mezmuredawit | Unsorted

Telegram-канал mezmuredawit - ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

28629

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ የመዝሙር ግጥሞችን እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን" መዝ 150÷6 " አሕዛብ ሁላችሁ፥ እጆቻችሁን አጨብጭቡ፥ በደስታ ቃልም ለእግዚአብሔር እልል በሉ።" (መዝሙረ ዳዊት 47:1) ለማንኛውም ሀሣብ, ጥቆማ, አስተያየት @Kidusyared_comment_bot ላይ ቢያስቀምጡልን ይደርሰናል

Subscribe to a channel

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

​​✞ ዮሐንስኒ ሐሎ በሔኖን ✞

ዮሐንስኒ ሐሎ ያጠምቅ በሔኖን/2×/
ያጠምቅ በሔኖን

መንግሥተ ሠማያት ቀርባለች እያለ
ዮሐንስ ሲያሰተምር ማነው ያስተዋለ
እንደ ተናገረ አዋጅ ነጋሪው
ተራራው ዝቅ ይበል ይሙላ ጎድጓዳው

         /አዝ * * * * *

እድገቱ ምናኔ ትምህርቱ ንስሐ
የጣዝማ ማር በልቶ ኖረ በበረሃ
መጓዝ እንዲያስችለን በሕይወት ጎዳና
ላይ ታቹ ይደልደል ጎባጣውም ይቅና

         /አዝ * * * * *

ሲኖር በምናኔ በሄኖን በረሃ
ያጠምቅ ነበረ ዮሐንስ በውሃ
በማየ ዮርዳኖስ በዮሐንስ እጅ
ጌታ ተጠመቀ ድኅነትን ሊያውጅ

         /አዝ * * * * *

ጌታውን አጥምቆ ለክብር የሚበቃ
ከእናቱ ማሕጸን ተገኘ ምርጥ ዕቃ
ኤልሳቤጥም ለክብር ሆና የታደለች
መልካም የነፍስ አባት መጥምቁን ወለደች
ዮሐንስኒ ሐሎ ያጠምቅ በሔኖን/፫/

#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።

   ╔​✞═══●◉❖◉●═══✞╗
       ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞
   ❖ @
mezmuredawit  ❖
   ❖ @mezmuredawit  ❖
   ❖ @mezmuredawit  ❖  
      ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞
  ╚✞═══●◉❖◉●═══​✞╝

✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

<<በዚያም ምድር መንጋቸውን በለሊት ሲጠብቁ በሜዳ ያደሩ እረኞች ነበሩ እነሆም የጌታ መላእክ ወደእነርሱ ቀረበ የጌታ ክብርም በዙሪያቸው አበራ ታላቅ ፍርሀትም ፈሩ መላእኩም እንዲህ አላቸው እነሆ ለህዝብ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምስራች እነግራቸዋለሁ እና አትፍሩ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና>>

የቅዱስ ሉቃ ወንጌል ፪-፰

#እንኳን_ለአምላከ_አማልክት_ወእግዚአ_አጋእዝት_ወንጉሠ_ነገሥት_ወልደ_እግዚአብሔር_ሕያው_ወወልደ_ማርያም_ሥግው_ኢየሱስ_ክርስቶስ_ከሰማየ_ሰማያት_ወርዶ_ከሁለት_አካል_አንድ_አካል_ከሁለት_ባሕርይ_አንድ_ባሕርይ_አድርጎ_ያለመከፈል_ያለመለወጥ_ከእመቤታችን_ከቅድስተ_ቅዱሳን_ከንጽሕተ_ንጹሐን_ከድንግል_ማርያም_ከሥጋዋ_ሥጋን_ከነፍሷም_ነፍስን_ነስቶ_ያለ_ዘርዓ_ብእሲ_በፍጹም_ተዋሕዶ_በዓለም_ለዓለም_ለታየባት_ተወልዶ_ላዳነን_ለቅድስት_ልደቱ_በሰላም_አደረሳችሁ።

መልካም በዓል


✍ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

✞ ድንግል ፈጣሪዋን ወለደችው ✞

ድንግል ፈጣሪዋን ወለደችው
በመጠቅለያም ጠቀቀለለችው
የለምና ስፍራ ለንግዶች ማረፊአ
ግርግም አስተኛችው በከብቶች ማደርያ /2/

ጨነቃት ጠበባት የዳዊት ከተማ
የጌታ መወለድ ታምሩ ሲሰማ
ወረደ መልአኩ ምስራች ሊያወራ
የህፃኑ ክብር በምድር አበራ
ይህ ሚስጢር ግሩም ነው ከቶ የማይነገር
ማርያምም በልቧ ትጠብቀው ነበር /2/

          /አዝ * * * * *

ሰብአ ሰገል መጡ ከሩቅ ምስራቅ ሀገር
ወርቅ እጣን ከርቤዉን ለርሱ ለመገበር
በእናቱም እቅፍ አገኙት ህፃኑን
ላለም ተናገሩ ንጉስ መወለዱን
ይህ ሚስጢር ግሩም ነው ከቶ የማይነገር
ማርያምም በልቧ ትጠብቀው ነበር /2/

          /አዝ * * * * *

የይሁዳ ምድር ምስጋና ተመላ
ንጉስ መቷልና ከናዝሬት ገሊላ
ታምሩን ትናገር ቤተልሄም ታዉራ
ዝማሬ ሲወጣ ከርስቱ ቆጠራ
ይህ ሚስጢር ግሩም ነው ከቶ የማይነገር
ማርያምም በልቧ ትጠብቀው ነበር /2/

          /አዝ * * * * *

የማይታይ ታየ ተዳሰሰ አንደ ሰዉ
በጠባቡ ደረት አዳምን መሰለዉ
ገረማት ጥበቡ ታናሹአን ሙሽራ
ተዋህዳልና ቃል ከ ስጋ ጋራ
ይህ ሚስጢር ግሩም ነው ከቶ የማይነገር
ማርያምም በልቧ ትጠብቀው ነበር /2/


#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።

   ╔​✞═══●◉❖◉●═══✞╗
       ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞
   ❖ @
mezmuredawit  ❖
   ❖ @mezmuredawit  ❖
   ❖ @mezmuredawit  ❖  
      ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞
  ╚✞═══●◉❖◉●═══​✞╝

✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

✞ ተወልደ ኢየሱስ ✞

ተወልደ ኢየሱስ በቤተልሔም /2×/
ዘይሁዳ በቤተልሔም /2×/
አዋልደ ጢሮስ አሜሃ ይሰግድ/2×/ በቤተልሔም /2×/

#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።

   ╔​✞═══●◉❖◉●═══✞╗
       ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞
   ❖ @
mezmuredawit  ❖
   ❖ @mezmuredawit  ❖
   ❖ @mezmuredawit  ❖  
      ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞
  ╚✞═══●◉❖◉●═══​✞╝

✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

✞ ቤዛ ኵሉ ✞

ቤዛ ኵሉ ዓለም ዮም ተወልደ/2×/
ቤዛ ኵሉ ዓለም ዮም ተወልደ/2×/

#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።

   ╔​✞═══●◉❖◉●═══✞╗
       ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞
   ❖ @
mezmuredawit  ❖
   ❖ @mezmuredawit  ❖
   ❖ @mezmuredawit  ❖  
      ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞
  ╚✞═══●◉❖◉●═══​✞╝

✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

✞ በእደ ዮሐንስ ✞

በእደ ዮሐንስ ተጠምቀ ኢየሱስ ናዝራዊ
ሰማያዊ (፫)ኢየሱስ ናዝራዊ

ሰማያዊው ጌታ ሰማያዊው ንጉስ
ለፈጠረው ፍጡር ተጠመቀ እየሱስ
ትህትናን ሰበከን ተሟልቶ ፍቅር
ከዙፋኑ ወርዶ ታየ በምድር
      እኸ ሰማያዊ (፫)ኢየሱስ ናዝራዊ

          /አዝ * * * * *

እንደ እንቦሳ ጥጃ ዮርዳኖስ ዘለለች
ጌታን በእንግድነት ስለተቀበለች
ካባናና ፈርፋ አንቺ ትበልጫለሽ
በብሉይ በሃዲስ የመዳን ተስፋ አለሽ
      እኸ ሰማያዊ (፫)ኢየሱስ ናዝራዊ

          /አዝ * * * * *

አምላክ በዮርዳኖስ ተጠምቆ ሲወጣ
ሰማያት ተከፍተው ከአርያም ቃል መጣ
መንፈስ ቅዱስ መጥቶ በእርግብ አምሳል
ሚስጥረ ስላሴ ለአለም ተገልጧል
      እኸ ሰማያዊ (፫)ኢየሱስ ናዝራዊ

          /አዝ * * * * *

አንከርዎ ለማይ አእኰትዎ ለኢየሱስ /፪/
ኸ በእንተ ማይ ዘኮነ ወይነ /፬/

እሺ እናቴ ሆይ አልካት በትህትና
በሰርጉ ቤት ሳለህ እየሱስ በቃና
የጌታ ታምራት የእመቤቴ ምልጃ
ለአለም ተገለፀ በገሊላ አውራጃ

          /አዝ * * * * *

አትዘን ዶኪማስ አትደናገጥ
በአይኖችህ ታያለህ ነገርና ሲለወጥ
በአዲስ የቀየራል መናኛው ደጅህ
እሰይ ደስ ይበለህ ስሙነው ጥሪህ

#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።

   ╔​✞═══●◉❖◉●═══✞╗
       ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞
   ❖ @
mezmuredawit  ❖
   ❖ @mezmuredawit  ❖
   ❖ @mezmuredawit  ❖  
      ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞
  ╚✞═══●◉❖◉●═══​✞╝

✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

​​​​ታህሳስ 24

በዚህች ቀን ታላቁ ጻድቅ አቡነ ተክልሃይማኖት የተወለዱበት ቀን ነው። የትውልድ ቦታቸው ሸዋ ጽላልሽ አወራጃ ዞረሬ ነው፤ የአባታቸው ስም ጸጋ ዘአብ የእናታቸው ስም እግዚ ሐርያ ይባላል መካን ነበሩ ልጅ እንዲሰጣቸው ወደ እግዚያብሔር ዘወትር ይጸልዩ ነበር፤ መጋቢት 12 ቀን እንዲህ ሆነ።

ሞተሎሜ የተባለ ጣኦት አምላኪ ንጉስ አገራቸውን ወረረ መንደሩንም አጠፋ ጸጋ ዘአብ ወንዝ ውስጥ ገብቶ አመለጠ እግዚ ሐርያ ግን ተማርካ ሄደች፤ በጣም መልከ መልካም ስለነበረች ሞቶሎሜ ሊያገባት አሰበ ታላቅ ድግስም ደገሰ አገር ምድሩ ተሰብስቦ ሲዘፍን ሲጨፍር ሳለ ቅዱስ ሚካኤል ታላቅ መብረቅ ነጎድጓድ አሰማ ብዙዎች ሞቱ እግዚሐርያን በክንፎ ተሸክሞ ዞረሬ ከቤተክርስቲያን ውስጥ አስቀመጣት ከባለቤቷ ጸጋ ዘአብ ጋር ተገናኙ ተቃቅፈው ተላቀሱ፤ከሁለት ቀን በኃላ መጋቢት 24 ቀን ተክለሃይማኖት ተጸነሱ።

በዛሬዋ ቀን 1167 ዓ/ም ተወለዱ ቀኑ አርብ ነበር፤ በተወለዱ በ3ኛ ቀናቸው እሁድ በ 3 ሰዓት “አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ” ብለው ሥላሴን አመሰገኑ፤ ሁለተኛ ተአምር ከዚህ በታች ያለው ስዕል ተክልዬ የአንድ ዓመት ከመንፈቅ ህጻን እያሉ ነው፤ በድፍን ሸዋ ርሃብ ተከስቶ ነበር በተለይም በዞረሬ እግዚሐርያ አዘነች አለቀሰች ምነው እርቧት ነው ጠምቷት ነው ቢሉ የለም እርቧትስ ጠምቷትስ አይደለም የቅዱስ ሚካኤል ዝክሩ ታጎለቢኝ ብላ እንጂ።

ህጻኑ ተክለሃይማኖት ከእናቱ ጭን ወርዶ እየዳኸ ወደ ጓዳ ሄደ አንስታ አቀፈችው እርሱ ግን አለቀሰ ዱቄት የተቀመጠበትን እንቅብ እንድትሰጠው በእጁ ጠቆማት ሊጫወትበት መስሏት ሰጠችው በትንንሽ እጆቹ እንቅቡ ላይ አማተበ ዱቄቱ ሞልቱ ፈሰሰ ዳግመኛ የቅቤ የዘይት ማስቀመጫ ማድጋዎች ላይ በተመሳሳይ አማተበ ሞልቶ ፈሰሰ ቤቱ በበረከት ተትረፈረፈ፤ የቅዱስ ሚካኤልን ዝክሩን አዘከረች አገሬውን ጠርታ መገበች፤ ለተቸገሩትም አብዝታ ሰጠች፤ ይህ በረከት ሁለቱም እስኪሞቱ ድረስ አላለቀም ይላል ገድላቸው።

ተክለ ሃይማኖት በ 99 ዓመት ከ8 ወር ከ5 ቀን በዚህ ምድር ኖረው ነሐሴ 24 ቀን አርፈዋል። በደብረሊባኖስ ገዳማቸው የንፍሮ ውኃ አይነስውር ያበራል ድውይ ይፈውሳል ገድላቸው ሊነበብ ሲወጣ አጋንንት ተቃጠልን ይላሉ ሲገርም ምን ያህል ባለጸጎች ነን። ከበዓሉ በረከት ያሳትፈን።

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

✞ አብስራ ✞

መጣ ከራማ ከመላእክት ሀገር
ለድንግል ማርያም ምስራች ሊነግር/2/

አብስራ አብስራ  አብስራ
አብስራ አብስራ  አብስራ
የራማው መልአክ  አብስራ
ሊቀ መላእክት  አብስራ
መጋቢ ሐዲስ ነው  አብስራ
ገብርኤል የኛ አባት  አብስራ
ተፈስሂ ብለን  አብስራ
ደስታን አሰማሀት  አብስራ
የጌታን መወለድ  አብስራ
ክብር ነገርካት  አብስራ

ገብርኤል ለማርያም/2/

  /አዝ * * * * *

አብስራ አብስራ አብስራ
አብስራ አብስራ  አብስራ
ጌታን የምቶድ  አብስራ
በመንደርሽ  አብስራ
በአገለገልኻት አብስራ
ፊቷ አጎንብሼ  አብስራ
ስትል ማርያም  አብስራ
በመሰዊያው ፊት አብስራ
ተፈስሂ አላት  አብስራ
ሊቀ መላእክት አብስራ

ገብርኤል ለማርያም/2/

  /አዝ * * * * *

አብስራ አብስራ  አብስራ
አብስራ አብስራ  አብስራ
ሀርና ወርቁን  አብስራ
እያስማማች አብስራ
ስትፈትል ሳለች  አብስራ
ቃሉን ሰማች  አብስራ
ደስ ይበልሽ  አብስራ
ጸጋ የሞላሽ  አብስራ
ከሴቶች ሁሉ  አብስራ
የተለየሽ  አብስራ

ገብርኤል ለማርያም/2/

  /አዝ * * * * *

አብስራ አብስራ አብስራ
አብስራ አብስራ  አብስራ
ትጸንሻለሽ  አብስራ
ትወልጃለሽ  አብስራ
ስሙን ኢየሱስ  አብስራ
ትይዋለሽ አብስራ
እርሱም ልዑል ነው አብስራ
የልዑል ልጅ  አብስራ
የሚወለደው  አብስራ
ሁሉን ወዳጅ  አብስራ

ገብርኤል ለማርያም/2/

መጣ ከራማ ከመላእክት ሀገር
ለድንግል ማርያም ምስራች ሊነግር

አብስራ አብስራ አብስራ/4/

#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።

   ╔​✞═══●◉❖◉●═══✞╗
       ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞
   ❖ @
mezmuredawit  ❖
   ❖ @mezmuredawit  ❖
   ❖ @mezmuredawit  ❖
✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞
  ╚✞═══●◉❖◉●═══​✞╝
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

✞ ድንግል_ማርያም ✞

ድንግል ማርያም በቤተ መቅደስ አሰምታ ትናገር ነበር ሠላም ላንቺ ይሁን አለኝ ቅዱስ ገብርኤል ሌላ ምንም አላውቅ ያውቃል እግዚአብሄር /2/


ከመቅደሱ ቁጭ ብዬ ትንቢት እየሰማው
ሐር ወርቅ አስማምቼ ጥበብ እየፈተልኩ
ሳለው በመገረም ያንን ቃል አስቤ
አምላክ ሰው ሆነብኝ ተመሰጠ ልቤ
ማን ናት ብዬ ሳስብ ያቺ ብላቴና
ገብርኤል ደረሰ ብስራቱን ያዘና
ዙፋኑ አደረገኝ የባሪያውን
ውርደት ተመልክቷ ልና

         /አዝ * * * * *

እንዴት ያለ ማኅጸን ሰማይን ይሆናል
የልዑሉ ዙፋን ወዴት ይተከላል
እያልኩኝ ስጠይቅ በልቤ ለራሴ
የመንፈስ ቅዱስ ሃይል አደረ በራሴ
ማን ናት ብዬ....

         /አዝ * * * * *

እንዴት ከደሀ ቤት ይሄ ንጉስ ያድራል
ለእርሱ የተገባ ከወዴት ይገኛል
ገሊላን አሰብኳት ዞሬ በህሊና
ለካስ ተሸንፏል በባሪያው ትህትና
ማን ናት ብዬ....

         /አዝ * * * * *

እሳት የማይበላው ሐመልማል አይኖርም
እንዲህ ያለ ቅጠል ናዝሬት አይገኝም
ህሊናዬ መጥቆ ሲበር ወደ ሲና
አንቺ እኮ ነሽ አለኝ ገብርኤል መጣና
ማን ናት ብዬ....


#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።

   ╔​✞═══●◉❖◉●═══✞╗
       ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞
   ❖ @
mezmuredawit  ❖
   ❖ @mezmuredawit  ❖
   ❖ @mezmuredawit  ❖  
      ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞
  ╚✞═══●◉❖◉●═══​✞╝

✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

✞ አይኖቼ ማዳኑን አይተዋልና ✞

ዓይኖቼ ማዳኑን አይተዋልና/2×/
ይገባዋል/2×/ክብርና ምስጋና

ከሰማይ ወረደ ሰውን በማፍቀር
ኃያሉ ጌታችን ቸሩ እግዚአብሔር
በቤተልሔም ዋሻ በዚያ በግርግም
ተወለደ ዛሬ መድኃኔዓለም

         /አዝ * * * * *

የተነበዩለት ብዙ ነቢያት
ከድንግል ተወልዶ አዳነን በእውነት
ከበደል ጉራንጉር አነሣን ከትቢያ
በአንድነት እንዘምር እንበል ሃሌሉያ

         /አዝ * * * * *

የተናቅን ስንሆን እኛን ሊያከብር ወድዶ
በፍቅር አከበረን ራሱን አዋርዶ
ምን አይነት ፍቅር ነው ፍጹም ምሕረት
የአምላክ መወለድ በከብቶች በረት

         /አዝ * * * * *

በንጽሕና ጸንተሽ ቤተ መቅደስ የኖርሽ
በሕቱም ድንግልና መድኃኒትን ወለድሽ
የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ ጌታ
ተወልዷል ከድንግል የሰዎች አለኝታ

👉ዘማሪ ተስፋዬ ኢዶ

#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።

   ╔​✞═══●◉❖◉●═══✞╗
       ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞
   ❖ @
mezmuredawit  ❖
   ❖ @mezmuredawit  ❖
   ❖ @mezmuredawit  ❖  
      ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞
  ╚✞═══●◉❖◉●═══​✞╝

✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

ገብርኤል ነዓ

በነደ እሳት ሥዑል በጌራ ብርሀን ክሉል
መላዕከ መዊል ወኃይል ገብርኤል ነዓ ለሣህል

ርዕሰ ኃያላን    ቅዱስ ገብርኤል
መላዕከ ሰላም   ቅዱስ ገብርኤል
ተረጋጋ ባንተ የመላዕክት አለም
ባለንበት እንቁም ብለህ በአርያም

           /አዝ=====

ዜናዊ ፍስሀ   ቅዱስ ገብርኤል
ሊቀ ትጉሃን    ቅዱስ ገብርኤል
ለድንግል አበሰርክ እንደምትወልድ ጌታን
ዘመኑ ሲፈጸም ያሰማኸን ደስታን

           /አዝ=====

መላዕከ አድኖ   ቅዱስ ገብርኤል
አርያዋዊ    ቅዱስ ገብርኤል
ናዛዚ ህዙናን ለብስራታዊ
በፊቱ ያቆመህ አምላክ ማህያዊ

           /አዝ=====

ሊቀ መላዕክት   ቅዱስ ገብርኤል
ጎፈ ነበልባል     ቅዱስ ገብርኤል
ወደኛ ቅረብ ለምህረት ወሳይ
አለቃ ገብርኤል ሀያል

#አዲስ_መዝሙር_በመናገሻ_ገነተ_ጽጌ_ቅዱስ_ጊዮርጊስ_ሰ_ት_ት_ቤት


#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።

       ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @enamsgn ❖  
❖ @enamsgn @enamsgn ❖         ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

✞ እሰይ እሰይ ተወለደ ✞

እሰይ እሰይ ተወለደ እሰይ እሰይ ተወለደ (፪) ከሰማየ ሰማያት ወረደ (፪) ከድንግል ማርያም ተወለደ

እሱ ባይወለድ እሰይ እሰይ
ቸሩ አባታችን "
መች ትገኝ ነበረ "
ገነት ምድራችን "

/አዝ=====

ብርሃን ወጣላቸው እሰይእሰይ
ለመላ ሕዝቦቹ "
በጨለማው ጉዞ "
እንዲያሲሰላቹ "

/አዝ=====

እግዚአብሔር አብ ላከ እሰይ እሰይ
አንድያ ልጁን "
እርሱ ወዷልና "
እንዲሁ ዓለሙን "

         /አዝ=====

እንደ ጠል ወረደ እሰይ እሰይ
ከሰማይ ወደ እኛ "
ወገኖቹን ሊያድን "
ከሰይጣን ቁራኛ "


#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።


╔ ​✞ ═════●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit
❖ @mezmuredawit @enamsgn
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
✥ ✢
╚✞ ═════●◉❖◉●═════​✞╝

✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

✞ አምላክ ሰው ሆነ ✞

አምላክ ሰው ሆነ ሰው አምላክ ሆነ(፪)
በድንግል ማርያም ተከናወነ

የአብ ሙሽራ የወልድ እናቱ
የመንፈስቅዱስ ጽርሐ ቤቱ
በሰማይ ሆኖ አብ አጸናሽ
ወልድም ለራሱ ቤት አረገሽ
መንፈስቅዱስ ነው(፪)የጸለለሽ

/አዝ=====

ከሦስቱ አካል ወልድ አንዱ አካል
መጣ ወረደ በገባው ቃል
ተጸንሶ ሳለ ወልድ ከእናቱ
አልተነጠለም ከሦስትነቱ
ተአምራት አርጓል ድውይ ፈውሷል በአምላክነቱ

/አዝ=====

ይህንን ድንቅ ምስጢር በሉ ግሩም
ምስጋና አቅርቡ ለዘለዓለም
በስነ ፍጥረት ይታወቃል
የዓለም ፈጣሪ የእግዚአብሔር ቃል
ደስ ይበላችሁ ደስ ይበለን በሉ እልል

/አዝ=====

የአብ ሙሽራ የወልድ እናቱ
የመንፈስቅዱስ ጽርሐ ቤቱ
በሰማይ ሆኖ አብ አጸናሽ
ወልድም ለራሱ ቤት አረገሽ
መንፈስቅዱስ ነው(፪)የጸለለሽ

👉ዘማሪ ቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ


#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።


╔ ​✞ ═════●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit
❖ @mezmuredawit @enamsgn
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
✥ ✢
╚✞ ═════●◉❖◉●═════​✞╝

✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

✞  ​​ጥምቀተ ባሕር ✞

ጥምቀተ ባሕር  ዮርዳኖስ ነያ(፪)
ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ(፪)

ጌታችን ሲጠመቅ ባሕር ምን አለች
አልችለውም ብላ ወደ ኋላ ሸሸች
ብርሃነ መለኮት በወንዞች ሲሞላ
ዮርዳኖስም ሸሸ  ቀረ ወደ ኋላ
    
            /አዝ=====

አብ በመጣ ጊዜ ደመናውን ጭኖ
መንፈስ ቅዱስ ታየ በርግብ አምሳል ሆኖ
ለልጁ ምስክር ሊሆን  ፈለገና
ቃሉን ተናገረ ሆኖ በደመና

            /አዝ=====

ጌታችን ሲጠመቅ በሰላሳ ዓመት
ባህር ኮበለለች ግዑዟ ፍጥረት
ሰማይ ተከፈተ ሆነልን ፀአዳ
ምስጢረ ሥላሴ ታወቀ ተረዳ

            /አዝ=====

እልል በይ ዮርዳኖስ የጥምቀት  መገኛ
የፅድቅ መሰላል ድህነታችን ለኛ
ቀላያት አብርህት ብዙዎች እያሉ
እንደምን ተመረጥሽ ዮርዳኖስ ከሁሉ


#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።


╔ ​✞ ═════●◉❖◉●═════✞╗
✢    ✥
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit
❖ @mezmuredawit @enamsgn
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
                                    ✥   ✢   
   ╚✞ ═════●◉❖◉●═════​✞╝

✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

✞ አንቺን ብቻ ቤተልሔም ✞

አንቺን ብቻ ቤተልሔም
አንቺን ብቻ በዛ ግርግም
ዮሐንስን በገሊላ በኤፍራታ አላየንም
አንቺን ብቻ ቀራንዮ አንቺን ብቻ በኮረብታ
ዮሴፍንም አላየንም ሊቶስጥራ ጎለጎታ

ገና በማለዳ በናዝሬቷ መቅደስ
ገብርኤል ብስራት ይዞ ከገሊላ ሲደርስ
ያን ዜና ስትሰሚ ደንግጠሽ በብርቱ
አንቺ ብቻ ነበርሽ ብላቴናይቱ/2/

          /አዝ=====

ህፃኑን ስትወልጂ ግርግም የነበሩ
የሉም በመከረው ቀራንዮን ፈሩ
በልደት ነው እንጂ የታሉ በሞቱ
አብረሽው የነበርሽ አንቺ ብቻ እናቱ/2/

          /አዝ=====

የግብፅን በረሀ አብረውሽ የወጡ
በቀያፋ ግቢ እንደምን አልመጡ
እርሱ ለሚገረፍ እነርሱ እየፈሩ
አንቺን ብቻ ትተው በመንደር ነበሩ/2/

          /አዝ=====

ሀሙስ ለት ፋሲካን ሲበሉ ያመሹ
አርብ ለት ተነስተው ከቶ ወዴት ሸሹ
ቃል ገብተው ነበር ላይከዱት መሃላ
ድንግል ከአንቺ በቀር ማን ነበረ ሌላ/2/

          /አዝ=====

በ30ው ዘመን በስጋው ወራቱ
መች ነበሩ ከቶ ደቀ መዛሙርቱ
የእጆቹን ታምራት ቀን ከሌት እያየሽ
በቃሉ ብርታት ፊት አንቺ ብቻ ነበርሽ/2/

          /አዝ=====

ቤተልሔም ያሉ ቀራንዮ የሉም
ቀራንዮም ያሉ ግርግም አልነበሩም
በሆነበት ዘመን በመስቀል በሞቱ
አብረሽው የነበርሽ አንቺ ብቻ እናቱ/2/

👉ዘማሪ ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ

#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።

╔ ​✞ ═════●◉❖◉●═════✞╗
        ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit
❖ @mezmuredawit @enamsgn
         ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ 
   ╚✞ ═════●◉❖◉●═════​✞╝

✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

#የጌታ_ልደት_በቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

ቀዳማዊ አምላክ ዛሬ ተወለደ፤ ጥንቱን ገንዘቡ ባይደለ ባህርይ ተገኝ፤ እርሱ ቀዳማዊ አምላክ ነው፤ ሰው በመሆኑም ከባህርይው አልተለወጠም፡፡ የመለኮቱ መገኝትም ከእመቤታችን ከተወለደ ወዲህ አይደለም፤ ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ዓለም ሳይፈጠር የነበረ ጥበብ ነው እንጂ፤ የማይታመም እርሱ ከባህርይ መለኮቱ ሳይለወጥ ሕማም የሚስማማውን ስጋን ተዋሃደ፡፡ ዳግመኛም በልዑል ዙፋን ላይ ተቀምጦ ያለ እርሱ በበረት ተጣለ ስጋ ሳይሆን የነበረ የማይዳሰስ ወልድ ዋህድ ዛሬ ስጋን በመዋሃድ ተዳሰሰ፤ ሃጢአትን የሚያስተሰርይ እርሱ በጨርቅ ተጠቀለለ፡፡

መፅሃፍ እንዲህ አለ፦ ብልህ ሽክላ ሰሪ የሚሰራውን የለዘበ ጭቃ በአገኝ ጊዜ ከእርሱ መልካም እቃ እንዲሰራ እንደዚሁ ጌታችን የዚህችን ድንግል ንፁህ ስጋዋን ንፅህት ነፍሷን ባገኘ ጊዜ ነፍስ ያለችውን ስጋ ሊዋሃደው ፈጠረ፡፡ እንደወደደ ከድንግል ነፍስን ስጋን ፈጥሮ ለበሰ እርሱንም ተዋህዶ ዛሬ ተወለደ ሕፀፅ ያለበት ነው ብሎ ባህርያችንን አልተወውም ፤ ስጋን በተዋህዶ ጊዜ ቃል ከምላቱ አልተወሰነም፤ ስጋ የፈጣሪ አካል ባህርይ በሆነ ጊዜ ፍፁም አምላክነትን አገኝ እንጂ፡፡ ምን እላለሁ? ምንስ እናገራለሁ? ከዘመን አስቀድሞ የነበረ እርሱ ትንሽ ህፃን ሆኗልና፡፡

እኔ ፈፅሜ አደንቃለሁ፤ ከሰማየ ሰማያት በላይ የሚሆን በዘላለማዊ ዙፋን የሚኖር እርሱ በበረት ተጣለ ከስጋዌ አስቀድሞ አይዳሰስ የነበረ አንዱ እርሱ በምድራውያን እጅ ተዳሰሰ ሃጢአትን የሚያስተሰርይ እርሱን በጨርቅ ጠቀለሉት፤ ይህን ወዷልና፡፡ ክብሩ ተለይቶት የነበረ ስጋን ክቡር አምላክ ሊያደርገው፤ የፀጋ ገዥነትን አጥቶ የነበረ ስጋንም የባህርይ ገዥ ሊያደርገው ወደደ፤ አዳም ከእኛ እንዳንዱ ሆነ ያለውንም ሰው በመሆን ሊገልጠው ወደደ፡፡

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

✞ ተወልደ ናሁ ✞

ተወልደ ናሁ እም ድንግል(፪)

ሲነገር ነበረ በነብያተ አፍ
   ተወልደ ናሁ እም ድንግል(፪)
በአንዱ በእግዚያአብሔር ባንዱ በመንፈስ
   ተወልደ ናሁ እም ድንግል(፪)
አንድ ቀን እንዲሆን ፀሐይ እንዲወጣ
   ተወልደ ናሁ እም ድንግል(፪)
የናፈቅነው ንጉሥ ሥጋ ለብሶ መጣ
   ተወልደ ናሁ እም ድንግል(፪)

        /አዝ * * * * *

አብርሃም ያንን ቀን ለማየት ናፈቀ
    ተወልደ ናሁ እም ድንግል(፪)
ዳዊት በኤፍራታ ልደቱን አወቀ
     ተወልደ ናሁ እም ድንግል(፪)
ኢሳያስ ከድንግል ሲወልድ አየና
     ተወልደ ናሁ እም ድንግል(፪)
ትንቢት ተናገረ ምልክት አለና
    ተወልደ ናሁ እም ድንግል(፪)

        /አዝ * * * * *

ኮከብ ከያዕቆብ ይወጣል ሲባል
       ተወልደ ናሁ እም ድንግል(፪)
ሰማይ  ሆነችለት እናቱ ድንግል
       ተወልደ ናሁ እም ድንግል(፪)
በህዝቡ መካከል ሆኖ የሚያበራ
       ተወልደ ናሁ እም ድንግል(፪)
በእርሱ ፈራረሰ የጨለማው ሥራ
      ተወልደ ናሁ እም ድንግል(፪)

        /አዝ * * * * *

ከእረኞች ጋራ ቤተልሔም ግቡ
      ተወልደ ናሁ እም ድንግል(፪)
ከነገሥታቱ ጋር አምኃን አቅርቡ
      ተወልደ ናሁ እም ድንግል(፪)
እንስገድ ለህጻኑ ይገባዋልና
      ተወልደ ናሁ እም ድንግል(፪)
አለቅነት ስልጣን በጫንቃው ነውና
     ተወልደ ናሁ እም ድንግል(፪)

👉 ዘማሪ ዳዊት በቀለ

#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።

   ╔​✞═══●◉❖◉●═══✞╗
       ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞
   ❖ @
mezmuredawit  ❖
   ❖ @mezmuredawit  ❖
   ❖ @mezmuredawit  ❖
      ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞
  ╚✞═══●◉❖◉●═══​✞╝

✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

✞ በኤፍራታ ምድር ✞

በኤፍራታ ምድር በቤተልሔም(፪)
ጌታ ተወለደ ከድንግል ማርያም(፪)
ብርሐናዊው ኮከብ ከሠማይ ዝቅ አለ(፪)
ፍጥረትም ዘመረ ሀሌሉያ እያለ(፪)

መንጋውን በለሊት ሲጠብቁ እረኞች
ከሰማይም ሠሙ ታላቅ የምስራች
በመላዕክት ግርማ ምድር ስታበራ
የሚያስጨንቅ ነበር እጅግ የሚያስፈራ

/አዝ * * * * *

ድንገትም በሠማይ ሠራዊት ተገልጠው
በአንድነት ዘመሩ ከኖሎት ጋር ሆነው
ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም ብለው
ሠላምም በምድር በጎ ፈቃድ ለሠው

/አዝ * * * * *

ቤተልሔም ሄደው ጌታን ተሣለሙት
ከእናቱ ጋር ሆነው በግርግም አገኙት
የመላዕክትን ዜማ እረኞች አወሩ
በልዩ ምስጋና አምላክን ሲያከብሩ

/አዝ * * * * *

በመዝሙር ቢሆን ፍስሐ ደስታ
በዳዊት ከተማ ተወለደ ጌታ
ህፃን ከእናቱ ጋር በግርግም ፈለጉት
እርሱ ነው ለሠዎች የድህነት ምልክት

👉 ሊ/መ ይልማ ሀይሉ


#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።

   ╔​✞═══●◉❖◉●═══✞╗
       ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞
   ❖ @
mezmuredawit  ❖
   ❖ @mezmuredawit  ❖
   ❖ @mezmuredawit  ❖  
      ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞
  ╚✞═══●◉❖◉●═══​✞╝

✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

✞ አንፈርዓጹ ✞

አንፈርዓጹ ሰብአ ሰገል/2×/
አሞኃሆሙ አምጽኡ መድምመ/2×/

#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።

   ╔​✞═══●◉❖◉●═══✞╗
       ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞
   ❖ @
mezmuredawit  ❖
   ❖ @mezmuredawit  ❖
   ❖ @mezmuredawit  ❖  
      ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞
  ╚✞═══●◉❖◉●═══​✞╝

✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

እም ሰማያት ወረደ ✞

እም ሰማያት ወረደ
ወእም ማርያም ተወልደ/2×/
ከመ ይኩን ቤዛ/2×/
ለኩሉ ዓለም ለብሰ ሥጋ ማርያም/2×/

#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።

   ╔​✞═══●◉❖◉●═══✞╗
       ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞
   ❖ @
mezmuredawit  ❖
   ❖ @mezmuredawit  ❖
   ❖ @mezmuredawit  ❖  
      ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞
  ╚✞═══●◉❖◉●═══​✞╝

✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

✞ እልል_ደስ_ይበለን ✞

እልል እልል ደስ ይበልን/2×/
አጀበን መጣን ታቦተ ህጉን
እልል ብላችሁ ተቀበሉን

የቃልኪዳን ታቦት እልል ደስ ይበለን
የክብሩ ዙፋን '' '' '' ''
ከመንበሩ ወርዶ '' ''  '' ''
እየባረከን  '' ''  '' ''
ቅዱሱ መጽሐፍ  '' ''  '' ''
እንደነገረን '' ''  '' ''
ወጣን ከሰፈሩ  '' ''  '' ''
እየተከተልን '' ''  '' ''

/አዝ*****

የሰማዩ መቅደስ
እላይ ሲከፈት '' ''  '' ''
ተገልጦ አየነው  '' ''  '' ''
የክብሩ ታቦት '' ''  '' ''
እልልታ ዝማሬ  '' ''  '' ''
እናቅርብ ምስጋና '' ''  '' ''
ታቦቱ ልጆቹን '' ''  '' ''
ሊባርክ ነውና '' ''  '' ''

/አዝ*****

በውስጥና በውጭ
በወርቅ ተለብጦ '' ''  '' ''
የእግዚአብሔር ቸርነት '' ''  '' ''
በእርሱ ላይ ተገልጦ '' ''  '' ''
እስራኤል በምህረት  '' ''  '' ''
ከሞት ተከለለ '' ''  '' ''
ታቦቱ ሲነካው '' ''  '' ''
ባህር ተከፈለ '' ''  '' ''

/አዝ*****

በእግዚብሔር ጣቶች
ተቀርጾ ትእዛዙ '' ''  '' ''
ካህናቱ ይዘው '' ''  '' ''
በስርአት ሲጓዙ '' ''  '' ''
ወድቀን እንሰግዳለን '' ''  '' ''
ለቅዱስ ታቦት '' ''  '' ''
የእግዚአብሔር ስም  '' ''  '' ''
ለተጻፈበት '' ''  '' ''

አጀበን መጣን እልል ብላችሁ ተቀበሉን፤

#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።

   ╔​✞═══●◉❖◉●═══✞╗ 
   ❖ @
mezmuredawit ❖
   ❖ @mezmuredawit ❖
   ❖ @mezmuredawit ❖  
  ╚✞═══●◉❖◉●═══​✞╝
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

✞ ​​በዮርዳኖስ የተጠመቀው ✞

በዮርዳኖስ የተጠመቀው
ወልደ አብ ወልደ ማርያም ነው
በዮሐንስ የተጠመቀው
ወልደ አብ ወልደ ማርያም ነው/፪/

የሠላሙ ንጉሥ የዓለም ጽናት
በዮርዳኖስ የተጠመቀው
ሊጠመቅ ሲል ገና ምድር ጨነቃት
በዮሐንስ የተጠመቀው
ዮርዳኖስም ፈራች እሣት መላባት
በዮርዳኖስ የተጠመቀው
የጸሐይ ፈጣሪ ቢገለጥባት
በዮሐንስ የተጠመቀው

      /አዝ * * * * *

እንደ ተናገረው ዳዊት በትንቢቱ
በዮርዳኖስ የተጠመቀው
ምሥክር ሊሆነው ለዝክረ ጥምቀቱ
በዮሐንስ የተጠመቀው
ተራሮች ኮረብቶች እጅግ ደሥ ቢላቸው 
በዮርዳኖስ የተጠመቀው
እንቦሳ እና ጊደር መሆን አማራቸው
በዮሐንስ የተጠመቀው

      /አዝ * * * * *

በደመና ወጥቶ ተሠማ ምሥጢር
በዮርዳኖስ የተጠመቀው
ሥለ አንድያ ልጁ አብ ሢመሰክር
በዮሐንስ የተጠመቀው
በርግብ አምሣል ታየ መንፈሥ ቅዱሥም
በዮርዳኖስ የተጠመቀው
አካላዊ ሕይወት አሐዜ ዓለም
በዮሐንስ የተጠመቀው

      /አዝ * * * * *

በዕደ ዮሐንስ ጌታችን ተጠምቆ
በዮርዳኖስ የተጠመቀው
ልጅነትን ተሠጠን ዕዳችንን ሠጥቶኝ 
በዮሐንስ የተጠመቀው
እንደ ምን ያለ ነው ይኼ ትሕትና
በዮርዳኖስ የተጠመቀው
በፈጣሪ ጥምቀት የተሠማው ዜና 
በዮሐንስ የተጠመቀው

      /አዝ * * * * *

ለጥምቀቱም ይውጣ የጥበቡ ሸማ 
በዮርዳኖስ የተጠመቀው
ታቦቱን አጅበን እንሂድ ከተራ
በዮሐንስ የተጠመቀው
ምድሪቱ ትቀደስ ሠይጣንም ይፈርዳል 
በዮርዳኖስ የተጠመቀው
እኛ ኢትዮጵያውያን ለአምላክ እንዘምር 
በዮሐንስ የተጠመቀው

      /አዝ * * * * *

ምንጣፍም ይዘርጋ ይጎዝጎዝ ቄጠማ 
በዮርዳኖስ የተጠመቀው
ተነስተን በአንድነት በያሬድ ውብ ዜማ 
በዮሐንስ የተጠመቀው
ደግሞ ለዓመቱ አድርሶን በጸጋ
በዮርዳኖስ የተጠመቀው
እንድናመሠግን ለአልፋ ዖሜጋ
በዮሐንስ የተጠመቀው

ማህበረ ፊልጶስ

#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።

   ╔​✞═══●◉❖◉●═══✞╗
       ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞
   ❖ @
mezmuredawit  ❖
   ❖ @mezmuredawit  ❖
   ❖ @mezmuredawit  ❖  
      ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞
  ╚✞═══●◉❖◉●═══​✞╝

✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

#ታኅሣሥ_22

#ብሥራተ_ቅዱስ_ገብርኤል

ታኅሣሥ ሃያ ሁለት በዚህች ዕለት ብርሃናዊው መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ለእመቤታችን አምላክን እንደምትወልድ ያበሰረበት መታሰቢያ ነው፡፡ ይኸውም ‹‹ልዑል እግዚአብሔር ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤልን ‹ሂድና ለጽዮን ልጅ ለድንግል የእግዚአብሔር የባሕርይ ልጅ ወደአንቺ መጥቶ ኃይለ ልዑል ወልድ ሥጋሽን ለብሶ ሰው ይሆናል፤ ይኸውም ካንቺ የሚወለደው ጽኑዕ ነው ብለህ ንገራት› አለው፡፡ ‹ደንቆሮዎች የሚሰሙበት፣ ድዳዎቸ የሚናገሩበት፣ ዕውራንም የሚያዩበት፣ ሙታን የሚነሡበት፣ ለምጻሞች የሚነጹበት፣ ሐንካሳዎች የሚሄዱበት፣ በጨለማ ውስጥ የነበሩ ሰዎች ብርሃን የሚያዩበት ጊዜ እነሆ ደረሰ ብለህ ንገራት› አለው፡፡

ቅዱስ ገብርኤልም ይህን ሰምቶ በግንባሩ ተደፍቶ ልዑል እግዚአብሔርን ‹ጌታ ሆይ! የምትነግረኝ ይደረግ ዘንድ እንደምን ይሆናል?› አለው፡፡ ጌታም ‹የጀመርኩትን ቸርነት ፈጸምኩ፣ የወይን ግንድ ይቆረጣል (ወልደ እግዚአብሔር ይሞታል)፣ ወይራም ከበለስ ጋር ይተከላል (መስቀል ይተከላል)፣ ቅጽሮችም ይቀጸራሉ (ምግባር ከሃይማኖት ጋር ይሠራል)፣ የኤልፍና የሌሚ ወገን ይነሣል፡፡ ገብርኤል ሆይ! ሄደህ ለዳዊት ልጅ ‹እግዚአብሔር ከአንቺ ጋር ነውና ደስ ይበልሽ› ብለህ አብሥራት› አለው፡፡ ‹ለዘለዓለም ነግሦ የሚኖረውን እነሆ ትፀንሳለሽ በላት› አለው፡፡ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤልም ይህን ሰምቶ ሰገደ፡፡ ልብሱንም በላዩ ይዞ በመስቀል ቀኝ ይወርድ ዘንድ ወደደ፡፡ ጌታም ‹መግባትህና መውጣትህ በፍቅር አንድነት ይሁን› አለው፡፡ ‹ዘካርያስን ረግመህ አንደበቱን እንዳሰርህ እርሷን እንዳታሳዝናት ይልቁንም አብዝተህ ደስ አሰኛት አንጂ› አለው፡፡ ቅዱስ ገብርኤልም ይህን ሰምቶ ፈጽሞ ደስ እያለው ሊባኖስ ከሚባል ተራራ እስኪሰማ ድረስ ክንፉን እያማታ ወረደ፡፡ በዚህም ጊዜ በዙሪያው ያሉ ሁሉ ‹ይህ የምንሰማው ምንድነው?› ይሉ ነበር፡፡ የተደረገበትንም ቦታ አላወቁትም ነበር፡፡››

እመቤታችንን በ3 ዓመቷ እናትና አባቷ ብፅዓት አድርገው ለእግዚአብሔር ሰጥተዋታልና ካህናትም በቤተ መቅደስ ከመካነ ደናግል አስገብተዋት በመልአኩ በቅዱስ ፋኑኤል አማካኝነት ኅብስት ሰማያዊ ጽዋዕ ሰማያዊ እየመጣላት ያንን እየተመገበች ቅዱሳን መላእክት እየጎበኟት 12 ዓመት ኖራለች፡፡ በ15 ዓመቷ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ለእመቤታችን ጌታችንን እንደምትወልድ በዚህች ዕለት አብሥሯታል፡፡ በመጀመሪያ እመቤታችን ውኃ ቀድታ ስትመለስ የጠተማ ውሻ እያለከለከ ሲመጣ ብታየው ለፍጥረት ሁሉ የምትራራ ናትና በወርቅ ጫማዋ ለዛ ለተጠማው ውሻ ውኃ ስታጠጣ አብሯት የነበሩ ሴቶች ‹‹ማድጋሽን አጎደልሺው፣ ቀድቼ እሞለዋለሁ እንዳትይ ጉድጓዱ ጥልቅ ነው መቅጃም የለሽም›› አሏት፡፡ ክብርት እመቤታችንም ‹‹ውሃ የሚገኘው ከወደላይ ነው እንጂ ከወደታች ነውን? ፍጥረቱን ያጠጣ ጌታ ይሞላልኛል›› አለቻቸው፡፡ ማድጋዋም በተአምራት ሞልቶ ተገኘ፡፡ ሴቶቹም ዳግመኛ ‹‹በዚህ ዘመን አምላክ ከድንግል ይወለዳል ይላሉ ካንቺ ይሆን?›› እያሉ ሲዘብቱባት ወዲያው ከወደኋላዋ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል መጥቶ ‹‹እነሆ ትጸንሻለሽ›› አላት፡፡ እመቤታችንም ዞር ብትል የተናገራትን አጣችው፡፡ በዚህም ጊዜ ‹‹አባቴን አዳምን እናቴን ሔዋንን ያሳተ ጠላት ይሆናል›› ብላ ሄደች፡፡

ዳግመኛም እመቤታችን ከቤት ደርሳ ማድጋዋን ስታስቀምጥ መልአኩ አሁንም በድምፅ ‹‹እነሆ ትጸንሻለሽ›› አላት፡፡ እመቤታችንም ይህን ጊዜ ‹‹ምነው ይህስ ነገር ደጋገመኝ እንዲህ ያለውን ነገር ቤተ መቅደስ ሄደው ሊረዱት ይገባል›› ብላ ወደ ቤተ መቅደስ ሄዳ ወርቅና ሐር እያስማማች ስትፈት መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል እሁድ ቀን በ3 ሰዓት በገሃድ ተገለጸላትና እጅ እየነሳ እየሰገደ አበሠራት፡፡ ‹‹የዕውነተኛ ንጉሥ እናቱ እመቤታችን ላንቺ ፍቅር አንድነት ይባል›› አላት፡፡ ዳግመኛም ‹‹አንቺ ከሴቶች ይልቅ ተለይተሸ ንዕድ ክብርት ነሽ›› አላት፡፡ አምላክን የወለደች በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የጸናቸ ክብርት እመቤታችንም የብርሃናዊውን መአልክ የቅዱስ ገብርኤልን ቃል በሰማች ጊዜ ‹‹እንዲህ ያለውን ሰላምታ እንደምን ይቀበሏል! እንዴትስ መቀበል ይቻላል? እንጃ›› አለችው፡፡ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤልም ‹‹ማርያም ሆይ! መንፈስ ቅዱስ ያድርብሻል፣ ኃይለ ልዑል ወልድም ሥጋሽን ይለብሳልና አይዞሽ አትፍሪ›› አላት፡፡ ዳግመኛም ‹‹ይህ ካንቺ የሚወለደው ጽኑ ከሃሊ ነው፡፡ ስሙንም ኢየሱስ ትዪዋለሽ፣ እርሱ ታላቅ ይሆናል የልዑል ልጅም ይባላል፣ ጌታ አምላክም የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል፣ በያዕቆብ ቤትም ላይ ለዘለላም ይነግሣል፣ ለመንግሥቱም መጨረሻ የለውም›› አላት፡፡ እመቤታችንም መልአኩን ‹‹ምድር ያለ ዘር ፍሬን አትሰጥምና እኔ ወንድ ስለማላውቅ ይህ እንዴት ይሆናል?›› አለችው፡፡ መልአኩም መልሶ ‹‹መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፣ የልዑልም ኃይል ይጸልልሻል ስለዚህ ደግሞ ከአንቺ የሚወለደው ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል። እነሆም ዘመድሽ ኤልሳቤጥ እርሷ ደግሞ በእርጅናዋ ወንድ ልጅ ፀንሳለች፡፡ ለእርስዋም መካን ትባል ለነበረችው ይህ ስድስተኛ ወር ነው፣ ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለምና›› አላት፡፡ ክብርት እመቤታችንም ይህን ጊዜ ‹‹እነሆኝ የጌታ ባሪያ እንደ ቃልህ ይሁንልኝ›› አለችው፡፡ መልአኩም ከእርሷ ዘንድ ሄዶ ተሠወረ፡፡ አካላዊ ቃልም በማኅፀኗ አደረ፡፡ በዚያችም ቅጽበት የእመቤታችን የፊቷ መልክ ተለወጠ፣ እንደፀሐይም አሸበረቀ፡፡

#ማስታወሻ
(መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል እመቤታችንን ያበሠራትና የጌታችንም ፅንሰት የተከናወነው በመጋቢት ወር በ29ኛው ቀን በዕለተ እሁድ በ3 ሰዓት ነው፡፡ ታዲያ ምነው በታኅሣሥ 22 ብሥራቱና ፅንሰቱ ተከበረ? ቢሉ መጋቢት 29 ቀን ሰሙነ ሕማማት ላይ ይውላልና በዚህ ወቅት ደግሞ ፍጹም ሐዘን ልቅሶ ጾም ጸሎት ይያዛል እንጂ ደስታ ፌሽታ እልልታ ጭብጨባ የለም፡፡


ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን፤ ለቅዱሳን የተለመነች ክብርን የተመላች ድንግል ወላዲተ አምላክ ለእኛም ትለመነን! አምላካችን ልጇ በምልጃዋ ይማረን!

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

✞ የአለምን_በደል ✞

የአለምን በደል የሰውን ግፍ አይቶ
ዘጠና ዘጠኙን መላእክቱን ትቶ
ጽድቅን ሊመሰርት በደልን አጥፍቶ

የሰላሙ መሪ የሰላሙ ዳኛ                  
አምላክ ተወለደ ተጠመቀ ለእኛ

የሰማያት ሰማይ የማይችለው ንጉስ
ተወልዶ ሲጠመቅ እኛን ለመቀደስ
ተራሮች ደንግጠው ዘለሉ በመንፈስ

         /አዝ * * * * *

ባሕር ተጨነቀች ጠበባት መሬቱ
ዮርዳኖስም ሸሸአልቆመም ከፊቱ
እንደተናግረዉ ዳዊት በትንቢቱ

         /አዝ * * * * *

ልጁ በዮርዳኖስ ጽድቅን ሲመሰርት
መጣ በደመና ሰማያዊው አባት
እየመሰከረ የልጁን ጌትነት

         /አዝ * * * * *

እንደምናነበው በወንጌል ተፅፎ
መንፈስ ቅዱስ ታየ በራሱ ላይ አርፎ
በእርግብ ምሳሌ ክንፉን አሰይፎ

         /አዝ * * * * *

ባሕር ስትጨነቅ ተራራ ሲዘምር
ሰማዩ ሲከፈት ደመና ሲናገር
አለም በዛሬው ቀን አየች ልዩ ምሥጢር

#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።

   ╔​✞═══●◉❖◉●═══✞╗
       ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞
   ❖ @
mezmuredawit  ❖
   ❖ @mezmuredawit  ❖
   ❖ @mezmuredawit  ❖  
      ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞
  ╚✞═══●◉❖◉●═══​✞╝

✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

#ታኅሣሥ_19

#ሊቀ_መላእክት_ቅዱስ_ገብርኤል

ታኅሣሥ ዐስራ ዘጠኝ በዚህች ቀን ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ሠለስቱ ደቂቅ ያዳነበት ነው፡፡ ንጉሥ ናቡከደነፆር ከአባታቸው ከይሁዳው ንጉሥ ከኢዮአቄም ጋር የማረካቸው አናንያ፣ ሚሳኤልና አዛርያ እግዚአብሔር በዚህች ዕለት መልአኩን ልኮ ታላቅ ተአምር አድርጎላቸዋል፡፡

ንጉሥ ናቡከደነፆር እነዚህን ወጣቶች በቤተ መንግሥቱ ውስጥ ጥበብን እያስተማረ ካሳደጋቸው በኋላ በባቢሎን ሀገሮች ሁሉ ውስጥ ሾማቸው፡፡ ከዚህም በኋላ ንጉሡ የወርቅ ምስል በሠራ ጊዜ መኳንንቱንና በግዛቱ ውስጥ ያሉ ሁሉ ለዚያ ምስል እንዲሰግዱ አዘዘ፡፡ በዚህም ጊዜ ለጣዖቱ ባለመስገድ እግዚአብሔርን ብቻ በማምለክ የጸኑት እነዚህ ሦስት ወጣቶች ብቻ ነበሩ፡፡ ስለ እነርሱ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ እንዲህ ተብሎ ነው የተጻፈው፡-
‹‹ንጉሡ ናቡከደነፆር ቁመቱ ስድሳ ክንድ ወርዱም ስድስት ክንድ የሆነውን የወርቁን ምስል አሠራ፤ በባቢሎንም አውራጃ በዱራ ሜዳ አቆመው፡፡ ንጉሡም ናቡከደነፆር መኳንንትንና ሹማምቶችን፥ አዛዦችንና አዛውንቶችን፥ በጅሮንዶችንና አማካሪዎችን፣ መጋቢዎችንም፣ አውራጃ ገዦችንም ሁሉ ይሰበስቡ ዘንድ፣ ንጉሡም ናቡከደነፆር ላቆመው ምስል ምረቃ ይመጡ ዘንድ ላከ፡፡ በዚያን ጊዜም መኳንንቱና ሹማምቶቹ፣ አዛዦቹና አዛውንቶቹ፣ በጅሮንዶቹና አማካሪዎቹ፣ መጋቢዎቹና አውራጃ ገዦቹ ሁሉ ንጉሡ ናቡከደነፆር ላቆመው ምስል ምረቃ ተሰበሰቡ፤ ናቡከደነፆርም ባቆመው ምስል ፊት ቆሙ፡፡ አዋጅ ነጋሪውም እየጮኸ እንዲህ አለ፡- ‹ወገኖችና አሕዛብ በልዩ ልዩ ቋንቋም የምትናገሩ ሆይ! የመለከትንና የእንቢልታን፣ የመሰንቆንና የክራርን፣ የበገናንና የዋሽንትን፣ የዘፈንንም ሁሉ ድምፅ በሰማችሁ ጊዜ፣ ተደፍታችሁ ንጉሡ ናቡከደነፆር ላቆመው ለወርቁ ምስል እንድትሰግዱ ታዝዛችኋል፡፡ ተደፍቶም የማይሰግድ በዚያን ጊዜ በሚነድድ እሳት እቶን ውስጥ ይጣላል፡፡› ስለዚህ በዚያን ጊዜ አሕዛብ ሁሉ የመለከቱንና የእንቢልታውን፣ የመሰንቆውንና የክራሩን፣ የበገናውንና የዘፈኑንም ሁሉ ድምፅ በሰሙ ጊዜ፣ ወገኖችና አሕዛብ በልዩ ልዩ ቋንቋም የተናገሩ ሁሉ ተደፉ፤ ንጉሡም ናቡከደነፆር ላቆመው ለወርቅ ምስል ሰገዱ፡፡

በዚያን ጊዜም ከለዳውያን ቀርበው አይሁድን ከሰሱ፡፡ ለንጉሡም ለናቡከደነፆር ተናገሩ እንዲህም አሉ ‹ንጉሥ ሆይ! ሺህ ዓመት ንገሥ፡፡ አንተ ንጉሥ ሆይ የመለከትንና የእንቢልታን፣ የመሰንቆንና የክራርን፣ የበገናንና የዋሽንትን፣ የዘፈንንም ሁሉ ድምፅ የሚሰማ ሰው ሁሉ ተደፍቶ ለወርቁ ምስል ይስገድ፤ ተደፍቶም የማይሰግድ በሚነድድ እሳት እቶን ውስጥ ይጣላል ብለህ አዘዝህ፡፡ በባቢሎን አውራጃ ሥራ ላይ የሾምሃቸው ሲድራቅና ሚሳቅ አብደናጎም የሚባሉ አይሁድ አሉ፤ ንጉሥ ሆይ! እነዚህ ሰዎች ትእዛዝህን እንቢ ብለዋል፤ አማልክትህን አያመልኩም፥ ላቆምኸውም ለወርቁ ምስል አይሰግዱም፡፡› ናቡከደነፆርም በብስጭትና በቍጣ ሲድራቅንና ሚሳቅን አብደናጎንም ያመጡ ዘንድ አዘዘ፤ እነዚህንም ሰዎች ወደ ንጉሡ ፊት አመጡአቸው፡፡ ናቡከደነፆርም ሲድራቅና ሚሳቅ አብደናጎም ሆይ! አምላኬን አለማምለካችሁ ላቆምሁትም ለወርቁ ምስል አለመስገዳችሁ እውነት ነውን? አሁንም የመለከቱንና የእንቢልታውን የመሰንቆውንና የክራሩን የበገናውንና የዋሽንቱን የዘፈኑንም ሁሉ ድምፅ በሰማችሁ ጊዜ ተደፍታችሁ ላሠራሁት ምስል ብትሰግዱ መልካም ነው፤ ባትሰግዱ ግን በዚያ ጊዜ በሚነድድ እሳት እቶን ውስጥ ትጣላላችሁ፤ ከእጄስ የሚያድናችሁ አምላክ ማን ነው?›› ብሎ ተናገራቸው፡፡ ሲድራቅና ሚሳቅ አብደናጎም መለሱ ንጉሡን ‹ናቡከደነፆር ሆይ! በዚህ ነገር እንመልስልህ ዘንድ አስፈላጊያችን አይደለም፡፡ የምናመልከው አምላካችን ከሚነድደው ከእሳቱ እቶን ያድነን ዘንድ ይችላል፤ ከእጅህም ያድነናል፡፡ ነገር ግን ንጉሥ ሆይ! እርሱ ባያድነን አማልክትህን እንዳናመልክ ላቆምኸውም ለወርቁ ምስል እንዳንሰግድለት እወቅ› አሉት፡፡

የዚያን ጊዜም ናቡከደነፆር በሲድራቅና በሚሳቅ በአብደናጎም ላይ ቍጣ ሞላበት፡፡ የፊቱም መልክ ተለወጠባቸው፡፡ እርሱም ተናገረ የእቶንም እሳት ይነድድ ከነበረው ይልቅ ሰባት እጥፍ አድርገው እንዲያነድዱት አዘዘ፡፡ ሲድራቅንና ሚሳቅንም አብደናጎንም ያስሩ ዘንድ ወደሚነድድም ወደ እቶን እሳት ይጥሉአቸው ዘንድ በሠራዊቱ ውስጥ ከነበሩት ኃያላን አዘዘ፡፡ የዚያን ጊዜም እነዚህ ሰዎች ከሰናፊላቸውና ከቀሚሳቸው ከመጐናጸፊያቸውም ከቀረውም ልብሳቸው ጋር ታስረው በሚነድድ በእቶን እሳት ውስጥ ተጣሉ፡፡ የንጉሡም ትእዛዝ አስቸኳይ ስለሆነ የእቶኑም እሳት እጅግ ስለሚነድድ፣ ሲድራቅንና ሚሳቅን አብደናጎንም የጣሉአቸውን ሰዎች የእሳቱ ወላፈን ገደላቸው፡፡ እነዚህም ሦስቱ ሰዎች ሲድራቅና ሚሳቅ አብደናጎም ታስረው በሚነድደው በእቶኑ እሳት ውስጥ ወደቁ፡፡ የዚያን ጊዜም ንጉሡ ናቡከደነፆር ተደነቀ ፈጥኖም ተነሣ፤ አማካሪዎቹንም ‹ሦስት ሰዎች አስረን በእሳት ውስጥ ጥለን አልነበረምን?› ብሎ ተናገራቸው፡፡ እነርሱም ‹ንጉሥ ሆይ! እውነት ነው› ብለው ለንጉሡ መለሱለት፡፡ እርሱም ‹እነሆ እኔ የተፈቱ በእሳቱም መካከል የሚመላለሱ አራት ሰዎች አያለሁ፤ ምንም አላቈሰላቸውም፤ የአራተኛውም መልክ የአማልክትን ልጅ ይመስላል› ብሎ መለሰ፡፡ የዚያን ጊዜም ናቡከደነፆር ወደሚነድደው ወደ እሳቱ እቶን በር ቀርቦ ‹እናንተ የልዑል አምላክ ባሪያዎች ሲድራቅና ሚሳቅ አብደናጎም! ኑ ውጡ› ብሎ ተናገራቸው፡፡ ሲድራቅና ሚሳቅም አብደናጎም ከእሳቱ መካከል ወጡ፡፡

መሳፍንቱና ሹማምቶቹም አዛዦቹና የንጉሡ አማካሪዎች ተሰብስበው እሳቱ በእነዚያ ሰዎች አካል ላይ ኃይል እንዳልነበረው፣ የራሳቸውም ጠጕር እንዳልተቃጠለች ሰናፊላቸውም እንዳልተለወጠ፣ የእሳቱም ሽታ እንዳልደረሰባቸው አዩ፡፡ ናቡከደነፆርም መልሶ ‹መልአኩን የላከ ከአምላካቸውም በቀር ማንም አምላክ እንዳያመልኩ ለእርሱም እንዳይሰግዱ ሰውነታቸውን አሳልፈው የሰጡትን የንጉሡንም ቃል የተላለፉትን በእርሱ የታመኑትን ባሪያዎቹን ያዳነ፣ የሲድራቅና የሚሳቅ የአብደናጎም አምላክ ይባረክ፡፡ እኔም እንደዚህ የሚያድን ሌላ አምላክ የለምና በሲድራቅና በሚሳቅ በአብደናጎም አምላክ ላይ የስድብን ነገር የሚናገር ወገንና ሕዝብ በልዩ ልዩም ቋንቋ የሚናገሩ ይቈረጣሉ፣ ቤቶቻቸውም የጕድፍ መጣያ ይደረጋሉ ብዬ አዝዣለሁ› አለ፡፡ የዚያን ጊዜም ንጉሡ ሲድራቅንና ሚሳቅን አብደናጎንም በባቢሎን አውራጃ ውስጥ ከፍ ከፍ አደረጋቸው፡፡›› ትንቢተ ዳንኤል 3፡1-30፡፡

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም መልአኩ በአማላጅነቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

#✞_ገብርኤል_ተሾመ_

የስሙ ትርጓሜ ሰው የሆነ አምላክ ነው
መልአኩ ገብርኤል በአምላክ ፊት ሚቆመው

ተፈጥሮህ ረቂቅ ከነፋስ ከእሳት
ነዱን የሚያደክም የሚያሳጣ ጉልበት
ሰባት እጥፍ ቢሆን የእሳቱ ነበልባል
አንተ ስትመጣ/2×/ አይችልም ሊያቃጥል

          /አዝ=====

ገብርኤል ተሾመ በሰማይ በራማ
መጽናናትን ልሰብክ ደስታን ልታሰማ
ርግማን ማለፉን በእውነት ነገረከን
ሰባኬ ወንጌል ነህ/2×/ የአዲሱ ኪዳን

          /አዝ=====

የተክህኖ ልብስህ እጅግ የሚያበራ
መብረቃዊ ኮከብ ለዓይን የሚያስፈራ
አየንህ ስትቆም በእግዚአብሔር ፊት
ምስጋናን ስትሰዋ/2×/ ስታሳርግ ጸሎት

       /አዝ=====

ትካዜና ኀዘን እጅግ የከበበው
ሁሉጊዜ ሚያነባ ከሰው ወገን ማነው
አረጋጊ መልአክ እንዳንተ የለምና
ገብርኤል ሆይ ድረስ/2×/ ስንጠራህ ቶሎ ና


👉ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ

#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።

╔​✞═══●◉❖◉●═════✞╗
   ❖   @mezmuredawit     ❖
   ❖   @mezmuredawit     ❖
   ❖   @mezmuredawit     ❖  
╚✞═══●◉❖◉●═════​✞╝

✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

✞  ​​ጥምቀተ ባሕር ✞

ጥምቀተ ባሕር  ዮርዳኖስ ነያ(፪)
ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ(፪)

ጌታችን ሲጠመቅ ባሕር ምን አለች
አልችለውም ብላ ወደ ኋላ ሸሸች
ብርሃነ መለኮት በወንዞች ሲሞላ
ዮርዳኖስም ሸሸ  ቀረ ወደ ኋላ
    
            /አዝ=====

አብ በመጣ ጊዜ ደመናውን ጭኖ
መንፈስ ቅዱስ ታየ በርግብ አምሳል ሆኖ
ለልጁ ምስክር ሊሆን  ፈለገና
ቃሉን ተናገረ ሆኖ በደመና

            /አዝ=====

ጌታችን ሲጠመቅ በሰላሳ ዓመት
ባህር ኮበለለች ግዑዟ ፍጥረት
ሰማይ ተከፈተ ሆነልን ፀአዳ
ምስጢረ ሥላሴ ታወቀ ተረዳ

            /አዝ=====

እልል በይ ዮርዳኖስ የጥምቀት  መገኛ
የፅድቅ መሰላል ድህነታችን ለኛ
ቀላያት አብርህት ብዙዎች እያሉ
እንደምን ተመረጥሽ ዮርዳኖስ ከሁሉ


#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።


╔ ​✞ ═════●◉❖◉●═════✞╗
✢    ✥
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit
❖ @mezmuredawit @enamsgn
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
                                    ✥   ✢   
   ╚✞ ═════●◉❖◉●═════​✞╝

✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

✞ ተወለደ ሩኅሩኅ ጌታ ✞

ተወለደ ሩኅሩኀ ጌታ(፪)
መድኃኔዓለም የዓለም መከታ
አማኑኤል የኛ መከታ

ተወለደ - - - የዓለም ፈጣሪ
ተወለደ - - - ቸሩ አባት
ተወለደ - - - እኛን ሊያድነን
ተወለደ - - - ከኃጢያት ሞት
ተወለደ - - - እርሱም እንደኛ
ተወለደ - - - እንደ ህፃን
ተወለደ - - - ድንቅ ነው ፍቅሩ
ተወለደ - - - መድኃኔዓለም

/አዝ=====

ተወለደ - - - ፍቅር ቢስበው
ተወለደ - - - የሠው ልጆች
ተወለደ - - - መጣ ከሠማይ
ተወለደ - - - ወልደ እግዚአብሔር
ተወለደ - - - ከእመቤታችን
ተወለደ - - - ተወለደልን
ተወለደ - - - በቤተልሔም
ተወለደ - - - በከብቶች ግርግም

/አዝ=====

ተወለደ - - - የምስራቅ ሠዎች
ተወለደ - - - መጡ ሊሠግዱ
ተወለደ - - - ስጦታን ይዘው
ተወለደ - - - እንደ ሥርዓቱ
ተወለደ - - - ወርቅ አመጡለት
ተወለደ - - - ስለ መንግስቱ
ተወለደ - - - ዕጣን ለክብሩ
ተወለደ - - - ከርቤን ለሞቱ


👉ዘማሪ ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ


#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።


╔ ​✞ ═════●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit
❖ @mezmuredawit @enamsgn
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
✥ ✢
╚✞ ═════●◉❖◉●═════​✞╝

✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

✞ ወዳንቺ የመጣው ✞

ወዳንቺ የመጣው በብሩህ ደመና
ከሦስቱ አካል አንዱ ክርስቶስ ነውና
የጠፋ በግ አዳም ታደሰ በጌታ
በአንቺ ተፈጸመ የሰው ልጆች ደስታ

በደይን የተጣለች ሄዋን ተደሰተች
የደስታ መፍለቂያ አንቺን ስላገኘች
የበረከት ፍሬ ካንቺ ተገኘልን
የወይን ቦታ ነሽ ድንግል እናታችን

          /አዝ=====

ወልድም ባህሪሽን ባህሪ አድርጎት
ለፍጥረታት ጌታ መዓዛሽ ተስማምቶት
ካንቺ ይወለድ ዘንድ ፍጹም ሊላላክሽ
በጥቂቱ አደገ ተልኮና ታዞሽ

          /አዝ=====

ከድንግልና ጋር አንድ የሆነ ሀሊብ
በሩካቤ ሳይሆን በመስራት እንደ ንብ
ከሆድ መጥበብ ጋራ የመለኮት ስፋት
እንቺ ሆነሽ ሳለ ታናሿ ሙሽሪት

          /አዝ=====

በፍጡር ህሊና የማይመረመር
እፁብ ነው ድንቅ ነው የመጽነሷ ነገር
እሳት ወነበልባል በሆድሽ ውስጥ ሲያድር
ነደ ነበልባሉ አልፈጀሽም ነበር

👉ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ

#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።

╔ ​✞ ═════●◉❖◉●═════✞╗
        ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit
❖ @mezmuredawit @enamsgn
         ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ 
   ╚✞ ═════●◉❖◉●═════​✞╝

✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

✞ በዛሬው_ጥምቀቱ ✞

በዛሬው ጥምቀቱ እሰይ እሰይ 
ተነግሮ አዋጅ እሰይ እሰይ 
ነጻነት አገኘን እሰይ እሰይ 
በእግዚአብሔር አብ ልጅ እሰይ እሰይ 
እሰይ እሰይ ተወለደ
እሰይ እሰይ ተተመቀ/2/ 
ከሰማየ ሰማይ ወረደ/2/ 
ከድንግል ማርያም ተወለደ

አብም መሰከረ እሰይ እሰይ 
ቃሉን አላበየም እሰይ እሰይ 
የምወደው ልጄ እሰይ እሰይ 
ይሄ ነው እያለ እሰይ እሰይ

/አዝ=====

ጌታ በዮሐንስ እሰይ እሰይ 
ሊጠመቅ ሲል ገና እሰይ እሰይ 
ወደ ኋላ ሸሸ እሰይ እሰይ 
ዮርዳኖስ ፈራና እሰይ እሰይ 

/አዝ=====

ተራሮች ዘለሉ እሰይ እሰይ 
እንደ ጊደር ሁሉ እሰይ እሰይ 
እፁብ ነው ድንቅ ነው እሰይ እሰይ 
ምን ይገርም እያሉ እሰይ እሰይ 

/አዝ=====

ውኃን ወይን አረገ እሰይ እሰይ 
በተጠራበት ቤት እሰይ እሰይ 
የብርሃናት ጌታ እሰይ እሰይ 
የዓለም መድኃኒት እሰይ እሰይ 

#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።

╔ ​✞ ═════●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit
❖ @mezmuredawit @enamsgn
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
✥ ✢
╚✞ ═════●◉❖◉●═════​✞╝
✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ

Читать полностью…
Subscribe to a channel