"እንግዲህ፡ንስሓ፡ግባ፤አለዚያ፡ፈጥኜ፡ እመጣብሃለሁ፡፡" ራዕ 2፥16
† † †
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
[ ቤተክርስቲያንን እንወቅ ]
[ ክፍል - ፲፱ - ]
[ ሥ ር ዓ ተ አ ም ል ኮ ! ]
🕊
ሥርዓት “ሠርዐ” ሠራ ከሚለው የግእዝ ቃል የወጣ ሲሆን ትርጉሙም ደንብ ፣ አሠራር ፣ መርሐ ግብር ማለት ነው። በሃይማኖት ውስጥ የሚፈጸም የመንፈሳዊ አገልግሎትና አሠራር እንዲሁም ክርስቲያናዊ ሥርዓትን ያመለክታል።
[ 🕊 ሥርዓተ አምልኮት 🕊 ]
የቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓተ አምልኮት ለአምላካችን እግዚአብሔር የሚቀርብ ሥርዓት ነው፡፡ ይህም ሥርዓተ ጸሎትን ፣ ሥርዓተ ጾምን ፣ ሥርዓተ ምጽዋት ፣ ሥርዓተ ስግደትን ፣ ሥርዓተ በዓላትን ፣ ሥዕላትን ፣ መስቀልንና ንዋያተ ቅድሳትን ያካትታል፡፡
፩ . [ 🕊 ሥርዓተ ጸሎት 🕊 ]
ጸሎት ቃሉ ግእዝ ሲሆን “ጸለየ ፣ ለመነ” ከሚለው ግሥ የወጣ ነው፡፡ የቃሉ ትርጉምም ልመና እንዲሁም ምስጋናም ነው፡፡ ለምሳሌ “ይትቀደስ ስምከ” [ ስምህ ይቀደስ ] ስንል ምስጋና ነው፡፡ “ሲሳየነ ዘለለዕለትነ ሀበነ ዮም” [የዕለት ምግባችንን ዛሬ ስጠን] ስንል ደግሞ ልመና ነው፡፡ እንዲሁም ጸሎት ሰው ከልዑል እግዚአብሔር ጋር የሚነጋገርበት ነው፡፡ [ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ ፲፬]
ሀ. [ 🕊 ሰባቱ የጸሎት ጊዜያት 🕊 ]
ነቢዩ ዳዊት “ስለ ጽድቅህ ፍርድ በቀን ሰባት ጊዜ አመሰግንሃለው” ብሎ እንደተናገረ በቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ ሰባት የጸሎት ጊዜያት አሉ፡፡ [መዝ.፻፲፰-፻፷፬]
- 💖 ጸሎተ ነግህ
ነቢዩ ዳዊት “አምላኬ አምላኬ በማለዳ ወደ አንተ እገሰግሳለሁ” በማለት እንደተናገረው ሌሊቱ አልፎ ቀኑ ሲተካ ከጥዋቱ በዐሥራ ሁለት ሰዓት የምንጸልየው የጸሎት ዓይነት ነው፡፡ [መዝ.፷፪÷፲፩]
በነግህ የምንጸልየው ፦
፩. በዚህ የጸሎት ጊዜም ሌሊቱን በሰላም ስላደረሰን አምላካችን እግዚአብሔርን እናመሰግናለን፡፡ ዕለቱንም ከክፋት እንዲሠውረን ፣ ከፈተና እንዲያወጣን እና በሰላም እንዲያውለን እንጸልያለን፡፡
እግዚአብሔር አምላክ አዳምን የፈጠረው በነግህ በመሆኑ ያንን ታሳቢ በማድረግ እንጸልያለን፡፡
፪. ቅዱሳን መላእክትም ለተልእኮ ሲፋጠኑ የሚገናኙበት ሰዓት በመሆኑ የእነርሱን አማላጅነትና ተራዳኢነት በመታመን እንዲሁም የሌሊቱ ጠባቂ መልአክ ተልእኮውን ጨርሶ በቀን በሚጠብቀን መልአክ የሚተካበት እንደመሆኑ ሁለቱ ጠባቂ መላእክት የሚገናኙበት ሰዓት በማሰብ በዚህም ሰዓት እንጸልያለን፡፡
፫. ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ሰው ልጆች በደል በጲላጦስ ዐደባባይ የቆመበት ሰዓት በመሆኑም እንጸልያለን።
- 💖 ጸሎተ ሠለስት
ይህ የጸሎት ሰዓት በሦስት ሰዓት የሚጸለይ ነው፡፡
በሦስት ሰዓት የምንጸልየው ፦
፩. እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የቅዱስ ገብርኤልን ብሥራት የሰማችበት በመሆኑ
፪. ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ሰው ልጆች ሲል በጲላጦስ አደባባይ የተገረፈበት ሰዓት ስለሆነ
፫. ነቢዩ ዳንኤል ፊቱን ወደ ኢየሩሳሌም አቅጣጫ መልሶና የቤቱን መስኮት ከፍቶ የጸለየበት ሰዓት በመሆኑ
፬. ለአባቶቻችን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስ የወረደበት [በኢየሩሳሌም ጸንተው በመቆየታቸው ከእግዚአብሔር ዘንድ ይህንን ታላቅ ጸጋ የተቀበሉበት] ሰዓት ነው፡፡
- 💖 ቀትር
የቀትር ሰዓት የሚጸለየው በዕለተ እኩሌታ [በስድስት ሰዓት] ላይ ነው፡፡ በዚህ ሰዓትም የምንጸልየው በሚከተሉት ምክንያቶች ነው፡፡
፩. አዳም በጥንተ ጠላት ዲያብሎስ ተታሎ ዕፀ በለስን በመብላቱ ከክብሩ የተዋረደበት ስለሆነ ያን በማስታወስ እንጸልያለን፡፡
፪. አዳም ዕፀ በለስን በልቶ የሞት ፍርድ ስለተፈረደበት ኃጢአተ በደሉን ሊያጠፋለት ሲል ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቀራንዮ ዐደባባይ የተሰቀለበት በመሆኑ
፫. ቀትር የቀን እኩሌታ በመሆኑ የፀሐይ ሙቀት የሚያይልበትና የሰው ልጅ ለድካም የሚዳረግበት በመሆኑ አጋንንት ስለሚበረቱበት በቀትር ሰዓት እንጸልያለን፡፡
- 💖 ተሰዓተ ሰዓት
በዚህ የጸሎት ጊዜ [በዘጠኝ ሰዓት ላይ] ዐራተኛውን ጸሎት እናደርሳለን። ጸሎት የምናደርግበት ምክንያቶችም የሚከተሉት ናቸው፡፡
፩. ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ መከራ ሥቃይን ተቀብሎ ቅዱስ ሥጋውን ከቅድስት ነፍሱ የለየበት ሰዓት ነው።
፪. ቅዱሳን መላእክት የሰው ልጆችን በጎም ሆነ ክፉ ሥራ ወደ ፈጣሪ የሚያሳርጉበት ነው፡፡
፫. በዚህ ጊዜ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን መከራ እና ሞት አያሰብን ቅዱሳን መላእክት ከፈጣሪያቸው እንዲያስታርቁን እየለመንንና እየተማጸንን እንጸልያለን፡፡
- 💖 ጸሎተ ሠርክ
የሠርክ ጸሎት ጊዜ በዐሥራ አንድ ሰዓት የሚጸለይ ጸሎት ነው፡፡ ቅዱስ ዳዊት እንዲህ ይላል፡፡ “ጸሎቴን እንደ ዕጣን በፊትህ ተቀበልልኝ እጅ መንሳቴም እንደ ሠርክ መሥዋዕት ትሁን” [መዝ.፻፵÷፪] ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዓለምን ለማዳን በፈቃዱ ነፍሱን ከሥጋው ከለየ በኋላ ወደ መቃብር የወረደበት ሰዓት ነው፡፡ [ማቴ.፳፯÷፶፯]
- 💖 ጸሎተ ንዋም
ንዋም መኝታ ማለት ነው ፤ ከምሽቱ ሦስት ሰዓት በሆነ ጊዜ ዕለቱን በሰላም አሳልፈን ለሌሊቱ ዕረፍት የምንዘጋጅበት በመሆኑ በሰላም ላዋለን ፈጣሪ በሰላም እንዲያሳድረን ከሌሊት አጋንንትና ከቅዠት እንዲጠብቀን እየተማጸንን እንጸልያለን፡፡
በዚህ ጊዜም የምንጸለየው ፦
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ ዛሙርቱን በጌቴሴማኒ ጸሎት ስላስተማራቸው እርሱ ስለጸሎት ማስተማሩን እያሰብን እንጸልያለን፡፡
- 💖 መንፈቀ ሌሊት [ እኩለ ሌሊት ]
ቅዱስ ዳዊት ‘’መንፈቀ ሌሊት እትነሣእ ከመ እግነይ ለከ በእንተ ኵነኔ ጽድቅከ ፤ ስለ ጽድቅህ ፍርድ በእኩለ ሌሊት አመሰግነህ ዘንድ እነሳለሁ” በማለት ይህ ሰዓት ከእግዚአብሔር ጋራ የሚነጋገርበት እንደሆነ ገልጿል፡፡ [መዝ.፻፲፰፥፷፪]
በመንፈቀ ሌሊት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቤተልሔም ዋሻ የተወለደበት በመሆኑ እንዲሁም ሞትን ድል አድርጎ በታላቅ ኃይልም የተነሣበት ሰዓት በሌሊት ያንን ታሳቢ በማድረግ ነው።
ከዚህ በተጨማሪ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግመኛ ለፍርድ ሚመጣበትም ሰዓት በመሆኑ ለከፈልንን መሥዋዕት እያመሰገንን ምሕረትን ድኅነትን እንድናገኝ ተስፋ በማድረግ በመንፈቀ ሌሊት እንጸልያለን፡፡
እግዚአብሔር አምላክ ቤተ ክርስቲያናችንን ሰላም ያድርግልን፤ አሜን፡፡
[ ይቆየን ]
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፥ ወለወላዲቱ ድንግል ፥ ወለመስቀሉ ክቡር፡፡
† † †
💖 🕊 💖
* እሑድ - ጥር 19 2016 ዓ.ም *
* ዘፍጥረት 33-36 *
ሰላም ለሁላችሁ ይሁን! በዛሬው ንባባችን ከምዕራፍ 33 እስከ 36 ድረስ እናነባለን።
ከንባብ በፊት የሚደረግ ጸሎት፡ “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፤ የአንተን ቃላት እሰማ እና እረዳ ዘንድ፥ እንዲያውም ፈቃድህን ለመፈጸም እበቃ ዘንድ የልቤን ጆሮዎች እና ዓይኖች ክፈትልኝ።” (ቅዱስ ኤፍሬም ሶሪያዊ)
በዛሬው ንባባችን ላይ የያዕቆብ እና የዔሳውን መታረቅ እናነባለን። ከታረቁም በሁዋላ፥ ያዕቆብ በሴኬም ሄዶ ይቀመጣል፤ በዚያም ልጁ ዲናን ያስነውሯታል። ወንድሞቿም በሰሙ ጊዜ በቁጣ አንድ እቅድ በማቀድ ይተገብራሉ። እግዚአብሔርም ያዕቆብ ወደ ቤቴል እንዲሄድ ያዝዘዋል፤ በዚያም ያዕቆብ መስዋእትን ለእግዚአብሔር ይሰዋል፥ እግዚአብሔርም እንደገና ተገልጦ ያዕቆብን ባረከው። ከዚህም በሁዋላ የብንያምን መወለድ፥ የራሔልን መሞት፥ የሮቤልን ጥፋት እና የኤዶማውያን አባት የዔሳውን የዘር ግንድ በዝርዝር እናነባለን።
* የክለሳ ጥያቄዎች * (መልሶቹን ማታ ከ 1፡00 በሁዋላ ጻፉ)
1) ያዕቆብ እና ዔሳው ከረዥም ጊዜ በሁዋላ ሲገናኙ ምን ተፈጠረ?
2) ያዕቆብ እና ዔሳው ከተገናኙ በሁዋላ ስምምነታቸው ምን ነበር?
3) በዘፍጥረት 34 መሠረት፥ ዲና ምን ሆነች? የወንድሞቿስ ምላሽ ምን ነበር?
4) የዲና ወንድሞች ስምዖን እና ሌዊ በዲና ላይ ለተፈጠረው ነገር ምን እርምጃ ወሰዱ?
5) በዘፍጥረት 35 ላይ ያዕቆብ ወደ ቤቴል የሄደው ለምንድር ነው? በዚያስ ምን ይፈጠራል?
6) በዘፍጥረት 35 መሠረት ራሔል ምን ሆነች? ያዕቆብስ ምን አደረገ?
መልካም ንባብ!
†
" የሞቱ ዝንቦች የተቀመመውን የዘይት ሽቱ ያገሙታል" [ መክ.፲፥፩ ]
-------------------------------------------------------
" ድቅድቅ ጨለማ ለዘላለም የተጠበቀላቸው እነዚህ ውኃ የሌለባቸው ምንጮች በዐውሎ ነፋስም የተነዱ ደመናዎች ናቸው። ...
ራሳቸው የጥፋት ባሪያዎች ሆነው። አርነት ትወጣላችሁ እያሉ ተስፋ ይሰጡአቸዋል ፤ ሰው ለተሸነፈበት ለእርሱ ተገዝቶ ባሪያ ነውና።
በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እውቀት ከዓለም ርኵሰት ካመለጡ በኋላ ዳግመኛ በእርስዋ ተጠላልፈው የተሸነፉ ቢሆኑ፥ ከፊተኛው ኑሮአቸው ይልቅ የኋለኛው የባሰ ሆኖባቸዋል።" [ ፪ጴጥ.፪፥፲፯ ]
† † †
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
* ቅዳሜ - ጥር 18 2016 ዓ.ም *
*ዘፍጥረት 29-32*
ሰላም ለሁላችሁ ይሁን! በዛሬው ንባባችን ከምዕራፍ 29 እስከ 32 ድረስ እናነባለን።
ከንባብ በፊት የሚደረግ ጸሎት፡ “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፤ የአንተን ቃላት እሰማ እና እረዳ ዘንድ፥ እንዲያውም ፈቃድህን ለመፈጸም እበቃ ዘንድ የልቤን ጆሮዎች እና ዓይኖች ክፈትልኝ።” (ቅዱስ ኤፍሬም ሶሪያዊ)
በዛሬው ንባባችን ከትላንቱ በመቀጠል ከያዕቆብ ጋር አብረን እንጓዛለን። ያዕቆብ ወደ ምሥራቅ መሄዱን፥ ራሔልንም መተዋወቁን እናነባለን። ያዕቆብ ራሔልን ወድዶ ሊያገባት ከአባቷ ከላባ ጋር ስምምነት ቢያደርገም፥ ላባ ግን ያዕቆብን በማታለል ታላቅ እህቷን ልያን ይድርለታል። በዚህ አይነት ሁኔታ አሥራ አራት ዓመታትን ለላባ ይገዛል። ከዚህ በተጨማሪ፥ በሁለቱ እህቶች መካከል ባለው ፉክክር ለያዕቆብ አሥራ አንድ ልጆች እንደተወለዱም እናነባለን። በያዕቆብ እና በላባ መካከል ያለውም ሁኔታ እየተባባሳ ሄዶ፥ ያዕቆብ ያለውን ነገር ሁሉ ይዞ ከላባ ፊት ኮብልሎ እንደጠፋም ተጽፎ ይገኛል።
* የክለሳ ጥያቄዎች * (መልሶቹን ማታ ከ 1፡00 በሁዋላ ጻፉ)
1) በዘፍጥረት 29 ላይ ያዕቆብ ማንን ተዋወቀ፥ ከአባቷስ ጋር ምን አይነት ስምምነት አደረገ?
2) ከራሔል ጋር የሚኖረውን ጋብቻ በተመለከተ፥ ላባ ያዕቆብን ያታለለው እንዴት ነው?
3) በዘፍጥረት 30 የምናነበው በልያ እና ራሔል መካከል ያለው ፉክክር ከምን የመነጨ ነው? ውጤቱስ ምንድር ነው?
4) ከያዕቆብ ልጆች መካከል ያለችው አንድ ሴት ልጅ ማን ናት? የስሟስ ትርጉም ምንድር ነው?
5) በዘፍጥረት 31 መሠረት፥ ያዕቆብ የላባን ቤት ትቶ የሄደው ለምንድር ነው?
6) ራሔል ከአባቷ ከላባ ቤት ምን ደብቃ ይዛ ወጣች?
7) በዘፍጥረት 32 መሠረት፥ ያዕቆብ ዔሳውን ለማግኘት የተዘጋጀው በምን መንገድ ነው? የፈራውስ ለምንድር ነው?
8) ያዕቆብ በሌሊት ምን ገጠመው? ምንስ በረከት ተቀበለ? ስሙስ ማን ተባለ?
መልካም ንባብ!
🕊
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡
† ጥር ፲፰ [ 18 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †
🕊 † ቅዱስ ጊዮርጊስ ልዳዊ † 🕊
መጽሐፈ ገድሉ እንደሚለው የሰማዕታት አለቃቸው : አንድም ሞገሳቸው ታላቅና ክቡር ሰማዕት ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ፯ ዓመታት
ስቃይ በኋላ ተሰይፏል:: ይህስ ጥንተ ነገሩ እንደምን ነው ቢሉ :-
- ቅዱሱ የተወለደው ከአባቱ ዘረንቶስ [ አንስጣስዮስ ] እና ከእናቱ ቴዎብስታ የድሮው ፋርስ ግዛት ፍልስጥኤም [ ልዳ ] ውስጥ ነው:: የተባረኩ ወላጆቹ ክርስትናን ጠንቅቀው አስተምረውት አባቱ ይሞታል::
- ቅዱስ ጊዮርጊስ ፳ ዓመት ሲሞላው የአባቱን ስልጣን እጅ ለማድረግ ሲሔድ የቢሩት [ የአሁኗ ቤይሩት-ሊባኖስ ] ሰዎች ዘንዶ/ደራጎን ሲያመልኩ አገኛቸው:: እርሱ ግን የከተማውን ሕዝብ አስተምሮ: አሳምኖ: ደራጎኑንም በፈጣሪው ኃይል ገድሎ መንገዱን ቀጥሏል::
- ቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ ዱድያኖስና ፸ ነገሥታት ዘንድ ሲደርስ ክርስቶስ ተክዶ ለጣዖት ይሠገድ ነበር:: በዚያች ሰዓት ድንግል እመቤታችን ወደ ሰማዕቱ መጥታ መከራውንና ክብሩን ነገረችው:: እርሱም በክርስቶስ ስም መሞት ምርጫው ነበርና ከእመቤታችን ተባርኮ ወደ ምስክርነት አደባባይ [ ዐውደ ስምዕ ] ደረሰ::
- ከዚያም ለተከታታይ ፯ ዓመታት ብዙ ጸዋትወ መከራዎችን ተቀበለ:: ፫ ጊዜ ሙቶ ተነሳ:: ከሰው ልጅ የተፈጥሮ ትዕግስት በላይ የሆነ ስቃይን ስለ ቀናች ሃይማኖት ሲል በመቀበሉ የሰማዕታት አለቃቸው: ፀሐይና የንጋት ኮከብ በሚል ይጠራል::
"ተውላጠ ጻማሁ ወሕማሙ:
ዘተለዐለ ሞገሰ ስሙ" እንዲል መጽሐፍ::
- ከ፯ ዓመታት መከራ በኋላም ከብዙ ተዓምራት ጋር ተሰይፎ ደም: ውሃና ወተት ከአንገቱ ፈሷል:: ፯ አክሊላትም ወርደውለታል::
† ዝርወተ ዓጽሙ †
- ይህቺ ዕለት ለሰማዕቱ 'ዝርወተ አጽሙ' ትባላለች:: በቁሙ 'አጥንቱ የተበተነበት' እንደ ማለት ነው:: ቅዱስ ጊዮርጊስን ለዘመናት በብዙ ስቃያት ሲያስጨንቁት ኖረው በጽናቱ አሸነፋቸው:: ፸ ነገሥታትን ከነ ሠራዊታቸው ከማሳፈሩ ባሻገርም በርካታ [ በመቶ ሺ የሚቆጠሩ ] አሕዛብን ማርኮ ለሰማዕትነት አበቃ::
- በዚህ የተበሳጨ ዱድያኖስም ኮከበ ፋርስ ቅዱስ ጊዮርጊስን እንዲቆራርጡት አዘዘ:: ወታደሮቹም ቅዱሱን ቆራርጠው: በብረት ምጣድ ላይ ጠበሱት:: ያለ ርሕራሔም አካሉን አሳረሩት:: ቀጥለውም ፈጭተው አመድ አደረጉት::
- በአካባቢው ወደ ነበረው ትልቅ ተራራ ጫፍ [ ደብረ ይድራስ ] ወጥተውም በነፋስ በተኑት:: "ሐረድዎ ወገመድዎ: ወዘረዉ ሥጋሁ ከመ ዓመድ" እንዲል:: [ ምቅናይ ]
- እነርሱ ይህንን ፈጽመው ዘወር ሲሉ ግን የቅዱሱ ዓጽም ባረፈባቸው ዛፎች: ቅጠሎችና ድንጋዮች ሁሉ "ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕታት" የሚል ጽሑፍ ተገኘ:: ስለዚህም ይህቺ ዕለት ቅዱሱ አለቅነትን የተሾመባት ናት ማለት ነው::
- ወዲያው ግን ኃያል ሰማዕት ቅዱስ ጊዮርጊስ ከተበተነበት ተነስቶ ወታደሮችን አገኛቸውና "በክርስቶስ እመኑ" ብሎ: አስደንቆ ወደ ሕይወት መራቸው:: ፹ው ነገሥታት ግን አፈሩ::
🕊 † ቅዱስ ባኮስ ጃንደረባው † 🕊
- 'ጃንደረባ' የሚለው ቃል በግዕዙ 'ሕጽው' ተብሏል:: ይህ ስም በቤተ ክርስቲያን የተለመደ እንጂ እንግዳ አይደለም:: መድኃኒታችን እንዳለው በተፈጥሮ የሆኑ: ሰዎች እንዲያ ያደረጉዋቸውና ራሳቸውን ስለ ጽድቅ ጃንደረባ ያደረጉ ብዙዎች ናቸውና::
- ኢትዮዽያዊው ጃንደረባ ቅዱስ ባኮስም [ አንዳንዴ አቤላክ / አቤሜሌክም ይባላል] :-
- በ፩ኛው መቶ ክ/ዘመን በሃገራችን ኢትዮዽያ ተወልዶ ያደገ
- ነገሥታቱንና ሃገሩን በሙያው ያገለገለ
- በተለይ ከ፴፬ እስከ ፵፮ ዓ/ም ለነገሠችው ንግሥት ሕንደኬ ገርስሞት በገንዘብ ሚንስትርነት ያገለገለ
- በገንዘቧ ላይ ሁሉ አዛዥ [ ታማኝ ] የነበረ
- ጃንደረባ በመሆኑ ለንግሥቲቱና ቤተሰቧ ቅርብ የነበረ
- መጻሕፍትን የሚያነብና የሚመረምር
- ዘወትር ወደ ኢየሩሳሌም እየሔደ ከቅዱሳት መካናት የሚሳለም በጐ ሰው ነበር::
- በግብረ ሐዋርያት ምዕ.፰፥፳፮ ላይ እንደ ተጠቀሰው ቅዱሱ ከኢየሩሳሌም ለፋሲካና ለእሸት በዓል ነበር የሔደው:: ሲመለስ መንፈስ ቅዱስ ከፊልዾስ ጋር በጋዛ አገናኝቶታል:: በዚያም ምሥጢረ ክርስትናን ተምሮ: በክርስቶስ አምላክነትና አዳኝነት አምኖ ተጠምቁዋል::
- ክርስትናን ለኢትዮዽያ በ፴፬ ዓ/ም አምጥቷል:: "ጃንደረባው ለወገኖቹ ሐዋርያ ሆነ" ሲል ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ እንደ ተናገረው ወደ ሃገራችን ተመልሶ: ስለ ክርስቶስ ሰብኮ በርካቶችን አሳምኗል::
- ቀጥሎም ሃብቱን ንቆ [ መንኖ ] : ከኢትዮዽያ እስከ ሕንድ ወንጌልን ሰብኮ በዚህች ዕለት በሰማዕትነት ዐርፏል:: [ ተሰውሯል የሚሉም አሉ ]
" በእውነት ለቅዱስ ባኮስ ክብር ይገባል:: "
🕊 † ቅዱስ ያዕቆብ ዘንጽቢን † 🕊
+ ይህ ቅዱስ ሰው :--
- እጅግ የተመሠከረለት ሊቅ
- በፍጹም ትሕርምት የኖረ ገዳማዊ
- በርካቶችን ወደ ክርስትና ያመጣ ሐዋርያዊ
- ለአእላፍ ምዕመናን እረኛ የሆነ የንጽቢን [ ሶርያ ] ዻዻስ
- ለጀሮ ድንቅ የሆኑ ተአምራትን የሠራ ገባሬ መንክራት
- ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊን ጨምሮ በርካታ ሊቃውንትን ያፈራ ታላቅ መምሕር
- ለክርስቶስና ለእመቤታችን ታጥቆ የተገዛ የፍቅር ሰው
- እጣቶቹ እንደ ፋና የሚያበሩለት ማኅቶት
- ራሱን ዝቅ አድርጐ በቆሸሸ ልብስ የሚኖር የትህትና ሰው ነው::
- በ፫፻፳፭ [፫፻፲፰] 325 (318) ዓ/ም: በኒቅያ 318ቱ ሊቃውንት ሲሰበሰቡና አርዮስን ሲያወግዙ እርሱ አንዱ ነበር:: በሥፍራውም ሙት አስነስቶ ሕዝቡን አስደምሟል:: በዚያም የቤተ ክርስቲያንን ሥርዓት ሠርቶ ወደ ሃገሩ ተመልሶ በቅድስና ኑሮ በዚህች ቀን ዐርፎ በክብር ተቀብሯል::
🕊 † ደናግል ማርያ ወማርታ † 🕊
- በዘመነ ሐዋርያት በተመሳሳይ 'እንተ ዕፍረት-ባለ ሽቱ' ተብለው የሚጠሩ ፪ እናቶች ነበሩ:: 2ቱም ስማቸው ማርያም ስለ ነበር ለመለየት እንዲያመች አንደኛዋን 'ማርያም ኃጥዕት- ከኃጢአት የተመለሰች': ፪ኛዋን ደግሞ 'ማርያም እኅተ አልዓዛር-በቢታንያ የነበረችው ብለው አበው ይጠሯቸዋል::
- በሉቃስ ወንጌል ላይ የምትገኘው ከኃጢአት ሕይወት የተመለሰችው ስትሆን በዮሐንስ ወንጌል ፲፪፥፩ ላይ ያለችው የአልዓዛር እህት [ ድንግሊቱ ] ናት:: ዛሬም የምናስባት ይህቺውን እናታችን ነው::
- ቅድስት ማርያም መድኃኒታችን ክርስቶስ ወደዚህ ዓለም መጥቶ በሚያስተመርበት ዘመን በቢታንያ አካባቢ ትኖር የነበረች ድንግል ወጣት ናት:: ወላጆች ባልነበረበት ቤት ውስጥ ታላቆቿ አልዓዛርና ማርታ አሳድገዋታል::
- በቤተሰብ ደረጃ እንግዳን ይቀበሉ ነበርና ጌታችን ወደዳቸው:: አልዓዛርን ከ፸፪ቱ አርድእት: ማርያምና ማርታን ደግሞ ከ፴፮ቱ ቅዱሳት አንስት ቆጥሯቸዋል:: ወንድማቸው አልዓዛር በታመመ ጊዜ ወደ ጌታ ልከው ነበር::
- ያለ ጊዜው የማይሠራ ጌታ ባይመጣ አልዓዛር ሞተ:: በ፬ኛው ቀን አምላክ ሲመጣ ቅድስት ማርያም በጌታ ፊት ሰግዳ
"እግዚእየ ሶበሰ ኀሎከ ዝየ እምኢሞተ እሑየ-አንተ በዚህ በኖርክስ ወንድሜ ባልሞተ ነበር" ብላ አለቀሰች:: [ ዮሐ.፲፩ ]
†
[ በ ቅ ር ብ ቀ ን የ ሚ ቀ ር ብ ! ]
በጣት የሚቆጠሩ የዘመኑ [ ሐሳዊ አጥማቂዎች ] እና አጋንንታዊ አሠራራቸውን የሚመለከት ተከታታይ መርሐ-ግብር ! በቅርቡ የሚቀርብ ይሆናል !
† † †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬
†
ፈገግ ያሰኘኝ የዛሬ ገጠመኜ !
በዚህ በቴሌግራም በኦርቶዶክሳውያን በሚቀርቡ መንፈሳዊ መርሐ-ግብሮች መሃል ሰይጣን ያሰማራቸው በመሪጌታ ስም የሚንቀሳቀሱ ጠንቋዮች ከሰይጣን የተማሩትን የክፋትን ስራ እንደ ጥበብና ዕውቀት እያስተዋወቁ ይነግዱበታል።
- ለገበያ
- ለግርማ ሞገስ
- ለመስተፋቅር
- ሰውን ለማፍዘዝ ለማደንገዝ
- ስራ እንድንቀጠር ማድረጊያ
- ደፋር ለመሆን
- ሕልም እንፈታለን 😁 የሚሉ ጠንቋዮችና መተተኞች ቤተክርስቲያንን ሲያቆስሉ ፣ ያልጸኑ የዋሃንን ሲያሰቃዩና ሲያንከራትቱ የቆዩ ነፍሰ ገዳዮች ናቸው።
እናም እኚህን ሰራዊተ አጋንንትን ባገኘንባቸው ግሩፖችና ቻናሎች ላይ Block እና Ban በሚባሉ መቅሰፍቶች እየቀጣን ድራሻቸውን ስናጠፋ ብዙ ጊዜ በውስጥ "ለምን ታጠፉብናላችሁ?" የሚሉ መልዕክቶችን ይልኩ ነበር።
የዛሬው ደፋርና ዓይኑን በጨው የታጠበ ጠንቋይ ግን ለየት ያለ ነበር።
" ለምን ግን አርፈህ አትቀመጥም ? ! "
የሚል መልዕክት ላከልኛ ! 😁 ማስፈራሪያ መሆኑ ነው። በቴሌግራም ጦሩን ሊወረውር 😁
የተዋረደውና የተጣለው ጠላት ሰይጣን ድፍረቱ ይደንቃል !
ይህን የሰይጣንን ሰራተኛ Block አድርጌ ከማሰናበቴ በፊት መልሴ አንድ ነበር።
" አነ ዘክርስቶስ ! "
ለነዚህ የክፋት ሰራተኞች ግን ዘላቂ መፍትሔ ሊሰጥ ይገባል !
† † †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬
†
[ ተዋሕዶ ፍጽምት የቅዱሳን ሃይማኖት ]
▬▬▬▬▬▬ † ▬▬▬▬▬▬
[ የፍቅር ሕግ ወንጌልን ሠራልን ! ]
--------------------------------------------------
" በአባታችን በአዳም በደል የተዘጋ የገነት ደጅን የከፈተልን ፤ ዕፀ ሕይወትን የሚጠብቅ ኪሩብንም ያስወገደው ፤ የእሳት ጦርን ከእጁ ያራቀ ፤ ወደ ዕፀ ሕይወት ያደረሰን እርሱ ነው፡፡ ፍሬውንም [ ሥጋውን ደሙን ] ተቀበልን ።
አባታችን አዳም ሊደርስበት ወደ አልተቻለው ፤ በራሱ ፈቃድ ተከልክሎበት ወደ ነበረው መዐርግ ደረስን ፤ ክፉውንና በጎውን ከሚያስታውቅ ፤ ወደ ጥፋት ከሚወስድ በአዳምና በልጆቹም ላይ ኃጢአት ካመጣበት ከዕፀ በለስ ፊታችንን መለስን ።
የፍቅር ሕግ ወንጌልን ሠራልን፡፡ የላም ሥጋ ፣ የፍየል ደም ሳንሻ ኃጢአታችንን ማስተስረይ ተቻለን፡፡ ያች ቀዋሚት ያልነበረች ሕግ ነበረች፡፡ ድኅነት የማይገኝባት ትእዛዝም ነበረች፡፡ በሚያድን እውነተኛ ምግብ በሚሆን በሥጋው ፤ እውነተኛ መጠጥ በሚሆን በንጹሕ ደሙ ነው እንጂ። [ዕብ.፯፥፲-፳፪ ። ፰፥፩-፲፫ ። ፬፥፲፩-፳፰]
ትእዛዙን ብንፈጽም ፤ በሕጉ ጸንተን ብንኖር እርሱ ቸር የሚሆን ፤ የባሕርይ አባቱ የሚያድን ፤ የባሕርይ እስትንፋሱ መንፈስ ቅዱስም መጥቶ እንዲያድርብን ነገረን፡፡ እርሱ ፦ የሰው እጅ በሠራው ቤት እኔ አላድርም ብሏልና። [ኢሳ.፳፮፥፩] [ ሰውነታችሁ የእግዚአብሔር መንፈስ ማደሪያ ነው ሲል ] "
[ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ]
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፤ ወለወላዲቱ ድንግል ፤ ወለመስቀሉ ክቡር። አሜን።
† † †
💖 🕊 💖
†
[ 🕊 " አበዊነ ቅዱሳን ! 🕊 ]
" አበዊነ ቅዱሳን መክሲሞስ ወዱማቴዎስ "
💖
እኒህ ቅዱሳን የሥጋ ወንድማማቾች ሲሆኑ በቤተ
ክርስቲያን ታሪክ እጅግ ተወዳጅ አባቶች ናቸው::
ስንጠራቸውም " አበዊነ ቅዱሳን : ወክቡራን : ሮማውያን : መስተጋድላን : ወከዋክብት ብሩሃን " ብለን ነው፡፡
በረከታቸው ይደርብን፡፡
† † †
💖 🕊 💖
* ዓርብ - ጥር 17 2016 ዓ.ም *
*ዘፍጥረት 25-28*
ሰላም ለሁላችሁ ይሁን! በዛሬው ንባባችን ከምዕራፍ 25 እስከ 28 ድረስ እናነባለን።
ከንባብ በፊት የሚደረግ ጸሎት፡ “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፤ የአንተን ቃላት እሰማ እና እረዳ ዘንድ፥ እንዲያውም ፈቃድህን ለመፈጸም እበቃ ዘንድ የልቤን ጆሮዎች እና ዓይኖች ክፈትልኝ።” (ቅዱስ ኤፍሬም ሶሪያዊ)
በዛሬው ንባባችን ላይ ከትላንቱ ቀጥለን የአብርሃምን ዘሮች ታሪክ እናነባለን። የአብርሃም ልጅ ይስሐቅ እና ሚስቱ ርብቃ ሁለት ልጆችን ይወልዳሉ፤ ያዕቆብ እና ዔሳው ይባላሉ። በአደን ጎበዝ የነበረው ዔሳው አንድ ቀን ደክሞት ወደ ቤት በገባ ጊዜ ምግብ ለመብላት ሲል ለታናሹ ያዕቆብ ብኩርናውን መስጠቱን፥ ያዕቆብ ደግሞ ዔሳውን መስሎ የታላቅ ወንድሙን በረከት ከአባቱ መውሰዱን እናነባለን። ያዕቆብ ወንድሙ ዔሳው ተናድዶ የሚያደርገውን በመፍራት፥ ወደ አጎቱ ቤት ይሰደዳል። በመንገዱም ላይ፥ በአንድ ቦታ ድንጋይ ተንተርሶ ተኝቶ ሳለ ሕልምን ያልማል፥ እግዚአብሔርም በዚያ ይባርከዋል።
*የክለሳ ጥያቄዎች* (መልሶቹን ማታ ከ 1፡00 በሁዋላ ጻፉ)
1) በዘፍጥረት 25 ላይ ከይስሐቅ እና ከርብቃ የተወለዱት መንታ ልጆች እነማን ናቸው?
2) ሁለቱ መንታዎች በተወለዱ ጊዜ ለየት ባለ ሁኔታ ነበር፤ ይህ ሁኔታ ምንድር ነው?
3) በዘፍጥረት 26 መሠረት ያዕቆብ ወደ ጌራራ የሄደው ለምንድር ነው?
4) ያዕቆብ በጌራራ ሆኖ ከዚህ በፊት አባቱ ያደረገውን አንድ ነገር አድርጓል፤ ይህ ምንድር ነው?
5) በዘፍጥረት 26 ላይ እግዚአብሔር ያዕቆብን በምን መልኩ ባረከው?
6) ያዕቆብ የዔሳውን በረከት ለመውሰድ አባቱን ያታለለው እንዴት ነው?
7) ያዕቆብ እንዳታለለው በተረዳ ጊዜ የዔሳው ምላሽ ምን ነበር?
8) ያዕቆብ ዔሳውን ሸሽቶ ወደ የት ሄደ?
9) ያዕቆብ ድንጋይ ተንተርሶ ተኝቶ የነበረበት ስፍራ ስሙ ምን ነበር? በዚያስ ምን አየ?
10) ያዕቆብ እግዚአብሔር በሕልም ከባረከው በሁዋላ፥ ተነስቶ ምን ለማድረግ ቃል ገባ?
መልካም ንባብ!
🕊
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ †
† ጥር ፲፯ [ 17 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት †
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †
🕊 † አበዊነ መክሲሞስ ወዱማቴዎስ † 🕊
- እኒህ ቅዱሳን የሥጋ ወንድማማቾች ሲሆኑ በቤተ ክርስቲያን ታሪክ እጅግ ተወዳጅ አባቶች ናቸው:: ስንጠራቸውም "አበዊነ ቅዱሳን: ወክቡራን: ሮማውያን: መስተጋድላን: ወከዋክብት ብሩሃን" ብለን ነው::
- ይኸውም "እንደ ንጋት ኮከብ የምታበሩ: ተጋዳይ: ቅዱሳንና ክቡራን የሆናችሁ ሮማውያን አባቶቻችን" ማለት ነው:: ሃገረ ሙላዳቸው ሮም ሁና አባታቸው ንጉሥ ለውንድዮስ ይባላል::
- ይህ ንጉሥ ሮምን በምታክል ታላቅ ሃገር በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን ነግሦ ሳለ መልካም ሰው ሆኖ ተገኝቷል:: ከመልካም ሚስቱ [ንግሥቲቱ] ከወለዳቸው መካከልም ፪ቱ ከዋክብት ይጠቀሳሉ:: ፪ቱ ቅዱሳን በአጭር የጊዜ ልዩነት የተወለዱ በመሆናቸው እንደ መንትያ ይቆጠራሉ::
- ንጉሡ ለውንድዮስም ከእግዚአብሔር ዘንድ ላገኛቸው ልጆቹ ስም ሲያወጣ ታላቁን መክሲሞስ: ታናሹን ደግሞ ዱማቴዎስ ብሎታል:: ቅዱሳኑ በንጉሥ አባታቸው መልካም ፈቃድ ክርስትናን ተምረዋል::
- ምንም እንኳ የንጉሥ ልጆች እና ልዑላን ቢሆኑም ተቀማጥለው አላደጉም:: ምቾት ብዙዎችን አጥፍቷልና:: ይህንን የተረዳ አባታቸው ሞገስን በፈጣሪያቸው ዘንድ እንዲያገኙ እንዲህ በበጐ ጐዳና አሳደጋቸው::
- ቅዱሳን መክሲሞስና ዱማቴዎስ ካደጉና ለአካለ መጠን ከደረሱ በኋላ ቅዱሳት መጻሕፍትን ለማንበብ ይተጉ ነበር:: በተለይ ዜና ቅዱሳንን ከማንበብ አይጠግቡም ነበር:: እግዚአብሔርንም በፍቅር እያመለኩ በጾምና በጸሎት ይገዙለት ነበር::
- ቅዱሳኑንም ለየት የሚያደርጋቸው አንዱ ይሔው ነው:: ወርቅና ብር በፊታቸው ፈሶ: በእግራቸው እየረገጡት: አገሩና ምድሩ እየሰገደላቸው: የላመ የጣመ ምግብ እየቀረበላቸው: የሞቀ የደመቀ መኝታ እየተነጠፈላቸው . . . ሁሉንም ስለ ፍቅረ ክርስቶስ መናቃቸው ይደነቃል::
- እነርሱ በክርስቶስ ፍቅር ሆነው የዚህን ዓለም ጣዕም ንቀዋልና የአባታቸውን ቤተ መንግስት ሊተዉ አሰቡ:: አሳባቸው ደግሞ በመመካከር ሳይሆን በመንፈስ ቅዱስ መሪነት: እንደ አንድ ልብ መካሪ: እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ እንዲሉ አበው በጌታ መሪነት ነው::
- ወደ በርሃ ሔደው ለፈጣሪ ለመገዛት ሲያስቡ መውጫ መንገዳቸውን ይሹ ነበርና አንድ ጐዳና ተገለጠላቸው:: ከዚያም ለንጉሥ አባታቸው ሔደው "አባ! እኛ ወደ ኒቅያ [ ታናሽ እስያ ] ሔደን መባረክ እንፈልጋለን" ሲሉ ጠየቁት::
- ወቅቱ ቦታዋ ስለ ፫፻፲፰ [ 318ቱ ] ቅዱሳን ሊቃውንት ሞገስን ያገኘችበት ጊዜ ነበር:: አባታቸውም መንፈሳዊ ሰው ነበርና ደስ እያለው ፈቀደላቸው:: ብዙ ወርቅን ሰጥቶ: ሸልሞ ከብዙ ሠራዊት ጋር ሸኛቸው::
- ቅዱሳኑ መክሲሞስና ዱማቴዎስም ለጥቂት ጊዜ በኒቅያ ሲጸልዩና ሲባረኩ ሰነበቱ:: ቀጥለውም የአባታቸውን ሰራዊት ሰብስበው "እኛ ሱባኤ ልንይዝ ስለ ሆነ እንመጣለን" የሚል ደብዳቤን ሰጥተው ወደ ሮም ሸኟቸው::
- ወታደሮችን ከሸኙ በኋላ ቅዱሳኑ በአካባቢው ወደ ሚገኝ አንድ ገዳም ሒደው ለአንድ ደግ መናኝ ምሥጢራቸውን ገለጹለት:: ልክ የንጉሡ ለውንድዮስ ልጆች መሆናቸውን ሲያውቅ 'አመንኩሰን' ያሉትን እንቢ አላቸው::
- "ለምን?" ሲሉት "ደጉን አባታችሁን ማሳዘን አልፈልግም:: ግን ፈቃዳችሁ እንዲፈጸምላችሁ ወደ ሶርያ ዝለቁ:: በዚያ አባ አጋብዮስ የሚባል ጻድቅ ገዳማዊ ሰው ታገኛላችሁ" ብሎ ወደ ሶርያ አሰናበታቸው::
- በምድረ ሮም: በተለይም በቤተ መንግስቱ አካባቢ የ፪ቱ ልዑላን መጥፋት [ መሰወር ] ሲሰማ ታላቅ ሐዘንና ለቅሶ ተደረገ:: ንጉሡ አባታቸው በወታደሮቹ ዓለምን ቢያካልልም ሊያገኛቸው አልቻለም:: እርሱ ፈጽሞ ሲያዝን እናታቸው ፈጽማ መጽናናትን እንቢ አለች::
- መክሲሞስና ዱማቴዎስ ግን ምድረ ሶርያ ገብትው የጻድቁ አባ አጋብዮስ ደቀ መዛሙርት ሆኑ:: በእርሱም ዘንድ ለምናኔ የሚያስፈልጉ በጐ ምግባራትንና ትሩፋትን ከተማሩ በኋላ ፪ቱንም አመነኮሳቸው:: በዚያ ቦታም እየታዘዙ: ፈጣሪን እያመለኩ: በጾም: በጸሎትና በትህትና ኖሩ::
- አንድ ቀን ግን አባ አጋብዮስ ጠርቶ " ልጆቼ ! ተባረኩ ! በእናንተ ምክንያት ደስ ብሎኛልና:: በዚህች ሌሊት የመነኮሳት ሁሉ አለቃ ታላቁ ቅዱስ መቃርዮስ በራዕ ተገልጦ: ልጆች እንዲሆኑኝ ስጠኝ ብሎኛልና እኔ ሳርፍ ወደ ግብጽ ገዳመ አስቄጥስ እንድትሔዱ" አላቸው::
- አባ አጋብዮስ ካረፈ በኋላ ግን እንደ ትዕዛዙ አልሔዱም:: ውዳሴ ከንቱን ይፈሩ ነበርና:: በዚያው በምድረ ሶርያ ግን በጥቂት ጊዜ: ገና በወጣትነት ከብቃት መዓርግ ስለ ደረሱ በርካታ ተአምራትን ሠሩ:: በሰው ዘንድም ፍጹም ተወዳጅ ሆኑ::
- ስም አጠራራቸውም ሶርያን መላት:: በዘመኑ በአካባቢው አንድ ግዙፍ ዘንዶ ተነስቶ ሰውንም እንስሶችንም ፈጃቸው:: ሕዝቡም ሒደው በቅዱሳኑ ፊት አለቀሱ:: ያን ጊዜ ቅዱስ መክሲሞስ [ ትልቁ ] ክርታስ አውጥቶ "አንተ ዘንዶ ይህ ክርታስ ወደ አንተ ሲደርስ ከማደሪያህ ውጣ: ሙት: ወፎችም ይብሉህ" ሲል ጻፈበት::
- "ሒዳችሁ በበሩ ጣሉት" አላቸው:: አንድ ደፋር ሰው ተነስቶ ሰዎች ሁሉ እያዩት ወስዶ በዘንዶው መውጫ ላይ ጣለው:: በቅጽበትም ዘንዶው ወጥቶ ሞተ:: አሞሮችም ተሰብስበው በሉት:: ከዚህ ድንቅ ተአምር የተነሳ ሕዝቡ የቅዱሳኑን አምላክ አከበረ::
- ከዚህ በተረፈም በቅዱሳኑ ስም ታላላቅ ተአምራት ተደረጉ:: ርኩሳት መናፍስት ሁሉ ስማቸውን እየሰሙ ይሸሹ ነበርና:: ድውያን እነሱ በሌሉበት ስማቸው ሲጠራላቸው ይፈወሱ ነበር:: የአካባቢው ሰው ስማቸውን እየጠራ: በእነርሱም እየተማጸነ ከመከራው ሁሉ ይድን ነበርና ለሕዝበ ክርስቲያኑ ሞገስ ሆኑ::
- መርከበኞች ደግሞ ከማዕበል ለመዳን የቅዱሳኑን ስም በጀልባዎቻቸው ላይ ይጽፉ ነበር:: አንድ ቀን ግን የንጉሡ ለውንድዮስ ባለሟል ይህንን ጽሑፍ ተመልክቶ ስለ ጠረጠረ መርከበኛውን በንጉሡ ፊት አቀረበው::
ንጉሡም መርከበኛውን "የጻፍከው የማንን ስም ነው?" ቢለው "በሶርያ የሚገኙ ፪ ወንድማማች ቅዱሳን ስም ነው" አለው:: ልጆቹ እንደ ሆኑ ገምቶ በመርከበኛው መሪነት ንግሥቲቱንና ሴት ልጁን ላካቸው:: እነርሱ በሐዘን ተሰብረው ነበርና::
- ወደ ሶርያ ወርደው ባገኟቸው ጊዜም ከናፍቆትና ደስታ የተነሳ ታላቅ ጩኸትን እየጮሁ አለቀሱ:: "እንሒድ ወደ ሮም" ሲሏቸው ግን ቅዱሳኑ "የለም! እኛ የክርስቶስ ነን" ብለው እንቢ ስላሏቸው እያዘኑ ተመለሱ:: ንጉሡ ግን ይህንን ሲሰማ ደስ አለው:: "እነርሱ የዚህን ዓለም ኃላፊነት ተረድተዋል" ሲልም አወደሳቸው::
- በኋላ ግን "የሮሜ ሊቀ ዻዻሳት መሆን አለባችሁ" የሚል ነገር ሲሰማ ቅዱሳን መክሲሞስና ዱማቴዎስ ከሶርያ ወጥተው ወደ ግብጽ ወረዱ:: የከታላቁ ቅዱስ መቃርስ ዘንድ ደርሰውም ልጆቹ እንዲሆኑ ለመኑት::
" ልጆቼ ! በርሃ አይከብዳችሁም ? " ቢላቸው " ግዴለም ! " አሉት:: በዚያም ከተራራው ሥር በዓት ሠርቶላቸው ለ ፫ ዓመታት በአርምሞ ቆዩ:: አንድ ቀንም ቅዱሳኑ እየጸለዩ ከአፋቸው የወጣ የብርሃን ምሰሶ ከመንበረ ጸባኦት ሲደርስ አይቶ ታላቁ መቃርስ አደነቀ::
- በ፭ኛው መቶ ክ/ዘመን መጀመሪያ አካባቢም ጥር ፲፬ ቀን ታላቁ ቅዱስ መክሲሞስ ዐረፈ:: በዕለቱም የሰማይ ቅዱሳን ሁሉ ወርደው እየዘመሩ ወሰዱት:: ከ፫ ቀን በኋላ ደግሞ ቅዱስ ዱማቴዎስ ዐረፈ::
†
[ 🕊 ፍኖተ ቅዱሳን 🕊 ]
[ የቅዱሳን አባቶቻችን የቅድስናና የተጋድሎ ሕይወት ]
🕊
[ የፍትወት ጾር ስለሚያስነሣው ፈተና ]
የፍትወት ክፉ ሃሳብ በተመለከተ አንድ አረጋዊ እንዲህ አለ ፦
" ምግብና መጠጥ በሚሽጥባቸው የገበያ ቦታዎች ፊት እንደሚያልፍና ምግቡ ሲጠበስና ሲዘጋጅ ሽታው ወደ እርሱ እንደሚመጣና እንደሚሽተው ሰው ሁን።
ሽታው ደስ ካሰኘውና ውስጡ ከተቀበለው ለመብላት ወደ ውስጥ ይገባል ፤ ካልሆነ ግን ሲያልፍ ብቻ ይሸተዋል ፣ እርሱ ግን መንገዱን ይቀጥላል ፣ አልፎትም ይሄዳል ለአንተም እንዲሁ ነው ፤ መጥፎውን ሽታ አትደሰትበት ፣ ወደ ውስጥህም አትቀበለው::
ተነሥና " የእግዚአብሔር ልጅ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ፣ ዕርዳኝ" ብለህ ጸልይ : ለሌሎች ፈተናዎችም እንዲሁ አድርግ፡፡ የሰውነት ስሜቶቻችንን ነቅለን ልናጠፋቸው ሳይሆን ልንቋቋማቸውና ልንቆጣጠራቸው ይገባልና።"
---------------------------------------------
አንድ ወንድም በፍትወት ጾር ተጠቃ ፣ ጦርነቱም በልቡ ውስጥ ቀንና ሌሊት እንደሚያቃጥል እሳት ነበር። ያም ወንድም ይህ ጾር ለሚያሳስበው የተዋረደ ሃሳብ በውስጡ ላለመስማማት ታገለ።
ከረጅም ጊዜ በኋላ ከጽናቱ የተነሣ ምንም ማድረግ ስላልቻለ ጦርነቱ ጠፋለት ፣ ወዲያውኑም ወደ ልቡ ውስጥ ብርሃን መጣ።
🕊
የአባቶቻችን ጸሎትና በረከት ይደርብን፡፡
† † †
💖 🕊 💖
📚ሦስት ስገድ
አንድ ሰው በጣም ይጸጸት እና ንስሐ ገብቶ ተገቢውን ቀኖና /ቅጣት/ ተቀብሎ ፈጣሪውን እያስደሰተ ለመኖር ወስኖ ወደ አንድ ካህን ይመጣል።
ካህኑም ተገቢውን የአባትነት አቀባበል አድርገውለት ሲያበቁ የመጣበትን ጉዳይ ማስረዳት ቀጠለ።
ከዚያም ልቦናውን ታዛቢ ፣ አንደበቱን ከሳሽ ፣ እግዚአብሔርን ዳኛ አድርጎ የሠራውን ልዩ ልዩ ዘግናኝና ከባድ ኃጢአት አንድ በአንድ በዝርዝር ተናገረ።
እኚያ አባት ሁሉን በትእግስት ካዳመጡ በኋላ ተገቢውን ምክርና ተግሳጽ ሰጥተው ሲጨርሱ "በል ሦስት ስገድ" ይሉታል።
ሰውዬውም "በየቀኑ ሦስት ሦስት ማለትዎ ነው አባቴ?" ይላቸዋል።
ካህኑም "የለም የለም ሦስት ብቻ ስገድ!" አሉት።
በዚህ ጊዜ ሰውዬው በጣም ተገርሞ "እንዴ አባቴ ሦስት ነው ወይስ ሦስት መቶ ነው?" ሲል አስረግጦ ይጠይቃቸዋል።
ካህኑም "ኧረ ሦስት ነው ያልኩህ ልጄ የምን ሦስት መቶ አመጣህብኝ? እንዴ ያላልኩትን? ብቻ ስትሰግድ በደልህን እያሰብክ የፈጣሪህን ምህረት እና ይቅርታ ከልብህ እየተማጸንክ በልብህ ጉልበት ጭምር ስገድ" ይሉታል። ሰውዬውም በጣም እየተገረመ እና እየተደነቀ የካህን ትዕዛዝ ነው እና አመስግኖ ተነስቶ ይሔዳል።
ከዚያም እግዚአብሔር ይገለጥለት እና የንስሐ አባት የሆኑትን አገልጋዩን "እንዴት ነው ያን ሁሉ ኃጢአት ነግሮህ ሲያበቃ ሦስት ብቻ ስገድ የምትለው?" ሲል ይጠይቃቸዋል።
እኚያ አባትም ፈገግ እያሉ "አይ ፈጣሪዬ...... ይሄንንም እኔ ሆኜ ነው እንጂ አንተ ብትሆን እኮ በነጻ ነበር የምታሰናብተው።" አሉት ይባላል።
ይኼ የእግዚአብሔርን ይቅር ባይነት በሚገባ የሚያስረዳ ምናባዊ ታሪክ ነው።
እንዲህ ሲባል ንስሐ አያስፈልግም ማለት ሳይሆን ያለ እግዚአብሔር ቸርነት ሦስትም ይሁን ሦስት መቶ ብንሰግድ ጥቅም እደሌለን እድናውቅ ነው።
ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ የእግዚአብሔርን መሐሪነት እዲህ ይገልጠዋል።
"የራበው ሰው ለምግብ ፤ የጠማው ሰው ለመጠጥ እደሚቸኩል እግዚአብሔርም እኛን ለመማር /ምሕረት ለመስጠት/ ይቸኩላል።"
እንደ ኃጢአታችን ክፋት አይቶ ምሕረቱን ከኛ ያላራቀ የቅዱሳን አምላክ ልዑል እግዚአብሔር ክብር ምስጋና ይግባው።
"ያልጠፋነው ከእግዚአብሔር ምሕረት የተነሳ ነው ፤ ርኀራኄው አያልቅምና።" ትንቢተ ኤር 3፥23
ውብ አሁን
- ወደ ቤቱ ተመልሶም የወላጆቹን ላም "እውነትን ተናገር" ብሎ ገስጾታል:: ላሙም ሰይጣን እንዳደረበት በሰው ልሳን ተናግሮ: የቅዱሱን ወላጆች ወግቶ ገድሏቸዋል:: ቅዱስ ፊላታዎስ ግን ላሙን አስገድሎ: ወላጆቹን ከሞት አስነስቶ ከአካባ
ቢው ሰው ጋር በስመ ሥላሴ አስጠምቁዋቸዋል::
- በድንግልና ኑሮም ዘመነ ሰማዕታት ሲጀምር በርጉም ዲዮቅልጥያኖስ እጅ ብዙ ተሰቃይቷል:: በጸሎቱም ጣዖታቱን [እነ አዽሎንን] ከነ አገልጋዮቻቸው ወደ ጥልቁ አስጥሟቸዋል:: እርሱም በዚህች ቀን በሰይፍ ተከልሎ ለክብር በቅቷል:: ለእኛ ለኃጥአን የሚሆን ቃል ኪዳንንም ከጌታው ተቀብሏል::
የቅዱሳን አባቶቻችን አማናዊት ርስት ድንግል ማርያም አትለየን::
🕊
[ † ጥር ፲፮ [ 16 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ቅዱስ ፊላታዎስ ሰማዕት
፪. አባ ዸላድዮስ ገዳማዊ
፫. ማር ዳንኤል ሶርያዊ
፬. አባ ዮሐንስ መሐሪ [ሊቀ ዻዻሳት]
፭. 11,004 ሰማዕታት [ የቅ/ቂርቆስ ማሕበር ]
፮. 11,503 [ የቅ/ፊላታዎስ ማሕበር ]
፯. አባ ጽሕማ [ ከተስዓቱ ቅዱሳን አንዱ ]
[ † ወርሐዊ በዓላት ]
፩. በዓለ ኪዳና ለድንግል
፪. ቅዱስ አኖሬዎስ ንጉሥ
፫. ቅዱስ ገብረ ማርያም [ንጉሠ ኢትዮዽያ]
፬. ቅድስት ኤልሳቤጥ
፭. አባ ዳንኤል
፮. አባ አቡናፍር ገዳማዊ
፯. አባ ዮሐንስ ወንጌሉ ዘወርቅ
" ጻድቅ እንደ ዘንባባ ያፈራል:: እንደ ሊባኖስ ዝግባም ያድጋል:: በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ ተተክለዋል:: በአምላካችንም አደባባይ ውስጥ ይበቅላሉ:: ያን ጊዜ በለመለመ ሽምግልና ያፈራሉ:: ደስተኞችም ሆነው ይኖራሉ::" [ መዝ.፺፩፥፲፪ ]
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖 🕊 💖
†
[ ራ ስ ! ]
" እነሆ ፥ እኔ እንደ በጎች በተኵላዎች መካከል እልካችኋለሁ ፤ ስለዚህ እንደ እባብ ልባሞች እንደ ርግብም የዋሆች ሁኑ።" [ ማቴ.፲፥፲፮ ]
† † †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬
†
† 🕊 ክብርት ሰንበት 🕊 †
💖
❝ ሰንበት ተዓቢ እምኵሉ ዕለት ፤ ወሰብእ ይከብር እምኵሉ ፍጥረት ፤ አዕበያ ኖኅ በውስተ ታቦት አብርሃም አክበራ በውስተ ምሥዋዕ ፤ አዘዞሙ ሙሴ ለትዕይንት ያክብሩ ሰንበተ በጽድቅ። ❞
❝ ስብሐተ ወአኰቴተ ናዓርግ ለከ እምኲሉ ዕለት ሰንበተ አክበርከ ስብሐተ ወአኰቴተ ናዓርግ ለከ እምኩሉ ፍጥረት ሰብአ ዘአዕበይከ። ❞
ትርጉም ፦
[ ሰንበት ከሁሉም ቀኖች ትበልጣለች ፣ ሰውም ከሁሉም ፍጥረታት ይከብራል። [ ሰንበትን ] ኖኅ በመርከብ ውስጥ አከበራት ፤ አብርሃምም በምስዋኡ ላይ አከበራት። ሙሴም ለተሰበሰቡት ሕዝብ ሰንበትን በእውነት [ በጽድቅ ] እንዲያከብሩ አዘዛቸው። ]
[ ክብርና ምስጋና እናቀርብልሃለን ፣ ከሁሉም ዕለታት ሰንበትን ያከብርህ ፣ ክብርና ምስጋና እናቀርብልሃለን ፣ ከሁሉም ፍጥረታት ሰውን ከፍ ከፍ ያደርግህ። ]
🕊
[ ድጓ ዘክረምት ]
† † †
💖 🕊 💖
🕊
[ † እንኳን ለጻድቅ አቡነ ያፍቅረነ እግዚእ ዘጉጉቤን ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ]
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †
🕊 † አቡነ ያፍቅረነ እግዚእ ዘጉጉቤን † 🕊
† በኢትዮዽያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ መካከለኛው ዘመን [ በተለይ ከ፲፫ኛው [13ኛው] እስከ ፲፭ኛው [15ኛው] መቶ ክ/ዘመን ድረስ ያለው] የብርሃን ዘመን ይባላል:: ምክንያቱም ዘመኑ
- ክርስትና ያበበበት::
- መጻሕፍት የተደረሱበት::
- ስብከተ ወንጌል የተስፋፋበት::
- ገዳማዊ ሕይወት የሠመረበት ወቅት በመሆኑ ነው::
ለዚህ ትልቁ አስተዋጽኦ ደግሞ :-
¤ አቡነ ተክለ ሃይማኖት::
¤ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ::
¤ አባ ሰላማ ካልዕ::
¤ አቡነ ያዕቆብ::
¤ ቅዱሱ ንጉሥ ዘርዓ ያዕቆብ::
¤ አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ::
¤ አቡነ መድኃኒነ እግዚእን የመሰሉ አበው መነሳታቸው ነው::
በተጨማሪም :-
¤ ፲፪ቱ [ 12ቱ ] ንቡራነ ዕድ::
¤ ፯ቱ [ 7ቱ ] ከዋክብት::
¤ ፵፯ [ 47ቱ ] ከዋክብት::
¤ ፭ቱ [ 5ቱ ] ከዋክብት የሚባሉ አበው አስተዋጽኦም ልዩ ነበር:: ከእነዚህ መካከልም የ፯ቱ [7ቱ] እና የ፵፯ቱ [47ቱ] ከዋክብት አስተማሪ: የአበው ፫ቱ [3ቱ] ሳሙኤሎች [ዘዋልድባ: ዘጣሬጣና ዘቆየጻ] : የሌሎችም እልፍ አእላፍ ቅዱሳን አባት የሆኑት አባ መድኃኒነ እግዚእ የአንበሳውን ድርሻ ይወስዳሉ::
ጻድቁ ቅዱሳኑን ሰብስበው: አስተምረው: አመንኩሰው: መርቀው ሰደው: ሃገራችንን እንዲያበሩ በማድረጋቸው እንደ አባ ኢየሱስ ሞዐ እርሳቸውም "ወላዴ አእላፍ ቅዱሳን" ይባላሉ::
ከእነዚህ ቅዱሳን የጻድቁ ፍሬዎች አንዱ አቡነ ያፍቅረነ እግዚእ ናቸው:: ጻድቁ አንዳንዴ "አፍቀረነ እግዚእ" እየተባሉም ይጠራሉ:: ትርጉሙም "ጌታ ወደደን" እንደ ማለት ነው::
ያፍቅረነ እግዚእ የነበሩት በ፲፬ኛው [14ኛው] መቶ ክ/ዘ ሲሆን ቁጥራቸው ከ፯ቱ [7ቱ] ከዋክብት ነው:: ጻድቁ ከልጅነት ጀምሮ በሥርዓቱ ከማደጋቸው ባሻገር እጅግ የተማሩ እንደነበሩም ይነገርላቸዋል::
ለምናኔ ከወጡ በሁዋላ ከኖሩባቸው ቦታዎችም ፫ቱ [3ቱ] ተጠቃሽ ናቸው:: የመጀመሪያውና ትልቁን ሥፍራ የሚይዘው ደግሞ ደብረ በንኮል ነው:: ጻድቁ በዚህ ገዳም ከታላቁ ቅዱስ አባ መድኃኒነ እግዚእ ሥርዓተ ገዳምን : ትኅርምተ አበውን : ተጋድሎተ ቅዱሳንን አጥንተው ለመዓርገ ምንኩስና በቅተዋል::
በገዳሙም ለተወሰነ ጊዜ አገልግለው ወደ ጣና አካባቢ ከአቡነ ያሳይና ከአባ ሳሙኤል ዘዋሊ ጋር መጥተዋል:: የመምጣታቸው ምክንያትም ስብከተ ወንጌልን ለማዳረስና ገዳማትን ለመመሥረት ነው::
ሶስቱ ቅዱሳን ለተወሰነ ጊዜ ከቆዩ በሁዋላ አቡነ ሳሙኤል ወደ ዋልድባ ሲሔዱ አቡነ ያሳይ ደግሞ ማንዳባን አቀኑ:: ያፍቅረነ እግዚእም ጌታ ባዘዛቸው መሠረት ጣና ውስጥ ገዳም አቅንተው ኑረዋል:: ይህ ገዳማቸው ዛሬም ድረስ በስማቸው ይጠራል::
ጻድቁ አፍቀረነ እግዚእ ፫ኛው [3ኛው] የሚታወቁበት ገዳም ማኅበረ ዴጌ [ጻድቃነ ዴጌ] ሲሆን ገዳሙ በአክሱም ዙሪያ ይገኛል:: እርሳቸው ፫ሺ [3ሺ] ቅዱሳን የተሠወሩበትን ገዳም በማገልገላቸውም ዛሬም ድረስ በአካባቢው የታወቁ ሆነዋል::
በተረፈም አክሱም አካባቢ ሌሎች ገዳማትን እንዳቀኑም ይነገርላቸዋል:: ጻድቁ አቡነ ያፍቅረነ እግዚእ ለብዙ ዘመናት በተጋድሎ : በስብከተ ወንጌልና ገዳማትን በማስፋፋት ከኖሩ በሁዋላ በዚህች ቀን ዐርፈው ለክብሩ : ለርስቱ በቅተዋል::
† አምላከ ቅዱሳን በጻድቁ አማላጅነት ይቅር ብሎ በረከታቸውን ያሳድርብን::
🕊
[ † ጥር ፲፱ [ 19 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ጻድቁ አቡነ ያፍቅረነ እግዚእ [አፍቀረነ እግዚእ ዘጉጉቤ - ጣና ውስጥ - ከሰባቱ ከዋክብት አንዱ]
፪. አባ ባሱራ
፫. ቅድስት ኔራ
፬. ቅድስት በርስጢና
፭. አባ ዝሑራ
[ † ወርሐዊ በዓላት ]
፩. ቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላዕክት
፪. ቅዱስ ኤስድሮስ ሰማዕት
፫. አባ ዓቢየ እግዚእ ጻድቅ [ታቦታቸው ጎንደር ከተማ ቀበሌ 09 አካባቢ ይገኛል]
፬. አቡነ ስነ ኢየሱስ
፭. አቡነ ዮሴፍ ብርሃነ ዓለም
† ቅዱሳንን ታስቡ ዘንድ ቸል አትበሉ::
† " እግዚአብሔር ፍርድን ይወድዳልና:: ቅዱሳኑንም አይጥላቸውምና:: ለዘለዓለምም ይጠብቃቸዋል . . . ጻድቃን ምድርን ይወርሳሉ:: በእርስዋም ለዘላለም ይኖራሉ:: የጻድቅ አፍ ጥበብን ያስተምራል:: አንደበቱም ፍርድን ይናገራል:: የአምላኩ ሕግ በልቡ ውስጥ ነው:: በእርምጃውም አይሰናከልም::" †
[መዝ.፴፮፥፳፰-፴፩]
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖 🕊 💖
†
[ 🕊 ሰማያዊቷን ቤተክርሰቲያን 🕊 ]
💖
❝ ቤተክርስቲያንን በሁለት መንገድ ማወቅህን አረጋግጥ። እንደ አሕዛብ ጠላቷ እንዳትሆን በትምህርት ዕወቃት ፤ እንደ ፈሪሳውያን እንዳትሆን በኑሮ ዕወቃት። ለሥርዓቷ ታማኝ ሁን ፥ አንተ ወደ ሥርዓቷ እደግ እንጅ ሥርዓቷ ወደ አንተ ፈቃድ እንዲወርድልህ አትውደድ ፤ ሰማያዊቷን ቤተክርሰቲያን ምድራዊት እንድትሆንልህ አትፍቀድ።
በቤተክርስቲያን መንፈሳዊ አንድነቶች ካልተሳተፍክ ከቤተክርስቲያን አንድነት እየተለየህ እንደሆነ እወቅ። እሊህም ፦ ኪዳን ማስደረስ ፥ ማስቀደስና ንስሐ ገብቶ [ በምክረ ካህን እየኖሩ ] መቁረብ ፥ በምህላ ጸሎቶቿ በአዋጅ አጽዋማቷ መተባበር ናቸው።
ከቤት ከሚጸለይ አሥር ጸሎት ይልቅ በቤተክርስታያን የሚደረግ አንድ ጸሎት እንደሚበልጥ አውቀህ በየቀኑ ወደ እርስዋ ገሥግሥ።
በሕይወትህ ሁሉ ቤተክርስቲያናዊ ሁን ! ❞
🕊
[ ርእሰ ሊቃውንት የኔታ አባ ገብረ ኪዳን ]
† † †
💖 🕊 💖
- ጌታም ስታለቅስ ባያት ጊዜ አምላክነቱ አራርቶት አለቀሰ:: ወዲያውም በስልጣነ ቃሉ አዞ አልዓዛርን አስነሳው:: ከፋሲካ [ ጌታ ከመሰቀሉ ፮ ቀናት ] በፊትም ቅዱሳኑ ለጌታ ግብር አገቡ:: እርሱም ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ታደመላቸው:: [ዮሐ.፲፪፥፩ ]
- በዚያም አልዓዛር ከጌታ ጐን ሲቀመጥ: ቅድስት ማርያም ከጌታ ሥር ተንበርክካ: ናርዶስ የሚሉትን የ፫ መቶ ዲናር ሽቱ በጌታ ላይ አፈሰሰች:: መዓዛ መለኮቱና ሽቱው ሲገናኝ "መልዐ መዓዛሁ" እንዲል ምስጥ የሚያደርግ ሽታ ቤቱን ሞላው::
- በወቅቱ ይሁዳ ቢቃወምም ጌታ ምላሹን ሰጥቶታል:: ቅድስት ማርያምንም "ማርያምሰ ኃርየት መክፈልተ ሠናየ ዘኢየኃይድዋ" ብሎ አመስግኗታል:: ያስመሰገናት ቁጭ ብላ በተመስጦ መማሯ ብቻ እንዳልሆነ አባ ሕርያቆስ መስከሯል::
- ሲመክረንም "አርምሞንና ትዕግስትን እንደ ማርያም ገንዘብ እናድርግ" ብሎናል:: [ ቅዳሴ ማርያም] ቅድስት ማርያም በጌታችን ክርስቶስ በኅማሙ ጊዜ: ሲቀብሩት ነበረች:: ትንሳኤውንም ዐይታለች::
- ከጌታ እርገት በኋላም መንፈስ ቅዱስን ተከትላ ለወንጌል አገልግሎት ተግታለች:: ቅድስት እናታችን ማርያም እንተ ዕፍረት ዛሬ በዓሏ ከእህቷ ቅድስት ማርታ ጋር ይከበራል::
❖ ከበረከታቸው ይክፈለን፡፡
🕊
[ † ጥር ፲፰ [ 18 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ቅዱስ ጊዮርጊስ መክብበ ሰማዕታት (ዝርወተ ዓጽሙ ]
፪.ቅዱሳት ደናግል ማርያ እና ማርታ [ ከ፴፮ቱ ቅዱሳት አንስት ]
፫. ቅዱስ ያዕቆብ ዘንፅቢን [ከ፫፻፲፰ቱ]
፬.ቅዱስ ባኮስ ኢትዮዽያዊ [ አቤላክ / አቤሜሌክ ]
[ † ወርኀዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ቅዱስ ፊልዾስ ሐዋርያ
፪. አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ሰባኬ ሃይማኖት [ ረባን ]
፫. አቡነ አኖሬዎስ ዘደብረ ጽጋጋ
፬. ማር ያዕቆብ ግብፃዊ
፭. ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ [ ከ፸፪ቱ አርድእት
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖 🕊 💖
🕊
እንኳን ለሰማዕቱ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ዓመታዊ በዓል [ ለዝርወተ ዓጽሙ ] በሰላም አደረሳችሁ።
💖
ሥለ ርትዕት ሃይማኖት ነብስህን የለወጥካት
የተዋህዶ መልካም ሽታ
ሰማዕቱ ጊዮርጊስ ይድረስህ ሰላምታ፡፡
† † †
" የልዳው ጊዮርጊስ ሆይ ፦ ለአንተ ሰላምታ ይገባሃል፡፡ የተወደደው የልጅዋ የኢየሱስ ክርስቶስና የድንግል ማርያም ዕውነተኛ ምስክር ሆይ ፦ ሰላምታ ይገባሃል፡፡ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ምስክርነት ልዩ ልዩ ሥቃዮችን የታገሥህ ጊዮርጊስ ሆይ ፦ ሰላምታ ይገባሃል፡፡
ሥጋህ ለአራት ለስድስት ክፍል የተከፋፈለው ጊዮርጊስ ሆይ ፦ ናርዶስ ከሚባል የሽቱ አበባ ይልቅ መዓዛህ ይጥመኛልና ሰላምታ ይገባሃል፡፡ "
[ መልክአ ጊዮርጊስ ]
የሰማዕቱን ፍቅር በልቦናችን ያሳድርብን፡፡ በምልጃውና በቃል ኪዳኑ ይማረን፡፡
† † †
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
💖 🕊 💖
†
[ 🕊 ፍኖተ ቅዱሳን 🕊 ]
[ የቅዱሳን አባቶቻችን የቅድስናና የተጋድሎ ሕይወት ]
† † †
[ የፍትወት ጾር ስለሚያስነሣው ፈተና ]
🕊
የሁለቱም ሰዎች ንስሐ እኩል ነው !
በፍትወት ጾር የተጠቁ ሁለት ወንድሞች ወደ ዓለም ተመልሰው ሚስት አገቡ። ኋላ ላይ እርስ በርሳቸው ፦ "የመላእክትን ሕይወት ትተን በዚህ ርኵሰት በመኖራችን ያገኘነው ነገር ምንድን ነው? ምንስ የተጠቀምነው ነገር አለ? በመጨረሻ ላይ እሳትና ቅጣት ይጠብቀናል፡፡ ስለዚህ ወደ በረሃው እንመለስና ንስሐ እንግባ" ተባባሉ።
ከዚያም ወደ ገዳማቸው ተመለሱና ያደረጉትን ተናዘው አባቶች ቀኖና እንዲሰጧቸው ጠየቁ፡፡ አረጋውያንም ለአንድ ዓመት ያህል ለብቻቸው ተወስነው ንስሐቸውን እንዲፈጽሙ ቀኖና ሰጧቸው፡፡ ለእያንዳንዳቸውም እኩል መጠን ያለው ዳቦና ውኋ ይሰጣቸው ነበር፡፡ መጀመሪያ ላይ ከዓለም ተመልሰው ሲመጡና ገና ቀኖናቸውን ሳይጀምሩ ሳሉ ሰውነታቸው በተመሳሳይ ሁኔታ ላይ ነበር፡፡
የቀኖና ጊዜያቸውን ጨርሰው ሲወጡ አባቶች አንደኛውን ሰውነቱ ገርጥቶና ድቅቅ ብሎ አዩት ፤ ሌላኛውን ደግሞ ሰውነቱ ደኅና ሆኖ ገጹም ብሩህ ሆኖ አዩት፡፡ ይሰጣቸው የነበረው ምግብ አንድ ዓይነት የነበረ በመሆኑ ባዩት ነገር ተደነቁ፡፡
ሰውነቱ ድቅቅ ያለውን ፦ "በበአትህ በቀኖና ሳለህ እንዴት አሳለፍክ? ምንስ ታስብ ነበር?" ብለው ጠየቁት። እርሱም ፦ "ያደረግሁትን ኃጢአትና ያገኘኝ የነበረውን ፍርድ አስብ ነበር ፣ ይህን ማሰቤ ሥጋዬን ከአጥንቶቼ ጋር እንዲጣበቅ አደረገው" አላቸው፡፡
ሌላውንም ያንኑ ጥያቄ ጠየቁት። እርሱም ፦ "ከዓለም ርኲሰትና ይጠብቀኝ ከነበረው ፍርድ ውስጥ ስላወጣኝና በኢየሱስ ክርስቶስ ወደዚህ ዓይነት የንስሐ ሕይወት ስለመራኝ እግዚአብሔርን አመሰግነው ነበር ፤ እግዚአብሔርን በማዘከርም ውስጤን እጅግ ደስ ይለው ነበር" አላቸው:: አረጋውያንም ፦ "በእግዚአብሔር ዘንድ የሁለቱም ሰዎች ንስሐ እኩል ነው" አሉ።
🕊
የአባቶቻችን ጸሎትና በረከት ይደርብን፡፡
† † †
💖 🕊 💖
† † †
[ በ ቅ ር ቡ ! ]
በሐሰተኛ መንፈስና አሠራር ቅድስት ቤተክርስቲያንን እየፈተኑና ምዕመናንን እያጎሳቆሉ ስለሚገኙ ሐሰተኛ አጥማቂያን !
በቅርቡ !
" ቶሎ ባለማስቆማችን ምክንያት ..... ! "
† † †
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
ማኅበረ ቅዱሳንና🤝የጃንደረባው ትውልድ
ትዝብታዊ ምስክርነታችንን እንቀጥላለን
ሩቅ አሳቢውን አዲሱን ትውልድ ለመደገፍ ያህል ከልብ ያረፉ ጥቂት ምክንያዊ ሙግቶችን ላሰፍር ወደድኩኝ። ጃንደረባው ትውልድ የተሰኝው ገና ጥቂት የውልደት ዓመት ያስቆጠረውን አንድነት ቅን ሂስ ሰጪዎች ጥቂት ስጋቶች የሚያነሱበት ዳግማኛ ቅንነት ሳይሆን የገነን ጉዳይ የሚያውካቸው ደግሞ የማያዘልቅ ዘለፋ ሲያቀርቡበት የተቀሩት ገሚሶቹ ደግሞ የብርሃን ብልጭታ ተመለከትንበት እያሉ የሚጽናኑበት ሆኗል። በጃንደረባው ትውልድ ላይ የሚነሱ ሂሶች መካከል ውስጥ ከልቤ ይገቡ ዘንድ ያልተቻላቸውን ጥቂት ነጥቦችን ላናግራቸው።
👉ማኅበረ ቅዱሳንን ለማፍረስ ነው.....
ማኅበረ ቅዱሳን ባሳለፍናቸው የቤተክርስቲያን ጉዞዎች ውስጥ በችግር ወቅት መደገፍያችን በሰላም ጊዜ መማማርያችን የእውቀታችን ገበታ አሰናጅ ሆኖ ያገለገለን ዘመን የማይሽራቸው የወንጌል ሠራተኞችን ያፈራ የገነነ የገነገነ መንፈሳዊ ተቋም ነው። በተለይ የተዘነጋቸውን የገጠሪቷን ቤተክርስቲያን የመንፈሳዊ ፍሬ አድባር የሆነውን የአብነት ትምህርት ቤት በማስታወስ ቀላል የማይባል ሥራ ሠርተዋል በህትመቱም ደረጃ ቀላል የማይባል አሻራን አሳርፏል። ጃንደረባው ትውልድን አውላላ ሜዳ ላይ በሲቃ አጥበው ለማስጣት የዳዱ ግለሰቦች ይህንንም ማኅበር በማይሽር ስድብ ከፍ ዝቅ ሲያደርጉት ታዘበን ነበር። ውጫዊም ውስጣዊም ፈተናዎች ሲያበረከርኩት ዳግመኛ ደግሞ ነፍስ ዘርቶ ሲቆም እያየን ከዚህ ትውልድ ደርሷል።
ከውስጥ ቀኝ ገዢ ሲባል ከውጭ ማኅበረ ሰይጣን ሲባል በመንፈሳዊ አክቲቪስቶች ደግሞ የመንግስት ሙሽራ አድርገው ሲሰንዱት ታዝበን አልፈናል። በጥቅሉ ሲፈራ ሲወደስ ሲሰደብ የነበረውን ይህን ትልቅ ማኅበር የሚያፈርሱ እኩይ ሐሳቦች የቤተክርስቲያኒቱ ጠበኛ ነው። ነገሩ ግን ወዲህ ነው ይህ ተቋማዊ ጠብ ሲበረታ ለእኩይ ሐሳብ ይመቻል በሚል ግላዊ ምልከታዎች ለማኅበሩ አስበው ሳይሆን ጭር ሲል ያልበኛል አልያም አንደበቴ ከጾም በምን ይግደፍ የሚሉ ኢመደበኛ አማኞች የተነሳ የማጋጫ መንገድ ነው። እውነቱ ግን ማኅበረ ቅዱሳን ህጋዊ ሰውነት ያገኝ ተቋም እስከመሆኑ ድረስ በጋጋታ ወይም ደግሞ በአዳዲስ ማኅበራት ማበብ ሊደበዝዝ የሚችል አይደለም።
እነኚህ ሁለት አደረጃጀቶች የራሳቸው ተልእኮና ራእዬ አላቸው ሁለቱም በተልእኳቸውና በራእያቸው መሠረት ለቤተክርስቲያን ይበጃል የሚሉትን ይሠራሉ የጋራ በሚሉት ጉዳይ ደግሞ በጋራ ተዓምር ያበጃሉ። ይነስም ይብዛም በየዘርፉ የተቋቋሙ ማኅበራት አሉ ጥንቃቄን መንፈሳዊ ክትትል ከተደረገባቸው ለቤተክርስቲያን የማይጠቅም አንድነት የለም። እንኳን ሁለት ማኅበራት ቀርቶ ከ500 ያላነሱ ስንበት ትምህርት ቤቶች እንኳን ተደራሽ መሆን ያልቻሉባችው ብዙ መንፈሳዊ ክንውኖች አሉ። ከትውልዱ ፍላጎት አንጻር ቀኖናውን የጠበቁ ዘርፋቸውን የለዩ ብዙ አደረጃጀቶች መኖራቸው ተገቢ ነው። ካልሆነ እኔ ከማወቀው አድባር ውጪ ሌላ አድባር አያሻም ይቆረጥ ማለት ከባሕር ውስጥ እንኮይን የመፈለግ ያህል የከበደ ነው።
ይህ የጃንደረባው ትውልድ አያት ማኅበሩን ለማፍረስ ይፋ ያደረገው ፕሮጀከት የለም የተገለጠ የታየ ነው። ትውልዱ በወደደው ዘርፍና ተቋም ቤተክርስቲያንን ማገለገሉ ብልህነት ነው። ስለዚህ ሂሱ ያልታለም ቢታለምም ፍቺ የሌለው ሲሆን ይህን ጸብ ጫሪ ሐሳብ በምሑራዊ ሐሳብ መቀየሩ ይበጃል። የጃንደረባው ፕሮጀክት አቅኚዎችም ይሁኑ አገልጋዮች የማኅበረ ቅዱሳን ትሩፋት ተቋዳሾች የነበሩ ማኅበሩን ያገለገሉ ይነስም ይብዛም በተቋሙ ላይ አስተዋጽኡ ያላቸው መሆናቸውን ልብ በሉ። አንድ ዓለም አቀፍ ማኅበርን ለማፍረስ የሚነሳ ሐሳብ ሞኝነት ብቻ ሳይሆን መንፈሳዊ ግብረ ገብነት እንዳልሆን እንኳን ጫፍ የደረሰ ሰው ይቅርና ጀማሪ አማኝ እንኳን ይረዳል።
ቤተክርስቲያኒቷ ገና ያልተነኩ ብዙ አቅጣጫዎች ያሉት በመሆኑ ትኩረት በሚያሻቸው ጉዳዮች ላይ እውቅና የተሰጣቸው አደረጃጀቶችን መፍጠራቸው የሚጠጥር ሐሳብ አይደለም። በሀገረ አቀፍ ደረጃ የጥናትና የምርምር መአከላትን ጨምሮ የመሳሰሉት ገና መቋቋም ያለባቸው እጹብ ኩነቶች ናቸው። ደጆችሽ አይዘጉ የተሰኝው ማኅበር የተዘጉ አብያተክርስቲያናትን በማስከፈት ዙርያ የሚንቀሳቀስ ማኅበር እንዳለ ሁሉ ሌሎቹም የተጠና በጎ ራእይ ያላቸው አደረጃጀቶችን መፍጠር የአገልግሎት ተደራሽነት ቢያመጣ እንጂ እንቅፋት ሊሆን አይችልም። አንድ እውቀ የሆነ አንድነት በመጣ ቁጥር እገሌን ሊያፈርስ ነው የሚለውን መንፈሳዊ መሰል ፖለቲካ መሥራት ለአንባሳ ሣር ካለሰጠውህ እንደማለት ያለ አለማወቅ ነው።
በጥቅሉ በጋራ ተልእኮ ትውልዱን የማዳን ሥራ እንዲሠሩ በቅንነት ከማሳሰብ ይልቅ አንዱ ፈራሽ ሌላው አፍራሽ አድርጎ ነገር መጎንጎን የቁም ቅዠት ነው። የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ የጋራ ኩነቶችን አዳብረው የሚገለጡበት ወቅት ረጅም አይደለም።
እንዲህ እያልን የሐሰት ብርኩማዎቸን እረፍት እናደርግባቸዋለን ከቅርብ ያየነውንም እንመሰክርበታለን። ሰሞኑን እንዲህና እንዲያ እያልን እንዘልቃለን...
ዲ/ን ሞገስ አብርሃም
#በር_ዘግቶ_ለመብሰልሰል_ያህል
--
"ሰብእ ለእከዩ ሃይማኖተ ያለብሳ-ሰው ክፋቱን ሃይማኖት ያለብሳታል።" #አበው።
“በእኛ አገር ጠቢብ መሆን አብሪ ትል መሆን ማለት ነው፡፡ አብሪ ትል ከሌሎች ትሎች የሚለየው ገላው እንደፍም ማብራቱ ነው፡፡ ታድያ ብላቴኖች በጨለማ ሲያበራ ሲያዩት በገዛ ብርሃኑ ተመርተው ይመጡና አንስተው ይጨፈልቁታል፡፡” #በዕውቀቱ ሥዩም
--
#ማኅበራት:- በቅዱስ ሲኖዶስ ደረጃ መመሪያ ዝርዝር ሕግ ወጥቶላቸዋል። አሠራራቸውን የሚከታተል በሊቀ ጳጳስ የሚመራ መምሪያ ተቋቁሟል። አሁን የመምሪያው የበላይ ጠባቂ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ ናቸው። የከፋ ስጋት ካለ ለመምሪያው ማሳወቅ ይቻላል። መታረም የሚገባው አካሔድ ካለ በቅንነት አስተያየት መስጠት ያንጻል።
#አንሳሳት:- ሁሉም እንደስጦታውና የትምህርት ዝግጅቱ በቤተክርስቲያን ጥላ ሆኖ የሚያገለግልባቸው ተጨማሪ አደረጃጀቶች ያስፈልጉናል። የቀረበውን መግራት አንድ ነገር ነው፣ ማስደንበር ግን የወዳጅ ሥራ አይደለም።
#ገበያው:- አሉባልታ ገበያ ያወጣበት ጊዜ ላይ ነን። ሀገራዊ ሰቆቃው በቀቢፀ ተስፋ፣ በሴራ፣ በበቀልና በወቀሳ ለተቃኘ ዘመቻ የጆሮ ገበያ ፈጥሯል። በዚህ የመረጃ ገበያ ጥንቁቅ ሸማች መሆን ከፀፀት ይጠብቃል።
#ደብተራ_በአማን_ነጸረ
- በተመሳሳይ ቅዱሳኑ ሲወስዱት 2ቱንም ቅዱሳን ታላቁ መቃርስ በበዓታቸው ቀብሯቸዋል:: ቦታውም ደብረ ብርስም [ በርሞስ ] ተብሏል:: ትርጉሙም የሮማውያኑ ቅዱሳን ደብር እንደ ማለት ነው::
አምላከ ቅዱሳን በእነርሱ ላይ የበዛች ፍቅሩን ለእኛም ያድለን:: ፍሬ ትሩፋት: ፍሬ ክብር እንድናፈራም ይርዳን:: ክብራቸውንም አያጉድልብን::
🕊
[ † ጥር ፲፯ [ 17 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ቅዱሳን እና ክቡራን የሚሆኑ አባቶቻችን "መክሲሞስ እና ዱማቴዎስ"
[ † ወርኀዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ቅዱስ እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት [ ቀዳሜ ሰማዕት ]
፪. ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ [ ወልደ ዘብዴዎስ ]
፫. ቅዱሳን አበው መክሲሞስና ዱማቴዎስ
፬. አባ ገሪማ ዘመደራ
፭. አባ ዸላሞን ፈላሢ
፮. አባ ለትጹን የዋህ
፯. ቅዱስ ኤዺፋንዮስ ሊቅ [ ዘደሴተ ቆዽሮስ ]
" ፍቅር ያስታግሳል:: ፍቅር ያስተዛዝናል:: ፍቅር አያቀናናም::ፍቅር አያስመካም:: ፍቅር አያስታብይም:: ብቻዬን ይድላኝ አያሰኝም:: አያበሳጭም:: ክፉ ነገርን አያሳስብም:: ከእውነት ጋር ደስ ይለዋል እንጂ ስለ ዓመፃ ደስ አይለውም:: ሁሉን ይታገሣል:: ሁሉን ያምናል:: ሁሉን ተስፋ ያደርጋል:: በሁሉ ይጸናል::" [ ፩ቆሮ.፲፫፥፬ ]
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖 🕊 💖
†
[ 🕊 አበዊነ ! 🕊 ]
ይህንን ድንቅ ተዓምር ሰምተነው ይሆን ?!
💖
" የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሩአችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ ፥ የኑሮአቸውንም ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነታቸው ምሰሉአቸው።
ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንትና ዛሬ እስከ ለዘላለምም ያው ነው።
ልዩ ልዩ ዓይነት በሆነ በእንግዳ ትምህርት አትወሰዱ ፤ ልባችሁ በጸጋ ቢጸና መልካም ነው እንጂ በመብል አይደለም ፤ በዚህ የሚሠሩባት አልተጠቀሙምና።" [ ዕብ.፲፫፥፯ ]
† † †
💖 🕊 💖
🕊
"ሶበሰ ኪዳንኪ ምክንያተ ድኂን ኢሀሎ ፈለገ እሳት ወደይን እም አሰጠመ ኩሎ ፤
[ የድኅነት ምክንያት የሆነው ቃል ኪዳንሽ ባይኖር ኖሮ የጥፋት እሳት ፣ መርገም [ኀጢአት] ባጠፋን ነበር ] "
[ አባ ጽጌ ድንግል ]
† † †
💖 🕊 💖
* ሐሙስ - ጥር 16 2016 ዓ.ም *
* ዘፍጥረት 19-24 *
ሰላም ለሁላችሁ ይሁን! በዛሬው ንባባችን ከምዕራፍ 19 እስከ 24 ድረስ እናነባለን።
ከንባብ በፊት የሚደረግ ጸሎት፡ “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፤ የአንተን ቃላት እሰማ እና እረዳ ዘንድ፥ እንዲያውም ፈቃድህን ለመፈጸም እበቃ ዘንድ የልቤን ጆሮዎች እና ዓይኖች ክፈትልኝ።” (ቅዱስ ኤፍሬም ሶሪያዊ)
በዛሬው ንባባችን፥ ታሪኩ ትላንት ካቆመበት በመቀጠል የሰዶምና የገሞራን መጥፋት፥ የሎጥና የሁለቱ ልጆች መትረፍን እናነባለን። የሎጥ ሚስት ግን ባለመታዘዟ እና ወደ ሁዋላዋ በመመልከቷ የጨው ሐውልት ሆና ቀርታለች። ሎጥና ሁለቱ ልጆቹ በተቀመጡበት ቦታ፥ ሴቶች ልጆቹ የቀሩት እነርሱ እና አባታቸው ብቻ እንደሆነ በማመን፥ ልጅ ለማግኘት እቅድን ነደፉ። በሌላ በኩል ደግሞ፥ አብርሃም ወደ ጌራራ በገባ ጊዜ ሚስቱ ሣራን “እህቴ ናት” በማለቱ፥ ከአቤሜሌክ ጋር ችግር መፈጠሩን እናነባለን። እግዚአብሔር ግን ጣልቃ ገብቶ ሣራን ከክፉ ጠበቃት፥ አቤሜሌክም ሣራን ለአብርሃም መለሰ።
ሣራም ከዚህ በፊት ቃል እንደተገባላት ይስሐቅን ወለደች። ሆኖም ግን ሣራ እስማኤል ወራሽ እንዳይሆን በመፍራት፥ አብርሃም አጋርን እስከ ልጇ እንዲያባርራት ታደርጋለች። እስማኤልን ግን እግዚአብሔር ከመሞት ያድነዋል። ከዚህ ባለፈ፥ አብርሃም በእግዚአብሔር ትእዛዝ ልጁን ይስሐቅን ለመሰዋት መሄዱን፥ እግዚአብሔር ይስሐቅን እንዳዳነ፥ አብርሃም ሚስቱ ሣራ በሞተች ጊዜ የመቃብር ቦታ ስለመግዛቱ፥ ለይስሐቅ ሚስት ማግኘቱን ሁሉ የምናነበው በእነዚህ ምዕራፎች ውስጥ ነው።
*የክለሳ ጥያቄዎች*
1) በዘፍጥረት 19 ላይ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ያልተከተለችው የሎጥ ሚስት ምን ሆነች?
2) ሎጥና ልጆቹ በዋሻ ሆነው ያቀዱት እቅድ ምንድር ነበር?
3) በዘፍጥረት 20 ላይ አብርሃም ወደ ጌራራ የሄደው ለምንድር ነው? በዚያስ ስለ ሣራ ምን ብሎ ተናገረ?
4) እግዚአብሔር ሣራን በጌራራ በምን አይነት ሁኔታ ጠበቃት?
5) በዘፍጥረት 21 ላይ እግዚአብሔር ለአብርሃም እና ለሣራ የገባውን ቃል የፈጸመበት አስደናቂ ነገር ምንድር ነው?
6) አጋር አና ልጇ እስማኤል እንዲባረሩ ያደረገው ምክንያት ምንድር ነው? በሣራ እና በአጋር መካከል ምን ተፈጠረ?
7) በዘፍጥረት 22 ላይ እግዚአብሔር የአብርሃምን እምነት በምን መንገድ ፈተነው?
8) እግዚአብሔር ይስሐቅን ከሞት ያተረፈው በምን መንገድ ነው?
9) በዘፍጥረት 23 ላይ አብርሃም የመቃብር መሬት የገዛው ለምንድር ነው? ከማንስ ገዛው?
10) በዘፍጥረት 24 ላይ ለይስሐቅ ሚስት እንዲፈልግ ኃላፊነት የተሰጠው ለማን ነው?
11) ለይስሐቅ ሚስት እንዲፈልግ ኃላፊነት የተሰጠው ሰው በምን መስፈርት ሚስትን መረጠለት?
12) ለይስሐቅ ሚስት እንድትሆን የተመረጠችውስ ማን ናት? የቤተሰቦቿስ ምላሽ ምን ነበር?
መልካም ንባብ!
🕊
[ † እንኩዋን ለአበው ቅዱሳን "አባ ዳንኤል" : "አባ ዸላድዮስ" : ወቅዱስ "ፊላታዎስ ሰማዕት" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ † ]
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †
🕊 † ማር ዳንኤል † 🕊
" ዘዓምድ " በሚል ስም ከሚታወቁ የቤተ ክርስቲያን አበው መካከል ፬ቱ ቅድሚያውን ይይዛሉ:: እነዚህም :-
፩. ቅዱስ ስምዖን ዘዓምድ:
፪. ቅዱስ አጋቶን ዘዓምድ:
፫. ቅዱስ ዳንኤል ዘዓምድ እና
፬. ቅዱስ ሉቃስ ዘዓምድ ናቸው::
- " ዘዓምድ " የሚለውን ቃል ምሥራቃውያን በልሳናቸው 'THE STYLITE' ይሉታል:: የእኛው ቃል ደግሞ ከግዕዝ የተወረሰ ነውና በቁሙ ቢተረጐም "የምሰሶው" የሚል ትርጉምን ይይዛል:: ይህም በ፪ ምክንያቶች ነው::
- አንደኛው ቅዱሳኑ ተጋድሏቸውን የፈጸሙት ከረዥም ምሰሶ ላይ ወጥተው በመጸለይ ስለሆነ ነው:: ሌላኛው ምክንያት ደግሞ እነዚህ አባቶች በዘመኑ ለነበሩ ምዕመናንና መነኮሳት አጽናኝ: አስተማሪ: መሪና ፈዋሽ በመሆናቸውና እንደ ምሰሶ ተተክለው ሳይነቃነቁ በመጸለያቸው ነው::
- ልክ ከዓለም ሃገራት ብዙ ስውራንን እና ቅዱሳን ነገሥታትን በመያዝ ሃገራችን ቀዳሚ እንደ ሆነችው ሁሉ ምሰሶ ላይ ወጥተው የሚጋደሉ ቅዱሳንም ሶርያውያንና ምሥራቃውያን ናቸው:: በዚህ ዕለትም ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የታላቁን ቅዱስ ማር ዳንኤልን በዓል ታከብራለችና ከዜና ሕይወቱ ለበረከት ጥቂት እንካፈል::
- ይህ ቅዱስ ሰው [ በስዕሉ የሚታየው ] ሶርያዊ ሲሆን ተወልዶ ያደገባት አካባቢ በቀድሞው አጠራር "ሃገረ ዓምድ" ይሏታል:: "ማር" የሚለው ቃል በቤተ ክርስቲያን ቅድስናንና አለቅነትን የሚገልጽ ስም ነው:: በዚህ ስም ጥቂቶች ብቻ ሲጠሩበት ለሊቃውንትም: ለሰማዕታትም: ለጻድቃንም አገልግሏል::
- ቅዱሱ "ማር" ብቻ ሳይሆን "ዘዓምድ" ተብሎም ተጠርቷል:: ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ እርሱም በፊት እንደ ጠቀስናቸው አበው ምሰሶ ላይ ተጠግቶ [ ቆሞ ] : ትኩል ከመ ዓምድ ሆኖ በመጸለዩ ነው::
- ማር ዳንኤል በምድረ ሶርያ ስመ ጥር ጻድቅ ነው:: በዘመነ ጻድቃን መጨረሻ አካባቢ ከክርስቲያን ወገኖቹ ተወልዶ: በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን አድጐ: ገና በልጅነቱ ለቤተ እግዚአብሔር ተሰጥቷል::
- የወቅቱ የሃገረ ዓምድ ዻዻስ [ አባ ዼጥሮስ ] ለማር ዳንኤል ፍኖተ ጽድቅን [ የሕይወት - የእውነትን ጐዳና] በማሳየት ከፍ ያለውን አስተዋጽኦ አበርክቷል:: አስተምሮም ለመዓርገ ክህነት አብቅቶታል::
- ቅዱሱ በእድሜው እየበሰለ ሲሔድ ግን ምርጫው ምናኔ ሆኖ በመገኘቱ በፈቃዱ ወደ በርሃ ሔደ:: በዚያም መዓርገ ምንኩስናን ተቀብሎ በጾም: በጸሎትና በትሕርምት ይጋደል ገባ::
- ማር ዳንኤል በበዓቱ ተወስኖ ሲጾም: ሲጸልይና እግዚአብሔርን ሲያመልክ ከጸጋ [ከብቅዓት] ደረሰ:: ብዙ ተአምራትንም በመሥራቱ ስም አጠራሩ በአካባቢው ተሰማ:: እርሱ ግን ከሰው: ይልቁንም ከሴቶች ይርቅ: ላለማየትም ራሱን ይከለክል ነበር::
- ለአንድ መናኝ በሰዎች መካከል: ይልቁንም በተቃራኒ ጾታ ጐን መኖር ያልተፈቀደ: ፈታኝም ድርጊት ነውና ከፈጣሪው ጋር እንዲህ የሚል ቃልን ገባ:: "ከዚህ በሁዋላ ሴት ልጅን አላይምም" አለ:: በእንዲህ ያለ የቅድስና ሕይወት ሳለ ወላጅ እናቱ ልታየው ተመኘች::
- ወደ ገዳሙ መጥታም "ልጄ ! ላይህ ሽቻለውና ልግባ : ወይ ብቅ በል" ስትል ላከከችበት:: ቅዱሱ ግን "እናቴ ! ሴትን አላይም ብየ ቃል ስለ ገባሁ አልችልም" ሲል መለሰላት:: በጣም አዝና "እኔ ወልጄ: አዝዬ: አጥብቼ: አሳድጌ እንደ ሌሎች ሴቶች አስመሰልከኝ? በል ፈጣሪ ፪ ሴቶች በአንድ ልብስ ሆነው ይዩህ!" ብላ ረግማው ወደ ቤቷ ተመለሰች::
- የሚገርመው ማር ዳንኤል በበርሃ የበቃውን ያህል እናቱ በዓለም ሳለች በጐ ሰርታለችና እርሷም ጸጋውን አብዝቶላታል:: በምን ይታወቃል ቢሉ :- ያቺ የተናገረቻት ነገር ሁሉ ደርሶበታልና::
- አንድ ቀን ለገንዘብ ሲል አንድ ሰው የገደለውን አምጥቶ በቅዱሱ በር ላይ ጣለው:: ቅዱሱም ያለ አበሳው ታሥሮ ወደ ከተማ ሲወሰድ መታጠቢያ [ shower ] ቤት ውስጥ የነበሩ ሴቶች ሊያዩት ቸኩለው: አንድ ልብስ ለብሰው ወጥተዋል:: ማር ዳንኤል ይህንን ሲያይ የእናቱ ነገር ትዝ ብሎት ሳቅ ብሏል::
- በታሠረበት ቦታ ግን የሞተውን ሰው በጸሎቱ በማስነሳቱ በክብር ወደ በዓቱ ተመልሷል:: የከተማዋ ንጉሥም ገዳምን አንጾለታል:: በተረፈ ዘመኑም ለብዙ ቅዱሳን አባት ሆኖ እስከ እርጅናው አገልግሏል:: በዚህች ቀንም በክብር ዐርፏል::
🕊 † አባ ዸላድዮስ † 🕊
- አባ ዸላድዮስም በተመሳሳይ የዘመነ ጻድቃን ፍሬ ነው:: በርሃ ከገባባት ቀን ጀምሮ ጾምን: ጸሎትን አዘውትሮ ክርስትናውን አጽንቷል:: ሙሉ እድሜውን በጐ በመሥራት በማሳለፉ ፈጣሪውን ሲያስደስት ለብዙዎች አንባ: መጠጊያ መሆን ችሏል::
- በጸሎቱ አካባቢውን በደህንነት ይጠብቅ ነበር:: ምዕመናን እንኩዋን ወደ እርሱ መጥተው ተባርከው ባሉበት ቦታ ሁነው ተማጽነው እንኩዋ መሻታቸውን አያጡም ነበር:: ምንም ያህል ኃጢአተኞች ይሁኑ እግዚአብሔር ስለ አባ ዸላድዮስ ሲል ይለመናቸው ነበር::
- አንድ ቀን አንድ ነጋዴ ሰው በባሕር ላይ ሲሔድ ድንገት ማዕበል ይነሳበታል:: ብቻውን ነበርና ጨነቀው:: እሱ ያለባት ጀልባም ትንሽ በመሆኗ ልትሠበር ደረሰች:: መዳን እንደ ማይችል ሲያውቅ ተስፋ ቆረጠ::
- ድንገት ግን አባ ዸላድዮስ ትዝ ብሎት ቀና ብሎ "ጌታየ! ስለ ቅዱሱ አባት ብለህ ብትምረኝ ለወዳጅህ መቶ ዲናር ወርቅ እሰጣለሁ" ሲል ተሳለ:: ቃሉን ተናግሮ ሳይጨርስ አባ ዸላድዮስ በጀልባው ላይ ቁጭ ብሎ ታየው:: ማዕበሉም ጸጥ እንዲል አድርጐ ከወደብ አድርሶ ተለየው::
- ነጋዴውም ፈጣሪውን ስለ ድኅነቱ እያመሰገነ ፻ ዲናር ወርቁን ይዞ አባ ዸላድዮስን ፍለጋ ወጣ:: የሚያውቀው በዝና ብቻ ነበርና:: መንገድ ላይም ሞሪት የሚባል መሪ አግኝቶ ከአባ ዸላድዮስ በዓት ደረሰ::
- ከቅዱሱ ተባርኮ ወርቁን ቢያቀርብለት "ልጄ! እኔ ይህን አልፈልገውም:: ለነዳያን በትነው" አለው:: ነጋዴው ሲወጣ ግን ሞሪት [መሪው] ገንዘቡን ፈልጐ ገደለውና ከጻድቁ በር ላይ ጣለው:: ሃገረ ገዢውም ሲሰማ አባ ዸላድዮስን አሠረው::
- ጻድቁ ግን የሞተውን ባርኮ አስነሳውና "ማን ገደለህ" ቢለው "ሞሪት" ሲል መልሷል:: መኮንኑ ሞሪትን ሊገድለው ቢልም "የለም" ብሎ ነጋዴውን በደስታ: ሞሪትን ደግሞ በንስሃ ሸኝቷቸዋል:: አባ ዸላድዮስ ግን ተረፈ ዘመኑን በቅድስና ሲጋደል ኑሮ በክብር ዐርፏል::
🕊 † ቅዱስ ፊላታዎስ ሰማዕት † 🕊
- "ፊላታዎስ" ማለት "መፍቀሬ እግዚአብሔር - እግዚአብሔርን የሚወድ: እርሱም የሚወደው" ማለት ነው:: ቅዱሱ የዘመነ ሰማዕታት [፫ኛው መቶ ክ/ዘመን] ፍሬ ሲሆን ለየት ያለ ታሪክ ያለው ቡሩክ ወጣት ነው::
- እርሱ የባለ ጸጐች ልጅ: ስለ ክርስትና ምንም ሰምቶ የማያውቅ ሕጻን ነበር:: ወላጆቹ የሚያመልኩት ላምን ሲሆን የአካባቢው ሰው ደግሞ ለጸሐይ ይንበረከክ ነበር:: ቤተሰቦቹ ስለ አምልኮ ሲጠይቁት "እናንተ የምታመልኯቸው ፍጡራን ስለ ሆኑ አልፈልግም" አላቸው::
- ሕጻን ቢሆንም ስለ ፈጣሪው ተመራመረ:: በመጨረሻውም ፀሐይን "አንተ ምንድነህ?" ቢለው "እኔ ፍጡር ነኝ" ሲል መልሶለታል:: በዚያች ዕለት ግን ቅዱስ መልአክ ወርዶ: ሁሉን ነገር አስተምሮ የክርስቶስ ወታደር አድርጐታል::
💛
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
🕊 ፍኖተ ተዋሕዶ 🕊
[ ዘወትር ረቡዕ ምሽት ]
የቅዱሳን አበው ሕይወት ፣ ድንቅ ተዓምራትና ምስክርነቶች ፣ መንፈሳዊ ትረካዎች ፣ መንፈሳዊ የኪነ-ጥበብ ዝግጅቶች ፣ አስደናቂ ምስጢራትና ከምዕመናን ለቀረቡ ጥያቄዎች አስደናቂ የሊቃውንት ምላሽ ፣ ኦርቶዶክሳዊ ማዕቀፈ እሳቤ በመ/ር ፋንታሁን ዋቄ የተሰጡ ተከታታይ አስደናቂ ትምህርቶችና የመሳሰሉት ዝግጅቶች በድምጽ ይቀርባሉ።
ይከታተሉ !
------------------------------------------
▷ " ከሞት ጋር ቀጠሮ "
[ " መንፈሳዊ ትረካ ... ! " ]
በዚች ሌሊት ነፍስህን ከአንተ ሊወስዱአት ይፈልጓታል !
[ 🕊 ]
------------------------------------------
" ነፍሴንም። አንቺ ነፍሴ ፥ ለብዙ ዘመን የሚቀር ብዙ በረከት አለሽ ፤ ዕረፊ ፥ ብዪ ፥ ጠጪ ፥ ደስ ይበልሽ እላታለሁ አለ።
እግዚአብሔር ግን። አንተ ሰነፍ ፥ በዚች ሌሊት ነፍስህን ከአንተ ሊወስዱአት ይፈልጓታል ፤ ይህስ የሰበሰብኸው ለማን ይሆናል ? አለው።" [ ሉቃ.፲፪፥፲፱ ]
† † †
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
👇