"እንግዲህ፡ንስሓ፡ግባ፤አለዚያ፡ፈጥኜ፡ እመጣብሃለሁ፡፡" ራዕ 2፥16
🕊
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡
❖ እንኳን አደረሳችሁ ❖
የካቲት ፫ [ 3 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
[ † 🕊 ቅዱስ ማሪ ኤፍሬም ሶርያዊ 🕊 † ]
እንደ ቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ቅዱስ ኤፍሬም የተወለደው ንጽቢን በምትባል የሶርያ ግዛት ውስጥ በ፪፻፺፰ [298] / ፫፻፮ [306] ዓ/ም ነው:: ወላጆቹ በክርስቶስ የማያምኑ አላውያን ነበሩ:: [ምንም አንዳንድ ምንጮች ክርስቲያኖች ነበሩ
ቢሉም]
ቅዱሱ ተወልዶ ባደገባት ንጽቢን ዽዽስናን የተሾመ ቅዱስ ያዕቆብ የሚባል ታላቅ ሰው ነበር:: የሰማዕትነት: የሐዋርያነት: የጻድቅነትና የሊቅነት ግብር ያለው አባት ነው:: ታዲያ ቅዱስ ኤፍሬም ይሔ አባት ሁሌ ሲያስተምር ይሰማው ነበርና በስብከቱ ተማርኮ ደቀ መዝሙሩ ለመሆን በቃ::
ቅዱስ ኤፍሬም በቅዱስ ያዕቆብ እጅ ከተጠመቀ በሁዋላ ሙሉ የጣትነት ጊዜውን ያሳለፈው በትምሕርት ነው:: የሚገርመው መምሕሩ ቅዱስ ያዕቆብ ዘንጽቢን እመቤታችን ድንግል ማርያምን በፍጹም ልቡ የሚወድና ጠርቷት የማይጠግብ አባት ነውና ለልጁ ለቅዱስ ኤፍሬም ይሕንኑ አጥብቆ አስተምሮታል::
ቅዱስ ኤፍሬም ክርስትናን ሲመረምር የእመቤታችን ፍቅር ይበዛለት ጀመር:: ምክንያቱም እመ ብርሃንን ሳይወዱ ክርስትና የለምና:: እንደ እርሱ የሚወዳት የለም እስኪባል ድረስ ያገለግላት: ይገዛላትም ገባ::
እንዲህ እንደ ዛሬ የድንግል ማርያም ምስጋና በአንደበት እንጂ በመጽሐፍ አይገኝም ነበር:: እርሱ ግን ከወንጌለ ሉቃስ በስድስተኛው ወርን [ይዌድስዋን] እና ጸሎተ ማርያምን [ታዐብዮን] አውጥቶ በየዕለቱ በዕድሜዋ ልክ ፷፬ ፷፬ [ 64 64 ]ጊዜ ያመሰግናት ነበር::
በእንዲህ ያለ ግብር እያለ አርዮስ በመካዱ እርሱን ለማውገዝና ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን ለማጽናት በ ፫፻፲፯/፫፻፳፭ [ 317 / 325 ] ዓ/ም ፫፻፲፰ [318] ቱ ሊቃውንት በኒቅያ ሲሰበሰቡ አንዱ መምሕረ ኤፍሬም ቅዱስ ያዕቆብ ነበር:: በዚህ ምክንያት ቅዱስ ኤፍሬም ከሊቃውንቱ ትምሕርትና በረከትን አግኝቷል::
ከጉባዔ መልስ መንገድ ላይ በራዕይ የብርሃን ምሰሶ አይቶ "ጌታ ሆይ! ምንድን ነው?" ብሎ ቢጠይቅ "ይህማ ታላቁ ቅዱስ ባስልዮስ ነው" አለው:: እርሱም መምሕሩን ቅዱስ ያዕቆብን ተሰናብቶ ወደ ቅዱስ ባስልዮስ [ቂሣርያ] ወረደ:: ተገናኝተውም በአንድ ሌሊት ቁዋንቁዋ ተገልጦላቸው ሲጨዋወቱ አድረዋል::
በቦታው ብዙ ተአምራት ተደርጉዋል:: ቅዱስ ኤፍሬም ከታላቁ ባስልዮስ ከተማረ በሁዋላ ሃገረ ስብከት ተሰጥቶት ያስተምር ጀመር:: ሁል ጊዜ ታዲያ ጸሎቱ ይሔው ነበር:: "እመቤቴ ሆይ! ምስጋናሽ እንደ ሰማይ ከዋክብት: እንደ ባሕር አሽዋ በዝቶልኝ: እንደ እንጀራ ተመግቤው: እንደ ውሃ ጠጥቼው: እንደ ልብስም ተጐናጽፌው" እያለ ይመኝ ነበር::
አፍጣኒተ ረድኤት: ፈጻሚተ ፈቃድ እመ ብርሃንም በገሃድ ተገልጻ የልቡን ፈቃድ ፈጸመችለት:: ዛሬ ጸጋ በረከት የምናገኝበትን ውዳሴ ማርያምን ደረሰላት:: ሲደርስላትም እርሷ አእላፍ መላእክትን: ጻድቃን ሰማዕታትን አስከትላ ወርዳ: በፊቱም ተቀምጣ ሲሆን እርሱ ደግሞ ባጭር ታጥቆ: በፊቷ ቆሞ: በመንፈስ ቅዱስም ተቃኝቶ ነው::
ውዳሴዋን በ፯ [7] ቀናት ከደረሰላት በሁዋላ በብርሃን መስቀል ባርካው: ሊቀ ሊቃውንትም እንዲሆን ምስጢር ገልጣለት ዐረገች:: ከዚህ በኋላ በምስጢር ባሕር ውስጥ ዋኝቶ ፲፬ [14] ሺህ ድርሰቶችንም ደርሷል:: ዛሬ ሶርያ ውስጥ የምንሰማውን ዜማም የደረሰው ይህ ቅዱስ ነው::
እንዲያውም አንድ ቀን የምሥጢር ማዕበል ቢያማታው "አሃዝ እግዚኦ መዋግደ ጸጋከ" ብሎ ጸልዩዋል:: [የጸጋህን ማዕበል ያዝልኝ] እንደ ማለት ነው:: ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ በመጨረሻ ሕይወቱ ተክሪት በምትባል ሃገር ኤዺስ ቆዾስ ሆኖ ተሹሟል::
በጣፋጭ ስብከቱ ብዙዎችን ካለማመን መልሷል: የምዕመናንንም ሕይወት አጣፍጧል:: ለመናፍቃንና ለአርዮሳውያን ግን የማይጋፉት ግድግዳ ሆኖባቸው ኑሯል:: በዘመኑም ብዙ ተጋድሎ አፍርቷል: ተአምራትንም ሠርቷል:: በተወለደ በ፷፯ [67] ዓመቱ በ፫፻፷፭/፫፻፸፫ [365 / 373 ዓ/ም ዐርፎ ተቀብሯል::
ቅዱሱ ለሶርያ ብቻ ሳይሆን እመቤታችንን ለምንወድ የዓለም ክርስቲያኖች ሁሉ ሞገሳችን ሆኗል:: ስለዚህም እንዲህ እያልን እንጠራዋለን :-
፩. ቅዱስ ኤፍሬም
፪. ማሪ ኤፍሬም
፫. አፈ በረከት ኤፍሬም
፬. ሊቀ ሊቃውንት ኤፍሬም
፭. ጥዑመ ልሳን ኤፍሬም
፮. አበ ምዕመናን ኤፍሬም
፯. ርቱዐ ሃይማኖት ኤፍሬም . . . አባታችን አንተ ነህ::
❖ የካቲት ፫ ቀን ለቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ዓመታዊ የፍልሠት በዓሉ ነው፡፡
ጽንዕት በድንግልና: ሥርጉት በቅድስና እመቤታችን ለቅዱስ ኤፍሬም የሰጠሽውን ጸጋውን: ክብሩን: አእምሮውን: ለብዎውን በልቡናችን ሳይብን: አሳድሪብን . . . አሜን::
[ † 🕊 አባ ያዕቆብ ገዳማዊ 🕊† ]
ነቢየ ጽድቅ ቅዱስ ዳዊት "ለስሒት መኑ ይሌብዋ- ስሕተትን ማን ያስተውላታል" [መዝ] ሲል የተናገረው ይፈጸም ዘንድ ይህ ታላቅ ቅዱስ ሰው በኃጢአት ብዙ ተፈተነ:: ወደ በርሃ ወጥቶ: በምናኔ ጸንቶ: በጾምና በጸሎት ተግቶ ዘመናትን ስላሳለፈ ሰይጣንን አሳፈረው::
ግን ደግሞ ክፉ ጠላት ባልጠረጠረው መንገድ መጥቶ መከራ ውስጥ ከተተው:: የአገረ ገዢው ልጅ ታማ "ፈውሳት" አሉት: ፈወሳት:: ወደ ቤቷ ስትመለስ ግን አመማት:: "ከአንተ ጋር ትቆይ" ብለው ትተዋት ቢሔዱ ከመለማመድ የተነሳ በዝሙት ወደቀ::
እንዳይገለጥበት ስለ ፈራም ገደላት:: በሆነው ነገር ተስፋ ቆርጦ ወደ ዓለም ሲመለስ: ቸር ፈጣሪ የሚናዝዝ አባትን ልኮ ንስሃ ሰጠው:: ጉድጓድ ምሶ: ድንጋይ ተንተርሶ ለ፴ [30] ዓመታት አለቀሰ:: እግዚአብሔርም ምሮት: የቀደመ ጸጋውን ቢመልስለት: ዝናምን አዝንሞ ሕዝቡን ከእልቂት ታድጓል:: በዚህች ዕለት ዐርፎም ለርስቱ በቅቷል::
[ † 🕊 ታላቁ አባ ዕብሎይ 🕊 † ]
ይህ ቅዱስ የአቡነ አቢብ ደቀ መዝሙር ሲሆን በዚህ ስም ከሚጠሩ ቅዱሳንም ቀዳሚው ነው:: ብዙ መጻሕፍት 'ርዕሰ ገዳማውያን' ይሉታል:: የቅዱሱ ተጋድሎ እጅግ ሰፊ ነው::
[ † የካቲት [ ፫ ] 3 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት † ]
፩. ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ [ አፈ በረከት-በዓለ ፍልሠቱ ]
፪. ቅዱስ አባ ዕብሎይ ገዳማዊ [ ሕይወቱ መላዕክትን የመሰለ ግብፃዊ አባት ]
፫. አባ ያዕቆብ መስተጋድል
[ † ወርኀዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. በዓታ ለእግዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ
፪. ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና
፫. ቅዱሳን ሊቃነ ካህናት አበው [ ዘካርያስና ስምዖን ]
፬. አባ ሊባኖስ ዘመጣዕ
፭. አቡነ ዜና ማርቆስ
፮. አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ዘደብረ በንኮል
፯. ቅዱስ ቄርሎስ ሊቅ [ ዓምደ ሃይማኖት ]
+ "ለምኑ ይሰጣችሁማል:: ፈልጉ ታገኙማላችሁ:: መዝጊያ አንኳኩ ይከፈትላችሁማል:: የሚለምነው ሁሉ ይቀበላልና:: የሚፈልገውም ያገኛል:: መዝጊያንም ለሚያንኳኳ ይከፈትለታል::" + [ማቴ.፯፥፯]
+ " የጻድቅ አፍ ጥበብን ያስተምራል:: አንደበቱም ፍርድን ይናገራል::የአምላኩ ሕግ በልቡ ውስጥ ነው:: በእርምጃውም አይሰናከልም::" [መዝ.፴፯፥፴]
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖 🕊 💖
†
[ 🕊 ድምፀ ተዋሕዶ 🕊 ]
🍒▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬🍒
[ ሕይወት የሚገኝባቸው የቅድስት ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ትምህርቶች በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን በድምፅ ይቀርባሉ። ]
[ ሳምንታዊ መርሐ-ግብር ]
🕊
[ " ቅ ዱ ሳ ት መ ጻ ሕ ፍ ት ! " ]
[ ክፍል አንድ ]
" ይህን በመጀመሪያ እወቁ ፤ በመጽሐፍ ያለውን ትንቢት ሁሉ ማንም ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደም ፤
ትንቢት ከቶ በሰው ፈቃድ አልመጣምና ፥ ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ተልከው ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ተናገሩ።" [፪ጴጥ.፩፥፳]
💖 ድንቅ ትምህርት 💖
[ በመምህራችን በቀሲስ ኅብረት የሺጥላ ]
" የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ፥ ከመከራም ሥጋት ያርፋል።" [ ምሳ.፩፥፴፫ ]
† † †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬
👇
†
[ ለጥያቄዎ ምላሽ ! ]
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡
[ " ሀጢያትን መናዘዝ ለምን አስፈለገ ? እንዲሁም ሀጢያታችንን ለምን በቀጥታ ለእግዚአብሄር ብቻ አንናዘዝም ?" ]
[ ከምዕመናን የቀረበ ጥያቄ ]
🍒
----------------------------------------------
[ የተሰጠ መልስ ] ፦
ሀጢያትን ለእግዚአብሄር በካህን በኩል መናዘዝ መፅሃፍ ቅዱሳዊ መሰረት ያለዉ ከኃጢዓት ሥርየት ጋር የተገናኘ መሠረታዊ ጉዳይ ነዉ፡፡ እግዚአብሄር አዳም በበደለ ጊዜ ፦ “ አዳም ሆይ ወዴት ነህ? ” ብሎ የጠየቀዉ አዳም እንዲናዘዝ ስለፈለገ እንጂ አዳም ያደረገዉን ሳያዉቅ ቀርቶ አልነበረም፡፡ “እምቅድመ ይፍጥሮ ለአዳም የአምር ግብሮ” ”አዳምን ከመፍጠሩ በፊት ስራዉን ያዉቃል” እንዲል፡፡ አዳምም እግዚአብሄር በጠየቀዉ ጊዜ "ከእኔ ጋር እንድትሆን የሰጠኸኝ ሴት እርስዋ ከዛፉ ሰጠችኝና በላሁ” በማለት ተናዝዋል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ በተለያዩ ቦታዎች ሰዎች ሀጢያታቸዉን ይናዘዙ እንደነበር በመፅሀፍ ቅዱስ ተገልጿል፡፡ [ሐዋ.፲፱፥፲፰ ] (19-18) ፣ ማቴ.፫፥፭] ፣ [ዘሌ.፭፥፲፮] (5-16) ፣ [ኢያ.፪፥፲፱] (2- 19)፡፡ ይሁን እንጂ “ሀጢያቴን ለመተዉ ከፈቀድኩ አይበቃም ወይ? መናዘዙ ለምን አስፈለገ?”
የሚሉ ሰዎች አሉ ሀጢያትን በካህን ፊት መናዘዝ ግን የሚከተሉት ጠቀሜታዎች አሉት ፡-
- ሀጢያትን በዝርዝር በካህን ፊት መናዘዝ ዳግመኛ በዚያ ሀጢያት ላለመያዝ ሀይልን ይሰጣል፡፡ ቅዱስ ዮሃንስ አፈወርቅ “በበደሉ ላይ ድፍረትና ሽንገላን የሚጨምር [ሀጢያት ሰርቶ እንዳልሰራ ዝም የሚል] ከዚያች ሀጢያት መጠበቅ አይችልም፡፡ እርስዋን በምትመስል ሀጢያት ከመዉደቅም አይድንም” እንዳለ፡፡
- ንጉስ የሚሽረዉና የሚሾመዉን ግራና ቀኝ አቁሞ የሚሽረዉን ወቅሶ የሚሾመዉን አሞግሶ እንደሚያከብር ያለፈ ሀጢያታችንን በካሀኑ ፊት ስንዘረዝርም ያለፈዉን ሀጢያታችንን ሽረን በሚመጣዉም ህይወት ያንን ሀጢያት ላለመድገም እየወሰንን ነው፡፡
- ኑዛዜ ያሳቅቃል፡፡ መሳቀቁ ደግሞ ለሰራነዉ ሀጢያት ዋጋ ነዉ፡፡ በፍርድ ቀን ጌታ በሰማይ መላእክት ፊት ሀጢያታችንን ገልጦ ከሚያሰቅቀን ይልቅ እኛዉ እራሳችን እዚሁ እንደኛዉ ደካማ ሰዉ በሆነው በካህኑ ፊት በመናዘዝ ለሰራነው እጅግ ግዙፍ ሃጢያት የምንቀበለው ኢምንት ቅጣት ነው፡፡
- በሽታውን የደበቀ መድሃኒት የለውም እንደሚባለው የነፍሱን ደዌ ሀጢያቱን የሚደብቅም እንዲሁ መፍትሄ አያገኝም፡፡ የካህኑን ፀሎትና ምክርም ያጣል፡፡ “ሀጢያቱን የሚደብቅ /የሚሰውር አይለማም፡ የሚናዘዛትና የሚተዋት ግን ምህረትን ያገኛል” እንደተባለ ፡፡[ምሳ.፰፥፲፫] (8-13)
- ሀጢያታችንን ለምን በቀጥታ ለእግዚአብሄር ብቻ አንናዘዝም ?
· ሀጢያትን ለካህን መናዘዝ ለእግዚአብሄር አለመናዘዝ አይደለም፡፡ ሀጢያትን ለካህን መንገር ለእግዚአብሄር መናዘዝና ክብር መስጠት ነው፡፡ እያሱ እንዳለ ፦ “ልጄ ሆይ ለአምላክ ከብርን ስጥ ፡ ለእርሱም ተናዘዝ ፡ ያደረግከውንም ንገረኝ አትሸሽገኝ” [ኢያሱ.፯፥፲፱] (7-19)፡፡ ኢያሱ “ክብርን ስጥ” ያለው ለእግዚአብሄር : “ተናገር” ያለው ግን ለራሱ መሆኑ ሀጢያትን ለካህን መናዘዝ ለእግዚአብሄር ክብር መስጠት እንደሆነ ያሳየናል፡፡
አበዉ ካሀናትም ኑዛዜን ከተቀበሉ በኋላ “እግዚአብሔር ይፍታህ” እንጂ “ፈትቼሃለሁ” አይሉም፡፡ ይህም ምንም በነሱ ፊት ብንናገርም ሰሚዉም ሆነ በእነርሱ እጅ ስርየት የሚሰጠዉ እርሱ ባለቤቱ ስለሆነ ነው፡፡
“ ሁለት ወይም ሶስት በሚሆኑበት በዚያ በመካከላችሁ እገኛለሁ” ብሎ ቃል የገባ አምላክ በአናዛዚው ካህንና በተናዛዚው ምእምን መካከል ሆኖ ይሰማል፡ ስርየትንም ይሰጣል፡፡
· ሰው ሲታመም ሀኪም ቤት ሄዶ በሀኪሙ ፊት
“ቆረጠኝ ወጋኝ. . . ” እያለ ህመሙን እንደሚያብራራው ሁሉ ፡ በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ ያሉት ካህናትም የነፍስ ሀኪሞች ናቸውና እያንዳንዱን የነፍስ በሽታ [ሀጢያት] በዝርዝር በእነርሱ ፊት ልንናዘዝ ይገባል፡፡ በሀኪሙ ፊት ምንናዘዘው የእግዚአብሔርን ፈዋሽነት ክደን እንዳልሆነው ሁሉ በካህናት ፊት የምንናዘዘውም የእግዚአብሔርን ሰሚነት ክደን አይደለም፡፡
· ለምን በቀጥታ ለእግዚአብሔር አልናዘዝም ማለት በራሱ ትዕቢት ነው፡፡ ንስሃ የሚገባ ሰው ሊል የሚገባው “ከበደሌ ብዛት የተነሳ ቀና ብዬ የሰማይን ርዝመት አይ ዘንድ እንኩዋ አገባቤ አይደለም” ነው [ፀሎተ ምናሴ]፡፡
· በወንጌል እግዚአብሔር “እርስ በርሳችሁ ሀጢያታችሁን ተናዝዙ” ያለው የሰው ልጅ ከፈጣሪ ይልቅ ሰውን ስለሚፈራና ስለሚያፍር በሃጢያቱ እንዲሳቀቅ ስለፈለገ ነው፡፡
እግዚአብሔር ያየኛል ይሰማኛል ሳይል የሰራውን ሀጢያት እንዴት እግዚአብሔር ያየኛል ይሰማኛል ብሎ ይናዘዛል? እነዚህ ከእግዚአብሔር ይልቅ ሰውን የሚፈሩትን መጽሐፍ እንዲህ ይላቸዋል “እስመ ዐይነ ሰብእ ያፈርሆሙ ወኢየአምሩ ከመ አይነ እግዚአብሔር ያበርህ እምእዕላፍ ፀሀይ” ”የሰው ዐይን ያስፈራቸዋል ፡ የእግዚአብሔር ዓይን ግን ከብዙ አእላፍ ፀሀያት ይልቅ እንደሚያበራ አያውቁም!”
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር፡፡
ይቆየን !
† † †
💖 🕊 💖
🕊
[ የካቲት ፪ [ 2 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ቅዱስ አባ ጳውሊ ገዳማዊ [ የባሕታውያን ሁሉ አባት ]
፪. ቅዱስ አባ ለንጊኖስ ሊቀ ምኔት [ ደብረ ዝጋግ ]
፫. ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ
[ † ወርኀዊ በዓላት ]
፩. ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት
፪. ቅዱስ ታዴዎስ ሐዋርያ
፫. ቅዱስ ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ [ የሃይማኖት
ጠበቃ ]
፬. ቅዱስ ኢዮብ ጻድቅ
፭. ቅዱስ አቤል ጻድቅ
፮. አባ ሕርያቆስ ዘሐገረ ብሕንሳ
† " የሚበልጠውን ትንሣኤ እንዲያገኙ እስከ ሞት ድረስ ተደበደቡ። ሌሎችም መዘበቻ በመሆንና በመገረፍ ከዚህም በላይ በእስራትና በወኅኒ ተፈተኑ። በድንጋይ ተወግረው ሞቱ። ተፈተኑ፤ በመጋዝ ተሰነጠቁ፤ በሰይፍ ተገድለው ሞቱ። ሁሉን እያጡ፣ መከራን እየተቀበሉ፣ እየተጨነቁ የበግና የፍየል ሌጦ ለብሰው ዞሩ። ዓለም አልተገባቸውምና በምድረ በዳና በተራራ በዋሻና በምድር ጉድጓድ ተቅበዘበዙ። " † [ ዕብ ፲፩፥፴፭-፴፰ ]
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖 🕊 💖
†
[ በግል የምንለው ነገር አይኖርም ! ]
" አጠቃላይ የቤተክርስቲያን ጉዳይ ስለሆነ በግል የምንለው ነገር አይኖርም አሁን ! "
ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የኒውዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በአሜሪካ የነበራቸውን ሐዋርያዊ አገልግሎት ጨርሰው ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ እንዳይገቡ በመከልከላቸው በዱባይ ወደ አሜሪካ በግዳጅ እንዲመለሱ ተደርጓል።
አሜሪካ ሲደርሱም ካህናት አባቶችና የመንፈስ ልጆቻቸው በምዕመናን ተቀብለዋቸዋል። በገቡ ወቅት ይህንን ቃል ተናግረዋል።
ብፁዕ አባታችን ቡራኬዎ ትድረሰን። በረከቶ ትደርብን።
† † †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬
†
[ 🕊 ቅዱስ ራጉኤል 🕊 ]
[ የብርሃናት አለቃ ፦
ከዘጠኙ ሊቃነ መላእክት አንዱ ሲሆን በብርሃናት ላይ ተሹሟል:: ለሃገራችን ልዩ ፍቅር ያለው መልአኩ ከሔኖክ ጀምሮ የብዙ ቅዱሳን ረዳት ነው:: ዛሬ ወርሃዊ በዓሉ ነው::
ከብርሃናት አለቃ ከራጉኤል በቀር ፀሐይና ጨረቃን ከዋክብትንም የሚያዝዛቸዉም የለም። ፀሐይን በጠፈረ ሰማይ ላይ በቀን ያበራ ዘንድ አሠለጠነው፡፡ ጨረቃንም ብርሃኑን በሊት ይሰጥ ዘንድ አሠለጠነው፡፡ ከዋክብትም እንዲሁ ለሰማይ የፈርጥ ጌጥ ናቸው፡፡
ልመናው አማላጅነቱ ለሁላችን ይደረግልን፡፡
† † †
💖 🕊 💖
ዓርብ - የካቲት 1 2016 ዓ.ም
ዘሌዋውያን 1-6
ሰላም ለሁላችሁ ይሁን! ዛሬ በእግዚአብሔር ቸርነት ኦሪት ዘሌዋውያንን ማንበብ እንጀምራለን። ኦሪት ዘሌዋውያን ሊቀ ነቢያት ሙሴ ከጻፋቸው አምስቱ መጻሕፍት ውስጥ አንዱ ሲሆን፥ ስለ መሥዋዕት አይነቶች እና እግዚአብሔርን በተገቢው መንገድ ማምለክ እና ተቀድሶ መኖር የሚቻልባቸውን መንገዶች የሚያትት መጽሐፍ ነው። በዛሬው እለት ንባባችን ከምዕራፍ 1 እስከ 6 ድረስ እናነባለን።
ከንባብ በፊት የሚደረግ ጸሎት፡ “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፤ የአንተን ቃላት እሰማ እና እረዳ ዘንድ፥ እንዲያውም ፈቃድህን ለመፈጸም እበቃ ዘንድ የልቤን ጆሮዎች እና ዓይኖች ክፈትልኝ።” (ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ)
በዛሬው ንባባችን ላይ እግዚአብሔር የሚቀርቡ መሥዋዕቶችን በተመለከተ ያስቀመጣቸውን ሕግጋት እናነባለን። እነዚህ የመሥዋዕት አይነቶች የኃጢአት፥ የበደል፥ የደህንነት፥ የእህል ቁርባን እና የሚቃጠል ሲሆኑ፥ እያንዳንዱ ለምን እንደሚቀርብ፥ ሲቀርብ ምን አይነት ሥርዓትን መከተል እንዳለበት በግልጽ ተቀምጧል።
*የክለሳ ጥያቄዎች*
1) በዘሌዋውያን 1 መሠረት፥ የሚቀርበው መባ ከእንስሳ ወገን የሚቀርብ መባ ከሆነ ከምንና ከምን ይቀርባል?
2) መባው የሚቀርበው ከወፎች ከሆነ፥ ከምንና ከምን ይቀርባል?
3) በዘሌዋውያን 2 መሠረት፥ የእህል ቁርባን ከቀረበ፥ ከምን ይቀርባል? ምንስ ይጨመርበታል?
4) ከእህል ቁርባኑ የተረፈው ምን ይሆናል?
5) ለእግዚአብሔር የሚሆን የእህል ቁርባን ውስጥ እንዳይገባ የተከለከለው ምንድር ነው?
6) በዘሌዋውያን 3 መሠረት፥ እስራኤላውያን ምን እንዳይበሉ ተከለከሉ?
7) በዘሌዋውያን 4 መሠረት፥ ለኃጢአት መሥዋዕት የሚቀርበው ምንድር ነው?
8 ) በዘሌዋውያን 5 መሠረት፥ ኃጢአት ያደረገ እስራኤላዊ የበደል መሥዋዕት ከማምጣቱ በፊት ምን ማድረግ ይኖርበታል?
9) የታዘዘውን የኃጢአት መሥዋዕት ለማምጣት ገንዘብ የሌለው ሰው በምን መተካት ይችላል?
10) በዘሌዋውያን 6 መሠረት፥ በመሠዊያው ላይ እሳት የሚነድደው እስከ መቼ ነው?
መልካም ንባብ!
/channel/OrthodoxTewahdoBooks
/channel/c/2014228571/1
"ጸሎት"ን የማታፈቅር ሰው ከሆንክ፥
ምንም ዓይነት በጎ ነገር በውስጥኽ እንደማይኖር ዕወቅ፤
ወደ እግዚአብሔር የማትጸልይ ከሆነ፣
በመንፈሳዊነትኽ ሞተኻል፣ ...
የውስጥ ሰላምም አይኖርኽም፣
የክፉ ሰዎች እና የአጋንንት መጫወጫም ትኾናለህ፣...
ሕይወትም የለኽም፣...
{[ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ]}
†
[ አንዳንዶች ይህን ሲመኙ ! ]
" ዳሩ ግን ባለ ጠጎች ሊሆኑ የሚፈልጉ በጥፋትና በመፍረስ ሰዎችን በሚያሰጥምና በሚያሰንፍ በሚጎዳም በብዙ ምኞትና በፈተና በወጥመድም ይወድቃሉ።
ገንዘብን መውደድ የክፋት ሁሉ ሥር ነውና ፥ አንዳንዶች ይህን ሲመኙ ፥ ከሃይማኖት ተሳስተው በብዙ ሥቃይ ራሳቸውን ወጉ።
አንተ ግን ፥ የእግዚአብሔር ሰው ሆይ ፥ ከዚህ ሽሽ ፤ ጽድቅንና እግዚአብሔርን መምሰል እምነትንም ፍቅርንም መጽናትንም የዋህነትንም ተከታተል።
መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደል ፥ የተጠራህለትንም በብዙም ምስክሮች ፊት በመልካም መታመን የታመንህለትን የዘላለምን ሕይወት ያዝ።"
[ ፩ጢሞ.፮፥፱]
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
🕊
[ † እንኳን ለቅዱሳት አንስት ሶፍያ ወአዋልዲሃ: ኦርኒ ወማኅበራኒሃ እና ለሊቁ ቅዱስ ጐርጐርዮስ ነባቤ መለኮት ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። † ]
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †
🕊 † ቅድስት ሶፍያና ልጆቿ † 🕊
† በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ታዋቂ ከሆኑ የእናቶቻችን ስሞች "ሶፍያ" ቀዳሚው ነው:: ቃሉ በጥሬው ሲተረጐም "ጥበብ [ጥበበ ክርስቶስ] Wisdom of God" ማለት ነው:: ከጻድቃንና ከሰማዕታት ወገን በዚህ ስም የተጠሩ እናቶች አሉ::
ከእነዚህ መካከል አንዷ የሆነችው በዕለቱ የምናስባት እናት ቁጥሯ ከሰማዕታት ነው:: ዋናው ዘመነ ሰማዕታት ከመጀመሩ በፊት የነበረችው ቅድስት ሶፍያ ከሕግ ትዳር ፫ ሴቶች ልጆችን አፍርታለች::
ስማቸውንም:- ጲስጢስ [ሃይማኖት] : አላጲስ [ተስፋ] : አጋጲስ [ፍቅር] ስትል ሰይማቸዋለች:: እንደሚገባም በሥርዓቱ አሳድጋ እድሜአቸው 9 : ፲ እና ፲፪ ሲደርስ ለሰማያዊ ሙሽርነት አጭታቸዋለች::
በዘመኑ "ክርስቶስን ካዱ" የሚል መሪ ተነስቶ ነበርና ቅዱሳቱ በመድኃኒታችን አምነው : ጣዖትን ዘልፈው አንገታቸውን ሰጥተዋል:: ክብረ ሰማዕትን : ሃገረ ክርስቶስንም ወርሰዋል::
🕊 † ቅድስት ኦርኒ ሰማዕት † 🕊
† "ኦርኒ" ማለት በምሥራቃውያን ልሳን "ሰላም" ማለት ነው:: ቅድስቲቱ አርበኛ የዘመነ ሐዋርያት የቤተ ክርስቲያን ፍሬ ስትሆን ተወልዳ ያደገችውም በቀድሞው የሮም ግዛት ውስጥ ነው::
ምንም ዛሬ ያለ ትውልድ ቢዘነጋት ቅድስት ኦርኒ ተወዳዳሪ የሌላት ሰማዕት : ሐዋርያዊት : ድንግል ናት:: እርሷ ውበቷን : ንግሥናዋን : ክብሯን : ሃብቷን : ወጣትነቷንና ያላትን ሁሉ ስለ ፍቅረ ክርስቶስ ሰውታለችና ክብርት ናት::
በ1ኛው መቶ ክ/ዘመን መጨረሻ አካባቢ ከሮም ቤተ መንግስት የተወለደችው ቅድስት ኦርኒ እስከ ወጣትነቷ ድረስ ክርስቶስን ልታውቀው አልተቻላትም ነበር:: ምክንያቱ ደግሞ ንጉሡ አባቷ ጣዖትን ማምለኩ ነበር::
ንግሥት እናቷ ምንም ክርስቲያን ብትሆንም ስለ ክርስትና ልትነግራት አልደፈረችም:: ይህን ብታደርግ የሚደርስባትን መከራ ታውቃለችና:: ግን ደግሞ ውስጥ ውስጡን ትጸልይላት ነበርና ፈጣሪ መንገዱን ሊከፍት ጀመረ::
መምለኬ ጣዖት አባቷ ሰው እንዳያያት ቤተ መንግስት ሠርቶ : ፲፪ ሞግዚቶችን መድቦ ጣዖት ከፊቷ አቁሞ ለዘመናት ዘጋት:: የሚገርመው ግን መልኳን እንዳያይ በበር ሆኖ የሚያስተምራት ፈላስፋ ተቀጥሮ ነበርና የዚህ ሰው ማንነቱ ነው::
መምለኬ ክርስቶስ ደግ ሰው ነበርና ፈሊጥን ይሻላት ገባ:: በዚህ መካከል ቅድስት ኦርኒ ራዕይን ታያለች:: የቤቷ መስኮቶች ተከፍተው ሳሉ በስተምሥራቅ ነጭ ርግብ : የዘይት [የወይራ] ዝንጣፊ ይዛ ገብታ : ከማዕዷ ላይ ጥላው ወጣች::
እርሷን ተከትሎ ቁራ በምዕራብ ገባ:: እባቡን ማዕዷ ላይ ጣለው:: በ3ኛው ደግሞ ንስር ገብቶ አክሊል ትቶላት ወጣ:: ቅድስቲቱም እየገረማት አረጋዊ መምህሯን "ተርጉምልኝ" አለችው::
† እርሱም :-
• ርግብ = ጥበብ [ መንፈስ ቅዱስ ]
• ዘይት = ጥምቀት
• ቁራ = ክፉ ንጉሥ
• እባብ = መከራ
• ንስር = ድል ነሺነት [ ልዑላዊነት ]
• አክሊልም = ክብረ ሰማዕታት ነው" ብሎ ተርጉሞ : ክርስቲያን ሆና ይህ ሁሉ እንደሚደረግ ነግሮ ተሰናበታት::
እርሷም ስትጸልይ ቅዱስ መልአክ ተገልጦ አጽናናት:: ያጠምቃትና ያስተምራት ዘንድም ሐዋርያው ቅዱስ ጢሞቴዎስን ልኮላታል:: ሐዋርያውም የቤተ መንግስቱን ግድግዳ ሰንጥቆ ገብቶ : ለሰማያዊ ሙሽርነት የሚያበቃ ትምህርትና ጥምቀትን ሰጥቷት ሔዷል::
ቅድስት ኦርኒም የአባቷን ጣዖታት ቀጥቅጣ ሰብራ ከአባቷ ጋር ተጣላች:: እርሱም "እገድላታለሁ" ብሎ በእንስሳት ጅራት ላይ ጸጉሯን ሲያስር እንስሶቹ ደንብረው : እጁን ገንጥለው መሬት ላይ ጥለው ገደሉት:: ቅድስት ኦርኒ ግን ጸሎት አድርሳ አባቷን ከሞት አስነሳችው:: እጁንም ቀጠለችለት::
በዚህ ምክንያት በዚያች ዕለት ብቻ አባቷና ፴ ሺህ [ 30,000 ] የከተማው አሕዛብ አምነው ተጠምቀዋል:: ቅድስት ኦርኒ ግን ኃይለ መንፈስ ቅዱስ ታጥቃ ክርስትናን ሰበከች:: ብዙም ተሰቃየች:: ንጉሡ ዳኬዎስ : ልጁና ሌሎች ፪ ያህል ነገሥታት በእሳት : በአራዊት : በግርፋትና በጦር ፈትነዋታል::
እርሷ ግን ሁሉን በኃይለ ክርስቶስ ድል ነስታለች:: ሙታም የተነሳችበት ጊዜ አለ:: በመጨረሻም በዚህች ቀን ወደ ሰማያዊ ርስት [ ገነት ] ተመስጣለች:: በዘመነ ስብከቷ ካሳመነቻቸው ባሻገር ፻፴ ሺህ [ 130,000 ] የሚያህሉ ሰዎች ለሰማዕትነት እንዲበቁም ምክንያት ሆናለች::
🕊 † ቅዱስ ጐርጐርዮስ ታኦሎጐስ † 🕊
† ቅዱሱ :-
• የዘመነ ሊቃውንት ፍሬ:
• የእንዚናዙ ኤጲስ ቆጶስ:
• የቁስጥንጥንያ ፓትርያርክ:
• የጉባዔ ቁስጥንጥንያ [ በ381 ዓ/ም] ፫ኛ ሊቀ መንበር:
• ባለ ብዙ ድርሳን:
• የቂሣርያ [ ቀጰዶቅያ ] ኮከብ:
• ብሩህ ገዳማዊ:
• መልካም እረኛ የነበረ አባት ነው::
መጽሐፈ ቅዳሴውን ጨምሮ በጻፋቸው ብዙ መጻሕፍትና በስብከቱ ከሊቃውንት ወገን "ታኦ(ዎ)ሎጐስ" ተብሎ የተጠራ እርሱ ብቻ ነው:: ትርጉሙም በግዕዙ "ነባቤ መለኮት" ማለት ነው:: በአማርኛም "አንድነትን : ሦስትነትን የተናገረ [ያመሠጠረ] እንደ ማለት ነው:: ቅዱሱ ዛሬ ዕረፍቱ ነው::
† አምላከ ቅዱሳን ከበረከታቸው ይክፈለን፡፡
በመጽናታቸውም ያጽናን፡፡
† እንዲህ ኃጢአታችን ጽዋዑን ሞልቶ በተረፈበት በዚህ ዘመን አንዲት ሰዓትም ውድ የሆነች የንስሃ ዕድሜ ናት:: እግዚአብሔር ግን ደግ ነውና ይሔው ጥርን አስፈጸመን:: ባይገባን ነው እንጂ በዚሕች ወር ውስጥ ሚሊየኖች በደዌ የአልጋ ቁራኛ ሁነዋል::
ሚሊየኖችም ለንስሃ ሳይበቁ እንዲሁ አንቀላፍተዋል [ሙተዋል]:: እስኪ እርሱ አምላካችን ቀሪውን ዘመን ደግሞ ለንስሃና ለመልካም ሥራ ባርኮ ይስጠን::
† ወርኀ ጥርን በቸር ያስፈፀመ አምላከ ቅዱሳን ወርኀ የካቲትን እንዲባርክልን እንለምነው::
🕊
[ † ጥር ፴ [ 30 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ቅድስት ሶፍያና ሦስቱ ሰማዕታት ልጆቿ [ጲስጢስ አላጲስና አጋጲስ]
፪. ቅድስት ኦርኒ ሰማዕት [በ፭ ነገሥታት እጅ የተሰቃየች : የሐዋርያው ጢሞቴዎስ ተከታይና ወደ ብሔረ ሕያዋን የተነጠቀች እናት]
፫. ቅዱስ ጐርጐርዮስ ነባቤ መለኮት
፬. አባ አክርስጥሮስ
፭. አምስቱ ደናግል ሰማዕታት [ጤቅላ: ማርያ: ማርታ: አበያ: ዓመታ]
፮. ጻድቃነ ዴጌ [የተሠወሩበት]
፯. አባ ሚናስ ሊቀ ጳጳሳት
፰. ፻፴ ሺህ "130,000" ሰማዕታት [የቅድስት ኦርኒ ማኅበር]
[ † ወርኀዊ በዓላት ]
፩. ቅዱስ ማርቆስ ዘአንበሳ
፪. ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት
፫. አባ ሣሉሲ ክቡር
† " ለእናንተም ጠጉርን በመሸረብና ወርቅን በማንጠልጠል ወይም ልብስን በመጐናጸፍ በውጭ የሆነ ሽልማት አይሁንላችሁ:: ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ዋጋው እጅግ የከበረ የዋህና ዝግተኛ መንፈስ ያለውን የማይጠፋውን ልብስ ለብሶ የተሰወረ የልብ ሰው ይሁንላችሁ:: " † [ ፩ጴጥ. ፫፥፫ ]
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖 🕊 💖
💛
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
🕊 ፍኖተ ተዋሕዶ 🕊
[ ዘወትር ረቡዕ ምሽት ]
የቅዱሳን አበው ሕይወት ፣ ድንቅ ተዓምራትና ምስክርነቶች ፣ መንፈሳዊ ትረካዎች ፣ መንፈሳዊ የኪነ-ጥበብ ዝግጅቶች ፣ አስደናቂ ምስጢራትና ከምዕመናን ለቀረቡ ጥያቄዎች አስደናቂ የሊቃውንት ምላሽ ፣ ኦርቶዶክሳዊ ማዕቀፈ እሳቤ በመ/ር ፋንታሁን ዋቄ የተሰጡ ተከታታይ አስደናቂ ትምህርቶችና የመሳሰሉት ዝግጅቶች በድምጽ ይቀርባሉ።
ይከታተሉ !
------------------------------------------
▷ " አ ስ ተ ካ ክ ለ ኝ "
[ " አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ ... ! " ]
[ 🕊 ]
----------------------------------------------
" ትእዛዝህን እንደ ወደድሁ ተመልከት ፤ አቤቱ ፥ በምሕረትህ ሕያው አድርገኝ። የቃልህ መጀመሪያ እውነት ነው ፥ የጽድቅህንም ፍርድ ሁሉ ለዘላለም ነው። " [ መዝ. ፻፲፱፥፻፶፱ ]
† † †
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
👇
ረቡዕ - ጥር 29 2016 ዓ.ም
ዘጸአት 33-36
ሰላም ለሁላችሁ ይሁን! በዛሬው እለት ንባባችን ከምዕራፍ 33 እስከ 36 ድረስ እናነባለን።
ከንባብ በፊት የሚደረግ ጸሎት፡ “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፤ የአንተን ቃላት እሰማ እና እረዳ ዘንድ፥ እንዲያውም ፈቃድህን ለመፈጸም እበቃ ዘንድ የልቤን ጆሮዎች እና ዓይኖች ክፈትልኝ።” (ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ)
በዛሬው ንባባችን ላይ እስራኤላውያን በሠሩት ኃጢአት አዝነው ጌጣቸውን ማውለቃቸውን፥ ሙሴም ከእግዚአብሔር ጋር ለመገናኘት ሕዝቡ እያየው ወደ መገናኛው ድንኳን ይገባ እንደነበር እናነባለን። እግዚአብሔር ለሙሴ ስሙን እንደገለጠ፥ ሕግጋቶችም እንደሠጠው፥ እስራኤል መጠበቅ ያለባቸውንም ሕግጋት በዝርዝር እንደሰጠው ተጽፎ ይገኛል። ሕዝቡም በተነገራቸው መሠረት፥ እንዳላቸው ጥበብ መጠን አምጡ የተባሉትን ሁሉ እንዳመጡም የምናነበው በእነዚህ ምዕራፎች ውስጥ ነው።
*የክለሳ ጥያቄዎች*
1) በዘጸአት 33 መሠረት እግዚአብሔርን የፈለገ ሁሉ ወደ የት ይወጣ ነበር?
2) ሙሴ እግዚአብሔር ክብሩን እንዲያሳየው በጠየቀ ጊዜ፥ የተሰጠው ምላሽ ምን ነበር?
3) በዘጸአት 34 መሠረት በተሰበሩት ጽላቶች ፈንታ ሙሴ ምን እንዲያደርግ ተነገረው?
4) ሙሴ ከሲና ተራራ ላይ በወረደ ጊዜ ፊቱ ምን ሆኖ ነበር?
5) በዘጸአት 35 መሠረት፥ ሙሴ ለእስራኤላውያን መጀመሪያ የነገራቸው ትእዛዝ ምንድር ነው?
6) በዘጸአት 36 መሠረት፥ እስራኤላውያን እግዚአብሔር ያዘዘውን ሥራ እንዲሠሩ ለቀረበላቸው ጥሪ ምላሻቸው ምን ነበር?
7) እግዚአብሔር ባዘዘው ሥራ ውስጥ በስልኤልና ኤልያብ የነበራቸው ሚና ምን ነበር?
መልካም ንባብ!
/channel/OrthodoxTewahdoBooks
/channel/c/2014228571/1
#ክፉ_ልማድ!
St. John merciful ቅዱስ ዮሐንስ መሐሪ የተባለ የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳስ በነበረበት በ555-619 A.D አንድ ክፉ ልማድ በተወሰኑ ክርስቲያኖች ዘንድ ተከስቶ ነበር።
በቅዳሴ ጊዜ ወንጌል ተነብቦ ትምህርት በሚሰጥበት ጊዜ፥ አቋርጠው ወጥተው የግላቸውን ወሬ አውርተው ክሩባዊው ዝማሬ በሚቀርብበት ጊዜ መልሰው ወደ ቤተክርስቲያን መግባት የለመዱ ክርስቲያኖች ነበሩ።
በዚህ ድርጊታቸው ጸንተው ሳይመለሱ ሲቀር፥ አንዴ ቅዱስ ዮሐንስ አብሯቸው የከበረ ልብሱን እንደለበሰ ወጥቶ አብሯቸው ውጭ ተቀመጠ። እነዚህ ክፉ ልማድ የያዛቸው ክርስቲያኖች ወዲያውኑ ሲያዩት ተደነቁ።
ቅዱስ ዮሐንስም አታድንቁ በጉ ባለበት እረኛው አብሮ ይኾናልና አላቸው። ወይ አብረን ሁላችንም ወደ ቤተክርስቲያን ውስጥ እንግባ ወይም ደግሞ እኔ ከእናንተ ጋር አብሬ እዚሁ ልቀመጥ። የእግዚአብሔርንም ቃል እዚሁ ውጭ ኾኜ ልስበክ።" በማለት እነዚህ ክፉ ልማድ የተጸናወታቸውን ክርስቲያኖች አስተካከላቸው።
(Orthodox parables and short stories)
ይህ ታሪክ ጥርት አድርጎ የአንዳንዶቻችንን ልማድ የሚያሳይ ነው። በቅድስት ቤተክርስቲያን ውስጥ የሚኖሩ አንዳንድ አገልጋዮች የቅዴውን ኃይል ባለመረዳት ቅዳሴውን ትተው የግላቸውን ወሬ በማውራት የሠለጠኑ እየተበራከቱ ነው ማለት ይቻላል።
በእርግጥ ከቅሴው ወጥቶ መሄድ ማለት በአካላዊ መውጣት መግባት ላይ ብቻ የተመሠረተ አለመኾኑ የታወቀ ነው። በሕሊናችን ወደ ተለያየ ቦታ በመዞር የቅዳሴን ጊዜ የምናሳልፍም ጥቂቶች አይደለንምና። ይህ ሁሉ ግን የያዝነው "የማይነገር ስጦታ" ባለማወቅና ዐውቆም በማቃለል የሚመነጭ ስሕተት ነው።
ሕይወታችን ሕያው ኾኖ የሚሠራበትን ቅዳሴን አቋርጦ እንደመውጣት ያለ ምንም ዓይነት ጉዳት የለም!! ቅዳሴው ላይ የሚነበበው ወንጌልን ስንሰማ ክርስቶስ በማይመረመር ምሥጢር በጆሯችን ውስጥ ገብቶ እንደሚቀድሰው አናውቅም ይኾን?!
በቅዳሴ ውስጥ በካህናት አድሮ የሚናገረን ኢየሱስ ክርስቶስ ነውና ከእርሱ ጋር ማውራት ትተን ወዴት ነው የምንሄደው?! ሰይጣን ጊዜያችንን እያስባከነብን ያለው በማይረባ ተራ ወሬ መኾኑን እንረዳ!! ወንጌሉን ትተን ወደ ውጭ መውጣታችን እጅግ ከባድ በደል መኾኑንም አንዘንጋ።
ወንጌሉ የቅዳሴው ክፍል መኾኑን ፈጽሞ አንርሳ። አንድ ወታደር ጠላቱን ድል የሚያደርግበትን ኃይል ትቶ ባዱ እጁን እንዴት ወደ ጠላቱ ይሄዳል?! እንዲያስ ቢያደርግ በጠላቱ ጦር ተወግቶ የሚሞት አይደለምን? እንግዲህ በቅዳሴ ጊዜ በሕሊናችን ወደየሥራችን አንጓዝ! ይልቁንም በቅዳሴው አማካኝነት ጠላታችንን የምናሸንፍበትን ጦር እንታጠቅ እንጂ!! በፍቅር ከሚያናግረን ንጉሥ የበለጠ ምንም በሥራዎቻችን ውስጥ አይኖርምና።
በቅዳሴ ውስጤ ያለውን ዜማ ወድደን ዋናውን ወንጌል ለምን እንጠላለን? በእርግጥ ቅዳሴ ማለት የክርስቶስ የማዳን ሥራ በእውነት የሚገለጥበት ልዩ አገልግሎት መኾኑን መርሳት የለብንም። ክርስቶስ ስለ እኛ መከራ በሚቀበልበት ሰዓት እንዴት የግል ተራ ወሬያችንን ለማውራት ከቀራንዮ እንወጣለን?! ቅዳሴን አቃልሎ ትቶ መውጣት ማለት በቀራኒዮ የተሰቀለውን ክርስቶስ አልፈልግም ብሎ መሄድ መኾኑን አንዘንጋው።
ማኅሌት ቆሞ ቅዳሴን አቋርጦ መውጣትና ዕጣነ ሞገድ ላይ መምጣት ማለት በር ከፍቶ ውስጥ አለመግባት ማለት ነው። እጅ ታጥቦ የቀረበን ምግብ አለመብላት ማለት ነው። ሰርግ ቤት ሄዶ ሙሽራው ሲመጣ መውጣት ማለት ነው። ሥራ ሠርቶ ያለ ዋጋ እንደመሄድ ያለ ነው!! ማኅሌትን በነቢያት ዘመን ብንመስላት ቅዳሴን በሐዋርያት ዘመን እንመስላለን። ማኅሌት ቆሞ በቅዳሴ ሰዓት መተኛት ማለት ትንቢት ተናግሮ የተመኙት ትንቢት ሲፈጸም ዐላይም ብሎ እንደ መተኛት ማለት ነው።
ቅዳሴ ማለት ድራማ ወይም ተራ መታሰቢያ ወይም ምሳሌ ማለት አይደለም። በእርግጥ ኢየሱስ ክርስቶስ ያኔ የተቀበለውን መከራ የሚቀበልበት ልዩ ሰዓት (Kairos) ማለት ነው። ሰማይና ምድር አንድ ኾነው የሚታዩበት አስደንጋጭና አስፈሪ ጊዜ ነው። እንግዲህ በዚህ ሰዓት የት ነው የምንሄደው?! ምሥጢራተ ቤተክርስቲያንን የምንረዳበት ኃይል በሚታደልበት ጊዜ ስለምን በከንቱ ወሬ ውስጥ እንታሸጋለን!!
በእርግጥ ቅዱስ ዮሐንስ መሐሪ (ምሕረት አድራጊ) ዛሬ ነው ከዚያ ጊዜ የበለጠ ከእኛ ጋር ሊቀመጥ የሚገባው። ቅዱስ ዮሐንስ ሆይ ዛሬ እኮ ዘረኝነት፣ ኢ ፍትሐዊነት፣ ትዕቢተኝነት፣ ዕቡይነትና የመሳሰሉት አረሞች አንቀውን በወንጌሉ ጊዜ ብዙዎቻችንን ውጭ አድርገውናል!! ያኔ እነዚያ ክርስቲያኖች ካደረጉት የስንፍና ኃጢአት በላይ ዛሬ እኛ ያደረግነው ይበልጣል። እባክህ ቅዱስ ዮሐንስ ሆይ ና! አብረህን ቁጭ በል! አስተሳሰባችንንም ቀይረህ ወደ ቅድስት ቤተክርስቲያን መልሰን። አንተ ካልመጣህ እኛ ሁል ጊዜም ውጭ እንቀራለንና፤ በግን ፍለጋ የሚመጣ እረኛ ጠፍቷል!! አምጪው ራሱ ውጭ ኾኗልና መሐሪው ዮሐንስ ሆይ እባክህ ወደ እያንዳንዳችን ልቦና ና! መልሰህ ወደ ቅዳሴው ውስጥ ክተተን አሜን።
በመምህር ዮሐንስ ጌታቸው
ውድ አንባብያን ይህ ጽሑፍ ብያንስ ለአንዲት ነፍስ ላኩ(Share አድርጉ) ምናልባት አንድ ሰው መልሰን ለነፍሳችን ምስክር እናገኝ ይሆናል።
/channel/BetMetsahfte
🕊
[ † እንኳን ለቅዱሳን ጻድቃነ ዴጌ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ]
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †
🕊 † ጻድቃነ ዴጌ † 🕊
† እነዚህ ጻድቃን ኢትዮዽያውያን ባይሆኑም ያበሩት በሃገራችን ነው:: ቅዱሳኑ በቁጥር ፫ ሺህ [3,000] : በዜግነት ሮማውያን ናቸው:: ከሺህ አዝማናት በፊት ከሮም ግዛት ተሰባስበው እንደ ተስዓቱ ቅዱሳን ወደ ኢትዮዽያ [አክሱም] መጥተዋል::
ቀጥለውም እዛው አካባቢ ወደሚገኝ ገዳም ገብተዋል:: ይህ ቦታ ለአክሱም ቅርብ ሲሆን በዘመነ ሐዋርያት የቅዱስ ማቴዎስ ወንጌላዊ በዓት ነበር:: የሐዋርያው በትረ መስቀልም እስካሁን አለች::
ጻድቃነ ዴጌ ሕጋቸው አንዲት : እርሷም ፍቅር ናት:: ለዘመናት በፍቅረ ክርስቶስ ታሥረው : ፍቅርን ለብሰው : በፍቅር ኑረዋል:: ሁሌም በ፳፱ [29] የጌታችንን ስም እየጠሩ ጽዋ ጠጥተዋል:: ስለ ፍቅራቸውም ጌታችን ፫ ሺህ ፩ኛ [3,001] ኛ ሆኖ : ነዳይ መስሎ አብሯቸው ጠጥቷል::
በመጨረሻም ፫ ሺው በአንድነት ተሠውረዋል::
† ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን:: እኛንም በወዳጆቹ ጸሎት ይማረን:: . . .አሜን !
🕊
[ † ጥር ፳፱ [ 29 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ጻድቃን ቅዱሳን ማሕበረ ዶጌ [ዴጌ ጻድቃን]
[አክሱም አካባቢ በቁጥር ወደ ፫ ሺህ [3,000] ሲሆኑ ከመድኃኔ ዓለም ጋር ማሕበር ይጠጡ የነበሩና በአንድ ላይ የተሠወሩ ቅዱሳን ናቸው]
፪. አባ ገብረ ናዝራዊ ዘቃውንት [ኢትዮዽያዊ]
፫. ቅድስት አክሳኒ ፈላሲት
፬. ቅዱስ ሰርያኮስ ሰማዕት
፭. አባ እስጢፋኖስ ገዳማዊ
፮. ከድሮዋ ሮም የተነሱ ቅዱሳት አንስት
[ † ወርሐዊ በዓላት ]
፩. ቅድስት አርሴማ ሰማዕት
፪. ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ እናታችን
፫. ቅዱስ ዼጥሮስ ተፍፃሜተ ሰማዕት
፬. ቅዱስ ማርቆስ ዘቶርማቅ
፭. ቅዱስ ዘርዐ ክርስቶስ
† " ጻድቃን ምድርን ይወርሳሉ:: በእርስዋም ለዘለዓለም ይኖራሉ:: የጻድቅ አፍ ጥበብን ያስተምራል:: አንደበቱም ፍርድን ይናገራል:: የአምላኩ ሕግ በልቡ ውስጥ ነው:: በእርምጃውም አይሰናከልም:: " † [መዝ.፴፮፥፳፱]
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖 🕊 💖
†
🕊 [ እመቤቴ ] 🕊
" የልዑል እግዚአብሔር እናቱ ድንግል ማርያም ሆይ ከኪሩቤል ትበልጫለሽ፡፡ ከሱራፌልም ትበልጫለሽ፡፡ ለሚያበራው የምስጋና ዙፋን አንቺ ነሽና፡፡ በዘመን የከበረ እግዚአብሔር በላዩ የተቀመጠበት ፣ የሚያንጸባርቅ የእሳት ሰረገላም አንቺ ነሽ፡፡ የእግዚአብሔር መልእክተኛ ዳንኤል ያየሽም አንቺ ነሽ፡፡
ድንግል ሆይ አንቺ ደመና ነሽ፡፡ ልጅሽም የይቅርታ ዝናም ነው፡፡ አንቺ መዝገብ ነሽ ልጅሽም የሀብት መገኛ ምንጭ ነው፡፡ አንቺ የወይን ሐረግ ነሽ ፣ ልጅሽም ፍሬ ነው፡፡ የእስራኤል ንጉሥ የዳዊት ልጅ ሙሽራ ሆይ በልመና እጠራሻለሁ ፤ በፊትሽም እማጸናለሁ፡፡ ከሚያስለቅስ የኀዘን መቅበዝበዝም አረጋጊኝ፡፡ የማይጎድል ሙሉ ደስታንም ስጪኝ፡፡ በዘመኔ ሁሉም ጤነኛ አድርጊኝ፡፡ ለዘላለሙ አሜን፡"
[ እንዚራ ስብሐት ]
† † †
💖 🕊 💖
ቅዳሜ - የካቲት 2 2016 ዓ.ም
ዘሌዋውያን 7-12
ሰላም ለሁላችሁ ይሁን! በዛሬው እለት ንባባችን ከምዕራፍ 7 እስከ 12 ድረስ እናነባለን።
ከንባብ በፊት የሚደረግ ጸሎት፡ “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፤ የአንተን ቃላት እሰማ እና እረዳ ዘንድ፥ እንዲያውም ፈቃድህን ለመፈጸም እበቃ ዘንድ የልቤን ጆሮዎች እና ዓይኖች ክፈትልኝ።” (ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ)
በዛሬው ንባባችን ላይ ከትላንቱ ሐሳብ በመቀጠል የበደል እና የደኅንነት መሥዋዕት እንዴት እንደሚቀርቡ፥ ስብና ደምን መብላት ተገቢ እንዳልሆነ እና ከደኅንነቱ እና ከበደል መሥዋዕቱ ውስጥ የካህናት ፈንታን በተመለከተ እናነባለን። ከዚህ በተጨማሪ ለአሮን እና ልጆቹ የተፈጸመውን የክህነት ሥርዓት፥ ናዳብና አብዩድ በእግዚአብሔር ፊት ስለሰሩት ስህተት፥ ስለሚበሉ እና ስለማይበሉ እንስሳት የተሰጠውን ዝርዝር ሕግ እና፥ ሴት ከወለደች በሁዋላ የምትነጻነበትን ጊዜ በተመለከተ ለእስራኤል የተሰጠውን ሕግ በዝርዝር እናነባለን።
*የክለሳ ጥያቄዎች*
1) በዘሌዋውያን 7 መሠረት፥ ለሰው የሚቃጠል መሥዋዕት ያቀረበ ሰው፥ የሚቃጠለውን መሥዋዕት ቁርበት ምን ያደርገዋል?
2) በዘሌዋውያን 7 መሠረት፥ እርሾ ያለበት መሥዋዕት መቅረብ የሚችለው በምን ሁኔታ ውስጥ ነው?
3) ሙሴ የአሮንን እና የልጆቹን የክህነት ሥርዓት ሲፈጽም፥ ለመሥዋዕት የሚሆን ምን እንስሳ አቀረበ?
4) ሙሴ ከእንስሳው ደም ወስዶ አሮንን እና ልጆቹን ምን ላይ ቀባቸው?
5) አሮንና ልጆቹ የክህነታቸው ቀን እስኪፈጸም ምን ያህል ቆዩ?
6) በዘሌዋውያን 9 መሠረት፥ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ከተሰዋ በሁዋላ፥ እግዚአብሔር በምን መልኩ ክብሩን ገለጠ?
7) በእግዚአብሔር ፊት የበደሉት የአሮን ልጆች እነማን ናቸው? በደላቸውስ ምን ነበር?
8 ) የአሮን ልጆች ለበደላቸው ምን ቅጣት ደረሰባቸው?
9) እስራኤላውያን ከሚበሩ እና አራት እግር ካላቸው ሁሉ የተፈቀደላቸው ብቸኛ ነገር ምንድር ነው?
10) በዘሌዋውያን መሠረት፥ የወለደች ሴት የመንጻትዋ ቀን እስኪፈጸም ድረስ ምን ያህል ትቆያለች?
መልካም ንባብ!
/channel/OrthodoxTewahdoBooks
💖
በምሽቱ የድምፀ-ተዋሕዶ መርሐ-ግብራችን "ቅዱሳት መጻሕፍት" በሚል ርዕስ በአባታችን በቀሲስ ኅብረት የሺጥላ የተሰጠ ተከታታይ ትምህርት ክፍል አንድ የሚቀርብ ይሆናል።
መጽሐፍ ቅዱስንና ሌሎች ቅዱሳት መጻሕፍትን እንደገዛ ምኞታቸው እየተረጎሙ ስተው የሚያስቱ ሰዎች በበዙበት በዚህ ጊዜ ይህንን የቤተክርስቲያንን ትምህርት መማር ራስንና የሚሰሙንን ከስህተትና ከጥፋት ለማዳን እጅግ ይጠቅማልና እንከታተል !
† † †
💖 🕊 💖
†
[ 🕊 መዝሙረ ተዋሕዶ 🕊 ]
🍒▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬🍒
[ ኦርቶዶክሳዊ የተቀደሰ ያሬዳዊ ዝማሬ ሰዓት ]
[ ሳምንታዊ መርሐ-ግብር ]
🕊
በስመ አብ ፡ ወወልድ ፡ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን፡፡
ኦርቶዶክሳዊ መዝሙር ንጹሕና የተቀደሰ ነው ፥ ለእግዚአብሔር ምስጋናና ልመና የሚቀርብበት ፣ ይቅርታና ምሕረት የሚጠየቅበት ፣ ሰውን ሳይሆን እግዚአብሔርን ደስ ለማሰኘት የሚዘጋጅ ንጹሕ መስዋዕት ነው ፥ በአበው ጸሎት ይዘጋጃል ፥ ከስጋዊና ከደማዊ ሀሳብ የራቀ ነው ፥ ልቦናን ወደ ንስሐ ይጠራል ፥ ከኃጢአትና ከክፉ ሥራ የመለየት ኃይል አለው ፥ ክፉ መንፈስን ከሰው ልብ ያርቃል ፥ መረጋጋትን ልቦናን ዘልቆ የሚሰማ ውስጣዊ ሰላምን ይሰጣል ፥ በአሚነ ሥላሴ ያጸናል ፥ የክርስቶስን የባህርይ አምላክነትና መሐሪነት ይመሰክራል ፥ የእመቤታችንን ፍቅር በልቦና ያሳድራል ፥ በእናትነቷና በምልጃዋ እንድንታመን ያደርጋል ፥ በቅዱሳን ጸሎትና በቃል ኪዳናቸው ያጸናል ፥ ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን እናውቅ ዘንድ መንገድ ይመራናል ፥ ፈሪሐ እግዚአብሔርንና ፍቅረ እግዚአብሔርን ያጎናጽፈናል፡፡
† † †
ተወዳጆችሆይ ፦ በተቀደሰ ሰማያዊ ያሬዳዊ ዜማ ነብሳችንን እናስጊጣት፡፡ ከደጋጎቹ አባቶቻችን ጋር ከዓለም ርኩሰት በተለየ የተቀደሰ ዝማሬ አምላካችን እግዚአብሔርን እናመሥግን፡፡ ለስጋዊ ጆሮዎች ከሚመች ከረከሰ የተሃድሶ የኑፋቄ እርሾ ልቦናችንን እንጠብቅ፡፡ ገንዘብን ስለመውደድ ከሆነ ከሥጋዊ ሥራ ፈጽሞ እንለይ፡፡
🍒
[ 🕊 መስቀል ቤዘወነ ! 🕊 ]
[ " ከቀስት ፊት ያመልጡ ዘንድ ፥ ለሚፈሩህ ምልክትን ሰጠሃቸው።" { መዝ.፷፥፬ } ]
† † †
💖 🕊 💖
🕊
[ † እንኳን ለታላቁ ገዳማዊ አባ ጳውሊ እና ለጻድቁ አባ ለንጊኖስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ]
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †
🕊 † ታላቁ ቅዱስ ጳውሊ † 🕊
† በቤተ ክርስቲያን አስተምሕሮ "ታላቁ /ዐቢይ/ THE GREAT" የሚል ስም የሚሰጣቸው አባቶች የተለዩ ናቸው። አንድም እጅግ ብዙ ትሩፋቶችን የሠሩ ናቸው። በሌላ በኩል ደግሞ በተመሳሳይ ስም ከሚጠሩ ሌሎች ቅዱሳን እንለይበታለን።
ገዳማዊ ሕይወት ጥንቱ ብሉይ ኪዳን ነው። በቀዳሚነትም በደብር ቅዱስ አካባቢ ይኖሩ የነበሩ ደቂቀ ሴት እንደ ጀመሩት ይታመናል። ሕይወቱ በጐላ በተረዳ መንገድ የታየው ግን በታላቁ ጻድቅ ሄኖክ ከዚያም በቅዱሱ ካህን መልከ ጼዴቅ አማካኝነት ነው።
ቀጥሎም እነ ቅዱስ ኤልያስ ነቢይ እነ ኤልሳዕ ደቀ መዝሙሩ ኑረውበታል። በሐዲስ ኪዳን ደግሞ ሙሉ ሕይወቱን በገዳም [በበርሃ] ያሳለፈው መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ቅድሚያውን ይይዛል።
ለስም አጠራሩ ስግደት ይሁንና መድኃኒታችን ክርስቶስ በገዳመ ቆረንቶስ ለአርባ ቀናት በትሕርምት ኑሮ ገዳማዊ ሕይወትን ቀድሷል፤ አስተምሯል። በዘመነ ስብከቱም ያድርባት የነበረችው የደብረ ዘይቷ በዓቱ [ኤሌዎን ዋሻ] በራሷ ለዚህ ሕይወት ትልቅ ማሳያ ናት።
ከጌታ ዕርገት በኋላም ክርስቲያኖቹ የዓለም ሁካታ ሲሰለቻቸው አንድም በንጹሕና በተሸከፈ ልቡና ለፈጣሪያቸው መገዛትን ሲሹ ከከተማ ወጣ እያሉ ይኖሩ እንደ ነበር የታሪክ መዛግብት ያሳያሉ። አኗኗራቸውም በቡድንም በነጠላም ሊሆን ይችላል። ዋናው ነገር ግን በጾምና በጸሎት መትጋታቸው ነው። ይህም ሲያያዝ እስከ ሦስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ደረሰ። በዚህ ዘመን ግን አባ ጳውሊ የሚባል ንጹሕ ክርስቲያን ይህንን ሕይወት ወደ ሌላ ደረጃ ከፍ አደረገው። ለሰማንያ ዓመታት ሰው ሳያይ ተጋድሎ "የባሕታውያን አባት" ተባለ። ደንብ ያለው ተባሕትዎም ጀመረ።
ይህ ከሆነ ከሃያ ዓመታት በኋላ ደግሞ አባ እንጦንስ የሚባሉ ደግ ክርስቲያን ይህንን ገዳማዊ ሕይወት በሌላ መንገድ አጣፈጡት። በቅዱስ ሚካኤል አመንኳሽነት ገዳማዊ ሕይወት በምንኩስና ተቃኘ። ስለዚህም አባ እንጦንስ የመነኮሳት አባት ተባሉ።
እርሳቸውም ሕይወቱን ለማስፋፋት ከተለያዩ አሕጉር ደቀ መዛሙርትን እየተቀበሉ አመንኩሰዋል። ቅዱሳን የአባ እንጦንስ ልጆችም ወደየ ሃገራቸው ተመልሰው ሕይወቱን በተግባር አሳይተው ገዳማዊነትን አስፋፍተዋል።
አንድ ቀን ቅዱስ እንጦንስ [የመነኮሳት ሁሉ አባት] እንዲህ ሲል አሰበ። "በውኑ በበርሃ ለበርካታ ዘመናት በመኖር ከእኔ የሚቀድም [የሚበልጥ] ሰው ይኖር ይሆን?"
ይህንን ሃሳቡን ገና ሳይጨርሰው ቅዱስ ሚካኤል ወደ እርሱ ዘንድ ደረሰ።
"እንጦንስ ሆይ! ከእኔ የሚቀድም የበርሃ ሰው ይኖር ይሆን ብለህ አስበሃል። በእርግጥም ከአንተ ሃያ ዓመታትን ቀድሞ ወደ በርሃ የገባ ፣ በቅድስናው ፈጣሪውን ያስደሰተ ፣ ዓለም ከነ ክብሯ የእግሩን መረገጫ ያህል እንኳ የማትመጥነው በጸሎቱና በምልጇው ዓለም የምትጠበቅለት ሞገስን የተሞላ አንድ ሰው በበርሃ ስላለ ሒድና ተመልከተው።" ብሎት ተሠወረው።
ቅዱስ እንጦንስም ከሰማው ነገር የተነሳ እየተደነቀ ተነሳ። እርሱ ካለበት በርሃ በራቀ መንገድም ለቀናት ተጉዞ አንድ በዓት [ዋሻ] በር ላይ ደረሰ። በበሩ አካባቢ የሰውና የአራዊት ኮቴ ተመልክቶ በሩን ጸፋ [ቆፈቆፈ]። በውስጥ ያለው አረጋዊ ሰው ግን ትልቅ ድንጋይ ገልብጦ በሩን አጠበቀው። ለሰማንያ ዓመታት ሰውን አይቶ አያውቅምና ሰይጣን ሊያታልለኝ መጥቷል ብሎ አስቧል። ቅዱስ እንጦንስ ግን "ኃሠሥኩ እርከብ ጐድጐድኩ ይትረኃው ሊተ - ሽቻለሁና ላግኝ፤ ደጅ መትቻለሁና ይከፈትልኝ።" ሲል አሰምቶ ተናገረ።
ቅዱሱ ገዳማዊም ሰው መሆኑን ሲያውቅ በሩን ከፈተለትና ወደ ዋሻው አስገባው። መንፈሳዊ ሰላምታንም ተለዋወጡ። ሲመሽም ቅዱስ እንጦንስ ሽማግሌውን ገዳማዊ "ስምህ ማን ነው?" ቢለው "ስሜን ካላወክ ለምን መጣህ?" ሲል መለሰለት።
ያን ጊዜ ቅዱስ እንጦንስ ቀና ብሎ ሰማይን ሲመለከት ምሥጢር ተገለጠለትና "ቅዱስ ጳውሊ ሆይ! ከአንተ ጋር ያገናኘኝ ፈጣሪ ይክበር፤ ይመስገን።" ሲል ፈጣሪውን ባረከ። ቅዱስ ጳውሊም መልሶ [በጸጋ አውቆት] "አባ እንጦንስ ሆይ! እንኳን ደህና መጣህ።" አለው። ሁለቱም ደስ ብሏቸው ፈጣሪያቸውን እያመሰገኑ ተጨዋወቱ።
ቤተ ክርስቲያን ለሁሉም ዓይነት የቅድስና ሕይወት የመጀመሪያ የምትላቸው አላት። ለምሳሌ፦
የመጀመሪያው ሐዋርያ ቅዱስ እንድርያስ፣
የመጀመሪያው ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስ፣
የመጀመሪያው ባሕታዊ [ገዳማዊ] ቅዱስ ጳውሊ እና የመጀመሪያው መነኮስ ቅዱስ እንጦንስን ማንሳት እንችላለን።
ቅዱስ ጳውሊ የተወለደው በሰሜናዊ ግብጽ በእስክንድርያ ከተማ ሲሆን ዘመኑም ሦስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ ነው። ወላጆቹ ባለጸጐች ነበሩ። ቅዱሱንና ታላቅ ወንድሙን አባ ጴጥሮስን ወልደዋል። ሁለቱ ክርስቲያን ወንድማማቾች ገና ወጣት ሳሉ ወላጆቻቸው ሞቱባቸው። ሃዘናቸውን ፈጽመው ሃብት ሲካፈሉ ግን መስማማት አልቻሉም።
ምክንያቱ ደግሞ ትልቁ ጴጥሮስ ደህና ደህናውን እቃ ወስዶ መናኛ መናኛውን ለትንሹ ለጳውሎስ [ጳውሊ] መስጠቱ ነበር። ስለዚህ ነገር ተካሰው ወደ ፍርድ ቤት ሲሔዱ ግን መንገድ ላይ አንድ ባለጸጋ ሙቶ ደረሱ።
ቆመው ሳሉም ቅዱስ መልአክ ሰው መስሎ ጳውሊን "ይህ ሰው ባለጸጋ ነው። በገንዘቡ የሰጠውን ፈጣሪ ሲበድልበት ኑሮ እነሆ ተሸኘ። በሰማይም አስጨናቂ ፍርድ ይጠብቀዋል።" ሲል ነገረው።
በዚያች ቅጽበት የወጣቱ ጳውሊ ሐሳብ ተለወጠ። ወደ ወንድሙ ተመልሶ "ወንድሜ ሆይ! ሁሉ ንብረት ያንተ ይሁን።" ብሎት ከአካባቢው ጠፋ። በመቃብር ሥፍራ ለሦስት ቀናት ያለ ምግብ ጸልዮ የእግዚአብሔር መልአክ ሰው ወደ ማይደርስበት በርሃ ወሰደው።
በዚያም ምንጭ ፈለቀችለት። እየጾመ ይጸልይ ይሰግድ ገባ። ሁሌ ማታ ግማሽ ሕብስት ከሰማይ እየወረደለት ቅዳሜና እሑድ መላእክት እያቆረቡት ለሰማንያ ዓመታት ኖረ። [አንዳንድ ምንጮች ግን ለዘጠና ዓመታት ይላሉ።] ከቅዱስ እንጦንስ ጋር የተገናኙትም ከዚህ በኋላ ነው።
ከቅዱስ እንጦንስ ጋር በነበራቸው የሁለት ቀናት ቆይታም ቅዱስ ጳውሊ ብዙ ትንቢቶችን ተናግሯል። በዚህች ቀን ሲያርፍም መቃብሩን አናብስቱ ቆፍረዋል። ቅዱስ እንጦንስም በክብር ቀብሮታል። ለሰማንያ ዓመታት የለበሳት የዘንባባ ልብሱም ሙት አስነስታለች።
† ጻድቅ ፣ ቡሩክ ፣ ቀዳሚው ገዳማዊ ፣ መላእክትን የመሰለና የባሕታውያን ሁሉ አባት ለተባለ ለቅዱስ ጳውሊ ክብር ይገባል!
🕊 † አባ ለንጊኖስ † 🕊
† ጻድቁ ከኪልቅያ እስከ ሶርያ ከሶርያ እስከ ግብጽ ድረስ በተጋድሎ የተጓዙ አባት ናቸው። በአምስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን አጋማሽም የደብረ ዝጋግ [ግብጽ ፤ እስክንድርያ] አበ ምኔት ሆነው አገልግለዋል።
ሙታንን አስነስተው ሃይማኖታቸውን ጠብቀው ብዙ ተአምራትን ሠርተው በዚህች ቀን ዐርፈዋል። ከድንቅ ነገራቸው ሰይጣን የእርሳቸውን የምንኩስና ቆብ ዐይቶ ደንግጦ መሸሹን እንጠቅሳለን።
"ኀበ ኢኀሎከ ሶበ ቆብዓከ ርዕየ
ሰይጣን ተኃፊሮ እፎኑመ ጐየ።" እንዲል።
[አርኬ]
† አምላክ በበረከታቸው ይባርከን።
†
[ 🕊 ፍኖተ ቅዱሳን 🕊 ]
[ የቅዱሳን አባቶቻችን የቅድስናና የተጋድሎ ሕይወት ]
† † †
[ ጽናትና በፈተናዎች መደራረብ አለመታወክ ]
🕊
[ ለአንተ የክብር አክሊል ሆነውሃል ! ]
........
አንድ ወንድም ገዳሙን ትቶ ከመውጣት ፈተና [ ጸብአ ፍልሰት ] ጋር እየታገለ ዘጠኝ ዓመታትን አሳለፈ፡፡ ሁል ጊዜ ጠዋት ላይ ሊሄድ ይዘጋጅና ማታ ሲሆን በልቡ " ነገ ይህን ቦታ ለቅቄ እሄዳለሁ። " ይላል። ጧት ሲሆን ደግሞ ፦ "ስለ እግዚአብሔር ስል የዛሬዋን ቀን ለመዋል ልበርታ" ይላል፡፡ ለዘጠኝ ዓመት እንዲህ ካደረገ በኋላ እግዘአብሔር ፈተናውን ሁሉ አራቀለት ፣ በሰላምም ኖረ፡፡
🕊
አንድ አረጋዊ አንድ ወንድም ለዘጠኝ ዓመት ያህል ድኅነቱን እንኳ እስኪጠራጠር ደርሶ በሃሳቡ ሲፈተን እንደ ኖረ ተናገረ፡፡ ከውስጡ የሚፈትነው የሃሳቡ ሁኔታ ስላስጨነቀው ራሱን አምርሮ ወቀሰ ፣ "እኔ ዋጋ የለኝም ፣ ነፍሴን አጥቻለሁ ፣ አንዴ የጠፋሁ ስለሆነና ዋጋ ስለሌለኝ ወደ ዓለም ልመለስ" አለ፡፡
ነገር ግን ገና በመንገድ ላይ ሳለ እንዲህ የሚል ድምፅ መጣለት ፦ " እነዚህ የተፈተንክባቸው ዘጠኝ ዓመታት ለአንተ የክብር አክሊል ሆነውሃል ፤ ወደ ቦታህ ተመለስ ፣ ይህን ሃሳብ አስወግድልሃለሁ፡፡ "
የአባቶቻችን ጸሎትና በረከት ይደርብን፡፡
† † †
💖 🕊 💖
†
[ ተዋሕዶ ፍጽምት የቅዱሳን ሃይማኖት ]
▬▬▬▬▬▬ † ▬▬▬▬▬▬
[ የኃጢኣትን ጨለማ እናርቅ ! ]
--------------------------------------------------
" አዝማነ መንግሥተ ሰማያትን ታዩ ዘንድ የምትወዱ ወንድሞቼ ሆይ ! ፈሪሃ እግዚአብሔርን አስተምራችሁ ዘንድ ኑ ! አንደበታችንን ከክፉ ነገር ፣ ከንፈሮቻችንንም ክዳት ሽንገላን ከመናገር እንከልክል፡፡ [መዝ.፴፬(፴፫)፥፲፩-፲፮ ፣ ፩ጴጥ.፫፥፲-፲]
እኛ ሊያደርጉልን እንደምንወድ ለባልንጀሮቻችን ለወንድሞቻችን ፤ ለጠላቶቻችንም በጎ ነገርን እናድርግ፡፡ 'ዓለም ሳይፈጠር የተዘጋጀላችሁን ትወርሱ ዘንድ የአባቴ ወዳጆች ወደ እኔ ኑ' የሚል ደስታን የተመላ ቃልን ከጌታችን እንሰማ ዘንድ። [ማቴ.፮፥፴፬ ። ፯፥፲፪ ። ፳፭፥፴፬ ። ገላ.፮፥፬-፯]
ከሥጋችን ከነፍሳችን ከልቡናችን ፤ የኃጢኣትን ጨለማ እናርቅ፡፡ ጠቁሮ የሚወርድ ዝገት ከእርሳስ ፣ ከብረት ከመዳብ በእሳትና በፈሉ የመድኃኒት ቅመማት እንዲርቅ ፤ እነዚህን በትሕትና በቀናች የእግዚአብሔርን የአካሉን ሦስትነት ፤ የባሕርዩን አንድነት በማመን የሚፈጸሙ ጾም ፣ ጸሎት ፣ ንጽሕና ፣ ምጽዋት ፣ ፍቅር ናቸው፡፡
ከኃጢአት የሚያነጹ ሙቀተ ጸጋን የሚሰጡ እሊህን አምስቱን ግብራት የሚመስላቸው የለም፡፡ ያንጊዜ የመለኮት ፍቅር ጸጋውም በልቡናችን ያድራል፡፡ እኛም ከኃጢአት ንጹሐን ብንሆን ያንጊዜ መጥቶ ያድርብናል፡፡ አባታችን በሚያወርሳት በመንግሥተ ሰማይ እንደ ፀሐይ እንበራለን። [ማቴ.፲፫፥፫። ዮሐ.፲፬፥፳፫ ። ፩ጴጥ.፬፥፲፬]
በመንግሥተ ሰማይ ያከብረናል በተራራ ላይ እንደተሠራች እንደጸናችው መንደር ለዓለም ሁሉ እንደሚያበራ ፋናም ያደርገናል። [ማቴ.፭፥፲፬-፲፮ ፣ ፪ጴጥ.፫፥፫ ፣ ራእ.ዮሐ.፳፩፥፩ ፣ ኢሳ.፰፥፲፯ ፣ ፳፮፥፳፪]
ዐይን ያላየውን ጆሮ ያልሰማውን ፤ በሰው ልቡና ያልታሰበውን ያን ተድላ ነፍስ እንወርሳለን፡፡ መላእክት በሚኖሩበት በመንግሥተ ሰማያት እንኖራለን፡፡ ከረቂቃን መላእክት ጋር እናመሰግናለን፡፡ የመላእክትን ምስጋና ምግብ አድርገን እንኖራለን፡፡ [መዝ.፻፰(ሮ፯)፥፳፭ ፣ ሉቃ፳፥፴፬–፴፱ ፣ ሮሜ.፰፥፲፯-፳፪] "
[ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ]
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፤ ወለወላዲቱ ድንግል ፤ ወለመስቀሉ ክቡር። አሜን።
† † †
💖 🕊 💖
ሐሙስ - ጥር 30 2016 ዓ.ም
ዘጸአት 37-40
ሰላም ለሁላችሁ ይሁን! በዛሬው እለት ንባባችን ከምዕራፍ 37 እስከ 40 ድረስ እናነባለን።
ከንባብ በፊት የሚደረግ ጸሎት፡ “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፤ የአንተን ቃላት እሰማ እና እረዳ ዘንድ፥ እንዲያውም ፈቃድህን ለመፈጸም እበቃ ዘንድ የልቤን ጆሮዎች እና ዓይኖች ክፈትልኝ።” (ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ)
በዛሬው ንባባችን ላይ ባስልኤል አስቀድሞ በተቀመጠው መመሪያ መካከል የቃል ኪዳኑን ታቦት፥ የኅብስተ ገጹን ገበታ፥ መቅረዙን፥ የሚቃጠል መሥዋእት መሠዊያውን እና የመታጠቢያውን ሰን መሥራቱን እናነብባለን። ከዚህም በተጨማሪ ለድንኳኑ ሥራ የተሰጠውን ወርቅና ብር በምን መንገድ እንደተጠቀመ፤ አልፎም ደግሞ ስለ ልብሰ ተክህኖ አሠራር በዝርዝር ተቀምጧል። በስተመጨረሻም የምስክሩ ድንኳን ተተክሎ አገልግሎት እንደጀመረ እና የእግዚአብሔር ክብር ድንኳኑን እንደሞላው ተገልጾ የኦሪት ዘጸአት መጽሐፍ ይጠናቀቃል።
*የክለሳ ጥያቄዎች*
1) በዘጸአት 37 መሠረት፥ ባስልኤል ታቦትን የሠራው ከምንድር ነው?
2) ባስልኤል የሠራው ታቦት ርዝመቱ፥ ወርዱ እና ቁመቱ ምን ያህል ነበር?
3) በዘጸአት 38 መሠረት፥ የሚቃጠል መሥዋዕቱ መሠዊያ የተለበጠው በምንድር ነው?
4) ለድንኳኑ ሥራ የተሰጠው ወርቅ እና ብር ምን ያህል ነበር?
5) በዘጸአት 39 መሠረት ሙሴ የተሠራውን ሥራ ሁሉ ካየ በሁዋላ ምላሹ ምን ነበር?
6) በዘጸአት 40 መሠረት፥ እግዚአብሔር ሙሴ የምስክር ድንኳኑን እንዲተክል ያዘዘው መቼ ነው?
7) በኦሪት ዘጸአት መጨረሻ ላይ የእግዚአብሔር ክብር በድንኳኑ የመሙላቱን ሁኔታ እንዴት ይገልጸዋል?
መልካም ንባብ!
/channel/OrthodoxTewahdoBooks
/channel/c/2014228571/1
🕊
[ † እንኳን ለተፍጻሜተ ሰማዕት ቅዱስ ዼጥሮስ እና ለ፻፶ [150] ው ቅዱሳን ሊቃውንት ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ]
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †
🕊 † ቅዱስ ዼጥሮስ ሰማዕት † 🕊
† የቅዱሳን ሰማዕታት መነሻቸው ቅዱስ እስጢፋኖስ ሲሆን ፍጻሜአቸው ደግሞ ቅዱስ ዼጥሮስ ሊቀ ዻዻሳት ነው::
ይህ ቅዱስ የሚታወቀው "ተፍጻሜተ ሰማዕት [የሰማዕታት መጨረሻ]" በሚለው ስሙ ነው:: ይሕስ እንደ ምን ነው ቢሉ :-
የቅዱሱ ሃገረ ሙላዱ ግብጽ ናት:: ዘመኑም 3ኛው መቶ ክ/ዘመን ነው:: ወላጆቹ ካህን ቴዎድሮስና ቡርክት ሶፍያ ልጅ አጥተው ሐምሌ ፭ ቀን ወደ ፈጣሪ ቢማጸኑ በራዕይ ዼጥሮስ ወዻውሎስ ተገልጠው ብሥራትን ለሶፍያ ነገሯት:: በወለደችው ጊዜም በራዕዩ መሠረት "ዼጥሮስ" አለችው::
ሰባት ዓመት በሆነው ጊዜም ለቤተ እግዚአብሔር ሰጥተው በሊቀ ዻዻሳቱ ቅዱስ ቴዎናስ እጅ አደገና በወጣትነቱ ሊቅ: ጥዑመ ቃልና በጐ ሰው ሆነ:: ዲቁናና ቅስናን ተሹሞ ሲያገለግል ቅዱስ ቴዎናስ በማረፉ ቅዱስ ዼጥሮስን የግብጽ ፲፯ [17] ኛ ፓትርያርክ አድርገው ሾሙት::
ዘመኑ ደግሞ እጅግ ጭንቅ ነበር:: ክርስቲያኖች በተገኙበት ስለሚገደሉ: አብያተ ክርስቲያናትም ስለ ተቃጠሉ የቅዱሱ መከራ የበዛ ነበር:: ለ፲፬ [14] ዓመታት በፍጹም ትጋት ከመንጋው ጋር ተጨነቀ::
አርዮስን [ተማሪው ነበር] አውግዞ ለየው:: ከጌታ ጋርም ብዙ ጊዜ ተነጋገረ:: ብዙ ተአምራትንም ሠራ:: በዚህ ሁሉ ጊዜ አንድም ቀን በመንበረ ዽዽስናው ላይ አልተቀመጠም:: በሁዋላ ግን ጨካኙ ንጉሥ እንዲገደል አዘዘ::
ሕዝቡ "ከእሱ በፊት እኛን ግደሉን" በማለታቸው ሁከት እንዳይነሳ ቅዱስ ዼጥሮስ ተደብቆ ሔደና በፈቃዱ ለወታደሮች ተሰጠ:: በዚያች ሌሊትም የእርሱ ደም የግፍ ማብቂያ እንዲሆን እያለቀሰ ጮኸ:: ከሰማይም "አሜን! ይሁን!" የሚል ቃል መጣ:: ያን ጊዜ የእርሱ አንገት ተሰየፈ:: ዘመነ ሰማዕታትም አለፈ::
† የቅዱሳንን ዝክር ከማንበብ ባለፈ በስማቸው መጸለይ [ዘፀ. ፴፪፥፲፫ ] : በምጽዋትም ማሰብ [ ማቴ.፲፥፵፩ ] ይገባል::
† ወርኀ የካቲትን ይባርክልን !
🕊
[ † የካቲት ፩ [ 1 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ፻፶ [ 150 ] ቅዱሳን ሊቃውንት ዻዻሳት [በቁስጥንጥንያ ተሠብሥበው መናፍቃንን ያወገዙበት: ትምሕርተ ቤተ ክርስቲያንን ያፀኑበት /ጉባዔ ቁስጥንጥንያ/ በ፫፻፲፰ [381] ዓ/ም::
ከወቅቱ ቅዱሳን ሊቃውንት እነዚህ ይጠቀሳሉ:-
- ቅዱስ ጐርጐርዮስ ዘኑሲስ
- ቅዱስ ጐርጐርዮስ ዘእንዚናዙ
- ቅዱስ ጢሞቴዎስ ዘአልቦ ጥሪት
- ቅዱስ ቄርሎስ ዘኢየሩሳሌም
፪. ቅዱስ ዼጥሮስ ተፍጻሜተ ሰማዕት [ቅዳሴ ቤቱ]
፫. ታላቁ ቴዎዶስዮስ ጻድቅ [ንጉሠ ቁስጥንጥንያ]
[ † ወርሐዊ በዓላት ]
፩. ልደታ ለቅድስት ድንግል ማርያም እግዝእትነ
፪. ቅዱስ በርተሎሜዎስ ሐዋርያ
፫. ቅዱስ ሚልኪ ቁልዝማዊ
፬. ቅዱስ ራጉኤል ሊቀ መላዕክት
፭. ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና
† " ስለዚህ በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያንን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ዻዻሳት አድርጎ ለሾመባት: ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ:: ከሄድሁ በሁዋላ ለመንጋው የማይራሩ ጨካኞች ተኩላዎች እንዲገቡባችሁ እኔ አውቃለሁ:: ስለዚህ 3 ዓመት ሌሊትና ቀን በእንባ እያንዳንዳችሁን ከመገሰጽ እንዳላቁዋረጥሁ እያሰባችሁ ትጉ:: " † [ ሐዋ. ፳፥፳፰ ]
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖 🕊 💖
†
[ 🕊 ፍኖተ ቅዱሳን 🕊 ]
[ የቅዱሳን አባቶቻችን የቅድስናና የተጋድሎ ሕይወት ]
† † †
[ ጽናትና በፈተናዎች መደራረብ አለመታወክ ]
🕊
[ እስከ መጨረሻው የሚከተለው ጥንቸሉን ያየው ነው ! ]
........
አንድን አባት ፦ " መንፈሰ ጠንካራና በጥሩ ተጋድሎ ላይ ያለ ወንድም ሌሎች ወደ ዓለም ሲመለሱና ሲደክሙ ሲያይ እርሱም ላይረበሽ የሚችለው እንዴት ነው ? " ብለው ጠየቁት።
እርሱም እንዲህ አለ ፦ " ጥንቸሎችን የሚያባርሩ ውሾችን ተመልከቱ። ከእነርሱ መካከል አንዱ ጥንቸል ሲያይ ስለ ሌላ ስለ ምንም ነገር ሳያስብ ያየውን ጥንቸል ብቻ እስኪይዝ ድረስ ይከተለዋል። ሌሎቹ ውሾች ግን ጥንቸሉን ያየውን ውሻ ሲሮጥ ስላዩት እስከ ተወሰነ ርቀት ድረስ አብረውት ይሮጣሉ ፣ ኋላ ግን ቀስ እያሉ ይመለሳሉ። እስኪይዘው ድረስ እስከ መጨረሻው የሚከተለው ጥንቸሉን ያየው ነው ፣ እርሱ ወደ ኋላ ስለሚመለሱት ስለ ሌሎቹ ውሾች ለማሰብም ሆነ እነርሱን ለማየት ጊዜ የለውም፡፡ ያየውን እስኪይዝ ድረስ እሾሁ ፣ ጠጠሩ ፣ ዓለቱ ሁሉ አይሰማውም፡፡
ክርስቶስን በሚፈልግ ሰውም እንዲሁ ነው ፣ ሁል ጊዜ በዓይነ ኅሊናው የሚታየው ዓላማው መስቀሉ ስለሆነ በመስቀል ላይ ወደ ተሰቀለው መድኃኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ እስኪደርስ ድረስ ከዚያ ውጭ የሚሆነው ማንኛውም ነገር ግድ አይሰጠውም፡፡ ስለሌሎች መመለስና መቅረት ለማሰብም ጊዜ የለውም ፣ ጉዳዩም አይደለም፡፡ "
የአባቶቻችን ጸሎትና በረከት ይደርብን፡፡
† † †
💖 🕊 💖
†
[ ተ ስ ፋ በ ቆ ረ ጥ ን ጊ ዜ ! ]
" ኑና እንዋቀስ ይላል እግዚአብሔር ፤ ኃጢአታችሁ እንደ አለላ ብትሆን እንደ አመዳይ ትነጻለች ፤ እንደ ደምም ብትቀላ እንደ ባዘቶ ትጠራለች። " [ ኢሳ.፩፥፲፰ ]
† † †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬
ካነበባችሁ በኃላ ለአንድ ወዳጃችሁ መላክ Share ማድረግ ልምድ ይኑራችሁ።
Читать полностью… †
[ ተዋሕዶ ፍጽምት የቅዱሳን ሃይማኖት ]
▬▬▬▬▬▬ † ▬▬▬▬▬▬
[ ላንተ ልጆች መባል አይገባንም ! ]
--------------------------------------------------
" ዘመናችን ሳይፈጸም እጁን ወደ እኛ ዘርግቶ የሚጠራን እንስማው፡፡ ፈጥነን በፊቱ ራሳችንን እናዋርድ፡፡ አቤቱ ፣ እነሆ አንተን በድለናል ፥ እኛን በዐይነ ምሕረት ተመልከት ፥ ፍጥረቶችህን አትጣል፡፡ የእጅህ ፍጥረቶች ነንና ፥ ከሞት በኋላ የሚያስብህ ፥ በመቃብርስ ተስፋ የሚያደርግህ ማነው? እያልን ፈጥነ ንስሓ እንግባ። [መዝ.፮፥፩-፯ ፣ ፻፴፰(፻፴፯)፥፰ ፤ ኢሳ.፳፪፥፪ ፣ ሉቃ.፲፭፥፲፩-፳፪ ]
ፋናዎቻችንን እናብራ [ምግባራችንን እንግለጥ] ደጁ ሳይዘጋ ሙሽራውን ለመቀበል እንፋጠን ፤ ያለዚያ ግን መግባት አይቻለንም። [ማቴ.፳፭፥፩-፲፫] ሌባ እንዳይመጣብን ፤ ተዘልለንም እንዳያገኘን እንጠንቀቅ ። [ማር.፲፫፥፴፪-፴፯] እንኪያስ ፈጥነን ንስሓ እንግባ ፥ እርያዎች ከሚበሉት ተረርቃሞ መጥገብ አይቻለንምና፡፡
ፈጣሪያችንን የሰማዩን የምድሩን ያህል አንተን በደልን ፥ ላንተ ልጆች መባል አይገባንም ፥ ከአገልጋዮችህ እንደ አንዱ አድርገን እንጂ እንበለው፡፡
እርሱ ፈጽሞ ከልጅነት እንደለየን አይቀርም ፥ በቸርነቱ ይቀበለናል እንጂ፡፡ የሠርግ ልብስን ያለብሰናል ፣ በጣታችን ቀለበትን ያገባልናል ፣ በእግራችንም ጫማ ያደርግልናል፡፡ በእኛ መመለስ ደስ ይለዋል ፥ ተስፋ ንስሓን እንደነገረን። [ሉቃ.፲፭፥፲፩-፪] "
[ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ]
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፤ ወለወላዲቱ ድንግል ፤ ወለመስቀሉ ክቡር። አሜን።
† † †
💖 🕊 💖
የብር ቦታ
"ገንዘብ ካለ በሰማይ መንገድ አለ"
ልክ ነው ገንዘብ ከፍለህ በአየር ላይ ትሄድ ይሆናል እንጂ ገንዘብ ፈሰስ አርገህ በሰማይ የምታስመርቀው አስፓልት የለም።
ገንዘብ የምድር ሥርዓቶች የሚፈቅዱትን ነገር ብቻ ያከናውናል።
ገንዘብ ምግብ ይገዛል ግን የምግብ ፍላጎትን መግዛት አይችልም።
ገንዘብ መድሀኒት ይገዛል ግን ጤናን መግዛት አይችልም።
ገንዘብ እውቀት ይገዛል ግን ጥበብን መግዛት አይችልም።
ገንዘብ ጓደኛን መግዛት ይችላል ግን እውነተኛ ወዳጅን መግዛት አይችልም።
ገንዘብ ሊያስቁን የሚችሉ እነ አርቲስት እገሌን መግዛት ይችላል ደስታን ግን መግዛት አይችልም።
ገንዘብ made in china ብልጭልጭ ነገር ይገዛ ይሆናል ውበትን ግን መግዛት አይችልም።
ገንዘብ አገልጋዮችን መቅጠር ይችላል ታማኝነትን ግን መግዛት አንችልም
እንዲህ አይነት አመለካከት ያለው ሰው ረክቶ መኖር ይችላል።
ይህ ውስን የሆነ መገልገያ በመጀመሪያዎቹ ክርስቲያኖች በሀዋርያት ዘንድ የነበረው ቦታ ተከብሮ፣ ተምነሽንሾ፣ በባንክ ውስጥ አልነበረም፤ አላነገሱትም። ቦታው ከእግር በታች ነበር። ዛሬ ግን እኛ ከእግራችን በታች መኖር ያለበት አቧራ ብቻ ነው ብለን ገንዘብን አዕምሯችን ውስጥ አስቀምጠነዋል።
ለኛ የተፈጠረው ነገር እኛኑ መግዛት ጀምሯል። ለገንዘብ ያለም አመለካከት ተንሾዋሮልና እይታችንን ልናስተካክል ይገባል።
ውብ አሁን
ማግሰኞ - ጥር 28 2016 ዓም
ዘጸአት 28-32
ሰላም ለሁላችሁ ይሁን! በዛሬው እለት ንባባችን ከምዕራፍ 28 እስከ 32 ድረስ እናነባለን።
ከንባብ በፊት የሚደረግ ጸሎት፡ “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፤ የአንተን ቃላት እሰማ እና እረዳ ዘንድ፥ እንዲያውም ፈቃድህን ለመፈጸም እበቃ ዘንድ የልቤን ጆሮዎች እና ዓይኖች ክፈትልኝ።” (ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ)
በዛሬው ንባባችን ላይ እግዚአብሔር ካህናት የሚለብሱትን ልብሰ ተክህኖ አሠራር በተመለከተ የሰጠውን ዝርዝር መመሪያ እንመለከታለን። በእስራኤል ሕዝብ እና በእግዚአብሔር መካከል ሆነው እንዲያገለግሉም አሮን እና የአሮን ልጆች በምን መንገድ ክህነት እንደተሾሙም እናነባለን። ሆኖም ግን፥ ሙሴ የእግዚአብሔርን ትእዛዛት ለመቀበል ወደ ተራራ በወጣ ጊዜ እስራኤላውያን እግዚአብሔርን ትተው ጣዖት ለማምለክ እንደተነሱ፥ እግዚአብሔርም እንደተቆጣ፥ ሙሴም ደግሞ ስለ ሕዝቡ እንደማለደ በዛሬው ንባባችን ላይ ተዳስሷል።
*የክለሳ ጥያቄዎች*
1) ሙሴ ለክህነት እንዲያቀረብ የተጠየቀው እነማንን ነው?
2) በልብሰ ተክህኖ ሥራ ውስጥ ጥቅም ላይ እንዲውሉ የታዘዙት ስንት ዕንቁዎች ናቸው? ስማቸውስ ምንድር ነው?
3) በዘጸአት 29 መሠረት፥ ሙሴ ክህነት የሚቀበሉትን ለመካን ምን ነገሮችን እንዲያዘጋጅ ታዘዘ?
4) በዘጸአት 29 መሠረት አዲስ የተሾሙት ካህናት በፊታቸው የሚቀርቡት እንስሳት ላይ መጀመሪያ የሚያደርጉት ነገር ምንድር ነው?
5) የመገናኛው ድንኳን ዋና ተግባር ምንድር ነው?
6) በዘጸአት 30 መሠረት፥ የዕጣን መሠዊያው ከምን ይሠራል?
7) በዘጸአት 31 መሠረት፥ የዕንቁ ድንጋይን እንዲቀርጽ እና እንጨትንም እንዲጠርብ የተመረጠው ማነው?
8) በዘጸአት 31 መሠረት፥ እግዚአብሔር ሰንበትን ስለማክበር ምን አለ?
9) እስራኤል እንደ በደሉ ባየ ጊዜ፥ እግዚአብሔር ስለ ሕዝቡ ለሙሴ ምን አለው?
10) ሙሴ ከተራራው ወርዶ ጥጃውን እና ዘፈኑን ባየ ጊዜ ምን አደረገ?
11) በዘጸአት 32 መሠረት፥ ሙሴ ለአሮን ምን አለው?
12) ሙሴ ስለ እስራኤል በእግዚአብሔር ፊት ምን ብሎ ማለደ?
መልካም ንባብ!
/channel/OrthodoxTewahdoBooks
/channel/c/2014228571/1
†
[ 🕊 ፍኖተ ቅዱሳን 🕊 ]
[ የቅዱሳን አባቶቻችን የቅድስናና የተጋድሎ ሕይወት ]
† † †
[ ጽናትና በፈተናዎች መደራረብ አለመታወክ ]
🕊
[ የድካምህን ዋጋ እንድሰጥህ ተልኬያለሁ ! ]
........
አኀው ከአረጋውያን አንዱን ከባድ የሆነ የብሕትውና ተጋድሎውንና አስጨናቂ ትኅርምቱን እንዲቀንስ ለመኑት እርሱ ግን እንዲህ ብሎ መለሰላቸው ፦ " ልጆቼ ፣ አብርሃም የእግዚአብሔርን ታላቅ ስጦታ ሲያይ የሚጸጸተው በኋላ ድካሙ ሳይሆን ቀደም አድርጎ ባለ መጋደሉ እንደሆነ እነግራችኋለሁ፡፡ "
🕊
አንድ አረጋዊ ውኃ ካለበት ቦታ አሥራ ሁለት ማይል ያህል ከሚርቅ በረሃ ይኖር ነበር፡፡ ሁል ጊዜ ውኃ ሊቀዳ በሄደ ቁጥር ከድካሙ የተነሣ ፦ " ይህ ድካም ምን ይጠቅመኛል? ወደ ውኃው ቀረብ ብዬ እኖራለሁ። " ይል ነበር፡፡
አንድ ቀን እንዲህ እያለ ሲሄድ ወደ ኋላ ዘወር ሲል አንድ የሆነ ሰው አብሮት እየሄደ እርምጃውን ሲቆጥር አየው፡፡ እርሱም ፦ " አንተ ማነህ ? " ብሎ ሲጠ ይቀው እርሱም ፦ " እኔ የጌታ መልአክ ነኝ ፣ እርምጃህን እንድቆጥርና የድካምህን ዋጋ እንድሰጥህ ተልኬያለሁ። " አለው፡፡ ይህን በሰማ ጊዜ ይህ አረጋዊ የበለጠ ተበረታታ ፣ ከነበረበት ቦታ እንደ ገና አምስት ማይል ያህል ርቆ ኖረ፡፡
🕊
ከታች ያለው ቅዱስ ስእል የአባታችን የቅዱስ ሙሴ ጸሊም ነው።
የአባቶቻችን ጸሎትና በረከት ይደርብን፡፡
† † †
💖 🕊 💖