mikreabew | Unsorted

Telegram-канал mikreabew - ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

874

"እንግዲህ፡ንስሓ፡ግባ፤አለዚያ፡ፈጥኜ፡ እመጣብሃለሁ፡፡" ራዕ 2፥16

Subscribe to a channel

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

                      †                           

[ "ከዚያ አታላይ ምን ትፈልጊያለሽ ? " ]

--------------------------------------------

እውነተኞቹ አባቶቻችን ቅዱሳን ግን እንዲህ ናቸው !
--------------------------------------------

" በጡቷ ካንሰር የነበረባት አንዲት ሴት ስለ አባ ሎንጊኖስ ሰማችና ልታገኘው ሄደች፡፡

የሚኖረው ከእስክንድርያ ወጣ ብሎ ነበርና ሴትዮዋ ስለ እርሱ እየጠየቀች ወደ እርሱ ስትሄድ በባሕሩ ዳርቻ እንጨት እየለቃቀመ አገኘችውና እርሱ መሆኑን ስላላወቀች ፦ " አባ ፣ የእግዚአብሔር አገልጋይ ሎንጊኖስ የሚኖረው የት ነው ? " አለችው:: እርሱም ፦ " ከዚያ አታላይ ምን ትፈልጊያለሽ? ወደ እርሱ አትሂጂ ፣ እርሱ አታላይ ነውና። ግን ጉዳይሽ ምንድን ነው ? " አላት፡፡

ሴትዮዋም ስለ ሕመሟ ነገረችው:: እርሱም በታመመው ሰውነቷ ላይ የመስቀል ምልክት አደረገና ፦ " ሂጂ ፣ የሚፈውስሽ እግዚአብሔር ነው ፣ ሎንጊኖስ ምንም የሚጠቅምሽ ነገር የለምና " አላት፡፡

እርሷም አምና ተመለሰች ፣ በአንዴ ወዲያውኑ ከሕመሟ ተፈወሰች፡፡ ከዚያ በኋላ ይህን ነገር ለሰዎች አወራች፡፡ የሰውዬውን ሁኔታ ገለጸችላቸው ፣ እነርሱም እርሱ ራሱ አባ ሎንጊኖስ እንደ ሆነ ነገሯት፡፡ "

በሰይጣን ተታለን ፈጽመን እንዳንጠፋ ፤ ነፍሳችንንም ማዳን እንዲቻለን ወደ እናታችን ቤተክርስቲያን እቅፍ እንመለስ !

         †              †               †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

🕊                    

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን †

[ † እንኩዋን ለታላቁ ሰማዕት "ቅዱስ ቴዎድሮስ ሮማዊ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ † ]


🕊  † ቅዱስ ቴዎድሮስ ዘሮም †  🕊

ሰማዕትነት በክርስትና ለሃይማኖት የሚከፈል የመጨረሻው ዋጋ [መስዋዕትነት] ነው:: ሰው ለፈጣሪው ሰውነቱን ሊያስገዛ: ሃብት ንብረቱን ሊሰጥ ይችላል:: ከስጦታ በላይ ታላቅ ስጦታ ግን ራስን አሳልፎ መስጠት ነው::

ራስን መስጠት በትዳርም ሆነ በምናኔ ውስጥ ይቻላል:: የመጨረሻ ደረጃው ግን ሰማዕትነት ነው:: "አማን መነኑ ሰማዕት ጣዕማ ለዝ ዓለም: ወተዓገሡ ሞተ መሪረ በእንተ መንግስተ ሰማያት" እንዳለው ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ሰማዕትነት ማለት መራራውን ሞት ስለ ፍቅረ እግዚአብሔር ሲሉ መታገስ ነው::

እርሱ ቅሉ መድኃኒታችን ክርስቶስ የሰማይና የምድር ጌታ ሲሆን ኃፍረተ መስቀልን ታግሦ ሙቶልን የለ ! በዓለም ያሉ ብዙ እምነቶች ስለ መግደል በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ያስተምራሉ:: ክርስትና ግን መሞትን እንጂ መግደልን የሚመለከት ሕግ የለውም::

እርሱ ባለቤቱ "ጠላቶቻችሁን ውደዱ: የሚረግሟችሁን መርቁ: ስለሚያሳድዷችሁ ጸልዩ" ብሎናልና:: [ማቴ.፭፥፵፬] [5:44] ነገር ግን ዕለት ዕለት ራሳችንን በሃይማኖትና በምግባር ካልኮተኮትነው ክርስትና በአንድ ጀምበር ፍጹም የሚኮንበት እምነት አይደለምና በፈተና መውደቅ ይመጣል::

በተለይ የዘመኑ ክርስቲያን ወጣቶች ልናስተውል ይገባናል:: የቀደሙ ወጣት ሰማዕታት ዜና የሚነገረን እንድንጸና ነውና::

ቅዱስ ቴዎድሮስ በዘመነ ሰማዕታት [በ፫ (3) ኛው መቶ ክ/ዘመን] በቀድሞው የሮም ግዛት ውስጥ ከተነሱ ታላላቅ ሰማዕታት አንዱ ነው:: በወቅቱ መሪ የነበረው ክሀዲው መክስምያኖስ "ክርስቶስን ክደህ ለጣኦት ስገድና በከተማዋ ላይ እሾምሃለሁ" ቢለው "ለእኔ ሃብቴም ሹመቴም የክብር ባለቤት ኢየሱስ ክርስቶስ ነው" በማለቱ ንጉሡ ተቆጥቶ በብረት ዘንግ አስደበደበው::

በመንኮራኩር አበራየው:: ለአናብስት ጣለው:: አካላቱን ቆራረጠው:: በእሳትም አቃጠለው:: ቅዱስ ቴዎድሮስ ስቃዮችን ስለ ቀናች ሃይማኖት ሲል በትዕግስት ተቀበለ:: በፍፃሜውም አንገቱን በሰይፍ ተመትቶ ፫ [3] አክሊላት ወርደውለታል::

ከፈጣሪው ዘንድም ነጭ መንፈሳዊ ፈረስና ቃል ኪዳን ተቀብሏል:: ስሙን የጠራ: መታሠቢያውን ያደረገ ዋጋው አይጠፋበትም:: [ማቴ.፲፥፵፩] [10:41]

አምላከ ቅዱሳን ከቅዱሱ ሰማዕት በረከት ይክፈለን:: አይተወን:: አይጣለን:: ጾሞ ለማበርከትም ያብቃን::

🕊

[ † የካቲት ፳፰ [ 28 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. ቅዱስ ቴዎድሮስ ሮማዊ [ሰማዕት]
፪. ፮ ሺህ ፫ መቶ ፬ [6,304] ሰማዕታት [በቅ/ቴዎድሮስ አምላክ አምነው ሰማዕትነት የተቀበሉ]

[ † ወርኀዊ በዓላት ]

፩. አማኑኤል ቸር አምላካችን
፪. ቅዱሳን አበው [አብርሃም: ይስሐቅና ያዕቆብ]
፫. ቅዱስ እንድራኒቆስና ሚስቱ ቅድስት አትናስያ
፬. ቅድስት ዓመተ ክርስቶስ

" እግዚአብሔር ለኛ የሰማዕትነትን ሥራ ይሰጠን ዘንድ ቅዱሳን ስለሚሆኑ ሰማዕታት እንማልዳለን:: " [ሥርዓተ ቅዳሴ ቁ. ፸፫] [73]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
💖                    🕊                     💖

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

🔔

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

የሐሳዊው መሲህ መንገድ ጠራጊዎች የሆኑት የሐሰተኛ አጥማቂያን ምስጢር !

----------------------------------------------

በእግዚአብሔር ቸርነት በእናታችን በቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ምልጃ ከሐሰተኛ አጥማቂያን ወጥመድ ያመለጠች እህታችን ወለተ አማኑኤል ምስክርነት ከሲዊድን !



- በመንፈሳዊ ለምድ የተሸፈኑት ሐሰተኛ አጥማቂያን ማን ናቸው ?
- የዋሃን ምዕመናንን እንዴት ያጠምዳሉ ?
- ምዕመናንን ከቅድስት ቤተክርስቲያን እንዴት ያርቃሉ ?
- የዋሃን ምዕመናንን ከአባቶች ካህናት እንዴት ይለያያሉ ?
- ምልክት የሚከተለውን ምዕመን በተለይም በውጪው ዓለም ያለውን ሕዝብ እንዴት ይዘርፋሉ ?
- ምዕመናንን ወደ መናፍስታዊ ዓለም በማስገባት እንዴት ከሃይማኖት ያስወጣሉ ?
- የረከሰ መንፈሳቸውን በሚከተላቸው ሕዝብ ላይ እንዴት ያሳድራሉ ?

---------------------------------------------

" አንዳንዶች ተከራካሪዎችንም ውቀሱ ፥ አንዳንዶችንም ከእሳት ነጥቃችሁ አድኑ፥" [ይሁ.፩፥፳፪]



የእህታችን የወለተ አማኑኤል ምስክርነት

         †              †               †
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
👇

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

🕊              

[ † እንኳን ለታላቁ ሊቅና ጻድቅ ቅዱስ አንስጣስዮስ እና አቡነ ዓምደ ሥላሴ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ]

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †

🕊  †  ቅዱስ አንስጣስዮስ ሊቅ  †  🕊

† ቅዱስ አንስጣስዮስ በ ፬ [4] ኛው ክ/ዘመን የተነሳ ሶርያዊ የነገረ መለኮት ሊቅ: ገዳማዊ ጻድቅና የመንበረ አንጾኪያ ሊቀ ዻዻሳት ነበር:: ቅዱሱ ርጉም አርዮስን ካወገዙ ፫፻፲፰ [318]ቱ ቅዱሳን ሊቃውንት አንዱ ነው:: በወቅቱ ታላላቅ ሊቃነ ዻዻሳት ሱባኤውንና ጉባኤውን የመሩ ሲሆን አንዱ ይህ ቅዱስ ነው::

ከ ፭ [5] ዓመታት በሁዋላም ብዙ ድርሳናትን ጽፎ: ሐዋርያዊ አገልግሎቱን ፈጽሞ በ፫፻፴ [330] ዓ/ም አርፏል:: ያረፈው ግን አርዮሳውያን ባቀረቡት ክስ በሃሰት ተመስክሮበት በግፍ ተሰዶ ነው:: ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ስለ ውለታው የውዳሴ ድርሳን ጽፎለታል::


🕊   †  አቡነ ዓምደ ሥላሴ  †  🕊

† እኒህ ታላቅ ጻድቅ ሐዋርያዊ አባት አቡነ ዓምደ ሥላሴ የትውልድ ሃገራቸው ጎጃም ሲሆን የተወለዱት በዚሁ ዕለት [የካቲት ፳፯ (27) ነው:: ጻድቁ በአጼ ሱስንዮስ [በ፲፯ [17]ኛው መቶ ክ/ዘ)] የነበሩ ድንቅ ሠሪ : ተአምረኛና ገዳማዊ አባት ናቸው::

የካቲት ፲፮ [16] ቀን መንኩሰው ወደ ተጋድሎ ገብተዋል:: በዋልድባ በነበራቸው ቆይታም እመቤቴ ኪዳነ ምሕረት የካቲት ፲፮ [16] ቀን እንድትከበር ማድረጋቸውም ይነገራል:: ጻድቁ በሌሎች ገዳማትም የነበሩ ሲሆን ዛሬም ድረስ ረድኤታቸው የሚደረግበት : ስማቸው የሚጠራበት ገዳም ግን ማኅበረ ሥላሴ ይባላል::

ገዳሙ የሚገኘው በሃገራችን ሰሜን ምዕራብ አቅጣጫ : በመተማ በርሃ ውስጥ ነው:: ይህንን ቅዱስ ገዳም የመሠረቱትም ራሳቸው አባ ዓምደ ሥላሴ ናቸው:: ገዳሙ ዛሬም ብዙ ምሑራንና መናንያን ያሉበት : በደህና ሁኔታም የሚገኝ ነው:: ግን በርሃውን የኔ ብጤ ደካማ ሰው የሚችለው አይደለም::

ስለ ጻድቁ ዓምደ ሥላሴ ከሚነገሩ ታሪኮች ቅድሚያውን የሚይዘው የተዋሕዶ ጠበቃነታቸው ነው:: በ፲፮፻፫ [1603] ዓ/ም ዼጥሮስ [ፔድሮ] ፓኤዝ የሚባል ካቶሊካዊ እሾህ ወደ ሃገራችን ገብቶ ነበርና ንጉሡን ሱስንዮስን አባብሎ ተዋሕዶን አስካዳቸው:: ነገሩ ውስጥ ለውስጥ ሲበስል ቆይቶ በ፲፮፻፱ [1609] ዓ/ም በመገለጡ እነ ራስ ዮልዮስ ለሃይማኖታቸው ጠዳ ላይ ተዋግተው ግንቦት ፮ [6] ቀን ተሰው::

ይህ ነገር ሲሰማ ወንድ ሴት : ትልቅ ትንሽ ሳይመረጥ በገጠሩም : በከተማውም : በገዳሙም ያሉት ሁሉ የተዋሕዶ ልጆች መንቀሳቀስ ጀመሩ:: ፯ [7] ዓመታት እንዲህ አልፈው በ፲፮፻፲፮ [1616] ዓ/ም ግጭቱ በይፋ ተጀመረ::

"ተዋሕዶን ካልካዳችሁ" በሚል በቀን እስከ ፰ሺህ [8,000] ሰው በሰይፍ ታረደ:: ይህን ያደረጉት ደግሞ አልፎንሱ ሜንዴዝ : ንጉሡ ሱስንዮስና ጀሌዎቻቸው ነበሩ::

በጊዜውም ከቤተ መንግሥት እነ ንግሥት ወልድ ሰዓላ [የሱስንዮስ ሚስት] : ከጻድቃን አበው ዘርዓ ቡሩክ ዘግሺ : ሐራ ድንግል ዘደራ : ምዕመነ ድንግል ዘጩጊ : ዓምደ ሥላሴ ዘማኅበረ ሥላሴ . . . ከቅዱሳት እነ ፍቅርተ ክርስቶስ : ወለተ ዼጥሮስ : ወለተ ዻውሎስ : እኅተ ዼጥሮስ . . . ለሃይማኖታቸው ተዋሕዶ ጥብቅና ቆመው ሕዝቡን አስተማሩ:: መከራም ተቀበሉ::

ብዙ ኢትዮዽያውያን የመከራ ጽዋን ተጐንጭተው ለክብር ከበቁ በሁዋላ የእግዚአብሔር ፍርድ ተገለጠ:: በጻድቃኑ እነ አባ ዓምደ ሥላሴ ሐዘን ንጉሡ ታመመ:: ምላሱ ተጐልጉሎ ወጣ::

በዚህ ጊዜ አቤቶ ፋሲለደስ ለአባ ዓምደ ሥላሴና ለሌሎቹ ቅዱሳን "አባቴን አድኑልኝ! ተዋሕዶም ትመለስ" አላቸው:: ጻድቁም ከባልንጀሮቻቸው ጋር ጸልየው ንጉሡን አዳኑት:: በፈንታውም ይህንን አሳወጁ::

† ፋሲል ይንገሥ!
ሃይማኖት (ተዋሕዶ) ይመለስ!
የሮም ሃይማኖት ይፍለስ! †

ከዚህ በሁዋላ በ፲፮፻፳፬ [1624] ዓ/ም ፋሲል ሲነግሥ አባ ዓምደ ሥላሴ ለገዳማቸው ብዙ ቦታ አስከልለው : በተጋድሎ ኑረው በዚህች ቀን ዐርፈዋል::

† አምላከ ቅዱሳን በቀናችው እምነት ተዋሕዶ ሁላችንም እስከ ፍጻሜ ዘመናችን ያጽናን:: ከበረከተ ቅዱሳንም ይክፈለን::

🕊

[ † የካቲት ፳፯ [ 27 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. አባ አንስጣስዮስ ርቱዓ ሃይማኖት [ዘአንጾኪያ]
፪. አቡነ ዓምደ ሥላሴ

[ † ወርኀዊ በዓላት ]

፪. የጌታችንና አምላካችን መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ በዓለ ስቅለት
፪. አቡነ መብዐ ፅዮን ጻድቅ
፫. ቅዱስ መቃርስ [የመነኮሳት ሁሉ አለቃ]
፬. ቅዱስ ፊቅጦር ሰማዕት
፭. ቅዱስ ያዕቆብ ዘግሙድ
፮. ቅዱስ ገላውዴዎስ ሰማዕት [ንጉሠ ኢትዮዽያ]
፯. ቅዱስ ቢፋሞን ጻድቅና ሰማዕት

" የተጠራችሁለት ለዚህ ነው:: ክርስቶስ ደግሞ ፍለጋውን እንድትከተሉ ምሳሌ ትቶላችሁ ስለ እናንተ መከራን ተቀብሏልና:: እርሱም ኃጢአት አላደረገም:: ተንኮልም በአፉ አልተገኘበትም:: ሲሰድቡት መልሶ አልተሳደበም:: መከራንም ሲቀበል አልዛተም . . . እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ::"
[፩ጴጥ.፪፥፳፩-፳፭] [1ዼጥ. 2:21-25]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
💖                    🕊                     💖

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

                         †                          

                 

" ሌላው ሁሉ ይቅርና እስቲ ያስቀድሱ ! "



         †              †               †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

🔔


የዘመናችን አጥማቅያን እና የአጋንንት ምስክርነት !


[  ክፍል  አሥር  ]

▬▬▬▬▬▬▬▬

የእናቱን መዓዛ የማይለይ ልጅ  !


ለሐሰተኛ አጥማቂያን መንሰራፋት አንዱ ምክንያት የቤተክርስቲያንን ድምጽ በአግባቡ ማዳመጥና ማስተዋል ያልቻለው ምዕመን መሆኑን መካድ አይቻልም !

ቅድስት ቤተክርስቲያ ልጆቿን ለእግዚአብሔር መንግሥት የተገቡ እንዲሆኑ ለማድረግ የተሰጣትን ሰማያዊ ተልዕኮን በብዙ ዓይነት ፈተና ውስጥ ሆና ትፈጽማለች። በጥምቀት ከማህፀነ ዮርዳኖስ ከአብራከ መንፈስ ቅዱስ ከማይጠፋና ከማይሞት ዘር ወልዳ ሀሊበ ጸጋዋን እየመገበች ታሳድጋለች።

ቤተ ክርስቲያን በእግዚአብሔር መለኮታዊ አሳብና አሠራር ውስጥ ያለች ፣ የሰው ልጅ ከርኩሰቱ የሚነጻባት ፣ ሰማያዊ ዜግነትን የምናገኝባት ፣ በክርስቶስ ደም የምንታተምባት ፣ ምድራዊም ሆነ ሰማያዊ በረከት የምንቋደስባት ፣ ሰማያዊውንም ምስጢር የምንመለከትባት ፣ በበደላችን ሙታን ሆነን ሳለ ትንሣኤ ዘለክብርን ያገኘንባት ፣ የእግዚአብሔር ማዳን የተፈጸመባት ኃይልን ከአርያም የተቀበለች የእግዚአብሔር ጥበብ ናት።

የኖኅ መርከብ ምሳሌነቷ ለአማናዊት ቤተክርስቲያን ነው። በኖኅ ዘመን ነፍሳት ከጥፋት ውኃ መዳን የቻሉባት የኖኅ መርከብ እንደሆነች እንዲሁ በፍጻሜ ዘመንም ፍጥረት ከመጨረሻው ፍርድ መዳን የሚችለው በአንዲቱ ቤተክርስቲያን ጸንቶ መኖር ሲችል ብቻ ነው። የእውነት አምድና መሠረት ከሆነችው ከአንዲቱ ቤተክርስቲያን ውጪ ማንም ከጥፋት ይድን ዘንድ አይቻለውም።

እውነተኛ ኦርቶዶክሳዊ ምዕመን የእናቱን የቤተክርስቲያንን ድምፅና መዓዛ ከሌሎች አካላት ለይቶ የሚያውቅ ፤ የእናቱን ድምፅ የሚሰማ ፤ ትእዛዟን የሚያከብርና ከአጠገቧ ሳይለይ አብሯት የሚኖር ታማኝ ልጅ ነው። እናቱን ጠንቅቆ የሚያውቅና መዓዛዋንም የሚለይ በመሆኑ  የሌሎችን ድምፅ ግን አይሰማም። አይከተልምም። የእናቱን መዓዛና ጠረን ለይቶ የማያውቅ ልጅ ለእናቱ ፍቅር አለው ሊባል አይችልም።

"በጎቹም ድምፁን ያውቃሉና ይከተሉታል ፤ ከሌላው ግን ይሸሻሉ እንጂ አይከተሉትም ፥ የሌሎችን ድምፅ አያውቁምና።"  [ዮሐ.፲፥፬]

በመሆኑም አንድ ኦርቶዶክሳዊ ምዕመን በሃይማኖት ወልደው በምግባር ኮትኩተው የሚያሳድጉትን አበው ጠንቅቆ ሊያውቅ ተጋድሏቸውን ሊያስብና የኑሮአቸውን ፍሬ እየተመለከተ በእምነት ሊመስላቸው ይገባዋል።

"የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሩአችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ ፥ የኑሮአቸውንም ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነታቸው ምሰሉአቸው። ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንትና ዛሬ እስከ ለዘላለምም ያው ነው።" [ዕብ.፲፫፥፯]

አበው የሚባሉት "የመቅረዝ ላይ ዕንቁዎች መሰወር የማይችሉ የተራራ ላይ ከተሞች ናቸው። ከፊሎቹ በመልአካዊ ባህርያቸው ብቻ የሚመሩ ከተድላ ስጋ ርቀው ጣዕመ ዓለምን ንቀው ከሞቀ ከደመቀ ቤታቸው ወጥተው ፤ ነገሥታቱ ደግሞ ሰማያዊውንና ድል ለነሱት ሁሉ የሰማይ አምላክ ያዘጋጀውን ዙፋን ፍለጋ ምድራዊ ዙፋናቸውን ለቀው ፤ አምላካዊውን ዘውድ ለመቀዳጀት ዘውዳቸውን ጥለው ዘመናቸውን ሙሉ በዋሻና በፍርኩታ የጨረሱ ፤ ሰው ሲሆኑ በአኗኗራቸው መላእክት ፤ ምድራውያን ሲሆኑ ሰማያውያን ተብለው የተሰየሙ ናቸው። ከፊሎቹ ደግሞ መልአካዊ ባህርያቸውንም ሆነ ሰብአዊ ባህርያቸውን አስተባብረው እንደ ሰው መኖር የቻሉ ናቸው። ይህን ዓለም በወዲያኛው ዓለም ለውጠው የሚኖሩ ፃድቃን እንዲሁም በህገ ሰብሳብ ተወስነው ቤት ሠርተው ዘር ዘርተው አሥራቱን በኩራቱን እያወጡ ካገኙት ከፍለው እየሰጡ ተርፏቸው ሳይሆን እየተራቡ ሲመጸውቱ የሚኖሩ ናቸው።

አበው ለርስታቸው [ለቅድስት ቤተክርስቲያን መንግሥተ ሰማያት] መከራ ለመቀበል የማይሰቀቁ ፤ እስከ ሞት ድረስ ዋጋ የሚከፍሉ ፤ ለሥርዓቷ መከበር ሀገር ጥለው የሚሰደዱ ፤ በእሥራት በወህኒ አብዝቶ በመገረፍ ፣ በመራብ ፤  በመጠማት ፣ በመራቆትና በመንገላታት የደም ዋጋ የከፈሉና የሚከፍሉ ናቸው።

ኦርቶዶክሳዊ ምዕመን ደግሞ የአበውን ፍኖት የሚያውቅ ለሥርዓተ ቤተክርስቲያን የማይደራደርና ጸንቶ የሚቆም ፤ ለምድ ከለበሱ ሕግ አፍራሾች ጋር የማይተባበር ቀናዒ ነው። በአበው ስም እየተጠሩ የአበውን ሥራ የማይሠሩ ፤ በክህነትና በብኅትውና ስም የሚነግዱ ፤ በክርስትና የሚቆምሩ ፤ ባህታዊ መሰል ጭምብል ያጠለቁ ፤ የበግ ለምድ ለብሰው የሚዞሩ ተኩላዎችን ለይቶ የሚያውቅና ቅድስት ቤተክርስቲያንን እንዲህ ካሉት ምንደኞች የሚጠብቅ ነው። በተለይ በማጥመቅና ተዓምራት በማድረግ የሥራ ዘርፍ የተሠማሩ ፤ በቁማቸው ገድል የሚተረክላቸውና ሲከፋም የተጻፈላቸው ፤ ዝናና ክብራቸው በዓለም የናኘላቸው ፤ በአደባባይ የሚሰገድላቸውን ዘባቾች ተከትሎ መንጎድ ኦርቶዶክሳዊ ማንነት አይደለም።

ተዓምራቶች የቅድስናና የእውነተኛነት ማረጋገጫ ምልክቶች አይደሉም። ይልቁንም ሰይጣናዊ የሆኑ የስህተት አሠራሮች በበዙበት በዚህ ጊዜ ምልክት ፈላጊ መሆን በራስ ላይ ጥፋትን ከመጋበዝ ተለይቶ የሚታይ አይደለም። ምልክት ፈላጊነት የክፋትና የጠማማነት ምልክት እንጂ ጤናማ ክርስቲያናዊ ባህርይ አይደለም። ብዙዎች ወደ ጥፋት መንደር ለመትመማቸው ምክንያቱ የትውልዱ ምልክት ፈላጊ መሆን ነው። ተዓምራት ማድረግና አጋንንትን ማውጣት ለአንድ ሰው የእምነትና የጽድቅ መመዘኛ ሊሆን አይችልም። በአጋንንታዊ ምትሐት /ድግምት/ የግብጽ አስማተኞች ኢያኔስና ኢያንበሬስ ጊዜያዊ ተዓምር ማድረጋቸው በቅዱስ መጽሐፍ ተመዝግቦልናል። [ዘፀ.፯፥፲፩] በዓይን ዶር የምትኖር አንዲት መናፍስት ጠሪ ሙት ማስነሳቷ በ ፩ኛ.ሳሙ.፳፰፥፲፩] ላይ ተመዝግቦልናል።

አጋንንትን ለማውጣት ሁለት ዓይነት መንገዶችን የሚጠቀሙ ግለሰቦች መኖራቸውን መምህራን ያስረዳሉ። የመጀመሪያው በድግምትና በዕፅዋት ሲሆን ሁለተኛው የአጋንንቱን አለቃ /ብኤል ዜቡል/ በሚዋረሰው ግለሰብ አማካኝነት ነው። የዘመናችን አጥማቂያንም ሱዳንን እንደ ኢየሩሳሌም ሳይሳለሙ የማይቀሩበትን ምስጢር ማጥናት ይገባል። ይህ ሁሉ ግን ከገሃነም ፍርድ የሚያድን አይደለም።

"ብዙዎች .. በስምህ አጋንንትን አላወጣንምን? በስምህስ ብዙ ተዓምራትን አላደረግንምን? ይሉኛል። ያንጊዜ ከቶ አላውቃችሁም ፤ ዐመጽን የምታደርጉ ሁላችሁ ከእኔ ራቁ እላቸዋለሁ።" [ማቴ.፯፥፳፩]

ኦርቶዶክሳዊ ምዕመን ተዓምራትና ድንቆችን የማይናፍቅና የማይከተል በእምነቱ እንደ ዓለት የጸና ነው። የሚኖረውም በእምነትና በመንፈሳዊ ሕይወት ነው። የኦርቶዶክሳዊ ዘለዓለማዊ ተዓምሩ ሃያውን ዓለማት የፈጠረውን ፤ ሰማይ ዙፋኑ ምድር የእግሩ መረገጫ የሆነለትን አምላክ በማህጸኗ የወሰነች ፥ በክንዶቿ የታቀፈች ፥ በጀርባዋ የተሸከመች ፤ የድንግልና ጡቶቿን እየመገበች ያሳደገች እመቤታችን ናት። የኦርቶዶክሳዊ ዘለዓለማዊ ተዓምሩ ህብስቱ ተለውጦ ስጋ መለኮት ወይኑ ተለውጦ ደመ መለኮት መሆኑ ነው። የኦርቶዶክሳዊ የሁልጊዜ ተዓምሩ አምላክ ሰው የሆነበት ምስጢር ነው። ከአምላክ መገለጥ በላይ ለኦርቶዶክሳዊ ምዕመን ሌላ የሚበልጥ ተዓምር ሊኖረው አይችልም።

"የዚህ የመልካም አምልኮ ምሥጢር ታላቅ ነውና። ይኸውም በሥጋ የተገለጠ ፥ በመንፈስ የተረዳ ፥ ለመላእክት የታየ ፥ በአሕዛብ ዘንድ የተሰበከ ፥ በዓለም የታመነ ፥ በክብር ያረገ ነው።" [፩ጢሞ.፫፥፲፮]

በዚህም በየትኛውም ዓይነት ምልክት ፥ በየትኛውም ዓይነት ድንቅና ተዓምር አንታወክም። አንናወጽም።

🔔

"ስለዚህ ምድር ብትነዋወጥ ፥ ተራሮችም ወደ ባሕር ልብ ቢወሰዱ አንፈራም።" [መዝ.፵፮፥፩]

         †              †               †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

       †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬

[   ኦርቶዶክሳዊ የመዳን ትምህርት   ]

[ በዚህ መርሐ-ግብር ኦርቶዶክሳዊ የመዳን ትምህርት ከቅዱሳት መጻሕፍት ፤ ከቅዱሳን አባቶቻችን ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን አስተምህሮ እንዲሁም ከመምህራን ትምህርቶች ላይ በየጥቂቱ ይቀርባል። እንዲሁም የተሐድሶ መናፍቃን የኑፋቄ ትምህርቶችና ምላሾቻቸው የሚቀርብ ይሆናል። ]

†                      †                       †

[   ኦርቶዶክሳዊ የመዳን ትምህርት   ]

[       ክፍል ሃያ ሁለት     ]

[ መዳን ማለት ምን ማለት ነው ?  ]

†                      †                       †

1) ኃጢአት ካመጣው ፍዳ ሁሉ መዳን

[ ፩ ]

በአዳምና ሔዋን ምክንያት በባሕርያችን የደረሰብን ጉዳት ሁለት ዘርፍ ያለው ነው:፡ ይህም በአንድ በኩል ሕጉን በማፍረሳቸውና ቃሉን ባለመጠበቃቸው ምክንያት ሕግ አፍራሾችና ወንጀለኞች ሆንን ፤ ከዚህም የተነሣ [ ሕጉን በማፍረስ ምክንያት ] በሕግ አፍራሾች ላይ የሚደርሰው “የሕግ ርግመት” ደረሰብን፡፡

ስለዚህም ቅጣት የሚገባን ወንጀለኞች ፣ ሕጉን በሚተላለፉ ላይ የሚደርሰው የሕግ ርግመት የደረሰብን ሆንን በሌላ በኩል ደግሞ ባሕርያችን በኃጢአት ምክንያት መለወጥና መጎስቆል አገኘውሕይወትን አጣንለሞት ተገዛን : ሞት ወደ ባሕርያችን ዘልቆ ገብቶ ተቆጣጠረንማርጀትና ማፍጀትመድከምና መዛልመታመምና መቸገር ሁሉ ወደ ባሕርያችን ውስጥ ገቡ፡፡

ስለዚህ መዳናችንም ይህንኑ መንገድ የተከተለ ይሆን ዘንድ ይገባው ነበር ፤ በአንድ በኩል በሕጉ ከመጣብን ርግመት ነጻ ያወጣንና ጸጋውን ይመልስልን ዘንድ ፣ በሌላ በኩል ደግሞ በኃጢአት ምክንያት ሙታን የሆንነውን ሕያዋን ያደርገንና ሕይወትን ይሰጠን ዘንድ ያስፈልገን ነበር።

የእግዚአብሔርን ሕግ በማፍረሳችን ያመጣነውን ርግመትና ዕዳ በሞቱ ከፈለልንካሰልን፡፡ በአዳምና በሔዋን ውድቀት ምክንያት የሰው ልጅ በኃጢአትና በዲያብሎስ ባርነት ሥር ወድቆ ነበር:: ስለዚህ ሰው ለመዳን ይህ ባርነቱና ርግመቱ መወገድ ነበረበት። ይህንንም የእግዚአብሔር አንድያ ልጅ የሆነው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ገንዘብ ባደረገው በእኛ ባሕርይ በመስቀል ላይ በመሞቱ በመነሣቱ በማረጉና በአብ ቀኝ በመቀመጡ ፣ እንዲሁም መንፈስ ቅዱስን ለቅዱሳን ሐዋርያቱ በመላኩ ፈጽሞታል

ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ “በእንጨት የሚሰቀል ሁሉ የተረገመ ነው ተብሎ ተጽፏልና ክርስቶስ ስለ እኛ እርግማን ሆኖ ከሕግ እርግማን ዋጀን” በማለት እንደ ገለጸው በመስቀል ላይ በመሞት በእኛ ላይ የነበረውን ርግመትና ዕዳ አስወገደልን ፣ ነጻ አወጣን : እንደዚሁም “በእንጨት ላይ የተሰቀለ በእግዚአብሔር ዘንድ የተረገመ ነው” እንደ ተባለ ጌታችን የእኛን ርግመት በመቀበል ከዚያ የሕግ ርግመት ዋጀን፡፡ [ ዘዳ. 21፡23 ፣ ገላ. 3፡13 ]

ኢተረክበ ሐሰት ውስተ አፉሁ - በአንደበቱ ሐሰት አልተገኘበትም” እንደ ተባለ ንጹሐ ባሕርይ የሆነ እርሱ የእኛን በደል ተሽክሞ ከዕዳ ነጻ አረደገን::
[ ኢሳ. 53፡9 ፤ 1 ጴጥ. 2፡22 ] “በመስቀል ላይ በመሞቱ በሞት ተይዘው የነበሩትን እንዳዳናቸው ሁሉ ርግመታችንን በመሽከም ደግሞ ከርግመት አዳነን” እንዳለ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ::

ስለዚህም በሰው ልጅ ላይ ተፈርዶበት የነበረው የሞት ፍርድ ተወገደለት ፣ ተነሥቶት [ ተወስዶበት ] የነበረው ሕይወትም ተመለሰለት::

ራሱ መድኃኒታችን በቅዱስ ቃሉ ፦ “እንዲሁም የሰው ልጅ ሊያገለግል፣ ነፍሱንም ለብዙዎች ቤዛ ሊሰጥ እንጂ እንዲያገለግሉት አልመጣም” በማለት የገለጸው ይህን ማዳኑን ነው። ]ማቴ. 20፥28 ] ሐዋርያውም “ራሱንም ለሁሉ ቤዛ ሰጠ” ይላል:: [ 1ጢሞ.2፡6 ]

ቅዱስ ባስልዮስም፦ “እርሱ ራሱ ስለ እኛ ርግመት በመሆን የተረገምን ከመሆን አዳነን ፣ የውርደት ሞት የሆነውን ሞት በመቀበል ደግሞ ወደ ከበረው ሕይወት እንደገና መለሰን” ብሏል።

ቅዱስ ቄርሎስ ዘእስክንድርያም ፦ “ዮሐንስ መጥምቅ እንዳለው ጌታችን አማናዊ በግ ነው ፤ የዓለምን ኃጢአት ያስወገደና የፍጥረትን አጥፊ ያጠፋ ነው። ስለ ሁሉ በመሞቱ ሞታችንን ያጠፋ ዘንድና በእኛ ላይ የነበረውን መርገም ያስወግድ ዘንድ አማናዊው በግ ፣ ንጹሑ መሥዋዕት እርሱ ወደ መታረድ ተወሰደ፡፡ በዚህም አፈር ነህና ወደ አፈር ትመለሳለህ የሚለው ቅጣት ይወገድና ሁለተኛው አዳም ከመሬት ሳይሆን ከሰማይ ይገለጥ ዘንድ ነው” ብሏል፡፡ [ ዘፍ. 3፡19 ፤ 1 ቆሮ.15:47]


[  በሐሙስ መርሐ-ግብር ፦  ]

1 ] ኃጢአት ካመጣው ፍዳ ሁሉ መዳን [ ፪ ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

🕊

[ † እንኳን ለታላቁ ነቢይ ቅዱስ ሆሴዕ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ]

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †

🕊  †  ቅዱስ ሆሴዕ ነቢይ  †  🕊

† ነቢይ ማለት በቁሙ ኃላፍያትን [አልፎ የተሠወረውን ምሥጢር] : መጻዕያትን [ገና ለወደ ፊት የሚሆነውን] የሚያውቅ ሰው ማለት ነው:: ሃብተ ትንቢት የእግዚአብሔር የባሕርይ ገንዘቡ ሲሆን እርሱ ለወደደው ደግሞ በጸጋ ይሰጠዋል:: እነዚህም ከጌታ ሃብተ ትንቢት የተሰጣቸው አባቶችና እናቶች "ቅዱሳን ነቢያት" በመባል ይታወቃሉ::

ዘመነ ነቢያት ተብሎ የሚታወቀው ብሉይ ኪዳን ቢሆንም እስከ ምጽዓት ድረስ ጸጋውን እግዚአብሔር ለፈቀደላቸው አይነሳቸውም:: በሐዋርያት መካከልም ቅዱስ አጋቦስን የመሰሉ ነቢያት ነበሩ:: [ሐዋ.፲፩፥፳፯] ቅዱሳን ነቢያት ከእግዚአብሔር እየተላኩ ሰውን ከፈጣሪው እንዲታረቅ ይመክራሉ: ይገስጻሉ::

ከበጐ ሃይማኖታቸውና ንጽሕናቸው የተነሳም እግዚአብሔርን በተለያየ አርአያና አምሳል አይተውታል::
"እስመ በአንጽሖ መንፈስ ርዕይዎ ነቢያት ለእግዚአብሔር: ወተናጸሩ ገጸ በገጽ" እንዳለ አባ ሕርያቆስ:: [ቅዳሴ ማርያም]

የብዙ ነቢያት ፍጻሜአቸው መከራን መቀበል ነው:: እውነትን ስለ ተናገሩ: አንዳንዶቹም በእሳት: አንዳንዶቹም በሰይፍ: አንዳንዶቹም በመጋዝ ተፈትነዋል:: ሌሎቹ ለአናብስት ሲጣሉ ቀሪዎቹ ደግሞ በድንጋይ ተወግረዋል::

ስለዚህም መከራቸው ለቤተ ክርስቲያን መሠረት ተብለዋል:: ጌታም ለደቀ መዛሙርቱ "ሌሎች ደከሙ: እናንተ በድካማቸው ገባችሁ" ብሎ የነቢያቱን መከራ ተናግሯል:: [ዮሐ.፬፥፴፮]

ነቢያት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እና ድንግል እናቱን ለማየት ብዙ ጥረዋል: ሽተዋልም:: "ብዙ ነቢያትና ጻድቃን እናንተ የምታዩትን ሊያዩ ሹ" እንዳለ ጌታ በወንጌል:: [ማቴ.፲፫፥፲፮ , ፩ዼጥ.፩፥፲] ዛሬ ግን በሰማያት ጸጋ በዝቶላቸው: ክብር ተሰጥቷቸው ሐሴትን ያደርጋሉ::

ቅዱሳን ነቢያት በዋነኝነት

¤ ፲፭ [15] ቱ አበው ነቢያት :
¤ ፬ [4] ቱ ዐበይት ነቢያት:
¤ ፲፪ [12] ቱ ደቂቀ ነቢያትና
¤ ካልአን ነቢያት ተብለው በ፬ [4] ይከፈላሉ::

"፲፭ [15] ቱ አበው ነቢያት" ማለት :-

- ቅዱስ አዳም አባታችን
- ሴት
- ሔኖስ
- ቃይናን
- መላልኤል
- ያሬድ
- ኄኖክ
- ማቱሳላ
- ላሜሕ
- ኖኅ
- አብርሃም
- ይስሐቅ
- ያዕቆብ
- ሙሴና
- ሳሙኤል ናቸው::

"፬ [4] ቱ ዐበይት ነቢያት"

- ቅዱስ ኢሳይያስ ልዑለ ቃል
- ቅዱስ ኤርምያስ
- ቅዱስ ሕዝቅኤልና
- ቅዱስ ዳንኤል ናቸው::

"፲፪ [12] ቱ ደቂቀ ነቢያት"

- ቅዱስ ሆሴዕ
- አሞጽ
- ሚክያስ
- ዮናስ
- ናሆም
- አብድዩ
- ሶፎንያስ
- ሐጌ
- ኢዩኤል
- ዕንባቆም
- ዘካርያስና
- ሚልክያስ ናቸው::

"ካልአን ነቢያት" ደግሞ :-

- እነ ኢያሱ
- ሶምሶን
- ዮፍታሔ
- ጌዴዎን
- ዳዊት
- ሰሎሞን
- ኤልያስና
- ኤልሳዕ . . . ሌሎችም ናቸው::

ነቢያት በከተማም ይከፈላሉ::

- የይሁዳ [ኢየሩሳሌም]:
- የሰማርያ [እሥራኤል] ና
- የባቢሎን [በምርኮ ጊዜ] ተብለው ይጠራሉ::

በዘመን አከፋፈል ደግሞ :-

- ከአዳም እስከ ዮሴፍ [የዘመነ አበው ነቢያት] :
- ከሊቀ ነቢያት ሙሴ እስከ ነቢዩ ሳሙኤል [የዘመነ መሳፍንት ነቢያት]
- ከቅዱስ ዳዊት እስከ ዘሩባቤል ያሉት [የዘመነ ነገሥት ነቢያት]
- ከዘሩባቤል ዕረፍት እስከ መጥምቁ ዮሐንስ ያሉት ደግሞ [የዘመነ ካህናት ነቢያት] ይባላሉ::

ስለ ቅዱሳን ነቢያት በጥቂቱ ይህንን ካልን ወደ ዕለቱ በዓል እንመለስ::

ቅዱስ ሆሴዕ ቁጥሩ ከ፲፪ [12] ቱ ደቂቀ ነቢያት ሲሆን ዘመነ ትንቢቱም ቅ/ል/ክርስቶስ በ፰ መቶ [800] ዓ/ዓ አካባቢ ነው:: "ደቂቀ ነቢያት" ማለት በጥሬው "የነቢያት ልጆች" ማለት ነው:: አንድም የጻፏቸው ትንቢቶች ሲበዙ ፲፬ [14] ምዕራፍ: ሲያንስ አንድ ምዕራፍ ያላቸው ናቸውና ደቂቅ ይላቸዋል::

ነቢይና ጻድቅ ቅዱስ ሆሴዕ 'ዖዝያ' በመባልም ይታወቃል:: ቅዱሱ ነቢይ የቅዱስ ኢሳይያስ ልዑለ-ቃል ባልንጀራ የነበረ ሲሆን በ፬ [4] ነገሥታት ዘመን [ዖዝያን : ኢዮአታም : አካዝና ደጉ ሕዝቅያስ] ብዙ ሐረገ ትንቢቶችን ተናግሯል:: የትንቢት ዘመኑም ከ፸ [70] ዓመት በላይ ነው::

ከ፲፪ [ 12 ]ቱ ደቂቀ ነቢያት አንዱ የሆነው ቅዱስ ሆሴዕ ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የማዳን ሥራም በስፋት ተንብዩዋል:: ፲፬ [14] ምዕራፎች ያሉት የትንቢቱ ጥራዝ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ይገኛል:: ሆሴዕ ማለት መድኃኒት ማለት ነው:: የመዳን ትምሕርትንና ትንቢትን ሊናገር ተመርጧልና::

† ቸር አምላከ ነቢያት የነቢያቱን መከራ አስቦ ከመከራ: በእንባቸውም ከእንባ ይሰውረን:: ከተረፈ በረከታቸውም አያጉድለን::

🕊

[ † የካቲት ፳፮ [26] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. ቅዱስ ሆሴዕ ነቢይ [ከ፲፪ [12]ቱ ደቂቀ ነቢያት]
፪. ቅዱስ ሳዶቅ ሰማዕት
፫. ፰፻፰ ["808"] ሰማዕታት [ከቅዱስ ሳዶቅ ጋር የተሰየፉ]

[ † ወርሐዊ በዓላት ]

፩. ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ
፪. አቡነ ሐብተ ማርያም ጻድቅ
፫. አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ
፬. ቅዱሳን ሰማዕታተ ናግራን
፭. አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን

" ኑ ወደ እግዚአብሔር ቤት እንመለስ:: እርሱ ሰብሮናልና: እርሱም ይፈውሰናል:: እርሱ መትቶናል: እርሱም ይጠግነናል:: ከሁለት ቀን በሁዋላ ያድነናል:: በሦስተኛውም ቀን ያስነሳናል:: በፊቱም በሕይወት እንኖራለን:: እንወቅ:: እናውቀውም ዘንድ እንከተል . . . "
[ሆሴዕ.፮፥፩-፫]  (6:1-3)

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
💖                    🕊                     💖

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

ሰኞ - የካቲት 25 2016 ዓም

ኢያሱ 20 - 24

ሰላም ለሁላችሁ ይሁን! በዛሬው እለት ንባባችን ከምዕራፍ 20 እስከ 24 ድረስ እናነባለን።

ከንባብ በፊት የሚደረግ ጸሎት፡ “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፤ የአንተን ቃላት እሰማ እና እረዳ ዘንድ፥ እንዲያውም ፈቃድህን ለመፈጸም እበቃ ዘንድ የልቤን ጆሮዎች እና ዓይኖች ክፈትልኝ።” (ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ)

በዛሬው ንባባችን ላይ ስለ መማጸኛ ከተሞች፥ ለሌዋውያን ስለተሰጡ ከተሞች፥ እስራኤል እረፍት ስለማግኘታቸው፥ ኢያሱ ከዮርዳኖስ ማዶ የመጡትን ስለማሰናበቱ እና በዮርዳኖስ አጠገብ መሠዊያ እንደተሠራ እናነባለን። በተጨማሪም፥ የኢያሱ የመሰናበቻ ንግግር፥ ኢያሱ በሴሎ ያደረገው የመጨረሻ ንግግር እና የኢያሱና የአልዓዛር ሞት ተጽፎ ይገኛል።

ለዛሬ የክለሳ ጥያቄዎች አይኖሩንም።

መልካም ንባብ!
/channel/OrthodoxTewahdoBooks

/channel/+3kpzSPDfiVMzYzQ0

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

        †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬

[ እግዚአብሔር ከፊትህ ያሳድዳቸዋል ! ]


" አስማተኛም ፥ መተተኛም ፥ በድግምት የሚጠነቍልም ፥ መናፍስትንም የሚጠራ ፥ ጠንቋይም ፥ ሙታን ሳቢም በአንተ ዘንድ አይገኝ።

ይህንም የሚያደርግ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት የተጠላ ነው ፤ ስለዚህም ርኵሰት አምላክህ እግዚአብሔር ከፊትህ ያሳድዳቸዋል።

አንተ ግን በአምላክህ በእግዚአብሔር ዘንድ ፍጹም ሁን።" [ ዘዳ.፲፰፥፲፩ ]

🔔

ይልቁንም በዘመናችን ቤተክርስቲያን በመናፍቃን እንድትሰደብ ፤ ክብረ ክህነትም እንዲደፈር በማድረግ አባቶቻችን ካህናትን ከምዕመናን ለመለየት ሰይጣን ያዘጋጃቸውን እንዲህ ያሉ የዲያብሎስ ሠራዊቶችን ከእኛ ዘንድ እናርቅ ! እንዲህ ያሉት የክፋት ሰራተኞች ለሐሰተኛ አጥማቂያን የገበያ ምንጭ በመሆን እየተመጋገቡ እንደሚሰሩም እናስተውል !

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

                        †                             

†  🕊  ጳውሎስ ብርሃነ ዓለም  🕊 †


    [    የግእዝ መዝሙር ጥናት    ]

            [ ክፍል  - ፲፬  -  ]

የወንድማችን ድንቅ አገልግሎት ! ከጣእሙ ብዛት አጥንትን የሚያለመልም ዝማሬ መላእክትን ያሰማልን።

†                       †                        †
💖                    🕊                     💖

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

                       †                       

  [  🕊  ድምፀ ተዋሕዶ   🕊  ]  

🍒▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬🍒               

[  ሕይወት የሚገኝባቸው የቅድስት ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ትምህርቶች በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን በድምፅ ይቀርባሉ።  ]

[ ሳምንታዊ መርሐ-ግብር ]

🕊             

[    " ቅ ዱ ሳ ት   መ ጻ ሕ ፍ ት ! "    ]
             
          [     ክፍል ስምንት    ]

" ይህን በመጀመሪያ እወቁ ፤ በመጽሐፍ ያለውን ትንቢት ሁሉ ማንም ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደም ፤

ትንቢት ከቶ በሰው ፈቃድ አልመጣምና ፥ ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ተልከው ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ተናገሩ።" [፪ጴጥ.፩፥፳]


       💖   ድንቅ ትምህርት  💖

[ በመምህራችን በቀሲስ ኅብረት የሺጥላ ]

" የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ፥ ከመከራም ሥጋት ያርፋል።" [ ምሳ.፩፥፴፫ ]

         †              †               †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬
                       👇

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

                        †                         

[     ማ ኅ በ ረ     ቅ ዱ ሳ ን      ]

" ቤተ ክርስቲያንን በማይጠቅማት ጉዳይ የግል ፍላጎትንና ምድራዊ ዓላማን መሠረት አድርጋችሁ ከቤተ ክርስቲያን ሕግና ቀኖና ውጭ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊን ለመተካት ፣ ፓትርያርክ ለመሾምና የመሳሰሉትን ለመፈጸም የምትንቀሳቀሱ አንዳንድ አባቶች ከድርጊታችሁ እንድትታቀቡ ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡ "

[ ማኅበረ ቅዱሳን ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

                       †                       
                    
†   🕊   ክብርት ሰንበት   🕊   †

💖

❝ ሰንበት ተዓቢ እምኵሉ ዕለት ፤ ወሰብእ ይከብር እምኵሉ ፍጥረት ፤ አዕበያ ኖኅ በውስተ ታቦት አብርሃም አክበራ በውስተ ምሥዋዕ ፤ አዘዞሙ ሙሴ ለትዕይንት ያክብሩ ሰንበተ በጽድቅ። ❞

❝ ስብሐተ ወአኰቴተ ናዓርግ ለከ እምኲሉ ዕለት ሰንበተ አክበርከ ስብሐተ ወአኰቴተ ናዓርግ ለከ እምኩሉ ፍጥረት ሰብአ ዘአዕበይከ። ❞

ትርጉም ፦

[ ሰንበት ከሁሉም ቀኖች ትበልጣለች ፣ ሰውም ከሁሉም ፍጥረታት ይከብራል። [ ሰንበትን ] ኖኅ በመርከብ ውስጥ አከበራት ፤ አብርሃምም በምስዋኡ ላይ አከበራት። ሙሴም ለተሰበሰቡት ሕዝብ ሰንበትን በእውነት [ በጽድቅ ] እንዲያከብሩ አዘዛቸው። ]

[ ክብርና ምስጋና እናቀርብልሃለን ፣ ከሁሉም ዕለታት ሰንበትን ያከብርህ ፣ ክብርና ምስጋና እናቀርብልሃለን ፣ ከሁሉም ፍጥረታት ሰውን ከፍ ከፍ ያደርግህ። ]

🕊

[    ቅዱስ ያሬድ     ]

†                       †                        †
💖                    🕊                     💖

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

ቅዳሜ - የካቲት 23 2016 ዓም

ኢያሱ 10-14

ሰላም ለሁላችሁ ይሁን! በዛሬው እለት ንባባችን ከምዕራፍ 10 እስከ 14 ድረስ እናነባለን።

ከንባብ በፊት የሚደረግ ጸሎት፡ “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፤ የአንተን ቃላት እሰማ እና እረዳ ዘንድ፥ እንዲያውም ፈቃድህን ለመፈጸም እበቃ ዘንድ የልቤን ጆሮዎች እና ዓይኖች ክፈትልኝ።” (ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ)

በዛሬው ንባባችን ላይ አሞራውያን በእስራኤል ስለ መሸነፋው፥ ኢያሱ ነገሥታቱን እንደ ገደለ፥ ኢያሱ ሌሎች ከተሞችን ስለ መያዙ፥ ኢያሱ ኢያቢስንና ሌሎች ነገሥታትን ድል ስለማድረጉ፥ ሌሎች ግዛቶችን መያዙን እና ድል ስላደረጋቸው ነገሥት እናነባለን። በተጨማሪም ያልተያዙት ግዛቶች የተኞቹ እንደሆኑ፥ በዮርዳኖስ ምሥራቅ ስላለው ግዛት አከፋፈል፥ ለሮቤል እና ለምናሴ ነገድ ስለተሰጠው ርስት እና በዮርዳኖስ ማዶ ስላለው ርስት አከፋፈልም ተጽፎ ይገኛል።

*የክለሳ ጥያቄዎች*

1) በኢያሱ 10 መሠረት፥ ኢያሱ ከየት እስከ የት ያለውን ግዛት መታ?

2) በኢያሱ 11 መሠረት፥ እስራኤልን ተሰብስበው ለመምታት የተሰበሰቡት ነገሥታት ምን ያህል ነበሩ?

3) በኢያሱ 12 መሠረት፥ ሙሴ ለሮቤል፥ ለጋድ እና ለምናሴ ነገድ ምን እንደሰጠ ተጽፏል?

4) እግዚአብሔር ኢያሱ በሸመገለ ጊዜ ምን ብሎ ተናገረው?

5) በኢያሱ 14 መሠረት፥ የይሁዳ ልጆች በጌልገላ ወደ ኢያሱ ቀርበው ምን አሉ?

መልካም ንባብ!
/channel/OrthodoxTewahdoBooks

/channel/+3kpzSPDfiVMzYzQ0

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

ሐሙስ - የካቲት 28 2016 ዓም

መሳፍንት 11 - 14

ሰላም ለሁላችሁ ይሁን! በዛሬው ንባባችን ከምዕራፍ 11 - 14 ድረስ እናነባለን።

ከንባብ በፊት የሚደረግ ጸሎት፡ “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፤ የአንተን ቃላት እሰማ እና እረዳ ዘንድ፥ እንዲያውም ፈቃድህን ለመፈጸም እበቃ ዘንድ የልቤን ጆሮዎች እና ዓይኖች ክፈትልኝ።” (ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ)

በዛሬው ንባባችን ላይ ስለ ዮፍታሔ እና ከገለዓዳዊያን ጋር ስለገባው ስምምነት፥ አሞናውያንን ለመግጠም ስለመውጣቱ እና በዮፍታሔ ልጅ ላይ ስለሆነው እናነባለን። በተጨማሪም፥ ስለ ሶምሶን መወለድ፥ ፍልስጤማዊ ሴት ስለማግባቱ እና ለፍልስጤማውያን ስለ ጠየቀው እንቆቅልሽ እናነባለን።

*የክለሳ ጥያቄዎች*

1) በመሳፍንት 11 መሠረት ፥ ዮፍታሔ ምን ብሎ ለእግዚአብሔር ተሳለ? ውጤቱስ ምን ነበር?

2) ገለዓዳውያን ኤፍሬማውያንን ይለዩበት የነበረው ስልት ምንድር ነው?

3) የእግዚአብሔር መልአክ ለሶምሶን እናት ስለ ልጇ የሰጠው መመሪያ ምን ነበር?

4) ሶምሶን ፍልስጤማዊቷን ሴት ሊያገባ ሲሄድ በመንገድ ምን ገጠመው? ከዚያስ በኋላ ምን ተፈጠረ?

5) ፍልስጤማውያን የሶምሶንን እንቆቅልሽ ሊያውቁ የቻሉት እንዴት ነው? የእርሱስ ምላሽ ምን ነበር?

መልካም ንባብ!
/channel/OrthodoxTewahdoBooks

/channel/+3kpzSPDfiVMzYzQ

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

                         †                          

                 
" እንግዲህ እንደ ጥበበኞች እንጂ ጥበብ እንደሌላቸው ሳይሆን እንዴት እንድትመላለሱ በጥንቃቄ ተጠበቁ ፤

ቀኖቹ ክፉዎች ናቸውና ዘመኑን ዋጁ። ስለዚህ የጌታ ፈቃድ ምን እንደ ሆነ አስተውሉ እንጂ ሞኞች አትሁኑ። " [ ኤፌ.፭፥፲፭ ]


         †              †               †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

ረቡዕ - የካቲት 27 2016 ዓም

መሳፍንት 6 - 10

ሰላም ለሁላችሁ ይሁን! በዛሬው ንባባችን ከምዕራፍ 6 - 10 ድረስ እናነባለን።

ከንባብ በፊት የሚደረግ ጸሎት፡ “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፤ የአንተን ቃላት እሰማ እና እረዳ ዘንድ፥ እንዲያውም ፈቃድህን ለመፈጸም እበቃ ዘንድ የልቤን ጆሮዎች እና ዓይኖች ክፈትልኝ።” (ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ)

በዛሬው ንባባችን ላይ የጌዴዎንን ለመስፍንነት መጠራት፥ ጌዴዎን መገለጡ ከእግዚአብሔር መሆኑን ለማረጋገጥ ያደረጋቸውን ተግባራት፥ እግዚአብሔር በምን አይነት መንገድ ወታደሮችን እንዲመርጥ እንዳደረገው እናነባለን። በተጨማሪም፥ አቤሜሌክ በወንድሞቹ ላይ ስላደረገው ግፍ፥ መጨረሻው ምን እንደሆነ እና ከዚያ በኋላ እግዚአብሔር ስላስነሳቸው የተለያዩ መሳፍንት ተጽፎ እናነባለን።

*የክለሳ ጥያቄዎች*

1) በመሳፍንት 6 መሠረት፥ የእግዚአብሔር መልአክ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር እንደሆነ ለጌዴዎን ሲነግረው፥ የጌዴዎን ምላሽ ምን ነበር?

2) ጌዴዎን በማታ ያደረገው ነገር ምንድር ነው? ለምንስ በማታ አደረገው?

3) ጌዴዎን መልእክቱ ከእግዚአብሔር እንደሆነ ለማረጋገጥ ያደረጋቸው ነገሮች ምንድር ናቸው?

4) ጌዴዎን ከተከተሉት ሕዝብ መካከል ለውጊያ የመረጠው እንዴት ባለ መንገድ ነው?

5) አቤሜሌክ ማነው? ኃጢአቱስ ምን ነበር?

6) የአቤሜሌክ መጨረሻ ምን ሆነ?

7) በመሳፍንት 10 መሠረት፥ እስራኤላውያን እግዚአብሔርን ምን ብለው ለመኑ?

መልካም ንባብ!
/channel/OrthodoxTewahdoBooks

/channel/+3kpzSPDfiVMzYzQ

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

                         †                          

                 

" የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ።" [ማቴ.፲፩፥፲፭]



         †              †               †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

                        †                             


አለቅየው እኔም አለብኝ ፤ ሁላችሁም አለባችሁ እያለ ነው !


         †              †               †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

ማግሰኞ - የካቲት 26 2016 ዓም

መሳፍንት 1 - 5

ሰላም ለሁላችሁ ይሁን! በዛሬው እለት ንባባችን መጽሐፈ መሳፍንትን እንጀምራለን። ይህ መጽሐፍ በእስራኤል ላይ ይፈርዱ የነበሩ መሳፍንትን ታሪክ የያዘ መጽሐፍ ነው። በዛሬው ንባባችን ከምዕራፍ 1 - 5 ድረስ እናነባለን።

ከንባብ በፊት የሚደረግ ጸሎት፡ “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፤ የአንተን ቃላት እሰማ እና እረዳ ዘንድ፥ እንዲያውም ፈቃድህን ለመፈጸም እበቃ ዘንድ የልቤን ጆሮዎች እና ዓይኖች ክፈትልኝ።” (ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ)

በዛሬው ንባባችን ላይ የይሁዳና የስምዖን ነገድ አዶኒቤዜቅን ስለመማረካቸው፥ ኢየሩሳሌምና ኬብሮን በይሁዳ ስለመያዛቸው፥ ጎቶንያል ዳቤንን ስለመያዙ፥ ስለ ኢያሱ ሞት እና እግዚአብሔር መሳፍንትን ስለማስነሳቱ እናነባለን። በተጨማሪም ስለ ዲቦራና ባርቅ እና ስለዘመሩት መዝሙርም ተጽፎ ይገኛል።

ለዛሬ የክለሳ ጥያቄዎች አይኖሩንም።

መልካም ንባብ!
/channel/OrthodoxTewahdoBooks

/channel/+3kpzSPDfiVMzYzQ

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

                      †                           

[    ፪ ተኛ ዓመት መታሰቢያ !     ]


ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ የካቲት ፳፭ ቀን ፳፻፲፮ ዓ.ም [ 25  2016 ዓ.ም ] ፪ ተኛ ዓመት መታሰቢያ !


ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን። የአባታችን በረከታቸው ፤ ድል የማትነሳ ጥርጥር የሌለባት ተዋሕዶ ሃይማኖታቸው በእውነት ከእኛ ጋር ጸንታ ለዘላለሙ ትኑር አሜን።

የቅዱስነታቸው በረከት አይለየን !

         †              †               †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

                        †                             

[ ሴቲቱም ገበያውን ተቀላቅላለች ! ]


የወንዶቹ ዘራፊዎች ሲገርመን እነሆ አጥማቂ ነኝ የምትል ግለሰብ አርሲ በቆጂ እግዚአብሔር አብ ቤተክርስቲያን ድረስ ሰተት ብላ ገብታ እያንጫጫችው ነው።

ምን ተሻለን ? !

         †              †               †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

🔔


የዘመኑ አጥማቅያን እና የአጋንንት ምስክርነት !

[   ክፍል ዘጠኝ   ]

▬▬▬▬▬▬

የኖላዊነት አደራ !

----------------------

የሐሰተኛ አጥማቂዎች የስህተት አሠራር የቅድስት ቤተክርስቲያንን ቅድስና የሚጻረር የሰይጣን ፈተና ነው። ቅድስት ቤተክርስቲያን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በገዛ ደሙ የመሠረታት የእውነት ሁሉ አምድ ናት። መልኳም ፍጹም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። የቅድስና ፥ የንጽሕናና የጸጋ ሁሉ ምንጭ ናት። ቅዱሳን ፥ ጻድቃንና ሰማዕታት ሁሉ የተጋደሉላት ማህደረ መንፈስ ቅዱስ ናት። አጋንንታዊ የሆኑ የስህተት አሠራሮች ለባህርይዋ ፈጽሞ የሚስማሙ አይደሉም። ሐሳውያንና የስህተት አሠራራቸው በቤተክርስቲያን መኖር የማይችሉበት ዋነኛ ምክንያት እርሷ የእውነት አምላክ ማደሪያ በመሆኗ ነው።

"በእግዚአብሔር ማደሪያ ቤት መኖር እንዴት እንደሚገባ ታውቅ ዘንድ እጽፍልሃለሁ ፤ ቤቱም የእውነት ዓምድና መሠረት ፥ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ነው።"
[፩ጢሞ.፫፥፲፭]

የእውነት ዓምድና መሠረት የሆነችው ቅድስት ቤተክርስቲያንን ፈጽሞ ሊያሸንፋት ባይችልም የጽድቅ ሁሉ ጠላት የሆነው ጠላት ዲያብሎስ ሊተኛላት ከቶ አይችልም። መልካም ሥራ በሽታው ፣ ጽድቅ መከራው ፣ መንግሥተ እግዚአብሔር ሽንፈቱ ፥ የሠው ልጅ ድህነት ውርደቱ ነውና መልካቸው ልዩ ልዩ በሆኑ ፈተናዎች ይዋጋታል። ይፈትናታል።

የስህተት መንፈስና አሠራርን ይዘው  ወደ ቤተክርስቲያን ሾልኮ የገቡት ሐሰተኛ አጥማቂያን በሌላቸው ሥራ የማይኖሩበትን ሕይወት በአደባባይ በማሳየት የጽድቅ አገልጋዮችና እውነተኛ መስለው ለመታየት ይጥራሉ።

የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ የሆኑት እውነተኞቹ አባቶቻችን ቅዱሳን ዓለምንና መልኳን በመናቅና በመጸየፍ ስለ እግዚአብሔር መንግሥት በሥውር ሲጋደሉ እንደኖሩና እንደሚኖሩ ሁሉ የሰይጣን ማደሪያ የሆኑት ሃሰተኞች ደግሞ በተቃራኒው ገንዘብን ስለመውደድና ስለ ሥጋ ምኞት በዓለም ነግሠውና ከብረው በዓለም ሰልጥነው ይኖራሉ። ዓለሙም ይከተላቸዋል።

" ገንዘብን መውደድ የክፋት ሁሉ ሥር ነውና ፥ አንዳንዶች ይህን ሲመኙ ፥ ከሃይማኖት ተሳስተው በብዙ ሥቃይ ራሳቸውን ወጉ።" [፩ጢሞ.፮፥፲]

ሐሰተኛ አጥማቂዎች ወደ ቤተክርስቲያን ሾልከው እንዲገቡና በጎቹን እንዲዘርፉ ምክንያት የሆኑትን ሁኔታዎች በሦስት መንገድ ማየት ይቻላል።

፩. የአጥሩና የቅጥሩ መላላት [የሥርዓተ ቤተ-ክርስቲያን መላላት]
፪. የመንጋው እረኞች መዘናጋትና የኖላዊነትን አደራ አለመወጣት
፫. በጎቹ የእረኛቸውን ድምፅ ለይተው አለማወቃቸው ዋነኞቹ ናቸው።

የቅድስት ቤተክርስቲያን አጥር ቅጥር ሥርዓተ ቤተክርስቲያን ነው። ይህ አጥር ነጣቂ ተኩላዎችና ጨካኝ አራዊት ወደ ዕረፍት ውኃና ወደ ለምለሙ መስክ እንዳሻቸው ገብተው በጎችን እንዳይበሉ ይጠብቃል። ከበስተውጪ ያስቀራቸዋል። አጥር ቅጥሩ ሲላላ ግን ውሻውም ጅቡም እንደፈለገ እየሾለከ እንዲገባ ቀዳዳ ያገኛል። ሐሳዊ አጥማቂዎች ወደ ቤተክርስቲያን ሾልከው መግባት የቻሉት ሥርዓተ ቤተክርስቲያን እንዲጣስ በመደረጉ ነው። በሌላቸው መንፈሳዊ ተጋድሎና የቅድስና ሕይወት አጥማቂ እገሌ ብለው ራሳቸውን ሲሾሙ ተዉ እረፉ የሚል አልነበረም። ቅብዓ ቅዱስ እያሉ ዘይት ሲያከፋፍሉ ፣ የአጋንንትን ስብከት በሲዲ ቀርጸው ሲሸጡ ፣ መቁጠሪያ እያሉ እያመረቱ ሲቸበችቡ ፣ ምስላቸው በመላው ዓለም ከፍ ብሎ ሲሰቀል ፣ ብዙ ምዕመናን ክብራቸውን ፣ ጤናቸውንና ሕይወታቸውን ሲያጡ ፣ ምስጢራተ ቤተክርስቲያን መቀለጃና መጫወቻ ሲሆኑ ጠያቂና ተቆጪ አልነበረም። በዚህ መልኩ የቤተክርስቲያን አጥር ቅጥር ሲነቃቀልና ሲፈራርስ ይዞት የሚመጣው ብርቱ መቅሰፍትና መከራ ሰው ሊሸከመው የሚችል አልነበረም። ሥርዓተ ቤተክርስቲያን የቤተክርስቲያን አጥር ነውና ሊከበር ይገባዋል። ይህንን የቤተክርስቲያን ሕይወት መጠበቂያ አጥርን ማጠባበቅ ሐሰተኞችን የመከላከያው ዋነኛው መንገድ ነው። ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን መጠበቅ የአባቶችም የምዕመናንም ድርሻና መንፈሳዊ ኃላፊነት ነው።

" ቅጥርንም የሚያፈርስን እባብ ትነድፈዋለች።"
[መክ.፲፥፰]

ሌላኛው የኖላዊነት ተግባር ነው። መንጋቸውን በሌሊት ሲጠብቁ የነበሩ የቤተልሔም እረኞች የአዲስ ኪዳን ካህናት ምሳሌዎች ናቸው። ሰው በተኛበት በሌሊት ሰዓት በጎቹን ነቅተው የሚጠብቁ ትጉኃን ናቸውና። የነቁ እረኞች አንዲቷንም የበግ ግልገል በአራዊት አያስነጥቁም። ስለበጎቹ ደህንነት ለእንቅልፍና ለስንፍና እጅ የሚሰጡ አይደሉም። በሌሊቱ ክፍል እንኳ ንቁዎች ናቸው። በትጉኃን እረኞች የሚጠበቁ በጎች በነጣቂ ተኩላዎች ከመነጠቅ ሥጋት ነጻ በመሆናቸው ያለ ሥጋት በመስኩ ላይ ይሰማራሉ። እውነተኛው የነብሳችን እረኛ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነብሱን ስለ በጎቹ አሳልፎ በመስጠት እውነተኛ ኖላዊትን አስተምሯል።

"መልካም እረኛ እኔ ነኝ። መልካም እረኛ ነፍሱን ስለ በጎቹ ያኖራል። እረኛ ያልሆነው በጎቹም የእርሱ ያልሆኑ ሞያተኛ ግን ተኵላ ሲመጣ ባየ ጊዜ በጎቹን ትቶ ይሸሻል ፤ ተኵላም ይነጥቃቸዋል በጎቹንም ይበትናቸዋል። ሞያተኛ ስለ ሆነ ለበጎቹም ስለማይገደው ሞያተኛው ይሸሻል።" [ዮሐ.፲፥፲፩]

ለአባቶች ካህናት የተሰጠው አደራ ይህ የኖላዊነት አደራ ነው። ቆጥሮ የሰጣቸውን በጎች ኋላ ይቆጣጠራቸዋልና። ሐሰተኛ ሠራተኛ ፥ መናፍቅ ጳጳስ ፥ አላዊ ንጉሥ በተነሣ ጊዜ መንጋውን ጥለው ሳይሸሹ ዋጋ እንዲከፍሉ ተሹመዋልና።

" የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ ፥ ትወደኛለህን? አለው። አዎን ጌታ ሆይ ፥ እንድወድህ አንተ ታውቃለህ አለው። ጠቦቶቼን ጠብቅ አለው" [ዮሐ.፳፩፥፲፮]

ሐሰተኛ አጥማቂያን ወደ ቅድስት ቤተክርስቲያን እንዲሰርጉ ዋነኛው ምክንያት ለገቢ እየተባለ የኖላዊነትን ሰማያዊ አደራ እያጎደሉ ባሉ የቤተክርስቲያን አስተዳዳሪዎችና የቤተክህነት ኃላፊዎች የተነሳ ነው። ይህ የገንዘብ ጉዳይ እናት ቤተክርስቲያንን ምን ያህል ለፈተና እንደዳረጋትና ልጆቿን እንዳጎሳቆለባት የሚያውቅ ያውቀዋል። የኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ሃይማኖት ልዕልናና ቅድስናዋን ፍጹም የሚቃረኑ የእርኩሰት ተግባራት ጉልበት እያገኙ የመጡት ስለ ገንዘብና ስለ ጥቅም ተብሎ ዕንቁዎቻችን በዕርያዎች ፊት በመጣላቸው የተነሳ ነው። አፍ ማዘጊያ የሚሆን ረብጣ ብር ለተሸከሙ ሲሞናውያን ቤተክርስቲያንንና የዋሃን ምዕመናንን አሳልፎ መስጠት በአስቸኳይ ሊቆም የሚገባው ለዘብተኛ ክህደት ነው። የኖላዊነት አደራ ብርቱ ነውና ኋላ ፍርድ አለበት። በገድል የተቀጠቀጡ ፤ በተጋድሎ የጸኑ አበው በቆሙበት የቅድስናው አደባባይ ላይ ገንዘብን ሥለመውደድ ምክንያት ሐሰተኞች እንዲፈነጩበት ፤ አጋንንት እንዲሰብኩበት ፤ ሰይጣናዊ ምልክትና ድንቆች እንዲታዩበት ፤ ምዕመናን በአደባባይ እንዲዘረፉበት ማድረግ እጅግ የሚያስፈራ ጥፋት ነው። ስለ እረኞች ፦

" ብዙ እረኞች የወይኑን ቦታዬን አጥፍተዋል ፥ እድል ፈንታዬንም ረግጠዋል ፤ የአምሮቴን እድል ፈንታ ምድረ በዳ አድርገውታል። " [ኤር.፲፪፥፲]

በሌላ ሥፍራም ፦

" የማሰማርያዬን በጎች ለሚያጠፉና ለሚበትኑ እረኞች ወዮላቸው! ይላል እግዚአብሔር።"
[ኤር.፳፫፥፩] ይላል።

የዚህ ችግር ሌላኛው ምክንያት ማለትም "በጎቹ የእረኛቸውን ድምፅ ለይተው አለማወቃቸውን በተመለከተ ብንኖር በቀጣይ መርሐ-ግብር የሚቀርብ ይሆናል።

የቅዱሳን አባቶቻችን አምላክ እግዚአብሔር ቤተክርስቲያንን ይጠብቅልን።

         †              †               †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

🕊

[ † እንኳን ለጻድቁ አባታችን ቅዱስ አቡፋና እና ቅዱስ እንጦኒ ሐዲስ ሰማዕት ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ]

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †


🕊  †  አባ አቡፋና   †    🕊

† ታላቁ አባ አቡፋና ፦
በምድረ ግብጽ ተጋድሏቸውን የፈፀሙ፣
በመዐልት አምስት መቶ ጊዜ በሌሊትም አምስት ጊዜ አቡነ ዘበሰማያትን ይጸልዩ የነበሩ፣
በአርባ ቀን አንድ ጊዜ ብቻ እህል ይቀምሱ የነበሩና ሙሉ ዘመናቸውን በበርሃ በታላቅ ጽሙና የፈፀሙ አባት ናቸው።

ጻድቁ በጣም የሚታወቁት ከማበጡ የተነሳ እጅግ ግዙፍ በነበረ እግራቸው ነው። ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ ስለ መድኃኔ ዓለም ፍቅር አልቀመጥም፤ አልተኛም ብለው ለአሥራ ስምንት ዓመታት በመቆማቸው ነው።

አሥራ ስምንት ዓመት የመቆማቸው ዜናስ እንደምን ነው ቢሉ ፦
አንድ ቀን "እኔ ግን ከዚህ ዓለም የምለየው መቼ ይሆን?" ሲሉ አሰቡ። በእርግጥ ይህንን ሐሳብ ብዙ ሰዎች ሊያስቡት ይችላል። ሐሳቡ ጠቃሚም ያልተፈቀደም ነው።
፩. "ጠቃሚ ነው።" ያልኩት አንድ ሰው ሞት እንዳለ ካወቀ ወይም 'መቼ ነው የምሞተው' ብሎ ካሰበ ንስሐ ይገባል ፤ ክፋትን ይተዋል ተብሎ ስለሚታመን ነው። ወገኔ ሁሉ እንደ አውሬ ሲባላ ፣ ደም ሲያፈስ ፣ ክፋትን ሲጐነጉን የሚውል "እሞት ባይ" ሳይሆን "እኖር ባይ" ሆኖ ነውና።
ግን ሞት በቅርቡ እንዳለ በኃያሉ አምላክ ፊት ራቁቱን ለፍርድ እንደሚቀርብ ለወገኔ ማን በነገረው !
፪. "ያልተፈቀደ ነው።" ያልኩት ደግሞ በሁለት ምክንያት ነው።
"ኢትበሉ ለጌሰም [ ለነገ አትበሉ። ]" የሚል አምላካዊ ቃል ስላለ። [ማቴ. ፮፥፴፬]
ሰው [በተለይ ዓለማዊው] የሚሞትበትን ቀን ቢያውቅ አጭር ጊዜ ከሆነ ሽብር ጭንቀት ይበላዋል። ወዲህ ደግሞ ጊዜው ረዥም ቢሆን እንደ ሰብአ ትካት [ማለትም በኖኅ ዘመን እንደ ነበሩ ሰዎች] 'ብዙውን ልዝናናበት [ኃጢአት ልሥራበት']ና ንስሐ እገባለሁ።' ይላልና ነው።

በዚያውም ላይ በቤተ ክርስቲያን ትውፊት መሠረት ቅዱስ ሰውና የነቢያት አለቃ ቅዱስ ሙሴ የሞቱን ጊዜ ጠይቆ እጅግ መቸገሩን መጥቀሱ በራሱ በቂ ነው። ጌታ "ዓርብ ቀን ትሞታለህ።" ብሎት ለሁለት ዓመታት ዓርብ ዓርብ ሲገነዝ ሲፈታ ኑሯል።

በመጨረሻም ዓርብ ቀን ድንገት መልአከ ሞት መጥቶበታል። ስለዚህ "ወድልዋኒክሙ ንበሩ - ተዘጋጅታችሁ ኑሩ። መባላችንን አስበን ልንኖር ግድ ይለናል። [ማቴ. ፳፬፥፵፬]

ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስና ቅዱስ አቡፋና ይህንን የዕረፍታቸውን ነገር ሲያስቡ ቅዱስ መልአክ ተገልጦ "ተርፈከ አሠርቱ ወሰመንቱ - አሥራ ስምንት ቀርቶሃል።" አላቸው። እርሳቸውም "ጌታዬ አሥራ ስምንት ምን?" ሲሉ ቢጠይቁትም ሳይመልስላቸው ተሠወረ።

ከደቂቃ እስከ ኢዮቤልዩ ብዙ አሥራ ስምንቶች አሉ። እርሳቸው ግን "አሥራ ስምንት ቀን ነው!" ብለው ለጌታ ተሳሉ። ስዕለታቸውም "ከዚህ በኋላ አልቀመጥም።" የሚል ነው። እየጾሙ እየጸለዩ ለአሥራ ስምንት ቀናት ቆሙ። ሞት አልመጣም።

"አሥራ ስምንት ሱባኤ ይሆን!" ብለው አሥራ ስምንት ሱባኤ [መቶ ሃያ ስድስት ቀናት] ቆመው ጸለዩ። አሁንም ሞት አልመጣም። "አይ! አሥራ ስምንት ወር ሊሆን ይችላል።" ብለው ለአሥራ ስምንት ወራት (ለአንድ ዓመት ከስድስት ወር) ቆመው ተጉ። አሁንም ግን ሞት የውኃ ሽታ ሆኖ ቀረ።

ይህን ጊዜ ግን ወደ ፈጣሪ ለመኑ። "ጌታዬ! ያልከኝ ምን አሥራ ስምንት ነው?"
ቅዱስ መልአኩም መጥቶ "አቡፋና ሆይ! የቀረህ አሥራ ስምንት ዓመት ነውና ጽና።" ብሏቸው ተሰወረ። ልብ በሉልኝ "እስክሞት አልቀመጥም።" ብለው ተስለዋል።

ቅዱሱ ገዳማዊ በቃላቸው የሚገኙ እውነተኛ ክርስቲያን ነበሩና ለአሥራ ስምንት ዓመታት እንደተተከለ ምሰሶ ቆመው ጸለዩ፣ ጾሙ። እንዲህ ያሉትን ቅዱሳን ሊቃውንት፦
"ሰላም ለከ ጽኑዕ ከመ ዓምድ
ዘኢያንቀለቅሎ ሞገድ።"
[ማዕበለ ዓለም የማያናውጸው ብርቱ ምሰሶ ሆይ! ምስጋና ይገባሃል።] የሚሏቸው።

ስለ ቅዱሱ የተጻፈ አርኬም ፦
"ሰላም ለቁመተ አቡፋና ዘአልቦ ኑታጌ
እስከ ተመሰለ እግሩ ከመ እግረ ነጌ።" ይላል። ከመቆም ብዛት አካላቸው ደቆ እግራቸው የዝሆን እግር እስኪመስል ወፍሮ ነበርና።

† አባ አቡፋና በዘመናቸው ብዙ ተአምራትን ሠርተው በዚህች ቀን አርፈዋል።


🕊 † ቅዱስ እንጦኒ ሐዲስ ሰማዕት †  🕊

† ቅዱስ እንጦኒ [Anthony] በትውልዱ ከሶርያ ዐረቦች ሲሆን በቀደመ ሕይወቱ ክርስቲያኖችን ያሳድድ ፣ ካህናትን ይደበድብ ፣ አብያተ ክርስቲያናትንም ያቃጥል ነበር። እግዚአብሔር በንስሐ ሲጠራው ግን ደግ ፣ ጻድቅና ምርጥ ዕቃ ሆኖ ተገኘ። በመጨረሻም ከብዙ መከራ በኋላ ለሰማዕትነት በቅቷል።

† አምላከ ቅዱሳን የወዳጆቹን ትጋት፣ ጽናት፣ ፍቅርና በረከት ያድለን። ከማስተዋልም አያጉድለን።

🕊

[ † የካቲት ፳፭ [ 25 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. ቅዱስ አባ አቡፋና ጻድቅ
፪. ቅዱስ እንጦኒ ሐዲስ ሰማዕት
፫. ቅዱሳን ሰማዕታት አውሳንዮስ፣ ፊልሞናና ሉቅያ ድንግል [የቅዱስ ጳውሎስ ሐዋርያ ደቀ መዛሙርት]
፬. ቅዱስ ቶና ዲያቆንና ሰማዕት
፭. ቅዱስ ሚናስ ዘሃገረ ቁስ

[ † ወርኀዊ በዓላት ]

፩. ቅዱስ መርቆሬዎስ ሰማዕት
፪. ቅድስት ቴክላ ሐዋርያዊት
፫. ቅዱስ አበከረዙን ሰማዕት
፬. ቅዱስ ዱማድዮስ ሶርያዊ
፭. አቡነ አቢብ [ አባ ቡላ ]

" ኃይል የሰጠኝን ክርስቶስ ኢየሱስን ጌታችንን አመሰግናለሁ። አስቀድሞ ተሳዳቢና አሳዳጅ አንገላችም ምንም ብሆን ይህን አደረገልኝ። ነገር ግን ሳላውቅ ባለማመን ስላደረግሁት ምሕረትን አገኘሁ።" † [፩ጢሞ ፩፥፲፪-፲፫]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
💖                    🕊                     💖

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

እሑድ - የካቲት 24 2016 ዓም

ኢያሱ 15-19

ሰላም ለሁላችሁ ይሁን! በዛሬው እለት ንባባችን ከምዕራፍ 15 እስከ 19 ድረስ እናነባለን።

ከንባብ በፊት የሚደረግ ጸሎት፡ “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፤ የአንተን ቃላት እሰማ እና እረዳ ዘንድ፥ እንዲያውም ፈቃድህን ለመፈጸም እበቃ ዘንድ የልቤን ጆሮዎች እና ዓይኖች ክፈትልኝ።” (ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ)

በዛሬው ንባባችን ላይ ለይሁዳ ስለተሰጠው ርስት፥ ካሌብ ኬብሮንን እና ዳቤርን ስለመያዙ፥ ለኤፍሬምና ለምናሴ ነገድ እኩሌታ ስለተሰጠው ርስት፥ ተጨማሪ ርስት ስለጠየቁት ነገዶች እና ለሌሎች ነገዶች የቀረው ርስት እንዴት እንደተከፋፈለ እናነባለን። 

ለዛሬ የክለሳ ጥያቄዎች አይኖሩንም።

መልካም ንባብ!
/channel/OrthodoxTewahdoBooks

/channel/+3kpzSPDfiVMzYzQ0

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

                        †                         

[   ሀ ገ ረ እ ግ ዚ አ ብ ሔ ር     ]

" አገራችን እንዲሁ በዋዛ የምትፈነከት ራስ አይደለችም... ኢትዮጵያ ኢትዮጵያዊነቷን አትለቅም "

[  ብፅዕ አባታችን አቡነ ሰላማ  ]

በረከታቸው ይደርብን።

         †              †               †
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

†                †                  †
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

[     ቤተክርስቲያንን እንወቅ     ]

         [  ክፍል -  ፳፩  -  ]
                   
[    ሥ ር ዓ ተ    አ ም ል ኮ !     ]

🕊

ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን። "ቤተክርስቲያንን እንወቅ" በተሰኘው ሳምንታዊ መርሐ-ግብር ባለፈው ሳምንት ሥርዓተ አምልኮት በሚለው ዓብይ ርዕስ ሥር ሥርዓተ ቅዳሴ በመጽሐፍ ቅዱስ የሚለውን ተመልክተን ነበረ። የዛሬው መርሐ-ግብር እነሆ !

[  🕊 ሥርዓተ ቅዳሴ  🕊 ]

" ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም ይሁን ሰላምም በምድር ለሰውም በጎ ፈቃድ" [ሉቃ፣ ፪ ፥ ፲፬]

ሥርዓተ ቅዳሴ የሚለውን ቃል ስንመለከት "ሥርዓት" ማለት አሠራር ፣ አፈፃጸም ተብሎ የሚተረጎም ሲሆን "ቅዳሴ" ደግሞ ምሥጋና ማለት ነው ፤ ይኸውም ለፈጣሬ ሰማያት ወምድር ለእግዚአብሔር የሚቀርብ ምሥጋና ማለታችን ነው።

እንግዲህ ቅዳሴ በሐዲስ ኪዳን የተጀመረው በቤተ ልሔም ሲሆን የጀመሩትም ሰማያውያን መላእክት ናቸው ፤ ጌታችንና አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአባታችን ለአዳም "በ፭ሺ ፭መቶ ዘመን ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ" ያለው አምላካዊ የተስፋ ቃል ሲፈጸም ቤተ ልሔም በምትባል የዳዊት ከተማ "ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት ወሰላም በምድር ስምረቱ ለሰብእ" ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም ይሁን ፤ ሰላምም በምድር ለሰውም በጎ ፈቃድ እያሉ ሰማያውያን መላእክት እንዳመሰገኑ በሉቃስ ወንጌል ምዕ. ፪ ቁ፥፲፬ ተጽፎ እናገኛለን።

የቅዳሴ አገልግሎት ማከናወኛ /መፈጸሚያ/ የሆነው ሥርዓታችን የተጀመረው ለስም አጠራሩ ክብር ምሥጋና ይግባውና ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በጸሎተ ሐሙስ ለደቀ መዛሙርቱ ኅብስቱን አንሥቶ ባርኮ ቆርሶ  “እንካችሁ ብሉ ይህ ሥጋዬ ነው ፤ ጽዋውንም ይዞ አክብሮ አመስግኖ ሁላችሁም ከእርሱ ጠጡ ስለ ብዙዎች ለኃጢአት ይቅርታ የሚፈስ የአዲስ ኪዳን ደሜ ይህ ነው” በማለት የቅዱስ ቁርባንን ሥርዓት ሲሰጠን ነው።  [ማቴ. ፳፮፣ ፳፮፥፳፱  ማር፥ ፲፬፣ ፳፪፥፳፭]

ሥርዓተ ቅዳሴ /የቅዳሴ ሥርዓት/ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከጸሎት ሁሉ በላይ የሆነ ፤ ምስጋናውን ከሰማያውያን መላእክት ፣ ሥርዓቱን በአባቶቻችን ሐዋርያት አማካኝነት ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ የተቀበልነው ታላቅ ጸሎትና በሀገራችን በኢትዮጵያ እንዲሁም አመቺ በሆኑ ቤተ ክርስቲያናችን በተስፋፋችባቸው የውጪ ሀገራት ሳይቋረጥ ዕለት ዕለት የሚፈጸም ሥርዓት ነው።

የቅዳሴ ሥርዓት አገልግሎት በሚፈጸምበት ቦታ ቅዱሳን መላእክት እንደ ቅጠል ረግፈው ፣ እንደ ሻሽ ተነጥፈው የሚያከብሩት ፣ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንም ኅብስቱን በጻሕል ፣ ወይኑን በጽዋ በማቅረብ ኅብስቱ ሥጋ ወልደ እግዚአብሔር ፤ ወይኑ ደመ ወልደ እግዚአብሔር ሆኖ የሚለወጥበትን ሥርዓት የምታከናውንበት ጸሎት ነው።

የቅዳሴ ሥርዓት ካህናትና ምእመናን በአንድነት በመሆን ለአምላካችን ምስጋና የምናቀርብበት ፣ ለበደላችን ይቅርታና ምሕረት የምንጠይቅበት ፣ ከላይ እንደተጠቀሰው ኅብስቱና ወይኑ የሚለወጥበት የጋራ የጸሎት ክፍለ ጊዜ ነው ፤ በቅዳሴ ጸሎት "እግዚኦ ተሣሃለነ" አቤቱ ይቅር በለን "ተዘከረነ እግዚኦ በውስተ መንግሥትከ…" አቤቱ በመንግሥትህ አስበን "ንዜኑ ሞተከ እግዚኦ ወትንሣኤከ ቅድስተ…" አቤቱ ሞትህንና ልዩ የሚሆን ትንሣኤህን እንናገራለን በማለት "እኔ" ብለን ሳይሆን "እኛ" እያልን ከፈጣሪያችን ጋር የምንገናኝበት የጸሎት ሰዓት በመሆኑ በቅዳሴ ጊዜ የግል ጸሎት የተከለከለ ነው። ከሁሉም በላይ ልናስተውለው የሚገባን በቅዳሴው አገልግሎት ከግል ጸሎት ተቆጥበን ኅሊናችንን በመሰብሰብ ስንሣተፍ /ስንቀድስም ሆነ ስናስቀድስ / የጸሎቱ/ የሥርዓቱ/ ተካፋዮች መሆናችንን ነው።

በቅዳሴ ጸሎት በመሳተፋችን የኃጢአት ስርየት እናገኛለን ፤ በረከተ ሥጋም በረከተ ነፍስም እንታደላለን ፤ ከሁሉም በላይ የክርስቶስን ቅዱስ ሥጋውን በልተን ክቡር ደሙን ጠጥተን የዘለዓለም ሕይወትን እናገኛለን።

ሌላው ነቢየ እግዚአብሔር ኢሳይያስ በትንቢቱ ምዕራፍ ፮ ቁጥር ፫ ላይ "አንዱም ለአንዱ ቅዱስ፣ ቅዱስ ፣ ቅዱስ ፣ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ምድር ሁሉ ከክብሩ ተሞልታለች እያለ ይጮኸ ነበረ" ያለውን ቃል መሠረት አድርገን የሰማያውያን መላእክት ምግብ የሆነውንና እነርሱ ፳፬ ሰዓት ያለማቋረጥ "ቅዱስ ፣ ቅዱስ ፣ ቅዱስ ፣ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር" እያሉ የሚያመሰግኑትን ምስጋና በሥርዓተ ቅዳሴ ውስጥ ስለምናገኘው እኛም በፍፁም መንፈሳዊነትና ፣ በንፁሕ ኅሊና ከቤተ ልሔም /ከጌታ መወለድ/ ተጀምሮ እስከ ቢታንያ /የጌታ ዕርገት/ ድረስ ያለውን ነገረ ክርስቶስ እያሰብንና ሥርዓቱን እየፈፀምን/በካህናት አባቶችና በዲያቆናት ሲፈጸም/ እያየን ሥርዓቱን በማክበርና የቅዳሴውን ጸሎት በመጸለይ የመላእክትን ሕይወት የምንኖርበት ታላቅ የቤተ ክርስቲያናችን ሥርዓትና ፣ የሃይማኖታችን ምሰሶ ነው።

የተወደዳችሁ የዚህ ጽሑፍ አንባቢዎች ከብዙ በጥቂቱ ስለ ሥርዓተ ቅዳሴ ይህን ካልን በልማድ ከመመላለስ ፣ የቅዳሴውን አገልግሎት እንደ ሥራ ከመቁጠርና ፣ ይህን ከመሳሰሉ ደካማና ፣ በክርስትና ሕይወት ከሚታዩ የስንፍና አስተሳሰቦች በመራቅ የቅዳሴውን ጸሎት ጥቅሙን በመረዳት ወደ ቤተ ክርስቲያን እንምጣ። ወደ ቅዳሴውም ስንመጣ የሚጠበቅብንን የነፍስ ፣ የኅሊናና ፣ የዕውቀት ፣ ዝግጁነታችንን በመፈተሽ ፣ የቤተ ክርስቲያንን ሥርዓት የማክበር መንፈሳዊ ግዴታችንን በሚገባ ተገንዝበን በሥርዓተ ቅዳሴው በመሳተፍ በረከተ ሥጋ በረከተ ነፍስ እንድናገኝ ፤ በንስሐ ሕይወት እየተመላለስን ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙንም ተቀብለን የዘለዓለም ሕይወት ርስተ መንግሥተ ሰማያትን እንወርስ ዘንድ አምላካችን ልዑል እግዚአብሔር በቸርነቱ ይርዳን።

እግዚአብሔር አምላክ ቤተ ክርስቲያናችንን ሰላም ያድርግልን፤ አሜን፡፡

[ ይቆየን ]

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፥ ወለወላዲቱ ድንግል ፥ ወለመስቀሉ ክቡር፡፡

†                       †                        †
💖                    🕊                     💖

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

🕊

[ † እንኳን ለአባታችን ቅዱስ አጋቢጦስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ]

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †


🕊  †  ቅዱስ አጋቢጦስ  †   🕊

+ ይህንን ዓለም ንቆ ለበርካታ ዘመናት በፍፁም ምናኔ የኖረ::
+ ምድራዊ ሃብትና ሹመት ሞልቶለት ሳለ ከሁሉ የክርስቶስን ፍቅር የመረጠ::
+ ከደግነቱ ብዛት የተነሳ ምግብ ሲያዘጋጅ ሽምብራውን ከክቶ ለሌሎች ከሰጠ በሁዋላ ለራሱ የሚመገበው ገለባውን [ አሠሩን ] ነበር::

ሌሊቱን በጸሎት ለመትጋት ማታ ማታ አመድ ይመገብ ነበር:: በዚህም ቅዱስ ዳዊት "አመድን እንደ እህል በላሁ" ያለው በዚህ ቅዱስ ሕይወት ላይ ተገልጧል:: [መዝ.፻፩፥፱] (101:9)

ቅዱስ አጋቢጦስ በዘመኑ ከሠራቸው ይህኛው እጅግ ይገርመኛል:: እርሱ በበርሃ የነበረበት ዘመኑ የሰማዕታት በመሆኑ ብዙ ክርስቲያኖች በርጉማን መክስምያኖስና ዲዮቅልጢያኖስ ተገድለዋል:: ቅዱሱን ግን በአካባቢው የነበረ ሃገረ ገዢ ከበዓቱ አስወጥቶ ወደ ውትድርና ሥራ አስገብቶታል::

ሰይጣን በዚህ ከተጋድሎና ከቅድስና ሕይወት እንደሚያርቀው ተማምኖ ነበር:: ቅዱስ አጋቢጦስ ግን በወታደሮች መካከል ሆኖም ተጋድሎውን ቀጠለ:: የጦር ሠራዊት አለቃ አድርገው ቢሾሙትም እርሱ ከበጐ ማንነቱ ፈጽሞ አልተለወጠም::

ክርስቲያን ማለት እንዲህ ነውና:: ክርስትና ሲመቸን : ሲመቻችልን : በአጋጣሚ ወይም በምክንያት የምንኖረው ሕይወት አይደለም:: ፍጹም ፍቅር የጊዜ : የቦታ : የሁኔታ ገደብ የለውምና አባቶቻችን በጊዜውም : ያለ ጊዜውም ጸንተው ክርስቶስ መድኃኒታችንን አስደሰቱ::

ከቅዱስ ዻውሎስ ጋርም እንዲህ ሲሉ ዘመሩ:- "መኑ ያኀድገነ ፍቅሮ ለክርስቶስ" [ ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል ! ]

ወደ ቀደመው ነገራችን እንመለስና ቅዱስ አጋቢጦስ ለዘመናት ሰው ሳይገድል : ፈጣሪውን ሳይበድል : ከጾም ከጸሎት : ከምጽዋትና ትሕርምት ሳይጐድል ኖረ:: በዚህም ሰይጣንን አሳፈረ:: ዘመነ ሰማዕታትም አለፈ::

በዚህ ጊዜም ወደ በዓቱ ለመመለስ መንገድን ይፈልግ : ይጸልይም ገባ:: እግዚአብሔርም ወደ በርሃ የሚመለስበትን መንገድ በቸርነቱ አቀናለት::
ነገሩ እንዲህ ነው:: ዘመነ ሰማዕታት አልፎ ራትዕ [የቀና] ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ ነገሠ:: ስደት ቆመ:: የታሠሩ ተፈቱ:: አብያተ ክርስቲያናት ታነጹ:: ለክርስቲያን ቀደምቶቻችንም ታላቅ ተድላ ሆነ::

ጊዜው ለሁሉ ክርስቲያን የተድላ ቢሆንም አንድ ወጣት በደዌ ሰይጣን ያሰቃየው ነበር:: ወጣቱ የንጉሡ የቅዱስ ቆስጠንጢኖስ ባለሟል : ባለብዙ ሃብት : መልኩ ያማረ ነውና ሁሉ ያዝንለታል:: ይልቁኑ ቅዱሱ ንጉሥ ተጨነቀለት::

አንድ ቀን ግን ከወታደሮቹ አንዱ ያን ወጣት "አንተንኮ አጋቢጦስ ይፈውስህ ነበር" ይለዋል:: ወጣቱ ግን አላወቀምና "ከመቼ ወዲህ የጦር አለቃ እንዲህ አድርጐ ያውቃል?" ሲል በጥያቄ ይመልስለታል:: ወታደሩ ግን ቀስ አድርጐ ምሥጢሩን ይነግረዋል::

ይህ ነገር ሲያያዝ ከንጉሡ ደርሶ ቅዱስ አጋቢጦስን አስጠርቶ "እባክህ ፈውስልኝ?" ይለዋል:: "ካዳንክልኝም የፈለግኸውን አደርግልሃለሁ" ሲል ያክልለታል:: ቅዱስ አጋቢጦስም ወደ ፈጣሪው ለምኖ ሰይጣንን ይገስጸዋል:: በቅጽበትም በክርስቶስ ኃይል ወጣቱ ይድናል::

ቅዱስ ቆስጠንጢኖስም ከደስታው ብዛት "ምን ላድርግልህ?" ቢለው ቅዱሱ "ከሹመቴ ሻረኝ : ወደ በርሃ አሰናብተኝ" ብሎ መሻቱን ገለጸለት:: ቅዱሱ ንጉሥም በመገረም ቡራኬውን ተቀብሎ ወደ በርሃ ሸኝቶታል::

ወገኖቼ ! . . . በዓለማዊም ሆነ በመንፈሳዊው እርከን ስልጣንን የሚንቁ ሰዎችን ካላገኘን መፍትሔው ሩቅ ነው:: እኛም ከሥልጣን መሻት እንራቅ:: ማር ይስሐቅ እንደ ነገረን ሰይጣን ያደረበት ሰው ሹመትን [ሥልጣንን] በመሻቱ ይታወቃልና::

ቅዱሱ በፍፃሜ ዘመኑ እረኝነት [ዽዽስና] ተሹሞ ብዙ ኢ-አማንያንን ወደ ክርስትና መልሶ: ድውያንን ፈውሶ: እውራንን አብርቶ: በርካታ ተአምራትንም አድርጎ በዚህች ቀን አርፏል::

††† ልመናው በረከቱ ይደርብን::

🕊

[ † የካቲት ፳፬ [ 24 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. ቅዱስ አጋቢጦስ [ ጻድቅ ኤዺስቆዾስ ]
፪. ቅዱስ ጢሞቴዎስ ሰማዕት [ዘጋዛ]
፫. ቅዱስ ሚናስ ዘቆዽሮስ

[ † ወርኀዊ በዓላት ]

፩. ቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት [ መምሕረ ትሩፋት ]
፪. ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ
፫. ቅዱስ ሙሴ ፀሊም
፬. ቅዱስ ቶማስ ዘመርዐስ
፭. ቅዱስ አብላርዮስ ታላቁ
፮. ፳፬ቱ "24ቱ" ካኅናተ ሰማይ [ ሱራፌል ]

" የሚያሳድዷችሁን መርቁ . . . ደስ ከሚላቸው ጋር ደስ ይበላችሁ:: ከሚያለቅሱም ጋር አልቅሱ:: እርስ በርሳችሁ በአንድ አሳብ ተስማሙ:: የትዕቢትን ነገር አታስቡ:: ነገር ግን የትሕትናን ነገር ለመሥራት ትጉ ::" † [ሮሜ.፲፪፥፲፬] (12:14-16)

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
💖                    🕊                     💖

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

                       †                       

  [  🕊  ድምፀ ተዋሕዶ   🕊  ]  

🍒▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬🍒               

[  ሕይወት የሚገኝባቸው የቅድስት ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ትምህርቶች በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን በድምፅ ይቀርባሉ።  ]

[ ሳምንታዊ መርሐ-ግብር ]

🕊             

[    " ቅ ዱ ሳ ት   መ ጻ ሕ ፍ ት ! "    ]
             
            [     ክፍል ሰባት    ]

" ይህን በመጀመሪያ እወቁ ፤ በመጽሐፍ ያለውን ትንቢት ሁሉ ማንም ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደም ፤

ትንቢት ከቶ በሰው ፈቃድ አልመጣምና ፥ ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ተልከው ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ተናገሩ።" [፪ጴጥ.፩፥፳]


       💖   ድንቅ ትምህርት  💖

[ በመምህራችን በቀሲስ ኅብረት የሺጥላ ]

" የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ፥ ከመከራም ሥጋት ያርፋል።" [ ምሳ.፩፥፴፫ ]

         †              †               †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬
                       👇

Читать полностью…
Subscribe to a channel