ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት የገሀነም ደጆች አያናውጧትም እ...ና...ታ...ች...ን አ...ት...ታ...ደ...ስ...ም፡፡
+++ምን ሰጡህ ይሁዳ+++
ሙትን ልታስነሳ ድውይን ልትፈውስ
ሥልጣን ሰጥቶህ ነበር ኢየሱስ ክርስቶስ
ልታስር ልትፈታ በነፍስም በሥጋ
ሥልጣን ሰጥቶህ ነበር አልፋና ኦሜጋ
ምን ሰጡህ ይሁዳ አይሁድ ወገኖችህ
ለነርሱ አሳልፈህ ጌታህን የሰጠህ
ከሁሉ የሚበልጥ ሥልጣን ሰጥቶህ ሳለ
ብርን ለመቀበል ልብህ ተታለለ
ሰማይና ምድርን በቃሉ የፈጠረ
እንዴት በመቃብር ሶሥት ቀን አደረ
አንተ የሰጠኸው አሳልፈህ ለሞት
ሞትን ድል አድርጎ ተነሳ በሰንበት
✍ ቤተ ክርስቲያን ሆይ ÷ የክብርሽና የልዕልናሽ ፀሐይ እንደ ትላንቱ ሁሉ÷ ዛሬም አይጠልቅም!!
Читать полностью…✝የማይቀርበት ታላቅ መንፈሳዊ ጉባዔ✝
"ያልተሟሸ ሸክላና ሰንበት ትምህርት ቤት ያልገባ ወጣት አንድ ናቸው።" ብፁዕ አቡነ ሰላማ
✍ እነሆ የአሳሳ ደብረ ምህረት ቅዱስ ገብርኤል #መሠረት_ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት #የ40ኛ_ዓመት_የልደት_በዓልን ምክንያት በማድረግ ከጳጉሜ 1-3 2011 ዓ/ም ድረስ ታላቅ መንፈሳዊ ጉባዔ ተዘጋጅቷል እርሶም ወዳጅ ዘመዶን በመጋበዝ የእግዚአብሔር ቃል ይሰሙ ዘንድ ተጋብዘዋል በእለቱም፦
☞ መጋቢ ሐዲስ ሄኖክ ፈንቴ
☞ ዘማሪ ዲያቆን ፍሬዘር ደሳለኝ
☞ ዘማሪ ቶማስ {መሰንቆ}... ተጋብዘዋል በመሆኑም የነፍሶን ማዕድ ተመግበው የሰንበት ትምህርት ቤታችንን ልደት አብረን እናከብር ዘንድ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ስም እናሳስባለን።
#አሳድገሽኛል_ቤቴና_ውበቴ
#አልለይም_ካንቺ_እስከ_እለተ_ሞቴ
#የፀጋው_ግምጃ_ቤት_ክብሬና_ማዕረጌ
#ሰንበት_ትምህርት_ቤት_የዘላለም_ቤቴ
#ሰንበት_ትምህርት_ቤት_ክብሬና_ውበቴ
✞ የአባቶቻችንን አምላክ ልዑል እግዚአብሔር ሰንበት ትምህርት ቤታችንን ይጠብቅልን!!!✞ አሜን!!! ✞✞✞
ማርያም እንደማንኛችንም አይነት ሴት ናት????
❖ @And_Haymanot ❖
አንድ እህታችን በውሥጥ የላከችልን መልዕክት ነው፡፡
ስለ እመቤታችን ሲነሳ አይናቸው ደም የሚለብሰው የተሃድሶ መናፍቃን ዛሬም ከእናታችን እቅፍ ሊለዩን ተነስተዋል ከጥፋት ትምህርታቸ አንዱ
ማርያም እንደማንኛችንም አይነት ሴት ናት። በዛ ዘመን ብንኖር ከእኛ መሃል ከአንዳችን ኢየሱስ ይወለድ ነበር ብለው ያስተምራሉ ያምናሉ።
-ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታችን መድሃኒታችን እየሱስ ክርስቶስን ከመውለድዋ በፊት በእግዚአብሔር ዘንድ የተመረጠች ሴት ናት ።
እንኳን የአምላክ ማደሪያ የሆነችው ቅድስት ድንግል ማርያም አይደለም ማንኛችንም እግዚአብሔር የፈጠረን ፍጡር ወደዚህ አለም ከመምጣታችን በፊት ለምን አላማ እንደምንወለድ
እንኳን ገና ሳንፈጠር እግዚአብሔር ያውቃል:: ለዚህም ማስረጃ የሚሆነን ኤርምያስ 1:5 እንዲህ ይላል ።
የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ በሆድ ሳልሰራህ አውቄሃለሁ ከማህፀንም ሳትወጣ ቀድሼሃለሁ
ለአህዛብም ነቢይ አድርጌሃለሁ።
-ቅድስት ድንግል ማርያም ለአምላክ እናት እንድትሆን ገና ሳትፈጠር እግዚአብሔር የመረጣት ሴት ናት።
ከእሷም ባይሆን ከሌላ ይወለድ ነበር ለሚሉ የጥፋት ልጆች ከእግዚአብሔር አላማና ሃሳብ ጋር የተጣሉ የእግዚአብሔርን ሃሳብ በራሳቸው አመለካከት እና ሃሳብ ለመቀየር የሚያስቡ ደፋሮች ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከቅድስት ድንግል ማርያም
እንዲወለድ ነበር የእግዚአብሔር አላማ::
ከእሷ ባይሆን ለሚሉት የእግዚአብሔር ሀሳብ ሳይሆን የቀረበት ግዜ የለምና ከእሷ ውጭ ከማንም ሊሆን አይችልም። የእግዚአብሔር ሃሳብ ከቅድስት ድንግል ማርያም እንዲወለድ እንጂ ሌሎች እንደሚፈላሰፉት ከአዳራሽ ጨፋሪዎቻቸው ሴቶች መሃከል ኢየሱስ ሊወለድ አይችልም::
ከፍጥረት ሁሉ ፣የአምላክ እናት እንድትሆን የተመረጠች ቅድስት ማርያም ብቻ ናት። ለመዳናችን ምክንያት ለሆነች ከሴቶች ሁሉ ለተለየች የአምላክ እናት ክብር ይገባታል ።
በተጨማሪም ሊታወቅ የሚገባው ማንኛውም ሠው በነብያትና በሐዋርያት መንገድ መጓዝ ከቻለ ሐዋርያት የደረሱበትን የክብር ደረጃ መድረስ ይችላል፡፡ ነገር ግን በክብር ላይ ክብር ብናገኝ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሠኝ ስራ ብንሠራ እንኳ ድንግል ማርያም የደረሰችበት የክብር ደረጃ ላይ መድረስ
የሚችል ሰው ማንም የለም፡፡ ወደፊትም እንደዚህ አይነት ክብር እና ጸጋ ለማንም አይሰጥም፡፡፡፡
.....ይቆየን ከሰሞኑ እመቤታችን አንዲት ድንግል እናት ሥለመሆኗ በሰፊው እንመለሳለን፡፡
ለአባ ሕርያቆስ ፤
ለቅዱስ ኤፍሬም ፤
ለቅዱስ ያሬድ ፤
ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
ለአባ ይስሀቅ
የተገለጸች እመቤታችን እኛንም በበረከት እና በረድኤት ትጎብኘን
፤ ከልጅዋ ከወዳጅዋ ከመድኃኔዓለም ዘንድ ታማልደን ፤ አሜን!!!
❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖
ከዋክብት የሚያመሰግኑት
በስማቸውም የሚጠራቸው:
የፀጋው ብዛት የማይታወቅ
ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ
ለሐዋሪያት እንዲሁም ለቀደሙ አባቶቻችን ምሥጢሩን እንደገለጽክላቸው
ለእኛም ግለጽልን።
አሜን አሜን አሜን!!!
❖ @And_Haymanot ❖
❖ @And_Haymanot ❖
❖ @And_Haymanot ❖
ደብተራ
@And_Haymanot
፠፠፠የደብተራ ትርጓሜ በመዛግበተ ቃላት ወጥበባት፠፠፠
፠ደስታ ተክለ ወልድ በመዝገበ ቃላቸው፡- ‹‹ደብተራ - ድንኳን፡፡ ደበተረ - ደብተር ዘረጋ፣ ጻፈ፣ ከተበ ፡፡ ተደበተረ - ተዘረጋ፡፡ ደብተራ - የድንኳን ስም፡፡ ደብተራ - ዜማ. ቅኔ፣ ሳታት (ሰዓታት)
የሚያውቅ፣ በደብተራ (በድንኳን) ውስጥ የሚመራ፣ የሚቀኝ፣ የሚዘምር፣ መንፈሳዊ አገልጋይ፣ ካህን፣ አወዳሽ ሳታት ቋሚ፡፡ ደብቴ - ከፊለ ስም ወይም ቁልምጫ፣ የደብተራ ወገን፣ የኔ
ደብተራ ማለት ነው፡፡›› ይሉናል፡፡
፠ግእዙም፡- ‹‹ደብተረ› ማለትን በአወራረዱ ሕግ በተንበለ ቤት
አስገብቶ ሲያበቃ ‹‹ተከለ›› ሲል ይተረጕምና ለድንኳን ይሰጠዋል፡፡ ግእዝ ድንኳን ለሚለው ቃል ከደብተራ በተጨማሪ ኀይመትና ደበና ማለትን ይጠቀማል፡፡ ደበና የንጉሥ ድንኳን
የሚጠራበት ስም ነው፡፡ ደበናንሳ (ባለእጅ) የሚለው ቃል ከዚህ
ስም ጋራ ስለመያያዝ አለመያያዙ አላውቅም!
፠የፕ/ር ሥርግው አማርኛ የቤ/ክ መዝገበ ቃላት፡- ‹‹ደብተራ የቃሉ ቀጥተኛ ትርጕም ድንኳን ማለት ነው፡፡ ግን በቤተ
ክርስቲያን ውስጥ በቅኔ ማኅሌት የያሬድን ዜማ የሚዘምር፣ የሚመረግድ እንዲሁም ቅኔን የሚቀኝ ደብተራ ይባላል፡፡›› ብሎናል፡፡
፠በኢንሳይክሎፒዲያ ኢትዮፒካ፡- ደብተራ የሚለው ቃል እንደ ወረደ ከግሪክ የተቀዳ ሲሆን ትርጓሜውም እንደ ድንኳን የሚያገለግል ውጥር ቆዳ /ሌዘር/ ማለት እንደሆነ ተገልጧል፡፡
ደባትርን በቤ/ክ ካሉ ምሁራን ሁሉ ለይቼ the most educated clerics ያልኳቸው እኔ አይደለሁም፤ እንደነ ደንጎለጥ አንጠልጥሎ ሳይሆን አንጠርጥሮ የተረዳቸው ፈረንጅ ነው፡፡ በቤ/ክ የውስጥ አገልግሎት የቅዳሴና ውዳሴ ይባላል፡፡ የውዳሴው ድርሻ የደባትር ነው፡፡ የሚያወድሱት አምላካቸውን ነው፡፡ ውዳሴ የሃይማኖት አገልግሎት ስለሆነ በመደበኛ ፍ/ቤት
እንኳ አይዳኝም፤ በመንፈሳዊ ፍ/ቤት ብቻ ነው! እኒያ እግራቸው እስኪቀበተት ቆመው የሚያነጉ አገልጋይ ምሁራን ከውጪ በድውያን መጽልማነ ስም ስማቸው ተቀረደደ፤ በውስጥም ቤተ
ክርስቲያንን እየጋጡ በሰቡና በረቡ አምስት ከለባት ተዘነጠሉ እንጂ አገልግሎታቸውስ ‹‹ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኵሎ ዓለመ - ዓለምን የፈጠረ (እርሱ) ፈጽሞ የተመሰገነ ነው›› እያሉ ማወደስ ነበር፡፡ እነርሱ ቢጽፉ ጠንቋይ፣ ቢያሸበሽቡ ደናሽ፣ በፈሊጥ ቢናገሩ ቃላቸው ‹‹ቃለ ደብተራ››፣ ቢቀኙ ሰዓት ገዳይና ምዕመን አሰልቺ፣ ሕክምና ባልነበረበት ጊዜ ቁስል በቅጠል ቢያደርቁ ‹‹ሥር ማሽ ቅጠል በጣሽ›› ተባሉ እንጂ የሙሉ ሰዓት
አገልግሎታቸውስ ውዳሴ አምላክ ነበር፡፡ ሙያዎች ሁሉ በተከበሩበት፣ የሃይማኖት ነጻነት በታወጀበት፣ የቡድን መብቶች
ሁሉ ልዕልና አግኝተዋል በተባለበት ዘመን እነሆ ‹‹ደብተራ›› የወግ ማሳመሪያ ሆነ፡፡
፠ልዩ ልዩ ሕዝባዊ ትርጕም፡- ደብተራ - ተማሪ፣ መምህር ያልሆነ አዲስ ምሩቅ፣ ቄስም መነኩሴም ወይም ዲያቆን ያልሆነ፣ ሥልጣነ ክህነት የሌለው፣ ያፈረሰ፣ የድብትርና መሬት የያዘ፣
ጸሀፊ፣ መድኃኒት ዐዋቂ፣ ጥፈት የሚጥፍ … ደግነቱ ሁሉም መማሩን አይክዱበትም፡፡ ‹‹ቃለ ደብተራ›› የተባለ እንደሁ የአሽሙርና የኵሸት ማበረታቻ (ወደ ተንኮል የሚገፋ) ንግግር ነው፡፡ ‹‹ዕፀ ደብተራ›› የምትባል የኵሸት ዕፅ አለች፤ ቀጠጥናም ትባላለች፡፡
፠መንፈሳዊ ተምሳሌት፡- እመቤታችን፣ መስቀል፣ የጌታ ሥጋ፣ ቤተ መቅደስ ሁሉም ደብተራ ይባላሉ፡፡ ቅጽል ከፊቱ እየገባና እየተዛረፈ ‹‹ደብተራ ብርሃን፣ ደብተራ ፍጽምት፣ …›› ይዜማል፤
ይመሰጠራል፡፡ ሐዋርያው በዕብራውያን 9 እና 10 ነገረ ድኅነትን ይተርክበታል፤ ሐዲስን ከብሉይ ያነጻጽርበታል ደብተራን፡፡
፠ትርጕሙ ሲጠቃለል፡- ደብተራ ማለት በመደበኛ ትርጓሜው ማኅሌታዊ ማለት ነው፡፡ መዓርጉ ‹‹ተማሪ›› የመባል ያህል
ይመስላል፤ ከማንም አይሰጥም፤ ግን ደግሞ ለማንም አይሰጥም፡፡ ዜማ፣ ቅኔና አቋቋም መሞካከርን ይጠይቃል፡፡
በመርህ ደረጃ መነኮሳት ደብተራ አይባሉም፡፡ ...ይቆየን
በአማን ነጸረ
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
ቬኒሲያ:
🔸🔸🔸በጨው ደንደስ🔸🔸
~~~~~~~~
እጅግ በጣም ግዙፍ የሆነው ዝሆንና ሚጥጥየዋ እንቁራሪት ጓድኝነት መሰረቱ። ይህ ባልከፋ ከእለታት አንድ ቀን አንድ ትልቅ ድልድይ ሲሻገሩ እንቁራሪቷ ዘወትር እንደምታደርገው ዝሆኑ ትከሻ ላይ ቂብ አለች። ከእድሜው ብዛት የተነሳ ያረጀው ድልድይ ዝሆኑ ሲራመድበት ሲጢጥ እያለ ጩኸቱን አቀለጠው። ይኼኔ እንቁራሪቷ ወደ ዝሆኑ ጆሮ ጠጋ ብላ "ፐ! ድልድዩን አነቃነቅነው አይደል" አለች አሉ......
ድንቄም...
🐘🐘🐘🐘🐘🐘🐘
የክርስትና ጉዞ የማህበር፣የአንድነት፣የፍቅር ጉዞ ነው። በዚህ ጉዞ የዝሆንን ያህል አስተዋጽኦ ካላቸው በልጠው የእንቁራሪት ያህል አስተዋጽኦ ያላቸው ሰዎች መታበይ የለባቸውም።
@ ⊰ቬ⊱⊰ኒ⊱⊰ሲ⊱⊰ያ⊱:
╭══•:|★✧♡💝♡✧★|: ══╮
@Vensi @Vensi @Vensi
╰══•:|★✧♡💝♡✧★|: ══╯
"ነገርህ የተወደደ የዕውቀት መገኛ ጳውሎስ ሆይ እንድታማልደን እንለምንሃለን የትምህርትህን ፍለጋ እንከተል ዘንድ በርስትህ በመንግሥተ ሰማያት ዕድል ፈንታ እናገኝ ዘንድ።
የምዕመናን አለቃ ሹመትህ ከሐዋርያት በላይ የሚሆን ክቡር ጴጥሮስ ሆይ እኛን ወገኖችህን እጅህን ጭነህ ባርከን አክብረን ካንተ ጋር ባንድነት እንቆም ዘንድ።"
#መጽሐፈ_ሰዓታት
@Tewahdo_Haymanote
@Tewahdo_Haymanote
ደብረ ምጥማቅ (ግንቦት 21)
✍ ከእመቤታችን 33ቱ በዓላት አንዱ ነው፤ በዚህ ቀን ግብጽ ደብረ ምጥማቅ በተባለ ቦታ በተሰራች ቤተክርስቲያን እመቤታችን ጻድቃንን መላእክትን አስከትላ ትገለጽላቸው ነበር፤ እስላምም ክርስቲያንም በግልጽ ይመለከቷት ነበር። ከየአገሩ ያሉ ሰዎች ይሰበሰባሉ ድንኳን ተክለው ሰቀላ ሰርተው አጎበር ጥለው ይከትማሉ፤ ድንግልም ከግንቦት 21 ቀን ጀምሮ ለአምስት ተከታታይ ቀናት ሳታቋርጥ ትገለጽላቸው ነበር፤ ህዝቡ የተለያየ ጥያቄ ይጠይቃታል አዳም አባታችንን አሳይን ይሏታል ገሚሱ ነብዩ ዳዊትን ገሚሱ ቅዱስ ጊዮርጊስን አሳይን ይሏታል አንዳንዱም ከዚህ ቀደም የሞተ ዘመዱን እንድታሳየው ይጠይቃታል፤ እርሷም ለሁሉም ፍቃዳቸውን ትፈጽምላቸው ነበር፤ አዳምን ስትጠራው ከሔዋን ጋር ዳዊትን ስትጠራው ከበገናው ጋር ቅዱስ ጊዮርጊስን ስትጠራው ከጸአዳ ፈረሱ ጋር ነው። ወይ ግሩም ታዲያ ይህ በዚያ ደጉ ዘመን ነበር፤ አሁን ግን ኃጢያታችን ሲበዛ በረድኤት ካልሆነ በገሃድስ ተገልጻ አትታይም ለበቁ ካልሆነ።
✞ከእመቤታችን ረድዔት በረከት ይክፈለን✞
👉 ከSolomon Ayalew የፌስቡክ ገጽ የተወሰደ
@Meserete_Yared_Asasa
@Meserete_Yared_Asasa
ዕለተ ዓርብ(ስቅለት) !
•
ለኃጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ፤ ፩ ጴጥ ፪፥፳፬
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደዚህ ዓለም የመጣው ስለ እኛ ቤዛ ሆኖ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ዓለምን ለማዳን ነው ጌታ መከራ ተቀበለ ስንልም እንደ እኛ ሳንወድ በግድ ድንገት መከራ
ደርሶብን እንደምንሰቃየው አይደለም። ቀድሞ በሕግ፤በነቢያት፤በመዝሙራት የተናገረውን ትንቢት ሊፈጽም ነው እንጂ
፤ ራሱም አስቀድሞ ስለሕማሙና ሞቱ ደቀመዛሙርቱን በሚያስተምርበት ጊዜ ትንቢት ሲናገር <<እነሆ ወደ ኢየሩሳለም
እንወጣለን የሰው ልጅም ለካህናት አለቆችና ለጸሐፍት ይሰጣል የሞት ፍርድም ይፈርዱበታል ሊዘባበቱበትም ሊገርፉትም ለአሕዛብ አሳልፈው ይሰጡታል በሦስተኛውም ቀን
ይነሣል>>። ይላቸው ነበር ማቴ ፳፥፲፰-፳
ሰለዚህ የተነገረው ትንቢት ይፈጸም ዘንድ በዕለተ ዓርብ አይሁድ በምቀኝነት ተነሣሥተው የተለያዩ ፅዋ መከራን አደረሱበት በመጨረሻም ሰቅለው ገደሉት ከዚህ በኃላ የተነገረው ትንቢት
መፈጸሙን አውቆ በመስቀል ላይ "ሁሉ ተፈጸመ" ብሎ ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው በፈቃዱ ለይቷል፤ክርስቶስ በመስቀል ላይ ሲሞት ነፍሱ ከሥጋው ተለየች እንጂ መለኮት ከሥጋው
አልተለየም። እናም በነፍሱ ወደ ሲኦል ወርዶ በዲያብሎስ የባርነት አገዛዝ ስር
የነበሩትን ነፃ አወጣ ፩ ጴጥ ፫፤፲፰-፳
በሞቱ ሞታችንን ድል የነሳልንን የድንግል ማርያም ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ከመከራ ሁሉ ይሰውረን።
አሜን አሜን አሜን
@Tewahdo_Haymanote
@Tewahdo_Haymanote
ውርጃ
የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ አስተምሮ
@Tewahdo_Haymanote
ምድሪቱ (የሴቲቱ ማኅፀን) ዘር ከዘራንባት በኃላ ፍሬ እንዳታፈራ የምናደርገው ስለ ምንድን ነው? ውርጃን የምናካሒደው ስለ ምንድን ነው? እናንተ ዘማውያን ሆይ! ዝሙት መፈጸማችሁ ሳይበቃ ሰውን መግደል ትጨምሩበታላችሁን? እንግዲህ ስካር እንደ ምን ሴተኛ አዳሪን እንደሚያደርግ፣ ሴተኛ አዳሪነትም ዘማዊ፣ ዝሙትም እንደ ምን ነፍሰ ገዳይ እንደሚያደርግ ታስተውላላችሁን?
ይህን ምን ብዬ እንደምጠራው አላውቅም ምክንያቱም ይህን ሕፃን ከተወለደ በኃላ ከቤት አስወጥተን አይደለም ያባረርነው፤ እንዳይወለድ ከለከልነው እንጂ ወዮ! ስለምን የእግዚአብሔርን ስጦታ ታቃልላላችሁ? ስለምን ሕጉን ትተላለፋላችሁ? ስለምን ርጉም የሆነን ግብር እንደ በረከት ትቆጥሩታላችሁ? ስለምን እግዚአብሔር ሰውን ለመፍጠር ያዘጋጀውን መንገድ መግደያ ታደርጉታላችሁ? ስለምን ልጅን አቅፋ እንድትስም የተፈጠረችውን ሴት ነፍሰ ገዳይ እንድትሆን ታደርጓታላችሁ? እህቴ ሆይ! ፍቅረ ንዋይ ዐይንሽን አሳውሮት፣ ዳግመኛም በፍትወት ከሚመስሉሽ ጋር ዝሙትን ለመሥራት ስትዪ ፍምን በራስሽ ላይ አታከማቺ ወንድሜ ሆይ! ምንም እንኳን ይህን አሰቃቂ ግድያ የምትፈጽመው እርሷ ብትሆንም አንተም ከእርሷ ጋር ተባባሪ ነህ። ✞
ምንጭ፦ ሰማዕትነት አያምልጣችው በገብረ እግዚአብሔር ኪደ ገፅ 53
@Tewahdo_Haymanote
@Tewahdo_Haymanote
+++ በእርሱ ቊስል እኛ ተፈወስን +++
@Tewahdo_Haymanote
‹‹ጲላጦስም የካህናት አለቆችንና መኳንንትን ሕዝቡንም በአንድነት ጠርቶ እንዲህ አላቸው ፡- ሕዝቡን ያጣምማል ብላችሁ ይህንን ሰው ወደ እኔ አመጣችሁት ፤ እነሆም በፊታችሁ መርምሬ ከምትከሱበት ነገር አንድ በደል ስንኳ በዚህ ሰው አላገኘሁበትም፡፡ ሄሮድስም ደግሞ ምንም አላገኘም ፤ ወደ እኛ መልሶታልና ፤ እነሆም ለሞት የሚያደርሰው ምንም አላደረገም፡፡ እንግዲያስ ቀጥቼ እፈታዋለሁ አላቸው›› (ሉቃ. ፳፫፥፲፬‐፲፮)
ጲላጦስ የጌታችንን ንጹሕ መሆን ካወቀ በኋላ ‹ቀጥቼ እፈታዋለሁ› አለ፡፡ ንጹሕ በመሆኑ ምክንያት የተቀጣ ከጌታችን በቀር ማን አለ? ጲላጦስ አይሁድን ደስ ለማሰኘት ስለፈለገ ያን ሁሉ ጥያቄና መልስና ሕጋዊውን የፍርድ ሒደት ማስፈጸም ትቶ በንጹሑ ጌታ ላይ ግርፋት እንዲወርድበት ፈረደ፡፡
ነቢዩ ኢሳይያስ ‹‹በውርደቱ ፍርዱ ተወገደ›› ብሎ እንደተናገረው ትንቢት ጲላጦስ በእርጋታ ጀምሮት የነበረውን ሕጋዊ የምርመራና የፍርድ ሒደት አሽቀንጥሮ ጥሎ (አስወግዶ) ከሕግ ውጪ በዚያች ቀን በአይሁድ እጅ የተዋረደውን ጌታ ያለ ፍትሕ እንዲገረፍ ወሰነበት፡፡ (ሐዋ. ፰፥፴፫)
ጲላጦስ ‹‹ኢየሱስን ይዞ ገረፈው›› (ዮሐ. ፲፱፥፩) የጲላጦስ አሳብ ‹በመሰቀሉ ፈንታ ግርፋት ቢገረፍ ሕይወቱን ካዳንኩለት ቢቆስል ምንም አይደለም› የሚል ነበር፡፡ አይሁድም የግርፋቱን ጽናት አይተው ይሙት ማለታቸው እንደሚቀር ተስፋ አድርጎ ነበር፡፡ በዚህ ምክንያት ከትናንት ምሽት ጀምሮ ታስሮ ሲንገላታ ያመሸውን ፣ በሐናና ቀያፋ ግቢ ውስጥ ሲደበደብና በጡጫ ሲመታ ያደረውን ጌታ በምሕረት የለሾቹ የሮም ወታደሮች እጅ እንዲገረፍ አሳልፎ ሠጠው፡፡
የሮማውያን ግርፋት እንደ አይሁድ ግርፋት በጅራፍ ብቻ አይደለም፡፡ የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ጸሐፊው አውሳብዮስ ዘቂሣርያ እንደገለጠው ጅራፉ በቆዳ ከተሠራ በኋላ በላዩ ላይ ስለታማ የሆኑ የብረት ኳሶች ፣ ሾለው የተሳሉ የአጥንት ስብርባሪዎች ይደረጉበታል፡፡ በዚህ አሰቃቂ የግርፋት መሣሪያና በጨካኞቹ ወታደሮች እጅ ወድቀው ሥቃዩን መቋቋም ተስኖአቸው የሞቱም ብዙዎች ናቸው፡፡
በጅራፉ ላይ የተሠሩት የብረት ኳሶችና የአጥንት ስብርባሪዎች በሚገረፈው ሰውነት ላይ ሲያርፉ ሥጋውን እየነጩ የሚነሡ ስለሆኑ ጅራፉ በሰውነት ላይ ማረፉ ብቻ ሳይሆን ከሰውነት ላይ የሚነሣበትም ቅጽበት እጅግ ለመግለጽ የሚከብድ ሥቃይ የሚያደርስ ነው፡፡ የግርፋቱ መጠን በጨመረ ቁጥር የደም ሥሮችና አጥንቶች እስከሚታዩ ድረስ የሚጎዳ ፣ የጎድን አጥንቶችን መሰባበር ፣ ከፍተኛ የሆነ ውጪያዊና ውስጣዊ የደም መፍሰስ ፣ የሳንባ መጎዳት የሚያስከትል አሰቃቂ ሒደት ነው፡፡
@Tewahdo_Haymanote
በዚያች ቀን ጌታችንን ለመግረፍ የተመደቡት ወታደሮች እስራኤልን በብርሃን ዓምድ በሌሊት የመራቸውን አምላክ ፣ ሙሴና አሮንን በደመና ዓምድ ያነጋገራቸውን አምላክ በድንጋይ ዓምድ ላይ ለመግረፍ ዕርቃኑን አሰሩት፡፡ የካህናት አለቆችን ደስ ለማሰኘት ሲሉም በሙሉ ኃይላቸው በታላቅ ጭካኔ እጅግ ብዙ ግርፋትን አዘነቡበት፡፡ አንድ ገጣሚ እንዳለው በሙሴ አድሮ የፈጣሪን ክብር ለማየት የለመነው የሰው ልጅ ፈጣሪ በጊዜው ‹ጀርባዬን ታያለህ› ብሎ የገባለትን ቃል ቢፈጽምለትና ጀርባውን ቢያሳየው ግርፋትን አዘነበበት፡፡ (ዘጸ. ፴፫፥፳፫) በእርግጥም ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ ‹‹ከጲላጦስ ግርፋትን ይቀበልበት ዘንድ ጀርባን ፈጠረ›› እንዳለው አምላክ ሰው የሆነውና ጀርባን ለራሱ ያዘጋጀው ስለ ሁላችን ኃጢአትን ግርፋትን ሊቀበልበት ነበር፡፡
የሮማውያን ግርፋት ቅዱስ ጳውሎስ እንደተገረፈው እንደ አይሁድ ግርፋት በመጠን ተወስኖ ‹አንድ ሲጎድል አርባ ግርፋት አምስት ጊዜ ገረፉኝ› እያለ የተገረፈው ሰው በሕይወት ተርፎ እያስታወሰ የሚናገረው ዓይነት ግርፋት አይደለም፡፡ (፪ቆሮ. ፲፩፥፳፬)
ቤተ ክርስቲያናችን የጌታችን ግርፋት ስድስት ሺህ ስድስት መቶ ስድሳ ስድስት ጊዜ እንደሆነ ስታስተምር አምስት ሺህ ነው ፣ አራት ሺህ ነው የሚሉም አሉ፡፡ ይህን አሰቃቂ ግርፋት በሺህ ለሚቆጠር ጊዜ መገረፉን ግን ሁሉም ሊቃውንትና የታሪክ ሰዎች ተስማምተውበታል፡፡ ጌታችን እጅግ መገረፉን የሚያሳየን መስቀሉን ባሸከሙት ጊዜ በየሥፍራው እስኪወድቅ ድረስ አቅም ማጣቱ ነው፡፡
የጌታን ግርፋቱንስ መቁጠር ቢቻልም እንኳን ሥቃዩን ግን እንዴት ልንቆጥረው እንችላለን? ቤተ ክርስቲያናችን ከሥጋው አልፎ አጥንቶቹ እስከሚታዩ ድረስ ስለ ተገረፈው አምላክ በዕለተ ዓርብ የምታነበውና የምታዜመው ራሱ ክርስቶስ አስቀድሞ በነቢዩ ዳዊት አድሮ ስለሕማሙ የተናገረው የትንቢት ቃል የሥቃዩ መጠን ጥቂትም ቢሆን ለማሰብ ያግዘናል፡-
‹‹እንደ ውኃ ፈሰስሁ … አጥንቶቼም ሁሉ ተለያዩ ፤
ልቤ እንደ ሰም ሆነ …. በአንጀቴም መካከል ቀለጠ…
አጥንቶቼ ሁሉ ተቈጠሩ … እነርሱም አዩኝ ተመለከቱኝም …
አጥንቶቼ ተነዋወጡ››
(መዝ. ፳፪፥፲፬፣፲፯፤፴፩፥፲)
ቅዳሴያችን እንዲህ ይላል ‹‹የወልድን መከራውን የሚናገር ምን ዓይነት አፍ ነው? ምን ዓይነት ከንፈር ነው? ምን ዓይነት አንደበት ነው? የፍቅር ጌታ ሕማማቱ በተነገረ ጊዜ ልብ ይለያል ፤ ሕሊናም ይመታል ፤ ነፍስም ትንቀጠቀጣለች ፤ ሥጋም ይደክማል›› በእውነትም የጌታችንን ሥቃይ ለመግለጽ ምንም ዓይነት ቋንቋ ፣ ምንም ያህል ቅኔ አቅም አይኖረውም፡፡
ቅዱስ ኤፍሬምም :-
‹‹በክርስቶስ የተወደዳችሁ ሆይ ኑ! ወዲህ ቅረቡ ፤ በዚች ዕለት በዳዊት ከተማ የሆነውን አብረን እንይ! በተስፋው ቃል ሲጠበቁ የነበሩት የተመረጡት የአብርሃም ዘሮች ዛሬ ምን እንዳደረጉ እንመልከት! ጌታ ሆይ ረዥሙን ሥቃይህን ማን ሊገልጸው ይችላል?›› ይላል፡፡
ይህ ሁሉ የሆነው ስለ እኛ ኃጢአት ነበር፡፡ ኦሪት የሚገረፍ ሰው ‹‹የግርፋቱም ቊጥር እንደ ኃጢአቱ መጠን ይሁን›› ትላለች፡፡ (ዘዳ.፳፭፥፪) ጌታችን ማንም ስለ ኃጢአቱ ሊወቅሰው የማይችል ንጹሕ ቢሆንም ‹‹እግዚአብሔር የሁላችንን በደል በእርሱ ላይ አኖረ›› ስለተባለ ግርፋቱም በተሸከመው የእኛ ኃጢአት መጠን ሆነ፡፡
‹‹እርሱ ስለመተላለፋችን ቈሰለ ፣ ስለ በደላችንም ደቀቀ ፤ የደኅንነታችንም ተግሣፅ በእርሱ ላይ ነበረ›› በአጋንንት እጅ ልትገረፍ የጸጋ ልብስዋን አውልቃ ዕርቃንዋን በሲኦል የወደቀች ነፍሳችንን ነጻ ያወጣት ዘንድ እርሱ በጨካኝ ወታደሮች እጅ ዕርቃኑን ተገረፈ፡፡
‹‹እኛን ከሚገባን ግርፋት ያድነን ዘንድ ኢየሱስ የማይገባውን ግርፋት ተገረፈ›› ‹‹የተገረፈባቸውም አለንጋና ገመድ በደም ታለሉ (ተነከሩ) ፤ ከግርፋቱ ጽናት የተነሣ ሥጋው ሁሉ አለቀ›› ሐዋርያው ጴጥሮስ ‹‹በመገረፉ ቊስል ተፈወሳችሁ›› በማለት እንደተናገረ ‹‹በእርሱም ቊስል እኛ ተፈወስን›› (፩ጴጥ. ፪፥፳፬፤ኢሳ. ፶፫፥፭)
("ሕማማት" ከተሰኘው የዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ ባለ 528 ገጽ መጽሐፍ ጥቂት ገጾች ተወስዶ ለመድኃኔ ዓለም ለበዓለ ስቅለቱ የዘነጋነውን መከራውን ለማስታወስ የተለጠፈ)
✥┈┈ • ┈┈•┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈ • ┈┈┈••✥
@Tewahdo_Haymanote
@Tewahdo_Haymanote
@Tewahdo_Haymanote
✥┈┈ • ┈┈•┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈ • ┈┈┈••✥
✅የጸሎት ጥበብ✅
በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
@Tewahdo_Haymanote
ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገርን የተማረው የሰው ልጅ እግዚአብሔርን እንደሚገባ’ው አድርጎ ሲያነጋግረው ከዚያን ጊዜ አንሥቶ መልአክ ይኾናል፡፡ ነፍስ ከፈቃዳተ ሥጋ ሰንሰለት ነጻ የምትወጣው በዚህ መንገድ ነውና፤ ሕሊና ከፍ ከፍ የሚለው በዚህ መንገድ ነውና፤ ማደሪያችን ወደ ሰማይ የሚሻገረው በዚህ መንገድ ነውና፤ አንድ ሰው ግብረ ዓለምን የሚንቀው በዚህ መንገድ ነውና፤ አንድ ሰው የቱንም ያህል ነዳይ ወይም ባሪያ ወይም ተራ ወይም ዝቅ ያለ ቢኾንም እንኳን በንጉሡ ዙፋን ፊት የሚቆመው በዚህ መንገድ ነውና፡፡ እግዚአብሔር የሚመለከተው የንግግርን ውበት ወይም የቃልን ርቱዕነት ሳይኾን የመንፈስን ንጹህነት ነውና፡፡ በዚህ መንገድ መጥተን ወደ አእምሮአችን የመጣውን ብንናገርም እንኳን፥ ጸሎታችን ግዳጅ የሚፈጽም ኾኖልን እንመለሳለን፡፡
እንግዲህ ይህን ማድረግ ምን ያህል ቀላል እንደ ኾነ ታስተውላለህን? በዚህ ዓለም ሰዎች ዘንድ አንድ ሰው ሌላውን ሰው ለመለመን የንግግር ክህሎት (ብልሐት) ያሻዋል፡፡ የሚለመነው ሰው በቀላሉ የማይገኝ ከኾነ ደግሞ አጃቢዎቹን ማሳመን ይኖርበታል፡፡ ጥሮ ለፍቶ ካገኘው በኋላም ጉዳዩን በዝርዝር ማስረዳት ይጠበቅበታል፡፡ እግዚአብሔርን ለማናገር ግን የዚሁ ተቃራኒ ነው፡፡ ከተሰበረ ልብ በቀር ሌላ ምንም ምን አያስፈልግም፤ ወደ እርሱ ለመቅረብ የሚከለክል ማንም አይኖርም፡፡ “እኔ የቅርብ አምላክ ነኝ እንጂ ሩቅ አምላክ አይደለሁም” ይላልና (ኤር.23፡23)፡፡ የምንርቀው እኛ ነን እንጂ እርሱ ዘወትር ቅርብ ነው፡፡
እግዚአብሔርን ለማነጋገር የንግግር ክህሎት (ብልሐት) አያስፈልገንም የምለውስ ለምንድን ነው? እንዲያውም ብዙ ጊዜ ድምፅም ቢኾን አያስፈልገንም፡፡ አንተ በልብህ ብትናገርና እግዚአብሔርን ማናገር እንዲገባ’ህ ብታናግረው እርሱ ጸሎትህን ለመስማት ዘንበል ይላል፡፡ ሙሴ ጸሎቱ የተሰማው በዚህ መንገድ ነውና፤ ሐና ጸሎትዋ የተሰማው በዚህ መንገድ ነውና፡፡ ወደ እግዚአብሔር እንዳይቀርቡ ብሎ ሕዝቡን ለማራቅ የሚቆም ወታደር የለም፤ አሁን ሰዓቱ አይደለም ብሎ የሚከለክል ዘበኛም የለም፡፡ እግዚአብሔርም፡- “አሁን ላነጋግርህ አልችልም፤ ሌላ ጊዜ ተመለስ” አይልም፡፡ ይልቅ ልታነጋግረው በመጣህበት ቅጽበት አንተን ለመስማት ይቆማል፡፡ የምሳ ሰዓትም ቢኾን፣ የእራት ሰዓትም ቢኾን፣ እጅግ አስቸጋሪ ጊዜም ቢኾን፣ በገበያ ቦታም ቢኾን፣ በመንገድ ላይም ቢኾን፣ በባሕር ውስጥም ቢኾን፣ በዳኛ ፊት በምትቆምበት በችሎት ፊትም ቢኾን፥ እግዚአብሔርን ብትጠራው መጥራት እንደሚገባህ አድርገህ እስከ ጠራኸው ድረስ ጸሎትህን እንዳይሰማ የሚከለክለው ግድግዳ የለም፡፡
👉 በገብረ እግዚአብሔር ኪደ
@Tewahdo_Haymanote
@Tewahdo_Haymanote
¶ በዩጋንዳ የኦርቶዶክስ ክርስትና አማኞች በሚገርም ፍጥነት
እየጨመረ ነው ። በ2019 ቁጥሩ 1 million ደርሷል ።
🙏🙏🙏🙏🙏🙏
@Tewahdo_Haymanote
@Tewahdo_Haymanote
+ አበው ስለ እመቤታችን ዕረፍት እንዲህ አሉ +
‹ሌሎች በድንግልና የኖሩ ሴቶች 'ለሞት የሚሆኑ ልጆችን አንሰጥህም" በማለት ሞትን ተቃወሙት፡፡ ድንግል ማርያም ግን አንድ ልጅ በመውለድ በልጅዋ ሞት ራሱ እንዲሞት አደረገችው፡፡ ከዐለት ጋር እንደተጋጨ የተፈረካከሰው በማሕፀንዋ ፍሬ ነውና ሞት ወደ እርስዋ ሲቀርብ ተብረከረከ›› ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ
‹‹ልጃቸው ተሰብስበው ወዳሉበት መጥታለችና አዳምና ሔዋን ዛሬ ደስ አላቸው … በዚህች ቀን ታላቁ ዳዊት በራሱ ላይ የተዋበ አክሊል የደፋችለትን ሴት ልጁን አይቶ ደስ አለው … በዚህች
ቀን ነቢዩ ኢሳይያስ ትንቢት የተናገረላት ድንግል ወደ ሙታን ሥፍራ ልትጎበኘው መጥታለችና ደስ አለው … በዚህች ቀን
ብርሃን ሲበራባቸው አይተዋልና ነቢያት ሁሉ ከመቃብራቸው ራሳቸውን ቀና አደረጉ … አርያም በጣፋጭ የመላእክት ዝማሬ ተሞላ ፣ ምድር ደግሞ ኀዘንን በተሞሉ በሐዋርያት ለቅሶ ተሞላች፡፡ ሙታንም ሕያዋንም ትርጉሙን ሊገልጹት በማይችሉት [የተለያየ] ዜማ ሰውና መላእክት በዚያች ዕለት አብረው ጮኹ››ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ (Homily on the Dormition)
‹‹የቃሉ አገልጋዮችና ምስክሮች የነበሩት ሐዋርያት በሥጋ የወለደችውን የእናቱን ዕረፍትና እርስዋን የሚመለከቱ
የመጨረሻዎቹን ምሥጢራትም ማየት ነበረባቸው፡፡ ይህም የሆነው የክርስቶስ የዕርገቱ የዓይን ምስክሮች እንደሆኑ ሁሉ
የወለደችውም እናቱ ወደዚያኛው ዓለም ለሸጋገርዋ ምስክሮች መሆን ስላለባቸው ነው›› ቅዱስ ዮሐንስ ዘደማስቆ (aka
Doctor of Dormition)
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
አስተርእዮ ማርያም
/channel/Tewahdo_Haymanote
የድንግልን ትንሣኤ በኩረ ፕሮቴስታንት የኾነው ማርቲን ሉተርና ስዊዘርላንዳዊው ቡሊንገር እንኳ በአንክሮ ያምናሉ ቡሊንገር ትንሣኤዋን ከኤልያስ ዕርገት ጋር በማነጻጸር ሲያስተምር ሉተር ደግሞ እንዲኽ ይላል" there can be no doubt that the Virgin Mary is in heaven, how it happened we do not know ፤ ጥርጥር ሊኖር አይችልም፡ ድንግል ማርያም በሰማይ ናት፡ እንዴት ኾነ? እኛ አናውቅም" ብሏል Martin Luther's works,vol.10, pg.268
ድንግል ማርያም አልተነሣችም ለሚሉ እሆነ ብለናል፡፡
@Tewahdo_Haymanote
@Tewahdo_Haymanote
ጌታችን ለወንበዴው «በመንግሥትህ በመጣህ ጊዜ አስበኝ» የሚል ልመና «እውነት እውነት እልሃለሁ፤ ዛሬ ከእኔ ጋር በገነት ትሆናለህ» ብሎ ወዲያውኑ መልሰ ሰጠ። በኃጢአተኞች ሰዎች ፊት የመሰከረለትን ወንበዴ በመላእክት ፊት እመሰክርልሃለሁ አለው።
በግራ ያለው ወንበዴ ሲሰድበው ዞሮ በቁጣ ሳያየው በትዕግሥት ሰምቶ ዝም ያለው ጌታ የቀኙ ማረኝ ሲለው ግን ከአፉ ተቀብሎ፣ ወደ እርሱ ዞሮ መለሰለት። «ከቁጣ የራቀ ምሕረቱ የበዛው» አምላክ ክፉ ሥራችንን ለማሰብ ሲዘገይ ማረኝ ስንለው ግን ለመማር ይፈጥናል።
"የራበው ሰው ለምግብ፣ የጠማው ሰው ለመጠጥ እንደሚቸኩል ክርስቶስ ይቅር ለማለት ይቸኩላል።" ስለዚህ ነው ወደ ወንበዴው ዞሮ "እውነት እልሃለሁ ዛሬ ከእኔ ጋር በገነት ትሆናለህ" ያለው፤ ይህን ምሕረት ተስፋ አድርገን "ጌታ ሆይ ወደ ቀኙ ወንበዴ ዘንበል ባለው ራስህ አጋንንት በኃጢያት በትር የመቱትን ራሴን ቀና አድርግልኝ» እያልን እንጸልያለን።
(ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ)
#{ሕማማት መጽሐፍ ገጽ 354}
@Tewahdo_Haymanote
@Tewahdo_Haymanote
ዛሬ በቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ መንግሥትን ወክለው
እየተሳተፉ የሚገኙት የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ፕሬዚደንት
"የኦሮምያ ቤተ ክህነት የሚባለው የማይታሰብ ጉዳይ ነውና
እኛም አንፈቅድም የሀገርን አንድነት የሚፈታተን ጉዳይ
እንደመንግስት መቸውኑ ተቀባይነት አይኖረውም" ማለታቸውን
የEOTC TV ጋዜጠኛው ዲ/ን ኃይሉ ገልጾልናል።
ቤተክርስቲያን ከፖለቲካ በላይ ናት።
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
ምሥጢረ ደብረታቦር
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
እንኳን ለደብረታቦር በዓል በሰላም በጤና አደረሰን አደረሳችሁ
ጌታ ሆይ፥ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው፤ ብትወድስ፥ በዚህ ሦስት ዳስ ፤ አንዱን ለአንተ አንዱንም ለሙሴ አንዱንም ለኤልያስ እንሥራ ›
ቅዱስ ጴጥሮስ
ታቦር ተራራ የዛሬ ገጽታው
ከስድስት ቀንም በኋላ ኢየሱስ ቅዱስ ጴጥሮስንና ያዕቆብን ወንድሙንም ዮሐንስን ይዞ ወደ ረጅም ተራራ ብቻቸውን አወጣቸው።በፊታቸውም ተለወጠ፥ ፊቱም እንደ ፀሐይ በራ፥ ልብሱም እንደ ብርሃን ነጭ ሆነ። እነሆም፥ ሙሴና ኤሌያስ ከእርሱ ጋር ሲነጋገሩ ታዩአቸው። ጴጥሮስም መልሶ ኢየሱስን። ጌታ ሆይ፥ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው፤ ብትወድስ፥ በዚህ ሦስት ዳስ አንዱን ለአንተ አንዱንም ለሙሴ አንዱንም ከኤልያስ እንሥራ አለ።
እርሱም ገና ሲናገር፥ እነሆ፥ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው፥ እነሆም፥ ከደመናው። በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት የሚል ድምፅ መጣ። ደቀ መዛሙርቱም ሰምተው በፊታቸው ወደቁ እጅግም ፈርተው ነበር። ኢየሱስም ቀርቦ ዳሰሳቸውና። ተነሡ አትፍሩም አላቸው።ዓይናቸውንም አቅንተው ሲያዩ ከኢየሱስ ብቻ በቀር ማንንም አላዩም። የማቴዎስ ወንጌል 17፡1-8
በቂሳርያ ጌታችን ለደቀመዛሙርቱ ለሰዎች የሰውን ልጅ ማን ይሉታል ብሎ ጠይቋቸው አንዳንዶች ከነቢያት አንዱ ነህ ይሉሃል፣ አንዳንዶች ሙሴ ነህ ይሉሃል፣ ሌሎች ደግሞ ኤልያስ ነህ ይሉሃል እያሉ መለሱለት ጌታችንም መልሶ እናንተስ ማን ትሉኛላችሁ ብሎ ሲጠይቃቸው የሐዋርያት አፈጉባዔ ሊቀ ሐዋርያት ቅ/ጴጥሮስ ‹አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር አብ የባሕርይ ልጅ ነህ› ብሎ በመመስከሩ ጌታም ‹የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ በሰማይ ያለው አባቴ እንጂ ሥጋና ደም ይህን አልገለጠልህምና ብፁዕ ነህ…› ተብሏል፡፡
ይህ በሆነ በሰባተኛው ቀን ሦስቱን ደቀ መዛሙርት ጴጥሮስ፣ ዮሐንስና ያዕቆብን ይዞ ወደ ታቦር ተራራ ወጣ፡፡ በዚያም እንደ ዮርዳኖስ ወንዝ መድኃኔዓለም ክብረ መንግስቱን ፤ ብርሃነ መለኮቱን ገልጧል ፡፡ከዘጠኙ ዐበይት በዓላት አንዱ የሆነው በዓለ ደብረታቦር የዚህ ታሪክ መታሰቢያ ነው ፡፡
ታቦር ተራራ ከገሊላ ባሕር በስተምዕራብ 17 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ፤ ከናዝሬት ከተማ በስተምስራቅ ፤ ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተምዕራብ አቅጣጫ ሲገኝ ከባሕር ጠለል በላይ 572 ሜትር ነው ፡፡ከላይ ወደታች ሲታይ ታቦር ተራራ ቅርጹ የተገለበጠ የሻይ ስኒ ይመስላል ይላሉ ፡፡
እርሱም ገና ሲናገር፥ እነሆ፥ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው፥ እነሆም፥ ከደመናው። በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት የሚል ድምፅ መጣ።
ምሥጢረ መንግሥቱን ለምን በታቦር ተራራ ገለጸው ?
መድኃኔዓለም ሌሎች ተራሮች እያሉ ክብሩን ለመግለጥ ስለምን ደብረ ታቦርን መረጠ ቢሉ ትንቢቱንና ምሳሌውን ለመፈጸም ነው፡፡
ትንቢት
“ ታቦር ወአርሞንኤም በስመ ዚአከ ይትፌሥሑ ወይሰብሑ በስምከ ”
ታቦርና አርሞንኤም በስምህ አምነው በተደረገላቸው ነገር ደስ ይላቸዋል፣ ስምህን ያመሰግናሉ፣ ለስምህም ምስጋና ያቀርባሉ፡፡ “ መዝ 88፡12
ምሳሌ
ባርቅ ሲሳራን ድል አድርጎበታል መሳፍንት 4፡6 ይኸውም ታሪኩ እንዲህ ነው፡፡‹… የእስራኤል ልጆች በእግዚአብሔር ፊት እንደገና ክፉ ሥራ ሠሩ፡፡ እግዚአብሔርም በአሶር በነገሠው በከነዓን ንጉሥ በኢያቡስ እጅ አሳልፎ ሰጣቸው የሠራዊቱም አለቃ በአሕዛብ አሪሶት የተመረጠው ሲሣራ ነበር… ዘጠኝ መቶ የብረት ሰረገሎች ነበሩትና የእስራኤልንም ልጆች ሃያ ዓመት ያስጨንቃቸው ነበር›/መሳ 4.1-3/
ሁሌም ቢሆን የሰውን በደል ዐይቶ እንደወጣችሁ ግቡት፣ እንደገባችኋት ውጧት የማይልና ‹… ከፈተናው ጋር መውጫውን ደግሞ ያደርግላችኋል› የተባለለት እግዚአብሔር ከዚህ ቀንበር የሚላቀቁበትን መላ ራሱ አመለከታቸው፡፡ /1ቆሮ. 10-13/፡፡
እስራኤላውያን ወደ ፈጣሪያቸው በጮኹ ጊዜ የለፊዶት ሚስት የሆነችውንና እስራኤልን በነቢይነትና ዳኝነት ታገለግል የነበረችው ነቢይቱን ዲቦራን ተጠቅሞ የማሸነፊያ መላውን አመለከታቸው፡፡ ነቢይቱ ዲቦራ ትንቢት ከመናገር አልፋ የእስራኤልን ንጉሥ ባርቅ ከእኔ ጋር ወደ ጦርነቱ ውጪ ብሎ ባስጨነቃት ጊዜ በጦር አዝማችነትም ተሳተፈች፡፡
እግዚአብሔር በነቢይቱ በዲቦራ በኩል ለእስራኤል ንጉሥ ‹ሔደህ ወደ ታቦር ተራራ ውጡ…› ብሎ አዞት ነበርና ንጉሡ ዐሥር ሺሕ ብረት ለበስ ያልሆነ እግረኛ ሠራዊት ይዞ ደብረ ታቦርን ተማምኖ በተራራው ላይ መሸገ ጦርነቱ ሳይጀመር አለቀ፡፡ ምክንያቱም ‹እግዚአብሔርም ሲሣራን ሰረገሎቹንም ሁሉ ሠራዊቱንም ሁሉ ከባርቅ ፊት በሰይፍ ስለት አስደነገጣቸው፡፡ ሲሣራም ከሰረገላው ወርዶ በእግሩ ሸሸ…› /መሳ. 4.15/
እስራኤል በእግዚአብሔር አጋዥነት በታቦር ተራራ ላይ የሃያ ዓመት የግፍና የሰቀቀን አገዛዝ ቀንበራቸውን ከትከሻቸው አሽቀንጥረው በምትኩ የድል ካባን ደረቡ ‹… በጦርነት ኃይለኞች ሆኑ የባዕድ ጭፍሮችንም አባረሩ› ተብሎም ጀግንነታቸው ተጻፈላቸው፡፡ የታቦር ተራራ ያኔ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ባለውለታቸው ነበር፡፡ /ዕብ. 11.32-34/
ጌታም በልበ ሐዋርያት ያለ ሰይጣንን ድል ያደርግበታልና ማለትም በልባቸው ጥርጥርን እና ፍቅረ ሢመትን( የሥልጣን ፍቅር) ያሳደረ ዲያብሎስን ድል ነስቶላቸዋል ፡፡ከዚህም በመነሳት ነው በዓለ ደብረታቦር የደቀመዛሙርት ተማሪዎች በዓል ነው የሚባለው ፡፡
ለምን 3ቱን ሐዋርያት ( ጴጥሮስ ፤ዮሐንስ እና ያዕቆብን) ብቻ ይዞ ወደ ተራራ ወጣ፡-
ለፍቅሩ ስለሚሳሱ ነው፡፡ ይህም በዕብራይስጡ ኬፋ ፤ በግሪኩ ጴጥሮስ ፤በግዕዙ ኰኲሕ( ዐለት) የተባለው የዮና ልጅ ስምዖን ጌታ እሞታለሁ እያለ ጌታችን ሲናገር አይሁንብህ በማለቱ ከባሕርይ አባቱ ከአብ እርሱን ስሙት የሚል መለኮታዊ ድምጽ ሰምቷል፡፡ዮሐንስና ያዕቆብ ጌታን ምድራዊ መሲህ አድርጎ በማሰብ ቀኝ ጌትነትን እና ግራ ጌትነትን በእናታቸው በኩል የማይገባ ልመና አቀረቡ ዮሐንስና ያዕቆብ እኔ የምጠጣውን ጽዋ ትጠጣላችሁ? ሲባሉ አዎ ብለው መለሱ በዚህም ከባሕርይ አባቱ እርሱን ስሙት የሚል ድምጽ ሰሙ፡፡
በይሁዳ ምክንያት ነው ኢሳ 26.13 ‹ኃጥእ ሰው የእግዚአብሔርን ክብር እንዳያይ ያርቁታል› እንዲል እርሱን ጥሎ አስራ አንዱን ወደ ተራራ ይዞ ቢወጣ ከምሥጢር ቢለየኝ በሞቱ ገባሁበት እንዳይል፡፡ ያም ባይሆን ስምንቱ ደቀ መዛሙርት ለምን ይከለከላሉ ቢሉ አልተከለከሉም በርዕሰ ደብር (በተራራው አናት) ለሦስቱ ደቀ መዛሙርት የተገለጸው ምስጢር በእግረ ደብር (በተራራው ግርጌ) ለነበሩት ስምንቱ ደቀ መዛሙርት ተገልጦላቸዋል፡፡ ይህም በደብረሲና ለሰባው ሊቃናት የተገለጠ ምሥጢር በከተማ ለነበሩት ለኤልዳድና ሙዳድ እንደተገለጠ ማለት ነው፡፡ ዘኁልቊ 11፡26
@Tewahdo_Haymanote
@Tewahdo_Haymanote
#መልአካይ_ሰይጣን ~ ሰባሪ ዜና
@Tewahdo_Haymanote
👉 "ኦርቶዶክስ" የሚለው ስም የኦርቶዶክሳውያን ብቻ ነው!!!!!
√Share √Share √Share
«ውሉደ ብርሃን የክርስቶስ ቤ/ክ» ብሎ ራሱን ሲጠራ የነበረው የውጉዙ አሰግድ ሣህሉ (?) የተሐድሶ መናፍቃን ቡድን ያሰበውን ያህል በጎችን ከበረት ማውጣት ስላልቻለ ስሙን «ቃለ ዐዋዲ ዘኦርቶዶክስ የክርስቶስ ቤ/ክ» ብሎ ቀይሮ የኦርቶዶክስ ቤ/ክ ነኝ በማለት ፈቃድ እንዲሰጠው ጠይቋል። ይህ በእምነታችን ኃጢአት፣ በባህላችን ነውር፣ በሕጋችንም ወንጀል የሆነ ቅጥፈት ነው። መንግስትም የሌላን ቤተ እምነት ስም በመጠቀምህ ፍቃድ አልሰጥም ማለት እየቻለ "ተቃዋሚ ካለ ሰኞ ሐምሌ 29 3:00 ሰዓት በሰላም ምኒስቴር የሃይማኖት ድርጅቶችና ማሕበራት ምዝገባ ዳይሪክቶሬት ይቅረብ" ብሎ የማርያም መንገድ የሰጠ ይመስላል።
ሰይጣን ሰዎችን ሲያታልል መልአክን እንጂ ራሱን መስሎ አይደለም። የራሱን ኃይልና ብርታት በመግለጥ፣ ከመልአክነት ይልቅ ሰይጣናዊነት እንደሚልቅ በማስረጃ በማስረገጥ አይቀርብም። ስለ ራሱ የሚያቀርበው ነገር የሌለው ባዶ ነውና፣ ሌላን መምሰል እንጂ ራስን መሆን አይሆንለትምና መልአክ-መሳይ (መልአካይ) ሆኖ ይቅበዘበዛል። ተሐድሶዎችም እንዲሁ በመብከን ተሐድሶነታቸውን ሳይሆን ኦርቶዶክስ-መሳይነታቸውን ሊነግሩን ሽሩገድ ይላሉ። 2 ቀናት ብቻ ቀርተውናል! ይህ የብሔርህ አልያም የፖለቲካ ወሬ አይደለም፣ የእውነትም የእምነትም ጉዳይ ነው! ይህንን መልዕክት በውስጥ መስመር ለመምህራን፣ ለሕግ ባለሞያዎች፣ ለባለሥልጣናትና ለብጹዓን አባቶች በማካፈልና በመላክ በቤ/ክ ጉዳይ ለውጥ እንፍጠር! ዳይ ወደ ስራ [©Binyam ZeChristos ሐምለ 26 - 2011]
፪ኛ ቆሮ ፲፩
26 “ብዙ ጊዜ በመንገድ ኼድኹ፤ በወንዝ ፍርኃት፥ በወንበዴዎች ፍርኃት፥ በወገኔ በኩል ፍርኃት፥ በአሕዛብ በኩል ፍርኃት፥ በከተማ ፍርኃት፥ በምድረ በዳ ፍርኃት፥ በባሕር ፍርኃት፥ በውሸተኞች ወንድሞች በኩል ፍርኃት ነበረብኝ፤
27 በድካምና በጥረት ብዙ ጊዜም እንቅልፍ በማጣት፥ በራብና በጥም ብዙ ጊዜም በመጦም፥ በብርድና በራቁትነት ነበርኹ።
28 የቀረውንም ነገር ሳልቆጥር፥ ዕለት ዕለት የሚከብድብኝ የአብያተ ክርስቲያናት ኹሉ ዐሳብ ነው።”
@Tewahdo_Haymanote
@Tewahdo_Haymanote
ሐምሌ 19 ዕለት
@Meserete_Yared_Asasa
❖የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል አምላካቸው ክርስቶስን አንክድም በማለታቸው የፈላ ጋን ውስጥ የተወረወሩት ቅዱስ ቂርቆስና እናቱን ቅድስት ኢየሉጣ ተራድቶ ያዳነበት በዓል ነው።
❖ ይኸውም የቅድስት ኢየሉጣን ልጅ ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ ከሐዲው መኰንኑ ይዞ “ስምኽ ማነው” ብሎ በጠየቀው ጊዜ “ነቅዕ ዘእምዐዘቅት ንጹሕ ወእማይ ዘኢይማስን ክርስቲያን ስምየ” (ከንጹሕ ዐዘቅትና ከማይለወጥ ከማይጠፋ ውሃ የተገኘ ስሜ ክርስቲያን ነው ሞክሼ ስም ከፈለግኽ ደግሞ እናቴ የሠየመችኝ ቂርቆስ ነው) በማለት ክርስትናው መመኪያው የኾነው ይኽ ቅዱስ ሕፃን መለሰለት፡፡
❖ መኰንኑም ለአማልክት ከሠዋኽ ስታድግ እሾምኻለኊ ክርስቶስን ካድ ቢለው ቅዱስ ቂርቆስ ግን “የሰይጣን መልእክተኛ ለእውነትም ጠላቷ የኾንኽ ከእኔ ራቅ” አለው፡፡ መኰንኑም ይኽነን ሰምቶ በመቈጣት የቅዱስ ቂርቆስ ደሙ እንደ ውሃ እስኪፈስስ ድረስ እንዲጨምቁት እና ጨውና ሰናፍጭ በኹለቱ የአፍንጮቹ ቀዳዳዎች እንዲጨመሩ ቢያደርግበት፤ በመንፈስ ቅዱስ ጸጋ የጠነከረው ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ ግን “ትእዛዝኽ ለጒረሮዬ ጣፋጭ ኾነ ከማርና ከሥኳርም ለአፌ ጣመኝ” እያለ አምላኩ ክርስቶስን አመሰገነ፡፡
❖ መኰንኑ በዚኽ ሳያበቃ እናትና ልጇ በክፉ አሟሟት እንዲሞቱ በማሰብ የረዘሙና የተሳሉ በእሳትም እንደ ፍም የጋሉ ዐሥራ አራት የብረት ችንካሮች እንዲመጡ አስደርጎ ሰባቱ በእናቱ አካላት፤ ሰባቱ በሕፃኑ ሰውነት ላይ እንዲሰካ ቢያስደርግም በጌታችን ትእዛዝ ግለቱ ጠፍቶ እንደ በረዶ በመቀዝቀዝ ምንም ምን ጒዳት ሳያደርስባቸው ቀረ፡፡
❖ ከዚያም ወደ ወኅኒ ቤት እንዲገቡና እንዲዘጋባቸው አደረገ፤ ከዚያም ሕፃኑና እናቱ የሚሠቃዩበት ታላቅ መንኰራኲር ለ፵ ቀናት ተሠርቶ ካለቀ በኋላ ኹለቱንም በደራቁ ራሳቸውን ላጭተው የእሳት ፍሕምን በላያቸው ላይ ቢያደርጉም የእግዚአብሔር መልአክ ሥቃዮቹን ኹሉ ከእነርሱ አራቀላቸው፡፡
❖ የሕፃኑ ምላስ እንዲቈረጥ አዝዞ ቢያስቈርጠውም ጌታችን ምላሱን መልሶለታል፡፡ “ወአዘዘ ካዕበ ያፍልሑ ማየ ውስተ ጽሕርት ዐቢይ ወይደይዎሙ ለሕፃን ቂርቆስ ወለእሙ ኢየሉጣ” ይላል በታላቅ ጋን ውሃ አፍልተው ሕፃኑንና እናቱን እንዲጨምሯቸው ሲያዝዝ ከሚፍለቀለቀው ውሃ ድምፅ የተነሣ ለጊዜው እናቱ ፍርሀት ሥጋዊ ቢያገኛትም ልጇም ወደ ጌታችን በጸለየላት ጊዜ ፍርሃቱ ርቆላት ከልጇ ጋር ስትገባ መልአከ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ወርዶ ውሃውን አቀዝቅዞ ሐምሌ ፲፱ አውጥቷቸዋል፡፡
❖ በመጨረሻም የሰማዕትነትን አክሊል የሚያገኝባት ጊዜ ሲደርስ ጌታችን ተገልጾለት ስሙን ለሚጠራ ኹሉ ቃል ኪዳንን ከሰጠው በኋላ ሥጋኽን በኤልያስ ሠረገላ ላይ አኖርልኻለኊ አለው፤ ይኽነን በሰማ ጊዜ በእጅጉ ተደሰተ፤ ከዚኽም በኋላ ጥር ፲፭ በሌሊቱ እኲሌታ ከእናቱ ጋር አንገቱ ተቈረጠ የሰማዕትነትን ክብር ተቀዳጅተዋል።
✞ የመልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ረድኤት፣ በረከትና ምልጃ አይለየን✞✞✞ አሜን✞
@Meserete_Yared_Asasa
@Meserete_Yared_Asasa
👉 የደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል ቤ/ከ አንቀጸ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት የ Facebook ገጽ የተወሰደ
✝ ጸሎት ክፋ ሀሳብ ከውስጣችን የሚወገድበት መንገድ ነው ። ከጨለማ ኃይላት ርቆ ወደ መንፈሳዊ ሕይወት መግባት የሚቻለው #በጸሎት_ነው።
አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ
@Tewahdo_Haymanote
@Tewahdo_Haymanote
#ሰበር_ዜና
👉 ብዙ ሚሊዬኖች በስሩ ያሉት የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤት በጽኑ አውግዟል።
@Meserete_Yared_Asasa
"ክፉም እንዳላደርግባችሁ በእጃችሁ ሥራ አታስቈጡኝ” ት. ኤርምያስ ፳፭፥፮
✞ ይሄ ቃዱስ ቃል የአምላካችን ከባድ ግሳጼ ነው፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ እንደምናነበው እግዚአብሔር አምላክ ሁለት ጊዜ ምድርን በታላቅ የቁጣ መቅሰፍት የመታትና የሰው ልጆችን በእሳትና በታላቅ የጥፋት ውሃ ያጠፋበት ዋና ምክንያት አስቀያሚ በሆነ ኃጢአት ነው፡፡ ይሄ ሰውን በእሳትና በውሃ እንዲጠፉ ምክንያት የኾነው አሁን በሀገራችን መነጋገሪያ እየሆነ ባለው ግብረ ሰዶም በመፈጸሙ ነው፡፡ ይሄ በሀገራችንም በሃይማኖታችንም ነውር የኾነው ድርጊት፣ ኃጢአት እንደሆነ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ በብሉይ ኪዳንም፣ በሐዲስ ኪዳን ላይም ተደጋግሞ ተገልጿል፡፡ በኖኅ ዘመን በጥፋት ውሃ፣ በሎጥ ጊዜ ደግሞ በእሳትና በዲኚ እግዚአብሔር የሰው ልጆችን ቀጥቷል። በኦ.ዘፍ ፮ ፥፮ “እግዚአብሔርም ሰውን በምድር ላይ በመፍጠሩ ተጸጸተ፥በልቡም አዘነ” ተብሎ ተጽፏል፡፡
✟ አሁን ደግሞ የእመቤታችን የአስራት ምድር ተብላ የምትጠራው ሀገራችን ለጉብኝት በሚል ምክንያት ግብረ ሰዶሞች ይህችን ቅድስት ሀገራችንን ከመጎብኘታቸው በላይ የቤተክርስቲያናችንን ቅዱስ ቦታዎች ላይም ከመሄድ አንቆጠብም ብለዋል፡፡ በሮሜ ምዕ. ፩ ፤፳፯፤ ላይ “እንዲሁም ወንዶች ደግሞ ለባሕርያቸው የሚገባውን ሴቶችን መገናኘት ትተው፤ እርስ በርሳቸው በፍትወታቸው ተቃጠሉ፤ ወንዶችም በወንዶች ነውር አድርገው በስሕተታቸው የሚገባውን ብድራት በራሳቸው ተቀበሉ። የሚለውን በተማርንበት ምድር በእኛ ጊዜና በእኛ ምድር ላይ አጨብጭበን አንቀበልም፡፡
✥ ይሄን የነውር ሥራ የዕለት ተግባራቸው የሆኑ ሰዎች ወደሀገራችን ሲመጡ በቀላሉ ከአንድም ሶስት ነገሮችን ይጥሳሉ፡፡
1ኛ ሕገ - ቤተክርስቲያናችንንና የፈጣሪ ትዕዛዝ፣
2ኛ. የሀገራችን ወንጀለኛ መቅጫ ህገ - መንግስት፣
3ኛ. የኢትዮጵያውያንን ባህል፣
የፈጣሪን ትዕዛዝ በማለፍ የሚመጣ ቁጣ ምን እንደኾነ ከላይ አይተናል፡፡ “ክፉም እንዳላደርግባችሁ በእጃችሁ ሥራ አታስቈጡኝ”ም ብሏል፡፡ እኛም በፈጣሪ የተወገዘውን ከሚያደርጉት ጋር በማበር፣ ዝም በማለት ፈጣሪን አናስቆጣው፡፡
✝ በኢትዮጵያ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 629፡- “መሠረት ግብረ ሶዶማዊነት በእስራት የሚያስቀጣ ወንጀል ነው፡፡ ቅጣቱም ከ1 አመት በማያንስ ቀላል እስራት ወይም ከባድ ሁኔታ እስሲያጋጥም ከ 10 ዓመት በማይበልጥ ፅኑ እስራት ያስቀጣል” ይላል፡፡ ይሄ አንቀጽ በህጉ ላይ እያለ እነሱን ወደሀገራችን እንዲገቡ መፍቀድና ምቹ ሁኔታን መፍጠር ህዝቡንም ባህሉንም መናቅ ነው፡፡
☨ እኛ ኢትዮጵያውያን ከባህላችን አንጻር እንኳን የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት ይቅርና በተለመደው በህግ ባልተሳሰረ በሚፈፀም ግንኙነት ላይ ያለን ምልከታ ይታወቃል፡፡ በዚህም መሠረት ወደ ሀገራችን ሊገቡ ያቆበቆቡ ሰዶማውያን ወደሀገራችን እንዲገቡ መፍቀድ የሀገራችንን ባህል መናቅ፤ ሀገራችን የምትመራበት ህግንም መናድ ነውና የሚመለከተው አካል ለጉዳዩ እልባት ሊሰጥ ይገባል፡፡
✔ የእኛም የአዲስ አበባ ሰ/ት/ቤት አንድነት ተግባሩን በፅኑ የምንቃወምና የምናወግዝ መኾኑን እናሳውቃለን፡፡
✞ሀገራችንን ኢትዮጵያ እግዚአብሔር አምላክ ይጠብቃት!✞✞✞
ሁልም #ሼር! #shareበማድረግ ይደግፍ።
@Meserete_Yared_Asasa
@Meserete_Yared_Asasa
ባትወለድ ኖሮ……
መለኮትን ያህል - በእጅ እንደ መጨበጥ - በሆድ እንደ መወሰን
ምን ክብር ይገኛል - ምን ምጡቅ ልዕልና? - ምንስ ገላጭ ልሳን?
ባትወለድ ኖሮ - ብላቴናዋ ባትኖር - ያች የምስጢር ማህደር
ተራ ተዓምር ሁሉ - እንደ አምልኮት - በሆነብን ነበር፡፡
ባትወለድ ኖሮ - እሷን ተመልክተን - መመኪያ ባላልናት
በሔዋን ተስፋ ውስጥ - ብርሃንን አዝላ - ደምቃ ባላየናት
የተዘጋች ገነት - ቀድሞ እንዳጣናት - ርስታችን ባላልናት፡፡
አዳም ባልተጽናና - ደሙም ባላቆመ - ሲፈስ በኖረ
“ህይወቴ ነሽ” ብሎ - ሔዋንን ባልጠራት - ተስፋው ባልነበረ
የማግሰኞም እርሻ - ዘርን ባላስገኘ - ባዶውን በቀረ
ሁሉም ይቀር ነበር - ሰውም በውድቀቱ - እንተቸገረ
ባትወለድ ኖሮ - አሁን አይኖርም ነበር - ጥንት እንደ ነበረ፡፡
ትንቢትን ባላየን - ይወለዳል ብለው - ተስፋ ባልሰነቁ
“ክንድህን ከአርያም ላክ” - ብለው ባልተጽናኑ - ፊቱ ባልወደቁ
ዘርም ባልቀረልን - እንደ ተበተንን - ከቤት እንደ ወጣን
ባላወቅን እረኛ - ጋጣ እንደሌለን - ማደሪያ እንዳጣን
እንደ ከንቱ ፍጥረት - በምድር እንደሚቀር - እንደ ዱር ቀበሮ
ሰው በሆነ ነበር - ያች እንቁ ፍሬ - ባትወለድ ኖሮ፡፡
ምስራቃዊት መቅደስ - የታተመችን በር - ህዝቅኤል ባላየ
የሙሴ ሐመልማል - በነበልባሉ ’ሳት - ተዋህዶ ባልቆየ
ረዥሙ ተራራ - ለዳንኤል ባልታየ - ተስፋ ባልሰነቀ
ባትወለድ ኖሮ - ሁሉም ጠፍቶ ነበር - ያኔ እንደ ወደቀ፡፡
ቴክታና ጴጥርቃ - (እ)ራዕይ ባላዩ - ህልም ባልታያቸው
ከጥጃ ጨረቃ - እንደምትወለድ - ባልተነገራቸው
ከጨረቃም ፀሃይ - ዓለምን ሲያበራ - ባልተመለከቱ
የጨለማ ዘመን - በዘለቀ ነበር - ልክ እንደበፊቱ፡፡
ሄርሜላና ማጣት - ሃናን ባልወለዷት - ተስፋም ባልቀረበ
ኢያቄም ባልመጣ - ከይሁዳ ነገድ - ድኅነት ባልታሰበ
ባልተነገራቸው - በስተ እርጅናቸው - ባላዩ' ደስታ
ባትወለድ ኖሮ - ሁሉም መራር ነበር - በመጣፈ ጥፈንታ፡፡
መልአኩም ባልመጣ - ብስራቱን ባልሰማን - ቃል ስጋ ባልሆነ
ልደቱን ስቅለቱን - ትንሳኤውን ባልሰበክን - ሁሉ በባከነ
ባትወለድ ኖሮ - እመአምላክን ባናይ - ያችን የድኅነት በር
ምክንያት ፈጥረን ሞተን - መልሰን ለመዳን - ምክንያት ባጣን ነበር፡፡
(አክሊሉ ደበላ ሚያዝያ 30/2006ዓ.ም)
@Meserete_Yared_Asasa
@Meserete_Yared_Asasa
የትሁታን አምላካቸው ኢየሱስ ክርስቶስ
@And_Haymanot
"-----4፤ ከእራት ተነሣ ልብሱንም አኖረ፥ ማበሻም ጨርቅ ወስዶ ታጠቀ፤
5፤ በኋላም በመታጠቢያው ውኃ ጨመረ፥ የደቀ መዛሙርቱንም እግር ሊያጥብና በታጠቀበትም ማበሻ ጨርቅ ሊያብስ ጀመረ።
6፤ ወደ ስምዖን ጴጥሮስም መጣ፤ እርሱም። ጌታ ሆይ፥ አንተ የእኔን እግር ታጥባለህን? አለው።
7፤ ኢየሱስም መልሶ። እኔ የማደርገውን አንተ አሁን አታውቅም፥ በኋላ ግን ታስተውለዋለህ አለው።
8፤ ጴጥሮስም። የእኔን እግር ለዘላለም አታጥብም አለው። ኢየሱስም። ካላጠብሁህ፥ ከእኔ ጋር ዕድል የለህም ብሎ መለሰለት።
9፤ ስምዖን ጴጥሮስም። ጌታ ሆይ፥ እጄንና ራሴን ደግሞ እንጂ እግሬን ብቻ አይደለም አለው።
10፤ ኢየሱስም። የታጠበ እግሩን ከመታጠብ በቀር ሌላ አያስፈልገውም፥ ሁለንተናው ግን ንጹሕ ነው፤ እናንተም ንጹሐን ናችሁ፥ ነገር ግን ሁላችሁ አይደላችሁም አለው።
11፤ አሳልፎ የሚሰጠውን ያውቅ ነበርና፤ ስለዚህ። ሁላችሁ ንጹሐን አይደላችሁም አለው።
12፤ እግራቸውንም አጥቦ ልብሱንም አንሥቶ ዳግመኛ ተቀመጠ፥ እንዲህም አላቸው። ያደረግሁላችሁን ታስተውላላችሁን?
13፤ እናንተ መምህርና ጌታ ትሉኛላችሁ፤ እንዲሁ ነኝና መልካም ትላላችሁ።
14፤ እንግዲህ እኔ ጌታና መምህር ስሆን እግራችሁን ካጠብሁ፥ እናንተ ደግሞ እርስ በርሳችሁ እግራችሁን ትተጣጠቡ ዘንድ ይገባችኋል።
15፤ እኔ ለእናንተ እንዳደረግሁ እናንተ ደግሞ ታደርጉ ዘንድ ምሳሌ ሰጥቻችኋለሁና።
16፤ እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ባሪያ ከጌታው አይበልጥም። መልእክተኛም ከላከው አይበልጥም።
17፤ ይህን ብታውቁ፥ ብታደርጉትም ብፁዓን ናችሁ።...."
(የዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 13)
@And_Haymanot
@And_Haymanot
#ወዳጄ ሆይ!!!
⛪የሚታገል ሰው ቢወድቅ አዲስ ነገር አይደለም፤ ወድቆ መቅረቱ ነው እንጂ፡፡ አንድ ቦክስ የሚጋጠም ሰውም ቢቆስል የሚያሳዝን ነገር አይደለም፤ የሚያሳዝነው ቁስሉን ችላ ያለው እንደ ኾነ ነው እንጂ፡፡ አንተም በመንፈሳዊ ሕይወትህ ብትወድቅ አይደንቅም፤ ለቅጽበትም የማይተኛልህ ጠላት አለህና፡፡ ነገር ግን ወድቀህ አትቅር፡፡
@Tewahdo_Haymanote
🔔 አንድ ወታደር ጦር ሜዳ ሔዶ ቢቆስል ማንም ጤነኛ አእምሮ ያለው ሰው አይወቅሰውም፡፡ አንተም ጠላትህ ዲያብሎስ ቢያቆስልህ ማንም አይወቅስህም፡፡ መንፈሳዊ ተጋድሎ ውስጥ ነውና ያለኸው፡፡ የምትወቀሰው ለቁስልህ መድኃኒት ማድረግህን ችላ ያልህ እንደ ኾነ ብቻ ነው፡፡ ይህ ከላይ የነገርኩህ ወታደር ከታከመ፥ ተመልሶ ወደ ጦር ሜዳ ይሔዳል፡፡ ጠላቱን ድል ሲያደርግም ሹመት ሽልማት ይሰጡታል፡፡ አንተም ከወደቅህበት ተነሥና ንስሐ የተባለ ሕክምናን ውሰድ፡፡ ከዚያም ጠላትህ ዲያብሎስን ድል አድርገህ ከክርስቶስ ዘንድ ሹመት ሽልማትን ተቀበል፡፡ ስለዚህ በርታ፡፡ በርታና ተነሥ ዘግይቻለሁ ብለህ በፍጹም ተስፋ አትቁረጥ፤ አሁንም መጀመር ትችላለህና፡፡
✍ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
#ይህ ጽሑፍ ለሌሎች እህት ወንድሞቻችን እንዲደርስ👉 Share ያድርጉ...
✥┈┈ • ┈┈•┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈ • ┈┈┈••✥
@Tewahdo_Haymanote
@Tewahdo_Haymanote
@Tewahdo_Haymanote
✥┈┈ • ┈┈•┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈ • ┈┈┈••✥
#ትግራይ ✞ #እና ✞ #አማሓራ
@Meserete_Yared_Asasa
✍ ሁለቱ ታላቅ ስብዕናን ያነገቡ ድንቅ ህዝቦች የሚኖሩበት ክልሎች ናቸው። ዛሬ ድሪቶ በሆነ የፓለቲካ ትብተባ ምክንያት በሁለት ጥጋ ጥግ ፅንፎች ላይ ሆነው የጥላቻ ቂሪላን በሚወረውሩ አካላት ልቦናቸው ሻክሮ፤ ቀልባቸው ሸውርሮ፤ ስሜታቸው ነዝሮ እንዲህ በጠላትነት እይታ ሲተያዩ ብቻ መመልከቱ በጣም ያማል።
❖ የፅዮን ደጅ የሆነው ክልል ከግማደ መስቀሉ አምባ ጋር ተኮራረፈ ሲባል በጣም ይደንቃል? የጣና ቂርቆሱ ምዕመናን ከደብረዳሞ መናኛን ጋር ተገለማምጦ መተላለፋቸው ማሰብ ብቻውን ኃጥያት ይመስለኛል።
✞ የቅዱስ ላሊበላ ልጆች ከአብረሃ አፅባህ ዘካሪዎች ጋር ጥርስ ተንካከሱ ከተባለ ሳናውቀው 8ኛው ሺህ መግባቱን የምናረጋግጥ ይመስለኛል።
✅ ከአንዱ አባታችን ከአዳም በስጋ ተወልደን ፤ከማህፀነ ዮርዳኖስ በቅድስና የተወለድን በስጋ ወደሙ የታተምን የአንድ መንግስት አመስጋኝ የሆነን ሰማያውያን እንዴት ስለምድራዊው ዓለም ስጋችንን እንቦጫጨቃለን?
♣ ለጊዚያዊ መኖሪያችን እንዴት ቋሚ ቂም በቀል ለልጅ ልጆቻችን እናወርሳለን? የአብርሃምን መገፋት የኢዮብን ፅናት የዳዊትን መሰደድ፤የሙሴን ቅንነት የድንግልን ትህትና በአውደምህረት የተማርን ህዝቦች እንዴት የሰናፍጭ ያክል ትዕግስት እናጣለን?
♦በአቡነ አረጋዊ እና በአቡነ ተክለሃይማኖት ምለን የምንገዘት ህዝቦች እንዴት የዓለም ፍልስፍና ይከፋፍለናል?
♠ ወላዲት አምላክን ከፊት አስቀድመን ለዲያቢሎስ የእግር እሳት የምንሆን ህዝቦች እንዴት ለእራሳችን መሆን አቃተን?
✍ ጎንደሬው ስለፅዮን እንደሚሞት አውቃለው ፤ትግራይዋውም ስለግሽን እንደሚሰዋ እርግጠኛ ነኝ የፅዮን ቅዳሴ ለአማራው ህብስቱ እንደሆነ የመርጦለማርያም ማህሌቱ ለአድዋዎች ምግባቸው ነው።
❖ብዙ የሚያሳስባችሁ ነገር እያለ በሚያራርቃችሁ ነጥብ በሆነች ዓለማዊ እሴት ላይ እንዴት እናተኩራለን? እልፍ አእላፍ የሆኑ መላእክታት ወደ እንጦሮንጦስ የወረደው በአንዱ ሳጥናኤል ክፉ ስራ ምክንያት ነው።
♣እስራኤላውያን ለ400 ዓመት ለግብፅ ባርነት ተዳርገው ለሽንኩርት ዱባ የተዳረጉት በ11 የያዕቆብ ልጆች ሴራ ነው ።እንግዲህ ክፋትን እንራቅ። እንኳን ከሰው ወገን ከመላእክትም ወገን ፍፁም የሆነ የለም።
♠ሳጥናኤል አጠፋ ማለት ሚካኤል አጠፋ ማለት አይደለም። አሮን ሳተ ማለት እስራኤላውያን ሳቱ ማለት አይደለም።
✅ስለዚህ በዝሆኖች ጠብ ሳሩ አይለቅ።
♦ከማንነትም ከዘርም ከክልልም በላይ ወንድማማችነት እና ክርስትናችን ይበልጣል እና የመስቀሉ ቃልን መከታ አድርገን በሰከነ መልኩ እንደ አቤላውያን እና እንደ ቃየላውያን ሳይሆን እንደ ታናናሽ ብላቴናዎች ዝቅ ብለን እንመካከር እንዘካከር።
✞ ያኔ ፅዮንም ትሰማናለች ፤የግሸኑም አንባ መስዋታችንን ይቀበለን ይሆናል።
#ወስብሐት_ለእግዚአብሄር
@Meserete_Yared_Asasa
@Meserete_Yared_Asasa
"የበለስ ቅጠል ሰፊና ደስ የምታሰኝ ናት፤ ወደ ጥፋት
የምትወስደው የኃጢአት መንገድም ሰፊ በር ናት፡፡ የበለስ ፍሬ
ሲበሉአትና ሲያላምጡአት ጣፋጭ ናት፡፡ ኃጢአትም ሲሠሩአት
ደስ ታሰኛለች፡፡ ከሠሩአት በኋላ ግን [እንደ በለሲቱ] መከራን
ታመጣለች፡፡ በሚሠሩአት ጊዜ ጣፋጭ፥ ከሠሩአት በኋላ ግን
መራራ ናትና እርስዋን ከመሥራት ሽሽ፡፡"
~ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ ወደ ቴዎድሮስ
ምዕራገ ጸሎት:
እግዚኦ መሀረነ ክርስቶስ በማለት የአራት ጣቶች አጽቅ መቁጠር
ተምሳሌትነታቸው ምንድነው?
"ከሺህ ሰራዊት አንድ አቡነ ዘበሰማያት:
አቡነ ዘበሰማያት: ጌታችን ተከታዮቹ እንዲጸልዩ ያስተማረው
ጸሎት ነው። ( ማቴ 6:5-15። ሉቃስ 11:1-4)።
ምንም ዕንኳን አጭር ቢሆንም የጸሎትን ነገር ሁሉ ያጠቃልላል።
በውስጡ 6 ነገሮችን ይዟል። ከዚህም ሶስቱ ስለ ሰዎች ጥቅም
ሶስቱ ስለ እግዚአብሔር ክብር ይናገራሉ።
1ኛ. ስለ እግዚአብሔር ክብር ስሙን መቀደስ: መንግሥቱን
መሻት: ፈቃዱን መጠየቅ።
2ኛ. ስለ ሰዎች ጥቅም የእለት እንጀራን: ይቅርታን ማግኘት:
ከክፉ ሁሉ መዳን ናቸው። ጽሎቱም በውዳሴ ይደመደማል።
*ከ81 መጽሐፍት ያለ 5ት ነገር አለበት እነርሱም
1. ሃይማኖት:- እግዚአብሔር አቡነ ማለት ነው።
2. ተስፋ:- ትምጻእ መንግሥትከ ማለት ነው።
3. ፍቅር:- ለነ ብሎ አንዱ ለአንዱ መጸለይ።
4. ትህትና:- ቅዱሳን ከበቁ በኃላ ኅድግ ለነ አበሳነ ማለት ነው።
5. ጸሎት:- መላው ጸሎት ነው።
በሰላመ ቅዱስ ገብርኤል መልአክ:
ደራሲው አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ሲሆን የተወሰደውም ከወበሳድስ
ነው።
ይኸውም መላኩ ቅዱስ ገብርኤል የተናገራቸው አራቱ ወርቃማ
ቃላት መሰረቶቹ ናቸው።
ሉቃስ 1:28 መልአኩም እሷ ወዳለችበት ገብቶ
1ኛ. ደስ ይበልሽ
2ኛ. ጸጋ የሞላብሽ ሆይ
3ኛ. ጌታ ከአንቺ ጋር ነው
4ኛ. አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ።
አምስተኛው በሐሳብሽ ድንግል ነሽ በስጋሽም ድንግል ነሽ
ይኸውም ድንግል ማርያም ወንድ ስለማላውቅ ይህ እንዴት
ይሆናል? ስትል በመላኩ ድንግልናዋን ያስረገጠችበት ነው።
ሉቃስ ( 1:34። ኢሳያስ 7:14 )
ስድስተኛው የአሸናፊ የእግዚአብሔር እናት ሆይ ሰላምታ ላንቺ
ይገባሻል።
ይኸን ቅድስት ኤልሳቤጥ የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ
እንዴት ይሆንልኛል ብላ የተናገረቸው ነው። ( ሉቃስ 1:42 )
አቡነ ዘበሰማያትና ( አባታችን ሆይ ) በሰላመ ቅዱስ ገብርኤል
መልአክን ( እመቤታችን ቅድስት ድግል ማርያም ሆይ ) አንድ
ላይ መጸለይ እንዲገባ እናትና ልጅን አስተባብራ ያመሰገነች
ቅድስት ኤልሳቤጥ " አንቺ ከሴቲች መካከል የተባረክሽ ነሽ
የማህፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው " በማለት አስተማራናለች
( ሉቃስ 1:42 )
ስለዚህ እናትን ከልጅ ልጅን ከእናት የሚለይ የለም። ( ማቴዎስ
2:11-13 )
ይህ ጸሎት ከተደመደመ በኃላ እግዚኦታ ይባላል።
እግዚኦ መሀረነ ክርስቶስ በማለት የአራት ጣቶች አጽቅ
እያንዳንዱ እየተቆጠረ ይዘልቃል። ይኸውም 12 ነው።
አቆጣጠሩም እንደሚከተለው ነው :-
-ከሌባ ጣት በስተጫፍ ከላይ ወደ ታች መቆጠሩ ከሰማይ
መውረዱን
-በሁለተኛው ጣት ወደ ላይ መቁጠር ወደ መስቀል መውጣቱን
-በሶስተኛው ጣት ወደ ታች መቁጠር ወደ መቃብር መውረዱን
-አራተኛው ጣት ወደ ላይ መቁጠር ወደ ሰማይ ማረጉን ያሳያል።
እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ 12 መሆኑ በ 12 ሰዓት መዓልት
የሰራነውን ኃጢአት ስለስምህ ብለህ ይቅር በለን ማለት ሲሆን:
በእንተ እግዝእትነ ማርያም የሚለው ደግሞ በ 12 ሰዓት ሌሊት
ጨለማን ተገን አድርገን የሰራነውን ኃጢአት ስለ እናትህ ቅድስት
ድንግል ማርያም ብለህ ይቅር በለን ማለት ነው።
አብ ወልድ መንፈስ ቅድሱ የሚለውን የእግዚአብሔር ሦስትነት
ሰመ ፊደል ስንቆጥርው 12 ነው እንዲሁም ቅድስት ድንግል
ማርያም የሚለውን ስመ ፊደል ስንቆጥረው 12 ይሰጠናል።"
ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጸሎታችንን
ይቀበልልን!!! የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ፀጋና
ረዕዴት ከኛ ጋር ይሁን አሜን !!!
ወስብሐት ከእግዚአብሔር
@Tewahdo_Haymanote
@Tewahdo_Haymanote
ቡሄ_በሉ
ቡሄ በሉ (፪) - - ሆ ልጆች ሁሉ - - ሆ
የኛማ ጌታ - - ሆ የዓለም ፈጣሪ - - ሆ
የሰላም አምላክ - -ሆ ትሁት መሀሪ -ሆ
በደብረ ታቦር - - ሆ የተገለጠው - ሆ
ፊቱ እንደ ፀሐይ - ሆ በርቶ የታየው -ሆ
ልብሱ እንደብርሃን -ሆ ያንፀባረቀው -ሆ
ድምጽህን ሰማና በብህሩ ደመና(፪)
የቡሄው ብርሃን ለኛ መጣልን(፪)
ያዕቆብ ዮሐንስ-ሆ እንዲሁም ጴጥሮስ-ሆ
አምላክን አዩት - - ሆ ሙሴ ኤልያስ - ሆ
አባቱም አለ - - ሆ ልጄን ስሙት - - ሆ
ቃሌ ነውና - - ሆ የወለድኩት - - ሆ
አዝ======
ታቦር አርሞንኤም-ሆ ብርሃን ታየባቸው ሆ
ከቅዱስ ተራራ ሆ ስምህ ደስ አላቸው- ሆ
ሰላም ሰላም - - ሆ የታቦር ተራራ - - ሆ
ብርሀነ መለኮት - ሆ ባንቺ ላይ አበራ -ሆ
አዝ======
በተዋህዶ - - ሆ ወልድ የከበረው - ሆ
የእግዚአብሔር አብ ልጅ - - ሆ ወልደማርያም ነው - -ሆ
ቡሄ በሉ - - ሆ ቡሄ በሉ - - ሆ
የአዳም ልጆች - - ሆ ብርሃንን - - ሆ ተቀበሉ - -ሆ
አዝ======
አባቴ ቤት - - ሆ አለኝ ለከት - - ሆ
እናቴ ቤት - - ሆ አለኝ ለከት - - ሆ
ከአጎቴም ቤት - - - ሆ አለኝ ለከት - ሆ
ተከምሯል - - ሆ እንደ ኩበት - - ሆ
አዝ======
የዓመት ልምዳችን - - ሆ ከጥንት የመጣው - - ሆ
ከተከመረው - ሆ ከመሶቡ ይውጣ - ሆ
ከደብረ ታቦር - - ሆ ጌታ ሰለመጣ - ሆ
የተጋገረው - ሆ ሙልሙሉ ይምጣ - ሆ
አዝ======
ኢትዮጵያውያን - -ሆ ታሪክ ያላችሁ - ሆ
ባህላችሁን - ሆ ያዙ አጥብቃችሁ - ሆ
ችቦውን አብሩት -ሆ እንዳባቶቻችሁ -ሆ
ምስጢር ስላለው -ሆ ደስ ይበላችሁ -ሆ
አዝ======
አባቶቻችን - - ሆ ያወረሱን - - ሆ
የቡሄን ትርጉም - - ሆ ያሳወቁን - - ሆ
እንድንጠብቀው - ሆ ለእኛ የሰጡን - ሆ
ይህን ነውና - - ሆ ያስረከቡን - - ሆ
አዝ======
ለድንግል ማርያም ሆ አሥራት የሆንሽ ሆ
ቅዱሳን ጻድቃን - - ሆ የሞሉብሽ - - ሆ
በረከታቸው - - ሆ ያደረብሽ - - ሆ
ሁሌም እንግዶች - ሆ የሚያርፉብሽ -ሆ
ሀገረ እግዚአብሔር -ሆ ኢትዮጵያ ነሽ ሆ
አዝ======
ለሐዋርያት - - ሆ የላከ መንፈስ - - ሆ
ዛሬም ለኢትዮጵያ -ሆ ጸጋውን ያፍስስ ሆ
በበጎ ምግባር - ሆ እንድንታነጽ - - ሆ
በቅን ልቦና - ሆ በጥሩ መንፈስ - - ሆ
በረከተ ቡሄ - ሆ ለሁላችን ይድረስ - ሆ
= = = = = =
ዓመት ዓውዳመት ድገም እና ዓመት ድገም እና
በጋሽዬ ቤ ድገም እና ዓመት ድገም እና
ያውርድ በረከት ድገም እና ዓመት ድገም እና
ወርቅ ይፍሰስበት ድገም እና ዓመት ድገም እና
በእማምዬ ቤት ድገም እና ዓመት ድገም እና
ይግባ በረከት ድገም እና ዓመት ድገም እና
ማርና ወተት ድገም እና ዓመት ድገም እና
ይትረፍረፍ በእውነት ድገም እና ዓመት ድገም እና
= = = = = =
እንዲሁ እንዳላችሁ - -በፍቅር አይለያችሁ - - በፍቅር
ላመቱ በሰላም - - በፍቅር ያድርሳችሁ - - በፍቅር
ክርስቶስ በቀኙ - - በፍቅር ያቁማችሁ - - በፍቅር
የመንግስቱ ወራሽ - - በፍቅር ያድርጋችሁ - - በፍቅር
እንዲሁ እንዳለን - - በፍቅር አይለየን - - በፍቅር
ለዓመቱ በሰላም - - በፍቅር ያድርሰን - - በፍቅር
አማኑኤል በቀኙ - - በፍቅር ያቁመን - - በፍቅር
የመንግስቱ ወራሽ - - በፍቅር ያድርገን - - በፍቅር
= = = = = =
የቅዱሳን መላክት የፃድቃን ሰማዕታት
ረድኤት በረከት ይግባ በሁሉም ቤት
በሁሉም ቤት(፪) ይግባ በረከት(፪)
እንቁም በሃይማኖት ፀንተን በትጋት
የአስራት አገር የአበው ቀደምት
የቅዱሳን አባቶች ትውፊት
ይገባልና ልንጠብቅ በእውነት
ባህላችንን የአባቶች ትውፊት (፫)
<< ታቦርና አርሞንኤም በስምህ ደስ ይላቸዋል >>
መዝ፹፰፥፲፪
የእግዚአብሔር ቤተሰቦች JOIN ጆይን ሳታረጉ እንዳታልፉ
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@Tewahdo_Haymanote
@Tewahdo_Haymanote
@Tewahdo_Haymanote
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈---