mezmuredawit | Unsorted

Telegram-канал mezmuredawit - ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

28629

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ የመዝሙር ግጥሞችን እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን" መዝ 150÷6 " አሕዛብ ሁላችሁ፥ እጆቻችሁን አጨብጭቡ፥ በደስታ ቃልም ለእግዚአብሔር እልል በሉ።" (መዝሙረ ዳዊት 47:1) ለማንኛውም ሀሣብ, ጥቆማ, አስተያየት @Kidusyared_comment_bot ላይ ቢያስቀምጡልን ይደርሰናል

Subscribe to a channel

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

⛪️📚🙏
1, እመጓ
2, ዝጎራ
3, መርበብት
4, ዴርቶጋዳ
5, ዮራቶራድ
6, ዣንቶዣራ
7,መጽሐፈ ሄኖክ
8, ቤተክርስቲያንህን እወቅ እንዳትሆን መናፍቅ
9, ፍኖተ አእምሮ
9, አዳም እና ጥበቡ
10, ዝክረ መስቀል
11, ሰይፈ ሥላሴ
12, ፍትሐ ነገስት
13, መጽሐፈ መነኮሳት
14, ከአክራሪ እስልምና ወደ ክርስትና
16, ህግጋተ ወንጌል
17, ነገረ ማርያም በጥንታዊቷ ቤተከርስቲያን
18, ድርሳነ ሚካኤል ወ ገብርኤል
19, ውዳሴ ማርያም በግእዝ
20, ግድለ ተክለሃይማኖት
21, ገድለ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሰጫ
22, የወጣቶች ህይወት
23, መጽሐፈ ገድለ ሐዋርያት
24, ኦርቶዶክስ መልስ አላት
25, የዋልድባ ገዳም ታሪክ


📚📚የቱን ኦርቶዶክሳዊ መፅሀፍ ማንበብ ይፈልጋሉ የሚፈልጉትን መፅሀፍ በመንካት ያንብቡ መልካም ንባብ📖

    
✝                      ይቀላቀሉን                    ✝

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

🌹 ከጠንጠውድምም ሞት በኋላ ማንም እንዳልነገሠ ሲያረጋግጡ የማን ልጅ እንደሆነ እንዲነግራቸው በእግዚአብሔር ስም ለመኑትና "የጠንጠውድም የታናሽ ወንድምና የዣን ስዩም ታላቅ ወንድም የሆነው የግርማ ስዩም ልጅ ነኝ" አላቸው፡፡ እነርሱም "የተነገረው ትንቢት ደርሷልና ሳንዘገይ እናንግሠው" ብለው ሥርዓተ መንግሥቱን ፈጽመው በዙፋን ላይ አስቀመጡት፡፡ ለቅዱስ ይምርሃነ ክርስቶስ ቅዱስ መስቀልና ሰማያዊውን ኅብስት ከሰማይ ይወርድለት ነበር፡፡

🌹 ቅዱስ ይምርሃነ ክርስቶስ በትረ መንግሥቱንም ከያዘ በኋላ ሁሉም ሰው እንደወንጌሉ ቃል በአንድ ለአንድ ጋብቻ ብቻ ተወስኖ እንዲኖር በግዛቱ ሁሉ አወጀ፡፡ እግዚአብሔርም የሚመሰገንበት ቤት መሥራት አሰበና የተፈቀደለትን ቦታ እንኪያገኝ ድረስ ዛዚያ በምትባል ልዩ በሆነች ስፍራ ድንኳን ተክሎ እንደሙሴ እግዚአብሔርን ማገልገል ጀመረ፡፡ ዘጸ 33፡7። ሰኔ 21 ቀንም ቀድሶ ሕዝቡን ከማቁረቡ በፊት ኅብስቱንና ጽዋውን የእግዚአብሔር መልአክ ሕዝቡን ከሚባርክበት ሰማያዊ መስቀል ጋር ከሰማይ አምጥቶለታል፡፡ በዚህ ዓይነት ሁኔታ ሕዝቡን ከሰማይ በወረደለት መስቀል እየባረከና ሰማያዊውን ኅብስትና ጽዋ እያቆረበ ለ22 ዓመት በድንኳኗ ውስጥ ኖሯል፡፡ ዛሬም ድረስ ያንን ሰማያዊው መስቀል በቤተመቅደሱ የሚያገለግሉት ካህናት አባቶች ቤተመቅደሱን ለመሳለም የሚመጣውን ሕዝበ ክርስቲያን በበዓል ቀን
ይባርኩበታል፡፡

🌹 ለቅዱስ ይምርሃነ ክርስቶስ ጌታችን ተገልጦለት ቤተ መቅደሱን በባሕር ላይ እንዲሠራ ነግሮታል፡፡ ቅዱስ ይምርሃነ ክርስቶስ ሰማያዊ ኅብስትና ጽዋ እየወረደለት ለ22 ዓመት በድንኳኗ ውስጥ ካገለገለ በኋላ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በክብር ተገልጦለት እንዲህ አለው፡- "ወዳጄ ይምርሃነ ክርስቶስ ይህን ሥፍራ (ዛዚያን) ልቀቅ፣ ከእንግዲህ ወዲህ በዚህ ቦታ ሰማያዊ ኅብስትና ሰማያዊ ጽዋ አይወርድልህም፡፡ ወደማሳይህ ቦታ ተነሥተህ ሂድ፣ በዚያም እስከ ዕረፍትህ ቀን ድረስ ሰማያዊ ኅብስትና ሰማያዊ ጽዋ ይወርድልሀል፡፡ ይህን ዓለም ለማሳለፍ እስከምመጣበት እስከ ዕለተ ምፅዓት ድረስ የእኔ ጌትነት የአንተም የቅድስና ሕይወት የሚነገርበት፣ የሥጋህ የዕረፍት ቦታ የሚሆንበት፣ ለምትሠራው መቅደስ ክዳን የሚሆን ሣር የማይፈልግ ሰፊ ዋሻ አለ፣ በዚያ ቤተ መቅደሴን ሥራ፣ እኔም በምትሠራው ቤተ መቅደስ ከአንተ ጋር ለዘለዓለም ቃልኪዳኔን አቆማለሁ፡፡ በምታንጸው ቤተ መቅደስ ውስጥ "አቤቱ የይምርሃነ ክርስቶስ አምላክ ሆይ! ስለወዳጅህ ስለ ቅዱስ ይምርሃነ ክርስቶስ ብለህ ይቅር በለኝ" እያለ "አባታችን ሆይ!" የሚለውን ጸሎት የሚጸልይ ዕለቱን እንደተጠመቀ አደርገዋለሁ፡፡ ነገ ማለዳ ተነሥተህ ወግረ ስሂን ወደሚባለው የዕረፍትህ ቦታ ወደሚሆነው ዋሻ ሕዝብህን አስከትለህ ሂድ፤ በዚያም ቤተ መቅደሴን ሥራ" ብሎ ጌታችን ቃልኪዳን ከሰጠው በኋላ ሰላምታ ሰጥቶት በክብር ወደ ሰማይ ዐርገ፡፡ በዚች ቦታ እስከመጫረሻው በገድል ተጠምዶ ኖሮ ከእግዚአብሔር አምላኩ ብዙ ቃል ኪዳንን ተቀብሎ ጥቅምት 19 ቀን በክብር ዐረፈ። ከጻድቁ ንጉሥ ከቅዱስ ይምርሃነ ክርስቶስ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤት በረከቱ ያሳትፈን፣ በጸሎቱ ይማረን!።

                             ✝ ✝ ✝
🌹 #አቡነ_ሐራ_ድንግል፡- ጻድቁ ከአባታቸው ከሬማው ካህን ከቅዱስ ዮሐንስ ከእናታቸው ብፅዕት ወለተ ጊዮርጊስ የተወለዱት ጥቅምት 19 ቀን 1534 ዓ.ም ነው፡፡ የትውልድ ሀገራቸው ጥንት በጌምድር ደብረ ታቦር አውራጃ ደራ ወረዳ ይባል በነበረው አሁን በምዕራብ ጎጃም ዞን ባሕር ዳር ዙሪያ ወረዳ ላጉና ቀበሌ ነው፡፡ ቅዱሳን የሆኑ ወላጆቻቸውም አባታችንን ከልጅነታቸው ጀምሮ በሃይማኖት በምግባር ኮትኩተው አሳደጓቸው፡፡ አባታችንም የቤተ ክርስቲያንን መጻሕፍት በሙሉ ተምረው በታላቅ መንፈሳዊ ተጋድሎና አገልግሎት ከኖሩ በኋላ ዓለምን ፍጹም ንቀው መንነው ወደ ሸዋ ተጉዘው ግራርያ ከሚባል አገር ደረሱ፡፡

🌹 በዚያም ዘመዶቻቸው ፈልገው ስላገኙዋቸውና ወደ ሀገራቸው ስለመለሷቸው በሌላ ጊዜ ጥቅጥቅ ያለውን ጫካ አቋርጠው አሁን ገዳማቸው ካለበት ጫካ ውስጥ ገቡና ገዳመ ወንያትን መሠረቱ፡፡ በዚያም ፈተናውን ሁሉ ድምጸ አራዊቱን፣ ግርማ ሌሊቱን፣ ብርዱን፣ ሐሩሩን፣ ረሃብ፣ ጥማቱን ታግሰው በታላቅ ተጋድሎ ኖሩ፡፡ ሰይጣንም በፈተና ሊጥላቸው አንድ ጊዜ በተዋበች ቆንጆ ሴት እየተመሰለ አንድ ጊዜ ደግሞ በሞተ ሰው እየተመሰለ እስከ ሰባት ተከታታይ ቀናት ድረስ ቢፈትናቸውም ድል አድርገውታል፡፡ አባታችን ቀን ላይ ጸሎት እያደረጉ እያለ ነብር የሚያባርራት አንዲት ሚዳቋ መጥታ ከቤት ገብታ ከአቡነ ሐራ ድንግል እግር ስር አረፈች፡፡ ነብሩም ደርሶ ከደጅ እየተቆጣ ቆመ፡፡ ይህን ጊዜ አባታችን "እርሷን ገድለህ ትበላ ዘንድ እግዚአብሔር አልሰጠህምና ሂድ" ባሉት ጊዜ ቃላቸውን ሰምቶ ሄደ፡፡ ሚዳቋዋም እዛው አድራ ሲነጋ በሰላም አሰናብተዋታል።

🌹 አባታችን መንኵሰው በገዳማቸው ከገቡበት ፈጽመው ሳይወጡ ለ14 ዓመት በተአቅቦ ተቀምጠዋል፡፡ በአንድ ወቅት ጠላት ተነስቶ አካባቢውን በሙሉ በመውረር ሁሉን ሲማርኩ ገዳሟን አይተው ወደ እርሷም ሊገቡ ሲሉ በተአምራት ባሉበት ተይዘው ቆመው በመቅረታቸው ጉዳት ሳይደርሱባት ተመልሰዋል፡፡ ሱስንዮስ "ሁለት ባሕርይ ሁለት አካል" የሚለውን የሮማን የረከሰ ሃይማኖት በሀገራችን ላይ አውጆ ብዙዎች ሰማዕትንትን ሲቀበሉ አቡነ ሐራ ድንግል በገዳማቸው ለብዙዎች መጠጊያ ሆነው ሃይማኖታቸውን ሲያስተምሯቸውና ሲያፀኗቸው ነበር፡፡ በንጉሡም ፊት ቀርበው በድፍረት "አንድ አካልና አንድ ባሕርይ የሆነውን መለኮትና ትስብእትን ለምን ከሁለት ወገን ትከፍለዋለህ?" ብለው ሲገስፁት ፈርቶ አሽከሮቹን "ይህን መነኵሴ ከቤቴ አውጥታችሁ በፍጥነት ወደ ገዳሙ አድርሱልኝ" ብሏቸዋል፡፡

🌹 እመቤታችንን እጅግ አድርገው ይወዷት ነበርና ምስጋናዋን ሲያደርሱ ሦስት ክንድ ከምድር ከፍ ይሉ ነበር፡፡ ቅዱስ ገብርኤልም የሁልጊዜ ጠባቂያቸው ነበር፡፡ በ1574 ዓ.ም አሁን በስማቸው ወደሚጠራው ገዳመ ወንያት መንነው ገቡ፡፡ በዚያም ወንጌልን እያስተማሩ፣እጅግ ድንቅ ድንቅ የሆኑ ተአምራትን እያደረጉ፣ ሙት እያስነሱ፣ ድውያንን
እየፈወሱ እግዚአብሔርን ሲያገለገሉ ኖረዋል።

🌹 አባታችን ሐራ ድንግል "የማነ ብርሃን" የሚባል ታማኝ አገልጋይ አህያ ነበራቸው፡፡ አህያውም ጸሎታቸው ይጠብቀው ነበር እንጂ እረኛ አልነበረውም፡፡ አንገቱ ላይ ቃጭል አስረው ወደ ገበሬው አውድማ ይልኩትና አህያውም ቃጭሉን እያጮኸ ወደ አውድማው ሁሉ ሄዶ እየዞረ "ማርያም ባርኪ" በረከት ሰፍረው ይጭኑታል፡፡ አህያውም ከገበሬው ሁሉ የሰበሰበውን እህል ይዞ ወደ አቡነ ሐራ ድንግል ይገባል፡፡ በፈለጉትም ሰዓት ራሱ አውቆ ይመጣላቸው ነበር፡፡ አህያውም አርጅቶ ሲሞት እንደ ሰው አልቅሰውና በአዲስ ጨርቅ ጠቅልለው ቀብረውታል፡፡ አህያቸው የማነ ብርሃን ከተቀበረበት ቦታ ላይ ጸበል ፈልቆ አስደናቂ ተአምራትን አድርጓል፡፡ የቅዱሳኑ በረከታቸው እስከምን ድረስ እንደሆነ ልብ ይሏል፡፡ ታላላቆቹ ቅዱሳን እንደነ በትረ ማርያም፣ ጽጌ ድንግል፣ ወለተጴጥሮስ ያሉ ሌሎችም በርካታ ደጋግ ቅዱሳን ዝናቸውን እየሰሙ ከያሉበት እየሄዱ ይጎበኙዋቸውና በረከታቸውን ይቀበሉ ነበር፡፡

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

1⃣7⃣ደቂቃ ቦኃላ ይጠፋል


የ 200 ብር ካርድ የሚያስሸልም ጥያቄ!

በኢትዮጵያ በጣም አስቸጋሪ የነበረዉ  ረሀብ መች አመተምህረት ነበረ

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

❤️ክርስቶስ በተሰቀለ ጊዜ ግራ ጎኑን የወጋው ወታደር ማን ነው⁉️

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

🇺🇸 DV-2026 Lottery ተመዝግበዋል ?

📝 2026 የዲቪ ሎተሪ ምዝገባ በይፋ ተጀምሯል እና ማመልከቻዎን ለማስገባት ጥቂት ቀናት ብቻ ነው ያለዎት! ይህ እድል እንዳያመልጥዎ

ጥንቃቄ በተሞላው እና መስፈርቱን በሚያውቁ ባለሙያዎች ለማስሞላት

@Slamanshdngl በዚህ Account ያናግሩን

⏱ ጊዜው እየሄደ ነው! 

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

🌹 "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። 🌹

           🌹 #ጥቅምት ፲፱ (19) ቀን።

🌹 እንኳን #ለኢትዮጵያዊው_ጻድቅ_ኤርትራ_አገር የሚገኘውን በተፈጥሮአዊ አቀማመጡ እጅግ አስደናቂውን #ፃዕዳ_ዓምባ_ቅድስት_ሥላሴ_ገዳምን ለመሠረቱት ለታላቁ አባት #ለአቡነ_ሰይፈ_ሚካኤል ለዕረፍታቸው ዓመታዊ መታሰቢያ በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።

                               ✝ ✝ ✝
🌹 #አቡነ_ሰይፈ_ሚካኤል፦ እኚህ ጻድቅ በ1669 ዓ.ም የገደሙት ይህ እጅግ ድንቅ የሆነ ገዳም ፃዕዳ ዓምባ ቅድስት ሥላሴ ከኤርትራ በዓንሰባ ዞን ከከረን 25 ኪ.ሜ እርቆ በደቡባዊ ምዕራብ ከባሕር ጠለል በላይ 2500 ሜትር ከፍታ ላይ ይገኛል፡፡ ወደዚህ ድንቅ ገዳም የሚያደርሰው መንገድ ዳገትና ቁልቁለት የበዛበት አስቸጋሪ ከመሆኑ የተነሣ ብርቱ ትዕግሥትና መንፈሳዊ ጽናት ይጠይቃል፡፡ ገዳሙ ለመድረስ ከከረን ከተማ በደቡባዊ ምዕራብ በኩል ወንዞችንና ጋራ ሸንተረሮችን ማቋረጥ ግድ ነው፡፡ ከዚያም "ድንጃ ወርቅ" በተባለ ከገዳሙ እግር ሥር በሚገኘው ረጅሞ ተራራ ከተደረሰ በኋላ ከድንጃ ወርቅ የአንድ ሰዓት ተኩል ዝግዛግ የእግር ጉዞ ያስኬዳል፡፡ ከዚያም "ማዕዶዋይ" ከተተባለው ቦታ ይደረሳል፡፡ ትርጓሜውም በርቀት የሚታይ ማለት ነው፡፡ ከማዕዶዋይ ወደ ገዳሙ ውስጥ ለመግባት ከእግር መረገጫ የማያልፍ ስፋት የሌላት በቀኝና በግራ የምታስፈራ በጭንቅ የሚሻገርዋት "ጸናፌ ጽልመት" ተብላ የምትጠራዋን አስጨናቂ ገደል ማለፍ ግድ ይላል፡፡ ይህቺን ለመሻገርም ሆነ ለማለፍ አስቸጋሪ የሆነችን መንገድ ለብዙ ጊዜ የተመላለሱባት ምእመናን ግን ከባድ እቃ በሸክም ይዘውም ቢሆን ያለ ምንም ፍርሃት ይሻገሩባታል፡፡ በጭንቅ የሚሻገርዋትን ይህችን አስጨናቂ ገደል ከታለፈ በኋላ ቀጥሎ "ደገ ሰላም" ና "መንገደ ሰማይ" የሚባል ወደ ገዳሙ የሚያስገባ ዝግዛግ መንገድ አለ፡፡

🌹 አባታችንን ወደዚህ ድንቅ ገዳም እየመራ ይዞአቸው የገባው የታዘዘ መልአክ ነው፡፡ ወደ ገዳሙ ቅጥር ውስጥ ከተገባ በኋላ ዕፁብ ድንቅ የሆኑ ልዩና መንፈሳዊ ሐሴትን የሚሞሉ በርካታ ተአምራት የተፈጸመባቸውን ነገሮችን መመልከት ይቻላል፡፡ተአምራቶቹም "ድሮ እንዲህ ነበር፣ እንደዛ ተደረገ…" ተብሎ በአፈ ታሪክ ብቻ የሚወራ ሳይሆን አሁንም ድረስ በዐይን የሚታዩ ናቸው፡፡ ለምሳሌ ገዳሙ አጠገብ የሚገኙት ዛፎች ብዙ ዕድሜ ከማስቆጠራቸው የተነሣ በንፋስ ኃይል ሲወድቁ ወደ ታች መውደቅ ሲገባቸው በተቃራኒው ግን ዛፎቹ የሚወድቁት ወደ ላይ ነው፡፡ በተጨማሪም ገዳሙ ውስጥ በላዔ ሥጋ ሥጋን የሚበላ ንስር ሳይቀር እንኳን የሞተ እንስሳም ቢያገኝ ሥጋ የሚባል ነገር አለመብላቱ አሁንም ድረስ በዐይን የሚታይ እውነታ ነው፡፡

🌹 እንዲሁም እዚህ ድንቅ ገዳም ውስጥ መርዛማ እባብም ነድፎ ሰው ሊገድል አይችልም፡፡ በእባቡ የተነደፈ ሰው እንኳን ቢኖር በጉንዳን የተነከሰ ያህል ይሰማዋል እንጂ ፈጽሞ አይሞትም፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቅዱስ ወንጌሉ ላይ "ለሚያምኑ እነዚህ ምልክቶች ይከተሉዋቸዋል፡- በስሜ አጋንንትን ያወጣሉ፣ እባቡን ይይዛሉ፣ የሚገድል መርዝ ቢጠጡ እንኳን ከቶ አይጎዳቸውም" ያለው አምላካዊ ቃል እዚህ ገዳም ውስጥ ባለንበት ዘመን በግልጽ በተግባር ይታያል፡፡ ማር 16፡16-18፣ ሐዋ 28፡3-6፡፡ እንዲሁም በዚህ ገዳም ውስጥ ከነበሩ ዛፎች ውስጥ አንዱ ዳዕሮ የተባለ ትልቅ ዛፍ አለ፡፡ ከዚህ ልዩ ዛፍ ተጠምቆ የሚዘጋጀው መጠጥ ከወይን የሚጥም ኅሊናን የሚመስጥና ሕመምን የሚፈውስ ነበር፡፡ ሌላው በገዳሙ ውስጥ በዐይን ከሚታዩትና ከሚያስደንቁት ተአምራቶች ውስጥ አንዱ በክረምት ወቅት ኃይለኛ ዝናብ ሲጥል በወረደ መብረቅ ምክንያት ገዳሙ ውስጥ የሚገኘው ዐለት ተሰንጥቆ የሀገሪቱ ምስል ተስሎበት ተገኝቷል፡፡ እነዚህና ሌሎችም በርካታ ተአምራት እስከ አሁን ድረስ ጸንተው የሚገኙት የዚህ የፃዕዳ ዓምባ ቅድስት ሥላሴ ገዳም መሥራች በሆኑ በአቡነ ሠይፈ ሚካኤል የምሕረት ቃልኪዳን ነው፡፡

🌹 አቡነ ሠይፈ ሚካኤል ከአባታቸው ከዓምደ ሚካኤልና ከእናታቸው ከኅሪተ ማርያም ተወለዱ፡፡ ወላጆቻቸው እግዚአብሔርን የሚፈሩና በጾም ጸሎት የተወሰኑ የዋኆች ስለነበሩ በሃይማኖትና በምግባር ኮትኩተው አሳድገዋቸዋል፡፡ አባታቸው ቃለ እግዚአብሔር እንዲማሩላቸው ልጃቸውን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ወስደው ለመምህር ሰጧዋቸው፡፡ መምህሩም በደስታ ተቀብለው ቅዱሳት መጻሕፍትንና ያሬዳዊ ዜማን አስተማሯቸው፡፡

🌹 ከዚህም በኋላ አቡነ ሠይፈ ሚካኤል "እኔን ሊከተለኝ የሚወድ ቢኖር ራሱን ይካድ መስቀሉን ተሸክሞ ይከተለኝ" የሚለውን ጌታችንን ቃል ለመፈጸም ዓለምን ከነምኞቷ ንቀው ትተው መስቀሉን ተሸክመው ጌታችን ተከተሉት፡፡ ከዚህም በኋላ አባታችን ወደ ዋሻዎችና ገዳማት እየሄዱ በአድያቦ ቤተ ቂርቆስ የሚባል ገዳም ደርሰው ከአቡነ ኖላዊነኄር ግብረ ምንኵስና እየተማሩ በገዳሙ ውስጥ የነበሩ መነኰሳት እስከሚደነቁ ድረስ በጽኑ ትጋትና በብዙ ትሩፋት በተጋድሎ አገልግሎታቸውን ይፈጽሙ ነበር፡፡ ከጽኑ ተጋድሏቸው የተነሣ ሰውነታቸው እንደ በረዶ ነጭ ሆነ፡፡ በዚህም ምክንያት አቡነ ዕንቆ ብርሃን ልብሰ ምንኵስናና አስኬማ መላእክት አለበሷቸው፡፡ እንዲህ ባለ ጽኑ ገድል በኣድያቦ ከመንፈስ አባታቸው ከአባ ዕንቆ ብርሃን ብዙ ዓመታትን ቆይተው በኋላ ወደ ዋልድባ ሄዱ፡፡ ዋልድባ ከገቡም በኋላ እዛ ከነበሩ ቅዱሳን ተባርከው ጽኑ ተጋድሏቸውን ቀጠሉ፡፡

🌹 ከዚያም በዋልድባ ቅዱሳን ፈቃድ ወደ ወገሪቆ አቡነ ተክለሃይማኖት ገዳም ሄደው አበምኔትና መምህር ሆነው አገለገሉ፡፡ አቡነ ሰይፈ ሚካኤል በተሰጣቸው ጸጋ ወንጌልን እያስተማሩና ሕሙማን እየፈወሱ እስከ ጋሽ ባርካ ደብረ ሳላ የሚባል ቦታ ዞሩ፡፡ ይሄን አገልግሎታቸው ከፈጸሙ በኋላ የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ገብርኤል እየመራ ማረፍያ ቤታቸው ወደሆነችው ፃዕዳ እምባ ሥላሴ ገዳም በደብረ ከባቦ አደረሳቸው፡፡ በዚያም በጾምና በጸሎት ተጠምደው እግዚአብሔርን አገለገሉ፡፡ሲጸልዩም እስከ ሰማይ ድረስ ዓምደ ብርሃን ተተክሎ ይታያቸው ነበር፡፡

🌹 አባታችን በጸሎት ላይ ሳሉ አጋንንት በእባብና በንብ እየተመሰሉ ይፈታተኗቸው ነበር ነገር ግን አባታችን በጾምና በጸሎት ድል ይነሷቸው ነበር፡፡ በደብረ ከባቦ ቤተ ክርስትያን አንጸው ማኅበር አቋቁመው ለ9 ዓመት ከ6 ወር አገልግሎታቸውን እየፈጸሙና መከራ እየተቀበሉ ከቆዩ በኋላ አንድ ቀን በሰርክ ጸሎት እየጸለዩ ሳለ መልአክ መጥቶ "…ወደ ገዳሙ አስገባሃለሁና ተከተለኝ" አላቸው፡፡ እሳቸውም ከኋላው እየተከተሉ መልአኩ ወደ ዛሬይቱ ወንዶች ብቻ ወደሚገቡባት ገዳም አስገባቸው፡፡ ያቺን ለማየትም ጭምር የምታስፈራዋን መንገድ አባታችን "ጸናፌ ፅልመት"ብለው ሰየሟት፡፡ ከገቡም በኋላ በገዳሙ ውስጥ ቤተ ክርቲያን አንጸው ቤተ ማኅበር አቋቋሙ።

🌹 አቡነ ሰይፈ ሚካኤል በተሰጣቸው ጸጋ ርኲሳን መናፍስትን ከሕሙማን ያወጡ ስለነበር እነዚያ አጋንንትም "እዚህ እንድትኖር አንፈቅድልህም" እያሉ በገሃድ ለሞት እስከሚደርሱ ድረስ ዐይናቸውን አፈሰሱባቸው ሆኖም ግን መልአከ እግዚአብሔር ዳስሶ ዐይናቸውን መልሶ አበራላቸው፡፡ እንዲሁም አጋንንቶቹ በማደርያ ቤታቸው እሳት እያቀጣጠሉ በላያቸውም ትላልቅ ድንጋዮችን እየወረወሩ ከበፊቱ በእጅጉ ይፈታተኗቸው ነበር፡፡ እነዚያ የተወረወሩባቸው ድንጋዮች ግን አቡነ ሰይፈ ሚካኤል ይጸሉዩበት በነበረ ቦታ በደቡብ አቅጣጫ ተተክለው ቀርተዋል፡፡ ድንጋዮቹ

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

👳‍♂አባቶች ይህንን ይመክሩናል
            እኛ የአባቶቻችን ልጆች ነን
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን

ለኦርቶዶኮስ አማኞች ብቻ የተከፈተ ቻናል ።
    ✝ክርስትናችን እንዳንኖረው የሚያደርጉን ምክንያቶች በእውኑ ታውቋቸዋላችሁ⁉️

ለዚህ ችግር አባቶች ምን አሉ⁉️
የምትፈልጉትን ለማግኘት ወደ ቻናላችን ተቀላቀሉ

ይህ ምክረ አበው ነው ሁላችሁም ተቀላቀሉ ትጠቀሙበታላችሁ open የሚለውን በመንካት ይቀላቀሉን👇👇👇👇👇👇👇
    ⬜️◻️◽️▫️ⓄⓅⒺⓃ⬛️⬛️⬛️⬛️
    ⬜️◻️◽️▫️ⓄⓅⒺⓃ▪️◾️◼️⬛️
    ⬜️⬜️⬜️⬜️ⓄⓅⒺⓃ▪️◾️◼️⬛️

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

📡 በዝህ ቻናል የተለያዩ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙሮች የሚያገኙበት ቻናል ነው።
        ◤◢◤◢◤◢◣◥◣◥◣◥
               ይ🀄️ላ🀄️ሉ
        ◤◢◤◢◤◢◣◥◣◥◣◥


🔑 የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ዘማሪዎች ውስጥ የማንን ዝማሬ ማግኘት ይፈልጋሉ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
🔴የቴዎድሮስ ዮሴፍ መዝሙር
⚫️የዳግማዊ ደርቤ መዝሙር
ዝ?የቀዳሜጸጋ መዝሙር
⚫️የዘማሪት ለምለም ከበደ መዝሙር
🔴የኪነጥበብ መዝሙር
⚫️የይልማ ኃይሉ መዝሙር
🔴የዘማሪ አቤል መክብብ መዝሙር
⚫️የዘማሪት ትንቢት ቦጋለ እና      ወ.ዘ.ተ......
        ◤◢◤◢◤◢◣◥◣◥◣◥
               ይ🀄️ላ🀄️ሉ
        ◤◢◤◢◤◢◣◥◣◥◣◥

🛑እነሆ አዲስ ቻናል ይዘንሎት መጣን🛑
በማርያም ይህን ቻናል ሳይቀላቀሉ እንዳያልፉ ይደሰቱበታል መርጠን ለናንተ አቀረብንሎ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

        ◤◢◤◢◤◢◣◥◣◥◣◥


         █   𝐉𝐎𝐈𝐍 𝐔𝐒 ➲      █       

 
         ◣◥◣◥◣◥◤◢◤◢◤◢

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

💁‍♂⛪️እርሶ በቴሌግራም የቱን ቢያገኙ ደስ ይሎታል⁉️

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

ሲመታ ቅዱስ እስጢፋኖስ
ጥቅምት 17-ቀዳሜ ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስ የተሾመበት ዓመታዊ በዓሉ ነው፡፡
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን ፡፡
ዳግመኛም ይህች ዕለት ቀዳሜ ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስ የተሾመባት ዕለት ናት፡፡ እስጢፋኖስ ማለት ‹‹መደብ›› ማለት ሲሆን በግሪክ ቋንቋ ‹‹አክሊል›› ማለት ነው፡፡ በግብሩ የቀን ሃሩር የሌሊት ቁር የማይለውጠው፣ መብራት ማለት ነው፡፡ ትውልዱ ከነገደ ብንያም ሲሆን አባቱ ስምዖን እናቱ ሐና ይባላሉ፡፡ እነርሱም እግዚአብሔርን ከሚፈሩ ከነቢያትና ከጻድቃን ወገን ናቸው፡፡ በመጀመሪያ ሁለት ወንድ ልጆችን ወለዱ፡፡ አንዱ ይሁዳ ሲባል ሁለተኛውም ቅዱስ እስጢፋኖስ (አስተፓኖስ) ነው፡፡ እስጢፋኖስ የተወለደው ጥር ፲ ቀን በእስራኤል ሀገር ውስጥ ልዩ ስሟ ሐኖስ በተባለች ቦታ ነው፡፡ የተወለደውም በስለት ነው፡፡ እርሱም ከመጥምቁ ዮሐንስ እግር ሥር በመሆን ተምሯል፡፡ በኋላም ወደ ቅዱሳን ሐዋርያት በመሄድ ይላላካቸውና ያገለግላቸው ነበር፡፡ በኢየሩሳሌም ቤተ ክርስቲያን ከተሾሙት ከ፯ቱ ዲያቆናት አንዱ ሲሆን የዲያቆናት አለቃ እርሱ ነው፡፡ ቅዱስ እስጢፋኖስ ወንጌልን በማስተማሩና ብዙዎችን ክርስቶስን ወደማመን ስለመለሳቸው ክፉዎች አይሁድ በጠላትነት ተነስተውበት ጥር ፩ ቀን በ ፴፬ ዓ.ም ከጌታችን ቀጥሎ ከምእመናን ወገን የመከራውን ጽዋ ስለተቀበለ (በድንጋይ ተወግሮ በሰማዕትነት ስላረፈ) ‹‹ቀዳሜ ሰማዕት›› ተሰኘ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ‹‹ሊቀ ዲያቆናት ቅዱስ እስጢፋኖስ›› እየተባለ ይጠራል፡፡ ይኸውም የከበሩ ቅዱሳን ሐዋርያት በሰባቱ ዲያቆናት ላይ አለቃ አድርገው በሾሙት ጊዜ የተሰጠው ስያሜ ነው፡፡
የመጀመሪያ ክርስቲያኖች የአማኞች ቊጥር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ በሄደ ጊዜ የማኅበራዊው ኑሮ አስተዳደር ማለትም የምግብንና የመሳሰሉትን ቁሳቁሶች (ገንዘብም ጭምሮ) በትክክልና በእኩልነት የማከፋፈሉ ሥራ በሐዋርያት ዘንድ አስቸጋሪ ሆኖ ተገኘ፡፡ እነርሱም ደግሞ ዋና ተግባር አድርገው በትጋት ለመያዝ የፈለጉት ማስተማርን ነበር፡፡ ስለዚህም አማኞችን ሁሉ ሰብስበው ከመካከላቸው በመልካም ጠባያቸው የተመሰገኑ በመንፈስ ቅዱስና በጥበብ የተሞሉ ሰባት ሰዎችን እንዲመርጡ አሳስቧቸው፡፡ አማኞችንም ነገሩ አስደስቷቸው ሰባት ሰዎችን መረጡ፡፡ እነርሱም፡- ቅዱስ እስጢፋኖስ (ዕረፍቱ ጥር ፩)፣ ቅዱስ ጵሮኮሮስ (ሰኔ፰፮)፣ ቅዱስ ጢሞና (ሚያዝያ ፲፮)፣ ቅዱስ ፊልጶስ (ጥቅምት ፲፬)፣ ቅዱስ ጰርሜና (መስከረም ፩)፣ ቅዱስ ኒቃሮና /፫/ ጊዜ ሞቶ የተነሣ)፣ ቅዱስ ኒቆላዎስ (ሚያዝያ ፲፭) ናቸው፡፡ ሐዋ ፮፡፭፡፡
እነዚህንም ቅዱሳን በከበሩ ሐዋርያት ፊት ባቆሟአቸው ጊዜ ጸልየው እጃቸውን በራሳቸው ላይ ጭነው ሾሟቸው፡፡ በከበሩ ሐዋርያት ጫንቃ ላይ ተጭኖ የነበረው ከባድ ሸክም ፤ ባሎቻቸው የሞቱባቸውን ሴቶችና ወላጆቻቸው የሞቱባቸውን ደሀ አደጎች በመርዳት ችግሮቻቸውን አቃለሉላቸው፡፡ በከበሩ ሐዋርያት ከተመረጡት ሰባቱ ዲያቆናት መካከል ሊቀ ዲያቆናት ተደረጎ የተመረጠው ቅዱስ እስጢፋኖስ ሲሆን ፤ ሌሎቹም ዲያቆናት እስከ ሕይወታቸው ፍጻሜ ወንጌልን በማስተማርና የመጀመሪያ ክርስቲያኖች በማስተዳደር በጽናት ተጋድለዋል፡፡ እነዚህም ሰባቱ ዲያቆናት ከአባቶቻቸው ከከበሩ ሐዋርያት አይተው የእነርሱንም መንፈስ ተቀብለው ያልተማሩ አሕዛብን ልቡናቸውን ለመስበርና የእግዚአብሔርን ኃይልነት ተረድተው እንዲገነዘቡ በማሰብ ብዙ ድንቅ ድንቅ ተአምራትን ያደርጉ ነበር፡፡ ከእነርሱም ውስጥ በዋነኛነት ቅዱስ እስጢፋኖስ በአህዛብ ፊት ያደረጋቸው ተአምራት እጅግ ድንቅ ናቸው፡፡
ቅዱስ እስጢፋኖስ በአህዛብ መካከል ቆሞ ሲያስተምር ከቆየ በኋላ አንድ አንደበቱ ዲዳ የሆነ ሰው አጠገቡ ቢመጣ በጆሮው የሕይወት እስትንፋስ እፍ ቢልበት መስማት የማይችለው መስማት ቻለ፡፡ በዚህም ጣኦት አምላኪው ናኦስ እና ተከታዮቹ ሁሉ ወደ ቅዱስ እስጢፋኖስ ተመለሱ፡፡ ጣኦት አምላኪው ናኦስ በድርጊቱ በጣም ከመናደዱ የተነሣ በአጠገቡ የቆመውን በሬ ጠንቋዩ ናኦስ በጆሮው እፍ ብሎ ቢተነፍስበት በሬው በምትሃት ለሁለት ተሰንጥቆ በመሞቱ ወደ ቅዱስ እስጢፋኖስ የተመለሱት በናኦስ ምትሃታዊ ድርጊት በመሳባቸው እንደገና ወደ ናኦስ ተመለሱ፡፡ ቅዱስ እስጢፋኖስም በዚህ ጊዜ የአህዛብ ልቡና ወላዋይ እንዳይሆንና እንዳይጠፉም በማሰብ ናኦስ እፍ ብሎ ለሁለት ሰንጥቆ የገደለውን በሬ መልሶ በሕይወት እንዲያስነሣው ናኦስን ጠየቀው፡፡ ነገር ግን ናኦስ ያንን ማድረግ አልቻለም፡፡ ከዚህም በኋላ ቅዱስ እስጢፋኖስ ‹‹ናኦስ ዳግመኛ ሕይወት ዘርቶ ማስነሣት ካልቻለ እኔ ነገሩ ሀሰተኛ ነው ማለት ነው፣ እኔ ግን በእግዚአብሔር ኃይልና ድንቅ ሥራ ይህን ለሁለት ተሰንጥቆ የሞተውን በሬ ዳግመኛ ሕይወት ዘርቶ እንዲነሣ አደርገዋለሁ›› በማለት ወደ እግዚአብሔር ከጸለየ በኋላ በሬውን አስነሣው፡፡ ይህንንም ተአምር አድርጎ በማስተማር ልቦናቸው ወላውሎ ወደ ናኦስ የተመለሱትን አህዛብ ገንዘቡ እንዲሆኑ በእግዚአብሔር ኃይልነት እንዲያምኑ አድርጓል፡፡ ናኦስ በአልሸነፍ ባይነትና በአጋንንት ረዳትነት ራሱን ወደ ላይ እንዲንሣፈፍ አድርጎ በአየር ላይ ቢወጣ ቅዱስ እስጢፋኖስ የእግዚአብሔርን ተአምር በማሳየት በትዕግስት ጠብቆ በአጋንንት ረዳትነት ወደ ላይ የተነሳውን ናኦስ በትምዕርተ መስቀል ቢያማትብበት ይዘውት የነበሩት አጋንንት ሁሉ ለቀውት ሲበተኑ ናኦስም ምድር ደርሶ ተንኮታኩቶ በመውደቁ በጣኦት አምላኪነት የነበሩ ሁሉ ዳግም ወደ ቅዱስ እስጢፋኖስ ተመልሰዋል፡፡
የሰማዕታት መጀመሪያ የሆነው ቅዱስ እስጢፋኖስ በትምህርቱና በተአምራቱ ብዙዎችን ወደቀናች ሃይማኖት ስለመለሰ ክፉዎች አይሁድ ቀኑበትና የሐሰት ምስክር አዘጋጁበት፡፡ ‹‹በእግዚአብሔርና በሙሴ ላይ የስድብን ቃል ሲናገር ሰምተነዋል›› ብለው በሐሰት ከሰሱትና በሸንጎአቸው አቆሙት፡፡ ቀዳሜ ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስም ከአብርሃም ጀምሮ እስከ ጌታችን ያለውን ሁሉንም እየጠቀሰ የሃይማኖትን ነገር አስተማራቸው፡፡ ነቢያትን ስለማሳደዳቸውና ስለመግደላቸው እየወቀሰ ሲናገራቸው በትምህርቱ ተናደው ጆሮአቸውን ይዘው በመጮህ በድንጋይ ወግረው ይገድሉት ዘንድ እየጎተቱ ከከተማው ውጭ አወጡት፡፡ ቅዱሱም በድንጋይ ወግረው ሲገድሉት ከጌታችን የተማረውን ‹‹አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይህን ኃጢአት አትቁጠርባቸው›› እያለ ስለገዳዮቹ ምሕረትን ይለምን ነበር፡፡ ሰማይም ተከፍቶ የእግዚአብሔርን ክብር ተመለከተ፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ይኸውም የቀድሞው ሳውል ቅዱስ እስጢፋኖስን በድንጋይ ሲወግሩት የገዳዮቹን ልብስ ይጠብቅና ድንጋይ ያቀብል ነበር፡፡ ‹‹የሰማዕትህንም የእስጢፋኖስን ደም ባፈሰሱ ጊዜ፥ ራሴ ደግሞ በአጠገባቸው ስቆም ተስማምቼ የገዳዮችን ልብስ እጠብቅ ነበር አልሁ›› ብሎ ራሱ ቅዱስ ጳውሎስ መስክሯል፡፡ ሐዋ ፳፪፡፳፡፡ የቅዱስ እስጢፋኖስ መምህር የነበረው ምሑረ ኦሪቱ ገማልያልና ልጁ አቢብ በእስጢፋኖስ ትምህርትና የሞቱ ሰዎች የሰጡትን ምስክርነት አይተው ከይሁዲነት ተመልሰው በክርስቶስ አምነው ተጠምቀዋል፡፡ ስለ ሰማዕቱ ቅዱስ እስጢፋኖስ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ እንዲህ ተብሎ ነው የተጻፈው፡- ‹‹እስጢፋኖስም ጸጋንና ኃይልን ተሞልቶ በሕዝቡ መካከል ድንቅንና ታላቅ ምልክትን ያደርግ ነበር፡፡ የነፃ ወጪዎች ከተባለችው ምኵራብም ከቀሬናና ከእስክንድርያም ሰዎች ፤ ከኪልቅያና ከእስያም ከነበሩት አንዳንዶቹ ተነሥተው እስጢፋኖስን ይከራከሩት ነበር፤ ይናገርበት የነበረውንም ጥበብና መንፈስ ይቃወሙ ዘንድ አልቻሉም፡፡ በዚያን ጊዜ በሙሴ ላይ በእግዚአብሔርም

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

💕ከዘማሪያን የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይ ፈ ል ጋ ሉ ? 🔔 💕

[┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
[┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ዘማሪ አቤል መክብብ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕ዘማሪት ሲስተር ህይወት ተፈራ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕ዘማሪ ዲያቆን ሙሉቀን ከበደ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ዘማሪት ፋሲካ ድንቁ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛


🌷👥 የሁሉንም ዘማሪያን መዝሙር ለማግኘት 🔔 👇
🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

🤔 የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ⁉️

📌 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
📌 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ
📌 ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ
📌 ዘማሪ አርቲስት ይገረም ደጀኔ
📌 ዘማሪ ገ/ዮሐንስን ገ/ፃዲቅ
📌 ቀሲስ ምንዴዬ ብርሀኑ
📌 ዘማሪት ሲስተር ህይወት ተፈራ
📌 ቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ
📌 ዘማሪ ዲ/ን አቤል መክብብ
📌 ዘማሪ ዲ/ን ሮቤል ማቲያስ
📌 ዘማሪት ፋሲካ ድንቁ
📌 ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን
📌 ዘማሪት አቦነሽ አድነው
📌 ዘማሪት ዶ/ር ሔለን ተስፋዬ


እና የሌሎችንም ...........

ዘማሪዎችን መዝሙሮች እና አዳዲስ
መዝሙሮችን ለማግኘት ከስር OPEN
የሚለውን ይጫኑት። 👇

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
█ ▒ ░✞ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ❖ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ✞░ ▒ █
█ ▒ ░✞ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ❖ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ✞░ ▒ █
█ ▒ ░✞ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ❖ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ✞░ ▒ █
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

💠የንስሐ ◇የሽብሻቦ ◇ወረብ ◇የቅዱሳን  እንዲሁም የመላእክት መዝሙር የምትፈልጉ ከሆነ አሁኑኑ JOIN  በሉት  ይሄ ቻናል ምርጥ ምርጥ መዝሙሮችን በጥራትና በፍጥነት ያሳያል። 𝐉𝐨𝐢𝐧👇👇👇

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

ከ15 ደቂቃ ቦኃላ ይጠፋል


የ 200 ብር ካርድ የሚያስሸልም ጥያቄ!

10+10×0+10=???

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

💁‍♂እቤቶ ቁጭ ብለው ገንዘብ ማግኘት ይፈልጋሉ ?

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

🌹 አባታችን አቡነ ሐራ ድንግልም በክብር ካረፉ በኋላ በመካነ መቃብራቸው ላይ ለ40 ቀን ብርሃን ሲወርድ በገሃድ ታይቷል፡፡ አፅማቸውም ከዚያው ከገዳማቸው በክብር አርፎ ይገኛል፡፡ በጸሎታቸው ያፈለቁት ጸበልና የመቃብራቸው አፈር ሕመምተኞችን ከተለያዩ ደውያት ሰውንም እንስሳትንም እየፈወሰ ይገኛል፡፡ አፈራቸውና ጸበላቸው ለሥጋ ደዌ፣ ለእብጠት፣ለቁስል፣ ለለምፅና ለመሳሰሉት ፍቱን መድኃኒት ነው፡፡ በዓለ ዕረፍታቸው ጥር 11 ቀን 1624 ዓ.ም ነው፡፡
ከአቡነ ሐራ ድንግል እግዚአብሔር አምላክ ረድኤት በረከትን ያሳትፈን። በጸሎታቸው ይማረን!።
ምንጭ፦ መዝገበ ቅዱሳን ከሚለው መጽሐፍ የተወሰደ።

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

🌹 "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። 🌹

        🌹 #ጥቅምት ፲፱ (19) ቀን።

🌹 እንኳን #ለኢትዮጵያዊው_ንጉሥ_ክህነት_ከንግሥና ጋር አስተባብሮ ለያዘው #40_ዓመት_ሙሉ_ሰማያዊ_ኅብስትና_ጽዋ ከሰማይ እየወረደለት ለቀደሰው #ለጻድቁ_ለቅዱስ_ለይምርሐነ_ክርስቶስ ለዕረፍት በዓል፣ ለታላቁ አባት ከመቃብራቸው በሚወጠው #በእምነታቸውና_በጠበል_ፈዋሽነታቸው ለመታወቁት #ለአቡነ_ሐራ_ድንግል_ለልደታቸው በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ እንደ በግ ከታረዱ #ከመጥራ_ጻድቃ ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።

             ✝ ✝ ✝🌹
#ጻድቁ_ንጉሥ_ቅዱስ_ይምርሃነ_ክርስቶስ፡- ከላስታ (ከዛጉዌ) ነገሥታት መካከል ቅዱስ ይምርሃነ ክርስቶስ፣ ቅዱስ ገብረ ማርያም፣ ቅዱስ ላሊበላና ቅዱስ ነአኵቶለአብ እነዚህ አራቱ ነገሥታት እንደ መልከጼዴቅ (ዘፍ 14፡18) ክህነትን ከንግሥና፣ ቅድስናን ከንጽሕና ጋር አንድ አድርገው በመያዝ እግዚአብሔርንም ሰውንም በቅድስና አገልግለው አልፈዋል፡፡ በንግሥናቸው ሀገርን በመልካም ሥራና በቅድስና ከማስተዳደራቸው በተጨማሪ ቅዱሳን ጻድቃን ሆነው እግዚአብሔርን በብዙ ድካም በመልካም ተጋድሎአቸው ያገለገሉና አገልግሎታቸውም ሆነ ቅድስናቸው በእግዚአብሔር ዘንድ የተመሰከረላቸው ቅዱሳን ናቸው፡፡

🌹 ከእነርሱም ውስጥ ሞትን ሳያይ እንደነ ሄኖክና ኤልያስ የተሰወረ አለ፤ ከእነርሱም ውስጥ በባሕር ላይ ቤተ መቅደሱን ያነጸ አለ፤ ከእነርሱም ውስጥ የታዘዘ መልአክ መጥቶ ወደ ሰማይ ነጥቆ ወስዶት የቤተ መቅደሶቹን አሠራር ራሱ ጌታችን በቃሉ ያስረዳው አለ፡፡ ከእነርሱም ውስጥ በክህነቱ ሲቀድስ 40 ዓመት ሙሉ ቅዱስ ቁርባኑን መላእክት ከሰማይ እያመጡለት የነበረ አለ፡፡ እነዚህ ቅዱሳን ነገሥታት ገድላቸውና ትሩፋታቸው፣ ምግባር ሃይማኖታቸው እጅግ ድንቅ ነው፡፡ የእነዚህ ቅዱሳን ነገሥታቱን የዘር ሐረጋቸው ከሰሎሞን ዘር ሲያያዝ የመጣ ነው፡፡ከ10ኛው እስከ 13ኛው መቶ ክፍለ ዘመን (920-1253 ዓ.ም ገደማ) በላስታ ቡግና ምድር የነገሡ የላስታ ቡግና ተወላጅ የሆኑ የኢትዮጵያ ቅዱሳን ነገሥታት የንግሥናቸው መጠሪያ "የዛጉዌ ሥርወ መንግሥት" ወይም "የላስታ መንግሥት" በመባል ይታወቃል፡፡ ከዛጉዌ ነገሥታት ውስጥ የመጀመሪያው ንጉሥ መራ ተክለሃይማኖት የዐፄ ድልነአድን ልጅ መሶበወርቅን አግብቶ አራት ልጆችን ወልዷል፡፡ ሦስቱ ወንዶች ጠንጠውድም፣ ግርማ ስዩምና ዣን ስዩም ይባላሉ፡፡ ጠንጠውድም ገብረ መስቀልን ወለደ፣ ግርማ ስዩም ቅዱስ ይምርሃነ ክርስቶስ ወለደ፣ ዣን ስዩም ደግሞ ቅዱስ ገብረማርያምንና ቅዱስ ላሊበላን ወለደ፡፡ ገብረ መስቀልም ጣራው ክፍት ሆኖ ዝናብ የማያስገባውን ገዳም የመሠረቱትን የመቄቱን ታላቁን አባት አቡነ አሮንን ወለደ፡፡ ቅዱስ ገብረማርያም ደግሞ ቅዱስ ነዓኵለአብን ወለደ፡፡

🌹 ቅዱስ ይምርሃነ ክርስቶስ በቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም ሳለ መልአኩ ቅዱስ ሩፋኤል "ከጠንጠውድም በኋላ የምትነግሠው አንተ ነህ" በማለት ከነገረው በኋላ በመንገዱ ሁሉ እየተራዳው ወደ ኢትዮጵያ ይዞት መጥቷል፡፡ በቤተ መቅደስ ገብቶ ሲቀድስ መላእክት ሰማያዊ ኅብስትንና ጽዋን አምጥተው እየሰጡት እርሱም ለሕዝቡ ሁሉ ያቆርባቸው ነበር፡፡ ሕዝቡን የሚባርክበትም መስቀል ከሰማይ ነው የወረደለት፡፡ ዛሬም ድረስ አለ፣ በዓል ሲሆን ካህናት አባቶች እያወጡ ሕዝበ ክርስቲያኑን ይባርኩበታል፡፡ ጌታችን ለይምርሃነ ክርስቶስ በአካል ተገልጦለት እስከ ዕለተ ምፅዓት ድረስ አካሉ እንደማይፈርስ ቃልኪዳን የሰጠውንና አሁን በላስታ ላሊበላ ያለውን ቤተመቅደሱን በባሕር ላይ እንዲሠራ ነግሮት በኋላም በቦታው ላይ እጅግ አስደናቂ ቃልኪዳን ሰጥቶታል፡፡

🌹 ቅዱስ ይምርሃነ ክርስቶስ ግንቦት 19 ቀን ሲወለድ እንደነ አቡነ ተክለሃይማኖትና እንደነ አቡነ ዜና ማርቆስ ወደ ምሥራቅ ዞሮ አምላኩን ያመሰገነ ሲሆን ቤቱም በብርሃን ተሞልቶ ታይቶ አዋላጆቹን ሁሉ አስገርሟል፡፡ እርሱ ገና ሳይወለድ በፊት አጎቱ ጠንጠውድም በንግሥና ላይ ሳለ "ከአንተ በኋላ የሚነግሠው ይምርሃነ ክርስቶስ የሚባል ሰው ነው" ተብሎ ሲነገረው "እንዲህ የሚባል ሰው በቤተ መንግሥቴ አለን?" በማለት ቢጠይቅም እንደነቢዩ ኤርሚያስ ከእናቱ ማኅፀን ጀምሮ የተመረጠ ሕፃን እንደሚወለድ ነግረውታል፡፡ አርባ ዓመት የነገሠው ጠንጠውድም ቀድሞ በትንቢት እንደተነገረው "ይምርሃነ ክርስቶስ" የሚባል የወንድሙ ልጅ መወለዱን ሲሰማ "የወንድሜን ልጅ አየው ዘንድ አምጡልኝ" ብሎ ላከ፡፡ ባየውም ጊዜ ደም ግባቱ እጅግ ያምር ስለነበር "ይህስ መንግሥቴን ይውረስ፣ በእውነት ልጄ ነው" ብሎ ባረከው፡፡ ሆኖም ከእርሱ ጋር ስምንት ቀን ተቀምጦ በወለዳቸው ልጆቹ መካከል በተመለከተው ጊዜ በልቡ ሰይጣን አደረበትና በቅናት ሆኖ "እርሱ ነግሦ ልጆቼ ወታደሮቹ ሊሆኑ ነው" በማለት ይገድለው ዘንድ አሰበ፡፡ሆኖም ግን "ለጊዜው ምንም አያውቅም ለወደፊቱም የንግሥና ምሥጢር እንዳያውቅ ወደ እናቱና አባቱ ዘንድ መልሰው በዚያ ከብት ሲያግድ ያድጋል እንጂ ሥርዓተ ንግሥናን አያውቅም" በማለት ስለተመከረ ወደ እናቱ ላከው፡፡ በኋላም በጥበብና በብልሃት አስተዋይ ሆኖ ማደጉን በሰማ ጊዜ ሊገድለው አሽከሮቹን ላከ፡፡ እናቱም ለተላኩት አሽከሮች ምግብ አቅርባ እርሷ ግን ነገሩን እንዲገልጽላት እግዚአብሔርን በስውር አልቅሳ ስትለምን የንጉሡ ተንኮል ስለተገለጠላት ልጇን ደበቀችው፡፡ በስውርም ወስዳ ከጳጳሱ ዘንድ ዲቁና እንዲቀበል ካደረገችው በኋላ "ልጄ ሆይ! አጎትህ ሊገድልህ ይፈልግሃልና በፊቴ ከሚገድልህ ርቀህ ብትሄድ ይሻላል፣ ያዕቆብን ከኤሳው የጠበቀ አንተንም ይጠብቅህ" ብላ ሸኘችው፡፡

🌹 ንጉሡ አጎቱም "ይምርሃነ ክርስቶስን ፈልጎ ላገኘልኝ የመንግሥቴን እኩሌታ እሰጣለሁ" ብሎ ቢያውጅም ይምርሃነ ክርስቶስ ግን ወደ ኢየሩሳሌም ተሰደደ፡፡ በዚያም የሌዋውያን ወገን የምትሆን ቅድስት ሕዝባን አግብቶ ቅስናም ተቀብሎ ሥጋዊውንና መንፈሳዊውን ጥበብ ተምሮ ካጠናቀቀ በኋላ ወንጌልን እየሰበከ፣ በተአምራቱም ሕመምተኞችን እየፈወሰ እግዚአብሔር እያገለገለ ኖረ፡፡ እግዚአብሔርም አጎቱ ንጉሥ መሞቱንና በንጉሡም ዙፋን እርሱ እንደሚነግሥ ነግሮት በመልአኩ ቅዱስ ሩፋኤል መሪነት ወደ ኢትዮጵያ ተመልሶ መጥቶ በላስታ ወረዳ ሳይ (ዛሬ ሸጐላ ማርያም) ከምትባል ሀገር ደርሶ በዚያ ወንጌልን እያስተማረ፣ ድውያንን እየፈወሰ ተቀመጠ፡፡ ትምህርቱንና ተአምራቱን ያዩት የአካባቢው ሰዎች "ነፃነትና ፍቅር የሚገኝብህ የእግዚአብሔር ሰው ሆይ! እኛ ሰላማዊ ብርሃናዊ ብለን ስም አወጣንልህ፣ ያንተ ግን ስምህ ማን ይባላል ንገረን" አሉት፡፡ እርሱም "ስሜ ይምርሃነ ክርስቶስ ነው" ባላቸው ሰዓት ሕዝቡ ሁሉ በሹክሹክታ "ይምርሃነ ክርስቶስ የሚባል ሲነግሥ ሃይማኖት ይቀናል፣ ፍርድ ይስተካከላል፣ በዘመኑም የሮም ሰዎች ለኢትዮጵያ ይገዛሉ" ሲሉ አባቶቻችን ሰምተናል አሉ፡፡

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

💁‍♂⛪️እርሶ በቴሌግራም የቱን ቢያገኙ ደስ ይሎታል⁉️

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

🫃👉መንታ ወንድና ሴት ቢወለዱ ክርስትና እንዴት  ይነሳሉ⁉️
👉ሴት በወር አበባ ጊዜስ⁉️
👉 ወንድ ህልመ ሌሊት ቢያጋጥመው ለስንት ቀን ይረክሳል ⁉️
👉 ሰባቱ አጽዋማት እነማን ናቸው⁉️
👉 አምስቱ አዕማደ ምስጢራት ማን ናቸው⁉️
👉 ከአስርቱ ትዕዛዛት ውጪ ያለው ትዕዛዝ ምነው⁉️


⛪️ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን አንፃር መልሱን ይመልከቱ⛪️
                    👇👇👇👇

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

እስከ አሁን ድረስ አሉ፡፡

🌹 አቡነ ሰይፈ ሚካኤል በአገልግሎታቸው ለሚያምኑ እያጽናኑና እያበረቱ፣ ለማያምኑ ደግሞ አሳምነው እያጠመቁ እስከ ማዕርገ ክህነት አድርሰው ቤተ ክርስትያን ይሠሩላቸው ነበር፡፡ በስተመጨረሻ ቅዱስ አባታችን በብዙ ተጋድሎ ሐዋርያዊ ተልዕኮአቸውንና አገልግሎታቸውን ከፈጸሙ በኋላ ከእግዚአብሔር የምሕረት ቃልኪዳን ተቀብለው ጥቅምት 19 ቀን 1722 ዓ.ም በ96 ዓመታቸው ራሳቸው በመሠረቱም በገዳም ፃዕዳ ዓምባ ቅድስ ሥላሴ ዐርፈዋል፡፡

🌹 የአባታችን የአቡነ ሰይፈ ሚካኤልን መንገድ የተከተሉ የዚህ ገዳም መነኰሳትም በጸምና በጸሎት ተወስነው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ "ሑሩ ወመሐሩ" (ማቴ 28፡19) ባለው አምላካዊ ቃል መሠረት ሐዋርያዊ ተልኮአቸውን እየፈጸሙ ብዙ አብያተ ክርስቲያናን ከከረን እስከ ኦምሓጃር ከዛ አልፎም እስከ ከሰላ ሱዳን አንጸዋል፡፡ በፃዕዳ እምባ ሥላሴ ገዳም ሐምሌ 7 ቀን የሥሉስ ቅዱስ ዓመታዊ ክብረ በዓል እና የአቡነ ሰይፈ ሚካኤል በዓለ ዕረፍታቸው ጥቅምት 19 ቀን በደማቅ ሁኔታ ይከበራል፡፡ በእነዚህ ክብረ በዓላት ላይ በርካታ ምእመናን ከተለያዩ ቦታዎች በመምጣት ከበረከቱ ይሳተፋሉ፡፡

ከአባታችን የአቡነ ሰይፈ ሚካኤል እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን በጸሎታቸውም ይማረን!። ምንጭ፦ ከገድላት አንደበት። 

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

✝መስቀሉን  ስትነኩት የሚወስዳችሁ ቻናል ለህይወታችሁ ጠቃሚ ስለሆነ መስቀሉን  ይጫኑ Join ይበሉት
/Start      

                  🔳🔳
                  🔳🔳
         🔳🔳🔳🔳🔳🔳
         🔳🔳🔳🔳🔳🔳
                  🔳🔳
                  🔳🔳
                  🔳🔳
                  🔳🔳

         መስቀሉ አርማችን ነው።

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

1⃣7⃣ደቂቃ ቦኃላ ይጠፋል


የ 200 ብር ካርድ የሚያስሸልም ጥያቄ!

በኢትዮጵያ በጣም አስቸጋሪ የነበረዉ  ረሀብ መች አመተምህረት ነበረ

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

💁‍♂እቤቶ ቁጭ ብለው ገንዘብ ማግኘት ይፈልጋሉ ?

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

ላይ የስድብን ነገር ሲናገር ሰምተነዋል የሚሉ ሰዎችን አስነሡ፡፡ ቀርበውም ያዙት ወደ ሸንጎም አመጡትና ‹ይህ ሰው በዚህ በተቀደሰው ስፍራ በሕግም ላይ የስድብን ነገር ለመናገር አይተውም፤ ይህ የናዝሬቱ ኢየሱስ ይህን ስፍራ ያፈርሰዋል ሙሴም ያስተላለፈልንን ሥርዓት ይለውጣል ሲል ሰምተነዋልና› የሚሉ የሐሰት ምስክሮችን አቆሙ፡፡ በሸንጎም የተቀመጡት ሁሉ ትኵር ብለው ሲመለከቱት እንደ መልአክ ፊት ሆኖ ፊቱን አዩት፡፡›› የሐ.ሥራ ፮-፲፭
የአይሁድ በቅዱስ እስጢፋኖስ ላይ ያቀረቡት የክሳቸው ምክንያት ጌታችንን ከከሰሱት ክስ ጋር በሁለት ነጥቦች ይመሳሰላል፡፡ የመጀመሪያው ክሳቸው ‹‹የሙሴን ሕግ ሽሯል›› የሚል ነው፡፡ ‹‹የሙሴን ሕግ በመሻር ኦሪት አትጠቅምም አትመግብም አታድንም፤ ሐዲስ ኪዳን (ወንጌል) ግን ትመግባለች ታድናለች›› ብሏል ብለው ከሰሱት፡፡ ሐዋ ፮፡፲፫፡፡ ሁለተኛው ክሳቸው ‹‹እግዚአብሔርንም ይሰድባል›› የሚል ነው፡፡ ሐዋ ፯፡፶፡፡ አይሁድም የቅዱስ እስጢፋኖስን የወንጌል ቃል ንግግሮች በእግዚአብሔር ላይ እንደተሰነዘሩ ስድቦች በመቁጠር ነበር የወነጀሉት፡፡ የኦሪት የካህናት አለቃውም ቅዱስ እስጢፋኖስ ለተከሰሰበት መልስ ይሰጥ ዘንድ ሲጠይቀው እርሱ ግን ለተከሰሰበት መልስ ከመስጠት ይልቅ ከአብርሃም ጀምሮ እስከ ክርስቶስ ድረስ ያለውን የመጽሐፍ ቅዱስ ጽሑፍ በዝርዝር በሚገባ ተረከላቸው፡፡
ቅዱስ እስጢፋኖስም እንዲህ አላቸው፡- ‹‹ከነቢያትስ አባቶቻችሁ ያላሳደዱት ማን ነው? የጻድቁንም መምጣት አስቀድሞ የተናገሩትን ገደሉአቸው፤ በመላእክት ሥርዓት ሕግን ተቀብላችሁ ያልጠበቃችሁት እናንተም አሁን እርሱን አሳልፋችሁ ሰጣችሁት ገደላችሁትም፡፡ ይህንም በሰሙ ጊዜ በልባቸው በጣም ተቈጡ ጥርሳቸውንም አፋጩበት፡፡ መንፈስ ቅዱስንም ተሞልቶ ወደ ሰማይ ትኵር ብሎ ሲመለከት የእግዚአብሔርን ክብር ኢየሱስንም በእግዚአብሔር ቀኝ ቆሞ አየና፡፡ እነሆ ሰማያት ተከፍተው የሰው ልጅም በእግዚአብሔር ቀኝ ቆሞ አያለሁ አለ፡፡ በታላቅ ድምፅም እየጮኹ ጆሮአቸውን ደፈኑ፣ በአንድ ልብ ሆነውም ወደ እርሱ ሮጡ፤ ከከተማም ወደ ውጭ አውጥተው ወገሩት፡፡ ምስክሮችም ልብሳቸውን ሳውል በሚሉት በአንድ ጎበዝ እግር አጠገብ አኖሩ፡፡ እስጢፋኖስም ‹ጌታ ኢየሱስ ሆይ ነፍሴን ተቀበል› ብሎ ሲጠራ ይወግሩት ነበር፡፡ ተንበርክኮም ‹ጌታ ሆይ ይህን ኃጢአት አትቍጠርባቸው› ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ፡፡ ይህንም ብሎ አንቀላፋ፡፡ ሳውልም በእርሱ መገደል ተስማምቶ ነበር፡፡ ፯፥፶፪-፷፡፡ ቅዱስ እስጢፋኖስ ስለንጽሕናው ስለድንግልናው፣ ስለሰማዕትነቱ ስለተጋድሎው እና ስለስብከቱ ስለተአምራቱ ሦስቱ አክሊላት ተቀዳጅቷል፡፡
ቅዱስ እስጢፋኖስ አምላኩን ክርስቶስን በብዙ ነገር መስሏል፡፡ በመጨረሻዋ የመሞቻው ሰዓት ላይ እንኳን ሆኖ አምላኩን አብነት አድርጎ ተገኝቷል፡፡ ጌታችን ‹‹ነፍሴን ተቀበላት›› እንዳለ ሁሉ ቅዱስ እስጢፋኖስም ‹‹አቤቱ ጌታ ሆይ ነፍሴን ተቀበላት›› ብሏል፡፡ ጌታችን ‹‹አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው›› እንዳለ እስጢፋኖስም ‹‹ጌታ ሆይ ይህን ኃጥአት አትቁጠርባቸው የሚያደርጉትን አያውቁምና›› በማለት ለገዳዩቹ ምሕረትን ለምኗል፡፡ በጌታችን ጸሎት እነ ፊያታዊ ዘየማንን ጨምሮ እልፍ ነፍሳት ወደ ንስሐ ተመልሰው ገነት መንግሥተ ሰማያትን እንደወረሱ ሁሉ በቅዱስ እስጢፋኖስም ጸሎት ብዙ ነፍሳት ድነው ገነት መንግሥተ ሰማያትን ወርሰዋል፡፡ የጌታችን ቅዱስ መስቀል እልፍ ሙታንን ያስነሣ ድውያንን ይፈውስ እንደነበር ሁሉ የቅዱስ እስጢፋኖስም ዐፅም ሙታንን ያስነሣ ድውያንን ይፈውስ ነበር፡፡ ቅዱስ እስጢፋኖስ የተወገረበት ድንጋይ ሰባት አብያተክርስቲያናት ታንጸውበታል፡፡
የቅዱስ እስጢፋኖስ ልደቱና ዕረፍቱ ጥር ፩ ቀን ነው፡፡ ምእመናንም ሥጋውን ወስደው በክብር ቀበሩት፡፡ ጥቅምት ፲፯ የተሾመበት ነው፡፡ መስከረም ፲፭ ቀን ፍልሰተ ሥጋው ነው፡፡ የቅዱስ እስጢፋኖስ ቅዱስ ዐፅሙ ሙትን ያስነሣ ድውይን ይፈውስ ነበርና አይሁድ በቅናት ተነሥተው እንደ ጌታችን ቅዱስ መስቀል የቅዱስ እስጢፋኖስን ዐፅም አርቀው በመቆፈር ቀብረው በላዩም ቆሻሻ በመጣል ለ፫፻ ዓመት ያህል ተቀብሮ ኖሮ በመጨረሻ በፈቃደ እግዚአብሔር እንደ ቅዱስ መስቀሉ ተቆፍሮ በመውጣት መስከረም ፲፭ ቀን ቅዱስ ዐፅሙ ወጥቶ በክብር በስሙ በታነጸው ቤተ ክርስቲያን በክብር ተቀምጧል፡፡ ይኸውም የሆነው እንዲህ ነው፡- ሰማዕቱ ቅዱስ እስጢፋኖስ ካረፈ ከ፫፻ ዓመት በላይ በሆነ ጊዜ ጻድቁ ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ ሲነገሥና ሃይማኖትን በመላው ዓለም አቀና፡፡ ተዘግተው የነበሩ ገዳማትና አብያተ ክርስቲያናት ተከፈቱ፡፡
በዚህም ወቅት የቅዱስ እስጢፋኖስ ሥጋው በሚገኝበት በኢየሩሳሌም አካባቢ ሉክያኖስ ለሚባል ሰው ቅዱስ እስጢፋኖስ በራእይ ተገለጠለትና ‹‹እኔ እስጢፋኖስ ነኝ፣ ሥጋዬ በዚህ ቦታ ተቀብሯል›› በማለት ሥጋውን ያወጡ ዘንድ አዘዘው፡፡ ሉክያኖስም ለኢየሩሳሌሙ ኤጰስ ቆጶስ ሄዶ ነገረውና ወደ ቦታው ሄደው ሲቆፍሩ ታላቅ ንውጽውጽታ ሆነና ሳጥኑ ተገኘ፡፡ ከሳጥኑ እጅግ ደስ የሚል በዓዛ ወጣ፡፡ በዚያ ቦታም ቅዱሳን መላእክት ሲያመሰግኑ ተሰሙ፡፡ ኤጲስ ቆጶሳቱና ካህናቱም የቅዱስ እስጢፋኖስን ሥጋ በክብር በታላቅ ዝማሬ ወስደው አስቀመጡት፡፡
ከዚህም በኋላ እንዲህ ሆነ፡- በኢየሩሳሌም የሚኖር የቁስጥንጥንያ ተወላጅ የሆነ ስሙ እለእስክንድሮስ የሚባል ሰው ነበር፡፡ እርሱም ለቅዱስ እስጢፋኖስ ውብ የሆነች ቤተ ክርስቲያን ሠርቶለት ሥጋውን አፍልሰው በዚያ በክብር አኖሩት፡፡ ከ፭ ዓመት በኋላም እለእስክንድሮስ ዐረፈና ሚስቱ በቅዱስ እስጢፋኖስ አስክሬን ጎን ቀበረችው፡፡ ከሌሎች ከ፭ ዓመቶችም በኋላ ሚስቱ የባሏን አስክሬን ወደ ቁስጥንጥንያ አገር ይዛ ልትሄድ አስባ ወደ መቃብሩ ስትሄድ የባሏን አስክሬን የወሰደች መስሏት በእግዚአብሔር ፈቃድ የቅዱስ እስጢፋኖስን ሣጥን ወስዳ እስከ አስቃላን ከተማ ድረስ ተሸከመችውና በመርከብ ተሳፍራ ወደ ቁስጥንጥንያ ሄደች፡፡
የእለእስክንድሮስም ሚስት በመርከብ ስትጓዝ ጣዕም ያለው የመላእክትን ዝማሬ ሰማች፡፡ ልታየውም በተነሣች ጊዜ ሣጥኑ የቅዱስ እስጢፋኖስ ሥጋ ያለበት መሆኑን ዐወቀቸ፡፡ ወደ ኢየሩሳሌምም ለመመለስ አልተቻላትም ይልቁንም ይህ እንዲሆን የእግዚአብሔር ፈቃድ መሆኑን ዐውቃ ለዚህ ክብር ስላበቃት አመሰገነች፡፡ ቁስጥንጥንያም እንደደረሰች ለሊቀ ጳጳሱ በእግዚአብሔር ፈቃድ የቅዱስ እስጢፋኖስብ ሥጋ ይዛ እንደመጣች ላከችበት፡፡ ካህናቱና ሕዝቡም ሁሉ በታላቅ ደስታ ወጥተው በክብር ተቀበሏት፡፡ ከሥጋውም ብዙ ተአምራት ተገልጠው ታዩ፡፡ ከዚህም በኋላ ሥጋውን በበቅሎ ጭነው ሲጎትቱ ቁስጣንጢኖስ ከሚባል ቦታ ሲደርሱ የቅዱስ እስጢፋኖስን ሥጋ የያዘችው በቅሎ አልንቀሳቀስ አለች፡፡ እግዚአብሔር የቅዱስ እስጢፋኖስ ሥጋው በዚህ ቦታ እንዲኖር የፈቀደ መሆኑን ዐወቁ፡፡ ሥጋውን የተጫነው በቅሎም በሰው አንደበት ‹‹የቅዱስ እስጢፋኖስን ሥጋ በዚህ ሊያኖሩ ይገባል›› ብሎ ተናገረ፡፡ ይህንንም ያዩና የሰሙ ሁሉ እጅግ አደነቁ፡፡ የበለዓምን አህያ ያናገረ አምላክ አሁንም የቅዱስ እስጢፋኖስን ሥጋ የተሸከመችውን በቅሎ እንዳናገራት ዐውቀው ደስ አላቸው፡፡ የሀገሪቱም ንጉሥ በቦታው ላይ ውብ ቤተ ክርስቲያን ሠርተውለት ሥጋውን በውስጧ በክብር አኖሩ፡፡ ከሥጋውም ብዙ አስገራሚ ተአምራት ተፈጽመው ታዩ፡፡

የቅዱስ እስጢፋኖስ ረድኤት በረከቱ ይደርብን፣ በጸሎቱ ይማረን!
ምንጭ፡- ስንክሳር ዘወርኃ ጥቅምት

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

መስቀል ማለት ምን ማለት ነው ?

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

መስቀል ማለት ምን ማለት ነው ?

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ያበሰራት ቅዱስ መላዕክ ማን ይባላል?

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

የጥቅምት ፲፯ ማኀሌተ ጽጌ ፣ ወረብ  ፣ ዚቅ እና መዝሙር

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

🫃👉መንታ ወንድና ሴት ቢወለዱ ክርስትና እንዴት  ይነሳሉ⁉️
👉ሴት በወር አበባ ጊዜስ⁉️
👉 ወንድ ህልመ ሌሊት ቢያጋጥመው ለስንት ቀን ይረክሳል ⁉️
👉 ሰባቱ አጽዋማት እነማን ናቸው⁉️
👉 አምስቱ አዕማደ ምስጢራት ማን ናቸው⁉️
👉 ከአስርቱ ትዕዛዛት ውጪ ያለው ትዕዛዝ ምነው⁉️


⛪️ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን አንፃር መልሱን ይመልከቱ⛪️
                    👇👇👇👇

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

💁‍♂⛪️እርሶ በቴሌግራም የቱን ቢያገኙ ደስ ይሎታል⁉️

Читать полностью…
Subscribe to a channel