1532594
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። @tikvahuniversity @tikvahethAfaanOromoo @tikvahethmagazine @tikvahethsport @tikvahethiopiatigrigna #ኢትዮጵያ
" የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ የነበሩት አቶ ተክሌ ጆንባ ወደ አዲስ አበባ ከተማ ሲዘዋወሩ አቶ ጥራቱ በየነ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ሆነው ስራ ጀምረዋል " - አንድ የክልሉ ከፍተኛ አመራር
" በነገው ዕለት የከተማው ምክር ቤት ሹመታቸውን ያፀድቃል ! "
በቅርቡ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ሆነው ተሹመው የነበሩት አቶ ተክሌ ጆንባ የፌደራል እንስሳት ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ሆነው እንዲሰሩ መመደባቸውንና በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የቀድሞ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራ ክህሎትና ኢንተርፕራይዝ ቢሮ ኃላፊ የነበሩት አቶ ጥራቱ በየነ ደግሞ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ሆነው ስራ መጀመራቸውን አንድ የሲዳማ ክልል ከፍተኛ አመራር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
እንደ አመራሩ ገለፃ አስቀድሞ ለአቶ ተክሌ ጆንባ የተፃፈዉን የሹመት ደብዳቤ በማህበራዊ ሚዲያዎች መሰራጨቱን እና በወቅቱም የብልፅግና አመራሮች በአዳማ ስልጠና ላይ እንደነበሩ ገልጸዋል።
ሹመቱ የተረጋገጠ መሆኑን አክለዋል።
የቀድሞ የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር፤ የትምህርት፣ ትራንስፖርትና የማዕድንና ኢነርጂ ሚንስትር ደኤታ ሆነዉ የሰሩት አቶ ሚልዮን ማቴዎስ በአቶ ጥራቱ ቦታ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራ ክህሎትና ኢንተርፕራይዝ ቢሮ ኃላፊ ሆነው መሾማቸዉን ገልፀዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ በጉዳዩ ዙሪያ መረጃ የጠየቃቸው አቶ ተክሌ ጆንባ የሹመት ደብዳቤ እሳቸው እንዳልደረሳቸዉ በመግለፅ ተጨማሪ መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል።
የሀዋሳ ከተማ ምክር ሕዳር 3 ቀን 2018 ዓ/ም አስቸኳይ ጉባኤ ጠርቷል በዚህም የአቶ ጥራቱ በየነን የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባነት ሹመት ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።
በሌላ በኩል ዛሬ አቶ ጥራቱ በየነ ከሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ እንዲሁም ከሌሎች የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ጋር በመሆን በሀዋሳ የልማት ስራዎችን ሲጎበኙ ውለዋል።
የአዲስ አበባ ከንቲባ ጽ/ቤት በይፋዊ የፌስቡክ ገፁ አቶ ሚሊዮን ማቴዎስ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የስራ ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ሆነው መሾማቸውን አስታውቋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa
@tikvahethiopia
" ጦርነት ጠቀሜታ የለውም፤ አውዳሚ ነው። ይህንን እውነታ ኤርትራውያንም ሆኑ ኢትዮጵያውያን በደንብ ይረዱታል። ስለጦርነት አውዳሚነት ከኛ በላይ የሚረዳ የለም " - አምባሳደር ዲና ሙፍቲ
በቀይ ባህር ጉዳይ ወደ ጦርነት እንዳይገባ ስጋቶች እንዳሉ ሲገለጽ ቆይቷል። ኤርትራ ኢትዮጵያ ላይ ተደጋጋሚ ክስ እያቀረበች ነው፤ ጉዳዩ በሰላማዊ መንገድ ለማሳካት ዲፕሎማሲው በምን መልኩ መሄድ አለበት ? ስንል በህዝብ እንደራሴዎች ምርት ቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባል አምባሳደር ዲና ሙፍቲን ጠይቀናል።
አምባሳደር ዲና ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን አሉ ?
" ጦርነት ጠቀሜታ የለውም፤ አውዳሚ ነው። ይህንን እውነታ ኤርትራውያንም ሆኑ ኢትዮጵያውያን በደንብ ይረዱታል። ስለጦርነት አውዳሚነት ከኛ በላይ የሚረዳ አገርም ህብረተሰብም የለም።
ይህ ስለማይፈለግ ነው ሰላማዊ በሆነ መንገድ መብት ማስከበር ያስፈልጋል የተባለው። በኢትዮጵያ በኩል ከጦርነትና ከግጭት በመለስ ይህንን ነገር ሰላማዊ መንገድ እንፍታ ነው የተባለው። የዲፕሎማሲ ስራው ይሄው ነው።
ከኢትዮጵያ አቋም ውጭ ኢትዮጵያን መክሰሱ ጠቀሜታ የለውም። ይህ ፕሮፓጋንዳ ነውና እንደማያዋጣ ለዓለም አቀፉ ማኀበረሰብ ማስረዳት ነው። የኢትዮጵያ ንግድ ቀጨጨ፣ ኢምፖርት ኤክስፓርት ተጎዳ ማለት ሌሎቹም ሀገራት ይጎዳሉ ማለት ነው።
ጉዳቶች ተዛማጅ ናቸው፤ ይህን ከግምት በማስገባት ኤርትራ መረዳት አለባት። ክሱ መሰረት የለውም፤ ክሱ ከኢትዮጵያ ፍላጎትና አቋም ውጭ ነው " ሲሉ ተናግረዋል።
ለኢትዮጵያ ስለባህር በር አስፈላጊነት ምን አሉ ?
" የኢትዮጵያን የባህር በር እንደሚገባት የታወቀ ነው። ዓለም አቀፉ ህግ በ1982 ዓ/ም ይህን ደንግጓል፤ እንደ ኢትዮጵያ ያሉ የባህር በር የሌላቸው ሀገራት ያስፈልጋቸዋል በሚል።
ኢትዮጵያ የባህር በር የምትፈልግባቸው ታሪካዊ ምክንያቶች አሉ፤ በአንድ ወቅት ባህር በር የነበራት ሀገር ናት፤ በተንሸዋረረ ሁኔታ ነበር የባህር በር ያጣችው። መልካዓ ምድራዊ ምክንያቶች አሏት፤ ከባህር በር 60 ኪሎ ሜትር ርቃ ምትገኝ ናት፤ የኢኮኖሚ ምክንያቶች አሏት።
እነዚህን ነባራዊ እውታዎች ሌላው ወገን መቀበል አለበት፤ ይሄ ምክንያት ተጨባጭና ተገቢ መሆኑን በደንብ ተረድቶ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለኤርትራ፣ ለምስራቅ አፍሪካ ያለውን ጠቀሜታ ከግምት በማስገባት ሌላው ወገን መገንዘብ አለበት " ብለዋል።
ኢትዮጵያ ቀይ ባህርን ስላጣችበት የተሳሳተ ሁኔታ አምባሳደር ዲና ምን አሉ ?
" ኢትዮጵያ ቀይ ባህርን ያጣችው በጣም ቅጽበታዊ በሆነና በተዛባ መንገድ፣ የኢትዮጵያ ህዝብ ፍላጎቱ ሳይጠየቅ፣ የኢትዮጵያ ተወካዮች በሚገባ ሳይመክሩበት፣ ምንም አይነት ውይይት ሳይካሄድበት ነው።
ኢትዮጵያ ይህን ሁሉ ዓመት የባህር በር ይዛ ቆይታ ለምን ባህር በር ታጣለች? ካጣችስ ምንድን ነው አማራጩ? ሳይባል፤ ምንም መፍትሄ ሳይበጅለት በድንገት የተፈጠረ ነገር ነው። ስለዚህ ኢ-ፍትሃዊነት፤ ግልጽነት የጎደለውና ያልተሟላ ነገር አለበት " ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
🌟✨ ቴሌብር ሐዋላ ከዕለታዊ ምንዛሬ ላይ 9% ስጦታ ጨምሮ ገንዘብዎን በምቾትና በቅልጥፍና ያስረክባል!!
ከባሕርማዶ በቴሌብር ሬሚት እንዲሁም በአጋሮቻችን
💳 VISA 💵 Dahabshiil
💸 Western Union 🔄 Thunes
🌍 Onafriq 📲 Taptap Send
🏦 CAC Bank 💰ሐabesha PAY
👉 ከወዳጅ ዘመድዎ የተላከልዎን ዓለም አቀፍ ሐዋላ በ #ቴሌብር ሲቀበሉ 9% ተጨማሪ ስጦታ ያገኛሉ፡፡
🔗 #ቴሌብር_ሬሚት ወዳጆችዎ እንዲጠቀሙ ያጋሯቸው 👉 https://onelink.to/telebirr-remit
#Ethiotelecom #telebirr #telebirrSuperApp #DigitalEthiopia #DigitalAfrica #RealizingDigitalEthiopia
የላጲሶ ጌ’ዴሌቦ (ፕ/ር) ሥርዓተ ቀብር በጴጥሮስ ወጳውሎስ መካነ መቃብር ተፈጽሟል።
ከስርዓተ ቀብራቸው አስቀድሞ የአስከሬን ሽኝት ሥነ ሥርዓት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 6 ኪሎ ካምፓስ ተካሂዷል።
የታሪክ ተመራማሪው ላጲሶ ጌ’ዴሌቦ (ፕ/ር) ባደረባቸው ሕመም ሕክምና ሲከታተሉ ቆይተው ጥቅምት 30 ቀን 2018 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ይታወቃል፡፡ #ኤፍኤምሲ
@tikvahethiopia
የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት
🗣 ቀጣዩ ሚሊየነር .......
እድል እየጠራዎት ነው፤ ሚሊየን ብሮች በስልክዎ ርቀት ብቻ ይገኛሉ፤ ዛሬ በሚቆርጡት ሎተሪ በሽልማት ይንበሽበሹ።
ዛሬ የ60 ሚሊዮን ብር ሎተሪን ከሚቆርጡ ደንበኞች መካከል ለ10 እድለኞች የ10 ሺህ ብር ሽልማት እንዲሁም ለ30 እድለኞች ለእያንዳንዳቸው የ1 ሺህ ብር ሽልማት ተዘጋጅቷል!
በቴሌብር ሱፐር አፕ እና ethiolottery.et ላይ አሁኑኑ ይቁረጡ!
መልካም ዕድል!
የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት
#ያንብቡ👆
የገንዘብ ሚኒስቴር የገቢ ግብር ማሻሻያ አዋጅ ጸድቆ በስራ ላይ የዋለ ቢሆንም የአዋጁ ማስፈጸሚያ ደንብ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቦ ያልጸደቀ መሆኑን በመጥቀስ በአዋጁ አንዳንድ አንቀጾች ላይ ማብራሪያ ሰጥቷል።
ማብራሪያው የተሰጠው የገቢዎች ሚኒስቴር ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ያነሷቸውን የተለያዩ ጥያቄዎች በማሰብሰብ በአዋጁ አንዳንድ አንቀጾች ላይ የገንዘብ ሚንስቴር ማብራሪያ እንዲሰጥበት በጠየቀው መሰረት ነው።
- የገንዘብ ሚንስቴር የአማራጭ አነስተኛ ግብር አፈጻጸምን በተመለከተ
- ቀደም ሲል በሌላ ህግ ነጻ የተደረጉ ግብር ከፋዮች የ2017 በጀት አመት የንግድ ትርፍ ግብር ተጠያቂነትን በተመለከተ
- የትርፍ ድርሻ ላይ ተፈጻሚ ስለሚሆን ታክስ
- የተጠቃለለ የሂሳብ ሰነድ ተግባራዊ ስለሚሆንበት አሰራር
- የቤት ኪራይ ገቢ ግብር ላይ አማራጭ አነስተኛ ግብር እና ቅድሚያ ታክስ ክፍያ የሚኖረው ተፈጻሚነት
- አማራጭ አነስተኛ ግብር እና የገቢ ግብር እፎይታ
- ሃላፊነቱ የተወሰነ የሽርክና ማህበር እና የጋራ ኢንቨስትመንት ፈንድን በተመለከተ
- የጥሬ ገንዝብ ግብይት ገደብን በተመለከተ
- የተርን ኦቨር ታክስ አዋጁ መሻርን በተመለከተ ባለ ዘጠኝ ነጥብ ዝርዝር ማብራሪያ ሰጥቷል።
(የማብራሪያውን ሙሉ ቃል ከላይ ይመልከቱ)
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
@tikvahethiopia
#Update
በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በኩል በኦሮሚያ ክልል በአርሲ ዞን የተለያዩ ወረዳዎች አጋጥሞ የነበረውን ጥቃት በሚመለከት የመጀመሪያ ዙር የጥናት ሪፖርት ቀርቧል።
የጥናት ሪፖርቱ በጥናት ቡድኑ ሰብሳቢ መላከ ሰላም ዳዊት ያሬድ የቀረበ ሲሆን በቀረበው ሪፖርት ዙሪያም ለሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዋና ጸሃፊ ለሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ እንዲሁም ለጥናት ቡድኑ ሰብሳቢ ከሚዲያ አካላት ጥያቄ ተነስቶ ምላሽ እና ማብራሪያ ሰጥተውበታል።
ከተነሱ ጥያቄዎች መካከል ፦
- " በአካባቢው ተመሳሳይ ጥቃት ሲፈጸም አዲስ አይደለም ከእዚህ ቀደምም ለተካታታይ አመታት ጥቃቶች ተፈጽመዋል እነሱን የማጣራት ስራ ተሰርቷል ወይ ? "
- " በአሁኑ ሰአት በአካባቢው የሚገኙ ነዋሪዎች ደህንነት ሁኔታ ምን ይመስላል ? "
- " በአማራ ክልል መካነ ሰላም አጋጥሞ የነበረው ጉዳይስ የማጣራት ሂደት ከምን ደረሰ ? " የሚሉት ይገኙበታል።
የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጸሃፊ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ ምን መለሱ ?
" ሪፖርቱ በአርሲ አካባቢ ስለተፈጸመው ክስተት ብቻ ነው።
ሌሎች ' በእዚህ አካባቢ እንደዚህ ተከስቷል ' እያልን ካነሳንማ ወለጋ ብዙ አለ ፤ በቅርቡ ቤተ እምነቶች አካባቢ በየቦታው በየቀኑ የሚገደል ወለጋ ውስጥ ብዙ ነው፣ ሌሎችም በቅርቡ ደቡብ አካባቢ የምንሰማቸው (የሰማናቸው) ግድያዎች ይኖራሉ እነሱን ከቆጠርን ከአዙሪት ውስጥ አንወጣም።
መካነ ሰላም ለተከሰተው መግለጫ ከማውጣት ባሻገር ምን ተሰርቷል የሚሉትን አጠቃላይ እንደጉባኤ እዛ አካባቢ የራሳችን መዋቅርም አለን ከዛ የምንጠብቀው ሪፖርት አለ።
የክልሉ የሃይማኖት ተቋማት የዞኑ የሃይማኖት ተቋማት በጋራ ሆነው ምን ሰሩ በትክክልም እዛ ቦታ ላይ የተከሰተው ችግር እንደዚህ እንደዚህ ነው ፣እኛም የቀረበልን ሪፖርት ከመጅሊሱ ተነስተን ነው ያንን መግለጫ ያወጣነው።
በዚህኛውም ጥቃት ሲኖዶሱ ካወጣው መግለጫ ተነስተን ነው ፣ በእኛ ተቋም አሰራር አንዳንዱ ከአስቸኳይነታቸው አንጻር ካልሆነ በስተቀር የምንሰጠው መላምት ነው ሊሆን የሚችለው ስህተትም ውስጥ ሊከተን ይችላል።
ልዑካኑን እኛ የላክናቸው የቅርቡን ክስተት መነሻ አድርገን ነው።
እነሱም (የሃይማኖት ተቋማቱ) እዚህ ልዑካን ልከው አልነበረም ያንን ነገር (መረጃ) ሲያቀርቡ የነበረው ፣ሲኖዶሱ ሲያቀርብ ሃገረስብከት መዋቅር አለ ከታች ያለ መዋቅር የሚያቀርብለትን ሪፖርት ተነስቶ ነው የሚያቀርቡት ያ በትክክል ተደርጓል ወይ ብሎ አጣሪ ቡድን ሲሄድ ደግሞ ሌላ ሆኖ ሊገኝ ይችላል።
ከእዚህ ቀደምም እንደዚህ አይነት ነገሮች ተክስተዋል የሚሉ ካሉ ምናልባት በሶሻል ሚዲያ ላይ እየተባለ ያለ ሊሆን ይችላል ፣ በትክክል በእሱ ነው በእሱ አይደለም የሚለውን ምክንያት ማጣራት ይፈልጋል።
በኋላ ላይ ሁለተኛ እና ሦስተኛ ዙር (ለማጣራት) ሊኬድ ይችላል ፣በሁለተኛ ዙርም ላይቆም ይችላል እነርሱ አጥርተው ሲያመጡልን ይህንንም ጭምር የሚያቀርቡ ከሆነ እና ምናልባትም ከ 20 እና 30 አመታት በፊት የተነሱ ጉዳዮችም የሚነሱ ከሆነ ማብቂያ የለውም።
አሁን (በጥናቱ) ለምን ተከሰተ ከዚያ በኋላ አብሮ መኖር ተጀምሮ አልነበረም ወይ?፣ የትኛው ጠላት መጥቶ እንደዚህ አደረገ የሚሉትን ነገር በደንብ ፍንትው አድርገው ያሳዩናል።
እነሱ የተላኩት በእዚህ ሰሞን ምን ተከሰተ የሚለውን ጉዳይ እንዲያጣሩ ነው " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
የአጣሪ ኮሚቴው ሰብሰቢ መላከ ሰላም ዳዊት ያሬድ ምን መለሱ ?
" በአካባቢው የኋላው የ 2016 ጀምሮ ጥቃቶች አሉ የሚለውን ጉዳይ በሚመለከት ጉዳዮችን በምናጣራበት ወቅት ጥያቄዎች አይነሱም አይደለም እየተነሱ ነው። ጉዳት ከኋላ ጀምሮ እየደረሰባቸው እንደነበረ እና በብዙ ችግር ውስጥ እያለፉ እዚህ ጋር እንደደረሱ ነገር ግን ከሆነ ሰአት በኋላ ጋብ እንደሚል እና ተመልሶ የሚመጣ ነገር እንደሆነ ከእነሱም የሰማነው ጉዳይ ነው።
እኛ እያቀረብን ያለነው ከማህበረሰቡ እያገኘን ያለነውን ምላሽ ነው የምንጨምረውም የምንቀንሰውም ነገር የለም።
ከየትኛውም ቤተ ዕምነት ምን ያህል ሰው ተጎዳ የሚለውን በተመለከተ አይደለም ምን ያህል ተጎዳ የሚለውን ቀርቶ ከእነ ስሙ ጭምር ማብራሪያዎች ይቀርባሉ ይህንን አሁን ገና እየሰራነው ያለነው ነገር ነው ተጣርቶ መሰራት እና ተጨባጭ መሆን አለበት።
እስካሁን ድረስ መረጃዎችን የሰጡን አሉ ያልተሰጠን ማስረጃም አለ እያመጣን ነው ያሉም አካላት አሉ ፣በአካልም ድጋሚ ሄዶ መፈተሽም ሊያስፈልገው ይችላል።
ነዋሪው በአሁኑ ሰአት በአካባቢው ምን ያህል የመኖር ዋስትና አለው በሚል ለተነሳው ጥያቄ ከዞኑ አስተዳደር ጋር በግልጽ ውይይት አድርገናል።
እስካሁን ድረስ ምን እያደረጋቹ ነው የሚለውን ነገር እነሱንም ጠይቀናል እነሱም ' ተገቢ የሆነውን ነገር ክትትል አድርገን እርምጃ እየወሰድን ያለባቸው ቦታዎች አሉ ' ብለዋል።
የጸጥታ ዘርፉ ስራዎችን እየሰራ እና እያጸዳ ነው ያለው ቀጣይም ይህንኑ ተግባራችንን አጠናክረን እንቀጥላለን የሚል ምላሽ ሰጥተውናል።
ለአይናችንም ስንመለስ መከላከያ በብዛት ወደ አካባቢው ሲሄድ ተመልክተናል፣ በብዙ ኦራል ተጭኖ ወደ አካባቢው ሲገባ ተመልክተናል ለየትኛው ተልዕኮ ነው እሱን የምናውቀው ነገር የለም።
እኛም እያልን ያለነው ይህንኑ ነው ተገቢውን ድጋፍ ይደረግላቸው ይደረስላቸው ምርታችንን በአግባቡ መሰብሰብ አልቻልንም እያሉ ነው ሰዎቹ።
ምርታቸውን በአግባቡ መሰብሰብ እንዲችሉ ተገቢውን ድጋፍ እና ክትትል ይደረግላቸው የሚለውን ጥያቄ አቅርበናል።
ያንን ደግሞ የማድረግ አቅም ያለው ባለድርሻ አካል አለ ይህንን ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ምላሽ ተሰጥቶናል" የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
የአጣሪ ቡድኑ የመጨረሻ ደረጃ ሪፖርቱን በምን ያህል ጊዜ እንደሚያቀርብ ከመናገር ተቆጥቧል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#Update
በአቶ አለማየሁ ጢሞቴዎስ እና አቶ ሽመልስ ቶማስ ላይ ክስ መመስረቱ ተገለጸ።
የቀድሞው የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አለማየሁ ጢሞቴዎስ በ4 የተለያዩ መዝገቦችና በ11 ተደራራቢ ክሶች እንዲሁም የፖሊስ ኮሚሽነር የነበሩት አቶ ሽመልስ ቶማስ ላይም በ3 መዝገቦችና በ7 ተደራራቢ ክሶች ማለትም ፦
- ስልጣንን አላግባብ በመገልገል፣
- የመንግስት ስራዎችን በማይመች አኳሗን በመምራት፣
- በህገ-ወጥ መሳሪያዎች ዝውውር፣
- በህገ-ወጥ ኮንትሮባንድ ንግድ፣
- በህገ ወጥ የፖሊስ ማዕረግ አሰጣጥ እና በሌሎች ወንጀሎች ክስ እንደተመሰረተባቸው የክልሉ ፍትሕ ቢሮ አሳውቋል።
በኢፌዴሪ የፍትህ ሚኒስቴር የሀዋሳ ቅርንጫፍ ዐቃብያነህግ የሚታዩ ክሶችንም በተመለከተ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችንና በግለሰብ እጅ እንዲያዙ የማይፈቀዱ የመገናኛና የጦር መሳሪያዎችን ይዞ የመገኘትና ተያያዥ ጉዳዮችም ጋር ተያይዞ ምርመራ መጠናቀቁን አመልክቷል።
#Hawassa
@tikvahethiopia
" አብዛኛው ህዝብ (ሊቀ ጳጳሱ) ከኃላፊነት ይነሱልን፣ ሰላማችንን ልናገኝ ይገባል። ስንሞት ' እግዚአብሔር ያጽናችሁ ' የሚለን አባት እንፈልጋለን የሚል ሀሳብ አንስቷል" - አመራርና ውይይቱ ተሳታፊ
በአርሲ ዞን የተደጋገመውን ግድያ በተመለከተ እየቀረቡ ባሉ ቅሬታዎች ውይይት ለማድረግና የህዝቡን አቋም ለማወቅ ቅዱስ ሲኖዶስ በሳምንቱ መጨረሻ ወደ ዞኑ ልዑካን ቡድን ልኮ እንደነበር በውይይቱ የተሳተፉ አንድ የዞኑ ወረዳ ቤተ ክህነት አመራር ለቲክቫህ ኢትጵጵያ ገልጸዋል።
በውይይቱ በዞኑ የተደጋገመውን ግድያ የተመለከቱ ዝርዝር ጉዳዮች መነሳታቸውን ገልጸው፣ ከሳምንት በፊት ከተፈጸመው ግድያ ውጭ ባለፉት ቀናት ተመሳሳይ ጥቃት እንዳልተፈጸመ ተሳታፊዎች ማስረዳታቸውን ተናግረዋል።
ይሁን እንጅ፣ በርካታ ኦርቶዶክሳውያን በታጣቂዎች የተገደሉበት የአርሲ ዞን ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ " ከኃላፊነት ይውረዱ" የሚል ሀሳብ ከተሳታፊዎች መነሳቱን እኝሁ በውይይቱ የተሳተፉት አመራር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
ሊቀ ጳጳሱ " ከኃላፊነት እንዲነሱ " የጠየቁት በአርሲ ዞን በተለይ በጥቅምት 2018 ዓ/ም ወር በተደጋጋሚ በታጣቂዎች ግድያ በተፈጸመባቸው ወረዳዎች ያሉ ኦርቶዶክሳውያን መሆናቸውን አስረድተዋል።
" 'ሊቀ ጳጳሱ ከኃላፊነት ይነሱ አይነሱ፣ ሀገረ ስብከቱ ሪፎርም ያስፈልገዋል' በሚል " ሁለት የተለያዩ አቋሞችን በመያዝ ሰሞንኛው ውይይት ከመካሄዱ በፊት ሰዎች ወደ ጠቅላይ ቤተ ክህነት አቤቱታ እየቀረቡ እንደነበር አስታውሰው፣ ይህን ተከትሎ " ቅዱስ ሲኖዶስ ሶስት አጣሪ ልዑካን ቡድን ወደ ዞኑ ልኳል " ብለዋል።
" በዚህ ልዑካን ላይ 'የሀገረ ስብከቱ እንደ ሀገረ ሰብከት እየሰራ አይደለም፣ አባታችን ይህ ሁሉ ሲገደል መግለጫ አልሰጡም፤ አላጽናኑም፤ በቦታው በሀገረ ሰብከታቸው የሉም " የሚል ቅሬታ ከተወያዮች መነሳቱን ገልጸዋል።
" እውነት ነው የሉም፤ ሰዎች ሲገደሉ ስልክ ስንደውል 'ቀላል ነው' እያሉ ነው ዝም ሲሉ የነበረው " ሲሉ የራሳቸውን አስተያየት የተናገሩት እኝሁ አመራር፣ " ያ የመረረው ህዝብ ፈንቅሎ አቋሙን አሳውቋል። 'እያገለገሉን አይደለም' በሚል ነው አቅጣጫ የተሰጠው " ሲሉም ውይይቱን አውድ አስረድተዋል።
በዚህም በውይይቱ " አብዛኛው ህዝብ (ሊቀ ጳጳሱ) 'ከኃላፊነት ይነሱልን፣ ሰላማችንን ልናገኝ ይገባል፣ ስንሞት እግዚአብሔር ያጽናችሁ የሚለን አባት እንፈልጋለን' " የሚል ሀሳብ መቅረቡንም አክለዋል።
ውይይቱ በዚሁ መጠናቀቁን፣ ልዑካን ቡድኑ የውይይቱን ቃለ ጉባዔ ይዘው ወደ ቅዱስ ሲኖዶስ እንደሚመለሱና ውሳኔው ከቅዱስ ሲኖዶስ እንደሚጠበቅ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድተዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
" በአደጋዉ የ6 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በ8 ሰዎች ላይ ጉዳት ደርሷል " - ፖሊስ
➡️ " አደጋው የደረሰዉ በአምላኮ ላይ በነበሩ አማኞች ላይ ነው። "
በሲዳማ ክልል ሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ቱላ ክፍለ ከተማ ዶሬ ባፋኖ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ በፍጥነት ሲጓዝ የነበረ ሲኖ ትራክ መንገድ ስቶ በአምልኮ ስርዓት ላይ በነበሩ ሰዎች ላይ በመዉደቅ ባስከተለው አደጋ የ6 ሰዎች ህይወት ማለፉን የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ረዳት ኮሚሽነር ግርማ ማቴዎስ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
የሰላዳ ቁጥሩ ኮድ 3 -89991 ኢት የሆነ ሲኖትራክ ከሀዋሳ ከተማ ወደ ዶሬባፋኖ በመጓዝ ላይ እያለ ከቀኑ 10 ሰዓት ገደማ ቱላ ክፍለ ከተማ ፊንጫ ቀበሌ በተለምዶ ቤተመንግስት ተብሎ በሚጠራዉ አከባቢ ሲደርስ መንገድ ስቶ በመዉጣቱ በአምልኮ ላይ በነበሩ ሰዎች ላይ ወድቆ አደጋ ማድረሱን ረዳት ኮሚሽነር ግርማ ማቴዎስ አስታዉቀዋል።
በአደጋዉ የ6 ሰዎች ህይወት ወዲያዉኑ ሲያልፍ በ3 ላይ ከባድ በ5 ሰዎች ደግሞ ቀላልና መጠነኛ ጉዳት መድረሱን ገልፀዋል።
ጉዳት የደረሰባቸው 8 ሰዎች ወደ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻልስት ሆስፒታል ተወስደዉ ሕክምና እየተደረገላቸዉ መሆኑንም ረዳት ኮምሽነር ግርማ ማቴዎስ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድተዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
@tikvahethiopia
የታሪክ ተመራማሪው ላጲሶ ጌ’ዴሌቦ (ፕ/ር) በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።
ተመራማሪው በሞት የተለዩት ባደረባቸው ህመም ህክምናቸውን ሲከታተሉ ቆይተው በ87 ዓመታቸው መሆኑን ቤተሰቦቻቸው ለኤፍኤምሲ ገልጸዋል።
ላጲሶ ጌ’ዴሌቦ (ፕ/ር) በኢትዮጵያ እንዲሁም በአፍሪካ የታሪክ ጥናትና ምርምር በማካሄድ የተለያዩ የታሪክ መፅሐፍትን ለአንባቢያን አበርክተዋል፡፡
የኢትዮጵያውያንን የጋራ እሴት፣ ባሕልና ቋንቋ በማውሳት የህዝብ ታሪክ ጎልቶ እንዲታወቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከታቸውም ተነግሮላቸዋል።
የአስክሬን ሽኝትና ቀብር ስርዓታቸው የፊታችን ማክሰኛ ህዳር 2 ቀን 2018 ዓ/ም እንደሚከናወን ተጠቁሟል፡፡ #FMC
@tikvahethiopia
" ቢያንስ 30 ሚሊዮን ሰዎች በሕይወት ዘመናቸው በአእምሮ ሕመም ሊጠቁ ይችላሉ " - ጥናት
በሀገር አቀፍ ደረጃ ቢያንስ 30 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች በሕይወት ዘመናቸው ለአእምሮ ሕመም ተጠቂ ሊሆኑ ይችላሉ ሲል ጤና ሚኒስቴር ገለጸ።
ሚኒስቴሩ ይህን ያለው ለአሐዱ ሬዲዮ ጣቢያ ነው።
በጤና ሚኒስቴር የአእምሮ ሕሙማን የጤና ፕሮግራም ባለሙያ የሆኑት አቶ ጀማል ተሾመ፤ " ኢትዮጵያ ካላት 120 ሚሊዮን ሕዝብ መካከል በሕይወት ዘመኑ ቢያንስ አንድ አራተኛው ወይም 30 ሚሊዮን የሚሆነው ሕዝብ በአእምሮ ሕመም እንደሚጠቃ በጥናት ተረጋግጧል" ብለዋል።
30 ሚሊዮን የሚሆን ሕዝብ ለአዕምሮ ሕመም ተጠቂ እንዲሆን ፦
- ግጭት፣
- ጦርነት፣
- ድህነት፣
- የቤተሰብ ጫና፣ ፆታዊ ጥቃትና አስገዳጅ መፈናቅል ዐብይ ምክንያቶች ናቸው ብለዋል፡፡
ከዚህ ውስጥ 500 ሺሕ የሚደርሰው ሕዝብ ለአእምሮ ሕመም የሚጋለጠው በጭንቀት ምክንያት መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
ሆኖም መንግሥት ችግሩ እንዳይከሰት " ከፌደራል እስከ ክልል ባሉት የሕክምና ተቋማት፤ የአእምሮ ሕሙማንን የሕክምና ተደራሽነትን በተገቢው መንገድ ለማረጋገጥ መዋቅራዊ አሰራር ዘርግቶ እየተሰራ ይገኛል " ሲሉ ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት 11 በመቶ የሚሆነው ሕዝብ ለአእምሮ ሕመም የተጋለጠ ሲሆን፤ ከእነዚህም መካከል 30 በመቶ የሚሆነውን የሕክምና አገልግሎት እየተሰጠ ያለው በአዲስ አበባ ከተማ መሆኑን አሐዱ ሬድዮ ዘግቧል።
ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የአሐዱ ሬድዮ ጣቢያ ነው።
@tikvahethiopia
#Ethiopia
ባንኮች እስከ ህዳር አጋማሽ ድረስ ከብሔራዊ መታወቂያ (ፋይዳ) ጋር የማስተሳሰር ሥራ ማጠናቀቅ ይኖርባቸዋል ተባለ።
ብሔራዊ ባንክ እና የብሔራዊ መታወቂያ በጋራ ባወጡት አዲስ የአተገባበር ሥርዓት መሰረት የፋይናንስ ተቋማት ብሄራዊ ኦፕሬተር በሆነው ኢት-ስዊች በኩል ከብሔራዊ መታወቂያ (ፋይዳ) ጋር የማስተሳሰር ሥራ መስራት መጀመራቸው ተገልጿል።
እስካሁን 10 የሚሆኑ የፋይናንስ ተቋማት ከብሔራዊ መታወቂያ (ፋይዳ) ጋር የማስተሳሰሩን ሥራ ጨርሰዋል ሲባል ሌሎች ባንኮች በሙከራ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።
የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ይለበስ አዲስ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደገለጹት ይህ አሰራር ባንኮች አገልግሎታቸው ቀልጣፋ እንዲሆንና ማዕከላዊ የመረጃ አያያዝ እንዲኖር ያስችላል ሲሉ ገልጸዋል።
አክለውም ትስስሩ ባንኮች ከደንበኞቻቸው ጋር ያላቸውን አገልግሎት ያሳልጥላቸዋል፤ ወጪንም ይቆጥብላቸዋል ነው ያሉት።
የኢት-ስዊች ቺፍ ፖርት ፎልዮ ኦፊሰር (CPO) አቤኔዘር ወንደሰን በበኩላቸው ከዚህ በፊት ደንበኞች አካውንት ሲያወጡ ባንኮች የደንበኛውን መታወቂያ ለማረጋገጥ ሁለት መቶ ብር በአንድ ሰው ክፍያ እንደሚጠበቅባቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
በአዲሱ አሰራር ባንኮች ስንት እንደሚከፍሉ ተመን ባይወጣላቸውም ክፍያው ሲወሰን ከሀምሳ ብር እንደማይበልጥና ይህም ባንኮችን ከብዙ ወጪ እንደሚያድናቸው አክለው ተናግረዋል።
ባንኮች እስከ ህዳር አጋማሽ ድረስ ጥምረት አድርገው መጨረስ እንዳለባቸውም ነው አቤኔዘር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የተናገሩት።
ባንኮቹ ከብሔራዊ መታወቂያ ጋር በቀጥታ ትስስር አይኖራቸውም ሲባል ትስስር የሚኖራቸው በኢት-ስዊች በኩል እንደሆነም ተገልጿል።
ኢት-ስዊች ሁሉንም ባንኮች ያስተሳሰረ ስለሆነ ብሔራዊ መታወቂያ ከኢት-ስዊች ጋር በመቀናጀት ሁሉንም ባንኮች በአንድ ጊዜ ማግኘት ይችላል።
የባንክ አካውንት ሲከፈት ባንኮች የብሔራዊ መታወቂያ ቁጥሩን ወደ ኢትስዊች ልከው ኢት-ስዊች ባንኩ ስለደንበኛው የሚያስፈልገውን መረጃ (KYC) ከብሔራዊ መታወቂያ ተቀብሎ ለባንኮቹ መልሶ ይልካል።
የብሔራዊ መታወቂያ የጣት አሻራን በክፍያ ወቅት እንደ ይለፍ ቃልም መጠቀም እንዲቻል አሁን ላይ የተጀመሩት ትስስሮች እንደሚያግዙም ተጠቅሷል።
ኢት-ስዊች የፋይናንስ ሪፖርቱን በቅርቡ ሲያቀርብ በባለፈው በጀት ዓመት፥ ጠቅላላ ገቢው 2.2 ቢሊዮን ብር መሆኑን ጠቅሶ ከታክስ በፊት 1.42 ቢሊዮን ብር ማትረፉንና ይህም ካለፈው የበጀት ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ34% ጭማሪ ማሳየቱን ገልጿል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
@tikvahethiopia
ዳሸን ባንክ እስከ 30 ሚሊዮን ብር ሽልማት ያለውን የ"ዳሸን ዕድል" ጨዋታ ይፋ አደረገ
ዳሸን ባንክ በዳሸን ሱፐር አፕ ላይ ብቻ የሚገኝ አዲስ የዲጂታል ሽልማት እና የጨዋታ ተሞክሮ የሆነውን ዳሸን እድልን በይፋ መጀመሩን አሳወቀ።
ይህበአይነቱ ልዩ የሆነው የሱፐር አፕ እድል እስከ 30 ሚሊዮን ብር የሚደርስ ጠቅላላ የሽልማት ገንዘብ ያለው ሲሆን፣ ይህም የዳሸን ሱፐር አፕ ተጠቃሚዎች የባንኩን ዘመናዊ ዲጂታል አገልግሎቶች በመጠቀም አስደሳች ሽልማቶችን የማግኘት ልዩ እድል የሚሰጣቸው ነው።
የዳሸን ዕድል ሎተሪ ደንበኞች እንዲሳተፉ እና እንዲያሸንፉ በአርኪ መንገድ የቀረበ ጨዋታ ነው፡፡ የዳሸን ሱፐር አፕ ተጠቃሚዎች በዕለት ተዕለት በሚያደርጓቸው ዲጂታል ግብይቶች፣ (ማለትም የገንዘብ ዝውውሮችን በማድረግ፣ ሱፐር አፕን በማውረድ እና በመጠቀም፣ ከሌሎች ባንኮች ገንዘብ በመቀበል፣ የንግድ ክፍያዎችን በመፈፀም፣ የአየር ሰዓት በመሙላት እንዲሁም ሌሎች በመተግበሪያው ውስጥ የሚገኙትን የቻት ባንኪንግና የበጀት አገልግሎቶችን) እና ሌሎች አገልግሎቶችን በመጠቀም በቀላሉ "ሳንቲሞችን" መሰብሰብ ይችላሉ፡፡
ደንበኞች ከዚያም የሰበሰቡትን ሳንቲሞች በመጠቀም ስልኮቻቸውን "በማወዛወዝ" እና ከሞባይል ዳታ ፓኬጆች አንስቶ ከ100 ብር እስከ 100,000 ብር የሚደርሱ የኤሌክትሮኒክስ የገንዘብ (e-money) ሽልማቶችን፣ ሳምሰንግ ጋላክሲ ኤስ 23 እና ኤ 54፣ አይፎን 16 ሞዴል ስልኮችን እንዲሁም አዲስ የቢዋይዲ መኪና ሽልማቶችን ማሸነፍ ይችላሉ።
ከጥቅምት 22 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ዳሸን ባንክ በዳሸን ዕድል የማስተዋወቅ ዘመቻው በሺዎች የሚቆጠሩ ሽልማቶችን ለአሸናፊዎች መስጠት ጀምሯል። ይህ የማስተዋወቅ ዘመቻ የዳሸንን ደንበኞች ለመሸለም ብቻ የቀረበ ሳይሆን ደንበኞች በዳሸን ሱፐር መተግበሪያ ላይ የቀረቡትን በርካታ የአገልግሎት አይነቶች እንዲጠቀሙ ለማነሳሳት የተነደፈ ነው።
ዛሬውኑ ይህን አስደሳች ጨዋታ ይቀላቀሉ!
የዳሸን ሱፐር መተግበሪያን ያውርዱ፣ ሳንቲሞችን ማግኘት ይጀምሩ፣ እና በዳሸን ባንክ የዲጂታል ባንክ ሕይወትን የሚቀይሩ ሽልማቶችን ለማሸነፍ እድልዎን ይጠቀሙ።
የዳሸን ባንክ ሱፐር አፕ መተግበሪያ ያውርዱ 👇 https://www.dashensuperapp.com/download
" ሕዝቡ ' እምቢ ለጦርነት ' ማለት አለበት " - የትግራይ ሙሁራን እና ባለሙያዎች ማሕበር
🚨" ህወሓት እና አንዳንድ የጦር ጀነራሎች የፕሪቶሪያ የተኩስ አቁም ስምምነትን መሰረት በማድረግ ነገሮችን በሰላማዊ መንገድ ከመፍታት ይልቅ ትግራይን ወደ ሌላ ዙር ጦርነት ለማስገባት እየፎከሩና የጦርነት ዝግጅት እያደረጉ ነው ! "
የትግራይ ሙሁራን እና ባለሙያዎች ማሕበር (GSTS) በትግራይ ያንዣበበው የጦርነት ዳመና በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ ጥሪ አቀረበ።
ማሕበሩ ባወጣው አስቸኳይ መግለጫ " የትግራይ ሕዝብ ዋናው ፍላጎት ሰላምና ሰላም ብቻ ነው " ብሏል።
ከጫፍ እስከጫፍ ያለው የትግራይ ህዝብ ጦርነትና የጦርነት ወሬ መስማት አይፈልግም ያለው ማሕበሩ " ህወሓት እና አንዳንድ የጦር ጀነራሎች የፕሪቶሪያ የተኩስ አቁም ስምምነትን መሰረት በማድረግ ነገሮችን በሰላማዊ መንገድ ከመፍታት ይልቅ ትግራይን ወደ ሌላ ዙር ጦርነት ለማስገባት እየፎከሩና የጦርነት ዝግጅት እያደረጉ ነው " ብሏል።
" ሕዝብን የሚመራ አካል ጦርነት ለማስቀረት ይጥራል እንጂ ወደ ጦርነት የሚያመሩ ንግግሮችና ተግባራትን መፈጸም የለበትም " በማለትም የክልሉን ጊዚያዊ አስተዳደርም ወቅሷል።
አሁን በአካባቢው እያንዣበበ ያለውን የጦርነት ድባብን ለማስቀረት ሕዝቡ፣ በትግራይ ሐይሎችና በዓፋር ያሉ የታጠቁ ሐይሎች እንዲሁም የዳያስፖራው ማሕበረሰብ ለሰላም መቆም እንዳለባቸው አሳስቧል።
የማሕበሩ የአመራር አባል የሆኑት ዶ/ር ገብረኪዳን ገ/ስላሴ ለዶቼ ቨለ ሬድዮ በሰጡት ማብራሪያ ምን አሉ ?
" የትግራይ ሕዝብ ፍላጎት ሰላም ነው።
ሁለተኛ ጦርነት እንዳይመጣ እንጸልያለን።
ሆኖም ግን እንደዛ አይነት ጥሪ (የጦርነት ጥሪ) የሚያደርጉ በሁሉም ወገን ካሉ ወጣቱ የዚህ ሰለባ እንዳይሆን፤ ሕዝባችንም በሰራዊት ያሉም አንዱ ሀራ መሬት የሚባል አለ፤ ሌላው ቲዲኤፍ ትግራይ ውስጥ ያለው በመካከላቸው ምንም ወደ ግጭት የሚወስዳቸው ነገር ስለሌለ ወደዛ እንዳይሄዱ፤ እና ወጣቱ የጦርነት ሰለባ እንዳይሆን ጥሪ አድርገናል።
ሕዝቡ ' እምቢ ለጦርነት ' ማለት አለበት።
ያለው ልዩነት የፖለቲካ ልዩነት ነው። በፖለቲካ ውይይት እንዲፈቱት ነው የምንጠይቀው። ከዚህ በተጨማሪ ግን ህብረተሰቡ እራሱ ሕብረተሰቡ ፖለቲከኞች በሚፈጥሩት ግጭት ወደ ጦርነት እንዳይገባ የራሱን ተፅዕኖ ማድረግ አለበት። ለጦርነት ' እምቢ ' ማለት አለበት። " ብለዋል።
#Tigray #Peace
@tikvahethiopia
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ለዳታ ማይኒንግ ድርጅቶች ከ ታህሳስ ወር ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ የታሪፍ ማሻሻያ ማድረጉን አሳውቋል።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል በክሪፕቶ ማይኒንግ ስራ ላይ ለተሰማሩ ድርጅቶች በፈረንጂዎቹ DEC 1/2025 ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ የታሪፍ ማሻሻያ ማድረጉን ተቋሙ ጥቅምት 17/2018 ዓም በጻፈላቸው ደብዳቤ ማሳወቁን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ተመልክቷል።
በደብዳቤው መሰረት የዳታ ማይኒንግ ድርጅቶች የታህሳስ ወር የኤሌክትሪክ ሽያጭ ሂሳብ የሚከፍሉት በተሻሻለው ታሪፍ መሰረት ይሆናል።
የተሻሻለው የታሪፍ መዋቅር የዳታ ማይኒንግ ካምፓኒዎች የኃይል ክፍያዎችን እንደ አጠቃቀም ሰአታቸው/ጊዜ(Time of use) እንዲከፍሉ የሚያደርግ ነው።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን የደብዳቤውን ትክክለኛነት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጠዋል።
አቶ ሞገስ በሰጡን ማብራሪያ " የታሪፍ ማሻሻያው ዝርዝር የአጠቃቀም ሰአቶች እና ታሪፍም ጭምር አለው ከእዚህ በፊት የነበረው የታሪፍ አተገባበር ፍላት ነው የአሁኑ እንደ አጠቃቀማቸው ፒክ በሆነ ሰአት እና እንደሚጠቀሙበት ሰዓት የተለያየ የክፍያ መጠን ይኖራቸዋል " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድተዋል።
@tikvahethiopia
#Hawassa
የሀዋሳ ከተማ ምክር ቤት በአንድ ወር ገደማ ለሁለተኛ ጊዜ በጠራው አስቸኳይ ጉባኤ ፤ የከተማይቱን አዲስ ከንቲባ ሹመት እንደሚያፀድቅ " ኢትዮጵያ ኢንሳይደር " ዘግቧል።
ምክር ቤቱ በነገው ዕለት በሚያካሄደው አስቸኳይ ጉባኤው ሹመታቸው የሚጸድቅላቸው፤ ከ5 ዓመት በፊት የከተማይቱ ከንቲባ የነበሩት አቶ ጥራቱ በየነ ናቸው።
ምክር ቤቱ ዛሬ ለአባላቱ ባስተላለፈው ጥሪ፤ በነገው ዕለት አስቸኳይ ጉባኤ እንደሚካሄድ አረጋግጧል።
ምክር ቤት በዚሁ ጥሪው፤ አባላቱ ነገ ጠዋት በሀዋሳ ከተማ ምክር ቤት በሚገኘው አዳራሽ እንዲገኙ ቢያሳስብም የጉባኤውን አጀንዳ ግን ከመግለጽ ተቆጥቧል።
የሀዋሳ ከተማ ምክር ቤት ባለፈው ጥቅምት ወር መጀመሪያ በተመሳሳይ መልኩ ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ፤ ከተማይቱን በከንቲባነት እንዲመሩ የተሾሙትን የአቶ ተክሌ ጆንባን ሹመት አጽድቆ ነበር።
የሲዳማ ክልል የእንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ የነበሩት አቶ ተክሌ፤ በዚህ የኃላፊነት ቦታቸው ላይ አንድ ወር ያህል ጊዜ እንኳ ሳይቆዩ ወደ ፌደራል ተቋም ተዘዋውረዋል ተብሏል።
አቶ ተክሌ ከጥቅምት 21፤ 2018 ጀምሮ የእንስሳት ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ሆነው መሾማቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ በማህበራዊ ሚዲያዎች ሲሰራጭ ነበር።
የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አርማ እና የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) ፊርማ የያዘው ይህ ደብዳቤ፤ በአድራሻቸው እንዳልደረሳቸው አቶ ተክሌ ባለፈው እሁድ በፌስ ቡክ ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት አስታውቀው ነበር።
" ኢትዮጵያ ኢንሳይደር " ከእንስሳት ጤና ኢንስቲትዩት አገኘሁት ባለው መረጃ ለአቶ ተክሌ የተጻፈ እና በእጃቸው የሚሰጥ ደብዳቤ ለመስሪያ ቤቱ ደርሷል።
አቶ ተክሌ ካለፈው አርብ ጀምሮ በስራ ገበታቸው (የሀዋሳ ከንቲባነት) ላይ አልተገኙም።
ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የኢትዮጵያ ኢንሳይደር ድረገጽ ነው።
@tikvahethiopia
#AddisAbaba
ከኤድናሞል በ22 ወደ እንግሊዝ ኤንባሲ የሚወስደው መንገድ ግንባታ በ1.2 ቢሊየን ብር አጠቃላይ በጀት በአዲስ መልኩ ስራዉ መጀመሩ ተገለጸ።
የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ እያሱ ሰለሞን ለመናኸሪያ ሬዲዮ በሰጡት ቃል ምን አሉ ?
" ከእንግሊዝ ኤንባሲ ወደ 22 እና ኤድናሞል የሚሄደው መንገድ ካሁን ቀደም ከአለም ባንክ በተገኘ በጀት ተጀምሮ ነበር።
ነገር ግን የወሰን ማስከበርን ጨምሮ በተለያየ ምክንያት ተቋርጦ ነበር።
አሁን ላይ ነባር መንገዱን በማንሳት ግንባታውን በአዲስ መልክ ተጀምሯል።
በአጠቃላይ የመንገዱ ፕሮጀክት 3.4 ኪ.ሜ እርዝማኔ አለው። 1.4 ኪሜ ያህሉን የግንባታ ስራ በቻይና ኮንስትራክሽን ኮፖሬሽን እንዲሁም ከኤድናሞል እስከ 22 ያለው በከተማ አስተዳደሩ እየተሰራ ነው።
የመንገድ ግንባታው 1.2 ቢሊየን ብር አጠቃላይ በጀት የተያዘለት ሲሆን የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሰርቪስን ባካተተ መልኩ እየተገነባ ነው።
ከፍተኛ የትራፊክ ፍሰት ያለበት መንገድ ነው። ለረጅም ጊዜያት ካለምንም ጥገና እስካሁን በመቆየቱ ህብረተሰቡ ከፍተኛ ቅሬታ ከሚያነሳባቸው መንገዶች መካከል ነበር።
አሁን ላይ ስራው በፍጥነት እየተሰራ ነው። ወደ 400 ሜትር በሚሆነው የመንገዱ ክፍል ላይ የፍሳሽ ማስወገጃ ቀበራና የቁፋሮ ስራው ተጀምሯል።
በዘንድሮው ዓመት መንገዱን ሙሉ በሙሉ አጠናቆ ለህዝብ ክፍት ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ ነው " ብለዋል።
ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የመናኸሪያ ሬድዮ ጣቢያ ነው።
@tikvahethiopia
" የአፋር ህዝብ ሰላምና ልማት ይፈልጋል፣ የጦርነትን ጉዳት እና አስከፊነት ጠንቅቆ ያውቃል። እኛ ከክልላችን አልፈን ወደየትም አልሄድንም፣ ስለዚህ በራሳችን ሀገር ሰላም ይስጡን " - የክልበት ዞን አስተዳደር ተወካይ
የህወሓት ቡድን ጥቅምት 26/02/2018 ዓ/ም በአፋር ክልል ወሰን ውስጥ በማግባት 6 መንደሮችን በጉልበት በመቆጣጠር ንጹሃንን በሞርታርና በዙ-23 ደብደባ በመፈጸም የፕሪቶሪያ ስምምነትን በግልጽ አፍርሷል ሲል የክልሉ መንግስት ማስታወቁ ይታወሳል።
ጊዜያዊ አስተዳደሩ ሆነ ህወሓት ይህን ክስ አጣጥለዋል።
በህወሓት " ተይዘዋል " በተባለባቸው በክልበት ዞን ስር በሚገኙ ሁሉም የገጠር ወረዳዎች እና ከተሞች የሚኖሩ ነዋሪዎች የህውሓት ቡድን በክልሉ " ከፍቷል " ያሉት ፤ ጦርነት የሚያወግዝ ሰላማዊ ሰልፍ ትላንት አካሂደዋል።
በሰልፉም ላይ :-
- " የሻቢያ ተላላኪዎች እኛን አይወክሉም "
- " የአፋር ተወላጅ ሆነው ወደ ኤርትራ ታጣቂዎች የሚሄዱ ወጣቶች የአፋርን ህዝብ አይወክሉም "
- " የፕሪቶሪያው ስምምነት በፌደራላዊ ስርአት ይከበር "
- " የአፋር ህዝብ ጦርነት ሳይሆን ሰላምና ልማት ነው የሚፈልገው "
የሚሉ እና ሌሎችም ደምጾችን አሰምተዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያም በሰልፉ ላይ የነበሩ የዞኑ ነዋሪዎችን፣ የተለያዩ የወረዳ ባለስልጣናትን እና የዞኑን አስተዳደር ተወካይ ስለጉዳዩ ጠይቋል።
የክልበት ዞን ኢኮኖሚ ዘርፍ ሃላፊ እና የዞኑ ወኪል አስተዳደር አቶ ኡስማን ሙቱህ በዝርዝር ምን አሉ ?
" ከ3 አመት በፊት የህወሓት ቡድን በአፋር ክልል ያደረገው ወረራ በርካታ ጉዳቶችን አስከትሎ ነበር። አሁንም በድጋሜ የጥፋት ቡድኑ ከሰሞኑ በዞናችን በመጋሌ ወረዳ ስር በሚገኙ በ6 መንደሮች ላይ ወረራ ፈጽሟል። ይህን እያደረገ ያለው ደግሞ ከኤርትራ መንግስት ጋር በመሆን ነው።
እኛ የአፋር ህዝቦች የማንንም መሬት አልወረርንም፣ ማንንም አልዘረፍንም ስለዚህ የሻቢያ እና የወያኔ ቡድን ተስማምተው የአፋርን ህዝብ የጦርነት ሰለባ እንዲሆን ለማድረግ የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ተቀባይነት የለውም፣ አሁንም ባሉበት ይቁሙልን፣ የወረሩትን አካባቢ ለቀው ይውጡልን፣ የሻቢያ ወታደሮች በአፋር ህዝብ ላይ እያደረሱት ያለው ጉዳት ይቁም።
ህዝባችን ሰልፍ የወጣንበት ዋና አላማ ይህንን የጥፋት ወረራ ለመቃወም ነው።
በዞናችን ስር በሚገኙ 9 ወረዳዎች እና በአንድ የከተማ አስተዳር ላይ ህዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ አካሂደናል። በሁሉም ሰልፎች ላይ የተነሱት ሃሳቦች ተመሳሳይ ናቸው።
የህወሓት ቡድን የወረራቸውን አካባቢዎች ለቋል የሚሉ መረጃዎች በስፋት እየተሰራጩ ነው ያሉት እውነታው ግን አለቀቁም፣ እኔም ያለሁት ታጣቂዎች በወረሩት አካባቢ ነው፣ የክልላችን ሚኒሻዎች እና የፖሊስ አባላት ታጣቂዎችን በቅርብ ርቀት እየተከታተሉ ነው።
የህወሓት ቡድን ከሰሞኑ ወረራ የፈጸመባቸውን 6 መንደሮች ለቋል የሚሉ መረጃዎች ሃሰተኛ ናቸው፣ ቡድኑ ለፕሮፓጋንዳ እየተጠቀመበት ነው እንጂ አለቀቀም፣ እኔ ራሱ በስፍራው ነኝ፣ እንኳን የወረራቸውን አካባቢዎች ሊለቅ ይቅር እና ተጨማሪ አካባቢዎችን ለመውረር እየጣረ ነው።
የአፋር ህዝብ ሰላምና ልማት ይፈልጋል፣ የጦርነትን ጉዳት እና አስከፊነት ጠንቅቆ ያውቃል። እኛ ደግሞ ከክልላችን አልፈን ወደየትም አልሄድንም፣ ስለዚህ በራሳችን ሀገር ሰላም ይስጡን፣ ኤርትራም ከእኛ የወሰደችው መሬት እንጂ እኛ ከእሷ የወሰድነው የለም። " ብለዋል።
ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡ አንድ የኢሬብቲ ወረዳ ባለስልጣን " የአፋር ተወላጅ ወጣቶች ከህውሓት እና ከኤርትራ ታጣቂዎች ጋር ጥምረት ፈጥረው በክልሉ የአፋርን ብሔራዊ ሰንደቅ አርማ ይዘው እንቅስቃሴ እያደረጉ ነው " የሚባለው ወሬ ውሸት ነው ብለዋል።
" አንድ ወጣት ' የአፋር ተወላጅ ነኝ ' እያለ በማህበራዊ ገፆች ላይ ' ከህውሓት እና ከኤርትራ ጋር የአፋር ወጣት ጥምረት ፈጥሯል ' እያለ እያወራ ነው " ሲሉ ተናግረዋል።
" ነገር ግን መዘንጋት የሌለበት ጉዳይ እሱ አንድ ሰው መሆኑ ነው። ይህም የአፋርን ህዝብ አይወክልም። በዞናችን አንድም ወጣት ከህውሓት እና ከኤርትራ ጋር የተስማማ የለም " ብለዋል።
የአብአላ ከተማ ከንቲባ አቶ ሀሰን አብደላ በበኩላቸው " የህዝቡ ፍላጎት ሰላም ነው፣ ቡድኑ ግን አሁንም በተለያዩ አካባቢዎች ጥቃት እየፈጸመ ነው። ከኤርትራ መንግስት ጋር ጥምረት በመፍጠር ከሰሞኑ በክልላችን እያደረሰ ያለውን ጉዳት በመቃወም ነው ማህበረሰቡ ዛሬ ሰልፍ የወጣው። ህዝቡም ከፍተኛ ቁጣ ላይ ነው ያለው " ብለዋል።
" አሁን ላይ በዞናችን የሚገኙ ወጣቶችን ወደ ህውሓት እና ኤርትራ ታጣቂዎች ጋር ጥምረት ለማስገባት ሰፊ እንቅስቃሴ እየተደረገ ነው፣ ' የአፋር ወጣቶች ከእኛ ጋር ጥምረት ፈጥረዋል ' እያሉም ነው። ይህ ግን የማስመሰል ነው። አንድም ወጣት አልተቀላቀለም። የህዝባችን ጥያቄ ህውሓት ከወረረባቸው አካባቢዎች በፍጥነት ለቆ ይውጣ ነው " ሲሉ አስረድተዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
ጉደኛው ማሽን ህይወት እንደጉድ እያቀለለ ነው!
ውድ ደንበኛችን
እነሆ ገንዘብ ገቢ፣ወጪ እንዲሁም ማስተላለፍ ሁሉንም በአንድ የሚያከናውኑበትን የሪሳይክለር ማሽን ይዘን መጥተናል። ይህን አገልግሎትም በካርድዎ፣ ያለ ካርድ በስልክዎ በሚደርስዎ አጭር ቁጥር አሊያም በሞባይል ባንክ መተግበሪያ ኪው.አር ኮድን በመጠቀም ማግኘት ይችላሉ።
#ወረቀትአልባየባንክአገልግሎት #Paperlessbranch#BanksinEthiopia#AddisAbaba#Ethiopia
" ዛሬም በትክክል ሦስት ሰዎች ተገድለዋል " - የአርሲ ዞን ሀገረ ስብከት
ተደጋጋሚ ግድያ እንደሚፈጸም በሚነገርበት በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ዛሬም (ህዳር 1 ቀን 2018 ዓ/ም) በግብርና ስራ በተሰማሩበት ዲያቆንን ጨምሮ ምዕመናን በታጣቂዎች መገደላቸውን በኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የአርሲ ዞን ሀገረ ስብከት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።
አንድ የሀገረ ስብከቱ አመራር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፣ " ዛሬም በትክክል ሶስት ሰዎች ተገድለዋል " ብለዋል።
ግድያው የተፈጸመው በዞኑ አሰኮ ወረዳ መሆኑን አስረድተው፣ ማቾቹ " አንደኛ ዲያቆን ኢዮብ እጅጉ፣ ሁለተኛ ጥላሁን ቦጌ ደመቀ፥ ሶስተኛዋ የ11 ዓመት ልጅ የሆነችው ፃድቃኔ ሰራዊት ይስሙ " የሚባሉ መሆናቸውን በዝርዝር አስረድተዋል።
ሰዎቹ የተገደሉት ዛሬ ከጠዋቱ ሁለት ሰዓት ተኩል እንደሆነ፣ ግድያ የተፈጸመበት ቦታ ልዩ ስም " ጠለታ ገብርኤል " እንደሚባልም እኝሁ አካል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
" ቦለቄ እየወቁ እያለ የተጠቀሰው ቦታ ላይ ነው የገደሏቸው " ሲሉም ያስረዱ ሲሆን፣ ግድያውን የፈጸሙት የታጠቁ ሓይሎች መሆናቸውን ተናግረዋል።
ከጥቅምት ወር ጀምሮ ስንት ምዕመናን ተገደሉ ማለት ነው ? ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ የሀገረ ስብከቱ አካል፣ " 33 ምእመናን ተገድለዋል " ሲሉ ተናግረዋል።
አዲሱ የአሰኮ ወረዳ ግድያ የተፈጸመው የኢትዮጵያ ኃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ከጥቅምት 2018 ዓ/ም አጋማሽ ጀምሮ በዞኑ የተፈጸመውን ግድያ ለማጣራት ላኩት ያለው ልዑካን ቡድን ያጠናቀረውን የመጀመሪያ ዙር ሪፖርት ባቀረበበት በተመሳሳይ ቀን ነው።
በዚህም ልዑካኑ በአራት ወረዳዎች አሰባሰብኩት ባለው ሪፖርት፣ ግድያ መፈጸሙን ገልጾ፣ " በአርሲ ዞን ምዕመናን ላይ የተፈጸመውን አሰቃቂ ግድያ የፈጸሙት በኦሮሚያና አማራ ክልል ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ ኃይሎች ስለመሆናቸው መረጃ አግኝተናል " ብሏል።
ይሁን እንጅ፣ በጥቅምት 2018 ዓ/ም ስለተፈጸው ግድያ ምላሽ እንዲሰጡ ምንም እንኳ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ወደ ክልሉና ዞኑ አካላት ሙከራ አደርጎ ቀጥተኛ ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ ባይሆኑም፣ የአርሲ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ኢብራሂም ከድር ግን በዞኑ ግድያ ተፈጸመ መባሉ " ሀሰት ነው " ሲሉ ለቢቢሲ በወቅቱ ገልጸው ነበር።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ስለጥቅምቱ ግድያ በወቅቱ ምላሽ የጠየቃቸው አንድ የክልሉ አካል ደግሞ " አርሲ ምን አጥፍቶ ነው የሚጠቃው " ብለው ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ተቆጥበው ነበር።
በሌላ በኩል ጉባዔው ዛሬ ባቀረበው ሪፓርት፣ " ግድያው አንድን ሃይማኖትና ብሔር ትኩረት ያደረገ አይደለም " ብሏል። ለዚሁ ሪፓርት አስተያየት እንዲሰጡ የአርሲ ዞን ሀገረ ስብከት አካልን የጠየቅን ሲሆን፣ በጉዳዩ " ተገርመው " ዝርዝር አስተያየት ከመስጠት ግን ታቅበዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
" 519 የባንክ አካውንቶች ታግደዋል " - አገልግሎት መ/ቤቱ
➡ " 112 ኢትዮጵያውያንና የተለያዩ የውጭ ሀገር ዜግነት ያላቸው ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ውለዋል። "
⚫ " የክሪፕቶ ከረንሲ መተግበሪያን በመጠቀም በሕገ ወጥ መንገድ የውጭ ምንዛሪን ሲያዘዋውሩ የነበሩ አካለት ላይ ርምጃ ተወስዷል። "
የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት (NISS) ፤ በተቀናጀ መንገድ ሕገ ወጥ የውጭ ምንዛሪ አሻጥሮችን ሲፈጽሙ ተደረሰባቸው ያላቸውን 112 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ገለጸ።
የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ፥ ከፋይናንስ ደኅንነት አገልግሎት፣ ከኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ፣ ከክልል የፀጥታ አካላት ጋር በመሆን በሕብረተሰቡ ጥቆማ በፋይናንስ አሻጥር ላይ በተሰማሩ አካላት ላይ ስምሪት መደረጉን አመልክቷል።
በዚህም 112 ኢትዮጵያውያንና የተለያዩ የውጭ ሀገር ዜግነት ያላቸው ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ገልጿል፡፡
ከሕገ ወጥ ተግባሩ ጋር ትስስር የነበራቸው 519 የባንክ አካውንቶች መታገዳቸውን የተለያዩ ኤግዚቢቶች መያዛቸውንም ጠቅሷል፡፡
° ሕገ ወጥ ሃዋላዎች ፣
° የገንዘብ ዝውውሮች፣
° የውጭ ምንዛሪ ስወራዎች ፣
° የግብር ስወራዎች፣
° ሕገ ወጥ ገንዘብን ሕጋዊ የማስመሰልና ሌሎች ተመሳሳይ ወንጀሎች በሀገር ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሲያስከትሉ እንዲሁም አሸባሪዎችንና የታጠቁ ቡድኖችን ለመደገፍ ሲውሉ መቆየታቸውን አመልክቷል።
በተለይም ፦
- ሕገ ወጥ በሆኑ ዓለም አቀፍ የገንዘብ አስተላላፊ ድርጅቶች፣
- ሕገ ወጥ የውጭ ምንዛሪ ማስተላለፊያ መተግበሪያዎች፣
- የክሪፕቶ ከረንሲ መተግበሪያዎች፣
- ሕገ ወጥ የሃዋላ አዘዋዋሪዎችና ደላላዎች፣
- በወጪና ገቢ ንግድ ላይ አሻጥር የፈፀሙ አስመጪዎችና ላኪዎች እንዲሁም ሕጋዊ ንግድ ሳይኖራቸው በሕገ ወጥ ሃዋላ ላይ በመሰማራት ከፍተኛ ገንዘብ በማንቀሳቀስ በሀገር ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ባደረሱ አካላት የማያዳግም ሕጋዊ ርምጃ መወሰዱን ጠቁሟል።
በተለያዩ ዓለማት የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የሚልኩት ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገባ የብሔራዊ ባንክን መመሪያ በሚጥስ ሁኔታ በሀገር ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሲያስከትሉ የቆዩ ሕጋዊ ፈቃዳቸው በፈጸሙት ተደጋጋሚ ጥፋት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የተሰረዘባቸው ዓለም አቀፍ የሃዋላ አስተላላፊዎችና ሕገ ወጥ የሃዋላ ድርጅቶችም ርምጃው እንደተወሰደባቸው አሳውቋል።
በተጨማሪም በሀገር ውስጥ ሕገ ወጥ የውጭ ምንዛሪ ማስተላለፊያ መተግበሪያዎችን በመጠቀም ሀብትን ከሀገር በማሸሽ ላይ ያሉ ድርጅቶች ባለቤቶችም በቁጥጥር ሥር እንደዋሉ አመልክቷል።
የብሔራዊ ባንክ ሕግን በሚጥስ ሁኔታና ያለምንም ፈቃድ የክሪፕቶ ከረንሲ መተግበሪያን በመጠቀም በሕገ ወጥ መንገድ የውጭ ምንዛሪን ሲያዘዋውሩ የነበሩ አካለት ላይም ርምጃ እንደተወሰደ አመልክቷል።
አሁንም የሚወሰደው ርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አገልግሎቱ በላከልን መግለጫ አሳውቋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
@tikvahethiopia
#Afar
በዛሬው እለት ህዳር 1/2018 ዓ.ም በአፋር ክልል አብዓላና ዙሪያዋ የሚኖሩ ነዋሪዎች ሰላማዊ ሰልፍ አካሂደዋል።
ሰላማዊ ሰልፉን አስመልክቶ ከክልሉ ኮሚኒኬሽን ባገኘነው መረጃ ነዋሪዎቹ በህወሓትና በሻዕብያ " ትብብር " በአከባቢያቸው ተቃጥቷል ያሉትን ጥቃት ክፉኛ አውግዘዋል።
" ህዝቡ ወደ ቀዩ ይመለስ የትግራይ ኃይል ከያዘው የዓፋር መሬት ይውጣ " ያሉት ተቃዋሚ ሰልፈኞቹ ፤ ይህን ሳይሆን ከቀረ ከዓፋር እና ከፌደራል መንግስታት ጋር ተሰልፈው መብታቸው ለማስከበር እንደሚንቀሳቀሱ ዝተዋል።
ሰላማዊ ሰልፉ በኢረቦቲ ፤ ባዱ፤ ዳሊፋጌ ከተሞች ጭምር መካሄዱ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ የደረሰ መረጃ ያስረዳል።
የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደርና ህወሓት ከቀናት በፊት ባወጡት መግለጫ የትግራይ ኃይል ወደ ዓፋር ክልል ዘልቆ ገብቷል የሚል ሰሞታ ውድቅ ማደረጋቸው ይታወሳል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
@tikvahethiopia
" ህጻናት ታግተው ገንዘብ መጠየቂያ ተደርገዋል፣ ወላጆች ገንዘብ መስጠት ስላልቻሉ ህጻናቱ ተገድለዋል " - አጣሪ ኮሚቴው
➡️ " ግድያው አንድን ሃይማኖት እና ብሄርን ትኩረት ያደረገ አይደለም "
የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ከጥቅምት ወር አጋማሽ ጀምሮ ለተከታታይ ቀናት በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን በሚገኙ አንዳንድ ወረዳዎች በሚኖሩ ዜጎች ላይ የተፈጸሙ ግድያ ፣እገታ እና ዝርፊያ በሚመለከት ልዑካኑን በአካባቢው በመላክ በጉዳዩ ላይ ሲያደርግ የቆየውን ጥናት የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርት በዛሬው ዕለት ይፋ አድርጓል።
በቀረበው የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርት ውጤት መሰረትም ገባኤው ጥቃቱ አንድን ሃይማኖት እና ብሄርን ትኩረት ያደረገ ግድያ ተፈጽሟል በማለት ሲዘዋወር የነበረውን መረጃ አጣጥሏል።
ጉባኤው ሪፖርቱን የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርት ሲል የጠራው " ያላለቀ በመሆኑ ፣የተጠቀሱት ወረዳዎች የተራራቁ በመሆናቸው እንዲሁም መሰረተ ልማት ውስንነት ያለበት ከመሆኑ አንጻር ሁሉም ቦታ ላይ ደርሶ የመጨረሻ ሪፖርት ለማውጣት ጊዜ የሚፈልግ በመሆኑ ነው " ብሏል።
የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ጸሐፊ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ " ጥቅምት ወር አጋማሽ ጀምሮ በምስራቅ አርሲ ዞን አንዳንድ ወረዳዎች በተለይም በአምስት ወረዳዎች የተፈጠረ ክስተት አለ በእዚህም የሰው ህይወት ጠፍቷል፣ አካል ጎድሏል ፣የተፈናቀሉ እና የጠፉ ንብረቶች ብዙዎች አሉ " ሲሉ ክስተቱን በተመለከተ መብራሪያ ስጠተዋል።
ጉባኤው በዛሬው ዕለት በሰጠው መግለጫ እንዳሳወቀው ጉዳዩን በአካባቢው በመሄድ አጣርተው የመጡት ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የተወከሉ ሦስት ፣ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት እና ከኦሮሚያ እስልምና ከፍተኛ ምክር ቤት ሁለት፣ ከጉባኤው ሁለት ባለሞያዎች በአጠቃላይ በዋና ሰብሳቢ፣ በምክትል ሰብሳቢ እንዲሁም በጸሃፊ የተዋቀረ 10 ልኡካን ናቸው።
ቀሲስ ታጋይ " ይህ የመጀመሪያ ደረጃ ምልከታ እና የማጣራት ሪፖርት ነው፣ ቀጣይ ተጨማሪ ማጣራት የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ካሉ ቦታው ድረስ እየሄዱ የማጣራት ስራ ጊዜ የሚፈልግ ነው በሦስት እና በአራት ቀናት ብቻ የሚያልቅ አይደለም ወራትም ሊወስድ ይችላል" ነው ያሉት።
የአጣሪ ኮሚቴው ሰብሰቢ መላከ ሰላም ዳዊት ያሬድ የመጀመሪያ ደረጃ የጥናት ሪፖርቱን ውጤት በሚመለከት ምን አሉ ?
" ዝርዝር ሃሳቡ በዋናው ማጠቃለያ ሪፖርት ላይ የሚገልጽ ሆኖ ጥናቱ የተደረገው ጉና፣ ሽርካ ፣ሆንኩሎ አቤ፣ መርቲ ወረዳዎች ናቸው።
አንደኛ በጉና ወረዳ ናኖ ጃዊ ቀበሌ ገበሬ ማህበር የሰው ህይወት መጥፋት፣ የንብረት መውደም ፣ዝርፊያ እንዲሁም እገታ ተፈጽሟል።
የክስተቱ ሁኔታ 12/02/18 ዓም ከቀኑ ስምንት ሰአት ታጣቂዎች አስገድደው ከማህበረሰቡ ጋር ምሳ በሉ በመጨረሻም የመንግስት ታጣቂ ሃይል መምጣቱን ሲያውቁ የተወሰኑ ሰዎችን አግተው እና ንብረት ይዘው ወደ ጫካ ሸሹ።
13/02/18 ዓም ምሽት ተመልሰው ተጨማሪ ሰው አግተው ወሰዱ።
14/02/18 ዓም ያገቷቸውን ሰዎች ገደሏቸው ከተጎጂ ቤተሰቦች እና ካነጋገርናቸው ሰዎች በተሰጠ ምላሽ ይህንን ድርጊት የፈጸሙት ራሳቸውን የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት/ሸኔ፣ ወይም ፋኖ ናቸው የሚል ምላሽ ነው።
አንዳንድ ግለሰቦች ደግሞ በሰጡት ምላሽ ማንነታቸውን እንደማያውቁ ነገር ግን በለሊት የሚንቀሳቀሱ ምንም አይነት የሃይማኖት መገለጫ የሌላቸው ግለሰቦች መሆናቸውን ነው።
ሁለተኛ በሸርካ ወረዳ 17/02/18 ዓም የሰው ህይወት ጠፍቷል እገታም ተፈጽሟል በወረዳው የተለያዩ ቀበሌዎች የሚገኙ ዜጎች ላይ በተለያየ ጊዜ ዘር ፣እምነት እንዲሁም እድሜ እና ጾታ ሳይለዩ ግድያዎች ተፈጽመዋል።
ህጻናት ታግተው ገንዘብ መጠየቂያ ተደርገዋል፣ ወላጆች ገንዘብ መስጠት ስላልቻሉ ህጻናቱ ተገድለዋል።
አንዳንድ ቦታዎች ላይ ህጻናቱ ተለቀው ወላጆች ከነገንዘባቸው ተወስደው ተሰቃይተዋል።
የተቀሩት ወረዳዎችም ተመሳሳይ ድርጊቶች መከናወናቸው ምላሽ ተሰጥቶናል።
የመንግስት በኩል የተገኘው ምላሽ ወታደራዊ እርምጃ መወሰዱን እና በመንግስት መዋቅር ጭምር መስዋዕትነት እየተከፈለ መሆኑን ተገልጾልናል።
በችግሩ ተጋላጮች ክስተቱ አንድ ወገንን ወይም ብሔር እና ሃይማኖትን መሰረት ያደረገ አለመሆኑን እና ሁሉንም የጎዳ መሆኑን ተገልጾልናል።
አጥኚ ቡድኑ በአራት ወረዳዎች በመንቀሳቀስ እና እውነታውን ለባለድርሻ አካላት ለማቅረብ ስራውን የጀመረ ሲሆን በአራት ወረዳዎች ባስቀመጠው የጥናት እቅድ መሰረት ተግባራዊ ስራውን ያከናወነ በመሆኑ ጥቅል ዝርዝር ሁኔታዎች ማለትም የሟች ማንነት ፣የአሟሟት ሁኔታ፣ ብዛት ፣የሃይማኖት ስብጥር በቀጣይ በጥናት የሚካተቱ እና የቀሩትን ወረዳዎች ባማከለ መልኩ የሚያቀርብ ይሆናል " ብለዋል።
ምክትል ሰብሳቢ ሃጂ አብድልሃኪም ሁሴን በሰጡት ቃል አንድ ወገን ላይ ያተኮረ ግድያ ተፈጽሟል መባሉ ስህተት መሆኑን ገልጸው " አጥቂዎቹ አንድን ሃይማኖት እንደማይለዩ ፣እንዲሁም ታጣቂዎቹ የሁሉም ሃይማኖት ስብጥር እንደሆኑ በአንዳንድ ወቅት በአጋቾቱ ታግተው ከተለቀቁ ሰዎች በተገኘ መረጃ ተገልጾልናል " ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
@tikvahethiopia
#MinistryofFinance
የገንዘብ ሚኒስቴር የገቢ ግብር (ማሻሻያ) አዋጅ ቁጥር 1395/2017 አፈጻጸም ላይ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ በመስጠት፣ በተለይ በአከፋፋይ ነጋዴዎች ላይ የሚሰላውን አማራጭ አነስተኛ ግብር በተመለከተ ከፍተኛ እፎይታ ይሰጣል የተባለ ማብራሪያ ሰጥቷል።
ይህ ውሳኔ ቀደም ሲል የንግዱን ማህበረሰብ አስጨንቆ የነበረውን የትርፍ ህዳግ (Profit Margin) ግዴታ የሚያነሳ በመሆኑ በነጋዴዎች ዘንድ በደስታ ተቀባይነትን እንዳገኘ ካፒታል ጋዜጣ ዘግቧል።
በሚኒስቴሩ ማብራሪያ መሰረት፣ የአከፋፋዮች አማራጭ አነስተኛ ግብር የሚሰላበት መንገድ ግልጽ ሆኗል።
በዚህ መሰረት ፤ ጅምላ ሻጭ/አከፋፋይ ከአምራቹ ወይም ከአስመጪው ጋር ባደረገው ውል የሚሸጥበት ዋጋ እና የሚያገኘው መቶኛ (ትርፍ ህዳግ) በግልጽ የተወሰነ ከሆነ፣ አማራጭ አነስተኛ ግብሩ የሚሰላው በጠቅላላ የሽያጭ ገቢው ላይ ሳይሆን፣ በውል ወይም በሕግ በተፈቀደለት የትርፍ መቶኛ ላይ ብቻ ይሆናል ተብሏል።
ይህ አዲስ አፈጻጸም የገቢዎች ሚኒስቴር በትንሹ 15 በመቶ ማትረፍ አለባችሁ በሚል ያስቀመጠው ግዴታ በንግዱ ላይ የፈጠረውን ጫና የሚያቃልል ነው።
ይሁንና፣ ይህንን ውሳኔ ለመጠቀም አከፋፋዩ የመሸጫ ዋጋ እና የትርፍ ህዳግ በውል መወሰኑን የሚያረጋግጥ ሕጋዊ ሰነድ ለግብር ባለስልጣናት ማቅረብ ይኖርበታል።
ካፒታል ጋዜጣ የገንዘብ ሚኒስቴርን ማብራሪያ ተከትሎ ቃላቸውን ሰጡኝ ያላቸው ነጋዴዎች ውሳኔው የንግዱን እንቅስቃሴ የሚያነቃቃ እና ከገበያ እውነታ ጋር የሚጣጣም ፍትሃዊ እርምጃ እንደሆነ ተናግረዋል።
አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ አከፋፋይ " የገቢዎች ሚኒስቴር በትንሹ 15 በመቶ አትርፉ ማለቱ እኛ የማንችለውና ንግዱን ለከፍተኛ መቀዛቀዝ የዳረገ ነበር። አሁን የገንዘብ ሚኒስቴር 'በውል የተቀበሉትን የትርፍ ህዳግ ተቀበሉ' ሲል ለገቢዎች ሚኒስቴር ያሳወቀው ነገር ትልቅ እፎይታ እና መተንፈሻ ሰጥቶናል " ብለዋል።
የገንዘብ ሚኒስቴር ይህንን ማብራሪያ የሰጠው የአዋጁ ማስፈጸሚያ ደንብ ገና ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቦ ያልጸደቀ በመሆኑ በአዋጁ ላይ የተፈጠረውን ግልጽነት የጎደለው ሁኔታ ለማስተካከል መሆኑ ተጠቁሟል።
ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የካፒታል ጋዜጣ ነው።
@tikvahethiopia
በኢትዮጵያ በአጋቾች ታግቶ የቆየው ኬንያዊ ዜጋ 3 ሚሊየን ሽልንግ ከተከፈለ በኋላ መለቀቁን ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ አስታወቁ።
የኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በመተባበር እና በአዲስ አበባ ያሉት አምባሳደራቸው ባደረጉት ጥረት 3 ሚሊየን የኬንያ ሽልንግ ለአጋቾች ከተከፈለ በኋላ ሳሙኤል ንጃጊ የተባለው ዜጋቸው መለቀቁን ገልፀዋል።
ሳሙኤል ከሳምንት በፊት በደብረ ብርሃን ከተማ ተቀጥሮ ከሚሰራበት ድርጅት ታግቶ የተወሰደ ሲሆን የኬንያ ኤምባሲ ለኢትዮጵያ መንግስት ጉዳዩን ካሳወቀ በኋላ ድርድሮች መደረጋቸው ተዘግቧል።
ዊሊያም ሩቶ 3 ሚሊየን የኬንያ ሽልንግ በአጋቾች መጠየቁን ገልፀው ሳሙኤል ይሰራበት የነበረው ድርጅት ክፍያውን መክፈሉን ገልጸዋል።
ሳሙኤል ከተለቀቀ በኋላ አዲስ አበባ በሚገኘው የኬንያ ኤምባሲ መቆየቱንና ወደ ኬንያ ሄዶ ከቤተሰቦቹ ጋር መቀላቀሉ ሲነገር ሩቶ ዜጎች የሚሰሩባቸው የውጪ ሃገር ድርጅቶች እንደ ሳሙኤል ሁሉ ከታወቀ መንግስት አስፈላጊዉን ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል።
#TikvahEthiopiaFamily
Via @TikvahethMagazine
" ግለሰቡ በህገወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር በሌለበት 10 ዓመት ተፈርዶበት ነበር " - ፖሊስ
በህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር በሌለበት ተፈርዶበት ተሰውሮ የቆየው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የትግራይ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።
በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን የእንዳስላሰ-ሽረ ከተማ ነዋሪ የሆነው ዋኘው ታፈረ ጥላሁን በህገ-ወጥ መሳሪያ ዝውውር ተከሶ በመሰወሩ በሌለበት የ10 ዓመት እስራት ተፈርዶበታል።
ግለሰቡ መስከረም 18 ቀን 2018 ዓ.ም ከምሽቱ 12:00 ሰዓት በእንዳስላሰ-ሽረ ከተማ ቀበሌ 04 መንደር 1 አራት ሽጉጦችን በህገ-ወጥ መንገድ ሲሸጥ በፀጥታ አካላት ቢያዝም በዋስ ከእስር ከተለቀቀ በኃላ ሊሰወር ችሏል።
ይሁን እንጂ የብር 50 ሺ ዋስ አስይዞ ተለቆ ጥቅምት 11 ቀን 2018 ዓ.ም በተሰጠው ቀነ ቀጠሮ ፍርድ ቤት መቅረብ ባለመቻሉ የዞኑ ማእከላዊ ፍርድ ቤት ጥቅምት 26 ቀን 2018 ዓ.ም በሌለበት የ10 ዓመት ፅኑ እስራት ፈርዶበታል።
የፍርድ ቤት ትእዛዝ እንዲፈፅም ሲፈለግ የነበረው ዋኘው ታፈረ ጥላሁን ጥቅምት 27 ቀን 2018 ዓ.ም በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን በቁጥጥር ስር መዋሉን ነው ፓሊስ ያስታወቀው።
መረጃው ከትግራይ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የተገኘ ነው።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
@tikvahethiopia
" ባለፉት ስድስት ወራት የንቁ ደንበኞችን ቁጥር በእጥፍ በማሳደግ 11.1 ሚሊየን መድረስ ችለናል " - ሳፋሪኮም
የሳፋሪኮም ኩባንያ የኢትዮጵያ ክንፍ የሆነው ሳፋሪኮም ቴሌኮሙኒኬሽን ኢትዮጵያ ኃ.የተ.የግ.ማ. የንቁ ደንበኞች ቁጥር 11.1 ሚሊዮን መድረሳቸውን ይፋ ተደርጓል።
ሳፋሪኮም ባለፉት ስድስት ወራት የንቁ ደንበኞቹን ቁጥር በእጥፍ በማሳደግ 11.1 ሚሊየን መድረስ መቻሉን ገልጿል።
ተቋሙ በኬንያ እያሳየው ያለው ቀጣይነት ያለው እድገት ዋነኛው የትርፍ አንቀሳቃሽ ሆኖ ቀጥሏል የተባለ ሲሆን በኢትዮጵያም እያጋጠመው ያለውን ኪሳራ ማጠበብ መቻሉን ተጠቁሟል።
በኢትዮጵያ የደረሰበት ኪሳራም ካለፈው በጀት ዓመት የመጀመሪያ አጋማሽ ጋር ሲነጻጸር በ59 በመቶ ቅናሽ አለው ነው የተባለው።
የሳፋሪኮም ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፒተር ንዴግዋ " አስቸጋሪ የስራ ሁኔታ ቢኖርም፣ በሁሉም ገበያዎች አውታረ መረባችንን በማስፋት እና በማሳደግ ጠንካራ እድገት አሳይተናል " ብለዋል።
ሳፋሪኮም በኢትዮጵያ የሚሰጠው አገልግሎት ባለፉት ስድስት ወራት 47.9 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘቱ የተገለጸ ሲሆን ይህም ከአንድ ዓመት በፊት ካለው አፈጻጸሙ ጋር ሲነጻጸር በእጥፍ ጭማሪ አለው።
ከአጠቃላይ ትርፉ የሞባይል ዳታ 66.7 በመቶ ሲይዝ የድምፅ 22.1 በመቶ እና የመልእክት ልውውጦች 11.2 በመቶ ይይዛሉ።
የሶስት ወራት ንቁ ደንበኞች ቁጥር በ83.7 በመቶ በመጨመር ወደ 11.2 ሚሊዮን ከፍ ማለቱን እና የአንድ ወር ንቁ ደንበኞች ቁጥር ደግሞ ወደ 8.51 ሚሊዮን ማደጉን ተገልጿል።
ሳፋሪኮም " ከኢትዮጵያ የሚገኘው ገቢ ከ60 በመቶ በላይ አድጓል፣ ይህም በሞባይል ዳታ እና በድምጽ አጠቃቀም መጨመር ምክንያት የመጣ ነው " ብሏል።
ይህም ኩባንያው በኬንያም ሆነ በኢትዮጵያ አፈጻጸሙን ማሻሻሉን ማሳያ መሆኑን ተገልጿል።
ኩባንያው በሃገሪቱ ካሉት የኔትወርክ ማማዎች ውስጥ 1847 የሚሆኑት በራሱ የተገነቡ ሲሆን 1,459 የሚሆኑት ደግሞ በኪራይ የሚጠቀማቸው ናቸው።
በተቋሙ በተገነቡ እና በኪራይ በሚጠቀማቸው የኔትወርክ ማማዎች አማካኝነትም 55 በመቶ የህዝብ ሽፋን (Population coverage) መድረስ መቻሉን አሳውቋል።
ኤም-ፔሳ ኢትዮጵያም ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ 12.3 ቢሊዮን ብር እንቅስቃሴ (ግብይት) እንደተከናወነበት ተገልጿል።
ከተንቀሳቀሰው ገንዘብ በተጨማሪም 3.4 ሚሊዮን የ90 ቀናት ንቁ ተጠቃሚዎችን ማፍራቱን ተጠቁሟል።
ኤም ፔሳ በመላ አገሪቱ ከ30,700 በላይ ደንበኞችን ማፍራቱን ይፋ የተደረገ ሲሆን፤316ቱ የነዳጅ ማደያዎች ናቸው ተብሏል።
በኢትዮጵያ የኤምፔሳ ተጠቃሚዎች ቁጥር ቢጨምርም ካለፈው በጀት አመት ጋር ሲነጻጸር ግን ገቢው በ64.3 በመቶ ቀንሷል ነው የተባለው።
ባለፈው ዓመት፣ የሳፋሪኮም ግሩፕ በሴፕቴምበር 30፣ 2024 መጨረሻ ላይ የስድስት ወራት ያልተጣራ ትርፉን ይፋ ሲያደርግ የኤም-ፔሳ በኢትዮጵያ ገቢ 24.4 ሚሊዮን የኬንያ ሽልንግ የነበር ሲሆን የዘንድሮ አመት የኢትዮጵያ የኤም-ፔሳ ገቢ ወደ 8.7 ሚሊዮን የኬንያ ሽልንግ ዝቅ ማለቱን ኩባንያው አሳውቋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
@tikvahethiopia
#SafaricomEthiopia
2 ቀን ብቻ ቀረው! ቀጣይ ሚሊየነር ማን ይሆን ?🏆💚 ዛሬዉኑ የበሽ ጥቅልን ይግዙ፤ ሚሊየነር የመሆን እድሎን ያስፉ!
📲 የM-PESA መተግበሪያን አሁኑኑ ያውርዱ፡
https://onelink.to/ewsb22
የቴሌግራም ቦታችን: /channel/official_safaricomet_bot
ወደ *777*0# ይደውሉ ወይም በM-PESA የበሽ ጥቅል ይግዙ!
#SafaricomEthiopia
#MPESASafaricom
#furtheraheadtogether
#besh
" የፕሮጀክቱ ቁልፍ ስራ ከሆነው የወንዝ ቅልበሳ ስራ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል " - ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአማራ ክልል ጎንደር እና ባሕር ዳር የስራ ጉብኝት አድርገዋል።
በጎንደር በነበራቸው የስራ ጉብኝት የመገጭ የመስኖ ልማት ፕሮጀክት የስራ ሁኔታ መገምገሙን ገልጸዋል።
870 ሄክታር ላይ እንዳረፈ የገለጹት ይኸው ፕሮጀክት 17,000 ሄክታር መሬት በመስኖ አቅርቦት ይሸፍናል ተብሎ እንደሚጠበቅ አመልክተዋል።
" የፕሮጀክቱ ቁልፍ ስራ ከሆነው የወንዝ ቅልበሳ ስራ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል " ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ " የተቀሩት ስራዎችም በተያዘላቸው የጊዜ ሰሌዳ እየተካሄዱ ይገኛሉ " ብለዋል።
በሌላ በኩል ፥ ከቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸውና ከከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ጋር በመሆን የታደሰውን የፋሲል ጊቢ መርቀዋል።
አጠቃላይ የእድሳት ሥራው ከአንድ አመት በታች የፈጀ እንደሆነ ተገልጿል።
" በእድሳቱ ፦
- በቅርስ ስፍራው ነባሩን ታሪክ በመጠበቅ ውበቱን እና ተደራሽነቱን የማስፋት ስራ ተሰርቷል።
- የቤተመንግሥቱ የግንባታ መዋቅር ተጠግኗል።
- የእግር መንገዶችን ማሻሻል ስራ ተሰርቷል።
- ቁልፍ የሆኑ ሕንፃዎችን ከዝግባ እና ዋንዛ ባሕላዊ ቁሳቁሶችን በመጠቀም በማደስ የስፍራውን ግለ ወጥ መልክ እና ባሕርይ የመጠበቅ ስራ ተሰርቷል።
- ለጎብኝዎች ምቾት የተሰናዱ አገልግሎት መስጫዎች ተሻሽለዋል።
- አዲስ የቱሪስት ማዕከል ተከፍቷል።
- ዘመናዊ መጸዳጃ ቤቶች፣ የተሻሻሉ የመብራት እና የደኅንነት ሥርዓቶችም ተሰናድተዋል።
- እንደ አፄ ፋሲል፣ አፄ ቀዳማዊ ዮሃንስ እና አፄ ቀዳማዊ ኢያሱ አቢያተ መንግሥት ብሎም ድልድዮች፣ መታጠቢያ ሥፍራዎች፣ ታሪካዊ በሮች ወዘተ ታድሰዋል።
- ከ40,000 ስኴር ሜትር በላይ የአካባቢው ምድር የማስዋብ ሥራ ተሰርቷል " ተብሏል።
ከዚህ በተጨማሪ ጣናነሽ የተሰኘችው ጀልባ ሥራ መጀመራ ተገልጿል።
" ጣናነሽ በጣና ውሃ ላይ እየቀዘፈች ባሕር ዳር ከተማን ከጎርጎራ ኤኮ ሎጅ ማገናኘት ጀምራለች " ሲሉ ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ገልጸዋል።
ጀልባዋ ከ180 ተጓዦች በላይ የማጓጓዝ አቅም እንዳላት አመልክተዋል።
" ለጉብኝት፣ ለመዝናናት እና አስደማሚውን የጣና ሀይቅ የተፈጥሮ ከባቢ ለመጎብኘት ወደ ጎርጎራ ኤኮ ሎጅ የሚደረገውን ጉዞ የበለጠ ምቹ አድርጋዋለች " ሲሉ አክለዋል።
#PMOEthiopia
@tikvahethiopia