neshatulama | Unsorted

Telegram-канал neshatulama - ነሲሐቱል ኣማ የልማትና መረዳጃ ተቋም/ Nesihatul ama development and relief institute

592

፨የተቋሙ ብቸኛ አላማ በዋነኝነት ቁርአንና ሀዲስ የተረዳ በአብሮነትና በመቻቻል በመከባበር መኖር የምያምን ትውልድ/ማህበረሰብ መፉጠር !!! 🌟ዋና ስራዎቻችን 👉የቲም፣አረጋውያ በቋምነት መርዳት!!! 👉ትምህርታው ኘሮግራም ማዘጋጀት!!! 👉ቂርዐት ማቋቋም!!!

Subscribe to a channel

ነሲሐቱል ኣማ የልማትና መረዳጃ ተቋም/ Nesihatul ama development and relief institute

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
እንኳን ለ1446ኛው ዓ.ሂ ረመዳን ወር አላህ አደረሳችሁ

ወሩን ከሚጠቀሙበት ምህረትን ከሚጎናፀፉት ሰዎች አላህ ያድርገን

Читать полностью…

ነሲሐቱል ኣማ የልማትና መረዳጃ ተቋም/ Nesihatul ama development and relief institute

📢 የሙሓደራ ፕሮግራም


🏷 || ለ2 ቀን የሚቆይ የረመዷን መግቢያ ሙሓደራ

🎙 || በኡስታዝ አብዱልዋሲዕ ሸይኽ ነስሮ

🕒 || የፊታችን ቅዳሜ እና እሁድ

🧩 || ከመግሪብ - ዒሻ

🕌 || ሳሪስ አቦ አስ ሷሊሂን መድረሳና መስጂድ

📍 ለሴቶችም ቦታ አለን !
---------------------------
@mesjidsualih

Читать полностью…

ነሲሐቱል ኣማ የልማትና መረዳጃ ተቋም/ Nesihatul ama development and relief institute

👆👆👆ትራንስፖርት ተዘጋጅቷል እሁድ ጠዋት አሷሊሂን መስጂድ እንገናኝ።

Читать полностью…

ነሲሐቱል ኣማ የልማትና መረዳጃ ተቋም/ Nesihatul ama development and relief institute

በአ/አ/ከ እስልምና ጉ/ከ/ም/ቤት


የሙስሊም ወጣቶች ሊግ ከተማ አቀፍ የዳዕዋ ፕሮግራም

Читать полностью…

ነሲሐቱል ኣማ የልማትና መረዳጃ ተቋም/ Nesihatul ama development and relief institute

ዘወትር ከመግሪብ እስከ ዒሻዕ ሳምንታዊ የደርስ ፕሮግራም

• በአስ ሷሊሂን መድረሳና መስጂድ
----------------------------
  ▸  @mesjidsualih

Читать полностью…

ነሲሐቱል ኣማ የልማትና መረዳጃ ተቋም/ Nesihatul ama development and relief institute

🔸 ቀጥታ የሙሃደራ ፕሮግራም live 🅾

🗓 ከመግሪብ እስከ ዒሻ

🕌 በሳሪስ አስ-ሷሊህን መስጂድ

🔸የነብያት ውርስ በሚል ርዕስ በኡስታዝ አብዱልዋሲእ ነስሮ ይቀርባል

🎧 በጉረባእ የቴሌግራም ቻናል ቀጥታ ይተላለፋል ይከታተሉ 👇
t.me/GHUREBAMEDIA

⚡️ጉረባእ ሚድያ-GHUREBA MEDIA

Читать полностью…

ነሲሐቱል ኣማ የልማትና መረዳጃ ተቋም/ Nesihatul ama development and relief institute

📢 || ልዩ የሙሐደራ ፕሮግራም በኡስታዝ ኸይረዲን ጤኔቦ

🕒 || ከመግሪብ እስከ ዒሻእ

🗓 || ሀሙስ መስከረም 30/2017

🕌 || ሳሪስ አቦ አስ ሷሊሂን መስጂድ

🔗 || @mesjidsualih

Читать полностью…

ነሲሐቱል ኣማ የልማትና መረዳጃ ተቋም/ Nesihatul ama development and relief institute

ይነበብ‼️

ሁላቹም ተጋብዛችኋል ✨

Читать полностью…

ነሲሐቱል ኣማ የልማትና መረዳጃ ተቋም/ Nesihatul ama development and relief institute

تقبل الله منا ومنكم صالح الأعمال..عيد مبارك كل عام وانتم بخير. عيد مبارك. 🎉

Читать полностью…

ነሲሐቱል ኣማ የልማትና መረዳጃ ተቋም/ Nesihatul ama development and relief institute

ما من أيام أفضل عند الله ولا العمل فيهن أحب إلى الله من هذه الأيام العشر، فأكثروا فيهن من التهليل والتكبير وذكر الله، وإن صيام يوم منها يعدل بصيام سنة، والعمل فيهن يضاعف سبعمائة ضعف

“በደረጃቸውም ሆነ በውስጣቸው በሚሠራ ሥራ ከነኚህ አሥር ቀናት የሚበልጥ በአላህ ዘንድ አንድም የለም። በነሱ ውስጥ ላኢላሀ ኢለላህ፣ አላሁ አክበር ማለትንና አላህን ማውሣት አብዙ። ከነሱ ውስጥ አንድ ቀን መፆም የአመት ፆምን ይስተካከላል። በነሱ ውስጥ የሚሠራ ሥራ እስከ ሰባት መቶ ድረስ እጥፍ ድርብ ይሆናል።” (በይሀቂና ኢማም አህመድ ዘግበውታል)

4. በነሱ ውስጥ ተክቢራ ማብዛት

ዐብዱላህ ኢብኑ ዑመር እና አቡ ሁረይራ (ረ.ዐ) በአሥርቱ ቀናት ውስጥ “አላሁ አክበር!” እያሉ ወደ ገበያ ይወጣሉ። ሰዎችም የነሱን ተክቢራ እየተቀበሉ “አላሁ አክበር!” ይሉ ነበር። እንዲህም ብለዋል። “ዑመር በሚና በሚገኘው ቁባቸው ውስጥ ተክቢራ ያደርጉ የነበረ ሲሆን በመስጅድ ውስጥ ያሉ ሰዎችም እርሣቸውን ይሰሙና ‘አላሁ አክበር!’ ይሉ ነበር። ገበያ ውስጥ ያሉ ሰዎችም ሚና በተክቢራ እስክትናወጥ ድረስ ‘አሏሁ አክበር!’ ይሉ ነበር።” ብለዋል። (ፈትሁል ገፋር ቀጽ 5፣ ገጽ 379)

5. ሀጅ ሥራ ውስጥ ላልተሠማራ ሰው የመጀመሪያዎቹን ዘጠኝ ቀናት መፆም

ይህንንም ሀሠን፣ ኢብኑ ሲሪን እና ቀታዳህን የመሣሰሉ ታቢዒዮችን ጨምሮ በርካታ ሰሃቦች ሰርተውታል። ኢማም ነወዊ እንዲህ ብለዋል፡-

ليس في صوم هذه التسعة كراهة بل هي مستحبة استحبابًا شديدًا، لا سيما التاسع منها، وهو يوم عرفة

“አነኚህ ዘጠኝ ቀናት መፆማቸው የሚጠላ አይደለም። ባይሆን እጅግ ተወዳጅ ነገር ነው። በተለይም ዘጠነኛው ቀን። እሱም የዐረፋ ቀን ነው።” (ሸርሁል ሙስሊም ቀጽ 3፣ ገጽ 245)

ከአቢ ቀታዳህ እንደተዘገበው ደግሞ የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ስለ ዐረፋ ቀን ፆም ተጠየቁ። እንዲህም አሉ፡-

يكفِّر السنة الماضية والباقية

“ያለፈውንና የሚመጣውን አመት ወንጀል ያብሳል።” (ኢማም ሙስሊም እና አህመድ ዘግበውታል)

6. ቁርዓንን ማንበብ

ከኢብኑ መስዑድ (ረ.ዐ) እንደተዘገበው የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡-

من قرأ حرفًا من كتاب الله فله به حسنة، والحسنة بعشر أمثالها، لا أقول الم حرف، ولكن ألف حرف، ولام حرف، وميم حرف

“ከአላህ ኪታብ አንድ ፊደል ያነበበ ሰው የመልካም ምንዳ አለው። አንዱ መልካም ምንዳ አሥር ተመሣሣይ እጥፍ ይባዛል። አንድ ሰው ‘አሊፍ-ላም-ሚም’ ያለ እንደሆነ አንድ ፊደል አይደለም። ነገርግን ‘አሊፍ’ አንድ ፊደል ነው፣ ‘ላምም’ አንድ ፊደል ነው፣ ‘ሚምም’ አንድ ፊደል ነው።” (ቡኻሪና ቱርሙዚ ዘግበውታል)

7. ኡድሂያ ማዘጋጀት

አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ አለ

فَصَلِّ لِرَبِّكَ وَانْحَرْ [١٠٨:٢]

“ስለዚህ ለጌታህ ስገድ፤ (በስሙ) ሰዋም።” (አል-ከውሰር 108፤ 3)

ከዓኢሻ (ረ.ዐ) እንደተዘገበው የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡-

ما عمل آدمي من عمل يوم النحر أحب إلى الله من إهراق الدم، وإنها لتأتي يوم القيامة بقرونها وأشعارها وأظلافها، وإن الدم ليقع من الله بمكان قبل أن يقع على الأرض فطيبوا بها نفسًا

“ከነህር /እርድ/ ቀን ሥራዎች ውስጥ የአደም ልጅ ደምን ከማፍሠስ በላይ ወደ አላህ ተወዳጅ የሆነ አንድም ሥራ አልሠራም። እርዷም የቂያማ ቀን ከነፀጉሯና ጥፍሯ ትመጣለች። ደሙም መሬት ላይ ከማረፉ በፊት ከአላህ ዘንድ ቦታ ይይዛል። በዚህም ነፍሣችሁን አስደስቱ (ደስ ይባላችሁ)።” (ቱርሙዚ፣ ሃኪም እና ኢብኑ ማጀህ ዘግበውታል)

ኡድሂያ ማረድ የተዘጋጀ ሰው ኡድሂያውን እስኪያርድ ድረስ ፀጉሩንም ሆነ ጥፍሩን የሰውነቱን መንካት የለበትም። ከኡሙ ሰለማ (ረ.ዓ) በተላለፈው ሀዲስም ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)፡-

إِذَا دَخَلَتِ الْعَشْرُ وَأَرَادَ أَحَدُكُمْ أَنْ يُضَحِّيَ فَلا يَمَسَّ مِنْ شَعَرِهِ وَبَشَرِهِ شَيْئًا

“አንዳችሁ ኡድሂያ ለማረድ አስቦ አሥርቱ ቀናት የገቡ እንደሆነ ከፀጉሩም ሆነ ከሰውነቱ አንዳቸም ነገር አይንካ።” ብለዋል። (ሙስሊም እና ነሣኢ ዘግበውታል።)

አላህ እነዚህን ውድ ቀናቶች ከሚጠቀሙት ያድርገን።»

منقول

Читать полностью…

ነሲሐቱል ኣማ የልማትና መረዳጃ ተቋም/ Nesihatul ama development and relief institute

አሰላሙ አለይከኩም ወራህመቱሏሂ ወበረካቱህ

በ1445 ዓ.ሒ የወርሀ ረመዷን ላይ የመስጂደ-ሷሊህ ኮሜቶ ከ መስጂዱ ወጣቶች ጋር በመተባበር በተደረገዉ የዘካተል ፊጥር ፕሮግራም ከ 210 በላይ የቲሞችና መሳኪኖች መስጠት ትችሏል።

መስጂዱ ኡማው የሰጠውን አማና ለመወጣት የተቻለውን ሁሉ ጥረት ያደረገ ሲሆን ዘካው የሚገባቸውና የማይገባቸውንም በሸሪዐ ሚዛን ልየታ እድርጓል ከዚህ መሀል ነሳራ(ካፊር) የሆኑ ሰዎችን፤በግላቸዉ ዘካ የማውጣት አቅም ያላቸውንና መሰል መስፈርቶችን በማድረግ በተጨማሪም ይበልጥ ትክክለኛ ዛካ ሚገባቸውን ለማግኘት እዛው ሰፈር ከሚገኘው ጀመዐ(ነሲሓቱል አማ) ጋር በመተባበር በሱ ስር ለሚገኙ የቲምና መሳኪኖች ቅድሚያ በመስጠት ዘካውን ተደራሽ ማድረግ ተችሏል።

አሏህ ሰጪውንም ተቀባዩን የአጅሩ ተካፋይ እንዲያይደርጋቸውና አማናቸውንም ከሚጠብቁት ተርታ ይመድበን አሚን።

🌹@mesjidsualih🌹

Читать полностью…

ነሲሐቱል ኣማ የልማትና መረዳጃ ተቋም/ Nesihatul ama development and relief institute

tiktok.com/@mesjideassualih

Читать полностью…

ነሲሐቱል ኣማ የልማትና መረዳጃ ተቋም/ Nesihatul ama development and relief institute

اَلسَلامُ عَلَيْكُم وَرَحْمَةُ اَللهِ وَبَرَكاتُهُ‎
በየአመቱ በነሲሀቱል አማ የሚደረገው ቁርአን የማዳረስ ዘመቻ የቀጠለ ሲሆን ዘንድሮም በወሎ ባቲ ኡመር ኢብኑል ኸጣብ መስጂድ ሁለት መቶ 30 ጁዝ ቁርአን አድረሰናል።

Читать полностью…

ነሲሐቱል ኣማ የልማትና መረዳጃ ተቋም/ Nesihatul ama development and relief institute

አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱሏሂ ወበረካቱህ

አመታዊ የረመዷን ወር እርዳታ በነሲሓቱል አማ

በዛሬው ዕለት መጋቢት 10/7/16 ወይም ረመዷን 9 1445 ዓ.ሒ በነሲሀቱል አማ ስር ላሉ የቲሞችና መሳኪኖች በመስጂደ ሷሊህ ቅጥር ግቢ ውስጥ የመስጂዱ ኮሚቴ ተወካይ እና የመስጂዱ ኢማም በተገኙበት የረመዷን አስቤዛ ድጋፍ ተደርጓል።

ድጋፉን ያበረከተዉ የጀመአው አሚር ወንድም ሰለሀዲን እንደተናገረው በተለያዩ ምክንያቶች ድጋፍ ከወትሮ ያነስ ቢሆንም ባለን አቅም ለሁሉም ባናዳረስም እንኳ በተለየ መልኩ ለሚገባቸዉና ለየቲሞች ቅድሚ እንደሰጡና፣ ላልደረሳቸው ቤተሰቦች በቀጣይ በሚኖሩ መሰል ድጋፎች ላይ ቅድሚያ እንዲሚሰጣቸው ተናግሯል።

በዚህ የእርዳታ ፕሮግራም ላይ የተሰጡ የአስቤዛ አይነቶች:- 5 ኪሎ የሾርባ እህል፣10 ኪሎ ዱቄትና 5 ሊትር ዘይት ናቸው።

በዚህ ፕሮግራም ላይ ለተሳተፋቹ አባሎቻችን እያመሰገንን፤ ጀዛቹንም ከአሏህ ታገኙት ዘንድ ምኞታችን ነው።

እኛም የአሏህን ፊት ፈልገው፤ አጅሩንም ተስፋ አርገው ከሰጡት ያርገን አሚንንን 🤲 ።


ነሲሓቱል አማ የልማትና የየቲሞች መርጃ ተቋም.

Читать полностью…

ነሲሐቱል ኣማ የልማትና መረዳጃ ተቋም/ Nesihatul ama development and relief institute

አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱሏሂ ወበረካቱህ

የረመዷን መግባትን አስመልክቶ የተዘጋጀ ወቅታዊና አስፈላጊ የ ፈትዋ ፕሮግራም

.በኡስታዝ ሙስጠፋ አደም ( አቡ ኢክራም) 🌹

በዕለተ እሁድ ( በረመዷን 7) ከአሱር ሶላት በኋላ በመስጂደ ሷሊህ ረመዷንን የሚመለከቱ ፈትዋዎች ስለሚሰጡ ሁላቹም ጥይቄያቹን ይዛችሁ እንድትመጡ እንጋብዛለን።
ከሰአትና ከቦታ ርቀት ለማይመቻቹ እህትና ወንድሞች ጥይቄያቹን በዚህ ሊንክ ብትሉክልን እኛ እናደርሳላን 👉 @fesbir_7

የጥያቄያቹን ምላሽ በመስጂዱ ግሩፕ በኦዲዮ መስማት ትችላለቹህ 👉 https//t.me/mesjidsualih

አዘጋጅ: የመስጂደ ሷሊህ ወጣቶች ጀምአ.✨

Читать полностью…

ነሲሐቱል ኣማ የልማትና መረዳጃ ተቋም/ Nesihatul ama development and relief institute

⚡️በረመዳን መቃረቢያ የተዘጋጀ ልዪ የዳእዋ ኮንፈረንስ በሚሊንየም አዳራሽ

#ነሲሓ_ኮንፈረንስ
#የፊታችን_እሁድ_የካቲት_16
#ከሶስት_ሰዓት_ጀምሮ
#በእዝነት_ጥላ_ስር
#በሚሊንየም_አዳራሽ

እሁድን ከነሲሓ ጋር ያሳልፉ ነፃ የመግቢያ ትኬት ይያዙ

www.conference.nesiha.tv/


⚡️ t.me/GHUREBAMEDIA

Читать полностью…

ነሲሐቱል ኣማ የልማትና መረዳጃ ተቋም/ Nesihatul ama development and relief institute

አስሰላሙ ዐለይኩም ወረህመቱሏሂ ወበረካቱህ

• ለሳምንት ተቋርጠው የነበሩት የኡስታዝ አብዱልዋሲዕ ሸይኽ ነስሮ የደርስ ፕሮግራሞች ከዛሬ ጀምሮ የሚኖሩ መሆናቸውን እንገልፃለን።

-------------------------------------
▸ @mesjidsualih
@as_sualihin_mesjid

Читать полностью…

ነሲሐቱል ኣማ የልማትና መረዳጃ ተቋም/ Nesihatul ama development and relief institute

ከረመዷን ጋር ተያያዥ የሆኑ ሙሃደራዎች የተዘጋጁበት ይህን ከተማ አቀፍ የዳዕዋ ፕሮግራም ለመሄድ የተመዘገባችሁ በሙሉ እሁድ ጠዋት 1፡00 ሰዓት በአስ ሷሊሂን መስጂድ ቅጥር ግቢ ውስጥ በሰዓቱ እንድትገኙ ስንል እናስባለን።

ያልተመዘገባችሁ የመኪና ቦታ ለማግኘት ስማችሁን እና ስልካችሁን ከታች በተቀመጠው ስልክ በመላክ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

+251931198631

Читать полностью…

ነሲሐቱል ኣማ የልማትና መረዳጃ ተቋም/ Nesihatul ama development and relief institute

👆👆👆ትራንስፖርት ተዘጋጅቷል እሁድ ጠዋት አሷሊሂን መስጂድ እንገናኝ።

Читать полностью…

ነሲሐቱል ኣማ የልማትና መረዳጃ ተቋም/ Nesihatul ama development and relief institute

📣  ሙሓደራ
"
ከሱረቱል ኢስራእ ድንቅ ምክሮች "

🎙 || በኡስታዝ ዐብዱልዋሲዕ ሸይኽ ነስሮ

🕌 || ሳሪስ አቦ አስ ሷሊሒን መድረሳና መስጂድ

  ▸  @mesjidsualih

Читать полностью…

ነሲሐቱል ኣማ የልማትና መረዳጃ ተቋም/ Nesihatul ama development and relief institute

💥 ልዩ የሙሐደራ ፕሮግራም በኡስታዝ አብዱልዋሲዕ ነስሮ

🕒 || ዛሬ ከመግሪብ እስከ ዒሻእ

📖 || የነቢያት ውርስ

🕌 || ሳሪስ አቦ አስ ሷሊሂን መስጂድ

📍 ለሴቶችም ቦታ አለን !

⚡️ጉረባእ ሚድያ-GHUREBA MEDIA
t.me/GHUREBAMEDIA

Читать полностью…

ነሲሐቱል ኣማ የልማትና መረዳጃ ተቋም/ Nesihatul ama development and relief institute

. የክረምት ኮርስ መዝጊያ ፕሮግራም

አሷሊሂን መድረሳና መስጂድ በ1446 ዓ.ሂ ለ2 ወር ሲሰጥ የቆየውን መሰረታዊ የሆኑ ቁርዐንና ዲናዊ የሆኑ ትምህርቶችን አጠናቆ የመዝጊያ ፕሮግራም አሰናድቷል።በእለቱም በተማሪዎች:-

✓ የ2 ጁዝዕ እና የ3 ጁዝዕ የቁርዓን ውድድር
✓ ኹጥባ
✓ ግጥም

እንዲሁም ሌሎች የተለያዩ ፕሮግራሞች ባማረና አስተማሪ በሆነ መልኩ ይቀርባል።በዚህ ውብ ፕሮግራማችን ላይ ትታደሙ ዘንድ እናንተም ተጋብዛችኋል።

🗓 || መስከረም 12/2017 የፊታችን እሁድ

🕞 || ከ2፡30 ጀምሮ

🕌 || ሳሪስ አቦ አሷሊሂን መስጂድ

▫️ ለሴቶች በቂ ቦታ አለ

Читать полностью…

ነሲሐቱል ኣማ የልማትና መረዳጃ ተቋም/ Nesihatul ama development and relief institute

🕌 ኢህሳን የሩቃ ማዕከል

በማዕከላችን የምንሰጣቸው አገልግሎቶች :-

1) ለሲህር(ድግምት)
2) ለቅዠት
3) ለስራ ፍላጎት መቀነስ
4) ዋግምት
5) ለሪህ
6) ለሰውነት ማሳከክ
7) ለእንቅልፍ ማጣት
8) ያለ ምክንያት ቁጣ ማብዛት
9) ለሰውነት ማቃጠል
10) ለራስ ምታት
11) ለአዙሪት በሽታ
12) ከቤተሰብ ጋር አለመግባባት
13) ለወሲብ ችግር
14) ለብርድ
15) ለሳይነስ
16) ለልብ ህመም
17) ለሰውነት ማበጥ
18) ለሰውነት መጣመም
19) ለነስር
20) ለማቅለሽለሽ
21) የምግብ ፍላጎት መቀነስ
22) ለወር አበባ ይገኙበታል።



‼️ማሳሰቢያ:-ሴት እህቶቻችን ለህክምና ወደ ማዕከላችን ሲመጡ ኢስላማዊ አለባበስን በጠበቀ መልኩ እንዲሁም ከቤተሰብ ጋር መምጣት ይኖርባቸዋል።ከዚህ ውጪ የማናስተናግድ መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን።


🕹አድራሻ:-ሳሪስ አቦ ሷሊህ መስጂድ አካባቢ

☎️ :-
09-12-88-47-59
09-77-20-40-50

Читать полностью…

ነሲሐቱል ኣማ የልማትና መረዳጃ ተቋም/ Nesihatul ama development and relief institute

በሃገረ ሳዑዲ ዐረቢያ የወርሃ ዙል-ሒጃህ ጨረቃ ዛሬ ሐሙስ ስለታየች ነገ ጁሙዓህ ግንቦት 30, 2016 E.C. የዙል-ሒጃህ ወር የመጀመሪያው ቀን ይሆንና ወርቃማዎቹ የዙል-ሒጃህ 10 ቀናት ከነገ ይጀምራሉ። ስለሆነም ቅዳሜ ጁን 15, 2024 (ሰኔ 08, 2016 E.C.) የዕለተ ዐረፋህ ቀን ሲሆን እሁድ ጁን 16 (ሰኔ 09) ዒደ-ል-አዽሓህ ይሆናል። አላህ በሰላም ያድርሰን‼

እነዚህን ወርቃማ ቀናቶች በዒባዳህ ለማሳለፍ ከወዲሁ ዝግጅት አድርጉ። ቀናቶቹን ከምታሳልፉባቸው ዒባዳዎች መካከል፤ ጾም፣ ዚክር፣ ቁርኣን መቅራት፣ ሶደቃ፣ ለቻለ ሰው ሐጅና መሰል በጎ ተግባራትን ማከናወን ይገኙበታል። አላህ ያበርታን።

ሌሎችንም አስታውሱ!


The Dhul Hijjah Crescent was SIGHTED today, hence Dhul Hijah.1445 will begin tomorrow Friday, 7th June 2024.

Читать полностью…

ነሲሐቱል ኣማ የልማትና መረዳጃ ተቋም/ Nesihatul ama development and relief institute

«አሥሩ የዚልሂጃ ቀናት- ከዱኒያ ቀናቶች ሁሉ በላጮች

ከዱኒያ ቀናቶች ሁሉ እጅግ በላጮች የሆኑት የመጀመሪያዎቹ አሥሩ የዚልሂጃ ወር ቀናት ናቸው። እነሆ እነኚህ ምርጥ ቀናት ከፊት ለፊታችን ተደቅነዋል። ለዚህም ይመስላል ሙስሊሙ የአላህን ቤት ከዕባን ለመጎብኘት ያለው ጉጉቱ ድንበር አልፏል፤ በከዕባ ዙሪያ ጠዋፍ ለማድረግ፣ በሶፋና መርዋ መካከል ለመሮጥ እና ዐረፋ ላይ ቆሞ አላህን ለመለመን ያለው ስሜት ጣሪያ ነክቷል። የታላቁን ነቢይ መስጅድ መስጅደ-ነበዊን ለመጎብኘትና በመስጅዱ ውስጥ በተከበረው ቦታ ረውደቱ ሸሪፋ ላይ ለመስገድ ያለው መነሣሣት ውስጥን ይነቀንቃል፤ በሀሣብ ያምሣል፣ ክንፍ ቢኖር “ምነዋ ወደዚያ ወደተቀደሰው ምድር በበረርኩ!” ያስብላል።

ወዳጆቼ! እኛስ እነኚህ እጅግ የተባረኩና የተከበሩ ቀናቶች ከያዙት ምንዳ ለመቋደስ ምን ማድረግ እንችል ይሆን?

አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ ዘወትር በትእዛዙ በመገኘት ለቋሚው ሀገራቸው ለሚሰንቁ መልካም ባሮቹ በነኚህ በተባረኩ ቀናት ውስጥ ምን ዓይነት ትልቅ ምንዳ ይሆን ያዘጋጀላቸው?

የዚልሂጃ ወር የመጀመሪያዎቹ አሥር ቀናት ታላቅነት

1. አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ የማለባቸው ቀናት መሆናቸው

አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ አለ

وَالْفَجْرِ ﴿١﴾ وَلَيَالٍ عَشْرٍ ﴿٢﴾ وَالشَّفْعِ وَالْوَتْرِ ﴿٣﴾

“በጎህ እምላለሁ። በዐሥር ሌሊቶችም። በጥንዱም በነጠላውም።” (አል-ፈጅር 89፤ 1-3)

ከጃቢር ኢብኑ ዐብዱላህ (ረ.ዐ) እንደተዘገበው የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እነኚህ አሥር ቀናቶች የትኞቹ እንደሆኑ በሚያመላክተው ሀዲሣቸው ውስጥ እንዲህ ብለዋል፡-

العشر عشر الأضحى، والوتر يوم عرفة، والشفع يوم النحر

“አሥሩ ማለት አሥሩ የአድሃ ቀናት ናቸው። ‘ወትር’ /ጥንዱ/ የተባለው የዐረፋ ቀን ሲሆን ‘ሸፍዕ’ /ነጠላው/ ማለት ደግሞ የነህር /የእርዱ/ ቀናት ናቸው።” ብለዋል። ሀዲሱን ኢማም ነሣኢ እና ሃኪም በሙስሊም መስፈርት መሠረት ሰሂህ ትክከለኛ ሀዲስ ነው ብለውታል።

ኢማም በይሀቂ ከዐብዱላህ ኢብኑ ዙበይር እንደዘገቡት ደግሞ:-

ليالٍ عشر، العشر الثماني، وعرفة، والنحر

“አሥርቱ ሌሊቶች የመጀመሪያዎቹ ስምንቶቹ፣ የዐረፋ ቀን እና የእርድ ቀን ናቸው።” ብለዋል።

2. እነኚህ ቀናት “አያም መዕሉማት” /የታወቁ ቀናት/ም ይባላሉ

ይህም በሚከተለው የቁርዓን አንቀፅ ውስጥ የተጠቀሠ ነው።

وَيَذْكُرُوا اسْمَ اللَّهِ فِي أَيَّامٍ مَّعْلُومَاتٍ [٢٢:٢٨]

“በታወቁ ቀኖችም ውስጥ የአላህን ስም ያወሱ ዘንድ” (አል-ሀጅ 22፤ 27)

“የቁርዓን ተርጓሚ” በመባል የሚታወቁት ታላቁ ሰሃባ ዐብዱላህ ኢብኑ ዐባስ እነኚህ ቀናት “አሥርቱ ቀናት” ናቸው ያሉ ሲሆን በነኚህ ቀናት ውስጥ ታላቁን ጌታ አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላን በብዛት ማውሳት የተወደደ ነው።

3. ከዱኒያ ቀናቶች ሁሉ በላጮቹ

ይህም በሚከተለው ሀዲስ ውስጥ ተነግሯል። ከጃቢር (ረ.ዐ) እንደተዘገበው የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡-

أفضل أيام الدنيا أيام العشر، يعني: عشر ذي الحجة، قيل: ولا مثلهن في سبيل الله؟، قال ولا مثلهن في سبيل الله إلا رجل عفر وجهه في التراب، وذُكر عرفة، فقال يوم مباهاة ينزل الله تبارك وتعالى إلى سماء الدنيا، فيقول: عبادي شعثًا غبرًا ضاحين، جاءوا من كل فجٍّ عميق يسألون رحمتي، ويستعيذون من عذابي ولم يروا، فلم نر يومًا أكثر عتيقًا وعتيقة من النار

“ከዱኒያ ቀናቶች ሁሉ በላጮቹ አስሩ ቀናት ናቸው። ማለትም አሥሩ የዚልሂጃ ቀናት። በአላህ መንገድ ላይ መውጣትም ቢሆን የነሱ አምሣያ የለምን? ተብለው ተጠየቁ። እርሳቸውም ‘በአላህ መንገድ ላይም ቢሆንም እነሱን የሚመስል የለም። ፊቱ ከአፈር የተገናኘ ሰው (በአላህ መንገድ ላይ የሞተ) ሲቀር።’ አሉ። ስለ ዐረፋም ተወሳና መልእክተኛው (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ ‘እሱ የሙባሃት /አላህ በባሮቹ የሚኩራራበት/ ቀን ነው። አላህ ወደ ቅርቢቱ ዓለም ይወርድና ባሮቼ ተንጨፋረው፣ አቧራ የለበሱ ሆነውና ተጎሣቁለው እሩቅ ከሆነ አቅጣጫ ሁሉ እዝነቴን ሊጠይቁ እሷን ያላዩ ሲሆን ከእሣቴም በኔ ሊጠበቁ መጡ። ወንድም ሆነ ሴት በብዛት ከእሣት ነፃ የሚወጡበት እንዲዚህ ቀን አላየንም’።” (በዛር ሀዲሱን ዘግበውታል)

4. በርካታ የሀጅ ሥራዎች የሚሠሩት በነኚህ ቀናት ውስጥ ነው

ከነኚህም መካከል የዚልሂጃ ስምንተኛ ቀን በሙዝደሊፋ ይታደራል፤ በዘጠነኛው ቀን በዐረፋ ላይ ይቆማል፤ ከዚህም በተጨማሪ ለመስዋእት የሚሆን እንሠሳት መንዳት፣ ጠጠር መወርወር፣ ፀጉር መላጨት አሊያም ማሣጠር፣ በዚልሂጃ አሥረኛው ቀን ጠዋፍ ማድረግንና የመሳሰሉትን ያጠቃልላል።

5. የአምልኮ ዘርፍ የሆኑት ዋና ዋናዎቹ የሚሰበሰቡባቸው ቀናቶች ናቸው

ኢማም ሃፍዝ ኢብኑ ሀጀር ፈትሁልባሪ በተሠኘው ታዋቂ ኪታባቸው ውስጥ እንዲህ ይላሉ

والذي يظهر أن السبب في امتياز عشر ذي الحجة لمكان اجتماع أمهات العبادة فيه، وهي الصلاة والصيام والصدقة والحج، ولا يتأتى ذلك في غيره

“የዚልሂጃ አሥርቱ ቀናትን ለየት ከሚያደርጉ ነገሮች መካከል ቦታው ከአምልኮ ተግባራት ዋና ዋና የሚባሉት በአንድ ላይ ተሰባስበው የሚሠሩበት መሆኑ ነው። ይሀውም ሰላትን፣ ፆምን፣ ሰደቃን (ምጽዋትን) እና ሀጅን ያጠቃልላል። ከነኚህ ቀናት ውጭ እነኚህ ሁሉ ነገሮች አንድ ላይ የሚሰባሰቡበትን አጋጣሚ አናገኝም።” (ፈትሁልባሪ ቅጽ 2፣ ገጽ 462)

በነኚህ ቀናት ውስጥ ከሚወደዱ ሥራዎች መካከል

1. ሐጅና ዑምራ ማድረግ

በነኚህ ቀናት ውስጥ የሚሠሩ ምርጥ የአምልኮ ሥራዎች ናቸው። ምክኒያቱም የነኚህ አምልኮ ሥራዎች ትክክለኛ ወቅቱ ይህ ነውና። ከአቢሁረይራ (ረ.ዐ) እንደተዘገበው የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ)እንዲህ አሉ:-

العمرة إلى العمرة كفارة لما بينهما، والحج المبرور ليس له جزاء إلا الجنة

“አንደኛው ዑምራ እስከ ሌላኛው ዑምራ በመካከላቸው የተሰራ ወንጀልን ያብሣል፤ መብሩር /የተሟላ/ የሆነ ሀጅ ምንዳው ጀነት ብቻ እንጂ ሌላ አይደለም።” (ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)

2. በበጎ ሥራዎች ላይ መበርታት

ከዐብዱላህ ኢበብኑ ዐባስ (ረ.ዐ) እንደተዘገበው የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡-

ما مِن عمل أفضل من عمل فى هذه الأيام العشر، قالوا: ولا الجهاد؟ قال ولا الجهاد إلا رجل خرج بماله ونفسه فلم يرجع منه بشيء

“በነኚህ አሥር ቀናት ውስጥ የሚሠራ ሥራን የሚበልጥ ምንም የለም። ‘ጅሃድም ቢሆን?’ አሏቸው። እርሣቸውም ‘አዎን ጅሃድም ቢሆን ገንዘቡንና ነፍሱን ይዞ ወጥቶ ያልተመለሰ ሰው ብቻ ሲቀር።’ አሉ።” (ኢማም አህመድና ቱርሙዚ ዘግበውታል)

እንዲሁ በሌላ ዘገባም:-

لا تطفئوا سرجكم ليالي العشر

“በአሥርቱ ቀናት ለሊቶች ውስጥ መብራታችሁን አታጥፉ።” የሚል ዘገባ የመጣ ሲሆን ይህም ትርጉሙ “በነኚህ ቀናት ውስጥ ቁርዓን ቅሩ፣ በሰላትም በርትታችሁ ቁሙ ለማለት ነው” ተብሏል።

3. ዚክር ማብዛት

ከኢብኑ ዑመር (ረ.ዐ) እንደተዘገበው የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ:-

Читать полностью…

ነሲሐቱል ኣማ የልማትና መረዳጃ ተቋም/ Nesihatul ama development and relief institute

የዒድ አደራ
~
አይናችንን እንስበር፣ አጅነቢይ ከመመልከት እንቆጠብ።
ሀሳን ብኑ አቢ ሲናን - ረሒመሁላህ - ከዒድ ሲመለሱ "ስንት ቆንጆ ሴቶችን ተመለከትክ?" ብላ ሚስታቸው ብትጠይቃቸው
"ወጥቼ እስከምመለስ ድረስ ከአውራ ጣቴ ውጭ አልተመለከትኩም" ብለው ነበር የመለሱት።

ሱፍያን አሠውሪ - ረሒመሁላህ - ደግሞ "በዚህ ቀናችን የመጀመሪያ ስራችን እይታችንን መስበር ነው" ብለዋል።
አደራ በዚህ በተከበረ ቀን ከየትኛውም ሐራም ነገር እንቆጠብ። ጌታችንን አናምፅ።
ተቀበለላሁ ሚና ወሚንኩም ሳሊሐል አዕማል።

Читать полностью…

ነሲሐቱል ኣማ የልማትና መረዳጃ ተቋም/ Nesihatul ama development and relief institute

mesjideassualih?_r=1&_d=e92gaiejb6gm62&sec_uid=MS4wLjABAAAAo4NszH59lClP1Urt_NerFWrDKxQgRpuI-RAjxlfjiYfogHgkAMgr1AixYHiX9Vrm&share_author_id=7351659443312247814&sharer_language=en&source=h5_m&u_code=edahfb96b8id8f&timestamp=1711702151&user_id=7351659443312247814&sec_user_id=MS4wLjABAAAAo4NszH59lClP1Urt_NerFWrDKxQgRpuI-RAjxlfjiYfogHgkAMgr1AixYHiX9Vrm&utm_source=more&utm_campaign=client_share&utm_medium=android&share_iid=7349444753953818374&share_link_id=977f0066-2f7a-4097-ba31-6f9d7d58a988&share_app_id=1233&ugbiz_name=ACCOUNT&ug_btm=b8727%2CEnlargeAvatarActivity&social_share_type=5&enable_checksum=1" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@mesjideassualih?_r=1&_d=e92gaiejb6gm62&sec_uid=MS4wLjABAAAAo4NszH59lClP1Urt_NerFWrDKxQgRpuI-RAjxlfjiYfogHgkAMgr1AixYHiX9Vrm&share_author_id=7351659443312247814&sharer_language=en&source=h5_m&u_code=edahfb96b8id8f&timestamp=1711702151&user_id=7351659443312247814&sec_user_id=MS4wLjABAAAAo4NszH59lClP1Urt_NerFWrDKxQgRpuI-RAjxlfjiYfogHgkAMgr1AixYHiX9Vrm&utm_source=more&utm_campaign=client_share&utm_medium=android&share_iid=7349444753953818374&share_link_id=977f0066-2f7a-4097-ba31-6f9d7d58a988&share_app_id=1233&ugbiz_name=ACCOUNT&ug_btm=b8727%2CEnlargeAvatarActivity&social_share_type=5&enable_checksum=1

Читать полностью…

ነሲሐቱል ኣማ የልማትና መረዳጃ ተቋም/ Nesihatul ama development and relief institute

ከዛሬው ፕሮግራም ላይ የተወሰደ፡

Читать полностью…

ነሲሐቱል ኣማ የልማትና መረዳጃ ተቋም/ Nesihatul ama development and relief institute

Teyaka kalachu kedm belachu betlku kihyr new

Читать полностью…

ነሲሐቱል ኣማ የልማትና መረዳጃ ተቋም/ Nesihatul ama development and relief institute

አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱሏሂ ወበረካቱህ ያ ጀማአ

ለነሲሓቱል አማ ቤተሰቦቻችን በሙሉ እንኳን ለ 1445 ዓ.ሒ ለተከበረው ረመዷን ወር እንኳን አደረሳችሁ እያልን በየሳምንቱ ጁምዐ ስናደረገው የነበረዉ ሳምንታዊው የጥያቄና መልስ ውድድራችን በረመዷን ምክንያት የማይኖር መሆኑን እየገለጽን ቢኢዝኒላህ ከረመዷን በኃላ የምንቀጥለው መሆኑን እንገልፃለን።

🌹ወሩ የኢባዳና ኽይር ስራ ምታበዙበት እንዲሆን እንመኛለን።

ነሲሓቱል አማ የልማትና የየቲሞች መርጃ ተቋም

Читать полностью…
Subscribe to a channel