richyaneyena | Unsorted

Telegram-канал richyaneyena - ንባብ ለአዕምሮ ጠብታ ማር ነው።

1900

በቻናሌ ውስጥ በማስተላልፈው ፕሮግራም አስተያየት ከአላችሁ ይህንን @Richyanyena ሊንክ በመጫን በግል አናግሩኝ!!

Subscribe to a channel

ንባብ ለአዕምሮ ጠብታ ማር ነው።

نصيحه ما بعد الرمضان فضيلة الشيخ صالح الفوزان الفوزان حفظه الله

Читать полностью…

ንባብ ለአዕምሮ ጠብታ ማር ነው።

ከጥቂት አመታት በፊት ሳውዲ አረቢያ ፡ ጅዳ ውስጥ አሮጌው ( አልባላድ ) ድልድይ የሚባለውን  አካባቢ የሚያውቅ  ሰው ይህንን የስምንት አመት ልጅ ያውቀዋል ።

ይህ ታዳጊ ከ12 አመቷ እህቱና ከእናቱ ጋር ፡ ኑሮን ለማሸነፍ ከኢንዶኔዥይ ወደ ሳውዲ አረቢያ ጅዳ መጥተው የሚኖሩ ሲሆን ፡ ይሻላል ያሉት የሳውዲ ኑሮ እንዳሰቡት አልሆን አለና ችግር ላይ ወደቁ
..
እና አንድ ቀን ይህንን የቤተሰቡን ችግር የተረዳው የ8 አመቱ ኢልያስ   እህቱ ዩስራ  አዘውትራ በደብተር ላይ የምትሞነጫጭራቸው ስእሎች እንድትሰጠው ጠየቃት ።

" እነዚህን ስእሎች ሽጨ ለእናታችን ገንዘብ ማምጣት እፈልጋለሁ "
...

እነዚህን ስእል ብሎ ማን ይገዛሀል አለችው
ብቻ ዝም ብለሽ ስጭኝ
ከደብተሯ ላይ የሞነጫጨረችውን ስእሎች እየቀደደች ሰጠችው ።
ትንሹ ኤልያስ ስእሎቹን ይዞ ፡ አሮጌው የባላድ ድልድይ ስር ተቀመጠ ።
.....
አላፊ አግዳሚው እያየው ያልፋል ። አንዳንዶቹ ደግሞ ይህ ትንሽ ልጅ መሬት ላይ ያስቀመጣቸውን በደብተር ሉክ ላይ በስክሪብቶና በከለር የተሞነጫጨሩ የልጅ ስእሎች እያየ ምንድነው ሲሉት ፡ እህቴ ዩስራ የሳለቻቸውን  ስእሎች እየሸጥኩ ነው
ስንት ነው ?
አንድ ሪያል
የልጁ ሁኔታ ያሳዘናቸው ሰወች የተወሰኑ ስእሎችን ገዙት
ከሰአታት በኋላ ኤልያስ ከያዛቸው ስእሎች ግማሹን በአንድ ሪያል ሂሳብ ሽጦ አስራ ሁለት ሪያል ይዞ ወደ ቤቱ ሄደ ።
....
ምንም ብር ለሌለው ለነኤልያስ ቤተሰብ ይህ ገንዘብ ብዙ ነበር ። እቤት እደገባም ለእህቱ ሉክና እስክሪብቶ አምጥቶ ፡ ሌሎች ስእሎችን ሳይ አላት ።
ነገ የምሸጣቸው ተጨማሪ ስእሎች ያስፈልጉኛል

እህቱ  ተጨማሪ ስእሎችን ስትስል አመሸች
ጠዋት ይዟቸው ወጣና  የተለመደው ቦታ ተቀመጠ ።
........
በዚህ መልኩ ጥቂት ቀናትን እንዳሳለፈም  አንድ የሳውዲ ጋዜጣ ( Saudi gazette ) ሪፖርተር ይህንን ህጻን ያየዋል።
..........
እና ይህንን ለልመና እጁን ያልዘረጋ ፡ ከዛ ይልቅ የእህቱን ስእሎች ሽጦ ቤተሰቡን ለመርዳት ስላሰበው የ8 አመት ኢንዶኔዥያዊ ህጻን በተመለከተ በጋዜጣው ላይ ጻፈ ።
ይህንን ተከትሎም የህጻኑ ሁኔታ ልባቸውን የነካቸው ሰወች ፡ በትዊተር ላይ ፡ አንድ ሪያል ላንድ ስእል በሚል ሀሽታግ ዘመቻ ጀመሩ ።
....
በዚህ የሶሻል ሚዲያ ካምፔን ብዙ ሰወች ዘመቻውን ተቀላቅለው የዚህን ታዳጊ ቤተሰብ ለመደገፍ ገንዘብ ሰበሰቡ ።
.........
የጉዳዩን ቫይራል መሆን ያዩት የሳውዲ አረቢያ የባህልና የኪነጥበብ ማህበር ሃላፊ ይህንን ታዳጊ ፈልጋችሁ አምጡልኝ ሲሉ ትእዛዝ ሰጡ ።
......
የሳውዲ ባህልና ኪነጥበብ አባላትና ትላልቅ ሚዲያዎች በተገኙበት አንድ ፕሮግራም ተዘጋጅቶ ታዳጊው ኤልያስ ፡ ከእህቱ ዩስራ እና ከእናቱ ጋር እንዲገኙ ተደረገ ።
.......
ባለሀብቶች ይህንን ቤተሰብ እንደግፋለን ሲሉ ቃል ገቡ ። ኤልያስና ዩስራ ትምህርት የሚገቡበት መንገድ ተመቻቸ ፡ ለእናቱ ስራ ተገኘላት ።
....
የእህቱን ስእሎች ሽጦ ቤተሰቡን ለመደገፍ በሞከረው ታዳጊና ፡ ይህንን በተረዱ መልካም ሰወች እገዛ  ምክንያት ነገሮች ተለዋወጡ ።

t.me/richyaneyena

Читать полностью…

ንባብ ለአዕምሮ ጠብታ ማር ነው።

ድክመትህን አላህ ፊት ብቻ ግለጥ። ዓለም ጉልበትህን ብቻ ይመልከት!…

ማንም ድክመትህን እንዳያይ! በመስታወት የሚያዩህ ዓይኖችህ እንኳን የጨፈገገና የተከፋ ፊትህን አይመልከቱ!

ደስታህ ሰዎች በሚዘረጉልህ የእዝነት እጅ ወይም በሚያሳዩህ ፊት ላይ አይቋጠር!…

የሰዎች እገዛም ሆነ ጫና ደስታህን ከፍም ሆነ ዝቅ አያድርጉብህ! የሰዎች መልካም ትድድር ተጨማሪ ነገር ሆኖ የደስታህና የእረፍትህ ምንጭ ቀልብህ ይሁን!
ህይወት ለደካሞች ጠባብ ናት!

Читать полностью…

ንባብ ለአዕምሮ ጠብታ ማር ነው።

የነጭ ሽንኩርት መድኃኒትነት

➊ ነጭ ሽንኩርት ስራን በትክክል ለማከናወን፣ የሰውነት ሕዋሳትን ጤናማ ለማድረግ ፣ድካምን ለማስወገድ፣ዕድሜን ለመጨመር፣በአይጥና በልዩ ልዩ ተባዮች የሚመጡትን ተስቦ በሸታዎችን ለመከላከል

➋ ማንኛውም ሰው መጥፎ ሽታ ባለበት አካባቢ ለፅዳት ከመሰማራቱ በፊት ነጭ ሽንኩርት ከትፎ ቢበላ ከማንኛውም በሽታ ከሚያመጡ ተዋህሲያን ለመዳን ይቻላል፡፡

➌ በቂ ሕክምና በሌለበት አካባቢ በቁስል ለሚሰቃይ ሕሙማን በነጭ ሽንኩርት ጭማቂ አጥቦ በቁስሉ ዙሪያ በመደምደም በፋሻ ወይም በንፁህ ጨርቅ በማሰር ሕመምተኛውን ለመፈወስ ይችላል፡፡

➍ ነጭ ሽንኩርት ቀቅሎ እንፋሎቱን የካንሰርንና የቲቢ በሽታዎችን ለመከላከልና በሳንባ አካባቢ ብርድና ጉንፋን ለማዳን ፍቱን መድኃኒቱ ነው፡፡

➎ ብርድ ብርድ በሚያሰኝ ሕመምና በተለይም በጥርስ ሕመም ለሚሰቃዩት ሕሙማን ሁለት ራስ ነጭ ሽንኩርት የውስጠኛውን ሽፋናቸውን በመላጥ በሁለቱም ጉንጫቸው በተለይም በተነቃነቀው ጥርስ በኩል ነክሰው ረዘም ላሉት ሰዓት ቢጠቀሙበት መልሶ ይጠነክራል፡፡

➏ ለአስም፣ ለጉሮሮ ክርካሪ ወይም ኮርታ ለተባለው በሽታ እንዲሁም ጉሮሮ ለማፅዳት የነጭ ሽንኩርት ጭማቂ በስኳር ወይም በማር መጠጣት የተፈተነ መድኃኒት ነው፡፡

➐ ነጭ ሽንኩርት የራስ ምታትና የደም ብዛት ያለባቸው ሰዎች ከ3 እስከ 5 ቀናት በማከታተል ሦስት ፍንካች በቀን ሦስት ጊዜ ቢበሉ ከድካምና ከደም ብዛት ሊፈወሱ ይችላሉ፡፡

➑ በደም መርጋት ምክንያት ለሚሰቃዩ ፣የልብ በሽታን፣ የፊንጢጣ ኪንታሮትና የእግር ደም ሥር እብጠት የተባሉትን በሽታዎች ለመከላከልና ለመዳን ነጭ ሽንኩርት በመብላት መፈወስ ይችላል፡፡

➒ ነጭ ሽንኩርት የቆላ ቁስል፣ችፌን፣የጨጓራ በሽታን ወረርሽኝን ኮሌራን ሳይቲካን የቁርጥማት ሕመምን እንደሚያድን የተረጋገጠ ነው፡፡

መልካም አዳር🥰

t.me/richyaneyena

Читать полностью…

ንባብ ለአዕምሮ ጠብታ ማር ነው።

25 ዓመት በ ትዳር ያለ ምንም ግጭት እንዴት ቆየህ ምክንያቱ ምንድነው ሲለው ከ 25 ዓመት በፊት እንደተጋባን ሚስቴ ጫጉላችን ላይ ፈረስ እየጋለበች ፈረሱ ፈርግጦ ጣላት በንዴት ተነሳች እና 1 ብያለው አለችው እና ፈረሱ ላይ ወጣች አሁንም ጣላት ድጋሚ ብስጭት ብላ ተነሳች እና ጮክ ብላ 2ብያለው ፈረሱ ላይ ወጣች ፈረሱ ግን አሁንም ጣላት ከዛ ወዲያው ሽጉጥ አውጥታ ፈረሱ ላይ በመተኮስ ገደለችው በድንጋጤ ምን ሆነሽ ነው ያምሻል እንዴ እንዴት እንዲ ታረግያለሽ ስላት 1 ብያለው አለች ከዛ እሄው 25 ዓመት ተከባብረን አለን እልሀለው ☺️

/channel/richyaneyena

Читать полностью…

ንባብ ለአዕምሮ ጠብታ ማር ነው።

​​አገባሁኝ እንጂ


አላገባም እንጂ ባገባማ ኑሮ
አሸወይና አይባል የለም እንጉርጉሮ
የምንስ መሰረግ በዚህ ውድ ኑኖ?
የምን እወቁልኝ የምን ጠጅ መጣል
ካርድ መበተኑ አገባች እንዲባል🙃
የምን ሚዜ መምረጥ
መኳል እና ማጌጥ
ቬሎ እየጎተቱ መረማመድ በቄንጥ 👰‍♀

የምን ችቦ አይሞላም የምንስ ሀይሎጋ
ሰርግን ሰበብ አርጎ መሰብሰብ በመንጋ
አንዴ ለቅልቅል አንዴ ደግሞ ለመልስ
በየ ዘመድ ቤቱ ለምን ልመላለስ?

ለምንስ ዳስ ይጣል ይበተን አበባ
ማንስ ያገባዋል ብፈታ ባገባ 🤨
በዚህ ለበርበሬ በዚህ ጋር ለሽንኩርት
ደግሞም አለፍ ብሎ ለቀብራራው ዘይት
ገንዘቤን ከስክሼ ከማቀርብ በየአይነት
በስሜ ባስቀምጥ ያበላኛል አመት🤣
😄
  እየበላን ወገን


t.me/richyaneyena

Читать полностью…

ንባብ ለአዕምሮ ጠብታ ማር ነው።

የቢዝነሥ ሃሣብ 2016ዓ.ም.
#002

የእቃ ማጠቢያ እሥፖንጅ መሥራት።

ትልቅ የሥፖንጅ ፍራሽ በ10,000ብር ትገዙና በምትፈልጉት ቅጥነት በረጅሙ ትሠነጥቁታላችሁ ምናልባት ለ አራት።መሠንጠቂያው በመኪና ባትሪ ተርሚናል ጠረጴዛችሁ ላይ በተወጠረ ቀጭን ሽቦ ነው።
ይህን ሥራ ቤታችሁ ሆናችሁ የምትሠሩት ነው።

አንዱ ሥንጥቅ ፍራሽ 1152 ሃፓ (በድሬዎች አባባል) ሊወጣው ይችላል።ለአራት የተሠነጠቀው ደሞ  4608 ሃፓ ።እያንዳንዱን በ 20ብር ብትሸጡት 92,000 ብር ትሸጡታላችሁ::
.........

አሁን ጥበቧ ያለችው እንዴት አረንጓዴዋን ፣ጠንካራዋን እሥፖንጅ እናምርታት ወይም ከተመረተ ቦታ አምጥተን እንለጥፋት ?

አረንጓዴዋን ከፖሊ ዩሪቴይን ኬሚካል እና አሸዋ (በጥንቃቄ) ወይም ከተፈጥሮ ሤሉሎሥና ቪሥኮሥ በማምረትና 'እንደማልማላት' ወይም እንደ 'ቃተኛ' የተሠነጠቀው እሥፖንጅ ላይ መቀባት ይቻላል።

የተመረተ የምትጠቀሙ ከሆነ ደሞ በማጣበቂያ(በግሉ ) ታጣብቁና በመሸንሸን ለገበያ ታዘጋጃላችሁ። ከሤሉሎሥ እንዴት እንደሚመረት ኣንብቡ ካልሆነም አኔ አብራራላችኋለሁ።

የአረንጓዴውን ልጥፍ ለመሥራት ከ10,000 ብር በላይ አይፈጅም።በቀን ለ 2 ሠራተኞች እና ለሌላ  2000 ብር ብትከፍሉ ፤ 1000 ብር የመጓጓዣ ክፍያ ብትጨምሩበት በአማካይ በ24,000 ብር ወጪ ፤ 92,160ብር ሽያጭ -24000 ወጪ = 68,000 ብር ጠቅላላ ትርፍ ታገኛላችሁ።ለመንግሥት የሚጠበቅባችሁን ክፍያ እንዳትዘነጉት።

በዚህ እሥፖንጅ ድንች፣ካሮትና የመሣሠሉትን  እንደሚላጥበት ያሣየችኝ ጥበበኛ አለች፣ድንቹ ሣይጎዳ እንዴት እንደምትልጠው ተመልከቱት።ደሞ ልጣጬ እንደሚበላም አትርሡ።

በርቱ!

Читать полностью…

ንባብ ለአዕምሮ ጠብታ ማር ነው።

ስኬት በገንዘብ ተገዝቶ ወይም በብር ቁልል ሚመጣ ሳይሆን በብዙ ፈተና ውስጥ አልፈህ በጠንካራ ትዕግስት ውስጥ የሚገኝ ጣፋጭ ደስታ ነው።ታገስ ከአሰብክበት ትደርሳለህ!!!

ሪች ነኝ።

Читать полностью…

ንባብ ለአዕምሮ ጠብታ ማር ነው።

ሰበር በጎ ዜና !!
አሏሁ አክበር
#ሼር_አድርጉት
ልበ ቀናው ታታሪው ብርቱው ታላቅ ወንድማችን ኡስታዛችን…ሃቢብና ኡስታዝ አቡኪ የ6ቱን ሸሂድ ወንድሞቻችንን (አሏህ በጀነት ያበሽራቸው) ቤተሰቦቻቸውን ቢሮው አምጥቶ አይዟችሁ ብሎ አጽናንቶ 600 ሺህ ብር አውጥቶ ለእያንዳንዳቸው 100 ሺህ ብር ስጦታ ሰጥቶ አብሽሩ ብሏል !!

አሏህ ደረጃውን በጀነትል ፊርዶውስ ያድርግለትና !!

t.me/richyaneyena

Читать полностью…

ንባብ ለአዕምሮ ጠብታ ማር ነው።

የዑለሞች ድንቃድንቅ ንግግሮች 8
───────────
ኢብኑል_ቀዪም ረሒመሁሏህ እንዲህ ይላሉ : -

«ሰደቃ የሚሰጥ የሆነ ሰው የሚሰጠው ሰደቃ በምስኪኑ እጅ ከማረፉ በፊት በአላህ እጅ ላይ እንደሚያርፍለት ቢያውቅ ኖሮ ተቀባዩ  ከሚያገኘው የደስታ ስሜት የበለጠ ሰጪው  ይደሰት ነበር።»

📚 ۞ مدارج السالكين【1/26】۞
───────────

Читать полностью…

ንባብ ለአዕምሮ ጠብታ ማር ነው።

نصيحه ما بعد الرمضان فضيلة الشيخ صالح الفوزان الفوزان حفظه الله

Читать полностью…

ንባብ ለአዕምሮ ጠብታ ማር ነው።

ሀይድ ላይ በሆነች ሴት ላይ 10 ነገር ሀራም ይሆንባታል፡፡
1-ሶላት
2-ጠዋፍ
3-ቁርአን መንካት
4-ቁርአን መሸከም(መያዝ)
5-ቁረአን መቅራት ቁርዐኑ በእጃ ይዛ ካሆነ በስልክ በቃል ይቻላል
6-መስጂድ መቀመጥ
7-ፆም
8-የጋብቻ ፍች
9-በመስጅድ ማለፍ(ይንጠባጠብብኛል ብላ ከፈራች)
10-ግኑኙነት ማድረግ

t.me/richyaneyena

Читать полностью…

ንባብ ለአዕምሮ ጠብታ ማር ነው።

«አላህ ለተበዳይ ያዘጋጀውን ልዩ ሽልማት በዳይ ቢያውቅ ኖሮ ተበዳይን ከመበደል ይሰስት ነበር»

አሸይኽ አሸ፞ዕራዊይ

Читать полностью…

ንባብ ለአዕምሮ ጠብታ ማር ነው።

አስቸኳይ ክፍት የስራ ማስታወቂያ

Читать полностью…

ንባብ ለአዕምሮ ጠብታ ማር ነው።

ቅርንፉድ እና ወተት

በባዶ ሆድ ቢወስዱ ፣ ምን ይደርስብዎታል!
ትንሽ የተፈጨ ቅርንፉድ እና ወተት ጠቀሜታ

፨የልብ ፣ የሆድ ፣ የጉበት ፣ የሆድ እና የኩላሊት ድክመት ፡፡
፨የልብ እና የመገጣጠሚያዎች ሪህ.
፨ አርትራይተስ.
(አስም ፣ አክታ ፣ ሳል እና የአፍንጫ መታፈን ሂኪፕስ
ደካማ መፈጨት)
፨ የተዛባ የማስታወስ ችሎታ እና አለመግባባት
፨በሆድ እና በአንጀት ውስጥ ጋዝ ፡፡
፨የፊኛ ጡንቻዎችን ማዳከም ፣ የአልጋ መውጣት እና የሽንት መለዋወጥ።
፨የድድ እና የጥርስ ድክመት
፨አጠቃላይ ድክመት እና ግድየለሽነት።
፨ደካማ የወር አበባ ዑደት.
፨ደካማ የማየት ችሎታ
፨ብጉር ፣ የቆዳ ኢንፌክሽኖች እና የነፍሳት ንክሻዎች ፡፡
፨በደም ውስጥ ያለውን የስኳር መጠን ያስተካክላል እንዲሁም የደም ስኳር መጠንን ይጠብቃል።
፨ጉንፋን እና ብሮንካይተስ.
፨የጉሮሮ ህመም እና የቶንሲል በሽታ.
፨ካንሰርን ለመከላከል ይረዳል ፡፡
፨ጭንቀት ፣ ድብርት እና ሥነልቦናዊ ሁኔታዎች ፡፡

Читать полностью…

ንባብ ለአዕምሮ ጠብታ ማር ነው።

ኢስላም እና ጫት በዶክተር አብይ አህመድ

t.me/richyaneyena

Читать полностью…

ንባብ ለአዕምሮ ጠብታ ማር ነው።

ለአንድ ባሪያ በጣም የሚጠቅመው 'አስቲግፋር' ነው ወይስ 'ተስቢሕ '?
ሸይኹል ኢስላም እብን ተይምያህ ተጠየቁ
እሳቸውም ፦
/ልብስ ንፁህ ከሆነ ሽቶና ቡኹር ይጠቅመዋል
ልብሱ ቆሻሻ ከሆነ ግን ሳሙናና ውሃ ይበልጥ ጠቃሚ ይሆናል •••
ተስቢሕ - ለንፁሖች እንደ መዋቢያ ሲሆን
እስቲግፋር - ለአመፀኞች እንደ ሳሙና ነው
____
t.me/richyaneyena

Читать полностью…

ንባብ ለአዕምሮ ጠብታ ማር ነው።

*በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

የመኝታ አዳቦች 11 ናቸው
1ኛ -- ከመተኛት በፊት በር መዝጋት፣ እቃወችን መከዳደን እና እሳት ማጥፋት።
**ነቢያችን ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ልትተኙ ስትሉ *እቃወችን ከዳድኑ፣ ኮዳወችንም እሰሩ፣ በሮችንም ዝጉ። ሾይጧን የታሰረን አይፈታም። በር አይከፍትም። የተከደነንም አይከፍትም። መክደኛ ካጣችሁ እቃችሁ ላይ እንጨት አድርጋችሁ ቢሆን እንኳ የአሏህን ስም ጥሩበት። እሳትንም አጥፉ አይጥ ቤታችሁን ታቀጣጥላለች። (ሙስሊም ዘህበውታል።

2ኛ-- ጀናባ ከሆኑ ውዱእ አድርጎ መተኛት። (አህመድ፣ ኢብኑ ማጃህ እና ሎሎችም ዘግበውታል)።

3ኛ-- ፍራሹን መጥረግ።
ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም "ለመተኛት ወደ ፍራሻችሁ ስትቀርቡ በሽርጣችሁ ውስጠኛ ክፍል ሶስት ጊዜ ጠረግ አድርጉት ብለዋል።"
(ቡኻሪና ሙስሊም)

4 -- ቤት ውስጥ ብቻን አለመተኛት።
ዐብደሏህ ኢብኑ ዑመር ረዲየሏሁ ዐንሁ እንዳስተላለፉት ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ለብቻ መተኛት እና ለብቻ ጉዞ መውጣትን ከልክለዋል።"
(አህመድ ዘግበውታል)

5 -- ውዱእ ማድረግ
ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ወደ መኝታ ስትሄድ ለሶላት የምታደርገውን ውዱእ አድርግና በቀኝ ጎንህ ተኛ ብለዋል።
(ቡኻሪና ሙስሊም)

6-- የመኝታ አዝካሮችን እና እንደ ሱረቱል ኢኽላስ፣ ሱረቱ ናስ፣ ሱረቱል ፈለቅ፣ አያተል ኩርሲ የመሳሰሉትን አንቀፆች ማንበብ አፈፃፀሙን እና ሙሉውን አዝካሮች ሂስኑል ሙስሊም ላይ ታገኟቸዋላችሁ።

7-- በቀኝ ጎን መተኛት።
(ቡኻሪና ሙስሊም)

8 -- በሆድ አለመተኛት።
ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም በሆዱ ተኝቶ ያዩትን ሶሃባ "ተነስ ይህ አተኛን አላህ የማይወደው ነው ብለውታል።"
(አህመድ፣ ቲርሚዚና ሌሎችም ዘግበውታል)

9 -- ከእንቅልፍ በድንጋጤ ከባነናችሁ።
اعوذ بكلمات الله التامات من غضبه وعقابه، وشر عباده، ومن همزات الشياطين وان يحضرون.

*አዑዙ ቢከሊማቲላሂ ታማቲ ሚን ገዶቢሂ፣ ወዒቃቢሂ፣ ወሸሪ ዒባዲሂ፣ ወሚን ሐማዛቲ ሸያጢን ወአን የህዱሩን።

(ትርጉም ( ሙሉ በሆኑት በአላህ ቃላቶች ከቁጣው፣ ከቅጣቱና ከባሮቹ ክፋት፣ እንዲሁም ከሾይጧን ጉትጎታና እንዳይቀርበኝም በአላህ እጠበቃለሁ።" ማለት።

10 -- መልካም ወይም መጥፎ ህልም ካያችሁ መልካምን ህልም ያየ ለሚወደው መናገር። መጥፎን ህልም ያየ ለማንም አለመናገር። (ሙስሊም)
በሌላ ዘገባ "መልካም ህልም ከአላግ ነው። መጥፎ ቅዠት ግን ከሾይጧን ነው። መጥፎን ቅዠት ያየ በስተግራው እየተፋ ከክፋቱ በአላህ ይጠበቅ ይህንን ካደረገ አይጎዳውም ብለዋል።
(ቡኻሪና ሙስሊም)
እንደ ባነናችሁ ወደግራ ዞራችሁ አዑዙቢላሂ ሚነ ሾይጧኒ ረጅም ብላችሁ ሶስት ጊዜ በስሱ ትፍ ትፍ ትፍ ብላችሁ አተኛኛችሁን አዙራችሁ ተኙ።

11 -- ከእንቅልፍ ስትነቁ አዝካሮችን ማለት።
ሙሉ አዝካሮችን ሂስኑል ሙስሊም ላይ ታገኟቸዋላችሁ።
ወሏሁ አዕለም.

t.me/richyaneyena

Читать полностью…

ንባብ ለአዕምሮ ጠብታ ማር ነው።

#የሀበሻ_መዝገበ_ቃላት

#ኑሮ:- ለሲዖል ህይወት ልምምድ የሚያደርጉበት ጠባብ ጂም

#ዘመድ:- ባልተዘጋጁበት ቀን የሚመጣ ተጨማሪ ችግር

#ጫማ:- አብሮ የሚደክም እውነተኛ ፍቅረኛ 

#ደሞዝ :- ከወጣበት ዕለት ውጭ ቁም ነገር የሌለው

#ብድር:- በፍቅር የወሰዱትን በጦርነት የሚመልሱበት የዝርፍያ ሙከራ።

Читать полностью…

ንባብ ለአዕምሮ ጠብታ ማር ነው።

ምቀኛ የሌሎች ጥገኛ ነው።እኛ የራሳችንን ኑሮ እንኖራለን እሱ ግን እራሱን ትቶ የእኛ ኑሮ ይኖራል።

Читать полностью…

ንባብ ለአዕምሮ ጠብታ ማር ነው።

አንድ ጊዜ የሞት መልእክተኛ ወደ አንድ ሰው ጋ ይመጣና

"ጓደኛዬ ዛሬ ያንተ ተራ ነው ልወስድህ መጥቻለሁ"
ይለዋል።

ሰውዬውም ተደናግጦ

"ግን እኮ አልተዘጋጀሁም" ብሎ ይመልስለታል።

የሞት መልክተኛውም

"እንግዲህ ምንም ማድረግ አልችልም ሊስቴ ላይ ያለው የመጀመሪያ ስም ያንተ ነው" ይለዋል ።

ሰውዬውም ተስፍ
በመቁረጥ

"እሺ በቃ ትንሽ አረፍ በል የሚበላ ነገር ላምጣልክ እኔም ቤተሰቦቼን እና ጕደኞቼን ልሰናበት ከዛ ይዘከኝ ትሄዳለክ"አለው።

መልእክተኛውም በሰውዬው ሀሳብ ተሰማምቶ ቁጭ አለ።

ሰውዬው አንድ ሀሳብ መጣለት።

ምግቡ ውስጥ የእንቅልፍ መድሀኒት ጨምሮ ለመልእክተኛው ሰጠው።

መልእክተኛው ምግቡን በልቶ ከጨረሰ በኃላ ወዲያው ጥልቅ እንቅልፍ ውስጥ ሲወድቅ ሰውዬው በፍጥነት መልእክተኛው ስም ዝርዝር የጳፈበትን ሊስት አንስቶ የሱን ስም ከመጀመሪያው አጥፍቶ መጨረሻ ላይ አደረገው ።

መልእከተኛው ከጥልቅ እንቅልፍ ሲነሳ ሊስቱን ያነሳና

"በል እንግዲህ ጓደኛዬ ስላደረክልኝ እንክብካቤ ሁሉ በጣም አመስግናለው በጥሩ ሁኔታ ሰላስተናገድከኝ ለዛሬ ከመጨረሻው እጀምራለው ።😊

ማንም ሰው ከቀኑ አያልፍም!!😅


t.me/richyaneyena

Читать полностью…

ንባብ ለአዕምሮ ጠብታ ማር ነው።

አዲሱ ዓመት
ከጎረቤት ረብሻ
ከባለትዳር ጥቅሻ
ከተናካሽ ውሻ
ከገቢዎች ፈለጣ
ከአለቃ ቁጣ
ከመንግስት ለበጣ
ከሞራል ስብራት
ከገንዘብ ብድራት
ከቀፋዮች ብልጠት
ባዶ ቤት ከመግባት
ከጅል ጋ ከመዋል
ቪዛ ከመከልከል
አጥር ከመዝለል
ጨጏራ ከሚልጥ
የመብራት መቆራረጥ
ከሰራዊት ማስታወቂያ
ከኢቲቪ ማስጠንቀቂያ
ከሰይፉ ፉገራ
ከፈሪ ፉከራ
የፀዳ ይሁንላችሁ።
ላላገባችሁ ትዳር
ላገባችሁ ፍቅር
ያድላችሁ።
ባዲሱ ዓመት
ከኪሳችሁ ፍራንክ
ከጥርሳችሁ ሳቅ
አይጥፋ።
ቤታችሁ ቄጠማ ጎዝጉዙ
ላንድ ልጅ አንድ ደብተር ግዙ
በጎ ሰሪዎችን አግዙ።
ወልዶ ለመሳም
ዘርቶ ለመቃም
ያብቃችሁ።
መርቅኖ ከማቀድ
አፍቅሮ ከማበድ
በግፍ ከመሰደድ
ካልተከደነ ጉድጏድ
ውሃ ካቆረ መንገድ
እጅ እጅ ከሚል ቀልድ
ጦምሮ ከመታሰር
ነግዶ ከመክሰር
ከባለጌ ወንበር
ከአሽሟጣጭ ከንፈር
ከንፁህ ሰው ደም
ከቆሸሸ ስም
ከስኯር ወረፋ
ከስልክ ጠለፋ
ቀጥሮ ከሚቀር
ከአካውንት ሀከር
ከውሃ ሙላት
ከወዳጅ ክህደት
ከfacebook ጅንጀና
ከውሸታም ዜና
ብሎክ ከመደረግ
like ከመነፈግ
ይሰውራችሁ።
አሜን!

Читать полностью…

ንባብ ለአዕምሮ ጠብታ ማር ነው።

ዘንድሮ

ሙስሊም ክርስቲያኑ አረፋ በገባበት ወጣቱ ሁሉም በዱዓ መበርታት አለበት ዘንድሮ ያለንበት ሁኔታ በጣም አሳሳቢ ላይ እየደረሰ ነው።

فَاسْتَجَابَ لَهُ رَبُّهُ فَصَرَفَ عَنْهُ كَيْدَهُنَّ ۚ إِنَّهُ هُوَ السَّمِيعُ الْعَلِيمُ

[ ሱረቱ ዩሱፍ - 34 ]
ጌታውም ጸሎቱን ተቀበለው፡፡ #ተንኮላቸውንም ከእርሱ መለሰለት፡፡ እነሆ! እርሱ ሰሚው ዐዋቂው ነውና፡፡

Читать полностью…

ንባብ ለአዕምሮ ጠብታ ማር ነው።

የኢትዮጵያ ግፍ የአለም ጫፍ ደርሶ አጠገባችን ያለው መንግስት እንዳልሰማ መሆን ያሳዝናል።
t.me/richyaneyena

Читать полностью…

ንባብ ለአዕምሮ ጠብታ ማር ነው።

መገፋት ጥሩ ነው እብዛም ሳይወድቁ
የተገፉት ቆመው የገፉ ወደቁ
እመኑኝ ያማያልፍ ነገር የለም ብርቱ መሆን ብቻ ነው

Читать полностью…

ንባብ ለአዕምሮ ጠብታ ማር ነው።

ኢድ ሙባረክ
🌙🌟عيد مبارك تقبل الله منا ومنكم صالح الأعمال كل عم وأنتم بخير🌙🌟

Читать полностью…

ንባብ ለአዕምሮ ጠብታ ማር ነው።

"አንተ የአላህ ነብይ! ጌታህ ፍትሃዊ ነው ወይስ በዳይ?" አለቻቸው በእጇ በያዘችው ከዘራ ላይ እየተደገፈች

ጌታዬ ሆይ!
ብዕሬን እንደ ኻሊድ ኢብኑልወሊድ ሠይፍ የሰላ አድርግልኝ
Mahi Mahisho

ዕድሜዋ የገፋ አሮጊት ናት። በጥያቄዋ ተቆጥተው ቀልቧን ከመስበራቸው በፊት ንግግራቸውን ቆጠብ አደረጉና ግራ በተጋባ መንፈስ አይዋት
"ምን ደርሶብሽ ነው?" በማለት ጠየቋት

ንግግሯን ጀመረች
"ሶስት ልጆች አሉኝ ጥጥ ፈትዬ፣ የፈተልኩትንም ሽጬ በማገኘው ገንዘብ እመግባቸዋለሁ። እንዝርቴን አሽከርክሬ ጉሮሯቸውን እደፍናለሁ። እንደተለመደው ፈትሌን በቀይ ፎጣ ጠቅልዬ ልሸጥ ወደ ሱቅ እያመራሁ ሳለ በድንገት በሠማይ ሲከንፍ የነበረ አሞራ የልጆቼን ጉሮሮ የምደፍንበትን ፈትል ነጥቆኝ ተፈተለከ...."
ይህን እያለች በሩ ተንኳኳ በከተማዋ አሉ የተባሉ አስር ነጋዴዎች ወደ ውስጥ ዘለቁ።

የያዙትን ገንዘብ ሰደቃ ሊሰጡ እጃቸውን ዘረጉ። ነብዩላህ ዳውድ ብሩን ከመቀበላቸው በፊት ለምን ሰደቃ ሊሰጡ እንደፈለጉ ጠየቋቸው እነርሱም እንዲህ አሉ
"ከሀገራችን ወጥተን የባህር ጉዞ ከጀመርን ሰነባበትን። ወደቀያችን ለመድረስ ጥቂት ርቀት ሲቀረን መርከባችን መስመጥ ጀመረች በህይወትና በሞት መሐል ሳለን አንድ አሞራ ጥጥ የያዘ ቀይ ፎጣን ወረወረልን። የመርከቡን ቀዳዳ በጨርቁ ደፍነን ጉዟችንን ቀጠልን። በህይወት ከተረፍን እያንዳንዳችን ሰደቃ ልንሰጥ ቃል በገባነው መሰረት ሰብስበን ወደርስዎ ይዘን መጣን" አሉ፡፡

ነብዩላህ ዳውድ ዲናሮቹን ተቀብለው ለሴትዮዋ እየሰጧት "ጌታሽ አንቺን ከድካም አሳርፎ በየብስ በባህሩ ይነግድልሻል አንቺ ፍትሀዊ ነው ወይስ በዳይ? ብለሽ ስለሱ ትጠይቂያለሽ በይ ሐቅሽን ይዘሽ ወደቤትሽ ሂጂ" አሏት፡፡

እናንተንም አላህ ከድካም አሳርፎ በድንገት ያስደስታችሁ

Читать полностью…

ንባብ ለአዕምሮ ጠብታ ማር ነው።

ሌባው ሌሊት ላይ አንዲት አሮጊት ቤት ዘሎ ገባ። እሷም ኮቴውን ስትሰማ ከእንቅልፏ ደንግጣ ነቃች። «ልጄ ሆይ ! ይህን አስከፊ የስርቆት መንገድ እንድትመርጥ ያስገደደህ የኑሮ ሁኔታ እንጂ ስመለከትህ መልካም ሰው እንደሆንክ ያስታውቃል። ስማ ልጄ ! እኔ በጣም ብዙ ገንዘብና ጌጣጌጥ ያለኝ ሰው ነኝ። ሀብቴን ሁሉ ይዘህ ብትሄድ አይደንቀኝም። ነገር ግን ከመሄድህ በፊት በድንጋጤ ከእንቅልፌ የቀሰቀሰኝን ህልም እንድትፈታልኝ እፈልጋለሁ» አለችው። ሌባውም «ይህች አሮጊት የምትናገረውን የማታውቅ ንክ ናት። ህልሟን ሰምቼ ከፈታሁላት በኋላ ቤቷን ለቅቄ ወደ ሌላ የስርቆት ተግባሬ ብሰማራ ይሻለኛል» ብሎ ወሬዋን ማዳመጥ ጀመረ።

እሷም «በህልሜ በአንድ ትልቅ ወንዝ ዳር እየተራመድኩ እያለ ድንገት እግሮቼ ተንሸራተው ወንዙ ውስጥ ወደቅሁ። ልክ እንደዚህ በጣም እየጮህኩ " ኧረ ጀማማማማማማል እርዳኝ "... "ጀማማማማል እርዳኝ " እያልኩ ድምጼን ከፍ አድርጌ በተደጋጋሚ ተጣራሁ። በድጋሚ ልክ እንደዚህ " ኧረ ጀማል ፈጠን ብለህ ና"... "ጀማማማማል እባክህን ውረድ"» በማለት ጮሁኩ አለችው።

ሌባውም «ለመሆኑ አሁን እንዲህ እየጮህሽ የጠራሽውን ጀማል ታውቂዋለሽ ?» ብሎ ከመጠየቁ የአሮጊቷ ልጅ ጀማል ከአንደኛው ፎቅ ላይ ሽመሉን ይዞ ከተፍ አለ። ጀማል በያዘው ሽመል የሌባውን ወገብ እንደ ገብስ ይፈትገው ገባ። አሮጊቷም «ጀማልዬ በእጅህ እንዳይሞትብህ በዚህ መጠን ከወቃኸው ይበቃዋል» አለች 😂

ሌባው ምን ቢል ጥሩ ነው ...

«እኔ መወቀጥ የሚገባኝ ሰው ነኝና ጀማል እባክህ ደህና አድርገህ ውቀጠኝ ፤ አሁን እኔ ሌባ ነኝ ወይስ ህልም ፈቺ ?? እኔን ብሎ ህልም ፈቺ !! ጀማል በል ሳታቋርጥ ደህና አድርገህ ቀጥቅጥኝ» አለው 😂

t.me/richyaneyena

ምጥን አስተምህሮ

አላማህን ከግብ ለማድረስ ግስጋሴህን የሚያሰናክሉ ነገሮች ላይ የጎላ ትኩረት ከመስጠት ተቆጠብ። ግብህን ለማሳካት ቀዳሚ ያልሆኑ ጉዳዮች ያንተ ገዳይ ሊሆኑ ይችላሉ !!!😁😁😁😁

Читать полностью…

ንባብ ለአዕምሮ ጠብታ ማር ነው።

የሻይ ጥቅም እና ጉዳት

ሰላም ጤና ይስጥልን ውድ የሃያት ቤተሰቦች ስለ ሻይ ምን ያህል እናውቃለን?

ለብዙ ሰዎች ሻይ የአመጋገብ ዋነኛ አካል ሆኖ ቆይቷል። ጤናማ ስሜትን ያነሳሳል እና ጥማትን ያስወግዳል። ነገር ግን ጎን ለጎን ጎጂ ባህሪያት እንዳለው ይታወቃል። በዚህ ረገድ የሻይ ጉዳትን እና ጥቅሙን ማወቁ ጤንነታቸውን ለሚደግፉ ሰዎች ጠቀሜታ አለው፡፡

👉 የሻይ ጥቅሞች

• ሻይ ከሌሎች ምርቶች ውስጥ የማይገኙ በርካታ ምግቦችን ያካትታል-ፍሎራይድ፣ ማንጋኒዝ፣ ካልሲየም፣ መዳብ፣ ብረት፣ ዚንክ፣ ተፈጥሯዊ እና ጥራት ያለው ሻይ በተወሰነ ጊዜ ብቻ በሰውነት ላይ በጎ ተጽእኖ ይኖረዋል፡፡

• እርጅናን ይከላከላል በውስጡ ቫይታሚን ኢን ይዟል፡፡ እንዲሁም የጉሮሮ መቁሰል እና ሌሎች የቫይረስ ኢንፌክሽኖች እንዳይከሰቱ ይከላከላል በተጨማሪ ድካምን ያስግሳል

👉 የሻይ ጉዳት

• ከመጠን በላይ ትኩስ ሻይ መጠጣት የውስጥ አካላትን ያቃጥላል

• በተቃራኒው ቀዝቃዛ ሻይ የኩላሊት ጠጠር እንዲፈጠር ሊያደርግ የሚችል ኦክሌትስ ይዟል

• በውስጡ ያለው የካፌን መጠን ከፍተኛ ስለሆነ በተለይ ለነፍሰ ጡር ጎጂ ነው ::

• ከምግብ ጋር አንድ ላይ ሲወሰድ ለሰውነታችን የሚያስፈልገውን አይረን መጠን ይቀንሰዋል

*ሆኖም አጠቃቀማችንን ካስተካከልን ከጉዳቱ ይልቅ ጥቅሙ ስለሚያመዝን በአግባቡ በመጠቀም መጠጣት እንችላለን፡፡

Читать полностью…

ንባብ ለአዕምሮ ጠብታ ማር ነው።

#ዛሬ ጨረቃ ባለመታየቷ ነገ እሮብ የሸዐባን 30ኛ ቀን ይሆናል ስለዚህ ረመዳን አንድ (1) የሚሆነው ሀሙስ ይሆናል إن شاء الله

Читать полностью…
Subscribe to a channel