ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። @tikvahuniversity @tikvahethAfaanOromoo @tikvahethmagazine @tikvahethsport @tikvahethiopiatigrigna #ኢትዮጵያ
#Amhara
የአማራ ብ/ክ/ም/ቤት ነባር 2 ቢሮዎችን በማጠፍ የአሥፈፃሚ አካላት ላይ ማሻሻያ አደረገ።
የአማራ ብሔራዊ ክልል ምክር ቤት እያካሄደ ባለው 6ኛ ዙር፣ 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን፣ 10ኛ መደበኛ ጉባኤ የተሻሻለውን የአሥፈፃሚ አካላት እንደገና ማቋቋሚያ፣ ሥልጣን እና ተግባራት መወሰኛ አዋጅን አጽድቋል።
ጉባኤው ነባር ሁለት ቢሮዎች ታጥፈው ከሌሎች ቢሮዎች ጋር እንዲዋኻዱ፤ ሁለት ተቋማትን ደግሞ እንደ አዲስ ራሳቸውን ችለው እንዲቋቋሙ የቀረበውን የአሥፈፃሚ አካላት ማቋቋሚያ አዋጅ በሙሉ ድምፅ አጽድቋል።
በዚህም " ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ " እና " መስኖ እና ቆላማ ቢሮ " ታጥፈው ከሌሎች ጋር ቢሮዎች ጋር ሲዋሀዱ ከተማና እና መሰረተ ልማት ቢሮ ስር የነበረው ኮንስትራክሽን ዘርፉ " የኮንስትራክሽን ባለስልጣን " እንዲሁም የአማራ ክልል አመራር አካዳሚ የነበረው " የአማራ ክልል ስቴት ዩኒቨርሲቲ " በሚል ስያሜ ራሳቸውን ችለው እንዲቋቋሙ ሆኗል።
ሌሎች ተቋማ ደግሞ የስያሜ ለውጥ ተደርጎባቸዋል።
የሥያሜ ለውጥ የተደረገባቸው ተቋማት፦
- የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን ወደ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን፤
- የመንግሥት ልማት ድርጅቶች አሥተዳደር ወደ የአማራ ክልል ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ፤
- የሙያ ብቃት ምዘና እና ማረጋገጫ ኤጀንሲ ወደ የሙያ ብቃት ምዘና እና ማረጋገጫ ባለሥልጣን፤
- የኅብረት ሥራ ማኅበራት ማስፋፊያ ኤጀንሲ ወደ የኅብረት ሥራ ኮሚሽን፤
- የዕፅዋት ዘር እና የሌሎች የግብርና ግብዓቶች ጥራት ቁጥጥር እና ኳራንታይን ባለሥልጣን ወደ የግብርና ጥራት እና ደኅንነት ቁጥጥር ባለሥልጣን፣
- የከተሞች ፕላን ኢንስቲትዩት ወደ ፕላን ኢንስቲትዩት፣
- የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ አገልግሎት ወደ የሲቪል እና የቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት በሚል የስያሜ ለውጥ ተደርጎባቸዋል።
በአዋጁ መሰረት በክልሉ የአሥፈፃሚ አካላትን እንደገና ማቋቋሚያ ሥልጣን እና ተግባራት መወሰኛ አዋጅ መሠረት የተቋቋሙ አሥፈጻሚ አካላት 23 መሆናቸው ተጠቅሷል።
(ዝርዝሩን ከምስሉ ይመልከቱ)
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ባሕር ዳር
#TikvahEthiopiaFamilyBahirdar
@tikvahethiopia
" የዛሬ አመት ነው ፈተና ፈትነው በቦታው የመደቡን አሁን ደግሞ በአመቱ የስራ ክፍሎቹ ተዘግተው ወደ ክፍለ ከተማ ይዘዋወራሉ በመባሉ በጣም ነው ሞራላችን የተነካው " - ቅሬታ አቅራቢዎች
የአዲስ አበባ ከተማ የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ በክፍለ ከተማ እና በወረዳ ደረጃ የሚገኙ አደረጃጀቶች መታጠፋቸውን ተከትሎ በቢሮው ይሰሩ ለነበሩ ባለሞያዎች ድልድል እየተከናወነ ይገኛል።
በታጠፉት የስራ ክፍል ውስጥ ይሰሩ የነበሩ ባለሞያ " የስራ ክፍላችን ሲታሸግ እኛን ያማከረን አካል የለም " ያሉ ሲሆን የስራ ክፍሎቹ ታጥፈው ወደ ክፍለ ከተማ ከመዘዋወራቸው ቀደም ብሎ የአገልግሎት ክፍያ ከፍለው በመጠባበቅ ላይ የነበሩ ደንበኞች ነበሩ ነው ያሉት።
ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቅሬታቸውን በዝርዝር ያቀረቡ ባለሞያ ምን አሉ ?
" በወረዳው የግንባታ ፈቃድ አገልግሎት ሲገለገሉ የነበሩ ተገልጋዮች በሙሉ ወደ ክፍለ ከተማ ሄደው እንዲገለገሉ የተነገራቸው ነው።
እኛ ደሞ በክፍሉ ስናገለግል የነበርነው ባለሞያዎች የኢንጂነሪንግ ምሩቃን ነን ትመደባላቹ እየተባልን ያለነው ደግሞ ' ተመድበዋል ' እንዲባል ብቻ ሞያችን የማይጋብዝ ቦታ ላይ ነው።
የስራ ክፍላችን ሲታሸግ እኛን ያማከረን አካል የለም በወረዳ ደረጃ አገልግሎት ሲሰጥባቸው የነበሩ የግንባታ ፈቃድ እና ቁጥጥር ፣ የመንግስት ቤቶች አስተዳደር እና የመሬት አስተዳደር ጽ/ቤቶች ተዘግተው ወደ ክፍለ ከተማ እንዲሄዱ ተደርገዋል።
በግንባታ ፈቃድ ክፍል ውስጥ ሲሰራ የነበረ መሃንዲስ ባለው ክፍት ቦታ ይመደባል እየተባለ ነው ያለሞያችን ለመመደብ አእምሮአችንም ዝግጁ አይደለም ቅዳሜ ቢሮአችን ሲታሸግ የአገልግሎት ክፍያ ፈጽመው ለሰኞ የቀጠርናቸው ተገልጋዮች ነበሩ።
የዛሬ አመት ነው ፈተና ፈትነው በቦታው የመደቡን አሁን ደግሞ በአመቱ የስራ ክፍሎቹን ተዘግተው ወደ ክፍለ ከተማ ይዘዋወራሉ በመባሉ በጣም ነው ሞራላችን የተነካው።
ተገልጋዮች በወረዳው ሲያገኙት የነበረውን የግንባታ ፈቃድ አገልግሎት ወደ ክፍለ ከተማ ሄደው እንዲያገኙ የሚል ማስታወቂያ ተለጥፏል።
አገልግሎቶችን ወደ ህብረተሰቡ ተደራሽ እናደርጋለን እየተባለ እየተነገረ ባለበት ሰአት እንዴት ከወረዳ ወደ ክፍለ ከተማ እንዲሄዱ በማድረግ ለእንግልት እንዲዳረጉ ይደረጋል።
ለምሳሌ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ላይ 12 ወረዳ አለ የ አስራ ሁለቱም ወረዳ የእድሳት ፈቃድ የሚጠይቅ ሰው አንድ ክፍለ ከተማ ላይ ሄዶ አገልግሎት ሲጠይቅ ይህን ሁሉ ሰው እንዴት ነው ሊያስተናግዱ የሚችሉት።
መሬት ተወርዶ በአግባቡ ቢጠና እንኳን የወረዳው ክፍለ ከተማ ሊሄድ የክፍለ ከተማው አንዳንድ አገልግሎቶች ወረዳ ይውረዱ ይባል ነበር።
በሁሉም ክፍለ ከተሞች ላይ የሚገኙ ወረዳዎች የሚሰሯቸው ከግንባታ ፈቃድ ጋር የተገናኙ ስራዎች በጠቅላላ ወደ ክፍለ ከተማ ታጥፈው ወረዳ ላይ ያለ ባለሞያ በተገኘበት ክፍት ቦታ ላይ ይመደብ ነው የተባለው።
ምደባው እስከሚያልቅ ቤታቹ ቁጭ በሉ ምደባቹን እናሳውቃቹሃለን አንድ ሳምንት ስጡን ተብለናል።
አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ላይ የምንገኝ ባለሞያዎች ማክሰኞ እለት ዋና ስራ አስፈጻሚው ጋር ለስብሰባ ተቀምጠን ነበር በተመሳሳይ የአንድ ሳምንት ጊዜ ስጡን ብለውናል።
ደሞዝ የሰኔ ገብቶልናል የሃምሌ ወር ይሰጠን አይሰጠን ሃምሌ መጨረሻ ላይ ነው የምናውቀው ፣ነገር ግን ' ደሞዝም ይሰጣቹሃል ከስራም አልተባረራቹም ' ነው የተባልነው።
እነሱ ' ባለው ክፍት ቦታ እንመድባቹሃለን ' ይላሉ የእኛ ጥያቄያችን የመመደብ ፣ የመንሳፈፍ አይደለም ጥያቄያችን እኛ ባለሞያዎችን ነን አስራ ምናምን አመት ዩኒቨርሲቲ ተምረን ወጥተን በማንፈልገው ቦታ ትመደባላቹ መባላችን ደስተኞች አይደለንም ነው።
የእኛ የግንባታ ፈቃድ ቢሮ ውስጥ በትንሹ ስምንት ባለሞያዎች ነበርን በሁሉም ክፍለ ከተሞች ተመሳሳይ ቁጥር ያለው ባለሞያ ይገኛል።
አዲስ ከተማ ፣ጉለሌ ፣አራዳ፣ ልደታ ኢነር ሲቲዎች ነን ስምንት ሰራተኛ አንድ የስራ ክፍል ውስጥ ይገኛል።
ቦሌ፣ ንፋስ ስልክ፣ ኮልፌ፣ ለሚ ኩራ እና ሌሎችም ጋር ብንሄድ ደግሞ ማስፋፊያዎች ስለሆኑ ከዛ በላይ ባለሞያ ይኖራቸዋል።
ይህ ሁሉ ባለሞያ የያዙ የስራ ክፍሎች ናቸው እንዲበተን እና በሌላ መዋቅር እንዲካተቱ እየተደረገ ያለው " ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰራተኞችን ቅሬታ ይዞ ምላሽ ይሰጡ እንደሆን ለፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ተደጋጋሚ ሙከራ ቢያደርግም ስልካቸውን ለማንሳት ፈቃደኛ አልሆኑም።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
" ማንኛውንም አይነት ከውጭ የሚገቡ የበይነ መረብ ግዢ የሆኑ ጥቅሎችን በኢትዮጵያ ፖስታ ከታዘዘ ተቀብለን ቤት ለቤት እናደርሳለን ለአገልግሎቱ የምናስከፍለው ሃምሳ ብር ነው " - የኢትዮጵያ ፖስታ
የኢትዮ ፖስታ እንደ አሊባባ፣ አማዞን እና አሊ ኤክስፕረስ ካሉ የኢኮሜርስ ገበያዎች ላይ የሚሸመቱ የበይነ መረብ ግዢ የሆኑ ጥቅሎችን ቤት ለቤት የማድረስ ስራ መጀመሩን አሳውቋል።
አገልግሎቱን ከጀመረ ሁለት ወር የተሻገረ ሲሆን ማንኛውም የበይነ መረብ ግዢ የሆኑ እቃዎችን ተቀብሎ እቤት ለቤት የማድረስ ስራ እየሰራ ስለመሆኑ ተቋሙ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቋል።
የኢትዮጵያ ፖስታ የማርኬቲንግ እና ኮምዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ በላይነህ ማሙሽ "ማንኛውንም አይነት ከውጭ የሚገቡ የበይነ መረብ ግዢ የሆኑ ጥቅሎችን በኢትዮጵያ ፖስታ ከታዘዘ ተቀብለን ቤት ለቤት እናደርሳለን ለአገልግሎቱ የምናስከፍለው ሃምሳ ብር ነው"ብለዋል።
ቤት ለቤት የማድረስ ስራው እየተከናወነ የሚገኘው በሙሉ የአዲስ አበባ እና የአዲስ አባባ ዙሪያ ከተሞች ነው።
ከአዲሱ አመት በኋላ በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ ዋና ዋና ከተሞች የመውጣት እቅድ እንዳለ እና አስፈላጊ የሆኑ ዝግጅቶች እየጨረሱ ስለመሆኑ አቶ በላይነህ ተናግረዋል።
አቶ በላይነህ ማሙሽ ስለ አገልግሎቱ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በዝርዝር በሰጡት ሃሳብ ምን አሉ?
" ቤት ለቤት ከማድረሱ በተጨማሪ ሰዎች በምርጫቸው መቀበል የሚፈልጉበትን ቦታ መርጠው እንዲቀበሉ ለማድረግ እየሰራን ነው።
ቤት ለቤትም ደንበኛው ስንት ሰአት እንደሚመቸው ጠይቀን በመረጠው ሰአት ነው የምንመጣው።
ከጂኦ ስፓሻል ኢንስቲቲዩት ጋር የጀመረነው የማፒንግ ስራዎች አሉ እነሱ ስራዎች ሲጠናቀቁ ብዙ ስልክ መደወል ሳይጠበቅብን ደንበኛው ባለበት ቦታ ተመልክተን እቃውን የምናደርስበት አሰራር ይኖራል።
በውጭ ሃገራት ባለው አሰራር እቃ ሲታዘዝ የቤት ቁጥሩን እና መንገዱን በማስገባት ብቻ ከታሰበበት ቦታ መደወል ሳያስፈልግ ማድረስ ይቻላል።
ኢትዮጵያ ውስጥ የማፒንግ እና ጂኦ ስፓሻል ስራዎች ገና እየተሰሩ ነው አላለቁም እሱ ሲያልቅ ቤትህ የቱ ጋር ነው ብሎ መጠየቅ ቀርቶ ደንበኛው ባለበት ቦታ በቤት፣ በብሎክ እና በመንገድ ቁጥሩ ላይ ተመስርተን የምናደርስ ይሆናል ይህንን ስራ ኢንስቲትዩቱ የሚያከናውነው ነው እኛ ለማስተባበር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመናል።
ወደ እዚህ አሰራር መምጣት ያስፈለገበት ምክንያት የኢትዮጵያ ፖስታ ትልቅ የሆነ የኢ-ኮሜርስ መተግበሪያ ገንብተን ጨርሰናል።
ስልጠናውን ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የኢተርፕራይዝ ዴቨሎፕመንት ዪኒት ጋር በጋራ በመሆን እየሰጠን እንገኛለን።
እስካሁን ከውጭ ኢ-ኮሜርሶች ጋር እንገበያያለን ፣ ሃገር በቀል የሆኑ የ ኢኮሜርስ ሳይቶችም አሉ ፣የዘረጋነው አሰራር ግን የኢትዮጵያ ምርቶች ድንበር ተሻግሮ ማቅረብ የሚቻልበት እና የውጭ ምንዛሬም ማግኘት የሚቻልበት የኢኮሜርስ ፕላትፎርም ነው።
አንድ ስሞል እና ሚዲየም ኢንተርፕራይዝ እቃ አምርቶ ሲጨርስ ለእሱ የሚሆን የገበያ ቦታ (Market Place) ፈጥረንለታል።
እንደዚህ አይነት ትልቅ የ ኢ ኮሜርስ ኢንዱስትሪ ውስጥ ስትገባ ቴክኖሎጂው አድቫንስመንት ይፈልጋል።
ቦታውን ከደንበኛው ጋር ስልክ በመደዋወል በጥቆማ ሳይሆን በትክክል ቦታውን አውቀን የምንሄድበትን ሁኔታ መፈጠር ስላለበት እና እየገነባነው ባለነው በጣም ትልቅ የ ኢኮሜርስ ኢኮ ሲስተም ላይም አጋዥ መሆን ስለሚገባው ከኢንስቲትዩቱ ጋር አብረን እየሰራን ነው " ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
" የህልፈታቸውን ትክክለኛ መንስኤ ለማጣራት ምርመራ እየተካሄደ ነው " - የህንድ ኤምባሲ
ህንዳዊ ዜግነት ያላቸው ግለሰብ አስክሬናቸው በአዳማ ፖሊስ መገኘቱን በኢትዮጵያ የህንድ ኤምባሲ አስታወቀ።
ህንዳዊ ዜግነት ያለው እና በአዳማ አከባቢ ቢሮውን ባደረገው በካልፓታሩ ፕሮጀክት ኢንተርናሽናል ሊሚትድ በተሰኘ ተቋም (KPIL) ሲሰራ የነበረ ግለሰብ በአዳማ አከባቢ ሞቶ መገኘቱን በኢትዮጵያ የሚገኘው የህንድ ኤምባሲ አስታውቋል።
ኤምባሲው ባወጣው አጭር መግለጫ ናቭ ሱቫሪዮ የተሰኙትና በአዳማ-አዋሽ ፈጣን መንገድ ፕሮጀክት ላይ የተቋሙ ምክትል ሥራ አስኪያጅ ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት ግለሰብ፥ " አስክሬናቸው በአዳማ ፖሊስ የተገኘ ሲሆን የሞቱን ትክክለኛ መንስኤ ለማጣራት ምርመራ እየተካሄደ ነው " ሲል አስታውቋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ስለ ጉዳዩ ለማጣራት ወደ ሚመለከታቸው የሥራ ኃላፊዎች ተደጋጋሚ የስልክ ጥሪ ቢያደርግም ለጊዜው ምላሽ ማግኘት አልቻለም።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahaEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#Ethiopia 🇪🇹 #Italy🇮🇹
ኢትዮጵያ ለመጪዎቹ ሶስት ቀናት በአዲስ አበባ ሁለተኛውን የተባበሩት መንግሥታት የምግብ ሥርዓት ጉባኤ ከጣልያን ጋር በጋራ ታዘጋጃለች።
ለዚሁ ጉባኤ የተለያዩ ሀገራት መሪዎች እና የተመድ አመራሮች እንዲሁም ሌሎች የጉባኤው ተሳታፊዎች ወደ አዲስ አበባ ገብተዋል።
እነማን ገቡ ?
- የጣሊያን ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የሚኒስትሮች ምክርቤት ፕሬዝደንት ጂኦርጂያ ሜሎኒን
- የተባበሩት መንግሥታት ምክትል ዋና ፀሐፊ የሆኑትን አሚና ጄ. መሃመድ
- የአለም የምግብ እና የእርሻ ድርጅት (ፋኦ) ዋና ዳይሬክተር ኩ ዶንግዩ
- የአለምአቀፍ የግብርና ልማት ፈንድ (IFAD) ፕሬዝዳንት አልቫሮ ላሪዮ
- የተባበሩት መንግሥታት ረዳት ዋና ፀሐፊ እና የዩኤንዲፒ የአፍሪካ ቀጠና ዳይሬክተር አሁና ኢዚያኮንዋ
- የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼህ መሃሙድ
- የኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ
ሌሎች በምክትል ፕሬዚዳንት ማዕረግ ያሉ የሀገራት ተወካዮችና መሪዎች እንዲሁም ከፍተኛ ሚኒስትሮች አዲስ አበባ ገብተዋል።
ከዚሁ ጉባኤ ጋር ለተያያዘ ፥ ወደ አዲስ አበባ የመጡ የተቋማት ኃላፊዎችን እና መሪዎችን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተቀብለው አነጋግረዋል።
ጠ/ ሚኒስትሩ የጣልያን ጠቅላይ ሚኒስትር፣ የሶማሊያውን ፕሬዚዳንት ፣ የተመድ ምክትል ዋና ፀሐፊ፣ የFAO ዋና ዳይሬክተር ፣ የIFAD ፕሬዝዳንት፣ የተመድ ረዳት ዋና ፀሐፊ እና የዩኤንዲፒ የአፍሪካ ቀጠና ዳይሬክተርን ተቀብለው አነጋግረዋል።
ፎቶ፦ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት
@tikvahethiopia
#DrBetlhemEwnetu👏
በስኬቶች የደመቀችው ተመራቂ 🎓
የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ተማሪዎቹን አስመርቋል።
ዶ/ር ቤተልሔም እውነቱ ከሕክምና ትምህርት ቤት የማዕረግ ተመራቂዎች አንዷ ስትሆን በርካታ አስገራሚ ስኬቶችን ተጎናፅፋለች።
🏅የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ - CGPA 3.95
🏆 የፕ/ር ዕደማሪያም ፀጋ አካዳሚክ ልህቀት በሕክምና ተሸላሚ
👩🎓 ከ2017 ሴት ተመራቂዎች ሰቃይ
🥇 ምርጥ ኢንተር – ከቀዶ ህክምና ትምህርት ክፍል
🥇 ምርጥ ኢንተር – ከህጻናት ህክምና ትምህርት ክፍል
Via @tikvahuniversity
ፎቶ ፦ በህመም ምክንያት በአሜሪካን ሀገር ሲያትል ከተማ ሐምሌ 2 ቀን 2017 ዓ/ም ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው ጋዜጠኛ ታደሰ ሚዛን (ዶ/ር) አስክሬኑ ወደ ሀገሩ ኢትዮጵያ መጥቶ ስርዓተ ቀብሩ በአዲስ አበባ መንበረ ፀባዖት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ዛሬ ተፈጽሟል።
የፎቶ ባለቤት ፦ ቴሌቪዥን ትግራይ
@tikvahethiopia
#AddisAbaba
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ የከተማዋ ካቢኔ በ4 ኛ አመት የስራ ዘመኑ በ11 ኛ መደበኛ ስብሰባው ላይ የጤና ባለሞያዎችን የጥቅማ ጥቅም ፓኬጅ በሚመለከት የተላለፈውን ውሳኔ ተግባራዊ እንዲሆን ውሳኔ አሳልፏል።
በቢሮው ሃላፊ ጀማሉ ጀንበር (ዶ/ር) ተፈርሞ ለ 11 ዱም ክፍለ ከተሞች የተላከው እና ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተመለከተው ባለ አራት ነጥብ ደብዳቤ ከ2018 ዓ/ም በጀት አመት ጀምሮ ለጤና ባለሞያዎች ጥቅማ ጥቅሞቹ ተግባራዊ እንዲሆኑ ይጠይቃል።
በዚህም መሰረት ተግባራዊ እንዲሆኑ የተወሰኑት ጥቅማጥቅሞች :-
1. የትርፍ ሰዓት ክፍያን በሚመለከት የጤና ባለሙያዎች የትርፍ ሰዓት አገልግሎት ክፍያ አፈፃፀምን መሰረት ባደረገ እና በአገልግሎት አሰጣጥ ስታንዳርድ መሰረት ተግባራዊ እንዲሆን።
2. የጤና ባለሙያዎች፣ የትዳር አጋራቸው እና ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ልጆቻቸው ቅድሚያ በሚሰሩበት የጤና ተቋም ፣ቀጥሎ በሌሎች የከተማ አስተዳደሩ የመንግስት ጤና ጣቢያዎች እና ሆስፒታሎች ነፃ የህክምና አገልግሎት እንዲያገኙ።
3. ከዚህ ቀደም በቀዳማዊ ልጅነት ልማት ፕሮጀክት በጊዚያዊነት የተቀጠሩ የቤት ለቤት፣ የወላጆች እና አሳዳጊዎች ምክር ሰጪ ሰራተኞች በቢሮው፣ በክፍለ ከተማ እና ጤና ጣቢያዎች ላይ የሚገኙ ሱፐርቫይዘሮች እና ኮኦርዲኔተሮች አሰራሩን ጠብቀው ቋሚ ሰራተኞች እንዲሆኑ።
4. የኑሮ ውድነቱን ጫና ለማቃለል በሁሉም የጤና ተቋማት ውስጥ የሸማቾች ህብረት ማህበራት ሱቆች በማቋቋም በመንግስት ድጎማ የሚቀርቡ ምርቶችን የጤና ባለሞያዎች በቀላሉ ማግኘት እንዲችሉ ሁኔታዎች እንዲመቻቹላቸው መወሰኑን ደብዳቤው ይገልጻል።
በመሆኑም ከላይ የተዘረዘሩት ጥቅማ ጥቅሞች ከ 2018 ዓም በጀት አመት ጀምሮ በከተማ አስተዳደሩ ስር ለሚገኙ የጤና ባለሞያዎች ተፈጻሚ እንዲሆንላቸው ለሚመለከታቸው የስራ ክፍሎች እና ሃላፊዎች መመሪያ መሰጠቱን ቲክቫህ ከደብዳቤው ተመልክቷል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamily
@tikvahethiopia
ከሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ጋር ዲጂታል እንሁን!
Esim ገዝተው የ50 ብር የአየር ሰዓት ሞልተው በተጨማሪ ስጦታዎች ይደሰቱ:
✅ 6ጊባ ዳታ
✅1000 ደቂቃ የድምፅ ጥሪ እና 1000 የSMS መልዕክት ወደ ሳፋሪ
✅ 50 ብር የአየር ሰአት
- ሁሉም ስጦታዎች ለሳምንት የሚቆዩ ናቸው።
በሁሉም የሳፋሪኮም ሱቆች ያገኝሉ! ዛሬውኑ ይቀላቀሉ!
#SafaricomEthiopia
" በደረሰዉ ድንገተኛ ቃጠሎ ምክንያት ሆስፒታሉ ሙሉ በሙሉ ስራ አቁሟል " - የወላይታ ዞን ጤና መምሪያ
➡ " የጤና ባለሙያዎች እና የአከባቢው ነዋሪዎች ተረባርበዉ ተኝተዉ የሚታከሙትንና በፅኑ ሕሙማን ክፍል የነበሩትን ማትረፍ ችለዋል!! "
የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ኮሚፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ዛሬ ከባድ የእሳት አደጋ እንዳጋጠመውና በቃጠሎው ምክንያት የሆስፒታሉ ዋናው የአገልግሎት ሕንፃ ሙሉ በሙሉ በመውደሙ ሆስፒታሉ አገልግሎት ማቆሙን የወላይታ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ፀጋዬ ኤካ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
የሆስፒታሉ ዋና ዋና ሕክምናዎችና የላብራቶሪ ስራዎች ይከናወኑበት የነበረዉ ይህ G+1 ሕንፃ ረጅም ዓመታትን ያስቆጠረና የቀዶ ሕክምናን ጨምሮ ተኝተዉ የሚታከሙና የፅኑ ሕሙማን ክፍሎችን የያዘ የሆስፒታሉ ዋነኛ ሕንፃ እንደነበር ገልጸዋል።
ይኸው ሕንፃ ከቀኑ 8:30 አከባቢ ጀምሮ ለጊዜው መንስኤው ባልታወቀ የእሳት አደጋ ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰበት አስታውቀዋል።
የጤና ባለሙያዎችና የአከባቢው ነዋሪዎች በመረባረብ ተኝተዉ የሚታከሙትንና በፅኑ ሕሙማን ክፍል ውስጥ የነበሩ ታካሚዎችን ማትረፋቸዉን የገለፁት አቶ ፀጋዬ ቁጥርና ሁኔታዉ በደንብ የሚጣራ ቢሆንም የሆስፒታሉ ትልልቅ የሕክምና መሳሪያዎችም ጉዳት ማስተናገዳቸውን ገልፀዋል።
ይህ ቃለ ምልልስ በተካሄደበትም ሰዓት በሁለት የእሳት ማጥፊያ መኪኖች ታግዞ የእሳት ማጥፋት ርብርቡ የቀጠለ ሲሆን እሳቱ ሙሉ በሙሉ አለመጥፋቱን አቶ ፀጋዬ ኤካ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamily
@tikvahethiopia
#Hawassa
በሰላም ተጠናቋል !!
በየአመቱ ሐምሌ 19 የሚከበረው የሀዋሳ ቅዱስ ገብርኤል ንግስ በዓል በድምቀት፣ ፍጹም ሰላማዊ በሆነ መልኩ መጠናቀቁን የክልሉ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አሳውቋል።
በዓሉ በሰላም ተከብሮ እንዲጠናቀቅ ሰላም ወዳድ የሆነው መላው የሀዋሳ ከተማ ነዋሪ ላበረከተው አስተዋፅኦ ምስጋና ቀርቧል።
ኃላፊነታቸውን በአግባቡ የተወጡ የፀጥታ ግብረሃይል እና ባለድርሻ አካላት ሁሉ ተመስግነዋል።
ከበዓሉ ጋር ተያይዞ በዕለቱ በተሰየመው ጊዜያዊ ችሎት የስርቆት ወንጀል ሲፈፅሙ በፀጥታ ግብረ ኃይል እጅ ከፍንጅ የተያዙ 03 ተጠርጣሪዎችን ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ ወንጀል ድርጊት በተያዘው ሪከርድ ከ3 ዓመት እስከ 13 ዓመት እስራት እንዲቀጡ ተወስኗል።
በዓሉን አስመልክቶ ለቀጣይ ቀናት ቆይታቸውን ሀዋሳ ለሚያደርጉ እንግዶች ቆይታቸው የሰመረ እንዲሆን የተመኘው የክልሉ ፖሊስ የእንግዶችን ደህንነት እንደሚያስጠብቅ አረጋግጧል።
መላ ነዋሪዎቿ በፍቅር ፣ በመከባበር ፣ በመተሳሰብ እና በአንድነት በሚኖሩባት ሀዋሳ በየዓመቱ ታህሳስ 19 እና ሐምሌ 19 የቅዱስ ገብርኤል ንግስ በዓል እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ኦርቶዶክሳዊ ምዕመን በተገኘበት ይከበራል።
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa
@tikvahethiopia
ፎቶ፦ የሐምሌ 19 የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ የንግስ በዓል በሀዋሳ ደብረ ምህረት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም በታላቅ ድምቀት እየተከበረ ይገኛል።
በዓሉ ላይ እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ኦርቶዶክሳዊ ምዕመን ተገኝቷል።
#ሐምሌ19 #ቅዱስ_ገብርኤል #ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa
@tikvahethiopia
#ለጥንቃቄ
" ' አሟታል ' ፣ ' ነፍሰ ጡር ናት ' ፣ ' መስኮት ክፈት ' ፣ ' ተባበራት ' ፣ ' ትራፊክ መጣ ዝቅ በል ' በማለት በማዋከብ ' ከታክሲው ውረጂ/ ውረድ ' ሌላም ምክንያቶችን በመናገር ገፍትረው የሚያመልጡ ስለሆነ ጥንቃቄ አድርጉ ! " -ፖሊስ
የአዲስ አበባ ፖሊስ CMC አካባቢ የማታለል (#ሿሿ) ወንጀል ላይ የተሰማሩ 9 ተጠርጣሪዎችን በተበዳይ ጥቆማ መያዙን አሳውቋል።
እነዚህ ግለሰቦች የግል ተበዳይን " የት ነህ ? " በማለት ከCMC ጋስትሞል ይጭናሉ።
የተወሰነ ርቀት እንደተጓዙ CMC የጋራ መኖሪያ ቤቶች (5 መቶ አፖርታማ) ጋር ሲደርሱ ግን " ትራፊክ አለ ውረድ " ብለው የተሽከርካሪውን በር ከፍተው ገፍትረው ጥለው ይሰወራሉ።
የግል ተበዳይም ጉዳዩን ለCMC አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ማመልከታቸውን ተከትሎ ፖሊስ ተጠርጣሪዎችን ወማደን ይገባል።
በዚህም በአራዳ ክፍለ ከተማ ፒያሳ አካባቢ ሹፌርና ረዳት እንዲሁም ተሳፋሪ በመምሰል ወንጀሉን የሚፈፅሙ 9 ተጠርጣሪዎችን ለወንጀል መፈጸሚያ ከሚገለገሉበት የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3 ኦ/ሮ 78652 ተሽከርካሪ ጋር መያዙን ፖሊስ ገልጿል።
በግለሰቦቹ ላይ አስፈላጊውን ማስረጃ በማሰባሰብ ምርመራ እየተጣራባቸው መሆኑን አሳውቋል።
ተመሳሳይ የማታለል ወይም የሿሿ ወንጀል የተፈፀመበት ማንኛውም ግለሰብ CMC አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ቀርቦ ወንጀል ፈፃሚዎቹን በመለየትና በመምረጥ ማስረጃ መስጠት የሚችል መሆኑ ተገልጿል።
የሿሿ የወንጀል ተግባር ላይ የተሰማሩ ሰዎች በተሽከርካሪዎቻቸው ውስጥ ወንድና ሴት በመጫን ፦
- " አሟታል "
- " ነፍሰ ጡር ናት "
- " መስኮት ክፈት "
- " ተባበራት "
- " ትራፊክ መጣ ዝቅ በል " በማለት በማዋከብ " ከታክሲው ውረድ " ሌላም ምክንያቶችን በመናገር ገፍትረው የሚያመልጡ በመሆኑ ህብረተሰቡ ለወንጀል ፈፃሚዎች ሰለባ ላለመሆን ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ ፖሊስ አሳስቧል።
የወንጀል ድርጊቱ ከተፈፀመበትም የሰሌዳ ቁጥር የመያዝ ልምዱን ሊያጎለብት እንደሚገባ አስገንዘቧል።
⚠️ ትራንስፖርት ስትጠቀሙ የምትጠቀሙበትን ተሽከርካሪ ታርጋ ቁጥር መያዝ እንዳትዘነጉ።
#AddisAbabaPolice
@tikvahethiopia
#ሴጅ_ማሰልጠኛ_ኢንስቲትዩት
32ኛ ዙር ሙሉ የሒሳብ መዝገብ አያያዝ (Modern Accountancy) ስልጠና የፊታችን ሰኞ ሐምሌ 21/2017 ዓ.ም እና ሐምሌ 26/2017 ዓ.ም ይጀመራል።
👉 ተግባርን ከንድፈ ሀሳብ ያስተሳሰረ ስልጠና
👉 መሠረታዊ አካውንቲንግ እና ኦዲት አሰራር፣ ሙሉ የአካውንቲንግ ሒሳብ አሰራር በፒስቺሪ ተደግፎ እና የግብር አያያዝ ትምህርቶችን አካቶ የሚሰጥ
☎️ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦ ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ እና ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ
Telegram
sage_training_institute">Tiktok
Linkedin
" የክልሉ ጤና ቢሮ አካባቢን ነው ጎርፉ በጣም የጎዳው። ዞን 1 ቀበሌ 05 በጣም ነው ጉዳት የደረሰው። ዞን ሦስት መጃንግ ብሔረሰብ አካባቢም ትልቅ ጉዳት ደርሷል " - የጋምቤላ ከተማ ከንቲባ
በጎርፍ መጥለቅለቅ ሳቢያ በቤትና ንብረት ላይ ከባድ ጉዳት መድረሱን የጋምቤላ ክልል ከተማ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።
የጋምቤላ ከተማ ከንቲባ ሳይመን ሙን (ዶ/ር) ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደገለጹት፣ ከንጋቱ 10 ሰዓት እስከ ጠዋቱ 1 ሰዓት ገደማ የዘለቀው ከባድ ዝናብ ሳቢያ የተከሰተው የጎርፍ መጥለቅለቅ በቤቶችና ንብረት ላይ ጉዳት አድርሷል።
ጉዳቱ የደረሰው የጎርፍ መሄጃ ቱቦዎች ተደፍነው ጎርፉ ከዋና መንገድ ዘሎ የራሱን መስመር ቀይሶ በመውጣቱ እንደሆነ፣ በቤትና ንብረት ስለደረሰው ጉዳት መረጃ ተሰብስቦ ሲጠናቀቅ እንደሚያሳውቁ፣ በሰዎች ላይ ግን የደረሰ ጉዳት እንደሌለ ተናግረዋል።
" የክልሉ ጤና ቢሮ ዙሪያ አካባቢን ነው ጎርፉ በጣም የጎዳው። ዞን 1 ቀበሌ 05 በጣም ነው ጉዳት የደረሰው። ዞን ሦስት መጃንግ ብሔረሰብ አካባቢም ትልቅ ጉዳት ደርሷል። 01 ቀበሌ ላይ ዞን 7 አካባቢ ደግሞ ጎርፉ መጠነኛ ጉዳት አድርሷል " ብለዋል።
በጤና ቢሮው ላይ ጉዳት ደርሶ እንደሆን የጠየቅናቸው አንድ የክልሉ ጤና ቢሮ አካል፣ በጤና ቢሮ ላይ ምንም የደረሰ ጉዳት እንደሌለ፣ የጎርፍ መጥለቅለቁ የተከሰተው በጤና ቢሮው አካባቢ ባሉ መንደሮች እንደሆነ አስረድተው፣ "ጤና ቢሮው አካባቢ ባሉ ሰዎች ቤቶች ጎርፉ በጣም ገብቷል፤ እቃ ጎድቷል፤ ቤት አፍርሶባቸዋል" ሲሉ አስረድተዋል።
አደጋው በተከሰተበት ቦታ ከዚህ ቀደም አደጋ አጋጥሞ እንደሆን፣ ከክረምቱ ጋር በተያያዘ ደግሞ ለአደጋ ተጋላጭ ቦታዎችን በመለየት ምን እየተሰራ እንደሆነ የጠየቅናቸው ከንቲባ ሳይመን (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ ጎርፉ በተከተባቸው ቦታዎች ከዚህ ቀደም ችግር አጋጥሞ እንደማያውቅና አደጋው ድንገተኛ እንደሆነ ገልጸዋል።
አክለውም፣ " የኮሪደር ልማት እየሰራን ስለሆነ ውሃው ከዚህ ቀደም እንደፈለገ ሲንቀሳቀስበት በነበሩ ቦታዎች በአንድ መስመር ኮሪደር አማካኝነት በአንድ ወይም በሁለት ዳይሬክሽን እየገባ ነው፤ ለወደፊቱ ዲሬኔጆቹን ለማስተካከል ጥናት እየተደረገ ነው " ብለዋል።
በዛሬው የጎርፍ አደጋ ምን ያክል ቤቶች ጉዳት እንደደረሰባቸው የጠቅናቸው የጋምቤላ ክልል አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ጃክ ጆሴፍ፣ " የጉዳት መጠኑ ገና አልተጠናከረም። ግን ጎርፉ ጉዳት እንዳስከተለ በተጨባጭ ማየት ችለናል። የጉዳት መጠኑን ባለሙያዎች እያጠናቀሩት ነው " ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
" የህንዳዊውን አሟሟት በተመለከተ መርማሪ ቡድን ተቋቁሞ እየተጣራ ነው " - የአዳማ ከተማ ፖሊስ
አንድ ህንዳዊ ዜግነት ያለው ግለሰብ በአዳማ ከተማ ሞቶ መገኘቱን ፖሊስ ገልጿል።
የአዳማ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ሻዋዬ ደቻሳ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በስልክ እንደተናገሩት የህንድ ዜግነት ያለው ኤን ቪ ስብ ራዩ የተባለው ግለሰብ ያለፈው ቅዳሜ ሀምሌ 19 ቀን 2017 ዓ.ም ሞቶ መገኘቱን አረጋግጠዋል።
የግለሰቡ አስክሬን በከተማው ፖሊስ አባላት መገኘቱንም አክለዋል።
የግለሰቡን አሟማት በተመለከተ የወንጀል ምርመሪ ቡድን ተቋቁሞ የምርመራ ሄደቱ ተጀምሯል ምርመራው እንደተጠናቀቀ ይፋ ይደረጋል ብለዋል ኮሚሽነሩ።
በአዲስ አበባ የሚገኘው የህንድ ኤምባሲ ኤን ቪ ስብ ራዩ የተባለው ግለሰብ የካልፓተሩ ፕሮጀክት የሚሰራው የፈጣን መንገድ ፕሮጅክት ሰራተኛ መሆኑን ጠቅሶ ሀምሌ 19 ቀን 2017 ዓ.ም ሞቶ አስክሬኑ በአዳማ ከተማ በፖሊስ መገኘቱን አሳውቋል።
ጉዳዩንም እየተከታተለ መሆኑን ጠቁሟል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ነቀምቴ
#TikvahEthiopiaFamilyNekemte
@tikvahethiopia
" ተፈናቃዮቹ ቤተክርስቲያን እና ሆቴል በር ላይ እየለመኑ ነው " - የተፈናቃይ ተወካይ
➡️ " እነሱ በሚሉት ልክ አይደለም የተቋረጠባቸው " - የዞኑ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ፅ/ቤት
በአማራ ክልል በሰሜን ጎንደር በደባርቅ ከተማ ከማህበረሰቡ ጋር ተቀላቅለው የሚገኙ የትግራይ ተፈናቃዮች የእርዳታ እህል ካገኙ ከ8 ወር በላይ እንደሆናቸው ተናግረዋል።
በማኅበር የተደራጅተው ችግራቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የተናገሩት ተፈናቃዮቹ የሚበሉት ከማጣታቸው የተነሳ ለልመና መውጣታቸውን የመሀበሩ ጸሐፊ መርጌታ ጠበቃው ወልደ ገብርኤል ተናግረዋል።
መርጌታ ጠበቃው እንደሚሉት ወትሮም አልፎ አልፎ ይሰጥ የነበረው እርዳታ ከቆመ 8 ወር ሆኖታል።
ከሰሜኑ የኢትዮጵያው ጦርነት ጋር በተያያዘ ተፈናቅለው በደባርቅ ከተማ መጀመሪያ በመጠለያ ጣቢያ በኃላም ከማህበረሰቡ ጋር ተቀላቅለው መቆየታቸውን የሚናገሩት መርጌታ ጠበቃው ካለፈው ህዳር ወር ጀምሮ እርዳታ እንደተቋረጠባቸው ተናግረዋል።
ምክንያቱ ደግሞ የአካባቢው ባለስልጣናት የወረዳና የከተማ ብለው ተፈናቃዮችን መከፋፈላቸው ነው ይላሉ።
" በከተማ ነዋሪነት የተመዘገቡ ተፈናቃዮች በየጊዜው እርዳታ ያገኛሉ በወረዳ ተፈናቃይነት የተመዘገቡት ግን እያገኙ አይደለም ሁለቱም በአንድ ሰፈር የሚኖሩ ናቸው " ብለዋል።
በጉዳዩ ዙሪያ የሰሜን ጎንደር ዞን አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሰላም ይሁን ሙላትን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ያነጋገረ ሲሆን " ተፈናቃዮቹ ለ8 ወራት ያህል እርዳታ ተቋረጠብን የሚሉት ስህተት ነው " ባይ ናቸው።
ከህዳር ወር በኃላ ወሩን በትክክል ባያስታውሱትም ለእያንዳንዱ ተፈናቃይ የሁለት ወር እርዳታ እንደተሰጣቸው አስረድተዋል።
ከዛም አመልድ ኢትዮጵያ 4 ሚልየን ብር በመመደብ ለ200 በጣም ችግር ውስጥ ላሉና ለአቅመ ደካማ ተፈናቃዮች ግንቦትና ሰኔ ወር ላይ ለእያንዳንዳቸው 10 ሺህ 10 ሺህ ሰጥቷል። ይህንን ቅሬታ እያነሳ ያለው ሰርቶ መብላት የሚችል ነው ተብሎ ያልተሰጠው ነው ሲሉ አቶ ሰላም ይሁን አክለው ገልፀዋል።
" ሌላው ባለፈው ሰኔ ወር ላይ ለነባር ተፈናቃዮች ለመስጠት የታቀደ እርዳታ ነበር ነገር ግን በአጋጣሚ በወረዳው ውስጥ ያሉ በተፈጥሮ አደጋ ምክንያት ተፈናቅለው የመጡ ሰዎች ስለነበሩ ቅድሚያ ለእነዚህ ተፈናቃዮች ሰጥተናል ይህም በተፈናቃዩ ዘንድ ብዙ ቅሬታ አስነስቶ ነበር " ሲሉ አስታውሰዋል።
በወረዳና በከተማ ተለይቶ ሲሰጥ ስለነበረው እርዳታና ሰለተፈጠረው ክፍተት ምን አሉ ?
" በወረዳው ውስጥ በሰው ሰራሽና ተፈጥሮ አደጋዎች ምክንያት ለችግር የተጋለጡ ሰዎች ከመንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች የሚገኝ እርዳታ ለሁሉም ተረጂዎች ሲሰጥ የቆየ ሲሆን የፌደራል አደጋ ስጋትና ስራ አመራር ኮሚሽን ለአሰራር ይመች ዘንድ አንድ ጥናት አጥንቶ ወደ ስራ ገብቷል።
ይህም በወረዳ የሚገኙ ተረጂዎች ማምረት ስለሚችሉ እርዳታ ይቁም በከተማ ለሚገኝ ተረጂዎች ግን ይቀጥል ብሎ ሲወስን እንዳጋጣሚ በወረዳ ደረጃ የተመደቡትን የትግራይ ተፈናቃዮችን ጨምሮታል።
ይህም ስህተት በመሆኑ ዞኑ ለተፈናቃዮቹ እርዳታ እንዲቀጥል እየጠየቀ ያለበት ሁኔታ ነው ያለው " ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ባሕር ዳር
#TikvahEthiopiaFamilyBahirdar
@tikvahethiopia
#Update
ተጠርጣሪው ተይዟል !
በእንዳስላሰ ሽረ በሁለት እንስቶች ላይ አሲድ በመድፋት ጉዳት እንዳደረሰ የተጠረጠረው ተጠርጣሪ ተያዘ።
በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን የእንዳስላሰ-ሸረ ከተማ ነዋሪ የሆነው ተጠርጣሪ ወላይ ተጠምቀ ሀምሌ 7 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 2:00 ሰዓት በከተማው በሚገኘው መጠጥ ቤት በሁለት እንስቶች ላይ አሲድ በመድፋት ተጠርጥሮ በፓሊስ ሲፈለግ እንደነበር ተጠቁሟል።
የእንዳስላሰ-ሸረ ከተማ የፀጥታ ፅህፈት ቤት ዛሬ ሀምሌ 20/2017 ዓ.ም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ በሰጠው መረጃ ፤ ተጠርጣሪው በፀለምቲ ወረዳ አዋሳኝ በሚገኘው የፌደራል ፓሊስ በቁጥጥር ስር ውሎ ተላልፎ ተሰጥቷል።
በተደፋባቸው አሲድ ክፉኛ ከተጎዱት አንድዋ ፍረይ ተክለሃይማኖት የተባለች እንስት ለከፍተኛ ህክምና በመቐለ ዓይደር ስፔሻላይዝድ ሪፈራል እንደምትገኝ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለመረዳት ችሏል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
@tikvahethiopia
#Tigray
ያልመከነ ተተኳሽ ፈንድቶ የሦሥት ህፃናት ህይወት ተቀጨ።
ሦሥቱ ወንድሟሟች የአንድ አባትና እናት ልጆች ናቸው።
አደጋው ሀሞሌ 18/2017 ዓ.ም በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን ታሕታይ ቆራሮ ወረዳ ልዩ ስሙ ዓዲ መናብር ነው ያጋጠመው።
ህፃናቱ ለጨዋታ በተንቀሳቀሱበት መንደራቸው አጠገብ የሚገኘው ጫካ ውስጥ የወደቀ ሹል ድምቡልቡል ብረት ያገኛሉ።
የልጅ ነገር ሆኖባቸው ብረቱ በደንጋይ እየቀጠቀጡ ሳጫወቱ ፈንድቶባቸው ወድያውኑ ህይወታቸው አልፈዋል።
በትግራዩ ጦርነት ምክንያት በየቦታው ያሉ ያልመከኑ ተተኳሾት በሰውና እንስሳት ከፍተኛ ጉዳት በማድረስ ላይ መሆናቸው በተደጋጋሚ መረጃ ማካፈላችን ይታወሳል።
ዓለም አቀፍ የቀይ መስቀል ኮሚቴና የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር በትግራይ የተለያዪ ወረዳዎች የሚገኙ ያልመከኑ ተተኳሾች በማስወገድ ሰብአዊ ኃላፊነታቸው በመወጣት ላይ ቢገኙም ጦርነቱ ከተካሄደበት የቦታ የቆዳ ስፋት አንፃር በቂ እንዳልሆነ ይገለፃል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamily
@tikvahethiopia
#ነዳጅ
የነሐሴ ወር የቤንዚል፣ የነጭ ናፍጣ፣ የኬሮሲን እና የአውሮፕላን ነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በነበረበት እንደሚቀጥል የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አሳውቋል።
በሌላ በኩል ቀላል ጥቁር ናፍጣ በሊትር 127 ነጥብ 22 ብር እንዲሁም ከባድ ጥቁር ናፍጣ በሊትር 124 ነጥብ 55 ብር ብቻ እንዲሸጥ ተወስኗል።
@tikvahethiopia
" የጤፍ መዝሪያ ወቅት እንዳያልፍብን የአፈር ማዳበሪያ በኩንታል እስከ 14 ሺህ ብር በጥቁር ገበያ እየገዛን ነው እሱንም ዛሬ ማግኘት አልቻልንም " - አርሶ አደሮች
በአማራ ክልል ከሞጣ ወደ አዴት የሚወስደው ዋና መንገድ ከሳምንት በላይ በመዘጋቱ ከፍተኛ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ተከስቷል ሲሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ያነጋገራቸው የገረገራ ቀበሌና የአዴት ከተማ ነዋሪዎች እንደተናገሩት ከሞጣ ወደ አዴት የሚወስደው መንገድ ከ10 ቀን በላይ በመዘጋቱ በተለይ ጤፍ ለመዝራት ጉልጓሎ ላይ ያሉ አርሶ አደሮች የሚያስፈልጋቸውን የአፈር ማዳበሪያ በኩንታል እስከ 14 ሺህ ብር በጥቁር ገበያ ለመግዛት ተገደዋል ብለዋል።
በይልማና ዴንሳ ወረዳ ግምብ አስቴሮ ቀበሌ " ቆሎ መሻጫ " ተብሎ በሚጠራ ጎጥ የሚኖሩ አርሶ አደር አያሌው በላቸው በቆሎ፣ በርበሬና ጤፍ ዘርተው ማዳበሪያ እያፈላለጉ እንደሆነ ይናገራሉ።
" ይህ ወቅት ጤፍ ዘርተን ጉልጓሎ የምናደርግበት ነበር፤ በጉልጓሎ ወቅት ደግሞ የአፈር ማዳበሪያ ያስፈልጋል፤ መንገዱ በመዘጋቱ ምክንያት ማዳበሪያ እየገባ አይደለም " በማለት " ነጋዴ አንድ ኩንታል ማዳበሪያ በ14 ሺ ብር በጥቁር ገበያ እየሸጠልን ነው " ሲሉ አስረድተዋል።
" እኔን ጨምሮ ሌሎች አርሶ አደሮች ይሁን ብለን ለመግዛት ብንሄደም ' ጨርሰናል ' ብለዋል ዋጋው ቢጨምርም ወቅቱ ከሚያልፍብን ብለን ከቦታ ቦታ እየተዘዋወርን እየፈለግን ነው " ብለዋል።
ነዋሪዎቹ እንደሚሉት ከወቅቱ ጋር ተያይዞ ችግሩ በአርሶ አደሮች ላይ በረታ እንጂ ከመንገዱ መዘጋት ጋር ተያይዞ በአካባቢው በኢንዱስትሪ ምርቶች ላይ ከፍተኛ የዋጋ ንረት እየታየ ነው በአንፃሩ ደግሞ የግብርና ምርቶችን አርሶ አደሩ ተዘዋዉሮ ባለመሸጡ በርካሽ እንዲሸጥ አስገድዶታል ብለዋል።
ለለቅሶ፣ ዘመድ ለመጠየቅ እና ለሌሎች ጉዳዮች ወደ ተለያዩ ቀበሌዎች መሄድ ፈልገው ትራንስፓርት ያጡ ሰዎች በእግራቸው እየተንቀሳቀሱ ነው ሲሉም አስተያየታቸውን አክለዋል።
መስመሩ ከአዲስ አበባ ተነስቶ በሞጣ ወደ ባህር ዳር እና ሌሎች አካባቢዎች የሚወስድ ዋና መንገድ በመሆኑ ከፍተኛ የትራንስፖርት ፍሰት የሚታይበት ነው።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ባሕር ዳር
#TikvahEthiopiaFamilyBahridar
@tikvahethiopia
#Update
" በርካታ ታካሚዎች የተኙባቸው ክፍሎች ስለነበሩ ያሉት ሠራተኞች በሙሉ ታካሚ ማውጣት ላይ ትኩረት ስላደረጉ በርካታ ንብረቶች ተቃጥለው ወድመዋል " - የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት
በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተከሰተው የእሳት አደጋ በሰዎች ጉዳት ባያደርስም በንብረት ላይ ከባድ ጉዳት ማድረሱን ዩኒቨርሲቲው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ጉቼ ጉሌ (ዶ/ር)፣ " በርካታ ታካሚዎች የተኙባቸው ክፍሎች ስለነበሩ ሠራተኞች በሙሉ ታካሚ ማውጣት ላይ ትኩረት ስላደረጉ በውስጥ የነበሩ በርካታ ንብረቶች ተቃጥለው ወድመዋል " ሲሉ ነግረውናል።
ፕሬዚዳንቱ፣ " የተጎዳ ሰው የለም። ታካሚ የነበረበት ክፍል ነበር አደጋው የደረሰው እሳቱ መቀጣጠል ከጀመረበት ጊዜ ጅምሮ ታካሚዎቹን ወደ ሌላ ክፍል አውጥተናል። ታካሚ አልተጎዳም " ብለዋል።
" በእርግጥ እሳት በማጥፋት ላይ እያለ አንድ ሠራተኛ መስታወት የቆረጠው አለ ሌላ የተጎዳ የለም " ሲሉም አክለዋል።
መንስኤው ምንድን ነው ? ተብሎ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ለቀረበላቸው ጥያቄም፣ "ገና ነው አልታወቀም። መንስኤው እየተጣራ ነው። እሳቱ በጣም ከጎበዘ በኋላ ስለሆነ የደረስነው እሩጫ ላይ ስለነበርን መንስኤውን አላገኘንም" ሲሉ መልሰዋል።
የሆስፒታሉ ዳይሬክተር ከአደጋው ጋር በተያያዘ አጣዳፊ ሥራ ላይ መሆናቸውን ገልጸው፣ ሲያጠናቅቁ ዝርዝር ማብራሪያ እንደሚሰጡን ገልጸዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
አቢሲኒያ ባንክ
#የሁሉም_ምርጫ
አቢሲኒያ ባንክ በ927 ቅርንጫፎቹ ሙሉ በሙሉ ወረቀት አልባ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ገለፀ።
አቢሲኒያ ባንክ በመላው ሀገራችን በሚገኙት 927 ቅርንጫፎቹ በአዲስ መልክ በተዋቀረ ራስ ልዩ ቅርንጫፍ ( Ras Premium Branch ) ሙሉ በሙሉ ወረቀት አልባ በሆነ መልኩ ሁሉንም አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ገልጿል።
ይህ ወረቀት አልባ አገልግሎት ስማርት ኪዮስኮችንና ታብሌቶችን እንዲሁም የጣት አሻራንና የፊት ገጽን እንደ መለያ የሚጠቀም ሲሆን ጊዜ የሚወስዱ የአሠራር ሂደቶችን ያስቀራል ሲሉ የባንኩ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ በቃሉ ዘለቀ ተናግረዋል።
ዋና ሥራ አስፈጻሚው በዝርዝር ምን አሉ ?
የባንኩ ደንበኞች ባላቸው የቴክኖሎጂ ክህሎት መጠን ሳይገደቡ የእንግሊዝኛ ቋንቋን ጨምሮ በተለያዩ አገራዊ የቋንቋ አማራጮች (በአማርኛ፣ በአፋን ኦሮሞ፣ በሱማሌኛ፣ በትግርኛ፣ በአፋርኛ እና በሲዳምኛ) አገልግሎቱን መጠቀም ይችላሉ።
የጥሬ ገንዘብ መቀበያና መክፈያ /Recyclers/ እና በመጠኑ ከፍተኛ የሆነ ገንዘብን ለመቀበል የሚያስችሉ ማሽኖች /Bulk Deposit Machines/ በተመረጡ ቅርንጫፎች ተዘጋጅተዋል። ወደፊት በሁሉም ቅርንጫፎች አገልግሎቱን ተደራሽ ለማድረግ እየሰራን ነው።
ደንበኞች በካርድም ሆነ ያለ ካርድ ጥሬ ገንዘብ ማስገባትና ማውጣት ይችላሉ። ይህ አጠቃቀም ከኤቲኤም የተለየ ነገር የለውም፣ ማንኛውም ሰው በቀላሉ መጠቀም ይችላል። በሁሉም ቅርንጫፎች ደንበኞች ስለ አጠቃቀሙ መጠየቅ ይችላሉ።
ይህንን ሙሉ በሙሉ ወረቀት አልባ የሆነ አገልግሎት መስጠት ስንጀምር በባንካችን በሰራተኞች ዘንድ ከስራ እንቀነሳለን የሚል ስጋት ሊፈጠር ይችላል።
ነገር ግን የባንኩን አሰራር በማዘመናችን አዳዲስ ሰራተኞችን ልንፈልግ ይንችላለን እንጂ ሰራተኛ የመቀነስ ሃሳብ የለንም፣ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀማችን ከዚህ በፊት የመጣ ከፍተኛ ለውጥ አለ።
ዛሬም በይፋ ስራ ያስጀመርነው አሰራር ሰራተኞችን በተለየ መልኩ የምንፈልግበት እና የምንጠቀምበት እድል ይኖራል ብለዋል።
በመድረኩ ላይ የተገኙት የብሔራዊ ባንክ ገዢ አቶ ማሞ ምህረቱ ባንኮች ብዙ ጊዜ አድስ አሰራር ሲያስጀምሩ በአንድ ቅርንጫፍ ብቻ ነው፣ አቢሲኒያ ግን ይህን ቴክኖሎጂ ሲያስጀምር በሁሉም ቅርንጫፎች አገልግሎት መስጠት እንድችሉ አድርጎ ነው። ይህንን ተግባር ብሄራዊ ባንክም ያበረታታል ብለዋል።
የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ዘርፍ ዘመናዊ እንዲሆን ለማድረግ ሶስት ነገሮች መደረግ አለባቸው። የባንኩ ዘርፍ ጤናማ፣ ባንኮች አምራች ዜጎችን መደገፍ እንዲችሉ ፣ የፋይናንስ ዘርፉ በተሻለ መጠን ተወዳዳሪ እና በቴክኖሎጅ የተደገፈ እንዲሆን ማድረግ ያስፈልጋል ሲሉ ነው የተናገሩት።
ሁሉም ባንኮች የማህበረሰቡን ፍላጎት ላይ ያተኮረ አገልግሎት መስጠት እና ተወዳዳሪ መሆን አለባቸው። ለዚህም እራሳቸውን ማዘጋጀት ይኖርባቸዋል፣ ይህ ግን ፍላጎት ብቻ ሳይሆን ግዴታቸውም ነው።
"ብሔራዊ ባንክ ባንኮች ኮርፖሬት ገቨርናንሳቸውን ፕሮፌሽናል በሆነ መልኩ ጤናማ እንዲያደርጉ ይደግፋል፣ ይህንን የሚያደናቅፍ አሰራር የሚከተሉ ካሉ ተቀባይነት የለውም። ባንኮች ከሼህ ሆልደር እስከ ደንበኞቻቸው ድረስ ያሉ አሰራሮችን ጤናማ በሆነ መልኩ መስራት ይኖርባቸዋል" ሲሉ አሳስበዋል።
@BoAEth
ፎቶ ፦ በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ውስጥ የተከሰተው የእሳት አደጋ በህዝቡ ብርቱ ጥረት በቁጥጥር ሥር ማዋል እንደተቻለ ተገልጿል።
በአደጋው የሆስፒታሉ ቀዶ ሕክምና ፣ የውስጥ ደዌ ሕክምና እና ተመላላሽ ሕክምና ክፍሎች ላይ ጉዳት መድረሱ ተጠቁሟል።
መንስኤው እየተጣራ ነው ተብሏል።
#WolaitaZoneAdministration
#TikvahEthiopiaFamilyWolaitaSodo
@tikvahethiopia
ቪድዮ / ፎቶ ፦ በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ላይ የእሳት አደጋ ተከስቷል።
እሳቱን ለመቆጣጠር ርብርብር እየተደረገ ነው።
ቪድዮ/ፎቶ ፦ MT
#TikvahEthiopiaFamilyWoliataSodo
@tikvahethiopia
በሰላም ተጠናቋል !
እጅግ ከፍተኛ ምዕመን የተገኘበት ዓመታዊው የቁልቢ ቅዱስ ገብርኤል የንግስ በዓል በሰላምና በድምቀት ተከብሮ መጠናቀቁን የፀጥታ ኮማንድ ፖስት አሳውቋል።
ኮማንድ ፖስቱ የትራፊክ አደጋን ጨምሮ ምንም ዓይነት ያጋጠመ ችግር እንዳልነበረ ገልጿል። #ኤፍኤምሲ
@tikvahethiopia
ፎቶ፦ ዓመታዊው የቅዱስ ገብርኤል የንግስ በዓል በቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስነ ሥርዓቶች በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።
ዛሬ ሐምሌ 19 እየተከበረ ባለው የዓመቱ የቅዱስ ገብርኤል ንግስ በዓል ላይ እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ምዕመን ቁልቢ ተገኝቷል።
#ቅዱስገብርኤል #ሐምሌ19
የፎቶ ባለቤት ፦ ኤፍኤምሲ
@tikvahethiopia
#USA #Egypt
የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ቢሮ ለግብፅ የ4.7 ቢሊየን ዶላር የመሳሪያ ሽያጭን አፅድቋል።
በመሳሪያ ሽያጩ መሰረት ግብፅ ራዳር፣ ሚሳኤሎች እና የሎጅስቲክስ እንደዚሁም የኢንጂነሪንግ ድጋፎችን ከአሜሪካ ታገኛለች።
አሜሪካ ለግብፅ የምትሰጠው የአየር ስርዓት መሳሪያ ሂሊኮፕተሮችን፣ ድሮኖችን እንደዚሁም ክሩዝ ሚሳኤሎችን ለመመከት ያስችላል።
አሜሪካ ይህንን ሽያጭ የኔቶ አባል ሃገር ካልሆኑት ዋነኛ አጋሮቿ ውስጥ የሆነችው የግብፅን ደህንነት ለማሻሻል መሆኑን ገልፃ ይህም በመካከለኛው ምስራቅ ሰላም እና የኢኮኖሚ ዕድገት እንዲኖር ያስችላል ብሏል።
በተጨማሪ ለግብፅ ጦር ስልጠና እና የቴክኒክ ድጋፍ ለማድረግ 26 የአሜሪካ መንግስት ሰራተኞች እና 34 ኮንትራክተሮች ወደ ግብፅ ያመራሉ ተብሏል።
የመሳሪያ ሽያጩን የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ቢሮ ያፀደቀው ሲሆን በቀጣይ የኮንግረሱ ውሳኔ ይቀረዋል።
ከ1979 ጀምሮ ግብፅ ከእስራኤል ጋር የሰላም ስምምነት በመፈራረሟ ከአሜሪካ የመሳሪያ ሽያጭ እና ድጋፍ በገፍ እያገኘች እንደሆነች ይታወቃል።
ግብፅ በተመሳሳይ በ2024 የ5 ቢሊየን ዶላር የመሳሪያ ግዢን ከአሜሪካ ፈፅማለች።
ሃገረ ግብፅ ከእስራኤል በመቀጠል ከአሜሪካ ሁለተኛዋ ከፍተኛ የወታደራዊ ድጋፍ የሚደረግላት ሃገር ስትሆን ከ1979 ጀምሮ በየአመቱ የ1.3 ቢሊየን ዶላር ወታደራዊ ድጋፍ ከአሜሪካ ታገኛለች።
የመረጃው ምንጮች አልጀዚራ፣ ማዳማስር ፣ እና ዲፌንስፖስት ናቸው።
Via @TikvahethMagazine
✨ንብተራ ኦንላይን ✨
በየትኛውም ጊዜ፣ በየትኛውም ቦታ!
***
ይሠሯል ከልብ፣ እንደ ንብ!
@Nibinternationalbanksc
#Nib #nibmobilebanking #NibQR #nib #nibtera #nibbank
Facebook / Instagram / linkedin / nibinternationalbank6204">X / nibinternationalbank6204">Youtube / nibinternationalbank">Tiktok / Website
#Update
የኢትዮጵያ ፓለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ከሰላም ሚኒስቴር ጋር በመተባበር " ሰላምን በማጽናት የፓለቲካ ፓርቲዎች ሚና " በሚል መሪ ቃል በቢሾፍቱ ሲያካሂድ የነበረውን የሰላም ኮንፈረንስ ' የቢሾፍቱ ቃልኪዳን ' መግለጫ በማውጣት አጠናቋል።
ይህ ቢሾፍቱ ቃልኪዳን መግለጫ 7 አንቀጾችን የያዘ ነው።
ቃልኪዳኑ ምን ይላል ?
አንቀጽ 1. ሠላማዊና የሠለጠነ የፖለቲካ አካሄድ የመከተል ቃል ኪዳን።
" የፖለቲካ ዓላማችንን በዲሞክራሲያዊ እና በሕግና በስርዓት እናከናወናለን " ብለዋል።
" ጸጥታን በማደፍረስ፣ የስም ማጥፋትና ጥላቻ እንዲሁም ለሰዉ ህይዎትና ንብርት መጥፋት ምክንያት ባላመሆን ለሰላም እንተጋለን " ሲሉ ገልጸዋል።
አንቀጽ 2 ፦ ለዲሞክራሲ ተቋማትና እሴቶች ክብር የመስጠት ቃል ኪዳን።
" ሕግና ሥርዓት፣ የህዝብ ውሳኔ ወሳኝነት፣ የምርጫ ሂደቶችና ዉጤት እንዲከበሩ " እንደሚሰሩ ገልጸዋል።
" በውሳኔዎች ላይ ልዩነት ቢኖር እንኳ ህጋዊነትን በማክበር አቋማችንን እናራምዳለን " ብለዋል።
አንቀጽ 3 ፦ ለአካታችነት፣ ለሀገራዊ መግባባትና ብሄራዊ ጥቅም አብሮ የመቆም ኪዳን።
" ያሉንን ልዩነቶችን ክብርና ልዩ ትኩረት በመስጠት ለህብረብሄራዊነት እሳቤ ግንባታ ለመስራት ተስማምተናል " ሲሉ አሳውቀዋል።
የወጣቶች፣ የሴቶችና የአካል ጉዳተኞች ተሳትፎ እንድያድግ በትኩረት እንደሚሰሩና ለብሄራዊ ጥቅም አብሮ የመቆም የፖለቲካ ባህል እንደሚገነቡ ገልጸዋል።
አንቀጽ 4 ፦ ለዲሞክራሲያዊ መልካም አስተዳደር መስፈን የመስራት ቃል ኪዳን።
" በአጀንዳ፣ በፖሊሲ፣ በችሎታ ላይ የተመሰረተ ፖለቲካዊ ስርዓት ለመገንባት እንሰራለን። የተለያዩ የፖለቲካ አስተሰሰብና ፍላጎት መኖር እንደ ጤናማ ዲሞክራሲ ምልክት እንቀበላለን " ብለዋል።
አንቀጽ 5 ፦ የግጭት አያያዝ እና የሰላም ግንባታ ዉጤታማነት የመስራት ቃል ኪዳን፡፡
" በየፓርቲዎቻችን ውስጥና በሌሎች ፓርቲዎች መካከል ለግጭቶች ምክንያት የሚሆኑ ጉዳዮች ላይ የመፍትሄ ሥርዓቶችን እንገነባለን " ያሉ ሲሆን " በማህበረሰብ፣ በአካዳሚያ፣ በተለያዩ መድረኮች እና ከፖለቲካ አመራሮች ጋር በሚካሄዱ የሰላም ውይይቶች በአጋርነት እንሳተፋለን " ብለዋል።
አንቀጽ 6 ፦ የግልጽነትና የተጠያቂነት መርህ የመዳበር ቃል ኪዳን፡፡
" በመንግስት እንዲሁም በፓርቲያችን ውስጥ ግልጽነት፣ የሐሳብ ነጻነትና መተማመን እንዲጎለብት እንተጋለን። የህዝብ ተሳትፎ የሚገድብ ሥራ እና ተቋማዊነት የሚጎዳ የፖለቲካ አካሄድ በጋራ አንታገላለን " ሲሉ በቢሾፍቱ ቃልቂዳን ላይ አስፍረዋል።
አንቀጽ 7 ፦ ለብሄራዊ ጥቅም እና ለዲሞክራሲ ስርዓት የመጽናት ቃል ኪዳን፡፡
" በሰላም፣ በዉጫዊ ችግሮች፣ በብሄራዊ ምርጫ እና በመንግሥት ልማት አካል እንደአንድ አካል እንሰራለን። በኢትዮጵያ የዜጎችና ህዝቦች ክብር እና በሀገራች የጋራ ዕጣ ፋንታችን ላይ በጋራ በመቆም ለተረጋጋ የፖለቲካ ስርዓት ለማጽናት እንሰራለን " ብለዋል።
#EthiopianPoliticalPartiesJointCouncil
#MinistryofPeace
@tikvahethiopia