#NGAT
ሀገር አቀፍ የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) አመልካቾች ምዝገባ ከታህሳስ 21 እስከ 25/2017 ዓ.ም ይከናወናል፡፡
ለመመዝገብ 👇
HTTPS://NGAT.ETHERNET.EDU.ET
ከምዝገባው ጋር ለተያያዘ ማንኛውም ጥያቄ በሥራ ሰዓት በኢሜል አድራሻ ngat@ethernet.edu.et ወይም በስልክ ቁጥር 0920157474 (Enatnesh Gebeyehu) እና 0911335683 (Fasil Tsegaye) ማብራሪያ መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን ተገልጿል።
የመፈተኛ ' USER NAME ' እና " PASSWORD ' በመመዝገቢያ ፖርታል በኩል የሚላክ ሲሆን፤ የመመዝገቢያ ክፍያ ብር 750 በቴሌብር በኩል ብቻ መፈጸም ይጠበቅባችኋል ተብሏል፡፡
ፈተናው የሚሰጥበትን ጊዜ በቀጣይ እንደሚያሳውቅ ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል፡፡
#MoE
Via @tikvahuniversity
#ብርሃን_ባንክ
#ይቀበሉ_ይመንዝሩ_ተጨማሪ_2%_ #እና_ልዩ_የበአል_ስጦታዎን_ይውሰዱ
ከውጪ ሃገራት የሚላክልዎትን ገንዘብ ከብርሃን ባንክ ጋር ከሚሰሩ አለምአቀፍ የገንዘብ አስተላላፊዎች #ሪያ #ዳሃብሽል #ዌስተርን_ዩኒየን #መኒግራም #ትራንስ_ፋስትና #ወርልድ_ረሚት በኩል ሲቀበሉ ወይም በእጅዎ ያለውን የውጭ ሃገር ገንዘብ በባንካችን ሲመነዝሩ ከእለቱ የምንዛሪ ተመን በተጨማሪ 2% እና ልዩ የበዓል ስጦታ ያገኛሉ!
እንደ ስማችን ብርሃን ነው ስራችን!
#moneytransfer #Stressfreebanking #berhanbank #bank #finance #bankinethiopia
ከታች የሚገኙትን ሊንኮች በመጫን የማህበራዊ ድህረ-ገጾቻችንን ይቀላቀሉ!
➡️ Facebook
➡️ Telegram
➡️ Instagram
➡️ Twitter
➡️ LinkedIn
➡️ YouTube
#Earthquake አዋሽ ፈንታሌ አካባቢ በተደጋጋሚ እየተከሰተ ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ አሁንም ቀጥሏል።
ንዝረቱ አዲስ አበባ ድረስ የተሰማ በሬክተር ስኬል 5 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ በድጋሚ ተከስቷል።
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፤ የጂኦፊዚክስ እና ስፔስ ሳይንስ ዳይሬክተር የሆኑት ኤሊያስ ሌዊ (ዶ/ር) ፤ ዛሬ ምሽት 2 ሰዓት ላይ በሬክተር ስኬል 5 ሆኖ የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረቱ በአዲስ አበባ በተደጋጋሚ መሰማቱን ተናግረዋል።
" በአካባቢው ያለው የቅልጥ ዓለት ድንጋይ (ማግማ) እንቅስቃሴ አሁንም ቀጥሏል " ያሉት ኤልያስ (ዶ/ር) " የመሬት መንቀጥቀጥ በተደጋጋሚ እንዲከሰት እያደረገ ያለውም ይኸው ነው " ሲሉ ለብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ተናግረዋል።
@tikvahethiopia
በሲዳማ ክልል በደረሰ አሰቃቂ የመኪና አደጋ ከ70 በላይ ሰዎች ህይወታቸው አለፈ።
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምስራቃዊ ሲዳማ ዞን በቦና ዙሪያ ወረዳ ጋላና ወንዝ ተብሎ በሚጠራዉ ድልድይ ላይ ከ70 በላይ ሰርገኞችን ይዞ ወደ በንሳ ወረዳ ሲጓዝ የነበረ አይሱዙ ክፍት መኪና ድልድዩን ስቶ ወንዝ ዉስጥ መግባቱን የበርካታ ሰዎች ህይወት ማለፉን የሲዳማ ክልል መንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስታዉቋል።
ቢሮው " እስካሁን ቁጥሩ ያልታወቀ ሰዉ ሕይወት አልፏል " ሲል ገልጿል።
የክልሉ ፖሊስ በሰጠን ቃል 71 ሰዎች ህይወታቸው ማለፉን አሳውቋል።
የአደጋ መንስኤ እየተጣራ ሲሆን አጠቃላይ የተጠቃለለ መረጃ ይገለጻል።
ነፍስ ይማር !
@tikvahethiopia
የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን ገንዘብ እያሰባሰበች ነው ?
👉 " ምዕመናን ፤ ቅዱሳን ገንዘባችሁን እንዳትበሉ ተጠንቀቁ " - መጋቢ ለወየሁ ስንሻው
➡ " የሚታየው የባንክ አካውንት ሆነ መልዕክት እኛ የማናውቀው ነው " - አገልጋይ ዮናታን አክሊሉ
" በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች ያሉ የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን አጥቢያ ቤተክርስቲያናት ከፓስተር/መጋቢ ዮናታን አክሊሉ ጋር በመተባበር የገቢ ማሰባሰቢያ / ገንዘብ መሰብስበ ስራዎች እየሰሩ ነው " በሚል በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ እንደሆነ ተገልጸ።
የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን በሰጠችው ይፋዊ መግለጫ ፥ የባንክ ቁጥር ጭምር በመግለጽ የተለያዩ ፖስተሮችንም በማሰራት በማህበራዊ ሚዲያ ላይ እየተደረገ ያለው የገንዘብ የማሰባሰብ እንቅስቃሴ ፍጹም የማታውቀው ስራ እንደሆነ ገልጻለች።
የቤተክርስቲያኗ ምክትል ፕሬዜዳንት መጋቢ ለወየሁ ስንሻው ፤ " ከወንድማችን ዮናታን አክሊሉ ጋር በዚህ ስራ ዙሪያ ንግግር አላደርግንም ይህንን መግለጽ እንፈልጋለን " ብለዋል።
የባንክ አካውንቶቹ በአንድ ግለሰብ ስም እንደተከፈቱ እንደተደረሰበትና ቤተክርስቲያኗ በሚመለከተው አካል በኩል ጉዳዩን እንደምትሄድበት ተገልጿል።
ጉዳዩ ቤተክርስቲያንን ያሳሰበና ያስደነገጠ እንደሆነ ተመላክቷል።
መጋቢ ለወየሁ ፤ " ምዕመናን ፣ ቅዱሳን የገንዘብ ማሰባሰቢያ ስራ የተባለው በፍጹም ማታለል እና ማጭበርበር የተሞላበት በመሆኑ በዚህ የማታለል ተግባር ገንዘባችሁን እንዳትበሉ፣ እንዳትሳተፉ " ሲሉ አሳስበዋል።
በተመሳሳይም አገልጋይ ዮናታን አክሊሉ ፥ ሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ በአዲስ አበባ ዙሪያ ካሉ የሙሉ ወንጌል አጥቢያ ቤተክርስቲያናት እና ከኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል ጋር በመተባበር የገቢ ማሰባሰቢያ እያካሄዱ እንደሆነ የሚገልጹት መልዕክቶች ፍጹም ሀሰተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል።
" በስሜ የተከፈተ ለዚህ የሙሉ ወንጌል አገልግሎት የሚውል የባንክ አካውንት እንደሌለ አሳውቃለሁ " ብለዋል።
አካውንቱን ማነው የከፈተው (በማስታወቂያዎች ላይ ያለውን) ስለሚለው ጉዳይም ፤ ማን እንደከፈረው እንደተደረሰበትና የቤተክርስቲያኒቱ እና የእሳቸውም የህግ ክፍል ጉዳዩን እንደሚከታተለው ጠቁመዋል።
" በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የሚታየው የባንክ አካውንት ሆነ መልዕክት እኔን እና ቤተክርስቲያናችንን የአዲስ ካህናት ቤተክርስቲያን የማይመለከት የማናውቀው ነው " ብለዋል።
" እራሳችሁን ከዚህ የማታለል ስራ ጠብቁ ፤ ምንም ተሳትፎም እንዳታደርጉ " ሲሉ አሳስበዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#Update
" ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቃዎች ታግተዋል " የተባሉት 3 የትግራይ ቴሌቪዥን ጋዜጠኞች ሜይሊ ተብሎ በሚጠራ ቦታ በሚገኝ እስር ቤት እንደሚገኙ የትግራይ ቴሌቪዥን ከደቂቃዎች በፊት ማረጋገጡ ይታወሳል።
አሁን ከስፍራው በተገኘው መረጃ ሦስቱ ጋዜጠኞች ከእስር ተለቀዋል።
የጋዜጠኞቹ መፈታት በማስመልከት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው ፥ ጋዜጠኞቹ መረጃ በማሰባሰብ ስራ እያሉ በአከባቢው በሚገኙ ፓሊስ እና ሚሊሻዎች ነው የተያዙት።
ጋዜጠኞቹ በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ ከወረዳው የፀጥታ እና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት መካከል በተደረሰ መግባባት ከሰዓታት እስር ሊለቀቁ ችለዋል።
ጋዜጠኞቹ በአከባቢው ያለውን ህገ-ወጥ የወርቅ ማዕድን ቁፋሮና ዝውውር የሚመለከት የምርመራ ዘገባ በመስራት ላይ እንደነበሩ ለወረዳው የፀጥታ እና አስተዳደር አካላት የተናገሩ ሲሆን የጋዜጠኞች እስር እና እንግልት በክልሉ ካለው የፓለቲካ ቀውስ ትስስር አለው ተብሏል።
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
@tikvahethiopia
#Update
ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቃዎች የታገቱት ሦስት የትግራይ ቴሌቪዥን ጋዜጠኞች በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን አስገደ ወረዳ ሜይሊ ተብሎ በሚጠራ ቦታ በሚገኝ እስር ቤት እንደሚገኙ የትግራይ ቴሌቪዥን ማረጋገጡን አስታውቋል።
ጋዜጠኞቹ ከህገ-ወጥ የወርቅ ማዕድን ፍለጋ እና ዝውውር ጋር ተያይዞ ስለሚነሳው ጉዳይ ለማጥራት በተሰማሩበት ነው በታጣቂዎች መታገታቸው የተበገረው።
አሁን ላይ ጋዜጠኞቹ እስር ቤት እንዳሉ ተነግሯል።
@tikvahethiopia
#ካናዳ
በካናዳ፣ ሀሊፋክስ ኤርፖርት ሲያርፍ የነበረ አንድ የመንገደኞች አውሮፕላን በእሳት መያያዙ ተሰምቷል።
73 መንገደኞችን እና የበረራ ሰራተኞችን የያዘው በፒኤኤል አየር መንገድ የሚሰራው የኤር ካናዳ በረራ ቁጥር 2259 አውሮፕላን በሚያስደነግጥ አኳኋን ሊቆም ችሏል።
በህይወት ላይ የደረሰ ጉዳት እንደሌለ ተነግሯል።
ከሴንት ጆንስ ተነስቶ ሀሊፋክስ ኤርፖርት ሲያርፍ የነበረው አውሮፕላን የቴክኒክ ችግር እንዳጋጠመው ነው የተነገረው።
አውሮፕላኑ ሲያርፍ ከማረፊያው መንገድ ወጥቶ በእሳት ተያይዟል።
ለሲቢሲ ኒውስ ቃላቸውን የሰጡ አንድ መንገደኛ ፥ " አውሮፕላኑ በሚያርፍበት ወቅት አንዱ ጎማ በትክክል አልተዘረጋም ነበር ፤ በጣም የሚያስፈራ ድምጽም ነበር " ብለዋል።
አንዱ የአውሮፕላን ክፍል በእሳት መጋየቱን ነው የጠቆሙት።
የክስተቱ ምክንያቱ እየተመረመረ ነው ተብሏል።
@tikvahethiopia
በደቡብ ኮሪያ ፣ ሙዋን በደረሰው አሰቃቂ የአውሮፕላን አደጋ አውሮፕላኑ ውስጥ ከነበሩት 181 ሰዎች 177 ሰዎች መሞታቸው መረጋገጡን " ሮይተርስ " ዘግቧል።
የቀሩት ሁለት ሰዎች በህይወት ይገኛሉ የሚለው ተስፋ እየተሟጠጠ ነው ተብሏል።
ንብረትነቱ የ " ጄጁ አየር መንገድ " በሆነው Boeing 737-800 የአውሮፕላን አደጋ በህይወት የተረፉት ሁለት ሰዎች ሲሆኑ እነሱም የበረራ ሰራተኞች ናቸው። የደረሰባቸው ጉዳት ለህይወታቸው የሚያሰጋ አይደለም ተብሏል።
ምንም እንኳ የአደጋው መንስኤ እየተመረመረ ቢሆንም ባለስልጣናት ግን " ከወፍ ተጋጭቶ ነው " ብለዋል። ከአደጋው ቀደም ብሎ የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች አውሮፕላኑን የወፎች ጥቃት ስጋት እንዳለ አሳውቀው ነበር ተብሏል።
ከአደጋው በህይወት ከተረፉ የበረራ አባላት መካከል እንደተሰማው ከአደጋው ቀደም ብሎ የወፎች ጥቃት እንደነበር መጠቆሙን " ዘጋርዲያን " ዘግቧል።
@tikvahethiopia
ቪድዮ፦ በአስደንጋጩ አውሮፕላን አደጋ እስካሁን 151 ሰዎች ሞቱ።
በደቡብ ኮሪያ ውስጥ በማረፍ ላይ የነበረ አንድ አውሮፕላን ባጋጠመው አደጋ እስካሁን ድረስ 151 ሰዎች መሞታቸው ተሰምቷል።
" ጄጁ " የተባለው አየር መንገድ ንብረት የሆነው አውሮፕላን ከባንግኮክ መጥቶ በደቡብ ኮሪያው ሙዋን አየር ማረፊያ ሲያርፍ ነበር መንገዱን ስቶ የአውሮፕላኑ የፊተኛው ክፍል በእሣት ሲያያዝ የታየው።
ምንም እንኳ እስካሁን ድረስ የአደጋው መንስዔ ባይታወቅም የእሣት አደጋ አገልግሎት " ምናልባት ከወፍ ተጋጭቶ አሊያም ባለው ከባድ የአየር ፀባይ ምክንያት ሊሆን ይችላል " ብሏል።
አውሮፕላኑ 181 ሰዎች አሳፍሮ ነው ከታይላንድ የተነሳው።
አብዛኛዎቹ ደቡብ ኮሪያዊያን መሆናቸውን መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
እስካሁን አንድ ተሳፋሪና አንድ የበረራ ሠራተኛ በሕይወት ሲተርፉ ሌሎች ከአደጋው የተረፉ ሰዎችን የማዳን ሥራው መቀጠሉን ቢቢሲ ኒውስ ፣ ቲአርቲ ወርልድና ሮይተርስ ዘግበዋል።
ቪድዮ ፦ ከማህበራዊ ሚዲያ
@tikvahethiopia
ዮናታን ቢቲ ፈርኒቸር !
በዓሉን ምክንያት በማድረግ በዕቃዎቻችን ላይ ልዩ ቅናሽ ማድረጋችንን ስናበስርዎ በታላቅ ደስታ ነው!
እነዚህን ረቂቅ የንድፍ ጥበብ የሚታይባቸውን ውብ ዕቃዎች ገዝተው የቤትዎን ድባብ ይቀይሩ!
የውበት፣ የጥራት እና የምቾት ዳር ድንበር ዮናታን ቢቲ ፈርኒቸር!
🌐 የማህበራዊ ገጾቻችንን ይቀላለቀሉ
Telegram 👉 Telegram/yonatanbtfurniture
Facebook 👉 Facebook/yonatanbtfurniture
Instagram👉Instagram/yonatanbtfurniture
TikTok 👉 yonatanbtfurniture?is_from_webapp=1&sender_device=pc">TikTok/yonatanbtfurniture
📍አድራሻችን፦
1. ፒያሳ እሪ በከንቱ ቢቲ ታወር (ከኢቲዮ ሴራሚክ ዝቅ ብሎ)
2. ከዊንጌት አደባባይ አለፍ ብሎ ከአቢሲኒያ ባንክ ፊትለፊት
3. ከሲኤምሲ አደባባይ ወደ አያት መንገድ መሪ ሳይደርስ (ዘመን ባንክ አጠገብ)
ስልክ ፦ +251957868686/ +251995272727/ +251993828282
#Earthquake : ዛሬ ቅዳሜ ምሽት ጨምሮ ቀን ላይ ተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ እንደነበር የአፋር ቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት ገልጸዋል።
የመሬት መንቀጥቀጥ ድግግሞሹ እየጨመረ ነው ብለዋል።
አንድ የቤተሰባችን አባል፥ " አላህ መፍትሄውን ይስጠን ፤ ያረጋጋው እንጂ እጅግ በጣም ያስፈራል ፤ የዓለሙ ፈጣሪ አላህ መጨረሻችንን ያሳምረው " ሲል ገልጿል።
መሬት መንቀጥቀጡ እየፈጠረ ያለው ንዝረት በተለያዩ ከተሞችም መሰማቱን ለመረዳት ችለናል።
በፈንታሌ አካባቢ በተደጋጋሚ የተለያየ መጠን ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ እየተከሰተ የሚገኝ ሲሆን ትላንትና ከፍተኛ የሆነው በሬክተር ስኬል 5 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቶ ነበር።
#TikvahEthiopiaFamilyAfar
@tikvahethiopia
#Somalia #Djibouti
ከቀናት በፊት ኤርትራ አስመራ የነበሩት የሶማሊያው ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሙሀመድ ዛሬ ጅቡቲ ገብተዋል።
ወደ ጅቡቲ ያቀኑት በፕሬዜዳንት ኢስማኤል ኡማር ጌሌህ ግብዣ እንደሆነ ተነግሯል።
ሁለቱ መሪዎች በሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ እንደሚወያዩ ተገልጿል።
@tikvahethiopia
#Update
🚨 " የመብት ጥየቄ በማንሳታችን ከስራ ታግደናል " - የመስፍን ኢንዳስትሪያል ኢንጅነሪንግ ሰራተኞች
🔴 " ባልተገባ አመፅ ድርጅቱን በማክሰራቸው ምክንያት ለ30 ቀናት ከስራ እንዲታገዱ ተወሰኗል " - ድርጅቱ
በመቐለ ከተማ የሚገኘው የትእምት (EFORT) ድርጅቶች አህት ኩባንያ በሆነው መስፍን ኢንዳስትሪያል ኢንጅነሪንግ እና ሰራተኞቹ መካከል የተፈጠረው ሰጣ ገባ ከጀመረ ቆይቷል።
ሰራተኞች ያሉባቸው የመብት እና ጥቅማ ጥቅም ጥያቄዎች እንዲፈቱላቸው በወርሃ ጥቅምት 2017 ዓ.ም ሰላማዊ ስልፈው አድርገው ነበር።
ያነሱዋቸው ጥያቄዎች ሳይመለሱ በመቅረታቸው ለሁለተኛ ጊዜ በያዝነው ወር ሁለተኛ ሳምንት መጀመሪያ ካለፈው የቀጠለ ሰላማዊ ሰልፍ አካሂደዋል።
ሰራተኞቹ ታህሳስ 11/2017 ዓ.ም ባካሄዱት ሰላማዊ ሰልፍ ፦
- በድርጅቱ የሰራተኞች አስተዳደር መመሪያ መሰረት በውድድር የተሰጠን የእድገት እርከን የሚመጥን ደመወዝ እንዲሰጠን ብንጠይቅም ' በጀት የለም ' በሚል ጥየቄያችን ጀሮ ዳባ ልበስ ተብሏል።
- ለድካም እና ልፋታችን የሚመጥን ደመወዝ ስለማይከፈለን ኑሮሯችንን ለመምራት ተቸግረናል።
- አንድ የሙያ እና የጉልበት ሰራተኛ በቀን ከ50 አስከ 200 ብር ነው የሚከፈለው በዚህ አነስተኛ ክፍያ ቤተሰብ ይቅር እና ራስን ማስተዳደር አቅቶናል ስለሆነም አስፈላጊ የደመወዝ ጭማሪ ይደረግልን።
- ለ10 አመታት የቆየው ጥያቄያችን " ስትራክቸር እየተሰራ ነው " በሚል ሽፋን ምክንያት እየተንከባለለ ቆይቶ በአሁኑ ወቅት " የፈለገ ይስራ ፤ ያልፈለገ ይሂድ " ወደ ማለት ተገብቷል ይህ ልክ አይደለም።
- አቅማችን አሟጠን እየሰራን የልፋታችን እያገኘን አይደለምን ... ሲሉ ድምፃቸው አሰምተዋል።
የድርጅቱ የገበያ ልማት እና የሰው ሃይል አስተዳደደር ታህሳስ 17/2017 ዓ.ም ባወጣው ማስታወቅያ ፤ ሰራተኞቹ ከታህሳስ 11 እስከ 16/2017 ዓ.ም የስራ ማቆም አድማ በማድረግ ድርጅቱን ላልተገባ ኪሳራ በመጣላቸእ ከታህሳስ 17/2017 ዓ.ም ጀምሮ ለ1 ወር ከስራ እንዲታገዱ መወሰኑን አስታውቋል።
ለአንድ ወር ከስራ የታገዱት ሰራተኞች ቁጥራቸው 250 መሆኑን ደርጅቱ ስማቸው ጠቅሶ ይፋ አድርጓል።
" የድርጅቱ ማኔጅመንት መብታችሁ እና የሚገባችሁ ለምን ትጠይቃላችሁ ? ለምን አጋላጥችሁን ? ስማችንን ጥላሸት ቀብታችሁታል ብሎ የወሰደው እርምጃ ተቀባይነት የለውም " ሲሉ ሰራተኞቹ ተቃውሟቸውን አሰምተዋል።
መስፍን ኢንዱስትሪያል ኢንጅነሪነንግ በብረታ ብረትና ሞደፊክ ስራዎች የተሰማራ ከትእምት (EFORT) ግዙፍ ካምፓኒዎች አንዱ መሆኑ ይታወቃል።
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
@tikvahethiopia
ፎቶ ፦ ዓመታዊው የታኅሣሥ 19 የሊቀ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል የንግሥ በዓል በሐዋሳ ከተማ ተከብሯል።
የንግሥ በዓሉ እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ኦርቶዶክሳውያን በተገኙበት ነው የተከበረው።
የሲዳማ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ በዓሉ ያለ አንዳች ኮሽታ በሰላም በከፍተኛ ድምቀት ተከብሯል ብሏል።
የፎቶ ባለቤት ፦ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር
@tikvahethiopia
" ከ2 ሺሕ 500 በላይ ሰዎች ተፈናቅለዋል " - አቶ አደም ባሂ
በአፋር ክልል አዋሽ ፈንታሌ አከባቢ በሚከሰት ተደጋጋሚ ርዕደ መሬት ከ100 በላይ ቤቶች ጉዳት የደረሰባቸዉ ሲሆን 2 ሺሕ 560 ሰዎች መፈናቀላቸውን እና እንሰሳት መሞታቸውን የአዋሽ ፈንታሌ ወረዳ አስተዳደር አቶ አደም ባሂ አሳውቀዋል።
ለአሐዱ በሰጡት ቃል ፤ " ይህ ክስተት በሚድያ እንደሚባለዉ በቀን ሦስቴ እና ሁለቴ የሚከሰት ሳይሆን ከዚያም በላይ አስጊ እየሆነ ይገኛል " ብለዋል።
በአካባቢዉ ያለዉ የከሰም ግድብን ጨምሮ ሌሎች መሰረተ ልማቶችስ ጉዳት ደርሶባቸዋል ወይ ? ለሚለው ጥያቄ " ግድቡን በተመለከተ ራሱን የቻለ አደረጃጀት ተደራጅቶ እየተጠበቀ ይገኛል " ሲሉ ተናግረዋል።
" እስካሁን በተፈጠረዉ ርዕደ መሬት ምክንያት ምንም ጉዳት ባይደርስበትም፤ በተደጋጋሚ በአቅራቢያው እየተከሰተ በመሆኑ በጥብቅ እየተከታተሉ ነው " ሲሉ አክለዋል።
በተጨማሪም በአካባቢዉ ያለዉ ተፈናቃይ ቁጥር በየቀኑ እየጨመረ መሆኑን አንስተው ፤ መጠለያ፣ ምግብ እና መሰረታዊ ግብአቶች እንደሚያስፈልጉ ተናግረዋል።
የክልሉ የአደጋ ስጋት ድጋፍ እንዲያደርግም እንደጠየቁ ገልጸዋል።
በተደጋጋሚ ጊዜ በተከሰቱ የመሬት መንቀጥቀጦች ምክንያት፤ እስከ አሁን በአዋሽ ፈንታሌ ወረዳ ሳቡሬ እና ዶኾ ቀበሌዎች ከ30 በላይ የመኖሪያ ቤቶች ላይ ጉዳት መድረሱም ተነግሯል።
ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የአሐዱ ነው።
@tikvahethiopia
#Update
" በአደጋዉ ሙሽራዉን ጨምሮ የ71 ሰዎች ሕይወት አልፏል " - ማቴ መንገሻ (ዶ/ር)
🚨 " አደጋዉ ' ከቡና ሳይት በሚመለሱ ሰዎች ላይ የተከሰተ ነዉ ' ተብሎ የተገለፀት አግባብ ሙሽራዉን ጨምሮ አብዛኞቹ ሟቾች የቡና ሳይት የሚሰሩ በመሆናቸዉ ነው ! "
ዛሬ በሲዳማ ክልል፣ ምስራቃዊ ሲዳማ ዞን ቦና ወረዳ ልዩ ስሙ ጋላና ድልድይ ተብሎ በሚጠራዉ አከባቢ ሰርገኞችን ጭኖ ሲጓዝ የነበረ አይሱዙ መኪና ተገልብጦ ሙሽራውን ጨምሮ የ71 ሰዎች ሕይወት ማለፉን የምስራቃዊ ሲዳማ ዞን አስተዳዳሪ ማቴ መንገሻ (ዶ/ር) ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
" አይሱዙው 11 ሰዓት አካባቢ መነሻዉን ቦና ወረዳ ሚሪዴ ገጠር ቀበሌ አድርጎ ወራንቻ ወደተባለ አጎራበች ቀበሌ የወንድ ወገን የሆኑ ከ70 በላይ ሰርገኞችን ጭኖ ወደ ሴቷ ቤት ጉዞ ላይ ነበር " ብለዋል።
ገላና ድልድይ ላይ ሲደርስ ግን ድልድዩን ስቶ ወደ ወንዝ ዉስጥ በመግባቱ እስካሁን በተጣራዉ መረጃ አስክሬናቸው ቦና አጠቃላይ ሆስፒታል የደረሰ 66 እንዲሁም ከአደጋዉ ቦታ በቀጥታ ቤተሰቦቻቼዉ የወሰዷቸዉን ጨምሮ በአጠቃላይ ወንድ 68 ሴት 3 በድምሩ 71 ሰዎች ሕይወት ማለፉን አረጋግጠዋል።
በ4 ሰዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱንና አንዲት ሴት ወደ ሀዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል መላኳንም ማቴ (ዶ/ር) ጨምረው ገልፀዋል
የአደጋው ትክክለኛ መንስኤ እየተጣራ ነዉ ያሉት ማቴ (ዶ/ር) ፤ " በገጠር አከባቢ በሰርግ እና ደስታ ወቅት በክፍት መኪኖች ላይ ከመጠን በላይ መጫንና አልፎ አልፎም መጠጥ የመቀማመስ ሁኔታዎች ስለሚኖሩ፤ ይህ ለአደጋው አንዱ መንስዔ ተደርጎ ይገመታል " ብለዋል።
" አደጋዉ ' ከቡና ሳይት በሚመለሱ ሰዎች ላይ የተከሰተ ነዉ ' ተብሎ የተገለፀት አግባብ ሙሽራዉን ጨምሮ አብዛኞቹ ሟቾች የቡና ሳይት የሚሰሩ በመሆናቸዉና ተሽከሪካሪዉም የቡና ሳይት በመሆኑ ነዉ " ሲሉም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድተዋል።
የክልሉ ፖሊስ ቀደም ብሎ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል መኪናው ላይ የነበሩት ወገኖች የቡና ሳይት ስራ ላይ ቆይተው ሲመለሱ የነበሩ እንደሆኑ ገልጾ ነበር።
እንደ ዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ማብራሪያ ግን ምንም እንኳን መኪናው ላይ የነበሩት አብዛኛዎቹ ወገኖች (ሙሽራውን ጨምሮ) የቡና ሳይት ስራ ላይ ተሰማርተው የሚሰሩና መኪናውም የቡና ሳይት ቢሆንም በሰዓቱ ሲጓዙ የነበረውና አደጋው የደረሰው ለሰርግ ወደ ሴቷ ቤት ማለትም ሙሽራው ሙሽሪትን ለመውሰድ ሲሄዱ ነው።
በአደጋዉ ከአንድ ቤተሰብ እስከ 4 ሰዉ የሞተበት ሁኔታ ስለመኖሩ የገለጹት ማቴ ማንገሻ (ዶ/ር) የአደጋው ሰለባ የሆኑት ሁሉም ሟቾች ከ40 ዓመት በታች የሆኑ ወጣቶች ስለመሆናቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልፀዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa
@tikvahethiopia
" የ71 ሰዎች ሕይወት አልፏል " - ፖሊስ
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምስራቃዊ ሲዳማ ዞን በቦና ዙሪያ ወረዳ ጋላና ወንዝ ተብሎ በሚጠራዉ አከባቢ 74 ሰዎችን ጭኖ ሲጓዝ የነበረ አይሱዙ መኪና ድልድዩን ስቶ ወንዝ ዉስጥ በመግባቱ የ71 ሰዎች ሕይወት ማለፉን የክልሉ ፖሊስ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስታዉቋል።
የሲዳማ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሽመልስ ቶማስ አደጋዉን አስመልክቶ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደገለፁት " በመኪናው ላይ የነበሩት የቡና ሳይት ስራ ላይ ቆይተዉ ወደ ከተማ ሲመለሱ የነበሩ ሰዎች ናቸዉ " ብለዋል።
የአደጋዉ መንስኤ የተጣራ ሲሆን 68 ወንዶችና 3 ሴት በድምሩ 71 ሰዎች ሕይወት ማለፉን አረጋግጠዋል።
የተረፉት 3 ሰዎች ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዉ በሕክምና እየተረዱ መሆኑን የገለፁት ኮሚሽነሩ ለሟች ቤተሰቦች መፅናናትን ተመኝተዋል።
ነፍስ ይማር !
@tikvahethiopia
አል-ሲሲ ምን እያሉ ነው ?
ኢትዮጵያ እና ሶማሌላንድ ከባህር በር ጋር በተያያዘ የመግባቢያ ስምምነት ከተፈራረሙ ማግስት አንስቶ ከሶማሊያው መሪ ጋር እየተደዋወሉ እና እየተገናኙ ፦
" ° አይዟችሁ እኛ አለን ፤
° ከፈለጋችሁ ወታደርም እንልካለን ፣
° የጦር መሳሪያ ድጋፍም ይኸው፣
° በሰላም ማስከበርም እንሳተፋለን ፣
° እናተን ማንም እንዲነካ አንፈቅድም " እያሉ ሲለፍፉ የከረሙት የግብጹ መሪ አብዱል ፈታህ አል-ሲሲ አሁን ደግሞ የአንካራውን ስምምነት " በቅርበት እየተከታተልን ነው ፤ መረጋጋትንም ሊያመጣ ይችላል " የሚል ዲስኩር ይዘው ብቅ ብለዋል።
ድሮውንም የኢትዮጵያ ነገር አይኗን የሚያቀላው ግብፅ ከመግባቢያ ስምምነቱ (MoU) በኃላ ስለ ኢትዮጵያ ብዙ አሉታዊ ነገር ስታወራ ፣ የማጠልሸት ስራ ስትሰራ ነበር የከረመችው።
ትላንት የግብፁ መሪ አል-ሲሲ በቅርብ ኢትዮጵያ መጥተው ከነበሩትና የኢትዮጵያ የባህር ባር ጥያቄን በይፋ ከደገፉት የፈረንሳዩ ፕሬዜዳንት ማክሮን ጋር የስልክ ውይይት አድርገው ነበር።
በዚህም ወቅት ፥ አል ሲሲ በቱርክ አሸማጋይነት ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ የፈረሙትን ስምምነት ጠቅሰው " በቅርብ እየተከታተልን ነው ፤ ስምምነቱ በአፍሪካ ቀንድ ፀጥታ እና መረጋጋት ሊያመጣ ይችላል " ሲሉ ተናግረዋል።
" ይህ ስምምነት በአፍሪካ ቀንድ መረጋጋት እንደሚያመጣ ተስፋ አለኝ ዓለም አቀፍ ሕግን ተከትሎ ሊሆን ይችላል። በአፍሪካ ቀንድ ያለው መረጋጋት እና የግብፅ ብሔራዊ ጥቅምት የተሳሰሩ ናቸው " ሲሉ እንደገለጹም ተነግሯል።
አል-ሲሲ " ለሶማሊያ ድጋፍ ለማድረግ እንሰራለን ይህ ድጋፍ በሁለትዮሽ ግንኙነት አሊያም በአፍሪካ ሕብረት የሰላም አስከባሪ ሚሽን አማካይነት ነው " ብለዋል።
ግብፅ ፤ ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ቁርሾ ውስጥ በከረሙበት ወራት ስታወጣ የነበረው መግለጫና ስታደርግ የነበረው እንቅስቃሴ ሀገራቱን ወደ መግባባትና ሰላም እንዲመጡ ለማድረግ ሳይሆን ነገሩን ለማጋጋል ፣ ለማባባስ ፣ የለየለት ቀውስና ጦርነት እንዲፈጠር ለማድረግ የታስበ እንደሆነ አመላካች እንደነበር ብዙዎች የሚገልጹት ነው።
#Ethiopia🇪🇹
@tikvahethiopia
" የሰላም ችግር ከሁሉም በፊት ቀድሞ መፍትሔ ማግኘት አለበት " - ፕ/ር መረራ ጉዲና
ባለፈው ሳምንት የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ ፓርቲ (ኦፌኮ) አዲሱን ዋና ፅ/ቤቱን በአዲስ አበባ አስመርቋል።
የቀድሞ ሜክሲኮ የሚገኘው ዋና ፅ/ቤቱ በኮሪደር ልማት ምክንያት በመፍረሱ አዲሱን ቢሮ ቀበና አደባባይ አከባቢ ከፍቶ ስራ አስጀምሯል።
በዚህ ወቅት የኦፌኮ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ንግግር ያደረጉ ሲሆን " አሁንም ሀገራችን ትልቅ ችግር ውስጥ ናት " ብለዋል።
የሰላም ችግር ከሁሉም በፊት ቀድሞ መፍትሔ ማግኘት እንዳለበትም ገልጸዋል። ለዚህ ደግሞ ወደጦርነት የሚመሩትን የፖለቲካ ችግሮች በውይይት መፍታት እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል።
" የኦሮሞ ህዝብ ፍላጎትም ሆነ የሌሎች ብሔር ብሔረሰቦች ፍላጎት ዘላቂ ሰላም ፣ ጠንካራ የዲሞክራሲ ስርዓት እና በኢኮኖሚ የበለፀገች ኢትዮጵያን ማየት ነው " ያሉ ሲሆን፤ " ይሄን ከግብ ለማድረስ ኦፌኮ'ን ጨምሮ ሌሎች የተቃዋሚ ፖርቲ ህብረቶች ትግላቸውን ማጠናከር አለባቸው " ሲሉ ተናግረዋል።
በወቅቱ ተገኝተው የነበሩ የተለያዩ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች " ህዝቡ ላይ እየደረሰ ያላውን ችግር ለመፍታት ህብረታችንን በደንብ በማጠናከር እና ህዝቡን ከጎን በማሰለፍ አንድላይ መቀጠል ይኖርብናል " ብለዋል።
ኦፌኮ አዲሱን ዋና ፅ/ቤቱን ስራ ባስጀመረበት ወቅት " በአገሪቱ ውስጥ ባለው ወቅታዊ ሁኔታ እና በቀጣዩ ትግል አቅጣጫ ላይ ዝርዝር ውይይት ተደርጓል " ያለ ሲሆን " በዚህ መሠረት በጦርነቱ ጉዳት፣ በኢኮኖሚ ውድቀት ምክንያት የማህበራዊ መቃወስና ወደ መፍረስ እየተኬደ ካለው መንገድ ኢትዮጵያን ለመታደግ ትኩረት ይሰጣል " ብሏል።
#OFC #AddisAbaba
@tikvahethiopia
#Update : ጅቡቲ የሚገኙት የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞትዎስ (ዶ/ር) ከጅቡቲው ፕሬዚዳንት እስማኤል ኦመር ጊሌ ጋር ተገናኝተው ውይይት አድርገዋል።
የውይይቱ ዓላማ የትውውቅ እና በሁለቱ ወንድማማች ሀገሮች መካከል ያለውን የቆየ ወዳጅነት ለማጠናከር ነው የተባለ ሲሆን በውይይታቸው የሁለትዮሽና አህጉራዊ ጉዳዮችን አንስተው መምክራቸውን በጅቡቲ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ የተገኘው መረጃ ያሳያል።
@tikvahethiopia
#Tigray
በወርቅ ማዕድን ቁፋሮ እና ዝውውር ዙሪያ መረጃዎች በማሰባሰብ ላይ የነበሩ የትግራይ ቴሌቪዥን ጋዜጠኞች በታጣቂዎች መታገታቸውን ተቋሙ አስታወቀ።
የታገቱት ጋዜጠኞች ብዛት 3 እንደሆነ የገለፀው የሚድያ ተቋሙ ሞባይላቸው ከአገልግሎት ውጪ መደረጉን ጨምሮ ገልጿል።
ትግራይ ቴሌቪዥን " በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን ከህገ-ወጥ የወርቅ ማዕድን ፍለጋ እና ዝውውር ጋር ተያይዞ የሚነሳው ጉዳይ ለማጥራት የተሰማሩ ጋዜጠኞች ናቸው በታጣቂዎች የታገቱት " ሲል አሳውቋል።
ሦስት አባላት የያዘ የጋዜጠኞች ቡድን ዛሬ ታህሳስ 20/ 2017 ዓ.ም ከረፋዱ 3:00 ጀምሮ በአስገዳ ወረዳ ' ሜይሊ ' ተብሎ ከሚጠራ ልዩ ቦታ በምትገኘው መንደር ነው የታገቱት ተብሏል።
ጋዜጠኞቹ በአከባቢው ስላለው ህገ-ወጥ የወርቅ ማዕድን ቁፋሮና ዝውውር በማስመልከት በአካል ቦታው ድረስ በመሄድ የአከባቢውን ነዋሪዎች ፣ አርሶ አደሮችና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ሲያነጋግሩ እንደሰነበቱ የገለፀው የትግራይ ቴሌቪዥን " የጋዜጠኞች ቡድኑ በስራ እያለ በታጣቂዎች ሊታገት እና ሊታሰር ችሏል " ሲል አመልክቷል።
የታገቱት የጋዜጠኞች ቡድን ከረፋዱ 4:00 ጀምሮ ሞባይላቸው ከአገልግሎት ውጪ በመደረጉ ምክንያት ያሉበት ሁኔታ እና ድህንነታቸው ማረጋገጥ እንዳልተቻለ አመልክቷል።
ጋዜጠኞቹን የሚመለከት መረጃ ለመጠይቅ በአከባቢው ለሚገኙ የመንግስት አመራሮች ተደጋጋሚ የስልክ ሙከራ ቢያደርግም እንዳልተሳከለት የትግራይ ቴሌቪዥን አሳውቋል።
እገታውን ስለፈጸሙ ታጣቂዎች ማንነት በዝርዝር የተባለ ነገር የለም።
ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የትግራይ ቴሌቪዥን ነው።
@tikvahethiopia
#Earthquake አዋሽ አካባቢ በተደጋጋሚ እየተከሰተ ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ መቀጠሉን የአካባቢው ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እየገለጹ ናቸው።
ትላንት ምሽት እንዲሁም ዛሬ ጥዋት አካባቢ ጠንከር ያለ የመሬት መንቀጥቀጥ እንደነበር ጠቁመዋል።
እንደ ' አሜሪካ የጂኦሎጂካል ሰርቬይ ድረገጽ ' መረጃ ዛሬ እሁድ ከአዋሽ 33 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሬክተር ስኬል 4.8 የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቶ ነበር።
@tikvahethiopia
" ከ30 በላይ የመኖሪያ ቤቶች ጉዳት ደርሶባቸዋል " - አቶ አብዱ ዓሊ
በአፋር ክልል ጋቢ ረሱ ዞን በተደጋጋሚ እየተከሰተ ባለው የመሬት መንቀጥቀጥ ከ30 በላይ የመኖሪያ ቤቶች ጉዳት ደርሶባቸው ነዋሪዎች ሌላ አማራጭ እንዲፈልጉ ማስገደዱ ተነግሯል።
በአዋሽ 7 ከተማ አሥተዳደር፣ በአዋሽ ፈንታሌ እና አሚባራ ወረዳዎች በሚገኙ የተወሰኑ ቀበሌዎች የመሬት መንቀጥቀጥ በተደጋጋሚ እየተከሰተ መሆኑን የዞኑ ዋና አሥተዳዳሪ አብዱ ዓሊ ገልጸዋል፡፡
በዚህም እስከ አሁን በአዋሽ ፈንታሌ ወረዳ ሳቡሬ እና ዶኾ ቀበሌዎች ከ30 በላይ የመኖሪያ ቤቶች ላይ ጉዳት መድረሱን አረጋግጠዋል፡፡
ጉዳት በደረሰባቸውና ሌሎችም ሥጋት ባለባቸው መኖሪያ ቤቶች ያሉ ወገኖችን ከአካባቢያቸው ሳይርቁ ቀለል ባለ ባህላዊ ቤት እንዲኖሩ እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡
በሰው ላይ የተመዘገበ ጉዳት ባይኖርም በሰብል የተሸፈኑ ማሳዎች እና የመኪና መንገዶች ላይ የከፋም ባይሆን የመሰነጣጠቅ አደጋ መድረሱን ገልጸዋል።
ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የኤፍ ኤም ሲ ነው።
@tikvahethiopia
#Architecture
በፍልስጤም ሀገር ለሚገነባ ትምህርት ቤት በተዘጋጀ ዓለም አቀፍ የአርክቴክቸራል ዲዛይን ውድድር ላይ ኢትዮጵያውያኑ ፦
➡️ አርክቴትክት ዳንኤል ዋጁ
➡️ አርክቴርክት ቢንያም በውቀቱ
➡️ አርክቴክት ፍሬዘር አብርሃ ከ231 ተወዳዳሪ አርክቴክቶች መካከል " የጣልያንን ተወዳዳሪዎች " በመከተል የ2ኛ ደረጃ በመያዝ አጠናቀዋል።
አርክቴክቶቹ " Mobile school as an emergency Response in Palestine " በተሰኘ ርዕስ በተዘጋጀው በዚህ ውድድር ከአፍሪካ ብቸኛ የደረጃ ተወዳዳሪ መሆን እንደቻሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
ከዚህ በፊት ለተከታታይ 5 የተለያዩ ዓለም አቀፍ ውድድሮችን ለ3 አመት ያክል የሞከሩ ሲሆን በነሱም የተለያዩ ውጤቶችን አስመዝበው እንደነበር ከ3 አመት በኋሏ ግን በአምላክ እርዳታ ለዚህ ከፍተኛ ስኬት መብቃታቸውን ገልጸዋል።
ወጣቶቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላኩት መልዕክት " በሃገራችን ኢትዮጵያም ብሎም በአፍሪካ ብዙ እምቅ ችሎታ ያለቸው ወጣቶች አንዳሉም በጥቂቱ ማሳየት በመቻላችን እጅግ ደስተኞች ነን " ብለዋል።
በውድድሩ ላይ በአርክቴክቸር ሙያ የታወቁ ሎሬቶች እና ባለሙያዎች በዳኝነት ተሳትፈዋል።
ከዚህ ዓለማቀፍ ውድድር 2ኛ በመሆን በማጠናቀቃቸው የ2000 ዩሮ እና የእውቅና ሰርተፍኬት ተሸላሚ በመሆን የሃገራቸውን ስም አስጠርተዋል።
(ያሸነፉበትን ስራ ከላይ ይመልከቱ)
@tikvahethiopia
#Update
“ ከተማሪዎች ጋር የመጣላት ፍላጎት የለንም። ተማሪዎቹ መነሻ አይደሉም ለብጥብጡ መነሻው ራሱ ዩኒቨርሲቲው ነው ” - የክፍለ ከተማው ጸጥታ ጽ/ቤት
ከአዲሱ የምግብ ሜኑ ትግበራ ጋር በተያያዘ ቅሬታ ያቀረቡ የመቐለ ዩኒቨርሲቲ 27 ተማሪዎች ታስረው እንደነበር፣ በኋላም ከእስር እንደተፈቱ የኢትዮጵያ ተማሪዎች ኀብረት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መግለጹ ይታወሳል።
ቅድሚያ ለሰብዓዊ መብት ኢትዮጵያ የተሰኘው ድርጅትም፣ ተማሪዎች ከተወካዮቻቸው በሚገናኙበት ቴሌግራም ላይ በሜኑው ዙሪያ ተቃውሟቸውን አሰሙ በተባሉ 2 ተማሪዎች አማካኝነት በተነሳው ተቃውሞ “14 ተማሪዎች ታስረዋል” ሲል መግለጫ ማውጣቱ ይታወሳል።
ነገር ግን አሁንም እስር ላይ ናቸው ያላቸውን ተማሪዎችን ስም፣ ዲፓርትመንት እና ስንተኛ ዓመት እንደሆኑ በይፋ በዝርዝር የሰጠው መረጃ የለም።
የመቐለ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ኅብረት ምንም ተማሪ ሳይቀር መፈታቱን አሳውቋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ ታሰሩ የተባሉት ተማሪዎች ሁሉም ተፈቱ ? ሲል የኣዲ ሓቂ ክፍለ ከተማ ጸጥታ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ክብረዓብ ሰለሞንን ምላሽ ጠይቋል።
የጸጥታ ኃላፊው ምን መለሱ ?
“ የተማሪዎች ኀብረት ማለት የተማሪዎች ተወካዮች ናቸው። ስለዚህ እነርሱ ከእኛ ጋር አብረው እየሰሩ ነው። ተደብቀን ዋሽተን የምንሰራው ሥራ የለም።
ያደረሱት ጉዳት ትልቅ በመሆኑ ሊፈቱ ባይገባቸውም የጉዳዩ መነሻ እነርሱ ሳይሆኑ ዩኒቨርሲቲው ሊያቀርበው የሚገባውን ነገር ባለማቅረቡ የተነሳ ስለሆነ እንደዚህ አድርገዋል ብለን አናስርም በሚገባ አስተምሮ ሰጥተን አንድም ልጅ ሳይቀር ፈትተናቸዋል።
የታሰረ ተማሪ የለንም ለቀናቸዋል። አሁንም ድጋሚ የሚሰሩት ስራ አለ ግን እየተከላከልን ነው።
አስረን የነበረው 13 ተማሪዎችን ነው። ከ13ቱ መካከል ዋና ዋና ለብጥብጡ ተዋናይ የነበሩ ተማሪዎችን ልንለቃቸው አልፈለግንም ነበር።
የተማሪዎች ኀብረት ግን ‘እንደዚህ ከሚሆን እኛው ራሳችን እናስተካክለዋለን’ ስላሉን ለቀናቸው ችግሩ እንዲፈታ እየሰራን ነው ” ብለዋል።
ከሌላና ከኣዲ ሓቂ ፓሊስ ጣቢያ ታስረው የነበሩ 27 ተማሪዎች (13ቱ ኣዲ ሓቂ) ከተፈቱ በኋላ በቴሌግራም ተቃውሞ አስነሱ የተባሉ 14 ተማሪዎች በክልሉ የጸጥታ አካላት ታስረዋል ተብሏል፤ እነርሱ ተፈቱ ወይ ? ስንል በድጋሚ ጥያቄ አቅርበናል።
ኃላፊው ምን አሉ ?
“ ከተማሪዎች ጋር የመጣላት ፍላጎትም የለንም። ተማሪዎቹ መነሻ አይደሉም ለብጥብጡ፣ ለብጥብጡ መነሻው ራሱ ዩኒቨርሲቲው ነው።
ዩኒቨርሲቲው ማቅረብ የነበረበት ጽዳቱና መጠኑ የተጠበቀ ምግብ እኛ ስናየው ተማሪዎቹን ምን ሆናችሁ ነው ከዚህ ደረጃ የሚያደርስ ነው እንዴ ? የሚያስብል ቢሆን ጥሩ ነበር።
ነገር ግን ራሳችን ሂደን ያረጋገጥነው ትልቅ ማስረጃ እያለ ተማሪዎቹ ጋር መበጣበጥ አልፈለግንም።
ተማሪዎቹ ሀሳባቸውን ሊያቀርቡ ተሰብስበው፣ እኛም ሂደን ስናበቃ ‘የታሰሩት ካልተፈቱ አንረጋጋም’ አሉ። አታስቡ ከወገናቸው ጋር ነው ያሉት፤ ፓሊስ ማለት ወገናችሁ ነው ብለናቸዋል።
ከተረዳዳን የታሰሩትን ሂደን እናመጣቸዋለን። የብጥብጡ መነሻ ደግሞ እነርሱ (ተማሪዎቹ) አይደሉም። መነሻው ‘በምግብ እየተቸገርን ነው’ ማለታችሁ ነው። ስለዚህ የታሰሩን እንለቃቸዋለን ብለን ለቀናቸዋል ” ብለዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
🚨 #ትኩረት
ዝም አትበሉ !!
በሴቶች ፣ በተለይም ምንም በማያውቁ ፤ ክፉ ደጉን እንኳን በማይለዩ ትንንሽ ህጻናት ላይ የሚፈጸመው የግብረ ስጋ መድፍረት ተግባር እጅግ አሳሳቢ እጅግም እየከፋ እየሄደ ነው።
ውድ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ፥ መቼም ሴት ልጆቻችን ፣ እህቶቻችን ላይ ስለሚፈጸም የአስገድዶ መድፈር / የግብረ ስጋ ድፍረትናከዛ ጋር ተያይዞ ስለሚሰጡ ፍርዶች ብዙ ጊዜ መልዕክት መለዋወጣችን ይታወሳል።
ብዙዎችሁ በምትሰሙት ፍርድ እንደምታዝኑም ህጉ ሊስተካከል እንደሚገባ ስትገልጹ ኖራችኋል።
አንዳንድ ጊዜ " እንደው የሚሰጠው ፍርድ ለጆሮ የሚቀፍ ፣ ሰው ለማስተማርና ለመቅጣት ሳይሆን ወንጀለኞችንና ግፈኞችን ለማበረታታ " እንደሚመስል በመግለጽ መሰል መረጃዎች ለብዙሃን እንዳይሰራጩ የጠየቃችሁ ሁላ አላችሁ።
በተለይ በተለይ ሴት ህጻናትን የሚደፍሩ ሰዎች ምንም በማያጠያይቅ ሁኔታ ' የሞት ቅጣት ' እንዲጣልባቸውም የሚገልጽ ሀሳብ ስትፅፉ ነበር።
ከሰሞኑን ደግሞ የተሰሙት ከህጻናት የግብረ ስጋት ድፍረት / መድፈር ጋር የተያያዙ ፍርዶች በርካታ የቲክቫህ አባላትን አስቆጥቷል፤ አሳዝኗል።
ለመረጃ ይሆናችሁ ዘንድ ...
1. ተከሳሽ ሙሉነህ ኡጋሞ የ37 ዓመት ጎልማሳ ሲሆን የባለቤቱን እህት የሆነችውን የ12 ዓመት ህጻን ከ3 ዓመት በላይ በቆየ ጊዜ ውስጥ " ለማንም ሰው ከተናገርሽ እገልሻለሁ ! " በማለት በማስፈራራት በተደጋጋሚ አስገድዶ የግብረ ስጋት ድፍረት እንደፈጸመ የክስ መዝገቡ እንደሚያስረዳ የሲዳማ ክልል ፍትህ ቢሮ ገልጿል።
ተከሳሹ ወንጀሉን የፈጸመው ባለቤቱ በወሊድ ምክንያት ታማ ለ2 ወር ሪፌራል ሆስፒታል ከተኛችበት ከቀን 11/04/2013 ዓ.ም. ወንጀሉ እስከታወቀበት 27/05/2016 ዓ.ም. ድረስ መሆኑ ነው የተገለጸው።
የቀረበውን ክስ ተቀብሎ ሲያከራክር የቆየው የሀዋሳ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በሰውና በሰነድ ማስረጃ በማስደገፍ በቀን 16/04/2017 ዓ.ም. በዋለው ችሎት ተከሳሽን ጥፋተኛ በማለት #በ14_ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኗል፡፡
2. የገዛ የአብራኩን ክፋይ የ9 ዓመት ልጁን የደፈረ ወላጅ አባት 17 ዓመት እስር ተፈርዶበታል።
ተከሳሽ አዶኒያስ አቡታ 40 ዓመቱ ሲሆን የ9 ዓመት ህጻን ልጁን በቀን 07/07/2016 ዓ.ም.ከምሽቱ 3፡30 አካባቢ ከቤተሰቦቹ ጋር ተከራይቶ በሚኖርበት ቤት ውስጥ መድፈሩን የዐቃቤ ህግ የክስ መዝገብ ያስረዳል።
ተከሳሹ ድርጊቱን የተበዳይ እናት ቤተሰቧን ለማስተዳደር በከፈተችው የቁርሳ ቁርስ ቤት ውስጥ ለማደር በሄደችበት ዕለት የፈጸመ ሲሆን ተጎጂ ህጻን ተኝታ ካለችበት ቀስቅሶ አስገድዶ መድፈሩ ነው የተጠቀሰው።
የቀረበውን ክስ ተቀብሎ ሲያከራክር የቆየው የሀዋሳ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በሰውና በሰነድ ማስረጃ በማስደገፍ በቀን 16/04/2017 ዓ.ም. በዋለው ችሎት ተከሳሽን ጥፋተኛ በማለት #በ17_ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኗል፡፡
3. የ31 ዓመቱ ከሳሽ ልደቱ አስፋ የ7 ዓመት ህጻን ከቀን 01/01/2016 ዓ.ም. ጀምሮ ለአንድ አመት ያህል የተለያ ማባበያዎችን በመስጠት የግብረ ስጋ ድፍረት ወንጀል ሲፈጽም መቆየቱን የአቃቤ ህግ የክስ መዝገብ ያስረዳል።
የቀረበውን ክስ ተቀብሎ ሲያከራክር የቆየው የሀዋሳ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በሰውና በሰነድ ማስረጃ በማስደገፍ በቀን 16/04/2017 ዓ.ም. በዋለው በህጻናት ችሎት ተከሳሽን ጥፋተኛ በማለት #በ18_ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኗል፡፡
4. የ5 ዓመት ህፃን ልጅ የደፈሩ 2 ግለሰቦች የ19 ዓመት እስር ተፈርዶባቸዋል።
በወናጎ ከተማ ቱቱፈላ ቀበሌ ኦዶላ ተብሎ በሚጠራበት አከባቢ የ5 ዓመቷ ህፃን ከቀኑ 8:00 ሰዓት ዳቦ ለመግዛት በሄደችበት የግብረ ስጋ ድፍረት ወንጀል ተፈጸሞባታል።
ወንጀሉን የፈጸሙት አቶ ኤልያስ ኤቶ እና አቶ ታምሩ ንጋቱ የተባሉ የዳቦ መጋገሪያ ቤቱ ሰራተኞች ናቸው።
በግብረ ስጋ ድፍረት ወንጀል ጥፋተኛ ሆነው ክስ የቀረበባቸው ወንጀለኞቹ ታህሳስ 17 ቀን 2017 ዓ.ም በወናጎ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በዋለ ችሎት ሁለቱም ተከሳሾች እያንዳንዳቸው #በ19_ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ተወስኗል።
5. የ3 ዓመት ከ6 ወር ህጻን ላይ የመድፈር ሙከራ ያደረገው ግለሰብ በ10 ዓመት ፅኑ እስራት ተፈርዶበታል።
ወጣት ኤርምያስ ፀጋዬ 3 ዓመት ከ 6 ወር በሆነችው ተበዳይ ህፃን ከምትጫወትበት ቦታ ወደ ኤት ኤል ትምህርት ቤት ይዞ በመሄድ የመድፈር ሙከራ ማድረጉን በምስክር ያረጋገጠው የወናጎ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ግለሰቡን #በ10_ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኗል።
ተጨማሪ ፦ የ28 ዓመት እድሜ ያለው ክብሮም ኣብርሃ የተባለ በትግራይ እንዳስላሰ ከተማ የሚኖር ወጣት የ11 እና 12 ዕድሜ ህፃናትን እንዲቀርቡትና እንዲላመዱት በማድረግ በጨርቅ እና በማጣበቂያ ማስቲሽ እንዳይጮሁ አፍኖ የግብረ ስጋ ድፍረት ወንጀል መፈጸሙ በመረጋገጡ #የ16_ዓመት ጽኑ እስራት ተፈርዶበታል።
ውድ የቲክቫህ አባላት ሆይ ፥ እነዚህ ያጋራናችሁ ከሰሞኑን የተላለፉ የፍርድ ውሳኔዎች ናቸው።
ድርጊቶቹ እጅግ አሰቃቂና ለጆሮም የሚከብዱ አስደንጋጭ ናቸው።
በህጻናት ላይ የሚፈጸሙ የጭካኔ ተግባራት በየጊዜው ይሰማሉ።
እኛ አሁን እየሰማን ያለነው ወደ ፍ/ቤትና ሚዲያ እየቀረቡ ያሉትን ነው በየመንደሩ በየአካባቢው ምን ያህል ልጆቻችን ጥቃት እየደረሰባቸው ይሆን ?
የፍርድ ውሳኔዎች አስተማሪ ናቸው ?
ልጆቻችንን ከዚህ የከፋ እና አስፈሪ ጊዜ ለመጠበቅ ምን መደረግ አለበት ?
መፍትሄው ምን ይሆን ?
በዚህ ጉዳይ ላይ የህግ ባለሙያ አስተያየት በቀጣይ የምናቀርብ ይሆናል። እናተም የሚሰማችሁን በ @tikvahethiopiaBot ላይ ፃፉ።
@tikvahethiopia
#Ethiopia #Djibouti
በኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) የተመራ ልዑክ ዛሬ ማምሻውን ጅቡቲ ገብቷል።
የልዑካን ቡድኑ አባላት ጅቡቲ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የሀገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መሃመድ አሊ የሱፍ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ልዑካኑ በጅቡቲ ቆይታቸው ከተለያዩ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ጋር ይመክራሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳውቋል።
Via The Ministry of Foreign Affairs of Ethiopia
@tikvahethiopia
ፎቶ ፦ የታኅሣሥ 19 የሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ክብረ በዓል በቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም በሰላም በድምቀት ተከብሮ ውሏል።
በበዓሉ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ፣ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ተገኝተው ነበር።
በክብረ በዓሉ ላይ ቅዱስነታቸው ቃለ ምዕዳን እና ቡራኬ ሰጥተዋል።
በቁልቢ የቅዱስ ገብርኤል ንግሥ በዓል ላይ እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ምእመን ተገኝቶ ነበር።
ዓመታዊው የታሥሣ 19 የሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ክብረ በዓል በተለያዩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አህጉረ ስብከቶችም ተከብሮ ውሏል።
የፎቶ ባለቤት ፦ የኢ/ኦ/ተ/ዋ/ቤተ ክርስቲያን የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
@tikvahethiopia
#አክሱም
🧕" እኛ የምንፈልገው ፍትህ ነው። ሂጃባችንን አድርገን ነው መማር የምንፈልገው። ያለ ሂጃብ ሸሪዓም አይፈቅድም አስቸኳይ እና ዘላቂ መፍትሄ ይሰጠን " - ተማሪዎች
➡️ " የአክሱም ሙስሊም ሴት ተማሪዎች በአጠቃላይ ሁሉም የሉም ከትምህርት ገበታ ላይ ወጥተዋል " - የክልሉ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት
👉 " ማንም ተማሪ በትምህርት ቤት ሃይማኖትን የሚያንጸባርቅ ነገር ማድረግ የለበትም " - የአክሱም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
በትግራይ ፣ አክሱም ከተማ ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ላለፉት 2 ሳምንታት የራስ መሸፈኛ ሂጃብ ለብሰው ወደ ትምህርት ቤት መግባት እንደተከለከሉና በዚህም ከትምህርት ገበታ መውጣታቸውን የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት አሳውቋል።
በዚህ ዓመት ከሂጃብ መልበስ ጋር በተያያዘ በአክሱም በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ውዝግቡ የጀመረው ጥቅምት ወር ነው።
ተቋሙ ለክልል ትምህርት ቢሮ አሳውቆ አውንታዊ ምላሽ ቢሰጠውም በተግባር የተቀየረ ነገር ግን የለም።
የምክር ቤቱ ፀሀፊ ሓጂ መሓመድ ካሕሳይ ምን አሉ ?
" ፀጉራቸውን ሸፍነው ትምህር ቤት እንዲሄዱ ማየት ያልተፈቀደበት መታየት የለበትም ፀጉሯ የአንድ ሴት ይሄ ሃይማኖታዊ ግዴታ ነው።
ሃይማኖት ውስጥ ፖለቲካ አይገባም፣ ፖለቲካ በሃይማኖት አይገባም እየተባለ በአንቀጽ ተቀምጦ እያለ አሁን ፖለቲካ በሃይማኖት እየገባ ነው።
ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ከትምህርት ቤት ዩኒፎርም ጋር የሚመሳሰል የፀጉር መሸፈኛ ሂጃብ መጠቀም እንደሚችሉ በ2000 ዓ/ም የወጣ ሀገር አቀፍ መመሪያ አለ።
ስለዚህ ዝም ብለን የምናየው ነገር አይሆንም።
በአሁኑ ጊዜ በአራት ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ወጥተዋል።
ዋናው ደግሞ 3 ወር ሲማሩ የነበሩ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ለብሔራዊ ፈተና የኦንላይ ምዝገባ የሚደረግበት ወቅት ነው በዚህ ሳምንት ያልቃል የአክሱም ሙስሊም ተማሪዎች እስካሁን አልተመዘገቡም።
የአክሱም ሙስሊም ሴት ተማሪዎች በአጠቃላይ ሁሉም የሉም ትምህርት ገበታ ላይ ወጥተዋል፤ አልገቡም እስካሁን።
ችግሩ እንዲፈታ ከክልሉ ትምህርት ቢሮ እና ከአክሱም ከተማ አስተዳደር ትምህርይ ፅ/ቤት ጋር ውይይት እየተደረገ ነው " ብለዋል።
ተማሪዎች ምን ይላሉ ?
" በጦርነት ምክንያት ለ2 ዓመታት ከሌሎች ተማሪዎች ወደኃላ ቀርተናል አሁን ደግሞ በሂጃብ ምክንያት ፈተና ሊያመልጠን ነው።
ፎርሙ እያመለጠን ነው። ሌሎች ተማሪዎች በሂጀብ ፎርም እንደሞሉ ነው የምናውቀው። እኛ የምንፈልገው ፍትህ ነው። ሂጃባችንን አድርገን ነው መማር የምንፈልገው።
ያለ ሂጃብ ሸሪዓም አይፈቅድም ፤ መፍትሄው ደግሞ በጣም አስቸኳይ እና ዘላቂ መሆን አለበት። እስካሁን መብታችን እየተከበረ አይደለም " ብለዋል።
NB. የክልል ትምህርት ቢሮ እና የአክሱም ከተማ አስተዳደር ምላሽ ለመስጠት ፍቃደኛ አልሆኑም።
የአክሱም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ምን አለ ?
ምክትል ርዕሰ መምህር ገ/መስቀል ገ/እግዚአብሔር ፦
" ' ትምህርት ቤቶች ከሃይማኖት እና ከፖለቲካ ነጻ መሆን አለባቸው ' ይላል የትግራይ ክልል የትምህርት ቤቶች አደረጃጀት መመሪያ ማንም ተማሪ በትምህርት ቤት ሃይማኖትን የሚያንጸባርቅ ነገር ማድረግ የለበትም።
ክርስቲያኑ መስቀል ወይም መጠምጠሚያ ፤ ሙስሊሙም ሂጀብ ወይም ኮፍያ ማድረግ አይፈቀድም። የትምህርት ቤቱ መለያ ዩኒፎርም ብቻ ነው መልበስ የሚገባው።
የተወሰኑ ተማሪዎች ሂጃባቸውን አናውልቅም ብለው ነበር አሁን ግን ተማሪዎች የትምህት ቤቱን መመሪያ ተከትለው እየገቡ ናቸው።
አሰራሩ ለዓመታት የቆየ ነው " ብለዋል።
አንድ በጉዳዩ ላይ ቃላቸው የሰጡ የክልል ትምህርት ቢሮ ሰራተኛ ፤ " በክልሉ ትምህርት ቤቶች ተግባራዊ እየሆነ ያለው በ1995 የወጣ መመሪያ ነው በዚያ መመሪያ ትምህርት ቤቶች የራሳቸውን መተዳደሪያ ማውጣት እንደሚችሉ ይደነግጋል " ሲሉ ተናግረዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የቪኦኤ ሬድዮ ጣቢያ ትግርኛ አገልግሎት መሆኑን ይገልጻል።
@tikvahethiopia