mikreabew | Unsorted

Telegram-канал mikreabew - ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

874

"እንግዲህ፡ንስሓ፡ግባ፤አለዚያ፡ፈጥኜ፡ እመጣብሃለሁ፡፡" ራዕ 2፥16

Subscribe to a channel

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

💛
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

🕊   ዐቢይ ጾም [  ጾመ እግዚእ  ]  🕊


▷  " በመንፈስ እንጂ በፊደል አይሆንም ! "


[  💖 " አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ ... ! " 💖  ] 

[                        🕊                        ]
----------------------------------------------

" እርሱም ደግሞ በመንፈስ እንጂ በፊደል ለማይሆን ለአዲስ ኪዳን አገልጋዮች እንሆን ዘንድ አበቃን ፤ ፊደል ይገድላልና መንፈስ ግን ሕይወትን ይሰጣል። "

[ ፪ቆሮ.፫ ፥፮ ]


🕊                       💖                   🕊

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

ማግሰኞ - መጋቢት 17 2016 ዓም   

ዮሐንስ 6-10  
  
ሰላም ለሁላችሁ ይሁን! በዛሬው የዐቢይ ጾም ንባባችን የዮሐንስ ወንጌልን ከምዕራፍ 6-10 ድረስ እናነባለን። 

ከንባብ በፊት የሚደረግ ጸሎት፡ “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፤ የአንተን ቃላት እሰማ እና እረዳ ዘንድ፥ እንዲያውም ፈቃድህን ለመፈጸም እበቃ ዘንድ የልቤን ጆሮዎች እና ዓይኖች ክፈትልኝ።” (ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ) 

የዛሬው ንባብ ዮሐ 6-10 ነውና፥ እርሱ እንዲነበብ ይሁን። 

መልካም ንባብ!
/channel/OrthodoxTewahdoBooks

/channel/c/2014228571/1

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

ሰኞ - መጋቢት 16 2016 ዓም   

ዮሐንስ 1-5  
  
ሰላም ለሁላችሁ ይሁን! በዛሬው የዐቢይ ጾም ንባባችን የዮሐንስ ወንጌልን ከምዕራፍ 1-5 ድረስ እናነባለን። 

ከንባብ በፊት የሚደረግ ጸሎት፡ “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፤ የአንተን ቃላት እሰማ እና እረዳ ዘንድ፥ እንዲያውም ፈቃድህን ለመፈጸም እበቃ ዘንድ የልቤን ጆሮዎች እና ዓይኖች ክፈትልኝ።” (ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ) 

የዛሬው ንባብ ዮሐ 1-5 ነውና፥ እርሱ እንዲነበብ ይሁን። 

መልካም ንባብ!
/channel/OrthodoxTewahdoBooks

/channel/c/2014228571/1

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

                        †                         

[ የድኅነት ምክንያት ቃል ኪዳንሽ ባይኖር ኖሮ ! ]

🕊                        💖                       🕊

[ ለጥፋት የቀረበ ሰው ለድንግል በተሰጣት ኪዳን ፤ ብርሃኗ በማይጨልም በመንግሥተ ሰማይ ዕረፍትና ጤንነትን ያገኛል። ]

[ በብር የተሠራች የርግብ ክንፍ ጐኖቿ በወርቅ ዐመልማሎ የተሸለመች አንቺ በምሥራቅ ስትመሰዪ ልጅሽ የእውነት ፀሐይ ነው፡፡ በእውነት ቃል ኪዳንሽ አያልቅም፡፡ ]

[ ቅዱስ ያሬድ ]

🕊                        💖                       🕊

"ሶበሰ ኪዳንኪ ምክንያተ ድኂን ኢሀሎ ፈለገ እሳት ወደይን እም አሰጠመ ኩሎ ፤

[ የድኅነት ምክንያት የሆነው ቃል ኪዳንሽ ባይኖር ኖሮ የጥፋት እሳት ፣ መርገም [ኀጢአት] ባጠፋን ነበር ] "

[ አባ ጽጌ ድንግል ]


🕊                        💖                       🕊

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

                           †                           

      [   🕊 ድንግል ሆይ ፦  🕊    ]  

🕊                        💖                       🕊


" ድንግል ሆይ ፦ እታመንሻለሁ ከተሠወረው መከራ በግልጽም ከሚመጣብኝ ጥፋት ሁሉ በዚህ ዓለም እንድታድኝኝ ፤ በሚመጣውም ዓለም ከገሃነመ እሳት ጥርስ ማፏጨት ፥ ጽኑ ልቅሶም ካለበት ከሚያስጨንቅ መቅሠፍት ትሠውሪኝ ዘንድ ፤ እኔም ባንቺ አማላጅነት በልጅሽም ምሕረት የታመንሁ ነኝ፡፡

በፈረሰኞች ሰልፍ በሠረገላም መንኰራኩር የምታመን አይደለሁም፡፡ ባንቺና በልጅሽ ብቻ እታመናለሁ እንጂ፡፡ "

🕊

[  አርጋኖን   ]


🕊                        💖                       🕊

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

                       †                       

  [  🕊  ድምፀ ተዋሕዶ   🕊  ]  

🍒▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬🍒               

[  ሕይወት የሚገኝባቸው የቅድስት ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ትምህርቶች በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን በድምፅ ይቀርባሉ።  ]

[ ሳምንታዊ መርሐ-ግብር ]

🕊             

[    " ቅ ዱ ሳ ት   መ ጻ ሕ ፍ ት ! "    ]
             
        [    የመጨረሻ ክፍል    ]

" ይህን በመጀመሪያ እወቁ ፤ በመጽሐፍ ያለውን ትንቢት ሁሉ ማንም ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደም ፤

ትንቢት ከቶ በሰው ፈቃድ አልመጣምና ፥ ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ተልከው ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ተናገሩ።" [፪ጴጥ.፩፥፳]


       💖   ድንቅ ትምህርት  💖

[ በመምህራችን በቀሲስ ኅብረት የሺጥላ ]

" የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ፥ ከመከራም ሥጋት ያርፋል።" [ ምሳ.፩፥፴፫ ]

         †              †               †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬
                       👇

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

እሑድ - መጋቢት 15 2016 ዓም   

ሉቃስ 21-24  
  
ሰላም ለሁላችሁ ይሁን! በዛሬው የዐቢይ ጾም ንባባችን የሉቃስ ወንጌልን ከምዕራፍ 21-24 ድረስ እናነባለን። 

ከንባብ በፊት የሚደረግ ጸሎት፡ “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፤ የአንተን ቃላት እሰማ እና እረዳ ዘንድ፥ እንዲያውም ፈቃድህን ለመፈጸም እበቃ ዘንድ የልቤን ጆሮዎች እና ዓይኖች ክፈትልኝ።” (ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ) 

የዛሬው ንባብ ሉቃ 21-24 ነውና፥ እርሱ እንዲነበብ ይሁን። 

መልካም ንባብ!
/channel/OrthodoxTewahdoBooks

/channel/c/2014228571/1

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

/channel/OrthodoxTewahdoBooks

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

Share 'የወጣቶች ሕይወት 2.pdf'

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

Kbr ystln enamesegnalen

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

Lela anbewalewu esuma

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

                       †                       

  [  🕊  ድምፀ ተዋሕዶ   🕊  ]  

🍒▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬🍒               

[  ሕይወት የሚገኝባቸው የቅድስት ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ትምህርቶች በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን በድምፅ ይቀርባሉ።  ]

[ ሳምንታዊ መርሐ-ግብር ]

🕊             

[    " ቅ ዱ ሳ ት   መ ጻ ሕ ፍ ት ! "    ]
             
        [    ክፍል  አስራ አንድ    ]

" ይህን በመጀመሪያ እወቁ ፤ በመጽሐፍ ያለውን ትንቢት ሁሉ ማንም ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደም ፤

ትንቢት ከቶ በሰው ፈቃድ አልመጣምና ፥ ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ተልከው ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ተናገሩ።" [፪ጴጥ.፩፥፳]


       💖   ድንቅ ትምህርት  💖

[ በመምህራችን በቀሲስ ኅብረት የሺጥላ ]

" የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ፥ ከመከራም ሥጋት ያርፋል።" [ ምሳ.፩፥፴፫ ]

         †              †               †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬
                       👇

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

ቅዳሜ - መጋቢት 14 2016 ዓም  

ሉቃስ 16-20 
 
ሰላም ለሁላችሁ ይሁን! በዛሬው የዐቢይ ጾም ንባባችን የሉቃስ ወንጌልን ከምዕራፍ 16-20 ድረስ እናነባለን።

ከንባብ በፊት የሚደረግ ጸሎት፡ “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፤ የአንተን ቃላት እሰማ እና እረዳ ዘንድ፥ እንዲያውም ፈቃድህን ለመፈጸም እበቃ ዘንድ የልቤን ጆሮዎች እና ዓይኖች ክፈትልኝ።” (ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ)

የዛሬው ንባብ ሉቃ 16-20 ነውና፥ እርሱ እንዲነበብ ይሁን።

መልካም ንባብ!
/channel/OrthodoxTewahdoBooks

/channel/c/2014228571/1

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

🕊

[ † እንኳን ለሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ ዓመታዊ የተአምር በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ]

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †


🕊  † ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ  †  🕊

† ከ ፲፪ [12] ቱ ቅዱሳን ሐዋርያት አንዱ የሆነው ቅዱስ ቶማስ ብዙ መከራን በማሳለፉና የጌታችንን ጐን በመዳሰሱ ይታወቃል::

ቅዱስ ቶማስ እንደ ሌሎቹ ሐዋርያት በእሥራኤል ተወልዶ በዚያውም በሥርዓተ ኦሪት አድጐ ገና በወጣትነቱ የሰዱቃውያንን ማሕበር ተቀላቅሏል:: ሰዱቃውያን ሰው ከሞተ በሁዋላ አይነሳም [አልቦ ትንሳኤ] የሚሉ ናቸው:: መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ማስተማር ሲጀምር ግን ቅዱስ ቶማስ ከነበረበት ማሕበር ወጥቶ ጌታችንን ተከተለ:: ጌታችንም ከ ፲፪ [12] ቱ ሐዋርያት አንዱ ይሆን ዘንድ ሾመው:: የቀደመ ስሙ "ዲዲሞስ" ሲሆን ጌታችን "ቶማስ" ብሎታል::

ቅዱስ ቶማስ ጌታ አልዓዛርን ለማስነሳት በሔደ ጊዜ ሌሎች ሐዋርያት ጌታን "አይሁድ ይገድሉሃል ቅር" ሲሉት እርሱ ግን "እንሒድና አብረን እንሙት" ሲል ፍቅሩን አሳይቷል:: [ዮሐ.፲፩፥፲፮]  (11:16)

ጌታችን ትንሳኤውን ለደቀ መዛሙርቱ በገለጠ ጊዜ ያልነበረው ቶማስ ካላየሁ አላምንም አለ:: ምክንያቱም :-

፩. ለጌታችን ከነበረው ፍቅር የተነሳ እውነት አልመስልህ ቢለው::
፪. አንድም ሌሎቹ ሐዋርያት "ትንሳኤውን አየን" እያሉ ሲያስተምሩ እኔ ግን "ሰማሁ" ብየ ማስተማሬ ነው ብሎ በማሰቡ ነበር::

ለጊዜው ጌታ ተገልጾ ቢገስጸው "እግዚእየ ወአምላኪየ [ጌታየና አምላኬ]" ብሎ ፍጹም ሃይማኖቱን ገልጿል:: ለፍጻሜው ግን የጌታችንን ጎን [መለኮትን] ይዳስስ ዘንድ ባለቤቱ እንዳደለው ያጠይቃል:: መለኮትን የዳሰሰች ይሕቺ ቅድስት እጁ ዛሬም ድረስ ሕያው ናት:: በሕንድ ቤተ ክርስቲያን ውስጥም በክብር ተቀምጣለች::

ቅዱሳን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ተቀብለው ሐገረ ስብከት ሲከፋፈሉ ለቅዱስ ቶማስ ሕንድና በዙሪያዋ ያሉ ሃገራት ደረሱት:: ከዚህ በሁዋላ ነው እንግዲህ ዘርዝረን የማንጨርሰውን ተጋድሎ የፈጸመው:: ቅዱሱ በነበረው ፍጹም ትጋት አባቶቻችን "ዘአሠርገዋ ለብሔረ ሕንደኬ [ሕንድን በወንጌል ያስጌጣት)]" ሲሉ ያከብሩታል::

ቅዱስ ቶማስ ንጉሥ ሉክዮስንና የሃገሩን ሕዝብ ለማሳመን በችንካር መሬት ላይ ወጥረው ቆዳውን ገፈውታል:: ቆዳውንም እንደ ገና ሰፍተው: አሸዋ ሞልተው አሸክመውታል:: በየመንገዱ የተገፈፈ ገላውን ጨው ቢቀቡት በጎች መጥተው ግጠው በልተውታል:: በዚሕ ምክንያት :-

"ኩሉ የአኪ እንዘ የአኪ ዘመኑ::
አባግዒሁ ለቶማስ እስመ አራዊተ ኮኑ::" ብለዋል ሊቃውንቱ::

በሁዋላ ግን ከፎቅ ወድቃ የሞተችውን የንጉሡን ሚስት በተገፈፈ ቆዳው በማዳኑ ሁሉም አምነው ተጠምቀዋል::

ቅዱሱ ሐዋርያ ልክ እንደ ቅዱስ ዻውሎስ አንዳንዴ በፈሊጥ: ሌላ ጊዜም በመከራ ለወንጌልና ለቤተ ክርስቲያን ተጋድሏል:: ያለ ማቁዋረጥም ከሕንድ እስከ ሃገራችን ኢትዮዽያ ድረስ ለ ፴፰ [38] ዓመታት ወንጌልን ሰብኩዋል::

በመጨረሻም በ ፸፪ [72] ዓ/ም በሰማዕትነት አርፏል:: መቃብሩና ቅድስት እጁ ዛሬ ድረስ ሕንድ ውስጥ አሉ:: ከኘሮቴስታንቶች በቀር መላው ዓለም ያከብረዋል::

† ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከአገልጋዩ ቅዱስ ቶማስ ጸጋ በረከት ይክፈለን::

🕊

[ † መጋቢት ፲፬ [ 14 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ [ጋኔን ያደረባት ሴትን ፈውሶ አሕዛብን ያሳመነበት]
፪. ቅዱስ አባ ባጥል ትሩፈ ምግባር [ባንድ ወቅት ከእስክንድርያ ዝሙትን ለማጥፋት የተጋደሉ ጻድቅና አረጋዊ አባት]
፫. ቅዱስ ሲኖዳ [ሺኖዳ] ሰማዕት
፬. ቅዱስ ቄርሎስ ሊቀ ዻዻሳት

[ † ወርሐዊ በዓላት ]

፩. አቡነ አረጋዊ [ ዘሚካኤል ]
፪. ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ መርዓዊ
፫. ቅዱስ ፊልዾስ ሐዋርያ
፬. ቅዱስ ሙሴ [ የእግዚአብሔር ሰው ]
፭. አባ ስምዖን ገዳማዊ
፮. አባ ዮሐንስ ጻድቅ
፯. እናታችን ቅድስት ነሣሒት

" ደጆች ተዘግተው ሳሉ ኢየሱስ መጣ:: በመካከላቸውም ቆሞ 'ሰላም ለእናንተ ይሁን' አላቸው:: ከዚያም በሁዋላ ቶማስን 'ጣትህን ወደዚህ አምጣና እጆቼን እይ:: እጅህንም አምጣና በጐኔ አግባው:: ያመንህ እንጂ ያላመንህ አትሁን' አለው:: ቶማስም 'ጌታዬ አምላኬም' ብሎ መለሰለት:: ኢየሱስም 'ስላየኸኝ አምነሃል:: ሳያዩ የሚያምኑ ብጹዓን ናቸው' አለው::" †††
[ዮሐ.፳፥፳፮] [20:26-29]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
💖                    🕊                     💖

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

                          †                          

  [     የትሕርምት ሕይወት !      ]  

🕊                       💖                   🕊

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን !
                              
🕊

[   በፈተና መጽናትን በተመለከተ  !   ]

------------------------------------------------

በዚች ሌሊት ነፍስህን ከአንተ ሊወስዱአት ይፈልጓታል !

" ተወዳጆች ሆይ በሰው ፊት በአግባቡ ተመላለሱ ፤ በእግዚአብሔርም የበረታችሁ ሁኑ፡፡ እርሱ ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና፡፡

ተወዳጆች ሆይ ! ሰዎች ከቤተሰቦቻችሁ ስለምትወርሱት ሀብት ያነሱባችሁ እንደሆነ ፦ “አንተ ሰነፍ ፥ በዚች ሌሊት ነፍስህን ከአንተ ሊወስዱአት ይፈልጓታል ፤ ይህስ የሰበሰብኸው ለማን ይሆናል?” ተብሎ ተጽፎአል በሏቸው፡፡ [ሉቃ.፲፪፥፳]

ጨምራችሁም ፦ “ብልሃተኞች እንዲሞቱ ፥ ሰነፎችና ደንቆሮች በአንድነት እንዲጠፉ ፥ ገንዘባቸውንም ለሌሎች እንዲተዉ አይቶአል” ተብሎ ተጽፎአል በሏቸው፡፡ ስለዚህ ገንዘብ መውደድ ለእኔ ጥፋትና የኃጢአት ሥር ነው፡፡

ጌታችንም ፦ “ብልና ዝገት በሚያጠፉት ሌቦችም ቆፍረው በሚሠርቁት ዘንድ ለእናንተ በምድር ላይ መዝገብ አትስብስብ፡፡ ነገር ግን ብልም ዝገትም በማያጠፉት ሌቦችም ቆፍረው በማይሠርቁት ዘንድ ለእናንተ በሰማይ መዝገብ ሰብስቡ ፤ መዝገብህ ባለበት ልብህ ደግሞ በዚያ ይሆናልና፡፡” ብሎ አስተምሮኛል በል” ብሎ ይመክራል፡፡ [ማቴ.፮፥፲፱]  "

🕊

[  ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ   ]

†                       †                         †
💖                    🕊                     💖

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

                          †                          

  [     የትሕርምት ሕይወት !      ]  

🕊                        💖                       🕊
                              

[ " በጥምቀት ለተሰቀለ ክርስቲያን ሁሉ ... " ]
.........

" አንድ ምእመን ፈጣሪውን ፣ አምላኩን ፣ ያዳነውን ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ከማንም ጋር ሊያነጻጽርና ሊያወዳድር አይገባውም፡፡

ስለዚህ ክርስቲያን ክርስቶስን መስሎና ተዋሕዶ መኖር ከተገባው የትሕርምት ሕይወት ግዴታው እንጂ በውዴታ የሚኖረው ሕይወት አንዳልሆነ በዚህ ማረጋገጥ ይቻላል፡፡ እንዲሁም ክርስቲያን ሲጠመቅና የእግዚአብሔር ልጅነትን ስልጣን ገንዘቡ ሲያደርግ ለእርሱ ለሞተለት ጌታ ይኖር ዘንድ ቃል ኪዳን ገብቶአል፡፡

እንዲህም በመሆኑ ቅዱስ ጳውሎስ “እኔ ለእግዚአብሔር ሕያው ሆኜ እኖር ዘንድ በሕግ በኩል ለሕግ ሞቼ ነበርና። ከክርስቶስ ጋር ተሰቅዬአለሁ ፤ እኔም አሁን ሕያው ሆኜ አልኖርም ክርስቶስ ግን በእኔ ይኖራል ፤ አሁንም በሥጋ የምኖርበት ኑሮ በወደደኝና ስለ እኔ ራሱን በሰጠው በእግዚአብሔር ልጅ ላይ ባለ እምነት የምኖረው ነው::” [ገላ.፪፥፲፱] ብሎ አስተምሮናል፡፡

ስለዚህ ለዓለም ፈቃድ መሞት ለደናግል ብቻ የተሰጠ ሕይወት ሳይሆን ከክርስቶስ ጋር በጥምቀት ለተሰቀለ ክርስቲያን ሁሉ እንደሆነ መረዳት ይገባል፡፡

ክርስቲያን ወደፊት የሥጋውን ፈቃድ ይፈጽም ዘንድ በክርስቶስ ዳግም አልተፈጠረም፡፡ [የሥጋውን ፈቃድ ገድሎ ለክርስቶስ እንዲኖር እንጂ] ስለሆነም ይህን ይህን የትሕርምት ሕይወት ለደናግል ወይም ለገዳማውያን ለይቶ መስጠት የተገባ እንዳልሆነ ይልቁኑ ክርስቲያን ነኝ ለሚል ሁሉ ግዴታው መሆኑን በዚህ መገንዘብ ይገባል።"

🕊

[  ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ   ]


🕊                        💖                       🕊

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

💖                   🕊                    💖

[ † በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! † ]

🕊 † አልዓዛር ሐዋርያ  †  🕊

† ቅዱስ አልዓዛር በሃገረ ቢታንያ ከእህቶቹ ማርያና ማርታ ጋር ይኖር ነበር:: ሦስቱም ድንግልናቸውን ጠብቅው ጌታችንን ያገለግሉት ነበርና አልዓዛርን ከ ፸፪ [ 72 ] ቱ አርድእት ማርያና ማርታን ደግሞ ከ፴፮ [ 36 ] ቱ ቅዱሳት አንስት ቆጥሯቸዋል::

በወንጌል ጌታችን ይወዳቸው እንደነበር ተገልጧል:: [ዮሐ.፲፩፥፫] [11:3] ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲወድ የሚያበላልጥ ሆኖ አይደለም:: ይልቁኑ በምሥጢር እነርሱ ተወዳጅ የሚያደርጋቸውን ሥራ ይሠሩ እንደነበር ሲነግረን ነው እንጂ::

ቅዱስ መጽሐፍ እንደ ነገረን ጌታችን በነ አልዓዛር ቤት በእንግድነት ይስተናገድ ነበር:: [ዮሐ.፲፪፥፩] [12:1] በመጨረሻዋ ምሴተ ሐሙስም ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ለሐዋርያቱ ያቀበላቸው በእነዚህ ቅዱሳን ቤት ውስጥ ነው::

ቅዱስ አልዓዛር በጽኑዕ ታሞ በዚሕች ቀን አርፏል:: ቅዱሳት እህቶቹ ማርያና ማርታ ከታላቅ ለቅሶ ጋር ዕለቱኑ ቀብረውታል:: [ዮሐ.፲፩] [11]

† ቸር ጌታችን ክርስቶስ ከ4 ቀናት በሁዋላ ሊያስነሳው ይመጣልና ከበረከቱ ይክፈለን:: [ይቆየን]

🕊

[ † መጋቢት ፲፯ [ 17 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. ቅዱስ አልዓዛር ጻድቅ ሐዋርያ
፪. ቅዱስ ቴዎቅሪጦስ አናጉንስጢስ [ሰማዕት]
፫. ቅዱስ ተላስስ ሰማዕት
፬. ቅዱስ ዮሴፍ ኤዺስ ቆዾስ
፭. ቅዱስ ጊዮርጊስ መስተጋድል

[ † ወርኀዊ በዓላት ]

፩. ቅዱስ እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት [ ቀዳሜ ሰማዕት ]
፪. ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ [ ወልደ ዘብዴዎስ ]
፫. ቅዱስ ኤዺፋንዮስ ዘቆዽሮስ
፬. ቅዱሳን አበው መክሲሞስና ዱማቴዎስ
፭. አባ ገሪማ ዘመደራ
፮. አባ ዸላሞን ፈላሢ
፯. አባ ለትጹን የዋህ

†  " ጌታ ኢየሱስም :- ' ትንሳኤና ሕይወት እኔ ነኝ:: የሚያምንብኝ ቢሞት እንኩዋ ሕያው ይሆናል:: የሚያምንብኝም ሁሉ ለዘለዓለም አይሞትም:: ይህን ታምኛለሽን?' አላት:: እርስዋም [ማርታ] :- 'አዎን ጌታ ሆይ: አንተ ወደ ዓለም የሚመጣው ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆንህ እኔ አምናለሁ::' አለችው::"† [ዮሐ.፲፩፥፳፭-፳፯] (11:25-27)

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

                          †                          

🌼  [     የትሕርምት ሕይወት !     ]  🌼

🕊                        💖                       🕊
                              

[ " ወደፊት የራሱ አይደለም የክርስቶስ እንጂ  ... " ]

.........

" ለክርስቲያን ሁለት ክርስቲያናዊ የሕይወት መንገድ ተፈቅዶለታል አንዱ በሕግ ሌላው በፈቃድ ነው፡፡ በሕግ ሲባል በጋብቻ ማለት ነው፡፡ በፈቃድ ሲል በፈቃድ ላይ የተመሠረተ በራስ ምርጫና ፍላጎት ሳያገቡ በድንግልና መኖር ማለት ነው፡፡

ነገር ግን እግዚአብሔርን ለማገልገል በድንግልና ጸንቶ መኖር ተመራጭ ነው፡፡ ጌታችንም ይህ የድንግልና ሕይወት ምርጫ ስለሆነ “ሊቀበለው የሚችል ይቀበለው” ብሎ አስተምሮናል፡፡ [ማቴ.፲፱፥፲፪]

አንዳንድ ስለ ቃሉ መረዳት የሌላቸው ወገኖች ማንም ወደ እኔ የሚመጣ ቢኖር አባቱንና እናቱን ሚስቱንም ልጆቹንም ወንድሞቹንም እኅቶቹንም የራሱን ሕይወት ስንኳ ሳይቀር ባይጠላ ፥ ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም፡፡” [ሉቃ.፲፬፥፳፮] የሚለውን የጌታችንን ቃል ለመናንያን ብቻ ሰጥተው ሲተረጉሙ እናያለን፡፡ ነገር ግን ይህ ትምህርት ክርስቲያን ነኝ ለሚል ሁሉ የተሰጠ መመሪያ ሲሆን እግዚአብሔርን መውደድ እስከ የት ድረስ ደርሰን ገንዘባችን ማድረግ እንዳለብን የሚያስተምረን ኃይለ ቃል ነው፡፡

እንዲህም ስለሆነ ጌታችን ነፍሱን የሚያገኝ ያጠፋታል ፥ ነፍሱንም ስለ እኔ የሚያጠፋ ያገኛታል” [ማቴ.፲፥፴፱] በማለት ለሁሉ ተናግሮአል፡፡

አንድ ሰው በሥላሴ ስም ሥልጣን ባለው ካህን ሲጠመቅ ለዚህ ዓለም ሞቶ በክርስቶስ ላለው ሕይወት ሕያው ይሆናል። ስለዚህ ወደፊት ለራሱ ሳይሆን ለተፈጠረበት በጎ ሥራ ሊኖር ተጠርቶአል፡፡ ምክንያቱም ክርስቶስ በሞቱ በአዲስ ተፈጥሮ ወልዶታልና ወደፊት የራሱ አይደለም የክርስቶስ እንጂ፡፡ 

ስለዚህ ክርስቶስን ተዋሕዶ ሊኖር በእርሱ ክርስቶስ ሊገለጥ ክርስቲያን ሆኖአል፡፡ ይህም የትንሣኤ ሕይወት ነው፡፡ አንድ ክርስቲያን በዚህ የትንሣኤ ሕይወት መኖር ካለበት ደግሞ ጌታችን እንዳስተማረው ከምንም አስቀድሞ ጌታችንን ሊወድና ፈቃዱን ሊፈጽም ይገባዋል።"

[  ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ   ]


🕊                        💖                       🕊

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

🕊

[ † እንኳን ለጻድቁ ሊቀ ጳጳሳት አባ ሚካኤል ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ]

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †

🕊 † አባ ሚካኤል ሊቀ ጳጳሳት † 🕊

† አባ ሚካኤል በትውልዳቸው ግብጻዊ ሲሆኑ ገና በሕፃንነታቸው ገዳማዊ ሕይወትን መርጠው ለዓመታት በተጋድሎ ገዳመ አስቄጥስ ውስጥ ኑረዋል:: በዘመኑ ግብጽ ሊቀ ጳጳሷ አርፎባት ነበርና በሱባዔ እያሉ "አባ ሚካኤልን ሹሙት" የሚል ቃል ከሰማይ ሰምተው "እንሹምህ" አሉት:: "እንቢ" ቢላቸው ግድ ብለው አስረው ሹመውታል::

አባ ሚካኤል በመንበረ ማርቆስ ላይ እረኝነት [ጵጵስና] ተሹሞ ጭንቅ ጭንቅ መከራዎችን ተቀብሏል:: በወቅቱ የነበረው የግብጽ ከሊፋ [አባቶቻችን ክፉ ሰው ማለት ነው ይላሉ] አባ ሚካኤልን አሥሮ በሕዝቡ ፊት ይደበድባቸው ነበር::

ከመከራው ብዛት የተነሳ በርካቶቹ ተገደሉ: ከ ፳ ሺህ [20,000] በላይ ምዕመናን ሃይማኖታቸውን ካዱ::
ይህንን የሰሙት የወቅቱ የኢትዮጵያ ንጉሥ በመንፈሳዊ ቅንዐት ፻ሺህ [100,000] ፈረሰኛ: ፻ሺህ [100,000] በበቅሎ: ፻ሺህ [100,000] ሠራዊት በግመል ጭነው ወደ ግብጽ ወርደው ከሊፋውን አስጨንቀው የግብጽን ክርስቲያኖች ከመከራ ታድገዋል::

አባ ሚካኤልም ከእሥር ከተፈቱ በኋላ የካዱ ምዕመናንን ለመመለስ ብዙ ደክመዋል:: ተሳክቶላቸውማል:: ጻድቁ ሊቀ ጳጳሳት ከዓመታት ተጋድሎ በኋላ በዚህች ቀን አርፈዋል::

† ፈጣሪ ከበረከታቸው አይንሳን::

🕊

[ † መጋቢት ፲፮ [ 16 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. ቅዱስ አባ ሚካኤል ሊቀ ጳጳሳት

[ † ወርኀዊ በዓላት ]

፩. ኪዳነ ምሕረት [የሰባቱ ኪዳናት ማሕተም
፪. ቅድስት ኤልሳቤጥ [የመጥምቁ ዮሐንስ እናት]
፫. ቅዱስ ገብረ ማርያም ጻድቅ ንጉሠ ኢትዮጵያ [የቅዱስ ላሊበላ ወንድም]
፬. ቅዱስ አኖሬዎስ ንጉሥ ጻድቅ
፭. አባ አቡናፍር ገዳማዊ
፮. አባ ዮሐንስ ወንጌሉ ዘወርቅ
፯. አባ ዳንኤል ጻድቅ

" በድካም : አብዝቼ በመገረፍ : አብዝቼ በመታሠር : አትርፌ በመሞት ብዙ ጊዜ ሆንሁ:: በድካምና በጥረት : ብዙ ጊዜም እንቅልፍ በማጣት : በራብና በጥም : ብዙ ጊዜም በመጦም : በብርድና በራቁትነት ነበርሁ . . . የቀረውን ነገር ሳልቆጥር ዕለት ዕለት የሚከብድብኝ የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ አሳብ ነው::" † [፪ቆሮ. ፲፩፥፳፫-፳፰]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

👆

[ ቅዱሳት መጻሕፍት ] የመጨረሻ ክፍል !

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

🕊                      💖                     🕊


[        🕊     ም ኵ ራ ብ      🕊       ]

💖

የሳምንት ሦስት ምኩራብ ቻሌንጅ ከዕለታዊ የመንፈሳዊ መግባራት መከታተያ ጋር

፩ ] ብዙ ጊዜ የምናጠፋበት የእጅ ስልካችን ውስጥ ያሉ ወደ ክርስቶስ እንዳንቀርብ የሚያደርጉ አላስፈላጊ የሆኑ ገጾችን : ዘፈኖችን ሌሎችም የማይጠቅሙ ፋይሎች: መተግበሪያዎች ጠርጎ ማስወገድ

፪ ] ለአእምሮአችን እረፍት በምናገኝባት ቅድስት ቤተክርስቲያን በመገኘት የጽሞና ጊዜ ማሳለፍ

፫ ] በምኩራብ ሰንበት የሚነበበውን ወንጌል [ ዮሐ ፪፥፲፪ ] { 2:12-ፍጻሜው } እንዲሁም መልእክታቱን [ ቆላ.፪፥፲፮ ] { 2:16-ፍጻሜው }
[ ያዕ ፪፥፲፬ ] { 2:14-ፍጻሜው } ማስታወሻ በመያዝ ማጥናት

፬ . በዚህ ሳምንት ውዳሴ ዘአምላክ የተባለውን የ7ቱ ቀናትን ውብ ጸሎት መጸለይ

፭ . ወንድምን ማማትን [ ሀሜትን ] ማስወገድ

ይህ ሳምንታዊ ቻሌንጅ እንዴት እየጠቀማችሁ እንደሆነ ያጋሩን::

[ ከጃንደረባው ገጽ ላይ የቀረበ ]


🕊                        💖                       🕊

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

🕊                      💖                     🕊

[      የዐቢይ ጾም ሦስተኛ ሳምንት      ]

💖

[        🕊     ም ኵ ራ ብ      🕊       ]


[ እንኳን ለዐቢይ ጾም ሦስተኛ ሳምንት እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። ]

                      †                           

[        ምኵራብ !           ]
 

🍒▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬🍒

[  🕊   ክብርት ቤተክርስቲያን   🕊 ]


[  የሕዝብ ኹሉ እናት የመላእክት መዘዋወሪያ !  ]

❝ ሰላም ለቤተ ክርስቲያን ቅድስት ማኅደረ ስብሐት ምዕዋደ መላእክት እም ኩሉ ሕዝብ ❞

[ የሕዝብ ኹሉ እናት የመላእክት መዘዋወሪያ [ ቦታ ] የምስጋና ማደሪያ ለኾነችው ለቅድስት ቤተክርስቲያን ሰላምታ ይገባል። ] [አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ]

" በመላእክት ፊት እዘምርልኻለሁ ወደ ቅዱስ መቅደስህ እሰግዳለሁ። "  [መዝ.፻፴፯፥፪ ]

†                       †                       †

ቤተ ክርስቲያንን  “ ቅድስት ” አላት ስለምን ቢሉ ?

የቅድስት ሥላሴ አንድነት ሦስትነት ይነገርባታልና ፤ አንድም ክርስቶስ በቅዱስ ደሙ አክብሯታልና። አንድም የክርስቶስ ቅዱስ ሥጋውና ደሙ ለምእመናን ይሰጥባታልና፡፡ አንድም በኀጢአት የረከሰ ሰው በንስሓ ከእግዚአብሔር ጋር ታርቆባት ይቀደስባታልና።

“ ማኅደረ ስብሐት ” [ የምስጋና ማደሪያ ] አላት ፦

የልዑል እግዚአብሔር ምስጋና በጸሎተ ኪዳን ፣ በስብሐተ ነግህ ፣ በጸሎተ ቅዳሴ ፣ በማሕሌት ፣ በሰዓታት ፣ በሰባቱ ጊዜያት ኹሉ ይነገርባታልና።

“ የመላእክት መዘዋወሪያ [ ቦታ ] ” አላት ፦

የመንግሥቱ ወንጌል በሚነገርበት ፣ ቅዱስ ሥጋው ክቡር ደሙ በሚፈተትበት ቤተ ክርስቲያን ምእመናን የጸለዩትን ጸሎት ለማሳረግ በቀን ስድስት መቶ በሌሊት ስድስት መቶ መላእክት ይጠብቋታልና።

“ እመ ኵሉ ሕዝብ ” የሕዝብ ኹሉ እናት ይላታል ፦

እናት ልጆቿን እንድታሳድግ ፣ እንድትጠብቅ ፣ ወደ ቀና ጐዳና መርታ እንድታደርስ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንም በምስጢረ ቤተ ክርስቲያን ይልቁኑ በሥጋውና በደሙ እናድግባታለን ፤ በርቱዕ ትምህርቷ ከክሕደት እንጠበቅባታለን ፤ በመጨረሻም ወደ አምሳያዋ ኢየሩሳሌም ሰማያዊት መርታ ታደርስናለችና። [ ገላ.፬፥፳፮-፳፯ ] ❞

🕊     ክብርት ሰንበት     🕊

†                       †                       †

[ " ኢየሱስም ወደ መቅደስ ገባና በመቅደስ የሚሸጡትንና የሚገዙትን ሁሉ አወጣ ፥ የገንዘብ ለዋጮችንም ገበታዎች የርግብ ሻጮችንም ወንበሮች ገለበጠና።

ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች ተብሎ ተጽፎአል ፥ እናንተ ግን የወንበዶች ዋሻ አደረጋችኋት አላቸው።
" [ ማቴ . ፳፩ ፥ ፲፪ ]

🕊                        💖                       🕊

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

Ftanegest metseihaf kalachu bzu tyake alebgn esu metsihaf kalachu lakulgn

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

ኣንድ ሴት ፐሬድ ከመጣባት ለስንት ቀን ነዉ ቤተክርስትያን ማትገባ

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

🕊

[ † እንኳን ለሰማዕቱ ቅዱስ ሰለፍኮስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ]

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †


🕊   †   ሰማዕቱ ሰለፍኮስ   †    🕊

† ቅዱስ ሰለፍኮስ በዘመነ ሰማዕታት የነበረ ክርስቲያን ወጣት ነው:: በወቅቱ ያ የጭንቅና የመከራ ዘመን ከመምጣቱ በፊት በተቀደሰ ጋብቻ ለመኖር አስጠራጦኒቃ የምትባል ደግ የሆነች ክርስቲያናዊት ወጣት አጭቶ ነበር::

በዕጮኝነት ዘመናቸው ጾምን: ጸሎትንና ንጽሕናን በመምረጣቸው ያየ ሁሉ ያደንቃቸው ነበር::
ታዲያ የሠርጋቸው ቀን እየቀረበ ሲመጣ ያ የመከራ ዘመን [ዘመነ ሰማዕታት] ጀመረ::

ሁለቱ ንጹሐን ወጣት ክርስቲያኖች ተመካከሩና ወሰኑ:: በምክራቸውም መሠረት ሁለቱም ከነ ድንግልናቸው ሰማዕትነትን ለመቀበል ተዘጋጁ:: በዚች ዕለትም ስለ ቀናች ሃይማኖትና ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፍቅር ከብዙ ስቃይ በሁዋላ በከሃዲው ንጉሥ ትዕዛዝ ቅዱስ ሰለፍኮስ በሰማዕትነት አልፏል::

† ከቅዱሱ ሰማዕት በረከት አምላከ ቅዱሳን ያድለን::

🕊

[ † መጋቢት ፲፭ [ 15 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. ቅዱስ ሰለፍኮስ ሰማዕት
፪. እናታችን ቅድስት ሣራ ጻድቅት [ግብፃዊት]
፫. አባ ሕልያስ ሰማዕት
፬. ቅዱስ ጊዮርጊስ ሐዲስ

[ † ወርሐዊ በዓላት ]

፩. ቅዱስ ቂርቆስና እናቱ ኢየሉጣ
፪. ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ አፈ በረከት
፫. ቅዱስ ሚናስ ግብፃዊ
፬. ቅድስት እንባ መሪና
፭. ቅድስት ክርስጢና

" ሰው ሁሉ እንደ እኔ ሊሆን እወዳለሁና:: ነገር ግን እያንዳንዱ ከእግዚአብሔር ለራሱ የጸጋ ስጦታ አለው:: አንዱ እንደዚህ ሁለተኛውም እንደዚያ:: ላላገቡና ለመበለቶች ግን እላለሁ:: እንደ እኔ ቢኖሩ ለእነርሱ መልካም ነው:: ነገር ግን በምኞት ከመቃጠል መጋባት ይሻላልና ራሳቸውን መግዛት ባይችሉ ያግቡ::" † [፩ቆሮ.፯፥፯] [7:7]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
💖                    🕊                     💖

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

የመጽሐፍ ቅዱሱ ከሆነ ይሄው👆👆

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

🕊                       💖                      🕊

[       የዐቢይ ጾም ሦስተኛ ሳምንት      ]

💖

[        🕊     ም ኵ ራ ብ      🕊       ]


[ እንኳን ለዐቢይ ጾም ሦስተኛ ሳምንት እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። ]

                      †                           

[        ምኵራብ !           ]


ሦስተኛው የዐቢይ ጾም ሳምንት " ምኵራብ " ይባላል፡፡ ምኵራብ አምልኮተ እግዚአብሔር ሲፈጸምበት ፣ ሕገ ኦሪት ሲነበብበት የነበረ በአይሁድ የሚሠራ መካነ ጸሎት ነው፡፡ ዘወትር ቅዳሜ ብዙ ሕዝብ ይሰበሰብበት ስለ ነበር ጌታችን ለማስተማር ብዙ ጊዜ በምኵራብ ተገኝቶአል፡፡

ስያሜው የተወሰደው በዮሐንስ ፪፥፲፬ "ወረከበ በምኵራብ እለ ይሠይጡ አልህምተ ወአባግዐ ወአርጋበ … ፤ በመቅደስም በሬዎችን ፣ ላሞችን ፣ በጎችን ፣ ርግቦችን ፣ የሚሸጡትን አገኘ …" ተብሎ ከተገለጸው ኃይለ ቃል ላይ ሲኾን ፣ ‹ምኵራብ› የሚለው ቃልም በአማርኛ ‹መቅደስ› ተብሎ ተተርጕሟል፡፡

ምኵራብ የሚባለው ሳምንት ጌታችን ወደ ምኵራብ ገብቶ ማስተማሩ የሚነገርበት ፤ "ቤቴ የጸሎት ቤት ይባላል ፤ እናንተ ግን የሌቦች ዋሻ አደረጋችሁት" ብሎ በምኵራብ ይሸጡ ፣ ይለውጡ የነበሩትን የገሠፀበት ፤ ቤተ መቅደስን የከብት መንጃ የወርቅና የብር መነገጃ ያደረጉ ሰዎችን ከነሸቀጣቸው ከቤተ መቅደስ ያስወጣበት ፤ ቤተ መቅደስ የእግዚአብሔር ማደሪያ ፣ የስሙ መጠሪያ፣ የጸሎት ሥፍራ መኾኗን ያስረዳበትና ያወጀበት ፤ በቤተ መቅደስ የንግድ ሥራ ማከናወን እንደማይገባ ያረጋገጠበት ዕለት ነው፡፡

[ በመምህር ምሥጢረ ሥላሴ ማናየ ]

†                       †                       †

[ " ኢየሱስም ወደ መቅደስ ገባና በመቅደስ የሚሸጡትንና የሚገዙትን ሁሉ አወጣ ፥ የገንዘብ ለዋጮችንም ገበታዎች የርግብ ሻጮችንም ወንበሮች ገለበጠና።

ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች ተብሎ ተጽፎአል ፥ እናንተ ግን የወንበዶች ዋሻ አደረጋችኋት አላቸው
።" [ ማቴ . ፳፩ ፥ ፲፪ ]

🕊                        💖                       🕊

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

                          †                          

     [   🕊  መዝሙረ ተዋሕዶ   🕊   ]  

🍒▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬🍒               

[  ኦርቶዶክሳዊ የተቀደሰ ያሬዳዊ ዝማሬ ሰዓት  ]

[ ሳምንታዊ መርሐ-ግብር ]

🕊

በስመ አብ ፡ ወወልድ ፡ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን፡፡

ኦርቶዶክሳዊ መዝሙር ንጹሕና የተቀደሰ ነው ፥ ለእግዚአብሔር ምስጋናና ልመና የሚቀርብበት ፣ ይቅርታና ምሕረት የሚጠየቅበት ፣ ሰውን ሳይሆን እግዚአብሔርን ደስ ለማሰኘት የሚዘጋጅ ንጹሕ መስዋዕት ነው ፥ በአበው ጸሎት ይዘጋጃል ፥ ከስጋዊና ከደማዊ ሀሳብ የራቀ ነው ፥ ልቦናን ወደ ንስሐ ይጠራል ፥ ከኃጢአትና ከክፉ ሥራ የመለየት ኃይል አለው ፥ ክፉ መንፈስን ከሰው ልብ ያርቃል ፥ መረጋጋትን ልቦናን ዘልቆ የሚሰማ ውስጣዊ ሰላምን ይሰጣል ፥ በአሚነ ሥላሴ ያጸናል ፥ የክርስቶስን የባህርይ አምላክነትና መሐሪነት ይመሰክራል ፥ የእመቤታችንን ፍቅር በልቦና ያሳድራል ፥ በእናትነቷና በምልጃዋ እንድንታመን ያደርጋል ፥ በቅዱሳን ጸሎትና በቃል ኪዳናቸው ያጸናል ፥ ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን እናውቅ ዘንድ መንገድ ይመራናል ፥ ፈሪሐ  እግዚአብሔርንና ፍቅረ እግዚአብሔርን ያጎናጽፈናል፡፡

†                       †                       †

ተወዳጆችሆይ ፦ በተቀደሰ ሰማያዊ ያሬዳዊ ዜማ ነብሳችንን እናስጊጣት፡፡ ከደጋጎቹ አባቶቻችን ጋር ከዓለም ርኩሰት በተለየ የተቀደሰ ዝማሬ አምላካችን እግዚአብሔርን እናመሥግን፡፡ ለስጋዊ ጆሮዎች ከሚመች ከረከሰ የተሃድሶ የኑፋቄ እርሾ ልቦናችንን እንጠብቅ፡፡ ገንዘብን ስለመውደድ ከሆነ ከሥጋዊ ሥራ ፈጽሞ እንለይ፡፡

🍒

[ 🕊 ወደ ምኵራብ ገብቶ አስተማረ ! 🕊 ]

[ ወደ ቅፍርናሆምም ገቡ ፤ ወዲያውም በሰንበት ወደ ምኵራብ ገብቶ አስተማረ።

እንደ ባለ ሥልጣን ያስተምራቸው ነበር እንጂ እንደ ጻፎች አይደለምና በትምህርቱ ተገረሙ።  ]

{  ማር. ፩ ፥ ፳፩   }  

†                       †                       †
💖                    🕊                    💖

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

💛
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

🕊   ዐቢይ ጾም [  ጾመ እግዚእ  ]  🕊


▷  " ት እ ግ ስ ት ና ታ ዛ ዥ ነ ት   "


[ " በቅዱሳን አባቶቻችን አስተምህሮ ... ! " ] 

[                        🕊                        ]
----------------------------------------------

" ልጆች ሆይ ፥ በሚገለጥበት ጊዜ እምነት እንዲሆንልን በመምጣቱም በእርሱ ፊት እንዳናፍር በእርሱ ኑሩ።

ጻድቅ እንደ ሆነ ካወቃችሁ ጽድቅን የሚያደርግ ሁሉ ከእርሱ እንደ ተወለደ እወቁ።" [፩ዮሐ.፪፥፳፰ ]



🕊                       💖                   🕊

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

ዓርብ - መጋቢት 13 2016 ዓም  

ሉቃስ 11-15 
 
ሰላም ለሁላችሁ ይሁን! በዛሬው የዐቢይ ጾም ንባባችን የሉቃስ ወንጌልን ከምዕራፍ 11-15 ድረስ እናነባለን።

ከንባብ በፊት የሚደረግ ጸሎት፡ “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፤ የአንተን ቃላት እሰማ እና እረዳ ዘንድ፥ እንዲያውም ፈቃድህን ለመፈጸም እበቃ ዘንድ የልቤን ጆሮዎች እና ዓይኖች ክፈትልኝ።” (ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ)

የዛሬው ንባብ ሉቃ 11-15 ነውና፥ እርሱ እንዲነበብ ይሁን።

መልካም ንባብ!
/channel/OrthodoxTewahdoBooks

/channel/c/2014228571/1

Читать полностью…
Subscribe to a channel