በቻናሌ ውስጥ በማስተላልፈው ፕሮግራም አስተያየት ከአላችሁ ይህንን @Richyanyena ሊንክ በመጫን በግል አናግሩኝ!!
ይ ቅ ና ህ!
እግርህ ከተነሳ፣ ለመሄድ ወስነህ፣
ልብህ ከሸፈተ፣ ካጠገቤ ሆነህ፣
ከኔ ርቆ መሄድ፣ ውሳኔህ ከሆነ፣
መለየትን ናፍቆ፣ ልብህ ከጨከነ፣
ወዴ! ሽኝሀለሁ ናፍቆትን ደርቤ፣
መሸኘት ልማዱ፣ ሆኗልና ልቤ፣
ፈጣሪ ካልጻፈው፣ የእህል ውሃን ነገር፣
ይቅናህ በሄድክበት ክፍም አልናገር፣
ያመጣህ ጎዳና፣ ይውሰድህ መልሶ፣
ወትሮም መንገደኛ፣ ይመስላል ደርሶ
/channel/richyaneyena
ምትሰራው ስራ ጠላቶችህን
ከአናደዳቸው ቀጥል ወዳጆችህ
ከአናደዳቸው አቁም።
ሁሉም የራሱ አላማ አለው ነገር ግን
አብዛኛ ሰው አላማውና ፍላጎቱ እስኪሳካ ለማይፈልገው ነገር እስረኛ ሆኖ ይኖራል።
የጉልበትህ ሁሉ መሰረቱ ትዕግስትህ ነው።
/channel/richyaneyena በትዳር ውስጥ አንዳንዴ አለ መግባባት ያለ ነው😄
Читать полностью…አንድ ዛፍ ሲወድቅ ሁሉም ሰው ድምፁን ይሰማዋል።ጫካው የሞላው ዛፍ ሲያድግ ግን ማንም አይሰማውም። ልብ በል ብዙ ሰዎች የሚመለከቱት እድገትህ ሳይሆን ውድቀትህን ነው። ስለዚህ ላለመውደቅ ጥረት አድርግ።
/channel/richyaneyena
ህይወት ብዙ አይነት ከለርነው ያላት የአንተም ህይወት ሳታስበው ልክ እንደ ቲማቲሙ ውብ ከለር በመሆን ሊቀየር ስለሚችል አሁን ያለህበት የህይወትህ ከለር አጣፍጠህ ኑረው
/channel/richyaneyena
ነገራቶችን ከሚገባቸው በላይ ቦታ አትስጥ ፣ ክብርህን በሰዎች እይታ ውስጥ አትፈልጋት፣ ህሊናህ ውስጥ ፈልጋት፣ህሊናህ ሲረጋጋ ክብርህም ከፍ ይላል…ራስህን ካወክ ስላንተ የተባለው አይጎዳህም፣የዱንያን ጭንቀት አትሸከም እሱ የአላህ ስለሆነ፣
ስለ እርዚቅም አትጨነቅ እሱም ከአላህ ስለሆነ
/channel/richyaneyena
"ሌባው" የመስጅድ ኢማም
=================
ባልና ሚስት ከረመዷን ወራት ባንዱ በሰፈራቸው የሚገኝ መስጂድ ኢማም የሆኑትን ሸይኽ ለፊጥራ ጋበዟቸው። ኢማሙም ግብዣውን በክብር ተቀበሉ። የቤቱ እማወራ የምግብ ማዕዱን ለማዘጋጀት ተፍ ተፍ እያለች ሳለ ገንዘቧን ጠረጴዛው ላይ ጥላ ወደ ኩሽና አመራች። ፊጥራው ተጠናቀቀ። ኢማሙም ሄዱ። ሚስት ገንዘቧ እንደጠፋ አስተዋለች።
«ገንዘቡን የሰረቀው ማን ነው?» ተብሎ አይጠየቅ ነገር ባልና ሚስት ልጆች የሏቸውም። በወቅቱ ወደቤት የመጡት የመስጂዱ ኢማም ብቻ ናቸው። ውስጧ በጥርጣሬ ተናጠ። ታሪኩን ለባለቤቷ አጫወተችው። የመስጂዱን ኢማም እንዲያማክራቸውና ጉዳዩን እንዲያረጋግጥ ጠየቀችው። «ኧረ ነውር ነው ፤ ባይሆን ከኢማሙ ጋር የፈጠርነውን ግንኙነት አቋርጠን ፋይሉን እንዘጋለን እንጂ እንዲህ አይነት ጥያቄ ማንሳት የማይታሰብ ነው» በማለት መለሰላት። ያም ቢሆን ባለቤቷ ኢማሙን ተከትሎ ሶላት ላለመስገድ ወሰነ።
ቀናት በንፋስ ፍጥነት ከነፉ። ቀጣዩ ረመዷን ገባ። ባል ከሚስቱ ጋር ተቀመጠ። «እንግዲህ የእዝነት እና የይቅርታ ወር ስለገባ ያለፈውን መርሳት አለብን። እንደምታውቂው ኢማሙም ቤተሰብ የላቸውም። ስለዚህ ዘንድሮም ቢሆን ፊጥራ ልንጋብዛቸው ይገባል» በማለት ሚስቱን ሹክ አላት። ሚስት ለአፍታ ዝም ካለች በኋላ «በሃሳብህ እስማማለሁ፤ ነገር ግን የማስቀምጠው ቅድመ ሁኔታ ይኖራል። እርሱም የባለፈው ዓመት ረመዷን ላይ ስለተሰረቀው ገንዘብ ጉዳይ በግልጽ እንድታወሩ እፈልጋለሁ» አለችው። እርሱም ባቀረበችው ሃሳብ ተስማማ።
የመስጅዱ ኢማም ግብዣውን ተቀብለው ከቤት መጡ። ፊጥራውን ከጨረሱ በኋላ የቤቱ አባወራ ጉዳዩን በይፋ አነሳው። ስለ ገንዘቡ ሁኔታ በቀጥታ ጠየቃቸው። ከፍተኛ የሀፍረት ስሜት ተሰማቸው። እንባቸው በጉንጮቻቸው ላይ ተንኳለለ። ካቀረቀሩበት ቀና አሉ። አይኖቻቸው የእንባ ቋጠሯቸውን እንደፈቱ ነው። ሚስት ፈጠን ብላ « ኢማም ሆይ! ምን ሆነው ነው የሚያለቅሱት ?» በማለት ጠየቀቻቸው። «አዎ! ገንዘቡን ያነሳሁት እኔ ነኝ። ያስቀመጥኩትም የመጽሃፍት መደርደሪያው ላይ ከተቀመጠው ብቸኛ ቁርኣን ውስጥ ነው። እንባዬ የፈሰሰውም ረመዷንን ጨምሮ ለ 365 ቀናት ያህል የአላህን መጽሃፍ ገልጣችሁ አንድ ፊደል እንኳ አለመቅራታችሁ ገርሞኝ ነው» በማለት ምላሽ ሰጡ። በዚህ ጊዜ የቤቱ አባወራ በፍጥነት መደርደሪያው ላይ ወደተቀመጠው ቁርኣን አመራ። ገንዘቡንም የቁርኣኑ የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ምዕራፍ መሃል ላይ ተቀመጦ አገኘው። ሚስት እንባዋ ግድቡን ጥሶ ፈሰሰ። ኢማሙን በክፉ በመጠርጠሯም ይቅርታ ጠየቀቻቸው። «ልጄ ሆይ! እኔ ደካማ የአላህ ባሪያ ነኝ፤ ይልቅ አመቱን ሙሉ ቁርኣኑን ችላ በማለትሽ ይቅርታና ምህረት ከአላህ ጠይቂ» በማለት መከሯት።
እኛስ መቼ ይሆን ለመጨረሻ ጊዜ የአላህን ቃል ከፍተን ያነበብነው? 😢 ነፍሳችንን ሳንዋሽ እውነቱን ለራሳችን እንገረው❗ ወገኖቼ የአላህ ቃል እየጠራን ቢሆንም ችላ ብለነዋል።
እንኳን ለተከበረው ሸህሩል ረመዷን በሰላም አደረሰህ! ያስቀየምኳችሁ ነገር ከአለ ለአሏህ ብላችሁ አፉ በሉኝ አፉሊላህ ብያለው!
Читать полностью…ግዙፍ ስጦታ ቁስ ሳይሆን መልካም
ንግግር ነው በመጥፎ ንግግርህ
የሰበርከው ልብ ቁስ እንደ ስጦታ
በመስጠት ወደ ቦታው መመለስ
አትችልም ።
በጣም ጎበዝ ሆኜ ሳይሆን ከችግር ጋር ለረጅም ጊዜ ስለቆየሁ ነው።ጎበዝ የሆንኩት።
@richyaneyena
እኔ የማመሰግነው እምቢ ያሉኝ ሰዎች ነው። በእነርሱ ምክንያት ነው ሁሉንም ነገር በራሴ ማድረግ የቻልኩት።
ሁላችንም የተጎሳቆለ ልብስ እና ጥራት የሌለው የቤት እቃ የሚያሳፍረን ከሆነ የተጎሳቆሉ አስተሳሰቦች እና ጥራት የሌላቸው ፍልስፍናዎችም ሊያሳፍሩን ይገባል......እንግዴህ፣ ከውስጥ ካለው ስጋ ይልቅ ከላይ ያለው የስጋው መጠቅለያ የተሻለ ጥራት ያለው ከሆነ አሳዛኝ ሁኔታ ነው የሚሆነው።
@richyaneyena
ጤነኛ ሆኖ እንዲኖር እንደ መድሀኒት
ሁሌም ሰበብ እየሆንክለት እሱ ግን የመታመምህና በሽተኛ የመሆንህ
ሰበብ የሚሆንም በሽተኛም ሰው አለ።
@richyaneyena
@richyaneyena
ሀዘን እና ጭንቀት ሲገጥምን ሊያጋጥሙን የሚችሉ.........
🔉 ብቻህንም ብትሆን
በሀቅላይ ፅና
ሰዎች አይጎዱህም
@richyaneyena
ሽህ ሷሊህ ፈውዛን
「 ሀፊዘሁሏህ」
ብሶት
በችግር መሰላል ብታንጠለጥይኝ
በገዛ ገንዘቤ ለሞት ብትሸጪኝ
አትጠራጠሪ አታስቢ ላፍታ
ይቅር እልሻለሁ ደሞ ለይቅርታ
ግን እንደው አንቺ ሴት
በይቅርታ ልኬት
ለበደልሽኝ ሁሉ ምህረት ባደርግም
ይቅር ስልሽ እንጂ ሳምንሽ ግን አልኖርም።😭
بَلِ اللَّهَ فَاعْبُدْ وَكُن مِّنَ الشَّاكِرِينَ
[ አል-ዙመር - 66 ]
ይልቅ አላህን ብቻ ተገዛም፡፡ ከአመስጋኞቹም ኹን፡፡
ሁለት አይነት ሰው እንጂ አንተን በቅጡ አይረዳህም።አንደኛው ባለፍክበት መንገድ ያለፈ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የሚወድህ ሰው ነው።
Читать полностью…ጌታዬ ሆይ
የማይመጣን ነገር እንድጠብቅ አታድርገኝ
ሀዘኔን በማይፈራ ሰው ላይ ችክ እንድል አታድርገኝ ለእኔ ባልፃፍከው እና ልቤን በሚጎዳ ነገር ላይም እንድንጠለጠል አታድርገኝ
/channel/richyaneyena
የሰው ልጅ መርሳት ባይችል ኖሮ፤በሚያውቃቸው መጥፎ ነገራት ብዛት ይሞት ነበር።
አንዳንዴ መርሳትም ፀጋ ነው!
”
ምን አልባትም ህልሞችህ በዩሱፍ ጉድጓድ ውስጥ ወድቀው ሊሆን ይችላል፣
የአሸናፊው(የአላህ) ቅፍለቶች እንደሚመጡ ግን አትዘንጋ።
በህይወትህ ውስጥ ጠንካራም ደካማም የመሆን ምርጫ አለህ ፣
የውሳኔው ባለቤት አንተ ነህ።
ድምፅህን ሳይሆን፤የቃላትህን ደረጃ ከፍ አድርግ ቡቃያን የሚያበቅለው ነጎድጓዱ ሳይሆን ዝናቡ ነው።
ምናልባት በህይወትህ ክፍተትን የፈጠረብህ ይበልጥ ውብ በሆነው ነገር ሊሞላህ ፈልጎ ይሆናል።
/channel/richyaneyena
አንተ! በችግሮችህ ምትረታ ሰው
ሳይሆን ችግሮችህ በአንተ ትግስትና
ጥንካሬ የሚረቱ ጀግና ሰው ሁን!
ከትግስተኛ ሰዎች ጥንካሬን ተማር
ከጥበኛ ሰዎች ደግሞ ብልሀትን ታማር
ከድሀዎች ደግሞ መብቃቃትን ተማር
ከችኩል ሰዎች ደግሞ ችኩልነት
መጨረሻው ፀፀት እንደ ሆነ ተማር።
ጊዜ ሁለት ነው አንድ ቀን ለአንተ ይሆናል፤ አንድ ቀን ባንተ ላይ ይሆንብሀል፤ ለአንተ ሲሆን አትኩራ፤ ........ባንተ ላይ ሲሆን አትጨነቅ ››*~ ~* -አሊይ ኢብን አቢ ጧሊብ (ረ.ዐ)
Читать полностью…ታላላቅ አእምሮዎች ሁሌም ከደካማ አእምሮዎች ከባድ ተቃውሞ እንደገጠማቸው ነው። @richyaneyena
Читать полностью…@richyaneyena
የፍቅር በረካ
ገና በጅምሩ በአቦል ፍቅርህ ያኔ
እንቅፋት ቢመታኝ ልደፋልሽ እኔ
አቦል ፍቅርህ አልቆ ቶና ሲጣድማ
እያየሽ አትሄጂም ወልጋዳ ጠማማ
የባሰው መጣና በፍቅርህ በረካ
ስትሳል ሰማውህ ለሰፈርህ አድባር
ከትልቋ ዋርካ
ድፍት አርጋት እያልክ በመንገዱ ሳንካ
ታጥቦ ተለቅልቆ የጥላቻ አተላ
ፊቴ ሳይደፋ
ማቄን ጨርቄን ሳልል አንተ ካለህበት ከአጠገብህ ልጥፋ።🏃♀
ደስተኛ ሕይወት ለመኖር ከፈለግክ አንተነትህን ከሠዎች ወይም ከነገሮች ጋር ከማወዳደር ይልቅ ከግብህ ወይም ከዓላማህ ጋር ራስህን እሠር።
Читать полностью…ሞኝ በሰራው ስህተት ዋጋ ሲከፍል
ብልጥ ደግሞ ሞኝ በሰራው ስህተት
ትምህርት በመውሰድ የራሱን ክፍተት
ይሸፍናል
የልቤ ሰው አጣሁ ከማለትህ በፊት
መጀመሪያ የልብህ ሰው ለማግኘት
አንተ ልብ ይኑርህ❤️።
@richyaneyena