"እንግዲህ፡ንስሓ፡ግባ፤አለዚያ፡ፈጥኜ፡ እመጣብሃለሁ፡፡" ራዕ 2፥16
ቅዳሜ - የካቲት 16 2016 ዓ.ም
ዘዳግም 6-10
ሰላም ለሁላችሁ ይሁን! በዛሬው እለት ንባባችን ከምዕራፍ 6 እስከ 10 ድረስ እናነባለን።
ከንባብ በፊት የሚደረግ ጸሎት፡ “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፤ የአንተን ቃላት እሰማ እና እረዳ ዘንድ፥ እንዲያውም ፈቃድህን ለመፈጸም እበቃ ዘንድ የልቤን ጆሮዎች እና ዓይኖች ክፈትልኝ።” (ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ)
በዛሬው ንባባችን ላይ ስለ ታላቁ ትእዛዝ፥ ስለ አለመታዘዝ የተሰጠ ማስጠንቀቂያ፥ ከአሕዛብ ስለ መለየት፥ ለእግዚአብሔር መታዘዝ ስለሚያስገኘው በረከት፥ የተስፋይቱን ምድር ለመውረስ ስለተሰጠ መመሪያ እና እግዚአብሔርን እንዳይረሱ ስለተሰጠው ማስጠንቀቂያ እናነባለን። በተጨማሪም፥ በእግዚአብሔር ላይ ማመፅ ስለሚያስከትለው መቅሰፍት፥ ሙሴ ዐሥሩ ትእዛዛትን እንደገና ስለመቀበሉ እና እግዚአብሔር ከእስራኤል የሚፈልገው ነገር ተጽፏል።
*የክለሳ ጥያቄዎች*
1) በዘዳግም 5 ላይ እግዚአብሔርን ብቻ ስለማምለክ ምን ተብሏል?
2) እስራኤላውያን ልጆቻቸው ስለ እግዚአብሔር ትእዛዝ ሲጠይቋቸው ምን ብለው እንዲመልሱ ተነገራቸው?
3) በዘዳግም 7 መሠረት፥ እግዚአብሔር ስለ አሕዛብ ምን አለ?
4) በዘዳግም 8 ላይ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሐዲስ ኪዳን የተናገረው ቃል ይገኛል። ይህ ቃል ምንድር ነው?
5) በዘዳግም 10 መሠረት፥ እግዚአብሔር ከእስራኤል የሚፈልገው ነገር ምንድር ነው?
መልካም ንባብ!
/channel/OrthodoxTewahdoBooks
/channel/c/2014228571/1
†
[ የጾመ ነነዌ መልዕክት ]
🕊
† † †
" ይህንን የነነዌ ጾም ልንቀበል ዋዜማ ላይ ባለንበት በዚህ ጊዜ በቤተክርስቲያናችን ጥንታዊ ከሆኑት ገዳማት አንዱ በሆነው በዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም የሚገኙ፣ ዓለሙን ትተው በፈቃዳቸው ረሀብተኛ እና ጥማተኛ ሆነው ሀገርን በጸሎት የሚጠብቁ መነኮሳት ጫካው መኖሪያችሁ፣ ዳዋው ልብሳችሁ፤ ቅጠሉ ምግባችሁ መሆን አይችልም ተብለው የሰማዕትነትን ጽዋ ተጎንጭተዋል፡፡ እነርሱ በሥጋ እየሞቱ እኛም በየቀኑ ሟቾችን እየቆጠርን በኀዘን ለመኖር የተፈረደብን ሆነናል፡፡
ይህ ለእነርሱ ክብር ቢሆንም ለቤተክርስቲያን ግን ታላቅ ደወል ያሰማ ክስተት ነውና ውሉደ ክህነት ቤተክርስቲያናችሁን የምትጠብቁበት፣ የመከራውን ማዕበል ለማለፍ በመንፈሳዊ ፍቅር አንድነትን ማጽናት የሚያስፈልግበት ጊዜ መሆኑን እናሳስባለን"
[ የቅዱስ ፓትርያርኩ የጾመ ነነዌ መልዕክት ]
† † †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬
†
🕊 እ ን ኳ ን አ ደ ረ ሳ ች ሁ 🕊
💖
“ ሚ ሠናይ ከመ ጼና ጽጌ ልሑይ ፣
በኲሉ ጊዜ ምሒረ ነዳይ ፣
በእንተ ኪዳንኪ ድንግል ለበላዔ ሰብእ ጊጉይ ፣
ሶበ ዐብየ እምኀጢአቱ ክበደ መድሎቱ ለማይ ፣
ለተአምርኪ በሰማይ ተገብረ ግናይ”
[ ኹል ጊዜ ለደኻ መራራት መመጽወት እንደ ለመለመ አበባ ያማረ ነው [ ምን ያምር ? ] ድንግል በቃል ኪዳንሽ ምክንያት ከበላዔ ሰብእ ኀጢአት የውሃ ሚዛን በልጦ በመታየቱ ለተአምርሽ በሰማይ ምስጋና ኾነ። ]
“አንቲ ውእቱ ለእግዚአብሔር አትሮኑሱ
ለአዳም ክብረ ሞገሱ
በኪዳንኪ ኃጥኣን መንግሥተ ሰማያት ይወርሱ"
[ የእግዚአብሔር አትሮንሱ [ ዙፋኑ ] የአዳም የግርማው ክብር አንቺ ነሽ ፤ ኃጥኣንም በቃል ኪዳንሽ መንግሥተ ሰማያትን ይወርሳሉ። ]
[ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ]
† † †
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
ዓርብ - የካቲት 15 2016 ዓ.ም
ዘዳግም 1-5
ሰላም ለሁላችሁ ይሁን! ዛሬ በእግዚአብሔር ቸርነት ኦሪት ዘዳግምን ማንበብ እንጀምራለን። ኦሪት ዘዳግም ሊቀ ነቢያት ሙሴ ከጻፋቸው አምስቱ መጻሕፍት ውስጥ የመጨረሻው ሲሆን፥ እርሱም ወደ ተስፋይቱ ምድር ስለማይገባ፥ ወደ ተስፋይቱ ምድር ለሚገቡት ሁሉ ስለ እግዚአብሔር ትእዛዝ እና እንዴት መኖር እንዳለባቸው የተናገረበት መጽሐፍ ነው።
በዛሬው እለት ንባባችን ከምዕራፍ 1 እስከ 6 ድረስ እናነባለን።
ከንባብ በፊት የሚደረግ ጸሎት፡ “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፤ የአንተን ቃላት እሰማ እና እረዳ ዘንድ፥ እንዲያውም ፈቃድህን ለመፈጸም እበቃ ዘንድ የልቤን ጆሮዎች እና ዓይኖች ክፈትልኝ።” (ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ)
በዛሬው ንባባችን ላይ እስራኤላውያን ሲናን ለቅቀው እንዲጓዙ ስለተሰጠው ትእዛዝ፥ ሙሴ የሕዝብ አለቆችን ስለ መሾሙ፥ ከቃዴስ በርኔ ወደ ከነዓን ስለተላኩ ሰዎች፥ እግዚአብሔር እስራኤልን ስለ መቅጣቱ፥ እስራኤል በበረሃ ስለዞሩባቸው ዓመታት እና ንጉሥ ሴዎንን ድል ስለማድረጋቻው እናነባለን። ከዚህ በተጨማሪ፥ እስራኤላውያን የባሳን ንጉሥ ዐግን ድል ስለመንሳታቸው፥ ከዮርዳኖስ በስተምሥራቅ ስለ ሰፈሩ ነገዶች፥ ሙሴ ወደ ተስፋይቱ ምድር እንዳይገባ ስለመከልከሉ፥ የእስራኤል ሕዝብ ታዛዦች እንዲሆኑ ስለተሰጠው ምክር እና ከጣዖት አምልኮ ርቀው የእግዚአብሔርን ሕግ እንዴት መጠበቅ እንዳለባቸውም ተጽፎ ይገኛል።
የክለሳ ጥያቄዎች
1) በዘዳግም 1 መሠረት፥ ሙሴ የሕዝብ አለቆችን የሾመበት ምክንያት ምን ነበር?
2) በዘዳግም 2 መሠረት፥ ተመልሰው ወደ ምድረበዳ የሄዱት የዞሩት ተራራ ምን ይባላል? ከዞሩት በኋላስ ምን ተነገራቸው?
3) በዘዳግም 3 መሠረት፥ ለሮቤል እና ለጋድ የተሰጠው ምድር ከየት እስከ የት ያለው ነው?
4) ሙሴ የተስፋይቱን ምድር እንዲያይ እግዚአብሔርን በጠየቀው ጊዜ የተሰጠው ምላሽ ምንድር ነው?
5) በዘዳግም 5 መሠረት፥ የተጠቀሱትን ዐሥሩን ትእዛዛት ጻፉ።
መልካም ንባብ!
/channel/OrthodoxTewahdoBooks
/channel/c/2014228571/1
†
እግዚአብሔር ያጽናናሽ ቅድስት ቤተክርስቲያን !
† † †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬
ሐሙስ - የካቲት 14 2016 ዓ.ም
ዘኁልቁ 33-36
ሰላም ለሁላችሁ ይሁን! በዛሬው እለት ንባባችን ከምዕራፍ 29 እስከ 32 ድረስ እናነባለን።
ከንባብ በፊት የሚደረግ ጸሎት፡ “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፤ የአንተን ቃላት እሰማ እና እረዳ ዘንድ፥ እንዲያውም ፈቃድህን ለመፈጸም እበቃ ዘንድ የልቤን ጆሮዎች እና ዓይኖች ክፈትልኝ።” (ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ)
በዛሬው ንባባችን ላይ እስራኤላውያን ከግብጽ አንስተው እስከ ሞዐብ ድረስ ስላደረጉት ጉዞ፥ ዮርዳኖስን ከመሻገራቸው በፊት ስለተሰጣቸው መመሪያ እና የተስፋይቱ ምድር ወሰኖች ምን እንደሆኑ እናነባለን። በተጨማሪም፥ ከእስራኤል መካከል የተስፋይቱን ምድር ለማከፋፈል ኃላፊነት ስለተሰጣቸው ሰዎች፥ ለሌዋውያን ስለተሰጡ ከተሞች፥ ነፍሰ ገዳይ ለሆኑ ስለተሰጡ የመማፀኛ ከተሞች እና ለአገቡ ሴቶች ስለተመደበ ርስት እናነባለን።
*የክለሳ ጥያቄዎች*
1) በዘኁልቁ 33 መሠረት፥ ካህኑ አሮን የሞተው መቼ፥ የት እና በስንት ዓመቱ ነበር?
2) እስራኤላውያን ወደ ከነዓን ምድር ዮርዳኖስን እንደተሻገሩ፥ ምን እንዲያደርጉ ተነገራቸው?
3) በዘኁልቁ 34 መሠረት፥ ምድሪቱን ለማከፋፈል ኃላፊነት የተሰጣቸው የመጀመሪያዎቹ ሰዎች ማን ናቸው?
4) በዘኁልቁ 35 መሠረት፥ ለሌዋውያን የተሰጣቸው ምድር እንዴት ተገልጿል? ከቅጥሩ ወደ ውጪስ ምን ያህል ክንድ ይሆናል? በየአንዳንዱ አቅጣጫስ ምን ያህል ክንድ ይሆናል?
5) የመማፀኛ ከተሞች አገልግሎት ምንድር ነው?
6) በዘኁልቁ 35 መሠረት፥ እግዚአብሔር ምድርን የሚያረክሳት ምንድር ነው ብሏል? የሚያነጻትስ?
7) በዘኁልቁ 36 መሠረት፥ የሰለጰአድ ሴቶች ልጆችን ጋብቻ በተመለከተ የተሰጠው ትእዛዝ ምንድር ነው?
መልካም ንባብ!
/channel/OrthodoxTewahdoBooks
/channel/c/2014228571/1
†
[ ከዚያች ከተማ ይልቅ ! ]
" ከማይቀበሉአችሁና ከማይሰሙአችሁ ስፍራ ሁሉ ፥ ከዚያ ወጥታችሁ ምስክር ይሆንባቸው ዘንድ ከእግራችሁ በታች ያለውን ትቢያ አራግፉ። እውነት እላችኋለሁ ፥ ከዚያች ከተማ ይልቅ ለሰዶምና ለገሞራ በፍርድ ቀን ይቀልላቸዋል አላቸው።" [ ማር.፮፥፲፩ ]
" የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ።" [ማቴ.፲፩፥፲፭]
† † †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬
†
እግዚአብሔር ያጽናናሽ ቅድስት ቤተክርስቲያን !
† † †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
[ ሰማዕትነት ተቀብለዋል ]
የዝቋላ አቦ አባቶች በጭካኔ ተገደሉ !
🕯
በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት በሚገኘው ጥታዊው የዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም እራሱን ኦነግ ሸኔ ብሎ በሚጠራው ቡድን የገዳሙን መጋቢ ጨምሮ አራት አባቶችን መግደሉን ገዳሙ አስታውቋል፡፡
ሰኞ የካቲት ፲፩ [11] ቀን ፳፻፲፮ [2016] ዓመተ ምሕረት ታጣቂዎቹ ሦስት አባቶችን አግተው ወደ በረሃ ከወሰዱ በኋላ የታገቱትን ለማስለቀቅ ገዳሙ ጥረት በሚያርግበት ወቅት የካቲት ፲፫ [13] ቀን ፳፻፲፮ [2016] ዓ.ም ተጨማሪ አባቶችን በመያዝ ፦
፩. የገዳሙ መጋቢ አባተክለማርያም ዐሥራት
፪. የገዳሙ ጸሐፊ አባ ኪዳነ ማርያም ጥላሁን
፫. የገዳሙ የመጽሐፍ መምህርና ቀዳሽ አባ ገ/ማርያም አበበ
፬. በአመክሮ የሚኖሩ መናኝ ኃይለማርያም ወልደሰንበት የተባሉት የገዳሙ የሥራ ኃላፊዎች እንደተገደሉና አብረው ከነበሩት አንድ አባት ብቻ በአጋጣሚ መትረፍ መቻላቸውን እንደተረዱ የገዳሙ ኃላፊዎች ለኢኦተቤ ቴቪ [ EOTC TV ] ገልጸዋል፡፡
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
🕊
[ † እንኳን ለታላቁ ሊቅና የተዋሕዶ ጠበቃ ቅዱስ ሳዊሮስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ]
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †
🕊 † ታላቁ ቅዱስ ሳዊሮስ † 🕊
† ቅዱስ ሳዊሮስ በስድስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጀመሪያ አካባቢ በሶርያ አንጾኪያ የተነሳ አባት ነው። ወቅቱ መለካውያን [ሁለት ባሕርይ ባዮች] የሰለጠኑበት እንደ መሆኑ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምእመናን ያነሱበትና የሚሰደዱበት ጊዜ ነበር። በዚህ ጊዜ ነበር ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ሳዊሮስ በሥላሴ ፈቃድ ለቤተ ክርስቲያን የተነሳው። ሊቃውንት አንበሳ ሲሉ ይጠሩታል።
ቅዱሱ ለተዋሕዶ ሃይማኖት ብዙ ሆኖላታል። የመናፍቃን ጸር በመሆኑ ብዙ ድርሰቶችን ደርሷል። ንጉሡን ዮስጢያኖስን [Justinian] ሳይቀር በይፋ ይገስጸው ነበርና ንጉሡ ሊገድለው ቆረጠ።
ሃይማኖቷ የቀና ንግሥቲቱ ታኦድራ ግን ይህንን ስትሰማ በሌሊት ወደ ሊቁ ሒዳ "እባክህን ሽሽ።" አለችው። እርሱ ግን "ሞት ለእኔ ክብር ነውና አልሔድም።" ሲል መለሰላት። አባቶችን ሰብስባ "ስለ ቤተ ክርስቲያን ስትል" ብለው ለምነው ወደ ግብጽ ሸኙት።
እርሱ እየሔደ ገዳዮቹ ያሳድዱት ገቡ። መንገድ ላይ ቢደርሱበትም ተሰወረባቸው። ለብዙ ቀናትም አብሯቸው ተጓዘ። እነርሱ ተስፋ ቆርጠው ሲመለሱ እርሱ ግን ምድረ ግብጽ ደረሰ።
በምድረ ግብጽም የጵጵስና ልብሱን ትቶ የመነኮሳትን አሮጌ ልብስ ለብሶ ሕዝቡንና መነኮሳቱን አስተማረ ፤ አጸና። በየቦታውም ብዙ ተአምራትን ሠራ።
አባቶች መነኮሳትም ማንነቱን ባወቁ ጊዜ ሰገዱለት። ዶርታኦስ ]ዱራታኦስ ] በሚባል አንድ ደግ ሰው ቤትም በስድስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን አጋማሽ አካባቢ የካቲት ፲፬ ቀን ዐርፏል።
† አምላከ ቅዱሳን ሊቃውንት የድንግል እመቤታችንን ጣዕሟን ፍቅሯን ያሳድርብን። የአበውን ሃብትና በረከትም አይንሳን።
[ † የካቲት ፲፬ ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ቅዱስ ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ
፪. ቅዱስ ቄርሎስ ሊቀ ጳጳሳት
፫. አባ ያዕቆብ ሊቀ ጳጳሳት
፬. ቅዱስ ዳርዮስ
፭. ቅድስት ሊድና
[ † ወርኀዊ በዓላት ]
፩. አቡነ አረጋዊ [ ዘሚካኤል ]
፪. ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ መርዓዊ
፫. ቅዱስ ፊልጶስ ሐዋርያ
፬. ቅዱስ ሙሴ [ የእግዚአብሔር ሰው]
፭. አባ ስምዖን ገዳማዊ
፮. አባ ዮሐንስ ጻድቅ
፯. እናታችን ቅድስት ነሣሒት
† " ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለ ተሰጠ ሃይማኖት እንድትጋደሉ እየመከርኋችሁ እጽፍላችሁ ዘንድ ግድ ሆነብኝ።" †
[ይሁዳ ፩፥፫]
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖 🕊 💖
ረቡዕ - የካቲት 13 2016 ዓ.ም
ዘኁልቁ 29-32
ሰላም ለሁላችሁ ይሁን! በዛሬው እለት ንባባችን ከምዕራፍ 29 እስከ 32 ድረስ እናነባለን።
ከንባብ በፊት የሚደረግ ጸሎት፡ “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፤ የአንተን ቃላት እሰማ እና እረዳ ዘንድ፥ እንዲያውም ፈቃድህን ለመፈጸም እበቃ ዘንድ የልቤን ጆሮዎች እና ዓይኖች ክፈትልኝ።” (ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ)
በዛሬው ንባባችን ላይ ለእግዚአብሔር መቅረብ ስላለባቸው የመሥዋዕት አይነቶች፥ እስራኤላዊያን ማድረግ ስላሉባቸው በዓላት፥ ወንድም ሆነ ሴት ስእለት ቢሳሉ ማድረግ ስላሉባቸው ነገሮች፥ እስራኤላውያን ምድያማውያንን እንደተበቀሉ፥ ምርኮንም እንደወሰዱ እናነባለን። በተጨማሪም፥ የጋድና የሮቤል ልጆች ስለጠየቁት የተለየ ጥያቄ እና ስለተሰጣቸው ምላሽም ተጽፎ ይገኛል።
*የክለሳ ጥያቄዎች*
1) በዘኁልቁ 29 መሠረት፥ እስራኤላውያን ለስንት ቀን በዓል እንዲያደርጉ ታዝዘዋል?
2) በዘኁልቁ 30 መሠረት፥ ስእለት የሚሳል ሰው ምን እንዲያደርግ ታዞአል?
3) እስራኤላውያን ወደ ምድያም በዘመቱ ጊዜ፥ ከእያንዳንዱ ነገድ ምን ያህል ሰው እንዲሄድ ተነገረ?
4) በዘመቻውስ አጠቃላይ ያስቀሩት ምርኮ ቁጥር ምን ያህል ነው?
5) የጋድ እና የሮቤል ልጆች ምን ጥያቄ ጠየቁ? የሙሴ ምላሽስ ምን ነበር?
መልካም ንባብ!
/channel/OrthodoxTewahdoBooks
/channel/c/2014228571/1
🔔
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
የዘመኑ አጥማቅያን እና የአጋንንት ምስክርነት !
[ ክፍል ሰባት ]
" የስሕተት አሠራር " [ ፪ተሰ.፪፥፲ ]
▪
የቤተክርስቲያን ባልሆነ እንግዳ መንፈስና በስህተት አሠራር ፥ ስለ ኃላፊ ጠፊው ዓለም ፥ ገንዘብን ስለመውደድ ፥ ስለ ዝናና ክብር ሲሉ የተነሱ በጣት የሚቆጠሩ ሐሰተኛ አጥማቂዎች የቤተክርስቲያን ፈተናዎች ሆነው መገለጣቸው በሁሉ ዘንድ የታወቀ ነው።
ሐሰተኛ አጥማቂዎች ምልክቶችንና ተዓምራትን እያሳዩ ዓለት በሆነው በቤተክርስቲያን መሠረተ እምነት ላይ ያልጸኑ የዋህ ምዕመናንን ይማርካሉ። እንዴት አድርገው ምዕመኑን ማሳመንና ተከታያቸው ማድረግ እንደሚችሉ ያውቃሉ። የምዕመናንን ስነ-ልቡናና ያሉባቸውን ተደራራቢ ሸክሞች ጠንቅቀው የተረዱ በመሆናቸው በችግሩ በኩል ይገቡበታል። በብዙ ዓይነት ፈተና ውስጥ ያለው ምዕመን ደግሞ ከችግሩ ለመገላገልና መፍትሔ ለማግኘት ሲል ግለሰቦቹን በፍጹም ልቡ ያምናቸዋል። ጆሮውንና ልቡናውን አሳልፎ ይሰጣቸዋል። በዚህ ላይ ምልክቶችን አከታትለው ያሳዩታል። የጽድቅ አገልጋዮች ይመሥሉ ዘንድ ራሳቸውን ለውጠው ጸሎትን ያስቆጥራሉ ፥ የሥግደትን ኃይል ይናገራሉ ፥ የጸሎት ቤት ንድፍን ያዘጋጃሉ ፥ የመቁጠሪያ ጦርነትን ያውጃሉ።
"እንደ እነዚህ ያሉ ሰዎች የክርስቶስን ሐዋርያት እንዲመስሉ ራሳቸውን እየለወጡ ፥ ውሸተኞች ሐዋርያትና ተንኮለኞች ሠራተኞች ናቸውና። ይህም ድንቅ አይደለም ፤ ሰይጣን ራሱ የብርሃንን መልአክ እንዲመስል ራሱን ይለውጣልና።
እንግዲህ አገልጋዮቹ ደግሞ የጽድቅን አገልጋዮች እንዲመስሉ ራሳቸውን ቢለውጡ ታላቅ ነገር አይደለም ፤ ፍጻሜአቸውም እንደ ሥራቸው ይሆናል።" [፪ቆሮ.፲፩፥፲፫]
ሐሰተኛ ሠራተኞች በየዋሃን ዘንድ በቀላሉ የማይለዩትና የማይታወቁት በዚህ የተነሳ ነው። ስመ እግዚአብሔርን ሊጠሩ ፥ ቃለ እግዚአብሔርን ሊያስተምሩ ፥ ድንቆችና ተዓምራትን ሊያሳዩና የጽድቅ አገልጋዮችን ሊመስሉ ይችላሉና።
ይህን በመሠለ የስህተት አሠራር መንፈሳቸውን ያሳደሩበትና ያቆራኙት ምዕመን በረቀቀ መንገድ በመንፈሱ ከቤተክርስቲያን ዕቅፍ እየራቀ ይሄዳል። አካሉ በቅጽረ ቤተክርስቲያን ቢገኝም ልቡናና መንፈሱ ግን ከአጥማቂያን መንደር ይሰደዳል። በኅሊናው ጓዳ በአዕምሮው ሰሌዳ የተቀረጹበትን እገሌ የተባሉ "አጥማቂ" ይናፍቃል። እናቱ ቤተክርስቲያንን ትቶ ወደ "አጥማቂ" እገሌ ጉዞ ይጀምራል። ከአንዱ ስፍራ ወደሌላው ስፍራ እነርሱን ፍለጋ ይማስናል። "የመምህርና የአጥማቂ" እገሌ ስም የአንደበቱ ጣፋጭ ዜማ ይሆናል። "መምህርና አጥማቂ" እገሌን የማይቀበል ፣ የሚተችና የሚቃወም ማንም የእርሱ ቀንደኛ ጠላቱ ይሆናል።
ለእርሱ የጸጋ ሁሉ ምንጭ አካለ ክርስቶስ ቅድስት ቤተክርስቲያን ያለ አጥማቂ እገሌ ምንም ናት ፤ በእርሱ ዘንድ ከክርስቶስ መስቀል በላይ አጥማቂ እገሌ ኃይል ያለው ነው ፤ በዚህ ሰው ዘንድ የቅዱስ ጴጥሮስን ሥልጣን የያዙና በቤቱ በትኅርምትና በትሕትና ጸንተው የሚኖሩ አባቶች ካህናት ትርጉም የላቸውም ፤ በዚህ ሰው ዘንድ በአንዲቷ ቅድስት ቤተክርስቲያን ያለው ጸበልና እምነት ኃይል የለውም። ስለዚህ ይህንን ሁሉ ጸጋ ረግጦና ጥሎ ወደ አጥማቂ እገሌ መንደር ዘወትር በነብስ በሥጋው ይሰደዳል።
ይህ የክህደትና የጥፋት መንገድ ነው። አሠራሩም የሰይጣን አሠራር ነው። እውነተኞቹ አባቶቻችን ቅዱሳን ከዓለም ራሳቸውን ሰውረው እየተጋደሉ ሰው ሁሉ የሕይወት መገኛ የሆነችውን ቅድስት ቤተክርስቲያንን እንዲወዳትና እስከ ፍጻሜም በእርሷ ኖሮ የዘለዓለም ሕይወትን ያገኝ ዘንድ ሕይወታቸውን ሁሉ በመከራ አሳለፉ። የዛሬዎቹ ሐሳዊ አጥማቂያን ደግሞ በብዙ ተጋድሎ በቤተክርስቲያን የተሰበሰበውን ምዕመን ተከታያቸውና የግል ንብረታቸው አድርገው ከቤተክርስቲያን ዕቅፍ ያሰድዱታል። ይመዘብሩታል፥ ይነግዱበታል፥ ይሸቅጡበታል።
የዚህ ስህተት አሠራርና ልምምድ ፍጻሜም ወደ ሐሳዊ መሲህ የሚያደርስ ነው። ለጊዜው የሥጋ ፈውስን ያገኘና መንፈሳዊ እንደሆነ የሚሰማው ምዕመን መጨረሻው በክህደት ጠውልጎ በሐሰተኛ ተአምራትና ድንቆች ደንዝዞ የአማናዊውን የክርስቶስን ድምፅ መለየት የሚሳነው ይሆናል። ሐሰተኛ አሠራሮች ሁሉ የሚወስዱት ወደ ሐሳዊው መሢሕ ነውና።
የሐሰተኛ አጥማቂያን ተከታዮች ዘወትር የሚናገሩት "መምህርና አጥማቂ እገሌ እኮ ከተያዝኩበት እሥራት እንድፈታ ያደረጉኝ ፥ ቃለ እግዚአብሔርን ያስተማሩኝ ፥ የጸሎትና የስግደት ጥቅምን ያሳወቁኝ ፥ ጸሎት ቤት እንዲኖረኝ ያስቻሉኝ ፥ ከነበርኩበት እንቅልፍ ያነቁኝ ናቸው። 'ጹሙ ፥ ጸልዩ ፥ ስገዱ ፥ በመቁጠሪያ ቀጥቅጡ ፥ ቁረቡ' ብለው ስንቱን ለንስሐና ለክብር ያበቁ ናቸው።" የሚል ነው።
በዚህ ሁኔታ በስህተት አሠራር ወጥመድ ውስጥ የገባን ምዕመን ወደ ቤተክርስቲያን ለመመለስ እጅግ ከባድ ነው። ሐሰተኞቹ ከቤተ ክርስቲያን ቢወገዙ እንኳን ግለሰቦቹን ተከትሎ ከመውጣት ወደ ኋላ የሚል አይደለም።
"አጥማቂያኑ" የሥጋን ፈውስ ሰጠንህ የሚሉትን ምዕመን የመንፈሳቸው ማደሪያ አድርገው ስለሚቆራኙት ሳያውቀው ሃይማኖቱን ትቶ የግለሰቡ ዘብና ተዋጊ ሠራዊት ይሆናል። ስለዚህ በመንፈሱ ቤተክርስቲያን ተው ብትለው የማይሰማና የማይታዘዝ ፤ ሊቃውንቱ መምህራንን ለማዳመጥ የማይፈቅድ፤ ክብረ ክህነትን የሚያቃልልና የሚቃወም፤ በቃላት የሚዋጋና ፍጹም የሚከራከር ተቃዋሚ ይሆናል።
ሐሰተኛ አጥማቂያን ተከታዮቻቸውን እየቀረጹትና እየሠሩት ያለበት መንገድ ነገ የቤተክርስቲያንን አንድነት ለብርቱ ፈተና የሚዳርግ መሆኑን መላው ኦርቶዶክሳዊ ሊያስተውል ይገባል። የፕሮቴስታንት ተሃድሶ መናፍቃን ቅድስት ቤተክርስቲያን ውስጥ ገብተው ይህንን የመሰለ ውጊያ ከፍተው እንደነበረ ሁሉ የሚያስታውሰው ነው። በዛም ወቅት ተከታይና አድናቂ የነበሩ ሰዎች "ሰባኪ እገሌና ዘማሪት እከሌን አትንኩብን ፤ ወንጌልን አስተማሩ እንጂ ምን አጠፉ?" እያሉ ቤተክርስቲያንን ያውኩ ነበረ። ዛሬ ሁሉ የት ሥፍራ እንዳለ የሚታወቅ ነው። በመንፈሳዊ ለምድ የተሸፈነውን የሰይጣንን መጀመሪያ ሳይሆን የክህደትና የጥፋት መጨረሻውን መመልከት የሚችለው በቤተ ክርስቲያን ዕቅፍ ጸንቶ በሃይማኖት የሚኖር ብቻ ነው።
የእግዚአብሔር መለኮታዊ ጥበቃ፤ የእመቤታችን አማላጅነት ፤ ቅዱሳን ቃልኪዳን ፤ የሊቃውንተ ቤተክርስቲያ የጸና ትምህርት ፥ የደጋግ አባቶቻችን ካህናት ጸሎት ፤ የእውነተኛ መምህራን ትጋት ፥ የምዕመናን ቅናት የማይለያት ቤተክርስቲያን ሆና እንጂ ዲያብሎስ የሚያስነሳቸው ፈተናዎች ቀላል የሚባሉ ሆነው አይደለም።
ይህ የሐሰተኛ አጥማቂዎች እንግዳ መንፈስና የስህተት አሠራር የንጽህይትና የቅድስት ቤተክርስቲያንን ክብር የሚጻረር ፥ ክብረ ክህነትን ጠብቀው ዘወትር በትሕርምት ሕይወት እየተመላለሱ በቤቱ ጸንተው የሚያገለግሉ አበው ካህናትን ስም የሚያስነቅፍ ፤ በየዋሃን ምዕመናን ዘንድ የእምነት መጉደልን ሊያስከትል የሚችል የሰይጣን ፈተና ነው።
በማናቸውም ፈተና እንዳንታወክና ከታነጽንበት መሠረት እንዳንናወጽ ቃለ እግዚአብሔር በብዙ ያስተምረናል። የጸኑትን እንመለከት ዘንድም ያዘናል። ከቅዱሳን ሐዋርያት መካከል የይሁዳ በክህደት መነሳትና በሠላሳ ብር አምላኩን ለመሸጥ መጨከን የሚያስተምረንም ይህንኑ ነው። የሐሳውያን መነሳት ከእምነት ለመናወጽ ምክንያት ሆኖ ሊቀርብ የሚችል ጉዳይ አይደለም።
▪
" በቤትህ የሚኖሩ ሁሉ የተመሰገኑ ናቸው"
[ መዝ.፹፬፥፬ ]
† † †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬
https://youtu.be/D2kBnAu3lpY?si=H5iJdT6ZcNG8d-Lb
Читать полностью… † † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
[ እየሆነ ያለው ይህ ነው ! ! ]
ሐሳዊ አጥማቂያን ተከታያቸውን ያደረጉትን ሕዝብ ምን ያህል እንዳጎሳቆሉት ይህንን አሳዛኝ ሁኔታ ተመልከቱ !
▪ ለሰማያዊ የልጅነት ክብር የተጠራውን ምዕመን ክርስቶሳዊነትን ከመሰለ የልዕልናና የክብር ሕይወት አውርደውት እንዴት እንዳጎሳቆሉት ተመልከቱ !
▪ ሰይጣን ምዕመኑን ከቤተክርስቲያን ፣ ከአበው ካሕናት ፣ ከሚስጥራት ፣ ከመስቀሉ ፣ ከጸበሉ ፣ ከጸሎቱ ፣ ከሥርዓቱ ሁሉ ለይቶ እራሱን በራሱ እንዴት እንዲያጎሳቁል እንዳደረጉት ተመልከቱ !
▪ኅብረታዊትና ሥርዓታዊት ከሆነች ከቅድስት ቤተክርስቲያን ነጥለውት ያለ እረኛ እንዴት እንዳስቀሩት ፣ ፕሮቴስታንታዊ መስመርን በተከተለ ግላዊ አካሔድ እንዴት ከሃይማኖት ጎዳና እያስወጡት እንዳለ ተመልከቱ !
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
[ ኦርቶዶክሳዊ የመዳን ትምህርት ]
[ በዚህ መርሐ-ግብር ኦርቶዶክሳዊ የመዳን ትምህርት ከቅዱሳት መጻሕፍት ፤ ከቅዱሳን አባቶቻችን ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን አስተምህሮ እንዲሁም ከመምህራን ትምህርቶች ላይ በየጥቂቱ ይቀርባል። እንዲሁም የተሐድሶ መናፍቃን የኑፋቄ ትምህርቶችና ምላሾቻቸው የሚቀርብ ይሆናል። ]
† † †
[ ኦርቶዶክሳዊ የመዳን ትምህርት ]
[ ክፍል ሃያ አንድ ]
[ መዳን ማለት ምን ማለት ነው ? ]
† † †
በኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ መዳን ስንል የኃጢአት ደመወዝ ከሆነው ከሞትና ከቅጣት መዳን ብቻ ፣ ወይም ከኩነኔ መዳንና ማምለጥ ብቻ አይደለም።
መዳን የኃጢአት ሥርየትን ማግኘትና ከቅጣት መዳን ብቻ ሳይሆን ከዚያ እጅግ ያለፈ ጥልቅና ሁለንተናዊ ነው:: ይህ መሠረታዊና ዋና ነገር ነው ፤ ሆኖም ግን ይህ እንዳለ ሆኖ በዚያ ላይ የተሰጡን ብዙ ጸጋዎችና ሀብታትም አሉ። ጌታችን ያደረገልን የመዳን ቸርነትና ስጦታ ስለ እኛ ተገብቶ የኃጢአታችንን ዕዳ መክፈልና እኛን ነጻ ማውጣት ብቻ አይደለም ፤ ከዚያ በላይ የሆነ እጅግ በጣም ብዙና ድንቅ ነገር ነው እንጂ። ይህን በተመለከተ ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ እንዲህ ብሏል ፦
" በአንድ ቃል ለመግለጽ መድኃኒታችን ሰው ሆኖ ለእኛ ያደረጋቸው ነገሮችና የሰጠን ጸጋዎች ብዙ ከመሆናቸው የተነሳ ሊቆጥራቸው የሚፈልግ ሰው ቢኖር የባሕርን ስፋ አይቶ ሞገዱን ለመቁጠር እንደሚፈልግ ሰው ያለ ነው። በባሕሩ ላይ ያለውን ሞገድ ሁሉንም በዓይኑ ስፍር ውስጥ ማስገባትና መቁጠር እንደማይችል ሁሉ ፣ ምክንያቱም ሞገዱ ወዲህና ወዲያ ሲል ዓይኑ አንዱን ሞገድ ሲከተል ሌላው ሁሉ እያመለጠው ኅሊናውን በተደሞ ይይዘዋልና ፤ ክርስቶስ በሥጋ ተገልጦ የሰጠንን ጸጋ ሁሉ ለመቁጠርና ለመስፈር የሚፈልግ ሰውም ሁሉንም መዘርዘርና መቁጠር ቀርቶ እንዲሁ በደፈናው ለመገመት እንኳ አይቻለውም ፤ አስቤዋለሁ ወይም ቆጥሬዋለሁ ብሎ ከሚያስበው ይልቅ ከኅሊናው ውጭና ከአእምሮው በላይ ሆኖ የሚቀረው እጅግ ብዙ ነውና። ስለዚህ የተወሰነውን እንኳ በሚገባ መናገርና መግለጽ የማይቻል ከሆነ ሁሉንም ለመናገር አለማሰብ የተሻለ ነው። "
[ በእንተ ተሠግዎተ ቃል ፣ ቁ. 54 ]
በአጠቃላይ መዳን ስንል የሚከተሉትን አራት መሠረታዊ የእግዚ ብሔር ስጦታዎችን ያጠቃልላል፡፡ እነዚህም ፦
1 ] ኃጢአት ካመጣው ፍዳ ሁሉ መዳን
2 ] ፈጣሪውን እንዲያውቅ መሆን
3 ] ሐዲስ ተፈጥሮ ፣ እና
4 ] በቅድስና [ እግዚአብሔርን በመምሰል ] ማደግ ናቸው።
ከዚህ በመቀጠል በኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ “መዳን” ስንል ምን ማለት እንደ ሆነ ፣ የእግዚአብሔር ማዳን ምን ምን ነገሮችን [ ጸጋዎችን ] እንደ ሰጠን መጀመሪያ በመጽሐፍ ቅዱስ በመቀጠልም በቀደምት ቅዱሳን አበው ትምህርት እንመለከታለን።
[ በሐሙስ መርሐ-ግብር ፦ ]
1 ] ኃጢአት ካመጣው ፍዳ ሁሉ መዳን
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
†
[ 🕊 ድምፀ ተዋሕዶ 🕊 ]
🍒▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬🍒
[ ሕይወት የሚገኝባቸው የቅድስት ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ትምህርቶች በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን በድምፅ ይቀርባሉ። ]
[ ሳምንታዊ መርሐ-ግብር ]
🕊
[ " ቅ ዱ ሳ ት መ ጻ ሕ ፍ ት ! " ]
[ ክፍል አምስት ]
" ይህን በመጀመሪያ እወቁ ፤ በመጽሐፍ ያለውን ትንቢት ሁሉ ማንም ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደም ፤
ትንቢት ከቶ በሰው ፈቃድ አልመጣምና ፥ ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ተልከው ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ተናገሩ።" [፪ጴጥ.፩፥፳]
💖 ድንቅ ትምህርት 💖
[ በመምህራችን በቀሲስ ኅብረት የሺጥላ ]
" የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ፥ ከመከራም ሥጋት ያርፋል።" [ ምሳ.፩፥፴፫ ]
† † †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬
👇
🕊
[ ኦርቶዶክሳዊ የተቀደሰ ያሬዳዊ ዝማሬ ሰዓት ]
[ ሳምንታዊ መርሐ-ግብር ]
🕊
በስመ አብ ፡ ወወልድ ፡ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን፡፡
† † †
"ሶበሰ ኪዳንኪ ምክንያተ ድኂን ኢሀሎ ፈለገ እሳት ወደይን እም አሰጠመ ኩሎ ፤
[ የድኅነት ምክንያት የሆነው ቃል ኪዳንሽ ባይኖር ኖሮ የጥፋት እሳት ፣ መርገም [ኀጢአት] ባጠፋን ነበር ] "
[ አባ ጽጌ ድንግል ]
[ 🕊 ኪዳነ ምህረት 🕊 ]
- " መታሰቢያዬን ለሚያደርጉ
- በስሜ አቢያተ ክርስቲያን ለሚሠሩ
- የተራቆተውን ለሚያለብሱ
- የተራበውን ለሚያጠግቡ
- የተጠማውንም ለሚያጠጡ
- የታመመውን ለሚጐበኙ
- ያዘነውን ለሚያረጋጉ
- የተከዘውንም ደስ ለሚያሰኙ
- ምስጋናዬን ለሚጽፉ
- ልጆቹንም በስሜ ለሚሰይም
- በበዓሌም ቀን በማኅሌት ለሚያመሰግን አቤቱ ዐይን ያላየውን ጆሮ ያልሰማውን በሰውም ልቡና ያልታሰበውን በጎ ዋጋ ስጣቸው።
በአማላጅነቴም የሚታመነውን ሁሉ ከሲኦል ነጻ አድርገው ከአንተ ጋር የደረሰብኝን ረኃቡንና ጥማቱን ፤ መከራውን ሁሉ አስብ አለችው።
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም እንዳልሽው ይሁንልሽ የሰጠሁሽም ቃል ኪዳን እንዳይታበል በራሴ ማልኩልሽ አላት።"
🕊
የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ጣዕሟን በአንደበታችን ፤ ፍቅሯን በልባችን ያሳድርልን። ጽኑ ቃል ኪዳኗ በአማላጅነቷ ከምናምን ከህዝበ ክርስቲያን ጋር ለዘላለም ጸንቶ ይኑር።
† † †
💖 🕊 💖
🕊
[ † እንኩዋን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ የኪዳን በዓል በሰላም አደረሳችሁ † ]
† ፯ [ 7 ] ቱ ኪዳናት †
'ተካየደ' ማለት 'ተስማማ: ተማማለ' እንደ ማለት ሲሆን 'ኪዳን' በቁሙ 'ውል: ስምምነት' እንደ ማለት ነው:: ይኸውም እግዚአብሔር ከሰዎች ጋር: ሰዎችም ከሰዎች ጋር የሚያደርጉት ሊሆን ይችላል:: ልዩነቱ የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ቅዱስና የማይለወጥ መሆኑ ነው::
እግዚአብሔር አምላክ ከሥነ ፍጥረት ጀምሮ በየጊዜው ከብዙ ወዳጆቹ ጋር ኪዳንን አድርጉዋል:: ቅድስት ቤተ ክርስቲያንም እነዚህን ኪዳናት ጥቅልል አድርጋ ፯ [7] እንደ ሆኑ ታስተምራለች:: ስለዚህም ዛሬ ፈጣሪ ቢረዳን እነዚሁን ፯ [7] ኪዳናት በጥቂቱ እንመለከታለን::
"ኪዳነ ተካየድኩ ምስለ ኅሩያንየ"
"ከመረጥኩዋቸው ጋር ቃል ኪዳንን አደረግሁ" [መዝ.፹፰፥፫] [88:3]
፩. " ኪዳነ አዳም "
አዳም ማለት የእግዚአብሔር ድንቅ ፍጥረት: የፍጡራን አስተዳዳሪ: ነቢይ: ካህንና ንጉሥ ነው:: እግዚአብሔር ከአዳም ጋር አስቀድሞ በእጸ በለስ አማካኝነት ቃል ኪዳን ነበራቸው:: ነገር ግን አባታችን በዲያብሎስ ሴራ በመረታቱ ኪዳኑ ፈረሰ:: [ዘፍ.፫፥፩] [3:1]
አዳምና ሔዋን ተጸጽተው ቢያለቅሱ ግን አዲስ የኪዳን ተስፋ: "ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ" የሚል ኪዳንን ተቀበሉ:: [ቀሌምንጦስ: ገላ.፬፥፬]
፪. " ኪዳነ ኖኅ "
ከአዳም እስከ ኖኅ ድረስ ባሉት ፲ [10] ትውልድ ዓለም በዓመፃ ተሞላች:: ቅዱስ ኖኅ በደግነቱ መርከብ ሠርቶ ቤተሰቡን ሲያተርፍ ዓለም በማየ ሥራዌ ጠፋች:: ከመርከቡ ከወጣ በሁዋላ ኖኅና እግዚአብሔር በቀስተ ደመና ምልክትነት ቃል ኪዳን ተጋቡ:: "ኢያማስና ለምድር ዳግመ በማየ አይኅ" እንዲል:: [ዘፍ.፱፥፲፪] [9:12]
፫. " ኪዳነ መልከ ጼዴቅ "
መልከ ጼዴቅ የእግዚአብሔር ካህኑ: የክርስቶስም ምሳሌው የሆነ የሳሌም ንጉሥ ነው:: በ፲፭ [15] ዓመቱ መንኖ: አጽመ አዳምን ይዞ: በቀራንዮ በሕብስትና በወይን ያስታኩት ነበር::
እግዚአብሔር ለመልከ ጼዴቅ: በሐዲስ ኪዳን ለምትሠራው ክህነትና ምሥጢረ ቁርባን ምሳሌ አድርጐ በቃል ኪዳን አትሞታል:: በዚህም ተሰውሮ ይኖራል እንጂ ሞትን እስካሁን አልቀመሰም:: ይህም ካህኑ መልከ ጼዴቅ ከአብርሃም ጋር በተገናኙበት ጊዜ ተገልጧል:: [ዘፍ.፲፬፥፲፯ ፣ ዕብ.፯፥፩]
፬. " ኪዳነ አብርሃም "
ቅዱስ አብርሃም የሕዝብና የአሕዛብ አባት: ሥርወ ሃይማኖት: የጽድቅም አበጋዝ ነው:: ስለ ፍቅረ እግዚአብሔር ሲል ከርስቱና ከወገኖቹ ተለይቶ በቅድስና ኑሯልና እግዚአብሔር "በዘርሕ አሕዛብ ይባረካሉ" አለው:: [ዘፍ.፲፪፥፩] የቃል ኪዳን ምልክትም ይሆነው ዘንድ ግዝረትን ሰጠው:: [ዘፍ.፲፯፥፩-፲፬]
፭. " ኪዳነ ሙሴ "
ቅዱስ ሙሴ የነቢያት አለቃ: የእሥራኤል እረኛ: የእግዚአብሔር ሰው እና ፍጹም ትሑት [የዋህ] ሰው ነው:: በፈጣሪው ትዕዛዝ እሥራኤልን ከግብጽ ባርነት አውጥቶ ለ፵ [40] ዘመናት በበርሃ ሲመራቸው ከእግዚአብሔር የኪዳንን ጽላትና አሠርቱን ትዕዛዛት ተቀብሏል:: [ዘጸ.፳፥፩ 20:1, ፴፩፥፲፰ (31:18)]
፮. " ኪዳነ ዳዊት "
ቅዱስ ዳዊት ሥርወ ነገሥት: ጻድቅ: የዋህና ቡሩክ የሆነ አባት ነው:: እግዚአብሔር ከእረኝነት ጠርቶ ንጉሥ አድርጐ ሹሞት "ከሆድህ ፍሬ በዙፋንህ ላይ አኖራለሁ" [መዝ.፻፴፩፥፲፩] [131:11] ሲል ምሎለታል:: አክሎም ሰፊ ቃል ኪዳን ሰጥቶ "አልዋሰሽህም" ብሎ ሲምልለት እንመለከታለን:: [መዝ.፹፰፥፴፭]
፯. " ኪዳነ ምሕረት "
በብሉይ ኪዳን የነበሩ ፮ [6] ቱ ኪዳናት በዘመናቸው ክቡርና ሕዝቡን ከመቅሰፍት ይታደጉ የነበሩ ቢሆንም ከሲዖል ማዳን ግን አልቻሉም:: ስለዚህም አንድ ፍጹም ኪዳን ያስፈልግ ነበር:: ይህን ፍጹም ኪዳን ይፈጽም ዘንድም ከቅድስት ሥላሴ አንዱ ወልድ ከሰማያት ወርዶ በድንግል ማርያም ማሕጸን አደረ::
በፍጹም ተዋሕዶም በሕቱም ድንግልና ተወልዶ: አድጎ: ተጠምቆ: አስተምሮ: ሙቶ: ተነስቶና ዐርጐ ሥጋ ማርያምን በዘባነ ኪሩብ አስቀመጠው:: ኪዳነ ምሕረት [የምሕረት ኪዳን] የምንለው አንዱ ታዲያ ይሔው ነው::
የጌታችን መጸነሱ: መወለዱ: መሰደዱ: መጠመቁ: ማስተማሩ: ሥጋውንና ደሙን መስጠቱ: መሰቀሉ: መሞቱና መነሳቱ: ማረጉና መንፈስ ቅዱስን መላኩ በአንድ ላይ ኪዳነ ምሕረት ይባላል:: ታዲያ ይህ ሁሉ የተደረገው በሥጋ ማርያም ነውና የኪዳኑ ባለቤት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት::
የእርሷ ኪዳን ፮ [6] ቱን አበው ኪዳናት ፍጹም በማድረጉ የኪዳናት ማሕተም ይባላል:: የድንግል ማርያም ኪዳኗ ከሲዖልና ከገሃነም ሊታደገን አቅሙ አለውና:: መድኃኒታችን ክርስቶስ ለድንግል እናቱ ቃል ኪዳኑን ያጸናላት ደግሞ ካረገ ከዓመታት በሁዋላ ጐልጐታ ላይ ነው::
እመ ብርሃን በዚያ ቁማ ስለ ኃጥአን ስታለቅስ "እናቴ ሆይ! በስምሽ ያመነውን: በቃል ኪዳንሽ የተማጸነውን እምርልሻለሁ" ብሎ ደስ አሰኝቷታልና:: ይሔው በእመ ብርሃን ምልጃና ቃል ኪዳን ምዕመናን ከመቅሰፍትና ከገሃነመ እሳት ማምለጥ ከጀመሩ ፪ [2] ሺ ዓመታት ሆኑ:: ዛሬም እኛ ኃጥአን ልጆቿ ከእሳት እንደምታድነን አምነን በጥላዋ ሥር እንኖራለን::
" ኢትዝክሪ ብነ አበሳነ: ኃጢአተነ: ወጌጋየነ:
ማርያም እሙ ለእግዚእነ:
በኪዳንኪ: ወበስደትኪ ድንግል ተማሕጸነ::"
"ድንግል ሆይ! ኃጢአታችን: አበሳችንና በደላችንን አታስቢብን ዘንድ በስደትሽና በኪዳንሽ ተማጽነናል::"
የአርያም ንግሥት: የሰማያውያንና ምድራውያን ኁሉ እመቤት: የአምላክ እናት: ቅድስት: ስብሕት: ክብርት: ልዕልት: ቡርክት: ፍስሕትና ጥዕምት የሆነች ድንግል ማርያም የድኅነታችን መሠረት: ላመኑባት አንገት የማታስደፋ እውነተኛ አማላጅ ናት::
በዚህች ዕለት የካቲት ፲፮ [16] ስለ ወገኖቿ የሰው ልጆች ፍቅር በእንባ ያቀረበችውን ልመና የባሕርይ አምላክ የሆነ ልጁዋ ተቀብሎ በማይዋሽ ንጹሕ አንደበቱ ቃል ኪዳን ገብቶላታል:: በስምሽ ያመነ በቃል ኪዳንሽ የተማመነ እሳት አያይም ብሏታል::
ቸሩ ልጇ ከበረከተ ኪዳኗ አይለየን:: በዓሉንም የሰላም: የፍቅርና የበረከት ያድርግልን::
🕊
[ † የካቲት ፲፮ [ 16 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ኪዳነ ምሕረት [የሰባቱ ኪዳናት ማሕተም]
፪. ቅድስት ኤልሳቤጥ [የመጥምቁ ዮሐንስ እናት / የእመቤታችን አክስት / የሶፍያ ልጅ]
፫. ቅዱስ ገብረ ማርያም ጻድቅ ንጉሠ ኢትዮዽያ [የቅ/ላሊበላ ወንድም]
[ † ወርኀዊ በዓላት ]
፩. ቅዱስ አኖሬዎስ ንጉሥ ጻድቅ
፪. አባ አቡናፍር ገዳማዊ
፫. አባ ዮሐንስ ወንጌሉ ዘወርቅ
፬. አባ ዳንኤል ጻድቅ
" . . . ኤልሳቤጥም የማርያምን ሰላምታ በሰማች ጊዜ ፅንሱ በማኅፀንዋ ውስጥ ዘለለ:: በኤልሳቤጥም መንፈስ ቅዱስ ሞላባት:: በታላቅ ድምፅም ጮኻ እንዲህ አለች:- አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ: የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው:: የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል? እነሆ የሰላምታሽ ድምፅ በጀሮየ በመጣ ጊዜ ፅንሱ በማኅፀኔ በደስታ ዘሎአልና:: ከጌታ የተነገረላት ቃል ይፈፀማልና ያመነች ብፅዕት ናት::" [ሉቃ.፩፥፴፱]
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖 🕊 💖
†
🕊 የአባቶቻችን የእምነት ቃል 🕊
💖
“ ክርስትያን ተብዬ ብቻ መጠራት የምፈልግ አይደለሁም ፤ ይልቁንም መሆንን እፈልጋለሁ ... ስጋዬን ለአውሬዎች ይስጡት በአውሬዎቹም ጥርስ ልፈጭ ፤ ንጹህ የክርስቶስ ህብስት ሆኜ ልገኝ ፤ ከአካሌም ምንም አያስቀሩ ፣ ምናልባት ለእናንተ ሥራ እንዳልሆንባችሁ፡፡ "
[ ቅዱስ አግናጥዮስ ዘአንጾክያ ለአራዊት ሊሰጥ ለሰማእትነት እየሄደ ሳለ ለሮሜ ሰዎች ከላከው መልእክት ]
† † †
💖 🕊 💖
†
እግዚአብሔር ያጽናናሽ ቅድስት ቤተክርስቲያን !
† † †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬
🕊
† እንኳን ለታላቁ ነቢይ ቅዱስ ዘካርያስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †
🕊 † ቅዱስ ዘካርያስ ነቢይ † 🕊
† ነቢይ ማለት በቁሙ ኃላፍያትን [አልፎ የተሠወረውን ምሥጢር] : መጻዕያትን [ገና ለወደ ፊት የሚሆነውን] የሚያውቅ ሰው ማለት ነው:: ሃብተ ትንቢት የእግዚአብሔር የባሕርይ ገንዘቡ ሲሆን እርሱ ለወደደው ደግሞ በጸጋ ይሰጠዋል:: እነዚህም ከጌታ ሃብተ ትንቢት የተሰጣቸው አባቶችና እናቶች "ቅዱሳን ነቢያት" በመባል ይታወቃሉ::
ዘመነ ነቢያት ተብሎ የሚታወቀው ብሉይ ኪዳን ቢሆንም እስከ ምጽዓት ድረስ ጸጋውን እግዚአብሔር ለፈቀደላቸው አይነሳቸውም:: በሐዋርያት መካከልም ቅዱስ አጋቦስን የመሰሉ ነቢያት ነበሩ:: [ሐዋ.፲፩፥፳፯] ቅዱሳን ነቢያት ከእግዚአብሔር እየተላኩ ሰውን ከፈጣሪው እንዲታረቅ ይመክራሉ: ይገስጻሉ::
ከበጐ ሃይማኖታቸውና ንጽሕናቸው የተነሳም እግዚአብሔርን በተለያየ አርአያና አምሳል አይተውታል::
"እስመ በአንጽሖ መንፈስ ርዕይዎ ነቢያት ለእግዚአብሔር : ወተናጸሩ ገጸ በገጽ::" እንዳለ አባ ሕርያቆስ:: [ቅዳሴ ማርያም]
የብዙ ነቢያት ፍጻሜአቸው መከራን መቀበል ነው:: እውነትን ስለ ተናገሩ: አንዳንዶቹም በእሳት: አንዳንዶቹም በሰይፍ: አንዳንዶቹም በመጋዝ ተፈትነዋል:: ሌሎቹ ለአናብስት ሲጣሉ ቀሪዎቹ ደግሞ በድንጋይ ተወግረዋል::
ስለዚህም መከራቸው ለቤተ ክርስቲያን መሠረት ተብለዋል:: ጌታም ለደቀ መዛሙርቱ "ሌሎች ደከሙ:: እናንተ በድካማቸው ገባችሁ::" ብሎ የነቢያቱን መከራ ተናግሯል:: [ዮሐ.፬፥፴፮]
ነቢያት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን እና ድንግል እናቱን ለማየት ብዙ ጥረዋል:: ሽተዋልም:: "ብዙ ነቢያትና ጻድቃን እናንተ የምታዩትን ሊያዩ ሹ" እንዳለ ጌታ በወንጌል:: [ማቴ.፲፫፥፲፮, ፩ጴጥ.፩፥፲] ዛሬ ግን በሰማያት ጸጋ በዝቶላቸው: ክብር ተሰጥቷቸው ሐሴትን ያደርጋሉ::
ቅዱሳን ነቢያት በዋነኝነት "አሥራ አምስቱ አበው ነቢያት" : "አራቱ ዐበይት ነቢያት" : "አሥራ ሁለቱ ደቂቀ ነቢያት" እና "ካልአን ነቢያት" ተብለው በ4 ይከፈላሉ::
† "አሥራ አምስቱ አበው ነቢያት" ማለት :-
፩. ቅዱስ አዳም አባታችን
፪. ሴት
፫. ሔኖስ
፬. ቃይናን
፭. መላልኤል
፮. ያሬድ
፯. ኄኖክ
፰. ማቱሳላ
፱. ላሜሕ
፲. ኖኅ
፲፩. አብርሃም
፲፪. ይስሐቅ
፲፫. ያዕቆብ
፲፬. ሙሴ እና
፲፭. ሳሙኤል ናቸው::
† " አራቱ ዐበይት ነቢያት "
፩. ቅዱስ ኢሳይያስ ልዑለ ቃል
፪. ቅዱስ ኤርምያስ
፫. ቅዱስ ሕዝቅኤል እና
፬. ቅዱስ ዳንኤል ናቸው::
† " አሥራ ሁለቱ ደቂቀ ነቢያት "
፩. ቅዱስ ሆሴዕ
፪. አሞጽ
፫. ሚክያስ
፬. ዮናስ
፭. ናሆም
፮. አብድዩ
፯. ሶፎንያስ
፰. ሐጌ
፱. ኢዩኤል
፲. ዕንባቆም
፲፩. ዘካርያስ እና
፲፪. ሚልክያስ ናቸው::
† " ካልአን ነቢያት " ደግሞ :-
- እነ ኢያሱ
- ሶምሶን
- ዮፍታሔ
- ጌዴዎን
- ዳዊት
- ሰሎሞን
- ኤልያስ እና
- ኤልሳዕ . . . ሌሎችም ናቸው::
† ነቢያት በከተማም ይከፈላሉ::
- የይሁዳ [ ኢየሩሳሌም ] :
- የሰማርያ [ እሥራኤል ] እና
- የባቢሎን [ በምርኮ ጊዜ ] ተብለው ይጠራሉ::
† በዘመን አከፋፈል ደግሞ :-
- ከአዳም እስከ ዮሴፍ [ የዘመነ አበው ነቢያት ] :
- ከሊቀ ነቢያት ሙሴ እስከ ነቢዩ ሳሙኤል [ የዘመነ መሳፍንት ነቢያት ]
- ከቅዱስ ዳዊት እስከ ዘሩባቤል ያሉት [ የዘመነ ነገሥት ነቢያት ] :
- ከዘሩባቤል ዕረፍት እስከ መጥምቁ ዮሐንስ ያሉት ደግሞ [ የዘመነ ካህናት ነቢያት ] ይባላሉ::
† ስለ ቅዱሳን ነቢያት በጥቂቱ ይህንን ካልን ወደ ዕለቱ በዓል እንመለስ::
† ቅዱስ ዘካርያስ ቁጥሩ ከአሥራ ሁለቱ ደቂቀ ነቢያት ሲሆን ዘመነ ትንቢቱም ቅ/ል/ክርስቶስ በ፬፻፶ [450] ዓ/ዓ አካባቢ ነው:: "ደቂቀ ነቢያት" ማለት በጥሬው "የነቢያት ልጆች" ማለት ነው:: አንድም የጻፏቸው ትንቢቶች ሲበዙ ፲፬ [14] ምዕራፍ: ሲያንስ አንድ ምዕራፍ ያላቸው ናቸውና ደቂቅ ይላቸዋል::
† ነቢዩ ቅዱስ ዘካርያስ :-
- ከክርስቶስ ልደት ፬፻፶ [450] ዓመታት በፊት የነበረ::
- በጻድቅነቱ የተመሰከረለት::
- ፲፬ [14] ምዕራፎች ያሉት ሐረገ - ትንቢት የተናገረ::
- ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የማዳን ሥራ በስፋት የተነበየ ነቢይ ሲሆን ከአሥራ ሁለቱ ደቂቀ ነቢያትም አንዱ ነው::
† የአባታችን በረከት ይደርብን::
🕊
[ † የካቲት ፲፭ [ 15 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ቅዱስ ዘካርያስ ነቢይ [ከአሥራ ሁለቱ ደቂቀ ነቢያት አንዱ]
፪. ቅዱስ አባ በፍኑትዮስ ገዳማዊ [ከጻድቅነቱ ባሻገር በግብጽ በርሃ የሚኖሩ የብዙ ቅዱሳንን ዜና ሕይወት የጻፈ አባት ነው::]
፫. ቅዱሳን አርብዐ ሐራ ሰማይ [፵ [40] የሰማይ ጭፍሮች] ለ፵ [40] ቀናት ሰብስጥያ በምትባል ሃገር መከራ ተቀብለው በሰማዕትነት ያለፉ ክርስቲያን ጓደኛሞች::
[ † ወርኀዊ በዓላት ]
፩. ቅዱስ ቂርቆስና እናቱ ኢየሉጣ
፪. ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ [አፈ በረከት]
፫. ቅዱስ ሚናስ ግብጻዊ
፬. ቅድስት እንባ መሪና
፭. ቅድስት ክርስጢና
† ". . . የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል:: 'ወደ እኔ ተመለሱ . . . እኔም ወደ እናንተ እመለሳለሁ::' " † [ዘካርያስ ፩፥፫]
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖 🕊 💖
†
[ ል ዩ መርሐ - ግ ብ ር ]
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በሰሜን ካሊፎርኒያ ኒቫዳ አሪዞና ሀ/ስብከት በሐሳዊ አጥማቂያን ተዘጋጅቶ የነበረው ኢ-ኦርቶዶክሳዊ ሐሰተኛ የፈውስ ቀጠሮ በሀገረ ስብከቱ ውሳኔ ተሰርዟል !
- በተደጋጋሚ ጊዜ በአሜሪካን ሀገር በሚሊየነሩ አጥማቂ ነኝ ባይ ግለሰብና የመንፈሱ ወራሽ በሆነው በልጁ ሲፈጸም በነበረው አጋንንታዊ ልምምድና በኦርቶዶክሳውያን ላይ የሚፈጸመው የሚሊየን ዶላሮች ዝርፊያ መቋጫ ያገኘ ይመስላል።
በዛሬው ዕለት ፦
▷ መልአከ ስብሐት አባ ኃ/ኢየሱስ ገሠሠ የሰሜን ካሊፎርኒያ ኒቫዳ አሪዞና ሀ/ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና
▷ መላከ ገነት ቀሲስ ጥላሁን አበበ በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው ሀገረ ስብከት የስብከተ ወንጌል ሃላፊ
በጉዳዩ ዙሪያ ለሰማያት ሚዲያ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
እነሆ ቀርቧል ይከታተሉ።
† † †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬
👇
በአሁኑ ሰዓትም ታጣቂዎቹ ወደ ገዳሙ ለመግባት እንቅስቃሴ የሚያደርጉበት መንገድ እንዳይኖርና መናንያኑና የገዳሙ ቅርስ አደጋ ላይ እንዳይወድቁ የፌዴራልና የክልሉ የጸጥታ አካላት ገዳማዊያኑንና ገዳሙን የመታደግ ሥራ እንዲሠሩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከአደራ ጭምር መልዕክቷን ታስተላልፋለች።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን
መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት
የካቲት ፲፬ቀኝ ፳፻ ፲ወ፮ ዓ.ም
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
በእደ ገብሩ ካህን ከመ ይባርከነ✅
በእደ ገብሩ ቆሞስ፣ በእደ ገብሩ መምህር፣ በእደ ብፁዕ ሊቀጳጳስነ፣ በእደ ክቡር መምህር❎
+++++
(መ/ር ኀይለ ማርያም ዘውዱ ዘቦሩ ሜዳ)
ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በልክ እና በመልክ የተሠራ ሥርዓተ አምልኮ አላት፤ ሦስት መዓርጋተ ክህነትም አላት:: እነርሱም
1 ድቁና፣
2 ቅስና፣
3 ጵጵስና
ለእነዚህ ለእያንዳንዳቸው በፍጹም ትሕትና ሁነው የሚያገለግሉባቸው መደቦች አሏቸው። ወደሰፊው ዝርዝር ሳልገባ ወተነሣሁበት ርእስ ለመመለስ ላሳጥረው።
የዲያቆናት አገልግሎት ተልዕኮ እና ማስተማር፤
የቀሳውስት ማስተማር ማጥመቅ ማቁረብ መናዘዝ መባረክ፤ የጳጳሳት ማስተማር ማጥበቅ ማቁረቡ መናዘዝ መባረክ ሌሎችን መሾም ነው። ምእመናን ደግሞ ተሠጥዎ አላቸው መቀበል ማለት ነው።
ቄሱ ወይም ጳጳሱ ሊለው ከሚገባው ቦታ ላይ መጽሐፉ "ይበል ካህን/ይካ" ይላል። ዲያቆኑ ሊለው የሚገባው ቦታ ላይ "ይበል ዲያቆን/ይዲ" ይላል። ምእመናን በሚቀበሉበት ቦታ ላይ "ይበሉ ሕዝብ/" ይላል።
አገልግሎቱ የሚመራው በዚህ ነው። አሁን አሁን ግን በከተሞች አካባቢ የምንሰማው ነገር መንፈሳዊ አገልግሎት መሆኑ ቀርቶ መሞጋገሻ አስመስሎታል።
"አድንኑ አርእስቲክሙ ቅድመ እግዚአብሔር አምላክነ በእደ ገብሩ ካህን ከመ ይባርከነ፤"
ትርጉም፦
"በአገልጋዩ በካህኑ እጅ ይባርከን ዘንድ በአምላካችን በእግዚአብሔር ፊት ራሳችሁን ዝቅ ዝቅ አድርጉ" በሚለው ቦታ ላይ አንዳንዱ ያልተጻፈውን "በእደ ብፁዕ ሊቀ ጳጳስ ከመ ይባርከነ" ይላል። ለጳጳሳቱኮ "ገብረ እግዚአብሔር" መባል ታላቅ ክብር ነው። እነ ቅዱስ ጴጥሮስን፣ እነ ቅዱስ ጳውሎስን "ገብሩ ወሐዋርያሁ" የምንል ሰዎች ገና በምድር ያሉ ጳጳሳትን "ገብሩ" ብንላቸው ያከብራቸዋል እንጂ አያዋርዳቸውም።
እመቤታችንም "ነየ አመተ እግዚአብሔር የእግዚአብሔር አገልጋዩ እነሆኝ" ነው ያለችው።
መጽሐፉም "ይካ" ይላል እንጂ "ይጳ፣ ይቆ፣ ይመ" አይልም።
ጳጳስም ቆሞስም ቄስም ካህናት ናቸው። በእደ ገብሩ ካህን የሚለው ያጠቃልላቸዋል፤ ስማቸው ነው።
ቀጠለና ደግሞ "በእደ ክቡር ቆሞስ" ማለት ተጀመረ:: ይህንን ሳናስተካክል ዝም ስንል ጊዜ ቀሳውስቱ አለቆች የኛስ ለምን ይቅርብን ብለው "በእደ ክቡር መምህር" ማስባል ጀምረዋል። በመሠረቱ መምህር የሙያ ስም እንጂ የክህነት ስም አይደለም።
ስለዚህ እባካችሁ ዲያቆናቱም "በእደ ገብሩ ካህን" በሉ:: አባቶችም "በእደ ገብሩ ካህን" መባል ታላቅ ክብር ስለሆነ ሌላ ነገር የሚጨማምሩ ልጇቻችሁን ገሥጿቸው።
(መ/ር ኀይለ ማርያም ዘውዱ ዘቦሩ ሜዳ)
+• ጊዜው ገና ነው •+
አንድ ምንጩ የማይታወቅ አስተማሪ የሆነ አፈ-ታሪክ አለ። በዚህ አፈ-ታሪክ መሠረት፥ ከእለታት በአንዱ ቀን አጋንንት ስብሰባ አደረጉ ይባላል። ይህንን ስብሰባ የጠራው የአጋንንቱ አለቃም “ዓለምን ሁሉ ከእኔ ጋር ለማሰለፍ እፈልጋለሁ። ምን ይደረግ? ማንንስ ልላክ?” ብሎ ጠየቀ። ከሥሩ ያሉትም አንድ በአንድ እየተነሱ አሳቦችን ማቅረብ ጀመሩ።
አንዱ ተነሳና፥ “እኔን ብትልከኝ፥ ፈጣሪ የለም ብዬ ሰዎችን ማሳመን እችላለሁ!” ብሎ ተናገረ። የአጋንንቱ አለቃ ግን፥ “እርሱ አይሠራም። ብዙዎቹ አያምኑህም። ፈጣሪ እንዳለ ያውቃሉ።” ብሎ መለሰ።
ሌላኛው ተነሳና፥ “እኔን ከላክኸኝ፥ ገነትም ሆነ ሲኦል የሚባል ቦታ እንደሌለ አሳምናቸዋለሁ!” አለ። የአጋንንቱ አለቃ ግን፥ “እርሱም አይሠራም። ብዙዎቹ ከሞት በኋላ ሕይወት እንዳለ ያውቃሉ።” ብሎ መለሰ።
ሌላው ደግሞ ተነሳና፥ “እኔን ላከኝ። ፈጣሪም አለ፥ ገነትም አለ፥ ሲኦልም አለ፤ ነገር ግን ስለዚህ ነገር ሁሉ ለማሰብ ጊዜው አሁን አይደለም ብዬ አሳምናቸዋለሁ።” አለ። የአጋንንቱ አለቃም ደስ እያለው “ይህ ጥሩ መንገድ ነው!” በማለት አሳቡን ተቀበለና ላከው ይባላል።
ሰይጣን ማዘግየት ጥሩ ስልት መሆኑን ስለሚያውቅ፥ ለማዘግየት ይፋጠናል። በሐዲስ ኪዳን ላይ ቅዱስ ጳውሎስ "ወደ እናንተ ልንመጣ ወደን ነበርና፥ እኔ ጳውሎስም አንድና ሁለት ጊዜ፥ ሰይጣን ግን አዘገየን።” (1 ተሰ 2:18) ሲል እናገኘዋለን። ሰይጣን ላያስቀረን ይችላል፥ ግን ቢያንስ ሊያዘገየን ብዙ ይሞክራል።
እርሱ ዓለማዊ ጓዞቻችንን ለአፍታ ስንኳ አውርደን ከእግዚአብሔር ጋር ስላለን ግንኙነት እንድናስብ አይፈልግም። ስለ ጸሎት ብታስብ፥ "አሁን ደክሞሃል። ጊዜው አይደለም። ሌላ ጊዜ ትጸልያለህ" ይልሃል። ለመጾም ብትዘጋጅ "አሁን ጉልበት ስለሚያስፈልግህ ብላ። የምትጾምበት ጊዜ አይደለም፤ ሌላ ጊዜ ትጾማለህ።" ይልሃል። ለመስገድ ብትዘጋጅ "ኧረ ተረጋጋ፤ ጊዜው አይደለም፥ ጾም ሲገባ ትሰግዳለህ" ይልሃል። ንስሃ ልትገባ ብትዘጋጅ "ቆይ እንጂ፥ ዘልለህ ጨርሰህ አንዴ ብትታጠበው አይሻልም?" ለማለት የሚቀድመው የለም። ቅዱስ ቁርባን ልቀበል ነው ካልክ "አንተኮ ገና ነህ፥ ለወደፊት ጣጣህን ስትጨርስ ቀስ ብለህ አመቻችተህ ትቆርባለህ" ብሎ ያዘናጋሃል።
በዚህ ሁሉ መዘግየት ውስጥ መልአከ ሞት መቼ እንደሚመጣ ማን ያውቃል? ለመንፈሳዊ ነገር ስንነሳ፥ ሰይጣን "ጊዜው ገና ነው" ማለቱ አይቀርም። እኛ ደግሞ የእግዚአብሔር ቃል“ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤ እነሆ፥ የመዳን ቀን አሁን ነው።” (2ኛ ቆሮ 6፥2) እንደሚል እናስታውስ። ለመዳናችን ቀጥሮ አንስጥ።
ውብ አሁን
💛
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
🕊 ፍኖተ ተዋሕዶ 🕊
[ ዘወትር ረቡዕ ምሽት ]
የቅዱሳን አበው ሕይወት ፣ ድንቅ ተዓምራትና ምስክርነቶች ፣ መንፈሳዊ ትረካዎች ፣ መንፈሳዊ የኪነ-ጥበብ ዝግጅቶች ፣ አስደናቂ ምስጢራትና ከምዕመናን ለቀረቡ ጥያቄዎች አስደናቂ የሊቃውንት ምላሽ ፣ ኦርቶዶክሳዊ ማዕቀፈ እሳቤ በመ/ር ፋንታሁን ዋቄ የተሰጡ ተከታታይ አስደናቂ ትምህርቶችና የመሳሰሉት ዝግጅቶች በድምጽ ይቀርባሉ።
ይከታተሉ !
------------------------------------------
[ ከምዕመን የቀረበ ጥያቄ ! ]
▷ " ካለብኝ ህመም ከተፈወስኩኝ ወደ እነዚህ ግለሰቦች ብሔድ ምን ችግር አለው ! "
- " ጹሙ ጸልዩ ፣ ስገዱ ፣ ንስሐ ግቡ ስለሚሉ ይህንን ከነሱ ብማርስ ? "
▷ ምላሽ !
[ በቀሲስ ኅብረት የሺጥላ ]
† † †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬
👇
†
[ ተዋሕዶ ፍጽምት የቅዱሳን ሃይማኖት ]
▬▬▬▬▬▬ † ▬▬▬▬▬▬
[ መክፈል ክሕደት ነውና ! ]
--------------------------------------------------
" አንድ አካል ፤ አንድ ባሕርይ ብለው የሚያምኑ ግን በክሕደት አይያዙም፡፡
ሁለት አካል ፥ ሁለት ባሕርይ ብለው የሚያምኑ ፤ ለአንዱ እንዲሰግዱ ፥ ለአንዱ እንዳይሰግዱ በመለኮት ባሕርይ እንዲጠመቁ ፥ በሥጋ ባሕርይም እንዳይጠመቁ ግድ ይሆንባቸዋል።
በጌታችን ሞት የምንከብር ከሆነ እምነታችን በሚታመም ትስብእትና በማይታመም መለኮት አንድ ባሕርይ ይሆናል፡፡ መክበራችን እንዲህ በእግዚአብሔር ይሆን ዘንድ በጌታችን ሞትም ፍጹማን እንሆናለን። [ሮሜ.፮፥፫-፬]
ጌታችንን ወደ ሁለት አካል የሚለዩ ሰዎች ቢነቅፉን ፥ በወንጌል ያለ በሐዋርያት ቃል የተነገረ ተዋሕዶን በምንናገርበት ጊዜም እግዚአብሔር ያጻፋቸው መጻሕፍትን ተመልክተን ወልድ ከሰማይ እንደ ወረደ በተናገርነ ጊዜ ፦ 'ሥጋ ከሰማይ ወረደ' ይላሉ ብለው ፤ ዳግመኛም የእግዚአብሔር ልጅ ከድንግል እንደ ተወለደ በተናገርን ጊዜ ፦ 'ቃል ከድንግል ተገኘ ይላሉ' ብለው በመለኮቱ ከአብ የተገኘ አይደለም እንደምንል መስሏቸው ቢያሙን አንፍራ። [ዮሐ.፩፥፲፬ ፣ ገላ.፬፥፩]
እኛ ግን ስለ መለኮት ስንናገር ወልድ ከሰማይ እንደ ወረደ እንናገራለን፡፡ ዳግመኛም ስለ ትስብእት ስንናገር ሁለተኛው ከድንግል እንደ ተወለደ እንናገራለን፡፡ አንዱ አካል ሁለት መሆኑን አናውቅም።
ሰማያዊ መለኮትን ከምድራዊ ሥጋ ፤ ምድራዊ ሥጋንም ከሰማያዊ መለኮት አንለየውም፡፡ መክፈል ክሕደት ነውና፡፡ ሁለት አካል ሁለት ባሕርይ ለሚሉ ሰዎች ለመለየት ምክንያት አንስጣቸውም፡፡ "
[ አቡሊዲስ ]
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፤ ወለወላዲቱ ድንግል ፤ ወለመስቀሉ ክቡር። አሜን።
† † †
💖 🕊 💖
🕊
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ †
[ ❖ የካቲት ፲፫ [ 13 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
🕊 † ማር ፊቅጦር † 🕊
ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን በደማቸውና በገድላቸው ያስጌጡ ብዙ ሰማዕታት አሉ:: ነገር ግን ከኮከብም ኮከብ ይበልጣልና ማን እንደ ጊዮርጊስና እስጢፋኖስ ! ከእነርሱ ቀጥለው ከሚጠሩ ሰማዕታት ደግሞ አንዱና ዋነኛው ቤተ ክርስቲያን "ማር" የምትለው ቅዱስ ፊቅጦር ነው::
እስኪ ከበዛው መዓዛ-ገድሉ ጥቂት እንካፈል :-
- ቅዱስ ፊቅጦር አባቱ ኅርማኖስ ይባላል:: አረማዊና ጨካኝ ነው:: እናቱ ግን የተመሰገች ቅድስት ማርታ ትባላለች:: ልጇን እንደሚገባ አሳድጋው ፳ [ 20 ] ዓመት ሲሞላው የአንጾኪያ ንጉሥ የሠራዊት አለቃና በመንግሥቱ ፫ [3] ኛ አድርጐ ሾመው::
የድሮዋ አንጾኪያ [ሮም] እንደ ዛሬዋ አሜሪካ ዓለምን የተቆጣጠረች ሃገር ነበረች:: ቅዱስ ፊቅጦር ደም ግባቱ ያማረ: በጦርነትም ኃይለኛ ስለ ነበር ሁሉ ያከብሩት: ይወዱትም ነበር::
እርሱ ግን ቀን ቀን ሲጾም: ነዳያንን ሲያበላ ይውል ነበር:: ሌሊት ደግሞ እኩሉን ሲጸልይና ሲሰግድ እኩሉን የእስረኞችን እግር ሲያጥብ ያድር ነበር:: ይህ ሁሉ ሲሆንኮ እርሱ የንጉሡ ፫ [3] ኛ : የሠራዊትም አለቃ ነው:: በዘመኑ የሚያገድፍ ምግብና የወይን ጠጅ በአፉ ዙሮ አያውቅም::
ከነገር ሁሉ በሁዋላ ንጉሡ ዲዮቅልጢያኖስ ካደ:: ዘመነ ሰማዕታትም ጀመረ:: አብያተ ክርስቲያናት ተቃጠሉ:: ከ፵፯ [47] ሚሊየን በላይ ክርስቲያኖች በመንኮራኩር ተፈጩ:: በመጋዝ ተተረተሩ:: ለአራዊት ተሰጡ:: በግፍም ተጨፈጨፉ:: ቀባሪ አጥተውም ወደቁ::
በዚሕ ጊዜ ማር ፊቅጦር እናቱን ቅድስት ማርታን በዕንባ ተሰናብቶ ወደ ንጉሡ ቀርቦ በክርስቶስ ስም ታመነ:: ክፉ አባትም በልጁ ላይ ሞትን መከረ::
ከዚያም ቅዱሱን አፉን በብረት ለጉመው ወደ ምድረ ግብፅ አወረዱት:: መሪያቸው እንዳልነበረ ወታደሮቹ መኩዋንንቱ ሁሉ ተዘባበቱበት:: እርሱ ከምድራዊ ንግሥና ሰማያዊ መንግስትን: በሰዎች ፊት ከመክበር ስለ ክርስቶስ ሲል መናቅን መርጧልና::
ለቀናት : ለወራትና ለዓመታት መኩዋንንቱ እየተፈራረቁ አሰቃዩት:: በርሱ ላይ ያልሞከሩት የስቃይ ዓይነት አልነበረም:: አካሉን ቆራርጠዋል: ዓይኖቹን አውጥተዋል: ምላሱንም ቆርጠዋል:: ሚያዝያ ፳፯ [ 27 ] ቀን ግን በሰይፍ አንገቱን ቆርጠውታል:: ስለዚህም እናት ቤተ ክርስቲያን በታላቅ ማክበር ታከብረዋለች::
❖ እግዚአብሔርም ለቅዱስ ፊቅጦር እንዲህ አለው :-
" እንደ አቅሙ ስምህን የጠራ: መታሠቢያህን ያደረገ : ስምህን ያከበረ: የብርሃን ልብስ አጐናጽፌ ወደ መንግስተ ሰማያት አስገባዋለሁ::"
❖ ይህች ቀን ማር ፊቅጦር የተወለደባት ናት፡፡ እናቱን ቅድስት ማርታ [ ሶፍያንም ] እናስባለን፡፡
❖ ቸሩ አምላከ ፊቅጦር ሁላችንም ይማረን:: ከቃል ኪዳኑ አሳትፎ ለርስቱ ያብቃን::
✞ 🕊 ቅዱስ አውሳብዮስ ካልዕ [ጥዑመ ዜና] 🕊 ✞
ቅዱስ አውሳብዮስ በወጣትነቱ ከተባረከች ሚስቱ ጋ በድንግልና የኖረ ፥ በዘመኑ ባሕር ውስጥ ሰጥሞ ይጸልይ ፥ ፬ ሺህ [4,000] አቡነ ዘበሰማያት በአንድ ቀን ያደርስ የነበረ : ስለ ሃይማኖትም በቀስት የተወጋ : በእሳት የቃጠለ : አካሉን ቆራርጠው የጣሉትና እግዚአብሔር ከሞት ያስነሳው ጻድቅና ሰማዕት ነው:: ከዚህ ሁሉ ነገር በኋላ ከነሥጋው ወደ ሰማይ ተነጥቆ ለ፲፬ [14] ዓመታት ቆይቷል:: ወደ ምድርም ተመልሶ ለ፵ [40] ዓመታት በሐዋርያነት ከ፹፭ ሺህ [85,000] በላይ አሕዛብን ወደ ሃይማኖት መልሷል:: ጌታም በስምህ የተማጸነውን እስከ ፯ [7] ትውልድ እምርልሃለሁ ብሎታል::"
❖ አባቶቻችን ደግሞ 'ስም አጠራሩ የከበረ ዜና ሕይወቱ ያማረ' ሲሉ ይጠሩታል::
❖ ከበረከቱ ያድለን::
[ ✞ የካቲት ፲፫ [ 13 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ቅዱስ አውሳብዮስ ጻድቅ [ ጥዑመ ዜና ]
፪. ቅዱስ ፊቅጦር ሰማዕት [ ልደቱ ]
፫. ቅዱስ ሰርግዮስ ሰማዕት
፬. ቅዱስ መፁን ቀሲስ
፭. ቅዱስ ቴዎድሮስ ሰማዕት [ የቅ/ፋሲለደስ ልጅ ]
፮. አባ ጢሞቴዎስ ሊቀ ዻዻሳት
፯. አባ ክፍላ
፰. አባ ኅብስ
[ † ወርኀዊ በዓላት ]
፩. እግዚአብሔር አብ
፪. ቅዱስ ሩፋኤል ሊቀ መላዕክት
፫. ፺፱ [ 99 ] ኙ ነገደ መላዕክት
፬. ቅዱስ አስከናፍር
፭. ፲፫ [ 13ቱ ] ግኁሳን አባቶች
፮. ቅዱስ አርሳንዮስ ጠቢብ ገዳማዊ
፯. አቡነ ዘርዐ ቡሩክ
" እግዚአብሔር ቅዱሳንን ስላገለገላችሁ : እስከ አሁንም ስለምታገለግሏቸው ያደረጋችሁትን ሥራ : ለስሙም ያሳያችሁትን ፍቅር ይረሳ ዘንድ ዓመጸኛ አይደለምና:: በእምነትና በትእግስትም የተስፋውን ቃል የሚወርሱትን እንድትመስሉ እንጂ ዳተኞች እንዳትሆኑ ተስፋ እስኪሞላ ድረስ እያንዳንዳችሁ ያን ትጋት እስከ መጨረሻ እንድታሳዩ እንመኛለን::" [ዕብ.፮፥፲-፲፫]
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖 🕊 💖
🔔
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
ሐሳዊ አጥማቅያን እና የአጋንንት ምስክርነት !
[ ክፍል ስድስት ]
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
" በመቁጠሪያ ቀጥቅጡት ! "
▪
በዚህ ወቅት እየተሰሙ ካሉ እንግዳ ትምህርቶች መካከል " ሰይጣንን በመቁጠሪያ ቀጥቅጡት ! " የሚለው የሐሰተኛ አጥማቂያን አስተምህሮ ዋነኛው ነው።
ሐሳውያኑ ተከታያቸው ያደረጉትን ሕዝብ ፦ "መተት ተደርጎብህ ነው ፥ በደጅህ ተቀብሮብህ ነው ፥ ተሠርቶብሽ ነው ፥ ተልኮብህ ነው ፥ ታድሶብሽ ነው። ዓይነ ጥላ አለብሽ" እያሉ የሰይጣን ምርኮኛ መሆኑን እንዲያምን ካደረጉት በኋላ መፍትሔ የሚሉት ደግሞ በሚሸጡለት መቁጠሪያ እራሱን እንዲደበድብ ማድረግ ነው።
ይህም ሰይጣን እራሱ ያስነሳው ፍጹም የስህተት ትምህርት መሆኑን ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ደጋግመው በመግለጽ ላይ ይገኛሉ።
በዚህ የስህተት አስተምህሮና ልምምድ ሰይጣን ምን ያህል በምዕመናን ላይ ሰልጥኖ እየቀለደና እየተሳለቀ መሆኑን በሃይማኖት የሚኖር ሁሉ የሚያስተውለው ነው።
መቁጠሪያን በተመለከተ የቅድስት ቤተክርስቲያን አስተምህሮ ግልጽና የሐሰተኞቹን የንግድ ዓላማ ከንቱ የሚያደርግ ነው ፦
" መቁጠሪያ በቤተ ክርስቲያናችን ለጸሎት መቀስቀሻና ማስታኮቻ የሚውል ነው፡፡ ምእመናን እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ ፣ በእንተ ማርያም መሐረነ ክርስቶስ ፣ ኪርኤ አላይሶን የተባሉትን የምሕላ ጸሎቶች በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን የተመደበላቸውን ቁጥር ሳይስቱ እንዲጸልዩ የተሠራ ሥርዓት ነው፡፡ በጸሎት ጊዜ ዝንጋኤ እንዳይገጥማቸው ኅሊናቸውን ለመሰብሰብም ይረዳል፡፡ አንድ ቅዱስ ለብዙ ዘመን የጸለየበት መቁጠሪያ ፣ የተደገፈበት መቋሚያ ፣ የቆመበት ምድር ፣ የለበሰው ልብስ ፣ የተጠቀመበት መጽሐፍ ተአምራት ቢያደርግ አይገርምም፡፡
ቅዱሳን የነፍሳቸው ቅድስና ለሥጋቸው ፣ የሥጋቸውም ለልብሳቸው ፣ የልብሳቸው ለጥላቸው ተርፎ አይተን እናውቃለንና [የሐዋ.፭፥፲፪-፲፯ ፤ ፲፱፥፲፩] ከዚህ ውጭ ግን የሚሸጥ መቁጠሪያ ሰይጣን የሚያስወጣበት ፣ ሰው ራሱን በመቁጠሪያ ስለደበደበ ከዲያብሎስ እሥራት የሚፈታበት ምንም ምክንያት የለም፡፡ ሰይጣን በጾምና በጸሎት እንጂ በመቁጠሪያ ድብደባ አይለቅም። [ማቴ.፲፯፥፳፩]
ያ መቁጠሪያ ተአምር የሚሠራ ቢሆን እንኳን አንድ ቅዱስ የተጋደለበት ፣ ከዚያ ቅዱስም በረከት ያተረፈ መሆን አለበት፡፡ ልክ የቅዱስ ጳውሎስ የጨርቁ እራፊ ይፈውስ እንደነበረው፡፡ በቤተ ክርስቲያን ታሪክም የትኛውም አባት መቁጠሪያ ሲያድልና በመቁጠሪያ ሰይጣን ታወጣላችሁ ብሎ ሲያስተምር አልታየም፡፡"
በቤተክርስቲያን አስተምህሮ ሰይጣንን መቃወምና ማሸነፍ የሚቻለው ወደ እግዚአብሔር በመቅረብና ከእግዚአብሔር ጋር በመኖር ነው። ከእግዚአብሔር ጋር ለመኖር ደግሞ የንጽሕናና የቅድስና ሕይወት ያስፈልጋል። ይህም ፊትን ወደ እግዚአብሔር በመመለስ በምህረቱና በቸርነቱ በመታመን በመንፈሳዊ ሕይወት የምናድግበት የትሕትና ሕይወት ነው። በቤተክርስቲያን ሕይወት መመላለስንና በምክረ ካህን እየተመሩ በምስጢራት ዘወትር ሱታፌ ማድረግን የሚጠይቅ የአበው ፍኖት ነው። መጀመሪያውንም ፈተና ወደ ሕይወታችን የሚመጣው ከእግዚአብሔር እቅፍ [ከመንፈሳዊ ሕይወት] በመራቃችን የተነሳ ነው። ይህም በቅዱስ ወንጌል በብዙ ሥፍራዎች በምሳሌ ተገልጾ እናገኘዋለን።
ከኢየሩሳሌም ወደ ኢያሪኮ ስለወረደው ሰው የተነገረው ታሪክ ይህንን በጉልህ ያስረዳናል።
"አንድ ሰው ከኢየሩሳሌም ወደ ኢያሪኮ ወረደ በወንበዴዎችም እጅ ወደቀ ፤ እነርሱም ደግሞ ገፈፉት ደበደቡትም በሕይወትና በሞት መካከልም ትተውት ሄዱ።" [ሉቃ.፲፥፴]
በቅዱስ ወንጌል ትርጓሜ ብዙ ምስጢሮችን ያዘለ ቃል ቢሆንም ካነሳነው ርዕስ ጋር ስንመለከተው ይህ ሰው በወንበዴዎች [በአጋንንት] እጅ የወደቀውና ልብሱን ገፈው በሕይወትና በሞት መካከል እስኪሆን ደብድበው የጣሉት የሰላም ንጉስ [ክርስቶስ] ካለባት የሰላም ከተማ ኢየሩሳሌም [ከቅድስት ቤተክርስቲያን] ተለይቶ ወደ ኢያሪኮ [ወደ ዓለም የኃጢዓት ሕይወት] በመውረዱ የተነሳ ነው። ይህ የአባታችን የአዳም የውድቀት ሕይወትና የእግዚአብሔር ርሕራሔ የተገለጠበት ቃል በምዕመን ዕለታዊ ሕይወትም የሚፈጸም ነው።
ስለዚህ አጋንንት የሚደበድቡን ከሰላም ንጉስ ከተማ [ ከቅድስት ቤተክርስቲያን ] ስለራቅን እንደሆነ ሁሉ ከእነርሱ እጅ መዳንና በሕይወት መኖር የሚቻለንም የእግዚአብሔርን ምህረትና ቸርነት በመታመንና ወደ ቅድስት ቤተክርስቲያን በመመለስ ነው።
ፊትን ወደ ሰይጣን አዙሮ ከሰይጣን ጋር ግብ ግብና ትግል መግጠም የኦርቶዶክሳዊ መንፈሳዊ ሕይወት ትክክለኛ አቅጣጫ አይደለም።
ሰይጣንን ለማሸነፍ ዋነኛውና ቁልፉ መሳሪያ ትሕትና ነው። በረከታቸው ይደርብንና ቅዱስነታቸው አቡነ ሺኖዳ ፫ኛ ይህንን ሃሳብ እንዲህ ይገልጹታል ፦
"ትሑት ሰው ምንግዜም ቢሆን የራሱን ድካም ስለሚያውቅና የእግዚአብሔርን እርዳታ ስለሚሻ የእግዚአብሔር ኃይል በእርሱ ላይ ያድራል። በክንዱ ሳይመካ በእግዚአብሔር እርዳታ ስለተመካ ያሸንፋል።"
በመንፈሳዊ ሕይወት ለማደግና ፍሬ ለማፍራት መላ ሕይወትን ለእግዚአብሔር አሳልፎ በመስጠትና በእግዚአብሔር ቤት ጸንቶ መኖር ይገባል። በእግዚአብሔር ዕቅፍ ውስጥ የምንኖረው ከአንድ የስጋ ደዌ ለመፈወስ ሳይሆን እግዚአብሔር ሕይወታችን ስለሆነ ነው። ስለዚህ የእግዚአብሔር ፍቅር አድሮበት በቤቱ ጸንቶ የሚኖር ሰው ምልክት ፣ ተዓምራትንና ድንቆችን እያነፈነፈ የሚከተል ሊሆን አይችልም። እውነተኛ ኦርቶዶክሳዊ ከተዓምራትና ከድንቆች ሁሉ በላይ የሆነ ታላቅ ተዓምር ዘወትር በምስጢራተ ቤተክርስቲያን በኩል ሲፈጸም በእምነት እየተመለከተ ጸጋንና ክብርን ይጎናጸፋል።
ለጊዜያዊ ጥቅም ብቻ በአቋራጭ ከሐሳዊ አጥማቂ ተአምርና ፈውስን አገኛለሁ ብሎ በማሰብ የሚገኝ እውነተኛ የነብስም የሥጋም መፈወስ ከቶ ሊኖር አይችልም። ወደ እግዚአብሔር መቅረብና በፈቃዱ ለመኖር መጋደል ሰይጣንን በትክክል መቃወም ነው። እኛ የእግዚአብሔር ስንሆን ሰይጣን ከእኛ ይሸሻል። ለዚህም ነው አባታችን ቅዱስ ያዕቆብ በመልዕክቱ ፦
"እንግዲህ ለእግዚአብሔር ተገዙ ፤ ዲያብሎስን ግን ተቃወሙ ከእናንተም ይሸሻል ፤ ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ ወደ እናንተም ይቀርባል። እናንተ ኃጢአተኞች ፥ እጆቻችሁን አንጹ ፤ ሁለት አሳብም ያላችሁ እናንተ ፥ ልባችሁን አጥሩ።" [ያዕ.፬፥፯]
ተዓምርና ምልክት የሚናፍቀውና ባለማስተዋል እነዚህን ሐሰተኛ አጥማቂያን እየተከተለ ያለው ምዕመን እንዴት አድርጎ እራሱን እየጎዳና እያጎሳቆለ እንዳለ መታዘብ ይቻላል። ብዙ የዋሃን ከግለሰቦቹ የሚገዙትን የአረብ ዘይት እየተቀቡ ፤ "በግዢ በመቁጠሪያ" ራሳቸውን እየገረፉ አድሮብናል ያሉትን ሰይጣን እራሳቸው ለመቆጣት ሲሞክሩ ይታያል። በእውነቱ እንዲህ ያለ እንግዳ ትምህርትና ልምምድ ከቅድስት ቤተክርስቲያን የተገኘ አይደለም። ሰይጣን በመቁጠሪያ የሚመታ ግዙፍ አካል ከቶ የለውም። በድብደባ ብዛትም ሰይጣን ከሰው ይወጣል የሚል አስተምህሮ በሃይማኖታችን ፈጽሞ የለም።
በሐሰተኛ አጥማቂዎች እየተፈጸመ ያለውን ነገር ላስተዋለው ሰው ምዕመናንን ከቅድስት ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ሕይወት ፥ ከአባቶች ካህናት ፥ ከመስቀሉ ፥ ከጸበሉና ከእምነቱ ለይቶ የግለሰብ ተከታይ በማድረግ ከሜዳ ለማስቀረት ሰይጣን ያዘጋጀው ተንኮል መሆኑን መረዳት የሚቸግር አይደለም።
▪
" ንቁ ፥ በሃይማኖት ቁሙ ፥ ጎልምሱ ጠንክሩ።"
[ ፩ቆሮ.፲፮፥፲፫ ]
† † †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬
ማግሰኞ - የካቲት 12 2016 ዓ.ም
ዘኁልቁ 25-28
ሰላም ለሁላችሁ ይሁን! በዛሬው እለት ንባባችን ከምዕራፍ 25 እስከ 28 ድረስ እናነባለን።
ከንባብ በፊት የሚደረግ ጸሎት፡ “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፤ የአንተን ቃላት እሰማ እና እረዳ ዘንድ፥ እንዲያውም ፈቃድህን ለመፈጸም እበቃ ዘንድ የልቤን ጆሮዎች እና ዓይኖች ክፈትልኝ።” (ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ)
በዛሬው ንባባችን ላይ ሞአባውያን እስራኤልን እንዳሳቱ፥ ስለ ሁለተኛው የእግዚአብሔር ሕዝብ ቆጠራ፥ የሰለጰአድ ሴት ልጆች ስለጠየቁት ጥያቄ እና የኢያሱን በሙሴ ምትክ ስለመመረጥ እናነባለን። በተጨማሪም ስለ ዘወትር እና ሰንበት መሥዋእት፥ በፋሲካ እና በሰዊት በዓልም ስለሚቀርብ መሥዋእት ተጽፎ ይገኛል።
*የክለሳ ጥያቄዎች*
1) በዘኁልቁ 25 መሠረት፥ እስራኤል ስተው የተከተሉት ማንን ነው?
2) እስራኤል በመሳታቸው ምክንያት በመቅሰፍት የሞተው ሰው ብዛት ምን ያህል ነው?
3) ፊንሐስ ምድያማዊቷን ሴት ባመጣው ሰው እና በእርሷ ላይ ምን አደረገ? ውጤቱስ ምን ነበር?
4) በዘኁልቁ 26 መሠረት፥ የተቆጠሩት እስራኤላውያን ቁጥር ስንት ሆነ?
5) ከተቆጠሩ በኋላ ለእስራኤል ልጆች ርስት የተከፋፈለው እንዴት ነው?
6) በዘኁልቁ 27 መሠረት፥ የሰለጰአድ ሴቶች ልጆች ጥያቄ ምን ነበር? ተእግዚአብሔር ምላሽስ?
7) በዘኁልቁ 28 መሠረት፥ የእስራኤል ልጆች እለት እለት እንዲያቀርቡ የታዘዙት መሥዋእት ምን ነበር?
መልካም ንባብ!
/channel/OrthodoxTewahdoBooks
/channel/c/2014228571/1