በቻናሌ ውስጥ በማስተላልፈው ፕሮግራም አስተያየት ከአላችሁ ይህንን @Richyanyena ሊንክ በመጫን በግል አናግሩኝ!!
#አቲካ
#ቆንጆ_ናት_ያገባት_ሁሉ_ሸሂድ_ነዉ።
#ክፍል_አስር_10
አላህን ፍሩ ሰሐቦችን በሚመለከት እኔ ከሞትኩ ቡሃላ ኢስላምን ለመውጋት እነርሱን ኢላማ ወይም አላማ አታድርጓቸው ።"*
በሌላ ሐዲስ ላይም
*" ባልደረቦቼን ኦንዳትሰድቧቸው ነፍሴ በእጁ በሆነችው ጌታ እምላለሁ አንዳችሁ የእሑድን ተራራ ያክል ብታወጡ የአንዳቸውንም ደረጃ አትደርሱም"* አሉ ረሡሉ አለይሂ ሰላቱ ወሰላም።
ከዚህ አስከፊ ማስጠንቀቂያ ቡሃላ እንግዲህ ሰሃቦችን በክፉ ማንሳት ማሚያስብ የሚደፍር ያለ አይመስለኝም። ወደ አቲካ ታሪክ አንመለስና ሰይዲና ዙበይር ረዲየሏሁ አንሁ አቲካ ላይ ከመቅናታቸው የተነሳ አንድ ቀን የሱብሒ ሰላት ለመስገድ ወደ መስጂድ ስትሄድ ሰይዲና ዙበይር ውዱእ አድርገው ወጡና በኒ ሰአድ የሚባለው ቦታ ላይ አድፍጠው ጠበቋት በዚያ ጭለማ ስታልፍ አንድ ግዜ መታ አርገዋት በፋጥነት ተሰወሩ። አቲካም ደንግጣ ዞር ብላ ስታይ ማንም የለም አላህ እጅህን ይቁረጠው አለችና በጣም ተደናግጣ ወደ ነብያችን አለይሂ ሰላቱ ወሰላም መስጂድ መሄዱን ትታ ወደ ቤቷ ተመልሳ ሄደች። ሰላቷንም በቤቷ ሰገደች ። ሰዎች እንዲህ አደብ አጡ በማለት በጣም አዝና ስለደረሰበት ነገር እያሰላሰለለች ሳለ እቤት ተመልሰው ምነው መስጂድ አላየሁሽም አሏት አላህ ይዘንልህ የአብደላህ አባት ካንተ ቡሃላ እኮ ሰዎች ተበላሹ። ዛሬ ለ ሴት ልጅ መስጂድ ከመስገድ ጓዳዋ ውስጥ መስገድ ይሻላታል በማለት ከዚያን ቀን ጀምሮ መስጂድ ሄዳ መስገድን አቆመች። ሰይዲና ዙበይርም በድርጊታቸው ቢፀፀቱም ሊቋቋሙት ያልቻሉት ስሜት እዚህ አደረሳቸው። አቲካ ሰይዲና ዙበይርን ወዳ እቤቷን አድምቃ ትዴሯን አሳምራ በደስታ እየኖሩ ሳለ የአቲካን ሀዘን ማስረሳት ሳይሆን የሚሸፋኑላት የሰይዲና ዙበይር ከልክ ያለፈ ውዴታንና እንክብካቤን በማሳየት ነበር። ያ ነብያችን አለይሂ ሰላቱ ወሰላም ተንብየውት ያለፉት ትንበያ ወይም ፊትና መዲና ውስጥ እንደ እሳት ሲቀጣጠል ወንድሜን አሊይ ኢብኑ አቡጧሊብን አልወጋም በማለታቸው ብቻ ሰይዲና ዙበይር ካፋሲቆች ከፍተኛ ተቃውሞ ገጠማቸው። ከዚያም መንገድ ላይ እየሄዱ በ አሰቃቂ ሁኔታ በ አምሩ ኢብኑ ጃሙዝ በተባለ ፋሲቅ ተገደሉ። ሰይዲና ዙበይር መንገድ ላይ ደማቸው ፈሶ በሚያስገርም ሁኔታ እነዚያ ወንጀለኞች ያ ንፁህ ደማቸው ላይ ተረማመዱበት። ሰይዲና ዙበይር ባላሰቡት ወቅት ነው የተገደሉት። አቲካ በሰማችው ዱብዳ ፊቷ ደም ለበሰ ፊቷ ጠቆረ አንተ ዙበይር ያስጀመርከኝን ፍቅር ሳታስጨርሰኝ እንደወጣህ ቀረህብኝ አለች። በታላቅ ሲቃ እየጮሀች እምባዋ መቆሚያ አነበረውም ለገዳዬ ደግሞ በግጥም ስትጠይቀው ።" ሳያስበው አድፍጠህ ከሃላው ገደልክብኝ ፤ አንተ ምን ክፉ ነህ ታውቀው ነበር እንዴ፤
ጀግናው ባለቤቴን ልገልህ ነው ብለህ በነገርከው ውዴን፤
ቀድመህ የተነገረው ፤
ደርሰህ ጀግና ብትሆን፤
ሰይፍህን አውጥተህ ብትሞክረው ባሌን፤
ነፍስህ ትሆን ነበር፤
በርሱ እጣ ኩታ፤
እጅህ ሽባ ይሁን፤
አንተ ፈሪ ሽፍታ፤
ገለህ ምን ተጠቀምክ፤
እርሱን አሳልፈፈህ የሸሂድ ደም አታውቅ፤
አንተማ ክፉ ነህ ..
እያለች ስንኟን አነበበችው።
አቲካ ከባድ የሆነ የሐዘን መአበል አሁንም መታት። ሌት ተቀንም አነባች አለቀሰች 3 ባል 3ፍቅር 3 ትዝታ 3 ሸሒድ። ሰይዲና ዙበይር ብዙ ንብረት ስለነበራቸው ከሌላ ሚስት የወለዷቸው ልጃቸው አብደላህ ለ አቲካ መቶ አቲካ ሆይ አታስቢ ሐዘንሽ ይብቃ አንቺም እናታችን ነሽ የ አባታችን ሐቅ ይገባሻል ነይ ውርስ ተካፈይ ብሎ ሲጠራት አቲካም እኔ የዙበይር ትዝታዎች ይበቁኛል ብላ ውርሱን እምቢኝ ብላ መለሰቻቸው። አብደላህ ግን እቤት ሄዶ ተመልሶ መጣና ድርሻዋን ለርሷ የሚሆን ስድስት መቶ ሺ ድርሃም አሸከማት። በአስገራሚ ሁኔታ አቲካ ሶስተኛውን ባሏን አጣችው። ሰይዲና ዙበይር እርሷን ከገቡ ቡሃላ ብዙ ትዝታነና ብዙ የማይረሱ ቀናትን አሳይተዋት ነበር ። ሀዘኗንም በዛ በላቀ ግጥሟ ገልፃው ነበር። ነገር ግን ከዚህ ሁሉ ሀዘን ጋር ተቋቁማ የቀረባትን ፈገግ ብላ ሊያፅናናት የሞከረውንም ከ አፅናኙ በተሻለ ሁኔታ የአላህ ራህመትንና እዝነት ሰፊነቱን በመናገር ትሸኝ ነበር። ነገር ግን ሰዎች ሁሉ ተሰናብተዋት ሲሄዱ እቤቷ ስትመለስ በጥልቅ የትዝታ ውቅያኖስ ውስጥ ትዋኛለች። ሰይዲና ዙበይር አንድ ነገር ትተተውላት የሄዱት ልብሳቸው ላይ የሚወዱት የእጥብ ሽታቸው ነበር። ሰይዲና ዙበይርንም ከመውደዷ የተነሳ ሞተውም እንኳ የሚፈፈልጉትን ነገር እያሟላች እየጠበቀችም ያንን የተወችውንም መስጂድ እንደተወች በዛው በአቋም ላይ ነበረች። የባል ሐቅ ከሞት ቡሃላም ይጠበቃል እሷ ዘንድ ያ ሰላም! እዚህ ላይ አሳሳቢው ነገር ለ ሰይዲና ዙበይር መገደል ምክንያት የነበረው በመዲና ውስጥ የተፈጠረው ከባድ ፊትና ትልቅ ደረጃ የመድረሱ ጉዳይ ነበር ከሰይዲና ኡመር ኢብኑ ኸጣብ ቡሃላ ኸሊፋ የነበሩት አሚረል ሙእሚኒንና ሰይዲና ኡስማን ኢብኑ አፋን ከ አስሩ በጀነት ቡሽራ ያገኙት ናቸው ። ረሱል አለይሂ ሰላቱ ወሰላም ሰይዲና ኡስማንን እንደወደዷቸው እንዳወደሷቸው ነበር የሞቱት----
t.me/richyaneyena
#ይቀጥላል
ካንሰር አደገኛ በሽታ አይደለም።
ዶክተር ጉፕታ ማንም ሰው በቸልተኝነት ካልሆነ በስተቀር በካንሰር መሞት የለበትም ይላሉ።
(1) የመጀመሪያው እርምጃ ስኳር መውሰድ ማቆም ነው። በሰውነትዎ ውስጥ ስኳር ከሌለ የካንሰር ሕዋሳት በተፈጥሯቸው ይሞታሉ።
(2) ሁለተኛው እርምጃ የሎሚ ጭማቂ በአንድ ኩባያ የሞቀ ውሃ ውስጥ በመጨመር በየቀኑ ጠዋት ከ1-3 ወራት ከምግብ በፊት መጠጣት እና ካንሰሩ ይጠፋል። በሜሪላንድ ሜዲካል ጥናት መሰረት፣ የሞቀ የሎሚ ውሃ ከኬሞቴራፒ 1000 እጥፍ የተሻለ፣ ጠንካራ እና ደህንነቱ የተጠበቀ ነው።
(3)። ሦስተኛው እርምጃ ጠዋት እና ማታ 3 የሾርባ ማንኪያ ኦርጋኒክ የኮኮናት ዘይት መጠጣት ነው ፣ ካንሰሩ ይጠፋል።
አለማወቅ ሰበብ አይደለም። ይህንን መረጃ ከ5 ዓመታት በላይ ሳካፍል ቆይቻለሁ። በካንሰር ሰው መሞት የለበትም።
t.me/richyaneyena
via Dr Gupta
#አቲካ
#ቆንጆ_ናት_ያገባት_ሁሉ_ሸሂድ_ነዉ።
#ክፍል_ስምንት_8
አቲካ ያገባቻቸው ወንዶች በሙሉ ሸሂዶች ብቻ ሳይሆኑ አቲካን እንደወደዱ እንዳፈቀሩ ሐቃቸውን እንደጠበቀች በዚያ ወደር በሌለው ቁንጅናዋ ሳትኩራራ ለአሉባልታና ሀሜት የትዳር በሯን ሳትከፍት ፤ የቀረባት ያገባት የአቲካን ትዳር የቀመሱ ወንዶች በጀነት አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላን አገናኘን እያሉ ነበር የሸሂድ ሞትን የሚሞቱት። አቲካን ያገባ ሁሉ ሸሂድ ነው ! ለሸሂድነት የጓጓ እና የተመኘ አቲካን ያገባል። ሸሂድን ፈልጎ አቲካን ፈልጎ ማግባት ያልቻለ ደግሞ በዚሁ ምኞቱ ሸሂድነትን በሌላ አጋጣሚ ያገኛል። ይህን እውነታም በተጨባጭ ለማረጋገጥም አቲካን ለማግባትና ሸሂድነትንም ፈልጎ እርሷን ለማግባት ሞክሮ ባለመቻሉ በምኞት ብቻ መጨረሻው ምን እንደሆነና እኚህ ታላቁ ሰሃብይ ማን እንደሆኑ ወደፊት የምናየው ይሆናል።
አቲካ የደረሰባትን ሀዘን መቋቋም አቃታት። መስጂድ መመላለስና ከሰው ተገልላ አላህን መገዛቱን ተያያዘችው። ትልቁ ችግር የፈጠረባት ግን የምሽቱ ያ አስፈሪ ህልም ነበር። አቲካ ከዚያን ቀን ጀምሮ አቡ ሉእሉእ ሰይዲና ኡመርን ሊወጋቸው ሲል ሰይዲና ኡመርን አድናለው ብላ ስትወራጭ እና ስትጮህ በላብ ተጥለቅልቃ ፀጥ ረጭ ባለበት ለሊት ከእንቅልፏ ሀይለኛው ጩኸቷ ያባንናታል።ምን አይነት የሚስት ፍቅር ነው? አቲካ ምን አይነት የባለትዳር በተለይ የሴቶች ተምሳሌት ነሽ?
አቲካ በዚህ ሁኔታ ላይ እንዳለች ቀስ በቀስ እያገገመች ኢዳዋን 3 ወሯን ጨረሰች። ይህች ውብ ሴት ግን ትዳር በቃት? እርሷን እና ሀዘኗን ለብቻ እንተዋቸው የሚል ወንድ አልነበረም። እርሷን ቢያገባ በሆነ አጋጣሚ ሸሂድ እንደሚሆን ልቡ እያወቀ የአላህን ውድ ባርያ አቲካን ከመጠየቅ ወደ ሃላ ያለ ወንድ የለም። አሁን ደሞ ማን ይሆን አቲካን ለትዳር የሚጠይቃት? ማንኛውም ሙስሊም ወይስ እዚያ ላይ ካሉት የረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ሰሃባዎች? አቲካም ብትሆን ከሰይዲና ዑመር ረዲየሏሁ አንሁ በሃላ ማንም ሰው ለትዳር ይፈልገኛል ብላ አላሰበችም። እዚህ ላይ ግን ተሳስታ ነበር ። አዎን አቲካ አሁንም እጩ ሚስት ሆናለች። እጅግ ካልጠበቀችው ሰሐብይ የትዳር ጥያቄ ቀረበላት። ሽማግሌም ተላከባት ። ይህ ሰሃብይ ነብያችን ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም በአንደበታቸው እንዲህ ሲሉ ተናግረውለታል "ሁሉም ነብያቶች ሀዋርይ ወይም ባልደረባ ነበራቸው የኔ ሀዋርይ እርሱ ነው" በማለት የተናገሩለት ውድ ሰሀብይ ነው። በአጭሩ ሀዋርይ ማለት ከዚያ ለሰዎች ከተላከው ነብይ በፍፁም የማይለኝ ፤የሚያገለግል፤ ምክርን የሚያማክር መልእክት የሚያስተላልፍ ለዚያ ነብይ ቅርብ የሆነ ሰው ነው። ይህ አቲካን ለትዳር የጠየቀው ሰሃብይ ቅፅል ስም የተሰጠው ነው። የረሱል ሰለላሁ ኡለይሂ ወሰለም የአክስት ልጅ ነው ። ማለትም የሰፍያ ልጅ። አስሩ በጀነት ቃል ከተገባላቸው ሰዎች ውስጥም አንዱ ነው። ከስድስቱ የሩሱል ሰለላሁ አሉይሂ ወሰለም አማካሪዎችም አንዱ ነው። ይህ ሰሃብይ እስልምናን የተዋወቀው የስምንት አመት ልጅ ሳለ ነበር። ህፃን ሆኖ የገዛ ስጋው የሆነው አጎቱ በእሳት እያቀጠለ በሙሐመድ ላይ ክፈር እያለ ሲያስፈራራው እና ሲያሰቃየው የነበረ ልጅ ነው። በ አስራ ስምንት አመቱ ነበር ከመካ ወደ መዲና የተሰደደው ይህ ታላቁ ሰሃብይ ወደ ሀገራችን ኢትዮጵያ በስደት ከመጡት ሰሃቦች አንዱም ነበር። በፍፁም ነብያችን አለይሂ ሰላቱ ወሰላም ገዝዋ ወይም ጦርነት ወተው ተለይቷቸው የማያውቅ ታላቅ ሰሃባ ነው። ኡሑድ በሚባለው ታሪካዊው ጂሃድ ላይ ሙስሊሞች ብዙ ተጎድተው ሳለ ሙሽሪኮች የጦርነት ሜዳውን ትተው ሲሄዱ ረሱል አለይሂ ሰላቱ ወሰላም የሚከተላቸው ብለው ሲጠይቁ ሳያመነቱ ብድግ ብለው ከተከተሏቸው ሰባ ሰሃባዎች ውስጥም አንደኛው ናቸው። አላህም ሱብሃነሁ ወተአላ በስራቸው የተነሳ ታላቅ ምንዳን እንዳዘጋጀላቸው በሱረቱል ኢምራን ላይ አንድ የቁርአን አንቀፅ አውርዶባቸዋል።
"እነዚያም መቁሰልን ካገኛቸው ቡሃላ ለአላህ እና ለመልእክተኛው የታዘዙት ከእነርሱ ውስጥ እነዚያ በጎ ለሰሩትና አላህን ለፈሩት ታላቅ ምንዳ አላቸው።"
ይህ ታላቅ ሶሃባ ማን ይሆን?አቲካስ ይህን የጋብቻ ጥያቄ ትቀበል ይሆን?
t.me/richyaneyena
---- #ይቀጥላል---
የኡድሒያ በሬ አስተራረድ ትምህርት
1/ መጀመሪያ ገበያ ወጥተን በሬውን search እናደርጋለን።
2/ ካገኘነው በኋላ: በተስማማነው መሰረት ዋጋውን ከፍለን በሬውን save ማድረግ ነው።
3/ ወደቤት እናመጣውና በ group በመሆን: መሬት ላይ በግራው download እናደርገዋለን።
4/ ከዛም የተቀደሰውን የጌታችንን የአላህን ስም በማውሳት shortcut እናደርገዋለን።
5/ ከዛም የበሬው ህይወት እስትንፋሱ swith off እስኪሆን እንጠብቀዋለን።
6/ ሲቀጥል ደግሞ ቆዳውን ከበሬው ሰውነት ላይ remove በማድረግ እናራቁተዋለን።
7/ በመቀጠል ወደ ሰውነቱ hack አድርገን እንገባለን።
8/ ከዚያም ከውስጡ ያሉትን applications አንድ በአንድ እናወጣቸዋለን።
8/ ያወጣናቸውን applications በፎልደር ላይ እንደረድራቸዋለን።
9/ ከዚያም ዘመድና ጎረቤት invite በማድረግ እንቃመሳቸዋለን።
10/ ምስኪኖችን ጠርተን ደግሞ share እናደርጋለን።
ትስማማላችሁ???
t.me/richyaneyena
በኡስታዝ አቡ ሀይደር የተፃፈ
#አቲካ
#ቆንጆ_ነች_ያገባት_ሁሉ_ሸሂድ_ነዉ#
#ክፍል_አምስት
አቲካ የሰይዲና ኡመር በእስልምና ታሪክ ውስጥ ያላቸውን ቦታ ታውቃለች በተቃራኒው ደግሞ እናታችን አዒሻን ማስከፋት አትፈልግም ። በተለይ ደግሞ ኡመልሙእሚኒን አዒሻ የወንድሟ አብደላህ ቃልኪዳን በአቲካ ሲፈርስ አቲካ ራሷ ምን እንደሚፈጠር አታውቅም። አቲካ በደንብ አስባበት የመጨረሻ ውሳኔዋ ላይ ደረሰች የአቲካ ውበት ቁንጅና አደብ እና አኽላቅ አላህ የሰጣት የግጥም ችሎታ ሁሉ ከሴቶች ጎላ ብላ እንድትታይ አድርጓት እዚህም ደረጃ ደረሰች የአቲካ ባል ሸሂዱ አብደላህ በሞት ሲለያት የገጠመችው ግጥም በመዲና ውስጥ ሰዎች ሐፍዘውት በሃዘናቸው እና በትካዜያቸው ጊዜ ይደጋግሙታል። መንገድ የኖሩ ልጆች እንኳን ሳይቀሩ በዚያ በጣፋጭ እና ማራኪ ልብ በሚነካ አንደበታቸው ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ሲገጥሙት መንገድ ላይ ጉዳይ ኖሮት ፈጠን ብሎ ሲሄድ የነበረው ሳይቀር ፈዞ ይሰማቸው ነበር ይባላል። በዘመኗ ብቻም ሳይሆን ዛሬም አቲካን ያስታወሰ ስለአቲካ ከየት ልጀምር ብሎ ይጠይቃል። አቲካ ቆረጠች። አቲካ ለሰይዲና ኡመር መልእክት ልካ ውሳኔዋን አሳወቀች ። ይህ ውሳኔዋ አንዳንዶችን ሊያስከፋ ይችላል ሌሎች ደሞ ሊያስደስት ይችላል። አዎ እኔ ፍቃደኛ ነኝ ፤ እኔ አንቱን ማግባት በምን እድሌ በየትኛውም ሰአት ዝግጁ ነኝ በማለት መልእክቷን አስተላለፈች። የኒካሑ ቀን ተወሰነ በዚህ ግዜ ኡመል ሙእሚኒን አዒሻ ይህ ኸበር እንደደረሳት የወንድሟ አብደላህ መሬት እንዲመለስላት አቲካ ዘንድ መልዕክተኛ በመላክ የወንድሟን መሬት ታስመልሳለች። ሰይዲና ኡመር ትልቅ ድግስ ደግሰው የነብያችን ﷺ ሰሃባዎች በተገኙበት የአቲካ ኒካህ ይታሰራል። አቲካ ምንኛ የታደለች ሴት ነች? አቲካ የሰይዲና ኡመር ሚስት ሆነች ። የመጀመርያውንም ለሊት አስመልክቶ ኢብኑ ሰዒድ ሲናገ አቲካ ከአዲሱ ባሏ ጋር ብቻዋን ስትቀር አብደላህን አስታውሳ እራሷን መቆጣጠር አቅቷት ስታለቅስ ሰይዲና ዑመር ሐቃቸውን እምቢ ብላ ነበር ብለዋል ሰይዲና ዑመርም ከፈጅር በፊት ጥለዋት እንደሄዱና በሚቀጥለውም ቀን እንዳልተመለሱላት ይናገራሉ። አቲካም ባጠፋችው ጥፋት ተፀፅታ ያ ኡመር ተመለስልኝ አጥፍቻለው በማለት ጠይቃቸው ብዙ ለምና ተለማምጣ ሰይዲና ኡመርን እንዳስመለሰች ተናግረዋል። ከዚያም ቡሃላ በጣም ወዳቸው ሐታ ወደ ውጪ ሲወጡም ሆነ ሲገቡ በመሳም ትቀበላቸው እንደነበረ ተናግረዋል። አቲካ ከሰይዲና ዑመር ጋር አላህን በመገዛት የባሏን ሐቅ በሚገርም መልኩ እየጠበቀች ሰይዲና ዑመር መስጂድ ለሰላት እንድትሄድ ሁሉ እንደፈቀዱላት ተናግረዋል። ከአቲካም ኢያድ የሚባል ልጅ አግኝተው በሰላም በደስታ በፍቅር ይኖሩ ነበር። ነገር ግን ይህ ፍቅር እና ደስታ ለብዙ ጊዜ አልቆየም። አቲካ ሌላ የሀዘን ጎዳና ልትገባ ነው ። ሰይዲና ዑመር ምን ይገጥማቸው ይሁን?
t.me/richyaneyena
.... #ይቀጥላል,,,,,,,,,,,,
#አቲካ
#ቆንጆ_ናት_ግን_ያገባት_ሁሉ_ሸሂድ_ነዉ።
#ክፍል_ሶስት_3
አብደላህም ሚስቱ ወዳለችበት ፈጥኖ በመሄድ የምስራቹን ይነግራታል። ሚስቱም ቀዝቀዝ ብላ አልመለስም ትለዋለች ። አብደላህም ሚስቱን ለብዙ ሰአት ይለማመጣል ይለምናታልም እሷ ግን አሻፈረኝ ትላለች። ከአሁን በሃላ እራሱን እንደሚያሻሽል ለዱንያውና ለአኼራው ለመስራት ታጥቆ እንደተነሳ ቢነግራትም አይሆንም ብላ ትእግስቱ እስከሚሟጠጥ ድረስ ደጅ ታስጠናዋለች። በመጨረሻም ከብዙ ድካም ቡሃላ ወደ ቤቱ ትመለሳለች። ይህንንም ያደረገችው ኩራት ኖሮባት ሳይሆን ወይም ስለወደዳት ንቃው ሳይሆን የምትወደውን ባሏን ለማሻሻል ብላ ነበር። ከዚህ ቀን ቡሃላ አብደላህ ወደ ኑሮው እና ኢባዳው ተመልሶ አባቱንም አስደስቶ ከሚስቱ ጋር የደስታ እና የፍቅር ኑሮ ሲኖር እንደ ተምሳሌት ይወስዷቸው ነበር። ነገር ግን ይህ ወደር ያልነበረው የባል እና ሚስት ደስታ እና ፍቅር በአጭሩ ሊቋጭ ሆነ። አብደላህ አንድ ቀን ለሚስቱ መጥቶ በቅርቡ የምሞት አይነት ስሜት አለኝ ከእኔ ቡሃላ ሌላ አታገቢ ይላታል አብደላህ በዚህ ንግግሩ ሚስቱን የውቅያኖስ ውዥንብር ውስጥ ይከታታል በጣም ተጨነቀች ተጠበበች ይባስ ብሎ አብደላህ ከኔ ሌላ ባል አታግቢ ድጋፍ ይሁንሽ ዘንድ በማለት አንድ ትልቅ አትክልት የሞላበት መሬት ይሰጣታል የሚስቱ ስጋት እና ጭንቀት ባሰ። አብደላህ እውነት ሊሞት ነው ? እንዴት? መቼ? እኔስ ? የሚሉት ነገሮች አሳሰቧት ቀጥሎ ምን ይሆን?
የአብደላህ ኢብኑ አቡበከር አልሲዲቅ ሚስት ከባሏ የሚመጡላት አንዳንድ ምልክቶች ከቀን ወደቀን እያስጨነቃት ይሄዳል። በቅርቡ ሳልሞት አልቀርም ማለት ምን ማለት ነው? የሰው ልጅ በዚህ ለጋ እድሜው ካለምንም በሽታ የሚሞትበት ቀን መቃረቡ የሚሰማው ከመች ጀምሮ ነው? የአብደላህ ሚስት ጭንቀቱ በዛባት አብደላህ ጠላቶች ይኖሩት ይሆን? እሺ ያ ከሆነ ለምን መዲናን እንለቅም በማለት ከራሷ ጋር ትሟገታለች። አብደላህ ከውጪ ሲመጣ ያ የነበረው ሳቅና ጨዋታ ከቤቱ ተኖ በምትኩ ሀዘን እና ውጥረት ሰፍኖበታል። የአብደላህ ንግግር አንድ ጥያቄ ላይ አተኮረ "ሀቢብቲ ከሞትኩ ቡሃላ ሌላ ባል ታገቢያለሽ? እስቲ ቃል ግቢልኝ ከኔ ቡሃላ ሌላ ባል እንዲነካሽ በፍፁም አልፈልግም!" ይላታል። የአብደላህ ሚስት ችግር ይህ አይደለም ሽግሯ ከአብደላ ጋር ያላት ፍቅር መተሳሰብ እና መተዛዘን ለምን በአጭሩ ይቀጭ? የሚል ነበር። ከነብያችን ሂጅራ በስምንተኛው አመት ረሱል ﷺ ጧኢፍን ሊወሩ ነው የሚባል ወሬ ብቻ ሳይሆን እንዲያውም ለጂሀድ ሰው እንዲዘጋጅ ከፍተኛ ጥሪ ይደረጋል። ሰሃባዎች ሙሐጂሮች እና አንሷሮች የተውጣጡበት መሪው ረሱል ﷺ በ እስራ ሁለት ሺ የሚገመት ከፍተኛ ጦር ይዘጋጃል ።ከጦሩም ውስጥ አንደኛው አብደላህ ኢብኑ አቡበከር አልሲድቅ ነው ።ያቺ ታሪካዊ ቀን አብደላህ ከሚስቱ የሚለያይበት ቀን ከተፍፍፍ አለ። የአብደላህ ሚስት በልቧ ውስጥ ማሰላሰል ጀመረች ያ አብደላህ አሁን ገባኝ ይህማ ማንም ወታደር በጦርነት ላይ የሚሰማው ስሜት ነው። ነገር ግን ምንም ሳትሆን እንደምትመለስልኝ እርግጠኛ ነኝ በማለት እራሷን አፅናናች። ያቺ አብደላህ ለመጨረሻ ጊዜ ሚስቱን የሚያገኝበት እሷም ባሏን ለመጨረሻ ጊዜ የምታይበት ሰአት መጣች! አብደላህ ሚስቱን በአይኑ ውስጥ ማየት አልቻለም እምባ አይኑን ጋረደው ። ይህን ጨረቃ የሚመስለውን ፊቷን ለመጨረሻ ጊዜ ለማየት ሞከረ ። የአይኑ ላይ እምባ አልተባበረውም መሰናበት ሳይሆን የያዘው ስሟን ብቻ ነበር ሚጠራው ኑዛዜም አልነበረውም በልቡ ግን ብዙ እያለ ነው ሌላ ባል አታግቢ አላህ ወፍቆኝ ሸሂድ ከሆንኩ ጀነት ውስጥ እጠብቅሻለው --- ሚስቱም እራሷን ሰብሰብ አድርጋ የአይኗን የልቧን የምላሷን ጉልበት አሰባስባ እንደሰመመን ባለበት አንደበት አንድ ጥያቄ ትጠይቀዋለች "ግን ትመለስልኛለህ አደል? ሄደህ እስከምትመለስ ድረስ ናፍቆቱ ስለሚያስቸግርህ ነው እንዲ ተረብሸህ ምታነባው ትለዋለች። አብደላህ የዚህን ጥያቄ መልስ ለመመለስ አቅምም ሆነ ጊዜ አልነበረውም ፤ ጦሩ ሊንቀሳቀስ ነው ። አብደላህ ሚስቱ ላይ ተጠምጥሞ ለሙጨረሻ ጊዜ የሚስቱ ቃና ታጥኖ ሚስቱን በቆመችበት ጥሏት እየሮጠ ቤቱን ለቆ ይወጣል። ሚስቱም አብደላህህ-- አብደላህህ አብደላህህ አለች። ይህ ወረራ ከአንድ ትልቅ ሁነይን ከሚባል ወረራ ቡሃላ ወዲያው የመጣ ጦርነት ሲሆን ሰቂፍ የሚባለው ጎሳ አደብ ለማስያዝ ነበር። በጧኢፍ ውስጥም ሰቂፎች ምሽግ ሰርተው ማንም እንዳይደርስባቸው የጧኢፍን ከተማ ከአጥር አጥረው ለአመት የሚበቃቸውን ስንቅ አስገብተው የጧኢፍን በር ዘጋግተው ቁጭ ብለው ነበር የሙስሊሞችንም ጦር እያንቀሳቀሰ የነበረው ኻሊድ ኢብኑ ወሊድ ሲሆን ነብያችን ﷺ ጣኢፍን ከ 15 እስከ 18 ቀናት ከበዋቸው ቆይተው ነበር ይባላል። ሰቂፎችም ጣኢፍ መከበቧን አይተው ከ አጥሩ በስተጀርባ ሆነው ሙስሊሞች ላይ ወስፈንጥር ያዘንቡባቸው ነበር አቡ መህጅን አል ሰቀፊ የሚባለው የሰቂፎች ታዋቂ ወታደር ከአጥሩ በስተጀርባ አነጣጥሮ አብደላን ያገኘዋል። የአብደላህ ከቁስሉ ክፋት የተነሳ ደሙ መፍሰስ ጀምሮ አልቆምም ይላል ። ብዙም ሳይቆይ አብደላህ ያኔ ለአባቱ ና ለሚስቱ እንዳለው ለዱንያም ለአኼራም ሊሰራ ቃል የገባውን ህይወቱን ለፊሰቢሊላህ በመስጠት ቃል ያስከብራል። አባቱም አቡበከር ሲዲቅ ረዲየሏሁ አንሁ በልጃቸው መሞት ቢያዝኑም በ ሸሂድ መሆኑ አፅናንቷቸዋል። ነገር ግን የአብደላህ ሚስት ኸበሩ እንደደረሳት ለቅሶዋን የሚያቆመው ጠፋ በለቅሶ ለባሏ ያላትን ፍቅር ውዴታ ከእርሱ መለየትን የሚገልፅ ግጥም በመግጠም አለቀሰች። አሁን በልቧ አብደላ ላይ የነበራት እምነት ከፍ አለ። አብደላ አልዋሸም መሞቻውን አውቆ ነበር እኔ ነኝ ግን ያልገባኝ አለች። ለአብደላ የገባችለትን ቃል ለመጠበቅ አንድ ወንድ ለጋብቻ እንዳይጠይቀኝ በማለት ከባሏ አብደላ ጋር ያሳለፈችውን ፍቅር እና መተዛዘን እንዲሁም ልዬ ትዝታዎች በማስታወስ ቆየች። ይህች ታላቅ የሸሂዶች ታሪክ ውስጥ የገባች ሴት ማን ትሆን? *አቲካ* ትባላለች በቅፅል ስሟ *የሸሂዶች ሚስት*
#ክፍል_አራት_ ይቀጥላል---,,,,,,,,,,,
t.me/richyaneyena
#አቲካ
#ቆንጆ_ናት_ያገባት_ሁሉ_ሸሂድ_ነዉ።
#ክፍል_ሁለት_2
ሰይዲና አቡበከር ሲዲቅ ረዲየሏሁ አንሁ ፍታት የሚለውን ቃል ልክ ከአፋቸው እንደወጣ ልጃቸው አብደላህ የሰማውን ማመን አቃተው በህልሜ ነው ወይስ በእውኔ? በአንድ አፍታ ብዙ ነገር በ አንጎሉ ተመላለሰ *ፍታት?* ማንን ነው ምፈታው? አብርያት እየዋልኩ አብርያት እያደርኩ ናፍቆትዋን አልቻልኩም ጠሏቅ የሚባለው የብረት አጥር ሲለያየን ምን ልሆን ነው? እያለ እያሰበ ሳለ አሁንም ።።፡፡፡"በል እያየሁህ እየሰማሁህ ሂድና ፍታት!" የሚለው የአባቱ ጠንካራ ትእዛዝ ያዘለ ንግግር ካለበት ውዥንብር ውስጥ ይቀሰቅሰዋል። አብደላህ ነብሱን ካወቀ ጀምሮ አባቱን አንድ ነገር እምቢ ብሎ አያውቅም ፤ አንድም ቀን በ አባቱ ላይ አምፆ አያውቅም ለአባቱ ታዛዥ ነበር ዛሬ ግን ሊገባበት የማይፈልገው ሁለት መንገድ ከፊቱ ድቅን አለበት ። አባቱን ማስቀየም አይፈልግም ፈፅሞ ማይታሰብ ነገር ነው። ነገር ግን ህይወት ከሚወዳት ሚስቱ ተለይቶ መሰቃየት መሆኑን እየተረዳ የአባቱን ሀቅ አብልጦ ወደ ሚስቱ እየተራመደ ሳይሆን እግሩ እየሳበው በህይወቱ ለመጀመርያ ጊዜ መናገር እንደጀመረ ህፃን እየተርበተበተ ለሚስቱ "አንቲ ጧሊቅ" አላት። ሚስቱም የሰማችውን ማመን አቃታት ከጥቂት ጊዜ በፊት አብደላህ ይነግራት የነበረው ባል ለሚስቱ የነበረው አክብሮት እና ፍቅር እዝነት የሚገልፅ ቃላቶች ነበር ግን አሁን ጠላቅ? ምን አጠፋው? ባሌን ምን በደልኩት? ምንስ ቀየረው እያለች ልትቆጣጠረው እና ልታቆመው የምትችለው እንዳሻው የሚወርድ እምባ ፊቷን አጥለቀለቀው! አብደላህ እና ሚስቱ ከተፋቱ በሃላ ስለተለያዩ የሁለቱም ሀል በጣም የሚያሳዝን ነበር።
ይህን ታሪክ የዘገበው ሰው የአብደላህን ሁኔታ ሲገልፀው " አብደላህ ሚስቱን ከፈታ በሃላ ያሳለፋቸው የለሊት ጨለማ የሚመስል ጥቁር ቀናቶችን ነበር ያሳለፈው" ብሏል። አሁን አብደላህ እያደር ሲሄድ ህይወቱ ለምን ወዳልፈለገበት መንገድ እንዳመራ ሰበቡን መመራመር ይጀምራል። ችግሩም ምኑ ላይ እንደሆነ ወዲያው ይደርስበትና በህይወቱ የሚጠበቅበትን ሀቆች ለሁሉም ሊሰጥና ሊያዳርስ ለራሱ ቃል ገብቶ ይነሳል። ባለቤቱም አይኗን ከፍታ ከአብደላህ ጋ የነበራትን ትዳር ፤ ያሳለፉትን ጊዜያት መለስ ብላ ስታስበው ባሏን በኸይራት በዒባዳው እና በኑሮው ማበረታታት ሲገባት በሁሉም ነገር እሱን መሽጉል ማድረግ ተሰማት። አንድ ቀን ለሊት አቡበከር ረዲየሏሁ አንሁ ሰላቱል ቂያም የቤታቸው ጣርያ ላይ ሆነው ሲሰግዱ ከታች የልጃቸውን የአብደላህን ድምፅ ይሰማሉ ወደታች ሲመለከቱም አብደላህ ና ሚስቱ በግርግዳ ተለያይተው እርሷ ከውጭ ሆና ጆሮዋን ግርግዳው ላይ ለጥፋ አብደላህ በዚያኛው ጎን ሆኖ በሰራው ባጎደለው የተፀፀተበትን እና የሚስቱን ናፍቆት አለመቻሉን የሚገልፅ ግጥም ሲገጥምላት አዩ ሰሙ --- አጂብ። አቡበከር ሲዲቅ ሰላተል ለይል ላይ ናቸው ልጃቸው ደግሞ ምን ያህል ፈተና ላይ ነው የወደቀው ፥ ሰይዲና አቡበከር ግጥሙንም ሰምተው የልጆቹንም ሁኔታ አይተው ሰላታቸውን አብቅተው "ያ አብደላህ" በማለት ተጣሩ ። አብደላህም እንደተነቃበት በመረዳት አሁንስ በቃ በኔና በሚስቴ መሀል ያለው ነገር ሁሉ አበቃለት ! እንዳላያት ታዘዝኩ አሁን ደሞ የተጠራሁት ድምፄንም እንዳትሰማ ድምፃንም እንዳልሰማ በቃቃቃ ያአላህህ በማለት ወደ አባቱ ዘንድ ቀረብ አለ። አብደላህ ውስጡ እየፈራ ጉልበቱ አልሸከመው እያለ ከአባቱ አንደበት የጠበቀው "አሁንም ሁለተኛውን ጠላቅ ስጣት!" የሚል ነበር። ሰይዲና አቡበከር ሲዲቅ ወደ አብደላህ ጠጋ ብለው "ያ አብደላህ ሚስትህን መልሳት!" አሉት። ---- t.me/richyaneyena
ጠላቅ የሚለው የአረብኛ ፍቺ. ፍቺ መፈፀም ማለት ነው።
#ክፍል_ሶስት_ይቀጥላል,,,,,,,,,,,,,,
#ቆንጆ ነች ግን ያገባት ሁሉ ሸሂድ ነው!
#ክፍል_አንድ_1
ሰሀባዎችን ያንበረከከችዋ እንስት
አባቷ ዘይድ ከ ሪሳላ በሃላ የሞተ ነገር ግን ነብያችን አለይሂ ሰላቱ ወሰላም ያማረ ልብሱን ጀነት ውስጥ ሲጎትት እንዳዩት የተናገሩለት ፤ ወንድሟ ሰይድ የሰይዲና ዑመር ረድየሏሁ አንሁን ልጅ ፋጢማን ያገባ ነው። በቁንጅናዋ መካ ውስጥ የሚወዳደራት አነበረም በወጣትነቷ ቤተሰቧን ያሰለቸው እሷን ሊጠይቅ የቤታቸውን ደጃፍ የሚጠናው የሰው ብዛት ነው። የቁንጅናዋ ሲገርም በተጨማሪ የቋንቋ ቅልጥፍናዋና በምትገጥመው ግጥም ማንም ሴት አይወዳደራትም ነበር። አኽላቋን እንደ ተምሳሌት አድርገው ቁረይሾች ሴት ልጆቻቸውን የሚመክሩበት ስነምግባር ነበራት። ቆንጆ ነች ያገባት ሁሉ ሸሂድ ነው? አዎ ባል ባገባች ቁጥር ባሏ በምንም ሰበብ አይሞትም ኢላ በአላህ መንገድ ላይ ሽሂድ ካልሆነ በስተቀር! እንዲያውም ታላቁ ሰሃብይ አብደላህ ኢብኑ ኡመር የሰይዲና ኡመር ኢብኑ ኸጣብ ልጅ ሲናገሩ ሸሂድ ሆኖ መሞት የሚመኝ ይህችን ሴት ያግባ ብለዋል።
ይህንን ታሪክ ዘጋቢ ሲገልፅ በለጋው እድሜዋ ወንዶች ሊያገቧት ጠዋፍ ያደርጉባት ነበር ብለዋል። ሁሉን ወንዶች አሸንፎ ነሲቡን ያገኘው አብደላህ የ ሰይዲና አቡበከር አልሲዲቅ ልጅ ነበር ። አብደላህ ይህችን ልጅ ካገባ ቡሃላ ሀሉ ተቀይሯል ከአጠገቧ አይለይም ከኢባዳው ከቲጃራው ከአባቱ በሷ መሽጉል ሆነ ይህም አባቱ አቡበከር ሲዲቅ ጠርተውት እስኪቆጡት ድረስ ነበር። አንድ ቀን አባቱ አቡበከር ሲዲቅ ሰላታቸውን ለመስገድ ወደነብያችን አለይሂ ሰላቱ ወሰላም መስጂድ ሲሄዱ እግረመንገዳቸው ልጃቸው አብደላህን ና አብረን እንሂድ በማለት አስነሱት አብደላህም መንገድ ከመጀመሩ በፊት ሚስቱን ሊሰናበት ማር የሆኑ ቃላቶችን እየነገራት ሳለ አባቱ አቡበከር ሲዲቅ ትተውት መንገዳቸውን ወደ መስጂድ አነበዊ ይቀጥላሉ። አቡበከርም ረዲየላሁ አንሁ ሰግደው ሲመለሱ ልጃቸው አብደላህ እስካሁን ድረስ ያንን ጣፋጭ ንግግሩን ከሚስቱ ጋርሲለዋወጥ ይደርሱበታል! 😳 እንዲ አይነትስ ሚስት ብትቀር ይሻላል ወንዶች ትስማሙ ይሆን?? አልሙሂም አባቱም ተደናግጠው ሰላትህን ጀምዕ አደረከው እንዴ ብለው ሲጠይቁት "ተሰገደ እንዴ?" በማለት መልሶ ጠየቀ። ሰይዲና አቡበከርም አዎ ብለው መለሱለት። ይህቺ ሴት ከንግድህ ከኑሮህ አሁን ደሞ ከፈርድ ሰላትህ መሽጉል አደረገችህ ፋታት ብለው ይጠይቁታል። ይህች አብደላን ከንግዱ ከኢባዳው ከማህበራዊ ህይወቱ ቢዚ ያደረገችው ሴት ማን ትሆን??ኢኽዋኒ ወአኸዋቲ ይህቺን የሚወዳትን ዱንያና አኼራን ያስረሳችውን ሚስቱን ይፈታታል? ወይስ ከነብያት ቀጥሎ ደረጃ የያዙት አባቱን አቡበከር ሲዲቅን አልፈታም ይላል? -----
t.me/richyaneyena
ይቀጥላል
[ ስለተጨነቅሽ ..... አታፈጥኝውም ]
ሴት መሆን ከባድ ነው። በተለይ በተለይ በእኛ ማህበረሰብ ውስጥ ሴት መሆን ፈተና ነው።
{መቼ ነው የምታገቢው?}
ትምህርት ከ10'ርም ይሁን ከ12'ት ብታቆሚ ... የመንገደኛው ሁሉ ጥያቄ ይሄ ነው።
ስራ ተቀጥረሽ ገና የመጀመሪያ ወር ፔሮልሽ ሳይመጣ ... የሁሉም ጥያቄ ይሄ ነው።
የታላቅ እህትሽ ሰርግ ላይ ለሰላምታ እጅሽን የዘረጋሽለት .... ሰው ሁሉ ጥያቄ ይሄ ነው።
የጓደኛሽ ሚዜ ሆነሽ በታደምሽበት ሰርግ ላይ ... ያየሽ ሰው ሁሉ ጥያቄ ይሄ ነው።
ጎረቤታችሁ ሰው ሞቶ ለቅሶ ልትደርሺ ስትሄጂ ... የለቀስተኛው ጥያቄ ይሄ ነው።
ሌላው ቀርቶ ቀበሌ ያላገባ ልታወጪ ብትሄጂ ... የመዝገብ ቤት ሰራተኛዋ ጥያቄ ይሄ ነው።
∞∞∞∞∞
ዛሬ ላንቺ እንደ ምሳሌ የሚነሱት ጓደኞችሽ ስላገቡ አልቀደሙሽም
አንቺም እስካሁን ባለማግባትሽ አልዘገየሽም
የማግባት ግቡ መውለድ ከሆነ በ24 አመቷ ያገባችው ጓደኛሽ እስከ 35 አመቷ ላትወልድ ትችላለች፤ ትዳር ለልጅ ዋስትና አይደለም
"የዘገየሽው" አንቺ በ36 አመትሽ አግብተሽ ከዘጠኝ ወር በኋላ የመንታ ልጆች እናት ልትሆኝም ትችያለሽ !!
በ 23 አመቷ ያገባችው ጓደኛሽ አመትም ሳትቆይ ልታፋታ ትችላለች፤ አንቺ በ38 አመት አግብተሽ 50ኛ አመት እዩቤልዩአችሁን በልጅ ልጆቻችሁ ሻማ ልታከብሪ ትችያለሽ .... ፈጥኖ ማግባት ለትዳር መዝለቅ ዋስትና አይደለም !!
በ25 አመት አመቷ ያገባችው ሴት በትዳሯ ተቃጥላ ሁለት አመት ሆስፒታል በመላለስ ደክማ በ27 አመቷ ልትሞት ትችላለች፤ በ40 አመትሽ የተባረከውን አግብተሽ 30 አመት በደስታ ኖረሽ ልጆችሽን ለመዳር ሽር ጉድ ለማለት ትበቂ ይሆናል .... ቀድሞ ያገባ ሁሉ ደስተኛ አይደለም !!
∞∞∞∞
ሁሉም ነገር የራሱ ጊዜ ትክክለኛ አለው .... በጊዜው የሆነ ነገር ሁሉ ደግሞ ትክክል ነው !!
ማግባት መታደል አይደለም ... አለማግባትም መረገም አይደለም !!
የተሳሳተ ሰው ያገባሽበትን ቬሎ ቁምሳጥን ውስጥ አምሮበት ከምታይው ..... ትክክለኛውን ሰው ሲጠብቅ ግድግዳ ላይ ተሰቅሎ ያደፈው ቬሎ የተሻለ ነው !!
ውስጥሽ እና ህይወትሽ በማይሆን ሰው ከሚቃጠል፤ ግድግዳ ላይ የተሰቀለው ጨርቅ ጦስሽን ይዞ ይሂድ !!
እህቴ አላገባሽም ... ግዴለሽም አትጨነቂ ... ማንም አልቀደመሽም !!
.... ብቻ ነገሩ ውስብስብ ነው።
t.me/richyaneyena
በትዕግስት ሁሉም ነገር ላይ ይደረሳል
አለም ጉድ ያስባለ ቪዲዮ
ወጣቶች ሆይ ወዴት እያመራን ነው? ትናንትና የሚደግፈው ቡድን ስለተሸነፈ እራሱን መስዕዋት ያደረገ ወጣት በእየ ሶሻል ሚዲያ መነጋገሪያ ሆኖዋል። ማንኛውም ነገር ከመጠን ስያልፍ ዋጋ ያስከፍላል።
t.me/richyaneyena
ባለቤቱ ለማግነት በቴሌግራም በዚህ የዘር ኔም አናግሩት
@C_H_U_L_Y_E
ኢስላም እና ጫት በዶክተር አብይ አህመድ
t.me/richyaneyena
ለአንድ ባሪያ በጣም የሚጠቅመው 'አስቲግፋር' ነው ወይስ 'ተስቢሕ '?
ሸይኹል ኢስላም እብን ተይምያህ ተጠየቁ
እሳቸውም ፦
/ልብስ ንፁህ ከሆነ ሽቶና ቡኹር ይጠቅመዋል
ልብሱ ቆሻሻ ከሆነ ግን ሳሙናና ውሃ ይበልጥ ጠቃሚ ይሆናል •••
ተስቢሕ - ለንፁሖች እንደ መዋቢያ ሲሆን
እስቲግፋር - ለአመፀኞች እንደ ሳሙና ነው
____
t.me/richyaneyena
*በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።
የመኝታ አዳቦች 11 ናቸው
1ኛ -- ከመተኛት በፊት በር መዝጋት፣ እቃወችን መከዳደን እና እሳት ማጥፋት።
**ነቢያችን ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ልትተኙ ስትሉ *እቃወችን ከዳድኑ፣ ኮዳወችንም እሰሩ፣ በሮችንም ዝጉ። ሾይጧን የታሰረን አይፈታም። በር አይከፍትም። የተከደነንም አይከፍትም። መክደኛ ካጣችሁ እቃችሁ ላይ እንጨት አድርጋችሁ ቢሆን እንኳ የአሏህን ስም ጥሩበት። እሳትንም አጥፉ አይጥ ቤታችሁን ታቀጣጥላለች። (ሙስሊም ዘህበውታል።
2ኛ-- ጀናባ ከሆኑ ውዱእ አድርጎ መተኛት። (አህመድ፣ ኢብኑ ማጃህ እና ሎሎችም ዘግበውታል)።
3ኛ-- ፍራሹን መጥረግ።
ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም "ለመተኛት ወደ ፍራሻችሁ ስትቀርቡ በሽርጣችሁ ውስጠኛ ክፍል ሶስት ጊዜ ጠረግ አድርጉት ብለዋል።"
(ቡኻሪና ሙስሊም)
4 -- ቤት ውስጥ ብቻን አለመተኛት።
ዐብደሏህ ኢብኑ ዑመር ረዲየሏሁ ዐንሁ እንዳስተላለፉት ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ለብቻ መተኛት እና ለብቻ ጉዞ መውጣትን ከልክለዋል።"
(አህመድ ዘግበውታል)
5 -- ውዱእ ማድረግ
ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ወደ መኝታ ስትሄድ ለሶላት የምታደርገውን ውዱእ አድርግና በቀኝ ጎንህ ተኛ ብለዋል።
(ቡኻሪና ሙስሊም)
6-- የመኝታ አዝካሮችን እና እንደ ሱረቱል ኢኽላስ፣ ሱረቱ ናስ፣ ሱረቱል ፈለቅ፣ አያተል ኩርሲ የመሳሰሉትን አንቀፆች ማንበብ አፈፃፀሙን እና ሙሉውን አዝካሮች ሂስኑል ሙስሊም ላይ ታገኟቸዋላችሁ።
7-- በቀኝ ጎን መተኛት።
(ቡኻሪና ሙስሊም)
8 -- በሆድ አለመተኛት።
ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም በሆዱ ተኝቶ ያዩትን ሶሃባ "ተነስ ይህ አተኛን አላህ የማይወደው ነው ብለውታል።"
(አህመድ፣ ቲርሚዚና ሌሎችም ዘግበውታል)
9 -- ከእንቅልፍ በድንጋጤ ከባነናችሁ።
اعوذ بكلمات الله التامات من غضبه وعقابه، وشر عباده، ومن همزات الشياطين وان يحضرون.
*አዑዙ ቢከሊማቲላሂ ታማቲ ሚን ገዶቢሂ፣ ወዒቃቢሂ፣ ወሸሪ ዒባዲሂ፣ ወሚን ሐማዛቲ ሸያጢን ወአን የህዱሩን።
(ትርጉም ( ሙሉ በሆኑት በአላህ ቃላቶች ከቁጣው፣ ከቅጣቱና ከባሮቹ ክፋት፣ እንዲሁም ከሾይጧን ጉትጎታና እንዳይቀርበኝም በአላህ እጠበቃለሁ።" ማለት።
10 -- መልካም ወይም መጥፎ ህልም ካያችሁ መልካምን ህልም ያየ ለሚወደው መናገር። መጥፎን ህልም ያየ ለማንም አለመናገር። (ሙስሊም)
በሌላ ዘገባ "መልካም ህልም ከአላግ ነው። መጥፎ ቅዠት ግን ከሾይጧን ነው። መጥፎን ቅዠት ያየ በስተግራው እየተፋ ከክፋቱ በአላህ ይጠበቅ ይህንን ካደረገ አይጎዳውም ብለዋል።
(ቡኻሪና ሙስሊም)
እንደ ባነናችሁ ወደግራ ዞራችሁ አዑዙቢላሂ ሚነ ሾይጧኒ ረጅም ብላችሁ ሶስት ጊዜ በስሱ ትፍ ትፍ ትፍ ብላችሁ አተኛኛችሁን አዙራችሁ ተኙ።
11 -- ከእንቅልፍ ስትነቁ አዝካሮችን ማለት።
ሙሉ አዝካሮችን ሂስኑል ሙስሊም ላይ ታገኟቸዋላችሁ።
ወሏሁ አዕለም.
t.me/richyaneyena
#የሀበሻ_መዝገበ_ቃላት
#ኑሮ:- ለሲዖል ህይወት ልምምድ የሚያደርጉበት ጠባብ ጂም
#ዘመድ:- ባልተዘጋጁበት ቀን የሚመጣ ተጨማሪ ችግር
#ጫማ:- አብሮ የሚደክም እውነተኛ ፍቅረኛ
#ደሞዝ :- ከወጣበት ዕለት ውጭ ቁም ነገር የሌለው
#ብድር:- በፍቅር የወሰዱትን በጦርነት የሚመልሱበት የዝርፍያ ሙከራ።
#አቲካ
#ቆንጆ_ናት_ያገባት_ሁሉ_ሸሂድ_ነዉ።
#ክፍል_ዘጠኝ_9
አቲካ የመጣላትን የትዳር ጥያቄ እስካሁን ድረስ ማመን አልቻለችም። የዙበይር ኢብኑል አዋምን ደረጃቸውን ታውቃለች። ለረሱል አለይሂ ሰላቱ ወሰላም የአክስት ልጅ፤ የነብይ ሀዋሪይ ታሪኩ ተወርቶ የማያልቅ ታላቅ ሰሀቢይ መሆኑን ታዉቃለች። አቲካ ስለዙበይር ሁሉንም ጠንቅቃ ስለምታዉቅ የትዳር ጥያቄውን ተቀበለች። ከኒካህ በፊት አንድ ሸርጥ አስቀመጠችለት። የ አቲካ ቅድመ ስምምነት ቤት በስሟ እንዲገዛላት? አረ በፋፁም ፤ሌላ ሚስት እንዳያገባ ወይም የበፊቱን ሚስት እንዲፈታ? በፋፁም አልነበረም የ አቲካ ሸርጧ አንድ እና አንድ ብቻ ነበር። ፈርድ ሰላት ለመስገድ መስጂድ መመላለሷን እንዳይከለክላት ነበር። ይህም ደግሞ ማንም ባል ሊነጥቃት የማይችለው የ ሰይዲና ኡመር ኢብኑል ኸጧብ ስጦታ ነበር ። ሰይዲና ዙበይርም በአቲካ ሸርጥ በመስማማት ኒካሐቸዉን አሰሩ። የሚገርመው ነገር አሁንም የመጀመርያው ለሊት ለአቲካ አስቸጋሪ ፤አሳዛኝ እና ሆድ የሚያባባ ነበር የሆነባት። ነገር ጎን ነገሮች ከ ቀን ወደ ቀን እየተለወጡ መጡ። ሰይዲና ዙበይር ቀን በቀን ለ አቲካ ያላቸው ፋቅር እየጨመረ መጣ። እንዴት አይጨምር አኽላቋ የሚረታ ውበቷ የሚማርክ ያገቧት ሁሉ አላህ የደነገገባት ሀቆች አሳምራ ሰታ። ማታ አጇን ወደ ሰማይ ዘርግታ ያረብ የባሌን ሀቅ አሟልቼ የምሰጥ ያጎደልኩትም ካለ ማረኝ የምትል ሴት ላይ እንዴት ውዴታ አይጨምርም ? ከዚህ ቡሃላ ግን ሰይዲና ዙበይር አዲስ ባህሪይ ይታይባቸው ጀመር ይሀውም በ አቲካ ላይ መቀናት ነበር። ያ ሰላም አቲካ የነብዩን ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም የአክስት ልጅ እና ሀዋሪይ በጦር ሜዳ ጠላታቸውን በሰይፍ እንደ ቅጠል የሚያረግፉትን ጀግና ሰሀብይ ዛሬ ባንቺ እቀናለው? ምንኛ አስገራሚ ሴት ነሽ? ከውዴታቸው የተነሳ እንደ ሚስት ብቻ ሳይሆን እንደ ሁሉም ነገር እየተንከባከባት የሞቀ ትዳራቸውን ይመሩ ነበር።
ሰይዲና ዙበይር በየቀኑ ቅናታቸው እየጎላ መጣና ከአንደበታቸው መደመጥ ጀመረ። አንድ ቀን አቲካ መስጂድ ለመሄድ ስትዘጋጅ ሰይዲና ዙበይር ያ አቲካ ከቤት የምትወጪው እኔ መውጣትሽን እየጠላሁት ነው አሏት እሷም ከበሩ ተመልሳ በፋቅር እና በተረጋጋ መልኩ አንተ የምትለኝን እሰራለሁ ካላስደሰሰተህ ይሀው አልሄድም በማለት አባበለችው። ያ አላህ አኽላቃችንን አሳምርልን🤲። ተመልከቱ እስቲ እርሷ እና ባለቤቷ ዙበይር የሚመላለሱትን የቃል መልስ በትህትናዋ የተማረከው ዙበይር ግን ከሀሳቡ መለስ አለና እንዴት እከለክልሻለው ስታገቢኝ እኮ ይህ መስፈፈርትሽ ነበር ብለው ከቤት ወታ ወደ መስጂድ እንድትሄድ ፈቀዱላት። አብረውም ወጡ። ምርጡ ትውልድ ምን አይ ነት ትውልድ ነበር? አንዱ ከ አነንዱ የሚሻልበት ለኢስላም የሚኖርበት ለኢስላም የሚሞትለት አቻ የለሽ ትውልድ!
አቲካ ማታ ላይ ለሰላት እንደወጣች ነው። ከመስጂድ ስትመለስ ግን አንድ ነገር ገጥሟት ነበርና በዚያ ነገር ተረባብሻለች። አቲካ የረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም የአክስት ልጅ ላይ እያሳደረች የነበረው ተፅእኖ ወደር አልነበረውም ሰይዲና ዙበይርም መቋቋም አልቻሉም ለሁለተኛ ጊዜ መስጂድ መሄዷን መጥላታቸውን ይነግሯታል። አቲካም ይህ ጥያቄያቸው ከቀናት የተመሰረተ እንደሆነና ሊቀይሩት ይችሉ ይሆን በማለት ለዘብ ባለ ቃል ያ አዋም ልጅ ሆይ ረሱል አለይሂ ሰላቱ ወሰላም ጋር ፤ አቡበከር ጋር ኡመር ጋር የሰገድኩበት ሙሰላዬን ለቅናትህ ብዬ እንድተተወው ከፈለክ እተወዋለው አለቻቸው። ሰይዲና ዙበይርም በፋፁም ወላሂ አልከለክልሽም አሉ። ነገ ግን ያደረባቸው ቅናት ቀላል አልነበረም በጣም ያሳዝናሉ ለሰላት ከወጣች የምትመለስ አይመስላቸው። ልባቸው አልረጋ አለ ማስገደድ ደግሞ ባህርያቸው አነበረም አትሂጂ ማለትም አይበቃላቸውም ነገር ግን ይህ ቅናት ወደ ሚያስገርም ድርጊት መራቸው። ከዚህ ቀጥሎ የማወጋቹህ በሰይዲና ዙበይር ድርጊት ተገርማቹ ምንም አይነት በጎ ያልሆነ እሳቤ እንዳታስቡ አደራ እየጠየኩኝ ነው። ምክንያቱም ከረሱል ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም ሰሐቦች ጋር ያለን በአደብ መዋብ ይኖርበታል ። ነብያችን አለይሂ ሰላቱ ወሰላም ይህንኑ ፈርተው በእጅጉ አስጠንቅቀዋል። *" አላህን ፍሩ ሰሐቦችን በሚመለከት እኔ ከሞትኩ ቡሃላ ኢስላምን ለመውጋት እነርሱን ኢላማ ወይም አላማ አታድርጓቸው ።"*
በሌላ ሐዲስ ላይም
*" ባልደረቦቼን ኦንዳትሰድቧቸው ነፍሴ በእጁ በሆነችው ጌታ እምላለሁ አንዳችሁ የእሑድን ተራራ ያክል ብታወጡ የአንዳቸውንም ደረጃ አትደርሱም"* አሉ ረሡሉ አለይሂ ሰላቱ ወሰላም።
ከዚህ አስከፊ ማስጠንቀቂያ ቡሃላ እንግዲህ ሰሃቦችን በክፉ ማንሳት ማሚያስብ የሚደፍር ያለ አይመስለኝም።
t.me/richyaneyena
---- #ይቀጥላል ---
"ልጅ እያለን ሌባ ሰርቆ ሲያዝ ፖሊሶች የሰረቀዉን አሸክመዉት የሰፈር ልጆች በባዶ እግራችን እየተከተልን ሌባ........ሌባ........ሌባ........ሌባ.........እያልን ነበር ሶስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ድረስ የምንሸኘዉ
እስከዛሬ የማይረሳኝ ሌባ ነበር አንድ ቀን አህያ ይሰርቅና እጅ ከፍንጅ ፖሊሶች ይይዙትና ተሸክመህ ወደ ጣቢያ ከፊት ከፊት ሂድ ይሉታል። እረ አልችላትም እንዴት ብዬ ልሸከማት ይላል ፖሊሶቹ ይማከሩና በል ከላይ አህያዋ ላይ ተቀመጥ ብለዉት ጉዞ ወደ ሶስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ይጀመራል
የሰፈር ልጆች ከወትሮ በተለየ ሌባ.....ሌባ.....ሌባ.....ሌባ.....ሌባ......ሌባ.....ሌባ.....እያልን መከተል ስንጀምር ፖሊሶቹ ተበተኑ ብለዉ ሲያባርሩን ሌባዉ አፍ አዉጥቶ እነሱ ካላጀቡኝ አልሄድም በማለቱ ተመልሰን
ሌባ....ሌባ......ሌባ.....ሌባ......ሌባ.......ሌባ......ሌባ......ማለቱን ቀጠልን በዛ ላይ የቀለመወርቅ ተማሪዎች ተለቀዉ ነበር እነሱም ተቀላቀሉን ሌባዉ ጭራሽ ተደስቶ ሁለት እጁን ወደላይ እያረገ ሰዉ ሰላም እያለ ነበር የሚሄደዉ ሰርቆ ሳይሆን ከኦሎምፒክ ሜዳሊያ ይዞ ለመጣ አትሌት አቀባበል ነበር የሚመስለዉ እንደዛ እንደጮህን ጣቢያ ደርሰን መርማሪዉ ፖሊሶቹን ምን አርጎ ነዉ ብሎ ጠየቃቸዉ ሰርቆ እጅ ከፍንጅ ይዘነዉ ነዉ ሲሉት አስገቡና ደና አርጋችሁ ግረፉት ብሎ ካፉ ሳይጨርስ
ሌባዉ ተንደርድሮ መርማሪዉ እግር ላይ ወድቆ ዛሬ የደስታዬ ቀን ነዉ የዛሬን እለፉኝ ሰርጌ እንኩዋን እንደዛሬም አልደመቀ ብሎ ልመናዉን ቀጠለ "
#አቲካ
#ቆንጆ_ናት_ያገባት_ሁሉ_ሸሂድ_ነዉ።
#ክፍል_ሰባት_7
ሰይዲና ዑመር ልጃቸውን ቀና ብለው አዩትና ኡሙል ሙእሚኒን አዒሻ ዘንድ ልላክህ አሉትአሁኑኑ እርሷ ዘንድ ሂድ እዛም ስትደርስ አሚረል ሙእሚኒን ላከኝ እንዳትላት አዎ እኔ ከዚህች ሰአትም ሆነ ደቂቃ ቡሃላ የናንተ አሚር አይደለሁም እርሷም የአሚር ትእዛዝ ነው ብላ የምጠይቃትን ፈርታ እሺ ልትለኝ ትችላለች ስለዚህ እንዲህ በላት ዑመር ከጓደኞቹ ጋር መቀበር ይፈልጋል ብቻ በላት አሉት። እዚህ ላይ ማወቅ ያለብን ነገር ነብያችን አለይሂ ሰላቱ ወሰላም የተቀበሩበት ይኖሩበት በነበረው አንድ ክፍል ቤታቸው ውስጥ ነው። እዚያው ቤት ውስጥ ሰይዲና አቡበከር ተቀብረዋል አሁን እዚያ ቤት ውስጥ የቀረው የአንድ ሰው መቀበርያ ቦታ ብቻ ሲሆን ይህም ቦታ የተቀመጠው ለኡሙል ሙእሚኒን አዒሻ ረዲየሏሁ አንሃ ነበር። ምክንያቱም እዚያ ቦታ ላይ የተቀበረው አንደኛው ነብያችን ረሱላችን አለይሂ ሰላቱ ወሰላም ሲሆኑ ሁለተኛው ደግሞ አባቷ የሆኑት አቡበከር ሲዲቅ ረዲየሏሁ አንሁ ናቸው። ሶስተኛውንና የመጨረሻውን ቦታ ያስቀመጠችው ለራሷ መሆኑን ልብ እንበል። አቲካ ይህ ሁሉ ሲሆን የወሬው ጫፍ ክደጇም አልደረሰም አልሰማችም። የሚያስገርመው ነገር መዲና ውስጥ በአንዳንድ ለወሬ የሚቸኩሉ ሰዎች አማካኝነት አንድ ወሬ ፋታ ሳይኖረው ሁሉም ጆሮ ይደርስ ነበር።አሁን ግን አብዛህኛው ሰው ይህን ግድያ ቢሰማም አቲካ ግን እስካሁን ከወሬው ጋር አልተቀራረበችም።እነዚህ ሰዎች እንኳን ወሬውን አለማድረሳቸው ተአምር ነው። ወኔውን እና ድፍረቱን ከየት ያምጣው ? የትኛው መርዶ ነጋሪ ነው ይህችን የፍቅር ተምሳሌትን ፍቅርሽ እና ታላቁ ሶሃባ የአላህ ወዳጅ ዛሬ ደፋር ሆኗል የሚል ደፋር? የቱ አርጂ ነው ቆፍጥኖ አቲካ ሆይ የሞቀው ትዳርሽ ዛሬ አብቅቶለታል የሚለው? ያ አቲካ የቆንጆዎች ቆንጆ በቁንጅናሽ እና በአኽላቅሽ ታላቁን ሶሃባ የማረክሽው ውዱ ባልሽ የሞት አፋፍ ላይ ነው ብሎ ማን ደፍሮ ይንገራት? በመጀመርያው ባልሽ ሸሂዱ አብደላህ ክፉኛ አዘንሽ ሀዘንና ሰብርን አቀናጅተሽ ባሏ ለሞተባት ሚስቱ ለሞተችበትም ወደር የሌለው አርአያ ሆነሻል አላህም አንቺንም በሸሂዶች ደረጃ አድርጎ ይቀበልሽ።
አብደላህ ኢብኑ ዑመር ይህን መልእክት ይዘው ወደ አዒሻ ሄዱ። ግና አኢሻ ይህንን አሳዛኝ ዜና ሰምታ ስለነበር በጣም ተደናግጣና በጣም አዝና አገኛት። አብደላህ ኢብኑ ኡመርም አባቴ ኡመር ኢብኑ ኸጣብ ከጓደኞቼ ጋር መቀበር እፈልጋለው ፍቃድ እንድትሰጪ ዘንድ ጠይቆሻል አላት። ሰይዳ አዒሻም ከድንጋጤዋና ከሀዘኗ የተነሳ ኡመርን እንዴት አይሆንም ልለው እችላለው? ሂድና ለአባትህ ፍቃዴ እንደሆነ ንገር አለች። ያ ሰላም! ያ አላህ! ምን አይነት ወርቃማ ትውልድ ነበር? ድሮም ከዚህ ትውልድ መልካምነት እንጂ ምን ይጠበቃል? አስተማርያቸው መርያቸው ስርአት አስይዞ የመራቸው ሙሐመድ ኢብኑ አብደላህ ረሱሉ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም አይደሉ? እስቲ አንድ ግዜ መለስ ብላቹ አስተውሉ የጠያቂው የአጠያየቁ ዘይቤ የመላሿ የአመላለስ አደብ! ያ አላህ በዱንያ ላይ የነሱን ባህሪይ አልብሰን በጀነትም ከነሱ አጎራብተን🤲። አብደላህ ኢብኑ ኡመር ይህንን የምስራች ከ አዒሻ ለአባቱ አምጥቶ ሲነግር ዑመር ኢብኑ ኸጣብ ደም እጅግ አድርጎ በጣም እየፈሰሳቸው ነው እየፈሰሳቸው ነው ሰከራተል መውት ውስጥ ገብተው በደከመ አንደበታቸው የመጨረሻውን ትንፋሻቸውን ሳይተነፍሱ በፊት አሁንም አዒሻን ላለማስከፋት ያ አብደላህ በሂወት እያለው አፍራ እሺ ልበል ብላ ሊሆን ይችላል እና ከሞትኩ ቡሃላ ይህንኑ ጥያቄ ደግመህ ጠይቃትና አረጋግጥ አሉት። አላሁ አክበር ! ሰይዲና ዑመር ይህን ካሉ ቡሃላ ሸሃዳቸውን ብለው የመጨረሻ ትንፋሻቸውን ተነፈሱ። እንደተመኙትም አላህን ተማፅነውት ነበርና ሁሉም ነገር እንደምኞታቸው ተፈፀመ። ሰይዲና ኡመር ሸሃዳን አገኙ። አሁን አቲካ የትም ብትሸሽ ልታመልጠው የማትችለው መርዶ ሰማች። ውዱ ባለቤቴ ዑመር ጂሃድ አልሄደ ፤ አላዘጋጀሁት አልተሰናበትኩት እንዴት እንደወጣ ቀረብኝ? ተመልሶ ሲመጣ እንዴት አድርጌ በፍቅር እንደምቀበለው ፤እንዴት እንደማስደስተው ሳስብ ነበር። አቡ ሉእሉእ ማነው ? ባሌስ ምን በደል አድርሶበት ነው? የምን በቀል ነው? አቲካ እራሷን መቆጣጠር አቃታት። ምን እየደረሰብኝ ነው ግን አግብቼ ወድጄ አፍቅሬ ትዳሬ ሞቋል ስል በሸሂድነት ማህተም ይዘጋል። አልሀምዱሊላህ አላኩሊ ሃል አለች። አቲካ እንደወትሮዋ ከብዙ ቤት የተቀናበረ ግጥሟን የሰይዲና ኡመር ኢማንን ጀግንነትን ቆራጥነትንና ለእርሳቸው የነበራትን ፍቅር እና አብሯት የቀረውን ትዝታዋን በግጥሟ በመክተት የመዲና ሰዎችን ዳግም አሳዘነቻቸው ።
t.me/richyaneyena
-------#ይቀጥላል-----
#አቲካ
#ቆንጆ_ናት_ያገባት_ሁሉ_ሸሂድ_ነዉ
#ክፍል_ስድስት_6
አቲካ ረዲየሏሁ አንሃ የሰይዲ ና ዑመር ኢብኑ ኸጧብ ሚስት ሆና ህይወት በጣም ተመችቷት ኢማኗ ከፍ ብሎ ኢባዳዋ በዝቶ የ አሚረል ሙእሚኒን ሐቅ እየጠበቀች ለሰይዲና ዑመር በዱንያ ላይ የሚገባቸውን እንክብካቤ እያደረገችላቸው ነበር። ሰይዲና ዑመር አቲካን አግብተው አሚር እንደመሆናቸው ለሊቱን መዲናን እየዞሩ ሰላም መሆናቸውን ያረጋግጡ ነበር።አቲካም በዚህ እና በሀገሪቱ አመራር ላይ ከጎናቸው ሆና ትረዳቸው ነበር። ምንኛ ትዳር ነበር? ውብ ድንቅ ሴት ለታላቅ ሰው! ነገር ግን ይህን ያማረ ትዳር በደንብ ሳይታሰብ ሰይዲና ኡመርም ሳይዘጋጁለት አቲካም ባልጠበቀችው ሰአት ይነጠቃሉ። በዙልሂጃ ወር አሚረል ሙእሚኒን ሰይዲና ዑመር ኢብኑል ኸጣብ በመስጂደነበዊ የፈጅርን ሰላት እያሰገዱ ሳለ አንድ ሰው ያንን ሁሉ የሰጋጁን ሰፍ እየሰነጠቀ ኢማሙ ሰይዲና ዑመር ጋ ይደርሳል። በሁለቱም በኩል ስለት ባለው ሳንጃው ሶስት ጊዜ ክፉኛ ይወጋቸዋል ። አቡ ሉእሉእ አል መጁሲይ እሳት ከሚገዙት አንዱ ነው። የማይሞከር ነገር ሞክሮ ተሳካለት ፤ መፈፀም ያልነበረበት ወንጀል ፈፀመ። ሰይዲና ዑመር እንደዚያ ክፉኛ ሲወጉ አንደኛው ከእምብርታቸው በታች የነበረ አደገኛ ሆኖ አንጀታቸው ይታይ ነበር። ሰይዲና ዑመር ዘውትር ከሰላታቸው ቡሗላ ሸሃዳን አላህን ሲጠይቁት ሲለምኑት የነበረውን አላህ እንደተቀበላቸው ተሰማቸው። እስቲ በዚህ መስጂድ ውስጥ እንዳላችችሁ ይህን አሳዛኝ ነገር ሳሉት? አቡ ሉእሉእ ማምለጫ አቶ የሰጋጆች ሰይፍ ሊወርድበት ሲል በዚያው ሰይዲና ዑመርን በወጋበት ሳንጃው ሙእሚኖችን እየመታ 13 ሰዎችን አቁስሎ ከዚያ ውስጥ ስድስቱ ይሞታሉ። ሰይዲና አብዱራህማን ኢብኑ አውፍ በሰይፍቸው አቡ ሉእሉእን አንድ ደህና ምት ሲያሳርፉበት መሬት ላይ ይወድቃል። ሙስሊሞች ከሚገድሉኝ ብሎ የአላህ ለእና ይውረድበትና እራሱን ያጠፋል።ይህ ሁሉ ሲሆን አቲካ ጉዷን አታውቅም። ወደ ሀቢባችን ሰይዲና ኡመር ስንመለስ ሰሃባዎች ከበዋቸው ልጃቸው አብደላህ ኢብኑ ዑመር እራሳቸውን ደረቱ ላይ ደግፎ አባቱን ያበረታታ ነበር ። ሰዎች ትንሽ ወተት አምጥተው ሲያጠጧቸው ያ ወተት በጉሮሯቸው እልፎ በተወጉበት ቀዳዳ ይፈሳል ------😪 ይህን ጊዜ ሰሐባዎች ተደናግጠው ያይዋቸው ነበር። የሰይዲና ኡመር እጅ መሬት ላይ ሲወድቅ እጃቸው መሬት ላይ ያለው ሳር ላይ ያርፍና ይህን ሳር በእጃቸው እፍኝ ወስደው ምነው የዑመር እናት ዑመርን ባልወለደች ምነው ይህንን ሳር ሆኜ በነበር ብለው ሰሓባዎችን አስለቀሱ። ዑመር ረዲየሏሁ አንሁ ያን ሳር እንዲሆኑ የተመኙት ለምን ይሆን? አቲካስ ይህንን ኸበር ስትሰማ እንዴት ትቋቋመው ይሆን
t.me/richyaneyena
---- #ይቀጥላል,,,,,,,,,,,,,,
#አቲካ
#ቆንጆ_ናት_ያገባት_ሁሉ_ሸሂድ_ነዉ
#ክፍል_አራት_4
አቲካ ባሏ ሸሂድ ሆኖ ከሞተባት በሃላ የሀዘንን ቀናት በመጠኑ እየተቋቋመች ከባሏ አብደላህ ጋር ያሳለፉትን ውስን ቀናቶች እያስታወሰች ተፅናንታ ነበር። በዚህ ላይ እንዳለች በፍፁም የማጠብቀው ነገር ይከሰታል። ከአብደላህ በሃላ በፍፁም አንድ ሰው አገባለው ብላ
አላሰበችም ነገር ግን ለትዳር መፈለጓ ብቻ ሳይሆን የፈለጋት ሰው በጣም አስደነገጣት ። ምንም ቆንጆ ብትሆን አኽላቅ እና ዲኗ ማንንም ወንድ ቢማርክም ይህን ያህል ተካብዶ ከሰሐባዎች ውስጥ በመጀመርያው ሰፍ ውስጥ ከሚገኙት ብርቅ እና ድንቅ ከሆኑት የኢስላም መሪዎች ውስጥ አንድ ሰው ሚያስታውሳት አልመሰላትም። ይህን ሰሃባ ማግባት በምን እድሏ ነበር ነገር ግን ለአብደላህ ከሱ ቡሃላ ሌላ ወንድ ላታገባ ቃል መግባቷን ምን ልታደርግ ነው? ላግባ እንኳን ብላ ብትወስን አብደላህ ሸሂድ ሆኖ ከመሞቱ በፊት ሌላ እንዳታገባ ቃል ሲያስገባት የሰጣትን በፍራፍሬና በአታክልት የተሞላበትን መሬት ምን ታድርገው? እኚህ ታላቅ ሰሃባ በሚናገሩት ንግግር አላህ አላሳፈራቸውም ደግፏቸው ወህይ አውርዶ በቁርአን ውስጥ ለዘላለም ይታወሳሉ። እሷን ግን ለትዳር ፈልገዋት እንዴት እምቢ ትበላቸው? እንዴት ታሳፍራቸው? የአቲካ ሀሳብ ተበታተነ። አቲካ ከዚህ ታላቅ ሰሃባ የመጣላትን የትዳር ጥያቄ እያሰላሰለች ሳለ እኚህ ሰሃባ እንደገና ሌላ ሰው ላኩባት። እኚህ ሰሃባ መንገድ እየሄዱ ሸይጧን ቢያያቸው በእርሳቸው ፍራቻ ሼይጧን መንገዱን ቀይሮ በሌላ መንገድ ይሄድ ነበር በማለት ነብያችን ﷺ የመሰከሩላቸው የቂያማ ቀን ከኡመት ሙሐመድ ﷺ ውስጥ የመጀመርያው ሰው ኪታባቸውን በቀኝ እጃቸው የሚቀበሉ ናቸው ተብሎ ሚወራላቸው አላህ ሱብሃነሁ ወተአላ በተደጋጋሚ እኚህን ሰሃባ ንግግራቸውን ደግፎ የቁርአን አንቀፅ ያወረደላቸው ሙእሚኖችን ሲመሩ ለሊቱን እንቅልፋቸውን ትተው መዲናን እየዞሩ ሲጠብቁ የሚያድሩ የአላህ ወታደር ታላቁ ሶሐባ ሰይዲና ዑመር ኢብኑል ኸጧብ ናቸው። ሰይዲና ዑመር አቲካን ለትዳር ጠይቀዋት ምን ልትመልስ ነው? የአብደላህን ቃልኪዳንስ ምን ልታደርግ ነው? ክህደት እና ውሸት ባህሏ አይደለም ያም ሆነ ይህ መልስ መስጠት አለባት እምቢ ወይም እሺ ግን መልስ ሲጠፋ ሰይድና ዑመር እንደገና ጠንከር ካለ ጥያቄ ጋር ላኩባት ። አንቺ አላህ ሀላል ያደረገልሽን ነገር እራስሽ ላይ ሀራም አድርገሻል ገንዘቡን ወይም ከሸሂዱ ባልሽ የወሰድሽውን መሬት ለባለቤቶቹ መልሺና አግቢ አሏት። ሰይዲና ዑመር በአቲካ ቁንጅናና አኽላቅ እጅጉን ተማርከዋል ይባላል። አቲካም እኚህ አላህን በማወቃቸው አላህ አውቋቸው በቁርአን ውስጥ ንግግራቸውን ያንፀባረቀላቸው ታላቅ ሰሀብይ ለአሚረል ሙእሚኒን ኡመር ኢብኑል ኸጣብ ተማረከች ግን የአብደላህ ኑዛዜ፤ ቃል ኪዳኑ ፤የሰጣት መሬት በተለይ የአቲካ ባል የነበረው ሸሂዱ አብደላህ የእናታችን አዒሻ ረዲየሏሁ አንሃ ወንድም እንደመሆኑ መጠን ይህንን መሬት ለ አቲካ ሲሰጥ አይታለች እናታችን አዒሻ ይህችን የወንድሟን ቃል ኪዳን የያዘችና አሁን ደሞ ከታላቅ ሰሃባ ጋር ልትጋባ መወራቱ ምን አይነት መንፈስ ያመጣባት ይሆን? ሰይዲና ዐሊም ከአብደላህ ጋር ቤተዘመድ በመሆኑ ምን ይሰማው ይሆን? አቲካስ ይህን ትዳር ትቀበል ይሆን? ያም ሆነ ይህ አቲካ ቆንጆ ብትሆንም ያገባችው ሁሉ ሸሂድ ነው!
t.me/richyaneyena
------ይቀጥላል-----
#ለፈገግታ
😂😂😂😂😂😂
የአንድ መስጅድ ኢማም ለሶላት የተሰበሰቡትን ሰጋጆች ለማዝናናት “ በህይወቴ ውስጥ ጥሩዎቹ አመታት ሚስቴ ካልሆነች ሴት ጋር ያሳለፍኳቸው አመታቶች ናቸው!” ይላል ።
በኢማሙ ንግግር ለሶላት የተሰበሰቡት ተዳሚዎች በሙሉ ይደናገጣሉ ይደመማሉም።
ኢማሙም አስከትሎ “ አዎን! ከእናቴ ጋር ያሳለፍኳቸው ግዜዎች ናቸው!" ይላቸውል። ታዳሚዎች በተክቢራ ቅውጥ ያደርጉታል ግማሾችም ያልቅሱ ያዙ ።
በቦታው ከተገኙት ሰዎች መካከል አንዱ ሚስኪን ወደ ቤት ሄዶ ከሸይኹ የሰማውን ገልብጦ ኩሽና እራት እያዘጋጀችለት ላለችው ሚስቱ እንዲህ ይላታል፦
“ በሕይወቴ ውስጥ ጥሩዎቹ ዓመታት ሚስቴ ካልሆነች ሴት ጋር ያሳለፍኳቸው ግዜዎች ናቸው!”
የሆስፒታሉ ኦፊሴላዊ ቃል አቀባይ እንዳሉት ቀዶ ጥገናው በተሳካ ሁኔታ የተጠናቀቀ ሲሆን። ጭንቅላቱ ላይ የተሰካውን "ቢላዋ" ከሰውየው ቅል ለመለየት ስድስት ሰዓታትን ፈጅቷል።
ሚስኪን “ከእናቴ ጋር” እንዲል እድል አልሰጠችውም። ሞኝ ነው! በኩሽና ውስጥ እንዲህ አይነት ቀልድ ይቀልዳል?
t.me/richyaneyena
እውር ድንብር😊
ሽማግሌ ሲልክ እራሱን አልቻለ
እሷም የእርሱ ቢጤ ራሷን ያልቻለች
ሁ
ለ
ት
ሁለት አለመቻል በአንድ ላይ ሲኖሩ
ሲኖሩ........ ሲኖሩ
ሲ
ኖ
ሩ
የወለዱትን ልጅ
መቻል ብለው ጠሩ🙊
t.me/richyaneyena
ቆንጆ ነች ያገባችው ሁሉ ሸሂድ ነው።
የአቲካ ታሪክ እየፖሰትኩ ለአስነብባችሁ ምትፈልጎ 👍 ላይክ አድርጉ። የማትፈልጉ 👎ዲስላክይ አድርጉ!
🚿#የውሃው #ገንዘብ ለውሃው
#የወተቱ #ገንዘብ ለወተቱ
አንድ ወተት እያዞረ የሚሸጥ በደንበኞቹ እጅግ ታማኝ የሆነ ወተት ነጋዴ ነበር አሉ።
እናም ለረጅም ዓመታት ያለምንም ማጭበርበር ንፁህ ወተት ለደንበኞቹ ሲሸጥ ከኖረ በኋላ ብዙ ሰዎች አንተ ብዙ ደንበኞች ስላሉህ ወተቱ ላይ ትንሽ ውሃ ጨመር እያደረክ ብትሸጥ እኮ ትርፋማ ትሆናለህ በማለት የሰይጣን ምክር ለገሱት።
ሰውዬውም በሃሳባቸው ተስማምቶ እሺ ይልና ወተቱን ካዘጋጃ በኋላ የወተቱ ግማሽ ቀድር የሚሆን ውሃ ወተቱ ላይ ቸልሶበት ወተቱን በአህያው ጭኖ
እንደተለመደው ለደንበኞቹ እየዞረ ወተቱን ማከፋፈል ጀመረ ።
ታማኝ ሰለሆነ ደንበኞቹም ወተቱን በሙሉ ገዝተው ሂሳቡን ከፈሉት ።
ሰውየም እስከዛሬ ከሚያጋኘው እጥፍ ትርፍ አግኝቶ ምክር የለገሱትን ሰዎች እያመሰገነ ፍራንኩን በከረጪት ቆጥሮ ወደ ቤቱ ጉዞውን ቀጠለ ።
ነገር ግን እቤቱ ከመድረሱ በፊት ይደክመውና አንድ ወንዝ ዳር ጥላ ያለው ዛፍ ስር አረፍ ይላል።
ባረፈበት ቦታ ከረጢቱ ያስቀምጥና ከወንዙ ውሃ ለመጠጣት ወደ ውሃው ቀረብ ብሎ ውሃውን በእጆቹ ጨለፍ እያደገ መጠጣት ሲጀምር ፣
ከየት እንደመጣ ሳያውቀው አንድ ዝንጀሮ መጣና ያንን ከረጢት ብድግ አድርጎ አፈተለኩም ይላል። ሰውዬው ከኋላ እየተከተለ ዝንጀሮው ላይ ድንጋይ ይወረውራል። ዝንጀሮው ከረጢቱ ውስጥ ያለውን ኑቁድ ወይም ፍራንክ እያወጣ ወደ ውሃው ይወረውራል ።
ሰውዬው ዝንጀሮው ላይ ድንጋይ ይወረውራል ፣
ዝምጀሮው ፍራንኩን እያወጣ ወደ ባህሩ ይጥላል ።በመጨረሻም ከስንት ድካም በኋላ በመከራ ያ ዝንጀሮ ከረጢቱ ጥሎለት ይሄዳል። ሰውዬም በጣም ተናዶ ከረጢቱ ብድግ አድርጎ ሲመለከት በውስጡ የተረፉ ጥቂት ፍራንኮች አሉ። ሰውዬውም ቁጭ ይልና ፍራንኮቹ መቁጠር ይጀምራል። ቆጥሮ ሲጨርስ ዝንጀሮው ውሃ ውስጥ የጣለበት ፍራንክ በሙሉ ወተቱ ላይ ውሃ ጨምሮ ያገኘው ትርፍ ሲሆን፣ ከረጢቱ ውስጥ የቀሩት ፍራንኮች ደግሞ ንፁሁ ወተት ሽጦ የሚያገኘው ፍራንክ ብቻ ነበር። 😃😄
ሰውዬው ታዲያ ምን ቢል ጥሩ ነው ፈገግ ብሎ አሃሃሃ የውሃው ገንዘብ ለውሃው፣ የወተቱ ገንዘብ ለወተቱ መሆኑ ነው? ይልና ንፁሁን ሀቁን የንፁሁን ወተት ገንዘብ ይዞ ወደ ቤቱ ገባ ይባላል።
t.me/richyaneyena
كم حياة ستعيش
ስንት ዓመት ትኖራለህ? ከሚለው የከሪም አልሻዘሊ የአረብኛ መፅሐፍ የተወሰደ!
*አንዳንዴ*
አንዳንድ ጊዜ ከዱንያ ኩርኩም ብዛት የተነሳ ይደክምሃል። ራስህን በትልቁ ይከብደሃል። ዝምታና ገለልተኝነት ብቻ ይናፍቅሃል።
አንዳንዴ የታክሲ ወያላ ራሱ "ወዴት ነህ?" ሲለን አንደበታችን የሚዘጋበት ሁኔታ አለ። «ወደርሱ እየሄድን ነው ምናባቱ ያስለፈልፈዋል እንላለን» ።
አንዳንድ ጊዜ ሰዎች «እስቲ ዛሬ ደክሞናል» ካሏችሁ ያ መጥፎ ስሜት እስኪያልፍላቸው ተዉዋቸው፣ ተረዷቸው እሺ።
t.me/richyaneyena
መልካም ቀን!
نصيحه ما بعد الرمضان فضيلة الشيخ صالح الفوزان الفوزان حفظه الله
Читать полностью…ከጥቂት አመታት በፊት ሳውዲ አረቢያ ፡ ጅዳ ውስጥ አሮጌው ( አልባላድ ) ድልድይ የሚባለውን አካባቢ የሚያውቅ ሰው ይህንን የስምንት አመት ልጅ ያውቀዋል ።
ይህ ታዳጊ ከ12 አመቷ እህቱና ከእናቱ ጋር ፡ ኑሮን ለማሸነፍ ከኢንዶኔዥይ ወደ ሳውዲ አረቢያ ጅዳ መጥተው የሚኖሩ ሲሆን ፡ ይሻላል ያሉት የሳውዲ ኑሮ እንዳሰቡት አልሆን አለና ችግር ላይ ወደቁ
..
እና አንድ ቀን ይህንን የቤተሰቡን ችግር የተረዳው የ8 አመቱ ኢልያስ እህቱ ዩስራ አዘውትራ በደብተር ላይ የምትሞነጫጭራቸው ስእሎች እንድትሰጠው ጠየቃት ።
" እነዚህን ስእሎች ሽጨ ለእናታችን ገንዘብ ማምጣት እፈልጋለሁ "
...
እነዚህን ስእል ብሎ ማን ይገዛሀል አለችው
ብቻ ዝም ብለሽ ስጭኝ
ከደብተሯ ላይ የሞነጫጨረችውን ስእሎች እየቀደደች ሰጠችው ።
ትንሹ ኤልያስ ስእሎቹን ይዞ ፡ አሮጌው የባላድ ድልድይ ስር ተቀመጠ ።
.....
አላፊ አግዳሚው እያየው ያልፋል ። አንዳንዶቹ ደግሞ ይህ ትንሽ ልጅ መሬት ላይ ያስቀመጣቸውን በደብተር ሉክ ላይ በስክሪብቶና በከለር የተሞነጫጨሩ የልጅ ስእሎች እያየ ምንድነው ሲሉት ፡ እህቴ ዩስራ የሳለቻቸውን ስእሎች እየሸጥኩ ነው
ስንት ነው ?
አንድ ሪያል
የልጁ ሁኔታ ያሳዘናቸው ሰወች የተወሰኑ ስእሎችን ገዙት
ከሰአታት በኋላ ኤልያስ ከያዛቸው ስእሎች ግማሹን በአንድ ሪያል ሂሳብ ሽጦ አስራ ሁለት ሪያል ይዞ ወደ ቤቱ ሄደ ።
....
ምንም ብር ለሌለው ለነኤልያስ ቤተሰብ ይህ ገንዘብ ብዙ ነበር ። እቤት እደገባም ለእህቱ ሉክና እስክሪብቶ አምጥቶ ፡ ሌሎች ስእሎችን ሳይ አላት ።
ነገ የምሸጣቸው ተጨማሪ ስእሎች ያስፈልጉኛል
እህቱ ተጨማሪ ስእሎችን ስትስል አመሸች
ጠዋት ይዟቸው ወጣና የተለመደው ቦታ ተቀመጠ ።
........
በዚህ መልኩ ጥቂት ቀናትን እንዳሳለፈም አንድ የሳውዲ ጋዜጣ ( Saudi gazette ) ሪፖርተር ይህንን ህጻን ያየዋል።
..........
እና ይህንን ለልመና እጁን ያልዘረጋ ፡ ከዛ ይልቅ የእህቱን ስእሎች ሽጦ ቤተሰቡን ለመርዳት ስላሰበው የ8 አመት ኢንዶኔዥያዊ ህጻን በተመለከተ በጋዜጣው ላይ ጻፈ ።
ይህንን ተከትሎም የህጻኑ ሁኔታ ልባቸውን የነካቸው ሰወች ፡ በትዊተር ላይ ፡ አንድ ሪያል ላንድ ስእል በሚል ሀሽታግ ዘመቻ ጀመሩ ።
....
በዚህ የሶሻል ሚዲያ ካምፔን ብዙ ሰወች ዘመቻውን ተቀላቅለው የዚህን ታዳጊ ቤተሰብ ለመደገፍ ገንዘብ ሰበሰቡ ።
.........
የጉዳዩን ቫይራል መሆን ያዩት የሳውዲ አረቢያ የባህልና የኪነጥበብ ማህበር ሃላፊ ይህንን ታዳጊ ፈልጋችሁ አምጡልኝ ሲሉ ትእዛዝ ሰጡ ።
......
የሳውዲ ባህልና ኪነጥበብ አባላትና ትላልቅ ሚዲያዎች በተገኙበት አንድ ፕሮግራም ተዘጋጅቶ ታዳጊው ኤልያስ ፡ ከእህቱ ዩስራ እና ከእናቱ ጋር እንዲገኙ ተደረገ ።
.......
ባለሀብቶች ይህንን ቤተሰብ እንደግፋለን ሲሉ ቃል ገቡ ። ኤልያስና ዩስራ ትምህርት የሚገቡበት መንገድ ተመቻቸ ፡ ለእናቱ ስራ ተገኘላት ።
....
የእህቱን ስእሎች ሽጦ ቤተሰቡን ለመደገፍ በሞከረው ታዳጊና ፡ ይህንን በተረዱ መልካም ሰወች እገዛ ምክንያት ነገሮች ተለዋወጡ ።
t.me/richyaneyena
ድክመትህን አላህ ፊት ብቻ ግለጥ። ዓለም ጉልበትህን ብቻ ይመልከት!…
ማንም ድክመትህን እንዳያይ! በመስታወት የሚያዩህ ዓይኖችህ እንኳን የጨፈገገና የተከፋ ፊትህን አይመልከቱ!
ደስታህ ሰዎች በሚዘረጉልህ የእዝነት እጅ ወይም በሚያሳዩህ ፊት ላይ አይቋጠር!…
የሰዎች እገዛም ሆነ ጫና ደስታህን ከፍም ሆነ ዝቅ አያድርጉብህ! የሰዎች መልካም ትድድር ተጨማሪ ነገር ሆኖ የደስታህና የእረፍትህ ምንጭ ቀልብህ ይሁን!
ህይወት ለደካሞች ጠባብ ናት!
የነጭ ሽንኩርት መድኃኒትነት
➊ ነጭ ሽንኩርት ስራን በትክክል ለማከናወን፣ የሰውነት ሕዋሳትን ጤናማ ለማድረግ ፣ድካምን ለማስወገድ፣ዕድሜን ለመጨመር፣በአይጥና በልዩ ልዩ ተባዮች የሚመጡትን ተስቦ በሸታዎችን ለመከላከል
➋ ማንኛውም ሰው መጥፎ ሽታ ባለበት አካባቢ ለፅዳት ከመሰማራቱ በፊት ነጭ ሽንኩርት ከትፎ ቢበላ ከማንኛውም በሽታ ከሚያመጡ ተዋህሲያን ለመዳን ይቻላል፡፡
➌ በቂ ሕክምና በሌለበት አካባቢ በቁስል ለሚሰቃይ ሕሙማን በነጭ ሽንኩርት ጭማቂ አጥቦ በቁስሉ ዙሪያ በመደምደም በፋሻ ወይም በንፁህ ጨርቅ በማሰር ሕመምተኛውን ለመፈወስ ይችላል፡፡
➍ ነጭ ሽንኩርት ቀቅሎ እንፋሎቱን የካንሰርንና የቲቢ በሽታዎችን ለመከላከልና በሳንባ አካባቢ ብርድና ጉንፋን ለማዳን ፍቱን መድኃኒቱ ነው፡፡
➎ ብርድ ብርድ በሚያሰኝ ሕመምና በተለይም በጥርስ ሕመም ለሚሰቃዩት ሕሙማን ሁለት ራስ ነጭ ሽንኩርት የውስጠኛውን ሽፋናቸውን በመላጥ በሁለቱም ጉንጫቸው በተለይም በተነቃነቀው ጥርስ በኩል ነክሰው ረዘም ላሉት ሰዓት ቢጠቀሙበት መልሶ ይጠነክራል፡፡
➏ ለአስም፣ ለጉሮሮ ክርካሪ ወይም ኮርታ ለተባለው በሽታ እንዲሁም ጉሮሮ ለማፅዳት የነጭ ሽንኩርት ጭማቂ በስኳር ወይም በማር መጠጣት የተፈተነ መድኃኒት ነው፡፡
➐ ነጭ ሽንኩርት የራስ ምታትና የደም ብዛት ያለባቸው ሰዎች ከ3 እስከ 5 ቀናት በማከታተል ሦስት ፍንካች በቀን ሦስት ጊዜ ቢበሉ ከድካምና ከደም ብዛት ሊፈወሱ ይችላሉ፡፡
➑ በደም መርጋት ምክንያት ለሚሰቃዩ ፣የልብ በሽታን፣ የፊንጢጣ ኪንታሮትና የእግር ደም ሥር እብጠት የተባሉትን በሽታዎች ለመከላከልና ለመዳን ነጭ ሽንኩርት በመብላት መፈወስ ይችላል፡፡
➒ ነጭ ሽንኩርት የቆላ ቁስል፣ችፌን፣የጨጓራ በሽታን ወረርሽኝን ኮሌራን ሳይቲካን የቁርጥማት ሕመምን እንደሚያድን የተረጋገጠ ነው፡፡
መልካም አዳር🥰
t.me/richyaneyena
25 ዓመት በ ትዳር ያለ ምንም ግጭት እንዴት ቆየህ ምክንያቱ ምንድነው ሲለው ከ 25 ዓመት በፊት እንደተጋባን ሚስቴ ጫጉላችን ላይ ፈረስ እየጋለበች ፈረሱ ፈርግጦ ጣላት በንዴት ተነሳች እና 1 ብያለው አለችው እና ፈረሱ ላይ ወጣች አሁንም ጣላት ድጋሚ ብስጭት ብላ ተነሳች እና ጮክ ብላ 2ብያለው ፈረሱ ላይ ወጣች ፈረሱ ግን አሁንም ጣላት ከዛ ወዲያው ሽጉጥ አውጥታ ፈረሱ ላይ በመተኮስ ገደለችው በድንጋጤ ምን ሆነሽ ነው ያምሻል እንዴ እንዴት እንዲ ታረግያለሽ ስላት 1 ብያለው አለች ከዛ እሄው 25 ዓመት ተከባብረን አለን እልሀለው ☺️
/channel/richyaneyena