"እንግዲህ፡ንስሓ፡ግባ፤አለዚያ፡ፈጥኜ፡ እመጣብሃለሁ፡፡" ራዕ 2፥16
የሳፋሪኮም ቦትን በስልኮት በመጠቀም ብቻ በወር ከ100,000 ብር በላይ ተከፋይ መሆን ይችላሉ!💸
🎁 የሳፋሪኮም ቦት ጋር ልክ እንደገቡ የ100 ብር ስጦታ ያገኛሉ በተጨማሪም 1 ሰዉ ወደ ቦቱ ሲጋብዙ በየቀኑ የ50 ብር ቋሚ ክፍያ ያገኛሉ!
👬 ይጋብዙ እና ገንዘብ ይስሩ!
☑️ ይህ የእርሶዎ መጋበዣ ሊንክ ነው ለወዳጅ ዘመድዎ ያጋሩ:🔰
/channel/Safaricom_BonusBot?start=r0222371916
ይቅርታ ስለመጠየቅ !
በጠዋቱ መርሐ-ግብር በቀረበው መዝሙር ላይ ምክንያቱ ምን እንደሆነ ያልታወቀ መጥፎ ምስል አብሮ በመውጣቱ በእግዚአብሔስ ስም ይቅርታ ለመጠየቅ እንወዳለን። በቀጣይ በሚቀርቡ መርሐ-ግብሮች ላይ በተቻለ መጠን ጥንቃቄ የሚደረግ ይሆናል።
ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን !
ሐሙስ - መጋቢት 12 2016 ዓም
ሉቃስ 6-10
ሰላም ለሁላችሁ ይሁን! በዛሬው የዐቢይ ጾም ንባባችን የሉቃስ ወንጌልን ከምዕራፍ 6-10 ድረስ እናነባለን።
ከንባብ በፊት የሚደረግ ጸሎት፡ “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፤ የአንተን ቃላት እሰማ እና እረዳ ዘንድ፥ እንዲያውም ፈቃድህን ለመፈጸም እበቃ ዘንድ የልቤን ጆሮዎች እና ዓይኖች ክፈትልኝ።” (ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ)
ዛሬ በአጣዳፊ ሥራ ምክንያት በመዘግየቴ ይቅርታ። የዛሬው ንባብ ሉቃ 6-10 ነውና፥ እርሱ እንዲነበብ ይሁን።
መልካም ንባብ!
🕊
[ † እንኳን ለአባታችን ቅዱስ ድሜጥሮስ ዓመታዊ የተአምር በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ]
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †
† 🕊 ቅዱስ ድሜጥሮስ ድንግል 🕊 †
† ቅዱስ ድሜጥሮስ በ ፫ [3] ኛው መቶ ክ/ዘመን የተወለደ: በመንፈሳዊ ለዛ ከአጐቱ ደማስቆስ ጋር ያደገ የዘመኑ ደግ ሰው ነበር:: በዘመኑ ክርስቲያኖች በሰማዕትነት ያለቁበት በመሆኑ ቤተሰቦቹ የአጎቱን ልጅ ልዕልተ ወይንን እንዲያገባ ግድ አሉት::
ቅዱስ ድሜጥሮስ የነርሱን ፈቃድ ለመፈፀም ጋብቻውን በተክሊል ፈፀመ:: የፈጣሪውን ፈቃድ ለመፈፀም ደግሞ ከቅድስት እናታችን ልዕልተ ወይን ጋር ተስማምተው ለ ፵፰ [48] ዓመታት በአንድ አልጋ ላይ እየተኙ: አንድ ምንጣፍና ልብስ እየተጋሩ በድንግልና ኑረዋል::
ቅዱስ ሚካኤልም ስለ ክብራቸው ከመካከላቸው ሆኖ ቀኝ ክንፉን ለርሱ : ግራ ክንፉን ለርሱዋ ያለብሳቸው ነበር:: ከ፵፰ [48] ዓመታት በሁዋላ ቅዱስ ድሜጥሮስ የግብፅ ፲፪ [12] ኛ ሊቀ ዻዻስ ሆኖ ተሹሞ: ምስጢር በዝቶለት ባሕረ-ሐሳብን ጽፎ ሠርቷል::
ሰይጣን በሰዎች አድሮ ቅዱሱን ሚስት አለው በሚል ቤተ ክርስቲያን ላይ ሁከት በመፈጠሩ ቅዱስ ድሜጥሮስ በመልዐኩ ትእዛዝ ሕዝቡን ሰብስቦ: እሳት አስነድዶ: ከቅድስት ልዕልተ ወይን ጋር እሳቱ ውስጥ ገብተው ለረዥም ሰዓት ጸልየዋል::
ሕዝቡም ይሕን ተአምር አይተው: የቅዱሳኑን ንጽሕና ተረድተው: "ማረን" ብለው በፍቅር የተለያዩት በዚሕ ዕለት ነው::
ቅዱስ ድሜጥሮስና እናታችን ልዕልተ ወይን ተረፈ ዘመናቸውን በቅድስና አሳልፈዋል:: በተለይ ሊቀ ዻዻሳቱ ድሜጥሮስ ብዙ ድርሳናትን ደርሷል:: እነ አርጌንስ [Origen] ና ቀሌምንጦስ ዘእስክንድርያ [Clement of Alexandria] የመሰሉ መናፍቃንንም አውግዟል::
ከጣዕመ ስብከቱም የተነሳ አርጅቶ እንኩዋ ምዕመናን እየተሰበሰቡ ይማሩ ነበር:: በአልጋ ተሸክመውም ይባርካቸው ነበር:: ቅዱሱ በ፻፯ [107] ዓመቱ ያረፈው በ ፫ [ 3 ] ኛው መቶ ክ/ዘመን አጋማሽ አካባቢ ነው::
† አምላከ ድሜጥሮስ ንጽሕናውን ያሳድርብን:: ጸጋ በረከቱን ደግሞ ያትረፍርፍልን::
🕊
[ † መጋቢት ፲፪ [ 12 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ቅዱስ ድሜጥሮስ ሊቀ ዻዻሳት [ድንግልናው የተገለጠበት]
፪. ቅድስት ልዕልተ ወይን
፫. ቅዱስ መላዚ ሰማዕት
[ † ወርሐዊ በዓላት ]
፩.ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላዕክት [ጠንቁዋዩን በለዓምን የገሰጸበትና አህያዋን እንድትናገር ያደረገበት]
፪. ቅዱስ ማቴዎስ ሐዋርያ
፫. ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ
፬. ቅዱስ ቴዎድሮስ ምሥራቃዊ [ሰማዕት]
፭. ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ
፮. አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ
† " ሥጋዊ ፈቃዳቸውን የሚሠሩ ሁሉ እነርሱ በላይኛው ዓለም የሞቱ ናቸው:: ግን በመንፈሳዊ ሥራ የሥጋችሁን ፈቃድ ድል ከነሳችሁት ለዘለዓለም በሕይወት ትኖራላችሁ:: የእግዚአብሔር መንፈስ የሚወደውን ሥራ የሚሠሩ ሁሉ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸው::" †
[ሮሜ.፰፥፲፫] (8:13)
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
💖 🕊 💖
ረቡዕ - መጋቢት 11 2016 ዓም
ሉቃስ 1-5
ሰላም ለሁላችሁ ይሁን! በዛሬው የዐቢይ ጾም ንባባችን የሉቃስ ወንጌልን ከምዕራፍ 1-5 ድረስ እናነባለን።
ከንባብ በፊት የሚደረግ ጸሎት፡ “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፤ የአንተን ቃላት እሰማ እና እረዳ ዘንድ፥ እንዲያውም ፈቃድህን ለመፈጸም እበቃ ዘንድ የልቤን ጆሮዎች እና ዓይኖች ክፈትልኝ።” (ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ)
በዛሬው ንባባችን ላይ ወንጌል ስለ መጻፉ፥ ስለ ዘካርያስና ስለ ኤልሳቤጥ፥ ቅዱስ ገብርኤል እመቤታችንን እንደ አበሠራት፥ እመቤታችን ወደ ኤልሣቤጥ ስለ መሄድዋ፥ ስለ መጥምቁ ዮሐንስ ልደት፥ ስለ ሕዝብ ቆጠራ፥ ስለ ጌታችን መወለድ፥ ስለ ሕፃኑ መገዘርና ወደ ቤተ መቅደስ መግባት፥ ስለ አረጋዊው ስምዖን፥ ስለ ነቢይቱ ሐና፥ በሊቃውንት መካከል ስለ መገኘቱ፥ ስለ መጥምቁ ዮሐንስ ስብከት፥ ስለ ዮሐንስ መጥምቅ መታሰር፥ ጌታችን ስለ መጠመቁ፥ ስለ ጌታችን ትውልድ መጽሐፍ፥ በዲያብሎስ ስለ መፈተኑ፥ ስለ መጀመሪያ ትምህርቱ፥ በናዝሬት ስለ ማስተማሩ፥ ወደ ቅፍርናሆም ስለ መሄዱ፥ ጋኔን የያዘውን ስለ ማዳኑ፥ ስለ ጴጥሮስ አማትና ስለ ሌሎችም በሽተኞች መፈወስ እናነባለን። በተጨማሪም፥ ስለ ስምዖንና ስለ ዘብዴዎስ ልጆች መጠራት፥ ለምጻሙን ስለ ማዳኑ፥ ስለ መጻጉዕ መፈወስ፥ ስለ ቀራጩ ሌዊ መጠራት እና ስለ ጾምም ተጽፎ እናገኛለን።
ለዛሬ የክለሳ ጥያቄዎች አይኖሩንም።
መልካም ንባብ!
/channel/OrthodoxTewahdoBooks
/channel/c/2014228571/1
†
🍒 [ ፍኖተ ሕይወት ! ] 🍒
🕊 💖 🕊
[ ከፍቅር ኹሉ ስለሚበልጠው የእግዚአብሔር ፍቅር ! ]
🕊
ሕይወትህ በመከራ ውስጥ ወደ ማለፍ ብትቃረብም እንኳ !
" ወዳጄ ሆይ ! መከራዎችህ በዚህ ዓለም ላይ ማብቅያ ካገኙ እግዚአብሔርን አመስግን፡፡ ሕይወትህ በመከራ ውስጥ ወደ ማለፍ ብትቃረብም እንኳ ፥ አሁንም ቢኾን እግዚአብሔርን አመስግን፡፡
የእግዚአብሔርን ወሰን የለሽ የኾነውንና እንዲህ ወይም እንዲያ ተብሎ የማይገለፀውን መግቦት በደንብ ዐውቀህ ፣ እያንዳንዱ ነገር በዚህ ዓለም ወይም በወዲያኛው ዓለም ማግኘት የሚገባውን ፍጻሜ እንደሚያገኝ በደንብ ተገንዝበህ አትሰናከል፡፡
አንድ ሰው ሊመጣ ስላለው ነገር ቢሰማና ፍጻሜውን እዚህ ለማየት እጅግ ቢቸኩል እውነተኛ ሕይወት ፣ የማይነዋወጹትና ቀዋምያን ነገሮች በወዲያኛው ዓለም የሚጠብቁን እንደ ኾነ እንነግረዋለን፡፡ አሁን ያሉት ነገሮች መንገዶች ፤ እነዚያ ግን የምንወርሳቸው መኖሪያዎቻችን እንደ ኾኑ እንነግረዋለን፡፡
የዚህ ዓለም ነገሮች እንደ መከር አበባዎች ፤ ሊመጡ ያሉት ነገሮች ግን እንደ ዓለት ተራራዎች መኾናቸውን እንነግረዋለን፡፡ በወዲያኛው ዓለም ፍጻሜ የሌላቸው አክሊላትና ደመወዞች እንዳሉ በዚያ ሹመቶችና ሽልማቶች እንዳሉ እንነግረዋለን፡፡ በዚያ ክፉ ለሠሩ ጽኑዓን የኾነ ቅጣቶችና ሥቃያት እንዳሉ እንነግረዋለን፡፡ "
🕊
[ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ]
🕊 💖 🕊
💛
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
🕊 ዐቢይ ጾም [ ጾመ እግዚእ ] 🕊
▷ " የ ማ ያ ቋ ር ጥ ው ጊ ያ "
[ " በሊቀ ዲያቆናት ሀቢብ ጊዮርጊስ ... ! " ]
[ 🕊 ]
----------------------------------------------
" በመጠን ኑሩ ንቁም ፥ ባላጋራችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሣ አንበሳ ይዞራልና ፤
በዓለም ያሉት ወንድሞቻችሁ ያን መከራ በሙሉ እንዲቀበሉ እያወቃችሁ በእምነት ጸንታችሁ ተቃወሙት።" [ ፩ጴጥ.፭፥፰ ]
🕊 💖 🕊
ማግሰኞ - መጋቢት 10 2016 ዓም
ማርቆስ 11-16
ሰላም ለሁላችሁ ይሁን! በዛሬው የዐቢይ ጾም ንባባችን የማርቆስ ወንጌልን ከምዕራፍ 11-16 ድረስ እናነባለን።
ከንባብ በፊት የሚደረግ ጸሎት፡ “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፤ የአንተን ቃላት እሰማ እና እረዳ ዘንድ፥ እንዲያውም ፈቃድህን ለመፈጸም እበቃ ዘንድ የልቤን ጆሮዎች እና ዓይኖች ክፈትልኝ።” (ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ)
በዛሬው ንባባችን ላይ ጌታችን በአህያ ላይ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም ስለ መግባቱ፥ ስለ ተረገመችው በለስ፥ ቤተ መቅደስን ስለሚያረክሱ፥ በደልን ይቅር ስለ ማለት፥ ስለ ሥልጣኑ፥ ስለ ወይኑ ቦታ፥ ለቄሳር ግብር ስለ መክፈል የቀረበ ጥያቄ፥ ትንሣኤ ሙታን የለም ከሚሉ ወገኖች ስለቀረበ ጥያቄ፥ ከአንድ ጸሐፊ ስለ ቀረበ ጥያቄ፥ ስለ ቤተ መቅደስ መፍረስና ስለ ዓለም ፍጻሜ፥ ስለ ሰው ልጅ መምጣት እና ስለ ዕለቲቱና ሰዓቲቱ ተጽፎ እናገኛለን። በተጨማሪም ስለ ሊቃነ ካህናት ምክር፥ ጌታችንን ሽቱ ስለ ቀባችው ሴት፥ ስለ ፋሲካ፥ ስለ ሥጋውና ደሙ ሥርዓት፥ ስለ ሐዋርያት መበተን፥ በጌቴሴማኒ ስለ መጸለዩ፥ ለአይሁድ ተላልፎ ስለ መሰጠቱ፥ በአደባባይ ስለ መቆሙ፥ ስለ ጴጥሮስ ክህደት፥ በጴላጦስ ፊት ስለ መቆሙ፥ ስለ ስቅለቱ፥ ወደ መቃብር ስለመውረዱ፥ ከሙታን ተለይቶ ስለመነሣቱ፥ ለብዙዎች ስለመታየቱ፥ ሐዋርያትን ስለ መሾሙ እና ወደ ሰማይ ስለማረጉም ተጽፎ ይገኛል።
ለዛሬ የክለሳ ጥያቄዎች አይኖሩንም።
መልካም ንባብ!
/channel/OrthodoxTewahdoBooks
/channel/c/2014228571/1
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
[ ኦርቶዶክሳዊ የመዳን ትምህርት ]
[ በዚህ መርሐ-ግብር ኦርቶዶክሳዊ የመዳን ትምህርት ከቅዱሳት መጻሕፍት ፤ ከቅዱሳን አባቶቻችን ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን አስተምህሮ እንዲሁም ከመምህራን ትምህርቶች ላይ በየጥቂቱ ይቀርባል። እንዲሁም የተሐድሶ መናፍቃን የኑፋቄ ትምህርቶችና ምላሾቻቸው የሚቀርብ ይሆናል። ]
† † †
[ ኦርቶዶክሳዊ የመዳን ትምህርት ]
[ ክፍል ሃያ አራት ]
[ መዳን ማለት ምን ማለት ነው ? ]
🕊 💖 🕊
1) ኃጢአት ካመጣው ፍዳ ሁሉ መዳን
[ - ፫ - ]
" ሞት በሰው [ በአዳም ] በኩል መጥቶ በሰው ላይ እንደ ነገሠ ሰው በሆነው የእግዚአብሔር ቃል በዳግማዊ አዳም ተወገደ ፣ ትንሣኤ ሕይወት ተገኘ፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ “ሞት በሰው በኩል ስለመጣ ትንሣኤ ሙታን በሰው በኩል ሆኗልና፡፡ ሁሉ በአዳም እንደሚሞቱ እንዲሁ ሁሉ በክርስቶስ ደግሞ ሕያዋን ይሆናሉና ” እንዳለ፡፡ [ 1 ቆሮ. 15፡21-22 ]
ስለሆነም ከጌታችን ሞትና ትንሣኤ ወዲህ ባለው ዘመን እስከ አሁን ድረስ፣ ወደፊትም እስከ ኅልቀተ ዓለም ድረስ ሰው የሚሞተው “አፈር ነህና ወደ አፈር ትመለሳለህ ” በሚለው በቀደመው ፍርድ ለኩነኔ አይደለም ፤ ለትንሣኤ ነው እንጂ፡፡ ከአሁን በኋላ እንደ ቀድሞው ለኩነኔ አንሞትም ፤ ነገር ግን ከሞት ተነሥቶ የሁሉን ትንሣኤ እንደሚጠብቅ ሰው በራሱ ጊዜ የሚያደርገውን ትንሣኤ ዘጉባኤን እንጠብቃለን፡፡ [ ዘፍ. 3:20 ፣ 1 ጢሞ. 6፡15 ]
ቅዱስ ጳውሎስ ይህን መሠረታዊ የሆነውን የትንሣኤ ምሥጢር በተመለከተ በቀዳማይ ቆሮንቶስ መልእክቱ ላይ ግልጽ አድርጎ አብራርቷል፡፡ “ነገር ግን ሰው ፦ ሙታን እንዴት ይነሣሉ? በምንስ ዓይነት አካል ይመጣሉ ? የሚል ይኖር ይሆናል፡፡ አንተ ሞኝ ፣ አንተ የምትዘራው ካልሞተ ሕያው አይሆንም” በማለት ዘር ካልተዘራና በአፈር ውስጥ ካልሞተ ሕያው ሆኖ ለመብቀልና ለማፍራት እንደማይችል ሁሉ የሰው ሞትም እንዲሁ በሐዲስ ሰውነት ለመነሣት መሆኑን አስረዳ፡፡ [ 1 ቆሮ. 15:35-36 ]
መቃብርም ለዘለዓለም በዚያው ውስጥ ይዞ የሚያስቀረን ሳይሆን እስከ ትንሣኤ ድረስ የምንቆይበትና ከዚያም የሚበሰብሰው የማይበሰብሰውን ፣ የሚሞተው የማይሞተውን ለብሶ የሚነሣበት ነው፡፡ በዚያን ጊዜም በኃጢአት ምክንያት ከሰው ተፈጥሮ በኋላ የመጣው “የኋለኛው ጠላት” - ሞት” - ድል ይነሣል፡፡ [1 ቆሮ. 15:26] እሳት የሚኖረው የሚቃጠል ነገር እስካለ ድረስ ብቻ እንደ ሆነ ሁሉ ሞትም ከትንሣኤ በኋላ የሚሞት ሰውነት ስለማይኖር “ይሞታል” ፤ ለዘለዓለምም ይጠፋል፡፡ ይህን ነው ሐዋርያው በመልእክቱ እንዲህ በማለት የገለጸው ፦
" ሙታንም የማይበሰብሱ ሆነው ይነሣሉ፣ እኛም እንለወጣለን፡፡ ይህ የሚበሰብሰው የማይበሰብሰውን ሊለብስ ፣ ይህም የሚሞተው የማይሞተውን ሊለብስ ይገባዋልና፡፡ ዳሩ ግን ይህ የሚበሰብሰው የማይበሰብሰውን ሲለብስ ፣ ይህም የሚሞተው የማይሞተውን ሲለብስ በዚያን ጊዜ ፦ ሞት ድል በመነሣት ተዋጠ ተብሎ የተጻፈው ቃል ይፈጸማል፡፡ " [ 1ቆሮ. 15:51-55 ]
በኃጢአት ምክንያት የእግዚአብሔር ልጅነታችንን አጥተን የዲያብሎስ ባሪያ ሆነን ነበር፡፡ ጌታችን ግን በቸርነቱ ያን ባርነታችንን አስወግዶ የልጅነትን ጸጋ ሰጠን፡፡ የጸጋ ልጅነቱንና ክብሩን አጥቶ በባርነት ውስጥ ሆኖና ተዋርዶ ለነበረው የሰው ልጅ ዳግመኛ ከእግዚአብሔር የሚወለድበትንና ልጅነትን የሚያገኝበትን ጥምቀትን ሰጠው፡፡ ይህ የልጅነት ጸጋም ለሌሎች ከእግዚአብሔር ለሚገኙ ጸጋዎች ሁሉ መሠረት ነው፡፡ ልጅ ከሆነ ዘንድ የአባቱን ንብረት ለመውረስ ይችላልና፡፡ ይህንም የአባትና የልጅነት ግንኙነት በውስጡ የሚያድርበት መንፈስ ቅዱስ እንዲመሰክርለት አደረገ፡፡
“የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን ያ መንፈስ ራሱ ከመንፈሳችን ጋር ይመሰክራል ” እንዳለ፡፡ [ ሮሜ. 8:16 ] እንዲሁም ይኸው ሐዋርያ ፦
“ልጆችም ስለ ሆናችሁ እግዚአብሔር አባ አባት ብሎ የሚጮኸ የልጁን መንፈስ በልባችሁ ውስጥ ላከ፡፡ ስለዚህ ከእንግዲህ ወዲህ ልጅ ነህ እንጂ ባሪያ አይደለህም ” ይላል፡፡ [ ገላ. 4:6 ] ስለሆነም ከእንግዲህ የባርነት መንፈስ ሳይሆን “አባ አባት ” ብለን የምንጠራበትን የልጅነት መንፈስ ሰጠን፡፡ [ ሮሜ 8:15 ] “አባታችን ሆይ” ብለን እንድንጠራውም ፈቀደልን፡፡
እንዲሁም “ከእንግዲህ ወዲህ ባሮች አልላችሁም ፤ ባሪያ ጌታው የሚያደርገውን አያውቅምና ፣ ወዳጆች ግን ብያችኋለሁ ፤ ከአባቴ የሰማሁትን ሁሉ ለእናንተ አስታውቄያችኋለሁና” በማለት በኃጢአት በተፈጠረ የጠብ ግድግዳ ምክንያት ከምሥጢሩ ርቀን ከአንድነቱ ተለይተን በባርነት እንኖር የነበረውን ሁኔታ አስወግዶ የዕርቅና የልጅነት መገለጫ የሆኑትን ፈቃዱን ማወቅንና ከባርነት ነፃ መውጣትን ሰጠን፡፡ [ ዮሐ. 15:15 ] “የፈቃዱን ምሥጢር አስታውቆናልና” ያለው ለዚህ ነው፡፡ [ ኤፌ. 1:9 ]
ስለሆነም መዳን ስንል በመጀመሪያ በሰው ኃጢአት ምክንያት በባሕርያችን ደርሶብን የነበረውን ነገር ሁሉ - ሞትን ፣ ርግመትን ፣ ጉስቁልናን ፣ ባርነትን ... ሁሉ - አስወገደልን ፤ በአንጻሩ ደግሞ ሕይወትን ፣ ልጅነትን ፣ ኢመዋቲነትን ሰጠን ማለት ነው። ይህ ግን አንዱ እንጂ ብቸኛው አይደለም።"
[ ይቆየን ]
ወስብሐት ለእግዚአብሔር : ወለወላዲቱ ድንግል : ወለመስቀሉ ክቡር።
🕊 💖 🕊
🕊
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን †
[ † እንኳን ለቅዱስ ዕፀ መስቀል ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ]
† መጋቢት ፲ [ 10 ] †
🕊 † ቅዱስ ዕፀ መስቀል † 🕊
ለስም አጠራሩ ጌትነት ይሁንና ቸር አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ለማዳን ከሰማያዊ ክብሩ ወደ ምድር ወርዶ: በማሕጸነ ማርያም እግዝእት በኪነ ጥበቡ ተጸንሶ: በኅቱም ድንግልና ተወልዶ: በፈቃዱ መከራ መስቀልን ተቀብሎ: ከግራ ቁመት: ከገሃነመ እሳት: ከሰይጣን ባርነት: ከኃጢአት ቁራኝነትም አድኖናል::
"እምእቶነ እሳት ዘይነድድ አንገፈነ" እንዳለ ሊቁ::
ምንም መስቀል በብሉይ የወንጀለኞች መቅጫ ሆኖ ቢቆይም እግዚአብሔር ለዓለም መዳኛነት የመረጠው ነውና ሕብረ ትንቢቶች ሲነገሩለት: በብዙ ሕብረ አምሳልም ሲመሰል ኑሯል:: ከተፈጥሯችን ጀምሮ ዓለም ራሷ አርአያ ትዕምርተ መስቀል ናት::
እግዚአብሔር ለቃየን እንዳይገድሉት ከሰጠው ምልክት [ዘፍ.፬፥፲፭] (4:15) ጀምሮ ይስሐቅ ሊሰዋ የተሸከመው እንጨት[ዘፍ.፳፪፥፮] (22:6): ቅዱስ ያዕቆብ ያያት የወርቅ መሰላል [ዘፍ.፳፰፥፲፪] (28:12): ያዕቆብ የዮሴፍን ልጆች የባረከበት መንገድ[ዘፍ.፵፰፥፲፬] (48:14): ባሕረ ኤርትራን የከፈለችው የሙሴ በትር [ዘጸ.፲፬፥፲፭] (14:15): የናሱ ዕባብ የተሰቀለበት እንጨት [ዘኁ.፳፩፥፰] (21:8) ጨምሮ በርካታ ምሳሌዎች ለቅዱስ መስቀሉ መኖራቸውን መተርጉማን ተናግረዋል::
ቅዱስ ዳዊትን የመሰሉ ነቢያት ደግሞ "ለሚፈሩሕ ከቀስት ያመልጡ ዘንድ ምልክትን ሰጠሃቸው" እያሉ መስቀሉን ከርቀት ተመልክተዋል:: [መዝ.፶፱፥፬] (59:4)
በሐዲስ ኪዳን ግን ምሳሌው ገሃድ ሆኖ: ጌታ በዕፀ መስቀል ላይ ተሰቅሎ ሥጋውን ቆረሰበት: ደሙን አፈሰሰበት: ዓለምንም አዳነበት:: ስለዚህም "መስቀል ብርሃን ለኩሉ ዓለም: መሠረተ ቤተ ክርስቲያን" ተብሎ የሚመሰገን ሆኗል::
+ቅዱስ ያሬድ ሊቁ አክሎ "መስቀል መልዕልተ ኩሉ ነገር: ያድኅነነ እምጸር" ብሎ ጠላትን ማሳፈሪያ መሆኑን ይነግረናል:: ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ዻውሎስም ስለ መስቀሉ አምልቶ አጉልቶ አስተምሯል:: መመኪያችን ነውና:: [፩ቆሮ.፩፥፲፰] (1:18), ]ገላ.፮፥፲፬] (6:14)
አንዳንዶቹ እኛን 'የተሰቀለውን ትታቹሃል' ይሉናል::
የተሰቀለውማ የጌቶች ጌታ: የነገሥታት ንጉሥ: የአማልክት አምላክ: ሁሉ በእጁ የተያዘ: ኢየሱስ ክርስቶስ ነውና ከኦርቶዶክስ በላይ የሚያመልክ በወዴት አለና::
ነገር ግን መስቀሉን ንቆ የተሰቀለውን ማክበር አይቻልምና እኛ ለመስቀሉ የጸጋ ስግደትን እንሰግዳለን : እናመሰግነዋለን: እናከብረዋለን: ቤዛ: ጽንዕ: መድኃኒት: ኃይል እያልንም እንጠራዋለን:: አባቶቻችን በመስቀሉ ምርኩዝነት ማዕበለ ኃጢአትን: ባሕረ እሳትን ተሻግረዋል::
በመስቀሉ ቢመኩ አጋንንትን ድል ነስተዋል:: ጠላትንም አሳፍረዋል:: እኛም በመስቀሉ አምነን ከብረን: ገነን እንኖራለን:: ተጠቅመንበታልና ከራሳችን ሕይወት በላይ ምስክርን አንፈልግም::
🕊 † በዓለ መስቀል † 🕊
በዚች እለት የክብር ባለቤት ጌታችን አምላካችንና መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት መስቀል የተገለጠበትና የተገኘበት ነው ። የዚህም የከበረ ዕፀ መስቀል መገለጡና መገኘቱ ሁለት ጊዜ ሆኗል።መጀመሪያ የፃድቁ ንጉስ የቆስጠንጢኖስ እናት በሆነች በንግስት ህሌኒ እጅ ነው።
"እርሷ ለእግዚአብሄር ተስላ ነበርና ልጇ ቆስጠንጢኖስ ወደ ክርስቲያን ሀይማኖት ቢገባ ወደ ኢየሩሳሌም ሄዳ መስቀሉን እስከ አገኘችው ድረስ ልትፈልግው በኢየሩሳሌም ያሉ ቅዱሳት መካናትንና አብያተ ክርስቲያናትን ልታንፃቸው ነው። ከዚህ በኃላ ልጇ አምኖ የክርስትና ጥምቀትን በተጠበቀ ጊዜ እሌኒ ቅድስት ወደ ኢየሩሳሌም ሄደች ከእረሷ ጋርም ብዙ ሰራዊት ነበር ደርሳም ስለ ከበረ መስቀል መረመረች የሚያስረዳት አላገኘችም የአይሁድ ወገን የሆነ አንድ ሽማግሌ ሰው አስራ በርሀብና በጥማት አሰቃየችው ።
በተጨነቀም ጊዜ ለንግስት እሌኒ የጉልጎታን ኮረብታ አስጠርጊ ብሎ ነገራት እርሷም ይጠርጉ ዘንድ አይሁድን አዘዘቻቸው። ቤቱን የሚጠርግ ሰው ሁሉ ጥራጊውን በውስጡ የከበረ መስቀል በአለበት በጌታችን መቃብር ላይ እንዲጥል አይሁድ አስቀድመው አዝዘው ነበርና ንግስት እሌኒ እስከ ደረሰችበት ጊዜ ከሁለት መቶ አመት በላይ ጥራጊያቸውን ሲጥሉበት ኖሩ ኮረብታም ሆነ።
አይሁድም በጠረጉ ጊዜ ሶስት መስቀሎች ተገለጡ የክብር ባለቤት ክርስቶስ የተሰቀለበት የትኛው እንደሆነ አላወቁም። የሞተ ሰውም አግኝተው አመጡ ። አንዱንም መስቀል አምጥተው በሞተው ሰው ላይ አኖሩት አልተነሳም ደግሞ ሌላውን መስቀል አምጥተው በሙቱ ላይ አኖሩ አሁንም አልተነሳም ከዚህም በኃላ ሶስተኛውን መስቀል አምጥተው በሙቱ ላይ አደረጉት ያንጊዜ የሞተው ሰው ተነሳ እሌኒም የክርስቶስ መስቀል እንደሆነ አውቃ ሰገደችለት የክርስቲያንም ወገኖች ሁሉ ሰገዱለት።
ለልጅዋ የላከችው ይህ መስቀል ነው የሚል በሌላ መፅሀፍ ይገኛል የቀረው ግን ግንዱ በውስጡ ተተክሎበት የነበረው ከእርሱም እኩሌታውን ከቅንዋቱ ጋራ ወደ ልጅዋ የላከችው ነው። ከዚህም በኃላ ስራአታቸውና የህንፃቸው ነገር በመስከረም ወር በአስራ ሰባት ተፅፎ የሚገኝ አብያተ ክርስቲያናትንና የከበሩ ቦታዎችን አነፀች።
ሁለተኛው በሮሙ ንጉስ በህርቃል ዘመን የሆነው ሲሆን የፋርስ ሰዎች በግብፅ አገር ሳሉ ወደ አገራቸው ሊመለሱ ወደዱ። ከሹማምንቶቻቸው አንዱ የጦር መኰንን ተነጥሎ ወደ ኢየሩሳሌም አልፎ ደረሰ ወደ ከበረ መስቀል ቤተ ክርስቲያንም ገባ። መስቀሉም በላዮ በተተከለበት ግንድ ፊት ታላቅ ብርሀን ሲበራ አይቶ ሊያነሳው እጁን ዘረጋ። እሳትም ወጥታ እጁን አቃጠለችው።
ከክርስቲያን በቀር ማንም ሊነካው እንደማይችል የመስቀልን የክብሩን ነገር ሰዎች ነገሩት። ሁለት ዲያቆናትንም ይዞ የከበረ መስቀልን እንዲሸከሙ አዘዛቸወወ ከኢየሩሳሌምም ብዙ ሰዎችን
ማርኮ ወደ አገሩ ተመለሰ።
የፋርስ ሰዎች ኢየሩሳሌምን እንዳጠፏት ብዙዎች ሰዎችንም እነድ ማረኩና የከበረ የክርስቶስንም መስቀሉን እንደ ወስዱየሮም ንጉስ ህርቃል በሰማ ጊዜ እጅግ አዘነ። ስለርሱም እንዲፆሙ ምእመናንን አዝዞ ወደፋርስ ዘምቶ ወጋቸው ብዙዎችንም ገደላቸው የከበረ እፀ መስቀልንም እየፈለገ በሀገራቸው ሁሉ ዞረ ግን አላገኘውም።
ያ ዲያቆናቱና መስቀሉን የወሰደ መኰንን ከቦታዎች በቤቱ አነፃር ባለ በአንድ ቦታ ላይ ወስዷቸው ጥልቅ ጉድጓድእንዲቆፍሩ አዝዞ በዚያ የከበረ መስቀልን አስቀበረ እነዚያንም ዲያቆናት ገደላቸው።
ነገር ግን ያ መኰንን የማረካት የካህናት ወገን የሆነች በእርሱ ቤት የምትኖር አንዲት ብላቴና ነበረች። እርሷም የከበረ መስቀልን ሲያስቀብርና ሁለቱን ዲያቆናት ሲገድላቸው በቤቱ ውስጥ ሁና በመስኮት ትመለከት ነበር ወደ ንጉስ ሕርቃልም ሂዳ መኰንኑ ያደረገውን ሁሉ ነገረችው።
ይህንንም ንጉስ ሰምቶ እጅግ ደስ አለው ያቺ ብላቴናም መራችው ከእርሱም ጋራ ብዙ ሰራዊት ሆኖ ኤጲስቆጶሳትና ካህናትም ነበሩ ።ወደ ቦታውም እስከምታደርሳቸው ያቺን ልጅ ተከተሏት ቅፍረውም የከበረ እፀ መስቀልን አገኙት ከአዘቅቱም አወጡት ንጉሱና ሰራዊቱም ሰገዱለት።
†
[ የትሕርምት ሕይወት ! ]
🕊 💖 🕊
[ ከፍቅር ኹሉ ስለሚበልጠው የእግዚአብሔር ፍቅር ! ]
------------------------------------------------
ይወድደናልም ጭምር እንጂ !
" ጤናማ አእምሮ ላላቸው ሰዎች እግዚአብሔር እንደሚመግበን ብቻ ሳይኾን እንደሚወደንም ጭምር ለማሳየት በገቢር ከመግለፁ በፊት ሳይቀር የእግዚአብሔር ምስክርነት በራሱ በቂ ነው፡፡
እንዲሁ የሚመግበን [ የሚጠብቀን ] ብቻ አይደለምና ፤ ይወድደናልም ጭምር እንጂ፡፡
የሚወደንም ሕሊናት ሊደርሱበት በማይችሉት ፣ ሕሊናት በማይደርሱበት ብቻ ሳይኾን እጅግ ጥልቅ ፣ ጽኑ ፣ እውነተኛ በኾነ ፣ በማይጠፋና በማይለወጥ ፍቅር ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ይህን መግለፅ ፈልጎ ምሳሌዎችን ከሰዎች ወስዷል፡፡ የዚህን ፍቅር እጅግ ብዙ ምሳሌዎችን ፣ የመግቦት አሳቦችንና መጨነቆችን አስቀምጧል፡፡
እነዚህ ምሳሌዎች ማስረዳት በሚችሉበት ዓቅም ላይ ብቻ እንድንወስን ግን አይፈልግም ፤ በእነርሱ መነሻነት ከእነርሱ አልፈን እንድንኼድም ያደርገናል እንጂ፡፡ የእግዚአብሔርን ፍቅር በምልአት ይገልጣሉ ተብለው የተቀመጡም አይደሉም ፤ መስማትን ሊሰሙአቸው ለሚወዱና ከሌሎች ምሳሌያት በላይ የፍቅሩን ጥልቀት ጭላንጭል ለመስጠትም ጭምር እንጂ፡፡
ለምሳሌ ፦ አንድ ቀን እያዘኑና እያለቀሱ ፦ "እግዚአብሔር ትቶኛል ፤ ጌታም ረስቶኛል" ላሉ ሰዎች ሲመልስላቸው ፦ "በውኑ ሴት ልጅዋን ትረሳለችን? ከማኅፀንዋ ለተወለደውስ አትራራምን?" ብሏቸዋል፡፡ [ኢሳ.፵፱፥፲፬]
ይኸውም አንዲት ሴት የገዛ ልጅዋን እንደማትረሳ ፥ እግዚአብሔርም የሰው ልጆችን አይረሳም ሲላቸው ነው፡፡"
🕊
[ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ]
🕊 💖 🕊
🕊
[ † እንኳን ለሐዋርያው ቅዱስ ኩትን ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ]
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †
🕊 † ሐዋርያው ቅዱስ ኩትን † 🕊
† ቅዱስ ኩትን በዘመነ ሐዋርያት የነበረ : ከአሕዛብ ወደ ክርስትና በቅዱስ ዻውሎስ አማካኝነት የተመለሰ : ከቅዱሳን ሐዋርያት እግር ሥር ቁጭ ብሎ ይማር ዘንድ የታደለ : በፍፁም ድንግልናው የተመሰገነ ሐዋርያዊ አባት ነው::
ይህ ቅዱስ ሚስት ነበረችው:: ግን በትዳር ውስጥ ሆኖ ድንግልናን መጠበቅ እንደሚቻል ያሳየ የሐዲስ ኪዳን ሰው ነው:: ቅዱስ ኩትን በንጽሕናው : በአገልግሎቱና በጣዕመ ስብከቱ በሐዋርያትና ምዕመናንም ተወዳጅ ነበር:: ለብዙ ዘመናት በወንጌል አገልግሎት ኑሮ በዚሕች ቀን በመልካም ሽምግልና አርፏል::
† ፈጣሪ ከበረከቱ ያድለን::
🕊
[ † መጋቢት ፱ [ 9 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
1. ቅዱስ ኩትን ሐዋርያ
2. ቅዱስ እንድርያኖስ ሰማዕት
3. ቅዱስ አውሳብዮስ ሰማዕት
4. ፳፻ [2,000] ሰማዕታት [የአባ ኖብ ማሕበር]
[ † ወርሐዊ በዓላት ]
፩. አባ በርሱማ ሶርያዊ [ለሶርያ መነኮሳት ኁሉ አባት]
፪. አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ]ኢትዮዽያዊ]
፫. ፫፻፲፰ [318ቱ] ቅዱሳን ሊቃውንት [ርቱዐነ ሃይማኖት ዘኒቅያ]
፬. የብሔረ ብፁዐን ጻድቃን
፭. አባ መልከ ጼዴቅ ዘሚዳ [ኢትዮዽያዊ]
፮. ቅዱስ ዞሲማስ ጻድቅ [ዓለመ ብፁዐንን ያየ አባት]
† " . . . ስለ ድንግልናው ያፈረ ሰው ቢኖር የወደደውን ያድርግ:: ቢያገባም ኃጢአት የለበትም:: ሳይናወጥ በልቡ የጸና ግን ግድ የለበትም:: የወደደውን እንዲያደርግ ተፈቅዶለታል:: ድንግልናውንም በልቡ ይጠብቅ ዘንድ ቢጸና መልካም አደረገ:: እንዲሁም ድንግልን ያገባ መልካም አደረገ:: ያላገባም የተሻለ አደረገ:: " † [ ፩ቆሮ.፯፥፴፮-፴፰ ] ( 7:36-38 )
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
💖 🕊 💖
†
[ 🕊 ድምፀ ተዋሕዶ 🕊 ]
🍒▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬🍒
[ ሕይወት የሚገኝባቸው የቅድስት ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ትምህርቶች በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን በድምፅ ይቀርባሉ። ]
[ ሳምንታዊ መርሐ-ግብር ]
🕊
[ " ቅ ዱ ሳ ት መ ጻ ሕ ፍ ት ! " ]
[ ክፍል አስር ]
" ይህን በመጀመሪያ እወቁ ፤ በመጽሐፍ ያለውን ትንቢት ሁሉ ማንም ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደም ፤
ትንቢት ከቶ በሰው ፈቃድ አልመጣምና ፥ ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ተልከው ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ተናገሩ።" [፪ጴጥ.፩፥፳]
💖 ድንቅ ትምህርት 💖
[ በመምህራችን በቀሲስ ኅብረት የሺጥላ ]
" የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ፥ ከመከራም ሥጋት ያርፋል።" [ ምሳ.፩፥፴፫ ]
† † †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬
👇
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬
[ ቤተክርስቲያንን እንወቅ ]
[ ክፍል - ፳፪ - ]
[ ን ዋ ያ ተ ቅ ድ ሳ ት ! ]
🕊
ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን። "ቤተክርስቲያንን እንወቅ" በተሰኘው ሳምንታዊ መርሐ-ግብር ባለፈው ሳምንት ሥርዓተ አምልኮት በሚለው ዓብይ ርዕስ ሥር ሥርዓተ ቅዳሴ በመጽሐፍ ቅዱስ የሚለውን ተመልክተን ነበረ። ንዋያተ ቅድሳት የተመለከተው የዛሬው መርሐ-ግብር እነሆ !
[ 🕊 ን ዋ ያ ተ ቅ ድ ሳ ት 🕊 ]
ቤተክርስቲያናችን በእግዚአብሔር የተወደደውን አገልግሎቷን ስትፈጽም እግዚአብሔር ለባህርዩ ቆሻሻ ነገር አይስማማውምና እንደ አቤል ለተወደደው መስዋዕቷ ማቅረቢያ ለአገልገሎቷም ማስፈጸሚያ ይሆኑ ዘንድ ንዋያተ ቅድሳቷን እንደየ ሥርዓቱ አዘጋጅታለች፡፡ እግዚአብሔር ቢፈቅድ የተወሰኑትን እንመልከት፡፡
፩. [ ታቦት / ark / ] ፦
ማለት ማደሪያ ማለት ነው ማደሪያነቱም ለልዑል እግዚአብሔር ነው፡፡ ጌታ ሙሴን ሸምሸርሸጢን ከሚባል ከማይነቅዝ እንጨት ርዝመቱን 125 ቁመቱን 75 ወርዱን 75 ሳ.ሜ አድርገህ ታቦትን ቅረጽ በውስጥና በውጭ በወርቅ ለብጠው ፣ ሁለቱን ኪሩቤል እንደሚናተፉ አውራ ዶሮዎች አስመስለህ ቅረጽበት ብሎ አዝዞት እንዳለው አድርጎ ሠርቶታል በአገልግሎት ረገድም የጽላቱ ማኖሪያና እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር የመኖሩ ምልክት ነበር። [ ዘጸ 25 ፥ 1-22 ፣ 40፥20 ]
እስራኤል ታቦትን ያከብሩ ጌታም በርሱአድሮ ብዙ ተአምራትን ያድርግላቸው ነበር። [ ኢያሱ 3፥6 ] [ ሳሙ 4፥6 ] ዛሬም በቤተ መቅደስ መሥዋዕተ ወንጌል የጌታ ሥጋና ደሙ ይፈተትበታል፡፡
ምሳሌነቱም ፦ ታቦት የእመቤታችን ፣ ጽላት የጌታ ፣አንድም ታቦት የእመቤታችን ፣ ጽላት የትስብዕት /የሥጋ/ ቃሉ የአካላዊ ቃል ምሳሌ ነው፡፡ አንድም ታቦት የጌታ ፣ የማይነቅዝ እንጨት የእመቤታችን ምሳሌ ፤ ከማይነቅዝ እንጨት መሠራቱ ጌታ በኃጢአት ከማትለወጥ ከእመቤታችን ለመወለዱ ምሳሌ ነው፡፡
፪. [ ጽላት /Tablet of the law/ ] ፦
ጽላት ማለት ሰሌዳ አንድም መጸለያ ማለት ነው የመጀመሪያዋ ጽላት በግብር አምላካዊ የተገኘች 2 ክፍሎች ያሏትና 10ሩ ትእዛዛት የተጻፈባት ሙሴ በደብረ ሲና ከጌታ የተቀበላት ኋላም እስራኤል ለጣኦት ሲሰግዱ አይቶ ቢደነግጥ ከእጁ ወድቃ የተሰበረችው የዕንቁ ጽላት ናት። [ ዘጸ 32፣15-20 ]
ሁለተኛዋ ሙሴ በፊተኛዋ አምሳል መሠረት በግብር አምላካዊ 10ሩ ትዕዛዛት የተጻፈባት በቤተ መቅደስ በታቦቱ ላይ ሆና ኃይል ታደርግ የነበረችና /ዘጸ 34፣1-28/ በንጉሥ ሰሎሞን ዘመን ወደ ሀገራችን መጥታ በአክሱም ጹዮን እንደተቀመጠች የሚነገርላት የዕብነበረድ ጽላት ናት፡፡ ምሳሌነቷ ከላይ ተገልጿል ጸሎተ ቅዳሴው ታቦቱንና ጽላቱን አንድ አድርጎ ታቦት እያለ ይጠራዋል፡፡
፫. [ መንበር / Throne / ] ፦
ከወርቅ ፣ ከብር ፣ ከብረት ወይም ከእንጨት ይሠራል አገልግሎቱም ከቤተ መቅደስ ታቦት /ጽላት/ ይቀመጥበታል። ጸሎት ይጸለይበታል ፤ መሠዋዕት ይሠዋበታል ፤ በመንበሩ ላይ በመደበኛነት የሚቀመጡ ንዋያተ ቅድሳት ታቦት /ጽላትና/ ሥዕለ ማርያም ምስለ ፍቁር ወልዳ ሲሆኑ በቅዳሴ ጊዜ ሥጋውን ደሙን ለመፈተት የምንገለገልባቸው ጻሕል ፣ ጽዋዕ ፣ ማኀፈዳት ፣ ዕረፈ መስቀል ፣ መስቀል ፣ ዕጣን ይቀመጡበታል፡፡
መንበሩን የሚዳስሱና የሚያገለግሉበት ቀሳውስቱ ናቸው ዲያቆናት ግን ከበውት ይቆማሉ፡፡
ምሳሌነቱም ፦ መንበር የእመቤታችን ፣ ታቦት /ጽላት / የጌታ ፣ አንድም መንበር የመንበረ ጸባዖት ፣ ታቦት /ጽላት/ የሰማያዊ ንጉሥ የጌታ ፣ ልዑካን የሠራዊተ መላእክት ምሳሌ ነው፡፡
[ በቀጣይ ብንኖር ታቦት በሐዲስ ኪዳን ያለውን ትርጓሜና አገልግሎት በሰፊው የሚቀርብ ይሆናል። ]
[ ይቆየን ]
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፥ ወለወላዲቱ ድንግል ፥ ወለመስቀሉ ክቡር፡፡
† † †
💖 🕊 💖
🕊
[ † እንኳን ለ ፵ [ 40 ] ቅዱሳን እና ለታላቁ ቅዱስ መቃርስ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ]
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †
🕊 † ታላቁ ቅዱስ መቃርስ † 🕊
† ታላቁ ቅዱስ መቃርስ [ቅዱስ መቃሬ] "ጽድቅ እንደ መቃርስ" የተባለለት: የመነኮሳት ሁሉ አለቃ: ከ፹ [80] ዓመታት በላይ በበርሃ የኖረ: በግብፅ ትልቁን ገዳም [አስቄጥስን] የመሠረተ: ከ ፶ ሺህ [50,000] በላይ መነኮሳትን ይመራና ይመግብ የነበረ ፍፁም ጻድቅ ነው::
በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን በዚሕች ዕለት አርዮሳውያን ደጉን ታላቅ አባት በሰንሰለት አስረው ከግብፅ ወደ እስያ በርሃ ከጉዋደኛው ቅዱስ መቃርዮስ እስክንድርያዊ ጋር አሰድደውታል:: በዚያ ለ፪ [2] ዓመታት ስቃይን ከተቀበሉ በሁዋላ በአረማውያን ፊት ድንቅ ተአምር አድርገው አረማውያንን ከነ ንጉሳቸው አጥምቀዋል::
በተሰደዱባት ሃገርም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ [ስም አጠራሩ ይክበርና] እመቤታችንን: ቅዱሳን ሐዋርያትን: አዕላፍ መላእክትን: በተለይ ደግሞ ቅዱሳኑን ዳዊትን: ዮሐንስ መጥምቁንና ወንጌላዊውን: ማርቆስን: ዼጥሮስን: ዻውሎስን አስከትሎ ወርዶ ተገልጦላቸዋል::
በቅዱስ አንደበቱም የምሕረት ቃል ኪዳን ገብቶላቸዋል:: ታላቁ ቅዱስ መቃርስና ባልንጀራው መቃርዮስ ከ ፪ [2] ዓመታት ስደትና መከራ በሁዋላ ስደት በወጡባት በዚችው ዕለት መልዐኩ ኪሩብ በክንፉ ተሽክሞ ወደ ግብፅ መልሷቸዋል:: በወቅቱም ጻድቁን ለመቀበል ከ ፶ ሺህ [50,000] በላይ የሚሆኑ ልጆቻቸው መነኮሳት በዝማሬ ወጥተዋል::
† ከቅዱሳን አባቶቻችን የስደት በረከት ፈጣሪ አይለየን::
🕊 † አርባ ሐራ ሰማይ † 🕊
† አርብዐ ሐራ ሰማይ ማለት በዘመነ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ ሰማዕትነትን የተቀበሉ 40 ጭፍሮች ናቸው:: "ሐራ ሰማይ" የተባሉት በምድር ሲሠሩት የቆዩትን የውትድርና ሥራ ትተው የክርስቶስ [የሰማያዊው ንጉሥ] ጭፍራ ለመሆን በመብቃቸው ነው::
አርባው ባልንጀሮች ወጣትና ጐበዝ ክርስቲያኖች ነበሩ:: በእርግጥ እነርሱ ሰማዕትነት የተቀበሉበት ጊዜ ዘመነ ሰማዕታት አልነበረም:: ነገር ግን ሰማዕትነት የጊዜ : የቦታ : የሁኔታ : የእድሜ : የጾታ : የዘር . . . ልዩነት አያግደውምና እነዚህ ወጣቶች ለዚህ ክብር በቅተዋል::
ነገሩ እንደዚህ ነው :-
በ፫፻፴ [330] ዎቹ አካባቢ የዓለም ንጉሥ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ አንዱን መኮንኑን ወደ ቂሣርያ አካባቢ ይልከዋል:: የተላከው አካባቢውን ለማስተዳደር ሲሆን ቦታው ስብስጥያ [ሴባስቲ] ይሰኛል::
መኮንኑ ክርስቲያኖችን እንዲንከባከብ ጥብቅ ትዕዛዝ ከንጉሡ ቢሰጠውም ፍቅረ ጣዖት በልቡ የነበረበት ሰው ነውና ክርስቲያኖችን ይጨቁን : ያሰቃይ : ይገድል : አብያተ ክርስቲያናትን ያፈርስ ገባ::
በጊዜው ይህንን የተመለከቱት ፵ [40] ው ጭፍሮች በአንድነት መክረው መኮንኑን ገሠጹት:: ስመ ክርስቶስንም ሰበኩለት:: እርሱም በፈንታው ፵ [40] ውን አስሮ ብዙ አሰቃያቸው::
በመጨረሻ ግን ፵ [40] ውንም የበረዶ ግግር አስቆፍሮ: ከነ ሕይወታቸው እስከ አንገታቸው ቀብሮ : ለ፴፱ [39] ቀናት ያለ ምግብ በጽኑ ስቃይ አቆያቸው:: በ ፵ [40] ኛው ቀን ግን ከ ፵ [40] ው አንዱ "ይህን ሁሉ መከራ የምቀበል ለምኔ ነው?" ብሎ "አውጡኝ!" እያለ ጮኸ::
ክርስቶስን አስክደው ወደ ውሽባ ቤት [ሻወር ቤት] ሲያስገቡት ፈጥኖ ሞተ:: በነፍስም በሥጋም ተጐዳ:: ነገር ግን ከአረማውያን ወታደሮች አንዱ "እኔን አስገቡኝ" ስላለ እንደገና ፵ [40] ሆኑ::
በዚህች ዕለትም ፵ [40] ውን ጭን ጭናቸውን በመጅ እየሰበሩ ሲገድሏቸው ቅዱሳን መላእክት በአክሊል ከልለው : በዝማሬ አጅበው ወደ ገነት ወስደዋቸዋል:: ታላቁ ቅዱስ ባስልዮስም በጊዜው ነበርና ገድላቸውን ጽፎ ውዳሴ ደርሶላቸዋል:: ቤተ ክርስቲያናቸውንም አንጾ የካቲት ፲፮ [16] ቀን እንዲቀደስ አድርጉዋል::
ብጹዕ አባታችን አባ ሕርያቆስም በቅዳሴ ማርያም ድርሰቱ ላይ በቅዱሳኑ ላይ የሆነውን ነገርና ሥልጣነ እግዚአብሔርን እያደነቀ እንዲህ ሲል ተናግሯል::
"ኦ አውጻኢሁ ለዘእንተ ውስጥ:: [በውስጥ ያለውን የምታስወጣ]"
"ወአባኢሁ ለዘእንተ አፍአ:: [በውጪ ያለውንም የምታስገባ]"
"ወይእዜኒ ስማዕ አውያቶሙ ለሕዝብከ እለ ይጼውዑከ በጽድቅ:: [እንግዲህ በእውነት የሚጠሩህን የወገኖችህን ጩኸት /ልመና/ ስማ]" [ቅዳሴ ማርያም ቁ.፻፵፮ [146)]
ስለዚህ በውስጥ ያለን አንታበይ:: ያለንበት የእኛ አይደለምና:: እንዳንወድቅም እንጠንቀቅ:: ብዙዎቹ የቆሙ ሲመስላቸው ወድቀዋልና:: ያሉ ሲመስላቸውም ወጥተዋልና::
በውጪ ያለንም ተስፋ አንቁረጥ:: ወደ ሁዋላም አንበል:: ወደ ቤቱ ሊመልሰን : በክብሩ ማደሪያ ሊያኖረን የታመነ አምላክ አለንና::
† ቸሩ አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ ገብቶ ከመውጣት : አግኝቶ ከማጣት ይሠውረን:: ከሰማዕታቱ በረከትም አይለየን::
🕊
[ † መጋቢት ፲፫ [ 13 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ታላቁ ቅዱስ መቃርስ [የመነኮሳት ሁሉ አለቃ-ስደቱ]
፪. ቅዱስ መቃርዮስ እስክንድርያዊ
፫. ፵ [40] ቅዱሳን ሰማዕታት [ከሃገረ ስብስጥያ]
፬. ቅዱስ ዲዮናስዮስ [ጻድቅ ሊቀ ዻዻሳት]
[ † ወርኀዊ በዓላት ]
፩. እግዚአብሔር አብ
፪. ቅዱስ ሩፋኤል ሊቀ መላዕክት
፫. ፺፱ ["99] ኙ" ነገደ መላዕክት
፬. ቅዱስ አስከናፍር
፭. ፲፫ ["13ቱ"] ግኁሳን አባቶች
፮. ቅዱስ አርሳንዮስ ጠቢብ ገዳማዊ
፯. አቡነ ዘርዐ ቡሩክ
† " ስለ ጽድቅ የሚሰደዱ ብጹዓን ናቸው:: መንግስተ ሰማያት የእነርሱ ናትና:: ሲነቅፏችሁና ሲያሳድዷችሁ: በእኔም ምክንያት ክፉውን ሁሉ በውሸት ሲናገሩባችሁ ብጹዓን ናችሁ:: ዋጋችሁ በሰማያት ታላቅ ነውና ደስ ይበላችሁ:: ሐሴትንም አድርጉ:: ከእናንተ በፊት የነበሩትን ነቢያትን እንዲሁ አሳደዋቸዋልና:: " † [ማቴ.፭፥፲] (5:10)
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
💖 🕊 💖
†
🍒 [ ፍኖተ ሕይወት ! ] 🍒
🕊 💖 🕊
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን !
🕊
[ ብዙዎች ግን ጸንተው ቆመዋል ! ]
------------------------------------------------
“ ለተሰናከሉ ሰዎች በዚያች ቀን የሚጠብቃቸው ግን ምንድን ነው ?
እጅግ ተጽደልድለው ስለሚያበሩ ሊነገሩ የሚችሉ አይደሉም፡፡ በተቃራኒው የንጽህና ልብስ የተጎናጸፉና አሁን ወደ ሐፍረት የወረዱ ፥ እነዚሀን በእኛ ፊት ታመጣለህ [ታነሣለህ]፡፡
የነጻ ወርቅን አላየህምን? የተፈተነ እርሳስን አላየህምን? ገለባ ከስንዴ ፍሬ ተለይቶስ? ተኵላዎች ከበጎች ተለይተውስ? በሐሰት የሚኖሩት በእውነት የንጽህና የቅድስና ሕይወት ከሚኖሩት ተለይተውስ? ስለዚህ የመጀመሪያዎቹን ጥፋት ስታይ ፥ የኋለኞቹን በጎ ዕድል ደግሞ አስብ፡፡
ጥቂቶች ተሰናክለዋል፡፡ ብዙዎች ግን ጸንተው ቆመዋል፡፡ ብዙ መከራን በሚያደርሱባቸው ኃይል ወይም በጊዜያቱ መክበድ ተስፋ ባለመቁረጥ ለራሳቸው ብዙ ሽልማትን ተቀብለዋል፡፡
የተሰናከሉት ሰዎች ለራሳቸው ያስቡ፡፡ ሠለስቱ ደቂቅ ከካህናት ፣ ከቤተ መቅደስ ፣ ከምሥዋቱና ሕጉ ከሚያዝዛቸው ከሌሎች ነገሮች ርቀው ተሰደዱ፡፡ በባዕድ አገር ውስጥ ተጣሉ፡፡ ሕጉን ግን እጅግ በጥንቃቄ ፈጸሙ። ዳዊትና ሌሎችም እንደዚሁ ! የተወሰኑት ወደ ምርኮ ተወሰዱ ፤ በፍጹምም አልተጎዱም፡፡ ሌሎች ግን በቤታቸው መኖር ቻሉ ፤ ከአገራቸው የሚገኘውን ጥቅምም ኹሉ አገኙ፡፡ ዳሩ ግን ተሰናከሉ ፤ ተወቀሱም፡፡ "
🕊
[ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ]
🕊 💖 🕊
🕊
[ † መጋቢት ፲፪ [ 12 ] † ]
🕊 💖 🕊
ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ወደ ጠንቋዩ በለዓም ተልኮ አህያዋን በሰው አንደበት አናግሮ የእስራኤልን እርግማን ወደ በረከት የመለሰበት ዕለት ነው፡፡
በለዓም እስራኤልን ይረግማቸው ዘንድ ባላቅ በጠራው ጊዜ ፤ በጐዳናም በፊቱ ቅዱስ ሚካኤል ቆሞ ስለተገለጠ አስደነገጠው ፤ አህያው በሰው አንደበት እስከተናገረች ድረስ ፤ መርገሙንም ወደ በረከት መለሰው።
" እግዚአብሔርም የበለዓምን ዓይኖች ከፈተ ፤ የእግዚአብሔርን መልአክ በመንገድ ላይ ቆሞ የተመዘዘም ሰይፍ በእጁ ይዞ አየ ፤ ሰገደም ፥ በግምባሩም ወደቀ።" [ዘኁ.፳፪፥፴፩]
የቅዱስ ሚካኤል በአማላጅነቱ ለዘላለሙ ይጠብቀን አሜን።
† † †
💖 🕊 💖
💛
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
🕊 ዐቢይ ጾም [ ጾመ እግዚእ ] 🕊
▷ " ራስን መመርመርና መጸጸት "
[ " በቅዱሳን አባቶቻችን አስተምህሮ ... ! " ]
[ 🕊 ]
----------------------------------------------
" በደሌን እናገራለሁና ፥ ስለ ኃጢአቴም እተክዛለሁ።"
[ መዝ . ፴፰ ፥ ፲፰ ]
🕊 💖 🕊
+++ዕንቁውን ወይስ ነፍስህን?+++
ሳር የለበሰ ትልቅ ሜዳ ላይ ጋደም ብሎ የነበረ አንድ ሰው ፤ አፍንጫው የሆነ የተቃጠለ ነገር እንዳለ ይነግረዋል። ዐይኖቹን ወደ ሰማይ አቅንቶ ሲመለከት ደመናውን ጢስ ጉም ሠርቶ ሸፍኖታል። ደንግጦ ዙሪያውን ሲመለከት ፤ ሜዳው በሙሉ በሰደድ እሳት ተከብቧል ፥ እሳቱም በፍጥነት እርሱ ወዳለበት አቅጣጫ ሲመጣ ተመለከተ። ከፊት ለፊቱ እሳቱ ያላገኘው ያልደረሰበት ቦታ ተመለከተ ፤ በዚሁ አቅጣጫ በርቀት ሲያማትር ይህ መንገድ ከፊት ለፊቱ ሰፊ የውኃ አካል ጋር የሚያደርስ ሆኖ አገኘው። እንደ ዕድል ሆኖ ከውኃው ዳር አንደ ጀልባ ተመለከተ። የጀልባዋ ካፒቴን (ሊቀ ሐመር) ጀልባዋን ያሰረበትን ገመድ ከወደቡ እየፈታ በሜዳው መካከል ያለውን ሰው በእጆቹ ወደ እርሱ እንዲመጣ ይጠቁመው ነበር።
በሜዳው መካከል ያለው ሰው ከባድ ነፋስ ሲነፍስ ይሰማው ነበር። እሳቱም ወደ እርሱ እየከነፈ ሲመጣ አየ። በዚህ ጭንቅ ውስጥ ዘወር ብሎ ጋደም ብሎ ወደነበረበት አካባቢ ሲያይ የበዛው አካሉ መሬት ውስጥ የተቀበረ አንድ ትልቅ ቋጥኝ ተመለከተ። ቋጥኙ ላይ ባልተጠበቀ መልኩ አንድ ቀዳዳ ትኩረቱን ሳበው ፥ ተጠግቶ ሲመለከት በቀዳዳዋ በኩል አንድ ክንድ ያህል ወደ ውስጥ ገብቶ የወይን ፍሬ የምታህል ዕንቁ ተመለከተ። በጣም ተገርሞ ወደ ጀልባዋ ቀና ብሎ ሲያይ ካፒቴኑ በፍጥነት እንዲመጣ ምልክት በመሥጠት ቆሞ እየጠበቀው መሆኑን አረጋገጠ።
አንዳች ጊዜ ሳያጠፋ እጆቹን እንደምንም በቀዳዳዋ ከትቶ ዕንቁዋን አጥብቆ ያዘ። ከዚያም ሊያወጣ ታገለ ፤ በእጆቹ ዕንቁውን እንደያዘ በገባባት ቀዳዳ ተመልሶ መውጣት አልቻለም። ብዙ ሲታገል ቆዳው ተላጠ ድንጋዩ ሥጋውን ፋቀው ተረተረው ፤ ሆኖም እጁን ዕንቁውን እንደጨበጠ ማውጣት ግን አልተቻለውም።
እሳቱ ወደ ሰውየው እየቀረበ መጣ ፤ ወላፈኑ ጀርባውን ይገርፈው ጀመረ። እሳቱ ሲያቃጥለው ያለቅስና ይጮኸ ነበር ፤ ሆኖም ይኼን ዕንቁ ቢያገኝ የሚኖረውን የድሎት ሕይወት እያሰበ ፤ ዕንቁውን በተለያየ ገጹ እየገለባበጠ ሊያወጣው መታገሉን ቀጠለ። በዚህ ሰዓት ከወደቡ ያለው ካፒቴን የጀልባዋን ገመድ ሙሉ በሙሉ ፈትቶ ፤ ጀልባዋን እያንቀሳቀሰ ፥ ሰውየው የያዘውን ትቶ ነፍሱን እንዲያድን ጮኾ ይጠራው ነበር።
+++
ሰውየው እኛ ነን ፤ እሳቱ ደግሞ የሞት ምሳሌ ነው ፤ ዕንቁው ደግሞ አስረው የያዙን የኃጢአት ምኞቶቻችን እና ምድራዊ ፍላጎቶቻችን ናቸው። እሳት ያላነደደው መንገድ ወደ መዳን የሚመሩን ጌታችን የሠጠን ትእዛዛት ናቸው። ጀልባዋ የቤተክርስቲያን ወይም የገነት ወይም ከእግዚአብሔር ጋር ያለን አንድነት ምሳሌ ስትሆን ፥ ካፒቴኑ ደግሞ የጠባቂ መልአካችን ወይም አምላክ የሠጠን ሕሊና ምሳሌ ነው። አስረው የሚይዙንን የኃጢአት ምኞቶቻችን እና ምድራዊ ፍላጎቶቻችን ይዘን ወደ ገነት ልንገባ አንችልም ፤ ወደ መዳን ጀልባ ለመድረስ እነዚህን የኃጢአት ፍላጎቶች በመጣል ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሠጠን መንገድ ልንጓዝ ይገባል።
የእኛ መዝገባችን ሀብታችን በምድራዊ ነገር ላይ ብቻ የተመሠረተ ሲሆን ልባችንም በምድር የተቀበረ ይሆናል።
«መዝገብህ ባለበት ልብህ ደግሞ በዚያ ይሆናልና።»
(ማቴ. 6፥21)
+++
በጎውን እንዳናደርግ ከታሰርንባቸው የኃጢአት ምኞቶች የምንለይበት የበረከት ጾም ያድርግልን!
🕊
[ † እንኳን ለጻድቁ አቡነ አሌፍ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ]
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †
🕊 † አባ አሌፍ † 🕊
† ጻድቁ ገድላቸውን የፈጸሙት በኢትዮዽያ ቢሆንም ሃገረ ሙላዳቸው የጥንቱ የሮም ግዛት የሆነችው ታናሽ እስያ ናት:: አባ አሌፍ ከዘጠኙ [ተስዓቱ] ቅዱሳን አንዱ ናቸው:: ዘጠኙ ቅዱሳን ተወልደው ያደጉት ምንም በአንድ የሮም ግዛት ሥር ቢሆንም መነሻ ቦታቸው ግን የተለያየ ነው::
ሁሉንም አንድ ያደረጋቸው መንፈስ ቅዱስ በኪነ ጥበቡ ነው:: በምክንያት ደረጃ እንግለጸው ከተባለ ደግሞ የአንድነታቸው ምሥጢር :-
፩. የቀናች ሃይማኖታቸው ተዋሕዶ::
፪. ዓላማ [የእግዚአብሔር መንግስት] እና
፫. ገዳማዊ ሕይወት ነው::
አባ አሌፍን ጨምሮ ሁሉም ቅዱሳን ዘራቸው ከቤተ መንግስት ነው:: እነርሱ ግን ምድራዊውን ክብር ንቀው ሰማያዊውን ክብር ገንዘብ ማድረግን መርጠዋል:: አስቀድመው ቅዱሳት መጻሕፍትን ያጠኑት አበው በተለያየ ጊዜ እየመነኑ ከሮም ግዛት ወደ ግብጽ በርሃዎች ወርደዋል::
በምናኔ ቅድሚያውን አባ ዸንጠሌዎንና አቡነ አረጋዊ ይይዛሉ:: ዘመኑ የተዋሕዶ አማኞች የሚሰደዱበት ፭ [5] ኛው መቶ ክ/ዘመን ነበርና እምነትን ላለመለወጥ ዘጠኙ ቅዱሳን ስደትን መረጡ::
በወቅቱ ደግሞ ለስደት መጠለያ የምትሆንና ከኢትዮዽያ የተሻለች ሃገር አልነበረችም:: ስለዚህም በ፬፻፸ [470] ዎቹ ዓ/ም አልዓሜዳ በኢትዮዽያ ነግሦ ሳለ ቅዱሳኑ በአረጋዊ መሪነት መጡ::
ንጉሡም ሲጀመር የእግዚአብሔር እንግዳ ስለሆኑ: ሲቀጥል ደግሞ ቅድስናቸውን ተመልክቶ መልካም አቀባበልን አደረገላቸው:: ማረፊያ ትሆናቸውም ዘንድ አክሱም ውስጥ አንዲት ቦታን ወስኖ ሰጣቸው:: ይህች ቦታ ቤተ ቀጢን ትባላለች::
አባ አሌፍና ፰ [8] ቱ ቅዱሳን ወደ ሃገራችን እንደ ገቡ የመጀመሪያ ሥራቸው ቋንቋን መማር ነበር::
ልሳነ ግዕዝን በወጉ ተምረው እዛው አክሱም አካባቢ ሥራቸውን አንድ አሉ:: በወቅቱ በአቡነ ሰላማ: በአብርሃ ወአጽብሐና በአቡነ ሙሴ ቀዳማዊ የተቀጣጠለው ክርስትና በተወሰነ መንገድ ተቀዛቅዞ ነበርና እነ አባ አሌፍ እንደ ገና አቀጣጠሉት::
ሕዝቡን በራሱ ልሳን ለክርስትና ይነቃቃ ዘንድ ሰበኩት:: የካደውን እየመለሱ: የቀዘቀዘውን እያሟሟቁ ለዓመታት ወንጌልን ሰበኩ:: ቀጣዩ ሥራቸው ደግሞ መጻሕፍትን መተርጐም ሆነ::
ከሃገራቸው ያመጧቸውን ቅዱሳት መጻሕፍት ተከፋፍለው ወደ ግዕዝ ልሳን ተረጐሟቸው:: በዚህም ለሃገራችን ትልቁን ውለታ ዋሉ:: ይህ ሁሉ ሲሆን እነ አባ አሌፍ የሚመገቡትም ሆነ የሚጸልዩት በማሕበር ነበር:: በመካከላቸውም ፍጹም ፍቅር ነበር:: ጸጋ እግዚአብሔር አልተለያቸውም::
† የነ አባ አሌፍ ቀጣዩ ተግባራቸው ደግሞ ገዳማዊ ሕይወትን ማስፋፋት ሆነ:: ይህንን ለማድረግ ግን የግድ መለያየት አስፈለጋቸው:: እያንዳንዱም መንፈስ ቅዱስ ወደ መራው ቦታ ሔደ::
† ዸንጠሌዎን በጾማዕት::
† ገሪማ በመደራ::
† ሊቃኖስ በቆናጽል::
† አረጋዊ በዳሞ::
† ጽሕማ በጸድያ::
† ሌሎችም በሌላ ቦታ ገዳማትን መሠረቱ::
† አባ ይምዓታ ደግሞ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ምርጫቸው ገርዓልታ [እዛው ትግራይ] ሆነ::
አባ አሌፍ የተወለዱት አውሎግሶንና አትናስያ ከተባሉ ደጋግ ወላጆች ቂሳርያ ውስጥ በ ፭ [5] ኛው መቶ ክ/ዘመን ነው:: ጻድቁ በሕጻንነታቸው ወደ አባ እንጦንስ ገዳም ገብተው ከዓመታት ተጋድሎ በሁዋላ ከ ፰ [8] ቱ ጉዋደኞቻቸው ጋር ወደ ኢትዮዽያ የመጡ ሲሆን ከተስዓቱ /፱ [9] ኙ/ ቅዱሳን አንዱ ናቸው::
በዐፄ አልዓሜዳ ዘመን አክሱም አካባቢ [ቤተ ቀጢን] የሃገራችንን ቋንቋ አጥንተው ቅዱሳት መጻሕፍትን ተርጉመዋል:: ለሕዝቡም የወንጌልን የምሥራች ሠብከዋል::
ከዚያም ገዳም መሥርተው : ፭፻ [500] መነካሳትን ሰብስበው ለ ፸ [70] ዓመታት በቅድስና ኑረዋል:: ለዘጠኙ ቅዱሳን ሁሉ ስም ያወጡት የዘመኑ ሰዎች ቀድመው ወደ አክሱም ስለ ገቡ ጻድቁን "አሌፍ" ብለዋቸዋል:: በዕብራይስጥኛ "አንደኛ" ማለት ነው:: ጻድቁ ከፈጣሪያቸው የምሕረት ቃል ኪዳን ተቀብለው በዚሕች ቀን አርፈዋል::
† አምላከ አበው ቅዱሳን በምልጃቸው ይማረን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን::
🕊
[ † መጋቢት ፲፩ [ 11 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. አባ አሌፍ ጻድቅ [ከተስዓቱ ቅዱሳን]
፪. ቅዱስ ቴዎቄጤኖስ ሰማዕት
፫. ቅዱስ ባስሊዖስ [ዻዻስና ሰማዕት]
፬. አባ ኤፍሬም ሰማዕት
፭. አባ ኤልያስ ሰማዕት
[ † ወርሐዊ በዓላት ]
፩. ቅዱስ ያሬድ ካህን
፪. ቅዱስ ገላውዴዎስ ሰማዕት
፫. ቅዱስ ፋሲለደስ ሰማዕት
፬. ብፁዐን ኢያቄም እና ሐና
፭. አቡነ ሐራ ድንግል ጻድቅ
† " ከእናንተ አንዱ ከባልንጀራው ጋር ሙግት ቢኖረው በቅዱሳን ፊት በመፋረድ ፋንታ በዓመፀኞች ፊት ሊፋረድ ይደፍራልን? ቅዱሳን በዓለም ላይ እንዲፈርዱ አታውቁምን? . . . የትዳር ጉዳይ ይቅርና በመላእክት እንኩዋ እንድንፈርድ አታውቁምን ? " † [፩ቆሮ.፮፥፩-፫] (6:1-3)
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
💖 🕊 💖
†
[ የትሕርምት ሕይወት ! ]
🕊 💖 🕊
[ ከፍቅር ኹሉ ስለሚበልጠው የእግዚአብሔር ፍቅር ! ]
------------------------------------------------
በሰማያት ያለው አባታችሁማ !
🕊
" አንዲት ሴት የገዛ ልጅዋን እንደማትረሳ ፥ እግዚአብሔርም የሰው ልጆችን ከቶ እንደማይረሳቸው ምሳሌ ሲያቀርብ ፦ የእግዚአብሔር ፍቅር ፥ እናት ከማኅፀንዋ ለተገኘ ልጅዋ ከሚኖራት ፍቅር ጋር ተነጻጻሪ እንደ ኾነ አድርገህ እንዳታስበው ፥ ይልቁንስ ይህ [የእናት] ፍቅር ከሌሎች እጅግ የተለየ እንደ ኾነ ፣ የእግዚአብሔር ፍቅር ግን ከዚህ ፍጹም ታላቅ እንደ ኾነ ያስረዳ ዘንድ ሽቶ ጨምሮ ፦
“ ሴት ይህን ብትረሳ ፥ እኔ ግን አንቺን አልረሳሽም” አለ [ኢሳ.፵፱፥፲፭]፡፡ እንግዲህ ከእናታዊ ፍቅር እንዴት ልቆ እንደ ኼደ ታስተውላለህን?
የእግዚአብሔር ፍቅር እናትና አባት ለልጆቻቸው ከሚኖራቸው ፍቅር ፍጹም የሚልቅ እንደ ኾነ ትረዳ ዘንድም ነቢዩ ፦ “አባት ለልጆቹ እንደሚራራ ፥ እንዲሁ እግዚአብሔር ለሚፈሩት ይራራላቸዋል” አለ [መዝ.፻፪፥፲፪]፡፡ ዳግመኛም ነቢዩ ይህን [የርኅራኄ] ምሳሌ የተጠቀመው ይህ [የወላጅ ርኅራኄ] ከሌሎች [አንድ ሰው ልጁ ላልኾነ ለሌላ ሰው ከሚያሳየው ርኅራኄ] አንጻር ለየት ያለ ነገር በውስጡ እንዳለው ስለሚያውቅ ነው፡፡
የነቢያትና የፍጥረታት ኹሉ ጌታ የሚኾን እርሱ ብርሃን ከጨለማ ፣ ክፋትም ከበጎነት የሚርቀውን ያህል የእግዚአብሔር ፍቅር ከወላጅ ፍቅር እጅግ የላቀ እንደ ኾነ ግልፅ አድርጎታል፡፡ ምን እንዳለ አድምጥ ፦
“ ከእናንተ ልጁ ዳቦ ቢለምነው ድንጋይ የሚሰጠው ማን ነው? ወይስ ዓሣ ቢለምነው እባብ ይሰጠዋልን? እንግዲህ እናንተ ክፉዎች ስትኾኑ ለልጆቻችሁ መልካም ስጦታ መስጠትን ካወቃችሁ ፥ በሰማያት ያለው አባታችሁማ ለሚለምኑት መልካሙን ነገር እንዴት አብልጦ ይሰጣቸው ይኾን ? ” [ማቴ.፯፥፲፩]፡፡
በክፋትና በመልካምነት መካከል ሰፊ ልዩነት እንዳለ ኹሉ ፥ በእግዚአብሔር መልካምነትና በአባቶች ፍቅር መካከል ያለው ልዩነት ደግሞ እጅግ ሰፊ እንደ ኾነ ሲያሳይ ነው፡፡ "
🕊
[ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ]
🕊 💖 🕊
†
🕊
🕊 † መስቀል † 🕊
[ መጋቢት ፲ [ 10 ] ]
" መስቀል ሰይጣንን የሚያጠፋ ምሳር ነው ፤ የአጋንንትንም ራሶች የሚቆርጥ ሰይፍ ነው ፤ መስቀል ርኩሳን መናፍስትን የሚወጋቸው የእሳት ዘገር ነው ፤ የአመስቴማውያንንም ሠራዊት የሚመታ የመብረቅ ጦር ነው፡፡
መስቀል ማኅተመ ሥላሴ የሌለው ሰው ወደ እርሱ ሊቀርበው የማይቻለው አምባ መጠጊያ ነው፡፡
መስቀል ከግራም ከቀኝም ለሚመጣ ጠላት የጽድቅ ጋሻ ነው፡፡ መስቀል የጦር ውጋት ሊቀድደው ፣ የቀስትና የዘንግም ጫፍ ሊበሳው የማይችል የሃይማኖት ጥሩር ነው፡፡
መስቀል አማሌቃውያንን ለመዋጋት በራፊድ በረሐ በተዘረጋው በሙሴ እጅ አምሳል የተሠራ ነው፡፡
መስቀል በሙሴ እጅ ወደ ውስጥ በተጨመረ ጊዜ መራራውን ውኃ በሱር በረሐ ያጣፈጠ ነው፡፡
መስቀል የቅድስናና የንጽሕና ማኅተም ነው፡፡ "
[ ውዳሴ መስቀል ]
🕊 💖 🕊
💠መስቀል💠
➕➕➕ ነደ እሳትን የተሸከመ የኪሩቤልም ባልንጀራ የሆነ እንደ ድንግል ማርያም ስም አራት ፊደል ያለው ነበልባላዊ የእሳት መንበር።
✣✣✣ አዳምን ከሞት ያወጣው የሕይወት ዛፍ።
✥✥✥ የኃጢአትን ቀላይ የገታ መርከብ።
❖❖❖ ባሕረ እሳትን ያሻገረ የድኅነት ትርክዛ።
✞✟✟ነፍሳት የሕይወት እንጀራን የጠገቡበት ማዕድ!
✟✟✟ክርስቶስና ቤተክረስተያን የተሞሸሩበት የሠርግ ቦታ።
✝✝✝ምእመናን የተጸነሱበት መካነ ክርስትና።
🔸🔸🔸 ቤተክርስቲያን የጸናችበት መሠረተ ሃይማኖት።
🔹🔹🔹የፍስሐ ኩሉዓለም ክርስቶስ ደም የፈለቀበት ሙሐዘ ትፍሥሕት!
🔶🔶🔶 ከሕይወት ውኃ ከክርስቶስ የተተከለ ሁል ጊዜ የሚያፈራ የሕይወት ዛፍ።
🔷🔷🔷 የንጉሥ ልጅ በአባቱ ኅልቀተ ወርቅ ማኅተም እንዲመካ፥ የንጉሠ ነገሥት ክርስቶስ ልጆች የምንለይበት የምንመካበት ትእምርተ ድኂን።
🔹✔ የጨለማውን አበጋዞችን ድቅድቅ የምንገፍበት
ጸዳለ ኩሉ ዓለም።
🔹🔹🔹✔ የሚወረወረውን ፍላጻ የምንሰብርበት ልብሰ ሃይማኖት ጥሩር።
✟✟✟✔ጦር ከነቀነቀ ጋሻ ከታጠቀ ከቀን ወራሪ ከሌሊት ሰባሪ የምንመክትበት ንዋየ ሐቅል።
🔷✅✅✅ ቢዋጉ ማሸነፊያ ቢሸሹ መጠጊያ ጸወነ ሥጋ ወነፍስ ወልታ ጽድቅ።
መስቀል መልዕልተ ለኩሉ ነገር
ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
ውብ አሁን
በልብሰ መንግስቱም አጐናፀፈው ታላቀወ ክብርንም አከበረው እጅግም ደስ አለው ከሰራዊቱ ጋር። የዚህም መስቀል ሁለተኛ የተገለጠበትና የተገኘበት በዚች ቀን በመጋቢት አስር ነው። ከዚህ በኃላ ንጉሱ የከበረ እፀ መስቀልን ተሸክሞ ወደ ቁስጥንጥንያ ከተማ ወሰደው።
መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ካረገ ከዓመታት በሁዋላ አይሁድ በአንድ ነገር ተቸገሩ:: የክርስቶስን ሐዋርያት እያሳደዱ ቢገድሉም ከመስቀሉና ሥጋ ክርስቶስ አርፎበት ከነበረው ጐልጐታ ላይ የሚደረገውን ተአምር ግን መግታት አልተቻላቸውም::
መቼም ለተንኮል አያርፉምና ቅዱስ መስቀሉን ሽፍቶቹ ከተሰቀሉባቸው ጋር ደርበው አርቀው ቀበሩት:: አካባቢው የጉድፍ መጣያ እንዲሆንም አዋጅ ነገሩ:: ለክፋት ሲሆን ተባባሪው ብዙ ነውና ለ፫፻ [300] ዓመታት ያህል ቆሻሻ ቢጥሉበት
ተራራ ሆነ::
ከዚህ ሁሉ ነገር በሁዋላ እናታችን ቅድስት እሌኒ [ሔለና] በመንፈስ ቅዱስ አነሳሽነት: በቅዱስ ኪራኮስ መሪነት: በቅዱስ ሚካኤል ረዳትነት ደመራ አስደምራ: እጣን አጢሳ መካነ መስቀሉን አገኘች::
መስከረም ፲፯ [17] ቀን የተጀመረው ቁፋሮ መጋቢት ፲ [10] ቀን ተጠናቆ: ንጹሕ መስቀሉ ወጥቶ ብርሃን በርቷል: ሙታን ተነስተዋል:: ከ፲ [10] ዓመት በሁዋላም የመስቀሉ ቤተ መቅደስ
ታንጾ መስከረም ፲፯ [17] ቀን ተቀድሷል::
ይህ ቅዱስ ዕፀ መስቀልም በደጉ አፄ ዳዊት ዘመን ወደ ሃገራችን መጥቶ: በጻድቁ አፄ ዘርዓ ያዕቆብ አማካኝነት በደብረ ከርቤ [ግሸን ማርያም] ተለብጦ ተቀምጧል::
አምላከ ቅዱሳን በኃይለ መስቀሉ: በሞገሰ መስቀሉ ይጠብቀን:: ከበረከቱ አሳትፎ በዓሉን የሰላም ያድርግልን::
🕊
[ † መጋቢት ፲ [10] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ቅዱስ ዕፀ መስቀል
፪. ቅድስት ዕሌኒ ንግሥት
፫. ቅዱስ ኪራኮስ አረጋዊ
፬. ቅዱስ መቃርስ ዘኢየሩሳሌም
[ † ወርሐዊ በዓላት ]
፩. ቅዱስ ናትናኤል ሐዋርያ
፪. ቅዱስ ኒቆላዎስ ዘሃገረ ሜራ
፫. ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ ጻድቅ ንጉሥ
፬. አቡነ መልክዐ ክርስቶስ
፭. ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ [ወልደ እልፍዮስ]
" የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት : ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነውና . . . መቼም አይሁድ ምልክትን ይለምናሉ:: የግሪክ ሰዎችም ጥበብን ይሻሉ:: እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን:: " [፩ቆሮ.፩፥፲፰-፳፫] (1:18-23)
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
💖 🕊 💖
💛
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
🕊 ዐቢይ ጾም [ ጾመ እግዚእ ] 🕊
▷ " ስ ለ ፈ ቃ ድ "
[ " በአቡነ አትናቴዎስ ዘእስክንድር ... ! " ]
[ 🕊 ]
----------------------------------------------------
" በውስጡ ሰውነቴ በእግዚአብሔር ሕግ ደስ ይለኛልና ፥ ነገር ግን በብልቶቼ ከአእምሮዬ ሕግ ጋር የሚዋጋውንና በብልቶቼ ባለ በኃጢአት ሕግ የሚማርከኝን ሌላ ሕግ አያለሁ።
እኔ ምንኛ ጎስቋላ ሰው ነኝ ! ለዚህ ሞት ከተሰጠ ሰውነት ማን ያድነኛል ? " [ ሮሜ.፯፥፳፪ ]
🕊 💖 🕊
ሰኞ - መጋቢት 09 2016 ዓም
ማርቆስ 5-10
ሰላም ለሁላችሁ ይሁን! በዛሬው የዐቢይ ጾም ንባባችን የማርቆስ ወንጌልን ከምዕራፍ 5-10 ድረስ እናነባለን።
ከንባብ በፊት የሚደረግ ጸሎት፡ “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፤ የአንተን ቃላት እሰማ እና እረዳ ዘንድ፥ እንዲያውም ፈቃድህን ለመፈጸም እበቃ ዘንድ የልቤን ጆሮዎች እና ዓይኖች ክፈትልኝ።” (ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ)
በዛሬው ንባባችን ላይ ጌታችን በናዝሬት ስለማስተማሩ፥ ሐዋርያትን ስለ መላኩ፥ ስለ ሄሮድስ እና ስለ መጥምቁ ዮሐንስ፥ ሐዋርያት ወደ ጌታ ስለመመለሳቸው፥ ሁለቱን ዓሣዎችና አምስቱን እንጀራ ስለ መባረኩ፥ በባህር ላይ ስለመሄዱ፥ በጌንሴሬጥ ተዓምራት ስለ ማድረጉ፥ ፈሪሳውያንን ስለ መገሰጹ፥ ስለ ሲሮኒፊቃዊቷ ሴት፥ ሁለቱን ዓሣዎችና ሰባቱን እንጀራ ስለማበርከቱ፥ ከሰማይ ምልክት ስለሚሹ ሰዎች፥ ስለ ፈሪሳውያን እርሾ፥ በቤተሳይዳ ስለፈጸመው ፈውስ፥ በቂሣርያ ሐዋርያትን ስለ መጠየቁ እና ስለ መከራው መናገሩን እናነባለን። በተጨማሪም፥ በደብረ ታቦር ክብሩን ስለ መግለጡ፥ ከደቀ መዛሙርቱ ስለ ቀረበው ጥያቄ፥ ጋኔን ይጥለው የነበረውን ሰው እንደ ፈወሰ፥ ስለ መከራው እና ሞቱ፥ አጋንንት ስለሚያወጣው ሰው፥ ስለ ፍቅርና ስለ ጋብቻ ስለማስተማሩ፥ ስለ ሕጻናት እና ስለ ባለጸጋው፥ የሚከተሉት ስለሚያገኙት ዋጋ፥ ስለ ዘብዴዎስ ልጆች ጥያቄ እና ስለ ዕውሩ ስለ ጤሜዎስ ልጅ መዳንም ተጽፎ እናገኛለን።
ለዛሬ የክለሳ ጥያቄዎች አይኖሩንም።
መልካም ንባብ!
/channel/OrthodoxTewahdoBooks
/channel/c/2014228571/1
† † †
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
[ እናታችን ቤተክርስቲያን ! ]
" መሓሪው አምላክ በዚህ ዓለምም ሆነ በሚመጣው ዓለም ደስታችን ፍጹም ይሆንልን ዘንድ ይፈልጋል፡፡ ለዚህም ሲል ቅድስት ቤተ ክርስቲያኑን በደሙ መሠረታት፡፡ ስለዚህ ከኃጢአት ሥርየት የምናገኝበትን ጸጋ ታጎናጽፈናለች፡፡ ትቀድሰናለች፡፡ ታስታርቀናለች፡፡ ሰማያዊ በረከትንም ታድለናለች፡፡
የቅድስት ቤተ ክርስቲያን በሮች ዘወትር የተከፈቱ ናቸውና ወደ እርስዋ እንፋጠን፡፡ ቤተ ክርስቲያንን ከነገርናት ሸክማችንን ሁሉ ትሸከምልናለች፡፡ ልባችን በደስታና በቅድስና እንዲመላ ታደርጋለች፡፡ "
[ ቅዱስ ቄርሎስ ዘእስክንድርያ ]
-----------------------------------------
" ምንም እንኳ የማልጠቅምና ሀጢያተኛ ብሆንም ያለማቋረጥ ደጆችህን አንኳኳለሁ፡፡ "
[ ቅዱስ ኤፍሬም ሶሪያዊ ]
🕊 💖 🕊
እሑድ - መጋቢት 08 2016 ዓም
ማርቆስ 1-5
ሰላም ለሁላችሁ ይሁን! በዛሬው የዐቢይ ጾም ንባባችን የማርቆስ ወንጌልን ከምዕራፍ 1-5 ድረስ እናነባለን።
ከንባብ በፊት የሚደረግ ጸሎት፡ “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፤ የአንተን ቃላት እሰማ እና እረዳ ዘንድ፥ እንዲያውም ፈቃድህን ለመፈጸም እበቃ ዘንድ የልቤን ጆሮዎች እና ዓይኖች ክፈትልኝ።” (ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ)
በዛሬው ንባባችን ላይ ስለ መጥምቁ ዮሐንስ ስብከት፥ ስለ ጌታችን ጥምቀት፥ ጌታችን ስለ ማስተማሩ፥ በምኩራብ ስለ ማስተማሩ፥ ጋኔን የያዛቸውን እና የታመሙትን ስለመፈወሱ፥ ስለ ጾም እና ስለ ሰንበት ስለቀረቡት ጥያቄዎች፥ እጁ ስለ ደረቀችው ሰው፥ ሐዋርያትን ስለ መምረጡ እና ፈቃዱን ስለሚያደርጉ ሰዎች እናነባለን። በተጨማሪም፥ ስለ ዘሩ ምሳሌ፥ ስለ ዘርና ስለ መከር ምሳሌ፥ ስለ ሰናፍጭ ቅንጣት ምሳሌ፥ ባሕሩንና ነፋሱን ስለ መገሰጹ፥ ሌጌዎን ያደረበትን በሽተኛ እንደ ፈወሰው፥ ስለ ምኩራብ ሹም፥ ደም ይፈሳት ስለነበረችው ሴት እና ስለ ምኩራቡ ሹም ልጅም ተጽፎ ይገኛል።
*የክለሳ ጥያቄዎች*
1) ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቁ ስለ ጌታችን ሲሰብክ ምን እያለ ነበር? በእኛ ሕይወት ውስጥስ ስለ ክርስቶስ ምን ብለን እንድንመሰክር ያስተምረናል?
2) ጌታችን ሐዋርያትን በመረጠ ጊዜ ምን ትተው ተከተሉት? እናንተስ፥ ስለ ጌታ ብላችሁ በሕይወታችሁ ውስጥ የተዋችሁት ነገር አለ?
3) በማርቆስ 2 ላይ ጓደኞቹ ይዘውት ስለመጡት ሽባ ተጽፏል? ያደረጉት ምንድር ነበር? ጌታችንስ ስለ እምነታቸው ምን ብሎ ተናገረ?
4) ጌታችን እጁ የሰለለችውን ሰው የፈወሰው በምን ቀን ነበር?
5) ጌታችን ያስተማረውን የዘሩን ምሳሌ በአጭሩ ግለጹ። ይህ ቅዱሱን ቃል ስለማንበብ እና የእግዚአብሔርን ቃል ስለመስማት ምን ያስተምረናል?
6) ጌታችን ደም ሲፈሳት ለነበረችው ሴት ምን ተናገራት?
7) ጌታችን “ልጅህ ሞታለች” ተብሎ መርዶ ለተነገረው የምኵራብ ሹም ምን አለው? የጌታችንን ንግግር ከሕይወታችሁ ጋር አዛምዳችሁ እንዴት መተግበር እንዳለባችሁ ጻፉ።
መልካም ንባብ!
/channel/OrthodoxTewahdoBooks
/channel/c/2014228571/1
🕊 💖 🕊
[ 🕊 ቅድስት 🕊 ]
💖
[ ቅድስና ምንድነው ? ]
ቅድስና ማለት ቀደስ ባረከ ፤ ለየ ፤ አከበረ ፤ አመሰገነ ፤ አነጻ ፤ ሰውነቱን ከርኩሰት ልቡን ከትዕቢት አራቀ ከሚለው ከግዕዝ ሥርወ ግሥ የተገኘ ኀይለ ቃል ሲሆን ቅድስና ማለት መለየት ፤ መክበር ፤ መመስገን ፣ መንጻትና መጽናት ማለት ነው፡፡
ሰውም ሆነ ሌላውም ነገር ቅዱስ የሚሆነው የእግዚአብሔር ስለሚሆን ብቻ ነው ፤ ሰው ሃይማኖት ይዞ በሥነ ምግባር እየተቀደሰ ሊሄድ ይችላል ፤ [ ዮሐ ፲፯ ፥ ፲፯ ] ዳግመኛ የሰው ልጅ ከመንፈስ ቅዱስ ሲወለድ የቅድስና ሥራ ይጀምራል ፤ በሕይወቱ ደግሞ ቅድስናውን እያሳደገ ይሄዳል ፤ በዕለተ ምጽአት ቅድስናው ፍጹም ይሆናል። [ ፩ኛ ቆሮ.፲፭ ፡ ፶፩ ፣ ፩ኛ ተሰ.፬ ፥ ፬ ]
ቅድስና በአማኝ ሕይወት ውስጥ የሚያድገው በእግዚአብሔር ኀይል ነው ፤ ነቢዩ ሕዝቅኤል " መቅደሴ ለዘለዓለም በመካከላቸው በሆነ ጊዜ እኔ እስራኤልን የምቀድሰው እግዚአብሔር እንደሆንኩ አሕዛብ ያውቃሉ::" በማለት ተናግሯል:: [ ሕዝ ፴፯ ፥ ፳፰ ]
የሰው ልጅ ለእግዚአብሔር አገልግሎት የተለየ በመሆኑ በፍጹም ኀይሉ በፍጹም ነፍሱ በፍጹም ልቡ እግዚአብሔርን መውደድ አለበት:: ቅድስናውና ፍቅሩ ደግሞ ትእዛዙን በመጠበቅ ይገለጣል። [ማር.፲፪ : ፴፫ ፣ ዮሐ.፲፬፥፳፩ ፣ ፊል.፪፥፲፪ ፣ ፩ኛዮሐ.፭፥፳፫ ፣ ዘሌዋ.፲፱፥፪ ፣ ፩ኛ ጴጥ.፩፥፲፭ ]
🕊 💖 🕊