mikreabew | Unsorted

Telegram-канал mikreabew - ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

874

"እንግዲህ፡ንስሓ፡ግባ፤አለዚያ፡ፈጥኜ፡ እመጣብሃለሁ፡፡" ራዕ 2፥16

Subscribe to a channel

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

1.ስራ የለኝም እና ምን ሠርቼ የተሻለ ገቢ ላግኝ? ከሆነ

2. ስራ አለኝ ግን በማገኘው ደሞዝ ብቻ ኑሮ ውድነቱን መቋቋም አልቻልኩም እና
እንዴት ተጨማሪ ገቢ ላግኝ? ከሆነ

3.ተማሪ ነኝ ግን ከትምህርቴ ጎን ለጎን ቢዝነስ በመስራት ለነገዬ የሚሆን ገቢ እንዴት ማግኘት ችላለው? ከሆነ

ለዚህ ሁሉ መልስ እኛጋ ያገኛሉ።

ቢሮአችን መታቹህ ሙሉ መረጃውን ለመውሰድ  ፍቃደኛ ከሆናቹህ!

👉ሰም
👉ሰልክ
👉አድራሻ( ከተማ) ይላኩልን!
ክፍላገር ለሆናቹም በ online ይህን ድንቅ እድል ማግኘት ይችላሉ
👇👇👇

address A.A
ለበለጠ መረጃ
የቴሌግራም አድራሻችን : @Eyu16f

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

ሰኞ - የካቲት 11 2016 ዓ.ም

ዘኁልቁ 20-24

ሰላም ለሁላችሁ ይሁን! በዛሬው እለት ንባባችን ከምዕራፍ 20 እስከ 24 ድረስ እናነባለን።

ከንባብ በፊት የሚደረግ ጸሎት፡ “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፤ የአንተን ቃላት እሰማ እና እረዳ ዘንድ፥ እንዲያውም ፈቃድህን ለመፈጸም እበቃ ዘንድ የልቤን ጆሮዎች እና ዓይኖች ክፈትልኝ።” (ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ)

በዛሬው ንባባችን ላይ እስራኤል ውሃ የለንም ብለው ስለማጉረምረማቸው እና ስለ ሙሴ ድርጊት፥ ስለ ካህኑ አሮን እና ስለ ማርያም ሞት፥ እስራኤላውያን በሚያደርጉት ጉዞ ውስጥ ተቃዋሚዎች እንደገጠሙዋቸው፥ በማጉረምረማቸው የተነሳም እግዚአብሔር እባብ ልኮ እንደቀጣቸው ተጽፎ ይገኛል። በተጨማሪም፥ በሞዓብ ንጉሥ እስራኤልን ይረግም ዘንድ ስለተጠራው በለዓምም እናነባለን።

*የክለሳ ጥያቄዎች*

1) በዘኁልቁ 20 ላይ ባለው ንባብ መሠረት፥ የሞቱት ሁለት ሰዎች ማን እና ማን ናቸው?

2) እግዚአብሔር ሙሴ እና አሮንን ለእስራኤል ወደ ሰጠው ምድር እንደማይገቡ የነገራቸው ለምንድር ነው?

3) በዘኁልቁ 21 መሠረት፥ ሕዝቡ በእግዚአብሔር ላይ ባጉረመረመ ጊዜ በምን ተቀጣ?

4) የሞዓብ ሽማግሌዎች አስቀድመው ወደ በለዓም በመጡ ጊዜ ምላሹ ምን ነበር?

5) በዘኁልቁ 22 መሠረት፥ እግዚአብሔር ለበለዓም ምን ነገረው?

6) የበለዓም አህያ በመንገድ ላይ ያስቸገረችው ለምንድር ነው? የእርሱስ ምላሽ ምን ነበር?

7) “በያዕቆብ ላይ አስማት የለም፥ በእስራኤልም ላይ ምዋርት የለም” የሚለው ቃል የሚገኘው በየትኛው ምዕራፍ እና ቁጥር ላይ ነው?

መልካም ንባብ!
/channel/OrthodoxTewahdoBooks

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

               †               


" ነገር ግን ክፉዎች ሰዎችና አታላዮች ፥ እያሳቱና እየሳቱ ፥ በክፋት እየባሱ ይሄዳሉ።" [፪ጢሞ.፫፥፲፫]


" ገንዘብንም በመመኘት በተፈጠረ ነገር ይረቡባችኋል" [፪ጴጥ.፪፥፫]


         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

የዘመኑ ሐሳዊ አጥማቅያን እና የአጋንንት ምስክርነት !

[  ክፍል አምስት  ]

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬


የአጋንንትን ምስክርነትና ትምህርት ማዳመጥ !


🔔

በዘመናችን የተነሱ በጣት የሚቆጠሩ ሐሳዊ አጥማቂያን የረከሱ አጋንንትን "ምስክርነት" ሕይወት እንደሆነው እንደ እግዚአብሔር ቃል ምዕመኑ እንዲያዳምጥ እያደረጉ ስለመሆናቸው በቀደመው ክፍል ተመልክተናል። ሰይጣን የሃሰት አባትና ነብሰ ገዳይ ፤ ምህረትን የማያውቅ ቋሚ የሰው ልጅ ጠላት ፤ ለቅጽበት እንኳን ከክፋት ከተንኮልና ሰውን ከእግዚአብሔር ለመለየት ወጥመዶችን ከማዘጋጀት የማያርፍ በመሆኑ የእርሱ ምስክርነት ፍጹም ተቀባይነት የሌለው አጥፊ መሆኑንም አይተናል።

በዚህ ክፍል ደግሞ ወዶ ፈቅዶና ልቡናን ከፍቶ የሰይጣንን ንግግርና ምስክርነት ማዳመጥ የሚያመጣውን ፈተና በጥቂቱ እንመለከታለን።

ሐሰተኛ አጥማቂዎች ተለይተው ከሚታወቁባቸው ተግባራት መካከል አንዱ ከአጋንንት ጋር እየተወያዩ ፥ አጋንንት የሚናገሩትን ንግግር "ምስክርነት" ብለው በተቀደሰው አውደ ምህረት ላይ እንዲደመጥ ማድረግ ፣ የጋኔንን ትምህርት በቪዲዮ ቀርጸው መሸጥ ፥ ይህንን የአጋንንትን ድምፅ በማህበራዊ ትሥሥር ገጾች ማሰራጨት ፣ ዜና አጋንንትን በገጠመኝ መልክ መተረክና ተያያዥ ከአጋንንት ጋር የተቆራኙ ተግባራትን ማከናወን ነው።

ብዙ የዋሃን ይህንን ኢ-ኦርቶዶክሳዊ ልምምድ እንደ ትክክለኛ መንገድ በመቁጠር ቁጭ ብለው የረከሱ አጋንንትን ንግግር ሲያደምጡ ይውላሉ። የሰይጣንን የረቀቀ ክፋትንና ተንኮልን ባለማስተዋል ልባቸውን ከፍተው ፈቃዳቸውንም ሰጥተው ይሰሙታል።

የከፉ የከረፉ አጋንንት እንዲናገሩ ዕድል ቢሰጣቸው እውነት የመሰከሩ መስለው አድማጩ ሊደርስበት የማይችል ከባድ ተንኮልና ወጥመድ አዘጋጅተው ፣ ክፋትን ሠርተው ፣ ልቡን ከፍቶ በሚያዳምጣቸው ሰው ላይም መንፈሳቸውን አሳድረው የረቀቀ ክፋትን ይፈጽማሉ።

ሰው ክቡርና ቅዱስ ሆኖ የተፈጠረ የእግዚአብሔር መንፈስ ማደሪያ ቤተ-መቅደስ ነው። ይህንንም ብርሃነ ዓለም ማኅቶተ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ጳውሎስ ሲገልጸው ፦ "የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደ ሆናችሁ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንዲኖርባችሁ አታውቁምን ? .... የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ቅዱስ ነውና ፥ ያውም እናንተ ናችሁ።" [፩ቆሮ.፫፥፲፮] ይላል።

ሰው [ኦርቶዶክሳዊ ክርስቲያን] የእግዚአብሔር መንፈስ ማደሪያ ቤተመቅደስ በመሆኑ የተለየና የከበረ ነው። ሆኖም ነፃ ፈቃዱን ተጠቅሞ ለአጋንንት ዕድል ቢሰጣቸውና መግቢያ ቀዳዳ ቢያገኙ ልቡን ዙፋን ፥ ሰውነቱን ድንኳን ፥ አዕምሮውን ጓዳ ፥ ኅሊናውን ሰሌዳ አድርገው ነፃነቱን ተጋፍተው ያጎሳቁሉታል። ይጫወቱበታል።

ቅዱስ የሆነው የእግዚአብሔር መንፈስ በእኛ የሚያድርባቸውን መንገዶችና በተቃራኒው የክፉው መንፈስ መግቢያ የሆኑ ምክንያቶችን በጥቂቱ መመልከት ይቻላል ፦

▪ ሰው ቅዱስ የሆነውን የእግዚአብሔርን ቃል ሲሰማ ፥ በቤተክርስቲያ መንፈሳዊ ሕይወት እየተመላለሰ ከምስጢራተ ቤተክርስቲያን ሱታፌ ሲያደርግ ፥ ማኅሌት ሲቆም ፥ ኪዳን ሲያደርስ ፥ ቅዳሴ ሲያስቀድስ ፥ ገድለ ቅዱሳንን ሲያደምጥና ሲያነብ ፥ ቅዱሳን መካናትን ሲሳለም ፥ በቤተ እግዚአብሔር ጸንቶ ሲኖር መንፈሰ እግዚአብሔር እንደሚያድርበትና ጸጋ እግዚአብሔርን እንደሚጎናጸፍ እንዲሁ የሃሰት አባት የሆነውን የሰይጣንን ንግግርና "ምስክርነት" ልቡን ከፍቶ ሲያደምጥም የክፉው መንፈስ እንዲያድርበት በር ይከፍታል።

▪ በቅድስት ቤተክርስቲያን ያሉ ቅዱሳት መጻሕፍትን ስንሳለም ፣ ስናነብ ፣ ስንሰማ ፣ በአቅራቢያችን ስናኖራቸው በቅዱሳት መጽሐፍቶቹ ያለው ቅዱስ መንፈስ በእኛ እንደሚያድርና ክፉውን ከእኛ እንደሚያርቅልን እንዲሁ የረከሱ የኑፋቄና የክህደት መጻሕፍቶችን የሚያነቡ ደግሞ የክፉው መንፈስ ማደሪያ በመሆን የጽርፈት መንፈስ ያርፍባቸዋል።

ለዚህም ነው የቤተክርስቲያናችን መጽሐፍ ማር ይስሐቅ "የመናፍቃንን መጽሐፍ ከመመልከት ተከልከል። "ዑቅ ከመ ኢትቅረብ ኀቤሃ" ወደ እርሷ ከመቅረብና ገልጾ ከማየት እንኳ ተጠንቀቅ። መንፈሰ ጽርፈት [የስድብ መንፈስ] እንዳያድርብህ ነው።" ይላል።

▪ እውነተኞቹ የእግዚአብሔር  ባለሟሎች ቅዱሳንን ፥ አበው ካህናትን ፥ ደጋግ የሆኑ መንፈሳዊ ሰዎችን ስንቀበል በእነርሱ የሚኖር የእግዚአብሔር መንፈስና የከበረ በረከታቸው በእኛና በቤታችን እንደሚያድር ቅዱስ ወንጌል ያስተምረናል። 

"ወደምትገቡበት ቤት ሁሉ አስቀድማችሁ። ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን በሉ። በዚያም የሰላም ልጅ ቢኖር ፥ ሰላማችሁ ያድርበታል ፤ አለዚያም ይመለስላችኋል።" [ሉቃ.፲፥፭]

"ሰላማችሁ ያድርበታል" ሲል የእግዚአብሔር ባለሟል የሆኑ ቅዱሳኑን ፥ አበው ካህናቱን ስንቀበል ሰላም የተባለ በእነርሱ የሚኖር የክርስቶስ መንፈስ በእኛና በቤታችን እንደሚያድር የሚያስረዳ ነው። ያልተቀበላቸው ግን የእግዚአብሔር መንፈስ በዚያ እንደማያድር ያስተምረናል። ይህንን በተቃራኒው ስንመለከተው በየትኛውም ሁኔታ የሰይጣንን ንግግርና "ምስክርነት" መስማትና መቀበል የእርሱ መንፈስ በእኛ እንዲያድር መፍቀድ ማለት ነው።

ከሰይጣን ጋር ንግግር ማድረግና ጆሮና ልቡናን ሰጥቶ የሰይጣንን ንግግር ማዳመጥ የክህደትና የውድቀት መግቢያ በር መሆኑን በእናታችን በሔዋን ታሪክ መማር እንችላለን።

በጸሎት ላይ የነበረው አባታችን አዳም የሰይጣንን ሽንገላ በማስተዋል ፦ "ለይተህ ተናገር" ብሎ ከአጠገቡ ያራቀውና መግቢያ በሩን የዘጋበት ቢሆንም ተቀምጣ የነበረችው ሔዋን ግን ነጻ ፈቃዷን ተጠቅማ የሰይጣንን ንግግር በማዳመጥና ከእርሱ ጋር በመመላለስ የሚገባበትን ትልቅ በር ከፍታለታለች።

ጠላት ሰይጣንም የተከፈተለትን ይህንን በር ምኞቱንና ዓላማውን ለማሳኪያነት ተጠቀመበት። አዋቂም ፥ አላዋቂም ፥ ጠያቂም መስሎ ሲሸነግላት ከቆየ በኋላ ጆሮዋን ፥ ልቧንና ነጻ ፈቃዷን ማግኘቱን ሲረዳ ሰውና እግዚአብሔር የሚለያዩበትን ፥ አዳምና ልጆቹ ወደ ዘለዓለማዊ ባርነት ፥ ጉስቁልናና ሞት የሚወርዱበትን ምክር ባለ ሙሉ ስልጣን ሆኖ መከራት።

"እባብም ለሴቲቱ አላት። ሞትን አትሞቱም ፤ ከእርስዋ በበላችሁ ቀን ዓይኖቻችሁ እንዲከፈቱ እንደ እግዚአብሔርም መልካምንና ክፉን የምታውቁ እንድትሆኑ እግዚአብሔር ስለሚያውቅ ነው እንጂ።" [ዘፍ.፫፥፬]

በዚህም የኃጢዓት ምኞት በእርሷ አደረ። በሔዋንና በሰይጣን መካከል በተደረገው ንግግርና ምልልስ የተነሳ ልቧን ከፍታ ፤ ፈቃዷን ሰጥታ በማዳመጧ የተነሳ መንፈሱን በእርሷ አሳደረ። አስቀድሞ በባህርይዋ የሌለው ጠባይ በእርሷ ተገለጠ። ይኸውም በሌላ ማሳበብና መካሰስ ነበር። አዳምና ሔዋን አስቀድመው ንጹሐንና ፍጹማን የነበሩ ቢሆንም ምክረ ከይሲን ከተቀበሉና መንፈሱን በእነርሱ እንዲያሳድር የነጻ ፈቃዳቸውን በር ወለል አድርገው ከከፈቱለት በኋላ የሰይጣን ባህርያት የነበሩት ሰበብና መካሰስ በነሱ ባህርይም ተገለጡ። አዳም በሔዋን ሲያሳብብ እርሷ ደግሞ በእባብ አሳበበች። እርስ በእርስ መካሰስም ወደ ባህርያቸው ገባ።

የሰይጣንን ንግግር እሺ በጄ ብሎ ፈቅዶ ማዳመጥ ለክህደት ለጥርጥር ለውድቀትና ለሞት የሚያበቃ ብርቱ ስህተት ነው።

ሐሰተኛ አጥማቂዎችን ከመከተልና የአጋንንትን ምስክርነት ከማዳመጥ እራሳችንን እንጠብቅ !

🔔

" የዲያብሎስን ሽንገላ ትቃወሙ ዘንድ እንዲቻላችሁ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ ልበሱ።" [ኤፌ.፮፥፲፩]

         †              †               †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

🕊

[ † እንኳን ለጻድቁ አባ አውሎግ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ]

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †

† 🕊 አባ አውሎግ አንበሳዊ 🕊 †

† አባ አውሎግ ማለት :-

- ከቀደመው ዘመን ጻድቃን አንዱ::
- እንደ ገዳማውያን ፍፁም ባሕታዊ::
- እንደ ሐዋርያት ብዙ ሃገራትን በስብከተ ወንጌል ያሳመኑ::
- በግብፅና በሶርያ በርሃዎች ለ፺ [90] ዓመታት የተጋደሉ ጻድቅና ሐዋርያ ሲሆኑ የሚጉዋዙበትና የሚታዘዛቸው ግሩም አንበሳ ነበር::
- በዚህም አባ አውሎግ "አንበሳዊ" ስትል ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ትጠራቸዋለች::

አባ አውሎግ ከሚታወቁበት አገልግሎት አንዱ ስብከተ ወንጌል ነው:: ምንም እንኩዋ ገዳማዊ ቅዱስ ቢሆኑም ያላመኑትን ለማሳመን : ያመኑትንም ለማጽናት ተጋድለዋል::

እግዚአብሔር በሰጣቸው አናብስት በአንዱ ላይ ተጭነው [መዝ.፺ (90) : በሌላኛው ላይ እቃቸውን አስቀምጠው በየአኅጉራቱ ከመምህራቸው ቅዱስ አውሎጊን ጋር ይዘዋወሩም ነበር:: የጌታ ቸርነት ሆኖም አናብስቱ የቅዱሳኑን ፈቃድ ሳይነገራቸው ያውቁ ነበር::

ሲርባቸውም ተግተው ይመግቧቸው ነበር:: እንዲያውም አንዴ ቅዱሳኑ እንደራባቸው አንዱ አንበሳ ሲያውቅ ከበርሐ ወደ ገበያ መንገድ ወጥቶ ተመለከተ:: በአህያ ላይ ልጁንና ስንቁን [ዳቦ] ጭኖ የሚሔድ ሽማግሌ ነበርና ዳቦውን አንስቶ ወስዶ ለእነ አባ አውሎግ ሰጣቸው::

ከድንጋጤ የተነሳም ሕጻኑ ሙቶ ነበርና ሽማግሌ አባቱ አዘነ:: አንበሳው ግን ሕጻኑንም ወደ ቅዱሳኑ ወስዶ አስረከበ:: ቅዱሳኑም ከሕብስቱ በመጠናቸው በልተው ቢባርኩት እንዳልተበላ ሆነ:: ሕጻኑንም ከሞት በጸሎታቸው አስነስተው ለአንበሳው ሰጥተውታል::

አንበሳውም ስንቁንና ልጁን ለአረጋዊው ሰጥቶት በደስታ ወደ ሃገሩ ተመልሷል:: ቅዱስ አባ አውሎግና መምህሩ አውሎጊን ከ፺ [90] ዓመታት በላይ በዘለቀ ተጋድሏቸው አጋንንትን ያሳፍሩ ዘንድ : ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ንጹሕ መስዋዕት ይሆኑለት ዘንድ በትጋት ኑረዋል::

¤ ብዙ ተአምራትን ሠርተው ፈጣሪያቸውን አክብረዋል::
¤ እንደ ሊቀ ነቢያት ቅዱስ ሙሴ ባሕር ከፍለዋል::
¤ እንደ ቅዱሳን ሐዋርያት ሙት አንስተዋል:: ድውያንን ፈውሰዋል::
¤ እንደ ቅዱስ ዳንኤል አናብስትን ገዝተዋል::
¤ ይህች ቀን ዕለተ ዕረፍታቸው ናት::

†  🕊 ቅዱስ በላትያኖስ 🕊 †

††† ይህ ቅዱስ ሐዋርያዊ ዻዻስ የቀድሞዋ ሮም ሊቀ ዻዻሳት ሲሆን ቸር : ትጉህና በጐ እረኛ ነበር:: መናፍቃንን ሲያርም : ምዕመናንን ሲመክር : ስለ መንጋው እንቅልፍ አጥቶ ኑሯል:: በፍጻሜውም በዚህች ቀን የሮም ንጉሥ ለ፩ (1) ዓመት አሰቃይቶ ገድሎታል:: ዕሴተ ኖሎትን [የእረኝነት ዋጋንም] ከጌታችን ተቀብሏል::

† አምላከ አበው ቅዱሳን በመጽናታቸው ያጽናን:: ከበረከታቸውም ያድለን::

[ † የካቲት ፲፩ [ 11 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. አባ አውሎግ አንበሳዊ
፪. አባ አውሎጊን ጻድቅ [የአባ አውሎግ መምሕር]
፫. አባ በትራ [የጻድቁ አባ ስልዋኖስ ደቀ መዝሙር]
፬. አባ በላትያኖስ ሰማዕት [የሮም ሊቀ ዻዻሳት የነበረ]
፭. አባ አብርሃም ኤዺስ ቆዾስ
፮. አባ መቃቢስ
፯. አባ ኮንቲ

[ † ወርሐዊ በዓላት ]

፩. ቅዱስ ያሬድ ካህን
፪. ቅዱስ ገላውዴዎስ ሰማዕት
፫. ቅዱስ ፋሲለደስ ሰማዕት
፬. ብፁዐን ኢያቄም እና ሐና
፭. አቡነ ሐራ ድንግል ጻድቅ

"በቅዱሳንም ዘንድ ያለው የርስት ክብር ባለ ጠግነት ምን እንዲሆን ለምናምንም ከኁሉ የሚበልጥ የኃይሉ ታላቅነት ምን እንደሆነ ታውቁ ዘንድ ነው::" † [ኤፌ.፩፥፲፱ (1:19)

†  ወስብሐት ለእግዚአብሔር  †
†  ወለወላዲቱ ድንግል   †
†  ወለመስቀሉ ከቡር አሜን   †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]

†          †         †
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
💖                    🕊                     💖

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

                       †                       

  [  🕊  ድምፀ ተዋሕዶ   🕊  ]  

🍒▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬🍒               

[  ሕይወት የሚገኝባቸው የቅድስት ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ትምህርቶች በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን በድምፅ ይቀርባሉ።  ]

[ ሳምንታዊ መርሐ-ግብር ]

🕊             

[    " ቅ ዱ ሳ ት   መ ጻ ሕ ፍ ት ! "    ]
             
             [     ክፍል አራት    ]

" ይህን በመጀመሪያ እወቁ ፤ በመጽሐፍ ያለውን ትንቢት ሁሉ ማንም ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደም ፤

ትንቢት ከቶ በሰው ፈቃድ አልመጣምና ፥ ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ተልከው ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ተናገሩ።" [፪ጴጥ.፩፥፳]


       💖   ድንቅ ትምህርት  💖

[ በመምህራችን በቀሲስ ኅብረት የሺጥላ ]

" የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ፥ ከመከራም ሥጋት ያርፋል።" [ ምሳ.፩፥፴፫ ]

         †              †               †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬
                       👇

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

†                †                  †
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

[     ቤተክርስቲያንን እንወቅ     ]

         [  ክፍል -  ፳  -  ]
                   
[    ሥ ር ዓ ተ    አ ም ል ኮ !     ]

🕊

ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን። "ቤተክርስቲያንን እንወቅ" በተሰኘው ሳምንታዊ መርሐ-ግብር ባለፈው ሳምንት ሥርዓተ አምልኮት በሚለው ዓብይ ርዕስ ሥር ሥርዓተ ቅዳሴን ተመልክተን ነበረ። የዛሬው መርሐ-ግብር እነሆ !

[ 🕊 ሥርዓተ ቅዳሴ በመጽሐፍ ቅዱስ 🕊 ]

ቤተ ክርስቲያናችን ሥጋ ወደሙን የምታከብርበት የተለየ ሥርዓተ ጸሎት አላት፡፡ ይህ ልዩ የምስጋና ጸሎት "ጸሎተ ቅዳሴ" ይባላል፡፡ ያለ ጸሎተ ቅዳሴ ሥጋ ወደሙ አይዘጋጀም [አይፈተትም]፡፡ ያለ ሥጋ ወደሙም ቅዳሴ አይቀደስም፡፡

በቤተ ክርስቲያን የታወቁና እስከአሁንም በአገልግሎት ላይ ያሉ ቅዳሴያት በዓይነት ፲፬ [14] ሲሆኑ ቀደም ባሉት ዘመናት በተለይ በወርኀ ጽጌ ይቀደስ የነበረ "መዓዛ ቅዳሴ" የሚባል ፲፭ኛ [15ኛ] ቅዳሴም በቤተ ክርስቲያናችን ይገኛል፡፡
ጸሎተ ቅዳሴ መሠረቱ መጽሐፍ ቅዱስ ነው፡፡

የዚህ አጭር ገጸ ንባብ /የመግቢያ ንግግር/ ዓይነተኛ ዓላማ ቅዳሴ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት ያለው መሆኑን ግልጽ ማድረግ ነው፡፡

ጌታችንና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ ምሥጢረ ቁርባንን በመፈጸም ከሥርዓተ ጸሎቱ ጋር ለሐዋርያት አሳይቷቸዋል፡፡ ቅዱስ ያሬድ "ወሎሙ አርአየ ሥርዓተ ምሥጢር ዘቁርባን" - "ለእነርሱም የምሥጢረ ቁርባንን ሥርዓት አሳያቸው" በማለት የዘመረው ስለዚህ ነው፡፡
መቼና የት አሳያቸው ለሚል ሰው ወንጌል "እንጀራንም አንሥቶ ባረከ ቆርሶም ለደቀ መዛሙርቱ ሰጠ" ትለናለች፡፡ [ማቴ.፳፮፥፳፮] (26፥26) ይህ የሆነው እንደ ነገ ዐርብ ሊሰቀል ሐሙስ ማታ ነው፡፡ ቦታውም ቤተ አልዓዛር ነው፡፡ በወቅቱ "እንጀራንም አንሥቶ" ያለው ተራ ማዕድን አይደለም፡፡ "ባረከ" የሚለውም የማዕድ ጸሎት አደረገ ለማለት አይደለም፡፡ ታዲያ ምንድን ነው ለሚል ሰው "እንጀራ" ያለው ወደ አማናዊ ሥጋ አምላክነት የሚለወጠውን "ኅብስት" ነው፡፡ "ባረከ" ያለውም በአንድ ቃል ቢገለጥም ለቁርባን ማክበሪያ የሚደረገውን የምስጋና ጸሎት ማለትም ቅዳሴውን ነው፡፡

ይህ የሚታወቀው በወንጌል ውስጥ ከዚህ አስቀድሞ ኢየሱስ ክርስቶስ ኅብስት አበርክቶ በተደጋጋሚ ሕዝብን መግቧል፡፡ እንጀራና ዓሣንም በሚያበረክትበት ጊዜም አመስግኗል፡፡ ይሁን እንጂ ምስጋናው "ጸሎተ ማዕድ" ምግቡም "ምግበ ሥጋ" እንጂ ከዚያ ያለፈ ምሥጢር አልነበረውም፡፡ በጸሎተ ሐሙስ የሆነው ግን እጅግ የተለየ ነበር፡፡

ምክንያቱም በጸሎተ ሐሙስ የምስጋና ጸሎት ኅብስቱ ወደ እውነተኛ ሥጋነት ወይኑም ወደ እውነተኛ ደምነት ተለውጧልና፡፡ ይህም አያይዞ "እንካችሁ፥ ብሉ ይህ ሥጋዬ ነው።" በማለቱ ይታወቃል፡፡ [ማቴ.፳፮፥፳፮] (26፥26)

ይህ ለሥጋ ወደሙ ማክበሪያ የምንጠቀምበት ልዩ የምስጋና ጸሎት "ጸሎተ አኮቴት" ወይም ደግሞ "አኮቴተ ቁርባን" ይባላል፡፡ ለዚህ ነው ገባሬ ሠናዩ ካህን በቅዳሴ ጊዜ ከሥርዓተ ቅዳሴ ወደ ፍሬ ቅዳሴ ሲገቡ "አኮቴተ ቁርባን ዘእግዝእትነ ማርያም ዘደረሰ ላቲ ፤ አኮቴተ ቁርባን ዘቅዱስ 'እገሌ' …" የሚሉት፡፡ እስከዚህ ያለው ስለ ሥጋው የተነገረው ነው፡፡

እንዲሁ ደግሞ ቅድስት ወንጌል ስለ አማናዊ ደሙ "ጽዋንም አንሥቶ አመስግኖም ሰጣቸው፡፡" ትለናለች፡፡ [ማቴ.፳፮፥፳፯] (26፥27) "አመስግኖ" የምትለዋን ቃል ልብ በሉ፡፡ ቀደሰ ማለት አመሰገነ ማለት ነውና፡፡ ቅዳሴ ማለት ደግሞ ምስጋና ማለት ነው፡፡ አመስግኖ ሲል ቀድሶ ማለቱ እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡

ስለዚህ ምንም እንኳን ምን ብሎ እንደቀደሰ በወንጌሉ ላይ በዝርዝር ባይቀመጥም ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋ ወደሙን ለሐዋርያት ያቀበላቸው ራሱ ቀድሶ ነው፡፡ "አመስግኖም ሰጣቸው" ይላልና፡፡ ጸሎተ ቅዳሴ መሠረቱ መጽሐፍ ቅዱስ ነው ያሰኘውም ይህ ቃል ነው፡፡

ድኅረ ቁርባን ያለው ከ "ነአኩቶ" እስከ "እትዉ በሰላም" ያለው ልዩ ልዩ ክፍሎች ያሉት የጸሎት ክፍልም እንዲሁ መሠረቱ መጽሐፍ ቅዱስ ነው፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ቀድሶ [አመስግኖ] ሥጋውና ደሙን ለሐዋርያቱ ካቀበላቸው በኋላ "መዝሙርንም ከዘመሩ በኋላ ወደ ደብረ ዘይት ወጡ" ይላል፡፡ [ማቴ.፳፮፥፴] (26፥30) እንግዲህ ከቁርባን በኋላ ሐዋርያት የዘመሩት ይህ መዝሙር ዲያቆኑ ከቁርባን በኋላ "ነአኩቶ" ብሎ ጀምሮ እትዉ በሰላም እስኪለን ድረስ ያለውን ክፍል የሚወክል ነው፡፡

ይህን በመሰለ ቅዳሴ የሚፈተተው አማናዊ ሥጋ የሚቀዳውም አማናዊ ደም ነው፡፡ ስለ ስጋው አማናዊነት ቀደም ሲል ጠቅሰናል፡፡ ስለ ደሙ አማናዊነት ደግሞ "ስለ ብዙዎች ለኃጢአት ይቅርታ የሚፈስ የአዲስ ኪዳን ደሜ ይህ ነው።" ይላል፡፡ [ማቴ.፳፮፥፳፯] (26፥27) "ደሜ" እያለ መስጠቱን ልብ ማለት ነው፡፡

"በረከትን የሚሰጥ የሕግ መምህር" ኢየሱስ ክርስቶስ የሐዲስ ኪዳንን ሕግ ሲሠራ በዝርዝር ሳይሆን አጠቃላይ መመሪያ እንደሰጠን አስቀድሞ መረዳት ያስፈልጋል፡፡ ዝርዝሩን ማዘጋጀት የእርሱ ተከታዮችና ሥልጣን የሰጣቸው አባቶች ድርሻ ነው፡፡ እነርሱ ሥርዓቱን ሲሠሩ ደግሞ "እስከ ዓለም ፍጻሜ" ከእነርሱ እንደማይለይ ቃል ኪዳን ገብቷል፡፡

ይህን ሐሳብ በምሳሌ እንመልከት ፦ ኢየሱስ ክርስቶስ "ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ" ወደ እግዚአብሔር መንግሥት እንደማይገባ አስረግጦ አስተምሯል፡፡ ነገር ግን መቼና የት መጠመቅ እንዳለብን ፣ ማን አጥማቂ መሆን እንዳለበት ወዘተ ዝርዝር መመሪያ አልሰጠንም፡፡
ስለ ሥጋ ወደሙም እንዲሁ ነው፡፡ ሥጋውንና ደሙን ያልበላ የዘለዓለም ሕይወት እንደሌለው ሲናገር ሥጋ ወደሙን እንዴት እንደምናገኝ ፣ ማን እንደሚያዘጋጀው ፣ እንዴት እንደሚዘጋጅ ፣ መቼና በምን ዓይነት ዝግጅት መቀበል እንዳለብን ዝርዝር መመረያ አልሰጠንም፡፡ ከዚህ የተነሣ የሚታወኩ በርካታ የእምነት ድርጅቶች አሉ፡፡ ቤተ ክርስቲያናችን ግን ከዚህ ሁከት ነጻ ናት፡፡ ይህን ሁሉ ኃላፊነት የተቀበሉ አባቶች ስላሏት በሚገባ አሰናድተዋታል፡፡

ከዚህ በመነሣት አባቶቻችን ወንጌል "አመስግኖም ሰጣቸው" ትላለች እኛም ሥጋ ወደሙን ለምእመናን ከማቀበላችን በፊት የምናቀርበው ወጥ የምስጋና ሥርዓት ያስፈልገናል ብለው በመንፈስ ቅዱስ ኃይል እየተመሩ በርካታ የቅዳሴ መጻሕፍትን አዘጋጁ፡፡ ሐዋርያት ከቁርባን በኋላ መዝሙር እንደዘመሩ ወንጌል ስለምትናገር እንዲሁ ድኅረ ቁርባን የሚገባውንም ጸሎት አዘጋጁ፡፡ ይህ ሐተታ ስለ ቅዳሴ አጠቃላይ ይዘት የሚናገር ነው፡፡ ስለ እያንዳንዱ ቅዳሴ የውስጥ ይዘት ፣ ስለ ዜማው ፣ ስለ ቅዳሴ ሥርዓት ፣ ስለካህናትና ስለተግባራቸው ፣ ስለአልባሳታቸው እንዘርዝር ብንል ጊዜ ያጥርብናል እንጂ ስለ ሁሉም እንዲሁ ከመጽሐፍ ቅዱስ እያመሳጠሩ ማሳየት ይቻላል፡፡

ይህን ከጣዕሙ ብዛት የተነሣ አጥንትን የሚያለመልም ዝማሬ በሥጋዊ ዓለም ሳለን ቀምሰን እንድናጣጥመው ያደረገን አምላክ ክብር ምስጋና ይድረሰው !

[ ቀሲስ ኅብረት የሺጥላ ]

እግዚአብሔር አምላክ ቤተ ክርስቲያናችንን ሰላም ያድርግልን፤ አሜን፡፡

[ ይቆየን ]

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፥ ወለወላዲቱ ድንግል ፥ ወለመስቀሉ ክቡር፡፡

†                       †                        †
💖                    🕊                     💖

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

እሑድ- የካቲት 10 2016 ዓ.ም

ዘኁልቁ 15-19

ሰላም ለሁላችሁ ይሁን! በዛሬው እለት ንባባችን ከምዕራፍ 15 እስከ 19 ድረስ እናነባለን።

ከንባብ በፊት የሚደረግ ጸሎት፡ “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፤ የአንተን ቃላት እሰማ እና እረዳ ዘንድ፥ እንዲያውም ፈቃድህን ለመፈጸም እበቃ ዘንድ የልቤን ጆሮዎች እና ዓይኖች ክፈትልኝ።” (ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ)

በዛሬው ንባባችን ላይ የመሥዋዕትን ሕግ፥ ሰንበትን በመሻር ምክንያት ስለተቀጣው ሰው፥ በልብስ ላይ ስለሚደረግ ዘርፍ፥ በሙሴ ላይ ስለተነሳበት ዐመፅ፥ አሮን ለሕዝቡ መዳን ስላደረገው ተግባር፥ ስለ በትሩ መለምለም፥ ስለ ካህናት እና ሌዋውያን ተግባር፥ ከመሥዋዕቱ ሌዋውያን ስላላቸው ድርሻ እና ስለ ዐሥራታቸው እናነባለን። ከዚህ በተጨማሪ፥ በሐመድ ስለሚፈጸም የኃጢአት ስርየት ሥርዓት እና በድን የሚነካ ሰው መከተል ስላለበት የመንጻት ሕግም ተጽፎ ይገኛል።

*የክለሳ ጥያቄዎች*

1) በዘኁልቁ 15 መሠረት፥ በሰንበት ቀን እንጨት ሲለቅም የተገኘው ሰው ምን ቅጣት ደረሰበት?

2) እስራኤላውያን በልብሳቸው ጫፍ ላይ ዘርፍ እንዲያደርጉ የታዘዙት ለምንድር ነው?

3) በዘኁልቁ 16 መሠረት፥ በሙሴ ላይ ያመጹት እነማን ናቸው?

4) በሙሴ ላይ ያመጹት ሰዎች ምን ለማድረግ ሞከሩ? እግዚአብሔርስ በምን መልኩ ቀጣቸው?

5) እስራኤላውያን በሙሴና በአሮን ላይ በማጉረምረማቸው ምክንያት ከመጣው መቅሰፍት እንዴት ዳኑ? በመቅሰፍቱ የሞቱ ሰዎች ቁጥርስ ምን ያህል ነው?

6) በዘኁልቁ 17 መሠረት፥ እግዚአብሔር አሮንን እንደመረጠ በምን ታወቀ?

7) በዘኁልቁ 18 መሠረት፥ በእስራኤል መካከል የአሮን ድርሻ ምንድር ነው?

8 ) ከእስራኤል አሥራት የሚቀበሉት ሌዋውያን አሥራት የሚያወጡት እንዴት ነው?

9) በዘኁልቁ 19 መሠረት፥ የሞተን ሰው በድን የሚነካ ሰው ለስንት ቀን ርኩስ ይሆናል?

10) በዘኁልቁ 19 መሠረት፥ በክደኛው ያልታሠረ የተከፈተ እቃ መንካት ይፈቀዳል? ካልሆነ ለምን?

መልካም ንባብ!

/channel/OrthodoxTewahdoBooks

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

                       †                       

  [  🕊  ድምፀ ተዋሕዶ   🕊  ]  

🍒▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬🍒               

[  ሕይወት የሚገኝባቸው የቅድስት ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ትምህርቶች በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን በድምፅ ይቀርባሉ።  ]

[ ሳምንታዊ መርሐ-ግብር ]

🕊             

[    " ቅ ዱ ሳ ት   መ ጻ ሕ ፍ ት ! "    ]
             
             [     ክፍል ሦስት    ]

" ይህን በመጀመሪያ እወቁ ፤ በመጽሐፍ ያለውን ትንቢት ሁሉ ማንም ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደም ፤

ትንቢት ከቶ በሰው ፈቃድ አልመጣምና ፥ ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ተልከው ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ተናገሩ።" [፪ጴጥ.፩፥፳]


       💖   ድንቅ ትምህርት  💖

[ በመምህራችን በቀሲስ ኅብረት የሺጥላ ]

" የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ፥ ከመከራም ሥጋት ያርፋል።" [ ምሳ.፩፥፴፫ ]

         †              †               †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬
                       👇

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

ቅዳሜ - የካቲት 9 2016 ዓ.ም

ዘኁልቁ 10-14

ሰላም ለሁላችሁ ይሁን! በዛሬው እለት ንባባችን ከምዕራፍ 10 እስከ 14 ድረስ እናነባለን።

ከንባብ በፊት የሚደረግ ጸሎት፡ “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፤ የአንተን ቃላት እሰማ እና እረዳ ዘንድ፥ እንዲያውም ፈቃድህን ለመፈጸም እበቃ ዘንድ የልቤን ጆሮዎች እና ዓይኖች ክፈትልኝ።” (ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ)

በዛሬው ንባባችን ላይ እግዚአብሔር እስራኤላውያን መለከት እየነፉ በምን መልኩ መንቀሳቀስ እንዳለባቸው እንደነገራቸው፥ ከሲና ተነስተው እንደ ተጓዙ፥ በአግዚአብሔር ላይ ያጉረመረሙ ሰዎች ስለደረሰባቸውን ቅጣት፥ ስለ ሰባው ሊቃናት መመረጥ እና ለእስራኤላውያን ድርጭት ስለ መውረዱ እናነባለን። በተጨማሪም፥ አሮን እና ማርያም በሙሴ ላይ ስለ ማጉረምረማቸው፥ ሰላዮች ወደ ከነዓን ስለመላካቸው እና ሕዝቡ በእግዚአብሔር ላይ ያነሳው አመጽ ስላስከተለው እርምጃም ተጽፎ ይገኛል።

*የክለሳ ጥያቄዎች*

1) በዘኁልቁ 10 መሠረት፥ የመለከቶቹ ዋና ተግባር ምን ነበር?

2) ሙሴ ታቦቷ በተጓዘች ጊዜ ምን አለ?

3) በዘኁልቁ 11 መሠረት፥ ሕዝቡ በእግዚአብሔር ላይ ባጉረመረሙ ጊዜ ምን ተከሰተ?

4) ሰባው ሊቃናት የተመረጡት ለምንድር ነው? የእግዚአብሔር መንፈስ በወረደላቸው
ጊዜስ ምን ተፈጠረ?

5) ሥጋ ካላገኘን ያሉት ሰዎች ሥጋውን በበሉ ጊዜ ምን ሆኑ?

6) በዘኁልቁ 12 መሠረት፥ አሮንና ማርያም በሙሴ ላይ ያጉረመረሙት ለምን ነበር?

7) በሙሴ ላይ ያጉረመረመችው ማርያም ምን ሆነች?

8 ) በዘኁልቁ 13 መሠረት፥ ከነዓንን ሰልለው የመጡት ሰዎች ምን አሉ?

9) በዘኁልቁ 14 መሠረት፥ ሕዝቡ በእግዚአብሔር ላይ ያጉረመረመው ምን ብሎ ነው?

10) በእግዚአብሔር ላይ ያጉረመረሙት ሕዝቡ በምን ተቀጡ?

መልካም ንባብ!
/channel/OrthodoxTewahdoBooks

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

🕊

[ † እንኳን ለአባታችን ታላቁ ቅዱስ በርሱማ ሶርያዊ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። † ]

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †

[ † 🕊 ታላቁ አባ በርሱማ 🕊 † ]

† ታላቁ [THE GREAT ይሉታል] አባ በርሱማ በሶርያ ቤተ ክርስቲያን ምንኩስናና ገዳማዊ ሕይወትን ያስፋፋ አባት ነው::

በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን ምድረ ሶርያን ጨምሮ በብዙ ቦታዎች የቅድስና ሕይወትን ያስፋፋው ቅዱስ በርሱማ ለቤተ ክርስቲያን ምሰሶ ከሆኑላት አበው አንዱ ነው:: እርሱ ከተጋድሎው ብዛት ለ54 ዓመታት ያለ እንቅልፍ ቆይቷል::

በእነዚህ ዘመናትም ግድግዳ ላይ ጠጋ ብሎ ከማረፉ በቀር መቀመጥን እንኩዋ አልመረጠም:: በመዓልትም በሌሊትም በፍቅር አብዝቶ ስለ ራሱና ስለ ሕዝቡ በመጸለዩ የብዙዎቹን ነፍስ ወደ ሕይወት ማርኩዋል::

ገዳማትን ከማስፋፋትና ደቀ መዛሙርትን ከማብዛቱ ባለፈ በስብከተ ወንጌልም የተመሰከረለት አባት ነበር:: በ፬፻፴፩ (431) ፬፻፳፫ (423) ዓ/ም በኤፌሶን በተደረገው የቅዱሳን ጉባኤ ላይ ከተገኙ ሊቃውንትም አንዱ ነው:: በቅድስና ሕይወቱ የተገረመው የቁስጥንጥንያው ንጉሥ [ትንሹ ቴዎዶስዮስ] የንግሥና ቀለበቱን እና ማኅተሙን ሸልሞታል::

ቅዱሱም የዋዛ አልነበረምና በንጉሡ ማኅተም እያተመ "ተፋቀሩ" የሚሉ ብዙ አዋጆችን ወደ መላው ዓለም ልኩዋል:: በ፬፻፶፩ [451] ፬፻፵፫ (443) ዓ/ም በኬልቄዶን ፮፻፴፮ [636] ሰነፍ ዻዻሳት ጉባኤ አድርገው አባ ዲዮርስቆሮስን እንደ ገደሉት ሲሰማም ወደ ቤተ መንግስት ሒዶ ከሃዲዎቹን [መርቅያንና ሚስቱ ብርክልያን] በአደባባይ ዘልፏቸዋል::

ስለ አዘነባቸውም ተቀስፈዋል:: ታላቁ ቅዱስ አባ በርሱማ ፀሐይን ማቆሙን ጨምሮ በርካታ ተአምራትን ሠርቶ በዚህች ቀን ዐርፏል::

† ቸር አምላኩ ከበረከቱ ይክፈለን::

[ † የካቲት ፱ [ 9 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. አባ በርሱማ ሶርያዊ [ለሶርያ መነኮሳት ኁሉ አባት]
፪. አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ [ኢትዮዽያዊ] የመነኮሱበት በዓል
፫. ቅዱስ ዻውሎስ ሶርያዊ [ሰማዕት]
፬. ቅዱስ ዼጥሮስ ሰማዕት

[ † ወርሐዊ በዓላት ]

፩. "318ቱ" ቅዱሳን ሊቃውንት [ርቱዐነ ሃይማኖት ዘኒቅያ]
፪. የብሔረ ብፁዐን ጻድቃን
፫. አባ መልከ ጼዴቅ ዘሚዳ [ኢትዮዽያዊ]
፬. ቅዱስ ዞሲማስ ጻድቅ [ዓለመ ብፁዐንን ያየ አባት]

" ምን ይዤ ወደ እግዚአብሔር ፊት ልምጣና በልዑል አምላክ ፊት ልስገድ? የሚቃጠለውን መስዋዕትና የአንዱን ዓመት ጥጃ ይዤ በፊቱ ልምጣን ? እግዚአብሔርስ በሺህ አውራ በጐች: ወይስ በእልፍ የዘይት ፈሳሾች ደስ ይለዋልን? . . . ሰው ሆይ! መልካሙን ነግሮሃል:: እግዚአብሔርም ከአንተ ዘንድ የሚሻው ምንድር ነው? ፍርድን ታደርግ ዘንድ: ምሕረትንም ትወድ ዘንድ: ከአምላክህም ጋር በትሕትና ትሔድ ዘንድ አይደለምን?" † [ሚክ.፮፥፮] (6:6)

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

                †               


[ ንህነሰ ዘክርስቶስ ! ]


"በዋጋ ተገዝታችኋልና ለራሳችሁ አይደላችሁም"

[ ፩ቆሮ.፮፥፲፱]


         †              †               †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

                           †                           

   [            ቀኑ አርብ ነው !           ]
▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬

[  " የዕለተ ዓርቡን መከራህን አሳየኝ ! "  ]

-------------------------------------------------

" ሕሊናቸው የክርስቶስን ሕማም ከማሰብ አቁሞ የማያውቀው አባ መብዓ ጽዮን መድኃኔዓለምን ፦ "ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ የዕለተ ዓርቡን መከራህን አሳየኝ፡፡ ስለ ራሴ ፈጽሞ አለቅስ ዘንድ" ሲሉ ለመኑት፡፡ ጌታም ፦ "መከራ መስቀሌን ለማየት ትፈቅዳለህን? " ብሎ ጠየቃቸው። ጻድቁ አባ መባዓ ጽዮንም ፦ "አዎ ! አይ ዘንድ እወዳለሁ" አሉት።

ያን ጊዜም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀሉ ላይ እጆቹና እግሮቹ ተቸንክረው ታየ ፣ በራሱም ላይ የእሾህ አክሊል ደፍቶ ነበር፡፡ እንዲህ ሆኖ በሮም አደባባይ ለቅዱስ ጴጥሮስ እንደታየው ታያቸው። ይህን የመድኃኔዓለም መከራ የተመለከቱ የጻድቁ ዓይኖችም ፈዝዘው እስኪጠፉ ድረስ ትኩስ እንባዎችን ሲያዘንቡ ኖረዋል።


"ኃይልየ ወጸወንየ ውእቱ እግዚእየ"  [ ኃይሌና መጠጊያዬ እርሱ ጌታዬ ነው ! ]

🕊

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፤ ወለወላዲቱ ድንግል ፤ ወለመስቀሉ ክቡር። አሜን።

†                       †                         †
💖                    🕊                     💖

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

ድንግል ማርያምን 'እንደኔ ሰውኮ ናት' ለሚሉ

ከ'የብርሃን እናት መጽሐፍ' የተወሰደ

/channel/OrthodoxTewahdoBooks

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

                        †                        


" ቤተ ክርስቲያን ተስፋህ ናት ፤ ቤተክርስቲያን መድኃኒትህ ናት ፤ ቤተክርስቲያን የመማፀኛ ከተማህ ናት፡፡ "

[ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ]


†                       †                        †
💖                    🕊                     💖

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

        †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬

[ እግዚአብሔር ከፊትህ ያሳድዳቸዋል ! ]


" አስማተኛም ፥ መተተኛም ፥ በድግምት የሚጠነቍልም ፥ መናፍስትንም የሚጠራ ፥ ጠንቋይም ፥ ሙታን ሳቢም በአንተ ዘንድ አይገኝ።

ይህንም የሚያደርግ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት የተጠላ ነው ፤ ስለዚህም ርኵሰት አምላክህ እግዚአብሔር ከፊትህ ያሳድዳቸዋል።

አንተ ግን በአምላክህ በእግዚአብሔር ዘንድ ፍጹም ሁን።" [ ዘዳ.፲፰፥፲፩ ]

🔔

ይልቁንም በዘመናችን ቤተክርስቲያን በመናፍቃን እንድትሰደብ ፤ ክብረ ክህነትም እንዲደፈር በማድረግ አባቶቻችን ካህናትን ከምዕመናን ለመለየት ሰይጣን ያዘጋጃቸውን እንዲህ ያሉ የዲያብሎስ ሠራዊቶችን ከእኛ ዘንድ እናርቅ ! እንዲህ ያሉት የክፋት ሰራተኞች ለሐሰተኛ አጥማቂያን የገበያ ምንጭ በመሆን እየተመጋገቡ እንደሚሰሩም እናስተውል !

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

🕊

[ † እንኳን ለኢትዮዽያውያን ሰማዕታት ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ]

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †

🕊 † ኢትዮዽያውያን ሰማዕታት †  🕊

† በ፲፱፻፳፱ [1929] ዓ/ም: የካቲት ፲፪ [12] ቀን ከ፴ ሺህ [30,000] በላይ ኢትዮዽያውያን አባቶች : እናቶች : ወጣቶችና ሕፃናት በሮማዊው የፋሽስት ጦር ደማቸው ፈሷል:: እነዚሕ ወገኖቻችን ደማቸው እንደ ጐርፍ አዲስ አበባ ላይ የፈሰሰው ስለ ሃገር ፍቅር ብቻ አልነበረም:: ስለ ቀናች ሃይማኖት ተዋሕዶ ጭምር ነው እንጂ::

† ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ግፃዌ ላይ ስማቸውን ጽፋ በቅዱስ ዳዊት መዝሙር እንዲህ ታስባቸዋለች::

"አቤቱ አሕዛብ ወደ ርስትህ ገቡ::
የቅድስናህንም መቅደስ አረከሱ::
ኢየሩሳሌምንም እንደ መደብ አደረጉአት::
የባሪያዎችህንም በድኖች ለሰማይ ወፎች አደረጉ::
የጻድቃንህንም ሥጋ ለምድር አራዊት::
ደማቸውንም በኢየሩሳሌም ዙሪያ እንደ ውሃ አፈሰሱ:: የሚቀብራቸውም አጡ::" [መዝ.፸፰፥፥፩]

† ሰማዕታቱን እናስባቸው !


🕊  †  ሶምሶን ረዓይታዊ †  🕊

† እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን : ፳፪ [22] ቱን ሥነ ፍጥረትን ፈጥሮ አዳምን ገዢ አደረገው:: አክሎም በነፍስ ሕያው አድርጐ : በመንፈስ ቅዱስ አክብሮ : ነቢይና ካህን አድርጐ : ካንዲት ዕፀ በለስ በቀር በፍጥረት ሁሉ ላይ አሰለጠነው::

አባታችን አዳም ግን ስሕተት አግኝቶት ከገነት ወጣ:: መከራና ፍዳም አገኘው:: በሁዋላም ለ፻ [100] ዓመት አልቅሶ ንስሃ ገባ:: ጌታም ንስሃውን ተቀብሎ "ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ" የሚል ተስፋ ድህነትን ሰጠው::

ስለዚህም ምክንያት ለ፭ ሺሀ ፭ መቶ [5,500] ዓመታት ትንቢት ሲነገር : ሱባኤ ወደ ታች ሲቆጠር : ምሳሌም ሲመሰል ኖረ:: ከደግ ፍጥረት አዳም እስከ ኖኅ ድረስ : የሴት ልጆች እግዚአብሔርን በንጽሕና ሁነው በደብር ቅዱስ አመለኩ::

ትንሽ ቆይተው ግን ስለተቀላቀሉ ከቃየን ልጆች ጋር በማየ ድምሳሴ ጠፉ:: በጻድቅ ሰው ኖኅ የተጀመረው ትውልድም እግዚአብሔርን ለመዘንጋት ጊዜ አልፈጀበትም:: ነገር ግን ከሴም ዘር ቅንና ጻድቅ ሰው አብርሃም ተገኘ::

ከእርሱም ይስሐቅ : ከዚያም ያዕቆብ [ደጋጉ] ተገኙ:: ያዕቆብም "እሥራኤል" ተብሎ: በልጆቹ "ሕዝበ እግዚአብሔር" የተባለ ነገድ ተመሠረተ:: በተስፋይቱ ምድር በከነዓን እንዳይኖሩም ርሃብ ምድረ ግብጽ አወረዳቸው::

በዚያም ለ፪ መቶ ፲፭ [215] ዓመታት በጭንቅ የባርነትን ሕይወትን አሳለፉ:: እግዚአብሔርም ስለ ወዳጁ አብርሃም ሲል እሥራኤልን አሰባቸው:: የዋሕና ጻድቅ ሰው ሙሴን አስነስቶ እሥራኤልን ከግብጽ ባርነት አዳናቸው::

ይኸውም በጸናች እጅ: በበረታችም ክንድ: በ፱ መቅሰፍት: በ፲ኛ ሞተ በኩር: በ፲፩ኛ ስጥመት ግብጻውያንን አጥፍቶ ነው:: በየመንገዱም ጠላቶቻቸውን እየተበቀለላቸው ነው:: ከዚህ ዘመን ጀምሮም እሥራኤል በመሳፍንትና በካህናት የሚተዳደሩ ሆኑ::

አስቀድሞ ሙሴ በምስፍና: አሮን በክህነት መሯቸው:: ቀጥሎም በቅዱስ ሙሴ ኢያሱ: በአሮን አልዓዛር ተተኩ:: እንዲህ እንዲህ እያለም ከኃያል ሰው ሶምሶን ረዓይታዊ ደረሱ:: ይኸውም ከዓለም ፍጥረት ፬ ሺህ ፪ መቶ [4,200] ዓመታት በሁዋላ መሆኑ ነው::

በጊዜው እሥራኤል ጣዖትን እያመለኩ እግዚአብሔርን ስላሳዘኑት ለጠላቶቻቸው አሳልፎ ይሰጣቸው ነበር:: የአካባቢው መንግስታት እነ አሞን: አማሌቅ: ኢሎፍሊ ስንኩዋ ያኔ ዛሬም ቢሆን እንደምትመለከቱት ዶሮና ጥሬ ናቸው::

በጊዜውም የእሥራኤል ኃጢአት ስለ በዛ ኢሎፍላውያን [ፍልስጤማውያን] ፵ [40] ዓመት በባርነት ገዟቸው:: ንስሃ ሲገቡ ደግሞ ልጅ በማጣት ያዘኑ ማኑሄ እና ሚስቱ [እንትኩይ] : በቅዱስ ሚካኤል ተበሥረው ኃያሉን ሶምሶንን ወለዱላቸው::

እርሱም ናዝራዊ [ከእናቱ ማኅጸን ለጌታ የተለየ] ነበርና ፍልስጤማውያንን ቀጥቶ ወገኖቹን እስራኤልን ከባርነት : በአምላኩ ኃይል ታደገ:: ከኃይሉ ብዛት የተነሳም :-

- አንበሳን እንደ ጠቦት ይገድል [መሣ.፲፬፥፭]
- 300 ቀበሮዎችን አባሮ ይይዝ [መሣ.፲፭፥፫]
- በብርቱ ገመዶች ሲያስሩት እንደ ፈትል ይበጣጥሰው [መሣ.፲፭፥፲፬]
- በአህያ መንጋጋ ሽህ ሰው ይገድል [መሣ.፲፭፥፲፭]
- ጠባቂዎችን ከነ መቃናቸው ተሸክሞ ይወረውር ነበር:: [መሣ.፲፮፥፫]

ውሃ ሲጠማውም ከአህያ መንጋጋ ላይ ፈልቆለት ጠጥቷል:: [መሣ.፲፭፥፲፰] በፍጻሜው ግን ደሊላ በምትባል ሴት ተታልሎ ምሥጢሩን በመግለጡና ጸጉሩ በመላጨቱ ኃይሉን አጥቷል:: ጠላቶቹም ዐይኑን አውጥተው መዘባበቻ አድርገውታል::

በፍጻሜው ግን ኃይሉ እንዲመለስለት ፈጣሪውን ለምኖ : አሕዛብ ለጣኦት በዓል እንደተሰበሰቡ የአዳራሹን ምሰሶ አፍርሶ አጥፍቷቸው ዐርፏል:: [መሣ.፲፫፥፲፮] ቅዱስ ሶምሶን የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጥላ [ምሳሌ] ነው::

† በዘመኑ ሁሉ ቅዱስ ሚካኤል ረድቶታልና በዚህች ቀን መታሠቢያው ይደረግለታል::

[ † 🕊 የካቲት ፲፪ [ 12 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. ፴ ሺህ [ 30,000 ] ሰማዕታተ ኢትዮዽያ [ሮማዊው ፋሽስት የገደላቸው]
፪. ቅዱስ ሶምሶን ረዓይታዊ [የእስራኤል መስፍን]
፫. ቅዱስ አባ ገላስዮስ ገዳማዊ
፬. ቅድስት ዶርቃስ

[ † 🕊 ወርሐዊ በዓላት ]

፩. ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላዕክት
፪. ቅዱስ ማቴዎስ ሐዋርያ
፫. ቅዱስ ድሜጥሮስ
፬. ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ
፭. ቅዱስ ቴዎድሮስ ምሥራቃዊ [ሰማዕት]
፮. ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ
፯. አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ
፰. ቅዱስ ላሊበላ ጻድቅ

† አምላከ አበው ቅዱሳን መዓዛ ቅድስናቸውን ያሳድርብን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን::

" ሶምሶንም :- 'ስለ ሁለቱ ዓይኖቼ ፍልስጥኤማውያንን አሁን እንድበቀል : እግዚአብሔር አምላክ ሆይ ! እባክህ አስበኝ ? አምላክ ሆይ ! . . . እባክህ አበርታኝ ?' ብሎ እግዚአብሔርን ጠራ:: . . . ሶምሶንም :- 'ከፍልስጤማውያን ጋር ልሙት' አለ:: ተጐንብሶም ምሰሶዎችን በሙሉ ኃይሉ ገፋ:: . . . በሞቱም የገደላቸው ሙታን በሕይወት ሳለ ከገደላቸው በዙ::" [መሣ.፲፮፥፳፰]

" እንግዲህ ምን እላለሁ? ስለ ጌዴዎንና ስለ ባርቅ: ስለ ሶምሶንም: ስለ ዮፍታሔም: ስለ ዳዊትና ስለ ሳሙኤልም: ስለ ነቢያትም እንዳልተርክ ጊዜ ያጥርብኛልና:: እነርሱ በእምነት መንግሥታትን ድል ነሡ:: ጽድቅንም አደረጉ . . ." † [ዕብ.፲፩፥፴፪]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ከቡር አሜን †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]


               †        †        †
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
💖                    🕊                     💖

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

        †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬

[       እየሆነ ያለው ይህ ነው ! !      ]

በሐሳዊ አጥማቂያን አድሮ ቅድስት ቤተክርስቲያንን እየተዋጋ ያለው ጥንተ ጠላት ሰይጣን ክፋቱና ተንኮሉ እዚህ ደረጃ ደርሷል !

▪ በተቀደሰው አውደ ምህረት አባቶች ካህናትን በምዕመናን ፊት አቁሞ ክብረ ክህነትን ማዋረድ !

▪ ካህን በሰይጣን ተያዘ ብሎ ሕዝበ ክርስቲያኑ ካህናትን እንዲንቅና እንዲጠላ ንስሐም አምኖ እንዳይገባ ማድረግ !

▪የተሻረውና የተዋረደው ሰይጣን ስልጣነ ክህነት ያላቸውን አባቶችን መያዝ ከቻለ ምዕመናንን በመላ መያዝና መቆጣጠር የሚችል ባለ ስልጣን ተደርጎ እንዲቆጠር በማድረግ ምዕመናንን ለዲያብሎስ ማስማረክ !

▪ካህናት አባቶችን በአደባባይ በማዋረድ ሚሊየነሩ አጥማቂ ከካህናት በላይ መሆኑን ለሕዝቡ ማሳየት !

" በሰይጣን እንዳንታለል ፤ የእርሱን አሳብ አንስተውምና።" [፪ቆሮ.፪፥፲፩]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

ኦርቶዶክሳዊያን ይህንን እድል ተጠቀሙበት

በወር አንድ እሁድ ከ4-6 በአካል በመገኘት ቀሪውን ቀናቶች የትምህርቶቹን ሞጅል በማንበብ እና አሳይመንት በመሰራት በማስታወቂያ ላይ ያሉት መምህራን በአካል በወር አንድ ቀን በዕለተ ሰንበት በመገኘት ነው ትምህርቱ የሚሰጠው ክፍያም የለውም ።

በአራቱም ሰንበት ከ7,000 በላይ አርቶዶክሳዊያን ይህን የተልዕኮ ትምህርት እየተማሩ ይገኛል ።

ስለሆነም የካቲት 17/6/2016 ዓ/ም ይጀመራል

በሚፈልጉት የማህበራዊ ሚዲያ ያሰተዋውቁልን ።

በተቀመጠው ሊንክ እየገባችሁ ተመዝገቡ

/channel/+N3tBr--BphphOGU0

መካነ ህያዋን የተልዕኮ ትምህርት

(ጎፋ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ሰ/ት/ቤት)

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

                        †                             

 †  🕊  ይቤሎ  ጴጥሮስ - ፪ -  🕊  †


    [    የግእዝ መዝሙር ጥናት    ]

            [ ክፍል  - ፲፪  -  ]

የወንድማችን ድንቅ አገልግሎት ! ከጣእሙ ብዛት አጥንትን የሚያለመልም ዝማሬ መላእክትን ያሰማልን።

†                       †                        †
💖                    🕊                     💖

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

📍ወዳጄ ሆይ

አትድከም፣ አትዘን ማን ያውቃል ሸክምህና ህመምህ ሁሉ ተራግፎ ሌላ ሰው ሆነህ ትነሳ ይሆናል። ያለን ፈጣሪ እንኳን በአንድ ሙሉ ሌሊት፣ በቅጽበት ጊዜ ዉስጥም ብዙ ተዓምር ይሠራል።

በቀልባቸው ንፅህና ብቻ ሰላማቸው የበዛ ሰዎች አሉ። ቀልባችሁ ንፁህ ሲሆን ሰላማችሁ ይበዛል፣  ለሌሎች መልካም ስትመኙ በረከታችሁ ይሰፋል። ልብህ የተጠራጠረዉን ነገር ተው፤ ልብ ከዐይን በላይ ያያልና።ወደ ፊት የሚሆነውን ሳትበሳጭ ሳትሰለች በትግስት ጠብቅ።የማይረባና ጥቅም የሌለው ነገር በመከተል ጉልበትህን አታባክን።

ወዳጄ ሆይ

ከሐዘን በኋላ ደስታ እንጂ ምን አለ!
ማጣትን ማግኘት እንጂ ሌላ ምን ይከተለዋል! ምሽቱስ እየነጋ አይደል የሚሄደው?? ከጨለማ በኋላ ብርሃን እንጂ ምን ይመጣል፡፡ የጨለመው ይበራል ፣ የጠፋዉም ይገኛል ።

ሕይወትህን መስዋዕት ያደረግህለት ሥራህ በፈረሰና በተናደ ጊዜ ይህንን ክፋ ፈተና ተቀብለህ ተስፋ ሳትቆርጥ የጠፋውን ሁሉ መልሰህ ለማቋቋም በደከመ መሣሪያ ለመሥራት ሳታመነታ ተነሣ።ያለነው የፈተና ምድር ውስጥ ነው። በበሽታ መፈተን አለ። በኀጢአት መፈተን አለ። በዕዳ መፈተን አለ ፣ የምድር ፈተናዎቿ ተዘርዝረው የሚያልቁ አይደሉም።

እናም ወዳጄ

ያለህን የሌለህን ገንዘብህን ሁሉ አንድነት አከማችተህ ስትሰራበት ሁሉንም ባንድ ጊዜ ስትከሥር አጣሁ ከሠርኩ ብለህ ቃል ሳትተነፍስ አሁንም ሰርተህ ለማተረፍ ከሥር ጀምረህ እንደ ገና አንድ ብለህ ድከም። ዐሳብህ ጉልበትህ ሥሮችህ ታክቶዋቸው በደከሙ ጊዜ ልብህ ብቻ ይበርታ።

ንፋስ የማይወዘዉዘው ዛፍ የለም። ሀሳብ ወስዶ የማይመልሰው ሰዉም የለም። እንዲህም ሆኖ የማይወድቅ ዛፍ አለ። በፈተና የሚፀና የሚበረታ ሰዉም አለ።

            ውብ አሁን❤️

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

                       †                       
                    
†    🕊   ክብርት ሰንበት   🕊    †

💖

"ልጆቻችሁን ይዛችሁ ወደ ቤተክርስቲያን ኑ !

ብቻችሁን አትምጡ፡፡ ብቻችሁን ከመጣችሁ ወደ ሌላ ይሔዳሉ እናንተ እዚህ መጥታችሁ የምትሰሩትን አያውቁም ፡፡ ወዴት እንደሔዳችሁ አያውቁም፡፡ ወራሾቻችሁ አይሆኑም ፡፡ ስለዚህም ወደ ቤተክርስቲያን ስትመጡ ልጆቻችሁን ይዛችሁ ኑ፡፡

አሳዩአቸው ሥዕሉን ይሳሙ ፡ ቅዳሴ ጠበል ይጠጡ ፡ በእምነት አሻሹአቸው ፡ መስቀል እንዲስሙ አስተማሯቸው ፡ ዕጣኑን ያሽትቱ ፡ ሥጋ ወደሙን ይቀበሉ ፡ ቃጭሉን ይስሙ ፡ ደውል ሲደወል ይስሙ ፡ ቄሳቸው ማን እንደሆነ ፡ ቤተክርስቲያናቸው ምን እንደሆነች ፡ በውስጧ ምን ምን እንደሚሰራ ያጥኑ ይማሩ፡፡

ወደ ሰንበቴው እጃችሁን ይዘው ይከተሉ ወደ ማህበር ስትሔዱም ይዛችኋቸው ሂዱ፡፡ ቆሎውን ዳቦውን ተሸክመው ወደ ሰንበቴው ይምጡ ይማሩ፡፡ እነርሱም ነገ ይሄን እንዲወርሱ የነገ ባለአደራዎች መሆናቸውን እንዲያውቁ ።"

[ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ በረከታቸው ይደርብን ]

መልካም ዕለተ ሰንበት !

†                       †                       †
💖                    🕊                    💖

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

🕊

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ አምላክ አሜን። ✞✞✞

[ † እንኩዋን ለቅዱሳን አባቶቻችን ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ: ቅዱስ ዮስጦስ ሰማዕትና አባ ኤስድሮስ ገዳማዊ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ † ]

🕊  †  ቅዱስ ያእቆብ †  🕊

ቅዱስ ያዕቆብ [ የእልፍዮስ ልጅ ] ከ፲፪ [12]ቱ ሐዋርያት አንዱ [ ማቴ.፲፥፩ ] ብዙ አሕጉር አስተምሮ በዚህ ቀን በሰማዕትነት ወደ ፈጣሪው ሔዷል::

ቅዱስ ዮስጦስ በ፫ኛው ክ/ዘመን መጨረሻ ምድራዊ የንግሥና ዙፋንን ንቆ በክርስቶስ ስም በሰማዕትነት ከሚስቱ ቅድስት ታውክልያና ከአንድ ልጁ ቅዱስ አቦሊ ጋር ሰማያዊ ክብርን ተቀዳጅቷል::

አባ ኤስድሮስ ግብፃዊ ሲሆኑ ሹመትን ጠልተው ፈርማ በሚባል ገዳም ለ፷ [ 60 ] ዓመታት በበርሃ ውስጥ ከ፲፰ ሺህ [ 18,000 ] በላይ ድርሳናትን ፅፈዋል:: ይሕም በዓለም ታሪክ ብዙ መጻሕፍትን በመጻፍ ቀዳሚው ያደርጋቸዋል:: ከድርሳናቱ መካከል ፪ ሺህ [ 2,000 ] ያህሉ ዛሬም ድረስ በግብፅ በርሃ ውስጥ ይገኛሉ::

ከስንክሳር


🕊  †  አባ ፌሎ †  🕊

በዚች ቀን የፋርስ ሀገር ኤጲስቆጶስ አባ ፌሎ በሰማእትነት አረፈ ። ይህንንም ቅዱስ ለእሳት እንዲሰዋ ለፀሀይም እንዲሰግድ የፋርስ ንጉስ አዘዘው እምቢ በአለውም ጊዜ ታላቅ ስቃይን አሰቃይቶ እራሱን በሰይፍ ቆረጠው በመንግስተ ሰማያት የሰማእትነትን አክሊል ተቀበለ ።
በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር።


🕊  †  አባ ኤስድሮስ †  🕊

በዚችም እለት በገድል የተጠመደ ምሁር የሆነ የአለሙ ሁሉ መምህር አባ ኤስድርስ ፈርማ ከሚባል አገር አረፈ። የዚህም ቅዱስ ወላጆቹ በምስር አገር የከበሩ ባለፀጉች ናቸው።

ለእስክንድርያ ሊቃነ ጳጳሳትም አባ ቴዎድሮስና አባ ቄርሎስ ዘመዶች ናቸውከእርሱም በቀር ልጅ የላቸውም መንፈሳዊ ትምህርትን ሁሉ አስተማሩት።

ግልፅ አድርጎ አጠናቸው ጠበቃቸውም ዳግመኛም የዮናናውያንን የፍልስፍና ትምህርት የከዋክብትን አካሄድና አለምን መዞራቸውን ተማረ በእውቀቱና በጥበቡም ከብዙዎች ከፍ ከፍ አለ በገድልም የተጠመደ ትሁትና የሚተጋ ሆነ።

በሀገሮችም ያለ ሰዎች ሰለርሱ በሰሙ ጊዜ በእስክንድርያ  አገር ላይ ሊቀ ጵጵስና ይሾመት ዘንድ ተማክረው ከኤጲስቆጶሳቱ ጋር ተስማሙ ። በሌሊትም ወጥቶ ሽሽ ወደ ፈረማ ገዳም ደርሶ በዚያ መነኮሰ።

ከዚያም ወጥቶ ወደ አንዲት አነስተኛ ዋሻ ገብቶ ብቻውን በወስጧ ብዙ ዘመናት ኖረ ብዙ ድርሳናትንና ተግሳፃትንም ደረሰ ከዕርሳቸውም ስለ ነገስታትና ስለ መኳንንት የደረሳቸው አሉ   የቤተ ክርስቲያንን መፃህፍቶችን ብሉያትና ሀዲሳትን ተረጉመ።

የመፅሀፍታቹም ቁጥራቸው አስራ ስምንት ሺህ ነው።  እነዚህም ድርሳናት ተግሳፃት ጥያቄዎችና መልሶች ወደ ሊቃነ ጳጳሳትና ኤጲስቆጶሳት የተላኩ መልእክቶች ናቸው። ወደ ምእመናንም ወንዞች ውኃዎችን እንደሚያፈልቁ እርሱ በመንፈስ ቅዱስ የሚያስፈልቃቸው ሆኗልና።

ይህንንም በጎ ስራውን ሲፈፅሙ መልካም ጉዞውንም አከናውኖ ወደ በጎ ሽምግልና ደርሶ እግዚአብሄርንም አግልግሎ በሰላም አረፈ።

[ † የካቲት ፲ [ 10 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ [ ወልደ እልፍዮስ ]
፪. ቅዱስ ዮስጦስ ሰማዕት
፫. አባ ኤስድሮስ ጻድቅ [ ዘሃገረ ፈርማ ]
፬. አባ ፌሎ ሰማዕት
፭. ቅዱስ ስምዖን
፮. ቅዱስ ኒቆላዎስ

[ † ወርሐዊ በዓላት ]

፩. ቅዱስ ዕፀ-መስቀል
፪. ቅዱስ ናትናኤል ሐዋርያ
፫. ቅዱስ ኒቆላዎስ ዘሃገረ ሜራ
፬. ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ ጻድቅ ንጉሥ
፭. ቅድስት ዕሌኒ ንግስት
፮. አቡነ መልክዐ ክርስቶስ

" . . . ራሳቸውም ስለ እናንተ ሲያማልዱ በእናንተ ላይ ከሚሆነው: ከሚበልጠው ከእግዚአብሔር ጸጋ የተነሳ ይናፍቁዋቹሀል:: ስለማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን::" [፪ኛ ቆሮ.፱፥፲፬ ]

" ለቅዱሳን እንደሚገባ ግን ዝሙትና ርኩሰት ሁሉ: ወይም መመኘት በእናንተ ዘንድ ከቶ አይሰማ:: " [ኤፌ.፭፥፫]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ከቡር አሜን †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]

               †        †        †
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
💖                    🕊                     💖

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

                          †                          

     [   🕊  መዝሙረ ተዋሕዶ   🕊   ]  

🍒▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬🍒               

[  ኦርቶዶክሳዊ የተቀደሰ ያሬዳዊ ዝማሬ ሰዓት  ]

[ ሳምንታዊ መርሐ-ግብር ]

🕊

በስመ አብ ፡ ወወልድ ፡ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን፡፡

ኦርቶዶክሳዊ መዝሙር ንጹሕና የተቀደሰ ነው ፥ ለእግዚአብሔር ምስጋናና ልመና የሚቀርብበት ፣ ይቅርታና ምሕረት የሚጠየቅበት ፣ ሰውን ሳይሆን እግዚአብሔርን ደስ ለማሰኘት የሚዘጋጅ ንጹሕ መስዋዕት ነው ፥ በአበው ጸሎት ይዘጋጃል ፥ ከስጋዊና ከደማዊ ሀሳብ የራቀ ነው ፥ ልቦናን ወደ ንስሐ ይጠራል ፥ ከኃጢአትና ከክፉ ሥራ የመለየት ኃይል አለው ፥ ክፉ መንፈስን ከሰው ልብ ያርቃል ፥ መረጋጋትን ልቦናን ዘልቆ የሚሰማ ውስጣዊ ሰላምን ይሰጣል ፥ በአሚነ ሥላሴ ያጸናል ፥ የክርስቶስን የባህርይ አምላክነትና መሐሪነት ይመሰክራል ፥ የእመቤታችንን ፍቅር በልቦና ያሳድራል ፥ በእናትነቷና በምልጃዋ እንድንታመን ያደርጋል ፥ በቅዱሳን ጸሎትና በቃል ኪዳናቸው ያጸናል ፥ ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን እናውቅ ዘንድ መንገድ ይመራናል ፥ ፈሪሐ  እግዚአብሔርንና ፍቅረ እግዚአብሔርን ያጎናጽፈናል፡፡

†                       †                       †

ተወዳጆችሆይ ፦ በተቀደሰ ሰማያዊ ያሬዳዊ ዜማ ነብሳችንን እናስጊጣት፡፡ ከደጋጎቹ አባቶቻችን ጋር ከዓለም ርኩሰት በተለየ የተቀደሰ ዝማሬ አምላካችን እግዚአብሔርን እናመሥግን፡፡ ለስጋዊ ጆሮዎች ከሚመች ከረከሰ የተሃድሶ የኑፋቄ እርሾ ልቦናችንን እንጠብቅ፡፡ ገንዘብን ስለመውደድ ከሆነ ከሥጋዊ ሥራ ፈጽሞ እንለይ፡፡

🍒

[    🕊  ምስጋና ይገባል !  🕊    ]

[  " የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ የእግዚአብሔርም ፍቅር የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን። አሜን። " ]

{ ፪ቆሮ.፲፫፥፲፬ }  

†                       †                       †
💖                    🕊                    💖

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

#ምክር_ለወዳጅ

ወዳጄ ሆይ !

"ጥረትህ እብቅ ገለባ ካወጣ በጥረትህ አትዘን። ዓለምን በታገሠው እግዚአብሔር ፣ ስንዴ ዘርቶ እንክርዳድ ስንሆንበት ባላጠፋን ጌታ ተጽናና። በየትም ዓለም ብቻውን የሚለማመድ ሯጭ ይኖራል ፣ ብቻውን የሚወዳደር ግን የለም። አንተ ግን ልምምድህም ሩጫህም ብቸኛ መስሎ ሲሰማህ ዳኛህ እግዚአብሔር ፣ ደጋፊዎችህ ቅዱሳን እንደሆኑ አስብ። ሕዝብ ከቦህ ኖረህ አንድ ሰው አጠገብህ የምታጣበት ዘመን አለ። እንዲደረግልህ ቀርቶ ያደረከው መልካም ላይመሰገን ይችላል። እምነት ማለት የሰውን ምላሽ ሳይሆን የእግዚአብሔርን ዋጋ እያሰቡ መሮጥ ነው።"

@marvellous2127

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

ዓርብ - የካቲት 8 2016 ዓ.ም

ዘኁልቁ 6-9

ሰላም ለሁላችሁ ይሁን! በዛሬው እለት ንባባችን ከምዕራፍ 6 እስከ 9 ድረስ እናነባለን።
ከንባብ በፊት የሚደረግ ጸሎት፡ “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፤ የአንተን ቃላት እሰማ እና እረዳ ዘንድ፥ እንዲያውም ፈቃድህን ለመፈጸም እበቃ ዘንድ የልቤን ጆሮዎች እና ዓይኖች ክፈትልኝ።” (ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ)

በዛሬው ንባባችን ላይ ራሳቸውን ለእግዚአብሔር መለየት የሚፈልጉ ናዝራውያን ምን ማድረግ እና ከምን መቆጠብ እንዳለባቸው፥ ካህናት ስለሚሰጡት ቡራኬ፥ የእስራኤል አለቆች ስላቀረቡት መባእ፥ ስለ ሰባቱ መብራቶች አቀማመጥ እና ስለ ሌዋውያን መቀደስና ስለ አገልግሎታቸው እናነባለን። በተጨማሪም የፋሲካ በዓል በሲና እንደተከበረ እና በእሳት አምሳል የታየው ደመና ድንኳኑን እንደ ጋረደውም ተጽፎ ይገኛል።

*የክለሳ ጥያቄዎች*

1) በዘኁልቁ 6 መሠረት፥ ራሱን ለእግዚአብሔር የሚለይ ናዝራዊ ምን ማድረግ ይጠበቅበት ነበር?

2) ካህናት ሕዝቡን ምን ብለው እንዲባርኩ ታዝዘዋል?

3) በዘኁልቁ 7 መሠረት፥ ሙሴ የእግዚአብሔርን ድምፅ ይሰማ የነበረው በየት ነበር?

4) በዘኁልቁ 8 መሠረት፥ ሰባቱ መብራቶች ይበሩ የነበሩት በየት ነው?

5) ሌዋውያን የሚያገለግሉት ከስንት እስከ ስንት ዓመታቸው ድረስ ነው?

6) በዘኁልቁ 9 መሠረት፥ ፋሲካን ማክበር ባለመቻላቸው አቤቱታ ያቀረቡት እነማን ናቸው? የእግዚአብሔርስ ምላሽ ምን ነበር?

7) እስራኤላውያን የሚጓዙት እና የሚቀመጡት ምን በማየት ነበር?

መልካም ንባብ!

/channel/OrthodoxTewahdoBooks

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

የዘመኑ [ሐሳዊ] አጥማቅያን እና የአጋንንት ምስክርነት !

[  ክፍል አራት  ]

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

" አጋንንት የእኛን ጉዳይ ይወስናሉ፡፡ " እስከማለት ለደረሱና የዘመናችንን ሀሰተኛ " አጥማቂያንን " ለሚከተሉ ፦


" ሕይወታችንን ሁሉ እንዲህ ለአጋንንት ሥልጣንንና ግዛት አሳልፈው የሚሰጡት እነዚህ ሰዎች ምን ዓይነት የተመሰቃቀለ ነገር አይተው ነው? "  [ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ]

🔔

" የእግዚአብሔር መለኮታዊ ጥበቃ ግልፅ ሆኖ የሚታየውን ያህል ፀሐይ እንኳ ደምቃ አትታይም፡፡ ሆኖም ግን አንዳንዶች አጋንንት የእኛን ጉዳይ ይወስናሉ እስከ ማለት ደርሰው ይናገራሉ፡፡ እኔ ምን ማድረግ እችላለሁ ? የሚወዳችሁ አፍቃሪ ጌታ አላችሁ ፤ እንደምትሉት ለአጋንንት አሳልፎ ሰጥቷችሁ እነርሱ እንዴት አድርገው እንደሚያስተዳድሩ በተጨባጭ ከሚያሳያችሁ ይልቅ የእናንተን ስድብና የማይገባ ንግግር ቢታገሥ ይመርጣልና፡፡

የምትሉትን በተግባር ታዩት ዘንድ ቢተዋችሁ ኖሮ ምን ያህል ክፉዎች እንደ ሆኑ ከምታዩትና ከሚገጥማችሁ ታውቁ ነበር፡፡ አዎ ፣ አሁን እንደ ምሳሌ በፊታችሁ ይህን ተመልከቱ፡፡ አጋንንት ያደሩባቸው ሰዎች ከመቃብር ወጥተው ክርስቶስን ተገናኙት ፤ አጋንንቱም ወደ እርያ መንጋ ይገቡ ዘንድ እንዲፈቅድላቸው ለመኑት፡፡ መድኃኒታችንም ፈቀደላቸው ፤ እነርሱም ወጥተው ወደ እርያዎቹ ሄዱና ገቡ፡፡ [ማቴ.፰፥፳፰]  ከዚያስ አጋንንቱ እርያዎቹን ምን አደረጓቸው ? በእርያዎቹ እንደ ገቡባቸው ወዲያውኑ በቅጽበት የእርያዎቹ መንጋ ከአፋፉ እየተጣደፉ ወደ ባሕር ውስጥ በመስጠም ሞቱ፡፡

አጋንንት የሚያስተዳድሩት እንዲህ ነው፡፡ ያውም ከእርያዎች ጋር የተለየ ጠላትነት የላቸውም ፣ ከአንተ ጋር ግን የማያቋርጥና የማይበርድ ፣ ዕርቅና የሰላም ውል የሌለው ጦርነት ላይ ናቸው ፣ ለአንተ ያላቸው ጥላቻም ቋሚና የማይሞት ነው፡፡ የተለየ ጠላትነት በሌላቸው በእርያዎች ላይ ሳይቀር እንዲህ ትንሽ እንኳን በሕይወት እንዲኖሩ ጊዜ ሳይሰጡ በቅጽበት እያጣደፉ ወደ ባሕር አስጥመው ካጠፏቸው ፣ በእኛ ላይ ሥልጣን ቢኖራቸው ኖሮ ሁል ጊዜ ጥፋታችንን የሚመኙልንን እኛን ምን የማያደርጉን ነገር ይኖር ነበር ?

አእምሮ በሌላቸው ፍጥረታት ላይ በሚያደርሱት ጥፋት የአጋንንት ክፋት ምን ያህል እንደ ሆነ ትረዳ ዘንድ ነው ወደ እሪያዎቹ ይገቡ ዘንድ ሲለምኑት የፈቀደላቸው፡፡

እንዲሁም አጋንንቱ ያደሩባቸው ሰዎች ባሉበት ሁኔታም ሆነው የእግዚአብሔር መለኮታዊ ጥበቃ ባይጠብቃቸው ኖሮ ልክ ሲፈቅድላቸው በእሪያዎቹ ላይ እንዳደረጉት እነርሱንም ወዲያውኑ እንዳደሩባቸው ባጠፏቸው ነበር፡፡ ሰዎቹን ግን ቢያድሩባቸውም የእግዚአብሔር መለኮታዊ ጥበቃ ስላልተለያቸው ሊያጠፏቸው አልቻሉም፡፡

ዛሬም ቢሆን አጋንንት ያደሩበት ሰው ብታይ እግዚአብሔርን አምልክ ፣ የአጋንንትንም ክፋት ተመልከትበት፡፡ በአጋንንት ድርጊት የእነርሱንም ክፋት ፣ የእግዚአብሔርንም ቸርነት ሁለቱንም ማየት ይቻላልና፡፡ የአጋንንትን ክፋት ያደሩባቸውን በማስጨነቃቸውና በማሰቃየታቸው እናያለን ፤ የእግዚአብሔርን ቸርነትና ጥበቃ ደግሞ በሰው ሲያድሩ ሰውየውን በእርያዎቹ እንዳደረጉት አጣድፈው ወደ ባሕርና ገደል ከተው ሊገድሉት ሲፈልጉ ክፋታቸውን ለመግለጥ ያህል በመጠኑ እንጂ ሙሉ ኃይላቸውን እንዲጠቀሙና ሰውዬውን እንዲያጠፉት አይፈቅድላቸውምና ጥበቃውን በዚህ እናያለን፡፡

እግዚአብሔር ኃይሉን እንዲጠቀም ሲፈቅድለት ጋኔን ነገሮችን እንዴት እንደሚያደርግ ለማየት ሌላ ምሳሌ ትፈልጋለህ ?

የኢዮብን የበግና የከብት መንጋዎች ሁሉንም በአንድ ጊዜ እንደ ደመሰሳቸው አስታውስ ፤ አሳዛኝ የሆነ የልጆቹን ሞት አስብ ፤ በሰውነቱ ላይ የወረደበትን ቁስልና ደዌ ልብ አድርግ፡፡ በዚህም የአጋንንትን ፍጹምና ይህን ያህላል ተብሎ ሊገለጽ የማይችል ጭካኔና ክፋት በግልጽ ታይበታለህ፡፡ ከነዚህም ነገሮች እግዚአብሔር በዚህ ዓለም ነገር ሁሉ ላይ ሥልጣን ሰጥቷቸው ቢሆን ኖሮና እንደ ፈለጉ ማድረግ ቢችሉ ኖሮ ማንኛውንም ነገር ምስቅልቅሉን ባወጡትና በእኛም ላይ ልክ በእሪያዎቹ ላይ እንዳደረጉት ባደረጉብን ነበር፡፡ ሌላው ቀርቶ ለአንዲት ቅጽበት ያህል እንኳ እንድንኖር አይፈቅዱልንም ነበር፡፡

አጋንንት በዚህ ዓለም ባሉ ነገሮች ላይ ሥልጣን ቢኖራቸው ኖሮ ካደሩባቸው ከእነዚያ ሰዎች የተሻለ ሕይወትና አኗኗር አይኖረንም ነበር፡፡ እንዲያውም ከእነርሱም የባስን እንሆን ነበር፡፡ ያደሩባቸውን ሰዎች ሙሉ በሙሉ ለአጋንንት ሥልጣን አሳልፎ አልሰጣቸውምና፡፡ እንዲያማ ባይሆን ኖሮ እንደ እሪያዎቹ ሰጥመው ይሞቱ ነበር፡፡ ነገር ግን ሙሉ በሙሉ ስላልተዋቸው ያደሩባቸውን ሰዎች እንኳን አጋንንቱ እንደ ፈለጉት ማጥፋት አልተቻላቸውም፡፡

እንዲህ የሚሉትን እኔ ይህን ልጠይቃቸው እፈልጋለሁ ፣ ሕይወታችንን ሁሉ እንዲህ ለአጋንንት ሥልጣንንና ግዛት አሳልፈው የሚሰጡት እነዚህ ሰዎች ምን ዓይነት የተመሰቃቀለ ነገር አይተው ነው ? "

[ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ]

------------------------------------------------

አጋንንትን የሁሉ ነገር አድራጊ ፈጣሪ እያደረጉ የፍርሃትን መንፈስን በየዋሃን ልብ በማንገስ ከሚሸቅጡ የዘመኑ [ሐሰተኛ] አጥማቅያንና ወደነሱ ከሚመሩ ምንደኞች እንጠበቅ ❗️

         †              †               †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

                           †                           

[ ተዋሕዶ ፍጽምት የቅዱሳን ሃይማኖት ]
▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬

[   ወደ ሁለት ባሕርይ አይከፈልም !   ]

--------------------------------------------------

" ከቅድስት ድንግል ማርያም የተወለደው ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው አንድ ወልድ ተብሎ ከተጠራ ሁሉ የተፈጠረበት እርሱ አንድ አካል ፤ አንድ ባሕርይ ነው፡፡ ወደ ሁለትነት መከፈል የለበትም።

ለሥጋውም ከመለኮቱ ወደ አንድ ወገን የተለየ ባሕርይ የለውም፡፡ መለኮቱም ከሥጋው ወደ አንድ ወገን የተለየ ባሕርይ የለውም፡፡

ሰው አንድ አካል አንድ ባሕርይ እንደሆነ ፥ ሰው የሆነ የባሕርይ ገዥ ክርስቶስም እንዲሁ አንድ አካል አንድ ባሕርይ ነው እንጂ፡፡ [ፊልጵ.፪፥፭-፮]

አንዱን እንደ መቶ ካላወቁትስ እነሆ ዳግመኛ አንዱን ሰው ወደ ብዙ ወገን ላይከፋፍሉት ይገባቸዋል፡፡ ሥጋ ከብዙ ወገን የተጠራቀመ ነውና ከአጥንት ፤ ከጅማት ከአሥራው ከሥጋ ከቍርበት ፥ ከጥፍር ፥  ከጠጕር ፥ ከደም ፥ ከነፍስ የተጠራቀመ ነውና፡፡ እነዚህም ሁሉ እርስ በርሳቸው ልዩ ልዩ ናቸው፡፡ ግን በእውነት አንድ አካል አንድ ባሕርይ ነው።

እንዲሁም መለኮት ከትስብእት አንድ አካል አንድ ባሕርይ ነው፡፡ ወደ ሁለት አካል ፣ ወደ ሁለት ባሕርይ አይከፈልም፡፡ "

[     አቡሊዲስ     ]

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፤ ወለወላዲቱ ድንግል ፤ ወለመስቀሉ ክቡር። አሜን።

†                       †                         †
💖                    🕊                     💖

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

አባታችን ሆይ - እመቤታችን ሆይ.pdf

ከ'የብርሃን እናት መጽሐፍ' የተወሰደ

/channel/OrthodoxTewahdoBooks

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

        †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬

[ እግዚአብሔር ከፊትህ ያሳድዳቸዋል ! ]


" አስማተኛም ፥ መተተኛም ፥ በድግምት የሚጠነቍልም ፥ መናፍስትንም የሚጠራ ፥ ጠንቋይም ፥ ሙታን ሳቢም በአንተ ዘንድ አይገኝ።

ይህንም የሚያደርግ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት የተጠላ ነው ፤ ስለዚህም ርኵሰት አምላክህ እግዚአብሔር ከፊትህ ያሳድዳቸዋል።

አንተ ግን በአምላክህ በእግዚአብሔር ዘንድ ፍጹም ሁን።" [ ዘዳ.፲፰፥፲፩ ]

🔔

ይልቁንም በዘመናችን ቤተክርስቲያን በመናፍቃን እንድትሰደብ ፤ ክብረ ክህነትም እንዲደፈር በማድረግ አባቶቻችን ካህናትን ከምዕመናን ለመለየት ሰይጣን ያዘጋጃቸውን እንዲህ ያሉ የዲያብሎስ ሠራዊቶችን ከእኛ ዘንድ እናርቅ ! እንዲህ ያሉት የክፋት ሰራተኞች ለሐሰተኛ አጥማቂያን የገበያ ምንጭ በመሆን እየተመጋገቡ እንደሚሰሩም እናስተውል !

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬

Читать полностью…
Subscribe to a channel