ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። @tikvahuniversity @tikvahethAfaanOromoo @tikvahethmagazine @tikvahethsport @tikvahethiopiatigrigna #ኢትዮጵያ
#የጤናባለሙያዎች🙏
የ21 ዓመት እድሜ ያላት እንስት እርጉዝ የመውለጃዋ ጊዜ ደርሶ መስከረም 12 ቀን 2018 ዓ.ም በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን ዋና ከተማ እንዳስላሰ-ሽረ የሚገኘው ስሑል አጠቃላይ ሆስፒታል ትደርሳለች።
ወደ ሆስፓታሉ የተጓዘችው የአስገደ ወረዳ ከሚገኝ ራህዋ የተባለ የገጠር ቀበሌ ገበሬ ማህበር በመሆኑ ድካምና የነበረባት ደም መፍሰስ ተደራርቦ ህይወት የሚቀማ አደጋ ተደቀነባት።
በዚህ ሰዓት ሃኪሞቹ ቀዶ ህክምና እንደሚያስፈልጋት ወስነው መጣደፍ ጀመሩ።
ይሁን እንጂ በሆስፒታሉ ለአደጋ ጊዜ ተብሎ ተጠራቅሞ በደም ባንክ የተቆጠበ ደም ባለመኖሩ እንዲሁም ለወላጅ እናትዋ ደም የሚለግስ የቅርብ ሰው ባለመኖሩ ምክንያት ሃኪሞቹ ጥረታቸው መና ሊቀር ሆነ።
እናም ቀዶ ህክምናውን የሚያከናውነው የሆስፓታሉ የእናቶችና የህፃናት ሃኪም ዶ/ር ኣርኣያ ወለገብርኤልና የፋርማሲ ባለሞያዋ ሲ/ር ምፅላል አብርሃ ደም ለመለገስ ወስነው አደረጉት።
ቀዶ ህክምናው ተከናወነ ፤ እናቲቱ ደም ተለገሰላት ፤ ራስዋንና የወለደችው ህፃን በአሁኑ ሰዓት በበጎ ሁኔታ ይገኛሉ።
" በአንድ የለስላሳ መጠጥ የሚተካ አንድ ሊትር ደም ለመለገሰ አንሳሳ ፤ ሃኪሞቹ መንታ ሰብአዊነት በመፈፀም አራስ እናቲቱና የወለደችውን ህፃን ታድገዋል፤ ረጅም የአገልግሎት ጊዜ ከመልካም ጤና ጋር እንመኝላቸዋለን " ሲሉ የወላጅ እናት ቤተሰቦች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
@tikvahethiopia
ሞት ተደርዶባቸዋል !
በምያንማር የወንጀል ካምፕ የሚመራ ቤተሰብ አባላት የሆኑ 11 ሰዎች ሞት ተፈረደባቸው።
' ሚንግ ' የተባለው ቤተሰብ በርካታ አባላት ጥፋተኛ ሆነው ተገኝተዋል። አብዛኞቹም የዓመታት እስራት ተፈርዶባቸዋል።
' ሚንግ ፋሚሊ ' የተባለው ቤተሰብ በምያንማር ራስ ገዝ አስተዳደር ሥር የምትገኘውን ላውካይንግ ከተማ ከሚያስተዳድሩ አራት ጎሳዎች መካከል ይገኝበታል።
በቻይና ድንበር ላይ በሚገኘው በዚህ ከተማ የወንጀል ካምፖች ከፍተዋል። በእነዚህ ካምፖች ቁማር፣ የበይረ መረብ ማጭበርበር እና የአደንዛዥ ዕፅ ዝውውር ይከናወናል።
ምያንማር እአአ በ2023 የቤተሰቡን አባላት በቁጥጥር ሥር በማዋል ለቻይና አስተላልፋ ሰጥታለች።
ሲሲቲቪ እንደዘገበው፤ በዌንዦው ከተማ ፍርድ ቤት ውሳኔ ያሳለፈው በ39 የቤተሰቡ አባላት ላይ ነው።
11 የቤተሰቡ አባላት ሞት ሲፈረድባቸው ሌሎች 11 የሚሆኑት የዕድሜ ልክ እስራት ተበይኖባቸዋል። የተቀሩት ከአምስት ዓመት እስከ 24 ዓመታት እንዲታሰሩ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ አሳልፏል።
ከ2015 ጀምሮ የሚንግ ቤተሰብ እና ሌሎች የወንጀል ቡድኖች ከመገናኛ መስመሮች (ቴሌኮሚዩኒኬሽን) ጋር የተያያዘ ማጭበርበር፣ ሕገ ወጥ ቁማር፣ የወሲብ ንግድ እንዲሁም የአደንዛዥ ዕፅ ዝውውር ላይ ተሰማርተዋል።
በቁማር እና በማጭበርበር 1.4 ቢሊዮን ዶላር እንዳገኙ በፍርድ ቤት ተገልጿል።
አራቱ ቤተሰቦች የከፈቷቸው የቁማር ቤቶች በየዓመቱ በቢሊዮን ዶላሮችን ያስገኙ ነበር።
በወንጀል ካምፖች ከታገቱ ሠራተኞች ሞት እንዲሁም ሠራተኞች ወደ ቻይና እንዳይገቡ ተኩሶ ከመግደል ጋር በተያያዘም ጥፋተኛ ሆነው ተገኝተዋል።
ቁማር ሕገ ወጥ በሆነባት ቻይና ያለውን ከፍተኛ ፍላጎት ተገን በማድረግ የቁማር ቤቶችን በመክፈት በወንጀል ድርጊቱ እንደተሰማሩ ተገልጿል።
በእነዚህ ቁማር ቤቶች ሕገ ወጥ ገንዘብን ወደ ሕጋዊ መስመር የማስገባት ድርጊት እና የበይነ መረብ ምዝበራ ካምፖችን መክፈት ውስጥም እጃቸው አለበት።
የተባበሩት መንግሥታት የውጭ አገራት ዜጎችን ያሳተፈ የበይነ መረብ ምዝበራ ወንጀል ሰንሰለት (scamdemic) ዋነኛ ማዕከል ሲል ላውካይንግ ከተማ ነች ሲል ፈርጇል።
ቻይናውያንን ጨምሮ ከ100,000 በላይ የውጭ አገራት ዜጎች በእነዚህ የወንጀል ካምፖች ውስጥ እንደሚገኙም ድርጅቱ አስታውቋል።
ሠራተኞቹ ታግተው ለረዥም ሰዓታት እንዲሠሩ ይገደዳሉ። በመላው ዓለም በበይነ መረብ እንዲያጭበረብሩም ይገደዳሉ።
በምያንማር ኃያል የሆነው የሚንግ ቤተሰብ ቢያንስ 10,000 ሠራተኞች የያዙ የወንጀል ካምፖች አሉት።
'ታይገር ቪላ' በመባል በሚታወቀው የወንጀል ካምፕ ውስጥ ሠራተኞች ይደበደባሉ እንዲሁም ስቅይት ይፈጸምባቸዋል።
ከሁለት ዓመት በፊት ታጣቂ ቡድኖች የከፈቱት ጥቃት የምያንማር ወታደሮች ወደ ሻን ግዛት እንዲሸሹ ምክንያት ሆኗል።
በእነዚህ ቡድኖች ላይ ጫና የምታሳድረው ቻይና ጥቃቱ እንዲፈጸም መፍቀዷ ይነገራል።
የሚንግ ቤተሰብ መሪ ሚንግ ዡንቻንግ ራሱን እንዳጠፋ ተዘግቧል። ሌሎቹ የቤተሰቡ አባላት ደግሞ ለቻይና ተላልፈው ተሰጥተዋል። ድርጊታቸውን መናዘዛቸውም ተገልጿል።
በወንጀል ካምፖቹ ይሠሩ የነበሩ በሺዎች የሚቆጠሩ ሠራተኞች ለቻይና መንግሥት መሰጠታቸው ተዘግቧል።
የፍርድ ቤቱ ውሳኔ ቻይና የወንጀል ካምፖች ላይ ጥብቅ እርምጃ ለመውሰድ ቆርጣ መነሳቷን ጠቋሚ ነው ተብሏል።
ታይላንድም የወንጀል ካምፖች ላይ እርምጃ እንድትወስድ በማድረግ የቻይና ሚና ጉልህ ነው።
ሆኖም ግን የወንጀል ካምፖች አሁንም ድረስ በምያንማር እንዲሁም በካምቦዲያም ተስፋፍተዋል።
መረጃውን የቻይናን ብሔራዊ ጣቢያን እና ሲሲቲቪን ዋቢ በማድረግ ያጋራው ቢቢሲ ነው።
@tikvahethiopia
🪪 ትክክለኛነቱ የተረጋገጠ የዲጂታል መታወቂያ (ፋይዳ) የካርድ ኅትመት አገልግሎት በቴሌብር ሱፐርአፕ!!
ምዝገባዎን በአገልግሎት ማዕከሎቻችን በነጻ አካሂደው በቴሌብር ሱፐርአፕ 'NID (Fayda) Printing' መተግበሪያ የካርድ ህትመትዎን በቀላሉ ይዘዙ፤ በመረጡት የመረከቢያ ቀንና ቦታ ይረከቡ!
🔗 ቴሌብር ሱፐርአፕን https://bit.ly/telebirr_SuperApp ይጫኑ!
የመረከቢያ ቦታዎችን ለመመልከት፡ https://bit.ly/40efSUZ
ቴሌብር - እጅግ ቀላል፣ ፈጣን፣ ምቹ እና አስተማማኝ!
#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
#AddisAbaba
“በበዓል ዋዜማ አንድ፣ የመስቀል በዓል እለት ሁለት የሞት አደጋዎች ተከስተዋል” - ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ
➡️ “ በቀጥታ ከበዓሉ ጋር የተገናኘ ወንጀል የተፈጸመበት በዓል አይደለም ! ”
ከ2018 ዓ/ም የመስቀል በዓል ጋር በተገናኘ ወንጀል እንዳልተፈጸመ፣ ይሁን እንጅ በዋዜማና የበዓሉ እለት በትራፊክ አደጋ የሦስት የሰዎች ሕይወት እንዳለፈ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጸ፡፡
የመምሪያው የህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ኃላፊ ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ፣ “ መስከረም 16 ቀን 2018 ዓ/ም ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ላይ 18 ማዞሪያ በሚባል ቦታ ከቀኑ 9 ሰዓት በደረሰ የትራፊክ አደጋ አለ ” ሲሉ ገልጸዋል፡፡
በዚህም፣ “ የእቃ ማንሻ (ፎርክሊፍት) ከሎቤድ ጋር ተጋጭቶ የ20 ዓመት የፎርክሊፍቱ ረዳት ሕይወቱ አልፏል፤ ይህ በቀን 16 የደረሰ የትራፊክ አደጋ ነው” ብለዋል፡፡ “ የመስቀል በዓል እለት (በቀን 17) ሁለት የሞት አደጋዎች ተከስተዋል ” ሲሉም አክለዋል፡፡
አንደኛው በልደታ ክፍለ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አካባቢ ማታ 1 ሰዓት የደረሰ አደጋ መሆኑን ተናግረው፣ “ ከሜክሲኮ ወደሳር ቤት ይጓዝ የነበረ ተሽከርካሪ መንገድ ሲቋርጡ የነበሩን የ72 ዓመት አረጋዊ ገጭቷቸው ሕይወታቸው አልፏል ” ነው ያሉት፡፡
ሁለተኛው የካ ክ/ከተማ ጉራራ ኪዳነ ምህረት የሚባል ቦታ ንጋት 12 ሰዓት ላይ የደረሰ አደጋ መሆኑን አስረድተው፣ “ተሽከርካው ቆሟል፤ ግን በሚነሳበት ወቅት ማርሽ ላይ ሲሆን ይዘላልና ዘሎ መንገድ ሲያቋርጡ የነበሩ የ52 እድሜ ያላቸውን እናት ገጭቷቸው ሕይወታቸው አልፏል” ብለዋል፡፡
ሰሞኑን በዓሉን በተመለከተ መግለጫ ካወጣችሁ በኋላም በዓሉ ገና እየተከበረ እንደነበር ይታወቃል፤ ከመግለጫው በኋላ የነበረው አጠቃለይ የወንጀል ሁኔታ ምን ይመስል ነበር ? የሚል ጥያቄ ለኮማንደር ማርቆስ ታደሰ አቅርበናል፡፡
እሳቸውም፣ “በዓሉ በሰላም ነው የተጠናቀቀው፡፡ ከ2300 በላይ በሆኑ የደመራ ቦታዎች ላይ ነው ጥበቃ የተደረገው የመስቀል አደባባዩን ጨምሮ” ሲሉ መልሰዋል፡፡
“ከ250 በላይ በሚሆኑ አብያተ ክርስቲያናትም የተደመሩ ደመራዎች በሰላም ነው ተደምረው የተጠናቀቁት፡፡ በቀጥታ ከበዓሉ ጋር የተገናኘ ወንጀል የተፈጸመበት በዓል አይደለም” ሲሉም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
“የእመቤታችንን ስዕል አድኖ ይዘው ወደ መስቀል አደባባ ሊገቡ የነበሩ ሰዎች ታግደዋል” የሚል መረጃ በማህበራዊ ሚዲያው ሲሰራጭ ነበር፤ እውነት ነው?የፓሊስ ምላሽ ምንድን ነው? በማለት የጠየቅናቸውም ኮማንደር ማርቆስ፣ “ይሄ መረጃ የለኝም” ብለዋል፡፡
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
የሰኞ ስጦታችን አሁንም እንደቀጠለ ነው! ስጦታውን ለማግኘት ሰኞ ከሌሊት 6፡00 እስከ ምሽት 12:00 ድረስ ዳታ እንጠቀም ፣ እንደዋወል ወይም መልእክት እንላላክ!
#SafaricomEthiopia #MPESASafaricom #FurtherAheadTogether
" ስልጠናውን በመጀመሪያ ዲግሪ ለመውሰድ ፍላጎት እና የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ ማምጣት ያስፈልጋል " - የኢፌዴሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት
በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) እና ሮቦቲክስ መስኮች የኢፌዴሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት በዚህ አመት ስልጠና እንደሚጀምር እና ከኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ጋር ስልጠናውን ለማስጀመር የሚያስችል ስምምነት መፈራረማቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።
የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ብሩክ ከድር (ዶ/ር) በደረጃ 6 (በመጀመሪያ ዲግሪ) ፕሮግራም ስልጠናው ይሰጣል፣ ይህ ስልጠና የሚሰጠውም በኢፌዴሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ነው ብለዋል።
ከኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ጋር በካሪኩለም ዝግጅት እና በቀጣይ ስልጠናው መሰጠት ሲጀምር በጋራ የወርክሾፕና የአሰልጣኞች በጋራ ሪሶርስን የመጠቀም ስምምነት አድርገናል ነው ያሉት።
ከዚህ በፊት በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስና ሮቦቲክስ ፕሮግራሞች ስልጠና የሚሰጠው በማስተርስ እና በPhD ነበር፣ አሁን ግን በመጀመሪያ ድግሪ ይሰጣል። ስልጠናውን መጀመር ያስፈለገው በገበያው ላይ ሞያው ተፈላጊ ስለሆነ መሆኑን ገልፀዋል።
ስልጠናውን በመጀመሪያ ዲግሪ ለመውሰድ ፍላጎት እና የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ ማምጣት ያስፈልጋል። የዚህ አመት አካዳሚክ Year ስልጠና የሚጀመርበት ወር ይታወቃል፣ ስለዚህ በዚህ Year አካዳሚክ ላይ ነው የሚጀመረው። ለዚህም የተለያዩ ማስታወቂያዎችን እናወጣለን ሲሉ ተናግረዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#UK
ባለፈው ቅዳሜ ዕለት አንዲት አነስተኛ ጀልባ 125 ሰዎችን አሳፍራ የእንግሊዝ ቻናልን ማቋረጧን ቢቢሲ ዘገበ።
በአንድ ጀልባ ውስጥ ይህን ያህል ቁጥር ያላቸው በርካታ ስደተኞች ሲጓጓዙ ይህ የመጀመርያው ነው ተብሏል።
በነሐሴ ወር 106 ሰዎች በአንድ ጀልባ ለመጓዝ ሞክረው የነበረ ሲሆን ከዚያ ጊዜ ወዲህ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ስደተኞች በአንድ ጀልባ ሲጓዙ ይህ የመጀመርያው ነው።
የአገር ውስጥ ሚኒስቴር ቅዳሜ ዕለት ብቻ 895 ስደተኞች ቻናሉን በ12 ጀልባዎች እንዳቋረጡ ፤ እአአ ከ2025 መጀመርያ ጀምሮ 33,000 ሰዎች ወደ ዩኬ በአነስተኛ ጀልባዎች እንደገቡ አመልክቷል።
በሰሜን ፈረንሳይ ቦሎኝ ሱር-ሜር አቅራቢያ በሚገኝ የባህር ዳርቻ ላይ ቻናሉን ለማቋረጥ ሲሞክር የሞተ ስደተኛ አስከሬን እሁድ ጠዋት መገኘቱን ኤኤፍፒ የዜና ወኪል ዘግቧል።
የግለሰቡ ዕድሜ እና ዜግነት እስካሁን ድረስ ያልታወቀ ሲሆን የፈረንሳይ ሚዲያዎች ሟቹ ወጣት ነበር ብለዋል።
ከቦሎኝ ሱር-መር በስተሰሜን ትንሽ ራቅ ብሎ በሚገኘው ኢኩሄን-ፕላጅ አቅራቢያ ወደ ዩኬ ለማቋረጥ በተደረገ ሙከራ እና አሁን በተገኘው አስከሬን መካከል ግንኙነት መኖር አለመኖሩ ላይ ምርመራ እንደሚደረግ ተነግሯል።
ቅዳሜ ዕለት ሁለት የሶማሊያ ሴቶች ጊዜያዊ ጀልባቸው ችግር አጋጥሞት ሕይወታቸውን ያጡ ሲሆን በዚህ ዓመት ከፈረንሳይ ወደ ዩኬ በሕገወጥ መንገድ ለመሻገር በተደረገ ሙከራ የሞቱት ሰዎች ቁጥር በትንሹ 27 ደርሷል።
ቅዳሜ ዕለት የነበረው የተመቻቸው የአየር ሁኔታ ስደተኞቹ ከፈረንሳይ ወደ ዩኬ ለማቋረጥ ያደረጉትን ጉዞ ቀለል ያደረገው ሲሆን 14 ሰው ብቻ የአደጋ ጊዜ ድጋፍን በባህር ተቆጣጣሪዎች ማግኘታቸው ተገልጿል።
ምንም እንኳን ስደተኞች አደገኛ በሆነ ሁኔታ ከፈረንሳይ ወደ እንግሊዝ በባህር እንዳያቋርጡ ለመከላከል ፈረንሳይ የተለያዩ ጥረቶችን እያደረገች ብትመጣም፣ ዩናይትድ ኪንግደም ከፍተኛ የገንዘብ ድጋፍ ብታደርግም ሙከራዎች ምንም የመቀነስ አዝማሚያ አላሳዩም።
አሁንም በርካታ ስደተኞች ፈረንሳይ ገብተው ወደ ዩኬ (ዩናይትድ ኪንግደም) ለመግባት ይሞክራሉ።
@tikvahethiopia
" በደረሰው ከባድ የትራፊክ አደጋ የ4 ሰዎች ሕይወት አልፏል " - የአፋር ክልል ዞን 3 ፖሊስ
በአፋር ክልል ዞን 3 ገለአለ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ4 ሰዎች ህይወት አለፈ።
የአፋር ክልል ዞን 3 ፖሊስ አዛዥ ምክትል ኮማንደር አሊ ፋራህ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደገለፁት በዞኑ ገላአለ ወረዳ አባ በረሃቤ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ በደረሰዉ ከባድ ጉዳት የአራት ሰዎች ሕይወት ማለፉን ተናግረዋል።
የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ- 4 -01303 አፋ የሆነ ላንድኩሩዘር የክልሉ ጤና ቢሮ ተሽከርካሪ ከአዋሽ ወደ ሰመራ ሲጓዝ ከጅቡቲ ወደ መሃል ሀገር በመጓዝ ከነበረ ከባድ የጭነት ተሳቢ መኪና ጋር በመጋጨቱ አደጋው መከሰቱን ገልጸዋል።
በአደጋው በትንሹ መኪና ውስጥ የነበሩ አራት ሰዎች ወዲያውኑ ሲሞቱ በአራት ሰዎች ላይ ከባድ ጉዳት መድረሱን አመልክተዋል።
ተጎጂዎች በአሁኑ ሰዓት በበርታ መሐመድ አክለ ሆስፒታል ሕክምና እየተደረገላቸው መሆኑንም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
#TikvahEthiopiaFamily
@tikvahethiopia
“በሺዎች የሚቆጠሩ የኢትዮጵያ ብራናዎች በምዕራባውን ዩኒቨርሲቲዎች አሉ፣ አብዛኛዎቹ የህክምና ምስጢራትን የያዙ ናቸው” - የ“ፓሌሮዳ” መፅሐፍ ደራሲ
የተለያዩ መፅሐፍት የደረሱትና ለ8 ዓመት በህክምና ሙያ ያገለገሉት ዶክተር ደሳለው ካሳ ጠፋ የሚባለው መፅሐፈ ሄኖክ ላይ የሚያተኩር "ፓሌሮዳ" የሚል መፅሐፍ ለንባብ ማብቃታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
“'አንድ ጠቃሚ የሆነ መፅሐፍ ከሀገር ወጥቷል፤ መፅሐፉ ቢገኝ ለሀገሪቱ ታላቅ መነሳት ይሆናል፤ በተለይ በህክምና ግኝት ትልቅ እምርታ ያመጣል፤ የምዕራባውያን የሕክምና ቴክኖሎጅ የሚቀዳው ከዚያ መፅሐፍ ነው'” የሚለው አፈታሪካዊ ንግግር መፅሐፉን ለመድረስ እንዳነሳሳቸው ተናግረዋል፡፡
“ለመጻፍ ያነሳሳኝ የኢትዮጵያ ድርሳናት የመዘረፍ ጉዳይ ነው” ያሉት ደራሲው፣ “በሺዎች የሚቆጠሩ ብራናዎች ምዕራባውን ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ አሉ” ብለዋል። ብዛታቸውንም ወደ 9 ሺሕ አድርሰውታል።
“ወደ 4 ሺሕ የሚሆኑትን ምዕራባውያኑ አምነው ደርድረዋቸዋል፡፡ ሌሎቹ ግን ከመጋረጃ ጀርባ በተለያዬ መንገድ ያሉ ናቸው፡፡ የጠፉት ድርሳናት ሃይማኖታዊ ብቻ አይደሉም፤ አብዛኛዎቹ ከፍተኛ መገለጥን ቢጠይቁም የህክምና ምስጢራትን የያዙ ናቸው” ብለዋል፡፡
ከእነዚህም የመፅፈ ሔኖክ ብራናዎች እንደሚገኙበትና ለኢትዮጵያ የሚጠቅሙ ድብቅ ጥበብም እንደያዙ ጠቅሰው፣ በዚሁ መነሻ በመፅሐፈ ሔኖክ የሚያጠነጥን “ፓሌሮዳ” የተሰኘውን መፅሐፍ መፃፋቸውን ገልጸዋል፡፡
የጠፋውና ስውር ጥበብ የያዘው እውነተኛው መፅሐፈ ሔኖክ አለመገኘቱ እንደ ሀገርም፣ እንደ ትውልድም አሳሳቢ መሆኑን መፅሐፉ በጥልቅ እንደሚያስረዳ አመልክተዋል፡፡
“የጠፋ መፅሐፍ በእርግጥም እንዳለ፣ ተገኘ ተብሎ ተተርጉሞ ያለው መፅሐፍ ሔኖክ ብቻ እንዳልሆነ ከራሱ ከመጽሐፉ ፍንጮችን አግንቻለሁ” ሲሉም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
ስለብራና መፅሐፍቱ ጥቅም ደራሲው ምን አሉ?
እነዚህን የብራና መፅሐፍት ከውጭ ሀገራት ማስመለስ ቢቻል ኢትዮጵያ የገባችበትን ወቅታዊ ፖለቲካዊ ችግር ለመፍታት እንደሚያስችል ገልጸው፣ “ዓለም ለሺሕ ዓመታት የሰራቸውን ቴክኖሎጅዎች ሁሉ በ10 ዓመታት መስራት ያስችላሉ" ነው ያሉት።
“ማንኛውም ሰው የሔኖክ ብራናዎችን መጥፋት ከልቡ ቢያይ እንቅልፍ የሚያስተኛ አይደል” የሚሉት ዶክተር ደሳለው፣ ይህም ለመጻፍ ያነሳሳቸውና መፅሐፍቱ ወደሀገር እንዲመለሱ አሳስበዋል።
“መፅሐፈ ሔኖክ የሃይማኖት እሳቤዎችን ሳይንሳዊ በሆነ መልኩ በንድፈ ሀሳብ ደረጃ ያስቀምጣል፡፡ ንድፈ ሀሳቦቹን አብዛኛዎቹ ምዕራባውያን በትምህርት ኳሪኩለም ቀርጸው ይማሩባቸዋል። ግን የድሮ አባቶቻችን ያለፉበት መንገድ ነው" ይላሉ ደራሲው።
የመፅሐፉ ስያሜ፣ ጭብጥና ግጭት ምንድን ነው?
መፅሐፉ፣ “ፓሌሮዳ” የሚል ስያሜ ተስጥቶታል፡፡ ስያሜውም “ፓሊሲፒታ፣ ሌሴፖስ፣ ሮፒልታ እና ዳሔር የሚባሉ የጠፉ አራቱን ብራና የሄኖክ መፅሐፍት የያዘ ምህጻረ ቃል ነው” ብለዋል፡፡
“ፓሌሮዳ” አራቱ የሔኖክ መፅሐፍት ላይ የሚያጠነጥንና ልብወለዱ አሁን ያለውን የሔኖክ መፅሐፍ ፍች የሚሰጥ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
በልብወለዱ ውስጥ የሔኖክ መፅሐፍን ፍለጋ የተነሱ የኢትዮጵያ ምሁራን “አብርሆት” የሚል ቡድን መስርተው ከኢትዮጵያ ገዳማት እስከ አውሮፓ ድብቅ የዋሻ ላይብራሪዎችን በማሰስ በሚያደርጉት ፍለጋ ላይ የልብወለድ ግጭቱን አድርጓል፡፡
ስውር ምስጢር የያዙ የብራና መፅሐፍት ከምዕራዊያን እጅ ማስመለስ፣ መፅሐፍቶቹ ቢገኙ ምዕራባውያኑ ያለፉበት ሥልጣኔ ከመከተል ይልቅ ከራሳችን አልፈን ለዓለም እንደምንተርፍ እውነታውን ፍንትው አድርጎ ማሳየት የመፅሐፉ ጭብጥ ነው፡፡
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
" በአፍሪካ ቀንድ ፣ በቀይ ባህር ፣ በናይል ተፋሰስ ዙሪያ ትርጉም ያለው ውይይት ለማድረግ ዝግጁ ነኝ " - ኤርትራ
በአሜሪካ የስቴት ዲፓርትመንት መሥሪያ ቤት የፕሬዜዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከፍተኛ አማካሪ የሆኑት ማሳድ ቡሎስ አሜሪካ ኒውዮርክ በተባበሩት መንግሥታት (UN) ጉባኤ ላይ የሚገኙ ሲሆን ከተለያዩ ሀገራት ተወካዮች ጋር እየመከሩ ነው።
ትላንትና ከኤርትራው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳሌህ ጋር ውይይት አደርገዋል።
ከትላንቱ ውይይት አንዱ #ኢትዮጵያ ወደ አደባባይ ይዛው የወጣችውና ዓለም አቀፍ አጀንዳ ያደረገችው የቀይ ባህር ጉዳይ ይገኝበታል።
የኤርትራው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፤ ሀገራቸው ብሔራዊ ሉዓላዊነቷን በጠበቀ ሁኔታ በጋራ ጉዳዮች ላይ በተለም በአፍሪካ ቀንድ ፣ በናይል ተፋሰስ፣ #በቀይ_ባህር ዙሪያ ትርጉም ያለው ውይይት ለማድረግ ዝግጁ እንደሆነች ተናግረዋል።
ኤርትራ ለቀጠናዊ ሰላምና ዘላቂ ልማት ቁርጠኛ መሆኗን የገለጹት ሳሌህ ከአሜሪካ ጋር ትብብር ለማድረግ የተፈጠረውን እድል ሀገራቸው በደስታ እንደምትቀበለ አመልክተዋል።
የአሜሪካው ከፍተኛ ባለስልጣን ማሳድ ቦሎስ ሀገራቸው አሜሪካ ለዓለም አቀፍ ንግድ፣ ደህንነት እና ፀረ-ሽብርተኝነት ጥረቶች ወሳኝ በሆነ ቀጠና ውስጥ ውይይት እና መግባባትን ለመፍጠር ፅኑ ፍላጎት እንዳላት አስምረውበታል።
ውይይቱ በአሜሪካ እና ኤርትራ ግንኙነት ላይ አዲስ ምዕራፍ ለመክፈት መንገድ የሚጠርግ እንደሆነና ይህም በንግድ፣ በኢንቨስትመንት፣ በመሠረተ ልማት፣ በትራንስፖርት፣ ግንኙነት እና ደህንነት አጋርነት ላይ ለውይይት በር ሊከፍት የሚችል እንደሆነ አመልክተዋል።
የቆዩ ችግሮችን ገንቢ በሆነ ማዕቀፍ ውስጥ ለመፍታት እንደሚያስችልም ጠቁመዋል።
ሁለቱም ወገኖች በሚቀጥሉት ወራት ግንኙነታቸው ለመቀጠል በመስማማት ውይይታቸውን ቋጭተዋል።
በአሜሪካ የስቴት ዲፓርትመንት መሥሪያ ቤት የፕሬዜዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከፍተኛ አማካሪ የሆኑት ማሳድ ቡሎስ ከቀናት በፊት እዚህ #ኢትዮጵያ ነበሩ።
በጠቅላይ ሚኒስትር በጽሕፈት ቤት ተገኝተውም ከጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጋር በበርካታ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አደርገው ነው የሄዱት።
#ቀይ_ባህር #RedSea
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
" ፍጹምና ዘላቂ ሰላምን የምንሻ ከሆነ፣ በመስቀሉ ቃል እንመራ፤ የመስቀሉ ቃል ማለት ይቅርታንና ዕርቅን፣ እኩልነትንና ኣንድነትን፣ ፍትሕንና ርትዕን ማረጋገጥ ማለት እንደሆነ በውል እንወቅ ! " - ቅዱስነታቸው
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፣ የ2018 ዓ/ም የመስቀል በዓልን አስመልክተው መልዕክት አስተላልፈዋል።
ከቅዱስነታቸው መልዕክት ፦
" የመስቀሉ ዓበይት መልእክቶች ሰው ሊያምንባቸው፣ ሊቀበላቸውና ሊኖርባቸው፣ በውጤቱም በሥጋውም ሆነ በነፍሱ ሊድንባቸው እንደ ተሰጡ የማንስተው ሓቅ ነው፡፡
ሆኖም ሰዎች በኣንድ ጆሮኣችን ሰምተን በሌላኛው ጆሮኣችን ከመጣል ባለፈ፣ ያመጣነው ለውጥ እንደሌለ ተግባራችን ራሱ ምስክር ነው።
ዛሬም ሕገ እግዚአብሔር በድፍረት ይጣሳል፤ የጥሰቱ ውጤትም እንደምናየው ዓለማችንን በኣጠቃላይ በመኖርና ባለመኖር ስጋት ውስጥ እየከተታት ይገኛል፡፡
ታድያ እኛስ በዚህ ሁሉ ኣልደከምንምን? የሚታደገን መስቀላዊ ኃይልስ ኣያስፈልገንምን? ለሰላማችን መጠበቅና ለድኅነታችን ዋስትናስ ከመስቀሉ ቃልና ኃይል የበለጠ ሌላ ኣለን? እንደ እውነቱ ከሆነ በንጹሁ ኣእምሮኣችን በደምብ ካስተዋልነው፣ ከመስቀሉ ቃል የበለጠ ለሰው ልጆች ሰላምንና ድኅንነትን የሚሰጥ ሌላ ኃይል በዓለማችን ውስጥ ኣይገኝም።
ስለሆነም ፍጹምና ዘላቂ ሰላምን የምንሻ ከሆነ፣ በመስቀሉ ቃል እንመራ፤ የመስቀሉ ቃል ማለት ይቅርታንና ዕርቅን፣ እኩልነትንና ኣንድነትን፣ ፍትሕንና ርትዕን ማረጋገጥ ማለት እንደሆነም በውል እንወቅ፤ በዚህ ሕይወት መኖር ከጀመርን ድክመታችን በመስቀሉ ተወገደ ማለት ነው። "
(የቅዱስነታቸው ሙሉ መልዕክት ከላይ ተያይዟል)
@tikvahethiopia
" የመስቀሉ ብርሃን በልባችን እንዲሰርፅና ለሌሎችም ማካፈል የምንችልበትን ማስተዋል እና ጥበብን እግዚአብሄር እንድሰጠን ምኞቴ ነው " - አባ ዳዊት ውብሸት
የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የ2018 ዓ.ም የመስቀል ደመራ በዓልን በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በሚገኘው በጽዮን ማርያም ቁምስና ከምዕመኗ ጋር አክብራለች።
በክብረ በዓሉ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት በኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የኮምቦኒ ማህበር ካህን አባ ዳዊት ውብሸት ፣ " የመስቀሉ ብርሃን በልባችን እንዲሰርፅና ለሌሎችም ማካፈል የምንችልበትን ማስተዋል እና ጥበብን እግዚአብሄር እንዲሰጠን ጾሎቴና ምኞቴ ነው " ብለዋል።
ለኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች " የመስቀል በዓል በመስቀል ዙሪያ ያለን ምንነትን የምንገልጽበት ነው። በታሪክ እንደሚታወቅውም ደመራን ስናከብር መስቀል የተገኘበትን ሚስጥር ነው የምንዘክረው " ሲሉ ተናግረዋል።
" የመስቀል ደመራ ክብረ በዓልን ስናስብ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አንደምታ አለው፣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ሞቶ እያንዳንዳችንን በህይወቱ ያዳነበትን ሚስጥር ነው የምንዘክረው። ለእኛ ለካቶሊክ እምነት ተከታዮች ደግሞ መስቀል የማንነት መገለጫችን ነው " ሲሉ ገልፀዋል።
" ከመስቀል መማር ያለብን ሁለት ነገር አለ ብዬ አስባለሁ " ያሉት አባ ዳዊት ውብሸት " የመጀመሪያው መስቀል የእግዚአብሔር ጥበብ እና ሚስጥር የሚገለጥበት መሆኑን ነው። እኛ የካቶሊክ እምነት ተከታዮች ይህንን ስናስብ ህይወታችንንም በጥበብ መምራት እንዳለብን እንገነዘባለን። እንዲሁም ጥበብ በሚያስፈልገን ጊዜ ጌታችን ላይ ትኩረት በመስጠት ነገሮችን በጥበብ ማለፍ እንዲንችል ያደርገናል " ብለዋል።
" ሌላው ደግሞ በዚህ በዓል ጊዜ እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ አደረሰሽ፣ አደረሰህ እየተባባልን ሰላምታ ስንለዋወጥ ከመስቀሉ በስተጀርባ ብርሀን አለ ማለታችን ነው። ስለዚህ በህይወታችን ጨለማ የሆነ እውነታም ካለ በጨለማው ላይ ይህ ብርሃን እንዲያንፀባርቅ እንፈልጋለን " ሲሉ አስረድተዋል።
" በግልና በማህበራዊ ህይወታችን፣ በዓለምም ሆነ በሀገር ደረጃ ብርሃን ነክ ባልሆኑ ነገሮች ላይ በእምነታችን ብርሃንን ማየት እንድንችል መስቀል የህይወታችን ብርሃን ይሆናል " ሲሉ አክለዋል።
አባ ዳዊት ውብሸት ፤ " ጌታችን ' እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ ' እንዳለው ሁሉ እኛም ብርሃን የምናገኘው በዚሁ ነው። ህይወታችንን በጥበብ መምራት እንድንችል እና ብርሃን በሌለበት ቦታ መስቀሉ ብርሃን መሆን የሚችልበትን ሃሳብ ነው በክርስትና ህይወታችን የምናገኘው። በዚህ ሃሳብ ስንማር እና ስንታግዝ እንዲህ አይነት ክብረ በዓል ማክበር ተገቢ ነው " ሲሉ ተናግረዋል።
በመጨረሻ የመስቀሉን ክብረ በዓል ለሚያከብሩ ሁሉ እና ለክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
መስቀል፣ ጋዜ መስቀላ እና ጋሪ ዎሮ የሞባይል ጥቅል!!
🌟 እንኳን አደረሳችሁ!!
እስከ 51% ቅናሽ የተደረገባቸውን ልዩ የበዓል ጥቅሎች በ*999#፣ በማይ ኢትዮቴል ወይም አርዲ ቻትቦት ይግዙ፤ ለሚወዷቸውም ስጦታ ያበርክቱ!
🔗 በቴሌብር ሱፐርአፕ https://bit.ly/telebirr_SuperApp ሲገዙ ተጨማሪ 20% ስጦታ ያገኛሉ!
🗓 እስከ መስከረም 18 ቀን 2018 ዓ.ም!
#Ethiotelecom #telebirr #telebirrSuperApp #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
ፎቶ ፦ የ2018 ዓ/ም የመስቀል ደመራ በዓል በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ !
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
መልካም የመስቀል ደመራ በዓል ይሁንላችሁ !
መልካም በዓል !
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
“ወደ ምክክሩ ለመመለስ አላሰብንም፤ ምክንያቱም ኮሚሽኑ ያስቀመጥነውን ቅድመ ሁኔታ አላሟላም፡፡ ቅንጅቱም አይመለሰም” - የቅንጅቱ አካል
የተወሰኑ ተፎካካሪ ፓርቲዎች “መጀመሪያ ጦርነት ይቁም፣ እስረኞች ይፈቱ” በሚል አቋም በሀገራዊ ምክክሩ እንደማይሳተፉ መግለጻቸው ይታወሳል፡፡ ኮሚሽኑም ለፓርቲዎቹ ተደጋጋሚ ጥሪ ማድረጉን ሲግልጽ ተስተውሏል፡፡
በምክክሩ ሂደት ለመሳተፍ ከታቀቡ እናት፣ መኢአድና ኢሕአፓ ፓርቲዎች ጋር በተለያዩ መድረኮች መወያየቱንም ኮሚሽኑ ከወራት በፊት አሳውቆ ነበር።
ፓርቲዎቹ በበኩላቸው ፣ ከኮሚሽኑ ጋር ውይይት እንዳደረጉ፣ በምክክሩ መሳተፍና አለመሳተፋቸውን ለመለየት ግን ካባሎቻቸው ጋር መወያየት እንዳለባቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸው ነበር።
ከኮሚሽኑ ካገለሉት መካከል ሰሞኑን “ቅንጅት” መሰረትን ያሉ ፓርቲዎች ይገኙበታል፡፡ ቲክቫህ ኢትዮጵያም ቅንጅት መሰረትን ያሉ ፓርቲዎች ከኮሚሽኑ ጋር አብረው ለመስራት አቅደው እንደሆን የጠየቀ ሲሆን፣ “የይስሙላ ሀገራዊ ምክክር አንገባም” ብለዋል፡፡
ወደ ኮሚሽኑ ለመመለስ አስቧችኋል ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ የጠየቃቸው ከቅንጅቱ አንዱ የሆነው የኢሕአፓ ፕሬዚዳንት መጋቢ ብሉይ አብርሃም ሃይማኖት፣ “ወደ ምክክሩ ለመመለስ አላሰብንም፤ ምክንያቱም ኮሚሽኑ ያስቀመጥነውን ቅድመ ሁኔታ አላሟላም፡፡ ቅንጅቱም አይመለሰም” ሲሉ መልሰዋል፡፡
“የምክክር ኮሚሽኑ የተመካከርንበትን መፍትሄ አላስቀመጠም፡፡ ከመንግስትም ጋራ ችግሮችን አልፈታም። የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ፣ ያለው አፈናም እንዲቆም ጠይቀን ነበር” ሲሉም አስታውሰዋል፡፡
“ጦርነት ቆሞ ድርድር እንዲካሄድ፣ በትጥቅ ትግል ውስጥ ያሉ ወገኖች ወደምክክሩ እንዲመጡ እውነተኛ ሰላም እንዲጸና ነበር ፍላጎታችን፡፡ ለዚህም ኮሚሽኑ አንዳች ጥረት ሲያደርግ ስላላገኘን ወደ ምክክሩ አንመለስም” ሲሉም አክለዋል፡፡
“ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ወደ ምክክሩ ልንመለስ የምችለው እሰረኞች ሲፈቱና ጦርነት ማስቆም ሲቻል ነው፡፡ ይህ ከሆነ ኮሚሽኑ እንዲጋብዘንም አንጠብቅም ራሳችን ለምነናቸው እንሄዳለን” ብለዋል፡፡
ምክክር ከመደረጉ በፊት ጦርነት መቆም አለበት በሚል ከፓርቲዎቹ ለሚነሳው ጥያቄ ምን ምላሽ እንዳለው ከዚህ ቀደም የጠየቅነው ኮሚሽኑ በበኩሉ፣ ምክክር “ጦርነት እየተካሄደም” እንደሚደረግ ገልጾ ነበር፡፡
ለዚሁ የኮሚሽኑ ሀሳብ አስተያየት የሰጡትን የኢሕአፓ ፕሬዚዳንት ደግሞ፣ “ጦርነት ሳይቆም ምክክር አድርጎ ስኬታማ የሆነ ሀገር ከጠቀሱ ኢሕአፓ ዝግጁ ነው፡፡ ሀገራት ጦርነት አቁመው ነው ወደ ምክክር የገቡት፡፡ ጦርነት ላይ ሆነው ምክክር የጀመሩ ነበሩ ግን ፈርሷል፤ የትም አልደረሱም” ባይ ናቸው፡፡
“ጦርነት ሳያቆሙ ምክክር አድርገው ውጤታማ የሆኑ ሀገራት ካሉ ኮሚሽኑ ይጥቀስልን፡፡ ግን ውሸት ነው የለም” ብለው፣ “ኮሚሽነሮቹ ጦርነት ማስቆም አይችሉም፤ ግን ብልጽግና ፓርቲን እንዲጫኑ ነው የምንፈልገው” ነው ያሉት፡፡
“አንድ ፓርቲ ከሀገራዊ ምክክር ከወጣ ምክክር ይፈርሳል፡፡ የቱ ጋ ነው ታዲያ ብሔራዊ ስምምነት መጣ የሚባለው? አንድ ፓርቲኮ በስሩ በሺዎች የሚቆጠሩ ተከታዮች አሉበት፡፡ ስለዚህ ህዝቡን ለማደናገር ካልሆነ በስተቀር በዚህ የትም አይደርሱም” ሲሉም ተናግረዋል፡፡
“ ግን የአንድ ፓርቲ ሳይሆን የሁሉንም ህዝብ ፍላጎት ይዘው ከሄዱ እውነተኛ ብሔራዊ መግባባትና ሰላም የሰፈነባት ኢትዮጵያን እንመረስታለን፡፡ የይስሙላ ምክክር ያቁሙ፡፡ እንዲያውም ህዝባቸውን ይቅርታ ጠይቀው በዚህ አይነት አካሄድ የትም አንደርስም ብለው ለመንግስት በይፋ መግለጫ ይስጡ” ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
ሚዛን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት !
የቴክኖሎጂ ኮርሶችንና የኮምፒዩተር ስልጠናዎችን ከፈለጉ፤ 1⃣0⃣ኛ ዙር ምዝገባ ጀምረናል።
የመክፈል አቅም ለሌላቸው በክሬዲት (ከወለድ ነፃ በሆነ ብድር/ዱቤ) መማር የሚችሉበት እድል አመቻችተናል። ምዝገባችን ከሃገራችን ኢትዮጵያ ባሻገር በጅቡቲ አዲሱ ቅርንጫፋችንም ስላለ መመዝገብ ይችላሉ።
ስለ ፓኬጆቹ፣ እያንዳንዱ ኮርስ የስንት ወር እንደሆነና ስለ ኮርሱ ምንነት ማብራሪያ፣ ስለ ክፍያው እንድሁም ሌሎች ዝርዝር መረጃዎችን በቻነላችን ያግኙ /channel/MizanInstituteOfTechnology/508
12ኛ ክፍል ማለፊያ ውጤት ላላመጡ ለ5 ቀናት የሚቆይ 20% ቅናሽ፣ ለመምህራንና የጤና ባለሙያዎች 12% ቅናሽ አድርገናል።
ለመመዝገብ፦ http://www.mizantechinstitute.com
በቴሌግራም @MizanInstituteOfTechnologyEthio አግኙን።
🗺በአካል: ቤተል አፕል ፕላዛ 7ኛ ፎቅ፣ 0987143030
በማህበራዊ ሚዲያ ገፆቻችን አገኙን፦
🌐👍mizantechinstitute?_t=ZM-8u1PtL1rMqD&_r=1">🌐📱✅mizaninstituteoftechnology7830?si=1GRXkSTCTu6p6ncD">▶️🌐📧 🗺
የ2018 ዓ/ም የድህረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) የምዝገባ ጊዜ ይፋ ተደረገ።
ትምህርት ሚኒስቴር በ2018 የትምህርት ዘመን የድህረምረቃ ፕሮግራሞች ለመማር ፍላጎት ላላቸው አመልካቾች የሚሰጠው የድህረምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ምዝገባ ከመስከረም 20 - 25/2018 ዓ.ም የሚካሄድ መሆኑን አሳውቋል።
አመልካቾች የመመዝገቢያ ቅጽ ላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች በማሟላት በ https://ngat.ethernet.edu.et በኩል መመዝገብ እንደሚችሉ ገልጿል።
ፈተና የሚሰጥበትን ጊዜ በቀጣይ ይፋ እንደሚደረግ አመልክቷል።
አመልካቾች ከምዝገባ ጋር ተያይዞ ለሚኖራቸው ጥያቄ ዘውትር በስራ ሰዓት በ0920157474 ወይም 0911335683 እንዲሁም በኢሜይል አድራሻ ngat@ethernet.edu.et በኩል ማብራሪያ መጠየቅ እንደሚችሉ ተገልጿል።
ትምህርት ሚኒስቴር ሁሉም አመልካቾች የብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ ሊኖራቸው እንደሚገባ አሳስቧል።
የምዝገባ እና የአገልግሎት ክፍያ 750 ብር በTeleBirr በኩል ብቻ መከፈል እንደሚኖርበት አስገንዝቧል።
#MoE
@tikvahethiopia
" ' የጸጥታ አካላትና አባል ነን ' በማለት የሚያስፈራሩና ተጽዕኖ የሚያሳደሩባችሁ ግለሰቦች ሲያጋጥማችሁ በወቅቱ አሳውቁኝ " - ፖሊስ
" የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት አባል ነኝ " በማለት ሰዎችን በማስፈራራት እያገተ ገንዘብ ሲቀበል የነበረን ግለሰብ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ።
ዳዊት ጥላሁን ወይም ምንተስኖት ጥላሁን የተባለው ግለሰብ ሀሰተኛ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት መታወቂያ በመጠቀም " የተቋሙ ሰራተኛ ነኝ " በማለት ሰዎችን በማገትና በማስፈራራት ገንዘብ እንደሚቀበል ከህብረተሰቡ የተሰጠን ጥቆማ መነሻ በማድረግ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት እና የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ በጋራ ባደረጉት ክትትል ግለሰቡን መስከረም 16/2018 ዓ/ም በቁጥጥር እንዲውል ማድረጋቸው ተገልጿል።
ተጠርጣሪው ከሜክሲኮ ወደ ጋርመንት በታክሲ ተሳፍራ የምትሄድን የግል ተበዳይን ሳሮን ተስፋዬን " ደህንነት ነኝ " በማለት በማስፈራራት እና በመደብደብ ጉዳት ያደረሰባት መሆኑን የግል ተበዳይ በማህበራዊ ሚዲያ አሰራጭታለች።
ግለሰቡ በግል ተበዳይ ላይ ባደረሰው ጉዳት በህግ የሚጠየቅ መሆኑን ፖሊስ አስታውቋል።
ግለሰቡ በቁጥጥር ስር በዋለበት ወቅት ሀሰተኛ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት መታወቂያ እንደተገኘበት ፖሊስ ገልጿል።
በግለሰቡ በተመሳሳይ የወንጀል ድርጊት የተፈጸመበት ግለሰብ እና ስለ ግለሰቡ ማንኛውም መረጃ ያለው ሰው ለአዲስ ለአበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ መረጃ በመስጠት ትብብር እንዲያደረግ ጥሪ ቀርቧል።
የአዲስ አበባ ፖሊስ ህብረተሰቡ " የጸጥታ አካላትና አባል ነን " በማለት የሚያስፈራሩና ተጽዕኖ የሚያሳደሩ ግለሰቦች ሲያጋጥሙት በወቅቱ እንዲያሳውቅ መልዕክት አስተላልፏል።
#AddisAbabaPolice
@tikvahethiopia
#NationalBankofEthiopia
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴ ስብሰባውን አድርጎ የገንዘብ ፖሊሲ ምክረ ሐሳቦች ለቦርድ አቅርቦ ማስወሰኑም የብሔራዊ ባንክ አሳውቋል።
ምን ወሰነ ?
1ኛ. የብሔራዊ ባንክ የፖሊሲ ተመን (National Bank Rate) አሁን ባለበት 15 በመቶ እንዲቆይ ፤ ብሔራዊ ባንክ ለሚሰጣቸው የተቀማጭ ሂሳብ አገልግሎት (standing deposit facility) እና የብድር አገልግሎት (standing lending facility) የሚከፈሉ የወለድ ተመኖች ባሉበት እንዲቀጥሉ፣ እንዲሁም ባንኮች በብሔራዊ ባንክ የሚያስቀምጡት የግዴታ መጠባበቂያ ምጣኔ በነበረበት እንዲቆይ ተወስኗል፡፡
2ኛ. በመስከረም ወር ላይ ሊነሣ ይችላል ተብሎ የተገመተዉ የባንኮች ዓመታዊ የብድር ዕድገት ጣሪያን ሙሉ ለሙሉ ሳይነሳ ገደቡ ለጊዜው ከ18 በመቶ ወደ 24 በመቶ ከፍ እንዲል ተወስኗል፡፡
3ኛ. ብሔራዊ ባንክ የዋጋ ግሽበቱ በሚፈለገው ልክ እንዲሆን ለማስቻል እንደ አስፈላጊነቱ ገበያ-መር የሆነ የገንዘብ ፖሊሲ መሣሪያዎችን በተናጠልም ሆነ በቅንጅት በቀጣይነት የሚጠቀም እንደሆነ ተገልጿል። እነዚህ የገንዘብ ፖሊሲ መሣሪያዎች፦
- የብሔራዊ ባንክ የወለድ ተመን፤
- ከባንኮች ጋር የሚደረግ የገንዘብ ግብይት (Open Market Operations)
- የውጭ ምንዛሬ ገበያ (foreign exchange interventions) እንዲሁም ባንኮች በብሔራዊ ባንክ የሚያስቀምጡት የግዴታ መጠባበቂያ ምጣኔ እንደሚሆኑ ተመላክቷል።
የኮሚቴው ስብሰባ ታህሳስ ወር 2018 እንዲሆን ተወስኗል፡፡
(ሙኩ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)
@tikvahethiopia
" በከተማው ተነስቶ በነበረው ግጭት ከፀጥታ አካላት በተተኮሰ ጥይት የሶስት ሰዎች ሕይወት አልፏል " - ነዋሪዎች
➡ " ሁከት በመቀስቀስ የተጠረጠሩ ታስረው ከተማው ወደ መደበኛ እንቅስቃሴ ተመልሷል " - ፖሊስ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምስራቅ ጉራጌ ዞን ቡታጀራ ከተማ በመስቃን ወረዳ እንቦር ቀበሌ ስር ይተዳደርበት የነበረ የስናኖ ሴራ የተባለ አካባቢን የዞኑ ስራ አስፈፃሚ አካላት " የዶቢ ቀበሌ ነው " ማለታቸዉን ተከትሎ ተቀሰቀሰ በተባለው ሁከት ከፀጥታ አካላት በተተኮሰ ጥይት የ3 ሰዎች ሕይወት ማለፉን የቡታጅራ ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
አንድ ማንነቱ እንድንገለፅ ያልፈለገ የከተማው ነዋሪና የዐይን እማኝ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደገለፁት በከተማው ከብራይት ወደ መድረሳ ሰፈር በሚወስደው መንገድ ላይ በተለምዶ አደባባይ ሰፈር አንዲት ሴት በአንድ አድማ በታኝ በተተኮሰ ጥይት መገደሏን መመልከቱንና ተኳሹ በቡታጅራ ከተማ በሚገኘው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከተማና ኮንስትራክሽን ቢሮ አከባቢ እንደነበር ተናግሯል።
" ሌላ ወጣት የተገደለው በትክክልና በተነጣጠረ ጥይት ነው " ሲሉ ሌላኛው የከተማው ነዋሪ ገልጿል።
አጠቃላይ የነበረው እንቅስቃሴ ችግሩን የሚያባብስ እንደነበር አክለዋል።
አንድ ታዳጊ፣ አንዲት ሴትና አንድ ወጣት በአጠቃላይ 3 ሰዎች መገደላቸውን የገለፁት ነዋሪዎቹ በርካቶችም በሁከቱ መቁሰላቸውንና ጉዳት እንደደረሰባቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ በጉዳዩ ዙሪያ የምስራቅ ጉራጌ ዞን ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር ሙሰማ ጀማል አነጋግሯቸዋል።
ስለሁኔታው ሰፊ ማብራሪያ ከመስጠት ተቆጥበዉ ሁከቱን በመቀስቀስና በማስተባበር እንዲሁም በመምራት የተጠረጠሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውንና ከትላንት ከሰዓት ጀምሮ ከተማው ወደ ቀደመ ሰላማዊ እንቅስቃሴ መመለሱንና ሌሎች መረጃዎችን በሌላ ጊዜ እንደሚሰጡ ተናግረዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ያነጋገራቸዉ አንድ የአከባቢዉ የመንግስት የስራ ኃላፊ የአመፁ መንስኤ የሆነው የመስቃን ጉራጌ የእንቦር ቀበሌ ባህላዊ የአስተዳደር ሴራ የሆነውን የስናኖ ሴራ ህዝቡ ባልተወያየበትና የወረዳው ምክር ቤት ባላፀደቀበት የዞኑ ስራ አስፈፃሚዎች " የባህል ሴራው የመስቃን ጉራጌ የእንቦር ቀበሌ ሴራ አይደለም የዶቢ ቀበሌ ሴራ ነው " በማለት መወሰናቸው መሆኑን ተናግረዋል።
ይህን ተከትሎም ከህዝቡም የተመረጡ ሽማግሌዎች በተደጋጋሚ " ይሄ የባህል ቅሚያ ትክክል አደለም ህዝቡን ወዳልሆነ መንገድ ይመራዋል አስቁሙ ፣ ህዝቡን አወያዩ " ቢሉም የዞኑ ስራ አስፈፃሚ ጉዳዩን በቸልተኝነት ማየቱ ችግሩ እንዲፈጠር ምክንያት ሆኗል ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የዞኑን አስተዳዳሪ ጨምሮ የስራ አስፈፃሚ አካላትን ለማግኘት ያደረገው ሙከራ ለጊዜው አልተሳካም ጉዳዩን ተከታትለን የምንዘግብ ይሆናል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa
@tikvahethiopia
ተከታታይ የአእምሮ ህክምና ድጋፍ የሚያስፈልገዉን ልጆን ወደ ጤና ተቋም በመዉስድዎ የመባረር እጣ ፈንታ አጋጥሞታልን
ህጎቻችን አካል ጉዳተኞችን ብቻ ሳይሆን ተንከባካቢዎቻቸዉንም መጠበቅ አለባቸዉ::
በቤት ዉስጥ እና በስራ ቦታዎች ላይ ለፍትሐዊነት እንቁም፡፡
Website: https://elda-eth.com/
Facebook: https://web.facebook.com/profile.php?id=61579398676431
Twitter: https://x.com/toelda2024
Linkdin: [https://www.linkedin.com/company/ethiopian-lawyers-with-disabilities-association/]
Tik tok : https://vm.tiktok.com/ZMSumrLhm/
የ5 ፓርቲዎች ቅንጅት መፍጠር በትብብር ከመስራታቸው ምን ይለየዋል ?
በትብብር ሲሰሩ የቆዩ አምስት የፓለቲካ ፓርቲዎች አንድነት ኢዮጵያ የሚል ቅንጅት መፍጠራቸውን አሳውቀዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያም ቅንጅት ለመሰረቱ ፓርቲዎቹ የተለያዩ ጥያቄዎችን አቅርቧል።
እስካዛሬም በትብብር ስትሰሩ ነበር፤ ታዲያ ቅንጅቱ ከትብብሩ የሚለየው ምንድን ነው ? ስንል የጠየቅናቸው የእናት ፓርቲው አቶ ጌትነት ወርቁ፣ " ቅንጅቱ እንደ ሁለተኛ ምዕራፍ የሚታይ ነው፡፡ ከዚህ ቀደሞ ከነበረው ሕጋዊ ማዕቀፍ ያለው ነው። ይህም የበለጠ እርግጠኝነት ሰጥቶና ትግሉን ገፋ አድርጎ ለማራመድ ይጠቅማል " ብለዋል።
" በራስ ጽ/ቤት ቁጭ ብሎ ስለሌላኛው ፓርቲ ማሰብ ማለት ነው፡፡ ለመንግስት በቀላሉ እንደበግ እየጎተቱ ለማሰር ምቹ አይሆንለትም፡፡ አንዱ ሲታሰር ሌላው ከሌላ ቦታ ብቅ ብቅ ይላል። በመላ ሀገሪቱ ያለው የእነዚህ የተበተኑ ኃይሎች መዋቅር እየተናበበ ይሄዳል " ነው ያሉት።
" በተናጠል ይባክን የነበረው ኃይል ሰብሰብ ብሎ ለአንድ ግብ ለአንድ ዓላማ መዋል ይጀምራል፡፡ መንግስት ላይ ጫና ለማሳደርና ልጓም ለማበጀት አቅም ያገኛል " ያሉት አቶ ጌትነት፣ በዲፕሎማቲክ ማኅበረሰቡም ዘንድ ትከሻ ሰፊ ሆኖ ለመቅረብና ሀገሩ ፖለቲካ ላይ አማራጭ ሆኖ ለመውጣት ወሳኝ ምዕራፍ ነው " ብለዋል።
" ቅንጅቱ ከትብብሩ ወቅት ከምንሰራው የተለየ ሳይሆን ከዚያኛው በተሻለ የተቀናጀና ሕዝብን ወደ ማስተባበር የምንሄድበትን እድል የሚሰጥ ነው፡፡ ትብብርን ሕጋዊ ማዕቀፍ አልበሰን ነው የመጣነው ” ሲሉም አስረድተዋል።
" ይህም ደፍሮ ወደ ሕዝብ ለመግባት፣ ከገዢው መንግሥት ጋር ትከሻ ለመለካካት ይጠቅማል፡፡ በምርጫ ቦርድ፣ በሚዲያ፣ በዲፕሎማቲክ ማኅበረሰቡ፣ በመንግስት ፊት ተጨማሪ አቅም ሆኖ ተሰሚነትን ስለሚጨምር ዋጋው ከፍ ያለ ነው " ነው ያሉት።
ፓርቲዎች ምርጫ ሲቃረብ ቅንጅት ሲፈጥሩ ይስተዋላሉ፤ የእናንተ ቅንጅት ለምርጫ ተብሎ የተመሰረተ ነው ? ተብለው የተጠየቁት ከቅንጅቱ አንዱ የሆነው የአማራ ግዮናዊ ንቅናቄው ምርጫው ስንሻው ደግሞ፣ " ለምርጫ ተብሎ መሳተፍ በራሱ ለእድል አያበቃም፡፡ በምርጫ ስለተሳተፍን እናሸንፋለን ማለት አይደለም " ብለዋል፡፡
" የተሸከምነው ዓላማ አለ፤ ለዛ ዓላማ ነው መሰለፍ ያለብን፡፡ ግን ይህ ምርጫ እድል ከሰጠን ያንን እድል ማሳለፍ የለብንም፡፡ የያዝነው ህዝብ የፍትህ ጥማቱ በቀላሉ አግዞን ለድል እንበቃለን ብለን እናስባለን " ሲሉም አክለዋል፡፡
የሚጣመሩ ፓርቲዎች ከመንግስት ጋር ሲወግኑም፣ ሳይወግኑም ይስተዋላሉ። የእናንተ ጥምረት ከገዢው ፓርቲ ጋር ይወግን ይሆን ? ተብለው የተጠየቁት የቅንጅቱ ፕሬዚዳንት አቶ አብርሃም ሄጡ ደግሞ፣ " ህዝብ ከገባበት መቀመቅ ለማውጣት የሚደረገውን ፖለቲካዊ ትግል አምኖ ከመጣ ቅንጅቱ ከማንም ኢትዮጵያዊ ኃይል ጋር አብሮ ይሰራል " ብለዋል።
አቶ ጌትነት ወርቁ የቅንጅቱን ትኩረት ሲያስረዱ፣ " በሕዝብ የተጋረጠን የሕልውና አደጋ መቀልበስ፣ ጦርነት፣ እገታ ማስቆምና በንግግር ወደ ተረጋጋ ፖለቲካ ማሸጋገር፣ ዜጋው የኑሮ ውድነት በልቶ ማደር ወደ ማይችልበት ደረጃ ያደረሰውን መንግስት መር የኢኮኖሚ ቀውስ በመቀልበስ ነው " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
" ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ትምህርት ቤቶችን በደንብ መመልከት እንጀምራለን በተማሪ ቁጥር ልክ መጻሕፍትን ገዝቶ ያላዳረሰ ት/ቤት ካለ የእውቅና ፈቃዱ ይሰረዛል " - ትምህርት ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ትምህርት ቢሮ በከተማዋ የሚገኙ የግል ትምህርት ቤቶች በተማሪዎቻቸው ቁጥር ልክ መጻሕፍትን ገዝተው ማሰራጨት ካልቻሉ የእውቅና ፈቃዳቸው እስከመሰረዝ የሚደርስ እርምጃ እንደሚወስድ ገልጿል።
የቢሮው ሃላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ " በግል ትምህርት ቤቶች አልፎ አልፎ የሚታየው የመጻሕፍት እጥረት ከህትመት ጋር በተገናኘ ምክንያት እጥረት ኖሮ ሳይሆን ገዝተው ለተማሪዎቻቸው ማሰራጨትን እንደ ወጪ እና እንደ ድካም ስለሚያስቡት ነው " ብለዋል።
ሃላፊው ይህን ያሉት በአዲስ ቲቪ በተላለፈ " በጠረጴዛ " በተሰኘ ፕሮግራም ላይ በቀረቡበት ወቅት ነው።
" የመማሪያ መጻሕፍት በበቂ ሁኔታ ታትመዋል?በተለይ በግል ት/ት ቤቶች ለተወሰነ ጊዜ መጻሕፍት ሽያጭ ይከናወን እና አልቋል ይባላል ይህ ለምን ሆነ ? " የሚል ጥያቄ ለትምህርት ቢሮ ሃላፊው ቀርቦላቸው ነበር።
የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ምን መለሱ ?
" በተለይ አዲሱ ስርአተ ትምህርት ተግባራዊ ከሆነ በኋላ በልዩ ሁኔታ ድጋፍ ተደርጎ ለተማሪዎቻችን አንድ ለአንድ እንዲደርስ ተደርጎ ህትመቱ በበቂ ሁኔታ ተሰራጭቷል።
የመጻሕፍት ህትመት እና ስርጭት ላይ ለመንግሥት ተማሪዎች መጻሕፍት በነጻ ይሰጣል ለግል ትምህርት ቤቶች በሪቮልቪንግ ፈንድ 250 ሚሊየን ተፈቅዶልን ይህንን ስራ እየሰራን እንገኛለን።
የግል ትምህርት ቤቶች ላይ ያለው ችግር ከተማሪዎች የመጽሐፍ ገንዘብ ሰብስበው ከትምህርት ቢሮ ስቶር ገዝተው ትምህርት ቤታቸው ማድረስ እና ማሰራጨት እንደ ትልቅ እዳ ነው የሚቆጥሩት ።
እንደከተማ ግን በቂ ህትመት ታትሞ ስቶራችን ሙሉ ነው ችግሩ ት/ቤቶች መጻሕፍቶቹን ከስቶር ወስደው ለተማሪዎች ማከፋል ላይ ነው ያለው።
በተለይ የትምህርት ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለሥልጣን ፈቃድ የሚሰጠው አካል እሱ ስለሆነ መጻሕፍት በተማሪዎቻቸው ቁጥር ልክ ወስደው ለተማሪዎቻቸው ያላዳረሱ ትምህርት ቤቶች ካሉ እውቅና ፈቃዳቸው እንዲሰረዝ ተግባብተናል።
በቂ መጻሕፍት አለን በግል ት/ቤቶች እየተሰራጨ ነው አሁንም በስርጭት ላይ ነው የሚገኘው ችግሩ ያለው ትምህርት ቤቶች ላይ ነው እንደ ወጪ እንደ ድካም ስለሚያስቡት ነው።
ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ትምህርት ቤቶችን በደንብ መመልከት እንጀምራለን በተማሪ ቁጥር ልክ መጻሕፍትን ገዝቶ ያላዳረሰ ት/ቤት ካለ የእውቅና ፈቃዱ ይሰረዛል።
አንድም ተማሪ ያለ መጽሐፍ መማር የለበትም ይሄንን አንታገስም ይህም የእርምጃችን አንዱ አካል ይሆናል " ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ አደረሳችሁ፤ መልካም በዓል !
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
" ትልቅ የሀገር ሽማግሌ በታጣቂዎች ተገድለውብናል " - የቡርጂ ዞን አስተዳደር
➡️ " መዉጫ መንገድ ተዘግቶበት በሰላም የተቀመጠን ሕዝብ እቤቱ እየመጡ መግደል ምን የሚሉት ጭካኔ ነው ! "
የቡርጂ ዞን አስተዳደር " ትልቅ የሀገር ሽማግሌ በታጣቂዎች በተፈፀመ ጥቃት ተገድለውብኛል " ሲል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናገረ።
የዞኑ መንግስት ኮሚኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ አቶ አቤል አይላ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደገለፁት በትላትናዉ ዕለት በዞኑ ሶያማ ዙሪያ ወረዳ ዋለያ ቀበሌ የዞኑ የሀገር ሽማግሌ የሆኑና በአከባቢው ማህበረሰብ ትልቅ ከበሬታ የሚሰጣቸዉ አባት ከምዕራብ ጉጂ ዞን በኩል በመጡ የታጠቁ ሃይሎች መገደላቸውን ተናግረዋል።
የሀገር ሽማግሌው አርሶ አደሮችን ለማበረታታትና የእርሻ ማሳ ለመጎብኘት በእርሻ አከባቢ ሲንቀሳቀሱ ከታጣቂዎች በተተኮሰ ጥይት ሕይወታቸው ማለፉን አቶ አቤል ገልጸዋል።
በአከባቢው በሚፈጠሩ ተደጋጋሚ ጥቃቶች ላለፉት በርካታ ዓመታት ሁለቱን ዞኖችን የሚያገናኘው መንገድ ተዘግቶ መቆየቱን ያነሱት አቶ አቤል " መውጫ መግቢያ መንገድ ተዘግቶበት በሰላም የተቀመጠን ሕዝብ እቤቱ እየመጡ መግደል ምን የሚሉት ጭካኔ ነዉ ? " ሲሉ አክለዋል።
በዞኑ ባለፉት ጥቂት ወራት በነዚህ ታጣቂዎች በርካታ ንፁሃን በገዛ ማሳቸዉ ላይ እንደተገደሉ የገለፁት መምሪያ ኃላፊው በተደጋጋሚ በአከባቢው ይንቀሳቀሳሉ የተባሉ ታጣቂ ቡድኖች በሰላማዊ መንገድ እጅ ሰጡ በተባለባቸዉ ማግስቶች ጥቃት እንደሚፈፅሙ ተናግረዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa
@tikvahethiopia
ፎቶ፦ የ2018 ዓ/ም የመስቀል ደመራ በዓል ኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ላዛሪስት ገዳም ፂዮን ማርያም ቤተክርስቲያን።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
ፎቶ፦ የ2018 ዓ/ም የመስቀል ደመራ በዓል በአከባበር በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ።
Photo Credit - FMC & ETV
@tikvahethiopia
#Ethiopia🇪🇹
" ሀገራዊ ስሜት የለም ፤ አትሌቶች ሀገራዊ ስሜት የላቸውም " - አትሌት ስለሺ ስህን
➡️ " ለጠፋው ውጤት ይቅርታ አይደለም መታሰርም ሲያንሰን ነው " - አትሌት የማነ ፀጋይ
በቅርቡ በጃፓን ቶኪዮ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ተካሂዶ እንደነበር ይታወሳል።
ኢትዮጵያ ስሟ በገነነበት የአትሌቲክስ ውድድር ቶኪዮ ላይ የተመዘገበው ውጤት አንገት የሚያስደፋ ፤ የስፖርቱን ቤተሰብ ፣ መላ ዜጎችን ያሳዘነ ሆኖ አልፏል።
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ዛሬ መግለጫ ሰጥቶ ነበር።
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ስለሺ ስህን በተገኘው ውጤት ፌዴሬሽኑና ልዑካን ቡድኑ ማዘናቸውን ገልጸው የተገኘው ውጤት ኢትዮጵያን የማይገልፅ መሆኑን ተናግረዋል።
" ህዝቡን ከልብ ይቅርታ እንጠይቃለን " ብለዋል።
ፕሬዚዳንቱ " አብሮ ለመስራት ፍላጎት አልነበረም ፤ አትሌቶች አብራችሁ ልምምድ ስሩ በቡድን ስሩ ሲባሉ በአፍ ' እሺ እሺ ' ብለው ነገርግን አይተገብሩትም ፍላጎት የላቸውም " ሲሉ ገልጸዋል።
" ሀገራዊ ስሜት የለም ፤ አትሌቶች ሀገራዊ ስሜት የላቸውም ይህ ለውጤቱ ተፅዕኖ አሳድሯል ወደፊት በስፋት ይሰራበታል " ብለዋል።
የአትሌቶች ማህበር ፕሬዝዳንት የሆኑት አትሌት የማነ ፀጋይ " ለጠፋው ውጤት ይቅርታ አይደለም መታሰርም ሲያንሰን ነው " ሲሉ ተናግረዋል።
" የተመዘገበው ውጤት የማይገባ ነው ፤ ይቅርታ አይደለም አለመታሰራችንም አንድ ነገር ነው " ሲሉ ገልጸዋል።
" እኔ በበኩሌ በርካታ አትሌቶች ማጣሪያውን እንደማያልፉ እርግጠኛ ነበርኩኝ " ብለዋል።
" እኛ አንጋፋዎቹም መከባበር፣ በቀራረብ፣ ማውራትና መነጋገር አለብን። የዚህ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ባለሪከርዶች ጥሩዬና ቀነኒሳ የት ናቸው ? ከምንገፋቸው ለምን አናቀርባቸውም ? " ሲሉ ጠይቀዋል።
" መወሻሸት አያስፈልግም አሁን ባሉት አትሌቶች መካከል የሀገር ፍቅር ከጠፋ ቆይቷል አብረው መዋል ፤ መመገብ እና መስራት አለባቸው ነገርግን አላደረጉም። " ብለዋል።
ቲክቫህ ስፖርት
Via @tikvahethsport
#ደመራ
የ2018 ዓ/ም የመስቀል ደመራ በዓል በዛሬው ዕለት በመላው ሀገሪቱ ይከበራል።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የመስቀል ደመራ በዓል በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ መስቀል አደባባይን ጨምሮ በ2375 አድባራት እና ቦታዎች ላይ ይከበራል።
ቤተክርስቲያኗ ምዕመናን ሁሉ ነጭ ልብሳቸውን ለብሰው እንዲገኙ መልዕክት አስተላልፋለች።
በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ከሚከበረው የመስቀል ደመራ በዓል ጋር በተያያዘ የአዲስ አበባ ፖሊስ መልዕክት አስተለልፏል።
በዚህም ፦
- ከበዓሉ ጋር የማይገናኙ ተንኳሽ፣ ግጭት ሊቀሰቅሱ የሚችሉ ማንኛውም መልዕክቶችን ይዞ መምጣት እንደማይቻል፤
- ርችት መተኮስ በፍጹም እንደማይቻል፤
- በከተማው የተለያዩ ቦታዎች ከፍተኛ ወጪ ወጥቶባቸው በተሰሩ የኮሪደር ቦታዎች ላይ ደመራ መደመር እንደማይቻልና ሌላ ተለዋጭ ቦታ ላይ ስርዓቱ እንዲካሄድ ጥሪ አስተላልፏል።
በመስቀል አደባባይ ከሚከበረው የደመራ በዓል ጋር በተያያዘ ምዕመና ሲመጡ ፍተሻ እንደሚኖር እንዲያውቁትና ተባባሪ እንዲሆኑ አደራ ብሏል።
NB. በሁሉም ቦታ የደመራ ስርዓት ሲካሄድ ከተቀጣጣይ እና ከኤሌክትሪክ መስመሮች በራቀ ሁኔታ እንዲሆን መልዕክት ተላልፏል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia