"እንግዲህ፡ንስሓ፡ግባ፤አለዚያ፡ፈጥኜ፡ እመጣብሃለሁ፡፡" ራዕ 2፥16
🕊
[ እ ን ኳ ን አ ደ ረ ሳ ች ሁ ! ! ]
❝ ከሚካኤል በቀር ማንም የሚያጸናኝ የለም። ❞
[ ዳን . ፲ ፥ ፳፩ ]
---------------------------------------------
💖
"የተጨነቀውን የተጨቆነውን ነፃ የምታወጣው ሚካኤል ሆይ ፦ ሰላም ላንተ ይሁን ፡ ሠራተኛው ሠርቶ እንዲበላ ውሎ እንዲገባ የምትጠብቀው ሚካኤል ሆይ ሰላም ላንተ ይሁን፡፡
ችግረኛውን ለመርዳት ከልዑል ዘንድ የምትላክ ሚካኤል ሆይ ሰላም ላንተ ይሁን አዳኝነትህን በማመን የለመነህን በክንፈ ረድኤትህ የምትሠውረው ሚካኤል ሆይ ሰላም ላንተ ይሁን፡፡
በኀዘን በትካዜ ላይ ወድቆ የሚፍገመገመውን የሚንፈራገጠውን ፈጥነህ ደርሰህ ደግፈህ የምታጽናናው ሚካኤል ሆይ ፤ አንገትህን ዘንበል ቀለስ አድርገህ በፈጣሪ ፊት ሰግደህ እኛ ባሮቹን በቸርነቱ ይጎበኘን ዘንድ የማናዊት እጁን ዘርግቶ ይባርከን ዘንድ ለምን አማልድ ለዘላለሙ አሜን፡፡"
[ መልክአ ሚካኤል ]
ኦ ሚካኤል ! ኦ ሚካኤል ! ኦ መተንብል !
ካህነ አርያም ትሰመይ ቢጸ ሱራፌል ፥
ዘም ርዑሳን ርዑስ ፥ ወዘም ልዑላን ልዑል
ጊዜ ጸዋይኩከ ቅረበኒ በምህረት ወሳህል !
† † †
💖 🕊 💖
🕊
[ የኢትዮጵያ ኃይሏ ግን እግዚአብሔር ነው።
በራሷም እውነት ትድናለች ! ]
† † †
💖 🕊 💖
🕊
[ እ ን ኳ ን አ ደ ረ ሳ ች ሁ ! ! ]
❝ ታላቁ እረኛ ክርስቶስ እስከሚመጣ ! ❞
---------------------------------------------
❝ ወብዙኃን ኖሎት መጽኡ ወስእኑ ከሲቶታ ለዕብን እም አፈ ዐዘቅት እስከ ይመጽእ ያዕቆብ ዘክቡት ውስተ ሐቌሁ ዘሀሎ ይሰጎ እምሰብእ ከሠተ ወአስተየ መርዔቶ። ወከማሁመ መጽኡ ብዙኃን ነቢያት ወስእኑ ከሲቶታ ለጥምቀት እስከ ይመጽእ ዐቢይ ኖላዊ እምሰማይ ከሠተ ወአጥመቀ ብዙኃነ አሕዛበ በውስቴታ። ❞
❝ ብዙ እረኞች መጡ ፤ ክርስቶስ ከእርሱ ዘር ሰው የሚሆንበት ያዕቆብ እስኪመጣ ድረስ ከጉድጓድ ውኃ ላይ የተገጠመውን ድንጋይ ማንከባለልና በጎቻቸውን ውኃ ማጠጣት አልቻሉም። ያዕቆብ ሲመጣ ግን ድንጋዩን ከጉድጓዱ አፍ ላይ አንሥቶ መንጋዎቹን አጠጣቸው።
እንዲሁም ብዙ ነቢያት ቢመጡም ከሰማይ የሚመጣው ታላቁ እረኛ ክርስቶስ እስከሚመጣና የጥምቀትን ምሥጢር ከፍቶ ብዙ አሕዛብን በውኃ እስኪያጠምቅ ድረስ የጥምቀትን ምሥጢር ሊገልጧት አልተቻላቸውም። ❞
[ ቅዱስ ያሬድ ቅዱስ ያሬድ ያመሠጠረው ታሪክ በዘፍ.፳፱፥፩-፲፩ [29፡1-11] ላይ ይገኛል። ]
እንኳን ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ ጥምቀት አደረሳችሁ !!!
🕊
[ ቤተክርስቲያን ቅድስት ባሕረ ጥበባት ! ]
† † †
💖 🕊 💖
🕊
[ የተቀደሰች ሃይማኖታችን ! ]
" ስለማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን። "
[ ፪ቆሮ.፱፥፲፭ ]
† † †
💖 🕊 💖
🕊
[ † እንኳን ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዓመታዊ የጥምቀት በዓል [ ኤጲፋንያ ] በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ]
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †
🕊 † በዓለ ኤጲፋንያ † 🕊
† "ኤጲፋንያ" የሚለው ቃል ከግሪክ [ጽርዕ] ልሳን የተወሰደ ሲሆን በቁሙ "አስተርእዮ: መገለጥ" ተብሎ ይተረጐማል:: በነገረ ድኅነት ምሥጢር ግን ኤጲፋንያ ማለት "የማይታይ መለኮት የታየበት: እሳተ መለኮት በተዋሐደው ሥጋ የተገለጠበት" እንደ ማለት ነው::
"ዘኢያስተርኢ ኅቡዕ እስመ አስተርአየ ለነ::
እሳት በላዒ አምላክነ::" እንዲል:: [አርኬ]
አንድም: ምሥጢር ሆኖ የቆየ አንድነቱ: ሦስትነቱ የተገለጠበት ቀን ነውና ዕለተ ጥምቀቱ ኤጲፋንያ ይሰኛል:: መድኃኒታችን ክርስቶስ አዳምንና ልጆቹን ያድን ዘንድ ከሰማያት ዙፋኑ ወርዶ: እንደ ሰውነቱ በሥጋ ማርያም ለ፴፫ [33] ዓመታት ተመላልሷል::
ጊዜው ሲደርስም በፈለገ ዮርዳኖስ: ከዮሐንስ ዘንድ ሊጠመቅ ሔደ:: መድኃኒታችን ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ የወረደው ጥር ፲ [10] ቀን አመሻሽ ላይ ሲሆን በፍጹም ትሕትና ተራ ሲጠብቅ አድሮ ሌሊት ፲ [10] ሰዓት ላይ ደረሰውና ሊጠመቅ ቀረበ::
አሥር ሰዓት መሆኑም ርግብ [መንፈስ ቅዱስ] ሲወርድ ሰዎች ሥጋዊት ርግብ ናት ብለው እንዳይጠራጠሩ ነው:: ርግብ በሌሊት መንቀሳቀስ አትችልምና::
መድኃኒታችን ወደ ቅዱስ ዮሐንስ ሲጠጋ አምላክነቱን ተረድቶ "እንዴት ፈጣሪየ ወደ እኔ ትመጣለህ? እንዴትስ በእኔ እጅ ትጠመቃለህ?" አለው:: ትህትና ለእናትና ልጅ ልማዳቸው ነውና:: ጌታ ግን "ጽድቅን ሁሉ ልንፈጽም ይገባል" ሲል እንዲያጠምቀው ፈቀደለት::
ቅዱስ ዮሐንስም "ስመ አብ በአንተ ሕልው ነው:: ስመ ወልድ ያንተ ነው:: ስመ መንፈስ ቅዱስም በአንተ ዘንድ ሕልው ነው:: በማን ስም አጠምቅሃለሁ?" ሲል ጠየቀው::
ጌታ "ወልዱ ለቡሩክ ከሣቴ ብርሃን ተሣሐለነ:: አንተ ካህኑ ለዓለም በከመ ሲመቱ ለመልከ ጼዴቅ" እያልክ አጥምቀኝ አለው:: ትርጉሙም "የቡሩክ አብ የባሕርይ ልጁ : ብርሃንን የምትገልጥ ሆይ ይቅር በለን! አንተ እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት የዓለም ካህኑ ነህና" እንደ ማለት ነው::
ከዚያም ጌታ ወደ ዮርዳኖስ ሲገባ ባሕር አይታ ደነገጠች : ሸሸችም:: [መዝ.፸፮፥፲፮ , ፲፩፥፫] ዮርዳኖስ ጨንቆት ግራ ቀኝ ተመላለሰ:: እሳተ መለኮት ቆሞበታልና ውኃው ፈላ:: በጌታ ትዕዛዝ ግን ጸና::
ጌታ ተጠምቆ: ሥርዓተ ጥምቀትን ሠርቶ: ዮርዳኖስን ብርህት ማሕጸን አድርጐ: የእዳ ደብዳቤአችንንም ቀዶ ከወጣ በኋላ ሰማያት ተከፈቱ:: ማለትም አዲስ ምሥጢር ተገለጠ::
አብ በደመና ሆኖ "የምወደው: የምወልደው: ሕልው ሆኜ ልመለክበት የመረጥኩት የባሕርይ ልጄ ይህ ነው!" ሲል በአካላዊ ቃሉ ፍጹም ተዋሕዶን መሰከረ:: መንፈስ ቅዱስም በአምሳለ ርግብ ወርዶ በራሱ ላይ ተቀመጠ:: ራሱንም ቆንጠጥ አድርጐ ያዘው:: በዚህም የሥላሴ አንድነቱ: ሦስትነቱ ታወቀ: ተገለጠ::
ቅዱስ ዮሐንስ "መጥምቀ መለኮት" የሚባልበትን ታላቁን ክብር ሲያገኝ ዮርዳኖስ የልጅነት መገኛ ቅዱስ ባሕር ሆነ::
🕊 † ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ † 🕊
ቅዱስ ወንጌል ላይ ቅዱስ ሉቃስ "ዘካርያስ ካህኑና ቅድስት ኤልሳቤጥ በሰውና በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ የሚኖሩ ጻድቃን ነበሩ" ይላቸዋል:: [ ሉቃ.፩፥፮ ]
እሊህ ቅዱሳን ባልና ሚስት ግን መካኖች በመሆናቸው ልጅ ሳይወልዱ ዘመናቸው አልፎ ነበር:: እንደ ቤተ ክርስቲያን ትውፊት ዕድሜአቸው የኤልሳቤጥ ፺ [90] የዘካርያስ ደግሞ ፻ [100] ደርሶ ነበር::
ፍጹም መታገሳቸውን የተመለከተ ጌታ ግን በስተ እርጅናቸው ከሰው ሁሉ በላይ የሆነ: ትንቢት ለብቻው የተነገረለት [ኢሳ.፵፥፫ , ሚል.፫፥፩] ታላቅ ነቢይን ይሰጣቸው ዘንድ መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤልን ላከላቸው::
ቅዱስ ዘካርያስ ሰው ነውና ከደስታ ብዛት በመከራከሩ ድዳ ሆነ:: ቅድስቲቷ ግን መስከረም ፳፮ [26] ቀን ታላቁን ሰው ጸንሳ ለ፮ [6] ወራት ራሷን ሠወረች:: በ፮ [6] ኛው ወር የፍጥረት ሁሉ ጌታ በተጸነሰ ጊዜ የአርያም ንግሥት ድንግል እመቤታችን ደጋ ደጋውን ወደ ኤልሳቤጥ መጣች:: ሁለቱ ቅዱሳት የእህትማማች ልጆች ናቸው::
የአምላክ እናቱ ስትደርስና "ሰላም" ስትላቸው መንፈስ ቅዱስ በእናትና ልጅ ወርዶ ኤልሳቤጥ በምስጋና: ዮሐንስ ደግሞ ገና በማሕጸን ሳለ በደስታ ዘለለ [ሰገደ]:: ከዚህ በኋላ ሰኔ ፴ [30] ተወልዶ: አባቱ ዘካርያስ "ዮሐንስ" ሲለው አንደበቱ ተፈትቶለታል::
ቅዱስ ዮሐንስ ከተወለደ ፪ ዓመት ከ፮ ወር በሆነው ጊዜ ሰብአ ሰገል በመምጣታቸው በእሥራኤል ምድር የሚገኙ ሕፃናትን ሔሮድስ ቁዝ አስፈጀ:: ትንሽ ቆይቶም አይሁድ ለሔሮድስ ስለ ቅዱሱ ሕፃን ነገሩት:: "ሲጸነስ የአባቱን አንደበት የዘጋ: ሲወለድ ደግሞ የከፈተ 'ዮሐንስ' የሚባል ሕፃን አለና እሱንም ግደል" አሉ::
እናቱ ቅድስት ኤልሳቤጥ ይዛው ስትሸሽ ካህኑን ዘካርያስን ግን በቤተ መቅደስ መካከል ገድለውታል:: አረጋይት ኤልሳቤጥም ሕፃኑን እያሳደገች በገዳመ ዚፋታ ለ፫ [፭] ዓመታት ቆይታለች:: ቅዱስ ዮሐንስ ፭ [፯] ዓመት ሲሞላው ግን እዚያው በበርሃ እናቱ ዐረፈች:: ከሰማይ ዘካርያስና ስምዖን ወርደው ቀበሯት::
ሕፃኑ ዮሐንስ ሲያለቅስ ድንግል ማርያም ስንት አገር አልፋ ሰማችው:: እርሷም ስደት ላይ ነበረችና:: ከጌታ ጋር በደመና ሒደው ድንግል አቅፋ አጽናናችው:: ጌታንም "እንውሰደው ይሆን?" አለችው:: ጌታችን ግን "ለአገልግሎት እስክጠራው እዚህ ይቆይ" አላት:: ባርካው: አጽናንታውም ተለያዩ::
ቅዱስ ዮሐንስ ከዚህ በኋላ በዚያ ቆላ የግመል ጠጉር ለብሶ: ጠፍር ታጥቆ ተባሕትዎውን ቀጠለ:: ለ፳፭ [፳፫] ዓመታትም በንጽሕና ሲኖር ከምድር አራዊትና ከሰማይ መላእክት በቀር ማንንም አላየም:: ይሕችን ዐመጸኛ ዓለምም አልቀመሳትም::
ከዚህ በኋላ ፴ [ 30 ] ዘመን ሲሞላው እግዚአብሔር ከሰማይ ተናገረው:: "ሒድ! የልጄን ጐዳና ጥረግ" አለው:: ነቢያት ስለዚህ ነገር ተናግረው ነበርና:: [ኢሳ.፵፥፫, ሚል.፫፥፩] አባቱ ዘካርያስም "ወአንተኒ ሕፃን ነቢየ ልዑል ትሰመይ: እስመ ተሐውር ቅድመ እግዚአብሔር ከመ ትጺሕ ፍኖቶ" [ሉቃ.፩፥፸፮] ብሎ መንገድ ጠራጊነቱን ተናግሮ ነበርና::
ቅዱስ ዮሐንስ በዚያ ጊዜ በኃይለ መንፈስ ቅዱስ እየገሰገሰ ከበርሃ ወደ ይሁዳ መጣ:: ያዩት ሁሉ ፈሩት: አከበሩት:: ቁመቱ ቀጥ ያለ: ጽሕሙ እንደ ተፈተለ ሐር የወረደ: ጸጉሩ የቁራ ያህል የጠቆረ: መልኩ የተሟላ: ግርማው የሚያስፈራ ገዳማዊ ነውና::
ፈጥኖም ሕዝቡን ለንስሐ ሰበከ: ለንስሐም በርካቶችን አጠመቃቸው:: በዚህ አገልግሎት ለ፮ ወራት ቆይቶ ጌታችን ወደ እርሱ ዘንድ መጣ:: ዮሐንስ ሰማይን ከነግሱ: ምድርን ከነልብሱ የያዘ ፈጣሪ "አጥምቀኝ" ብሎ ሲመጣ ደነገጠ:: የሚገባበትም ጠፋው::
" እንቢ ጌታየ ! አንተ አጥምቀኝ " አለው:: ጌታ ግን "ፈቅጄልሃለሁ" አለው: አጠመቀው:: በዚህ ምክንያት ይሔው እስከ ዛሬም "መጥምቀ መለኮት" ሲባል ይኖራል:: ቅዱስ ዮሐንስ በመጨረሻ ሔሮድስን ገሰጸው:: ንጉሡም ተቀይሞ ለ፯ ቀናት አሠረው::
† † †
“ ያን ጊዜ ኢየሱስ በዮሐንስ ሊጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መጣ። ” — [ ማቴዎስ ፫፥፲፫ ]
. .
እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ጥምቀት በሰላምና በጤና አደረሳችሁ
Congratulations on the baptism of our Lord and Savior Jesus Christ in peace and health
Baga gooftaa fi fayyisaa keenya Iyyasuus Kiristoos nagaa fi fayyaan cuuphame
እንኳዕ ጥምቀት ጎይታናን መድሓኒናን ኢየሱስ ክርስቶስ ብሰላምን ብጥዕናን ኣብጽሓና።
تهانينا على معمودية ربنا ومخلصنا يسوع المسيح بسلام وصحة
Félicitations pour le baptême de notre Seigneur et Sauveur Jésus-Christ dans la paix et la santé
Herzlichen Glückwunsch zur Taufe unseres Herrn und Erlösers Jesus Christus in Frieden und Gesundheit
† † †
💖 🕊 💖
🕊
[ እ ን ኳ ን አ ደ ረ ሳ ች ሁ ! ! ]
❝ ያን ጊዜ ጌታ ኢየሱስ በዮሐንስ ሊጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መጣ። ❞ [ ማቴ ፫÷፲፫ ]
---------------------------------------------
❝ ክርስቶስ በዮርዳኖስ ወንዝ በመጠመቁ ምክንያት ጥምቀትን በእርሱ ጥምቀት ባርኮ ሰጠን። ክርስቶስ የተጠመቀበት የዮርዳኖስ ወንዝ መለኮታዊውን ብርሃን ለበሰ። በእርሱ ጥምቀት ወንዞች ፣ ጅረቶች ፣ ምንጮች ፣ ሁሉ ተቀደሱ። ... መድኅናችን ሆይ በአንተ ጥምቀት የውኃ ምንጮች ሁሉ ተቀደሱ ፤ ስለዚህም ውኃ የመንፈሳውያን ልጆች መገኛ ማኅፀን ሆነች። ❞
[ ቅዱስ ኤፍሬም ]
❝ ጥምቀትን ለኃጢአት ሥርየት ሰጠን እንዲሁም በዚሁ ጥምቀት ከፍዳ እንድንድንና መንግሥቱን እንድንወርስ አደረገን፡፡ ❞
[ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ]
🕊
[ ከንግግር ይልቅ ተግባር የገለጸሽ
ፍኖተ ክርስቶስ ተዋሕዶ አንቺ ነሽ ! ]
† † †
💖 🕊 💖
# ከተራ_ምንድን_ነው ?
ከተራ ማለት ቃሉ የግእዝ ሲሆን መከተር፣ መገደብ ፣ ፣ ማቆም የሚል ትርጉም አለው ፡፡ ለጥምቀት በዓል ማክበሪያነት የሚከተረውን ፣ የሚገደበውን ውኃ ያሳያል ።
በጥምቀት ዋዜማ ታቦተ ሕጉ ከቤተ መቅደስ ወጥቶ ውኃ ባለበት አካባቢ ስለሚያድር የየአጥቢያው ሕዝብ እየተሰበሰቡ በወንዝ ዳር ወይም በምንጭ አካባቢ ድንኳን ይተከላሉ፡፡ ድንኳንም ከሌለ ዳስ ሲጥሉ ይውላሉ፡፡ የምንጮች ውኃ እንዲጠራቀም ይከተራሉ (ይገድባሉ) ጉድጓድ እየተቆፈረ ውኃው እንዳይሄድ በመገደብ ለመጠመቂያ (ለጥር 11) ዝግጁ የሚያደርጉበት ዕለት ነው፡፡
በተጨማሪ በአቅራቢያ የሚገኙት ቤተክርስቲያናት ተሰብስበው ከዚሁ ከተቆፈረው ገንዳ ወይም ከተገደበው ጅረት አጠገብ ባለው ዳስ ወይም ድንኳን ታቦቶቻቸውን ያሳድራሉ ሊቃውንቱም በዚያው እግዚአብሔርን በማህሌት ሲያመሰግኑ ያድራሉ።
በበዓለ ጥምቀት የታቦታቱ ወደ ወንዝ መውረድ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ በእደ ዮሐንስ ለመጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ በዋዜማው የመሄዱ ምሳሌ ነው፡፡ ታቦቱ የጌታችን፣ ምሳሌ ሲሆኑ ካህናቱ የመጥምቁ ዮሐንስ ምሳሌ ናቸው፡፡ መዘምራኑና ሕዝቡ ደግሞ ዮሐንስ ያጠመቃቸው ሕዝቦች ምሳሌዎች ናቸው፡፡
መልካም የከተራ በዓል በ፭ ኪሎ ግቢ ጉባኤ ትምህርት ክፍል ትምህርታዊ ሥነ-ጽሑፍ ንዑስ ክፍል የተዘጋጀ
🕊
"በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"።
ጥር ፲ [ 10 ] ቀን።
† እንኳን ለገሀድ [ ጋድ ] ጾመ ፣ ለከተራ በዓልና ለአባ ታውብንጦ ለዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ከሚታሰቡ ፦ ከሰማዕት ከጠምያኒ ፣ ከኪናርያና ከንግሥት በጥሪቃ ከመታሰቢያቸው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። †
†
- የዕለቱ ሰላም ፦ "ተሣሐልከ እግዚኦ ምድረከ ሃሌ ሉያ ፤ ወረደ ወልድ እምሰማያት ውስተ ምጥማቃት ፤ በፍሥሐ ወበሰላም"። [ቅዱስ ያሬድ በድጓው ላይ]
+ + +
- በዚች ዕለት ምንም ምን መብልን ሰይቀምሱ ምእመናን ሁሉ እስከ ምሽት ይጾሙ ዘንድ ከእኛ አስቀድመው የነበሩ ታላላቅ ሊቃውንት የቤተ ክርስቲያን መምህራን ሥርዓትን ሠሩ በምሽትም ቢሆን በታላቁ ጾም ከሚበላው በቀር ጥሉላትን እንዳይቀምሱ። በዚች ዕለት ምእመናን እስከ ምሽት እንደመጾሙን ያዘዙበት ምክንያቱ ይህ ነው የልደትና የጥምቀት በዓል በዓል በረቡዕ ወይም በዓርብ ቀን ቢሆን በበዓለ ኃምሳ የሚበላውን የጥሉላት መብል በጥዋት በመብላት ምእመናን ሁሉ በዓሉን እንዲአከብሩ የከበሩ አባቶቻችን ሐዋርያት አዝዘዋል እሊህ ሁለቱ የእግዚአብሔር ታላላቅ በዓላቶቹ ናቸውና።
- እኛ በዚህ በኅላፊው ዓለም ተድላ ደስታ ደስ የሚለን ለሌሎች እንዳይመስላቸው እንደ አይሁድና እንደ አረማውያን በዓል በመብልና በመጠጥ ብቻ እንዳናደርግ ስለዚህ ከልደትና ከጥምቀት በዓል በዋዜማ ያሉትን ሁለቱን ዕለታት እንድንጾም አዘዙን የልደትና የጥምቀት በዓል በረቡዕና በዓርብ ላይ በሚሆን ጊዜ በረቡዕና በዓርብ ፈንታ እንድንጾማቸው ይገባልና በዚህም ሁለት ሥራ ይፈጸምልናል የጾም ሥራና የበዓል ማክበር ሥራ ነው። እንዲሁም በግብፃውያን አብያተ ክርስቲያን የተሠራ ነው።
- በይረሙን በእሑድ ወይም በአይሁድ ሰንበት ቀን ቢሆን ይህም ጌታ የተገለጸበት ጥር ዐሥራ ቀን ነው በዋዜማው ዐርብ እስከ ምሽት ይጹሙ አስቀድመን እንደተናገርን ጥሉላት አይብሉ የልደትና የጥምቀት በዓልም ሰኞ ቀን ቢሆን በሰንበት ቀን ይጾም ዘንድ አይቻልም ነገር ግን ጥሉላትን ከመብላት ይጠበቁ።
- በጥምቀትም ዕለት ከእኵለ ሌሊት በፊት ተነሥተው በውኃው ላይ ይጸልዩና ይጠመቁ ሕፃናትም በሚጠመቁ ጊዜ በውኃ እንዳይገድፉ ካህናቱም ከመንጋቱ በፊት ቀድሰው ቊርባኑን ያሳርጉ እጅግም ማልደው በጥዋት ከቤተ ክርስቲያን ይውጡ በከበረ ሥርዓታቸው ጌቶቻችን ሐዋርያት እንዳዘዙ።
- የመለካውያን ወገኖች ግን የልደትና የጥምቀት ዋዜማ በቅዳሜ ቀን ወይም በእሑድ ቀን ቢሆን በሦስት ሰዓት ይቀድሳሉ ከወደዱም የተባረከ ኅብስት ተመግበው ውኃ ይጠጣሉ ከዚህም በኋላ ካህናቱ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሁነው በየሰዓቱ በመጸለይ ለበዓሉ የሚገባውን የነቢያትን ትንቢቶች ያነባሉ በዚያች ቀን በምሽት ይኸውም ጥር ዐሥር ነው በውኃው ላይ ይጸልያሉ ይህም አባቶቻችን ሐዋርያት እንዳዘዙት አልሆነም። እርሳቸው የኤጲፋንያን በዓል እንዲአክብሩ አዘዋል ይኸውም መድኃኒታችን የተገለጠበት ካኑን በሚባል በሮም ሁለተኛ ወር በሰባት ይህ ጥር ዐሥራ አንድ ቀን ነው።
- መለካውያን ግን የከበሩ አባቶች የቤተ ክርስቲያን መምህራን ያዘዙትን ይተላለፋሉ በልደትና በጥምቀት በዓል ዓርብም ረብዕም ቢሆን አስቀድመው በርሱ ፈንታ ሳይጾሙ በጥዋት ተነሥተው ይበላሉና። እኛንም ከበደላችን ያነጻን ዘንድ በዮርዳኖስም ወንዝ እንደ ተገለጸ የጌትነቱን ክብር በልቡናችን ይገልጥልን ዘንድ የክብር ባለቤት የሆነ ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን እንለምነው ጌትነት ክብር ስግደት ለእርሱ ይገባልና ከቸር አባቱ ጋር ይቅር ባይ ከሆነ መንፈስ ቅዱስም ጋር ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ አሜን።
+ + +
- አባ ታውብንጦስ ፦ ይህም ቅዱስ ከታናሽነቱ ጀምሮ አባ ታኡና በሚባል በሮሜው ሊቀ ጳጳሳት ቤት አደገ እርሱም የምንኵስናን ልብስ አለበሰው። መንፈሳዊ ዕውቀትና ኃይል እንደተሰጠው አይቶ ከእስክንድርያ አገር ውጭ ስሙ ጤናዲራን በሚባል ቦታ ኤጲስቆጶስነት ሹሞ የገዳም አበ ምኔት አደረገው ከእርሱ ሥር ያሉ መነኰሳትም ሰባት መቶ ናቸው።
- ከዚህም በኋላ ከእርሱ ጋር ላሉ መነኰሳት አለቃ የሆነ ኤጲስቆጶስ ታውብንጦስ ከከሀዲ ንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስ ስለሆነው ሁከት በሰማ ጊዜ ሸሽቶ ወደ ደብረ ሲሐት ገዳም ሒዶ እግዚአብሔርን ከምትፈራ ከአንዲት ድንግል ዘንድ ተቀመጠ። በእርሷ ቤትም ብዙ ዘመናት ኖረ በመጀመሪያ ወደርሷ በገባ ጊዜ ግን ንጉሡን ስለ መፍራት ጣዖትን ስታመልክ አገኛትና የክብር ባለቤት ጌታችን ክርስቶስን ወደ ማመን መለሳት።
- ከዚያም ተርኑጥና መርኑስ ወደ ሚባሉ ገዳማት ሔደ የአብያተ ክርስቲያናትን ወሬ ይሰማ ዘንድ ፈልጎ በጾም በጸሎት ሌሊትም በመትጋት እያገለገለ በአንዲት ገዳም ውስጥ ሁለት ሦስት ቀን ተሠውሮ ያድር ነበር። የመንፈስ ቅዱስም ጸጋ በላዩ እንዳደረ እግዚአብሔርም በእጆቹ ድንቆች ተአምራቶችን እንዳደረገ ከወንበዴዎችና ከዓመፀኞች ብዙዎችን መነኰሳትን አድርጎ ለክርስቶስ ወደ መገዛት እስከ መላሳቸው ድረስ መነኰሳቱ ሁሉ መሰከሩለት።
- ከዚህም በኋላ ፈጽሞ በአረጀ ጊዜ የሚሞትበትን ቀን ዐወቀ ልጆቹንም የክርስቶስ በሆነች በቀናች ሃይማኖት እንዲጸኑ ትእዛዙንም እንዲጠብቁ አስተማራቸው ወዲያውኑ ጥር ፲ [10] ቀን በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ታውብጦስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
[ ምንጭ ፦ የጥር ፲ ስንክሳር ]
+ + +
"ሰላም እብል ለጾመ ዕለት ዋሕድ። ዘስሙ ገሀድ። መምህራነ ሥርዓት አቀሙ ለዘይመጽእ ትውልድ። እመባልዕት ጥሉላት ወእምነ ቅሡም ማዕድ። አንስት ይትሀረማ ወይጹሙ ዕድ። ሊቁ አርከ ሥሉስ [ አርኬ ] የጥር ፲ [10]
+ + +
- የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ ፦ "ለበስኩ ሠቀ ወኮንክዎሙ ነገረ። ላዕሌየ ይዛውዑ እለ ይነብሩ ውስተ አናቅጽ። ወኪያየ የኀልዩ እለ ይሰትዩ ወይነ"። [ መዝ.፷፰፥፲፩ ] የሚነበበው ወንጌል [ ማር.፩፥፩-፱ ]
+ + +
- የዕለቱ የቅዳሴ ምስባክ ፦ "ሣህል ወርትዕ ተራከባ። ጽድቅ ወሰላም ተሰዐማ። ርትዕሰ እምድር ሠረፀት"። [ መዝ.፹፬፥፲ ]የሚነበቡት መልዕክታት [ ገላ.፫፥፳-ፍጻሜ ] ፣ [፩ኛ ዮሐ.፬፥፲፬-፲፰] እና [የሐዋ ሥራ.፲፫፥፳፬-፴ ] የሚነበበው ወንጌል [ማቴ.፫፥፩-፲፫] ። የሚቀደሰው ቅዳሴ ቅዳሴ እግዚእነ ነው። መልካም የጾም ቀንና የከተራ በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።
🕊
[ † ጥር ፲ [ 10 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ጾመ ገሃድ
፪. አባ ታውብንስጦስ ዘሲሐት
፫. ቅዱስ ኪናርያ
፬. ቅድስት ጠምያኒ
[ † ወርሐዊ በዓላት ]
፩. ቅዱስ ናትናኤል ሐዋርያ
፪. ቅዱስ ኒቆላዎስ ዘሃገረ ሜራ
፫. አቡነ መልክዐ ክርስቶስ
፬. ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ [ወልደ እልፍዮስ]
፭. ቅድስት ዕሌኒ ንግስት
፮. ታላቁ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ
፯. ቅዱስ እፀ መስቀል
" እነርሱ እሥራኤላውያን ናቸውና:: ልጅነትና ክብር: ኪዳንም: የሕግም መሰጠት: የመቅደስም ሥርዓት: የተስፋውም ቃላት ለእነርሱ ናቸውና:: አባቶችም ለእነርሱ ናቸውና:: ከእነርሱም ክርስቶስ በሥጋ መጣ:: እርሱም ከሁሉ በላይ ሆኖ ለዘላለም የተባረከ አምላክ ነው:: አሜን::" [ሮሜ.፱፥፬]
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖 🕊 💖
🕊
[ በዚህም እጅግ ደስ ይላችኋል ! ]
" በዚህም እጅግ ደስ ይላችኋል ፥ ነገር ግን በእሳት ምንም ቢፈተን ከሚጠፋው ወርቅ ይልቅ አብልጦ የሚከብር የተፈተነ እምነታችሁ ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲገለጥ ፥ ለምስጋናና ለክብር ለውዳሴም ይገኝ ዘንድ አሁን ለጥቂት ጊዜ ቢያስፈልግ በልዩ ልዩ ፈተና አዝናችኋል።"
[ ፩ጴጥ.፩፥፮ ]
† † †
💖 🕊 💖
† † †
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
🕊 ተ ዋ ሕ ዶ ሰ ማ ያ ዊ ት 🕊
💖
[ የታቦታቱ ወደ ባሕረ ጥምቀቱ መውረድ ከክርስቶስ ወደ ባሕር መሄድ ጋር እንዴት ተገናኘ ? ]
“ ያን ጊዜ ጌታ ኢየሱስ በዮሓንስ ሊጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መጣ። [ ማቴ ፫÷፲፫ ] እንደተባለው ፦
◽️ ጌታችን ከተጸነሰባት ካደገባት ከናዝሬት ገሊላ ለመጠመቅ ወደ ዮርዳኖስ እንደሄ ታቦታትም ከማደሪያቸው ከመንበራቸው ተነስተው ወደባሕረ ጥምቀቱ ይሄዳሉ።
“ ሕዝቡም ዅሉ ከተጠመቁ በዃላ ጌታ ኢየሱስ ደግሞ ተጠመቀ። [ ሉቃ ፫÷፳፩ ] እንደተባለው ፦
◽️ጌታችን ከባሕረ ጥምቀቱ እንደደረሰ ኣልተጠመቀም ሕዝቡ ሁሉ ተጠምቀው ከጨረሱ በኋላ ነው የተጠመቀው ታቦታትም ወደ ባሕረ ጥምቀቱ እንደደረሱ ሳይሆን በተዘጋጀላቸው ቦታ ካረፉና ከቆይታ በኋላ ነው ሥርዓተ ጥመቀቱ ይፈጸማል።
“ ባሕር ዓየች ሸሸችም፥ ዮርዳኖስም ወደ ዃላው ተመለሰ። ” [ መዝ ፻፲፫፥፫ ] እንደተባለው ፦
◽️ ጌታችን ወደ ዮርዳኖስ ለመጠመቅ ሲገባ ባሕረ ዮርዳኖስ እንደሸሸች እና ለሁለትም ተከፍላ እንደ ግድግዳ እንደቆመች [ እንደተከተረች ] ዛሬም ምዕመናን ከመጠመቃቸው በፊት ውኃ በተዘጋጀው ገንዳ ውስጥ ይከተራል በመቀጠልም ጌታችንም እንደተጠመቀ ምዕመናንም የመታሰቢያ ጥምቀትን ይጠመቃሉ።
[ አምኃ ሥላሴ / መኩሪያ ተስፋዬ ]ከምናነበው የምንጠቀም ያድርገን, አሜን
╭══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╮
✥ ተ ዋ ሕ ዶ ሰ ማ ያ ዊ ት ✥
╰══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╯
† † †
💖 🕊 💖
eske 1 sat yemtlw terestalech libel?
Читать полностью…- እርሱ አነጋግሯቸው: ባርኩዋቸው ዐርጉዋል:: ለምልክትም በዓታቸው እንደ ተሰነጠቀ ቀርቷል:: ዘወትርም በዕለተ ሰንበት ይገለጥላቸው ነበር:: ቅዱሳን አባ ገዐርጊና አባ አብርሃም በርካታ ተአምራትን ሲሠሩ ኑረዋል::
- አባ አብርሃም ጥር ፱ [ 9 ] ቀን ሲያርፉ አባ ገዐርጊ ግንቦት ፲፰ [18] ቀን ዐርፎ ተቀብሯል:: በዓታቸው በግቢግም ዛሬ ድረስ በምድረ ግብጽ አለች::
አምላከ ቅዱሳን አበው በፍቅሩ ይገለጥልን:: ከአባቶቻች ጸጋ በረከትም አይለየን::
🕊
[ † ጥር ፱ [ 9 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. አባ አብርሃም ገዳማዊ
፪. አባ ገዐርጊ ጻድቅ
፫. ቅዱስ ዲዮስቅርስ ዘሮሜ
፬. አባ ኪናፎርያ
[ † ወርሐዊ በዓላት ]
፩. ቅዱሳን ፫፻፲፰ [318]ቱ ሊቃውንት
፪. አባ በርሱማ ሶርያዊ [ ለሶርያ መነኮሳት ኁሉ አባት ]
፫. አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ
፬. የብሔረ ብፁዐን ጻድቃን
፭. አባ መልከ ጼዴቅ ዘሚዳ
፮. ቅዱስ ዞሲማስ ጻድቅ
" በረከት በጻድቅ ሰው ራስ ላይ ነው:: የኀጥአንን አፍ ግን ግፍ ይከድነዋል:: የጻድቅ መታሰቢያ ለበረከት ነው:: የኀጥአን ስም ግን ይጠፋል:: " [ ምሳ.፲፥፮ ]
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖 🕊 💖
#በኹኔታዎች_የማይለወጥ_ፍቅር!
በአንድ ወቅት ቀላል ሕይወትን የሚኖር ፣ ያገኘውን የሚበላ ፣ በአቅራቢያው ካገኘው ወንዝ የሚጠጣ ፤ ከከተማ ዳርቻ ከሚገኘው ጫካ ውስጥ በጸሎት የሚተጋ አንድ ታላቅ መናኝ ነበር። ስለ መናኙ ብዙ ይወራ ስለነበር ፤ የአገሩ ንጉሥ ስለ መናኙ ስለሰማ መናኙን በአካል ማግኘት ፈለገ። መናኙ ራሱን አዋርዶ የሚኖር እዩኝ እዩኝ የማይል ከመሆኑ የተነሣ ንጉሡ በጣም ተደንቆበትና ይኼ ጠባዩ አስገርሞት ፤ በቤተ መንግሥት አብሮት እንዲኖር ለመናኙ ጥሪ አቀረበለት።
መናኙም በደስታ ወደ ቤተ መንግሥት የቀረበለትን ጥሪ ተቀበለ ፤ ንጉሡ መናኙ ግብዣውን ይቀበለው ዘንድ እርሱን ለማሳመን ብዙ እደክማለሁ ብሎ አስቦ ስለነበር ፤ በመናኙ ፈጣን መልስ ተገርሟል። ንጉሡ ምላሹን ከሰማ በኋላ ለመናኙ መቆያ የሚሆን ከመጠን በላይ ድሎት የበዛበት ምቹና የሚያስደስት ቦታን አዘጋጀለት። መናኙም ለእግዚአብሔር ያለው ፍቅሩ ሳይጎድል ፤ ወደ ቤተ መንግሥቱ ከመጣ በኋላ ኑሮውን በአጭር ጊዜ ተላምዶ ፤ የቤተ መንግሥቱን የምቾት ሕይወት ማጣጣም ጀመረ። የተቀዳደደ ልብሱን አውልቆ የከበሩ የቤተ መንግሥት አልባሳትን መልበስ ፤ የተመረጡ ምግቦችን መብላት ፤ ፍጹም የሆነ የምቾት ሕይወትን መኖር ጀመረ። በሰዎችም ፊት ራስን የመግዛት አንዳችም ምልክት አይታይበትም ነበር።
በዚህ ጊዜ ንጉሡ በሚያየው ነገር ስለ መናኙ በመጀመሪያ በነበረው እሳቤ እንደታለለ እንደተሸወደ መጠርጠር ጀመረ። ቢሆንም ግን ሀሳቡን በልቡ ይዞ ሳይናገር ቆየ። ስድስት ወራት ሆነ ፤ ሆኖም መናኙ የቅንጦት ሕይወትን ከመኖር ባለፈ አንዳች የተለየ ነገር አልታየበትም። ንጉሡም መናኙን አሁን ባየበት ማንነቱ ፤ ከዚህ ቀደም መናኙ ጫካ ውስጥ የማስመሰል ኑሮ እየኖረ ነበር ማለት ነው ፤ ብሎ አመነና ሊያነጋግረው ፈለገ። ሊነጋገሩ በተገናኙም ጊዜ ንጉሡ "በመጀመሪያ ሳገኝህ ባየሁብህ ምቾት የለሽ
ሕይወት እና ባለህ ትንሽ ፍላጎት ተደንቄ ነበር ፤ የአንተ ሕይወት ነገሮችን ሁሉ በይፋ ለመተው እንደሚቻል ምሳሌ የሚሆን ነበረ። ነገር ግን አሁን የማይብህ ነገር መጀመሪያ ካየሁብህ ፈጽሞ ተቃራኒ ነው። በቁሳዊ በዓለማዊ ደስታ ሁሉ የምትደሰት ሆነህ አግኝቼሃለሁ ፤ ስለዚህ በእኔና በአንተ መካከል ያለው ልዩነት ምንድር ነው?" አለው። መናኙም ይህን ሲሰማ ሳቀና "ይህን ጥያቄ እስክትጠይቀኝ እየጠበቅኹኝ ነበር ፤ መልሱን ነገ ጠዋት እመልስልሃለሁ" አለው። በቀጣዩ ቀን ጠዋት መናኙ ፤ ንጉሡ ፊት የቆሸሸ ቡቱቱ የተቀዳደደ ልብሱን ለብሶ ቀረበ ፤ ለንጉሡም "ወደማይታወቅ ቦታ ልሔድ ነው ፤ መልሱን እንድመልስልህ ከፈለግኽ አንተም ቤተ መንግሥትህን ፣ ቤተሰብህንና መንግሥትህን ትተህ ተከተለኝ" አለው።
ንጉሡም ደነገጠ ለመናኙም "ያንን ማድረግ እንደማልችል አንተም ታውቃለህ!" አለው። መናኙም ሳቀና "አዎ አውቃለሁ ፤ እኔና አንተ መካከል ያለው ልዩነት ይኼ ነው። ሁሉንም ደስታና ምቾት ፤ በፈለግኹ ጊዜ መተው እችላለሁ ፤ ምክንያቱም እኔ ከእነዚህ ነገሮች ጋር ተጣብቄ ያለሁ አይደለሁም ፤ አንተ ግን ከደስታና ከምቾት ጋር ተጣብቀህና ተይዘህ ነው ያለኽው ፤ አሁን ለጥያቄህ መልስ እንዳገኘህ ተስፋ አደርጋለሁ" አለው። ንጉሡ እውነትም መናኙ ታላቅ መሆኑንና በድሎት ውስጥ በቤተ መንግሥት ይህን ሁሉ ያደርግ የነበረው እርሱን ለማስተማር እንደሆነ ተረዳ ፤ መናኙም አብሮት እንዲቆይ ለመነው ፤ ነገር ግን መናኙ ከልብ ወስኖ ስለነበረ ሀሳቡን አልለወጠም። መናኙ እንደተናገረው ሊሔድ ሲል ለንጉሡ እንዲህ አለው: "አስተውል! አንተ የያዝኽው የማይጠቅም ነገር ፤ አንተንም ይይዝሃል ፤ እኔ ግን አንተ በተያዝኽበት ስላልተያዝኹኝ የምተወው ልማድ የለብኝም ፤ እኔ ከአምላኬ ጋር ነውና ያለሁት ለዘለዓለም ነፃ ነኝ" አለው።
+++
(ከክፉ) መለየት ፤ (ከኃጢአት) የመጣበቅ ተቃራኒ ነው እንጂ የእውነተኛ ፍቅርና ደስታ ተቃራኒ አይደለም!
[Detachment is the opposite of attachment, not the opposite of True Love and Enjoyment.]
+++
+ ተወዳጆች ሆይ! ዛሬ ቤተ ክርስቲያን መሔድ ሳንችል ፤ በቤታችን መቆየታችን ከእኛ ጋር መጣበቅ እና ነገ ላይ በሰላሙ ዘመን ወደ ቤተ ክርስቲያን ከመሔድ የሚያስረን የሚከለክለን መሆን የለበትም።
+
ኃጢአትን ልማድ እስኪሆን ቸል ካልነው ፤ ነገ ለመተው የማይቻል ከባድና ዋጋ የሚያስከፍል ይሆናል። ስለዚህ ኃጢአትን ልማድ ሳትሆን በጊዜ በንስሓ ከእኛ ልንለያት ይገባል።
+
ከእግዚአብሔር ጋር መሆን በምድር ላይ ካሉት ነገሮች ሁሉ የሚወዳደር አይደለም። እርሱ እግዚአብሔር "የደስታ ምንጭ" ነውና!!
+++
ውብ አሁን
† † †
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
🕊 የጥምቀት ምስጢር 🕊
💖
[ ጥምቀት በቅዱሳን ሐዋርያትና በሊቃውንት ]
† † †
❝ ለማያምኑት አልቅሱላቸው የጥምቀትን ማኅተም ሳያገኙ ለሞቱት አልቅሱላቸው። እነርሱ ከመንግሥተ ሰማያት ውጭ ናቸውና ልናለቅስላቸው ይገባናል። ሰው ከውኃና ከመንፈስ ቅዱስ ካልተወለደ በስተቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም ተብሏልና።
ጥምቀትን ለኃጢአት ሥርየት ሰጠን እንዲሁም በዚሁ በጥምቀት ከፍዳ እንድንድንና መንግሥቱን እንድንወርስ አደረገን ❞
[ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ]
❝ ማንም ሰው ካልተጠመቀ በቀር መዳንን አያገኝም ፤ በውኃ ሳይሆን በደማቸው ከተጠመቁ ከሰማዕታት በስተቀር። ጌታችን ዓለምን በመስቀሉ ባዳነ ጊዜ ጎኑን ተወጋ ፣ ያን ጊዜም ደም እና ውኃ ከጎኑ አፈለቀልን። ይህም በሰላም ጊዜ የሚኖሩ ሰዎች በውኃው ይጠመቁ ዘንድ ፣ በስደትና በመከራ ጊዜ የሚኖሩ ሰዎች ደግሞ በደማቸው ይጠመቁ ዘንድ ነው።
ሰማዕትነትን ጌታችንም ጥምቀት ብሎታል ፤ እንዲህ ሲል - እኔ የምጠጣውን ጽዋ ልትጠጡ ፣ እኔም የምጠመቀውን ጥምቀት ልትጠመቁ ትችላላችሁን? ሰማዕታት ስለ ክርስቶስ ፍቅር ደማቸውን በማፍሰስና ስለ እርሱ መከራ በመቀበል የእምነታቸውን ምስክርነት በደማቸው ይሰጣሉና። ❞
[ ቅዱስ ቄርሎስ ዘኢየሩሳሌም ]
† † †
💖 🕊 💖
🕊
" የእግዚአብሔር መንግሥት ጽድቅና ሰላም በመንፈስ ቅዱስም የሆነ ደስታ ናት እንጂ መብልና መጠጥ አይደለችምና።" [ ሮሜ.፲፬፥፲፯ ]
† † †
💖 🕊 💖
🕊
[ ከጌታ ፊት ምድር ተናወጠች ! ]
" ባሕር አየች ሸሸችም ፥ ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ። ተራሮች እንደ ኮርማዎች ፥ ኮረብቶችም እንደ ጠቦቶች ዘለሉ።
አንቺ ባሕር የሸሸሽ ፥ አንቺም ዮርዳኖስ ወደ ኋላሽ የተመለስሽ ፥ ምን ሆናችኋል ?
እናንተም ተራሮች ፥ እንደ ኮርማዎች ፥ ኮረብቶችስ ፥ እንደ ጠቦቶች ለምን ዘለላችሁ ? ከያዕቆብ አምላክ ፊት ፥ ከጌታ ፊት ምድር ተናወጠች "
[ መዝ.፻፲፬፥፬ ]
† † †
💖 🕊 💖
🕊
" አባትህን ጠይቅ ፥ ያስታውቅህማል ፤ ሽማግሌዎችህን ጠይቅ ፥ ይነግሩህማል።"
[ ዘዳ.፴፪፥፯ ]
† † †
[ እግዚአብሔርን ባለማወቅ ፣ ፈቃዱንም ባለማስተዋል ፣ በክህደት ፣ በኑፋቄ ፣ በአመጻ ሥራና ይህን በመሰሉ ጥንተ ጠላት በሚያስነሳቸው የጥፋት ነፋሳትና ማዕበላት ተወስደን እንዳንጠፋ ደገኛዋን ጥበብ የሚያስተምሩን አባቶች ሊቃውንትን በዘመኑ ሁሉ የሚሰጠን የቅዱሳን አባቶቻችን አምላክ እግዚአብሔር ይክበር ይመሥገን። ]
" ስለማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን።" [ ፪ቆሮ.፱፥፲፭ ]
† † †
💖 🕊 💖
ልደቱን ባከበረ ጊዜ ወለተ ሔሮድያዳ በዘፈን አጥምዳ አስማለችው:: እርሱም የታላቁን ነቢይ ራስ አስቆርጦ በወጪት አድርጐ ሰጣት:: አበው "እምሔሶ ለሔሮድስ ይብላዕ መሐላሁ - ሔሮድስ መሐላውን በበላ በተሻለው ነበር" ይላሉ:: የቅዱስ ዮሐንስ ራሱ በርራ ስትሔድ አካሉን ግን ደቀ መዛሙርቱ ቀብረውታል:: [ማቴ.፫፥፩ , ማር.፮፥፲፬ , ሉቃ.፫፥፩ , ዮሐ.፩፥፮]
- " አስማተ-ዮሐንስ መጥምቅ /የመጥምቁ ዮሐንስ ስሞች "
፩. ነቢይ
፪. ሐዋርያ
፫. ሰማዕት
፬. ጻድቅ
፭. ካሕን
፮. ባሕታዊ / ገዳማዊ
፯. መጥምቀ መለኮት
፰. ጸያሔ ፍኖት [መንገድ ጠራጊ]
፱. ድንግል
፲. ተንከተም [የብሉይና የሐዲስ መገናኛ ድልድይ]
፲፩. ቃለ አዋዲ [አዋጅ ነጋሪ]
፲፪. መምሕር ወመገሥጽ
፲፫. ዘየዐቢ እምኩሉ [ከሁሉ የሚበልጥ]
አምላከ ቅዱሳን በጥምቀቱ ይቀድሰን:: ከበረከተ ጥምቀቱም ያድለን::
🕊
[ † ጥር ፲፩ [ 11 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ በዓላት ]
፩. በዓለ ኤጲፋንያ
፪. ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ
፫. አቡነ ሐራ ድንግል ጻድቅ
፬. አባ ወቅሪስ ገዳማዊ
፭. አባ ዮሐንስ ሊቀ ጳጳሳት
፮. ቅዱስ እንጣልዮስ ሰማዕት
[ † ወርኀዊ በዓላት ]
፩. ቅዱስ ያሬድ ካህን
፪. ማር ገላውዴዎስ ሰማዕት
፫. ቅዱስ ፋሲለደስ ሰማዕት
፬. ቅድስት ሐና ቡርክት
" ጌታ ኢየሱስም ከተጠመቀ በኋላ ወዲያው ከውኃ ወጣ:: እነሆም ሰማያት ተከፈቱ:: የእግዚአብሔርም መንፈስ እንደ ርግብ ሲወርድ: በእርሱ ላይም ሲመጣ አየ:: እነሆም ድምጽ ከሰማያት መጥቶ :- 'በእርሱ ደስ የሚለኝ: የምወደው ልጄ ይህ ነው' አለ::" [ማቴ. ፫፥፲፮]
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖 🕊 💖
🕊
" በተቀደሰ አሳሳም እርስ በርሳችሁ ሰላምታ ተሰጣጡ። የክርስቶስ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል።" [ ሮሜ.፲፮፥፲፮ ]
[ 🕊 ተ ዋ ሕ ዶ ሰ ማ ያ ዊ ት 🕊 ]
† † †
💖 🕊 💖
" በነጻነት ልንኖር ክርስቶስ ነጻነት አወጣን ! " [ ገላ.፭፥፩ ]
Читать полностью…🕊
[ ዕ ለ ተ ከ ተ ራ ! ]
💖
እንኳን ለከተራ ክብረ በዓል በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ
[ ከተራ ምን ማለት ነው ? ]
“ ከተራ” ከተረ ከሚለው የግዕዝ ቃል የተወረሰ ሲሆን አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ “ከተረ” ፣ ወሃ ገደበ፣ ውሃ አገደ፣ ውሃ ዘጋ በማለት ወደ አማርኛ ተርጉመውታል ።
ታዲያ በየአመቱ ጥር ፲ [ 10 ] የጥምቀት ዋዜማ ዕለት ጀምበር ከመጥለቋ በፊት ቀደም ብለው የቤት ክህነት አገልጋዮች ተሰባስበው ጊዜዊ ውሃ ማጠራቀሚያ ገንዳ በመቆፈር ወይም በአቅራቢያቸው ያለውን ጅረት በመገደብ ለሚቀጥለው ጥር ፲፩ [ 11 ] የጥምቀትን ክብረ በዓል ለማክበር የሚሰበሰቡት ምዕመናን እንዲጠመቁ የመጠመቂያ ስፋራ የሚያዘጋጁበት ዕለት ነው።
በተጨማሪ በአቅራቢያ የሚገኙት ቤተክርስቲያናት ተሰብስበው ከዚሁ ከተቆፈረው ገንዳ ወይም ከተገደበው ጅረት አጠገብ ዳስ ወይም ድንኳን ጥለው ታቦቶቻቸውን ያሳድራሉ።
ቅዱሳን አባቶቻችንም በየአመቱ በከተራ ዕለት በዚሁ በአዘጋጁት የመጠመቂያ ስፍራ አጠገብ በጣሉት ጊዚያዊ ዳስ ወይም ድንኳን ውስጥ አንድ ላይ ተሰባስበው እየጸለዩ በማደር እግዚአብሔር ለነብዩ ሙሴ “የታቦት መኖር የእኔ ከእናንተ ጋር የመኖሬ ምልክት ነው” ብሎ የገለጸለትን ቃል ይፈጽማሉ።
የተባረከ ዕለተ ከተራ [ የጥምቀት ዋዜማ ] ይሁንላችሁ።
† † †
💖 🕊 💖
ጾመ ገሃድ /ጾመ ድራረ ጥምቀት/
ጾመ ገሃድ (ጋድ)፦ የቃሉ ትርጕም «ገሃድ» ሲል መገለጥ፥ «ጋድ» ሲል ለውጥ ማለት ነው። ይኸውም የአምላካችን የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ መገለጥን የምናስብበት ነው። አንድም ጋድ ተብሎም ይጠራል፤ ጥምቀት ረቡዕ፣ ዓርብ ቢውል በዚያ ለውጥ ማግሰኞና ሐሙስ ይጾማልና።
ጋድ /ጾመ ድራረ ጥምቀት/፦ ይህ ጾም የአምላካችን የጌታችንና የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ጥምቀት በማሰብ የጥምቀትን ዋዜማ ከምግብ መከልከል ነው። የሚቆርብ ሰው አክፍሎ የሚያድር ስለሆነ የጥምቀት ድራር /ዋዜማ/ ጾም ነው።
የጥምቀት በዓል በረቡዕና በዓርብ ዕለት በሚውልበት ጊዜ በረቡዕና በዓርብ ፈንታ ማግሰኞንና ሐሙስን በመጾማችን ሁለት ሥራ ይፈጸምልናል። በዚህም የጾምና የበዓል ማክበር ይከናወንልናል።
የጥምቀት ዋዜማ ሰኞ፣ ማግሰኞ፣ ሐሙስ ከሆነ ጾም ነው፤ በአጋጣሚ ደግሞ ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ ከጥሉላት ምግቦች ብቻ ይጾማል። ሆኖም ጥምቀት በየትኛውም ዕለት ቢውል በየዓመቱ ሁልጊዜ የጥምቀትን ዋዜማ እስከ ዕርበተ ፀሐይ እንጾም ዘንድ አባቶቻችን በረከታቸው ይደርብንና ከሰባቱ አጽዋማት አንዱ ይሆን ዘንድ ሥርዓትን ሠርተውልናል።
ስለሆነም በ2016 ዓ.ም የጌታችን በዓለ ጥምቀት ጥር 11 ቀን በዕለተ ቅዳሜ ስለሆነ ጾመ ጋድ /ገሃድ/ ጥር 10 ቀን 2016 ዓ.ም በዕለተ አርብ ይሆናል ማለት ነው። ዕለተ አርብ ራሱን የቻለ የጾመ ድኅነት ቀን ሲሆን በዚህ ዓመት ጾመ ገሃድ በዚህ ዕለት ውሏልና ዕለቱ ጾመ ድኅነትና ጾመ ገሃድ የተገጣጠሙበት ዕለት ሆኗል።
ምንጭ፡
- የጽድቅ በር /አለቃ አያሌው ታምሩ/
- ሰባቱ አጽዋማትና ታሪኮቻቸው /በመ/ር ኃ/ሚካኤል ተፈራ/
@MikreAbew
+• እግዚአብሔር ይይልህ •+
በአንድ ወቅት አንድ የምንወደውን የቤተክርስቲያን አገልጋይ “እግዚአብሔርን ብታየው ምን ትለዋለህ?” ብዬ ጠየቅሁት። እርሱም “እኔ ከማየው፥ እርሱ ቢያየኝ እመርጣለሁ” አለኝ። የመልሱ ብስለት እስከዛሬ ይደንቀኛል።
የሀገራችን ሰው ክፉኛ ሲማረር “እግዚአብሔር ይይልህ” ይላል። ይህ ምርቃትም እርግማንም ነው። በበጎ ሥራ ለሚተጋ ሰው፥ በእግዚአብሔር መታየት ክብሩ ነው። የልባችን እምነት፥ የጸለይነው ጸሎት፥ የሰገድነው ስግደት፥ የጾምነው ጾም፥ የመጸወትነው ምጽዋት ሁሉ በእግዚአብሔር ካልታየ ከንቱ ነው። በዚያው ልክ፥ ጠብን ለሚዘራ አንደበት፥ ሤራን ለሚተበትብ እጅ፥ ክፉ ሀሳብን ለሚፈትል አእምሮ ደግሞ በእግዚአብሔር መታየቱ የፍርድ ዋዜማ ነው። ጻድቅ በእግዚአብሔር መታየትን ሲናፍቅ፥ ኃጢአተኛ ደግሞ ከእግዚአብሔር እይታ ሲሸሽ ይኖራል።
በዘፍጥረት ላይ የመጀመሪያው ቀናተኛ ሰው ታሪክ ተጽፎ ይገኛል። ቃየን እና አቤል የተሰኙት ወንድማማቾች ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ማቅረብ ፈለጉ። ቃየን ገበሬ ስለነበረ ከምድር ፍሬ፥ አቤል ደግሞ መልካም እረኛ ስለነበረ ከበጎቹ መርጦ መሥዋዕታቸውን አቀረቡ። የመሥዋዕታቸውን ውጤት መጽሐፍ ቅዱስ ሲነግረን “እግዚአብሔር ወደ አቤልና ወደ መሥዋዕቱ ተመለከተ፥ ወደ ቃየንና ወደ መሥዋዕቱ ግን አልተመለከተም።” (ዘፍ 4፡4) ይለናል።
እግዚአብሔር መሥዋዕትህን ሲያይ፥ አንተንም አብሮ ያይሃል። መዝሙረኛው “እነሆ፥ የእግዚአብሔር ዓይኖች ወደሚፈሩት ናቸው፥ በምሕረቱም ወደሚታመኑ” (መዝ 33፡18) ይላል። እግዚአብሔር ልብን እና ኩላሊትን የሚመረምር አምላክ ስለሆነ፥ የቃየንን መሥዋዕት እና መሥዋዕቱን አግበስብሶ ያቀረበውን ቃየንን ቸል አለ፥ የአቤልን መሥዋዕት እና መሥዋዕቱን መርጦ ያቀረበውን አቤልን ግን ተመለከተ። ቃየን በዚህ ተናደደ፥ ዓይኑ ደም ለበሰ፥ ፊቱም ጠቆረ፥ ወንድሙን በመግደልም የዓለማችን የመጀመሪያው ነፍሰ ገዳይ ሆነ።
በእግዚአብሔር የታየው አቤል ሲሞት ግን ሞቱ ተዳፍኖ አልቀረም። እግዚአብሔር ቃየንን “ምን አደረግህ? የወንድምህ የደሙ ድምጽ ከምድር ወደ እኔ ይጮኻል።” (ዘፍ 4፡10) ብሎ ጠይቆታል። አንተ በእግዚአብሔር የታየህ ስትሆን፥ ሞተህም ቢሆን የደምህ አቤቱታ በእግዚአብሔር ፊት ይታይልሃል። እግዚአብሔር ያየህ ስትሆን፥ ቃልህን ገድበኸው ስንኳ ዝምታህ በእርሱ ፊት ይጮሃል። በእግዚአብሔር ዓይን ሚዛን ሲኖርህ፥ ሕይወትህ ጭጭ ቢል ስንኳ ሞትህ ይናገራል። ፍርድ ለጊዜው የዘገየ ቢመስልም፥ ቃየንም ቢሆን የወንድሙ ደም እንዳቅበዘበዘው በከንቱ ሞቷል።
በዓለማዊ ውጣ ውረድህም ሆነ በመንፈሳዊ አገልግሎትህ የሰውን ዓይን አትፈልግ። ምንም ይሁን ምን፥ መሥዋዕትህን ሲያይ አንተንም አብሮ የሚያይ እግዚአብሔር ብቻ ይይልህ!
🖋 Fresenbet G.Y Adhanom
----------
የፌስቡክ ገጽ: https://www.facebook.com/fre.asalib
ቴሌግራም: /channel/fresenbett
ቲክቶክ: fr3senbet?_t=8eAM1NzgeQw&_r=1" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@fr3senbet?_t=8eAM1NzgeQw&_r=1
🕊
[ የምወደው ልጄ ! ]
💖
" የእግዚአብሔር መሥዋዕት የተሰበረ መንፈስ ነው ፥ የተሰበርውንና የተዋረደውን ልብ እግዚአብሔር አይንቅም።" [ መዝ.፶፩፥፲፯ ]
" እግዚአብሔር ፥ ቅዱሳንን ስላገለገላችሁ እስከ አሁንም ስለምታገለግሉአቸው ፥ ያደረጋችሁትን ሥራ ለስሙም ያሳያችሁትን ፍቅር ይረሳ ዘንድ ዓመፀኛ አይደለምና።" [ ዕብ.፮፥፲ ]
† † †
💖 🕊 💖
† † †
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
🕊 ሰ ማ ያ ት ተ ከ ፈ ቱ 🕊
💖
[ " አንዲት ጥምቀት " [ ኤፌ.፬፥፭ ] ]
🕊
ምስጢረ ጥምቀት ከአምስቱ አዕማደ ምስጢራት መካከል አንዱ ነው፡፡
ምስጢረ ጥምቀትን የመሠረተልን ለሥም አጠራሩ ክብር ምስጋና ይግባውና ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ አምላካችን በጥምቀቱ ፦
፩. በተግባር በመጠመቅ ጥምቀት ለፍጥረታዊው ሰው አስፈላጊ መሆኑን
፪. በውኃ በመጠመቅ ማያት [ ውሆች ] ዳግመኛ የምንወለድባቸው ማኅፀኖች ይሆኑ ዘንድ ኃይልን ሰጣቸው
፫. ጌታችን መጠመቅ ሳይኖርበት ስለ እኛ ሲጠመቅ ምስጢረ ሥላሴ ተገልጦ የባህርይ አባቱ አብ ልጅነቱን እንደመሰከረለት እኛም ስንጠመቅ ከእርሱ ዳግመኛ መወለዳችንና የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችን ይመሠክርልናል፡፡
፬. እርሱ ሲጠመቅ " ሰማያት ተከፈቱ " እንደተባለ በጥምቀቱ አገራችን በሰማይ መሆኑን የአገራችንን በር ከፍቶ አሳየን ፤ የምንጠመቀው ያንን ሰማያዊ ሀገር ለመውረስ የሚያበቃ ልጅነት ለማግኘት መሆኑን በተግባር አሳየን፡፡
† † †
💖 🕊 💖
† † †
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
🕊 ጾ መ ገ ሃ ድ 🕊
💖
[ ጾመ ገሃድ /ጾመ ድራረ ጥምቀት/ ]
ጾመ ገሃድ [ ጋድ ] ፦ የቃሉ ትርጕም "ገሃድ" ሲል መገለጥ ፥ " ጋድ " ሲል ለውጥ ማለት ነው። ይኸውም የአምላካችን የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ መገለጥን የምናስብበት ነው። አንድም ጋድ ተብሎም ይጠራል ፤ ጥምቀት ረቡዕ ፣ ዓርብ ቢውል በዚያ ለውጥ ማግሰኞና ሐሙስ ይጾማልና።
ጋድ [ ጾመ ድራረ ጥምቀት ] ፦ ይህ ጾም የአምላካችን የጌታችንና የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ጥምቀት በማሰብ የጥምቀትን ዋዜማ ከምግብ መከልከል ነው። የሚቆርብ ሰው አክፍሎ የሚያድር ስለሆነ የጥምቀት ድራር [ ዋዜማ ] ጾም ነው።
የጥምቀት በዓል በረቡዕና በዓርብ ዕለት በሚውልበት ጊዜ በረቡዕና በዓርብ ፈንታ ማግሰኞንና ሐሙስን በመጾማችን ሁለት ሥራ ይፈጸምልናል። በዚህም የጾምና የበዓል ማክበር ይከናወንልናል።
የጥምቀት ዋዜማ ሰኞ ፣ ማግሰኞ ፣ ሐሙስ ከሆነ ጾም ነው ፤ በአጋጣሚ ደግሞ ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ ከጥሉላት ምግቦች ብቻ ይጾማል። ሆኖም ጥምቀት በየትኛውም ዕለት ቢውል በየዓመቱ ሁልጊዜ የጥምቀትን ዋዜማ እስከ ዕርበተ ፀሐይ እንጾም ዘንድ አባቶቻችን በረከታቸው ይደርብንና ከሰባቱ አጽዋማት አንዱ ይሆን ዘንድ ሥርዓትን ሠርተውልናል።
† † †
💖 🕊 💖
🕊
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ አምላክ ፡፡ አሜን ። †
" እንኩዋን ለአበው "ቅዱሳን አባ አብርሃም ወአባ ገዐርጊ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ "
🕊 † ቅዱሳን አብርሃም ወገዐርጊ † 🕊
† ተጋድሎተ ቅዱሳን †
- ቅዱሳኑን የመሰሉ አባቶች "መስተጋድላን" ይባላሉ በግዕዙ:: ለሃይማኖታቸው እስከ ደም ጠብታና እስከ መጨረሻዋ ህቅታ ድረስ መጋደላቸውን የሚያሳይ ነው:: መጋደል ጐዳናው ብዙ ዓይነት ነው::
- ከራሱ ጋር የሚጋደል አለ:: ከዓለም ጋር የሚጋደልም አለ:: የቅዱሳኑ ተጋድሎ ግን በዋነኝነት ከ፪ አካላት ጋር ነው:: በመጀመሪያ ፍትወታት እኩያትን [ ኃጣውዕን ] ከሚያመጡ አጋንንት ጋር ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ "ሃይማኖቸታችሁን ካዱ: ለጣዖትም ስገዱ" ከሚሉ ከሃድያን ጋር የሚደረግ ትግል ነው::
- በተለይ ፪ኛው እስከ ሞት የሚያደርስ ውሳኔን ይጠይቃል:: የዚህን ቅዱስ ሕይወት ለመረዳት ግን አንድ ነገርን ልብ እንድትሉልኝ እፈልጋለሁ::
- ያለንበት ዘመን ክርስትና በራድ [ ቀዝቃዛ ] በመሆኑ የቀደሙ አባቶች የጸና ተጋድሎ አንዳንዴ ግራ ሲያጋባን ተመልክቻለሁ:: ቅዱሳኑ ሁሌም አንድ ነገርን እያሰቡ ይኖራሉ:: ይኼውም በዘመኑ በርካቶቻችን የረሳነው: ወይም ማስታወስ የማንፈልገው ነገር ይመስላል::
- ሰማያዊው አምላክ ከዙፋኑ ወርዶ በተዋሐደው ሥጋ በቃል ሊገለጽ የማይችል መከራን ስለ እኛ ተቀብሏል:: ክርስትና ማለት ቀራንዮን በልብ ውስጥ መሳል ነው:: ፍቅረ መስቀሉን: የጌታንም ውለታ የሚያስብ ማንኛውም ሰው: የትኛውም ዓይነት መከራ ቢመጣበት አይታወክም::
- ቅዱሳኑም የፍቅራቸውና የትእግስታቸው ምሥጢር ይኼው ነው:: ጌታችን "የሚወደኝ ቢኖር የሞቱን መስቀል ተሸክሞ ይከተለኝ" [ማቴ.፲፮፥፲፰] እንዳለው ቅዱሳኑ ይህንን ቃል በቃል ሲፈጽሙት እነሆ እንመለከታለን::
† ገዳማዊ ሕይወት †
- ገዳማዊ ሕይወት ጥንቱ ብሉይ ኪዳን ነው:: በቀዳሚነትም በደብር ቅዱስ አካባቢ ይኖሩ የነበሩ ደቂቀ ሴት እንደ ጀመሩት ይታመናል:: ሕይወቱ በጐላ: በተረዳ መንገድ የታየው ግን በታላቁ ጻድቅ ሄኖክ: ከዚያም በቅዱሱ ካህን መልከ ጼዴቅ አማካኝነት ነው::
- ቀጥሎም እነ ቅዱስ ኤልያስ ነቢይ: እነ ኤልሳዕ ደቀ መዝሙሩ ኑረውበታል:: በሐዲስ ኪዳን ደግሞ ሙሉ ሕይወቱን በገዳም [ በበርሃ ] ያሳለፈው መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ቅድሚያውን ይይዛል::
- ለስም አጠራሩ ስግደት ይሁንና መድኃኒታችን ክርስቶስ በገዳመ ቆረንቶስ ለ፵ [ 40 ] ቀናት በትሕርምት ኑሮ ገዳማዊ ሕይወትን ቀድሷል: አስተምሯል:: በዘመነ ስብከቱም ያድርባት የነበረችው የደብረ ዘይቷ በዓቱ [ ኤሌዎን ዋሻ ] በራሷ ለዚህ ሕይወት ትልቅ ማሳያ ናት::
- ከጌታ ዕርገት በሁዋላም ክርስቲያኖቹ የዓለም ሁካታ ሲሰለቻቸው: አንድም በንጹሕና በተሸከፈ ልቡና ለፈጣሪያቸው መገዛትን ሲሹ ከከተማ ወጣ እያሉ ይኖሩ እንደ ነበር የታሪክ መዛግብት ያሳያሉ:: አኗኗራቸውም በቡድንም: በነጠላም ሊሆን ይችላል::
- ዋናው ነገር ግን በጾምና በጸሎት መትጋታቸው ነው:: ይሕም ሲያያዝ እስከ ፫ኛው መቶ ክ/ዘመን ደረሰ:: በዚህ ዘመን ግን አባ ዻውሊ የሚባል አንድ ንጹሕ ክርስቲያን ይሕንን ሕይወት ወደ ሌላ ደረጃ ከፍ አደረገው:: ለ፹ [ 80 ] ዓመታት ሰው ሳያይ ተጋድሎ "የባሕታውያን አባት" ተባለ:: ደንብ ያለው ተባሕትዎም ጀመረ::
- ይህ ከሆነ ከ፳ [ 20 ] ዓመታት በሁዋላ ደግሞ አባ እንጦንስ የሚባሉ ደግ ክርስቲያን ይህንን ገዳማዊ ሕይወት በሌላ መንገድ አጣፈጡት:: በቅዱስ ሚካኤል አመንኩዋሽነት ገዳማዊ ሕይወት በምንኩስና ተቃኘ:: ስለዚህም አባ እንጦንስ የመነኮሳት አባት ተባሉ::
- እርሳቸውም ሕይወቱን ለማስፋፋት ከተለያዩ አሕጉር ደቀ መዛሙርትን እየተቀበሉ አመንኩሰዋል:: ቅዱሳን የአባ እንጦንስ ልጆችም ወደየ ሃገራቸው ተመልሰው: ሕይወቱን በተግባር አሳይተው ገዳማዊነትን አስፋፍተዋል::
- አባ እንጦንስ አባ መቃርስን: አባ መቃርስ አባ ዮሐንስን ወልደዋል:: አባ ዮሐንስም የታላቁ ገዳመ አስቄጥስ አበ ምኔት ሆነው በጸጋ አገልግለዋል:: አስቄጥስ በምድረ ግብጽ የሚገኝ: በስፋቱና ብዙ ቅዱሳንን በማፍራቱ ተወዳዳሪ የሌለው የዓለማችን ቁጥር አንድ ገዳም ነው::
- ሕይወተ ምንኩሰናም ወደ መላው ዓለም የተስፋፋ በዚህ ገዳም መናንያን አማካኝነት ነው:: በዚህ ገዳም ላይ የሚሾሙ አበው ደግሞ በብዛት መንፈስ ቅዱስ ያደረባቸውና አባታቸውን ቅዱስ መቃርስ ታላቁን የመሰሉ ናቸውና ኃላፊነቱ እጅግ ከባድ ነው::
- በ፭ [5] ኛው መቶ ክ/ዘመን በምድረ ግብጽ ተወልደው ያደጉት አባ ዮሐንስ ከመነኑባት ዕለት ጀምረው በፍጹም ተጸምዶና ተጋድሎ ለፈጣሪያቸው ስለ ተገዙ የታላቁ ገዳም አበ ምኔት ሊሆኑ ተገባቸው::
- በአበ ምኔትነት ዘመናቸውም መንጋውን ይጠብቁ ዘንድ ብዙ ደከሙ:: በተለይ ቅዱስ ቃሉን ያስተምሩ ዘንድ ተጉ:: ሕይወተ መላእክትንም ያሳዩ ዘንድ በቃል ብቻ ያይደለ በተግባር ሆነው : ከመንፈሳዊ አብራካቸው ብዙ ቅዱሳንን ወለዱ::
- ከዋክብቱ አባ ገዐርጊ: አባ አብርሃም: አባ ሚናስ: አባ ዘካርያስ . . . የአባ ዮሐንስ ፍሬዎች ናቸውና:: ጻድቁ በዘመናቸው ብዙ ተአምራትን ሠርተዋል:: ከዕረፍታቸው በሁዋላ እንኩዋ መግነዛቸውና የልብሳቸው እራፊ ብዙ ድውያንን ፈውሷል::
† 🕊 ቅዱሳን አብርሃም ወገዐርጊ 🕊 †
- እነዚህ ፪ ቅዱሳን በግብጽ በርሃ ያበሩ የቅዱሱ አባ ዮሐንስ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቹ ናቸው:: አስቀድሞ ወደ በርሃ የወጣ አባ አብርሃም ሲሆን እርሱም በምድረ ግብጽ የተባረኩ ሰዎች ልጅ ነው::
- ወላጆቹ በፈቃደ እግዚአብሔር እርሱን ከወለዱ በሁዋላ ብዙ በጐነትን አሳይተዋል:: ዘመኑ ዘመነ ዐጸባ [ የችግርና የረሃብ ጊዜ ] ነበርና ሃብታቸውን በምጽዋት ጨርሰዋል:: የሚገርመው የቅዱሱ አባት "ነዳያን እየተራቡ ዝም አልልም" ብሎ እየተበደረ ያበላቸው ነበር::
- እርሱ ባረፈ ጊዜም የተባረከች ሚስቱ መልካምን እየሠራች ብዙ ተፈትናለች:: ለባርነት ተማርካ እስክትሔድ ድረስም ታግሣለች:: ቅዱሱን ልጇን አብርሃምንም እንደሚገባ አሳድጋ "ሚስት ላጋባህ" አለችው::
- እርሱ ግን "እናቴ ሆይ! እኔ ይህንን ዓለም አልፈልገውም" ሲል መለሰላት:: ይህንን ስትሰማም ሐሴትን አድርጋ አብርሃምን ወደ በርሃ ሸኘችው:: አባ አብርሃምም ወደ ገዳመ አስቄጥስ ሔዶ በደብረ አባ መቃርስ መነኮሰ:: ተጋድሎንም በዚያው ጀመረ::
- ሲጾም: ሲጸልይ: ሲጋደልም ዘመናት አለፉ:: በዚህ ጊዜም ታላቁ አባ ገዓርጊ ከዓለም ወደ በርሃ መጥቶ መነኮሰ:: የአባ ዮሐንስ የመንፈስ ልጆች ውስጥም እንደ አንዱ ተቆጠረ:: አባ ገዐርጊን የተመለከተው አባ አብርሃምም ስለ ወደደው አብረው መኖር ጀመሩ::
- ፪ቱ ቅዱሳንም "በግቢግ" በምትባል በዓታቸው በፍቅር ለፈጣሪያቸው ሲገዙ ዘመናት አለፉ:: በነዚህ ዘመናትም በርካታ ቅዱሳን ከመንፈሳዊ አብራካቸው አፈሩ ከቅድስናቸው ብዛትም ከሰንበት በቀር እህልን አይቀምሱም ነበር::
- የክብር ባለቤት መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም አንድ ቀን ከዓለት በተወቀረች በዓታቸው ውስጥ በጸሎት ላይ ሳሉ ወረደላቸው:: የበዓታቸውን ዓለት ሰንጥቆ ሲገባ ታላቅ ግርማና ብርሃን አካባቢውን ዋጠው:: ቅዱሳኑም ለመድኃኒታችን ተደፍተው ሰገዱ::
🕊
በነጻነት ልንኖር ዘንድ ክርስቶስ ነጻ አወጣን !
[ ገላ.፭፥፩ ]
-------------------------------------------
[ በዓለ ጥምቀቱን እንዴት እናክብር ? ]
" ነገር ግን እላለሁ ፥ በመንፈስ ተመላለሱ ፥ የሥጋንም ምኞት ከቶ አትፈጽሙ። ... በመንፈስ ብትመሩ ግን ከሕግ በታች አይደላችሁም።
የሥጋ ሥራም የተገለጠ ነው እርሱም ዝሙት ፥ ርኵሰት ፥ መዳራት ፥ ጣዖትን ማምለክ ፥ ምዋርት ፥ ጥል ፥ ክርክር ፥ ቅንዓት ፥ ቁጣ ፥ አድመኛነት ፥ መለያየት ፥ መናፍቅነት ፥ ምቀኝነት ፥ መግደል ፥ ስካር ፥ ዘፋኝነት ፥ ይህንም የሚመስል ነው። አስቀድሜም እንዳልሁ ፥ እንደዚህ ያሉትን የሚያደርጉ የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም።
የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር ፥ ደስታ ፥ ሰላም ፥ ትዕግሥት ፥ ቸርነት ፥ በጎነት ፥ እምነት ፥ የውሃት ፥ ራስን መግዛት ነው።" [ ገላ.፭፥፲፮-፳፪ ]
† † †
" በክርስቶስ ያለውን መልካሙን ኑሮአችሁን የሚሳደቡ ሰዎች ክፉን እንደምታደርጉ በሚያሙበት ነገር እንዲያፍሩ በጎ ሕሊና ይኑራችሁ።" [ ፩ጴጥ.፫፥፲፮ ]
† † †
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
🕊
[ የታቦት ሥራ አለብን ! ]
💖
" የእምነታችሁን ስራ የፍቅራችሁንም ድካም በጌታችንም በኢየሱስ ክርስቶስ ያለውን የተስፋችሁን መጽናት በአምላካችንና በአባታችን ፊት ሳናቋርጥ እያሰብን ፥ እግዚአብሔርን ሁል ጊዜ በሁላችሁ ምክንያት እናመሰግናለን "
[ ፩ ተሰ. ፩፥፪ ]
† † †
💖 🕊 💖