"እንግዲህ፡ንስሓ፡ግባ፤አለዚያ፡ፈጥኜ፡ እመጣብሃለሁ፡፡" ራዕ 2፥16
አንድ ሰው ሁለት ልጆች ነበሩት
ወደ አንደኛው ቀርቦ፦ ልጄ ሆይ፥ ዛሬ ሂድና በወይኔ አትክልት ሥራ አለው።
እርሱም መልሶ፦ እንቢ አለ፤ ኋላ ግን ተጸጸተና ሄደ።
ወደ ሁለተኛውም ቀርቦ እንዲሁ አለው እርሱም መልሶ፦ እሺ ጌታዬ አለ፤ ነገር ግን አልሄደም።
ከሁለቱ የአባቱን ፈቃድ ያደረገ ማን ነው? አላቸው
ፊተኛው አሉት።
ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፦ እውነት እላችኋለሁ፥
ቀራጮችና ጋለሞቶች ወደ እግዚአብሔር መንግሥት በመግባት ይቀድሙአችኋል።
ማቴዎስ 21÷28
ወገኔ እኛ እሺ ብለነው ነገር ግን ትእዛዙን ሳንፈጽም በሃሜት እና ንስሃ በገቡት ሰዎች ላይ አቃቂር በመፈለግ ተጠምደናል ፤ ግን እነርሱ ትእዛዙን እንቢ ብለው ነገር ግን ተጸጽተው ተመልሰው ትእዛዙን እየፈጸሙ የእግዚአብሔርን መንግስት በመውረስ እየቀደሙን ነው።
እባካችሁ ወሬውን ትተን ለመንግስተ ሰማያት የሚያበቃ ሥራ እንስራ።
ስለሌላው ሃሳብ መስጠት የመንግስተ ሰማያት ቁልፍ አይሆነንም።
ውብ አሁን
💛
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
🕊 ዐቢይ ጾም [ ጾመ እግዚእ ] 🕊
▷ " የ ጸ ሎ ት ባ ህ ር ያ ት ! "
[ 💖 ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ 💖 ]
[ 🕊 ]
---------------------------------------------------
" እንግዲህ እግዚአብሔርን በመምሰልና በጭምትነት ሁሉ ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖር ፥ ልመናና ጸሎት ምልጃም ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁሉ እንዲደረጉ ከሁሉ በፊት እመክራለሁ።"
[ ፩.ጢሞቴ.፪፥፩ ]
🕊 💖 🕊
ማግሰኞ - ሚያዚያ 08 2016 ዓ.ም
ቆላስይስ 1-4
ሰላም ለሁላችሁ ይሁን! በዛሬው የዐቢይ ጾም ንባባችን ቆላስይስ 1-4 ድረስ እናነባለን።
ከንባብ በፊት የሚደረግ ጸሎት፡ “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፤ የአንተን ቃላት እሰማ እና እረዳ ዘንድ፥ እንዲያውም ፈቃድህን ለመፈጸም እበቃ ዘንድ የልቤን ጆሮዎች እና ዓይኖች ክፈትልኝ።” (ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ)
የዛሬው ንባብ ቆላስይስ 1-4 ነውና፥ እርሱ እንዲነበብ ይሁን።
መልካም ንባብ!
/channel/c/2014228571/1
@OrthodoxTewahdoBooks
ሰኞ - ሚያዚያ 07 2016 ዓ.ም
ፊልጵስዩስ 1-4
ሰላም ለሁላችሁ ይሁን! በዛሬው የዐቢይ ጾም ንባባችን ፊልጵስዩስ 1-4 ድረስ እናነባለን።
ከንባብ በፊት የሚደረግ ጸሎት፡ “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፤ የአንተን ቃላት እሰማ እና እረዳ ዘንድ፥ እንዲያውም ፈቃድህን ለመፈጸም እበቃ ዘንድ የልቤን ጆሮዎች እና ዓይኖች ክፈትልኝ።” (ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ)
የዛሬው ንባብ ፊልጵስዩስ 1-4 ነውና፥ እርሱ እንዲነበብ ይሁን።
መልካም ንባብ!
/channel/c/2014228571/1
@OrthodoxTewahdoBooks
💛
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
🕊 ዐቢይ ጾም [ ጾመ እግዚእ ] 🕊
▷ " ሸ ክ ማ ች ሁ የ ከ በ ደ ! "
[ 💖 አቡነ አትናቴዎስ ዘእስክንድር 💖 ]
[ 🕊 ]
---------------------------------------------------
" እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ ፥ ወደ እኔ ኑ ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ።"
[ ማቴ . ፲፩ ፥ ፰ ]
🕊 💖 🕊
🕊
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን †
[ † እንኩዋን ለጻድቅ ሰው "ቅዱስ ኢያቄም" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ † ]
🕊 † ቅዱስ ኢያቄም † 🕊
ቅዱስ ሰው ኢያቄም የሰማይና የምድር ንግስት እመቤታችን ድንግል ማርያም አባት ነው:: ቅዱሱ ከቅስራ አባቱ የተወለደ የቅዱስ ዳዊት ዘመድ ሲሆን "ኢያቄም : ሳዶቅ እና ዮናኪር" በሚባሉ ፫ [3] ሰሞቹ ይታወቃል::
ቅዱስ ኢያቄም እንደ ኦሪቱ ሥርዓት አድጎ : ከነገደ ሌዊ የተወለደች : የማጣትና ["ጣ" ጠብቆ ይነበብ] ሔርሜላን ልጅ ሐናን አግብቷል:: ሁለቱም በንጽሕናና በምጽዋት እንደ ሕጉ ቢኖሩም መውለድ የማይችሉ መካኖች ነበሩ::
በዚሕ ምክንያት ከወገኖቻቸው ሽሙጥን ታግሰው በታላቅ ሐዘን ኑረዋል:: ከጊዜ በሁዋላ ግን ስም አጠራሯ የከበረ : ደም ግባቷ ያማረ ልጅን ይሰጣቸው ዘንድ እግዚአብሔር መረጣቸውና ከተባረከ ሰውነታቸው ድንግል ማርያምን ወለዱ::
እርሷ "ወላዲተ አምላክ" ተብላ እነርሱን "የእግዚአብሔር የሥጋ አያቶች" አሰኘቻቸው:: ቅዱስ ኢያቄም እመቤታችንን ቤተ መቅደስ ካስገቡ ከጥቂት ዓመታት በሁዋላ በመልካም ሽምግልና አርፎ ከቅድስት ሐና ጋር በጌቴሴማኒ ተቀብሯል::
+ ቅዱሱ ሰው ያረፈበት ዓመት ግልጽ ባይሆንም ድንግል እመቤታችን ፰ ዓመት ሲሞላት ፪ ቱም ቅዱሳን ወላጆቿ በሕይወተ ሥጋ እንዳልነበሩ አበው ነግረውናል:: በማረፍ ደግሞ ቅድስት ሐና ትቀድማለች:: መቃብሩ ዛሬ ድረስ አለ:: ያደለው ከቦታው ደርሶ ይሳለመዋል::
አምላካችን ከቅዱስ ኢያቄም በረከት ያሳትፈን::
🕊
[ † ሚያዝያ ፯ [ 7 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ቅዱስ ኢያቄም [ የድንግል ማርያም አባት ]
፪. ቅዱስ አጋቦስ ሰማዕት
፫. ቅድስት ቴዎድራ ሰማዕት
፬. ቅዱስ አባ መቅሩፋ ጻድቅ
[ † ወርሐዊ በዓላት ]
፩. ሥሉስ ቅዱስ [ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ]
፪. አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
፫. አባ ሲኖዳ [ የባሕታውያን አለቃ ]
፬. አባ ዳንኤል ዘገዳመ ሲሐት
፭. አባ ባውላ ገዳማዊ
፮. ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ
፯. ቅዱስ አግናጥዮስ [ ለአንበሳ የተሰጠ ]
" መሠረቶቿ በተቀደሱ ተራሮች ናቸው::
ከያዕቆብ ድንኩዋኖች ይልቅ እግዚአብሔር የጽዮንን ደጆች ይወዳቸዋል:: የእግዚአብሔር ከተማ ሆይ በአንቺ የተደረገው ነገር ድንቅ ነው . . . ሰው እናታችን ጽዮን ይላል:: በውስጥዋም ሰው ተወለደ:: እርሱ ራሱም ልዑል መሠረታት:: " [መዝ.፹፮፥፩-፮]
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖 🕊 💖
🕊
† [ ከዚህ ሰውነት ማን ያድነናል ? ! ] †
🕊 💖 🕊
[ ሁለት ኦርቶዶክሳዊ መዝሙሮች ]
የሥጋ ፈቃዶቻችን ከማንም ይልቅ የገዛ ራሳችን ጠላቶች ናቸው። የማንወደውን ክፉ ነገር እናደርጋለን ፤ የምንወደውን በጎ ነገር ደግሞ ያንን ደግሞ አናደርግም። እነዚህ ሁለት መዝሙሮች ይህንን ያሳስባሉ።
†
" በእኔ ማለት በሥጋዬ በጎ ነገር እንዳይኖር አውቃለሁና ፤ ፈቃድ አለኝና ፥ መልካሙን ግን ማድረግ የለኝም። የማልወደውን ክፉን ነገር አደርጋለሁና ዳሩ ግን የምወደውን በጎውን ነገር አላደርገውም።
የማልወደውን የማደርግ ከሆንሁ ግን ያን የማደርገው አሁን እኔ አይደለሁም ፥ በእኔ የሚኖር ኃጢአት ነው እንጂ። እንግዲያስ መልካሙን አደርግ ዘንድ ስወድ በእኔ ክፉ እንዲያድርብኝ ሕግን አገኛለሁ።
በውስጡ ሰውነቴ በእግዚአብሔር ሕግ ደስ ይለኛልና ፥ ነገር ግን በብልቶቼ ከአእምሮዬ ሕግ ጋር የሚዋጋውንና በብልቶቼ ባለ በኃጢአት ሕግ የሚማርከኝን ሌላ ሕግ አያለሁ።
እኔ ምንኛ ጎስቋላ ሰው ነኝ ! ለዚህ ሞት ከተሰጠ ሰውነት ማን ያድነኛል?
በኢየሱስ ክርስቶስ በጌታችን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን። እንግዲያስ እኔ በአእምሮዬ ለእግዚአብሔር ሕግ ፥ በሥጋዬ ግን ለኃጢአት ሕግ እገዛለሁ። " [ ሮሜ.፯፥፲፰-፳፭ ]
† 🕊 ክብርት ሰንበት 🕊 †
💖
🕊 💖 🕊
[ † ሚያዝያ ፮ [ 6 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ቅዱሳን አዳምና ሔዋን [ የዕረፍታቸው መታሠቢያ ]
፪. ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት [ ልደቱ ]
፫. አባታችን ቅዱስ ኖኅ [ ልደቱ ]
፬. ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ [ የጌታችንን ጐኑን የዳሰሰበት ]
፭. ቅድስት ማርያም ግብፃዊት [ ከኃጢአት ሕይወት ተመልሳ በፍፁም ቅድስናዋ የተመሠከረላት እናት ]
[ † ወርኀዊ በዓላት ]
፩. ቅድስት ደብረ ቁስቁዋም
፪. እናታችን ሐይከል
፫. ቅዱስ ኤልያስ ነቢይ
፬. ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያ
፭. ቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊ
፮. ቅድስት ሰሎሜ
፯. አባ አርከ ሥሉስ
፰. አባ ጽጌ ድንግል
፱. ቅድስት አርሴማ ድንግል
" እንግዲህ ምን እላለሁ? ስለ ጌዴዎንና ስለ ባርቅ: ስለ ሶምሶንም: ስለ ዮፍታሔም: ስለ ዳዊትና ስለ ሳሙኤልም: ስለ ነቢያትም እንዳልተርክ ጊዜ ያጥርብኛልና::
እነርሱ በእምነት መንግሥታትን ድል ነሡ:: ጽድቅን አደረጉ:: የተሰጠውን የተስፋ ቃል አገኙ:: የአንበሶችን አፍ ዘጉ:: የእሳትን ኃይል አጠፉ:: ከሰይፍ ስለት አመለጡ:: ከድካማቸው በረቱ:: በጦርነት ኃይለኞች ሆኑ:: የባዕድ ጭፍሮችን አባረሩ:: " [ ዕብ. ፲፩፥፴፪-፴፭ ] (11:32-35 )
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖 🕊 💖
ቅዳሜ - ሚያዚያ 05 2016 ዓ.ም
ገላትያ 1-6
ሰላም ለሁላችሁ ይሁን! በዛሬው የዐቢይ ጾም ንባባችን ገላትያ 1-6 ድረስ እናነባለን።
ከንባብ በፊት የሚደረግ ጸሎት፡ “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፤ የአንተን ቃላት እሰማ እና እረዳ ዘንድ፥ እንዲያውም ፈቃድህን ለመፈጸም እበቃ ዘንድ የልቤን ጆሮዎች እና ዓይኖች ክፈትልኝ።” (ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ)
የዛሬው ንባብ ገላትያ 1-6 ነውና፥ እርሱ እንዲነበብ ይሁን።
መልካም ንባብ!
/channel/c/2014228571/1
@OrthodoxTewahdoBooks
"መኑ ውእቱ ገብር ኄር ወምእመን ዘይረክቦ እግዚኡ በምግባረ ሠናይ ወይሰይሞ ዲበ ኩሉ ንዋዩ ካዕበ ይቤሎ እግዚአብሔር ገብር ኄር ወምእመን ዘበዉኁድ ምእመነ ኮንከ ዲበ ብዙኅ እሠይመከ ባእ ውስተ ፍሥሐሁ ለእግዚእከ።"
@MeladeMelad
🕊
[ † እንኳን አምላካችን እግዚአብሔር ከሥራው ሁሉ ላረፈባት የመጀመሪያዋ ዕለተ ሰንበትና ለቅዱስ ሕዝቅኤል ነቢይ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ]
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †
† አምላካችን እግዚአብሔር በ፮ [6] ቱ ቀናት ፳፪ [22] ቱን ሥነ ፍጥረት ፈጥሮ በ፯ [7] ኛዋ ዕለት ደክሞት ያይደለ ለእኛ ያስተምረንና ሰንበትን ይቀድስልን ዘንድ አረፈ::
ዕለተ ሰንበት ማለት አንዳንድ ልባቸውን ያሳወሩ ሰዎች እንደሚያወሩት የሥራ መፍቻ ቀን ሳትሆን :-
፩. ከሥጋዊ ተግባራችን ታቅበን መንፈሳዊ ተግባራትን [፮ [6] ቱ ቃላተ ወንጌልን] የምንፈጽምባት:
፪. ለጊዜውም ቢሆን ጥቂት እርፍ ብለን አማናዊቷን ዕረፍተ መንግስተ ሰማያት የምናስብባት ዕለት ናት::
እንደ ቤተ ክርስቲያን ስርዓትም ለሰንበተ ክርስቲያን ቀዳሚውን ቦታ ሰጥተን ቀዳሚት ሰንበትንም እንደሚገባ ልንጠቀምባት ይገባል::
† የሰንበት ጌታዋ: የምሕረትም አባቷ ጌታችን እግዚአብሔር ለዕረፍተ መንግስቱ የተዘጋጀን ያድርገን::
🕊 † ቅዱስ ሕዝቅኤል ነቢይ † 🕊
† ነቢዩ ቅዱስ ሕዝቅኤል የነበረው ቅ/ል/ክርስቶስ በ፭፻ [500] ዓመት አካባቢ ሲሆን የጼዋዌ [ምርኮ] አባልም ነበር:: እሥራኤልና ይሁዳ ወደ ባቢሎን በምርኮ ሲወርዱ አብሮ ወርዷል:: ቅዱሱ ከ፬ [4]ቱ ዐበይት ነቢያት አንዱ ሲሆን ሐረገ ትንቢቱም በ፵፰ [48] ምዕራፎች የተዋቀረ ነው::
በዘመኑ ሁሉ ቅድስናን ያዘወተረው ቅዱሱ ከደግነቱ የተነሳ በጸጋማይ [ግራ] ጐኑ ተኝቶ ቢጸልይ ፮፻ [600] ሙታንን አስነስቷል:: ወገኖቹ እሥራኤልንም ያለ መታከት አስተምሯል:: ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በዚህች ዕለት ታላቁን ራዕይ እንዳየ ታስተምራለች:: ነቢዩ በፈለገ ኮቦር ካያቸው ምሥጢራት እነዚህን ያነሷል :-
፩. እግዚአብሔርን በዘባነ ኪሩብ ተቀምጦ ሲሠለስና ሲቀደስ አይቶታል:: የኪሩቤልንም ገጸ መልክእ በጉልህ ተመልክቷል:: [ሕዝ.፩፥፩]
፪. በመጨረሻው ቀን ትንሳኤ ሙታን : ትንሳኤ ዘጉባኤ እንደሚደረግም ተመልክቷል:: [ሕዝ.፴፩፥፩]
፫. እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ኆኅት ኅትምት/ኆኅተ ምሥራቅ [የምሥራቅ ደጅ] ሁና አይቷታል::
ይሕ የምሥራቅ ደጅ [በር] ለዘለዓለም እንደታተመ ይኖራል:: የኃያላን ጌታ ሳይከፍት ገብቶ: ሳይከፍት ወጥቷልና:: [ሕዝ.፵፬፥፩] በመጨረሻ ሕይወቱ እሥራኤል ለክፋት አይቦዝኑምና ነቢዩን አሰቃይተው ገድለውታል::
† ከነቢዩ በረከት አምላኩ ያድለን::
🕊
[ † ሚያዝያ ፭ [ 5 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ በዓላት ]
፩. እግዚአብሔር ሰንበትን ቀደሰ
፪. ቅዱስ ሕዝቅኤል ነቢይ
፫. ቅዱስ ዲዮስቆሮስ [ክፉ ላለመናገር ድንጋይ ጐርሶ የኖረ አባት]
፬. ቅድስት ታኦድራ
፭. ቅዱስ አርሳኒ
፮. ቅዱስ ያሬድ ካህን [ልደቱ]
[ † ወርሐዊ በዓላት ]
፩. ቅዱስ ዼጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት
፪. ቅዱስ ዻውሎስ ሐዋርያ
፫. አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ጻድቅ [አባ ገብረ ሕይወት]
፬. ቅዱስ ዮሐኒ ኢትዮዽያዊ
፭. ቅዱስ አሞኒ ዘናሒሶ
† " እግዚአብሔር ሰንበቴን ስለሚጠብቁ: ደስ የሚያሰኘኝንም ነገር ስለሚመርጡ: ቃል ኪዳኔንም ስለሚይዙ ጃንደረቦች እንዲህ ይላልና :- በቤቴና በቅጥሬ ውስጥ ከወንዶችና ከሴቶች ልጆች ይልቅ የሚበልጥ መታሰቢያና ስም እሰጣቸዋለሁ:: የማይጠፋም የዘለዓለም ስም እሰጣቸዋለሁ:: " † [ኢሳ.፶፮፥፬-፭]
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖 🕊 💖
💛
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
🕊 ዐቢይ ጾም [ ጾመ እግዚእ ] 🕊
▷ " የ ጽ ሞ ና ጊ ዜ ! "
[ 💖 አቡነ አትናቴዎስ ዘእስክንድር 💖 ]
[ 🕊 ]
---------------------------------------------------
" በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ አልሁ።
ከዝምታ የተነሣ እንደ ዲዳ ሆንሁ ፥ ለበጎ እንኳ ዝም አልሁ ፥ ቍስሌም ታደሰብኝ።" [ መዝ.፴፱ ፥ ፩ ]
🕊 💖 🕊
†
[ ተዋሕዶ ፍጽምት የቅዱሳን ሃይማኖት ]
▬▬▬▬▬▬ † ▬▬▬▬▬▬
[ አንድ አካል አንድ ባሕርይ ነው እንጂ ! ]
--------------------------------------------------
" ከሦስቱ አካላት አንዱ አካል ከሰማይ መውረዱን ፤ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ነፍስና ሥጋን ነሥቶ ሰው መሆኑን ፤ እግዚአብሔር ቃል መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእርሷ ተወልዶ መገለጡን ፤ በተዋሕዶ ሰው የሆነ አምላክ ሆኖ በሰዎች መካከል መመላለሱን አምናለሁ፡፡
አንዱ አምላክ ነው ፥ አንዱ ዕሩቅ ብእሲ ነው አልልም፡፡ እግዚአብሔር ቃል ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ከነሣው ሥጋው ጋር አንድ አካል አንድ ባሕርይ ነው እንጂ !
ከእግዚአብሔር የተወለደው ከድንግል የተወለደው ይኸው አንዱ ነው ። አንድ ሲሆንም ይታመማል ፤ አይታመምም፡፡ በሥጋው ይታመማል ፤ ሕማማችንንም ገንዘብ ያደርጋል ፤ በመለኮቱ ሕማማችንን ያርቃል፡፡ በሞቱም ሞታችንን ያጠፋል ፤ ለእኛ ለአገልጋዮቹ ድኅነትን የሰጠን እርሱ ነው፡፡ ለአመኑበትም ትንሣኤን ገለጠላቸው፡፡ የዘለዓለም ሕይወትን በጌትነቱ በሚያወርሳት በመንግሥተ ሰማያት ትሰጥ ዘንድ ያላት ተድላ ነፍስንም ሰጣቸው፡፡"
[ አቡሊዲስ ]
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፤ ወለወላዲቱ ድንግል ፤ ወለመስቀሉ ክቡር። አሜን።
† † †
💖 🕊 💖
🕊
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን †
† ሚያዝያ ፬ †
🕊 ቅዱሳን ፊቅጦር: ዳኬዎስና ኤርሞ [ ሰማዕታት ] 🕊
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሚያዝያ አራት በዚች ቀን የከበሩ ፊቅጦርና ዳኬዎስ ኤርሞ ሌሎችም ብዙዎች ሰዎች ሴቶችና ወንዶች ደናግሎች በሰማዕትነት ሞቱ።
እሊህም ቅዱሳን በታላቁ ቈስጠንጢኖስና በልጁ ዘመነ መንግስት የጣዖታትን ቤቶች አፍርሰው ጣዖታትንም ሰብረው አቃጥለው በቦታቸውም አብያተ ክርስቲያናትን ሠርተው አምላክን በወለደች በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ስም በሌሎችም በብዙዎች ቅዱሳን ስም ታቦቱን ሰይመው ነበር።
ከሀዲ ዮልያኖስም በነገሠ ጊዜ የጣዖትን አምልኮ አቆመ የጣዖቱንም ካህናቶች አከበራቸው ብዙዎች ክርስቲያኖችንም አስገደለ።
የእሊህ ቅዱሳን ዜናቸው አስቀድሞ በጣዖታት ቤቶች ላይ ያደረጉት ጣዖታትን እንደሰበሩ ሁሉ ተሰማ።ይዘውም ጽኑ ሥቃይን አሠቃዩአቸው ብዙ ቀንም ሲሰቅሏቸውና ሲገርፉአቸው ቆዳቸውንም በሾተል ሲነጥቁ ኑረው በኃላም ቸብቸቧቸውን በሰይፍ ቆረጡ።
በመንግሥተ ሰማያትም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበሉ በረከታቸው ከእኛ ጋር ለዘላለሙ ትኑር አሜን።
🕊
[ † ሚያዝያ ፬ [ 4 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ በዓላት ]
፩. እግዚአብሔር የሰው ልጅን ፈጠረ
፪. ቅዱሳን አብርሃ ወአጽብሐ [ጻድቃን ነገሥት]
፫. ቅዱሳን ፊቅጦር: ዳኬዎስና ኤርሞ [ሰማዕታት]
[ † ወርኀዊ በዓላት ]
፩. ቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጉዋድ [ወንጌላዊው]
፪. ቅዱስ እንድርያስ ሐዋርያ
፫. ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት
፬. ቅዱስ ዮሐንስ ዘሐራቅሊ [ሰማዕት]
" እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ:: በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው:: ወንድና ሴት አድርጐ ፈጠራቸው . . . እግዚአብሔርም ያደረገውን ሁሉ አየ:: እነሆም እጅግ መልካም ነበረ:: " [ዘፍ.፩፥፳፮]
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖 🕊 💖
†
💖 [ የትሕርምት ሕይወት ! ] 💖
🕊 💖 🕊
[ “ አገልግሎትን በተመለከተ ! " ]
[ ሥራን አስመልክቶ የሰጠው ትምህርት ! ]
--------------
ወደጄ ሆይ ! በምትሠራው ሥራ ምክንያት አትዘን፡፡
“በምትሠራው ሥራ ላይ በፍጹም ስኬታማ ልሆን አልቻልኩም፡፡ እኔ ስንፍናን የተሞላሁ ፣ የደነዘዝሁ ነኝና በፍጹም ይህን ተግባር ልፈጸም አልችልም፡፡ እጆቼ ያለ ፍሬ ከሥራው ብዛት የተነሣ ዝለዋል፡፡ ሥራውን ለመሥራት አሁን አቅሙ የለኝም ስለዚህ ወደመጣሁበት እመለሳለሁ ... የሚል ሐሳብ በአእምሮህ ውስጥ ከቶ አይመላለስ::
እንደ አንድ አማኝ በእግዚአብሔር ታመን ፥ እንዲህ ባለ ነገርም ተስፋ አትቁርጥ፡፡ ነገር ግን ወደ መንግሥቱና ወደ እርሱ ደስታ ስለጠራህ ስለ ጌታችን ስለ መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብለህ መከራውን ሁሉ ታግሠህ ኑር፡፡ እንዲህ ተብሎ እንደተጻፈ ፦ “እውነት እላችኋለሁ ፥ የሰናፍጭ ቅንጣት የሚያህል እምነት ቢኖራችሁ ፥ ይህን ተራራ ከዚህ ወደዚያ እለፍ ብትሉት ያልፋል ፤ የሚሳናችሁም ነገር የለም፡፡” [ማቴ.፲፯፥፳]
ስለዚህ ተወዳጆች ! ሆይ እምነት ይኑረን ፤ እኛ ተስፋ ያደረግናቸው ከቶ ሊያድኑን የማይችሉ ሰዎችን ሳይሆን እግዚአብሔርን ነው፡፡ እንዲህ ተብሎ እንደተጻፈ ፦ “በእግዚአብሔር የታመኑ እንደማይታወክ ለዘላለም እንደሚኖር እንደ ጽዮን ተራራ ናቸው::” [መዝ.፻፳፬፥፩] የኃያላን ጌታ ሆይ በአንተ ተስፋ የሚያደርጉ ብፁዓን ናቸው፡፡ "
[ ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ]
🕊 💖 🕊
🕊
[ † እንኳን ለብጹዐን ጻድቃን: ቅዱስ ዞሲማስ እና አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ]
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †
🕊 † ብጹዐን ጻድቃን † 🕊
† በዚህ ቀን ብሔረ ብጹዐን ውስጥ የሚኖሩ ጻድቃን ይታሠባሉ:: በሃይማኖት ትምሕርት ፭ [5] ዓለማተ መሬት አሉ:: እነሱም አቀማመጣቸው ቢለያይም ከላይ ወደ ታች ፦
፩. ገነት [ በምሥራቅ ]
፪. ብሔረ ሕያዋን [ በሰሜን ]
፫. ብሔረ ብጹዐን [ ብሔረ - አዛፍ - እረፍት ] {በደቡብ}
፬. የእኛዋ ምድር [ ከመሐል ] እና
፭. ሲዖል [ በምዕራብ ] ናቸው::
† ከእነዚሕ ዓለማት ባንዱ የሚኖሩ የብሔረ ብጹዐን ጻድቃን ፦
- ኃጢአትን የማይሠሩ::
- ለ ፲፻ [1,000] ዓመታት የሚኖሩ::
- ሐዘን የሌለባቸው::
- በዘመናቸው ፫ ልጆችን ወልደው ፪ ወንድና አንድ ሴት] ሁለቱ ለጋብቻ: አንዱን ለቤተ እግዚአብሔር አገልግሎት የሚያውሉ ሰዎች ናቸው::
† ቅዱሳኑ ወደዚሕ ቦታ የገቡት በነቢዩ ኤርምያስ እና በቅዱስ እዝራ ዘመን ሲሆን አንዴ የተወሰኑት በዘመነ ሰማዕታት ወጥተው በዚሕ ቀን ተሰይፈዋል::
† በመጨረሻ ግን በሐሳዌ መሲሕ ዘመን ወጥተው ሰማዕትነትን ይቀበላሉ::
† የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምሕረቱና ይቅርታው ለምናምን ሁሉ ይደረግልን:: ከደግነታቸውም በረከትን አይንሳን::
🕊 አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ 🕊
አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ አባታቸው መልአከ ምክሩ : እናታቸው ወለተ ማርያም ይባላሉ፡፡ የተወለዱበት ልዩ ቦታው ወሎ ክፍለ ሀገር ዳውንት ነው፡፡ በተወለዱ ዕለት ተነስተው በእግራቸው ቆመው ሦስት ጊዜ "ስብሐት ለአብ : ስብሐት ለወልድ : ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ" ብለው አመስግነዋል፡፡
- የስማቸው ትርጓሜ "የአብ : የወልድ : የመንፈስ ቅዱስ እስትንፋስ" : አንድም "የክርስቶስ እስትንፋስ" ማለት ነው፡፡ ቅዱስ ሚካኤል እየጠበቃቸውና በመንገዳቸው ሁሉ እየመራቸው ነው ያደጉት፡፡ መንፈስ ቅዱስ ልቡናቸውን ብሩህ አድርጎላቸው በ፭ ዓመታቸው የቅዱሳት መጽሐፍት ቃላትን፣ ብሉያትንና ሐዲሳትን፣ ድርሳናትንም ጠንቅቀው ዐውቀዋል፡
+ በተወለዱ በ፲፬ ዓመታቸው ወደ አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ደብረ ሐይቅ ገዳም ሄደው ከባሕር ዳር ቆመው የሙሴን ጸሎት ወደ እግዚአብሔር በጸለዩ ጊዜ የታዘዘ መልአክ መጥቶ ባህሩን አሻግሯቸው ወደ ቤተክርስቲያን ገብተዋል፡፡ ለ፫ ዓመትም በኃይቅ ገዳም ለመነኮሳት እንጨት በመልቀምና ውሃን በመቅዳት : ለአባቶች መነኮሳት ምግብ ሊሆናቸው ከባህር ውስጥ አሳን በማውጣት አገልግለዋል፡፡
አባታችን እስትንፋሰ ክርስቶስ ፵ መዓልትና ፵ ሌሊት ከጾሙ በኋላ ምንም እህል ሳይቀምሱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አስቀድሞ ለሙሴ በደብረ ሲና እንደሰጠው ለአባታችንም ወደ እርሳቸው መጥቶ ዓሥሩን ቃላተ ኦሪትና ስድስቱን ቃላተ ወንጌል በውስጣቸው የተጻፈባቸው ሁለት ጽላቶችን ሰጥቷቸዋል፡፡
+አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ከሠሩ በኋላ ዕለቱን ስንዴ ዘርተው፣ ወይን ተክለው፣ ጽድን ወይራንና ግራርን ተክለው በአንዲት ቀን ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ዕለቱን አድርሰዋል፡፡ስንዴውን ለመስዋዕት ወይኑን ለቁርባን በታምራት አድርሰዋል፡፡
+አባታችን በጸሎት ላይ እንዳሉ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ተልኮ መጥቶ አባታችንን በደመና ጭኖ ወስዶ ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ፊት አቆማቸው፡፡ ጌታንም በቅዱሳኖቹ ሁሉ እንዲባረኩ ካደረጋቸው በኋላ መልአኩን "ወደ ተወለድኩባትና ወደ ኖርኩባት ቦታ ወደ
ኢየሩሳሌም አድርሰው" ብሎት ኢየሩሳሌምን አሳልሞ ሀገራችን መልሶ አምጥቷቸዋል፡፡ ሁሉንም የኢትዮጵያን ቅዱሳት ገዳማትንም ተዘዋውሮ ሲጎበኙ በሕይወተ ሥጋ የሌሉት የየገዳማቱ ቅዱሳን ሁሉ በአካል ይገለጡላቸው ነበር፡፡
+ጎጃም ውስጥ እያስተማሩ፣ እያጠመቁ፣ ! የታመሙትን እየፈወሱ፣ የዕውራንን ዐይን እያበሩና ሙታንን እያስነሱ ብዙ ካገለገሉ በኋላ ለዘጠኝ ዓመታት በባሕር ውስጥ ገብተው ቁልቁል ተዘቅዝቀው ለኢትዮጵያ ጸልየው የምሕረት ቃልኪዳን ተቀብለዋል፡፡ ከዘጠኝ ዓመት በኋላ ጌታችን መጥቶ "ከመነኮሳት ሁሉ ብልጫ ያለህ ወዳጄ እስትንፋሰ ክርስቶስ ሆይ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ምሬልሃለሁ ከዚህች ባሕር ውጣ" በማለት በሞት የሚያርፉበትን ቦታ ነግሯቸዋል፡፡
+ጻድቁ ወደ ደብረ አስጋጅ በሚሄዱበት ጊዜ ጸሐይ ልትገባ ስትል "በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አውግዤሻለሁ፡፡ ለመስፍን ኢያሱ በገባኦን እንደቆምሽ አሁን ቀጥ ብለሽ ቁሚ" ብለው ገዝተው ፀሐይን አቁመዋል፡፡
+አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስም ደብረ አስጋጅ ሲደርሱ ፀሐይ አፍ አውጥታ "አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ሆይ እገባ ዘንድ ፍታኝ" ስትላቸው "እግዚአብሔር ይፍታሽ" ባሏት ጊዜ ጠልቃለች፡፡ ጻድቁ ሌላው በእጅጉ የሚታወቁበት አንድ ትልቅ ቃል ኪዳን አላቸው፡፡
+በአምላክ ፣ በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ፣ በቅዱስ ሚካኤልና በቅዱስ ገብርኤል ልቡና የሚገኝ እንደ መልክአ ኢየሱስ ያለች እጅግ አስገራሚ ጸሎት አለቻቸው፤ እርሷን ጸሎት በጸለዩ ጊዜ እልፍ ነፍሳትን ከሲኦል ያወጣሉ፡፡ ጸሎቷም የመድኃኔዓለምን የሰውነት ክፍሎች በሙሉ እየጠቀሰች እያንዳንዱ የሰውነት ክፍሎቹ የተቀበሉትን ጸዋትዎ መከራዎች ሁሉ ታዘክራለች፡፡ በእያንዳንዱ ክፍልም የጸሎት ማሳረጊያ አቡነ ዘበሰማያት ይደግማሉ፡፡
+ንስሓ የገባ ኃጢአተኛ ሰው እንኳን ቢሆን ይህችን የአቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስን ጸሎት በጸለየ ጊዜ ሺህ ነፍሳትን ከሲኦል እንደሚያወጣ ጌታችን በማይታበል ቃሉ ለአባታችን ነግሯቸዋል፡፡ እያንዳንዱን የመድኃኔ ዓለምን የሰውነት ክፍሎች በሙሉ እየጠቀሰች መከራዎቹን የምታዘክረውን ይህቺን በአምላክ ልቡና ያለች ግሩም የሆነች ጸሎት "ነፍሳትን ከሲኦል አታወጣም" ብሎ የሚጠራጠር ቢኖር ግን መንግስተ ሰማያትን አያያትም፡፡
+ ጻድቁ አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ታህሳስ ፱ ቀን ተወልው ሚያዝያ ፱ ቀን በታላቅ ክብር ዐርፈዋል፡፡ [ገድለ አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ]
አምላከ ቅዱሳን በጻድቁ አማላጅነት ሃገራችንን
ይጠብቅልን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን::
🕊
[ † ሚያዝያ ፱ [ 9 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ቅዱሳን የብሔረ ብጹዐን ጻድቃን
፪. አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ጻድቅ [ኢትዮዽያዊ]
፫. ቅዱስ ዞሲማስ ገዳማዊ [ብሔረ ብጹዐንን ያየ እና ዜናቸውን የጻፈ አባት]
፬. ቅዱስ ኤስድሮስ ሕጻን ሰማዕት [ገና በ፲ ወር ዕድሜው ሰማዕት የሆነ]
፭. አባ ሱንቱዩ ሊቀ ዻዻሳት
[ † ወርሐዊ በዓላት ]
፩. አባ በርሱማ ሶርያዊ [ለሶርያ መነኮሳት ኁሉ አባት]
፪. ፫፻፲፰ "318ቱ" ቅዱሳን ሊቃውንት [ርቱዐነ ሃይማኖት ዘኒቅያ]
፫. አባ መልከ ጼዴቅ ዘሚዳ [ኢትዮዽያዊ]
† " ስለዚህ የልቡናችሁን ወገብ ታጥቃችሁና በመጠን ኑራችሁ: ኢየሱስ ክርስቶስ ሲገለጥ የምታገኙትን ጸጋ ፈጽማችሁ ተስፋ አድርጉ:: እንደሚታዘዙ ልጆች ባለ ማወቃችሁ አስቀድሞ የኖራችሁበትን ምኞት አትከተሉ:: ዳሩ ግን 'እኔ ቅዱስ ነኝና ቅዱሳን ሁኑ' ተብሎ ስለ ተጻፈ የጠራችሁ ቅዱስ እንደ ሆነ እናንተ ደግሞ በኑሯችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ:: " † [፩ዼጥ.፩፥፲፫-፲፭]
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖 🕊 💖
†
💖 [ የትሕርምት ሕይወት ! ] 💖
🕊 💖 🕊
[ ዓለምንና ፈቃዷን ስለመተው ! ]
------------------------------------------------
" ልጆቼ ሆይ ! ከሁሉ በፊት ሁል ጊዜም ቢሆን ጽድቁንና መንግሥቱን ልታስቀድሙ ይገባችኋል፡፡
ስለ ጌታ ስትሉ ዓለምንና ፈቃዷን ልትተዉ ፣ እግዚአብሔር መፍራት በውስጣችሁ ሊያድር ፣ በመንፈስም ልትቃጠሉ ይገባችኋል፡፡ ይህን እስከ ዕድሜ ፍጻሜአችሁ ድረስ ጠብቁት፡፡ ቃሉ እንደመሰከረው እስከ መጨረሻ የሚጸና እርሱ ይድናል፡፡
ወደ ኋላ ሳትመለከቱ የሰውን ሳይሆን የራሳችሁን ጉድፍ የምታወጡና በጽናት የምትመላለሱ ከሆነ ስለ ጽናታችሁ ዘለዓለማዊ ሕይወት ዋጋ ሆኖ ይሰጣችኋል፡፡
ምክንያቱም ሁሉን ነገር በመናቅ እውነተኛ አምላክ ወደ ሆነው ክርስቶስ ቀርባችኋልና፡፡
ለእርሱ ክብር ይሁን ዛሬም ዘወትርም ለዘለዓለሙ አሜን፡፡ "
[ ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ]
🕊 💖 🕊
🕊
[ እንኩዋን ለቅዱሳት ደናግል ዓመታዊ የሰማዕትነት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ! ]
🕊 ቅዱሳት ደናግል 🕊
ቅዱሳት ደናግሉ አጋሊዝ [አጋሊስ] : ኢራኒና ሱስንያ ይባላሉ:: በ፫ኛው መቶ ክ/ዘመን መጨረሻ አካባቢ ተሰሎንቄ የምትባል ሃገር ውስጥ ይኖሩ ነበር:: ሦስቱም እጅግ ቆንጆዎችና ከብዙ ወንዶች ዐይን የሚገባ መልክ ቢኖራቸውም የእነርሱ ምርጫ ግን ሰማያዊ ሙሽርነት ነበርና በጾምና በጸሎት ተወሰኑ::
ለብዙ ዓመታትም ደናግሉ በሚኖሩበት ደብር ውስጥ በቅድስና ኑረዋል:: ከቆይታ በሁዋላ ያ የመከራ ዘመን [ ዘመነ ሰማዕታት ] ሲመጣ ለጊዜውም ቢሆን ወደ በርሃ ሸሽተው ተቀመጡ::
ያሉበትን ቦታ የምታውቅ አንዲት ደግ ባልቴት እየሔደች ትጎበኛቸው : በእጃቸው የሚሠሩዋቸውን የተለያዩ እቃወችንም እየሸጠች እኩሉን በስማቸው መጽውታ በተረፈው ለራት የሚሆን ደረቅ ቂጣ ትገዛላቸው ነበር::
አንድ ቀን ግን አንድ አረማዊ ሰው ተከትሏት መጥቶ በማየቱ ፫ ቱንም ደናግል ወደ ከሐዲው ንጉሥ አቀረባቸው:: ንጉሡ ሃይማኖታቸውን ቢክዱ የሐብትና የስልጣን ተስፋ እንዳላቸው ነገራቸው:: ደናግሉ ግን በፍቅረ ክርስቶስ በመጽናታቸው ከብዙ ስቃይ በሁዋላ በዚሕች ቀን አስገድሏቸዋል::
የጌታችን በጐ ምሕረቱ በሁላችን ትደርብን:: ከደናግሉ በረከትን ያሳትፈን::
🕊
[ † ሚያዝያ ፰ [ 8 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ቅዱሳት ደናግል አጋሊዝ: ኢራኒና ሱስንያ
፪. ፻፶ "150" ቅዱሳን ሰማዕታት [ፋርስ [ኢራን] ውስጥ የተሰየፉ]
፫. አባ ጢሞቴዎስ ሊቀ ዻዻሳት
[ † ወርሐዊ በዓላት ]
፩. ቅዱስ ሙሴ ሊቀ ነቢያት
፪. ኪሩቤል [አርባዕቱ እንስሳ]
፫. አባ ብሶይ [ቢሾይ]
፬. አቡነ ኪሮስ
፭. አባ ሳሙኤል ዘደብረ ቀልሞን
፮. ቅዱስ ማትያስ ሐዋርያ [ከ፲፪ [12]ቱ ሐዋርያት]
" ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ: ወይስ ጭንቀት : ወይስ ስደት : ወይስ ራብ: ወይስ ራቁትነት : ወይስ ፍርሃት : ወይስ ሰይፍ ነውን? ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን:: እንደሚታረዱ በጐች ተቈጠርን ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው:: በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን:: " [ሮሜ.፰፥፴፭-፴፰]
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖 🕊 💖
እሑድ - ሚያዚያ 06 2016 ዓ.ም
ኤፌሶን 1-6
ሰላም ለሁላችሁ ይሁን! በዛሬው የዐቢይ ጾም ንባባችን ኤፌሶን 1-6 ድረስ እናነባለን።
ከንባብ በፊት የሚደረግ ጸሎት፡ “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፤ የአንተን ቃላት እሰማ እና እረዳ ዘንድ፥ እንዲያውም ፈቃድህን ለመፈጸም እበቃ ዘንድ የልቤን ጆሮዎች እና ዓይኖች ክፈትልኝ።” (ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ)
የዛሬው ንባብ ኤፌሶን 1-6 ነውና፥ እርሱ እንዲነበብ ይሁን።
መልካም ንባብ!
/channel/c/2014228571/1
@OrthodoxTewahdoBooks
†
💖 [ የትሕርምት ሕይወት ! ] 💖
🕊 💖 🕊
[ “ ስለ ሐሜት መጥፎነት በተመለከተ ! " ]
[ ስለ ሐሜት መጥፎነት በተመለከተ ! ]
------------------------------------------------
" ሴሰኝነትና ሐሜት ነገ ጽኑ ቅጣትን ይዘው ይመጣሉ፡፡
ጽናትን ፣ ትጋትን ፣ ራስን በአምላክ ፊት ማዋረድን ዛሬ ገንዘብህ አድርግ፡፡ የድፍረት ኃጢአትን ፣ እንቅልፍ መውደድን ፣ አለመታዘዝ እነዚህን የመሳሰሉ ነገ ጽኑ ቍጣን የሚያመጡ ናቸውና ካንተ አርቃቸው፡፡
ከዓለም መለየት ፣ ምድራዊ ፈቃዶችን መተው ፣ ከጌታ ያለውን ተስፋ ለማግኘት ብለን ከትውልድ ሥፍራችን ፣ ከዘመድና ፣ ከወዳጅ መለየት ለነገ የማንተዋቸው የዛሬ ተግባራቶቻችን ናቸው፡፡
ሀገር ፣ የትውልድ ሥፍራና ርሥት ጉልትን መሻት በብዙ ክፋቶች ውስጥ እንድናልፍ የሚያደርጉን ናቸውና ነገ ክፉ ብድራትን ይዘው እንዳይመጡብን እነዚህን ከመሻት እንራቅ፡፡
የሎጥ ሚስት ወደ ኋላ በመመልከትና በእግዚአብሔር ፍርድ ላይ የማይገባ በመናገሯ የጨው ሐውልት ሆና ቀርታለች፡፡ ይህ በእኛም ላይ እንዳይመጣ ጌታችን “ማንም ዕርፍ በእጁ ይዞ ወደ ኋላ የሚመለከት ለእግዚአብሔር መንግሥት የተገባ አይደለም ” በማለት አስጠንቅቆናልና ጥለነው ወደመጣነው ነገር አንመለስ፡፡ [ሉቃ.፱፥፷፪] "
[ ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ]
🕊 💖 🕊
†
[ 🕊 ድምፀ ተዋሕዶ 🕊 ]
🍒▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬🍒
[ ሕይወት የሚገኝባቸው የቅድስት ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ትምህርቶች በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን በድምፅ ይቀርባሉ። ]
[ ሳምንታዊ መርሐ-ግብር ]
🕊
[ " መኑ ውእቱ ገብር-ኄር ! " ]
" ታማኝ አገልጋይ ማነው ? "
" እንኪያስ ምግባቸውን በጊዜው ይሰጣቸው ዘንድ ጌታው በቤተ ሰዎች ላይ የሾመው ታማኝና ልባም ባሪያ ማን ነው?" [ ማቴ.፳፬፥፵፭ ]
💖 ድንቅ ትምህርት 💖
[ በመምህራችን በቀሲስ ኅብረት የሺጥላ ]
" የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ፥ ከመከራም ሥጋት ያርፋል።" [ ምሳ.፩፥፴፫ ]
† † †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬
👇
🕊
† [ ገ ብ ር ኄ ር ] †
🕊 💖 🕊
" አምስት መክሊት የተቀበለውም ቀረበና ሌላ አምስት መክሊት አስረክቦ። ጌታ ሆይ ፥ አምስት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር ፤ እነሆ ፥ ሌላ አምስት መክሊት አተረፍሁበት አለ።
ጌታውም። መልካም ፥ አንተ በጎ ታማኝም ባሪያ ፤ በጥቂቱ ታምነሃል ፥ በብዙ እሾምሃለሁ ፤ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ አለው።
ሁለት መክሊትም የተቀበለው ደግሞ ቀርቦ። ጌታ ሆይ ፥ ሁለት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር ፤ እነሆ ፥ ሌላ ሁለት መክሊት አተረፍሁበት አለ።
ጌታውም። መልካም ፥ አንተ በጎ ፥ ታማኝም ባሪያ ፤ በጥቂቱ ታምነሃል ፥ በብዙ እሾምሃለሁ ፥ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ አለው።" [ ማቴ.፳፭፥፳ ]
🕊
[ 🕊 የሰንበት ምስባክ 🕊 ] ፦
" አቤቱ ፈጣሪዬ ወደህ የሠራኻትን ሕግ አስተምር ዘንድ ወደድኩ:: አንድም ሕግህን እጠብቃለሁ ብዬ መጥዎተ ርእስን ለማድረግ ወደድኩ:: አንድም ነውር ነቀፋ የሌለበትን እንከን የማይወጣለትን ፈቃድህን እፈጽም ዘንድ ወደድኩ ፤ አንድም ፈቃድህን ከፈቃዴ ሐሳብህን ከሐሳቤ ምኞቴና ከምኞትህ ጋር ለማዋሐድ ወደድኩ፡፡ አንድም የራሴን ፈቃድ ትቼ በአንተ ፈቃድ ልኖር ወደድኩ::
ፈቃድህን ለማደረግ ከመውደዴ የተነሣ የፈቃድህ መገለጫ የኾነው ሕግህ በልቡናዬ ሰሌዳ ላይ ተጽፎ ይኖራል። አንድም ሕግህን ዘወትር በልቤ ሳስብ ስዘክር እኖራለሁ::
ቸርነትህንና ከሃሊነትህን ለብዙ ጉባኤ ተናገርኩ። አንድም ያደረክልኝን የቸርነት ሥራ የዋልክልኝን ውለታ ብዙ ሕዝብ በተሰበሰበበት እግዚአብሔር እንዲህ አደረገልኝ ብዬ መስከርኩ። መዝ ፴፱ ፥ ፰
† 🕊 ክብርት ሰንበት 🕊 †
💖
🕊 💖 🕊
🕊
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን †
እንኳን አደረሳችሁ ፤ አደረሰን።
† ሚያዝያ ፮ [ 6 ] †
ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በዚህች ዕለት እነዚህን ታላላቅ ቅዱሳን ታስባለች:-
† 🕊 ቅድስት ማርያም ግብፃዊት 🕊 †
† በዚች ቀን በበረሀ የምትኖር ግብፃዊት ማርያም አረፈች። ይቺም ቅድስት ከእስክንድርያ አገር ሁና ወላጆቿ ክርስቲያን ናቸው። እድሜዋ አስራ ሁለት አመት በሆናት ጊዜ የመልካም ስራና የሰው ሁሉ ጠላት ሸንግሎ አሳታት በእርሷም የማይቆጠሩ የብዙዎችን ነፍስ አጠመደ እርሱ ሰይጣን ስለ ዝሙት ፍቅር ያለ ዋጋ ስጋዋን እስከ መስጠት አድርሷታልና ።
በዚህም በረከሰ ስራ ውስጥ ኖረች በየእለቱም የኃጢአት ፍቅር በላይዋ ይጨመርባት ነበር። ሰውን የሚወድ የእግዚአብሄርም ቸርነት ወደ ክብር ባለቤት ወደ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መቃብር ሊባረኩ ወደ ኢየሩሳሌም ለመሄድ የሚሹ ሰዎችን ገለጠላት።
ከእሳቸውም ጋራ ትሄድ ዘንድ ልቧ ተነሳሳ ከብዙ ሰዎችም ጋራ በመርከብ ተሳፈረች። ባለ መርከቦችም የመርከብ ዋጋ በጠየቋት ጊዜ ስለ መርከብ ዋጋ ያመነዝሩባት ዘንድ ሰውነቷን ሰጠቻቸው ኢየሩሳሌምም እስከ ደረሰች ይህን ስራ አልተወችም።
የክብረ ባለቤት በሆነ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መቃብር ወደ አለች ቤተ ክርስቲያን ትገባ ዘንድ በወደደች ጊዜ መለኮታዊት ኃይል መግባትን ከለከለቻት። እርሷም ከሚገቡ ሰዎች ጋራ ትገባ ዘንድ ብዙ ጊዜ ደከመች ነገር ግን ከለከላት እንጂ የጌታ ኃይል አልተዋትም።
ከዚህም በኃላ ስለ ረከሰ ስራዋ አሰበች በልቧም እያዘነችና እየተከዘች ወደ ሰማይ ወደ እግዚአብሔር አይኖቿን አቀናች በማንጋጠጥዋም ውስጥ አምላክን የወለደች የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን ስእል አየች።
በፊቷም አለቀሰች ፍጥረቶችን ሁሉ የምትረጅአቸው አምላክን የወለደሽ እመቤቴ ተዋሽኝ ከሁሉ ሰዎች ጋራ ገብቼ የመጣሁበትን ስራዬን የፈፀምኩ እንደሆነ ያዘዝሽኝን ሁሉ እኔ አደርጋለሁ ብላ በማመን ለመነቻት።
ቤተ ክርስቲያን ፈጥና ገባች በገባችም ጊዜ የበአሉን ስራ ፈፀመች። ከዚህም በኃላ አምላክን ወደ ወለደች ወደ እመቤታችን ወደ ከበረች ድንግል ማርያም ስእል ተመልሳ ወደ እርሷ መሪር ልቅሶ እያለቀሰች ረጅም ፀሎትን ፀለየች ነፍሰዋን ለማዳን እርስዋ ወደ ወደደችው ትመራት ዘንድ አምላክን ከወለደች ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ስእል ከዮርዳኖስ በረሀ ብትገቢ አንቺ እረፍትንና ድኀነትን ታገኚ አለሽ የሚል ቃል ወጣ።
ከእመቤታችን አምላክን ከወለደች ከቅድስት ድንግል ማርያም ስእል ይህን ቃል ተቀብላ ወድያውኑ ወጣች። በውጪም አንድ ሰው አግኝታ ሁለት ግርሽ ሰጣትና አምባሻ ገዛችሸት።
ከዚያም በኃላ የዮርዳኖስን ወንዝ ተሻግራ ፅኑእ ተጋድሎ እየተጋደለች በበረሀው ውስጥ አርባ ሰባት አመት ኖረች ሰይጣንም አስቀድማ በነበረችበት በዝሙት ጦር ይዋጋት ነበር።
እርሷ ግን በተጋድሎ ፀናች ከዚያም ከገዛችው አምባሻ ብዙ ቀን ተመገበች። ሁለት ሁለት ቀን ሶስት ሶስት ቀን ፁማ ከዚያ አምባሻ ጥቂት ትቀምስ ነበር በአለቀም ጊዜ የዱር ሳር ተመገበች።
በዚያችም በዮርዳኖስ በረሀ እየተዘዋወረች አርባ አባት አመት ሲፈፀምላት እንደ ገዳሙ ልማድ የከበረች አርባ ፆምን ሊፈፅም ቅዱስ ዘሲማስ ወደዚያች በረሀ መጣ። በሱ ደብር ላሉ መነኲሳት ልማዳቸው ስለሆነ በየአመቱ ወደ በረሀ ወጥተው የከበረች የአርባ ቀን ፆም እስከ ምትፈፀም በፆምና በፀሎት ተፀምደው በገድል ይቆያሉ ።
ስለዚህም ዘሲማስ ወደ ዮርዳኖስ በረሀ በወጣ ጊዜ የሚፅናናበትን ያሳየው ዘንድ እግዚአብሄርን ለመነው። በበረሀውም ውስጥ ሲዘዋወር ይቺን ቅድስት ሴት ከሩቅ አያት የሰይጣን ምትሀት መሰለችው በፀለየም ጊዜ ከሰው ወገን እንደሆነች ተገለጠለችለት።
ወደርሷም ሄደ እርሷ ግን ከእርሱ ሸሸች ወደርሷም ይደርስ ዘንድ ከኃላዋ በመሮጥ ተከተሉት። ከዚህም በኃላ ዘሲማስ ሆይ ከእኔ ጋራ መነጋገር ከፈለግህ ጨርቅን በምድር ላይ ጣልልኝ እከለልበት ዘንድ ብላ በስሙ ጠራችው።
በስሙ በጠራችውም ጊዜ እጅግ አድንቆ ጨርቁን ጣለላት ያን ጊዜም ለብሳ ሰገደችለት እርሱም ሰገደላት እርስበርሳቸውም ሰላምታ ተሰጣጥተው በላዩዋ ይፀልይላት ዘንድ ለመነችው እርሱ ካህን ነውና ካህን ሰለሆነ።
ከዚህም በኃላ ገድሏን ታስረዳው ዘንድ ቅዱስ ዘሲማስ ለመናት ከእርሷ የሆነውን ሁሉ ከመጀመሪያው እስከመጨረሻው ነገረቸው። እርሷም በሚመጣው አመት የክብር ባለቤት የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ስጋውንና ደሙን ከእርሱ ጋራ ያመጣላት ዘንድ ለመነችው እርሱም እሺ አላት።
አመትም በሆነ ጊዜ ስጋውንና ደሙን በፅዋ ውስጥ ያዘ ደግሞ በለስ ተምርንና በውኃ የራሰ ምስርን ይዞ ወደርሷ ወደ ዮርዳኖስ በረሀ መጣ ቅድስት ማርያምን በዮርዳኖስ ወንዝ ዳር ስትሄድ አያት ወደርሱም ደርሳ እርስበርሳቸው ሰላምታ ተሰጣጡ በአንድነትም ፀለዩ ከዚህም በኃላ ስጋውንና ደሙን አቀበላት።
በለሱን ተምሩንና ምስሩንም አቀረበላትና ትመገብለት ዘንድ ለመናት ስለ በረከት ከምስሩ በእጇ ጥቂት ወሰደች። ደግሞም በሁለተኛው አመት ወደእርሷ ይመለስ ዘንድ ለመነችው ።ሁለተኛ አመትም በሆነ ጊዜ ወደዚያ ወደ ዮርዳኖስ በረሀ መጣ ያቺ ቅድስት ሴት ሙታ አገኛት በራስጌዋም ድኀዪቱን ግብፃዊት ማርያምን ከተፈጠረችበት አፈር ውስጥ ቅበራት የሚል ፅሁፍ አገኘ።ከፅሁፉ ቃልም የተነሳ አደነቀ።
ያን ጊዜም ከግርጌዋ አንበሳን ሲጠብቃት አየ እርሱ መቃብርዋን በምን እቆፍራለሁ ብሎ ያስብ ነበር በዚያም ጊዜ ያ አንበሳ በጥፍሮቹ ምድሩን ቆፈረ የከበረ ዘሲማስም በላይዋ ፀሎት አድርጎ ቀበራት ።
ወደ ገዳሙም ተመልሶ ለመነኮሳቱ የዚችን የከበረች ግብፃዊት ማርያምን ገድሏን እንዳስረዳችው ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ነገራቸው እጅግም አደነቁ ምስጉን ልኡል እግዚአብሄርንም አመስገኑት። መላው እድሜዋም ሰማንያ አምስት ሆኗታል።
† 🕊 ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ 🕊 †
በዚች እለት የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በትንሳኤው ሳምንት ለሀዋርያው ቶማስ ተገለጠለት በእጆቹና በእግሮቹ ውስጥ የችንካሮቹን ምልክትም አሳየው የቶማስንም እጅ ይዞ በመለኮታዊ ጉኑ ውስጥ አኖረውና በጦር የተወጋበትን ቦታ አሳየው ቶማስም ጌታዬና ፈጣሪዬ መነሳትህን አመንኩ አለ።
ጌታችንም ብታየኝ አመንከኝ የሚመሰገንስ ሳያየኝ የሚአምንብኝ ነው ብሎ መለሰለት። በትርጓሜ ወንጌልም እንዲህ ይላል ቶማስ በመድኀኒታችን ጐን ውስጥ እጁን በአስገባ ጊዜ እጁ በመለኮት እሳት ተቃጠለ ፣በመለኮቱም ደግሞ በታመነ ጊዜ እጁ ከመቃጠል ዳነች ።
† 🕊 " አባታችን አዳም " 🕊 †
አባታችን አዳም የመጀመሪያው ፍጥረት [በኩረ ፍጥረት] ነው:: አባታችን አዳም :-
- በኩረ ነቢያት
- በኩረ ካኅናት
- በኩረ ነገሥትም ነው::
- በርሱ ስሕተት ዓለም ወደ መከራ ቢገባም ወልድን ከዙፋኑ የሳበው የአዳም ንስሃና ፍቅር ነው::
አባታችን ለ፻ [100] ዓመታት የንስሃ ለቅሶን አልቅሷል:: ስለዚህ አባታችን አዳም ቅዱስ ነው:: ከሌሎቹ ቅዱሳን ቢበልጥ እንጂ አያንስም::
ለአባታችን አዳም የተናገርነው ሁሉ ለእናታችን ሔዋንም ገንዘቧ ነው:: ዛሬ የሁለቱም የዕረፍታቸው መታሠቢያ ነው::
አባታችን ቅዱስ ኖሕም ከላሜሕ የተወለደው በዚሁ ቀን ነው::
አምላካችን እግዚአብሔር ለሰማይ ለምድሩ በቅድስናቸው ከከበዱ ወዳጆቹ በረከትን ያድለን::
†
[ 🕊 የዐቢይ ጾም ስድስተኛ ሳምንት 🕊 ]
† [ ገብር ኄር ] †
🕊 💖 🕊
ስድስተኛው ሳምንት ‹ገብር ኄር› የሚል ስያሜ አለው፡፡
‹ገብር ኄር› ማለት ‹በጎ ፣ ታማኝ አገልጋይ› ማለት ነው፡፡ ስያሜው ከማቴዎስ ወንጌል ፳፭፥፲፬ የተወሰደ ሲኾን ፣ ታሪኩም እግዚአብሔር በሰጠው ጸጋ በታማኝነት ማገልገል የሚያስገኘውን ዋጋ ያስረዳል፡፡
አንድ ሰው አገልጋዮቹን ጠርቶ ወጥተው ፣ ወርደው ፣ ነግደው እንዲያተርፉ ለአንዱ አምስት ፤ ለአንዱ ሁለት ፤ ለአንዱ ደግሞ አንድ መክሊት ሰጣቸው፡፡ አምስት መክሊት የተቀበለው በተሰጠው መክሊት ነግዶ ፣ ሌላ አምስት መክሊት አትርፎ ፣ ዐሥር አድርጎ ፣ "ጌታዬ አምስት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር ፤ ወጥቼ ወርጄ አምስት አትርፌአለሁ" ብሎ ለጌታው አቀረበ፡፡
ጌታውም " አንተ ጎበዝ እና ታማኝ ባሪያ ! በጥቂቱ ታምነሃልና በብዙ እሾምሃለሁ ፤ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ ! " አለው፡፡ ሁለት መክሊት የተቀበለውም ወጥቶ ፣ ወርዶ ፣ አትርፎ አራት አድርጎ አቀረበ፡፡ እርሱንም ጌታው " አንተ ታማኝ ባሪያ በጥቂቱ ታምነሃልና ወደ ጌታህ ደስታ ግባ ! " አለው፡፡
አንድ የተቀበለው ሰው ግን መክሊቱን ወስዶ ቀበራት፡፡ ጌታው በተቈጣጠረው ጊዜም የቀበራትን መክሊት አምጥቶ " አንተ ካልዘራህበት የምታጭድ ፣ ካልበተንህበት የምትሰበስብ ጨካኝ እንደ ኾንኽ ዐውቃለሁ፡፡ ስለዚህ ፈራሁና የሰጠኸኝን መክሊት ቀበርኳት ፤ እነሆ መክሊትህ ! " ብሎ ምንም ሳያተርፍ መክሊቱን ለጌታው መልሶ አስረከበ፡፡ ጌታውም " አንተ ክፉና ሐኬተኛ ባሪያ ! ወርቄን በጊዜው አታስረክበኝም ነበር ? ነግዶ ለሚያተርፍ እሰጠው ነበር፡፡ ይህን ክፉና ሐኬተኛ ባሪያ እጅ እግሩን አስራችሁ ጨለማና ጥርስ ማፋጨት ወዳለበት ሥፍራ ውሰዱት ! መክሊቱን ቀሙና ለባለ ዐሥሩ ጨምሩለት ! " ብሎ አዘዘ፡፡
በዚህ ታሪክ እንደምናየው በተሰጠው መክሊት ያተረፈ ሰው [ ክርስቲያን ] ዋጋ አለው፡፡ በፈጣሪው ዘንድ መልካም ፣ በጎ ፣ ታማኝ ባሪያ ተብሎ ይሸለማል፡፡ ባያተርፍ ደግሞ ሐኬተኛ ባሪያ [ አገልጋይ ] ይባላል ፤ ቅጣቱንም ይቀበላል፡፡ እንግዲህ እኛም ታማኝ አገልጋይ መኾን ይጠበቅብናል፡፡ ሳምንቱ ይህ መልእክት የሚተላለፍበት ወቅት ነው፡፡ በዚህ ዘመን በመክሊታቸው የሚያተርፉ እንዳሉ ዅሉ ፣ መክሊታቸውን [ ጸጋቸውን ] ዝገት እስከሚያጠፋው ድረስ የሚቀብሩ ብዙዎች ናቸው፡፡ መክሊትን [ ጸጋን ] መቅበር ዋጋ የማያሰጥ መኾኑን ተገንዝበን በቻልነው መጠን ለማትረፍ መትጋት እና ታማኝ አገልጋይ መኾን እንደሚገባን ከገብር ኄር ታሪክ እንማራለን፡፡
[ በመምህር ምሥጢረ ሥላሴ ማናየ ]
🕊 💖 🕊
"ኒቆዲሞስ የዐቢይ ጾም 7ኛ እሑድ"
የዐቢይ ጾም 7ኛ እሑድ ሳምንታት ኒቆዲሞስ ይባላል።
የዐቢይ ጾም 7ኛ እሑድ ኒቆዲሞስ የተባለ የአይሁድ አለቃ የነበረ ፈሪሳዊ በሌሊት ወደ ጌታችን እየሄደ ምስጢረ መጻሕፍትን ሲማር መኖሩን የምናስታውስበት ዕለት ነው።
በቅዱስ ዮሐንስ ወንጌል እንደምንመለከተው በሀብት በእውነትና በሹመት የላቀ ከፈሪሳውያን ወገን የሚሆን ኒቆዲሞስ የተባለ የአይሁድ አለቃ የነበረ መምህር በሌሊት ወደ ጌታችን ሒዶ ሊቀ መምህር ሆይ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ከሆነ ከአንተ በስተቀር አንተ የምታደርጋቸውን ተአምራት የሚያደርግ ከቶ ማንም የለምና አንተ ልታስተምር ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደመጣህ እናውቃለን አለው።
"ጌታችንም እውነት እውነት እላችኋለሁ ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በስተቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት አያይም የሚል ድንገተኛ የሆነ ምስጢር ነገረው። ዮሐ፦3፥1።"
በትርጓሜው መሰረት እንደምንገነዘበው ኒቆዲሞስ ወደ ጌታችን ሔዶ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ከሆነ ከአንተ በስተቀር አንተ የምታደርጋቸው ታአምራት የሚያደርግ ከቶ ማንም የለምና ልታስተምር ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደመጣህ እናውቃለን ማለቱ ፦ጌታችን ምስጢሩን ስለ ገለጸለት እግዚአብሔር አብ በህልውና ከእርሱ ጋር ካለ ካአንተ በቀር እንደዚህ ያለውን አምላካዊ የሆነ ድንቅ ሥራን ሊሰራ የሚችል ከቶ ማንም የለምና አንተ ከእግዚአብሔር አብ፣አካል ዘእም አካል፣ባሕርይ ዘእም ባሕርይ ተወልደህ ልታስተምር ዓለምን ልታድን እንደመጣህ እናውቃለን ሲለው ፈጣሪው እግዚአብሔር በገለጸለት መሠረት አንድነቱን ሲናገር ነው ማለት ነው።
ጌታችን"አማን አማን እብለከ ዘኢተወልደ ዳግመ እማይ ወእመንፈስ ቅዱስ ኢይክል በዊአ ውስተ መንግሥተ እግዚአብሔር "
እውነት እውነት እልሃለሁ ዳግመኛ ከውሃና ከመንፈስ ቅዱስ( ከአብራከ መንፈስ ቅዱስ በማኅጸነ ዮርዳኖስ) ያልተወለደ ማለትም ተምሮ ተረድቶ አምኖ በአብ በወልድ በወንፈስ ቅዱስ ስም በውሃ ያልተጠመቀ መንግሥተ እግዚአብሔር አይገባም አለው።
"ዘኢተወልደ ዳግመ እማይ "
ዳግመኛ ከውሃ ያልተወለደ ብሎ እግዚአብሔር ወልድን፤
"ወእመንፈስ ቅዱስ"
ከመንፈስ ቅዱስ ብሎ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስን፤
"መንግሥተ እግዚአብሔር "
መንግሥተ እግዚአብሔር ብሎም እግዚአብሔር አብን አስተምሮታል ።
በአጠቃላይ ምስጢረ ሥላሴን ምሥጢረ ጥምቀትን በምሳሌ አድርጎ በሚገባ ገልጾለታል ማለት ነው።
"ምሥጢሩ በአበው ትርጓሜ መሠረት ሲብራራ ነው "
ከዚህ በኋላ ኒቆዲሞስ የጌታችን የመዳኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ ሆነ ጌታችን በመስቀል በተሰቀለ ጊዜም ከዮሴፍ ጋር በመሆን በክብር ገንዞ ቀበረው።
አዎ መዳኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምሥጢረ ሥላሴን ፤ ምሥጢረ ጥምቀትን ማለትም የእግዚአብሔርን አንድነት ሦስትነትን ተምሮ አውቆ አዳኝነቱን ተረድቶ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ያልተጠመቀ ወደ መንግሥተ እግዚአብሔር (መንግሥተ ሰማያት) መግባት እንደማይችል ለሁላችንም በዚሁ ምሥጢር አረጋግጦልናል ማለት ነው።
"ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር ይቆየን አሜን"
"አንብቢክሙ አንትሙ ለዘኢያንበበ አይድኡ (እናንተ አንብባችሁ ላላነበበው ንገሩ)"
@MeladeMelad
ዓርብ - ሚያዚያ 04 2016 ዓ.ም
2 ቆሮንጦስ 11-13
ሰላም ለሁላችሁ ይሁን! በዛሬው የዐቢይ ጾም ንባባችን ሁለተኛው የቆሮንጦስ መልእክት 11-13 ድረስ እናነባለን።
ከንባብ በፊት የሚደረግ ጸሎት፡ “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፤ የአንተን ቃላት እሰማ እና እረዳ ዘንድ፥ እንዲያውም ፈቃድህን ለመፈጸም እበቃ ዘንድ የልቤን ጆሮዎች እና ዓይኖች ክፈትልኝ።” (ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ)
የዛሬው ንባብ 2 ቆሮ 11-13 ነውና፥ እርሱ እንዲነበብ ይሁን።
መልካም ንባብ
/channel/c/2014228571/1
@OrthodoxTewahdoBooks
†
💖 [ የትሕርምት ሕይወት ! ] 💖
🕊 💖 🕊
[ “ ስለ ሐሜት መጥፎነት በተመለከተ ! " ]
" የመፍረድ ስልጣን ሳይኖረው በሰው ላይ የሚፈርድ ሰውን በተመለከተ ጌታችን ፦ “እንዳይፈረድባችሁ አትፍረዱ በምትፈርዱበት ፍርድ ይፈረድባችኋሁ በምትሰፍሩትም መስፈሪያ ይሰፈርባችኋልና” በማለት አስተምሮናል፡፡ [ማቴ.፯፥፩]
እንዲሁ የጌታ ወንድም ያዕቆብ ፦ “ወንድሞች ሆይ ፥ እርስ በርሳችሁ አትተማሙ:: ወንድሙን የሚያማ በወንድሙም የሚፈርድ ሕግን ያማል በሕግም ይፈርዳል” [ያዕ.፬፥፲፩] ብሎ ጽፎልናል፡፡
ተወዳጆች ሆይ ! ከጌታ ቃልና ከጌታ ወንድም ከያዕቆብ ምን ተማራችሁ? ጻድቁ ሎጥ በሰዶም ተቀምጦ ነበር ፤ ነገር ግን “ጻድቅ ሎጥም በመካከላቸው ሲኖር እያየና እየሰማ ዕለት ዕለት በዓመፀኛ ሥራቸው ጻድቅ ነፍሱን አስጨንቆ ነበር ” [፪ጴጥ.፪፥፯] ተብሎ እንደተጻፈልን ራሱን በጽድቅ አስጨንቆ ይኖር ነበር እንጂ በማንም ላይ እጁን አልጠቆመም ነበር፡፡ ሐሜት በሰው ላይ መፍረድ ነውና፡፡
ነገር ግን ሐዋርያው ይህን ከጻፈልን በኋላ “ጌታ እግዚአብሔርን የሚያመልኩትን ከፈተና እንዴት እንዲያድን ፥ በደለኞችንም ይልቁንም በርኵስ ምኞት የሥጋን ፍትወት እየተከተሉ የሚመላለሱትን ጌትነትንም የሚንቁትን እየቀጣቸው ለፍርድ ቀን እንዴት እንዲጠብቅ ያውቃል” [፪ጴጥ.፪፥፱] በማለት ፍርድን መስጠት የእግዚአብሔር ድርሻ እንደሆነ እርሱም በኃጢአተኞችና በዓመፀኞች ላይ አንደሚፈርድባቸው ጽፎልናል፡፡ ስለዚህ ራስን በመግዛትና በትሕትና መመላለስ ጊዜ የሚሰጠው ጉዳይ አይደለም ፤ ጊዜውም ዛሬ ነው፡፡"
[ ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ]
🕊 💖 🕊
ወዳጄ ሆይ!
❤️❤️❤️
📖ሁሉም ነገር ሲሳካልህና ከፈተና ነጻ ስትሆን ፍራ። ይህ ጸሎትን ያስረሳልና። ጸሎት የረሳ ሰው በጦር ሜዳ ዉስጥ ትጥቁን የጣለ ሰዉን ይመስላል። ጸሎት ስታቆም የገዛ (የራስህ) ወዳጆችህ ሳይቀሩ ይነሱብሃል።
📖አንተ ከምታዉቀዉ ብቻ ሳይሆን እርሱ ከሚያዉቀዉም እንዲጋርድህ ፈጣሪን ለምን።
📖ነገ የማትደግመዉን ዛሬ አታስለምድ። ለቀጣዩ የማትቀበለውን አመል ዛሬ በዝምታ አትለፍ። አዉነትን ግን በፍቅር ግለጥ።
ይ🀄 ላ 🀄ሉ 👇👇👇
/channel/Fabulous212
🌟🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌟
መጽሐፍ ቅዱስ ብዙ ለማመን የሚከብዱ ታሪኮች አሉበት፡፡
እባብ ከሰው ጋር ሲነጋገር
አህያ ጌታዋን ስትመክር
ኤልያስ ዝናብን እንደ ቧንቧ ውኃ ሲከፍትና ሲዘጋ
ቁራ አስተናጋጅ ሲሆን
ኤልያስ በእሳት ሰረገላ ሲሳፈር
ዮናስ በአሳ አንበሪ ሆድ ውስጥ ሲጸልይ
የኤልሳዕ አጥንት ሙት ሲያስነሳ
የኤልያስ ልብስ ባሕር ሲከፍል
የሙሴ በትር እባብ ሲሆን
ጌታ በምራቁ ዓይን ሲፈጥር
የአራት ቀን ሬሳ በስም ተጠርቶ ሲወጣ
የጴጥሮስ ጥላ ሲፈውስ
የጳውሎስ ጨርቅ ሙት ሲያስነሣ ተጽፎ ታገኛለህ፡፡
ይሄንን ሁሉ እግዚአብሔር ሁሉን ማድረግ ይችላል ብለህ በእምነት ካልተቀበልከው በስተቀር እንዴት ታደርገዋለህ?
አንድ አባት "ዮናስን አሣ አንበሪ ዋጠው የሚለውን ታሪክ እንዴት ማመን ይቻላል?" ተብለው ሲጠየቁ
"የምናወራው ስለ እግዚአብሔር ከሆነ እንኳንስ ዓሣ አንበሪው ዮናስን ዋጠው ተብሎ ይቅርና ዮናስ ዓሣ አንበሪውን ዋጠው ቢባልም አምናለሁ" ብለዋል፡፡
"አይ ይኼ እኮ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተጻፈ ነው" ካልከኝ ደግሞ እግዚአብሔር መጽሐፍ ቅዱስ ተጽፎ ሲጠናቀቅ ሥራ አቁሟል ማለት ነው?"
እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ከእናንተ ጋር ነኝ! ሲል አብረን አልሰማነውም?
(ማቴ. 28፡19)
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ውብ አሁን
ሐሙስ - ሚያዚያ 03 2016 ዓ.ም
2 ቆሮንጦስ 6-10
ሰላም ለሁላችሁ ይሁን! በዛሬው የዐቢይ ጾም ንባባችን ሁለተኛው የቆሮንጦስ መልእክት 6-10 ድረስ እናነባለን።
ከንባብ በፊት የሚደረግ ጸሎት፡ “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፤ የአንተን ቃላት እሰማ እና እረዳ ዘንድ፥ እንዲያውም ፈቃድህን ለመፈጸም እበቃ ዘንድ የልቤን ጆሮዎች እና ዓይኖች ክፈትልኝ።” (ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ)
የዛሬው ንባብ 2 ቆሮ 6-10 ነውና፥ እርሱ እንዲነበብ ይሁን።
መልካም ንባብ!
/channel/c/2014228571/1
@OrthodoxTewahdoBooks