የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ የመዝሙር ግጥሞችን እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን" መዝ 150÷6 " አሕዛብ ሁላችሁ፥ እጆቻችሁን አጨብጭቡ፥ በደስታ ቃልም ለእግዚአብሔር እልል በሉ።" (መዝሙረ ዳዊት 47:1) ለማንኛውም ሀሣብ, ጥቆማ, አስተያየት @Kidusyared_comment_bot ላይ ቢያስቀምጡልን ይደርሰናል
✞ ድንግል በድንግልና ✞
ድንግል በድንግልና ጸንሳ
በድንግልና ትወልዳለች
ስሙንም አማኑኤል ትለዋለች/2/
ገና ሳይጸነስ ዘመኑ ሳይገባ
ገረድ መሆን ሻተች ትንቢቱን አንብባ
ልታያት ናፈቀች ያችን ቅድስት እናት
ለክብርዋ ተገዝታ ውሃ ልትቀዳለት
ባርያ ልሁን አለች ዝቅ አድርጋ ራሷን
መች አወቀችና እናቱ መሆኗን
ጥቂት ለሚሻ ሰው ያውቃል ብዙ መስጠት
በማህጸኗ መቅደስ ሲቀድስ ኖረበት
/አዝ=====
ሐር ወርቁን ስትፈትል በቤተ መቅደሱ
ማደርያው እንድትሆን መረጣት ንጉሱ
በህሊናው ተስላ የነበረች ምናብ
መሰላል ሆነችው ለአዳም ድህነት ርካብ
በጎ መዓዛዋን ውበቷን ወደደ
በማህፀኗ ሊያድር እግዚአብሔር ወረደ
ከኪሩቤል ይልቅ ጀርባዋ ተመቸው
ንጽህይት ናትና የማትቆረቁረው
/አዝ=====
የተዘጋች መቅደስ ከቶ ማትከፈት
ታትማ የኖረች የክብሩ ሰገነት
ማንም አይከፍታትም ጥበብ አላትና
የእስራኤል ቅዱስ ገብቶባታልና
በረቀቀ ጥበብ ድንግል ተደነቀች
በሆዷ ቅዳሴን እያስተናገደች
ጎንበስ አለች ማርያም ውዳሴ ልትሰማ
ከቅኔያት ሀገር ከሆዷ ከተማ
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔ ✞ ═════●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit @enamsgn ❖
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
✥ ✢
╚✞ ═════●◉❖◉●═════✞╝
✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
አትልየኝም ወይ
ናፍቆት ባዛላቸው ደጅ የጠኑ ጣቶች የበሬ መቃኑ
ሰርክ ቢቀረቀር አትዘኝ ጌታዬ ከፍቼ ብትገባስ
ምን አሳይሃለው ከበደሌ በቀር ጣትህ እስኪ ቆስል
ታንኳኳለህ አንተ ሃጢያት ለጠፈራት የመከነች ፍሬ
ተኝቼ እንዳይመስልህ ክፋት ያከረፋው አያስጠጋም ነውሬ /2/
"መቼ ትሄዳለህ ከደሳሳው ቤቴ ተስፋ
ማድረግ ትተህ ካልጎደለ በረት ላንዲት
ግልገል ፍቅር ምን አንከራተተህ አትፈልገኝ
ልቅር ይደብቀኝ ቤቴ ሽፍንፍኑን ታኮ
በሚሰጡ እጆች ፊት ለመቀበል ማነስ
ያሳፍራል እኮ መቼ ትሄዳለህ" ?
ምን ስስት ነው በጨለማ በሬ ድረስ የሚያደክምህ
ለአንድ ሰው ሊተና ምን ጎደለው ጌትነትህ
ምን ብትወደኝ የኔ ጌታ እግርህ ማይዝል ሊከተለኝ
ከጥፋቴ ቁስል በላይ ትዕግስትህ ነው የገደለኝ
መናፈቅህ መጠን ጎድሎት መፈለግህ ባይለካ
ያሳፍራል ቸር እጆች ፊት ለመቀበል ማነስ ለካ
አዝ
"አትግለጠኝ ልቅር ይሸሸግ እርቃኔ
ጨለማው ታኮ በሚምር ልብ ፊት
ለይቅርታ ማነስ ያሳፍራል እኮ "
መቼ ትሄዳለህ
ወደ ክብርህ እልፍኝ ማደሪያን ከሰህ
ካልጎደለው በረት ላንዲት ባዶ ግልገል
ምን አስተናነሰህ ባንዲት ድኩን መቃን
ካንተ ለመሰወር እንደማልችል ባውቅም
ባፍረት አደቀቀኝ ምህረትህ ጉልበቱ
የድፍረቴን አቅም ተመልከተኝ እማ
ተመልከተኝ እስቲ ጥፋት እኮ ስም
ቢፈልግ ኮርቶ በኔ በተጠራ
ነውር እኮ ቤት ቢኖረው ሰውነቴ የሱ
ስፍራ ሃጢያት እኮ እናት ቢሻ ደም
አምጬ በወለድኩት ክፋት እኮ መልክ
ቢሆን ቁርጥ እሱን በመሰልኩት በደል
እኮ ትግል ቢሻ እኔ እኮ ነኝ ጦር ጉልበቱ
ዝሙት እኮ ውበት ቢሆን መልኬ
ነበር ምልክቱ ደግ እኮ ነህ ሁሉን ሸፋኝ
ምን በግጼ ተገለጠ መራቆቴ ምህረት
አቅፎት በቸር ክንድህ ባመለጠ
እንኳን ልትፈርድ በሸሸከው በመረሳት
ዋጋ ቀለህ እንደገና ለመክዳት
ዛሬም በሬን ታንኳኳለህ
ዛሬም አለህ ዛሬም አለህ ለአትልየኝም ወይ?
ምን ፍቅር ቢያስርህ ነው እንደትጠየፈኝ
የጥፋቴ ፍሬ ካቆሰለኝ በላይ
ትዕግስትህ ገረፈኝ "
ሰርክ በሬ ቢቀረቀር ብማጸንህ ተወኝ ብዬ
ከበደሌ ክምር በቀር አንዳች የለም በጎጆዬ
አትሄድም ወይ መድሃኒቴ ነውሬ ጸንቶ እየገፋህ
ጻድቃን ሞልቶው ከበረትህ ለአንዲት ግልገል ምን
አለፋህ ቆመህ ባይህ ከደጃፌ ልቀበልህ አቅም ከዳኝ
ከመጥፋቴ ህመም በላይ መፈለግህ ፍፁም ጎዳኝ
አዝ
ጥፋት እኮ ስም ቢፈልግ ኮርቶ በኔ በተጠራ
ነውር እኮ ቤት ቢኖረው ሰውነቴ የሱ ስፍራ
ሃጢያት እኮ አባት ቢሻ ደም አምጬ በወለድኩት
ክፋት እኮ መልክ ቢሆን ቁርጥ እሱን በመሰልኩት
በደል እኮ ትግል ቢሻ እኔ እኮ ነኝ ጦር ጉልበቱ
ዝሙት እኮ ውበት ቢሆን መልኬ ነበር ምልክቱ
ደግ እኮ ነህ ሁሉን ሸፋኝ ምን በግጼ ተገለጠ
መራቆቴ ምህረት አቅፎት በቸር ክንድህ ባመለጠ
እንኳን ልትፈርድ በሸሸከው በመረሳት ዋጋ ቀለህ
እንደገና ለመክዳት ዛሬም በሬን ታንኳኳለህ
"ዛሬም አለህ ዛሬም አለህ ለአትልየኝም ወይ?
ምን ፍቅር ቢያስርህ ነው እንደትጠየፈኝ
የጥፋቴ ፍሬ ካቆሰለኝ በላይ
ትዕግስትህ ገረፈኝ "
ሰፈር አልባ ፍቅርህ ዛሬም ወደ እቅፉ
ቢስበኚም ባርኮ እንደምን ልነሳ
በሚምሩ አይኖች ፊት ለመታየት ማነስ
ያሳፍራል እኮ እንጂ ናፍቀህናል
በአርያዎች መሃል እርሃብ አስተናንሶኝ
በገፋውህ እጥፍ ውርደት አጎናብሶኝ
በመከራ ጽናት ፍፁም ተጠንፍጥፎ
የልጅነት ወዜ የፍቅርህ እልፍኝ
የእቅፍክን መዓዛ ባስታወስኩት ግዜ
አንገቴን ሰብሬ ላራውኝ አይኖችህ
ቀን ከሌም ባነባም አባቴ ባንተ ፊት
ልጅ ልባል አይገባም አትቀፈኝ ልቅር
የምህረትህ ዜማ ቢጠራኝ ማርኮ
እንደምን ልነሳ በንጽህ ልብ ፊት
ለመፈቀር ማነስ ያሳፍራል እኮ "
ወደ ፍቅሩ ቢጠሩኝም ብርቱ አካልህ ተንበርክኮ
ያሳፍራል መሃሪ ፊት ለይቅርታ ማነስ እኮ
ምህረት ታቅፈህ ልትኳትን ደስታ ቤቴን እንዲያርሰው
ባዶ ልጅክን አታንኳኳኝ መሸሸጊያ እንደጣ ሰው
ከአይኖችህ ፊት ለመከለል ድኩን ቤቴ ባይደብቀኝ
በምህረትህ ጽኑ ጉልበት ሃፍረት ሰብሮ አደቀቀኝ
ሊመልሰኝ ምን ቢወደም አንደበትህ ምህረት ሰብኮ
ያሳምማል ደግ አባት ፊት ለልጅነት ማነስ እኮ
"መቼ ትሄዳለህ ወደ ክብርህ እልፍኝ
ማደሪያዬን ከሰህ ካልጎደለው በረት ላንዲት
ባዶ ግልገል ምን አስተናነሰህ ያውም
በጨለማ ዘጠኛዘጠኙን በግ ምድረ
በዳ ትተህ መዋረድ ሳይገድህ ከጌትነት
ማዕረግ አንዲት ሃጥእ ሽተህ ከመጓዙ
ብዛት ባይዝልም አካልህ አቅፎኝ እስኪረካ
እንደምን ልቅረብህ ከመልካም አባት ፊት
ለልጅነት ማነስ ያሳፍራል ለካ
እንጂ ናፍቀህኛል በስምህ መስክ ላይ
አጊጦ መታደስ በምስጋናህ ውበት
ዘላለም መቀደስ በደስታህ ወይን
ስር በሃሴት መዋኝት ከሰላምህ
እቅምህ በክብር መገኘት
እንጂ ናፍቀህኛል በጨለማው
ቁስል የብቻ ዓለም ሙሾ ምድረድር እኔ
ቢቸግረኝ እንጂ ልክ አልባ ፍቅርህ
የመሸከም ወኔ እንጂማ እንኳንስm
እንደኔ ላለ ነፍስ በርክሰት በርሃ ስምህን
ተጠምቶህ ለክብርህ ምስጋና ከመቅደስ
ያደረስ መች ይጠግባል ጠርቶህ
መጽናናቴ ሆይ የልጅነት ልቤን ትቢት
አስኮብልሎት ከመንገድ ቢቀርም
አንተ ግን አንተ ነህ ፍቅርህ አይቀየርም
በሊት ተንከራተው ከገፋውት በረት በፍቅር
የጠሩኝ ከጸጸቴ ገዝፈው መማር የቸኮልት
አይኖችህ ሰበሩኝ በገፋሁት ልኬት
በጠፋኩት መጠን እየተከተለ
ላይተወኝ ምን ፍቅር
ላይረሳኝ ምን ስስት
ከእግሮችህ ተሳለ "
በዚህ ሁሉ መጠን መጎንበስ
ልብህን ያላደነደነው በዚህ
ሁሉ ልኬት መገፋት ክብርህን
ያልተፈታተነው በዚህ ሁሉ ስሌት
መፈለግ ተስፋህን ያላመነመነው
ዛሬም ከበራፌ አምነህ ምንታኳኳኝ
እንዴት ብትወደኝ ነው "
ገጣሚ ህሊና ደሳለኝ
ዘማሪ ዲ/ን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
✍ EmeAmelaken
╔✞═══●◉❖◉●═════✞╗
❖ @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit ❖
╚✞═══●◉❖◉●═════✞╝
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
እርሱ ግን በጦርነት እጅግ የበረታ ኃይለኛ ስለነበረ አሁን በታናሽ ሴት ብላቴና ስለተሸነፈ አፈረ፡፡ በዚህም እጅግ ተናዶ ለሥጋዊ ፈቃዱም እንደተመኛት ሊያገኛት ስላልቻለ ተስፋ ቆርጦ በንዴት አንገቷን ይቆርጧት ዘንድ አዘዘ፡፡ የቅድስት አርሴማንም ራሷን ቆረጧትና የሰማትነት ፍጻሜዋ ሆነ፡፡ ከአንገቷም ደም፣ ውኃ፣ ወተትና ማር ወደ አራቱም አቅጣጫ ፈሰሰ፡፡ እርሷና ሌሎቹም 72 ሰማዕታት ከተሰየፉ በኃላ ሥጋቸው ቀምድር ላይ ተጥሎ ቀረ፡፡ ንጉሡም ጋኔን ተጭኖበት መልኩ ተለውጦ እንደ እሪያ ሆነ፡፡ ከዚያ በፊት የአርማንያውን ሊቀ ጳጳሳት አቡነ ጎርጎርዮስን ንጉሡ ድርጣድስ ዕጣን ሊያሳርግ ወደ ጣዖት ቤቱ ሲገባ አቡነ ጎርጎርዮስን ጠርቶ ለአማልክት ዕጣን አሳርጉ ቢላቸው እሳቸውም ትእዛዙን አልፈጽምም ባሉት ጊዜ እጅግ ጽኑ በሆኑ በተለያዩ ሥቃዮች ካሠቃያቸው በኃላ ጥልቅ ጉድጓድ አስቆፍሮ በዚያ ውስጥ ጣላቸው፡፡ አባታችንም በዚያ ጥልቅ ጉድጓድ እንደተጣሉ ለ15 ዓመታት ኖሩ፡፡ ስለምግባቸውም እግዚአብሔር አንዲት እናትን አዘዘላቸው፡፡ በንጉሡ አዳራሽ አቅራቢያም የምትኖረው ይህች ሴት በእግዚአብሔር ታዝዛ እንጀራን እየጋገረች ወደ ጉድጓዱ ትጥልላቸው ነበር፡፡ ከእርሷም በቀር አባታችን በሕይወት መኖራቸውን የሚያውቅ ሰው የለም፡፡ እንዲህም እያደረገች 15 ዓመት ኖራለች፡፡
ንጉሡ ድርጣድስም ቅድስት አርሴማን ማግባት ፈልጎ ሳለ ፈጽሞ እምቢ ብትለው በእርሷ ምክንያት ብዙ ደናግል ሴቶችን ገደለ፡፡ ሰይጣን በልቡ ያደረበት ይህ ንጉሥ ድርጣድስም ደናግሎቹን እና ቅድስት አርሴማን በብዙ ሥቃይ ከገደላቸው በኋላ ሥጋቸውን በተራራ ላይ ጥሎት ነበር፡፡ ነገር ግን ምንም ሳይሆን በጌታችን ጥበቃ ኖረ፡፡ የቅድስት አርሴማንም ውበቷን እያሰበ ስላስገደላት የሚጸጸት ሆነ፡፡ ወገኖቹም ‹‹ከሀዘንህ ታርፍ ዘንድ ወደ ጫካ ሄደን አውሬ አድን›› አሉት፡፡ ንጉሡም በፈረሱ ተቀምጦ ወደ ጫካ ወጣ፡፡ ነገር ግን ሰይጣን ተዋሃደውና በእነ ቅድስት አርሴማና በአቡነ ጎርጎርዮስ ላይ በሠራው ግፍ እግዚአብሔር የተፈጥሮ መልኩን ቀይሮት እንደ እሪያ አደረገው፡፡ ንጉሥ ናቡከደነጾር ከእግዚአብሔር ቁጣ የተነሣ አእምሮው ስቶ ልቡ ተሰውሮ ወደ እንስሳነት እንደተለወጠ ሁሉ (ዳን 4፡28-37) ንጉሥ ድርጣድስም እንዲሁ ከእግዚአብሔር ቁጣ የተነሣ ወደ እሪያነት ተለወጠ፡፡
ንጉሡ ድርጣድስ ወደ እሪያነት ከተለወጠ በኋላ ያገኘውን ሁሉ የሚናከስ ሆነ፡፡ በቤተ መንግሥቱም ባሉ ሰዎች ላይ ሰይጣን አደረባቸውና ታላቅ ጭንቅ ሆነ፡፡ የንጉሡም እኅት በሌሊት "ጎርጎርዮስን ከጉድጓድ ካላወጣችሁት በቀር አትድኑም" የሚል ራእይ አየችና ለወገኖቿ ነግረቻቸው፡፡ የሞተ መስሏቸው ስለነበር ይህን ሲሰሙ እጅግ ደነገጡና ሄደው ቅዱስ ጎርጎርዮስን 15 ዓመት ተጥሎ ከኖረበት ጉድጓድ ውስጥ በገመድ ጎትተው አወጡትና አክብረው ወሰዱት፡፡
እርሱም የእነ ቅድስት አርሴማን ሥጋ ወዴት እንዳደረሱት ሲጠይቅ በተራራው ላይ እንዳለ ነግረውት ሄዶ ሲያየው ምንም ሳይነካው በደህና አገኘው፡፡ አንሥቶም ባማሩ ቦታዎች አኖራቸው፡፡ ሰይጣን ያደረባቸውን የቤተ መንግሥቱንም ሰዎች ፈወሳቸው፡፡ ስለ ንጉሡም ወደ አውሬነት መለወጥ ነግረውት እንዲፈውሰው ለመኑት፡፡ አቡነ ጎርጎርዮስም ወደ ንጉሡ ሄደው በእሪያነቱ ሳለ "ብፈውስህና ባድንህ ከክፉ ሥራህ ትመለሳለህ? በእውነተኛው አምላክ በኢየሱስ ክርስቶስ ታምናለህ?" አሉት፡፡ እሪያ የነበረው ንጉሥም "አዎ" ቢላቸው ጸሎት አድርገው ፈውሱት፡፡ አእምሮውና የቀድሞው መልኩም ተመለሰለት፡፡ ነገር ግን አቡነ ጎርጎርዮስ ንጉሡ ዳግመኛ እንዳይታበይ በማለት ከእግሩ ላይ የእሪያ ጥፍር አስቀሩለት፡፡
የቤተ መንግሥንም ሰዎች ሁሉ ከፈወሳቸው በኋላ 8 ቀን እንዲጾሙ አዘዛቸው፡፡ ሃይማኖትንም አስተምሮ ሥርዓት ሠራላቸው፡፡ እርሱም ክህነት አልነበረውምና ወደ ሮሜው ንጉሥ ወደ አኖሬዎስና ወደ ሊቀ ጳጳሳቱ መልአክት ላኩና ጳጳስ ይላኩላችሁ አላቸው፡፡ የሮሙ ሊቀ ጳጳሳትም ጎርጎርዮስን ሾሞ ላከላቸው፡፡ ንጉሡ አኖሬዎስም በዚህ ተደሰተ፡፡ ጎርጎርዮስም ተሹሞ ከመጣ በኋላ ሁሉንም አጠመቃቸው፡፡ አርማንያም በቅዱስ ጎርጎርዮስ ትምህርት በክርስትና የምትታወቅ አገር ሆነች፡፡ እርሱም በእመቤታችን ስም ቤተ ክርስቲያን ሠራላቸው፡፡ ምእመናንያንም የሰማዕታቱን ሥጋ ሰብስበው በመልካም ቦታ ካስቀመጡት በኃላ የመከራው ዘመን ሲያልፍ የተዋበች ቤተ ክርስቲያን ሠርተው የቅዱሳኑን በዚያ አኖሩ፡፡ ከሥጋቸውም ብዙ ድንቅ ድንቅ ተአምራት ተፈጽመው ታዩ፡፡
የቅድስት አርሴማ ዕረፍቷ መስከረም 29 ነው፡፡ የቤተክርስቲያኗም ቅዳሴ በአርማንያ አገር፣ በኪልቂያ፣ በሶርያ፣ በአንጾኪያና በግብፅ አውራጃዎች ሁሉ በታኅሣሥ ወር በ6ኛው ቀን ሆነ፡፡ ጌታችን ከገባላት ብዙ ቃልኪዳን ውስጥ አንደኛው "ልጁን በአንቺ ስም የጠራውን በመንግሥተ ሰማያት የበለጠና የከበረ ስምን እኔ እሰጠዋለሁ" የሚል ነው፡፡
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በደናግል ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
ሰማዕታቱም አርማንያ አገር እንደደረሱ ጭፍሮቹ የሰማዕታቱን እግሮቻቸውንና እጆቻቸውን እንዳሠሯቸው ለንጉሥ ድርጣድስ አስረኩቧቸው፡፡ መኮንኑም ለንጉሡ "ጌታዬ ሆይ እነሆ አንተ የምታመልካቸውን ጣዖቶችህን የማያመልኩትን ብዙ ክርስቲያኖችን ሰቀልናቸው፣ ገደልናቸው፡፡ የቀሩትንም እየገረፍን ይኸው ከፊትህ አቁመናቸዋል የወደድከውን አድርግባቸው፡፡ አንዲትም ውብ ሆነች ሴት ልጅ አብራቸው መከራ መቀበልን መርጣ መጥታለች የመልኳንም ማማርና ደም ግባቷን ባየን ጊዜ ደንግጠን በእርሷ ላይ አንዳች ክፉ ማድረግ አልተቻለንም" አለው፡፡ ንጉሡም ያመጧት ዘንድ ሲነግረው መኮንኑ "ነገር ግን ጌታዬ ሆይ እርሷ በመልክ የሚስተካከላት የሌለ እጅግ ውብ ብትሆንም 'ከሕይወት ይልቅ መሞት ይሻለኛል' ይምትል ናት" አለው፡፡ ከዚህም በኋላ ሰማዕታቱን ወደ እሥር ቤት በመውሰድ ቅድስት አርሴማን ግን ይዘው ወደ ንጉሡ ዘንድ አመጧት፡፡ እርሷም ወደ ንጉሡ አዳራሽ እያማተበች ስትገባ ንጉሡ ባየት ጊዜ ልቡ ታወከ፡፡ ሰማዕቷ ግን "ከሰማያትና ከምድር ንጉሥ ከእግዚአብሔር አምላኬ ትለየኝ ዘንድ የወደድክ ሰነፍ ንጉሥ ሆይ! የሰይጣን መልአክተኛና የጥፋት ልጅ የይሁዳ ወገን ከእኔ ምን ትሻለህ? ከወደድክስ በእጅህ ሰማዕት እሆን ዘንድ እወዳለሁ" አለችው፡፡ ከዚህም በኋላ ሰማዕቷ በጸለየች ጊዜ ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤል በታላቅ ግርማ ተገለጡላት ነገር ግን ቅድስት አርሴማ "ጌቶች ሆይ! ነፍሰ ገዳይ እንዳልባል በማንም ላይ ጥፋት አይድረስ" ብላ ለመነቻቸው፡፡ ሊይዟት የመጡት ሰዎችም ግርማዋን አይተው ፈሩ፡፡ ሰውነቷንም ቀርበው እንዳይነኳት የመለኮት ኃይል ከለከላቸው፡፡ እነርሱም "ይህች ሴት አስማተኛ ናት፣ ጥበብና ምትሃት አላት" ብለው ለንጉሡ በነገሩት ጊዜ እርሱም "ዛሬ ያሸነፍሽኝ እንዳይመስልሽ ነገ ብርቱዎች በሆኑ አማልክቶቼ ኃይል ድል አደርግሻለሁ" አላት፡፡ እርሷም "ዛሬም ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ይረዳኛል፣ በእኔ በኃጢአተኛይቱና በደካማይቱ ኃይል አይደለም፡፡ በእነዚህ ቅዱሳን ሰማዕታት የጸሎት ኃይል እንጂ" በማለት መለሰችለት፡፡ ሰማዕታቱም ከቅድስት አርሴማ ጋር በእሥር ቤት ሳሉ "የእግዚብሔርን ኃይል በአንቺ ላይ አይተናልና በጸሎትሽ አስቢን" አሏት፡፡ እርሷም "በገድላችሁ ብርታት ለእኔ ጸልዩልኝ" አለቻቸው፡፡ ቅድስት አርሴማ ሌሊት ታላቅ ምሥጢርን አየች፡፡ እልፍ አእላፋት የብዙ ብዙ የሚሆኑ ቅዱሳን መላእክት የሥላሴን ዙፋን ከበው "የጌትነትህ ምስጋና ሰማይንና ምድርን መላ ፍጹም አሸናፊ እግዚአብሔር ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ" እያሉ ሲጮኹ ተመለከተች፡፡ ይህንንም የመላእጅትን ዜማ እንደሰማችና እንዳየች ለሰማዕታቱ ነገረቻቸው፡፡ "ከእነዚህም መላእክት ውስጥ አንዱ ወደ እኔ ተልኮ መጣና በቀኜ ቆሞ በጥላው ሸሽጎ የሕይወትን እንጀራ መግቦኝ የድኅነትን ጽዋ አጠጣኝ፡፡ ያንጊዜም ሥጋዬ ወደ ምድር ወረደ፣ በላዬም ነፍሴ ተመለሰቸ፡፡ ከእንቅልፍ እንደሚነቃና የወይን ጠጅ ጠጥቶ ስካሩ እንደተወው ሰው ነቃሁ" አለቻው፡፡
በነጋም ጊዜ ንጉሡ በፍርዱ ዙፋን ተቀምጦ ሰማዕታቱን ከእሥር ቤቱ አውጥተው ወደ ፍርድ አደባባይ ያመጧቸው ዘንድ አዘዘ፡፡ በፊቱም አቁሞ ለጣዖታት አማልክቶቹ እንዲሰግዱና እንዲሠው አዘዛቸው፡፡ እነርሱም "እኛስ የምናመልከው እውነተኛ አምላክ አለን ለረከሱ ጣዖታት አንገዛም" ባሉት ጊዜ "ትእዛዜን ካልፈጸማችሁ ሰውነታችሁን በትንሽ በትንሹ እየቆራረጥኩ እጥለዋለሁ" አላቸው፡፡ ሰማዕታቱም "በሚያስፈራ ቃልህና በቅጣትህ የምንፈራና አምላካችንን ክርስቶስን የምክደው አይደለንም፡፡ ስለ አምላካችን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነፍሳችንን እንሰጥ ዘንድ ወደ አንተ መጥተናል" አሉት፡፡ ያን ጊዜም ንጉሡ ድርጣድስ እጅግ ተቆጥቶ "ይህችን ሴት በማስቀደም ጽኑ ቅጣት ቅጧቸው የምታስተምራቸው እርሷ ናትና" ብሎ አዘዘ፡፡ ጭፍሮቹም "የሴት ልቧ ደካማ ነውና ቅድሚያ ወንዶችን አሠቃይተን ብንገድል ሴቶቹ ለጣዖቶችህ ይገዛሉ" በማለት ወንዶቹን ለብቻ ወስደው ለተራቡ አንበሶችና ሌሎች አውሬዎች ሰጧቸው፡፡ ቅድስት አርሴማም አጽናናቻቸውና ተሰነባብተው ወደ ሰማዕትነት ገቡ፡፡ ነገር ግን የተራቡት አንበሶችና ሌሎችም አውሬዎች ወደ ሰማዕታቱ መቅረብ አልተቻላቸውም ይልቁንም በሰማዕታቱ ፊት ሰገዱላቸው፡፡ በጅራታቸውም እየዳሰሷቸው አጫወቷቸው፡፡ የቅድስት አርሴማንም የእግሯን ትቢያ ላሱ፡፡ እርሷም በእጆቿ ዳሰሰቻቸው፡፡ አውሬዎቹም ብረቱን እየበጠሱ ንጉሡ ከመንግሥቱ ዙፋን እስኪወድቅ ድረስ አባረሩት፡፡ ወታደሮቹንም ሲያባርሯቸው ከእነርሱ ውስጥ 300 ጭፍሮች ሞቱ፡፡ የተረፉትም ይህንን ተአምር ሲያዩ እጅግ እያደነቁ ሰማዕታቱ ምትሃተኞች መሆናቸውን ተናገሩ፡፡ ይልቁንም ቅድስት አርሴማን "እርሷ መመኪያቸውና መሪያቸው ናትና አስቀድመን እንግደላት" አሉ፡፡
ከዚህም በኋላ ጥልቅ ጉድጓድ ቆፍረው በውስጡ እሳትን አንድደው ሰማዕታቱን ከዚያ ይጨምሯቸው ዘንድ ሲመክሩ ንጉሡ በዚህ ምክራቸው ደስ ተሰኘ፡፡ እንደምክራቸውም ጥልቅ ጉድጓድ ቆፍረው በውስጡ እሳት አንድደው የተለያዩ ሰውነትን ቆራርጠው የሚጥሉ እንደ ዲን፣ ሙጫ፣ ቅንጭብ ጨምረው የእሳቱ ነጎድጓድ እስኪሰማ ድረስ አንድደው ሰማዕታቱን ከዚያ እንዲጨምሯቸው ንጉሡ አዘዘ፡፡ ቅድስት አርሴማንም "አሁን ከዚህ ማን እንሚያድንሽ አያለሁ" አላት፡፡ እርሷም "እኛንስ አምላካችን እንደሚያድነን አሁን ታያለህ አንተ ግን ከዚህ ክፋትህ ካልተመልስክና ጣዖት ማምለክህን ትተው እውነተኛውን አምላክ ካላመለክህ በኋላ ከዘላለማዊው እሳት ወዴት ትሸሻለህ? በማስ ትማጸናለህ? በዕንጨት ነውን ወይስ በድንጋይ?..." በማለት ስለ ዕለተ ምጽዓት ሌላም ብዙ ነገር አስተማረችው፡፡ በዚህም ጊዜ ከወታደሮቹ አንዱ ተነሥቶ በኃይል ሲመታት ከአፍንጫዎቿ ደም እንደ ውኃ ፈሰሰ፡፡ ንጉሡም "በዚህ የምተውሽ አይደለሽም ሥጋሽን በእሳት አቃጥለዋሁ" በማለት ተናገራት፡፡ ያንጊዜም ምድር አፏን ከፍታ ያንን የመታትን ወታደር ዋጠችው፡፡ ይህንንም ያዩ ሁሉ በማድነቅ እጅግ ፈሩ፡፡ ንጉሡም ፈርቶ ከዙፋኑ ላይ ፈጥኖ ተነሣ፡፡ ቅድስት አርሴማም ፈገግ ብላ በእርሱ ይመጣ ዘንድ ያለውን ነገር ትንቢት ነገረችው፡፡ "እግዚአብሔር ስለ እኛ ይበቀልሃል፣ የአጋንንትም ማደሪያ ያደርግሃል፣ እንደ ጅብ በራስህ ሥጋህን እስከምትበላ ድረስ ያሳብድሃል፡፡ መልክህና ምሳሌህ ይለወጣል፣ እንደ በረሃ እሪያም ትሆናለህ፣ የምትናገረውን አታውቅም፣ የእርኩሳን አጋንንት የእግራቸው መረገጫ ትሆናለህ፡፡ ያንጊዜም የሙታንን ትንሣኤ ተስፋ ትታመን ዘንድ አለህ ይህ እንደሚሆንብህ በእውነት እነግርሃለሁ" አለችው፡፡ ንጉሡም ይህን ጊዜ "እናተን በክፉ ቅጣት አሠቃይቼ ከገደልኩ በኋላ ይህን አሁን ያልሽውን ብሆን አይሳዝነኝም" አላት፡፡ ይህንንም ሲነጋገሩ ወታደሮቹ መጥተው የእሳቱ ነበልባል ከሩቅ እስኪታይ ድረስ እንደነደደ ነገሩት፡፡ እርሱም ሰማዕታቱን ከእሥር ቤት አውጥተው በማምጣት ከቅድስት አርሴማ ጋር በእቶኑ እሳት ውስጥ ይጥሏቸው ዘንደ አዘዘ፡፡ ቅድስት አርሴማም ሰማዕታቱን ካጽናናቻቸውና ከመከረቻቸው በኋላ በመስቀል ምልክት አማትባ ማንም ገፍቶ ሳይጨምራት ራሷን ወደ እሳቱ ውስጥ ወረወረች፡፡ ቀጥሎም ዲያቆን ጤሜልዮስ ወደ እሳቱ ተወርውሮ ገባ፡፡ ታላቃቸው ጌርሎስም እንዲሁ ራሱን ወርውሮ ወደ እሳቱ ውስጥ ገባ፡፡ ሁሉም እንዲሁ በየተራ ራሳቸውን እየወረወሩ ገቡ፡፡ በጎች ወደ ወንዝ ውኃ እየሮጡ እንደሚገቡ ሁሉም ሰማዕታት ራሳቸውን እየወረወሩ ወደ እቶኑ እሳት ገቡ፡፡ ይህንንም ሲያደርጉ ያዩአቸው ወታደሮች ሁሉ በሀዘኔታ አለቀሱላቸው፡፡ ነገር ግን ወዲያው
#🖋አዲስ_ዝማሬ_በዘማሪ_ዲያቆን _አቤል_መክብብ
✞ ተናገር አለኝ ✞
ተናገር አለኝ መስክር
ተናገር አለኝ ዘምር
ለቀራንዮ ውለታ
አርምሞ የለም ዝምታ
ለመድኃኔዓለም ውለታ
አርምሞ የለም ዝምታ
ሰው አድርጎኝ ሞቶ በደሙ
ኑሮዬን ባርኮት ሕመሙ
ሰላም አውጥቶ ካስገባ
ልያዝ ለክብሩ ዘንባባ
ሆሳዕና ልበል መድኃኒት
ከፍ በልልኝ የኔ አባት
ተጠምተኸ እኔ ረካሁ
ስራህ ግሩም ነው ደነቀኝ
/አዝ=====
እጆቹን እዩት በእምነት
ቆሰለ ሊሰጠኝ ሕይወት
በዚያ ታትሞ ውበቴ
እየሱስ ለኔ ብርታቴ
ከማንም በላይ ከምንም
ለኔ ልዩ ነው ዘላለም
ሕይወቴን ለእርሱ አስማርኬ
እኔስ በረታሁ በአምላኬ
/አዝ=====
የእሾህ አክሊሉ በራሱ
ለእኔ ቤዛ ነው ሞገሱ
ሞቴን ገድሎታል አባቴ
ሰላሜ እርሱ ነው እረፍቴ
ሰው የመሆኔ ምስጢሩ
የማይለወጥ ነው ፍቅሩ
የገባኝ እውነት በምድር ላይ
ፍቅር ነው ጌታ ኤልሻዳይ
/አዝ=====
ክብሩን ለማወጅ ተነሳሁ
ሲያድነኝ ከሞት እያየሁ
ገመና ሸፋኝ ኪዳኔ
ተራበ ውዴ መድኃኔ
ይሄ ነው የቆመኝ በፊቱ
ወሰን የሌለው ምሕረቱ
ለዚህ ደግነት ውለታ
ምን ይከፈላል ለጌታ
👉ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔✞═══●◉❖◉●═════✞╗
❖ @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit ❖
╚✞═══●◉❖◉●═════✞╝
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
✞ ንፅህተ ንፁሐን
ንፅህተ ንፁሐን ከዊና ከመታቦት ዘዶር ዘሲና
ውስተ ቤተ መቅደስ ነበረት በድንግልና ነበረት
ሲሳያ ህብስተ መና ወስቴ ሀኒ ስቴ ፅሙና
ስታድጊ በቤተመቅደስ
በቅዱስ በእግዚአብሔር መንፈስ
አጊጠሽ በትህትና
ተውበሽ በቅድስና
ምግብሽ የሰማይ መና
ከምድር አደለምና
አካላዊ ቃል መርጦሻል
ትውልዱ ብፅዕት ይሉሻል
አዝ =====
መልዐኩ ፋኑኤል ወርዶ
በክንፉ ለብቻሽ ጋርዶ
መገበሽ ህብስተ መና
አቅርቦ ስግደት ምስጋና
ምግብሽ የሰማይ መና
ከምድር አደለምና
አካላዊ ቃል መርጦሻል
ትውልዱ ብፅዕት ይሉሻል
አዝ =====
ሐርና ወርቁ ተስማምቶ
አጌጠ በእጅሽ ተሰርቶ
በመቅደስ ያለው ማህሌት
አስናቀሽ የአባትሽን ቤት
ምግብሽ የሰማይ መና
ከምድር አደለምና
አካላዊ ቃል መርጦሻል
ትውልዱ ብፅዕት ይሉሻል
አዝ ======
በአምላክ ህሊና ታስበሽ
ከፍጥረት ሁሉ ተመርጠሽ
ዳግሚት ሰማይ ሆነሻል
መለኮት ባንቺ አድሮብሻል
ምግብሽ የሰማይ መና
ከምድር አይደለም እና
አካላዊ ቃል መርጦሻል
ትውልዱ ብፅዕት ይልሻል
ዘማሪ ታዲዎስ ግርማ
╔✞═══●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
❖ @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit ❖
✥ ✢
╚✞═══●◉❖◉●═════✞╝
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
+"+ ቅድስት ቤርሳቤህ +"+
=>ይህቺ እናት አስቀድማ የኦርዮ ሚስት: ቀጥሎ ደግሞ
የልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት ሚስትና የሰሎሞን እናት
ለመሆን በቅታለች:: ቁጥሯ ከደጋግ እናቶቻችን ሲሆን
የድንግል ማርያም ቅድመ አያትም ናት:: አንዳንድ
ሊቃውንት ደግሞ ስሟን "ቤትስባ (ቤተ ሳባ)" :
ትውልዷንም ከኢትዮዽያ ያደርጉታል::=>አምላከ ኤልያስ በምልጃው ለሃገራችንና ለሕዝቧ
ርሕራሔውን ይላክልን:: ከቅዱሳኑም በረከትን ይክፈለን::
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር>>>
✞ ኤልያስ በሰረገላ ✞
ኤልያስ በሰረገላ ሰወረው ደመና{፬}
ደመና ደመና በሰረገላ/2×/
በመንፈስ ቅዱስ ሃይል-----በሰረገላ
ታንፃ በስሙ------በሰረገላ
ይታደሉባታል-------በሰረገላ
ጽድቅና ስላመኑ------በሰረገላ
ቤተክርስቲያን ሆይ-----በሰረገላ
የእግዚአብሔር ስጦታ-----በሰረገላ
አነጸሽ በደሙ-------በሰረገላ
አማኑኤል ጌታን-----በሰረገላ
ደመና ደመና በሰረገላ/2×/
/አዝ=====
በሰማይ ለሚኖር-----በሰረገላ
የእግዚአብሔር መንግስት-----በሰረገላ
መገለጫ ይሁን------በሰረገላ
የምድር በረከት------በሰረገላ
የቅዱሳን አምላክ-----በሰረገላ
እድሮች ሚኖርባት-----በሰረገላ
መላእክትና ሰው-----በሰረገላ
ያመሰገኑባት------በሰረገላ
ደመና ደመና በሰረገላ/2×/
/አዝ=====
የሕይወት መገኛ------በሰረገላ
የፅድቅ ታዛቢነት ነክ-----በሰረገላ
አጌጥሽ በመንፈሱ-----በሰረገላ
በደሙ ተሰርተሽ------በሰረገላ
አምላክ ተገለጠ------በሰረገላ
ከሰማያት ወረዶ-----በሰረገላ
ስርየት አግኝተናል-----በሰረገላ
ባንቺ ተዋህዶ-----በሰረገላ
ደመና ደመና በሰረገላ/2×/
/አዝ=====
ሁሉን አሳልፋ-----በሰረገላ
ፀንታ የኖረች-----በሰረገላ
ከቶ ስትናወጥ-----በሰረገላ
በሲኦል ደጆች-----በሰረገላ
የዳቢሎስ ሴራ-----በሰረገላ
ቀስቱ ያልነካት------በሰረገላ
ያልተቀላቀለች------በሰረገላ
ተዋህዶ ንፅሂት-----በሰረገላ
ደመና ደመና በሰረገላ/2×/
በበሰረገላ በሰረገላ በሰረገላ ሰውረው ደመና{፪}
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔✞══●◉❖◉●═══✞╗
❖ @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit ❖
╚✞═══●◉❖◉●══✞╝
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
እምከብካበ ወልዳ ለድንግል
እንዘ ንብል ኢንትኃጎል
እምከብካበ ወልዳ ለድንግል/2/
ኧኸ
እምከብካበ ወልዳ ለድንግል /2/
ቃል አብ ሕያው የመረጠሽ በተዋሕዶ ያደረብሽ
አማናዊት ጽዮን ማርያም አንቺ ነሽ ማኅደረ
መለኮት ድንግል አንቺ ነሽ
አዝ =====
ረቂቅ ቃል የተጻፈብሽ የድኅነታችን
የታወጀብሽ ኅትምት ሰሌዳ ንጽሕት
አንቺ ነሽ የኪዳኑ ጽላት ብፅዕት አንቺ ነሽ
አዝ ======
ሙሽራሽ ሆነ ቸሩ ልጅሽ ሥጋችንን
ነሥቶ ከሥጋሽ በመርገመ ኀጢአት
ሰንቆሽሽ ሕይወትን አደለን ሆነልን ፈዋሽ
አዝ ======
ንግሥተ ሰማይ በመሆንሽ ባለሟልነትን
ስለታደልሽ ከሠርጉ እንዳይለየን ቅዱሱ
ልጅሽ ተማጽነንብሻል እኛ ልጆችሽ
ቤዛዊተ ኩሉ ይርዳን ጸሎትሽ መንግሥቱን
ለመውረስ ያግዘን ምልጃሽ
ዘማሪ ዲያቆን ፍሬዘር ደሳለኝ
╔✞═══●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
❖ @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit ❖
✥ ✢
╚✞═══●◉❖◉●═════✞╝
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
#ይህንን_ያውቁ_ኖሯል
የ24ቱ ካህናተ ሰማይ ስማቸው የሚከተለው ነው
፩. አካኤል
፪. ፋኑኤል
፫. ጋኑኤል
፬. ታድኤል
፭. አፍድኤል
፮. ዘራኤል
፯. ኤልኤል
፰. ተዳኤል
፱. ዮአኬል
፲. ገርድኤል
፲፩. ልፍድኤል
፲፪. መርዋኤል
፲፫. ኑራኤል
፲፬. ክስልቱኤል
፲፭. ኡራኤል
፲፮. ባቱኤል
፲፯. ሩአኤል
፲፰. ሰላትኤል
፲፱. ጣውርኤል
፳. እምኑኤል
፳፩. ፔላልኤል
፳፪. ታልዲኤል
፳፫. ፐሰልዱኤል
፳፬. አሌቲኤል
(ከአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ - ተአምኆ ቅዱሳን ንባቡና ትርጓሜው ገጽ 149)
✞ ይርየኒ ዓይነሞት ✞
ይርየኒ ዓይነሞት
ወይርከበኒ ኩነኒ
ነፍሴን አደራ በሰማይ /2/
ተክልዬ ፀሐይ
ጽላሌ ፆረኔ ነይመስክሪ
የተክለሃይማኖትን ዝና አውሪ
የንቁርቁሪት ፀበል ማርቀተት
ሁሉም ተፈወሱ ሲጠጡት/2/
/አዝ======
ትትናህ ግሩምነው ቅድስናህ
ሃይቅ እስጢፋኖስ አገልግለህ
ደብረዳም ዘልቀህ ክንፍ አወጣህ
ደብረሊባኖስ ላይ ፍፁም ጸናህ
ደብረሊባኖስ ላይ አርፏል አጽምህ
/አዝ======
ከተታና ደሞት ተሻግረህ
ማርያንን ሁሉ አሳፈርክ
በንብ ቀፎአርገው ቢጥሉህ
ሚካኤል በክንፉ አቀፍህ/2/
/አዝ======
በደብረ አስቦውስጥ ጦር ተክለህ
ሀያዘጠኝ ዘመን ተጋድልህ
ወዝህ ያረፈበት ነጠብጣቡ
ድዊ ይፈውሳል ቃልኪዳኑ
/አዝ======
ይህን ሁሉጸጋ ተችረሀል
ቁጥርህ ከመላእክት ተስተካክሎ
አባቴ አባቴ ስልህ
ነፍሴን ታደግልኝ በምልጃህ /2/
መላከ ሰላም ቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ
╔✞═══●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
❖ @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit ❖
✥ ✢
╚✞═══●◉❖◉●═════✞╝
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
#ኅዳር_21
#ቅድስት_ጽዮን_ድንግል_ማርያም
ኅዳር ሃያ አንድ በዚች ቀን የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የበዓልዋ መታሰቢያ ነው።
"ጽዮን" ማለት "ጸወን - አምባ - መጠጊያ" ማለት ነው። አንድም በምሥጢሩ "ማሕደረ አምላክ" ማለት ነው። ጽዮን የሚለው ስም በቁሙ ለቅዱስ ዳዊት ተራራና ለኪዳኑ ጽላት ሲያገለግል በትንቢታዊ ምሥጢሩ ግን ለድንግል ማርያም ለቤተ ክርስቲያንና ለዘለዓለማዊት ርስት ያገለግላል።
እግዚአብሔር ከዘመነ አበው በሁዋላ በጊዜው ለእሥራኤላውያን ክብር፣ ሞገስ፣ አምባ የምትሆናቸውን ታቦተ ጽዮንን በቅዱስ ሙሴ አማካኝነት ሰጥቷቸዋል። (ዘጸ. 31፥18) ከዚያም ለ500 ዓመታት ከእነሱ ጋር በመሆኗ በፈጣሪና በእነሱ መካከል ድልድይ ሆና ኖራለች።
ከዚያም ባለቤቱ ሲፈቅድ በዘመነ ሳባ በቀዳማዊ ምኒልክ (እብነ መለክ-እብነ ሐኪም) አማካኝነት ወደ ኢትዮዽያ መጥታለች። እነሆ በሃገራችን የ3ሺ ዓመት ቆይታዋን ልትደፍን የቀራት ጥቂት ዓመታት ብቻ ናቸው። ጌታ እንደ ፈቀደ ቅዱስ መስቀሉንና ታቦተ ጽዮንን ይዘን ይሔው በቸርነቱ እንኖራለን።
ያም ሆኖ ታቦተ ጽዮንን መስረቅ የሚፈልጉ ብዙ ቀሳጢዎች እንዳሉ እናውቃለን። ግን አንጨነቅም። ምክንያቱም የመጣችውም የምትጠበቀውም በፈቃደ እግዚአብሔር ነውና እንጸልያለን እንጂ አንጨነቅም። በተለያየ ወሬም ራሳችንን አናማጥንም። ባለቤቱ እንድትሔድ ከፈቀደ ደግሞ ማንም ጉልበተኛ አያስቀራትም።
ታቦተ ጽዮን ብዙ ጊዜ "ጽላተ ኪዳን፣ ታቦተ ሕጉ" እየተባለች ትጠራለች። "ጽሌ" ማለት "ሰሌዳ" እንደ ማለት ሲሆን "ጽላት" ደግሞ በብዙ ቁጥር ነው። "ኪዳን" ደግሞ በፈጣሪና በሰው ልጆች መካከል ያለ "ውል - ስምምነት" ነው።
"ታቦት" ማለት "ማሕደር-ማደሪያ" እንደ ማለት ነው። ሕጉ የተጻፈባቸውን ሰላድው "ጽላት" ስንላቸው የጽላቱ ማደሪያ ደግሞ "ታቦት" ይባላል። ጽላት (ታቦትን) ያመጣ ፈጣሪ ነው። በሐዲስ ኪዳንም ምሥጢርና ሐተታ ቢኖረውም 2 ቦታ ላይ ስለ ታቦት ተጠቅሶ እናገኛለን። (2ቆሮ.6፥16 ፣ ራዕይ.11፥19)
በመጨረሻም ኅዳር ሃያ አንድ ቀን ጽዮን ማርያምን የምናከብርባቸውን ምክንያቶች እንመለከታለን።
#በዚህች_ቀን:-
✞ ታቦተ ጽዮን (ጽላተ ኪዳን) ለሊቀ ነቢያት ቅዱስ ሙሴ መሰጠቷን እናስባለን።
✞ ታቦተ ጽዮን በምርኮ በሄደችበት በሀገረ ፍልስጤም ዳጎን የተባለ የአህዛብን ጣኦት አድቅቃ በድል የተመለሰችበትን ዕለት በማሰብ።
✞ በዘመነ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት በአሚናዳብ ሠረገላ ሁና ከአቢዳራ ቤት ስትመጣ ቅዱሱ ንጉሥ በታላቅ ሐሴት በፊቷ ዘመረ። አገለገለ። ምድራዊ ክብሩን እስኪረሳ ድረስ ለታቦተ አምላክ የተቀኘላት በማሰብ።
✞ ታቦተ ጽዮን ንጉሥ ሰሎሞን ወደ ሠራላት ቤተመቅደስ በክብር የገባችበትን ዕለት በማሰብ፤
✞ የቀደሙ ነብያት ስለእመቤታችን በተለያየ አምሳል ያዩበት ለምሳሌ፦ ነብዩ ዕዝራ በሃገር መንፈሳዊት፣ ሕዝቅኤል በተዘጋች ቤተመቅደስ፣ ዘካርያስ በተቅዋመ ወርቅ ወዘተ ያዩበትን ዕለት በማሰብ፤
✞ ቀዳማዊ ምኒሊክ ከዐሥራ ሁለቱ ነገድ እስራኤል የበኩር ልጅ ጋር ሊቀ ካህናቱን አዛሪያስንና ታቦተ ጽዮንን ይዞ አክሱም የደረሰበትን ዕለት በማሰብ፤
✞ በዘመነ አፄ ባዜን (በ4 ዓ/ም አካባቢ) አማናዊት ጽዮን ድንግል ማርያም ወደ አክሱም ጽዮን በስደት መጥታ ገብታለች። በዚህ ጊዜም 2ቱ ጽዮኖች ሲገናኙ ታላቅ ብርሃን አክሱምን ውጧታልና ይህንንም በማሰብ፤
✞ በአብርሃ ወአፅብሃ ዘመነ መንግስት ክርስትና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሃይማኖት ሆኖ አዋጅ የታወጀበትን በማሠብ፤
✞ አብርሃ ወአጽብሃ በወርቅና በዕንቁ ያሠሩት ባለ አሥራ ሁለት ክፍል ቤተ መቅደስ ለመጀመሪያ ጊዜ ቅዳሴ ቤቱ የተከበረበት ዕለት በመሆኑ፤
✞ በዘጠነኛው መቶ ክፍለ ዘመን ዮዲት ጉዲት አብያተ ክርስቲያንን ስታቃጥል ታቦተ ጽዮንን ይዘው ወደ ዝዋይ ሀይቅ ከተሰደዱ በኋላ ዘመነ ሰላም ሲጀመር አክሱም በነበሩ ካህናት አስታዋሽነት ከዝዋይ ወደ አክሱም የገባችበት ዕለት በመሆኑ፤
በእነዚህ ምክንያቶች በመላው ኢትዮጵያ በተለይም በርእሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ከፍ ባለ መንፈሳዊ በዓል እናከብራለን።
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በእመቤታችን በጸሎቷ የሚገኝ በረከቷም ከሁላችን የክርስቲያን ወገኖች ጋር ይኑር።
( ስንክሳር ዘተዋሕዶ እና #ዲያቆን_ዮርዳኖስ_አበበ)
እንኳን አደረሰን አደረሳችሁ!
✞ እመብርሃን መመኪያችን ✞
እመብርሃን መመኪያችን/2/
የአዳም ተስፋ አለኝታችን
እመብርሃን መመኪያችን
እመብርሃን የአባቶቻችን
እመብርሃን ቃና ለዛቸው
እመብርሀን በችግር ጊዜ
እመብርሀን መንገድ መሪያቸው
እመብርሃን ምን ብዬ ልጥራሽ
እመብርሃን ላወድስሽ
እመብርሃን የምግባር ደሀ
እመብርሃን ባዶ ልጅሽ
/አዝ=====
እመብርሃን የቅዱሳኑ
እመብርሃን ጣዕመ ዜማቸው
እመብርሃን አንቺ ነሽና
እመብርሃን ውብ ድርሰታቸው
እመብርሃን የኛ ስጦታ
እመብርሃን የድል አክሊል
እመብርሃን ባማላጅነት
እመብርሃን ለታመነብሽ
/አዝ=====
እመብርሀን የይስሀቅ መዓዛ
እመብርሃን በፍኖተ ሎዛ
እመብርሃን የያዕቆብ መሠላል
እመብርሃን የአቤል የዋኅት
እመብርሃን የዕሴ ቸርነት
እመብርሃን የኢያሱ ሐውልት
እመብርሃን የሕይወት ውሃ
እመብርሃን የሳሙኤል ዘይት
እመብርሃን ርግበ ሠናይት
እመብርሃን ንግሥተ ሠማይ
/አዝ=====
እመብርሃን መልካሟ ርግብ
እመብርሃን የኖሕ መልክቱ
እመብርሃን የኅጥአን ተስፋ
እመብርሃን የልብ ብርታቱ
እመብርሃን ምስራቻችን
እመብርሃን ውስጣችን ያለሽ
እመብርሃን በምድር በሰማይ
እመብርሃን አምሳያም የለሽ
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔✞═══●◉❖◉●═════✞╗
❖ @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit ❖
╚✞═══●◉❖◉●═════✞╝
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
#ኅዳር_15
#ቅዱስ_ሚናስ_ሰማዕት
ኅዳር ዐሥራ አምስት በዚህች ቀን የስሙ ትርጓሜ ቡሩክና የታመነ የሆነ ቅዱስ ሚናስ በሰማዕትነት አረፈ። የዚህም ቅዱስ አባቱ አናቅዮስ ከሚባል አገር ነው ስሙም አውዶክስዮስ ነው እርሱም አገረ ገዥነት ተሹሞ ሳለ ወንድሙ ቀንቶበት በንጉሥ ዘንድ ነገር ሠራበት ንጉሡም ወደ አፍራቅያ አገር ሰደደውና በዚያም አገረ ገዢ አድርጎ ሾመው የአገር ሰዎችም ሁሉ ደስ አላቸው እርሱ ለሰው የሚራራ እግዚአብሔርንም የሚፈራ ደግ ሰው ነውና ።
እናቱም ልጅ አልነበራትም በአንዲት ዕለት ወደ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን በበዓልዋ ቀን ገብታ የክርስቲያንን ወገኖች ያማሩ ልብሶችን ለብሰው ከልጆቻቸው ጋር ደስ እያላቸው ሲገቡ አየቻቸው። በእመቤታችንም በቅድስት ድንግል ማርያም ሥዕል ፊት አለቀሰች ልጅን ይሰጣት ዘንድ ወደ ልጅዋ ወደ እግዚአብሔር እንድትለምንላትም ለመነቻት በዚያንም ጊዜ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ሥዕል አሜን የሚል ቃል ወጣ።
ከዚህም በኋላ ወደ ቤቷ ገብታ ይህን ቃል ለባሏ ነገረችው እርሱም የእግዚአብሔር ፈቃዱ ይሁን አለ። ከጥቂት ቀኖችም በኋላ እግዚአብሔር ይህን የተባረከና የከበረ ልጅን ሰጣት የእመቤታችንም ሥዕል ሚናስ ብላ እንደሰየመችው ስሙን ሚናስ ብለው ሰየሙት። ጥቂት በአደገ ጊዜም የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት አስተማሩት። ዐሥራ ሁለት ዓመትም ሲሆነው በመልካም ሽምግልና አባቱ አረፈ ከእርሱም በኋላ በሦስተኛ ዓመት እናቱ አረፈች ቅዱስ ሚናስም ብቻውን ቀረ።
መኳንንቱም አባቱን አብዝተው ከመውደዳቸው የተነሣ ሚናስን በአባቱ ፈንታ ምስፍናን ሾሙት እርሱም የክርስቶስን አምልኮት አልተወም።
ዲዮቅልጥያኖስም በካደ ጊዜ ሁሉንም ሰዎች ጣዖታትን እንዲአመልኩ አዘዛቸው ብዙዎችም ክብር ይግባውና በክርስቶስ ስም በሰማዕትነት ሞቱ ። በዚያንም ጊዜ ሚናስ ሹመቱን ትቶ ወደ ገዳም ገባ ታላቅ ተጋድሎን እየተጋደለ ብዙ ዘመናት ኖረ ። በአንዲትም ዕለት ሰማይ ተከፍቶ ሰማዕታትን የብርሃን አክሊሎችን ሲያቀዳጇቸው አየ። ስለ ክርስቶስ ስም በመከራ የደከመ ይህን አክሊል ይቀበላል የሚል ቃልን ሰማ። በዚያንም ጊዜ ወደ ከተማ ተመለሰና ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ታመነ ሰዎችም አብዝተው አባበሉት በወገን የከበረ እንደሆነ እነርሱ ያውቁ ነበርና።
መኰንኑም ብዙ ቃል ኪዳን ገባለት ባልሰማውም ጊዜ ጽኑዕ በሆነ ሥቃይ እንዲአሠቃዩት አዘዘ። ማሠቃየቱንም በሰለቸ ጊዜ ራሱን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ ። በመንግሥተ ሰማያትም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበለ ብዙዎችም በእርሱ ምክንያት ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም በሰማዕትነት ሞቱ።
የቅዱስ ሚናስንም ሥጋ ወደ እሳት እንዲጥሉት መኰንኑ አዘዘ እሳትም አልነካውም ምእመናን ሰዎችም የቅዱስ ሚናስን ሥጋ ወስደው በአማሩ ልብሶች ገነዙት የስደቱ ወራትም እስከሚፈፀም በአማረ ቦታ ውስጥ አኖሩት።
በዚያንም ወራት የመርዩጥ አገር ሰዎች ከአምስቱ አገሮች ሠራዊትን ሊአከማቹ ወደዱ የቅዱስ ሚናስንም ሥጋ ረዳት ይሆናቸው ዘንድ በመንገድም እንዲጠብቃቸው ከእርሳቸው ጋር ወሰዱት።
እነርሱም በባሕር ላይ በመርከብ ውስጥ ሳሉ ፊታቸው እንደ ከይሲ አንገታቸው እንደ ግመል አንገት ያለ አውሬዎች ከባሕር ወጡ ይልሱትም ዘንድ ወደ ቅዱስ ሚናስ ሥጋ አንገታቸውን ዘረጉ ከቅዱስ ሚናስም ሥጋ እሳት ወጥታ እነዚያን አራዊት አቃጠለቻቸው ሰዎችም አይተው አደነቁ ደስታም አደረጉ ፈርተው ነበርና።
ወደ እስክንድርያ አገርም ደርሰው ሥራቸውን ፈጽመው ወደ ሀገራቸው በሚመለሱ ጊዜ የቅዱስ ሚናስን ሥጋ ከእሳቸው ጋር ሊወስዱ ወደው በገመል ላይ በጫኑት ጊዜ ገመሉ ከቦታው የማይነሣ ሆነ። ሁለተኛም በሌላ ገመል ጫኑት እርሱም መነሣትን እምቢ አለ። አብዝተውም ደበደቡት ገመሉም ከቶ አልተንቀሳቀሰም እነርሱም ያ ቦታ እግዚአብሔር የፈቀደለት መሆኑን አወቁ ቦታውንም አዘጋጅተው በዚያ ቀበሩት።
ጌታችንም በበግ እስከገለጠው ድረስ ብዙ ዘመናትን በዚያ ቦታ ኖረ ይህም ቤተ ክርስቲያኑ በከበረችበት በሰኔ ዐሥራ አምስት ቀን ተጽፎአል።
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ኅዳር_እና_ጥር_15)
✞ ሚካኤል ✞
የከበርክ ታላቁ መልአክ
ሚካኤል ህይወቴን ባርክ
አምናለሁ ምልጃህ ፈጣን ነው
ለኔማ የተለየ ነው
በቃላት የማይገለጽ አለብኝ ትልቅ ውለታ
ልጅግን አቁመኸኛል ጠላቴን አንተ እየረታ
አይችልም ስምህ ሲጠራ ሽንፈቱን ያውቀዋልና
እኔ ግን ላመሰግንህ መጣሁኝ በአዲስ ምስጋና
ሚካኤል ርግባ ለገነተ ሰማይ
ተአምርህ ተገልጧል በኔ ላይ
/አዝ=====
አይነሳም የቀድሞ እባብ የለኝን የውስጤን ሰላም
አየሁት ያኔ በውጊያ አይችልም አንተን መቋቋም
በጠጠር ይወድቃል ጎልያድ ለዳዊት ይሆናል ድሉ
ልትረዳኝ ከኔ ጋራ ነህ ሁል ጊዜ ሚካኤል ኃያሉ
/አዝ=====
ፈጠነ ፈርኦን ለጥፋት ለመልቀቅ ሕዝቡን ዘገየ
ሚዋጋው እግዚአብሔር ሆኖ እርሱ ግን ልቡ ታበየ
ለሊቱን በልዩ ብርሃን ቀኑን ጋርደህ ደመና
ተሻገርን በታላቅ ክብር ፈርኦን ባህር ገባና
/አዝ=====
ስለ ሕዝብ እንደምትቆም በመጽሐፍ እንደተጻፈ
ይረታል አይችልም በውጊያ በምልጃህ ያልተደገፈ
እኔ ግን ምልጃህን አምኜ ሚካኤል እጠራሃለው
መንገዴን የምትመራ ነህና አከብርሃለው
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔✞═══●◉❖◉●═════✞╗
❖ @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit ❖
╚✞═══●◉❖◉●═════✞╝
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
✞ ተወለደ ሩኅሩኅ ጌታ ✞
ተወለደ ሩኅሩኀ ጌታ(፪)
መድኃኔዓለም የዓለም መከታ
አማኑኤል የኛ መከታ
ተወለደ - - - የዓለም ፈጣሪ
ተወለደ - - - ቸሩ አባት
ተወለደ - - - እኛን ሊያድነን
ተወለደ - - - ከኃጢያት ሞት
ተወለደ - - - እርሱም እንደኛ
ተወለደ - - - እንደ ህፃን
ተወለደ - - - ድንቅ ነው ፍቅሩ
ተወለደ - - - መድኃኔዓለም
/አዝ=====
ተወለደ - - - ፍቅር ቢስበው
ተወለደ - - - የሠው ልጆች
ተወለደ - - - መጣ ከሠማይ
ተወለደ - - - ወልደ እግዚአብሔር
ተወለደ - - - ከእመቤታችን
ተወለደ - - - ተወለደልን
ተወለደ - - - በቤተልሔም
ተወለደ - - - በከብቶች ግርግም
/አዝ=====
ተወለደ - - - የምስራቅ ሠዎች
ተወለደ - - - መጡ ሊሠግዱ
ተወለደ - - - ስጦታን ይዘው
ተወለደ - - - እንደ ሥርዓቱ
ተወለደ - - - ወርቅ አመጡለት
ተወለደ - - - ስለ መንግስቱ
ተወለደ - - - ዕጣን ለክብሩ
ተወለደ - - - ከርቤን ለሞቱ
👉ዘማሪ ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔ ✞ ═════●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit @enamsgn ❖
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
✥ ✢
╚✞ ═════●◉❖◉●═════✞╝
✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
📋📌ማስታወቂያ
#ባቀረብንላችሁ_ምርጫ_መሰረት_በእናንተ_የተመረጠው_ምርጫ_የልደትና(ገና)_እና_የጥምቀት_መዝሙሮችን_ከነገ_ጀምሮ_ወደእናንተ_እናደርሳለን::
እስከዛው የምትወዷቸውን ሰዎች በምናስቀምጥንናችሁ link እንዲቀላቀሉን share በማድረግ የበኩልዎን ይወጡ ስንል በታላቅ ትህትና እንጠይቆታለን!🙏
👇👇👇👇👇👇👇👇
/channel/enamsgn
/channel/mezmuredawit
እስከምንለቅ በትእግስት ይጠብቁን!
ሰማዕታቱ ከእሳቱ ውስጥ ሆነው እግዚአብሔርን በሰላም ሲያመሰግኑ አዩአቸውና እጅግ ተደነቁ፡፡ ቅድስት አርሴማም በዚያ ላሉት ሁሉ ወደፊት በንጉሡ ላይ የሚሆነውን ነገር በትንቢት ነገረቻቸው፡፡
ከዚህም በኋላ ንጉሥ ድርጣድስ ቅድስት አርሴማን እንደበቀሉለትና እንዲያጠፉለት ወደ አማላከቶቹ ቤት ይወስዷት ዘንድ የሠራዊቱን አለቆች አዘዛቸው፡፡ ወደ አማልክቶቹም ቤት በወሰዷት ጊዜ በዚያ ሆና ስትጸልይ በወንዶች አምሳል የተሠሩ 77 እና በሴቶች አምሳል የተሠሩ 33 ጣዖታት ሁሉ ተሰባበሩ፡፡ ከአንገታቸው የተሰበሩ አሉ፣ እግሮቻቸውና እጆቻቸው የተሰበሩ አሉ፣ ወገባቸው የደቀቁ አሉ፣ እንደትቢያም የተነተኑ አሉ፡፡ በምድርም ታላቅ ንውጽውጽታ ሆነ፡፡ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልም እንደመብረቅ ባለ ድምጽ መጥቶ ምድሪቱን መላትና በዚያ ያሉ ጣዖታት በሙሉ እንደትቢያ ጠፉ፡፡ ቅድስት አርሴማም ይህንን ባየች ጊዜ ደስ ተሰኝታ የሆነውን መጥቶ ያይ ዘንድ ወደ ንጉሡ ላከችበት፡፡ ንጉሡም በመጣ ጊዜ "አምላኬ መልአኩን ልኮ አዳነኝ፣ ጣዖታቶችህንም እንዳልነበሩ አደረጋቸው እህግዲህስ እፈር" አለችው፡፡ ንጉሡም "በምትሃትሽ ይህንን እንዳደረግሽ ዐውቀለሁ" አላትና ወደ እስር ቤት ወስዶ ከሰማዕታቱ ጋር ጨመራት፡፡
ሰማዕታቱም በእስር ቤት ሆነው እህልና ውኃ ከቀመሱ ሰባት ቀን ሆኗቸዋልና ርሀቡና ጥሙ እጅግ ጠናባቸው፡፡ ያንጊዜም ቅድስት አርሴማ ተነሡ እንጸልይ አለቻቸውና ቢጸልዩ ብርናኤልና አቅናኤል በሚባሉ ሁለት ቅዱሳን መላእክት እጅ ሰማያዊ ኅብሥትባ የገነት ውኃ መጣላቸው፡፡ ከመካከላቸውም ካህኑ ኢያሴኖስ ባርኮ ለሌሎቹ ሰማዕታት ሰጣቸውና ተመግበው ፈጣሪያቸውን አመሰገኑ፡፡ የተረፋቸውም ኅብሥት በመላአክቱ እጅ ወደ ሰማይ ወጣ፡፡
በማግሥቱም ንጉሡ ወደ ፍርድ አደባባይ ባወጣቸው ጊዜ ሰማዕታቱ ፊታቸው እንደፀሐይ ያበራ ነበር፡፡ የእሥር ቤት ጠባቂውንም ጠርቶ "እህል ያበላሃቸውና የነገሥታትን ልብስ ያለበስካቸው ለምንድነው?" ብሎ ተቆጣው፡፡ ጠባቂውም "ጌታዬ ሆይ እነርሱስ ሳይበሉ ሳይጠጡ ይረካሉ እንጂ የሰጠኃቸው ምንም ነገር የለም"*አለው፡፡ ቃሉንም በመሐላ ካጸናለት በኋላ "ነገር ግን ንጉሥ ሆይ በሌሊት እሥር ቤት በብርሃን ተጥለቅልቆ አይቼዋለሁ፡፡ ዳግመኛም ሃያ ሰባት የብርሃን አክሎችም ሲወርዱ አየሁ" አለው፡፡ ቀጥሎም ይህ ጠባቂ "ንጉሥ ሆይ እኔም በእነዚህ ሰማዕታት አምኛለሁ" አለው፡፡ ወደ ቅድስት አርሴማም ዞሮ "እመቤቴ ሆይ በጸሎትሽ አስቢኝ" በማለት ሌሎቹንም ሰማዕታት ተመጸናቸው፡፡ ንገሡም በዚህ እጅግ ተቆጥቶ ራሱን በሰይፍ አስቆረጠው፡፡ እርሱም በጣዖት የሚያመልክ አረማዊ ቢሆንም አምኖ በደሙ ተጠምቋልና የሰማዕትነትን የክብር አክሊል ተቀዳጀ፡፡ ቅዱሳን የሆኑ ሰማዕታቱም ይህን አደነቁ ሰማዕትነትን በመፈጸም ቀድሟቸዋልና፡፡ በድኑንም በምድረ በዳ ጣሉት ነገር ግን አውሬዎችና አሞራዎች አልበሉትም ቅዱሳን መላእክት ይጠብቁታልና፡፡
ንጉሡም ሰማዕታን በጽኑ ዱላዎች ካስደበደባቸውና ለእያንዳንዳቸው ሌላ ሦስት ሦስት መቶ ግርፋት ካስገረቸው በኋላ ወደ እሥር ቤት መለሳቸው፡፡ በመግስቱም ቅድስት አርሴማን አስመጥቶ ከእርሱ ጋር ትሴስን ዘንድ አባበላት፡፡ "ንግሥት አድርጌሽ በወርቅ ዙፋኔ ላይ ትቀመጫለሽ፣ በአርማንያ ካሉ ሴቶች ሁሉ በላይ አደርግሻለሁ…" እያለ አባበላት፡፡ ቅድስት አርሴማ ግን "ልብህ የደነደነ ሰነፍ ሆይ ኃጢአትህን ሁሉ ይቅር ይልህ ዘንድ ወደ አምላክህ እግዚአብሔር ትመለስ ዘንድ በተሻለህ ነበር …" እያለች አስተማረችው፡፡ ስለ ጌታችንም መንገሥት ካስተማረችው በኋላ "እኛ ሰማዕታቱ ስለ አንተ እንጸልይልሃለን" አለችው፡፡ ንጉሡ በዚህ ጊዜ ማመኔን ብትወጂ ግን ከእኔ ጋር ተስማምተሽ እንጋባለን ለአምላክሽም እገዛለሁ" ሲላት ወዲያው እርኩስ መንፈስ ፊቱን መታውና "ከእናትህ መኅፀን ጀምሮ ያሳደኩህና በሥራህ ሁሉ ልብ፣ አፍና ብርታት ሆኜ በኃይሌም ብርታት የክርስቲያን ልጆችን እንድታስጨንቃቸውና እንትገድላቸው ያደረኩህን እኔን ለምን ተውከኝ? ስለዚህች ሴት ብለህ እግዚአብሔር አምላክን ታመልክ ዘንድ ወደድክን! ..." እያለ በቁጣ ሆኖ አፉን አጣመመውና ምድር ላይ ጣለው፡፡ ከዚህም በኋላ ለጣዖታቱ ይሰግዱ ዘንድ ሰማዕታቱን በቁጣ አዘዛቸው፡፡ ነገር ግን የጣዖታቱ ካህናት መጥተው ጣዖታቱን ቅድስት አርሴማ እንዳጠፋቻቸው ነገሩት፡፡ ዳግመኛም "እርሷን ካልገደልካት አገራችን ትጠፋለች፣ መንግሥትህ ተሻራላች" አሉት፡፡
ከዚህም በኃላ ከቅድስት አርሴማ ጋር ያሉትን 27ቱን ሰማዕታት ስሙ ጋብጋቦ ወደሚባል ወንዝ ወስደዋቸው አንገታቸውን በሰይፍ ቆረጧቸውና የሰማዕትነት ፍጻሜአቸው ሆነ፡፡ ከእነርሱም አንደኛውን በቅድሚያ አንገቱን ሲቆርጡት ሥጋው ወደ ምድር ወደቀ፡፡ ራሱ ግን ለብቻ ለአንድ ሰዓት ያህል ቆመች፡፡ ቡርክት ቅድስት አርሴማም ሮጣ ሄዳ የሰማዕቱን በርቲኖስን ራስ ያዘቻትና ወደ አንገቱ መለሰቻት፡፡ እርሱም "ሰማዕት ለመሆን እኔን ስላስቀደመ አምላኬ እግዚአብሔርን አመሰግነዋለሁ" እያለ ሦሰት ጊዜ ተነፈሰ፡፡ ለቅድስት አርሴማም "እመቤቴ ሆይ መምጣትን እንዲያፋጥኑ ከፀሐይ ይልቅ የምታበራ አገርን እንዲያዩ ለወንድሞቻችን ለእኅቶቻችን ነገሪያቸው" አላት፡፡ እርሷም ወደ ሰማዕታቱ ዞራ "ወንድማችን በገነት ያየውን ይነግረንና ያሳየን ዘንድ በሕይወት ኖሯል እንጂ አልሞተም" አለቻቸው፡፡
ከዚህም በኃላ ሰማዕታቱ እግዚአብሔርን አመስግነው "እኔ አስቀድሙ እኔ አስቀድሙ..." እያሉ ወታደሮቹን ለመኗቸው፡፡ እየተሻሙ በየተራ እየተሰየፉ ሰማዕትነታቸውን ፈጽመው የክብር አክሊልን ተቀዳጁ፡፡ የእነዚህም የ27ቱ ክቡራን ሰማዕታት ስማቸው ይህ ነው፡- ካህኑ ኢያሚኖስ፣ አፍጢኖስ፣ በርቲኖስ፣ ጢሞና፣ ጢሞዓና፣ ዘኬዎስ፣ እስጢፋኑ፣ አርሞና፣ ኪርያኮስ፣ አንጥያኮስ፣ ያዕቆብ፣ ቡራኬሌስ፣ አስቂርያቆስ፣ አስኪርያኖስ፣ ሚርያኖስ፣ ትትግርጦስ፣ ያስቲኖስ፣ ጥልያኖስ፣ ዑልያኖስ፣ ጴርቅላስ፣ ኬብያኖስ፣ ጴጥሮስ፣ ጳክንዮስ፣ ሐናንያ፣ ሐሊባኖስ፣ ኤስያኖስ እና ኤልያብ ናቸው፡፡
ቅድስት አርሴማም የሰማዕታቱን ራሶቻቸውን ትሰበስብ ነበር፡፡ ወደ ሥጋቸውም ታጋጥመው ነበር በዚያም ጊዜ እንደመጀመሪያው ይሆናል፡፡ እንዳልተቆረጠም ይሆናል፡፡ ልብሶቻቸውንም ታለብሳቸዋለች፡፡ ይህንንም ታላቅ ተአምር ያዩ 92 የንጉሡ ወታደሮች ወደ ንጉሡ ሄደው "እኛም በአምላካቸው አምነን ክርስቲያን ሆነናል" በማለት መሰከሩ፡፡ ንጉሡም በፈረስ ገመድ ላይ አስሮ ሥጋቸው ተቆራርሶ እስኪወድቅ ድረስ ካሠቃያቸው በኃላ አንገታቸውን ሰየፋቸውና የክብር አክሊልን ተቀዳጁ፡፡ ዳግመኛም በእነርሱ ምክንያት ሌሎችም አመኑ፡፡ ከዚህም በኃላ ንጉሡ ቅድስት አርሴማን ውበቷን እያሰበ ልቡናውን ሳተ፡፡ ድንግልናዋንም ሊያረክስ ሽቶ እናቷን አጋታን እንድታባብልለት አዘዛት፡፡ እናቷም ሄዳ "ልጄ ሆይ ስሚ ይህ አረማዊ እንዳያረክስሽ ተጠንቀቂ" አለቻት፡፡ ንጉሡም ቅድስት አርሴማን "መንግሥቴንና ግዛቴን ሁሉ አወርስሻለሁ" እያለ በመሀላ ቢለምናትም እሺ እንደማትለው ሲያውቅ ይዞ በግድ ወደ እልፍኙ ሊያስገበት ሲል ቅድስት አርሴማ ይዛ መሬት ላይ ጣለችው፡፡ በእርሷ ላይ ያደረ የመንፈስ ቅዱስ ኃይል ሞገስ ሆኗታልና፡፡
#ታኅሣሥ_6
#ታላቋ_ሰማዕት_ቅድስት_አርሴማ
ታኅሣሥ ስድስት በዚህች ዕለት የታላቋ ሰማዕት የቅድስት አርሴማ ቤተ ክርስቲያኗ የከበረችበትና የሥጋዋ ፍልሰት የተከናወነበት ነው፡፡ ከእርሷም ጋር አብረው የተሰየፉ 27 ደናግልም የሥጋቸው ፍልሰት ሆነ፡፡
የቅዱስት አርሴማ አባቷ ቴዎድሮስ ከሌዋውያንና ከኃያላን ነገሥታት ወገን ሲሆን እናቷ አትኖስያ ደግሞ ከጳጳሳት አለቆች ወገን ናት፡፡ ወላጆቿ በሃይማኖት በምግባር ያጌጡ በበጎ ትሩፋት የተመሰገኑ ደጋግ ቅዱሳን ናቸው፡፡ በጾም፣ በጾሎት፣ በምጽዋትና ዓሥራት በኩራትን በማውጣት በመንፈሳዊ ሥራ ሁሉ እየተጉ ቢኖሩም ነገር ግን እስክ እርጅናቸው ዘመን ድረስ ልጅ ስላልነበራቸው ያዝኑ ነበር፡፡ እናቷ ቅድስት አትኖስያ እንደ ነቢዩ ሳሙኤል እናት ሐና ጠዋት ማታ ወደ ቤተ ክርስቲያን በመሄድ በእግዚአብሔር ፊት ታለቅስ ነበር፡፡ እግዚአብሔር የልቧን ፈቃድ ይፈጽምላት ዘንድ ወደደና የቂሣርያውን ሊቀ ጳጳሳት ልድዮስን ስለ እርሷ ይጸልይላት ዘንድ አዘዘው፡፡
ሊቀ ጳጳሳቱም ስለ ቅድስት አትኖስያ ጸለየላት፡፡ እግዚአብሔር አምላክም የሊቀ ጳጳሳቱንና የቅድስት አትኖስያን ጸሎት ሰምቶ መልኳ እጅግ ያማረችን ሴት ልጅ ቅድስት አርሴማን ሰጣት፡፡ እናቷም እየተንከባከበች አሳድጋት ዕድሜዋ ከፍ ሲል አምላክን በወለደች በእመቤታችን ስም ወደተሠራች ቤተ ክርስቲያን ታገለግል ዘንድ ሰጠቻት፡፡ ቅድስት አርሴማ ወጣት በሆነች ጊዜ ወላጆቿ ባል ያጋቧት ዘንድ ወደዱ ነገር እርሷ ይህንን ፈጽሞ አልወደደችምና ወላጆቿን "እኔ የሰማያዊው የክርስቶስ ሙሽራ ነኝ እንጂ ምድራዊ ሙሽራ አይደለሁም" አለቻቸው፡፡
ቅድስት አርሴማ ከእርሷ በፊትም ሆነ ከእርሷ በኋላ በመልክና በውበት የሚመስላት የለም፡፡ ይህን ዓለም እንደትቢያ በመቁጠርና ፍጹም በመናቅ ጌታችንን ከተከተሉት ቅዱሳት ደናግል አንስት ውስጥ በመልክና በውበት ቅድስት አርሴማን የሚመስል የለም፡፡ አምላክን ከወለደች ከእመቤታችን በቀር የሚበልጣት ማንም የለም፡፡ እርሷም በምግባር በሃይማኖት ያጌጠች በመንፈሳዊ ተጋድሎ የበረታች በትሩፋት የበለጸገች ናት፡፡ ብሉይን ከሐዲስ አጠናቃ ተማረች፡፡ የአገሮችንም (የሮምያን፣ የጽርዕን፣ የሶርያን፣ የኪልቅያን) ቋንቋዎች ታውቅ ስለነበር ቅዱሳት መጻሕፍትንም ወደ ተለያዩ አገራት ቋንቋዎች ትተረጉማለች፡፡
ቅድስት አርሴማ 15 ዓመት በሆናት ጊዜ ከሃዲውን ዲዮቅልጥያኖስን ሰይጣን አስነሥቶት ነገሠ፡፡ ይኸውም ከሃዲ ንጉሥ ሚስት ያባ ዘንድ በመልኳ ውብ የሆነች ሴት ልጅን ይመርጡለት ዘንድ በሀገሩ ሁሉ እንዲሄዱ ጭፍሮቹን አዘዘ፡፡ ያገኟትንም ውብ የሆነችን ሴት መልኳን ሥለው ያመጡለት ዘንድ ሠዓሊዎችንም አብሮ ላከ፡፡ የተላኩትም ሰዎች ወደ ሮሜ አገር በደረሱ ጊዜ ቅድስት አርሴማ ያለችበትን የደናግል ገዳም አገኙ፡፡ ወደ ገዳሙም ገብተው ቅድስት አርሴማን አይተዋት በመልኳ ማማር እጅግ ተደስተው "ለንጉሡ ሚስት የምትሆነው ይህች ናት" ብለው መልኳን በሥዕል ቀርጸው ለንጉሡ ላኩለት፡፡ ንጉሡም ሥዕሏን በተመለከተ ጊዜ ፈጽሞ ተደሰተ፡፡ ስለ ሠርጉ ወደ እርሱ ይመጡ ዘንድ ሕዝቡን ይጠሩአቸው ዘንድ ወደ ነገሥታቱና ወደ መኳንንቱ ሁሉ ላከ፡፡
በገዳም ያሉ ደናግልም ይህን በሰሙ ጊዜ እጅግ አዝነው አለቀሱ፡፡ ድንግልናቸውን እንደጠበቁ ያገለግሉት ዘንድ እግዚአብሔርን እየለመኑት ከገዳሙ ወጥተው ወደ ንጉሥ ድርጣድስ የግዛት አገር ወደ አርማንያ ደረሱ፡፡ በዚያም በምድረ በዳ ዋሻ ውስጥ ተቀመጡ፡፡ ቁጥራቸውም 75 ወንዶችና 39 ደናግል ሴቶች ነበሩ፡፡ በዋሻም ውስጥ በረሃብና በጥም እየተቸገሩ ተቀመጡ፡፡ ንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስ ቅድስት አርሴማን ፈልጎ ባጣት ጊዜ እጅግ ቢያዝንም ነገር ግን ቆይቶ በአርማንያ እንዳለች ሰማ፡፡ እርሷንም ይዞ ይልክለት ዘንድ ወደ አርማንያው ንጉሥ ድርጣድስ መልእክት ላከ፡፡ ድርጣድስም ለጣዖት የሚሰግድ ፀሐይና ጨረቃን የሚያመልክ ነው፡፡ በሰው እጅ የተጠረቡ ዕንጨቶችንና ድንጋዮችንም በቤቱ አስቀምጦ "አማልክት" እያለ በመጥራት እንደ አምላክ ያመልካቸው ነበር፡፡ በውስጡም ሰይጣን አድሮበታልና የእርሱን ጣዖታት ሕዝቡም እንዲያመለኩ ያስገድዳቸው ነበር፡፡ ክርስቲያኖችንም እያሰረ በመግረፍ ያሠቃይ ነበርና ቅድስት አርሴማ በዋሻ ውስጥ ሆና አንዱ መኮንን ክርስቲያኖችን በመግረፍ ሲያሠቃይ ታየዋለች፡፡ ስለ ሰማዕታቱም ወደ እግዚአብሔር ስትጸልይ የብርሃን አክሊል የያዙ ቅዱሳን መላእክት ሰማዕታቱ ሲሰጧቸው አየች፡፡ ይህንንም ታላቅ ምሥጢር ባየች ጊዜ "አቤቱ አምላኬ ሆይ ስለስምህ እኔም ሰማዕት እሆን ዘንድ እርዳኝ" እያለች ለመነች፡፡
ከዚህም በኋላ ወደ ሰማዕታቱ ዘንድ ስትሄድ መኮንኑ አያት ከመልኳ ማማር የተነሣ ደነገጠና "እመቤቴ ሆይ እዛው ባለሽበት ሆነሽ ተዋቸው ብትይኝ ፈትቼ እለቃቸው ነበር አንቺ ከዚህ መምጣት አያስፈልግሽም" አላት፡፡ ቅድስት አርሴማም "እኔም የእነዚህን ሰማዕታት መከራ እሸከም ዘንድ እወዳለሁ፣ የእነርሱንም የክብር አክሊል አገኝ ዘንድ እሻለሁ" አለችው፡፡ እርሱም "እመቤቴ ሆይ አንቺስ ከመንግሥት አዳራሽ ውጭ መኖር አይገባሽምና ለምን ይህን ከንቱ ነገር (ሞትን) ትወጃለሽ?" አላት፡፡ ቅድስት አርሴማም "የጎሰቆልክ ጤልሜዎስ ሆይ ለእኔስ ሰማያዊው ንጉሥ በመንገሥቱ አዳራሽ አዘጋጅቶልኛል" አለችው፡፡ ከዚህም በኋላ መኮንኑ ሰማዕታቱን ከእሥር ቤት ጣላቸውና ቅድስት አርሴማን ግን ከአጃቢዎች ጋር በክብር አስቀምጦ ምግብ መጠጡን አዘጋጀላት፡፡ እርሷ ግን ለሰማዕታቱ ስለ ሰማያዊው ስጦታቸው ትነግራቸው ነበር እንጂ ምግቡን አልቀመሰችም፡፡ ከሃዲው መኮንኑም ቅድስት አርሴማን "እሽ ብለሽኝ አንቺን ካገባሁ በቤቴ ያሉትን ሚስቶቼን ሁሉ አባርሬ አንቺን ብቻ ሚስት አድርጌ እስከ ዕለተ ሞቴ ድረስ እኖራለሁ ለዚህም በትላልቅ አማልክቶቼ ስም እምምልሻለሁ" ብሎ መልእክተኛ ላከባት፡፡ ቅድስት አርሴማም መልአክተኞቹን መጻሕፍትን እየጠቀሰች የዓለምን ከንቱነትና የክርስቶስን ፍቅር አስተማረቻቸው፡፡ እርሷም የእግዚአብሔርን ቃል ስትነግራቸው ልባቸው እየተቃጠለ ያለቅሱ ነበር፡፡ እነርሱም "በቃልሽ አምነናል ጸሎትሽ ኃይል ይሁነን" አሏት፡፡
መኮንኑም የቅድስት አርሴማን መልስ በሰማ ጊዜ በታላቅ ቁጣ ሆኖ ሰማዕታቱን ይዞ በማሠቃየት የበላዩ ወደ ሆነው ወደ አርማንያው ንጉሥ ድርጣድስ ዘንድ እንዲወስዷቸው አዘዘ፡፡ የአገሩ ሰዎችም ቅድስት አርሴማ ሰማዕት ትሆን ዘንድ ፈቅዳ ወደ ንጉሡ ዘንድ እንደሄደች ለእናቷ ለአትኖስያ ነገሯት፡፡ እናቷም መጥታ "ልጄ ሆይ ወደሞት ለምን ትሄጃለሽ? ወደ ሞት መሄድሽን እያየሁ አሁን ልቤ እንዲህ በሀዘን ከሚሰበር መነው መጀሪያውኑ ባልወለድኩሽ ይሻለኝ ነበር" አለቻት፡፡ ቅድስት አርሴማ ግን የክርስቶስን ፍቅር ለእናቷ አስረዳቻት፡፡ በኪልቂያ አጋታ ብለው የሚጠሯት ወላጅ እናቷ አትኖስያም "አስተማሪዬ ልጄ አርሴማ ሆይ! እባክሽ እሺ በይኝ…" እያለች ብዙ ብትለምናትም ቅድስት አርሴማ ግን እናቷንና የአገሯን ሰዎች ተሰናብታ ስትሄድ ሁሉም እያለቀሱ ሸኟት፡፡ በመንገድም ሳለች ቅድስት አርሴማን ወደ ንጉሥ ድርጣድስ የሚወስዷት ጭፍሮች ከሰማዕታቱ ጋር ሄዳ ሰማዕት ከምትሆን ይልቅ ወደ እናቷ መመለስ ብትፈልግ እንደሚመልሷት ነገሯት፡፡ እርሷ ግን "ከሰው ፍቅር ይልቅ የእግዚአብሔር ፍቅር ይበልጣል" አለቻቸው፡፡
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
🕯 #በዓታ_ለእግዝእትነ_ማርያም_ውስተ_ቤተመቅደስ
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከአባቷ ከቅዱስ ኢያቄምና ከእናቷ ከቅድስት ሐና ግንቦት አንድ ቀን ተወለደች፡፡ ከዕለታት አንድ ቀን ሐና ከእቅፍ አውርዳት ወደ ጎረቤቶቿ በሄደችበት ጊዜ ቅዱስ ገብርኤል ደብቆባት ጥራ ግራ አግኝታታለች፡፡ በዚህም ሐና ኢያቄምን ‹‹ይህች ብላቴና ሆዷ ዘመድ ሳይወድ አፏ እህል ሳይለምድ ወስደን ለቤተ መቅደስ አንሰጥምን? አንዳች ብትሆንብን ከልጃችንም ከእግዚአብሔርም ሳንሆን እንቀራለን›› አለችው፡፡ ኢያቄምም ፈቃዱን ገለፀላትና ቅድስት ድንግል ማርያም ሦስት ዓመት ሲሆናት በታኅሣሥ ሦስት ቀን ወደ ቤተ መቅደስ አስገቧት፡፡ ሊቀ ካህናቱ ዘካርያስ የምግቧ ነገር ይያዝልኝ ብሎ መጥቅዕ (ደወል) በመምታት ሕዝቡን ካሰባሰበ በኋላ የምግቧን ነገር እንዴት እናድርግ እያሉ ሲጨነቁ መልአኩ ቅዱስ ፋኑኤል ኅብስት ሰማያዊ ጽዋዕ ሰማያዊ ይዞ ረቦ ታያቸው፡፡
ዘካርያስ ከዚህ በፊት በሥውር ይቀበል ነበርና ለእርሱ የመጣ ሀብት መስሎት ዛሬስ ክብሬን በሰው ፊት ሊገልጸው ነው ብሎ ታጥቆ ሊቀበል ሲነሳ መልአኩ ወደ ላይ ራቀበት፤ የእግዚአብሔር ጥበብ አይመረመርምና ምን አልባት ለዚህች ብላቴና የመጣ ሀብት እንደሆነ እስኪ እንየው ብለው ለብቻዋ አድርገዋት ፈቀቅ ሲሉ ድንግል ማርያም ሐናን ስትከተል መልአኩ ፈጥኖ ወርዶ አንድ ክንፉን አንጥፎ አንድ ክንፉን ጋርዶ በሰው ቁመት ልክ ከምድር ከፍ አድርጎ መግቧታል፡፡ በተመሳሳይ ታኅሣሥ ሦስት ቀን ቅዱስ ፋኑኤል የተሾመበት መታሰቢያ በዓሉ በመሆኑ በድምቀት ይከበራል፡፡ ይህም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ወደ ቤተ መቅደስ በገባችበት ጊዜ ኅብስት ሰማያዊና ጽዋዕ ሰማያዊ መግቧታልና ነው፡፡ ቅዱስ ፋኑኤል እግዚአብሔርን በምሥጋና የሚያገለግል ለበቁ ሰዎች መና ሰማያዊ የሚመግብ ለኃጥአን ምሕረትን የሚለምን ቅዱሳንን የሚጠብቅ መልአክ ነው፡፡
ከዚህ በኋላ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በቤተ መቅደስ ዐሥራ ሁለት ዓመት መላእክት እያረጋጓት ምግቧን እያመጡላት ሐርና ወርቅ እየፈተለች ኑራለች፡፡ ቅዱስ ያሬድ በአንቀጸ ብርሃን ድርሰቱ ‹‹ከመዝ ነበርኪ ውስተ ቤተ መቅደስ ወመላእክት ያመጽኡ ወትረ ሲሳየኪ ከመዝ ነበርኪ ፲ወ፪ተ ዓመተ እንዘ ትትናዘዚ እምኀበ መላእክት ስቴኪኒ ስቴ ሕይወት ውእቱ ወመብልዕክኒ ኅብስት ሰማያዊ›› እንዲል፡፡ በቤተ መቅደስ ሳለች አይሁድ ሊጣሏት ይሹ ነበር፤ በዚህም መጥቁል የሚባል ምትሀተኛ 300 የአየር አጋንንትን አውርዶ ላካቸው፤ እመቤታችን ደግሞ የአምላክ ኅቡዕ ስም ተገልጦላት ትጸልይ ነበርና መልአክ ወርዶ ሰይፉን መዞ ሁሉንም አጥፍቷቸዋል፡፡ በዚህ ጊዜ ከአዳም ጀምሮ እስከ እርሷ ድረስ ያሉ አበው ‹‹በአማን ስብሕት በአማን ውድስት›› እያሉ አመስግነዋታል፤ ከዚያም ቀን ጀምሮ በአይሁድ ዘንድ ተፈርታ ተከብራ ኑራለች፡፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ወደ ቤተ መቅደስ የገባችበት የበዓሏ መታሰቢያ ታኅሣሥ 3 ቀን ነው፡፡ ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በረከት ረድኤት ያሳድርብን አሜን!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!!
ምንጭ፦ ስንክሳር ዘታኅሣሥ 3 ፣ መድበለ ታሪክ
✞ በዓታ ማርያም እናቴ ✞
በዓታ ማርያም እናቴ /2/
በዓታ ማርያም
ኧኸ.......እኔ እወድሻለሁ
እስከ እለተ ሞቴ
ኧኸ....... እኔ እወድሻለሁ
እስክትወጣ ነፍሴ
በዓታ ማርያም እናቴ /2/
በዓታ ማርያም እናቴ /2/
በዓታ ማርያም
ኧኸ....... እኔ እወድሻለሁ
እስከ ዕለተ ሞቴ
ኧኸ....... እኔ እወድሻለሁ
እስክትወጣ ነፍሴ
በዓታ ማርያም እናቴ/2/
በዓታ ማርያም እናቴ /2/
በዓታ ማርያም
ኧኸ....... አኔ እወድሻለሁ
እስከ እለተ ሞቴ
ኧኸ....... እኔ እወድሻለሁ
እስክትወጣ ነፍሴ
በዓታ ማርያም እናቴ /2/
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔✞═══●◉❖◉●═════✞╗
❖ @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit ❖
╚✞═══●◉❖◉●═════✞╝
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
✞✞✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞
❖ ታኅሣሥ ፩ (1) ❖
✞✞✞✝ እንኩዋን ለታላቁ ነቢይ "ቅዱስ ኤልያስ" :
"ቅዱስ ዼጥሮስ ዘጋዛ" እና "ቅድስት ቤርሳቤህ"
ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞
+*" ታላቁ ቅዱስ ኤልያስ "*+
=>ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ከሊቀ ነቢያት ቅዱስ ሙሴ
ቀጥላ ቅዱስ ኤልያስን ታከብራለች:: "ርዕሰ ነቢያት - የነቢያት ራስም" ትለዋለች:: እርሱ ሰማይን የለጐመ:
እሳትን ያዘነመ: ፍጥረትንም በቃሉ ያዘዘ አባት ነውና::
ይሕስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-
+ቅዱሱ ትውልዱ (ነገዱ) ኢዮርብዓም ነጥሎ
ከወሰዳቸው እሥራኤል (10ሩ ነገድ) ሲሆን አባቱ
"ኢያስኑዩ" : እናቱ ደግሞ "ቶና (ቶናህ)" ይባላሉ:: በጐ
አምልኮ ነበራቸውና እግዚአብሔር ማሕጸነ ቶናህን ቀድሶ
ይህንን ቅዱስ ፍሬ ፈጠረ::
+ቅዱስ ኤልያስ በተወለደ ቀን በቤታቸው ብርሃን ተሞልቶ
ታይቷል:: ብርሃን የለበሱ 4 ሰዎች (መላእክት)
መጥተውም በእሳት ሰፋድል (መጐናጸፊያ) ሲጠቀልሉት
ወላጆቹ በማየታቸው ደንግጠው ለነቢያትና ለካህናት ነገሯቸው::
+ካህናቱ ግን ነገሩ ቢረቅባቸው "ምን ዓይነት ፍጥረት
ይሆን? በእሥራኤል ይነግሥ ይሆን! ወይስ ነቢይ
ይሆን?" ብለውም አድንቀዋል:: ቅዱስ ኤልያስ ከልጅነቱ
ጀምሮ ኮስታራ: ቁም ነገረኛ: ንጽሕናንም የሚወድ
እሥራኤላዊ ነው::
+ወቅቱ (ከክርስቶስ ልደት 900 ዓመት በፊት) ሕዝቡና
ነገሥታቱ የከፉበት: እግዚአብሔር ተክዶ ጣዖት
የሚመለክበት ነበር:: ድሮ በኢሎፍላውያን እጅ የነበሩት
ጣዖታት (ዳጐንና ቤል) በዚያ ዘመን ወደ እሥራኤል
ገብተው ነበር::
+ቅዱስ ኤልያስ ግን በዚህ ክፉ ትውልድ መካከል
ሆኖም ሥርዓተ ኦሪትን የጠነቀቀ: የንጽሕናና የአምልኮ ሰው ነበር::
+በዚያ ወራትም እግዚአብሔር ለነቢይነት ጠራው::
እርሱም "እሺ" ብሎ ታዞ የእግዚአብሔርን የጸጋ ጥሪ
ተቀበለ::
ቅዱሱ ብዙ ጊዜ ለጉዳይ ካልሆነ ከሰው ጋር መዋል:
ማደርን አይወድምና መኖሪያውን በተራሮችና በዱር
አደረገ::
+በተለይ ደብረ ቀርሜሎስ ለእርሱ ቤቱ ነበር:: በዚህ
ሕይወቱም ከመልከ ጼዴቅ ቀጥሎ:-
1.ለድንግልና (ድንግል ነበርና)
2.ለብሕትውና (ብቸኛ ነበርና)
3.ለምንኩስና (ተሐራሚ ነበርና) በብሉይ ኪዳን መሠረትን
የጣለ ነቢይ ይባላል::
+መቼም በብሉይ ኪዳን የቅዱስ ኤልያስን: በዘመነ
ክርስቶስ የመጥምቁ ዮሐንስን: በዘመነ ሊቃውንት ደግሞ
የአፈ ወርቅ ዮሐንስን ያህል ደፋርና መገሥጽ አስተማሪ
አልነበረም:: በጊዜው ደግሞ አክአብና ኤልዛቤል የሚባሉ
ክፉ ባልና ሚስት በእሥራኤል ላይ ነግሠው ሕዝቡን
ጣዖት አስመለኩት::
+ይባስ ብለው ደግሞ በወይኑ እርሻ አማካኝነት
ኢይዝራኤላዊው ናቡቴን በሃሰት ምስክር ደሙን
አፈሰሱት:: ናቡቴም "የአባቶቼን ርስት አልሸጥም:
አልለውጥም::" በማለቱ እንደ ሰማዕት ይቆጠራል::
+ኤልያስ ግን ይህንን ሲሰማ ወደ አክአብና ኤልዛቤል
ቀርቦ "የናቡቴ ደም በእናንተ ላይ አይቀርም:: የአንቺንም
ደም ውሻ ይልሰዋል" አላቸው:: በዚህ ምክንያትም
ኤልዛቤል ልትገድለው ብትፈልገውም እርሱ
የእግዚአብሔር ነውና አላገኘችውም::
+በዚህ ብስጭትም ይመስላል አንድ ሺህ ነቢያትን
ሰብስባ "ፍጇቸው" አለች:: 900ው ሲታረዱ አንድ
መቶውን ግን ቅዱስ አብድዩ በዋሻ ውስጥ ደብቆ
እየመገበ አተረፋቸው:: በእሥራኤል ውስጥ ግን ዓመጻና
ኃጢአት እየተስፋፋ ሔደ:: የእግዚአብሔርን ስጦታ
እየተመገበ ሕዝቡ ለቤል (ለበዓል) ሰገደ::
+ይህን ጊዜ ግን ቅዱስ ኤልያስ እንዲህ አለ:-
"ሕያው እግዚአብሔር አምላከ ኃይል: ዘቆምኩ
ቅድሜሁ: ከመ ኢይረድ ጠል በእላ መዋዕል ዘእንበለ
በቃለ አፉየ::" ብሎ ዝናም ከሰማይ እንዳይወርድ
ከለከለ::
ለ3 ዓመታት ከ6 ወራት ሰማይ ዝናም ለዘር ጠል
ለመከር ከመስጠት ተከለከለ::
+ሕዝቡ በኃጢአቱ ምክንያት ተጐዳ:: እርሱን ቁራ
ይመግበው: ምንጭ ፈልቆለት ይጠጣ ነበር:: ይሔው
ቢቀርበት ጸለየ:: እግዚአብሔርም ከፈለገ ኮራት ወደ
ሰራፕታ እንዲወርድ አዘዘው:: በዚያም የነቢዩ ዮናስ እናት
እንጐቻ ጋግራ ብታበላው ቤቷ በበረከት ተሞላ::
+ልጇ ሕጻኑ ዮናስ ቢሞትም በጸሎቱ አስነሳላት::
ቀጥሎም 7 ጊዜ በትጋት ጸልዮ ለ3 ዓመታት ከ6 ወራት
የዘጋውን ሰማይ ከፍቶታል:: ሕዝቡም ዕለቱኑ ከበረከቱ
ቀምሰዋል::
+ከዚያ አስቀድሞ ግን ከኤልዛቤል 850 ነቢያተ ሐሰትና
ካህናተ ጣዖት ጋር ተወዳድሮ አሸንፏቸዋል:: መስዋዕት
ሰውተው የእርሱን ብቻ እሳት ከሰማይ ወርዳ
በልታለታለችና ሕዝቡ 850ውን ሐሰተኛ ነቢያት በወንዝ
ዳር በሰይፍ መትተዋቸዋል::
+ይሕንን የሰማች ኤልዛቤልም ትገድለው ዘንድ
አሳደደችው:: "አቤቱ ከአባቶቼ አልበልጥምና ውሰደኝ!
ብቻየን ቀርቻለሁና" ብሎ ቢጸልይ እግዚአብሔር ለጣዖት
ያልሰገዱ ሰባት ሺህ ሰዎችን እንዳተረፈ: እርሱንም ወደ
ብሔረ ሕያዋን እንደሚወስደው ብሥራትን ነገረው::
+ደክሞት ተኝቶ ሳለም ቅዱስ መልአክ (ሚካኤል)
ቀስቅሶ ታየው:: እንጐቻ ባገልግል: ውሃ በመንቀል
አቅርቦ "ብላ! ጠጣ!" አለው:: በላ: ጠጣ: ተኛ:: እንደ
ገና ቀስቅሶ አበላው:: በ3ኛው ግን "ብላዕ እስከ ትጸግብ
እስመ ርሑቅ ፍኖትከ - ጐዳናህ ሩቅ ነውና
እስክትጠግብ ብላ" አለው::
+ኤልያስም ለ40 ቀናት ያለ ምግብ ተጉዟል:: ከዚያ
በሁዋላም ምድራዊ ሕብስትን አልተመገበም::
እግዚአብሔር አክአብና ኤልዛቤልን ከተበቀላቸው
በሁዋላም ቅዱስ ኤልያስ በክፋተኞች ላይ 2 ጊዜ እሳትን
አዝንሟል::
+የሚያርግበት ጊዜ ሲደርስም ደቀ መዝሙሩን ኤልሳዕን
"የምትሻውን ለምነኝ" ቢለው "እጥፍ መንፈስህን"
አለው:: 3 ጊዜ ሊያስመልሰው ሞከረ:: ቅዱስ ኤልሳዕ
ግን በብርታት ተከተለው:: ዮርዳኖስን ከፍለው ከተሻገሩ
በሁዋላ ግን ቅዱስ ኤልያስን ሠረገላ እሳት ወርዶ
ነጠቀው:: ለኤልሳዕም እኩሉን ግምጃውን ጣለለት::
+ዛሬ ቅዱስ ኤልያስ በብሔረ ሕያዋን ያለ ሲሆን በዘመነ
ሐሳዌ መሲሕ መጥቶ በሰማዕትነት ከቅዱስ ሔኖክ ጋር ያርፋል:: (ራዕይ)
¤ለተጨማሪ ንባብ ( ከ1ነገ. 17-2ነገ. 2, እና ዕርገተ ኤልያስን ያንብቡ::)
<<ነቢዩ ኤልያስ በእውነት ታላቅ ነው!>>
+"+ ቅዱስ ዼጥሮስ ዘጋዛ +"+
=>ይህ ቅዱስ በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን በታናሽ እስያ
አካባቢ የተወለደ ሲሆን የክቡራኑ የመሣፍንት ልጅ ነው::
በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን አድጐ የቁስጥንጥንያ ንጉሥ
ትንሹ ቴዎዶስዮስ ወደ ቤተ መንግስቱ ወሰደው::
+በዚያም "አገረ ገዥ ላድርግህ" ብሎ ቢጠይቀው
"ትንሽ ቆየኝማ" ብሎት ጠፍቶ በርሃ ገብቶ መነኮሰ::
ቅዱስ ዼጥሮስ በምንኩስና ሲጋደል: ካለበት በርሃ
መጥተው በግድ ወስደው: የጋዛ (አሁን የፍልስጤምና
እሥራኤል ደንበር) ዻዻስ አደረጉት::
+ከደግነቱ የተነሳም በቅዳሴ ጊዜ ሥጋ ወደሙ ሲለወጥ
ያየው ነበር:: መላእክትም ያጫውቱት ነበር:: ሕዝቡ
ሲያጠፉ በየዋሕነት ዝም ቢላቸውም ቅዱስ መልአክ ገሥጾታል::
+የፋርስ ነገሥታት አጽመ ሰማዕታትን ሲያቃጥሉም እርሱ
የቅዱስ ያዕቆብ ዘግሙድን አጽም ይዞ ተሰዷል:: ለብዙ
ዘመናት በቅድስና ኑሮም በዚህች ቀን ዐርፏል::
ኅዳር 27
ቅዱስ ጢሞቴዎስ ሰማዕት
በዚህችም ቀን በንሑር ከሚባል አገር ቅዱስ ጢሞቴዎስ በሰማዕትነት አረፈ። ይህም ቅዱስ ከታናሽነቱ ጀምሮ እግዚአብሔርን የሚፈራ ሁልጊዜ በጾም በጸሎት ተጠምዶ የሚኖር ነው ስሟ ሞራ የሚባል ሚስት አለችው እርሷም የአጎቱ ልጅ ናት በሥራዋ ሁሉ ደስ የምታሰኘው መልካም ሴት ናት።
እንደዚህም በፍቅርና በስምምነት ሲኖር ከከሀዲ ንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስ ዘንድ የጣዖታት ቤቶች ይከፈቱ ዘንድ አብያተ ክርስቲያናት እንዲዘጉ ትእዛዝ ወጣ። ቅዱስ ጢሞቴዎስም ይህን ሰምቶ እጅግ ደስ አለው። እርሱ ስለ ክርስቶስ ፍቅር ደሙን ያፈስ ዘንድ ይህን ዘመን ይጠብቀው ነበርና ለሚስቱም ሊሠራው ያሰበውን ነገራት እርሷም የእግዚአብሔር ፈቃድ ይሁን አለች።
ከዚህም በኋላ መንገዱን ያቀናለት ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ ጌታችንም በዚያች ሌሊት በሕልሙ ተገልጾለት ወዳጄ ጢሞቴዎስ ሆይ ሰላም ላንተ ይሁን እነሆ ከጻድቃኖቼ ቁጥር ውስጥ ቆጥሬሃለሁ አሁንም ተነሣ ሚስትህንም ይዘህ ወደ ብህንሳ ከተማ ሒዳችሁ ጣዖታትን በሚያመልኩ ሁሉ ሕዝብ ፊት በስሜ ታመኑ አለው። በነቃ ጊዜም ለሚስቱ ነገራት እርሷም ይህንኑ የሚመስል ሕልሟን ነገረችው።
ከዚህም በኋላ ተነሥተው በአንድነት ሔዱ ወደ መኰንኑ ወደ ቊልቊልያኖስም ደረሱ መሰንቆና እንዚራ እያስመታ ለጣዖታቱ በዓልን ሲያከብር አገኙት ያንጊዜ ወታደሮቹ ይዘው በመኰንኑ ፊት አቆሙት ሚስቱም ተከተለችው መኰንኑም ለጣዖት መስገድን እያግባባ በርኅራኄ ቃል ተናገረው ቅዱሱ ግን እርሱንና የረከሰች ሃይማኖቱን ሰደበ ስለዚህም መኰንኑ ተቆጥቶ ከሚስቱ ጋር ወደ ወህኒ ቤት እንዲአስገቡት አዘዘ።
ከጥቂት ቀኖች በኋላም ከሚስቱ ጋር አውጥተው ደማቸው እንደ ውኃ እስቲፈስ በአለንጋዎች እንዲገረፉአቸው አዘዘ ያለ ርኅራኄም ገረፏቸው ሚስቱም በዚህ ሥቃይ ምስክርነቷን ፈጸመች።
ዳግመኛም ለጣዖታት መስገድን እሺ ይለው ዘንድ ቅዱስ ጢሞቴዎስን ማባበል ጀመረ እምቢ ባለውም ጊዜ የነዳጅ ድፍድፍ ሥጋውን ቀብተው ከእሳት ማንደጃ ውስጥ እንዲጨምሩት አዘዘ በጨመሩትም ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ወርዶ ከዚህ ቃጠሎ አዳነው ።
ከዚህም በኋላ ሁለተኛ ወደ ወህኒ ቤት መለሱት ተአምራትንም የሚያደርግ ሆነ በአንዲት ዕለትም በዚያ ሲጸልይ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደርሱ መጥቶ ቃል ኪዳንን ገባለት ሰላምታንም ሰጠው።
በማግሥቱም ከእሥር ቤት አውጥተው ወደ በንሑር ከተማ ወስደው ቅድስት ራሱን ቆረጡ ያን ጊዜ ንውጽውጽታ ሆነ አየርም መላእክትን ተመላች አማንያን ሰዎችም መጥተው ሥጋውን ወስደው በመልካም አገናነዝ ገንዘው ቀበሩት። የመከራውም ዘመን በአለፈ ጊዜ ቤተ ክርስቲያን ሠሩለት ሰኔ ሃያ ሰባት ቀንም አከበርዋት ሥጋውንም በውስጥዋ አኖሩ።
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን" ❤
❤ ኅዳር ፳፬ (24) ቀን።
❤ እንኳን ለኢትዮጵያኑ ጻድቃን ለታላቁ አባት ለሐዲስ ሐዋርያ ለአቡነ ተክለ ሃይማኖት ሃያ አምስተኛ ሆነው አብራው ከሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ ጋር የቅድስት ሥላሴ ዙፍን ላጠኑበት በዓልና ለአቡነ ዜና ማርቆስ በቅዱስ ማርቆስ አብሳሪነት ለተወለዱበት (ለልደታቸው) በዓላቸው በሰላም አደረሰን።
+ + +
❤ አቡነ ተክለ ሃይማኖትም ከሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ ጋር የቅድስት ሥላሴን መንበር እንዳጠኑ፡- አቡነ ተክለ ሃይማኖት ወደ አቡነ ኢየሱስ ሞዐ መጥተው በሐይቁ ዳር ቆመው ሳለ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ተገልጦላቸው ነው በእግሩ በውኃው ላይ እየሄደ እያሳያቸው ተከትለውት እንዲሄዱ የነገራቸው። አባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖትም መልአኩን ተከትለው ሐይቁን በእግራቸው ተራምደው ተሻግረው አቡነ ኢየሱስ ሞዐን አገኟቸው፡፡ እርሳቸውም አቡነ ተክለ ሃይማኖት ወደ እርሳቸው እየመጡ እንደሆነ በመንፈስ ዐውቀው ነበርና ሲያገኟቸው በጣም ተደስተው ከተቀበሏቸው በኋላ አመነኩሰዋቸዋል፡፡
❤ ከዚህም በኋላ አባታችን በዚያው በሐይቅ በታላቅ ተጋድሎ መኖር ጀመሩ፡፡ አክፍሎትንም በየሳምንቱ ያከፍላሉ፣ ከእሁድና ከቅዳሜ በቀር ምንም አይቀምሱም ነበር፡፡ በእነዚህም ዕለት የአጃ ቂጣ ወይም የዱር ቅጠል ይመጉ ነበር፡፡ ወዛቸው እንደ ውኃ ፈስሶ ምድሪቷን እስኪያርሳት ድረስ እስከ 70 ሺህ ስግደትንም በመስገድ ራሳቸውን እጅግ አደከሙ፡፡ በእነደዚህ ዓይነቱ ተጋድሎ ላይ ሳሉ ነው ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ድንገት ነጥቆ ወስዶ ከሥሉስ ቅዱስ ዙፋን ፊት ያቆማቸው፡፡ ከዚህ በኋላ ስለሆነው ነገር ራሳቸው አባታችን ተክለ ሃይማኖት ሲናገሩ "…ከዚህ በኋላ መልአኩ ወደ ሰማይ አውጥቶ ከመጋረጃው ውስጥ አስገብቶ ከሥላሴ ዙፋን ፊት አቆመኝና ሰገድኩለት፡፡ ከዚያ አስቀድሞ በማላውቀው በሌላ ምስጋና አመሰገንኩት፡፡ "ተክለ ሃይማኖት ክፍልህ ከ24ቱ ካህናቶቼ ጋር ይሁን" የሚል ቃል ከዙፋኑ ውስጥ ወጣ፡፡ የወርቅ ጽና አምጥተው ሰጡኝና ከእነርሱ ጋር አንድነት አጠንሁ፡፡ ምስጋናዬ ከምስጋናቸው ጋር ልብሴም እንደልብሳቸው ሆነ፡፡ ፈጣሪዬንም በሦስትነቱ ተገልጦ አየሁት፡፡ በጸሎትህ የሚታመን ሰው ሁሉ ስለአንተ ይድናል አለኝ….." ምንጭ፦ ገድለ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ምዕራፍ 43።
+ + +
❤ አቡነ ዜና ማርቆስ በወንጌላዊ በቅዱስ ማርቆስ ብሥራት እንደተወለዱ፡- አባታችን ዜና ማርቆስ ሀገራቸው ጽላልሽ አውራጃ ምድረ ዞረሬ ሲሆን ትውልዳቸው ከነገደ ሌዊና ከእስራኤል ነገሥት ወገን ነው፡፡ ወላጆቻቸው ልጅ በማጣት ሲያዝኑ አንድ ዕለት ሐዋርያውና ወንጌላዊው ቅዱስ ማርቆስ ወደ እናታቸው ማርያም ዘመዳ ሌሊት መጥቶ "ገድሉና ትሩፋቱ በዓለም ሁሉ የመላ ጻድቅ ልጅ እንደምትወልድ አበሠራት፡፡ ለአባቱ ለቀሲስ ዮሐንስም እንዲሁ ተገልጦለት "ሚስትህ ማርያም ዘመዳ የካቲት 24 ፀንሳ ኅዳር 24 ቀን ይኸውም በካህናተ ሰማይ በዓል ቀን ትወልዳለች፣ ስሙም ዜና ማርቆስ ይባላል" በማለት ብሥራቱን ነግሮታል፡፡
❤ በወንጌላዊው ቅዱስ ማርቆስ ብሥራት መሠረት አባታችን ዜና ማርቆስ በዚህች ዕለት ኅዳር 24 ቀን በተወለዱ ጊዜ ቅዱስ ዑራኤልና ቅዱስ ሩፋኤል የብርሃን ልብስ አልብሰው በክንፋቸው ሲጋርዱአቸው ለሰዎች ሁሉ ታይቷል፡፡ የአቡነ ሳሙኤል ዘወገግ አባት ቅዱስ እንድርያስና የአቡነ ተክለሃይማኖት አባት ቅዱስ ጸጋ ዘአብ እስኪደነቁ ድረስ ይህን በዓይናቸው ተመልክተዋል፡፡ ሁለቱ መላእክትም አቡነ ዜና ማርቆስን ከእናታቸው ዕቅፍ ወስደው ወደ ሐዋርያው ማርቆስ መቃብር ወስደው ለማርቆስና ለቅዱሳን ጳጳሳት አስባርከዋቸው መልሰው ለእናታቸው ሰጧቸው፣ እናታቸው ግን ይህን አታውቅም ነበር፡፡ አቡነ ዜና ማርቆስ በተወለዱ በሦስተኛው ቀን በእግራቸው ቆመው "አንድ አምላክ ለሆኑ ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ እሰግዳለሁ" ብለው ሦስት ጊዜ አምላካቸውን አመስግነው ሰግደዋል፡፡
ምንጭ፦ መዝገበ ቅዱሳን።
ከተክለሃይማኖት ረድኤት በረከት ያሳትፈን።
ይቆየን!
✞ የክብርን ዘውድ ጭኖ ✞
የክብርን ዘውድ ጭኖ ታየ ካህኑ
በወርቅ ማዕጠንት ሞልቶ ሲያርግ እጣኑ
እንደ ሱራፌል መልዐክ ደራርቦ አክናፍ
ቆመ ተክለሐይማኖት ከእሳቱ ደጃፍ
ነበልባል ከጋረደው ከሥላሴ ሰገነት
ባለ ግርማ ሞገስ ነው ሲሰየም ለአገልግሎት
ሀያ አራቱን ካህናት ተቀላቅሎ ተክልዬ
ህዝቤን ማርልኝ ይላል አክብርልኝ ጌታዬ
/አዝ=====
በትረመስቀሉን ተክሎ ከጭንጫ ውሀ አመነጨ
ሰላም ለብሶ እንዲሄድ ጸበሉን የተረጨ
በረገጠው ምድር ላይ ቃልኪዳኑ ፈሰሰ
የሰማዩን በረከት በእኛ ላይ ነሰነሰ
/አዝ=====
ተቀጣጠለ ዝናው ከአድማስ ማዶ ተሰማ
በጸሎቱ ዘለፈው ድፍንፍኑን ጨለማ
ከመናንያን ጋራ ይመንናል በፍቅር
አባ ተክለሐይማኖት የኢትሳው መምህር
/አዝ=====
አለው ጥዑም መዓዛ የእጁ ጠረን ሽታ
ለተሳለመው ሁሉ ይሰጣል ልዩ ደስታ
ገና ከገድሉ መፃፍ ስንኞች ሲበተኑ
የቤልሆን ሰራዊት እንደ እንፋሎት ተነኑ
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔✞═══●◉❖◉●═════✞╗
❖ @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit ❖
╚✞═══●◉❖◉●═════✞╝
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
#ሰንበት
ሰንበተ ክርስቲያን (እሑድ)
እሑድ ማለት ‹‹አሐደ›› ከሚለው የግእዝ ቃል የወጣ ሲሆን ትርጉሙም የመጀመሪያ ማለት ነው፡፡ ይህቺ ዕለት በመጽሐፍ ቅዱስ ‹‹ከሳምንቱ በፊተኛው ቀን›› በመባል ትታወቃለች፡፡
ዮሐንስም በራዕዩ ‹‹የጌታ ቀን›› ያላት ናት (ራእይ 1፤10)፡፡ ቅዱስ ያሬድም በድጓው ላይ ‹‹ዕለተ እግዚአብሔር›› የሚላት ዕለተ እሑድ ናት፡፡
ዕለተ እሑድ እንደ ሰንበት የሚከበርበት ምክንያቶች፡-
👉 እግዚአብሔር ሥራውን የጀመረባት ለሥነፍጥረት መጀመሪያ ዕለተ (ጥንተ ዕለት) ናትና
👉 ዕለተ ሥጋዌ ናት፡፡ ጌታ የተፀነሰባትና እርቅ የተወጠነባት የፍሰሐ ቀን፡፡
👉 ዕለተ ትንሣኤ ናት፡፡ ጌታ ከሙታን ተለይቶ የተነሳባት ዕለት
👉 የቤተ/ክ የልደት ቅን ናት፡፡ መንፈስ ቅዱስ ለሐዋሪያት የወረደባት ኃይልና ፅናትን ያገኙባት ዕለት
👉 ጌታ በክበበ ትስብእት በግርማ መለኮት ዳግም በቅዱሳን መላእክቱ ታጅቦ በጌትነቱ ለፍርድ የሚመጣባት ታላቅ የፍርድ ቀን ናትና የተለያዩ መንፈሳዊ አገልግሎቶች የሚካሄዱባት ዕለት ናት(1ኛ ቆሮ 16፤1)
👉 የሐዋሪያት ዘመንም በጤሮዓዳ ያሉ ክርስቲያኖች እሑድ ቀን ይሰበሰቡ ነበር (የሐዋ. 20፤7 በቤተክርስቲያን ታሪክ ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ ዕለተ እሑድ የክርስቲያኖች ሰንበት ናት በማለት
ሥራ እንዳይሰራባት አዋጅ አስነግሮ ነበር፡፡
ምንም እንኳን ይህቺ ዕለት በሐዲስ ኪዳን መከበር የጀመረ ቢሆንም በብሉይ ኪዳን ከፋሲካ በፊት የሰንበት (የቀዳሚት) ማግስት በመባል በኩራት እና ቀዳሚያት የሚያቀርቡበት ቀን ነበር። (ራዕ 1፡10)
በቀዳሚት ሰንበት ቅዱስ እግዚአብሔር ከሥራው ሁሉ አርፎ ሥጋዊ እረፍትን ለሰው እንዳስተማረ በእሑድ ቀን (በሰንበተ ክርስቲያን) በጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት የተገኘውን የዘላለማዊ የነፍስ ዕረፍት የምናስብበት ነው፡፡ (ዕብ 4፡1-10)
#ከሰንበት_ረድኤት_በረከት_ይካፍለን!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
✞ ጽዮንን መርጧታል ✞
ጽዮንን መርጧታል ይህንን አምናለሁ
እናቱ ናትና ብፅዕት እላታለሁ
ከሴቶች ሁሉ የተለየች ናት
በድንቅ ጥበብ ቃል ተዋሓዳት
ዓለም እንዲድን ምክንያት ሆና
እንዴት አላቀርብ ለእርሷ ምስጋና
የናቁሽ ሁሉ ወደ እግርሽ ጫማ ይሰግዳሉ
አማልጅን ድንግል ማርያም እያሉ
/አዝ=====
የሰላም ንጉሥ ስለወደዳት
ርግቤ ሆይ ልበል ልዘምርላት
ቅዱሱ መንፈስ በልቤ ላይ ነው
እያነሳሳኝ ማርያም እላለሁ
የናቁሽ ሁሉ ወደ እግርሽ ጫማ ይሰግዳሉ
አማልጅን ድንግል ማርያም እያሉ
/አዝ=====
የገነት መግቢያ ተከፍቷል በሩ
ብፁዓን ናቸው ስሟን የሚጠሩ
ከንዑዳን ጋር በመሰለፌ
ክብርት ሆናለች ቅኔ መፅሐፌ
የናቁሽ ሁሉ ወደ እግርሽ ጫማ ይሰግዳሉ
አማልጅን ድንግል ማርያም እያሉ
/አዝ=====
ውዳሴ ሰማሁ ከራማ ሀገር
ድምጿ አፅናናኝ በኤፍሬም መንደር
በትሕትና ውስጤን ሸልሜ
አከብራታለሁ በዜማ ቆሜ
የናቁሽ ሁሉ ወደ እግርሽ ጫማ ይሰግዳሉ
አማልጅን ድንግል ማርያም እያሉ
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔✞═══●◉❖◉●═════✞╗
❖ @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit ❖
╚✞═══●◉❖◉●═════✞╝
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
✞ መሠረቷ ጉልላቷ ✞
መሠረቷ ጉልላቷ እርሱ ነው
ሙሽራዋ መስቀል ላይ የምተው
ዛሬም ነገም ህያው ነው ለዘላለም
አትንገሩን አዲስ ጌታ የለም/2×/
የእንግዳው ትምርት የጠላት እንክርዳድ
በመከሩ ጊዜ ይለያል ሲታጨድ
ጌታ ጌታ ያለው እንዲሁ በብልጠት
አይወርስም ፈፅሞ የሰማዩን እርስት/2×/
/አዝ=====
እራስ ለሆነላት ሆናለች አካሉ
ትታዘዘዋለች ዘወትር ለቃሉ
የፊት መጨማደድ ሣያገኛት ድካም
ታምና ትኖራለች እስኪመጣ ዳግም/2×/
/አዝ=====
የሠማይታቱ ደም የከፈሉት ዋጋ
የመላክቱ ዜማ የሰማዩ ፀጋ
የሀዋርያት ስብከት የነብያት ትንቢት
ይገኛል በውስጧ በፀጋው ግምጃ ቤት/2×/
/አዝ=====
ጎዳናውን ጥሰን ብንጋዝ በ ሀሰት
ለ አንደበታችን አውጀን አርነት
አይዘጋም ደጇ አይጠፋም መብራቷ
ኢየሱስ ነው ክብሯ ጌጥና ውበቷ /2×/
👉ዘማሪ ሊቀ ዲ/ን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔✞═══●◉❖◉●═════✞╗
❖ @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit ❖
╚✞═══●◉❖◉●═════✞╝
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
✞ ሚናስ ሚናስ ይላል ✞
ሚናስ ሚናስ ይላል አንደበቴ 2
አማልዶኛል እና ከሰማዩ አባቴ
ሚናስ ሚናስ ይላል አንደበቴ
አምላከ ሚናስ ደስ ይላል 2
የሰማዕቱ ልጆች አርጎናል 2
ሚናስ ሚናስ ይላል ምድር እና ሰማዩ
ሚናስ ሚናስ ይላል ታምርክን ይንገሩን
ሚናስ ሚናስ ይላል ፍጥረታት በሙሉ
ሚናስ ሚናስ ይላል ለክብሩ ዘምሩ
አምላከ ሚናስ ደስ ይላል /2×/
የሰማዕቱ ልጆች አርጎናል /2×/
/አዝ=====
ሚናስ ሚናስ ይላል ለእምነትህ መቆምህ
ሚናስ ሚናስ ይላል አድርሶሃል ለሞት
ሚናስ ሚናስ ይላል ሲቆረጥ አንገትህ
ሚናስ ሚናስ ይላል ፈሶሃል ደም ወተት
አምላከ ሚናስ ደስ ይላል /2×/
የሰማዕቱ ልጆች አርጎናል /2×/
/አዝ=====
ሚናስ ሚናስ ይላል በሠራህው መቅደስ
ሚናስ ሚናስ ይላል በረከት ጠገቡ
ሚናስ ሚናስ ይላል አቡነ ሐራ ድንግል
ሚናስ ሚናስ ይላል ቀድሰው ቆረቡ
አምላከ ሚናስ ደስ ይላል /2×/
የሰማዕቱ ልጆች አርጎናል /2×/
/አዝ=====
ሚናስ ሚናስ ይላል ያከበርከው ጌታ
ሚናስ ሚናስ ይላል ከፍ ከፍ በልልን
ሚናስ ሚናስ ይላል ከዓለም አንስቶ
ሚናስ ሚናስ ይላል በሚናስ ባረከን
አምላከ ሚናስ ደስ ይላል /2×/
የሰማዕቱ ልጆች አርጎናል /2×/
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔✞═══●◉❖◉●═════✞╗
❖ @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit ❖
╚✞═══●◉❖◉●═════✞╝
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
✞ ፀሎት ልመናዬን
✞
ጸሎት ልመናዬን ፈጥነህ የምትሰማ
አለቃ ነህ በኢዮር በኤረር በራማ
ምክርህን ለግሰኝ ጥበብ አስተምረኝ
አባት እንዳረኩህ አንተም ልጅ አድርገኝ
ለሕዝብ የተሾመ የታመነ መልአክ
ለብዙ ምሕረት ከእግዚአብሔር የሚላክ
ስለ ሰው ልጅ መዳን ዘውትር የሚተጋ
እርሱ ነው ሚካኤል የመላእክት አለቃ
ምክንያት አለኝ ለአንተ መዘመሬ ሚካኤል ክብሬ
እናት አባት ሆነህ አሳድገኸኝ
ለዚህ አበቃኽኝ
/አዝ=====
ግርማ ሞገስ ሆነኝ ጦማሬን ቀይሮ
ለዚህ አደረሰኝ ከክፉ ሰውሮ
ውለታውን ልገልጽ አጣሁለት ቋንቋ
በእግዚአብሔር ፊት ቆሞ ሆነልኝ ጠበቃ
ወደ ሚበልጠው ክብር እኔን እየመራ
ድካሜን ያገዘ ጽልመቱን ያበራ
ጉልበቴ ነው እርሱ የልቤ ወዳጅ
ሚካኤል አባቴ የነፍሴ አማላጅ
ጠዋትና ማታ ከመቅደሱ ተክሎ
ሕይወት የመገበኝ ከሞት አፍ ከልሎ
ሚካኤል/2/ እላለሁ ዘወትር /3/
እጅግ ተለይቷል ለርሱ ያለኝ ፍቅር
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔✞═══●◉❖◉●═════✞╗
❖ @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit ❖
╚✞═══●◉❖◉●═════✞╝
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ