"እንግዲህ፡ንስሓ፡ግባ፤አለዚያ፡ፈጥኜ፡ እመጣብሃለሁ፡፡" ራዕ 2፥16
* ረቡዕ - ጥር 15 2016 ዓ.ም *
* ዘፍጥረት 12-18 *
ሰላም ለሁላችሁ ይሁን! በዛሬው ንባባችን ከምዕራፍ 12 እስከ 18 ድረስ እናነባለን።
በእነዚህ ምዕራፎች መጀመሪያ እግዚአብሔር አብራምን ይጠራዋል፥ ታላቅ ሕዝብ እንደሚያደርገውም ቃል ይገባለታል። ሆኖም ግን አብራም የእግዚአብሔርን ጥሪ ተከትሎ በሚያደርገው ጉዞ ውስጥ በምድር ላይ ረሃብ ሲያጋጥም፥ አብራምም ወደ ግብጽ በተሰደደ ጊዜ በግብጽ እንዳይገድሉት ፈርቶ ሚስቱን ሦራ 'እህቴ ናት' ብሎ ሲያቀርብም እየተገረምን አብረነው በእምነት እንጓዛለን።
ሃብታቸው ከመብዛቱ የተነሳ ቦታ እንዲበቃቸው አብራም ከወንድሙ ልጅ ከሎጥ ጋር ቦታ መርጠውም ሰፈሩ፥ አዲስ በሰፈረበት ቦታ ሎጥ እንደተማረከ በሰማ ጊዜ ደግሞ አብርሃም ተዋግቶ አዳነው። በተጨማሪ፥ ልጅን መውለድ ያልቻለችው ሦራ፥ ከግብጻዊት ባሪያዋ አጋር ልጅን እንዲወልድ ባሏ አብራምን ትመክረዋለች፤ እስማኤልም በዚህ መካከል ይወለዳል። እግዚአብሔር ግን ለአብራም የገባውን ቃሉን ሳያጥፍ አብራም ልጅ እንደሚያገኝ ይነግረዋል፥ መገረዝን በማጽናትም ቃልኪዳኑን ከአብርሃም ጋር ያደርጋል። እግዚአብሔር የአብራምን ስም ወደ 'አብርሃም'፥ የሦራን ስም ደግሞ ወደ 'ሣራ' ሲቀይር፥ አልፎም ደግሞ አብርሃም ስለ ሰዶም ሲማልድ የምናነበውም በእነዚህ ምዕራፎች ውስጥ ነው።
* የክለሳ ጥያቄዎች *
1) በዘፍጥረት 12 መሠረት፥ አብራም ይኖርበት የነበረውን ቦታ ለቅቆ የወጣው ለምንድር ነው?
2) አብራም በግብጽ ሀገር ምን ገጠመው? ችግሩስ በምን አይነት መንገድ ተፈታ?
3) በዘፍጥረት 13 መሠረት በአብራም እና በሎጥ መካከል የተፈጠረው አለመግባባት ምክንያት ምን ነበር?
4) አብራም እና ሎጥ አለመግባባታቸውን በምን መልክ ፈቱት?
5) ሎጥ ከአብራም ከተለየ በሁዋላ ምን ድረሰበት? የአብራም ምላሽስ ምን ነበር?
6) በዘፍጥረት 14 ላይ የተጠቀሰው መልከጼዴቅ ማነው? ያለውስ ሚና ምንድር ነው?
7) በዘፍጥረት 15 መሠረት እግዚአብሔር ለአብራም ምን ብሎ ቃልኪዳን ገባለት?
8) በዘፍጥረት 15 ላይ እግዚአብሔር የአብራምን ዘሮች በምን መሠላቸው?
9) ሦራ አብራም ከአጋር ልጅ እንዲወልድ አሳብ ያቀረበችው ለምንድር ነው?
10) ከአብራም እና ከአጋር የተወለደው ልጅ ስሙ ማን ተባለ?
11) በዘፍጥረት 17 መሠረት እግዚአብሔር የአብራምን እና የሦራን ስም ማን ብሎ ቀየረ?
12) በዘፍጥረት 17 መሠረት እግዚአብሔር ለአብርሃም እንዲጠብቅ የሰጠው ቃልኪዳን ምንድር ነው?
13) በዘፍጥረት 18 ላይ አብርሃም በማን ተጎበኘ? ስለ ሚስቱ ሣራስ ምን ሰማ?
14) በዘፍጥረት 18 ላይ አብርሃም ለሰዶም ምን ብሎ አማለደ?
መልካም ንባብ!
ታቦት በሐዲስ ኪዳን (2).pdf'
/channel/EthioBooksClub
🕊
[ እንኳን ለሰማዕታት ቅዱሳን ቂርቆስ ወኢየሉጣ : ወነቢይ አብድዩ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። ]
[ 🕊 ስሜ ክርስቲያን ነው 🕊 ]
---------------
" እስክንድሮስ የክህደት አዋጅን ሲያውጅም ቅድስቲቱ ለሕጻን ልጇ ራርታ ሽሽትን መረጠች:: ሃብት ንብረቷን: ወገንና ርስቷንም ትታ: ሕጻን ልጇን ተሸክማ ተሰደደች:: መከራው ግን በሔደችበት አለቀቃትም።
እስክንድሮስ ተከትሎ ባለችበት ቦታም አገኛት። ወታደሮች ልጇን ሳያገኙ እርሷን ብቻ ይዘው ወደ መኮንኑ አቀረቧት። መኮንኑም "ስምሽን ንገሪኝ" ቢላት "ስሜ ክርስቲያን ነው" አለችው:: ተቆጥቶ "ትክክለኛውን ስምሽን ተናገሪ" ቢላት "እውነተኛው ስሜ ክርስቲያን ነው:: ሞክሼ [ሞክሲ] ስም ከፈለግህ ኢየሉጣ እባላለሁ" አለችው።
"ለጣዖት ልትሰግጂ ይገባል" ሲላትም "እውነትን ይነግረን ዘንድ የ፫ [3] ዓመት ሕጻን ፈልገህ አምጣና ተረዳ" ስላለችው ወታደሮቹን እንዲፈልጉ ላካቸው። የሃገሩ ሰዎች ልጆቻቸውን ስለደበቁ የተገኘ ቅዱስ ቂርቆስ ነበር።
ቅዱሱ ሕጻን በወታደሮች ተይዞ ሲቀርብ መልኩ ያበራ ነበርና መኮንኑ "በሐከ ፍሡሕ ሕጻን - ደስ የተሰኘህ ሕጻን እንዴት ነህ" ቢለው "ትክክል ነህ ! እኔ በጌታዬ ክርስቶስ ዘንድ ደስታ ይጠብቀኛል:: አንተ ግን በክህደትህ ወደ ገሃነም ትወርዳለህ" አለው::
በሕጻኑ ድፍረት የደነገጠው መኮንኑ በብስጭት "እሺ! ስምህን ንገረኝ" አለው። ያን ጊዜ "ከንጹሕ ምንጭ የተቀዳ: ስሜ ክርስቲያን ነው። እናቴ የሰየመችኝን ከፈለክ ግን ቂርቆስ ነው" ሲል መለሰለት።
[ በረከታቸው ይደርብን ምልጃ ጸሎታቸው አይለየን፡፡ ]
† † †
💖 🕊 💖
†
[ " ትቶአቸውም ሄደ። " ] ማቴ.፲፮፥፬
" እነሆ ፥ ቤታችሁ የተፈታ ሆኖ ይቀርላችኋል።"
[ ማቴ.፳፫፥፴፰ ]
† † †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬
ዲዮጋን
፨፨፨
📖 የታላቁ ፈላስፋ የዲዩጋን ምርጥ ምላሾች!!
❇️ በቆሻሻ ቦታ ሲዘዋወር የተመለከተው የአቴና ነዋሪ ወዳጁ
ቢገስጸው፡-
‹‹አትሳሳት! ጸሀይ የማትወጣበት ቦታ የለም እስከዛሬ ግን አልቆሸሸችም ብሎታል››፡፡
❇️ በሌላ ግዜም በገበያ ቦታ ላይ ሲበላ የተመለከቱት የአቴና ነዋሪዎች በዙሬያው ተሰብስበው
‹‹ውሻ ውሻ ! ›› በማለት ሲጮሁበት፡-
‹‹እኔ የማውቀው ሰው ምግብ ሲበላ በዙሪያው ከቦ የሚመለከትና የሚጮህ ብቻ ነው››በማለት
መልሳል፡፡
❇️ ሰዎች ለለማኝ እንጂ ለምን ለፈላስፋ ገንዘብ እንደማይሰጡ ሲጠይቁት
‹‹ምክንያቱም አንድ ቀን ለማኝ እንጂ ፈላስፋ እንደማይሆኑ ስለሚያውቁ ነው›› ብላቸዋል፡፡
❇️ ምግብ ለመመገብ የተመቸ ሰአት የቱ እንደሆነ ተጠይቆ፡-
‹‹ሀብታም ከሆንክ ስትፈልግ ድሀ ከሆንክ ደሞ ስትችል ምግብ ለመመገብ ጥሩ ሰአት ነው››ብላል፡፡
❇️ ለዲዩጋን ምጽዋት የሚሰጡት ሰዎች ለምን
እንደማያመሰግናቸው ሲጠይቁት
‹‹እናንተ በመስጠታችሁ ብቻ ሳይሆን እኔም የናንተን ምጽዋት በመቀበሌ ምስጋን ይገባኛል››ብላቸዋል፡፡
❇️ ስለጸሎተኛ ሰው ሲጠይቁት
‹‹ጸሎተኛ ሰው የሚፈልገውን እንጂ መጠየቅ የሚገባው የማይጠይቅ ሰው ነው››ብላል፡፡
❇️ ሲሞት እንዴት እንዲቀብሩት እንደሚፈልግ ሲጠየቅም
‹‹ፊቴን ወደታች ዘቅዝቃችሁ ቅበሩኝ
ምክንያቱም ዝቅ ያለ ነገር ጥቂት ቆይቶ ከፍ ማለቱ እንደማይቀር ስለማውቅ ነው›› ብላቸዋል፡፡
❇️ እንድ የአቴና አስተማሪ ስለህይወት ክፉነት ደጋግሞ ሲያስተምር ሰምቶ
‹‹ህይወት ክፉ ያደረጋት የሚኖራት እንጂ ህይወት በራሷ ክፉ አይደለችም››ብሎታል፡፡
❇️ በባርነት የገዛው ዜነዲየስ ‹‹እኔን ልትታዘዝ የግድ ነው››አለው፡፡
‹‹ምንም እንኳን ባሪያህ ብሆንም አዋቂና የነቃ ሰው በባርነትም ሆኖም ሊታዘዙት ያስፈልጋል››፡፡
ሠናይ አሁን
†
[ ጥር ፲፬ / ፳፻፲፭ [ 14/2015 ! ]
በዚህች ቀን ዘረኞችና ሔሮድሳውያን ሕገ ወጥ ጳጳሳትን የሾሙባት ፣ በቤተ ክርስቲያን ከባድ መከራ የወረደባት ዕለት ናት።
ቤተ ክርስቲያን ጥቁር እንድትለብስ ፣ እንድታለቅስ ምክንያት የሆናት ቀን !
† † †
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
ዋኝተው ወጥተው ወደ ዳርቻ ሲደርሱም ማዕበል የተፋው አንድ በድን ወድቆ ተመልክተው ፈጸመው አለቀሱ:: ወዲያውም በልባቸው የዚህን ዓለም ኃላፊነት አሰቡ:: ሹመት ፍለጋ መሔዳቸውን ትተው ወደ ገዳም ሔዱ::ወደ ምድረ ሶርያ ደርሰው በታላቁ ደብረ ሮማኖስ መዓርገ ምንኩስናን ተቀበሉ:: በእጃቸው የነበረውን ፪፻ [200] ዲናር ወርቅም ለገዳሙ አበረከቱ:: ለጥቂት ጊዜ በገዳሙ ካገለገሉ በሁዋላም ጾማዕት [በዓት] ተሰጣቸው::
በዚህ ጊዜም "እንግዲህ ወደ ዓለም አልወጣም:: የሴቶችን መልክም አልመለከትም" ሲሉ ቃል ገቡ:: በተጋድሏቸውም በጾምና በጸሎት: በትጋሃ ሌሊት ለ፲፪ [12] ዓመታት ቀጠሉ:: ጾማቸውም 7 ቀን ነበር:: አምላክ ጸጋውን ስላበዛላቸውም ብዙ ድውያንን ፈወሱ::
ዜናቸውም እስከ ምድረ ሮሜ ተሰማ:: እናታቸው [ሰንደሊቃ] የመርከቡን ዜና ከሰማች በሁዋላ የሞቱ መስሏት አልቅሳ ቤቷን የእንግዳ ቤት አድርጋ: በበጎ ምግባር ትኖር ነበርና አንድ ቀን የልጇን ዜና ሕይወት ሰማች::
ከደስታዋ የተነሳ ፈጥና ወደ ደብረ ሮማኖስ ደርሳ "ልጄን ልይ" አለች:: ግን "ሴትን አላይም" ብለው አባ አርከሌድስ ቃል ገብተዋልና ምን ይሁን! ሰንደሊቃም "አራዊት ይብሉኝ እንጂ ልጄን ሳላይ አልሔድም" አለች:: ወዲያው ግን "አባ አርከሌድስ ፈቅደዋልና ግቢ" የሚል መልእክት መጥቶላት ገባች::
ግን ያገኘችው የጻድቁን ልጇን ሥጋ ነበር:: ምክንያቱም የፈጣሪንም: የእናታቸውንም ልብ ላለማሳዘን እንዲወስዳቸው ለምነውት ዐርፈው ነበር:: እናትም በልጇ ሥጋ ላይ እያለቀሰች እዚያው ዐረፈች:: "አብራችሁ ቅበሩን" የሚል ቃል ከቅዱሱ ሥጋ ስለ ተሰማም አብረው ቀብረዋቸዋል::
† አምላከ ቅዱሳን ለእነርሱ ካደለው ፍቅራቸው ለእኛም አይንሳን:: በረከታቸውንም ያብዛልን::
🕊
[ † ጥር ፲፬ [ 14 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. አቡነ አረጋዊ [ ዘሚካኤል ]
፪. ቅዱስ አባ መክሲሞስ
፫. ቅዱስ አባ አርከሌድስ
፬. ቅድስት እምራይስ
፭. ቅድስት ምሕራኤል
፮. "4034"ሰማዕታት [ማሕበራነ ቅዱስ ቂርቆስ]
[ † ወርሐዊ በዓላት ]
፩. አባ ስምዖን
፪. አባ ዮሐንስ
፫. ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ [ ሙሽራው ]
፬. ቅዱስ ሙሴ
፭. ቅዱስ ፊልዾስ [ ከ፸፪ [72] አርድዕት ]
፮. ቅድስት ነሣሒት
† " እግዚአብሔር ፍርድን ይወድዳልና:: ቅዱሳኑንም አይጥላቸውምና:: ለዘለዓለምም ይጠብቃቸዋል . . . ጻድቃን ምድርን ይወርሳሉ:: በእርስዋም ለዘላለም ይኖራሉ:: የጻድቅ አፍ ጥበብን ያስተምራል:: አንደበቱም ፍርድን ይናገራል:: የአምላኩ ሕግ በልቡ ውስጥ ነው:: በእርምጃውም አይሰናከልም::" † [መዝ.፴፮፥፳፰]
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖 🕊 💖
🕊
[ O R T H O D O X Y ! ]
💖
[ የገጠሪቱ እናታችን ቤተክርስቲያን ! ]
ወላይታ ሁምቦ ቦላ ፍንጎ ቅድስት ኪዳነ ምህረት ቤተክርስቲያን ከ ፲፩ [ 11 ] ዓመት በኋላ የተገኘ ደስታ !
† † †
💖 🕊 💖
*ሰኞ - ጥር 13 2016 ዓ.ም*
*ዘፍጥረት 1-5*
በዛሬው እለት ኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ 1 እስከ 5 ድረስ እናነባለን። በእነዚህ ምዕራፎች ውስጥ እግዚአብሔር በስድስት ቀናት ውስጥ ፍጥረታትን እንዴት እንደፈጠረ፥ በስድስተኛው ቀን አዳምና ሔዋንን ፈጥሮ በሰባተኛው ቀን እንዳረፈ እናነባለን። በገነት ውስጥ አዳም እና ሔዋን እግዚአብሔርን እንዳልታዘዙ፥ በዚህም ምክንያት ከገነት እንደተባረሩም ተጽፎ ይገኛል። በተጨማሪም በልጆቻቸው በአቤል እና በቃየን መካከል ችግር ተፈጥሮ፥ ቃየን ወንድሙ አቤልን እንደገደለው የምናነበውም በእነዚህ ምዕራፎች ውስጥ ነው። በምዕራፍ አምስት ላይ ከአዳም እስከ ኖኅ ድረስ ያለውን የዘር ግንድ የምናገኝ ሲሆን፥ ይህም ቀጣይ ለምናነባቸው ታሪኮች ያዘጋጀናል።
*የክለሳ ጥያቄዎች*
1) እግዚአብሔር በመጀመሪያው ቀን ምን ፈጠረ?
2) እግዚአብሔር የሰው ልጅን የፈጠረው በስንተኛው ቀን ነው?
3) በዘፍጥረት 2 መሠረት፥ አዳም የተፈጠረው እንዴት ነው?
4) እግዚአብሔር በገነት ውስጥ ለአዳም እና ሔዋን የሰጠው ኃላፊነት ምን ነበር?
5) አዳም እና ሔዋን እግዚአብሔርን ባለመታዘዝ የበሉት ምን ነበር?
6) የአዳም እና ሔዋን አለመታዘዝ ምን ውጤት አስከተለ?
7) በዘፍጥረት 4 ላይ የተጠቀሱት የአዳም እና የሔዋን ልጆች እነማን ናቸው?
8) በአቤልና ቃየን መካከል የነበረው ግጭት በምን ተነሳ? ፍጻሜውስ ምን ሆነ?
9) በዘፍጥረት 5 ያለው የዘር ግንድ ዓላማው ምንድር ነው?
10) በዘፍጥረት 5 መጨረሻ ላይ የተጠቀሰው ሰው ማን ነው?
ለውይይት እና ክትትል እንዲመች ከዚህ በኃላ ንባቡን ለመቀጠል የሚከተለውን join አድርጉ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
/channel/+3kpzSPDfiVMzYzQ0 /channel/BetMetsahfte
- በወቅቱ መልካቸው የወጣት ነው:: እድሜአቸው ግን ፬ መቶ ሊሞላ ትንሽ ቀርቶት ነበር:: ልክ እንደ አቤሜሌክ ብዙ መተኛታቸው አልታወቃቸውምና ከመካከላቸው አንዱ የራት ዳቦ ሊገዛ ቢወጣ ግራ ተጋባ:: ኤፌሶን የማያውቃት ሌላ ሃገር ሆነችበት:: ከተማዋ ዘምናለች::
- በየቦታው አብያተ ክርስቲያናት: ቅዱስ መስቀልም በየአደባባዩ ተተክለዋል:: ነገሩ ግር ቢለው አንዱን ከመንገድ ጠርቶ "ወንድሜ! ይህቺ ከተማ ኤፌሶን አይደለችምን?" አለው:: እርሱም "አዎ ናት" ብሎት አለፈ::
- ችግሩ ግን "ራት ልግዛ" ብሎ ወደ ገበያ ሲሔድ: እርሱ የያዘው ገንዘብ የዳኬዎስ ስም የተጻፈበት መሆኑ የፈጠረው ነበር:: በነጋዴዎቹ "የተደበቀ የጥንት ገንዘብ አግኝተሃል" በሚል ተከሶም ወደ ንጉሡ ቴዎዶስዮስ ዘንድ ቀረበ:: [ትንሹ ቴዎዶስዮስ ነው:: የነገሠውም በ፭ኛው መቶ ክ/ዘመን ነው]
- በክርክሩ መካከል ቅዱሱ የእሱንና የወንድሞቹን ነገር ሲናገር ንጉሡም: ሊቀ ዻዻሱም [አባ ቴዎድሮስ ይባላል] ተገረሙ:: አብረው ከከተማ ወጥተው ሔደው: ፯ቱንም ሲጸልዩ አገኟቸው:: ፊታቸውም እንደ እግረ ፀሐይ ያበራ ነበር:: ፯ቱም ለ፯ ቀናት በኤፌሶን ድውያንን እየፈወሱ: ሰውን ሁሉ እየባረኩ ቆዩ::
- ይህ ሁሉ የተደረገው በወቅቱ "ትንሳኤ ሙታን የለም" የሚሉ መናፍቃን ተነስተው ብዙ ሰው ክዶ ነበርና ለእነሱ ምሥክር ሊሆንባቸው ነው:: በርካቶችም በዚህ ድንቅ ተስበው ወደ ሃየማኖት ተመልሰዋል:: ፯ቱ ቅዱሳን ግን በ፯ኛው ቀን በክብር ዐርፈዋል:: ንጉሡ ፯ የወርቅ ሣጥኖች ቀብሯቸዋል::
አምላከ አበው ቅዱሳን በመጽናታቸው ያጽናን:: ከበረከታቸውም ያድለን::
🕊
[ † ጥር ፲፫ [ 13 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. አቡነ ዘርዓ ቡሩክ ኢትዮዽያዊ [ እረፍታቸው ]
፪. ሰባቱ ደቂቅ ቅዱሳን [ ከኤፌሶን ]
፫. ቅዱስ አባ ነካሮ
፬. ቅዱስ ቃሮስ
[ † ወርሐዊ በዓላት ]
፩. እግዚአብሔር አብ
፪. ቅዱስ ሩፋኤል ሊቀ መላእክት
፫. ቅዱስ አስከናፍር
፬. "፲፫ ግኁሳን ጻድቃን"
፭. ቅዱስ አርሳንዮስ ጠቢብ
፮. ዘጠና ዘጠኙ ነገደ መላእክት
" በተቀደሰ አሳሳም እርስ በርሳችሁ ሰላምታ ተሰጣጡ:: ቅዱሳን ሁሉ ሰላምታ ያቀርቡላቹሃል:: የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ : የእግዚአብሔርም ፍቅር : የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን:: አሜን::" [፪ቆሮ.፲፫፥፲፪]
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖 🕊 💖
+ የትውውቅ መርሐ ግብር + (ቻሌንጅ/ሞክረኛ)
ከውሃ የወጣ ዓሳ፥ ከአፈር የተነቀለ ተክል፥ ከአየር የተለየ ሰው ሙት መሆኑ እርግጥ ነው። ለክርስቲያን ደግሞ ሞቱ ከእግዚአብሔር መለየት ነው። አንድ ክርስቲያን ከእግዚአብሔር ቃል ጋር ያለው ግንኙነት ከተቋረጠ፥ በጸሎትም አምላኩን ማነጋገሩን ከተወ የሞቱ ዋዜማ ላይ መሆኑን እንረዳለን። የቫይታሚን እጥረት የሰውነት መቀንጨርን እንደሚያስከትል ሁሉ፥ ከእግዚአብሔር ቃል ስንለይ መንፈሳዊ ሕይወታችን ይቀነጭራል። ይህ እንዳይሆን መጸለይ፥ የእግዚአብሔርም ቃል በውስጣችን እንዲያድር ቅዱስ መጽሐፉን በርትተን በጸሎት መንፈስ ማንበብ ይኖርብናል።
ብዙ ጊዜ “ሰው ከእግዚአብሔር ቃል አልገናኝ አለ! ሰው የአምላኩን ቃል አያውቅም!” ወዘተ እየተባለ አስተያየት ሲሰጥ ይስተዋላል። በእርግጥ እውነት ሊሆን ይችላል። ሆኖም ግን ችግሩን እያገዘፉ ከመኖር፥ መፍትሔው ላይ ማተኮሩ ብልህነት ነው። ጨለማውን እያማረሩ መኖር ይቻላል፤ ወይም ደግሞ እንደ አቅማችን ሻማ መለኮስ። ምርጫው እንግዲህ የእኛው ነው።
ይህንን ታሳቢ በማድረግ አንድ ቻሌንጅ/ሞክረኛ አዘጋጅቻለሁ። ይህም ቻሌንጅ መጽሐፍ ቅዱስን ከኦሪት ዘፍጥረት አንስቶ እስከ ዮሐንስ ራእይ ድረስ በስድስት ወር ውስጥ አንብቦ ማጠናቀቅ ነው። በአጭሩ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር የሚደረግ የትውውቅ መርሐ ግብር ብሎ ማሰብ ይቻላል። መጽሐፍ ቅዱስ ሁሌም አዲስ እንደመሆኑ፥ ሁሌም ትውውቅ ይፈልጋል። “አውቄዋለሁ። ጨርሼዋለሁ።” የሚል ቃል ለመጽሐፍ ቅዱስ አይሠራም። ቤተ-ክርስቲያንንም ለመረዳት ትልቁ ቁልፍ መጽሐፍ ቅዱስ መሆኑ እሙን ነው። እግዚአብሔር ቢፈቅድ እና ብንኖር፥ በዓመት ሁለት ጊዜ መጽሐፍ ቅዱስን ከጫፍ እስከ ጫፍ ማንበብ እንችላለን ማለት ነው። ንባቡን ሳያውቁ ምስጢሩን መጠየቅ የማይሆን ነውና፥ አስቀድመን ንባቡን ማወቅ ይገባል። ጥልቅ የሆነው የእውቀት ጉዞም የሚነሳው ማንበብ ከመጀመር ነው።
ክርስትና የኅብረት ጉዞ እንደመሆኑ መጠን፥ ይኽም ጉዞ የኅብረት ቢሆን ጥቅሙ ብዙ ነው። እግዚአብሔር ቢፈቅድ ይህ ጉዞ በነገው እለት ጥር 13 2016 ይጀምርና ሐምሌ 16 2016 ይጠናቀቃል። ይኽንን ጉዞ አብራችሁ ከእኔ ጋር ለመጓዝ ፈቃደኛ የሆናችሁ ሁሉ፥ በኮሜንት ላይ አሳውቁኝ። የፌስቡክ ቻት ግሩፕ ከፍተን አብረን ጉዞውን እንጀምራለን።
ኑ፥ ከእግዚአብሔር ቃል ጋር አብረን እንጓዝ!!
#ለማንበብ_ፍቃደኛ_የሆናችሁ_ፍላጎታችሁ_በ❤️👏👍 ግለጹ።
🖋 Fresenbet G.Y Adhanom
🕊
[ ቅ ድ ስ ት ሀ ገ ር ኢ ት ዮ ጵ ያ ! ]
---------------------------------------------
💖
ኢትዮጵያ በሠረገላ ሆና የነቢያትን መጻሕፍት ስታነብ ምዕራባውያን ሀገራት ባዶ ምድረ በዳዎች ነበሩ። ሌሎችም በጣዖት አምልኮ የሚኖሩ ነበሩ። የእግዚአብሔር የምስጢር ሀገር ቅድስት ኢትዮጵያ በሕገ ልቡና ፥ በሕገ ኦሪት ፥ በሕገ ወንጌል በአምልኮተ እግዚአብሔር ጸንታ የተገኘች የቅዱሳን አምባ የከበረች ምድር ናት።
በመንፈስ ቅዱስ ተመርጦ ፥ የተነገረው ትንቢት የተቆጠረው ሱባኤ መፈጸሙን ተረድቶ ገና በ፴፬ ዓ.ም [ በ34 ዓ.ም] የክርስቶስን የባህርይ አምላክነት አምኖ የመሠከረና የልጅነት ክብርን በአማናዊው ጥምቀት የተጎናጸፈ አንድም ሀገር የለም ከኢትዮጵያ በቀር !
† † †
" የጌታም መልአክ ፊልጶስን። ተነሥተህ በደቡብ በኩል ከኢየሩሳሌም ወደ ጋዛ ወደሚያወርደው ምድረ በዳ ወደ ሆነ መንገድ ሂድ አለው። ተነሥቶም ሄደ። እነሆም ፥ ህንደኬ የተባለች የኢትዮጵያ ንግሥት አዛዥና ጃንደረባ የነበረ በገንዘብዋም ሁሉ የሠለጠነ አንድ የኢትዮጵያ ሰው ሊሰግድ ወደ ኢየሩሳሌም መጥቶ ነበር ፤
. . .
በመንገድም ሲሄዱ ወደ ውኃ ደረሱ ፤ ጃንደረባውም። እነሆ ውኃ ፤ እንዳልጠመቅ የሚከለክለኝ ምንድር ነው ? አለው።
ፊልጶስም። በፍጹም ልብህ ብታምን ፥ ተፈቅዶአል አለው። መልሶም። ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ አምናለሁ አለ።
ሰረገላውም ይቆም ዘንድ አዘዘ ፥ ፊልጶስና ጃንደረባው ሁለቱም ወደ ውኃ ወረዱ ፥ አጠመቀውም። " [ሐዋ.ሥራ.፰፥፳፮-፴፰]
ኢትዮጵያ ከሕገ ኦሪት ወደ ሕገ ወንጌል የተሸጋገረችው በዘመነ ሐዋርያት ነው። ኢትዮጵያን ያጠመቀውም ቅዱስ አባታችን ፊልጶስ ነው።
"ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች።" [ መዝ.፷፰፥፴፩ ]
† † †
💖 🕊 💖
🕊
[ የቀደመችውን መንገድ ! ]
💖
"በመንገድ ላይ ቁሙ ፥ ተመልከቱም የቀደመችውን መንገድ ጠይቁ በእርሷም ላይ ተመላለሱ፡፡ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፡፡"
[ ኤር . ፮ ፥ ፲፮ ]
† † †
💖 🕊 💖
🕊
[ 💖 ORTHODOXY 💖 ]
† † †
ፕሬዝዳንት ፑቲንን ጨምሮ በርካታ ሩሲያውያን ጥምቀትን በተለያዩ ስፍራዎች አክብረዋል
ከ ፺ [ 90 ] ሚሊዮን በላይ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ያሏት ሩሲያም የጥምቀት በዓልን በድምቀት ከሚያከብሩ ሀገራት መካከል ተጠቃሽ ነች።
የሩሲያ ኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዮርዳኖስ ወንዝ መጠመቅን እና ምስጢረ ሥላሴን መሠረት በማድረግ በበረዶ ውሃ ውስጥ ራሳቸውን ሶስት ጊዜ ይነከራሉ።
† † †
💖 🕊 💖
🕊 † ኃያል ቴዎድሮስ በናድሌዎስ † 🕊
- በ፫ኛው መቶ ክ/ዘመን በምሥራቅ [በአንጾኪያ] ያበራ:
- ድንግልናውን በንጹሕ የጠበቀ:
- ቅዱሳን መላእክት የሚያነጋግሩት:
- የአንጾኪያ ሠራዊት ሁሉ አለቃ የነበረ:
- በጦርነት ተሸንፎ የማያውቅ:
- አሕዛብ ስሙን ሲሰሙ የሚንቀጠቀጡለት:
- ከአማልክት ወን ነው እያሉ የሚፈሩት
- እግዚአብሔርን በፍጹም ልቡ የሚያመልክ የወቅቱ ወጣት ክርስቲያን ነው::
- ዲዮቅልጢያኖስ በካደ ጊዜም ጌታ ከባልንጀሮቹ ለውንድዮስና ኒቆሮስ ጋር መላእክት ወደ ሰማይ አሳርገውታል:: በዚያም መድኃኒታችን ክርስቶስን ፊት ለፊት አይቶ: በእሳት ባሕርም ተጠምቁዋል:: በዚህች ቀንም ከቅዱሳን ለውንድዮስና ኒቆሮስ: እንዲሁ ከ፪.፭ ሚሊየን ሰራዊቱ ጋር ለመከራ ተሰጥቷል:: እርሱንም በ፻፶፫ ችንካር ወግተው ገድለውታል::
አምላከ ቅዱሳን ወይነ ቃና ፍቅሩን ያሳድርብን::
ከድንግል እናቱ ምልጃና ከቅዱሳኑ በረከትም አይለየን::
🕊
[ † ጥር ፲፪ [ 12 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት † ]
፩. ቃና ዘገሊላ
፪. ቅዱስ ያዕቆብ እሥራኤል
፫. ቅዱስ ቴዎድሮስ በናድሌዎስ
፬. ቅዱሳን ለውንድዮስ እና ኒቆሮስ
፭. "፪.፭ ሚሊየን" ሰማዕታት [ የቅዱስ ቴዎድሮስ ማሕበር ]
[ † ወርኀዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላእክት
፪. ቅዱስ ላሊበላ ጻድቅ (ንጉሠ ኢትዮዽያ)
፫. ቅዱስ ማቴዎስ ሐዋርያ
፬. ቅዱስ ድሜጥሮስ
፭. ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ
፮. ቅዱስ ቴዎድሮስ ምሥራቃዊ [ ሰማዕት ]
፯. ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ
፰. አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ
" አሳዳሪውም የወይን ጠጅ የሆነውን ውሃ በቀመሰ ጊዜ አደነቀ:: ከወዴት እንደ መጣ አላወቀም:: ውሃውን የቀዱት አገልጋዮች ግን ያውቁ ነበር:: አሳዳሪውም ሙሽራውን ጠርቶ :- 'ሰው ሁሉ አስቀድሞ መልካሙን የወይን ጠጅ ያቀርባል:: ከሰከሩም በኋላ መናኛውን:: አንተስ መልካሙን የወይን ጠጅ እስከ አሁን አቆይተሃል' አለው:: " [ዮሐ.፪፥፱]
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖 🕊 💖
†
[ 🕊 አጽዋማትና በዓላት 🕊 ]
የ፳፻፲፮ [ 2016 ] ዓመተ ምህረት ቀሪ አጽዋማትና በዓላት ፦
🕊
† [ ጾመ ነነዌ ] = ሰኞ የካቲት ፲፰ [ 18 ] ቀን ይገባል ።
† [ ዓቢይ ፆም ] = መጋቢት ፪ [ 2 ] ይገባል።
† [ ደብረ ዘይት ] = መጋቢት ፳፱ [ 29 ] ይሆናል ።
† [ ሆሣዕና ] = ሚያዚያ ፳ [ 20 ] ይውላል ።
† [ ስቅለት ] = ሚያዝያ ፳፭ [ 25 ] ይሆናል ።
† [ ትንሣኤ ] = ሚያዚያ ፳፯ [ 27 ] ይውላል።
🕊
† [ ርክበ ካህናት ] = ግንቦት ፳፩ [ 21 ] ይሆናል። ።
† [ ዕርገት ] = ሰኔ ፮ [ 6 ] ይሆናል።
† [ ጰራቅሊጦስ ] = ሰኔ ፲፮ [ 16 ] በዓለ ጰራቅሊጦስ ይውላል ።
† [ ፆመ ሐዋርያት ] = ሰኔ ፲፯ [ 17 ] ይገባል ።
† [ የጾመ ድህነት ] = ሰኔ ፲፱ [ 19 ] ይገባል።
† † †
💖 🕊 💖
†
[ አ ት ደ ነ ቁ ! ]
እንኳን ሐሳዊ ሲኖዶስ ሐሳዊ ክርስቶስም አለ። አትደነቁ !
[ ዲ/ን አባይነህ ካሴ ]
† † †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬
🕊
[ † እንኳን ለሰማዕታት ቅዱሳን ቂርቆስ ወኢየሉጣ : ወነቢይ አብድዩ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ]
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †
🕊 † ቂርቆስ ወኢየሉጣ † 🕊
† ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ካሏት ዐበይት ሰማዕታት አንዱ ቅዱስ ቂርቆስ ነው:: በተለይ በዘመነ ሰማዕታት ተነስተው እንደ ከዋክብት ካበሩትም አንዱ ነው:: ቅዱስ ወንጌል እንዲህ ይላል:- "መልካም ዛፍ መልካም ፍሬን ያፈራል::" [ማቴ.፯፥፲፯]
መልካም ዛፍ ቅድስት ኢየሉጣ መልካም ፍሬ ብጹዕ ቂርቆስን አፍርታ ተገኝታለችና ክብር ይገባታል:: ቡርክተ ማሕጸንም እንላታለን:: የተባረከ ማሕጸኗ የተባረከ ልጅን ለ፱ ወር ተሸክሟልና::
በዚያ ክርስቲያን መሆን መከራ በነበረበት ዘመን ይህንን ደግ ሕጻን እርሷን መስሎ: እርሷንም አህሎ እንዲገኝ አስችላለችና:: አበው በትውፊት እንዳቆዩልን ከሆነ በ፫ኛው መቶ ክ/ዘመን እናታችን ቅድስት ኢየሉጣ ብጹዕ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስን ወልዳለች::
በ፫ኛው መቶ ክ/ዘመን በሮም ግዛት ክርስትና ቢስፋፋም በዚያው ልክ መምለክያነ ጣዖቱ የገነኑ ነበሩ:: በተለይ ከነገሥታቱ ጀምሮ ዋና ዋና የሥልጣን ቦታዎች በአሕዛብ እጅ በመሆናቸው ለዘመኑ ክርስቲያኖች ፈታኝ ነበር::
ማንኛውም ክርስቲያን መሠረታዊ ፍላጐቶቹ እንዲሟሉለት አሕዛብ ላቆሟቸው ጣዖቶች መንበርከክ ነበረበት:: መብቱን ከመገፈፉ ባሻገር "ተበድያለሁ" ብሎ ወደ ፍርድ ቤት ሔዶ እንኩዋ የመጮህ እድል አልነበረውም:: ምክንያቱም የሚሰማው አልነበረም::
በዚያ ላይ በየጊዜው ለክርስቲያኖች ፈታኝ የሆኑ አዋጆች ይወጣሉ:: የክርስትናን ጐዳና ይበልጥ የሚያጠቡ ሕጐችም ዕለት ዕለት ይፈበረኩ ነበር:: ስለዚህም በወቅቱ የነበረ አንድ ክርስቲያን ሃይማኖቱን ከወደደ ወይ እስከ ሞት መታገስ: ካልሆነ ደግሞ ሃገርን ጥሎ በዱር: በገደል መሰደድ ነበረበት::
እውነት ለመናገር ዜና ሰማዕታትን የማያውቅ ክርስቲያን ክርስቶሳዊ ነው ሊባል አይችልም:: ምክንያቱም ዛሬ እንዲህ እንደ ዋዛ የያዝናት ሃይማኖታችን እንዴት እንደ መጣችና ምን እንደ ተከፈለባት አብዛኛው ትውልድ አያውቅምና::
ሕጻኑ ቅዱስ ቂርቆስና እናቱ ብጽዕት ኢየሉጣም የዚህ ዘመን [የዘመነ ሰማዕታት] ፍሬ ናቸው:: በጊዜው በሮም ግዛት ሥር እስክንድሮስ የሚሉት ክፉ ንጉሥ ነግሦ ነበርና ብዙ ክርስቲያኖች ተሰደዱ:: ጣዖትን ላለማምለክም ተሰው::
በዚህ ጊዜ አንጌቤናይት [ኢጣልያዊት] ብጽዕት ኢየሉጣም በመበለትነት [ባሏ በሕይወት ባለ መኖሩ] ትኖር ነበር:: ልጇ ቅዱስ ቂርቆስ ምንም ገና ፫ ዓመቱ ቢሆንም ነገረ ሃይማኖትን ታስተምረው: ፍቅረ ክርስቶስን ትስልበት ነበር::
እስክንድሮስ የክህደት አዋጅን ሲያውጅም ቅድስቲቱ ለሕጻን ልጇ ራርታ ሽሽትን መረጠች:: ሃብት ንብረቷን: ወገንና ርስቷንም ትታ: ሕጻን ልጇን ተሸክማ ተሰደደች:: መከራው ግን በሔደችበት አለቀቃትም::
እስክንድሮስ ተከትሎ ባለችበት ቦታም አገኛት:: ወታደሮች ልጇን ሳያገኙ እርሷን ብቻ ይዘው ወደ መኮንኑ አቀረቧት:: መኮንኑም "ስምሽን ንገሪኝ" ቢላት "ስሜ ክርስቲያን ነው" አለችው:: ተቆጥቶ "ትክክለኛውን ስምሽን ተናገሪ" ቢላት "እውነተኛው ስሜ ክርስቲያን ነው:: ሞክሼ [ሞክሲ] ስም ከፈለግህ ኢየሉጣ እባላለሁ" አለችው::
"ለጣዖት ልትሰግጂ ይገባል" ሲላትም "እውነትን ይነግረን ዘንድ የ፫ ዓመት ሕጻን ፈልገህ አምጣና ተረዳ" ስላለችው ወታደሮቹን እንዲፈልጉ ላካቸው:: የሃገሩ ሰዎች ልጆቻቸውን ስለደበቁ የተገኘ ቅዱስ ቂርቆስ ነበር::
ቅዱሱ ሕጻን በወታደሮች ተይዞ ሲቀርብ መልኩ ያበራ ነበርና መኮንኑ "በሐከ ፍሡሕ ሕጻን - ደስ የተሰኘህ ሕጻን እንዴት ነህ" ቢለው "ትክክል ነህ! እኔ በጌታየ ክርስቶስ ዘንድ ደስታ ይጠብቀኛል:: አንተ ግን በክህደትህ ወደ ገሃነም ትወርዳለህ" አለው::
በሕጻኑ ድፍረት የደነገጠው መኮንኑ በብስጭት "እሺ! ስምህን ንገረኝ" አለው:: ያን ጊዜ "ከንጹሕ ምንጭ የተቀዳ: ስሜ ክርስቲያን ነው:: እናቴ የሰየመችኝን ከፈለክ ግን ቂርቆስ ነው" ሲል መለሰለት::
ከዚያም እየደጋገመ "እኔ ክርስቲያን ነኝ" ብሎ በመጮሁ መኮንኑ ስቃይን በቅዱሱ ሕጻን እና በቡርክት እናቱ ላይ አዘዘ:: ከዚህ በሁዋላ በእነርሱ ላይ የተፈጸመውን ግፍና የወረደባቸውን የመከራ ዶፍ እናገር [እጽፍ] ዘንድ ግን የሚቻለኝ አይመስለኝም::
በግርፋት የጀመረ ስቃይ ሊሰሙት ወደ ሚጨንቅ መከራ ቀጠለ::
- ፯ ብረት አግለው በዐይናቸው: በጆሯቸው: በአፋቸውና በልባቸው ከተቱ::
- በ፬ ችንካሮች ላይ አስቀመጧቸው::
- በእሳት አቃጠሏቸው::
- ጸጉራቸውን ከቆዳቸው ጋር ገፈፉ::
- ከዚህ በላይ ብዙ ስቃይንም አመጡባቸው::
እናትና ልጅ ግን ለክርስቶስ ታምነዋልና ጸኑ:: ቅድስት ኢየሉጣ ብትደነግጥ ልጇ አጸናት:: ከብዙ ስቃይና መከራ በሁዋላም በዚህች ዕለት በሰማዕትነት ሲያርፉ ጌታ እንደ ቃሉ የሕጻኑን ሥጋ በሠረገላ ኤልያስ አኑሮታል:: ለእኛ የሚጠቅም ብዙ ቃል ኪዳንንም ሰጥቶታል::
🕊 † ቅዱስ አብድዩ ነቢይ † 🕊
† "አብድዩ" ማለት "የእግዚአብሔር አገልጋይ" ማለት ነው:: ቁጥሩ ከ፲፪ቱ ደቂቀ ነቢያት ሲሆን የቅዱስ ኤልያስ ታላቁም ደቀ መዝሙር ነው:: ቅዱሳን ነቢያት ዮናስና ኤልሳዕም ባልንጀሮቹ ነበሩ::
ቅዱስ አብድዩ ቅድመ ልደተ ክርስቶስ በ፰ መቶ ዓመት አካባቢ የከሃዲው ንጉሥ የጦር መሪ ሆኖ በሃምሳ አለቃነት አገልግሏል:: ግፈኛዋ ኤልዛቤል ነቢያተ እሥራኤልን ስታስፈጅ ፶ውን በአንድ ዋሻ : ፶ውን ደግሞ በሌላ ዋሻ አድርጐ አትርፏቸዋል:: ፱ መቶው ግን ተጨፍጭፈዋል::
ያተረፋቸውንም ክፉ ዘመን እስኪያልፍ ድረስ መግቧቸዋል:: አክአብና ኤልዛቤል ከሞቱ በሁዋላም ቅዱስ ኤልያስን ተከትሎ ሹመቱን ትቷል:: እግዚአብሔር ገልጾለትም ትንቢት ሲናገር: ሕዝቡንም ሲገሥጽ ኑሯል::
በብሉይ ኪዳን ካሉ የትንቢት መጻሕፍትም በጣም አጭሩን የጻፈው ይሕ ነቢይ ነው:: ትንቢተ አብድዩ ባለ አንድ ምዕራፍ ብቻ ናትና:: ቅዱሱ በዚህች ቀን ዐርፎ ወገኖቹ ቀብረውታል::
† አምላከ ሰማዕታት በምሕረቱ ይማረን:: በይቅርታው ኃጢአታችንን ይተውልን:: ከበረከተ ሰማዕታትም ይክፈለን::
[ † ጥር ፲፭ [ 15 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ቅዱስ ቂርቆስና እናቱ ቅድስት ኢየሉጣ
፪. ቅዱስ አብድዩ ነቢይ
፫. ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ
፬. ቅድስት ሶፍያ
፭. ቅድስት አድምራ
፮. "11,004" ሰማዕታት [ ከቅዱስ ቂርቆስ ጋር በሰማዕትነት ያለፉ ]
[ † ወርሐዊ በዓላት ]
፩. ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ
፪. ቅዱስ ሚናስ ሰማዕት
፫. ቅድስት ክርስጢና
፬. ቅድስት እንባ መሪና
† " በተሰነጠቀ ዓለት ውስጥ የምትኖር: ማደሪያህንም ከፍ ከፍ ያደረግህ: በልብህም:- 'ወደ ምድር የሚያወርደኝ ማን ነው?' የምትል አንተ ሆይ! የልብህ ትዕቢት አታልሎሃል:: እንደ ንስር መጥቀህ ብትወጣ: ቤትህም በከዋክብት መካከል ቢሆን: 'ከዚያ አወርድሃለሁ' ይላል እግዚአብሔር::" † [ አብድዩ.፩፥፫ ]
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖 🕊 💖
†
[ 🕊 ፍኖተ ቅዱሳን 🕊 ]
[ የቅዱሳን አባቶቻችን የቅድስናና የተጋድሎ ሕይወት ]
🕊
[ የፍትወት ጾር ስለሚያስነሣው ፈተና ]
የፍትወት ጾር ያሸነፈው አንድ እኁ ወደ አንድ ታላቅ አረጋዊ ሄደና ፦ "በዝሙት ጾር ድል ሆኛለሁና እባክህ ጸልይልኝ" አለው::
ያ አባትም ስለ እርሱ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ። ሁለተኛ ጊዜ ወደዚህ አባት መጣና ያንኑ አለው። ያ አባትም አሁንም ስለዚህ ወንድም " ጌታ ሆይ ፣ የዚህን ወንድም ሕይወት ግለጥልኝ ፣ ይህ የዲያብሎስ ጦርስ ከምን የመጣ ይሆን ፣ አንተን ጠይቄህ ሳለ እርሱ ግን አሁንም ከፈተና አልተገላገለምና" በማለት ያን ጊዜ ስለዚህ ወንድም እግዚአብሔርን መማጸኑን ቀጠለ።
እግዚአብሔር ለዚህ አረጋዊ ይህን ገለጠለት ፦ እርሱ ተቀምጦ ፣ ሰይጣነ ዝሙት በጎኑ ሆኖ ፣ እርሱን ለመርዳት የተላከ መልአክ ደግሞ በጎኑ ሆኖ ያ ወንድም በእግዚአብሔር ፊት ወድቆ የሚለምን ሳይሆን ለሚያሳስበው ነገር ልቡን በሙሉ ለሰይጣኑ ግብር ከፍቶ ሰጥቶ በውስጥ በሚያሳስበው በሃሳቡ ደስ እየተሰኘ በመሆኑ በእርሱ እየተበሳጨ ተመለከተው። ስለዚህ ይህ አረጋዊ የዚያ ወንድም የችግሩ ምክንያት ከራሱ መሆኑን አወቀ።
እንዲህም አለው :- "ለሃሳብህ እየተስማማህና ኃይል እየሰጠኸው ያለኸው አንተው ራስህ ነህ፡፡" ከዚያም ክፉ ሃሳብን እንዴት እንደሚቋቋም አስተማረው:: በዚህ አባት ጸሎትና ትምህርት ከፈተና ድኖ ዕረፍትን አገኘ::
🕊
የአባቶቻችን ጸሎትና በረከት ይደርብን፡፡
† † †
💖 🕊 💖
†
[ የ ጊ ዜ ው መ ከ ራ ች ን ! ]
" ቀላል የሆነ የጊዜው መከራችን የክብርን የዘላለም ብዛት ከሁሉ መጠን ይልቅ ያደርግልናልና ፤ የሚታየው የጊዜው ነውና ፥ የማይታየው ግን የዘላለም ነው።" [ ፪ቆሮ. ፬ ፥ ፲፯ ]
† † †
" በዚህም እጅግ ደስ ይላችኋል ፥ ነገር ግን በእሳት ምንም ቢፈተን ከሚጠፋው ወርቅ ይልቅ አብልጦ የሚከብር የተፈተነ እምነታችሁ ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲገለጥ ፥ ለምስጋናና ለክብር ለውዳሴም ይገኝ ዘንድ አሁን ለጥቂት ጊዜ ቢያስፈልግ በልዩ ልዩ ፈተና አዝናችኋል።" [ ፩ጴጥ.፩፥፮ ]
† † †
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
* ማግሰኞ - ጥር 14 2016 ዓ.ም *
* ዘፍጥረት 6-11 *
በዛሬው ንባባችን ኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ 6 እስከ 11 ድረስ እናነባለን። ምዕራፉ ትላንት ካቆምንበት በመቀጠል ትኩረቱ በዋናነት የኖኅ ታሪክ ላይ ያደርጋል። በእነዚህ ስድስት ምዕራፎች ውስጥ ብዙ ነገሮችን እንመለከታለን። እግዚአብሔር የሰው ልጆች ኃጢአት በምድር ላይ እጅግ መብዛቱን ተመልክቶ የጥፋት ውኃን ከማምጣቱ በፊት ኖኅ ግዙፍ መርከብ እንዲሠራ ያዝዘዋል። የጥፋት ውሃ በመጣ ጊዜም በመርከቡ ውስጥ ካሉት ውጪ ሁሉንም ያጠፋል። ይህ ሁሉ አልፎም እግዚአብሔር ከኖኅ ጋር ቃልኪዳን ሲያደርግ እናነባለን፥ ይህም ኪዳን በቀስተደመና ተወክሏል። እግዚአብሔርም ዳግመኛ በጥፋት ውሃ ምድርን ላያጠፋም ቃል ይገባል። የሰው ልጅ ግን ከትእቢት መለየት አልቻለምና፥ ሰዎች ተሰብስበው የሰናዖርን ግንብ ይሠራሉ፤ በዚህም ምክንያት እግዚአብሔር የሰዎችን ቋንቋ እንዲደባለቅ ያደርጋል።
* የክለሳ ጥያቄዎች *
1) በዘፍጥረት ስድስት መሠረት፥ እግዚአብሔር የጥፋት ውሃን ያመጣው ለምንድር ነው?
2) ከጥፋት ውሃው ለማምለጥ መርከብ እንዲሠራ እግዚአብሔር ያዘዘው ማንን ነው?
3) ኖኅ ከእያንዳንዱ እንስሳ ስንት ስንት ወደ መርከቡ አስገባ?
4) ውሃው እየቀነሰ ስለመሆኑ ኖኅ የተቀበለው ምልክት ምንድር ነው?
5) ውሃው መቀነሱን ለማወቅ ኖኅ መጀመሪያ የላካት ወፍ ምንድር ናት?
6) ሁሉም ካበቃ በሁዋላ፥ ኖኅ ለእግዚአብሔር ያቀረበው መስዋእት ምንድር ነው?
7) እግዚአብሔር ከኖኅ ጋር የገባውን ቃልኪዳን በምን ወከለው?
8) በዘፍጥረት 10 ላይ የትውልድ ዝርዝር ለምን ተጠቀሰ?
9) በዘፍጥረት 10 ላይ የተብራራው የትውልድ ዝርዝር የነማን ነው?
10) ሰዎች የሰናዖርን ግንብ ለመገንባት የፈለጉት ለምንድር ነው?
11) ሰዎች የሰናዖርን ግንብ ሲገነቡ የእግዚአብሔር ምላሽ ምን ነበር? ሰዎቹስ ምን ደረሰባቸው?
🕊
[ † እንኳን ለጻድቃን ቅዱሳን አቡነ አረጋዊ እና አባ አርከሌድስ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ]
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †
🕊 † አቡነ አረጋዊ ዘደብረ ዳሞ † 🕊
† ጻድቁ ገድላቸውን የፈጸሙት በኢትዮዽያ ቢሆንም ሃገረ ሙላዳቸው የጥንቱ የሮም ግዛት የሆነችው ታናሽ እስያ ናት:: አቡነ አረጋዊ ከዘጠኙ [ ተስዓቱ ] ቅዱሳን አንዱ ናቸው:: ዘጠኙ ቅዱሳን ተወልደው ያደጉት ምንም በአንድ የሮም ግዛት ሥር ቢሆንም መነሻ ቦታቸው ግን የተለያየ ነው::
ሁሉንም አንድ ያደረጋቸው መንፈስ ቅዱስ በኪነ ጥበቡ ነው:: በምክንያት ደረጃ እንግለጸው ከተባለ ደግሞ የአንድነታቸው ምሥጢር :-
፩. የቀናች ሃይማኖታቸው ተዋሕዶ:
፪. ዓላማ [ የእግዚአብሔር መንግስት ] እና
፫. ገዳማዊ ሕይወት ነው::
አቡነ አረጋዊን ጨምሮ ሁሉም ቅዱሳን ዘራቸው ከቤተ መንግስት ነው:: እነርሱ ግን ምድራዊውን ክብር ንቀው ሰማያዊውን ክብር ገንዘብ ማድረግን መርጠዋል:: አስቀድመው ቅዱሳት መጻሕፍትን ያጠኑት አበው በተለያየ ጊዜ እየመነኑ ከሮም ግዛት ወደ ግብጽ በርሃዎች ወርደዋል::
በምናኔ ቅድሚያውን አባ ዸንጠሌዎንና አቡነ አረጋዊ ይይዛሉ:: ዘመኑ የተዋሕዶ አማኞች የሚሰደዱበት ፭ኛው መቶ ክ/ዘመን ነበርና እምነትን ላለመለወጥ ዘጠኙ ቅዱሳን ስደትን መረጡ::
በወቅቱ ደግሞ ለስደት መጠለያ የምትሆንና ከኢትዮዽያ የተሻለች ሃገር አልነበረችም:: ስለዚህም በ፬፻፸ [470] ዎቹ ዓ/ም አልዓሜዳ በኢትዮዽያ ነግሦ ሳለ ቅዱሳኑ በአረጋዊ መሪነት መጡ::
ንጉሡም ሲጀመር የእግዚአብሔር እንግዳ ስለሆኑ: ሲቀጥል ደግሞ ቅድስናቸውን ተመልክቶ መልካም አቀባበልን አደረገላቸው:: ማረፊያ ትሆናቸውም ዘንድ አክሱም ውስጥ አንዲት ቦታን ወስኖ ሰጣቸው:: ይህች ቦታ ቤተ ቀጢን ትባላለች:: አቡነ አረጋዊና ፰ቱ ቅዱሳን ወደ ሃገራችን እንደገቡ የመጀመሪያ ሥራቸው ቋንቋን መማር ነበር::
ልሳነ ግዕዝን በወጉ ተምረው እዛው አክሱም አካባቢ ሥራቸውን አንድ አሉ:: በወቅቱ በአቡነ ሰላማ: በአብርሃ ወአጽብሐና በአቡነ ሙሴ ቀዳማዊ የተቀጣጠለው ክርስትና በተወሰነ መንገድ ተቀዛቅዞ ነበርና እነ አቡነ አረጋዊ እንደገና አቀጣጠሉት::
ሕዝቡን በራሱ ልሳን ለክርስትና ይነቃቃ ዘንድ ሰበኩት:: የካደውን እየመለሱ: የቀዘቀዘውን እያሟሟቁ ለዓመታት ወንጌልን ሰበኩ:: ቀጣዩ ሥራቸው ደግሞ መጻሕፍትን መተርጐም ሆነ::
ከሃገራቸው ያመጧቸውን ቅዱሳት መጻሕፍት ተከፋፍለው ወደ ግዕዝ ልሳን ተረጐሟቸው:: በዚህም ለሃገራችን ትልቁን ውለታ ዋሉ:: ይህ ሁሉ ሲሆን እነ አቡነ አረጋዊ የሚመገቡትም ሆነ የሚጸልዩት በማሕበር ነበር:: በመካከላቸውም ፍጹም ፍቅር ነበር:: ጸጋ እግዚአብሔር አልተለያቸውም::
የነ አቡነ አረጋዊ ቀጣዩ ተግባራቸው ደግሞ ገዳማዊ ሕይወትን ማስፋፋት ሆነ:: ይህንን ለማድረግ ግን የግድ መለያየት አስፈለጋቸው:: እያንዳንዱም መንፈስ ቅዱስ ወደ መራው ቦታ ሔደ::
- ዸንጠሌዎን በጾማዕት :
- ገሪማ በመደራ :
- ሊቃኖስ በቆናጽል :
- አባ ይምዓታ በገርዓልታ :
- ጽሕማ በጸድያ :
- ሌሎችም በሌላ ቦታ ገዳማትን መሠረቱ::
- አባ አረጋዊ ደግሞ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ምርጫቸው ዳሞ [እዛው ትግራይ] ሆነ::
በሃገራችን ስም አጠራራቸው ከከበረ አባቶች አንዱ እኒህ ጻድቅ ናቸው:: ጻድቁ የተወለዱት በ፭ኛው መቶ ክ/ዘ አጋማሽ አካባቢ ሲሆን ወላጆቻቸው ንጉሥ ይስሐቅና ቅድስት እድና ይባላሉ:: የተለወለዱበት አካባቢም ሮም ነው::
ስማቸው ብዙ ዓይነት ነው:: ወላጆቻቸው " ዘሚካኤል" ሲሏቸው በበርሃ "ገብረ አምላክ" ተብለዋል:: በኢትዮዽያ ደግሞ "አረጋዊ" ይባላሉ:: አቡነ አረጋዊ ምንም የንጉሥ ልጅ ቢሆኑም በልጅነታቸው መጻሕፍትን ተምረው ነበርና ጠፍተው ገዳም ገቡ::
በዚያም በገዳመ ዳውናስ [ግብጽ] የታላቁ ቅዱስ ዻኩሚስ ደቀ መዝሙር ሆነው ከነ አባ ቴዎድሮስ ጋር ሥርዓተ መነኮሳትን ተምረዋል:: ከመነኮሱ ከዓመታት በሁዋላም ወደ ሃገራቸው ሮም ተመልሰው በማስተማር ፯ ያህል የቤተ መንግስት ሰዎችን ወደ ምናኔ ማርከዋል::
"የት ልሒድ" ብለው ሲያስቡም ቅዱስ መልአክ በክንፉ ጭኖ ወስዶ ኢትዮዽያን አሳያቸው:: ተመልሰውም ለ፰ ባልንጀሮቻቸው "ሃገርስ ባሳየሁዋችሁ! ሐዋርያ ሳያስተምራት በሕጉ በሥርዓቱ ጸንታ የምትኖር" ብለው ከ፰ቱ ጋር ወደ ኢትዮዽያ መጡ::
በዚህ ጊዜም እናታቸው ቅድስት እድናና ደቀ መዝሙራቸው አባ ማትያስ አብረው ነበሩ:: ወደ ሃገራችን የመጡ በ፬፻፸ [470]ዎቹ አካባቢ ሲሆን አልዓሜዳ በክብር ተቀብሏቸዋል:: በቤተ ቀጢን [አክሱም] ተቀምጠውም መጻሕፍትን እየተረጐሙ: ወንጌልን እየሰበኩ ቆይተዋል::
ለሥራ በተለያዩ ጊዜም አቡነ አረጋዊ በዓት ፍለጋ ብዙ ደክመዋል:: በመጨረሻ ግን ደብረ ዳሞን [ደብረ ሃሌ ሉያን] አይተው ወደዷት:: የሚወጡበት ቢያጡም ጅራቱ ፷ [60] ክንድ የሚያህል ዘንዶ ተሸክሞ ከላይ አድርሷቸዋል::
እንደ ወጡም "ሃሌ ሉያ ለአብ: ሃሌ ሉያ ለወልድ: ሃሌ ሉያ ለመንፈስ ቅዱስ" ብለው ቢያመሰግኑ ከሰማይ ሕብስት ወርዶላቸው ተመግበዋል:: በዚህም ቦታዋ "ደብረ ሃሌ ሉያ" ተብላለች:: ጻድቁ ቦታውን ከገደሙ በሁዋላ ከተለያየ ቦታ መጥተው 6ሺ ያህል ሰዎች በእጃቸው መንኩሰዋል::
ምናኔን በማስፋፋታቸውና ሥርዓቱን በማስተማራቸውም "አቡሆሙ ለመነኮሳት ዘኢትዮዽያ - የኢትዮዽያ መነኮሳት አባት" ይባላሉ:: አቡነ አረጋዊ በሕይወታቸው ከተጋድሎ ባሻገር በወንጌል አገልግሎትና መጻሕፍትን በማዘጋጀትም ደክመዋል::
ቅዱስ ያሬድና አፄ ገብረ መስቀልም ወዳጆቻቸው ነበሩ:: በተራራው ግርጌ ያለችውን ኪዳነ ምሕረትን ለሴቶች ሲገድሟት ቀዳሚዋ መነኮስ እናታቸው ንግስት እድና ሁናለች::
ጻድቁ ንጹሕ ሕይወታቸውን ፈጽመው በተወለዱ በ99 ዓመታቸው በገዳሙ በስተ ምሥራቅ አካባቢ ተሰውረው ብሔረ ሕያዋን ገብተዋል:: ጌታም ፲፭ [15] ትውልድን የሚያስምር የምሕረት ቃል ኪዳን ሰጥቷቸዋል:: ዛሬ ጻድቁ የተወለዱበት ቀን ነው::
🕊 † አባ አርከሌድስ † 🕊
† በዚህ ስም የሚጠሩ ቅዱሳን በግብጽም በሃገራችንም አሉ:: ዋናውና በብዙ መጻሕፍት ዜናቸው የተጻፈላቸው ግን ዛሬ የምናከብራቸው ናቸው:: አባ አርከሌድስ የነበሩት በዘመነ ጻድቃን ሲሆን ሃገረ ሙላዳቸው ሮም ናት::
ወላጆቻቸው ክርስቲያን: በዚያውም ላይ ባለ ጠጐች ነበሩ:: አባታቸው ደግሞ መስፍነ ሃገር ነበር:: ቅዱሱን ወልደው: በሕግ በሥርዓት አሳድገዋል:: ለአካለ መጠን አባ አርከሌድስ ሲደርሱ ግን አባታቸው ሞተ::
መዋዕለ ሐዘናቸው ከተፈጸመ በሁዋላም እናት አባ አርከሌድስን ጠርታ:- "ልጄ! ሒድና የአባትህን ሹመት እጅ አድርግ" አለችው:: ለመንገድ የሚያስፈልገውን ሁሉ አሰናድታ: አገልጋዮችንና ብዙ ወርቅ (ለሿሚው አካል የሚሰጥ) ጨምራም ልጇን ሸኘች::
ቅዱስ አርከሌድስም ከእናታቸው ተለይተው በአገልጋዮች ተከበው ወደ መርከብ ገቡ:: በባሕር መካከል ሳሉ ግን ታላቅ ማዕበል ተነስቶ መርከቡን በታተነው:: በመርከቡ የነበረው ሰው ሁሉ ሲያልቅ አባ አርከሌድስ ግን በስባሪ ላይ ተንጠልጥለው ተረፉ::
🕊
[ O R T H O D O X Y ! ]
💖
❝ ጥበብ ከቀይ ዕንቍ ትበልጣለችና የከበረ ነገር ሁሉ አይተካከላትም። ❞ [ ምሳ.፰፥፲፩ ]
❝ የምድር ነገሥታት አሕዛብም ሁሉ ፥ አለቆች የምድርም ፈራጆች ሁሉ ... የእግዚአብሔርን ስም ያመስግኑ ፤ ስሙ ብቻውን ከፍ ከፍ ብሎአልና ፥ ምስጋናውም በሰማይና በምድር ላይ ነው። ❞
[ መዝ.፻፵፰፥፲፩ ]
† † †
💖 🕊 💖
ሰላም! በየእለቱ የሚከተለውን ቅድመ ተከተል ይከተሉ፦
1 - ለማንበብ አመቺ ቦታ ተቀምጠው አሳብዎትን ይሰብስቡ።
2 - እግዚአብሔር የቃሉን ምስጢር እንዲገልጥልዎት አጭር ጸሎት ይጸልዩ። ከዚህ ሥር የሠፈረውን የቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ጸሎት መጸለይ ይችላሉ፦
“ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፤ የአንተን ቃላት እሰማ እና እረዳ ዘንድ፥ እንዲያውም ፈቃድህን ለመፈጸም እበቃ ዘንድ የልቤን ጆሮዎች እና ዓይኖች ክፈትልኝ።”
3 - በእለቱ ስለሚነበበው ክፍል የቀረበውን አጭር መግለጫ ያንብቡ።
4 - በእለቱ የሚነበበውን ክፍል በተመስጦ ሆነው ያንብቡ።
5 - ያነበቡትን በሚገባ እንደተገነዘቡት ለማረጋገጥ የቀረቡትን ጥያቄዎች ይሞክሩ።
🕊
[ † እንኩዋን ለጻድቃን ቅዱሳን አቡነ ዘርዓ ቡሩክ እና ፯ቱ ደቂቅ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ። ]
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †
🕊 † አቡነ ዘርዓ ቡሩክ † 🕊
ሃገራችን ኢትዮዽያ :-
- ብሉይ ከሐዲስ ያልጐደለባት
- በክርስቶስና በድንግል እናቱ ኪደተ እግር የተቀደሰች
- የቅዱሳን መጠጊያ እና
- ብዙ ቅዱሳንን ከእቅፏ ያፈራች ስለ ሆነች የተባረከች ሃገር ትባላለች::
- ሁሉም የሃገራችን ክፍሎች ቅዱሳንን አፍርተዋል:: በምሥራቅም: በምዕራብም: በሰሜንም: በደቡብም ያሉ አካባቢዎች ሁሉ የቅዱሳን ቤቶች ናቸው:: ቅዱሳንን በብዛት ካፈሩ አካባቢዎች አንዱ ደግሞ ምድረ ጐጃም ነው::
- በጐጃም አካባቢ ከተነሱ ቅዱሳን ደግሞ አንዱና ስመ ጥሩ ጻድቅ አቡነ ዘርዓ ቡሩክ ናቸው:: አቡነ ዘርዓ ቡሩክ በብዙ ጐዳና የተለዩ አባት ናቸው:: ለመጥቀስ ያህል እንኩዋ :-
፩. በታሪክ ዓለምን ከበው የያዙ ፪ቱ ግሩማን አራዊት [ብሔሞትና ሌዋታንን] ጥርስ ቆጥረው: ብዙ ምሥጢራትንም ተመልክተው ተመልሰዋል:: [በነገራችሁ ላይ ይህ ጉዳይ ዛሬም ድረስ ሳይንሱ በብዙ ድካም ያልደረሰበት ነው]
፪. ጻድቁ በልደታቸው ጊዜ ዓይነ ስውራንን አብርተዋል:: ለራሳቸው ግን ይህን የግፍ ዓለም ላለማየት ጸልየው ዓይናቸው እንዲጠፋ አድርገዋል::
፫. መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚል ቅዱስ ኢያሱ በገባኦን ፀሐይን አቁሟል:: ዘርዓ ቡሩክ ግን በጥበበ እግዚአብሔር ፀሐይን ለ፭ ዓመት አቁመዋል::
፬. ጻድቁ ከንጽሕናቸው ብዛት ፲፪ ክንፍ [መንፈሳዊ ክንፍ] ተሰጥቷቸው ነበር:: ከዚህ በተረፈም በጾም: በጸሎት: በትርምትና በስብከተ ወንጌል ፍጹም ጽሙድ ነበሩ::
- ጻድቁ የተወለዱት በ፲፮ኛው መቶ ክ/ዘመን እዚያው ጐጃም ውስጥ ሲሆን አባታቸው ደመ ክርስቶስ: እናታቸው ደግሞ ማርያም ሞገሳ ይባላሉ:: ወላጆች በልጅ እጦት ተማለው ይህን የተቀደሰ ፍሬ አገኙ:: "ጸጋ ኢየሱስ" ብለውታል:: ከኢየሱስ ክርስቶስ ተሰጥቷቸዋልና::
- ቀጥሎ የወለዱትንም "ተስፋ ኢየሱስ" ብለውታል:: ይህም የጻድቁ ታናሽ ወንድም ነው:: በሒደት ግን የጸጋ ኢየሱስ ስም በፈቃደ እግዚአብሔር ወደ ዘርዓ ቡሩክነት ተቀይሯል:: ጻድቁን ስመ ጥር ካደረጉዋቸው ሥራዎቻቸው መካከል በአፄ ሱስንዮስ ዘመን የሠሩት ቅድሚያውን ይወስዳል::
- ነገሩ እንዲህ ነው:: በ፩ ሺህ ፭ መቶ ፺፰ [1598] ዓ/ም በኢትዮዽያ ላይ የነገሡት አፄ ሱስንዮስ ዼጥሮስ ፓኤዝ [ፔድሮ ፓኤዝ] ከሚባል ፈረንጅ መናፍቅ ጋር በፈጠሩት ወዳጅነት ሃይማኖታቸውን ለወጡ:: ካቶሊክ [ሮማዊ]ም ሆኑ::
- በሁዋላም አልፎንሱ ሜንዴዝ የሚሉት እሾህ መጥቶ ሁሉም የኢትዮዽያ ሕዝብ መናፍቅ እንዲሆን ከንጉሡ ጋር መከረ:: ለጊዜው በቤተ መንግስቱ አካባቢ የነበሩ መሣፍንት ተቀላቀሉ:: እየቆየ ግን ዜናው በመላ ሃገሪቱ ተሰማ::
- በተለይ በ፩ሺህ ፮ መቶ ፲፩ [1611] በተዋሕዶ አማኞችና በመናፍቁ ንጉሥ መካከል ነገሩ ተካሮ ዻዻሱ አቡነ ስምዖን ጠዳ ላይ መገደላቸው ተሰማ:: በዚህ ጊዜ ገበሬው ከእርሻው: ሴቷ ከማዕድ ቤት: ካህኑ ከመቅደሱ: ነጋዴው ከገበያው እየወጡ ስለ ቀናችው ሃይማኖት ደማቸውን አፈሰሱ::
- በበዓት የተወሰኑ በሺህ የሚቆጠሩ ቅዱሳንም ወጥተው ተሰየፉ:: በዚህ ጊዜም የግሺው አቡነ ዘርዓ ቡሩክ ዳዊታቸውን አንግበው ለሰማዕትነት ሔዱ:: ዓባይ ወንዝ ላይ ሲደርሱ ዳዊታቸውን ወደ ወንዙ ውስጥ ጣሉት::
- ተሻግረውም ከንጉሡ አደባባይ ደንቀዝ ደረሱ:: በጊዜውም ልክ እንደነ ፍቅርተ ክርስቶስና ወለተ ዼጥሮስ እርሳቸውም መከራ ደረሰባቸው:: ንጉሡም ሳይገደሉ እንዲታሠሩ አደረገ:: በጨለማ እስር ቤትም ፭ ዓመታትን ሲያሳልፉ ትኩስ ምግብን ያመጡላቸው ነበር::
- እርሳቸው ግን ምግባቸው ሰማያዊ ነበርና አልነኩትም:: ከ፭ ዓመት በሁዋላም ያ ሁሉ ምግብ በተአምራት በትኩስነቱ እየጨሰ ተገኝቷል:: ዘርዓ ቡሩክም ከእሥር ተፈትተዋል::
- እግዚአብሔርም በከሐዲው ንጉሥ ላይ ፈርዶ ፋሲል ነግሷል: ሃይማኖት ተመልሷል:: ጻድቁም በዓባይ ወንዝ ላይ የጣሉት ዳዊታቸውን ሳይርስ አግኝተውታል::
- ጐጃም ሲደርሱም ሰይጣን እርሳቸውን መስሎ ሲያስት ስላገኙት ወደ ጥልቁ አስጥመውታል:: በተረፈ ዘመናቸው አቡነ ዘርዓ ቡሩክ ብዙ ተጋድለው ጥር ፲፫ ቀን ዐርፈዋል:: ታኅሳስ ፲፫ ቀን ልደታቸው ነው::
" ድንቅ ሠሪ አባት ናቸውና ዛሬም በግሺ ብዙ ተአምራት ይደረጋሉ "
🕊 † ቅዱሳን ፯ [ 7 ]ቱ ደቂቅ † 🕊
እነዚህ ፯ ቅዱሳን ከዘመነ ሰማዕታት እስከ ዘመነ ጻድቃን የተዘረጋ ታሪክ አላቸው:: ፯ቱም ባልንጀሮች ሲሆኑ በ፪ኛው መቶ ክ/ዘመን በኤፌሶን ተወልደው አድገዋል:: ክርስትናን ተምረውም በወጣትነታቸው የንጉሥ ጭፍሮች ሁነዋል:: የተቀጠሩትም የቤተ መንግስቱን ግምጃ ቤት ለመጠበቅ ነው::
- በሥራቸውም ሆነ በጠባያቸው ደጐች ነበሩና ንጉሡ ዳኬዎስም: ሕዝቡም ይወዷቸው ነበር:: እነርሱ ግን በጉብዝና ወራት ፈጣሪን ማሰብን መርጠው በፍቅር: በጸሎትና በምጽዋት ይተጉ ነበር:: ከጥቂት ዓመታት በሁዋላ ግን ጭንቅ መከራ መጣ::
- ንጉሡ ዳኬዎስ ክርስትናውን ትቶ ጣዖት አምላኪ ሆነ:: አዋጅም አስነገረ:: አዋጁም "ክርስቶስን ያልካደ: ለጣዖትም ያልሰገደ: ሃብት ንብረቱ ለዘረፋ: እጅ እግሩ ለእስር: ደረቱ ለጦር: አንገቱ ለሰይፍ: ቤቱም ለእሳት ይሰጣል" የሚል ነበር:: በዚህ ምክንያት ብዙ ክርስቲያኖች ተሰደዱ::
- የበርካቶቹም ደማቸው ፈሰሰ:: ኤፌሶን የግፍና የአመጻ ከተማ ሆነች:: የመከራ ጽዋው ጊዜውን ጠብቆ ወደ ፯ቱ ወጣቶች ዘንድ ደረሰ:: ንጉሡ እነሱንም አስጠርቶ "ለጣዖት ስገዱ" አላቸው:: እነርሱ ግን የአምላካቸውን ፍቅር በዋዛ የሚቀይሩ አልነበሩምና "እንቢ" አሉት::
- ንጉሡ ምንም ክፉና አውሬ ቢሆንም ይወዳቸዋል:: ሊገድላቸው አልፈለገምና አሳሰራቸው:: ከቀናት በሁዋላ አስጠርቶ ሊያታልላቸው ሞከረ:: ግን አልተሳካለትም:: በዚያ ወራት ጦርነት ይበዛ ነበርና ግዛት ለማስፋትም ቢሉ ለማስገበር ዳኬዎስ ወጣ::
- ከመውጣቱ በፊት ግን ፯ቱን አስጠርቶ "አሁን ከእስር ፈትቻቹሃለሁ:: ከጦርነት እስክመለስ ከልባችሁ ጋር ምከሩ:: ካልሆነ ሞት ይጠብቃቹሃል" ብሏቸው ነበር የወጣው:: ቅዱሳኑ ንጉሡ እንደ ወጣ ተቀምጠው መከሩ:: ውሳኔንም አስተላለፉ::
- ዓለምን ንቀው: ሃብት ንብረታቸውን መጽውተው: ትንሽ ሳንቲም ብቻም ይዘው በድብቅ ወጡ:: አንድ ወታደር [በጐች አሉት] ይከተላቸው ነበርና የት እንደ ገቡ ተመለከተ:: ቅዱሳኑ ዘወትር በመዓልትና በሌሊት በበዓታቸው ውስጥ ይተጉ ነበር:: ከእነሱም አንዱ በተራ እየወጣ ቂጣ ይገዛ ነበር::
- አንድ ቀን ግን ከእነሱ አንዱ ራት ሊገዛ ሲወጣ ንጉሡ መመለሱን ሰማ:: ወደ በዓቱ ተመልሶ ለወንድሞቹ ነገራቸው:: ከዚያች ቀን በሁዋላ ፯ቱም አልወጡም:: በዓታቸውን ዘግተው ሲጸልዩ ደክሟቸው ተኙ:: ከዚያች ቀን በሁዋላ ግን አልነቁም::
- ያ የበጐች ባለቤት [ወታደር] ለብዙ ቀናት አለመውጣታቸውን ሲመለከት "ሙተዋል" ብሎ አዘነ:: በድብቅ ክርስቶስን ያመልከው ነበርና:: እርሱ የቅዱሳኑን ተጋድሎ በድንጋይ ሰሌዳ ላይ ጽፎ ወደ በዓታቸው ውስጥ ጣለው::
- ትልቅ ድንጋይም አምጥቶ ገጠመው:: እነዚህ ቅዱሳን ተኝተዋልና አልነቁም:: ቀናት: ወራት: ዓመታት ተዋልደው ለ፫፻፸፪ ዓመት ተኙ:: አንድ ቀን አንድ እረኛ ለሥራ ፈልጐት ድንጋዩን ፈነቀለው:: በዚህ ጊዜ ቅዱሳኑ ነቁ::
🕊
[ O R T H O D O X Y ! ]
💖
[ አሜሪካ ዋሽንክተን ሲያትል ] [ Washington, D.C., Seattle ]
† † †
💖 🕊 💖
🕊
[ አ ን ዲ ት ጥ ም ቀ ት ! ]
💖
" አንድ ጌታ ፥ አንድ ሃይማኖት ፥ አንዲት ጥምቀት " [ኤፌ.፬፥፭]
" ክርስቶስ ወደ ጥምቀቱ መጣ በመጠመቂያው ውሃ ውስጥ አዳም በኃጢአት ምክንያት ተገፍፎት የነበረውን የጸጋ ልብስ አኖረ ... ስለዚህም አንድ ሰው ሲጠመቅ ያን በዛፎች መካከል ከእርሱ ተገፎ የነበረውን የጸጋ ልብስ ዳግም ይለብሰዋል፡፡"
[ ቅዱስ ያዕቆብ ዘስሩግ ]
† † †
💖 🕊 💖
🕊
[ "ሙሽራዋ ንጹሕ የሆነ ንጽሕይት የሰርግ ቤት ናት" ]
" የሐዲስ ኪዳኑ ታላቅ ሰርግ የተፈጸመባት ሰርግ ቤት በቃና ዘገሊላ የታደመችው እመቤታችን ናት፡፡ ይህቺን የሰርግ ቤት ሶርያዊው ቅዱስ ኤፍሬም ፦ "ሙሽራዋ ንጹሕ የሆነ ንጽሕይት የሰርግ ቤት ናት" በማለት ሲያመሰግናት አባ ሕርያቆስ ደግሞ በቅዳሴው ፦ "የሚልክያስ ንጹሕ አዳራሽ" በማለት በ ታላቅ አዳራሽ መስሎ ይገልጻታል፡፡ ቅዱስ ዳዊትም ስለ ጌታችን ፦ "እርሱም እንደ ሙሽራ ከእልፍኙ ይወጣል" በማለት እልፍኝ ከተባለችው እናቱ እንደሚወለድ ትንቢት ተናግሮ ነበር፡፡ [ ውዳ.ማር ፤ ቅዳ.ማር. ፤ መዝ.፲፰፥፭ ]
" ሰርግ ቤት " በተሰኘችው እመቤታችን በሰርግ ቤት ውስጥ የሚከናወኑ አራት ነገሮች ተፈጽመዋል፡፡
" በሰርግ ቤት ውስጥ ሙሽራውና ሙሽሪቱ አንድ ሆነው እንደሚዋሐዱ በእመቤታችን ውስጥም መለኮትና ሥጋ አንድ ሆነዋል፡፡ በሰርግ ቤት የሙሽራውና የሙሽሪት ዘመዶች አንድ ቤተሰብ እንደሚሆኑ በእመቤታችን ማኅጸን በተፈጸመው የአምላክና ሰው ተዋሕዶ ምክንያት ሰውና መላእክት ፤ ነፍስና ስጋ ፤ ሕዝብና አሕዛብ አንድ ሆነዋል፡፡
በሰርግ ቤት መብልና መጠጥ እንደሚቀርብ በእርስዋ በተደረገው ተዋህዶ ምክንያት ሥጋወደሙ ለሁላችን ማዕድ ሆኖ ተሰጥቷል፡፡
በሰርግ ቤት ዘፈንና ጨዋታ እንዳለ ደግሞ ሁሉን የሚያስደስቱ ታላላቅ ተአምራት በአምላክ ሰው መሆን ምክንያት ታይተዋል፡፡ " [ ውዳ.ማር.ትር.ገጽ ፶፪ ]
[ ቃና ዘገሊላ ]
† † †
💖 🕊 💖
🕊
[ ጠባቂያቸውን እየጠበቁ ያሉት የገጠሩ ካህን ]
† † †
ጥር ፲፩ [ 11 ] ፳፻፲፭ [ 2015 ዓ.ም ] ታቦታቱ ሁሉ ወደ መንበረ ክብራቸው ተመልሰው ታቦተ ሚካኤል ግን ነገ ሊመለስ ከባሕረ ጥምቀት በድንኳን ቀርቷል። ካህኑ ከጥር ፲ [ 10 ] ጀምሮ አላረፉም። ዋዜማ ቆመዋል ፥ ታቦት አክብረው ረዥም መንገድ በመጓዝ ከባሕረ ጥምቀት አድርሰዋል ፥ ሌሊቱን ማኅሌት ቆመዋል ፥ ቀድሰው አቁርበዋል ፥ ባሕረ ጥምቀቱን ባርከው ጠበል ሲረጩ አርፍደዋል።
የሚቀጥለውን ሌሊት ገና ማኅሌት ይቆማሉ ፥ በዕለቱም ቀድሰው ያቆርባሉ። በመጨረሻም የቃና ዘገሊላ ዕለት ታቦተ ሚካኤልን አክብረው ወደ መንበረ ክብሩ ይመልሱታል። እስከዚያው ጠባቂያቸውን እየጠበቁት ነው። ዋጋ ከፋይ እግዚአብሔር ቢሆንም ከሰው ወገን የሚያዝንላቸው ፥ የሚያመሰግናቸው ይኖር ይሆን ? እኔ ነኝ የምትል የሚካኤል ወዳጅ ማን ትሆን ?
[ ቀሲስ ደጀኔ ሽፈራሁ ]
† † †
💖 🕊 💖
🕊
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ †
🕊 † እንኳን አደረሰን † 🕊
ጥር ፲፪ [ 12 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
🕊 † ቃና ዘገሊላ † 🕊
'ቃና' የሚለው ቃል በሃገራችን ልሳን [ በአማርኛ ] የምግብን: የመጠጥን ጥፍጥና ወይም በጐ መዓዛን የሚያመለክት ነው:: ምንአልባትም ከዚህ በዓል ምሥጢር የተወሰደ ሳይሆን አይቀርም::
- በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ግን ቃና ከገሊላ አውራጃዎች አንዷ ናት:: ለስም አጠራሩ ስግደት ይሁንና የክብር ባለቤት መድኃኒታችን ክርስቶስ በዚህች ሥፍራ ተገኝቶ በድንግል እናቱ ምልጃ ታላቅ ተአምርን በዚህች ዕለት ሠርቷል::
- ተአምር የሚለውን ቃል በቁሙ 'ምልክት' ብሎ መተርጐም ይቻላል:: መሠረታዊ መልዕክቱ ግን ነጮቹ በልሳናቸው Miracle የሚሉት ዓይነት ነው:: ከተፈጥሮ ሕግ ውጪ [ በላይ ] : ከፍጡራንም ችሎታ የላቀ ነገር ሲሠራ [ ሲፈጸም ] ተአምር ይባላል:: ተአምር የእግዚአብሔር የባሕርይ ገንዘቡ ነው:: እርሱ ዓለምን ከመፍጠሩ ጀምሮ እያንዳንዷ ተግባሩ ለእኛ ተአምራት ናቸው::
- ስለዚህም ነው 'ኤልሻዳይ [ ከሐሌ ኩሉ ] ሁሉን ቻይ' እያልን የምንጠራው:: እግዚአብሔር ፍጡራኑን ይወዳልና እርሱ ለወደዳቸውና ደስ ላሰኙት ተአምራት ማድረግን ሰጥቷል:: በብሉይ ኪዳን እነ ሙሴ ባሕር ሲከፍሉ: መና ሲያዘንሙ: ውሃ ሲያፈልቁ [ ኦሪትን ተመልከት ] እነ ኤልያስ ሰማይን ሲለጉሙ: እሳትን ሲያዘንሙ: ሙታንን ሲያስነሱ [ ፩ኛ ነገሥትን ተመልከት ] እንደ ነበር
ይታወቃል::
- እንዲያውም በሙሉ መጽሐፍ ቅዱስ የተአምር መጽሐፍ ነው ብሎ ለመናገርም ያስደፍራል:: በሐዲስ ኪዳንም መድኃኒታችን ብዙ ተአምራትን ሠርቶ ለሐዋርያቱ የተአምራት ጸጋውን ሰጥቷቸዋል:: [ ማቴ.፲፥፰ , ፲፯፥፳ , ማር.፲፮፥፲፯ , ሉቃ.፲፥፲፯ ]
- እነርሱም በተሰጣቸው ሥልጣን ብዙ ተአምራትን ሠርተዋል:: [ሐዋ.፫፥፮ , ፭፥፩ , ፭፥፲፪ , ፰፥፮ , ፱፥፴፫-፵፫ , ፲፬፥፰ , ፲፱፥፲፩ ]
- ቅዱስ ዮሐንስ ሐዋርያ በወንጌሉ ምዕራፍ ፪ ላይ እንዳስቀመጠው የቃና ዘገሊላው ተአምር የመጀመሪያው ነው:: "ወዝንቱ ቀዳሜ ተአምር ዘገብረ . . ." እንዲል:: [ዮሐ.፪፥፲፩] ያ ማለት ግን ጌታ ከዚያ በፊት ተአምራትን አልሠራም ማለት አይደለም::
ይልቁኑ ራሱን ከገለጠና ከተጠመቀ በኋላ የሠራው የመጀመሪያው ተአምር ነው ሲል ነው እንጂ:: ምክንያቱም መድኃኒታችን እንደ ተጠመቀ ዕለቱኑ ገዳመ ቆረንቶስ ገብቷልና:: [ማቴ.፬፥፩] አንድም በቃና ሌሎች ተአምራትን የሚሠራ ነውና ይህ ተአምር በቃና የመጀመሪያው ሆነ::
- ትክክለኛው የቃና ዘገሊላ ቀን የካቲት ፳፫ ነው:: ጥር ፲፩ ተጠምቆ : የካቲት ፳፩ ቀን ከጾም ተመልሷል:: ከዚያም የካቲት ፳፫ ቀን ደቀ መዛሙርቱን ሰብስቦ ሒዷል:: ነገር ግን አበው መንፈስ ቅዱስ እንደ መራቸው የውሃ በዓል ከውሃ በዓል ጋር ይስማማል ብለው ጥር ፲፪ ቀን አድርገውታል::
- በቃና ዘገሊላ ሙሽራው ዶኪማስ ሲሆን ባለ ሠርጉ ደግሞ አባቱ ዮአኪን ነው:: ይህም ለሐዋርያው ቅዱስ ናትናኤል አጐቱ ነው:: የልጁ ጋብቻ የተቀደሰ ይሆን ዘንድም ጌታ ክርስቶስን: ድንግል እናቱንና ባለሟሎቹ ሐዋርያትን ወደ ሠርጉ ጠራ::
- ምንም እንኳ መድኃኒታችንና እመቤታችን ከድግሱ የማይበሉ ቢሆኑም [በትሕርምት ኗሪዎች ነበሩና] ጠሪውን ደስ ለማሰኘት ሠርጉን [ብቻውን] ለመቀደስና የጋብቻን ክቡርነት ለማሳየት አብረው ታደሙ::
የሠርጉ ሥነ ሥርዓት ሲጀመር በድንኳኑ ውስጥ ጌታ ከመካከል ተቀመጠ:: ድንግል በቀኙ: ዮሐንስ በግራው ሲቀመጡ: ሌሎች ሐዋርያት ግራና ቀኝ ከበው ተቀመጡ:: ሲበላና ሲጠጣ ድንገት የተደገሰው ምግብና መጠጥ አለቀ:: ደጋሾቹ በጭንቅ ላይ ሳሉም አይጠና ሆዷ ድንግል እመ ብርሃን የሆነውን አወቀች:: እንዴት አወቀች ቢሉ :- በጸጋ: አንድም 'ከልጅሽ አማልጂን' ብለው ቢለምኗት ነው ይሏል:: እመቤታችን በዚያ ጊዜ ወደ ልጇ ቀርባ ቸር ልጇን "ወይንኬ አልቦሙ ወይኑኮ አልቆባቸዋል" አለችው::
- ለጊዜው ወይኑም: ምግቡም ስላለቀባቸው እንዲህ አለች:: በምሥጢሩ ግን ወይን ያለችው ፍቅርን: ቅዱስ ቃሉንና ክቡር ደሙን ነው:: ጌታም ይመልሳል :- "ምንት ብየ ምስሌኪ ኦ ብእሲቶ: ዓዲ ኢበጽሐ ጊዜየ-አንቺ ሆይ ! [ እናቴ ሆይ ! ] ያልሺኚን አላደርግ ዘንድ ካንቺ ጋር ምን ጠብ አለኝ ? ነገር ግን ጊዜው ገና አልደረሰም ብየ ነው እንጂ" አላት:: ምክንያቱም ጌታ :-
- የወይን ጋኖቹ እስኪያልቁ ይጠብቅ ነበር:: [ አበረከተ ይሉታልና ]
- አንድም ይሁዳ ወጥቶ ነበርና እርሱ እስኪመለስ ነው:: [ እኔ ስወጣ ጠብቆ ተአምር ሠራ ብሎ ለክፋቱ ምክንያት እንዳያቀርብ ] አንድም "ወይን [ ቅዱስ ደሜን ] የምሰጠው በቀራንዮ አንባ ነው" ሲል "ጊዜየ ገና ነው" ብሏታል:: አንዳንድ ልቡናቸው የጠፋ ወገኖቻችን ጌታ እመቤታችንን እንዳቃለላት [ ሎቱ ስብሐት ! ወላቲ ስብሐት ! ] አስመስለው ይናገራሉ::
- ይህንን ስእንኅን ጌታ ባለጌዎቹ እነሱም አያደርጉት:: "አባትህንና እናትህን አክብር" [ዘጸ.፳] ያለ ጌታ እንዴት ለእናቱ ክብርን ይነፍጋል ? ልቡና ይስጠን !
ወደ ጉዳያችን ስንመለስ መድኃኒታችን እንዲህ ሲል መለስላት:: ተግባብተዋልና እመ ብርሃን አሳላፊዎቹን "ኩሎ ዘይቤለክሙ ግበሩ -የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ" አለቻቸው:: [ ዮሐ.፪፤፥፭ ] ጌታም በ፮ቱ ጋኖች ውሃ አስሞልቶ በተአምራት ወይን አደረጋቸው::
- እንጀራውን ወጡን በየሥፍራው ሞላው:: ታላቅ ደስታም ሆነ:: የአሳላፊዎቹ አለቃም [ለአባታችን አብርሃም ምሳሌ ነው] ከወይኑ ጥፍጥና የተነሳ አደነቀ:: በዚህም የድንግል ማርያም አማላጅነት: የመድኃኒታችን ከሃሊነት ታወቀ: ተገለጠ::
🕊 † ቅዱስ ያዕቆብ ርዕሰ አበው † 🕊
- የአባቶች አለቃ የተሰኘ ቅዱስ ያዕቆብ ለ፪ቱ ታላላቅ አባቶቹ እርሱ ፫ተኛቸው ነው:: እነርሱን መስሎ: እነርሱንም አህሎ በጐዳናቸው ተጉዟል:: በፈቃደ እግዚአብሔር ብኩርናን ከኤሳው ተቀብሎ ወደ ሶርያ ሲሸሽ ቤቴል [ ፍኖተ ሎዛ ] ላይ ድንጋይ ተንተርሶ በተኛበት ግሩም ራዕይን አይቷል::
- ይህችውም የወርቅ መሰላል የድንግል ማርያም ምሳሌ ናት::
"አንቲ ውዕቱ ሰዋስው ዘርእየ ያዕቆብ" እንዳለ ቅዱስ ኤፍሬም [ ውዳሴ ማርያም ዘሠሉስ ]
- ተነስቶም "ዛቲ ይእቲ ኈኅታ ለሰማይ: ዝየ ይትሐነጽ ቤተ እግዚአብሔር - ይህች የሰማይ ደጅ ናት: ቤተ እግዚአብሔርም ይታነጽባታል" ብሎ ትንቢት ተናግሯል::
- ይህ ቅዱስ አባት ለድንግል ማርያም ቅድመ አያት ከመሆኑ ባሻገር ነቢያትን: ካህናትን: ነገሥታትንና መሣፍንትን ወልዷል:: ከ፪ቱ ሚስቶቹ [ልያና ራሔል] : ከ፪ቱ ደንገጥሮች ፲፪ ልጆችን ወልዷል::
- ከአጐቱ ከላባ ዘንድ ለ፳፩ ዓመታት አገልግሎ: ሃብት ንብረቱን ጠቅልሎ ወደ ርስቱ ከነዓን ሲመለስ ለብቻው ራቅ ብሎ ይጸልይ ገባ:: በዚያም እግዚአብሔር ሲታገለው አደረ::
[ ይኸውም የፍቅርና የምሥጢር ነው ] ለጊዜው ጌታ ያዕቆብን "ልቀቀኝ" ቢለው "ካልባረከኝ አለቅህም" አለው:: ጌታም ስሙን "እሥራኤል" ብሎ ባርኮታል::
- ቅዱስ ያዕቆብ በስተእርጅና ብዙ መከራ አግኝቶታል:: ልጁን ዮሴፍን ወንድሞቹ ሽጠው "አውሬ በላው" ብለውታልና በለቅሶ ዐይኑ ጠፋ::
- በረሃብ ምክንያትም በ፻፴ ዓመቱ ከ፸፭ ያህል ቤተሰቦቹ ጋር ወደ ግብጽ ወረደ:: በዚያም ለ፯ ዓመታት ኑሮ በ፻፴፯ ዓመቱ ዐርፏል:: ልጆቹም ቀብረውታል::