mikreabew | Unsorted

Telegram-канал mikreabew - ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

874

"እንግዲህ፡ንስሓ፡ግባ፤አለዚያ፡ፈጥኜ፡ እመጣብሃለሁ፡፡" ራዕ 2፥16

Subscribe to a channel

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

       †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬

[   ኦርቶዶክሳዊ የመዳን ትምህርት   ]

[ በዚህ መርሐ-ግብር ኦርቶዶክሳዊ የመዳን ትምህርት ከቅዱሳት መጻሕፍት ፤ ከቅዱሳን አባቶቻችን ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን አስተምህሮ እንዲሁም ከመምህራን ትምህርቶች ላይ በየጥቂቱ ይቀርባል። እንዲሁም የተሐድሶ መናፍቃን የኑፋቄ ትምህርቶችና ምላሾቻቸው የሚቀርብ ይሆናል። ]

†                      †                       †

[   ኦርቶዶክሳዊ የመዳን ትምህርት   ]

[       ክፍል ሃያ ሦስት     ]

[ መዳን ማለት ምን ማለት ነው ?  ]

†                      †                       †

1) ኃጢአት ካመጣው ፍዳ ሁሉ መዳን

               [  -   ፪  -    ]

ጌታችን እኛ ከሞትና ከርግመት እንድን ዘንድ ራሱን የተወደደ መሥዋዕት አድርጎ አቀረበ ፤ ክርስቶስም ደግሞ እንደ ወደዳችሁ ለእግዚአብሔርም የመዓዛ ሽታ የሚሆንን መባንና መሥዋዕትን አድርጎ ስለ እናንተ ራሱን አሳልፎ ሰጠ” እንዲል። [ ኤፌ.5፡2 ] ክርስቶስ የመጣው ከኃጢአት ብቻ ሳይሆን ከሞትም ሊያድነን ነው:: በሞት የደረሰብንን የነፍስና የሥጋ መለያየት ያድን ዘንድ ሥጋችንንና ነፍሳችንን ተዋሐደ። ለዚህም መድኃኒታችን ነፍሱና ሥጋው በሞት ጊዜ እንዲለያዩ ፈቀደ፡፡ ሆኖም መለኰት ከሁለቱም ጋር - ከሥጋውና ከነፍሱ ጋር - የተዋሐደ ስለሆነና ስለማይለይ ሞት ሥጋውንም ሆነ ነፍሱን ይይዛቸው ዘንድ አልቻለም ፣ ምክንያቱም መለኰት ከሁለቱም ጋር ተዋሕዷልና።

ከሦስት ቀን በኋላም ቅድስት ነፍሱንና ክቡር ሥጋውን በትንሣኤ እንደገና አዋሓዳቸው:: ስለዚህም ሞትን አጠፋው:: በጌታችን ሞት ሞት ድል ሆነ ፣ ሲኦል ተመዘበረ መቃብር ተከፈተ፡፡ ለዚህም ምስክሮችና በኩራት ይሆኑ ዘንድ በኢየሩሳሌም ሞተው ተቀብረው ከነበሩት ቀደምት ወገኖች መካከል የተወሰኑት ከመቃብር በመነሣት ለሰዎች እንዲታዩ አደረጋቸው:: በቅዱስ ወንጌል “ከትንሣኤውም በኋላ ከመቃብሮች ወጥተው ወደ ቅድስት ከተማ ገቡና ለብዙዎች ታዩ” እንደ ተባለ። [ማቴ. 27:53]

በሞቱ ሞትን ሻረው ፤ “የኋለኛው ጠላት የሚሻረው ሞት ነው” የተባለው ለዚህ ነው:: [1ቆሮ. 15፥26] ስለዚህም “አሁን ነፍሴ ታውካለች ምንስ እላለሁ? አባት ሆይ ፥ ከዚህ ሰዓት አድነኝ" ነገር ግን ስለዚህ ወደዚህ ሰዓት መጣሁ” አለ። ይህም ማለት ጌታችን ሰው የሆነውና ወደ ሕማማቱ የገባው ስለ እኛ እስከ ሞትና መቃብር ድረስ የደረሰ መከራን በፈቃዱ ለመቀበል መሆኑን ነው:: [ ዮሐ.12፡27 ፣ ቆላ.1፡20 ፤ የሐዋ.20፡28 ፤ ሮሜ.5:9 ፤ ኤፌ.17 ቆላ.1:14 ፤ ዕብ. 9:22 ፤ ራእ.1:5-6 ፣ ራእ. 5:9 ]

የሰው ልጅ “በበላህ ቀን ሞትን ትሞታለህ” ተብሎ አስቀድሞ ተነግሮት የነበረው የሞት ማስጠንቀቂያ በገቢር ተፈጽሞበት በሰውነቱ ላይ ሞት ነግሦበት የሞት ተገዢ ሆኖ ነበር። [ዘፍ.2:17 ] በሕይወተ ሥጋ እያለም ኑሮው በጽላሎተ ሞት [በሞት ጥላ ሥር] ውስጥ የወደቀና በሞት ስጋትና ፍርሃት የታጠረ ሲሞትም ነፍሱ በጻዕር ተለይታ ሥጋው ወደ መቃብር ነፍሱ ወደ ሲዖል በመውረድ በጭንቅና በመከራ ይኖር ነበር:: ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሞት የሚስማማውን የእኛን ሥጋ በመዋሓድ ሞታችንን ሞቶ በሞቱ ሞትን አጠፋልን ፣ የእርሱን ሕይወት ለእኛ ሰጠን ፣ ሞትን በትንሣኤ ለወጠልን የመቃብርን ይዞ የማስቀረትና ሰውነታችንን የማፍረስና የመለወጥ ኃይል ድል በማድረግ በመቃብር ተይዞ ፈርሶ በስብሶ መቅረትን አጠፋልን።

በብሉይ ኪዳን የነበሩ ወገኖቻችን የሚኖሩት በሞት ፍርሃት ውስጥ ነበር፡: ሲሞቱም በጻዕርና በመከራ ነበር:: ነቢዩ ዳዊት ይህን በዚያን ዘመን የነበረውን ፍርሃተ ሞት ሲገልጽ እንዲህ ይላል ፦
" ወደንገጸኒ ልብየ በላዕሌየ ወመጽአኒ ድንጋፄ ሞት ፍርሃት ወረዓድ አኃዘኒ ወደፈነኒ ጽልመት ወእቤ መኑ ይሁበኒ ክንፈ ከመ ርግብ እስርር ወአእርፍ - ልቤ በላዬ ተናወጠብኝ ፣ የሞት ድንጋጤም ወደቀብኝ ፣ ፍርሃትና እንቅጥቅጥ መጡብኝ ፣ ጨለማም ሽፈነኝ ፣ በርሬ ዐርፍ ዘንድ እንደ ርግብ ክንፍን ማን በሰጠኝ?" [መዝ. 54:4-7]

ልበ አምላክ የተባለ ዳዊት በመዝሙሩ እንዲህ አድርጎ የገለጸው በዘመነ ኦሪት ሰው ሁሉ በሞት ፍርሃትና ጭንቀት ውስጥ የነበረ መሆኑን ነው፡፡ ይህን የሰውን ልጅ ሲያስፈራና ሲያስደነግጥ የኖረውን ሞት ከሥሩ ነቅሎ ያጠፋልንና ያስወግድልን ዘንድ ክብር ምስጋና ለዘለዓለሙ ለእርሱ ይሁንና ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው ሆነልን ሐዋርያው “ እርሱ ደግሞ በሞት ላይ ሥልጣን ያለውን በሞት እንዲሽር ፣ ይኸውም ዲያብሎስ ነው ፣ በሕይወታቸውም ሁሉ ስለ ሞት ፍርሃት በባርነት ይታሰሩ የነበሩትን ሁሉ ነፃ እንዲያወጣ በሥጋና በደም እንዲሁ ተካፈለ” እንዳለ። [ ዕብ.2:14-15 ]

ስለሆነም ክርስቶስ በሞቱ ድል ካደረገው ወዲህ ሞት ኃይሉን ያጣ ደካማ የቀድሞ አስፈሪነቱ ቀርቶ በክርስቲያኖች ዘንድ መሳለቂያና ወደማያልፈው ዓለም መሄጃ መንገድ ሆኗል፡፡ ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ እንደ ገለጸው በዘመነ ክርስትና ሞት ጥፍሩ እንደ ወለቀ ፣ ጥርሱ እንደ ረገፈና ኃይሉ እንደ ደከመ ፣ ከዚህም የተነሣ የሕፃናት መጫወቻ እንደ ሆነ አንበሳ ፤ እንዲሁም መርዙ እንደ ወጣና ምንም ጉዳት ማድረስ እንደማይችል እባብ ሆኗል፡፡

[  በማክሰኞ መርሐ-ግብር ፦  ]

1 ] ኃጢአት ካመጣው ፍዳ ሁሉ መዳን [ ፫ ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

💛
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

🕊   ዐቢይ ጾም [  ጾመ እግዚእ  ] 🕊


▷   "  የመንፈሳዊ ሰው ልብ   "


[    " አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ ... ! "    ] 

[                        🕊                        ]
----------------------------------------------

" ከኃጢአቴ ፊትህን መልስ ፥ በደሌንም ሁሉ ደምስስልኝ።

አቤቱ ፥ ንጹሕ ልብን ፍጠርልኝ ፥ የቀናውንም መንፈስ በውስጤ አድስ። ከፊትህ አትጣለኝ ፥ ቅዱስ መንፈስህንም ከእኔ ላይ አትውሰድብኝ።" [ መዝ.፶፩፥፱ ]


🕊                       💖                   🕊

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

ሰኞ - መጋቢት 02 2016 ዓም

ማቴዎስ 1-5

ሰላም ለሁላችሁ ይሁን! በዛሬው የዐቢይ ጾም ንባባችን የማቴዎስ ወንጌልን ከምዕራፍ 1-5 ድረስ እናነባለን። 

ከንባብ በፊት የሚደረግ ጸሎት፡ “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፤ የአንተን ቃላት እሰማ እና እረዳ ዘንድ፥ እንዲያውም ፈቃድህን ለመፈጸም እበቃ ዘንድ የልቤን ጆሮዎች እና ዓይኖች ክፈትልኝ።” (ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ) 

በዛሬው ንባባችን ላይ ስለ ጌታችን የትውልድ ቁጥር፥ ስለ ጌታችን ልደት፥ ሰብአ ሰገል ወደ ኢየሩሳሌም ስለመምጣታቸው፥ ጌታችን ከእናቱ ጋር ስለመሰደዱ እና ንጉሥ ሄሮድስ ሕጻናት እንዲገደሉ ስለማድረጉ፥ ስለ መጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ የንስሃ ስብከት፥ ጌታችን ስለመጠመቁ እና ጾሞ በዲያብሎስ ስለመፈተኑ፥ ደቀ መዛሙርትን ስለመጥራቱ፥ ተዓምራትን ማድረስ ስለመጀመሩ እናነባለን። በተጨማሪም “አንቀጸ ብፁዓን” ተብሎ የሚጠራውን ትምህርቱን ስለማስተማሩም ተጽፎ እናገኛለን። 

*የክለሳ ጥያቄዎች*

1) ሐዋርያው ቅዱስ ማቴዎስ በዘረዘረው የጌታችን የትውልድ ቁጥር በስንት በስንት ትውልድ የተዋቀረ ነው? በትውልድ ቁጥሩ ውስጥስ ምን ያህል ሴቶች ተጠቅሰዋል? 

2) በማቴዎስ 1 መሠረት፥ ጌታችን “ኢየሱስ” የሚለው ስም የተሰጠው ለምንድር ነው? 

3) ሰብአ ሰገል ወደ ኢየሩሳሌም ሲመጡ የጠየቁት ጥያቄ ምንድር ነው? ስለ ሕጻኑ መወለድ የሰማው የሄሮድስ ምላሽስ ምን ነበር? 

4) ጻድቁ ቅዱስ ዮሴፍ ጌታችንን እና እመቤታችንን ይዞ ወደ የት ሸሸ? ሄሮድስ በሞተ ጊዜስ ወደ የት ተጓዙ? 

5) የመጥምቁ ዮሐንስ ስብከት ምን የሚል ነበር? ስለ ጌታችንስ ምን ተናገረ? 

6) ጌታችን ቅዱስ ዮሐንስ እንዲያጠምቀው ወደ ዮርዳኖስ በሄደ ጊዜ የቅዱስ ዮሐንስ ምላሽ ምን ነበር? 

7) ዲያብሎስ ጌታችንን በፈተነ ጊዜ ከብሉይ ኪዳን የጠቀሰው ቃል ነበር። ይህ የጠቀሰው ቃል ምን የሚል ነው?

8) በማቴዎስ 4 መሠረት፥ ጌታችን መጀመሪያ የጠራቸው ደቀ መዛሙርት እነማን ናቸው? የትስ አገኛቸው? 

9) ጌታችን በትምህርቱ ላይ “ብጹዓን ናቸው” የሚለውን የጠቀሰው ምን ያህል ጊዜ ነው? ብጹዓን ናቸው የተባሉትስ ምን የሆኑ ወይም ምን የሚያደርጉ ናቸው? 

10) ጌታችን “እኔ ግን እላችኋላሁ…” በማለት ከተናገራቸው ቃላት የመጀመሪያው “በወንድሙ ላይ በከንቱ የሚቆጣ ሁሉ እርሱ ይፈረድበታል” የሚል ነው። የተቀሩት ስንት ናቸው? እነርሱን ጥቀሱ። 

መልካም ንባብ!
/channel/OrthodoxTewahdoBooks

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

ሰላም ወዳጆች፥ እንደምን አላችሁ?

በዛሬው እለት መጽሐፈ ሩትን ጀምረን ጨርሰናል። በመሆኑም ብዙ ሰው በመረጠው መሠረት፥ የብሉይ ኪዳን ንባባችንን ለጊዜው ገታ አድርገን በነገው እለት የማቴዎስ ወንጌልን ጥናት እንጀምራለን። እግዚአብሔር ቢፈቅድ፥ ሙሉ ሐዲስ ኪዳኑን በዐቢይ ጾም ውስጥ አንብበን እንጨርሳለን።

ደስ የሚለው የብሉይ ኪዳንን ንባባችንን ዛሬ ያቆምንበት ቦታ ጥሩ ቦታ ነው። መጽሐፈ ሩት እስራኤላውያን በመሳፍንት በሚመሩበት እና በነገሥታት በሚመሩበት ጊዜ መሸጋገሪያ ላይ የተተረከ ነው። በመሆኑም እግዚአብሔር ቢፈቅድ ቀጣይ ላይ ብሉይ ኪዳንን መልሰን ካቆምንበት ስንጀምር፥ እስራኤላውያን በነገሥታት ሥር ሆነው የኖሩበትን ሁኔታ ማየት እንጀምራለን።

በዚህ ጾም ውስጥ በሐዲስ ኪዳን ንባብ እንበርታ። እስካሁን በቸርነቱ ጠብቆ ያበረታን አምላክ ጾሙንም አበርትቶ ለብርሃነ ትንሣኤው ያድርሰን።

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

                        †                             

†  🕊   ጴ ጥ ሮ ስ ኒ   🕊 †


    [    የግእዝ መዝሙር ጥናት    ]

            [ ክፍል  - ፲፭  -  ]

የወንድማችን ድንቅ አገልግሎት ! ከጣእሙ ብዛት አጥንትን የሚያለመልም ዝማሬ መላእክትን ያሰማልን።

†                       †                        †
💖                    🕊                     💖

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

ለመጀመሪያ ጊዜ ሳላቋርጥ የጨረስኩት ከድንቅ ልጆች

በጣጣጣጣጣምምም ነው የተማርኩበት የወደድኩት ተጋበዙልኝ 👇👇👇

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

Watch "አባ አርሴኒ፡ ካህን፡ እስረኛ፡ መንፈሳዊ (ክፍል ሁለት) Father Arseny, : Priest, Prisoner, Spiritual Father (PART TWO)" on YouTube
https://youtu.be/5Naw_jeDheY?si=0_BaGj_Z2bStLeIV

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

ታላቁ አባታችን ዩሀንስ አፈወርቅ ወደ ዕብራዊያን መልእክት በተረጎመበት ድርሳን ላይ እንዲ ይላል
ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የተዋሀደው ስጋ ከመላእክት ባህርይ የነሳው አደለም ከአብርሀም እንጂ
" የአብርሃምን ዘር ይዞአል እንጂ የያዘው የመላእክትን አይደለም።"
(ወደ ዕብራውያን 2:16)
ለዚም ታላቅ ፍቅር አንክሮ ይገባል÷ ከእግዚአብሔር ዘንድ ለሰው ወገን ለተደረገው ለማይመረመር ለዚህ ታላቅ ፍቅር አንክሮ ይገባል÷ ይህ ለመላእክት ያላደረገው ነው ።
የተናገረውን አስተውል እግዚአብሔር ከእኛ ባህርይ የተዋሀደው ተዋሕዶ ጥቂት አይምሰላችሁ ይህ ለመላእክት አላደረገውምና÷ የመላእክትን ባህሪ አልተዋሀደም የኛን ባህሪ እንጂ ።

ባህሪያችን ተዋህዶል እንጂ ከባህሪያችን ከፍሎ ተዋሀደ ለምን አላልንም? ወዳጁ እንደኮበለለ እስኪያገኘውም ድረስ እንደ ሄደና እንደአገኘው ሰው የእኛ ባህሪይ እንደዚህ ከእግዚአብሄር ተለይታ ነበርና÷ከእርሱም ፈፅማ ርቃ ነበርና ስጋ በሚሆን ገንዘብ እስኪ አደርጋት ደርሶ ፈጥኖ ፈለጋት እርሶም ተዋሀደችው ይህንንም ተዋሀዶ እኛን በመውደድ እንዳደረገው የታወቀ ነው ።

(የማቴዎስ ወንጌል ምዕ. 18)
----------
12፤ ምን ይመስላችኋል? ለአንድ ሰው መቶ በጎች ቢኖሩት ከእነርሱም አንዱ ቢባዝን፥ ዘጠና ዘጠኙን በተራራ ትቶ ሄዶም የባዘነውን አይፈልግምን?
13፤ ቢያገኘውም፥ እውነት እላችኋለሁ፥ ካልባዘኑቱ ከዘጠና ዘጠኙ ይልቅ በእርሱ ደስ ይለዋል።

14፤ እንደዚሁ ከእነዚህ ከታናናሾቹ አንዱ እንዲጠፋ በሰማያት ያለው አባታችሁ ፈቃድ አይደለም።

/channel/+SgNDpz7jxXEzN2Vk

ሀይማኖተ አበው ዘዩሀንስ አፈወርቅ ምዕ 62:3-5

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

ቅዳሜ - የካቲት 30 2016 ዓም

መሳፍንት 20 - 21

ሰላም ለሁላችሁ ይሁን! በዛሬው ንባባችን ከምዕራፍ 20 - 21 ድረስ በማንበብ መጽሐፈ መሳፍንትን እናጠናቅቃለን።

ከንባብ በፊት የሚደረግ ጸሎት፡ “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፤ የአንተን ቃላት እሰማ እና እረዳ ዘንድ፥ እንዲያውም ፈቃድህን ለመፈጸም እበቃ ዘንድ የልቤን ጆሮዎች እና ዓይኖች ክፈትልኝ።” (ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ)

በዛሬው ንባባችን ላይ እስራኤላውያን በአጠቃላይ እንደተሰበሰቡ እና እንደተማከሩ፥ ሌዋዊውም የደረሰበትን እንደተናገረ፥ እነርሱም ደግሞ ለበቀል እንደተነሱ እና ለብንያም ሰዎች ምናምንቴዎቹን እንዲያወጡ መልእክት እንደላኩ እናነባለን። የብንያም ወገኖች ግን ይህንን እንዳልሰሙ፥ በዚህም ምክንያት ጦርነት እንደተፈጠረ እና እስራኤላውያን በብንያም ወገኖች ላይ ስለተማማሉት መሃላም ተጽፎ እናገኛለን።

*የክለሳ ጥያቄዎች*

1) እስራኤላውያን የተሰባሰቡት በምን ምክንያት ነው? ስንት ሰዎችስ ተሰበሰቡ?

2) ሕዝቡ ሌዋዊው የደረሰበትን ሲሰሙ ምላሻቸው ምን ነበር?

3) እግዚአብሔር ስለ ብንያም ነገድ ለእስራኤላውያን ምን ብሎ ተናገረ?

4) የእስራኤል ልጆች በብንያም ነገድ ላይ የማሉት መሃላ ምን ነበር?

5) እስራኤላውያን ጮክ ብለው እንዲያለቅሱ ምክንያት የሆናቸው ምንድር ነው?

መልካም ንባብ!
/channel/OrthodoxTewahdoBooks

/channel/+3kpzSPDfiVMzYzQ

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

                       †                       


" እንግዲህ ምሕረትን እንድንቀበል በሚያስፈልገንም ጊዜ የሚረዳንን ጸጋ እንድናገኝ ወደ ጸጋው ዙፋን በእምነት እንቅረብ። "

[ ዕብ.፬፥፲፮ ]

†                       †                       †
💖                    🕊                    💖

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

                          †                          

     [   🕊  መዝሙረ ተዋሕዶ   🕊   ]  

🍒▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬🍒               

[  ኦርቶዶክሳዊ የተቀደሰ ያሬዳዊ ዝማሬ ሰዓት  ]

[ ሳምንታዊ መርሐ-ግብር ]

🕊

በስመ አብ ፡ ወወልድ ፡ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን፡፡

ኦርቶዶክሳዊ መዝሙር ንጹሕና የተቀደሰ ነው ፥ ለእግዚአብሔር ምስጋናና ልመና የሚቀርብበት ፣ ይቅርታና ምሕረት የሚጠየቅበት ፣ ሰውን ሳይሆን እግዚአብሔርን ደስ ለማሰኘት የሚዘጋጅ ንጹሕ መስዋዕት ነው ፥ በአበው ጸሎት ይዘጋጃል ፥ ከስጋዊና ከደማዊ ሀሳብ የራቀ ነው ፥ ልቦናን ወደ ንስሐ ይጠራል ፥ ከኃጢአትና ከክፉ ሥራ የመለየት ኃይል አለው ፥ ክፉ መንፈስን ከሰው ልብ ያርቃል ፥ መረጋጋትን ልቦናን ዘልቆ የሚሰማ ውስጣዊ ሰላምን ይሰጣል ፥ በአሚነ ሥላሴ ያጸናል ፥ የክርስቶስን የባህርይ አምላክነትና መሐሪነት ይመሰክራል ፥ የእመቤታችንን ፍቅር በልቦና ያሳድራል ፥ በእናትነቷና በምልጃዋ እንድንታመን ያደርጋል ፥ በቅዱሳን ጸሎትና በቃል ኪዳናቸው ያጸናል ፥ ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን እናውቅ ዘንድ መንገድ ይመራናል ፥ ፈሪሐ  እግዚአብሔርንና ፍቅረ እግዚአብሔርን ያጎናጽፈናል፡፡

†                       †                       †

ተወዳጆችሆይ ፦ በተቀደሰ ሰማያዊ ያሬዳዊ ዜማ ነብሳችንን እናስጊጣት፡፡ ከደጋጎቹ አባቶቻችን ጋር ከዓለም ርኩሰት በተለየ የተቀደሰ ዝማሬ አምላካችን እግዚአብሔርን እናመሥግን፡፡ ለስጋዊ ጆሮዎች ከሚመች ከረከሰ የተሃድሶ የኑፋቄ እርሾ ልቦናችንን እንጠብቅ፡፡ ገንዘብን ስለመውደድ ከሆነ ከሥጋዊ ሥራ ፈጽሞ እንለይ፡፡

🍒

[  🕊 ከጦመ በኋላ ተራበ ! 🕊  ]

[  " ከዚያ ወዲያ ኢየሱስ ከዲያብሎስ ይፈተን ዘንድ መንፈስ ወደ ምድረ በዳ ወሰደው ፥ አርባ ቀንና አርባ ሌሊትም ከጦመ በኋላ ተራበ። "  ]

{ ማቴ.፬፥፩ }  

†                       †                       †
💖                    🕊                    💖

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

🕊                   

[ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። ]

✞ እንኩዋን ለዐቢይ ጾም በሰላም አደረሳችሁ ✞
                   

[ ዐቢይ ጾም  " የጌታ ጾም " ]

 🍒

ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በአዋጅ ምዕመናን እንዲጾሟቸው የሠራቻቸው ፯ [ 7 ] አጽዋማት አሏት:: " ጾም " ማለት "መከልከል" ነው::

የምንከለከለው ደግሞ ከኃጢአትና ከክፋት ሲሆን አንድም ሰውነትን ወደዚያ ከሚወስዱ መባልዕት መከልከልን ይመለከታል::

ጾም ለክፉ ሥራ ከሚያነሣሱ የምግብ ዓይነቶች መከልከል ወይም ለተወሰነ ጊዜና ሰዓት ሰውነት ከሚፈልጋቸው ነገሮች ሁሉ መወሰን [ መታቀብ ] ማለት ነው፡፡ ለሰውነት የሚያምረውንና የሚያስጎመዠውን ነገር ሁሉ ስለ ፍቅረ እግዚአብሔር ብሎ መተው ነው፡፡

ጾም ከመንፈሳዊ ተጋድሎዎች አንዱ ነው፡፡ ለሥጋም መንፈሳዊ ልጓም ነው፡፡ ጸዋሚ ሰው ፈቃደ ሥጋውን እየገታ ነፍሱን የሚያለማምድበት ስንቅ ነው፡፡ "ጾም ቁስለ ነፍስን የምትፈውስ ፤ ኃይለ ፍትወትን የምታደክም ፤ የበጎ ምግባራት ሁሉ መጀመሪያ ፤ ከእግዚአብሔር ጸጋን የምታሰጥ ፤ የወንጌል ሥራ መጀመሪያ ፤ የጽሙዳን ክብራቸው ፤ የድንግልና የንጽሕና ጌጣቸው ፤ የንጽሕና መገለጫ ፤ የጸሎት ምክንያት እናት ፤ የዕንባ መገኛ መፍለቂያዋ ፤ አርምሞን የምታስተምር ፤ ለበጎ ሥራ ሁሉ የምታነቃቃ ፣ ሰውነትን በእግዚአብሔር ፊት በማዋረድ ትሕትናን ገንዘብ ለማድረግ የምትረዳ መድኃኒተ ነፍስ ናት፡፡" [ማር ይስሐቅ አንቀጽ ፬፥፮]

ጾም ተድላ ሥጋን የምታጠፋ ፥ የሥጋን ጾር የምታደክም ፥ ቁስለ ነፍስን የምታደርቅ ፥ ለጎልማሶች ጸጥታንና ዕርጋታን የምታስተምር ፥ ከግብረ እንስሳዊ የምትከለክል ፥ ሰው መላእክትን መስሎ የሚኖርባትና ኃይል መንፈሳዊን የሚጎናጸፍባት ደገኛ መሣሪያ ናት፡፡ ከኃጢአት ፆር ከፍትወት አንዱንም አንዱን ድል ለመንሳት ለማጥፋት ፥ የዲያብሎስን ረቂቅ ፍላጻ ለመመከት በጾም መድከም የሥራ ሁሉ መጀመሪያ እንደሆነች የታወቀ ነው፡፡ ጾም ምህረት መለመኛ ፥ የንስሐ መገለጫ ፥ ከመከራ የሚሠወሩባት ፥ ሰውን ከእግዚአብሔር ጋር አስታርቃ ርስት መንግሥተ ሰማያት የምታስገባ "ኆኅተ ጽድቅ - የጽድቅ በር" ሆና የተሰጠች ቀዳማዊት ሕግ ናት፡፡

🕊       💖      🕊

[ ዐቢይ ጾም [ ጾመ እግዚእ ] ]


ከ፯ [7] ቱ አጽዋማት አንዱ የሆነው ይህ ጾም

፩. ዐቢይ [ ታላቁ ] ጾም
፪. የጌታ ጾም
፫. ጾመ ሑዳድ
፬. የድል ጾም
፭. የካሳ ጾም
፮. አርባ ጾም
፯. የፍቅር ጾም . . .
በሚሉ መጠሪያዎችም ይታወቃል::

የጾሙ መግቢያ የመጀመሪያ ሳምንት ደግሞ =

፩. ጾመ ሕርቃል
፪. ጾመ በረከት ዘሐዋርያት
፫. ሰሙነ ዘወረደም ይባላል::

የጾሙ የመጀመሪያው ሳምንት [ዘወረደ] የሚጾመው እስከ ፲፪ [ 12 ] ሰዓት ሲሆን ከቅድስት [ ከ፪ [ 2 ] ኛው ሳምንት እስከ ተጽኢኖ [ የኒቆዲሞስ ዓርብ ] ድረስ ደግሞ እስከ ፲፩ [ 11 ] ሰዓት ይጾማል::

በሰሙነ ሕማማት ግን የምንጾመው "እስከ ይሠርቅ ኮከብ" [ እስከ ምሽት ፩ [ 1 ] ሰዓት ] ድረስ ይሆናል::

ነገር ግን ሁሉም እንደ መጠኑ ነውና ከመምሕረ ንስሃ ጋር ሊጨዋወቱት ይገባል:: በዓቢይ ጾም ለቻለ ቂጣ በጨው እየበላ : ውሃ እየተጐነጨ ሊጾም ይገባል:: በእነዚህ ፶፭ [ 55 ] ቀናትም ከዕለተ ሆሳዕና በቀር ከበሮ አይጐሰምም:: ጸናጽል አይጸነጸልም:: ተድላ ደስታም አይደረግም::

አብዝቶ መብላት : ሳቅ ማብዛትና ጌጥን ማብዛትም እንዲሁ አይገባም:: ለቻለ ደግሞ በሌሊት ሰዓታቱን ፡ በነግህ ኪዳንና ስብሐተ ነግሁን : በመዓልት ቅዳሴውን : በሰርክ [ ምሽት ] ደግሞ ምሕላውን ሊሳተፍ ይገባል::

በእነዚህ ፶፭ [ 55 ] ቀናት ፈቃደ ሥጋ ሊደክም : ፈቃደ ነፍስ ልትሰለጥን ግድ ነውና:: ከሌላው ጊዜ በተሻለ ወቅቱ ምጽዋትና ጸሎት የሚደረግበት ነው:: በዚያውም ላይ ነገሮችን እያመቻቹ በእነዚህ ዕለታት ቅዱስ ቃሉን መስማት [ማንበብ] ይገባል:: በትዳር ውስጥ ላሉም መኝታን መለየት ግድ ነው::


ጾሙን የሰላም : የፍቅር : የምሕረት : የፀጋ : የበረከት ያድርግልን:: ጾሞ ለማበርከትም ያብቃን፡፡

" አሁንስ ይላል እግዚአብሔር በፍጹም ልባችሁ በጾምም በልቅሶና በዋይታ ወደ እኔ ተመለሱ:: ልባችሁን እንጂ ልብሳችሁን አትቅደዱ:: አምላካችሁም እግዚአብሔር ቸርና መሐሪ: ቁጣው የዘገየ: ምሕረቱም የበዛ: ለክፋትም የተጸጸተ ነውና ወደ እርሱ ተመለሱ:: " [ትን. ኢዩኤል.፪፥፲፪ (2:12) ]


ወስብሐት ለእግዚአብሔር : ወለወላዲቱ ድንግል : ወለመስቀሉ ክቡር !

         [       ይቆየን ! ]

†                       †                         †
💖                    🕊                     💖

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

ዓርብ - የካቲት 29 2016 ዓም

መሳፍንት 15 - 19

ሰላም ለሁላችሁ ይሁን! በዛሬው ንባባችን ከምዕራፍ 15 - 19 ድረስ እናነባለን።

ከንባብ በፊት የሚደረግ ጸሎት፡ “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፤ የአንተን ቃላት እሰማ እና እረዳ ዘንድ፥ እንዲያውም ፈቃድህን ለመፈጸም እበቃ ዘንድ የልቤን ጆሮዎች እና ዓይኖች ክፈትልኝ።” (ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ)

በዛሬው ንባባችን ላይ ሳምሶን በሚስቱ መዳር ምክንያት ስላደረገው ነገር፥ ከደሊላ ጋር ስለነበረው ወዳጅነት፥ ፍልስጤማውያን ስላደረጉበት ነገር እና ስለ ፍጻሜው እናነባለን። በተጨማሪም፥ ሚካ ስለተባለው ሰው፥ እስራኤላውያን በወቅቱ ስለነበሩበት ሁኔታ እና አንዲት እቁባት ስለነበረው ሌዋዊ ታሪክም ተጽፎ ይገኛል።

*የክለሳ ጥያቄዎች*

1) በመሳፍንት 15 መሠረት ፥ ሶምሶን በፍልስጤማውያን ላይ ክፉ ለማድረግ የተነሳው ለምንድር ነበር? ምንስ አደረገባቸው?

2) የሶምሶን ጥፋት ምክንያት የሆነችው ሴት ማን ትባላለች? ምንስ አደረገችበት?

3) የሶምሶን መጨረሻ ምን ነበር? እግዚአብሔርንስ ለመጨረሻ ጊዜ ምን ብሎ ተማጸነ?

4) የዳን ልጆች ከሚካ ዘንድ ያለውን ጣዖት እና ሌዋዊ ይዘውበት በሔዱ ጊዜ ምላሹ ምን ነበር?

5) በመሳፍንት 19 ላይ ያለው የሌዋዊው እና የሽማግሌው ሁኔታ በኦሪት ዘፍጥረት ውስጥ የማንን ታሪክ ያስታውሳችኋል?

6) ሽማግሌው ሌዋዊውን በቤቱ እንግዳ አድርጎ የተቀበለው ለምንድር ነው?

7) የከተማው ወስላቶች በሌዋዊው እቁባት ላይ ምን አደረጉባት? መሞቷን ሲረዳስ በሐዘን ለእስራኤል ሁሉ የላከው መልእክት ምን ነበር?

መልካም ንባብ!
/channel/OrthodoxTewahdoBooks

/channel/+3kpzSPDfiVMzYzQ

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

ከዚያም የተወሰኑ አገልጋዮችን አስቀምጣላቸው ወደ ኢየሩሳሌም በመሄድ ለ፯ [7] ዓመታት በአየሩሳሌም ከኖረች በኋላ የእመቤታችን በዓል ለማክበር ወደ ግብፅ በመሄድ ላይ ሳለች በመንገድ አንድ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ገብታ ስትፀልይ እመቤታችን በስዕሏ ላይ ተገልጣ: ቦታዋ በኢትዮጵያ መሆኑን ነግራ: እጇን ዘርግታ "ወደ ኢትዮጵያ ሂጂ" ብላ ነገረቻት::

በኋላ በብርሃን አምድና በቅዱስ ሚካኤል እየተመራች አሁን ወደ ምትታወቅበትና የእግዚአብሔር ድንቅ ሥራ ወደ ተገለፀበት እመ ምዑዝ ኪዳነ ምህረት ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ አንድነት ገዳም ደርሳለች፡፡ በቦታው ስትደርስ የቦታው ልምላሜ የሚያስደስት ነበርና "ይህች ቦታ ምን ታምር!" ብላለች፡፡ ቦታውም እስከ አሁን ድረስ ምንታምር በመባል ይጠራል፡፡

ምንታምር ላይ ከአገልጋዮቿ ጋር በመሆን አርፋ ሳለ ከኢየሩሳሌም መርቶ ያመጣት የብርሃን አምድ በዚያ ቦታ ላይ በስፋት ረቦ [ከምድር እስከ ሰማ ተተክሎ] ብታየው: መልአኩም "ቦታሽ ይሄ ነው" ብሎ ቢነግራት በዚያው ተቀምጣለች፡፡

የቦታው ባለ አባት "ይህን ቦታ ልቀቂ" ቢሎ ቢጠይቃት "እግዚአብሔር የሰጠኝ ቦታዬ ነው" ብላዋለች፡፡ እርሱም ለክስ ወደ ጎንደር በመሄድ አፄ ሱስንዮስ አርፈው አፄ ፋሲል ነግሰው ነበርና እሳቸውን ፍርድ ቢጠይቃቸው በዝና ያውቋት ነበርና "ቤተ ክርስቲያን ካልተሰራ ትልቀቅልህ: ከተሠራ ግን ሌላ ቦታ ይሰጥሃል" የሚል ፍርድ አስፈርዶ ነበር::

ሲመለስ ቅዱስ ሚካኤል ቀድሞ "ቶሎ ቤተ ክርስቲያን ስሪ እንዲህ የሚል ፍርድ ተፈርዷል ብሎ ነግሯት " ታህሳስ ፲፬ [14] ቀን ከነግህ ፀሎት በኋላ በሰንሰልና በስሚዛ ግድግዳዋን: በአይጥ ሀረግ ማገር አድርጋ: የግድግዳ ቤተ መቅደስ በዕለተ አርብ: በአንድ ቀን ሰርታ ታህሳስ ፲፮ [16] ቀን እሁድ ታቦተ ኪዳነ ምህረትን አስገብታ ቅዳሴ አስቀድሳለች::"

ቅዳሴውም ከተፈፀመ በኋላ ጌታችን ከቅዱስ መንበሩ ላይ እንዳለ ሆኖ ከእናቱ ከእመቤታችን ጋራ ታያቸው፡፡ ከመንበሩ ወርዶም ይህን ቦታ በባረከው ጊዜ የስሚዛው ቤተ መቅደስ በአራቱም አቅጣጫ ለፈጣሪው ሰገደ፡፡

የመሬት መናወጥም ሆነ:: ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስም
"ልታጠፋን መጣህን? ቤተ ክርሰቲያኔንስ ልታፈርሳት ነው?" ብላ ብትጠይቀው "ይህ የሰንሰል ቤተ መቅደስሽ ዳግም እስከምመጣ ድረስ ሳይፈርስ: ሳይታደስ ፀንቶ ይኖራል ፣ በውስጡም እስከ ዓለም ፍፃሜ ድረስ የክሀድያንና ፣ መናፍቃን እግር አይገባበትም ፣ በውስጧ ቁርባንን የተቀበሉ ሁለ ኃጢያታቸው ይሰረይላቸዋል ፣ ዘወትር ምህረቴ በረከቴ ከእነርሱ ጋር ይኖራል" በማለት ተናግሮ ተሰወራቸው፡፡

ከዚያም በኋላ መነኮሳትና መነኮሳይያት የቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስን የትሩፋት ዜናዋን ሰምተው ከየአቅጣጫው ተሰበሰቡ፡፡ ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስም በአምላክ ሀይል ተጋድሎአቸውን ይፈፅሙ ዘንድ ታስተምራቸው ፣ ትመክራቸው ፣ በተግባርም እያሳየቻቸው ለብዙ ዘመናት ከኖሩ በኋላ በገዳሙ ላይ የአጋንንት ፆር እንዳይነሳ ወንዶቹን ለብቻ ሴቶቹን ለብቻ አደረገች፡፡

ዘወትርም እንዳይተያዩ የእግዚአብሔር መልዐክ በቅድስተ ፍቅርተ ክርሰቶስ ፀሎት ይጠብቃቸው ነበር፡፡ ከዚህ በኋላ እናታችን ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ከዚህ ኃላፊ ዓለም መለየቷ በቀረበ ጊዜ ሁለት መላዕክት ወደ እርሷ መጥተው በብርሃን  ሰረገላ ጭነው ወደ ደብረ ነባት [ወደ ብሔረ- ህያዋን] ወስደው በዚያ ቅዱስ ቁርባንን አቀብለው ወደ ቦታዎ መለሷት፡፡

መልዐኩም "ከጻማ: ከድካም: ከመታረዝ: ከረሐብ ከጥም: ከመትጋት: ከእንባ: ከዚህ ዓለም የምትለይበት ጊዜ እነሆ ደረሰ" አላት፡፡ የካቲት ፳፯ [27] ቀንም ወደ ምስራቅ እጇን ዘርግታ ቆማ ስትጸልይ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ከደስታ ብርሀን ጋር ያማረ ሽታ መላ::

ጌታችን ከአዕላፋት መላዕክትና ቅዱሳን ጋር ወደ እርሷ መጣ፡፡ እናታችን ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስም ሰገደች፡ ተንበረከከች: እጅግም አለቀሰች፡፡ ከወደቀችበት ቦታ አንስቶ "ላጠፋሽ አልመጣሁም ወዳጄ ላከብርሽ ነው እንጂ" አላት፡፡

"የዘለአለም መንግስት አዘጋጅቼልሻለሁና ደስ ይበልሽ"፡፡ ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስም ቃል ኪዳን እንዲገባላት ተማጸነችው:: ጌታችንም "ሁሉም እንደ ቃልሽ ይሁንልሽ:: በስምሽ ስሜ ተጨምሯልና ለቤተ ክርስቲያንሽ መባ የሰጠ ፣ የተላከ ፣ የተቀበረ ፣ ቤተ መቅደስሽ መጥቶ የተሳለመ ፣ እስከ ፲፪ [12] ትውልድ የምህረት ቃል ኪዳን ሰጠሁሽ::

በረከቴም በቤቱና በልጆቹ በገንዘቡም ላይ ይደር:: የገድልሽ መጽሐፍ ባለበት አጋንንት [ሰይጣናት] አይቀርቡም:: በአዝመራ ስምሽን በጠሩት ጊዜ የለመለመ ይሁን:: በጸሎትሽ የተማጸነ ሁሉ ባለጤና ይሁን::

ስምሽን በእውነት የሚጠራ የከበረ ነው፡፡ ያለመጠራጠር በቀናች ሐይማኖት የገድልሽን መጽሐፍ የጻፈ : ያጻፈ : ያነበበ : የተረጎመ በሐይማኖት የሰማ: እስከ ቀዝቃዛ ውሃ ድረስ የሰጠ ኃጢያቱ ይሰረይለታል:: ስለ ድካምሽ ስለ ትሩፋትሽ ፯ [7] አክሊሎችን እና ይህን ሁሉ ቃል ኪዳን ሰጠሁሽ፡፡ ላልምረው ቦታሽን አላስረግጠውም" ብሏት ወደ ሰማይ አረገ፡፡

በማግስቱ ትንሽ ህመም ታመመች ደናግል መነኮሳትን ጠርታ የእረፍት ቀኗ መድረሱን ነገረቻቸው:: ከመካከላቸው አንዷን ለገዳሙ አስተዳዳሪነት መርጣ በፍቅር ስም ተሰናበተቻቸው፡፡ የዳዊት መዝሙርንም ስትጸልይ የካቲት ፳፱ [29] ቀን እሁድ አጥቢያ ጠዋት በጌታ በዓል አንቀላፋች [ነፍሷ ከስጋዋ ተለየች]፡፡

ጌታችንም ከእናቱ: ከቅዱሳኑ ጋር መጥቶ ነፍሷን ተቀብሎ ወደ ዘለዓለም ገነት ወሰዳት፡፡ ቅዱሳንም
ከመላእክት ጋር እልል እያሉ እያመሰገኑ ወደ ዘለዓለም ቦታ ገነት አስገቧት፡፡ ከቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ መቃብር ላይ ፵ [40] ቀናት ብርሃን ሲበራበት ታይቷል፡፡

በሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት : በመቂት ወረዳ ጥባ ማርያም ቀበሌ ውስጥ ምን ታምር በመትባል ቦታ ላይ በ፲፮ [16] ኛው መቶ ክ/ዘመን በኢትዮጵያዊቷ ሰማዕትና ጻድቅ ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ የተመሰረተቸው እመ ምዑዝ ኪዳነ ምህት ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ አንድት ገዳምም በዓላቶቿ የሚከበሩት ታህሳስ ፲፮ [16] የቅዳሴ ቤቷ እንዲሁም የካቲት ፳፱ [29] ቀን በዓለ እረፍቷ ይከበራል፡፡

† ከቅድስት እናታችን በረከት አምላክ አይለየን::

🕊

[ † የካቲት ፳፱ [ 29 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ኢትዮዽያዊት
፪. ቅዱስ ዘርዐ ክርስቶስ [ጻድቅና ሰማዕት]
፫. ቅዱሱ ሕፃን [የፍቅርተ ክርስቶስ ልጅ]
፭. ቅዱስ ቢላካርዮስ ዘሃገረ አርሞኒ [አረጋዊ: ደራሲ: ጻድቅና ሰማዕት]

[ † ወርኀዊ በዓላት ]

፩. የፈጣሪያችንና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት
፪. ቅድስት አርሴማ ድንግል
፫. ቅዱስ ዼጥሮስ ተፍጻሜተ ሰማዕት
፬. ቅዱስ ማርቆስ ዘቶርማቅ

" መልካም ያደረጉ ብዙ ሴቶች አሉ:: አንቺ ግን ከሁሉ ትበልጫለሽ:: ውበት ሐሰት ነው:: ደም ግባትም ከንቱ ነው:: እግዚአብሔርን የምትፈራ ሴት ግን እርስዋ ትመሰገናለች:: ከእጇ ፍሬ ስጧት:: ሥራዎቿም በሸንጐ ያመስግኗት::" † [ምሳሌ.፴፩፥፳፱]  [31:29]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
💖                    🕊                     💖

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

                         †                          

                 

" የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ።" [ማቴ.፲፩፥፲፭]



         †              †               †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

🕊

[ † እንኳን ለአባታችን ቅዱስ ቆዝሞስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ]

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †


🕊 † ቆዝሞስ ሊቀ ጳጳሳት  †  🕊

† "ጳጳስ" ማለት "አባት - መሪ - እረኛ" ማለት ነው:: በቅድስት ቤተ ክርስቲያን አስተምሕሮ በሐዲስ ኪዳን የመንፈሳዊ ስልጣን ደረጃዎች በጥቅሉ ፫ [3] ናቸው:: እነሱም ዲቁና: ቅስና: ጵጵስና ሲሆኑ በሥራቸው ወደ ፱ [9] ያህል ክፍሎች አላቸው:: ከእነዚህም ከፍተኛው ስልጣን ጵጵስና ነው::

ጵጵስና ማለት የክርስቶስን መንጋ እንደ ባለቤቱ አድርጐ መጠበቅ ማለት ነው:: ሥልጣኑ በምድር "ሸክም: ዕዳ" ሲሆን በሰማይ ግን "ክብር" ነው:: ማንም በሥጋው ላይ ካልጨከነ በቀር ጵጵስናን አይመኝም::

ቅዱስ ጳውሎስ "ሠናየ ግብረ ፈተወ - ማንም ጵጵስናን ቢመኝ መልካም ሥራን ተመኘ" [፩ጢሞ.፫፥፩] [3:1] ማለቱን ይዞ "ሹሙኝ" ማለት ወደ ማይጠፋ እሳት የሚያስጥል ከባድ ውሳኔ ነው:: ምክንያቱም አንድ ክርስቲያን የሚጠየቅ በራሱ ኃጢአት ሲሆን አንድ ካህን ደግሞ ስለ ልጆቹ ይጠየቃል:: የከፋው ግን የጳጳሱ ነው::

አንድ ጳጳስ ቢጾም ቢጸልይም እንኳ ለድኅነቱ በቂ አይደለም:: ምክንያቱም በመንበሩ ላይ ያስቀመጠው መንጋውን እንጂ ራሱን እንዲያድን አይደለምና:: ጌታ እንዳለ መልካም እረኛ "ይሜጡ ነፍሶ ቤዛ አባግኢሁ - መልካሙ እረኛ ስለ በጐቹ ቤዛ ራሱን አሳልፎ የሚሰጥ ነው::" [ዮሐ.፲ [10] ስለዚህም ክህነት [ጵጵስና] ሐዋርያዊ አገልግሎት ከባድም ኃላፊነት ነው::

አባቶቻችን ሐዋርያትና ተከታዮቻቸው ሐዋርያውያን ታላላቅ የጵጵስና መንበሮችን መሥርተው: ትምሕርቱን ከነ ወንበሩ አስተላልፈዋል:: ከእነዚህ መንበረ ጵጵስናዎች አራቱ የበላይ ናቸው::

እነዚህም የቅዱስ ጴጥሮሱ የሮም: የቅዱስ ዮሐንሱ የአንጾኪያ: የቅዱስ ማርቆሱ የእስክንድርያና የቅዱስ ጳውሎሱ የኤፌሶን መናብርት ናቸው::

እነዚህ መንበሮችም ከክርስቶስ ዕርገት እስከ ፬፻፵፫ [፬፻፶፩] [443 (451] ዓ/ም: ጉባኤ ኬልቄዶን ድረስ በአንድነት ቆይተው ተለያይተዋል:: ከእነዚህ መናብርት መካከል የእስክንድርያው [የግብጹ] እና የአንጾኪያው [የሶርያው] ዛሬም ድረስ በተዋሕዶ እምነት የጸኑ ናቸው::

የእኛ ቤተ ክርስቲያንም ሐዋርያዊት እንደ መሆኗ ሐዋርያትን መስለው: ሐዋርያትን አህለው የተነሱ አበው ጳጳሳትን በየጊዜው በበዓላት ታስባለች: ታከብራለች::

በተለይ ደግሞ የእስክንድርያና የአንጾኪያ በርካታ አባቶችን እናከብራለን:: እነርሱ ለቀናች ሃይማኖትና ለመንጋው ሲሉ ብዙ መከራን በአኮቴት ተቀብለዋልና:: ከእነዚህም መካከል አንዱ ቅዱስ ቆዝሞስ የእስክንድርያ [የግብጽ] ፶፰ [58] ኛ ሊቀ ጳጳሳት የነበረ አባት ነው:: ዘመኑ እስልምና የሰለጠነበት ነበርና በዚያ ጊዜ እረኝነት [ጵጵስና] መመረጥ እንደ ዛሬው ዘመን ሠርግና ምላሽ አልነበረም:: በከሃዲዎች እሳትና ስለት መከራን ለመቀበል መወሰን እንጂ::

ከ6ኛው መቶ ክ/ዘመን በኋላ በዓለማችን ከተነሱ ሊቃነ ጳጳሳት ለግብጻውያኑ ቤተ ክርስቲያን ልዩ ቦታ አላት:: ምክንያቱም በወቅቱ በጎቻቸውን [ምዕመናንን] ለመጠበቅ ከግብጽ ከሊፋዎች የግፍ ጽዋዕን ጠጥተዋልና:: ከነዚህም አንዱ የእመቤታችን ፍቅር የበዛለትና በዚህ ቀን ያረፈው ቅዱስ ቆዝሞስ ነው::

† አምላከ ቅዱሳን ሊቃውንት በጸሎታቸው እኛንም: ቤተ ክርስቲያናችንንም ከክፉ ጠላት ይጠብቅልን::

🕊

[ † መጋቢት ፫ [ 3 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. ቅዱስ አባ ቆዝሞስ [የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት]
፪. አባ በርፎንዮስ ክቡር

[ † ወርኀዊ በዓላት ]

፩. በዓታ ለእግዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ
፪. ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና
፫. ቅዱሳን ሊቃነ ካህናት አበው [ዘካርያስና ስምዖን]
፬. አባ ሊባኖስ ዘመጣዕ
፭. አቡነ ዜና ማርቆስ
፮. አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ዘደብረ በንኮል

" ነገር ግን ወንድሞች ሆይ! እናንተ የተማራችሁትን ትምህርት የሚቃወሙትን: መለያየትንና ማሰናከያን የሚያደርጉትን ሰዎች እንድትመለከቱ እለምናቹሃለሁ:: ከእነርሱ ዘንድ ፈቀቅ በሉ:: እንዲህ ያሉት ለገዛ ሆዳቸው እንጂ ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ አይገዙምና:: በመልካምና በሚያቆላምጥ ንግግርም ተንኮል የሌለባቸውን ሰዎች ልብ ያታልላሉ::" † [ሮሜ ፲፮፥፲፯]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
💖                    🕊                     💖

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

                        †                           

†   🕊   ዘ ወ ረ ደ   🕊   †


[ የጾምን መግባት ምክንያት በማድረግ የተሰጠ ትምህርት ! ]

💖

" የእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን እንደዚህ በልጆቿ ስትደምቅ እናንተም ጉባኤውን ለመታደም ደስ ብሏችሁ ተሰባስባችሁ ስትመጡ ዐይቼ ሐሴት አደረግሁኝ ፤ ደስም አለኝ፡፡ ፊታችሁ እንዴት በደስታ እንደተመላ ስመለከት ጠቢቡ ፦ "ልብ ደስ ሲለው ፊት ይበራል" እንዳለው ልባችሁ ምን ያህል እንደተደሰተ ተገነዘብሁኝ፡፡ [ምሳ.፲፭፥፲፫] በመሆኑም ዛሬ ማለዳ የተነሳሁት ከወትሮ በተለየ ትጋት ነው፡፡ ይኸውም ይህን መንፈሳዊ ደስታ ከእናንተ ጋር እንድካፈልና ቀጣዩ ወራት ቁስለ ነፍሳችሁ ድኅነት የሚያገኝበት ወርሐ ጾም መኾኑን አበስራችሁ ዘንድ ነው፡፡ የሁላችንም ጌታ ልዑል እግዚአብሔር ልክ እንደ ደግ አባት ባለፉት ወራት ለሠራነው ኃጢአት ሥርየት እናገኝበት ዘንድ ሽቶ መድኃኒት የሚሆን ቅዱስ ጾምን አዘጋጅቶልናል፡፡

ስለዚህ የነፍሳችን ጠባቂ እግዚአብሔር የሕመማችንን ፈውስ የምናገኝበትን መድኃኒት ስላዘጋጀልን እያመሰገንን ወርሐ ጾሙን ደስ ብሎን ልንቀበለው ይገባናል፡፡ ከእኛ መካከል ጾም በመግባቱ አንድስ እንኳን የሚከፋው ወይም የሚበሳጭ ሊኖር አይገባም፡፡ ወርሐ ጾሙን እንዲህ ደስ ተሰኝተን መቀበላችንን ዐይተውም አሕዛብ ይፈሩ ፤ አይሁድም ይራዱ፡፡ በእኛና በእነርሱ መካከል ሰፊ ልዩነት እንዳለ ዐይተው የማሩ፡፡

የእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን በዓል የምትሠራው ምእመናን ራሳቸውን መግዛት እንዲችሉ ፣ በበጎ ምግባር ያጌጡ ያሸበረቁ እንዲሆኑ እንደሆነ እነርሱ ግን በዓላትን የሚያደርጉት በዘፈንና በስካር ይህንም በመሰለ በሌላ ጸያፍ ግብር ለመንከባለል እንደኾነ ለይተው ይወቁ፡፡ በእርግጥም በዓል ተከበረ የሚባለው ፦ ሰዎች ነፍሳቸውን ካዳኑበት ፣ ውስጣዊ ሰላምንና ፍቅረ ቢጽን [ወንድምን መውደድ] ገንዘብ ካደረጉበት ፣ ዕለት ዕለት ከሚያጋጥማቸው የነፍስ መታወክ ካረፉበት ፣ ያለ ሁካታና ጋጋታ እንዲሁም እንስሳትን በማረድ ከልክ በላይ ከኾነ መብልና መጠጥ ርቀው ያከበሩት እንደሆነ ነው፡፡

ከዚህ በተጨማሪ በዓል ተከበረ የሚባለው ፦ አርምሞንና ጸጥታን ፣ ፍቅርንና ደስታን ፣ ሰላምንና ራስን መግዛትን ፣ እንዲሁም ሌሎች እዚህ መዘርዘር የማንችላቸውን ብዙ ምግባር ትሩፋቶችን ገንዘብ ያደረግንበት እንደ ኾነ ነው፡፡"

[  ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ  ]

         †               †               †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

🕊

[ † እንኳን ለጻድቁ አባታችን ቅዱስ ጐርጐርዮስ ረዓዬ ኅቡዓት ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ]

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †


🕊 † ቅዱስ ጐርጐርዮስ ረዓዬ ኅቡዓት † 🕊

† ቅዱስ ጐርጐርዮስ ሃገሩ ሮሃ [ሶርያ አካባቢ] ሲሆን ረዓዬ ኅቡዓት [ምሥጢራትን የተመለከተ] ይባላል:: ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ :-
ቅዱሱ ተወልዶ ባደገባት ሃገር ይህ ቀረው የማይባል ኃጢአተኛ ሰው ነበር:: ታዲያ ምንም ኃጢአተኛ ሰው ቢሆን እመቤታችን ድንግል ማርያምን በፍፁም ልቡ ይወዳት ነበርና በመዳን ቀን ጥሪ ለንስሐ አበቃችው::

ከዚያች ዕለት ጀምሮም ቅዱስ የእግዚአብሔር ሰው : ንጹሕ የቤተ ክርስቲያን መስዋዕት : ጽኑዕ የበርሃ ምሰሶ ሆነ:: ድንግል እመቤታችንም ከነሥጋው ወደ ሰማያት ወስዳ ገነትና ሲዖልን አሳይታ : ከአዳም : ኖኅ : አብርሃም : ሙሴ : ዳዊትን ከመሰሉ ቅዱሳን ጋር አስተዋውቃ : ከዚህም በላይ የሆነና በሰብአዊ አንደበት የማይነገር ብዙ ምሥጢር አሳይታ ወደ ምድር መልሳዋለች::

ቅዱስ ጐርጐርዮስ በሰማይ [በገነት] በነበረው ቆይታ ክብረ ቅዱሳንን ተመልክቶ አድንቋል:: በተለይ በፍጹምነት ድንግልናቸውን የጠበቁ ቅዱሳንና ቅዱሳት ደናግል አኗኗራቸው ከአምላክ እናት : ከሰማይ ንግሥት : ከእመቤታችን ከድንግል ማርያም ጋር መሆኑን አይቷል::

"የለበሱት ልብስም በፍጡር አንደበት ተከናውኖ ሊነገር የሚቻል አይደለም" ይላል:: የደናግል ፊታቸው ከፀሐይ ፯ [7] እጅ ያበራልና ግርማቸው ያስፈራል::

ቅዱሱ ሰው በዚያው በሰማይ ሳለ ደግሞ ይህንን ተመለከተ:: አንድ አረጋዊ : ጽሕሙ ተንዠርግጐ : የብርሃን ካባ ላንቃ ለብሶ ይመጣል:: ቅዱሳን መላእክት በፊት በኋላ : በቀኝ በግራ ከበውት ሳለ እግዚአብሔርን ሊያመሰግን ጀመረ::

"እግዚኦ እግዚእነ : ጥቀ ተሰብሐ ስምከ በዲበ ምድር [አቤቱ ጌታችን : በምድር ሁሉ ስምህ የተመሰገነ ሆነ]" ሲል . . . መላእክቱ በዝማሬ አጀቡት:: በዚህ ጊዜም ታላቅ መናወጥ ሆነ:: ደናግሉም የቅዱሱን ሽማግሌ በረከቱን ተሳተፉ::

ይህ አመስጋኝ ሽማግሌ ልበ-አምላክ : ጻድቅ : የዋህና የእሥራኤል ንጉሥ የሆነው ዳዊት ነበር:: በምን ታወቀ ቢሉ :- በበገናው:: አንድም እመቤታችን "አባቴ ዳዊት!" ብላ ስትጠራው ጐርጐርዮስ ሰምቷልና::

በመጨረሻም እመቤታችንን በፍጹም ክብርና ግርማ ተመልክቷት ሐሴትን አድርጓል:: እመ-ብርሃንም "ተወዳጅና ንጹሕ ሰው ነህ" ስትል ቅዱስ ጐርጐርዮስን አመስግናዋለች:: ስለዚህ ዓለምም እንዲህ የሚል መልእክትን ልካለች::

"ልጆቼ ሆይ! ከብርሃን ጨለማን : ከደግነት ክፋትን : ከጽድቅ ይልቅ ኃጢአትን . . . ምነው መምረጣችሁ? እኔ ስለ እናንተ በየቀኑ እየለመንሁ እነሆ አለሁ:: ወደ ጨለማ ገሃነም እንዳትወርዱ እባካችሁ ንስሐ ግቡ !"

ቅድስት ድንግል ማርያም ይህንን ለቅዱሱ ሰው ነግራው : ቅዱስ ዳዊትን አስከትላ : በግሩማን መላእክት ታጅባ ወደ ውሳጤ መንጦላዕት [የእሳት መጋረጃዎች ወደ ተተከሉበት ድንኳን] ገባች:: በዚያም ተመሰገነች::

ለዛም አይደል ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ:- "ይዌድስዋ መላእክት ለማርያም በውስተ ውሳጤ መንጦላዕት : ወይብልዋ : በሐኪ ማርያም ሐዳስዩ ጣዕዋ::" ሲል ያመሰገናት::

ቅዱስ ጐርጐርዮስም ከሰማይ ቆይታ መልስ ያየውን ሁሉ ጽፎ ለአበው ሰጥቷል:: ስለዚህም ረዓዬ ኅቡዓት [ምሥጢራትን ያየ] ይሰኛል:: ቅዱሱ ተረፈ ዘመኑን በተጋድሎ ፈጽሞ በዚህች ቀን አርፏል::

† የቅዱሱ እመቤት ድንግል እመ ብርሃን መዓዛ ፍቅሯን ታብዛልን::

🕊

[ † መጋቢት ፪ [ 2 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. ቅዱስ ጐርጐርዮስ ረዓዬ ኅቡዓት [ዘሃገረ ሮሃ]
፪. አቡነ መክፈልተ ማርያም ጻድቅ [ኢትዮጵያዊ]
፫. አባ መከራዊ ዘሃገረ ኒቅዮስ [አረጋዊ: ጻድቅ: ጳጳስና ሰማዕት]

[ † ወርኀዊ በዓላት ]

፩. ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት
፪. ቅዱስ ታዴዎስ ሐዋርያ
፫. ቅዱስ ኢዮብ ጻድቅ ተአጋሲ
፬. ቅዱስ አቤል ጻድቅ
፭. ቅዱስ አባ ጳውሊ ገዳማዊ [ታላቁ]
፮. ቅዱስ ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ
፯. አባ ሕርያቆስ ዘሃገረ ብሕንሳ

" ኃጢአተኞችን ሊያድን ክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዓለም መጣ የሚለው ቃል የታመነና ሁሉ እንዲቀበሉት የተገባ ነው:: ከኃጢአተኞችም ዋና እኔ ነኝ:: ስለዚህ ግን የዘላለምን ሕይወት ለማግኘት በእርሱ ያምኑ ዘንድ ላላቸው ሰዎች ምሳሌ እንድሆን ኢየሱስ ክርስቶስ ዋና በምሆን በእኔ ላይ ትዕግስቱን ሁሉ ያሳይ ዘንድ ምሕረትን አገኘሁ::" † [፩ጢሞ. ፩፥፲፭]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
💖                    🕊                     💖

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

እሑድ - መጋቢት 01 2016 ዓም

ሩት 1-4

ሰላም ለሁላችሁ ይሁን! በዛሬው ንባባችን ከምዕራፍ 1-4 ድረስ በማንበብ መጽሐፈ ሩትን ጀምረን እናጠናቅቃለን።

ከንባብ በፊት የሚደረግ ጸሎት፡ “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፤ የአንተን ቃላት እሰማ እና እረዳ ዘንድ፥ እንዲያውም ፈቃድህን ለመፈጸም እበቃ ዘንድ የልቤን ጆሮዎች እና ዓይኖች ክፈትልኝ።” (ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ)

በዛሬው ንባባችን ላይ አቤሜሌክና ቤተሰቡ ወደ ሞአብ ስለመሰደዳቸው፥ ኑኃሚን ከሩት ጋር ወደ ቤተልሔም መመለሷ፥ ሩት በቦዔዝ እርሻ ቃርሚያ ለመልቀም ስለ መሄዷ፥ በሩት እና ቦዔዝ መካከል ስለተፈጠረው ነገር፥ ስለ ጋብቻቸው እና በመጨረሻም ስለ ዳዊት የትውልድ ሐረግ እናነባለን።

በዛሬው እለት የክለሳ ጥያቄ አይኖረንም።

መልካም ንባብ!
/channel/OrthodoxTewahdoBooks

/channel/+3kpzSPDfiVMzYzQ

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

https://youtu.be/bRKiuAEcqOs?si=fSECZtfACsiH7ywf

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

🕊                  💖                   🕊      
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

[    ዐቢይ ጾም   [   ጾመ እግዚእ  ]     ]


💖 



" ትሕትናን እንደ ልብስ ታጠቁ "

-----------------------------------------------

🕊  †  [        ት ሕ ት ና         ]  †  🕊


🕊 [ በመምህራችን በቀሲስ ኅብረት የሺጥላ ]

💖          ድንቅ ትምህርት          💖


" እንዲሁም ፥ ጐበዞች ሆይ ፥ ለሽማግሌዎች ተገዙ፤ ሁላችሁም እርስ በርሳችሁ እየተዋረዳችሁ ትሕትናን እንደ ልብስ ታጠቁ ፥ እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማልና ፥ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል።

እንግዲህ በጊዜው ከፍ እንዲያደርጋችሁ ከኃይለኛው ከእግዚአብሔር እጅ በታች ራሳችሁን አዋርዱ ፤ እርሱ ስለ እናንተ ያስባልና የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉት።" [ ፩ጴጥ.፭፥፭ ]

[   ትምህርቱን በማስተዋል ይከታተሉ  ]

         †              †               †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬
                       👇

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

                       †                       

[ ተቀነዩ ለእግዚአብሔር በፍርሃት  ]

💖

መዝሙር ፦ " ተቀነዩ ለእግዚአብሔር በፍርሃት ወተሐሠዩ ሎቱ በረዓድ እስመ ለዓለም ምሕረቱ ለትውልደ ትውልድ ጽድቁ ንሕነሰ ሕዝቡ ባኡ ቅድሜሁ በተጋንዮ ወውስተ አዕፃዲሁ በስብሐት እመንዎ እስመ ለዓለም ምሕረቱ ለትውልደ ትውልድ ጽድቁ ንሕነሰ ሕዝቡ ንጹም ጾመ ወናፍቅር ቢጸነ ወንትፋቀር በበይናቲነ እስመ ለዓለም ምሕረቱ አክብሩ ሰንበተ ተገበሩ ጽድቀ እስመ ሰንበትሰ በእንተ ሰብእ ተፈጥረት እስመ ለዓለም ምሕረቱ ምሕረተ ወፍትሐ አሐሊ ለከ እዜምር ወእሌቡ ፍኖተ ንጹሐ እስመ ለዓለም ምሕረቱ ለትውልደ ትውልድ ጽድቁ ንሕነሰ ሕዝቡ አባግዓ መርዔቱ።

ትርጉም ፦

[ ለእግዚአብሔር በፍርሃት ተገዙ ፤ ለእርሱም በመገዛታችሁ ደስ ይበላችሁ እግዚአብሔር ቸር ምሕረቱም ለዘለዓለም ፣ እውነቱም ለልጅ ልጅ ነውና፡፡ እኛስ ሕዝቡ የማሰማሪያው በጎች ነን ፤ ወደ ደጁ በመገዛት ፣ ወደ አደባባዮችም በምስጋና ግቡ ፤ ጾምን እንጹም ፤ ባልንጀሮቻችንን እናፍቅር ፤ እርስ በርሳችንም እንፋቀር።

ሰንበት ስለሰው ተሠርታለችና ሰንበትን እናክብር:: እውነትንም እንሥራ ፤ አቤቱ ምሕረትንና ፍርድን እቀኝልሃለሁ ፤ እዘምራለሁ ፤ ንጹሕ መንገድንም
አስተውላለሁ:: ]

በማለት ሊቁ የምግባራት ፣ የጥበባት ፣ የሃይማኖትና የአምልኮት መጀመሪያ ፈሪሃ እግዚአብሔር መሆኑ ለማስገንዘብ ዝማሬውን በፈሪሃ እግዚአብሔር ጀምሯል። [ መዝ ፪ ፥ ፲፩፣ መዝ ፺፱ ፥ ፭ ]

ጾም የትሩፋት መጀመሪያ እንደሆነ ፈሪሃ እግዚአብሔርም የጥበባት መጀመሪያ ነው ፤ ቀዳሚነትንና ቀዳሚነትን በማነጻጸር የትሩፋት መጀመሪያ በሚሆን ያውም በዐቢይ ጾም መጀመሪያ የጥበባት መጀመሪያ በሆነው በፈሪሃ እግዚአብሔር ጀምሯል። ባሕረ ጥበባት ቅዱስ ያሬድ እግዚአብሔርን ደስ ለማሰኘት ለእግዚአብሔር በፍርሃት መገዛት እንዳለብን ፤ በመገዛታችንም ደስተኞች መሆን እንዳለብን ፤ በዘለዓለም ምሕረቱ ፣ ለልጅ ልጅ በሚተርፈው እውነቱ እኛ በጎቹን እንደታደገን ፤ የዚህ እውነታ ተጠቃሚ የምንሆነው ደግሞ ለእርሱ ስንገዛ ፣ ስንጾም ፣ ስናመሰግን ፣ ስንዋደድ ፣ ሰንበትን ስናከብር ፣ ጽድቅ ሁሉ ስናደርግ እንደሆነ ክርስቲያናዊ ጥብቅ መመሪያ ነግሮናል፡፡

†                       †                       †
💖                    🕊                    💖

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

🕊

[ ✞ እንኩዋን ከተባረከ ወር መጋቢትና ከሁለተኛው መንፈቀ ዘመን የመጀመሪያ ዕለት በሰላም አደረሳችሁ ✞ ]

ወርኀ መጋቢት መዐልቱና ሌሊቱ እኩል [12:00] ናቸው:: ከዛሬዋ ዕለት ጀምሮ ለሚቀጥሉት ፮ [6] ወራት [ ፻፹፮ [186] ቀናት] ከማይጠቅም ወሬ ተቆጥበን: ከክፋትም ርቀን መልካሙን የእግዚአብሔር ጐዳና ለመከተል ራሳችንን ልናዘጋጅ ይገባል::

በዚህ ዕለትም ከአዳም ፰ [8] ኛ ትውልድ የሆነው አባታችን ማቱሳላ በዓሉ ይከበራል:: ቅዱስ ማቱሳላ የጻድቅ ሰው ኄኖክ ልጅ: የደጉ ላሜሕ አባት ሲሆን በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ረዥም ዕድሜ [፱፻፷፱ [969] ዓመት] የቆየ ባለ ረዥም ዕድሜ አባት ነው:: ከአሥሩ ቅዱሳን አባቶች አንዱ ነው::

፲ [ 10 ] ቅዱሳን አባቶች ማለት :-

- ቅዱስ አዳም አባታችን
- ሴት
- ሔኖስ
- ቃይናን
- መላልኤል
- ያሬድ
- ኄኖክ
- ማቱሳላ
- ላሜሕ
- ኖኅ ናቸው::


🕊  †  ቅዱስ በርኪሶስ  †    🕊

በዚች ቀን የኢየሩሳሌም አገር ኤጲስቆጶስ ቅዱስ በርኪሶስ አረፈ።ይህም አባት ክርስቲያኖችን በሚወዳቸው በቄሳር እለእስክንድሮስ ዘመነ መንግስት ተሹሞ ሳለ ሀዋርያት ሲጠብቋቸው እንደነበር በበጎ አጠባበቅ ህዝቡን ጠበቃቸው ።

" ከጥቂት ጊዜ በኃላ እለእስክንድሮስ ሞተ ከእርሱ በኃላ ቄሳር መክስሚያኖስ ነገሰ። ክርስቲያኖችውም በፅኑእ መከራ አሰቃያቸው ከእርሳቸውም ብዙዎችን ገደላቸው።

ሀገሮቻቸውን ትተው የተሰደዱም አሉ። ይህም አባት ሽሽቶ ወደ ገዳም ገባ ህዝቡም ፈልገው አጡት።

ከዚህም በኃላ ስሙ ዲዮስ የተባለ ሌላ ኤጲስቆጶስ በላያቸው ሾሙ። እርሱም በጥቂት ቀን አረፈ። ከዚህ በኃላ ስሙ አግርንዲኖስ የሚባል ሌላ ኤጲስቆጶስ ሾሙ።

የስደቱም ወራት በአለፈ ጊዜ ይህ አባት በርኪሶስ ወደ ኢየሩሳሌም ከተማ ተመለሰ ።አግርንዲኖስ የሚባል ሌላ ኤጲስቆጶስ ሹመው አገኛቸው።

ወደርሳቸውም በደረሰ ጊዜ ህዝብ በመምጣቱ ደስ አላቸው አግርንዲኖስም ተመልሶ በመንበረ ጵጵስናው ላይ እንዲ ቀመጥ ለመነው በታላቅ ድካምም በወንበሩ ላይ አስቀመጡት። ከአግርንዲኖስም ጋራ አንዲት አመት ኖረ አግርንዲኖስም አረፈ።

አባ በርኪሶስም እጅግ እስኪያረጅና እስኪያረጅና እስኪደክም ድረስ ኖረ ወገኖቹንም ሌላ ኤጲስ ቆጶስ በላያቸው እንዲሾሙ ለመናቸው እነርሱም አይሆንም አሉ።

በዚያም ወራት የቀጰዶቅያ ኤጲስቆጶስ ስሙ እለእስክንድሮስ የሚባል አንድ ሰው ነበር። እርሱም በውስጥዋ ሊፀልይና ወዳገሩ ሊመለስ ወደ ኢየሩሳሌም መጣ።ስራውንም በጨረሰ ጊዜ የበአሉም ቀኖች በተፈፀሙ ጊዜ ወዳገሩ ሊመለስ ወደደ።

በመድኃኒታችን ትንሳኤ በአል በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ወደ ኢየሩሳሌም ከተማ መግቢያ ወደ እገሌ ደጃፍ ውጡ ወደ ደጃፉ መጀመሪያ የሚገባውን ያዙት በጵጵስና ስራም ይረዳው ዘንድ ከበርኪሶስ ጋር አድርጉት የሚል ቃል እነሆ ተሰማ።

ወጥተውም ወደ ደጃፉ በደረሱ ጊዜ እለእስክንድሮስን አገኙት ይረዳውም ዘንድ ያለ ፈቃዱ ከአባት በርኪሶስ ጋራ አደረጉት። እስከሚአርፍበትም ጊዜ አብሮት ኖረ።

መላ የህይውቱ ዘመን አንድ መቶ አስራ ሰባት አመት ሆነ ኤጲስቆጶስነት ሳይሾም ሰማንያ አንድ አመት ኖረ በሹመቱም ላይ ሰላሳ ስድስት አምታትን ኖረ። እግዚአብሄርንም አገልግሎ በሰላም አረፈ።


🕊  †  ቅዱስ እለእስክንድሮስ  †  🕊

በዚችም እለት የሰማእቱ የቅዱስ እለእስክንድሮስ መታሰቢያው ነው። ይህም ቅዱስ ሰማእት የሮም ሀገር ሰው ነው ለእርሱ ባለመታዘዙና ለረከሱ ጣኦቶቹ ባለመሰዋቱ ከሀዲው መክስሚያኖስ ፁኑእ ስቃይን አሰቃየው።

እጅግ ከባድና ታላቅ የሆነ ደንጊያ በእጆቹና በእግሮቹ ላይ አስሮ ሰቀለው። ብዙ ግርፋትንም ገረፈው ጎኖቹንም ቀደደ በፊቱም ላይ የእሳት መብራት ጨመሩ።

ስቃዩንም ባልፈራ ጊዜ ራሱን በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘ። በመንግስተ ሰማያትም የሰማእታትን አክሊል ተቀዳጀ።

ዕድሜ ማቱሳላን ለንስሃ አምላከ ቅዱሳን ይስጠን!

🕊

[ † መጋቢት ፩ [ 1 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. ቅዱስ ማቱሣላ [በ፱፻፷፱ ዓመቱ ያረፈበት]
፪. ቅዱስ በርኪሶስ ዘኢየሩሳሌም
፫. ቅዱስ እለእስክንድሮስ
፬. ቅዱስ መርቆሬዎስ
፭. አባ ሚካኤል ዘሃገረ አትሪብና አባ ዮሐንስ ዘሃገረ ቡርልስ

[ ሃይማኖተ አበውን: ግፃዌንና ስንክሳርን ያዘጋጁ ናቸው ]

[ † ወርኀዊ በዓላት ]

፩. ልደታ ለማርያም ድንግል እግዝእትነ
፪. ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና
፫. ቅዱስ ራጉኤል ሊቀ መላዕክት
፬. ቅዱስ በርተሎሜዎስ ሐዋርያ
፭. ቅዱስ ሚልኪ ትሩፈ ምግባር

" ከእንቅልፍ የምትነሱበት ሰዓት አሁን እንደ ደረሰ ዘመኑን እወቁ:: ካመንንበት ጊዜ ይልቅ መዳናችን ዛሬ ወደ እኛ ቀርቧልና:: ሌሊቱ አልፏል: ቀኑም ቀርቧል:: እንግዲህ የጨለማውን ሥራ አውጥተን የብርሃንን ጋሻ ጦር እንልበስ::" [ሮሜ.፲፫፥፲፩]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
💖                    🕊                     💖

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

                       †                       

[  🕊 የዐቢይ ጾም ሳምንታት  🕊  ]

💖

ዐቢይ ጾም በያዘው በ፶፭ ቀኑ ውስጥ ሰባት ቅዳሜና ስምንት እሑዶቸን ይዟል ፤ የእነዚህ የስምንቱ እሑዶች የተለያየ ስያሜ አላቸው፡፡ ስያሜአቸውንም የሰጣቸው የቤተ ክርስቲያናችን የዜማው ሊቅ የሆነው ቅዱስ ያሬድ ነው፡፡ ዘወረደቅድስትምኩራብደብረዘይትገብረ ኄርኒቆዲሞስመፃጉዕሆሣዕና ናቸው፡፡
 
[ ፩ ኛ. ዘወረደ ፦ ]

በመጀመርያው ሳምንት ዘወረደ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሰማያት መውረዱን ፣ ከአመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም መወለዱን እና እኛን ማዳኑን በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን የሚወሳበትና የሚዘከርበት ወቅት ሲሆን ይህንንም የሚዘክሩ መዝሙሮች ይቀርባሉ ፤ ትምህርቶች ይሰጣሉ ፤ ይህንንም እያሰብን ጾሙን እንጾማለን፡፡

ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ፥ ለሐዋርያት እንዲሁም ለቀደሙ አባቶቻችን በሥርዓቱ ጹመን እንዲንጠቀም እርዳን ፤ አሜን !

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፥ ወለወላዲቱ ድንግል ፥ ወለመስቀሉ ክቡር !

†                       †                       †
💖                    🕊                    💖

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

🕊                  💖                   🕊      
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

[    ዐቢይ ጾም   [   ጾመ እግዚእ  ]     ]


💖  የዐቢይ ጾም የመጀመሪያ ሳምንት ፦



" በክርስቶስ ያለውን መልካሙን ኑሮአችሁን የሚሳደቡ ሰዎች ክፉን እንደምታደርጉ በሚያሙበት ነገር እንዲያፍሩ በጎ ሕሊና ይኑራችሁ

የእግዚአብሔር ፈቃድ እንዲህ ቢሆን ፥ ክፉ ስለ ማድረግ ሳይሆን በጎ ስለ ማድረግ መከራን ብትቀበሉ ይሻላችኋልና።

ክርስቶስ ደግሞ ወደ እግዚአብሔር እንዲያቀርበን እርሱ ጻድቅ ሆኖ ስለ ዓመፀኞች አንድ ጊዜ በኃጢአት ምክንያት ሞቶአልና ፤ በሥጋ ሞተ በመንፈስ ግን ሕያው ሆነ" [ ፩ጴጥ.፫፥፲፮ ]

-------------------------------------------------

🕊  †  [       በጎ ሕሊና       ]  †  🕊


🕊  [  በመምህራችን በዲ/ን ብርሃኑ አድማስ  ]

💖          ድንቅ ትምህርት          💖

- የበጎ ሕሊና ትርጉም !
- እግዚአብሔር የሚቀበለው ጾም !
- የቅበላ ትርጉም ምንድን ነው ! ?
- ይህ ሁሉ መከራ ስለምን ሆነብን ! ?

[   ትምህርቱን በማስተዋል ይከታተሉ  ]

         †              †               †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬
                       👇

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

🕊

[ † እንኳን ለታላቁ ነቢይና ሰማዕት ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ]

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †


🕊  ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ   🕊

† ቅዱስ ወንጌል ላይ ከእመቤታችን ቀጥሎ የነ ዘካርያስን ቤተሰብ ያህል ክብሩ የተገለጠለት ፍጡር ይኖራል ብሎ መናገሩ ይከብዳል:: ቅዱስ ሉቃስ ወንጌሉን የጀመረው በዚህ ቅዱስ ቤተሰብ ነውና መንፈስ ቅዱስ እንዲህ ሲል አጽፎታል::
"ዘካርያስ ካህኑና ቅድስት ኤልሳቤጥ በሰውና በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ የሚኖሩ ጻድቃን ነበሩ" ይላቸዋል:: [ሉቃ.፩፥፮]

የሰውን እንተወውና በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ መኖር ምን ይረቅ? ለዚህ አንክሮ [አድናቆት] ይገባል! እሊህ ቅዱሳን ባልና ሚስት ግን መካኖች በመሆናቸው ልጅ ሳይወልዱ ዘመናቸው አልፎ ነበር:: እንደ ቤተ ክርስቲያን ትውፊት ዕድሜአቸው የኤልሳቤጥ ፺ የዘካርያስ ደግሞ ፻ ደርሶ ነበር::

ፍጹም መታገሳቸውን የተመለከተ ጌታ ግን በስተ እርጅናቸው ከሰው ሁሉ በላይ የሆነ: ትንቢት ለብቻው የተነገረለት [ኢሳ.፵፥፫] , ሚል.፫፥፩] ታላቅ ነቢይን ይሰጣቸው ዘንድ መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤልን ላከላቸው::

ቅዱስ ዘካርያስ ሰው ነውና ከደስታ ብዛት በመከራከሩ ድዳ ሆነ:: ቅድስቲቷ ግን መስከረም ፳፮ [26] ቀን ታላቁን ሰው ጸንሳ ለ፮ [6] ወራት ራሷን ሠወረች:: በ፮ [6] ኛው ወር የፍጥረት ሁሉ ጌታ በተጸነሰ ጊዜ የአርያም ንግሥት ድንግል እመቤታችን ደጋ ደጋውን ወደ ኤልሳቤጥ መጣች:: ሁለቱ ቅዱሳት የእህትማማች ልጆች ናቸው::

የአምላክ እናቱ ስትደርስና "ሰላም" ስትላቸው መንፈስ ቅዱስ በእናትና ልጅ ወርዶ ኤልሳቤጥ በምስጋና: ዮሐንስ ደግሞ ገና በማሕጸን ሳለ በደስታ ዘለለ [ሰገደ]:: ከዚህ በሁዋላ ሰኔ ፴ [30] ተወልዶ: አባቱ ዘካርያስ "ዮሐንስ" ሲለው አንደበቱ ተፈትቶለታል::

ቅዱስ ዮሐንስ ከተወለደ ፪ [2] ዓመት ከ፮ [6] ወር በሆነው ጊዜ ሰብአ ሰገል በመምጣታቸው በእሥራኤል ምድር የሚገኙ ሕጻናትን ሔሮድስ ቁዝ አስፈጀ:: ትንሽ ቆይቶም አይሁድ ለሔሮድስ ስለ ቅዱሱ ሕጻን ነገሩት:: "ሲጸነስ የአባቱን አንደበት የዘጋ: ሲወለድ ደግሞ የከፈተ 'ዮሐንስ' የሚባል ሕጻን አለና እሱንም ግደል" አሉ::

እናቱ ቅድስት ኤልሳቤጥ ይዛው ስትሸሽ ካህኑን ዘካርያስን ግን በቤተ መቅደስ መካከል ገድለውታል:: አረጋይት ኤልሳቤጥም ሕጻኑን እያሳደገች በገዳመ ዚፋታ ለ ፫ [3] ፭ [5] ዓመታት ቆይታለች:: ቅዱስ ዮሐንስ ፭ [5] ፯ [7] ዓመት ሲሞላው ግን እዚያው በበርሃ እናቱ ዐረፈች:: ከሰማይ ዘካርያስና ስምዖን ወርደው ቀበሯት::

ሕጻኑ ዮሐንስ ሲያለቅስ ድንግል ማርያም ስንት አገር አልፋ ሰማችው:: እርሷም ስደት ላይ ነበረችና:: ከጌታ ጋር በደመና ሒደው ድንግል አቅፋ አጽናናችው:: ጌታንም "እንውሰደው ይሆን?" አለችው:: ጌታችን ግን "ለአገልግሎት እስክጠራው እዚህ ይቆይ" አላት:: ባርካው: አጽናንታውም ተለያዩ::

ቅዱስ ዮሐንስ ከዚህ በሁዋላ በዚያ ቆላ የግመል ጠጉር ለብሶ: ጠፍር ታጥቆ ተባሕትዎውን ቀጠለ:: ለ፳፭ [25] ፳፫ [23] ዓመታትም በንጽሕና ሲኖር ከምድር አራዊትና ከሰማይ መላእክት በቀር ማንንም አላየም:: ይሕችን ዐመጸኛ ዓለምም አልቀመሳትም::

ከዚህ በሁዋላ ፴ [ 30 ] ዘመን ሲሞላው እግዚአብሔር ከሰማይ ተናገረው:: "ሒድ! የልጄን ጐዳና ጥረግ" አለው:: ነቢያት ስለዚህ ነገር ተናግረው ነበርና:: [ኢሳ.፵፥፫]  , [ሚል.፫፥፩] አባቱ ዘካርያስም "ወአንተኒ ሕጻን ነቢየ ልዑል ትሰመይ: እስመ ተሐውር ቅድመ እግዚአብሔር ከመ ትጺሕ ፍኖቶ" [ሉቃ.፩፥፸፮]  ብሎ መንገድ ጠራጊነቱን ተናግሮ ነበርና::

ቅዱስ ዮሐንስ በዚያ ጊዜ በኃይለ መንፈስ ቅዱስ እየገሰገሰ ከበርሃ ወደ ይሁዳ መጣ:: ያዩት ሁሉ ፈሩት: አከበሩት:: ቁመቱ ቀጥ ያለ: ጽሕሙ እንደ ተፈተለ ሐር የወረደ: ጸጉሩ የቁራ ያህል የጠቆረ: መልኩ የተሟላ: ግርማው የሚያስፈራ ገዳማዊ ነውና::

ፈጥኖም ሕዝቡን ለንስሃ ሰበከ: ለንስሃም በርካቶችን አጠመቃቸው:: በዚህ አገልግሎት ለ6 ወራት ቆይቶ ጌታችን ወደ እርሱ ዘንድ መጣ:: ዮሐንስ ሰማይን ከነግሱ: ምድርን ከነልብሱ የያዘ ፈጣሪ "አጥምቀኝ" ብሎ ሲመጣ ደነገጠ:: የሚገባበትም ጠፋው::

"እንቢ ጌታየ! አንተ አጥምቀኝ" አለው:: ጌታ ግን "ፈቅጄልሃለሁ" አለው: አጠመቀው:: በዚህ ምክንያት ይሔው እስከ ዛሬም "መጥምቀ መለኮት" ሲባል ይኖራል:: ቅዱስ ዮሐንስ በመጨረሻ ሔሮድስን ገሰጸው:: ንጉሡም ተቀይሞ ለ፯ [ 7 ] ቀናት አሠረው::

ልደቱን ባከበረ ጊዜ ወለተ ሔሮድያዳ በዘፈን አጥምዳ አስማለችው:: እርሱም የታላቁን ነቢይ ራስ አስቆርጦ በወጪት አድርጐ ሰጣት:: አበው "እምሔሶ ለሔሮድስ ይብላዕ መሐላሁ - ሔሮድስ መሐላውን በበላ በተሻለው ነበር" ይላሉ:: የቅዱስ ዮሐንስ ራሱ በርራ ስትሔድ አካሉን ግን ደቀ መዛሙርቱ ቀብረውታል:: [ማቴ.፫፥፩] , ማር.፮፥፲፬ , [ሉቃ.፫፥፩] , [ዮሐ.፩፥፮] ርጉም ሔሮድስ አንገቱን ካስቆረጠው በሁዋላ የመጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ ራሱ የጸጋ ክንፍ ተሰጥቷት ጌታችን ወዳለበት ደብረ ዘይት ሔዳ በፊቱ ሰገደች:: ቅዱሳን ሐዋርያት በአዩት ነገር ተገርመው ራሱን እጅ ነሷት::

ከዚሕ በሁዋላ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቅዱስ ዮሐንስ ራስ የማስተማር ስልጣን ሰጥቶ አሰናበታት:: በመላው ዓለም ለ፲፭ [15] ዓመታት ስትሰብክ ኑራ ዓረቢያ ውስጥ ዓርፋለች::

† አስማተ-ዮሐንስ መጥምቅ [የመጥምቁ ዮሐንስ ስሞች]

፩. ነቢይ
፪. ሐዋርያ
፫. ሰማዕት
፬. ጻድቅ
፭. ካሕን
፮. ባሕታዊ/ገዳማዊ
፯. መጥምቀ መለኮት
፰. ጸያሔ ፍኖት [መንገድ ጠራጊ]
፱. ድንግል
፲. ተንከተም [የብሉይና የሐዲስ መገናኛ ድልድይ]
፲፩. ቃለ አዋዲ [አዋጅ ነጋሪ]
፲፪. መምሕር ወመገሥጽ
፲፫. ዘየዐቢ እምኩሉ [ከሁሉ የሚበልጥ]

† ጌታችን መድኃኔ ዓለም መጥምቁ ዮሐንስን አስቦ ይቅር ይበለን:: ጸጋውን: በረከቱንና ክብሩንም ያሳድርብን::

🕊

[ † የካቲት ፴ [ 30 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት
[ታላቁ ነቢይና ካህን መጥምቁ ዮሐንስ ሔሮድስ በግፍ አንገቱን ካስቆረጠው በሁዋላ ቅድስት ራሱ ለ፲፭ [15] ዓመታት ዙራ አስተምራ አርፋለች:: በዚህ ዕለትም በልሑክት [በሸክላ ዕቃ] የተገኘችበት በዓል ይከበራል:: በዓሉም "ተረክቦተ ርዕሱ" በመባል ይታወቃል::]
፪. አባ ሚናስ ሊቀ ዻዻሳት

[ † ወርኀዊ በዓላት ]

፩. ቅዱስ ማርቆስ ዘአንበሳ [ሐዋርያ]
፪. አባ ሣሉሲ ክቡር
፫. ቅዱስ ጐርጐርዮስ ነባቤ መለኮት
፬. ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት

" ጌታ ኢየሱስ ለሕዝቡ ስለ ዮሐንስ ሊናገር ጀመረ . . . ምን ልታዩ ወጣችሁ? ነቢይን? አዎን እላችሁአለሁ ከነቢይም የሚበልጠውን . . . እውነት እላቹሃለሁ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ አልተነሳም . . . ነቢያት ሁሉና ሕጉ እስከ ዮሐንስ ድረስ ትንቢት ተናገሩ:: ልትቀበሉትስ ብትወዱ ይመጣ ዘንድ ያለው ኤልያስ ይሕ ነው:: የሚሰማ ጀሮ ያለው ይስማ::" † [ማቴ.፲፩፥፯-፲፭]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
💖                    🕊                     💖

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

ወዳጄ እንዴት ነህ በከፈትካቸው ግሩፕ ውስጥ እያስተላለፍክ ያለኸው መልዕክት በጣም ገንቢ ነው ከቅዱሳን ጋር እርፍ ትውውቅ አለው እንደኔ♥️


ግን እስቲ አሁን እባክህን አንድ ጥያቄ እስከ ነገ ጠዋት ስራ ከሌለህ ፈልገህ መልስልኝ
እኔ ስልተጠየከኝ አጥጋቢ መልስ ለመስጠት እየተዘጋጀው ስለሆነ ነው እስኪ አንተም አግዘኝ

፩ ጠንቋይ ቤት እሄዳለው የምሄደው ግን በሰው ላይ ለማሰራት ሳይሆን ለራሴ ቸግሮኝ ነው። ከቤተክርስትያን አስተምህሮ አንጻር?
፪ ከብት ሞተብኝ እና የሚገርመው ኦርቶዶክሳውያን ጭምር ለምን ወደ ጠንቋይ ወይም አዋቂ አትሄድም አሉኝ እኔ ደግሞ እዮብ የት ሄደ? አልኩኝ አንተስ ምን ትላለህ?

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

                           †                           

[ ተዋሕዶ ፍጽምት የቅዱሳን ሃይማኖት ]
▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬

[    የማይከፈለውን አንከፍለውም !    ]

--------------------------------------------------

" መለኮት ያልተፈጠረ ነው ፥ ሥጋ ግን የተፈጠረ ነው፡፡ መለኮት የማይታመም ነው፡፡ ሥጋ ግን የሚታመም ነው፡፡ ጳውሎስ "ክርስቶስ ታመመ ፥ ሞተ" ሲል እንደሰማን ሲለየው አልሰማንም ፣ ሃይማኖታችንም መለኮት በባሕርዩ እንደታመመ ፥ እንደ ሞተ አይናገርም። [ሮሜ.፭፥፮]

እንዲሁ እንደ ፍጡር ፥ እንደ ተገዥም ወደ ሁለት አይለይም፡፡ መለኮትን ፍጡር ፥ ግቡር አንለውም ፤ ያልተፈጠረ ነውና፡፡ ዳግመኛም ሥጋን ያልተፈጠረ ነው አንልም፡፡ ወልድን አንዱ የመለኮት ፥ አንዱ የትስብእት ብለን ሁለት ባሕርይ አንለውም፡፡

እምነታችሁም እንዲህ ይሁን ፣ አዋሕዳችሁ አንድ አካል ፥ አንድ ባሕርይ ፤ አንድ ገጽ በማለት ጸንታችሁ ኑሩ፡፡ [ዮሐ.፫፥፲፫-፲፱ ፥ ኤፌ ፬፡፭ ]

ከሚያስፈሩ ከእሊህ ዘወርዋራ ነገሮች ተለዩ ፤ ከንቱ ነገራቸውን ሰምተን ሃይማኖትን አንክፈል ፣ በምግባር አንድ ሆነን እንኑር እንጂ፡፡

ሥጋ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም መለኮት ከአብ የተገኘ እንደሆነ አንድ ሆነን እንመን። ሥጋ በማሕፀን የተፈጠረ ነው፡፡ መለኮት ግን ፈጽሞ ያልተፈጠረ ነው፡፡ በጊዜው ሁሉ የነበረ ፥ ያለ ፥ የሚኖር ፈጣሪ ነው እንጂ፡፡

ቃል ሥጋን በተዋሐደ ፥ ከሥጋም ጋር አንድ በሆነ ጊዜ መለኮት ከቀደመ ግብሩ አልተለወጠምና ፥ ከሥጋም አልተለየምና፡፡ [ዕብ.፲፫፥፰]

መጻሕፍት ሳይከፍሉ አምላክ እንደሆነ ከተናገሩ ዳግመኛም ፥ ሳይከፍሉ ሰው እንደሆነ ከተናገሩ ፥ እኛም የእግዚአብሔርን ነገር እንካተላለን፡፡

የማይከፈለውን አንከፍለውም፡፡ ሥጋ በማሕፀን የተፈጠረ እንደሆነ በተነገረ ጊዜም እንደምናከብረው ፤ እንደምናመሰግነው አድርገን መለኮትን ከትስብእት [ ከሥጋ ] አንለየውም፡፡ ዳግመኛም ያልተፈጠረ እንደመሆኑ መጠን መለኮት በሚከብርበት ፥ በሚመሰገንበት ጊዜ ያልተፈጠረ እንደሆነ ስለማመናችን ሥጋን ከመለኮት አንለየውም።

ሁለት አካል ፥ ሁለት ባሕርይ ብለው ለሚያምኑ የመጻሕፍትን ቃል ወደ ባህላቸው ለውጠው ቀዋሚ እንደሆነ አድርገው ይህን ለሚታመኑ ፥ በመጻሕፍት መካከል ክርክርን ለሚያገቡ ሰዎች የሚያሳፍር ሥራ እንደምን አይሆንባቸውም? [፪ጴጥ.፫፥፲፮] "

[     አቡሊዲስ     ]

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፤ ወለወላዲቱ ድንግል ፤ ወለመስቀሉ ክቡር። አሜን።

†                       †                         †
💖                    🕊                     💖

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

🕊

[ † እንኳን ለኢትዮዽያዊቷ እናታችን ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ]

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †


🕊 † እመ ምዑዝ [ እም ምዑዝ ] †  🕊

† ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ሐዋርያዊት: ጻድቅትና ሰማዕት ናት:: ይህስ እንደምን ነው ቢሉ :-

- ወር በገባ በ፳፱ [29] በቤተክርስቲያናችን ታስበው ከሚውሉት እግዚአብሔር አምላክ ቃል ኪዳን ከገባላቸው [ ከሰጣቸው ] እናቶች ኢትዮጵያዊቷ ሰማዕትና ጻድቅት ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ [ እመ ምዑዝ ] ትገኛለች:: ፍቅርተ ክርስቶስ [ እመ ምዑዝ ] ማን ናት? ምን ቃል ኪዳን ተሰጣት ? ያደረገችውን ተጋድሎ በጥቂቱ እንመልከት :-

✞ ጻድቅን በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ
ይወስዳል፡፡ [ ማቴ.፲፥፵ ] [ 10፡40 ] ✞

በሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት በመቂት ወረዳ ጥባ ማርያም ቀበሌ ውስጥ ምን ታምር በመትባል ቦታ ላይ በ፲፮ [16] ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በኢትዮጵያዊቷ ሰማዕትና ጻድቅ ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ የተመሰረተቸው እመ ምዑዝ ኪዳነ-ምህት ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ አንድት ገዳም ትገኛለች፡፡

ይህች ገዳም ከአዲስ አበባ በደሴ ወደ ጎንደር በሚወስደው መንገድ ፮፻፷፭ [665] ኪሎ ሜትር ከተጓዙ በኋላ ገራገር [ፍላቂት] ከምትባለው ከተማ በመውረድ በእግር 2፡30 እንደተጓዙ ከ፫፻፸ [370] ዓመት ባለይ ያስቆጠረችውን እመ ምዑዝ ኪዳነምህት ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ በአንድ ቀን የሠራቻትና ለጌታ በአራቱም አቅጣጫ የሰገደችውን ታላቅና ድንቅ ቤተመቅደስ ያገኛሉ፡፡

የዚህች ታላቅ ገዳም መስራች ኢትጵያዊት ሰማዕትና ጻድቅ ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ በደቡብ ጎንደር ደራ ፎገራ አንበሳሜ ወረዳ ልዩ ስሙ አቡነ ሐራ ገዳም አዋሳኝ ከተታ ማርያም ተብሎ በሚጠራ ቦታ በሚያዚያ ፬ [4] ቀን ተፀንሳ ታህሳስ ፳፱ [29] በጌታ ልደት ቀን ተወለደች፡፡

አባቷ ላባ እናትዋ ወንጌላዊት የተባሉ እግዚዘብሔርን የሚወዱ ትዕዛዙን የሚከብሩ ደጋግ ሰዎች ነበሩ፡፡ መሀን ሆነው ልጅ ባመውለዳቸው እያዘኑ ተግተው ወደ እግዚአብሔር በመፀለያቸው ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስን የመሰለች ልጅ: በፀሎትዋ ለሀገር ለወገን የምትበቃ ሰጥቷቸዋል፡፡

ከዚያም ፹ [80] ሲሆናት ለልጅነት ጥምቀት ወደ ቤተ መቅደስ በወሰዷት ጊዜ ከጥምቀት በኋላ ስጋ አምላክ ስትቀበል [ስትቆርብ] "ሕይወት የሆነውን ቅዱስ ስጋህን ክቡር ደምህን የሰጠኸኝ አምላኬ ክብር ምስጋና ይግባህ" ብላ አመስግናለች፡፡ ስመ ክርስትናዋ ማርያም ፀዳለ ሲሆን የአለም ስሟ 'ሙዚት' ነው፡፡ ፍቅርተ ክርስቶስ የምንኩስና [የቆብ] ስሟ ነው፡፡

እናታችን ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ አባ ዳንኤል ከሚባል አባት መፅሐፍን እየተማረች ካደገች በኋላ ለአቅመ ሄዋን ስትደርስ እናትና አባቷ ሊድሯት በመፈለጋቸው ዘርዓ ክርስቶስ ለሚባል ከደጋግ ሰዎች ወገን ለሆነ ሰው አጋቧት፡፡

ማታ እንደ ሙሽሮች ደምብ ወደ ጫጉላ ቤት ሲገቡ ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ዘርዓ ክርስቶስን "ወንድሜ ሆይ! እኔ የእናት አባቴን ፍቃድ ለመፈፀም ነው እንጂ ስጋዊ ሙሽራ መሆን አልፈልግም ፡፡ ፍላጎቴ የእግዚአብሔር ሙሽራ መሆን ነው" በማለት ብታማክረው ቅዱስ ዘርዓ ክርስቶስም ፀጋ እግዚአብሔር የበዛለት ሰው ነበርና "እኔም እናት አባቴን ላክበር ፈቃዳቸውን ለመፈፀም ነው እንጂ የስጋ ፈቃድ የለኝም በማለት ተነጋገሩ::

በኋላ በአንድ ቤት ውስጥ ለቤተሰቦቻቸው: ለአገሬው እንደ ባልና ሚስት ግን በንፅህና ለ፵ [40] ዓመት ሁለቱም በድንግልና ኖረዋል፡፡

ከዚያም በኋላ በእግዚአብሔር ፈቃድ ቅዱስ ሚካኤል መጥቶ ወንድ ልጅ እንደሚወልዱ ቢግራቸውም ሁለቱም "ይህስ አይሆንም" ብለው ለ፵ [40] ቀን በጾም: ፀሎት: በትጋት ጸልየዋል፡፡ መልአኩ ተገልጦ "ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው ሁለታችሁም ድንግልናችሁ አይፈርስም ብሎ ነግሮአቸዋል፡፡

ከዚያም ወንድ ልጅ ወልደዋል:: ህፃኑ በተወለደ በ፯ [7] ዓመቱ በቅዱስ ሚካኤል እቅፍ ገነትን ለ፯ [7] ቀናት ከጎበኛት በኋላ ወደ ምድር ሲመልሰው "በእናት አባቴ አምላክ ይዤሃለሁ ወደዚች ወደ ከፋች ዓለም አትመልሰኝ" ብሎ ቢለምነው ቅዱስ ሚካኤልም ከአምላክ ጠይቆ በብሔረ ህያዋን የህፃናት አለቃ ተብሎ እንዲቀመጥ አድርጎታል፡፡ ስሙም ዳግማዊ ቂርቆስ ተብሏል፡፡

ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶና ቅዱስ ዘርዓ ክርስቶስም ልጅ ከወለዱ በኋላ እንደ ቀደሞው በቅድስና: በንፀህና ፀንተው ኑረዋል፡፡ በዘመናቸው በኢትዮጵያ ነግሶ የነበረው አፄ ሱስንዮስ ሃይማኖቱን ለውጦ 'ሁለት ባህርይ የሚሉ ካቶሊኮችን በመቀበሉ ክርስቲያኖችን እየገደለ ነው' የሚል ወሬ ሰምተው ወደ ንጉሱ በመሄድ ሳይፈሩ ስለ ተዋህዶ ሃማኖታቸው በንጉሱ ፊት መስክረዋል፡፡

ንጉሱም በጣም የበዛ መከራን አድርሶባቸዋል፡፡ መከራ በበዛ ቁጥር እነርሱም እየፀኑ ተከታዮቻቸውንና የንጉሱን ሠራዎቶች ሳይቀር አሳመኑ:: ፷ ሺህ [60,000] ክርስቲያኖችም ሰማዕትነትን ተቀብለዋል፡፡

ንጉሱም በጣም የበዛ መከራ አድርሶባቸዋል፡፡ መከራ በበዛ ቁጥር እነርሱም እየጸኑ ተከታዮቻቸውንና የንጉሱን ሰራዊቶች እያሳመኑ ቢያስቸግሩ በሰማዕትነት አንገታቸውን አስቆርቷቸዋል፡፡ አንገታቸውም ሲቆረጥ ከሁለቱም ደም ውሃ ወተት ፈሷዋል፡፡

በዚያን ዘመን ከእነ ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ጋር ሰማዕትነት ከተቀበሉት ውስጥ የማህበረ ስላሴው ጻድቁ አምደ ስላሴ: የጎረጉር ማርያም አባ መርአዊ: የመሲ ኪዳነ ምህረት እመ ወተት እና ከ፷ [60] ሺ በላይ ክርስቲያኖች ሰማዕትነት ተቀብለዋል፡፡

ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ አንገቷ ከተቆረጠና ሰማእትነት ከተቀበለች በኋላ ወደ ምድር መልሶ አንገቷን ከቀሪው የሰውነቷ ክፍል ጋር አዋህዶ ከአንቅልፍ አንደሚነቃ ሰው ቀስቅሶ አስነስቷቷል፡፡ ከዚያም ከአቡነ ማርቆስ ስርዓተ ምንኩስናን በመቀበል ዋልድባ ገዳም ለ፬ [4] ዓመት አገልግላለች፡፡

ከዚህም ከ፭፻ [500] የሚበልጡ ተከታዮችዋን መነኮሳትን አስከትላ በሰሜን ወሎ ቆቦ ወረዳ ወደምትገኘውና በፃድቁ በአባ ጉባ ተመስርታ ጠፍታ ወደ ነበረችው ራማ ኪደና ምህረት አንድነት ገዳም በመሄድ ገዳሟን አቅንታ: የወንድ የሴት ብላ ስርዓት ሰርታ: ገዳሟን አስተካክላ: ፭፻ [500] የሚሆኑ አገልጋች መነኮሳትን አኑራ ወደ ኢየሩሳሌም ጉዞ ጀምራለች፡፡

በመንገዷም ላይ ሰውን የሚበሉ ወደ ሚኖሩበት አካባቢ በመድረስ እነርሱም እርሷንና ፷ [60] የሚሆኑ አገልጋዮችዋን ዓይኖቻቸውን በጉጠት በማውጣት ለ፬ [4] ወራት በጨለማ ቤት ውስጥ ዘግተውባቸዋል፡፡ ከአራት ወር በኋላም በዓል አድገው ለመብላት ከቤት ቢያወጧቸው መልካቸው እንደ ፀሐይ የሚያበራ ቢሆንባቸው "አንቺ ሴት ምንድን ናችሁ?" ብለው ጠይቀዋታል፡፡

እርሷም ክርሰቲያን መሆናቸውንና እነሱ የስላሴ ሕንፃ የሆነውን የሰውን ልጅ መብላት እንደሌለባቸው ብትመክራቸው "ምን አንብላ?" ብለዋታል፡፡ እርሷም ከራማ ኪዳነ ምህረት ስትነሳ የእህል ዘርን በአገልጋዮቿ አሲዛ ነበርና ስንዴውን በአንድ ቀን ዘርታ: በቅሎ: ታጭዶ: ደርቆ: ተፈጭቶ ለምግብነት በቅቷል፡፡

እርሷ ቀምሳ ብታቀምሳቸው እንደማር እንደ ወተት የሚጣፍጥ ሆኖላቸው በደስታ ተመግበውታል፡፡ ከዚያም እንደዚህ እያደረጉ እየሰሩ እንዲበሉ አስተምራ: አስጠምቃ ከ፮ [6] የሚበልጡ አብያተ ክርስቲያናትን አስተክላላቸዋለች፡፡

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

                         †                          

                 

" የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ።" [ማቴ.፲፩፥፲፭]



         †              †               †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬

Читать полностью…
Subscribe to a channel