ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። @tikvahuniversity @tikvahethAfaanOromoo @tikvahethmagazine @tikvahethsport @tikvahethiopiatigrigna #ኢትዮጵያ
#ሓሸንገ_ሃይቅ
🕯ዩኒቨርሲቲ ሊገባ የመግቢያ ቀኑን እየተጠባበቀ የነበረው ተማሪ ለሽርሽር በወጣበት ሓሸንገ ሃይቅ ላይ ህይወቱ አለፈ።
በኦፍላ ሓሸንገ ሃይቅ ምንድነው ያጋጠመው?
ተማሪ ልኡል ገ/ኪዳን በትግራይ ደቡባዊ ዞን ኮረም ከተማ አሉ ከሚባሉ ብርቱ ተማሪዎች አንዱ ነው።
በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ከፍል አገር አቀፍ ፈተና ተፈትኖ 430 ነጥብ በማምጣት ጅማ ዩኒቨርሲቲ ደርሶት ለመግባት ቅድመ ዝግጅቱ አጠናቆ በመጠባበቅ ላይ ነበር።
ጅማ ዩኒቨርስቲ የሚገባበት ቀነ ቀጠሮ ጥቅምት 6 ቀን 2018 ዓ.ም መሆኑን የተገነዘቡት ጓደኞቹ የመሸኛ ሽርሽር ዛሬ እሁድ ጥቅምት 2 ቀን 2018 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ በሓሸንገ ሃይቅ አዘጋጁለት።
ሆኖም ዝግጅቱ ተጨናገፈ ፤ ባለራዕዩ ተማሪ ልኡል ገ/ኪዳን ሓሸንገ ሀይቅ ላይ ህይወቱ አለፈ።
የተማሪ ልኡል ገ/ኪዳን አስከሬን ከብዙ ፍለጋ በኃላ ዛሬ ከቀኑ 11:30 ተገኝቷል።
የተማሪ ልኡል ገ/ኪዳን የቀብር ስነ-ስርዓት ነገ ሰኞ ጥቅምት 3/2018 ዓ.ም በኮረም ከተማ ይፈፀማል።
መረጃውን አዘጋጅቶ የላከው የቲክቫህ ኢትዮጵያ መቐለ ቤተሰብ አባል ነው።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
@tikvahethiopia
" አደጋው ከባድ በመሆኑ የተጎጂዎች ቁጥር ሊጨምር ይችላል " - ፖሊስ
በአማራ ክልል በኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር በአርጡማ ፋርሲ ወረዳ በጃራ ቀበሌ በተከሰተ በትራፊክ አደጋ እስካሁን ባለው 11 ሰዎዥ ህይወታቸው አልፏል።
የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ አዛዥ እንስፔክተር ኡመር መሀመድ አደጋው የደረሰው በጨፋ ሮቢት ከተማ ልዩ ስሙ ' ጃራ ' ድልድይ አከባቢ መሆኑን ገልጸዋል።
ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ ሲጓዝ የነበረ የሰሌዳ ቁጥሩ ኢት 73290 የሆነ ታታ አውቶቡስ እና ከደሴ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ የነበረ የሰሌዳ ቁጥሩ ኢት 41157 ተሳቢ መኪና ተጋጭተው አደጋው መድረሱን ገልጸዋል።
እስካሁን ባለው መረጃ 8 ወንድ 3 ሴት ባጠቃላይ 11 ሰዎች ህይወታቸው ሲያልፍ 23 ሰዎች ደግሞ ከባድ እና ቀላል ጉዳት እንደረሰባቸው ተናግረዋል።
አደጋው ከባድ በመሆኑ የተጎጂዎች ቁጥር ሊጨምር ይችላል ብለዋል።
@tikvahethiopia
#Afar
በአፋር ክልል ሰሜናዊ ዞን በባራሕሌ ወረዳ ትናንት ምሽት በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ እድሜው 12 ዓመት የሆነ ልጅ ህይወት ሲያልፍ 6 ሰዎች ላይ ጉዳት ደርሷል።
የሰሜናዊ ዞን አስተዳደር የመሬት መንቀጥቀጡ በዞኑ ባራሕሌ፣ ኮናባ እና ዳሎል ወረዳዎች መከሰቱን አሳውቋል።
በዚህም የ12 ዓመት ልጅ ህይወቱ ሲያልፍ 6 ሰዎች ተጎድተዋል።
በቡሬ እና ዓስጉቢ ቀበሌዎች በርካታ ቤቶች ፈርሰዋል።
በመሬት መንቀጥቀጡ 43 ሺህ 456 የሚሆኑ ሰዎች ቤታቸው ሙሉ በሙሉ መውደሙንና ያለመጠለያ ቀርተዋል።
ለተጎጂዎች ድጋፍ ለማድረግ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ዞኑ ለኤፍ ኤም ሲ ገልጿል። #ኤፍኤምሲ
@tikvahethiopia
ነፃ የትምህርት ዕድል !
የኢትዮጵያ ወጣት ወንዶች ክርስቲያናዊ ማህበር (ወወክማ)፦
➡️ ስልጠናውን ላጠናቀቁ ሰልጣኞች የራሳቸውን ስራ/ቢዝነስ ለመጀመር የገንዘብ ድጋፍ ይሰጣቸዋል!
➡️ ሴት አመልካቾች ይበረታታሉ
➡️ በፋሽን ዲዛይን የትምህርት ዘርፍ ለመሰልጠን ፍላጎት ያለው/ያላት
ለመመዝገብ የሚያስፈልጉ ሰነዶች፦
ዕድሜ ፡ ከ 18 እስከ 29 ዓመት
ፎቶ ፡ አምስት (5) ጉርድ ፎቶ
የቀበሌ መታወቂያ
የድጋፍ ደብዳቤ፦ በክፍያ መማር አለመቻልን የሚያሳይ የድጋፍ ደብዳቤ ከወረዳ
የትምህርት ደረጃ፡ 8ኛ ክፍል እና ከዚያ በላይ
አድራሻ፦ መስቀል ፍላወር፣ ቅዱስ ያሬድ ቤተክርስቲያን ፊት፣ ዶንቦስኮ ገዳም አጠገብ (ወደ ግራ 100 ሜትር ገባ ብሎ) ለበለጠ መረጃ፡ 0114160640
@tikvahethiopia
ፎቶ ፦ 6ተኛው ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር ትላንት ተጀምሯል።
ወሩ “የሳይበር ደህንነት - የዲጂታል ኢትዮጵያ መሰረት” በሚል መሪ ቃል ነው የሚከበረው።
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር በኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት ከማደጉ ጋር ተያይዞ በዜጎች፣ በተቋማት እና ቁልፍ መሰረተ ልማቶች ላይ የሚደርሰው የሳይበር ጥቃት በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል ብሏል።
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ ምን አሉ ?
" ከጥቅምት 1-30/2018 ዓ.ም 6ኛውን ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር ይከበራል።
የሳይበር ደህንነት ወሩ የሚከበረው የተቋማትን እና የኅብረተሰቡን የሳይበር ደህንነት ንቃተ-ህሊና በማጎልበት ለሳይበር ደህንነት ተገቢ ትኩረት እንዲሰጡ ለማስቻል ነው።
ወሩ ሲከበር የሃሰተኛ መረጃ ዝግጅትና ስርጭት መከላከል ላይ እና ዲጂታላይዜሽን እንዲሁም የሳይበር ደህንነት ላይ የሚያተኩር ይሆናል " ብለዋል።
የጥቅምት ወርን ሙሉ ቀናት የሕብረተሰቡንና የተቋማትን የሳይበር ደህንነት ንቃተ ሕሊና የሚያጎለብቱ ስራዎች እንደሚሰሩ ተገልጿል።
የሳይበር ደህንነት ወር በዓለም አቀፍ ደረጃ ዘንድሮ ለ22ኛ ጊዜ የሚከበር ሲሆን በኢትዮጵያ ለ6ኛ ጊዜ ነው መከበር የጀመረው።
ፎቶ ፦ INSA
@tikvahethiopia
#Earthquake
ሌላ የመሬት መንቀጥቀጥ ከዓዲግራት ደቡባዊ ምስራቅ 44 ኪ/ሜ ላይ ከደቂቃዎች በፊት ተከስቷል።
የመሬት መንቀጥቀጡ በሬክተር ስኬል 4.8 የተለካ ሲሆን ንዝረቱ በተለያዩ ከተሞችም ተሰምቷል።
@tikvahethiopia
#SocialMedia
የአሜሪካዋ ኒውዮርክ ከተማ ታላላቅ የሚባሉ የማህበራዊ ሚዲያዎችን ህፃናትን ሱስ በማስያዝ ከሳለች።
ከተማዋ ፌስቡክ፣ ጎግል፣ ስናፕቻትና እንደ ቲክቶክ ያሉ የማህበራዊ ሚዲያዎች ህፃናትን ሱስ በማስያዝ አዕምሯዊ ጤናቸውን እየጎዱ ነው በማለት 327 ገፅ ያለው ክስ በፍርድ ቤት አቅርባለች።
በኒውዮርክ ከተማ ከሚኖሩ 8 ሚሊየን ሰዎች ውስጥ 1.8 ሚሊየኑ ህፃናት ናቸው።
የጎግል ቃለ አቀባይ በዩቲዩብ ላይ የተከፈተው ክስ ትክክል አይደለም ሲሉ ዩቲዩብ ሰዎች ቪዲዮ የሚያዩበት እንጂ ከጓደኞቻቸው ጋር የሚገናኙበት የማህበራዊ ሚዲያ አይደለም ብለዋል።
በክሱ 77.3% የሚሆኑት በኒውዮርክ የሚኖሩ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች በቀን ከሶስት ሰዓት በላይ በስክሪን ላይ እንደሚያጠፉ ተገልፆ ይህም የተማሪዎቹን ጤና እየጎዳ ነው ተብሏል።
ከዚሁ ከማህበራዊ ሚዲያ ጋር በተያያዘ ዜና ዴንማርክ ከ15 ዓመት በታች ያሉ ህፃናት ማህበራዊ ሚዲያዎችን እንዳይጠቀሙ እገዳ ለማስቀመጥ እየሰራች ነው።
የዴንማርክ ጠቅላይ ሚኒስትር ሜት ፍሬድሪክሰን ማህበራዊ ሚዲያዎች" የልጆቻችንን ህፃንነት እየሰረቁ" ነው ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሯ የሃገሪቱ ህግ አውጪዎች ከ15 አመት በታች ያሉ ህፃናት ማህበራዊ ሚዲያን እንዳይጠቀሙ እንዲከለክሉ ጠይቀዋል።
በአውሮፓ ህብረት ሃገራት ህፃናት 13 አመት ሳይሞላቸው የማህበራዊ ሚዲያ አካውንት መክፈት እንደማይችሉ ቢቀመጥም ጠቅላይ ሚኒስትሯ 94 በመቶ የዴንማርክ ህፃናት እዚህ ዕድሜ ላይ ሳይደርሱ ይከፍታሉ ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሯ " ህፃናት ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ማየት የሌለባቸውን ነገሮች ያያሉ" ያሉ ሲሆን ይህም ጭንቀትና ድብርትን ጨምሮ ሌሎቸ መዘዞችን እያዋለደ ነው ብለዋል።
ዘገባዎቹ የተገኙት ከዩሮ ኒውስና ከአሌጄዘራ ነው።
Via @TikvahethMagazine
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ን የሰዎችን ከቦታ ቦታ የመዘዋወር ነጻነት በተሟላ ሁኔታ መፈጸም የሚያስችሉ እርምጃዎች በአፋጣኝ እንዲወሰዱ አሳሰበ።
በተለያዩ ክልሎች በመንገድ ላይ ለሚደርሱ ጥቃቶች ፣ እገታዎች፣ የንብረት ዘረፋዎች እና ውድመቶች የሰዎች ከቦታ ቦታ የመዘዋወር ነጻነት አደጋ ላይ እንደወደቀ ገልጿል።
መንግሥት በተለያዩ ቦታዎች የተፈጸሙ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ላይ የተሟላ ማጣራት በማድረግ ተጠያቂነትን ሊያረጋግጥ እንዲሁም በድርጊቶቹ ተጎጂ ለሆኑ ሰዎች ፍትሕ ሊያሰፍን እንደሚገባ አሳስቧል።
(ኮሚሽኑ የላከው መግለጫ ከላይ ተያይዟል)
@tikvahethiopia
#YonatanBTFurniture
የቢሮዎን እቃዎች ለመቀየር አስበዋል?
ዮናታን ቢቲ ፈርኒቸር ለቢሮዎ ግርማሞገስ፣ ምቾት፣ ጥንካሬ እና ዘመናዊነትን የሚያላብሱ የቢሮ ወንበሮች፣ ጠረጴዛዎች እንዲሁም ለቢሮዎ ያስፈልገኛል ብለው የሚያስቧቸውን ምርቶች በፈለጉት አማራጭ እና ዲዛይን አቅርበንሎታል።
ይምጡ እና ይጎብኙን!
📍አድራሻችን
1. ፒያሳ እሪ በከንቱ ቢቲ ታወር
2. ከዊንጌት አደባባይ አለፍ ብሎ ከአቢሲኒያ ባንክ ፊትለፊት
3. ከሲኤምሲ አደባባይ ወደ አያት መንገድ መሪ ሳይደርስ (ዘመን ባንክ አጠገብ)
☎️ ይደውሉልን
+251957868686/ +251995272727/ +251993828282
Telegram/Facebook/Instagram/yonatanbtfurniture?is_from_webapp=1&sender_device=pc">TikTok
#OfficeFurniture #ConferenceTables #OfficeTable
በአዲሱ ታርጋ ላይ የሚቀመጡት 3ቱ ፊደላት ምንድናቸው ? የታርጋ ቁጥሩስ እንዴት ነው የሚቀጥለው ?
በትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር አማካሪ አቶ የድልማግስት ኢብራሂም (ለኤፍኤምሲ) ፦
" ሶስቱ ፊደላት የተቀመጡት ከዚህ ቀደም ከነበሩት ከቁጥሮች አያያዝ አንጻር ችግሮች አጋጥመውን ብዙ የተሽከርካሪ ቁጥርን ሰሌዳችን ሊመዘግብ ባለመቻሉ ምክንያት ነው።
ከዚህ ቀደም የነበረው ሰሌዳ 5 ነበር ቁጥሩ ከፊት ለፊት አልፋ ቤት አለው ያ አጠቃላይ ሆኖ 9 ሚሊዮን ሰሌዳዎችን ነው ሊይዝልን የሚችለው። አሁን 1.6 ሚሊዮን ሰሌዳዎችን መዝግበናል ግን እንለጥጠው ብንል 9 ሚሊዮን ሰሌዳ ብቻ ነው የሚችለው።
አሁን በመጣው ታርጋ አልፋቤቱና አራቱ ዲጅት እስከ 121 ሚሊዮን ተሽከርካሪ ድረስ መመዝገብ ይቻላል።
ለምሳሌ ፦ AAA0000 የሚለውን ታርጋ እንውሰድ። በቀኝ በኩል ያለችው ሶስተኛዋ A የምትቀየረው ቁጥሩ 9999 (AAA9999) በሚሆንበት ጊዜ ነው። ልክ AAA9999 ሲሆን AAA የነበረው ሰሌዳ ወደ AAB ይሄዳል። ልክ AAB ሲሆን 0001 ብሎ (AAB0001) ይቀጥላል። አሁንም AAB9999 ሲደርስ B ወደ C ትሄዳለች ማለትም AAC0001 ይሆናል። "
#ማሳያ ፦
የአዲሱ ታርጋ ቁጥር የሚሄደው በዚህ መልኩ ነው።
AAA0000
⬇️
AAA9999
⬇️
AAB0001
⬇️
AAB9999
⬇️
AAC0001
... እያለ ይቀጥላል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
#ቲክቫህ_ኢትዮጵያ
@tikvahethiopia
" አሽከርካሪው ' ቁም ' የሚል የፖሊስ ትእዛዝ ጥሶ ቢያመልጥም መኪናው በጥይት ተመቶ ቆሟል " - ፖሊስ
የትግራይ ደቡባዊ ምስራቅ ዞን ፓሊስ እንዳስታወቀው ሀሙስ መስከረም 29/2018 ዓ.ም ሌሊት በአንድ አይስዙ የተጨኑና ለህገወጥ ስደት ከቤታቸው የወጡ 67 ወጣቶችን በቁጥጥር ስር እንዳዋለ ገልጿል።
አዘዋዋሪዎቹ አልተያዙም።
ወዴት ቦታና አቅጣጫ በመጓዝ እያሉ እንደተያዙ ያልገለፀው ፓሊስ ሰው አዘዋዋሪዎቹ አይስዙው ላይ ጥለዋቸው መጥፋታቸውን አስታውቋል።
የመኪናው አሽከርካሪ ጨለማ ተገን አድርጎ እያሽከረከረ እያለ " ቁም " የሚል የፓሊስ ትእዛዝ ጥሶ ቢያመልጥም መኪናዋ በጥይት ተመትታ ለመቆም ችላለች።
ወጣቶቹ " አዛዋዋሪዎቹ ' መስከረም 29/2018 ዓ.ም ከሌሊቱ 7:00 ሰዓት ኬላ ሳትፈተሹ ታልፋላችሁ ' በማለት አጓጉዘውናል " በማለት ለፓሊስ ቃላቸውን ሰጥተዋል።
ወጣቶች በህገ-ወጥ ደላሎች የሚካሄድ ህገ-ወጥ ስደት እንዲፀየፉ ያሳሰበው ፓሊስ ፤ ሰው አዘዋዋሪዎቹ እንዲያዙ የህዝብ ትብብር ጠይቋል።
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
@tikvahethiopia
#MoE
ዩኒቨርሲቲዎች ስለተማሪዎቻቸው ትክክለኛ መረጃ ካላቀረቡ ፕሬዝዳንቱን ጨምሮ ሀላፊዎቻቸው ከስራ ይባረራሉ ተባለ።
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በቀጣይ 6 ወራት ዩኒቨርሲቲዎች ስለተማሪዎቻቸውና ሌሎችም ጉዳዮች መረጃ በትክክል ለትምህርት ሚኒስቴር ማቅረብ አለባቸው ብለዋል።
ይህንን ያላደረገ የዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት በስራው አይቀጥልም ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
" ይህንን ስራ እኔ በቀጥታ እከታተለዋለሁ " ማለታቸውን ሸገር ኤፍ ኤም ዘግቧል።
ከወራት በፊት ሚኒስትሩ " ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን ከነፎቶ እንዲሁም ስለሚሠሩት ሥራ ትክክለኛ መረጃ ስጡን ብለን ከጠየቅን ሦስት ዓመት አልፎናል፡፡ ሆኖም እስካሁን የተሟላ መረጃ ለማግኘት ችግር ሆኖብናል፡፡ በዩኒቨርሲቲዎች ዘንድ እውነተኛ መረጃ መስጠት አልተለመደም " ማለታቸው ይታወሳል።
ዩኒቨርስቲዎች ከተማሪዎች ምገባ ጋር ተያይዞ የውሸት ሪፖርት ያቀርቡ እንደነበር ዩኒቨርሲቲዎች የተማሪ ቁጥር በውሸት በመጨመር በጀት እንዲጨመርላቸው ያደርጉም እንደበር ተናግረው ነበር።
#TikvahEthiopiaFamily
@tikvahethiopia
#Ethiopia
በተፈጥሮ ጋዝ የሚሰሩ ማናቸውም አይነት የደረቅና የፈሳሽ ጭነት እንዲሁም የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ከጉምሩክ ቀረጥ ነጻ ወደ ሀገር እንዲገቡ መፈቀዱን የገንዘብ ሚኒስቴር አሳውቋል።
" ኢትዮጵያ ከፍተኛ መጠን ያለው የተፈጥሮ ጋዝ ክምችት ያላት መሆኑ ቢታወቅም ለዘመናት የዚህ የተፈጥሮ ሃብት ተጠቃሚ ሳትሆን ቆይታለች " ያለው ሚኒስቴሩ " ይህንን ሁኔታ ለመለወጥ መንግስት ሲያደርግ የቆየው እልህ አስጨራሽ ጥረት ተሳክቶ በቅርቡ በካሉብ አካባቢ የሚገኘውን የተፈጥሮ ጋዝ ጥቅም ላይ ማዋል የሚያስችል ኢንዱስትሪ ተመርቆ የተፈጥሮ ጋዝ የማምረት ስራ በይፋ ተጀምሯል " ብሏል።
" ይህን ምርት ለሀገር ውስጥ ገበያ በማቅረብ ቤንዚንና ናፍታ የሚጠቀሙ ተሽከርካሪዎችን የተፈጥሮ ጋዝ በሚጠቀሙ ተሽከርካሪዎች መተካት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል " ሲል ገልጿል።
" የተፈጥሮ ጋዝ የሚያመነጨው በካይ አየር እጅግ በጣም ዝቅተኛ የሆነ፤ ለተለያየ የኃይል ምንጭ አገልግሎት ሊውል የሚችል፤ በኃይል አጠቃቀም ረገድ ውጤታማነት ያለው ነው " ብሏል።
" የተፈጥሮ ጋዝ በኢትዮጵያ የሚመረት በመሆኑ ለነዳጅ ግዥ ታወጣ የነበረውን የውጭ ምንዛሬ የሚያስቀር በመሆኑ መንግስት የተፈጥሮ ጋዝ አጠቃቀምን ለማበረታታት ወስኗል፤ በዚህም መሰረት ይህ መመሪያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሙሉ በሙሉ በተፈጥሮ ጋዝ የሚሰሩ ማናቸውም አይነት የደረቅ እና የፈሳሽ ጭነት እና የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ከጉምሩክ ቀረጥ ነጻ ወደ ሀገር እንዲገቡ ተፈቅዷል " ሲል አሳውቋል።
ይህ መመሪያ ከወጣበት ቀን በፊት በትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር እና በሌሎች ተቋማት ወደ ሀገር እንዲገቡ ከተፈቀደላቸውና በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ ወደ ሀገር ከሚገቡት በስተቀር በቤንዚን እና በናፍጣ የሚሰሩ የጭነት እና የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ወደ ሀገር እንዳይገቡ ጥብቅ ቁጥጥር እንዲደረግ ሚኒስቴሩ አዟል።
@tikvahethiopia
🌟 የአሜሪካ ደርሶ መልስ ትኬት መግዣን ጨምሮ የተለያዩ አጓጊ ሸልማቶችን ከ11% የገንዘብ ስጦታ ጋር ይሸለሙ!!
የግራንድ አፍሪካ ሩጫን አስመልክቶ እስከ ጥቅምት 21 ቀን 2018 ዓ.ም ከአሜሪካ በቴሌብር ሬሚት እና በአጋሮቻችን በኩል የተላከልዎን ዓለም አቀፍ ሐዋላ በቴሌብር ሲቀበሉ 11% የገንዘብ ስጦታ ያገኛሉ።
በተጨማሪ 300 ዶላር እና ከዚያ በላይ ሲቀበሉ
✈️ 💰 300ሺህ ብር አሜሪካ ደርሶ መልስ ነጻ የበረራ ትኬት
💻 ላፕቶፕ ኮምፒተሮች
📲 የስልክ ቀፎዎች
🌐 የብሮድባንድ ኢንተርኔት የ6 ወር ክፍያዎች
📶 ከ10,000 በላይ 1GB የሞባይል ዳታ ስጦታዎችን ለሚያሸልመው የዕድል ጨዋታ ብቁ ይሆናሉ!
ዕጣዎቹ ቴሌብር ሱፐርአፕ https://bit.ly/telebirr_SuperApp ላይ ከጥቅምት 22 እስከ ጥቅምት 28/2018 ዓ.ም ክፍት ይሆናሉ!
#Ethiotelecom #telebirr #telebirrSuperApp #DigitalEthiopia #DigitalAfrica #RealizingDigitalEthiopia
" ቅዱስነታቸው በተሟላ ጤንነት ላይ ይገኛሉ " - የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽሕፈት ቤት
ከሰሞኑ ቅዱስ ፓትርያርኩ " እንደራሴ እንዲሾምላቸው በደብዳቤ ጥያቄ አቀረቡ " በሚል በተለያዩ ማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ ሲዘዋወር ነበር።
የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽሕፈት ቤት ዛሬ ባወጣው መግለጫ፥ ቅዱስነታቸው ሐዋርያዊ ተግባራትን ለመምራት ሆነ ለማከናወን የማያስችል ምንም ዓይነት የጤና እክል እንዳልገጠማቸው አሳውቋል።
ልዩ ጽሕፈት ቤቱ ፥ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ላለፉት ተከታታይ ዓመታት ወደ ሰሜን አሜሪካ በማምራት የሕክምና ክትትል ሲያደርጉ እንደቆዩ ፤ በቅርቡም ተመሳሳይ ጉዞ አድርገው ጳጉሜን 1 ቀን 2017 ዓመተ ምሕረት ወደ ሀገራቸው ኢትዮጵያ መመለሳቸውን አስታውሷል።
የመስቀል ደመራ በዓልንም በመስቀል አደባባይ ተገኝተው በማክበር ለመላው ሕዝበ ክርስቲያን አባታዊ ትምህርተ ወንጌል ፣ ቃለ ምእዳንና ቡራኬ እንዳስተላለፉም አስታውሷል።
እንዲሁም ቤተክርስቲያኗ በየዕለቱ የምታከናውናቸው መንፈሳዊ፣ ማኅበራዊ እና ዓለም አቀፍ ተግባራትን በጽሕፈት ቤታቸው ሆነው በአባትነት እየመሩ በተሟላ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ገልጿል።
" ይሁን እንጂ ድብቅ አጀንዳ ይዘው ሐሰተኛ መረጃን በማሰራጨት መደበኛውን የቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊ ተልእኮ ማደናቀፍ ዓላማቸው ያደረጉ አካላት በማኅበራዊ የትስስር ገጾቻቸው ባጋሩት ፍጹም ከእውነት የራቀ መረጃ ውሉደ ክህነት እና በጎ ሕሊና ያላቸው ምእመናን በእጅጉ መጨነቃቸውን ለመገንዘብ ችለናል " ብሏል።
" ስለሆነም ቅዱስነታቸው ሐዋርያዊ ተግባራትን ለመምራትም ሆነ ለማከናወን የማያስችል ምንም ዓይነት የጤና እክል ያልገጠማቸው፤ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ያቀረቡት ጥያቄ የሌለ መሆኑን እንገልጻለን " ሲል ልዩ ጽሕፈት ቤቱ አሳውቋል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#እንድታውቁት
ከነሐሴ 1 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ በከፊል ዝግ ሆነው የቆዩት የፌደራል ፍርድ ቤቶች ከሰኞ ጥቅምት 3/2018 ዓ/ም ጀምሮ መደበኛ አገልግሎት መስጠት ይጀምራሉ።
የፌደራል ፍርድ ቤቶች ዳኞች የሚሰጡት የዳኝነት አገልግሎት ክብደትና ዉስብስብነትን ግምት ውስጥ በማስገባት በቂ እረፍት እንደሚያስፈልጋቸው ታምኖበት በየዓመቱ መጨረሻ ለተከታታይ ለሁለት ወራት ማለትም ከነሐሴ 01 እስከ መስከረም 30 በከፊል ዝግ እንደሚሆኑ ይታወቃል።
ፍርድ ቤቶቹ በከፊል ዝግ ሆነው በሚቆዩባቸው የሁለት ወራት ጊዜ በባህሪያቸዉ አስቸኳይ የሆኑና ጊዜ የማይሰጡ እንዲሁም ለዉሳኔ የደረሱ መዛግብትን መርምረው ውሣኔ የመስጠት አገልግሎቶች ቀጥለው ቆይተዋል።
በከፊል ዝግ ሆነው የቆዩት ፍርድ ቤቶች ከሰኞ ጥቅምት 3 ቀን 2018 ዓም ጀምሮ መደበኛ አገልግሎታቸውን መስጠት እንደሚጀምሩ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አሳውቋል።
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት አድራሻም ቀድሞ ከነበረበት አድራሻ በመቀየር ከአብረሆት ቤተ መጸሕፍት 100 ሜትር ዝቅ ብሎ ፍርድ ቤቱ አዲስ እያስገነባ ባለው ህንጻ ውስጥ የሚጀምር መሆኑን ገልጿል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#Tigray
ጥቅምት 1/2018 ዓ.ም የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት በትግራክ 6 የመኖሪያ ቤቶች አፈረሰ።
የመሬት ንዝረቱ ዛሬም ተከስቷል።
በትግራይ ክልል ከምስራቃዊ ኣፅቢ ወምበርታ ወረዳ 26 ኪ/ሜ ርቀት ላይ የተከሰተው በሬክተር ስኬል 5.6 የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከትሎ በቃል ኣሚን ቀበሌ ገበሬ ማህበር ቡሐለ መንደር 6 ቤቶች በከፊል እንደፈረሱ ወረዳው አሳውቋል።
እንደ ትናንትናው ከበድ ባይሆንም ዛሬ ጥቅምት 2/2018 ዓ.ም የመሬት ንዝረቱ በተወሰነ መልኩ መቀጠሉ የገለፀው የወረዳው አስተዳደር በሰው ፣ በእንስሳትና በንብረት ያስከተለው አደጋ እንደሌለ ገልጿል።
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
@tikvahethiopia
“ በርህሌ አካባቢ ሰዎች በቤት ውስጥ እያሉ ቤቶች ፈርሰው ሰዎች ላይ አደጋ ደርሷል፣ ለህክምና ወደ ሆስፒታሎች ሂደዋል ” - ፕሮፌሰር አታላይ አየለ
መቐለ ከተማና አካባቢው ከትላንት ጀምሮ ተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ እንደተከሰተ፣ ይህም በተለያዩ የክልሉና አጎራባች ቦታዎች እንደተሰማ ተነግሯል፡፡
ለአደጋው መከሰት ምን የተለየ ምክንያት አለ? ስንል የጠየቅናቸው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦ ፊዚክስ ስፔስ ሳይንስና አስትሮኖሚ ኢንስቲትዩት ተማራማሪ ፕ/ር አታላይ አየለ፣ “በቆላማው የአፋር ክፍልና በደጋማው ክፍል በግልጽ የሚታይ ዝንፈት አለ፣ በተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ የሚያዘወትረው ቦታ ነው” ብለዋል፡፡
“አሁን በተፈጠበት አካባቢ በተደጋጋሚ ተፈጥሮ ያውቃል፡፡ ትላንት ከእኩለ ቀን ጅምሮ ከ4.2 በሬክተር ስኬል ጀምሮ እስከ 5.6 ከፍተኛው የሆነ መሬት መንቀጥቀጥ ከሰሜን ምሥራቅ መቐሌ ጀምሮ እስከ ምሥራቅ መቐለ ድረስ ተሰምቷል” ሲሉም ገልጸዋል፡፡
“በርህሌ አካባቤ ጉዳት እንዳዳረሰ እየተዘገበ ነው፡፡ ሰዎች በቤት ውስጥ እያሉ ቤቶች ፈርሰው ሰዎች ላይ አደጋ ደርሷል፣ ለህክምና ወደ ሆስፒታሎች ሂደዋል”፣ ያሉት ፕሮፌሰር አታላይ፣ ይህ ክስተት በዚህ ጊዜ ይመጣል ተብሎ “የሚተነበይ" እንዳለሆነም ተናግረዋል፡፡
ጉዳት ያስተናገዱት ቤቶች ደረጃቸውን ያልጠበቁ ሊሆኑ እንደሚችሉ ጠቅሰው፣ “ደረጃውን የጠበቀ ህንጻ ቢሆን ኑሮ እንደዚህ አይፈጥርም ነበር” ሲሉም ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ የመሬት መንቀጥቀጥ ተጋላጭ አገር መሆኗን፣ በዚህም በሂደት ያለ የስምጥ ሸለቆ ተፈጥሮ እያስተናግደን ስለሆነ ከቀይ ባህርና ከአፋር አካባቢ ጀምሮ በድሬዳዋን፣ ናዝሬት፣ ሀዋሳ፣ አርባምንጭ እያካለለ እንደሚሄድ ገልጸዋል፡፡
አሁን በትግራይ የተፈጠረው የመሬት መንቀጥቀጥ ከፍተኛው 5.6 ስኬል እንደሆነና የተጋነነ እንዳልሆነ አብራርተው፣ “በዚያው ይቀራል ብለን ተስፋ እናደርጋለን” ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል፡፡
“5.6 የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል፤ እንኳ 5.6 ሦስትና ሁለት” ያሉት ተመራማሪው፣ የት ነው አደጋው የተፈጠረው? የሚለው እንደሚወስነው፣ የሬክተር ስኬሉ ሁለት የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥም ቢከሰት ቤት እንደሚያፈርስ አስረድተዋል፡፡
ምን ጥንቃቄ መደረግ እንዳለበት ሲያስረዱ ደግሞ፣ “የግንባታ ደረጃን ማሻሻል” እንደሚገባ ገልጸው፣ በስምጥ ሸለቆ ዙሪያ የሚሰሩ ቤቶች ትንሽም ቢሆኑ ተደርምሰው አደጋ ሊያደርሱ እንደሚችሉ ገልጸዋል፡፡
እንዲሁም በፈንታሌው ጊዜ እንደተማርነው ባለመረበሽ ግንዛቤ መውሰድ እንደሚያስፈልግ መክረዋል፡፡
“መሬት መንቀጥቀጡ ብቻውን ምንም ጉዳት ሊያደርስ አይችልም” ብለው፣ ግን ከህንጻና ከመሰረተ ልማት አጠገብ፣ ከቮልቴጅ አካባቢ ከሆነ አደጋ እንደሚያደርስ አስረድተዋል፡፡
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
“ በተያዘው ዓመት ለመጀመሪያ ጊዜ የሪሜዲያል ተፈታኞችን እቀበላላሁ ” - ኢንስቲትዩቱ
የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት በ2018 ዓ/ም ለመጀመሪያ ጊዜ የሪሜዳል ተፈታኞችን እንደሚቀበልና አዲስ የተቀረጹ የስልጠና መርሃግብሮችንም ይፋ እንዳደረገ ገልጿል።
የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ያመጡ ተማሪዎችን ተቀብሎ እስከ 3 ዲግሪ ባሉት ደረጃዎች እንደሚያሰለጥን ያስታወቀው ተቋሙ፣ በዚሁ ዓመት ለመጀመሪያ ጊዜ የሪሚዳል ተፈታኞችን እንደሚቀበልም ጠቁሟል፡፡
በመደበኛው በቅዳሜ እና እሁድ እንዲሁም በክረምት የስልጠና መርሃግብሮች ከደረጃ ስድስት እስከ 8 (ከመጀመሪያ እስከ 3ኛ ዲግሪ) የቴክኒክና ሙያ ስልጠና አንደሚሰጥ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ብሩክ ከድር (ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡
ኢንስቲትዩቱ ሰልጣኞችን የሚቀበልባቸው አራት መንገዶች ምን ምን ናቸው?
- ደረጃቸውን ለማሻሻል የቴክኒክና ሙያ አመራሮችና ሰልጣኞችን፣
- የኢንዱስትሪ ቴክኒሻኖችን በማታው፣ በቅዳሜና እሁድ ፕሮግራሞች፣
- የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስደው የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ውጤት ያመጡትን፣ እንዲሁም የሪሜዳል ተፈታኞችን (ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ) እንደሚቀበል ነው የገለጸው፡፡
ተደራሽነቱ ምን ይመለስላል?
ኢንስቲትዩቱ በአዲስ አበባ ከሚገኘው ዋና ካምፓሱ በተጨማሪ የሀዋሳ ካምፓስና የብየዳ ስልጠና ልህቀት ማዕከል ካምፓሶች፣ በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች በሚገኙ 16 የሳተላይት ተቋማት በደረጃ 6 ወይም በመጀመሪያ ዲግሪ ስልጠና እየሰጠ መሆኑን አስረድቷል፡፡
አዲስ የተቀረጹት አጫጭር የስልጠና መርሃግብሮች ምንድን ናቸው?
በዘንደሮው አመት 11 አዳዲስ የስልጠና ፕርግራሞች ከመታከላቸው በተጨማሪ አዳዲስ የተቀረጹ የአጭር ጊዜ የስልጠና መርሃ ግብሮችም ይፋ ተደርገዋል፡፡ በዚህም፦
- በሲቪል ቴክኖሎጂ፣
- በኤሌክትሪክ እና አይሲቲ፣
- በመካኒካል ቴክኖሎጂ፣
- በቴክስታይል እና አፓረል፣
- በአግሪካልቸራል እና አግሮፕሮሰሲንግ፣
- በሉባን ወርኪንግ የሚሰጡ ሲሆኑ፣ በእነዚህ ስር ያሉ ዝርዝሮችና ሌሎች የስልጠና ዝርዝሮች ከላይ ተያይዘዋል፡፡
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
" የውሃ አገልግሎት በከፊል እና ሙሉ ለሙሉ ስለሚቋረጥ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት አድርጉ " - ውሃ እና ፍሳሽ ባለሥልጣን
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውሃ እና ፍሳሽ ባለሥልጣን የለገዳዲ ግድብ የጥሬ ውሃ ማስተላለፊያ ቫልቭ ቅየራ ስራ ከጥቅምት 2/2018 ዓም እስከ ጥቅምት 16/2018 ዓም ድረስ የሚከናወን መሆኑን ገልጿል።
የጥገና ስራው እስከሚጠናቀቅም በአንዳንድ የከተማዋ አካባቢዎች የውሃ አገልግሎት በከፊል እና ሙሉ በሙሉ የሚቋረጥ ይሆናል ብሏል።
የውሃ አገልግሎት በከፊል የሚቋረጥባቸው አካባቢዎች :-
- በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2፣ 3፣ 5፣ 8፣ 9፣ 10 እና 13
- በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1፣ 2፣ 3፣ 4፣ 5፣ 6፣ 7፣ 11፣ 13 እና14
- በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1፣ 2፣ 3፣ 7፣ 8፣ 10 እና 11
ስራው እስከሚጠናቀቅ የውሃ አገልግሎት በከፊል እና ሙሉ ለሙሉ ስለሚቋረጥ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንድታደርጉ ሲል ባለሥልጣኑ አሳስቧል።
Credit - AAWSA
@tikvahethiopia
#Afar #Tigray
ዛሬ በትግራይ እና አፋር ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ተደጋግሞ የተሰማ የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት ተከስቷል።
የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ ይፋ ባደረገው መረጃ በተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት ተሰምቷል።
የመጀመሪያው ከመቐለ ሰሜን ምስራቅ 47 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ 4.2 በሬክተር ስኬል የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቶ ነበር ፤ ንዝረቱ በተለያዩ የትግራይ እና አፋር አካባቢዎች ተሰምቷል።
ከዚህ ቀጥሎ ከመቐለ ሰሜን ምስራቅ 58 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ 5.3 በሬክተር ስኬል የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቶ ንዝረቱ መቐለን ጨምሮ በርካታ ከተሞች ተሰምቷል።
ቅርብ ሰዓት ደግሞ በሬክተር ስኬል 5.6 የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ ከመቐለ ሰሜን ምስራቅ 53 ኪሎ ሜትር ላይ ተከስቶ ነበር።
@tikvahethiopia
“ጠዋት በተኙበት ነው እናትና አባቴን የገደሉብኝ፤ ታናሽ እህታችንም ታግታለች” - የሟቾች ልጅ
➡️ “ አራት ሰዎች ተገድለዋል፤ ስድስት ደግሞ ታግተዋል፣ 81 የግለሰብ ከብቶች ተወስደዋል ” ባለስልጣን
በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ወረጃርሶ ወረዳ ጊርሚጎባ ቀበሌ ታጣቂዎች በንጹሐን ላይ የሞትና እገታ፣ በንብረት ላይ የውድመት ጥቃት ማድረሳቸውን ነዋሪዎችና ባለስልጣን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡
ነዋሪዎቹ፣ መስከረም 29 ቀን 2018 ዓ/ም፣ “ህዝቡ በተኛበት ንጋት 11 ሰዓት አካባቢ ተኩስ ከፍተው አራት ሰዎች ገድለዋል፤ ስድስት ሰዎች አግተዋል፤ ቤትም አቃጥለዋል” ብለዋል፡፡
“ወደ 100 ከብቶች” እንደተነዱና “ወደ 100 ቤቶች” እንደተቃጠሉ፣ ጥቃቱን ያደረሰው "ሸኔ" እንደሆነ ገልጸው፣ “ከሦስት ወራት በፊትም ተራራ ላይ መሳሪያ አጥምደው አጋምሳ መንደርን አቃጥለው ዘጠኝ ሰዎች ገድለዋል” ሲሉም አስታውሰዋል።
ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡ የሁለት ሟቾች ልጅ፣ "ጠዋት 12 ሰዓት አካባቢ በተኙበት ነው እናትና አባቴን የገደሉብኝ፤ ታናሽ እህታችንም ታግታለች፡፡ ከብቶችንም ወስደዋል " ብለዋል።
“አባቴ ከአመት በላይ ታሞ ተኝቶ ነበር፤ እግሩ ተዘርግቶ መሄድ አይችልም በበሽታ ምክንያት፤ እናቴ ደግሞ ሌላው ሰው ሲሸሽ 'ባለቤቴን ትቼ አልሄድም' ብላ እዚያው ሲያገኟቸው ገደሏቸው " ሲሉ ገልጸዋል።
" ሸሽቶ ስለነበር በሰዓቱ ብዙ ሰው የለም ነበር፤ ባለው ትንሽ ሰው በአንድ ጉድጓድ ነው የተቀሩት፡፡ እኔ የሟቾች ልጅ ነኝ። መንግስት እንዲህ ያለጥቃት እንዲቆም መስራትና ለተጎጂዎች መድረስ አለበት ” ሲሉ አስገንዝሸዋል።
ስለጥቃቱ ማረጋገጫ የተጠየቅናቸው አንድ የቀበሌው ከፍተኛ አመራር በበኩላቸው፣ “አራት ሰዎች ገድለዋል፤ ስድስት ታግተዋል፣ 81 የግለሰብ ከብቶች ተወስደዋል። በአካባቢው ነበርኩ በርካታ ጥይቶች ተተኩሰውብናል፡፡ 50 የሚጠጉ ቤቶች ተቃጥለዋል፡፡ አንድ የህዝብ ወፍጮ ተቃጥሏል” ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
ቀበሌውን ከወረዳው በስተደቡብ “አብዛኛዎቹ በሸኔ ታጣቂዎች የተያዙ” ቀበሌዎች እንደሚያዋስኑት ገልጸው፣ “ከዚህም በፊትም ከአንዴም ሁለት ጊዜ ነዋሪውን ለማጥቃት ተሞክሯል፡፡ መስከረም 29/2018 ዓ/ም የደረሰው ጥቃት ግን ከምንም በላይ የከፋ ነበር” ነው ያሉት፡፡
እኝሁ አካል፣ ጥቃቱ ከተፈጸመት “ከንጋት ከ11 ሰዓት ጀምሮ ለሚመለከተው አካል ደውለናል፤ ግን ጎሃጽዮን ታጣቂዎች መኪና ራሱ እንዳይወጣ የሚያደርጉበት በመሆኑ መከላከያ አልደረሰልንም” ነው ያሉት፡፡
“ከዚህ በፊት ጥቃት ተፈጽሞ በአንድ ቀን ስምንት ሰዎች ተገድለዋል፡፡ 47 ቤቶች ተቃጥለዋል፤ በርካታ ሰዎችም ታግተው ገንዘብ ከፍለው የተመለሱ አሉ” ሲሉ ያስታወሱት አመራሩ፣ ጥቃቱ እየተደጋገመ መሆኑን አልደበቁም፡፡
ቀሪ ነዋሪዎች ዳግም እንዳይጠቁ ምን እየተሰራ እንደሆነ ሲያስረዱ ደግሞ፣ መከላከያ በቋሚነት በአካባቢው እንዲመደብ እንዳሳሰቡና ህዝቡ ራሱን እንዲከላከል አቅጣጫ እንደተቀመጠ ገልጸዋል፡፡
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#SafaricomEthiopia
ቀጣይ የ1 ሚሊየን ዕደለኛ ማን ይሆን! 2ቀን ብቻ ቀረው! 🏆💚 ዛሬዉኑ የበሽ ጥቅልን ይግዙ፤ ሚሊየነር የመሆን እድሎን ያስፉ!
📲 የM-PESA መተግበሪያን አሁኑኑ ያውርዱ፡
https://onelink.to/ewsb22
የቴሌግራም ቦታችን: /channel/official_safaricomet_bot
ወደ *777*0# ይደውሉ ወይም በM-PESA የበሽ ጥቅል ይግዙ!
#MPESASafaricom
#furtheraheadtogether
#Besh
#AbayBank
ዓባይ ባንክ የ15ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን ምክንያት በማድረግ ከኢትዮጵያ ደም ባንክና የሕብረ ሕዋስ አገልግሎት ጋር በመተባበር በሀገር አቀፍ ደረጃ የደም ልገሳ መርሀ ግብር ማካሄድ ጀምሯል።
በደም ልገሳ ማስጀመሪያ መርሀ ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የዓባይ ባንክ የስትራቴጂ ዋና መኮንን አቶ ወንድይፍራው ታደስ በዛሬው እለት በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በ6 ቅርንጫፎች ደም እየተለገሰ መሆኑን ገልጸዋል።
"በቀጣይ ሰኞም ደም ልገሳው ይቀጥላል፣ ወደ 90 የሚሆኑ ሰዎችም ደም ይለግሳሉ የሚል እቅድ አለን። በሀገር አቀፍ ደረጃ ከ600 በላይ ለጋሾች ደም ይለግሳሉ ብለን እናስባለን" ሲሉ ተናግረዋል።
አክለው በሁሉም ቅርንጫፍቻችን ከሚገኙ ሠራተኞቻችን፣ ደንበኞቻችንና ከመላው የባንካችን ቤተሰቦች ከተውጣጡ ከ1ሺህ በላይ በጎ ፈቃደኛ ደም ለጋሾችን በማንቀሳቀስ ለሕይወት አድን ዓላማ ቀጥተኛ አስተዋጽዖ በማድረጋችን ደስተኞች ነን ብለዋል፡፡
"ይህ የበጎ አድራጎት ሥራ የ15 ዓመት ጉዟችንን በድምቀት ለማክበርና ለማኅበራዊ ኃላፊነት ያለንን ዘላቂ ቁርጠኝነት ያጠናክራል" ሲሉ ነው የተናገሩት።
በዚህ መርሐግብር ላይ የተገኙት በኢትዮጵያ ደም ባንክና የሕብረ ሕዋስ አገልግሎት ውስጥ የደም ለጋሾች ተወካይ ደስክ ሃላፊ ሙላት በቀለ በበኩላቸው አባይ ባንክ በመላዊ ሀገሪቱ በሚገኙ ቅርንጫፎቹ የደም ልገሳ ፕሮግራም በማካሄድ የወገንን ህይወት እየታደገ ነው ሲሉ ተናግረዋል።
በባለፉት በዓላት ወቅት ከፍተኛ የሆነ የደም እጥረት ተከስቶ እንደነበር ያስታወሱት ሃላፊው "አባይ ባንክ እጥረቱን በመገንዘብ በዛሬው እለት ሰራተኞቹ ደም እንድለግሱ እያደረገ ነው። በሚተካ ደም የማይተካውን የሰው ልጅ ህይወት ለማዳን ፕሮግራሙን በማዘጋጀቱም ደስ ብሎናል" ሲሉ ነው የገለጹት።
አባይ ባንክ ከ71 ቢሊዮን በላይ ተቀማጭ ገንዘብ፣ 7 ቢሊዮን ብር የተከፈለ ካፒታል እንዲሁም ጠቅላላ ሀብቱ 91 ቢሊዮን ብር መድረሱም ተነስቷል።
#ዓባይባንክ
Proud to D🩸nate
አዲሱን የተሽከርካሪ መለያ ሰሌዳ (ታርጋ) ለመቀየር ስንት ነው የሚከፈለው ?
አዲሱ የተሽከርካሪ መለያ ሰሌዳ (ታርጋ) በሚቀየርበት ጊዜ ወጪውን እራሳቸው የተሽከርካሪ ባለንብረቶች እንደሚሸፍኑት የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር ማሳወቁ ይታወሳል።
ክፍያውን በተመለከተ ግን እስካሁን ምን ያህል ይሁን የሚለው ተቆርጦ አልተቀመጠም ሲል ሚኒስቴሩ ገልጿል።
በሚኒስቴሩ አማካሪ የሆኑት የድልማግስት ኢብራሂም ለፋና ቴሌቪዥን በሰጡት ቃል " እስካሁን ክፍያው ተቆርጦ አልተቀመጠም። አሁን እየተሰራ ያለው ሲስተም የመዘርጋት ነው። ይህ ነው መጀመሪያ የሚጠናቀቀው " ብለዋል።
የተሽከርካሪ ባለንብረቶች እስከዛው የተሽከርካሪውን ሙሉ መረጃ አደራጅተው መጠበቅ እንዳለባቸው ጠቁመዋል።
ታርጋ በመቀየሩ ሂደት የምርመራ ማዕከላት እንደሚኖሩና ተሽከርካሪዎቹ ሄደው መመርመር እንዳለባቸው ፤ ተመርምረውም ህጋዊ ሰነዳቸውን ይዘው በሚወጣላቸው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ቀጥታ ሰሌዳቸውን እንደሚቀይሩ አስረድተዋል።
#ታርጋ #ኢትዮጵያ
@tikvahethiopia
" አራት አርሶ አደሮችን ከቤት በማውጣት በጥይት ደብድበው ገድለዋል፤ 10 ሰዎች አግተው ወስደዋል" - ነዋሪዎች
➡️ " የስንት ሰው ሕይወት አለፈ የሚለውን ዝርዝር መረጃ ገና እያጣራን ነው ያለነው " - የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ
በምሥራቅ ጉራጌ ዞን ሶዶ ወረዳ ታጣቂዎች አደረሱት በተባለ ጥቃት በንጹሐንና በቤት ላይ ጉዳት መድረሱን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል፡፡
የአካባቢው ነዋሪዎች ታጣቂዎች ትላንት በፈጸሙት ጥቃት ንጹሐን መገዳቸውን የገለጹ ሲሆን፣ ስለጉዳዩ ማብራሪያ የጠየቅናቸው የቢሮው ኃላፊ አቶ ተመስገን ካሳ በበኩላቸው፣ ጥቃት ተፈጽሟል መባሉ እውነት መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡
" የሸኔ ጽንፈኞች ትላንትና ማምሻውን በሰዶ ወረዳ ሰመሮ አካባቢ ገብተው እየተታኮሱ እንደነበርና ቤቶች ላይም ጉዳት እንዳደረሱ መረጃው አለን " ብለዋል፡፡
" የስንት ሰው ሕይወት አለፈ የሚለውን ዝርዝር መረጃ ገና እያጣራን ነው ያለነው " ሲሉም አክለዋል፡፡
ታጣቂዎች በተለያዩ ጊዜያቶች እንደዚህ አይነት ጥቃቶችን ሰነዘሩ ሲባል ይደመጣል፤ ጉዳዩ መፍትሄ እንዲያገኝ ምን እየተሰራ እንደሆነ ስንጠይቃቸውም፣ " ይሄኮ ታጣቂ አይደለም፤ ጽንፈኛ ሸኔ ነው ሌላ የመንግስት ታጣቂ አይደለም ጉዳት እያደረሰ ያለው " ብለዋል፡፡
" አሳቻ ሰዓት ተጠቅሞ ነው ይህ ድርጊት ፈጸመ የሚል መረጃ ደረሰን " ያሉት ኃላፊው፣ ስለዝርዝር ጉዳቱን ገና መረጃዎች እያጣሩ እንደሆነና በአካባቢው ተመሳሳይ ችግር እንዳይፈጠር ጥበቃ የማጠናከር ሥራ እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
የአካባቢው ነዋሪዎች በበኩላቸው፣ ታጣቂዎች ትላንት 12 ሰዓት ገደማ ባደረሱት ጥቃት አራት ሰዎች ተገድለው አሥር ደግሞ ታግተዋል ማለታቸውን ዶቼቨሌ ዘግቧል፡፡
ሦስት ነዋሪዎች፣ ከአጎራባች የኦሮሚያ ክልል ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን የተሻገሩ ናቸው ያሏቸው ታጣቂዎች እየተኮሱ መንደሩን መክበባቸውን ተናግረው፣ " አራት አርሶ አደሮችን ከቤት በማውጣት በጥይት ደብድበው ገድለዋል " ነው ያሉት፡፡
ሌሎች ነዋሪዎች ተደናግጠው ከመንደሩ ሲሸሹም " 15 የመኖሪያ ጎጆዎችን በእሳት አቃጥለዋል፡፡ ማምለጥ ያልቻሉ ሴቶችና ህጻናትን ጨምሮ 10 ሰዎችን አግተው ወስደዋል " ሲሉም ነዋሪዎቹ ተናግረዋል፡፡
የአራቱን አስከሬን ዛሬ እንደቀበሩና የታገቱት ደግሞ ይኑሩ ይሙቱ እንደማይታወቅ ገልጸዋል፡፡
(ጉዳዩን የምንከታተለው ይሆናል)
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#Ethiopia
በቤንዚን እና በናፍጣ የሚሰሩ ከባድ ተሽከርካሪዎች ወደ ሀገር እንዳይገቡ ተከልክሏል።
በተፈጥሮ ጋዝ የሚሰሩ የጭነትና የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ከጉምሩክ ቀረጥ ነፃ እንዲገቡ መመሪያ ወጥቷል።
ይህ መመሪያ ከወጣበት ቀን በፊት በትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር እና በሌሎች ተቋማት ወደ ሀገር እንዲገቡ ከተፈቀደላቸውና በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ ወደ ሀገር ከሚገቡት በስተቀር በቤንዚን እና በናፍጣ የሚሰሩ የጭነት እና የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ወደ ሀገር እንዳይገቡ ክልከላ ተላልፏል።
@tikvahethiopia
" በሚቀጥሉት ዓመታት የተማሪዎች ምደባ ይቆማል " - ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ
ትምህርት ሚኒስቴር በሚቀጥሉት ዓመታት የተማሪዎች ምደባ እንደሚያቆም ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ አስታወቁ።
ይህ ያሳወቁት የትምህርት ሚኒስቴር ከመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ጋር የ2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የቁልፍ ተግባራት የፊርማ ስነስርዓት ባከናወነበት ወቅት ነው።
በዚሁ ወቅት ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ጠንካራ የስራ አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡
ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ እንደገለፁት፤ በሚቀጥሉት ዓመታት የትምህርት ሚኒስቴር የተማሪዎችን ምደባ እንደሚያቆምና የማለፊያ ነጥብ የሚያስመዘግቡ ተማሪዎች በሚፈልጓቸው ዩኒቨርሲቲዎችና የትምህርት መስኮች እንዲያመለክቱ ይደረጋል፡፡
" የዩኒቨርሲቲ ትምህርት እንደከዚህ ቀደሙ በትምህርት ሚኒስቴር ምደባ ሳይሆን በተማሪዎቹ ምርጫ ይሆናል " ብለዋል።
" ተማሪዎች የሚማሩበትን ዩኒቨርሲቲ ሲመርጡም ምክንያታዊ በመሆን በዬትኛው ዩኒቨርሲቲ የተሻለ የትምህርት መስክ፣ እውቀትና የስራ እድል ላገኝ እችላለሁ በማለት ይመርጣሉ " ሲሉ ገልጸዋል። #ኢፕድ
@tikvahethiopia
" የትግራይ ህዝብ ' ከሻዕቢያ መንግስት ጋር የሚደረግ ትብብር/ፅምዶ አልፈልግም ' ነው ያለው " - ሌ/ጄነራል ፃድቃን ገብረትንሳኤ
ትግራይ የሚገኙት የህወሓት አመራሮች ከሻዕቢያ (ከኢሳያስ መንግሥት ጋር) ሽርክና በመፍጠር ጦርነት ለመቀስቀስ እየሰሩ እንደሚገኙ የቀድሞ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር አመራር ሌ/ጄነራል ፃድቃን ገብረትንሳኤ ተናገሩ።
ይህን የተናገሩት ኤን ቢ ሲ - ኢትዮጵያ ከተባለ የቴሌቪዥ ጣቢያ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ነው።
ሌ/ጄነራል ፃድቃን ፤ የህወሓት ሰዎች ከኢሳያስ መንግስት ጋር በማበር ጦርነት ለመቀስቀስ እየሰሩ ያሉት የወንጀል ስራዎቻቸውን ለመሸፈን እንደሆነ ጠቁመዋል።
" የወንጀል ስራዎች እና ወደ ጦርነት የተገባበት ውሳኔ እራሱ (የቀድሞው ጦርነት) accountable መሆን አለበት " ብለዋል።
ሌ/ጄነራሉ ፥ እጅግ በጣም ብዙ የጠፉ ፣ የተሰረቁ ፣ የተዘረፉ ንብረቶች፣ ወርቅ፣ መሬት ፣ ገንዘብ እንዳለ ጠቁመዋል። በዚህ የወንጀል ተግባር ውስጥ በግልጽ የሚታወቁ ትላልቅ አመራሮች እንዳሉበት ገልጸዋል።
እነዚህ አካላት የወንጀል ስራዎቻቸውና የፖለቲካ ስልጣን ፍላጎታቸው አንድ ላይ እንደተቀላቀሉ ፤ ይህን ለመከላከል ወይም ከሰሯቸው የወንጀል ስራዎች ነጻ ለመሆን የሚያስችላቸው አንዱ መንገድ #ጦርነት መፍጠር እንደሆነ እንደሚያምኑ አመልክተዋል። ለዚህም " ከኢሳያስ መንግሥት ጋር መተባበር ነው - ፅምዶ " ብለው እየሰሩበት እንደሆነ ገልጸዋል።
" የትግራይ ህዝብ እያንዳንዱ የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ አውቆባቸዋል " ያሉት ሌ/ጄነራሉ ፤ የትግራይ ጄኖሳይድ ኮሚሽን ባጠናው ጥናት በትግራይ ጦርነት ወቅት 75% የግፍና የወንጀል ስራዎችን የሰራው የኤርትራ ሰራዊት እንደሆነ መመላከቱን ተናግረዋል።
- ሰው የገደለው
- ሴቶች የደፈረው
- ሴቶች ማዕፀን ላይ ያልሆነ ነገር ያስገባው የኤርትራ ሰራዊት እንደሆነ ገልጸዋል።
" የአክሱም ነፍሰ ገዳይ የሻዕቢያ ወታደር ነው ፤ የማህበረ ደጎ ነፍሰ ገዳይ የሻዕቢያ ወታደር ነው ፤ የማርያም ደንገላት ነፍሰ ገዳይ የሻዕቢያ ወታደር ነው ፤ ደቡብ ትግራይ ራያ ላይ መጥቶ በመቶዎች የሚሆኑ ሰዎችን ረሽኖ የሄደው የሻዕቢያ ወታደር ነው " ብለዋል።
ህዝቡ ይሄንና የወታደራዊ እና የፖለቲካ መሪዎቹን ፍላጎት እንዲሁም የሚያደርጉትን ግንኙነት ስለሚያውቅ ከሻዕቢያ ጋር የሚደረግ ትብብር /ፅምዶ " አልፈልግም " ነው ያለው ሲሉ ተናግረዋል።
ከእነሱ ጋር በወንጀል የተሳሰረው ካልሆነ በስተቀር ህዝቡ ከኢሳያስ መንግሥት ጋር መተባበር ጥፋት እንደሚያመጣ አምኖ አልተቀበለውም ሲሉ አክለዋል።
እነዚህ ጦርነት እንዲነሳ የሚፈልጉ እና እየሰሩ ያሉ አካላት በኤርትራ ፣ በሱዳን በኩል ጥይት፣ ጠመንጃ እንደሚያስገቡ ፤ የጦር መሳሪያም እንደሚገዙ ይህንንም ሰው እንደሚያውቅ ሌ/ጄነራል ፃድቃን ገብረትንሳኤ ተናግረዋል።
ሌ/ጄነራሉ በትግራይ ጦርነት ወቅት ጦር የመሩ፣ በኃላም የሰላም ስምምነቱን ተከትሎ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ውስጥ ከፍተኛ አመራር ሆነው የሰሩ ፣ አለመግባባት ሲፈጠር ትግራይን ለቀው የወጡ አንጋፋ የትግራይ ጄነራል ናቸው።
(የሌ/ጄነራል ፃድቃን ገብረትንሳኤ ንግግር ከላይ ተያይዟል - ኤን ቢ ሲ ቴሌቪዥን ኢትዮጵያ)
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
#SafaricomEthiopia
አምስተኛው ዙር የበሽ ሽልማት ስነ-ስርዓት በባህርዳር እና በአዲስ አበባ ከተማ የተከናወነ ሲሆን የ1,000,000 ብር አሸናፊዎች ሽልማታቸዉን ተቀብለዋል። አሸናፊዎቻችን እንኳን ደስ አላችሁ!
ዛሬ ነገ ሳይሉ እድልዎን ይሞክሩ! ቀጣይ ዕድለኛ እርስዎ ይሆኑ ይሆናል!
📲 የM-PESA መተግበሪያን አሁኑኑ ያውርዱ። https://onelink.to/ewsb22
ወደ *777*0# ይደውሉ ወይም በM-PESA የበሽ ጥቅል ይግዙ!
#besh
#HappyNewYear
#furtheraheadtogether