mikreabew | Unsorted

Telegram-канал mikreabew - ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

874

"እንግዲህ፡ንስሓ፡ግባ፤አለዚያ፡ፈጥኜ፡ እመጣብሃለሁ፡፡" ራዕ 2፥16

Subscribe to a channel

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

               †               

" በውኑ ኢትዮጵያዊ መልኩን ወይስ ነብር ዝንጕርጕርነትን ይለውጥ ዘንድ ይችላልን ? " [ ኤር.፲፫፥፳፫ ]


" እግዚአብሔር ተዋጊ ነው ፥ ስሙም እግዚአብሔር ነው "
[ ዘጸ.፲፭፥፫ ]

         †              †               †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

Watch "ጣማፍ ሄራኒ ሙሉ ትረካ #tamav_Irene #ታማቭ ሄራኒ ሙሉ ትረካ #ethiopia #orthodox #tewahido" on YouTube
https://youtu.be/DNHS-mKtZiM?si=4nX5L9lFn-Lg9Mqu

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

🕊               

ንጉሥ አጤ ምኒልክ !


" ኢጣሊያኖችን ጦርነት ይቅር ፤ የክርስቲያን ደም በከንቱ አይፍሰስ ፤ እርቅ ይሻላል ብላቸው እምቢ ብለው መጥተው በጥጋባቸው አድዋ ላይ ተዋግተው ድል ሆኑ።

እኔ ግን በድንቁርናቸው ብዛት የነዚያን ሁሉ ክርስቲያን ደም በከንቱ መፍሰሱን እያየሁ ድል አደረኳቸው ብዬ ደስ አይለኝም። ነገር ግን በግፍ የመጡ ሰዎች ናቸውና እግዚአብሔር ግፉን አነጣጠረን፡፡"


[ ንጉሥ አጤ ምኒልክ ለሙሴ ሸፍኔ ከላኩት ደብዳቤ የተወሰደ፡፡ ]


🕊                💖                   🕊

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

🕊

[ † እንኳን ለታላቁ ሐዋርያና ሰማዕት ቅዱስ ፖሊካርፐስ እና ቅዱስ አውሳብዮስ ሰማዕት ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ]

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †

🕊    ቅዱስ ፖሊካርፐስ    🕊

† ቅዱስ ፖሊካርፐስ :-

+ ከ፸ [70] እስከ ፻፶፮ [156] ዓ/ም የነበረ::
+ ዮሐንስ ወንጌላዊ በራዕዩ ከመሰከረላቸው ፯ [7]ቱ አብያተ ክርስቲያናት የአንዱ [የሰርምኔስ] ዻዻስ የነበረ::
+ ከሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ ቃል በቃል የተማረና ደቀ መዝሙሩ የነበረ አባት ነው::

ታላቁ አግናጥዮስ [ምጥው ለአንበሳ] የዚህ ቅዱስ ባልንጀራ ነበር:: ከ፵፮ [46] ዓመታት በላይ በፍፁም ትጋት ቤተ ክርስቲያንን አገልግሎ አረማውያን በ፹፮ [86] ዓመቱ በአደባባይ በእሳት አቃጥለው ገድለውታል:: አባቶቻችን "ሐዋርያዊ" ሲሉ ይጠሩታል::


🕊  †  ዳግመኛ በዚህ ዕለት በ፩፰፻፹፰ [1888] ዓ/ም በቅዱስ ጊዮርጊስ ምልጃና ረዳትነት አባቶቻችን አድዋ ላይ ጣልያንን ድል አድርገዋል:: ቅዱስ ጊዮርጊስን እና ደጉን ንጉሥ ዳግማዊ አፄ ምኒልክን እናስባቸው ዘንድ ይገባል::


🕊  † ቅዱስ አውሳብዮስ ሰማዕት †  🕊

በቤተ ክርስቲያን ስመ ጥር ከሆነ ቅዱሳን ሰማዕታት አንዱ ቅዱስ አውሳብዮስ ነው:: ተወልዶ ያደገው በምድረ አንጾኪያ (ሶርያ) ሲሆን ዘመኑም ፫ [3] ኛው መቶ ክ/ዘ ነው:: አባቱ ታላቁ ሰማዕት ቅዱስ ፋሲለደስ ነው:: እናቱም ቡርክት ሶፍያ ትባላለች::

ሰማዕቱ ቅዱስ መቃርስ ትንሽ ወንድሙ መሆኑም ይታወቃል:: ቅዱሳን እነ ፊቅጦር : ገላውዴዎስ : ቴዎድሮስ : ዮስጦስ : አባዲር . . . ባልንጀሮቹ ሆነው ኑረዋል::

ቅዱስ አውሳብዮስ የቅዱስ ፋሲለደስ ፍሬ ነውና ጾምና ጸሎትን የሚያዘወትር ሆነ:: በቤተ መንግስት ውስጥ ስንት የተደላደለና የተቀማጠለ ነገር እያለ እርሱ ግን እንደ ቡሩክ አባቱ ንጽሕናን መረጠ:: የወርቅ ካባ ደርቦ ሲሰግዱ ማደር ምን ይደንቅ!

ያ ዘመን እጅግ ግሩም የሆኑ ቅዱሳን በቤተ መንግስት የታዩበት ነበር:: ቅዱስ አውሳብዮስ በምጽዋት : በጾምና ጸሎት የሚኖር ቢሆንም በየጊዜው ወደ ጦርነት ይላክ ነበር:: ምክንያቱም እርሱ ኃያል የጦር ሰው : የሠራዊቱም ሁሉ አለቃ ነውና:: በሔደበት ሁሉም በእግዚአብሔር ኃይል ድል ያደርግ ነበር::

አንድ ጊዜም ከፋርስ ቁዝ ሰዎች ጋር ጦርነት ውስጥ ገቡ:: ይህንን ጦርነት በበላይነት እንዲመሩ ቅዱሳን አውሳብዮስና ዮስጦስ በኑማርያኖስ [ንጉሡ ነው] ተሹመው ወደ ሠልፍ ገቡ::

በጦርነቱ ጐዳና ላይ ሳሉ ግን አንድ አታላይ ሰላይ በጠላት እጅ እንዲወድቁ አደረጋቸው:: የተማረኩና የታሠሩ ዮስጦስና ሠራዊቱ ሲሆኑ ቅዱስ አውሳብዮስ ይህን ሰምቶ አለቀሰ:: ወደ ፈጣሪውም እየተማጸነ ለመነ::

በዚህ ጊዜ ቅዱስ ሚካኤል ከሰማይ ወርዶ አረጋጋው:: ድል መንሳትንም ሰጥቶት አደጋ ጥሎ ባልንጀራውን ዮስጦስን አስፈታው:: ጠላቶቻቸውንም እያሳደዱ አዋረዷቸው:: "ወመጠውከኒ ዘባኖሙ ለጸርየ" እንዳለ ቅዱስ ዳዊት በመዝሙሩ::

ከዚህ ሠልፍ በሁዋላ ቅዱሳን አውሳብዮስና ዮስጦስ በድል አድራጊነት ወደ አንጾኪያ ሲመለሱ ግን አንጀትን የሚቆርጥ ዜና ደረሳቸው:: አምላከ አማልክት ክርስቶስ ተክዶ ጣዖታት [እነ አዽሎን : አርዳሚስ] እየተሰገደላቸውም ደረሱ:: ይህንን ያደረገ ደግሞ የሰይጣን ታናሹ የሆነ ርጉም ዲዮቅልጢያኖስ ነው::

ቅዱሳኑንም ለጣዖት ስገዱ ሲል በአደባባይ ጠየቃቸው:: ድፍረቱ ያናደደው ቅዱስ አውሳብዮስ ግን ሰይፉን መዞ ወደ ንጉሡ ተራመደ:: ያን ጊዜ ንጉሡ ሸሽቶ ሲያመልጥ መሣፍንቱን ሜዳ ላይ በተናቸው:: አባቱ ቅዱስ ፋሲለደስ ባይገለግለው ኖሮ ኃያል ነውና ባላተረፋቸው ነበር::

ከቀናት በሁዋላ ግን ቅዱስ አውሳብዮስ በጾምና ጸሎት ሰንብቶ ሰማዕት ለመሆን ልቡ ቆረጠ:: ቅዱስ ሚካኤልና አባቱ ፋሲለደስም በምክር አበረቱት:: እርሱም በአጭር ታጥቆ በከሐዲው ንጉሥ አደባባይ ላይ ቆመ::

"እኔ ክርስቲያን ነኝ:: ክርስቶስን አመልካለሁ:: ለእርሱም እገዛለሁ:: ጣዖታት ግን ድንጋዮቸ ናቸውና አይጠቅሙም:: የሚሰግድላቸውም የረከሠ ነው::" ሲል አሰምቶ ተናገረ:: ንጉሡ ዲዮቅልጢያኖስ እዚያው ሊገድለው ፈልጐ ነበር:: ቅዱሱ ተወዳጅ ሰው ነበርና ሁከት እንዳይነሳ አውሳብዮስ ወደ አፍሪቃ [ግብጽ] ሒዶ እንዲገደል ተወሰነበት::

በምድረ ግብጽም አረማውያን በእሳትም : በግርፋትም : በስለትም ብዙ አሰቃዩት:: ቅዱስ ሚካኤል ግን ገነትን አሳይቶ ከደዌው እየፈወሰ ተራዳው:: በመጨረሻም በዚህች ቀን ገድለውት አክሊለ ክብርን ተቀዳጅቷል::

† አምላከ ቅዱሳን ሰማዕታት ጽናታቸውን አድሎ ከበረከታቸው ይክፈለን::

🕊

[ † የካቲት ፳፫ [23] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. ቅዱስ ፖሊካርፐስ ሐዋርያዊ ሰማዕት [የሰርምኔስ ዻዻስ]
፪. ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕታት [አባቶቻችንን አድዋ ላይ የረዳበት]
፫. ቅዱስ አውሳብዮስ ሰማዕት [የቅዱስ ፋሲለደስ ልጅ]
፬. ቅዱስ አውስግንዮስ ሰማዕት

[ † ወርኀዊ በዓላት ]

፩. ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት
፪. ቅዱስ ሰሎሞን ንጉሠ እስራኤል
፫. አባ ጢሞቴዎስ ገዳማዊ
፬. አባ ሳሙኤል
፭. አባ ስምዖን
፮. አባ ገብርኤል

" በሰርምኔስም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልዐክ እንዲህ ብለህ ጻፍ:- ሞቶ የነበረው: ሕያውም የሆነው: ፊተኛውና መጨረሻው እንዲህ ይላል :- 'መከራህንና ድህነትህን አውቃለሁ . . . እስከ ሞት ድረስ የታመንህ ሁን: የሕይወትንም አክሊል እሰጥሃለሁ::" † [ራእይ.፪፥፰] (2:8)

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
💖                    🕊                     💖

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

ዓርብ - የካቲት 22 2016 ዓ.ም

ኢያሱ 6-9

ሰላም ለሁላችሁ ይሁን! በዛሬው እለት ንባባችን ከምዕራፍ 6 እስከ 9 ድረስ እናነባለን።

ከንባብ በፊት የሚደረግ ጸሎት፡ “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፤ የአንተን ቃላት እሰማ እና እረዳ ዘንድ፥ እንዲያውም ፈቃድህን ለመፈጸም እበቃ ዘንድ የልቤን ጆሮዎች እና ዓይኖች ክፈትልኝ።” (ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ)

በዛሬው ንባባችን ላይ እስራኤል ወደ ኢያሪኮ ለመግባት እንደተዘጋጁ፥ ከተማዪቱን እንደያዙ፥ ቆይተው ግን እግዚአብሔርን ስለ መበደላቸው እና ከጋይ ሰዎች ፊት ስለመሸሻቸው እንዲሁም ኢያሱ ስለ እስራኤል መማጸኑን እናነባለን። በተጨማሪም፥ የጋይን ከተማ ለማጥፋት ኢያሱ ስላደረገው ብልሃት እና የገባዖን ሰዎች ነፍሳቸውን ለማዳን ስላደረጉት ነገር እና ስለሆነባቸው ነገርም ተጽፎ ይገኛል።

*የክለሳ ጥያቄዎች*

1) በኢያሱ 6 መሠረት፥ ካህናቱ እና ሰልፈኞቹ ለሰባት ቀን ምን እንዲያደርጉ ታዘዙ?

2) ኢያሱ ኢያሪኮን ለመሥራት ስለሚነሳ ሰው ምን አለ?

3) ኢያሱ በእግዚአብሔር ፊት በግንባሩ የተደፋው ለምንድር ነው? እግዚአብሔርስ ምን አለው?

4) ኢያሱ የጋይ ከተማን ያጠፋበትን ብልሃት ግለጹ።

5) በኢያሱ 9 መሠረት፥ የገባዖን ሰዎች ሕይወታቸውን ለማትረፍ ምን አደረጉ?


መልካም ንባብ!

/channel/OrthodoxTewahdoBooks

/channel/c/2014228571/1

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

                           †                           

   [            ቀኑ አርብ ነው !           ]
▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬

[  "  ሕይወትን ለሁሉ ይሰጣል !  "  ]

-------------------------------------------------

" ታመመ ፤ ሞትን ከተቀበለበት ከሥጋ ተዋሕዶ በመስቀል ላይ በፈቃዱ ለሥጋውያን ሞተ ፣ ባሕርየ መለኮት ሥጋን ተዋሕዶ በማኅፀን ካደረ ጀምሮ ሥጋ ገንዘቡ እንደመሆኑ በሥጋ ይኸንን ሥርዓት ፈጸመ፡፡ ለማይመረመር ለመለኮቱ ባሕርይ እንደሚገባ ደግሞ እርሱ ኅብስት አበርክቶ ሁሉን ያጠግባል፡፡ አይራብም ፣ አይጠማም ፣ አይደክምም ፣ አያንቀላፋም ፣ አይታመምም ፣ አይሞትም ሕይወትን ለሁሉ ይሰጣል፡፡ ዳግመኛ በዚያ በሲኦል ተገዝተው ያሉ ነፍሳትን ያድን ዘንድ በአካለ ነፍስ ወደ ሲኦል ወረደ በመለኮቱም ሲኦልን በዘበዘ፡፡"

[ ቅዱስ ቄርሎስ ]

"ኃይልየ ወጸወንየ ውእቱ እግዚእየ"  [ ኃይሌና መጠጊያዬ እርሱ ጌታዬ ነው ! ]

🕊

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፤ ወለወላዲቱ ድንግል ፤ ወለመስቀሉ ክቡር። አሜን።

†                       †                         †
💖                    🕊                     💖

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

                        †                         

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት  እንኳን ለ ፲፩ ኛ ዓመት በዓለ ሢመትዎ በሰላምና በጤና አደረስዎ !

የቅዱስነትዎ ቡራኬ አይለየን !



አንዲት ቤተ ክርስቲያን !
                 አንድ ሲኖዶስ !
                 አንድ ፓትርያርክ !
                 አንድ የሹመት ሥርዐት !

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቀኖናዊት ናት !

         †              †               †
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

† አምላከ ቅዱሳን ይራዳን: ይባርከን: ይቀድሰን:: ከወዳጆቹ በረከትም ያሳትፈን:: የቅዱሳኑን ግፍና መከራ አስቦም ከምንፈራው ጭንቅ ሁሉ ይሰውረን:: ለመንግስቱም ያብቃን::

🕊

[ † የካቲት ፳፪ [ 22 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. ቅዱሳን ሰማዕታተ ፋርስ [ፍልሠታቸውና ቅዳሴ ቤታቸው]
፪. ቅዱስ አባ ማሩና ጻድቅ ኤዺስ ቆዾስ [የፋርስ ሰማዕታትን አጽም የሠበሠበ]
፫. ቅዱስ አባ ቡላ

[ † ወርኀዊ በዓላት ]

፩. ቅዱስ ዑራኤል ሊቀ መላእክት
፪. ቅዱስ ሉቃስ ወንጌላዊ
፫. ቅዱስ ደቅስዮስ [የእመቤታችን ወዳጅ]
፬. አባ እንጦንዮስ [አበ መነኮሳት]
፭. አባ ዻውሊ የዋህ

" ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ: ወይስ ጭንቀት: ወይስ ስደት: ወይስ ራብ: ወይስ መራቆት: ወይስ ፍርሃት: ወይስ ሰይፍ ነውን?
'ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን:: እንደሚታረዱ በጐች ተቆጠርን::' ተብሎ እንደተጻፈው ነው:: በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን::
"
† [ሮሜ.፰፥፴፭-፴፯]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
💖                    🕊                     💖

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

                         †                         


[ ይህ ሁሉ የሆነብን ስለ ምንድን ነው ? ]


" ከእንቅልፍ የምትነሡበት ሰዓት አሁን እንደ ደረሰ ዘመኑን እወቁ ፤ ካመንንበት ጊዜ ይልቅ መዳናችን ዛሬ ወደ እኛ ቀርቦአልና።" [ ሮሜ.፲፫፥፲፩ ]


" ትምህርትህም ለዘላለም ታጠናኛለች ፥ ተግሣጽህም ታስተምረኛለች።" [ መዝ.፲፰፥፴፭]


         †              †               †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

                        †                         

የዘመኑ [ሐሰተኛ] አጥማቂያንና የአጋንንት ምስክርነት ]


🕊   የሊቃውንትና የመምህራን ምላሽ  !   🕊


- ምዕመናን በሃይማኖት ስር ሰደው እንዳይታነጹ ፣ በቤተክርስቲያንም ጸንተው እንዳይኖሩ ፦

- " እቤትህ ጸልይ ፣ እቤትህ ስገድ ፣ እቤትህ በመቁጠሪያ ቀጥቅጥ ፣ እቤትህ እጣን እጠን ፣ እቤትህ እራስህን ቅብዓ ቅዱስ ቀባ ፣ እቤትህ ሱባኤ ያዝ" በሚል እንግዳ [ የክህደት ] ትምህርት የዋሁን ምዕመን ከቅድስት ቤተክርስቲያን ዕቅፍ በመነጠል

- እውነተኞቹ የመንጋው እረኞች ካህናትን እንዲጠራጠርና እንዲጠላቸው በማድረግ ከንስሐ አርቀው ፣ ከምስጢራት ነጥለው ተከታያቸው አድርገው ከሕይወት እየለዩ የሚገኙ በጣት የሚቆጠሩ የዘመኑ [ ሐሳዊ ] አጥማቂያንን በተመለከተ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን የሰጡት አስደናቂ ምላሽ !

----------------------------------------

- ሐሰተኛ አጥማቂዎችን በምን ለይተን እንወቃቸው ?
- ለምን በቤተክርስቲያን ገብተው ያጠምቃሉ ?
- የእግዚአብሔርን ፣ የእመቤታችንንና የቅዱሳንን ስም እንዴት ይጠራሉ ?
- "ጹሙ ጸልዩ ስገዱ" የሚሉን አባቶች እንዴት ሐሰተኛ ይባላሉ ?
- ሐሰተኛ አጥማቂዎች ለምን አይወገዙም ?

ለሚሉት የምዕመናን ጥያቄዎች ሊቃውንት ምላሹን ሰጥተዋል። ይከታተሉ !



" እንግዲህ እንደ ጥበበኞች እንጂ ጥበብ እንደሌላቸው ሳይሆን እንዴት እንድትመላለሱ በጥንቃቄ ተጠበቁ ፤ ቀኖቹ ክፉዎች ናቸውና ዘመኑን ዋጁ።" [ኤፌ.፭፥፲፭]

         †              †               †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬
                        👇

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

ሰላም ወዳጆች እንደምን አላችሁ?

በእግዚአብሔር ፈቃድ እና ቸርነት አምስቱን የሙሴ መጻሕፍት ዘፍጥረት፥ ዘጸአት፥ ዘሌዋውያን፥ ዘኁልቅ እና ዘዳግምን ማንበብ ችለናል። እነዚህ አምስቱ መጻሕፍት በዋናነት "የሕግ መጻሕፍት" ተብለው የሚታወቁ ሲሆን፥ ለእስራኤል ሕዝብ እና ባህል ታላቅ መሠረት የሆኑ ናቸው።

የአምስቱ መጻሕፍት ንባብ እንዴት ነበር? በየእለቱ መጽሐፍ ቅዱስ የማንበብን ልምድ ማዳበርንስ እንዴት አገኛችሁት?

እስቲ አሳባችሁን አጋሩ 😊

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ:
"ኃጢአት ከበጎ ነገር በተቃራኒ መስራት ብቻ አይደለም። በጎውን አውቆ አለመስራትም ኃጢአት ነው።"

(#ብፁዕ_ወቅዱስ_አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ)

“ወደ ቤተ ክርስቲያን መጥተህ እግዚአብሔርን ለአምላክነቱ እንደሚገባ አምልከህ ከዚያ በኋላ ወደ ሥራህ ብትሔድ የምትሠራው ሥራ የተባረከና የሰመረ እንደሚሆንልህ አታውቅምን?"

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

🕊

[ 🕊 ድንግል ሆይ 🕊 ]

" ድንግል ሆይ የሚወዱሽ የተወደዱ ናቸው ፤ ንግስት ሆይ የሚያከብሩሽ የከበሩ ናቸው ፤ ንፅሕት ሆይ የሚቀድሱሽ የተቀደሱ ናቸው ፤ ፍስሕት ሆይ የሚመርቁሽ የተመረቁ ናቸው ፤ ልዕልት ሆይ የሚያደንቁሽ የተደነቁ ናቸው ፤ ውድስት ሆይ ለንግሥትነትሽ የሚገዙ ሁሉ የተባረኩ ናቸው። "

[ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ]

†                       †                        †
💖                    🕊                     💖

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

​​ጾመ ነነዌ

        ክፍል አንድ

             ከፈለገ ሰላም ቅዱስ ገብርኤል ቤ/ክ

የነነዌ ጾም ከሰባቱ የቤተክርስቲያን አጽዋማት አንዱና የዐቢይ ጾም ማዘጋጃ ደወል ነው፡፡ ይህ የነነዌ ሰዎች የንስሐ ታሪክ በቤተክርስቲያናችን በጣም ታላቅ ዋጋ ያለውና የራሱ መዝሙር የሚዘመርለት፣ ቅዳሴ የሚቀደስበት ታላቅ መታሰቢያ ያለው ታሪክ ነው፡፡

ራሱ ጌታችንም የነዌ ሰዎችን የንስሐ ታሪክ በመጥቀስ አይሁድን ገስጾበታል፤ በፍርድ ቀንም በዚያ ትውልድ ዘንድ እንደሚፈርዱበት ተናግሯል፡፡

ይህም የሆነበት የነነዌ ሰዎች ደስ የሚያሰኝ የንስሐ ታሪክ ስላላቸው ነው፡፡ በዚህ ጽሑፍ ይህን አስደሳች የንስሐ ታሪክ በጾመ ነነዌ ከሚነበቡ የቅዳሴ ምንባባት አንጻር ለመመርመር እንሞከራለን፡፡

ኃጢአት ከእግዚአብሔር መለየት እንደሆን ሁሉ ንስሐ ደግሞ ወደ እግዚአብሔር መመለስ ነው፡፡

በዚህ ከእግዚአብሔር ሊለዩ የሚችሉ ብዙ ፈተናዎች ባለቡት ዓለም እስካለን ድረስ ሕይወታችን ሁሉ የንስሐ ጊዜ ነው፡፡

ይሁን እንጂ ከሁሉም ጊዜ በተለየ ወደ እግዚአብሔር የምንመለስባቸው የጾም ወቅቶች ሲሆኑ ከእነዚህም ታላቁና ዋነኛው ዐቢይ ጾም ነው፡፡

ቅድስት ቤተክርስቲያናችን በዐቢይ ጾም ከእያንዳንዱ ምእመን ልቦና የንስሐ ፍሬን ትፈልጋለች፤ ያለትንሣኤ ልቦና /ንስሐ/ የክርስቶስን ትንሣኤ በእውነትና በደስታ ማክበር አይቻልምና፡፡

ለመሆኑ ከንስሐ የሚያሰናክሉን ነገሮች ምን ምን ናቸው? የነነዌ ሰዎች ታሪክ ስለዚህ ምን ያስተምረናል?

1.ቅንጦትን መውደድ

ምንም እንኳን በደፈናው ገንዘብ የኃጢአት ምንጭ ነው ባንልም እንደ ወንጌል ትእዛዝ በክርስቲያናዊ መንገድ ካልተያዘ ግን እግዚአብሔርን ሊያስረሳና የኃጢአት ማስፈጸሚያና ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡

ብዙ ጊዜም ገንዘብና ባለጸግነት ከእግዚአብሔር በመለየታችን ያጣነውን ሰላምና ደስታ ለማግኘት ተስፋ የምንጥልበት ጣኦት ሆኖ ሊቀየር ይችላል፡፡

በሀብታችን በምናገኘው ጊዜያዊ ደስታና ሰላም ዘላለማዊውንና ፍጹምን የእግዚአብሔር ስጦታ መፈለግ፣ ወደ እግዚአብሔር መመለስን መናፈቅ ልናቆም እንችላለን፡፡

በዚህ መልኩ ብልጽግና ከንስሐ የሚያሰናክል ወጥመድ ይሆናል ማለት ነው፡፡

እግዚአብሔር ሀብት እንኳ ቢሰጠን ለተቸገረ በመመጽወት፣ ልጆቻችን በክርስቲያናዊ መንገድ በማሳደግ፣ የቤተክርስቲያንን አገልግሎት በማፋጠን የእውነተኛ ደስታና የጽድቅ መንገድ እንድናደርገው እንጂ እግዚአብሔርን የተጠማች ነፍሳችንን ጥሪዋን በማደናቀፍና ጩኸቷን በማፈን በሥጋ ድሎት ውስጥ የምንደበቅበት መሣሪያ እንድናደረገው አይደለም፡፡ ለ"ታላቂቷ ከተማ" ነነዌም የጥፋት መንገድ የሆናት በብልጽግናዋና በታላቅነቷ እግዚአብሔርን ረስታ የኃጢአት ከተማ መሆኗ ነው፡፡

በነቢዩ በዮናስ ታሪክ ውስጥ ገንዘብ ለዮናስ ከእግዚአብሔር የመከለያ መሣሪያ ሲሆን እናገኘዋልን፡፡"... ከእግዚአብሔርም ፊት ኮብልሎ ከእነርሱ ጋር ወደ ተርሴስ ይሔድ ዘንድ ዋጋ ሰጥቶ ወደ እርሷ /ወደ መርከቧ/ ገባ"እንዲል ዮና፩፥፫

በዚህ ሰዓት ለዮናስ ገንዘብ ባይኖረው ይሻል ነበር፡፡ እኛም ቢሆን ከንስሐ የሚመልስ፣ ለኃጢአት መሣሪያ የሚሆን ሀብት ከሚኖረን በድኅነት ብንኖር ይሻለናል፡፡

ምንም እንኳ በቤተክርስቲያናችን ትውፊት ዐቢይ ጾም አብዝተን የምንጸልይበት፣ በጾም በስግደትና በምጽዋት ልናሳልፈው የሚገባ ወቅት ቢሆንም ፤ አሁን አሁን ግን ገንዘብ ማግበስበሻ እየሆነ እንደሆነ እናያለን፡፡

በመሠረቱ በጾም ወቅት ከሆዳችን የምንቀንሰው ገንዘብ እንድናጠራቅመው ሳይሆን እንድንመጸወተው የሚገባ ነው፡፡

ለማጠራቀምማ የማያምኑ ሰዎችስ ምግብ ይቀንሱ የለ? ለዚህ ነው በነነዌ ጾም በመጀመሪያው ቀን /ሰኞ/ የሚነበበው የቅዱስ ያዕቆብ መልእክት "አሁንም እናንተ ባለ ጠጎች ስለሚደርስባችሁ ጭንቅ ዋይ ዋይ እያላችሁ አልቅሱ፡፡ ሀብታችሁ ተበላሽቷል፣ ልብሳችሁም በብል ተበልቷ፡፡ ወርቃችሁም ብራችሁም ዝጓል፤ ዝገቱም ምስክር ይሆንባችኋል፤ ሥጋችሁንም እንደ እሳት ይበላል፡፡ ለኋለኛው ቀን መዝገብን አከማችታችኋል፡፡ እነሆ እርሻሁን ያጨዱት የሠራተኞች ደመወዝ በእናንተ ተቀምቶ ይጮኻል፣የአጫጆችም ድምፅ ወደ ጌታ ጸባዖት ጆሮ ገብቷል፡፡ በምድር ላይ ተቀማጥላችኋል፤ በሴሰኝነትም ኖራችኋል፤ ለእርድ ቀን እንደሚወፍር ልባችሁን አወፍራችኋል፡፡"
ያዕ ፭፥፩
በማለት አስፈሪ ተግሳጽ የሚያስተላልፈው፡፡

ስለዚህ በዐቢይ ጾም አብዝተን የምንመጸውትበት፣ ከእግዚአብሔር የሆነውን ስጦታ የምንፈልግበት፣ የንስሐ ጊዜ ሊሆን ይገባል፡፡


💚💛❤
❤💛💚
     
        ✥┈┈•◦●◈◎❖◎◈●◦•┈┈✥
  ✧━━━━━━━━━━━━━━━━━✧
     
ለኦርቶዶክሳውያን ያጋሩ

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

..........................................



" እውነትም አርነት ያወጣችኋል " [ ዮሐ.፯፥፴፪ ]


         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

🕊

" እነርሱ ... በጦርነት ኃይለኞች ሆኑ ፥ የባዕድ ጭፍሮችን አባረሩ።" [ ዕብ.፲፩፥፴፫ ]


"የካቲት ፳፫ ፲፰፻፹፰ ዓ.ም [march 1 1896] አነጋጉ ላይ በቤተክርስቲያኑ የነበረው ሁሉም ሰዉ ቅዱስ ቁርባንን ተቀበለ፡፡ ከዚያም አረንጓዴ ፣ ቢጫና ቀይ ቀለም ያለው ሰንደቅ ዓላማ በመስቀል ቅርፅ ተሰቀለ፡፡ የቆረብነውም ሁሉ ጎንበስ ብለን ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሀገሪቱን ፤ ንጉሰ ነገሥቱን እና ኃይማኖቱን እንዲያስጠብቅና እንዲረዳን ለመንን፡፡ እንደ ነጋም ጦሩ ሁሉ የጦር መሳሪያውን ታጥቆ ወደ ውጊያ ገባ"

[ ከዳግማዊ ምኒሊክ እና እቴጌ ጣይቱ መፅሐፍ የተወሰደ ]


" እነርሱ በእምነት መንግሥታትን ድል ነሡ ፥ ጽድቅን አደረጉ ፥ የተሰጠውን የተስፋ ቃል አገኙ ፥ ከድካማቸው በረቱ ፥ በጦርነት ኃይለኞች ሆኑ ፥ የባዕድ ጭፍሮችን አባረሩ። [ ዕብ.፲፩፥፴፫ ]

- " አድዋ ባ'ፍ አይገባም "
- [ በገጣሚ አበባው መላኩ ]

         †               †               †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

🕊


[ የንጉሥ አጼ ምኒልክ ስለት ! ]


" ቅዱስ ጊዮርጊስ ሆይ በጦርነቱ ድል ብትሰጠኝ በሣር ያለውን ቤተ ክርስቲያንህን ባማረ ሕንጻ እሠራለሁ "

ብለው ተሳሉ። ሰማዕቱም ጸሎታችን ሰምቶ ድል አቀዳጃቸው።

በቅዱስ ጊዮርጊስ ስምም የተዋበች ቤተ ክርስቲያን አሠሩ፡፡ ስሟንም "ገነተ ጽጌ" ብለው ሰየሟት፡፡


[ ሙሉ ግጥሙ ከቆይታ በኋላ ይቀርባል ! ]


🕊                💖                    🕊

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

ጤናይስጥልኝ ውድ አባቶች፤ወንድሞች እና እህቶች የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ላይ እንድንበረታ እንድያበረቱን እንድናበረታቸው የምንፈልጋቸውን ኦርቶዶክሳውያን Add አድርጓቸው።ወይም linkኩን
/channel/+3kpzSPDfiVMzYzQ0
እንላክላቸው።

መጽሐፍ ቅዱስ አንባቢ ወዳጅ ብያንስ አንድ ይኑረን❤️🙏

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

                     †                       

[       የካቲት ፳፫ / 23 አድዋ      ]

🕊 እ ን ኳ ን አ ደ ረ ሳ ች ሁ 🕊

💖

የልዳ ሰማዕት የፋርሱ ኮከብ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕታት [ አባቶቻችንን አድዋ ላይ የረዳበት ] ቀን።

የካቲት ፳፫/23 አድዋ !

[   ዝክረ ቅዱሳን   ]


         †              †               †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

                        †                         

የዘመኑ ሐሰተኛ አጥማቅያን እና የአጋንንት ምስክርነት !

🔔

▷ ❝ ሐሳውያን ምዕመናንን የሚያታልሉባቸው ሥልቶች !

[ በመምህራችን በዲ/ን ያረጋል አበጋዝ ]

†                      †                      †

▷ ❝ የከሸፈው ትንቢት

[ በመምህራችን በመጋቢ ሐዲስ እንዳልካቸው ንዋይ ]

🔔

" በሰይጣን እንዳንታለል ፤ የእርሱን አሳብ አንስተውምና።"

[፪ኛ ቆሮ.፪፥፲፩]

         †              †               †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬
👇

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

                       †                         

[   "  ሃይማኖቴን አልካድህም ! "    ]

እኛ ክርስቲያኖች የሚደርሱብን መከራዎች እንደወርቅ የምንጠራባቸው እቶኖች ናቸው።
           
[  ቅዱስ  ዮሐንስ አፈወርቅ ]



አንዲት ቤተ ክርስቲያን !
                 አንድ ሲኖዶስ !
                 አንድ ፓትርያርክ !
                 አንድ የሹመት ሥርዐት !

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቀኖናዊት ናት !

†                      †                      †

" የሰይጣን ዙፋን ባለበት የምትኖርበትን አውቃለሁ ፤ ስሜንም ትጠብቃለህ ፥ ሰይጣንም በሚኖርበት ፥ በእናንተ ዘንድ የተገደለው የታመነው ምስክሬ አንቲጳስ በነበረበት ዘመን እንኳ ሃይማኖቴን አልካድህም።" [ ራእ.፪፥፲፫ ]

          †             †             †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

🕯

በሰሜን ጎጃም ሀገረ ስብከት በላይ ጋፊት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን 11 የቅኔ ተማሪዎች ተገደሉ !

🔔

በሰሜን ጎጃም ሀገረ ስብከት ሜጫ ወረዳ ብራቃት ቀበሌ በሚገኘው በላይ ጋፊት  ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን የአብነት ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩ 11 የቅኔ ተማሪዎች  እንዲሁም 1 በግብርና የሚተዳደር የአካባቢው ነዋሪ ከመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት ተገድለዋል።

ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል ጉዳዩን አስመልክቶ ከአንዱ ሟች የቅኔ ተማሪ አባትና ወንድም እንዲሁም የአካባቢው ነዋሪ ከሆኑ መምህር ጋር የስልክ ቆይታ ያደረገ ሲሆን ድርጊቱ የተፈጸመው የካቲት 20 ቀን 2016 ዓ.ም ከሌሊቱ 6:00 ገደማ እንደሆነ እና ተማሪዎቹ በጎጇቸው ሳሉ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ፋኖን ታስጠልላላችሁ ፣ ለፋኖ አባላት ጥይት የማያስመታ መድኃኒት ትሰጣላችሁ እናንተም የፋኖ አባላት ናችሁ በማለት 11 ተማሪዎች እንዲሁም የጩኸት ድምፅ ሰምቶ ወደ ጉባኤ ቤቱ ሲሄድ የነበረን የአካባቢው ነዋሪ መግደላቸውን ለሚዲያችን ገልጸዋል።

አክለውም አሁን የተገለጸው የሟቾች ቁጥር በዛሬው ዕለት በትክክል የተገኘ እንደሆነ እና በሰዓቱም በጉባኤ ቤቱ የነበሩ በርካታ ተማሪዎች ወደተለያየ አቅጣጫ ስለተበታተኑ የሟቾች ቁጥር አሁን ከተጠቀሰው ቁጥር ሊልቅ እንደሚችል ጠቁመዋል።

ከጉዳዩ ጋር ተያይዞ የዞኑን ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ለማነጋገር ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።

ከጥቂት ጊዜያት በፊት በተመሳሳይ ሁኔታ ከ12 ያላነሱ የአቋቋም ተማሪዎች በአዴት ፍልሰታ ደብር መገደላቸው ይታወሳል።

[     ዘገባው የ  T.M.C  ነው     ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

🕊

✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞

†  የካቲት ፳፪ [ 22] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት

🕊  †  አቡነ አቢብ [ አባ ቡላ ]  †   🕊

ይህን ታላቅ ቅዱስ በምን እንመስለዋለን !
- እኛ ኃጥአን ጣዕመ ዜናውን: ነገረ ሕይወቱን ሰምተን ደስ ተሰኝተናል !
- ቅዱሱ አባታችን :- "ቡላ-የእግዚአብሔር አገልጋይ" ብለን እንጠራሃለን::
- ዳግመኛም "አቢብ-የብዙኃን አባት" ብለን እንጠራሃለን::

- እርሱ ቅሉ አባትነትህ አንተን ለመሰሉ ቅዱሳን ቢሆንም እኛን ኃጥአንን ቸል እንደማትለንም እናውቃለን::
- አባ! ማነው እንዳንተ የክርስቶስን ሕማማት የተሳተፈ !
- ማን ነው እንዳንተ በፈጣሪው ፍቅር ብዙ መከራዎችን የተቀበለ !
- ማንስ ነው እንዳንተ በአንዲት ጉርሻ አማልዶ ርስትን የሚያወርስ !
- የፍጡራንን እንተወውና በፈጣሪ አንደበት ተመስግነሃልና ቅዱሱ አባታችን ላንተ ክብር: ምስጋናና ስግደት በጸጋ ይገባሃል እንላለን::

†    ልደት   †

አባታችን አቡነ አቢብ የተወለደው በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን መጨረሻ አካባቢ ሲሆን ሃገረ ሙላዱ ሮሜ ናት:: ወላጆቹ ቅዱስ አብርሃምና ቅድስት ሐሪክ እጅግ ጽኑ ክርስቲያኖች ነበሩ:: ልጅ ግን አልነበራቸውም:: ዘመነ ሰማዕታት ደርሶ ስደት በሆነ ጊዜ እነርሱም በርሃ ገቡ::

- በዚያም ሳሉ በቅዱስ መልአክ ብሥራት ሐሪክ ጸንሳ ብሩሕ የሆነ ልጅ ወለደች:: ቅዱሱ ሕጻን ሲጸነስ ማንም ሳይተክለው የበቀለው ዛፍ ላይ መልአኩ እንዲህ የሚል የብርሃን ጽሑፍ ጽፎበት ወላጆቹ ዐይተዋል::
"ቡላ ገብሩ ለእግዚአብሔር: ወቅዱሱ ለአምላከ ያዕቆብ: ዘየኀድር ውስተ ጽዮን"

†   ጥምቀት   †

ቅዱሱ ሕጻን ከተወለደ በኋላ ሳይጠመቅ ለ ፩ ዓመት ቆየ:: ምክንያቱም ዘመኑ የጭንቅ ነውና ካህናትን እንኳን በዱር በከተማም ማግኘት አይቻልም ነበር:: እመቤታችን ግን ወደ ሮሙ ሊቀ ዻዻሳት አባ ሰለባስትርዮስ ሒዳ 'አጥምቀው' አለችው::

ወደ በርሐ ወርዶ ሊያጠምቀው ሲል ሕጻኑ ተነስቶ: እጆቹንም ዘርግቶ :- "አሐዱ አብ ቅዱስ: አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውዕቱ መንፈስ ቅዱስ" ብሎ አመስግኖ ተጠመቀ:: ከሰማይም ሕብስና ጽዋዕ ወርዶላቸው ሊቀ ዻዻሳቱ ቀድሶ ሁሉንም አቆረባቸው:: የሕጻኑ ወላጆች "ለልጃችን ስም አውጣልን" ቢሉት "ቡላ" ብሎ ሰየመው:: እነርሱም ምሥጢሩን ያውቁ ነበርና አደነቁ::

†  ሰማዕትነት   †

የቅዱሱ ቡላ ወላጆች ለ፲ [10] ዓመታት አሳድገውት ድንገት ሕዳር ፯ [7] ቀን ተከታትለው ዐረፉ:: ሕጻኑን የማሳደግ ኃላፊነትን የአካባቢው ሰዎች ሆነ:: ሕጻኑ ቡላ ምንም የ፲ [10] ዓመት ሕጻን ቢሆንም ያለ ማቁዋረጥ ሲጾም: ሲጸልይ ክፉ መኮንን "ለጣዖት ስገዱ" እያለ መጣ::

በዚህ ጊዜ በሕጻን አንደበቱ አምልኮተ ክርስቶስን ሰበከ:: በዚህ የተበሳጨ መኮንኑ ስቃያትን አዘዘበት:: በጅራፍ ገረፉት: በዘንግ ደበደቡት: ቆዳውን ገፈፉት: በመጋዝ ቆራርጠውም ጣሉት:: ነገር ግን ኃይለ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበርና ፪ [2] ጊዜ ከሞት ተነሳ:: በመጨረሻ ግን ሚያዝያ ፲፰ [18] ቀን ተከልሎ ሰማዕት ሆኗል::

†   ገዳማዊ ሕይወት   †

ቅዱስ ቡላ ሰማዕትነቱን ከፈጸመ በኋላ ቅዱስ ሚካኤል በአክሊላት አክብሮ ወስዶ በገነት አኖረው:: ከሰማዕታትም ጋር ደመረው:: በዚያም ቡላ ቅዱስ ጊዮርጊስን ተመልክቶ ተደነቀ:: መንፈሳዊ ቅንዐትን ቀንቷልና "እባክህን ወደ ዓለም መልሰኝና ስለ ፍቅርህ እንደ ገና ልጋደል" ሲል ጌታን ለመነ::

ጌታችን ግን "ወዳጄ ቡላ! እንግዲህስ ሰማዕትነቱ ይበቃሃል:: ሱታፌ ጻድቃንን ታገኝ ዘንድ ግን ፈቃዴ ነውና ሒድ" አለው:: ቅዱስ ሚካኤልም የቅዱስ ቡላን ነፍስ ከሥጋው ጋር አዋሕዶ: ልብሰ መነኮሳትንም አልብሶ ግብጽ በርሃ ውስጥ አኖረው::

†  ተጋድሎ   †

አባ ቡላ ወደ በርሃ ከገባ ጀምሮ ዐርብ ዐርብ የጌታን ሕማማት እያሰበ ራሱን ያሰቃይ ገባ:: ራሱን ይገርፋል: ፊቱን በጥፊ ይመታል: ሥጋውን እየቆረጠ ለአራዊት ይሰጣል: ከትልቅ ዛፍ ላይ ተሰቅሎ ወደ ታች ይወረወራል::

በጭንቅላቱ ተተክሎ ለብዙ ጊዜ ጸልዮ ጭንቅላቱ ይፈሳል:: ሌላም ብዙ መከራዎችን የጌታን ሕማማት እያሰበ ይቀበላል:: ስለ ጌታ ፍቅርም ምንም ነገር ሳይቀምስ ለ፵፪ [42] ዓመታት ጹሟል:: ጌታችንም ስለ ክብሩ ዘወትር ይገለጥለት ነበር::

የሚታየውም እንደ ተወለደ: እንደ ተጠመቀ: እንደ ተሰቀለ: እንደ ተነሳ: እንዳረገ እየሆነ ነበር:: አንድ ቀንም ጌታችን መጥቶ "ወዳጄ ቡላ! እንዳንተ ስለ እኔ ስም መከራ የተቀበለ ሰው የለም:: አንተም የብዙዎች አባት ነሕና ስምህ አቢብ [ሃቢብ] ይሁን" አለው::

"እስከ ይቤሎ አምላክ ቃለ አኮቴት ማሕዘኔ: ረሰይከኑ ለባሕቲትከ ኩነኔ:
ዘመጠነዝ ታጻሙ ነፍስከ በቅኔ" እንዲል::

†   ዕረፍት   †

አቡነ አቢብ ታላቁ ዕብሎን ጨምሮ በርካታ ደቀ መዛሙርትን አፈራ:: ከእመቤታችን ጋርም ዕለት ዕለት እየተጨዋወተ ዘለቀ:: በተጋድሎ ሕይወቱም ከ፲ [10] ጊዜ በላይ ሙቶ ተነስቷል:: በዚህች ቀን ሲያርፍ ገዳሙ በመላእክት ተሞላ::
- ጌታም ከድንግል እናቱ ጋር መጥቶ "ወዳጄ ቡላ! ስምህን የጠራውን: መታሰቢያህን ያደረገውን እምርልሃለሁ:: አቅም ቢያጣ 'አምላከ አቢብ ማረኝ' ብሎ ፫ [3] ጊዜ በዕለተ ዕረፍትህ የሚለምነኝን: በስምሕ እንኳ ቁራሽ የሚበላውን ሁሉ እምርልሃለሁ" ብሎት ነፍሱን በክብር አሳረገ: በሰማይም ዕልልታ ተደረገ::


🕊 † ሰማዕታተ ፋርስ †  🕊

† ሰማዕትነት በክርስትና ለሃይማኖት የሚከፈል የመጨረሻው ዋጋ [መስዋዕትነት] ነው:: ሰው ለፈጣሪው ሰውነቱን ሊያስገዛ: ሃብት ንብረቱን ሊሰጥ ይችላል:: ከስጦታ በላይ ታላቅ ስጦታ ግን ራስን አሳልፎ መስጠት ነው::

ራስን መስጠት በትዳርም ሆነ በምናኔ ውስጥ ይቻላል:: የመጨረሻ ደረጃው ግን ሰማዕትነት ነው:: "አማን መነኑ ሰማዕት ጣዕማ ለዝ ዓለም: ወተዓገሡ ሞተ መሪረ በእንተ መንግስተ ሰማያት" እንዳለው ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ሰማዕትነት ማለት መራራውን ሞት ስለ ፍቅረ እግዚአብሔር ሲሉ መታገስ ነው::

እርሱ ቅሉ መድኃኒታችን ክርስቶስ የሰማይና የምድር ጌታ ሲሆን ኃፍረተ መስቀልን ታግሦ ሙቶልን የለ! በዓለም ያሉ ብዙ እምነቶች ስለ መግደል በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ያስተምራሉ:: ክርስትና ግን መሞትን እንጂ መግደልን የሚመለከት ሕግ የለውም::

እርሱ ባለቤቱ "ጠላቶቻችሁን ውደዱ: የሚረግሟችሁን መርቁ: ስለሚያሳድዷችሁ ጸልዩ" ብሎናልና:: [ማቴ.፭፥፵፬] ነገር ግን ዕለት ዕለት ራሳችንን በሃይማኖትና በምግባር ካልኮተኮትነው ክርስትና በአንድ ጀምበር ፍጹም የሚኮንበት እምነት አይደለምና በፈተና መውደቅ ይመጣል::

በተለይ የዘመኑ ክርስቲያን ወጣቶች ልናስተውል ይገባናል:: የቀደሙ ወጣት ሰማዕታት ዜና የሚነገረን እንድንጸና ነውና::

ፋርስ [ persia ] በአሁን መጠሪያዋ "ኢራን" የምትባል: በቀደመው ዘመን የበርካታ እውነተኛ ክርስቲያኖች ቤት ነበረች:: ሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስን ጨምሮ ቅዱስ ያዕቆብ ዘግሙድን የመሰሉ አእላፍ ሰማዕታት በዚሕች ሃገር ውስጥ በ2ኛውና ፫ኛው መቶ ክ/ዘመን የሰማዕትነት ጽዋዕን ጠጥተዋል:: በ፬ኛው መቶ ክ/ዘመንም አባ ማሩና በተባለ ጻድቅ ሰው በዚህች ቀን ዐፅማቸው ተሰብስቦ ቅዳሴ ቤታቸው ተከብሯል::

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

                        †                         

[ ለሐሳዊ አጥማቂያን ተጋላጭ የሆኑ ወገኖች እነማን ናቸው ? ]


" ማንም በማናቸውም መንገድ አያስታችሁ ፤ ክህደቱ አስቀድሞ ሳይመጣና የዓመፅ ሰው እርሱም የጥፋት ልጅ ሳይገለጥ ፥ አይደርስምና።
. . .
ይድኑ ዘንድ የእውነትን ፍቅር ስላልተቀበሉ ለሚጠፉ ፥ የእርሱ መምጣት በተአምራት ሁሉና በምልክቶች በሐሰተኞች ድንቆችም በዓመፅም መታለል ሁሉ እንደ ሰይጣን አሠራር ነው።"

[ ፪ተሰሎ.፪፥፫ ] [2፥3]

         †              †               †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

ሐሙስ - የካቲት 21 2016 ዓ.ም

ኢያሱ 1-5

ሰላም ለሁላችሁ ይሁን! ዛሬ በእግዚአብሔር ቸርነት መጽሐፈ ኢያሱን ማንበብ እንጀምራለን። መጽሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ ከሙሴ ሞት በኋላ እስራኤላውያን በኢያሱ መሪነት የነበራቸውን ጉዞ የሚተርክ መጽሐፍ ነው።

በዛሬው እለት ንባባችን ከምዕራፍ 1 እስከ 5 ድረስ እናነባለን።

ከንባብ በፊት የሚደረግ ጸሎት፡ “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፤ የአንተን ቃላት እሰማ እና እረዳ ዘንድ፥ እንዲያውም ፈቃድህን ለመፈጸም እበቃ ዘንድ የልቤን ጆሮዎች እና ዓይኖች ክፈትልኝ።” (ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ)

በዛሬው ንባባችን ላይ ስለ ከነዓን ድል መሆን፥ ኢያሱ ወደ ኢያሪኮ ሰላዮችን ስለመላኩ እና ስለ እስራኤል የዮርዳኖስን ወንዝ መሻገር እናነባለን። በተጨማሪም፥ እስራኤል መታሰቢያ ድንጋዮችን እንዳቆሙ፥ በጌልጌላ እንደ ተገረዙ እና ኢያሱ ከባለ ሰይፉ ሰው ጋር ስለመገናኘቱም ተጽፎ እናገኛለን።

*የክለሳ ጥያቄዎች*

1) በኢያሱ 1 መሠረት፥ እግዚአብሔር ኢያሱን ምን ብሎ አበረታው? ሕዝቡስ ምን ብለው አበረቱት?

2) በኢያሱ 2 መሠረት፥ ኢያሱ የላካቸው ሰላዮች በማን ቤት ገቡ? ሰዎች በመጡስ ጊዜ ምን አደረገቻቸው?

3) ሰላዮቹ ለሴቲቱ ምን የሚል ቃል ገቡ?

4) በኢያሱ 3 መሠረት፥ ታቦት የያዙ ካህናት ወደ ዮርዳኖስ ሲገቡ ምን ተፈጠረ?

5) በኢያሱ 4 መሠረት፥ እስራኤል ስንት መታሰቢያ ድንጋዮች አቆሙ? ለምንስ አቆሙ?

6) በኢያሱ 5 መሠረት፥ እግዚአብሔር በዮርዳኖስ ባሕር ያደረገውን የሰሙ አሕዛብ ምላሻቸው ምን ነበር?

7) ኢያሱ ባለ ሰይፉን ሰው ባገኘው ጊዜ ምን አለው? የባለ ሰይፉ ሰው ምላሽስ ምን ነበር?

መልካም ንባብ!
/channel/OrthodoxTewahdoBooks


/channel/c/2014228571/1

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

"ተወዳጁ ልጅሽ እንዲመግበኝ ትለምኝልኝ ዘንድ እማጸንሻለሁ"

እመቤቴ ድንግል ማርያም ሆይ እሰግድልሻለሁ። የመድኃኒት እናት ሆይ በመዓልትም በሌሊትም አማላጅ ትሆኝኝ ዘንድ እሰግድልሻለሁ። እመቤቴ ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ ከእርሱ የሚገኘውን ኃይልን ይሰጠኝ ዘንድ ከአንቺ ወደ ተወለደው ልጂሽ እንድትለምኝልኝ እማጸናለሁ። በመወለዱ ድኅነት የተገባሽ ሆነሻልና። በሔዋን ውድቀት ሆነ። አብ በመላእክት አለቃ በቅዱስ ገብርኤል አማካኝነት ሰላምን የላከልሽ እመቤቴ ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ እሰግድልሻለሁ። ሰላምታን ሰጠሽ ሰገደልሽም። ጸጋን የተመላሽ ሆይ እግዚአብሔር ከአንቺ ጋር ነውና ሰላምታ ይገባሻል። እነሆ ትጸንሻለሽ ልጅም ትወልጃለሽ፣ ስሙንም አማኑኤል ትይዋለሽ። የልዑል ኃይል ይጸልልሻል፤ ከአንቺ የሚወለደውም ቅዱስ ነው፤ እርሱም የልዑል ልጅ ይባላል አለሽ።

በተቀደሰው ስሙ ኅሊናዬን ልቡናዬን እንዲቀድስ ትለምኝው ዘንድ እማጸንሻለሁ። ንጽሕት ድንግል ማርያም ሆይ እሰግድልሻለሁ። የሕይወት ቃል ከአንቺ ሰው ይሆን ዘንድ በሥጋ ከአንቺ ይወለድ ዘንድ የተገባሽ የመድኃኒት እናት እመቤታችን ድንግል ማርያም ሆይ እሰግድልሻለሁ። ከአንቺ በመዋሐዱም እኛ ዳንን። እመቤቴ ድንግል ማርያም ሆይ እሰግድልሻለሁ። በእናታቸው ማሕፀን ሕፃናትን የሚስላቸው ከአባቱ እና ከመንፈስ ቅዱስ ጋርም ሁሉን የፈጠረው በማሕፀንሽ የተቀረጸብሽ የብርሃን እናት ሆይ እሰግድልሻለሁ። ረቂቅ ድንቅ ምሥጢርን ዓለምንም ካለመኖር ወደ መኖር ያመጣውን እመቤቴ ድንግል ማርያም ሆይ እለምንሻለሁ። በመንፈሳዊ ልደት ይወልደኝ ዘንድ ወደ እርሱ ዓለምና አዳኝ ወደ ሆነች ዕውቀት ከፍ ያደርገኝ ዘንድ ወደ እርሱ እንድትለምኝልኝ እለምንሻለሁ፣ አማጸንሻለሁ።

የሕይወት መገኛ የነገሥታት ንጉሥ የባለሥልጣናቱ ባለሥልጣን የአምላኮችን አምላክ በበረት ያስተኛሽው እመቤቴ ድንግል ማርያም ሆይ እሰግድልሻለሁ። አዳኝ ስለሆነው ስለስምሽ እንዲረዳኝ ትለምኝልኝ ዘንድም ወደ አንቺ እለምናለሁ፤ እማልዳለሁም። በማየቱ አዳምንና ከእርሱ ጋር ያሉትን ሁሉ ነጻ ያወጣውን በክንድሽ የታቀፍሽው እመቤቴ ድንግል ማርያም ሆይ እሰግድልሻለሁ።

በረቂቅ መመልከቱ እንዲመግበኝ ከሰይጣን መሰናክልም እንዲያድነኝ ትለምኝልኝ ዘንድ እለምንሻለሁ፤ እማጸንሽማለሁ። ዓለማትን ሁሉ ለሚመግበው ጡትሽን ያጠባሽው የመድኃኒት እናት እመቤቴ ድንግል ማርያም ሆይ እሰግድልሻለሁ፤ የሰማይ ኃይላት የሚመገቡትም ከእርሱ ነው። ነፍሴን በፈቃዱ ከጸጋው ይመግባት ዘንድ ወደ እርሱ እንድትለምኝልኝ እማጸንሻለሁ።

እመቤቴ ድግል ማርያም ሆይ ተወዳጁ ልጅሽ እንደ ፍጹም ፈቃዱ እንዲመግበኝ በየጊዜው በየሰዐቱ አማላጅ ሁኚኝ። ይህችም ወደ እርሱ የምትለምኝውን ልመና የተመላች መጽሐፍ ናት ። የለመንሁትን ሁሉ እርሱ ያደርግልሻልና። ኃጢአቴን ይቅር ይለኝ ዘንድ ወደ እርሱ እንድትለምኝልኝ እማጸንሻለሁ። ሰላምን ስለሰጠሽ ስለ አብ ከአንቺ ስለተወለደው አንቺንም ስለተዋሐደው ከአንቺም ሰው ስለሆነው ስለወልድ ፣ ስለቀደሰሽ፣ ከሦስቱ ቅዱስ ለአንዱ ማደሪያ ለመሆን እስከሚገባሽ ድረስ ስላነጻሽ ስለመንፈስቅዱስም እለምንሻለሁ። አገልጋይሽን ተወዳጁ ልጅሽ እንዲመግበኝ ትለምኝልኝ ዘንድ እማጸንሻለሁ። ለዘለዓለሙ አሜን።

#ቅዱስ_ባስልዮስ_ዘቂሳርያ
Deacon Birhanu Admass ( Birhanu Admass Anleye) የተረጎመው

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

...............................................

[ የማኅበረ ቅዱሳን መግለጫ ]

🔔

ማኅበረ ቅዱሳን ከቤተ ክርስቲያን ህልውና በላይ የሚያስቀድመው አንዳች ነገር የሌለ በመሆኑ ቤተ ክርስቲያናችን የገጠማትን ፈተና ለማለፍ  የሚጠበቅበትን መንፈሳዊ ግዴታ ለመወጣት ዝግጁ መሆኑን ዛሬ የካቲት 19/2016 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ አስታወቀ።

ማኅበሩ በመግለጫው የብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትን መንፈሳዊ አንድነት የጠየቀ ሲሆን "ቤተ ክርስቲያንን በማይጠቅማት ጉዳይ የግል ፍላጎትንና ምድራዊ ዓላማን መሠረት አድርገው ከቤተ ክርስቲያን ሕግና ቀኖና ውጭ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊን ለመተካት፣ ፓትርያርክ ለመሾምና የመሳሰሉትን ለመፈጸም" የሚንቀሳቀሱ ያላቸውን "አንዳንድ አባቶች" ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ በማሳሰብ ጉዳዩንም በመከታተል መረጃውን ለምእመናን አደርሳለሁ ብሏል።፡፡

ይመለከታቸዋል ላላቸው ሌሎች የቤተ ክርስቲያን አካለትም ጥሪውን አስተላልፏል።

1.   የተከበራችሁ አበው ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ሆይ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በመልእክቱ “በገዛ ደሙ        የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁ ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ   ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ፡፡ እንዳለ በዚህ ታላቅ የፈተና   ወቅት የቤተ ክርስቲያንን አንድነት ለማስጠበቅ፤ ቅዱስ ሲኖዶስ የሰጣችሁን ኃላፊነት ለመወጣት ምእመናንን አቅጣጫ በመስጠት የቀደሙ አባቶቻችሁን ፈለግ በመከተል ዛሬም በጽናት እንድትተጉ፤ ያከበረቻችሁን ቤተ ክርስቲያን በአንድነት ሆናችሁ እንድትጠብቁ በልጅነት መንፈስ በትሕትና እንጠይቃለን፡፡ በተጨማሪም የአባትነት የዋህ ልቦናችሁን በመጠቀም ያዘኑ፣ የጠቀሙ፣የተቆረቆሩ መስለው ቀርበው የግል ፍላጎታቸውን ለመፈጸም የሚጥሩ ስለሚኖሩ ሁሉንም በጥንቃቄ   እንድትመረምሩ፤ቀኖች ክፉዎች ናቸውና ዘመኑን በመዋጀት አንድነታችሁን እንድታጠነክሩና በቤተክርስቲያን ዙሪያ   ስለሚፈጠሩ ችግሮች በጥልቀት እንድትወያዩና እንድትመካከሩ እናሳሰስባለን።

2.   ከዚህ ውጭ ቤተ ክርስቲያንን በማይጠቅማት ጉዳይ የግል ፍላጎትንና ምድራዊ ዓላማን መሠረት አድርጋችሁ ከቤተ ክርስቲያን ሕግና ቀኖና ውጭ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊን ለመተካት፣ ፓትርያርክ ለመሾምና የመሳሰሉትን ለመፈጸም የምትንቀሳቀሱ አንዳንድ አባቶች ከድርጊታችሁ እንድትታቀቡ ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡ ማኅበራችን ይህንን ጉዳይ እየተከታተለ መረጃውን ለምእመናን የሚያደርስ መሆኑንም በዚሁ አጋጣሚ እንገልጻለን፡፡

3.     ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ መምህራነ ወንጌል፣ ካህናት ሆይ በጸሎትና በትምህርት ምእመናንን በማጽናናት፤ ከእውነት ጋር በመቆም እውነታውን በማሳየት ምእመናን ለቤተ ክርስቲያን ዘብ እንዲቆሙ በማድረግ ድርሻችሁን እንድትወጡ እናሳስባለን።

4.     ውድ ምእመናንና የማኅበራችን አባላት የታሪክ አጋጣሚ ሆኖ በዚህ ዘመን ቤተ ክርስቲያንን ከአሳዳጆቿ የመጠበቁ ዋነኛ ኃላፊነት በዘመኑ ባለን ብፁዓን አባቶች፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርሰቲያን፣ ካህናትና ምእመናን ሁላችን እጅ ላይ ወድቆአል፡፡  የቤተ ክርስቲያንን ጉዳይ ለአባቶችና ለካህናት ትተን “እኔ አያገባኝም፤ አይመለከተኝም” ልንል አይገባም፡፡ ሁሉም በየድርሻው ቤተክርስቲያኑን ለመጠበቅ መትጋት አለበት፡፡ በቤተ ክርስቲያን ላይ የደረሰውን ጥፋትና ሊመጣ ያለውን ፈተና አስቀድሞ በመረዳት ቅዱስ ሲኖዶስ ቀደም ሲል በወሰነው መሠረት በየአጥቢያችን፤ በተለያየ መልኩ በመደራጀት፤ በቤተክርስቲያን ላይ ጥፋት ለማድረስ የሚመጡትን በመከላከል የቤተ ክርስቲያንን ስደት ለማስቆም መንፈሳዊ ግዴታችንን እንድንወጣ እንጠይቃለን፡፡

5.     በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በልዩ ልዩ አገልግሎት እየተሳተፋችሁ ያላችሁ ሰንበት ትምህርት ቤቶች፣ ማኅበራትና ሌሎችም ሁላችንም አንድነታችንን በመጠበቅ በጋራ አገልግሎቶችን በመፈጸም  ድርሻችንን እንድንወጣ ለተግባራዊነቱ ጥሪ እናቀርባላን፡፡

6.     ገዳም ድረስ ገብቶ መሣሪያ ያልያዙና: ራሳቸውን  እንደሞቱ ቆጥረው እየኖሩ ያሉ መነኮሳት ላይ  ግድያ የፈጸመ ማንኛውም የታጠቀ ኃይል (መደበኛም ይሁን ኢመደበኛ: በግልም ይሁን በቡድን: አማኝም  ይሁን ኢአማኝ)  ድርጊቱ ከሰውነት ተፈጥሮ የወጣ ነው፡፡ ምናኔንና የክህነት ክብርን በተቃረነ መልኩ ሰብእና የጎደለው ጥቃት ማድረስ ኢትዮጵያዊ ባህልም አይደለም፡፡ ጥቅም የሌለው ከንቱ ተግባር ነው፡፡ በዚህ የሚገኝ የፖለቲካ ትርፍ ይኖራል ብለን አናምንም፡፡ ጤነኛ በሆነ አእምሮ ታስቦ የተፈጸመ ነው ማለትም አይቻልም፡፡  ማስተዋል ተወስዶባቸው እውቀት ተሰውሮባቸው እንጂ ይህንን ማድረግ ቀርቶ ማሰቡም የሙት ሐሳብ ነው፡፡ ቀድሞ የሞተው ሟቹ ሳይሆን ገዳዩ ነው፡፡ በዚህ መንገድ የቤተ ክርስቲያን አማኞች  ሲበዙ እንጂ ሲያንሱ በታሪክ አልታየም:: ይህ ድርጊት ክርስቲያኖችን ሲያጠነክር እንጂ ሲያዳክም ታይቶ አይታወቅም፡፡ መጽሐፍ “ጎርፍም መጣ ነፋስም ነፈሰ ያንን ቤት ገፋው በዓለት ላይ ስለተመሠረተ አልወደቀም ” ባለው መሠረት ቤተክርስቲያን በጽኑ ዐለት ላይ የተመሠረተች ስለሆነ አታሽነፏትም። ዲዮቅልጥያኖስም አላጠፋትም:: ዲያብሎስም ዝናሩን እንዲሁ ጨረሰ:: ስለዚህ አትድከሙ: አትሳቱም እናንተ ሳትወለዱ የነበረች ቤተ ክርስቲያን እናንተ አልፋችሁም እንደ እናንተ ላሉት በስሑት መንገድ ለሚጓዙት ሁሉ እየጸለች ትቀጥላለች:: ሐሳቧም፣ ሥራዋም፣ ዓላማዋም፣ ግቧም ሰማያዊ ነውና።

  በመጨረሻም ማኅበረ ቅዱሳን ከቤተ ክርስቲያን ህልውና በላይ የሚያስቀድመው አንዳች ነገር የሌለ በመሆኑ ቤተ ክርስቲያናችን የገጠማትን ፈተና ለማለፍ ከሚመለከታቸው የቤተ ክርስቲያን አካላት ጋር በመናበብ የሚጠበቅበትን መንፈሳዊ ግዴታ ለመወጣት ዝግጁ መሆኑን በዚሁ አጋጣማ እያሳወቅን፥ የሁላችንም የመሰባሰብና የአገልግሎት ማእከል ቤተ ክርስቲያን በመሆኗ ከሁሉም ነገር በፊት ቅድሚያ ሰጥተን ሊመጣ ካለው አደጋ ቤተ ክርስቲያናችንን የመጠበቅ ኀላፊነት በትጋት እንወጣ ሲል ማኅበረ ቅዱሳን በመግለጫው ጥሪ አቅርቧል፡፡

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

🕊

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †

[ 🕊  †  እንኩዋን ለቅዱስ "አናሲሞስ ሐዋርያ" እና ለእመቤታችን "ቅድስት ድንግል ማርያም" በዓል በሰላም አደረሳችሁ  †   🕊 ]


🕊  †  ድንግል ማርያም †   🕊

የአምላክ እናቱ እመ-ብርሃን ድንግል ማርያም :-
- በ፫ [3] ወገን [በሥጋ: በነፍስ: በልቡና] ድንግል
- በ፫ [3] ወገን [ከኀልዮ: ከነቢብ: ከገቢር] ንጽሕት
- ሳትጸንስ: በጸነሰች ጊዜና ከጸነሰች በሗላ ድንግል
- ጌታን ሳትወልድ : በወለደችው ጊዜና ከወለደችው በሗላ ድንግል ስትሆን እናትም ድንግልም መሆኗን አምነን እመሰክራለን::

- እመቤታችን ከፍጥረት ሁሉ በላይ ክብርትና ንዕድ ናት:: ሊቃውንት አበው እንዳስተማሩን በዚህ ዕለት እንዲህ ብለን እንጸልያለን::
"ረስዪ ፍና ትሕትና አእጋርየ ይሑሩ:
ትዕቢትሰ ለአምላክ ጸሩ"
[እመቤቴ ሆይ ትዕቢትን አምላክ ይጠላልና እግሮቻችን በትሕትና እንዲሔዱ አድርጊ]


🕊  †  ቅዱስ አናሲሞስ ሐዋርያ †  🕊

በዘመነ ሐዋርያት ምስጉን ከነበሩ አበው አንዱ ቅዱስ አናሲሞስ ነው:: ስለ ቀና አገልግሎቱና መልካም እረኛነቱ አባቶቻችን ሐዋርያት አብዝተው በቀኖናቸው መስክረውለታል:: እርሱ ከኃጢአት ኑሮ ወደ ዘለዓለማዊ የቅድስና ሕይወት መጥቷልና::

¤ ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ :-

በሮም ከተማ የሚኖር ፊልሞና የሚባል አንድ ባለጸጋ ነበር:: ይህ ሰው በስብከተ ቅዱስ ዻውሎስ አምኖ ከርስቲያን ሆነና በመንፈሳዊ አገልግሎት ተጠመደ:: ነገር ግን ከአገልጋዮቹ መካከል ያላመነ አንድ ሰው ነበር:: "ተጽዕኖ አላደርግበትም" ብሎ ዝም ይለዋል:: ግን ክርስትና እንዲገባው ለተልዕኮ መንፈሳዊ በሚሔድበት ሥፍራ ያስከትለው ነበር::

አገልጋዩ ግን በመለወጥ ፈንታ ሌብነትን ለመደ:: ይባስ ብሎም የአሳዳሪውን [የፊልሞናን] ገንዘብ ሠርቆ ወደ ሮም ጠፍቶ ተመለሰ:: ቅዱስ ፊልሞናም ለገንዘቡ ሳይሆን ለሕይወቱ አዘነ::

ያ ሠርቆ የጠፋው አገልጋይ ግን በሮም ከተማ ሲመላለስ ስብከተ ወንጌልን ይሰማል:: ሰባኪው ደግሞ ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ዻውሎስ ነበር:: ቁጭ ብሎ ሲማርም ልቡናው በርቶለት ተጸጸተ:: ከሐዋርያውም ዘንድ ቀርቦ ኃጢአቱን ተናዞ ተጠመቀ::
ከዚያች ዕለት ጀምሮም ብርቱ ክርስቲያን ሆነ:: በጥቂት ጊዜም የተጋ ሰባኪ : ርሕሩሕ እረኛ ሆነ:: ፈጣሪውንም ደስ አሰኘ:: ነገር ግን ስለ አንድ ነገር ፈጽሞ ያዝን : ይተክዝም ነበር::

+ የድሮ አሳዳሪው ቅዱስ ፊልሞና እንዳዘነበት እያወቀ ዝም ማለት ባያስችለው ለመምህሩ ቅዱስ ዻውሎስ ነገረው:: ያን ጊዜም ሐዋርያው በእሥራትና በግርፋት ይሰቃይ ነበር:: በሮም ሳለም አጭር ክታብ [ደብዳቤን] ጽፎ ለዚህ ደቀ መዝሙሩ ሰጠውና ወደ ቀድሞ አሳዳሪው ወደ ፊልሞና ላከው::

+ ይህች ጦማር [ክታብ] ዛሬም ድረስ ከ፹፩ [81] ዱ አሥራው መጻሕፍት : ከቅዱስ ዻውሎስ ፲፬ [14] መልዕክታት አንዷ ሆና ተቆጥራ እንጠቀምባታለን:: ክታቧ እጅግ አጭር ብትሆንም ምሥጢሯ ግን ሰፊ ነው::

+ ያ የተላከ ክርስቲያንም ያችን ክታብ ወስዶ ለቅዱስ ፊልሞና [ለቀድሞ አሳዳሪው] አስረከበ:: ቅዱስ ፊልሞናም በደስታ አቅፎ ሳመው:: ቀድሞውንም ያዘነ በወጣቱ አገልጋይ የነፍስ እዳ እንጂ በገንዘቡ አልነበረምና:: ያ ተላኪ ሰውም በአካባቢው ሲያገለግል ቆይቶ ወደ ቅዱስ ዻውሎስ ተመልሷል:: ደቀ መዝሙሩ ሆኖም ብዙ አገልግሏል::

+ ቅዱስ አናሲሞስ ማለት . . . የቀድሞ የሰው አገልጋይ . . . ዛሬ የክርስቶስ ባሪያ . . . ቀድሞ ሠራቂ . . . ዛሬ ግን ለመንጋው የሚራራ ሰው የሆነው ይህ ክርስቲያን ነው::

+ በ፷፯ [67] ዓ/ም ቅዱስ ዻውሎስ መሰየፉን ተከትሎ እርሱንም አሳድደው : አሰቃይተው : ጭኑንም ሰብረው አሕዛብ ገድለውታል:: በሰማይም የሐዋርያነትና የሰማዕትነት አክሊልን ተቀዳጅቷል:: [ጢሞ.፬፥፮-፰ [4:6-8] , ፊልሞና.፩፥፩-፳፭] 1:1-25]

አምላከ ቅዱሳን የአናሲሞስን መመለስ : ንስሃና በረከት ያድለን::

🕊

[ † የካቲት ፳፩ [ 21 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. ቅዱስ አናሲሞስ ሐዋርያ [የቅዱስ ዻውሎስ ሐዋርያ ደቀ መዝሙር ሲሆን ከ፲፬ [14] ቱ መልዕክታት አንዱ የሆነው 'ወደ ፊልሞና' የተጻፈው በዚህ ቅዱስ ምክንያት ነው:: [ፊል.፩፥፲፩ 1:11]
፪. አባ ዘካርያስ ዘሃገረ ስሃ
፫. አባ አካክዮስ ጻድቅ
፬. አባ ገብርኤል ሊቀ ዻዻሳት
፭. አባ ገብርኤል [የኢትዮዽያ ዻዻስ]

[ + ወርኀዊ በዓላት ]

፩. ቅድስት ድንግል እመቤታችን ማርያም
፪. አበው ጎርጎርዮሳት
፫. አቡነ ምዕመነ ድንግል
፬. አቡነ አምደ ሥላሴ
፭. አባ አሮን ሶርያዊ
፮. አባ መርትያኖስ ጻድቅ

" ስለ ጽዮን ዝም አልልም . . . አሕዛብም ጽድቅሽን ነገሥታትም ሁሉ ክብርሽን ያያሉ:: የእግዚአብሔርም አፍ በሚጠራበት በአዲሱ ስም ትጠሪያለሽ:: በእግዚአብሔር እጅ የክብር አክሊል በአምላክሽም እጅ የመንግሥት ዘውድ ትሆኛለሽ:: " [ኢሳ.፷፪፥፩-፫] [62:1-3)

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

🕊

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †

[ 🕊  †  እንኩዋን ለቅዱስ "አናሲሞስ ሐዋርያ" እና ለእመቤታችን "ቅድስት ድንግል ማርያም" በዓል በሰላም አደረሳችሁ  †   🕊 ]


🕊  †  ድንግል ማርያም †   🕊

የአምላክ እናቱ እመ-ብርሃን ድንግል ማርያም :-
- በ፫ [3] ወገን [በሥጋ: በነፍስ: በልቡና] ድንግል
- በ፫ [3] ወገን [ከኀልዮ: ከነቢብ: ከገቢር] ንጽሕት
- ሳትጸንስ: በጸነሰች ጊዜና ከጸነሰች በሗላ ድንግል
- ጌታን ሳትወልድ : በወለደችው ጊዜና ከወለደችው በሗላ ድንግል ስትሆን እናትም ድንግልም መሆኗን አምነን እመሰክራለን::

- እመቤታችን ከፍጥረት ሁሉ በላይ ክብርትና ንዕድ ናት:: ሊቃውንት አበው እንዳስተማሩን በዚህ ዕለት እንዲህ ብለን እንጸልያለን::
"ረስዪ ፍና ትሕትና አእጋርየ ይሑሩ:
ትዕቢትሰ ለአምላክ ጸሩ"
[እመቤቴ ሆይ ትዕቢትን አምላክ ይጠላልና እግሮቻችን በትሕትና እንዲሔዱ አድርጊ]


🕊  †  ቅዱስ አናሲሞስ ሐዋርያ †  🕊

በዘመነ ሐዋርያት ምስጉን ከነበሩ አበው አንዱ ቅዱስ አናሲሞስ ነው:: ስለ ቀና አገልግሎቱና መልካም እረኛነቱ አባቶቻችን ሐዋርያት አብዝተው በቀኖናቸው መስክረውለታል:: እርሱ ከኃጢአት ኑሮ ወደ ዘለዓለማዊ የቅድስና ሕይወት መጥቷልና::

¤ ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ :-

በሮም ከተማ የሚኖር ፊልሞና የሚባል አንድ ባለጸጋ ነበር:: ይህ ሰው በስብከተ ቅዱስ ዻውሎስ አምኖ ከርስቲያን ሆነና በመንፈሳዊ አገልግሎት ተጠመደ:: ነገር ግን ከአገልጋዮቹ መካከል ያላመነ አንድ ሰው ነበር:: "ተጽዕኖ አላደርግበትም" ብሎ ዝም ይለዋል:: ግን ክርስትና እንዲገባው ለተልዕኮ መንፈሳዊ በሚሔድበት ሥፍራ ያስከትለው ነበር::

አገልጋዩ ግን በመለወጥ ፈንታ ሌብነትን ለመደ:: ይባስ ብሎም የአሳዳሪውን [የፊልሞናን] ገንዘብ ሠርቆ ወደ ሮም ጠፍቶ ተመለሰ:: ቅዱስ ፊልሞናም ለገንዘቡ ሳይሆን ለሕይወቱ አዘነ::

ያ ሠርቆ የጠፋው አገልጋይ ግን በሮም ከተማ ሲመላለስ ስብከተ ወንጌልን ይሰማል:: ሰባኪው ደግሞ ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ዻውሎስ ነበር:: ቁጭ ብሎ ሲማርም ልቡናው በርቶለት ተጸጸተ:: ከሐዋርያውም ዘንድ ቀርቦ ኃጢአቱን ተናዞ ተጠመቀ::
ከዚያች ዕለት ጀምሮም ብርቱ ክርስቲያን ሆነ:: በጥቂት ጊዜም የተጋ ሰባኪ : ርሕሩሕ እረኛ ሆነ:: ፈጣሪውንም ደስ አሰኘ:: ነገር ግን ስለ አንድ ነገር ፈጽሞ ያዝን : ይተክዝም ነበር::

+ የድሮ አሳዳሪው ቅዱስ ፊልሞና እንዳዘነበት እያወቀ ዝም ማለት ባያስችለው ለመምህሩ ቅዱስ ዻውሎስ ነገረው:: ያን ጊዜም ሐዋርያው በእሥራትና በግርፋት ይሰቃይ ነበር:: በሮም ሳለም አጭር ክታብ [ደብዳቤን] ጽፎ ለዚህ ደቀ መዝሙሩ ሰጠውና ወደ ቀድሞ አሳዳሪው ወደ ፊልሞና ላከው::

+ ይህች ጦማር [ክታብ] ዛሬም ድረስ ከ፹፩ [81] ዱ አሥራው መጻሕፍት : ከቅዱስ ዻውሎስ ፲፬ [14] መልዕክታት አንዷ ሆና ተቆጥራ እንጠቀምባታለን:: ክታቧ እጅግ አጭር ብትሆንም ምሥጢሯ ግን ሰፊ ነው::

+ ያ የተላከ ክርስቲያንም ያችን ክታብ ወስዶ ለቅዱስ ፊልሞና [ለቀድሞ አሳዳሪው] አስረከበ:: ቅዱስ ፊልሞናም በደስታ አቅፎ ሳመው:: ቀድሞውንም ያዘነ በወጣቱ አገልጋይ የነፍስ እዳ እንጂ በገንዘቡ አልነበረምና:: ያ ተላኪ ሰውም በአካባቢው ሲያገለግል ቆይቶ ወደ ቅዱስ ዻውሎስ ተመልሷል:: ደቀ መዝሙሩ ሆኖም ብዙ አገልግሏል::

+ ቅዱስ አናሲሞስ ማለት . . . የቀድሞ የሰው አገልጋይ . . . ዛሬ የክርስቶስ ባሪያ . . . ቀድሞ ሠራቂ . . . ዛሬ ግን ለመንጋው የሚራራ ሰው የሆነው ይህ ክርስቲያን ነው::

+ በ፷፯ [67] ዓ/ም ቅዱስ ዻውሎስ መሰየፉን ተከትሎ እርሱንም አሳድደው : አሰቃይተው : ጭኑንም ሰብረው አሕዛብ ገድለውታል:: በሰማይም የሐዋርያነትና የሰማዕትነት አክሊልን ተቀዳጅቷል:: [ጢሞ.፬፥፮-፰ [4:6-8] , ፊልሞና.፩፥፩-፳፭] 1:1-25]

አምላከ ቅዱሳን የአናሲሞስን መመለስ : ንስሃና በረከት ያድለን::

🕊

[ † የካቲት ፳፩ [ 21 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. ቅዱስ አናሲሞስ ሐዋርያ [የቅዱስ ዻውሎስ ሐዋርያ ደቀ መዝሙር ሲሆን ከ፲፬ [14] ቱ መልዕክታት አንዱ የሆነው 'ወደ ፊልሞና' የተጻፈው በዚህ ቅዱስ ምክንያት ነው:: [ፊል.፩፥፲፩ 1:11]
፪. አባ ዘካርያስ ዘሃገረ ስሃ
፫. አባ አካክዮስ ጻድቅ
፬. አባ ገብርኤል ሊቀ ዻዻሳት
፭. አባ ገብርኤል [የኢትዮዽያ ዻዻስ]

[ + ወርኀዊ በዓላት ]

፩. ቅድስት ድንግል እመቤታችን ማርያም
፪. አበው ጎርጎርዮሳት
፫. አቡነ ምዕመነ ድንግል
፬. አቡነ አምደ ሥላሴ
፭. አባ አሮን ሶርያዊ
፮. አባ መርትያኖስ ጻድቅ

" ስለ ጽዮን ዝም አልልም . . . አሕዛብም ጽድቅሽን ነገሥታትም ሁሉ ክብርሽን ያያሉ:: የእግዚአብሔርም አፍ በሚጠራበት በአዲሱ ስም ትጠሪያለሽ:: በእግዚአብሔር እጅ የክብር አክሊል በአምላክሽም እጅ የመንግሥት ዘውድ ትሆኛለሽ:: " [ኢሳ.፷፪፥፩-፫] [62:1-3)

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

🕊


[ በእግዚአሔርም ቤት ለዘላለም እኖራለሁ ! ]


" እግዚአብሔር እረኛዬ ነው ፥ የሚያሳጣኝም የለም። በለመለመ መስክ ያሳድረኛል ፤ በዕረፍት ውኃ ዘንድ ይመራኛል።

ነፍሴን መለሳት ፥ ስለ ስሙም በጽድቅ መንገድ መራኝ። በሞት ጥላ መካከል እንኳ ብሄድ አንተ ከእኔ ጋር ነህና ክፉን አልፈራም ፤ በትርህና ምርኵዝህ እነርሱ ያጸናኑኛል።

በፊቴ ገበታን አዘጋጀህልኝ በጠላቶቼ ፊት ለፊት ራሴን በዘይት ቀባህ ፥ ጽዋዬም የተረፈ ነው። ቸርነትህና ምሕረትህ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ ይከተሉኛል ፥ በእግዚአሔርም ቤት ለዘላለም እኖራለሁ።"

[ መዝ.፳፫፥፩-፮ ]

†                        †                        †
💖                    🕊                     💖

Читать полностью…
Subscribe to a channel