1532594
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። @tikvahuniversity @tikvahethAfaanOromoo @tikvahethmagazine @tikvahethsport @tikvahethiopiatigrigna #ኢትዮጵያ
ማርበርግ ቫይረስ (Marburg Virus) ምንድነው ነው ?
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የተከሰተው እና ምንነቱ ለማረጋገጥ የዘረመል ምርመራ ሲካሄድበት የቆየው ሄሞራጂክ ፊቨር በሽታ መንስኤ ማርበርግ ቫይረስ (Marburg Virus) መሆኑን መረጋገጡን የጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በጋራ በሰጡት መግለጫ ማሳወቃቸው ይታወቃል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ስለ ማርበርግ ቫይረስ ምሁራዊ ማብራሪያ እንዲሰጡን የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስት እና የተላላፊ በሽታዎች ፌሎ የሆኑትን ዶ/ር ሰላም ቦጋለን አነጋግሯል።
የማርበርግ ቫይረስ መንስኤ ምንድነው ?
" ማርበርግ ቫይረስ 'ማርበርግ' ተብሎ በሚጠራ አር ኤን ኤ ቫይረስ ምክንያት ይከሰታል። "
በምን አይነት መንገድ ይተላለፋል?
" በመጀመርያ ከለሊት ወፍ ወደ ሰው ይተላለፋል።
በመቀጠል በበሽታው ከተያዘ ሰው (በህይወት ካለም ይሁን ከሞተ ሰው) ጋር በሚኖር የደም ወይም ማንኛውም ፈሳሽ ንክኪ ከሰው ወደ ሰው ይተላለፋል።
በበሽታው የታመመ ሰው ፈሳሽ ያለበት ማንኛውም ነገር ለምሳሌ ልብሶች፣ ፎጣ፣ አልጋ ወዘተ መንካት በሽታውን ያስተላልፋል።
ማርበርግ እንደኮሮና በትንፋሽ አይተላለፍም። "
በበሽታው የተያዘ ሰው ምልክቶቹን በምን ያህል ጊዜ ውስጥ ያሳያል ?
" ምልክቶች ከተጋለጡ በኋላ 2–21 ቀን ውስጥ ይታያሉ። "
የበሽታው ምልክቶች ምን ምን ናቸው?
" ህመሙ ሲጀምር እንደሌሎች ትኩሳት አምጪ ተላላፊ ህመሞች ፦
• ትኩሳት
• ከባድ ራስ ምታት
• ጡንቻ ህመም
• ብርድ ብርድ ማለት
• ድካም
• የጉሮሮ ህመም
• ትውከት እና የምግብ ፍላጎት መቀነስ ያስከትላሉ።
በቀጣይ ህመሙ ቀስ በቀስ ከበድ ማለት ሲጀምር ደግሞ:-
• ማቅለሽለሽ
• ማስቀመጥ
• የሆድ ህመም
• ደም መፍሰስ(ከአፍ ፣ከአፍንጫ ከተለያዩ ሰውነት ክፍሎች)
• የቆዳ ሽፍታ
• ትንፋሽ ማጠር ራስ መሳት
• የሰውነት ክፍሎች (ኦርጋኖች) ለምሳሌ ሳንባ፣ ኩላሊት፣ ጉበት ስራቸው መዳከም ወይም ማቆም
• ደም ግፊት መውረድና ሌሎችም የሰውነት አካሎች ጉዳትና ሞት ሊያስከትሉ ይችላሉ። "
መከላከያ መንገዶቹ ምንድን ናቸው?
" • ከታመመ ሰው፣ በዚህ ህመም ከሞተ ሰው፣ እና ይህ ህመም ያለበት ሰው የተጠቀመበትን ማንኛውም ነገር አለመንካት ።
• እጅን አዘውትሮ መታጠብ ( በሳሙና ወይም አልኮል)
• ለጤና ባለሞያዎች ህክምና ሲሰጡ እንደ ኮቪድ ከላይ እስከ ታች የሚለበስ መከላከያ(PPE) ማድረግ
• በበሽታው ህይወቱ ካለፈ ሰው ቀብር ላይ ጥንቃቄ በማድረግ መከላከል ይቻላል። "
በበሽታው መያዛችንን እንዴት ይረጋገጣል?
" ከላይ የተጠቀሱ ምልክቶች ከተከሰቱ ወደ ጤና ተቋም በመሄድ የህመሙን ትክክለኛ መንስኤው በደም ወይም ሰውነት ፈሳሽ ናሙና ምርመራ ማረጋገጥ ይቻላል። "
በበሽታው መያዛችን ከተረጋገጠ ምን አይነት ህክምና ይደረጋል?
" እንዳስፈላጊነቱ ግሉኮስ ፣ደም መስጠት፣የደም ፕሮዳክቶችን መስጠት፣ ህመም ማስታገስ፣ ኦክስጅን እንዲሁም መተንፈሻና የኩላሊት ህክምና እንደየ ክብደቱና አይነቱ ይደረጋሉ። "
ዶ/ር ሰላም " የተወሰኑ በሙከራ ላይ ያሉ እና በተወሰነ መልኩ ውጤታማ የሆኑ የህክምና አይነቶች እንዳሉ የቅርብ ጊዜ ጥናቶች ያሳያሉ " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሱጡት ቃል አስረድተዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
2 የእጣ ቁጥር በM-PESA!
ሚሊየነር የመሆን ዕድላችንን በእጥፍ ለማሳደግ የሳፋሪኮምን የበሽ ጥቅል በM-PESA እንግዛ።
መተግበሪያውን ለማውረድ ይህንን ይጫኑ:
https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle
ለተጨማሪ መረጃ በቴሌግራም ያግኙን፥
/channel/MPesaETCustomerCare
#MPESASafaricom #MPESAEthiopia
#Tecno_Spark_40_Pro+
ቻርጀር ሳልይዝ ስልኬ ሊዘጋ ነው! የሚል ስጋት በአዲሱ Tecno Spark 40 Pro+ ታሪክ ነው፡፡ ምክንያቱም 30W Wireless ወይንም ገመድ አልባ የቻርጅ ቴክኖሎጂ ስላለው ያለምንም ሃሳብ ስልኮን በትንሽ ደቂቃ ቻርጅ አድረገው ወደ ስራዎት መመለስ ያስችሎታል፡፡ Tecno Spark Pro+ በልዩነት የሚገዙት ስልክ ነው፡፡
#Spark40Pro+ #SlimeverStrongForever #TecnoAI #TecnoSpark40Series
@tecno_et
" የፊት ገፃቸው እንዳለ ክርር ብሎ ስለነበር ወንድሞቻችንን ለመለየት አልተቸገርንም ብለዋል " -የተጎጂ ቤተሰብ
ከ20 ወራት በፊት በደላንታ ወረዳ በማዕድን ቆፋሮ ላይ እንዳሉ " ናዳ ተደርምሶባቸው " የሞቱ ሰዎች አስከሬናቸው ወጥቶ መቀበሩን የወርቅ ዋሻ የማዕድን አምራቾች ማህበር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።
የማኅበሩ ሊቀመንበር ተስፋዬ አጋዥ ፤ የካቲት 1 ቀን 2016 ዓ.ም በአማራ ክልል፣ ደቡብ ወሎ ዞን፣ ደላንታ ወረዳ " ቆቃ ውሃ " ተብሎ በሚጠራው ስፍራ ማዕድን ለማውጣት መሬት ሲቆፍሩ የነበሩ 8 ሰዎች ነበሩ ናዳ የተደረመሰባቸው ሲሉ አስታውሰዋል።
አቶ ተስፋዬ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደተናገሩት እነዚህ 8 የማህበሩ አባላት የነበሩትን ተጎጂዎችን በወቅቱ ለማውጣት የአካባቢው ማህበረሰብ፤ የተጎጂ ቤተሰቦች እንዲሁም የአካበቢዉ የመንግስት ባለስልጣናት ከፍተኛ ጥረት ቢያደርጉም የቦታው አቀማመጥ ለማሽንም ለሰው ጉልበትም የተመቸ እንዳልነበር ገልጸዋል።
እስከ 70 ሜትር ርዝመት ውስጥ ለውስጥ ቁፋሮ ተደርጎ የነበረ ቢሆንም ከዚህ በላይ ቢቆፈር መሬቱ ተደርምሶ ተጨማሪ ጉዳት ሊያስከትል ይችላል በሚል ስጋት የነፍስ አድን ጥረቱ ሳይሳካ እንደቀረም መለስ ብለው አስታውሰዋል።
ላለፉት 20 ወራት ማለትም አንድ አመት ከ10 ወር ተዳፍኖ የቆየው የተጎጂዎች አስከሬን የማህበሩ አባላት በሌላ አቅጣጫ ማዕድን ለማውጣት ሲቆፍሩ የሟቾችን አስከሬን ህዳር 4/2018 ዓ.ም በማየታቸው እና ይህንኑ መረጃም ለማህበሩ አመራሮች በመናገራቸው የተጎጂ ቤተሰቦች እና የአካባቢው ማህበረሰብ በተገኙበት የ8ቱም አስከሬን ወጥቶ በወገል ጤና ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን ከቀኑ 6:00 ላይ ስርዓተ ቀብራቸው እንደተፈጸመ ተናግረዋል።
" የሟቾችን አስከሬን ቤተሰቦቻቸው ተገኝተው በለበሱት ልብስና ይዘውት በነበረው ተንቀሳቃሽ ስልክ እንዲሁ በመታወቂያቸው ለይተው አስከሬናቸውን ለይተው ተረክበዋል " ሲሉም አክለዋል።
የ25 አመት ወጣት ባለ ትዳርና የአንድ ልጅ አባት የሆነው መራጃው አበበ የተባለውን የእህታቸው ልጅ በዚህ የመሬት ናዳ ያጡት አቶ ተስፋየ የተባሉ የአካባቢው ነዋሪ ከአንድ አመት ከ10 ወር በኃላ የእህታቸውን ልጅ አስከሬን አግኝተው አፈር ማልበሳቸው የመንፈስ እረፍት እንደሰጣቸው ይናገራሉ።
የመሬት ናዳው በተከሰተበት ወቅት ቤተሰብ፣ የአካባቢው ማህበረሰብ እና መንግስት ርብርብ አድርጎ እንደነበር የገለፁት አቶ ተስፋየ እግዜር ባለው ቀን ጏደኞቻቸው በሌላ አቅጣጫ ሲቆፍሩ አስከሬናቸውን አይተው እንደተናገሩ ገልጸዋል።
" እኛም አስከሬናቸው ሲወጣ ተገኝተን እንደተመለከትነው የፊት ገፃቸው እንዳለ ክርር ብሎ ስለነበር ወንድሞቻችንን ለመለየት አልተቸገርንም " ብለዋል።
" ከቤተዘመድ ጋር በወገል ጤና ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን አፈር አልብሸዋለሁ " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ባሕር ዳር
@tikvahethiopia
#SafaricomEthiopia
2 ቀን ብቻ ቀረው! ቀጣይ ሚሊየነር ማን ይሆን ?🏆💚 ዛሬዉኑ የበሽ ጥቅልን ይግዙ፤ ሚሊየነር የመሆን እድሎን ያስፉ!
📲 የM-PESA መተግበሪያን አሁኑኑ ያውርዱ፡
https://onelink.to/ewsb22
የቴሌግራም ቦታችን: /channel/official_safaricomet_bot
ወደ *777*0# ይደውሉ ወይም በM-PESA የበሽ ጥቅል ይግዙ!
#SafaricomEthiopia
#MPESASafaricom
#furtheraheadtogether
#Besh
" ተጠርጣሪው ጭካኔ በተሞላበት መልኩ ሕፃኑን በመግደል ተከራይቶ ይኖርበት በነበረው የሟች ታዳጊ አያት ግቢ በሚገኝ መፀዳጃ ቤት መጣሉን ከተያዘ በኋላ በሰጠው መረጃ አስክሬኑ ተገኝቷል " - ፖሊስ
➡️ " የአርባምንጭ ነዋሪዎችን ያስቆጣ ድርጊት የፈፀመዉ ግለሰብ በጭር ጊዜ ውስጥ ተገቢዉን ፍርድ ያገኛል "
በአርባ ምንጭ ከተማ በቀን 3/3/18 ዓ/ም ናትናኤል ማይክል የተባለ በግምት የ10 ዓመት ታዳጊ ከቤት መጥፋቱን ቤተሰቦች ለፖሊስ ያሳውቃሉ።
ይህን ተከትሎ ፖሊስ ፍለጋ ይጀምራል።
ፖሊስ ከሁሉም የፀጥታ መዋቅሮች ጋር በመሆን ክትትልና አፕሬሽን ሲያደርግ ቆይቶ ዛሬ አንድ ተጠሪጣሪ ለማምለጥ ሲሞክር በቁጥጥር ስር መዋሉን የአርባ ምንጭ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ክበበው አዳል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልፀዋል።
ተጠርጣሪው ወርቁ አሰፋ ይባላል።
ግለሰቡ በአርባ ምንጭ ከተማ ሴቻ ቀበሌ ዶሳ ቀጠና ፖሪቲ ስፕሪንግ ሆቴል ጀርባ ተከራይቶ በሚኖርበት ግቢ ውስጥ የነበረን ታዳጊ አፍኖ በመውሰድ ከወላጆቹ ገንዘብ መጠየቁንና የሕፃኑ ወላጅ እናት የተጠየቀችውን 50 ሺህ ብር በባንክ ማስተላለፏን መረጃ ማግኘታቸውን ኮማንደር ክበበው ገልፀዋል።
ግለሰቡ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተምሮ የተመረቀ እንደሆነ በሚገልፅ ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ ምክንያት በቅርቡ ከሚሰራበት ትምህርት ቤት መባረሩን መረጃዎች እንደሚያመላክቱ ኮማንደር ክበበው ተናግረዋል።
ይኸው ግለሰብ ኢ-ሰብዓዊ በሆነ ጭካኔ በተሞላበት መልኩ ሕፃኑን በመግደል ተከራይቶ ይኖርበት በነበረው የሟች ታዳጊ አያት ግቢ በሚገኝ መፀዳጃ ቤት ውስጥ መጣሉን ከተያዘ በኋላ በሰጠው መረጃ አስክሬኑ መገኘቱንም አስረድተዋል።
ግለሰቡ ይህን ሕዝብን ያስቆጣ ዘግናኝ ድርጊት ከፈፀመ በኋላ በሚኒባስ ተሳፍሮ ከከተማ ለመውጣት ሲሞክር የፀጥታ ኃይሉ ከመረጃና ደህንነት ተቋም ጋር በመሆን ባደረገው ክትትል በጋሞ ዞን ምዕራብ አባያ ወረዳ ፉራ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ በቁጥጥር ስር መዋሉን አስታውቀዋል።
ፖሊስ አስፈላጊውን ምርመራ በማድረግ በአጭር ጊዜ ውስጥ ሕዝቡን ያስቆጣ ዘግናኝ ድርጊት የፈፀመውን ግለሰብ ለሕግ በማቅረብ ፈጣንና ተገቢውን ፍርድ እንደሚያሰጥም ገልፀዋል።
ሕብረተሰቡ በትዕግስት እና በመፅናናት የምርመራና የፍርድ ውሳኔዉን እንዲጠባበቅ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ማህበረሰቡ ፦
- መኖሪያ ቤቶችን በሚያከራይበት ወቅት፣
- የአልጋ ቤት አገልግሎት በሚሰጥበት ወቅት፣
- በቅጥርና ውሎች ወቅት ግለሰቦችን ህጋዊ የቀበሌ ነዋሪነት ወይም ፋይዳ የዲጂታል መታወቂያ መያዛቸውንና ትክክለኛ አድራሻቸውንና የመጡበት ምክንያት ፣ የሚሰሩበት ተቋም ወይም ድርጅትን በማጣራት እንዲሁም ህጋዊ ተያዥ መኖሩን በማረጋገጥ ማከራየትና አገልግሎት መስጠት እንደሚያስፈልግ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል አሳስበዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHawssa
@tikvahethiopia
" የበሽታዉ መንስኤ ማርበርግ ቫይረስ (Marburg Virus) መሆኑን መለየት ተችሏል " - ጤና ሚኒስቴር
የጤና ሚኒስቴር በደቡበ ኢትዮጵያ ክልል በጅንካ ከተማ የሄሞራጅከ ፊቨር (Viral Hemorragic Fever) በሽታ መከሰቱን እና የበሽታዉን ምንነት በማረጋገጥ ላይ መሆኑን መግለጹ ይታወቃል፡፡
ሚኒስትሩ በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ የበሽታዉ መንስኤ ማርበርግ ቫይረስ (Marburg Virus) መሆኑን መለየት ተችሏል ብሏል።
የዘረመል ምርመራው የተከናወነው በኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ብሄራዊ ሪፈረንስ ላብራቶሪ ነው።
መግለጫው "በዚህም የዘረመል ምርመራ በአሁኑ ሰዓት ኢትዮጵያ ውስጥ የተገኘዉ ቫይረስ ሌሎች ምስራቅ አፍሪካ ሃገራት ላይ ከዚህ በፊት ከተከሰቱት ጋር ተመሳሳይ ዝርያ ያለዉ መሆኑ ታዉቋል" ነው ያለው።
በተጨማሪም በዛሬው እለትም አዲስ የበሽታውን ምልክት ያሳየ ወይም በቫይረሱ የተጠረጠረ ሰው ያልተገኘ መሆኑን ሚኒስትሩ ያሳወቀ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት የተለያዩ የሙያ ስብጥር ያካተተ ከፍተኛ ፈጣን ምላሽ ሰጭ ቡድን ወደ ከልሉ በመላከ በሽታዉን የመከላከል እና የመቆጣጠር ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ ብሏል።
ከነዚህም ውስጥ :-
° የማህበረሰብ አቀፍ የቅኝት ስራዎች፣
° በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ለይቶ ማከም፣
° የማህበረሰብ ግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች እና ከተጠረጠሩ ሰዎች ጋር ንክኪ ያላቸዉን ሰዎች የመለየት ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ተገልጿል።
በሃገር አቀፍ እንዲሁም በክልል ደረጃ የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች የክስተት አስተዳደር ስርዓት (Incident Management System) ተቋሞ የፈጣን ምላሽ ስራዎችን በማስተባበር ላይ ይገኛል ተብሏል።
ጤና ሚኒስቴር:-
➢ ከጤና ሚኒስቴር እና ከኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የሚተላለፉ መረጃዎችንና የጥንቃቄ መልዕክቶችን መከታተልና መተግበር፣
➢ የበሽታው ምልከት የሆኑትን በአፍ፣አፍንጫ እና ሌሎች የሰውነት ክፍሎች የመድማት፣ትኩሳት፣ማስቀመጥ እና ማስመለስ ምልከት ሲኖር ወደ ህክምና ተቋማት መሄድና በወቅቱ የላቦራቶሪ ምርመራ ማድረግ፣
➢ ምልክት ከታየበት ማንኛዉም ሰዉ ጋር ንክኪ በሚኖርበት ግዜ ራስን የመከላከያ ዘዴዎችን መጠቀም፣
➢ ሁልጊዜ እጅን በውሃና ሳሙና መታጠብ ወይም በሳኒታይዘር ማጽዳት እንደሚያስፈልግ አሳስቧል።
ማንኛውም ጤና ተቋም ለታካሚዎች ልየታ ልዩ ትኩርት በመስጠት የማርበርግ በሽታ (Marburg viral disease) መሰል በሸታ መለየት፣ ማከም እና በአፋጣኝ ሪፖርት ማድረግ እንደሚያስፈልግም በመግለጫው ጠቁሟል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
@tikvahethiopia
#Tecno_Spark_40_Pro+
Tecno Spark 40 Pro+ 16 GB RAM እንዲሁም 256 GB የሚሞሪ ስፔስን አካቶ ስለመጣ አግጅ ማራኪ እና ፈጣን ስልክ ከበቂ ስፔስ ጋር በአንድ ላይ ሰጥቶታል፡፡ ታዲያ ምን ይጠብቃሉ የTecno Spark 40 Pro+ ስልኮችን ዛሬ ነገ ሳይሉ በእጆት ያስገቡ!!
#Spark40Pro+ #SlimeverStrongForever #TecnoAI #TecnoSpark40Series
@tecno_et
'' ማህበራዊ ሚድያ የልጆቻችንን ጊዜ ፣ ልጅነታቸውን እና ደህንነታቸውን እየሰረቀ ነው " - ካርሎን ስቴጅ ኦልሰን
ከ15 ዓመት በታች የሆኑ ልጆች የማህበራዊ ሚድያ እንዳይጠቀሙ እገዳ ለመጣል መወሰኑን የዴንማርክ መንግስት አሳወቀ።
የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሜት ፍሬድሪክሰን በባለፈው ወር ለፓርላማ መክፈቻ ባደረጉት ንግግር የህፃናት የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ላይ እገዳ እንዲጣል ጥሪ አቅርበው ነበር። ይህንን ተከትሎ በዴንማርክ ፓርላማ ውስጥ ያሉ አብዛኛዎቹ ፓርቲዎች ዕቅዱን እንደሚደግፉ ተናግረዋል፡፡
'' ማህበራዊ ሚድያ የልጆቻችንን ጊዜ ፣ ልጅነታቸውን እና ደህንነታቸውን በመስረቅ ላይ ሲሆን እኛም ይህንን በማስቆም ላይ ነን ፤ ይህም የሚደረገው በዲጂታል ዓለም ውስጥ ህፃናትን እና ወጣትቶችን ለመጠበቅ ነው '' ሲሉ የዲጂታል ጉዳዮች ሚኒስትር ካርሎን ስቴጅ ኦልሰን ተናግረዋል፡፡
ሚኒስትሯ የትኞቹ የማህበራዊ ሚዲያ ላይ እገዳ እንደሚጣል እና እንዴት እንደሚተገበር በግልፅ አላሳወቁም ፤ ነገር ግን ወላጆች ከ13 ዓመት ዕድሜ ጀምሮ ያሉ ልጆች የተወሰኑ መተግበሪያዎች ለመጠቀም እንዲችሉ ይፈቀድላቸዋል ብለዋል፡፡
ዴንማርክ በአውሮፓ ህብረት ውስጥ ከመጀመሪያዎቹ ሀገራት አንዷ እንደመሆኗ መጠን በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የዕድሜ ገደቦችን ለማስተዋወቅ አንድ ትልቅ እርምጃ እንደምተወስድ ተገልጿል።
#SocialMedia #Denmark
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#እንድታውቁት
ስለ ዓይን ጤና የሚነገሩ የተሳሳቱ እምነቶች / አመለካከቶች ምን ምን ናቸው ?
ብዙ ሰዎች በማህበረሰብ ውስጥ ስለ ዓይን ጤና የሚነገሩ ነገሮችን እውነት እንደሆኑ ያምናሉ። ነገር ግን እነዚህ ብዙ እምነቶች የተሳሳቱ እና ከሳይንስ ውጪ ናቸው።
በእነዚህ አንዳንድ እምነቶች ወይም አመለካከቶች ምክንያት ዓይናችንን በተገቢው መንገድ መንከባከብ ወይም መጠበቅ እንዳንችልና የዓይን ክትትል እንዳይኖረን ያደርጋል።
ማህበረሰብ ውስጥ በስፋት ከተሰራጩ የተሳሳቱ አመለካከቶች ፦
1. " መነጽር ማድረግ ዓይንን ያበላሻል ወይም አንዴ መነፅር ማድረግ ከተጀመረ በዛው ይለምዳል "
ይህ የተሳሳተ አመለካከት ነው።
መነጽር እይታን አያበላሽም፣ በትክክል እንዲታየን ይረዳናል። ለምሳሌ፦ ለቅርብ ዕይታ ችግር ፣ ለርቀት ዕይታ ችግር ፣ ዕድሜያቸው ከ40 ዓመት በላይ ለሆኑ አዋቂዎች ማንበቢያ ወዘተ... ጥራት ያለው ዕይታ ያስገኛል።
የዕይታችን ጥራት በተፈጥሮ ወይም በሌላ በሽታ ይቀየራል ይህ ደግሞ መነፅር ከማድረግ ጋር ሚያገናኘው ነገር የለም።
ጥንቃቄ ፦ በዓይን ሀኪም ብቻ የታዘዘ መነፅር ይጠቀሙ።
2. " ካሮት መብላት የእይታ ችግርን ይፈውሳል "
ካሮት ቫይታሚን A እናገኝበታለን ይህም ለዓይንም ሆነ ለሌሎች ሰውነታችን ክፍል በጣም አስፈላጊ ነው ነገር ግን በራሱ በሽታን አይፈውስም።
3. " የእይታ ችግር እድሜያቸው የገፋ ሰዎች ላይ ብቻ ነው የማከሰተው "
ይህ ፍጹም ስህተት ነው።
የእይታ ችግር በህፃናትና በወጣቶችም ላይም በሰፊው ይስተዋላል። ለዓይን ጤና እንክብካቤ ካልተደረገ ችግሩ በየትኛውም እድሜ ሊከሰት ይችላል።
በእድሜ ምክኒያት ብቻ የሚመጡ የዓይን ህመሞች ግን አሉ።
4. " የዓይን ምርመራ ሚያስፈልገው የዓይን ህመም ሲኖር ብቻ ነው "
ይህም የተሳሳተ አመለካከት ነው።
መደበኛ የዓይን ምርመራ ማድረግ ቀደም ብሎ የዓይን ችግር እንዲታወቅ ይረዳል።
በርካታ የዓይን ችግሮች በጊዜው ከታወቁ አመርቂ ህክምና አላቸው። ምሳሌ ፦ amblyopia (የዓይን መስነፍ) amblyopia በጊዜ ታውቆ ካልታከመ የህክምናው ውጤት እምብዛም ነው።
5. " የፀሐይ መነጽር ለማጌጥ ብቻ ነው "
ይህ የተሳሳተ አመለካከት ነው።
ትክክለኛ የፀሐይ መነጽር ማድረግ ከፀሀይ የሚመጣ የUV ጨርን ከዓይን ይጠብቃል፣ ስለዚህ የዓይን ጤና መንከባከብያም ጭምር ነው።
💬 በእውነታዊ መረጃዎች የዓይናችንን ጤና እንከባከብ፣ መደበኛ ምርመራ እናድርግ። የተሳሳቱ አስተሳሰቦች የዓይን ጤና ይጎዳሉ።
ምንጮች፦
- World Health Organization (WHO), Eye Care Guidelines 2023
- American Academy of Ophthalmology (AAO), Common Eye Myths and Facts
- Centers for Disease Control and Prevention (CDC), Vision Health Initiative
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
@tikvahethiopia
እኛ እንድንበደር ቴሌብር ዋስ ሆኖልናል!
በቴሌብር በኩል እስከ 15 ሺህ ብር ድረስ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያለማስያዣ መበደር የምንችል ሲሆን በ60 ቀን ተመላሽ እናደርጋለን። ደሞዛችንን በቴሌብር የምንቀበል የቴሌብር ደንበኞች ደግሞ የደሞዛችንን 4 እጥፍ ድረስ መቀበል እንችላለን!
እንቆጥብም ካልን በየቀኑ በሚታሰብ ወለድ አልያም እንደምርጫዎ ያለወለድ የምንቆጥብበት 'ስንቅ' ቀርቦልናል።
*127# ደውለን ወይም ቴሌብርን በስልካችን በዚህ ሊንክ
https://bit.ly/telebirr_SuperApp ጭነን ስንመዘገብ እንዲህ ነን!
#ደንበኛ_ስንሆን_እንዲህ_ነን
#ስንመዘገብ_እንዲህ_ነን
#ስንጭን_እንዲህ_ነን
#ስናስጀምር_እንዲህ_ነን
የዓለም ጤና ድርጅት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለተከሰተው በሽታ አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት 300 ሺ የአሜሪካ ዶላር ድጋፍ መደረጉን አሳወቀ።
የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባጋሩት መግለጫ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የተከሰተውን ቫይራል ሄሞራጂክ ፊቨር (Viral Hemorrhagic Fever) ህመም አፋጣኝ ድጋፍ ለመስጠት ከአለም ጤና ድርጅት የአደጋ ጊዜ ፈንድ 300 ሺ የአሜሪካ ዶላር ድጋፍ መደረጉን ይፋ አድርገዋል።
ዳይሬክተሩ የዓለም ጤና ድርጅት አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜ ሁሉ ድጋፍን ለማሳደግ ዝግጁ መሆኑንም አክለው ገልጸዋል።
መግለጫው ድንበር ዘለል የሆነ ስርጭትን ለመከላከል በኢትዮጵያ እና በደቡብ ሱዳን የሚገኙ የዓለም ጤና ድርጅት ቢሮዎች በቅንጅት እየሰሩ መሆኑን ጠቁሟል።
የዓለም ጤና ድርጅት በሽታው ወደ ተቀሰቀሰበት አካባቢ ባለሞያዎችን ጨምሮ የተለያዩ መድኃኒት እና ቁሳቁሶችን መላኩንም ዳይሬክተሩ አሳውቀዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
@tikvahethiopia
" ወንጀል ፈጻሚው በፈጸመው ወንጀል ልክ ተመሳሳይ የሆነ ፍርድ እንዲሰጠው እጠይቃለሁ " - የተማሪ ሊዛ ቤተሰብ
በደሴ ከተማ "ተደፍራና ተገድላ" ተገኘች የተባለችው በዘንድሮው አመት ለምርቃት ስትጠበቅ የነበረችው የሦስተኛ አመት በኮሌጅ ተማሪ ሊዛ ደሳለ ግድያ የተጠረጠረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉን የደሴ ከተማ ፓሊስ መምሪያ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።
ጉዳዩ በምርመራ ላይ መሆኑን ከዚህ ቀደም ገልጸውልን የነበሩ የፓሊስ አካል ዛሬ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ደግሞ፣ " ሰውየው/ተጠርጣሪው በቁጥጥር ስር ውሏል። ቀጣዩ ሥራ ይቀጥላል " ብለዋል።
የድርጊቱን ሁኔታ በተመለከተ ዝርዝር ማብራሪያ ስንጠይቃቸውም፣ " ከሳምንት በኋላ ሙሉ መግለጫ ጠብቁ፤ አሁን ብናብራራው የፍትህ ስርዓቱ ይበላሻል " ብለዋል።
" ምርመራው አልቆ የጨመረሻው ውጤት ሲደርስ ሙሉ ማብራሪያ ይሰጣል፤ በመካከል ላይ ካለ ግን ይባላሻል። ወንጀሉ የተፈጸመው ምሽት ላይ ስለሆነ ፓሊስ ጉዳዩን እስከሚጨርስ ድረስ ጥንቃቄ ያስፈልጋል፤ የተጠርጣሪውን ፎቶ ራሱ አለጠፍንም " ነው ያሉት።
የደሴ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ በበኩሉ፣ የተቋቋመው የምርመራ ቡድን ባደረገው የክትትልና ማጣራት " ህዳር 2 ቀን 2018 ዓ/ም ዋና ወንጀል ፈፃሚው በቁጥጥር ስር መዋሉን " ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
ተማሪዋ " መስከረም 28/2018 ዓ/ም የእህቷን የተበላሸ ሞባይል ለማሰራት አምሽታ ወደ ጓደኛዋ ቤት ሰመሀል ዝናቡ ለማደር ስትሄድ ጭንቅላቷ አንገቷን ከኋላና ከፊት ድብደባ ተፈፅሞባት ወደ ሆስፒታል የሄደች ሲሆን ህይወቷ መትረፍ አለመቻሉ ይታወቃል " ሲልም አስታውሷል።
በተማሪ ሊዛ ግድያ የተጠረጠረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉን ሰምታችኋል ? ፓሊስ አነጋግሯችሁ ነበር? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ ዛሬ የጠየቃቸው አንድ የተማሪዋ ቤተሰብ፣ ተጠርጣሪው መያዙንና ቀጣዩን ሂደት በተመለከተ ፓሊስ እንዳነጋገራቸው ተናግረዋል።
" የኢትዮጵያ ህዝብ በሙሉ እንባ ነው ያነባው፤ እኛ ቤተቦች ደግሞ ደም ነው ያለቀስነውና ወንጀሉን ፈጻሚው አካል በፈጸመው ወንጀል ልክ ተመሳሳይ የሆነ ፍርድ እንዲሰጠው እጠይቃለሁ " ሲሉም ቀጣዩ የፍርድ ሂደት ፍትሃዊ እንዲሆንላቸው ከወዲሁ አሳስበዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
" ያለ ስራ ስነምግባር በስራ ቦታ ባልተገባ መንገድ ሰራተኛን የደበደበ ቻይናዊን ጨምሮ በአራት ሰዎች ላይ እርምጃ ተወስዷል " - የሀዋሳ ኢንዱስትሪያል ፓርክ
➡️ " ልጁ ሕክምና ተደርጎለት በመልካም ጤንነት ላይ ይገኛል "
በሀዋሳ ኢንዱስትሪያል ፓርክ የሚሰሩ ሰራተኞች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ባደረሱት ቅሬታ በፓርኩ ውስጥ በተለያዩ ጊዜያት በውጭ ሀገራት ዜጎች አካላዊና ስነልቦናዊ ጥቃት እንደሚደርስባቸው ገልጸዋል።
ባሳለፍነው እሁድም በፓርኩ ውስጥ በሚገኝ 'ቶዮ ሶላር' በተባለ ኩባንያ አንድ ቻይናዊ አንድን ኢትዮጵያዊ ሲደበደበዉና ልጁም መሬት ላይ ወድቆ የሚያሳይ ቪዲዮም ልከዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያም ቪዲዮዉን ከተመለከተ በኋላ የቶዮ ሶላር ካምፓኒ ሰራተኞችንና አመራሮች እንዲሁም የሀዋሳ ኢንዱስትሪያል ፓርክ ሥራ አስኪያጅ ለማነጋገር ሞክሯል።
ሰራተኞች ምን አሉ ?
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የቶዮ ሶላር ካምፓኒ ሰራተኞች አግኝቶ ለማነጋገር ቢሞክርም ለደህንነታቸው ሲሉ ለጊዜዉ ያለውን ችግር ለማውራት እንዳልተመቻቸው ገልፀው በሌላ ጊዜ መረጃ እንደሚሰጡ ተናግረዋል።
በሌላ መልኩ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የቶዮ ሶላር ካምፓኒ አመራሮችን ለማግኘት ጥረት ቢያደርግም ስልክ ባለማንሳታቸው ለጊዜው አልተሳካም።
ነገር ግን በሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ የሚሰሩ ሌሎች ሰራተኞች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፥ " መብታችን ተረግጦ ነው እየሰራን ያለነው። የዚህ ልጅ ድብደባ በቪድዮ ወጣ እንጂ ሌሎችም ብዙ መሰል ነገር ያጋጥማቸዋል። ለሰው ኃይል ክፍል ሲከሱ ብር ይቀጧቸውና ወደ ስራ ነው የሚመልሷቸው " ብለዋል።
" አቤት የምንልበት አጥተናል ሰው እንዴት በሀገሩ እንዲህ ይደረጋል ? የምንሰራው አስራ ሁለት ሰዓት ነው። በዛ ላይ ክፍያው ልፋታችንን የሚመጥን አይደለም ለመኖር ነው የምንሰራው። እንደዛም ሆኖ ግን ክብር በሌለበት ነው የምንሰራው። ኢትዮጵያውያን ሰራተኞች ድብደባ፣ ስድብ ፣ ማንቋሸሽ ይደርስባቸዋል፤ የጉልበት ስራ እንደ አህያ እያሸከሙ ነው የሚያሰሩት " ሲሉ ገልጸዋል።
" ይሄን ነገር መንግሥት ያውቀዋል ? ከባድ ነገር ነው እየገጠመን ያለው፤ ድምጻችንን ስሙልን " ብለዋል።
ፓርኩ ምን ምላሽ ሰጠ ?
ቲክቫህ ኢትዮጵያ በኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የሀዋሳ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን ስራ አስኪያጅ አቶ ማቴዎስ አሸናፊን አግኝቶ አነጋግሯል።
አቶ ማቴዎስ ፤ " በፓርኩ በሚገኘዉ ቶዮ ሶላር ኩባንያ ውስጥ ተቀጥሮ በሚሰራ ኢትዮጵያዊ ሞያተኛ እና የውጪ ሀገር (ቻይናዊ) ዜግነት ባለው ሱፐር ቫይዘር መካከል በስራ ቦታቸዉ ላይ በተፈጠረ አለመግባባት የተስተዋለው ጠብና ድብድብ ፍፁም ከስራ መርህ ውጭ የሆነና የፓርኩን መተዳደሪያ ደንብ የሚፃረር ነው ፤ የሚወገዝም ተግባር ነው " ብለዋል።
ፓርኩ ከኢትዮጵያ ኢንዱትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ጋር በመሆን አስፈላጊውን ማጣራት አድርጎ በሂደቱ ውሰጥ ቀጥተኛ ተሳትፎ የነበራቸውን ሁለት የውጪ ዜጎች ከስራ እንዲባረሩና #ከሀገር_እንዲወጡ እንዲሁም በካምፓኒዉ ውስጥ ያሉ በጉዳዩ ቀጥተኛ ተሳታፊ ያልሆኑ ሶስት አመራሮች ደግሞ ከባድ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ እንዲደርሳቸው መደረጉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስታውቀዋል።
ከዚህ ባለፈ ፥ ካምፓኒው ጉዳዩ በቪዲዮ ከተላለፈው በዘለለ በሰራተኛውና በቅርብ አለቃው መካከል ለተስተዋለው ግጭት መነሻ የነበሩ ምክንያቶችን በመዘርዘር ሁለቱም የተጋጩበትን መንገድ ፤ ኢትዮጵያዊውም የነበረውን ጥፋቶች በመዘርዘር ከስራ እንዲባረር ወስኖ የነበረ ሲሆን ፓርኩ ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ወደ ስራ እንዲመለስ መወሰኑን ተናግረዋል።
ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ በማህበራዊ ሚዲያዎች የሚዘዋወሩ መረጃዎች መበራከታቸውን በመግለፅ " ልጁ ሞቷል፣ አጥንቱ ተሰብሯል " የሚሉና መሰል መረጃዎች የተሳሳቱ መሆናቸውን ገልጸዋል።
" ልጁ ሕክምና ተደርጎለት በመልካም ጤንነት ላይ ይገኛል " ሲሉ አክለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHawssa
@tikvahethiopia
#Tecno_Spark_40_Pro+
አዲሱ የTecno Spark 40 Pro+ ሁለት የ Dolby Atmos የድምፅ ቴክኖሎጂ የተገጠመላቸው ስፒከሮች ያሉት ሲሆን ሙዚቃ ለመስማት፣ ማህበራዊ ሚዲያ ለመጠቀም፣ ፊልም ለማየት እንዲሁም ኩልል ያለ ጥራት ያለው ድምፅ የሚሰጥ በመሆኑ ስፒከሩ ተመስክሮለታል!!
#Spark40Pro+ #SlimeverStrongForever #TecnoAI #TecnoSpark40Series
@tecno_et
" አሁን ላይ በየሆቴሉ የሚሰሩ ሴት አስተናጋጆች ምሽት ሲሆን በማናጀራቸው አማካኝነት ሰውነታቸውን የሚያሳይ ወይም አጫጭር ልብስ እንዲለብሱ እየተደረጉ ነው፣ በየቀኑ ብዙ ስልክ እየተደወለልኝ ነው " - የኢትዮጵያ መስተንግዶ ባለሙያዎች ማህበር
የኢትዮጵያ መስተንግዶ ባለሙያዎች ማህበር በባለፈው አመት የአዲስ አበባ ከተማ ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ በሆቴልና መሰል ተቋማት ለሚሰሩ አስተናጋጆች ያዘጋጀው የአለባበስ ደንብ በአግባቡ ተፈጻሚ እየሆነ አለመሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።
የማህበሩ መስራችና ፕሬዝዳንት አቶ ያሬድ ደገፉ " ደንቡ ተግባራዊ ቢደረግም አሁን ላይ በየሆቴሉ የሚሰሩ ሴት አስተናጋጆች ምሽት ሲሆን በማናጀራቸው አማካኝነት ሰውነታቸውን የሚያሳይ ወይም አጫጭር ልብስ እንዲለብሱ እየተደረጉ ነው፣ በየቀኑ ብዙ ስልክ እየተደወለልኝ ነው " ብለዋል።
አቶ ያሬድ ደገፉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በዝርዝር ምን አሉ ?
" ማህበሩ ከተቋቋመ ሶስት አመት ሆኖታል፣ 480 የሚሆኑ አባላቶችም አሉን፣ ሁሉም የመስተንግዶ ባለሙያዎች ናቸው።
በባለፈው አመት በሆቴል እና መሰል አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ለሚሰሩ አስተናጋጆች የአለባበስ ደንብ ወጥቶ ነበር።
ይህንን ደንብ ለማስፈጸም ከፀጥታ ተቋማት፣ ከደንብ ማስከበር ባለስልጣን፣ ከፍትህ ሚኒስቴር እና ከሚመለከታቸው የመንግስት ተቋማት ጋር በመሆን የአፈጻጸም ደንብ አዘጋጅተን ጸድቆ ተግባራዊ ተደርጓል። ይህን በሃላፊነት ሊሰራ የሚችለው ተቋም ቱሪዝም ኮሚሽን ነው።
እስካሁን ድረስ በወረዳ እና በክፍለ ከተማ ላይ ደንቡን የሚያስፈጽሙ አካላቶች ነበሩ ፣ አሁን ላይ ግን ይህ የለም፣ ቁጥጥር የሚያደርግም የለም። ቱሪዝም ኮሚሽን እየተቋቋመ ያለው በከተማ ደረጃ ነው። ይህ ደግሞ ለሰራተኞችም፣ ለማህበራችንም አስጊ ነው።
በአንዳንድ ሆቴሎች ላይ በሴት አባላቶቻችን ላይ እየተደረገ ያለው ምሽት 12 ስአት ሲሆን ' እየመሸ ስለሆነ ምን ችግር አለው አጭር ቀሚስ ልበሱ ' እያሏቸው ነው የሆቴል ማናጀሮች፣ ይህ ደግሞ መብታቸውን ይጋፋል። አስተናጋጆችም መብታችንን ለማስጠበቅ የወጣው ደንብ በአግባቡ ተግባራዊ ይደረግልን እያሉ ለማህበራችን ጥያቄ እያቀረቡልን ነው " ብለዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ቱሪዝም ኮሚሽን ኮሚሽነር ሁንዴ ከበደ በጉዳዩ ላይ ምን አሉ ?
" የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር አንዱ ከሰራቸው ትልቅ ስራዎች የሆቴል ሰራተኞች ወይም አስተናጋጆች የአለባበስ ኮድ አዋጅ ማዘጋጀት ነው። ይህ አዋጅ በጣም ጥሩ ነው፣ በተለይም የሀገራችንን ባህል እና አገልግሎታችንን ከማስጠበቅ አንፃር ትልቅ ሚና አለው። አዋጁ ተፈጻሚነት እንዲኖረው እስከታች ድረስ ወርዷል።
ከዚህ በፊት በየወረዳው የኛ ቡድን ነበረ፣ አሁን ላይ ደግሞ በወረዳ ደረጃ ያለው መዋቅር ስለታጠፈ ከአለባበስ ጋር ያሉ ጉዳዮችን መቆጣጠር አልቻልንም። ነገር ግን በየወረዳው ካሉ ደንብ ማስከበር ጋር በአለባበስ ዙሪያ ውይይት አድርገናል። ችግሮች አልፈው አልፈው ይኖራሉ፣ እንደዚህ ያሉ ጉዳዮችን ለመቅረፍ ከሌሎች አካላቶች ጋር በመሆን በቅንጅት መስራት ያስፈልጋል። ህጉን የሚጥስ አካልም በህግ ይጠየቃል።
ከዚህ በሗላ ህግ ወጥቶለታል፣ አሰራርም አለው፣ ህጉን ለማስከበር ደግሞ ከከተማ ደንቦች ጋር እየተነጋገርን ነው። ስራውንም ለእነሱ አሳልፈን የምንስጥበት እና እየተከታተሉ የሚያስፈጽሙበት ሁኔታ ይኖራል። በተለይ አሁን ላይ መዋቅሩን ስንሰራ አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ላይ ሰፊ እና አድካሚ ስራ ተሰርቷል፣ ከላይ ያሉ ባለሙያዎች እስከታች ድረስ ወርደው እየተነሱ ያሉ ችግሮችን እንዲያዩ እየተደረገ ነው። " ብለዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ በባለፈው አመት ያወጣው ደንብ በውስጡ የሰራተኛ አለባበስ የማያስተካክሉ አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ላይ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ፣ ከ1 እስከ 50ሺህ ብር የሚያስቀጣ እና የብቃት ማረጋገጫ ፈቃድን እስከማገድ የሚደርስ ቅጣት እንደተካተተበት መገለፁ ይታወሳል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
" በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ አምስት ኢትዮጵያዊያን ተገድለዋል" - ኢትዮጵያዊያን ከደቡብ አፍሪካ
ከሰሞኑ ሁለት ጓደኛሞችን ጨምሮ አምስት ኢትዮጵያዊያን በደቡብ አፍሪካ የተለያዩ ከተሞች በተሰነዘረባቸው ጥቃት ሕይወታቸዉ ማለፉን በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
ነዋሪዎቹ እንደሚሉት በተለያዩ ጊዜያት ኢትዮጵያውያንን ያነጣጠረ ጥቃት በታጠቁ ሰዎች ተደጋጋሚ እንደሚፈፀም ተናግረዉ ይህም የበርካታ ኢትዮጵያዊን ሕይወት መቅጠፉን ገልፀዋል።
ለደህንነታቸዉ ሲሉ ማንነታቸዉን እንዲገለፅ ያልፈለጉ በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደገለፁት ከሁለት ቀናት በፊት በደቡብ አፍሪካ ደርባን ከተማ 2 ኢትዮጵያዊያን ጓደኛማቾች ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች መገደላቸዉን ተናግረዋል።
በተመሳሳይ መልኩ የጆሀንስበርግ ከተማ ነዋሪ የሆነ የሶስት ልጆች አባት ከስራ ወደቤቱ በሚመለስበት ወቅት በታጠቁ ሰዎች በበርካታ ጥይት ተደብድቦ መገደሉን አስረድተዋል።
በሌላ መልኩ አንድን ወጣትና ሌላ ታዳጊ በዚሁ በጁሀንስበርግ ከተማ አቅራቢያ በስራ ቦታ ሱቅ ዉስጥ እያሉ በጠራራ ፀሐይ በታጠቁ ሰዎች በጥይት ተደብድበው ተገድለዋል ሲሉ ገልጸዋል።
በሀገሪቱ በኢትዮጵያዊያን ላይ ተደጋጋሚ ጥቃት የሚፈፀም ቢሆንም በፈረንጆች አዲስ ዓመት ዋዜማ ጎልቶ ይስተዋላል ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ በጉዳዩ ዙሪያ ያነጋገራቸው በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ አመራሮች መከካል የሆኑ አንድ ስማቸው እንዳይገለፅ ያልፈለሁ የመረጃ ምንጭ በተለያዩ ጊዜያት በኢትዮጵያውያን ላይ የሚፈፀመው ጥቃት የበርካቶችን ሕይወት እየቀጠፈ መቆየቱን ተናግረዉ ከላይ በሟቾች ቁጥር ጉዳይ ግን መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa
@tikvahethiopia
#UK🇬🇧
በዩናይትድ ኪንግደም (UK) የጥገኝነት ጥያቄያቸው ተቀባይነት ያገኘ ስደተኞች በአገሪቱ በቋሚነት እንዳይቆዩ እንደሚደረግ ተገለጸ።
ይህ ጉልህ የፖሊሲ ለውጥ የፊታችን ሰኞ በአገር ውስጥ ሚኒስቴሯ ሻባና መሕሙድ በኩል በምክር ቤት ይፋ እንደሚደረግ ቢቢሲ ዘግቧል።
በፖሊሲው መሠረት፤ ጥገኝነት ያገኙ ስደተኞች በዩኬ ለተወሰነ ጊዜ ብቻ የሚቆዩ ይሆናል።
ዩኬ ጥገኝነት ጠያቂዎችን በዘላቂነት የምታኖርበት አሠራር ሊለወጥ እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን፤ የፖሊሲ ለውጥ የተደረገው በጀልባ የሚገቡ ስደተኞችን ቁጥር ለመቀነስ ነው ተብሏል።
የጥገኝነት ጥያቄያቸው ተቀባይነት ያገኘ ሰዎች " አገራቸው መመለስ አስጊ አይደለም " ተብሎ በሚታመንበት ወቅት ላይ ወደ አገራቸው እንደሚመለሱ ይደረጋል።
አሁን ላይ ዩኬ ለጥገኝነት ጠያቂዎች የአምስት ዓመት የቆይታ ጊዜ ትፈቅዳለች። ከዚያም ስደተኞች በዩኬ በዘላቂነት ለመቀጠል ማመልከት ይችላሉ።
ፖሊሲው የተወሰደው ከዴንማርክ እንደሆነ ተነግሯል።
የዴንማርክ ግራ ዘመም ሶሻል ዴሞክራት መንግሥት በአውሮፓ ጠንካራውን የስደተኞች ፖሊሲ በመተግበር ይታወቃል።
ጥገኝነት ጠያቂዎች የሁለት ዓመት የመኖሪያ ፈቃድ ከተሰጣቸው በኋላ በድጋሚ ማመልከት አለባቸው። ዜግነት ለማግኘት ያለው ሒደት ግን ከጊዜ ወደ ጊዜ ፈታኝ እየሆነ መጥቷል።
የዴንማርክን አሠራር ያደነቁት የዩኬ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር፤ " በምርጫ ወቅት የተሻለ የሕዝብ ድምጽ ያስገኘ አካሄድ ነው " ሲሉ አሞካሽተውታል።
የዩኬ ሌበር ፓርቲ ጠንካራ እርምጃ ካልወሰደ " የጨለማ ኃይሎች ይወርሱናል " ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
ዴንማርክ ስደተኞች ቤተሰቦቻቸውን የሚወስዱበትን ሒደት በማራዘም የምትታወቅ ሲሆን፤ ይህ አሠራርም በአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትሯ ተወድሷል።
ዩኬ ለስደተኞች ያላት መልካም አቀባበል በጀልባ ወደ አገሪቱ የሚገቡ ጥገኝነት ጠያቂዎች ቁጥር እንዲጨምር ማድረጉን ገልጸዋል።
ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የቢቢሲ ነው።
@tikvahethiopia
#Afar
ዛሬ 10ኛ የኢትዮጵያ ከተሞች ፎረም የመክፈቻ መርሃ ግብር በአፋር ክልል ሠመራ ሎጊያ ከተማ ዛሬ እየተካሄደ ይገኛል።
በመርሃ ግብሩ መክፈቻ ወቅት ፦
- የአፋር ክልል ፕሬዚዳንት ሐጂ አወል አርባ፣
- የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ፣
- የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል፣
- የብልጽግና ፓርቲ ም/ፕሬዜዳንት አቶ አደም ፋራህ፣
- የሠመራ ሎጊያ ከተማ ከንቲባ አቶ አብዱ ሙሳ፣
- የአፋር እና ጅቡቲ ባህል ቡድን ማዕከል እንዲሁም ሌሎች ባለስልጣናትና እንግዶችና በርካታ ነዋሪዎች ተገኝተው ነበር።
የሠመራ ሎጊያ ከተማ ከንቲባ አቶ አብዱ ሙሳ፤ በከተማዋ በርካታ የልማት ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነና ስራው በዚህ አመትም እንደሚቀጥል ጠቁመዋል።
" ሠመራ ከተማ በ10ኛው የኢትዮጵያ ከተሞች ፎረም ራሷን ለማሰለፍ አምራና ተውባ ለገበያ ወጥታለች " ሲሉ ለአልሚ ባለሃብቶች መልዕክት አስተላልፈዋል።
የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ወ/ሮ ጫልቲ ሳኒ፣ ከተሞችን የማስፋፋት ስራ እየተሰራ መሆኑን አንስተው፣ " ዛሬ እዚህ የተገኘነው ከተሞችን ለመገንባትና የከተሞችን የወደፊት እጣ ፋንታ ለመወሰን ነው " ብለዋል።
የኢትዮጵያ ከተሞች ፎረም የከተሞች የእርስ በእርስ ቅርርብ የሚደረግበት መሆኑን አስረድተው፣ " ከተሞችን የብልጽግና ማዕከላት ለማድረግ ጥረት እየተደረገ ይገኛል " ሲሉም ተደምጠዋል።
ነዋሪውን የቤት ባለቤት ለማድረግ፣ አለም አቀፍ ተወዳዳሪ የሆኑ ከተሞችን ለማስፋፋት እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።
የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዜዳንት አቶ አደም ፋራህ በበኩላቸው፣ " ከደረጃ በታች ያሉ ቤቶችን ማሻሻል ያስፈልጋል " ሲሉ ተደምጠዋል።
የአፋር ክልል ፕሬዜዳንት ሐጂ አወል አርባ በበኩላቸው፣ " የኛ ጥያቄ የሕዝባችን የልማት ጥያቄ ነው " በማለት ተናግረዋል። በዚህም " ሰፋፊ የልማት ሥራዎችን መስራት ተችሏል " ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አፋር
ሠመራ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
ዳሸን ባንክ !
ዳሸን ባንክ እስከ 30 ሚሊዮን ብር ሽልማት ያለውን የ"ዳሸን ዕድል" ጨዋታ ይፋ አደረገ
ዳሸን ባንክ በዳሸን ሱፐር አፕ ላይ ብቻ የሚገኝ አዲስ የዲጂታል ሽልማት እና የጨዋታ ተሞክሮ የሆነውን ዳሸን እድልን በይፋ መጀመሩን አሳወቀ።
ይህበአይነቱ ልዩ የሆነው የሱፐር አፕ እድል እስከ 30 ሚሊዮን ብር የሚደርስ ጠቅላላ የሽልማት ገንዘብ ያለው ሲሆን፣ ይህም የዳሸን ሱፐር አፕ ተጠቃሚዎች የባንኩን ዘመናዊ ዲጂታል አገልግሎቶች በመጠቀም አስደሳች ሽልማቶችን የማግኘት ልዩ እድል የሚሰጣቸው ነው።
የዳሸን ዕድል ሎተሪ ደንበኞች እንዲሳተፉ እና እንዲያሸንፉ በአርኪ መንገድ የቀረበ ጨዋታ ነው፡፡ የዳሸን ሱፐር አፕ ተጠቃሚዎች በዕለት ተዕለት በሚያደርጓቸው ዲጂታል ግብይቶች፣ (ማለትም የገንዘብ ዝውውሮችን በማድረግ፣ ሱፐር አፕን በማውረድ እና በመጠቀም፣ ከሌሎች ባንኮች ገንዘብ በመቀበል፣ የንግድ ክፍያዎችን በመፈፀም፣ የአየር ሰዓት በመሙላት እንዲሁም ሌሎች በመተግበሪያው ውስጥ የሚገኙትን የቻት ባንኪንግና የበጀት አገልግሎቶችን) እና ሌሎች አገልግሎቶችን በመጠቀም በቀላሉ "ሳንቲሞችን" መሰብሰብ ይችላሉ፡፡
ደንበኞች ከዚያም የሰበሰቡትን ሳንቲሞች በመጠቀም ስልኮቻቸውን "በማወዛወዝ" እና ከሞባይል ዳታ ፓኬጆች አንስቶ ከ100 ብር እስከ 100,000 ብር የሚደርሱ የኤሌክትሮኒክስ የገንዘብ (e-money) ሽልማቶችን፣ ሳምሰንግ ጋላክሲ ኤስ 23 እና ኤ 54፣ አይፎን 16 ሞዴል ስልኮችን እንዲሁም አዲስ የቢዋይዲ መኪና ሽልማቶችን ማሸነፍ ይችላሉ።
ከጥቅምት 22 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ዳሸን ባንክ በዳሸን ዕድል የማስተዋወቅ ዘመቻው በሺዎች የሚቆጠሩ ሽልማቶችን ለአሸናፊዎች መስጠት ጀምሯል። ይህ የማስተዋወቅ ዘመቻ የዳሸንን ደንበኞች ለመሸለም ብቻ የቀረበ ሳይሆን ደንበኞች በዳሸን ሱፐር መተግበሪያ ላይ የቀረቡትን በርካታ የአገልግሎት አይነቶች እንዲጠቀሙ ለማነሳሳት የተነደፈ ነው።
ዛሬውኑ ይህን አስደሳች ጨዋታ ይቀላቀሉ!
የዳሸን ሱፐር መተግበሪያን ያውርዱ፣ ሳንቲሞችን ማግኘት ይጀምሩ፣ እና በዳሸን ባንክ የዲጂታል ባንክ ሕይወትን የሚቀይሩ ሽልማቶችን ለማሸነፍ እድልዎን ይጠቀሙ።
የዳሸን ባንክ ሱፐር አፕ መተግበሪያ ያውርዱ 👇 https://www.dashensuperapp.com/download
#MoE
በዛሬው እለት የህዝብ ተወካዮች የሰው ሃብት ልማት ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የትምህርት ዘርፉን የ1ኛ ሩብ ዓመት ሥራ አፈፃፀም ተመልክቶ ነበር።
በዚሁ ጊዜ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በከፍተኛ ትምህር ተቋማት የክብር ዶክትሬት አሰጣጥን በተመለከተ ችግር የነበረበት በመሆኑ ወጥ አሰራር መከተል በማስፈለጉ የክብር ዶክትሬት አሰጣጥን ሀገራዊ መመሪያ ተዘጋጅቶ ለትግበራ ዝግጁ መሆኑን ገልፀዋል።
ሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋም በመመሪያው መሰረት ተፈፃሚ ማድረግ ያለባቸው ሲሆን የክብር ዶክትሬት ማዕረግ የሚያገኙ ሰዎች ዶክተር ወይንም የክብር ዶክተር በሚል መጠሪያነት መጠቀም እንደማይቻል አሳስበዋል።
የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የክብር ዶክትሬት ማዕረግ ለመስጠት ሀገራዊ እና አለም አቀፍ መስፈርቶችን ማሟላት እንዳለባቸው በመመሪያ መመላከቱን አንስተዋል።
በሙያው የተለየ ስራ ያበረከተ ኢትዮጵያዊም ሆነ ሌላ ዜጋ በመመሪያው የተዘረዘረውን መስፈርት የሚያሟላ ከሆነ የክብር ዶክትሬት ማዓረግ ማግኘት እንደሚችል ጠቅሰዋል። ይሁን እንጂ የተሠጠውን የክብር ዶክትሬት ለመጠሪያነት መጠቀም እንደማይቻል አብራርተዋል።
ትምህርት ሚኒስቴር የክብር ዶክትሬት መስጠት የሚችሉ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን በተመለከተ እንዲሁም የክብር ዶክትሬት የተሰጠው ግለሰብ ዶክተር፣ የክብር ዶክተር እና መሰል መጠሪያዎችን በየትኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት መጠቀም እንደማይችል መመሪያ አዘጋጅቶ ለሚመለከታቸው መላኩ ይታወቃል።
#MoE
@tikvahethiopia
በታጣቂዎች የሚገደሉት በመንግስት የፀጥታ ሀይሎች ደግሞ ታፍሰው የሚታሰሩበት አሳሳባቢው የአማራ ክልል የጤና ባለሙያዎች ጉዳይ !
የአማራ ክልል የጤና ባለሙያዎች ማህበር ፀሀፊ አቶ ተስፋ መኮነን በክልሉ ባሉ የጤና ባለሙያዎች ላይ በመንግስትም በታጣቂዎችም እየደረሰ ያለው ግድያ፣ እስር አስመልክተው ሰፋ ያለ ማብራሪያ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ሰጥተዋል።
አቶ ተስፋ ምን ምን አሉ ?
" በያዝነው ሳምንት ብቻ 2 የጤና ባለሙያዎች ተገድለዋል።
አንዷ ቤተልሄም አዲስ የምትባል በምዕራብ ጎጃም ዞን በደንበጫ ጤና ጣቢያ በስራ ላይ እያለች ጥቅምት 29/2018 ዓ.ም በታጣቂዎች ተገድላለች።
ባለፈው ጥቅምት 19/2018ዓ.ም በምዕራብ ጎንደር ዞን ገንደ ውሃ ሆስፒታል የሚሰራ ዶ/ር ዳንኤል ነጋ የተባለ የአይን ስፔሻሊስት በታጣቂዎች ታግቶ ገንዘብ እንደተጠየቀበት ሰምተን ነበር ህዳር 1/2018ዓ.ም መገደሉን ሰምተናል።
ይህ የአንድ ሳምንት አሳዛኝ ክስተት ነው።
ሌላው በምስራቅ ጎጃም ዞን ስናን ወረዳ አርብ ገበያ በተባለ ከተማ ውድነህ አንዳርጋቸው የተባለ ነርስ ባለፈው መስከረም ወር 2018 ዓ.ም በታጣቂዎች መገደሉን መረጃ ደርሶኛል።
ሌላው ደግሞ፥ ከጥቅምት 23 እስከ 27 ድረስ 5 የጤና ባለሙያዎች በመንግስት የፀጥታ ኃይሎች ተይዘው 8ተኛ ፖሊስ ጣቢያ ይገኛሉ።
የዋስትና መብት ተሰጥቷቸው ከእስር እንዲለቀቁ ቤተሰቦቻቸው ቢጠይቁም የሰማቸው አልነበረም። ከሳምንት በኃላም የዋስ መብታቸው ተጠብቆ እላንት ህዳር 3/2018ዓ.ም 4ቱ ዶክተሮች ሲለቀቁ አንዱ ነርስ ግን እስካሁን አልተፈታም።
ታስረው የነበሩ የጤና ባለሙያዎች ስም፦
1. ዶ/ር መኩ ዳምጤ የአዲናስ ጠቅላላ ሆስፒታል ስራ አስኪያጅና እውቅ የቀዶ ህክምና ባለሙያ
2. ዶ/ር ስመኘው ዘላለም የጠቅላላ ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት
3. ዶ/ር ዳምጤ ዘውዴ የጥበበ ግዮን የነርቭ እና የጭንቅላት ቀዶ ህክምና ስፐሻሊስት
4. ዶ/ስመኘው ተስፋ ከአሜን ሆስፒታል የቀዶህክምና ባለሙያ
5, ታደሰ ዳቤ ነርስ ከአሜን ሆስፒታል አሁን ያልተፈታ
እነዚህ በቅርቡ የተከሰቱ ግድያዎችና አፈሳዎች ናቸው።
እኔም በመንግስት የፀጥታ ኃይሎች ተይዤ ታስሬ ነበር። ባለቤቴ ደግሞ ለዘረፋ በተደራጁ ታጣቂዎች ተይዛ ገንዘብ ከፍለን ነው ያስለቀቅናት።
ነገሩ እንዲህ ነበር ጥቅምት 5/2018 ዓ.ም ሆምላንድ በተባለ ሆቴል ከ5 ባለደረቦቼ ጋር ስብሰባ አምሽተን ስንወጣ ፖሊሶች መጥተው ያዙን ከዚያም 4ተኛ ፖሊስ ጣቢያ ወስደው አሰሩን። ምን አደረግን ? ብለን ጠየቅናቸው ' ስልጣናችሁን ያለ አግባብ ተጠቅማችኃል ' አሉን የቱን ስልጣን ? እኛኮ የጤና ባለሙያዎች ነን የምንሰራውም በማህበሩ ውስጥና ጤና ቢሮ ነው አልናቸው ሁለት ቀን በእስር ካቆዩን በኃላ የወሰዱን ፖሊሶች በመጥፋታቸው ይቅርታ ብለው ሌሎች ለቀቁን።
እንደገና ሰኔ 25/2017 ዓ.ም ባለቤቴን ጨምሮ 3 ነርሶች ከፈለገ ህይወት ስፒሻላይዝድ ሆስፒታል አምሽተው በሰርቪስ ወደ ቤታቸው ሲሂዱ ከምሽቱ 2:00 ላይ ታጣቂዎች ከመኪና አስወርደው አግተው ወሰዷቸው። በብዙ ድርድር ብር ከፍለን ነው ያስለቀቅናቸው።
ይህ ጥቃት የሆነው በክልሉ ርዕሰ መዲና ባህር ዳር ነው በወረዳና በዞኖች ላይ ደግሞ በጣም የከፋ እንደሆነ መረጃ ይደርሰናል ግን ለማን አቤት እንደሚባል ግራ ገብቶናል " ብለዋል።
በአማራ ክልል በጤና ባለሙያዎች ላይ እየተፈጸመ ያለው ግድያና አፈና ምን አስከትሏል ?
አቶ ተስፋ መኮነን እንደሚሉት ባለፈው አመት የጥበበ ጊዮን ስፔሻላይዝ ሆስፒታል የቀዶ ጥገና ህክምና ክፍል ዳይሬክተር የነበሩት ዶ/ር አንዱአለም ዳኜ በክልሉ ርዕሰ መዲና ባህር ዳር ጥር 24/2017 ዓ.ም ከስራ አምሽተው ወደ ቤታቸው በመጏዝ ላይ እያሉ በዘራፌዎች ከተገደሉ በኃላ ከ30 እስከ 40 የሚሆኑ እውቅ የጤና ባለሙያዎች ክልሉን ለቀው ወደ መሀል ከተማ ሂደዋል።
ሰሞኑን በተከሰተው ግድያና እስራትም ብዙ የጤና ባለሙያዎች ክልሉን ለመልቀቅ አኮብኩበዋል።
በዚህም በህክምና እጥረት ህዝቡ እየተሰቃየ ነው። ሆስፒታሎችም የባለሙያ ያለህ እያሉ ነው።
" ሀኪሙስ የትም ቦታ ተዘዋውሮ ሰላም ያለበት ሀገር ሄዶ ተቀጥሮ ይሰራል ህዝቡ የት ይሄዳል ? " ሲሉም ይጠይቃሉ።
" በተለይ በአሁኑ ሰዓት እየተሰቃየ ያለው የገጠሩ ማህበረሰብ ነው ከተሜውስ በአውሮፕላን ተሳፍሮ ሄዶ ታክሞ እየመጣ ነው " ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
ጥቃት አድራሾቹ እነማን ናቸው ?
" እስርን በተመለከተ የመንግሰት የጸጥታ ኃይሎች ናቸው፤ ምክንያታቸው ደግሞ ' ታጣቂዎችን ታክማላችሁ ' በሚል ነው።
ታጣቂዎቹ ደግሞ 'ለብልፅግና ታግዛላችሁ' ነው የሚሉት እንደሚታወቀው ህክምና ሰብዓዊ አገልግሎት የሚሰጥበት ነው ሀኪም ዘርን፤ ቀለምን፤ ሀይማኖትን እንዲሁም ብሄርን ሳይለይ አገልግሎት እዲሰጥ ነው ቃል የገባው ይህንን መንግስትም ታጣቂዎችም መረዳት አለባቸው።
ከሁለቱ ውጭ ያለው ደግሞ የታጠቀ ዘራፈ ቡድን ነው እነዚህን ለህዝብ ቁመናል የሚሉ ሁለቱ ኃይሎች ተባብረው ማጥፋት አለባቸው። "
ማህበሩ ምን እያደረገ ነው ?
" የአማራ የጤና ባለሙያዎች ማህበር ከአማራ የግል ጤና ድርጅቶች ማህበር ጋር በመሆን በጤና ባለሙያው ላይ እየደረሰ ያለው አፈናና ግድያ ይቁም! ህግ ይከበር! ቤተሰቦቻችን የህክምና አገልግሎት ያግኙ ! የሚል ደብዳቤ በመያዘ፦
-ለአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ፅ/ቤት
-ለአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን
- ለአማራ ክልል አስተዳደርና ፀጥታ ቢሮ አስገብተናል።
ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትንም ለማነጋገር እየጣርን ነው። በቀጣይም ለሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ድምፃችን እናሰማለን " ብለዋል።
ሰሞኑን እንደገና ባገረሸው የሙያ አጋሮቻቸው ግድያና እስር ምን ይላሉ ?
በምዕራብ ጎንደር ዞን ገንዳውሃ ከተማ የገንዳዋ አጠቃላይ ሆስፒታል ሀኪም የሆነውና ስሙ እንዳይጠቀስ የጠየቀን አንድ የጤና ባለሙያ ስራውን እና ከተማውን ለመልቀቅ በዝግጅት ላይ መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግሯል።
ይህው የመረጃ ምንጫችን በገንዳዋ አጠቃላይ ሆስፒታል ይሰራ የነበረው እና ሰሞኑን በታጣቂዎች ታግቶ ተወስዶ የቤዛ ገንዘብ የተጠየቀበትና ኃላም ተገሎ ተጥሎ ስለተገኘው ዶ/ር ዳንኤል ነጋ እንዲህ ሲል ተናግሯል።
" ዶ/ር ዳንኤልን የማውቀው ከ2015ዓ.ም ጀምሮ ነው በጣም ስነ ምግባር ያለውና ሙያውን የሚወድ ህመምተኞችን አክባሪ ነው።
ዶክተር ባለትዳርና የአንዲት ሴት ልጅ አባትም ነበር።
ባለፈው ጥቅምት 19/2018ዓ.ም በሆስፒታሉ አቅራቢያ ባለ አንድ ምግብ ቤት እራት እየበላ እያለ ነው ከብዙ ሰዎች መካከል ታጣቂዎች እሱን መርጠው አስነስተው ይዘውት የሄዱት ከዚያም 5 ሚልየን ብር እንዲከፈላቸው ጠየቁ።
ብሩን ማሰባሰብ ተጀምሮ ነበር ቤተሰቦቹ 600 ሺህ ብር ለአጋቾቹ እንደከፈሉ ሰማን ግን ብሩን ከመክፈላቸው በፊት ነው ልጁን ገድለው የጣሉት አስከሬኑ ሲገኝ ያመላከተውም ይህንን ነው። "
ከዶክተሩ እገታ ጋር በተያያዘ እርሱን ጨምሮ 6 የጤና ባለሙያዎች ከጥቅምት 21 እስከ 27 /2018 ዓ.ም ማለትም ለ6 ቀናት ታስረው እንደነበር ይህው የመረጃ ምንጫችን ነግሮናል።
ከሀኪሞች በተጨማሪም 7 በምግብ ቤቱ አቅራቢያ የሚኖሩ ሰዎች ታስረዋል ብሏል።
የመረጃ ምንጫችን በመተማ ሆስፒታል ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ 5 የጤና ባለሙያዎች ታግተው የተገደሉ ሲሆን 4 የጤና ባለሙያውች ደግሞ ብር ተዋጥቶ ተከፍሎላቸው መለቀቃቸውን ተናግሯል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ባሕር ዳር
@tikvahethiopia
#ፍርድ⚖️
የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ የግድያና የከባድ ውንብድና ወንጀል ችሎት የአባተ አበበን ገዳይ ተስፋዬ ሆርዶፋ ላይ የ20 ዓመት ፅኑ እስራት ፍርድ አስተላልፏል።
አባተ አበበ ታህሳስ 7 ቀን 2016 ዓ/ም ምሽት አዲስ አበባ ቦሌ ኤድና ሞል ወረድ ብሎ በሚገኝ አንድ የመዝናኛ ስፍራ አካባቢቢ በጥይት ተመቶ መገደሉ ይታወሳል።
@tikvahethiopia
" 753 ሺሕ 000 ብር ወዴት ገባ ? " - የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ዳር ፓሊ ካምፓስ ተማሪዎች
➡️ " አንዳንድ ተማሪዎች የመረጃ እጥረት ስለነበረባቸው ካፌ እየገቡ ልነበረም። ለዚህ ግቢው ተጠያቂ አይደለም" - የካምፓሱ ተማሪዎች ኀብረት
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፓሊ ካምፓስ ተማሪዎች ከኪሳቸው አውጥተው ከግቢው ካፌ ውጭ የተመገቡበት የአምስት ቀናት ገንዘብ በትክክል እንዳልተከፈላቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
ከጥቅምት 7 እስከ 11 2018 ዓ/ም ድረስ የካፌ አገልግሎት እንደተቋረጠ በማስታወቂያ እንደተነገራቸው ያስረዳው አንድ የግቢ ተማሪ፣ "ጥቅምት 11 ቀን 2018 ዓ/ም ከሰዓት የካፌ አገልግሎት አልተቋረጠም ተባለ። እኛ ግን ለ5 ቀናት የካፌ አገልግሎት እንደተቋረጠ ነው የምናውቀው። አንድ ተማሪ ለ5 ቀን ካፌ አልገባም ማለት በቀን 100 ብር ሲታሰብ በአምስተኛው ቀን 500 ብር ይጠብቃል" ብሏል።
ሌሎች ተማሪዎች በበኩላቸው ይህንኑ ሀሳብ ተጋርተው፣ አጠቃላይ የነን ካፌ ተማሪዎች ቁጥር "1,506" እንደሆነ፣ በዚህም አንድ ተማሪ 500 ብር ሲደመደብ፣ ድምሩ 753 ሺሕ ብር እንደሚሆን በመግለጽ፣ "ይሄ 753 ሺሕ ብር ወዴት ገባ?" ሲሉ ጠይቀዋል።
የፓሊ ካምፓስ ተማሪዎች ኀብረት ፕሬዚዳንት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን መለሰ ?
በዩኒቨርሲቲው የፓሊ ካምፓስ ተማሪዎች ፕሬዚዳንት ቃለዓብ ሰሙንጉስ፣ " እውነት ለመናገር በቀን 7 የተለጠፈ ማስታወቂያ ነበር። በማግስቱ ግን ተማሪዎች 'ብራችን እየገባ አይደለም ካፌ መግባት አለብን' አሉ። የግቢው ኃላፊዎች ተነጋግረው አስገቧቸው " ብሏል።
" ከዚያን ቀን ጀምሮ እንደገና መግባት ትችላላችሁ ተብሎ ማስታወቂያ ተለጠፈ፥ ግን ተማሪው መረጃ እጥረት ነበረበት ሁለተኛ የተለጠፈውን አላዩትም፥ ያዩት ግን ገብተው ካፌ ሲመገቡ ነበር፤ አንዳንድ ተማሪዎች የመረጃ እጥረት ስለነበረባቸው ካፌ እየገቡ አልነበረም። ለዚህ ደግሞ ግቢው ተጠያቂ አይደለም " ሲል አክሏል።
ሲጀመር ለምን ብሩ በወቅቱ አልተላከላቸውም ? ገብተው የተመገቡትስ በቀን ስንት ነው ? የመረጃ እጥረት ካለስ ማሳወቅ የእናንተ ፋንታ አይደለም ወይ ? ስንል ላቀረብነው ጥያቄም፥ " ብሩ ዘግይቶ ነው የሚገባው፤ ፋይናንስ ላይ ችግር ስለሚፈጠር በጣም ቀስ ብለው ነው የሚሰሩት። ከቀን 8 ጀምሮ ገብተው እየተመገቡ ነበር፤ ግቢው እንዳሳወቀ መረጃው አለኝ " ሲል መልሷል።
" ተማሪው እየተመገበ ነበር ስለዚህ ግቢው ያወጣውን ወጭ ሊከፍል አይችልም " ብሏል።
ስለዚህ ተማሪዎች ከቀን 8 እስከ 11/2018 ዓ/ም የግቢው ካፌ ገብተው እየተመገቡ ነበር ባይ ነህ ? ለሚለው ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄም፣ " በደንብ ነው እየተመገቡ የነበረው " ሲል ምላሽ ሰጥቷታ።
ፕሬዚዳንቱ ቀጠል አድርጎም " ነገር ግን የመረጃ እጥረት የነበረባቸው ተማሪዎች ነበሩ፤ ያልተመገቡ ተማሪዎች እንዳሉ መረጃው አለኝ " ሲል በራሱ መስክሯራ።
ነንካፌ ተጠቃሚ ተማሪዎች 1506 እንደሆኑ፣ የ5 ቀናት ገንዘብ ሙሉው እንዳልተከፈላቸው፣ ከቀን 12 በኋላ ቢሆን ለእያንዳንዱ ተማሪ መከፈል ከነበረበት 3,000 ብር የተፈላቸው 1,800 ብር እንደሆነ በመግለጽ፣ " 753 ሺሕ ብር የት ገባ?" የሚል ጥያቄ አላቸው። ለዚህ ያላችሁ ምላሽ ምንድን ነው ? የሚል ጥያቄም ለፕሬዚዳንቱ አቅርበናል።
በምላሹም " እንደ ተማሪ ህብረት ለመጠየቅ ሞክረናል፤ የተማሪ ተወካዮችን ሰብስበን ያለውን ነገር አሳውቀናል። መረጃ ባለማግኘታቸው የተጎዱ ተማሪዎች አሉ። ግቢውም ብሩን ማጣት አይገባውም። ብሩ አልጠፋም በነገራችን ላይ። ስለዚህ ያለን አማራጭ ተማሪውም ግቢው በጣም በማይጎዱበት መልኩ ባላንስ ማድረግ ነበር ከ12 ጀምሮ እንዲከፈላቸው አድርገናል " ብሏል።
አንድ የግቢው ተማሪ ግን፣ "በጣም የሚያሳፍር ስራ ነው እየተሰራ ያለው። በ5 ቀናት ክፍተት የትኛውም ነንካፌ ተማሪ ካፌ አልገባም። ውጭ ነበር ሲጠቀም የነበረው በብድርም በምንም እያደረገ" ሲሉ ከሰዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
የኢትዯጰያ ሎተሪ አገልግሎት!
የ1 ሚሊዮን ብር ሽልማት ለእርስዎ!
ከ48 ሠአታት በኋላ የ1 ሚሊዮን ብር ሽልማት፤ ዛሬ ደግሞ ለ 30 እድለኞች ለእያንዳንዳቸው የ1ሺህ ብር ሽልማት ተዘጋጅቷል።
እድልዎን እጅዎ ድረስ አምጥተናል🤳 በእጅ ስልክዎ *8989# በመጫን፣ ወደ www.ethiolottery.et ድረ ገፅ በመግባት፣ በቴሌ ብር ሱፐር አፕ እንዲሁም በነጻ የስልክ መስመር 8989 በመደወል ሎተሪ መቁረጥ ይችላሉ።
መልካም እድል!
#60ሚሊዮን
#ትኩረት🚨
ሄሞራጂክ ፊቨር (Hemorrhagic Fever ) ምንድን ነው ?
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጂንካ ከተማ ምንነቱ በመረጋገጥ ላይ ያለ Hemorrhagic Fever (ሄሞራጂክ ፊቨር) መከሰቱን የጤና ሚኒስቴር በትላንትናው ዕለት በሰጠው መግለጫ ማሳወቁ ይታወቃል።
ምንነቱ በመረጋገጥ ላይ ያለው በሽታ ምክንያት በጂንካ ከተማ ሁለት የጤና ባለሞያዎችን ጨምሮ በአጠቃላይ ስድስት ሰዎች ህይወት ማለፉን መዘገባችን ይታወሳል።
እስካሁን ስለበሽታው በጤና ሚኒስቴር የተገለጹ መረጃዎች ምንድን ናቸው ?
እንደ ጤና ሚኒስቴር መረጃ እስካሁን በበሽታው ስምንት ሰዎች ተጠርጥረዋል።
ተጨማሪ ስርጭትን ለመግታት እና ለመከላከል እንዲሁም ምንነቱን ለማወቅ የላብራቶሪ ምርመራዎች እየተከናወኑ ነው።
በላብራቶሪ ምርመራ ውጤቱ እና በምንነቱ ዙሪያ እስካሁኗ ሰአት ድረስ ከጤና ሚኒስቴርም ሆነ ከኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የተሰጠ መግለጫ የለም።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቫይራል ሄሞራጂክ ፊቨር ምንድነው ? ምልክቶቹ እና መከላከያ መንገዶቹስ ? በሚለው ዙሪያ የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስት እና የተላላፊ በሽታዎች ፌሎ የሆኑትን ዶ/ር ሰላም ቦጋለን አነጋግሯል።
ቫይራል ሄሞራጂክ ፊቨር (Viral Hemorrhagic Fever) ምንድን ነው ?
" ቫይራል ሄሞራጂክ ፊቨር (Viral Hemorrhagic Fever) በተለያዩ ምድቦች ሚከፈሉ የቫይረስ አይነቶች ሚከሰት ከባድ ምልክቶችን ያከተተ የህመም አይነት ስብስብ ሲሆን ፦
- ትኩሳት፣
- ደም መድማት፣
- የሰውነት ክፍሎች (ኦርጋኖች) ስራ እክል የእነዚህ ህመሞች ምልክት ነው።
በተለያዩ የቫይረስ አይነቶች ሲከሰት ሚያመሳስላቸው ምልክት እንዳለ ሆኖ የህመሙ መተላለፊያ፣ ክብደት እና መከላከያ እንደየ ቫይረሱ አይነት ይለያያል። "
ለቫይራል ሄሞራጂክ ፊቨር መከሰት መንስኤዎች ምንድን ናቸው ?
" ለቫይራል ሄሞራጂክ ፊቨር መከሰት :-
➡️ ኢቦላ (Ebola virus)
➡️ ማርበርግ (Marburg virus)
➡️ Lassa fever virus(ላሳ ፊቨር ቫይረስ)
➡️ ደንጉ (Sever Dengue virus)
➡️ የሎው ፊቨር (Yellow fever virus)
➡️ ሪፍት ቫሊ ፈቨር ቫይረስ (Rift Valley Fever virus)
➡️ ክሪሚየን ኮንጎ (Crimean-Congo haemorrhagic fever) እና ሌሎች ቫይረሶች መንስኤ ናቸው። "
በበሽታው የተያዘ ሰው የህመሙን ምልክቶችስ በምን ያህል ቀናት ውስጥ ማሳየት ይጀምራል ?
" እነዚህ ህመሞች አንድ ሰው ከተያዘ በአማካኝ ከ2 እስከ 21 ቀን ምልክት ማሳየት ይጀምራሉ። "
በበሽታው የተያዘ ሰው የሚያሳያቸው ምልክቶች ምንድን ናቸው ?
" ሲጀምሩ እንደሌሎች ትኩሳት አምጪ ተላላፊ ህመሞች ፦
• ራስ ምታት፣
• ትኩሳት፣
• ብርድ ብርድ ማለት፣
• ጡንቻ ህመም፣
• ድካም ፣
• ትውከት እና የምግብ ፍላጎት መቀነስ ያስከትላሉ።
ቀስ በቀስ ከበድ በማለት ደም ከተለያዩ የሰውነት ክፍሎች መድማት ይጀምራል።
እንዲሁም የሰውነት ክፍሎች (ኦርጋኖች) ለምሳሌ ሳንባ፣ ኩላሊት ፣ ጉበት ስራቸው ይዳከማል እንዲሁም ደም ግፊት መውረድና ሌሎችም የሰውነት አካሎች ጉዳትና ሞት ሊያስከትሉ ይችላሉ። "
የበሽታው ክብደት እና የሞት ምጣኔ ምን ይመስላል ?
" የሞት ምጣኔ እንደየ ቫይረሱና ክብደቱ ሲለያይ ደንጉ (Sever Dengue virus) ከባድ ህመም ሳያመጣ ከመዳን እስከ ተወሰነ ሞት ያስከትላል፣ ላሳ (Lassa fever virus) እስከ 20 በመቶ ሞት ሲያስከትል እንዲሁም እነ ማርበርግ ቫይረስ ደግሞ እስክ 80 በመቶ ሞት ሊያስከትሉ ይችላሉ።
ከላይ የተጠቀሱት ምልክቶች በሂሞራጂክ ፊቨር ብቻ ሳይሆን በሌሎች ህመሞችም ምክንያትም ሊከሰቱ ይችላሉ ለምሳሌ ከባድ ወባ፣ በባክቴርያ የሚመጣ ሴፕሲስ (sepsis)፣ ሜኒንጆኮከስ ተብሎ ሚጠራው ማጅራት ገትር አምጪ ተህዋስ እነዚህን መሰል ምልክቶች ሊያስከትሉ ይችላሉ ስለዚህ የህመሙ ምንነት በምርመራ መረጋገጥ አለበት። "
መተላለፊያ መንገዶቹ አስተላላፊዎቹስ ምን ምን ናቸው ?
" የቫይራል ሄሞራጂክ ፊቨር (Viral Hemorrhagic Fever) መተላለፍያ መንገዶች እንደየ ቫይረሱ ይለያያል።
ቢንቢ (Aedes aegypti ተብሎ ሚጠራው ትንኝ) ፡- ደንጉ (Sever Dengue virus) እና የሎው ፊቨር (Yellow fever virus) ያስተለልፋል።
የለሊት ወፍ (bat) ፡ ኢቦላ (Ebola virus) እና ማርበርግ (Marburg virus) ያስተላልፋል።
የአይጥ አይነቶች ( rodents) ፦ ላሳ የተሰኘውን ፊቨር ቫይረስ (Lassa) ያስተላልፋል።
መዥገር (tick) :- ክሪሚየን ኮንጎ (Crimean-Congo haemorrhagic fever) የተሰኘውን ያስተላልፋል።
ከላይ የተጠቀሱት የቫይረሱ አይነት እና አስተላላፊዎች ሲሆኑ በተለይ ኢቦላ (Ebola virus) እና ማርበርግ (Marburg virus) በበሽታው ከታመመ ሰው ጋር በሚኖር የቅርብ አካላዊ ንክኪ (ደም ወይም ፈሳሽ) ይተላለፋሉ። "
በበሽታው መያዛችንን ከጠረጠርን ምን እናድርግ ?
" ከላይ የተጠቀሱ ምልክቶች ሲከሰቱ በቶሎ ጤና ተቋም መሄድ ያስፈልጋል።
እነኚህ ህመሞች ሰውነት ላይ ያስከተሉት ጉዳት በተለያዩ ምርመራዎች ይታያል እንዲሁም ትክክለኛ መንስኤው በደም ወይም ሰውነት ፈሳሽ ናሙና ምርመራ መረጋገጥ አለበት።
የህክምና እርዳታ በቶሎ ማድረግ ለማገገም እንዲሁም መተለለፍን ለመቀነስ ይረዳል። "
በበሽታው መያዛችን ከተረጋገጠ ምን አይነት ህክምናዎች ይሰጣሉ ?
" ባለሞያዎች የተለያየ ለምሳሌ ግሉኮስ ወይም እንዳስፈላጊነቱ ደም መስጠት፣ ህመም ማስታገስ፣ ኦክስጅን እንዲሁም መተንፈሻና የኩላሊት ህክምና እንደየ ክብደቱና አይነቱ ያደርጋሉ።
በስፋት ባይገኙም ለተወሰኑት አይነቶች የተዘጋጁ መድሃኒቶች አሉ።
የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት የታወቀን ህመምተኝ ለይቶ ማከም፣ ንክኪን ማስወገድ መሰረታዊ ነው ሌሎች መተላለፍያ ዘዴዎችን መቆጣጠርም ያሻል።
የሎው ፊቨር እና ደንጉ ለረጅም ግዜ ሚታወቁ ክትባቶች አላቸው ኢቦላም ክትባት አለው። "
ዶ/ር ሰላም ስለህመሙ የበለጠ ለማወቅ የህብረተሰብረተሰብ ጤና ኢንስቲቱት እና ጤና ሚኒስተር ስለመንስኤው የሚሰጡዋቸውን የክትትል ውጤቶችን እና መግለጫዎች መከታተል አስፈላጊ መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል አሳስበዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
" ድምፃችን ይሰማ ፤ ፍትህ እስክናገኝ እንታገላለን ፤ አሁንም ለመብታችን እንሰዋለን ! " - የትግራይ ኃይል አባላት ሰላማዊ ሰልፈኞች
በፀደቀ ደንብ መልስ እንደተሰጠው የተነገረውና በሚድያዎች በይፋ የተዘገበው የትግራይ ኃይል አባላት የመብት ጥያቄ እንደገና አግርሽተዋል።
ዛሬ ሀሙስ ህዳር 4/2018 ዓ.ም ከዓዲግራት ወደ መቐለ የሚወስደው ዋናው የመኪና መንገድ የመብት ጥያቄ ባነሱ የትግራይ ኃይል አባላት ተዘግቶ ውሏል።
የሰራዊት አባላቱ ዛሬ በዓዲግራት ከተማ ዋና ዋና መንገዶች ባካሄዱት ሰላማዊ ሰልፍ ፦
- ደመወዛችንና መሬታችን ይሰጠን !
- መሪዎቻችን ድምፃችን ሰምተው መልስ መስጠት ሲገባቸው ተደብቀውብናል !
- ፍትህ እስክናገኝ እንታገላለን !
- አሁንም ለመብታችን እንሰዋለን !
- ድምፃችን ይሰማ !
- ጥያቄያችን የማይመልስ አይመራንም !
የሚሉና ሌሎች መፈክሮች አሰምተዋል።
" ጥያቂያችን አልተመለሰም የተገባልን ቃል አልተፈፀመም " ያሉት ሰላማዊ ሰልፈኞቹ ከጥዋት ጀምሮ የዘጉት ዋና መንገድ እንዲከፍቱ በአገር ሽማግሌዎችና በከተማው አስተዳደሮች ቢለመኑም የሚመለከተውን አመራር ሳያገኙ አንደማይከፍቱ በመንገር ይህን መረጃ እስከተዘጋጀበት እስከ ቀኑ 11:00 ድረሰ ፍቃደኞች ሳይሆኑ ቀርተዋል።
ከጥቅምት 3- 7/2018 ዓ.ም ለተከታታይ አምስት ቀናት ዋና የመኪና መንገድ በመዝጋት የተካሄደ የትግራይ ኃይል አባላት ሰልፍና ተቃውሞ ተከትሎ የትግራይ ጊዚያዊ እስተዳደሩ የክልሉ የፀጥታ ሃይሎች ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ረቂቅ ደንብ ማፅደቁ ይታወሳል።
የፀደቀው ደንብ መሰረታዊ ፍላጎቶች ፣ የህክምና አገልግሎት ፣ የቤት መስሪያ መሬት ፣ በመንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት የሚሰጥ የክብር አገልግሎት ፣ ትምህርት ስልጠናና ሌሎች ጥቅማ ጥቅሞች ያካተተ እንደሆነ ዘግበናል።
የፀደቀው የትግራይ ኃይል አባላት ተጠቃሚነት ደንብ ለረጅም ጊዜ ጥናት የተደረገበት ከፀጥታ አመራሮች ውይይት ሲካሄድበት የቆየ ነው ቢባልም ፤ ከአንድ ወር በኋላ የትግራይ ኃይል አባላት ተቃውሞ መልሶ አገርሽቷል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
@tikvahethiopia
ከዘመን ፈጥነው እንዲራመዱ IPHONE 17 PRO MAX እንሸልምዎት!
ዛሬ የ60 ሚሊዮን ብር ሎተሪ ከሚቆርጡ ደንበኞች መካከል 1 እድለኛ የ IPHONE 17 PRO MAX ባለቤት ይሆናል!
በተጨማሪም ለ 30 እድለኞች የ 1ሺህ ብር እንዲሁም በሳምንቱ መጨረሻ የ 1 ሚሊዮን ብር ሽልማት ተዘጋጅቷል!
ይፍጠኑ ይቁረጡ!
በቴሌብር ሱፐር አፕ፤ www.ethiolottery.et፤ *8989# እንዲሁም 8989 ላይ በመደወል አሁኑኑ ይቁረጡ!
መልካም ዕድል!
የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት!
የንግድ ድርጅቶች ቆጠራ ምን ፋይዳ አለው?
ከጥቅምት ወር መግቢያ ጀምሮ በሁለት ምዕራፍ እስከ የካቲት 30 ድረስ በአዲስ አበባ ከ5 ሺህ 600 በላይ ባለሙያዎች የሚሳተፉበት የንግድ ተቋማት ቆጠራ መጀመሩ ተነግሮ ነበር።
ቆጠራውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕላንና ልማት ቢሮ እንዲሁም የኢትዮጵያ ስታትስቲክስ አገልግሎት በጋራ የሚያከናውኑት ሲሆን ከወረቀት ነፃ በሆነ መንግድ በዲጂታል የሚደረግ ነው።
በዚህ የኢኮኖሚ ቆጠራ ከአንስተኛ ንግዶች እስከ ግዙፍ ተቋማት እንደሚካተቱም ተገልጾ ነበር።
ለመሆኑ የንግድ ድርጅቶች ቆጠራ ምንድን ነው ?
ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቀቋም አይ ኤም ኤፍ (IMF) የንግድ ድርጅቶች ቆጠራ በአንድ ግዛት ውስጥ በተወሰነ ጊዜ የሚደረግ የተሟላና ስልታዊ (systematic) የንግድ ተቋማት ቆጠራና ምዘገባ እንደሆነ ይገልፃል።
ይህ ቆጠራ የግዛቱን የንግድ መዋቅር እና ክንውን የተመለከተ መረጃ (Data) ያመነጫል።
የንግድ ተቋማት ቆጠራ ጥቃቅን፣ አነስተኛ፣ ከፍተኛ፣ መደበኛና መደበኛ ያልሆኑ የንግድ ድርጅትና እንቅስቃሴዎችን እንደሚያካትት የመንግስታቱ ድርጅት የስታስቲክስ ሥራ ክፍል (Statistics Division/ UNSD) አስቀምጧል።
የንግድ ድርጅቶች ቆጠራ ምን ፋይዳ አለው ?
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፋይናንስና ኢንቨስትመንት ረዳት ፕሮፌሰር የሆኑት ዶ/ር ሰውአለ አባተ የንግድ ተቋማት ቆጠራ ኢኮኖሚው የሚያመነጨውን የገቢ መጠን ለመለካት እንደሚረዳ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
" በቆጠራው ወቅት የሚሰበሰቡት የተለያዩ መረጃዎች በአገልግሎት አሰጣጥ ወቅት ክፍተቶችን ለመለየት እና አሰራርን ለማሳለጥ ይረዳል… [ቆጠራው] መንግስት ምን፣ እንዴትና መቼ መስራት አለብኝ የሚለውን ለማወቅ ከፍተኛ ግብዓት ይሰጠዋል ፤ የኢኮኖሚው ተዋናዮች የሆኑ ተቋማትን በየፈርጅ በየፈርጁ አስቀምጦ ለመተንነተን እና ለተለያዩ ፓሊሲ ግብአቶች ጠቀሜታ አለው " ብለዋል።
" መንግስት፣ መንግስታዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት የሚያስችለውን ሪሶርስ ለመሰብሰብ የሚችልበት አንዱ መንገድ ኢኮኖሚ ውስጥ አሉ ብሎ ሚያስባቸውን የንግድ ድርጅቶች በአግባቡ ማወቅ ሲችል ነው " ሲሉም ጨምረዋል።
የስታትስቲክስና የጂኦግራፊ መረጃ ባለሙያው አቶ አለሙ ሰለሞን ደግሞ የንግድ ድርጅቶች ቆጠራ በአንድ ሀገር ወይም ከተማ ያለውን የንግድ አይነት ሰብጥር ለመለየትና ለፖሊስ ውሳኔ ግብዓት እንደሚረዳ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልፀዋል።
" ምንድን ነው ተደራሽ የሆነው? ምንድን ነው ችግሩ? የትኛወ ዘርፍ ነው የበዛው፣ በየትኛው ዘርፍ ደግሞ ምን ማድረግ አለበት የሚለውን " ለመወሰን እንሰሚያግዝም ጠቁመዋል።
ዶ/ር ሰውአለ በንግድ ድርጅቶች ቆጠራ አማካኝነት የሚገኘው መረጃ የመንግስትን እቅድ ስኬታማ ለማድረግ ይጠቅማል ይላሉ።
" እነዚህ ዴታዎች በሌሉበት የቢሮ ሥራ ነው የሚሆነው። ቢሮ ላይ የሚሰራው ዕቅድ ደግሞ ወደ መሬት ሲወርድ ለመፈፀም የማይቻልበት ሁኔታ አለ። የዕቅድ አፈፃፀም ክፍተት የሚመጣው አውዱን እና እውነተኛውን ኢንቫይሮመንት ሳያውቁ ከሚሰሩ ሥራዎች ጋር በተያያዘ ነው " ሲሉም አክለዋል።
በተጨማሪም ግብር መክፈል ያለባቸውን የንግድ ድርጅቶች በአግባቡ ለማወቅ ቆጠራው ይጠቅማል ሲሉ አንስተዋል።
አቶ ዓለሙ ከግብርና ወደ ሌሎች ዘርፎች እየተደረጉ ያሉ ሽግግሮችን ለማወቅ " ቆጠራ ግድ ነው " ሲሉ ገልፀዋል።
ጨምረው የንግድ ቆጠራ መንግስት ግልጽ የሆነ ለውሳኔ የሚረዳ መረጃ እንዲያገኝ ይረዳል ብለዋል።
" አለበለዚያ፣ ድካሞች በሙሉ ከንቱ ነው ሚሆነው። በደፈናው መመራት ነው ሚሆነው። ዳታ ካልሰበሰበ እያንዳንዱ ነገር በግምት ነው ሚሆነው " ብለዋል።
ዶ/ር ሰውአለ ጥቅሙ ከመንግስት ተቋማት እንደሚሻገር አንስተዋል።
" ቆጣሪ ድርጅቱ ለምን ዓለማ እየቆጠረ ያለው? ምን ለማሳካት ነው የሚለው መሠረታዊ ነገር ሆኖ ይኼ ዴታ ግን ለብዙ ነገር ጠቃሚ ነው። ዴታው ለህዝብ ይፋ የሚሆን ከሆነ ለጥናት እና ምርምር ይሆናል። ለመንግስት ብቻ ሳይሆን ለሌሎች የመረጃ ቋት ሆኖ ያገለግላል " ብለዋል።
ባለሙያዎቹ ቆጠራው ቤት ለቤት የሚካሄድ በመሆኑ አድካሚ እና ውስብስብ ሊሆን እንደሚችል ጠቅሰዋል።
በቆጠራው እንዲሳተፉ የሚጠበቁ ሰዎች ጉዳዩን ከግብር ወይም ከሌሎች ነገሮች ጋር በማያያዝ የተሳሳተ መረጃ ሊሰጡ ይችላሉ የሚል ስጋት እንዳላቸውም ነው ያነሱት።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
@tikvahethiopia
አቢሲንያ ባንክ
ባንካችን ለመቄዶንያ ከ14 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አደረገ
ባንካችን አቢሲንያ ለመቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማኅበር ከብር 14 ሚሊዮን በላይ የገንዘብ ድጋፍ አደረገ።
የባንካችን ዋና የኮርፖሬት የሰው ሃብት ኦፊሰር አቶ ሰይፉ ቦጋለ በማዕከሉ ተዘዋውረው ባዩት ነገር መደሰታቸውን ገልጸው የ14,488,000.00 (አሥራ አራት ሚሊዮን አራት መቶ ሰማንያ ሥምንት ሺሕ) ብር የገንዘብ ድጋፉን ለማኅበሩ መሥራች እና በጎ አድራጊ አቶ ቢንያም በለጠ (የክብር ዶ/ር) አስረክበዋል።
አቶ ቢንያም በበኩላቸው ድጋፉ የበጎ አድራጎት ማህበሩ በከፍተኛ ደረጃ ገንዘብ በሚያስፈልገው ሰዓት የተደረገ እገዛ መሆኑን ገልጸው በዚህም ባንካችን ላደረገላቸው ድጋፍ በማመስገን ባንካችን አቢሲንያ በየዓመቱ ኅዳር 2 ቀን 2018 በመቄዶንያ የሚታወስ መሆኑን በመግለጽ መሰል ድጋፎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል።
የባንካችን አመራሮች እና ሠራተኞች ለአረጋውያን መኖሪያ እና የህክምና ማዕከል ሆኖ እንዲያገለግል ተደርጎ እየተሠራ በሚገኘውን ባለ 15 ወለል ዘመናዊ ህንጻ ተጠልለው ያሉና በማዕከሉ ድጋፍ እየተደረገላቸው የሚገኙ ወገኖቻችንን ተዘዋውረው የጎበኙ ሲሆን ለአረጋውያኑ ልዩ የምሳ ግብዣም አድርገዋል።
በመጨረሻም ባንኩ በቀጣይም ከሰራተኞች በየወሩ ከደሞዛቸው በፈቃዳቸው ከሚያደርጉት መዋጮ ከብር 1 ሚሊዮን በላይ እየሰበሰበ ለማህበሩ ለመስጠት ቃል ገብቷል።
አቢሲንያ ባንክ