"እንግዲህ፡ንስሓ፡ግባ፤አለዚያ፡ፈጥኜ፡ እመጣብሃለሁ፡፡" ራዕ 2፥16
🌿🕊🌿🕊🌿🕊🌿🕊🌿🕊🌿🕊🌿🕊
✨✨✨ ነጻ የሚያወጣ ፍቅር ✨✨✨
ንፁህ እና እውነተኛ ፍቅር ለምንወደው ሰው ያለ ምንም ገደብ ታላቅ ነፃነትንና ሰላምን ይሰጣል። ይህም ሰላም እና ነፃነት የሚፈጠረው ከምንም በላይ አብልጠን የምንወደው ሰው ከቶ በኛ ቁጥጥር ውስጥ እንዲሆን ባለመፍቀዳችን ነው። ማለትም አንድን የምንወዳትን ወፍ በማሰርያ ውስጥ አስረናት የኛ እንድትሆን ከማድረግ ይልቅ እንደልቧ እንድትበር ፈቅደን ነገር ግን ቤት አዘጋጅተንላት በነጻነት በራሷ ፍላጎት ተመልሳ ወደሰራንላት ቤት እንድትመጣ ነፃነትን መስጠት እንደማለት ነው።
እግዚአብሔር ለኛ ያለው ፍቅርም እንዲህ ያለ ነው። ከእርሱ የተሰጡን ትእዛዛቱም ቢሆን የሚገድቡ ሳይሆኑ ይህን ነጻነት በመጠቀም ወደ ላይ እንድንወጣ የሚያስችሉን ናቸው። ሐዋርያው ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ሰዎች በጻፈው መልእክቱ የፍቅርን ምንነት ባማረ ሁኔታ ገልጿል:: የፍቅርን ታጋሽ፣ ደግ እና ከራስ ወዳድነት ነፃ የሆነውን መገለጫዎቹን አፅንዖት ሰጥቷል። (ቆሮ 13፥4-7)። ይህ በእውነተኛ ፍቅር ውስጥ ያለውን ነፃነት ለመረዳት መሠረት ይጥላል። ሆኖም በዚህ ነፃነታችን ሁሉም ነገር ተፈቅዶልናል ወይም ፈጣሪ ለእኛ ደንታ እንደሌለው የሚያመለክት እንዳልሆነ ልብ ማለት ያስፈልጋል። ይልቁንም፣ እግዚአብሔር በእኛ ላይ በኃይል መጫንን ሳይሆን ከእርሱ ጋር ያለን ግንኙነት በፈቃዳችን እና በምርጫችን ላይ የተመሠረተ ግንኙነት እንዲሆን ስለሚፈልግ ነው።
በራእይ መጽሐፍ ውስጥ የክርስቶስ በነፍሳችን ደጃፍ ላይ ቆሞ መገኘቱ በፍቅር የተሞላ እና የነፍሳችን በር እንድንከፍት የሚያበረታታ ለስለስ ያለ ማንኳኳት ሆኖ ተገልጧል።
“እነሆ፣ በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ። ማንም ድምፄን ቢሰማ ደጁንም ቢከፍትልኝ ወደ እርሱ እገባለሁ ከእርሱም ጋር እራት እበላለሁ እርሱም ከእኔ ጋር ይበላል።” ራእይ 3፥20
“የራሳችሁ አይደላችሁም ፤ በዋጋ ተገዝታችኋል ። ” 1ኛ ቆሮንቶስ 6፥20
“እርሱ ግን ስለኅጢአታችን ቈሰለ፤ ስለ በደላችንም ታመመ፤ የሰላማችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፤ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን።” ት.ኢሳ 53፥5
“ፍቅር ታጋሽ ነው፤ ደግሞም ቸር ነው። ፍቅር አይመቀኝም፤ አይመካም፤ አይታበይም፤ ተገቢ ያልሆነ ነገር አያደርግም፤ ራስ ወዳድ አይደለም፤ አይበሳጭም፤ በደልን አይቈጥርም። ፍቅር ከእውነት ጋር እንጂ በዐመፃ ደስ አይሰኝም።ፍቅር ሁልጊዜ ይታገሣል፤ ሁልጊዜ ያምናል፤ ሁልጊዜ ተስፋ ያደርጋል፤ ሁልጊዜ ጸንቶ ይቆማል።” 1 ቆሮ 13፥4-7
ሊቁ አውግስጢኖስ “ለእግዚአብሔር በሙሉ ልብ መገዛት ከሁሉ የላቀ ፍቅር ነው፤ እርሱን መሻት ትልቁ የሕይወት ጉዞ ፤ እሱን ማግኘት ደግሞ ትልቁ የሰው ልጅ ስኬት ነው”
“ያም ቃል ሥጋ ሆነ፤ በእኛም አደረ፤ ለአባቱ አንድ እንደ ሆነ ልጅ ክብር ያለ ክብሩን አየን፤ ጸጋንና እውነትን የተመላ ነው” ዮሐ 1:14
“ሊቀ ካህናታችን ለድካማችን መከራ መቀበልን የማይችል አይደለምና፤ ነገር ግን ከብቻዋ ከኀጢአት በቀር እኛን በመሰለበት ሁሉ የተፈተነ ነው። እንግዲህ ምሕረትን እንድንቀበል፥ በሚያስፈልገንም ጊዜ የሚረዳንን ጸጋ እንድናገኝ፥ ወደ ጸጋው ዙፋን በእምነት እንቅረብ” ዕብ 4:15-16
“ትእዛዜ ይህች ናት፤ እኔ እንደ ወደድኋችሁ እናንተም እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ” ዮሐ 15፥12
“ ለምኑ፤ ይሰጣችሁማል፤ ፈልጉ፤ ታገኙማላችሁ፤ መዝጊያን አንኳኩ፤ ይከፈትላችሁማል። የሚለምነው ሁሉ ይቀበላልና፤ የሚፈልገውም ያገኛል፤ መዝጊያንም ለሚያንኳኳ ይከፈትለታል።” ማቴ 7፥7-8
“ እኔ የወይን ግንድ ነኝ ፤ ቅርንጫፎ ቹም እናንተ ናችሁ፤ በእኔ የሚኖር እኔም በእ ርሱ፥ ብዙ ፍሬ የሚያፈራ እርሱ ነው፤ ያለ እኔ ምንም ማድረግ አትችሉምና” ዮሐ 15፥5
“ ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ” (ፊልጵ. 4፥13)
🕊
[ እንኩዋን ለጻድቁ አባታችን "ቅዱስ መርቄ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ]
🕊 ጻድቁ ቅዱስ መርቄ 🕊
ቅዱስ መርቄ በሁለት ዓለም የተሳካለት ደግ ሰው ነው:: ነገሩ እንዲህ ነው :-
ቅዱሱ በዓለም የሚኖር ታዋቂ ነጋዴ ነው:: ከእግዚአብሔር ጋር ለመኖር እንደ አስቸጋሪ ከሚታዩ የሥራ ዘርፎች አንዱ የንግድ ሥራ ቢሆንም እርሱ ግን "ቅዱሱ ነጋዴ" ለመባል በቅቷል::
ለዚህም ምክንያቱ ፪ ነገሮች ናቸው :-
፩. በንግድ ሕይወቱ ማንንም ሳያጭበረብር ከመኖሩ ባለፈ ፍጹም ጸሎትን ጾምንና ምጽዋትን ያዘወትር ነበር::
፪. ለንግድ በተዘዋወረባቸው ሃገራት ሁሉ ስለ ክርስቶስ ያለማቁዋረጥ የሚሰብክ በመሆኑ በርካቶችን አሳምኖ ሐዋርያዊ ክብርን አግኝቷል::
ቅዱስ መርቄ በሕይወቱ ይሕንን ከፈጸመ በሁዋላ አንድ አረማዊ ጉዋደኛ ነበረውና : ሐብት ንብረቱን ሰብስቦ "ጌታችን ክርስቶስ ከቤተ ክርስቲያን ውስጥ ስላለ ለርሱ ስጥልኝ" ብሎ ላከው::
አረማዊው ጉዋደኛውን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በፍፁም ግርማ አግኝቶ ንብረቱን ከእጁ ተቀብሎታል::
አረማዊውም በዚህ ምክንያት ከ፸፭ ቤተሰቦቹ ጋር አምኖ ተጠምቁዋል:: ቅዱስ መርቄ በርሃ ውስጥ ባረፈ ጊዜ ቅዱስ ዳዊት ከሰማይ ወርዶ ዘምሮለታል:: መላዕክት በምስጋና ገንዘውት አንበሶች ቀብረውታል::
አምላክ ከቅዱሱ በረከትን ያድለን::
🕊
[ † ሚያዝያ ፫ [ 3 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ቅዱስ መርቄ ጻድቅ [ክርስቲያናዊ ነጋዴ]
፪. ቅዱስ ዮሐንስ ዘኢየሩሳሌም
፫. አባ ሚካኤል ዘእስክንድርያ
፬. እግዚአብሔር:- በእግር የሚራመዱ : በክንፍ የሚበሩና በልብ የሚሳቡ : በየብስ የሚኖሩ ፍጥረታትን ፈጠረ
[ † ወርኀዊ በዓላት ]
፩. በዓታ ለእግዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ
፪. ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና
፫. ቅዱሳን ሊቃነ ካህናት አበው [ዘካርያስና ስምዖን]
፬. አባ ሊባኖስ ዘመጣዕ
፭. አቡነ ዜና ማርቆስ
፮. አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ዘደብረ በንኮል
" እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ:: በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሰወር አይቻላትም:: መብራትንም አብርተው በዕንቅብ በታች አይደለም እንጂ በመቅረዙ ላይ ያኖሩታል:: በቤት ላሉት ሁሉም ያበራል:: መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ::" [ማቴ.፭፥፲፬-፲፮]
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖 🕊 💖
💛
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
🕊 ዐቢይ ጾም [ ጾመ እግዚእ ] 🕊
▷ " የ ድ ፍ ረ ት ኃ ጢ ዓ ቶ ች ! "
[ 💖 አቡነ አትናቴዎስ ዘእስክንድር 💖 ]
[ 🕊 ]
---------------------------------------------------
" የድፍረት ኃጢአት እንዳይገዛኝ ባሪያህን ጠብቅ ፤ የዚያን ጊዜ ፍጹም እሆናለሁ ፥ ከታላቁም ኃጢአት እነጻለሁ።
አቤቱ ፥ ረድኤቴ መድኃኒቴም ፥ የአፌ ቃልና የልቤ አሳብ በፊትህ ያማረ ይሁን።" [ መዝ.፲፱፥፲፫ ]
🕊 💖 🕊
▫️Add member
ሰላም Ermias Mihret እንኳን ወደ ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍ ግሩፕ በደህና መጡ‼️
👥 በዚህ ግሩፕ መጽሐፍ መጠየቅ እና መላክ ትችላላችሁ ነገርግን መጽሐፍ ከመጠየቅዎ እና ከመላክዎ በፊት 20
member add ማድረግ አለቦት እስካሁን 0
member add አድርገዋል።
✅ውድ Ermias Mihret በተጨማሪ የግሩፑን ተወዳጅ ቻናሎች ይቀላቀሉ!
👇👇👇
🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔻
@ORTHODOX_ADDIS_MEZMUR
@ORTHODOX_SPIRITUAL_POEMS
@EOTC_BOOKS_BY_PDF
@LESANGEEZ128
🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔺
👆👆👆
🤗መልካም ጊዜ🤗
▫️Subscribe to the channel
⚠ Dear user "Ermias Mihret", to send message in the group, you must be a member of the following channel: @eotc_books_by_pdf .
🕊
[ † እንኳን ለሰማዕቱ ቅዱስ ክርስቶፎሮስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ]
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †
🕊 † ቅዱስ ክርስቶፎሮስ † 🕊
† ክርስቶፎሮስ ትርጉሙ "ለባሴ ክርስቶስ" እንደ መሆኑ በሐዋርያት ዘመን የነበሩ ብዙ ቅዱሳን በዚህ ስም ይጠሩ ነበር:: ከነዚህ አንዱ ቅዱስ ክርስቶፎሮስ ሃገሩ በላዕተ ሰብእ [ሰውን የሚበሉ] ውስጥ ነበር::
ይህች ሃገር አሁን የት እንዳለች በውል ባይታወቅም የቅዱስ ማትያስ ሃገረ ስብከት በመሆኗ አውሮፓና እስያ ድንበር አካባቢ እንደሆነች ይገመታል::
የአካባቢው ሰዎች ከሰው ሥጋ ውጪ እህልን አይቀምሱም ነበር:: ቅዱስ ማትያስ በነርሱ ያደረውን ርኩስ መንፈስ አስወጥቶ አሳምኗቸዋል::
ከሃገሩ ሰዎችም አንዳንዱ ገጻተ ከለባት [የውሻ መልክ ያላቸው] ነበሩ:: ክርስቶፎሮስም ከነርሱ አንዱ ነበር:: በክርስቶስ አምኖ ከተጠመቀ በሁዋላ በስብከቱ ብዙዎችን አሳምኖ : ስለ ሃይማኖትም ብዙ ጸዋትወ መከራ ተቀብሎ በዚህች ቀን በሰማዕትነት አርፏል::
† ከሰማዕቱ በረከት አምላኩ ያድለን::
🕊
[ † ሚያዝያ ፪ [ 2 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ቅዱስ ክርስቶፎሮስ [ሐዋርያና ሰማዕት]
፪. አባ ስምዖን ዘሃገረ ሐሊባ
፫. ቅዱስ መላልኤል [የያሬድ አባት - ከአዳም ፭ኛ ትውልድ]
፬. እግዚአብሔር ፀሐይን : ጨረቃን : ከዋክብትን ፈጠረ
[ † ወርኀዊ በዓላት ]
፩. ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት
፪. ቅዱስ ታዴዎስ ሐዋርያ
፫. ቅዱስ ኢዮብ ጻድቅ ተአጋሲ
፬. ቅዱስ አቤል ጻድቅ
፭. ቅዱስ አባ ዻውሊ ገዳማዊ [ታላቁ]
፮. ቅዱስ ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ
፯. አባ ሕርያቆስ ዘሃገረ ብሕንሳ
† " ስለዚሕ ወንድሞቼ ሆይ ጣዖትን ከማምለክ ሽሹ:: ልባሞች እንደመሆናችሁ እላለሁ:: በምለው ነገር እናንተ ፍረዱ:: የምንባርከው የበረከት ጽዋ ከክርስቶስ ደም ጋር ኅብረት ያለው አይደለምን? የምንቆርሰውስ እንጀራ ከክርስቶስ ሥጋ ጋር ኅብረት ያለው አይደለምን? . . . እኛ ብዙዎች ስንሆን አንድ ሥጋ ነን:: ሁላችን ያን አንዱን እንጀራ እንካፈላለንና::" † [፩ቆሮ.፲፥፲፬-፲፰]
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖 🕊 💖
💛
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
🕊 ዐቢይ ጾም [ ጾመ እግዚእ ] 🕊
▷ " እርሱ የሚፈልገው የጠፋውን ነው ! "
[ 💖 በብፁዕ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ 💖 ]
[ 🕊 ]
---------------------------------------------------
" የሰው ልጅ የጠፋውን ለማዳን መጥቶአልና።
ምን ይመስላችኋል ? ለአንድ ሰው መቶ በጎች ቢኖሩት ከእነርሱም አንዱ ቢባዝን ፥ ዘጠና ዘጠኙን በተራራ ትቶ ሄዶም የባዘነውን አይፈልግምን ?
ቢያገኘውም ፥ እውነት እላችኋለሁ ፥ ካልባዘኑቱ ከዘጠና ዘጠኙ ይልቅ በእርሱ ደስ ይለዋል። " [ ማቴ.፲፰፥፩ ]
🕊 💖 🕊
†
💖 [ የትሕርምት ሕይወት ! ] 💖
🕊 💖 🕊
[ “ ትዕቢትን በተመለከተ ! " ]
" አንድ ክርስቲያን የትሕርምት ሕይወትን ሊመራ ቢመጣ በትዕቢት መንፈስ ተይዞ ባለመታዘዝ ጠንቅ እንዳይጠፋ የትዕቢትን መንፈስ ከሚያሳድሩ አጋንንት ምክር ራሱን ይጠብቅ፡፡
በዓለም የነበረውን ክብር ፈጽሞ ከማሰብ ይከልከል፡፡ ወዳጄ ሆይ ! ለእግዚአብሔር ፈቃድ በመታዘዝ ያም ማለት በገዛ እጅህ ደክመህ በምታገኘው ልታፍር አይገባህም፡፡ ከአምላክ ታዞ የሚያገኝህ ትንሽ መከራ ዘለዓለማዊ ሕይወትን ለማግኘት ምክንያት ይሆንሃል፡፡
ከዚህ ላይ ምን ልጨምርልህ ? ወዳጄ ሆይ አምስት መክሊት ተቀብሎ የነበረው ሰው ነግዶ አምስት ያተረፈውን ትጉ ባሪያን ምሰለው፡፡ ክፉ የሠሩ በምጽአት የሚያገኘቸውን ዘለዓለማዊ ፍርድ አስበን በትሕርምት ሕይወት ነፍሳችንን በጽድቅ ሕይወት አስጨንቀን ልናኖራት ይገባናል።
እንዲህ ካደረግን በዚህ ዓለም የተቀበልነው ትንሽ መከራ በሚመጣ ዓለም ትልቅ ዋጋን ሲያሰጠን እናገኘዋለን፡፡ ስለዚህ እንደ መልካም ወታደር ሁል ጊዜ በንቃት ሆናችሁ ተመላለሱ፡፡
እግዚአብሔርን ደስ ሳያሰኙ ወደ መቃብር እንደሚወርዱ የሥጋ ዘመዶችህ እድል ፈንታህ እንዳይሆን በአንተ ውስጥ ያለውን ጸጋ እግዚአብሔርን ቸል አትበለው፡፡ ጌታችን ፡- “መልካም ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያክብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ” ብሎ እንዳስተማረን በአንተ መልካም ሥራ እግዚአብሔር እንዲመሰገን ትጋ፡፡
ራስህን ከትዕቢት ጠብቅ እንዲህ ካደረግህ እግዚአብሔር አምላክህ ይሆናል፡፡ ለእርሱ ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ክብር ይሁን አሜን፡፡"
[ ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ]
🕊 💖 🕊
💛
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
🕊 ዐቢይ ጾም [ ጾመ እግዚእ ] 🕊
▷ " በሰው ከመታመን ይልቅ ! "
[ 💖 በብፁዕ አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ 💖 ]
[ 🕊 ]
---------------------------------------------------
" በሰው ከመታመን ይልቅ በእግዚአብሔር መታመን ይሻላል። በገዦች ተስፋ ከማድረግ ይልቅ በእግዚአብሔር ተስፋ ማድረግ ይሻላል።"
[ መዝ.፻፲፰ ፥ ፰ ]
🕊 💖 🕊
የእምነት ሕይወት
በገበያ ላይ
የብፁዕ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ የምንጊዜም ወርቃማ ብሒሎች
፩. የንስሓ አባት ማለት እርሱን ስትመለከት እግዚአብሔርን እና ትዕዛዛቱን የምታስታውስበት ሰው ማለት ነው፡፡
፪. ኃጢአት ከበጎ ነገር በተቃራኒ መስራት ብቻ አይደለም። በጎውን አውቆ አለመስራትም ኃጢአት ነው።
፫. ኃጢአት ምን እንደሆነና ፍፃሜውንም ብታውቅ ትሸሸዋለህ፡፡
፬. ሊቅ በሊቅነቱ ቢያስተምርህ ሊቅ ትሆናለህ ሊቅ በሕይወቱ ቢያስተምርህ ግን ክርስቲያን ትሆናለህ።
፭. አንተ ሐሳብህን ልትመራው እንጂ፤ ሐሳብህ አንተን እንዲመራህ ቦታ አትስጠው፥ እውነተኛ ክርስቲያን ስሜቱ የሚመራዉ ሳይሆን ስሜቱን የሚመራ ነዉ።
፮. ያልገደለ እጅ ግን ያላዳነ፣ ያልሰረቀ አጅ ግን ያልመፀወተ በእግዚአብሔር ፊት ሞገስ የለውም። እውነተኛው መልካምነት ክፋ አለማድረግ ብቻ ሳይሆን መልካም ማድረግም ነው። የሚጎዳንን መተው ብቻ ሳይሆን ስለ ሌሎች ጥቅም መድከምም ነው።
፯. በዚህ ዓለም እንግዳ መሆንህንና ወደ ሰማያዊው ቤትህ እንደምትመለስ ዘወትር አስታውስ። ያን ጊዜ በዚህ ዓለምና በደስታው ተስፋ ማድረግን ትተዋለህ።
ከመጽሐፉ የተወሰደ
አዘጋጅ:- ዲ/ን ዮርዳኖስ ፍሬው
አሳታሚና አከፋፋይ:- ሀሁ መጻሕፍት መደብር
ስልክ:- 0911006705
🕊
[ † እንኳን ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ቅዱስ ሶምሶን [ መስፍነ እስራኤል ] ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ]
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †
🕊 † ቅዱስ ገብርኤል † 🕊
† ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል:-
- ከ፯ [ 7 ] ቱ ሊቃናት አንዱ::
- በራማ አርባብ በሚባሉ ፲ [10] ነገደ መላእክት ላይ የተሾመ::
- በመጀመሪያዋ የፍጥረት ቀን መላእክትን ያጸና::
- ቅዱሳንን ሁሉ የሚረዳ::
- ሠለስቱ ደቂቅን : ዳንኤልን : ሶስናን ከሞት የታደገ ታላቅ መልዐክ ነው::
ከምንም በላይ ግን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ቅዱሱን መልዐክ "መጋቤ-ሐዲስ" ብላ ታከብረዋለች:: ቅዱስ ገብርኤል የስሙ ትርጉዋሜ "አምላክ ወሰብእ - እግዚእ ወገብር" ነውና ለሥነ ፍጥረት ሁሉ የሚሆን ሐዲስ ዜናን ወደ እመቤታችን ድንግል ማርያም አምጥቷል::
መልዐኩ እመቤታችንን ከመጸነሷ ጀምሮ ባይለያትም መጋቢት ፳፱ [ 29 ] ቀን ከእግዚአብሔር ዘንድ ተልኮ አብስሯታል:: ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በማግስቱ በድምቀት እንዲከበር በወሰኑት መሠረት ዛሬ ፴ [ በ30 ] ይከበራል::
🕊 † ሶምሶን ረዓይታዊ † 🕊
† እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን: ሀያ ሁለቱን ሥነ ፍጥረትን ፈጥሮ አዳምን ገዢ አደረገው:: አክሎም በነፍስ ሕያው አድርጐ: በመንፈስ ቅዱስ አክብሮ: ነቢይና ካህን አድርጐ: ካንዲት ዕፀ በለስ በቀር በፍጥረት ሁሉ ላይ አሰለጠነው::
አባታችን አዳም ግን ስህተት አግኝቶት ከገነት ወጣ:: መከራና ፍዳም አገኘው:: በኋላም ለ፻ [100] ዓመት አልቅሶ ንስሃ ገባ:: ጌታም ንስሃውን ተቀብሎ "ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ" የሚል ተስፋ ድህነትን ሰጠው::
ስለዚህም ምክንያት ለ፶፻፭፻ [5,500] ዓመታት ትንቢት ሲነገር: ሱባኤ ወደ ታች ሲቆጠር: ምሳሌም ሲመሰል ኖረ:: ከደግ ፍጥረት አዳም እስከ ኖኅ ድረስ: የሴት ልጆች እግዚአብሔርን በንጽሕና ሁነው በደብር ቅዱስ አመለኩ::
ትንሽ ቆይተው ግን ስለተቀላቀሉ ከቃየን ልጆች ጋር በማየ ድምሳሴ ጠፉ:: በጻድቅ ሰው ኖኅ የተጀመረው ትውልድም እግዚአብሔርን ለመዘንጋት ጊዜ አልፈጀበትም:: ነገር ግን ከሴም ዘር ቅንና ጻድቅ ሰው አብርሃም ተገኘ::
ከእርሱም ይስሐቅ: ከዚያም ያዕቆብ [ደጋጉ] ተገኙ:: ያዕቆብም "እሥራኤል" ተብሎ: በልጆቹ "ሕዝበ እግዚአብሔር" የተባለ ነገድ ተመሠረተ:: በተስፋይቱ ምድር በከነዓን እንዳይኖሩም ርሃብ ምድረ ግብጽ አወረዳቸው::
በዚያም ለ፪፻፲፭ [215] ዓመታት በጭንቅ የባርነትን ሕይወትን አሳለፉ:: እግዚአብሔርም ስለ ወዳጁ አብርሃም ሲል እሥራኤልን አሰባቸው:: የዋሕና ጻድቅ ሰው ሙሴን አስነስቶ እሥራኤልን ከግብጽ ባርነት አዳናቸው::
ይኸውም በጸናች እጅ: በበረታችም ክንድ: በ፱ [9] መቅሰፍት: በ፲ [10] ኛ ሞተ በኩር: በ፲፩ [11] ኛ ስጥመት ግብጻውያንን አጥፍቶ ነው:: በየመንገዱም ጠላቶቻቸውን እየተበቀለላቸው ነው:: ከዚህ ዘመን ጀምሮም እሥራኤል በመሳፍንትና በካህናት የሚተዳደሩ ሆኑ::
አስቀድሞ ሙሴ በምስፍና: አሮን በክህነት መሯቸው:: ቀጥሎም በቅዱስ ሙሴ ኢያሱ: በአሮን አልዓዛር ተተኩ:: እንዲህ እንዲህ እያለም ከኃያል ሰው ሶምሶን ረዓይታዊ ደረሱ:: ይኸውም ከዓለም ፍጥረት ፬፻፪፻ [4,200] ዓመታት በኋላ መሆኑ ነው::
በጊዜው እሥራኤል ጣዖትን እያመለኩ እግዚአብሔርን ስላሳዘኑት ለጠላቶቻቸው አሳልፎ ይሰጣቸው ነበር:: የአካባቢው መንግስታት እነ አሞን: አማሌቅ: ኢሎፍሊ ስንኳ ያኔ ዛሬም ቢሆን እንደምትመለከቱት ዶሮና ጥሬ ናቸው::
በጊዜውም የእሥራኤል ኃጢአት ስለ በዛ ኢሎፍላውያን [ፍልስጤማውያን ፵ [40] ዓመት በባርነት ገዟቸው:: ንስሃ ሲገቡ ደግሞ ልጅ በማጣት ያዘኑ ማኑሄ እና ሚስቱ [እንትኩይ] : በቅዱስ ሚካኤል ተበሥረው ኃያሉን ሶምሶንን ወለዱላቸው::
እርሱም ናዝራዊ [ከእናቱ ማኅጸን ለጌታ የተለየ] ነበርና ፍልስጤማውያንን ቀጥቶ ወገኖቹን እስራኤልን ከባርነት : በአምላኩ ኃይል ታደገ:: ከኃይሉ ብዛት የተነሳም :-
¤ አንበሳን እንደ ጠቦት ይገድል [መሣ.፲፬፥፭]
¤ ፫፻ ቀበሮዎችን አባሮ ይይዝ (መሣ.፲፭፥፫]
¤ በብርቱ ገመዶች ሲያስሩት እንደ ፈትል ይበጣጥሰው (መሣ.፲፭፥፲፬]
¤ በአህያ መንጋጋ ሽህ ሰው ይገድል [መሣ.፲፭፥፲፭]
¤ ጠባቂዎችን ከነ መቃናቸው ተሸክሞ ይወረውር ነበር:: [መሣ.፲፮፥፫]
ውኃ ሲጠማውም ከአህያ መንጋጋ ላይ ፈልቆለት ጠጥቷል:: [መሣ.፲፭፥፲፰] በፍጻሜው ግን ደሊላ በምትባል ሴት ተታልሎ ምሥጢሩን በመግለጡና ጸጉሩ በመላጨቱ ኃይሉን አጥቷል:: ጠላቶቹም ዐይኑን አውጥተው መዘባበቻ አድርገውታል::
በፍጻሜው ግን ኃይሉ እንዲመለስለት ፈጣሪውን ለምኖ : አሕዛብ ለጣኦት በዓል እንደተሰበሰቡ የአዳራሹን ምሰሶ አፍርሶ አጥፍቷቸው ዐርፏል:: [መሣ.፲፫፥፲፮] ቅዱስ ሶምሶን የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጥላ [ምሳሌ] ነው::
† "ክፉ ናችሁ: ኃጢአታችሁ በዝቷል" የማይል ጌታ በመከራችን ሁሉ ተራዳኢ መልዐክን [ቅዱስ ገብርኤልን] ይዘዝልን:: ወርኀ መጋቢትን በሰላም እንዳስፈጸመ ወርኀ ሚያዝያን በምሕረቱ ይባርክልን::
🕊
[ † መጋቢት ፴ [ 30 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላእክት [እመቤታችንን ያበሠረበት መታሠቢያ]
፪. ቅዱስ ሶምሶን [መስፍነ እስራኤል]
፫. ቅዱስ ያዕቆብ ዘግሙድ [ፍልሠቱ]
፬. ቅዱስ ዮሐንስ ዘአክሱም [ድርሳነ ሚካኤልን መጻፉ የሚነገርለት አባት]
፭. እግዚአብሔር ውሃን ከ፫ ከፈለው [ጠፈርን ፈጠረ]
[ † ወርኀዊ በዓላት ]
፩. ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት
፪. ቅዱስ ማርቆስ ዘአንበሳ [ሐዋርያ]
፫. አባ ሣሉሲ ክቡር
፬. ቅዱስ ጐርጐርዮስ ነባቤ መለኮት
፭. ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት
† " . . . በአምላኬም በእግዚአብሔር ፊት ስለ ተቀደሰው ስለ አምላኬ ተራራ ስለምን : ገናም በጸሎት ስናገር አስቀድሜ በራእይ አይቼው የነበረው ሰው ገብርኤል እነሆ እየበረረ መጣ:: በማታም መሥዋዕት ጊዜ ዳሰሰኝ:: አስተማረኝም . . . " † [ዳን.፱፥፳]
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖 🕊 💖
†
[ 🕊 ድምፀ ተዋሕዶ 🕊 ]
🍒▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬🍒
[ ሕይወት የሚገኝባቸው የቅድስት ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ትምህርቶች በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን በድምፅ ይቀርባሉ። ]
[ ሳምንታዊ መርሐ-ግብር ]
🕊
[ " ስለ እናንተ ይታገሳል ! " ]
" ለአንዳንዶች የሚዘገይ እንደሚመስላቸው ጌታ ስለ ተስፋ ቃሉ አይዘገይም ፥ ነገር ግን ሁሉ ወደ ንስሐ እንዲደርሱ እንጂ ማንም እንዳይጠፋ ወዶ ስለ እናንተ ይታገሣል።" [፪ጴጥ.፫፥፱]
💖 ድንቅ ትምህርት 💖
[ በመምህራችን በቀሲስ ኅብረት የሺጥላ ]
" የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ፥ ከመከራም ሥጋት ያርፋል።" [ ምሳ.፩፥፴፫ ]
† † †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬
👇
ለእኔ መልካም ያደረጉትን አትርሳ
ሲገፉህ ፍቅር ላይ እንጂ ጥላቻ ላይ አትውደቅ ፡፡ ወደ ላይ መውጣት ያቃተውን ይገፉታል ፡፡
መገፋት ለዕድገት ነው ፡፡ የገፉህ ታች ሁነው ፣ አንተ ግን ከላይ ትሆናለህ ፡፡ የተገፋ ወተት ቅቤ ይወጣዋል ፣ የተገፋ ዓለት ቤት ይወጣዋል ፣ የተገፋ አፈር ወርቅ ይወጣዋል ፡፡
የተገፋ ሰውም ክብር ይጫንለታል ፡፡ በጎልጎታ ለመነሣት በሩ ቀራንዮ ነው ፡፡ አማራጭ የለም ቀራንዮን ካላዩ ወደ ጲላጦስ አደባባይ መመለስ እንጂ የጎልጎታን ድል ማየት አይቻልም ፡፡
ላንተ የፈሰሰ ቃለ እግዚአብሔር ቤትህን ባርኮ አንተ ግን ሳትባረክ እንዳትቀር እባክህ ተጠንቀቅ ፡፡ በእግዚአብሔር ከብረህ እግዚአብሔርን እንዳትንቅ ደግመህ አስብ ፡፡ ከሙሉ ፍቅር ጎዶሎ ጥላቻ ሊታወስህ አይገባም ፡፡
በሚጠሉህ መሐል የሚወድህን ካገኘኸው የሚጠሉህን እርሳቸው ፡፡ ጤፍን የቆጠረ ፣ ሰማይን የለካ ፣ አሸዋን የደመረ ፣ ውቅያኖስን የሰበሰበ ማንም የለም ፡፡ እግዚአብሔርም ታውቆ የማይጨረስ ነው ፡፡
ንስሐህ የኅሊናን ድምፅ ፀጥ ለማሰኘት ሳይሆን አባትህን ለመታረቅ ይሁን ፡፡ ኃጢአት ስትሠራ ለሰይጣን ተላልፈህ የተሰጠህ መስሎህ ትፈራለህ ፣ ተላልፈህ የተሰጠኸው ግን ለምኞትህ ነውና ምኞትህን ፍራው ፡፡
ስትጸልይ ከራሴ አድነኝ በል ፡፡ ትዕግሥትህን ለካው ፡፡ ሰዎች ሲናገሩ ስንት ደቂቃ መስማት ትችላለህ ? መጓጓዣው እስኪመጣ በደስታ እስከ ስንት ደቂቃ ትጠብቃለህ ? የትራፊክ መብራት እስኪለቅህ ምን ያህል ትረጋጋለህ ?
ከአፍህ ይህን ጸሎት አትለየው ፡- “የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ እባክህ ትዕግሥት ስጠኝ፡፡” ትዕግሥት ያስፈለገህ መከራን ብቻ ሳይሆን ጥጋብንም እንድትችል ነው ፡፡
ከራስ ወዳዶች ጋር ስትኖር ተጠንቀቅ ፡፡ ለራሳቸው እንጂ ላንተ ስሜት አይጨነቁምና ፡፡ ራስ ወዳዶች ሁልጊዜ ተበዳይነት ይሰማቸዋል እንጂ እነርሱ እንደሚበድሉ አያስቡም ፡፡
ራስ ወዳዶች ጫካ ይፈልጋሉና ብዙዎቹ የተደበቁት መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ነው ፡፡ በእግዚአብሔር ቤት ያለ ሽፍታን ፣ በዓለም ያለ ባሕታዊን አምላክ ብቻ ይወቀው ፡፡
ፀጥታህ ሌላውን የሚያውክ አይሁን ፡፡ ፍቅርህ አያስጨንቅ ፡፡ ሰላምህ ሌላውን አይረብሽ ፡፡ ኑዛዜህ ሌላውን አይፈትን ፡፡
ግልጽነትህ መራቆት አይሁን ፡፡ ድብቅነትህ ድፍን ቅል አይምሰል ፡፡ መሽቀርቀርህ ጭንቀት የወለደው አይሁን ፡፡ ለባዕድ ካባ ልበስ ፣ ለወዳጅህ ግን ተገለጥ ፡፡
የሌላው መጨቆን ያንተ መሆኑን አስብ ፡፡ እኔ ሳይሆን እኛ በል ፡፡ የሚመክር ወዳጅ ፣ የሚቀጣ አባት ከሌለህ አልቅሰህ እግዚአብሔርን ለምን ፡፡ አገልግሎትህን ሰዎችን አገኝበታለሁ ብለህ አታድርገው ፡፡ በእግዚአብሔር ከረካህ ሌላ አያምርህም ፡፡ የረካን ማርካት አይቻልምና ፡፡
ትንሽ ሱቅ ትልቅ ሙዚቃ ይለቀቅባታል ፡፡ ትንሽ ጉዳይ ትልቅ ጠብ ይታወጅባታል ፡፡ ጉዳዩ ሲያንስ ጠቡ ትልቅ ይሆናልና የሚጮኹ ጠቦችን ናቃቸው ፡፡ መልካም አጋጣሚ ለማታውቀውና ውለታ ለማይመልስ ሰው ዛሬ የምታደርገው ደግነት ነው ፡፡
ሰው መሆን ሰውን ለመደገፍ ነው ፡፡ እያንዳንዱ ሰዓት የብዙ መልካም ተግባሮች አጋጣሚ ነው ፡፡ ባዶ ቤት ይጮኻል ፣ ብዙ አውቃለሁ ማለትም የባዶነት ምልክት ነው ፡፡
ጥሩ ድምፅ ሲኖርህ ጥሩ እውቀት ጨምርበት ፡፡ አሊያ “ድምፅና ቁንጫ ባዶ ቤት ይወዳል” እያሉ ይሰድቡሃል ፡፡ ሌላውን የማያስተምር እውቀት የጋን ውስጥ መብራት ነው ፡፡
የተዳፈነ እሳት አይሞቅም ፣ ያልተገለጠ ፍቅርም አያስደስትም ፡፡ መብትህን ሳታውቀው ከመልቀቅ አውቀህ መልቀቅ ጠቢብነት ነው ፡፡ ለባለጌ ከሮጡለት ፣ ለውሻ ከደነገጡለት አይሆንም ፡፡ ያለ ምክንያት አትቆጣ ፡፡
ካንተ ቢያንሱም ልጆችህንና ሠራተኞችህን አታሸብር፡፡ አምላካቸው ያዝንብሃል ፡፡ ዋጋ በማይሰጡ ሰዎች ፊት ደግነት ፍርሃት ነው፡፡ ተቀብሎ የማያመሰግን ሰውን አስተምረው ፡፡ በዘመኑ ድሀ ይሆናልና ፡፡
ሰው መቼ እንደሚወድቅ ማወቅ ከፈለግህ ቀላል ነው ፡፡ ትዕቢት የውድቀት ዋዜማ ነው ፡፡ ሁሉን ልያዝ የሚል ሁሉን ያጣል ፡፡ ማሊያ እየለወጠ የሚጫወት መክኖ የሚቀር ነው ፡፡
በራሱ ከፍ ያለ የወደቀ ቀን ትንሣኤ የለውም ፡፡ እግዚአብሔር ያነሣው ቢገፉት ተመልሶ ይቆማል ፡፡ እግዚአብሔር ከሾመው ጋር መታገል ከእግዚአብሔር ጋር መታገል ነው ፡፡
ወሰን ሳትሰጠው ወሰን አላወቀም ብለህ አትውቀሰው ፡፡ እንዲወዱህ ብለህ አትጎዝጎዝ ፣ እንዲያከብሩህ ብለህ አትበጥ ፡፡
የሰው ፍቅር ከሞት አያድንም ፣ ክብሩም ከንቱ ነው ፡፡ ችሎ የቀረብህን ሳይችል ከቀረው ጋር አትደምረው ፡፡ ምክንያቱን ሳትሰማ ማንንም አትውቀስ ፡፡
በወዳጅህ ቅር ካለህ መጀመሪያ ሰላም በለው ፡፡ ለመወቃቀስም መኖር ያስፈልጋልና ፡፡ ቀጥሎ ምክንያቱን ጠይቀው ፡፡ ግምትህ ሊያሳስትህ ይችላልና ፡፡
በመጨረሻ እውነተኛ ሁኖ ካገኘኸው ቅሬታህን ግለጠው ፡፡ ያሰቡት ሁሉ አይወራም ፡፡ ግምትም ከአደጋ ይጥላል ፡፡ ክፉ ልብ ይዘህ ከሰው ጋር እንጀራ አትቁረስ ፡፡ አብሮ መብላት አብሮ የመቁረብ ያህል ነውና ፡፡
ሥራህን በብልሃት እንጂ በጉልበት አትሥራው ፡፡ ይህ ዓለም ከጉልበት ይልቅ ለዘዴ የተሠራ ዓለም ነውና ፡፡ ሃይማኖት በመጀመሪያ ነጻነትን ማወቅና ማክበር አለበት ፡፡ ምክንያቱም እግዚአብሔር የነጻነት አምላክ ነውና ፡፡
በሚያሰለች ስብከት ሰውን ዕረፍት አትንሣ ፡፡ ድኛለሁ እያልህ ከምታወራ ድነህ አሳይ ፡፡ ብዙ ስለ ራሳቸው የሚያወሩ ምንም ያልሠሩ ናቸው ፡፡ ደጋግ ነገሥታት ነጻነትን አይሰጡም ፣ ያስመልሳሉ እንጂ ፡፡
ነጻነት በተፈጥሮ ለሰው የተሰጠ ገንዘቡ ነውና ፡፡ የሰውን ነጻነት መግፈፍ እግዚአብሔርን ማዋረድ ነው ፡፡
በምድር ያሉ ነገሥታት በቅዱስ መጽሐፍ አራዊት የሚል ስያሜ ተሰጥቷዋል ፡፡ ንጉሥ ሁኖ በግ የተባለው የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው ፡፡
የምግብ ለነገ ይጠቅማል ፣ የሥራ ለነገ አይጠቅምም ፡፡ ብዙ ከሠራህ ብዙ ትወገራለህ ፡፡ ካልሠራህ ትወደሳለህ ፡፡ ምክንያቱም ሰነፎች ይጽኑብሃልና ፡፡ የተቀመጡ ሰዎች የቆሙ ሰዎችን አይወዱም ፡፡
ይቅርታ የማያውቅ ሕዝብ አይከብርም ፡፡ በዘመኔ እንስሳ ተቀይመው ላም ያሳረዱ ፣ ውሻ ያስገደሉ አውቃለሁ ፡፡
ቂማችን እስከ መቃብር ነው ፡፡ ከሰው አልፈን እንስሳ የምንቀየም ነን ፡፡ ራሳችንን ደግሞ እንደ እኛ ይቅር የሚል ሕዝብ የለም ፡፡ አንተ ግን ይቅርታ እንዲሰጥህ ለምን ፡፡ ይቅር ማለት ሲያቅትህ ያስቀየሙህን ሰዎች ስም ጠርተህ ጸልይላቸው ፡፡ እግዚአብሔር ልብህን ጥሩ ውኃ ሲረጭበት ታያለህ ፡፡
መልካም ምክር ከእግዚአብሔር ነው፡፡ ሰው የሞተው መልካም ምክርን የናቀ ቀን ነው ፡፡ “ለእኔ መልካም ያደረጉትን አትርሳ” ብለህ ጸልይ ፡፡
እግዚአብሔር ዘመናችን ይባርክ !!!
የሰላም እንቅልፍ ያድርግልን
ሠናይ ዕለተ ሰንበት
✝ 📚ደብረ ዘይት የዐቢይ ጾም አምስተኛው ሳምንት📚 ✝
"ደብረዘይት "የዐቢይ ጾም አምስተኛ እሑድ ነው።
ዘይት የወይራ ስም ሲሆን ፣ደብርም ተራራ ማለት ነው። ስለዚህች "ደብረ ዘይት "ማለት የወይራ ዛፍ ያለበት ተራራ ማለት ነው። "ደብረ ዘይት " በምስራቃዊ ኢየሩሳሌም የቀድሞ የሰሎሞን ቤተ መቅደስ ትይዩ የሚገኝ የጌታችንና የመዳኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀመዛሙርቱን ሐዋርያትን ሰብስቦ የዳግማይ ምጽአቱንንና የዓለም ፍጻሜ ሁኔታን በምሳሌ አድርጎ ያስተማረበት ተራራ ነው። "ደብረ ዘይት " ከኢየሩሳሌም በስተምሥራቅ 75/፸፭ ኪሎ/ሜ ርቀት ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል።
(1ኪ/ሜ ያህል የሰንበት መንገድ ያህልም ይላል።ዮሐ/ሥራ፦1፥12/ ፩፥፲፪: የዐቢይ ጾም ውስጥ ያለው የጾም አምስተኛ እሑድ ሳምንታቱም "ደብረ ዘይት "ይባላል።
"ደብረ ዘይት " በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፦24፥1/ ፳፬፥፩፦ጀምሮ እንደምንመለከተው የጌታችን የዳግማይ ምጽአትና የዓለም ፍጻሜ ሁኔታን የምናስታውስበት ዕለት ነው።
ጌታችን የሚመጣበት ዓመተ ምህረትና ሰዓቱ ተለይቶ ባይታወቅም ዘመኑ ዘመነ ዮሐንስ፣ ወሩ ወርኀ መጋቢት ፣ዕለቱ እለተ እሑድ፣ጊዜው መንፈቀ ሌሊት እንደሚሆን በአባቶቻችን ሊቃውንተ ቤተክርስትያን ተገልጾኣል።ነገር ግን ብዙ ዘመን ዮሐንስ ፣ብዙ ወር መጋቢት፣ ብዙ ዕለት እሑድና ብዙ መንፈቀ ሌሊት ስለ አለ በዚህ ጊዜ ነው ተብሎ ሰዓቱ ተለይቶ እንደማይታወቅ የተነገረ ሲሆን የመቃረቡ ምልክቶችና ምሳሌዎቹ ደግሞ ከላይ በተጠቀሰው የማቴዎስ ወንጌል፦ 24፥1፦አማካኝነት በጌታችን አንድ በአንድ ስለተገለጹ ልብ ብለን ሌናስተውላቸው ይገባናል።
ጌታችንምንም እንኳን የሚመጣበት ጊዜ ባይታወቅም መምጣቱ ግን አንዳችን ጥርጥር ስለሌለው ሰው ሁሉ በሐይማኖትና በሐይማኖታዊ መልካም ምግባር ዝግጁ ሆኖ እንዲኖር አስቀድሞ መክሮኣል እንዳትሳሳቱ ብሎም አስጠንቅቆኣል።
ጌታችን ደቀመዛሙርቱን ሐዋርያትን "ደብረ ዘይት "በተባለው ቦታ ሰብስቦ ከእኔ በኋላ በስሜ የሚነግዱ ብዙ አታላዮች ይመጣሉና እንዳትታለሉ ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ ሁልጊዜም ዝግጁዎች ሆናችሁ ኑሩ በማለት አስተምሮአቸዋል። ትምህርቱና መልእክቱ ሁላችንንም ይመለከታል።
"አዎ በመዝሙረ ዳዊት ፦49፥2/፵፱፥፪፦ እግዚአብሔር ገሃደ ይመጽ ወአምላክነሂ ኢያረምም እሳት ይነድድ ቅድሜሁ" ተብሎ በግእዝ እንደ ተጠቀሰልን እግዚአብሔር አምላካችን በግልፅ ይመጣል መጥቶም ዝም አይልም በጻድቃንና በኃጥኣን መካከል ሆኖ ይፈርዳል። ለሁሉም እንደየሥራው ይሰጠዋል። ለጻድቃን ይፈርድላቸዋል በኃጢኣተኞች ላይም ይፈርዳል ማለት ነው።
በሚመጣበት ጊዜ እሳት በፊቱ ይቃጠላል በዙሪያውም ብዙ ዓውሎ አለ ይላል ነቢዩ ዳዊት።
ይህ ማለት የጻድቃን የሚድኑበት ሕይወት፣ ኃጥኣን ግን የሚጠፉበት መቅዘፍት በባሕርዩ አለው ማለት ነው።
ምንጭ፦ ፍሬ ሕይወት/የሕይወት ፍሬ
✍ ይቀላቀሉ👇
@MeladeMelad
🕊
[ † እንኳን ለጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዓመታዊ የጽንሰት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ]
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †
🕊 † በዓለ ጽንሰት † 🕊
† ይሕች ቀን ለቤተ ክርስቲያን በእጅጉ ልዩ ናት:: በዓመቱ ከሚከበሩ በዓላትም አንደኛውን ሥፍራ ትይዛለች::
በዚሕ ዕለት አምላካችን እግዚአብሔር:-
፩. ሰማይና ምድርን ፈጠረ:: [ዘፍ.፩፥፩]
፪. በቅዱስ ገብርኤል ብሥራት በድንግል ማርያም ማኅፀን አደረ [ተጸነሰ]:: በዓሉም "በዓለ ትስብእት" ይባላል:: "አምላክ ሰው : ሰው አምላክ የሆነበት" ማለት ነው:: [ሉቃ.፩፥፳፮]
፫. የክብር ባለቤት መድኃኔ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን ድል አድርጎ ተነሳ:: [ማቴ.፳፰፥፩ ፣ ማር.፲፮፥፩ ፣ ሉቃ.፳፬፥፩ ፣ ዮሐ.፳፥፩]
፬.ጌታችን ዳግመኛ ለፍርድ በዚሕች ቀን ይመጣል:: [ማቴ.፳፬፥፩]
††† በነዚሕ ታላላቅና ድርብርብ በዓላት ምክንያት ቀኑ "ርዕሰ በዓላት" [የበዓላት ራስ] : "በኩረ በዓላት" እየተባለም ይጠራል::
† ቸሩ እግዚአብሔር ዓለምን ከመፍጠሩ : ከጽንሰቱ : ልደቱና ትንሣኤው በረከትን ይክፈለን:: በጌትነቱም ሲመጣ በርሕራሔው ያስበን::
† ዳግመኛ በዚህች ቀን ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እልዋሪቆን ገብቷል:: ይህች ሃገር የምድራችን መጨረሻ ናት:: ከዚያ በኋላ ሰውና ሃገር የለም:: እንደ ቅዱስ ጳውሎስ ወንጌልን የሰበከ ሐዋርያ የለም::
† ከቅዱሱ ሐዋርያ ትጋት : ቅናት : መንፈሳዊነትና ንጽሕና አምላካችን ይክፈለን::
🕊
[ † መጋቢት ፳፱ [ 29 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ በዓላት ]
፩. ጥንተ ዕለተ ፍጥረት [ዓለም የተፈጠረችበት]
፪. በዓለ ትስብእት [የጌታችን ጽንሰቱ]
፫. ጥንተ በዓለ ትንሣኤ
፬. ዳግም ምጽዐት
፭. ቅድስት ማርያም መግደላዊት
፮. ቅዱስ ጳውሎስ ሐዋርያ
፯. ቅዱሳት አንስት [ትንሣኤውን የሰበኩ]
፰. ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ [ጽንሰታ]
፱. አብርሃ ወአጽብሐ [ጽንሰታቸው]
፲. ቅዱስ ኢያሱ ነቢይ [ጽንሰቱ]
፲፩. ቅዱስ ላሊበላ [ጽንሰቱ]
፲፪. አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ [ጽንሰታቸው]
[ † ወርኀዊ በዓላት ]
፩. የፈጣሪያችንና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት
፪. ቅድስት አርሴማ ድንግል
፫. ቅዱስ ጴጥሮስ ተፍጻሜተ ሰማዕት
፬. ቅዱስ ማርቆስ ዘቶርማቅ
፭. ቅዱስ ዘርዐ ክርስቶስ [ጻድቅና ሰማዕት]
† " እነሆ ከደመና ጋር ይመጣል:: ዓይንም ሁሉ : የወጉትም ያዩታል:: የምድርም ወገኖች ሁሉ ስለ እርሱ ዋይ ዋይ ይላሉ:: አዎን አሜን:: ያለውና የነበረው: የሚመጣውም: ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ: አልፋና ኦሜጋ እኔ ነኝ ይላል::" ††† [ራእይ ፩፥፯]
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖 🕊 💖
†
[ የዐቢይ ጾም አምስተኛ ሳምንት ]
🕊 [ ደብረ ዘይት ] 🕊
ሊፈርድ የሚመጣውን ዳኛ - አማላጅ አትበል !
🕊 💖 🕊
- በዓለ ደብረ ዘይት በሰቂለ ሕሊና በተመስጦ ልቡና የሚከበር ታላቅ በዓለ እግዚእ ነው። በግርማ መለኮት በክበበ ትስብእት ይመጣል። የሚመጣውም ሊፈርድ ነው። ያማልዳል የምትል ሁሉ መጽሐፍኽን ፈልግ።
----------------------------------------------
ቅዱስ ዳዊት ይመጣል ያለን እግዚአብሔርን ነው። "ከክብሩ ውበት ከጽዮን እግዚአብሔር ግልጥ ኾኖ ይመጣል" እንዲል። [መዝ ፵፱፡፪]
ደግሞም "ይመጣልና በምድር ላይ ሊፈርድ ይመጣል ፤ እርሱም ዓለምን በጽድቅ አሕዛብንም በቅንነት ይፈርዳል" ይላል። [መዝ ፺፭፡ ፲፫]
ሲሠልስም "ወንዞች በአንድነት በእጅ ያጨብጭቡ፣ ተራሮች ደስ ይበላቸው፤ በምድር ሊፈርድ ይመጣልና" ብሏል። [መዝ ፺፯፡ ፰]
ነቢየ ልዑል ኢሳይያስም "እነሆ እግዚአብሔር መዓቱን በቁጣ ዘለፋውንም በእሳት ነበልባል ይመልስ ዘንድ ከእሳት ጋር ይመጣል፤ ሠረገሎቹም እንደ ዐውሎ ነፋስ ይኾናሉ" ሲል ተናግሯል። [ኢሳ ፷፮፡ ፲፭]
ቅዱሳን መላእክትም "ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ የወጣው ኢየሱስ [ክርስቶስ] ወደ ሰማይ ሲሔድ እንዳያችሁት እንዲሁ ይመጣል እሏቸው" ተብሎ ተጽፏል። [ሥራ ፩፡ ፲፩]
የመጀመሪያው መጽሐፍ ጸሐፊ ነቢዩ ሔኖክም "እነሆ ጌታ በሁሉ ላይ እንዲፈርድ . . . ከአእላፋት ቅዱሳኑ ጋር መጥቷል" በማለት ተናግሯል። [ሔኖ ፩፡ ] ሐዋርያው ይሁዳም አጽንቶታል። ይሁዳ ቁ ፲፬።
ከሁሉም በላይ የራሱ የጌታችን ምስክርነት ወደር አይገኝለትም።
"ከዚያች ወራትም መከራ በኋላ ወዲያው ፀሐይ ይጨልማል፥ ጨረቃም ብርሃኗን አትሰጥም፥ ከዋክብትም ከሰማይ ይወድቃሉ፥የሰማያትም ኃይላት ይናወጣሉ። በዚያን ጊዜም የሰው ልጅ ምልክት በሰማይ ይታያል፥ በዚያን ጊዜም የምድር ወገኖች ሁሉ ዋይ ዋይ ይላሉ፥ የሰው ልጅንም በኃይልና በብዙ ክብር በሰማይ ደመና ሲመጣ ያዩታል፤ መላእክቱንም ከታላቅ መለከት ድምፅ ጋር ይልካቸዋል፥ ከሰማያትም ዳርቻ እስከ ዳርቻው ከዐራቱ ነፋሳት ለእርሱ የተመረጡትን ይሰበስባሉ" በማለት በማያወላዳ ቃል ነግሮናል። ማቴ ፳፬፡ ፳፱-፴፩፡፡
"የሰው ልጅ በክብሩ በሚመጣበት ጊዜ ከእርሱም ጋር ቅዱሳን መላእክቱ ሁሉ፥ በዚያን ጊዜ በክብሩ ዙፋን ይቀመጣል፤ አሕዛብም ሁሉ በፊቱ ይሰበሰባሉ፤ እረኛም በጎቹን ከፍየሎች እንደሚለይ እርስ በርሳቸው ይለያቸዋል፥ በጎችን በቀኙ ፍየሎችንም በግራው ያቆማቸዋል። የንጉሡም በቀኙ ያሉትን እንዲህ ይላቸዋል፦ እናንተ የአባቴ ቡሩካን፥ ኑ፤ ዓለም ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ። . . .
በዚያን ጊዜ በግራው ያሉትን ደግሞ ይላቸዋል፦ እናንተ ርጉማን፥ ለሰይጣንና ለመላእክቱ ወደ ተዘጋጀ ወደ ዘለዓለም እሳት ከእኔ ሒዱ" ይላቸዋል። ማቴ ፳፭፡ ፴፩-፵፩።
ይህንን ጌታ አማላጅ እያልህ መጠበቁ በየት እንደሚያቆምህ ዐውቀኽ ከአሁኑ ተመለስ።
እንኳን ለበዓለ ደብረ ዘይት አደረሳችሁ !
[ ዲ/ን ዓባይነህ ካሤ ]
🕊 💖 🕊
ወዳጄ የአንተን መኖር የሚፈልጉ ብዙ ናቸው:: ፈጣሪ ወደዚህች ዓለም ያለ ምክንያት አላመጣህም:: በአንተ አለመኖርም የሚጎድል ነገር አለ:: አንተን የሚመስል ሌላ ሰው አልፈጠረምና ለዚህ ዓለም አንተን የሚተካ የለም:: በክብር ወደዚህ ዓለም የመጣህ አምላክ በክብር ወደራሱ እስኪወስድህ ድረስ በራስህ ላይ ክፉ ነገር አታድርግ”
''የወኅኒውም ጠባቂ ከእንቅልፉ ነቅቶ የወኅኒው ደጆች ተከፍተው ባየ ጊዜ፥ እስረኞቹ ያመለጡ መስሎት ራሱን ይገድል ዘንድ አስቦ ሰይፉን መዘዘ። ጳውሎስ ግን በታላቅ ድምፅ፦ ሁላችን ከዚህ አለንና በራስህ ክፉ ነገር አታድርግ፡ ብሎ ጮኸ” ሐዋ.
16:27-28
ይህ ሰው እስረኛ ያመለጠ መስሎት ራሱን ሊያጠፋ ሲል ጳውሎስ "ሁላችን ከዚህ አለንና በራስህ ክፉ ነገር አታድርግ" አለው::
ወዳጄ አንተስ ተስፋ የቆረጥኸው ምን ያመለጠ መስሎህ ነው?
@diyakonhenokhaile
የትምህርት ዕድል ያመለጠህ መስሎህ ነው? ገና ሸህ የትምህርት ዕድሎች አለህ:: ዕድሜህ ያመለጠህ መስሎህ ነው? ነገ የሚጠብቁህ ብሩሕ ዘመናት እኮ ቁጭ ብለው አሉ? የሚረዳኝ ሰው የሚያስብልኝ ሰው አጥቼያለሁ ብለህ ከሆነም ካልሰሙህ ጥቂቶች በላይ ልንሰማህ የምንሻ “ሁላችን ከዚህ አለንና በራስህ ክፉ ነገር አታድርግስንልህ ስማን::
ይልቅ አንተም እንደ ወኅኒው ጠባቂ ''እድን ዘንድ ምን ላድርግ ብለህ? ነፍስህን የምታድንበትን መንገድ ወደ ብለህ?"ነፍስህን መቅደሱ ቀርበህ ጠይቅ::
ወዳጄ ይህንን ጽሑፍ ያነበብኸውም በሕይወት ስላለህ ነው:: የአንተን ዓይን የሚጠብቁ ብዙ ጽሑፎች ፣ የአንተን ጆሮ የሚፈልጉ ብዙ ድምፆች ፣ የአንተን መሐረብ የሚፈልጉ ብዙ ዕንባዎች ፣ የአንተን ሳቅ የሚፈልጉ ብዙ ቀልዶች ... ገና ብዙ ብዙ አሉ::
ስለዚህ ሰይጣንን አሳፍረው:: እንዲህ በለው –
''ጠላቴ ሆይ፥ ብወድቅ እነሣለሁና፥ በጨለማም ብቀመጥ እግዚአብሔር ብርሃን ይሆንልኛልና በእኔ ላይ ደስ አይበልሽ“ ሚክ. 7:8
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ጥቅምት 2016 ዓ.ም.
ሜልበርን አውስትራሊያ
▫️ @diyakonhenokhaile
/channel/diyakonhenokhaile
ረቡዕ - ሚያዚያ 02 2016 ዓ.ም
2 ቆሮንጦስ 1-5
ሰላም ለሁላችሁ ይሁን! በዛሬው የዐቢይ ጾም ንባባችን ሁለተኛው የቆሮንጦስ መልእክት 1-5 ድረስ እናነባለን።
ከንባብ በፊት የሚደረግ ጸሎት፡ “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፤ የአንተን ቃላት እሰማ እና እረዳ ዘንድ፥ እንዲያውም ፈቃድህን ለመፈጸም እበቃ ዘንድ የልቤን ጆሮዎች እና ዓይኖች ክፈትልኝ።” (ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ)
የዛሬው ንባብ 2 ቆሮ 1-5 ነውና፥ እርሱ እንዲነበብ ይሁን።
መልካም ንባብ!
/channel/OrthodoxTewahdoBooks
/channel/c/2014228571/1
†
💖 [ የትሕርምት ሕይወት ! ] 💖
🕊 💖 🕊
[ “ አገልግሎትን በተመለከተ ! " ]
" ተወዳጆች ሆይ ! ጅማሬአችሁን መልካም እንዳደረጋችሁ እንዲሁ የዕርጅና ዘመናችሁን በደስታ ልትፈጽሙ ይገባችኋል። ብርሃናችሁም በዝቶ ለዓለም እንዲያበራ በቅድስና ሕይወት ተመላለሱ፡፡
ተወዳጆች ሆይ ! ከእናታችሁ ማሕፀን ኃጢአት የሚስማማው ባሕርይን ገንዘባችሁ አድርጋችሁ ተወልዳችሁ ነበር። በኃጢአት ሕይወትም ተመላልሳችሁ ነበር፡፡ ስለዚህ በጽድቅ ሥራ ስለመጽናትና እግዚአብሔርን ወደ መምሰል በማደግ ራሳችሁን ጽኑ በሆነ መሠረት ላይ ትመሠረቱ ዘንድ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ተጠምቃችሁ አዲሱን ሰው ክርስቶስን ለብሳችሁታል፡፡
ስለዚህ ወንድሞች ሆይ ከሁሉ በላይ በጻድቃን የሚመሰገነውን እግዚአብሔር አምላካችሁን በመፍራት ተመላለሱ፡፡
ተወዳጆች ሆይ ! ትሑት የሆነውና እናንተን ከልጅነት ጀምሮ በጥበብ ያሳደጋችሁ እርሱ አምላካችሁ እስትንፋችሁ እንክትቋረጥ ድረስ የሚተዋችሁ አምላክ አይደለም፡፡
ከታዳጊነት ዕድሜአችሁ ጀምሮ የእርሱ ምርጥ ዕቃ ትሆኑ ዘንድ ለራሱ ካጫችኹ ከእግዚአብሔር ዘንድ ምስጋናን ትቀበሉና በእናንተ ምክንያት ሰዎች እርሱን እንዲያከብሩ ፍጻሜ ዘመናችሁን በቅድስና ፈጽሙ፡፡
እርሱ ሁሉ የእርሱ ሲሆን እኛን ባለጠጎች ሊያደርገን ደሀ ሆነ፡፡ ስለዚህ ተወዳጆች ሆይ ! ለነፍሳችሁ ዕረፍትን ታገኙ ዘንድ ራሳችሁን ከእርሱ ቀንበር በታች አኑሩ። “ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ይዋረዳልና።” [ሉቃ.፲፬፥፲፩] ብሎ ጌታችን አስተምሮአልና በትሕትና ሆነን እንመላለስ፡፡
ለእርሱ ክብር ይሁን ዛሬም ዘወትርም ለዘለዓለሙ አሜን፡፡ "
[ ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ]
🕊 💖 🕊
†
[ ተዋሕዶ ፍጽምት የቅዱሳን ሃይማኖት ]
▬▬▬▬▬▬ † ▬▬▬▬▬▬
[ ቃልን ከሥጋ አዋሕደን እንሰግድለታለን ! ]
--------------------------------------------------
" ማርያም የወለደችው ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው የሆነ አምላክ እንደሆነ ፥ ከአብ ጋርም አንድ እንደሆነ ፥ ሥጋን በመዋሐድ የማይለወጥ በመለኮትም የማይታመም ቀዳማዊ አምላክ እንደሆነ የማያምን ቢኖር ውጉዝ ይሁን። [ሮሜ.፩፥፫]
' መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የነሣው ሥጋ ከሰማይ የተገኘ ነው ' የሚል ቢኖር ፤ ሥጋ በባሕርዩ ፍጡር አይደለም ጥንት ሳይኖረው ከእግዚአብሔር ጋር በአንድነት በቅድምና ነበር የሚል ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም የተገኘ እንደሆነ የማያምን ቢኖር የተወገዘ የተለየ ይሁን፡፡
አምላክ የተዋሐደው ሥጋ ነው የሚል ፤ ያልተፈጠረ የቃል ፦ ሥጋ ነው ብሎ ሳይለይ በአንድነት የሚሰግድለት ግን የተመሰገነ ይሁን ፤ ቃል ሥጋ በመሆኑ ፤ መከራም በመቀበሉ አልተጠራጠረምና ።
ዳግመኛም ቃልን ከሥጋ ፤ አዋሕደን እንሰግድለታለን ፤ ቅድመ ዓለም የነበረ ለዘላለም የሚኖር የእግዚአብሔር ልጅ እርሱ አንድ ወልድ ነውና ፥ ዳግመኛ የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ትምህርት እንደ መሆኑ ሁለተኛ መምጣቱን እናምን ዘንድ ያስተምረናል፡፡"
[ አቡሊዲስ ]
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፤ ወለወላዲቱ ድንግል ፤ ወለመስቀሉ ክቡር። አሜን።
† † †
💖 🕊 💖
ማግሰኞ - ሚያዚያ 01 2016 ዓ.ም
1 ቆሮንጦስ 11-16
ሰላም ለሁላችሁ ይሁን! በዛሬው የዐቢይ ጾም ንባባችን የመጀመሪያውን የቆሮንጦስ መልእክት 11-16 ድረስ እናነባለን።
ከንባብ በፊት የሚደረግ ጸሎት፡ “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፤ የአንተን ቃላት እሰማ እና እረዳ ዘንድ፥ እንዲያውም ፈቃድህን ለመፈጸም እበቃ ዘንድ የልቤን ጆሮዎች እና ዓይኖች ክፈትልኝ።” (ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ)
የዛሬው ንባብ 1 ቆሮ 11-16 ነውና፥ እርሱ እንዲነበብ ይሁን።
መልካም ንባብ!
/channel/OrthodoxTewahdoBooks
/channel/c/2014228571/1
🕊
[ ✞ እንኩዋን ከተባረከ ወር "ሚያዝያ" እና ከጻድቁ አባታችን "ቅዱስ ስልዋኖስ" "ወቅዱስ አሮን ካህን" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞ ]
🕊 አባ ስልዋኖስ 🕊
ጻድቁ አባ ስልዋኖስ ግብፃዊ ሲሆኑ ከታላቁ መቃርስ መንፈሳዊ ልጆች አንዱ ናቸው:: ገና በሕጻንነታቸው ወደ ገዳም ገብተው ጾምን : ጸሎትን : ትሕርምትን ገንዘብ በማድረግ ታላቅ የንጽሕና ሰው ሁነዋል::
ከመካከለኛ እድሜአቸው ጀምረው ደግሞ የገዳመ አስቄጥስ አበ ምኔት ሆነው በመልካም እረኝነት አገልግለዋል:: ጻድቁን ለየት የሚያደርጉዋቸው አንዳንድ ተግባራት ነበሩ::
እርሳቸውን ጨምሮ ሁሉም ገዳማዊ ከጾምና ከጸሎት ባሻገር ሥራ ሠርቶ ማታ መመጽወት አለበት:: ያ ማለት ያለ ምጽዋት ውሎ ማደር አይፈቀድም ነበር:: ይሕም መነኮሳቱን ከጽድቅ ባለፈ ታታሪና ባተሌ አድርጉዋቸዋል::
አባ ስልዋኖስ በተሰጣቸው ጸጋ መላእክትን : ገነትና ሲዖልን ያዩ ነበር:: በዚሕ ምክንያት ስለ ኃጥአን ከማልቀስ ዐይናቸው ቦዝኖ አያውቅም:: የዚሕን ዓለም ብርሃን አላይም ብለው ቆባቸውን ዓይናቸው ላይ ጥለው በመልካም ሽምግልና በዚሕች ቀን አርፈዋል::
አምላካችን ከጻድቁ በረከት ያሳትፈን::
🕊 ቅዱስ አሮን ካህን 🕊
† ቅዱስ አሮን ፦
- የሊቀ ነቢያት ቅዱስ ሙሴ ወንድም::
- የነቢዪት ማርያም ታናሽ::
- የዮካብድና ዕንበረም ልጅ::
- የእግዚአብሔር ካህን እና
- የብሉይ ኪዳን ሊቀ ካህናት ነው::
† እግዚአብሔር በብሉይ ኪዳን የነበረው የክህነት አገልግሎት ከእርሱ ዘር እንዳይወጣ ምሎለታል:: ዳታን : አቤሮንና ቆሬ ይህንን ቢቃወሙ ከነ ሕይወታቸው መሬት ተከፍታ ውጣቸዋለች:: በድፍረት "እናጥናለን" ብለው ወደ ደብተራ ኦሪት የገቡትንም እሳት ከሰማይ ወርዶ በልቷቸዋል::
ቅዱስ አሮንም በጌታ ትእዛዝ በትሩ ለምልማ : አብባና አፍርታ ተገኝታለች:: ይህም ለጊዜው ክህነት ከሱ ልጆች እንዳይወጣ ሲያደርግ በፍጻሜው ለድንግል ማርያም ምሳሌ ሆኗል::
የአሮን በትር ሳይተክሏት : ሳይደክሙባትና ውሃ ሳያጠጣት አብባና አፍርታ እንደተገኘች ድንግል ማርያምም የወንድ ዘር ምክንያት ሳይሆናት ፍሬ አፍርታለች [ክርስቶስን ወልዳለችና]::
አባ ሕርያቆስ "ጸናጽል ዘውስተ ልብሱ ለአሮን ካህን:: ወዓዲ በትር እንተ ሠረጸት : ወጸገየት : ወፈረየት" እንዳለ:: [ቅዳሴ ማርያም]
ቅዱስ አሮን በማዕጠንቱና በመስዋዕቱ ፈጣሪውን አገልግሎ : ድውያንንም ፈውሶ : እስራኤል በበርሃ ሳሉ አርፎ ተቀብሯል:: [ዘኁ.፳፥፳፭]
[ ለተጨማሪ ንባብ ፫ [3] ቱን ብሔረ ኦሪት [ከኦሪት ዘጸአት ምዕራፍ ፬ ጀምረው እስከ ኦሪት ዘኁልቁ ምዕራፍ ፳ ድረስ] ያንብቡ]
ክብሩ : በረከቱ ይደርብን::
🕊
[ † ሚያዝያ ፩ [ 1 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ቅዱስ አሮን ካህን [የሊቀ ነቢያት ሙሴ ወንድም]
፪. አባ ስልዋኖስ ጻድቅ
፫. ቅዱሳን መነኮሳት
፬. ቅድስት መጥሮንያ
[ † ወርኀዊ በዓላት ]
፩. ልደታ ለማርያም ድንግል እግዝእትነ
፪. ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና
፫. ቅዱስ ራጉኤል ሊቀ መላዕክት
፬. ቅዱስ በርተሎሜዎስ ሐዋርያ
፭. ቅዱስ ሚልኪ ትሩፈ ምግባር
" ስለ ሕዝብ እንደሚያቀርብ እንዲሁ ስለ ራሱ ደግሞ መስዋዕትን ስለ ኃጢአት ሊያቀርብ ይገባዋል:: እንደ አሮንም በእግዚአብሔር ከተጠራ በቀር ማንም ክብሩን ለራሱ የሚወስድ የለም::" [ዕብ.፭፥፫]
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖 🕊 💖
†
💖 [ የትሕርምት ሕይወት ! ] 💖
🕊 💖 🕊
[ “ ቅዱሳንን ትመስላቸው ዘንድ ! " ]
" ወዳጄ ሆይ ! ፍቅርንና ራስን መግዛትን ገንዘብህ አድርገህ ተመላለስ፡፡ ምክንያቱም ትልቅ ዋጋ አላቸውና፡፡ እነዚህ ካሉህ እግዚአብሔር ሰውነትህን ማደሪያው ያደርገዋል። አንተም የእውነተኛ ተሐራሚ ጠባይን ገንዘብህ ታደርጋለህ፡፡ ስለዚህም ቅብዝብዝና በአንድ ቦታ ረግቶ የማይቀመጥ ሰው እንዳትሆን አንተን ከወንድሞች ኅብረት ሊነጥሉህ የሚያስቡትን ሰዎች ምክር አትስማ፡፡
በወጣኒነት ሳለህ የነበረህን ትጋት እንዳታጣ ተጠንቀቅ፡፡ ነገር ግን ይህን ትጋትህን እስከ መጨረሻው ጠብቅ፡፡ ክፉ ንግግር ወይም መሓላ ከከፈርህ አይገኝ፡፡ ቅዱሳንን ትመስላቸው ዘንድ ትሕትናን ገንዘብህ አድርግ፡፡
በንግግርህ ሁሉ “ይቅር በሉኝ” ማለትን ልመድ፡፡ ይህ ከዚህ ዓለም ተግባር ፈጽሞ እንድትርቅ በማድረግ ከእግዚአብሔር ዘንድ ምስጋናን የምታገኝበት ሕይወት እንዲኖርህ ያግዝሃል፡፡ ወደ ትሕርምት ሕይወት በመጣህ ጊዜ ወርቅ ወይም ብር ወይም ልብስ ይዘህ አትምጣ [ወይም የአንተ እንዳልሆኑ ከእግዚአብሔር ያገኘሃቸው እንደሆኑ አስብ]
በፊትህ እግዚአብሔርን አድርግ እንጂ ፤ እንደ ጌታችን እንደ መድኀኒታችን አስተምህሮ እነዚህ ከአንተ ዘንድ እንዲኖሩ ፈልግ፡፡
እነዚህም እምነት ፣ ራስን መግዛት ፣ ትዕግሥት ፣ ትሕትናና እነዚህን የመሳሰሉት ናቸው፡፡ እነዚህ ከእግዚአብሔር የምናገኛቸው የእርሱ ስጦታዎች ናቸው፡፡ ለእርሱ ክብር ይሁን ዛሬም ዘወትርም ለዘለዓለሙ አሜን፡፡"
[ ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ]
🕊 💖 🕊
ሰኞ - መጋቢት 30 2016 ዓ.ም
1 ቆሮንጦስ 6-10
ሰላም ለሁላችሁ ይሁን! በዛሬው የዐቢይ ጾም ንባባችን የመጀመሪያውን የቆሮንጦስ መልእክት 6-10 ድረስ እናነባለን።
ከንባብ በፊት የሚደረግ ጸሎት፡ “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፤ የአንተን ቃላት እሰማ እና እረዳ ዘንድ፥ እንዲያውም ፈቃድህን ለመፈጸም እበቃ ዘንድ የልቤን ጆሮዎች እና ዓይኖች ክፈትልኝ።” (ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ)
የዛሬው ንባብ 1 ቆሮ 6-10 ነውና፥ እርሱ እንዲነበብ ይሁን።
መልካም ንባብ!
/channel/OrthodoxTewahdoBooks
/channel/c/2014228571/1
†
† [ መዝሙረ ዳዊት ] †
† 🕊 ታ ላ ቁ ጸ ሎ ት 🕊 †
🕊 💖 🕊
እሑድ - መጋቢት 29 2016 ዓም
1 ቆሮንጦስ 1-5
ሰላም ለሁላችሁ ይሁን! በዛሬው የዐቢይ ጾም ንባባችን የመጀመሪያውን የቆሮንጦስ መልእክት 1-5 ድረስ እናነባለን።
ከንባብ በፊት የሚደረግ ጸሎት፡ “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፤ የአንተን ቃላት እሰማ እና እረዳ ዘንድ፥ እንዲያውም ፈቃድህን ለመፈጸም እበቃ ዘንድ የልቤን ጆሮዎች እና ዓይኖች ክፈትልኝ።” (ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ)
የዛሬው ንባብ 1 ቆሮ 1-5 ነውና፥ እርሱ እንዲነበብ ይሁን።
መልካም ንባብ!
/channel/OrthodoxTewahdoBooks
/channel/c/2014228571/1
†
† [ ደብረ ዘይት ] †
🕊 💖 🕊
" እኔ በሕይወቴ ሦስት ነገሮችን ሳስብ እፈራለሁ:: ነፍሴ ከሥጋዬ የምትለይበት ሰዓት ፤ ወደ እግዚአብሔር ፊት እንድቀርብ መላእክት በሚወስዱኝ ሰዓት ፤ ከፈጣሪም አንደበት የፍርድ ቃል ለመስማት በፊቱ የምትቆምባትን ሰዓት::"
[ ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ ]
አመ ይመጽእ ወልድኪ መንፈቀ ሌሊት በሥልጣን ፥ አሜሃ ይበክዩ ኃጥአን ፥ ወይትፌሥሑ ጻድቃን ፥ ትብሕም አፍ ወትትዓሠር ልሳን ፤ አሜሃ ዕለተ ያቊመነ በየማን ፤ ምስለ አባግዒሁ ቡሩካን ፥ በደብረ ጽዮን መካን።
† 🕊 ክብርት ሰንበት 🕊 †
💖
🕊 💖 🕊
🌅"እግዚአብሔር ሰ ገሀደ ይመጽእ ወ አምላክነሂ ኢያረምም እሳት ይነድድ ቅድሜሁ"🌅
✤መዝ ፦፵፱፥-፫✤
💫እግዚአብሔር ግልጥ ሆኖ ይመጣል። አምላካችን ይመጣል ዝምም አይልም በፊቱም እሳት ይቃጠላል።💫
@MeladeMelad
†
[ 🕊 ድምፀ ተዋሕዶ 🕊 ]
🍒▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬🍒
[ ሕይወት የሚገኝባቸው የቅድስት ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ትምህርቶች በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን በድምፅ ይቀርባሉ። ]
[ ሳምንታዊ መርሐ-ግብር ]
🕊
[ " ይ መ ጣ ል ! " ]
" ያን ግን እወቁ ፤ ባለቤት ከሌሊቱ በየትኛው ክፍል ሌባ እንዲመጣ ቢያውቅ ኖሮ ፥ በነቃ ቤቱም ሊቈፈር ባልተወም ነበር።
ስለዚህ እናንተ ደግሞ ተዘጋጅታችሁ ኑሩ ፥ የሰው ልጅ በማታስቡበት ሰዓት ይመጣልና።"
[ ማቴ . ፳፬ ፥ ፵፫ ]
💖 ድንቅ ትምህርት 💖
[ በመምህራችን በቀሲስ ኅብረት የሺጥላ ]
" የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ፥ ከመከራም ሥጋት ያርፋል።" [ ምሳ.፩፥፴፫ ]
† † †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬
👇
ቅዳሜ - መጋቢት 28 2016 ዓም
ሮሜ 11-15
ሰላም ለሁላችሁ ይሁን! በዛሬው የዐቢይ ጾም ንባባችን የሮሜ መልእክትን 11-15 ድረስ እናነባለን።
ከንባብ በፊት የሚደረግ ጸሎት፡ “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፤ የአንተን ቃላት እሰማ እና እረዳ ዘንድ፥ እንዲያውም ፈቃድህን ለመፈጸም እበቃ ዘንድ የልቤን ጆሮዎች እና ዓይኖች ክፈትልኝ።” (ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ)
የዛሬው ንባብ ሮሜ 11-15 ነውና፥ እርሱ እንዲነበብ ይሁን።
መልካም ንባብ!
/channel/c/2014228571/1
@OrthodoxTewahdoBooks