tikvahethiopia | Unsorted

Telegram-канал tikvahethiopia - TIKVAH-ETHIOPIA

1532594

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። @tikvahuniversity @tikvahethAfaanOromoo @tikvahethmagazine @tikvahethsport @tikvahethiopiatigrigna #ኢትዮጵያ

Subscribe to a channel

TIKVAH-ETHIOPIA

" ሀገራችንን አላህ ሰላም ያድርግልን። ሀገራችንን አላህ አማን ያድርግልን።

እኛም የምንዋደድ አላህ ያድርገን። የምንከባብር አላህ ያድርገን። የምንረዳዳ አላህ ያድርገን። የምንመካከር አላህ ያድርገን።

ጥላቻን ከውስጣችን አላህ ያጥፋው።

በሃይማኖትም ሆነ በፖለቲካ መገዳደልን፣ መጋጨትን፣ መለያየትን ከሀገራችን ከውስጣችን አላህ ያንሳልን።

እንደ አባቶቻችን ከዛም በበለጠ የምንተባበር ፣ የምንከባበር፣ የምንዋደድ ፣ የምንረዳዳ አላህ ያድረገን። " - ታላቁ አባት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" እርቦናል፤ ጠምቶናል ፣ የ8 ወር ደመወዝ አልተከፈለንም። ... በመጠጥ ውሃም ችግር ላይ ወድቀናል፣ እኛ ማንን እንጠይቅ፣ በየጊዜው አመራሮች ይቀያየራሉ፣ ህዝቡ ተቸግሯል " - ሰልፈኞቹ

➡️ " የሀገር ሽማግሌዎች መጥተው ' ለ3 ቀን ታገሱን ' ሲሉ ጠየቁን፣ እኛም አባቶቻችንን ማስከፋት ስላልፈለግን እሺ ብለናቸዋል "

በአፋር ክልል የገዋኔ ወረዳ ዞን 3 ነዋሪዎች ከደመወዝ ጥያቄ እና ከመጠጥ ውሃ ችግር ጋር በተገናኘ በዛሬው እለት ጥቅምት 10/2018 ዓ/ም ከጠዋቱ ሶስት ሰአት አካባቢ ህዝባዊ ተቃውሞ ሰልፍ መንገድ በመዝጋት አካሂደዋል።

ሰልፈኞቹ በሰልፉ ላይ ፦
- " ካልተከፈለን አናስተምርም "
- " እኛ የገዋኔ ነዋሪዎች እርቦናል ፤ ጠምቶናል "
- " ለወላጅ አልባ ህጻናት የ8 ወር ደመዝ ይሰጠን " የሚሉ እና ሌሎችም ደምጾችን አሰምተዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም በሰልፉ ላይ የነበሩ የወረዳ ነዋሪዎችን ስለጉዳዩ ጠይቋል።

ነዋሪዎቹ በዝርዝር ምን አሉ ?

" የገዋኔ ወረዳ ሁሉም የመንግስት ሰራተኞች በ2017 ዓ.ም የ5 ወር ደመወዝ አልተከፈለንም፣ በ2018 ዓ.ም በጀት አመት ደግሞ የሀምሌ፣ የነሀሴ እና የመስከረም ወር አልተከፈለንም። በአጠቃላይ የ8 ወር ማለት ነው።

ይህ የሆነው በወረዳው የፋይናንስ ጽህፈት ቤት ሃለፊ ነው። ሃላፊው ወረዳው ላይ አይኖርም፣ አዲስ አበባ እና አዋሽ እንደሚኖር ነው የሰማነው። ቢሮ ስንሄድ አናገኘውም። ችግሩ የማን እንደሆነም እንኳ ማወቅ አልቻልንም።

ክልሉ እራሱ ጥያቄያችንን ሰምቷል፣ በባለፈው አመት ሲከፍሉን የመቼ፣ የመቼ ወር እንኳ እንደከፈሉ አልነገሩንም።

አልፎ አልፎ ይከፍላሉ፣ እኛን እያዘናጉን ነው፣ በዘንድሮው አመት ችግሮች ይስተካከላሉ ብለን ስንጠብቅ ይሄው መስከረም አልቆ ጥቅምት ላይ ነን፣ እስካሁን ግን የተስተካከለ ነገር የለም።

የመጠጥ ውሃ ችግር በክልሉ እንደአጠቃላይ እንዳለ እናውቃለን፣ ነገር ግን የእኛ የተለየ ነው፣ ይህን የውሃ ችግር ለመቅረፍ በ2012 ዓ.ም ከወረዳዋ 30 ኪሎሜትር እርቀት ላይ ከሚገኝ ቦታ ተቆፍሮ ተሰርቶ ነበር። ነገር ግን ብዙም ሳይቆይ ተበላሽቷል፣ ከዛም በኋላ ችግሩ ተበብሶ ቀጥሏል።

አሁን ላይ አንዱን የሮቶ ውሃው ከ250 እስከ 350 ብር እየገዛን ነው፣ ይህንን ራሱ ለመግዛት እንኳ ደመወዛችን እየተሰጠን አይደለም። የገዋኔ ነዋሪ እያየው ያለው ሰቆቃ በጣም ያሳዝናል።

የወረዳዋ ነዋሪዎች አብዛኞቹ ወላጅ አልባ ህፃናት ናቸው። እርዳታ አያገኙም፣ በጣም ችግር ላይ ናቸው፣ ደመወዝ በአግባቡ ቢሰጥ ኖሮ በቤተሰቦቻቹው የጡረታ ገንዘብ ይተዳደሩ ነበር። ይህ ግን አልሆነም።

ከሌላ አካባቢ መጥተው በወረዳዋ በመምህርነት የሚያገለግሉ መምህራኖች ስራቸውን ለቀው ወጥተዋል። በዛሬው እለትም ከትምህርት ቤት ተማሪዎች ተመልሰዋል።

መብላት እና መጠጣት ያልቻለ መምህር እንደት አድርጎ ያስተምራል ? እኛ ማንን እንጠይቅ፣ በየጊዜው አመራሮች ይቀያየራሉ፣ ህዝቡ ተቸግሯል።

ይህን ተከትሎ በዛሬው እለት የወረዳው ነዋሪ ሰላማዊ ሰልፍ ወጥተን ነበር። ሰልፍ የወጡት ወጣቶች በመሃል መንገድ ላይ ደረቅ እንጨት እሳት በመለኮስ ተቃውሞ አሰምተናል። ለተወሰነ ደቂቃም የትኛውም ተሽከርካሪ እንዳይንቀሳቀስ አግደን ነበር። ሰልፍ ላይ እያለን የሀገር ሽማግሌዎች መጥተው ' ለ3 ቀን ታገሱን ' ሲሉ ጠየቁን፣ እኛም አባቶቻችንን ማስከፋት ስላልፈለግን እሺ ብለናቸዋል።

አባቶች በስአቱ ያሉን ' መንገዱን ክፈቱት መኪኖች ይሒዱ፣ ለእኛ ደግሞ የሶስት ቀን እድሜ ስጡን፣ ችግሩን ለመቅረፍ በዚህ ሶስት ቀን እኛ የወረዳውን አስተዳደር እንጠይቅ፣ መፍትሔ ከሌለው ግን ለእናንተ እናሳውቃለን ' ነው ያሉት፣ እነሱን የላካቸው የወረዳው አስተዳደር እንደሆነም ሰምተናል።

ሰልፍ የወጣንበት ዋነኛ ምክንያት ለ8 አመት በመጠጥ ውሃ ችግር ላይ በመሆናችን፣ የመንግስት ሰራተኛው ደግሞ የ8 ወር ደመወዝ ስላልተከፈለው ነው። የጡረታ ደመወዝ የሚያገኙ ህፃናት በርሃብ ውስጥ ስለሆኑ ነው።

ውሃ የምንገዛው በየወሩ ነው። ይህንንም የምናገኘው በመከራ ነው። ውሃውን የሚያመጡት የመንግስት መኪኖች ናቸው። በየጊዜው ጥያቄ ስንጠይቅ መፍትሔ እናመጣለን ነው ወረዳው ምላሹ፣ ዛሬ ደግሞ የሀገር ሽማግሌዎች ሰልፍ ላይ እያለን ለሶስት ቀን እንዲንታገስ ጠይቀውናል፣ ነገር ግን አስቡት እስኪ 8 አመት ለተጠየቀ ጥያቄ በ8 አመት መመለስ ሳይችሉ በሶስት ቀን ይመለሳል ብሎ ማሰብ ከባድ ነው " ብለዋል።

ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቃላቸውን ከሰጡ መካከል በወረዳው የአመራርነት የስራ ሃላፊነት ያላቸው አንድ አካል ጉዳዩ በቀላሉ እንደማይፈታ እና የፌደራል መንግስት የማህበረሰቡን ችግር ተገንዝቦ መፍትሔ ቢሰጥ የተሻለ እንደሚሆን ተናግረዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

የታላቁ የሃይማኖት አባት የቀድሞው የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝደንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ ሥርዓተ ቀብር ተፈጽሟል።

ከስርዓተ ቀብራቸው ቀደም ብሎ በሚሊኒየም አዳራሽ ሽኝት ተደርጓል።

ታላቁ የሃይማኖት አባት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር በታላቁ አንዋር እና በኑር (በኒ) መስጂዶች ከአራት አስትርት ዓመታት በላይ ኢስላማዊ ሃይማኖታዊ ትምህርት አስተምረዋል።

ከ50 በላይ ሃይማኖታዊ መጽሐፍትንም ጽፈዋል፡፡

ቅዱስ ቁርአንንም ተርጉመዋል፡፡ የቁርአን ትርጉም ሥራቸውን በሲዲ በማሳተም አሰራጭተዋል፡፡

ከ50 ዓመታት በላይ በዘለቀ የአዲስ አበባ ቆይታ ቅዱስ ቁርአንን ከ300 ጊዜ በላይ በትርጉም (ተፍሲር) አስተምረዋል፡፡

ተቀዳሚ ሙፍቲ በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች የተፈጠሩ ሃይማኖታዊ አለመግባባቶችን በመፍታት የሃይማኖታዊ አባትነታቸውን ሚና ተወጥተዋል።

በ1967 ዓ.ም የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ሲመሰረት የምክር ቤቱ አባልና የዑለማ ሊቀመንበር በመሆን አገልግለዋል።

ከ2010 መጋቢት እስከ ግንቦት ወር 2014 ዓ.ል ድረስ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤትን በፕሬዚዳንትነት እንዲሁም የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የበላይ ጠባቂ በመሆን አገልግለዋል፡፡

ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ ባለትዳርና የአምስት ወንዶችና የአራት ሴቶች አባት እንደነበሩ ከጠቅላይ ምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

ፎቶ፦ የታላቁ አባት የተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ አስክሬን ፒያሳ በሚገኘው ኑር መስጂድ የዱዓ እና የሽኝት ሥነ-ሥርዓት ተካሄደ።

የተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ አስከሬን ለ40 ዓመታት ባስተማሩበት ኑር መስጂድ ሶላተል ጀናዛ ተሰግዶበታል።

ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ ሥርዓተ ቀብራቸው የሚፈፀም ይሆናል።

Photo Credit - EBC & ENA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Update

የታላቁ አባት የተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ የቀብር ስነ ስርዓት ዛሬ ሰኞ ከቀኑ 10:00 ሰዓት እንደሚፈጸም የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አሳውቋል።

ስርዓተ ቀብራቸውን ለማስፈጸምም ኮሚቴ ተዋቅሮ እየሰራ ሲሆን ኮሚቴ ከቤተሰቦቻቸው ጋር በመነገገር በወሰነው መሰረት አጠቃላይ መርሃግብሩ ይህን ይመስላል።

1) ሰላተል ጀናዛው ከቀኑ 6፣00 በዙሁር ወቅት ላይ ለ40 አመታት ባስተማሩበት ፒያሳ በሚገኘው የኑር (በኒ) መስጂድ ይሰገዳል።

2) ከቀኑ 8:00 ሰአት ጀምሮ በሚሊኒየም አዳራሽ ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎች በተገኙበት የሽኝት ፕሮግራም ይከናወናል።

3) ከቀኑ 10 ሰአት የቀብር ስነስርዓታቸው ይፈጸማል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

ታላቁ አባት ሐጂ ኡመር ኢድሪስ አረፉ።

የቀድሞ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት የክቡር ዶ/ር ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ኡመር ኢድሪስ ወደ አኼራ ሄደዋል።

ታላቁ የሃይማኖት አባት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ኡመር ኢድሪስ ባጋጠማቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ዛሬ ወደ አኼራ ሄደዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለአባታችን ሐጂ ኡመር ኢድሪስ ቤተሰቦች እንዲሁም ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ መፅናናትን ይመኛል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

‎" ተገቢዉን ፍትሕ አለማግኘቷ ያንገበግበኛል " - ወላጅ አባት

‎አርሶ አደር ዳንሳሞ አሌ በሲዳማ ክልል ምስራቃዊ ሲዳማ ዞን ዳኤ'ላ ወረዳ ቃዳዶ ቀበሌ ዳዱርቾ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ነዋሪ ናቸው።

ከዛሬ ሶስት ዓመታት በፊት ደጌ ዳንሳሞ አሌ የተበለች የ15 አመቷ ታዳጊ ልጃቸውን 'አበበ ክፍሌ' የተባለ ወጣት ግብራበሮቹን በማሰባሰብ ለቅሶ ቤት ተልካ ከምትመለስበት አፍነው ወደ ጫካ በመውሰድ ጭካኔ በተሞላበት መልኩ ጓደኞቹ አፍነዉ ይዘዋት በግድ ይደፍራታል።

‎ታዳጊዋ ደጌ በደም ተለውሳ፣ ትንፋሽ አጥሯት ከወደቀችበት አንስተው ቦታ በመቀየር ይህን እንስሳዊ ድርጊት ሲፈፅሙባት የተመለከች አንዲት ሴት ጩኸት ታሰማለች፤ እነሱም ተሸክመዋት ለማምለጥ ይሞክራሉ።

አባቷን ጨምሮ ከለቅሶ ቤት ሲመለሱ የነበሩ የአከባቢዉ ነዋሪዎች ጩኸቱን ወደ ሰሙበት ለእርዳታ ሲሯሯጡ በመጨረሻም ክፍሌና ጓደኞቹ ደጉን ጥለዋት ይሸሻሉ።

ሰው ለማገዝ ከሌሎች ሰዎች ጋር አብሮ ሮጦ የደረሰዉ አባቷ አቶ ዳንሳሞ አሌ የሚያየውን ማመን ያቅተዋል፤ የገዛ ልጁ በደም ተለውሳ በእርቃኗ ተዝለፍልፋ ወድቃ ሲያያት የሚይዘዉ የሚጨብጠውን ያጣል።

ከዚህ በኃላ ምን ተፈጠረ ?

‎አርሶ አደር ዳንሳሞ አሌ ስለሁኔታው ለቲክቪህ ኢትዮጵያ እስረድተዋል።

" ሰው ለመርዳት በሮጥኩበት ልጄ ተደፍራ በወደቀችበት ነበር የደረስኩት እርቃኗን ሆና ሳይ እራሴን መቆጣጠር አቃተኝ፣ የምይዘዉ የምጨብጠዉን አጣሁ፤ የለበስኩትን ጃኬት ነበር አውልቄ ሸፈንኳት፤ ጮሆኩ ሰዎች ሊያረጋጉኝ ሞከሩ፤ በጣም አሳዛኝ ልብ ሰባሪ ድርጊት ነበር " ብለዋል።

‎" አበበ ክፍሌና ጓደኞቹ ከአከባቢው ተሰወሩ ደጉ በዛኑ ምሽት ብዙ ደም ፈሷት ስለነበር ወደ ዳኤላ ሆስፒታል ተወሰደች ከዚያም ለተሻለ ሕክምና ወደ ሐዋሳ እንድትጓዝ ተደረገ " ሲሉ ገልጸዋል።

‎ደጌ ከአካላዊ መደፈር በዘለለ ከፍተኛ ስነልቦናዊ ጉዳት ስለደረሰባት እዚያዉ ሀዋሳ በአንድ ድርጅት ውስጥ እንድትቆይ ተደረገች።

‎ፖሊስ ዋናው ተጠርጣሪ ግለሰብ አበበ ክፍሌና ቀንደኛ ተባባሪ ጓደኛዉ ኢያሱ ግዴሳ ማምለጣቸዉንና ሶስቱን ግብራበሮች ግን መያዙን ገልፆ ክስ መሰረተባቸዉ።

‎ፍርድ ቤቱ በነዚህ ሶስት ግብራበሮቹ ላይ የ6 አመት ፅኑ እስር ፈርዶባቸው የነበር ቢሆንም ከ2 አመት እስር በኋላ በአመክርዎ ይለቀቃሉ።

ዋናው ወንጀለኛ እና በታዳጊዋ ላይ ጥቃት ያደረሰው " አበበ ክፍሌ" የተባለው ሰው ግን እስከ ዛሬ ድረስ አልተያዘም ለፍርድም አልቀረበምም።

የደጉ አባት ይህን ጉዳይ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ሲያስረዱ " ከተፈፀመባት ነውረኛ ተግባር በላይ ተገቢዉን ፍትሕ አለማግኘቷ ያንገበግበኛል " ሲሉ ነው የገለፁት።

‎በዚህ መሃል አርሶ አደር ዳንሳሞ ሌላ አሳዛኝ ጉዳይ አጋጠመኝ ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል። ይህም የአከባቢው ሽማግሌዎች " ነገሩን በሽምግልና ካልፈታን " ማለት መጀመራቸው ነው።

" ፖሊስ ' ማግኘት አልቻልኩም ተሰውሮብኛል ' ያለውን ግለሰብ ሽማግሌዎቹ ከየት አመጡት " በማለት ሽምግልናውን እምቢ ማለታቸውን ገልጸዋል።

ሽማግሌዎችም " እንዴት አምቢ ትላለህ ? ሌላስ ልጅህ ላይ መሰል ነገር ቢደርስ ሽማግሌ አይደል የሚፈታው ? " እያሉ ያስጨንቋቸው እንደጀመረ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ደጌ አሁንም ፍትሕ እንደተጠማች ሀዋሳ እንደርሷ ጥቃት የደረሳቸውን ታዳጊዎች ሰብስቦ በሚያኖር ድርጅት ውስጥ ናት።

" የደጌ ታናሽ ግን ገና 12 አመቷ ነው ሽማግሌዎችን እምቢ አልክ ብለው በሷ እንዳይበቀሉኝ እፈራለሁ " ሲሉ አባት ተናግረዋል።

" ‎ስለ ጉዳዩ ከወረዳው እስከ ክልሉ ባለድርሻ አካላት መስሪያ ቤት ደጅ ብጠናም ' የተዘጋ ፋይል ነው ፤ የነሱ ፋይል ጠፍቶብናል ስናገኝ እናሳውቃለን ' በማለት ብዙ አንገላቱኝ " ሲሉ ስለ ፍትህ ድምጻቸውን አሰምተዋል።

‎ቲክቫህ ኢትዮጵያ በጉዳዩ ዙሪያ የዳ'ኤላ ወረዳ እና ምስራቃዊ ሲዳማ ዞን ፖሊስና ፍትሕ (ዐቃቤ ሕግ) አካለትን ለማነጋገር ቢሞክርም " በአካል ካልተገኛችሁ መረጃ መስጠት አንችልም " በማለታቸው በዚህ መረጃ ምላሻቸዉን ማካተት አልተቻለም ፤ መረጃዉ እንደደረሰን የምናቀርብ ይሆናል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

ሚዛን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት !

1⃣0⃣ኛ ዙር የቴክኖሎጂና የቋንቋ ኮርሶች ምዝገባችንን በማጠናቀቅ ላይ እንገኛለን።
የመክፈል አቅም ለሌላቸው በክሬዲት (ከወለድ ነፃ በሆነ ብድር/ዱቤ) መማር የሚችሉበት እድል ከማመቻቸት ባሻገር፤
✔️ ተመርቀው ሥራ ላጡ ሁሉ 25% ቅናሽ (መስፈርት: ከቀበሌ ደብዳቤ ማፃፍ)፣
✔️ ለዩኒቨርስቲና ኮሌጅ ተማሪዎች 12% ቅናሽ (መስፈርት: የታደሰ የትምህርት ቤት መታወቂያ ማሳየት)፣
✔️ ለመምህራንና ለጤና ባለሙያዎች 12% ቅናሽ (መስፈርት: ሙያዊ ማስረጃንና ተመጣጣኝ ህጋዊ ማስረጃ ማሳየት)፣
✔️ 12ኛ ክፍል ማለፊያ ውጤት ላላመጡ 20% ቅናሽ (መስፈርት: ስም እና አድሚሽን ቁጥር ማሳየት)፣
እነዚህን እድሎች አመቻችተናል።

ለመመዝገብ፦ http://www.mizantechinstitute.com

📱 በቴሌግራም @MizanInstituteOfTechnologyEthio አግኙን።

🗺በአካል: ቤተል አፕል ፕላዛ 7ኛ ፎቅ፣ 0987143030
በማህበራዊ ሚዲያ ገፆቻችን አገኙን፦
🌐👍mizantechinstitute?_t=ZM-8u1PtL1rMqD&_r=1">🌐📱mizaninstituteoftechnology7830?si=1GRXkSTCTu6p6ncD">▶️🌐📧 🗺

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

‎" ወጣቶቹ ያለ ፍርድቤት ትዕዛዝ ታስረዋል፤ ቤተሰብ እንዳይጠይቃቸውም ተደርጓል " - ቤተሰቦችና ነዋሪዎች

‎በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጌዴኦ ዞን ኮቾሬ ወረዳ ፍሰሃ ገነት ተብሎ የሚጠራዉ አከባቢ ነዋሪዎች እና " ልጆቻችን ያለ አግባብ ታስረዋል " የሚሉት ወላጆች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቅሬታቸውን አሰምተዋል።

በአከባቢዉ ማህበረሰብ በተደጋጋሚ ሲጠየቅ የቆየዉን የፍሰሃ ገነት የወረዳ መዋቅርነት ጥያቄ " በማህበራዊ ሚዲያዎች አሰራጭታችኋል " በሚል ወጣቶችን እያሰሱ እያሰሩ ነው ሲሉ ነው ቃላቸውን የሰጡት።

" ‎ስድስት ወጣቶች ያለ ፍ/ቤት ትዕዛዝ ታስረዋል " የሚሉት ነዋሪዎቹ የፍሰሃ ገነት ወረዳ በቀደመዉ ጊዜ የወረዳ መዋቅር የነበረዉ መሆኑንና የመዋቅር ጥያቄዉ የሕብረተሰቡ በመሆኑ እነዚህም ወጣቶች ይህንኑ ሃሳባቸዉን በማህበራዊ ሚዲያ በማሰራጨታቸው ብቻ ከስራና የትምህርት ገበታቸው እየታሰሱ መታሰራቸውንና ቤተሰብ እንዳይጠይቃቸዉ መደረጉን ገልጸዋል።

‎" ፖሊስ ልጆቻችንን እንዳናገኝ ከማድረጉም በላይ ' በተባባሪነት አስራችኋለዉ ' እያለ እያስፈራራን ነዉ " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የተናገሩት የአከባቢው ወጣቶች " እኛም እየተፈለግን በመሆኑ አከባቢያችንን ለቀን ሸሽተናል " ሲሉ ተናግረዋል።

‎ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከጌዴኦ ዞንና የኮቾሬ ወረዳ ፖሊስ በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ያደረገው የዞኑ ፖሊስ አዛዥ ፈቃደኛ ባለመሆናቸዉ የኮቾሬ ወረዳ አዛዥ ደግሞ ስልካቸዉ ባለመስራቱ ለጊዜው አልተሳካም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

‎" የ12 ዓመት ህጻን ልጅ ላይ የግብረ ስጋ ድፍረት ወንጀል የፈፀመው የ65 ዓመት አዛዉንት የ23 ዓመት ፅኑ እስራት ተፈርዶበታል " - የይርጋለም ከተማ ፖሊስ

➡️ ‎" ግለሰቡ የኤችአይቪ/ኤድስ ታማሚና የመድሐኒት ተጠቃሚ ነበር "


‎በሲዳማ ክልል ማዕከላዊ ሲዳማ ዞን የይርጋለም ከተማ አስተዳደር የ12 ዓመት ህጻን ልጅ ላይ የግብረ ስጋ ድፍረት ወንጀል የፈጸመው የ65 ዓመት ግለሰብ የ23 ዓመት እስራት ተፈርዶበታል።

የከተማው ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር ደግነት ደስታ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደገለፁት ፥ የከተማው ነዋሪ የሆነ አቶ ናስር ኑር የተባለ የ65 ዓመት ግለሰብ ነሐሴ 6/12/2017 ዓ.ም በከተማው 06 ቀበሌ የ12 አመት ታዳጊ ላይ የግብረ ስጋ ድፍረት መፈጸሙን የሚገለፅ መረጃ ለፖሊስ ይመጣል።

ፖሊስም ጉዳዩን ከፍትህ መዋቅር ጋር በመመርመር በሰውና በህክምና ማስረጃ በማጣራት ለከተማው ዐቃቤ ህግ አስተላልፏል።

‎በምርመራና መረጃ በማሰባሰብ ሂደትም ግለሰቡ ይህን አስነዋሪ ድርጊት ከመፈፀሙ ባሻገር የኤችአይቪ /ኤድስ (HIV/AIDS) ታማሚና እንደሆነና እራሱን አውቆ የመድሐኒት ተጠቃሚ እንደነበር ማወቅ መቻሉን አዛዡ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

‎ጉዳዩን የያዘዉ የይርጋለም ከተማ አስተዳደር ዐቃቤ ህግ በተከሳሹ ላይ ያቀረበውን የክስ መዝገብ ሲያጣራ የቆየው የከተማ አስተዳደር መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ተከሳሹን " ጥፋተኛ ነህ " በማለት ተከሳሹ  እንዲከላከል ቢጠይቅም መከላከል አልቻለም።

‎እንዲሁም የኤችአይቪ/ኤድስ ታማሚ መሆኑን እያወቀ በታዳጊዋ ላይ በፈፀመው አስነዋሪ ድርጊት ጥፋቱን በማክበድ በቀን 4/2/2018 በዋለው ወንጀል ችሎት ተከሳሹን በ23 ዓመት ከ6 ወር ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኗል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Kenya

የኬንያው ጉምቱ ፖለቲከኛ ራይላ ኦዲንጋ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።

የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ ህንድ ሀገር በህክምና ሲረዱ ቆይተው በ80 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

ራይላ ኦዲንጋ ለኬንያ ፕሬዚዳንትነት 5 ጊዜ ዕጩ ሆነው ቢቀርቡም አልተሳካላቸውም።

በተጨማሪ በቅርቡ ለአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበርነት ቦታ ቢወዳደሩም ማሸነፍ ሳይችሉ ቀርተዋል።

ለረጅም አመታት በፖለቲካ ውስጥ የቆዩት ኦዲንጋ በኬንያ የበዛ ድጋፍ ያላቸው ሲሆን የኦሬንጅ ዴሞክራቲክ ሙቭመንት መሪ ነበሩ።

ለዴሞክራሲ፣ ለመድብለ ፓርቲ ስርዓት፣ ከህገመንግስት ሪፎርም በመታገል ይታወቃል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ የኢፌዴሪ ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በራይላ ኦዲንጋ ህልፈት የተሰማቸውን ሀዘን በኢትዮጵያ ህዝብ ስም ገልጸዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Haile

“ በየቦታው የሰራናቸውን ሆቴሎች አይነት አንዷን ድሬዳዋ እናስቀምጣለን ብለን አቅደናል” - ሻለቃ ኃይሌ

➡️ “ደብረ ብርሃን ሆቴል የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ነው፤ በቀጣዮቹ ሦስት፣ አራት ወራት ወደ ሥራ ይገባል” - አቶ ጋዲሳ ግርማ

አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገ/ስላሴ በሆቴልና ሪዞርት ግንባታ ረገድ ወደ ድሬዳዋ ከተማ እየገቡ መሆኑን፣ የከተማዋን ከንቲባና ካቢኔውን አግኝተውም ቃል እንደተገባላቸው ዛሬ ገልጸዋል፡፡

የኃይሌ ሆቴሎች ሪዞርቶች ግሩፕ ማኔጅንግ ዳይሬክተር አቶ ጋዲሳ ግርማ በበኩላቸው፣ ድሬዳዋ ላይ የሆቴልና ሪዞት ግንባታ በቅርቡ እንደሚጀመር ዛሬ ምሽት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጠዋል፡፡

ሻለቃ ኃይሌ፣ በድሬ ከተማ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር፣ “ኃይሌ ሆቴልና ሪዞርት በየከተማዎቹ እየገነባን ነን፡፡ እስካሁን በአስር ከተሞች ተከፍተዋል፡፡ ሌላ ሦስት ደግሞ በግንባታ ላይ ናቸው፡፡ አሁን ደግሞ የድሬው 14ኛው ይሆናል” ብለዋል፡፡

“መምጣት ካለብን በጣም የዘገየንበት ቦታ ነው፡፡ ግን አሁን ድሬዳዋ እየገባን ነው፤ ክቡር ከንቲባውንም ካቢኔውንም አግኝተን በጣም ጥሩ ቃል ገብተውልናል” ሲሉም ተናግረዋል፡፡

ሥራው ቶሎ እንደሚጀመር ጠቁመው፣ “በየቦታው የሰራናቸውን ሆቴሎች አይነት አንዷን ድሬዳዋ እናስቀምጣለን ብለን አቅደናል፡፡ መጀመሪያ ስናጠና ቢዝነሱ እንዴት ነው ? የሚለውን ነው፤ ድሬዳዋም ከኢትዮጵያ ቀደምት ከተሞች አንዷ ነች፤ በቢዝነሱም” ነው ያሉት፡፡

ስለድሬዳዋው ሆቴል ግንባታ ተጨማሪ ማብራሪያ የጠየቅናቸው የኃይሌ ሆቴሎች ሪዞርቶች ግሩፕ ማኔጅንግ ዳይሬክተር አቶ ጋዲሳ ግርማ፣ “የቦታ ልየታና ገበያውን ለማየት ሂደን ነበር ዛሬ፡፡ ኢንቨስትመንት ላይ የሚሰሩ የመንግስት አካላት ቦታዎችን አሳይተውናል፤ ወደ ቀጣዩ ሂደት እንቀጥላለን” ብለዋል፡፡

ግንባታውን በቅርቡ የመጀመር እቅድ እንዳላቸው፣ በዚህ ቀን ይጀመራል የሚል ቀን ገና እንዳላስቀመጡ ገልጸው፣ “የመሬት ርክክብ ባለቀ በማግስቱ ግንባታ እንጀምራለን” ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል፡፡

የጎንደርና ደብረ ብርሃን ፕሮጀክቶችን እያጠናቀቁ በመሆኑ ቀጣዩ አቅጣጫ ወደ ድሬ እንደሆነ የጠቆሙት አቶ ጋዲሳ፣ “ደብረ ብርሃን ሆቴል የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ነው ያለው፤ በቀጣዮቹ ሦስት አራት ወራት ውስጥ ወደ ሥራ ይገባል፡፡ የጎንደር ደግሞ ከሰባት ውራት እስከ አንድ አመት ይወስዳል” ብለዋል፡፡

በጎንደሩ ፕሮጀክት የጸጥታው ሁኔታ ምን አይነት እንቅፋት እንዳፈጠረባቸው ማብራሪያ ሲጠየቁም፣ በዚህ ረገድ አስተያየት አለመስጠትን መርጠዋል፡፡

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#MoE

" ውጤት በቅርቡ ይፋ ይደረጋል " - ትምህርት ሚኒስቴር

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሲሰጥ የነበረው የ2018 የድህረ ምረቃ ትምህርት መግቢያ ፈተና መጠናቀቁን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

ፈተናው ለመውሰድ ከተመዘገቡ 29 ሺ491 አመልካቾች መካከል 96 በመቶ ፈተናውን እንደወሰዱ አመልክቷል።

በ2017 ዓ.ም. መጨረሻ ላይ ይሰጥ የነበረው የድህረ ምረቃ መግቢያ ፈተና በተለያዩ ምክንያቶች ተራዝሞ ጥቅምት 3 ቀን 2018 ዓ.ም. በ53 የፈተና ማዕከላት ነው የተሰጠው።

የፈተናው ውጤትም በቅርቡ ለተማሪዎች ይፋ እንደሚደረግ ሚኒስቴሩ አመልክቷል።

የድህረ ምረቃ ትምህርት መግቢያ ፈተና (NGAT) ከሌሎች አገር አቀፍ ፈተናዎች የተለየና የ2ኛ እና የ3ኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን መቀጠል የሚፈልጉ አመልካቾች ለትምህርቱ ምን ያክል ዝግጁ ናቸው የሚለውን ለማረጋገጥ ደረጃውን ጠብቆ የሚሰጥ ምዘና ነው።

#DrEbaMijena

መረጃው የትምህርት ሚኒስቴር ነው።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

ደንበኛዎትን በቀላሉ ካሉበት ለመድረስ የሚያስችልዎትን የዲጂታል ሱቅ በዘመን ገበያ ላይ አሁኑኑ ይክፈቱ፣ ተደራሽነትዎን ያስፉ።

የበለጠ መረጃ ለማግኘት 3131 ላይ ይደውሉ!

ዘመን ገበያ የዲጂታል ኢትዮጵያ የግብይት መዳረሻ!

#ZemenGEBEYA
#Ethiotelecom #telebirr #telebirrSuperApp #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#ETHIOPIA🇪🇹

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው መደበኛ ስብሰባዉ የኢትዮጵያ ኒውክሊየር ኃይል ኮሚሽን ማቋቋሚያ ደንብን መርምሮ በሙሉ ድምጽ አጸደቀ።

ይህ ደንብ በነጋሪት ጋዜጣ በይፋ ታትሞ ከወጣ በኋላ ተግባራዊ የሚሆን ሲሆን፣ ኢትዮጵያ የኒውክሌር ቴክኖሎጂን ለሰላማዊ ልማት የመጠቀም ጥረቷን ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚያሸጋግር ይጠበቃል።

ኮሚሽኑ በዓለም አቀፍ ማዕቀፎች መሰረት የኒውክሌር ቴክኖሎጂን ለሰላማዊ ዓላማዎች የመጠቀም ሀገራዊ ጥረትን የመምራትና የማስተባበር ዋነኛ ኃላፊነት ይኖረዋል ተብሏል።

ትኩረት አድርጎ የሚሠራባቸው ቁልፍ ዘርፎችም የኤሌክትሪክ ኃይል ተደራሽነት፣ የኢንዱስትሪ ልማት፣ የምግብ ዋስትና፣ የጤና አገልግሎት እንዲሁም ሳይንስና ምርምር መሆናቸው ተመላክቷል።

በሌላ በኩል ፥ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከጥቅምት 4 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ አቶ ሳንዶካን ደበበ የኢትዮጵያ ኒውክሊየር ኃይል ኮሚሽን ኮሚሽነር አድርገው ሾመዋል።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Earthquake

ዛሬ ጥቅምት 10 ቀን 2018 ዓ.ም ምሽት ላይ ከዓዲግራት ደቡባዊ ምስራቅ 43 ኪሎሜትር የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቶ በበርካታ አከባቢዎች ላይ ንዝረት ተሰምቷል።

ከምሽቱ 1:30 የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ በሬክተር ስኬል 4.5 የተለካ እንደሆነ የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቨይ መረጃ ያሳያል።

የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረቱ ከተሰማባቸው አካባቢዎች አንዷ የትግራይ መዲና መቐለ ስትሆን ንዝረቱ በተለይም በፎቅ/ህንፃዎች ላይ አስፈሪ ስሜት እንደነበር የቲክቫህ ኢትዮጵያ መቐለ ቤተሰብ አባል ገልጿል።

ከጥቅምት 2 ቀን 2018 ዓ.ም ወዲህ ንዝረቱ ትግራይ እና አፋር በርካታ አካባቢዎች ጎልቶ የሚሰማ የተለያየ ልኬት ያለው መሬት መንቀጥቀጥ እየተሰማ ነው።

በተለይ እሁድ ጥቅምት 2/2018 ዓ.ም የተከሰተው በሬክተር ስኬል 5.6 የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ አፋር ክልል የሰው ህይወት ቀጥፎ በርካታ ቤቶችን አፍርሶ ከ40 ሺህ በላይ ሰዎች ያለመጠለያ እንዲቀሩ አድርጓል። በተመሳሳይ በትግራይ ምስራቃዊ ዞን አፅቢ ወምበርታ ወረዳ ቤቶች እንዲፈርሱ ምክንያት ሆኗል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" ኢትዮጵያ በጣት ከሚቆጠሩ አረጋውያን፣ አፈ ማር ከሆኑ መካሪዎችዋ መካከል አንዱ የሆኑትን፣ ለመወደድ የታደሉትን የዘመናችን ጌጥ አጥታለች።

ይህንን የድካም ዓለም መገላገል ለእርሳቸው ዕረፍት ቢሆንም ለአገር ግን ታላቅ ጉዳት ከመሆኑም በላይ ዕድሜን ከጥበብ ጋር ያዋሐዱ በሁሉ ዘመን አይገኙምና ኀዘናችን ጥልቅ ነው። " - ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ  ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት

ፎቶ ፦ ቅዱስነታቸው በተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ ሽኝት ላይ በእምባ ተሞልተው ነበር።

Photo Credit - Ahmed Nega

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የ2018 የቲክኒክና ሙያ ሰልጣኞች መግቢያ ነጥብ ይፋ አድርጓል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተመለከተው የተቋሙ ደብዳቤ፣ በ2018 ዓ/ም የስልጠና ዘመን ወደ ቲክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት የሚገቡ ሰልጣኞች የመግቢያ ነጥብ በ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ውጤታቸው መሰረት ለተፈጥሮና ማህበራዊ ሳይንስ የመግቢያ ውጤት ከደረጃ 1 እስከ 5 በዝርዝር አስቀምጧል።

የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ እና ቅድመ ዝግጅት (12ኛ ክፍል) ላጠናቀቁ ደረጃ 1 እና ደረጃ 2 ሰልጣኞች መቁረጫ ነጥብ፦

-ለወንዶች አርብቶ አደር አካባቢዎችን ሳይጨምር 134 እና ከዚያ በታች፣
-ለወንዶች አርብቶ አደር አካባቢዎች 132 እና ከዚያ በታች፣
-ሴቶች አርብቶ አደር አካባቢዎችን ሳይጨምር 121 እና ከዚያ በታች፣
-ሴቶች አርብቶ አደር አካባቢዎች 120 እና ከዚያ በታች፣
-ለሁሉም ክልል አካል ጉዳተኞች 120 እና ከዚያ በታች ሆኖ ተቆርጧል።

የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ እና ቅድመ ዝግጅት (12ኛ ክፍል) ላጠናቀቁ  ደረጃ 3 እና 4  ሰልጣኞች መቁረጫ የጥብ፦

-ወንዶች አርብቶ አደር አካባቢዎችን ሳይጨምር 135 እና ከዚያ በላይ፤
-ወንዶች አርብቶ አደር አካባቢዎች 133 እና ከዚያ በላይ፤
-ሴቶች አርብቶ አደር አካባቢዎችን ሳይጨምር 122 እና ከዚያ በላይ፤
-ሴቶች አርብቶ አደር አካባቢዎች 121 እና ከዚያ በላይ፤
-ለሁሉም ክልል አካል ጉዳተኞች 121 እና ከዚያ በላይ ሆኖ ተቆርጧል።

እንዲሁም፣ የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ እና ቅድመ ዝግጅት (12ኛ ክፍል) ላጠናቀቁ ደረጃ 5 ሰልጣኞች መቁረጫ ነጥብ፦

-ወንዶች አርብቶ አደር አካባቢን ሳይጨምር 179 እና ከዚያ በላይ፤
-ወንዶች አርብቶ አደር አካባቢዎች 168 እና ከዚያ በላይ፤
-ሴቶች አርብቶ አደር አካባቢን ሳይጨምር 168 እና ከዚያ በላይ፤
-ሴቶች አርብቶ አደር አካባቢ 157 እና ከዚያ በላይ፤
-ለሁሉም ክልል አካል ጉዳተኞች 142 እና ከዚያ በላይ ሆኖ ተቆርጧል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" ይህንን የድካም ዓለም መገላገል ለእርሳቸው ዕረፍት ቢሆንም ለአገር ግን ታላቅ ጉዳት ነው " - ቅዱስነታቸው

" እግዚአብሔር በየዘመናቱ አገርን ያለ መካሪ፣ ሕዝብን ያለዘካሪ አይተወውም ! "

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ  ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ እረፍት የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸዋል።

" እግዚአብሔር በየዘመናቱ አገርን ያለ መካሪ፣ ሕዝብን ያለዘካሪ አይተወውም  " ያሉት ቅዱስነታቸው " ለዚህም ምስክሩ ታላቅ አረጋዊ ፣ የበሳል አእምሮ ባለቤት፣ አገርን የሚወዱ፣ ሕዝባቸውን የሚያከብሩ፣ የተጠቁት ወዳጅ ፣ የትውልድ አባት የሆኑት የክብር ዶክተር ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ ነበሩ " ብለዋል።

" ኢትዮጵያ በጣት ከሚቆጠሩ አረጋውያን፣ አፈ ማር ከሆኑ መካሪዎችዋ መካከል አንዱ የሆኑትን፣ ለመወደድ የታደሉትን የዘመናችን ጌጥ አጥታለች " ሲሉ ገልጸዋል።

" ይህንን የድካም ዓለም መገላገል ለእርሳቸው ዕረፍት ቢሆንም ለአገር ግን ታላቅ ጉዳት ከመሆኑም በላይ ዕድሜን ከጥበብ ጋር ያዋሐዱ በሁሉ ዘመን አይገኙምና ኀዘናችን ጥልቅ ነው " ብለዋል።

ቅዱስነታቸው ለቤተሰቦቻቸው፣ ለእስልምና ሃይማኖት ተከታዮችና ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ መጽናናትን ተመኝተዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#SamiTech

አዳዲስ ላፕቶፕች ከአንድ ዓመት ዋስትና ጋር!!
@samcomptech

በጥራት፣ በብራንድና በባትሪ ቆይታ አስተማማኝ የሆኑ የተለያዩ ሞዴል ላፕቶፖች በፈለጉት ስክሪን መጠን፣ ኮር አይ እና ጀነሬሽን አሉን።

ለቢሮዎች፣ ለተማሪዎች፣ ለዲዛይን ባለሙያዎች፣ ለጌመሮች ወ.ዘ.ተ. ሁሉም አሉን።

የዕቃዎች ዋጋ፣ ዓይነት እና አድራሻ ለማግኘት 👉 @samcomptech

@sww2844
0928442662 / 0940141114

Telgram : /channel/samcomptech

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

ኢትዮጵያ የዩሮ ቦንድ ዕዳዋን መልሶ ለማዋቀር ያደረገችው ድርድር መክሸፍና መዘዞቹ ምን ይሆናሉ ?

ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ. 2014 ከዓለም አቀፍ ገበያ በዩሮ ቦንድ አንድ ቢሊየን ዩሮን ለመበደር የበቃችው የአገሮችን ብድር የመክፈል አቅም የሚለኩት እንደ ፊች፣ ፑር እና ሙዲ የመሳሰሉ ተቋማት በአማካይ ‹‹B›› የተሰኘውንና በአንፃሩም ጥሩ የተባለ ደረጃ ሰጥተዋት እንደሆነ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

እነዚሁ የአገሮችን ብድር የመክፈል አቅም የሚለኩ ተቋማት አገሪቱ ብድር የመክፈል ጊዜዋ በደረሰ ጊዜ ከሁለት ዓመታት በፊት ማለትም በ2023 ዓ.ም. ደረጃዋን በእጅጉ አውርደው ወደ cc- ድረስ ዝቅ አድርገውታል።

ያኔም ብድሩ የተወሰደው በኢንዱስትሪ ፓርኮች ግንባታ ላይበማዋል ምርታማነትን አሳድጎ ብድሩንም መመለስ ይቻላል በሚል ነበር፡፡

ከዚያ ወዲህ ግን ኢትዮጵያ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ እና ከሁለት ዓመታት በላይ በዘለቀ ደም አፋሳሽ ጦርነት ስትናጥ ኢኮኖሚዋ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ገብቷል።

በዩሮ ቦንድ ከተበደረችው ብድር ባለፈ ከተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማትና መንግስታት የተበደረቻቸውን ብድሮች የመክፈሏ ነገር ችግር ውስጥ ስለገባ የብድር መክፈያ ጊዜዋ እንዲራዘምላት ከአበዳሪዎቿ ጋር ተደጋጋሚ ድርድሮችን ስታደርግ ቆይታለች፡፡

ሆኖም ድርድሩ ውጤታማ መሆን ባለመቻሉና አገሪቱ ከብድርና ዕርዳታ እየተገለለች መጥታ ብድር መክፈል እያቃታት በመሆኑ የብድር መክፈያ ጊዜ ሽግሽግ ድርድሩ እስኪሳካ ጊዜያዊ የብድር መክፈያ ጊዜ የማራዘም መርሐ ግብር ውስጥ ተገብቶ ቆይቷል፡፡

ከሰሞኑም ኢትዮጵያ ከአንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ ዕዳዋን የመክፍያ ጊዜ ለማራዘም ያደረገችው ድርድር ያለ ውጤት የተጠናቀቀ ሲሆን፣ የአበዳሪዎቹ ኮሚቴ ጉዳዩን ወደ ሕግ ለመውሰድ እንደሚገደድ አስታውቋል፡፡

የገንዘብ ሚኒስቴር ማክሰኞ ጥቅምት 4 ቀን 2018 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ እ.ኤ.አ. በ2024 ተከፍሎ መጠናቀቅ የነበረበትን ከ13 ዓመታት በፊት በዩሮ ቦንድ ሽያጭ የተበደረችውን አንድ ቢሊዮን ዶላርና 6.625 በመቶ ወለድ ያካተተ ዕዳ መልሶ ማዋቀር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ፣ ቦንዱን ከገዙት (አበዳሪዎች) ቡድን ጊዜያዊ ኮሚቴ ጋር ለሶስት ሳምንታት ገደማ የተገደበ ውይይት ሲካሄድ መቆየቱን አስታውቋል።

ኢትዮጵያ ከአንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ ዕዳዋን የመክፍያ ጊዜ ለማራዘም ያደረገችው ድርድር ያለ ውጤት ተጠናቀቀ፣ የአበዳሪዎቹ ኮሚቴ ጉዳዩን ወደ ሕግ ለመውሰድ እንደሚገደዱ አስታውቀዋል፡፡

በውይይቱ ላይም ከኢትዮጵያ መንግሥት ተወካዮች በተጨማሪ በኢትዮጵያ መንግሥት የተቀጠሩት ዋይት ኤንድ ኬዝ ኤልኤልፒ የተባለ የሕግ አማካሪና ላዛርድ የተባለ የፋይናንስ አማካሪ መሳተፋቸውን ገልጿል።

የኢትዮጵያን ቦንድ የገዙ ቡድኖች በመወከል ደግሞ ቡድኖቹ ያቋቋሙት ጊዜያዊ ኮሚቴና የሕግና የፋይናንስ አማካሪዎች መሳተፋቸውን ጠቅሷል።

ጉዳዩን በሚመለከት ባለሙያዎች ምን አሉ ?


የቢዝነስና ኢንቨስትመንት አማካሪው አቶ ከፈለኝ ኃይሉ የድርድሩ አለመሳካት ምንነት እንዲሁም ሊኖረው የሚችለውን ተፅዕኖ ለሪፖርተር ጋዜጣ ሲያብራሩ፣ ቴክኒካል የሚሏቸውን ሁነቶች በመጥቀስ " አለመተማመን እንዳለ አመላካች ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

" አልተሳካም ማለት መሉ በሙሉ ተስፋ የለውም ማለት አይደለም፣ መስማማት ያልቻሉት ፋይናንስ ነክ ባልሆኑ ጉዳዮች ነው። በቀጣይ በሚኖር ድርድር መስማማት ካልቻሉ ግን ኢትዮጵያ ዕዳዋን መከፍል የማትችልበት ሁኔታ (Default) ውስጥ ትገባለች ይህ ደግሞ ለኢትዮጵያ ጥሩ አይደለም " ብለዋል።

ኢትዮጵያ ዕዳዋን መክፈል ከማትችልበት ሁኔታ (Default) ውስጥ ከማስገባቱ በተጨማሪም ተሻጋሪ ተጽዕኖ እንደሚኖረው ፤ በዋናነትም ኢትዮጵያ የወሰደችውን በድር መክፈል የማትችል ተደርጋ እንድትቆጠርና በዚህም ከሌሎች የግል አበዳሪዎች አዲስ ብድር ለማግኘት እንዳትችል እንደሚያደርጋት ወይም ብታገኝ እንኳን ፍተኛ ወለድ ክፍያ እንደሚሆን ገልጸዋል።

" በአጠቃላይ ይህ ሁኔታ ከተፈጠረ የኢትዮጵያን ብድር የመክፈል እይታ ያበላሻል " ብለዋል።

ድርድሩን ያለስምምነት መጠናቀቁን ተከትሎ የአበዳሪዎቹ ኮሚቴ ጉዳዩን በሕግ አግባብ ለማየት መወሰኑ ምን ዓይነት የሕግ አግባቦችን ያካትታል በሚል ጥያቄ ቀርቦላቸው መልሰዋል።

" ኢትዮጵያ ወደ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ገበያው ወጥታ ሌሎች ብድሮችን እንዳታገኝ ሊያሳግዱ ይችላሉ። ከዚህ በተጨማሪም ሸቀጦችን ወደ አገር ለማስገባት ኤልሲ (Letter of Credit) ሙሉ በሙሉ መክፈት የማይቻልበት ሁኔታ ሊፈጥር ይችላል "  ብለዋል።


" በተጨማሪም በውጭ አገር የሚገኙ የኢትዮጵያ መንግሥት ሀብትና ንብረቶችን አስገድደው በማሸጥ እንዲከፈላቸው ሊያደርጉ ይችላሉ፣ በዚህም የኢትዮጵያ ንብረቶች ሊያዙ ይችላሉ " ሲሉ አስረድተዋል።


በሌላ በኩል በዚህ ምክንያት በኢትዮጵያ ላይ የሚፈጠረው የገጽታ መበላሸት ደግሞ የውጭ አገር ባለሀብቶች ወደ ኢትዮጵያ እንዳይመጡ ሊገድብ እንደሚችል ገልጸዋል።

የኢኮኖሚ ተንታኙ (ዶ/ር) ተስፋቸው ተፈራ ደግሞ ፥ ኃያላን መንግሥታት በአነስተኛ ወለድ ይሰጡ የነበረው ብድር እየተመናመነ በመምጣቱ አገሮች የካፒታል ፍላጎታቸውን ለማሟላት ወደ ዓለም አቀፍ የቦንድ ገበያ በመውጣት በቦንድ ሽያጭ ብድር የሚየመገኙበት ሁኔታ በገቡበት ወቅት ኢትዮጵያ በዩሮ ቦንድ ሽያጭ የተበደረችውን መክፈል ባለመቻሏ ድርድር ውስጥ መግባቷና ድርድሩም በስኬት አለመጠናቀቁ ዋጋ እንደሚያከፍል ተናግረዋል።

" ኢትዮጵያ የዩሮ ቦንድ ዕዳዋን መልሶ ለማወቀርና የክፍያ ጊዜውን ለማራዘም ያደረገችው ድርድር አለመሳካቱ እንዳለ የሚቀጥል ወይም በቀጣይ ድርድር ስምምነት የማይደረስበት ከሆነ፣ ከፓሪስ ክለብ አበዳሪዎች ተመሳሳይ የዕዳ ቅነሳና የመክፈያ ጊዜ ለማግኘት የመግባቢያ ስምምነት የደረሰችበትን ጉዳይ እንደሚያበላቸው ገልጸዋል።

የዩሮ ቦንድ አበዳሪዎች ጊዜያዊ ኮሚቴ አባላት ከኢትዮጵያ ጋርየተደረገው ድርድር ባለመሳካቱ መበሳጨታቸውንና በቀጣይከኢትዮጵያ መንግሥት የተሻሻሉ የድርድር ፍሬ ሐሳቦችን ለመስማት ዝግጁ መሆናቸውን፣ ነገር ግን አሁን ባለበት ደረጃ ድርድሩ እክል እንደገጠመውና መፍትሔ ካልተገኘም ኢትዮጵያን በሕግ እንደሚጠይቁ ገልጸዋል።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የሪፖርተር ጋዜጣ ነው።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#NGAT

የድኅረ ምረቃ ፕሮግራም የመግቢያ ፈተና (NGAT) ውጤት ተለቋል።

የ2018 ዓ.ም የመጀመሪያ ዙር የድኅረ ምረቃ ፕሮግራም የመግቢያ ፈተና (NGAT) ውጤት ዛሬ ከሰዓት መለቀቁን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከትምህርት ሚኒስቴር አረጋግጧል።

ውጤት ለማየት 👇
https://result.ethernet.edu.et/

ከ28 ሺህ በላይ ተፈታኞች ጥቅምት 03/2018 ዓ.ም በ53 የፈተና ማዕከላት  የተሰጠውን ፈተና መውሰዳቸው ይታወሳል።

ሁለተኛው ዙር የ NGAT መግቢያ ፈተና በጥር 2018 ዓ.ም ይሰጣል።

Via @tikvahuniversity

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

" የኑሮ ሁኔታ በጣም ከባድ ነው የሚከፈለን ብር 760 ነው፡፡ ... እኛ ሴቶች እንጨት ለቅመን ነው የምንማረው ወንዶችም እንጨት እየለቀሙ እየጋገሩ ይማራሉ " - የመምህራን ማሰልጠኛ ተማሪዎች

ከ40 አመት በላይ መምህራንን በማሰልጠን የሚታወቀዉ የደሴ መምህራን ማሰልጠኛ ኮሌጅ በመምህርነት በዲግሪና ዲፕሎማ የሚሰለጥኑ ተማሪዎች በወር ለምግብ የሚሰጣቸዉ 760 ብር ለመኖር ስላላስቻላቸዉ ሰዉ ቤት ተቀጥረዉ በቤት ሰራተኝነት ከጫካ ጭራሮ እየለቀሙ የራሳቸውን ምግብ ለማብሰል መገደዳቸውን ገልጸዋል።

ከእነዚህ ተማሪዎች አንዱ በእንጨት ለቀማ ወቅት ሕይወቱ እንዳለፈም ሰልጣኞቹ ተናግረዋል።

በወር የሚከፈላቸው 760 ብር ነው ፤ አንድ እንጀራ ለመግዛት የዋጋውን ውድነት አልቻሉትም ከዚህ ኑሮ ውድነት በመነሳት ወንዶች ኩሽና ተፈቅዶላቸው እንጀራ እየጋገሩ እየኖሩ ናቸው። 

ነገ ተማሪዎችን ለማስተማር የሚሰለጥኑ መምህራን የሚማሩትን ሳይሆን የሚበሉትን በማሰብ የማገዶ እንጨት በመልቀም፣ የቀን የጉልበት ሠራተኛ በመሆን፣ እንዲሁም ሊጥ አብኩተው ለምግባቸው የሚሆን እንጀራ በመጋገር ጊዜያቸውን ያሳልፋሉ ነው የተባለው።

ሰልጣኝ መምህራኑ ለዶቼ ቨለ ሬድዮ ምን አሉ ?

በ760 ብር የምግብ ወርሃዊ ክፍያ የመኖሪያ ቤት ተሰጥቷቸው በኮሌጅ የሚማሩ ተማሪዎች ከትምህርት በኋላ የሚመገቡትን ምግብ ለማብሰል በደሴ ወደሚገኙት የጦሳ፣ አዘዋና ሌሎች እንጨት ለመልቀም ወደሚያስችላቸው ጫካዎች ሲያመሩ ከሞት ጋርም ተጋፍጠዋል፡፡

ለመማር በጣም አስቸጋሪ ስለሆነ በጦሳ ተራራ እንደዚሁም በአዘዋ ተራራ ካለቀምን በስተቀር እንጨት አይገኝም ብለዋል።

በዚህም አንድ ሳሙኤል የተባለ የእንግሊዝኛ ክፍል የዲግሪ ተማሪ በጦሳ ተራራ እንጨት ሊለቅም ሄዶ ህዳር 28 ቀን ህይወቱ አልፏል፡፡

ችግሩ በተለይ ሴቶች ላይ የጎላ ነው የምትለው ሠልጣኝ ተማሪ የግማሽ ቀን የቤት ሰራተኝነትና በሌሎች ስራዎች እራሳችን እየደጎምን ነው ትምህርት የምንማረው ብላለች፡፡ 

" የኑሮ ሁኔታ በጣም ከባድ ነው የሚከፈለን ብር 760 ነው፡፡ ባለን አቅም እየሰራንም ነው የምንማረው በትምህርታችን ላይ ውጭ ውለን ስንገባ እየደከመን ማጥናት እንቸገራለን እንጨት ለቅመን ነው የምንማረው ወንዶችም እንጨት እየለቀሙ እየጋገሩ ይማራሉ " ስትል ተናግራለች።

" አሁን አሁንማ ሥራም ጠፍቷል ፤
አሁን የቀን ስራ ሰርተን ለመማር የማንችልበት ጊዜ ላይ እንገኛለን " የሚለው ተማሪ " ወቅታዊ ሁኔታው ተጨማሪ ስራ ሰርተን ለመማር አላስቻለንም " ብሏል።

" ሴቶች የግማሽ ቀን ስራ ካገኙ ይሰራሉ ወንዶች ቅዳሜና እሁድ ይሰራሉ። ዘንድሮ ግን የለም፤ መስራት አትችልም የተግባር ልምምድ ስለምንሄድ ትንሽ ከበድ ይላል። ባለፈው አመት ይሻላል ውጭ ላይም ትንሽ አስፈሪ ነው ሰዓቱ " ሲል ገልጿል።

በትምህርቱ ላይ ተፅዕኖ እየፈጠረ ነው መባሉን
የደሴ መምህራን ማሰልጠኛ ኮሌጅ መምህር የሆኑት መምህር አበበ ደሴ እንደሚገልፁት ተማሪዎች የዕለት ኑሯቸውን በማሰብ ስለሚጠመዱ ትምህርት የመቀበል አቅማቸው ውስን ሆኗል ብለዋል፡፡ 

" ግማሾች የቀን ስራ ሰርተው ነው የሚኖሩት። ሴቶችም ቢሆኑ በእንጀራ ጋጋሪና ካፍቴሪያ ውስጥ ተቀጥረው እየሰሩ ነው። ክፍል ውስጥም ገብተው ስታይ በአብዛኛዉ ከሚማሩበት የሚያንቀላፉበት ነው የሚበልጠው። ወጥተው የሚመገቡት የለም " ሲሉ አስረድተዋል።

የደሴ መምህራን ማሰልጠኛ ኮሌጅ ዲን ዶ/ር ሀሰን ወርቁ በበኩላቸው ተማሪዎቹ ያሉበት ችግር ለመማር ማስተማር ሂደቱ ላይ እንቅፋት ፈጥሯል ብለዋል።

ወርሃዊ የምግብ ክፍያቸውም ከ760 ብር ከፍ እንዲል ለክልሉ ትምህርት ቢሮ/ጥያቄ መቅረቡን አመልክተዋል።

" በአብዛኛው ከመማር ማስተማሩ ይልቅ ስለ እሚበሉት ፣የሚጠጡት ነው የሚያስቡት በትምህርት ላይ ተፅዕኖ አለው። ይህንን ታሳቢ አድርገን ክልል ላይም ጥያቄ እያቀረብን ነው፡፡ " ብለዋል።

Credit - ዶቼ ቨለ ሬድዮ

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Tigray

የትግራይ ኃይል አባላት ለአምስተኛ ቀን ያካሄዱት የመኪና መንገድ መዝጋት ያካተተ ሰልፍ ተከትሎ የክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር የሰራዊት አባላት ተጠቃሚ የሚያረጋግጥ ደንብ ማጸደቁ አስታውቋል።

እሁድ ጥቅምት 3/2018 ዓ.ም የጀመረው የትግራይ ኃይል ሰልፍና ተቃውሞ ዛሬ ቀጥሎ ከእንዳስላሰ-ሽረ ፣ አክሱም ፣ ዓድዋና ተምቤንና ሌሎች አከባቢዎች ወደ መቐለ የሚያስገባ መንገድ ተዘግቶ ውሏል።

ይህንን ተከትሎ ዛሬ ጥቅምት 7/2018 ዓ.ም ከሰዓት በኃላ የፅሁፍ መግለጫ ያወጣው የጊዚያዊ እስተዳደሩ ፕሬዜዳንት ፅህፈት ቤት ካቢኔ ጥቅምት 5/2018 ዓ.ም ያወጣው የትግራይ የፀጥታ ሃይሎች ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ረቂቅ ደንብ ዛሬ ማፅደቁን አመልክተዋል።

ካቢኔው በዛሬው አስቸኳይ ስብሰባው  የትግራይ የፀጥታ ሃይሎች ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ደንብ በዝርዝር ተወያይቶ ተግባራዊ እንዲሆን በሙሉ ድምፅ አፅድቆታል።

የፀደቀው ደንብ ፦
- መሰረታዊ ፍላጎቶች
- የህክምና አገልግሎት
- የቤት መስሪያ መሬት
- በመንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት የሚሰጥ የክብር አገልግሎት
- ትምህርት ስልጠናና ሌሎች ጥቅማ ጥቅሞች ያካተተ ነው ብሏል ከፕሬዜዳንት ፅህፈት ቤት የተሰጠው የፅሁፍ መግለጫ።

" የፀደቀው የትግራይ ፀጥታ ኃይሎች ተጠቃሚነት ደንብ ለረጅም ጊዜ ጥናት የተደረገበት ከፀጥታ አመራሮች ውይይት ሲካሄድበት የቆየ ነው " ሲል ገልጿል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Update

ወደ መቐለ የሚያመሩ መንገዶች ዛሬም ለሁለተኛ ቀን በሁለት አቅጣጫ በትግራይ ኃይል ሰልፈኞች ተዘግተዋል።

የተዘጉት መንገዶች በትግራይ ምስራቃዊ ዞን ከመቐለ በ35 ኪሎ ሜትር ርቀት በምትገኘው የኣጉላዕ ከተማ ፤ በደቡባዊ ዞን ከመቐለ 100 ኪሎ ሜትር አከባቢ በምትርቀው የመኾኒ ከተማ መሆኑ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ መረጃ ደርሶታል።

በተጨማሪ በሰሜን ምዕራብ ዞን ወደ እንዳስላሰ-ሽረ ከተማ የሚወስደው መንገድ ከከተማዋ 20 ኪሎ ሜትር ርቀት በሚገኘው እንዳባጉና ከተማ በሰልፈኞች ተዘግቷል።

ሰልፈኞቹ ጥቅምት 3/2018 ዓ.ም ከመቐለ ከተማ ወደ አሉላ አባነጋ አውሮፕላን ማረፍያ የሚወስደው ዋና መንገድ ዘግተው ውለው በዚያው ቀን ምሸት ከጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕረዜዳንት ታደሰ ወረደ (ሌ/ጀ) ተወያይተው " ጥያቄያችሁ ልክ ነው ፤ በየደረጃው ይመለሳል " ተብለው ነበር።

ጉዳዩን ተከታትለን መረጃውን የምንልክ ይሆናል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia            

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

የኢትዮጵያ መንግስት ለአካል ጉዳተኞች ጤና-ነክ መልሶ ማቋቋም እና ፆታን ታሳቢ ያደረጉ አገልግሎቶች ተደራሽ መሆናቸውን ለማረጋገጥ አግባብነት ያላቸውን እርምጃዎች በሙሉ ለመውሰድ በአለምአቀፉ የአካል ጉዳተኞች ስምምነት አንቀጽ 25 መሰረት ግዴታዎችን ተቀብሏል! በተለይም የአካል ጉዳተኞች የስነተዋልዶ እና የቤተሰብ እቅድ አገልግሎት መብቶች እውን እንዲሆኑ፤ አካል ጉዳተኞች ጾታዊ ግንኙነት፣ የስነ ተዋልዶ ጤና አገልግሎትን እንዲሁም ስነ ህዝብን መሠረት ያደረገ የህዝብ ጤና ፕሮግራሞችን በሚመለከት ከአድልዎ በጸዳ ሑኔታ እና ከሌሎች ሰዎች ጋር እኩል በሆነ መልኩ አገልግሎቶቹን የማግኘት መብት አላቸው! አካል ጉዳተኞች እነዚህን አገልግሎቶችን በሚያገኙበት ወቅት ለሌሎች ሰዎች እንደሚሰጠው ባለ ተመሳሳይ አይነት፣፣ ጥራትና ደረጃ መሆኑን ማረጋገጥ ይገባል! የስነተዋልዶ እና የቤተሰብ አገልግሎቶች በነፃ ወይም የአካል ጉዳተኞችን የመክፈል አቅምን ያገናዘቡ መሆን አለባቸው!
አካል ጉዳተኞች በአካል ጉዳታቸው ምክንያት አድልዎ ሳይደረግባቸው ሊደረስበት ለሚቻለው ከፍተኛው የጤና ደረጃ ባለቤትነት መብት እንሰራለን!
አካል ጉዳተኞችን ያካተተ የስነተዋልዶ እና የቤተሰብ እቅድ አገልግሎት ስርአት፤ለጤናማ ማህበረሰብ የእድገት እና የጥንካሬ ጉልላት።
የኢትዮጵያ የሕግ ባለሞያ አካል ጉዳተኞች ማህበር


Tel: 9110/ +251115581164
Website:
Facebook,
Twitter:
LinkedIn

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Tigray

በመቐለና ዙሪያዋ የሚገኙ የትግራይ ኃይል አባላት ትናንት ሰኞ ጥቅምት 3/2018 ዓ.ም የጀመሩት የመኪና መንገድ በመዝጋት የተደገፈ የተቃውሞ ሰልፍ ዛሬም በሌሎች አቅጣጫዎች ሲካሄድ ውሏል።

ዛሬ ማክሰኞ ጥቅምት 4/2018 ዓ.ም ከትግራይ ምስራቃዊ ዞን ወደ መቐለ ከተማ የሚያስገባው ዋና አስፋልት ከጥዋት ጀምሮ ተዘግቶ ነበር።።

ሰልፈኞቹ ኣጉላዕና ጉርመዶ በሚባሉ ሁለት ቦታዎች መንገድ በመዝጋታቸው ምክንያት መኪኖች ቆመው ተጓዦች መስተጓጎላቸው የታወቀ ሲሆን ማምሻውን መንገዶች ተከፍተዋል ብለዋል ተጓዦች።

መንገድ በመዘጋቱ ምክንያት ከፍተኛ እንግልት እንደደረሰባቸውና ሰላማዊ ሰልፈኞቹ ተቋውሟቸውን ከመንገድ መዝጋት ውጪ ቢያደርጉት የሚል ምክረ ሃሳብ ሰጥቷል።

ዛሬ ጥቅምት 4/2018 ዓ.ም ከሰዓት በኃላ መግለጫ ያወጣው  የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ፅህፈት ቤት " የሰራዊት አባላት ሰልፈኞቹ ጥያቄ ልክ ነው " ብሏል።

የሰላማዊ ሰልፈኞቹ ጥያቄዎች ኑሮን ማሻሻልና የደመወዝ ጭማሪ መሆናቸው ያስታወቀውና የተቀበለው የጊዚያዊ አስተዳዳሩ ጥያቄዎቹ እንዲፈቱ ከሚመለከታቸው አካላት በመቀናጀት እሰራለሁ ብሏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

ብሔራዊ ባንክ ዛሬ የውጭ ምንዛሪ ጨረታ አካሂዷል።

ባንኩ መሰል ጨረታ ሲያወጣ ለ10ኛው ዙር ሲሆን በዚህ ዙር  150  ሚሊዮን ዶላር ነበር ያቀረበው።

በጨረታው የአንድ የአሜሪካን ዶላር አማካይ የምንዛሪ ተመን 148.1007 ብር ሆኖ ተመዝግቧል። / 1 ዶላር በ148.1007 ተሽጧል /

ይህ አዲስ አማካኝ ዋጋ ከሁለት ወራት በፊት በ9ኛው ዙር ጨረታ ከተመዘገበው 138.2  ብር አማካይ ዋጋ ጋር ሲነጻጸር፣ የ9  ብር ከ90 ሳንቲም ወይም የ 7.16 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል።

ዛሬ በተካሄደው የውጭ ምንዛሪ ድልድል 31 ባንኮች የውጭ ምንዛሪ በማግኘት ተሳክቶላቸዋል።

ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ ገበያው በሚፈቅደው ጊዜ ጨረታዎቹን ማካሄዱን እንደሚቀጥል አስታውቋል። #ካፒታል

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

#Update

የትግራይ ኃይል አባላት ሰልፍ ዛሬም በሌላ አቅጣጫ ሰልፍ ማድረግ ቀጥለዋል።

በመቐለና ዙሪያዋ የሚገኙ የትግራይ ኃይል አባላይ ትናንት ሰኞ ጥቅምት 3/2018 ዓ.ም ከጥዋቱ 2:30 እስከ ምሽት ሰላማዊ ሰልፍ አካሂደው ነበር።

በዚያው ቀን ምሸት የሰላማዊ ሰልፈኞቹ ተወካዮች የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዚዳንት ታደሰ ወረደ (ሌ/ጀ) ከሚገኙባቸው የህወሓትና የሰራዊት አዛዦች ቢነጋገሩም ፤ ስለተደረሰው ስምምነት በይፋ ለህዝብ የተሰጠ መረጃ የለም።

ሆኖም ከሰብሰባው አዳራሽ ተቆርጦ የወጣው ቪድዮ እንደሚያመለክተው ሰላማዊ ሰልፈኞቹ የደመወዝ ፣ የጥቅማጥቅምና ለቤተሰቦቻቸው መኖሪያ የሚውል የመስሪያ ቦታ ጥያቄ አንስተዋል።

የትናንትናው ውይይት ውጤት ለህዝብ ሳይነገር ታድያ ዛሬ ማክሰኞ ጥቅምት 4/2018 ዓ.ም ከትግራይ ምስራቃዊ ዞን ወደ መቐለ ከተማ የሚያስገባው ዋና አስፋልት ከጥዋት ጀምሮ ይህ መረጃ እስከተጠናቀረበት ሰዓትና ደቂቃ በሁለት ቦታ ተዘግተዋል።

የትግራይ ኃይል አባላት ሰላማዊ ሰልፈኞች ኣጉላዕና ጉርመዶ በሚባሉ ሁለት ቦታዎች መንገድ በመዝጋታቸው ምክንያት መኪኖች ቆመዋል ተጓዦች ተስተጓጉለዋል።

ሰላማዊ ሰልፈኞቹ ጥያቄያቸው ከትናንትናው ሰልፍ ተመሳሳይ እንደሆነ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ቦታው ድረስ ደውሎ አረጋግጠዋል።

በዚህ ዙሪያ የሚኖሩ አዳዲስ መረጃዎች ተከታትለን እናቀርባለን።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Читать полностью…

TIKVAH-ETHIOPIA

ወረቀት የለም! ጊዜ ማባከን የለም!
ቀላልና ፈጣን የባንክ አገልግሎት ብቻ!

የጣት አሻራንና የፊት ገጽን እንደ መለያ የሚጠቀመው አዲሱ የአቢሲንያ ባንክ ወረቀት አልባ አገልግሎት ደንበኞች በጊዜና ቦታ ሳይገደቡ ያለማንም እርዳታ በራስ-አገዝ (Self-Service) ወይም በሠራተኞች በመታገዝ (Assisted Service) ደህንነቱ በተጠበቀና ፈጣን በሆነ መልኩ የሚፈልጉትን የባንክ አገልግሎት መጠቀም ይችላሉ፡፡ #ወረቀትአልባየባንክአገልግሎት #Paperlessbranchmodel #BanksinEthiopia #AddisAbaba #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ

Читать полностью…
Subscribe to a channel