mikreabew | Unsorted

Telegram-канал mikreabew - ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

874

"እንግዲህ፡ንስሓ፡ግባ፤አለዚያ፡ፈጥኜ፡ እመጣብሃለሁ፡፡" ራዕ 2፥16

Subscribe to a channel

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

                         †                        

[   ሰ በ ር መ ረ ጃ !  ]

ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ወደ አገር እንዳይገቡ ተከለከሉ

ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የኒውዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በአሜሪካ የነበራቸውን ሐዋርያዊ አገልግሎት ጨርሰው ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ እንዳይገቡ መከልከላቸው ተሰምቷል።

ብፁዕነታቸው ከሳምንታት በፊት በቋሚ ሲኖዶስ እውቅና ወደ ሀገረ ስብከታቸው በመሄድ የአጋእዝተ ዓለም ሥላሴ ዓመታዊ በዓል፣ የከተራና የጥምቀት በዓላትን ከመንፈስ ልጆቻቸው ጋር ያከበሩ ሲሆን ለአዳጊ ሕጻናትም ማዕረገ ዲቁና መስጠታቸው ይታወቃል።

ብፁዕነታቸው በአሁኑ ሰዓት ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያው እንደሚገኙ ታውቋል።

© [ MK ]

         †              †               †

▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

🕊

[ † እንኳን ለጌታችን አማኑኤል ክርስቶስ ዓመታዊ የተአምር በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ]

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †

[ 🕊  † ተአምረ እግዚእ †  🕊 ]

† " ተአምር " የሚለውን ቃል በቁሙ "ምልክት" ብሎ መተርጐም ይቻላል:: መሠረታዊ መልዕክቱ ግን ነጮቹ በልሳናቸው Miracle የሚሉት ዓይነት ነው:: ከተፈጥሮ ሕግ ውጪ [በላይ] : ከፍጡራንም ችሎታ የላቀ ነገር ሲሠራ [ሲፈጸም] ተአምር ይባላል::

ተአምር የእግዚአብሔር የባሕርይ ገንዘቡ ነው:: እርሱ ዓለምን ከመፍጠሩ ጀምሮ እያንዳንዷ ተግባሩ ለእኛ ተአምራት ናቸው:: ስለዚህም ነው "ኤልሻዳይ - ከሐሌ ኩሉ - ሁሉን ቻይ" እያልን የምንጠራው::

እግዚአብሔር ፍጡራኑን ይወዳልና እርሱ ለወደዳቸውና ደስ ላሰኙት ተአምራት ማድረግን ሰጥቷል:: በብሉይ ኪዳን እነ ሙሴ ባሕር ሲከፍሉ: መና ሲያዘንሙ: ውሃ ሲያፈልቁ [ኦሪትን ተመልከት] እነ ኤልያስ ሰማይን ሲለጉሙ: እሳትን ሲያዘንሙ: ሙታንን ሲያስነሱ [፩ ነገሥት] እንደ ነበር ይታወቃል::

እንዲያውም በሙሉ መጽሐፍ ቅዱስ የተአምር መጽሐፍ ነው ብሎ ለመናገርም ያስደፍራል:: በሐዲስ ኪዳንም መድኃኒታችን ብዙ ተአምራትን ሠርቶ ለሐዋርያቱ የተአምራት ጸጋውን ሰጥቷቸዋል:: [ ማቴ.፲፥፰ , ፲፯፥፳ , ማር.፲፮፥፲፯, ሉቃ. ፲፥፲፯, ዮሐ.፲፬፥፲፪ ]

እነርሱም በተሰጣቸው ሥልጣን ብዙ ተአምራትን ሠርተዋል:: [ሐዋ. ፫፥፮ , ፭፥፩ , ፭፥፲፪ , ፰፥፮ , ፱፥፴፫-፵፫ , ፲፬፥፰ , ፲፱፥፲፩]


[ 🕊  † ተአምራተ እግዚእ †  🕊 ]

† ጌታችን በመዋዕለ ስብከቱ ብዙ ተአምራትን ሰርቷል:: እያንዳንዱ ግን ቢጻፍ ዓለም ለራሷ ባልበቃች ነበር:: ከእነዚህ መካከልም አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለ ሥጋዌው በዚህ ዕለት በ፯ እንጀራ እና በጥቂት ዓሣ ሴቶችና ሕፃናትን ሳይጨምር ፬ ሺህ ሰዎችን በቸርነቱ አበርክቶ አጥግቡዋል:: ደቀ መዛሙርቱም ፯ ቅርጫት ማዕድ አንስተዋል::

ጌታችን በከሃሊነቱ የተራቡትን ሲያጠግብ እንዲሁ አይደለም:: በጊዜው የነበሩ አይሁድ ጠማሞች ነበሩና እነሱን ምላሽ በሚያሳጣ መንገድ ነበር እንጂ:: አይሁድ ላለማመን ብዙ ጥረት ነበራቸውና::

በዚህ ዕለትም እንጀራውን አበርክቶ ሲያበላቸው :-

፩. ጊዜው አመሻሽ ላይ ነበር:: ምክንያት :- ጧት ላይ ቢሆን ከቤታችን የበላነው ሳይጐድል ብለው ከማመን ይርቁ ነበርና::

፪. ከውሃ ዳር አድርጐታል:: መታጠቢያ ብናጣ በደንብ ሳንበላ ቀረን እንዳይሉ::

፫. ሳር የበዛበት ቦታ ላይ አድርጐታል:: ምክንያቱም መቀመጫ ብናጣ በደንብ ሳንበላ ቀረን እንዳይሉ::

፬. ከከተማ አርቆ ምድረ በዳ ላይ አድርጐታል:: ያማ ባይሆን "ፈጣን: ፈጣን ደቀ መዛሙርቱ ተሯሩጠው እየገዙ አቀረቡለት" ባሉ ነበርና::

† ለመድኃኒታችን ክርስቶስ አምልኮና ምስጋና ይሁን !

አማኑኤል አምላካችን ጣዕመ ፍቅሩን ያሳድርብን::

🕊

[ † ጥር ፳፰ [ 28 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. ቅዱስ ቀሌምንጦስ ሰማዕት [ስለ ሃይማኖት ፯ ጊዜ ሙቶ የተነሳ , ፯ አክሊል የወረደለት ]
፪. ቅዱስ አካውህ መነኮስ
፫. ፰ መቶ "800" ሰማዕታት
፬. ቅዱስ ዮሴፍ አይሁዳዊ [የእመቤታችን ወዳጅ]
፮. ቅድስት ሳቤላ

[ † ወርሐዊ በዓላት ]

፩. አባቶቻችን አብርሃም: ይስሐቅና ያዕቆብ
፪. ቅዱስ ቴዎድሮስ ሮማዊ
፫. ቅዱስ እንድራኒቆስና አትናስያ
፬. ቅድስት ዓመተ ክርስቶስ

" ጌታ ኢየሱስም ደቀ መዛሙርቱን ጠርቶ :- ሕዝቡ ከእኔ ጋር እስከ አሁን ሦስት ቀን ውለዋልና የሚበሉት ስለ ሌላቸው አዝንላቸዋለሁ:: በመንገድም እንዳይዝሉ ጦማቸውን ላሰናብታቸው አልወድም' አላቸው::

ደቀ መዛሙርቱም :- 'ይህን ያህል ሕዝብ የሚያጠግብ ይህን ያህል እንጀራ በምድረ በዳ ከወዴት እናገኛለን?' አሉት:: ጌታ ኢየሱስም:- 'ስንት እንጀራ አላችሁ?' አላቸው:: እነርሱም:- 'ሰባት: ጥቂትም ትንሽ ዓሣ' አሉት::

ሕዝቡም በምድር ላይ እንዲቀመጡ አዘዘ:: ሰባቱንም እንጀራ: ዓሣውንም ይዞ አመሰገነ:: ቆርሶም ለደቀ መዛሙርቱ ሰጠ:: ደቀ መዛሙርቱም ለሕዝቡ:: ሁሉም በሉና ጠገቡ:: የተረፈውንም ቁርስራሽ ሰባት ቅርጫት ሙሉ አነሱ:: የበሉትም ከሴቶችና ከልጆች በቀር አራት ሺህ ወንዶች ነበሩ::
"
† [ ማቴ.፲፭፥፴፪ ]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

                       †                       

   [    🕊  ፍኖተ ቅዱሳን   🕊    ]

[  የቅዱሳን አባቶቻችን የቅድስናና የተጋድሎ ሕይወት ]

†                       †                       †

[ ጽናትና በፈተናዎች መደራረብ አለመታወክ ]

🕊

እግዚአብሔርም ትዕግሥቱን አይቶ !   ]

........

አንድ አረጋዊ እንዲህ አለ ፦ "ፈተና ወደ ሰው ሲመጣ ያ ሰው እንዲደክምና እንዲዝል ፣ እንዲሁም እንዲማረር ለማድረግ ሌሎች ፈተናዎችም ከተለያዩ አቅጣጫዎች ተደራርበው ይመጡበታል።"

ይህ አረጋዊ የሚከተለውን ታሪክ አስከትሎ ተናገረ ፦

"ፈተና የመጣበት አንድ ወንድም ነበር፡፡ በፈተና ላይ ሳለ ሌሎች ወንድሞች ባዩት ጊዜ ሰላም አላሉትም ፣ ወደ በአታቸውም አልወሰዱትም፡፡ ኅብስተ ሠርክ በፈለገ ጊዜም ማንም ምንም ነገር አልሰጠውም፡፡ ከሥራ ሲመለስ በቤተ ክርስቲያን ይደረግ ወደ ነበረው ወደ አንድነት ማዕድ እንዲመጣ ማንም አልጋበዘውም፡፡ ከተሰማራበት ሥራ ውሎ ሲመለስ በበኣቱ ውስጥ ምንም የሚቀመስ ነገር አልነበረውም፡፡

እርሱም ስለዚህ ሁሉ እግዚአብሔርን አመሰገነ፡፡ እግዚአብሔርም ትዕግሥቱን አይቶ ይህን ፈተና አራቀለት፡ ወዲያውኑም ዳቦ በግመል የጫነ ከግብፅ የመጣ አንድ ሰው በሩን አንኳኳ፡፡

ያ ወንድም ግን ፦ "ጌታ ሆይ ፣ ስለ ስምህ ስል ትንሽ መከራ እንኳ ለመቀበል የበቃሁ አይደለሁም ማለት ነው?" እያለ አለቀሰ፡፡ ፈተናው ሲያልፍ እነዚያ ወንድሞች በሰላምታቸውም ሆነ በፍቅራቸው እንደ ቀድሟቸው ሆኑለት ፣ በበአታቸውም ተቀበሉት፡፡

🕊

የአባቶቻችን ጸሎትና በረከት ይደርብን፡፡

†                       †                        †
💖                    🕊                     💖

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

🕊

[   † ቅዱስ ሱርያል ሊቀ መላዕክት †   ]

† ከታላላቅ ሊቃናት አንዱ የሆነው ቅዱስ ሱርያል ክብሩ ብዙ ቢሆንም ብዙ ምዕመናን አያውቁትም:: የመላእክት መዓርግ ሲነገር ቅዱስ ሚካኤል: ቅዱስ ገብርኤል: ቅዱስ ሩፋኤል ብሎ ቀጥሎ የሚመጣው ቅዱስ ሱርያል ነው::

በሦስቱ ሰማያት ካሉት ዘጠኙ ዓለመ መላእክት የአንዱ [የሥልጣናት] መሪ [አለቃ] ነው:: መልአኩ እጅግ ርሕሩሕ እና ተራዳኢ ነውና አንዘንጋው::

ለኖኅ መርከብን ያሠራው: ከጥፋት ውኃም ያዳነው ይህ ቅዱስ መልአክ ነው::

በገድለ ሰማዕታትም ላይ እንደተጠቀሰው የሰማዕታት ረዳትና አዳኝም ነው:: ቅዱስ ሱርያል በሌላ ስሙ "እሥራልዩ" ይባላል:: "የእሥራኤል ረዳት" እንደ ማለት:: ዛሬ ደግሞ የሊቀ መልአኩ ቅዳሴ ቤቱ ነው::

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]

†                       †                          †
💖                    🕊                      💖

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

                        †                             

 †    🕊   ይቤሎ ጴጥሮስ  🕊   †


    [    የግእዝ መዝሙር ጥናት    ]

            [ ክፍል  - ፲፩  -  ]

የወንድማችን ድንቅ አገልግሎት ! ከጣእሙ ብዛት አጥንትን የሚያለመልም ዝማሬ መላእክትን ያሰማልን።

†                       †                        †
💖                    🕊                     💖

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

†                †                  †
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

[     ቤተክርስቲያንን እንወቅ     ]

         [  ክፍል -  ፳  -  ]
                   
[  ሥ ር ዓ ተ  አ ም ል ኮ !  ]

🕊

ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን። "ቤተክርስቲያንን እንወቅ" በተሰኘው ሳምንታዊ መርሐ-ግብር ባለፈው ሳምንት ሥርዓተ አምልኮት በሚለው ዓብይ ርዕስ ሥር ኦርቶዶክሳዊ ሥርዓተ ጸሎትን ተመልክተን ነበረ። ሰባት የጸሎት ጊዜያት መኖራቸውን አንስተናል። እነርሱም ፦

- 💖 ጸሎተ ነግህ
- 💖 ጸሎተ ሠለስት
- 💖 ቀትር
- 💖 ተሰዓተ ሰዓት
- 💖 ጸሎተ ሠርክ
- 💖 ጸሎተ ንዋም
- 💖 መንፈቀ ሌሊት [ እኩለ ሌሊት ] ናቸው። የዛሬው መርሐ-ግብር እነሆ !

[ 🕊 ሥርዓተ ቅዳሴ 🕊 ]

ቅዳሴ ምሥጋና ማለት ነው ፤ ይኸውም ለፈጣሪያችን እግዚአብሔር የምናቀርበው ምስጋና ነው፡፡ ሥርዓተ ቅዳሴ ወይም የቅዳሴ ሥርዓት በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከጸሎት ሁሉ በላይ የሆነ፡፡ ለአምላካችን እግዚአብሔር የምናቀርበው ምስጋና ከሰማያውያን መላእክት የተጀመረ ነው፡፡

ቅዳሴንም የጀመሩትም ሰማያውያን መላእክት ናቸው ፤ ጌታችንና አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአባታችን ለአዳም ከልጅ ልጁ ተወልዶ እንደሚያድነው ቃል የገባለት አምላካዊ የተስፋ ቃል ሲፈጸም ቤተ ልሔም በምትባል የዳዊት ከተማ “ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት ወሰላም በምድር ስምረቱ ለሰብእ” ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም ይሁን ፤ ሰላምም በምድር ለሰውም በጎ ፈቃድ እያሉ እንዳመሰገኑ በሉቃስ ወንጌል ላይ ተጽፎ እናገኛለን። [ ሉቃ.፪፥፲፬ ]

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በጸሎተ ሐሙስ ለደቀ መዛሙርቱ ኅብስቱን አንሥቶ ባርኮ ፈትቶ  “እንካችሁ ብሉ ይህ ሥጋዬ ነው ፤ ጽዋውንም ይዞ አክብሮ አመስግኖ ሁላችሁም ከእርሱ ጠጡ ስለ ብዙዎች ለኃጢአት ይቅርታ የሚፈስ የአዲስ ኪዳን ደሜ ይህ ነው” በማለት የቅዱስ ቁርባንን ሥርዓት በሠጠን መሠረትም ቅዱስ ቁርባን በቅዳሴ ሥርዓት ውስጥ ይፈጸማል፡፡ [ማቴ. ፳፮፣ ፳፮፥፳፱  ማር፥ ፲፬፣ ፳፪፥፳፭]

የቅዳሴ ሥርዓት አገልግሎት በሚፈጸምበት ቦታ ቅዱሳን መላእክት እንደ ቅጠል ረግፈው ፣ እንደ ሻሽ ተነጥፈው የሚያከብሩት ፣ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንም ኅብስቱን በጻሕል ፣ ወይኑን በጽዋ በማቅረብ ኅብስቱ ሥጋ ወልደ እግዚአብሔር ፤ ወይኑ ደመ ወልደ እግዚአብሔር የሚሆንበት ነው።

ቅዱሳን ሐዋርያት ይህንን ሥርዓት ተረክበው ለትውልድ ትውልድ በማስተላለፋቸው ሥርዓቱ ሳይቋረጥ በቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዘወትር ይፈጻማል፡፡

በቅዳሴ ሥርዓት ወቅትም ለዕለቱ በተመደቡ ካህናትና ምእመናን በአንድነት በመሆን ለአምላካችን ምስጋና እናቀርባለን ፤ ለበደላችን ይቅርታና ምሕረት እንጠይቃለን ፤ ለኃጢአት ሥርየትን እናገኛለን ፤ ሥጋ ወደሙ የበቃንም ቅዱስ ቁርባንን እንቀበላለን፡፡ በዚያም የዘለዓለም ሕይወትን እናገኛለን።

እግዚአብሔር አምላክ ቤተ ክርስቲያናችንን ሰላም ያድርግልን፤ አሜን፡፡

[ ይቆየን ]

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፥ ወለወላዲቱ ድንግል ፥ ወለመስቀሉ ክቡር፡፡

†                       †                        †
💖                    🕊                     💖

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

እሑድ - ጥር 26 2016 ዓ.ም

ዘጸአት 16-21

ሰላም ለሁላችሁ ይሁን! በዛሬው እለት ንባባችን ከምዕራፍ 16 እስከ 21 ድረስ እናነባለን።

ከንባብ በፊት የሚደረግ ጸሎት፡ “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፤ የአንተን ቃላት እሰማ እና እረዳ ዘንድ፥ እንዲያውም ፈቃድህን ለመፈጸም እበቃ ዘንድ የልቤን ጆሮዎች እና ዓይኖች ክፈትልኝ።” (ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ)

በዛሬው ንባባችን ላይ እስራኤላውያን በበረሃ ውስጥ ስላደረጉት ጉዞ እናነባለን። እግዚአብሔር በበረሃ ሳሉ የሚበሉትን መና እንዳወረደላቸው፥ ሆኖም ግን ሰንበትን በማክበር ዙሪያ እንደፈተናቸው ተጽፏል። እስራኤላውያንም በተለያየ አጋጣሚ ሙሴ እና አሮን ላይ ሲያጉረመርሙ እናገኛቸዋለን። እግዚአብሔር ግን ለረሃባቸው መና፥ ለጥማቸው መልካም ውሃ እንዲያገኙ እያደረገ በበረሃ መርቷቸዋል። እስራኤላውያን ከአማሌቃውያን ጋር በተዋጉ ጊዜም በምን መንገድ ድል እንዳደረጉ እናነባለን። እግዚአብሔር በሲና ተራራ ላይ ለሙሴ አሥርቱን ትእዛዛት መስጠቱን፥ ከዚያም ደግሞ ማኅበራዊ ፍትሕን፥ የንብረት ባለመብትነትን እና መሠል ጉዳዮችን የሚመለከቱ ሕጎችንም ለእስራኤል እንደሰጠ የምናነበው በእነዚህ ምዕራፎች ውስጥ ነው።

*የክለሳ ጥያቄዎች*

1) በዘጸአት 16 ላይ እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን ምን ሰጣቸው? መታዘዛቸውንስ በምን ፈተነ?

2) እስራኤላውያን መናውን ባዩ ጊዜ ምላሻቸው ምን ነበር? ሰንበትን ስለማክበርስ ምን ትእዛዝ ሰጣቸው?

3) በዘጸአት 17 ላይ ለእስራኤላውያን ውሃ የሰጣቸው በምን መንገድ ነው?

4) እስራኤላውያን ከአማሌቃውያን ጋር በነበራቸው ጦርነት የእስራኤላውያንን ጦር የመራው ማነው? በጦርነቱ ላይ የሙሴ ሚናስ ምን ነበር?

5) ዘጸአት 18 ላይ ሙሴን የጎበኘው ሰው ማነው? ምን ምክርስ ሰጠው?

6) ዘጸአት 19 ላይ የሲና ተራራ ምን ሆነ? በዚያስ ምን ተፈጠረ?

7) እግዚአብሔር በሲና ተራራ ላይ መገለጡን ያወቁ እስራኤላውያን ምላሻቸው ምን ነበር?

8 ) እስራኤላውያን ወደ እግዚአብሔር ለመቅረብ ምን አይነት ዝግጅት አደረጉ?

9) በዘጸአት 20 ላይ ከተሰጡት ትእዛዛት ውስጥ የመጀመሪያዎቹ ሁለቱ ምን ይላሉ?

10) ዘጸአት 21 ላይ የተሰጡት ሕግጋት ምንን የተመለከቱ ናቸው?

መልካም ንባብ!

/channel/OrthodoxTewahdoBooks

/channel/c/2014228571/1

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

                         †                        

[ 🕊 ሥ ላ ሴ  ያ ስ ጨ ክ ና ሉ  🕊 ]  

🍒▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬🍒               

🕊

" አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ያጸናሉ ።
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ያስጨክናሉ ።
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ያስተምራሉ ። "

[ አባ ሕርያቆስ ቅዳሴ ማርያም ]


†                       †                       †
💖                    🕊                    💖

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

                      †                       

   [       ለጥያቄዎ ምላሽ !        ]

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡


[ " እግዚአብሔር ይፍታችሁ! ብቻ አይበቃም ? " ]

[ ከምዕመናን የቀረበ ጥያቄ ]
                                
🍒

" ከቅዳሴ በኋላም ሆነ ከጉባኤ በኋላ የሚያሳርጉት ካህን "እግዚአብሔር ይፍታችሁ" ይሉናል፡፡ እኛም ፦ ስናውቅ በድፍረት ሳናውቅ በስሕተት ከሠራነው የኃጢአት ማሠሪያ እንደምንፈታ እናምናለን፡፡ በመሆኑም ኃጢአታችንን ለንስሓ አባታችን ሳንናዘዝ ሥጋ ወደሙ ብንቀበል ምናለበት? በጉባኤው ላይ "እግዚአብሔር ይፍታችሁ" የተባለው አይበቃም?"

------------------------------------------------

[ የቅድስት ቤተክርስቲያን መልስ ]

አባቶች ካህናት ከቅዱሳን ሐዋርያት ጀምሮ ሲያያዝ በመጣው መዓርገ ክህነት መሠረት የመፍታትና የማሠር ሥልጣን አላቸው። [ማቴ. ፲፮፥፲፱ ፤ ፲፰፥፲፰] ጌታችን ለደቀ መዛሙርቱ ፦ "እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ፡፡" ማለቱ የሚያረጋግጥልን ይህንኑ ነው፡፡ [ማቴ.፳፰፥፳] በመሆኑም እነርሱ አዝዘው ኃጢአቱን ይቅር ያሉለት ሰው ሁሉ ኃጢአቱ ይቀርለታል ፣ የያዙበትም ሰው እንዲሁ ይያዝበታል፡፡ ይህም ኃጢአቱን ላስተሠረዩለት ሰው ይሠረይለታል ፤ ላላስተሠረዩለት ሰው ደግሞ አይሠረይለትም ማለት ነው። [ዮሐ፳፥፳፫]

በዚህም መሠረት የመጥምቀ መለኮት የቅዱስ ዮሐንስን የንስሐ ስብከት ሰምተው በዮርዳኖስ የተሰበሰቡ ሁሉ ኃጢአታቸውን ለቅዱስ ዮሐንስ ይናዘዙ እንደነበረ እኛም ኃጢአታችንን ለካህኑ እንናዘዛለን [ማቴ.፫፡፮] ካህኑም ኃጢአቱን ሰምተው ቀኖና ይሰጡናል፡፡ ቀኖናው ጾም ወይም ስግደት ወይም ምጽዋት ሊሆን ይችላል፡፡ በዚህ ዓይነት የተሰጠንን ቀኖናም ከፈጸምን በኋላ ወደ ካህኑ ስንመለስ "እግዚአብሔር ይፍታችሁ" ይሉናል፡፡ በዚህን ጊዜም ከኃጢአት ማሰሪያ ሁሉ የተፈታን እንሆናለን፡፡ ከዚህም የምንማረው ኃጢአትን ለንስሓ አባት መናዘዝ ግዴታ መሆኑን ነው፡፡

ይኸንን ይዘን ወደ ጥያቄው መንፈስ ስንመጣ እርስ በርሱ የሚጋጭ ይመስለን ይሆናል፡፡ ነገር ግን ለእኛ ይምሰለን እንጂ አባቶቻችን እርስ በርሱ የሚጋጭ ምንም ነገር አልሠሩልንም፡፡ ምክንያቱም በእነርሱ አድሮ ሥራ የሠራው መንፈስ ቅዱስ ነውና። እንግዲህ ከቅዳሴም ሆነ ከጉባኤ በኋላ "እግዚአብሔር ይፍታችሁ" ስንባል የምንፈታው እግዚአብሔር ከሚያውቀው እኛ ግን ከማናውቀው ኃጢአት ሲሆን ፣ በተጨማሪም የሰው ልጅ ከበደል ስለማይነጻ በየደቂቃውና በየሰዓቱ ከምንፈጽመውና አስታውሰነው ከማንናዘዘው ኃጢአት ነው፡፡ አባቶቻችን ካህናት ሲያሳርጉ "ሰይጣን ከሸመቀው / ከዓይነ ሥጋ እና ከአይነ ልቡና ከሰወረው/ መንፈስ ቅዱስ ግን ካወቀው ኃጢአት እግዚአብሔር ይፍታችሁ" የሚሉት ለዚህ ነው።

ተሳስተንም ይሁን በድፍረት ስለሠራነው እና ስለምናውቀው ኃጢአት ግን የግድ መናዘዝ አለብን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር፡፡

ይቆየን !

†                       †                       †
💖                    🕊                    💖

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

ሰላም ወዳጆች፥ እንደምን አላችሁ?

ንባቡን ከጀመርንበት እለት አንስቶ በእግዚአብሔር ቸርነት እስካሁን ደርሰናል። ኦሪት ዘጸአትንም ወደ ማጋመስ እየተቃረብን ነው። ሆኖም ግን በዚህ ግሩፕ ያለው ሰው ብዛት ከተሳታፊዎች አንጻር ጥቂት በመሆኑ፥ የተሳታፊውን መጠን ለማወቅ ያህል ከላይ ያለውን ጥያቄ ትመልሱ ዘንድ በትህትና እጠይቃለሁ።

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

[ † ጥር ፳፭ [ 25 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. ቅዱስ መርቆሬዎስ ሰማዕተ ሮሜ
፪. ቅዱሳን ባስልዮስና ጎርጎርዮስ
፫. ብፁዕ አባ ዼጥሮስ ጽሙድ [ለምጽዋት ራሱን የሸጠ አባት]
፬. ቅዱስ ሰብስትያኖስ ሰማዕት
፭. ቅዱስ አስኪላ ሰማዕት

[ † ወርሐዊ በዓላት ]

፩. ቅዱስ አበከረዙን ሰማዕት
፪. ቅዱስ ዱማድዮስ ሶርያዊ
፫. ቅድስት ቴክላ ሐዋርያዊት
፬. አቡነ አቢብ
፭. አባ አቡፋና

" የሚበልጠውን ትንሳኤ እንዲያገኙ እስከ ሞት ድረስ ተደበደቡ:: ሌሎችም መዘበቻ በመሆንና በመገረፍ ከዚህም በላይ በእስራትና በወኅኒ ተፈተኑ:: በድንጋይ ተወግረው ሞቱ:: ተፈተኑ: በመጋዝ ተሰነጠቁ: በሰይፍ ተገድለው ሞቱ:: ሁሉን እያጡ: መከራን እየተቀበሉ: እየተጨነቁ: የበግና የፍየል ሌጦ ለብሰው ዞሩ:: ዓለም አልተገባቸውምና . . . " † [ ዕብ.፲፩፥፴፭ ]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

                       †                       

   [    🕊  ፍኖተ ቅዱሳን   🕊    ]

[  የቅዱሳን አባቶቻችን የቅድስናና የተጋድሎ ሕይወት ]

†                       †                       †

[  የፍትወት ጾር ስለሚያስነሣው ፈተና ]

🕊

ወደ በአታቸው በሰላም ተመለሱ !  ]

........

አንድ ቀን አንድ ወንድም አንድን አረጋዊ ሊጠይቀው መጣና ፦ " ወንድሜ እዚህና እዚያ እንሂድ እያለ አደከመኝ ፣ እኔም በጣም ተቸገርሁ " አለው፡፡ አረጋዊውም እንዲህ በማለት አበረታታው  " ወንድምህን ታገሠው ፣ እግዚኣብሔር ትዕግሥትህን አይቶ ይጠብቅሃል፡፡ ጋኔን ጋኔንን ሊያስወጣው እንደማይችለው ሁሉ አንዱም ሌላውን በሻካራነትና በክፋት ሊረዳው አይችልም፡፡ ነገር ግን በቅንነትና በደግነት ሆነህ አስብለት ፣ ተንከባከበውም፡፡ አምላካችን ሰዎችን የሚጠብቃቸው በማጽናናትና በማበረታታት ነውና፡፡"

እንዲሁም ይህን ታሪክ ነገረው ፦ " በቲቤያድ ሁለት ወንድሞች ነበሩ። አንደኛውም በዝሙት ጾር ተፈተነና ለሌላኛው ፦ "ወደ ዓለም ልሄድ ነው" አለው፡፡ ያኛው ወንድምም ፦ "ወንድሜ ፣ እኔስ የድካምህንና የድንግልናህን ፍሬ ታጣ ዘንድ እንድትሄድ አልተውህም " እያለው ያለቅስ ጀመር፡፡ ሆኖም ይህ ወንድም ፦ " እኔ እዚህ አልቆይም ፣ ልሄድ ነው፡፡ ወይ ከእኔ ጋር አብረኸኝ ሂድና ኋላ አብሬህ እመለሳለሁ ፣ አለዚያ ደግሞ እሄድና በዓለም እኖር ዘንድ ተወኝ " በማለት ከሃሳቡ ሊመለስ አልቻም፡፡

ያኛው ወንድም ወደ አንድ ታላቅ አረጋዊ ጋር ሄደና ይህን ነገር ነገረው፡፡ አረጋዊውም እንዲህ አለው ፦ " አብረኸው ሂድ ፣ አንተ እየተቀበልከው ካለኸው ድካም የተነሣ እግዚአብሔር ወንድምህን በፈተናው እንዲወድቅ አይተወውም፡፡" ያ ወንድምም አብሮት ተነሣና ወደ ዓለም ለመመለስ ጉዞ ጀመሩ፡፡

ነገር ግን ገና ወደ መንደር ሊጠጉ ሲሉ እግዚአብሔር የዚህን ወንድም ድካምና ትዕግሥት አይቶ ፈተናውን ከወንድሙ አራቀለት። እርሱም ፦ ወንድሜ ፣ ወደ በረሃችን እንመለስ ፣ በኃጢአት ከመኖር ምንም ጥቅም እንደማላገኝበት ተገንዝቤአለሁና " አለው፡፡ ሁለቱንም ምንም ጉዳት ሳያገኛቸው ወደ በአታቸው በሰላም ተመለሱ፡፡"

🕊

የአባቶቻችን ጸሎትና በረከት ይደርብን፡፡

†                       †                        †
💖                    🕊                     💖

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

        †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬

[ እግዚአብሔር ከፊትህ ያሳድዳቸዋል ! ]


" አስማተኛም ፥ መተተኛም ፥ በድግምት የሚጠነቍልም ፥ መናፍስትንም የሚጠራ ፥ ጠንቋይም ፥ ሙታን ሳቢም በአንተ ዘንድ አይገኝ።

ይህንም የሚያደርግ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት የተጠላ ነው ፤ ስለዚህም ርኵሰት አምላክህ እግዚአብሔር ከፊትህ ያሳድዳቸዋል።

አንተ ግን በአምላክህ በእግዚአብሔር ዘንድ ፍጹም ሁን።" [ ዘዳ.፲፰፥፲፩ ]

🔔

እንዲህ ያሉትን የእግዚአብሔርን ጠላቶች ፤ ሰራዊተ አጋንንትንና ነፍሰ ገዳዮችን ከእኛ ዘንድ እናርቅ !

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

ዓርብ - ጥር 24 2016 ዓ.ም

ዘጸአት 6-11

ሰላም ለሁላችሁ ይሁን! በዛሬው እለት ንባባችን ከምዕራፍ 6 እስከ 11 ድረስ እናነባለን።

ከንባብ በፊት የሚደረግ ጸሎት፡ “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፤ የአንተን ቃላት እሰማ እና እረዳ ዘንድ፥ እንዲያውም ፈቃድህን ለመፈጸም እበቃ ዘንድ የልቤን ጆሮዎች እና ዓይኖች ክፈትልኝ።” (ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ)

በዛሬው ንባባችን ላይ እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን የገባውን ቃል እንዳጸና እና ከግብጽ ባርነትም ነጻ እንደሚያወጣቸው እንዳሳየ እናነባለን። ሙሴ እና አሮን በእግዚአብሔርን ትእዛዝ በመመራት ብዙ ተዓምራትን በግብጽ ምድር ማድረጋቸውን፥ አስቀድሞ የከፋውን የፈርዖን ልብ እግዚአብሔር እንዳጸና፥ በግብጽ ምድር ታይተው የማያውቁ ትላልቅ ተዓምራትም እንደተደረጉ በምዕራፎቹ ውስጥ ተጽፈው ይገኛሉ።

* የክለሳ ጥያቄዎች * (መልሶቹን ከማታ 1፡00 በሁዋላ ጻፉ)

1) በዘጸአት 6 መሠረት፥ እግዚአብሔር ምን ብሎ ቃልኪዳኑን አጸና? 

2) እግዚአብሔር ወደ ፈርዖን ገብተው እንዲናገሩ ባዘዛቸው ጊዜ፥ የሙሴ ምላሽ ምንድር ነበር?

3) እግዚአብሔር በግብጽ ላይ የሰደደው የመጀመሪያው መቅሰፍት ምንድር ነበር? 

4) በዘጸአት 7 መሠረት፥ የመጀመሪያውን መቅሰፍት ከተመለከተ በሁዋላ፥ የፈርዖን ምላሽ ምን ነበር?  

5) በዘጸአት 8 መሠረት፥ በግብጽ ላይ የመጣው ሁለተኛው መቅሰፍት ምን ነበር?
 
6) ፈርዖን የጓጉንቸሮቹን መቅሰፍት ከተመለከተ በሁዋላ ለሙሴ እና ለአሮን ምን አላቸው? 

7) በዘጸአት 9 መሠረት በግብጽ ላይ የወረደው አምስተኛው መቅሰፍት ምን ነበር? 

8 ) በግብጽ ላይ በረዶ በወረደ ጊዜ፥ ፈርዖን ለሙሴ እና ለአሮን ምን አላቸው?
 
9) በዘፍጥረት 10 ላይ እንደምናነበው፥ በግብጽ የወረደው ስምንተኛው መቅሰፍት ምን ነበር? 

10) የአንበጣዎቹን መቅሰፍት ከተመለከተ በሁዋላ፥ የፈርዖን ምላሽ ምን ነበር?

11) የመጨረሻውን መቅሰፍት ከማምጣቱ በፊት እግዚአብሔር ለሙሴ ምን አለው? 

12) በግብጽ ላይ የታዘዘው የመጨረሻው መቅሰፍት ምን ነበር?

መልካም ንባብ!
/channel/OrthodoxTewahdoBooks

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

                       †                       

[  🕊 ሰላሜን እሰጣችኋለሁ  🕊 ]


" ሰላምን እተውላችኋለሁ ፥ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ ፤ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጥ አይደለም። ልባችሁ አይታወክ አይፍራም።" [ዮሐ.፲፬፥፳፯ ]


†                       †                        †
💖                    🕊                     💖

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

🕊                💖                  🕊

ድንግል ሆይ ፦

" ድንግል ሆይ ፦ እታመንሻለሁ ከተሠወረው መከራ በግልጽም ከሚመጣብኝ ጥፋት ሁሉ በዚህ ዓለም እንድታድኝኝ ፤ በሚመጣውም ዓለም ከገሃነመ እሳት ጥርስ ማፏጨት ፥ ጽኑ ልቅሶም ካለበት ከሚያስጨንቅ መቅሠፍት ትሠውሪኝ ዘንድ ፤ እኔም ባንቺ አማላጅነት በልጅሽም ምሕረት የታመንሁ ነኝ፡፡

በፈረሰኞች ሰልፍ በሠረገላም መንኰራኩር የምታመን አይደለሁም፡፡ ባንቺና በልጅሽ ብቻ እታመናለሁ እንጂ፡፡ "

[ አርጋኖን ]

ቅዱስ አማኑኤል አምላካችን ጣዕመ ፍቅሩን ያሳድርብን::

†                       †                        †
💖                    🕊                     💖  

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

                         †                        

[  ከ ሰ ኞ ጀ ም ሮ  የ ሚ ቀ ር ብ !  ]


በጣት የሚቆጠሩ የዘመኑ [ ሐሳዊ አጥማቂዎች ] እና አጋንንታዊ አሠራራቸውን የሚመለከት ተከታታይ መርሐ-ግብር  !

[ እንደ እግዚአብሔር መልካም ፈቃድ ከሰኞ ጀምሮ ተከታታይ መርሐ-ግብሩ መቅረብ ይጀምራል። ]

         †              †               †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

ሰኞ - ጥር 27 2016 ዓም

ዘጸአት 22-27

ሰላም ለሁላችሁ ይሁን! በዛሬው እለት ንባባችን ከምዕራፍ 22 እስከ 27 ድረስ እናነባለን።

ከንባብ በፊት የሚደረግ ጸሎት፡ “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፤ የአንተን ቃላት እሰማ እና እረዳ ዘንድ፥ እንዲያውም ፈቃድህን ለመፈጸም እበቃ ዘንድ የልቤን ጆሮዎች እና ዓይኖች ክፈትልኝ።” (ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ)

በዛሬው ንባባችን ላይ እግዚአብሔር እስራኤላውያን ሊከተሉ የሚገባቸውን የተለያዩ ሕግጋት ሲሰጣቸው እናነባለን። እነዚህ ሕግጋቶች በመካከላቸው ባለው መስተጋብር ውስጥ ለሚፈጠሩ የተለያዩ አለመግባባቶች መፍትሔ ሊሆኑ የሚችሉ የማኅበረሰብ ድንበሮች ናቸው። በዚህ ውስጥም ማኅበራዊ ፍትሕ፥ ሥነ-ምግባር እና ሃይማኖታዊ ሥርዓቶች የተካተቱ ሲሆን፥ እግዚአብሔርን በምን መልኩ ማምለክ እንዳለባቸውም ተነግሯቸዋል።ታቦተ ጽዮንን፥ የካህናት ልብስን እና የመሳሰሉትን የሚመለከቱ ሕግጋትም ቀርበዋል።

*የክለሳ ጥያቄዎች*

1) በዘጸአት 22 ስለ ማኅበራዊ ፍትሕ እና ሥነ ምግባር የተሰጡ ሕግጋት ምንድር ናቸው?

2) በዘጸአት 22 ላይ እግዚአብሔር ስለ ድሆች እና ብድር ስለሚያበድራቸው ሰው ምን አለ?

3) በዘጸአት 23 ላይ እግዚአብሔር ስለ ድሆች እና ስለ ስደተኞች ምን ሕግን ሰጠ?

4) እግዚአብሔር እስራኤላውያንን በዓመት ሦስት ጊዜ እንዲያከብሯቸው ያዘዛቸው በዓላት ምንድር ናቸው?

5) በዘጸአት 24 መሠረት በእግዚአብሔር እና በሕዝቡ መካከል ቃልኪዳን የሆነው እንዴት ነው?

6) በዘጸአት 25 መሠረት የታቦቱ ዋና ዓላማ ምንድር ነው?

7) በዘጸአት 26 መሠረት ለድንኳን የሚሆኑት መጋረጃዎች ስንት ናቸው?

8 ) በድንኳን መጋረጃዎቹ ዘርፍ ላይስ ስንት ቀለበት እንዲኖር ታዘዘ? በላያቸውስ ላይ የምን መልክ ይኖራል?

9) ሙሴ እንዲሠራ የታዘዘው መሠዊያ ከምን እንጨት ይሠራል?

10) በዘጸአት 27 እንደታዘዘው ከሆነ፥ በቤተመቅደስ ምን ይበራል? ማንስ ያበራዋል? ለምን ያህል ጊዜ? 

መልካም ንባብ!

/channel/OrthodoxTewahdoBooks

/channel/c/2014228571/1

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

🕊

[ † እንኳን ለቅዱሳን ቅዱስ ኄኖክ : ቅዱስ ጢሞቴዎስ ሐዋርያ : ቅዱስ ሱርያል ሊቀ መላዕክት ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ]

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †

🕊  †  ቅዱስ ኄኖክ   †   🕊

† ቅዱስ መጽሐፍ እንደሚነግረን ቅዱስ ኄኖክ ከአዳም ሰባተኛ ትውልድ ነው:: አዳም: ሴት: ሔኖስ: ቃይናን: መላልኤል: ያሬድ ብለን ሰባተኛው ኄኖክ ነውና::

ቅዱሱ የማቱሳላ አባትም ነው:: አካሔዱን ከእግዚአብሔር ጋር በማድረጉም ሞትን ያላየ: ብሔረ ሕያዋን የገባ የመጀመሪያው ሰው ሁኗል:: ለአዳም ልጆችም ተስፋ ድኅነት እንዳለ ማሳያ ሁኗል:: "በአቤል አፍርሆሙ: ወበኄኖክ አንቅሆሙ" እንዳለ ሊቁ::

ቅዱስ ኄኖክ በ፲፬፻፹፮ [1486] ዓ/ዓ የመጀመሪያውን የቅዱስ መጽሐፍ ክፍል [መጽሐፈ ኄኖክን] ከመጻፉ ባሻገር በብዙ ሥፍራ በክብር ተጠቅሶ ይገኛል::


🕊 † ቅዱስ ጢሞቴዎስ ሐዋርያ †  🕊

† ይህ ቅዱስ ሐዋርያ አንድ የቤተ ክርስቲያናችን መብራት ነው:: ወደ ክርስትና የመጣው በ40ዎቹ ዓ/ም አካባቢ ሲሆን አሳምኖ ለቅድስና ያበቃው ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ ነው::

በጊዜውም በነበረው ትጋትና ተጋድሎ ፍሬ አፍርቷል:: ሆዱንም እጅግ ያመው ነበር:: ቅዱስ ጳውሎስ ሲጠራው "የምወድህ ልጄ" እያለ ነበር:: በኤፌሶንም ጵጵስናን ሹሞ ፪ መልዕክታትን ልኮለታል:: ቅዱስ ጢሞቴዎስ ቤተ ክርስቲያንን ለብዙ ዘመናት አገልግሎ በሰማዕትነት ዐርፏል::
ዛሬ ሥጋው ከኤፌሶን ወደ ቁስጥንጥንያ የፈለሰበት ነው፡፡ ጊዜውም ፫፻፴ [330] ዎቹ መጀመሪያ ላይ እንደሆነ ይታመናል፡፡

"መድኃኒታችን እግዚአብሔር: ተስፋችንም ኢየሱስ ክርስቶስ እንዳዘዘው ትእዛዝ የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ የሆነ ጳውሎስ: በእምነት እውነተኛ ልጄ ለሆነ ለጢሞቴዎስ:: ከእግዚአብሔር ከአባታችን: ከክርስቶስ ኢየሱስም ከጌታችን: ጸጋና ምሕረት: ሰላምም ይሁን . . ." [፩ጢሞ. ፩፥፩]


🕊 † ቅዱስ ሱርያል ሊቀ መላዕክት † 🕊

† ከታላላቅ ሊቃናት አንዱ የሆነው ቅዱስ ሱርያል ክብሩ ብዙ ቢሆንም ብዙ ምዕመናን አያውቁትም:: የመላእክት መዓርግ ሲነገር ሚካኤል: ገብርኤል: ሩፋኤል ብሎ ቀጥሎ የሚመጣው ሱርያል ነው::

በሦስቱ ሰማያት ካሉት ዘጠኙ ዓለመ መላእክት የአንዱ [የሥልጣናት] መሪ [አለቃ] ነው:: መልአኩ እጅግ ርሕሩሕ እና ተራዳኢ ነውና አንዘንጋው:: ለኖኅ መርከብን ያሳራው: ከጥፋት ውኃም ያዳነው ይህ ቅዱስ መልአክ ነው::

በገድለ ሰማዕታትም ላይ እንደተጠቀሰው የሰማዕታት ረዳትና አዳኝም ነው:: ቅዱስ ሱርያል በሌላ ስሙ "እሥራልዩ" ይባላል:: "የእሥራኤል ረዳት" እንደ ማለት:: ዛሬ ደግሞ የሊቀ መልአኩ ቅዳሴ ቤቱ ነው::

† የይቅርታ ጌታ መድኃኔ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ አይተወን . . . አይጣለን !

[ † ጥር ፳፯ [ 27 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. ቅዱስ ኄኖክ ነቢይ [ወደ ብሔረ ሕያዋን ያረገበት]
፪. ቅዱስ ጢሞቴዎስ ሐዋርያ [ፍልሠቱ]
፫. ቅዱስ አባ ቢፋሞን ሰማዕት
፬. ቅዱስ ሰራብዮን ሰማዕት
፭. ቅዱስ ሱርያል ሊቀ መላዕክት [ከሰባቱ ሊቃናት አንዱ]

[ † ወርኀዊ በዓላት ]

፩. መድኃኔ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ
፪. አቡነ መባዐ ጽዮን
፫. አባ መቃርስ ርዕሰ መነኮሳት
፬. ቅዱስ ገላውዴዎስ ሰማዕት [ንጉሠ ኢትዮጵያ]
፭. ቅዱስ ፊቅጦር ሰማዕት
፮. ቅዱስ ያዕቆብ ዘግሙድ

" የተጠራችሁለት ለዚህ ነው:: ክርስቶስ ደግሞ ፍለጋውን እንድትከተሉ ምሳሌ ትቶላችሁ ስለ እናንተ መከራን ተቀብሏልና:: እርሱም ኃጢአት አላደረገም:: ተንኮልም በአፉ አልተገኘበትም:: ሲሰድቡት መልሶ አልተሳደበም:: መከራንም ሲቀበል አልዛተም . . . እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ:: " † [፩ጴጥ. ፪፥፳፩-፳፭]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

                       †                       

  [  🕊  ድምፀ ተዋሕዶ   🕊  ]  

🍒▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬🍒               

[  ሕይወት የሚገኝባቸው የቅድስት ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ትምህርቶች በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን በድምፅ ይቀርባሉ።  ]

[ ሳምንታዊ መርሐ-ግብር ]

🕊             

[ " ሕይወተ ዘራዙት - የወጣቶች ሕይወት ! " ]
             
             [     ክፍል አምስት    ]

" ጕልማሳ መንገዱን በምን ያነጻል ? ቃልህን በመጠበቅ ነው።" [ መዝ.፻፲፱፥፱ ]


       💖   ድንቅ ትምህርት  💖

[ በመምህራችን በቀሲስ ኅብረት የሺጥላ ]

" የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ፥ ከመከራም ሥጋት ያርፋል።" [ ምሳ.፩፥፴፫ ]

         †              †               †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬
                       👇

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

                       †                       
                    
†   🕊   ክብርት ሰንበት   🕊   †

💖

" አቤቱ ፥ በድንኳንህ ውስጥ ማን ያድራል ? በተቀደሰውም ተራራህ ማን ይኖራል ?

በቅንነት የሚሄድ ፥ ጽድቅንም የሚያደርግ ፥ በልቡም እውነትን የሚናገር። በአንደበቱ የማይሸነግል ፥ በባልንጀራው ላይ ክፋትን የማያደርግ ፥ ዘመዶቹንም የማይሰድብ።

ኃጢአተኛ በፊቱ የተናቀ ፥ እግዚአብሔርንም የሚፈሩትን የሚያከብር ፥ ለባልንጀራው የሚምል የማይከዳም። ገንዘቡን በአራጣ የማያበድር ፥ በንጹሑ ላይ መማለጃን የማይቀበል። እንዲህ የሚያደርግ ለዘላለም አይታወክም።" [ መዝ.፲፭፥፩-፭]


†                       †                       †
💖                    🕊                    💖

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

🕊

[ † እንኳን ለቅዱሳን አርባ ዘጠኝ አረጋውያን ሰማዕታት ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ]

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †

🕊  †  አረጋውያን ሰማዕታት †  🕊

† ሰማዕትነት በክርስትና ለሃይማኖት የሚከፈል የመጨረሻው ዋጋ [መስዋዕትነት] ነው:: ሰው ለፈጣሪው ሰውነቱን ሊያስገዛ: ሃብት ንብረቱን ሊሰጥ ይችላል:: ከስጦታ በላይ ታላቅ ስጦታ ግን ራስን አሳልፎ መስጠት ነው::

ራስን መስጠት በትዳርም ሆነ በምናኔ ውስጥ ይቻላል:: የመጨረሻ ደረጃው ግን ሰማዕትነት ነው:: "አማን መነኑ ሰማዕት ጣዕማ ለዝ ዓለም: ወተዓገሡ ሞተ መሪረ በእንተ መንግስተ ሰማያት" እንዳለው ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ሰማዕትነት ማለት መራራውን ሞት ስለ ፍቅረ እግዚአብሔር ሲሉ መታገስ ነው::

እርሱ ቅሉ መድኃኒታችን ክርስቶስ የሰማይና የምድር ጌታ ሲሆን ኃፍረተ መስቀልን ታግሦ ሙቶልን የለ! በዓለም ያሉ ብዙ እምነቶች ስለ መግደል በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ያስተምራሉ:: ክርስትና ግን መሞትን እንጂ መግደልን የሚመለከት ሕግ የለውም::

እርሱ ባለቤቱ "ጠላቶቻችሁን ውደዱ: የሚረግሟችሁን መርቁ: ስለሚያሳድዷችሁ ጸልዩ" ብሎናልና:: [ ማቴ.፭፥፵፬ ] ነገር ግን
ዕለት ዕለት ራሳችንን በሃይማኖትና በምግባር ካልኮተኮትነው ክርስትና በአንድ ጀምበር ፍጹም የሚኮንበት እምነት አይደለምና በፈተና መውደቅ ይመጣል::

በተለይ የዘመኑ ክርስቲያን ወጣቶች ልናስተውል ይገባናል:: የቀደሙ ሰማዕታት ዜና የሚነገረን እንድንጸና ነውና::

የእነዚህ ሰማዕታት ቁጥራቸው ፵፱ [49] ሲሆን አባ ቢስዱራ የሚባል ጻድቅ ሰው ፶ [50] ኛ ሁኖ ይመራቸው ነበር:: መኖሪያቸው ገዳመ አስቄጥስ [ግብጽ] ሆኖ ዘመኑ ፭ [5] ኛው መቶ ክ/ዘ ነበር::

ሃምሳውም ሙሉ ዘመናቸውን በምናኔና በቅድስና ፈጽመው በስተእርጅና ደግሞ ሰማዕትነት መጣላቸው:: በ፬፻፴ [430] ዎቹ አካባቢ
የዚያን ጊዜ በርበር ይባሉ የነበሩት አረማውያኑ [የዛሬዎቹ አሕዛብ አባቶች] "ሃይማኖት ካዱ" እያሉ ሰይፍን መዘዙባቸው::

በጊዜው አባ ቢስዱራ በማረፉ ሃላፊነቱን የወሰዱት አባ ዮሐንስ ከአርባ ስምንቱ ባልንጀሮቻቸው ጋር ተስማምተው በበርበር እጅ ሰማዕትነትን ተቀብለዋል:: ከንጉስ ቴዎዶስዮስ [ትንሹ] ተልኮ የነበረ አንድ ክርስቲያንም በፍቅረ ክርስቶስ ተስቦ ከወጣት ልጁ ጋር ተሰይፏል:: የብርሃን አክሊልም ለሃምሳ አንዱም ወርዷል::

† አምላከ ቅዱሳን ከተከፈተ ገነት : ከተነጠፈ ዕረፍት በቸርነቱ ያድርሰን::

[ † ጥር ፳፮ [ 26 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. አርባ ዘጠኝ አረጋውያን ሰማዕታት [ግብጽ ገዳመ አስቄጥስ ውስጥ]
፪. ቅድስት አንስጣስያ [በ፭ኛው መቶ ክ/ዘ ከቁስጥንጥንያ ወደ ግብጽ ወርዳ ፡ ንግሥናን ንቃ በበርሃ ስትጋደል የኖረች ቅድስት
እናት ናት::]
፫. ቅዱስ ዮሴፍ [ መፍቀሬ ነዳያን ]
፬. አባ ጽሕማ [ ከተስዓቱ ቅዱሳን ]

[ † ወርኀዊ በዓላት ]

፩. ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ
፪. አቡነ ሐብተ ማርያም ኢትዮጵያዊ
፫. አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ
፬. አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን

" ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ: ወይስ ጭንቀት: ወይስ ስደት: ወይስ ራብ: ወይስ ራቁትነት: ወይስ ፍርሃት: ወይስ ሰይፍ ነውን? 'ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን:: እንደሚታረዱ በጐች ተቈጠርን' ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው:: በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን:: " † [ ሮሜ. ፰፥፴፭-፴፰ ]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

                       †                       

  [  🕊  ድምፀ ተዋሕዶ   🕊  ]  

🍒▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬🍒               

[  ሕይወት የሚገኝባቸው የቅድስት ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ትምህርቶች በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን በድምፅ ይቀርባሉ።  ]

[ ሳምንታዊ መርሐ-ግብር ]

🕊             

[ " ሕይወተ ዘራዙት - የወጣቶች ሕይወት ! " ]
             
             [     ክፍል አራት    ]

" ጕልማሳ መንገዱን በምን ያነጻል ? ቃልህን በመጠበቅ ነው።" [ መዝ.፻፲፱፥፱ ]


       💖   ድንቅ ትምህርት  💖

[ በመምህራችን በቀሲስ ኅብረት የሺጥላ ]

" የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ፥ ከመከራም ሥጋት ያርፋል።" [ ምሳ.፩፥፴፫ ]

         †              †               †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬
                       👇

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

                          †                          

     [   🕊  መዝሙረ ተዋሕዶ   🕊   ]  

🍒▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬🍒               

[  ኦርቶዶክሳዊ የተቀደሰ ያሬዳዊ ዝማሬ ሰዓት  ]

[ ሳምንታዊ መርሐ-ግብር ]

🕊

በስመ አብ ፡ ወወልድ ፡ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን፡፡

ኦርቶዶክሳዊ መዝሙር ንጹሕና የተቀደሰ ነው ፥ ለእግዚአብሔር ምስጋናና ልመና የሚቀርብበት ፣ ይቅርታና ምሕረት የሚጠየቅበት ፣ ሰውን ሳይሆን እግዚአብሔርን ደስ ለማሰኘት የሚዘጋጅ ንጹሕ መስዋዕት ነው ፥ በአበው ጸሎት ይዘጋጃል ፥ ከስጋዊና ከደማዊ ሀሳብ የራቀ ነው ፥ ልቦናን ወደ ንስሐ ይጠራል ፥ ከኃጢአትና ከክፉ ሥራ የመለየት ኃይል አለው ፥ ክፉ መንፈስን ከሰው ልብ ያርቃል ፥ መረጋጋትን ልቦናን ዘልቆ የሚሰማ ውስጣዊ ሰላምን ይሰጣል ፥ በአሚነ ሥላሴ ያጸናል ፥ የክርስቶስን የባህርይ አምላክነትና መሐሪነት ይመሰክራል ፥ የእመቤታችንን ፍቅር በልቦና ያሳድራል ፥ በእናትነቷና በምልጃዋ እንድንታመን ያደርጋል ፥ በቅዱሳን ጸሎትና በቃል ኪዳናቸው ያጸናል ፥ ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን እናውቅ ዘንድ መንገድ ይመራናል ፥ ፈሪሐ  እግዚአብሔርንና ፍቅረ እግዚአብሔርን ያጎናጽፈናል፡፡

†                       †                       †

ተወዳጆችሆይ ፦ በተቀደሰ ሰማያዊ ያሬዳዊ ዜማ ነብሳችንን እናስጊጣት፡፡ ከደጋጎቹ አባቶቻችን ጋር ከዓለም ርኩሰት በተለየ የተቀደሰ ዝማሬ አምላካችን እግዚአብሔርን እናመሥግን፡፡ ለስጋዊ ጆሮዎች ከሚመች ከረከሰ የተሃድሶ የኑፋቄ እርሾ ልቦናችንን እንጠብቅ፡፡ ገንዘብን ስለመውደድ ከሆነ ከሥጋዊ ሥራ ፈጽሞ እንለይ፡፡

🍒

[   🕊 መርቆሬዎስ ! 🕊    ]

[ የአብ ወዳጅ ኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ ]

🕊

" ሃብትከ ወክብርከ ይኩንከ ለኃጉል:: ሊተሰ ክብርየ ክርስቶስ ውዕቱ:: [ ለእኔስ ክብሬ ክርስቶስ ነውና ንብረትህ ለጥፋት ይሁንህ ]" ሲልም ንጉሡን በአደባባይ ዘለፈው:: ዳኬዎስም በቁጣ እሳት አስነድዶ: የብረት አልጋውንም አግሎ ቅዱስ መርቆሬዎስን በዚያ ላይ አስተኛው::

ያም አልበቃ:: ወታደሮች እየተፈራረቁ ሲደበድቡት ደሙ ፈሶ እሳቱን አጠፋው::

†                       †                       †
💖                    🕊                    💖

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

ቅዳሜ - ጥር 25 2016 ዓ.ም

ዘጸአት 12-15

ሰላም ለሁላችሁ ይሁን! በዛሬው እለት ንባባችን ከምዕራፍ 12 እስከ 15 ድረስ እናነባለን።

ከንባብ በፊት የሚደረግ ጸሎት፡ “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፤ የአንተን ቃላት እሰማ እና እረዳ ዘንድ፥ እንዲያውም ፈቃድህን ለመፈጸም እበቃ ዘንድ የልቤን ጆሮዎች እና ዓይኖች ክፈትልኝ።” (ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ)

በዛሬው ንባባችን ላይ እስራኤላውያን በግብጽ ላይ ከሚመጣው የመጨረሻ መቅሰፍት በምን አይነት መንገድ እንደተረፉ፥ የፋሲካ በዓል መመሪያ እና በበራቸው ላይ ማድረግ ያለባቸውን ምልክት በተመለከተ እናነባለን። በዚህ መቅሰፍት ምክንያት ፈርዖን እስራኤላውያንን ከለቀቃቸው በሁዋላ ለአምልኮ እንደወጡ፥ እግዚአብሔርም በብርሃን ይመራቸው እንደነበረ እና ግብጻውያን እስራኤላውያንን ባሳደዱ ጊዜ እግዚአብሔር በሙሴ እጅ ባደረገው ድንቅ ተዓምር እንዴት እንዳዳናቸውም የምናነበው በእነዚህ ምዕራፎች ውስጥ ነው።

*የክለሳ ጥያቄዎች* (መልሶቹን ከማታ 1፡00 በሁዋላ ጻፉ)

1) በዘጸአት 12 ላይ የታዘዘው የፋሲካ በዓል ዓላማው ምንድር ነው? የሚከበረውስ በምን መንገድ ነው?

2) በዘጸአት 12 ላይ እንደምናነበው ከሆነ፥ ፈርዖን እስራኤላውያንን እንዲለቅ ያደረገው ሁኔታ ምንድር ነው?

3) በዘጸአት 13 ላይ እስራኤላውያን ከግብጽ መውጣታቸውም በምን አይነት መንገድ እንዲዘክሩት ታዘዙ?

4) እስራኤላውያን እርሾ የሌለበት የቂጣ እንጀራ እንዲበሉ የታዘዙት ለምንድር ነው?

5) እስራኤላውያን ከግብጽ ከወጡ በሁዋላ እግዚአብሔር በምን መልኩ ጠበቃቸው?

6) እስራኤላውያን ቀይ ባሕርን ሲሻገሩ እግዚአብሔር በተከተሏቸው ግብጻውያን ላይ ምን አደረገ?

7) በዘጸአት 15 እስራኤላውያን የዘመሩት መዝሙር ዋና አሳብ ምንድር ነው?

8) በሴቶች መካከል ሆና ዝማሬውን ስትመራ የነበረችው ሴት ማን ናት? 

መልካም ንባብ!
/channel/OrthodoxTewahdoBooks

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

🕊

[ † እንኳን ለታላቁ ሰማዕት ቅዱስ መርቆሬዎስ [ ፒሉፓዴር ] ዓመታዊ የተአምር በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ]

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †

🕊  †  ቅዱስ መርቆሬዎስ ኃያል †  🕊

† ለክርስትና ሃይማኖት የሚከፈል ትልቁ ዋጋ ሰማዕትነት ነውና ቤተ ክርስቲያን ለምስክሮቿ ሰማዕታት ልዩ ክብር አላት:: ከኮከብ ኮከብ እንዲበልጥ ሁሉ ከሰማዕታትም ቅዱስ ጊዮርጊስን እና ቅዱስ መርቆሬዎስን የመሰሉት ደግሞ ክብራቸው በእጅጉ የላቀ ነው::

ቅዱስ መርቆሬዎስን ብዙ ጊዜ ሊቃውንት "ካልዕ [ ሁለተኛው ] ሊቀ ሰማዕታት" ሲሉ ይገልጹታል:: ጥንተ ነገሩስ እንደ ምን ነው ቢሉ :-
በ፪ኛው መቶ ክ/ዘመን መጨረሻ አካባቢ ከሮም ግዛቶች በአንዱ [ አስሌጥ ] ከአባቱና ከሚስቱ ጋር የሚኖር "አሮስ" የሚሉት ሰው ይኖር ነበር:: ሚስቱ ደም ግባት የሠመረላት: እርሱም ደግነት ያለው ሰው ቢሆኑም የሚያመልኩት ግን ጣዖትን ነበር::

አንድ ቀን አሮስ ሚስቱን ከቤት ትቶ ለአደን ከአባቱ ጋር ወጣ:: እንደ ልማዳቸው ወጥመዱን አስተካክለው ተደበቁ:: የወጥመዱ ደወል ሲያቃጭል: "እንስሳ ተያዘልን" ብለው ሲሯሯጡ ዐይናቸው ያየው ነገር በድንጋጤ እንዲፈዙ አደረጋቸው:: ፪ ገጻተ ከለባት በወጥመዱ ውስጥ ተይዘው ነበር::

እነዚህ ፍጡራን ሰዎች ናቸው:: ግን ባልታወቀ የተፈጥሮ አጋጣሚ እንደዚህ እንደ ሆኑ ይታመናል:: ግን እጅግ ግዙፍ: ከአንገታቸው በላይ እንደ ውሻ: ወገባቸው እንደ ሰው: ጉልበታቸው እንደ አንበሳ ሲሆን ታችኛው እግራቸው የጋለ የናስ ብረት ነው የሚመስል::

እነዚህን ፍጡራን ሰማያዊ ካልሆነ ምድራዊ ፍጡር አይችላቸውም:: አንበሳና ነብርን እንኩዋ እንደ ጨርቅ በጣጥሰው ይጥሏቸው እንደ ነበር ይነገራል:: ዐይናቸው እንደ እሳት ይነድ ስለ ነበር ማንም ትክ ብሎ ሊያያቸው አይችልም:: ምሥጢራቸውን ግን የሚያውቀው የፈጠራቸው አምላክ ነው::

ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስና:- አሮስና አባቱ ባዩአቸው ጊዜ ደንግጠው ወደቁ:: ገጻተ ከለባቱ የብረት ወጥመዱን እንደ ክር በጣጥሰው የአሮስን አባት በቅጽበት በሉት:: አሮስን ሊበሉት ሲሉ ግን ድንገት ቅዱስ መልአክ ወርዶ በእሳት ሰይፍ አጠራቸው::

"ከእርሱ የሚወጣ ቅዱስ ፍሬ አለና እንዳትነኩት" አላቸው:: ወዲያውም መልአኩ ያንን ኃይለኝነታቸውን አጠፋው:: በዚህ ጊዜ ፪ቱም ወደ አሮስ ሒደው ሰገዱለት:: አሮስም ወደ ቤቱ ወስዶም ደበቃቸውና የሆነውን ሁሉ ለሚስቱ ነገራት::

ጥቂት ቆይታም ጸንሳ ወለደች:: ልጃቸውን ፒሉፓዴር [ ፒሉፓተር ] ሲሉ ስም አወጡለት:: ትርጉሙም "መፍቀሬ አብ - የአብ ወዳጅ" ማለት ነው:: ከዚያም አሮስ ሚስቱን : ልጁንና ፪ቱን ገጻተ ከለባት ይዞ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሒዶ ተጠመቀ::

አበው ካህናት እሱን "ኖኅ" : ሚስቱን "ታቦት" : ልጁን ደግሞ "መርቆሬዎስ" ሲሉ ሰየሟቸው:: መርቆሬዎስ ማለትም "ገብረ ኢየሱስ ክርስቶስ - የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ" እንደ ማለት ነው::

ከዚያም ደስ እያላቸው: ክርስቶስን እያመለኩ: ነዳያንን እያሰቡ: ልጃቸውን መርቆሬዎስን አሳደጉ:: ነገር ግን የገጻተ ከለባት ወሬ በመሰማቱ ንጉሡ "ካላመጣሃቸው" አለው:: ኖኅ ጸልዮ ወደ ኃይለኝነታቸው መልሷቸው ስለነበር ፊታቸው ገና ሲገለጥ ብዙ አሕዛብ በድንጋጤ ሞቱ::

ንጉሡም ስለ ፈራ ኖኅን የጦር መኮንን አደረገው:: በጦርነት ጊዜም ገጻተ ከለባቱ ኃይላቸው ስለሚመለስ ተሸንፎ አያውቅም ነበር:: አንድ ጊዜ ግን 2ቱን ገጻተ ከለባት ንጉሡ አታሎ ወሰዳቸው:: ሃይማኖታቸውን ሊያስክዳቸው ሲል "እንቢ" በማለታቸው አንዱ ሲገደል ሌላኛው አምልጦ ጠፋ::

በዚያ ወራትም ኖኅ ለጦርነት ወጥቶ ተማረከ:: ንጉሡ ደግሞ ታቦትን "ላግባሽ" ስላላት የ፭ ዓመት ልጇን ቅዱስ መርቆሬዎስን ይዛ ተሰደደች:: በስደት ጥቂት እንደ ቆየች ግን ባሏን ኖኅን አየችው::

እርሷ ብታውቀውም እርሱ ዘንግቷት ነበር:: በሁዋላ ግን በሕጻኑ መርቆሬዎስ አማካኝነት ማስታወስ በመቻሉ ደስ አላቸው:: በዚያው በሮም ዙሪያ ሳሉም አንዱ ገጸ ከልብ መጥቶ አገኛቸው:: በዚህም ምክንያት በስደት ሃገርም መኮንን ሆኖ ተሾመ::

በዚያም ቤተ ክርስቲያንን አንጾ: ቤቱን ቤተ ነዳያን አድርጐ ኖኅ ለዓመታት ኖረ:: ቅዱስ መርቆሬዎስ ወጣት ሲሆንም ወላጆቹ ታቦትና ኖኅ ዐረፉ:: እርሱ ከባልንጀራው ገጸ ከልብ ጋር ሆኖ በጾምና ጸሎት ሲኖር ስለ አባቱ ፈንታ የጦር መሪ አደረጉት::

በጦርነትም እጅግ ኃያል: በሰው ዘንድም ፍጹም ተወዳጅ: የጾምና የጸሎት ሰው ሆነ:: ያን ጊዜ ግን ዳክዮስ ንጉሡ ክርስቶስን በመካዱ ምዕመናን ላይ ሞት ታወጀ:: በጊዜው ደግሞ የበርበር ሰዎች በሮም መንግስት ላይ ጦርነትን በማንሳታቸው ዳኬዎስና ቅዱስ መርቆሬዎስ ለጦርነት ወጡ::

ነገር ግን በርበሮች እንደ አሸዋ ፈሰው ብዛታቸውን ሲያይ ንጉሡ ደነገጠ:: ለማግስቱ ቀጠሮ ተይዞ ቅዱስ መርቆሬዎስ ሲጸልይ ቅዱስ ገብርኤል ወርዶ ሰይፍ ሰጠው::

በማግስቱም "ምን ይሻላል?" ሲባል ቅዱስ መርቆሬዎስ "እኔ የክርስቶስ ባሪያ ነኝና ብቻየን እቋቋማቸዋለሁ" ቢል ሳቁበት::

እርሱ ግን በጥቁር ፈረሱ [ አብሮት ያደገ ነው ] ተጭኖ በርበሮችን "ጠብ ይቅርባችሁ: በሰላም ሒዱ" ቢላቸው ተሳለቁበት:: ያን ጊዜም ጸሎት አድርሶ የመልአኩን ሰይፍ ሲመዘው ብዙዎቹ ወደቁ:: ከበርበሮችም ለወሬ ነጋሪነት እንኩዋ የተረፈ አልነበረም::

ነገሩ በሮም ሲሰማ ታላቅ ሐሴት ሆነ:: ዳሩ ግን ከሃዲው ዳኬዎስ "ድሉ የጣዖቶቼ የነ አዽሎን ነው" በማለቱ ቅዱስ መርቆሬዎስ ሲያዝን አደረ::

በ፫ኛው ቀንም "ለጣዖት ሠዋ" የሚል ትዕዛዝ ከንጉሡ ዘንድ መጣ:: ቅዱሱ ግን ወደ አደባባይ ሔደ:: የክብር ልብሱንና መታጠቂያውን አውልቆ በንጉሡ ፊት ወረወረው::

"ሃብትከ ወክብርከ ይኩንከ ለኃጉል:: ሊተሰ ክብርየ ክርስቶስ ውዕቱ:: [ ለእኔስ ክብሬ ክርስቶስ ነውና ንብረትህ ለጥፋት ይሁንህ ]" ሲልም ንጉሡን በአደባባይ ዘለፈው:: ዳኬዎስም በቁጣ እሳት አስነድዶ: የብረት አልጋውንም አግሎ ቅዱስ መርቆሬዎስን በዚያ ላይ አስተኛው::

ያም አልበቃ:: ወታደሮች እየተፈራረቁ ሲደበድቡት ደሙ ፈሶ እሳቱን አጠፋው:: ለዚያ ነው ሊቃውንት :-

"አመ አንደዱ ላእሌከ ውሉደ መርገም::
እምቅሡፍ አባልከ እንተ ውኅዘ ደም::
አርአያ ዝናም ብዙኅ አጥፍኦ ለፍህም::" ያሉት::

ከዚያም ወስደው ወኅኒ ቤት ውስጥ ጣሉት:: ክርስቶስን ያስክደው ዘንድ በረሃብ: በግርፋት: በእሳት: በስለትም አሰቃየው:: በመጨረሻ ግን አሰቃይተው እንዲገድሉት ወደ እስያ ሰደደው:: በስፍራውም ብዙ አሰቃይተው ኅዳር ፳፭ ቀን አንገቱን ሰይፈውታል::

እርሱ ካረፈ በሁዋላም የተባረከ ፈረሱ ለዓመታት ወንጌልን ሰብኩዋል:: አረማውያንንም ከአፉ በወጣ እሳት አጥፍቷል:: ተአምረኛውና ኃያሉ ሰማዕት ቅዱስ መርቆሬዎስ በ፪ መቶ [200] ዓ/ም እንደ ተወለደ: በ፪ መቶ ፳ [220] ዓ/ም መከራ መቀበል እንደ ጀመረና በ፪ መቶ ፳፭ [225] ዓ/ም ሰማዕት እንደሆነ ይታመናል::
ሰማዕቱ በዚህች ዕለት : በ፬ኛው መቶ ክ/ዘመን ክርስቲያኖችን ያሰቃይና ይገድል የነበረውን ዑልያኖስን ያጠፋበት መታሠቢያ ይከበራል::
የቅዱሱ ክብር ታላቅ ነው !

† አምላከ ቅዱስ መርቆሬዎስ በከበረ ቃል ኪዳኑ ይጠብቀን:: ከርስቱም አያናውጠን:: ከበረከቱም ይክፈለን::
ቸሩ እግዚአብሔር እድሜ ለንስሃ ዘመን ለፍሥሃ አይንሳን::

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

        †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬

[   ይህን የመሰለ ኪዳን አለን !   ]

ለእኛ ለተዋሕዶ ክርስቶሳውያን ግን ይህን የመሰለ ጽኑ ኪዳን አለን። ጠንቋዮችና አስማተኞች ፤ መተተኞችና ምዋርተኞች በእኛ ላይ አንዳች ስልጣን የላቸውም !

---------------------------------------------

" በያዕቆብ ላይ አስማት የለም ፥ በእስራኤልም ላይ ምዋርት የለም።" [ዘኁ.፳፫፥፳፫] {23፥23}


" እነሆ ፥ እባቡንና ጊንጡን ትረግጡ ዘንድ ፥ በጠላትም ኃይል ሁሉ ላይ ሥልጣን ሰጥቻችኋለሁ ፥ የሚጐዳችሁም ምንም የለም።" [ ሉቃ.፲፥፲፱ ] {10:19}

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

🕊                   

ሰዳዴ ጽልመት አባታችን ቅዱስ ተክለሐይማኖት

"አንተ የደከምክበት ያ መልካም አዝመራ
እንክርዳድ ሞላበት ተክለ አብ ቶሎ ና
አውሬው ሰልጥኖብን ተፍገምግመናል
ኪዳን የሚጠብቅ አባት ያስፈልጋል፡፡"

የኢቲሳ አንበሳ ፤ የኢትዮጵያ ብርሃን ፤ ሐራሴ ወንጌል የጣኦታት ጠላት ፤ ጣኦታትን የሰባበሩ ፤ የአምላካቸውን ስም ያስከበሩ ሐዲስ ሐዋርያ ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት።

†                     †                        †
💖                    🕊                     💖

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

🕊

[ † እንኳን ለቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ]

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †

🕊 † ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ሐዋርያዊ † 🕊

† ልደት †

† መልካም ዛፍ መልካም ፍሬን ያፈራልና ተክለ ሃይማኖትን የወለዱት ደጋጉ: ጸጋ ዘአብ ካህኑና እግዚእ ኃረያ ናቸው:: እርሱ በክህነቱ: እርሷ በደግነቷ: በምጽዋቷ ጸንተው ቢኖሩ እግዚአብሔር ጣፋጭ ፍሬን ሰጥቷቸዋል::

በዳሞቱ ገዢ በሞተለሚ አደጋ ቢደርስባቸው ቅዱስ ሚካኤል: ጸጋ ዘአብን ከሞት: እግዚእ ኃረያን ከትድምርተ አረሚ [ከአረማዊ ጋብቻ] አድኗቸዋል:: በኋላም የቅዱሱን መወለድ አብስሯቸዋል::

ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት የተጸነሱት መጋቢት ፳፬ [24] ቀን በ፲፪፻፮ [1206] ዓ/ም ሲሆን የተወለዱት ደግሞ ታኅሣሥ ፳፬ [24] ቀን በ፲፪፻፯ [1207] ዓ/ም ነው:: በተወለዱበት ቀንም ብዙ ተአምራት ተገልጸዋል:: ቤታቸውም በበረከት ሞልቷል::

† ዕድገት †

የጻድቁ የመጀመሪያ ስማቸው "ፍሥሃ ጽዮን" ይሰኛል:: ይሕንን ስም ይዘው: አባታቸው ጸጋ ዘአብን ተከትለው አድገዋል:: በተለይ ቅዱሳት መጻሕፍትን [ብሉያት: ሐዲሳትን] ተምረዋል:: በሥጋዊው ጐዳናም ብርቱ አዳኝ እንደ ነበሩ ይነገራል:: ዲቁናም ከወቅቱ ጳጳስ አባ ጌርሎስ ተቀብለዋል::

† መጠራት †

አንድ ቀን ፍሥሃ ጽዮን ለአደን ወጥቶ ሲያነጣጥር ድንገት ከሰማይ አስደንጋጭ ድምጽ ተሰማ:: የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አእላፍ መላእክት እያመሰገኑት በሚካኤል ክንፍ ተቀምጦ ወረደ::

የወጣቱን አዳኝ ፍርሃቱን አርቆ ጌታችን ተናገረ:: "ከዛሬ ጀምሮ ስምህ ተክለ ሃይማኖት [ተክለ ሥላሴ] ይሁን:: ከዚህ በኋላ አራዊትን ሳይሆን ነፍሳትን ታድናለህ:: ዘወትር ካንተ ጋር ነኝ" ብሎ በግርማ ዐረገ:: ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ከዚህ ጊዜ በኋላ ሰዓትን አላጠፉም:: ንብረታቸውን ለነዳያን በትነው በትር ብቻ ይዘው ቤታቸው እንደ ተከፈተ ወደ ምናኔ ወጡ::

† አገልግሎት †

ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ከጳጳሱ ቅስና ተቀብለው የወንጌል አገልግሎትን ጀመሩ:: በመጀመሪያ ስብከታቸው እዚያው ሽዋ [ጽላልሽ] አካባቢ ብቻ በ፲ [10] ሺ የሚቆጠሩ ሰዎችን አሳምነው አጠመቁ:: ያን ጊዜ ኢትዮጵያ ፪ [2] መልክ ነበራት::

፩ኛ. ዮዲት [ጉዲት] በፈጠረችው ጣጣና በእስላሞች ተጽዕኖ ወደ ደቡብ አካባቢ ያለው ነዋሪ አንድም ሃይማኖቱን ክዷል: ወይም በባዕድ አምልኮ ተጠምዷል::
፪ኛው ደግሞ በዛግዌ ነገሥታት ጥረት ክርስትናና ምናኔ
ተነቃቅቶ ነበር::

ግማሹ ሃገር በጨለመበት ወቅት የደረሱት ሐዲስ ሐዋርያ አባ ተክለ ሃይማኖት በወጣት ጉልበታቸውና በኃይለ መንፈስ ቅዱስ ብዙ ቦታዎችን አደረሱ:: ሕዝቡን: መሣፍንቱን ወደ ሃይማኖት መልሰው: ማርያኖችን [ጠንቋዮችን] አጥፍተዋል::

† ገዳማዊ ሕይወት †

† ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት በወንጌል ብርሃን ኢትዮጵያን ከማብራታቸው ባለፈ ገዳማዊ ሕይወትንም አስፋፍተዋል:: እርሳቸው ከሁሉ የተሻሉ ሳሉም በ፫ [3] ገዳማት በረድዕነት አገልግለዋል::

እነዚህም በአቡነ በጸሎተ ሚካኤል ገዳም ለ፲፪ [12] ዓመታት: በአቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ ገዳም ለ፯ [7] ዓመታት: በደብረ ዳሞ ከአቡነ ዮሐኒ ጋር ለ፯ [7] ዓመታት: በአጠቃላይ ለ፳፮ [26] ዓመታት አገልግለዋል::

በአቡነ ኢየሱስ ሞዐ ከመነኮሱ በኋላም ወደ ምድረ ሽዋ [ዞረሬ] ተመልሰው በአንዲት በዓት ውስጥ ለ፳፪ [22] ዓመታት ቆመው ጸልየዋል:: በተሰበረ እግራቸውም ፮ [6] ጦሮችን በግራና በቀኝ ተክለው ለ፯ [7] ዓመታት ጸልየዋል::

† ስድስት ክንፍ †

ኢትዮጵያዊው ጻድቅና ሐዋርያ ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ከኢትዮጵያ ወደ ኢየሩሳሌም ተጉዘው ከቅዱሳት መካናት ተባርከዋል:: ጻድቁ ምድረ እሥራኤል የገቡት በየመንገዱ መንፈሳዊ ዘርን እየዘሩ: እያስተማሩና እያሳመኑ ነበር::

ከወቅቱ ሊቀ ጳጳሳት አባ ሚካኤል ጋርም ተገናኝተው ቡራኬን ተሰጣጥተዋል:: ዋናው ጉዳይ ግን ከዚህ በኋላ ነው:: ጻድቁ እመቤታችንና ጌታችን ከጽንሰታቸው እስከ ዕርገታቸው የረገጧቸውን ቦታዎች ሲመለከቱ በፍጹም ተደሞ እንባቸው ይፈስ ነበር::

ምክንያቱም እግዚአብሔር ስላበቃቸው ተክለ ሃይማኖት የሚያዩት ቦታውን አልነበረም:: በገሃድ :-

- በቤተ መቅደስ ብስራቱን
- በቤተ ልሔም ልደቱን
- በቤተ ዮሴፍ ግዝረቱን
- በፈለገ ዮርዳኖስ ጥምቀቱን
- በቤተ አልዓዛር ተአምራቱን ይመለከቱ ነበር::

የጉብኝታቸው የመጨረሻ ክፍል ወደ ሆነው ቀራንዮ ደርሰው ጌታቸውን እንደ ተሰቀለ ሆኖ ቢመለከቱት ከዓይናቸው ይፈስ የነበረው ቁጡ እንባ መልኩን ቀየረና ዓይናቸው ጠፋ::

በዚያች ቅጽበት ስም አጠራሯ የከበረ እመቤታችን ድንግል ማርያም ፈጥና ደርሳ አቡነ ተክለ ሃይማኖትን ወደ ሰማይ አሳረገቻቸው::

† በዚያም :-

- የብርሃን ዐይን ተቀብለው
- ፮ [6] ክንፍ አብቅለው
- የወርቅ ካባ ላንቃ ለብሰው
- ማዕጠንተ ወርቁን ይዘው
- ከ24ቱ ካህናተ ሰማይም ተደምረው
- ሥላሴን በአንድነቱና ሦስትነቱ ተመልክተው
- "ስብሐት ወክብር ለሥሉስ ቅዱስ ይደሉ" ብለው መንበረ ጸባኦትን አጥነው ወደ መሬት ተመልሰዋል::

† ተአምራት †

የቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ተአምራት እንደ ሰማይ ከዋክብት የበዛ ነው::
- ሙት አንስተዋል
- ድውያንን ፈውሰዋል
- አጋንንትን አሳደዋል
- እሳትን ጨብጠዋል
- በክንፍ በረዋል
- ደመናን ዙፋን አድርገዋል::

ብዙ ደቀ መዛሙርትን አፍርተው ደብረ ሊባኖስን መሥርተዋል:: በዚያም ሴትና ወንድ መነኮሳት እንደ ሕጻናት አብረው ኑረዋል:: በዘመናቸው ሰይጣን ታሥሯልና::

† ዕረፍት †

† ጻድቅ: ሰማዕትና ሐዋርያ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ብርሃን ሆነው: መከራን በብዙ ተቀብለው: እልፍ አእላፍ ፍሬን አፍርተው: በተወለዱ በ፺፱ [99] ዓመት: ከ፰ [8] ወር: ከ፩ [1] ቀናቸው ነሐሴ ፳፬ [24] ቀን በ፩፻፮ [1306] ዓ/ም ዐርፈዋል:: ጌታ: ድንግል ማርያምና ቅዱሳን ከሰማይ ወርደው ተቀብለዋቸዋል:: ፲ [10] ትውልድ የሚያስምር ቃል ኪዳንም ተቀብለዋል::

† በዚህ ዕለት አባታችን ተክለ ሃይማኖት ለ፳፪ [22] ዓመታት የቆሙበት ቀኝ እግራቸው መሠበሩንና በአንድ እግራቸው ለ፯ [7] ዓመታት ቆመው መጸለያቸውን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ታስባለች::

[ † ጥር ፳፬ [24] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. አቡነ ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት
፪. ቅድስት ማርያ ግብጻዊት
፫. ታላቁ አባ ቢፋ
፬. አባ አብሳዲ ቀሲስ
፭. ቅዱሳን ጻድቃነ ሐውዚን

[ † ወርኀዊ በዓላት ]

፩. አቡነ ዘዮሐንስ [ዘክብራን ገብርኤል-ጣና]
፪. ቅድስት እናታችን ክርስቶስ ሠምራ
፫. ቅዱስ ቶማስ ዘመርዓስ
፬. ቅዱስ ሙሴ ጸሊም
፭. ቅዱስ አጋቢጦስ
፮. ሃያ አራቱ ካህናተ ሠማይ

" በድካም : አብዝቼ በመገረፍ : አብዝቼ በመታሠር : አትርፌ በመሞት ብዙ ጊዜ ሆንሁ:: በድካምና በጥረት : ብዙ ጊዜም እንቅልፍ በማጣት : በራብና በጥም : ብዙ ጊዜም በመጦም : በብርድና በራቁትነት ነበርሁ . . . የቀረውን ነገር ሳልቆጥር ዕለት ዕለት የሚከብድብኝ የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ አሳብ ነው:: " † [፪ቆሮ ፲፩፥፳፫]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖

Читать полностью…

ምክር ፣ ተግሣፅ ወትምህርተ አበው ✞

                       †                       

   [    🕊  ፍኖተ ቅዱሳን   🕊    ]

[  የቅዱሳን አባቶቻችን የቅድስናና የተጋድሎ ሕይወት ]

†                       †                       †

[  የፍትወት ጾር ስለሚያስነሣው ፈተና ]

🕊

ክርፋቱንና አስጸያፊነቱን አይቻለሁና ! ]

........

አንድ ሰው ሊመነኩስ ወደ አስቄጥስ መጣ፡፡ ገና የእናቱን ጡት የጣለ ልጁ ከእርሱ ጋር አብሮት ነበር፡፡

ይህ ልጁ አድጎ ሙሉ ሰው ሲሆን ውጊያ ጀመረውና አባቱን ፦ "ፈተናውን አልቻልኩትምና ወደ ዓለም ልመለስ ነው" አለው፡፡ አባቱ ደጋግሞ ቢያበረታታውና ቢያጽናናውም ፦ "አባ ፣ ከዚህ በላይ ምንም ለማድረግ አልችልም ፣ ልሂድ" አለው:: አባቱም ፦ "ልጄ ፣ አንድ ጊዜ ብቻ ስማኝ፡፡ ለዓርባ ቀን የሚሆንህን ዳቦና ለዚሁ ቀን የእጅ ሥራህ የሚበቃህን ያህል ሰሌን ውሰድና ወደ ውስጠኛው በረሃ ሂድ ፣ በዚያም ለዓርባ ቀናት ቆይ ፤ ከዚያ በኋላ የእግዚአብሔር ፈቃድ ይሁን" አለው፡፡

የአባቱን ነገር ሰምቶ በመታዘዝ ወደ ውስጠኛው በረሃ በመሄድ በዚያ ደረቅ ዳቦ እየበላና ሰሌን እየታታ በከባድ ሁኔታ ቆየ፡፡ ሃያ ቀናት እንደቆየ የሰይጣን ኃይል ወደ እርሱ እየመጣ ታየው ፣ ከክርፋቷ የተነሣ ሽታዋን ሊታገሠው በማይችለው በጥቁር ሴት ሁኔታ ተገለጠለት፡፡ ከክርፋቷ የተነሣም ከእርሱ አርቆ ወደዚያ እልፍ አደረጋት። እርሷም ፦ " ብዙውን ጊዜ ለሰዎች ልቡና አስደሳች እመስላለሁ ፣ አንተን ግን ስለ ስለ መታዘዝህና ስለ ድካምህ እግዚአብሔር በእኔ ትታለል ዘንድ አልተወህም ፤ ስለሆነም አስጠሊታነቴንና መጥፎ ሽታዬን ገልጦልሃል " አለችው።

በዚህ ጊዜ ተነሣና እግዚኣብሔርን እያመሰገነ ወደ አባቱ ተመልሶ ፦ " አባ ፣ ከእንግዲህ ፈጽሞ ወደ ዓለም መመለስ አልፈልግም ፣ የሰይጣነ ዝሙትን ኃይሉን ፣ ክርፋቱንና አስጸያፊነቱን አይቻለሁና " አለው፡፡

የሆነው ነገር ለአባቱም ተገልጦለት ስለ ነበር ፦ " ዓርባ ቀን ቆይተህና ያዘዝኩህን ጠብቀህ ቢሆን ኖሮ የበለጠ ነገር ነገር ታይ ነበር " አለው።

🕊

የአባቶቻችን ጸሎትና በረከት ይደርብን፡፡

†                       †                        †
💖                    🕊                     💖

Читать полностью…
Subscribe to a channel