"እንግዲህ፡ንስሓ፡ግባ፤አለዚያ፡ፈጥኜ፡ እመጣብሃለሁ፡፡" ራዕ 2፥16
🕊
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡
❖ እንኳን አደረሳችሁ ❖
[ የካቲት ፰ [ 8 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
[ † 🕊 በዓለ ስምዖን 🕊 † ]
ቅዱስ መጽሐፍ እንደሚነግረን ጌታ በተወለደ በ፵ [40] ቀኑ ራሱ የሠራውን ሕግ ይፈፅም ዘንድ ወደ ቤተ መቅደስ ገብቷል:: እንደ ሥርዓቱም እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያምና አገልጋዩዋ ቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊ የርግብ ግልገሎችና ዋኖስ አቅርበዋል::
ለ፪፻፹፬ [284] ዓመታት የአዳኙን [የመሢሁን] መምጣት ይጠብቅ የነበረው አረጋዊው ስምዖን በዚህች ዕለት ስላየውና ስለታቀፈው ዕለቱ በዓለ ስምዖን ይባላል:: [ሉቃ.፪፥፳፪] (2:22) ከዘጠኙ የጌታ ንዑሳን በዓላት አንዱ ነው::
ይሕስ እንደ ምን ነው ቢሉ :-
ከዓለም ፍጥረት በ፭ ሺህ ፪ መቶ [5,200] ዓመታት [ማለትም ከክርስቶስ ልደት ፫፻ [300] ዓመታት በፊት] በጥሊሞስ የሚሉት ንጉሥ በግሪክ ነገሠ::
በጊዜውም በኃይለኝነቱ ሁሉን አስገብሮት ነበርና "ዓለሙን እንደ ሰም አቅልጬ: እንደ ገል ቀጥቅጬ ገዛሁት:: ምን የቀረኝ ነገር አለ?" ሲል ተናገረ:: ባሮቹም "አንድ ነገር ቀርቶሃል:: በምድረ እሥራኤል ጥበብን የተሞሉ ፵፮ [46] መጻሕፍት አሉ:: እነርሱን አስተርጉም" አሉት::
ያን ጊዜ እሥራኤላውያንን አስገብሯቸው ነበርና ፵፮ [46] ቱን የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ከ፸፪ [72] ምሑራን [ተርጉዋሚዎች] ጋር እንዲያመጡለት አዛዦቹን ላከ:: እነርሱም ፵፮ [46] ቱን መጻሕፍተ ብሉይ ኪዳን ከ፸፪ [72] ምሑራን ጋር አመጡለት::
አይሁድ ክፋተኞች መሆናቸውን ሰምቷልና ፴፮ [36] ድንኩዋን አዘጋጅቶ: ጥንድ ጥንድ ሆነው እንዲሠሩ: ሲተረጉሙ እንዳይመካከሩ ፴፮ [36] ጠባቂዎችን ሾመባቸው:: ይህ ነገር ለጊዜው ከንጉሡ ቢመስልም ጥበቡ ግን ከእግዚአብሔር ነው::
ምንያቱም በጊዜ ሒደት መጻሕፍተ ብሉያት በአደጋ እንደሚጠፉ ያውቃልና ሳይበረዙ ለሐዲስ ኪዳን ክርስቲያኖች ለእኛ እንዲደርሱ ነው:: ስለዚህም ከክርስቶስ ልደት ፪፻፹፬ [284] ዓመት በፊት ፵፮ [46] ቱም ሁሉም መጻሕፍት [ብሉያት] ከእብራይስጥ ወደ ጽርዕ ልሳን በ፸ [70] ው ሊቃናት አማካኝነት ተተረጐሙ:: [በእርግጥ ከዚያ አስቀድሞ መጻሕፍት [ብሉያት] ወደ ሃገራችን መምጣቸውና ወደ ግዕዝ ልሳን መተርጐማቸውን ሳንዘነጋ ማለት ነው]
ወደ ዋናው ጉዳያችን ስንመለስ ከ፸ [70] ው ሊቃናት መካከል በእድሜው አረጋዊ የሆነ [እንደ ትውፊቱ ከሆነ ፪፻፲፮ [216] ዓመት የሆነው] ስምዖን የሚሉት ምሑረ ኦሪት ነበር:: በፈቃደ እግዚአብሔር ለእርሱ መጽሐፈ ትንቢተ ኢሳይያስ ደርሶት እየተረጐመ ምዕራፍ ፯ [7] ላይ ደረሰ::
ቁጥር ፯ [ 7 ] ላይ ሲደርስ ግን "ናሁ ድንግል ትጸንስ: ወትወልድ ወልደ" የሚል አይቶ "አሁን እንኳን የአሕዛብ ንጉሥ የእሥራኤልስ ቢሆን ድንግል በድንግልና ጸንሳ ትወልዳለች ብለው እንዴት ያምነኛል!" ሲል አሰበ:: "በዚያውስ ላይ ኢሳይያስ በምናሴ የተገደለው ስለዚህ አይደል!" ብሎ ቃሉን ሊለውጠው ወሰነ::
አመሻሽ ላይም 'ድንግል' የሚለውን 'ወለት-ሴት ልጅ' ብሎ ቀየረው:: እርሱ ሲያንቀላፋ ቅዱስ መልአክ ወርዶ 'ድንግል' ብሎ አስተካከለው:: ከእንቅልፉ ሲነቃ ግራ ተጋብቶ እንደ ገና ፍቆ ቀየረው::
አሁንም መልአኩ 'ድንግል' ሲል ቀየረበት:: ፫ [3] ጊዜ እንዲህ ከሆነ በኋላ ግን መልአኩ ተገልጦ ገሰጸው:: በዚያውም ላይ "ይህችን ድንግልና መሲሑን ልጇን ሳታየውና ሳትታቀፈው ሞትን አታይም" ብሎት ተሰወረው:: አረጋዊ ስምዖን ከዚያች ዕለት በኋላ የመድኅን ክርስቶስን መምጣት ሲጠብቅ ለ፪፻፹፬ [284] ዓመታት የአልጋ ቁራኛ ሁኖ ኖረ:: አካሉም አለቀ::
ለስም አጠራሩ ስግደት የሚገባው አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው በሆነበት በዚያ ሰሞን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምና ቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊ ወደ ቤተ መቅደስ ወጡ::
ሕግን የሠራ ጌታ እርሱ 'ፈጻሜ ሕግ' ይባል ዘንድ የርግብ ግልገሎችን [ዋኖሶችን] ይዘው በተወለደ በ ፵ [40] ቀኑ ወደ ቤተ መቅደስ አስገቡት:: በዚህች ቀንም ቅዱስ መልአክ መጥቶ ቅዱስ ስምዖንን ከአልጋው ቀሰቀሰው:: ተስፋ የሚያደርገው አዳኙ [መሲሑ] እንደ መጣም ነገረው::
ይህን ጊዜ አረጋዊው አካሉ ታድሶ እንደ ፪ [30] ዓመት ወጣት እመር ብሎ ከአልጋው ተነሳ:: እንደ በቅሎ እየሠገረም ወደ መቅደስ ወጣ:: በዚያ መሲሑን [ፈጣሪውን] ሲመለከት እንደ እንቦሳ ዘለለ:: ቀረብ ብሎም ሕጻን ጌታን ከድንግል እናቱ እጅ ተቀበለው::
ከደስታው ብዛት የተነሳም "ይእዜ ትስዕሮ ለገብርከ: በሰላም እግዚኦ በከመ አዘዝከ-አቤቱ ባሪያህን እንደ ቃልህ በሰላም አሰናብተው" ሲል ጸለየ:: ትንቢትንም ተናገረ:: በዚያችው ዕለትም ዐርፎ ተቀበረ::
[ † 🕊 ሐና ነቢይት 🕊 † ]
ዳግመኛ በዚህች ቀን አረጋዊቷን ነቢይት ቅድስት ሐናን እናስባለን:: ይህች ቅድስት ትውልዷ ከነገደ አሴር ሲሆን አባቷ ፋኑኤል ይባላል:: በትውፊት ትምሕርት ሐና የተዳረችው በልጅነቷ [በ፲፪ [12] /፲፭ [15] / ዓመቷ] ነው:: ለ፯ [7] ዓመታት ከልጅነት ባሏ ጋር ኖራ ዕድሜዋ ፲፱ [19] ፳፪ [22] ሲደርስ ሞተባት::
እንደ እሥራኤል ልማድ ሌላ እንድታገባ ብትጠየቅም 'እንቢ' ብላ መበለት ሆነች:: ራሷንም ለእግዚአብሔር አሳልፋ ሰጠች:: በቤተ መቅደስም ለ፹፬ [84] ዓመታት ለፈጣሪዋ ተገዛች:: ፈጽማ ትጸልይና ትጾም ነበርና በእነዚህ ሁሉ ዓመታት ውጪውን አልተመለከተችም::
ለእርሷ ፻፫ [103] ፻፮ [106] ዓመት ሲሆን መድኃኒታችን ተወለደ:: በዚህች ቀን ወደ ቤተ መቅደስ ሲገባ ተመልክታም ጌታን ባረከች:: ደስ እያላትም ትንቢትን ተናገረች:: ወደ ቤቷ ገብታም ነፍሷን ሰጠች:: [ሉቃ.፪፥፴፮-፴፰] [2:36-38)
ቸሩ መድኃኒታችን ተርፎ ከሚቀረው ዘመን ዕድሜ ለንስሃ: ዘመን ለፍሥሐ አይንሳን:: ከቅዱሳኑ በረከትም አይለየን::
[ † የካቲት ፰ [ 8 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ቅዱስ ስምዖን አረጋዊ
፪. ቅድስት ሐና ነቢይት [የፋኑኤል ልጅ]
፫. ቅድስት ዓመተ ክርስቶስ እግዝእት
፬. አባ ኤልያስ ገዳማዊ [በትህትና ያጌጠ ቅዱስ ሰው]
[ † ወርሐዊ በዓላት ]
፩. ቅዱስ ሙሴ ሊቀ ነቢያት
፪. ኪሩቤል [ አርባዕቱ እንስሳ ]
፫. አባ ብሶይ [ ቢሾይ ]
፬. አቡነ ኪሮስ
፭. አባ ሳሙኤል ዘደብረ ቀልሞን
፮. ቅዱስ ማትያስ ሐዋርያ [ ከ፲፪ [12]ቱ ሐዋርያት ]
አረጋዊ ስምዖንን ከድካም አልጋ ያነሳ አምላከ ቅዱሳን እኛንም ድካመ ነፍስን ከሚያመጣ የበደል ምኝታ በቸርነቱ ያንሳን::
" እንደ ሕጉ ልማድ ያደርጉለት ዘንድ ሕጻኑን ጌታ ኢየሱስን በአስገቡት ጊዜ እርሱ ደግሞ ተቀብሎ አቀፈው:: እግዚአብሔርንም እየባረከ እንዲህ አለ :- 'ጌታ ሆይ! አሁን እንደ ቃልህ ባሪያህን በሰላም ታሰናብተዋለህ:: ዓይኖቼ በሰዎች ሁሉ ፊት ያዘጋጀኸውን ማዳንህን አይተዋልና:: ይህም ለአሕዛብ ሁሉን የሚገልጥ ብርሃን: ለሕዝብሕም ለእስራኤል ክብር ነው:: 'ዮሴፍና እናቱም ስለ እርሱ በተባለው ነገር ይደነቁ ነበር::" [ሉቃ.፪፥፳፯] (2:27)
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖 🕊 💖
†
[ ልዩ መርሐ-ግብር ]
አጋንንት የማስወጣት ስርዓት በቤተክርስቲያን !
🕊 በቀሲስ ኅብረት የሺጥላ 🕊
" ኢየሱስም። ዝም በል ከእርሱም ውጣ ብሎ ገሠጸው። ጋኔኑም በመካከላቸው ጥሎት ሳይጐዳው ከእርሱ ወጣ።"
[ ሉቃ.፬፥፴፭]
" የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ።"
[ማቴ.፲፩፥፲፭]
† † †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
[ ኦርቶዶክሳዊ የመዳን ትምህርት ]
[ በዚህ መርሐ-ግብር ኦርቶዶክሳዊ የመዳን ትምህርት ከቅዱሳት መጻሕፍት ፤ ከቅዱሳን አባቶቻችን ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን አስተምህሮ እንዲሁም ከመምህራን ትምህርቶች ላይ በየጥቂቱ ይቀርባል። እንዲሁም የተሐድሶ መናፍቃን የኑፋቄ ትምህርቶችና ምላሾቻቸው የሚቀርብ ይሆናል። ]
† † †
[ ኦርቶዶክሳዊ የመዳን ትምህርት ]
[ ክፍል ሃያ ]
3.3 የሰው ልጅ ድኅነት [ መዳን ] የእግዚአብሔር ዓላማ መሆኑ
እግዚአብሔር ለእኛ ያደረጋቸው የተለያዩ የቸርነት ነገሮች ሁሉ እኛን ለማዳንና ስለ እኛ መዳን የተደረጉ ናቸው::
† † †
መ. ቅዱሳት መጻሕፍት የተጻፉት ለሰዎች የመዳን እውቀትን ለመስጠት ነው::
ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌሉን ሊያጠቃልል ሲል ወንጌሉን የጻፈበትን ዋና ምክንያት እንዲህ ሲል ገለጸ ፦ “ኢየሱስም በዚህ መጽሐፍ ያልተጻፈ ሌላ ብዙ ምልክት በደቀ መዛሙርቱ ፊት አደረገ ፤ ነገር ግን ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ ታምኑ ዘንድ ፣ አምናችሁም በስሙ ሕይወት ይሆንላችሁ ዘንድ ይህ ተጽፏል። ” [ዮሐ. 20፡30-31] ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብዙ ትምህርት አስተምሯል ፣ ብዙ ተአምራት አድርጓል። ሆኖም ሁሉም አልተጻፉም። ቅዱሳን ሐዋርያት በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ተቃኝተው ከእነዚያ መካከል መርጠው በወንጌል የጻፉልን ኢየሱስ ክርስቶስ መድኃኒት መሆኑን አምነን በስሙ ሕይወት ለማግኘት የሚረዳንን ያህል ነው ማለት ነው::
ቅዱስ ጳውሎስ ደቀ መዝሙሩን ጢሞቴዎስን ፦ “ከሕፃንነትህም ጀምረህ ክርስቶስ ኢየሱስን በማመን ፥ መዳን የሚገኝበትን ጥበብ ሊሰጡህ የሚችሉ ቅዱሳን መጻሕፍትን አውቀሃል” ሲል
የጻፈለት ለዚህ ነው:: [1ጢሞ.3:15] ካህኑ ዘካርያስም አንደበቱ በተከፈተ ጊዜ በመንፈስ ቅዱስ በተናገረው ጸሎት ስለ ልጁ ስለ ዮሐንስ መጥምቅ ሲናገር ፦ “እንደዚህም የኃጢአታቸው ስርየት የሆነውን የመዳን እውቀት ለሕዝቡ ትሰጣለህ ” ያለው ይኸንኑ የሚያስረዳ ነው። [ሉቃ.1፥77]
መጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈበት መሠረታዊና ተቀዳሚ ዓላማ በሥነ ፍጥረት ስላለው ነገር ወይም ስለ ሌሎች የተለያዩ ጉዳዮች ጥልቅ እውቀት ለማሳወቅና ለማራቀቅ ሳይሆን ሰው በእግዚአብሔር አምኖ የሚድንበትን የሕይወት መንገድ ለማሳየት ነው:: “የመዳን እውቀት ” የሚባለውም እግዚአብሔር በቸርነቱ የሰጠንን ድኅነት አውቀን በዚህ በመዳን መንገድ እንድንጓዝና ዘለዓለማዊ ሕይወትን ገንዘብ እንድናደርግ የሚረዳን እውቀት ነው። ለመዳን የማይጠቅም እውቀት በእግዚአብሔር ዘንድ ሞኝነት ነው:: ከመዳን የሚያሰናክል እውቀት ደግሞ የተከለከለ “የእውቀት ዛፍ” ነው፡፡ እውቅት ማለት “የመዳን እውቀት” ነው። “የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው ” የተባለውም ለዚህ ነው፡፡
[ በማክሰኞ መርሐ-ግብር ! ]
- መዳን ማለት ምን ማለት ነው ?
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
🕊
[ † እንኳን ለጻድቁ አባታችን አባ አብዱልማዎስ ገዳማዊ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ]
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †
[ † 🕊 አባ አብዱልማዎስ ገዳማዊ 🕊 † ]
† ጻድቁ ግብጻዊ ሲሆኑ በበርሃ ሰው ሳያዩ ለ፸ [70] ዓመታት በቅድስና ኑረዋል:: በጊዜውም እግዚአብሔር አባ አብዱልማዎስን ወደ አባ ዕብሎይ ልኳቸው ነበር:: ሁለቱ ተገናኝተው አብረው ለ፫ [3] ቀናት ሲቆዩ ቅዱስ መልአክ እየተገለጸ አጽናንቷቸዋል:: ከሥውራን ማኅበርም ተቀላቅለው ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ተቀብለዋል::
† አባ ዕብሎይ ሲያርፍ አንበሶች እያገዟቸው ቀብረዋቸዋል:: እርሳቸውም "እኔን የሚቀብረኝ ስጠኝ" ብለው ጸልየው ነበርና ፫ [3] ገዳማውያን መጥተውላቸዋል:: የካቲት ፭ [5] ቀን አባ ዕብሎይን ገንዘው ቀብረው በ ፫ [3] ኛው ቀን አርፈዋል::
† የጻድቁ ክብር ይደርብን።
[ 🕊 † የካቲት ፯ [ 7 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
1.አባ አብዱልማዎስ ገዳማዊ
2.አባ ቴዎድሮስ ሊቀ ጳጳሳት
3.አባ እለ እስክንድሮስ ሊቀ ጳጳሳት
4.ቅዱስ አባዲር
[ 🕊 † ወርኀዊ በዓላት 🕊 ]
፩. ሥሉስ ቅዱስ [አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ]
፪. አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
፫. አባ ሲኖዳ [የባሕታውያን አለቃ]
፬. አባ ዳንኤል ዘገዳመ ሲሐት
፭. አባ ባውላ ገዳማዊ
፮. ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ
፯. ቅዱስ አግናጥዮስ
† የአብ በረከት: የወልድ ፍቅር: የመንፈስ ቅዱስ አንድነት: የድንግል ማርያም ምልጃ: የቅዱሳኑ ፀጋ በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን::
† "ስለ ጽድቅ የሚሰደዱ ብጹዓን ናቸው:: መንግስተ ሰማያት የእነርሱ ናትና:: ሲነቅፉአችሁና ሲያሳድዷችሁ በእኔም ምክንያት ክፉውን ሁሉ በውሸት ሲናገሩባችሁ ብጹዓን ናችሁ:: ዋጋችሁ በሰማያት ታላቅ ነውና ደስ ይበላችሁ:: ሐሴትም አድርጉ::" † [ማቴ. ፭፥፲]
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖 🕊 💖
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
የዘመኑ አጥማቅያን እና የአጋንንት ምስክርነት !
[ ክፍል ሦስት ]
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
ዘይት የሚሸጡ ሐሰተኞች !
-----------------------------------
ቤተ ክርስቲያን ንጉሠ ነገሥታት ኢየሱስ ክርስቶስ የሚገለጥባት ፣ እርሱ የሚሰየምባት [የሚፈተትባት] ፣ ለተነሣሕያንም መብል ሆኖ የሚሰጥባት ፣ ፍጹም ይቅርታን ሥርየተ ኃጢአትን የሚያሰጡ ባለሙሉ ሥልጣን ካህናት የሚገኙባት ፣ ምእመናንም ምሕረትን ከእግዚአብሔር የሚያገኙባት የምሕረት አደባባይ ናት።
በእርሷም የሰው አዕምሮ ተመራምሮ ሊደርስባቸው የማይችላቸው የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ የሆኑ አማናዊ ምስጢራት ይፈጸማሉ። ምስጢራተ ቤተክርስቲያን በሚታይ አገልግሎት የማይታየውን ረቂቁን ጸጋ መንፈስ ቅዱስ የምናገኝባቸው መሣሪያዎች ናቸው። እነዚህም ምስጢራት ሰባት ናቸው።
ሐዋርያዊት የሆነችው እናታችን ቅድስት ቤተክርስቲያን እነዚህን ምስጢራት በፍጹም ጥንቃቄ እየፈጸመች ለዚህ ዘመን ደርሳለች።
ሆኖም በዘመናችን የተነሱ ፣ በድፍረት የተሞሉና ገንዘብን መሰብሰብ ዓላማቸው ያደረጉ ሐሰተኛ አጥማቂያን የከበሩትንና የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ የሆኑትን ምስጢራት የሚፈታተን እግዚአብሔርንም የሚያሳዝን ተግባር በመፈጸም ላይ ይገኛሉ።
ከከበሩ ምሥጢራተ ቤተክርስቲያናት መካከል በኤጲስ ቆጶሳት ወይም በካህናት ክህነታዊ ስልጣንና ሕብረታዊ ሥርዓተ ጸሎት በኩል ብቻ የሚፈጸመው ምሥጢረ ቀንዲል [ቅብዓ ቅዱስ] አንዱ ነው። ሐሰተኛ አጥማቂያን በዚህ ፈውሰ ሥጋና ፈውሰ ነብስ በሚያሰጠው ምስጢር ስም የቤተክርስቲያንን ቅድስና በሚፈታተን ተግባር ተሰማርተው ፦
- "ቅብዓ ቅዱስ ቀብተን አጋንንት እናስወጣለን ፣ ከደዌ እንፈውሳለን" እያሉ በከፈቷቸው ሱቆች ውስጥ ዘይት በመሸጥ የገንዘብና የሃብት ምንጭ በማድረግ
- ከኤጲስ ቆጶሳት ወይም ከካህናት በቀር ዲያቆናት እንኳን እንዲፈጽሙትና እንዲነኩት የማይፈቀደውን ለምዕመኑ በማደል አስተምህሮና ሥርዓት በማጥፋት
- የክርስቶስ አካል ከምትሆን ከቅድስት ቤተክርስቲያን ምዕመኑን በማፍለስ ተከታያቸው አድርገው ፕሮቴስታንታዊ መስመርን በመከተል ምዕመኑን ከሃይማኖት መንገድ እያስወጡት ይገኛል።
ለመሆኑ ምስጢረ ቀንዲል [ቅብዓ ቅዱስን] በተመለከተ የቅድስት ቤተክርስቲያን አስተምህሮ ምን ይላል ?
ምስጢረ ቀንዲል በቤተክርስቲያን አስተምህሮ
ምሥጢረ ቀንዲል ሕመምተኞች በሃይማኖት ከአካላዊና ሥነ ልቦናዊ ሕመም የሚፈወሱበት ከሰባቱ ምሥጢራተ ቤተክርስቲያን አንዱ የሆነ ቅዱስ ምሥጢር ነው። ካህናተ ቤተክርስቲያን መብራት አብርተው ፣ ልብሰ ተክህኖ ለብሰው መጽሐፈ ቀንዲል ዘርግተው ሲጸልዩ የሚታይ ሲሆን በጸሎቱ ኃይል ከበሽተኛው ደዌው እንዴት እንደሚርቅ ሥርየተ ኃጢአት እንዴት እንደሚሰጠው በሥጋዊ ዓይን ስለማይታይና ሁኔታውንም ለመግለጽ ለአእምሮ ስለሚረቅ ቀንዲል ምስጢር ተብሏል።
የምሥጢረ ቀንዲል አፈጻጸም
የቀንዲልን ምሥጢር የሚፈጽሙት ሰባት ኤጲስ ቆጰሳት ወይም ሰባት ቀሳውስት ናቸው፡፡ እነዚህም ዮሐንስ በራእዩ ያያቸው ሰባት ብርሃናት ምሳሌ ናቸው [ራእ.፩፥፲፫]
ቅዱስ ያዕቆብ እንዳለው በቤተክርስቲያን ሥርዓት ቀንዲል የሚደረግለት ምእመን በቅድሚያ መናዘዝ አለበት:: ከዚያ በኋላ ምሥጢሩን የሚፈጽሙት ኤጲስ ቆጰሳት ወይም ቀሳውስት ንጹሕ ዘይት አቅርበው ለዚህ የተወሰነውን ጸሎት ያደርሳሉ፡፡ ሰባቱም በየተራ በምእመናኑ ራስ ላይ ወንጌል ያነባሉ፡፡ ይህም የጌታ አንብሮተ እድ ምሳሌ ነው፡፡ ወንጌል ከተነበበ በኋላ ሰባቱም እጃቸውን በራሱ ላይ ጭነው ይጸልዩለታል፡፡
በመጨረሻም በጫፋቸው ጥጥ የተጠመጠመባቸው ሰባት እንጨቶች ይይዛሉ፡፡ ይህንን በየተራ ወደ ተጸለየበት ዘይት እየነከሩ በትእምርተ መስቀል ይቀቡታል ፤ በሥርዓተ ሜሮን እንዳየነው አምስቱን ሕዋሳቱን ፣ ዓይን ፣ ጆሮውን ፣ አፉን ፣ አፍንጫውን እጁን ይቀቡታል፡፡ በዓይኑ አይቶ በጆሮው ሰምቶ ፣ በአፉ ተናግሮ በአፍንጫው አሽቶ ፣ በእጁ ዳሶ ለሠራው ኃጢአት ሥርየት እንዲኖረው ሲሉ አምስቱን ሕዋሳት ይቀቡታል።
ይህ ቅዱስ ቅባት የሚቀባው አንደኛ ግንባር ላይ እርሱም የአምስቱ ሕዋሳት ማዕከልና የማሰብ ኃይል የሚገኝበት በመሆኑ ፤ ሁለተኛ ደረቱ ላይ እርሱም የልብ ማረፊያ በመሆኑ ፤ ሦስተኛ እጆቹ ላይ እነርሱም ማንኛውንም ሥራ ለመሥራት የሚንቀሳቀሱ በመሆናቸው ነው፡፡
ምሥጢረ ቀንዲልን መፈጸም የሚችሉት በቤተክርስቲያን ሥርዓት የቅስና መዓርግና ከዚያ በላይ መዓርግ የተቀበሉ አባቶች ብቻ ናቸው። ዲያቆናት ይህን ምስጢር እንዲፈጽሙ አልተፈቀደላቸውም። በምስጢረ ቀንዲል የምናገኘውም ፦
ፈውሰ ሥጋ
ሥጋዊ ጤንነታችን በተለያዩ ምክንያቶች ሊታወክ |ሊቃወስ/ ይችላል። ቤተክርስቲያን ተልእኮዋ ምእመናንን ለመንግሥተ ሰማያት ማዘጋጀትና ማብቃት ሲሆን ከመንፈሳዊ ሕይወታችን ጎን ለጎን ለሥጋዊ ጤንነታችንም በማሰብ ከሕመማችን እንድንፈወስ የምትፈጽመው ሥርዓት አላት፡፡ ለምሳሌ ሌሊት ሰዓታት የተባለውን የጸሎትና ማኅሌት [ምሥጋና] የምልጃ ጸሎት [መስተብቁዕ] ስታደርስ ፦
“ልዑል እግዚአብሔርን ስለታመሙ ወንድሞቻችን ዳግመኛ እንማልዳለን ደዌውን [በሽታውን] ሁሉ ሕማሙንም ሁሉ ያርቅላቸው ዘንድ የደዌውን መንፈስ አርቆ ሕይወትን [ፈውስን] ይሰጣቸው ዘንድ የደዌን መንፈስ አርቅ : ደዌውን ሁሉ ሕማሙንም ከእነርሱ አሳልፍ አቤቱ ይቅርታህ ፈጥኖ ይደረግልን ሁሉን የምትጎበኝ አንተ ነህ፡፡ በርኩሳን መናፍስት የሚጨነቁትን ነጻ አድርግ: ደዌውን ሁሉ ከዚህ ቤት አስወጥተህ ስደድ ፡ ምሥጉን የሚሆን ስምህን ከሚጠሩትም ዘንድ. . ."
በማለት ዘወትር ወደ ፈጣሪ የምታቀርበው ምልጃና ጸሎት ለዚህ ዐቢይ ማስረጃ ነው:፡ ይኽም ምሥጢረ ቀንዲል ነው፡፡ ምሥጢረ ቀንዲል በዋነኛነት ዓላማው ሕሙማነ ሥጋን ማዳን መፈወስ ነው፡፡
ፈውሰ ነፍስ
ቅዱስ ያዕቆብ እንዳስተማረው ይህን ቅዱስ ቅባት [ምሥጢረ ቀንዲል] የሚፈጽሙ ሰዎች አስቀድመው በንስሐ ሊዘጋጁ ይገባቸዋል:: ከዚህ የምንማረው ንስሐ ፣ ኑዛዜ ኃጢአትና ቀኖና የሚያስፈልገው ለፈውሰ ነፍስ እንጂ ለፈውሰ ሥጋ ባለመሆኑ በቀንዲል ከሚገኘው ጸጋ አንዱና ዋንኛው ፈውሰ ነፍስ መሆኑን ነው። [ ሰባቱ ምስጢራተ ቤተክርስቲያን ]
ከላይ እንደተመለከትነው ምስጢረ ቀንዲል
- ከከበሩት ከሰባቱ ምስጢራተ ቤተክርስቲያን መካከል አንዱ ነው።
- ኤጲስ ቆጶሳት ወይም ካህናተ ቤተክርስቲያን መብራት አብርተው ፣ ልብሰ ተክህኖ ለብሰው መጽሐፈ ቀንዲል ዘርግተው የሚፈጽሙት አማናዊ ምስጢር ነው።
- ሰባት ኤጲስ ቆጶሳት ወይም ካህናተ ቤተክርስቲያን የሚያደርሱት ሥርዓተ ጸሎትና የአፈጻጸም ሥርዓት ያለው ነው።
ሐሳዊ አጥማቂያን ይህንን በመሰለው ምስጢር ስም ነው ሱቅ ከፍተው ሃይማኖት እያጠፉ ያሉት !
------------------------------
ቅብዐ ቀንዲልን ፣ ቅብዐ ቅዱስንም ሆነ ቅብዐ ሜሮንን በየሱቁ መግዛትም ሆነ መሸጥ የተከለከለና ከሥርዓተ ቤተክርስቲያን የወጣ ተግባር መሆኑን ብጹዓን አበው እያሳሰቡ ይገኛል።
" ቅብዐ ሜሮንን በየሱቁ መግዛትም ሆነ መሸጥ የተከለከለ ነው። ቅብዓ ሜሮን የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ የሚታደልበት በመሆኑ ይህንን ማድረግም በመንፈስ ቅዱስ ላይ በደልን መሥራት ነው።"
[ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ ]
ከታች በምትመለከቱት ቪዲዮ ግለሰቡ ሕዝቡን ከቤተክርስቲያን አስወጥቶ ወደ ሱቁ የሚያፈልስበት አሳዛኝ ትዕይንት ይታያል !
† † †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬
†
[ ተዋሕዶ ፍጽምት የቅዱሳን ሃይማኖት ]
▬▬▬▬▬▬ † ▬▬▬▬▬▬
[ እርሱ የሚታይ ሲሆን የማይታይ ነው ! ]
--------------------------------------------------
" ሰው የሆነ የእግዚአብሔር ቃል አንድ አካል ፥ አንድ ገጽ ፥ አንድ ባሕርይ እንደሆነ እናምናለን፡፡
ዳግመኛም ያለዘር መፀነሱን እናምናለን፡፡ [ኢሳ.፯፥፲፬ ፣ ማቴ፩.፲፰-፳፭ ፣ ሉቃ.፩፥፳፭–፴፱] በሥጋ መወለድ ፤ በመስቀል መከራ መቀበል ፤ መሞት ፤ መነሣት ገንዘቡ የሆነ እርሱ እግዚአብሔር ቃል ነው። [ዮሐ.፲፰፥፴፯]
ስለዚህም በመስቀል ላይ ሳለ ከጥንት ጀምሮ በመቃብር ያሉ ሙታንን ሁሉ አስነሣ፡፡ ለአባቱ ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው አንድ ነው፡፡ በሰማይ ያለ ፤ በምድር ያለ እርሱ ነው፡፡ እርሱ የሚታይ ሲሆን የማይታይ ነው። [ማቴ.፳፯፥፶፩–፴፫ ። ቈላ.፩፥፲፭ ። ዮሐ.፫፥፲፫ ፡፡ ሮሜ.፲፥፭፰]
ዓለም ሳይፈጠር [ ከዘለዓለም ] ከእግዚአብሔር አብ የተወለደው በኋላ ዘመን በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ማኅፀን ያደረ እርሱ ነው፡፡ እርሱ ሰውም ቢሆን አንድ አካል ፤ አንድ ገጽ ፤ አንድ ባሕርይ ነው፡፡ እንዲህ አንድ አካል አንድ ባሕርይ ብሎ የማያምነውን የማይታመነውን እናወግዛለን። "
[ ቅዱስ ፊልክስ ]
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፤ ወለወላዲቱ ድንግል ፤ ወለመስቀሉ ክቡር። አሜን።
† † †
💖 🕊 💖
†
[ እየሆነ ያለው ይህ ነው ! ]
" እንግዲህ በነቢዩ በዳንኤል የተባለውን የጥፋትን ርኩሰት በተቀደሰችው ስፍራ ቆሞ ስታዩ ፥ አንባቢው ያስተውል" [ ማቴ. ፳፬ ፥ ፲፭ ]
----------------------------------------------
ይህ እየሆነ ያለው በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ሃይማኖት ውስጥ ነው ቢባል ማን ሊያምን ይችላል ?! በሚመጣው ዘመንስ ምን ልንሆን ነው ?
ምልክትና ድንቅ ተከታይ [ አመንዝራዎች ] ፤ እምነት አልባ ጎስቋላዎች ፤ በየጊዜው የሚነሱ ነጣቂዎች እንደ ጠፍ ከብት የሚነዱን ቀሊሎች ሆነን ስንገኝ በየበረሃው ወድቀው የሚጋደሉ የደጋጎቹ አባቶቻችን አምላክ እግዚአብሔር እንደምን ያዝን !
አበው ቅዱሳን በብዙ መከራና ተጋድሎ በንጽህናና በቅድስና የጠበቋትን ፤ ሰማዕታት የሞቱላትን ቅድስት ቤተክርስቲያንን እንዲህ ስናጎሳቁላት እግዚአብሔር እንደምን ያዝን !
ከእኛ በላይ ክብርት ቤተክርስቲያንን የጎዳስ ማን አለ ?
መልቲ ሚሊየነሮቹ [ የእኛ ቤት ጩፋዎች ] እንዲህ ከነዱን በምትሐት ፀሃይን በእጁ ጨብጦ በስህተት አሰራር በምልክቶችና በድንቆች ታጅቦ የሚታየው ሲመጣስ ምን ልንሆን ነው ? !
" ክፉና አመንዝራ ትውልድ ምልክት ይሻል ፥ ... ትቶአቸውም ሄደ።" [ማቴ.፲፮፥፬]
የቤተክርስቲያን አምላክ ይማረን። ማስተዋልን ይመልስልን !
† † †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
[ ኦርቶዶክሳዊ የመዳን ትምህርት ]
[ በዚህ መርሐ-ግብር ኦርቶዶክሳዊ የመዳን ትምህርት ከቅዱሳት መጻሕፍት ፤ ከቅዱሳን አባቶቻችን ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን አስተምህሮ እንዲሁም ከመምህራን ትምህርቶች ላይ በየጥቂቱ ይቀርባል። እንዲሁም የተሐድሶ መናፍቃን የኑፋቄ ትምህርቶችና ምላሾቻቸው የሚቀርብ ይሆናል። ]
† † †
[ ኦርቶዶክሳዊ የመዳን ትምህርት ]
[ ክፍል አሥራ ዘጠኝ ]
🔴 [ ይልቁንም የክርስቶስን የባህርይ አምላክነት ክደው እንደ ነቢይ ፣ እንደ መልአክ ፣ እንደ አማላጅ [ ሎቱ ስብሐት ] ለሚያዩ መናፍቃን !
3.3 የሰው ልጅ ድኅነት [ መዳን ] የእግዚአብሔር ዓላማ መሆኑ
እግዚአብሔር ለእኛ ያደረጋቸው የተለያዩ የቸርነት ነገሮች ሁሉ እኛን ለማዳንና ስለ እኛ መዳን የተደረጉ ናቸው::
ሐ. የሐዋርያት ተልእኮና ስብከት ዓላማው የሰው መዳን ነው::
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መዳናችንን በሥጋዌው ከፈጸመ በኋላ ቅዱሳን ሐዋርያቱን በኃይለ መንፈስ ቅዱስ ቀድሞ የነበረባቸውን ፍርሃትና አለማስተዋል አስወግዶ እንዲህ ሲል ወደ ዓለም ላካቸው ፦ “እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ፡፡ ” [ማቴ.28፥19-20]
እንዲሁም ፦ “ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ። ያመነ የተጠመቀም ይድናል ፣ ያላመነ ግን ይፈረድበታል ” አላቸው:: [ማር.16፡15-16] በዚሁ ተልእኮ መሠረት ደቀ መዛሙርቱ በየደረሱበት የመዳንን ቃል ለሕዝቡ ይናገሩ ነበር።
የስብከታቸውም ዓላማ ሰዎች የመዳንን አስፈላጊነትና እንዴትም እንደሚዳን ተረድተው እንዲድኑ የእግዚአብሔርን የመዳን ጸጋና ጥሪ ለሰዎች ማድረስ ነበር። ለአብነትም ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በመጀመሪያው ሐዋርያዊ ጉዞው ከጓደኞቹ ጋር ጳፉ ከተባለው ቦታ ተነሥቶ የጲስድያ ወደምትሆን ወደ አንጾኪያ ደረሱና በሰንበት ቀን ወደ ምኵራብ ገብተው ተቀመጡ። በዚያም ሕግና ነቢያትም ከተነበቡ በኋላ የምኵራቡ አለቆች ፦ “ወንድሞች ሆይ ፣ ሕዝብን የሚመክር ቃል እንዳላችሁ ተናገሩ ” ብለው በላኩባቸው ጊዜ ቅዱስ ጳውሎስ ተነሣና በእጁ ጠቅሶ እንዲህ አለ ፦
" የእስራኤል ሰዎችና እግዚአብሔርን የምትፈሩት ሆይ ፣ ስሙ ፤ የዚህ የእስራኤል ሕዝብ አምላክ አባቶቻችንን መርጦ በግብፅ አገር በእንግድነት ሳሉ ሕዝቡን ከፍ ከፍ አደረጋቸው ፣ ከፍ ባለችውም ክንዱ ከዚያ አወጣቸው። ... ከዚህም ሰው ዘር [ ከዳዊት ] እግዚአብሔር እንደ ተስፋው ቃል ለእስራኤል መድኃኒትን እርሱም ኢየሱስን አመጣ። ከመምጣቱ በፊት ዮሐንስ አስቀድሞ ለእስራኤል ሕዝብ ሁሉ የንስሐን ጥምቀት ሰብኮ ነበር። ... እናንተ ወንድሞቻችን የአብርሃም ዘር ልጆች ከእናንተ መካከልም እግዚአብሔርን የምትፈሩ ሆይ ፣ ለእናንተ የዚህ የመዳን ቃል ተላከ። [የሐዋ.13:14-26] "
ለቆሮንቶስ ምእመናን ስለ ወንጌል ምንነትና ዓላማ በመልእክቱ ሲያስታውሳቸውም እንዲህ አለ ፦ “ወንድሞች ሆይ ፥ የሰበክሁላችሁን ደግሞም የተቀበላችሁትን በእርሱም ደግሞ የቆማችሁበትን በእርሱም ደግሞ የምትድኑበትን ወንጌል አሳስባችኋለሁ::” [1ቆሮ.15:1] የሐዋርያት ስብከት ለሚቀበሉትና ለሚጠቀሙበት የሕይወት መንገድ ፣ ለማይቀበሉት ደግሞ ያው የመዳን ቃል የሚፈርድባቸው ስለሆነ የሞት መንገድ የሚሆንባቸው መሆኑን ሲናገር ፦ “ለእነዚህ ለሞት የሚሆን የሞት ሽታ ፣ ለእነዚያም ለሕይወት የሚሆን የሕይወት ሽታ ነን ” አለ፡፡ [2ቆሮ.2፥16]
ቅዱስ ጴጥሮስም ፦ “ጌታ ቸር መሆኑን ቀምሳችሁ እንደ ሆነ ለመዳን በእርሱ እንድታድጉ አሁን እንደ ተወለዱ ሕፃናት ተንኰል የሌለበትን የቃልን ወተት ተመኙ ” በማለት ቃለ እግዚአብሔር ዓላማው መዳን መሆኑን ገልጿል። [1ጴጥ 1፡2-3] ቅዱስ ጳውሎስ ደቀ መዝሙሩን ቲቶን ሲመክረው “አንተ ግን ሕይወት ለሚገኝበት ትምህርት የሚገባውን ተናገር ” ብሎታል። [ቲቶ 2፡21]
[ በሐሙሱ መርሐ-ግብር ! ]
መ. ቅዱሳት መጻሕፍት የተጻፉት ለሰዎች የመዳን እውቀትን ለመስጠት ነው።
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
🕊
[ በብዙ መከራ ! ]
በብዙ መከራ ፣ በብዙ ችግር ፣ በብዙ ምድራዊ ጉስቁልና ውስጥ ሆነው ፤ ረሀቡን ጥሙን ሁሉ እየታገሱ በፍጹም ትሕትናና በትሕርምት ያለ እረፍት እግዚአብሔርን እያመሰገኑ ፤ መንጋው በአራዊት እንዳይነጠቅ ፤ ነፍሳት ሁሉ ለእግዚአብሔር መንግስት እንዲበቁና እንዲድኑ የሚተጉ እውነተኛ ንጹሐን አባቶቻችንን በዕድሜ በጤና በቤቱ ያቆይልን። ያለ ካህናት አባቶቻችን ፣ ያለ ጠባቂና ያለ እረኛ ከመቅረት የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ይሰውረን።
[ እጹብ የሚያሰኘው የአባቶቻችን ክብር ! ]
ስለ አበው ካህናት ሰማያዊ ስልጣንና ክብር ቤተክርስቲያን እንዲህ ትላለች ፦
" ይህን እሳት ያለ ጉጠት ሳይፈራ የሚዳስስ ካህን እንደምን ያለ ነው? ለዚህ ለመዳሰሱ አንክሮ ይገባል ! በመሰዊያ ላይ ይህን ሕብስቱን የሚፈትተው ካህን እንደምን ያለ ነው? ለዚህ አንክሮ ይገባል ! ... የእግዚአብሔርን በግ ለመሰዋት ጣቶቹ ወቅለምት የሆኑለት ይህ ካህን እንደምን ያለ ነው?! ለዚህ አንክሮ ይገባል! አንደበቱም መናፍቃንን ከምዕመናን ለመለየት ሰይፍ ሆነለት ፤ ምዕመናንን ከአምላካቸው ደም አንድ የሚያደርጋቸው ይህ ካህን እንደምን ያለ ነው?! ለዚህ አንክሮ ይገባል!" [አርጋኖን ዘሰኑይ]
"አቤቱ ጌታ ሆይ አሁንም ሁል ጊዜ የክህነትን ሥራ ለሚሠሩ ለንፁሐን አገልጋዮችህ ክህነትን ሰጠህ ፤ በምድር ላይ ያስሩ ዘንድ ፥ ይፈቱ ዘንድ የኃጢአትን ማሠሪያ ሁሉ ከእኛ ያርቁ ዘንድ፡፡" [ ጸሎተ ፍትሐት ዘወልድ ]
ሰይጣን ዓለምን ወደ ፍጹም ጥፋት ሊወስድ ሲፈልግ ምዕመናን ከካህናት እንዲለያዩ ይሠራልና !
የነፍስ አባቶቻችን ካህናትን እግዚአብሔር ይጠብቅልን፡፡ የአባትነትና የልጅነት ፍቅርን ያጽናልን፡፡
† † †
▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬
†
" የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ።" [ማቴ.፲፩፥፲፭]
† † †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
ሐሳዊ አጥማቅያን እና የአጋንንት ምስክርነት !
[ ክፍል አንድ ]
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
"በደሙ ክቡር በዕፀ መስቀሉ ተቀደሰት ቤተክርስቲያን እምድኅረ ተንሥአ እሙታን።"
[ ከሙታን ከተነሣ በኋላ በክቡር ደሙ ቤተ ክርስቲያን ተቀደሰች።] [ ቅዱስ ያሬድ ]
-------------------------------------------------------
አማናዊት የድኅነት መርከብ ቅድስት ቤተክርስቲያን እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ በገዛ ደሙ የመሠረታት ፥ የቀደሳትና ያከበራት ፣ በሐዋርያት አጥንት የተማሰች ፤ በሰማዕታት ደም የተለሰነች ፤ በሊቃውንት ምስጢር የተገነባች ፤ ይህ ቀረሽ የማትባል ምልዕተ ምስጢር ፤ የጸጋ ሁሉ ግምጃ ቤት ናት።
እርሷ አንድ ጊዜ ፍጽምት ፥ ቅድስትና ክብርት ሆና ተሰጥታናለችና የተዳደፉት ሁሉ በእርሷ የሚታጠቡባት ፤ የረከሱት ሁሉ በእርሷ የሚቀደሱባት ፤ የወደቁት ሁሉ በእርሷ የሚነሱባት ፤ በጽኑ ደዌ የታመሙት ሁሉ የሚፈወሱባት ፤ በበደል የጎሰቆሉ ሁሉ የሚታደሱባት ፤ በነብስም ሆነ በሥጋም ፍጥረታ ሁሉ ታክመው የሚድኑባት ሰማያዊ ሃኪም ቤት ናት፡፡
አካለ ክርስቶስ ቅድስት ቤተክርስቲያን ለልጆቿ የነብስም የሥጋም ፈውስን በተቀደሰው ሥርአቷ መሠረት ታድላለች። ለነብስ ደዌም ሆነ ለደዌ ሥጋ ፈውስ የሚሰጥበት አስተምህሮ ፤ የተቀደሱ ምሥጢራትና ሥርዓት አላት።
ከሰባቱ ምስጢራተ ቤተክርስቲያን አንዱ ምስጢረ ቀንዲል ነው። በዚህ ምስጢር ፦ አባቶች ኤጲስ ቆጶሳት እንዲሁም ካህናት ለታመሙ ሰዎች በሚያደርጉት ጸሎት ፥ በሚሰጡት ቡራኬና በሚቀቡትም ቅብዐ ቅዱስ አማካኝነት በእግዚአብሔር ጸጋ የሥጋና የነፍስ ፈውስ ይደረጋል። ከሥጋ ፈውስ ጋር የኅጢዓት ሥርየት የሚገኝበት በመሆኑ እጥፍ ድርብ ጸጋን የሚያሰጥ ምስጢር ነው። ይህ ምስጢር በመንፈስ ቅዱስ የሚፈጸም የቅድስት ቤተክርስቲያን ጸጋና ሃብት ነው። በዚህ ዘመን ይህንን የከበረ ምስጢር ለማጥፋትና ለማቃለል ሰይጣን ሐሰተኛ አጥማቂያንን እየተጠቀመባቸው ስለመሆኑ በቀጣይ መርሐ ግብር በሰፊው እንመለከተዋለን።
በአጠቃላይ ቅድስት ቤተክርስቲያን የኃጢዓት ሥርየት መገኛ የጸጋ ሁሉ ግምጃ ቤት የሆነች ፤ በተለያዩ ምክንያቶች በደዌ ለታመሙ ፥ በአጋንንት አሽክላ ተይዘው ለሚንገላቱ ምዕመናን በትምህርቷና በምስጢራቷ በኩል ፥ በምልጃና በጸሎት ሥርዓቷ ፥ በቅዱስ መስቀሉ ኃይል ፥ በጸበሉና በእምነቱ እግዚአብሔር በፈቀደውና በወደደው ሥርዓት ፥ በወሰነውም ጊዜ ፈውስ ይፈጸማል።
ጉዞዋ ሁሉ ከፍኖተ መስቀል የማይለየው ቅድስት ቤተክርስቲያን በዚህ ዘመን ከገጠሟት ፈተናዎች አንዱ የሐሳዊ አጥማቂዎች ተግባር ነው።
ሃሳዊ አጥማቂዎች አበው ቅዱሳን ከተጓዙበት የንጽሕናና የመንፈሳዊ ተጋድሎ ሕይወት የተለዩ ፥ አንዳች የቅድስና ፍሬ የማይገኝባቸው "አጋንንትን እናስወጣለን" ፤ "ፀበል እናጠምቃለን" ፤ "ቅብዓ ቅዱስ እንቀባለን" እያሉ ምዕመኑን ከቤተክርስቲያን እያፈለሱ ተከታያቸው በማድረግ ከፍተኛ የሆነ ገንዘብና "ሃብት" ማከማቸት የቻሉ ለመንጋው የማይራሩ ነጣቂዎች ናቸው። ሥርዓታዊትና ኅብረታዊት የሆነችውን ቅድስት ቤተክርስቲያን በረቀቀ ሁኔታ እየተዋጉ እንደ ፕሮቴስታንት መናፍቃኑ ግለሰባዊ የሆኑ ሐሰተኛ አጋንንታዊ ምልክቶችንና ውሸተኛ ተአምራትን እያሳዩ ሕዝቡን ከሃይማኖት መንገድ እያስወጡት ይገኛል።
በነዚህ ሃሳዊ አጥማቂያን የተነሳ የእውነት መንገድ በዘመናችን እየተሰደበ ፤ የቅድስናና የንጽሕና ሕይወትም ትርጉምም እየተፈተነ ፤ ሥርዓተ ቤተክርስቲያን እየተፋለሰ ፤ ምዕመኑም እየተንገላታና እየተጎሳቆለ ይገኛል። ብዙዎች የአጋንንትን ትምህርትና ስብከት እያዳመጡ የቤተክርስቲያንን ድምፅ ለመስማት ፥ የአበውን ትምህርትና የተግሳጽ ቃል ለማዳመጥ የሚቸገሩበት ደረጃ ላይ ደርሰዋል።
ከሃይማኖት ይልቅ ድንቅና ተአምራትን የሚወዱና የሚከተሉ ብዙዎች ከዘላለማዊ ሕይወት ጋር ግንኙነት ስለሌለው ስለ ሥጋዊ ፈውስና ስለምድራዊ ጉዳይ ብለው የነዚህ ግለሰቦች ተከታይና የስህተት አሠራራቸው ሰለባ ሲሆኑ ይታያሉ። እነዚህ ሃሰተኛ አጥማቂዎች በግብራቸው ከሚነቀፉ ይልቅ ሃይማኖታቸውን ቢክዱ እንደሚመርጡ እስከመናገር የሚጨክኑ ምዕመናን በመፈጠር ላይ ናቸው። ይህም በመጨረሻው ዘመን የአጋንንትን ትምህርት እያዳመጡ ሃይማኖታቸውን ብዙዎች እንደሚክዱ ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ አስቀድሞ የተናገረው ቃል ነው። [፩ጢሞ.፬፥፩]
----------------------------------------------------
" ከሄድሁ በኋላ ለመንጋው የማይራሩ ጨካኞች ተኩላዎች እንዲገቡባችሁ ፥ ደቀ መዛሙርትንም ወደ ኋላቸው ይስቡ ዘንድ ጠማማ ነገርን የሚናገሩ ሰዎች በመካከላችሁ እንዲነሡ እኔ አውቃለሁ።" [ሥራ.፳፥፳፱]
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
🔔
ሰኞ - የካቲት 4 2016 ዓ.ም
ዘሌዋውያን 16-20
ሰላም ለሁላችሁ ይሁን! በዛሬው እለት ንባባችን ከምዕራፍ 16 እስከ 20 ድረስ እናነባለን።
ከንባብ በፊት የሚደረግ ጸሎት፡ “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፤ የአንተን ቃላት እሰማ እና እረዳ ዘንድ፥ እንዲያውም ፈቃድህን ለመፈጸም እበቃ ዘንድ የልቤን ጆሮዎች እና ዓይኖች ክፈትልኝ።” (ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ)
በዛሬው ንባባችን ላይ ስለተሠራው ኃጢአት መደረግ ያለበትን ለስርየት የሚሆን መሥዋዕት እና ለእስራኤል ስለሚሆነው የስርየት ቀን፥ የሕዝቡን ኃጢአት ተሸክሞ ወደ በርሃ ስለሚለቀቀው የፍየል ጠቦት፥ ደም መብላት ክልክል ስለመሆኑ፥ በእግዚአብሔር ፊት የረከሱ የሆኑ ሩካቤ ሥጋዎችን፥ ስለ ቅድስና እና ስለ ፍትሕ ለእስራኤል ስለተሰጡ ሕግጋት እና ሕግን ተላልፈው ቢገኙ ደግሞ ስለሚያገኟቸው ቅጣቶች አይነት እናነባለን።
*የክለሳ ጥያቄዎች*
1) በዘሌዋውያን 16 መሠረት፥ አሮን በመቀሰፍ እንዳይሞት ምን እንዳያደርግ ታዘዘ?
2) አሮን የሚያቀርበው የሁለት ፍየሎች እና አንድ አውራ በግ መሥዋዕት ለማን ኃጢአት ማስተሰርያ ነው?
3) ከእስራኤል ሕዝብ ወይም እንግዶቻቸው ውስጥ ደም የሚበላ ምን ፍርድ ይፈረድበታል?
4) በዘሌዋውያን 18 መሠረት፥ የሩካቤ ኃጢአቶች ከተዘረዘሩ በሁዋላ፥ ከእስራኤል በፊት ስላሳደዳቸው አሕዛብ እግዚአብሔር ምን አለ?
5) እስራኤል አሕዛብ በረከሩሳበው የሩካቤ ኃጢአት ከረከሱ፥ ምድሪቱ ምን እንደምታደርጋቸው ተጽፏል?
6) በዘሌዋውያን 19 ላይ ለእስራኤላውያን የተሰጠው የመጀመሪያው ትእዛዝ ምንድር ነው?
7) እስራኤላውያን ሲያጭዱ የእርሻቸውን ድንበር ፈጽመው እንዳያጭዱ የታዘዙት ለምንድር ነው?
8 ) በዘሌዋውያን 20 መሠረት፥ መናፍስት ጠሪ እና ጠንቋዮችን የሚከተል ምን ይደረጋል?
9) አባቱን እና እናቱን ለሚሰድብ የሚሰጠው ፍርድ ምንድር ነው?
10) በዘሌዋውያን 20 መሠረት፥ እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን ዳግም የሚያስታውሳቸው እና ከዚህ በፊት የገባላቸው ቃልኪዳን ምንድር ነው?
መልካም ንባብ!
/channel/OrthodoxTewahdoBooks
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
[ እግዚአብሔር ከፊትህ ያሳድዳቸዋል ! ]
" አስማተኛም ፥ መተተኛም ፥ በድግምት የሚጠነቍልም ፥ መናፍስትንም የሚጠራ ፥ ጠንቋይም ፥ ሙታን ሳቢም በአንተ ዘንድ አይገኝ።
ይህንም የሚያደርግ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት የተጠላ ነው ፤ ስለዚህም ርኵሰት አምላክህ እግዚአብሔር ከፊትህ ያሳድዳቸዋል።
አንተ ግን በአምላክህ በእግዚአብሔር ዘንድ ፍጹም ሁን።" [ ዘዳ.፲፰፥፲፩ ]
🔔
እንዲህ ያሉትን የእግዚአብሔር መንግሥትን ጠላቶች ፤ ሰራዊተ አጋንንትንና ነፍሰ ገዳዮችን ከእኛ ዘንድ እናርቅ !
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
†
[ 🕊 ድምፀ ተዋሕዶ 🕊 ]
🍒▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬🍒
[ ሕይወት የሚገኝባቸው የቅድስት ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ትምህርቶች በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን በድምፅ ይቀርባሉ። ]
[ ሳምንታዊ መርሐ-ግብር ]
🕊
[ " ቅ ዱ ሳ ት መ ጻ ሕ ፍ ት ! " ]
[ ክፍል ሁለት ]
" ይህን በመጀመሪያ እወቁ ፤ በመጽሐፍ ያለውን ትንቢት ሁሉ ማንም ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደም ፤
ትንቢት ከቶ በሰው ፈቃድ አልመጣምና ፥ ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ተልከው ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ተናገሩ።" [፪ጴጥ.፩፥፳]
💖 ድንቅ ትምህርት 💖
[ በመምህራችን በቀሲስ ኅብረት የሺጥላ ]
" የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ፥ ከመከራም ሥጋት ያርፋል።" [ ምሳ.፩፥፴፫ ]
† † †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬
👇
🕊
🕊 † ቅዱስ ማሪ ኤፍሬም ሶርያዊ † 🕊
† ታላቁ ሊቅና አፈ በረከት ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ዛሬ የፍልሰቱ መታሰቢያ ነው። †
----------------------------------------------
† [ ከስብከቱ ] †
+ " መለኮት ሥጋን ካልለበሰ በቀር ሞትን ሊሞት ሲኦልም ልትሸከመው ስለማትችል በሥጋ ከድንግል ማርያም መወለድ አስፈለገው። በዚህ ምክንያት ጌታችን የኢየሩሳሌምን ውድቀትና የልጆቿን ጥፋት ለማወጅ በአህያይቱ ውርንጫ ላይ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም እንደገባ እንዲሁ ሲኦል እርሱን ትገናኘውና በሆዷ ትሸከመው ዘንድ ልትቀበለው ከድንግል ተወለደ። ከድንግል በነሣውም ሥጋ ወደ ሲኦል በመውረድም በዘበዛት ሀብቶቿን ሁሉ በማራቆት ባዶ አደረጋት።"
† [ ከተግሣጽ ] †
+ "ፌዘኝነትን የምታፈቅራት ከሆነ ፣ ሁለመናህ እንደ ሰይጣን ነው። በባልንጀራህ ላይ የምታፌዝ ከሆነ ፣ ራስህን የዲያብሎስ አንደበት አድርገሃል። በባልንጀራህ ጉድለት ድክመት ላይ ስም እየሰጠህ የምትሳለቅ ፣ በዚህም ደስ መሰኘትን የምትወድ ከሆነ ፣ ይህን ትፈጽም ዘንድ ያተጋህ ሰይጣን አይደለም ፣ ነገር ግን አንተ የእርሱን ቦታ በጉልበት ነጥቀህ ይዘህበት ነው እንጂ።"
🕊
† ጽንዕት በድንግልና: ሥርጉት በቅድስና እመቤታችን ለቅዱስ ኤፍሬም የሰጠሽውን ጸጋውን: ክብሩን: አእምሮውን: ለብዎውን በልቡናችን ሳይብን: አሳድሪብን . . . አሜን::
† † †
💖 🕊 💖
.
[ የሰይጣን ቴያትር ! ]
ይህንን የሰይጣንን ተንኮል ተመልከቱ !
....
ከቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ሕይወት የራቀ ፤ በጽኑ መሠረተ እምነት ላይ ያልተመሰረተ ማንም ይህንን በመሰሉ አጋንንታዊ ቴያትሮች መታለሉ አይቀርም።
መንፈሳዊው ጦርነት የረቀቀ በመሆኑ የዋሃን በሰይጣን ቴያትር ውስጥ ያሉ ወጥመዶችን ለማስተዋል ይቸግራቸዋል። በመናፍቃን አዳራሽ በሰይጣንና በዋናው ፓስተር ትብብር የሚቀርቡ ቴያትሮች በአጥማቂነት ስም ወደ ቅድስት ቤተክርስቲያን ሾልከው ከገቡ ውለው አደሩ።
ቤተክርስቲያንን ያለ ዕረፍት የሚዋጋት ሰይጣን እንዲህ በቤተ ሰዎቹ በኩል ቴያትርን ያዘጋጃል። መውደቅ መነሳቱ ጩኸቱና ሽንገላው ሁሉ የቴያትሩ አካል ነው። ነብሳትን በመማረክ ከበረት ቤተክርስቲያን ለመለየት!
"የአጥማቂውን" የሚዲያ ክንፍ የሚመራው ይህ ግለሰብ እንዲህ የታጨና ለተልዕኮ የተሰማራ ነው። ያለ ዕረፍት ምዕመናንን ከካህናት አባቶቻቸው እንዲለያዩ ይሰራል። ምዕመናን ካህናትን እንዳያምኑ፣ እንዲርቁና እንዲጠሉ በማድረግ ከንስሃና ከሁሉም ምስጢራት እንዲለዩና ከቤተክርስቲያን እቅፍም ሸሽተው የአጥማቂ እገሌ ተከታይ እንዲሆኑ ይተጋል።
በዚህች ቅጽበት ብቻ ሰይጣን የሰራውን ተንኮል ያስተዋለ ማን ነው ?
ይህ የዋናውን አጥማቂ መንፈስ የተዋረሰ ግለሰብ መሰረተ እምነትን ያልተማሩ፤ ከቤተክርስቲያን የራቁ፤ በምክረ ካህን መመላለስ ያልቻሉ በዓረቡ ዓለም ያሉ ምስኪኖችን በአጋንንታዊው የገጠመኝ ትረካ እያጠመደና እያደነዘዘ ለዋናው ያስረክባል። ኑሮውንም በዚህ ይመራል።
ይህንን አጋንንታዊ አሠራር የሚቃወምን ሁሉ ጠንቋይና መተተኛና "ደብተራ" የሚል ስያሜን ያሸክማል።
" ቀኖቹ ክፉዎች ናቸውና ዘመኑን ዋጁ። "
[ኤፌ.፭፥፲፮]
† † †
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
†
የመርሐ-ግብር ማሳወቂያ !
" አጥማቂ ነን ፤ ባህታዊ ነን ፤ መምህር ነን " ብለው በአባቶቻችን ስም ስለመጡና አጋንንታዊ አሰራርን እየተከተሉ ቤተክርስቲያንን እየፈተኑ ፤ ምዕመናንንም እያጎሳቆሉ ስለሚገኙ ግለሰቦች በሚመለከት እየቀረበ የሚገኘው ተከታታይ መርሐ-ግብር
- ዛሬ ምሽት ፦ [ ልዩ መርሐ-ግብር ! ]
- [ አጋንንት የማስወጣት ስርዓት በቤተክርስቲያን ]
- [ በቀሲስ ኅብረት የሺጥላ ]
በጣት የሚቆጠሩ የዘመኑ [ ሐሳዊ አጥማቂዎች ] እና አጋንንታዊ አሠራራቸው !
† † †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬
ሐሙስ - የካቲት 7 2016 ዓ.ም
ዘኁልቁ 1-5
ሰላም ለሁላችሁ ይሁን! ዛሬ በእግዚአብሔር ቸርነት ኦሪት ዘኁልቁን ማንበብ እንጀምራለን። ኦሪት ዘኁልቁ ሊቀ ነቢያት ሙሴ ከጻፋቸው አምስቱ መጻሕፍት ውስጥ አንዱ ሲሆን፥ በዋናነት የሚነግረንም እስራኤላውያን በሲና ከተደረገው ኪዳን በሁዋላ በምድረበዳ ስላሳለፏቸው ረዥም ዓመታት ነው። በዛሬው እለት ንባባችን ከምዕራፍ 1 እስከ 5 ድረስ እናነባለን።
ከንባብ በፊት የሚደረግ ጸሎት፡ “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፤ የአንተን ቃላት እሰማ እና እረዳ ዘንድ፥ እንዲያውም ፈቃድህን ለመፈጸም እበቃ ዘንድ የልቤን ጆሮዎች እና ዓይኖች ክፈትልኝ።” (ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ)
በዛሬው ንባባችን ላይ ስለ መጀመሪያው የእስራኤል ሕዝብ ቆጠራ፥ የእስራኤላውያን ነገድ በሰፈር እንዴት እንደተመደቡ፥ ስለ አሮን ወንድ ልጆች፥ ሌዋውያን በእስራኤል ሕዝብ መካከል ስላላቸው ሚና፥ ስለ ሌዋውያን ቆጠራ፥ በእስራኤል የበኩር ልጆች ስለመተካታቸው፥ ስለ ቀዓት፥ ጌድሶን እና ሜራሪ ልጆች ተግባር እናነባለን። በተጨማሪም ንጹሓን ስላልሆኑ ሰዎች፥ ስለ በደል ካሣ እና ባሏ ስለሚጠራጠራት ሴት ጉዳይም ተጽፎ ይገኛል።
*የክለሳ ጥያቄዎች*
1) በዘኁልቁ 1 መሠረት፥ የእስራኤል ሕዝብ ቆጠራ የተደረገው መቼ ነው?
2) ከተቆጠሩት ውስጥ ዝቅተኛ እና ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ነገዶች የትኞቹ ናቸው?
3) በዘኁልቁ 2 መሠረት፥ ሁሉም ከተቆጠሩ በሁዋላ አጠቃላይ ድምራቸው ስንት ሆነ?
4) በዘኁልቁ 3 መሠረት የሌዋውያን ተግባር ምንድር ነው?
5) ሌዋውያን ሲቆጠሩ ከስንት ዓመት በላይ ያሉት ተቆጥረዋል?
6) በዘኁልቁ 4 መሠረት፥ የቀዓት ልጆች የተለዩት ለምን አይነት ተግባር ነው?
7) የጌድሶን እና የሜራሪ ልጆች ተግባርስ ምን ነበር?
8 ) በዘኁልቁ 5 መሠረት፥ እስራኤላውያን ከመካከላቸው እንዲያወጡ የተነገራቸው ምን አይነት ሰዎችን ነው?
9) አንድ ባል ሚስቱ ከሌላ ሰው እንደተኛች ቢጠረጥር ምን ያደርጋል?
10) በካህኑ ፊት ጥፋተኛ ሆና ብትገኝ ምን ትሆናለች? ጥፋተኛ ካልሆነችስ?
መልካም ንባብ!
/channel/OrthodoxTewahdoBooks
†
[ በክፋት እየባሱ ይሄዳሉ ! ]
" ነገር ግን ክፉዎች ሰዎችና አታላዮች ፥ እያሳቱና እየሳቱ ፥ በክፋት እየባሱ ይሄዳሉ።
አንተ ግን በተማርህበትና በተረዳህበት ነገር ጸንተህ ኑር ፥ ከማን እንደ ተማርኸው ታውቃለህና"
[ ፪ጢሞ. ፫ ፥፲፫ ]
[ ነውሩ የት እንደደረሰ ይህን ተመልከቱ ! ]
† † †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬
ረቡዕ - የካቲት 6 2016 ዓ.ም
ዘሌዋውያን 25-27
ሰላም ለሁላችሁ ይሁን! በዛሬው እለት ንባባችን ከምዕራፍ 25 እስከ 27 ድረስ እናነባለን።
ከንባብ በፊት የሚደረግ ጸሎት፡ “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፤ የአንተን ቃላት እሰማ እና እረዳ ዘንድ፥ እንዲያውም ፈቃድህን ለመፈጸም እበቃ ዘንድ የልቤን ጆሮዎች እና ዓይኖች ክፈትልኝ።” (ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ)
በዛሬው ንባባችን ላይ በሰባተኛው ዓመት መደረግ ስላለበት ሰንበት፥ ስለ ኢዮቤልዩ ዓመትና ሥርዓቱ፥ ዕዳ ላለበት ሰው መደረግ ስላለበት ምሕረት፥ ለድኃ በወለድ ስለማበደር የተቀመጠውን ሕግ እና ስለ ባሪያ ነጻነት እናነባለን።በተጨማሪም፥ ለእግዚአብሔር በመታዘዝ ስለሚገኝ በረከት፥ ባለመታዘዝ ደግሞ ስለሚመጣው ቅጣትም ተጽፎ ይገኛል። በስተመጨረሻም፥ ለእግዚአብሔር የሚቀርበውን መባእ በተመለከተ የተሰጠውን ሕግ በማተት ኦሪት ዘሌዋውያን ይጠናቀቃል።
*የክለሳ ጥያቄዎች*
1) በዘሌዋውያን 25 መሠረት፥ በሰባተኛው ዓመት ምን ይከናወናል?
2) በአርባ ዘጠነኛው ዓመትስ ምን የተለየ ነገር አለ? ምን እንዲደረግስ ታዝዟል?
3) ካልዘራን እና ካላከማቸን በሰባተኛው ዓመት ምን እንበላለን ብለው ለሚጠይቁ ከእግዚአብሔር የተሰጠው መልስ ምንድር ነው?
4) በዘሌዋውያን 25 ላይ ለወንድም ስለማበደር እና መኖን ስለመስጠት ምን ሕግ ተሰጥቷል?
5) በዘሌዋውያን 26 መሠረት፥ እስራኤላውያን ሕግጋቱን ከጠበቁ እግዚአብሔር ሊሰጣቸው ቃል የሚገባላቸው የመጀመሪያው በረከት ምንድር ነው?
6) ሕግጋቱን ካልጠበቁ እንደሚደርስባቸው የተነገራቸው የመጀመሪያው ነገር ምንድር ነው?
7) በዘሌዋውያን 27 መጨረሻ መሠረት፥ እግዚአብሔር እነዚህን ሁሉ ሕግጋት ለሙሴ የሰጠው በየት ነው?
መልካም ንባብ!
/channel/OrthodoxTewahdoBooks
🕊
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን †
[ † እንኩዋን ለእናታችን "ቅድስት ማርያም እንተ ዕፍረት" እና "ቅዱስ አቡሊዲስ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ † ]
[ † 🕊 ቅድስት ማርያም 🕊 † ]
ቅድስት ማርያም እንተ ዕፍረት ቅዱስ መጽሐፍ እንደሚለን በስምዖን ቤት የመድኃኔ ዓለምን እግር በእንባዋ አጥባለች:: በፀጉሯም አብሳ የ300 ብር ሽቱ ቀብታዋለች:: ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም የቀደመ ኀጢአቷን ይቅር ብሎ ከ36ቱ ቅዱሳት አንስት ደምሯታል:: [ሉቃ.፯፥፴፮-፶] (7:36-50)
+ ስለዚህች ቅድስት ሙሉ ታሪክ :-
፩. ትርጉዋሜ ወንጌልን
፪. ተአምረ ኢየሱስን
፫. ስንክሳርን እና
፬. መጽሐፈ ግንዘትን በማንበብ ማግኘት ይቻላል::
እንት ዕፍረት [ባለ ሽቱዋ ማለት ነው] ማርያም መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሚያስተምርበት ዘመን [በዘመነ ስብከቱ] የነበረችና ይህ ቀረሽ የማይሏት ቆንጆ ሴት ነበረች:: ግን መልክ የመልካም ነገሮች ምንጭ ሲሆን አይታይም::
በመልካቸው ማማር የጠፉና ያጠፉ ብዙ ሴቶችን ዓለማችን አስተናግዳለች:: ከክሊዎፓትራ እስከ ዘመናችን "ሞዴል" ነን ባዮች : እግዚአብሔር የሰጣቸውን ጸጋ የሰይጣን መደሰቻ : የገሃነም መንገድ አድርገውት ማየት [መስማት] እጅግ ያሳዝናል::
በአንጻሩ ደግሞ ብዙዎችን ያስደመመ መልካቸውን ንቀው : ሰማያዊ ሙሽርነትን የመረጡትን ቅዱሳቱን:- አርሴማን : ቴክላን : ጤቅላን : መሪናን : ጣጡስን : ሔራኒን : ኢራኒን : አትናስያን : ሶፍያን : ኢላርያን . . . ስናስብ ደስ ይለናል:: ዛሬም ጌታ በሚያውቀው ብዙ እናቶቻችን [እህቶቻችንም] ተመሳሳዩን በጐ ጐዳና መርጠው እየተጉዋዙ መሆኑን እናውቃለን::
ቅድስት ማርያምም ከፈጣሪዋ በተሰጣት ቁንጅና ክፋትን ትሠራ ዘንድ ሰይጣን ሲያገብራት "እሺ" ብላ የእሱ ወጥመድ ልትሆን ተራመደች:: ለዘመናትም ዓይነ-ዘማ : ልበ-ስስ የሆኑ ወንዶችን ወደ ኃጢአት ጐዳና ማረከች::
ለመልኩዋ ከነበራች ስስት የተነሳም ቶሎ ቶሎ ራሷን በመጽሔት [መስታውት ማለት ነው] ትመለከት ነበር:: መቼም አምላካችን ለሁሉም የመዳን ቀን ጥሪ አለውና [የሚያስተውለው ቢገኝ] ለማርያም ጥሪውን ላከላት:: ጥሪው ግን በስብከት : በመዝሙር : በመጽሐፍ . . . አልነበረም::
እንዳስለመደች ውበቷን ለመመልከት መስታውት ፊት ቆማ የራሷን ጸጉር : ግንባር : ዐይን : አፍንጫ : ጥርስ . . . እየተመለከተች ተደመመች:: ወዲያው ግን ይህ አካል አፈር እንደሚበላው የሚያስብ ልቡና መንፈስ ቅዱስ አምጥቶባት በጣም አዘነች:: የመኖር ተስፋዋ እንዳይቆረጥ ደግሞ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ዜና ሰማች::
መወሰን ነበረባትና ከሞት ወደ ሕይወት : ከጨለማ ወደ ብርሃን ልትሔድ ቆረጠች:: በአምላኩዋ ፊት የሚቀርቡም 3 ስጦታዎችን አዘጋጀች:: ሰይጣን ሊያጣት አልፈለገምና ወደ ክርስቶስ እንዳትደርስስ ብዙ መሰናክልን ፈጠረባት:: ግን ውሳኔዋ የእውነት ነበርና እያሳፈረችው ወደ አምላኩዋ ገሰገሰች::
የስምዖን ዘለምጽ በረኞችም ሊያስቀሰሯት አልተቻላቸውም:: ወደ ውስጥ ዘልቃ የያዘችውን ሁሉ ለመድኃኒታችን ሰዋች::
፩. ከውስጧ እንባዋን:
፪. ከአካሏ ጸጉሯን:
፫. ከንብረቷ ውድ የሆነውን ሽቱ አቀረበች::
ብዙ ወዳለችና ብዙ ኃጢአቷ ተሠርዮ ቅድስት እናታችን ሆነች:: ብዙ አዝማናትን ከሐዋርያት ጋር አገልግላም በዚህች ቀን ዐርፋለች::
" ቅዱስ አቡሊዲስ መምህረ ኩሉ ዓለም "
+ የዓለም ሁሉ መምህር:
¤ ባለ ብዙ ድርሳንና ተግሣጽ:
¤ የቤተ ክርስቲያን ምሰሶ:
¤ ፴፰ [38] ሕግጋትን የደነገገ:
¤ ስለ ቀናች እምነት የተጋደለ:
¤ መራራ ሞትን በደስታ የተቀበለ:
¤ የቀደመችዋ ሮም ሊቀ ዻዻሳት የነበረና:
¤ ሐዋርያትን የመሰለ አባት ነው::
+በ2ኛው መቶ ክ/ዘመን መጨረሻ አካባቢ ያበራው ይሀን ኮከብ ካቶሊካውያን ክደውታል:: እነርሱ "አቡሊዲስ የሚባል ዻዻስ አልነበረም" ቢሉም ምክንያታቸው ግን ከሰይጣን ነው:: ሃይማኖታቸውን ከመለወጣቸው 250 ዓመታት በፊት ስለተናገረባቸውና አንድ ባሕርይን ስላስተማረ መሆኑን ዓለም ያውቃል::
አባታችን ቅዱስ አቡሊዲስ የተገደለ የካቲት ፭ [5] ሲሆን የካቲት ፮ [6] ሥጋው የተገኘበት ነው::
አምላከ ቅዱሳን ከቅድስት ማርያም ንስሃዋን : ከአባ አቡሊዲስ ምሥጢረ ቅድስናውን ያድለን::
[ † የካቲት ፮ [ 6 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ቅድስት ማርያም እንተ ዕፍረት
፪. የዓለም ኁሉ መምሕር ቅዱስ አቡሊዲስ [ብዙ መንፈሳዊ ድርሳናትን የደረሰ ሊቀ ዻዻስና ሰማዕት]
፫. ቅዱሳን አቡቂርና ዮሐንስ [ሰማዕታት]
፬. ቅድስት አትናስያና ፫ [3] ቱ ሰማዕታት ልጆቿ [ቴዎድራ : ቴዎፍናና ቴዎዶክስያ]
[ † ወርኀዊ በዓላት ]
፩. ቅድስት ደብረ ቁስቁዋም
፪. አባታችን አዳምና እናታችን ሔዋን
፫. አባታችን ኖኅና እናታችን ሐይከል
፬. ቅዱስ ኤልያስ ነቢይ
፭. ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያ
፮. ቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊ
፯. ቅድስት ሰሎሜ
፰. አባ አርከ ሥሉስ
፱. አባ ጽጌ ድንግል
፲. ቅድስት አርሴማ ድንግል
ከበረከተ ቅዱሳን ይክፈለን::
" . . . አንተ ራሴን ዘይት አልቀባኸኝም:: እርሷ ግን እግሬን ሽቱ ቀባች:: ስለዚህ እልሃለሁ : እጅግ ወዳለችና ብዙ ያለው ኃጢአቷ ተሰርዮላታል:: ጥቂት ግን የሚሰረይለት ጥቂት ይወዳል:: እርስዋንም:- 'ኃጢአትሽ ተሰርዮልሻል' አላት:: ከእርሱም ጋር በማዕድ ተቀምጠው የነበሩት በልባቸው:- 'ኃጢአትን እንኩዋ የሚያስተሰርይ ይህ ማነው' ይሉ ጀመር:: ሴቲቱንም:- 'እምነትሽ አድኖሻል: በሰላም ሒጂ' አላት::" [ሉቃ.፯፥፳፮] (7:46)
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖 🕊 💖
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
የዘመኑ አጥማቅያን እና የአጋንንት ምስክርነት !
[ ክፍል ሁለት ]
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
"ቤተክርስቲያን ዘወትር ዐርብ ላይ ናት "
[ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ]
---------------------------------------------------
፩. ሃሳዊ አጥማቂዎች በፍሬያቸው ይታወቃሉ !
ለስም አጠራሩ ክብር ምስጋና ይግባውና ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ሃሰተኛ ሠራተኞች አስቀድሞ በቅዱስ ቃሉ አስተምሮናል። በዘመን ፍጻሜ ብዙ ሐሰተኞች እንደሚነሱ ፣ ሐሰተኛ የሆኑ ተአምራትና ምልክቶችን እንደሚያደርጉና በዚህም ብዙዎች እንደሚሰናከሉ ተናግሯል።
ሁሉ በፍሬው ተለይቶ ይታወቃል። የእውነትንም ሆነ የሐሰትን ሥራ የሚሠሩ ሁሉ በፍሬያቸው ይታወቃሉ። የእግዚአብሔር የሆኑት በጽድቅ ሥራ እንደሚታወቁት እንዲሁ የዲያብሎስን ሥራ የሚሠሩት ደግሞ የሃሰትን ሥራ በመሥራታቸው ተለይተው ይታወቃሉ።
"ስለዚህም ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ።" [ማቴ.፯፥፳]
በቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ሕይወት የእውነተኞቹ አበው የኑሮ ፍሬ የተገለጠ ነው። ገዳማዊ ሕይወት ፥ ክርስቲያናዊ የጸና ምግባር ፥ የጸሎት ሕይወትና መንፈሳዊ ተጋድሎ የአበው ሕይወት መገለጫዎች ናቸው። የቅድስናና የጽድቅ ሕይወት ሳይኖራቸው ማጥመቅን ብቻ መተዳደሪያ ሥራቸው ያደረጉ ከአበው መካከል ከቶ አልነበሩም።
ሀብተ ፈውስ የተሰጣቸው አባቶቻችን ይህ ጸጋቸው የመንፈሳዊ ተጋድሎ ሕይወታቸው ውጤት [ ነጸብራቅ ] እንጂ ቀጥተኛ ሥራቸው አልነበረም። አይደለምም።
የእውነተኞቹ የቅዱሳን አባቶቻችንን የቅድስና ፥ የንጽሕናና የተጋድሎ ሕይወትን መማር ዲያብሎስ በየዘመኑ ከሚያስነሳቸው ከሐሳዊ ሠራተኞች ወጥመድ ራሳችንን እንጠብቅ ዘንድ ያስችለናል።
አጋንንትን ለመቅጣት ፣ ለመስደድና ለማባረር የቅድስናና የጽድቅ ሕይወት ያስፈልጋል። ከሁሉ አስቀድመው ራሳቸውን የካዱ ፤ መስቀል መከራውን የተሸከሙ ፤ ኃላፊ ጠፊውን ዓለም የናቁ ፤ የሥጋ ፈቃዳቸውን ያሸነፉ ፤ የሰይጣንን ፈተና ድል ያደረጉ ፤ ሕጉንና ትእዛዙን እየጠበቁ እግዚአብሔርን ደስ ያሰኙ ፤ በፍጹም ትሕትና ከዓለም ተሰውረው ራሳቸውን የሚያዋርዱ ፤ በገድል የተቀጠቀጡ ፤ ሰማዕትነትን የከፈሉ ፤ በመንፈሳዊ ተጋድሎ የጽድቅን ፍሬ አፍርተው የመንፈስ ቅዱስ ማህደር የሆኑ እውነተኞቹ ቅዱሳን ናቸው ሰይጣንን ማስጨነቅ ፥ መቅጣትና መስደድ የሚቻላቸው። ያለ ተጋድሎና ያለ መንፈሳዊ ሕይወት ደረጃ ከመከራ አስቀድሞ የሚገኝም ሆነ የሚሰጥ ጸጋ የለም።
በመሆኑም ፈውስና ተዓምራት ማድረግ በብርቱ መንፈሳዊ ተጋድሎና በመንፈሳዊ ሕይወት እያደገ የብቃት ደረጃ ላይ ሲደረስ የሚገኝ እንጂ እንዲሁ በድንገት የሚገኝ አንድ የሞያ ዘርፍ አይደለም። ወትሮውንም በራሱ አጋንንትን ማስወጣት የቅድስናና የእውነተኝነት ማረጋገጫ ሊሆን አይችልም። የመተዳደሪያና የሃብት ማፍሪያ መንገድም አይደለም። ቅዱሳን አባቶቻችን ንጽሕናን ገንዘብ ሲያደርጉና የጽድቅን ፍሬን ሲያፈሩ የነብሳቸው ቅድስና ለሥጋቸው ፥ የሥጋቸው ለልብሳቸው ፥ የልብሳቸው ለጥላቸው ለነኩትና ለረገጡት ሁሉ ይተርፋል። እግዚአብሔርም ተጋድሏቸውንና ንጽህናቸውን በወደደው ሁኔታና ጊዜ ክብራቸውን ይገልጠዋል። የእግዚአብሔር ቃልና የቅዱሳን አባቶቻችን ሕይወት የሚያስተምረን ይህንን ነው።
አበው ስለ ጽድቅ ኃላፊ ጠፊውን ዓለም ንቀው ፤ የሞቀ የደላ ቤታቸውን ትተው በየበረሃው በየፍርኩታው እየተንከራተቱ ፤ በዱር በገደሉ እየተሰደዱ ግርማ ሌሊቱን ፥ ድምፀ አራዊቱን ፥ ጸብዓ አጋንንቱን ታግሠው ዳዋ ጥሰው ጤዛ እየላሱ ድንጋይ ተንተርሰው ለቁመተ ስጋ ጥቂት ጥሬዎችን እየቆረጠሙ ፤ የቀኑን ሀሩር የሌሊቱን ቁር ፣ ረሀቡን ጥሙን መከራውን ሁሉ ችለው ዘመናቸውን ሁሉ በጾምና በጸሎት ፣ በቀዊምና በስግደት ያሳለፉ ፤ ሥጋቸውን ለልዩ ልዩ መከራ በመስጠት ሰማዕትነትን በሕይወታቸው የኖሩ ናቸው። የዓለምን መልክና ውበት ንቀው ዘመናቸውን ሁሉ የክርስቶስን መከራና ግፈ ሰማዕታትን እያሰቡ በትሕርምት የሚኖሩ ናቸው።
እውነተኞቹ አባቶቻችን ስለ ክርስቶስ በአላውያን ነገሥታትና በመናፍቃን ጳጳሳት ፊት እሳቱንና ስለቱን ሳይፈሩ አንገታቸውን ለስለት ፥ ጀርባቸውን ለግርፋት ፥ እግራቸውን ለሰንሰለት ሰጥተው ጽኑ ግፍና ስቃያትን ሁሉ እየተቀበሉ የተመላለሱ ናቸው።
ስለዚህ እውነተኛ አባቶቻችን ፦
- ያላቸውን ሁሉ ትተው አምላካቸውን የተከተሉ ናቸው።
- ሕይወታቸውን በተጋድሎ ያሳለፉ ናቸው።
- ሩጫቸውን በድል የተወጡ ናቸው።
- በአንዲቱ ሃይማኖት የፀኑ በጠባቧ መንገድ የተጓዙ ናቸው።
- ከተድላ ሥጋ የሸሹ
- በትግሃ ሌሊት የጸኑ
- ያላቸውን ለድሆች በትነው በመንኖ ጥሪት የሚመላለሱ
- በትሕትና የሚኖሩ
- በአፍቅሮተ ቢጽ የሚቃጠሉ እግዚአብሔር የሚያውቃቸው ዓለም ግን የማያውቃቸው ናቸው።
የአበው ሕይወት ይህ ነው ! የቅድስት ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ሕይወት መዓዛዎች ስለ ክርስቶስ መከራንና መራራ ሞትን የታገሱ ደጋግ አባቶቻችን ናቸው። የቅድስት ቤተክርስቲያን የልዕልና መሠረት በአምላካችን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ የተሰጠውና በቅዱሳን ሕይወት የተገለጠው የንጽህና ፣ የቅድስናና የእምነት ሕይወት ነው። ቅድስት ቤተክርስቲያን አጋንንትና ሰራዊቱን ድል የምትነሳው መሠረቷ ጽድቅና እውነት በመሆኑ ነው።
" ልጆች ሆይ ፥ ማንም አያስታችሁ ፤ እርሱ ጻድቅ እንደ ሆነ ጽድቅን የሚያደርግ ጻድቅ ነው።" [፩ዮሐ.፫፥፯]
በዚህ የፍኖተ ቅድስና ሚዛንነት አሁን የተነሱ አጥማቂ ነን ባዮችንና ተግባራቸውን በመመዘን በዘመናችን የሃሰት ሥራና ክፋት የት ደረጃ እንደደረሰ ማወቅና ማስተዋል ይቻላል።
ጋኔንን በሲዲ ቀርጾ መሸጥን ፥ ቅብዓ ቅዱስ እያሉ ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን እያጠፉ የመንፈስ ቅዱስ ጸጋን እያቃለሉ ዘይትን በመቸርቸር ማከፋፈልን [ ከፕሮቴስታንት መናፍቃን በሐሰተኛ አጥማቂያን በኩል ወደ ቤተክርስቲያን ሾልኮ የገባ የኑፋቄ ልምምድ ] ፥ መቁጠሪያ ብለው እያመረቱ በገበያ መቸብቸብን ፥ በደመ ክርስቶስ የተዋጀውን የምዕመናንን ሕይወት ለአጋንንት ግዛት አሳልፎ በሚሰጥ ጸረ ክርስትና አስተምህሮና የስህተት መንፈስ ምዕመኑን ከቅድስት ቤተክርስቲያን እያፈለሱ የግል ተከታያቸውና ካዳሚያቸው ማድረግን ፥ የራስን ምስል በመላው ዓለም ከፍ ከፍ በማድረግ ዝናና ዕውቅና መሸመትን ፥ ዜና አጋንንትን በዩቲዩብ በማሠራጨት ሳንቲም መልቀምን ፥ ስግብግብነትን ፣ ነውረኝነትን ፣ አጋንንታዊ አሠራርን ፣ ከድሆችና ከምስኪኖች በተሰበሰበ ገንዘብ በቅንጡ ቪላ እየኖሩ ውድ መኪኖችን እያሽከረከሩ በቅምጥል ሕይወት መመላለስን ስንመለከት ክፋቱ ፣ ተንኮሉ ፣ ትዕቢቱ ፣ ርኩሰቱና ሰይጣናዊ አሠራሩ ሁሉ የፍጻሜ ዘመን ላይ መሆናችንን ያስረዳናል።
" ገንዘብን መውደድ የክፋት ሁሉ ሥር ነውና ፥ አንዳንዶች ይህን ሲመኙ ፥ ከሃይማኖት ተሳስተው በብዙ ሥቃይ ራሳቸውን ወጉ።" [፩ጢሞ.፮፥፲]
የሃሰተኛ አጥማቂያን ፍሬ ከማን ወገን መሆናቸውን የሚያስረዳ ነውና ከስህተት መንፈስ ራሳችንን ልንጠብቅ ያስፈልገናል።
-----------------------------------------------
"ወዳጆች ሆይ ፥ መንፈስን ሁሉ አትመኑ ፥ ነገር ግን መናፍስት ከእግዚአብሔር ሆነው እንደ ሆነ መርምሩ ፤ ብዙዎች ሐሰተኞች ነቢያት ወደ ዓለም ወጥተዋልና።" [፩ዮሐ.፬፥፩]
† † †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬
ማግሰኞ - የካቲት 5 2016 ዓ.ም
ዘሌዋውያን 21-24
ሰላም ለሁላችሁ ይሁን! በዛሬው እለት ንባባችን ከምዕራፍ 21 እስከ 24 ድረስ እናነባለን።
ከንባብ በፊት የሚደረግ ጸሎት፡ “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፤ የአንተን ቃላት እሰማ እና እረዳ ዘንድ፥ እንዲያውም ፈቃድህን ለመፈጸም እበቃ ዘንድ የልቤን ጆሮዎች እና ዓይኖች ክፈትልኝ።” (ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ)
በዛሬው ንባባችን ላይ ስለ ካህናት ቅድስና የተሰጠውን መመሪያ፥ የመሥዋዕት ቅድስና ምን መሆን እንዳለበት፥ ስለ በዓለ ፋሲካና በዓለ ናዕት፥ ስለ በዓለ መጥቅዕ፥ ዕለተ አስተስርዮ እና የዳስ በዓል እናነባለን። በተጨማሪም፥ ስለ መብራት ማብራት ሥርዓት እና በእግዚአብሔር ላይ ክፉ የተናገረ ሰው ስለሚደርስበት ቅጣትም እንዳስሳለን።
*የክለሳ ጥያቄዎች*
1) ካህን እንዲያገባ የታዘዘው ምን አይነት ሴትን ነው?
2) አንድ ሰው ሳያውቅ ከተቀደሰው ቢበላ ምን እንዲያደርግ ታዝዟል?
3) በዘሌዋውያን 23 መሠረት፥ የፋሲካ እና የቂጣ በዓል መቼ ይከበራል?
4) በሰባተኛው ወር በአሥረኛው ቀን ላይስ ምን ይከበራል?
5) በዘሌዋውያን 24 መሠረት፥ በእግዚአብሔር ላይ ስድብን የተናገረው ሰው ምን ተደረገ?
መልካም ንባብ!
/channel/OrthodoxTewahdoBooks
🕊
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን †
[ † እንኩዋን ለአባታችን "አባ ብሶይ ዼጥሮስ" እና "ቅዱስ ዕብሎይ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ † ]
[ † 🕊 አክርጵዮስ 🕊 † ]
በዚች ቀን የእስክንድሪያ አገር ሊቀ ጳጳሳት የከበረ አባት አክርጵዮስ አረፈ። እርሱም ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት አስረኛ ነው። ይህም አባት እግዚአብሄርን የሚፈራ ንፁህ ቅዱስ ነው ።
በእስክንድርያ አገርም ቄስ ሆኖ የሚያገለግል ነበር ከእርሱ በፊት የነበረ ሊቀ ጳጳሳት አባ ከላድያኖስ በአረፈ ጊዜ የእስክንድር አገር ህዝብና ኤጲስቆጶሳቱ መረጡት በወንጌላዊው ማርቆስ ወንበር ላይ ሊቀ ጵጵስና ሾሙት።
ከዚህም በኃላ እንደ ሀዋሪያት መልካም ጉዞን ተጓዘ የእግዚአብሄርን ሀይማኖት ህይወት የሆነ ህጉንም እያስተማረ ቅዱሳት መፅህፍትንም እያነበበላቸውና እያስተማራቸው መንጋዎቹን ይጠብቃቸው ነበር ሁል ጊዜም ይመለከታቸዋል አንድ የብር አላድን ወይም አንድ የወርቅ ዲናርን ጥሪት አላኖረም ከእለት ምግቡ ከቁርና ከሀሩር ስጋውን ከሚሸፈንበት ልብስ በቀር ምንም አላከማቸም።
በዚህም ተጋድሎ አስራ ሁለት አመት ኑሮ ጌታችንንም አገልግሎ በሰላም አረፈ።
[ † 🕊 ቅዱስ ዕብሎይ 🕊 † ]
አባ ዕብሎይ በቀደመ ሕይወቱ ለ፵ [ 40 ] ዓመታት በኀጢአት የኖረ: እግዚአብሔር ለንስሃ ሲጠራው "እሺ" ብሎ : ለ፵ [ 40 ] ዓመታት በንስሃ ሕይወት ተመላልሶ በበርሃ የተጋደለ: እንባው እንደጐርፍ ይፈስ የነበረ: አጋንንትንም ድል የነሳና ለፍሬ: ለትሩፋት የበቃ ቅዱስ አባት ነው:: እግዚአብሔርም ብዙ ቃል ኪዳን ገብቶለታል::
" ባርያ ሆኖ ያለ ኀጢአት: ጌታ ሆኖ ያለ ምሕረት የለምና ይቅር በለን !! " [የአባ ዕብሎይ የንስሃ ጸሎት]
[ † 🕊 አባ ብሶይ [ዼጥሮስ] 🕊 † ]
ብሶይ [ቢሾይ] በቤተ ክርስቲያን ታሪክ የተለመደ
የቅዱሳን ስም ነው:: በተለይ በምድረ ግብ በዚህ ስም ሰማዕታትም : ጻድቃንም ተጠርተውበታል:: ከእነዚህ ቅዱሳን [ከገዳማውያኑ] አንዱ የሆነው አባ ብሶይም [አንዳንዴ አባ ዼጥሮስም ይባላል] የዘመነ ጻድቃን ፍሬ ነው::
ቤተ ክርስቲያን የቅዱሳን ቤት ናት:: ያ ማለት ራሳቸውን ለክርስቶስ የለዩ ሰዎች ይኖሩባታል:: እነዚህ ሰዎች ከተለያየ ጐዳና እና ማንነት ሊመጡ ይችላሉ:: ቢያንስ ግን በንስሃ የታጠቡ መሆናቸው ወደ ተቀደሰው አንድነት እንዲገቡ ትልቅ መሠረት ይሆናቸዋል::
ቅዱሳንም አንዳንዶቹ ከእናታቸው ማኅጸን ሲመረጡ : ሌሎቹ ደግሞ ከኃጢአት ሕይወት የተመለሱ ሆነው ይታያሉ:: ደስ የሚለው ደግሞ በንስሃ ከታጠቡ በሁዋላ በፍጹም ልባቸው በመጋደላቸው እነሆ በሰማያዊ አክሊል ተከልለዋል::
አባ ብሶይ ዼጥሮስም ከኃጢአት ተመልሰው ለቅድስና ከበቁ ቀደምት አበው አንዱ ነው:: ቅዱሱ ተወልዶ ባደገባት ምድረ ግብጽ የታወቀ ሽፍታ : ዝሙተኛና ክፋቱ የተገለጠ ሰው ነበር:: ለብዙ ዘመናት በእንዲህ ካለ ግብሩ መላቀቅ ባይችል እግዚአብሔር ጥሪውን ላከለት::
የአምላካችን የጥሪ መንገዱ ብዙ ነውና ለእርሱ ደዌን ላከለት:: መቼም ወደድንም ጠላንም በሽታ ወደ እግዚአብሔር የሚያቀርብ ጥሩ ፈሊጥ [አጋጣሚ] ነው:: ዛሬም ቢሆን ዘለን : ዘለን ስንሰበርና የሐኪም መፍትሔ ሲጠፋ የግዳችን ወደ እግዚአብሔር ቤት [ወደ ጸበሉ] እንቀርባለንና:: አምላካችን ስለዚህ ጥበቡ ይክበር ይመስገን::
ቅዱስ አባት ብሶይም በሽፍትነትና በኃጢአት ኑሮ ሳለ ለሞት የሚያበቃ ደዌ ደርሶበት የአልጋ ቁራኛ ሆነ:: ኃይሉም ደከመ:: በእንዲህ እያለም በራዕዩ ያየው ነገር ፍጹም አስደነገጠው::
መላእክት ነፍሱን ወስደው መካነ ኩነኔን ካሳዩት በሁዋላ አለቀሰ::
ይልቁን ሌቦችና ዝሙተኞችን ከ፬ [4] ሲቆራርጣቸው ስላየ ፈጽሞ አዘነ : ተጸጸተ:: ፈጣሪውንም ዕድሜ ለንስሃ እንዲሰጠው ተማጸነ:: ጌታንም "አምላኬ ሆይ! ከበሽታየ ብታድነኝ : ዳግመኛ አልበድልህም:: ዓለምን ሁሉም ንቄ አገለግልሃለሁ" ሲል ተማጸነው::
እግዚአብሔርም ሰምቶት ፈጥኖ ፈወሰው:: አባ ብሶይም እንደ ቃሉ በፍጹም ልቡ ንስሃ ገብቶ መነነ:: በገዳመ አስቄጥስ [ግብጽ] ለ፴፰ [38] ዓመታት ሲኖር የላመ የጣመ በልቶ : ከሞቀ መኝታ ተኝቶ አያውቅም::
ሰውነቱን ይቀጣት ዘንድም እስከ ፴ [30] ቀን ያለ እህል ውሃ ይጾም ነበር:: በዘመኑ ሁሉም የሴት መልክን አላየም:: ንስሃን የሚወድ ጌታም ጸጋውን አብዝቶለት ብዙ ድርሳናትን ጽፏል:: የሚገርመው ደግሞ ከትህትናውና ቅድስናው የተነሳ የእያንዳንዱ ሰው ኃጢአት ተገልጦ ይታየው ነበር::
ቅዱሱ አባታችን ብሶይ ዼጥሮስ በንስሃና በቅድስና ሕይወት እንዲህ ተመላልሶ በዚህች ቀን ዐርፎ በገዳሙ ተቀብሯል:: የድካሙን ዋጋም አድልዎ ከሌለበት : ከእውነተኛው ፈራጅ ከመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተቀብሏል::
አምላከ ቅዱሳን ዕድሜ ለንስሃ : ዘመን ለፍስሐ
አይንሳን:: ከክብረ ቅዱሳንም ያካፍለን . . . አሜን !!
[ † የካቲት ፭ [ 5 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ቅዱስ አባ ዕብሎይ ገዳማዊ
፪. ቅዱስ አባ ብሶይ ጻድቅ
፫. አባ አክርዽዮስ
፬. ፵፱ "49" አረጋውያን ሰማዕታት [ፍልሠታቸው]
፭. ቅዱስ አሞኒና ሚስቱ ቅድስት ሙስያ [የታላቁ ዕብሎይ ወላጆች]
፮. አባ ኖብ ጻድቅ : መነሳንሱ ዘወርቅ
[ † ወርሐዊ በዓላት ]
፩. ቅዱስ ዼጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት
፪. ቅዱስ ዻውሎስ ሐዋርያ
፫. አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
፬. ቅዱስ ዮሐኒ ኢትዮዽያዊ
፭. ቅዱስ አሞኒ ዘናሒሶ
አምላክ በበረከታቸው ይባርከን::
" መቶ በግ ያለው : ከእነርሱም አንዱ ቢጠፋ ዘጠና ዘጠኙን በበርሃ ትቶ የጠፋውን እስኪያገኘው ድረስ ሊፈልገው የማይሔድ ከእናንተ ማን ነው? ባገኘውም ጊዜ ደስ ብሎት በጫንቃው ይሸከመዋል:: ወደ ቤትም በመጣ ጊዜ ወዳጆቹንና ጐረቤቶቹን በአንድነት ጠርቶ 'የጠፋውን በጌን አግኝቼዋለሁና ከእኔ ጋር ደስ ይበላችሁ' ይላቸዋል:: እላችሁአለሁ: እንዲሁ ንስሃ ከማያስፈልጋቸው ከዘጠና ዘጠኝ ጻድቃን ይልቅ ንስሃ በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ በሰማይ ደስታ ይሆናል።" [ሉቃ.፲፭፥፫-፯] (15:3-7)
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖 🕊 💖
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
[ እየሆነ ያለው ይህ ነው ! ! ]
ግለሰቡ ፦ ይጠይቃል
ሰይጣን ፦ " እሳት ነህ ! አባ .... ስምህን የጠራ ቦታህን የጠቀጠቀ [ የረገጠ ] የዘለዓለም ሕይወት አለው። ....
ወደድክም ጠላህም የመጨረሻው ሐዋርያ ! "
ህዝብ ፦ ዕልልታና ጭብጨባ !
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
†
[ 🕊 አጽዋማትና በዓላት 🕊 ]
የ፳፻፲፮ [ 2016 ] ዓመተ ምህረት ቀሪ አጽዋማትና በዓላት ፦
🕊
† [ ጾመ ነነዌ ] = ሰኞ የካቲት ፲፰ [ 18 ] ቀን ይገባል ።
† [ ዓቢይ ፆም ] = መጋቢት ፪ [ 2 ] ይገባል።
† [ ደብረ ዘይት ] = መጋቢት ፳፱ [ 29 ] ይሆናል ።
† [ ሆሣዕና ] = ሚያዚያ ፳ [ 20 ] ይውላል ።
† [ ስቅለት ] = ሚያዝያ ፳፭ [ 25 ] ይሆናል ።
† [ ትንሣኤ ] = ሚያዚያ ፳፯ [ 27 ] ይውላል።
🕊
† [ ርክበ ካህናት ] = ግንቦት ፳፩ [ 21 ] ይሆናል። ።
† [ ዕርገት ] = ሰኔ ፮ [ 6 ] ይሆናል።
† [ ጰራቅሊጦስ ] = ሰኔ ፲፮ [ 16 ] በዓለ ጰራቅሊጦስ ይውላል ።
† [ ፆመ ሐዋርያት ] = ሰኔ ፲፯ [ 17 ] ይገባል ።
† [ የጾመ ድህነት ] = ሰኔ ፲፱ [ 19 ] ይገባል።
† † †
💖 🕊 💖
†
[ ውሻዎችና አስማተኞች ! ]
" ዓመፀኛው ወደ ፊት ያምፅ ፥ ርኵሱም ወደ ፊት ይርከስ ፥ ጻድቁም ወደ ፊት ጽድቅ ያድርግ ፥ ቅዱሱም ወደፊት ይቀደስ አለ።
. . .
ውሻዎችና አስማተኞች ሴሰኛዎችም ነፍሰ ገዳዮችም ጣዖትንም የሚያመልኩት ውሸትንም የሚወዱና የሚያደርጉ ሁሉ በውጭ አሉ።"
[ ራእ.፳፪፥፲፩ ]
ይልቁንም በዘመናችን ቤተክርስቲያን በመናፍቃን እንድትሰደብ ፤ ክብረ ክህነት እንዲደፈር በማድረግ አባቶቻችን ካህናትን ከምዕመናን ለመለየት ሰይጣን ያዘጋጃቸውን እንዲህ ያሉ የዲያብሎስ ሠራዊቶችን ከእኛ ዘንድ እናርቅ !
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
🕊
[ † እንኳን ለሐዋርያው ቅዱስ አጋቦስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። † ]
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †
† 🕊 ቅዱስ አጋቦስ ሐዋርያ 🕊 †
† ከ፸፪ [ 72 ] ቱ አርድዕት አንዱ የሆነው ቅዱሱ ሐዋርያ ሃብተ-ትንቢት የተሠጠውና በዘመነ ሐዋርያት [በቀላውዴዎስ ቄሳር ጊዜ] በዓለም ላይ ከባድ ረሃብ እንደሚሆን ትንቢት የተናገረና በርካታ ክርስቲያኖችን ከረሃብና ከሞት የታደገ ትልቅ ሐዋርያ ነው:: [ሐዋ.፲፩፥፳፯ ] (11:27)
በቅዱስ ጳውሎስ ላይ የሚደርሰውን መከራ በመናገሩም "ሐዋርያ ትንቢት" ተብሏል:: በአገልግሎቱ ከአይሁድና ከአረማውያን ብዙዎችን ወደ ክርስትና በመሳቡ የተበሳጩ አይሁድም በዚህች ቀን ገድለውታል:: በተቀደሰ ሥጋው [መቃብሩ] ላይ ብርሃን ሲወርድ ያየች አይሁዳዊት ሴትም በክርስቶስ አምና ተሰውታለች::
††† የአባታችን በረከት ይደርብን::
[ † ካቲት ፬ [ 4 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ቅዱስ አጋቦስ ነቢይ: ሐዋርያና ሰማዕት
፪. አባ ዘካርያስ ትሩፈ ምግባር
[ † ወርኀዊ በዓላት ]
፩. ቅዱስ ዮሐንስ ሐዋርያ ወልደ ነጎድጓድ
፪. ቅዱስ እንድርያስ ሐዋርያ
፫. ቅድስት ሶፊያ ሰማዕት
፬. ቅዱስ ዮሐንስ ዘሐራቅሊ
† " በዚያም ወራት ነቢያት ከኢየሩሳሌም ወደ አንጾኪያ ወረዱ:: ከእነርሱም አጋቦስ የሚሉት አንድ ሰው ተነስቶ በዓለም ሁሉ ታላቅ ራብ ሊሆን እንዳለው በመንፈስ አመለከተ:: ይህም በቀላውዴዎስ ቄሣር ዘመን ሆነ::
ደቀ መዛሙርትም እያንዳንዳቸው: እንደ ችሎታቸው መጠን አዋጥተው በይሁዳ ለሚኖሩት ወንድሞች እርዳታን ይልኩ ዘንድ ወሰኑ:: እንዲህም ደግሞ አደረጉ:: በበርናባስና በሳውልም እጅ ወደ ሽማግሌዎቹ ሰደዱት::" † [ሐዋ. ፲፩፥፳፯]
† " ስለ እኛ ትጸልዩ ዘንድ ይገባቹሃል: ለሁሉ መልካም ነገርን እንደምትወዱና እንደምትሹ እናምናለን:: " † [ዕብ. ፲፫፥፲፰]
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖 🕊 💖
እሑድ - የካቲት 3 2016 ዓ.ም
ዘሌዋውያን 13-15
ሰላም ለሁላችሁ ይሁን! በዛሬው እለት ንባባችን ከምዕራፍ 13 እስከ 15 ድረስ እናነባለን።
ከንባብ በፊት የሚደረግ ጸሎት፡ “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፤ የአንተን ቃላት እሰማ እና እረዳ ዘንድ፥ እንዲያውም ፈቃድህን ለመፈጸም እበቃ ዘንድ የልቤን ጆሮዎች እና ዓይኖች ክፈትልኝ።” (ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ)
በዛሬው ንባባችን ላይ እግዚአብሔር ለሙሴ ስለሰጠው የለምጽ ደዌ ሕግ እናነባለን። ይህም በሰው ላይ ቢወጣ ወይም በልብስ ላይ ቢታይ ካህኑ ምን ማድረግ እንደሚኖርበት ተገልጾ እናገኛለን። በተጨማሪም፥ ከሰውነቱ ፈሳሽ ለሚወጣ ሰው ስለሚፈጸም የመንጻት ሕግም ተጽፏል።
*የክለሳ ጥያቄዎች*
1) በዘሌዋውያን 13 መሠረት፥ የለምጽ ደዌ ያለበት ሰው ምን እንዲያደርግ ታዝዟል?
2) ካህኑ ስለሚነጻው ሰው የሚያቀርበው መሥዋዕት ምንድር ነው?
3) በቤት ግንብ ላይ ደዌ ካለ ካህኑ ምን እንዲያደርግ ታዝዟል?
4) ከሰውነቱ ፈሳሽ የሚወጣ ሰው ምን እንዲያደርግ ታዝዟል?
5) ሴት ፈሳሽ ነገር ቢኖርባት በመርገሟ ስንት ቀን እንድትቀመጥ ታዝዟል?
መልካም ንባብ!
/channel/OrthodoxTewahdoBooks
†
† 🕊 ክብርት ሰንበት 🕊 †
💖
" ለክርስቶስ ፡ ይደሉ ፡ ስብሐት ፤ ለዘአብጽሐነ ፡ እስከ፡ ዛቲ ፡ ሰዓት ፤ እግዚኣ ፡ ለሰንበት ፤ አኰቴተ ፡ ነዓርግ ለመንግሥትከ ፡ ወመኑ ፡ መሐሪ ፡ ዘከማከ።
ትርጉም ፦
[ እስከዚኽች ሰዓት ለአደረሰን ለክርስቶስ ክብር ምስጋና ይገባል፡፡ የሰንበት ጌታዋ ነው፡፡ ለጌትነትህ ምስጋና እናቀርባለን፡፡ እንዳንተ ያለ ይቅር ባይ ማነው ? ]
[ ቅዱስ ያሬድ ]
† † †
💖 🕊 💖