mezmuredawit | Unsorted

Telegram-канал mezmuredawit - ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

28629

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ የመዝሙር ግጥሞችን እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን" መዝ 150÷6 " አሕዛብ ሁላችሁ፥ እጆቻችሁን አጨብጭቡ፥ በደስታ ቃልም ለእግዚአብሔር እልል በሉ።" (መዝሙረ ዳዊት 47:1) ለማንኛውም ሀሣብ, ጥቆማ, አስተያየት @Kidusyared_comment_bot ላይ ቢያስቀምጡልን ይደርሰናል

Subscribe to a channel

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

ቃልሽ ተቀየረ

ቃልሽ ተቀየረ አንቺ እየሩሳሌም
ሆሳዕና እንዳላልሽ ክብር በአርያም
ስቀለው ስቀለው ብለሽ መጮህሽ
ያልሰጠሽ ምን አለ ያጎደለብሽ

ደም ግባቱ ጠፍቶ የአብ አንድ ልጅ
ሲገርፉት አመሹ በቀያፋ ደጅ
አፉን አልከፈተም መልስንም ለመስጠት
የውኃውን አምላክ ሃሞት ሲያጠጡት
        /አዝ = = = = =      
መቆም እስኪያቅተው ሰውነቱ ዝሎ
መከራውን አየ ስለኛ ኃጢያት ብሎ
የአማልክት አምላክ ተንገላታ እንደሰው
የጠፋው አዳምን ቤቱ ሊመልሰው
/አዝ = = = = =
በሸላቾቹ ፊት ዝም እንደሚል በግ
ዝምታን መረጠ መልካምን ለማድረግ
ለሰው ያለው ፍቅር ወሰን አልነበረው
እርሱ እየሸሸው በፍቅር ተከተለው

👉ዘማሪት ለምለም ከበደ

#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።

  ╔✞═════●◉❖◉●════✞╗
       ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞
❖ @
enamsgn @enamsgn
❖ @enamsgn @enamsgn
       ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞
╚✞═════●◉❖◉●════​✞╝
✍ ወድሰኒ

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

የአእላፋት ዝማሬ ኦርቶዶክሳዊ መዝሙሮችን በስልክዎ ለማጥናት ከስር ያለዉን ሊንክ (JOIN) የሚለዉን በመንካት ይቀላቀሉ አሁኑኑ እንዳያመልጥዎት 🎉

/channel/addlist/gpX29GzfGs43MWE0

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

ና ና የምስጋና ጌታ

ና ና የምስጋና ጌታ ና ና የምሕረት ጌታ(፪)
ማዳንህ ተገኝታለችና ሰላምህ ተገኝታለችና(፪)

ኢየሩሳሌም ሆይ ምስጋና ጀምሪ
መለከትን ንፊ ነጋሪት ጎስሚ
ሰላምሽ ታውጇል መዳንሽም ቀርቧል
ጌታ ሊጎበኝሽ ከበራፍሽ ቆሟል
       /አዝ = = = = =
ያልታደልሽው ሀገር ጌርጌሴዮን ሆይ
ለምን ተቃወምሽው አምላክሽን ስታይ
የከተማውን በር መዝጊያውን ቆልፈሽ
ከሩቅ የሸኘሽው ሲመጣ ሰላምሽ
       /አዝ = = = = =
የቢታንያ ድንጋይ አንደበት አውጥቶ
ምስጋና ጀመረ አምላኩን ለይቶ
ሣርና ቅጠሉ ዘንባባው ሰገደ
ፍጥረት ሊያመሰግን አምላኩን ወደደ
       /አዝ = = = = =
ሕጻን ሽማግሌ ምስጋና ሲያቀርቡ
ተቆልፎ ነበር ፈሪሳዊ ልቡ
ዛሬም ለምስጋና ልባችን ይለወጥ
የሆሣዕና ጌታ ይመላለስበት

👉ሊቀመዘምራን ይልማ ኃይሉ

#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።

  ╔✞═════●◉❖◉●════✞╗
       ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞
❖ @
enamsgn @enamsgn
❖ @enamsgn @enamsgn
       ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞
╚✞═════●◉❖◉●════​✞╝
✍ ወድሰኒ

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

💁‍♂⛪️እርሶ በቴሌግራም የቱን ቢያገኙ ደስ ይሎታል⁉️

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

https://youtu.be/3uqGKn8kXd0

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

🗓⚪️#አንድ_ጥያቄ

●✥ ከመንፈስ ፍሬዎች መካከል ቀዳሚነትን የሚይዘው የትኛው ነው❓ ●✥

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

https://youtube.com/shorts/Xk4rG22YVgI?si=mUXIQT5WhwBQqiGY

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

💕ከዘማሪያን የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይ ፈ ል ጋ ሉ ? 🔔 💕

[┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
[┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ዘማሪ አቤል መክብብ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕ዘማሪት ሲስተር ህይወት ተፈራ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕ዘማሪ ዲያቆን ሙሉቀን ከበደ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ዘማሪት ፋሲካ ድንቁ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛


🌷👥 የሁሉንም ዘማሪያን መዝሙር ለማግኘት 🔔 👇
🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

የ100 ብር ካርድ ሊለቀቅ ነው 9 ደቂቃ ብቻ ነው የቀራው። ቶሎ ከስር JOIN ሚለውን ነክታቹ JOIN REQUEST ላኩ 🏃‍♀️🏃‍♂️

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

መጋቢት ፳፯ /27/


በዚችም ቀን የክብር ባለቤት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ አለም ድኅነት በሥጋ ተሰቀለ።

ፈጣሪዋ በዕንጨት መስቀል ላይ ተዘርግቶ ተሰቅሎ በአየችው ጊዜ ፀሐይ ጨለመች እርሱም ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም የነሣትን ለባዊት ነባቢት የሆነች ነፍሱን ከሥጋው ለያት ሐዋርያ ጴጥሮስ በሥጋ የሞተ ሲሆን በመለኮት ሕያው ነው እንዳለ ነፍሱ ከመለኮት ሳትለይ ከሥጋ ተለየች በዚያ ጊዜ ሥጋ ከመለኮት ሳትለይ በዕንጨት መስቀል ላይ ተሰቅሎ ነበር።

እንዲሁም ነፍስ ከመለኮት ጋራ አንድ ሁና እሥረኞች ነፍሳትን ትፈታቸው ዘንድ ወደ ሲኦል ወረደች።

እርሱ ከሰማያት በላይ ከፍ ከፍ ያለ ልዑለ ባሕርይ ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋራ በጌትነቱ ዙፋን ተቀምጦ ያለ ለእርሱም ምስጋና የክብር ክብር ገንዘቡ የሆነ ራሱን ሠውቶ ያደነን የመንግሥቱን ደጆች በፈሳሽ ደሙ የከፈተልን ለእርሱ ስግደት አምልኮት ይገባዋል ለዘላለሙ የመስቀሉም በረከት በላያችን ይደር አሜን።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

♥️🌹ጋብቻ ምን ማለት ነው⁉️🌹
ጋብቻ እና የዘር ሐረግ ምን ያገናኛቸዋል⁉️
ጋብቻ የሚፈቀደው ከስንት ዓመት ጀምሮ ነው⁉️
ሴት ሙሽራ ከወንድ ሙሽራ ቀኝ ለምን ትሆናለች⁉️
🌹ሙሽሮች በጫጉላ ጊዜያቸው ለምን አይጾሙም⁉️
ያገባሁት ሰው ካልተመቸኝ ብፈታው ምን ችግር አለው⁉️
እንደምንጋባ እርግጠኛ ከሆንን ግብረስጋ ግንኙነት ብንፈጽም ምን ችግር አለው⁉️

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

የአለቃ ገ/ሐናን #ታሪካቸውን እና እማይጠገቡ #ቀልዶቻቸውን ማግኘት ማንበብ ለምትፈልጉ ከታች ባሉት ሊንኮች ይቀላቀሉን
👇👇👇👇👇👇👇

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

በ30 ሰከንድ ውስጥ ስለሚጠፍ ምርጥ ቻናል ነው ይቀላቀሉ 👇

/channel/addlist/isQbYInIIR0zNTc0

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

ልብን_በሐዘን_የሚመስጠው_መልክአ_ሕማማት_ክፍል_የሕማማት_ሰላምታ
📌በዓብይ ጾም በሰሞነ ሕማማት እና በአርብ ስቅለት የሚባል በአራራይና በእዝል

📌 በመምህር_መንክር_ሐዲስ

🖋ሰብስክራይብ(subscribe) ማድረጎን አይርሱ!

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

6. #ገብርኄር
  ገብርኄር ማለት ታማኝ አገልጋይ ማለት ነው፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ አገልጋዮችና አገልግሎታቸው በምሳሌ ያስተማረው ትምህርት የሚነገርበት ሳምንት ነው፡፡

ይኽውም አንድ ባለጸጋ ሰው ወደ ሌላ ሀገር ከመሔዱ አስቀድሞ ለሦስት አገልጋዮቹ እንደየአቅማቸው አንድ፣ ሁለት እና አምስት መክሊት እንደሰጣቸውና ከሔደበትም በተመለሰ ጊዜ ሁሉንም ጠርቶ ከነትርፉ መክሊቱን እንዲመልሱለት እንደጠየቃቸው ያስተማረበት ነው፡፡ ሁለቱ አገልጋዮች በእጥፍ አትርፈው ባለአምስቱ ዐሥር አድርጎ፣ ባለሁለቱም አራት አድረጎ መልሰውለታል፡፡ ባለአንዱ መክሊት ደግሞ መክሊቱን መሬት ቆፍሮ ቀብሮት ነበርና ሳያተርፍበት ያንኑ መልሶለታል፡፡ የቀበረበትንም ምክንያት ሲናገር ‹‹ጌታ ሆይ አንተ እኮ ካልዘራህበት የምታጭድ ካልበተንህበት የምትሰበስብ ጨካኝ ሰው መሆንህን አውቃለሁ፤ ስለዚህ ፈራሁ ሔጄም መክሊትህን በምድር ቀበርኩት›› ብሏል፡፡ ባለጸጋውም አትርፈው የመለሱለትን ‹‹እናንተ ታማኝ አገልጋዮች በጥቂቱ ታምናችኋልና በብዙ እሾማችኋለሁ ወደ ጌታ ደስታ ግቡ›› ብሎ ሾሟቸዋል፡፡ ቀብሮ የመለሰውን ግን ‹‹አንተ ክፉና ሀኬተኛ ባሪያ…አትርፈህ ብትመልስ በተሸለምክ ነበር፤ ስለዚህ ያለውን ውሰዱበትና ዐሥር ላለውም ጨምሩለት ላለው ይጨመርለታል ከሌለው ግን ያንኑ ይወስዱበታል፤ እርሱን ግን ወደ ውጭ አውጥታችሁ ጣሉት›› ብሎ ፈረደበት፤ (ማቴ 25፥14-30)፡፡
   በምሰሌያዊ ትምህርት ባለጸጋ የተባለው የሁሉ ጌታ እግዚአብሔር ነው፤ አገልጋዮች የተባሉት ምእመናን ናቸው፤ መክሊት የተባለው ደግሞ ለምእመናን የተሰጣቸው መንፈሳዊ ጸጋዎች ናቸው፡፡ አትርፈው የመጡት በተሰጣቸው ጸጋ ለራሳቸው ተጠቅመው ለሌላውም ተርፈው መልካም አርአያና ምሳሌ ሆነው የሚኖሩ አገልጋዮች ምሳሌ ሲሆኑ የተሰጠውን መክሊት ቀብሮ ሰንብቶ ያንኑ የመለሰው ደግሞ የተሰጠውን ጸጋና ዕድሜን በከንቱና በዋዛ ነገር ሲያባክን  የሚኖር ምእመን ምሳሌ ነው፡፡ አትርፈው የመጡት የተሸለሙት መንግሥተ ሰማያትን ሲሆን ቀብሮ የመጣው ደግሞ የተፈረደበት ትሉ ወደማያንቀላፋ እሳቱ ወደማይጠፋ ገሃነመ እሳት ነው፡፡ የተማረውን በልቡ ይዞ የኖረ ሰው፣ ሃይማኖት በልብ ነው፤ መናገር አያስፈልግም፤ የልቤን እግዚአብሔር ያውቀዋል፤ የእንጀራ ጉዳይ ነው ምን ላድርግ? እያሉ ራሳቸውን የሚያታልሉ ባለሥልጣናት የባለአንድ መክሊቱ አገልጋይ ምሳሌ ናቸው፡፡ ሳምንቱ ገብርኄር ተብሎ የተሰየመው በታማኞቹ አገልጋዮችና በታማኝነታቸው ነው፡፡
   በዚህ ሰንበት የሚሰበከው ምስባክ ‹‹አምላኬ ሆይ ፈቃድህን ለማድረግ ወደድሁ ሕግህም በልቤ ውስጥ ነው፤ በታላቅ ጉባኤ ጽድቅን አወራሁ እነሆ ከንፈሮቼን አልከለክልም አቤቱ አንተ ጽድቄን ታውቃለህ›› (መዝ 39፥8-9) የሚለው ነው፡፡ እኛም ሳምንቱን ስንዘክር ከእግዚአብሔር የተሰጠንን ጸጋ መጠቀም እንጂ መቅበር እንደሌለብን ራሳችንን እየጠየቅን መሆን አለበት፡፡ ቀሪ ዘመናችንንም ስላለፈው ዘመን ኃጢአት ንስሐ ለመግባት መወሰን ይገባናል፡፡
         ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!!
ምንጭ፦ መጽሐፍ ቅዱስ ፣  ሰባቱ አጽዋማት
           ━━━━━✦📖 ❖ 📖✦━━━━━

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

8. 🌿 #ሆሣዕና
   ሆሣዕና ማለት አሁን አድን ማለት ነው፡፡ ይህች ሰንበት ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ኢየሩሳሌም ከተማ ሲገባ የእስራኤል ሕዝብ የዘንባባ ዝንጣፊ ይዘው ሆሣዕና በማለት እየዘመሩ ያጀቡበት ዕለት መታሰቢያ ሰንበት ናት፡፡ ይህም ኢየሱስ ክርስቶስ ቤተ ፋጌ በደረሰ ጊዜ ሁለት ደቀ መዛሙርትን ልኮ የታሰረች አህያና ውርንጫዋን ይዘው እንዲመጡ አዘዛቸው፤ ካመጡለት በኋላም ጌታ ተቀመጠባቸው፤ ሕዝቡም ልብሳቸውን ሌሎችም ዘንባባን እየዘነጠፉ በመንገድ ላይ እያነጠፉ ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፤ ሆሣዕና በአርያም እያሉ ይጮሁ ነበር፡፡ (ማቴ 21፥1-17)፡፡
   ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህች ሰንበት ያደረጋቸው ነገሮች የየራሳቸው ትንቢትና ምሳሌ አላቸው፤ አህያዋና ውርንጫዋ የሁለቱ ኪዳናት (የሐዲስ ኪዳንና የብሉይ ኪዳን) ምሳሌ ናቸው፡፡

አህያ የተመረጠችበት ምክንት
1. ትንቢቱ ይፈጸም ዘንድ፡- ‹‹አንቺ የጽዮን ልጅ እጅግ ደስ ይበልሽ እነሆ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ የሆነው ትሑትም ሆኖ በአህያዋ በአህያይቱም ግልገል በውርንጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል›› (ዘካ 9፥9)፡፡
2. ትሕትናን ለማስተማር፡- አህያ በብዙዎች ዘንድ የተናቀች እንስሳ ነበረች፤ በአህያ መቀመጥም ራስን ማዋረድ ነውና ጌታም ትሕትናን ለማስተማር በተናቀችው አህያ ተቀምጧል፡፡ አንድም የዓለም ጥበብና ክብር በእግዚአብሔር ዘንድ ሞኝነትና ውርደት መሆኑን ለማስረዳት ዓለም የሚያደንቃቸውን ትቶ ዓለም የናቀውን ተጠቅሞበታል፡፡
3. እኔ የሰላም አምላክ ነኝ ሲል፡- አህያ የሰላም ምሳሌ ነች፡፡ በጥንት ዘመን ነቢያት በአህያ ተቀምጠው የመጡ እንደሆነ መልካም የምሥራች ትንቢት ሊናገሩ መሆኑ ይታወቃል፤ በፈረስ ተቀምጠው ከመጡ ደግሞ ስለመቅሰፍት ወይም መአት ትንቢት እንደሚናገሩ ይታወቅ ነበርና፡፡
4. እኔ የቅርብ አምላክ ነኝ ሲል፡- በአህያ ላይ የተቀመጠ ሰው ቢያሳድዱት አያመልጥምና ብትፈልጉኝ እኔ ቅርባችሁ ነኝ ታገኙኛላችሁ ሲለን ነው፤ (ኤር 23፥23)
5. በትሑት ሰው ልቦና አድሬ እኖራለሁ ሲል፡- አህያ ብዙ ጫንክብኝ፣ ጎዳኸኝ ብላ ሳታማርር ራሷን ዝቅ አድርጋ ባለቤቷን ታገለግላለችና እኔም ራሱን ዝቅ አድርጎ በሚገዛልኝ ትሑት ሰው ልብ አድሬ እኖራለሁ ሲል ነው፡፡
አህዮቹን ፈትታችሁ አምጡ ለምን አለ?
   አባታችን አዳም ከዲያብሎስ እስራት የሚፈታበት ጊዜ መድረሱን ለማመልከት ነው፤ አንድም ለደቀ መዛሙርቱ የማሰርና የመፍታት ሥልጣን (ሥልጣነ ክህነት) መስጠቱን ለማጠየቅ ነው፤ (ማቴ 16፥18-19 ፣ ዮሐ 20፥22-23)፡፡
ሕፃናቱ ለምን አመሰገኑት?
   አስቀድሞ ዳዊት በመዝሙሩ ‹‹ከሕፃናትና ከሚጠቡ ለራስህ ምስጋና አዘጋጀህ›› (መዝ 8፥2) ብሎ የተናገረው ትንቢት ይፈጸም ዘንድ ነው፡፡ ይህ የመዝሙር ክፍል የዚህች ሰንበት ምስባክም ነው፡፡

ሕፃናቱ ዘንባባ ይዘው የዘመሩበት ምክንያት
ሀ. ዘንባባ በእስራኤል ባሕል የሰላም የደስታ ምልክት ስለሆነ፤ (ነህ 8፥14-15)
ለ. የዘንባባ የሚዋጋ እሾህ የእግዚአብሔር ምሳሌ ነው፤ ‹‹እግዚአብሔር ተዋጊ ነው›› ይላልና ዘጸ 14፥14፡፡
ሐ. ዘንባባ የመለኮት ምሳሌ ነው፤ ዘንባባ ቢደርቅ እንኳ በእሳት ይለበለባል እንጂ አይነድምና፡፡ የመለኮትንም ምጥቀቱንና ጥልቀቱን የሰው ኅሊና ሊመረምረው አይችልም፡፡

ጾም ጸሎታችን የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ይቀበልልን አሜን፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦ መጽሐፍ ቅዱስ ፣  ሰባቱ አጽዋማት

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

ቃልሽ ተቀየረ

ቃልሽ ተቀየረ አንቺ እየሩሳሌም
ሆሳዕና እንዳላልሽ ክብር በአርያም
ስቀለው ስቀለው ብለሽ መጮህሽ
ያልሰጠሽ ምን አለ ያጎደለብሽ

ደም ግባቱ ጠፍቶ የአብ አንድ ልጅ
ሲገርፉት አመሹ በቀያፋ ደጅ
አፉን አልከፈተም መልስንም ለመስጠት
የውኃውን አምላክ ሃሞት ሲያጠጡት
        /አዝ = = = = =      
መቆም እስኪያቅተው ሰውነቱ ዝሎ
መከራውን አየ ስለኛ ኃጢያት ብሎ
የአማልክት አምላክ ተንገላታ እንደሰው
የጠፋው አዳምን ቤቱ ሊመልሰው
/አዝ = = = = =
በሸላቾቹ ፊት ዝም እንደሚል በግ
ዝምታን መረጠ መልካምን ለማድረግ
ለሰው ያለው ፍቅር ወሰን አልነበረው
እርሱ እየሸሸው በፍቅር ተከተለው

👉ዘማሪት ለምለም ከበደ

#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።

  ╔✞═════●◉❖◉●════✞╗
       ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞
❖ @
enamsgn @enamsgn
❖ @enamsgn @enamsgn
       ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞
╚✞═════●◉❖◉●════​✞╝
✍ ወድሰኒ

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

🇪🇹 የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን አስተምህሮ ና ስርአትን የጠበቁ የትኞቹን መዝሙራት ማግኝት ይፈልጋሉ❓

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

📌ሰላም ውድ የወድሰኒ በቴሌግራም ተከታታዮቻችን እንደሚታወቀው የወድሰኒን የመዝሙር ቻናል ለማስፋት በዮቲዩብ ቻናል መጥተናል በይዘቱ አዳዲስ የሆኑ ነገሮችን አካተን ወደ እናንተ ለማድረስ ዝግጅታችንን ጨርሰናል።

📌ከእናንተ የሚጠበቀው ከላይ ያለውን ሊንክ ተጠቅማችሁ Subscriber እንድታደርጉልን ነው።

ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን! አሜን

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

🙏 በማርያም ይሄን ቻናል ሳታዩ እንዳታልፉት ✅JOIN✅ የምትለውን ብቻ ይንኳት።🙏

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

⁉️ጥያቄና መልስ
🌺🌺🌺🌺

❤️፩. ኦርቶዶክስ ማለት ምን ማለት ነው?❤️

፪. ጌታ ለምን ድንግል ከሆነች ማርያም ተወለደ? (ለምን በድንግልና ተወለደ?)

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

የዓብይ ጾም 7ኛ ሳምንት ምን በመባል ይታወቃል?

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

የዓብይ ጾም 6ኛ ሳምንት ምን በመባል ይታወቃል?

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

7. ኒቆዲሞስ
   ኒቆዲሞስ ከፈሪሳውያን ወገን የሆነ የአይሁድ አለቃና መምህር ነበር፡፡ ኒቆዲሞስ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የምናገኘው መምህር መሆኑን የሚከተለው ጽሑፍ ያስገነዝበናል፡፡ ‹‹ከፈሪሳውያን ወገን የአይሁድ አለቃ የሆነ ኒቆዲሞስ የሚባል አንድ ሰው ነበረ፤ እርሱም በሌሊት ወደ ኢየሱስ መጥቶ መምህር ሆይ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ከሆነ በቀር አንተ የምታደርጋቸውን እነዚህን ምልክቶች ሊያደርግ የሚችል የለምና መምህር ሆነህ ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደ መጣህ እናውቃለን›› አለው፡፡ ኢየሱስም መልሶ ‹‹እውነት እውነት እልሃለሁ ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም›› አለው፡፡ ኒቆዲሞስም ‹‹ሰው ከሸመገለ በኋላ እንዴት ሊወለድ ይችላል?›› አለው፡፡ ኢየሱስም ‹‹እውነት እውነት እልሃለሁ ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካለተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም፤ ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው፤ ከመንፈስም የተወለደ መንፈስ ነው፤ ዳግመኛ ልትወለዱ ያስፈልጋችኋል ስላልሁ አታድንቅ፤ ነፋስ ወደሚወደው ይነፍሳል፤ ድምፁንም ትሰማለህ ነገር ግን ከወዴት እንደመጣ ወዴትም እንዲሔድ አታውቅም፤ ከመንፈስ የተወለደ ሁሉ እንዲሁ ነው›› አለው፤ (ዮሐ 3፥1-8)፡፡ ከውኃና ከመንፈስ ዳግም መወለድ የእግዚአብሔር ልጆች ለሆኑት ልዩ መገለጫ ነው፡፡
  
ኒቆዲሞስ በሌሊት እየመጣ ከኢየሱስ ክርስቶስ እግር ሥር ቁጭ ብሎ ወንጌልን ይማር ነበር፡፡ ሰንበቱ በእርሱ ስም የተሰየመው ሥራውን ለመዘከር ነው፡፡ በሌሊት መጣ የሚለው በምሥጢር ሲተረጎም አንደኛ ወደፊት በቀን ይመጣልና ከዚያ አስቀድሞ መጣ ለማለት ነው፤ አንድም በኋላ በዕለተ ዓርብ የጌታን ሥጋ ከመስቀሉ አውርዶ ገንዞ ለመቅበር ይመጣልና ከዚያ አስቀድሞ ለመማር መጣ ለማለት ነው፡፡ አንድም ፀሐየ ጽድቅ ክርስቶስን ሳያምን በፊት በኦሪት ጨለማ እያለ መጣ ለማለት በሌሊት መምጣቱን ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን አመሥጥረው ያስተምራሉ፡፡
ኒቆዲሞስ ከመዓልት ይልቅ በሌሊት መማር የመረጠበት ምክንያቶች
ሀ. ውዳሴ ከንቱ ሽቶ፦ እርሱ ራሱ የአይሁድ አለቃና መምህር ስለነበር ከሌላ መምህር (ከኢየሱስ ክርስቶስ) እግር ሥር ተቀምጦ ሲማር አይሁድ ቢያዩት ሳይገባው ነው መምህር ያልነው ብለው ይነቅፉት ነበር፡፡ በሌላ አገላለጽ ኒቆዲሞስ መማርን ይፈልጋል ደቀ መዝሙር መባልን ግን አይፈልግም፡፡ በአንጻሩም ምሁረ ኦሪት ነበረና መምህር መባልን ይፈልጋል፡፡

ለ. የአይሁድን ዛቻና ማስጠንቀቂያ ፈርቶ፦ አይሁድ በክርስቶስ የሚያምንና ትምህርቱንም የሚሰማ ቢገኝ ከማኅበራችን ይለይ ቤቱም የጉድፍ መጣያ ይሁን ብለው ተስማምተው ሕግ አውጥተው ነበርና ቅጣቱን ፈርቶ ላለመታየት ሌሊት መማርን መርጧል፡፡

ሐ. አእምሮ ልቡናውን ሰብስቦ ለመማር ፈልጎ፦ መዓልት ዓይንን፣ ጆሮንና አእምሮን የሚሰርቅ ነገር ብዙ ነውና ከቀን ይልቅ ሌሊትን መረጠ፡፡ አንድም አለቃ እንደመሆኑ ቀን ቀን የራሱ ሥራ ይበዛበት ነበረና ሌሊትን መረጠ፡፡
   በዚህ ሳምንት ቤተ ክርስቲያን ስለ ምሥጢረ ጥምቀት ታስተምራለች፡፡ ጥምቀት ሰው ከአብራከ መንፈስ ቅዱስ ከማኅፀነ ዮርዳኖስ ዳግመኛ ተወልዶ የክርስቶስ አካል የማኅበረ ምእመናንም አባል የሚሆንበት ምሥጢር ነው፡፡ በጥምቀት ኃጢአት ይሰረያል፤ የእግዚአብሔር ልጅነት ይሰጣል፤ ልጅ ለሆነው ሁሉ ርስት ገነትና መንግሥተ ሰማያትም ይወረሳል፡፡
   በዚህ ሰንበት የሚሰበከው ምስባክ ‹‹ልቤን ፈተንኸው በሌሊትም ጎበኘኸኝ ፈተንኸኝ ምንም አላገኘኽብኝም፤ የሰውን ሥራ አፌ እንዳይናገር ፈቃዴ ነው››፤ (መዝ 16፥3-4) የሚለው የቅዱስ ዳዊት መዝሙር ነው፡፡
   ዛሬ ብዙዎቻችን ባለሥልጣን ስለሆንን በቤተ ክርስቲያን ቅጽር ውስጥ ባለው መሬት ላይ ቁጭ ብለን መማር ያሳፍረናል፤ ሌሎቻችንም ባለሀብት ስለሆንን ለገንዘባችን እንጂ ለእግዚአብሔር የሚሆን ጊዜ አጥተናል፤ ሌሎች ደግሞ መምህር ነኝ አለቃ ነኝ በቅቻለሁ ነቅቻለሁ ትምህርት አያስፈልገኝም በማለት ከቤቱ ርቀናል፡፡ ቀሪዎቻችን ደግሞ የየራሳችን ምክንያት አበጅተናል፡፡ ኒቆዲሞስ ግን ከጌታ እግር ሥር ቁጭ ብሎ ለመማር እነዚህ ሁሉ ምክንያቶች አልከለከሉትም፡፡ እነዚህን ሁሉ ተጋፍጦ በመማሩ ከዮሴፍ ጋር የክርስቶስን ሥጋ ገንዞ ለመቅበርና በመጽሐፍ ቅዱስ ተመዝግቦ በታሪክ ለመዘከር በቅቷል፤ (ዮሐ 19፥38-42)፡፡ የእኛንም ሕይወት መቃኘት እንደሚገባን ቤተ ክርስቲያን በዚህ ሳምንት ከኒቆዲሞስ ሕይወት ጋር በማነጻጸር ታስተምረናለች፡፡

#
ጾም ጸሎታችን የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ይቀበልልን አሜን፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦ መጽሐፍ ቅዱስ ፣  ሰባቱ አጽዋማት

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

📌 የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ?

📌 ሊቀ መዝሙራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
📌 ሊቀ መዝሙራን ይልማ ኃይሉ
📌 ዘማሪ አርቲስት ይገረም ደጀኔ
📌 ዘማሪ ገ/ዮሐንስን ገ/ፃዲቅ
📌 ቀሲስ ምንዴዬ ብርሀኑ
📌 ቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ
📌 ዘማሪ ምርትነሽ ጥላሁን
📌 ዘማሪት አቦነሽ አድነው
እና የሌሎችንም ...........


የዘማሪዎችው መዝሙሮችን ለማግኘት ከስር Join የሚለውን ንኩት 🔻🔻🔻
                   👇👇👇

/channel/+2ua4-eAbNTI1MTRk
/channel/+2ua4-eAbNTI1MTRk

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

ኃይልህ ሲገለጥ

ኃይልህ ሲገለጥ በሰማይ❨፪×❩
አቤት ማን ይቆም ይሆን ከፊትህ
ማን ይቆም ይሆን❨፪×❩ ከፊትህ
ማን ይቆም ይሆን

አቤት ቀንደ መለከት ሲነፋ
አዋጅ ሲታወጅ በይፋ
ጻድቃን ሲጠሩ ለተድላ
ምን ይሆን የእኛ ተስፋ
    /አዝ = = = = =
አቤት መላእክት ሰማዩን ሲያርሱት
ቀድመው ሲሰሙ መባርቅት
ያልታየና ያልተሰማ
ድምጽ ሲሰማ ከራማ
    /አዝ = = = = =
አቤት ሰባቱ ነፋስ ተከፍተው        
ምድርን ሲያውኳት ቀዝፈው
ሲታዘዝ የባሕር ሞገድ
ምድሪቷን ሊከድናት ለፍርድ
    /አዝ = = = = =
አቤት ሲጠሩ ጻድቃን ቅዱሳን
መልካም የሰሩ ቡሩካን
በምድር የሰሩ ትሩፋት
ሲያቀርቡ ለአምላክ ስብሐት
    /አዝ = = = = =
አቤት ኃጥአን ግን ለፍርድ ሲጠሩ
በጨለማ ዓለም ሊቀሩ
የማይጠቅም ዋይታ ሆኖ
መዋረድ ይሆናል አዝኖ
/አዝ = = = = =
አቤት ሲጠሩ ጻድቃን ቅዱሳን
መልካም የሰሩ ቡሩካን
በምድር የሰሩ ትሩፋት
ሲያሰሙ ለአምላክ ስብሐት
    
👉ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ

#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።

   ╔​✞═══●◉❖◉●═══✞╗
       ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞
   ❖ @
mezmuredawit  ❖
   ❖ @mezmuredawit  ❖
   ❖ @mezmuredawit  ❖  
      ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞
  ╚✞═══●◉❖◉●═══​✞╝

✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

👑  ስለ ንጉስ ቴዎድሮስ     🤴


🩸 ትንቢት የተነገረለትን ንጉስ የቴዎድሮስ የሚነሳበት አስደናቂና ምስጢራዊ ስፍራ

🩸 እውነት ትንቢት የተነገረለት ንጉስ ቴዎድሮስ ይመጣል ?

🩸 በፍካሬ ኢየሱስና በገድለ ፊቅጦር ስለ ትንቢታዊው ንጉስ ቴዎድሮስና ተጽፎ ይገኛል

🩸 የየረር ተራራ አስገራሚ ምስጢሮች


ለእነዚህ ጥያቂዎች መልስ ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ

እዚህ ጋር ይጫኑ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇
➢ JOIN  ➢  JOIN  ➢ JOIN ➢JOIN
➢ JOIN  ➢  JOIN  ➢ JOIN ➢JOIN
➢ JOIN  ➢  JOIN  ➢ JOIN ➢JOIN
➢ JOIN  ➢  JOIN  ➢ JOIN ➢JOIN

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

❓ምን አይነት መዝሙር ማግኘት ይፈልጋሉ   የምት ፈልጉትን መዝሙር በመምረጥ ተቀላቀሉ ❗️❗️

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

📍 ሕማማት 📍

📍በዲያቆን ሄኖክ ሃይሌ ተጽፎ በ ቢኒያም ብርሃኑ የተተረከውን ሕማማት የተሰኘውን መጽሐፍ በትረካ ለማግኘት
👇👇👇

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

💕ከዘማሪያን የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይ ፈ ል ጋ ሉ ? 🔔 💕

[┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
[┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ዘማሪ አቤል መክብብ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕ዘማሪት ሲስተር ህይወት ተፈራ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕ዘማሪ ዲያቆን ሙሉቀን ከበደ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ዘማሪት ፋሲካ ድንቁ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛


🌷👥 የሁሉንም ዘማሪያን መዝሙር ለማግኘት 🔔 👇
🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧

Читать полностью…
Subscribe to a channel