ሙሌ ስፖርት ስፖርታዊ መረጃዎችን ከእሁድ እስከ እሁድ ያገኙበታል የሃገር ቤት መረጃ የአውሮፓ ሊግ መረጃ ቀጥታ ስርጭት የዝውውር ዜና ለማስታወቂያ ስራ @Mulesporta @Teme_Ayu ስልክ ቁጥር +251911857852
ሪካርዶ ካላፊዮሪ በዛሬው እለት በለንደን ተገኝቶ የህክምና ምርመራውን እንደሚያጠናቅቅ ይጠበቃል።
-Sky Sports
SHARE @MULESPORT
ኑስር ማዝራዊ በብዙ ክለቦች ተፈላጊ ነው ግን ምርጫው ማንቸስተር ዩናይትድ ነው።
ምክንያቱም ልጁ ከኤሪክ ቴን ሆግ ጋር እንደገና መስራት ይፈልጋል።
-Santi Aouna
SHARE @MULESPORT
በሪያል ማድሪድ እና በአልፎንሶ ዴቪስ መካከል ዝውውሩ በነፃ እንደሚጠናቀቅ ስምምነት አለ።
-diarioas
SHARE @MULESPORT
✍️ የፓሪስ 2024 ኦሊምፒክ የመክፈቻ ስነስርዓት ላይ የኢትዮጵያን ሰንደቅዓላማ የሚይዙ አትሌቶች ታወቁ።
የ20 ኪሜ የርምጃ ተወዳዳሪው አትሌት ምስጋና ዋቁማ እና የ50ሜ የነጻ ቀዘፋ የውሃ ውና ተወዳዳሪዋ ሊና አለማየሁ ዛሬ ምሽት ከ2:30 ጀምሮ በሚከናወነው 33ኛው የፓሪስ ኦሊምፒያድ የመክፈቻ ስነስርዓት ላይ የኢትዮጵያን ሰንደቅዓላማ በመያዝ ልዑኩን የሚመሩ ይሆናል። (ልዩ ስፖርት)
SHARE @MULESPORT
✍️ ኢትዮጵያ በዘመናዊ ኦሊምፒክ ...
በጋዜጠኛ Tamiru Alemu
🇪🇹 በሶስት የስፖርት አይነቶች ትሳተፋለች፤ አትሌቲክስ፣ ውሀ ዋናና ቦክስ
🇪🇹 35 ስፖርተኞችን፣ 18 አሰልጣኞችን፣ 10 የህክምና ባለሙያዎችንና ቁጥራቸው ይፋ ያልሆነ አመራሮችን ትልካለች
🇪🇹 በአትሌቲክስ በ16 ወንድና 17 ሴት በአጠቃላይ በ33 አትሌቶች ትወከላለች
🇪🇹 በ1500፣ በ3000 መሰናክል፣ በ5000፣ በ10000 ሜትርና በማራቶን በሁለቱም ፆታዎች ለሜዳሊያ ትፋለማለች
🇪🇹 በ800 በሴት ብቻ፥ በእርምጃ ደግሞ በአንድ ወንድ አትሌት ትሳተፋለች
🇪🇹 በውሀ ዋና በሊና አለማየሁ በቦክስ ደግሞ በፍቅረማርያም ያደሳ ተወክላለች
🇪🇹 የ42 አመቱ ቀነኒሳ በቀለ በእድሜ ትልቁ አትሌት ነው፤ የልዑኩም አምበል ጭምር
🇪🇹በ5ሺህ የሚሳተፈው ቢኒያም መሀሪ በእድሜ ትንሹ ስፖርተኛ ነው፥ 17 አመት
🇪🇹 የመጀመሪያው ልዑክ ትናንት ሌሊት ወደ ፓሪስ ሄዷል
🇪🇹 ፓሪስ ለኢትዮጵያ 15ኛ የኦሊምፒክ ተሳትፎዋ ነው
🇪🇹 በኦሊምፒክ ታሪክ እስካሁን 23 ወርቅ፣ 12 ብርና 23 ነሀስ በአጠቃላይ 58 ሜዳሊያ አግኝታለች፤ ሁሉም በአትሌቲክስ የመጡ ናቸው።
(ልዩ ስፖርት)
SHARE @MULESPORT
🗣 ሃሪ ማጓየር ፡-
"አሁንም የአንድ አመት ኮንትራት አለኝ እና በኮንትራቴ ውስጥ የማራዘም አማራጭ አለ, ነገር ግን ወደ እኔ መጥተው ከእንግዲህ አልፈልግም ቢሉኝ, እኔ ራሴ ሌላ አማራጮችን እፈልጋለሁ, ግን ለእኔ እንደዚህ አይነት ነገር ተናግረው አያውቁም እናም ሙሉ ትኩረቴ እዚህ ዋንጫዎችን በማሸነፍ ላይ ነው።"
SHARE @MULESPORT
የናፖሊው አማካኝ ጄስፐር ሊንድስትሮም በ22.5 ሚሊዮን ዩሮ የውል ማፍረሻ ክፍያ ውል ኤቨርተንን ተቀላቅሏል።
SHARE @MULESPORT
አስቶንቪላ በክረምቱ በሁሉም የአውሮፓ ቡድኖች ከፍተኛውን የዝውውር ክፍያ ፈፅሟል።
አማዱ ኦናና 60 ሚሊየን ዩሮ
ጃን ማትሰን 44.5 ሚሊዮን ዩሮ
ካሜሮን አርከር 16.65 ሚሊዮን ዩሮ
ጄደን ፊሎገን 16 ሚሊዮን ዩሮ
ሳሙኤል ኢሊንግ ጁኒየር 14 ሚሊዮን ዩሮ
ሉዊስ ዶቢን 11.8 ሚሊዮን ዩሮ
ኢንዞ ባርናቻ 8 ሚሊዮን ዩሮ
ባርክሌይ 5.9 ሚሊዮን ዩሮ
SHARE @MULESPORT
የማንቸስተር ሲቲ የ2024/25 ሲዝን ሶስተኛው ማሊያ ይፋ ሆኗል።
SHARE @MULESPORT
🏆 Betwinwins ከፍ የተደረገ (ኦዶች)ዕድሎች - ከፍተኛ ዕድሎች፣ ከፍተኛ ድሎች! 🏆
የእርስዎን የስፖርት ውርርድ ትርፍ ማሳደግ ይፈልጋሉ? Betwinwins boosted odd ከፍ ያለ ዕድሎች ባላቸው ታዋቂ ግጥሚያዎች ላይ ለውርርድ እድል ይሰጥዎታል። ከፍ የተደረጉ ኦዶች ክፍልን ይጎብኙ እና የበለጠ ለማሸነፍ ዕድል ለማግኘት ውርርድዎን ያስቀምጡ!
👉 https://t.betwinwins.net/2hrmpcjn
📱 t.me/betwinwinset
አርሰናል ትኩረታቸው የካላፊዮሪን ውል በማጠናቀቅ ላይ ስለነበር ለሚኬል ሜሪኖ ምንም አይነት ይፋዊ ጥያቄ አላቀረቡም።
ለአዲሱ አማካይ መደበኛ ግንኙነቶች በሚቀጥሉት ቀናት ውስጥ ይጀምራሉ። በተጫዋቾች በኩል ግን ግንኙነቶች ተካሂደዋል።
- FabrizioRomano
SHARE @MULESPORT
ኤምሬ ቻን በኑሪ ሳሂን ስር አምበልነቱን እንደሚነጠቅ ይጠበቃል።
SHARE @MULESPORT
✅OFFICIAL፦
የማንችስተር ዩናይትድ ተስፈኛ ታዳጊ አጥቂ ጆ ሁጊል ወደ ዊጋን አትሌቲክ በውሰት አምርቷል።
SHARE @MULESPORT
ዝላታን ኢብራሂሞቪች በአንድ ወቅት የተናገራቸው አስገራሚ ንግግሮች !
🗣 " አንበሶች እራሳቸውን ከሰዎች ጋር አያወዳድሩም።
🗣 " እኔ በፍፁም እግር ኳስ አልተከተልኩም ፤ እግር ኳስ ይከተለኛል።
🗣 " እግር ኳስ ለመጫወት ሁለቱን እግሮቼን እጠቀማለሁ ነገርግን ጎል ለማስቆጠር ሰውነቴን በሙሉ እጠቀማለሁ።
ጋዜጠኛ 🗣 " ጎል ካስቆጠርክ በኋላ ምን ተሰማህ?"
🗣 " እኔ ጎል በማግባቴ ምን እንደተሰማው ግቡን ጠይቁት።
SHARE @MULESPORT
ኒኮ ዊሊያምስ በቅርቡ ውሳኔውን ይወስዳል። የሚቀጥሉት ጥቂት ሰአዓቶች ወሳኝ ይሆናሉ።
-TJuanMarti
SHARE @MULESPORT
አርሰናል ኤሚል ስሚዝ ሮውን ለፉልሃም በ35 ሚሊዮን ፓውንድ ለመሸጥ ተስማምቷል።
-Evening Standard
SHARE @MULESPORT
ፌይኖርዶች ፋኩንዶ ቦናኖቴን ለማስፈረም ከብራይተን ንግግር እያደረጉ ነው።
SHARE @MULESPORT
✍️ ጥቂት መረጃዎች ስለ ፓሪስ ኦሊምፒክ የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት ...
በ ጋዜጠኛ ብዙአየሁ ዋጋዉ
የ2024 የኦሎምፒክ ጨዋታዎች የመክፈቻ ስነ ስርዓት ከእስከዛሬ ለየት ያለ እና የማይረሳ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል። ዛሬ በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ምሽት ሁለት ሰዓት ተኩል ላይ እንደሚጀምር የሚጠበቀው የፓሪስ 2024 በኦሎምፒክ የመክፈቻ ስነ ስርዓት በታሪክ ውስጥ በጣም ከማይረሱት አንዱ እንደሚሆን ይገመታል።
የመክፈቻ ስነስርዓቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ከስታዲየም ውጭ በሴይን ወንዝ ላይ በጀልባዎች በሚያልፉ አትሌቶች ሰልፍ እና ሌሎች ትዕይንቶች ታጅቦ ይካሄዳል።
ዝግጅቱ ከመቼውም ጊዜ በተሻ ለህዝብ ክፍት የሚሆን ሲሆን በፓሪስ ዙሪያ የተዘጋጁት 80 ግዙፍ ስክሪኖች እና ድምጽ ማጉያዎችም በስፍራው ለሚገኙ ሁሉ የትእይንቱን ልዩ ስሜት እንዲጋሩ ያስችላቸዋል ተብሎ ይታመናል።
6 ኪሜ - የወንዝ ላይ ትዕይንተ ሰልፉ ጉዞ ርዝመት
94 - ጀልባዎች
በኦሊምፒክ ጨዋታ ታሪክ በውሀማ አካል ላይ በሚደረገው የመጀመሪያው የመክፈቻ ስነ-ስርዓት በሴይን ወንዝ ላይ ለሚካሄደው ሰልፍ የሚያገለግሉት ጀልባዎች ግምታዊ ብዛት 94 ነው። የውድድሩ ልዑካን ቡድኖች እና ትርኢት አቅራቢዎች ከተሳፋሪዎቻቸው መካከል ይሆናሉ።
የፕሮግራሙ ተሳታፊዎች
206 ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴዎችን የሚወክሉ አትሌቶች እና ወደ 120 የሚጠጉ የሀገር መሪዎች፣ ሉዓላዊ ገዢዎች እና ርዕሰ መስተዳድሮች ይገኛሉ።
ተመልካቾች
የፓሪስ ኦሎምፒክን የመክፈቻ ስነ ስርዓት በቴሌቪዥን እና ኦንላይን የሚከታተሉት ተመልካቾች አማካይ ቁጥር መቶ ሚሊዮኖች የሚገመት ነው። ዝግጅቱ በመላው አለም የቀጥታ ስርጭት ሽፋን ያገኛል።
የመክፈቻ ስነ ስርዓቱ አራት ሰዓት ተኩል ይወስዳል ተብሎ ተገምቷል።
ልዩ ስፖርት
SHARE @MULESPORT
🗣 ኔይማር ስለ ፍጹም ተጫዋቹ፡-
"የክርስቲያኖ የአካል ብቃት፣ የዝላታን የመለጠጥ ችሎታ፣ የራሞስ ጭንቅላት፣ የምባፔ ፍጥነት፣ የሜሲ ግራ እግር ፣ የኔ ቀኝ እግር ፣ የሌዋንዶውስኪ አጨራረስ፣ የካንቴ ታክል እና የቬራቲ ፈጠራ።"
SHARE @MULESPORT
ፉልሀም ስኮት ማክቶሚኒን ለማስፈረም አሁንም እየሰራ ነው። በማንቸስተር ዩናይትድ የዋጋ ግምት እና በፉልሃም አቅርቦት መካከል ክፍተት ስላለ በቅርቡ አዲስ ጥያቄ ይቀርባል ተብሎ ይጠበቃል።
ስካይ ስፖርት
SHARE @MULESPORT
በሳውዲ አረቢያው አል ኢቲሃድ እና በማንቸስተር ሲቲ መካከል ለኤደርሰን የተደረገው ድርድር ያልተሻሻለ እና አሁንም የተወሳሰበ ነው።
የሲቲ አቋም ግልጽ ነው, ከ 50-60 ሚሊዮን ዩሮ ይፈልጋሉ አለዚያ ተጫዋቹ የሚለቅበት ምንም አይነት መንገድ የለም።
አል ኢቲሃድ ከላሊጋ ሌሎች አማራጮችን እያጤነ ነው።
- Fabrizio Romano
SHARE @MULESPORT
ተወዳጁ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሊጀምር 21 ቀና ብቻ ቀርተዋል 🔥
የአለማችን ምርጡ ሊግ ሊመለስ ነው 👌
SHARE @MULESPORT
🗣 ሃሪ ማጓየር ስለወደፊቱ ህይወቱ፡-
"እውነቱን ለመናገር የሰማሁት ነገር ቢኖር እዚህ ማንቸስተር ዩናይትድ ውስጥ የእቅዱ አካል መሆኔን ነው። ለታላቅ ዋንጫዎች ለመታገል ዝግጁ ነኝ።"
SHARE @MULESPORT
ካርሎ አንቸሎቲ ፌርላንድ ሜንዲን ዝቅተኛ ደረጃ የተሰጠው እና ጥሩ ተጫዋች አድርጎ ይመለከተዋል። ካርሌቶ የሜንዲን አዲስ ውል ለመፈጸም ወሳኙ ሰው ነበር።
- FabrizioRomano
SHARE @MULESPORT
አል ሂላል ባርሳን ስለ ቪቶር ሮኬ አነጋግሯቸዋል፣ እሱም በዚህ ክረምት በእጩ ዝርዝራቸው ላይ ነው።
ባርሴሎና እሱን ለመሸጥ ዝግጁ ሊሆን ይችላል።
ቪቶር ሮኬ ባርሴሎናን የተቀላቀለው በጥር 2024 ነበር።
- FabrizioRomano
SHARE @MULESPORT
✅OFFICIAL፦
የፈረንሳዩ ክለቦ ቦርዶ በኪሰራ ምክንያት የልምምድ መዕከሉን እስከመዘጋት ድረስ ደርሷል።
SHARE @MULESPORT
አሁን የሚደረጉት ድርድሮች በጥሩ ሁኔታ ላይ ሲደርሱ ጁቬንቱሶች ለካሪም አይዴሚ የመጀመሪያ ጥያቄኣቸውን ለዶርትሙንድ ያቀርባሉ።
-Fabrizio Romano
SHARE @MULESPORT
ጄሰፐር ሊንድስትሮም እንደ አዲስ የኤቨርተን ተጫዋች ሜዲካሉን ጨርሷል አሁን ኮንትራቱን ሊፈራረም ተዘጋጅቷል።
-Fabrizio Romano
SHARE @MULESPORT