mikreabew | Unsorted

Telegram-канал mikreabew - ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

874

"እንግዲህ፡ንስሓ፡ግባ፤አለዚያ፡ፈጥኜ፡ እመጣብሃለሁ፡፡" ራዕ 2፥16

Subscribe to a channel

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

🔔

[ ጉስቁልናችን እዚህ ደረጃ ላይ ደርሷል ! ]

-

[ ለዚህ ውድቀት ተጠያቂው ማነው ? ! ]

- ኦርቶዶክሳዊነትን ከመሰለ ክርስቶሳዊ የልዕልና ሕይወት እንዲህ መውረድ

- የክርስቶስ አካሉ ከምትሆን ከጸጋ ሁሉ ግምጃ ቤት ከሆነችው ከቅድስት ቤተክርስቲያ ተለይቶ ከነጣቂ ወንበዴ ስር መውደቅ

- በቤቱ በመጽናት ፥ በመንፈሳዊ ተጋድሎም በመትጋት ምሕረትንና ይቅርታን ከእግዚአብሔር ከመለመን ይልቅ እንደ መናፍቃኑ ከግለሰብ ምልክትና ተአምር ለማግኘት መቋመጥና ነዳይ መሆን

- ከእመቤታችንና የክርስቶስ አካሉ ከሚሆኑ እውነተኛ ወዳጆቹ ከቅዱሳን ፣ ከጻድቃን ከሰማዕታት ቃል ኪዳን ተለይቶ እንዲህ የነጣቂ መጫወቻ መሆን

- ኅብረታዊት ፥ ሥርዓታዊት - ሰማያዊት ከሆነችው ከቅድስት ቤተክርስቲያን የኪዳን ፣ የቅዳሴና የጸሎት መንፈሳዊ ሥርዓቶች የሚገኘውን እውነተኛ የነፍስና የሥጋ ድኅነት ጥሎ የሃሳዊው መሢሕ መንገድ ጠራጊ በሆኑት ሃሰተኛ አጥማቂያን እጅ መውደቅ !

ይህ እንደምን ያለ ጉስቁልና ነው ! ?


- ይህ ግለሰብና መሰሎቹ የሚኖሩባቸውን እጅግ ዘመናዊ ቪላ ቤቶችን የገነባቸው ማን ነው ?! ይህንን ቅንጡና በሚሊየን ብሮች የሚገዛውን መኪናስ የገዛው ማን ነው ? ! ግለሰቡ በጉልበቱ ድካም በላቡ ወዝ የገዛው ነውን ? ! እንዲህ ባለ ኑሮስ የሚገኝ ቅድስናና ፈውስስ ከማን የሚገኝና እንዴት ያለ ነው ? !

የቅዱሳን አባቶቻችን ሕይወትስ እንደምን ያለ ነበረ ? !


▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
              

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

እንረጋጋ ! እንዲህ አላልንም። ከመናገር መማር ይቅደም።

" መላእክቱን ስለ አንተ ያዝልሃል እግርህንም በድንጋይ ከቶ እንዳትሰናከል በእጃቸው ያነሡሃል ተብሎ ተጽፎአልና ..." [ማቴ.፬፥፮] ያለው ሰይጣን ነው። ቃሉን የወሰደው ከመዝሙር መጽሐፍ ላይ ነው። ሰይጣን የተቀደሰውን ቃልና ሃሳብ ለክፋት ዓላማ ይጠቀምበታል። እውነትና መልካም የሆነውን ቃልና ሃሳብ ስለተጠቀመ ብቻ ልንቀበል አይገባም።

ተናጋሪው ማነው ? ቃሉን ለምን ዓላማ ተጠቀመው ? በመልካም ቃላት መሃል የተሰወረው የጥፋት ወጥመድ ምንድን ነው ? ብሎ መመርመር ከክርስቲያኖች እንደሚጠበቅ ያስተምረን ዘንድ ክብር ይግባውና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመጽሐፍ የመጣውን የጸላኢን ክፋት በመጽሐፍ ጠቅሶ ድል ነስቶታል።

መረጋጋትና ማስተዋል ይኑረን። ቁራጭ ስጋ መንትፎ የሚበረው ጩልሌ ነውና እንዲህ ልንሆን አይገባም። እግዚአብሔር ማስተዋሉን ያድለን።

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

🔔

" ጸሎት ቤት ሥሩ " የነጣቂዎቹ ሐሳዊ አጥማቂያን ማጠንጠኛ ማዕከል ለምን ሆነ ?

ከደቂቃዎች በኋላ በሚቀርበው የምሽት መርሐ-ግብር ይጠብቁ !


         †              †               †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

youtube ላይ አይቼዋለሁ
እኔ ግን እነሱን አልከተልም ደግሞም አልቃወምም
እንደማንኛውም ምእመን እግዚአብሔር በሰጣቸው ፀጋ ግን እጠቀማለው...መቃወም ሳይሆን ሁለቱም አካላት በአንድ መረሀግብር ተገናኝተው ፊትለፊት አውርተው የሚወሰነውን ውሳኔ እቀበላለሁ እንጁ አንዱን አካል ብቻ መቀበል ይከብደኛል

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

ረቡዕ - የካቲት 20 2016 ዓ.ም

ዘዳግም 28-34

ሰላም ለሁላችሁ ይሁን! በዛሬው እለት ንባባችን ከምዕራፍ 28 እስከ 34 ድረስ እናነባለን።

ከንባብ በፊት የሚደረግ ጸሎት፡ “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፤ የአንተን ቃላት እሰማ እና እረዳ ዘንድ፥ እንዲያውም ፈቃድህን ለመፈጸም እበቃ ዘንድ የልቤን ጆሮዎች እና ዓይኖች ክፈትልኝ።” (ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ)

በዛሬው ንባባችን ላይ በታዛዥነት ስለሚገኝ በረከት፥ በማይታዘዙ ላይ ስለሚደርስ ርግማን፥ በሞአብ ምድረ በዳ ስለተሰጠው ቃል ኪዳን፥ ወደ እግዚአብሔር በመመለስ ስለሚገኘው በረከት፥ ስለ ሕይወት እና ሞት፥ ስለ ኢያሱ በሙሴ ፋንታ መተካት፥ የእግዚአብሔር ሕግ በየሰባት ዓመት መነበብ እንደሚገባው እና ሙሴ እና ኢያሱ ከእግዚአብሔር መመሪያ ስለመቀበላቸው እናነባለን። በተጨማሪም፥ የሙሴን መዝሙር፥ የመጨረሻ ምክሩን፥ ስለ ሙሴ ሞት፥ እስራኤልን ስለ መባረኩ እና ስለ ሞቱ እና ቀብሩ ተጽፎ ይገኛል።

*የክለሳ ጥያቄዎች*

1) በዘዳግም 28 መሠረት፥ እግዚአብሔርን በመታዘዝ ከሚገኝ በረከት እና ካለመታዘዝ ከሚድርስ እርግማን ሦስት ጥቀሱ።

2) በዘዳግም 29 መሠረት፥ እግዚአብሔር ቃልኪዳን ያደረገው ከማን ጋር ነው?

3) በዘዳግም 31 መሠረት፥ ሙሴ በኢያሱ  ሲተካ ስንት ዓመቱ ነበር?

4) በዘዳግም 32 መሠረት፥ የሙሴ የመጨረሻ ምክር ምንድር ነበር?

5) በዘዳግም የመጨረሻ ምዕራፍ መሠረት፥ ሙሴ የሞተው በየት ነው? የእስራኤል ልጆችስ ስንት ቀን አለቀሱለት?

መልካም ንባብ!

/channel/OrthodoxTewahdoBooks

/channel/c/2014228571/1

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

የዘመኑ ሐሳዊ አጥማቂያንንና የአጋንንትን ምስክርነት በተመለከተ የተጀመረው መርሐ-ግብር ከነገ ምሽት ጀምሮ መቅረቡን የሚቀጥል ይሆናል።

ይከታተሉ !!!

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

ማግሰኞ - የካቲት 19 2016 ዓ.ም

ዘዳግም 23-27

ሰላም ለሁላችሁ ይሁን! በዛሬው እለት ንባባችን ከምዕራፍ 23 እስከ 27 ድረስ እናነባለን።

ከንባብ በፊት የሚደረግ ጸሎት፡ “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፤ የአንተን ቃላት እሰማ እና እረዳ ዘንድ፥ እንዲያውም ፈቃድህን ለመፈጸም እበቃ ዘንድ የልቤን ጆሮዎች እና ዓይኖች ክፈትልኝ።” (ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ)

በዛሬው ንባባችን ላይ እስራኤላውያን ስለ ጋብቻና ፍቺ ሥርዓት፥ ለድሃው ስለማዘን፥ ስለ ዋርሳ ሥርዓት እና አሥራትና በኩራት ስለመስጠት የተሰጣቸውን መመሪያ በተመለከተ እናነባለን። በተጨማሪም፥ እስራኤላውያን ዮርዳኖስን ከተሻገሩ በኋላ ማድረግ ስላለባቸው ነገር እና እርግማንን ስለሚያስከትሉ ነገሮችም ተገልጿል።

*የክለሳ ጥያቄዎች*

1) በዘዳግም 23 መሠረት፥ ስለ ብድር እና ስለ ስእለት ምን ሕግ ተሰጥቷል?

2) በዘዳግም 24 መሠረት፥ ወፍጮ ወይም መጅ እንደ መያዣ መጠቀም የተከለከለው ለምንድር ነው?

3) በዘዳግም 25 መሠረት፥ የጫማ ፈቱ ቤት ምን ማለት ነው?

4) በዘዳግም 27 መሠረት፥ በተራራ ላይ ቆመው ምርቃት ለመናገር የተመረጡት እነማን ናቸው? እርግማንስ?

5) በዘዳግም 27 መሠረት፥ እርግማንን የሚያስከትሉ ሦስት ነገሮችን ጥቀሱ።

መልካም ንባብ!

/channel/OrthodoxTewahdoBooks


/channel/c/2014228571/1

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

🕊

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። †

🕊 † ታላቁ አባ መርትያኖስ † 🕊

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም የካቲት ዐሥራ ዘጠኝ በዚች ዕለት የተጋዳይ መነኰስ የአባ መርትያኖስ ሥጋው ከአቴና አገር ወደ አንጾኪያ የፈለሰበት ሆነ። እርሱም ሽንግላ በኃጢያት ልትጥለው በወደደች ጊዜ ከአመንዝራ ሴት ከተፈተነ በኋላ እርሱ ግን መንኵሳ በገድል እስከ ተጸመደች ድረስ ስቦ ወደ ንስሓ መልሷታል።

ከዚህም በኋላ መኖሪያውን ትቶላት ከሀገር ወደ ሀገር የሚዞር ሆነ ከአቴና አገርም ደርሶ በዚያ ጥቂት ቀን ኖረ ጥቂትም ታመመና በሰላም አገፈ ዜናው በግንቦት በሃያ አንድ ቀን እንደተጻፈ።

የከበረ ቴዎድሮስም ለአንጾኪያ ሀገር በከሀዲው የፋርስ ንጉሥ ዘመን ሊቀ ጵጵስና በተሾመ ጊዜ ይህ አባት የካህናት አለቆችንና ምእመናንን ልኮ ሥጋውን ከአቴና አፍልሰው ወደ አንጾኪያ ከተማ አመጡት በምስጋናም እየዘመሩ አክብረው ተቀበሉት ሊቀ ጳጳሳቱም ተሳለመው በሣጥንም አድርጐ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ አኖረው። በዚችም ዕለት በዓልን አደረጉለት።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

[ † የካቲት ፲፱ [ 19 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. ታላቁ አባ መርትያኖስ [በዝሙት ላለመሰናከል እግራቸውን በእሳት ያቃጠሉ አባት]

[ † ወርሐዊ በዓላት ]

፩. ቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላእክት
፪. ቅዱስ ኤስድሮስ ሰማዕት
፫. አቡነ ዓቢየ እግዚእ ጻድቅ
፬. አቡነ ስነ ኢየሱስ
፭. አቡነ ዮሴፍ ብርሃነ ዓለም

" . . . በእስራትና በወኅኒ ተፈተኑ:: በድንጋይ ተወግረው ሞቱ:: ተፈተኑ:: በመጋዝ ተሰነጠቁ:: በሰይፍ ተገድለው ሞቱ:: ሁሉን እያጡ መከራን እየተቀበሉ: እየተጨነቁ የበግና የፍየል ሌጦ ለብሰው ዞሩ:: ዓለም አልተገባቸውምና በምድረ በዳና በተራራ: በዋሻና በምድር ጉድጉዋድ ተቅበዘበዙ::" [ዕብ.፲፩፥፴፮]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

🕊

በስመ አብ : ወወልድ : ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን።

[ " ከዮናስ የሚበልጥ እዚህ አለ " ]

[ማቴ.፲፪፥፵፩]

💖

ጌታና ዮናስ በምን ይመሳሰላሉ ?

• በየዋህነት ፤ [ማቴ.፲፩፥፳፱]

• በነቢይነት ፤ [ሉቃ.፲፫፥፴፫]

• መርከቡ ላይ በመተኛት ፤ [ማቴ.፰፥፳፬]
• ወዲህም መርከቡ የመስቀል ምሳሌ ነው ፤ ጌታ መስቀል ላይ መሞቱን የሚያመለክት ነው።
• ዕጣ የወጣበት በመሆን ፣ ዮናስ ወደ ባሕሩ ለመጣል ዕጣ እንደወጣበት ጌታም የእኛን ዕጣ ሞትን መሞቱ
• አንድም ጌታ በአካለ ነፍስ ወደሲኦል የመውረዱ ምሳሌ ነው።
• ዮናስ ወደ ባህሩ ሲጣል ማዕበሉ ጸጥ ማለቱ ጌታም በሞቱ ሞገደ ፍዳን ማዕበለ መርገምን ጸጥ ማድረጉ

• ዮናስ በዓሣ ሆድ ፫ ቀንና ሌሊት እንደቆየ ሕያውም ሆኖ እንደወጣ ፤ ጌታም በምድር ሆድ በመቃብር ፫ [ 3 ] ቀንና ሌሊት ቆይቶ ሞትን በማሸነፍ ሕያው መሆኑ ፤ [፩ቆሮ.፲፭፥፶፭]
• ዮናስ ማለት ርግብ ማለት ነው ፤ የጌታንም ጸዓዳ ርግብ ይለዋልና

---------------------------------------------

ሕዝበ ነነዌና ምእመናነ ሐዲስ ፦

• እነሱ በዮናስ ስብከት ንስሐ ገቡ ፤ እኛስ በጌታ ስብከት በወንጌል አምነን ንስሐ ገብተን ይሆንን ?

• ነነዌን ያስተማረ ፍጡር ዮናስ ነው ፤ እኛን ግን ያስተማረ የዮናስ ፈጣሪ ነው

• እነሱ በዮናስ ስብከት አምነው ንስሐ ገብተው እኛ ግን በጌታ ቃል አምነን መምህራንን ሰምተን ፤ በዓለማችን ላይ ያሉትን ጌታ የሚያደርጋቸውን ተአምራት ተመልክተን ንስሐ ካልገባን የነነዌ ሕዝብ መፈራረጃ ሆነው እንደሚመሰክሩብን የሚያጠይቅ ምሥጢር ነው።

ጾሙን ለበረከት ፤ ለሥርዬተ ኃጢአት ያድርግልን !

አሜን !!!

[ መጋቤ ሐዲስ ነቅዐጥበብ ከፍ ያለው ]


†                       †                        †
💖                    🕊                     💖

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

                         †                         


" አቤቱ ፥ የሆነብንን አስብ " [ ሰቆ.ኤር.፭፥፩ ]


         †              †               †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

🕊

✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞

[ የካቲት ፲፰ [ 18 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

🕊 †  ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ †  🕊

ቅዱስ ያዕቆብ ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ያደገ : የአረጋዊው ቅ/ዮሴፍ የመጨረሻ ልጅ : በንጽሕናውና ድንግልናው የተመሠከረለት : ከጸሎትና ገድል ብዛት እግሩ ያበጠ : የመጀመሪያው የኢየሩሳሌም ኤዺስ ቆዾስ ሲሆን ቁጥሩም ከ፸፪ [72] ቱ አርድዕት ነው:: ይሕስ እንደ ምን ነው ቢሉ :-

ይህ ቅዱስ ሐዋርያ በአባቶቻችን ሐዋርያት መካከል ትልቅ ሞገስ የነበረውና የጌታችን ወንድም ተብሎ የተጠራ ነው:: ቅዱስ ያዕቆብ ወላጅ አባቱ አረጋዊው ቅዱስ ዮሴፍ [የእመቤታችን ጠባቂ] ሲሆን በልጅነቱ ጥላው የሞተችው እናቱ ደግሞ ማርያም ትባላለች:: በቤት ውስጥም ስምዖን: ዮሳና ይሁዳ የተባሉ ወንድሞችና ሰሎሜ የምትባል እህትም ነበረችው::

እናቱ ማርያም ከሞተች በሁዋላ ዕጉዋለ ማውታ [ደሃ አደግ] ሆኖ ነበር:: ነገር ግን በፈቃደ እግዚአብሔር አረጋዊ ዮሴፍ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ከቤተ መቅደስ ሊጠብቃት [ሊያገለግላት)] ተቀብሎ ሲመጣ ያ ቤተሰብ ተቀየረ:: የበረከት: የምሕረትና የሰላም እመቤት የአምላክ እናቱ ገብታለችና ያ የሐዘን ቤት ደስታ ሞላው::

እመ ብርሃን ግን ገና ወደ ዮሴፍ ልጆች ስትደርስ አለቀሰች:: የአክስቷ ልጆች የሚንከባከባቸው አጥተው ቆሽሸው ነበር:: በተለይ ደግሞ ትንሹ ቅዱስ ያዕቆብ ያሳዝን ነበር:: እመ ብርሃን ማረፍ አልፈለገችም:: ወዲያው ማድጋ አንስታ ወደ ምንጭ ወርዳ ውሃ አምጥታ የሕጻኑን ገላ አጠበችው:: [በአምላክ እናት የታጠበ ሰውነት ምስጋና በጸጋ ይገባዋል!]

እመቤታችን ጌታ ከመወለዱ በፊት ለ፱ [9] ወራት: ከተወለደ በሁዋላ ደግሞ ለ፪ [2] ዓመታት ሕጻኑን ያዕቆብን ተንከባከበችው::

ለ፫ [3] ዓመታት ከ፮ [6] ወራት ግን ድንግል ማርያም አምላክ ልጇን ይዛ ተሰዳለችና ተለያዩ:: ከስደት መልስ ግን ለ፳፭ [25] ዓመታት ቅዱስ ያዕቆብ ከጌታችን ጋር ሲያድግ ወላጅ እናቱ ትዝ ብላው አታውቅም:: አማናዊቷ እናት ከጐኑ ነበረችና::

ሊቃውንት እንደ ነገሩን እመቤታችን ለቅዱስ ያዕቆብ ያልሰጠችው ነገር ቢኖር ሐሊበ ድንግልናዌ [የድንግልና ወተትን] ብቻ ነው::

ስለዚህም :-

"እመ ያዕቆብ በጸጋ ማርያም ንግሥተ ኩሉ" ይላል መጽሐፍ:: [መልክዐ ስዕል]

ቅዱስ ያዕቆብ "የጌታ ወንድም" ተብሎ በተደጋጋሚ በሐዲስ ኪዳን ተጠርቷል:: ለዚህ ምክንያቱ :-

፩. ለ፴ [30] ዓመታት ሳይነጣጠሉ አብረው በማደጋቸው፡፡
፪. የጌታችን የሥጋ አያቱ [የቅድስት ሐና] የእህት ልጅ በመሆኑ፡፡
፫. በዮሴፍ በኩልም የአንድ ቅድመ አያት ልጆች
በመሆናቸው፡፡
፬. ጌታችን ከትህትናው የተነሳ ደቀ መዛሙርቱን "ወንድሞች" ይላቸው ስለ ነበር ነው:: [ሥጋቸውን ተዋሕዶ ተገኝቷልና]

ራሱ ቅዱስ ያዕቆብ ግን "የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ ነኝ" ብሎ በፈጣሪና በፍጡር መካከል ያለውን ልዩነት ገልጧል:: [ያዕ.፩፥፩] (1:1) ቅዱስ ያዕቆብ ጌታችን ሲያስተምር ተከተለው::

¤ ከ፸፪ [72] ቱ አርድእት ተቆጠረ
¤ ፫ [3] ዓመት ከ፫ [3] ወር ወንጌልን ተማረ
¤ ለመጀመሪያ ጊዜ ከድንግል ማርያምና ከቅዱስ ዮሐንስ ጋር ሆኖ "የጌታን ትንሳኤ ሳላይ እሕል አልቀምስም" ብሎ ማክፈልን አስተማረ
¤ መንፈስ ቅዱስን ተሞልቶ ወንጌልን አስተማረ
¤ የኢየሩሳሌም የመጀመሪያው ሊቀ ዻዻስ ሆኖ አገለገለ
¤ በመጀመሪያዎቹ የክርስትና ዘመናት የሐዋርያት
ሲኖዶሶችን በሊቀ መንበርነት መራ
¤ ሙታንን አስንስቶ: ድውያንን ፈውሶ: የመካኖችን ማሕጸን ከፍቶ: አጋንንትንም አስወጥቶ ብዙ ተእምራትን ሠራ:: እጅግ ብዙ አይሁዳውያንን ወደ አሚነ ክርስቶስ መልሶ መልካሙን ገድል ተጋደለ::

በመጨረሻ ዘመኑ ያላመኑ የአይሁድ አለቆች ወደ ቤቱ ተሰብስበው "የናዝሬቱ ኢየሱስ ማነው የማንስ ልጅ ነው?" ሲሉ ጠየቁት:: እነርሱ ሰይጣን በሰለጠነበት ልቡናቸው "የዮሴፍ ልጅ ነው: የእኔም ወንድሜ ነው" እንዲላቸው ጠብቀው ነበር:: [ሎቱ ስብሐት ወአኮቴት!]

በልቡናቸው ያሰቡትን ተንኮል የተረዳው ሐዋርያ ወደ ቤቱ ጣራ ወጥቶ መናገር ጀመረ:: "ለስም አጠራሩ ጌትነት ይሁንና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ ወልደ አምላክ: ወልደ አብ ወልደ ማርያም: ሥግው ቃል: እግዚአብሔር ነው:: እኔም ፍጡሩና ባሪያው እንጂ እንደምታስቡት ወንድሙ አይደለሁም" አላቸው::

ንዴታቸውን መቆጣጠር ያልቻሉት አይሁድ ከላይ ወጥተው ወደ መሬት ወረወሩት:: በገድል የተቀጠቀጠ አካሉንም እየተፈራረቁ ደበደቡት:: አንዱ ግን ከእንጨት የተሠራ ትልቅ ገንዳ አምጥቶ የቅዱሱን ራስ ደጋግሞ መታው:: ጭንቅላቱም እንዳልነበር ሆነ:: ሰማዕቱ ሐዋርያ ቅዱስ ያዕቆብ ወደ ወደደው ክርስቶስ በዚህች ቀን ሔደ::

ቅዱሱ ሐዋርያ ያዕቆብ ቤቱን እንደ ቤተ መቅደስ አበው ሐዋርያት ይጠቀሙባት ነበር:: በመላ ዘመኑ የሚያገድፍ ነገር [ጥሉላት] ቀምሶ: ጸጉሩን ተላጭቶ: ገላውን ታጥቦና ልብሱን ቀይሮ አያውቅም::

"ወዝንቱ ጻድቅ እኅወ እግዚእነ::
ኢያብአ ውስተ አፉሁ ሥጋ ወወይነ::
ወኢገብረ ሎቱ ክልኤተ ክዳነ::" እንዲል::

ከጾም: ከጸሎትና ከመቆሙ ብዛትም እግሩ አብጦ አላራምድህ ብሎት ነበር:: ስለዚህም አበው "ጻድቁ [ገዳማዊው] ሐዋርያ" ይሉታል:: ቅዱሱ ሐዋርያ "የያዕቆብ መልዕክት" የሚለውን ባለ፭ [5] ምዕራፍ መልዕክት ጽፏል::

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወንድሙ ይባል ዘንድ ካደለው ሐዋርያ በረከትን ያድለን:: በምልጃውም ምሕረትን ይላክልን::

🕊

[ † የካቲት ፲፰ [ 18 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ [የቅዱስ ዮሴፍ ልጅ : ከ፸፪ [72] ቱ አርድእት አንዱ]
፪. ቅዱስ አባ መላልዮስ ጻድቅ ሊቀ ዻዻሳት [በአንጾኪያ ሊቀ ዽዽስና ተሹሞ በአርዮሳውያን ብዙ ግፍ የደረሰበትና በስደት ያረፈ አባት ነው]

[ † ወርሐዊ በዓላት ]

፩. ቅዱስ ፊልዾስ ሐዋርያ
፪. አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ሰባኬ ሃይማኖት
፫. አቡነ አኖሬዎስ ዘደብረ ጽጋጋ
፬. ማር ያዕቆብ ግብፃዊ

" የእግዚአብሔርና የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ ያዕቆብ: ለተበተኑ ለአሥራ ሁለቱ ወገኖች:: ሰላም ለእናንተ ይሁን:: ወንድሞቼ ሆይ! የእምነታችሁ መፈተን ትዕግስትን እንዲያደርግላችሁ አውቃችሁ ልዩ ልዩ ፈተና ሲደርስባችሁ እንደ ሙሉ ደስታ ቁጠሩት:: ትዕግስትም ምንም የሚጐድላችሁ ሳይኖር ፍጹማንና ምሉዓን ትሆኑ ዘንድ ሥራውን ይፈጽም::" [ያዕ.፩፥፩]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

አደራ አለብኝ!

የ 2016 ዓ.ም 2ኛ ዙር ጉባኤ

ዓለም ዓቀፍ የግቢ ጉባኤ ምሩቃን ኅብረት ጉባኤ

• ቀን፡ መጋቢት 08/2016 ዓ.ም
• ሰዓት፡ ከ 7፡00 ጀምሮ
• ቦታ፡ በጠቅላይ ቤተ ክህነት አዳራሽ

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

በእርግጥም ዮናስ በሽተኛ አክሞ ስለዳነለት የሚበሳጭ ሐኪም ሆነ፡፡ የነነዌ ሰዎች ግን የሰባኪው ማንነት ፣ የስብከቱ ውበት አልባነት ፣ የአነጋገሩ ለዛ ምክንያት ሳይሆናቸው ተስፋ በማይሰጥ ስብከት ተሰብረው ራሳቸውን አዳኑ፡፡ ብዙ ስብከት አልፈለጉም ፤ ክፋትን ለመተው እና ይቅር በለን ለማለት የተሰበረ ልብ እንጂ በእውቀት መሞላት አያስፈልግም፡፡ ኃጢአታችን ከነነዌ ሰዎች ከበለጠ ቆየ ፤ የጋራ ክፋታችንን በጋራ ንስሓ እንጠበው፡፡

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
/channel/MikreAbew

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

                         †                         

[ ጨረቃ ደም የለበሰችበት ምሽት ! ]

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

- በቀን ፲፮/፮/፳፻፲፮ ዓ.ም [ 16.6.2016 ዓ.ም ]

- ንጹሐን መነኮሳት በግፍ ሰማዕትነት ተቀብለው ቅድስት ቤተክርስቲያን በጽኑ ሐዘን ውስጥ በወደቀችበት ዕለት

- ከምሽቱ ፪ ሰዓት [ 02:00 ] ላይ ከከባድ ዓውሎ ነፋስ በኋላ በሰማይ የታየው ምልክት !

†                       †                       †

" ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ የፈሰሰው የነቢያት ሁሉ ደም ፥

ከአቤል ደም ጀምሮ በመሠዊያውና በቤተ መቅደስ መካከል እስከ ጠፋው እስከ [ ካህኑ ] ዘካርያስ ደም ድረስ ፥ ከዚህ ትውልድ እንዲፈለግ አዎን እላችኋለሁ ፥ ከዚህ ትውልድ ይፈለጋል።" [ ሉቃ.፲፩፥፶ ]

         †              †               †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

እሑድ - የካቲት 17 2016 ዓ.ም

ዘዳግም 11-16

ሰላም ለሁላችሁ ይሁን! በዛሬው እለት ንባባችን ከምዕራፍ 11 እስከ 16 ድረስ እናነባለን።

ከንባብ በፊት የሚደረግ ጸሎት፡ “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፤ የአንተን ቃላት እሰማ እና እረዳ ዘንድ፥ እንዲያውም ፈቃድህን ለመፈጸም እበቃ ዘንድ የልቤን ጆሮዎች እና ዓይኖች ክፈትልኝ።” (ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ)

በዛሬው ንባባችን ላይ እግዚአብሔርን መታዘዝ የሚያስገኘው ጥቅም፥ አምልኮት በየት ሊፈጸም እንደሚገባ፥ ለጣዖት ከመስገድ መከልከል እንደሚገባ እና ስለተከለከለ የልቅሶ ልማድ እናነባለን። ከዚህ በተጨማሪ፥ ስለሚበሉና የማይበሉ እንስሶች፥ ስለዐሥራት አወጣጥ ሕግ፥ ዕዳ ስለሚሠረዝበት ዓመት፥ ባሮች ነጻ ስለሚወጡባት ዓመት፥ ስለ ፋሲካ፥ መከር እና የዳስ በዓል እንዲሁም ስለ ፍርድ አሰጣጥ እና አምልኮ ጣዖትን ስለመከላከል ተጽፎ እናገኛለን።

*የክለሳ ጥያቄዎች*

1) በዘዳግም 11 መሠረት፥ እስራኤላውያን ወደ መልካሚቱ ምድር በገቡ ጊዜ በረከቱን እና መርገሙን በየት እንዲያኖሩ ተነገራቸው?

2) በዘዳግም 12 መሠረት፥ እስራኤል እንስሳትን ሲበሉ፥ ደሙን ምን እንዲያደርጉ ተነገራቸው?

3) በዘዳግም 12 ላይ አሕዛብ አማልክቶቻቸውን ያመለኩበት መንገድ በምን መልኩ ተገልጿል?

4) እስራኤላውያን ነቢይ ወይም ሕልም አላሚ ቢነሳ ምን እንዲያደርጉ ተነገራቸው?

5) በዘዳግም 14 መሠረት፥ እርያ የማይበላበት ምክንያት ምን ተብሎ ተጠቅሷል?

6) በየሰባት ዓመት መጨረሻ የዕዳ ምሕረት ሲደረግ ሰዎች ምን እንዲያደርጉ ታዝዘዋል?

7) የዳስ በዓል በሚከበርበት ጊዜ ምን እንዲደረግ ታዝዟል?

መልካም ንባብ!

/channel/OrthodoxTewahdoBooks

/channel/c/2014228571/1

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

🔔

ሐሳዊ አጥማቅያን እና የአጋንንት ምስክርነት !

[  ክፍል ስምንት  ]


" ጸሎት ቤት ሥሩ ¡ "  - ፩ -

▬▬

" ጸሎት ቤት ሥሩ " የነጣቂዎች ማጠንጠኛ ማዕከል ለምን ሆነ ?

ብርሃነ ዓለም ማኅቶተ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ጳውሎስ ፦

" የዲያብሎስን ሽንገላ ትቃወሙ ዘንድ እንዲቻላችሁ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ ልበሱ።" [ኤፌ.፮፥፲፩] ይለናል።

ዲያብሎስ ሸንጋይ ነው። ብርቱም ተዋጊ ነው። የእግዚአብሔርን ሕዝብ ለማሳት የብርሃን መልአክ እንዲመስል ራሱን ይለውጣል። አገልጋዮቹም እንዲሁ የጽድቅን አገልጋዮች እንዲመስሉ ራሳቸውን ይለውጣሉ።

መልካምና በጎ የሚመስሉ ከሰይጣን የሚመጡና በረቀቁ ተንኮሎች የተመሉ ሃሳቦች ሰውን በብርቱ ያሰናክላሉ።

በረከታቸው ይደርብንና ብፁዕ አቡነ ሺኖዳ የዲያብሎስ ውጊያዎች በተሰኘው መጽሐፋቸው ስለዚህ የሰይጣን ክፋት ሲገልጹ ፦

"የዲያብሎስ ጥበብ ግን ማጭበርበር ፣ ጮሌነትና ሰውን መጉዳት የተሞላበት ነው። አደገኛ ከሚባሉ ዘዴዎቹም ፦ መዋሸት ፣ ማታለልና ማጭበርበር ስለሚገኙበት የሚዋጋው ሰው አመጣጡን ለማወቅ ግራ ይጋባል።" በማለት ገልጸውታል።

በዘመናችን የተነሱ ሐሰተኛ አጥማቂዎች በዋናነት ተለይተው ከሚታወቁባቸው አስተምህሮዎች ዋነኛው "ጸሎት ቤት ሥሩ" የሚለው ነው።  የግለሰቦቹን የተንኮል ዓላማና እውነተኛ ማንነታቸውን ላልተረዳ ሰው ጉዳዩ እጅግ ግራ ሊያጋባው ይችላል። ጸሎት ለክርስቲያኖች እስትንፋስ ነውና ጸሎት ቤት መሠራቱ ምን ክፋት አለው ? ይህ ይጠቅማል እንጂ ማንን ይጎዳል? የሚሉ ጥያቄዎች የዋሃን ከሆኑ ምዕመናን ሊነሱ ይችላሉ። ጸሎት ቤት መኖሩ ክፉ ሆኖ አልነበረም። ሰይጣኑ ያለው ዝርዝሩ ላይ ሆኖ ነው እንጂ !

የአምልኮተ እግዚአብሔር ጠበቆች ፣ ጸሎተኞችና የስግደት አስተማሪዎች መስለው የተገለጡት እነዚህ ሐሳዊያን ይህንን አስተምህሮ በዋናነት የሚያቀነቅኑት ስለምንድን ነው?

ሐሰተኛ አጥማቂዎች ይህንን አስተምህሮ የሚያስፋፉበት ዋነኛው ዓላማቸው ሰው በማያስበውና በማይገምተው መንገድ ከቅድስት ቤተክርስቲያን እየራቀ እንዲሄድና በመጨረሻም ፍጹም እንዲለይ ለማድረግ ነው። የዋሁን ምዕመን በዚህ የረቀቀ የጥፋት ወጥመድ ጠላልፈው ከቅድስት ቤተክርስቲያን እቅፍ ለይተው በየቤቱ በየስርቻው ያስቀሩታል። መንፈሳዊ የሆነ እንዲመስለው አድርገው የግል ተከታያቸው ያደርጉታል።

ሰው ከቤተክርስቲያን ከተለየ ከዘለዓለማዊው ሕይወት እንደሚለይ ሰይጣን ጠንቅቆ ያውቃል። የክርስቶስ አካሉ ፤ የእግዚአብሔር ኃይል የሚገለጥባት ፤ አጋንንት የሚሸነፉባት ፤ የጸጋ ሁሉ መገኛ ፤ የቅዱሳን ቃል ኪዳን መገለጫ ቅድስት ቤተክርስቲያን ናት። ሰይጣንና ሰራዊቱ ቅድስት ቤተክርስቲያንን በእጅጉ ይፈሯታል። ይጠሏታል። በቻሉት ሁሉ ይዋጓታል። እናታችን ቅድስት ቤተክርስቲያን ከእግዚአብሔር ጋር የምንገናኝባት የሰማይ ደጅ ናት። እርሷ የእግዚአብሔር የክብሩ ዙፋን መሆኗን ሊቁ ቅዱስ ያሬድ ሲመሰክር ፦

"በዕፀ መስቀሉ የተባረከች ፤ በደሙ የተቀደሰች ፤ በስሙ የታነጸች ፤ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የእግዚአብሔር የምስጋናው የክብሩ ዙፋን ናት ፤ የሰው እጅ ያልሠራት ያማረች የተወደደች ፍጽምት ድንኳን ናት።" ይላል።

ቅድስት ቤተክርስቲያን ምእመናንን መክራ አስተምራ ከኃጢአት ባርነት ፣ ከጣዖት አምልኮ ነጻ የምታወጣ ፤ በክርስቶስ ደም የተመሠረተች ፤ በኃይለ መለኮቱ የጸናች ፤ በሐዋርያት አጥንት ተምሳ በሰማዕታት ደም ተለስና ፤ በሊቃውንት ትሩፋት ተደምድማ ያለቀች የተጠናቀቀች ውብ ሰማያዊት የክርስቶስ ሙሽራ ናት። ቤተክርስቲያን ከአፍአዊም ሆነ ከውስጣዊ እድፍ ንጽሕይት ናት ፤ በውስጧም የሚፈጸመው ሥርዓት ምድራዊ ያይደለ ሰማያዊ ፣ ሥጋዊ ያይደለ መንፈሳዊ ፣ ጊዜያዊ ያይደለ ዘለዓለማዊ ሥርዓት ነውና የረከሱትን የምታነጻ ፍጥረት የእግዚአብሔርን መንግስት የሚወርስባት ንጽሕይት የክርስቶስ ሙሽራ ናት። ክፋትን የሚሠሩ ሰዎች መዋቅሯ ውስጥ ተመሳስለው ሊገቡ ቢችሉም ሕብረቷ ውስጥ ግን ሊገቡ አይቻላቸውም። ከሕብረቷ መቀላቀል ያለ ንጽሕና አይሆንምና። እርሷ ክርስቶስ ራስ የሆነላት በሰማይና በምድር የሞላች መንፈሳዊት አካል ናትና።

ስለዚህ የእኛ የክርስቲያኖች ሕይወት ከቤተክርስቲያን የተለየ ሊሆን አይችልም። ዓሳ ከውኃ ከወጣ ሕይወት እንደማይኖረው እንዲሁ ምዕመናንም ከቤተክርቲያን ተለይተው በሕይወት መኖር አይቻላቸውም። ከአካል ተለይቶ ሕያው መሆን የሚቻለው ህዋስ ከቶ የለምና።

ስለዚህም ኦርቶዶክሳዊ ምዕመን ጠዋትና ማታ የጸጋው ዙፋን ከሆነች ፤ እግዚአብሔር በምህረትና በጸጋ አድሮ ከሚኖርባት ፤ ቅዱስ ሥጋውና ክቡር ደሙ ከሚፈተትባት ፤ እመቤታችንና ቅዱሳኑ ከማይለዩባት ፤ ያለማቋረጥ በማኅሌቱ በሰዓታቱ በኪዳኑና በቅዳሴው የምስጋና መስዋዕት ከሚቀርብባት ፤ የኃጢዓት ሥርየት ምህረትና ይቅርታ ከሚደረግባት ፤ ከተወደደችው የእግዚአብሔር ማደሪያ ቤተመቅደስ እየተገኘ እግዚአብሔርን ደጅ ሊጠና ፤ በምክረ ካህን እየተመላለሰ ከምስጢራትም እየተካፈለ ፤ በረድኤተ እግዚአብሔር ተጠብቆ መቅደስ ሰውነቱንም በንጽሕና ሊያከብር ይገባዋል።

ሰው ከቤተ እግዚአብሔር እንዲርቅና በቤቱ እንዲቀር ሐሰተኛ አጥማቂያን የፈለጉበት ምክንያት ምንድን ነው ?

- ምዕመኑን የጸጋው ዙፋን ከሆነችው ከቅድስት ቤተክርስቲያን
- ከቅዱሳኑ ቃል ኪዳን
- ከምክረ ካህን
- ከምስጢራተ ቤተክርስቲያን
- ከመስቀሉ ከእምነቱ ከጸበሉ በአጠቃላይ ከቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ሕይወት ቀስ በቀስ በማራቅ ለመለየትና አሁን እንደሚታየው ተከታያቸው አድርገው በውጪ ሊያስቀሩት የሰይጣንና የአገልጋዮቹ ቁልፉ ዓላማቸው ነው።

- ህብረታዊትና ሥርዓታዊት ከሆነችው አንዲቷ የክርስቶስ አካል ከቅድስት ቤተክርስቲያን ሕዝቡን በመለየት ግላዊ አምልኮግላዊ ሕይወትግላዊ አስተሳሰብ በማንገስ ፕሮቴስታንታዊ መስመርን የተከተለ እረኛ የሌለውከእናቱ ከቤተክርስቲያን ዕቅፍ የራቀ ከመዓዛዋ የተለየድምጿን የማያውቅለእርሷም የማይታዘዝየግለሰቦች ተከታይ የሆነበቀላሉ ለክህደትና ለኑፋቄ የተሰጠ ሕዝብን መፍጠር የሐሳዊው መሲህ መንገድ ጠራጊ የሆኑ የሐሰተኛ አጥማቂያን መሠረታዊ ዓላማቸው ነው

ሕዝቡን ከቅድስት ቤተክርስቲያን ለመነጠል በሠሩት የጥፋት ሥራ የተነሳ በአሁኑ ወቅት ተከታዮቻቸው የከበሩ አማናዊ የቤተክርስቲያን ምስጢራትን ሲያቃልሉና መጫወቻ ሲያደርጉ ፣ "የጸሎት ቤት" በሚሉት ስፍራ ቅዱሳት ስዕላትን ዕጣን በማጠን ኑፋቄያዊ ልምምዶችን ሲፈጽሙ ፤ "ቅብዓ ቅዱስ" እያሉ የአረቦችን የአትክልት ዘይት ሲቀቡ ፤ በመቁጠሪያ እራሳቸውን እየደበደቡ "በውስጤ ያለህ ሰይጣን ተሰብስበህ ና ግንባሬ ላይ ታሰር" እያሉ የሰይጣን መዘበቻና መሳለቂያ ሲሆኑ ይታያል።

ከቅዱሳት መጻሕፍት ይልቅ "በማለዳ መያዝን" የመሰሉ መናፍስታዊ መጽሐፍትን ሲያነቡ የሚውሉ ምርኮኛ አድርገዋቸዋል። ይህ ሁሉ ውድቀት የመጣው ምዕመኑን ከእረኞቹ ከካህናት አባቶች በመለየት ወደ ከፋ የክህደት አዘቅት ለመውሰድ በሐሰተኛ አጥማቂያን በተዘራው ሰይጣናዊ ትምህርት የተነሳ ነው።

ምዕመኑን እንዲህ ከቤተክርስቲያን እቅፍ ካራቁት ፤ ምስጢራተ ቤተክርስቲያንን እንዲክድ ካደረጉት ፤ ከእውነተኞቹ አበው ካህናት ካለያዩት በኋላ ለቤተክርስቲያን ብቻ ሊሰጥ የሚገባውን አሥራት በኩራትና መባን በመሰብሰብና በመቆጣጠር ሚሊየነር ከበርቴ መሆን ችለዋል።



"ለምድርና ለባሕር ወዮላቸው፥ ዲያብሎስ ጥቂት ዘመን እንዳለው አውቆ በታላቅ ቍጣ ወደ እናንተ ወርዶአልና።" [ራእ.፲፪፥፲፪]

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

ሀሳቡ ጥሩ ሆኖ ሳለ
ሀሰተኛና...እውነተኛም እንዳለ እንወቅ

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

..........................................

በአሰቦት ደብረወገግ ቅድስት ሥላሴ ወአቡነ ሳሙኤል አንድነት ገዳም አካባቢ የተነሳውን የእሳት አደጋ መቆጣጠር መቻሉ እና ገዳሙ በአሁኑ ሰዓት ከሰደድ እሳት ስጋት መውጣቱን የገዳሙ ኃላፊዎች ገልጸዋል።

በገዳሙ በከፍተኛ ደረጃ የሰደድ እሳት እንደነበር ይታወሳል። ሰደድ እሳቱን ለመቆጣጠር የአካባቢው ማህበረሰብ ወደገዳሙ እንዳይዛመት ባደረጉት ጥረት ሰደድ እሳቱን መቆጣጠር መቻሉ ታውቋል።

ተጨማሪ ዝርዝር መረጃዎች የሚቀርቡ ይሆናል !

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

ቀድመው የቀረቡ መርሐ-ግብሮችንና የቪዲዮ ማስረጃዎችን ከላይ ከክፍል አንድ ጀምሮ ይከታተሉ !

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

ሐሰተኛ የሆኑት በምን መስፈርት ነው...ሐዋርያት የፈውስ አገልግሎት አልሰጡም ነበር

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

🕊

✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞

[ ✞ እንኩዋን ለጻድቁ "አቡነ ክፍለ ማርያም" እና ለሰማዕቱ ቅዱስ "ፊልሞን መዓንዝር" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞ ]

🕊 ✞ አቡነ ክፍለ-ማርያም ✞  🕊

ኢትዮዽያዊው ጻድቅ አቡነ ክፍለ-ማርያም በሐዋርያዊ አገልግሎቱ የተመሠከረለት: ለበርካታ ዓመታት በጾምና በጸሎት በአቱን አጽንቶ የኖረ: ከቅድስናው የተነሳ መላዕክት ሰማያዊ ኅብስት ይመግቡት: ውሃም ከአለት ላይ ይፈልቅለት የነበረ አባት ነው::

በዘመኑም ረሃብ ነበርና እርሷ ሳታውቀው እናቱን በረሃብ ጠውልጋ ቢያያት በጣም በማዘኑ እንዲባርከው ከቀረበለት የሰንበት ቁርስ ለእናቱ አድልቶ ብዙ ሰጣት:: በዚሕ ምክንያት መልዐኩም ሰማያዊ ኅብስቱን አስቀረበት: ምንጩም ደረቀች::

ጥፋቱ የገባው አባ ክፍለ-ማርያም ለ፲፩ [11] ዓመታት ንስሃ ገብቶ እግዚአብሔር መልሶለታል:: ከብዙ የገድል ዓመታት በሁዋላም በዚህች ቀን ተሠውሯል::


🕊 ✞ ቅዱስ ፊልሞን ሰማዕት ✞  🕊

ይህን ቅዱስ "ፊልሞን መዓንዝር" ብሎ መጥራቱ የተለመደ ነው:: እርሱ በቀደመ ሕይወቱ አዝማሪ [ዘፋኝ] ነበርና:: ዘፋኝነት [አዝማሪነት] ደግሞ በክርስትና ከተከለከሉ ተግባራት አንዱና ዋነኛው በመሆኑ ዘፈን [ሙዚቃ] መስማትም ሆነ ማድመጡ ኃጢአት ነው::

ነገር ግን ሁሉ እንዲድን የሚፈቅድ ጌታችን ጥሪውን ወደ ሁሉም ሰው በየጊዜው ይልካል:: ቅዱስ ፊልሞንም የክርስቶስ ጥሪ የደረሰው በከንቱ የዘፋኝነት [የአዝማሪነት] ኑሮ ውስጥ ሳለ ነው:: ነገሩ እንዲህ ነው :-

በ፫ [3] ኛው ክ/ዘ መጨረሻ [በ፪፻፺ [290] ዎቹ] አርያኖስ የሚባል ሹም በግብጽ [እንዴናው] ክርስቲያኖችን ጨፈጨፈ:: ባለማወቅም ክርስቶስን የሚያመልኩ ሚሊየኖችን በሰይፍ በላቸው:: ከዚህ ድርጊቱ መልስ ደግሞ በጣዖቱ [አዽሎን] ፊት እያስዘፈነ ከንቱነትን ይሰዋ : ይዝናናም ነበር::

ከዘፋኞቹ መካከል ደግሞ ይህ ፊልሞን አንዱ ሆኖ ለዘመናት በፊቱ ተጫወተለት:: አንድ ቀን ግን እንዲህ ሆነ:: አስቃሎን የሚባል ቅዱስ ክርስቲያን ለጣዖት እንዲሰዋ ታዘዘ::

ይህ አስቃሎን [አብላንዮስም ይባላል] ወንድሙን ፊልሞንን ያድነው ዘንድ ተጠበበ:: ወደ ፊልሞን ሒዶ "እኔ ገንዘብ እሰጥሃለሁ:: የእኔን ልብስ ለብሰህ : እኔን መስለህ ለጣዖት ሰዋልኝ" አለው:: አስቃሎን ይህንን ያለው ለጥበቡ ሲሆን ፊልሞን ግን "ገንዘብ ካገኘሁ" ብሎ የባልንጀራውን ልብስ ተሸፋፍኖ ወደ ጣዖቱ ፊት ቀረበ::

ያን ጊዜ ተሸፍኖ መስዋዕት ማቅረብ ክልክል ነውና ሹሙ አርያኖስ ግለጡት ሲል አዘዘ:: ቢገልጡት ፊልሞን ሁኖ ተገኘ:: መኮንኑ ገርሞት "ምን እያደረክ ነው?" ቢለው "እኔ ክርስቲያን ነኝ" ሲል አሰምቶ ተናገረ::

ለጊዜው ሁሉም እየቀለደ መስሏቸው ነበር:: ፊልሞን ግን ይህንን ያለው ከልቡ ነው:: ምክንያት በቅዱስ አስቃሎን ልብስ ተመስሎ መንፈስ ቅዱስ ልቡን ለውጦለት ነበር:: ተገልጦ ቀና ሲልም ቅዱሳን መላእክት ከበውት አይቶ ልቡ ጸንቶለታል::

ሹሙ አርያኖስም የቀልዱን እንዳልሆነ ሲያውቅ "ታብዳለህ?" ቢለው ፊልሞን "ምን አብዳለሁ! ዛሬ ገና ከእብደቴ ሁሉ ዳንሁ እንጂ" ሲል መልሶለታል:: አሕዛብ ሁሉ እያዩም በዚያች ቅጽበት መንፈስ ቅዱስ በደመና አምሳል ወርዶ አጥምቆታል::

በሆነው ሁሉ የተበሳጨው ሹሙም ቅዱስ ፊልሞንን ከክርስቶስ ፍቅር ይለየው ዘንድ ደበደበው : ገረፈው : ጥርሱን አረገፈው : ደሙንም መሬት ላይ አፈሰሰው:: በዚህ ሁሉ ግን ጸና:: ቅዱስ አስቃሎንም ፈጥኖ መጥቶ በመከራው መሰለው::

በመጨረሻም ፪ [2] ቱም ቅዱሳን በቀስት ተነድፈው ይገደሉ ዘንድ ተፈረደባቸው:: ነገር ግን ለእነሱ የተወረወረ ቀስት መንገዱን ስቶ የሹሙን [የአርያኖስን] ዐይን በማጥፋቱ ወታደሮቹ በንዴት ፪ [2] ቱንም ሰይፈው ገድለዋቸዋል::

ዐይኑ የጠፋበት አርያኖስም ስቃዩ ሲበዛበትና ከሚያመልካቸው የረከሱ ጣዖታት መፍትሔ ሲያጣ ከቅዱሳኑ ደም ተቀባ:: ዐይኑም ፈጥኖ በራለት:: በዚህም ምክንያት ምድራዊ ሹመቱን : ሃብት ንብረቱን : ትዳርና ቤቱን : ጣዖት አምልኮውን ትቶ በክርስቶስ አምኖ ለሰማዕትነት በቅቷል::

አምላከ ቅዱሳን በወዳጆቹ አማላጅነት የምናስተውልበትን አዕምሮ አይንሳን:: በረከታቸውንም ያድለን::

🕊

[ † የካቲት ፳ [ 20 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. አቡነ ክፍለ-ማርያም ዘዲባጋ [የተሰወረበት]
፪. አቡነ ገብረ-መርዐዊ ዘአግዶ [ኢትዮዽያዊ]
፫. ቅዱስ ፊልሞን መዐንዝር [ከአዝማሪነት በክርስቶስ አምኖ ለሰማዕትነት የበቃ ቅዱስ ሰው]
፬. ቅዱስ አስቃሎን አናጉንስጢስ [ሰማዕት]
፭. ቅዱስ ዼጥሮስ ሊቀ ዻዻሳት [የታላቁ ሐዋርያዊ አትናቴዎስ ደቀ መዝሙር]

[ † ወርኀዊ በዓላት ]

፩. ቅዱስ ቴዎድሮስ ሊቀ ሠራዊት (ሰማዕት)
፪. ቅዱስ ዮሐንስ ሐፂር
፫. ቅዱስ አክሎግ ቀሲስ
፬. ቅዱስ አፄ ካሌብ ጻድቅ
፭. አባ አሞንዮስ ዘሃገረ ቶና
፮. ቅድስት ሳድዥ የዋሒት

" ስትጦሙም እንደ ግብዞች አትጠውልጉ . . . አንተ ግን ስትጦም በስውር ላለው አባትህ እንጂ እንደ ጦመኛ ለሰዎች እንዳትታይ ራስህን ተቀባ: ፊትህንም ታጠብ:: በስውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ያስረክብሃል:: " [ማቴ.፮፥፲፮]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

🕊


"  ጾም  "


🕊  [ በርእሰ ሊቃውንት የኔታ አባ ገብረ ኪዳን ]

--------------------------------------------

[ ለታላቁ የዓቢይ ጾም ዝግጅት ]

💖   ድንቅ ትምህርት   💖


              †       †       †

"ጾም ሙሽሪትን ትመስላለች ፤ ሙሽሪትን በሠርግ አዳራሽ ኾነው የሚቀበሏት ሰዎች ቤቱን ያስጌጡታል ፤ ይሸልሙታል፡፡ ወደ ሠርጉ አዳራሽ የሚገባውን ሰው የሠርግ ልብስ ለብሶ እንደኾነ ፣ የቆሸሸ እንዳልኾነ አይተው ያስገቡታል፡፡ እኛም እንዲኽ ልንኾን ይገባናል ብዬ እነግራችኋለኹ፡፡

ልቡናችንን በማንጻት ፣ ልል ዘሊል ከመኾን በመራቅ ፣ የክፋት እርሾን በማስወገድ ፣ ከጾም ጋር አብረው የሚመጡትን የሚያጅቧትን መልካም ምግባራትንም ለመቀበል የልቡናችንን ውሳጤ በመክፈት የምግባር እናት ፣ የማስተዋል እንዲኹሁም ለሌሎች ምግባራት ኹሉ ንግሥት የምትኾን ጾምን ልንቀበላት ይገባናል ብዬ እነግራችኋለኹ፡፡ ይኽን ያደረግን እንደኾነ ታላቅ ሐሴት እናደርጋለን ፤ ርሷም ቁስለ ነፍሳችንን ትፈውስልናለች፡፡ "

[ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ]

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
                   👇

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

                         †                         



" የሠራዊት አምላክ አቤቱ ፥ መልሰን ፥ ፊትህንም አብራ ፥ እኛም እንድናለን። " [ መዝ.፹፥፯ ]



         †              †               †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

ሰኞ - የካቲት 18 2016 ዓ.ም

ዘዳግም 17-22

ሰላም ለሁላችሁ ይሁን! በዛሬው እለት ንባባችን ከምዕራፍ 17 እስከ 22 ድረስ እናነባለን።

ከንባብ በፊት የሚደረግ ጸሎት፡ “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፤ የአንተን ቃላት እሰማ እና እረዳ ዘንድ፥ እንዲያውም ፈቃድህን ለመፈጸም እበቃ ዘንድ የልቤን ጆሮዎች እና ዓይኖች ክፈትልኝ።” (ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ)

በዛሬው ንባባችን ላይ በካህናት ስለሚሰጥ ፍርድ፥ ንጉሥ ስለመሾም፥ ስለ ካህናትና ሌዋውያን ድርሻ፥ እንደ ሙሴ ያለ ነቢይ እግዚአብሔር እንደሚያስነሳ የሰጠው ቃል፥ ስለ መማጸኛ ከተሞች፥ ስለ ምስክሮች እና ስለ ጦርነት መመሪያዎች እናነባለን። በተጨማሪም፥ ባልታወቀ ሰው ስለሚፈጸም ግድያ፥ በጦርነት ስለተማረኩ ሴቶች፥ ስለ በኩር ልጆች መብት፥ ስለማይታዘዙ ልጆች እና ድንግልናን ስለ መጠበቅም ተጽፎ ይገኛል።  

*የክለሳ ጥያቄዎች*

1) በዘዳግም 17 መሠረት፥ በጣዖት አምልኮ የተጠረጠረን ሰው ስለማጣራት ምን ተጽፏል?

2) በሕዝብ ላይ የሚሾም ንጉሥ ወይም አለቃን በተመለከተ የተሰጠው ሕግ ምንድር ነው?

3) በዘዳግም 18 መሠረት፥ በሬ ወይም በግ ለመሥዋዕት ከሚያቀርቡት ሕዝብ የካህናቱ ድርሻ ምንድር ነው?

4) እግዚአብሔር እንደ ሙሴ ያለ ነቢይ ስለማስነሳት ምን ተናገረ?

5) በዘዳግም 19 መሠረት፥ በመማጸኛ ከተማ ውስጥ መሸሸግ የማይችለው ምን አይነት ነፍሰ ገዳይ ሰው ነው?

6) ምስክርነትን በተመለከተ በስንት እንደሚጸና ተጽፏል?

7) በዘዳግም 20 መሠረት፥ በጦርነት ጊዜ ወደ ቤቱ ተመልሶ እንዲሄድ የተፈቀደለት ሰው በምን ሁኔታ ውስጥ ያለ ነው?

8 ) እስራኤላውያን አንድን ከተማ በያዙ ጊዜ ዛፍ መቁረጥን በተመለከተ ምን ትእዛዝ ተሰጣቸው?

9) በዘዳግም 21 መሠረት፥ ባልታወቀ ሰው ግድያ ቢፈጸም ምን ይደረጋል?

10) በዘዳግም 22 መሠረት፥ የአመንዝራነት ቅጣቱ ምንድር ነው?

መልካም ንባብ!

/channel/OrthodoxTewahdoBooks

/channel/c/2014228571/1

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

                         †                         



" አቤቱ ፥ የሆነብንን አስብ " [ ሰቆ.ኤር.፭፥፩ ]



         †              †               †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

                        †                             

 †  🕊       ይ  ቤ ሎ ሙ       🕊  †


    [    የግእዝ መዝሙር ጥናት    ]

            [ ክፍል  - ፲፫  -  ]

የወንድማችን ድንቅ አገልግሎት ! ከጣእሙ ብዛት አጥንትን የሚያለመልም ዝማሬ መላእክትን ያሰማልን።

†                       †                        †
💖                    🕊                     💖

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

                       †                       

  [  🕊  ድምፀ ተዋሕዶ   🕊  ]  

🍒▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬🍒               

[  ሕይወት የሚገኝባቸው የቅድስት ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ትምህርቶች በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን በድምፅ ይቀርባሉ።  ]

[ ሳምንታዊ መርሐ-ግብር ]

🕊             

[    " ቅ ዱ ሳ ት   መ ጻ ሕ ፍ ት ! "    ]
             
            [     ክፍል ስድስት    ]

" ይህን በመጀመሪያ እወቁ ፤ በመጽሐፍ ያለውን ትንቢት ሁሉ ማንም ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደም ፤

ትንቢት ከቶ በሰው ፈቃድ አልመጣምና ፥ ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ተልከው ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ተናገሩ።" [፪ጴጥ.፩፥፳]


       💖   ድንቅ ትምህርት  💖

[ በመምህራችን በቀሲስ ኅብረት የሺጥላ ]

" የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ፥ ከመከራም ሥጋት ያርፋል።" [ ምሳ.፩፥፴፫ ]

         †              †               †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬
                       👇

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

+++ ጣዕም የሌለው ስብከት ++

ወደ ከተማችን አንድ ሰባኪ ሊሰብክ መጣ ፣ የመጣው ለመስበክ ፈልጎ አልነበረም፡፡ እኛን ለማዳን ጉጉት አድሮበት ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ሊያሰማን ጓጉቶ አልነበረም፡፡ በግድ ተገፍትሮ ፣ ተተፍቶ ፣ ተወርውሮ የመጣ ዓይነት ሰው ነበር፡፡ ወደ መሃል ከተማም አልገባም የከተማችን አንድ ሦስተኛውን ብቻ ከተጓዘ በኋላ ስብከቱን ጀመረ፡፡ የሰበከው ስብከት  ሰላምታ የለውም ፣ መግቢያ የለውም ፣ መውጫም የለውም ፣ ማጽናኛም የለውም ፣ ‹ንስሓ ግቡ› የሚል አዋጅ የለውም፡፡ በጩኸት የተናገረው አንድ አስደንጋጭ ዐረፍተ ነገር ብቻ ነበር ‹‹በሦስት ቀን ውስጥ ነነዌ ትገለበጣለች!!›› ከነነዌ ነዋሪዎች አንዱ የነነዌን ታሪክ ቢጽፈው የሚጽፈው እንዲህ ነበር፡፡

የነነዌ ሰዎች እግዚአብሔርን የማያውቁ አሕዛብ ናቸው፡፡ ዮናስ ደግሞ እነርሱ የማያውቁትን አምላክ የሚያመልክ ነቢይ ነው፡፡ ዮናስ ወደ እነርሱ የመጣው የማዳን ተልዕኮ ይዞ አልነበረም፡፡ ወደ አሕዛብ መላኩ አላስደሰተውም፡፡ ዮናስ ወደ ነነዌ የመጣው እንደ ሌላ ሰባኪ በየትኛውም ትራንስፖርት ተጉዞ ሳይሆን በዓሣ አንበሪ ወደ ነነዌ ተተፍቶ ነው፡፡ የተተፋ ሰባኪ እንዴት ደስ ብሎት ይሰብካል? እንኳን ስብከት ይቅርና ማንኛውም ሥራ ያለ ፍላጎት እንዴት ሊሳካ ይችላል? ዮናስ የነነዌ ሕዝብ እንዲድን ፍላጎትም አልነበረውም፡፡ እንዲያውም ከመጀመሪያውም ፍርሃቱ ‹ትጠፋላችሁ› ብሎ ተናግሮ ሳይጠፉ ቢቀሩስ የሚል ነበር፡፡

ዮናስ ወደ ከተማይቱ  ዘልቆ ሲገባም በፍላጎት አልሰበከም ፤ የሰበከው ስብከት ተስፋ የሚያስቆርጥ ፣ እንደ ሰይፍ የሚቆራርጥ ነበር፡፡ የነነዌ ሰዎች የማያውቁትን አምላክ እንዲያውቁ ዕድል የሚሠጥ ትምህርት አልተሠጣቸውም፡፡ ዮናስም እንደ ኖኅ ‹ይኼንን ያህል ዘመን ተሠጥቷችኋል ተመለሱ› ብሎ አልሰበከም፡፡ መርከብ ሠርቶ ግቡም አላላቸውም፡፡ ‹በሦስት ቀን ውስጥ ነነዌ ትገለበጣለች› ብሎ ጮኸ፡፡

የነነዌ ሰዎች ግን ‹ማን ነው የሚገለብጣት?› ‹ለምን ትገለበጣለች?› ‹ለመሆኑ አንተ ማን ነህ?› ‹ዝም ብሎ ትገለበጣላችሁ ይባላል? መጀመሪያ ትምህርት አይቀድምም?› አላሉም፡፡ራሳቸውን እንጂ ሰባኪውንና ስብከቱን ለመገምገም ጊዜ አልነበራቸውም፡፡ ‹‹እግዚአብሔርን አመኑ ለጾም አዋጅ ነገሩ ከታላቁ ጀምሮ እስከ ታናሹ ድረስ ማቅ ለበሱ››

አንድ ላይ ኃጢአት መሥራት ቀላል ነው ፤ አንድ ላይ ንስሓ መግባት ግን ይከብዳል፡፡ በሀገር ደረጃ ንስሓ መግባት ግን እጅግ ያስደንቃል፡፡ ‹ነነዌ የምትገለበጥ ከሆነ ሀገር እንቀይር› አላሉም ፤ ሀገር ከመቀየር ይልቅ ራሳቸውን መቀየር እንደሚሻል ተረድተው ነበር፡፡ ሁሉም እኩል ልቡ ተሰበረ ፤ ሁሉም ማቅ ለበሰ፡፡

የሰባኪው ስብከት ጣዕም የለውም ብለው አላማረሩም ፣ ‹ተስፋ የሚሠጥ ስብከት መቼ ሰማን› አላሉም፡፡ ሰባኪው እያዋዛ አላስተማራቸውም ፣ ምሳሌ አልነገራቸውም ፣ ቅኔ አልተቀኘላቸውም ፣ ቅዱስ ኤፍሬም እንዲህ ይላል ‹‹የተላከላቸው ጨካኝ ሐኪም ነበር ፤ የያዘው መድኃኒትም የሚያቃጥል ነበር ፤ እንደ ሰይፍ የሚቆራርጥ ቃል ተናገራቸው ፤ እነርሱ ግን አቁስሏቸው ተፈወሱ››   

የነነዌ ሰዎች ንስሓ ከላይ እስከታች ነበር፡፡ ነገሥታቱ ሳይቀር ማቅ ለበሱ፡፡ ‹‹ነነዌ ትገለበጣለች› ብሎ ሲናገር ንጉሡ ወታደሮች ልኮ ዮናስን ማሰር ይችል ነበር፡፡ ‹‹ምን በሀገራችን ላይ ታሟርታለህ?›› ብለው አፉን አላፈኑትም፡፡ መፍትሔውን ንገረን ያለውም የለም ፤ ችግሩ እነርሱ ናቸውና መፍትሔውንም ያውቁታል፡፡ ስለዚህ ራሳቸውን መውቀስ ወደዱ፡፡

ሀገሪቱ በአንድ ልብ አለቀሰች፡፡  ንጉሡ ፡- ሰዎችና እንስሶች አንዳች አይቅመሱ! ብሎ አዋጅ አስነገረ፡፡ ከቤተ መንግሥት ጾም የሚታወጅባት ነነዌ እንዴት የታደለች ናት? ‹‹መኳንንቶችሽ ማልደው የሚበሉ አገር ሆይ ወዮልሽ›› ተብሎ ከተጻፈ መኳንንቶችዋ የሚጾሙላት ሀገር እንዴት የታደለች ትሆን? (መክ. 10፡16) መቼም ሕዝብ ብቻ መጾሙ ነገሥታት ቢበሉ የተለመደ ነው፡፡ ነገር ግን እየበሉ የሚጾምን ሕዝብ መምራት እንዴት ይቻላል? ሲጠጡ እያደሩስ ሲጸልይ የሚያድርን ሕዝብ መምራት እንዴት ይቻላል?

ንጉሥሽ ላንቺ ማቅ ለብሶ ያለቀሰልሽ ፣ እንስሳት ሳይቀር የጾሙልሽ ነነዌ ሆይ ምንኛ የታደልሽ ነሽ? ሕዝብሽ ጾም ሲታወጅ የማያላግጡ ፣ ‹እኔ በፈለግሁበት ጊዜ ነው የምጾመው› ብለው የማይመጻደቁ ፣ እንኳን ከቤተ ክህነት ይቅርና ከቤተ መንግሥት የታወጀን ጾም በትሕትና የሚጾሙብሽ ነነዌ ሆይ ምንኛ የታደልሽ ነሽ? የዋሐን ሕጻናትን ጡት ከልክለው የፈጣሪን ርኅሩኅ ልብ የሚያስጨንቁ ፣ እንስሳትን ከውኃ ከልክለው ለምህላ የታጠቁ የነነዌ ሰዎች ምንኛ ድንቅ ናቸው፡፡

ቅዱስ ኤፍሬም ያቺን ከተማ በዓይነ ሕሊናው በጎበኛት ጊዜ እንዲህ ብሏል ፡-
‹‹የንጉሥ ቤት ግብዣ ተቋረጠ ፣ ንጉሥ ማቅ ለበሰ ፤ ንጉሥ ማቅ ከለበሰ ደግሞ የጌጥ ልብስ ይለብሳል፡፡ በዚያን ጊዜ በነነዌ ወርቃችሁን ብትጥሉ ማንም አይሰርቀውም፤ ሀብታችሁ ያለበትን ቤት ክፍት ትታችሁ ብትሔዱ ማንም ዘው ብሎ አይገባም፡፡ ወንዶች ወደ ሴቶች በምኞት አይመለከቱም ፤ ሴቶችም የሚያያቸውን ለመማረክ ጌጦቻቸውን አላደረጉም፡፡ ከልጆቻቸው ጋር አብረው ወደ መቃብር ሊወርዱ ነውና አረጋውያን በላያቸው አመድን ነሰነሱ፡፡ ወላጆች በልጆቻቸው ጥያቄ ተጨነቁ ፤ አብርሃም ልጁ ይስሐቅ ‹የመሥዋዕቱ በግ ወዴት ነው› ሲለው የተጨነቀው ጭንቀት በነነዌ ወላጆች ተደገመ››   

ሶርያዊው የበተ መንግሥቱን ሁኔታም እንዲህ ይሥለዋል፡፡ 

‹‹የነነዌ ንጉሥ ወታደሮቹን ሰብስቦ እንዲህ አላቸውም ፡- ይህ ድል እንደተጎናጸፍንባቸው ውጊያዎቻችን አይደለም ፤ ከባዕድ ሀገር በተሰማው ዜና ኃያላኖቻችን ሳይቀሩ ተብረክርከዋል ፤ አንድ ዕብራዊ መጥቶ በቃሉ አብረከረከን፡፡የጀግኖች እናት ነነዌ አንድን ለብቻው የመጣ ደካማ ሰው ቃል ፈርታለች፡፡
ስለዚህ ወገኖቼ ፤ የማይፈርስ አጥር እንገንባ ፤ ይህች አጥር ንስሓ ናት ፤ ሥውር ጦርነት ታውጆብናልና ራሳችንን ሥውር መሣሪያ እናድርግ!!››

ዮናስ በነነዌ መመለስ ደስ አልተሰኘም ፤ ትንቢቱ ስለማይፈጸምለት ብቻ አይደለም፡፡ ‹‹የእስራኤል ሽማግሌዎች በሚቀማጠሉባት ሰዓት የነነዌ ሽማግሌዎች ሲያለቅሱ አየ ፤ ጽዮን በዝሙት እንደ ሰም ስትቀልጥ ነነዌ ታነባ ነበር›› እስራኤል ከፈጣሪ በራቁበት ሰዓት አሕዛብ የንስሓ ዕንባ ሲታጠቡ ሲያይ ክብር ከእስራኤል መልቀቁን አይቶ ተከፋ፡፡
ዮናስ እስከመጨረሻው ሰዓት የነነዌን መጥፋት ይጠባበቅ ነበር፡፡ ዮናስ ነነዌ የምትገለበጥበትን ቀን ሲቆጥር ነነዌ ደግሞ ኃጢአትዋን ትቆጥር ነበር፡፡

ዮናስ ስለ ነነዌ እንደ ሙሴ ‹እነርሱን ከምታጠፋ እኔን አጥፋኝ› አላለም ፤ በተቃራኒው ‹እነርሱን ካላጠፋህ እኔን አጥፋኝ› እስከማለት ደረሰ፡፡ ቅዱስ ኤፍሬም ነነዌን ወከሎ ነቢዩን እንዲህ ይለዋል ፡-
‹‹አንተ ዕብራዊ ሆይ ሁላችን ብንጠፋ ምን ይጠቅምሃል? አንተ ሰባኪ ሆይ በሁላችን መሞትስ ምን የተሻለ ነገር ይገኛል? የማቴ ልጅ ሆይ ወደ መቃብር በጸጥታ ብንወርድ ምን ታገኛለህ? በቃልህ ፈውሰኸን ልናመሰግንህ ስንመጣ ለምን ታዝናለህ? ዕጣህ ነነዌን ተናግሮ ያጠፋት ከመባል ይልቅ ተናግሮ ያተረፋት መባል ቢሆን አይሻልህም? መላእክት በሰማይ ሲደሰቱ አንተ ለምን ታዝናለህ? ዮናስ ሆይ ከእንግዲህ በስምህ የምትጠራ ናትና ነነዌን አመስግናት››

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

💛
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

🕊          ክብርት ሰንበት             🕊

    [  እንኳን ለነነዌ ጾም አደረሰን   ]


" የነነዌም ሰዎች እግዚአብሔርን አመኑ ፥ ለጾም አዋጅ ነገሩ ፥ ከታላቁም ጀምሮ እስከ ታናሹ ድረስ ማቅ ለበሱ ። ወሬውም ወደ ነነዌ ንጉሥ ደረሰ ፤ እርሱም ከዙፋኑ ተነስቶ
መጎናጸፊያውና አወለቀ ማቅም ለበለ ፥ በአመድም ላይ ተቀመጠ ። አዋጅም አስነገረ በነነዌም ውስጥ የንጉሡንና የመኳንቱን ትእዛዝ አሳወጀ ፥ እንዲህም አለ ፦ ሰዎችን
እንስሶች ላሞችና በጎች አንዳችን እንዳይቀምሱ አይሰማሩም ውኃንም አይጠጡ ፤ ሰዎችና እንስሶችም በማቅ ይከደኑ ፥ ወደ እግዚአብሔርም በብርቱ ይጩኹ ሰዎችም ሁሉ ከክፉ መንገዳቸውና በእጃቸው ካለው ግፍ ይመለሱ ፥እኛ እንዳንጠፋ እግዚአብሔር ተመልሶ ይጸጸት እንደ ሆነ ፥ ከጽኑ ቁጣውም ይመለስ እንደ ሆነ ማን ያውቃል ?

እግዚአብሔርም ከክፉ መንገዳቸው እንደ ተመለሱ በሥራቸውን አየ ፤ እግዚአብሔርም ያደርግባቸው ዘንድ በተናገረው ክፉ ነገር ተጸጽቶ አላደረገውም።"

[ ት.ዮናስ ፫፥፭ -፲ ]
------------------------------------------

▷   "  ነ ነ ዌ ና ነ ቢ ዩ ዮ ና ስ   "

🕊 [  በብፁዕ አቡነ ሺኖዳ  ]   🕊

[                     🕊                       ]
------------------------------------------

" ወደ ጥልቁ ወደ ባሕሩ ውስጥ ጣልኸኝ ፥ ፈሳሾችም በዙሪያዬ ነበሩ ፤ ማዕበልህና ሞገድህ ሁሉ በላዬ አለፉ። እኔም። ከዓይንህ ፊት ተጣልሁ ፤ ነገር ግን ወደ ቅዱስ መቅደስህ ደግሞ እመለከታለሁ አልሁ። " [ዮና.፪፥፬]

         †              †               †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬
                    👇

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

🕊

[ † እንኩዋን ለሊቀ ነቢያት ቅዱስ ሙሴ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ † ]


🕊 †  ቅዱስ ሙሴ ሊቀ ነቢያት †  🕊

ቅዱሳን ነቢያት እጅግ ብዙ ናቸው:: ከፈጣሪያቸው የተቀበሉት ጸጋም ብዙና ልዩ ልዩ ነው:: ያም ሆኖ ከሁሉም ነቢያት ቅዱስ ሙሴ ይበልጣል:: መጽሐፍ እንደሚል ከእርሱም በፊት ቢሆን ከእርሱ በሁዋላ እንደ እርሱ ያለ ነቢይ አልተነሳምና:: ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-

ዓለም በተፈጠረ በ ፫ ሺህ ፮ መቶ [ 3,600 ] ዓመት እሥራኤል በረሃብ ምክንያት ፸፭ [ 75 ] ራሱን ወደ ምድረ ግብፅ ወረደ:: በዚያም ልጆቹና የልጅ ልጆቹ ለ፪ መቶ ፲፭ [ 215 ] ዓመታት ተከብረው: ለ፪ መቶ ፲፭ [ 215 ] ዓመታት ደግሞ በባርነት: በድምሩ ለ፬ መቶ ፴ [ 430 ] ዓመታት በምድረ ግብፅ ኑረዋል::

- በባርነት ዘመናቸውም 'ራምሴና ጋምሴ' የሚባሉ ፪ [2] ከተሞችን [ዛሬ ፒራሚዶች የምንላቸውን] ገንብተዋል:: ግፋቸው እየበዛ ሲሔድ ግን ጩኸታቸው ቅድመ እግዚአብሔር ደረሰ:: ያድናቸውም ዘንድ አንድ ቅዱስ ሰው እንዲወለድ አደረገ:: ይኽም ሰው ሙሴ ይባላል::

- ወላጆቹ መታመናቸውን በፈጣሪያቸው ያደረጉ 'እንበረም'ና 'ዮካብድ' ሲሆኑ ከሌዊ ነገድ ናቸው:: ከሙሴ ውጪም አሮንና ማርያምን ወልደዋል:: ቅዱስ ሙሴ በተወለደበት ወራት ወንድ የእሥራኤል ሕጻናት ይፈጁ ነበር:: ጌታ ግን በገዳዮቹ ልቡና ርሕራሔን አምጥቶ አትርፎታል::

- በሁዋላም በ፫ [ 3 ] ወሩ ዓባይ ወንዝ ላይ ጥለውት ተርሙት [የፈርኦን ልጅ ናት] ወስዳ በቤተ መንግስት አሳድጋዋለች:: 'ሙሴ' ያለችውም እርሷ ናት:: 'ዕጉዋለ ማይ / እማይ ዘረከብክዎ' [ከውሃ የተገኘ] ለማለት ነው:: ወላጆቹ ያወጡለት ስም ግን 'ምልክአም' ይባላል:: ገና ሲወለድ ፊቱ እንደ መልአክ ያበራ ነበርና::

- ቅዱስ ሙሴ ፭ [ 5 ] ዓመት በሆነው ጊዜ ፈርኦንን በጥፊ በመማታቱ ለፍርድ ቀርቦ እሳትን በመብላቱ አንደበቱ ኮልታፋ ሆኖ ቀርቷል:: እናቱ ዮካብድ ሞግዚት ሆና ስላሳደገችው ፵ [40] ዓመት በሆነው ጊዜ የፈርኦንን ቤት ምቾትና የንጉሥ ልጅ መባልን ናቀ:: ቅዱስ ዻውሎስ እንደሚለው በአሕዛብ ቤት ካለ ምቾት ከእግዚአብሔር ሕዝብ ጋር መከራን ሊቀበል ወዷልና:: [ዕብ.፲፩፥፳፬] [11:24]

- አንድ ቀንም ለዕብራዊ ወገኑ ተበቅሎ ግብጻዊውን ገድሎት ወደ ምድያም ሸሸ:: በዚያም ለ፵ [40] ዓመታት የካህኑን ዮቶርን በጐች እየጠበቀ: ኢትዮዽያዊቱን ሲፓራን አግብቶ ኖረ:: ልጆንም አፈራ:: ፹ [80] ዓመት በሞላው ጊዜ እግዚአብሔር በደብረ ሲና ተናገረው:: ሕዝቡንም ከባርነት ቀንበር እንዲታደግ ላከው::

- ቅዱስ ሙሴም ከወንድሙ አሮንና ከአውሴ [ኢያሱ] ጋር ግብጻውያንን በ፱ [9] መቅሰፍት: በ፲ [10] ኛ ሞተ በኩር መታ:: እሥራኤልንም ነጻ አወጣ:: ሊቀ ነቢያት የሠራቸው ሥራዎች ተዘርዝረው የሚያልቁ አይደሉም::

- እርሱ ባሕረ ኤርትራን ከፍሎ ሕዝቡን በደረቅ አሻግሯል::
- ግብጻውያንን ከነሠረገሎቻቸው በባሕር ውስጥ አስጥሟል::
- ለሕዝቡ መና ከደመና አውርዷል::
- ውሃን ከጨንጫ [ከዓለት] ላይ አፍልቁዋል::
- በብርሃን ምሰሶ መርቷቸዋል::
- በ፯ [7] ደመና ጋርዷቸዋል::
- ጠላቶቻቸውን ሁሉ ድል ነስቶላቸዋል::

- ስለዚህ ፈንታ ግን ወገኖቹ ብዙ አሰቃይተውታል:: እርሱ ግን ደግ: ቅንና የዋህ ሰው ነውና ብዙ ጊዜ ራሱን ለእነሱ አሳልፎ ሰጥቷል:: "ሙሴሰ የዋህ እምኩሎሙ ደቂቀ እሥራኤል" እንዲል:: [ዘኁ.፲፪፥፫] [12:3] ቅዱስ ሙሴ ለ፵ [40] ዓመታት ሕዝቡን ሲመራ ከእግዚአብሔር ጋር ለ፭ መቶ ፸ [570] ጊዜ ተነጋግሯል::

- ከጸጋው ብዛትም ፊቱ ብርሃን ስለ ነበር ሰዎች እርሱን ማየት አይችሉም ነበር:: ታቦተ ጽዮንንና 10ሩ ቃላትን ተቀብሎ ጽላቱ ቢሰበሩ ራሱ ሠርቶ በጌታ እጅ ቃላቱ ተጽፈውለታል:: "የቀረው የቅዱሱ ሕይወት በመጻሕፍተ ኦሪት [በብሔረ ኦሪት] ውስጥ የተጻፉ አይደሉምን?"

- እኔ ግን ደካማ ነኝና ይህቺ ትብቃኝ:: ቅዱስ: ክቡር: ታላቅ: ጻድቅ: ነቢይና ደግ ሰው ቅዱስ ሙሴ በ፻፳ [120] ዓመቱ ዐርፎ በደብረ ናባው ሊቃነ መላእክት ቅዱሳን ሚካኤል: ገብርኤልና ሳቁኤል ቀብረውታል:: መቃብሩንም ሠውረዋል:: [ይሁዳ.፩፥፱] [1:9]

አምላከ ሊቀ ነቢያት ደግነቱን አስቦ ከግራ ቁመት: ከገሃነመ እሳት ይሰውረን:: በረከቱንም አብዝቶ ያድለን::

🕊

[ † የካቲት ፲፯ [ 17 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. ቅዱስ ሙሴ ሊቀ ነቢያት [በ፻፳ [120] ዓመቱ ደብረ ናባው ላይ ተቀብሯል]
፪. ቅዱስ ሚናስ ግብፃዊ [ኁለተኛው]

[ † ወርኀዊ በዓላት ]

፩. ቅዱስ እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት [ቀዳሜ ሰማዕት]
፪. ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ [ወልደ ዘብዴዎስ]
፫. ቅዱስ ኤዺፋንዮስ ዘቆዽሮስ
፬. ቅዱሳን አበው መክሲሞስና ዱማቴዎስ
፭. አባ ገሪማ ዘመደራ
፮. አባ ዸላሞን ፈላሢ
፯. አባ ለትጹን የዋህ

" ሙሴ ካደገ በሁዋላ የፈርኦን የልጅ ልጅ እንዳይባል በእምነት እምቢ አለ:: ከግብጽም ብዙ ገንዘብ ይልቅ ስለ ክርስቶስ መነቀፍ እጅግ የሚበልጥ ባለጠግነት እንዲሆን አስቧልና:: ለጊዜው በኃጢአት ከሚገኝ ደስታ ይልቅ ከእግዚአብሔር ሕዝብ ጋር መከራ መቀበልን መረጠ:: ብድራቱን ትኩር ብሎ ተመልክቷልና::" † [ዕብ.፲፩፥፳፬] [11:24]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖

Читать полностью…
Subscribe to a channel