሩት ዶ/ር ኃይሉ አበበ ከ20 ዓመት በላይ በአቶሞቲቭ ሥራና ስልጠና ላይ ቆይተዋል።

እንደሳቸው ገለፃ ማንኛውም ተሽከርካሪ የሞተሩ “ጤንነት” ታይቶ ሊቀየር ይችላል ሲሉ ገልፀዋል። ሆኖም ግን ቤንዚን የሚጠቀሙ ተሽከርካሪዎችን ወደ ጋዝ ማሸጋገር ከናፍጣ ይልቅ ቀላል እንደሆነ ያስረዳሉ።

“ከዋጋውም ከምቹነትም አኳያ የቤንዚን መኪናንን መቀየር ነው ብዙ ጊዜ የሚመከረው።” ብለው፤ የናፍጣ ተሽከርካሪን መቀየር ግን በጣም ውስብስብና ከፍ ያለ ዋጋ እንደሚጠይቅ አክለዋል።

የሳሚ አቶሞቲቭ ባለቤት እና የአውቶሞቲቭ ቴክኖሎጂ ባለሙያው ሳሙኤል ደጀኔንም በዚህ ኃሳብ ይስማማሉ።

ሳሙኤል በተፈጥሮ ጋዝ (CNG) የሚሰሩ መኪኖች ከቤንዚንና ከናፍጣ የበለጠ ርካሽ በመሆኑ የነዳጅ ወጪን በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚቆጥቡም ተናግረዋል።

መደበኛ ተሽከርካሪዎችን ወደ ጋዝ መቀየር ምን ያህል ያዋጣል ? ምን ያህል ገንዘብስ ያስፈልጋል ?

መደበኛ ተሽከርካሪዎች የተፈጥሮ ጋዝን መጠቀም እንዲችሉ ሲቀየሩ፤ የነዳጅ ማከማቻው (ስልባቲዮ/ Tanker)፣ የግፊት መቆጣጠሪያና የነዳጅ መርጫ (injector) ይቀየራል። ይህም ተሽከርካሪው ወደ ቤንዝን የሚቀየርበትን ዋጋ ይወስናል።

የአውቶሞቲቪው ባለሙያዊ ሳሙኤል የማስቀየሪያ ወጪ ከፍተኛ መሆን እንደ አንድ ችግር ይቆጥሩታል።

በተጨማሪም ጋዝ በመጠቀሙ ብቻ የመኪናው ጉልበት እሰከ 15 በመቶ ይቀንሳል ይላሉ።

ዶ/ር ኃይሉ የተፈጥሮ ጋዝ ከቤንዝል አንጻር ከ40 እስከ 60 በመቶ ያነሰ ዋጋ እንዳለው ይጠቅሳሉ። ሆኖም ሞተርን ለማንቀሳቀስ ከፍ ያለ ፍጆታ አለው ብለዋል።

“ለምሳሌ አንድ መኪና በአንድ ሊትር ቤንዝን ሁለት ኪሎ ሜትር ይኼዳል ብንል፤ በተፈጥሮ ጋዝ ግን ሁለቱን ኪሎ ሜትር ለመሄድ 1.5 ሊትር ይፈጃል” ሲሉ ገልፀዋል።

ቀጣዩ ጥያቄ የመቀየር ሂደቱ ኪስን ምን ያህል ይፈትሻል? የሚል ነው።

ጋዝ የተለየ ባህሪ ስላለው ከፍ ያለ እና ባለሁለት ሽፋን  (layers)  ነደጅ መያዣ እንደሚፈልግ ያነሱት ዶ/ር ኃይሉ “ለመቀየር የቤንዚን ከሆነ ከ500 እስከ 1500 የአሜሪካ ዶላር ያስፈልጋል። የናፍጣ ከሆነ ከ3000 ዶላር ይበልጣል” ብለዋል።

ሳሙኤል ደግሞ፣ “ከፍተኛ የመቀየሪያ ወጪ አውጥቶ ጋዝ እንደልብ ማግኘት ካልተቻለ ለተራ ተጠቃሚ አዋጭ አይሆንም። ጠቃሚ የሚሆነው በየቀኑ ብዙ ርቀት ለሚጓዙ እና የጋዝ አቅርቦት በቀላሉ ለሚያገኙ ብቻ ነው” ብለዋል።

በተፈጥሮ ጋዝ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ከተጠቃሚው አንጻር ምን ጉዳት ወይም ጥቅም አላቸው?

የተፈጥሮ ጋዝን የሚጠቀሙ ተሽከርካሪዎች  አነስተኛ ተፅዕኖ እንዳላቸው ባለሙያዎቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልፀዋል።

ዋጋው ከቤንዚን እና ነፍጣ ዝቅ ማለቱ ሌላኛው ጥቅሙ ነው።

“ሆኖም፣ በብዙ ቦታዎች የጋዝ መሙያ ጣቢያዎች ውስን መሆን ትልቅ ተግዳሮት ነው። በተጨማሪም ወደ ጋዝ ለመቀየር የሚወጣው ወጪ ከፍተኛ መሆኑ እና በጋዝ በሚሰሩበት ጊዜ የጉልበት መቀነስ መኖሩ ዋና ዋናዎቹ ጉዳቶች ናቸው” ሲሉ ሳሙኤል ይናገራሉ።

ጉልበት የሚቀንስበትን ምክንያት ሲያስረዱ “ጋዙ ራሱ ያለው የኃይል ይዘት (energy density) ዝቅተኛ መሆኑ ነው። በዚህ ምክንያት በተፈጥሮ ጋዝ የሚሰሩ መኪኖች ተመሳሳይ መጠን ካላቸው የቤንዚን ሞተሮች  ያነሰ ኃይል አላቸው” ይላሉ።

ዶ/ር ኃይሉ ተሽከርካሪዎች ወደ ጋዝ በሚቀየሩበት ወቅት ከባድና መጠኑ ከፍ ያለ ነዳጅ መያዣ (ሲሊንደር) እንደሚገጠምለት ጠቅሰዋል።

“ታንከሩ፣ ከፍተኛ ግፊት መቋቋም  የሚችል ስለሆነ ከፍ ያለ ነው። ስለዚህ ቦታ ይይዝብናል። መኪናችን ላይ እቃ የምናስቀምጥበትን ቦታ ሊወስደው ይቻላል። በተጨማሪም የመኪናውን ክብደት ይጨምርብናል” ሲሉ አስረድተዋል።

ሌላው በጋዝ የሚሠራ መኪና ከመደበኞቹ በተቃራኒ ሞተራቸው ለመነሳት ይዘገያል።

“ የ cold start [በፍጥነት የመነሳት] ችግር ስላለ አንዳንድ ጊዜ በቤንዚን እንዲነሱ ተደርጎ በጋዝ run እንዲያደርጉ (ስራቸውን እንዲቀጥሉ) የሚደረግበት ሁኔታ አለ” ሲሉ ዶ/ር ኃይሉ ገልፀዋል።

ቀድመው የተዘረጉ የነዳጅ ማሰያዎች የተፈጥሮ ጋዝ ሊቀርብባቸው ይችላል?

ባለሙያዎች ለዚህ ጥያቄ ምላሻቸው “አይሆንም” የሚል ነው።

ሳሙኤል “የተፈጥሮ ጋዝ መሙያ ጣቢያዎች የራሳቸው የሆነ ልዩ መሠረተ ልማት ያስፈልጋቸዋል” ብለዋል።

ሆኖም ሥራ ላይ ያሉ ማደያዎች ላይ ከፍተኛ ለውጥ በማድረግ የተፈጥሮ ጋዝን እንዲይዙና እንዲከፋፈልባቸው ማድረግ እንደሚቻል ጠቅሰዋል።

ዶ/ር ኃይሉ፥ የተፈጥሮ ጋዝ ከፍ ያለ ግፊት ስላለው ከፍተኛ የደህንነት ስጋት እንደሚጋርጥ ይናገራሉ። ስለዚህ የተለየ ስርዓት (System) እንደሚፈልጉ አንስተዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" በአርሲ ዞን አራት ወረዳዎች ተከሰተ የተባለውን ችግር የሚያጣራ የልዑካን ቡድን የማጣራት ሥራውን በዛሬው ዕለት ጀምሯል " - የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ " በኦሮሚያ ክልል፣ አርሲ ዞን በጉና፣ በመርቲ፣ በሸርካ እና በሆሎንቆ ዋቢ ወረዳዎች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታዮች እና ካህናት እንዲሁም በሌሎችም የሃይማኖት ተቋማት አገልጋዮች እና ምዕምናን ላይ ግድያ እና ስቃይ መከሰቱን የሚያሳይ መረጃ መውጣቱን መነሻ በማድረግ ጉዳዩን ከመሰረቱ የሚያጣራ የተለያዩ የባለድርሻ አካላት ተወካዬች የተካተቱበት አጣሪ ቡድን ተቋቁሞ በዛሬው ዕለት የተከሰተውን ችግር በአካል ለማጣራት ችግሩ ወደ ተከሰተባቸው ቦታዎች በመጓዝ ሥራውን በይፋ ጀምሯል " ሲል አሳውቋል።

" የሉዑካን ቡድኑ የማጣራት ሥራውን ጨርሶ የመጨረሻ ሪፖርቱን ሲያቀርብ በጉዳዩ ላይ በጉባኤችን በኩል ይፋዊ መግለጫ እና ማብራርያ የሚሰጥ በመሆኑ ሁሉም ዜጋ በትእግስት የማጠቃለያ ሪፖርቱን እንዲጠብቅ ጉባኤችን በአክብሮት ይጠይቃል " ብሏል።

ጉባኤው " ይህ በእንዲህ እንዳለ አንዳንድ አካላት ኃላፊነት በጎደለው መልክ ከግምት እና ካልተሟላ መረጃ በመነሳት በማሕበራዊ ሚዲያ ጉዳዩን አስመልክተው መረጃዎች መስጠታቸውን ተመልክተናል " ሲል ገልጿል።

መረጃዎቹ ምን እደሆኑ በግልጽ ያላሰፈረው ጉባኤው " ይህ ተግባር የማጣራቱን ሂደት የሚጎዳ እና አንዳንድ አካላትን ወደ ተሳሳተ ድምዳሜ ሊወስድ የሚችል ተግባር በመሆኑ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ መረጃ የምታሰራጩ አካላት በሙሉ ከፍ ያለ ጥንቃቄ እንድታደርጉ እናሳስባለን " ብሏል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

ባንካችን የዲጂታል ግብይት ተጠቃሚ ደንበኞችን ለማበረታታት ያዘጋጀውን የመኖሪያ ቤት ሽልማት አሸናፊ ይፋ አደረገ

   የአባመላ ቅርንጫፍ ደንበኛችን የባለ 2 መኝታ አፓርታማ ዕድለኛ ሆነዋል

ባንካችን አቢሲንያ ላለፉት አምስት ወራት ሲያከናውን የቆየውን በተለያዩ የዲጂታል ባንክ አማራጮች ግብይት የሚያከናውኑ ደንበኞችን የሚያበረታታ ዘመቻ (Merchant Engagement Campaign) በይፋ በማጠናቀቅ በዛሬው ዕለት ለአሸናፊ ደንበኞች የተዘጋጀውን የመኖሪ ቤት ዕጣ የማውጣት ሥነ-ሥርዓት አከናወነ።

ዕጣ የማውጣቱ ሥነ-ሥርዓት ዛሬ ጥቅምት 25 ቀን 2018 ዓ.ም  የባንካችን የዲጂታል ባንክ ዋና ኦፊሰር የሆኑት ወ/ሮ ሶስና መንገሻና ሌሎች የስራ ሃላፊዎች፣ተጋባዥ እንግዶችና ታዛቢዎች በተገኙበት በኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ዕድል አዳራሽ ተካሂዷል።

በወጣው ዕጣ መሰረትም ባለ 2 መኝታ አፓርታማ የሚያስገኘው አሸናፊ የዕጣ ቁጥር 0001801876786 ሆኖ የወጣ ሲሆን ዕድለኛውም የባንካችን አባመላ ቅርንጫፍ ደንበኛ የሆኑትና በንግድ ሥራ የሚተዳደሩት የአዲስ አበባ ነዋሪው አቶ መሐመድ ከድር ሆነዋል።

ይህ የሽልማት መርሃ-ግብር ይፋ ከተደረገበት ከሚያዚያ 28 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ባለፉት  አምስት ወራት ከ10 ሚሊዮን በላይ ግብይቶች የተከናወኑ ሲሆን በዚህም ከብር 138 ቢሊዮን በላይ ማንቀሳቀስ ተችሏል።

ባንካችን አቢሲንያ የዲጂታል መተግበሪያ በመጠቀም የሚደረጉ ግብይቶችን ለማበረታታትና አዳዲስ የዲጂታል ባንክ ደንበኞችን ለማፍራት ለመጀመሪያ ጊዜ ባዘጋጀው በዚህ መርሃ-ግብር በሞባይል ባንክ፣በፖስ  እና በሌሎች የዲጂታል አማራጮች ከብር 500 ጀምሮ ግብይት ለፈጸሙ ደንበኞች ከ3 ሚሊዮን በላይ የዕጣ ቁጥሮችን ወይም ኩፖኖችን ተደራሽ አድርጓል።  

ባንካችን ዕድለኞችን እንኳን ደስ አላችሁ እያለ በቀጣይም የባንካችንን እጅግ ዘመናዊ የዲጂታል ባንክአማራጮች በመጠቀም እግረ መንገዳቸውንም የተለያዩ ዕጣዎች ባለዕድል እንዲሆኑ ይጋብዛል።

/channel/BoAEth

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" ቤተክርስቲያናችን ይህን አይነቱን ኢ-ሰብዓዊ ተግባር አጥብቃ ታወግዛለች " - የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የጳጳሳት ጉባኤ

የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የጳጳሳት ጉባኤ ጥቅምት አጋማሽ 2018 ዓ.ም. በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሀረርጌ ሚደግዱ አስተርዮ ማርያም ካቶሊክ ቤተክርስቲያን አካባቢ ግድያ መፈጸሙንና የካቶሊካውያን ሕይወት ማለፉንና ንብረት መቃጠሉን ገልጾ " ታላቅ ሀዘን ተሰምቶናል " ሲል ባወጣው የሀዘን መግለጫ ገልጿል።

የቤተ-ክርስቲያኒቱ ጳጳሳት ጉባኤ አክሎም፥ በኦሮሚያ ክልል በአርሲ ዞን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እና የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት  ምዕመናን ላይ ተመሳሳይ ግድያ መፈጸሙን ተቋማቱ ያወጡትን መግለጫ ጠቅሶ " ቤተክርስቲያናችን ይህን አይነቱን ኢ-ሰብዓዊ ተግባር አጥብቃ ታወግዛለች " ሲል አስታውቋል።

" የዜጎችን ሰላም እና ደህንነት ለማረጋገጥ መንግስት አስቀድሞ አስፈላጊውን የሕግ ማስከበር ሥራ እንዲሠራ ቤተክርስቲያናችን ጥሪዋን ታቀርባለች " ሲል ነው በመግለጫው ተጠቅሷል። 

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

🔵⚽️ በዲኤስቲቪ እናያለን ገና!!

ሁሉንም የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ጨምሮ ከ125 በላይ ምርጥ የመዝናኛ ቻናሎችን
👉 በስልክዎ ዳታ አልያም
👉 በቤትዎ ፋይበር በስማርት ቲቪዎ
እንዳሻዎ መመልከት ይችላሉ!

💁‍♂️ DStv Stream ሜዳ ፓኬጅ ከ10GB ጋር በ1240 ብር ወርኅዊ ክፍያ ብቻ!

ዛሬውኑ ይግዙ፤ ዘና ብለው በአማራጭ ይዝናኑ!!

🔗 ለተጨማሪ መረጃ: https://bit.ly/DSTV_Bundle

📍 የአገልግሎት ማዕከሎቻችንን ይጎብኙ!

#DSTV
#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#ብርሃን_ባንክ
በተመረጡ ቅርንጫፎች የሥራ ሰዓት ተራዘመ!
*****************************
ብርሃን ባንክ ሁሌም ለደንበኞቹ ምቾት ቅድሚያ በመስጠት የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ ሲሆን አሁን ደግሞ የአገልግሎት አቅርቦቱን ለማሳደግ በተመረጡ 16 ቅርንጫፎች የሥራ ሰዓት ማራዘሙን ስንገልጽ በደስታ ነው!

የተሻሻለው የሥራ ሰዓት
ከሰኞ እስከ አርብ፡ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ምሽቱ 2:00 (8:00 PM)
ቅዳሜ፡ ከጠዋቱ 2:00 እስከ ምሽቱ 12:00 (በነበረበት ይቀጥላል)

ፈጣንና አስፈላጊ መረጃ እንዲደርስዎ የባንካችንን ማኅበራዊ ሚዲያዎች ይቀላቀሉ!

Telegram፡ /channel/berhanbanksc
Facebook: https://www.facebook.com/berhanbanksc
LinkedIn : https://www.linkedin.com/company/76151001

#ብርሃን_ባንክ
እንደ ስማችን ብርሃን ነው ሥራችን!

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸውን ተሽከርካሪዎች ከፖሊስ ፈቃድ ውጭ መጠገን ፣ ቀለም መቀየር ወይም ሌላ ይዞታ መለወጥ በወንጀል ያስጠይቃል " - የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት

በማንኛውም ምክንያት ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸውን ተሽከርካሪዎች ከፖሊስ ፈቃድ ሳያገኙ መጠገን፣ ቀለማቸውን መቀየር ወይም ሌላ ማናቸውንም የቀደመ ይዞታቸውን የሚለውጥ ጥገና ማካሄድ በወንጀል እንደሚያስጠይቅ የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት አስታውቋል። 

መመሪያውን የሚተላለፉ የተሽከርካሪ ሰርቶ ማሳያ ወርክሾፕ (ጋራዥ) ባለቤቶ ከ20 ሺሕ ብር የገንዘብ መቀጮ ጀምሮ በወንጀል እስከመጠየቅ የሚያደርስ ቅጣት ይጠብቃቸዋል።

ይህ አስገዳጅ መመሪያ ተግባራዊ የተደረገው የትራፊክ አደጋ አድርሰው የሚሰወሩ ወንጀለኞችን ሕገ-ወጥ ድርጊት ለመቆጣጠር እንደሆነ የትራፊክ ማኔጅመንት የባለሥልጣን የትራፊክ ቁጥጥር እና ሁነት አስተዳደር ዳይሬክተር አቶ አያሌው አቲሳ ለአሐዱ ተናግረዋል።

አቶ አያሌው አቲሳ ምን አሉ ?

" ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው ተሽከርካሪዎች ያለ ፖሊስ እውቅና የቀደመ ይዞታቸውን መለወጣቸው ፖሊስ አደጋ አድርሰው የሚሰወሩ ተሽከርካሪዎችን በቁጥጥር ሥር ለማዋል የሚያደርገውን ጥረት በማደናቀፍ ወንጀለኞች ለጥፋታቸው እንዳይቀጡ እድል ይሰጣል።

በአስገዳጅ መመሪያው መሠረት ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸውን ተሽከርካሪዎች የሚጠግኑ ጋራዦች በተሽከርካሪው ላይ ምንም አይነት ለውጥ ከማካሄዳቸው በፊት፤ ተሽከርካሪው አደጋ አለማድረሱን እና በፖሊስ እንደማይፈለግ የሚገልጽ ማስረጃ ከፖሊስ መውሰድ ይጠበቅባቸዋል።

ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበትን ተሽከርካሪ ያለ ፖሊስ ዕውቅና የሚጠግኑ የጋራጅ ባለንብረቶች በወንጀል ይጠየቃሉ ፤ የገንዘብ መቀጮም እንደሚጠብቃቸው የመንገድ ትራንስፖርት ትራፊክ መቆጣጠሪያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቀጥር 567/2016 ይደነግጋል። "

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የአሐዱ ነው።

Credit - አሐዱ (Ahadu)

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#SafaricomEthiopia

😲 እስቲ አስቡት ስልካችሁን ስትከፍቱት የበሽ 1 ሚሊዬን እንዳሸነፋችሁ ብታውቁ! 🎉🎉🎉 ዛሬውኑ በሽ ይግዙ ቀጣዩ ሚሊየነር ሊሆኑ ይችላሉ!

ወደ *777*0# ይደውሉ ወይም በM-PESA የበሽ ጥቅል ይግዙ!

📲 የM-PESA መተግበሪያን አሁኑኑ ያውርዱ፡ https://onelink.to/ewsb22

የቴሌግራም ቦታችን👉🏽 /channel/official_safaricomet_bot

#MPESASafaricom
#furtheraheadtogether
#besh

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Earthquake

ዛሬ ጥቅምት 10 ቀን 2018 ዓ.ም ምሽት ላይ ከዓዲግራት ደቡባዊ ምስራቅ 43 ኪሎሜትር የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቶ በበርካታ አከባቢዎች ላይ ንዝረት ተሰምቷል።

ከምሽቱ 1:30 የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ በሬክተር ስኬል 4.5 የተለካ እንደሆነ የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቨይ መረጃ ያሳያል።

የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረቱ ከተሰማባቸው አካባቢዎች አንዷ የትግራይ መዲና መቐለ ስትሆን ንዝረቱ በተለይም በፎቅ/ህንፃዎች ላይ አስፈሪ ስሜት እንደነበር የቲክቫህ ኢትዮጵያ መቐለ ቤተሰብ አባል ገልጿል።

ከጥቅምት 2 ቀን 2018 ዓ.ም ወዲህ ንዝረቱ ትግራይ እና አፋር በርካታ አካባቢዎች ጎልቶ የሚሰማ የተለያየ ልኬት ያለው መሬት መንቀጥቀጥ እየተሰማ ነው።

በተለይ እሁድ ጥቅምት 2/2018 ዓ.ም የተከሰተው በሬክተር ስኬል 5.6 የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ አፋር ክልል የሰው ህይወት ቀጥፎ በርካታ ቤቶችን አፍርሶ ከ40 ሺህ በላይ ሰዎች ያለመጠለያ እንዲቀሩ አድርጓል። በተመሳሳይ በትግራይ ምስራቃዊ ዞን አፅቢ ወምበርታ ወረዳ ቤቶች እንዲፈርሱ ምክንያት ሆኗል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" ኢትዮጵያ በጣት ከሚቆጠሩ አረጋውያን፣ አፈ ማር ከሆኑ መካሪዎችዋ መካከል አንዱ የሆኑትን፣ ለመወደድ የታደሉትን የዘመናችን ጌጥ አጥታለች።

ይህንን የድካም ዓለም መገላገል ለእርሳቸው ዕረፍት ቢሆንም ለአገር ግን ታላቅ ጉዳት ከመሆኑም በላይ ዕድሜን ከጥበብ ጋር ያዋሐዱ በሁሉ ዘመን አይገኙምና ኀዘናችን ጥልቅ ነው። " - ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ  ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት

ፎቶ ፦ ቅዱስነታቸው በተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ ሽኝት ላይ በእምባ ተሞልተው ነበር።

Photo Credit - Ahmed Nega

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የ2018 የቲክኒክና ሙያ ሰልጣኞች መግቢያ ነጥብ ይፋ አድርጓል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተመለከተው የተቋሙ ደብዳቤ፣ በ2018 ዓ/ም የስልጠና ዘመን ወደ ቲክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት የሚገቡ ሰልጣኞች የመግቢያ ነጥብ በ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ውጤታቸው መሰረት ለተፈጥሮና ማህበራዊ ሳይንስ የመግቢያ ውጤት ከደረጃ 1 እስከ 5 በዝርዝር አስቀምጧል።

የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ እና ቅድመ ዝግጅት (12ኛ ክፍል) ላጠናቀቁ ደረጃ 1 እና ደረጃ 2 ሰልጣኞች መቁረጫ ነጥብ፦

-ለወንዶች አርብቶ አደር አካባቢዎችን ሳይጨምር 134 እና ከዚያ በታች፣
-ለወንዶች አርብቶ አደር አካባቢዎች 132 እና ከዚያ በታች፣
-ሴቶች አርብቶ አደር አካባቢዎችን ሳይጨምር 121 እና ከዚያ በታች፣
-ሴቶች አርብቶ አደር አካባቢዎች 120 እና ከዚያ በታች፣
-ለሁሉም ክልል አካል ጉዳተኞች 120 እና ከዚያ በታች ሆኖ ተቆርጧል።

የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ እና ቅድመ ዝግጅት (12ኛ ክፍል) ላጠናቀቁ  ደረጃ 3 እና 4  ሰልጣኞች መቁረጫ የጥብ፦

-ወንዶች አርብቶ አደር አካባቢዎችን ሳይጨምር 135 እና ከዚያ በላይ፤
-ወንዶች አርብቶ አደር አካባቢዎች 133 እና ከዚያ በላይ፤
-ሴቶች አርብቶ አደር አካባቢዎችን ሳይጨምር 122 እና ከዚያ በላይ፤
-ሴቶች አርብቶ አደር አካባቢዎች 121 እና ከዚያ በላይ፤
-ለሁሉም ክልል አካል ጉዳተኞች 121 እና ከዚያ በላይ ሆኖ ተቆርጧል።

እንዲሁም፣ የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ እና ቅድመ ዝግጅት (12ኛ ክፍል) ላጠናቀቁ ደረጃ 5 ሰልጣኞች መቁረጫ ነጥብ፦

-ወንዶች አርብቶ አደር አካባቢን ሳይጨምር 179 እና ከዚያ በላይ፤
-ወንዶች አርብቶ አደር አካባቢዎች 168 እና ከዚያ በላይ፤
-ሴቶች አርብቶ አደር አካባቢን ሳይጨምር 168 እና ከዚያ በላይ፤
-ሴቶች አርብቶ አደር አካባቢ 157 እና ከዚያ በላይ፤
-ለሁሉም ክልል አካል ጉዳተኞች 142 እና ከዚያ በላይ ሆኖ ተቆርጧል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…
Subscribe to a channel