mikreabew | Unsorted

Telegram-канал mikreabew - ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

874

"እንግዲህ፡ንስሓ፡ግባ፤አለዚያ፡ፈጥኜ፡ እመጣብሃለሁ፡፡" ራዕ 2፥16

Subscribe to a channel

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

                         †                         

🕊 የዐቢይ ጾም አምስተኛ ሳምንት 🕊 ]

     †     [      ደብረ ዘይት     ]       †

🕊                       💖                   🕊

አምስተኛው የዐቢይ ጾም ሳምንት ‹ደብረ ዘይት› ይባላል፡፡

ስያሜው የተወሰደውም ከማቴዎስ ወንጌል ፳፬፥፫ ካለው ትምህርት ነው፡፡ ደብረ ዘይት ከኢየሩሳሌም በስተምሥራቅ አቅጣጫ የሚገኝ በወይራ ዛፎች የተሸፈነ ትልቅ ተራራ ነው፡፡ ጌታችን ምሥጢራትን በተለያየ ቦታ ገልጧል፡፡

ምሥጢረ ጸሎትን በጌቴሴማኒ ፤ ምሥጢረ መንግሥቱን በደብረ ታቦር ፤ ምሥጢረ ቊርባንን በቤተ አልዓዛር ፤ ምሥጢረ ትንሣኤ ሙታንን በቤተ ኢያኢሮስ ፤ ምሥጢረ ምጽአቱን ደግሞ በደብረ ዘይት ገልጧል፡፡

ደብረ ዘይት ጌታችን ዳግም ለፍርድ መምጣቱንና ምሥጢረ ምጽአቱን ለደቀ መዛሙርቱ በሚገባ የገለጠበት ዕለት ነው፡፡ ደብረ ዘይትን ጌታችን በመዋዕለ ስብከቱ ለማደሪያነት ተጠቅሞበታል፡፡

ቀን ቀን በምኲራብ ያስተምራል ፤ ሌሊት ሌሊት ደግሞ በደብረ ዘይት ያድራል፡፡ ይህንም ቅዱስ መጽሐፍ እንዲህ በማለት ይመሰክራል ፤ "ዕለት ዕለት በመቅደስ ያስተምር ነበር፡፡ ሌሊት ግን ደብረ ዘይት ወደምትባል ተራራ ወጥቶ ያድር ነበር፡፡ ሕዝቡ ዅሉ ይሰሙት ዘንድ ማልደው በመቅደስ ወደ እርሱ ይመጡ ነበር" [ሉቃ. ፳፩፥፴፯]፡፡ በዚህ ለማደሪያነት ባገለገለው ተራራ ምሥጢረ ምጽአቱን ስለ ገለጠበት አምስተኛው የዐቢይ ጾም ሳምንት ደብረ ዘይት የሚል ስያሜ ተሰጥተታል፡፡

ደብረ ዘይት ጾሙ እኩል የሚኾንበት ፤ አምላካችን በግርማ መንግሥቱ ለፍርድ በመጣ ጊዜ መልካም ለሠሩ ክብርን ፣ ክፉ ለሠሩ ቅጣቱን የሚያስተላልፍ መኾኑ የሚነገርበት ፤ ስለ ዓለም መጨረሻ እና ስለሚመጣው ሕይወት የምንማርበት የክርስቲያኖች ማስጠንቀቂያ ዕለት ነው፡፡

[ በመምህር ምሥጢረ ሥላሴ ማናየ ]


🕊                       💖                   🕊

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

🕊

[ † እንኳን ለታላቁ ክርስቲያናዊ ንጉሥ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ]

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †

🕊  †  ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ †   🕊

† ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ ለቤተ ክርስቲያን የፈፀመውን መልካም ተግባር ያሕል መሥራት የቻለ ንጉሥ በሐዲስ ኪዳን የለም:: ጻድቁ ንጉሥ ከቅድስት እናቱ እሌኒና ከአረማዊ አባቱ ቁንስጣ በበራንጥያ ተወለደ::

ዘመኑ ዘመነ ዐጸባ [የመከራ ጊዜ] ወይም የሰማዕታት ዘመን በመሆኑ ክርስቲያኖች በግፍ የሚጨፈጨፉበት ወቅት ነበር:: ክርስቲያኖችን ከምድረ ገፅ ለማጥፋት በተደረገው የ፵ [40] ዓመታት ዘመቻ አብያተ መቃድስና መጻሕፍት ተቃጠሉ:: ብዙዎቹ በየበርሃው ተሰደዱ:: ሚሊየኖች በግፍ አለቁ::

የዚሕን ዘመን መከራ በውል ያልተረዳ ሰው ቅዱስ ቆስጠንጢኖስን ሊያከብር አይችልም:: ምክንያቱም ይህን የመከራ ዘመን በፈቃደ እግዚአብሔር አስቁሞ : ቀርነ ሃይማኖት የቆመው : ብዙ ሥርዓት የተሠራው : ቤተ ክርስቲያንም ያበራችው በዘመኑ ነውና::

ቅዱሱ ንጉሥ ለሁሉም ነቢያት : ሐዋርያትና ሰማዕታት አብያተ ክርስቲያናትን ራሱ በመሠረታት በቁስጥንጥንያ አንጿል:: በዘመኑ ቤተ ክርስቲያን በሰላም ኖራለት : በኃይለ መስቀሉ ጠላት ጠፍቶለት ኑሮ በዚህች ቀን አርፏል:: "ቆስጠንጢኖስ" ማለት "ሐመልማል" ማለት ነው::

††† ዳግመኛ በዚሕ ቀን የዓለማት ፈጣሪ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ እኛ በሆነው ሞቱ በመቃብር ውስጥ አድሯል::

††† ጌትነት ያለው አምላካችን በይቅርታው ይጐብኘን:: መልካም መሪንም ይስጠን::

🕊

† መጋቢት ፳፰ [ 28 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት

፩. ታላቁ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ (ጻድቅ ንጉሥ)
፪. ቅድስት እሌኒ ንግስት

[ † ወርኀዊ በዓላት ]

፩. አማኑኤል ቸር አምላካችን
፪. ቅዱሳን አበው [አብርሃም: ይስሐቅና ያዕቆብ]
፫. ቅዱስ እንድራኒቆስና ሚስቱ ቅድስት አትናስያ
፬. ቅድስት ዓመተ ክርስቶስ
፭. ቅዱስ ቴዎድሮስ ሮማዊ [ሰማዕት]

† " እንግዲህ እግዚአብሔርን በመምሰልና በጭምትነት ሁሉ: ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖር: ልመናና ጸሎት: ምልጃም: ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ: ስለ ነገሥታትና መኳንንትም ሁሉ እንዲደረጉ ከሁሉ በፊት እመክራለሁ:: ሰዎች ሁሉ ሊድኑና እውነቱን ወደ ማወቅ ሊደርሱ በሚወድ በእግዚአብሔር በመድኃኒታችን ፊት መልካምና ደስ የሚያሰኝ ይህ ነው::" † [፩ጢሞ. ፪፥፩-፬

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

ዓርብ - መጋቢት 27 2016 ዓም    

ሮሜ 6-10

ሰላም ለሁላችሁ ይሁን! በዛሬው የዐቢይ ጾም ንባባችን የሮሜ መልእክትን 6-10 ድረስ እናነባለን።  

ከንባብ በፊት የሚደረግ ጸሎት፡ “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፤ የአንተን ቃላት እሰማ እና እረዳ ዘንድ፥ እንዲያውም ፈቃድህን ለመፈጸም እበቃ ዘንድ የልቤን ጆሮዎች እና ዓይኖች ክፈትልኝ።” (ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ)  

*የክለሳ ጥያቄዎች*

1) ቅዱስ ጳውሎስ ከክርስቶስ ጋር በሞቱና በትንሣኤው ስለመተባበር ምን ይላል? (ሮሜ 6)

2) የሰው ልጅ ለሚታዘዝለት ነገር ባሪያ መሆኑ የተገለጸው እንዴት ነው? ከመንፈሳዊ ሕይወት ጋር አዛምዳችሁ መልሱ። (ሮሜ 6)

3) ቅዱስ ጳውሎስ ሕግ ኃጢአትን አጉልታ እንደምታሳይ ያስረዳው ምን ብሎ ነው? (ሮሜ 7)

4) ቅዱስ ጳውሎስ ሳይፈልጉ ለኃጢአት ተገዢ ሆኖ ስለመገኘት ምን ይላል? (ሮሜ 7)

5) ቅዱስ ጳውሎስ ስለ ሥጋ እና መንፈስ ማሰብን በምን መልኩ አነጻጸረው? (ሮሜ 8)

6) ብርቱ ክርስቲያን ከክርስቶስ ፍቅር አይለዩትም ተብለው የተዘረዘሩት ነገሮች ምንድር ናቸው? (ሮሜ 8)

7) ቅዱስ ጳውሎስ ከሆሴዕ ትንቢት የጠቀሰው ቃል ምን ይላል? (ሮሜ 9)

8) ቅዱስ ጳውሎስ በአሕዛብ እና በአይሁዱ ዙሪያ ያነሳው ንጽጽር ምንድር ነው? (ሮሜ 9)

9) የሕግ ፍጻም ማን ነው? (ሮሜ 10)

10) ቅዱስ ጳውሎስ ለመዳን ስለሚያስፈልገው እምነት እና ምስክርነት ምን አለ? (ሮሜ 10)

መልካም ንባብ!
/channel/c/2014228571/1

@OrthodoxTewahdoBooks

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

                      †                       

[      🕊  መድኃኔ  ዓለም   🕊     ]

† እንኳን ለጌታችንና አምላካችን መድኃኔ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ዓመታዊ የስቅለት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። †

🕊                       💖                   🕊

" ይትፌሣሕ ሰማይ ወትትሐሠይ ምድር ወይንፍሑ ቀርነ መሠረታተ ሕምዝ ወይወውዑ አድባር ወአውግር ወኵሉ ዕፀወ ገዳም ወዮምሰ ዓባይ ፍሥሐ በሰማያት ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ ተሐፂባ በደመ ክርስቶስ ፤ "

ትርጉም ፦ [ ሰማይ ደስ ይለዋል ፣ ምድር ፍስሐን ታደርጋለች የምድር መሠረቶችም መለከትን ይነፋሉ ፣ ተራሮችና ኮረብቶችም ይነዋወጣሉ ፣ ሁሉም የበረሃ ዛፎችም [ይነዋወጣሉ] በሰማያትም ዛሬ እጅግ ትልቅ ደስታ ይደረጋል፣ ምድርም በክርስቶስ ደም ታጥባ ፋሲካን [ በከርስቶስ ደም በተገኘ ማዕዶት የተገኘ ደስታን ] ታደርጋለች። ]

[ ድጓ ዘፋሲካ ]

🕊                       💖                   🕊

" ብርሃን ዘመጽአ ውስተ ዓለም ዘያበርህ ላዕለ ጻድቃን መርአዊሃ ለቤተ ክርስቲያን ይርዳዕ ዘተኃጕለ ያስተጋብእ ዝርዋነ መጽአ ኀቤነ ፤ "

ትርጉም ፦ [ ወደ ዓለም የመጣው ብርሃን በጻድቃን ላይ የሚያበራ ነው ፣ የቤተ ክርስቲያን ሙሽራዋ ነው ፣ የጠፋው ይረዳ ዘንድ የተበተኑትን ይሰበስብ ዘንድ ወደ እኛ መጣ [ ሰው ሆነ ] ]

[ ድጓ ዘአስተምህሮ ]

†                       †                        †
💖                    🕊                     💖

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

🕊

[ † እንኳን ለጌታችንና አምላካችን መድኃኔ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ዓመታዊ የስቅለት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ]

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †


††† መድኃኔ ዓለም †††

† ጌታችን መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ለእኛ ሲል በፈጸመው የማዳን ሥራ በዚሕ ዕለት ክፉዎች አይሁድ ከምሽቱ ፫ ሰዓት [3:00] ጌቴሴማኒ ውስጥ ያዙት:: ሙሉውን ሌሊት ከቀያፋ ወደ ሐና: ከሐና ወደ ቀያፋ ሲያመላልሱት: አስረው ሲደበድቡት አድረዋል::

ዝም ቢላቸው ዓይኑን ሸፍነው በጥፊ መቱት:: ምራቃቸውን ተፉበት:: ዘበቱበት:: ራሱንም በዘንግ መቱት:: እርሱ ግን ሁሉን ታገሰ::

በጧት ከገዢው ዘንድ ሞት እንዲፈረድበት አቀረቡት:: በሠለስት [ሦስት ሰዓት ላይ] አካሉ እስኪያልቅ እየተዘባበቱ ፮ ሺህ ፮ መቶ ስድሳ ፮ [6,666] ገረፉት:: ሊቶስጥሮስ አደባባይ ላይ እርጥብ መስቀል አሸክመው ወደ ቀራንዮ ወሰዱት::

ስድስት ሰዓት ላይ በረዣዥም ብረቶች አምስት ቦታ ላይ ቸንክረው ሰቀሉት:: ሰባት ታላላቅ ተአምራት በምድርና በሰማይ ታዩ:: ዓለም በጨለማ ሳለች ጌታ በመስቀል ላይ ሰባት ቃላትን ተናገረ::

ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ላይ በባሕርይ ሥልጣኑ ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው ለየ:: በዚያች ሰዓትም ወደ ሲዖል ወርዶ የታሠሩትን ሁሉ ፈታ:: አሥራ አንድ ሰዓት ላይ ደጋጉ ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ከታላቅ ክብርና ሐዘን ጋር በአዲስ መቃብር ቀበሩት::

በዚያች ቀን ድንግል ማርያም ልቧ በሐዘን ተቃጠለ:: ወዳጁ ቅዱስ ዮሐንስም ፍፁም ለቅሶን አለቀሰ:: ቅዱሳት አንስት በዋይታ ዋሉ:: [ማቴ.፳፯፥፩ (27:1), ማር.፲፭፥፩ (15:1), ሉቃ.፳፫፥፩ (23:1), ዮሐ.፲፱፥፩ (19:1) ]

ፈጣሪያችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለው መጋቢት ፳፯ [ 27 ] ቀን ቢሆንም በዓሉ ወደ ጥቅምት እንዲመጣ ያደረጉት አበው ሊቃውንት ናቸው:: ምክንያቱም ብዙ ጊዜ መጋቢት
፳፯ [27] የሚውለው ዓቢይ ጾም ውስጥ በመሆኑና የንግሥ በዓላት በዓቢይ ጾም ስለማይፈቀዱ ነው::

ምንም እንኩዋ በቅርብ ጊዜ በዓቢይ ጾም የሚያነግሡ አንዳንድ አብያተ ክርስቲያናት ቢኖሩም አባቶቻችን ግን እንዲህ ያለውን ሥርዓት አላቆዩልንም:: ከበሮና የቸብቸቦ ዝማሬም በወቅቱ የተፈቀደ አይደለም::

በዚህም ምክንያት የበዓለ ስቅለት ንግሡ ወደ ጥቅምት
፳፯ [27] ሲመጣ: የመጋቢት ፭ [5] ገብረ መንፈስ ቅዱስ ንግሥ ወደ ጥቅምት ፭ [5] : የመጋቢት ፲ [10] መስቀል ወደ መስከረም ፲፯ [17] መጥቶ እንዲከበር ሆኗል::


🕊  † ቅዱስ መቃርስ ብጹዓዊ  †  🕊

በዚህ ስም የሚጠሩ ቅዱሳን ብዙ ናቸው:: "ታላቁ መቃርዮስ": "መቃርስ እስክንድርያዊ": "መቃርስ ባሕታዊ"ን እንደ ምሳሌ መጥቀስ ይቻላል:: ይህኛው ቅዱስ ደግሞ "መቃርስ ኤዺስ ቆዾስ: መቃርስ ብጹዓዊ: መቃርስ ዘሃገረ ቃው" ይባላል:: ሁሉም መጠሪያዎቹ ናቸው::

ቅዱሱ የ፭ኛው መቶ ክ/ዘመን ሰው ሲሆን የቅዱስ ቄርሎስና የቅዱስ ዲዮስቆሮስ ተከታይ ነው:: ከሕይወቱ ማማርና ከቅድስናው መሥመር የተነሳ አበው አመስግነውት አይይጠግቡም:: ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት "ጻድቅ እንደ ዘንባባ ያፈራል" እንዳለው:: [መዝ.፺፩]

ዳግመኛ "ወይከውን ከመ ዕጽ እንተ ትክልት ኀበ ሙሐዘ ማይ" [መዝ.፩፥፫] እንዳለው ቅዱስ መቃርስ እጅግ ብዙ ትሩፋቶችን አፍርቷል:: ከሁሉ አስቀድሞ በበርሃ ኗሪ ከሆነበት ቀን ጀምሮ ስለ ጌታ ፍቅር እንባው እንደ ዥረት እየፈሰሰ:: ራሱን በብረት ዘንግ ይመታ ነበር::

"ቃው" በምትባል ሃገር ዻዻስ ሆኖ በተሾመ ጊዜም ተጋድሎውን አልቀነሰም:: ዻዻስ ቢሆንም የሚለብሰው የበርሃዋን ደበሎ ነው:: ከብቅዓቱ የተነሳ የሕዝቡ ኃጢአት በግንባራቸው ላይ ተጽፎ እየታየው ስለ ወገኖቹ ያለቅስ ነበረ:: በቤተ መቅደስ ውስጥ ቆሞ አንጀቱ ቅጥል እስኪል ድረስም ያለቅስ ነበር::

ሁልጊዜ ሲቀድስ ጌታችንን ከመላእክቱ ጋር ያየው ነበር:: አንድ ቀንም ጌታ ቅዱስ መቃርስን "ዻዻሱ ሆይ ሕዝቡን ገስጻቸው:: ብትገስጻቸውና ባይሰሙህ እዳው በእነርሱ ላይ ነው" አለው:: ቅዱስ መቃርስም ሕዝቡ ከኃጢአታቸው ይመለሱ ዘንድ ይመክራቸው: ይለምንላቸውም ነበር::

ከዚህ ሁሉ በሁዋላ በጉባኤ ኬልቄዶን [ጉባኤ አብዳን] ፮፻፴፮ ዻዻሳት ንጉሡን ፈርተው ሃይማኖታቸውን ሲክዱ ቅዱሳኑ ዲዮስቆሮስና መቃርስ "ተዋሐዶን አንክድም" በማለታቸው ዘበቱባቸው:: ብዙ አሰቃይተውም ወደ ጋግራ ደሴት አሳደዷቸው::

ቅዱስ ዲዮስቆሮስ ጋግራ ውስጥ ሲሞት ቅዱስ መቃርስ ወደ እስክንድርያ ተመልሶ ሕዝቡን ሲመክር ያዙት:: ከመሬት ላይ ጥለውም እየደጋገሙ ኩላሊቱን ረገጡት:: ከመከራው ብዛትም በዚህች ቀን ነፍሱን አሳልፎ ሰጠ:: ቅዱሱ ሙታንን ማስነሳትን ጨምሮ ብዙ ተአምራትን ሠርቷል::

አበውም ስለ ቅዱስ መቃርስ ብሎ ጌታ እንዲምራቸው እንዲህ ይጸልዩ ነበር :-

"ሰላም ሰላም ለፈያታዊ ዘቀደሶ::
ሃገረ ጽጌ የአኀዝ ምስለ ጻድቃን በተዋርሶ::
ተዘከረኒ ክርስቶስ አመ ትመጽእ ለተዋቅሶ::
በእንተ መቃርስ ጻድቅ እንተ መጠወ ነፍሶ::
ወበበትረ መስቀል ዘይዘብጥ ርዕሶ::" [አርኬ ዘጥቅምት ፳፯]


🕊  †  አቡነ መብዓ ጽዮን  †  🕊

ሃገራችን ኢትዮዽያ እጅግ በርካታ ቅዱሳንን ስታፈራ አንዳንዶቹ ደግሞ የተለዩ ናቸው:: ጻድቁ አባ መባዓ ጽዮን በ፲፭ኛው መቶ ክ ዘመን በሽዋ [ሻሞ] አካባቢ የተነሱ ጻድቅ ናቸው:: ገና ከልጅነታቸው የእመቤታችንና የጌታችን ፍቅር የሞላባቸው ነበሩ::

በ፫ ዓመታቸው ከእንግዳ የወሰዷት ስዕለ አድኅኖ ተለይታቸው አታውቅም ነበር:: በወጣትነታቸው ጊዜም ብሉያት ሐዲሳትን: ቅኔንም ጨምሮ ተምረው: ከቤተሰባቸው አስፈቅደው በምናኔ ገዳም ገቡ::

ከዚያ በሁዋላ ያለውን ገድላቸውን ማን ችሎ ይዘረዝረዋል!

በተለይ ዐርብ ዐርብ የጌታን ፲፫ ሕማማት ለማዘከር ሲቀበሉት የኖሩት መከራ እጅግ ብዙ ነው:: ድንጋይ ተሸክመው እንባና ላበታቸው እየተንጠፈጠፈ ይሰግዳሉ:: በድንጋይ ደረትና ጀርባቸውን ይደቃሉ:: ራሳቸውን ይገርፋሉ:: በዋንጫ ሐሞት [ኮሶ] ሞልተው ይጠጣሉ::

ከዚህ ሁሉ በሁዋላ ወር በገባ በ፳፯ ስለ መድኃኔ ዓለም ጠላ ጠምቀው: ንፍሮ ነክረው ወደ ገበያ ይወጡና ይዘክሩ ነበር:: ከዝክሩ የነካ ሁሉ ይፈወስ ነበር:: ከእንባ ብዛት ዓይናቸው ቢጠፋ ድንግል ማርያም መጥታ ብርሃናዊ ዓይንን ሰጠቻቸው:: ስለዚህም "ተክለ ማርያም [በትረ ማርያም]" ይባላሉ::

ጌታችንም ስለ ፍቅራቸው በአምሳለ ሕጻን ይገለጽላቸው: እርሳቸውም አቅፈው ይስሙት ነበር:: ጻድቁ ተናግረን የማንጨርሰውን ተጋድሎ ተጋድለው ጌታ በዚህ ቀን ነፍሳትን ከሲዖል እንዲያወጡበት ስልጣንን ሰጣቸው:: አባታችን ቅዱሱና ጻድቁ መብዓ ጽዮን ከብዙ ትሩፋት በሁዋላ ዐርፈዋል::


🕊 † አባ ጽጌ ድንግል ዘወለቃ † 🕊

ጻድቁ አቡነ ጽጌ ድንግል በ፲፬ኛው መቶ ክ/ዘመን የነበሩ ሊቅና ገዳማዊ ናቸው:: የዘር ሐረጋቸው ምንም ከቤተ እሥራኤል እንደሚመዘዝ ቢታወቅም ኢትዮዽያዊ ናቸው:: አስቀድመው አይሁዳዊ በመሆናቸው ኢየሱስ ክርስቶስንና ድንግል እናቱን አያምኑም ነበር::

የተማሩትም ብሉይ ኪዳንን ብቻ ነበር:: በጊዜውም "ክርስቶስ አልተወለደም:: ትክክለኛው እምነት ይሁዲ ነው::" እያሉ ከክርስቲያኖች ጋር ይከራከሩ ነበሩ:: አንድ ቀን ግን ከታላቁ ሊቅና ገዳማዊ አቡነ ዜና ማርቆስ ጋር ተገናኙ:: ጻድቁን ስላልቻሏቸው ተሸንፈው በክርስቶስ አመኑ:: አቡነ ዜና ማርቆስም አስተምረው ክርስትና ሲያነሷቸው [ሲያጠምቁዋቸው] "ጽጌ ድንግል" አሏቸው::

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

                          †                          

💖  [     የትሕርምት ሕይወት !     ]  💖

🕊                       💖                   🕊


[     "   ለቃሉም ታዛዥ ሁን !   "        ]

🕊

" ወዳጄ ሆይ ! በሙሉ ልብህ መዝሙራትን ለመድገምና ቅዱሳት መጻሕፍት ለማንበብ ትጋ፡፡ ሕፃን ከእናቱ ጡት የተነሣ እንዲፋፋ እንዲሁ ነፍስህ ከቃሉ ወተት ጠጥታ ትፋፋ ዘንድ ቅዱሳት መጻሕፍትን ዘወትር በማንበብ ትጋ፡፡

ከእነርሱ የመልካም ሥነ ምግባርን ዋጋ ትረዳለህ ፤ ለነፍስህም ደስታና ሐሴት ትሰጣታለህ፡፡ ወዳጄ ሆይ ! የዋህ ፣ ታዛዥና ትሑት ሁን፡፡ እንደ ሕፃናት የዋህ ከሆንህ እርሱን መከተልና ፈቃዱን መፈጸም ይቻልሃል። በበአትህ [በመኖሪያህ በቤትህ] ሆነህ አርምሞን ገንዘብህ አድርገህ ኑር፡፡ ብዙ ከመናገር ተከልክለህ አርምሞን ውደድ፡፡ በልብህ ግን ወደ አምላክህ ጸልይ ለቃሉም ታዛዥ ሁን ፤ በእግዚአብሔር ዘንድ ሰውነትህ ቅድስናን ገንዘብ ታደርግ ዘንድ በጌጠኛ ልብስ ሥጋህን አታስጊጣት፡፡

ባለጸጋ ዘመድ ስላለህም ራስህን አታስታብይ፡፡ ሊመካ የሚወድ በእግዚአብሔር ይመካ ይላልና፡፡ ሥጋ ሁሉ እንደ ሣር የሰው ሁሉ ክብር እንደ ምድር አበባ ነውና፡፡ ሣሩ ይደርቃል አበባውም ይረግፋል የእግዚአብሔር ቃል ግን ለዘለዓለም ይኖራል፡፡

ተወዳጆች ሆይ ! በጌታችን ሆኜ ሌላ ተጨማሪ መመሪያን እሰጣችኋለሁ፡፡ እርሱን ፈጽማችሁ ከተገኛችሁ እግዚአብሔር በመንግሥቱ ደስ ያሰኛችኋል፡፡

ከንቱ የሆነውን ሕይወት ክደህ ወደ ቅዱሳን ሕብረት ከገባህ በኋላ ማኅበሩን ጥለህ ትወጣ ዘንድ የጠላት ዲያብሎስን ምክር አትስማ፡፡

በፍጹም ትሕትና ሆነህ ሥራህን ጀምር፡፡ ከጠላትህ የተነሣብህን ፈተና እንደ በቀቀን መልሰህ አታስተጋባው። ብፁዓን ከሆኑት ቍጥር ትሆን ዘንድ ታጋሽ ሁን፡፡ እንዲህ ተብሎ እንደተጻፈ ፦ “በፈተና የሚጸና ሰው የተባረከ ነው ፤ ከተፈተነ በኋላ ለሚወዱት ተስፋ ስለ እርሱ የሰጣቸውን የሕይወትን አክሊል ይቀበላልና፡፡” [ያዕ.፩፥፲፪] "

🕊

[  ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ   ]


🕊                       💖                   🕊

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

ሐሙስ - መጋቢት 26 2016 ዓም    

ሮሜ 1-5

ሰላም ለሁላችሁ ይሁን! በዛሬው የዐቢይ ጾም ንባባችን የሮሜ መልእክትን 1-5 ድረስ እናነባለን።  

ከንባብ በፊት የሚደረግ ጸሎት፡ “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፤ የአንተን ቃላት እሰማ እና እረዳ ዘንድ፥ እንዲያውም ፈቃድህን ለመፈጸም እበቃ ዘንድ የልቤን ጆሮዎች እና ዓይኖች ክፈትልኝ።” (ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ)  

*የክለሳ ጥያቄዎች*

1) ቅዱስ ጳውሎስ ስለ ሮማውያኑ እግዚአብሔርን ያመሰገነው ለምንድር ነው? (ሮሜ 1)

2) እግዚአብሔርን አውቀው ያላከበሩት ሰዎች ምን ሆኑ? እግዚአብሔርስ ለምን አሳልፎ ሰጣቸው? (ሮሜ 1)

3) ቅዱስ ጳውሎስ ፈራጅ የሆኑትን ሰዎች ምን ብሎ ይገስጻል? (ሮሜ 2)

4) ቅዱስ ጳውሎስ በመገረዝና ሕግን በመፈጸም መካከል በማነጻጸር ያስተላለፈው መልእክት ምንድር ነው? (ሮሜ 2)

5) ቅዱስ ጳውሎስ የሰው ልጆች ሁሉ በኃጢአት ስለመውደቃቸው ጠቅሶ ሲናገር ምን አለ? (ሮሜ 3)

6) ቅዱስ ጳውሎስ ስለ ትምክህት፥ በእምነትና በሕግ መካከል ስላለው ግንኙነትስ ምን አለ? (ሮሜ 3)

7) ቅዱስ ጳውሎስ ከዳዊት መዝሙር የጠቀሰው ቃል ምን ይላል? (ሮሜ 4)

8) ቅዱስ ጳውሎስ የአብርሃም እምነት ጽድቅ ሆኖ እንደተቆጠረለት ሲያስረዳ ምን ይላል? (ሮሜ 4)

9) ቅዱስ ጳውሎስ ስለ መከራ ምን ይላል? (ሮሜ 5)

10) ቅዱስ ጳውሎስ በአዳም እና በክርስቶስ መካከል ምን አይነት ንጽጽር ያሳያል? (ሮሜ 5)

መልካም ንባብ!
/channel/c/2014228571/1

@OrthodoxTewahdoBooks

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

ሲራክ ጸሐፊ:
ሰላም🙏🙌⛪️✝️

ይህ ያለንበት ዓመት የክርስቶስ መምጫ ጊዜ ቢሆንስ ማን ያውቃል?

መጋቢት 29/2016 ዓ/ም ዘመነ ዮሐንስ
■ዕለተ ሰንበት
■ደብረ ዘይት ዕለተ ምጽዓት
■ በዓለ ትስብእት
■ ፍጥረተ ዓለም
■ ጥንተ ትንሣኤ
ዘመነ ዮሐንስ አምስት በዓላት በአንድነት ውለዋል።  እግዚአብሔር ይሁነን የንስሐ ጊዜ ያድርግልን።

《 ስለዚያች ቀንና ስለዚያች ሰዓት ግን ከአባት ብቻ በቀር የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ ልጅም ቢሆን የሚያውቅ የለም።》(ማቴ. 24፣36)
~

ጌታ
ችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሚመጣበትን ቀን ማንም አያውቅም።
ዘመኑ ዘመነ ዮሐንስ፣
ዕለቱ ዕለተ እሑድ፣
ሰዓቱ መንፈቀ ሌሊት
እንደሆነ ቢታወቅም ብዙ ዘመነ ዮሐንስ፦ ብዙ ዕለተ እሑድ፦ ብዙ መንፈቀ ሌሊት አለና አይታወቅም አለ። የሰማይ መላእክትም አያውቁትም። ልጅም አያውቀውም ማለቱ፦ 《ልጅ》ያለው ማንን ነው ከተባለ ፍጥረታትን ሁሉ ማለቱ ነው።  ኦሪት ዘልደት ሲል ኦሪት ዘፍጥረት ማለት እንደሆነ ሁሉ ፦ ልጅም ቢሆን አያውቅም የሚለው ቃል መላእክትም ሌሎች ፍጥረታትም አያውቁም ማለት ነው።

ከአብ በቀር የሚያውቃት የለም ማለቱ 《በቀር》 የሚለው ቃል 《ከፍጡራን》 ሲለየው ነው እንጂ ከወልድና ከመንፈስ ቅዱስ ሲለየው አይደለም። ይህን የመሰለ አገላለጽ 1ኛ ጢሞ. 1፣17 ብቻውን አምላክ ለሚሆን ለማይሞተው ለማይታየውም ለዘለዓለም ንጉሥ ምስጋናና ክብር እስከ ዘለዓለም ድረስ ይሁን አሜን" የሚል ቃል አለ፦
በዚህ አገላለጽ 《ብቻውን》 ስላለ አምላክ 《አብ ብቻ》 ሊመስለን ይችላል ነገር ግን 《ብቻውን》 የሚለው ከፍጥረታት ሲለየው ነው እንጂ ከወልድና ከመንፈስ ቅዱስ ሲለየው እንዳልሆነ ልንረዳ ይከባል።
ምክንያቱ ሥላሴ፦
በአብ፦ ልብነት ያስባሉ
በወልድ፦ ቃልነት ይናገራሉ
በመንፈስ ቅዱስ፦ እስትንፋስነት ለዘለዓለም ይኖራሉ
አጋዕዝተ ዓለም ሥላሴ፦ የአለምን መጨረሻ በአብ ልብነት ያውቃሉ። በወልድ ቃልነት የሚነገርበት ጊዜ ሲደርስ ይናገራሉ። በመንፈስ ቅዱስ እስትንፋስነት  ጊዜው ሲደርስ ዓለምን ያሳልፋሉ ማለት ነው።

  ሞት በሰዎች ትከሻ ላይ የተሰየመ ነውና ምጽዓተ ክርስቶስን ብቻ አንጠብቅ። ሞት ለሰው ልጅ ዕለተ  ምጽዓት ነው። ምክንያቱም፦ከሞት በኋላ ጽድቅ ሥራ መሥራት፣መፆም፣ መጸለይ፣ መስገድ፣ ንስሐ መግባት፣ አይቻልምና። ስለዚህ ሁል ጊዜ ከኃጢአት ርቀን ሕጉን ጠብቀን ንስሐ ገብተን ተዘጋጅተን እንኑር።

ይህ ያለንበት ዓመት የክርስቶስ መምጫ ጊዜ ቢሆንስ ማን ያውቃል?
●ዘመነ ዮሐንስ፤
●ደብረ ዘይት፤
●መጋቢት 29፤
●ዕለተ እሁድ ተገጣጥመዋል።
ሙሽራውን ክርስቶስ ለመቀበል ተዘጋጅተናል ወይ???
ስንቶቻችን ክፉ ሥራችንን አቁመናል?
ስንቶቻችን ንስሐ ገብተናል?
ስንቶቻችን ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ተቀብለናል?
ሁል ጊዜ ተዘጋጅታችሁ ኑሩ ተብሏልና ተዘጋጅተን እንኑር።
መድኃኔዓለም ክርስቶስ ሁላችንንም ከቁጥር  ሳያጎድለን በቀኙ ያቁመን።

የደብረ ዘይት በአሁኑ እሁድ በደብራችን መናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ታቦታቱ ወጥተዉ እንባረካለን የምንችል ከምሽቱ 2፡00 ጀምሮ ስለሚደወል አብረን ስናመሰግን እንደር


ያስተዋውቁት የደብረዘይትን በዓል "በጴጥሮሳውያን የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ን"ግሩፕ ላይ ሰፈሩ ፈርሷል(ፒያሳ)አካባቢ እናም ምእመናን መጥተው እንዲያከብሩ ⛪️
👉አድራሻ መናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን( ፒያሳ አራዳ ጊዮርጊስ )

ሰናይ አሁን

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

💛
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

🕊   ዐቢይ ጾም [  ጾመ እግዚእ  ]  🕊


▷  "   ባ ዶ ነ ት  !  "


[ 💖  በብፁዕ አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ  💖 ] 

[                        🕊                        ]
----------------------------------------------------

" ከእናንተ ዘንድ በአንዱ ስንኳ እንዳንከብድበት ፥ ሌሊትና ቀን በድካምና በጥረት እየሠራን እንኖር ነበር እንጂ ፥ ከማንም እንጀራን እንዲያው አልበላንም።"

[ ፪ተሰ . ፫ ፥ ፰ ]


🕊                       💖                   🕊

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

ረቡዕ - መጋቢት 25 2016 ዓም    

ሐዋ 25-28
   
ሰላም ለሁላችሁ ይሁን! በዛሬው የዐቢይ ጾም ንባባችን የሐዋርያት ሥራ ከምዕራፍ 25-28 ድረስ እናነባለን።  

ከንባብ በፊት የሚደረግ ጸሎት፡ “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፤ የአንተን ቃላት እሰማ እና እረዳ ዘንድ፥ እንዲያውም ፈቃድህን ለመፈጸም እበቃ ዘንድ የልቤን ጆሮዎች እና ዓይኖች ክፈትልኝ።” (ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ)  

የዛሬው ንባብ ሐዋ 25-28 ነውና፥ እርሱ እንዲነበብ ይሁን።  

መልካም ንባብ!
/channel/c/2014228571/1

@OrthodoxTewahdoBooks

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

🕊

[ † እንኳን ለዘመነ ሐጋይ [ በጋ ] የመጨረሻ ዕለትና ለሐዋርያው ቅዱስ አንሲፎሮስ በዓለ ዕረፍት በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ]

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †

† አምላካችን እግዚአብሔር ሁሉን ስነ ፍጥረት የፈጠረ ለሰው ልጆች ጥቅም ነው:: ጌታ አዝማናትን : ወሮችን : ሳምንታትን : ቀኖችንና ሰዓታትን ፈጥሮ : ወስኖ ሰጥቶናል:: የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጥንታዊት እንደ መሆኗ ሁሉ ነገሯ በሥርዓት ይፈፀማል::

በራሷ የዘመን ቀመር ስሌት መሠረትም አንድ ዓመት በአራት ወቅቶች ይከፈላል:: አባታችን ሊቁ ቅዱስ ያሬድም እነዚህን ወቅቶች መሠረት አድርጎ መንፈሳዊ ድርሰቶችን ደርሷል::

እነዚሕ አዝማናት [ ወቅቶች ] :-

፩. ዘመነ ክረምት [ ከሰኔ ፳፮ (26) እስከ መስከረም ፳፭ (25) ]
፪. ዘመነ መፀው [ ከመስከረም ፳፮ (26) እስከ ታኅሣሥ ፳፭ (25) ]
፫. ዘመነ ሐጋይ [ ከታኅሣሥ ፳፮ (26) እስከ መጋቢት ፳፭ (25) ]
፬. ዘመነ ፀደይ [ ከመጋቢት ፳፮ (26) እስከ ሰኔ ፳፭ (25) ] መሆናቸው ይታወቃል::

ዘመነ ሐጋይ [ በጋን ] የባረከ አምላክ ዘመነ ፀደይ [ መከርን ] እንዲባርክልን : የንስሐ ጊዜም እንዲያደርግልን ቅዱስ ፈቃዱ ይሁን::


🕊  †  ቅዱስ አንሲፎሮስ  †    🕊

† በዚህች ዕለት ጌታችንን በሃገረ ናይን የተከተለ : ከዋለበት ውሎ : ካደረበት ያደረ : ከሰባ ሁለቱ አርድእት የተቆጠረ ሐዋርያው ቅዱስ አንሲፎሮስ አርፏል::

† ዳግመኛ በዚህ ዕለት አይሁድ ለመጨረሻ ጊዜ ጌታችንን ሊገድሉት ተስማሙ:: ይሁዳም በ፴ [30] ብር ይሸጠው ዘንድ ከአይሁድ ጋር ተዋዋለ::

† የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይቅርታውና ምሕረቱ ከሁላችን ጋር ይሁን::

🕊

[ † መጋቢት ፳፮ [ 25 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. ቅዱስ አንሲፎሮስ ሐዋርያ [ከሰባ ሁለቱ አርድእት]

[ † ወርኀዊ በዓላት ]

፩. ቅዱስ መርቆሬዎስ ሰማዕት
፪. ቅድስት ቴክላ ሐዋርያዊት
፫. ቅዱስ አበከረዙን ሰማዕት
፬. ቅዱስ ዱማድዮስ ሶርያዊ
፭. አቡነ አቢብ [አባ ቡላ]
፮. ቅዱስ አባ አቡፋና ጻድቅ

" ከጥንት ጀምሮ እግዚአብሔር በብዙ ዓይነትና በብዙ ጐዳና ለአባቶቻችን በነቢያት ተናግሮ: ሁሉን ወራሽ ባደረገው ደግሞም ዘመናትን በፈጠረበት በልጁ በዚህ ዘመን መጨረሻ ለእኛ ተናገረን:: እርሱም . . . ኃጢአታችንን በራሱ ካነጻ በኋላ በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ::" † [ዕብ. ፩፥፩]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

ማግሰኞ - መጋቢት 24 2016 ዓም    

ሐዋ 21-24
   
ሰላም ለሁላችሁ ይሁን! በዛሬው የዐቢይ ጾም ንባባችን የሐዋርያት ሥራ ከምዕራፍ 21-24 ድረስ እናነባለን።  

ከንባብ በፊት የሚደረግ ጸሎት፡ “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፤ የአንተን ቃላት እሰማ እና እረዳ ዘንድ፥ እንዲያውም ፈቃድህን ለመፈጸም እበቃ ዘንድ የልቤን ጆሮዎች እና ዓይኖች ክፈትልኝ።” (ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ)  

የዛሬው ንባብ ሐዋ 21-24 ነውና፥ እርሱ እንዲነበብ ይሁን።  

መልካም ንባብ!
/channel/c/2014228571/1

@OrthodoxTewahdoBooks

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

🕊 

[ † እንኳን ለጻድቁ አባታችን ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ዓመታዊ በዓለ ፅንሰት በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። † ]

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †

🕊 †  ቅዱስ  ተክለ ሃይማኖት ሐዋርያዊ † 🕊

† ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ለኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ዐይን ናቸው:: ጻድቁን መንካት የቤተ ክርስቲያንን ዐይኗን መጠንቆል ነው::

ተክለ ሃይማኖት እንደ ሊቃውንት ሊቅ: እንደ ሐዋርያት ሰባኬ ወንጌል: እንደ ሰማዕታት ብዙ ግፍ የተቀበሉ: እንደ ጻድቃን ትሩፋት የበዛላቸው: እንደ ደናግል ንጽሕናን ያዘወተሩ: እንደ ባሕታውያን ግኁስ: እንደ መላዕክትም ባለ ክንፍ አባት ነበሩ:: ለዚሕ ነው ተክለ ሃይማኖትን የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ዐይኔ የምትላቸው::

🕊  ቅዱስ ተክለ-ሃይማኖት  ሐዋርያዊ  🕊

🕊 [ ልደት ]

መልካም ዛፍ መልካም ፍሬን ያፈራልና ተክለ ሃይማኖትን የወለዱት ደጋጉ:  ጸጋ-ዘአብ  ካህኑና  እግዚእ-ኃረያ  ናቸው:: እርሱ በክህነቱ: እርሷ በደግነቷ : በምጽዋቷ ጸንተው ቢኖሩ እግዚአብሔር ጣፋጭ ፍሬን ሰጥቷቸዋል::

በዳሞቱ ገዢ በሞተለሚ አደጋ ቢደርስባቸው  ቅዱስ ሚካኤል : ጸጋ ዘአብን ከሞት : እግዚእ ኃረያን ከትድምርተ አረሚ (ከአረማዊ ጋብቻ) አድኗቸዋል:: በኋላም የቅዱሱን መወለድ አብስሯቸዋል::

አቡነ ተክለ ሃይማኖት የጸነሱት መጋቢት ፳፬, በ፲፪፻፮ (፲፩፻፺፮) ሲሆን የተወለዱት ታሕሳስ ፳፬, በ፲፪፻፯ (፲፩፻፺፯) ዓ/ም ነው:: በተወለዱበት ቀንም ብዙ ተአምራት ተገልጸዋል:: ቤታቸውም በበረከት ሞልቷል::

🕊 [ ዕድገት ]

የጻድቁ የመጀመሪያ ስማቸው " ፍሥሃ_ጽዮን " ይሰኛል:: ይሕንን ስም ይዘው: አባታቸው ጸጋ ዘአብን ተከትለው አድገዋል:: በተለይ ቅዱሳት መጻሕፍትን [ብሉያት: ሐዲሳትን] ተምረዋል:: በሥጋዊው ጐዳናም ብርቱ አዳኝ እንደ ነበሩ ይነገራል:: ዲቁና ከወቅቱ ዻዻስ  አባ ጌርሎስ  ተቀብለዋል::

🕊 [ መጠራት ]

አንድ ቀን ፍሥሃ ጽዮን ለአደን ወጥቶ ሲያነጣጥር ድንገት ከሰማይ አስደንጋጭ ድምጽ ተሰማ:: የክብር ባለቤት  ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ  አእላፍ መላእክት እያመሰገኑ በሚካኤል ክንፍ ተቀምጦ ወረደ::

የወጣቱን አዳኝ ፍርሃቱን አርቆ ጌታችን ተናገረ ፦

"ከዛሬ ጀምሮ ስምህ ተክለ ሃይማኖት [ተክለ ሥላሴ] ይሁን:: አራዊትን ሳይሆን ነፍሳትን ታድናለህ:: ዘወትር ካንተ ጋር ነኝ" ብሎ በግርማ ዐረገ:: ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ከዚህ ጊዜ በኋላሰዓትን አላጠፉም:: ንብረታቸውን ለነዳያን በትነው በትር ብቻ ይዘው ቤታቸው እንደ ተከፈተ ወደ ምናኔ ወጡ::

🕊 [ አገልግሎት ]

ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ከዻዻሱ ቅስና ተቀብለው የወንጌል አገልግሎትን ጀመሩ:: በመጀመሪያ ስብከታቸው እዚያው ሽዋ [ጽላልሽ] አካባቢ ብቻ በ፲ ሺ የሚቆጠሩ ሰዎችን አሳምነው አጠመቁ:: ያንጊዜ ኢትዮዽያ ፪ መልክ ነበራት::

፩. ዮዲት [ጉዲት] በፈጠረችው ጣጣና በእስላሞች ተጽዕኖ ወደ ደቡብ አካባቢ ያለው ነዋሪ አንድም ሃይማኖቱን ክዷል: ወይም በባዕድ አምልኮ ተጠምዷል::

፪. ደግሞ በዛግዌ ነገሥታት ጥረት ክርስትናና ምናኔ ተነቃቅቶ ነበር::

ግማሹ ሃገር በጨለመበት ወቅት የደረሱት  ሐዲስ ሐዋርያ  አባ ተክለ ሃይማኖት በወጣት ጉልበታቸውና በኃይለ መንፈስ ቅዱስ ብዙ ቦታዎችን አደረሱ:: ሕዝቡን: መሣፍንቱን ወደ ሃይማኖት መልሰው: ማርያኖችን [ጠንቁዋዮችን] አጥፍተዋል::

🕊 [ ገዳማዊ ሕይወት ]

ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት በወንጌል ብርሃን ኢትዮዽያን ከማብራታቸው ባለፈ ገዳማዊ ሕይወትንም አስፋፍተዋል:: እርሳቸው ከሁሉ የተሻሉ ሳሉም በ፫ ገዳማት በረድዕነት አገልግለዋል::

እነዚህም በአቡነ በጸሎተ ሚካኤል ገዳም ለ፲፪ ዓመታት: በአቡነ  ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ ገዳም ለ፯ ዓመታት: በደብረ ዳሞ ከአቡነ ዮሐኒ ጋር ለ፯ ዓመታት: በአጠቃላይ ለ፳፮ ዓመታት አገልግለዋል::

በአቡነ ኢየሱስ ሞዐ ከመነኮሱ በኋላም ወደ ምድረ ሽዋ  ዞረሬ  ተመልሰው በአንዲት በዓት ውስጥ ለ፳፪ ዓመታት ቆመው ጸልየዋል:: በተሰበረ እግራቸውም ፮ ጦሮችን በግራና በቀኝ ተክለው ለ፯ ዓመታት ጸልየዋል::

🕊 [ ስድስት ክንፍ ]

ኢትዮዽያዊው ጻድቅና ሐዋርያ ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ከኢትዮዽያ ወደ ኢየሩሳሌም ተጉዘው ከቅዱሳት መካናት ተባርከዋል:: ጻድቁ ምድረ  እሥራኤል  የገቡት በየመንገዱ መንፈሳዊ ዘርን እየዘሩ: እያስተማሩና እያሳመኑ ነበር::

የወቅቱ ሊቀ ዻዻሳት  አባ ሚካኤል ጋርም ተገናኝተው ቡራኬን ተሰጣጥተዋል:: ዋናው ጉዳይ ግን ከዚህ በኋላ ነው:: ጻድቁ እመቤታችንና ጌታችን ከጽንሰታቸው እስከ ዕርገታቸው የረገጧቸውን ቦታዎች ሲመለከቱ በፍጹም ተደሞ እንባቸው ይፈስ ነበር::

ምክንያቱም እግዚአብሔር ስላበቃቸው ተክለ ሃይማኖት የሚያዩት ቦታውን አልነበረም:: በገሃድ:-

¤ በቤተ መቅደስ ብስራቱን
¤ በቤተ ልሔም ልደቱን
¤ በቤተ ዮሴፍ ግዝረቱን
¤ በፈለገ ዮርዳኖስ ጥምቀቱን
¤ በቤተ አልዓዛር ተአምራቱን ይመለከቱ ነበር::

የጉብኝታቸው የመጨረሻ ክፍል ወደሆነው  ቀራንዮ  ደርሰው ጌታቸውን እንደ ተሰቀለ ሆኖ ቢመለከቱት ከዓይናቸው ይፈስ የነበረው ቁጡ እንባ መልኩን ቀየረና ዓይናቸው ጠፋ::
በዚያች ቅጽበት ስም አጠራሯ የከበረ  እመቤታችን ድንግል ማርያም  ፈጥና ደርሳ ተክልየን ወደሰማይ አሳረገቻቸው::

በዚያም :-

¤ የብርሃን ዐይን ተቀብለው
¤ ፮ ክንፍ አብቅለው
¤ የወርቅ ካባ ላንቃ ለብሰው
¤ ማዕጠንተ ወርቁን ይዘው
¤ ከ፳፬ቱ ካህናተ ሰማይም ተደምረው
¤ ሥላሴን በአንድነቱና ሦስትነቱ ተመልክተው
¤ "ስብሐት ወክብር ለሥሉስ ቅዱስ ይደሉ" ብለው መንበረ ጸባኦትን አጥነው ወደ መሬት ተመልሰዋል::

🕊 [ ተአምራት ]

የተክልየ ተአምራት እንደ ሰማይ ከዋክብት የበዛ ነው::

† ሙት አንስተዋል፥ ድውያንን ፈውሰዋል፥ አጋንንትን አሳደዋል፥ እሳትን ጨብጠዋል፥ በክንፍ በረዋል፥ ደመናን ዙፋን አድርገዋል::

ብዙ ደቀ መዛሙርትን አፍርተው ደብረ ሊባኖስን መሥርተዋል:: በዚያም ሴትና ወንድ መነኮሳት እንደ ሕጻናት አብረው ኑረዋል:: በዘመናቸው ሰይጣን ታሥሯልና::

🕊 [ ዕረፍት ]

ጻድቅ: ሰማዕትና ሐዋርያ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ብርሃን ሆነው መከራን በብዙ ተቀብለው: አእላፍ ፍሬን አፍርተው: በተወለዱ በ፺፱ ዓመት: ከ፰ ወር: ከ፩ ቀናቸው ነሐሴ ፳፬, በ፲፫፻፮ (፲፪፻፺፮) ዓ/ም ዐርፈዋል:: ጌታ: ድንግል ማርያምና ቅዱሳን ከሰማይ ወርደው ተቀብለዋቸዋል:: ፲ ትውልድ የሚያስምር ቃል ኪዳንም ተቀብለዋል::

ይህች ዕለት ለጽንሰታቸው መታሰቢያ በዓል ናት፡፡

† አምላከ ቅዱሳን ከጻድቁ አባታችን በረከትን ይክፈለን::

[ † መጋቢት ፳፬ [ 24 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት [ጽንሰቱ]
፪. ቅዱሳን እግዚእ ኃረያና ጸጋ ዘአብ
፫. ቅዱስ አባ መቃርስ ሊቀ ጳጳሳት

[ † ወርኀዊ በዓላት ]

፩. ቅዱስ አጋቢጦስ ጻድቅ
፪. ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ
፫. ቅዱስ ሙሴ ፀሊም
፬. ቅዱስ ቶማስ ዘመርዐስ
፭. ቅዱስ አብላርዮስ ታላቁ
፮. ሃያ አራቱ ካኅናተ ሰማይ

"በረከት በጻድቅ ሰው ራስ ላይ ነው:: የኀጥአንን አፍ ግን ግፍ ይከድነዋል:: የጻድቅ መታሰቢያ ለበረከት ነው:: የኀጥአን ስም ግን ይጠፋል::" † [ ምሳሌ.፲፥፮ ]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር
† ወለወላዲቱ ድንግል
† ወለመስቀሉ ክቡር

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]

🕊                       💖                   🕊

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

                          †                          

💖  [     የትሕርምት ሕይወት !     ]  💖

🕊                        💖                       🕊

🍒

[ " ተጋድሎአችሁን እስከ መጨረሻ ለመፈጸም ትጉ ! ... " ]

🕊                        💖                       🕊

" ተወዳጆች ሆይ ! እናንተ በእግዚአብሔር ጸጋ ክርስቲያን የሆናችሁ አይደላችሁምን ?

ስለዚህ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሕግጋትን ጠብቁ፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ፦ “ እግዚአብሔር ለሰው ፊት እንዳያደላ ፥ ነገር ግን በአሕዛብ ሁሉ እርሱን የሚፈራና ጽድቅን የሚያደርግ በእርሱ የተወደደ እንደ ሆነ በእውነት አስተዋልሁ” [የሐዋ.፲፥፴፬] ብሎ የተናገረውን ቃል ልብ በሉ፡፡

ስለዚህ ክርስቲያን በመሆናችን ብቻ እንዳንታበይ እንጠንቀቅ፡፡ ይልቁኑ እርሱን በመፍራት የትሕርምትን ሕይወት ገንዘባችን አድርገን ልንመላለስ ይገባናል፡፡

እኛ በጽድቅ ሕይወት የምንደክመው መሠረት ለመጣል ብቻ አይደለም፡፡ ሕንፃውን ለመጨረስ ነው እንጂ፡፡ ሕንፃን የሚገነባ ሰው ድካሙ ሕንፃው እስኪጠናቀቅ ድረስ ነው፡፡ ያለበለዚያ መድኅን ዓለም ክርስቶስ ፦ “ከእናንተ ግንብ ሊሠራ የሚወድ ለመደምደሚያ የሚበቃ ያለው እንደ ሆነ አስቀድሞ ተቀምጦ ኪሳራውን የማይቈጥር ማን ነው? ያለዚያ መሠረቱን ቢመሠርት ፥ ሊደመድመውም ቢያቅተው ፥ ያዩት ሁሉ ይህ ሰው ሊሠራ ጀምሮ ሊደመድመው አቃተው ብለው ሊዘብቱበት ይጀምራሉ።” [ሉቃ.፲፬፥፳፰-፴] ብሎ እንዳስተማረው ይሆንብናል፡፡

የምደራዊ ወታደር የጦርነት ቆይታው አጭር ነው፡፡ ነገር ግን የአንድ ተሐራሚ ተጋድሎ እስከ ዕድሜ ፍጻሜው ነው፡፡ እንዲህም ስለሆነ ተጋድሎን በፍጹም ጽናት ትጋትና ትዕግሥት ሊጀመር ይገባናል፡፡

ተወዳጆች ሆይ ! አንበሳን መግደል ካሻችሁ እናንተን አግኝቶ እንደ ሸክላ ዕቃ እንዳይሰብራችሁ አድፍጣችሁ ትጠብቁታላችሁ እንጂ ፊት ለፊት አትጋፈጡትም፡፡ እንዲሁ ባሕር ውስጥ ብትሰጥሙ ደረቅ ምድር እስከታገኙ ድረስ ነፍሳችሁን ለማዳን ትጥራላችሁ እንጂ በውኃ ውስጥ ሰጥሞ ለመሞት እጅ አትሰጡም፡፡

እጅ ከሰጣችሁ ግን በውኃ ውስጥ እንደተጣለ ድንጋይ ሰጥማችሁ ትቀራላችሁ፡፡ ስለዚህ ወንድሞቼ ሆይ ! ጠላት ዲያብሎስ ድል እንዳይነሣችሁና በእናንተ ላይ እንዳይሰለጥን እንዲሁም ከድል አክሊል ይልቅ ውርደትን እንዳትለብሱ ተጋድሎአችሁን እስከ መጨረሻ ለመፈጸም ትጉ፡፡"

🕊

[  ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ   ]


🕊                        💖                       🕊

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

ሰኞ - መጋቢት 23 2016 ዓም    

ሐዋ 16-20
   
ሰላም ለሁላችሁ ይሁን! በዛሬው የዐቢይ ጾም ንባባችን የሐዋርያት ሥራ ከምዕራፍ 16-20 ድረስ እናነባለን።  

ከንባብ በፊት የሚደረግ ጸሎት፡ “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፤ የአንተን ቃላት እሰማ እና እረዳ ዘንድ፥ እንዲያውም ፈቃድህን ለመፈጸም እበቃ ዘንድ የልቤን ጆሮዎች እና ዓይኖች ክፈትልኝ።” (ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ)  

የዛሬው ንባብ ሐዋ 16-20 ነውና፥ እርሱ እንዲነበብ ይሁን።  

መልካም ንባብ!

/channel/c/2014228571/1

@OrthodoxTewahdoBooks

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

የዕለቱ ስንክሳር ዘግይቶ በመቅረቡ በእግዚአብሔር ስም ይቅርታ ለመጠየቅ እንወዳለን። 💖

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

                          †                          

💖  [     የትሕርምት ሕይወት !     ]  💖

🕊                       💖                   🕊


[ “ በፈተናህ ላይ ልትሰለጥን ትፈልጋልህን ? ! " ]

------------------------------------------------

" የዓይን አምሮትህንና የሥጋ ፍትወትህን ሁሉ ከአንተ ቆርጠህ ጣላቸው። በጌታህ ዘንድ ዋጋ የሚያሰጥህ በጎ ሥራ እንዳለ ካሰብህ በእርሱ እንዳይፈረድብህ መልካሙን ሥራ በፍጹም ታዛዥነት ፈጽም፡፡

ጠብን በመውደድ የራስን ፈቃድ ብቻ ተከትሎ መጓዝ ትልቅ ጥፋትን ያመጣል፡፡ ወጣኒ ተሐራሚ ሆኖ ለቃሉ ታዛዥ ያልሆነ እርሱ የቍጣ ልጅ የሚል ስምን ያገኛል። ይህን በተመለከተ ዳዊት ፦ “ተግሣጹን ተቀበሉ ጌታ እንዳይቈጣ እናንተም በመንገድ እንዳትጠፉ ቍጣው ፈጥና ትነድዳለችና፡፡ በእርሱ የታመኑ ሁሉ የተመሰገኑ ናቸው፡፡ " [መዝ.፪፥፲፪] በማለት መክሮናል፡፡

ነገር ግን ከስህተቱ መታረም የማይወድ ሰው ራሱን ያጠፋል፡፡

አዲስ ወይንን አሮጌ አቁማዳ እንዳይዙት ቢይዙት ግን አቁማዳው እንዲጠፋ ወይኑም እንደሚፈስ ፥ በትሕርምት ሕይወት ውስጥ ሳሉ ከስህተት አለመማር ለከፋ ጥፋት ይዳርጋል፡፡ ስለዚህ ሐዋርያው ፦ “ጽድቅ ከዓመፅ ጋር ምን ተካፋይነት አለውና? ብርሃንም ከጨለማ ጋር ምን ኅብረት አለው? ክርስቶስስ ከቤልሆር ጋር ምን መሰማማት አለው? " [ ፪ቆሮ.፮፥፲፬ ] በማለት በዓመፃ ሥራችን እንዳንጸና ይመክረናል፡፡"

🕊

[  ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ   ]


🕊                       💖                   🕊

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

"ሁሉን የያዘውን ያዙት፤ ሁሉን የሚገዛውን አሠሩት፤ የህያውን አምላክ ልጅ አሠሩት፤ በቁጣ ጎተቱት፤ በፍቅር ተከተላቸው። በሚሸልተው ፊት እንደማይናገር እንደ የዋህ በግ በኋላቸው እየተከተለ ወሰዱት፤ ሊቃነ መላእክት በመፍራት እና በመንቀጥቀጥ ከፊቱ የሚቆሙለትን በአደባባይ አቆሙት፤

ኃጢአትን ይቅር የሚለውን ኃጥእ አሉት፥ በመኳንንት የሚፈርደውንም በእርሱ ፈረዱበት፤ ለሱራፌል ዘውድ የሚያቀዳጃቸውን የሾህ ዘውድ አቀዳጁት፤ ለኪሩቤል የገርማ ልብስ የሚያለብሳቸውን ለመዘበት ቀይ ግምጃ አለበሱት፤ ኪሩቤል በእሳት ክንፍ ተሸፍነው በፊቱ የሚሰወሩለትን እርሱን ክፉ ባሪያ አሥሮ ፊቱን ጸፋው፤ የመላእክት ሠራዊት በፍጹም መደንገጥ የሚሰግዱለት እየዘበቱበት በፊቱ ተንበረከኩ፡፡

ይህን ያህል ትህትና እንደምን ያለ ትህትና ነው? ይህን ያህል ትእግስት እንደምን ያለ ትእግስት ነው? ይህን ያህል ዝምታ እንደምን ያለ ዝምታ ነው? ይህን ያህል ቸርነት እንደምን ያለ ቸርነት ነው? ኃያል ወልድን ፍቅር ከዙፋኑ ሳበው እስከ ሞትም አደረሰው በደል የሌለበትን እንደበደለኛ ሰቀሉት፡፡ ህይወትን የሠራውን ከበደለኞች ጋር ቆጠሩት፤ አዳምን የሠሩ እጆች በመስቀል ቀኖዎት ተቸነከሩ፤  ወዮ በገነት የተመላለሱ እግሮች በመስቀል ተቸነከሩ፡፡

ወዮ በአዳም ፊት የህይወት እስትንፋስን እፍ ያለ አፍ ከሃሞት ጋር የተቀላቀለ የኮመጠጠ መፃፃን ጠጣ፤... ወዮ የወልድን መከራውን የሚናገር ምን አፍ ነው? ምን ከንፈር ነው? ምንስ አንደበት ነው? የፍቁሩ የጌታ ህማማት በተነገረ ጊዜ ልብ ይለያል፤ ህሊናም ይመታል፤ ነፍስም ትንቀጠቀጣለች፤ ሥጋም ይደክማል የማይሞተው ሞተ፤ ሞትን ይሽረው ዘንድ ሞተ፤ ሙታንን ያድናቸው ዘንድ ሞተ። የምትወዱት ሰዎች ፈጽሞ አልቅሱለት፡፡"

/ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ/

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

ሲመነኩሱም "ጽጌ ብርሃን" ተብለዋል:: ቀጥለውም በጾምና በጸሎት ሲጋደሉ: እመቤታችንንም ሲለምኑ ምሥጢር ተገለጠላቸው::

የእመ ብርሃንን ስዕለ አድኅኖ በአበባ ተከባ: በብርሃንም ተውጣ ተመለከቱ:: በዚህ ምክንያትም ዛሬ በጣፋጭነቱ የሚታወቀውን ማኅሌተ ጽጌን ፩ መቶ ፶ ዓርኬ አድርገው ደረሱ:: እስከ ዕለተ ዕረፍታቸውም እመቤታችንና ልጇን በገዳማቸው [ወለቃ አካባቢ የሚገኝ] ሲያመሰግኑ ኑረዋል:: በዚህች ቀንም ዐርፈዋል::

አምላከ ቅዱሳን በአማኑኤል ስሙ: በማርያም እሙ: በፈሰሰ ደሙ: በተወጋ ጐኑ: በንጹሐን ቅዱሳኑ ይማረን:: ከመስቀሉና ከቅዱሳኑ በረከትም አይለየን::

† መድኃኔ ዓለም ከወዳጆቹ ጸጋ ክብርን ያድለን:: 

🕊

[ † መጋቢት ፳፯ [ 27 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. ቅዱስ ዮሐንስ [ፍቁረ እግዚእ]
፪. ቅዱሳት አንስት [ከእግረ መስቀሉ ያልተለዩ]
፫. ቅዱሳን ባልንጀሮች [በጌታ ስቅለት ጊዜ ከሞት የተነሱ]
፬. ቅዱሳን ዮሴፍና ኒቆዲሞስ
፭. ታላቁ ቅዱስ መቃርስ [የመነኮሳት አለቃ]
፮. ማር ገላውዴዎስ ሰማዕት [የኢትዮዽያ ንጉሥ]
፯. ቅዱስ ዕፀ መስቀል 

[ † ወርኀዊ በዓላት ]

፩. አቡነ መብዐ ፅዮን ጻድቅ
፪. ቅዱስ ፊቅጦር ሰማዕት
፫. ቅዱስ ያዕቆብ ዘግሙድ
፬. ቅዱስ ቢፋሞን ጻድቅና ሰማዕት

" የተጠራችሁለት ለዚህ ነው:: ክርስቶስ ደግሞ ፍለጋውን እንድትከተሉ ምሳሌ ትቶላችሁ ስለ እናንተ መከራን ተቀብሏልና:: እርሱም ኃጢአት አላደረገም:: ተንኮልም በአፉ አልተገኘበትም:: ሲሰድቡት መልሶ አልተሳደበም:: መከራንም ሲቀበል አልዛተም . . . እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ::" † [፩ጴጥ. ፪፥፳፩-፳፭]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

                      †                       

[            መድኃኔ  ዓለም             ]

🕊

† እንኳን ለጌታችንና አምላካችን መድኃኔ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ዓመታዊ የስቅለት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። †

[ አቤቱ ፥ ነፍሴን ከሲኦል አወጣሃት ! ]

🕊                       💖                   🕊

" ጌታዬና መድሃኒቴ ኢየሱስ ክርስቶስ የደረሰበትን ጉስቁልና ሊተካከል የሚችል ጉስቁልና እንደምን ያለ ነው? ቀላያት ፊቱን በተመለከቱ ጊዜ የሚንቀጠቀጡለት ፀሐይ ብርሃኗን የምትከለክልለት : ጨረቃ የምታለቅስለት : ከዋክብት የሚረግፉለት : ክፉዎች አይሁድ ተፉበት : እጃቸውን አክርረው መቱት : ከስድብ ሁሉ የከፋ ስድብ ሰደቡት::

ስድባቸው እንዲሁ የቃላት ብቻ አልነበረምና ምራቅና ቡጢም አለበት እንጂ : ይህ ብቻ አይደለም : - ክርስቶስ ሆይ በጥፊ የመታህ ማን ነው? ትንቢት ተናገርልን ¡ የሚል ስላቅም አለበትና:: ጌታዬና ንጉሴ መከራ ያልደረሰበት አካል አልነበረውም:: ጭንቅላቱ ላይ የእሾኽ አክሊል ደፉበት : ፊቱን በጥፊ መቱት ፡ ትከሻውን መስቀል አሸከሙት : እጁን በችንካር ቸነከሩት : እግሩን በምስማር ቸነከሩት : አፉን ኮምጣጤ አጠጡት : መላ አካልቱን በጅራፍ ገረፉት :: ወዮ ! እንዲህ ያለ መውደድ እንደምን ያለ ፍቅር ነው፡፡ "

[  ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ  ]

🕊

[        መድኃኔ  ዓለም         ]

💖    ድንቅ ትምህርት   💖

[ በመምህራችን በቀሲስ ኅብረት የሺጥላ ]

" አቤቱ ፥ ነፍሴን ከሲኦል አወጣሃት ፥ ወደ ጕድጓድም እንዳልወርድ አዳንኸኝ።" [መዝ.፴፥፫]


🕊                       💖                   🕊

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

#የጌታ_ስቅለት_በአበው

"አደምን የፈጠሩ እጆቹ በመስቀል ቀኖች ተቸነከሩ ወዮ በገነት የተመላለሱ እግሮች በመስቀል ቀኖች ተቸነከሩ ወዮ የማይሞተው ሞተ ሞትን ይሽረው ዘንድ ሞተ ሙታንን ያድናቸው ዘንድ ሞተ የምትወዱት ሰዎች ፈጽሞ አልቅሱለት፡፡" #ቅዳሴ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

“እጆቹን እግሮቹን በተቸነከረባቸው ችንካሮች መወጋቱንም እናምናለን፡፡ ነቢዩ ኢሳይያስ እርሱ ደዌያችንን ወሰደ ሕማማችንንም ተሸከመ፤ እኛን ለማዳን ኃጢአታችንንም ለማሥተሥረይ መከራ ተቀበለ እንዳለ፣ በባሕርዩ ሕማም የሌለበት ሲሆን በሥጋ የታመመ ነው፤ በእርሱ ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ድነናል አለ፡፡ በተገረፈና በተቸነከረም ጊዜ በመከራው ሁሉ መለኮትን ሕማም ተሰማው የሚል ሰው ቢኖር የተለየ የተወገዘ ይሁን፡፡” #ቅዱስ_ጎርጎርዮስ_ሊቀ_ጳጳስ

‹‹የሚሠዋ በግ እርሱ ነው፤ የሚሠዋ ካህን እርሱ ነው፡፡ ከባሕርይ አባቱ ከአብ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋርም መሥዋዕት የሚቀበል እርሱ ነው፡፡ በፈቃዱ መከራን በሥጋው የተቀበለ መከራንም ሁሉ የታገሠ እርሱ ነው፡፡ እንደ በግ ሊሠዋ መጣ፤ በግ በሚሸልተው ሰው ፊት እንዳይናገር አልተናገረም፤ በአንደበቱ ሐሰት አልተገኘበትም፡፡›› #ቅዱስ_ጎርጎርዮስ_ዘኑሲስ

‹‹ታመመ ሞትን ከተቀበለበት ከሥጋ ጋር ተዋሕዶ በመስቀል ላይ በፈቃዱ ለሥጋውያን ሞተ፤ ባሕርየ መለኮት ሥጋን ተዋሕዶ በማኅፀን ካደረ ጀምሮ ሥጋ ገንዘቡ እንደመሆኑ በሥጋ ይኸንን ሥርዐት ፈጸመ፡፡ ለማይመረመር ለመለኮቱ ባሕርይ እንደሚገባ ደግሞ እርሱ ኅብስት አበርክቶ ሁሉን ያጠግባል፤ አይራብም፤ አይጠማም፤ አይደክምም፤ አያንቀላፋም፤ አይታመምም፤ አይሞትም፤ ሕይወትን ለሁሉ ይሰጣል፡፡ ዳግመኛ በዛ በሲኦል ተገዝተው ያሉ ነፍሳትን ያድን ዘንድ በአካለ ነፍስ ወደ ሲኦል ወረደ በመለኮቱም ሲኦልን በዘበዘ›› #ቅዱስ_ቄርሎስ_ዘእስክንድርያ
    
‹‹ሙሴም ሞትን ያጠፋ ዘንድ አልቻለም፤ እርሱንም ይዞ ገዛው እንጂ፤ ከእርሱም በኋላ የተነሡ ነቢያትንም ሁሉ ሞት ገዛቸው እንጂ፡፡ ክርስቶስ ግን በቸርነቱ ለሁሉ ሕይወትን ሰጠ››  #ቅዱስ_አቡሊዲስ_ዘሮም

‹‹ምትሐት ያይደለ በእውነት ተራበ፣ ተጠማ እንጂ፡፡ ዳግመኛም ከኃጥአን ከመጸብሐን ጋር በላ ጠጣ፤ ያቀረቡለትንም በላ፡፡ ራሱን አሳልፎ ለመስቀል ሰጠ፤ እጁን እግሩን ተቸነከረ፤ ጎኑን በጦር ተወጋ፤ ከእርሱም ቅዱስ ምሥጢር የተገለጠበት ደምና ውኃ ፈሰሰ /ወጣ/፡፡›› #ቅዱስ_ባስልዮስ_ዘቂሳሪያ

ውብ አሁን

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

የሐዋርያው የቅዱስ  ጳውሎስ መልእክት ወደ ሮሜ ሰዎች።

የሮሜ መልእክት ዋና አሳብ ነገረ ድኅነት ወይም ጽድቅ ነው። ሰው ከኃጢያቱ የተነሳ ፍፁም በሽተኛና ወደ እግዚአብሔር መቅረብ የማይችል ደካማ ፍጥረት ሆኖ ነበር። እግዚአብሔር ግን በቀደመ የዘላለም አሳቡ ሰውን ለማዳን ወደራሱም ለማቅረብ አንድ ልጁን ላከልን። በእርሱም ሥራ ወደ አብ መግባትን አገኘን። ኤፌሶን 2፥18 ይሄ የሮሜ መጽሐፍ ይህ ሥራ ምንድን ነው? ምንስ ውጤት አመጣ የሚለውን ይመልስልናል።

የመልእክቱ አከፋፈል

1ኛ ከምዕ 1 እስከ ምዕ 3፡20 መዳን ለምን አስፈለገ? የሚለውን የሚመልስ ነው።

2ኛ ከምዕ 3፥21 እስከ ምዕ 5፥21ድኅነትን ያገኘነው እንዴት ነው?

3ኛ ከምዕ 6 እስከ ምዕ 8 እንዴት እንቀደስ? በቅድስና የመኖር መንፈሳዊ መመሪያ።

4ኛ ከምዕ 9 እስከ ምዕ 11 የእስራኤል መመረጥና የመዳን መንገድ መመረጥ

5ኛ ከምዕ 12 እስከ 15 ተግባራዊ ዕለታዊ የክርስትና ሕይወት እንዴት እንመላለስ?

6ኛ የመጨረሻው ምዕራፍ በአስደናቂ ሰላምታ ይጠናቀቃል።

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

🕊

[ † እንኳን ለጥንተ በዓለ ምሴተ ሐሙስ እና ኢዮጰራቅስያ ድንግል ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ]

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †

🕊   †  ምሴተ ሐሙስ  †    🕊

† ስም አጠራሩ ከፍ ከፍ ይበልና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከአንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ሰባ ስምንት [1978] ዓመታት በፊት "ምሴተ ሐሙስ" በምትባለው በዚሕች ዕለት :-

፩. በወዳጁ በዓልዓዛር ቤት የዓለማት ፈጣሪ ሲሆን በትሕትና ዝቅ ብሎ የደቀ መዛሙርቱን እግር አጥቧል::
፪. ለእኛ ድኅነት ይሆነን ዘንድ ቅዱስ ሥጋውን : ክቡር ደሙን ለመጀመሪያ ጊዜ ሰጥቷል::
፫. በጌቴሴማኒ ላበቱ እንደ ደም እየተንጠፈጠፈ ጸልዮ "ወደ ፈተና እንዳትገቡ ጸልዩ" ሲል አስተምሯል::
፬. ምሽት ፫ (3) ሰዓት አካባቢ ይሁዳ ሊቃነ ካህናቱን አስከትሎ መጥቶ ለ30 ብር አሳልፎ ሰጥቶታል:: [ማቴ.፳፮፥፳፮] (26:26) ዮሐ.፲፫፥፩] (13:1)

ይሕ ሁሉ ለእኛ ድኅነት ተፈጽሟልና ምስጋናና ክብር ለፈጣሪያችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይሁን::


🕊 †  ኢዮጰራቅስያ ድንግል †   🕊

† ዳግመኛ በዚህ ዕለት እናታችን ቅድስት ኢዮጰራቅስያ ድንግል አርፋለች::

ቅድስቲቱ በ፭ [ 5 ] ኛው መቶ ክ/ዘመን የነበረች እናት ስትሆን ገና በ9 ዓመቷ ምድራዊ ሐብትን ንቃ መንናለች:: ምክንያቱም ዘመዶቿ የሮም ነገሥታት እነ አኖሬዎስ ነበሩና:: ድንግል ኢዮጰራቅስያ በገዳም : በጾምና በጸሎት : በፍፁም ትሕትናና ታዛዥነት : እንዲሁም በፍቅር ኑራ በዚህች ቀን አርፋለች::

† ከቅድስት እናታችን በረከት አምላኩዋ ይክፈለን::

🕊

[ † መጋቢት ፳፮ [ 26 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. ቅዱሳን ሐዋርያት
፪. ቅድስት ድንግል ኢዮጰራቅስያ
፫. ቅዱስ ፍርፍርዮስ ሰማዕት

[ † ወርሐዊ በዓላት ]

፩. ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ
፪. አቡነ ሐብተ ማርያም ጻድቅ
፫. አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ
፬. ቅዱሳን ሰማዕታተ ናግራን
፭. አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን

† " ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ የዘለዓለም ሕይወት አለው:: እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሳዋለሁ:: ሥጋዬ እውነተኛ መብል : ደሜም እውነተኛ መጠጥ ነውና:: ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ በእኔ ይኖራል:: እኔም በርሱ እኖራለሁ::"  † [ ዮሐ.፮፥፶፫ ]  (6:53-56)

" እግራቸውን አጥቦ : ልብሱንም አንስቶ ዳግመኛ ተቀመጠ :: እንዲሕም አላቸው :- 'ያደረግሁላችሁን ታስተውላላችሁን ? እናንተ መምሕርና ጌታ ትሉኛላችሁ:: እንዲሁ ነኝና መልካም ትላላችሁ:: እንግዲህ እኔ ጌታና መምሕር ስሆን እግራችሁን ካጠብሁ እናንተ ደግሞ እርስ በርሳችሁ እግራችሁን ትተጣጠቡ ዘንድ ይገባል::' " † [ዮሐ.፲፫፥፲፪-፲፬] (13:12-14)

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

                          †                          

💖  [     የትሕርምት ሕይወት !     ]  💖

🕊                       💖                   🕊


[         "  አንተ ግን .... !   "        ]

🕊

" ወዳጄ ሆይ ! ራስህን ክደህ ከተሐራምያን ጋር የአንድነት ኑሮን ከጀመርኽና ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ማገልገል ከፈቀድን ከወንድሞች መካከል አንዳንዶች ያልተገባ ጠባይ ሲያሳዩ ብትመለከት ወይም እግዚአብሔርን ደስ የማያሰኝ ንግግርን ሲናገሩ ብትሰማ አትደነቅ፡፡ ከዚህ ይልቅ እንዳልሰማ ሁነህ እለፈው፡፡

ቃላቸውንም ከልብህ አታኑረው፡፡ በተቻለህ ፍጥነትም ከእነርሱም ፈጥነህ ሽሽ፡፡ እግዚአብሔርን ደስ የማያሰኝ ንግግርን በሚነጋገሩ ሰዎች ዘንድ እግዚአብሔርን መፍራት የለምና፡፡ ነገር ግን ጊዜአቸውን ከንቱ በሆነ መለፍለፍ ያሳልፋሉ፡፡ ሁልጊዜም ንግግራቸው በትዕቢት የተሞላ ነው፡፡

አንተ ግን ዳዊት በመዝሙሩ “ሁልጊዜ እግዚአብሔርን በፊቴ አየዋለሁ ፤ በቀኜ ነውና አልታወክም” [መዝ.፲፮፥፰] እንዲል ሁል ጊዜም ቢሆን እግዚአብሔርን በፊትህ አድርገህ ተመላለስ፡፡ ክፋትን በወንድሞች ኅብረት ውስጥ እና ውጭ ሆነው የሚፈጽሙ ወገኖች የክፉው የዲያብሎስ ልጆች ናቸው፡፡ እነዚህ ወገኖች በስንዴ መካከል እንዳሉ እንክርዳዶች ናቸው፡፡

እናንተ ወደ ጌታ ጎተራ ስትሰበሰቡ እነርሱ ደግሞ ተሰብስበው ወደ ዘለዓለማዊ እሳት ይጣላሉ፡፡ "

🕊

[  ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ   ]


🕊                       💖                   🕊

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

📜📜📜 መልሶ ይከፍላል📜📜📜

አንድ ወጣት የዩንቨርሲቲ ተማሪ ከፕሮፈረሰሩ አስማሪው ጋር መናፈሻው ላይ ቁጭ ብለው ያወራሉ። አስተማሪው ከተማሪዎች ሁሉ ይህን ተማሪ በጣም ስለሚወደው እንደጓደኛው አድርጎ ነው ሚያየው። ፊት ለፊታቸው ጫማውን አውልቆ የመናፈሻውን ፅዶችና ሳሮችን የሚያስተካክል ሰራተኛአለ ፤ ተማሪው የጵዳት ሰራተኛውን እያየ ለአስተማሪው “ቲቸር ዛሬ አንተም እኔም
ደብሮናል ፤ ለምን ያኛውን ሰውዬ ትሪክ አንሰራውም ? ያወለቀውን ጫማ ደበቅ እናርግበትና ጫማዎቹን ሲያጣቸው እንዴት
እንደሚበረግግ እኛም እዛጋ ደበቅ ብለን እንመልከተው” ይለዋል፡፡ አስተማሪውም “ወጣቱ ጓዴ ምንም እንኳ ቢደብረን ድሃዎችን እያሰቃየን እኛ መደሰት የለብንም ፡፡ ባይሆን እኛ ገንዘብ አለን
በገንዘባችን የበለጠ ደስታን ማግኘት እንችላለን ፤ ሂድና ቀስ ብለህ ሰውዬው ሳያይህ ባወለቀው ጫማዎች ላይ ገንዘብ ከተህበት ና ፤ ከዛም ተደብቀን የሚሆነውን እናያለን” አለው።
ተማሪው አስተማሪው እንዳለው ቀስ ብሎ የሰውዬው ጫማላይ በርካታ ገንዘብ ከቶበት መጣና ከአስተማሪው ጋርደበቅ ብለው የሰውዬውን ሁኔታ መከታተል ጀመሩ።
ሰውዬው ፅዳቱን ጨርሶ ኮቱን ለበሰና ጫማውን ለማድረግ ሲታገል ይቆረቁረውና ጎንበስ ብሎ ጫማውን ሲያራግፈው ብሮችን ያገኛል ፡፡ ሰውዬው ደነገጠ!! ዙሪያውን ቢያይ ማንም የለም ፤ ደግሞ ደጋግሞ ቀኝና ግራ ሲመለከት ማንም ሰው የለም፡፡ ሰውዬው በአግራሞት አንገቱን እየነቀነቀ ገንዘቡን ኪሱ ውስጥ ከከተተው በሗላ ሁለተኛ እግሩ ጫማውን ለማድረግ ሲያነሳ በተመሳሳይ ገንዘብ ያገኛል ፤ ሰውዬው አላመነም !! በጉልበቱ
ተንበረከከ አንገቱንም ወደ ሰማይ ቀና አደርጎ ጮክ ብሎ “ጌታዬ የሚስቴን መታመም አውቀህ ነው አይደል ፤ ካንተ ሌላ ማንም እንደማይረዳት አውቀህ ነው አይደል !! የልጆቼ ዳቦ ማጣታቸውን
አይተህ ነው አይደል !! ምስጋና ይግባህ ጌታዬ” አለ። ተማሪው የሰውዬውን ሁኔታ ሲመለከት ልቡን ነካው አይኑ እንቧ አቀረረች ፡፡ አስተማሪውም “ቅድም ካሰብከው ትሪክ ይልቅ አሁን የተሻለ ደስታ እንዳገኘህ አልጠራጠርም” አለው ፤ ተማሪው
እንባውን እየጠረገ “ፕሮፌሰር እስከዛሬ ካስተማሩኝ ሁሉ እንደዚህ ያለ ትምህርት አስተምረውኝ አያውቁም ፤ በህይወቴ የማረሳውን
ትምህርት ነው ያስተማሩኝ ፤ እውነትም ከመቀበል መስጠት የተሻለ ነው” በማለት መለሰላቸው ፡፡ "ደግ ደጉን እናስብ መልካምነት መልሶ ይከፍላልና"

                 መልካም አሁን

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

                          †                          

💖  [     የትሕርምት ሕይወት !     ]  💖

🕊                       💖                   🕊


[ " እስከ ፍጻሜ መጽናትን በተመለከተ ! ... " ]

🕊

" በትሕርምት ሕይወት ውስጥ ሊኖር የሚወድ ሰው ቢኖር ሁሌም በንቃትና በታላቅ ትዕግሥት ሊመላለስ ይገባዋል እንጂ በድንገት ተነሥቶ ወደዚህ ሕይወት በመግባት ያለ ስልት ሊዋጋ አይገባውም፡፡ ያለበለዚያ ወደ ተስፋ መቁረጥ ይደርሳል፡፡ እንዲህ ዓይነት ፈተናዎች እንደሚመጡብህ አውቀህ ትጠቀምበት ዘንድ ከተማርከው ትምህርት በተጨማሪ ይህን ምክር እንደሰጠሁ ልብ በል፡፡

ስለዚህ ወዳጄ ሆይ የተማርከውን አስተውል ዛሬ በጅማሬህ እነዚህን ፈተናዎች ሁሉ ተቋቁሜ ማለፍ ይቻለኛል ባልከው ቃልህ ነገ እንድትገኝ ተጠንቀቅ፡፡ ምክንያቱም ከአንደበትህ የሚወጣውን እያንዳንዱን ቃል በእግዚአብሔር ፊት ስለ አንተ የሚቆመው ጠባቂ መልአክህ ያደምጠዋልና፡፡

ስለዚህ ወዳጄ ሆይ ያለ ፈቃድህ የሚያስገድድህ አካል እንደሌለ ልብ በል፡፡ ከልብህ ለመታዘዝ ከቆረጥህ የማታደርገውን አደርገዋለው ብለህ ሐሰት አትናገር፡፡ ሐሰትን የሚናገረውን ሰው እግዚአብሔር ይጸየፈዋልና፡፡ "

🕊

[  ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ   ]


🕊                       💖                   🕊

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

                       †                        

🕊  ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት   🕊 

💖

[ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሥላሴን በማመን ተተከለ [ ተገኘ ]። በማስተዋል ስሙት ፣ በጸጥታ እና በርጋታም ሆናችሁ አድምጡት። በጌታው የሠርግ ቀን [ በዕለተ ምጽዓት ] በመከራው ከሚገኘው ደስታ ትሳተፉ ዘንድ ፣ የነፍስ አባታችን ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ብላችሁ መጥራት ይቻላችሁ ዘንድ በመገዛት ፣ በማኅሌት እና ኅሊናን በመሰብሰብ በዐሉን አክብሩ። ]

[ ገድለ ተክለ ሃይማኖት ]

እንኳን ለአቡነ ተክለ ሃይማኖት ለበዓለ ጽንሰቱ አደረሳችሁ።


†                       †                        †
💖                    🕊                     💖

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

💛
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

🕊   ዐቢይ ጾም [  ጾመ እግዚእ  ]  🕊


▷  "  ከ ጨ ለ ማ   መ ው ጣ ት  !  "


[ 💖 በብፁዕ አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ  💖 ] 

[                        🕊                        ]
----------------------------------------------------

" መብራትንም አብርተው ከዕንቅብ በታች አይደለም እንጂ በመቅረዙ ላይ ያኖሩታል በቤት ላሉት ሁሉም ያበራል።

መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ።" [ ማቴ.፭፥፲፭ ]


" ሁላችሁ የብርሃን ልጆች የቀንም ልጆች ናችሁና። እኛ ከሌሊት ወይም ከጨለማ አይደለንም"

[ ፩ ተሰሎ.፭፥፭ ]


🕊                       💖                   🕊

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

🕊

† እንኳን ለጻድቁ አባታችን ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ዓመታዊ በዓለ ፅንሰት በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። †

🕊                        💖                       🕊

ሰዳዴ ጽልመት አባታችን ቅዱስ ተክለሐይማኖት

"...ከበዐቱ ሳይወጣ ሌሊትና ቀን ቆመ። አልተቀመጠም ወደ ግራና ወደ ቀኝም አልተንቀሳቀሰም። ውኃም ቅጠልም ቢሆን ከቅዳሜና ከእሑድ በቀር በዚያ ወራት ምንም ምን አልቀመሰም። እህል ግን ከመነኰሰ ጀምሮ እስከ ዕለተ ሞቱ ድረስ አልቀመሰም። ፀሓይንም ጨረቃንም ከዋክብትን በጋና ክረምትንም ቡቃያና አበባንም ፍሬውንም አላየም። ዓይኖች ሳሉት እንደ ዕውር ጆሮዎች ሳሉት እንደ ደንቆሮ የሚናገር የተከናወነ አንደበት እያለው እንደ ዲዳ ሆነ። ከምስጋና በቀር ምንም ምን አይናገርም። ሌሊትና ቀንም እግዚአብሔርን አመሰገነ። ዓለምንም እንደ ትቢያና እንደ ጉድፍ ቆጠረው ከክርስቶስ ጋር እንደተሰቀለ ሆነ ልቡናውም ዘወትር ወደ ዓየር የተመሰጠ ነበር።

እንዲህ ባለም ገድል ብዙ ዘመን [፳፪ [22] ዓመታት] ኖረ። ቁመትንም ካበዛ ወዲህ አንዲቱ የእግሩ አገዳ ተሰበረች ደቀ መዛሙርቱ አንሥተው አክብረው በሰበን ጠቅልለው ከመንበሩ እግር በታች ቀበሯት። ከዚህም ባንዲት እግሩ ሰባት ዓመት ቆመ። ከነዚህም አራቱን ዓመት ውሃው  አልጠጣም"።

[ ገድለ ተክለ ሃይማኖት ]

🕊                        💖                       🕊

የኢቲሳ አንበሳ ፥ የኢትዮጵያ ብርሃን ፥ ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ሐራሴ ወንጌል ፥ የጣኦታት ጠላት ፥ ጣኦታትን የሰባበሩ ፥ የአምላካቸውን ስም ያስከበሩ ፥ ሐዲስ ሐዋርያ በረከታቸው ይደርብን ምልጃ ጸሎታቸው አይለየን፡፡


🕊                        💖                       🕊

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

🕊

[ † እንኳን ለታላቁ ነቢይና ጻድቅ ቅዱስ ዳንኤል ዓመታዊ በዓለ ዕረፍት በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። † ]

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †


🕊   †   ቅዱስ ዳንኤል  †     🕊

† ነቢይ ማለት በቁሙ ኃላፍያትን [አልፎ የተሠወረውን ምሥጢር]: መጻዕያትን [ለወደ ፊት የሚሆነውን] የሚያውቅ ሰው ማለት ነው:: ሃብተ ትንቢት የእግዚአብሔር የባሕርይ ገንዘቡ ሲሆን እርሱ ለወደደው በጸጋ ይሰጠዋል:: እነዚህም ከጌታ ሃብተ ትንቢት የተሰጣቸው አባቶችና እናቶች "ቅዱሳን ነቢያት" በመባል ይታወቃሉ::

ዘመነ ነቢያት ተብሎ የሚታወቀው ብሉይ ኪዳን ቢሆንም እስከ ምጽዓት ድረስ ጸጋውን እግዚአብሔር ለፈቀደላቸው አይነሳቸውም:: በሐዋርያት መካከልም ቅዱስ አጋቦስን የመሰሉ ነቢያት ነበሩ:: [ሐዋ.፲፩፥፳፯] (11:27) ቅዱሳን ነቢያት ከእግዚአብሔር እየተላኩ ሰውን ከፈጣሪው እንዲታረቅ ይመክራሉ: ይገስጻሉ::

ከበጐ ሃይማኖታቸውና ንጽሕናቸው የተነሳም እግዚአብሔርን በተለያየ አርአያና አምሳል አይተውታል::
"እስመ በአንጽሖ መንፈስ ርዕይዎ ነቢያት ለእግዚአብሔር: ወተናጸሩ ገጸ በገጽ" እንዳለ አባ ሕርያቆስ:: [ቅዳሴ ማርያም]

የብዙ ነቢያት ፍጻሜአቸው መከራን መቀበል ነው:: እውነትን ስለ ተናገሩ: አንዳንዶቹም በእሳት: አንዳንዶቹም በሰይፍ: አንዳንዶቹም በመጋዝ ተፈትነዋል:: ሌሎቹ ለአናብስት ሲጣሉ ቀሪዎቹ ደግሞ በድንጋይ ተወግረዋል::

ስለዚህም መከራቸው ለቤተ ክርስቲያን መሠረት ተብለዋል:: ጌታም ለደቀ መዛሙርቱ "ሌሎች ደከሙ: እናንተ በድካማቸው ገባችሁ" ብሎ የነቢያቱን መከራ ተናግሯል:: [ዮሐ.፬፥፴፮] (4:36)

ነቢያት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስና እና ድንግል እናቱን ለማየት ብዙ ጥረዋል: ሽተዋልም:: "ብዙ ነቢያትና ጻድቃን እናንተ የምታዩትን ሊያዩ ሹ" እንዳለ ጌታ በወንጌል:: [ማቴ.፲፫፥፲፮] (13:16) [፩ጴጥ.፩፥፲] (1:10) ዛሬ ግን በሰማያት ጸጋ በዝቶላቸው: ክብር ተሰጥቷቸው ሐሴትን ያደርጋሉ::

† ቅዱሳን ነቢያት በዋነኝነት አሥራ አምስቱ አበው ነቢያት: አራቱ ዐበይት ነቢያት: አሥራ ሁለቱ ደቂቀ ነቢያትና ካልአን ነቢያት ተብለው በአራት ይከፈላሉ::

† "አሥራ አምስቱ አበው ነቢያት" ማለት ፦

† ቅዱስ አዳም አባታችን
† ሴት
† ሔኖስ
† ቃይናን
† መላልኤል
† ያሬድ
† ኄኖክ
† ማቱሳላ
† ላሜሕ
† ኖኅ
† አብርሃም
† ይስሐቅ
† ያዕቆብ
† ሙሴና
† ሳሙኤል ናቸው::

† " አራቱ ዐበይት ነቢያት " ፦

† ቅዱስ ኢሳይያስ ልዑለ ቃል
† ቅዱስ ኤርምያስ
† ቅዱስ ሕዝቅኤልና
† ቅዱስ ዳንኤል ናቸው::

† " አሥራ ሁለቱ ደቂቀ ነቢያት " ፦

† ቅዱስ ሆሴዕ
† አሞጽ
† ሚክያስ
† ዮናስ
† ናሆም
† አብድዩ
† ሶፎንያስ
† ሐጌ
† ኢዩኤል
† ዕንባቆም
† ዘካርያስና
† ሚልክያስ ናቸው::

† " ካልአን ነቢያት " ደግሞ :-

† እነ ኢያሱ
† ሶምሶን
† ዮፍታሔ
† ጌዴዎን
† ዳዊት
† ሰሎሞን
† ኤልያስና
† ኤልሳዕ ሌሎችም ናቸው::

† ነቢያት በከተማም ይከፈላሉ::
† የይሁዳ ኢየሩሳሌም :
† የሰማርያ [ እሥራኤል ] ና
† የባቢሎን [ በምርኮ ጊዜ ] ተብለው ይጠራሉ::

† በዘመን አከፋፈል ደግሞ :-

† ከአዳም እስከ ዮሴፍ [የዘመነ አበው ነቢያት]:
† ከሊቀ ነቢያት ሙሴ እስከ ነቢዩ ሳሙኤል [የዘመነ መሳፍንት ነቢያት]
† ከቅዱስ ዳዊት እስከ ዘሩባቤል ያሉት [የዘመነ ነገሥት ነቢያት]:
† ከዘሩባቤል ዕረፍት እስከ መጥምቁ ዮሐንስ ያሉት ደግሞ [የዘመነ ካህናት ነቢያት] ይባላሉ::
ስለ ቅዱሳን ነቢያት በጥቂቱ ይህንን ካልን ወደ ዕለቱ በዓል እንመለስ::

ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳንኤል ቅድመ ልደተ ክርስቶስ በ፮፻ [600] ዓመታት አካባቢ ከይሁዳ ነገሥታት ዘር ተወለደ:: ገና በሕፃንነቱ ናቡከደነጾር ኢየሩሳሌምን አቃጥሎ : ሕዝቡን ማርኮ ወደ ባቢሎን ሲያወርዳቸው አብሮ ወርዷል::

ከሕፃንነቱ ጀምሮ በአምላኩ ፍቅር የታሠረ : ከሦስቱ ጓደኞቹ [አናንያ : አዛርያና ሚሳኤል] ጋር ጾምና ጸሎትን ያዘወትር ነበር:: በዘመኑ እንደርሱ ያለ መተርጉመ-ሕልም አልተገኘምና ለወገኖቹ ሞገሳቸው ነበር::

ኃይለኛውን ንጉሥ ናቡከደነጾርን ጨምሮ የባቢሎንና ፋርስ ነገሥታት ያከብሩት : ይወዱትም ነበር::

ቅዱስ ዳንኤል በጥበብና በሃይማኖት የአሕዛብን አማልክት ድል ነስቷል:: አሕዛብ በተንኮል ወደ አናብስት ጉድጓድ ውስጥ ቢያስጥሉት እግዚአብሔር የአናብስቱን አፍ ዘግቷል:: ዕንባቆምንም አምጥቶ መግቦታል::

ቅዱስ ዳንኤል የብሉይ ኪዳኑ "አቡቀለምሲስ" ይባላል:: ስለ ጌታችን የማዳን ሥራና ስለ ዳግም ምጽዐቱ በግልጥ ተናግሯል:: ሐረገ ትንቢቱም ፲፪ [12] ምዕራፍ ነው:: የዘመኑ አይሁድ ክርስቶስ ገና አልተወለደም ለማለት ዳንኤልን ጠልተውታል::

ታላቁ ነቢይና ጻድቅ ቅዱስ ዳንኤል እስራኤል ወደ ሃገራቸው ሲመለሱ አብሯቸው አልመጣም:: ከ70 ዓመታት በላይ በጸጋ ትንቢት ኑሮ እዛው ባቢሎን ውስጥ አርፏል::

† ፈጣሪ ከበረከቱ ለሁላችን ያድለን::

† በዚህች ቀን ክፉዎች አይሁድ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ይገድሉ ዘንድ በቤተ ቀያፋ መከሩ::

† እርሱ ቸሩ አምላክ ከክፉ መካሪዎች ይሠውረን::

🕊

[ † መጋቢት ፳፫ [ 23 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩.ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳንኤል [የስሙ ትርጓሜ- እግዚአብሔር ፈራጅ ነው ማለት ነው::

[ † ወርኀዊ በዓላት ]

፩. ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት
፪. ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕታት
፫. ቅዱስ ሰሎሞን ንጉሠ እስራኤል
፬. አባ ጢሞቴዎስ ገዳማዊ
፭. አባ ሳሙኤል
፮. አባ ስምዖን
፯. አባ ገብርኤል

" የዚያን ጊዜም ንጉሡ አዘዘ:: ዳንኤልንም አምጥተው በአንበሶች ጉድጓድ ጣሉት . . . ድንጋይም አምጥተው በጉድጓዱ አፍ ላይ ገጠሙት . . . በነጋውም ንጉሡ ማልዶ ተነሳ . . . ወደ ዳንኤል በቀረበ ጊዜ በኀዘን ቃል ጠራው . . . ዳንኤልም ንጉሡን . . . በፊቱ ቅንነት ተገኝቶብኛልና . . . አምላኬ መልዐኩን ልኮ የአንበሶቹን አፍ ዘጋ:: አንዳችም አልጐዱኝም አለው . . . ዳንኤልም ከጉድጓድ ወጣ:: በአምላኩም ታምኖ ነበርና አንዳች ጉዳት አልተገኘበትም::" † [ዳን.፮፥፲፮-፳፫]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖

Читать полностью…
Subscribe to a channel