nesiha | Unsorted

Telegram-канал nesiha - سماحة الإسلام የኢስላም ገራገርነት

986

ይሄ ቻናል የቁርአንና የሀዲስን አስተምህሮቶች በሰለፎች አረዳድ ማሰራጫ ነው ከፖለታካ ነፃ ነው።

Subscribe to a channel

سماحة الإسلام የኢስላም ገራገርነት

ሙሣፊር
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።
4፥101 *"በምድርም ላይ በተጓዛችሁ ጊዜ እነዚያ የካዱት ያውኩናል ብላችሁ
ብትፈሩ ከሶላት ባለ አራት ረክዓት የኾኑትን ብታሳጥሩ በእናንተ ላይ ኃጢአት
የለም"*፡፡ ﻭَﺇِﺫَﺍ ﺿَﺮَﺑْﺘُﻢْ ﻓِﻲ ﺍﻟْﺄَﺭْﺽِ ﻓَﻠَﻴْﺲَ ﻋَﻠَﻴْﻜُﻢْ ﺟُﻨَﺎﺡٌ ﺃَﻥ ﺗَﻘْﺼُﺮُﻭﺍ ﻣِﻦَ ﺍﻟﺼَّﻠَﺎﺓِ ﺇِﻥْ ﺧِﻔْﺘُﻢْ ﺃَﻥ
ﻳَﻔْﺘِﻨَﻜُﻢُ ﺍﻟَّﺬِﻳﻦَ ﻛَﻔَﺮُﻭﺍ
"ሙሣፊር" ﻣُﺴﺎﻓِﺮ የሚለው ቃል "ሣፈረ " ﺳَﺎﻓَﺮَ ማለትም "ተጓዘ" ከሚል ሥርወ-ቃል
የመጣ ሲሆን "ተጓዥ" "መንገደኛ" ማለት ነው፥ ዱዓቸው አሏህ ዘንድ መቅቡል
ከሆኑት ሦስት ሰዎች መካከል አንዱ የሙሣፊር ዱዓእ ነው፦
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 34, ሐዲስ 36
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም " ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"ሦስት
ልመናዎች ያለጥርጥር ተቀባነት አላቸው፥ እነርሱም፦ የተበዳይ ልመና፣ የመንገደኛ
ልመና እና ወላጅ ለልጁ የሚያደርገው ልመና ናቸው"*። ﻋَﻦْ ﺃَﺑِﻲ ﻫُﺮَﻳْﺮَﺓَ، ﻗَﺎﻝَ ﻗَﺎﻝَ
ﺭَﺳُﻮﻝُ ﺍﻟﻠَّﻪِ ـ ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ ـ " ﺛَﻼَﺙُ ﺩَﻋَﻮَﺍﺕٍ ﻳُﺴْﺘَﺠَﺎﺏُ ﻟَﻬُﻦَّ ﻻَ ﺷَﻚَّ ﻓِﻴﻬِﻦَّ ﺩَﻋْﻮَﺓُ
ﺍﻟْﻤَﻈْﻠُﻮﻡِ ﻭَﺩَﻋْﻮَﺓُ ﺍﻟْﻤُﺴَﺎﻓِﺮِ ﻭَﺩَﻋْﻮَﺓُ ﺍﻟْﻮَﺍﻟِﺪِ ﻟِﻮَﻟَﺪِﻩِ "
አምላካችን አሏህ ሙሣፊርን "ኢብኑ አሥ-ሠቢል " ﭐﺑْﻦ ﺍﻟﺴَّﺒِﻴﻞ ማለትም "የመንገድ
ልጅ" ይላቸዋል፥ "ኢብን " ﭐﺑْﻦ ማለት "ልጅ" ማለት እንደሆነ ልብ አድርግ! ዘካህ እና
ሶዶቃህ ከሚገባቸው አንዱ ሙሣፊሮች ናቸው፦
9፥60 *ግዴታ ምጽዋቶች የሚከፈሉት ለድኾች፣ ለምስኪኖችም፣ በርሷም ላይ
ለሚሠሩ ሠራተኞች፣ ልቦቻቸውም በኢሥላም ለሚለማመዱት፣ በባርነት
ተገዢዎችን ነጻ በማውጣት፣ በባለ ዕዳዎችም፣ በአላህ መንገድም በሚሠሩ፣
በመንገደኛም ብቻ ነው"*፡፡ ﺇِﻧَّﻤَﺎ ﺍﻟﺼَّﺪَﻗَﺎﺕُ ﻟِﻠْﻔُﻘَﺮَﺍﺀِ ﻭَﺍﻟْﻤَﺴَﺎﻛِﻴﻦِ ﻭَﺍﻟْﻌَﺎﻣِﻠِﻴﻦَ ﻋَﻠَﻴْﻬَﺎ ﻭَﺍﻟْﻤُﺆَﻟَّﻔَﺔِ
ﻗُﻠُﻮﺑُﻬُﻢْ ﻭَﻓِﻲ ﺍﻟﺮِّﻗَﺎﺏِ ﻭَﺍﻟْﻐَﺎﺭِﻣِﻴﻦَ ﻭَﻓِﻲ ﺳَﺒِﻴﻞِ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﻭَﺍﺑْﻦِ ﺍﻟﺴَّﺒِﻴﻞِ
2፥215 *"ምንን ለማንም እንደሚለግሱ ይጠይቁካል፥ "ከመልካም ነገር
የምትለግሱት ለወላጆች፣ ለቅርብ ዘመዶች፣ ለየቲሞችም፣ ለድሆችም እና
ለመንገደኞች ነው" በላቸው፡፡ ﻳَﺴْﺄَﻟُﻮﻧَﻚَ ﻣَﺎﺫَﺍ ﻳُﻨﻔِﻘُﻮﻥَ ۖ ﻗُﻞْ ﻣَﺎ ﺃَﻧﻔَﻘْﺘُﻢ ﻣِّﻦْ ﺧَﻴْﺮٍ ﻓَﻠِﻠْﻮَﺍﻟِﺪَﻱْﻥِ
ﻭَﺍﻟْﺄَﻗْﺮَﺑِﻴﻦَ ﻭَﺍﻟْﻴَﺘَﺎﻣَﻰٰ ﻭَﺍﻟْﻤَﺴَﺎﻛِﻴﻦِ ﻭَﺍﺑْﻦِ ﺍﻟﺴَّﺒِﻴﻞِ
እነዚህ አናቅጽ ላይ "መንገደኞች" ለሚለው የገባው ቃል "ኢብኑ አሥ-ሠቢል " ﭐﺑْﻦ
ﺍﻟﺴَّﺒِﻴﻞ መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። "ቀስር " ﻗَﺼْﺮ የሚለው ቃል "ቀሶረ " ﻗَﺼَﺮَ
ማለትም "አጠረ" ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "አጭር" ማለት ነው፥
የሙሣፊ ሶላት "ሶላቱል ቀስር " ﺻَّﻠَﺎﺓ ﺍﻟﻘَﺼْﺮ ይባላል። አንድ ሙሣፊር በመንገድ ላይ
እያለ ባለ አራት ረክዓት የነበሩት ሶላት ባለ ሁለት ረከዓት በመሆን ያጥራሉ፦
4፥101 *"በምድርም ላይ በተጓዛችሁ ጊዜ እነዚያ የካዱት ያውኩናል ብላችሁ
ብትፈሩ ከሶላት ባለ አራት ረክዓት የኾኑትን ብታሳጥሩ በእናንተ ላይ ኃጢአት
የለም"*፡፡ ﻭَﺇِﺫَﺍ ﺿَﺮَﺑْﺘُﻢْ ﻓِﻲ ﺍﻟْﺄَﺭْﺽِ ﻓَﻠَﻴْﺲَ ﻋَﻠَﻴْﻜُﻢْ ﺟُﻨَﺎﺡٌ ﺃَﻥ ﺗَﻘْﺼُﺮُﻭﺍ ﻣِﻦَ ﺍﻟﺼَّﻠَﺎﺓِ ﺇِﻥْ ﺧِﻔْﺘُﻢْ ﺃَﻥ
ﻳَﻔْﺘِﻨَﻜُﻢُ ﺍﻟَّﺬِﻳﻦَ ﻛَﻔَﺮُﻭﺍ
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 5, ሐዲስ 1121
ኢብኑ ዐባሥ እንደተናገረው፦ *"አሏህ በነቢያችሁ " ﷺ " ልሣን ግዳጅ ያረገው
በከተማ መኖሪያ አራት ረክዓትን ሲሆን በመንገድ ደግሞ ሁለት ረክዓትን ነው"*።
ﻋَﻦِ ﺍﺑْﻦِ ﻋَﺒَّﺎﺱٍ، ﻗَﺎﻝَ ﺍﻓْﺘَﺮَﺽَ ﺍﻟﻠَّﻪُ ﺍﻟﺼَّﻼَﺓَ ﻋَﻠَﻰ ﻟِﺴَﺎﻥِ ﻧَﺒِﻴِّﻜُﻢْ ـ ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ ـ ﻓِﻲ ﺍﻟْﺤَﻀَﺮِ
ﺃَﺭْﺑَﻌًﺎ ﻭَﻓِﻲ ﺍﻟﺴَّﻔَﺮِ ﺭَﻛْﻌَﺘَﻴْﻦِ
"ረክዓህ" ﺭَﻛْﻌَﺔ ማለት "ዙር" ማለት ሲሆን የረክዓህ ብዙ ቁጥር ደግሞ "ረክዓት "
ﺭَﻛْﻌَﺖ ነው፥ በሙሰና ሲመጣ ደግሞ "ረክዐተይን " ﺭَﻛْﻌَﺘَﻴْﻦ ነው። የሙሣፊር ሶላት
ዙህር 4 ረክዓት እና ዐስር 4 በጥቅሉ 8 ረክዓት የነበረው ዙህር አዛን ካለበት
እስከ ዐስር ባለው ጊዜ ዙህር ሁለት ዐስር ሁለት ሆኖ 4 ረክዓት ይሰገዳል፥
እንዲሁ መግሪብ 3 ረክዓት እና ዒሻእ 4 በጥቅሉ 7 ረክዓት የነበረው መግሪብ
አዛን ካለበት እስከ ዒሻእ ባለው ጊዜ መግሪብ ሦስት ዒሻእ ሁለት ሆኖ 5 ረክዓት
ይሰገዳል፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 19, ሐዲስ 52
ዐምር እንደተረከው፦ አቡ አሽ-ሸዕሳእ ሲናገር ሰማሁኝ፥ ጃቢር ሲናገር ኢብኑ
አባሥ"ረ.ዐ." እንደሰማሁት እርሱም እንዲህ አለ፦ *"ከአሏህ መልእክተኛ " ﷺ" ጋር
ስምንት ረክዓት በአንድ ላይ እንዲሁ ሰባት ረክዓት በአንድ ላይ ሰገድኩኝ"*። ﻋَﻦْ
ﻋَﻤْﺮٍﻭ، ﻗَﺎﻝَ ﺳَﻤِﻌْﺖُ ﺃَﺑَﺎ ﺍﻟﺸَّﻌْﺜَﺎﺀِ، ﺟَﺎﺑِﺮًﺍ ﻗَﺎﻝَ ﺳَﻤِﻌْﺖُ ﺍﺑْﻦَ ﻋَﺒَّﺎﺱٍ ـ ﺭﺿﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻨﻪ ـ ﻗَﺎﻝَ ﺻَﻠَّﻴْﺖُ
ﻣَﻊَ ﺭَﺳُﻮﻝِ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ ﺛَﻤَﺎﻧِﻴًﺎ ﺟَﻤِﻴﻌًﺎ ﻭَﺳَﺒْﻌًﺎ ﺟَﻤِﻴﻌًﺎ .
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 6, ሐዲስ 62
ሙዓዝ እንደተረከው፦ *"ከአሏህ መልእክተኛ " ﷺ " ጋር በተቡክ ጉዞ ተጓዝን፥
እርሳቸውም ዙህርን እና ዐስርን አንድ ላይ እንዲሁ መግሪብን እና ዒሻእን በአንድ
ላይ ሰገዱ"*። ﻋَﻦْ ﻣُﻌَﺎﺫٍ، ﻗَﺎﻝَ ﺧَﺮَﺟْﻨَﺎ ﻣَﻊَ ﺭَﺳُﻮﻝِ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ ﻓِﻲ ﻏَﺰْﻭَﺓِ ﺗَﺒُﻮﻙَ
ﻓَﻜَﺎﻥَ ﻳُﺼَﻠِّﻲ ﺍﻟﻈُّﻬْﺮَ ﻭَﺍﻟْﻌَﺼْﺮَ ﺟَﻤِﻴﻌًﺎ ﻭَﺍﻟْﻤَﻐْﺮِﺏَ ﻭَﺍﻟْﻌِﺸَﺎﺀَ ﺟَﻤِﻴﻌًﺎ .
የዐስርን ሶላት ዙህር አዛን ባለበት ሰዓቱ ላይ እንዲሁ የዒሻእን ሶላት መግሪብ
አዛን ባለበት ሰዓቱ ላይ መስገድ ተመራጭ ሲሆን በዙህር እና በዐስር መካከል
እንዲሁ በመግሪብ እና በዒሻእ መካከል ማሠላመት እንዳለ መዘንጋት የለበትም።
አንድ ሰው በጉዞ ላይ እያለ በረመዷን ፆም ወቅት አለመፆም ይችላል፥ ነገር ግን
ሙቂም ሲሆን ከፋራህ ያወጣል፦
2፥185 *"በሽተኛ ወይም በጉዞ ላይ የኾነም ሰው ከሌሎች ቀኖች ቁጥሮችን
በልኩ መጾም አለበት! አላህ በእናንተ ገሩን ነገር ይሻል፥ በእናንተም ችግሩን
አይሻም"*፡፡ ﻭَﻣَﻦ ﻛَﺎﻥَ ﻣَﺮِﻳﻀًﺎ ﺃَﻭْ ﻋَﻠَﻰٰ ﺳَﻔَﺮٍ ﻓَﻌِﺪَّﺓٌ ﻣِّﻦْ ﺃَﻳَّﺎﻡٍ ﺃُﺧَﺮَ ۗ ﻳُﺮِﻳﺪُ ﺍﻟﻠَّﻪُ ﺑِﻜُﻢُ ﺍﻟْﻴُﺴْﺮَ ﻭَﻟَﺎ ﻳُﺮِﻳﺪُ
ﺑِﻜُﻢُ ﺍﻟْﻌُﺴْﺮَ
አንድ ሰው በአንድ ከተማ ከተወለደ ወይም ከከተመ "ሙቂም " ﻣُﻘِﻴﻢ ሲባል
የተወለደበት ወይም የከተመበት ደግሞ "ኢቃማህ " ﺇِﻗَﺎﻣَﺔ ይባላል፥ በተቃራኒው
አንድ ሰው ከሚኖርበት ቀዬ ከተጓዘ "ሙሣፊር " ﻣُﺴﺎﻓِﺮ ሲባል ጉዞው ደግሞ
"ሠፈር" ﺳَﻔَﺮ ይባላል። ስለ ሙሣፊር በግርድፉ እና በሌጣው ይህንን ይመስላል

Читать полностью…

سماحة الإسلام የኢስላም ገራገርነት

ጌታዬ አላህ ሆይ! ከመጥፎ ጎረቤትና እድሜዬ ሳይደርስ እንድሸብት
ከምታደርገኝ ሚስት በአንተ እጠበቃለሁ»።
ነቢዩ ﷺ ስለአሏሁ አለይሂ ወሰለም
አስ ሶሒሀህ (3137)

Читать полностью…

سماحة الإسلام የኢስላም ገራገርነት

አላህን ፈሪዋ ሴት ታሪክ ክፍል አምስት _______
/channel/httpstmejoinchatAAMuktarhussen
ሁሉም በአንድ ላይ በአንድ ቀን የአላህ ፍቃድ ሆነና ተያይዘው እሷ ዘንድ ደረሱ
።እሷም ታሪካዊ ጠላቶቿን ገና ከመድረሳቸው ሁሉንም አዉቃቸዉ ነበር ።እናም
ሁሉንም በአንድ ላይ ግቡ አለቻቸው ።እሷ ከመጋረጃ ጀርባ ስለነበረች አትታይም
።አትታወቅም ሁሉንም ከገቡ በኃላ እንዲህ አለች ፤<<ስራዉን ያጋለጠ ዱአ
ይደረግለታል ።እያንዳንዳችሁ እንዴት እንዲህ አይነት በሽታ ሊያጋጥማችሁ
እንደቻለ ተናገሩ ፤ችግሩን ያልተነገረ መፍትሄ አይገኝለትም ዱአም
አላደርግለትም>>ትላለች። በዚህ ግዜ የባለቤቷ ወንድም<<እኔ ጥፋቴን
በወንድሜ ፊት አልናገርም አፍራለሁ ወንድሜ ባለበት አልናገርም >>ሲል
ወንድሙ <<ምንም አይደል ተናገር የአንተን መዳን ነው የምፈልገው >>አለው
አልናገርም ተናገር አልናገርም ተናገረ እየተበበለ በመጨረሻ ደፍሮ <<እንግዳውስ
ይቅርታ አድርግልኝ ሚስትህን ያባረርኳት እኔ ነኝ፤ደብድቤያታለሁ፣በህይወት ትኑር
ትሙት አላዉቅም ።ላንተ ትነግርብኛለች በሚል ስጋት ዝሙት እንደሰራች
አስመስክሬባታለሁ>>በማለት ራሱን አጋለጠ ።ወንድምያዉ ምን ያክል ሊሰማዉ
እንደሚችል መገመት ይከብዳል ።ያልጠበቀው አሳዛኝ መርዶ ሲያረደዉ በድንጋጤ
እንደ እንጨት ደርቆ ቀረ።። ከዚያም ምስክሮቹም እንዲሁ ገንዘብ ሰጥቶን በሀሰት
መስክሩ ብሎን ከመሰከርን በኃላ ነው ለዚህ አይነት ችግር የተጋለጥነዉ በማለት
ራሳቸውን ያጋልጣሉ ።
ሌላዉም በተራው አንዲት ሴት አስፈራራለሁ ብሎ ህፃን ልጅ እንደገደለና ሌላ
እንደማያውቅ ተናገረ ።ሌለው ደግሞ ከሞት የዳነችውን ጨዋይቱን ሴት
300(ሶስት መቶ ዲናር)የሸጠ መሆኑን ና የገዛትም እንደዚሁ ባሪያዬ ናት ብሎ
ሲስማት በመርከቡ መገልበጡን ከዛ ዉጭ ምንም እንደማያዉቁ-----ሁሉንም ተራ
በተራ ካናዘዘች በኃላ ማንነቷን ሳትነግረዉ ከሀጅ የመጣውን ባለቤቷን ወደ
መጋረጃው ውስጥ (እሷ ወዳለችበት ክፍል )እንዲገባ ትነግረዋለች ።እሱም
ተስፋ ቆርጦ ስለነበር ባለቤቴ ትሆናለች የሚል እሳቤም ስላልነበረው <<እኔ
አጅነቢ ጋር አልገባም >>ይላል::__________ክፍል ስድስት እና የመጨረሻው
ክፍል በአላህ ፍቃድ ነገ ይቀጥላል ሼር አድርጉ።

Читать полностью…

سماحة الإسلام የኢስላም ገራገርነት

የአላህ መልእክተኛ ነቢዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል
የአማኝ የሆነ ሰው ነገሩ ያስገርማል (ግሩም)ነው አማኝ የሆነ ሰው ነገሩ ሁሉ
የተሻለ ነው
ይህ ኸይር ነገር ለአማኝ ካልሆነ ለማንም አይሆንም
ሚያስደስት ነገር ሲያገኘው አላህን ያመሰግናል ለሱ የተሻለ ነው ችግር
ሲገጥመው ይታገሳል ይህ ለሱ የተሻለ ነው።
መልካም ነገር ሲያገኙ ከሚያመሰግኑ ሲቸገሩ ከሚታገሱ ወንጀል ላይ ሲወድቁ
ምህረት ከሚጠይቁ ባርያዎች ያድርገን አላሁ አሚን።

Читать полностью…

سماحة الإسلام የኢስላም ገራገርነት

__ አላህን ፍሪዋ ሴት ታሪክ ክፍል አንድ ____
በበኒ እስራኤል ዘመን የነበረች የአንድ ሰው ሚስት ታሪክ ሲሆን ወደ ሀጅ ለመሄድ
አሰብና የሚወዱትን ባለቤቱን ብቻዋን ስለነበረች አይዞሽ እንዲላትና ችግር
እንዳይደርስባት በቅርብ የነበረው ወንድሙን አደራ በማለት ይሄዳል ።ከቀናት በኃላ
አጅነብይ ነበርና ሰይጣን በዚያም በዚህ ብሎ ያልሆነ ነገር እንዲጠይቃት
ይወሰዉሰዋል።እሱም ስሜቱንና የሰይጣኑን ጉትጐታ መቋቋም አቅቶት የወንድሙን
አደራ በመጣስ ያልሆነ ነገር ሲጠይቃት ሴትዮዋ በሀይመኖቷ ጠንካራ ነበረችና
<<የወንድምህን አደራ አትብላ ከሌባ ጠብቅ ብትባል አንተው ሌባ ትሆናለህ
>>በማለት ቁርጥ አቋሟን ስትነግረው ፣እንደማትቀመስ ስታስረዳዉ ዝሙት
ፈፅማለች በማለት ክብርሽን በማጉደፍ አዋርድሸለሁ እያለ ለማስፈራራት
ቢሞክርም እሷ ግን የፈለከውን ነገር አድርግ አላህ ምንግዜም ከእኔ ጋር ነው
አለችው ።የፈለገው ነገር ባለመሳካቱ ለግዜው በፊቷ አፍሮ ቢመለስም ሰይጣን
አቅጣጫውን ቀይሮ ላይሆንልህ ነገር ጠይቀህ ቀርቶብህ ቢሆን ይሻልህ ነበር
ወንድምህ ሲመጣ ልትነግርብህ ነው ያንተ ነገር አለቀለት ዋልህ ባይሆን
መፍትሄው ልንገርህ ዝሙት ስትሰራ አገኘኃት በልና ደብድባት፤ህይወቷ
እንዳይተርፍ አድርገህ በመደብደብ ከቤት አዉጥተህ ሌላ ቦታ ለብልግና ሄዳ
ችግር እንደደረሰበት በማስመሰል ሌላ ሰፈር ወስደህ ጠላት ሲለው ምክሩን
በመተግበር እንዳለው ያደርጋል ።ከዚህም በኃላ ከቤት ወጥታ እንደባለገች
በማስወራት የሀሰት ምስክር ሁለት ሰዎችን ቀጥሮ እየወጣች ታድራለች፤ከብዙ
ሰዎች ጋር ስትማግጥ አይተናታል ብለው እንዲመሰክሩ በማድረግ ወንድሙ
ሲመጣ ለማሳመን ይበጀናል ያለዉን መረጃ ሁሉ ይዞ ይጠብቀዋል ።እሷም
ከወደቀችበት መንደር ላይ ስታንቋርር(ስታጣጥር) ያየ ሰው ሁኔታዋ አሳዝኖት
ከወደቀችበት አንስቶ እቤቱ ይወስዳታል ____እንሻ አላህ ክፍል ሁለት ነገ
ይቀጥላል ሼር ይደረግ ።

Читать полностью…

سماحة الإسلام የኢስላም ገራገርነት

(........ምናባዊ ጉዞ ወደ አርሽ.......)
ክፍል አምስት
ሌላ ዐለም.....፣ ግሩም ፍጥረት...፣አስደማሚ ትዕይንት...በዚህ ሁኔታ ሳለን
አንዲት ትልቅ ዛፍ ተመለከትን
ሲድረቱል ሙንተሀ ትሰኛለች። የዝሆን ጆሮዎች በሚመስሉ ቅጠሎች ተውባ
የምትታየው ይህች ዛፍ ከስሯ አራት ጅረቶች ስንመለከት ዐጀ....ብ!!! እያልን
ሚስጥሩን ማጤን ጀመርን።
በመጨረሻም ሁለት ጅረቶች ወደ ጀነት የሚፈሱ እና ሁለቱ ደግሞ አባይ እና ፉራታ
መሆናቸውን ስንሰማ፦" ሱበሀነከላሁመ እያልን ትተን አለፍን። (አባይ ግን
አይገርምም....? አባይ ሁለት እዚህ መገደብ አዋጭ ነው።)
ጉዞው ቀጥሏል....በመንገዳችን የምናስተውላቸው ድንቃድንቆች ቆመን
እንድንመለከት ቢያስገድዱንም ከግዜው አንፃር ጉዞውን መርጠናል።
11: 40 ሆኗል.....
ጉዞአችን ቀጥሏል...፣ አይኖቻችን ሌላ እንግዳ ነገር እየጠበቁ ነው...፣ አራት
ግዙፍ መላዕክት ይታዩናል። የቁመታቸው መርዘም የእግራቸውን ማረፊያ እንዳናይ
አድርጎናል። ለአራት የቆሙት መላዕክት ለእያንዳንዳቸው አራት.....አራት ፊቶች
አሏቸው። የሰው፣ የአንበሳ፣ የአሞራ፣ የበሬ...
ፍርሀታችን ጨመረ....፣ ዙሪያችንን ስንቃኝ በተመለከትነው በህር አማካይነት
ያለነው ኩርስይ ላይ መሆናችንን አረጋገጥን።
የመላዕክቱ ገፅታ አሸብሮን ዳግም አስተዋልን ስንመለከታቸው፤ ምድርንና
ሰማያትን ከበው እንደቆሙ አረጋገጥን በግንባራችን ለጌታችን ልዕልና ተደፋን።
ፍጥረተ አለሙን ከበው የቆሙትን መላዕክቱን ስንመለከት፤ ፍጥረተ ዐለሙን
ውስብስብነት በግልፅ ተረድተን ዳግም ጉዞአችንን ቀጠልን።
11: 45 ሆኗል.....
አሁን የጉዞአችን መቋጫ እየተቃረበ ይመስላል። ውዳሴ እና ቅዳሴዎች በዝግታ
ከርቀት ይደመጣል። ከብዙ ጉዞ በሗላ አራት ግሩም ውቅያኖሶች ክብ ሰርተው
በቅደመ ተከተል አንድን አካል ከበውታል።
ወቅያኖሶቹ በምድር ህይወት እንደምገምታቸው ሳይሆኑ፤ ሌላ ገፅታ ይዘው ነው
ያገኘናቸው። አንዱ ውቅያኖስ ከብርሀን የተሰራ ሲሆን እያብረቀረቀ አከባቢው ላይ
አስደማሚ ድባብ ፈጥሮለታል።
ሁለተኛው ውቅያኖስ እጅግ የሚያስፈራ ሲሆን ከሚንቀለቀል እሳት ነው የተሰራው
ማዕቀላቱ ያስፈራሉ።
ሶስተኛው ከነጭ ግግር በረዶ ሲሆን ነፀብራቁ አይናችንን ሊያጠፋ ተቃርቧል።
አራተኛው የውሃ ውቅያኖስ ውበቱ Wow ያሰኛል።
በዚህ ውቅያኖስ መሀከል የቆሙትን ስምንት መላዕክት ስንመለከት አንድ ነገር ትዝ
አለን። ሱረቱል ሀቃህ ላይ ስምንት መላዕክት ዙፋኑን እንደሚሸከሙ ያወሳልንን
ስናስታውስ ሁላችንም አንገታችንን ወደ ላይ ከፍ አደረግን...።
የጌታችንን ዐርሽ በውበት፣ በግርማ ሞገስ እና ክብር ተመለከትነው። ለአላህ
ክብር ዳግም በግንባራችን ተደፋን።
ከሱጁድ ተነስተን ዙሪያውን ስንቃኝ፤ መላዕክት በ70.000 ረድፍ ሆነው ዐርሹን
እየጠወፉት ተመለከትን።
የጌታቸውን ዙፋን በውዳሴ የሚዞሩት መላዕክቱ አንዱ ዙር ከዞሩ በሗላ ፊት ለፊት
ሲገጣጠሙ፦"ላ ኢላሀ ኢላ'ላህ" የሚሉት መስጦን በግርምት ስንመለከታቸው፤
ከበስተጀርባው ያሉ ሌላ በ70.000 ረድፍ የቆሙት መላዕክት የነዚያን ታህሊል/ላ
ኢላሀ ኢላ'ላህ ሲሰሙ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው፦"ጥራት ከምስጋና ጋር ላንተ
የተገባ ይሁን፤ አንተ ያ ካንተ ሌላ አምላክ የሌለው ጌታ ነህ። የላቅከው እና
የፍጥረትም አለኝታ አንተ ብቻ ነህ" ሲሉ ትኩረታችንን ወደ እነሱ አደረግን።
ከእግር እስከ ራሳቸው ያለው የሰውነታቸው ክፍል በተለያዪ ዜማዎች አላህን
ሲያወድሱ ለስፍራው ለየት ያለ ድባብ ፈጥሮለታል...
ይቀጥላል....

Читать полностью…

سماحة الإسلام የኢስላም ገራገርነት

ለውዷ_ሙስሊሟ_እህቴ .....
ሸኽ ሷሊህ አልፈውዛን ሀፊዘሁላህ እንዲህ ይላሉ፦
# እህቴ_ሆይ_ልብ_በይ !
⫸ ሂጃብ እኮ መርዛማ ከሆኑ እይታዎች ይጠብቅሻል!
⫸ከበሽተኛ ልብ እና ከሰው ውሾች የመነጨ እይታ ይከላከልልሻል!
⫸የአሳዳጆችን ክጀላ ካንቺ ላይ ይቆርጣል
☞ ስለዚህ ሂጃብሽ እንዳይለይሽ
☞ ለአዘናጊዎች ጥሪ ጆሮሽን አትስጪ
☞ሂጃብን የሚዋጉ የሆኑትን ጥሪ (አትስሚ)
☞ ወይም ጉዳዩን የሚያቃልሉትን ጥሪ (አትስሚ)
☞ እነሱ ላንቺ መጥፎን ይፈልጉልሻልና!!
አላህ እንዲህ እንዳለው
﴿ ﻭَﻳُﺮِﻳﺪُ ﺍﻟَّﺬِﻳﻦَ ﻳَﺘَّﺒِﻌُﻮﻥَ ﺍﻟﺸَّﻬَﻮَﺍﺕِ ﺃَﻥْ ﺗَﻤِﻴﻠُﻮﺍ ﻣَﻴْﻠًﺎ ﻋَﻈِﻴﻤًﺎ ﴾ .“
﴾ እነዚያ ስሜታቸውን የሚከተሉት ደግሞ ከባድ የሆነን መዘንበል እንድትዘነበሉ
ይፈልጋሉ! ﴿
【ከተንቢሀት ኪታብ የተወሰደች】

Читать полностью…

سماحة الإسلام የኢስላም ገራገርነት

ነብዩ ረህማ (የእዝነት ነብይ ስንል በምክንያት ነው)
ትልቁን ማሳያ እንመልከት
የትኛውም ነብይ ከህዝቦቹ ስቃይ ሲደርስበት የሚያደርገው አላህም ወድያው
ምላሽ የሚሰጠው የሆነ ዱአ አለ ይህ ዱአ ሁሉም ነብይ ተጠቅሞበታል ለዚህም
ብዙ ማስረጃ አለ የኛው የእዝንት ነብይ ሲቀር ዱንያ ላይ አልተጠቀሙበትም
ስቃይ እየደረሰባቸው በትእግስት አለፉ ለምን?
ምክንያቱም ለህዝባቸው ዱአ የሚያደርግ እንጂ ህዝባቸው ላይ ዱኣ የሚያደርግ
ልብ የላቸውም
ታድያ አጋጣሚውን ምን አደረጉት ??
አጋጣሚውንማ ለኡመታቸው ሸፈአ ይለምኑበት ዘንድ ለአኺራ አሸጋገሩት የኔውን
ስቃይ እችለዋለው የኡመቴን ስቃይ ግን ማየት አልችልም ብለው ሳይጠቀሙበት
ለጭንቁ ቀን አሸጋገሩት
ህዝባቸውን ያማልዱበት ዘንድ ለአኺራ ሸሽገው አስቀመጡት
ህዝባቸው እየቀጣቸው ለህዝባቸው የነገ ጭንቀት ማቅለያ ይሆን ዘንድ ዱአቸውን
ለኡመታቸው አስቀመጡት
ለአለማት እዝነት ቢሆን እንጂ አልላክንህም
አላሁመ ሰሊ ወሰሊም አላ ነቢዪና ሙሀመድ
ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም

Читать полностью…

سماحة الإسلام የኢስላም ገራገርነት

ምላሱን እና ብልቱን የጠበቀ ሰው
ጀነት ገባ
ነቢዩ ﷺ ስለአሏሁ አለይሂ ወሰለም
(ቲርሚዚ ዘግበውታል)

Читать полностью…

سماحة الإسلام የኢስላም ገራገርነት

ነብያችን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል: –
~
"አሸናፊውና የላቀው አላህ የጨለማውን ዘመን ኩራትና በአባቶች መጎረርን
አስወግዶላችኋል።
(ሰዎች ወይ):
★ አማኝ አላህን ፈሪ ናቸው።
★ ወይ አመፀኛ መናጢ ናቸው።
እናንተ የኣደም ልጆች ናችሁ።
ኣደም ከአፈር ነው።
ሰዎች የጀሀነም ከሰል በሆኑ ወገኖች መጎረራቸውን ያቁሙ ካልሆነ ግን
አላህ ዘንድ መጥፎ ሽታን በአፍንጫዋ ከምትገፋው 'ኩስ አንከብል' ጥንዚዛ
የወረዱ ይሆናሉ።"
[አቡ ዳውድ: 5116]

Читать полностью…

سماحة الإسلام የኢስላም ገራገርነት

አስፈላጊ ስለሆነ ይነበብ ሼርርር አድርጉት!!
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
እሰኪ አንድ ጥያቄ ልጠይቃችሁ፦
1.ሶላት ላይ ተሽሁድ ስንቀመጥ የምንለዉ
’’ አተሂያቱ ’’ ትርጉም ምን እንደሆነ የምናዉቀዉ ስነቶቻችን ነን?
’’አታህያቱ’’ በእለት ተእለት ሰላታችን ዉስጥ
የምንፈፅመዉ ምርጥ ዱአ ነዉ፡፡እኔ አተሂያቱ ተሽሁድ ላይ ስቀራ በጣም ሃሴት
ይሰማኛል፡፡ምክኒያቱም ከንግግሮች ሁሉ የላቀ ንግግር፤
በፈጣሪያችን አላህ(ሱወ) እና ለአለማት እዝነት በሆኑት ሃቢቡና ሙሰጠፋ ሰለዋቱ
ረቢ ወሰላሙን አለይሒ መካከል የተደረገ እዝነትና መተናነስ የተሞላበት እፁብ
ድንቅ ንግግር በመሆኑ ነዉ፡፡ይህም ነቢያችን ( ሰለላሁ አለሂ ወሰላም ) በኢሰራዕ
ወል ሚዕራጀ ጉዞዋቸዉ ወቅት ነበር፡፡
ትርጉሙም እነደሚከተለዉ ነዉ፡-
ነቢያችን ( ሰለላሁ አለሂ ወሰላም) በኢሰራዕ ወል ሚዕራጀ
ጉዞዋቸዉ ወቅት አላህ (ሱወ) ሲገናኙ አሰላሙአለይኩመ አላሉትም ምክኒያቱም
አላህ(ሱወ) ከኛ የሰላም ምኞት የተብቃቃና የሠላም ሁሉ ምንጭ በመሆኑ ይህ
ሰላምታ አይገባዉም፡፡እናም ነቢያችን ( ሰለላሁ አለሂ ወሰላም)እነዲህ ነበር ያሉት
’’አተሂያቱሊላሂ ወሰለዋቱ ፤ ወጠይባ’’ ’’ .....ክብር ሁሉለአላህ ነዉ፡፡ሰላቶች እና
መልካም ተግባራቶችም ለአላህ ሲባል የሚደረጉ ናቸዉ አሉ::
አላህም፤- መለሰላቸዉ ’’አሰላሙ አለይካ አዩሀነቢዩ
ወራህመቱላ ወበረካቱ’´ ’’አነተ ነብይ ሆይ! ሰላም
ባንተ ላይ ይዉረድ፡፡ የአላህ እዝነትና ዉዴታም ይስፈንብህ፡፡ አለ
ነቢያችን (ሰለላሁ አለሂ ወሰላም ) እንዲህ በማለት መለሱ፤-
’አሰላሙ´አለይና ዋኣላ ኢባዲላሂ አሳሊሂነ’’´
በእኛ እና በአላህ ቅን ባሪያዎችም ላይ ሰላም ይስፈን፡፡አሉ ይህንን የሰላምታ ቃለ
ምልልስ እየሰሙ የነበሩ መላይካዎች እንዲህ አሉ፤-
’’አሽሃዱ አንላኢላሃኢለላህ ዋአሽሃዱ አነ
ሙሃመደን አብዱሁ ወረሱሉሁ’’´ ’’ከአላህ ዉጪ ሌላ
አምላክ እንደሌለ እመሰክራለሁ፡፡ ሙሃመድም የአላህ
ባሪያና መልዕክተኛዉ እነደሆነ አመሰክራለሁ፡፡ አሉ
እንግዲህ ይህ ነዉ በጌታችንና በነቢያችን (ሰዐወ)
መካከል የተደረገዉ የሰላምታ ልዉዉጥ፡፡ጥበብ
የተሞላበት የነቢያችን ኡመትን ሁሉ ያካለለ ቅዱስ ንግግር ነዉ፡፡ልብ ብላችሁ
ከሆነ አላህ (ሱወ)’’ ነብይ ሆይ! ሰላም ባነተ ላይ ይዉረድ፡፡ የአላህ እዝነትና
ዉዴታም ይስፈንብህ፡፡ ሲላቸዉ በእኛ እና በአላህ ቅን ባሪያዎችም ላይ ሰላም
ይስፈን፡፡ ነበር ያሉት ነቢያችን በእኔ ላይ ሰላም ይስፈን አላሉም
ይልቁንስ በእኛ የሚለዉን ቃል ነዉ የተጠቀሙት፡፡ለዚህም ነዉ ተሸሁድ ስቀመጥ
አታህያቱን ስቀራበተመስጦ የምቀራዉ፡፡ከዚህ በፊት ትረጉሙን የማታዉቁ ሰዎች
ካሁን በሑዋላ እነደኔ አይነት ስሜትይኖራችሁዋል ብየ አሰባለሁ፡፡ወሰላሙ
አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱ።
ፁሁፉ ኮፒ ነው ስዞር የገኛሁት ነው ጠቃሚ በመሆኑ ለእናንተ ለመክፈል ወደድኩ
አንድ አንድ የፁሑፍ ማስተካከያ አድርጌያለሁ።

Читать полностью…

سماحة الإسلام የኢስላም ገራገርነት

"በአላህ እና በመጨረሻው ቀን (መምጣት )ያመነ
መልካምን ይናገር ወይም ዝም ይበል "
ነብዩ ሙሀመድ (ሰአወ)

Читать полностью…

سماحة الإسلام የኢስላም ገራገርነት

ቀልብህ እንዲለሰልስ ከፈለግክ ዳሃን መግብ፣
የየቲምን ራስ ዳብስ (የቲምን እርዳ)»።
★彡 ረሱል (ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) 彡★
ምንጭ፦ ሶሒሁል ጃሚዕ (1410)

Читать полностью…

سماحة الإسلام የኢስላም ገራገርነት

ሚስት እንዳገባ ተመኘሁ ፡ አገባሁም
ግን ትዳር ያለ ልጆች አያምርምና ፡ ልጅ እንዲሰጠኝ ተመኘሁ፡ ልጆችም አገኘሁ።
ትንሽ ሳልቆይ የቤቱ ግድግዳ እይታው ሰለቸኝ፡
ሌላ ሰፊ ቤትም እንዲኖረኝ ተመኘሁ፡ ከብዙ ልፋትና ትጋት በኋላም ቤቱን አገኘሁ፡
ልጆቼ ግን አደጉ!
እንዲያገቡም ተመኘሁ፡ እነሱም አገቡ፡ ስራዬ ግን እያደከመኝ መጣ ፡ አስጠላኝ!
ጡረታ መውጣት አማረኝ ፡ ትንሽ ቆይቼም ወጣሁ ፡ህይወትም መልሳ አስጠላችኝ
፡ ልክ ገና አሁን ስራ ምፈልግ መሰለኝ!
ልዩነቱ ግን ያኔ ወደ ህይወት እየመጣሁ ነበር ፡ አሁን ግን ልሰናበታት ነው፡
አሁንም ግን ምኞቴን አልጨረስኩም!
☞ # ቁርኣን መሀፈዝ ተመኘሁ፡ ትውስታዬ ግን ከዳኝ
☞ # ለአላህ ፊትም መጾም ተመኘሁ፡ ጤናዬ ግን አልቻለም
☞ # ለሊቱን ቆሜ መስገድ ተመኘሁ፡እግሮቼ ግን እኔንም ማቆም አልቻሉም
እኔም ረሱል ( ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ ) ያለውን አስታወስኩ፥
5 ነገር ከ 5 ነገር አስቀድም(ተጠቀምበት)
➊)ጡንቻክን ከ ድካም
➋)ጤናክን ከ ህመም
➌)ንብረትክን ከ ማጣት
➍)ሰፊ ጊዜክ ከ መጥበብ
➎)ኑሮክን ከ ሞትክ
ስለዚህ ለምን አላህን አትፈራም? ለምንስ ወደ አላህ አትመለስም? መካሪ
አልመከረህም? አስታዋሽ አላስታወሰህም? ሰው ሲሞት በአይንህ
አልተመለከትክም? ቀብር አልጎበኘህም? ወዳጅ ዘመዶችህን አልቀበርክም?
ዛሬ ሒጃብ በሥርኣት አልለብስ ያለው ገላ ነገ ከፈንን በግድ ይለብሳል፡፡
ዛሬ መሬት ላይ ሥርኣት ያልያዘን ወጣት ነገ መሬት ሥር መቃብር ሥርኣት
ያስይዘዋል፡፡
እንደ ዩሱፍ መሸሽ የሚችል ወጣት ጠፋ!
እንደ መርየም ለንጽህናዋ የምትጨነቅ ሴት ታጣች፡፡
አንድ ቀን እስከመጨረሻው ትሄድና አትመለስም ይሆናል።
አንድ ቀን አይኖችህ እስከዘላለሙ ጨፍነው ይቀሩ ይሆናል። በዚያን ጊዜ
ከቀናቶች በኋላ ሁሉም ሰው ይረሳህ ይሆናል።
ለጀነት አልጓጓህም ሑረል አይን አልናፈቀችህም?
ሁላችንም ወደ አላህ እንመለስ

Читать полностью…

سماحة الإسلام የኢስላም ገራገርነት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡
7፥3 *ከጌታችሁ ወደ እናንተ የተወረደውን ተከተሉ*። ﺍﺗَّﺒِﻌُﻮﺍ ﻣَﺎ ﺃُﻧﺰِﻝَ ﺇِﻟَﻴْﻜُﻢ ﻣِّﻦ ﺭَّﺑِّﻜُﻢْ
ዘመን መለወጫ የሚባል በዓል በኢሥላም ውስጥ የለም። ሙሥሊም ያሉት
ዓመታዊ በዓል ሁለት ብቻ ናቸው፥ እነርሱም ዒዱል ፊጥር እና ዒዱል አድሓ
ናቸው፦
ሡነን አቢ ዳዉድ መጽሐፍ 2, ሐዲስ 745
አነሥ ኢብኑ ማሊክ እንደተረከው፤ የአላህ መልእክተኛም ” ﷺ ” መዲና ሲገቡ
የመዲና ሠዎች የሚደሰቱባቸው ሁለት በዓላት እንዳሏቸው አወቁ። እርሳቸውም
እነዚህ ሁለቱ ቀናት ምንድን ናቸው? በማለት ጠየቁ፤ ሰዎችም በጃሂሊያ ጊዜ
እንጫወትባቸው የነበሩ በዓላት ናቸው አሏቸው። የአላህ መልእክተኛም ” ﷺ ፦”
*”አላህ ከእነርሱ የተሻሉ ሁለት ዒዶችን ሠጥቷችኋል፤ እነርሱም፦ ዒዱል ፊጥር
እና ዒዱል አድሓን። አሏቸው”*። ﻋَﻦْ ﺃَﻧَﺲٍ، ﻗَﺎﻝَ ﻗَﺪِﻡَ ﺭَﺳُﻮﻝُ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ
ﺍﻟْﻤَﺪِﻳﻨَﺔَ ﻭَﻟَﻬُﻢْ ﻳَﻮْﻣَﺎﻥِ ﻳَﻠْﻌَﺒُﻮﻥَ ﻓِﻴﻬِﻤَﺎ ﻓَﻘَﺎﻝَ ” ﻣَﺎ ﻫَﺬَﺍﻥِ ﺍﻟْﻴَﻮْﻣَﺎﻥِ ” . ﻗَﺎﻟُﻮﺍ ﻛُﻨَّﺎ ﻧَﻠْﻌَﺐُ ﻓِﻴﻬِﻤَﺎ ﻓِﻲ
ﺍﻟْﺠَﺎﻫِﻠِﻴَّﺔِ . ﻓَﻘَﺎﻝَ ﺭَﺳُﻮﻝُ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ ” ﺇِﻥَّ ﺍﻟﻠَّﻪَ ﻗَﺪْ ﺃَﺑْﺪَﻟَﻜُﻢْ ﺑِﻬِﻤَﺎ ﺧَﻴْﺮًﺍ ﻣِﻨْﻬُﻤَﺎ ﻳَﻮْﻡَ
ﺍﻷَﺿْﺤَﻰ ﻭَﻳَﻮْﻡَ ﺍﻟْﻔِﻄْﺮِ ” .
ጃሚዒ አት-ቲርሚዚህ መጽሐፍ 8, ሐዲስ 121
ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው የአላህ መልእክተኛም ” ﷺ ” እንዲህ አሉ፦
*“ዒዱል ፈጥር ሰዎች ጾም የሚፈቱበት ነው፤ ዒዱል አደሐ ደግሞ መስዋዕት
የሚያቀርቡበት ቀን ነው”*። ﻋَﻦْ ﻋَﺎﺋِﺸَﺔَ، ﻗَﺎﻟَﺖْ ﻗَﺎﻝَ ﺭَﺳُﻮﻝُ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ “
ﺍﻟْﻔِﻄْﺮُ ﻳَﻮْﻡَ ﻳُﻔْﻄِﺮُ ﺍﻟﻨَّﺎﺱُ ﻭَﺍﻷَﺿْﺤَﻰ ﻳَﻮْﻡَ ﻳُﻀَﺤِّﻲ ﺍﻟﻨَّﺎﺱُ ”
ጃሚዒ አት-ቲርሚዚህ መጽሐፍ 8, ሐዲስ 91
አቡ ሰዒደል ኹድሪይ እንደተረከው፥ የአላህ መልእክተኛም ” ﷺ ” ”* በሁለቱ በዓል
በዒደል አደሐ እና ዒደል ፈጥር መጾም ከልክለዋል”*። ﻋَﻦْ ﺃَﺑِﻲ ﺳَﻌِﻴﺪٍ ﺍﻟْﺨُﺪْﺭِﻱِّ، ﻗَﺎﻝَ
ﻧَﻬَﻰ ﺭَﺳُﻮﻝُ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ ﻋَﻦْ ﺻِﻴَﺎﻣَﻴْﻦِ ﻳَﻮْﻡِ ﺍﻷَﺿْﺤَﻰ ﻭَﻳَﻮْﻡِ ﺍﻟْﻔِﻄْﺮِ .
”ዒድ“ ﻋِﻴﺪ የሚለው ቃል “ዓደ ” ﻋَﺎﺩَ ማለትም “ተመላለሰ” ከሚል ሥርወ-ቃል
የመጣ ሲሆን “ምልሰት” ማለት ነው፥ ይህ “መደሰቻ” ወይም “በዓል” በየዓመቱ
ስለሚመላለስ ይህንን ስያሜ አግኝቷል። ስለዚህ ከአላህ የወረዱትን ቁርኣን እና
ሐዲስ ብቻ መከተል አለብን፦
7፥3 *ከጌታችሁ ወደ እናንተ የተወረደውን ተከተሉ*። ﺍﺗَّﺒِﻌُﻮﺍ ﻣَﺎ ﺃُﻧﺰِﻝَ ﺇِﻟَﻴْﻜُﻢ ﻣِّﻦ ﺭَّﺑِّﻜُﻢْ
“ ተከተሉ” የሚለው ቃል “ኢተቢዑ ” ﺍﺗَّﺒِﻌُﻮﺍ ሲሆን “ኢትባዕ ” ﺇِﺗْﺒَﺎﻉ ማለት ከአላህ ወደ
”ነቢያችን ﷺ ” የተወረደውን ብቻ መከተል ማለት ነው። ሙሥሊም የተወረደውን
ብቻ ሲከተል ሁለት ብቻ ዒድ ያከብራል። ከዚህ ውጪ በዓል እያሉ ማክበር
ቢድዓህ ነው፥ “ቢድዓህ ” ﺑِﺪْﻋَﺔ ደግሞ “በደዐ ” ﺑَﺪَّﻉَ ማለትም “ፈጠረ” ከሚል
ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ፈጠራ” ማለት ነው። ቢድዓህ የኢትባዕ ተቃራኒ ነው።
“ቢድዓህ” ማለት አላህ ሳያዘን እና ሳይፈቅድልን ዝንባሌአችንን ተከትለን
የምናደርገው አዲስ አምልኮ ማለት ነው፦
ኢማም ቡኻርይ : መጽሐፍ 53, ሐዲስ 7
ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው የአላህ መልእክተኛም ” ﷺ ” እንዲህ አሉ፦
“ማንኛውም ሰው ከትእዛዛችን ያልሆነ አንድ ነገር ቢፈጥር ተቀባይነት የለውም ﻋَﻦْ
ﻋَﺎﺋِﺸَﺔَ ـ ﺭﺿﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻨﻬﺎ ـ ﻗَﺎﻟَﺖْ ﻗَﺎﻝَ ﺭَﺳُﻮﻝُ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ “ ﻣَﻦْ ﺃَﺣْﺪَﺙَ ﻓِﻲ
ﺃَﻣْﺮِﻧَﺎ ﻫَﺬَﺍ ﻣَﺎ ﻟَﻴْﺲَ ﻓِﻴﻪِ ﻓَﻬُﻮَ ﺭَﺩٌّ .”
ሡነን ኢብኑ ማጃህ : መጽሐፍ 1, ሐዲስ 210
ከሲር ኢብኑብ ዐብደላህ እንደተረከው አባቱ ከአያቱ የአላህ መልእክተኛ ” ﷺ ”
እንዲህ ሲሉ ሰማው ያለው፦ “ማንኛውም ሰው የእኔን ሡናህ ሱናህ ያደረገ ከእኔ
በኃላ የእኔን ፈለግ የሚከተሉትን ሰዎች የሚያገኙትን አጅር ከእነርሱ ላይ ሳይቀነስና
ሳይጨመር ያገኛል፤
ማንም ሰው አላህ እና መልእክተኛው ያልደነገጉትን ቢድዓን ያስተዋወቀ ያንን
ፈለግ የተከተሉትን ሰዎች የሚያገኙትን ኀጢአት ከእነርሱ ላይ ሳይቀነስና
ሳይጨመር ይሸከማል። ﺣَﺪَّﺛَﻨِﻲ ﻛَﺜِﻴﺮُ ﺑْﻦُ ﻋَﺒْﺪِ ﺍﻟﻠَّﻪِ، ﻋَﻦْ ﺃَﺑِﻴﻪِ، ﻋَﻦْ ﺟَﺪِّﻩِ، ﻗَﺎﻝَ ﺳَﻤِﻌْﺖُ ﺭَﺳُﻮﻝَ
ﺍﻟﻠَّﻪِ ـ ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ ـ ﻳَﻘُﻮﻝُ “ ﻣَﻦْ ﺃَﺣْﻴَﺎ ﺳُﻨَّﺔً ﻣِﻦْ ﺳُﻨَّﺘِﻲ ﻗَﺪْ ﺃُﻣِﻴﺘَﺖْ ﺑَﻌْﺪِﻱ ﻓَﺈِﻥَّ ﻟَﻪُ ﻣِﻦَ
ﺍﻷَﺟْﺮِ ﻣِﺜْﻞَ ﺃَﺟْﺮِ ﻣَﻦْ ﻋَﻤِﻞَ ﺑِﻬَﺎ ﻣِﻦَ ﺍﻟﻨَّﺎﺱِ ﻻَ ﻳَﻨْﻘُﺺُ ﻣِﻦْ ﺃُﺟُﻮﺭِ ﺍﻟﻨَّﺎﺱِ ﺷَﻴْﺌًﺎ ﻭَﻣَﻦِ ﺍﺑْﺘَﺪَﻉَ ﺑِﺪْﻋَﺔً ﻻَ
ﻳَﺮْﺿَﺎﻫَﺎ ﺍﻟﻠَّﻪُ ﻭَﺭَﺳُﻮﻟُﻪُ ﻓَﺈِﻥَّ ﻋَﻠَﻴْﻪِ ﻣِﺜْﻞَ ﺇِﺛْﻢِ ﻣَﻦْ ﻋَﻤِﻞَ ﺑِﻬَﺎ ﻣِﻦَ ﺍﻟﻨَّﺎﺱِ ﻻَ ﻳَﻨْﻘُﺺُ ﻣِﻦْ ﺁﺛَﺎﻡِ ﺍﻟﻨَّﺎﺱِ
ﺷَﻴْﺌًﺎ ” .
ሡነን ነሣኢ : መጽሐፍ 19, ሐዲስ 23
ጃቢር ኢብኑ ዐብደላህ እንደተረከው፦ የአላህ መልእክተኛ ” ﷺ ” ሑጥባቸው ላይ
እንደተናገሩት፦ “አላህ የመራውን ማንም አያጠመውም፤ አላህ ያጠመመውን
ማንም አያቀናውም። ከንግግር ሁሉ በላጩ የአላህ መጽሐፍ ነው፤ ከመመሪያ ሁሉ
በላጩ የሙሐመድ መመሪያ ነው። ከሁሉ የተጠላ ነገር ቢድዓህ ነው፤ ቢድዓህ
ሁሉ ጥመት ነው፤ ጥመት ሁሉ የእሳት ነው። ﻋَﻦْ ﺟَﺎﺑِﺮِ ﺑْﻦِ ﻋَﺒْﺪِ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﻗَﺎﻝَ ﻛَﺎﻥَ ﺭَﺳُﻮﻝُ ﺍﻟﻠَّﻪِ
ﺻَﻠَّﻰ ﺍﻟﻠَّﻪُ ﻋَﻠَﻴْﻪِ ﻭَﺳَﻠَّﻢَ ﻳَﻘُﻮﻝُ ﻓِﻲ ﺧُﻄْﺒَﺘِﻪِ ﻳَﺤْﻤَﺪُ ﺍﻟﻠَّﻪَ ﻭَﻳُﺜْﻨِﻲ ﻋَﻠَﻴْﻪِ ﺑِﻤَﺎ ﻫُﻮَ ﺃَﻫْﻠُﻪُ ﺛُﻢَّ ﻳَﻘُﻮﻝُ ﻣَﻦْ ﻳَﻬْﺪِﻩِ
ﺍﻟﻠَّﻪُ ﻓَﻠَﺎ ﻣُﻀِﻞَّ ﻟَﻪُ ﻭَﻣَﻦْ ﻳُﻀْﻠِﻠْﻪُ ﻓَﻠَﺎ ﻫَﺎﺩِﻱَ ﻟَﻪُ ﺇِﻥَّ ﺃَﺻْﺪَﻕَ ﺍﻟْﺤَﺪِﻳﺚِ ﻛِﺘَﺎﺏُ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﻭَﺃَﺣْﺴَﻦَ ﺍﻟْﻬَﺪْﻱِ ﻫَﺪْﻱُ
ﻣُﺤَﻤَّﺪٍ ﻭَﺷَﺮُّ ﺍﻟْﺄُﻣُﻮﺭِ ﻣُﺤْﺪَﺛَﺎﺗُﻬَﺎ ﻭَﻛُﻞُّ ﻣُﺤْﺪَﺛَﺔٍ ﺑِﺪْﻋَﺔٌ ﻭَﻛُﻞُّ ﺑِﺪْﻋَﺔٍ ﺿَﻠَﺎﻟَﺔٌ ﻭَﻛُﻞُّ ﺿَﻠَﺎﻟَﺔٍ ﻓِﻲ ﺍﻟﻨَّﺎﺭِ .
ከሁሉ የተጠላ ነገር ቢድዓህ ነው፤ ቢድዓህ ሁሉ ጥመት ነው፤ ጥመት ሁሉ የእሳት
ከሆነ ካየን ቢድዓህ የሚያራምድ ማንኛውም ሰው “ሙብተዲዕ ” ﻣﺒﺘﺪﺉ ይባላል።
ስለዚህ የጎርጎሳውያን ሆነ የሒጅራን ዘመን መለወጫ በዓል አድርጎ በመያዝ
እንኳን አደረሳችሁ ማለት ቢድዓህ ነው።
አሏህ ከሙብተዲዕ ፈሣድ ይጠብቀን! አሚን።

Читать полностью…

سماحة الإسلام የኢስላም ገራገርነት

# እንዴት_ታዝናለህ !...
ሌላው ለሌላ አካል እያጎበደደ፤አላህ አንተን መርጦ
እስልምናን ሰቶ ለርሱ ብቻ እንድታጎበድድ ፈቀደልህ!
እንዴት ታዝናለህ!...
ስንቱ በተከበረበት ተዋርዶ፤ረበል ዓለሚን ያንተን ወንጀልህንና ነውርህን ደብቆልህ
ለምን ታዝናለህ!...
ስንቱ ነው አንድ አፉን ሚመገበው ጎኑን
ሚያሳርፍበት ማደሪያ የሌለው፤አዛኙ ጌታህ ቤትህን በምግብና በመጠጥ
ሞልቶልህ ማደሪያ ሰጠህ
ስለምንስ ታዝናለህ!
ስንቱ ጤናውን አቶል ፤ራህማኑ አንተን ሰላም አደረገህ
አትዘን!
የሰው ፊት የሚገርፈው ሚለምን ስንቱ መሰለህ!?
ጀልሉ ግን አንተን ከሰዎች አብቃቃህ!
በፍፁም እንዳታዝን!
ከህመም ብዛት በስቃይ አይኑን ሳይከድን የተኛ ስንቱ መሰለህ!?፤ወዱዱ ላንተ
ሰላማዊ እንቅልፍን
ሰጠህ
ያጣሀውን አትመልከት ፤ያለህን ተመልከትና
(አልሃምዱሊላህ) በልና አላህም እንህ
ካላቸው ሰዎች ሁን....
" ﻭَﻗَﻠِﻴﻞٌ ﻣِّﻦْ ﻋِﺒَﺎﺩِﻱَ ﺍﻟﺸَّﻜُﻮﺭُ "
"ከባሮቼ በጣም አመስጋኞቹም ጥቂቶች ናቸው፡፡"
[ሱረቱ ሰበዕ:13]

Читать полностью…

سماحة الإسلام የኢስላም ገራገርነት

_አላህን ፈሪዋ ሴት ታሪክ ክፍል ሶስት_________
/channel/httpstmejoinchatAAMuktarhussen
ገንዘባችንን ካላመጠህ እንገድልሃለን ፣እንሰቅልሃለን እያሉ ሲያስጨንቁት የነበረ
አንድ ሰው አይታ አሳዘናትና ገንዘቡን ካላገኙ የሚገድሉት መስሏት የተሰጣትን
ገንዘብ ከመስጠት ከሞት ታድነዋለች ።ሰዉዬዉም እዳዬን ከፍለሽ ከሞት
ስላዳንሽኝ ካልሸኛሁሽ እያለ ይከተላታል።ልሸኝሽ ልከተልሽ ሲላት የአጅነቢይ ኸይር
የለዉምና አልፈልግም አለች ።እሱ ደግሞ ዉለታዋን የሚከፍል መስሎ ለሷ
አሳቢና ተቆርቋሪ በመምሰል ቢከተላትም አጅነቢ ነበርና እሱም የዋለችለትን
በመርሳትና ቃሉን በማፍረስ ቦታና ሁኔታ አመቻችቶ ብትጮህ ረዳት የማታገኝበት
ቦታ ሲደርሱ አላህ የጠላውን ነገር ይጠይቃታል ።።<<ገንዘቤን ከፍዬ ከሞት
አድኜህ ለኔ የተቆረቆርክ መስለህ የዚህ አይነት ጥያቄ ትጠይቀኛለህ ?፣ይህ ነው
ወለታዬ?በጣም አዝናለሁ ፣ጥያቄህ እንደማይሳካ ተስፋ ቁረጥ>>ትለዋለች
።ይህንኑ እየተመላለሱ ከዋናው መንገድ ዳር ደርሰው ነበርና ሰዎች ሲያገኝ
<<አንዲት ባሪያ አለችኝ ፤ልሸጣት እፈልጋለሁ ግዙኝ>>ብሎ ይጠይቃል ።ሰዉን
ባሪያ ነው ብሎ መሸጥ በጊዜው የነበረ ስርአት ነበርና ይህቺን በደለኛ ሲያዩ
ወደዷት ፤እሷም <<ባሪያ አይደለሁም >>ብትል ማን ሰምቷት፤ከእነሱ ጋር ዋጋ
ጨርሶ በ300ዲናር ይሸጣተል።ደግማደ ደጋግማ ራሷን ለማደን <<እኔ ጨዋ ነኝ
ባሪያ አይደለሁም >>ብትል <<እኛ ገዝተናል አያገባንም >>በማለት በጃልባ
ይዘዋት ይሄዳሉ ።ጀልባው ላይ ሆነዉ ባለመብት ነኝ ባዩ <<ከአሁን ጀምሮ የኔ
ባሪያ ነሽ >>እያለ ሊያቅፋትና ሊስማት እጁን ይዘረጋል ።<<አላህን ፍራ>>እያለች
ብትጮህም አትጩሂ ብሎ በጥፊ ይመታታል ።በዚህ ላይ እንዳሉ ማዕበል ተነስቶ
የነበሩበት ጀልባ ትገለበጣለች ።እሷም አላህ ጠብቋት ዋኝታ ወዳላሰበችዉና
ወደማታውቀው ባህር ዳርቻ ላይ ስትወጣ ከሷ ጋር በጀልባ የነበሩት ሰዎችም
ተበታትነው በተለያየ መንገድ ከባህሩ ይወጣሉ ።እሷ ከባህሩ በወጣችበት
አቅጣጫ አንድ አህለል ኸይር የጎሳ መሪ የሆነን ሰው ንጉሥ ታገኛለሽ።ታሪኳን
ስትነግረው በጣም ስላሳዘነችዉ ባለቤቷ ከሐጅ ተመልሶ ሀገሩ እስከሚገባ
ያለምንም ችግር ለብቻ ቤት ተሰጥቷት እንድትኖር ያደርጋል ።ቤቱ የአላህን ፈሪ
ቤት ስለነበር ተረጋግታ እየጾመች አላህን መለመን ትጀምራለች ____ክፍል
አራት በአላህ ፍቃድ ነገ ይቃጥለል ሼር ይደረግ ።

Читать полностью…

سماحة الإسلام የኢስላም ገራገርነት

«አንድ ሰው 3 ሴት ልጆች ኑረውት ከሚችለው ካበላቸው፣ ካጠጣቸው
እንዲሁም ካለበሳቸው የቂያማ ቀን ለሱ ከጀሀነም እሳት ከለላ ይሆኑለታል»።
◦•●◉✿ ነቢዩ ﷺ ስለአሏሁ አለይሂ ወሰለም ✿◉●•◦
ምንጭ:- ኢብኑ ማጀህ (2974)

Читать полностью…

سماحة الإسلام የኢስላም ገራገርነት

በአሸባሪዋ እስራኤል ውስጥ ከ1100 አመት በፊት የተቀበረ የወርቅ ሳንቲም
ተገኘ !! በሳንቲሙ ላይ
ﻻﺇﻟﻪ ﺍﻻ ﺍﻟﻠﻪ ﻣﺤﻤﺪ ﺭﺳﻮﻝ ﺍﻟﻠﻪ
ከአላህ ውጪ በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም
ሙሐመድም የአላህ መልዕክተኛው ነው። የሚል ጹሁፍ አለው !
https://www.timesofisrael.com/pure-gold-425-islamic-coins-
from-1100-years-ago-found-at-israel-dig/
ታሪክ ይናገራል ። ፍልስጤም ታሪክሽ ይህ ነው።

Читать полностью…

سماحة الإسلام የኢስላም ገራገርነት

አቢ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደነገረን፡ የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ
ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡-
"እስክታምኑ ድረስ ጀነትን አትገቡም፣ እስካልተዋደዳችሁ ደግሞ
አላመናችሁም፡፡ ታዲያ ከሰራችሁት ሊያዋድዳችሁ የሚችል ነገርን
ልጠቁማችሁን? በመሀከላችሁ ሰላምታን አብዙ"
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 1, ሐዲስ 101

Читать полностью…

سماحة الإسلام የኢስላም ገራገርነት

ኢንና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን!
Innaa Lillaahi Wa Innaa Ilayhi Raaji'un
ወንድማችን ሙነሺድ ሙሐመድ አወል ሷላህ ወደ ቀጣዩ ዓለም
ተሸጋግሯል።አላህ ይዘንልህ።በሰፊው ምህረቱ ጀነተል ፊርደውስን
ያጎናጽፍህ።አላህ ለቤተሰቦችህ መጽናናቱንና ትዕግስቱንም ይለግሳቸው።«እኛ
የአላህ ነን።ወደ እርሱም ተመላሾች ነን።»
✺✺✺✺✺✺✺✺✺✺✺✺✺✺✺✺✺✺✺✺✺✺
Obboleessi keenya munashid Muhammed Awwol Saalah gara
aakiraatti deemeera. Rabbiin siif haraaramu. Rahmata isaa
balla ta'een jannattal firdawsiin sihabadhaasu. Allaahin maati
keetiifis Obsaa fi tasgabbi hakeennuufi. "Nuti kan Rabbiiti.
Gara isaattis warra debi'uu."

Читать полностью…

سماحة الإسلام የኢስላም ገራገርነት

ከአቢ ሁረይራህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) በድጋሚ እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ
(ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡-
"በቀን ውስጥ ለመቶ ጊዜ ያህል ‹‹ሱብሐነላሂ ወቢ ሐምዲሂ›› ያለ ሰው፡
ኃጢአቱ እንደ ባሕር ዐረፋ የበዛ ቢኾንም ይሰረዛል"
(ቡኻሪይ 6042)

Читать полностью…

سماحة الإسلام የኢስላም ገራገርነት

ጫት በሀገራችን ሙስሊሞች ያደረሰው አደጋ እና ተፅእኖ !!
ይነበብ
አሰላሙ አሌይኩም ዉድ የዚህ ፁሁፍ አንባቢያን እንዴት ናችሁ
አልሃምዱሊላህ እኔ ሰላም ነኝ ይህንን ፁሁፍ አንብባችሁ ለወዳጅ ዘመዶቻችሁ እና
ጓደኞቻችሁ ሼርርር ማድረግን አትርሱ ።
ተፃፈ በሙክታር ሁሴን
እንደሚታወቀው በሀገራችን ሙስሊሞች ብዙ ነገር እየተቆጣጠረቸዉ ይገኛል

ከዚህ ዉሰጥ በዋነኝነት የሚጠቀሰው ይህ ጫት የተባለ የሚጠራው ሰዎች
ያልተረዱት አደገኛ ቅጣል ነዉ።
ጫት ማለት የሰውን ልጆች እንደ እሳት እየበላቸዉ ይገኛል ከዚህም ዉስጥ
ጫት በህብረተሰቡ ከደረሰው አደጋ ውስጥ-------
ባልና ሚስትን የፋታል
የሌለን በሽታ የመጣል
ሰዉን የሰክራል
ሰውን ለማኝ ያደርጋል
ልብስን ያቆሽሻል
ኢኮኖሚን ያወድማል
ጥርስን ይጨርሳል
ደስታህን ይነጥቃል
ወደ እብድነት ይወስዳል
ወደ ዝሙት ይወስዳል
ከእምነትህ ያርቃል
በራስ መተማመን ያሰጣል
ሚስኪን እንድትሆን ያደርጋል
እዚህ ሁሉ ጫት ከሚያመጣቸው አደጋ ነገሮች በጥቂቱ ናቸዉ ሆኖም ከዚህም
የባሰ ብዙ ጉዳትን እያስከተለ ይገኛል ።
ለምሳሌ አንድ ሰው ጫት እየበላ ከሆነ የአዛን ድምፅ በሚሰማበት ሰአት
ለሶላት የለው አቅም ወይም ተነሳሽነት በጣም የወረዳ እና የናሳ ነው ።
ምክንያቱም በአፉ የለው ጫት በብር አዉጥቶ ስላጋዘዉ ለሶላት አዛን
በሚባልበት ሰአት ጫቱን አዉጥቶ ሰላት ለመስገድ ይቸገራል ።
ከዛም በቃ ዙህርን ሰላት ከአስር
መግሪብን ከኢሻ ሰላት እያደረገ መስገድ ይጀምራል እንደዉም አብዛኛው ጫት
ቀሚ ወጣት ሰላት አይሰግድም ቢባል መግነን አይሆንም ።
ጫት በወጣቶች ዘንድ እና በሽማግሌዎች ዘንድ የለው ከአምልኮ የተገኘው
እዉነታ !!
# ጫት በሽማግሌዎች እይታ!!
በእድሜ የገፉት ወይም ደሞ አባቶቻችን ያለምንም ጥርጥር ጫት የዱረ መስሪያ
አድርገው ያዩታል በአፋቸውም ተናግረዉታል ጫት ወደ አላህ መቃረቢያ ነው
ብለው መቶ100% ያምናሉ ።
እኛ ደሞ ይህ የዱአ መስሪያ ሰይሆን የሰይጣን መስሪያ መሆኑን ለአባቶቻችን
መነገር አለብን እናንተ ቢያንስ ለወላጆቻችሁ ይህንን ዉለታ መዋል አለባችሁ ።
ጫት በወጣቱ ዘንድ !!
ጫት በወጣቱ ዘንድ የዱአ መስሪያ አድርገው የሚይዙም አሉ ግን አብዛኛዎቹ
ግዜ ማሳለፊያ እና የአራዳነት መስፈርት አድርገው ያዩታል ጫት የማይቅም ሰው
እነሱ ጋር በጣም ፋራ አላዋቂ አድርገው ይመለከቱታል ግን የዱአ መስሪያ ብለው
ልክ እንደ አባቶቻችን አያዩትም ።
# ወለሂ_እላቸዋለሁ
በእኔዉ እድሜ በጫት የተነሳ ልብሳቸውን ጥለው እብድ ሆነው የሄዱ ከአራት
ያለነሱ ሰዎችን አዉቃለሁ ።
ትናንት ጥሩ ተማሪ የነበሩ ከኔ ጋር የተማሩ ዛሬ በጫት የተነሳ ሚስኪን እና
እብድ ሆኖ ስታያቸው ምን አይነት ስሜት እንደሚሰማ አስቡት ።
ሁላችንም ቤተሰቦችን ጓደኞቻችን ዘመዶቻችንን ከዚህ እርጉም ቅጣል
ማስጠንቀቅ አለብን ።
አላህ ከእንደዚህ አይነት ቆሻሻ ሀራም ከሆኑ ነገሮች ይጠብቀን አላህ
# በተዉሂድ መንገድ አንድ ያድርገን ።
ጫት የሰይጣን ጩቤ መሆኑን በተቻለን አቅም እንንገራቸው እንደ ቀለል
አንየው በማለት መልእክቴን እዚህ ለይ አበቃሁ።
ሼርርርርርርር ማድረግን አትርሱ

Читать полностью…

سماحة الإسلام የኢስላም ገራገርነት

«ሁለት ነገሮች በሙእሚን ላይ አይሰባሰቡም ስስት እና መጥፎ ስነ-
ምግባር»።
ነቢዩ ﷺ ስለአሏሁ አለይሂ ወሰለም
ምንጭ:-[ ቲርሚዚ (1962) ዘግበውታል አልባኒ ሶሒህ

Читать полностью…

سماحة الإسلام የኢስላም ገራገርነት

ቡሄ
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡
59፥7 *መልክተኛውም የሰጣችሁን ማንኛውንም ነገር ያዙት፡፡ ከእርሱም
የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ*፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና። ﻭَﻣَﺂ
ﺀَﺍﺗَﻯٰﻜُﻢُ ﭐﻟﺮَّﺳُﻮﻝُ ﻓَﺨُﺬُﻭﻩُ ﻭَﻣَﺎ ﻧَﻬَﻯٰﻜُﻢْ ﻋَﻨْﻪُ ﻓَﭑﻧﺘَﻬُﻮﺍ۟ ۚ ﻭَﭐﺗَّﻘُﻮﺍ۟ ﭐﻟﻠَّﻪَ ۖ ﺇِﻥَّ ﭐﻟﻠَّﻪَ ﺷَﺪِﻳﺪُ ﭐﻟْﻌِﻘَﺎﺏِ
መጣና መጣና
ደጅ ልንጥና፤
መጣና ባመቱ
እንዴት ሰነበቱ፣
ክፈት በለዉ በሩን
የጌታዬን፣
ክፈት በለዉ ተነሳ
ያንን አንበሳ፣
መጣሁኝ በዝና
ተዉ ስጠኝ ምዘዝና።
እየተባለ ሆያ ሆዬ በልጅነት ያለ ዕውቀት ሙሥሊሙ ከክርስቲያኑ ጋር ተደባልቆ
የክርስቲያን ሠው ሥራሽ በዓል ሲያከብር አድጓል። “ቡሄ” ማለት “ገላጣ”
“የተገለጠ” ማለት ነው፥ በአገራችን የክረምቱ አፈና ተወግዶ የብርሃን ወገግታ
የሚታየውም በዚህ በዓል አካባቢ ስለሆነ ይህ ዕለት “ቡሄ” ተባለ። ኢየሱስ
ሦስቱን ተከታዮች ጴጥሮስንና ያዕቆብን ወንድሙንም ዮሐንስን ይዞ ወደ ረጅም
ተራራ አወጣቸው፦
ማቴዎስ 17፥1 *ኢየሱስ ጴጥሮስንና ያዕቆብን ወንድሙንም ዮሐንስን ይዞ ወደ
ረጅም ተራራ ብቻቸውን አወጣቸው*።
ይህ ተራራ የትኛው ተራራ እንደሆነ በባይብል አልተጠቀሰም። አንዳንድ ምሁራን
"አርሞንኤም ነው" ይላሉ፥ የእኛዎቹ "ታቦር ነው" ይላሉ። “ደብር” ማለት የግዕዝ
ቃል ሲሆን “ተራራ” ማለት ነው፥ የደብር ብዙ ቁጥር “አድባር” ሲሆን “ተራሮች”
ማለት ነው። “ደብረ-ታቦር” ማለት “የታቦር ተራራ” ማለት ነው፥ ይህ ቡሄ በዓል"
ደብረ-ታቦር" ይባላል።
፨ ሲጀመር በባይብል የተራራው ስም የለም፣
፨ ሲቀጥል ይህ እለት "ነሐሴ 13 ነው" የሚል የለም፣
፨ ሢሰልስ "ይህንን ቀን አክብሩ" የሚል የለም፣
፨ ሲያረብብ በዚህ ቀን ዳንኪራ ሆያ ሆዬ አድርጉ" የሚል የለም።
ይህ ሁሉ ሰው ሠራሽ ሕግ ነው። በገጠርም ሆነ በየከተማው ልጆች ጅራፋቸውን
ገምደው ሲያጮሁ ይሰነብታሉ። እናቶችም ለበዓሉ ዝግጅት ስንዴ ሲለቅሙ፣
ሲፈትጉ፣ ሲፈጩ ይሰነብታሉ። ቡሄ ለሚሉ ልጆች ሙልሙል ዳቦ በመስጠት እና
ችቦ በማብራት በዓሉን ያከብራሉ። ይህ ሁሉ ከንቱ እዚሁ የሚቀር ምድራዊ ነገር
ነው። ይህንን የክርስትና ሰው ሠራሽ በዓል ሙሥሊሙ ባለማወቅ ሲያከብረው
ኖሯል። ይህ ስህተት ነው። ነቢያችን ” ﷺ ” የነገሩን ዓመታዊ በዓል ሁለት ብቻና
ብቻ ናቸው፤ እነርሱም፦ ዒዱል ፊጥር እና ዒዱል አድሓ ናቸው፦
ሡነን አቢ ዳዉድ መጽሐፍ 2, ሐዲስ 745
አነሥ ኢብኑ ማሊክ እንደተረከው፤ የአላህ መልእክተኛም ” ﷺ ” መዲና ሲገቡ
የመዲና ሠዎች የሚደሰቱባቸው ሁለት በዓላት እንዳሏቸው አወቁ። እርሳቸውም
እነዚህ ሁለቱ ቀናት ምንድን ናቸው? በማለት ጠየቁ፤ ሰዎችም በጃሂሊያ ጊዜ
እንጫወትባቸው የነበሩ በዓላት ናቸው አሏቸው። የአላህ መልእክተኛም ” ﷺ ፦”
“አላህ ከእነርሱ የተሻሉ ሁለት ዒዶችን ሠጥቷችኋል፤ እነርሱም፦ ዒዱል ፊጥር እና
ዒዱል አድሓን። አሏቸው። ﻋَﻦْ ﺃَﻧَﺲٍ، ﻗَﺎﻝَ ﻗَﺪِﻡَ ﺭَﺳُﻮﻝُ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ ﺍﻟْﻤَﺪِﻳﻨَﺔَ
ﻭَﻟَﻬُﻢْ ﻳَﻮْﻣَﺎﻥِ ﻳَﻠْﻌَﺒُﻮﻥَ ﻓِﻴﻬِﻤَﺎ ﻓَﻘَﺎﻝَ ” ﻣَﺎ ﻫَﺬَﺍﻥِ ﺍﻟْﻴَﻮْﻣَﺎﻥِ ” . ﻗَﺎﻟُﻮﺍ ﻛُﻨَّﺎ ﻧَﻠْﻌَﺐُ ﻓِﻴﻬِﻤَﺎ ﻓِﻲ ﺍﻟْﺠَﺎﻫِﻠِﻴَّﺔِ .
ﻓَﻘَﺎﻝَ ﺭَﺳُﻮﻝُ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ ” ﺇِﻥَّ ﺍﻟﻠَّﻪَ ﻗَﺪْ ﺃَﺑْﺪَﻟَﻜُﻢْ ﺑِﻬِﻤَﺎ ﺧَﻴْﺮًﺍ ﻣِﻨْﻬُﻤَﺎ ﻳَﻮْﻡَ ﺍﻷَﺿْﺤَﻰ
ﻭَﻳَﻮْﻡَ ﺍﻟْﻔِﻄْﺮِ ” .
ጃሚዒ አት-ቲርሚዲህ መጽሐፍ 8, ሐዲስ 121
ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው የአላህ መልእክተኛም ” ﷺ ” እንዲህ አሉ፦ “ዒዱል
ፈጥር ሰዎች ጾም የሚፈቱበት ነው፤ ዒዱል አደሐ ደግሞ መስዋዕት የሚያቀርቡበት
ቀን ነው። ﻋَﻦْ ﻋَﺎﺋِﺸَﺔَ، ﻗَﺎﻟَﺖْ ﻗَﺎﻝَ ﺭَﺳُﻮﻝُ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ “ ﺍﻟْﻔِﻄْﺮُ ﻳَﻮْﻡَ ﻳُﻔْﻄِﺮُ
ﺍﻟﻨَّﺎﺱُ ﻭَﺍﻷَﺿْﺤَﻰ ﻳَﻮْﻡَ ﻳُﻀَﺤِّﻲ ﺍﻟﻨَّﺎﺱُ ”
ጃሚዒ አት-ቲርሚዲህ መጽሐፍ 8, ሐዲስ 91
አቡ ሰዒደል ኹድሪይ እንደተረከው፥ የአላህ መልእክተኛም ” ﷺ ” በሁለቱ በአል
በኢደል አደሐ እና ኢደል ፈጥር መጾም ከልክለዋል። ﻋَﻦْ ﺃَﺑِﻲ ﺳَﻌِﻴﺪٍ ﺍﻟْﺨُﺪْﺭِﻱِّ، ﻗَﺎﻝَ ﻧَﻬَﻰ
ﺭَﺳُﻮﻝُ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ ﻋَﻦْ ﺻِﻴَﺎﻣَﻴْﻦِ ﻳَﻮْﻡِ ﺍﻷَﺿْﺤَﻰ ﻭَﻳَﻮْﻡِ ﺍﻟْﻔِﻄْﺮِ .
ቡሄ የአገር ባህል ይመስለን ነበር፥ ቅሉ ግን እንደዛ አይደለም። ይህንን በዓል
መልእክተኛው ያልሰጡን ዕቡይ ተግዳሮት መሆኑን ዐውቀን መሳተፍ የለብንም።
የታሪክ ምፀት ከዐሊሞቻችን ለሚቀጥለው ትውልድ የሚሆን ሰፊ ምዕላድ ትተን
መሄድ ግድ ይለናል፥ ይህን ለማድረግ አስረግጦ እና ረግጦ መረዳትና ማስረዳት
ይጠበቅብናል። ያኔ የኢሥላም ልዕልና ለካፊሩን የልብ ፍልጠት፣ የራስ ምታት፣
የሆድ ቁርጠት፣ የጎን ውጋት እና የእግር ቁርጥማት ኢንሻላህ ይሆናል።

Читать полностью…

سماحة الإسلام የኢስላም ገራገርነት

የአሹራ ፆም ምንነት፣ ወቅት፣ ሰበብና ትሩፋት እንዲሁም የአጿጿ ሙ አይነት
የአሹራ ፆም ምንድነው ? የመፆሚያ ወቅቱስ ?

````````````````````````````````````````````````````````

የአሹራ ፆም የሚባለው ሙሀረም የተሰኘው በሒጅራ አቆጣጠር የመጀመርያው
ወር ሲሆን የአሹራ ፆሙ የሚፈፀምበት በዚሁ ወር አስረኛው ቀን ነው።
እነሆ… አሁን የጀመርነው ወር ማለት ነው።
ከላይ እንደጠቀስነው በሒጅሪያ አቆጣጠር የአመቱ መጀመሪያ ወር ሲሆን፣ አላህ
ሱብሃነሁ ወተዓላ ከአስራሁለቱ የአመቱ ወራት መካከል የተከበሩ ብሎ ከጠቀሳቸው
ከአራቱ ክቡራን ወራት አንዱ ነው ።
ይህን በማስመልከት አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ እንዲህ ይላል፦
ﺇِﻥَّ ﻋِﺪَّﺓَ ﺍﻟﺸُّﻬُﻮﺭِ ﻋِﻨﺪَ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﺍﺛْﻨَﺎ ﻋَﺸَﺮَ ﺷَﻬْﺮًﺍ ﻓِﻲ ﻛِﺘَﺎﺏِ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﻳَﻮْﻡَ ﺧَﻠَﻖَ ﺍﻟﺴَّﻤَﺎﻭَﺍﺕِ ﻭَﺍﻟْﺄَﺭْﺽَ ﻣِﻨْﻬَﺎ
ﺃَﺭْﺑَﻌَﺔٌ ﺣُﺮُﻡٌ ۚ ﺫَٰﻟِﻚَ ﺍﻟﺪِّﻳﻦُ ﺍﻟْﻘَﻴِّﻢُ ۚ ﻓَﻠَﺎ ﺗَﻈْﻠِﻤُﻮﺍ ﻓِﻴﻬِﻦَّ ﺃَﻧﻔُﺴَﻜُﻢْ ۚ
የወሮች ቁጥር አላህ ዘንድ በአላህ መጽሐፍ ውስጥ ሰማያትንና ምድርን
በፈጠረበት ቀን ዐሥራ ሁለት ወር ነው፡፡ ከእነሱ አራቱ የተከበሩ ናቸው፡፡ ይህ
ቀጥተኛው ሃይማኖት ነው፡፡ በእነርሱ ውስጥም ነፍሶቻችሁን አትበድሉ፡፡ (ሱረቱ
አል-ተውባህ - (36)
````````````````````````````````````````````````````````

የአሹራእ ፆም የሚፆምበት ሰበብ ...
አብደላህ ኢብን አባስ ረዲየሏሁ ዐንሁማ እንዳስተላለፉት: -
ነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ወደ መዲና በመጡ ጊዜ ይሁዶች የአሹራን ቀን
ሲፆሙ አገኟቸው። በዚህን ግዜ የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም
ይህ የምትፆሙት ቀን ምንድን ነው? ብለው ጠየቋቸው፡
አይሁዶችም ይህ ቀን ሙሳ በፊርዐውን ላይ የበላይነትን የተቀዳጀበት ቀን ነው አሉ

ነበዩም ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ለሰሃቦቹ
ከነርሱ ይልቅ (ከይሁዶቹ) ለሙሳ ቅርበት (ወዳጅነት) እናንተ የተገባችሁ ናችሁና
(ይህን እለት) ፁሙት ። ኣሏቸው። በዚህም ሰበብ ፆሙ ተጀመረ።
ﺳﺒﺐ ﺻﻴﺎﻡ ﻋﺎﺷﻮﺭﺍﺀ ﻭﺍﻟﺤﻜﻤﺔ ﻣﻨﻪ ﻗَﺪِﻡَ ﺍﻟﺮﺳﻮﻝ - ﺻﻠّﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠّﻢ - ﺇﻟﻰ ﺍﻟﻤﺪﻳﻨﺔ ﺍﻟﻤُﻨﻮَّﺭﺓ،
ﻓﻮﺟﺪ ﺍﻟﻴﻬﻮﺩ ﻳﺼﻮﻣﻮﻥ ﻳﻮﻡ ﻋﺎﺷﻮﺭﺍﺀ، ﻭﻋﻨﺪﻣﺎ ﺳﺄﻟﻬﻢ ﻋﻦ ﺳﺒﺐ ﺻﻴﺎﻣﻬﻢ ﺃﺟﺎﺑﻮﺍ ﺇﻧّﻪ ﻳﻮﻡٌ ﻧﺠّﻰ ﺍﻟﻠﻪ
-ﺗﻌﺎﻟﻰ - ﻓﻴﻪ ﻣﻮﺳﻰ - ﻋﻠﻴﻪ ﺍﻟﺴﻼﻡ - ﻭﻗﻮﻣﻪ، ﻭﺃﻏﺮﻕ ﻓﺮﻋﻮﻥ ﻭﺟﻨﺪﻩ، ﻭﻛﺎﻥ ﻣﻮﺳﻰ - ﻋﻠﻴﻪ ﺍﻟﺴﻼﻡ -
ﻳﺼﻮﻣﻪ؛ ﺷُﻜﺮﺍً ﻟﻠﻪ - ﺗﻌﺎﻟﻰ - ؛ ﻓﺼﺎﻣﻪ ﺍﻟﺮﺳﻮﻝ - ﺻﻠّﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠّﻢ - ، ﻭﺃﻣﺮَ ﺑﺼﻴﺎﻣﻪ، ﻓﻘﺎﻝ
ﻟﻠﺼﺤﺎﺑﺔ : ‏( ﺃﻧﺘُﻢْ ﺃﺣَﻖُّ ﺑﻤُﻮﺳَﻰ ﻣﻨﻬﻢْ ﻓَﺼُﻮﻣُﻮﺍ ‏)
````````````````````````````````````````````````````````

ዓሹራን የመጾም ትሩፋት!
በሌላም ሀዲስ ነቢዩ(ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም) (የዓሹራ ቀን ጾም ያለፈውን
ዓመት ወንጀል ያስምራል[ያስሰርዛል] ብዬ ከአሏህ ላይ ተስፋ አደርጋለሁ) ብለዋል
ﻗﺎﻝ ﺍﻟﻨﺒﻲ ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ
ﺻِﻴَﺎﻡُ ﻳَﻮْﻡِ ﻋَﺎﺷُﻮﺭَﺍﺀَ ﺃَﺣْﺘَﺴِﺐُ ﻋَﻠَﻰ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﺃَﻥْ ﻳُﻜَﻔِّﺮَ ﺍﻟﺴَّﻨَﺔَ ﺍﻟَّﺘِﻲ ﻗَﺒْﻠَﻪُ ﺭﻭﺍﻩ ﻣﺴﻠﻢ
የዓሹራ ቀን ጾም ያለፈውን ዓመት ወንጀል ያስምራል ያስሰርዛል በቀላል ስራ ይህን
የምያህል ምንዳ የሚገኝ ሆኖ ሳለ ብዙ ለአኼራቸው ግድ የለሽ የሆኑ ሰዎች
እድሉን ችላ ሲሉ እንመለከታለን።
```````````````````````````````````````

```````````

የዓሹራእ ጾም ሙሐረም ስንተኛው ቀን ላይ ነውን ?
የዓሹራእ ጾም ማለት የሙሐረም ወር 10ኛው ቀን ላይ ሲሆን ከፊቱ ወይም
ከኋላው አንድ ቀን (9ኛውን ወይም 11ኛውን) ቀን ጨምሮ መጾም ይመረጣል።
ምክኒያቱም ነቢዩ ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ዓሹራን ሲጾሙና ሷሓባዎችም
እንዲጾሙት በመከሯቸው ጊዜ አይሁዶች የሚያከብሩት ቀን እንደሆነ ለነቢዩ
(ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) ሲነግራቸው የሚከተለውን ብለዋል:- (አሏህ ካለ
የሚመጣው ዓመት ላይ 9ኛውንም ቀን እንጾማለን) ብለዋል
ﻭﺭﺩ ﻓﻲ ﺻﺤﻴﺢ ﻣﺴﻠﻢ ﻋﻦ ﺍﺑﻦ ﻋﺒﺎﺱ ﺭﺿﻲ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻨﻬﻤﺎ ﺃﻧّﻪ ﻗﺎﻝ : ‏( ﺣﻴﻦ ﺻﺎﻡ ﺭﺳﻮﻝ ﺍﻟﻠﻪ - ﺻﻠّﻰ
ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠّﻢ - ﻳﻮﻡ ﻋﺎﺷﻮﺭﺍﺀ، ﻭﺃﻣﺮ ﺑﺼﻴﺎﻣﻪ، ﻗﺎﻟﻮﺍ ﻳﺎ ﺭﺳﻮﻝ ﺍﻟﻠﻪ : ﺇﻧّﻪ ﻳﻮﻡ ﺗﻌﻈّﻤﻪ ﺍﻟﻴﻬﻮﺩ
ﻭﺍﻟﻨّﺼﺎﺭﻯ ! ﻓﻘﺎﻝ ﺭﺳﻮﻝ ﺍﻟﻠﻪ ﺻﻠّﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠّﻢ : ﻓﺈﺫﺍ ﻛﺎﻥ ﺍﻟﻌﺎﻡ ﺍﻟﻤﻘﺒﻞ ﺇﻥ ﺷﺎﺀ ﺍﻟﻠﻪ،
ﺻﻤﻨﺎ ﺍﻟﻴﻮﻡ ﺍﻟﺘﺎﺳﻊ . ﻗﺎﻝ : ﻓﻠﻢ ﻳﺄﺕ ﺍﻟﻌﺎﻡ ﺍﻟﻤﻘﺒﻞ، ﺣﺘﻰ ﺗﻮﻓّﻲ ﺭﺳﻮﻝ ﺍﻟﻠﻪ ﺻﻠّﻰ ﺍﻟﻠﻪ
ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠّﻢ ‏) ﺭﻭﺍﻩ ﻣﺴﻠﻢ
ከዚህም በመነሳት ዑለማዎች ዘጠነኛውንም ቀን መጾም ሱና ነው ብለዋል።
ከዓሹራ ጋር 9ኛውን ቀን መጾም ምክኒያቶች አሉት ከነዚህም መሀል አንዱ
10ኛውን ቀን ብቻ መጾም ከአይሁዶች ጋር መመሳሰልን ስለሚያመጣ አንድ ቀን
ጨምሮ መጾሙ ከነሱ ጋር መለያየትን ያስገኛል።
ከጠመሙ ህዝቦች ጋር መመሳሰል በዲናችን ( በእስልምና ሃይማኖት) የተከለከለ
ነው።
ይህ በንዲህ እንዳለ ምናልባት የቀን አቆጣጠር ላይ ስህተት ቢፈጠር እና የወሩ
መግቢያ አሻሚ ቢሆን ሁለቱን ቀናት መጾም የዓሹራን ቀን ማግኘት ላይ እርግጠኛ
ያደርጋል።
በላጩ 9 እና 10ኛውን ቀን መጾሙ ሲሆን ያልተመቸው ሰው 10 እና 11ኛውን
ቀን መጾም ይችላል።
እንዲሁ ዋናውን የዓሹራን ቀን ብቻ እንጂ ሌላ ተጨማሪ ቀን መጾም ያልቻለ ሰው
ብቻውን መጾም እንደማይከለከል ዑለማዎች ገልጸዋል።
ዓሹራን መጾም የቱን ወንጀል ነው የሚያስምረው?
ዓሹራን መጾም ያለፈውን ዓመት ወንጀል እንደሚያሠርዝ ጠቅሰናል ይህ ምህረት
ጥቃቅን ወንጀሎችን ነው የሚመለከተው ወይስ ከበባዶችንም ጭምር?
ይህን አስመልክተው ኢማም አንነወዊይ የሚከተለውን ብለዋል፦
የዓረፋ ጾምም ይሁን የዓሹራ ሌሎችም ወንጀልን ያስምራሉ የተባሉ ኢባዳዎች
ጥቃቅን የሚባሉ ወንጀሎችን በሙሉ ያሰርዛሉ ጥቃቅን ወንጀሎች የሌሉበት
እንደሆነ በምትኩ መልካም ስራዎች ( በላቀ ደረጃ) ይመዘገብለታል አላህ ዘንድም
ያለው ደረጃ ይጨምራል:
````````````````````````````````````````````````````````

ቀዷ ያለበት ሰው ዓሹራ መጾም ይችላልን ?
እንደ ዓሹራ ያሉ ሱና ጾሞችን ያለምንም ጥርጣሬ ለመጾም ያለብንን ቀዷ ፈጠን
ብለን ማውጣቱ ይመረጣል።
ቀዳውን ሳይጾም ወቅቱ የሚያልፍ የሱና ጾም የደረሰበት ሰው በቀጣይ ለቀዳ ሰፊ
ጊዜ እስካለው ድረስ ፈርዱን ቀዷ ሳያወጣ ሱና ቢጾም ችግር አይኖረውም።
````````````````````````````````````````````````````````

ወሏሁ አእለም
ﻭﺍﻟﻠﻪ ﺃﻋﻠﻢ
ﻭﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻰ ﻧﺒﻴﻨﺎ ﻣﺤﻤﺪ ﻭﻋﻠﻰ ﺍﻟﻪ ﻭﺻﺤﺒﻪ ﺍﺟﻤﻌﻴﻦ ዝግጅት ሸህ ሙሀመድ ኢብራሂም

Читать полностью…

سماحة الإسلام የኢስላም ገራገርነት

~ሑረል=ዓይን
ክፍል አራት
የሑረል አይኗኗ የዱንያዋ እንስት ተረብ
================================
ሑረል ዓይን
እናተ የዱንያ ሴቶች ሆይ! ቁንጅናችን የሚያፈዝ ጸባያችን የሚማርክ ቁርዓኣን እና
በሐዲስ ተደጋግመን የተወሳን ውብ እንስቶች ነን። ረሱል (ሰዐወ) ስለኛ ያሉትን
ስሙ....
አንዲት እንስት ወደ ምድር ብትመለከት ፀሀይንና ጨረቃን ጋርዳ ምድርን በተለየ
ብርሃን ባካበበች ነበር።
አላህም እንዲህ ይላል.....
ፀባየ መልካሞች ፤ መልከ ውብ ሴቶች አሉ
[አል ረህማን = 55 70
ጌታችን አላህ ለጀነት ሰዎች ያዘጋጀን ከውቦች ሁሉ ያስበለጠን ያለ ምክንያት
አይደለምና ቆንጆዎችን ለማየት ከፈለጋችሁ ወደ እኛ መዞር ብቻ ነው ምርጫችሁ።
የዱንያ እንስት
በቁንጅና ከእናተ በሰባገ(70) እጥፍ እንድንበልጥ ተደርገን ተፈጥረናል ጀነትን
የተጎናጸፉ የዱንያ ሴቶች በደከሙት ኢባዳ ምክንያት ከሑረል ዓይን በ70 እጥፍ
የበለጠ ቁንጅና ይኖራቸዋል ተብሎ በረሱል (ሰዐወ) አንደበት የተነገረልንን
አትዘንጉ።
ሑረል = ዐይን
እኛ በጀነት ውስጥ እጅ ለእጅ ተያይዘን ፍጥረታት ሰምቶ በማያቀው ተስረቅራቂ
አንደበታችን እንዲህ እያልን እንዘፍናለን። እኛ ስንስቅ እኮ
የጨረቃ ገላ እስኪያልቅ ይሸረፋል
ሙሉ፣ ግማሽ ፣ ሩብ እያለ ይጠፋል
ከዋክብት እንደ ቅጠል እግር ስር ይረግፋል።
የዱንያ እንስት
የዱንያ ሴቶች ሆይ! እናታችን ዓዒሻ ሑረል ዓይኖች ይህን ሲሉ ተገርመው እናተን
ወክለው የሰጡትን ምላሽ አዳምጡ ሑረል አይኖች እጅ ለእጅ ተያይዘው በአንድነት
ሲዘፍኑ የዱንያ ሴቶች ተቃቅፈው ምላሽ ይሰጣሉ።
ለጌታችን ሱጁድ ወርደናል
ጾመናል ፣ ሰድቀናል
በውዱእ ፊታችን አብርቷል
አላገኛችሁም እናተ ይሄን እድል
እልፍ አላፍ አይኖች እኛ ላይ ያርፋሉ
እንኳን እኛን ያዪን ቀርቶ ስለኛ የሰሙ ቆንጆ ናት ይላሉ
ውበት እና ጣፋጭ በእኛ ይመሳሰላሉ
ሁሌም ያዪን ለታ የማናት ይላሉ
ሑረል ዓይኗ
እኛ ለባሎቻችን ኮኮቦቹ ጨረቃ ወለደች እየተባባሉ
እኛን ተጠግተው ብርሃን ተሞሉ
የዱንያ እንስት
ቃላት አሳምረው ስለናንተ ውበት አድንው የፃፉ
እኛ የመጣን እለት ትተዋቹህ አለፉ
ሑረል ዐይኗ
ውበት ከኛ ነው ዘንቦ የሚንጠባጠበው ቆንጆና ጣፋጭ ውበት መሳጭ የሚሉ
ቃላቶች ሁሉ አይገልጹንም ያዪን ፈዘው ቀልባቸው ይሰረቃል። ጨረቃ ከኛ
ትደበቃለች አይናችን ሳይኳል የተኳለ ነው። ጡባ ሊመን ኩና መካነ ለና።
የዱንያዋ እንስት
አይኖቻችንን አይተው ከዋክብት አፈሩ
ድንቄም ብርሃን ሆንን ብለው ተናገሩ
ፀሀይዋም ጠለቀች ባለችበት ቦታ
እኛን ስታይ ግዜ ተደናግራ ፈርታ
ዓኢሻ አስከተሉና በአላህ እምላለሁ አሸነፍናቸው
ውዷ እህቴ ሆይ በጀነት ውስጥ የሑረል ዓይኖች ሁላ አለቃ ነሽ እንኳን ደስ አለሽ።
ሁለት ውብ እንስቶች
ሁለት ታላላቅ ብርሃናት
ቢያበሩ በምድር
ምድር ያን ግዜ እንዴት ትሆን ነበር።
ይቀጥላል........

Читать полностью…

سماحة الإسلام የኢስላም ገራገርነት

ከሚስትህ ጋር መቀለድ::::::
ባለቤትህን ማጫወትና ማቃለድ በትዳር ላይ ደስታና ፍቅር እንዲያገኙ ያደርጋል
አብዛኛው ጊዜ ወንዶች ኮስታራ እና ቁጡ መሆን ይቀናቸዋል ብቻ ግን ደስ ባለው
ጊዜ የፍላጎቶን መፈፀም ይወዳሉ
የሴት ልብ ጫወታ፣ሳቅና ደስታ ይገዘዋል
እሷን ማቃለድ ፈገግታዋ ባንተ ሰበብ
እንዲ ፍለቀለቅ ስታደርግ ላንተ ያላት ፍቅር እና ክብር ይጨምራል
ስትወጣ ትናፍቃታለክ ስትገባ እንዳትሄድባት ትሳሳልካለች
ፍቅርና ደስታ የሚሸመቱ ሸቀጦች አይደሉም በተግባርና በቃላትህ የሚታገኛቻው
የጌታክ አላህ ውድ ስጦታዎች ናቸው
አንተ በተቻለክ አቅም ሚስትን ማቃለድና የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም ውዴታክን
የምትገልፅበትን መንገድ አመቻች።

Читать полностью…

سماحة الإسلام የኢስላም ገራገርነት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡
7፥3 *ከጌታችሁ ወደ እናንተ የተወረደውን ተከተሉ*። ﺍﺗَّﺒِﻌُﻮﺍ ﻣَﺎ ﺃُﻧﺰِﻝَ ﺇِﻟَﻴْﻜُﻢ ﻣِّﻦ ﺭَّﺑِّﻜُﻢْ
ዘመን መለወጫ የሚባል በዓል በኢሥላም ውስጥ የለም። ሙሥሊም ያሉት
ዓመታዊ በዓል ሁለት ብቻ ናቸው፥ እነርሱም ዒዱል ፊጥር እና ዒዱል አድሓ
ናቸው፦
ሡነን አቢ ዳዉድ መጽሐፍ 2, ሐዲስ 745
አነሥ ኢብኑ ማሊክ እንደተረከው፤ የአላህ መልእክተኛም ” ﷺ ” መዲና ሲገቡ
የመዲና ሠዎች የሚደሰቱባቸው ሁለት በዓላት እንዳሏቸው አወቁ። እርሳቸውም
እነዚህ ሁለቱ ቀናት ምንድን ናቸው? በማለት ጠየቁ፤ ሰዎችም በጃሂሊያ ጊዜ
እንጫወትባቸው የነበሩ በዓላት ናቸው አሏቸው። የአላህ መልእክተኛም ” ﷺ ፦”
*”አላህ ከእነርሱ የተሻሉ ሁለት ዒዶችን ሠጥቷችኋል፤ እነርሱም፦ ዒዱል ፊጥር
እና ዒዱል አድሓን። አሏቸው”*። ﻋَﻦْ ﺃَﻧَﺲٍ، ﻗَﺎﻝَ ﻗَﺪِﻡَ ﺭَﺳُﻮﻝُ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ
ﺍﻟْﻤَﺪِﻳﻨَﺔَ ﻭَﻟَﻬُﻢْ ﻳَﻮْﻣَﺎﻥِ ﻳَﻠْﻌَﺒُﻮﻥَ ﻓِﻴﻬِﻤَﺎ ﻓَﻘَﺎﻝَ ” ﻣَﺎ ﻫَﺬَﺍﻥِ ﺍﻟْﻴَﻮْﻣَﺎﻥِ ” . ﻗَﺎﻟُﻮﺍ ﻛُﻨَّﺎ ﻧَﻠْﻌَﺐُ ﻓِﻴﻬِﻤَﺎ ﻓِﻲ
ﺍﻟْﺠَﺎﻫِﻠِﻴَّﺔِ . ﻓَﻘَﺎﻝَ ﺭَﺳُﻮﻝُ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ ” ﺇِﻥَّ ﺍﻟﻠَّﻪَ ﻗَﺪْ ﺃَﺑْﺪَﻟَﻜُﻢْ ﺑِﻬِﻤَﺎ ﺧَﻴْﺮًﺍ ﻣِﻨْﻬُﻤَﺎ ﻳَﻮْﻡَ
ﺍﻷَﺿْﺤَﻰ ﻭَﻳَﻮْﻡَ ﺍﻟْﻔِﻄْﺮِ ” .
ጃሚዒ አት-ቲርሚዚህ መጽሐፍ 8, ሐዲስ 121
ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው የአላህ መልእክተኛም ” ﷺ ” እንዲህ አሉ፦
*“ዒዱል ፈጥር ሰዎች ጾም የሚፈቱበት ነው፤ ዒዱል አደሐ ደግሞ መስዋዕት
የሚያቀርቡበት ቀን ነው”*። ﻋَﻦْ ﻋَﺎﺋِﺸَﺔَ، ﻗَﺎﻟَﺖْ ﻗَﺎﻝَ ﺭَﺳُﻮﻝُ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ “
ﺍﻟْﻔِﻄْﺮُ ﻳَﻮْﻡَ ﻳُﻔْﻄِﺮُ ﺍﻟﻨَّﺎﺱُ ﻭَﺍﻷَﺿْﺤَﻰ ﻳَﻮْﻡَ ﻳُﻀَﺤِّﻲ ﺍﻟﻨَّﺎﺱُ ”
ጃሚዒ አት-ቲርሚዚህ መጽሐፍ 8, ሐዲስ 91
አቡ ሰዒደል ኹድሪይ እንደተረከው፥ የአላህ መልእክተኛም ” ﷺ ” ”* በሁለቱ በዓል
በዒደል አደሐ እና ዒደል ፈጥር መጾም ከልክለዋል”*። ﻋَﻦْ ﺃَﺑِﻲ ﺳَﻌِﻴﺪٍ ﺍﻟْﺨُﺪْﺭِﻱِّ، ﻗَﺎﻝَ
ﻧَﻬَﻰ ﺭَﺳُﻮﻝُ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ ﻋَﻦْ ﺻِﻴَﺎﻣَﻴْﻦِ ﻳَﻮْﻡِ ﺍﻷَﺿْﺤَﻰ ﻭَﻳَﻮْﻡِ ﺍﻟْﻔِﻄْﺮِ .
”ዒድ“ ﻋِﻴﺪ የሚለው ቃል “ዓደ ” ﻋَﺎﺩَ ማለትም “ተመላለሰ” ከሚል ሥርወ-ቃል
የመጣ ሲሆን “ምልሰት” ማለት ነው፥ ይህ “መደሰቻ” ወይም “በዓል” በየዓመቱ
ስለሚመላለስ ይህንን ስያሜ አግኝቷል። ስለዚህ ከአላህ የወረዱትን ቁርኣን እና
ሐዲስ ብቻ መከተል አለብን፦
7፥3 *ከጌታችሁ ወደ እናንተ የተወረደውን ተከተሉ*። ﺍﺗَّﺒِﻌُﻮﺍ ﻣَﺎ ﺃُﻧﺰِﻝَ ﺇِﻟَﻴْﻜُﻢ ﻣِّﻦ ﺭَّﺑِّﻜُﻢْ
“ ተከተሉ” የሚለው ቃል “ኢተቢዑ ” ﺍﺗَّﺒِﻌُﻮﺍ ሲሆን “ኢትባዕ ” ﺇِﺗْﺒَﺎﻉ ማለት ከአላህ ወደ
”ነቢያችን ﷺ ” የተወረደውን ብቻ መከተል ማለት ነው። ሙሥሊም የተወረደውን
ብቻ ሲከተል ሁለት ብቻ ዒድ ያከብራል። ከዚህ ውጪ በዓል እያሉ ማክበር
ቢድዓህ ነው፥ “ቢድዓህ ” ﺑِﺪْﻋَﺔ ደግሞ “በደዐ ” ﺑَﺪَّﻉَ ማለትም “ፈጠረ” ከሚል
ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ፈጠራ” ማለት ነው። ቢድዓህ የኢትባዕ ተቃራኒ ነው።
“ቢድዓህ” ማለት አላህ ሳያዘን እና ሳይፈቅድልን ዝንባሌአችንን ተከትለን
የምናደርገው አዲስ አምልኮ ማለት ነው፦
ኢማም ቡኻርይ : መጽሐፍ 53, ሐዲስ 7
ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው የአላህ መልእክተኛም ” ﷺ ” እንዲህ አሉ፦
“ማንኛውም ሰው ከትእዛዛችን ያልሆነ አንድ ነገር ቢፈጥር ተቀባይነት የለውም ﻋَﻦْ
ﻋَﺎﺋِﺸَﺔَ ـ ﺭﺿﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻨﻬﺎ ـ ﻗَﺎﻟَﺖْ ﻗَﺎﻝَ ﺭَﺳُﻮﻝُ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ “ ﻣَﻦْ ﺃَﺣْﺪَﺙَ ﻓِﻲ
ﺃَﻣْﺮِﻧَﺎ ﻫَﺬَﺍ ﻣَﺎ ﻟَﻴْﺲَ ﻓِﻴﻪِ ﻓَﻬُﻮَ ﺭَﺩٌّ .”
ሡነን ኢብኑ ማጃህ : መጽሐፍ 1, ሐዲስ 210
ከሲር ኢብኑብ ዐብደላህ እንደተረከው አባቱ ከአያቱ የአላህ መልእክተኛ ” ﷺ ”
እንዲህ ሲሉ ሰማው ያለው፦ “ማንኛውም ሰው የእኔን ሡናህ ሱናህ ያደረገ ከእኔ
በኃላ የእኔን ፈለግ የሚከተሉትን ሰዎች የሚያገኙትን አጅር ከእነርሱ ላይ ሳይቀነስና
ሳይጨመር ያገኛል፤
ማንም ሰው አላህ እና መልእክተኛው ያልደነገጉትን ቢድዓን ያስተዋወቀ ያንን
ፈለግ የተከተሉትን ሰዎች የሚያገኙትን ኀጢአት ከእነርሱ ላይ ሳይቀነስና
ሳይጨመር ይሸከማል። ﺣَﺪَّﺛَﻨِﻲ ﻛَﺜِﻴﺮُ ﺑْﻦُ ﻋَﺒْﺪِ ﺍﻟﻠَّﻪِ، ﻋَﻦْ ﺃَﺑِﻴﻪِ، ﻋَﻦْ ﺟَﺪِّﻩِ، ﻗَﺎﻝَ ﺳَﻤِﻌْﺖُ ﺭَﺳُﻮﻝَ
ﺍﻟﻠَّﻪِ ـ ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ ـ ﻳَﻘُﻮﻝُ “ ﻣَﻦْ ﺃَﺣْﻴَﺎ ﺳُﻨَّﺔً ﻣِﻦْ ﺳُﻨَّﺘِﻲ ﻗَﺪْ ﺃُﻣِﻴﺘَﺖْ ﺑَﻌْﺪِﻱ ﻓَﺈِﻥَّ ﻟَﻪُ ﻣِﻦَ
ﺍﻷَﺟْﺮِ ﻣِﺜْﻞَ ﺃَﺟْﺮِ ﻣَﻦْ ﻋَﻤِﻞَ ﺑِﻬَﺎ ﻣِﻦَ ﺍﻟﻨَّﺎﺱِ ﻻَ ﻳَﻨْﻘُﺺُ ﻣِﻦْ ﺃُﺟُﻮﺭِ ﺍﻟﻨَّﺎﺱِ ﺷَﻴْﺌًﺎ ﻭَﻣَﻦِ ﺍﺑْﺘَﺪَﻉَ ﺑِﺪْﻋَﺔً ﻻَ
ﻳَﺮْﺿَﺎﻫَﺎ ﺍﻟﻠَّﻪُ ﻭَﺭَﺳُﻮﻟُﻪُ ﻓَﺈِﻥَّ ﻋَﻠَﻴْﻪِ ﻣِﺜْﻞَ ﺇِﺛْﻢِ ﻣَﻦْ ﻋَﻤِﻞَ ﺑِﻬَﺎ ﻣِﻦَ ﺍﻟﻨَّﺎﺱِ ﻻَ ﻳَﻨْﻘُﺺُ ﻣِﻦْ ﺁﺛَﺎﻡِ ﺍﻟﻨَّﺎﺱِ
ﺷَﻴْﺌًﺎ ” .
ሡነን ነሣኢ : መጽሐፍ 19, ሐዲስ 23
ጃቢር ኢብኑ ዐብደላህ እንደተረከው፦ የአላህ መልእክተኛ ” ﷺ ” ሑጥባቸው ላይ
እንደተናገሩት፦ “አላህ የመራውን ማንም አያጠመውም፤ አላህ ያጠመመውን
ማንም አያቀናውም። ከንግግር ሁሉ በላጩ የአላህ መጽሐፍ ነው፤ ከመመሪያ ሁሉ
በላጩ የሙሐመድ መመሪያ ነው። ከሁሉ የተጠላ ነገር ቢድዓህ ነው፤ ቢድዓህ
ሁሉ ጥመት ነው፤ ጥመት ሁሉ የእሳት ነው። ﻋَﻦْ ﺟَﺎﺑِﺮِ ﺑْﻦِ ﻋَﺒْﺪِ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﻗَﺎﻝَ ﻛَﺎﻥَ ﺭَﺳُﻮﻝُ ﺍﻟﻠَّﻪِ
ﺻَﻠَّﻰ ﺍﻟﻠَّﻪُ ﻋَﻠَﻴْﻪِ ﻭَﺳَﻠَّﻢَ ﻳَﻘُﻮﻝُ ﻓِﻲ ﺧُﻄْﺒَﺘِﻪِ ﻳَﺤْﻤَﺪُ ﺍﻟﻠَّﻪَ ﻭَﻳُﺜْﻨِﻲ ﻋَﻠَﻴْﻪِ ﺑِﻤَﺎ ﻫُﻮَ ﺃَﻫْﻠُﻪُ ﺛُﻢَّ ﻳَﻘُﻮﻝُ ﻣَﻦْ ﻳَﻬْﺪِﻩِ
ﺍﻟﻠَّﻪُ ﻓَﻠَﺎ ﻣُﻀِﻞَّ ﻟَﻪُ ﻭَﻣَﻦْ ﻳُﻀْﻠِﻠْﻪُ ﻓَﻠَﺎ ﻫَﺎﺩِﻱَ ﻟَﻪُ ﺇِﻥَّ ﺃَﺻْﺪَﻕَ ﺍﻟْﺤَﺪِﻳﺚِ ﻛِﺘَﺎﺏُ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﻭَﺃَﺣْﺴَﻦَ ﺍﻟْﻬَﺪْﻱِ ﻫَﺪْﻱُ
ﻣُﺤَﻤَّﺪٍ ﻭَﺷَﺮُّ ﺍﻟْﺄُﻣُﻮﺭِ ﻣُﺤْﺪَﺛَﺎﺗُﻬَﺎ ﻭَﻛُﻞُّ ﻣُﺤْﺪَﺛَﺔٍ ﺑِﺪْﻋَﺔٌ ﻭَﻛُﻞُّ ﺑِﺪْﻋَﺔٍ ﺿَﻠَﺎﻟَﺔٌ ﻭَﻛُﻞُّ ﺿَﻠَﺎﻟَﺔٍ ﻓِﻲ ﺍﻟﻨَّﺎﺭِ .
ከሁሉ የተጠላ ነገር ቢድዓህ ነው፤ ቢድዓህ ሁሉ ጥመት ነው፤ ጥመት ሁሉ የእሳት
ከሆነ ካየን ቢድዓህ የሚያራምድ ማንኛውም ሰው “ሙብተዲዕ ” ﻣﺒﺘﺪﺉ ይባላል።
ስለዚህ የጎርጎሳውያን ሆነ የሒጅራን ዘመን መለወጫ በዓል አድርጎ በመያዝ
እንኳን አደረሳችሁ ማለት ቢድዓህ ነው።
አሏህ ከሙብተዲዕ ፈሣድ ይጠብቀን! አሚን።

Читать полностью…

سماحة الإسلام የኢስላም ገራገርነት

የዘውትር # ጭንቁ_አኼራ የሆነ ሰው አላህ ሀብትን በልቡ ያደርግለታል፣
ጉዳዩን ይሰበስብለታል፣ ዱንያ የግዷን ወደሱ ትመጣለች፣ የዘውትር
#ጭንቁ_ዱንያ የሆነ ሰው ድህነትን በአይኖቹ መሀል ያደርግበታል፣ ጉዳዩንም
ይበታትንበታል»።
•.¸♡ ነቢዩ ﷺ ስለአሏሁ አለይሂ ወሰለም ♡¸.•
ቲርሚዚ ዘግበውታል ታላቁ
ሙሐዲስ ሼይኽ አልባኒ ሰሒህ ብለውታል

Читать полностью…
Subscribe to a channel