mikreabew | Unsorted

Telegram-канал mikreabew - ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

874

"እንግዲህ፡ንስሓ፡ግባ፤አለዚያ፡ፈጥኜ፡ እመጣብሃለሁ፡፡" ራዕ 2፥16

Subscribe to a channel

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

ከነቢያት አሻግሮ ማየትን ፣ ከሐዋርያት እውነትን መግለጥን ፣

ከወንጌላውያን የምሥራቹን ማዳረስን ፣ ከአስተማሪዎች ተክሉን ማጠጣትን ፣

ከእረኞች መንከባከብን ፣ ከሰማዕታት ቆራጥነትን ፣ ከጻድቃን ዓለም መናቅን ፣

ከደናግል በተሰጠን መኖርን ፣ ከመነኮሳት በኪዳን መጽናትን ፣ ከካህናት ምሥጢር መሰወርን ፣ ከሊቃውንትን ቃለ አሚንን ፣

ከእመቤታችን ከድንግል ማርያም ትሕትናን ተማር ።

እግዚአብሔር ያከበረውን ማክበር በረከት እንዳለው አትርሳ።

መልካም ዕለት ሰንበት

/channel/Fabulous212

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

                         †                        


" ችግረኛውን ከቀማኛው እጅ ፥ ረዳት የሌለውንም ምስኪን ያድነዋልና።"

[ መዝ.፸፪፥፲፪]

🕊                        💖                       🕊

" ነፍሴ ሆይ ፥ እግዚአብሔርን ባርኪ ፥ አጥንቶቼም ሁሉ ፥ የተቀደሰ ስሙን። ነፍሴ ሆይ ፥ እግዚአብሔርን ባርኪ ፥ ምስጋናውንም ሁሉ አትርሺ ፤ ኃጢአትሽን ሁሉ ይቅር የሚል ፥ ደዌሽንም ሁሉ የሚፈውስ ፥ ሕይወትሽን ከጥፋት የሚያድናት፥ በምሕረቱና በቸርነቱ የሚከልልሽ ፥

ምኞትሽን ከበረከቱ የሚያጠግባት ፥ ጕልማስነትሽን እንደ ንስር ያድሳል። እግዚአብሔር ይቅርታ አድራጊ ነው ፤ ለተበደሉ ሁሉ ይፈርዳል። "

[ መዝ.፻፫ ፥ ፩ - ፮ ]


🕊                        💖                       🕊

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

🕊                       💖                      🕊

[       የዐቢይ ጾም አራተኛ ሳምንት      ]

💖

[        🕊     መ ጻ ጉ ዕ      🕊       ]


[  እንኳን ለዐቢይ ጾም አራተኛ ሳምንት እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።  ]                        

                         †                        

🕊   [   ሰንበት ይእቲ ቅድስት   ]    🕊


" እግዚአብሔር ይረድኦ ውስተ ዐራተ ሕማሙ ወይመይጥ ሎቱ ኩሎ ምስካቢሁ እምደዌሁ አንሰ እቤ እግዚኦ ተሣሃለኒ፡፡"


[  እግዚአብሔር በደዌ አልጋ ሳለ ይረዳዋል መኝታውንም በበሽታው ጊዜ ያነጥፍለታል እኔም አቤቱ ማረኝ እልሃለሁ፡፡        
    
[ መዝ . ፵፥፫ ]


🕊                        💖                       🕊

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

Yenege yekdas msbak newu

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

ቅዳሜ - መጋቢት 21 2016 ዓም    

ሐዋ 6-10 
   
ሰላም ለሁላችሁ ይሁን! በዛሬው የዐቢይ ጾም ንባባችን የሐዋርያት ሥራ ከምዕራፍ 6-10 ድረስ እናነባለን።  

ከንባብ በፊት የሚደረግ ጸሎት፡ “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፤ የአንተን ቃላት እሰማ እና እረዳ ዘንድ፥ እንዲያውም ፈቃድህን ለመፈጸም እበቃ ዘንድ የልቤን ጆሮዎች እና ዓይኖች ክፈትልኝ።” (ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ)  

የዛሬው ንባብ ሐዋ 6-10 ነውና፥ እርሱ እንዲነበብ ይሁን።  

መልካም ንባብ!
/channel/c/2014228571/1

@OrthodoxTewahdoBooks

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

ውድ ቤተሰቦች በመንበረ መንግሥት ግቢ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ዓምደ ሃይማኖት ሰንበት ት/ቤት ርቀት ትምህርት ማዕከል የተዘጋጀውን የ2016 ሐ ወሰነ ትምህርት መንፈሳዊ የርቀት ትምህርት ለመመዝገብ በቅድሚያ

1. ሙሉ ስምዎትን
2. የመኖሪያ አድራሻዎትን (ክፍለ ከተማ)
3. ስልክ ቁጥርዎትን በዚህ ቴሌግራም ገፅ ላይ ያስቀምጡልን::

💠 ምዝገባ:- ከመጋቢት 10 - ሚያዝያ 10
💠 ትምህርቱ የሚጠናቀቀው በ1ዓመት ነው::
💠 11ኮርሶች በሊቃውን ጉባኤ በተገመገሙ 5መጽሐፍት ይማሩ::
💠 በወር አንዴ እሑድ ከ4:00-6:00 ቲቶሪያል ይኖራል::
💠 ትምህርቱን ላጠናቀቁ በመንበረ መንግሥት ግቢ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም እና የምስክር ወረቀት የሚሰጥ ይሆናል::
👇🏾👇🏾👇🏾👇🏾👇🏾👇🏾👇🏾👇🏾👇🏾👇🏾
/channel/amdehaymanotdistance

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

#ጸሎታቸው_የማይሰማው_ለምንድን_ነው?

ክቡር ዳዊት ሲናገር፡- “እግዚአብሔር ወደ እርሱ በተጣራሁ ጊዜ ይሰማኛል” ብሏል (መዝ.4፡3)፡፡ በዚህ መነሻነትም፡- “ታዲያ ብዙ ሰዎች ጸሎታቸን የማይሰማው ለምንድን ነው?” ብሎ የሚጠይቅ ሰው ሊኖር ይችላል፡፡ እኔም እንዲህ ብዬ እመልስለታለሁ፡- እነዚህ ሰዎች የማይጠቅማቸውን ጸሎት ስለሚጸልዩ ነው፡፡ አዎ! በዚህ ጊዜ ጸሎታቸው ባይሰ’ማ ለእነርሱ በጎ ነው፡፡ እግዚአብሔር የማይረባንን ነገር በለመንነው ጊዜ፥ ልመናችንን የሚሰማ ቢኾን ኖሮ ጸሎታችን በመሰማቱ ብቻ ደስ ባልተሰኘን ነበርና፡፡ ስለዚህ እግዚአብሔርን ተጣርተን ባልሰማን ጊዜ እናመስግነው፡፡ የማይረባንን ነገር ለምነነው ጸሎታችን ከሚሰማን ባይሰማን ይሻለናልና፡፡

አንዳንድ ጊዜም ጸሎታችን በግድየለሽነት የሚቀርብ ከኾነ፥ እግዚአብሔር መልሱን ያዘገይብናል፡፡ ለምን? ከልብ የመነጨ ጸሎት እስክናደርስ ድረስ! ይህ በራሱ ለእኛ የሚሰጠው በቁዔት ቀላል አይደለምና፡፡ መጽሐፍ እንዳለ “እናንተ ክፉዎች ስትኾኑ ለልጆቻችሁ መልካም ስጦታ መስጠትን ካወቃችሁ፥ ከእናንተ በላይ የስጦታን ምንነት፣ መቼ መስጠት እንደሚገባ፣ ምን መስጠትም እንዳለበት የሚያውቅ እግዚአብሔርም መስጠት ያውቅበታል።" (ማቴ.7፡11)፡፡ ለዚህም ነው ብፁዕ ጳውሎስ የማይረባውን ነገር ለምኖ እግዚአብሔር ጸሎቱን ያልሰማው! ለዚህም ነው የተወደደ ሙሴ “ፊትህን አሳየኝ” ብሎ በለመነው ጊዜ ልመናውን ያልተቀበለው።

ስለዚህ እኛም ጸሎታችን ባይሰ’ማ እንኳን እግዚአብሔርን እናመስግን እንጂ ተስፋ አንቁረጥ፡፡ ልል ዘሊል ኾነን ጸልየን ከኾነም ልል ዘሊልነታችንን አስወግደን እንጸልይ እንጂ ድኩማን አንኹን፡፡ እንደዚህ አድርገን ጸልየን ሳለ ጸሎታችን ባይሰ’ማ ግን አምላክ የሚያደርገው ኹሉ ለጥቅማችን ነውና በፍጹም አንዘን፡፡

(#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ)

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

💛
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

🕊   ዐቢይ ጾም [  ጾመ እግዚእ  ]  🕊


▷  "  የ ን ስ ሐ ሕ ይ ወ ት  !  "


[  💖 " በቅዱሳን አባቶቻችን ... ! " 💖  ] 

[                        🕊                        ]
----------------------------------------------

" ተነሥቼም ወደ አባቴ እሄዳለሁና። አባቴ ሆይ ፥ በሰማይና በፊትህ በደልሁ ፥ ወደ ፊትም ልጅህ ልባል አይገባኝም ፤ ከሞያተኞችህ እንደ አንዱ አድርገኝ እለዋለሁ።

ተነሥቶም ወደ አባቱ መጣ። እርሱም ገና ሩቅ ሳለ አባቱ አየውና አዘነለት ፥ ሮጦም አንገቱን አቀፈውና ሳመው። " [ ሉቃ.፲፭፥፲፰ ]


🕊                       💖                   🕊

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

                           †                           

[ ተዋሕዶ ፍጽምት የቅዱሳን ሃይማኖት ]
▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬

ገዥ አንድ እርሱ ነውና እናመስግነው ! ]

--------------------------------------------------

" ዳግመኛም ሃይማኖትን ፍጹም ለማድረግ እርሱ የእግዚአብሔር የባሕርይ ልጅ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ሥጋን እንደተዋሐደ ፤ ከሰው ጋርም እንደኖረ እናስተምራለን። [ገላ.፬፥፬]

ፈጣሪ እርሱ በሰው ያደረ [ በህድረት ] አይደለም፡፡ በነቢያት በሐዋርያት አድሮ ሥራ የሠራ ፍጹም አምላክ በሥጋ ተገለጠ እንጂ፡፡ ሰውም ቢሆን በመለኮቱ ፍጹም ነው

ሁለት ማለት አንዱ በሰው ያደረ የባሕርይ አምላክ ወልድ ፤ አንዱ ከሰማይ የወረደ ከእግዚአብሔር የተወለደ ያይደለ ዕሩቅ ብእሲ አይደለም፡፡ ከአብ አንድ ብቻውን የተወለደ ከድንግልም አንድ ብቻውን የተወለደ እርሱ አንድ ነው እንጂ፡፡  በተዋሕዶ ሰው የሆነ የባሕርይ አምላክ ነው፡፡  [፩ዮሐ.፭፥፳ ።

አምላክ እንደ መሆኑ ሰው ሆኖ ዓለምን ያድናል ፤ ሰው ሆኖም በንፍሐት የሰጠንን መለኮታዊ እስትንፋሱን እንደ ተቀበልን ሰው ሆኖ በሰማይ ላሉት ፤ በምድር ላሉት ፤ ከምድርም በታች ላሉት ገዥ እርሱ ነው፡፡ ገዥ አንድ እርሱ ነውና እናመስግነው፡፡  [ዮሐ.፳፥፳፪ ፣ ቆላ.፩፥፲፪–፲፱ ፣ ፊልጵ.፪፥፭–፲፩ ፣ ይሁ.፩፥፬]

ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ስለተገኘው ስለ ጌታችን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ከሰማይ ከእግዚአብሔር ዘንድ የመጣ ሰው ማርያም በወለደችው አደረ የሚል ፤ ፍጹማን የሆኑ ሁለት ገጽ እንደሆነ ይህን የሚናገር ቢኖር እግዚአብሔር ከሚሰጠው ተስፋ ፈጽሞ የተለየ እንደሆነ ይወቅ። "

[     አቡሊዲስ     ]

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፤ ወለወላዲቱ ድንግል ፤ ወለመስቀሉ ክቡር። አሜን።

†                       †                         †
💖                    🕊                     💖

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

🕊

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †

[ † እንኩዋን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አልዓዛርን ከሞት ላስነሳበት ደግ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ † ]


🕊 †  ሐዋርያ ቅዱስ አልዓዛር  †  🕊

ከቀናት በፊት ጻድቅና ሐዋርያ ቅዱስ አልዓዛር አረፈ ብለን ነበር:: ለስም አጠራሩ ስግደት: ክብር: ጌትነት ይድረሰውና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ አልዓዛር ባረፈ በአራተኛው ቀን ወደ ቢታንያ ደረሰ::

ማርታ ቀድማ ወጥታ ከእንባ ጋር ተቀበለችው::
"አዳም ወዴት ነህ" ያለ [ዘፍ.፫፥፲] (3:10) የአዳም ፈጣሪ "አልዓዛርን ወዴት ቀበራችሁት" አለ:: ቸርነቱ: ባሕርዩ ያራራዋልና ማርያም ስታለቅስ ባያት ጊዜ አብሮ አለቀሰ::

ከዚያም በባሕርይ ስልጣኑ "አልዓዛር! አልዓዛር!" ብሎ አልዓዛርን አስነሳው:: ይሕች ተአምርም በአይሁድ ዘንድ ግርምት ሆነች:: ለጌታም የሞት ምክንያት አደረጉዋት:: ቅድስት ቤተ ክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስን መሠረት አድርጋ እንዲህ ታስተምራለች:: [ዮሐ.፲፩፥፩] (11:1-ፍጻሜው)

ቅዱስ አልዓዛር ጌታችን ካስነሳው በሁዋላ በበዓለ ሃምሳ መንፈስ ቅዱስን ተቀብሎ [ቁጥሩ ከ ፸፪ቱ (72ቱ) አርድእት ነውና] : ለ ፵ [40] ዓመታት ወንጌልን አስተምሮ : በ፸፬ [74] ዓ/ም አካባቢ ቆዽሮስ ውስጥ አርፏል::

የጌታችን ቸርነቱ : የአልዓዛር በረከቱ ይድረሰን::

🕊

[ † መጋቢት ፳ [20] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. ቅዱስ አልዓዛር ጻድቅ ሐዋርያ [የጌታ ወዳጅ]
፪. ቅድስትና ብጽዕት ሰማዕት አስጠራጦኒቃ [ከታላላቅ ሰማዕታት አንዱዋ]
፫. ቅዱሳን ሰማዕታት [የቅ/አስጠራጦኒቃ ማሕበር]
፬. እናታችን ቅድስት ጽጌ-ሥላሴ [ኢትዮዽያዊት]
፭. ቅዱስ አስቃራን ሰማዕት
፮. አባ ሚካኤል ሊቀ ዻዻሳት

[ † ወርኀዊ በዓላት ]

፩. ቅዱስ ቴዎድሮስ ሊቀ ሠራዊት [ሰማዕት]
፪. ቅዱስ ዮሐንስ ሐፂር
፫. ቅዱስ አክሎግ ቀሲስ
፬. ቅዱስ አፄ ካሌብ ጻድቅ (ንጉሠ ኢትዮዽያ)
፭. አባ አሞንዮስ ዘሃገረ ቶና
፮. ቅድስት ሳድዥ የዋሒት

" ጌታ ኢየሱስም 'ብታምኚስ የእግዚአብሔርን ክብር እንድታዪ አልነገርሁሽምን?' አላት . . . ይሕንም ብሎ በታላቅ ድምጽ 'አልዓዛር ሆይ ወደ ውጭ ና' ብሎ ጮኸ:: የሞተውም እጆቹና እግሮቹ በመግነዝ እንደ ተገነዙ ወጣ:: ፊቱም በጨርቅ እንደ ተጠመጠመ ነበረ:: ጌታ ኢየሱስም 'ፍቱትና ይሂድ ተውት' አላቸው:: " [ዮሐ.፲፩፥፵] (11:40-44)

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

                          †                           

💖  [     የትሕርምት ሕይወት !     ]  💖

🕊                        💖                       🕊

🍒

[ " የእግዚአብሔር አርአያ ያለውን ሰው የምትሳደብ ከሆነ ! ... " ]

------------------------------------------------

" የእግዚአብሔር አርአያ ያለውን ሰው የምትሳደብ ከሆነ የነፍስ ገዳዮች ፍርድ ይጠብቅሃል፡፡ ሰዎችን የምትንቅና የምታቃልል ከሆነ ያንተ ማቃለል በእግዚአብሔር አርአያ ላይ ነው፡፡

ለወንድምህ አክብሮትን ስጥ ፤ እነሆ አንተም በእግዚአብሔር ፊት የከብርኽ ትሆናለህ፡፡ ነገር ግን ወንድምህን የምታቃልል ከሆነ ወንድምህን በአንተ ላይ በቍጣ ታነሣሣዋለህ፡፡

እንደ ቅዱሳኑ ክፉ ንግግር ወይም መሓላ ከአንደበትህ አይውጣ፡፡ ነገር ግን ትሑት እንደሆነ ሰው ተመላለስ፡፡ ንግግሮችህ ሁሉ በትሕትና ይሁኑ፡፡ ይህም ከማይጠቅም ዓለማዊ ጠባይ እንድትጠበቅ ይረዳሃል፡፡ ጌታህን ደስ የሚያሰኝ አኗኗርንም ገንዘብህ ታደርጋለሀ፡፡ ከእርሱም ዘንድ ምስጋናን ታገኛለህ፡፡

በአካል ክፍሎች መካከል ምንም ዓይነት ክፋትና ቅናት የለም፡፡ በፍቅር በመሆን ጆሮአቸውን ወደ ራስ ያዘነብላሉ፡፡ በጥንቃቄም በእርሱ ይጎበኛሉ፡፡ ለአካል ሕዋሳት ጠባቂያቸው እና ራሳቸው እርሱ ነው፡፡ እርሱም በሁሉ አቅጣጫ እነርሱን ከጉዳት ይጠብቃቸዋል፡፡ ምንም እንኳ የሁሉ ሕዋሳት የበላይ ቢሆንም ዝቅ ብሎ በትሕትና እግርን ከእንቅፋት ይታደጋል፡፡ "

🕊

[  ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ   ]


🕊                        💖                       🕊

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

📖ሚስጢረ ስላሴ🙏 በአጭሩ ኮንሴብቱ 🙏❤️🙏
              ┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
🗣ሥላሴ ማለት ሦስትነት ማለት ሲሆን በልዩ አገላለፅ ሰለሠ ወይም ሦስት ሆነ ማለት ነው። ቅዱሳት መፃህፍት መሠረት በማድረግ እግዚአብሔር በአንድነትና በሦስትነት እናምነዋለን።
              ┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
💁‍♂አንድነቱ ➫በአገዛዝ፥ በሥልጣን፥ ይህን ዓለም በመፍጠርና በማሳለፍ፥በሕልውና፥ በመለኮት፥ በልብ፥ በቃል፥ በእስትንፉስና ይህን በመሳሰሉ ሁሉ የመለኮት ባሕርያት አንድ ሲሆን።
💁‍♂ሦስትነት➫ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ በስም በአካል በግብር ሲገለፅ
              ┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
🗣የአካል ሦስትነት➫ ለአብ ፍፁም ገፅ፥ ፍፁም አካል፥ ፍፁም መልክ አለው ለወልድም ፍፁም ገፅ፥ ፍፁም አካል፥ ፍፁም መልክ አለው ለመንፈስ ቅዱስም ፍፁም ገፅ፥ ፍፁም አካል፥ ፍፁም መልክ አለው።
              ┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
🗣የስም ሦስትነት➫ አብ የአብስም ነው፥ ወልድ መንፈስ ቅዱስ አይጠሩበትም፥ ወልድ የወልድ ስም ነው፥ አብ መንፈስ ቅዱስ አይጠሩበትም፥ መንፈስ ቅዱስም የመንፈስ ቅዱስ ስም ነው፥ አብ ወልድ አይጠሩበትም።
              ┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
🗣የግብር ሦስትነት➫ የአብ ግብሩ ወልድን መውለድ ፥ መንፈስ ቅዱስን ማስረፅ፥ የወልድ ግብሩ መወለድ ከአብ መወለድ፥ የመንፈስ ቅዱስ ግብሩ ከአብ መሥረፅ ነው። መንፈስ ቅዱስ ከአብ የሰረፀ እንጂ ከወልድ አይደለም፥ ወልድ ቢወለድ እንጂ አይወልድም አያሰርፅም አይሰርፅምም።
              ┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
🙏እግዚአብሔር አንድ ሲሆን ሦስት፥ ሦስት ሲሆን አንድ ነው። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ ይባላል እንጂ ሦስት አማልክት አይባልም።
              ┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
💁‍♂አብ ወልድ ስለወለደ መንፈስ ቅዱስ ስላሰረፀ አይበልጣቸውም አይቀድማቸውም። ይህንንም እንደሚከተለው ያስረዳናል።
              ┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
📖እግዚአብሔርም አለ። ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር  ዘፍ 1፥26
              ┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
🗣እግዚአብሔር አለ ብሎ አንድነቱን በመልካችን እንደ ምሳሌያችን እንፍጠር ሲል ደግሞ ብዛትን[ሶስትነት] ይገልፃል።
              ┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
📖እግዚአብሔር አምላክም አለ። እነሆ አዳም መልካምንና ክፉን ለማወቅ ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ ዘፍ3፥22
              ┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
🔊ከእኛ የሚለውና እንደ አንዱ የሚለው እግዚአብሔር ከአንድ በላይ እንደሆነ የጠቁሙን ናቸው።
              ┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
📖ኑ፥ እንውረድ፤ አንዱ የአንዱን ነገር እንዳይሰማው ቋንቋቸውን በዚያ እንደባልቀው።ዘፍ 11፥7
              ┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
🗣ኑ የሚለውን ቃል የሚያስረዳን አንዱ አካል ሌሎችን ሁለትና ከዚያም በላይ ሊሆን ይችላል መጥራቱን ነው።
              ┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
📖በቀትርም ጊዜ እርሱ በድንኳኑ ደጃፍ ተቀምጦ ሳለ እግዚአብሔር በመምሬ የአድባር ዛፍ ተገለጠለት።ዓይኑንም አነሣና እነሆ፥ ሦስት ሰዎች በፊቱ ቆመው አየ፤ ባያቸውም ጊዜ ሊቀበላቸው ከድንኳኑ ደጃፍ ተነሥቶ ሮጠ፥ ወደ ምድርም ሰገደ፥ እንዲህም አለ። አቤቱ፥ በፊትህስ ሞገስ አግኝቼ እንደ ሆነ ባሪያህን አትለፈኝ ብዬ እለምናለሁ፤ ጥቂት ውኃ ይምጣላችሁ፥ እግራችሁን ታጠቡ፥ ከዚህችም ዛፍ በታች ዕረፉ...)ዘፍ 18፥1-5
              ┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
📖አንዱም ለአንዱ። ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ ምድር ሁሉ ከክብሩ ተሞልታለች እያለ ይጮኽ ነበር። ኢሳ 6፥1-3
              ┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
📖አንዱ ቅዱስ አብ ሁለቱኛው ቅዱስ ወልድ ሦስተኛው ቅዱስ መንፈስ ቅዱስ መሆኑን ልብ እንበል ይህንን በድጋሜ ራዕ 4:8 እናገኘዋለን
              ┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
📖ያዕቆብ ሆይ፥ የጠራሁህም እስራኤል ሆይ፥ ስማኝ፤ እኔ ነኝ፤ እኔ ፊተኛው ነኝ እኔም ኋለኛው ነኝ።እጄም ምድርን መሥርታለች ቀኜም ሰማያትን ዘርግታለች፤ በጠራኋቸው ጊዜ በአንድነት ይቆማሉ። . . ወደ እኔ ቅረቡ ይህንም ስሙ፤ እኔ ከጥንት ጀምሬ በስውር አልተናገርሁም፤ ከሆነበት ዘመን ጀምሮ እኔ በዚያ ነበርሁ፥ አሁንም ጌታ እግዚአብሔርና መንፈሱ ልከውኛል።ኢሳ 48፥12-16
              ┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
📖ኢየሱስም ከተጠመቀ በኋላ ወዲያው ከውኃ ወጣ፤ እነሆም፥ ሰማያት ተከፈቱ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንደ ርግብ ሲወርድ በእርሱ ላይም ሲመጣ አየ፤ እነሆም፥ ድምፅ ከሰማያት መጥቶ። በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው አለ።ማቴ 3፥16-17
              ┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
📖እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።ማቴ  28፥19-20
              ┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
📖መልአኩም መልሶ እንዲህ አላት። መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፥ የልዑልም ኃይል ይጸልልሻል ስለዚህ ደግሞ ከአንቺ የሚወለደው ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል።ሉቃ 1፥35
              ┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
📖ከእናንተ ዘንድ ስኖር ይህን ነግሬአችኋለሁ፤አብ በስሜ የሚልከው ግን መንፈስ ቅዱስ የሆነው አጽናኝ እርሱ ሁሉን ያስተምራችኋል እኔም የነገርኋችሁን ሁሉ ያሳስባችኋል።ዮሐ 14፥25-26
              ┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈

📖የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ የእግዚአብሔርም ፍቅር የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን። አሜን። 2ኛ ቆሮ13፥14
             

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

                         †                         

[              ምስጢረ ሥጋዌ               ]

- መናፍቃንና አሕዛብ በብዙ የሳቱበትና የተሰናከሉበት የአምላክ ሰው የመሆን ምስጢር !

†                   †                      †

" ስለዚህ ከሰማነው ነገር ምናልባት እንዳንወሰድ ፥ ለእርሱ አብልጠን ልንጠነቀቅ ያስፈልገናል።

በመላእክት የተነገረው ቃል ጽኑ ከሆነ ፥ መተላለፍና አለመታዘዝም ሁሉ የጽድቅን ብድራት ከተቀበለ ፥ እኛስ እንዲህ ያለውን ታላቅ መዳን ቸል ብንለው ፥ እንዴት እናመልጣለን ? "

[ ዕብ . ፪ ፥ ፩ ]


         †              †               †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

                          †                          

  [     የትሕርምት ሕይወት !      ]  

🕊                        💖                       🕊
                              
🕊

[ " ወደ ሕይወት የምትወስደዋ ጎዳና ! ... " ]

------------------------------------------------

“ ወደ ሕይወት የምትወስደዋ ጎዳና ጠባብ ናት ወደ ጥፋት የምትወስደዋ ጎዳና ሰፊ ናት፡፡

ጸሎት አንድን ሰው ወደ እግዚአብሔር መንግሥት እንዲገባ የማብቃት አቅም ያላት ጠባቧ ጎዳና ናት፡፡ ከኃጢአት ንጹሕ ሆነው የሚያቀርቧት ጸሎት ፍጹም ሥራን ትሠራለች።

ንጹሐ ባሕርይ የሆነውን ክርስቶስን የመሰለ ክርስቲያን በጨለማ የነቃና ለጸሎት የሚተጋ ሰውን ይመስላል። ይህ ሰው በጨለማ ውስጥ ቢሆንም በዓይን በማይታይ ብርሃን የተከበበ ነው፡፡

ክፉ የሆነ ሰው ግን በሚታየው ብርሃን ውስጥ ሆኖ የጨለማው ልጅ እንደ መሆኑ መጠን የእርሱን ግብር ይፈጽማል፡፡ ስለዚህ ይህ ሰው በውጭ ሲታይ በብርሃን ውስጥ ነው ፤ በውስጥ ግን የሚዳሰስው ጨለማ አሳውሮታል፡፡

ተወዳጆች ሆይ ! እንደዚህ ዓለም ልጆች ዓይኖቻችሁ በዚህ ዓለም ብርሃን ድጋፍ ብቻ የሚመለከቱ እንዳይሆኑ ተጠንቀቁ፡፡ በዚህ ዓለም ዓይናማ መሆን ወደ ቅድስና የሚያመጣ ዓይናማነት አይደለምና፡፡ በዚህ ዓለም ብርሃን የሚመላስ ሰው ይመለከታል ግን አንቀላፍቶአል፡፡ ምልከታው ጤናማ አይደለም እይታውም ሁሉ ምድራዊ ነው፡፡ "

🕊

[  ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ   ]


🕊                        💖                       🕊

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

ረቡዕ - መጋቢት 18 2016 ዓም    

ዮሐንስ 11-15   
   
ሰላም ለሁላችሁ ይሁን! በዛሬው የዐቢይ ጾም ንባባችን የዮሐንስ ወንጌልን ከምዕራፍ 11-15 ድረስ እናነባለን።  

ከንባብ በፊት የሚደረግ ጸሎት፡ “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፤ የአንተን ቃላት እሰማ እና እረዳ ዘንድ፥ እንዲያውም ፈቃድህን ለመፈጸም እበቃ ዘንድ የልቤን ጆሮዎች እና ዓይኖች ክፈትልኝ።” (ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ)  

የዛሬው ንባብ ዮሐ 11-15 ነውና፥ እርሱ እንዲነበብ ይሁን።  

መልካም ንባብ!
/channel/OrthodoxTewahdoBooks

/channel/c/2014228571/1

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

                       †                       

  [  🕊  ድምፀ ተዋሕዶ   🕊  ]  

🍒▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬🍒               

[  ሕይወት የሚገኝባቸው የቅድስት ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ትምህርቶች በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን በድምፅ ይቀርባሉ።  ]

[ ሳምንታዊ መርሐ-ግብር ]

🕊             

[ " እኔ ፈዋሽህ እግዚአብሔር ነኝና ! " ]
             
🕊                        💖                       🕊

" አንተ የአምላክህን የእግዚአብሔርን ቃል አጥብቀህ ብትሰማ ፥ በፊቱም የሚበጀውን ብታደርግ ፥ ትእዛዙንም ብታደምጥ ፥ ሥርዓቱንም ሁሉ ብትጠብቅ ፥ በግብፃውያን ላይ ያመጣሁትን በሽታ አላደርስብህም ፤ እኔ ፈዋሽህ እግዚአብሔር ነኝና አለ። " [ ዘጸ.፲፭፥፳፮ ]


       💖   ድንቅ ትምህርት  💖

[ በመምህራችን በቀሲስ ኅብረት የሺጥላ ]

" የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ፥ ከመከራም ሥጋት ያርፋል።" [ ምሳ.፩፥፴፫ ]

         †              †               †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬
                       👇

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

🕊                       💖                      🕊

[       የዐቢይ ጾም አራተኛ ሳምንት      ]

💖

[        🕊     መ ጻ ጉ ዕ      🕊       ]

አራተኛው የዐቢይ ጾም ሳምንት ‹መጻጒዕ› ይባላል፡፡

ስያሜው በዮሐንስ ወንጌል ፭፥፩ ላይ ከሚገኘው ኃይለ ቃል የተወሰደ ነው፡፡ በዚህ የወንጌል ክፍል ጌታችን በቤተ ሳይዳ ሕሙማንን እንደ ፈወሰ ተነግሮአል፡፡ ብዙ ሕሙማን ፈውስ ሽተው አንዲት የመጠመቂያ ሥፍራን ከበው ይኖሩ ነበር፡፡ በዚያች ሥፍራ ቀድሞ የወረደ እና የተጠመቀ አንድ በሽተኛ ብቻ ይፈወስ ነበር፡፡

ጌታችን በዚህ ሥፍራ ተገኝቶ በሽተኞችን ጐብኝቷል፡፡ በዚያም ልዩ ልዩ ደዌ ያለባቸው አምስት ዓይነት ሕሙማን እንደ ነበሩ ተገልጧል ፤ እነዚህም ፦ ሰውነታቸው የደረቀ ፣ የሰለለና ያበጠ ፤ እንደዚሁም ዕውራን እና ሐንካሳን ነበሩ፡፡ ከዚህ አምስት የተለያየ ዓይነት በሽታ ከተያዙ ሰዎች መካከል ደዌው የጸናበት ፣ ለሠላሳ ስምንት ዓመታት በደዌ ዳኛ ፣ ባልጋ ቍራኛ ተይዞ የኖረው ፤ ከደዌው ጽናት የተነሣ ‹መጻጒዕ› ተብሎ የተጠራው በሽተኛ አንዱ ነበር፡፡

መጻጒዕ ስም አይደለም፡፡ ደዌ የጸናበት በሽተኛ ሕመምተኛ ማለት ነው እንጂ፡፡ ሰውየው ከበሽታው ጽናት የተነሣ ስሙ ጠፍቶ በበሽታው ሲጠራ የነበረ ነው፡፡ አምላካችን ይህን ሰው "አልጋህን ተሸክመህ ሒድ" ብሎ ሠላሳ ስምንት ዘመን የተኛበትን አልጋ ተሸክሞ ወደ ቤቱ እንዲገባ ማድረጉ የሚነገርበት ወቅት በመኾኑ ሳምንቱ ‹መጻጒዕ› ተብሎ በተፈወሰው በሽተኛ ስም ተሰይሟል፡፡ [ሙሉ ታሪኩን በዮሐንስ ወንጌል ፭፥፩-፲፯ ይመልከቱ]፡፡

ዛሬም ቢኾን በሰዎች ላይ ልዩ ልዩ ደዌያት አሉ ፤ የሥጋውን ደዌ ሐኪሞች ያውቁታል፡፡ ከዚህ የከፉ የነፍስ ደዌያት እጅግ ብዙዎች ናቸው፡፡ በኃጢአት ብዛት ልባቸው የደረቀና ያበጠ ፤ ሰውነታቸው የሰለለ ፤ ዓይነ ሕሊናቸው የታወረ ፤ እግረ ልቡናቸው የተሰበረ ብዙዎች ሕሙማን አሁንም አሉ፡፡ ፈውስን ይሻሉ ፤ ድኅነትን ይፈልጋሉ፡፡ እንደ መጻጕዕ ቦታቸውን ሳይለቁ እግዚአብሔርን በተስፋ ቢጠብቁት አንድ ቀን ይፈወሳሉ፡፡

[ በመምህር ምሥጢረ ሥላሴ ማናየ ]


🕊                        💖                       🕊

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

🕊

[ † እንኳን ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጥንተ በዓለ ሆሳዕና በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ]

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †

🕊  †  ጥንተ በዓለ ሆሳዕና  †   🕊

† "ጥንተ በዓል" ማለት በዓሉ : ተአምሩ [የማዳን ሥራው] የተፈፀመበት የመጀመሪያው ቀን ማለት ነው:: በዚህም መሠረት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ከሆሳዕና ጀምሮ እስከ ዸራቅሊጦስ ድረስ ያሉ ዐበይት በዓላትን ሁለት ጊዜ ታከብራለች::

፩ኛው. "ጥንተ በዓል" ሲሆን
፪ኛው. ደግሞ "የቀመር በዓል" ይሠኛል::
መሠረቱ የቅዱሳን ሐዋርያት ቀኖና እና የአባታችን የድሜጥሮስ መንፈሳዊ ቀመር ነው::

ስለሆነም ዓለም ከተፈጠረ በአምስት ሺህ አምሥት መቶ ሠላሳ አራት [5,534] ዓመት : የዛሬ አንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ሰባ አራት [1,974] ዓመት : ልክ በዛሬዋ ቀን [መጋቢት ፳፪] (22) ስም አጠራሩ ከፍ ከፍ ይበልና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በፍጹም ትሕትና በአህያዋና በውርንጫዋ ጀርባ ላይ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም [ ቤተ መቅደስ ] ገብቷል::

ታላቅ የምስጋና መስዋዕትም ከመላዕክት : ከሐዋርያት : ከሕጻናት : ከአረጋውያን : ከፀሐይ : ከጨረቃ : ከከዋክብት : ከቢታንያ ድንጋዮች . . . በአጠቃላይ ከፈጠረው ፍጥረት ሁሉ ቀርቦለታል:: ጌትነቱንም በገሃድ ገልጧል::

† ከበዓሉ በረከት ይክፈለን:: እኛንም ለጣዕመ ምስጋናው የተዘጋጀን ያድርገን::

🕊

[ † መጋቢት ፳፪ [ 22 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. ቅዱሳን ሐዋርያት : ንጹሐን አርድእትና ቅዱሳት አንስት [የጌታችን ፻፳ [120] ቤተሰቦች]
፪. ቅዱስ ቄርሎስ መንፈሳዊ [የቅድስት ሃገር ኢየሩሳሌም ዻዻስ የነበረ : ንጽሕናው የተመሠከረለት አባት ሲሆን በ፫፻፹፩ [381] ዓ/ም በቁስጥንጥንያ ከተሠበሠቡ ፻፶ [150] ቅዱሳን ሊቃውንት አንዱ ነው:: ብዙ ድርሳናትንም ጽፏል::]

[ † ወርኀዊ በዓላት ]

፩. ቅዱስ ዑራኤል ሊቀ መላእክት
፪. ቅዱስ ሉቃስ ወንጌላዊ
፫. ቅዱስ ደቅስዮስ [የእመቤታችን ወዳጅ
፬. አባ እንጦንዮስ [አበ መነኮሳት]
፭. አባ ዻውሊ የዋህ

" አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ እጅግ ደስ ይበልሽ:: አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ እልል በዪ:: እነሆ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው:: ትሑትም ሆኖ በአህያም: በአህያይቱ ግልገል በውርንጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል::" † [ዘካ.፱፥፱] (9:9)

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

🕊                      💖                     🕊

[      የዐቢይ ጾም አራተኛ ሳምንት      ]

💖

[        🕊     መ ጻ ጒ ዕ      🕊       ]


[ እንኳን ለዐቢይ ጾም አራተኛ ሳምንት እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። ]

መጻጒዕ

አራተኛው የዐቢይ ጾም ሳምንት " መጻጒዕ " ይባላል፡፡ ስያሜው በዮሐንስ ወንጌል ፭ ፥ ፩ ላይ ከሚገኘው ኃይለ ቃል የተወሰደ ነው፡፡

በዚህ የወንጌል ክፍል ጌታችን በቤተ ሳይዳ ሕሙማንን እንደ ፈወሰ ተነግሮአል፡፡ ብዙ ሕሙማን ፈውስ ሽተው አንዲት የመጠመቂያ ሥፍራን ከበው ይኖሩ ነበር፡፡ በዚያች ሥፍራ ቀድሞ የወረደ እና የተጠመቀ አንድ በሽተኛ ብቻ ይፈወስ ነበር፡፡ ጌታችን በዚህ ሥፍራ ተገኝቶ በሽተኞችን ጐብኝቷል፡፡ በዚያም ልዩ ልዩ ደዌ ያለባቸው አምስት ዓይነት ሕሙማን እንደ ነበሩ ተገልጧል ፤

እነዚህም ፦ ሰውነታቸው የደረቀ ፣ የሰለለና ያበጠ ፤ እንደዚሁም ዕውራን እና ሐንካሳን ነበሩ፡፡ ከዚህ አምስት የተለያየ ዓይነት በሽታ ከተያዙ ሰዎች መካከል ደዌው የጸናበት ፣ ለሠላሳ ስምንት ዓመታት በደዌ ዳኛ ፣ ባልጋ ቍራኛ ተይዞ የኖረው ፤ ከደዌው ጽናት የተነሣ " መጻጒዕ " ተብሎ የተጠራው በሽተኛ አንዱ ነበር፡፡

መጻጒዕ ስም አይደለም፡፡ ደዌ የጸናበት በሽተኛ ሕመምተኛ ማለት ነው እንጂ፡፡ ሰውየው ከበሽታው ጽናት የተነሣ ስሙ ጠፍቶ በበሽታው ሲጠራ የነበረ ነው፡፡ አምላካችን ይህን ሰው "አልጋህን ተሸክመህ ሒድ " ብሎ ሠላሳ ስምንት ዘመን የተኛበትን አልጋ ተሸክሞ ወደ ቤቱ እንዲገባ ማድረጉ የሚነገርበት ወቅት በመኾኑ ሳምንቱ ‹መጻጒዕ› ተብሎ በተፈወሰው በሽተኛ ስም ተሰይሟል፡፡

[ ሙሉ ታሪኩን በዮሐንስ ወንጌል ፭፥፩-፲፯ ይመልከቱ ]፡፡

ዛሬም ቢኾን በሰዎች ላይ ልዩ ልዩ ደዌያት አሉ ፤ የሥጋውን ደዌ ሐኪሞች ያውቁታል፡፡ ከዚህ የከፉ የነፍስ ደዌያት እጅግ ብዙዎች ናቸው፡፡ በኃጢአት ብዛት ልባቸው የደረቀና ያበጠ ፤ ሰውነታቸው የሰለለ ፤ ዓይነ ሕሊናቸው የታወረ ፤ እግረ ልቡናቸው የተሰበረ ብዙዎች ሕሙማን አሁንም አሉ፡፡ ፈውስን ይሻሉ ፤ ድኅነትን ይፈልጋሉ፡፡ እንደ መጻጕዕ ቦታቸውን ሳይለቁ እግዚአብሔርን በተስፋ ቢጠብቁት አንድ ቀን ይፈወሳሉ፡፡

🕊                        💖                       🕊

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

                           †                           

[  🕊 የእግዚአብሔር እናቱ እመቤቴ 🕊  ]  

🕊                      💖                      🕊

[  ኦርቶዶክሳዊ የተቀደሰ ያሬዳዊ ዝማሬ ሰዓት  ]

" ኤሎሄ የተባለ [ የአምላኬ ] የእግዚአብሔር እናቱ እመቤቴ ማርያም ሆይ አንቺ ዘወትር ፍጹም የተመሰገንሽ ነሽ፡፡ በትግሥት መጐናጸፊያ የተጋረድሽ በይውህና ልብስም ያጌጥሽ ነሽ።

ብሩህ የሆነ የማስተዋል መብራትንም በአዕምሮዬ አብሪልኝ ለምስጋናሽ የነቃሁ ለውዳሴሽም የተጋሁ እሆን ዘንድ ለዘለዓለሙ አሜን።

እመቤቴ ማርያም ሆይ የየዋሁ በግ እናት የሆንሽ በግ ነሽ:: አነጋገርሽ ያማረ ፊትሽም የሚያበራ መልካም ሙሽራም ነሽ። ከጥዋት እስከማታ ከማታ እስከ ጥዋት ትጠብቂኝ ዘንድም እማጸንሻለሁ:: ለውዳሴሽ እንድተጋ ፣ ለምስጋናሽ እንድነቃም አድርጊኝ። ከሚያስደነግጥ የኀዘን ዜና ከሚያስፈራ ጨለማ ነገርም አድኚኝ። ለዘለዓለሙ አሜን። "

🕊

[  እንዚራ ስብሐት   ]


†                       †                      †
💖                    🕊                   💖

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

🕊

†  በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ †

[ †  እንኩዋን ለጌታችን "ኢየሱስ ክርስቶስ" ዓመታዊ በዓልና ለእመቤታችን "ቅድስት ድንግል ማርያም" ወርኀዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ † ]


🕊 †  ቅዱሱ ቤተሰብ እና ጌታ  † 🕊

ለስም አጠራሩ ስግደት ይሁንና የዓለም ሁሉ ጌታ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚች ቀን ወደ ቢታንያ ሔዶ: እነ ቅዱስ አልዓዛርና ቤተሰቦቹ እንግድነት ተቀብለውታል::

በዚያም ቅድስት ማርታ በጌታ ፊት ስታገለግል: ቅዱስ አልዓዛር ከጌታ ጐን ተቀምጦ: ቅድስት ማርያ በ፫፻ [300] ዲናር የገዛችውን ሽቱ በጌታ ላይ አፈሰሰች:: እግሩንም በጠጉሯ አበሰች:: [ዮሐ.፲፪፥፩] (12:1)

ለዛ የተባረከ ቤተሰብም ታላቅ በረከት ሆነ:: በርግጥም ድንቅ ነው:: ጌታን በቤት ማስተናገድ ፍፁም መታደል ነው::

ዳግመኛ በዚህ ቀን ይሁዳ በ፫፻ [300] ዲናሩ ሽቱ አመካኝቶ በጌታ ላይ አንጎራጎረ:: አይሁድ ደግሞ አልዓዛርን ይገድሉት ዘንድ ተማከሩ:: ምክንያቱም ጌታችን በርሱ ላይ የሠራትን ድንቅ እያዩ ከአይሁድ ወገን ብዙዎቹ ያምኑ ነበርና::

ቤተ አልዓዛርን የባረከ ጌታ በቸርነቱ የኛንም ይባርክርልን::

🕊

[ † መጋቢት ፳፩ [ 21 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ] =

፩. ቅዱሱ ቤተሰብ [አልዓዛር: ማርያና ማርታ]
፪. አባታችን ላሜኅ [የማቱሳላ ልጅ-የጻድቁ ኖኅ አባት]
፫. ቅዱስ ቴዎድሮስ ሰማዕት
፬. ቅዱስ ጢሞቴዎስ ሰማዕት

[ † ወርኀዊ በዓላት ]

፩. ቅድስት ድንግል እመቤታችን ማርያም
፪. አበው ጎርጎርዮሳት
፫. አቡነ ምዕመነ ድንግል
፬. አቡነ አምደ ሥላሴ
፭. አባ አሮን ሶርያዊ
፮. አባ መርትያኖስ ጻድቅ

" የወንድማማች መዋደድ ይኑር:: እንግዶችን መቀበል አትርሱ:: በዚህ አንዳንዶች ሳያውቁ መላእክትን እንግድነት ተቀብለዋልና:: ከእነርሱ ጋር እንደታሰረ ሆናችሁ እስሮችን አስቡ:: የተጨነቁትንም ራሳችሁ ደግሞ በሥጋ እንዳለ ሆናችሁ አስቡ:: " [ዕብ.፲፫፥፩] (13:1)

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

ዓርብ - መጋቢት 20 2016 ዓም    

ሐዋ 1-5  
   
ሰላም ለሁላችሁ ይሁን! በዛሬው የዐቢይ ጾም ንባባችን የሐዋርያት ሥራ ከምዕራፍ 1-5 ድረስ እናነባለን።  

ከንባብ በፊት የሚደረግ ጸሎት፡ “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፤ የአንተን ቃላት እሰማ እና እረዳ ዘንድ፥ እንዲያውም ፈቃድህን ለመፈጸም እበቃ ዘንድ የልቤን ጆሮዎች እና ዓይኖች ክፈትልኝ።” (ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ)  

የዛሬው ንባብ ሐዋ 1-5 ነውና፥ እርሱ እንዲነበብ ይሁን።  

መልካም ንባብ!

/channel/c/2014228571/1

@OrthodoxTewahdoBooks

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

                          †                          

💖  [     የትሕርምት ሕይወት !     ]  💖

🕊                        💖                       🕊

🍒

[ " ለዚህ ዓለም ሊኖረን ስለሚገባ አመለካከት ! ... " ]

------------------------------------------------

" ፍጹም የሆነውን የትሕርምት ሕይወት መኖር ከፈለግህ መልካምን ነገር መረጥህ፡፡ የዚህ ዓለም ደስታና ሕይወት አንድ ቀን አንደሚነቀል ድንኳን ተነቅሎ የሚጠፋ መሆኑን ካልተረዳህ በቀር ዓለሙን ተከትለው እንደጠፉ ወገኖችህ አንተም ይህችን ዓለም ድል መንሳትን ገንዘብ ሳታደርግ ታልፋለህ፡፡

በዚህ ዓለም ማታለል ተይዘን እንዳንጠፋ ጌታችን እንዲህ በማለት ያሳስበናል ፦ “እኔን መከተል የሚወድ ቢኖር ፥ ራሱን ይካድ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ፡፡ ነፍሱን ሊያድን የሚወድ ሁሉ ያጠፋታል ፤ ስለ እኔ ግን ነፍሱን የሚያጠፋ ሁሉ ያገኛታል። ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ሲያጐድል ምን ይጠቅመዋል? ወይስ ሰው ስለ ነፍሱ ቤዛ ምን ይሰጣል? [ማቴ.፲፮፥፳፬]

🕊

[  ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ   ]


🕊                        💖                       🕊

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

"አንድ ሰው በጣም የሚወደው ወዳጁ ኅዘንና ጭንቀት ሲገጥመው ሌላ ሰውን ሳይልክ እርሱ ራሱ እንደሚሔድለት ኹሉ እግዚአብሔርም ከቀናይቱ መንገድ ወጥቶ የወደቀውን የሰው ልጅን ያነሣው ዘንድ ሌላ ሦስተኛ አካል ሳያስፈልግው እርሱ ራሱ ይቀርበው ዘንድ ሽቶ ወረደ እንጂ መልአክ ወይም የመላእክት አለቃ ወይም ከአገልጋዮቹ አንዱን እንዳልላከለት አስተውል፡፡"

(ትምህርት በእንተ ምክንያት ሐውልታት፣ በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፥ ገጽ 161)

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

💛
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

🕊   ዐቢይ ጾም [  ጾመ እግዚእ  ]  🕊


▷  "  ሰ ፊ ው መ ን ገ ድ ! "


[  💖 " በቅዱሳን አባቶቻችን ... ! " 💖  ] 

[                        🕊                        ]
----------------------------------------------

" በጠበበው ደጅ ግቡ ፤ ወደ ጥፋት የሚወስደው ደጅ ሰፊ ፥ መንገዱም ትልቅ ነውና ፥ ወደ እርሱም የሚገቡ ብዙዎች ናቸው ፤

ወደ ሕይወት የሚወስደው ደጅ የጠበበ፥ መንገዱም የቀጠነ ነውና ፥ የሚያገኙትም ጥቂቶች ናቸው።" [ ማቴ.፯፥፲፫ ]


🕊                       💖                   🕊

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

ሐሙስ - መጋቢት 19 2016 ዓም    

ዮሐንስ 16-21  
   
ሰላም ለሁላችሁ ይሁን! በዛሬው የዐቢይ ጾም ንባባችን የዮሐንስ ወንጌልን ከምዕራፍ 16-21 ድረስ እናነባለን።  

ከንባብ በፊት የሚደረግ ጸሎት፡ “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፤ የአንተን ቃላት እሰማ እና እረዳ ዘንድ፥ እንዲያውም ፈቃድህን ለመፈጸም እበቃ ዘንድ የልቤን ጆሮዎች እና ዓይኖች ክፈትልኝ።” (ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ)  

የዛሬው ንባብ ዮሐ 16-21 ነውና፥ እርሱ እንዲነበብ ይሁን።  

መልካም ንባብ!

https://t.me
/OrthodoxTewahdoBooks

/channel/c/2014228571/1

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

       †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬

[   ኦርቶዶክሳዊ የመዳን ትምህርት   ]

[ በዚህ መርሐ-ግብር ኦርቶዶክሳዊ የመዳን ትምህርት ከቅዱሳት መጻሕፍት ፤ ከቅዱሳን አባቶቻችን ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን አስተምህሮ እንዲሁም ከመምህራን ትምህርቶች ላይ በየጥቂቱ ይቀርባል። እንዲሁም የተሐድሶ መናፍቃን የኑፋቄ ትምህርቶችና ምላሾቻቸው የሚቀርብ ይሆናል። ]

†                      †                       †

[   ኦርቶዶክሳዊ የመዳን ትምህርት   ]

[       ክፍል ሃያ አምስት     ]

[ መዳን ማለት ምን ማለት ነው ?  ]

🕊                         💖                         🕊

፪ ] [ ፈጣሪውን እንዲያውቅ መሆን ፣ ]

እግዚአብሔር ሰውን በመልኩና በአርአያው የፈጠረው ሩቅ ያልሆነውንና በእርሱ ዘንድ ያለውን የፈጣሪውን አርአያ እያሰበና እየተመለከተ በፍቅሩ ሆኖ በተዘክሮው ጸንቶ አንዲኖር ነበር፡፡

ሰው ግን የተደረገለትን ታላቅ ነገር ረስቶ በጸጋው መጠቀምን ትቶ በአርአያውና በመልኩ የፈጠረውን እግዚአብሔርን ረሳ፡፡ መርሳት ብቻም ሳይሆን እርሱን ያገለግሉትና ይጠቀምባቸው ዘንድ የተፈጠሩለትን ከእርሱ በታች ያሉትን የተለያዩ ፍጥረታትንና ቁሳ ቁሶችን አመለካቸው ፣ ተገዛላቸውም፡፡

በፈጣሪ ፋንታ ለፍጡር ተንበረከከ ፤ ከዚህም በላይ የእግዚአብሔርን ክብር ለዕቃውና ለድንጋዩ ፤ ለቁሳቁሱ ሁሉ ሳይቀር ሰጠ፡፡ ከዚህም ወደ ባሰ ሄዶ “ውኃ የሚወስደው ሰው ዐረፋ ይዞ ለመትረፍ ይሞክራል” እንደሚባለው ሆነና የሰው ልጅ አጋንንትን እንኳ እስከ ማምለክ ደረሰ፡፡

በጨለማ የተቀመጠ ሰው አገኝ አጣውን እንደሚዳስስ እንዲሁ ሳይመርጥ ያገኘውን ሁሉ የሚያመልክ ሆነ፡፡ [ ሮሜ 1:19-25 ] እርሱ ሊገዛቸውና ሊያገለግሉት ፣ እንዲሁም የፈጣሪውን ህልውናና ሥራ ለማወቅ እንዲረዱት ለአንክሮና ለተዘክሮ የተፈጠሩለትን ፍጥረታት አመለካቸው::

ነቢዩ ይህን በተመለከተ በማዘንና በመገረም እንዲህ ይላል ፦

" የዝግባን ፣ የዞጲንን ፣ የኮምቦልንና የጥድን ዛፍ ይተክላል ፣ ዝናብም ያበቅለዋል፡፡ ለሰውም ማገዶ ይሆናል ፣ ከእርሱም ወስዶ ይሞቃል ፣ አንድዶም እንጀራ ይጋግርበታል ፤ ከእርሱም አምላክ አበጅቶ ይሰግድለታል ፣ የተቀረጸውንም ምስል ሠርቶ በእርሱ ፊት ይንበረከካል፡፡ ግማሹን በእሳት ያቃጥላል ፤ ሥጋም ይጠብስበትና ይበላል ... የቀረውንም እንጨት አምላክ አድርጎ ምስል ይቀርጽበታል ፤ በፊቱም ተጎንብሶ ይሰግዳል ፣ ወደ እርሱም እየጸለየ ፦ አምላክ ነህና አድነኝ ይላል፡፡ " [ ኢሳ. 44:12-17 ]

ሰው እንዲያ ሥነ ፍጥረትን ሲያመልክ በአንጻሩ የራሱን አስገኚና ሥነ ፈጥረትን ሁሉ የፈጠረውን እግዚአብሔርን ግን ረሳው፡፡ የሰው ልጅ በጊዜያዊ ተድላ ደስታና በአጋንንት ምትሐት በመታለል ራሱን ወደ እውነት መምራት አልቻለም፡፡ ሰው እንዲህ ፈጣሪውን አውቆ እንዲኖር ለክብር ተፈጥሮ ሳለ ከእርሱ በታች ያሉትን አስከ ማምለክ ድረስ ተዋርዶ ፣ ፈጣሪውን ማወቅ ተስኖት በነበረበት ሁኔታ እንዲቀር እግዚአብሔር አልፈቀደም፡፡ ይህም ከቸርነቱ የተነሣ ነው፡፡ ስለዚህ የአግዚአብሔር ቃል ሰው በመሆን ሰውን እርሱን እንዲያውቀው አደረገ፡፡

ሰዎች አወቅን ፣ ተጠበብን እያሉ ነገር ግን የጥበብ መጀመሪያ የሆነውን ፈጣሪያቸውን ማወቅ ስላልቻሉ ፣ የሰው ጥበብና ዕውቀት ሰፊ ጊዜ ተሰጥቶት [ ቅድመ ሥጋዌ የነበሩት ብዙ ሺህ
ዓመታት ] ተፈትኖ ስለ ወደቀ አምላክ በሚታይ ሥጋ በመገለጥ ራሱን ለሰው ገለጠ፡፡
" [ 1 ጢሞ. 3:16 ]

ሐዋርያው ፦ “ ዓለም በጥበብዋ እግዚአብሔርን ስላላወቀች በስብከት በሞኝነት የሚያምኑትን ሊያድን የእግዚአብሔር በጎ ፈቃድ ሆኗልና” ያለው ለዚህ ነበር፡፡ [ 1 ቆሮ. 1:21 ]

ቅዱስ አትናቴዎስ የቃልን ሰው መሆን [ በእንተ ተሠግዎተ ቃል ] በተናገረበት ድርሳኑ ስለዚህ ጉዳይ ሰፋ አድርጎ በመተንተን እንዲህ ይላል ፦

" ሰዎች እግዚአብሔርን ማሰብ ትተው ለራሳቸው መዋትያን ሰዎችንና አጋንንትን አምላክ አድርገው ማምለካቸውን ባየ ጊዜ ሰውን ወዳጅ የሆነው የዓለም መድኃኒት እግዚአብሔር ወልድ ሥጋን ተዋሐደ ፣ እንደ ሰውም በመመላለስ ሰው እርሱን ወደ ማወቅ እንዲመለስ አደረገ፡፡ ፍጥረትን በመፍራት ፍጥረታትን አምላክ ብለው እስኪያመልኩ ከደረሱ የፍጥረቱ ባለቤት ሰው ሆኖ ሲመጣ ያምኑ ዘንድ ፣ ሕሊናቸው ወደ ሰዎች አዘንብሎ አማልክት ናቸው እስከ ማለት ከደረሱ የእርሱን ሥራውን አይተውና ሌሎች ፍጡራን ካደረጉት ጋር አነጻጽረው ከዚያ በፊት እንደ አማልክት ያከብሯቸው ለነበሩት ሁሉ ጌታቸውና ፈጣሪያቸው መሆኑን አውቀው አምልኮታቸውን ወደ እርሱ እንዲመልሱ ፣ ርኵሳን መናፍስትን ወደ መፍራት ፣ ማመንና ማምለክ ያዘነበሉትንም እነዚያን ክርስቶስ ሲያባርራቸውና ሲያስወጣቸው አይተው እርሱ ብቻ አምላክ እንደ ሆነና ርኵሳን መናፍስት ግን ምንም አለመሆናቸውን እንዲረዱ ነው::

የሞቱ ሰዎችን [ ሙታንን ] እንደ ጀግናና እንደ አማልክት የሚያከብሩና የሚያመልኩም ቢሆኑ የጌታን ትንሣኤ አይተው የእነዚያን ሐሰትነትና ጌታችን የፍጡራን ብቻ ሳይሆን የሞት እንኳ ጌታ መሆኑንና ብቸኛው አምላክ እርሱ መሆኑን ያውቁ ዘንድ፡፡ ስለዚህ ምክንያት ጌታችን ሰው በመሆን ተገለጸ ፣ የሰዎችን ሥራ ኢምንት የሚያደርግ ሥራ ሠራ ፣ ሰውን በማንኛውም መንገድ ቢስት ይመልሰውና ያድነው ዘንድ ፣ እውነተኛ አምላክ እርሱ ብቻ መሆኑን ያሳውቀው ዘንድ፡፡ ይህም አምላክ ሰው የሆነበት ሁለተኛው ምክንያት ነው፡፡ "

[ በእንተ ተሠግዎተ ቃል ፣ ቁ. 11-16 ]

[ ይቆየን ]

ወስብሐት ለእግዚአብሔር : ወለወላዲቱ ድንግል : ወለመስቀሉ ክቡር።


🕊                         💖                         🕊

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

🕊

[ † እንኳን ለቅዱሳኑ የአስከናፍር ቤተሰብ ዓመታዊ በዓለ ዕረፍት በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ]

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †


🕊  †  ቅዱስ አስከናፍር   †   🕊

† ከብዙ መቶ ዓመታት በፊት አስከናፍር የሚባል ደግ ክርስቲያን ማርታ የምትባል በሃይማኖትና ምግባር የምትመስለውን ሴት አግብቶ ይኖር ነበር:: እንደ ሕጉና ሥርዓቱ በሥጋ ወደሙ ተወሥነው እንግዳ ቢቀበሉ: ነዳያንን ቢያበሉ እግዚአብሔር ጸሎታቸውን ሰምቶ አርቃድዮስና ዮሐንስ የሚባሉ ልጆችን ሰጣቸው::

አስከናፍርና ማርታ ልጆቻቸውን ጥበብ መንፈሳዊን [ቃለ እግዚአብሔርን] አስቀድመው አስተምረው : ሥጋዊ ጥበብን እዲማሩላቸው ቢልኩዋቸው መንገድ ላይ መርከብ ተሰብሮባቸው ብዙዎቹ ሲሞቱ ወንድማማቾች ግን የመርከብ ስባሪ ወደተለያየ ቦታ አድርሷቸዋል::

አርቃድዮስና ዮሐንስ "ወደ ዓለም አንመለስም" ብለው መነኑ:: ወላጆቻቸው የሆነውን ሰምተው በጭንቅ ሃዘንና ለቅሶ ለብዙ ጊዜ ኑረዋል:: ከዘመናት በሁዋላ ግን የልጆቻቸውን መኖር በራዕይ የተረዱት አስከናፍርና ማርታ ሃብት ንብረታቸውን ለነዳያን አካፍለው ወደ በርሃ መንነው ሔደዋል::

ጥበበኛ እግዚአብሔር አራቱንም አገናኝቷቸው ለብዙ ዓመታት በአንድ ገዳም ውስጥ ተጋድለዋል:: በዚሕች ዕለትም አራቱም ወደ ሰማያዊው ሠርግ ተጠርተዋል::

† ቸር አምላክ ከቅዱሱ ቤተሰብ በረከት ይክፈለን::

🕊

[ † መጋቢት ፲፱ [19] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. ቅዱስ አስከናፍር : ሚስቱ ማርታ : ልጆቹ አርቃድዮስና ዮሐንስ
፪. ቅዱስ አርስጥቦሎስ ሐዋርያ [ከ፸፪ [72]ቱ አርድእት-የቅዱስ ዻውሎስ ደቀ መዝሙር]
፫. ሰባቱ ቅዱሳን ሰማዕታት [ከተለያየ ቦታ ተሰብስበው በክርስቶስ ስም የሞቱ)]

[ † ወርሐዊ በዓላት ]

፩. ቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላእክት
፪. ቅዱስ ኤስድሮስ ሰማዕት
፫. አቡነ ዓቢየ እግዚእ ጻድቅ
፬. አቡነ ስነ ኢየሱስ
፭. አቡነ ዮሴፍ ብርሃነ ዓለም

" እንግዲህ ወንዶች በሥፍራ ሁሉ አለ ቁጣና አለ ክፉ አሳብ የተቀደሱትን እጆች እያነሱ እንዲጸልዩ እፈቅዳለሁ:: እንዲሁም ደግሞ ሴቶች በሚገባ ልብስ ከእፍረትና ራሳቸውን ከመግዛት ጋር ሰውነታቸውን ይሸልሙ:: እግዚአብሔርን እንፈራለን ለሚሉት ሴቶች እንደሚገባ መልካም በማድረግ እንጂ በሽሩባና በወርቅ: ወይም በዕንቁ: ወይም ዋጋው እጅግ በከበረ ልብስ አይሸለሙ::" † [፩ጢሞ.፪፥፰] (2:8)

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

ተወዳጆች ሆይ! እየጦሙ የጦምን ፍሬ ፃማ የማያገኙበት ሁኔታ እንዳለ ታውቁ ዘንድ እወዳለሁ፡፡ ይህስ እንደ ምን ነው ያላችሁኝ እንደሆነም፦

✟ ከምግበ ሥጋ ተከልክለን ከምግበ ኃጢአት
     ያልተከለከልን እንደ ሆነ፣
✟ ከጥሉላት ርቀን ነዳያንን ያልጎበኘን እንደ ሆነ፣
✟ ወይን ከመጠጣት ታቅበን በክፉ መሻት ከመስከር
     ያልራቅን እንደ ሆነ፣
✟ ጀምበር እስክትጠልቅ ድረስ ከእህል ከውኃ ርቀን
     በዓይናችን መልካም ያልሆኑ ትዕይንቶችን ከማየት
     ያልጦምን እንደሆነ ነው ብዬ በእውነት ያለ ሐሰት
     እመልስላችኋለሁ፡፡

ስለዚህ እየጦሙ እንዲህ አለመጦም እንዳለ ዕወቁ፤ ተረዱም፡፡

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

      አምላከ ቅዱሳን እየጦሙ ካለመጦም ይሰውረን!

ሰናይ አሁን

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

🕊

[ † እንኳን ለቅዱስ ኤስድሮስ ሰማዕት ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ]

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †

🕊  †   ቅዱስ ኤስድሮስ  †   🕊

† ሰማዕትነት በክርስትና ለሃይማኖት የሚከፈል የመጨረሻው ዋጋ [መስዋዕትነት] ነው:: ሰው ለፈጣሪው ሰውነቱን ሊያስገዛ: ሃብት ንብረቱን ሊሰጥ ይችላል:: ከስጦታ በላይ ታላቅ ስጦታ ግን ራስን አሳልፎ መስጠት ነው::

ራስን መስጠት በትዳርም ሆነ በምናኔ ውስጥ ይቻላል:: የመጨረሻ ደረጃው ግን ሰማዕትነት ነው::
"አማን መነኑ ሰማዕት ጣዕማ ለዝ ዓለም:: ወተዓገሡ ሞተ መሪረ በእንተ መንግስተ ሰማያት::" እንዳለው ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ
ሰማዕትነት ማለት መራራውን ሞት ስለ ፍቅረ እግዚአብሔር ሲሉ መታገስ ነው::

እርሱ ቅሉ መድኃኒታችን ክርስቶስ የሰማይና የምድር ጌታ ሲሆን ኃፍረተ መስቀልን ታግሦ ሙቶልን የለ!

በዓለም ያሉ ብዙ እምነቶች ስለ መግደል በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ያስተምራሉ:: ክርስትና ግን መሞትን እንጂ መግደልን የሚመለከት ሕግ የለውም::

እርሱ ባለቤቱ "ጠላቶቻችሁን ውደዱ:: የሚረግሟችሁን መርቁ:: ስለሚያሳድዷችሁ ጸልዩ::" ብሎናልና:: [ማቴ.፭፥፵፬] (5:44) ነገር ግን ዕለት ዕለት ራሳችንን በሃይማኖትና በምግባር ካልኮተኮትነው ክርስትና በአንድ ጀምበር ፍጹም የሚኮንበት እምነት አይደለምና በፈተና መውደቅ ይመጣል::

በተለይ የዘመኑ ክርስቲያን ወጣቶች ልናስተውል ይገባናል:: የቀደሙ ወጣት ሰማዕታት ዜና የሚነገረን እንድንጸና ነውና::

ቤተ ክርስቲያናችን ኢትዮዽያዊውን የጐንደር ዘመን ሊቅ ጨምሮ በዚህ ስም የምትዘክራቸው አያሌ ቅዱሳንና ሊቃውንት አሏት::

ዛሬ የምናከብረው ሰማዕቱ ቅዱስ ኤስድሮስ በዘመነ ሰማዕታት የነበረ: ቅዱስ ፃና የሚባል ደግ ጉዋደኛ የነበረው: ሁለቱንም እናቶቻቸው እንደሚገባ ያሳደጉዋቸው የ፫ (3) ኛው መቶ ክ/ዘመን ክርስቲያኖች ነበሩ::

በወጣትነት ዘመናቸው በድንግልና: ቅዱስ ፃና የሠራዊት አለቃ: ቅዱስ ኤስድሮስ ደግሞ የልብስ ዝግጅት ባለሙያ ነበሩ:: ከሚያገኙት ገቢ ለዕለት ጉርስ ብቻ እያስቀሩ ለነዳያን ይመጸውቱ ነበር::
በመከራ ዘመን [ዘመነ-ሰማዕታት] ቅዱሳኑ ያላቸውን ሁሉ ለነዳያን አካፍለው በክርስቶስ ስም መሞትን መርጠዋል::

በዚህች ቀንም አስቀድሞ ቅዱስ ኤስድሮስ አንገቱን ተሰይፎ የክብርን አክሊል ተቀዳጅቷል::

† ፈጣሪ ከሰማዕቱ ክብር ያድለን::

🕊

[ † መጋቢት ፲፰  [ 18 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. ቅዱስ ኤስድሮስ ሰማዕት

[ † ወርሐዊ በዓላት ]

፩. ቅዱስ ፊልዾስ ሐዋርያ
፪. አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ሰባኬ ሃይማኖት [ረባን]
፫. አቡነ አኖሬዎስ ዘደብረ ጽጋጋ
፬. ማር ያዕቆብ ግብፃዊ

" የጭንቀት ቀን ሳይመጣ በጉብዝናህ ወራት ፈጣሪህን አስብ:: ደስ አያሰኙም የምትላቸውም ዓመታት ሳይደርሱ: ፀሐይ: ጨረቃና ከዋክብትም ሳይጨልሙ . . . አፈርም ወደ ነበረበት ምድር ሳይመለስ: ነፍስም ወደ ሰጠው ወደ እግዚአብሔር ሳይመለስ ፈጣሪህን አስብ::
ሰባኪው:- "ከንቱ: ከንቱ: ሁሉ ከንቱ ነው
" ይላል::"
  † [መክ.፲፪፥፩-፱] (12:1-9)

" ዳሩ ግን የነገር ሁሉ መጨረሻ ቀርቦአል:: እንግዲህ እንደ ባለ አእምሮ አስቡ:: ትጸልዩም ዘንድ በመጠን ኑሩ:: ፍቅር የኃጢአትን ብዛት ይሸፍናልና ከሁሉ በፊት እርስ በርሳችሁ አጥብቃችሁ ተዋደዱ:: † [፩ዼጥ.፬፥፯] (4:7)

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖

Читать полностью…
Subscribe to a channel