"እንግዲህ፡ንስሓ፡ግባ፤አለዚያ፡ፈጥኜ፡ እመጣብሃለሁ፡፡" ራዕ 2፥16
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
[ ኦርቶዶክሳዊ የመዳን ትምህርት ]
[ በዚህ መርሐ-ግብር ኦርቶዶክሳዊ የመዳን ትምህርት ከቅዱሳት መጻሕፍት ፤ ከቅዱሳን አባቶቻችን ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን አስተምህሮ እንዲሁም ከመምህራን ትምህርቶች ላይ በየጥቂቱ ይቀርባል። እንዲሁም የተሐድሶ መናፍቃን የኑፋቄ ትምህርቶችና ምላሾቻቸው የሚቀርብ ይሆናል። ]
† † †
[ ኦርቶዶክሳዊ የመዳን ትምህርት ]
[ ክፍል አሥራ ስምንት ]
🔴 [ ይልቁንም የክርስቶስን የባህርይ አምላክነት ክደው እንደ ነቢይ ፣ እንደ መልአክ ፣ እንደ አማላጅ [ ሎቱ ስብሐት ] ለሚያዩ መናፍቃን !
3.3 የሰው ልጅ ድኅነት [ መዳን ] የእግዚአብሔር ዓላማ መሆኑ
እግዚአብሔር ለእኛ ያደረጋቸው የተለያዩ የቸርነት ነገሮች ሁሉ እኛን ለማዳንና ስለ እኛ መዳን የተደረጉ ናቸው::
ለ. የነቢያት የትንቢታቸው ዋና ማዕከል የሰው መዳን [ ድኅነት ] ነበር።
ከጥንት ጀምሮ የተነሡ የተለያዩ አበው ነቢያት የሰው ልጅ መዳን ከመድረሱና ከመፈጸሙ አስቀድሞ ተስፋውን በትንቢት በተምሳሌትና በተለያዩ ነገሮች ይናገሩ ነበር፡፡ ይህም የሰው ሕሊና በተስፋ እንዲጠብቅና እንዲዘጋጅ እንዲሁም ስለ ሌሎች የተለያዩ ምክንያቶች ነበር።
ቅዱስ ጴጥሮስ ይህን የነቢያትን የትንቢት ጭብጥና ተልእኮ ጉዳይ በተመለከተ በመልእክቱ እንዲህ ሲል ገልጾታል ፦
" ለእናንተም ስለሚሰጠው ጸጋ ትንቢት የተናገሩት ነቢያት ስለዚህ መዳን ተግተው እየፈለጉ መረመሩት ፤ በእነርሱም የነበረ የክርስቶስ መንፈስ ፣ ስለ ክርስቶስ መከራ ከእርሱም በኋላ ስለሚመጣው ክብር አስቀድሞ እየመሰከረ በምን ወይም እንዴት ባለ ዘመን እንዳመለከተ ይመረምሩ ነበር። ለእነርሱም ከሰማይ በተላከ በመንፈስ ቅዱስ ወንጌልን የሰበኩላችሁ ሰዎች አሁን ባወሩላችሁ ነገር እናንተን እንጂ ራሳቸውን እንዳላገለገሉ ተገለጠላቸው ፤ ይህንም ነገር መላእክቱ ሊመለከቱ ይመኛሉ። [1ጴጥ.1፥10-12]
እነ ነቢዩ ኢሳይያስ ፦ “ስለ ጽዮን ዝም አልልም ፥ ስለ ኢየሩሳሌምም ጸጥ አልልም ፣ ጽድቅዋ እንደ ጸዳል መዳኗም እንደሚበራ ፋና እስኪወጣ ድረስ ” እያለ ስለ መዳናችን ትንቢት ይናገሩ ነበር። [ኢሳ.62፡1]
ነቢዩ ኤርምያስም በትንቢቱ ፦ “በእውነት የእስራኤል መዳን በአምላካችን በእግዚአብሔር ዘንድ ነው " ይል ነበር። [ኤር.3:23] የዮሐንስ መጥምቅ አባት ካህኑ ዘካርያስም የመዳናችን ፈጻሚና ራስ የሆነው የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መንገድ ጠራጊ ይሆን ዘንድ መንፈቅ ተቀድሞ የተላከው ዮሐንስ መጥምቅ በተወለደና ስም በወጣለት ጊዜ ተዘግቶ የነበረው አንደበቱ ሲከፈት በመንፈስ ቅዱስ እንዲህ አለ ፦ “አንሥአ ለነ ቀርነ መድኃኒትነ እምቤተ ዳዊት ገብሩ በከመ ነበበ በአፈ ነቢያቲሁ ቅዱሳን እለ እመዓለም - ቀድሞ ከጥንት ጀምሮ በነበሩት በቅዱሳን ነቢያት አፍ እንደ ተናገረ ፣ በብላቴናው በዳዊት ቤት የመዳን ቀንድን አስነሥቶልናል” በማለት ከጥንት ጀምሮ በየዘመኑ የተነሡ የተለያዩ ነቢያት የትንቢታቸው ዋና ማእከልና ዓላማ የመዳናችን ፈጻሚ የኢየሱስ ክርስቶስ የመገለጥና የመምጣት ጉዳይ የነበረ መሆኑንና ያን ጊዜ ዮሐንስ መጥምቅ ሲወለድ ደግሞ ያ የመዳን ቀን ጊዜው የደረሰ መሆኑን በመንፈስ ቅዱስ አናጋሪነት ተናገረ፡፡ [ሉቃ.1፡69-70]
[ በማክሰኞ መርሐ-ግብር ! ]
ሐ. የሐዋርያት ተልእኮና ስብከት ዓላማው የሰው መዳን ነው።
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
ሐሙስ - ጥር 23 2016 ዓ.ም
ዘጸአት 1-5
ሰላም ለሁላችሁ ይሁን!
ዛሬ በእግዚአብሔር ቸርነት ኦሪት ዘጸአትን ማንበብ እንጀምራለን። ኦሪት ዘጸአት ሊቀ ነቢያት ሙሴ ከጻፋቸው አምስት መጻሕፍት መካከል ሁለተኛ ላይ የሚቀመጠው ሲሆን፥ በዋናነት የእስራኤል የነጻነት ታሪክ የሚተርክ ነው። በዛሬው እለት ከምዕራፍ 1 እስከ 5 ድረስ እናነባለን።
ከንባብ በፊት የሚደረግ ጸሎት፡ “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፤ የአንተን ቃላት እሰማ እና እረዳ ዘንድ፥ እንዲያውም ፈቃድህን ለመፈጸም እበቃ ዘንድ የልቤን ጆሮዎች እና ዓይኖች ክፈትልኝ።” (ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ)
በኦሪት ዘጸአት ላይ የንባቡ ትኩረት ወዲያው ወደ እስራኤላዊያን ባርነት ሲለወጥ እናነባለን። ዮሴፍን የማያውቅ ፈርዖን በመጣ ጊዜ፥ በእስራኤላውያን ላይ መከራን አጸናባቸው፤ አዋላጆችም ወንዶች ልጆች ከወለዱ እንዲገድሏቸው አዘዘ። ሙሴን እግዚአብሔር አትርፎት በፈርዖን ቤት ለማደግ የቻለው በዚህ አጋጣሚ ነበር። ትልቅ በሆነም ጊዜ አንድ ግብጻዊ በመግደሉ ምክንያት ከግብጽ ምድር ሲሰደድ፥ በሄደበት ቦታም አግዚአብሔር እንደመረጠው እና በግብጽ በባርነት ወዳሉት ወደ እስራኤላውያን እንደላከው የምናነበው በዛሬው የንባብ ክፍላችን ላይ ነው።
* የክለሳ ጥያቄዎች * (መልሱን ከማታ 1፡00 በሁዋላ ጻፉ)
1) በዘጸአት 1 መሠረት፥ ፈርዖን የሚወለዱ ወንድ እስራኤላዊያን እንዲገደሉ ያዘዘው ለምንድር ነው?
2) አዋላጆች ፈርዖንን ለምን አልታዘዙትም? ለእርሱስ ምን የሚል ምክንያትን ሰጡት?
3) ሙሴ በደንገል ሳጥል ተደርጎ በወንዝ ከተለቀቀ በሁዋላ ምን ገጠመው?
4) ሙሴ ከግብጽ ሀገር የተሰደደው ለምንድር ነው?
5) በዘጸአት 3 መሠረት፥ እግዚአብሔር ራሱን ለሙሴ የገለጠው እንዴት ነው? ምን ተልእኮስ ሰጠው?
6) እግዚአብሔር ለሙሴ የገለጠው ስሙ ማን ነው?
7) በዘጸአት 4 መሠረት፥ እግዚአብሔር ለሙሴ በፈርዖን ፊት እንዲያሳይ የሰጠው ምልክቶች ምንድር ናቸው?
8) ሙሴ እግዚአብሔር ለተልእኮ በጠራው ጊዜ ምላሹ ምን ነበር?
9) ሙሴ በፈርዖን ፊት ቀርቦ ምን ጠየቀ? የፈርዖንስ ምላሽ ምን ነበር?
10) በዘጸአት 5 መሠረት፥ ፈርዖን የእስራኤላውያንን መከራ ያበዛው ምን አድርጎ ነው?
መልካም ንባብ!
/channel/OrthodoxTewahdoBooks
†
[ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ አንሡ ]
🕊
" መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና ፥ ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር ከዚህም ከጨለማ ዓለም ገዦች ጋር በሰማያዊም ስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት ጋር ነው እንጂ።
ስለዚህ በክፉው ቀን ለመቃወም ፥ ሁሉንም ፈጽማችሁ ለመቆም እንድትችሉ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ አንሡ።" [ ኤፌ.፮፥፲፪ ]
† † †
💖 🕊 💖
†
[ ተዋሕዶ ፍጽምት የቅዱሳን ሃይማኖት ]
▬▬▬▬▬▬ † ▬▬▬▬▬▬
[ ሙሽራውን ለመቀበል እንፋጠን ! ]
--------------------------------------------------
" እኛ ግን ከሕጉ ብንለይ ትእዛዙን ብናፈርስ መኖሪያችን እሳቱ በማይጠፋበት ትሉ በማያንቀላፋበት በዘላለም ኵነኔ ውስጥ ይሆናል፡፡
ይህ ጨለማነት ያለው ፥ ብርሃን የሌለበት ጽኑ ጨለማ ብሎ የጠራው እሳት ልቅሶ ጥርስ ማፋጨት ያለበት ቦታ ነው፡፡ [ማቴ.፳፭፥፬ ። ማር.፲፥፵፩-፰] ጌታ ሕጉን መጠበቃችንን ነው እንጂ ከእኛ ከባድ ሥራ አልፈለገብንም፡፡ በበደልም ልባችንን አናጽና ፈጥነን ወደ ንስሐ እንመለስ እንጂ፡፡ ኃጢአታችንንም እርስበርሳችን እንናዘዝ እንጂ! ሐዋርያው ያዕቆብ እንደተናገረ"
[ማቴ.፲፩፥፳፰ ። ሮሜ.፪፥፬-፮ ። ያዕ.፭፥፲፮]
የካህኑን ትእዛዙን ተግሣፁን አንሰቀቅ ነፍስን የሚያድን በዓለ መድኃኒት ነውና፡፡ [ማቴ.፰፥፬ ። ዮሐ.፳፥፳፫] የነፍሳትን ደዌ የሚያርቅ ቃሉስ ይቅርና የሥጋ ባለመድኃኒት ስንኳ ወደ ሥጋዊ በሽተኛ በመጣ ጊዜ ክፉ ምግብ ከመመገብ ይከለከል ዘንድ ያዝዘዋል ፤ መራራ ቅጠልን ፥ ምረቱ ጭንቅ ሽታው ክፉ የሚሆን ከብዙ ወገን የተቀመመ መድኃኒትን ያጠጣዋል፡፡ በድውዩ አካል ያለ የተለያየ ሕዋሳትን አንድ ያደርግለት ዘንድ።
ዘመናችን ሳይፈጸም እጁን ወደእኛ ዘርግቶ የሚጠራንን እንስማው፡፡ ፈጥነን በፊቱ ራሳችንን እናዋርድ፡፡ አቤቱ እነሆ አንተን በድለናል ፥ እኛን በዐይነ ምሕረት ተመልከት ፥ ፍጥረቶችህን አትጣል የእጅህ ፍጥረቶች ነንና፡፡ ከሞት በኋላ የሚያስብህ በመቃብርስ ተስፋ የሚያደርግህ ማነው? እያልን ፈጥነን ንስሓ እንግባ። [መዝ.፮፥፩-፯ ፣ ፻፴፰ (፻፴፯)፥፰ ፣ ኢሳ.፳፪፥፪ ፣ ሉቃ.፲፭፥፲፩-፳፮]
ፋናዎቻችንን እናብራ [ምግባራችንን እንግለጥ] ደጁ ሳይዘጋ ሙሽራውን ለመቀበል እንፋጠን፡፡ ያለዚያ ግን መግባት አይቻለንም። [ማቴ.፳፭፥፩-፲፫] ሌባ እንዳይመጣብን ፤ ተዝልለንም እንዳያገኘን እንጠንቀቅ። [ማር.፲፫፥፴፪-፴፯] እንኪያስ ፈጥነን ንስሓ እንግባ፡፡ "
[ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ]
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፤ ወለወላዲቱ ድንግል ፤ ወለመስቀሉ ክቡር። አሜን።
† † †
💖 🕊 💖
ማንበብ ፣ መጸለይ ፣ንስሐ መግባት
"ያለመረዳትም ቢኾን ቅዱሳት መጻሕፍትን ማንበብ አታቋርጥ! ሙቀት ባይኖረውም ጸሎትኽን አታቋርጥ! ያለ ንስሓም ቢኾን ኑዛዜኽን አታቋርጥ! ንጹሕ በኾነ ብርታትኽ ውስጥ የእግዚአብሔር ጸጋ ይፈልግኻል፡፡ ቅዱሳት መጻሕፍትን መረዳትን ፣ በጸሎት ውስጥ ሙቀትን ፣ በንስሓኽ ውስጥ ጸጸትን ያድልሃኻል።" ይላል።
++++++++
ኑ እናንብብ
👇👇👇
/channel/OrthodoxTewahdoBooks
🕊
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ †
[ † ጥር ፳፪ [ 22 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
🕊 † አባ እንጦንስ † 🕊
በቤተ ክርስቲያን አስተምሕሮ " ታላቁ / ዓቢይ / THE GREAT" የሚል ስም የሚሰጣቸው አባቶች የተለዩ ናቸው:: አንድም እጅግ ብዙ ትሩፋቶችን የሠሩ ናቸው:: በሌላ በኩል ደግሞ በተመሳሳይ ስም ከሚጠሩ ሌሎች ቅዱሳን እንለይበታለን::
ገዳማዊ ሕይወት ጥንቱ ብሉይ ኪዳን ነው:: በቀዳሚነትም በደብር ቅዱስ አካባቢ ይኖሩ የነበሩ ደቂቀ ሴት እንደ ጀመሩት ይታመናል:: ሕይወቱ በጐላ: በተረዳ መንገድ የታየው ግን በታላቁ ጻድቅ ሄኖክ: ከዚያም በቅዱሱ ካህን መልከ ጼዴቅ አማካኝነት ነው::
ቀጥሎም እነ ቅዱስ ኤልያስ ነቢይ: እነ ኤልሳዕ ደቀ መዝሙሩ ኑረውበታል:: በሐዲስ ኪዳን ደግሞ ሙሉ ሕይወቱን በገዳም [በበርሃ] ያሳለፈው መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ቅድሚያውን ይይዛል::
ለስም አጠራሩ ስግደት ይሁንና መድኃኒታችን ክርስቶስ በገዳመ ቆረንቶስ ለ40 ቀናት በትሕርምት ኑሮ ገዳማዊ ሕይወትን ቀድሷል: አስተምሯል:: በዘመነ ስብከቱም ያድርባት የነበረችው የደብረ ዘይቷ በዓቱ (ኤሌዎን ዋሻ) በራሷ ለዚህ ሕይወት ትልቅ ማሳያ ናት::
ከጌታ ዕርገት በኋላም ክርስቲያኖቹ የዓለም ሁካታ ሲሰለቻቸው: አንድም በንጹሕና በተሸከፈ ልቡና ለፈጣሪያቸው መገዛትን ሲሹ ከከተማ ወጣ እያሉ ይኖሩ እንደ ነበር የታሪክ መዛግብት ያሳያሉ:: አኗኗራቸውም በቡድንም: በነጠላም ሊሆን ይችላል::
ዋናው ነገር ግን በጾምና በጸሎት መትጋታቸው ነው:: ይሕም ሲያያዝ እስከ ፫ኛው መቶ ክ/ዘመን ደረሰ:: በዚህ ዘመን ግን አባ ዻውሊ የሚባል አንድ ንጹሕ ክርስቲያን ይሕንን ሕይወት ወደ ሌላ ደረጃ ከፍ አደረገው:: ለ፹ [80] ዓመታት ሰው ሳያይ ተጋድሎ 'የባሕታውያን አባት'
ተባለ:: ደንብ ያለው ተባሕትዎም ጀመረ::
ይህ ከሆነ ከ፳ [20] ዓመታት በኋላ ደግሞ አባ እንጦንስ የሚባሉ ደግ ክርስቲያን ይህንን ገዳማዊ ሕይወት በሌላ መንገድ አጣፈጡት:: በቅዱስ ሚካኤል አመንኳሽነት ገዳማዊ ሕይወት በምንኩስና ተቃኘ:: ስለዚህም አባ እንጦንስ የመነኮሳት አባት ተባሉ::
እርሳቸውም ሕይወቱን ለማስፋፋት ከተለያዩ አሕጉር ደቀ መዛሙርትን እየተቀበሉ አመንኩሰዋል:: ቅዱሳን የአባ እንጦንስ ልጆችም ወደየ ሃገራቸው ተመልሰው: ሕይወቱን በተግባር አሳይተው ገዳማዊነትን አስፋፍተዋል::
🕊 † አባ እንጦንስ † 🕊
አባ እንጦንስ የመነኮሳት ሁሉ አባታቸው: ለገዳማውያን ሁሉም ሞገሳቸው ናቸው:: እንዲያውም ብዙ ጊዜ "ኮከበ ገዳም: ማኅቶተ ገድል [የበርሃው ኮከብ: የተጋድሎ መብራት]" ተብለውም ይጠራሉ::
ቤተ ክርስቲያን ለጀማሪዎች ትልቅ ትኩረት ትሰጣለች:: ለምሳሌ:- አባ ዻውሊን [የካቲት ፪ የሚከበሩ] ለብሕትውና መሠረትን ስለ ጣሉ "አበ ባሕታውያን" ብላ ታከብራለች:: አባ እንጦንስን ደግሞ "አበ መነኮሳት [የመነኮሳት አባት] : ቀዳሚሆሙ ለመነኮሳት [ለመነኮሳት ቀዳሚና ጀማሪ] ስትል ትጠራቸዋለች::
አባ እንጦንስ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ለሚነሱ ቅዱሳን መነኮሳት ሁሉ መንገድን ይጠርጉ ዘንድ ብዙ መከራን በትዕግስትና በአኮቴት ተቀብለዋል:: ላለፉት ፩ ሺህ ፯ መቶ [1,700] ዓመታት እንደ ሻማ እየቀለጡ ያበሩ አበው ቅዱሳን ሁሉ የአባ እንጦንስ ልጆች ናቸው::
ከምጥ የከፋ የዲያብሎስ ፈተናን ተቀብለው ከመንፈሳዊ አብራካቸው ቅዱሳኑን ወልደዋል:: የመነኮሳት አለቃ የሆኑትን ታላቁን መቃርዮስን ጨምሮ በርካቶችን አመንኩሰው ለቅድስና አብቅተዋል::
አባ እንጦንስ ግብጻዊ ሲሆኑ የተወለዱት አቅማን በምትባል ቦታ አካባቢ ነው:: ጊዜውም በ፪መቶ ፶፪ [252] ዓ/ም ነው:: የተባረኩ ወላጆች ለቅዱሱ እንጦንስና አስከትለው ለወለዷት ሴት ልጃቸው አስቀድመው ፍቅረ ክርስቶስን: አስከትለውም ሃብት ንብረታቸውን አውርሰው ዐርፈዋል::
በዚህ ጊዜ የአባ እንጦንስ እድሜ አፍላ ወጣትነት ላይ ነበር:: በልጅነት ጊዜአቸውም አባ እንጦንስን ሲስቁ: ሲጫወቱ: አልያም ሲቀልዱ አየሁ የሚል ሰው አልነበረም:: ፍጹም ቁም ነገረኛና ታዛዥ: በዚያ ላይም አስተዋይ ነበሩና ሙሉ ጊዜአቸውንም ከቅዱስ ቃሉ በመመገብ: በትምሕርትና በማስቀደስ ያሳልፉ ነበር::
ዘወትርም ዜና ሐዋርያትን እያነበቡ በመንፈሳዊ ቅናት ይቃጠሉ ነበር:: በጊዜው የምናኔ ሕይወት ጐልቶ ባለ መገለጡ አባ እንጦንስ የሚያደርጉት ይጨንቃቸው ነበር:: ሲጸልዩም "አበው ሐዋርያት ይሕንን ክፉ ዓለም ንቃችሁ ጌታችሁን የተከተላችሁበት ጥበብ እንደ ምን ያለ ነው!" እያሉ ይደነቁ ነበር:: መሻታቸውን ያወቀ ጌታም ምሥጢርን ገለጠላቸው::
አንድ ቀን በቅዳሴ ላይ ወንጌል ሲነበብ ካህኑ ስለ ምናኔ የሚጠቅሰውን ክፍል አነበበ:: ለአንድ ባለ ጠጋ ሕግጋትን ከነገረው በኋላ "ፍጹም ልትሆን ከወደድክስ ያለህን ሁሉ ሸጠህ ተከተለኝ" [ማር.፲፥፲፯] የሚለውን ጥቅስ ሲሰሙ ተገርመው "ጌታ ሆይ! ይህንን የተናገርኸው ለእኔ ነው" ሲሉ አሰቡ:: በቀጥታም ሃብታቸውን ለአካባቢው ሰው አካፍለው: እህታቸውን ከደናግል ማኅበር ደምረው እርሳቸው ወደ ዱር ሔዱ::
ከዚህች ቀን ጀምረው አባ እንጦንስ ከ፹ [80] እስከ መቶ ለሚገመቱ ዓመታት ከአጋንንት ጋር በጦርነት ነበር የኖሩት:: በንጹሕ አምልኮታቸውና በቅድስናቸው የቀና ጠላት ሰይጣን በብዙ ጐዳና ፈተናቸው:: አቅም ቢያጥረው አራዊትን መስሎ ታገላቸው::
በዚህ አልሳካ ቢለው የእሳት ሰንሰለትን አምጥቶ ገረፋቸው:: በሞትና በሕይወት መካከል ጥሏቸው ሔደ:: ወድቀው ያገነኟቸው ሰዎች ለዘመዶቻቸው ሰጥተዋቸው አገገሙ:: ልክ ሲነቁ ግን ፈጥነው ወደ በርሃ ተመለሱ::
ሰይጣን በርሃው የቅዱሳን ማደሪያ እንዳይሆን ሰግቷልና ጨክኖ ታገላቸው:: ግን አልቻላቸውምና ተረታ:: አምላከ ኃያላን ክርስቶስ ከቅዱሱ ጋር ነበርና:: ከዚህ በኋላ ግን ጸጋው በዝቶላቸው ድውያንን የሚፈውሱና ሰይጣን የማይቀርባቸው ሰው ሆኑ::
በረዥም ዘመነ ቅድስናቸውም :-
፩. ብዙ አርድእትን ከመላው ዓለም ሰብስበው: አስተምረው: ምናኔ ከግብጽ ማዶ በመላው ዓለም አስፋፉ::
፪. በደመና እየተጫኑ ብዙ አሕጉራትንም እየዞሩ ሰበኩ:: በዚህም አሕዛብን ወደ እምነት: ኃጥአንን ወደ ንስሃ መለሱ::
፫. ጊዜው ዘመነ ሰማዕታት ነበርና ወደ አደባባይ ሒደው ከሃዲዎችን ገሠጹ:: ማንም ደፍሮ ግን አልገደላቸውም::
እነዚህንና ሌሎች ተግባራትን እየሠሩ በቅዱስ ሚካኤል እጅ መነኮሱ:: እርሳቸውም ብዙዎችን አመነኮሱ:: አርጅተው እንኳ ከተጋድሎ ያላረፉት አባታችን የጣመ ነገር ቀምሰው: ገላቸውን ታጥበው አያውቁም:: በ፫፻፸፪ [372] ዓ/ም በዚህች ቀን ሲያርፉም ዕድሜአቸው ፻፳ [120] ደርሶ ነበር::
የአባ እንጦንስን በዓል ለማክበር የምትሹ ቤተ ክርስቲያናቸው ጎንደር ከተማ ከቀሃ ኢየሱስ በላይ ይገኛል::
" ለአባታችን እንጦንዮስ / እንጦንስ / እንጦኒ ክብር
ይገባል::"
†
† 🕊 ንግሥታችን ፣ እናታችን 🕊 †
💖
❝ ጸጋን የተመላሽ ሆይ ! ተዝቆ ከማያልቀው ጸጋሽ እንባረክ ዘንድ እነዚኽ ጥቃቅኖች ቃሎቻችንን እንደ ቁም ነገር ቈጥረሽ ተቀበዪልን ከመትከፈ ልቡናችን እንደወጡና ክብርሽን ለማመስገን የበቁ እንደኾኑ አድርገሽ ተቀበዪልን።
ጸጋን የተመላሽ ፣ እመቤታችን ፣ ንግሥታችን ፣ እናታችን ፣ ወላዲተ አምላክና ዓለም በመላ የሚቀደስበትን መዝገብ የተሸከመች አማናዪቱ ታቦት ሆይ ከንግግሮቻችን አንዳች መልካም ነገር ብታገኚባቸው እያልን እኛና ፍጥረታት ኹላችን አምኃ ዝማሬያችንን እናቀርብልሻለን ...
ድንግል ሆይ ! በእውነቱ አንቺ ከታላላቆች ይልቅ ታላቅ ነሽ ማኅደረ ቃለ አብ ሆይ ! አንቺን ሊተካከል የሚችል ታላቅ ማን ነው ? ድንግል ሆይ ! ከየትኛው ፍጥረት ጋር አወዳድርሻለኊ ?
አንቺ ቀድሞ በወርቅ ካጌጠችው የሕጉ ታቦት ይልቅ በንጽሕና ያጌጥሽ ታላቅ ነሽ ! እውነተኛውን መና የተሸከምሽ የወርቅ መሶብ አንቺ ነሽ መና የተባለውም መለኮት የተዋሐደው ሥጋው ነው። ❞
[ ቅዱስ አትናቴዎስ ]
† † †
💖 🕊 💖
🕊
[ አርያም በጣፋጭ የመላእክት ዝማሬ ተሞላ ]
" ልጃቸው ተሰብስበው ወዳሉበት መጥታለችና አዳምና ሔዋን ዛሬ ደስ አላቸው። በዚህች ቀን ታላቁ ዳዊት በራሱ ላይ የተዋበ አክሊል የደፋችለትን ሴት ልጁን አይቶ ደስ አለው። በዚህች ቀን ነቢዩ ኢሳይያስ ትንቢት የተናገረላት ድንግል ወደ ሙታን ሥፍራ ልትጎበኘው መጥታለችና ደስ አለው።
በዚህች ቀን ብርሃን ሲበራባቸው አይተዋልና ነቢያት ሁሉ ከመቃብራቸው ራሳቸውን ቀና አደረጉ። አርያም በጣፋጭ የመላእክት ዝማሬ ተሞላ ፣ ምድር ደግሞ ኀዘንን በተሞሉ በሐዋርያት ለቅሶ ተሞላች፡፡ ሙታንም ሕያዋንም ትርጉሙን ሊገልጹት በማይችሉት [ የተለያየ ] ዜማ ሰውና መላእክት በዚያች ዕለት አብረው ጮኹ።"
[ ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ ]
† † †
[ መጽሐፍ እንደተናገረ በፈጣሪ እና በፍጡራን መካከል ለዕረፍት የቃል ኪዳን ማደሪያ [ ምልክት ] የሆንሽ የብርሃን ቀን ሰንበተ ሰንበታት ማርያም ሆይ በገነት ያሉ ጻድቃን በአንቺ ደስ ይላቸዋል፡፡ ኃጥአንም ከደይን በአንቺ ይወጣሉ፡፡ ]
[ አባ ጽጌ ድንግል ]
† † †
💖 🕊 💖
- በታላቅ ወንድሙ ቅዱስ ባስልዮስ መሪነት ገዳማዊ ሕይወትን ተምሯል::
- በመንኖ ጥሪት ተመስግኗል::
- ተገብቶትም በኑሲስ ደሴት ላይ ዻዻስ ሆኗል::
- እርሱ ሲሔድ በከተማው የነበሩ ክርስቲያኖች ፲፩ [11] ብቻ የነበሩ ሲሆን እርሱ ሲያርፍ ክርስቶስን የማያመልኩ ሰዎች ቁጥር ፲፩ [11] ብቻ ነበር::
- ቅዱስ ጐርጐርዮስ ፍጹም ሊቅ ነበርና ከቁጥር የበዙ ድርሳናትን ደርሷል::
- ታላቁን ጉባኤ ቁስጥንጥንያን [በ፫፻፹፩ [381] ዓ/ም] መርቷል:: ብዙ መናፍቃንንም አሳፍሯል::
ከንጽሕናው የተነሳ መላእክት ያቅፉት: እመ ብርሃንም ትገለጥለት ነበር:: ለ፴፫ [33] ዓመታት እንደ ሐዋርያት ኑሮ በዚህ ቀን ድንግል ጠራችው:: ቀድሶ አቁርቦ: ሕዝቡን አሰናብቶ: የቤተ መቅደሱን ምሰሶ እንደ ተደገፈ ዐርፎ ተገኝቷል:: በዝማሬና በፍቅር ቀብረውታል::
🕊 † ቅድስት ኢላርያ † 🕊
† "ኢላርያ" ማለት "ፍሥሕት [ደስ የተሰኘች]" እንደ ማለት ነው:: ከተባረኩ ቅዱሳት አንስት ትልቁን ሥፍራ ትይዛለች:: ማን እንደ እርሷ !
ቅድስት ኢላርያ ማለት :-
- የታላቁ ንጉሠ ነገሠት: የደጉ ዘይኑን [Emperor Zenon] የበክር ልጅ
- በ፮ኛው መቶ ክ/ዘመን የተወለደች
- ትምሕርተ ሃይማኖትን: ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን የተማረች
- ምድራዊ ንግሥናን ንቃ ፍቅረ ክርስቶስን የመረጠች
- የአባቷን ቤተ መንግስት ትታ ከሮም ግዛት ወደ ግብጽ [ገዳመ አስቄጥስ] የወረደች:
- ስሟን ከኢላርያ ወደ ኢላርዮን ቀይራ በወንዶች ገዳም የመነኮሰች
- ራሷን በፍጹም ገድል ቀጥቅጣ ከወንዶቹ በላይ በሞገስ ከፍ ከፍ ያለች
- ትንሽ እህቷን ጨምሮ በርካቶችን የፈወሰች
- በእርሷ ምክንያት ለግብጽና በመላው ዓለም ለሚገኙ ገዳማት ብዙ ቸርነት በዘይኑን የተደረገላት ታላቅ እናት ናት::
ቅድስት ኢላርያ ማንም ሴት መሆኗን ሳያውቅባት: አባ ኢላርዮን እንደ ተባለች በዚህች ቀን ዐርፋለች:: ቤተ ክርስቲያንም እነሆ ላለፉት ፩ ሺህ ፬ መቶ [1,400] ዓመታት: ቅድስቲቱንና የተባረከ አባቷን ዘይኑንን: ስለ በጐነታቸውና ውለታቸው ታስባቸዋለች::
† የእመቤታችን ድንግል ማርያም ጣዕሟ: ፍቅሯ: ጸጋዋና በረከቷ ይደርብን:: †
[ † ጥር ፳፩ [ 21 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ በዓላት ]
፩. በዓለ አስተርዕዮ ማርያም [እመቤታችን ከእረፍቱዋ በሁዋላ ለደቀ መዛሙርት በዚሁ ቀን ተገልጣ ነበር]
፪. ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ [ታላቅ ሊቅና ጻድቅ]
፫. ቅድስት ኢላርያ እናታችን [የዘይኑን ንጉሥ ልጅ]
፬. ቅዱስ ኤርምያስ ነቢይ
፭. ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ
፮. ቅዱስ ኒቆላዎስ ሰማዕት
፯. አባ ፊቅጦር
[ † ወርሐዊ በዓላት ]
፩. አባ ምዕመነ ድንግል
፪. አባ አምደ ሥላሴ
፫. አባ አሮን ሶርያዊ
፬. አባ መርትያኖስ
፭. አበው ጎርጎርዮሳት
† " ወደ ማደሪያዎቹ እንገባለን:: እግሮቹ በሚቆሙበት ሥፍራ እንሰግዳለን:: አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነስ:: አንተና የመቅደስህ ታቦት:: ካህናቶችህ ጽድቅን ይልበሱ:: ቅዱሳንህም ደስ ይበላቸው:: ስለ ባሪያህ ስለ ዳዊት. . ." [መዝ.፻፴፩፥፯]
† " ወዳጄ ሆይ ! ተነሺ:: ውበቴ ሆይ ! ነዪ:: በዓለት: በንቃቃትና በገደል መሸሸጊያ ያለሽ ርግብ ሆይ ቃልሽ መልካም: ውበትሽም ያማረ ነውና: መልክሽን አሳዪኝ:: ድምጽሽንም አሰሚኝ:: " [መኃ.፪፥፲፫]
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖 🕊 💖
†
"ሥርጋዌ ሰማይ ትእምርተ ዓመታት ፀሐይ ወወርኅ ወከዋክብት
ወሥርጋዌ ምድር ጽጌያት
የኀልፉ ግብተ ከመጽላሎት
ለኪሰ ማርያም ንግሥት
ኢየኀልፍ ለዓለም ሠርጕኪ ስብሐት"
[ ሰማይ የተሸለመባቸው የዘመናት ምልክቶች ፀሐይ ፣ ጨረቃ ፣ ከዋክብት፡፡ ምድር የተሸለመችባቸው አበቦችም ድንገት እንደ ጥላ ያልፋሉ ይጠፋሉ፡ ንግሥት ማርያም ላንቺ የሚቀርበው ሽልማት ምስጋና ግን ለዘላለም አያልፍም አይጠፋም፡፡ ]
[ አባ ጽጌ ድንግል ]
† † †
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
💖 🕊 💖
🕊
[ ዮም በፍሥሐ ለማርያም እምነ ፤ አስተርእዮ በሰማይ ኮነ ]
እንኳን አደረሳችሁ።
----------------------------------------
" አስደናቂው የእመቤታችን እረፍት "
[ " አቤቱ ፥ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ ፥ አንተና የመቅደስህ ታቦት።" [ መዝ.፻፴፪፥፰ ]
💖 ድንቅ ትምህርት 💖
[ በዲ/ን ብርሃኑ አድማስ ]
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
----------------------------------------
👇
†
[ 🕊 ሕይወት እናት ሞት ! 🕊 ]
🍒▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬🍒
❝ የአምላክ እናት ሆይ ጌታን በመውለድሽ ምክንያት ድንግልናሽን እንዳልተውሽ በመሞትሽም ይህንን ዓለም አልተውሽውም:: የሕይወት እናት ነሽና ዛሬ ወደ ሕይወት ተሻገርሽ:: በአማላጅነትሽም ነፍሳችንን በኃጢአት ከመሞት ታደጊ"
‹ ሌሎች በድንግልና የኖሩ ሴቶች 'ለሞት የሚሆኑ ልጆችን አንሰጥህም" በማለት ሞትን ተቃወሙት፡፡ ድንግል ማርያም ግን አንድ ልጅ በመውለድ በልጅዋ ሞት ራሱ እንዲሞት አደረገችው፡፡ ከዐለት ጋር እንደተጋጨ የተፈረካከሰው በማሕፀንዋ ፍሬ ነውና ሞት ወደ እርስዋ ሲቀርብ ተብረከረከ ❞
[ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ]
❝ ልጃቸው ተሰብስበው ወዳሉበት መጥታለችና አዳምና ሔዋን ዛሬ ደስ አላቸው … በዚህች ቀን ታላቁ ዳዊት በራሱ ላይ የተዋበ አክሊል የደፋችለትን ሴት ልጁን አይቶ ደስ አለው … በዚህች ቀን ነቢዩ ኢሳይያስ ትንቢት የተናገረላት ድንግል ወደ ሙታን ሥፍራ ልትጎበኘው መጥታለችና ደስ አለው … በዚህች ቀን ብርሃን ሲበራባቸው አይተዋልና ነቢያት ሁሉ ከመቃብራቸው ራሳቸውን ቀና አደረጉ … አርያም በጣፋጭ የመላእክት ዝማሬ ተሞላ ፣ ምድር ደግሞ ኀዘንን በተሞሉ በሐዋርያት ለቅሶ ተሞላች፡፡ ሙታንም ሕያዋንም ትርጉሙን ሊገልጹት በማይችሉት [የተለያየ] ዜማ ሰውና መላእክት በዚያች ዕለት አብረው ጮኹ ❞
[ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ] (Homily on the Dormition)
❝ በእርሱ ምክንያት ሰማይ ተብላ የተጠራችበት የሚመስለው የሌለ የማሕፀንዋ ፍሬ ለመሞትና ለመቀበር ፈቃደኛ ከሆነ ያለ ዘር የወለደችው እናቱ እንዴት ሞትን ትፈራለች ? ❞
[ ቅዱስ ዮሐንስ ዘደማስቆ ] (The life of Virgin Mary)
❝ የቃሉ አገልጋዮችና ምስክሮች የነበሩት ሐዋርያት በሥጋ የወለደችውን የእናቱን ዕረፍትና እርስዋን የሚመለከቱ የመጨረሻዎቹን ምሥጢራትም ማየት ነበረባቸው፡፡ ይህም የሆነው የክርስቶስ የዕርገቱ የዓይን ምስክሮች እንደሆኑ ሁሉ የወለደችውም እናቱ ወደዚያኛው ዓለም ለሸጋገርዋ ምስክሮች መሆን ስላለባቸው ነው ❞
[ ቅዱስ ዮሐንስ ዘደማስቆ ] (aka Doctor of Dormition)
† † †
💖 🕊 💖
†
ፎቶ ፦ " አልታወቁም " በተባሉ የታጣቂ ኃይሎች በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ፤ በቦሰት ወረዳ ቤተ ክህነት የመርቆ መካነ ሕይወት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን መቃጠሉን የተዋሕዶ ሚዲያ አገልግሎት አሳውቋል።
" ባልታወቁ የታጠቁ ኃይሎች " ተፈፅሟል የተባለው ይህ የመቃጠል ተግባር ከትናንት በስቲያ ጥር ፲፯ [ 17 ] ቀን ፳፻፲፮ ዓ.ም [ 2016 ዓ.ም ] አመሻሽ ላይ መፈፀሙ ተመላክቷል።
" በቦታው ላይ የተለያዩ አካላት በተደጋጋሚ ጊዜ ዛቻና ማስፈራሪያ ሲያደርጉ ቆይቷል " ያለው ዘገባው ትላንንት ሙሉ በሙሉ ንዋዬ ቅድሳቱ የተቃጠለ ሲሆን የቤተ መቅደሱ የውስጥና የውጭ ክፍል ጉዳት ያደረሰ ከፍተኛ ቃጠሎ መድረሱ ተገልጿል።
† † †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬
ቅዱስ ዮሐንስ በላዩ ላይ የነበረችውን ልብስ በመንገድ ለነዳይ ሰጥቶ: በፈንታው ቆሻሻ ጨርቅ ለብሶ ከወላጆቹ በር ላይ ለመነ:: "እባካችሁ አስጠጉኝ" አላቸው:: ወላጆቹ በጭራሽሊለዩት አልቻሉም:: ነገር ግን አሳዝኗቸዋልና በበራቸው አካባቢ ትንሽ ቤት ሠሩለት::
በዚያች በዓት ውስጥ እንዳስለመደ በትጋት ለ፯ ዓመታት ተጋደለ:: በእነዚህ ዓመታት እንኳን ሌላው ሰው ወላጆቹም ቢሆኑ ፍርፋሪ ከመስጠት በቀር አይቀርቡትም ነበር:: ምክንያቱ ደግሞ "ይሸተናል" የሚል ነበር:: በመጨረሻም መልአከ እግዚአብሔር ከሰማይ ወርዶ "ከ፯ ቀናት በኋላ ታርፋለህ" አለው::
እናቱን ጠርቶ "አንድ ነገር ልለምንሽ" አላት:: "እሺ" አለችው:: "ከሞትኩ በኋላ በለበስኳት ጨርቅ እንድትገንዙኝ: በበዓቴ ውስጥም እንድትቀብሩኝ" አላትና የወርቅ ወንጌሉን አውጥቶ ሰጣት:: ያን ጊዜ አባቱም ደርሶ ነበርና ደነገጡ::
የወርቅ ወንጌሉን ለዩት:: ልጃቸውን ግን መለየት አልቻሉምና እያለቀሱ ስለ ልጃቸው የሚያውቀው ካለ እንዲነግራቸው ለመኑት:: እርሱም "ልጃችሁ ዮሐንስ እኔ ነኝ" አላቸው::
በዚያ ቅጽበት ወላጆቹ የሰሙትን ማመን አልቻሉም:: በፍጹም ዋይታ እየጮሁ አለቀሱ:: ለቅሷቸውን የሰሙ ሁሉ ተሰበሰቡ:: ለ7 ቀናት እኩሉ እያለቀሰ: እኩሉ እየተባረከ በዓቱን ከበው ሰነበቱ:: በ7ኛው ቀን መልአኩ መጥቶ በክብር ነፍሱን ተቀበለ::
እናቱ የልጇን አደራ ረስታ [እሷስ መልካም አደረግሁ ብላ ነው] ለሠርጉ ባዘጋጀችው የወርቅ ልብስ ገነዘችው:: ወዲያው ግን በጽኑ ታመመች:: አባት ግን ፈጠን ብሎ በዚያች ጨርቅ ገንዞ በበዓቱ ውስጥ ቀበረው:: ያን ጊዜ እናት ፈጥና ዳነች:: ከቅዱሱ መቃብርም ብዙ ተአምራትና ፈውስ ተደርጓል::
† ቸሩ እግዚአብሔር ከወዳጆቹ በረከት ያሳትፈን፡፡
🕊
[ † ጥር 20 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ቅዱስ አክሎግ ቀሲስ [ ሰማዕትና ጻድቅ ]
፪. ቅዱስ መርምሕናም ሰማዕት [ ቅዳሴ ቤቱ ]
፫. ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌሉ ዘወርቅ [ ቅዳሴ ቤቱ ]
፬. አባ አብድዩ ጻድቅ
፭. ቅዱስ ብሕኑ ሰማዕት
፮. ቅዱስ አብሮኮሮስ ሐዋርያ [የወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ ደቀ መዝሙር]
፯. አባ ኖሕ
[ † ወርኀዊ በዓላት ]
፩. ቅዱስ ዮሐንስ ሐፂር
፪. ቅዱስ ቴዎድሮስ ሊቀ ሠራዊት
፫. ቅዱስ አሞንዮስ
፬. ቅዱስ ካሌብ ንጉሠ ኢትዮጵያ
፭. ቅድስት ሳድዥ የዋሂት
† " እንግዲህ ወገባችሁን በእውነት ታጥቃችሁ: የጽድቅንም ጥሩር ለብሳችሁ: በሰላም ወንጌልም በመዘጋጀት እግሮቻችሁ ተጫምተው ቁሙ:: በሁሉም ላይ ጨምራችሁ የሚንበለበሉትን የክፉውን ፍላጻዎች ሁሉ ልታጠፉ የምትችሉበትን የእምነትን ጋሻ አንሱ:: የመዳንንም ራስ ቁር: የመንፈስንም ሰይፍ ያዙ:: እርሱም የእግዚአብሔር ቃል ነው:: በጸሎትና በልመናም ሁሉ ዘወትር በመንፈስ ጸልዩ:: በዚህም አሳብ ስለ ቅዱሳን ሁሉ እየለመናችሁ በመጽናት ሁሉ ትጉ::" † [ኤፌ. ፮፥፲፬]
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖 🕊 💖
†
† 🕊 ዘእግዚአብሔር ፈነዎ 🕊 †
[ የግእዝ መዝሙር ጥናት ]
[ ክፍል - ፲ - ]
የወንድማችን ድንቅ አገልግሎት ! ከጣእሙ ብዛት አጥንትን የሚያለመልም ዝማሬ መላእክትን ያሰማልን።
† † †
💖 🕊 💖
†
[ 🕊 ሰማያዊቷን ቤተክርሰቲያን 🕊 ]
💖
❝ ቤተክርስቲያንን በሁለት መንገድ ማወቅህን አረጋግጥ። እንደ አሕዛብ ጠላቷ እንዳትሆን በትምህርት ዕወቃት ፤ እንደ ፈሪሳውያን እንዳትሆን በኑሮ ዕወቃት። ለሥርዓቷ ታማኝ ሁን ፥ አንተ ወደ ሥርዓቷ እደግ እንጅ ሥርዓቷ ወደ አንተ ፈቃድ እንዲወርድልህ አትውደድ ፤ ሰማያዊቷን ቤተክርሰቲያን ምድራዊት እንድትሆንልህ አትፍቀድ።
በቤተክርስቲያን መንፈሳዊ አንድነቶች ካልተሳተፍክ ከቤተክርስቲያን አንድነት እየተለየህ እንደሆነ እወቅ። እሊህም ፦ ኪዳን ማስደረስ ፥ ማስቀደስና ንስሐ ገብቶ [ በምክረ ካህን እየኖሩ ] መቁረብ ፥ በምህላ ጸሎቶቿ በአዋጅ አጽዋማቷ መተባበር ናቸው።
ከቤት ከሚጸለይ አሥር ጸሎት ይልቅ በቤተክርስታያን የሚደረግ አንድ ጸሎት እንደሚበልጥ አውቀህ በየቀኑ ወደ እርስዋ ገሥግሥ።
በሕይወትህ ሁሉ ቤተክርስቲያናዊ ሁን ! ❞
🕊
[ ርእሰ ሊቃውንት የኔታ አባ ገብረ ኪዳን ]
† † †
💖 🕊 💖
🕊
[ † እንኳን ለቅዱስ ጢሞቴዎስ ሐዋርያ : እና ጻድቅ ንጉሥ ቴዎዶስዮስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ]
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †
🕊 † ቅዱስ ጢሞቴዎስ ሐዋርያ † 🕊
† ይህ ቅዱስ ሐዋርያ አንድ የቤተ ክርስቲያናችን መብራት ነው:: ወደ ክርስትና የመጣው በ40ዎቹ ዓ/ም አካባቢ ሲሆን አሳምኖ ለቅድስና ያበቃው ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ዻውሎስ ነው::
በጊዜውም በነበረው ትጋትና ተጋድሎ ፍሬ አፍርቷል:: ሆዱንም እጅግ ያመው ነበር:: ቅዱስ ዻውሎስ ሲጠራው "የምወድህ ልጄ" እያለ ነበር:: በኤፌሶንም ዽዽስናን ሹሞ ፪ መልዕክታትን ልኮለታል:: ቅዱስ ጢሞቴዎስ ቤተ ክርስቲያንን ለብዙ ዘመናት አገልግሎ በሰማዕትነት ዐርፏል::
ከሐዋርያው ቅዱስ ጢሞቴዎስ በረከትን እንሳተፍ ዘንድ ጊዜ ካለን ቅዱስ ዻውሎስ ለልጁ ጢሞቴዎስ ከላካቸው መልዕክቶች ጥቂት እናንብብ::
🕊 † ቴዎዶስዮስ † 🕊
† በዚህ ስም የሚጠሩ ብዙ አበው አሉ:: ሰማዕታትም: ጻድቃንም: ሊቃውንትም: ነገሥታትም ተጠርተውበታልና:: ዛሬ የምናከብረውም ቴዎዶስዮስ ዘየዓቢ [ ታላቁ ] የሚባል ሲሆን ይህን የምንለው ከትንሹ ቴዎዶስዮስ [ የልጅ ልጁ ነው ] ለመለየት ነው::
ታላቁ ቴዎዶስዮስ በሮም የነገሠው በ፫፻፸ [370] ዓ/ም አካባቢ ሲሆን ከነ ቤተሰቡ ክርስቲያን ነበር:: እነዚህ ነገሮቹ ደግሞ በቤተ ክርስቲያን እንዲታሰብ አድርጐታል :-
፩. በዓለም ታሪክ ክርስትና በሮም ግዛት ሁሉ ብሔራዊ ሃይማኖት እንዲሆን አውጇል::
፪. የቤተክርስቲያንን ትልቁን 2ኛ ጉባኤ ቁስጥንጥንያን በ፫ መቶ ፹፩ [381 (373) ዓ/ም አሰናድቷል::
፫. ከበጐነቱ የተነሳ የተቀደሱ ልጆችን አፍርቷል:: ሙሽራው ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ: ቅዱስ አኖሬዎስ: ቅዱስ አርቃዴዎስ እና ቅድሰት ታኦድራ ልጆቹ ሲሆኑ አቡነ ኪሮስ ትንሽ ወንድሙ ናቸው::
ጻድቁ ንጉሥ ቴዎዶስዮስ በ፫፻፺ [ 390 ] ዓ/ም አካባቢ ዐርፏል::
† አምላከ ቅዱሳን ስለ አባቶቻችን ሲል ይማረን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን::
🕊
[ † ጥር ፳፫ [ 23 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ቅዱስ ጢሞቴዎስ [ ሐዋርያና ሰማዕት-የቅዱስ ዻውሎስ ደቀ መዝሙር ]
፪. ቅዱስ ጌርሎስ ሰማዕት
፫. ቅዱስ አትናቴዎስ ሰማዕት
፬. ጻድቅ ንጉሥ ቴዎዶስዮስ [ ዘቁስጥንጥንያ ]
[ † ወርሐዊ በዓላት ]
፩. ቅዱስ ዳዊት ልበ አምላክ
፪. ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕታት
፫. ቅዱስ ሰሎሞን ንጉሠ እሥራኤል
፬. አባ ጢሞቴዎስ ገዳማዊ
፭. አባ ሳሙኤል
፮. አባ ስምዖን
፯. አባ ገብርኤል
† " መድኃኒታችን እግዚአብሔር: ተስፋችንም ኢየሱስ ክርስቶስ እንዳዘዘው ትእዛዝ የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ የሆነ ዻውሎስ: በእምነት እውነተኛ ልጄ ለሆነ ለጢሞቴዎስ::
ከእግዚአብሔር ከአባታችን: ከክርስቶስ ኢየሱስም ከጌታችን: ጸጋና ምሕረት: ሰላምም ይሁን . . ." †
[፩ጢሞ.፩፥፩]
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖 🕊 💖
†
[ 🕊 ፍኖተ ቅዱሳን 🕊 ]
[ የቅዱሳን አባቶቻችን የቅድስናና የተጋድሎ ሕይወት ]
† † †
[ የፍትወት ጾር ስለሚያስነሣው ፈተና ]
🕊
[ ሞትን እና የሚመጣውን ዘለዓለማዊ ቅጣት ! ]
........
አንድ ወንድም በዝሙት ሰይጣን በከባድ ሁኔታ ተፈተነ፡፡
አራት አጋንንት በጣም ቆንጆ በሆነች ሴት አምሳል ተገልጠው እርሱን በሃሳቡ ተራክቦን ወደ ማሰብ ኅሊናውን ለማውረድና ለመጣል አርባ ቀናት አጽንተው ተዋጉት፡፡ እርሱ ግን በርትቶ ተዋጋ ፣ ድልም አልሆነም፡፡ እግዚአብሔርም ጽናቱንና ቆራጥነቱን አይቶ ከዚያ ወዲያ የዝሙት ጾር እንዳይፈትነው አደረገው፡፡
🕊
አንድ እኁ አንድን አረጋዊ ፦ " ክፉ ሃሳቦች አሰቃዩኝ ፣ ምን ባደርግ ይሻለኛል? " አለው፡፡ አረጋዊውም ፦ " እናት ልጇን ጡት ማስጣል ስትፈልግፍ ጡቷን እሬት መራራ ነገር ትቀባዋለች ፣ ሕፃኑም እንደ ለመደው ሊጠባ ሲመጣ የተቀባው ምሬት ያስተወዋል።
ታዲያ አንተስ እንዲሁ ጡት ማስጣያ እሬት ትጠ ቀማለህ? " አለው፡፡ ያ ወንድምም ፦ "ልጠቀማቸው የሚገቡኝ እነዚህ ጡት ማስጣያ መራራ ነገሮች ምንድን ናቸው? " አለው፡፡
አረጋዊውም ፦ " እነዚህ እሬቶችማ ሞትን እና የሚመጣውን ዘለዓለማዊ ቅጣት ማሰብና ማስታወስ ናቸው " አለው፡፡
🕊
የአባቶቻችን ጸሎትና በረከት ይደርብን፡፡
† † †
💖 🕊 💖
* ረቡዕ - ጥር 22 2016 ዓ.ም *
* ዘፍጥረት 46-50*
ሰላም ለሁላችሁ ይሁን! በዛሬው ንባባችን ከምዕራፍ 46 እስከ 50 ድረስ በማንበብ ኦሪት ዘፍጥረትን እናጠናቅቃለን።
ከንባብ በፊት የሚደረግ ጸሎት፡ “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፤ የአንተን ቃላት እሰማ እና እረዳ ዘንድ፥ እንዲያውም ፈቃድህን ለመፈጸም እበቃ ዘንድ የልቤን ጆሮዎች እና ዓይኖች ክፈትልኝ።” (ቅዱስ ኤፍሬም ሶሪያዊ)
የዛሬው ንባባችን ትኩረት የሚያደርገው የዮሴፍን ታሪክ ማጠቃለል ላይ ነው። በዛሬው ንባብ ላይ የዮሴፍ ቤተሰቦች ወደ ግብጽ ሄደው ከዮሴፍ ጋር እንደተገናኙ፥ እርሱም በደስታ እንደተቀበላቸው እናነብባለን። ያዕቆብም ከመሞቱ በፊት ልጆቹን ባረከ፥ ለወደፊት ስለሚገጥማቸውም ትንቢትን ተናገረ። ዮሴፍ ለወንድሞቹ ይቅርታ ማድረጉን እና ነገሮች መልካም መሆናቸውንም በዚሁ ምዕራፍ ማጠቃለያ ላይ እናነብባለን።
* የክለሳ ጥያቄዎች * (መልሶቹን ማታ ከ1፡00 በሁዋላ ጻፉ)
1) በዘፍጥረት 46 መሠረት፥ ያዕቆብ እና ቤተሰቡ ወደ ግብጽ የሄዱት ለምንድር ነው?
2) ዮሴፍ አባቱን በምን እይነት መንገድ ተቀበለው?
3) ዮሴፍ ቤተሰቡን ፈርዖን ፊት ባቀረበ ጊዜ ሙያቸው ምንድር ነው አለ? ለምን?
4) በዘፍጥረት 47 መሠረት፥ ያዕቆብ ዮሴፍን ምን መሃላ አስማለው?
5) ያዕቆብ ኤፍሬም እና ምናሴን ሲባርክ ምን የተለየ ነገር አደረገ? ለምን?
6) ያዕቆብ የዮሴፍን ልጆች በተመለከተ ምን ትንቢት ተናገረ?
7) ያዕቆብ ለልጁ ለይሁዳ ምን የሚል ትንቢትን ተናገረለት?
8) ያዕቆብ ስለ አቀባበሩ የሰጠው መመሪያ ምን ነበር?
9) ያዕቆብ ከሞተ በኋላ ወንድሞቹ ዮሴፍን ምን ብለው ይቅርታ ጠየቁ?
10) ዮሴፍ በመጨረሻው ጊዜ ለወንድሞቹ ምን አላቸው? ምንስ ብሎ አማላቸው?
መልካም ንባብ!
🕊 † ቅዱስ ዑራኤል † 🕊
በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ትውፊት መሠረት ከ፯ [7]ቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ የሆነው ቅዱስ ዑራኤል :-
፩. ድንግል ማርያም በአካለ ሥጋ እያለች ወደ ሰማይ አሳርጉዋታል:: በሠረገላ ብርሃን ጭኖ: በክንፎቹም ተሸክሞ: አስቅድሞ ገነትን ቀጥሎም ሲዖልን አስጐብኝቷታል:: በዚህም ምክንያት እመ ብርሃን ስለ ኃጥአን የምታለቅስ: የምትለምንና የምትማልድ ሆናለች:: ለምናም አልቀረች የምሕረት ቃል ኪዳን ተቀብላለች::
፪. ቅዱሱ መልአክ እመ ብርሃንን በስደቷ ጊዜ ወደ ኢትዮዽያ መርቶ አምጥቷታል:: በክንፉ ተሸክሞ: በ፬ አቅጣጫ አዙሮ አሳይቶ አሥራት እንድትቀበል አድርጉዋል::
፫. ጌታችን በተሰቀለ ጊዜ ደሙን በጽዋዕ አድርጐ በኢትዮዽያ ወንዞች ላይ አፍስሷል::
፬. ለብዙ ቅዱሳን [አባ ጊዮርጊስን ጨምሮ] ጽዋዐ ልቡናን አጠጥቷል::
አምላከ ቅዱሳን ስለ ወዳጆቹ በጐ ምኞታችንን
ይፈጽምልን:: ከበረከታቸውም ያድለን::
🕊
[ † ጥር ፳፪ [ 22 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ቅዱስ አባ እንጦንስ [የመነኮሳት አባት-የበርሐው
ኮከብ /ልደቱና ዕረፍቱ]
፪. ቅዱስ ዑራኤል ሊቀ መላዕክት [ለተጠሙ ጽዋዓ
ልቡናን የሚያጠጣ: ምሥጢር ገላጭ መልዐክ]
፫. ቅዱስ ሚናስ ኤዺስ ቆዾስ
[ † ወርኀዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ቅዱስ ዑራኤል ሊቀ መላእክት
፪. ቅዱስ ሉቃስ ወንጌላዊ
፫. ቅዱስ ደቅስዮስ [ የእመቤታችን ወዳጅ ]
፬. አባ እንጦንስ አበ መነኮሳት
፭. አባ ዻውሊ የዋህ
" እኔን መከተል የሚወድ ቢኖር ራሱን ይካድ:: መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ:: ነፍሱን ሊያድን የሚወድ ሁሉ ያጠፋታል:: ስለ እኔ ግን ነፍሱን የሚያጠፋ ሁሉ ያገኛታል::" [ማቴ.፲፮፥፳፬]
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖 🕊 💖
†
[ 🕊 ፍኖተ ቅዱሳን 🕊 ]
[ የቅዱሳን አባቶቻችን የቅድስናና የተጋድሎ ሕይወት ]
† † †
[ የፍትወት ጾር ስለሚያስነሣው ፈተና ]
🕊
[ የተመኘኸው ይኸውልህ ! ]
በአስቄጥስ አንድ በብርቱ የሚጋደል ወንድም ነበር። ጠላት መልከ መልካም የነበረችን አንዲት ሴት በማሳሰብ አጥብቆ ተዋጋው ፣ እርሱም እጅግ ተሰቃየ፡፡ በእግዚአብሔር የቸርነት አሠራር ሌላ ወንድም ከግብጽ ወደ አስቄጥስ መጣና ሲነጋገሩ ፦ " የእገሌ ሚስት ሞታለች " አለው፡፡
ይህቺም ይህን ገዳማዊ ጠላት ምክንያት አድርጎ እየተዋጋው ያላት ሴት ነበረች። ይህን ሲሰማ በሌሊት ሄደና መቃብሩን ከፍቶ ዐጽፉን [ ልብሱን ] እየበሰበሰ ባለው ሰውነት ላይ ጣለው፡፡ ከዚያም ያን መጥፎ ሽታ ይዞ ወደ በአቱ ተመለሰና ፦ " የተመኘኸው ይኸውልህ አለልህ ፣ ተደሰትበት " እያለ ከክፉ ሀሳቡ ጋር ይታገል ነበር፡፡ የተነሣበት ጾር እስኪጠፋለት ድረስ በዚያ መጥፎ ሽታ ራሱን ይገሥፅ ነበር።
🕊
የአንድ ታላቅ አባት ረድእ በፍትወት ጾር ተጠቃ አረጋዊውም በጸሎቱ ጊዜ ይህን ሁኔታ አየና ፦ " ከዚህ ውጊያ እንዲገላግልህ እግዚአብሔርን እንድጠይቅልህ ትፈልጋለህ ? " አለው፡፡ ያም ወንድም ፦ " አባ ፣ እየተሰቃየሁ እንደሆነ ግልጽ ነው ፣ ነገር ግን ይህ መፈተኔ በእኔ ውስጥ ፍሬ እያፈራ አያለሁ ፤ ስለዚህ እችለው ዘንድ ጽናቱን እንዲሰጠኝ እግዚአብሔርን ለምንልኝ " አለው፡፡ አባቱም ፦ " አንተ በፍጹምነት እንደ በለጥኸኝ ዛሬ ተገነዘብሁ " አለው፡፡
🕊
የአባቶቻችን ጸሎትና በረከት ይደርብን፡፡
† † †
💖 🕊 💖
* ማግሰኞ - ጥር 21 2016 ዓ.ም *
* ዘፍጥረት 42-45*
ሰላም ለሁላችሁ ይሁን! በዛሬው ንባባችን ከምዕራፍ 42 እስከ 45 ድረስ እናነባለን።
ከንባብ በፊት የሚደረግ ጸሎት፡ “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፤ የአንተን ቃላት እሰማ እና እረዳ ዘንድ፥ እንዲያውም ፈቃድህን ለመፈጸም እበቃ ዘንድ የልቤን ጆሮዎች እና ዓይኖች ክፈትልኝ።” (ቅዱስ ኤፍሬም ሶሪያዊ)
የዛሬው ንባባችን ትኩረት የሚያደርገው የዮሴፍ ወንድሞች ወደ ግብጽ ባደረጉት ጉዞ ላይ ነው። በግብጽ በተገኙ ጊዜ ዮሴፍ ወንድሞቹን ስላወቃቸው፥ በተለያየ መንገድ እንደፈተናቸው እናነባለን። ወንድሞቹም አንዱን ወንድማቸውን በግብጽ ትተው ብንያምን ለማምጣት እንደሄዱ፥ አባታቸው እስራኤል (ያዕቆብ) በብዙ ማንገራገር እንደሰጣቸው፥ እነርሱም ወደ ግብጽ ተመልሰው በሄዱ ጊዜ ያላሰቡት መስተንግዶ፥ ከዚያም ደግሞ ያላሰቡት ፈተና እንደገጠማቸው፥ በስተመጨረሻም ወንድማቸው ዮሴፍ ራሱን ለእነርሱ እንደገለጠ እናነባለን።
* የክለሳ ጥያቄዎች * (መልሶቹን ማታ ከ1፡00 በሁዋላ ጻፉ)
1) በዘፍጥረት 42 መሠረት፥ የዮሴፍ ወንድሞች ወደ ግብጽ የሄዱት ለምንድር ነው?
2) በዮሴፍ ፊት ወንድሞቹ በቀረቡ ጊዜ፥ ዮሴፍ ምን ብሎ ተናገራቸው?
3) እስራኤል (ያዕቆብ) ልጁ ብንያም ከወንድሞቹ ጋር ወደ ግብጽ እንዲሄድ የፈቀደበት ምክንያት ምንድር ነው?
4) በዘፍጥረት 43 መሠረት ዮሴፍ ወንድሞቹ ሲመጡ በምን መልኩ አስተናገዳቸው?
5) በዘፍጥረት 44 መሠረት፥ ዮሴፍ በብያም ከረጢት ውስጥ ምን እንዲቀመጥ አዘዘ?
6) የጠፋው እቃ በብንያም ከረጢት ውስጥ በተገኘ ጊዜ የወንድሞቹ ምላሽ ምን ነበር?
7) ዮሴፍ ራሱን ለወንድሞቹ የገለጠው በምን መልኩ ነው?
8) ዮሴፍ ወንድሞቹ እርሱን ስለሸጡት እንዳያዝኑ ወደ ግብጽ ስለመጣበት ምክንያት እና ስለ እግዚአብሔር እቅድ ምን አላቸው?
መልካም ንባብ!
https://youtu.be/h0CB2vkeKaI?si=tbr0VjXILYptwHFh
Читать полностью…🕊
[ † እንኳን ለእመቤታችን ንጽሕት ድንግል ወላዲተ አምላክ ማርያም ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ]
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †
🕊 † ዕረፍተ ድንግል † 🕊
† እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቅድመ ዓለም በአምላክ ልቡና ታስባ ትኖር ነበር:: ከነገር ሁሉ በፊት እግዚአብሔር እናቱን ያውቃት ነበር::
- ዓለም ተፈጥሮ: አዳምና ሔዋን ስተው: መርገመ ሥጋና መርገመ ነፍስ አግኝቷቸው: በኃዘን ንስሃ ቢገቡ "እትወለድ እም ወለተ ወለትከ - ከ፭ ቀን ተኩል [5500 ዘመናት] በሁዋላ ካንተ ባሕርይ ከምትገኝ ንጽሕት ዘር ተወልጄ አድንሃለሁ" ብሎ ተስፋ ድኅነት ሰጠው::
- ከአዳም አንስቶ ለ፭ ሺህ ፭ መቶ [5500] ዓመታት አበው: ነቢያትና ካህናት ስለ ድንግል ማርያም ብዙ ሐረገ ትንቢቶችን ተናገሩ:: መዳኛቸውን ሱባኤ ቆጠሩላት:: ምሳሌም መሰሉላት:: ከሩቅ ዘመን ሁነውም ሊያገኟት እየተመኙ እጅ ነሷት::
"እምርሑቅሰ ርእይዋ: ወተአምኅዋ" እንዲል::
† የድንግል ማርያም ሐረገ ትውልድ ፦
- ከአዳም በሴት
- ከያሬድ በሔኖክ
- ከኖኅ በሴም
- ከአብርሃም በይስሐቅ
- ከያዕቆብ በይሁዳና በሌዊ
- ከይሁዳ በእሴይ: በዳዊት: በሰሎሞንና በሕዝቅያስ ወርዳ ከኢያቄም ትደርሳለች::
- ከሌዊ ደግሞ በአሮን: አልዓዛር: ፊንሐስ: ቴክታና በጥሪቃ አድርጋ ከሐና ትደርሳለች::
- አባታችን አዳም ከገነት በወጣ በ፭ ሺህ ፬ መቶ ፹፭ [5,485] ዓመት ወላዲተ አምላክ ንጽሕና ሳይጐድልባት: ኃጢአት ሳያገኛት: ጥንተ አብሶ ሳይደርስባት ከደጋጉ ኢያቄም ወሐና ትወለዳለች:: [ ኢሳ.፩፥፱ , መኃ.፬፥፯ ] "ወኢረኩሰት በምንትኒ እምዘፈጠራ" እንዳለ:: [ ቅዱስ ቴዎዶጦስ ዘዕንቆራ ]
ከዚያም ከእናት ከአባቷ ቤት ለ፫ [3] ዓመታት ቆይታ ወደ ቤተ መቅደስ ትገባለች:: በቤተ መቅደስም ለ፲፪ [12] ዓመታት ፈጣሪዋን እግዚአብሔርን እያመሰገነችና እያገለገለች: እርሷን ደግሞ መላእክተ ብርሃን እያገለገሏት: ሕብስት ሰማያዊ ጽዋዕ ሰማያዊ እየመገቧት ኑራለች:: ፲፭ [15] ዓመት በሞላት ጊዜ አረጋዊ ዮሴፍ ያገለግላት ዘንድ ወደ ቤቱ ወሰዳት::
- በዚያም መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ዜና ድኅነትን ነግሯት አካላዊ ቃልን በማሕጸንዋ ጸነሰችው:: ነደ እሳትን ተሸከመችው: ቻለችው:: "ጾርኪ ዘኢይትጸወር: ወአግመርኪ ዘኢይትገመር" እንዳለ:: [ ሊቁ ቅዱስ ኤፍሬም ለብሐዊ ]
- ወልደ እግዚአብሔርን ለ፱ [9] ወራት ከ፭ [5] ቀናት ጸንሳ: እንበለ ተፈትሆ [በድንግልና] ወለደችው:: [ኢሳ.፯፥፲፬] "ኢየሱስ" ብላ ስም አውጥታለት በገሊላ ለ፪ [2] ዓመታት ቆዩ::
- አርዌ ሔሮድስ እገድላለሁ ብሎ በተነሳበት ወቅትም ልጇን አዝላ በረሃብ እና በጥም: በላበትና በድካም: በዕንባና በኃዘን ለ፫ [3] ዓመታት ከ፮ [6] ወራት ከገሊላ እስከ ኢትዮዽያ ተሰዳለች:: ልጇ ጌታችን ፭ [5] ዓመት ከ፮ [6] ወር ሲሆነው: ለድንግል ደግሞ ፳፩ [21] ዓመት ከ፫ [3] ወር ሲሆናት ወደ ናዝሬት ተመለሱ::
- በናዝሬትም ለ፳፬ [24] ዓመታት ከ፮ [6] ወራት ልጇን ክርስቶስን እያሳደገች: ነዳያንን እያሰበች ኑራለች:: እርሷ ፵፭ [45] ዓመት ልጇ ፴ [30] ዓመት ሲሆናቸው ጌታችን ተጠምቆ በጉባኤ ትምሕርት: ተአምራት ጀመረ:: ለ፫ [3] ዓመታት ከ፫ [3] ወራትም ከዋለበት እየዋለች: ካደረበትም እያደረች ትምሕርቱን ሰማች::
- የማዳን ቀኑ ደርሶ ልጇ ክርስቶስ ሲሰቀልም የመጨረሻውን ፍጹም ሐዘን አስተናገደች:: አንጀቷ በኃዘን ተቃጠለ:: በነፍሷም ሰይፍ አለፈ:: [ሉቃ.፪፥፴፭] ጌታ በተነሳ ጊዜም ከፍጥረት ሁሉ ቀድማ ትንሳኤውን አየች:: ለ፵ [40] ቀናትም ሳትለይ ከልጇ ጋር ቆየች::
- ከልጇ ዕርገት በሁዋላ በጽርሐ ጽዮን ሐዋርያትን ሰብስባ ለጸጋ መንፈስ ቅዱስ አበቃች:: በጽርሐ ጽዮንም ከአደራ ልጇ ከቅዱስ ዮሐንስ ጋር ለ፲፭ [15] ዓመታት ኖረች:: በእነዚህ ዓመታት ሥራ ሳትፈታ ስለ ኃጥአን ስትማልድ: ቃል ኪዳንን ከልጇ ስትቀበል: ሐዋርያትን ስታጽናና: ምሥጢርም ስትገልጽላቸው ኑራለች::
- ዕድሜዋ ፷፬ [64] በደረሰ ጊዜ ጥር ፳፩ [21] ቀን መድኃኒታችን አእላፍ ቅዱሳንን አስከትሎ መጣ:: ኢየሩሳሌምን ጨነቃት:: አካባቢውም በፈውስ ተሞላ:: በዓለም ላይም በጐ መዓዛ ወረደ:: እመ ብርሃን ለፍጡር ከዚያ በፊት ባልተደረገ: ለዘለዓለምም ለማንም በማይደረግ ሞገስ: ክብርና ተአምራት ዐረፈች:: ሞቷ ብዙዎችን አስደንቁአል::
"ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ::
ሞታ ለማርያም የአጽብ ለኩሉ::" እንዲል::
- ከዚህ በሁዋላ መላእክት እየዘመሩ: ሐዋርያቱም እያለቀሱ ወደ ጌቴሴማኒ: በአጐበር ሥጋዋን ጋርደው ወሰዱ:: ይሕንን ሊቃውንት :-
"ሐራ ሰማይ ብዙኃን እለ አልቦሙ ሐሳበ::
እንዘ ይዜምሩ ቅድሜኪ ወመንገለ ድኅሬኪ ካዕበ::
ማርያም ሞትኪ ይመስል ከብካበ" ሲሉ ይገልጡታል::
- በወቅቱ ግን አይሁድ በክፋት ሥጋዋን እናቃጥል ስላሉ ቅዱስ ገብርኤል [ጠባቂ መልአክ ነው] እነርሱን ቀጥቶ: እርሷን ከቅዱስ ዮሐንስ ጋር ወስዶ በዕጸ ሕይወት ሥር አኑሯታል:: በዚያም መላእክት እያመሰገኗት ለ፪፻፭ [205] ቀናት ቆይታለች::
- ቅዱስ ዮሐንስ መጥቶ ለሐዋርያቱ ክብረ ድንግልን ቢነግራቸው በጐ ቅንአት ቀንተው በነሐሴ ፩ [1] ሱባኤ ጀመሩ:: ፪ [2] ኛው ሱባኤ ሲጠናቀቅም ጌታ የድንግል ማርያምን ንጹሕ ሥጋ ሰጣቸው:: እየዘመሩም በጌቴሴማኒ ቀብረዋታል::
- በ፫ [3]ኛው ቀን [ነሐሴ ፲፮ (16)] እንደ ልጇ ባለ ትንሳኤ ተነስታ ዐርጋለች:: ትንሳኤዋንና ዕርገቷንም ደጉ ሐዋርያ ቅዱስ ቶማስ አይቶ: መግነዟን ተቀብሏል:: ሐዋርያቱም መግነዟን ለበረከት ተካፍለው: እንደ ገና በዓመቱ ነሐሴ ፩ [1] ቀን ሱባኤ ገቡ::
- ለ፪ [2] ሳምንታት ቆይተው: ሁሉንም ወደ ሰማይ አወጣቸው:: በፍጡር አንደበት ተከናውኖ የማይነገር ተድላ: ደስታና ምሥጢርንም አዩ:: ጌታ ራሱ ቀድሶ ሁሉንም አቆረባቸው:: የበዓሉን ቃል ኪዳን ሰምተው: ከድንግል ተባርከው ወደ ደብረ ዘይት ተመልሰዋል::
† ጽንዕት በድንግልና ሥርጉት በቅድስና እመቤታችን: ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኚልን:: አእምሮውን: ለብዎውን: ጥበቡን በልቡናችን ሳይብን አሳድሪብን:: †
🕊 † ቅዱስ ጐርጐርዮስ ሊቅ † 🕊
† ለዚህ ቅዱስ አባት ብጹዕ መባል ተገብቷል:: ክቡር: ምስጉን: ንዑድ ሰው ነውና:: በ፬ [4]ኛው መቶ ክ/ዘመን በቂሣርያ ቀዸዶቅያ የተወለደው ቅዱሱ ሰው ለደሴተ ኑሲስ ብርሃኗ ነው:: አባቱ ኤስድሮስ: እናቱ ኤሚሊያ: ወንድሞቹ ቅዱሳን "ባስልዮስ: ዼጥሮስ: መክርዮስና መካርዮስ" ይባላሉ::
የተቀደሰች እህቱም ማቅሪና ትባላለች:: ከዚህ የተባረከ ቤተሰብ ለቅድስና ያልበቃ አንድም ሰው የለም:: ሊቁ ቅዱስ ጐርጐርዮስም ከማር በጣፈጠ ዜና ሕይወቱ እንደ ተጻፈው :-
- በልጅነቱ ቅዱሳት መጻሕፍትን ተምሯል::
- ሥጋውያን ጠቢባንን ያሳፍር ዘንድም የግሪክን ፍልሥፍና በልኩ ተምሯል::
†
[ 🕊 የሕይወት እናት ሞት ! 🕊 ]
🕊
[ ሰማይ የተሸለመባቸው የዘመናት ምልክቶች ፀሐይ ፣ ጨረቃ ፣ ከዋክብት፡፡ ምድር የተሸለመችባቸው አበቦችም ድንገት እንደ ጥላ ያልፋሉ ይጠፋሉ ፡ ንግሥት ማርያም ላንቺ የሚቀርበው ሽልማት ምስጋና ግን ለዘላለም አያልፍም አይጠፋም፡፡ ]
[ አባ ጽጌ ድንግል ]
† † †
💖 🕊 💖
†
† 🕊 [ አስተርዮ ማርያም ] 🕊 †
💖
በዘመነ አስተርዮ የጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥ የሆነበትና የአምላካችን አንድነትና ሦስትነት የተገለጠበት ብቻም ሳይሆን በጥር ፳፩ የከበረች እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያም የዕረፍት ቀን በመሆኑ “አስተርዮ ማርያም” በማለት በዓልን አናደርጋለን፡፡
የአምላክ እናት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዚህ ምድር ላይ ፷፬ ዓመታትን ከኖረች በኋላ መንፈስ ቅዱስ ባስገነዘባት መሠረት በክብር ዐርፋለች፡፡ የዚህን ዓለም መከራና ሥቃይ ለሰዎች ድኅነት የተቀበለችው ክብርት እናታችን በሥጋ ብትሞትም እንደ ልጇ ደግሞ በትንሣኤዋ ተነሥታለች ፤ ይህም የሆነው በተቀደሰች ዕለት ነሐሴ ፲፮ ነው፡፡
እመ ብርሃን ከእናትና ከአባቷ ጋር ሦስት ዓመት ፣ በቤተ መቅደስ ፲፪ ዓመት ፣ ከተወዳጁ ልጅዋ ጋር ፴፫ ዓመት ከሦስት ወር ፣ ከጌታችን ዕርገት በኋላ ከወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ ጋር ፲፭ ዓመት ፣ በድምሩ ፷፬ ዓመት በዚህ በኃላፊው ዓለም ኖራ ጥር ፳፩ ቀን በ፵፱ ዓመተ ምሕረት በክብር ዐርፋለች፡፡
ክርስቲያኖች በሙሉ ይህንን በዓል ልናከብር ይገባልና ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ሥርዓትን ሠርታልናለች፡፡ “አስተርዮ ማርያም” በሕዝበ ክርስቲያን ዘንድ የሚከበር በዓል በመሆኑ በሀገራችን ኢትዮጵያ እና በመላው የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ማኅበረሰብ ዘንድ በድምቀት ይከበራል፡፡ በዓሉን የምናከብረውም የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ከዚህ ዓለም ድካም ማረፍ በማዘከር ብቻ ሳይሆን አማላጅነቷና ተረዳኢነቷን በማሰብና ተስፋ በማድረግ ነው፡፡
ስለዚህም እመ ብዙኃን እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዐሥራት ሀገሯን ኢትዮጵያን እንድታስባት ፣ ለእኛም ለሕዝቦቿ ሰላምን ፣ ፍቅርንና አንድነትን ታሰጠን እንዲሁም ለነፍሳችን ድኅነትን ትለምንልን ዘንድ ዕረፍቷን መዘከር ይገባል፡፡
የአምላካችን እግዚአብሔር ቸርነት ፣ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነትና ተረዳኢነት አይለየን ፤ አሜን !!!
† † †
💖 🕊 💖
* ሰኞ - ጥር 20 2016 ዓ.ም *
* ዘፍጥረት 37-41*
ሰላም ለሁላችሁ ይሁን! በዛሬው ንባባችን ከምዕራፍ 37 እስከ 41 ድረስ እናነባለን።
ከንባብ በፊት የሚደረግ ጸሎት፡ “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፤ የአንተን ቃላት እሰማ እና እረዳ ዘንድ፥ እንዲያውም ፈቃድህን ለመፈጸም እበቃ ዘንድ የልቤን ጆሮዎች እና ዓይኖች ክፈትልኝ።” (ቅዱስ ኤፍሬም ሶሪያዊ)
የዛሬው ንባባችን ትኩረት የሚያደርገው በያዕቆብ የመጨረሻ ልጅ በዮሴፍ ላይ ነው። ወንድሞቹ በዮሴፍ ላይ ሲቀኑበት፥ ከዚያም ለነጋዴዎች አሳልፈው ሲሸጡት እናነባለን። እግዚአብሔር ግን ዮሴፍን አልተለየውም ነበር። በሄደበት በግብጽም ሞገስን አገኘ። ሆኖም ግን፥ የጲጥፋራ ሚስት በዮሴፍ ላይ ዓይኗን ጥላ ከእርሷ ጋር እንዲተኛ ግድ አለችው፤ እርሱም ከእርሷ ፊት ሸሸ። በዚህም ተበሳጭታ በሐሰት ክስ ዮሴፍን በእሥር ቤት አስወረወረችው። እግዚአብሔር ግን በእሥር ቤትም ዮሴፍን አልተለየውም ነበር። በዚያ ለሁለት ሰዎች ሕልምን ሲተረጉም፥ በዚህም ምክንያት የግብጽ ፈርዖን ሕልምን ባለመ ጊዜ ደግሞ ዮሴፍ ለእርሱ ሕልምን እንደፈታለት በምዕራፎቹ ውስጥ እናነባለን።
* የክለሳ ጥያቄዎች * (መልሶቹን ማታ ከ1፡00 በሁዋላ ጻፉ)
1) በዘፍጥረት 37 መሠረት፥ የዮሴፍ ወንድሞች የቀኑበት ለምንድር ነው?
2) የዮሴፍ ወንድሞች በእርሱ ላይ ምን አደረጉ? ዮሴፍስ በእነርሱ ምክንያት ምን ሆነ?
3) በዘፍጥረት 38 ላይ ትዕማር ዘር ለማግኘት ስትል ምን አደረገች?
4) በዘፍጥረት 38 መሠረት ከትዕማር የተወለዱት ልጆች ማን ይባላሉ? ሲወለዱስ ምን ተፈጠረ?
5) ጲጥፋራ ለዮሴፍ በቤቱ ላይ ሁሉ ሥልጣን የሰጠው ለምንድር ነው?
6) በዘፍጥረት 39 መሠረት ዮሴፍ የተከሰሰው የሐሰት ክስ ምንድር ነው?
7) ዮሴፍ በእሥር ቤት እያለ ለሁለት ሰዎች ሕልም ተርጉሟል። እነዚህ እነማን ናቸው? ሕልማቸውስ ምን ነበር?
8) ዮሴፍ ለሁለቱ ሰዎች የተረጎመው ሕልም ትርጓሜ እውን የሆነው በምን መልኩ ነው?
9) በዘፍጥረት 41 ዮሴፍ ለግብጽ ፈርዖን የተረጎመው ሕልም ምንድር ነው? ትርጉሙስ ምን ነበር?
10) ለፈርዖን በተረጎመው ሕልም የተነሳ ዮሴፍ ምን አገኘ?
መልካም ንባብ!
🕊
[ † እንኳን ለቅዱሳን አክሎግ ቀሲስ : መርምሕናም : ወዮሐንስ ወንጌሉ ዘወርቅ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ]
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †
🕊 † ቅዱስ አክሎግ ሰማዕት † 🕊
† ቤተ ክርስቲያን ካፈራቻቸው ዓበይት ሰማዕታት አንዱ ይህ ቅዱስ ነው:: "አክሎግ" ማለት "በእግዚአብሔር ዘንድ ጣፋጭ [ተወዳጅ]" ማለት ነው:: እውነትም ጥዑም ዜና: ጣፋጭ ሕይወት ያለው አባት ነው:: "መልአክ ስምን ያወጣል" የሚባለው እንዲህ ላለው ነውና::
እርሱ የወላጆቹ ፍሬ ነው:: በ፫ኛው መቶ ክ/ዘ የነበሩ ወላጆቹ ለልጃቸው ያወረሱት ሞልቶ የተረፈ ሃብታቸውን አልነበረም:: ይልቁኑ ፍቅረ ክርስቶስን: ምሥጢረ መጻሕፍትን: ክርስቲያናዊ ስምን ነው እንጂ::
ቅዱስ አክሎግ ገና ከልጅነቱ ወደ ት/ቤት ገብቶ: ቅዱሳት መጻሕፍትን ተምሮ: ሐዲስ ኪዳንን በሙሉ: መኀልየ ነቢያትን: መዝሙረ ዳዊትን አክሎ በቃሉ አጠና:: ቅዱስ ቃሉ ለእርሱ እውቀት አልነበረም: ሕይወት እንጂ:: ሳይሰለች ያነበው: በሕይወቱም ይተረጉመው ነበርና::
በዚህ ንጹሕ ሕይወቱም ፈጣሪውን አስደስቶ ብዙ ተአምራትን ሠርቷል:: ከዚያም ተጋድሎውን ቀጥሎ በትሕርምት ኑሯል:: ቀሲስ ሆኖ ሲሾምም ቅዱሳን መላእክት "ይገባዋል!" ሲሉ ፫ ጊዜ ጮሁ:: በጽድቅ ጸንቶም ዘመናት አለፉ::
በዘመነ ሰማዕታትም ነጭ በነጭ ለብሶ ብዙ መከራን ተቀበለ:: በዚህች ቀንም ከብዙ ተከታዮቹ ጋር ደሙ ፈሷል:: ስለዚህም ቤተ ክርስቲያን "ጻድቅ: ንጹሕ: ድንግል: ባሕታዊ: ቀሲስ ወሰማዕት" ብላ ታከብረዋለች:: ጌታም "ስምህን ያከበረውን: የተሰየመውን እምርልሃለሁ" ብሎታል::
🕊 † ቅዱስ መርምሕናም ሰማዕት † 🕊
† ሰማዕቱ በቤተ ክርስቲያን ትልቅ ቦታ ከሚሰጣቸው ዐበይት ቅዱሳን አንዱ ነው:: በየአብያተ ክርስቲያናቱ ከሚሳሉ ቅዱሳንም አንዱ ነው:: ሃገሩ አቶር [በፋርስ አካባቢ] ሲሆን አባቱ ሰናክሬም የሚባል ንጉሠ ነገሥት ነው::
እናቱ ምንም ክርስቲያን ብትሆንም ስለ ፈራች ሁለቱን ልጆቿን [መርምሕናምና ሣራን] ክርስትናን አላስተማረቻቸውም:: ሁለቱም ወጣት በሆኑ ጊዜም ከንጉሥ አባታቸው ጋር ይወጡ ይገቡ ነበርና እናታቸው በሐዘን ጸለየች:: ወዲያውም ወጣቷ ሣራ በለምጽ ተመታች::
የሚፈውሳት ጠፋ:: መርምሕናም ግን ጐበዝ ወጣት ነውና ፵ [40] የጦር አለቆችን ይመራ ነበር:: በዚያው በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን ቅዱስ መርምሕናም ፵ [40] ተከታዮቹን ይዞ ለአደን ወደ ዱር ሲወጣ ከአባ ማቴዎስ ገዳማዊ ጋር ተገናኘ::
ጻድቁ ለብዙ ዓመታት በበርሃ የኖሩ አባት ናቸው:: አካላቸው በጸጉር ስለ ተሸፈነ ደንግጦ ሲሸሽ "ልጄ አትፍራ! እኔም እንዳንተ የክርስቶስ ፍጡር የሆንኩ ሰው ነኝ" አሉት::
እርሱ ግን "ደግሞ ክርስቶስ ማነው?" ሲል ጠየቃቸው:: አባ ማቴዎስም ምሥጢረ ክርስትናን ከመሠረቱ አስተምረው የክርስቶስን የባሕርይ አምላክነት ነገሩት::
ቅዱስ መርምሕናም ግን "ክርስቶስ አምላክ እንደ ሆነ አምን ዘንድ እህቴን አድንልኝ" አላቸው:: "አምጣት" ብለውት አመጣት:: ጻድቁ ጸሎት አድርሰው መሬትን ቢረግጧት ውኃን አፈለቀች:: "በእምነት: በስመ ሥላሴ ተጠመቁ" አሏቸው::
ቅዱሱ: እህቱ ሣራና ፵ [40] የጦር አለቆች ተጠምቀው ሲወጡ ሣራ ከለምጿ ነጻች:: ፈጽሞም ደስ አላቸው:: ወደ ቤተ መንግስት ተመልሰውም ቅዱስ መርምሕናም ከእናቱ: ከእህቱና ከ40 ተከታዮቹ ጋር ክርስቶስን ሊያመልኩ ጀመሩ::
ንጉሡ ሰናክሬም ግን ነገሩን ሲሰማ ተቆጣ:: እነርሱም ወደ ተራራ ሸሹ:: ንጉሡ "ልጆቼ! መንግስቴን ውረሱ" ብሎ ቢልክባቸውም እንቢ አሉ:: ስለ ተበሳጨም ቅዱስ መርምሕናምን: ቅድስት ሣራንና ፵ [40ውን] ቅዱሳን በሰይፍ አስመታቸው::
ሥጋቸውን በእሳት ሊያቃጥሉ ሲሉ ግን መነዋወጥ ሆኖ ብዙ አረማውያን ሞቱ:: ንጉሡም አብዶ አውሬ [እሪያ] ሆነ:: ያን ጊዜ አባ ማቴዎስ ከበርሃ ወጥተው ንጉሡን ሰናክሬምን ፈወሱት::
እርሱም አምኖ የልጆቹና የ40ውን ሥጋ በክብር አኖረ:: በሃገሩ አቶርም የእመ ብርሃን ማርያምን ቤተ መቅደስ አነጸ:: በክርስትና ኑሮም ዐረፈ:: እርሱ ከተቀበረ በኋላ ግን የከለዳውያን ንጉሥ መጥቶ አቶርን ወረራት::
ንግሥቲቱን [የቅዱሳኑን እናት] ከሕፃኑ ልጇ ጋርም ገደለ:: በኋላም "ለጣዖት ስገዱ" ማለቱን የሰሙት የቅዱስ መርምሕናም ወታደሮች ደርሰው በምስክርነት ተሰየፉ:: ቁጥራቸውም መቶ ሰባ ሺህ [170,000] ሆነ::
🕊 † ቅዱስ ዮሐንስ ጻድቅ [ ወንጌሉ ዘወርቅ ] † 🕊
† ቅዱሱ "ወንጌሉ ዘወርቅ" እየተባለ የሚጠራው ከሌሎች "ዮሐንስ" ከሚባሉ ቅዱሳን ለመለየት ቢሆንም ዋናው ምክንያት ግን እድሜ ልኩን የሚያነበው: ከእጁ የማይለየውና አቅፎት የሚተኛ በወርቅ የተለበጠ ወንጌል ስለ ነበረው ነው::
የቅዱስ ዮሐንስ ታሪኩ በሆነ መንገድ ከመርዓዊ [ሙሽራው] ገብረ ክርስቶስ እና ከቅዱስ ሙሴ ሮማዊ ጋር ተመሳሳይነት አለው::
ይሕስ እንደ ምን ነው ቢሉ :-
በሮም ግዛት ሥር የሚኖሩ አጥራብዮስና ብዱራ የሚባሉ ደጋግ ክርስቲያኖች ነበሩ:: እግዚአብሔር በቀደሰው ትዳር የሚኖሩና ነዳያንን የሚዘከሩ ነበሩና ይህንን ቅዱስ ወለዱ:: ስሙን ዮሐንስ ብለው: እንደሚገባም አሳድገው: ምሥጢረ መንግስተ ሰማያትን እንዲረዳ ለመምህር ሰጡት:: ቅዱስ ዮሐንስ ከመምህሩ ዘንድ ቁጭ ብሎ መጻሕፍተ ቤተ ክርስቲያንን ተማረ::
ለወላጆቹ ቅንና ታዛዥ ነበርና አባቱ "ልጄ ! የምትፈልገውን ጠይቀኝ:: ምን ላደርግልህ ትወዳለህ?" አለው:: ቅዱስ ዮሐንስ ዘንድሮ እኛን የሚያምረን ሁሉ አላሰኘውም:: አባቱን "ቅዱስ ወንጌልን ግዛልኝ: በወርቅም አስለብጠው" አለው:: አባትም የተባለውን ፈጸመ::
ከዚያች ሰዓት ጀምሮ ከዚህ ዓለም ተለይቶ እስካረፈባት ቀን ድረስ ቅዱስ ዮሐንስና የወርቅ ወንጌሉ ተለያይተው አያውቁም:: ሁሌም ያለመታከት ያነበዋል:: ሲቀመጥም ሲነሳም: ሲሔድም ሲተኛም አብሮት ነበር::
ቅዱስ ዮሐንስ ወጣት በሆነ ጊዜ ወላጆቹ ይድሩት ዘንድ ተዘጋጁ:: ልብሰ መርዐም [የሙሽራ ልብስ] አዘጋጁ:: በዚያው ሰሞን ግን አንድ እንግዳ መነኮስ ወደ ቤታቸው መጥቶ ያድራል:: በዚያች ሌሊት መነኮሱ በጨዋታ መካከል ስለ ቅዱሳን መነኮሳት ተጋድሎና ክብር ነገረው:: የሰማው ነገር ልቡናውን የማረከው ቅዱስ ዮሐንስ ከዚያች ቀን ጀምሮ ወደ ፈጣሪው ይለምን ነበር::
አንድ ቀን ግን ያ መነኮስ በድጋሚ መጥቶ አደረ:: ቅዱስ ዮሐንስ መነኮሱን ወደ ገዳም እንዲወስደው ቢጠይቀው "አይሆንም: አባትህ ያዝንብኛል" አለው:: ቅዱሱ ግን "በእግዚአብሔር ስም አማጽኜሃለሁ" ስላለው ሁለቱም በሌሊት ወጥተው ወደ ገዳም ሔዱ::
አበ ምኔቱ "ልጄ! የበርሃውን መከራ አትችለውም: ይቅርብህ" ቢለውም "አባቴ! አይድከሙ:: ከክርስቶስ ፍቅር ምንም ነገር አይለየኝም'' ስላላቸው እንደሚገባ ፈትነው አመንኩሰውታል:: ቅዱስ ዮሐንስ ከመነኮሰ በኋላ በጾም: በጸሎት: በስግደትና በትሕርምት ያሳየው ተጋድሎ በርካቶችን አስደነቀ::
ለሥጋው ቦታ አልሰጣትምና በወጣትነቱ አካሉ ረገፈ:: ቆዳውና አካሉም ተገናኘ:: ሥጋውን አድርቆ ነፍሱን አለመለማት:: በእንዲሕ ያለ ሕይወት ለ7 ዓመታት ከተጋደለ በኋላ በራዕይ "ወደ ወላጆችህ ተመለስ" እያለ ፫ ጊዜ አናገረው::
ቅዱስ ዮሐንስ ወደ አበ ምኔቱ ሔዶ ቢጠይቀው "ራዕዩ ከእግዚአብሔር ነው" ብሎ ወደ ቤተሰቦቹ አሰናበተው::
†
[ 🕊 ድምፀ ተዋሕዶ 🕊 ]
🍒▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬🍒
[ ሕይወት የሚገኝባቸው የቅድስት ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ትምህርቶች በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን በድምፅ ይቀርባሉ። ]
[ ሳምንታዊ መርሐ-ግብር ]
🕊
[ " ሕይወተ ዘራዙት - የወጣቶች ሕይወት ! " ]
[ ክፍል ሦስት ]
" ጕልማሳ መንገዱን በምን ያነጻል ? ቃልህን በመጠበቅ ነው።" [ መዝ.፻፲፱፥፱ ]
💖 ድንቅ ትምህርት 💖
[ በመምህራችን በቀሲስ ኅብረት የሺጥላ ]
" የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ፥ ከመከራም ሥጋት ያርፋል።" [ ምሳ.፩፥፴፫ ]
† † †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬
👇