nesiha | Unsorted

Telegram-канал nesiha - سماحة الإسلام የኢስላም ገራገርነት

986

ይሄ ቻናል የቁርአንና የሀዲስን አስተምህሮቶች በሰለፎች አረዳድ ማሰራጫ ነው ከፖለታካ ነፃ ነው።

Subscribe to a channel

سماحة الإسلام የኢስላም ገራገርነት

አጂብ ቂሷ
ነብዩ ﷺ ሲሰደቡ የተቆጣው አስገራሚ ውሻ!
" ክስተቱን ኢብኑ ሀጀር የተባሉት ታላቁ አሊም "አዱረሩል ካሚናህ"
ኪታባቸው ላይ አስፍረውታል
ቀደም ሲል ከነበሩ ሞጎላውያው አንድ ባለስልጣን የክርስትናን ሃይማኖት
ከተቀበለ ጥቂት ጊዜያት በኋላ ሀይማኖቱን መቀበሉን አስመልክቶ በተዘጋጀ
ድግስ ከተወሰኑ ቄሳውስቶች ጋር ሰብሰብ ብለው ተቀምጠዋል። በጊዜው
ከአቅራብያቸው አንድ የአደን ውሻም ታስሮ ነበር።
በወቅቱ ከነበሩ ቄሶች አንዱ ለአለማት እዝነት የተላኩትን ታላቁን ነብይ
ሙሀመድ ﷺ በመጥፎ ማንሳትና መተቸት ብሎም መሳደብ ይጀምራል።
ታድያ ይህንን ይሰማና ይታዘብ የነበረው ውሻ እጅግ ተቆጣ ፤ ወዲያውኑ
በከፍተኛ ድምፅ እየጮኸ ተሳዳቢውን ቄስ ዘሎ ነከሰውና አቆሰለው ፤
በአቅራቢያው የነበሩ ሰዎችም ተረባርበው አዳኑት ። ሰዎቹም፦ "ውሻው
የምትናገረው ነገር አልተስማማውምና ሰለ ሙሀመድ ( ﷺ ) መጥፎ
ከመናገር ተቆጠብ"ይሉታል ፤ ሰውየው ግን ፦ "አይ ችግሩ ከምናገረው
አይመስለኝም ባይሆን በምናገርበት ወቅት እጄን ስዘረጋና ሳንቀሳቅስ
ስለነበር እሱ ላይ የጠቆምኩበት መስሎት ነው" በማለት ስድብና ትችቱን
ቀጠለ። ውሻው ግን ከመጀመሪያው በከፋ መልኩ በከፍተኛ ቁጣና ንዴት
ዘሎ ጉሮሮውን በመንከስ ገነጠለውና ሰውየውን ገደለው
ሱብሃነሏህ!
ይህ ክስተት በጊዜው የነበሩ ሰዎችን በከፍተኛ መልኩ አስገርሞ ነበር ፤
በዚህም ውሻ ምክንያት በወቅቱ ወደ 40 ሺህ የሚደርሱ ሰዎች እስልምናን
ተቀበሉ።
በእውነቱ የአሏህን ሰራዊቶች እርሱ እንጂ ማንም አያውቃቸውም አይደል!

Читать полностью…

سماحة الإسلام የኢስላም ገራገርነት

=> እሕቴ ሀያእ ማለት 20 ግዜ መቀያየር ወይም 20 ነገር ማዉራት እና 20
ግዜ የምዕራባዊያን ፋሽንን መቀያየር አይደለም ።
=> ሀያእ ማለት በኔ እና ባአንች ቀልብ ዉስጥ ሊኖረን የሚገባ ኢማን ነዉ ።
=> ትልቅ የቀልብ ልብስ ሀያዕ ነዉ ለኔ እና ላንች ።
=> ያኡሕቲ ስለዚሕ ልባችንን ቀልባችንን ሀያእ እናልብሰዉ ኢንሻ አላሕ ።
\\\ አላሕ ሁላችንንም ከሀያዕ ንግስቶች መካከል ያድርገን አሚንንንንንንን

Читать полностью…

سماحة الإسلام የኢስላም ገራገርነት

ሁረል=ዐይን
~ክፍል ሶስት
እግራቸው ከሚስክ እና ከዘዕፈራን መሬትም እንደረገጠች ፊታቸው በእምባ
ተሞልቶ ምስጋናን ማቅረብ ጀምረዋል።
ምስጋና ለአላህ ለዚያ ተስፋ ቃሉን ለሞላልን። የጀነትን ምድር በምንሻው ስፍራ
የምንሰፍር ስንኾን ላወረሰን ይገባው ይላሉም። የሠሪዎችም ምንዳ ምን ያምር!
[ አል-ዙመር -74 ]
ሙእሚኖች ልባቸው የጓጓለት ዘውትር የሚናፍቁት ሀገራቸው ጀነትን፤ በውስጧ
ከተዘጋጀላቸው ፀጋዎች ውስጥ አንዷ የሆነችውን ሑረል ዓይን ለማግኘት
ቀልባቸው ተንጠልጥሏል።
የጀነት እንግዶች ወደ ውስጥ በመራመድ ላይ ናቸው። ከበስተግራ በኩል ከወተት
የነፁ ጅረቶች ይፈሳሉ። ከበስተቀኝ በኩል ከወርቅና ብር የተሰሩ ህንፃዎች
ይታያሉ።
ፊት ለፊት ፏፏቴ አለ። በፏፏቴው ዙሪያ ውቧ እንስት ሑረል ዓይን ቆማለች።
የባሏን መምጣት በጉጉት ትጠባበቃለች። በጣፋጭ እና ልብን በሚሰልብ
ድምጿን ታዜማለች። እንደማር በሚጣፍጥ አንደበቷ እንዲህ እያለች ትዘምራለች።
የዱንያ ድሎት የማይወዳደረው
ጀነት ምነኛ ያማረ ትልቅ ፀጋ ነው
ዓይኗ በጣም በናፈቀቺው ውድ ባሏ አረፈ በሩጫም ወደሱ አመራች
አንተን በመጠባበቅ ረጅም ዘመናት አሳለፍኩ። ሁሌም ወዳድ ፤ የማልጠላ፤
ዘውታሪ የማልሞት በቤቴ ውስጥ የረጋሁ አንተን ጥዮ የማልሄድ ፣ ፍቅሬ ውዴ
ናልኝ ናፍቀኸኛል በማለት ተጠመጠመችበት ተቃቅፈው ጉዟቸውን ሽቅብ ቀጠሉ።
በል ና ተከተል ወንድሜ.....ጡቶቿ እንደ ፓም ፍሬ ቀጥ ቀጥ ብለው የቆሙትን
የጀነቷን እንስት ሑረል ዓይንን እንግለፃት።
ቀልብህን ከፍተህ በጆሮህ ስማኝ.......በዓረብኛ ቋንቋ ﺣﻮﺭ ሑር የሚለው ቃል
የአይኗን ብርሃን በጣም አንፀባራቂ ጥቁረቱ ደማቅ ከወተት በላይ ነጭ ቆንጆ
ማለት ሲሆን አይን ማለት ደግሞ ዓይኗ ጎላ ብሎ የሚታይ ውብ ሴት ማለት ነው።
# የጀነቷ አበባ
የአላህ መልክተኛ (ሰዐወ) እንዲህ ብለዋል.....ከጀነት እንስቶች መካከል አንዲት
ሀውራ ወደ ምድር ብትመለከት ከምስራቅ እስከ ምዕራብ ብርሃኗ ያንፀባርቃል፣
ባመረ ሽታም ምድርን ባወደች ነበር። በጭንቅላቷ ላይ ምታደርገው ከዱንያና
ከውስጧ ካለ ሁሉ የተሻለ ነው
[ቡኻሪ ዘግቦታል]
ሻሿ ከዱንያና በውስጧ ካሉ ሀብቶች ሁሉ ውድ ከሆነ የሻሿ ባለቤት እንስት
ቁንጅና እንዴት ይገለጽ ይሆን?
አላህ ጀነት ውስጥ ሞትን ስላስወገደ እንጂ በውበቷ ምክንያት በሞቱ ነበር። እጇን
ወደ ምድር ብታወጣው ፍጥረታት በሙሉ በውበቷ በተፈተኑ ነበር።
# እኔን አጭተህ ትተኛለህ?........
ከሰለፎች መካከል አንዱ ዛሬ ሁረል ዓይን ብዙ ግዜ ቁርአንን በማክተም የግሌ
አደርጋለሁ በማለት ቆርጦ ተነሳ ንባቡም ጀመረ። በመሀል እንቅልፍ አሸንፎት
አሸለበ።
የኔን አይነት መሰል አጭተህ ትተኛለህ?
እንቅልፍ አብዝቶ መተኛት በኛ ወዳጅ ላይ እኮ ክልክል ነው። እኛ የተፈጠርነው
አብዝቶ ለጾመና ለሰገደ ነው።
የሰውነቷ ቅርጿ ፤ የቆዳ ቀለሟ ፤ ተክለ ሰውነቷ ያፈዛል፤ የማይጠወልገውና
የማይረግፍ ውበትን አላህ አጎናጽፏታል።
ይቀጥላል.......

Читать полностью…

سماحة الإسلام የኢስላም ገራገርነት

የኢስላም ወንድሞቼ
~~~~~~~~~~~
አስፈላጊ መልእክት ስለሆነ ሼርር አድርጉት
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
➦አላህን የሚፈሩት አንሰው አላህን የሚያምፁ ሰዎች በበዙበት ግዜ እንገኛለን
።አላህ ሁላችንም ሀቅን ከሚቀበሉት ያድርገን አላህን ከሚፈሩት ያድርገን እላለሁ

➣Fashion በማለት ሴቶቻችን እራቆት እየሄዱ ያለበት ግዜ ላይ ደርሰናል
አላህን የሚፈሩት ሲቀሩ አብዛኞቹ ለብሰው እንደለበሱ ሆኖዋል ።
➣ስለዚህ ወንድሞቼ በአሁን ሰአት እህቶቻችን መምከር አለብን እህቶቻችን ኒቃብ
እንዲለብሱ አላህን እንዲፈሩና Fashion የሚሉትን ኮተት እንዲርቁ መምከር እና
መበረታታት አለብን ።ይባስ ብሎ ኒቃብ ለባሽ የነበረችውን ጀግና እህታችንን የሌላ
ስም እየለጠፉ ሌላ ስም እየሰጡ እናያለን ።
➣እሷን አላዋቂ ስልጠኔ ያልገባት አድርጎ ማየት በማህበረሰባችን እናያለን ይችን
እህት ጀግና በዚህ አቋምሽ ቀጥ በይ ማለት ሲገባን ከትክክለኛው ሂጂብ
እንድትርቅ ሲደረግ ይታያል ።
➣ከኢስላም የበለጠ ስልጣኔ የገባው የለም [[በጌታዬ ይሁንብኝ]] ኢስላም
ስልጣኔ አይፈልግም ምክንያቱም የለን እምነት ድሮውኑ የሰለጠነው ነው ።
➣ማሻሸያ አያስፈልገውም ስለሆነም የድሮው የኢስላምና ትክክለኛው አለባበስ
ድሮው የነበረው ነብዩ ሙሀመድ ሰለላሁ አለሂ ወሰላም የነገሩን እና የነቢያት
ሚስቶች የለበሱት ያሳዩት መሆን አለበት ይህ ነው ዘመን የማይቀይረዉ አለባበስ

➣ስለዚህ ወንድሞቼ አካባቢያችን የሚገኙ ኒቃብ የለበሱ እህቶችን መበረታታት
እና ከዚህ በፊት ኒቃብስት ያልሆነች እህት እንድትላብስ መድረግ አለባችሁ
ተገቢዉን ትብብር አድርጉለት።
➣እናንተ እያላችሁ ኒቃብስቶች ባይተዋር መሆን የለባቸውም ጀግንነታቸው
እንዲቀጥል አድርጉ በማለት ወንድማዊ መልእክቴን እዚህ ላይ አበቃለሁ።አላህ
በተዉሂድ በሱና አንድ ያድርገን ጠንካራ ወንድማማቾች ጠንካራ እህትማማቾች
ያድርገን ።

Читать полностью…

سماحة الإسلام የኢስላም ገራገርነት

አላህ የጀነቱ ይበላቸውና ሽህ አህመድ ዲዳት ከሽአዎች ጋር
ለሚያደርጉት ሀይማኖታዊ ክርክር ወደ ሚጠብቋቸው የሽአ ሸኮች ወደ
መስጅዳቸው ውስጥ ሲገቡ ጫማቸውን በእጃቸው ታቅፈው ገቡ ። ይሄኔ
ሽአዎቹ ሸኮች በሁኔተው ተገርመው ለምን ጫማቸውን ይዘው እንደገቡ
ሽህ ዲዳትን ጠየቁ ? ሸህ ዲዳትም ቀልጠፍ ብለው "በረሱል ዘመን
ከመስጅድ ጫማ የሚሰርቁት ሽአዎች እንደነበሩ ትዝ ብሎኝ ነው
ጫማየኝ መያዜ" የሚል መልስ ይሰጣሉ ። ይሄኔ የሽአዎቹ ሸኮች
ተገርመው እርስ በርሳቸው በቀስታ ከተነጋገሩ ቡኋላ ከመሀለቸው አንዱ
ወደ ሸህ ዲዳት ዞረና "የሆነስ ሆነና ሽአ በረሱል ጊዜ መች አለና? መች
ተፈጠረና ነው ? ይህን የምትለው ?" ብሎ ሸህ ዲዳትን ጠየቀ? ሸህ
ዲዳትም "በረሱል ጊዜ አለመኖሩን ይሄው እራስህ መሰከርክ ታድያ አንተ
ከየት ነው ያመጣሀው?" ብለው ሽአውን አፋጠጡት ??? በዚህም ጥበብ
የታከለበት ዘዴያቸው ተሳክቶላቸው የመጡበትን ሀይማኖታዊ ክርክር
በብቃት አሸንፈው ተመለሱ ።

Читать полностью…

سماحة الإسلام የኢስላም ገራገርነት

:::::::::ትዳርና ልጆች::::::::::

ትናንት ከነበሩ ፕሮግራሞች አንዱ ትዳርንና ልጆችን የተመለከተ ቤተሰባዊ ጉዳይ
ነበር። በአሁኑ ወቅት የፍች መጠን (Divorce Rate) በሃገራችንና በአጠቃላይ
በዓለም በከፍተኛ መጠን እየጨመረ ይገኛል።
ምክንያቱ ምን ይሆን? ጥንዶች ከመጋባታቸው በፊት "የፍቅር ጓደኛ" በሚለው
ስያሜ "መጠናናት" የሚለው ነገር ስለማይኖር ነው እንዳትሉኝ። ምክንያቱም
ከፍተኛ የፍች መጠን የሚታይባቸው ሃገራት ይህን ሃሳብ የሚደግፉትና
የሚተግብሩት ናቸው።
ሁሉም የሚያውቃት አሜሪካ ከፍተኛ የፍች መጠን ካለባቸው ሃገራት መካከል
ከማልዲቭስና ቤላሩስ ቀጥላ በሦስተኛ ደረጃነት Guinness World Records
ላይ ተቀምጣለች።
ዋና ዋና የሚባሉት ለፍች የሚዳርጉ ምክንያቶች፦
√ አለመቻቻል፣ አለመተዛዘን፣ ጥቃቅን ክፍተቶችን ከመተላለፍ ይልቅ መጠባበቅ፣
በጥቅሉ የጸባይ ጉዳይ ነው።
√ ከትዳር የሚጠበቀውን ተገቢውን ፍቅርና አገልግሎት ለትዳር አጋር በበቂ ሁኔታ
አለመስጠት፣
√ የኢኮኖሚ አቅም ማጣትና ከትዳር በፊት በሐሰተኛ ማንነት መቀራረብ!
*
√ ልጆችን በተመለከተ፤ አላህ ለአንድ ሰው በተፈጥሮው የሚያድለው ትህትናና
ጸባይ እንዳለ ሆኖ የወላጆች የአስተዳደግ ሁኔታ (ተርቢያ) ራሱን የቻለ ተፅዕኖ
አለው። ልጆችን በቀላሉ አመለካከታቸውን መቀየር የሚቻለው ገና በለጋ
እድሚያቸው ላይ ሳሉ ነው። Unfortunately አብዛኛዎቹ ወላጆች ልጆቻቸውን
ገና በለጋ እድሚያቸው ነፃነታቸውን ልንነፍጋቸው አይገባም፣ አሁን ላይ እንደፈለጉ
ይዝናኑና ኋላ ነፍስ ሲያውቁ ይመከራሉ በሚል ሲዘናጉ ይታያል። በዚህ የተነሳ
ብዙዎች ኋላ ላይ ማስተካከል የማይቻሉበት ደረጃ ላይ ይደርሳሉ። በመጨረሻም
እንኳን የወላጆቻቸውን ሐቅ በአግባቡ የሚወጡ ልጆች ሊሆኑ፤ ጭራሽ በተለያዬ
መልኩ የሚያስቸግሩ ይሆናሉ። ገና በለጋ እድሚያቸው ከአላስፈላጊ ጓደኞች ጋር
ሆነው ያድጉና፤ የዛሬ የሰባት ወይም የስምንት አመት ልጅ ከአንደበቱ የሚወጣውን
የብልግና ቃልና ተግባር ለኔ ያሳፍረኛል።
*
ለነፃነት የምንሰጠው ትርጉምና አረዳድ እንደ ግንዛቢያችን ስለተለያዬ እንጅ፤ አንድ
ህፃን መናገር ሲጀምር KG (መዋዕለ ህላን) ከመግባቱ በፊት የዐረብኛ ፊደላትን
እያስቆጠሩ፣ ከዘፈንና መሰል ክላሲካል ነገሮች ይልቅ ቁርኣንን እያዳመጠ ካደገ፤
በልጅነት አዕምሮው በተቀረጸበት ህይዎት ላይ ማደጉ አይቀርም።
ይህ የሚደረገው ደግሞ በማጨናነቅና በማስገደድ መልክ ሳይሆን ዘና በማድረግ፤
ይህን ካደረግክ የሆነ የሚወደውን ነገር ስሙን ጠርታችሁ «ያንን ገዝቼ
እሸልምሀለሁ!» በማለት Surprise በማድረግ ነው።
ከዚህ ባሻገር ልጆች ከወላጆቻቸው አንደበት ከሚወጡት ቃላት ይልቅ
ተግባራቸውን ይቀስማሉ። እናቱ ወይም አባቱ ሲሰግዱ ካየ አብሮ ይሰግዳል።
ውዱእ አደርጋለሁ እያለ ይጥራል… ወዘተ።
አንተ ጫት ስትበላ ወይም መጠጥ ስትጠጣ ወይም ስታጨስ እያየ፤ አትቃም፣
አትጠጣ ወይም አታጭስ ብትለው ይሰማሃል እንደ
ምናልባት አንተ ፊት ባያደርገው እንኳ ተደብቆ ያደርገዋል።
ልጆች አንድ ጊዜ ከተበላሹ መመለስ ከባድ ነው።
ከሚስትህ ጋር ካልተግባባህና ያልተግባባችሁበት ነገር ደግሞ ከአቅም በላይ ሆኖ
ማስተካከል ባይቻል፤ ፍች የሚባል የመጨረሻ አማራጭ ስላለ ያንን ለመጠቀም
ትገደዳላችሁ።
የልጅን ጅል ግን የት ይጥሉታል ቢክዱትም አንጀት አይችልም። የአብራክህ ክፋይ
ነዋ! የሞተም ከሆነ ጊዜ በኋላ በአንፃሩ ይረሳል። ይሄን ጧት ማታ ፊትህ ላይ
የምታየውን ጅልህን ግን የት ታደርገዋለህ? «የእገሌ ገንዘብ ተሰረቀ!፣ የእገሌ ልጅ
ተደፈረች!፣ እገሌ ተደበደበ!…» ወዘተ ሲባል፤ «ያው የኔ ልጅ ይሆናል ይህን
የሚያደርገው!» ብለህ የምትሰጋ ከሆነ ይህ ኑሮ ነው እንደ
አለፍ ሲል ደግሞ ለጫቱና ለሲጋራው ገንዘብህን የሚዘርፍህና የሚጣላህ ከሆነ፣
ጭራሽ ሊገድልህ የሚያስብ ሁሉ ከሆነ ከባድ ነው። ብታሳስረውም ያንተው ልጅ
ነው። አላሁ-ል-ሙስተዓን! ኋላ እድሜህ ሲገፋ መጦሩ ቀርቶብህ አሁን ራሱ
በሰላም በኖርክ!
እንዲህ አይነት ልጅ እንዳይፈጠርብህ ከፈለግክ፤ ከወዲሁ በኢስላማዊ
አስተዳደግ ኮትኩተው። ልጆችን በጥሩ ኢስላማዊ ተርቢያ ለማሳደግ ደግሞ
ከአንተ ይልቅ ሚስትህ የአንበሳውን ድርሻ ትይዛለች። አንተ ለሥራ ጧት ወጥተህ
ማታ የምትገባ ሰው ትሆን ይሆናል። ቀን ልጆችህ የት እንደዋሉ፣ ቤት ውስጥ
ቢሆኑ ራሱ በቲቪና መሰል ነገሮች ምን እንደሚሠሩ አታውቅም። እርሷ ግን ካንተ
በተሻለ መልኩ ታውቃለች።
ዘለህ ወደ ትዳር ከመግባትህ በፊት ቅድሚያ በተረጋጋ መልኩ መልካም የትዳር
አጋር ምረጥ። «Well begining is hakf done!» (በመልካም መልኩ
የተጀመረ ነገር ግማሽ ያክል እንደተፈጸመ ይቆጠራል!» እንደሚባለው፤ ከምንም
በፊት ጥሩዋን የትዳር አጋር ካገኘህ በአላህ ፈቃድ ለወደፊቱ የትዳር ህይዎትህና
ለልጆችህ መልካምነት የሆነ ዋስትና አለህ። አንቺም እንደዛው ተረጋግተሽ
መልካሙን ምረጭ!
አለበለዚያ አንተ እንደሌለህላት እርሷ ፊልሟንና ድራማዋን እየቀጠቀጠች ልጆቹ
ከርሷ ምን ይማሩ
አላህ ከሁሉም ይጠብቀንና በልጅ መፈተን በትዳር አጋር ከመፈተንም ይብሳል።
እናም ነጋችንን በዛሬ ተግባራችን እንገንባው።
አላህ ለሁላችሁም መልካሙን ይግጠማችሁ።

Читать полностью…

سماحة الإسلام የኢስላም ገራገርነት

ﺃَﺑِﻲ ﻫُﺮَﻳْﺮَﺓَ ﻋَﺒْﺪِ ﺍﻟﺮَّﺣْﻤَﻦِ ﺑْﻦِ ﺻَﺨْﺮٍ  ﻗَﺎﻝَ : ﺳَﻤِﻌْﺖ ﺭَﺳُﻮﻝَ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ ﻳَﻘُﻮﻝُ :
" ﻣَﺎ ﻧَﻬَﻴْﺘُﻜُﻢْ ﻋَﻨْﻪُ ﻓَﺎﺟْﺘَﻨِﺒُﻮﻩُ، ﻭَﻣَﺎ ﺃَﻣَﺮْﺗُﻜُﻢْ ﺑِﻪِ ﻓَﺄْﺗُﻮﺍ ﻣِﻨْﻪُ ﻣَﺎ ﺍﺳْﺘَﻄَﻌْﺘُﻢْ، ﻓَﺈِﻧَّﻤَﺎ ﺃَﻫْﻠَﻚَ ﺍﻟَّﺬِﻳﻦَ ﻣِﻦْ ﻗَﺒْﻠِﻜُﻢْ
ﻛَﺜْﺮَﺓُ ﻣَﺴَﺎﺋِﻠِﻬِﻢْ ﻭَﺍﺧْﺘِﻠَﺎﻓُﻬُﻢْ ﻋَﻠَﻰ ﺃَﻧْﺒِﻴَﺎﺋِﻬِﻢْ ." ﺭَﻭَﺍﻩُ ﺍﻟْﺒُﺨَﺎﺭِﻱُّ ‏[ﺭﻗﻢ 7288: ‏] ، ﻭَﻣُﺴْﻠِﻢٌ ‏[ﺭﻗﻢ :
አቡ ሁረይራ የአላህ መልእክተኛ ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ እንዲህ ሲሉ
ሰምቻቸዋሎህ አለ። “ የከለከልኳቹሁን ሁሉ ተከልከሉ። ካዘዝኳቹህ ውስጥ ደግሞ
የቻላችሁትን ስሩ። ከናንተ በፊት የነበሩትን ህዝቦች ያጠፋቸውኮ ጥያቄ
ማብዛታቸው እና ከነብዮቻቸው መለያየታቸው ነው።” ሓዲሱን ቡኻሪና ሙስሊም
ዘግበውታል።

Читать полностью…

سماحة الإسلام የኢስላም ገራገርነት

ፍቅር በቁርአን
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡
መግቢያ
በቁርአን ከተገለጹት የአላህ ስሞች አንዱ “አል-ወዱድ” ﻭَﺩُﻭﺩٌ ሲሆን ትርጉሙ
“ወዳድ” ወይም “አፍቃሪ”lover” ማለት ነው፦
11:90 ጌታችሁንም ምሕረትን ለምኑት፤ ከዚያም ወደርሱ ተመለሱ፤ ጌታዬ አዛኝ
“ወዳድ” ﻭَﺩُﻭﺩٌ ነውና አላቸው።
85:14 እርሱም ምሕረተ ብዙ “ወዳድ” ﻭَﺩُﻭﺩٌ ነው።
ነጥብ አንድ
“አላህ የሚወደው”
አላህ የሚወደው እነማንን ነው? ስንል አላህ የሚወደው ትክክለኞችን፣
አስተካካዩችን፣ ጥንቁቆችን፣ በራሱ ላይ ተመኪዮችን፣ በትክክል ፈራጆችን፣ በጎ
ሠሪዎችን እና ትዕግሥተኞችን ነው፦
60:8 አላህ ትክክለኞችን ይወዳልና።
49:9 አላህ አስተካካዩችን ይወዳልና።
9:4 አላህ ጥንቁቆችን ይወዳልና።
3:159 አላህ በራሱ ላይ ተመኪዮችን ይወዳል።
5:42 አላህ በትክክል ፈራጆችን ይወዳልና።
5:93 አላህም በጎ ሠሪዎችን ይወዳል።
5:13 አላህ መልካም ሠሪዎችን ይወዳልና።
3:148 አላህም በጐ አድራጊዎችን ይወዳል።
9:108 አላህም ተጥራሪዎችን ይወዳል።
3:146 አላህም ትዕግሥተኞችን ይወዳል።
ነጥብ ሁለት
“አላህ የሚጠላው”
አላህ የሚጠላውስ እነማንን ነው? ስንል አላህ የሚጠላው ኩራተኛን፣ ጉረኛን፣
ከዳተኞችን፣ አበላሺዎችን፣ ወሰን አላፊዎችን እና በዳዮችን ነው፦
57:23 አላህም ኩራተኛን ጉረኛን ሰው አይወድም።
31:18 አላህ ተንበጥራሪን፣ ጉረኛን ሁሉ አይወድምና።
8:58 አላህ ከዳተኞችን አይወድምና።
22:38 አላህ ከዳተኛን፣ ውለታቢስን ሁሉ አይወድም።
5:64 አላህም አበላሺዎችን አይወድም።
5:87 አላህ ወሰን አላፊዎችን አይወድምና።
3:57 አላህም በዳዮችን አይወድም።
አላህ አፍቃሪ ነውና በአማኞች መካከል ፍቅር፣ ሰላም፣ መግባባት እንዲኖር
ይፈልጋል፦
49:9 ከምእምናንም የሆኑ ሁለት ጭፍሮች ቢጋደሉ በመካከላቸው አስታርቁ፤
ከሁለቱ አንደኛይቱም በሌላይቱ ላይ ወሰን ብታልፍ ያችን ወሰን የምታልፈውን ወደ
አላህ ት እዛዝ እስክትመለስ ድረስ ተጋደሉ፤ ብትመለስም በመካከላቸው በትክክል
አስታርቁ፤ በነገሩ ሁሉ አስተካክሉም፤ አላህ አስተካካዩችን ይወዳልና።
49:10ምዕመናኖች ወንድማማቾች ናቸው፤ በሁለት ወንድሞቻችሁም መካከል
አስታርቁ ይታዘንላችሁም ዘንድ አላህን ፍሩ።
49:12 እናንተ ያመናችሁ ሆይ ከጥርጣሬ ብዙውን ራቁ፤ ከጥርጣሬ ከፊሉ
ኃጢአት ነውና፤ ነውርንም አትከታተሉ፤ ከፊላችሁም ከፊሉን አይማ አንደኛችሁ
የወንድሙን ስጋ የሞተ ሆኖ ሊበላው ይወዳልን?መብላቱን ጠላችሁትም፤
ሐሜቱንም ጥሉት ፤ አላህንም ፍሩ፤ አላህ ጸጸትን ተቀባይ አዛኝ ነውና።
አላህ አፍቃሪ ነውና በጎረቤት መካከል ፍቅር፣ ሰላም፣ መግባባት እንዲኖር
ይፈልጋል፦
60:8 “ከእነዚያ በሃይማኖት ካልተጋደሏችሁ ከአገሮቻችሁም ካላወጡዋችሁ
ከሓዲዎች መልካም ብትውሉላቸውና ወደእነርሱ ብታስተካክሉ አላህ
አይከለክላችሁም፡፡ አላህ ትክክለኞችን ይወዳልና፡፡”
60:9 “አላህ የሚከለክላችሁ ከእነዚያ በሃይማኖት ከተጋደሉዋችሁ፣ ከቤቶቻችሁም
ካወጡዋችሁ፣ እናንተም በማውጣት ላይ ከረዱት ከሓዲዎች እንዳትወዳጁዋቸው
ብቻ ነው፡፡ ወዳጅ የሚያደርጓቸውም ሰዎች እነዚያ እነርሱ በዳዮቹ ናቸው፡፡”
ማጠቃለያ
ስለ ፍቅር ቁርአን የሚለውን በግርድፉና በሌጣ ካየን ዘንዳ፣ ይህን ነጥብ
ያነሳሁበት ከክርስቲያኖች ጋር ስንወያይ የመጽሐፍ ቅዱሱ አምላክ አፍቃሪ ነው፤
ነገር ግን አላህ አፍቃሪ አልተባለም ብለው በመሰለኝና በደሳለኝ ለተናገሩበት
ቅጥፈት ከላይ ያለውን መልስ ለመስጠት እና በመቀጠል፦ “”የመጽሐፍ ቅዱሱ
አምላክ ሁሉን ይወዳል የሚጠላው አጢያትን እንጂ አጢያተኞችን አይደለም””
በማለት አንብበው ባላረጋገጡትና መሬት ባረገጡበት ነገር ሲዘላብዱ ነው።
እግዚአብሔር የሚጠላቸው ሰዎች ማስረጃ በቁና ይኸው ሰፍረን ማቅረብ
እንችላለን፦
ሆሴእ 9፥15 ክፋታቸው ሁሉ በጌልገላ አለ፤ በዚያ # ጠልቻቸዋለሁ #፤ ስለ ሠሩት
ክፋት ከቤቴ አሳድዳቸዋለሁ፤ ከእንግዲህ ወዲያ #አልወድዳቸውም #፤
አለቆቻቸው ሁሉ ዓመፀኞች ናቸው።
መዝሙር 11፥5 እግዚአብሔር ጻድቅንና ኅጥእን ይመረምራል ዓመፃን የወደዳት
ግን ነፍሱን # ጠልቶአል#።
ሚልክያስ 1፥2 ወድጃችኋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር እናንተ ግን፦ በምን
ወደድኸን? ብላችኋል። ዔሳው የያዕቆብ ወንድም አልነበረምን? ይላል
እግዚአብሔር ያዕቆብንም ወደድሁ፥ ዔሳውንም #ጠላሁ#
ሮሜ 9፥13 ያዕቆብን ወደድሁ ኤሳውን ግን #ጠላሁ # ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው።
ዘዳግም 18፥11-12 አስማተኛም፥ መተተኛም፥ በድግምት የሚጠነቍልም፥
መናፍስትንም የሚጠራ፥ ጠንቋይም፥ ሙታን ሳቢም በአንተ ዘንድ አይገኝ።
# ይህንም የሚያደርግ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት # የተጠላ # ነው ስለዚህም
ርኵሰት አምላክህ እግዚአብሔር ከፊትህ ያሳድዳቸዋል።
ሳያውቁ መናገር ኃላ ለማፈር ይባል የለ እንዴ ምን መጥላት ብቻ ጥላቻው
አንገሽግሾት ይጸየፍ የለም እንዴ? እስቲ እንመልከት፦
ምሳሌ 6፥16-19 እግዚአብሔር #የሚጠላቸው # ስድስት ነገሮች ናቸው፥
# ሰባትንም# ነፍሱ አጥብቃ #ትጸየፈዋለች #
1.ትዕቢተኛ ዓይን፥
2.ሐሰተኛ ምላስ፥
3.ንጹሕን ደም የምታፈስስ እጅ፥
3.ክፉ አሳብን የሚያበቅል ልብ፥
5.ወደ ክፉ የምትሮጥ እግር፥
6.በሐሰት የሚናገር ሐሰተኛ ምስክር
7.በወንድማማች መካከልም # ጠብን የሚዘራ#።
ዘሌዋውያን 20፥23 ከፊታችሁ በምጥላቸውም ሕዝብ ወግ አትሂዱ ይህን ሁሉ
አድርገዋልና # ተጸየፍኋቸው#።
ዘሌዋውያን 26.30 የኮረብታ መስገጃዎቻችሁንም አፈርሳለሁ፥ የፀሐይ
ምስሎቻችሁንም አጠፋለሁ፥
ሬሳችሁንም በጣዖቶቻችሁ ሬሳዎች ላይ እጥላለሁ ነፍሴም # ትጸየፋችኋለች#።
ከወንድም ወሒድ ዑመር
ወሰላሙ አለይኩም

Читать полностью…

سماحة الإسلام የኢስላም ገራገርነት

© የፍጥረታት የበላይ የሆኑትን ነብይህን ﷺ
መተናነስ ተመልከትልኝ ከርሳቸው ምን ያህል ትምህርት ትወስድ ይሆን?
…………………………………
<< ባሪያ እንደሚበላው እበላለው ባሪያ እንደሚቀመጠው እቀመጣለው>> ይሉሃል
…………………………
© ባሪያ ለምግብ ሲቀመጥ ካየኸው አጎንብሶ
አለቃው ከመችመች ጠራኝ በሚል ተቻኩሎ
ጥቂት ጥቂት ነው የሚመገበው
…………………………
© ያንተ መሪ ነብይም ﷺ ተመቻችተው ወይም
ተደግፈው አይበሉም
ሆዳቸው እስኪሞላም አይመገቡም
ይልቅ እንደ ባሪያው እራሳቸውን ዝቅ አድርገው የታቻኮለ አቀማመጥ በሚመስል
መልኩ ተቀምጠው
ሆዳቸውን ለአየር ለምግብ ለውሃ ከፍለው ይመገባሉ
[ እናቴም አባቴም መስዋዕት ይሁንልዎ]
………………………………
© አንተም ነብዩን ﷺ መልካም ሞዴል እንድታደርግ ታዘሃል
ያን ከፈፀምክ በዱንያም ሆነ በአኼራ ፈላህ ትወጣለህ

Читать полностью…

سماحة الإسلام የኢስላም ገራገርነት

# ኢብን_ጀብሪን እንዲህ ይላሉ።?
1፦"አይን-ናስ ያለበት.. የማን አይን እንዳገኘው እና መፍትሄውን ያጣ ሰው
2፦"ሀሰድ ያገኘው ሰው እና ሀሰዱም ያለተወገደለት ሰው
3፦"ድግምት ያለበት ሰው እና ድግምቱም ያለተወገደለት ሰው... ለ3 ቀናት
ማድረግ ያለበትን 7 ተግባራት እንደሚከተሉት ይሆናሉ።
በአንድ እቃ ውሀ ያዘጋጅ'ና ባዘጋጀው እቃ ላይ
1፦ሱረቱል ፋቲሀ 7/ግዜ
2፦አየተል ኩርሲይ 7/ግዜ
3፦ሱረቱል በቀራ ከመጀምሪያው 5 አያቶችን 7/ግዜ
4፦ሱረቱል ካፊሩን 7/ግዜ
5፦ሱረቱል ኢክላስ 7/ግዜ
6፦ሱሩቱል ፈለቅ 7/ግዜ
7፦ሱረቱ ናስ 7/ ግዜ
እነዚህን የተዘረዘሩትን አያቶች ከቀራ በኋላ ውሀውን በመጠጣት በተረፈው ውሀ
መላ ሰውነቱን ይታጠብበት።
እነዚህን ተግባራት በቀን ሶስት ግዜ ጠዋት፣ቀን፣ማታ በተከታታይ ለሶስት ቀናት
ይተግብራቸው።
በያንዳንዱ የትጥበት ሰዐት ከላይ ያሉት ቂራአቶች በውሀው ላይ እንደ አዲስ
ይቀራሉ።
አይን ናስ/የሰው ዐይን ድግምት እና... ሀሰድ ያለበት ሰው በየቂን ከተገበራቸው
ያለጥርጥር በአላህ ፍቃድ ይወገድለታል። ኢንሻ አላህ...
ማሳሰቢያ፦ እነዚህን ተግባራት በቀን ሶስት ግዜ ስትተገብሩ በያንዳንዱ የትጥበት
ሰአት ሌላ ውሀ እና እንደ አዲስ ትቀራላችሁ እንጂ አንዴ በቀራችሁት
አትደጋግሙት።
እንብበህ ስትጨርስ ለሌላው ማስተላለፍህን አትዘንጋ አንተ ሼር ባደረግከው
ስንት የተጨነቀች ነፍስ እረፍት እንደምታገኝ አታውቅም'ና።
እኔንም ከመልካም ዱዓዎቻችሁ አትርሱኝ ያ ጀማዓ...

Читать полностью…

سماحة الإسلام የኢስላም ገራገርነት

# ነብዩሏህ_ሙሳ_ዐለይሂ_ሰላም_ታሪክ
ክፍል1
ግዜው ዩሱፍ ዐ ሰ ከሞተ 97 አመታትን አስቆጥሯል።በዩሱፍ አማካኝነት የግብፅን
ምድር ገብተው በመንፊስ ከተማ መኖር የጀመሩት የያዕቁብ ልጆች ሁሉ ሞተው
አልቀው የልጅ ልጆቹ ግን በመተካካት ግብፅን እጅጉን እየሞሏት ነው።
ምንም እንኳን ያኔ በዩሱፍ (ዐ ሰ) ዘመን እነዚህ በኒ ኢስራኢሎች (የያዕቁብ
ልጆች) በግብፅ ምድር የተከበሩ ሰዎች ቢሆኑም አሁን ላይ ያለው ንጉስ ግን
እጅጉን ይበድላቸው ጀምሯል።
ይሄን ግዜ ነበር እንግዲ አላህ በኒ ኢስራኢሎችን ነፃ እንዲያወጣ ሙሳን የላከው።
የሙሳ የዘር ሀረግ፦
ሙሳ ኢብን...ዒምራን ኢብን...የስሀር ኢብን...ቃሂስ ኢብን...ላዊ ኢብን...ያዕቁብ
ኢብን...ኢስሀቅ ኢብን...ኢብራሂም ኢብን....አዛር......ምናምን እያለ ይቀጥላል።
ሙሳ ከመወለዱ በፊት ፊርዐውን አንድ ቀን በህልሙ የሆነች እሳት ከእየሩሳሌም
ወደ ግብፅ መጥታ የግብፃውያንን ቤት እየዞረች ታቃጥል'ና የበኒ ኢስራኢሎችን
ቤት ስትተው ተመለከተ።
እና ይህ ህልም እረፍት የነሳው ንጉስ በነጋታው ጠንቋዮችን እና ኮከብ
ቆጣሪዎችን ሰብስቦ የህልሙን ፍች ሲጠይቃቸው፦"ከነዚህ የያዕቁብ ልጆች(ከበኒ
ኢስራኢሎች) አንድ ንግስናህን የሚሽር ልጅ ሊወለድ ነው" አሉት።
ፊርዐውን ይህን ሲሰማ በጣም በመደንገጥ የበኒ ኢስራኢል ወንድ ልጆችን እንዳለ
እንዲገደሉ አዘዘ...ምንም አይነት ወንድ ልጅም ቢረገዝ እንደሚገድልም ትዕዛዝ
አስተላለፈ።
የፊርዐውን ትዕዛዝ መተግበር ተጀመረ...በጣም ለቁጥር የሚያዳግቱ የበኒ
ኢስራኢል ወንድ ልጆች እንደ ገፍ ተገደሉ። በመጨረሻም ይህ ህግ ማሻሻያ
መደረግ እንዳለበት የግብፅ ህዝብ አቤቱታ ሲያቀርብ ፊርዐውንም ዘወትር
የሚተገበረውን የግድያ ተግባር አንድ አመት ግድያ እንዲቆም እና አንድ አመት
እንዲገደል አደረገ.....
በዚህ ሁኔታ ነበር የማይገደልበት አመት ላይ ሀሩን የተባለው የሙሳ ወንድም
ተወልዶ፤ በሚገደልበት አመት ደሞ ሙሳ የተወለደው።
ሙሳ ልክ እንደተወለደ የሙሳ እናት ህፃኗን አይኗ እያየ እንዳይገድሉባት በጣም
ተጨነከች።ምታደርገው ጠፍቷት በመዋለል ላይ ሳለች አላህም እናትየውን
ከእንጨት የሆነ ሳጥን ሰርታ፤በዚያ ሳጥን ውስጥ ህፃኑን እንድታስገባው'ና
ሳጥኑንም ከነ ህፃኑ ወንዝ ላይ እንድትጥለው አዟት፤ ይህንንም ህፃን ነቢይ አድርጎ
እንደሚመልስላት ቃል ገባላት።
በዚህ መሰረት የሙሳ እናት ህፃን ልጇን በጨርቅ ጠቅልላ በሳጥን አሽጋ ሆዷ
እየባባ በናይል ወንዝ አሻግራ ሸኘችው።
ውሀውም ሳጥኑን ከነ ህፃኑ እያንሳፈፈ የልጆችን ግድያ ትዕዛዝ ወደሰጠው ፊርዐን
ግቢ ይዞት ገባ።በሰዐቱ የፊርዐውን የሚስቱ አገልጋዮች እዚያ ወንዝ ዳር እየታጠቡ
ነበር'ና ይህን ሳጥን ሲመለከቱ በውስጡ ወርቅ ያለ መስሏቸው ለእመቤታቸው
ሳጥኑን ሳይከፍቱ በስጦታ መልክ ወስደው አስረከቧት።
የሙሳ እህት እዚያ ቤተ መንግስት ውስጥ ተቀጥራ ትሰራ ነበር'ና እናቷ
የጣለችው ሳጥን በገዳዮች እጅ መግባቱን ስታረጋግጥ ወደ እናቷ ስትከንፍ ሄዳ
ነገረቻት።እናትም ልጇን ተመልሳ ሄዳ ሁኔታውን እንድታጣራላት ላከቻት። ልጅቷም
ሁኔታውን ለማጣራት ቤተመንግስት ተመልሳ መጣች።
ንግስቲቱም አገልጋዮቿ እና ባለቤቷ ባሉበት ቦታ ሳጥኑ እንዲከፈት አዘዘች፤ሳጥኑ
ሲከፈትም ልብን የሚያማልል ውብ እና ማራኪ ልጅ በሳጥኑ አገኙ።የፊርዐውን
ሚስት ልጅ መውለድ አትችልም ነበር'ና፦"ልጅ ስለሌለን እባክህ ይሄን ህፃን
አትግደለው።ወደ ፊትም ልጃችን አድርገን እንይዘዋለን " አለችው።
እሱ ህፃኑን መግደል ቢፈልግም የሚስቱን ሀሳብ መቃረን አልፈለገም'ና በሀሳቧ
ተስማማ።
አሁን አስቸጋሪው ነገር መጣ....ይህን ምግብ ያልጀመረ ህፃን ማን
ያጥባው??????
የተለያዩ አጥቢ እናቶች ይህን ህፃን ሊያጠቡ ቢሞክሩም ህፃኑ ግን የማንንም ጡት
ከአፉ ሊያስጠጋ ፍቃደኛ አልሆነም።ይልቁኑ አጥቢዎቹ ሲመጡ ይባስ ያለቅስ ነበር።
የፊርዐውንም ሚስት እጅጉን ተጨነቀች አላህ በልቧ የሙሳን ፍቅር ስለከተበባትም
በህፃኑ ለቅሶ ጭንቀት ምትገባበት ጠፋት።
ይሁ ሁሉ ሲሆን ሁኔታዎችን ትከታተል የነበረችው የሙሳ እህት ምንም
እንደማያውቅ ሆና፦"ይህን ህፃን ለናንተ የሚያሳድግላችሁን ቤተሰብ
ለመላክታችሁ!! ታማኝም ናቸው" አለቻት።
የህን ስትሰማ የፊርዐውን ሚስት ደስታዋ ወደር አጣ።የፈለጉትን ክፍያም
ለአጥቢዋ እንደሚከፍሉም ቃሉ ገቡላት'ና የሙሳ ትክክለኛዋ እናት እንድትመጣ
አደረጉ።
የሙሳ እናት ቤተ መንግስት ገብታ ልክ ልጇን ስትመለከት ልቧ
ተንሰፈሰፈ...፣እንባዋ ከአይኗ ሊሾልክ ተቃረበ።እንደምንም ራሷን ተቋቁማ ህፃኑን
ልታጠባ ስታቅፈው ህፃኑ ለቅሶውን ትቶ ጡቷን ይሞጥሙጥ ጀመር።ፊርዐውን እና
ኣሲያ(የፊርዐውን ሚስት) ይህን ሲመለከቱ በጣም ተደሰቱ።
በዚህ ሁኔታ የሙሳ እናት እየተከፈላት ልጇን ለ2 አመታት ያህል አጠባችው።
ግዜ ግዜን እየተካ ሙሳም ትልቅ ልጅ ሆነ።ምንም እንኳን ሙሳ የፊርዐውን ያብራኩ
ክፋይ ባይሆንም በህዝቡ ዘንድ ግን የፊርዐውን ልጅ በመባል ነው ሚታወቀው።
ከእለታት አንድ ቀን ሙሳ በጠራራ ፀሀይ ከተማ ውስጥ እየተራመደ ሳለ አንድ
ግብፃዊ እና አንድ በኒ ኢስራኢላዊ ሲደባደቡ ተመለከተ። በኒ ኢስራኢላዊውም
ሙሳን አድነኝ በማለት ተጣራ።
ሙሳም ይህን ግዜ ግብፃዊው ላይ ገራሚ ቦክስ ሰነዘረበት'ና ሳያስበው
የግብፃዊው ህይወት በሙሳ እጅ አለፈች።ይሁን እንጂ ማንም አላወቀበትም
ነበር።
ይሄን ግዜ ሙሳ በጣም በመፀፀት አላህን ምህረት ለመነው። አላህም ተውበቱን
ተቀብሎት፦"ሙሳ ሆይ! በልቅናዬ እምላለሁ ይህች የገደልካት ነፍስ ለቅፅበት
እንኳን በኔ ጌትነት ያመነች ብትሆን ከባድ ቅጣትን አቀምስህ ነበር" አለው።
ሙሳም ከዚያ ቀን አንስቶ የግብፃዊው ሟች ወገን መጥተው እንዳይበቀሉት
በጣም ስለሰጋ እንቅስቃሴውን በጥንቃቄ ማድረግ ጀመረ።
በማግስቱም ሙሳ ከተማ ላይ ሳለ ይህ ትናንት ሲደባደብ የነበረው (በኒ
ኢስራኢላዊው) የሙሳ ዘመድ ዛሬም ከሌላ ግብፃዊ ጋር ሲደባደብ ተመለከተው።
የሙሳ ዘመድ ሙሳን ሲመለከት ዛሬም የእርዳታ ጥሪውን ለሙሳ አሰማ።
ሙሳም ወገኑን(በኒ ኢስራኢሉን) ሲመለከት፦"አንተ በእርግጥ ግልጽ ጠማማ ነህ"
አለው።
ወገኑም፦"በትናንትናው ቀን ነፍስን እንደ ገደልክ ልትገድለኝ ትፈልጋለህን በምድር
ለይ ጨካኝ መሆንን እንጅ ሌላ አትፈልግም፡፡ ከመልካም ሠሪዎችም መሆንን
አትፈልግም" አለው።
በዚያ አካባቢ የነበሩ የግብፅ ነዋሪያንም ወገናቸውን የገደለው ሙሳ መሆኑን
ሲያውቁ እሱን ሊገድሉት መመካከር ጀመሩ።
ይህን የሰማ ሂዝቂል የተባለ ግብፃዊ ሙእሚን ለሙሳ፦"ግብፃውያን አንተን
ሊገድሉ እየተመካከሩ ስለሆነ የግብፅን ምድር ለቅቀህ እንድትወጣ እመክርሀለሁ"
ብሎ መከረው።
# ይቀጥላል ..............

Читать полностью…

سماحة الإسلام የኢስላም ገራገርነት

አብዛኛው ሰው እኔ ደሃ ነኝ ሲል ይሰማል ለመደሰትም ገንዘብ እስኪያገኝ
ይጠብቃል!! አይገርምም ሀብታም ገንዘብ ሲፈልግ በጣም ያስቃል። ሁላችንም
ሃብታም መሆናችንን ብነግራችሁስ ምን ትላላችሁ?
ለምሳሌ፡- አሁን ይህንን ፅሁፍ እያነበባችሁ ነው!! ይህንን ፅሁፍ የምታነቡበትን
አይን አንድ ሃብታም በ10 ሚሊየን ብር ሽጡልኝ ቢላችሁ ትሸጡለታላችሁ??
በእርግጠኝነት አታደርጉትም ምክንያቱም አያዋጣማ ከ10 ሚሊየን ብሩ ይልቅ
አይናችን ይጠቅመናልና።
አያችሁ አሁን በ10 ሚሊየን ብር እንኳን የማይተመን ውድ ሃብት አለን ማለት
ነው፡፡ ችግሩ ይህንን ሃብት መጠቀም አለመጠቀማችን ነው ስለዚህ እነዚህን
ሃብቶች ስንጠቀም ሀብታም ነን ማለት ነው አልሀምዱሊላህ። ደሃ ነኝ ብለህ
አትዘን "ገንዘብና እንቅልፍ በራሳቸው ጊዜ ይመጣሉ" ካንተ የሚጠበቀው መስራት
ብቻ! ስለዚህ ገንዘብ ማጣት ደስታህን አያጠፋውም ምክንያቱም አንተ ሃብታም
ስለሆንክ ደስተኛ ሆነህ ኑር

Читать полностью…

سماحة الإسلام የኢስላም ገራገርነት

«# በላጭ_የሆነ_ኒካህ ማለት መህሩ በጣም ቀላል የሆነበት ነው»።
˙·٠ •● ነቢዩ ﷺ ስለአሏሁ አለይሂ ወሰለም ●•٠ ·˙
ምንጭ:- ኢብኑ ሒባን (4163)

Читать полностью…

سماحة الإسلام የኢስላም ገራገርነት

አብሽር * ﺃﺑﺸﺮ ★
* አብሽሩ በቸሩ ፣ በአዛኙ ጌታችን አላህ ከፍ ያለ ተስፋ ይኑረን : አብሽር ችግር
በድሎት ይቀየራል ፣ በሽታ በጤና ይቀየራል ፣ ጦርነት በወዳጅነት ይለወጣል ፣
አብሽር ረብሻና ግርግር በሰላምና በመረጋጋት ይተካል። ፣ አብሽር ! አማኝ መቼም
ቢሆን በአላህ ላይ ተስፋ አይቆርጥም
★ ከፍ ያለው አላህ እንዲህ ይላል ፣ (( «ከጠማማዎችም በስተቀር ከጌታው
እዝነት ተስፋን የሚቆርጥ ማነው» ፡፡))
ﻗﺎﻝ ﺍﻟﻠﻪ ﺗﻌﺎﻟﻰ : } ﻗَﺎﻝَ ﻭَﻣَﻦ ﻳَﻘْﻨَﻂُ ﻣِﻦ ﺭَّﺣْﻤَﺔِ ﺭَﺑِّﻪِ ﺇِﻟَّﺎ ﺍﻟﻀَّﺎﻟُّﻮﻥَ } (ሱረቱ አል-ሒጅር - 56)
* አብሽር ሁሉም ለበጎ ነው
ﻗﺎﻝ ﺍﻟﻠﻪ ﺗﻌﺎﻟﻰ : } ﺇِﻥَّ ﻣَﻊَ ﺍﻟْﻌُﺴْﺮِ ﻳُﺴْﺮًﺍ }
አዛኙ አላህ እንዲህ ይላል: ((ከችግር ጋር በእርግጥ ምቾት አልለ፡፡))
(ሱረቱ አል - ኢሻራሕ - 6)
* ውዱ ነብያችንም ሷለላሁ አለይሂ ወሰለም አቢ ሁረይራ ባስተላለፉት ሀዲስ
እንዲህ ይላሉ ፤ ( አላህ ፍጥረታትን ፈጥሮ እንዳጠናቀቀ ከአርሹ በላይ እሱ ዘንድ
እንዲህ ብሎ ጽፎዋል " እዝነቴ ቁጣዪን ቀድማለች " )) ቡኻሪ ዘግበውታል
ﻋَﻦْ ﺃَﺑِﻲ ﻫُﺮَﻳْﺮَﺓَ ، ﻋَﻦِ ﺍﻟﻨَّﺒِﻲِّ ﺻَﻠَّﻰ ﺍﻟﻠَّﻪُ ﻋَﻠَﻴْﻪِ ﻭَﺳَﻠَّﻢَ ﻗَﺎﻝَ : " ﺇِﻥَّ ﺍﻟﻠَّﻪَ ﻟَﻤَّﺎ ﻗَﻀَﻰ ﺍﻟْﺨَﻠْﻖَ ﻛَﺘَﺐَ ﻋِﻨْﺪَﻩُ
ﻓَﻮْﻕَ ﻋَﺮْﺷِﻪِ : ﺇِﻥَّ ﺭَﺣْﻤَﺘِﻲ ﺳَﺒَﻘَﺖْ ﻏَﻀَﺒِﻲ ((." ﺭﻭﺍﻩ ﺍﻟﺒﺨﺎﺭﻱ
*አብሽሩ ነገን በመልካም ተስፋ አስቡ አትጨናነቁ
*አብሽሩ በገጠማችሁ እንቅፋት አትደናገጡ
*አብሽሩ የጨላለመው የተሻለ ነገር ሊመጣ ነው ።
*አብሽሩ አላህን የያዘ አይወድቅም ከወደቀም ይነሳል ።
*** ስለዚህ :—
★አብሽር ! አብሽር ! አብሽር !

Читать полностью…

سماحة الإسلام የኢስላም ገራገርነት

እውነተኛ ፍቅር ""
ነብዩ ሙሐመድ ( ﷺ ) ሰውባን (ረ.ዐ) የተባለ ባልደረባቸውን «ገጽታህን የቀየረው
ምንድን ነው ??» በማለት በጠየቁት ጊዜ «በሽታም ሆነ የስቃይ ስሜት አጋጥሞኝ
ሳይሆን እርሰዎን ባላየሁ ጊዜ እስከማገኝዎት ድረስ ውስጤ በጥልቅ ሀዘን
ስለሚናጥ ነው» በማለት መለሰላቸው።
የሰውባን ፊት የገረጣው በነብዩ ሙሐመድ ( ﷺ ) ጥልቅ ፍቅር ሲሆን የኛ ደግሞ
በወርሃ ታኀሳስ ብርድ ነው
አላህ ሆይ !
ከዘመናት ጥግ ላይ ሆነው በአካል ሳይመለከቱን በናፍቆት ለተንሰፈሰፉልን ድንቅ
ስብዕና ልቦቻችን ይማረኩ ዘንድ የታሸጉባቸውን ቁልፎች ከፍተህ በርሳቸው ናፍቆት
ሙላልን

Читать полностью…

سماحة الإسلام የኢስላም ገራገርነት

ሱብሃነላህ
➊. ጂንን የሚፈራው ቀበሮ ሳይሆን፤ ጂኒ ቀበሮን እንደሚፈራ ያውቃሉ?!!
➋. ግመል የበደለውን እንደማይረሳ ያውቃሉ?!!
➌. ንስር አሞራ በህመም ምክንያት እራሱን በማጥፋት እንጂ በኖርማል ሁኔታ
እንደማይሞት ያውቃሉ?!!
➍. ቀጭኔ በቀን ሶስት ግዜ፤ በጥቅሉ ለ9 ደቂቃዎች ያህል ብቻ እንደሚተኛ
ያውቃሉ?!!
➎. ዝሆን ሀዘን ሲሰማው እንደሚያለቅስ ያውቃሉ?!!
➏. አንበሳ የአወራ ዶሮ ጩኸት እንደሚፈራ ያውቃሉ?!!
➐. ጉንዳን ስታስነጥስ እራሷን እንደምትስት ያውቃሉ?!!
በመጨረሻም ኀያሉ ጌታችን አላህ (ሱ.ወ) ጥራት ይገባው ማለት ይገባናል።
# ሱብሃነላህ
١٠

Читать полностью…

سماحة الإسلام የኢስላም ገራገርነት

ዓሹራ
ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ
- ዓሹራን እንዴት እናሳልፈው
- ነቢያችን ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም
ዓሹራን እንዴት ያሳልፉት ነበር
* ውድ ወንድሞች እና እህቶች የአሹራን ቀን አስመልክቶ ብዙ ግራ ሚያጋቡ
መሰረተቢስ የሆኑ ነገራቶች በብዛት እየተሰራጩ እውነታዎችንና ሱናዎችን እያስረሱ
ስለሆነ ሀቁን አውቆ ለመተግበርና ስህተቱን አውቆ ለመጠንቅ ይህን ፁሁፍ
ያንብቡ ።
* ዓሹራን አስመልክቶ ከነብያችን ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም እና ሰሃቦቻቸው
(ረዲየላሁ አንሁም) የተላለፉ መልእክቶች ፡-
1- ﻋﻦ ﻋﺎﺋﺸﺔَ ﺭﺿﻲَ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻨﻬﺎ ﻗﺎﻟﺖْ :ﻛﺎﻥَ ﻳﻮﻡ ﻋﺎﺷﻮﺭﺍﺀَ ﺗَﺼﻮﻣُﻪُ ﻗُﺮَﻳْﺶٌ ﻓﻲ ﺍﻟﺠﺎﻫِﻠَﻴَّﺔِ، ﻭﻛﺎﻥَ
ﺭﺳﻮﻝُ ﺍﻟﻠﻪ - ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ - ﻳﺼﻮﻣُﻪُ، ﻓَﻠﻤﺎ ﻗَﺪﻡَ ﺍﻟﻤﺪﻳﻨَﺔَ ﺻَﺎﻣَﻪُ، ﻭﺃَﻣَﺮَ ﺑِﺼﻴﺎﻣِﻪِ ﻓَﻠﻤﺎ -
ﻓُﺮِﺽَ ﺭﻣﻀﺎﻥُ؛ ﺗَﺮﻙَ ﻳﻮﻡَ ﻋﺎﺷُﻮﺭﺍﺀَ، ﻓَﻤﻦ ﺷﺎﺀَ ﺻﺎﻣَﻪُ، ﻭﻣﻦ ﺷﺎﺀ ﺗَﺮﻛَﻪُ . ‏( ﺍﻟﺒﺨﺎﺭﻱ )
* እናታችን አኢሻ ረዲየላሁ አንሃ እንዳወሩትና ቡካሪ እንደዘገቡት በጃሂሊያው
ዘመን (ነብይነት ሳይመጣ) የአሹራን ዕለት ቁረይሾች ይጾሙት ነበር የአላህም
መልእክተኛ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ይጾሙት ነበር ወደ መዲና አገር ሲመጡም
ጹመውት ሰውም እንዲጾመው አዘዙ የረመዷን ወር መጾም ግዴታ ሲሆን አሹራ
ተትቶ (በግዴታነት) ( በሱናነት) የፈለገ ጾመው ያልፈለገ ተዋው (አል-ቡካሪ)
2- ﻋﻦ ﺍﺑﻦِ ﻋﺒﺎﺱٍ، ﻗﺎﻝ : ﻟﻤﺎ ﻗَﺪِﻡَ ﺍﻟﻨﺒﻲ - ﺻﻠَّﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ - ﺍﻟﻤﺪﻳﻨﺔَ ﻭﺟﺪ ﺍﻟﻴﻬﻮﺩَ ﻳﺼﻮﻣﻮﻥ
ﻋﺎﺷُﻮﺭﺍﺀ، ﻓﺴُﺌِﻠﻮﺍ ﻋﻦ ﺫﻟﻚ، ﻓﻘﺎﻟﻮﺍ : ﻫﻮ ﺍﻟﻴﻮﻡُ ﺍﻟﺬﻱ ﺃﻇﻬﺮ ﺍﻟﻠﻪ ﻓﻴﻪِ ﻣﻮﺳﻰ ﻋﻠﻰ ﻓِﺮﻋﻮﻥَ، ﻭﻧﺤﻦُ
ﻧﺼﻮﻣُﻪ ﺗﻌﻈﻴﻤﺎً ﻟﻪ، ﻓﻘﺎﻝ ﺭﺳﻮﻝُ ﺍﻟﻠﻪ - ﺻﻠَّﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ :- " ﻧﺤﻦُ ﺃﻭﻟﻰ ﺑﻤﻮﺳﻰ ﻣِﻨْﻜُﻢ "
ﻭﺃﻣﺮ ﺑﺼﻴﺎﻣﻪ ‏( ﺍﻟﺒﺨﺎﺭﻱ ).
* አብደላህ ብን አባስ ረዲየላሁ አንሁማ እንዳወሩትና ቡካሪ እንደዘገቡት ነቢያችን
ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም መዲና አገር እንደመጡ የሁዳዎች አሹራን ሲጾሙ
አይተዋቸው ሲጠየቁ አላህ በፈርኦን ላይ ለሙሳ ድል የሰጠበት ዕለት ስለሆነ
እሱን ለማክበድ ብለን ነው ብለው መለሱ በዚህ ግዜ የአላህ መልዕክተኛ ሰለላሁ
አለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ (( ከናንተ ይልቅ ለሙሳ እኛ ቅርብና በላጭ ነን
ብለው ሰው እንዲጾመው አዘዙ)) (አል- ቡካሪ)
3- ﻋﻦ ﻋﺒﺪَ ﺍﻟﻠﻪ ﺑﻦَ ﻋﺒﺎﺱٍ ﺭﺿﻲ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻨﻬﻤﺎ ﻗﺎﻝ : ﺣﻴﻦ ﺻﺎﻡ ﺍﻟﻨﺒﻲ - ﺻﻠَّﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ -
ﻳﻮﻡَ ﻋﺎﺷﻮﺭﺍﺀ ﻭﺃﻣﺮﻧﺎ ﺑِﺼﻴﺎﻣِﻪ، ﻗﺎﻟﻮﺍ : ﻳﺎ ﺭﺳﻮﻝَ ﺍﻟﻠﻪِ، ﺇﻧﻪ ﻳﻮﻡٌ ﺗُﻌﻈِّﻤﻪ ﺍﻟﻴﻬﻮﺩُ ﻭﺍﻟﻨﺼﺎﺭﻯ، ﻓﻘﺎﻝ
ﺭﺳﻮﻝُ ﺍﻟﻠﻪ - ﺻﻠَّﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ :- " ﻓﺈﺫﺍ ﻛﺎﻥ ﺍﻟﻌﺎﻡُ ﺍﻟﻤﻘﺒﻞُ ﺻُﻤْﻨﺎ ﻳﻮﻡَ ﺍﻟﺘَّﺎﺳِﻊِ " ﻓﻠﻢ ﻳﺄﺕِ
ﺍﻟﻌﺎﻡُ ﺍﻟﻤُﻘْﺒِﻞُ ﺣﺘﻰ ﺗﻮﻓﻲ ﺭﺳﻮﻝُ ﺍﻟﻠﻪِ - ﺻﻠَّﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ - ‏( ﻣﺘﻔﻖ ﻋﻠﻴﻪ ).
* አብደላህ ብን አባስ ረዲየላሁ አንሁማ እንዲህ ይላሉ ነቢያችን ሰለላሁ አለይሂ
ወሰለም አሹራን ጹመው እኛም እንድንጾመው ሲያዙን እንዲህ ተባሉ ፤ የአላህ
መልዕክተኛ ሆይ ይህ ዕለት የሁዳዎችና ነሳራዎች የሚያከብሩት እለት ነውእኮ
የዚህን ግዜ የአላህ መልዕክተኛ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ
(( የሚቀጥለው አመት ሲመጣ ዘጠነኛውን ቀን እንጾማለን )) የሚቀጥለው አመት
ሳይመጣም የአላህ መልዕክተኛ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም አረፉ ፡፡ (ሙተፈቁን
አለይሂ )
4- ﻋﻦِ ﺍﺑﻦِ ﻋﺒَّﺎﺱٍ ﺭﺿﻲَ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻨﻬﻤﺎ ﻗﺎﻝَ : ﻣﺎ ﺭﺃَﻳْﺖُ ﺍﻟﻨﺒﻲَّ - ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ - ﻳَﺘَﺤَﺮَّﻯ
ﺻِﻴﺎﻡَ ﻳَﻮﻡٍ ﻓَﻀَّﻠﻪُ ﻋﻠﻰ ﻏَﻴﺮﻩِ ﺇﻻ ﻫﺬﺍ ﺍﻟﻴﻮﻡَ، ﻳﻮﻡَ ﻋﺎﺷﻮﺭﺍﺀَ، ﻭﻫﺬﺍ ﺍﻟﺸﻬﺮَ . ﻳَﻌﻨﻲ ﺷﻬﺮَ ﺭﻣﻀﺎﻥَ .
‏( ﺍﻟﺒﺨﺎﺭﻱ ).
* አብደላህ ብን አባስ ረዲየላሁ አንሁማ እንዲህ ይላሉ የአላህ መልዕክተኛ
ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ከቀናት ሁሉ አስበልጠው ትኩረት ሰጥተውት እንደ አሹራ
ቀን የጾሙት ቀን አላውቅም እንዲሁም ይህን ወር (ረመዷን)፡፡
5- ﻋَﻦْ ﺃَﺑِﻲ ﻗَﺘَﺎﺩَﺓَ، ﺃَﻥَّ ﺭَﺳُﻮﻝَ ﺍﻟﻠﻪِ ﺻَﻠَّﻰ ﺍﻟﻠﻪُ ﻋَﻠَﻴْﻪِ ﻭَﺳَﻠَّﻢَ ﺳُﺌِﻞَ ﻋَﻦْ ﺻَﻮْﻡِ ﻳَﻮْﻡِ ﻋَﺮَﻓَﺔَ . ﻓَﻘَﺎﻝَ : "
ﻛَﻔَّﺎﺭَﺓُ ﺳَﻨَﺘَﻴْﻦِ ." ﻭَﺳُﺌِﻞَ ﻋَﻦْ ﺻَﻮْﻡِ ﻳَﻮْﻡِ ﻋَﺎﺷُﻮﺭَﺍﺀَ . ﻓَﻘَﺎﻝَ : " ﻛَﻔَّﺎﺭَﺓُ ﺳَﻨَﺔٍ " ‏( ﺃﺣﻤﺪ )
* አቢ ቀታዳህ ረዲየላሁ አንሁ እንዳወሩትና ኢማሙ አህመድ አንደዘገቡት የአላህ
መልዕክተኛ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ስለ አረፋ ዕለት ጾም ተጠይቀው የሁለት
አመት ወንጀል ያስምራል ) ስለ አሹራ ዕለትም ተጠይቀው የአመት ወንጀል
ያስምራል ) ብለዋል ፡፡
* የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም እና ሰሃቦቻቸው (ረዲየላሁ
አንሁም) እንዲሁም በምርጦቹ ክፍለ ዘመናት የነበሩ ታላላቅ የዲን መሪዎች እንደ
አቡ ሀኒፋ ፤ ኢማሙ ማሊክ ፤ ኢማሙ አሻፊኢይ ፤ ኢማሙ አህመድ ፤ ኢማሙ
አል ቡካሪ ፤ ኢማሙ ሙስሊም እና ሌሎችም (ረሂመሁሙላሁ ረህመተን
ዋሲዐህ ) የዓሹራን ቀን ያሳልፉ የነበረው በዚህ መልክ ነበር እሱም ዘጠነኛውንና
አስረኛውን ቀን ወይም አስረኛውንና አስራ አንደኛውን ቀን ወይም 9ኛ 10ኛ 11ኛ
ቀናት በመጾም ብቻ ነበር ፡፡
* በእነዚህ ቀናት ውስጥ ለየት ያሉ ከዚህ ውጭ የሚደረጉ ማንኛውም የኢባዳ
አይነቶች ወደ አላህ ሳይሆን የሚያቃርቡት ወደ ሸይጣን በተለይ ነገራቶቹን ወደ
ፈለሰፉዋቸው የሁዳዎች ጋር ብቻ ነው ፡፡
* ስለሆነም በእነዚህ ቀናት ሺዓዎች የሚያደርጉዋቸው የሚደሰኩሩዋቸው
የሚተሩኩዋቸው ነገራቶች በሙሉ ከኢስላም ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸውና
እንዲያውም ኢስላምን የሚያፈርሱ ተግባራቶች ናቸው ፡፡
* እንዲሁም ሺዓ አይደሉም ብለን ከምናስባቸው አካሎችም ቢሆን እነዚህን
ቀናቶች ምክንያት በማድረግ ከቁርኣንና ሀዲስ ውጭ በግላዊ ምልከታና ምናለበት
ባይነት የሚደረጉ የቀብር ዚያራዎች፤ የምግብ ዝግጅቶች፤ አዝካሮች ፤ መኳኳሎች
እና ሌሎችም ነገራቶች ከኢስላም የራቁና በእነዚህ ዙርያ የሚወሩ ሀዲሶች
በነብያችን ላይ በውሸት የተቀጠፉ መሆናቸውን አውቀን ነቢያችን ሰለላሁ አለይሂ
ወሰለም እና ሰሀቦቻቸው (ረዲየላሁ አንሁም) ያደርጉት በነበረው ብቻ
በመብቃቃት ወደ አላህ እንቃረብ እያልኩ እመክራለሁ ፡፡
* ባወቅነው የምንሰራ ሰዎች አላህ የድርገን
* ከአሳሳቾች አላህ ይጠብቀን ፡፡

Читать полностью…

سماحة الإسلام የኢስላም ገራገርነት

"ሶ.ዐ.ወ. aww , as wr wb...
ጥያቄ
ብዙ ሰዎች ሜሴጅ ላይም ይሁን ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ለሰላምታ
# aww ወይም # as_wr_wb እና ለሶለዋት ደግሞ # ሶ_ዐ_ወ ብለው ይፅፋሉ
እንዴት ይታያል
መልስ
በሸሪዓችን የተደነገገው # በንግግርም ጊዜ ይሁን # በፅሁፍ ሰላምታንም ይሁን
ሶለዋትን አጅሩ ሙሉ ይሆን ዘንድ # ሙሉ ቃሉን መናገርና መፃፍ ግዴታ ነው። ልክ
በንግግር እንዲህ አሳጥሮ መናገር # እንደማይቻለው ሁሉ በፅሁፍ እንዲሁ
የተከለከለ ተግባር ይሆናል።
ከዚህም በተጨማሪ ከደጋግ # ሰለፎች በዚህ መልኩ አሳጥሮ የተጠቀምም
ይሁን የፃፈ # ስለሌለ ወደ ቢድዐ ሊያመራም ይችላል። እንዲሁም ነብዩ ሶለሏሁ
ዓለይሂ ወሰለም በእኔ ላይ ሶለዋት የማያወርድ ነው # ስስታም እያሉ ያውም
ሶለዋት #አጅር ያለው ተግባር ሆኖ እያለ ቃሉን ሙሉ በሙሉ ለመፃፍ እንዲህ
# መስነፍ ተገቢ አይደለም።ስለዚህ ፀሀፊዎች ሊጠነቀቁና ከዚህ ድርጊት ሊታቀቡ
ይገባል።
ምንጭ :— ሸይኽ አልባኒ ፣ ሲልሲቱል ሁዳ ወኑር ፣ 165 ፣ ኢብኑ
ዑሰይሚን ፣ ሲልሲለቱ ሊቃዕ አልመፍቱህ ፣ 185 ፣ ኢብኑ ሶላህ ፣ ኪታብ
ኡሉሙል ሀዲስ

Читать полностью…

سماحة الإسلام የኢስላም ገራገርነት

*የሪዝቅ በር መክፈቻ*
1. *ኢማን* ፡- ይህኒን በተመለከተ አሏህ(ሱወ) በተከበረው ቃሉ እንዲህ ሲል
ገልጿል፡-
” _የከተማዋም ሰዎች ባመኑና በተጠነቀቁ ኖሮ በእነሱ ላይ ከሰማይም ከምድርም
በረከቶችን በከፈትንላቸው ነበር፡፡ ግን አስተባበሉ፡፡ ይሠሩት በነበሩትም ኃጢኣት
ያዝናቸው_ ፡፡” አል- አዕራፍ፡96
2. *ተቅዋ* ፡- ይህኒን በተመለከተ አሏህ (ሱወ) በተከበረው ቃሉ እንዲህ ሲል
ገልጿል፡-
” _አላህንም የሚፈራ ሰው ለእርሱ መውጫን ያደርግለታል፡፡ ከማያስበውም በኩል
ሲሳየን ይሰጠዋል፡፡ በአላህም ላይ የሚጠጋ ሰው እርሱ በቂው ነው_፡፡” አጥ-
ጦላቅ፡2-3
3. *ኢስትግፋር ማድረግ* ፡- ይህኒን በተመለከተ አሏህ
(ሱወ) በተከበረው ቃሉ እንዲህ ሲል ገልጿል፡-
” _«አልኳቸውም፡- ጌታችሁን ምሕረትን ለምኑት ፡፡ እርሱ በጣም መሐሪ ነውና_፡፡
« _በእናንተ ላይ ዝናምን ተከታታይ አድርጎ ይልካል_፡፡ « _በገንዘቦችና በልጆችም
ይለግሰላችኋል፡፡ ለእናንተም አትክልቶችን ያደርግላችኋል_፡፡ _ለእናንተም ወንዞችን
ያደርግላችኋል፡፡»_ ” ኑሕ፡ 10-12
4. *ሹክር* (አሏህን ማመስገን)፡- ይህኒን በተመለከተ አሏህ(ሱወ) በተከበረው
ቃሉ እንዲህ ሲል ገልጿል፡-
” _ጌታችሁም «ብታመሰግኑ በእርግጥ እጨምርላችኋለሁ ብትክዱም
(እቀጣችኋለሁ) ቅጣቴ በእርግጥ ብርቱ ነውና_» በማለት ባስታወቀ ጊዜ
(አስታውሱ)፡፡” ኢብራሂም፡ 7
5. *መለገስ* (መስጠት)፡- ከአሏህ(ሱወ) ምንዳን በመፈለግ መለገስ ነው፡፡
ይህኒን በተመለከተ አሏህ (ሱወ) በተከበረው ቃሉ እንዲህ ስል ገልጿል፡-
” « _ጌታዬ ሲሳይን ከባሮቹ ለሚሻው ሰው ያሰፋል፡፡ ለእርሱም ያጠብባል፡፡
ከማንኛውም ነገር የምትለግሱትን እርሱ ይተካዋል_፡፡
_እርሱም ከሲሳይ ሰጪዎች ሁሉ በላጭ ነው» በላቸው_፡፡” ሰባእ፡ 39
6. *ትዳርን መያዝ* (ማግባት)፡- ይህኒን በተመለከተ አሏህ(ሱወ) በተከበረው
ቃሉ እንዲህ ሲል ገልጿል፡- ” _ከናንተም ትዳር የሌላቸውን አጋቡ_፡፡ _ከወንዶች
ባሮቻችሁና ከሴቶች ባሮቻችሁም ለጋብቻ ብቁ የኾኑትን (አጋቡ)፡፡ ድኾች ቢኾኑ
አላህ ከችሮታው ያከብራቸዋል_ ። _አላህም ስጦታው ሰፊ ዐዋቂ ነው_፡፡ ” አን-
ኑር፡ 32
7. *ተወኩል* ፡- ይህኒን በተመለከተ የአላህ መልእክተኛ(ሰዐወ) ተወኩልን ሪዝቅ
እንደሚያሰፋ ስገልጹ እንዲህ ብለዋል፡- ” _ትክክለኛ(ተገቢ)የሆነች መመካትን
በአሏህ ላይ ብትመኩ ኖሮ በራሪ ወፍ ምግብዋ እንደምረዝቃት ሁሉ እናንተም
ይረዝቃችሁ ነበር፡፡ ጥዋት በባዶ ሆድዋ ወጥታ ማታ ሆድዋ ሞልታ
ትመለሳለች_፡፡ ” ትርሚዚይ ዘግበውታል ሸኽ አልባኒም ሐዲሱ
ሰሒሕ ብለውታል
8. *ስለቱ ረሒም* (ዝምድና መቀጠል) ፡- ይህኒን በተመለከተ የአላህ
መልእክተኛ(ሰዐወ) ዝምድናን መቀጠል የሪዝቅ በር እንደሚያሰፋ ስገልጹ እንዲህ
ብለዋል፡- ” _ሪዝቁን እንዲሰፋለት ደስ የሚለው ሰው፣ ወይም ዕድሜውን
እንዲረዝምለት የሚፈልግ ሰው ዝምድናን ይቀጥል_፡፡” ቡኻሪ
ዘግበውታል
9. *ሐጂና ዑምራ ማከታተል* ፡- ይህኒን በተመለከተ የአላህ መልእክተኛ (ሰዐወ)
ሐጂና ዑምራ የሪዝቅ በር እንደሚያሰፉ ስገልጹ እንዲህ ብለዋል፡-
” _ሐጅና ዑማራ አከታትሉ፡፡ ወናፍ ነፊ (ብረት ቀጥቃጭ) የብረት፣ የወርቅና
የቡሩር ቆሻሻ እንደሚያመነጥረው ሁሉ ሐጂና ዑምራም ድህነትና ወንጀል
ያስወግዳሉና_፡፡ ” ትርሚዚይ
ዘግበውታል ሸኽ አልባኒም ሐዲሱ ሰሒሕ ብለውታል
10. *ደካማዎች ማገዝ* ፡- የሪዝቅን በር ልያሰፉ ከሚችሉ መልካም ነገሮች
መካከል ሌላው ደግሞ ለደካሞች መልካምን መዋል ነው፡፡ ይህኒን በተመለከተ
የአላህ መልእክተኛ (ሰዐወ) ለደካሞች መልካምን መዋል የሪዝቅ በር እንደሚያ
እንደሚያሰፋ ስገልጹ እንዲህ ብለዋል፡-
” _ነስር (ድል)ና ሪዝቅ እያገኛችሁት ያለው በደከማዎቻችሁ (ላይ በምታደርጉት
በጎ ነገር) ምክንያት እንጂ በሌላ አይደለም_፡፡”
ቡኻሪ ዘግበውታል
*አላህ ሀላል የሆነ የሪዝቅ በሩን ይክፈትልን፣ ሪዝቃችንንም ያስፋልን*።
ይህ መልእክት ለወዳጅ ዘመዶቻችን እንዲደርስ ላይክ ስታረጉ ሼር ማድረግ
አትርሱ።
١٣ ﺳﺎﻋﺔ

Читать полностью…

سماحة الإسلام የኢስላም ገራገርነት

በሒጅራ አቆጣጠር አዲሱ አመት
የፊታችን ማክሰኞ (Aug 10)
ሙሐረም 1 ይገባል!
1443 አመተ ሒጅራ የኸይር አመት
አሏህ ያድርግልን!

Читать полностью…

سماحة الإسلام የኢስላም ገራገርነት

ታዋቂው ሸይኹልኢስላም እንድህ አሉ
ﺍﻟﻘﻠﺐ ﻻ ﺗﺪﺧﻠﻪ ﺣﻘﺎﺋﻖ ﺍﻹﻳﻤﺎﻥ ، ﺇﺫﺍ ﻛﺎﻥ ﻓﻴﻪ ﻣﺎ ﻳﻨﺠﺴﻪ ﻣﻦ ﻛﺒﺮ ﺍﻭ ﺣﺴﺪ .
የኩራት እና ምቀኝነት ነጃሳ እየነጀሰው እስካለ ድረስ በቀልብ ውስጥ እውነተኛ
እምነት ሊገባ አይችልም
《 ﺍﻟﻔﺘﺎﻭﻯ 343/13 》

Читать полностью…

سماحة الإسلام የኢስላም ገራገርነት

እንቅልፍ
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።
39፥42 *"አላህ ነፍሶችን በሞታቸው ጊዜ ይወስዳል፥ ያችንም ያልሞተችውን
በእንቅልፏ ጊዜ ይወስዳታል"*፡፡ ﭐﻟﻠَّﻪُ ﻳَﺘَﻮَﻓَّﻰ ﭐﻟْﺄَﻧﻔُﺲَ ﺣِﻴﻦَ ﻣَﻮْﺗِﻬَﺎ ﻭَﭐﻟَّﺘِﻰ ﻟَﻢْ ﺗَﻤُﺖْ ﻓِﻰ ﻣَﻨَﺎﻣِﻬَﺎ
እንቅልፍ ሰውነታችን በሽታ የመከላከል ዐቅሙን በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምራል፣
የበላነውን ምግብ ከሰውነታችን ጋር በቀላሉ ውሕደት ይፈጥራል፣ አካላችን እረፍት
በማግኘት ኃይልን ያሰባስባል፣ የአእምሮ የማስታወስ ብቃትን ያጎለብታል። ቅሉ
ግን በኢሥላም እንቅልፍ ከዚህም ባሻገር ዘርፈ-ብዙ እና መጠነ-ሰፊ አንድምታ
አለው፥ እረ እንቅልፍ እንደውም ከሕልም፣ ከሩሕ፣ ከሞት ጋር ጥብቅ ተዛምዶ
አለው። አምላካችን አሏህ ሰውን ሲያሞት የሞት መልአክ ልኮ ሩሓችንን
ይወስዳል፦
32፥11 *"«በእናንተ የተወከለው መልአከ ሞት ”ይወስዳችኃል”፡፡ ከዚያም ወደ
ጌታችሁ ትመለሳላችሁ» በላቸው"*፡፡ ﻗُﻞْ ﻳَﺘَﻮَﻓَّﻯٰﻜُﻢ ﻣَّﻠَﻚُ ﭐﻟْﻤَﻮْﺕِ ﭐﻟَّﺬِﻯ ﻭُﻛِّﻞَ ﺑِﻜُﻢْ ﺛُﻢَّ ﺇِﻟَﻰٰ
ﺭَﺑِّﻜُﻢْ ﺗُﺮْﺟَﻌُﻮﻥَ
" ይወስዳችኃል" ለሚለው የገባው ቃል "የተወፋኩም " ﻳَﺘَﻮَﻓَّﻯٰﻜُﻢ ነው። "ነፍሥ " ﻧَﻔْﺲ
ማለት እራሱ "ማንነት" ሲሆን የነፍሥ ብዙ ቁጥር "አንፉሥ " ﺃَﻧْﻔُﺲ ነው፥ የሰው
ማንነት ደግሞ ወደ አፈር የሚሄድ ሟች አካል እና ወደ አሏህ የሚሄድ ሩሕ ነው።
አሏህ ሩሕን በሞት ጊዜ ይወስዳል፦
39፥42 *"አላህ ነፍሶችን በሞታቸው ጊዜ ይወስዳል፥ ያችንም ያልሞተችውን
በእንቅልፏ ጊዜ ይወስዳታል"*፡፡ ﭐﻟﻠَّﻪُ ﻳَﺘَﻮَﻓَّﻰ ﭐﻟْﺄَﻧﻔُﺲَ ﺣِﻴﻦَ ﻣَﻮْﺗِﻬَﺎ ﻭَﭐﻟَّﺘِﻰ ﻟَﻢْ ﺗَﻤُﺖْ ﻓِﻰ ﻣَﻨَﺎﻣِﻬَﺎ
" ሞታቸው" ሲል ነፍሥ በአካል ሟች መሆኗን ሲያሳይ "ይወስዳል" ሲል ደግሞ
ነፍስን በሩሕዋ ተወሳጅ መሆኗን ነው። "ሩሕ " ﺭُّﻭﺡ ማለት “መንፈስ” ማለት ሲሆን
አሏህ ሩሓችንን በእንቅልፍ ጊዜ ወስዶ በንቃት ጊዜ ይመልሳል፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 97, ሐዲስ 97
አቡ ቀታዳህ እንደተረከው፦ "ከሶላት ሰዎች በተኙ ጊዜ የአሏህ ነቢይም " ﷺ"
እንዲህ አሉ፦ *"አሏህ በሚሻው ጊዜ ሩሓችሁን ይወስዳል፥ በሚሻው ጊዜ
ይመልሳል"*። ﻋَﻦْ ﻋَﺒْﺪِ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﺑْﻦِ ﺃَﺑِﻲ ﻗَﺘَﺎﺩَﺓَ، ﻋَﻦْ ﺃَﺑِﻴﻪِ، ﺣِﻴﻦَ ﻧَﺎﻣُﻮﺍ ﻋَﻦِ ﺍﻟﺼَّﻼَﺓِ، ﻗَﺎﻝَ ﺍﻟﻨَّﺒِﻲُّ ﺻﻠﻰ
ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ " ﺇِﻥَّ ﺍﻟﻠَّﻪَ ﻗَﺒَﺾَ ﺃَﺭْﻭَﺍﺣَﻜُﻢْ ﺣِﻴﻦَ ﺷَﺎﺀَ، ﻭَﺭَﺩَّﻫَﺎ ﺣِﻴﻦَ ﺷَﺎﺀَ "
"አርዋሕ" ﺃَﺭْﻭَﺍﺡ ማለት "መንፈሶች" ማለት ሲሆን "ሩሕ " ﺭُّﻭﺡ ለሚለው ብዙ ቁጥር
ነው፥ አሏህ ነፍሥን በእንቅልፏ ጊዜ ሲወስዳት ያለ ዓይን ታያለች፣ ያለ ጆሮ
ትሰማለች፣ ያለ እግር ትሄዳለች፣ ያለ አፍ ትናገራለች፥ የሕልም ዓለም ሩሕ
ከአካል ከተለየች በኃላ ያለውን ሕይወት ማሳያ ናሙና ነው። አምላካችን አሏህ
በሌሊት ይወስደናል፥ ከዚያም በቀን ይቀሰቅሰናል፦
6፥60 *"እርሱም ያ በሌሊት የሚወስዷችሁ በቀንም የሠራችሁትን ሁሉ የሚያውቅ
ከዚያም የተወሰነው ጊዜ ይፈፀም ዘንድ በእርሱ በቀን ውስጥ የሚቀሰቅሳችሁ
ነው"*፡፡ ﻭَﻫُﻮَ ﺍﻟَّﺬِﻱ ﻳَﺘَﻮَﻓَّﺎﻛُﻢ ﺑِﺎﻟﻠَّﻴْﻞِ ﻭَﻳَﻌْﻠَﻢُ ﻣَﺎ ﺟَﺮَﺣْﺘُﻢ ﺑِﺎﻟﻨَّﻬَﺎﺭِ ﺛُﻢَّ ﻳَﺒْﻌَﺜُﻜُﻢْ ﻓِﻴﻪِ ﻟِﻴُﻘْﻀَﻰٰ ﺃَﺟَﻞٌ ﻣُّﺴَﻤًّﻰ
" የሚወስዷችሁ" ለሚለው የገባው ቃል "የተወፋኩም " ﻳَﺘَﻮَﻓَّﺎﻛُﻢ ነው፥ በቁርኣን
ውስጥ "እንቅልፍ" ለሚለው የገባው የስም መደብ "ነውም " ﻧَﻮْﻡ "ኑዓሥ" ﻧُّﻌَﺎﺱ
"ሩቁድ" ﺭُﻗُﻮﺩ ነው። አሏህ ሩሕን በሌሊት እንቅልፍ ጊዜ ወስዶ አካላችንን
ያሳርፋል፦
78፥9 *"እንቅልፋችሁንም ዕረፍት አደረግን"*፡፡ ﻭَﺟَﻌَﻠْﻨَﺎ ﻧَﻮْﻣَﻜُﻢْ ﺳُﺒَﺎﺗًﺎ
10፥67 እርሱ ያ *"ሌሊትን በውስጡ ልታርፉበት፥ ቀንን ልትሠሩበት ብርሃን
ያደረገላችሁ ነው፡፡ በዚህ ውስጥ ለሚሰሙ ሕዝቦች በእርግጥ ተአምራት አሉ"*፡፡
ﻫُﻮَ ﺍﻟَّﺬِﻱ ﺟَﻌَﻞَ ﻟَﻜُﻢُ ﺍﻟﻠَّﻴْﻞَ ﻟِﺘَﺴْﻜُﻨُﻮﺍ ﻓِﻴﻪِ ﻭَﺍﻟﻨَّﻬَﺎﺭَ ﻣُﺒْﺼِﺮًﺍ ۚ ﺇِﻥَّ ﻓِﻲ ﺫَٰﻟِﻚَ ﻟَﺂﻳَﺎﺕٍ ﻟِّﻘَﻮْﻡٍ ﻳَﺴْﻤَﻌُﻮﻥَ
አምላካችን አሏህ በቀን ደግሞ ይቀሰቅሰናል፥ "በቀን ውስጥ የሚቀሰቅሳችሁ ነው"
የሚለው ይሰመርበት። ሰው አካሉ በሌሊት እንቅልፍ እንደሚያርፍ እና በቀን
እንደሚቀሰቀስ ሁሉ በሞትን ጊዜ አካሉ በትልቁ እንቅልፍ ያርፍ እና በትንሳኤ ቀን
ይቀሰቀሳል፦
36፥51 *"በቀንዱም ይነፋል፥ ወዲያውኑም እነርሱ ከመቃብሮቻቸው ወደ ጌታቸው
በፍጥነት ይገሰግሳሉ"*፡፡ ﻭَﻧُﻔِﺦَ ﻓِﻲ ﺍﻟﺼُّﻮﺭِ ﻓَﺈِﺫَﺍ ﻫُﻢ ﻣِّﻦَ ﺍﻟْﺄَﺟْﺪَﺍﺙِ ﺇِﻟَﻰٰ ﺭَﺑِّﻬِﻢْ ﻳَﻨﺴِﻠُﻮﻥَ
36፥52 *«ወይ ጥፋታችን! ከእንቅልፋችን ማን ቀሰቀሰን? ይህ ያ አዛኙ ጌታ
በእርሱ የቀጠረን እና መልክተኞቹ እውነትን የነገሩን ነው» ይላሉ*፡፡ ﻗَﺎﻟُﻮﺍ ﻳَﺎ ﻭَﻳْﻠَﻨَﺎ ﻣَﻦ
ﺑَﻌَﺜَﻨَﺎ ﻣِﻦ ﻣَّﺮْﻗَﺪِﻧَﺎ ۜ ۗ ﻫَـٰﺬَﺍ ﻣَﺎ ﻭَﻋَﺪَ ﺍﻟﺮَّﺣْﻤَـٰﻦُ ﻭَﺻَﺪَﻕَ ﺍﻟْﻤُﺮْﺳَﻠُﻮﻥَ
እንቅልፍ ሩሕ እና አካል የሚለያዩበት ስለሆነ የሞት ወንድም ተብሏል፥ እንቅልፍ
ትንሹ ሞት ስለሆነ ለዛ ነው የምሽት ዚክር ላይ "አሏህ ሆይ! በስምህ እሞታለው
ሕያው እሆናለው" የንጋት ዚክር ላይ ደግሞ፦ "ለአሏህ ምስጋና ይሁን! ለዚያ
ከአሞተን በኃላ ሕያው ላደረገን፥ መቀስቀስም ወደ እርሱ ነው" የምንለው፦
አል-ሙጀመል አውሠጥ ሐዲስ 938
ጃቢር ኢብኑ ዐብደሏህ እንደተረከው፦ "የአሏህ ነቢይም " ﷺ" እንዲህ ተጠየቁ፦
*"የአሏህ መልእክተኛ ሆይ! የጀናህ ባለቤቶች ይተኛሉን? የአሏህ
"መልእክተኛም ﷺ" እንዲህ ሲሉ መለሱ፦ "እንቅልፍ የሞት ወንድም ነውና የጀናህ
ባለቤቶች አይተኙም"*። ﻋَﻦْ ﺟَﺎﺑِﺮِ ﺑْﻦِ ﻋَﺒْﺪِ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﻗَﺎﻝَ ﺳُﺌِﻞَ ﻧَﺒِﻲُّ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﺻَﻠَّﻰ ﺍﻟﻠَّﻪُ ﻋَﻠَﻴْﻪِ ﻭَﺳَﻠَّﻢَ
ﻓَﻘِﻴﻞَ ﻳَﺎ ﺭَﺳُﻮﻝَ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﺃَﻳَﻨَﺎﻡُ ﺃَﻫْﻞُ ﺍﻟْﺠَﻨَّﺔِ ﻓَﻘَﺎﻝَ ﺭَﺳُﻮﻝُ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﺻَﻠَّﻰ ﺍﻟﻠَّﻪُ ﻋَﻠَﻴْﻪِ ﻭَﺳَﻠَّﻢَ ﺍﻟﻨَّﻮْﻡُ ﺃَﺧُﻮ ﺍﻟْﻤَﻮْﺕِ
ﻭَﺃَﻫْﻞُ ﺍﻟْﺠَﻨَّﺔِ ﻻ ﻳَﻨَﺎﻣُﻮﻥَ
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 97, ሐዲስ 23
ሑዘይፋህ እንደተረከው፦ *"ነቢዩ " ﷺ" ወደ አልጋቸው በሄዱ ጊዜ፦ "አሏህ ሆይ!
በስምህ እሞታለው ሕያው እሆናለው" ይሉ ነበር፥ በነቁ ጊዜ፦ "ለአሏህ ምስጋና
ይሁን! ለዚያ ከአሞተን በኃላ ሕያው ላደረገን፥ መቀስቀስም ወደ እርሱ ነው"*። ﻋَﻦْ
ﺣُﺬَﻳْﻔَﺔَ، ﻗَﺎﻝَ ﻛَﺎﻥَ ﺍﻟﻨَّﺒِﻲُّ ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ ﺇِﺫَﺍ ﺃَﻭَﻯ ﺇِﻟَﻰ ﻓِﺮَﺍﺷِﻪِ ﻗَﺎﻝَ " ﺍﻟﻠَّﻬُﻢَّ ﺑِﺎﺳْﻤِﻚَ ﺃَﺣْﻴَﺎ
ﻭَﺃَﻣُﻮﺕُ ." ﻭَﺇِﺫَﺍ ﺃَﺻْﺒَﺢَ ﻗَﺎﻝَ " ﺍﻟْﺤَﻤْﺪُ ﻟِﻠَّﻪِ ﺍﻟَّﺬِﻱ ﺃَﺣْﻴَﺎﻧَﺎ ﺑَﻌْﺪَ ﻣَﺎ ﺃَﻣَﺎﺗَﻨَﺎ ﻭَﺇِﻟَﻴْﻪِ ﺍﻟﻨُّﺸُﻮﺭُ "
እውነት ነው! በእንቅልፍ ውስጥ ለሚሰሙ ሕዝቦች በእርግጥ ተአምራት አሉበት።
አሏህ ከሚሰሙ ባሮቹ ያድርገን! አሚን።
ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ

Читать полностью…

سماحة الإسلام የኢስላም ገራገርነት

የፍቅር አይነት ብዙ ነዉ ነገር ግን ቁርአን ማፍቀር መታደል ነዉ ።
ቁርአን የልቤ መፅናኛ
የመፈሴ ቀለብ
የሂወቴ ቀመሬ የአሄራ ሰንቄ
ፈዉስ መድኃኒቴ ነዉ ።
ያረብ ልባችንን በቁርአን ፍቅር ሙላልን አሏሁመ አሚን
የነገሮች ሁሉ መፍትሔ የችግሮች ሁሉ ቁልፍ ያአላሕ ቃል ቁርአን ብቻ ነዉ ።
ቁርአን የልብ ዉስጥ ዘላለማዊ ብርሀን ነዉ ።
አልሀምዱሊላሕ
በሒወት ዉስጥ ቁርአን ወደ ብሩሕ ተስፋ ይጣራል ።
የማሰብ የማስተዋል ችሎታን ይጨምራል ።
ደስተኛ እንድንሆን ይጋብዘናል ።
ጠንካራ መሀሪ ሃኪም ሰዉ ለሰዉ አዛኝ ታማኝ ቅን እንድንሆን ያግዛል ።
የሚጠበቅብሕ ያለብሕን ያለሕንም የሚኖርብሕንም
የሚኖርሕንም ያሳዉቀሀል ።
የሕመሜ ፈዋሽ የልቤ እርካታ የነፍሴ ደስታ የሂወቴ ቀመሬ የአሄራ ሸፈአየ
ቁርአን ቁርአን ቁርአን ብቻ አልሀምዱሊላሕ ።
መቸም ቢሆን የማልጠግበዉ የማልሰለቸዉ ነገር ቢኖር ቁርአን ብቻ ነዉ ።
አልሀምዱሊላሕ
. ሒወቴን በሙሉ ሳዳምጠዉ ልኑር ኢንሻ አላሕ

Читать полностью…

سماحة الإسلام የኢስላም ገራገርነት

ገንዘብ ትዳር ይሆናል ወይ??
አንድ ስው ትዳር ፈለገና ጠየቀ ስውየውም ልጂን ስጠው ።
ስለ መኸር ሲነጋገሩ አባት አድ ኩንታል ሺንኩርት ከከፈልክ ይበቃል አለው ።
ልጁም ተስማማ !!!
ተጋብተው ሲኖሩ ልጅም ወለዱ
አንድ ቀን ቤተስብ ለመዘየር አስበችና ነገርችው
እሱም ተስማማ መንገድ ላይ አያሉ
ልጂቷ ወደቀችና እንዲረዳት ጠየቀችው
...እሱም አባትሽ የወስደው ሽንኩርት የርዳሺ በማለት መለስላት ።
አባት ይሄን ሲስማ ልጂቱን ፍታ ብለዉ እንዲፈታ አደረጉት ።
አባትም ልጀን መልስህ ማግባት ከፈለክ አድ
ኩንታል ወርቅ ይዘህ ና በማለት የወለደዉን ልጁን አሳቅፈው ።
ባልም አድ ኩንታል ወርቅ ካወጣሁ ሌላ መርጨ አገባለሁ ብሎ ልጁን ይዞ ሄደ ።
ነገር ግን ሚስት ቢፈልግም አጣ ።
የልጂቷ አባት ባለው መስርት ወርቁን ይዞ
በመሄድ መልሶ አገባት ።
አድ ቀን አብረዉ እየሄዱ ልጂቷ አንዳለጣትና
ወደቀች ።
እሩጦ በመሄድ ያነሳታል ።
ልጂቷም አሁን ምን ተለወጠና አነሳኸኝ
መጀመሪያ ፈቃደኛ አልነበርክም በማለት
ጠየቀችው ።
ልጁም እድህ አላት
መጀመሪያ ሳገባሺ በሺንኩርት ነው
አሁን ግን ወርቅ ከፍየብሻለሁ እና ውድ ነሽ ብሎ መለስላት ።
አላሁ ሙስተአን
ﻣﺎ ﺑﻴﻔﻢ ﻏﻴﺮ ﺑﻌﺜﺮﻩ ﻛﻼﻡ ﺍﻻﺍﺏ
ሁሉም ወዶች አንድ ናቸው ማለት ባይቻልም ግን አዳድ ወዶች መስፈሪያቸው
ትዳር ሳይሆን ገንዘብ ነው ።
ግልባጭ በብር የሚያስቡ ወንዶች እና ትዳር ብር ካለዉ ጋር ነዉ ለምትሉ ሴቶች።

Читать полностью…

سماحة الإسلام የኢስላም ገራገርነት

# አግብታ_የፈታች_አልያም_ባል_የሞተባት_ሴት_ክብር !
≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅
☞አላህን እንፍራ!
≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅
☞አንዲት በሰሓቦች ዘመን የነበረች ሴት ባሏ የሞተ አልያም የፈታት ግዜ
ሰሓቦች እሷን ለመንከባከብና ለመደገፍ ክብር በተላበሰ መልኩ ይቻኮሉ ነበር።
☞የሰሓቦችን ታሪክ ብናገላብጥ አንዲት ሰሓቢይ ሴት አራት ሰሓቦችን በተለያየ
ግዜ እንዳገባች እንረዳለን። አንዱ ሲሞት ሌላውን እያገባች ተከብራ ኖራለች።
እሷን የመሰሉ ሴቶችን በንቀትና በጉድለት በፍፁም አይመለከቷቸውም ነበር።
☞ዐቲካ የምትባልን ሴት ተመልከት! የአቡ በክር ልጅ አገባት በጣም ታፈቅረው
ነበር እሱም በቃላት ሊገለፅ በማይችል መልኩ ይወዳታል ከግዜያት ቡኃላ ሸሂድ
ሆኖ ሞተ። ከዛም ታላቁ ሰሓቢይ ዑመር አልፋሩቅ አገባትና እሱም ሸሂድ ሆኖ
ሞተ። ከዛም እሷን ለማግባትና ለማክበር የመልእክተኛው ሓዋሪይ የሚባለው
ታላቁ ሰሓባ ዙበይር ኢብኑል ዓዋም ተቻኮለ፤ አገባትም። ከጥቂት ግዜ ቡኃላም
ሸሂድ ሆኖ ሞተ። እነዚህ ሁሉ ታላላቅ ሰዎች ሲሞቱ "በባሎቿ ላይ ሙሲባ
የምታመጣ" አልተባለችም። እንደውም "ሸሂድ መሆን የፈለገ ዐቲካን ያግባ!"
ተብሏል።
☞የአስማዕ ቢንት ዑመይስን ታሪክ እናገላብጥ። የመጨረሻ ባሏ ታላቁ ጀግና
ፈረሰኛው ሰሓቢይ ዐሊይ ኢብን አቢ ጧሊብ ነበር። ከሌሎች ባሎቿ
የወለደቻቸውን ልጆች ያጫውት የሷን ጣፋጭ ንግግርና የልጆቿን ጨዋታ
በመስማት በደስታ ፈገግ ይል ነበር። በቀደሙ ባሎቿ በፍፁም ቅናት
አይሰማውም። "በቀደሙ ባሎችሽ ላይ ስሞቷ ብታሰሚ እቆጣሻለው! በፍፁም
በመጥፎ ስታነሺያቸው እንዳልሰማ እነሱ ወዳጆቼ ናቸው።" ይላት ነበር።
(ሁሉንም አላህ ስራቸውን ይውደድ!)
☞የትኛዋም ሰሓቢያ ሌላ ባል ስታገባ የመጀመሪያ ባሏን እያወሳች በክህደት
አልተጠረጠረችም።
☞የአላህ መልእክተኛም ከእናታችን ዐይሻ በስተቀር ድንግል ሴት አላገቡም።
መጀመሪያ ትዳርን የመሰረቱትም ከሳቸው በፊት ትዳርን ከምታውቀው ከእናታችን
ኸዲጃ ቢንት ኹወይሊድ ጋር ነበር።
☞የተፈታችን አልያም ባል የሞተባትን ሴት ማግባት እንዲሁም ከአንድ በላይ
ማግባት ስነ ምግባርን የሚጥስ፣ ክብርን የሚነካና የሚጠየፉት የወረደ ተግባር
ቢሆን ቀድሞውንም ኢስላም ይከለክለዋል። ስነ ምግባርን፣ ልቅናንና እውነተኛ
ሰብኣዊነትን ያስተማረን ኢስላም ነውና!
☞የተፈታች ሴት በፍፁም የውድቀት ምልክት አይደለችም። አላህን ከፈራች
ከፍቺውም ቡኃላ አላህ ከችሮታው ያብቃቃታል። የተሻለ የህይወት መስመር
ያበጅላታል።
☞ከመጀመሪያ ባልሽ የተሻለ መልካም የትዳር አጋር አላህ ሊሰጥሽ ይከጀላል።
መጪው ቀናት በአላህ ፈቃድ መልካም ብስራትና ተስፋ ይዞ ብቅ ይላል።
አንገትሽን አትድፊ!
☞እኛም የደረሰባቸውን ሀዘን ለመጠገን መሯሯጥ ይገባናል። በብዛት
የሚያጋጥማቸውን ሞራላዊና ማህበረሰባዊ ተፅእኖ በመልካም ለመግፈፍ መታተር
ይጠበቅብናል።
☞በክፉ ከሚመለከቷቸው የሰው አውሬዎች ልንከላከላቸውና በደካማ ጎናቸው
ለማጥቃት ካሰፈሰፉ ዋልጌዎች ልንጠብቃቸው የበኩላችንን ጥረት ማረግ
አለብን።
☞በሚያሳዝን ሁኔታ በአሁን ወቅት አግብታ የፈታችን ሴት ለማግባት የሚያስብ
የሷን መብት ልክ እንደ አሮጌና ያገለገለ መኪና አስመስሎ ፕሮፖዛል የሚያቀርብ
አለ።
☞ይህ በሴቶች መብት ላይ ግፍና በደል ነው።
አሏህን ልንፈራ ይገባል!
☞ባል የሞተባት አልያም የፈታች እህትና ልጅ ቢኖረህ ለሷ የምትመኘውን
ለሎችም እህቶችን መመኘት አለብህ። ስሜት ካወረው ፅልመት ተላቀህ
ሰብኣዊነት የተሞላ ኢስላሚዊ መንፈስ ይኑርህ።
☞ቁምነገሩ ያንተ ወንዳ ወንድነትና ስብእና እንጂ የሷ የቀደመ ትዳር ተፅእኖ
አይደለም።
☞በብልሀትና በስነምግባር የተሞላህ መሆንህ በአላህ ፈቃድና ችሮታ ያለፈ
ህይወቷን አስረስቶ ስኬታማ ትዳርን በሀሴት ይለግሳታል።
☞ኋላ ቀር የሆኑ አባባሎች ጠፍረው አይከርችሙህ። መመሪያህ ኢስላም ብቻ
ይሁን።
በሙስሊም እህቶቻችን ላይ አላህን እንፍራ!
ከተወሰነ ማብራሪያ ጋር የተተረጎመ!
ዐብዱረዛቅ አል-ሐበሺይ

Читать полностью…

سماحة الإسلام የኢስላም ገራገርነት

# የዱአ_አደራረግ_አዳብ (ስርአት)
አብዛኞቻችን ዱአ ማድረግ ስንፈልግ ዝምብለን በቀጥታ እጃችንን አንስተን ወደ
ጉዳያችን እንገባለን ፥ ይህ መሆን የለበትም ምክንያቱም ነብያችን ያስተማሩን
የዱአ አደራረግ ይህ አይደለምና ።
ዱአ ማድረግ ስንፈልግ መጀመሪያ አላህ በኛ ላይ የዋለልንን ፀጋ በማስታወስ
ከልብ እናመስግነው ከዚህም የሱን ታላቅነትና ለጋሽነት መሃሪነት ... እያወሳን
እናልቀው እናወድሰው ፥ ከዚያም በነብያችን ላይ ሶለዋት እናውርድ ከዚያ ወደ
ጉዳያችን እንገባለን መጠየቅ የምንፈልገውን ሁሉ እንጠይቀዋለን እንለምነዋለን ።
ይህ ነው ነብያችን ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም ያስተማሩን የዱአ አደ

Читать полностью…

سماحة الإسلام የኢስላም ገራገርነት

# ሳያነቡ እንዳያልፉ
አንድ ትንሽዬ ልጅ ለወላጆቹ፦"3 ጥያቄዎቼን
የሚመልስልኝ
ጠንካራ ዑለማእ
አምጡልኝ" አላቸው።
ወላጆቹም በአከባቢያቸው ያለ አንድ ኡስታዝ አመጡለትና
አገናኙት።
ልጁ፦"ማን ነህ አንተ? እኔ ስለምጠይቀውስ ጥያቄ መልስ
እንዳለህ ምን ያህል
እርግጠኛ ነህ?"
ኡስታዙ፦"ስሜ ዐብዱላህ ይባላል ከአላህ ባሪያዎችም
አንዱ ነኝ።ለምትጠይቀኝ
ጥያቄዎችም በአላህ ፍቃድ መልስ እሰጥሀለሁ።"
ልጁ፦"አንተ ግን ብዙ ዑለማኦች ሊያብራሩልኝ ያልቻሉትን
ጥያቄዬን እንደምትመልስልኝ
ሙሉ በሙሉ እርግጠኛ ነህ?
ኡስታዙ፦"ልመልስልህ እሞክራለሁ በአላህ እገዛ።"
ልጁ፦" 3 ጥያቄዎች አሉኝ።
1=>እውነት ፈጣሪ አለ? አዎ አለ የምትል ከሆነ አሳየኝ
የት
ነው ያለው?
2 => ቀዷ እና ቀደር ምንድነው?
3 =>እውነት ሸይጣን ከእሳት የተፈጠረ ከሆነ እንዴት
በእሳት ይቀጣል? ከእሳት ተፈጥሮ
እሳት አያቃጥለውም።"
ይሄን ግዜ ኡስታዙ እሳት በሆነች ጥፊ ልጁን አጮለው።
ልጁ፦"እንዴ!!! ለምን ትመታኛለህ? ምን ሚያስመታ ነገር
ተናገርኩ?
ኡስታዙ፦"አረ!!! እኔ አልተቆጣሁም ግን ያሁኗ ጥፊ
ለሶስቱም ጥያቄዎችህ መልስ ናት።
ልጁ፦"እንዴት? አልገባኝም...
ኡስታዙ፦"በጥፊ ስመታህ ምን ተሰማህ?
ልጁ፦"በጣም ህመም ተሰማኝ።
ኡስታዙ፦"ህመም እንዳለ ታምናለህ?"
ልጁ፦"አዎ አምናለሁ።"
ኡስታዙ፦"አሳየኝ የት ነው ያለው?"
ልጁ፦"አይ አለ ግን ማየት እንኳን አይቻልማ"
ኡስታዙ፦"ይህ ለመጀመሪያ ጥያቄህ መልስ
ነው።ሁላችንም
አላህ እንዳለ እናምናለን
ነገር ግን ማየት አንችልም።እሺ ዛሬ እንደምመታህ ትናንት
ማታ ገምተህ ነበር?"
ልጁ፦"አልገመትኩም።"
ኡስታዙ፦"እሺ እኔስ አንተን ዛሬ እንደምመታህ ትናንት ማታ
አስቤ ነበር?
ልጁ፦"አላሰብክም።"
ኡስታዙ፦"ለ2ኛ ጥያቄህ መልስ ይህ ነው ቀዷ ቀደር
የሚባለው።
እሺ እኔ አንተን የመታሁበት እጄ ከምንድነው የተፈጠረው?"
ልጁ፦"ከአፈር"
ኡስታዙ፦"እሺ በእጄ የመታሁት ያንተ ፊትስ ከምንድነው
የተፈጠረው?"
ልጁ፦"ከአፈር"
ኡስታዙ፦"ስመታህ ምን ተሰማህ?"
ልጁ፦"አመመኝ"
ኡስታዙ፦"ከአፈር የተሰራ አፈርን ሲመታው
እንደሚያሳምመው ሁላ ከእሳት የተሰራውም
ሸይጣን በእሳት ሲቀጣ በጣም ያመዋል።"
ክብር በየሀገሩ ላሉ ዑለማኦች ይገባቸዋል።

Читать полностью…

سماحة الإسلام የኢስላም ገራገርነት

«አስገራሚ የቁርአን የአገላለፅ ምጥቀት ‏»
ቁርአን አንድ ሐሳብ ሲናገር እውነት መሆኑን የተነገረባቸው ፊደላት ቃላቶች
ላስተላለፉት እውነታ ራሳቸው ምስክርነት የሚሰጡ ናቸው።
ቁርአን እጅግ ጥልቅ በኮምፒዩተር ታግዘህ ኮድ የማይደረግ እና ዘርፈ ብዙ
ተአምር የያዘ ቢሆንም ማንኛውም የኔ ቢጤ ሰው በተሻለ መልኩ እንዲረዳው
ግልፅ እና ቀላል ናቸው።
ለምሳሌ ሳይንስ ቫይረስን በአይን የማትታይ ትንጥየ አካል ናት ይላል።
የሰው ልጅ ቫይረስ ትንጥየ መሆኑን ለማረጋገጥ መጀመሪያ ማይክሮስኮፕ መስራት
ያስፈልገናል።
የተሰራው ማይክሮስኮፕ ለመጠቀም የብዙ አመት ስልጠና እና ባለሙያ መሆን
ያስፈልጋል ።
የሰው ልጅ እዚህ ብቃት ላይ ለመድረስ ብዙ ሺ አመት ፈጅቶበታል።
እውነታውን ለማወቅ ያለውን ብዙ ድካም አስተውል።
ቁርአን ግን እስካሁን የሰው ልጅ ያልደረሰበት ሩቅ እና ጥልቅ ሚስጥር እንዴት
ግልፅ አድርጎ እንደሚያሳይህ ከዚህ በታች ያለውን የቁርአን የአገላለፅ ምጥቀት
ከፎቶው ጋር አዛምደህ አስተውለህ መርምር ።
ቁርአን ሰባት ሰማያት አለ ይልሀል ።
«ሰባት ሰማያት» የሚለው ቁርዓን ላይ የተጠቀሰው ሰባት ግዜ ብቻ ነው።
ከዚያም ሰባት ሰማያት የሚለው የፊደላቸው ብዛት «ሰባት» ፊደል ናቸው ።
የሩቅ ጉዳይ የሆነው የሰማይን ጉዳይ እውነት መሆኑን የቁርአን ቃላቱ ማይክሮስኮፕ
ሆኖ ብዙ አመት ድካም ሆነ ስልጠና ሳያስፈልግህ ራሱ ያሳይሀል አጂብ ።
ሰባት ሰማይ የለም ብሎ መካድ አይደለም ቃላቱን እንኳን አንተ በመሰካከት
ሐሳቡን ውሸት ልታደርገው አትችልም ።
ወይም አመሳስለህ አንተ ቃላቱን በውሸት መፍጠር አትችልም።
ሱብሀነአላህ

Читать полностью…

سماحة الإسلام የኢስላም ገራገርነት

ፈገግ ይበሉ! ፈገግታ ሱና ነው
••••••የእብድ ኹጥባ•••••
በጁሙዐ ቀን ኹጥባ የሚያደርጉት የመስጅድ ኢማም በጊዜ አልመጡም
( ዘግይተው) ነበርና አንድ እብድ መጣና ሚንበሩ ላይ ወጣ። የተወሰኑ ሰዎች
ሊያስወርዱት ሞከሩ። በመስጅዱ ውስጥ ሀላፊነት ካላቸው ሰዎች መካከል አንዱ
ባለበት እንድተውትና ኹጥባ እንድያደርግ አዘዘ። እብዱም ኹጥባ ማድረግ
ጀመረ:_
" ምስጋና ለአሏህ ይገባው። ያ ከሁለት አይነት የፈጠራችሁና ለሁለት አይነት
አድርጎ ለከፈላችሁ። ከናንተ ውስጥ ልታመሰግኑ ዘንድ ሀብታሞችን አደረገ።
ከናንተም ውስጥ ትታገሱ ዘንድ ድሆችን አደረገ።
ከናንተ ውስጥ ሀብታም የሆነውም አላመሰገነ፣ ድሀ የሆነውም አልታገሰ።
የአሏህ እርግማን በሁላችሁም ላይ ይሁን!
ቁሙ ወደ ሶላታችሁ!"
የእብዱ ንግግርሀቅ ነው ያወራው
ﺍﻟﻠﻬﻢ ﺻﻞ ﻭﺳﻠﻢ ﻋﻠﻰ ﻧﺒﻴﻨﺎ ﻣﺤﻤﺪ

Читать полностью…

سماحة الإسلام የኢስላም ገራገርነት

የደግነትህ መለኪያ !! ✿◉●•◦
=============
«ስማኝማ አንተ ለአጭር ጊዜ ለምታገኘው ሰው መልካም መሆን ቀላል ሊሆን
ይችላል፣
ነገር ግን ሁሌም አብራህ ለምትኖረዋ የትዳር አጋርህና ለቤተሰቦችህ መልካም
መሆን ግን ያንተ ደግነት መለኪያ ነው» !!
ነቢዩ ﷺ ስለአሏሁ አለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ:-
«ከእናንተ መሀል በላጭ ሰው ብሎ ማለት # ለሚስቱ_መልካም የሆነ ሰው ነው»።
ቲርሚዚ ዘግበውታል

Читать полностью…
Subscribe to a channel