" በወረዳው የሚገኙ 23 ትምህርት ቤቶች አሁንም በኤርትራ መንግስት ወታደሮች ቁጥጥር ስር ናቸው " - የኢሮብ ወረዳ ትምህርት ፅ/ቤት
በትግራይ ፤ በምስራቃዊ ዞን የኢሮብ ወረዳ ትምህርት ፅሕፈት ቤት ከሰሞኑን ከተሰጠው የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ጋር በተያያዘ ለትግራይ ቴሌቪዥን ቃሉን ሰጥቶ ነበር።
ፅ/ ቤቱ ፤ በወረዳው በሦስት ቀበሌዎች በሚገኙ ሦስት ትምህርት ቤቶቸ 118 ተማሪዎች ብቻ ፈተናውን እንደተፈተኑ ገልጿል።
በወረዳው ከሚገኙ 47 ትምህርት ቤቶች 23 ሙሉ በሙሉ በኤርትራ ወታደሮች ቁጥጥር ስር እንደሚገኙ ገልጿል።
22 አንደኛ ደረጃ አንድ ደግሞ ሁለተኛ ደረጃ ናቸው።
በ23 ትምህርት ሲማሩ የነበሩት 7300 ተማሪዎች ላለፉት አራት ዓመታት በምን አይነት ሁኔታ እንደሚገኙ ለማወቅ አልተቻለም።
ፅ/ቤቱ " በአንዳንድ በኤርትራ ወታደሮች ቁጥጥር ስር በሚገኙ ትምህርት ቤቶች በኤርትራ ስርዓተ ትምህርት (curriculum ) እየተማሩ እንደሆነ መረጃው ደርሶናል " ብሏል።
" የኢሮብ ብሄረሰብ እንደ ብሄረሰብ የመጥፋት አደጋ ተጋርጦቦታል ስለሆነም የክልሉ ጊዚያዊ አስተደደርና የፌደራል መንግስት በአስቸኳይ ሊታደጉት ይገባል " በማለት ጠንካራ ጥሪም አቅርቧል
@tikvahethiopia
#DStvEthiopia
ደማቁ እንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ወደ ሜዳ ተመልሰዋል💥
ቶተንሃም ከሊቨርፑል በ ቶተንሀም ስታዲየም የሚያደርጉተን ደመቅ ጨዋታ በቀጥታ በSS Premier League Ch 223 በሜዳ ፓኬጅ በቀጥታ ይከታተሉ!
👉እነዚህን ድንቅ ፍልሚያዎች ጨምሮ ሌሎች የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎችን በቀጥታ በዲኤስቲቪ ሱፐርስፖርት ይመልከቱ።
ዲኤስቲቪ ያስገቡ ፣ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ!
👇
https://bit.ly/3RFtEvh
ደንብና ሁኔታዎች ተፈፀሚነት አላቸው! ለበለጠ መረጃ
👇
www.dstv.com/en-et
#PremierLeagueallonDStv #ሁሉምያለውእኛጋርነው
#MPESASafaricom
የመብራት ክፍያችንን በM-PESA በመክፈል 10% ተመላሽ ገንዘባችንን አሁኑኑ እናግኝ ፤ መብራታችንም እንደበራ ይቆየን!
የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያን በዚህ ሊንክ እናውርድ ፡ https://play.google.com/store/apps/details... የቴሌግራም ቻናላችንን እዚህ እንቀላቀል 👉/channel/Safaricom_Ethiopia_PLC
ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ በቴሌግራም ቻናላችን /channel/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!
#FurtherAheadTogether
ፎቶ፦ ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ለሁለተኛ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ የመጡትን የፈረንሳይ ፕሬዜዳንት ኢማኑኤል ማክሮንን ተቀብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ማክሮንን " ወንድሜ እና የኢትዮጵያ የልብ ወዳጅ " ሲሉ ገልጸዋቸዋል።
" በሁለቱ ሀገሮች መካከል ያለው ግንኙነት የበለጠ በመጠናከር ላይ ይገኛል " ያሉት ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) ፕሬዚዳንቱ በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታ ፍሬያማ ውይይት እንደሚኖር እምነታቸውን ገልጸዋል።
የማክሮንን ወደ ኢትዮጵያ መምጣት ተከትሎ ዋና ዋና የአዲስ አበባ መንገዶች ላይ የተተከሉ የማስታወቂያ ስክሪኖች " ፕሬዜዳንት ማክሮን እንኳን ወደ ኢትዮጵያ በሰላም መጡ " የሚሉ መልዕክቶች እየተላለፈባቸው ነው።
ማክሮን ፤ ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ወደ ስልጣን ከመጡ ወዲህ ኢትዮጵያ ለስራ ጉብኝት ሲመጡ በ6 ዓመታት ይህ ሁለተኛቸው ነው።
Photo Credit - PM Office & Oliver Liu
@tikvahethiopia
" የመምህራን ደመወዝ አለመከፈልና መቆራረጥ ትምህርታችን ላይ ከፍተኛ ተፅእኖ እያሳደረ ነዉ "- በከምባታ ዞን የሚገኙ ተማሪዎች
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል፤ ከምባታ ዞን ስር በሚገኙ ወረዳዎች ዉስጥ ባሉ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሚማሩ ተማሪዎች " የበጀት እጥረት " እየተባለ በሚነገራቸዉ ምክንያት የመምህራን ወርሃዊ ደመወዝ መቆራረጥና መዘግየት በትምህርታቸው ላይ ከፍተኛ ተፅእኖ እያሳደረ ስለመሆኑ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
ቅሬታ ካሰሙ ተማሪዎች መካከል በዳንቦያ ወረዳ የፉንጦ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ፣ በቃዲዳ ጋሜላ ወረዳ ጆሬ 1ኛ እና 2ኛ ደረጃ እንዲሁም በሀዳሮ ጡንጦ ዙሪያ ወረዳ አመሌቃ 1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ትምህረት ቤት ተማሪዎች ይገኙበታል።
ቅሬታቸዉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ያሰሙ ተማሪዎች ምን አሉ ?
- በደሞዝ መዘግየትና መቆራረጥ ምክንያት መምህራን በተደጋጋሚ ከት/ት ቤት ስለሚቀሩ በየወሩ ከ5-14 ቀናት የማንማርበት አጋጣሚ እየተዘወተረ መጥቷል።
- አንዳንዶቻችን ወደ ትምህርት ቤት ከ30 ደቂቃ በላይ በእግር ተጉዘን ከደረስን በኋላ " በደሞዝ ምክንያት መምህራን አልገቡም " እንባላለን።
- አሁን አሁን በደመወዝ ወቅት መረጃ እየተቀባበልን ለመምህራን ደሞዝ አለመከፈሉን ካረጋገጥን ከትምህርት ቤት እንቀራለን።
- ይህ ተግባር እየተዘወተረ መምጣቱን ተከትሎ በርካታ ወጣቶች ዉሏቸዉን ወደ ፑልና ጆቶኒ ጫወታዎች አዙረዋል።
- ትምህርታቸውን አቋርጠዉ የሚያገቡ ሴት ተማሪዎችም አሉ።
- አከባቢያችን በብዛት ወጣቶች ወደ ዉጪ ሀገራት ከሚሰደዱባቸዉ አንዱና ዋነኛው ነዉ። ባለፈዉ ዓመት በትምህርቱ ላይ ተስፋ ቆርጦ አቋርጦ የተሰደደ ተማሪ አለ።
- ቅሬታችንን ለየትምህርት ቤቶች ርዕሳነ መምህራን እና ዩኒት ሊደሮች እኛም ወላጆቻችንም በተደጋጋሚ አቅርበናል ግን " የደመወዝ ጉዳይ ከትምህርት ቤት አቅም በላይ ነዉ፤ መምህራን ሳይበሉና ሳይጠጡ አስተምሩ ብለን ማስገደድ አንችልም " የሚል ምላሽ ነው የተሰጠን።
ከቅሬታ አቅራቢዎቹ መከካል ዘንድሮ ሀገር አቀፍ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ፈተና ተፈታኞች እንደሆኑ የነገሩን የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች " የዘመናት ልፋታችንና የወደፊት ህልማችን አደጋ ላይ እየወደቀ ነዉ የሚመለከታቸው አካላት አፋጣኝ መፍትሔ " ይስጡልን ብለዋል።
" ለሀገር አቀፉ የዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተና ለመዘጋጀት ተጨማሪ የቲቶሪያል ትምህርት ሊሰጠን ቀርቶ መደበኛ የትምህርት መረሃግብሮች በአግባቡ አይሸፈኑም አሁን በዚህ ወቅት እንኳን አንዳንድ የትምህርት ዓይነቶች ገና አንድና ሁለት ዩኒቶችን (ምዕራፎችን) ብቻ ነዉ በተንጠባጠበ ሁኔታ የተማርነዉ " ሲሉ ገልጸዋል።
መምህራን ምን አሉ ?
" ብዙ ጊዜ ጮኼን ሰሚ አላገኘንም " የሚሉት በከንባታ ዞን የዳንቦያ፣ ሀዳሮ ጡንጦና ቃዲዳ ጋሜላ ወረዳዎች የሚያስተምሩ መምህራን " የደመወዝ በወቅቱ አለመከፈል፣ መቆራረጥና አልፎ አልፎም በፐርሰንት የመክፈል ችግሮች ባላፉት ሁለት ዓመታት እየተባባሱ መጥተዋል ፤ በርካታ መምህራን በዚህ ምክንያት ስራ ገበታቸዉ ላይ በአግባቡ አይገኙም " ሲሉ ገልፀዋል።
የከንባታ ዞን መምህራን ማህበር ተወካይ አቶ አለሙ አቡዬ ምን አሉ ?
° የደመወዝ መዘግየትና እያቆራረጡ መክፈል በከንባታ ዞን ባሉ ሁሉም መዋቅሮች እየተለመደ መጥቷል።
° ችግሩን ለመቅረፍ የሚደረጉ ተግባራት ጉዳዩ ከሚያስፈልገዉ ትኩረትና ከሚያሳድረዉ ተፅእኖ አንፃር በጣም ዝቅተኛ ነዉ።
የከምባታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዳዊት ለገሠ (ዶ/ር) ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደተናገሩት ፤ ችግሩ ባለፉት ጊዜያት ዞኑ ያለበትን የብድር ዕዳ ተከትሎ በተከሰተ የበጀት እጥረት በሁሉም የመንግስት መዋቅሮች የሚስተዋል ነው።
" የዞኑ መንግስት ካቢኔ መምህራንን ጨምሮ ለፀጥታ፣ ፍትህ እና የጤና ባለሙያዎች ደመወዝ ቅድሚያ ተሰጥቶ እንዲከፈል ባሳለፈዉ ዉሳኔ መሰረት እየተተገበረ ነዉ " ብለዋል።
" አንዳንድ ወረዳዎች የኋላውን እየሸፈኑና በብድር የተጠቀሟቸዉን በጀቶች እያተካኩ በሚሄዱበት ወቅት የደሞዝ መዘግየቶች ሊያጋጥሙ ይችላሉ። የመማር ማስተማሩ ተግባር እንዳይቆራረጥ በተቻለ መጠን ሁሉ የዞኑና የክልሉም መንግስት ትኩረት ነዉ " ብለዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyHW
@tikvahethiopia
የበዓል ስጦታ ከወጋገን ባንክ
ከውጭ ሀገር የሚላክልዎትን ገንዘብ እስከ ጥር 30 ከወጋገን ባንክ ሲቀበሉ እና ሲመነዝሩ ከዕለቱ የምንዛሬ ዋጋ ላይ 2% በመጨመር ገንዘብዎን ከቀልጣፋ መስተንግዶ ጋር ያስረክብዎታል፡፡
ለበለጠ መረጃ ከስር የተቀመጠውን የማህበራዊ ገፆቻችንን ሊንክ ተጭነው ይቀላቀሉ https://linktr.ee/WegagenBank
#ግብር #ተሽከርካሪዎች
የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ከተሽከርካሪ አስመጪዎች ለቀረበበት ቅሬታ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጠው ሙሉ ምላሽ ምንድን ነው?
" አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ላይ ያሉ ዋና ዋና የሚባሉ የታክስ ስወራ አለባቸው የሚባሉ ዘርፎች ተለይተው ጥናት ተደርጓል፡፡
አንዱ ከቋሚ ንብረት፣ ከቤት፣ ከሪልስቴት ጋር ሽያጭ ጋር፣ ሌላው ደግሞ ከመኪና ጋር የተገናኘ ጥናት ነው፡፡
እነዚህ ጥናቶች 2015 ዓ/ም ተጠንተው ተጠናቀው 2016 ዓ/ም ሚያዝያ ጀምረው ተግባራዊ እንዲደረጉ በከተማ አስተዳደሩ ተወስኖ ሰርኩላር ተላልፏል፡፡
የቤትና መኪና ሻጮችን በተመለከተ ማለት ነው፡፡ የቤት ወዲያውኑ ተግባራዊ ተደርጓል፡፡ ከመኪናም ሽያጭ ጋር በተገናኘ የመኪና ሽያጭ በሚከናወንበት ጊዜ ሁለት ቢሮዎች ናቸው በዋናነት ግብር የሚሰበስቡት፡፡
አንዱ የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ነው፡፡ ሁለተኛው ደግሞ በትራንስፖርት ቢሮ ውስጥ ያለው የከተማው የአሽከርካሪና ተሸከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ነው፡፡
በጥናት እንዲጠና የተደረገው ከተማው የሚሸጡ ተሽከርካሪዎች የሚሸጡበት ዋጋና ተሸጠዋል ተብሎ ለገቢወዎች ቢሮ በሚቀርበው የገንዘብ መጠን መካከል በጣም ሰፊ የዋጋ ልዩነት በመኖሩ ነው።
ጥናቱን ከፌደራልም ከአዲስ አበባም የተለያዩ ባለሙያዎች ናቸው ያጠኑት፡፡ በገበያው ዋጋና ለገቢዎች ቢሮ በሚቀርበው ሪፖርት መካከል በጣም ሰፊ ሆነ የዋጋ ልዩነት እንዳለው ጥናቱ አሳይቷል።
10 ሚሊዮን ብር የሚሸጥ መኪና በ3 ሚሊዮን ብር፣ በ6 ሚሊዮን ብር የሚሸጥ መኪና በ1 ሚሊየን ብር እየሆነ ያለው፡፡ በሚቆረጠው ደረሰኝና ገበያ ላይ ባለው ዋጋ መካከል ያለው ልዩነት በጣም ሰፊ ነው፡፡
ይህንን ለማስተካከል ነው ጥናቱ የተጠናው። ጥናቱ በወቅቱ የነበረውንም የዋጋ ግሽበት ከውጭ ምንዛሬ ጋር የተያያዘውንም ጉዳይ ግምት ውስጥ ያስገባ ነው።
ስለዚህ ተግባራዊ መደረግ የነበረበት አምና ነው፡፡ 2016 ዓ/ም በዚሁ ነው መሰራት የነበረበት፡፡ ነገር ግን በተለያየ ምክንያት 2016 ዓ/ም ሳይተገበር ቆይቷል፡፡
ከተማ አስተዳደሩ ‘2016 አለመተግበሩ ትክክል አይደለም፡፡ በ2016 ዓ/ም የግብር ዘመን ላይ ተግባራዊ አልተደረገም፡፡ አሁን ግን የ2017 ዓ/ም ግብር በሚከፈልበት ጊዜ ህጉ መከበር አለበት’ የሚል አሰራር ስለተቀመጠ ያንን አሰራር ነው የተገበርነው፡፡
በተከታታይ አስመጭዎቹ ሰዎችን ወክለው የሂሳብ ባለሙያዎቹ ጭምር መጥተው በተሰራው ፎርሙላ ላይ ቁጭ ብለን አንድ በአንድ ተወያይተናል፡፡ ተግባብተናል ብዙ ልዩነት አልነበረም።
በውይይታችን በተለይ ቴክኒካል የሆነውን ነገር የሒሳብ ባለሙያዎቻቸው ባሉበት ተወያይተን እነሱን የሚያከስር እንዳልሆነ ነገር ግን የግብር ስወራውን ለመከላከል የተዘጋጀ ፎርሙላ እንደሆነ ከውጭ ምንዛሬ ጋር ያለውንም ችግር ግምት ውስጥ እንዳስገባ በመድረኩ ላይ ተግባብተናል፡፡
አንድ ሰው መኪና ሲገዛ ደረሰኙን ይዞ ታርጋ ለመውሰድ ወይም ለማዞር በሚሄድበት ጊዜ አምና ጭምር መኪና ሻጮቹ የሰጡትን ደረሰኝ አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ባለስልጣን ‘አልቀበልም’ እያለ በፎርሙላው መሰረት እየሰራ ትክክለኛውን እያሰላ ከመኪና ገዥዎቹ አስፈላጊውን ክፍያ ሲቀበል ነው የነበረው፡፡
ሻጮቹ የሸጡት የገንዘብ መጠን ገዢው ታርጋ ለመሸጥ በሚሄድበት ጊዜ ተቀባይነት እንዳላገኘ እዛ በትክክለኛው ዋጋ የስም ዝውውር እንደፈጸመ ያውቃሉ፡፡ ስለዚህ አምናም እነሱ ላይ አለመተግበሩ ካልሆነ በስተቀር አዲስ የመጣ ነገር አይደለም፡፡
ምንም አስመጪዎቹን የሚጎዳ፣ የሚያከስር ነገር የለውም፡፡ በጣም መሠረታዊ ሚባሉ ጉዳዮችን ግምት ውስጥ ያስገባ አሰራር ነው፡፡
እንደ ጉዳት እየወሰዱት ያለው አምና ስንከፍል በነበረው አይነት ብቻ እንክፈል ለምን ተጨማሪ ክፍያ እንከፍላለን? ከሚል አስተሳሰብ የመነጨ ጥያቄ ነው፡፡
ይሄ ደግሞ ተቀባይነት የለውም፡፡ የታክስ ስወራን መከላከል ያስፈልጋል፡፡ የከተማ አስተዳደሩ በከተማው የሚሰራውን ይህን ሁሉ ልማትና ህዝብ ጥያቄ የሚመልሰው ከተማዋ ከምታመነጨው ገቢ ነው፡፡
እዚህ ገቢ ውስጥ የግብር ስወራውን የመከላከል የገቢዎች ቢሮ ኃላፊነት አለበት፡፡ የዋጋ ጥናትን በተመለከተ በግልጽ በታክስ አስዳደር አዋጁ ላይ ስልጣን ለገቢዎች ቢሮ ተሰጥቷል፡፡ ግልጽ ነው፡፡
አዋጁም ይሄ በዋናው የፌደራል የታክስ አስተዳደር አዋጅ የሚባል አለ በሱ አዋጅ ላይ በግልጽ የተቀመጠ፣ አንቀጽ 3 ላይ ለገቢዎች ቢሮ ተሰጠ ስልጣን አለ " ብሏል።
አንዱ የአስመጪዎቹ ቅሬታ መመሪያውን ማውረድ ያለበት የገቢዎች ሚኒስቴር ነው እንጂ ቢሮው አይደለም የሚል ነውና የቢሮው ምላሽ ምንድን ነው ? ሲንል ለቢሮ ኃላፊው ተጨማሪ ጥያቄ አቅርበናል።
ምን ምንላሽ ተሰጠ ?
" አይ አይልም። የአዲስ አበባ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የተሰጠ ስልጣን በታክስ አስተዳደር ተቀምጧል። የፌደራል ግብር ከፋይ የሚባሉ አሉ። አዲስ አበባ ላይ ደግሞ የአዲስ አበባ ግብር ከፋይ አለ።
በአዲስ አበባም ሆነ በየትኛውም የሀገሪቱ ክልል ላይ PLC የሆኑ ግብር ከፋዮች ለፌዴራል መንግስት ነው ግብር የሚከፍሉት። እነሱን የተመለከተ አሰራር ሊያወርድ ይችላል ፌደራል መንግስት።
የአዲስ አበባ ከተማ ግብር ከፋዮችን በተመለከተ አሰራር መዘርጋት፣ ዋጋ ማጥናት፣ በዋጋ ጥናቱ መሰረት ግብር እንዲሰበስቡ የማድረግ ስልጣን ደግሞ ለከተማ አስተዳደሩ ገቢዎች ቢሮ መሆኑ በአዋጁ በግልጽ ተቀምጧል። "
" ግብር የሚከፈለው ህግ ወጥቶ በህግ ደረጃ ነው እንጂ ጥናት ተጠንቶ አይደለም፣ ይሄ ጥናት ደግሞ 2015 ዓ/ም ላይ ‘ተጠንቶ አይሆንም ትክክል አይደለም’ በሚል ነበር ቆይቶ የነበረው፣ አሁን ለአዲስ አበባ መኪና አስመጪዎች ብቻ በሚል ጥናትን መሰረት ተድርጎ የወጣ፣ ህግን መሰረት ያላደረገ ነው " የሚል ቅሬታም ቀርቧል። የቢሮው ምላሽ ምንድን ነው? ለሚለው ጥያቄ ምላሽ ትጥቷል።
ቢሮው በምላሹ ምን አለ ?
" በታክስ አስተዳደር አዋጁ ላይ በግልጽ የተቀመጠው በማንኛውም ምርት፣ አገልግሎት፣ ሽያጭ በሚከናወንበት በማንኛውም እቃ ላይ የገቢዎች ቢሮ ዋጋ ማጥናት፣ ዋጋን Set የማድረግ፣ በዚህ ዋጋን በመቀነስ የሚመጣን የግብር ስወራ ለመከላከል ዋጋ መተመን እና በዚያ መሰረት ግብር ማስከፈል እንደሚችል ተቀምጧል።
ስለዚህ መመሪያም፣ ሌላ አዋጅም አያስፈልገውም አሰራር ብቻ ነው መዘርጋት የሚያስፈልገው። ይጠናል ያ የተጠናው ጥናት ወደ አሰራር ይቀየርና ተግባራዊ ይደረግ ተብሎ ለየቅርንጫፍ ይወርድና ነው ተግባራዊ የሚደረገው።
ይሄ ነው አሰራሩ። ምንም የተጣሰ የህግ ክፍተትም የለው። ከተማው በማንዴቱ ነው የሰራው። "
(ገቢዎች ሚኒስቴር በጉዳዩ ዙሪያ ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ ከሆነ በቀጣይ የምናቀርብ ይሆናል)
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
🎉✨ ቴሌብር አዲስ ገና 2017 ኤክስፖ ተከፈተ!!
የአገራችን ትልቁ የበዓል ኤክስፖ በኤግዚቢሽን ማዕከልና በመስቀል አደባባይ በድምቀት ተከፍቷል፤ ግብይቱ ቢሉ መዝናኛው ሁሉ ተሰናድቷል፡፡
💁♂️ የመግቢያ ትኬትዎን በቴሌብር ሲቆርጡና ያሻዎን ሲገበዩ እስከ ብር 2500 ላለው 10% ተመላሽ ያገኛሉ!
ቴሌብር ሱፐርአፕን https://onelink.to/uecbbr ወይም *127# ይጠቀሙ!
🏑 በገና ሸመታ አይቆጡም ጌታ!!
ቴሌብር - እጅግ ቀላል፣ ፈጣን፣ ምቹ እና አስተማማኝ!
#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
" መልሼ አጤነዋለሁ " - ሶማሊያ
የሶማሊያ መንግሥት የኢትዮጵያ ወታደሮች በአፍሪካ ኅብረት ልዑክ ውስጥ መካተታቸውን በተመለከተ " መልሶ ለማጤን " ዝግጁ መሆኑን አስታውቋል።
አንድ የሶማሊያ መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣን ለቪኦኤ ሬድዮ በሰጡት ቃል፤ " የሶማሊያ መንግሥት ለልዑኩ ኅይል ከሚያዋጡት ሀገራት ዩጋንዳ፣ ኬንያ፣ ጂቡቲ እና ቡሩንዲ ወታደሮችን አግኝቶ ደልድሏል " ሲሉ አስታውቀዋል።
ኢትዮጵያ እና ሱማሊያ አንዳቸው የሌላውን ሉዐላዊነት፣ እንዲሁም የግዛት አንድነት እንደሚያከብሩ አንካራ፣ ቱርክ ላይ ባለፈው ሳምንት ስምምነት መፈጸማቸውን ገልጸዋል።
ስምምነቱ በመፈጸሙም ሶማሊያ የኢትዮጵያ ወታደሮች በአዲሱ ልዑክ ውስጥ የመካተታቸውን ጉዳይ " እንደገና እንደምታጤን " ባለስልጣኑ አስታውቀዋል።
ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋራ የፈጸመችውንና የባሕር በርን የተመለከተውን የመግባቢያ ስምምነት የማትሰርዝ ከሆነ የኢትዮጵያ ወታደሮች ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ ሶማሊያ ስትጠይቅ ቆይታ ነበር።
ሶማሊያ ይህን ብትልም ኢትዮጵያ ግን በሶማሊያ የሚገኙት ወታደሮቹ አል ሻባብን መዋጋት እንደሚቀጥሉ ሲያስታውቃ ነበር።
የኢትዮጵያ ትኩረት ' አል ሻባብ ' ላይ መሆኑን የኢትዮጵያው የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነቢያት ጌታቸው በቅርቡ አስታውቀው ነበር።
የኢትዮጵያ 🇪🇹 ወታደሮች ለሶማሊያ ሰላም፣ ደህንነት እና መረጋጋት የደም ዋጋ ከፍለዋል ፤ ዛሬም ድረስ እየከፈሉ ነው።
ኢትዮጵያ ለሱማሊያ ያልከፈለችው መስዕዋትነት የለም ፤ ይህ ውለታ ተረስቶ ነው የሶማሊያው መሪ ሀሰን ሼክ መሀሙድ አስተዳደር ስለ ኢትዮጵያ መከላከያ ብዙ የሚያስተዛዝብ ንግግር ሲናገር የከረመው።
በአንካራው ስምምነት ፕሬዜዳንቱ ፤ ሶማሊያ በአፍሪካ ህብረት ተልዕኮ ውስጥ የኢትዮጵያ ወታደሮች ለሀገራቸው (ሶማሊያ) ለከፈሉት መስዋዕትነት በይፋ እውቅና ሰጥተዋል።
@tikvahethiopia
" የሟችዋ ገዳይ አልተገኘም ፤ አሟሟትዋ እጅግ ዘግናኝ እና ያልተለመደ ነው " - የእንዳባጉና ከተማ ነዋሪዎች
ሟች እንስት ኣልማዝ ፀሃየ የትግራይ ክልል ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን እንዳባጉና ከተማ ነዋሪ ነበረች።
ማችዋ በአከባቢው የሚገኘው አንድ ዴቄት ፋብሪካ ስራ አስኪያጅ ስትሆን ታህሳስ 05 ቀን 2017 ዓ.ም ከስራ ገበታዋ እንደወጣች አልተመለሰችም።
መሰወሯ ያስጨነቃቸው ወዳጅ ዘመዶች በከተማ በገጠሩ ፣ በዱር ሸንተረሩ ለ4 ቀናት ፈልገው አላገኟትም።
በአምስተኛው ቀን ታድያ በአከባቢው ከአንድ ቤተ እምነት አጠገብ ከሚገኘው ወንዝ ዳር ህይወትዋ አልፎ ተጥላ ትገኛለች።
የአከባቢው ህዝብ ከሞትዋ በላይ አሟሟትዋ ከፍተኛ ድንጋጤና ቁጣ ፈጥሮቦታል።
የሟችዋ አንድ አግር በአራዊት ተበልቶ ይሁን ሌላ አልተገኘም።
የሟችዋ አስክሬን ከተገኘበት ቦታ 400 ኪሎ ሜትር ያህል ርቀት ተጉዞ መቐለ በሚገኘው ዓይደር ኮምፕሬሄንሲቭ ሪፈራል ሆስፒታል ምርመራ ከተካሄደበት በኋላ ስርዓተ ቀብር ዛሬ ሀሙስ ታህሳስ 10/2017 ዓ.ም በእንዳባጉና ከተማ ተፈፅሟል።
እንስትዋ እንዴት ለህልፈት በቃች ? ማን ገደላት ? በምን ምክንያት ? እንዴት ? የሚሉ የህዝብ ጥያቄዎች የማጣራት ጉዳይ ለአከባቢው ፓሊስ የተተው ሆኗል።
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
@tikvahethiopia
#Ethiopia 🇪🇹 #AddisAbaba
የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ መቼ ይካሄዳል ?
38ኛው የአፍሪካ ኀብረት የመሪዎች ጉባኤ የካቲት መጀመሪያ ሳምንት ይካሄዳል።
አዲስ አበባ የፊታችን የካቲት ወር መጀመሪያ ሳምንት የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ ታስተናግዳለች።
ለዚህም ጉባኤ ሁሉን አቀፍ ቅድመ ዝግጅት እያደረገች እንደሆነ ተገልጿል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጉባዔውን የኢትዮጵያን ገጽታና የኮንፈረንስ ቱሪዝም ማዕከልነት በሚያሳድግ መልኩ ለማስተናገድ ቅድመ ዝግጅት ስለመደረጉ አሳውቋል።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ የአገልግሎት አሰጣጣጥና የሆቴል ፋሲሊቲዎች መሰረት በማድረግ 42 ሆቴሎች እንግዶቹን እንዲያስተናገዱ መመረጣቸውን የአዲስ አበባ ሆቴል እና ቱሪዝም ባለሙያዎች ማህበር መረጃ ያሳያል።
ሆቴሎቹ በሕብረቱ ጉባዔ ለመሳተፍ የሚመጡ እንግዶችን ለመቀበል አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት አጠናቀዋል።
38ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ የካቲት 8 እና 9 ቀን 2017 ዓ.ም እንዲሁም 46ኛው የህብረቱ የሥራ አስፈጻሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ የካቲት 5 እና 6 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል። #ENA
Photo Credit - Addis Ababa Mayor Office
@tikvahethiopia
#JawarMohammed
የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ አመራሩ አቶ ጃዋር መሐመድ ' አልጸጸትም / HIN GAABBU ' መጽሐፍ ዛሬ ሳይመረቅ ቀረ።
መጽሐፉ ዛሬ በኬንያ፣ ናይሮቢ ሊመረቅ ቀጠሮ ተይዞለት ነበር።
አቶ ጃዋር መሐመድ ናይሮቢ ሊካሄድ የነበረው የመፅሐፍ ምርቃት ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙን አረጋግጠዋል።
ጃዋር " በተሳታፊዎች ብዛት እና በደህንነት ስጋት ምክንያት የምረቃ አዳራሹ አስተዳደር ላልተወሰነ ጊዜ ማስተላለፉን " ገልጸዋል።
" በቅርብ ቀን ተቀያሪ ቦታ እናሳውቃለን " ብለዋል።
ቢቢሲ አማርኛው አገልግሎት ደግሞ ምንጮቼ እንደገለጹልኝ የመጽሐፍ ምርቃቱ ሳይካሄድ የቀረው ከተለያዩ አካላት ማስፈራሪያዎች እና ዛቻዎች በመድረሳቸው ነው ብሏል።
መጽሐፉ የሚመረቅበት ናይሮቢ የሚገኘው የኬንያታ ዓለም አቀፍ የስብሰባ ማዕከል መሆኑ ከታወቀ በኋላ የተለያዩ ማስፈራሪያዎች ደርሰዋል ተብሏል።
ዛቻው እና ማስፈራሪያው የጸጥታ ስጋት እንዳለ በመጥቀስ ማዕከሉን ለሚያስተዳደሩት አካላት በመድረሱ ምርቃቱ መሰረዙን እኚሁ ምንጮች ገልጸዋል።
እኚህ አካላት እነማን እንደሆኑ ግን ዘገባው በግልጽ አላሰፈረም።
በቅርቡ አቶ ጃዋር መሐመድ ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ መጽሃፋቸውን በኢትዮጵያ ለማስመረቅ እንደሚፈልጉ ነገር ግን "... በአገሪቱ መጽሐፍ ማስመረቅ ይቅርና ለመተንፈስ ከባድ ነው " የሚል ነገር ተናግረዋል።
" ኢትዮጵያ ለማስመረቅ ፍላጎት ነበረኝ " ያሉ ሲሆን " ሆኖም ግን ገዢዎቹ ደስተኛ አልነበሩም። አሁን አገራችን ካለችበት ሁኔታ አንጻር ለመጽሐፍ ብዬ አምቧጓሮ ውስጥ ለመግባት አልፈለግኩም " በማለት በጎረቤት አገር መዲና መጽሐፉን ለማስመረቅ የወሰኑበትን ምክንያት አስረድተዋል።
አቶ ጃዋር መሐመድ የፖለቲካ ጉዞ እና የሕይወት ታሪካቸውን በሚመለከት ' አልጸጸትም / HIN GAABBU ' በሚል ርዕስ በአፋን ኦሮሞ እና በአማርኛ መጽሐፍ ጽፈው አሳትመዋል።
@tikvahethiopia
#DStvEthiopia
🎊ልጆች የሚዝናኑባቸው የተለያዩ ቻናሎች በዚህ ሰሞን ለደንበኞቻችን በሽበሽ ናቸው!
👉ከታህሳስ 3 እስከ ታህሳስ 28 ድረስ ብቻ በሚቆየው ይህ ልዩ ጊዜ ሁሉንም ምርጥ የልጆች ቻናሎች በዲኤስቲቪ ጎጆ ፓኬጅ በ400 ብር ብቻ ያገኛሉ!
ይፍጠኑ ! ይህ አጋጣሚ ለእርሶም ሆነ ለቤተሰብዎ አያምልጥዎ!!
ዲኤስቲቪ ያስገቡ ፣ደንበኝነትዎን ያራዝሙ!
👇👇👇
https://bit.ly/48oVhj8
#ሁሉምያለውእኛጋርነው
ባለፉት ቀናት " መኪናችን ከቆመበት ተሰረቀብን " ያሉ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መኪናቸውን ያየ እንዲጠቁማቸው ጥሪ አቅርበዋል።
የመጀመሪያው መኪና ኮድ 3 ኦሮ የሆነ ታርጋ ቁጥሩ 23853 ከትላንት በስቲያ ጠዋት ኮዬ ፈጬ ን/ስልክ ከቆመበት ቦታ መሰረቃቸውን የመኪናው ባለቤቶች ተናግረዋል።
መኪናውን ያያችሁ በ0929124436 / 0913212174 / 0911411036 በመደወል እንድታሳውቋቸው ጠይቀዋል።
ሌላው ፤ ኮድ 3 ኦሮ ታርጋ ቁጥሩ 31420 የሆነ ሚኒባስ መኪና ጉርድ ሾላ ልዩ ቦታው አረቡ ወፍጮ ቤት አካባቢ ከቆመበት መዘረፋቸውን የመኪናው ባለቤቶች ተናግረዋል።
ዝርፊያው የተፈጸመው ታህሳስ 7 ቀን 2017 ዓ/ም ነው።
መኪናው የተዘረፈው ከግቢ ውጭ ሲሆን በየወሩ ለጥበቃ እየተከፈለ ከሚያድርበት ነው። ጥዋት ላይ ከቆመበት አልተገኘም።
ከመኪናው ዝርፊያ ጋር ተጠርጥረው 2 ጥበቃ እና ሹፌሩ ታስረዋል።
መኪናውን ያያችኩ በ0911458521 ወይም 0938485386 ላይ እንድትጠቁሟቸው ባለቤቶቹ ጥሪ አቅርበዋል።
@tikvahethiopia
#AAiT
Call for Applications in MSc and PhD Programs 2024/25 Second Semester
1. Computer Engineering - MSc and PhD
2. Communication Engineering - MSc and PhD
3. Control Engineering - MSc and PhD
4. Electrical Power Engineering - MSc and PhD
School of Electrical & Computer Engineering, Addis Ababa University,
Application Deadline for GAT: Friday December 20, 2024
More information, see our channel /channel/TrainingAAiT or check application procedure here.
Email: dean.sece@aait.edu.et
🔈#የነዋሪዎችድምጽ
“ ባለስልጣናቱ ህገ ወጥ ስራ ሲሰራ ለማስቆም ምንም አይነት ፍላጎት የላቸውም ” - ነዋሪዎች
በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ አምስት ልዩ ስሙ ‘ሰፈረ ገነት’ በተባለ ቦታ የሚገኙ ነዋሪዎች ካሳና ምትክ ቦታ ሳይሰጣቸው የመስሪያ ቦታቸው ለባለሃብት ተላልፎ በመሰጠቱ በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል ቅሬታ አሰሙ።
ቦታቸው ጋራዥ፣ ላቢያጆ የመሳሰሉት ስራዎች የሚሰሩበትና በቤተሰብ ደረጃ ወደ 100 የሚጠጉ ሰዎች የሚተዳደሩበት 12 ሺሕ ካሬ መሆኑን ገልጸው፣ ቦታው ከህግ ባፈነገጠ አሰራር ለአንድ ባለሃብት ስለተሰጠባቸው መብታቸው ተከብሮ መፍትሄ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።
ቅሬታ አቅራቢዎቹ በዝርዝር ምን አሉ ?
“ መጀመሪያ ወረዳው ጠራንና ‘ቦታችሁ ለባለሃብት ተሰጥቷል። የተወሰነው በካቤኔ ነው’ አለን። ከዛ ክፍለ ከተማ ሄደን የካቢኔው ውሳኔ ነው ወይ? አሳዩን አልናቸው።
‘ይህንን የመጠየቅ መብት የላችሁም። ጥቅማችሁን ነው ፕሮሰስ ማድረግ ያለባችሁ እንጂ ይሄ የኛ ጉዳይ ነው’ አለን። እሺ ብለን የሚያስፈልጉ ዶክሜንቶችን አቅርበን ፕሮሰስ ማድረግ ጀመሩ ክፍለ ከተማውና ወረዳው።
በመካከል የወረዳው ሥራ አስፈጻሚና የመሬት ልማት ማኔጅመንትን ሰብስበውን ‘የምትለቁ ከሆነ በፍጥነት ልቀቁ አለበለዚያ ልክ እንደ ህገ ወጥ ግንባታ በጫጭቄ እጥለዋለሁ’ አለ።
በዚህም ምትክ ቦታ ሳይሰጥ፣ የካሳ ክፍያ ሳይኖረው በሚል ሰው ተደናገጠ። ክፍለ ከተማ ሄደን ስናናግር ‘ማን ሰብስብ አለው?’ የሚል ጥያቄ አዘል ምላሽ ነው የሰጠን።
ከንቲባ ጽህፈት ቤትም ሄደን ቅሬታ አቀረብን ዓባይነህ ለሚባል ሰው፣ የካቢኔው ውሳኔ መሆኑን ማረጋገጥ እንፈልጋለን ስንለው ጌታቸው ለሚባል መራን። ጌታቸውን ስናናግራቸው ‘አረጋግጨ ይነገራችኋል እሱ የኛ ጉዳይ ነው’ አሉን።
በዚሁ ሁኔታ ቀጥለን በኋላ ስንጠይቅ ‘የካቢኔ ውሳኔ የተሰጠው ባለሃብቱ ወረዳ 10 ነው እንጂ ወረዳ አምስት ላይ አይደለም’ ተባልን።
በኋላም የወረዳ ዘጠኝ እንደሆነ ቀሪ ወረቀት ላይ አገኘን። ሄደን ቀጥታ ዓባይነህን ስናናግራቸው ለአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ደውለው ሲያናግሩ ‘በካቢኔ ውሳኔ ነው ፕሮሰስ የተደረገው ገንዘብ እየገባላቸው ነው’ አላቸው።
ከዛ ወረቀቱን ለዓባይነህ ስናቀርብ ለክፍለ ከተማው ‘አይ የካቢኔ ውሳኔ አይደለም፣ ከኛ መዝገብ ቤት ያለውንና ይሄንን አያይዤ እልክልሃለሁ ቼክ አድርገው’ አሉት። ከዚያ በኋላ ግን ማንም ምላሽ የሚሰጠን የለም። ባለሃብቱ የኛን ቦታ ሙሉ ለሙሉ አጥሮታል።
የኛ ቅሬታ ውሳኔው የካቢኔ ውሳኔ አይደለም ባለን ማስረጃ። ሲቀጥል የካቢኔው ውሳኔ ቢሆን እንኳ መጀመሪያ ካሳና ምትክ ቦታ ሊሰጠን ይገባል።
ባለስልጣናቱ ‘ይሄኮ ያስጠይቀናል። የእናንተ ጉዳይ እንዲፋጠን 22 ነው ግፊት ማድረግ ያለባችሁ’ የሚል አስተያዬት ነው የሚሰጧቸው እንጂ ህገ ወጥ ስራ ሲሰራ ለማስቆም ፍላጎት የላቸውም። ፍ/ቤት ሂደን እግድ ስናወጣ መደናገጥ ጀመሩ” ብለዋል።
NB. " 22 " ተብሎ የተገለጸው እዛ ያለውዥ የመሬት አስተዳደር ጉዳዩን እንደያዘ ለመግለጽ ሲሆን እነርሱ ባለወቁት መልኩ እዛ እንዲታይ መደረጉ አሻጥር እንደሆነ ገልጸዋል።
ለቅሬታው ምላሽ ለማግኘት ወደ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ሙከራ ያደረግን ሲሆን፣ ለጊዜው የስልክም ሆነ የፅሑፍ ምላሽ አልሰጡም።
ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ጉዳዩ እንደሚመለከታቸው በቅሬታ አቅራቢዎቹ የተነገረላቸው አቶ ግታቸው የተባሉ አካል፣ በስልክ ማብራሪያ እንደማይሰጡ ለቲክቫህ ገልጸዋል። በአካል ምላሽ ከሰጡ በቀጣይ ይቀርባል።
(ነዋሪዎች ህዝቡ ይወቅልን ብለው አጠቃላይ ቦታውን የተመለከተ ዶክመንት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላኩት መሰረት ከላይ ተያይዟል)
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#Update
“ 11 ሰዎች አሁንም ያሉበት አልታወቀም። አንድ ሰው መገደሉ ተረጋግጧል ” -የሽርካ ወረዳ ቤተ ክኀነት
በአርሲ ዞን፤ ሽርካ ወረዳ በታጣቂዎች ታገቱ የተባሉ በርካታ ነዋሪዎች ያሉበት እንደማይታወቅ የወረዳው ቤተ ክኀነትና ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
የአካቢው ነዋሪዎች፣ “ ታጣቂዎቹ እገታውን የፈጸሙት ታኃሳስ 5 እና 6 ቀን 2017 ዓ/ም ነው። ከ20 በላይ ሰዎች ናቸው በታጣቂዎች የተወሰዱት ” ብለዋል።
የታገቱት የወረዳው ቤተ ክኀነት ስራ አስኪያጅ ጭምር መሆኑን ተናግረው፣ ሥራ አስኪያጁን ጨምሮ ዘጠኝ ሰዎች ገንዘብ ከፍለው እንደተለለቁም ሰሞኑን ገልጸውልን ነበር።
ቁጥራቸው በትክክል ባይታወቅም ከታጋቾቹ ውስጥ የተገደሉ ሳይኖሩ እንዳልቀረ፣ ቀሪዎቹ ታጋቾች ከእገታ እንዳልተመለሱ፣ ጭራሹንም ያሉበት እንደማይታወቅ ነዋሪዎቹ አስረድተዋል።
“ እንዲህ አይነት ድርጊት ሲፈጸም ይህ የመጀመሪያው አይደለም። በየጊዜው የሸኔ ታጣቂዎች በሚፈጽሙት እገታ ብዙ ሰዎች ተገድለዋል፣ እድለኛ የሆኑት በ100 ሺዎች ገንዘብ እየከፈሉ የተለቀቁ አሉ ” ሲሉ አስታውሰዋል።
“ እስከመቼ ድረስ ነው ህዝቡ በተወለደበት አገር በእንዲህ አይነት ሰቀቀን የሚኖረው ? የፍርድ ቀን እስኪመጣ ጮኸታችንን አሰሙልን ” ሲሉ ተማጽነዋል።
ስለጉዳዩ ማብራሪያ እንዲሰጡን የጠየቅናቸው የወረዳው ቤተ ክኀነት ሥራ አስኪያጅ ከቀናት በፊት በሰጡን ቃል፣ “ አሁን እቤቴ ገባሁ። ከእኔ ጋር ተይዘው የነበሩ ስምንት ሰዎች ጋር በአጠቃላይ ዘጠኝ ሰዎች ተለቀዋል ” ብለዋል።
የወረዳው ቤተ ክኀነት በዛሬው ዕለት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል ደግሞ፣ “ 11 ሰዎች ያሉበት አይታወቅም። አንድ ሰው መሞቱ ተረጋግጧል ” ብሎ የሁነቱን አሳሳቢት አስረድቷል።
የተለቀቁት ሰዎች ምን ያህል ገንዘብ በመክፈል እንደተለቀቁ ላቀረብነው ጥያቄ ሥራ አስኪያጁ በሰጡት ማብራሪያ፣ የገንዘቡ ጉዳይ ለመናገር እንኳ የሚመር መሆኑን ገልጸው፣ ብቻ የተለቀቁት ገንዘብ ከፍለው መሆኑ እንዲታወቅ ገልጸዋል።
“ የተወሰድንበት አቅጣጫው ስለሚለያይ፣ እኔም ሰሞኑን ችግር ላይ ስለከረምኩ መረጃውን ገና በደንብ ሰብስቤ ተጨማሪ ማብሪራያ እሰጣለሁ ” ሲሉ ጠቁመዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#Ethiopia #USA #Starbucks
የአሜሪካው ' ስታርባክስ / Starbucks ' ኤክስኪዩቲቭ ቫይስ ፕሬዝዳንት ሚሼል በርን ኢትዮጵያ፣ አዲስ አበባ ይገኛሉ።
በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ማሲንጋ እና የUSAID ዳይሬክተር ሆክላንደር ለበርን አቀባበል አድርገውላቸዋል።
አሜሪካ በኤምባሲዋ በኩል የስታርባክስን አመራር " እንኳን ወደ ኢትዮጵያ፤ ወደ ቡና መገኛዋ ሀገር በደህና መጡ " ብላለች።
የስታር ባክስ አመራር ሚሼል በርን በኢትዮጵያ ቆይታቸው በኢንዱስትሪው ውስጥ ስላለው አስደናቂ እድገት፣ በምርታማነት ላይ ስላሉ ኢንቨስትመንቶች ይመክራሉ ተብሏል።
በተጨማሪም በኢትዮጵያ ላሉ የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች የንፁህ ውሃ አቅርቦትን ማሳደግ በተመለከተ ይወያያሉ።
ስታር ባክስ (starbukcs) በቡና አቅርቦቱ በመላው ዓለም የሚታወቅ ከፍተኛ ሃብት ያለው ኩባንያ ነው።
@tikvahethiopia
#Ethiopia #France
የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢትዮጵያ ገቡ።
የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ከደቂቃዎች በፊት ኢትዮጵያ አዲስ አበባ ገብተዋል።
ፕሬዝዳንቱ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ነው አዲስ አበባ የገቡት።
ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ሲደርሱ የኢፌዴሪ ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተቀብለዋቸዋል።
ማክሮን አዲስ አበባ ከመምጣታቸው በፊት በጎረቤት ሀገር ጅቡቲ የስራ ጉብኝት አድርገዋል።
ቪድዮ ፦ ቢኤፍኤም ቲቪ
@tikvahethiopia
🚨 “ የሚላስ የሚቀመስ የለም ” - የአካባቢው ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ
🔴 “ ችግር እንዳለ ይታወቃል ” - የአማራ ክልል አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን
በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ቡግና ወረዳ በምግብ እጥረት ሳቢያ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እንደተጎዱ፣ በተለይ ጨቅላ ህፃናት የከፋ ስቃይ ላይ እንደሆኑ የአካባቢው ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
“ ጉዳዩ በጣም አሳዛኝ ነው። በእኛ ቦታው ያልሆነ ሰው አይገባውም ” ሲሉም የሁነቱን አስከፊነት አስረድተዋል።
ስሜ ከመነገር ይቆይ ያሉ የመረጃ ምንጭ በበኩላቸው፣ “ በቡግና ወረዳ ጉልሃ ቀበሌ አንድ ህፃን በምግብ እጥረት ሞቷል ” ብለዋል።
የቡግና ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ገብረ መስቀል አለሙ በበኩላቸው፣ በክልሉ ባለው ግጭትና ተፈጥሯዊ ተፅዕኖ ምክንያት ወረዳው ለድርቅና ለምግብ እጥረት በመጋለጡ ህፃናትን ጨምሮ ከ10 በላይ ሰዎች መጎዳታቸውን ሰሞኑንን ለቢቢሲ አማርኛ መናገራቸው አይዘነጋም።
በወረዳው በተከሰተ የምግብ እጥረት በተለይ ጨቅላ ህፃናት ስለተጎዱ ነዋሪዎቹ የድረሱልን ጥሪ ማሰማታቸውን በመግለጽ ችግሩን ለመቅረፍ ምን እየተሰራ ነው ? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ የጠየቀው የቡግና ወረዳ ኮሚዩኒኬሽን ጽህፈት ቤት፣ “ እኛ ጋር ስራ የለም ” የሚል አጭር ምላሽ ሰጥቷል።
ጽሕፈት ቤቱ፣ “ እውቅናው የለኝም ” ያለ ሲሆን፣ ጉዳዩን እንደሚያውቁት ነዋሪዎች መናገራቸውን ብንገልጽለትም፣ “ እስካሁም ምንም አይነት በሪፓርትም የመጣ ነገር የለም ” ብሏል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከቡግና ወረዳ በተጨማሪም ለአማራ ክልል ስጋት አደጋ ሥራ አመራር ኮሚሽን ተመሳሳይ ጥያቄ ያቀረበ ሲሆን፣ ኮሚሽኑ ችግሩ መኖሩን አምኗል።
የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ወ/ሮ ፍቅሬ ሙሉጌ በሰጡን ቃል፣ “ ጉዳዩ በኛ ቁጥጥር ውስጥ ነው። ከእኛ አቅም ውጪ የሆነ ነገር የለም ” ሲሉ ተናግረዋል።
አክለውም፣ “ ችግር እንዳለ ይታወቃል። ድጋፍ እየቀረበ ነው። ምንም የተለዬ ነገር የለም” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
“ የአምናውን ድርቅ ችግር ተቋቁመናል አሁን እንዲያውም ጥሩ ነው ምርት አምርተዋል ” ሲሉ ተናግረዋል።
ድጋፍ እየተደረገላቸው ከሆነ ምን ያክል ድጋፍ ተደርጓል ? ሰሞኑን ያደረጋችሁት ድጋፍ ነበር ? በተለይ ሰሞኑን ህፃናቱን የሚመግቡት እንደተቸገሩ ነዋሪዎቹ እየገለጹ ነው፣ ስንል ለወ/ሮ ፍቅሬ ተጨማሪ ጥያቄ አቅርበናል።
እሳቸውም በምላሻቸው፣ “ በቂ ድጋፍ እየተደረገላቸው ነው በተለመደው አግባብ (ድጋፉ የሚሰጥበት ቀመር አለው) ድጋፍ እየደረሳቸው ነው ” ከማለት ውጪ የችግሩን አስከፊነት ከመግለጽ ተቆጥበዋል።
ነዋሪዎቹ የላኳቸው ፎቶዎች ህፃናቱ በምግብ እጥረት እንደተጎዱ የሚመሰክሩ እንደሆኑ ገልጸን፣ ድጋፍ ካለ ጉዳዩ እንዴት በዚህ ልክ ጉዳት እንዳደረሰ ማብራሪያ እንዲሰጡ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ኃላፊዋን ጠይቋል።
በዚህም፣ “ ይለካል እኮ ማልኑውትሬሽን፣ ሞዴሬት የሆኑት እየተለካ ምግብ ሁሉ ይሰጣቸዋል ለእናቶች፣ ለህፃናት ” የሚል ምላሽ ሰጠተዋል።
“ ለዩኒሴፍም ይቀርባል። ለአዋቂዎች ደግሞ እህል ይቀርባል። የገንዘብ ደጋፍም ይሰጣልና ክትልትል እየተደረገ ነው ” ያሉት ወ/ሮ ፍቅሬ፣ “ በመሀል ደግሞ በህመምም በምንም ጉዳት ሊያጋጥም ይችላል ” ነው ያሉት።
የቡግና ወረዳ ኮሚዩኒኬሽንና ኮሚሽኑ ይህን ይበሉ እንጂ የቡግና ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤት ግን ለቢቢሲ አማርኛ በሰጠው ቃል፣ “ ማህበረሰቡ ምርት ባለማግኘቱ እናቶች ልጆቻቸውን ባግባቡ መግበው የተሻለ የጤና እድገት እንዳይኖራቸው አድርጓል ” ብሏል።
በሌላ በኩል ፤ የሰሜን ወሎ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አለሙ ይመር ዛሬ ለቪኦኤ በሰጡት ቃል " አካባቢው በፋኖ ታጣቂዎች ስር በመሆኑ ለተከሰተው የምግብ እጥረት መንግሥት በቶሎ ምላሽ መስጠት አልቻለም " ብለዋል።
የአካባቢው የሀገር ሽማግሌዎችና የኃይማኖት አባቶች በአደረጉት ጥረትም አሁን ላይ የርዳታ እህል ወደ ስፍራው እየተጓጓዘ መሆኑን አስታውቀዋል።
የወረዳው ነዋሪ ያለበትን የምግብና የጤና ችግር ለፋኖ ታጣቂዎችና ለመንግሥት አካላት ለማስረዳት ከተመረጡት 18 ግለሰቦች መካከል አንዱ ነበርኩ ያሉት ቄስ ገብረ እግዚአብሔር ዝናቤ ይርዳው " በአካባቢው የመንግሥት ባለሥልጣናትና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል በተደረሰው ስምምነት መድኃኒቶችንና አልሚ ምግቦች ወደ ወረዳው እየገቡ ነው " ብለዋል።
የኤሪካ ኤምባሲ ደግሞ ፤ የምግብ እጥረት ቀውስ ሰለመኖሩ የወጡ ሪፖርቶችን እየተከታተለ እንደሆነ አመልክቷል።
ቀውሱ መወገዱን ለማረጋገጥ እንደሚሠራም ጠቅሷል።
ኤምባሲው ቀውሱን በተመለከተ ዝርዝር መረጃዎችን አላካተተም።
የኢትዮጵያን ሕዝብ ለመደገፍ ፣ አጋሮቹ በአሁኑ ሰዓት በችግሩ በተጠቁት አብዛኞቹ ስፍራዎች የምግብ እና አልሚ ንጥረ ምግቦች ስርጭትን ያጠናከሩ መሆናቸውን አክሏል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#ደስደስበንጉስማልት
ንጉስ ማልት ከየትኛው ምግብ ጋር ተጣመረሎት? ስክሪን ሾት ያድርጉ፣ ከዛም ያገኛችሁትን ደስ ደስ የሚል ጥምረት በፌስቡክ ወይም በቴሌግራም ቻናሎቻችን ያጋሩን!
https://fb.watch/wiDa1wrfDa/ /channel/Negus_Malt
#nonalcoholic #ንጉስማልት #DesDesWithNegus #ደስደስበንጉስ #የጣዕምልኬት_የደስታስሜት
#ግብር
🔴 " አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ አዲስ መመሪያ አውጥቶ መክፈል የማንችለውን ግብር እየጠየቀን ነው " - መኪና አስመጪዎች
🔵 " የግብር ስወራው ተጨባጭ እንደሆነ በሸጡት መኪና ልክ ዋጋ እንደማይቆረጥ የተረጋገጠ ነው " - የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ
በአዲስ አበባ ከተማ ያሉ ተሽከርካሪ አስመጪዎች፣ " በ2015 ዓ/ም ተጠንቶ ተግባራዊ እንዳይሆን በሚል ቆይቶ ነበር " የተባለ መመሪያ ተግባራዊ በማድረግ የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ከአቅም በላይ የሆነ ግብር እየጠየቃቸው መሆኑን በመግለጽ ቅሬታቸውን በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል አሰምተዋል።
" በ2015 ዓ/ም ነበር ጥናቱ የተጠናው ፤ ከዛ 'ተግባራዊ አይሁን፣ ትክክል አይደለም' ተብሎ የተቀመጠ ጥናት ነው አሁን መመሪያ ተደርጎ በትዕዛዝ የወረደው " ሲሉ ነው የተናገሩት።
አስመጪዎቹ ስለዝርዝር ቅሬታቸው ምን አሉ ?
" አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ አዲስ መመሪያ አውጥቶ መክፈል የማንችለውን አላስፈላጊ ግብር እየጠየቀን ነው። ይሄን የሚያደገው 'ሲስተም አዘጋጅቻለሁ' በሚል ነው።
አዲሱ ሲስተም የስሪት፣ የተመረተበትና የመጣበት አገር ይጠይቃል፣ በጥናት መልክ ተዘጋጅቶ ተግባራዊ እንዲሆን ብሎ በአዲስ አበባ በሁሉም ቅርንጫፎች ኤክስኤል ሰርቶ አውርዶ ሥሩ ብሏል።
'ከጉምሩክ ዴክላራሲዮን ላይ ሒሳቡ ሲሰላ ከ45 በመቶ በላይ የሆነ ትርፍ እያተረፋችሁ ነው’ በሚል ነው አዲስ አሰራር ያመጣው።
ይህ መመሪያ ከገቢዎች ሚኒስቴር የተለዬ፣ ፌደራልና ክልል ላይ የሌለ፣ በአዲስ አበባ ብቻ፣ የመኪና አስመጪዎችን ብቻ በተመለከተ የተዘጋጀ መመሪያ ነው።
በዚህ መመሪያ መሠረት የተጠየቅነው ግብር አላስፈላጊ፣ ከህግ አግባብ ውጪ የሆነ ነው። ምክንያቱም ግብር በህግ ነው እንጂ በጥናት አይደለም የሚከፈለው።
ግብር ሲከፈል ህግ ተረቆ፣ በተወካዮች ምክር ቤት ጸድቆ ነው። ለአዲስ አበባና ለድሬዳዋ ከተማ አስተዳደሮች የግብር መመሪያ የሚያወጣው ደግሞ ገቢዎች ሚኒስቴር ነው።
ይሄን አዲስ መመሪያ ግን የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ በራሱ በደብዳቤ መልኩ ነው ወደታች ያወረደው ከአሰራር ውጪ በሆነ መልኩ።
እስከዛሬ ጉምሩክ ባስቀመጠው መሠረት ከፍተኛው ጣራ 9% ተደርጎ እኛም 4ም፣ 5ም% አተረፍን ብለን አቅርበን ነበር የምንፈፍለው።
አሁን ግን ቢሮው ሌላ የራሱን ሰንጠረዥ አዘጋጅቶ ለ11ዱም ክፍለ ከተሞች ይህንን መመሪያ አወረደ በትዕዛዝ መልክ። መመሪያው የወረደው ‘ከ45 በመቶ በላይ እያተረፋችሁ ነው የዚህን ግብር ክፈሉ’ በሚል ነው።
ከዚህ ቀደሙ ግብር ጋር ሲነጻጸር 5% አትርፌአለሁ ብለሸ አሳውቆ ግብር ሲከፍል የነበረን ሰው ‘45% ታተርፋለህ’ ማለት በጣም ብዙ እጥፍ ነው። የህግ አግባብ የለውም አሰራሩ።
በፌደራል ደረጃ ንግድ ፈቃድ አስመጪዎች ያላቸው መኪና መሸጫ አላቸው። የእነርሱ በኖርማሉ ነው፣ እነርሱን አይመለከትም መመሪያው። ክልል ያሉትንም በተመሳሳይ አይመለከትም።
አዲስ አበባ ውስጥ ሆነው ክፍለ ሀገርም ሆነው የክፍለ ሀገር ፈቃድ አውጥተው (ለምሳሌ የክልል፣ የፌደራል ፈቃድ ያላቸው) ከኛ ጋር ተመሳሳይ መኪና የሚሸጡ አሉ።
እነርሱን ግን ይሄ አዲሱ የግብር መመሪያ አይመለከትም። አንድ ከተማ ውስጥ ተመሳሳይ አይነት መኪና እየሸጡ እያሉ።ይሄ ትልቅ ልዩነት ነው የሚያመጣው።
የፌደራል ገቢዎች የማያውቀውን ተመን እንዴት አንድ የከተማ አስተዳደር በራሱ ያወጣል? ይሄ አሰራር የህግ ግራውንድ የለውም። ቅሬታችን ይሰማልንና ትግበራው ይስተካከልልን” ብለዋል።
አዲስ አበባ ያሉ ተሽከርካሪ አስመጭዎች ከዚህ ቀደም ያልነበረ አሰራር ወርዶ ከመጠን ያለፈ ግብር ተጠየቅን ለሚለው ቅሬታቸው ያላችሁ ምላሽ ምንድን ነው ? ስንል ለአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ጥያቄ አቅርበናል።
የቢሮው ኃላፊ አቶ ቢኒያም ምክሩ ምን ምላሽ ሰጡ?
" በሚቆረጠው ደረሰኝና ገበያ ላይ ባለው ዋጋ መካከል ያለው ልዩነት በጣም ሰፊ ነው፡፡ ይህንን ለማስተካከል ነው ጥናቱ የተጠናው።
የግብር ስወራው ተጨባጭ እንደሆነ በሸጡት መኪና ልክ ዋጋ እንደማይቆረጥ የተረጋገጠ ነው።
ምንም የተጣሰ የህግ ክፍተትም የለውም። ከተማው በማንዴቱ ነው የሰራው። ዋናው ዓላማ ግን ከፍተኛ የሆነ የታክስ ስወራ ስላለ ያን ለማስቀረት ነው።
ከተማው ማንኛውም መኪና የሚገዛ ሰው ስንት ብር ነው የገዛው? በትክክል በገዛውና በከፈለው ገንዘብ ልክ ደረሰኝ ተሰጥቶታል ወይ? በስት አካውንት ነው ገንዘብ እንዲያስገባ የሚጠየቀው? የሚለው የአደባባይ ምስጢር ነው።
ስለዚህ የግብር ስወራው ተጨባጭ እንደሆነ በሸጡት መኪና ልክ ዋጋ እንደማይቆረጥ የተረጋገጠ ነው።
እዚህ ላይ ልዩነት አለኝ የሚል ማንኛውም ሰው መጥቶ ልንወያይ እንችላለን በራችን ክፍት ነው " ብለዋል።
(ኃላፊው፣ ቅሬታ አቅራቢዎቹ በገለጹት መሠረት ላቀረብንላቸው ጥያቄዎች የሰጡን ሙሉ ማብራሪያ በቀጣይ ይቀርባል)
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
ታታሪ የወጣቶች ዋዲያህ የቁጠባ ሒሳብ
የሸሪዓውን የዋዲያህ መርህ ተከትሎ በሕብር ሀቅ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ስር የሚገኘውን እና እድሜያቸው ከ 18-30 ዓመት ለሆኑ ወጣቶች የቀረበውን ታታሪ የወጣቶች የቁጠባ ሒሳብ እንድትጠቀሙ ተጋብዘዋል፡፡
ጁመዓ ሙባረክ!
ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!
📞 ለበለጠ መረጃ ወደ 995 ነፃ የጥሪ ማዕከል ይደውሉ፡፡
🤳 በቀላሉ አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ የቴሌግራም ገፃችንን አሁኑኑ ይቀላቀሉ፡፡ /channel/HibretBanket
🌐 ሌሎች የማህበራዊ ገፆቻችንን እና ድህረ ገፃችንን linktr.ee/Hibret.Bank ይጎብኙ፡፡
#islamicbanking #islamicfinance #interestfree #YouthfulIslamicBanking
" የኑሮ ውዶነቱ ከህዝብ አቅም በላይ ሆኖ ምሬትና ተስፋ መቁረጥ በአደገኛ ሁኔታ የመሰደድን ምርጫ እያጎላው መጥቷል " - ተቃዋሚ ፓርቲዎች
የተቃዋሚ ፓርቲዎች ኮከስ (ኮከስ) ምን አለ ?
- የመድረክ
- የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ)
- የኅብር ኢትዮጵያ
- የዎላይታ ብሔራዊ ንቅናቄ
- የኦሮሞ ነጻነት ግንባር
- የኢሕአፓ ... ተቃዋሚ ፓርቲዎች ኮከስ በወቅታዊ ሁኔታ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መግለጫ ልኳል።
ኮከሱ ምን አለ ?
የተቃዋሚ ፓርቲዎች ኮከሱ ገዢውን የብልጽግና ፓርቲ አስተዳደር በእጅጉ ኮንኗል።
በብልፅግና ፓርቲ የሚመራው መንግስት ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ " የአገራችን ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ተጨባጭ ሁኔታዎች ከዕለት-ወደ ዕለት ከድጡ ወደ ማጡ እየተጓዙ ነው " ብሏል።
ይህም ለሁለንተናዊ ምስቅልቅሎሽ እየዳረገን ነው ሲል ወቅሷል።
" ፖለቲካችን የተለመደውን የአፈናና አግላይነት፣ የአንድ ፓርቲ የበላይነትና ጠቅላይነት አጠናክሮ ቀጥሏል " ያለው ኮከሱ " የፖለቲካ ፓርቲዎች ከአጃቢነት፣ ህዝብ ከአገልጋይነት ያለፈ የፖለቲካ መብታቸውን የማንሳት ህገመንግስታዊ መብት ተነፍጓቸው በወንጀል ተቆጥሮባቸው ፀጥ-ለጥ ብለው እንዲገዙ ተፈርዶባቸው በከፍተኛ ድብርት ውስጥ ናቸው " ብሏል።
ኢኮኖሚው ወደ ጦርነት ኢኮኖሚ ተሸጋግሮ ለተለያዩ የልማት መሰረተ ልማት አውታሮች ሊውል የሚችል የዓመታዊ በጀት ከፍተኛውን ድርሻ ለጦርነትና ጸጥታ ማስከበር ግብዓቶች እንዲውል ተደርጓል ሲል ወቅሷል።
" ልማትና ዕድገት ከቀለም-ቅብ ያለፈ መሰረት እንዳይኖረው ተገደናል " ሲልም አክሏል።
" የኑሮ ውድነቱ ከህዝብ አቅም በላይ ሆኖ ምሬትና ተስፋ መቁረጥ በአደገኛ ሁኔታ የመሰደድን ምርጫ እያጎላው መጥቷል " ሲልም ገልጿል።
ኮከሱ " ማኅበራዊ ህይወታችን በሥራ አጥነት፣ መፈናቀል፣ የማኅበራዊ ተቋማት መዳከምና የአገልግሎት መቋረጥ ወይም መቀንጨር፣ የሠራተኞች ብሶት መገለጫቸው ከሆነ ውሎ አድሯል " ብሏል።
" በየአቅጣጫው የሚነሱት ጥያቄዎችም የሚያረጋግጡት ይህንኑ ነው " ሲል ገልጿል።
" ከትምህርትና ጤና አገልግሎት ተቋማትና ሠራተኞች የሚሰማው ጩሄት በእጅጉ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል " ሲልም አመልክቷል።
ኮከሱ፦
- " ግጭትና ጦርነትን እያስፋፉ - የይስሙላ አግላይ የምክክርና ውይይት ስብከት ሊቆም ይገባል " ብሏል። " መንግስት / ገዢው ፓርቲ / ከማስመሰል ተላቆ ራሱንና የአገሪቱን የፖለቲካ መድረክ ለሁሉን አካታችና አሳታፊ ተዓማኒና በባለድርሻ አካላትና አስፈጻሚዎች ተቀባይነት ያለው ሃቀኛ የምክክር ፣ ድርድር ፣ ውይይት መድረክ እንዲያመቻች ሽግግሩ በመጨናገፉ የቀጠለውና የተስፋፋው ጦርነት በአስቸኳይ እንዲቆም " ሲል ጠይቋል።
- የመድብለ ፓርቲ ሥርዓት ማጠናከር ዓላማና ተልዕኮ ይዞ ፤ የገዢውን ፓርቲ ጨምሮ ሌሎች የፖለቲካ ኃይሎች ያቋቋሙት የጋራ ምክር ቤት ከተቋቋመበት ዓላማና ተልዕኮ እየራቀ የገዢው ፓርቲ ታዛዥ ጉዳይ ፈጻሚና አስፈጻሚ እንዲሆነ ጫና እየተደረገበት ነው " ብሏል።
- " የፖለቲካ ድርጅቶች ሃሳብ መለዋወጫ እንዲሆን የመሠረቱትን የጋራ ምክር ቤትን ብልጽግና ቀስ በቀስ በስልታዊውና በሚታወቀው የኢህአዴግ አካሄድና ዘዴዎች አሽመድምዶታል " ሲል ገልጿል።
- " ህወሓት መር የነበረው ኢህአዴግ ይሠራቸው የነበሩት ዕመቃዎች፣ ጥሰቶች፣ ተንኮልና ደባዎች፣ አስርጎ የማስገባትና የመከፋፈል ሤራዎች፣አሁን በወራሹ ብልጽግና ደምቀውና ጎልተው ያለድብብቆሽና ይሉኝታ እየተደገሙ ነው " ሲል ወቅሷል።
- " ብልጽግና በአደባባይ ኃሳብን በነጻነትና ያለመሸማቀቅ የመግለጽ መብት መከበርን ቢሰብክም በተግባር ግን ህገመንግስታዊ ድንጋጌዎችን በአዋጅ፣ በመመሪያና ደንብ እያፈነ ይገኛል " ሲል ከሷል።
- " ሽግግር በሌለበት የሽግግር ፍትህ ውዳሴ " ከንቱ ነው በማለት ከመንግስት/ የገዢ ፓርቲ ተጽዕኖ ነጻ የሆነ የፍትህ ሥርዓት እንዲኖር ጠይቋል። በመንግሥት አደራጅነት የሚቋቋም የሽግግር ፍትህ ተቋም ከዚህ በፊት ከተቋቋሙትና ያለውጤትና ሪፖርት ከተበተኑት ኮሚሽኖች የተለየ ውጤት አይጠበቅም ብሏል። ለአካታች፣ አሳታፊና ተዓማኒ የሽግግር ሂደትና ተቀባይነት ያለው ህጋዊ የፍትህ ሥርዓት እንዲዘረጋ፣ እንዲተገበርና ሠላምና መረጋጋት እንዲሰፍን ጥሪ አቅርቧል።
- " የሰብዐዊ መብት ተሟጋቾችና የዲሞክራሲ አጋሮች እየተበረታቱ ሳይሆን እየተሸማቀቁ ነው " ብሏል።
- " ዕለት ከዕለት የገዥው ብልጽግና አምባገነዊነትና አማቂነት እየጎላና እየተበራከተ ነው የመጣው " ያለ ሲሆን " የፖለቲካ ምህዳሩ እየጠበበ መጥቶ ተኮማትሯል። " ሲል ገልጿል። " በተቃዋሚነት የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ድርጅቶች ነፃነትና ሊጫወቱ የሚችሉት ሚና በመግለጫዎች እንዲወሰን ተደርጓል " ሲልም ወቅሷል። " ሠላማዊ ሠልፍ ለመጥራት መዘጋጀት፣ ህገመንግሥት የሚፈቅደው መብት ሆኖ ሳለ- ያሳስራል፣ ለከፋም ጉዳት ይዳርጋል " ብሏል።
- " በገዥው የብልጽግና ፓርቲ ሹመኞች፣ ሃላፊነት በጎደለው ፍላጎትና ውሳኔ፣ በዋና ከተማችን ‹የኮርደር ልማት› በሚል የተጀመረው የመኖሪያና ንግድ ቤቶችንና ህንጻዎችን በማፍረስ ህዝብን በማፈናቀል ለከፍተኛ ማኅበረ-ኢኮኖሚ ቀውስና ለጎዳና ተዳዳሪነት አጋልጧል " ብሏል። " ይህ ኅብረተሰቡንና ባለድርሻ አካላት ተሳትፎና ከፖለቲካ ገለልተኛ ሙያዊ ጥናት ውጪ የሚደረገው ዜጋ አሰቃይ እርምጃ ወደ ክልል ከተሞች እየተዛመተና ሥቃዩን በመላ አገሪቱ እያዳረሰ ነው " ሲል ተቃውሟል። " ግቡ ለቀጣዩ ምርጫ የቅስቀሳ ግብዓት ነው " ብሏል። " የኮርደር ልማት በገዥዎች የረጅም ጊዜ አብሮነታቸውና ማኅበረ-ኢኮኖሚ ቁርኝታቸው የማይፈለገውን የማኅበረሰብ አባላት ማፈናቀልና መበተን ስለሆነ ሥራው ያለምንም ተጠያቂነት፣ በማናለብኝነት መንፈስ፣ በጥድፊያ እየተካሄደ ነው " ሲል ወቅሷል።
- " በርካታ የህዝብ የመሰረተ ልማት ፍላጎቶችና ጥያቄዎች ወደ ጎን ተብለዋል። ውዱን የአገርና ህዝብ ሃብት ከመንገድ ስፋትና፣ ህንጻ መቀባትና ሣር መትከል አልፎ ለቤተመንግሥት ግንባታ ጭምር እየዋለ መሆኑ ለዜጎች ህይወትና ኑሮ ደንታ ማጣት- ኢሰብዐዊነት ነው " ሲል ወቅሷል።
ኮከሱን መንግስትን " ጦርነትን እንደ መግዣ ሥልቱ እየተጠቀመ ነው " በሚል ወቅሶ እንዲህ አይነት መንግሥት " የሠላምና ልማት ጠንቅ ነው " ብሏል።
" አገሪቱ ከገባችበትና ካለችበት እጅግ አሳሳቢና ፖለቲካዊ ማህበረ-ኢኮኖሚ ምስቅልቅል እንድትወጣ፣ በየአቅጣጫው ከሚሰማውና ህዝባዊ የህልውና ጥያቄ፣ ከሚታየው የትጥቅ ትግል መፍትሄ ለመስጠት ተኩስ ቆሞ ሃቀኛ፣ ሁሉን-አቀፍ፣ አሳታፊ፣ ብሄራዊ መግባባትና ዕርቅ ለማውረድ ተዓማኒ ውይይት/ምክክርና ድርድር እንዲደረግ " ሲል ጥሪ አቅርቧል።
(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)
@tikvahethiopia
#Tigray
በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ሚመራው የህወሓት ቡድን በቀጣይ " አዲስ እና ሰላማዊ የትግል ስልት እከተላለሁ " ብሏል።
ቡድኑ በቀጣይ አጠቃላይ አባላቶቹ በመጠቀም " የእምቢተኝነት ዘመቻ " ያለውን እንቅስቃሴ ለማድረግ እንዳቀደ ተነግሯል።
ለዚህ ዘመቻ " እምቢ ለብሔራዊ ክህደት፣ ለአገዛዝ እና ብተና " የሚል መፈክር እንደሰጠው ዶቼ ቨለ ሬድዮ ዘግቧል።
ትላንት እና እና ዛሬ የደብረፅዮን (ዶ/ር) ቡድን ከፍተኛ ካድሬዎቹ ስብሰባ ተቀምጠው ነው የዋሉት።
@tikvahethiopia
#Update
🚨“ አቶ ክርስቲያን ታደለና ዮሐንስ ቧያለው ዛሬ የሐኪም ቀጠሮ ነበራቸው ማረሚያ ቤቱ አልወሰዳቸውም ” - ቤተሰቦቻቸው
🔴 “ በሕይወት የመኖር መብታቸውን ነው ያሳጧቸው። የእስረኛ ዝውውር ወይስ በሕይወት የመኖር መብት ነው የሚቀድመው ? ” - ጠበቃ ሰለሞን ገዛኸኝ
አዋሽ አርባ እስር ቤት በነበሩበት ወቅት ባደረባቸው የጤና እክል በወቅቱ ባለመታከማቸው ለአንጀት ድርቀት ህመም የተዳረጉት አቶ ክርስቲያን ታደለና አቶ ዮሐንስ ቧያለው፣ ሰሞኑን የቀዶ ህክምና ተደርጎላቸው ወዲያው ወደ ማረሚያ ቤት በመመለሳቸው ደም እየፈሰሳቸው እንደሆነ፣ ዛሬም የሀኪም ቤት ቀጠሮ እንደነበራቸው ቤተሰቦቻቸው ትላንት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸው ነበር።
ለዛሬው ሀኪም ቤት ቀጠሯቸው ሄዱ ?
ሁሉቱም ዛሬ (ሐሙስ ታህሳስ 10 ቀን 2017 ዓ/ም) ለቸካፕ ቀጠሮ የነበራቸው ቢሆንም ማረሚያ ቤቱ እንዳልወሰዳቸው ቤተሰቦቻቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
አቶ ዮሐንስ ቧያለው እና አቶ ክርስቲያን ታደለ ተደጋጋሚ የደም መፍሰስ እያጋጠማቸው በመሆኑ ቁስላቸው ለኢንፌክሽን እንዳይጋለጥ ለቸካፕ ለዛሬ በመቅረዝ ሆስፒታል ቀጠሮ እንደነበራቸው አስረድተዋል።
ቀጠሮው ስለሰርጀሪው ፣ ለቅድመ ካንሰር ምርመራ ውጤቱ፣ ለቀጣይ ተከታታይ ህክምና የሚሰጣቸውን የቀጠሮ ቀን የሚውቁበት እንደነበር ገልጸው፣ “ ቢሆንም ማረሚያ ቤቱ አልወሰዳቸውም ” ሲሉ ወቅሰዋል።
የእነ የአቶ ክርስቲያንና ዮሐንስ ጠበቃ ሰለሞን ገዛኸኝ በበኩላቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን አሉ ?
“ በቀጠሮው አለመሄዳቸው ጉዳት ያመጣል። ለሁለት ነገር ነው በምርመራ ላይ ያሉት። አንደኛ በፊንጢጣ በኩል ኦፕራሲዮን ተደርገው ደም እየፈሰሳቸው ነው።
አዋሽ አርባ በነበሩበት ወቅት የአንጀት ድርቀት ገጥሟቸው ባለመታከማቸው በኋላ ላይም በሽብር ወንጀል ተከሰው ፍርድ ቤት ከቀረቡ በኋላ በብዙ ጭቅጭቅ ማረሚያ ቤቱ ወደ ሀኪም ቤት ቢሄዱም የሰርጀሪ ደሙ አልቆመም።
ሆስፒታሉም ‘በዚህ ቀን ይዛችሁ ኑ’ ብሎ ፐርስክርፒሽን ሰጥቷል። ይሄ ህመም ነው የጤና ጉዳይ ነው። የዛሬ የሆስፒታል ቀጠሮ የሚፈሰውን ደምና የቁስሉን ምንነት ለማረጋጠጥ ነበር።
ሁለተኛ የአንጀታቸውን በተመለከተ ኦፕራሲዮን ለማድረግ የካንሰር ምርመራ አድርገዋል። ውጤት ለማወቅ ነበር ቀጠሮው። ግን ከቤተሰቦቻቸው የሰማሁት በቀጠሯቸው መመሠረት ሀኪም ቤት እንዳልወሰዷቸው ነው።
ማረሚያ ቤቱ ያቀረበው ምክንያት ‘እስረኞቹን ወደ ሌላ ቦታ እያዘዋወርን በመሆኑ አጃቢና መኪና ስሌለ ነው’ በሚል ነው። ይሄን በተመለከተ ፍርድ ቤት ምስክር በምናሰማቸው በነ ዶክተር ወንድወሰን አሰፋ መዝገብ ዐቃቢ ህግ ምስክር እያሰማ እዛው ውለናል ከትላንትና ትላንት ወዲያ።
‘እስረኛ እያዘዋወርን ስለሆነ አናመጣቸውም’ የሚል ወረቀት ቢያስገቡም ‘አይቻልም’ ብሎ ፍርድ ቤቱም ትዕዛዝ ስለሰጣቸው ትላንትናም አምጥተዋቸዋል። ትላንትም ምስክር ሰምተናል፣ ዛሬም ምስክር ሰምተናል።
ታዲያ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሲሆን ብቻ ነው እንዴ እነርሱ የሚያከብሩት ? በእርግጥ እስረኛ እያዘዋወሩ እንደሆነ ይታወቃል። ግን ምስክር ለመስማት ‘አምጡ’ ሲባሉ ነው ተገደው ማምጣት ያለባቸው ወይስ የሕይወትና የሞት ጉዳይ ሲሆን ነው አፋጣኝ እርምጃ ወስደው ማምጣት ያለባቸው ?
መቼም የማረሚያ ቤት አስተዳደር ብዙ ጠባቂዎች አሉ። እንደምንም ተፈልጎም መኪናም ተከራይተውም ቢሆን የሕይወት ጉዳይ ስለሆነ በቀጠሯቸው መሠረት አምጥተው ማሳከም ነበረባቸው።
ስለዚህ ድርጊቱ አግባብ አይደለም። ይሄ በሕይወት የመኖር መብትንም የሚጣረስ ነው። እነዚህ ሰዎች አሁን ደም እየፈሰሳቸው ነው በቀጣይነት ደሙ ቢፈስስ? የቅድመ ካንሰር ምርመራ ሕይወት ወደማሰጣት ቢደርስስ ?
በመሆኑም በሕይወት የመኖር መብታቸውን ነው ያሳጧቸው። የእስረኛ ዝውውር ነው ወይስ በሕይወት የመኖር መብት የሚቀድመው? በሕይወት የመኖር መብት ነው መቅድም ያለበት ” ሲሉ ተናግረዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
" ትኩረት መነፈጋችን እጅጉን አሳዝኖናል " - የሽርካ ወረዳ ነዋሪዎች
በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት ሽርካ ወረዳ ታኅሣሥ 5 እና 6 ቀን 2017 ዓ.ም የወረዳ ቤተ ክህነቱን ሥራ አስኪያጅ ጨምሮ 20 ኦርቶዶክሳውያን በታጣቂዎች ግድያና እገታ እንደተፈጸመባቸው ነዋሪዎቹን ዋቢ በማድረግ የቤተክርስቲያኒቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
ከታገቱት ውስጥ የወረዳው ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅና ሌሎች 8 ሰዎች ገንዘብ ከፍለው ተለቀዋል።
ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ሰዎችም ግድያ እንደተፈጸመባቸው እንዲሁም ያሉበት እንደማይታወቅ ነዋሪዎች አመልክተዋል።
ታጣቂዎች ከ80 በላይ ከብቶችን መውሰዳቸውም ተነግሯል።
ሀገረ ስብከቱ በየዓመቱ በሚካሄደው በ43ኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ በ2016 ዓ.ም 271 ኦርቶዶክሳውያን መገደላቸውን ገልጾ ነበር።
በተጨማሪ ከ10 ቀበሌ ገበሬ ማኅበር ውስጥ 91 ሰዎች ሕይወታቸው ሲያልፍ ቁጥራቸው ከፍተኛ የሆነ ምእመናን ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል ሲል ሪፖርቱን አቅርቦ ነበር።
በዚሁ ሪፖርት በጀጁ ወረዳ ቡርቃ ጉራቻ ቅ/ማርያም ቤተ ክርስቲያን አካባቢ የሚኖሩ 150 ምእመናን በጉሬ ደቢኖ ቅ/እግዚአብሔር አብና አርጆ ቅ/ጊዮርጊስ ከ30 በላይ ምእመናን መገደላቸው የተገለጸ ሲሆን 499 አባወራና እማወራ ተፈናቅለዋል።
ባለፈው ኅዳር 19 እና 20 ቀን 2017 ዓ.ም ደግሞ የ13 ዓመት ታዳጊና የ80 ዓመት አዛውንትን ጨምሮ 11 ሰዎች በጥምቀተ ባሕር ማክበሪያ ላይ ተወስደው መገደላቸውን 6 ምእመናን ደግሞ ያሉበት አለመታወቁ መገለጹ አይዘነጋል።
የዚህ አካባቢ ጉዳይ በጠቅላይ ቤተ ክህነትም ሆነ በመንግሥት ትኩረት ተነፍጎታል ሲሉ ነዋሪዎች ወቅሰዋል።
ነዋሪዎቹ ግድያና ስደት እንዲሁም የሀብት ዝርፊያ ሰሚ ያጣና በወረዳው ተጠናክሮ የቀጠለ በመሆኑ የአካባቢው ምእመናን በትልቅ ተስፋ መቁረጥ ውስጥ መሆኑን ተናግረዋል።
" የማይጠቅሙና አንዳች ፋይዳ የሌላቸው ጉዳዮችን ሲዘግቡ የሚስተዋሉ ሚዲያዎች የእኛ ሞት እንደምን ቀለላቸው ? እንዲሁም ከሀገረ ስብከቱ ጀምሮ እስከ ጠቅላይ ቤተ ክህነት በወረዳችን እየተፈጸመ ያለው ግፍ ትኩረት አለመሰጠቱ እጅጉን አሳዝኖናል " ሲሉ ወቅሰዋል።
" መንግሥትም የዜጎቹን ደህንነት የመጠበቅ ግዴታ እንዳለበት በመገንዘብ ሞታችንን ሊያስቆምና መፍትሔ ሊያመጣ ይገባዋል " ሲሉ ማሳሰባቸውን ማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት ዘግቧል።
ፎቶ ፦ ፋይል
@tikvahethiopia
#Update
🚨 “ ግብረሰዶም ወደ ሚፈጸምበትና ኩላሊት እያወጡ የሚሸጡበት ሰዎች ወዳሉበት ኮሎምቢያ ሊሸጧቸው እንደሆነ ሰምተናል” - በማይናማር ያሉ ኢትዮጵያዊያን ወላጆች ኮሚቴ
➡️ “ አዲስ መረጃ ካለ አሳውቃለሁ ” - ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር
ኑሮን ለማሻል በሚል ወደ ታይላንድ የሄዱና በኃላም ወደ ማይናማር የተወሰዱ ኢትዮጵያዊያን በጋንግስተሮች እጅ ወድቀው ከውላቸው ውጪ ህገወጥ የዶላር ማጭበርበር ሥራ ለመስራት እንደተገደዱ ቤተሰቦቻቸው ጭምር መግለጻቸው ይታወሳል።
የታጋቾቹ ወላጆች ያቋቋሙት ኮሚቴም፣ “ ልጆቻቸን በስቃይ ውስጥ ነው ያሉት መንግስት አንድ መፍትሄ ይፍጠርል ” ሲል በቅርቡ በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል ማሳሰቡ አይዘነጋም።
በወቅቱ ምላሽ የጠየቅነው የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ደግሞ፣ ቶኪዮ ባለው ኤምባሲ አማካኝነት ንግግር እየተደገ መሆኑን ገልጾ፣ “ ልጆቹ የማይናማር መንግስት የሚቆጣጠረው ቦታ ላይ አይደለም ያሉት ለዛ ነው ችግሩ እጅግ አስቸጋሪ የሆነው ” ብሎ ነበር።
የኢትዮጵያውያኑ ጉዳይ ከምን ደረሰ ?
የኢትዮጵያዊያኑ ወላጆች ኮሚቴ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል፣ “ ግብረሰዶም ወደሚፈጸምበትና ኩላሊት እያወጡ የሚሸጡበት ሰዎች ወዳሉበት ኮሎምቢያ ሊሸጧቸው እንደሆነ ሰምተናል ” ሲል ገልጿል።
ኮሚቴው በዝርዝር ምን አለ ?
“ ልጆቻችን ገና አልወጡም። ወደ ሦስት ሀገራት ዜጎቻቸውን አስወጥተዋል። የ18 የመካከለኛው ምሥራቅ ሀገራት ልጆች ናቸው እየተሰቃዩ ያሉት።
ሦስቱ ሀገራት ከእነዛ ጋንግስተር ቡድን ተነጋግረው አቅጣጫዎችን አስቀምጠው የሚከፈለውን ዋጋ ከፍለው ነው ልጆቻቸውን ያስወጧቸው።
በአጋጣሚ ከወጡት ከፊሊፒን ዜጎች ወክሎ ሲንቀሳቀስ የነበረን ሰው አድራሻ አግኝተን (የታይላንድ ፓሊስ ኮማንደር ነው) በምን አይነት ሁኔታ ልጆቻቸውን እንዳስወጡ ኮንታክት እያደረግን ነበር። ያንን ኢንፎርሜሽን ለውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ለመስጠት ሞክረናል።
ሌሎች ዜጎች ስለወጡ በአሁኑ ወቅት ልጆቻችን ብቻቸውን በግላጭ ስለቀሩ ስቃዩ በርትቷል። ጭራሽ እንዲያውም በግብረሰዶም ወደምታትታወቀው ኮሎምቢያ ሊሸጧቸው እንደሆነ ሰምተናል። ፈጣሪ ይጠብቅልን እንጂ።
እጅ በእጅ ነው ልጆቹን አስተላልፈው የሚሸጡትና ይሄ ጊዜ የማይሰጥ ጉዳይ ስለሆነ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ትኩረት በመስጠት ልጆቻችንን በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደ ሌሎችንም ሀገራት ወዳሉበት ቀርቦ በተለይ ከታይላንድ መንግስት ጋር ተነጋግሮ መፍትሄ ይስጠን።
ማይናማርን ማነጋገር እንዳለ ሆኖ የታንላንድን መንግስት ማነጋገር ለሁለት ነገር ይጠቅማል። ለክፍያ የሚጠይቁትን ገንዘብ በማስቀረት እንዳይታሰሩ ለማድረግና ካሉበት መከራ እንዲወጡ ለማድረግ።
ከጋንግስተሮቹ ጋር ቀረቤታ አለው ተብሎ ነው የሚታሰበው የታይላንድ መንግስት። ሌሎች ሀገራትም ይህንኑ ሲስተም ነው የተጠቀሙት የኢትዮጵያ መንግስትም ይህን መንገድ ተጠቅሞ ልጆቹ የሚወጡበትን መንገድ እንዲያመቻች በአጽንኦት እንጠይቃለን” ሲል አሳስቧል።
ወደ 111 ወላጆች ቆንስላ ጽህፈት ቤት ለአንድ አመት ተመላልሰው መፍትሄ ባለማግኘታቸው ትላንት ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ባነር ይዘው ከሚኒስትሮች መፍሄ እንደጠየቁ፣ ሚኒስቴሩም ከኢትዮጵያ ሰዎችን ለመላክ እንደተወሰነና በአጭር ጊዜ ውስጥ ምላሽ ለመስጠት ቃል እንደገባ ኮሚቴው አስረድቷል።
ምን አዲስ ነገር አለ? ጉዳዩ ከምን ደረሰ? ተብሎ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ የቀረበለት ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር በበኩሉ፣ “አዲስ መረጃ ካለ አጋራለሁ” ብሏል። (ጉዳዩን እስከመጨረሻው የምንከታተለው ይሆናል)
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#ዮናታንቢቲፈርኒቸር
በዓሉን ምክንያት በማድረግ ልዩ ቅናሽ የተደረገባቸውን ውብ እና ምቹ የመመገቢያ ጠረጴዛዎቻችንን አሰናድተን ሞቅ ካለ መስተንግዶ ጋር እይጠበቅንዎ እንገኛለን! 🎁
🌐 የማህበራዊ ገጾቻችንን ይቀላቀሉ
Telegramyonatanbtfurniture?is_from_webapp=1&sender_device=pc">👉 Telegram/yonatanbtfurniture
Facebook👉 Facebook/yonatanbtfurniture
Insagram👉 Instagram/yonatanbtfurniture
TikTok 👉 yonatanbtfurniture?is_from_webapp=1&sender_device=pc">TikTok/yonatanbtfurniture
የውበት፣ የጥራት እና የምቾት ዳር ድንበር
ዮናታን ቢቲ ፈርኒቸር !
📍አድራሻችን
1.ፒያሳ እሪ በከንቱ ቢቲ ታወር (ከኢቲዮ ሴራሚክ ዝቅ ብሎ)
2.ከዊንጌት አደባባይ አለፍ ብሎ ከአቢሲኒያ ባንክ ፊትለፊት
3.ከሲኤምሲ አደባባይ ወደ አያት መንገድ መሪ ሳይደርስ (ዘመን ባንክ አጠገብ)
☎️ +251957868686/ +251995272727/ +251993828282
#Arabic
" የአረብኛ ቋንቋ ትምህርት ለማስጀመር ዝግጅት ተጠናቋል " - የስልጤ ዞን ትምህርት መምሪያ
የስልጤ ዞን ትምህርት መምሪያ በዞኑ ውስጥ ባሉ 45 ትምህርት ቤቶች የአረቢኛ ቋንቋ ትምህርት ሊጀመር እንደሆነ አሳውቋል።
ለዚህም ሁሉም ዝግጅት መጠናቀቁን ፤ የመማሪያ መፅሀፍትም መሰናዳታቸውን ገልጿል።
የስልጤ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሹክራላ አወል ምን አሉ ?
" በዞኑ ካሉ ትምህርት ቤቶች መካከል በ45 ትምህርት ቤቶች በፓይሌት ደረጃ የአረብኛ ቋንቋ ትምህርት ለማስጀመር ከ1-3ኛ ክፍል ማስተማሪያ መጽሀፍ ዝግጅት ተጠናቋል።
የመማሪያ መጽሀፍ የትውውቅ እና አረቢኛ ለማስተማር ለተመለመሉ መምህራን ስልጠና ተሰጥቷል።
ተማሪዎች ከእንግሊዝኛ በተጨማሪ ያሉ የውጭ ቋንቋ ቢማሩ ከራሳቸው አልፎ ለሀገር ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው።
ከአረቡ ሀገር እየተስፋፋ ካለዉ ሰፊ የስራ ዕድል ተጠቃሚነት አንፃር አረብኛን ቋንቋ ከታች ጀምሮ ተማሪዎች ቢማሩ ተመራጭ ነው።
እንዲሁም ሀገራችን ከአጎራባች ሀገሮች ጋር በተለይም ከአረቡ ዓለም ጋር ለምታደርገዉ የጋራ ጥቅምን መሰረት ያደረገ መልካም ግንኙነት ለመመስረት ያግዛል " ብለዋል።
ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የስልጤ ዞን ኮሚኒኬሽን ነው። #SilteZoneCommunication
@tikvahethiopia