mezmuredawit | Unsorted

Telegram-канал mezmuredawit - ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

28629

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ የመዝሙር ግጥሞችን እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን" መዝ 150÷6 " አሕዛብ ሁላችሁ፥ እጆቻችሁን አጨብጭቡ፥ በደስታ ቃልም ለእግዚአብሔር እልል በሉ።" (መዝሙረ ዳዊት 47:1) ለማንኛውም ሀሣብ, ጥቆማ, አስተያየት @Kidusyared_comment_bot ላይ ቢያስቀምጡልን ይደርሰናል

Subscribe to a channel

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

✞ ሱራፌል ይሰግዱልኃል ✞

ሱራፌል ይሰግዱልኃል
ኪሩቤል ያመሰግኑኃል
በሞገስ ላለኸው በግርማ
ምስጋናው እልልታው ተሰማ

አይናወጽ መንግስትህ
አይደፈር ዙፋንህ
ዛሬም አለህ በከፍታ
ጌትነትህ ምድርን መልታ
    
     /አዝ=====

ጭንቁን ሌሊት ያነጋህ
ድቅድቁንም ያጠራህ
ምታኖረን በሰላም
ንገሥልን ዘለዓለም
    
     /አዝ=====

በማያልፈው መቅደስህ
በማይፈርሰው ማደሪያህ
ትኖራለህ ስትወደሥ
የነገሥታት ሁሉ ንጉሥ

     /አዝ=====

ኃይላት እና ሥልጣናት
መናብርት እና ሊቃናት
ፍጥረት ሁሉ ሚሰግደው
በመውደድህ ተማርኮ ነው

👉ዘማሪት አዜብ ከበደ

#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።

╔​✞═══●◉❖◉●═════✞╗
   ❖   @mezmuredawit     ❖
   ❖   @mezmuredawit     ❖
   ❖   @mezmuredawit     ❖  
╚✞═══●◉❖◉●═════​✞╝

✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

#እንኳን_እመቤታችን_ከስደት_ተመልሳ_ቁስቋም_የገባችበት_በዓል_ቀን_በሰላም_አደረሳችሁ!

​​#ህዳር 6

+በዚች ቀን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከልጇ እንዲሁም ከዮሴፍ እና ሰሎሜ ጋር 3 ዓመት ከ 6 ወር በስደት ከተንገላታች በኋላ ወደ ሀገራቸው የተመለሱበት ቀን ነው።

ታድያ ጌታችን በእመቤታችን ጀርባ ላይ ሆኖ በእነዛ የምህረት ጣቶቹ ወደ #ኢትዮጵያ ይጠቁም ነበር እመቤታችንም ልጄ ሆይ ለምንድነው ጣትህን ምታመለክተው ስትለው ""ያቺ የተባረከች ሀገር ናት"" እኔን የሚያመልኩ አንቺን የሚማልዱ በፍቅርሽ የነደዱ ቅዱሳን መነኮሳት የሚፈልቁባት አገር ናት!!ያንቺ ዘመዶች ሰቅለው ይገሉኛል በዚች አገር ያሉ ግን ሳያዩ ያምኑኛል አስራት በኩራት ትሁንሽ ብሎ ሰቷታል በቅዱስ እግራቸውም ጣና ሀይቅን ዋልድባንና ሌሎችንም ዞረው እንደባረኩም ድርሳነ ኡራኤልና ታምረ ማርያም ላይ በስፋት ተጽፏል።

እመቤታችንን ከሐና መሀፀን ፈጥሮ ከፍጥረት አለም ለይቶ ከሁሉ አልቆ የእናት አማላጅ ትሁናችሁ ብሎ የሰጠን ልዑል እግዚአብሔር ይመስገን ! የእመቤታችን ቁስቋም ማርያም ምልጃዋና በረከቷ አይለየን !! ሀገራችንን ሰላም ታድርግልን !!
ኀዳር 6 ቀን ወደ ግብጽ አገር ተሰዳ ስትመለስ ቁስቋም በምትባል አገር ገብታ ያረፈችበት በዓል ነው፡፡

ከገነት የተሰደደውን አዳም ወደ ገነት ለመመለስ ሲል ወልደ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናቱ ከድንግል ማርያም ከአረጋዊው ዮሴፍና ከሰሎሜ ጋር ወደ ግብጽ ተሰደደ፡፡

ጌታችን ከ3 ዓመት ከ6 ወር የግብጽ ስደት በኋላ ወደ እስራኤል እንደሚመለስ አስቀድሞ ነቢየ ልኡል ሆሴዕ በትንቢት መነጽርነት ተመልክቶ “ልጄንም ከግብጽ ጠራሁት ” ብሎ ተናግሯል ሆሴ 11÷1
ተፈጸመ ናሁ ማኅሌተ ጽጌ ሥሙር - እነሆ የተወደደው ማኅሌተ ጽጌ ተፈጸመ!

«ተመየጢ ተመየጢ ሱላማጢስ ...ሱላማጢስ ሆይ ተመለሽ ተመለሽ » መኃ ፯፥፩

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

✞ ኢየሐፍር_ቀዊመ ✞

ኢየሐፍር /ቀዊመ/ (፪) ቅድመ ስዕልኪ
ወርኃ ጽጌረዳ (፬) አመ ኃልቀ ወርኃ ጽጌረዳ
#ትርጉም
በስዕልሽ ፊት የቆመ አያፍርም
የ ጽጌረዳ(አበባ)ወቅት ቢያልቅም

#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።

  ╔​✞═══●◉🌹◉●════✞╗
   🌹  @mezmuredawit  🌹
   🌹  @mezmuredawit  🌹
   🌹  @mezmuredawit  🌹  
  ╚✞═══●◉🌹◉●════​✞╝
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

ተፈጸመ ናሁ ማኅሌተ ጽጌ ሥሙር🌹፤ እነሆ የተወደደች ማኅሌተ ጽጌ ተፈጸመ!

ሥርዓተ ማኅሌት ዘዘመነ ጽጌ "በዓለ ቅዱስ ታዴዎስ ሐዋርያ፣ ወኢዮብ ጻድቅ፣ ወአቤል" "፮ኛ ሳምንት" "ተፈጸመ"

የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ (ሥርዓተ ነግሥ)
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገአርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገጸከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ እዝነከ ኀቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል።

መልክአ ሥላሴ
ሰላም ለኲልያቲክሙ እለ ዕሩያን በአካል፤ ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወጸ በሣሕል፤ እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር ቃል፤ ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል፤ ወበቀራንዮ ተተክለ መድኃኒት መስቀል።

ዚቅ
ሃሌ ሉያ፤ ለክርስቶስ ይደሉ ስብሐት፤ ለዘአብጽሐነ እስከ ዛቲ ሰዓት፤ እግዚአ ለሰንበት፤ አኮቴተ ነዓርግ ለመንግሥትከ፤ ምድረ በጽጌ አሠርጎከ።

ማኅሌተ ጽጌ
ኢየኃፍር ቀዊመ ቅድመ ስዕልኪ ወርኃ ጽጌረዳ አመ ኃልቀ፤ ዘኢየኃልቅ ስብሐተ እንዘ እሴብሐኪ ጥቀ፤ ተአምርኪ ማርያም ከመ አጠየቀ፤ ጸውዖ ስምኪ ያነሥእ ዘወድቀ፤ ኃጥአኒ ይሬሲ ጻድቀ።

ወረብ
ኢየኃፍር ቀዊመ ቅድመ ስዕልኪ ወርኃ ጽጌረዳ አመ ኃልቀ/፪/
ዘኢየኃልቅ "ስብሐተ"/፪/ እንዘ እሴብሐኪ/፪/

ዚቅ
እለ ትነብሩ ተንሥኡ፤ ወእለ ታረምሙ አውሥኡ፤ ማርያምሃ በቃለ ስብሐት ጸውኡ፤ ቁሙ ወአጽምዑ ተአምረ ድንግል ከመ ትስምዑ፤ ጸልዩ ቅድመ ስዕላ ለቅድስት ድንግል፤ መርዓተ አብ ወእመ በግዑ።

ማኅሌተ ጽጌ
እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕፃንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ፤ አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ በዕለተ ተአምር ወንጽሕ፤ ንዒ ርግብየ ትናዝዝኒ እምላህ፤ ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ፤ ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ።

ወረብ
እንዘ ተሐቅፊዮ "ለሕፃንኪ"/፪/ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ/፪/
ንዒ ርግብየ ምስለ ገብርኤል ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ሚካኤል/፪/

ዚቅ
ንዒ ርግብየ ሰላማዊት፤ ንባብኪ አዳም፤ ከመ ፍሕሶ ቀይሕ ከናፍሪሃ፤ እሞሙ ለሰማዕት ወእኅቶሙ ለመላዕክት፤ አልቦ ዘይመስል ዘከማኪ ክብረ፤ እግዚአ ለሰንበት በማኅፀንኪ ተጸውረ።

ዓዲ (ወይም)
ዚቅ
ንዒ ኀቤየ ኦ ድንግል ምስለ ኲሎሙ መላእክት፤ ከመ ታዕርጊ ጸሎተነ ጊዜ መንፈቀ ሌሊት።

ማኅሌተ ጽጌ
ሰዊተ ሥርናዩ ለታዴዎስ ወለበርተሎሜዎስ ወይኑ፤ እንተ ጸገይኪ አስካለ በዕለተ ተከልኪ እደ የማኑ፤ ማርያም ለጴጥሮስ ጽላሎቱ ወለጳውሎስ ሰበኑ፤ ብኪ ምውታን ሕያዋነ ኮኑ፤ ወሐዋርያት መላእክተ በሰማይ ኮነኑ።

ወረብ
ማርያም ለጴጥሮስ "ጽላሎቱ"/፪/ ወለጳውሎስ ሰበኑ/፪/
ወሐዋርያት "መላእክተ"/፪/ በሰማይ ኮነኑ/፪/

ዚቅ
ኦ መድኃኒት ለነገሥት፤ ማኅበረ ቅዱሳን የዓውዱኪ፤ ነቢያት የዓኲቱኪ፤ ወሐዋርያት ይሴብሑኪ፤ እስመ ኪያኪ ኀቤ ለታዕካሁ ከመ ትኲኒዮሙ ማኅደረ፤ መላእክት ይኬልሉኪ፤ ጻድቃን ይባርኩኪ፤ አበው ይገንዩ ለኪ፤ እስመ ኪያኪ ኀቤ ለታዕካሁ ከመ ትኲኒዮሙ ማኅደረ።

ማኅሌተ ጽጌ
ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቌ ባሕርይ ዘየኀቱ፤ ዘተጽሕፈ ብኪ ትእምርተ ስሙ ወተዝካረ ሞቱ፤ አክሊለ ጽጌ ማርያም ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግሥቱ፤ አንቲ ኲሎ ታሰግዲ ሎቱ፤ ወለኪኒ ይሰግድ ውእቱ።

ወረብ
ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ ክበበ ጌራ ወርቅ ዘየኀቱ እምዕንቊ ባሕርይ/፪/
አክሊለ ጽጌ ማርያም ቀጸላ መንግስቱ ለጊዮርጊስ መንግስቱ ለሕዝበ ክርስቲያን/፪/

ዚቅ
ውድስት አንቲ በአፈ ነቢያት፤ ወስብሕት በሐዋርያት፤ አክሊለ በረከቱ ለያዕቆብ፤ ወትምክሕተ ቤቱ ለ፳ኤል።

ማኅሌተ ጽጌ
ኅብረ ሐመልሚል ቀይሕ ወፀዓድዒድ አርአያ ኮስኮስ ዘብሩር፤ ተአምርኪ ንፁሕ በአምሳለ ወርቅ ግቡር፤ ተፈጸመ ናሁ ማኅሌተ ጽጌ ሥሙር፤ አስምኪ ቦቱ ንግሥተ ሰማያት ወምድር፤ ከመ በሕጽንኪ ያሰምክ ፍቁር።

ወረብ
ናሁ "ተፈጸመ"/፪/ ናሁ ማኅሌተ ጽጌ ሥሙር ተፈጸመ ናሁ/፪/
"አስምኪ ቦቱ"/፪/ ንግሥተ ሰማያት /፪/

ዚቅ
ሃሌ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ፤ ጥቀ አዳም መላትኅኪ ከመ ማዕነቅ፤ ይግበሩ ለኪ ኮስኮሰ ወርቅ።

ሰቆቃወ ድንግል
ተመየጢ እግዝእትየ ሀገረኪ ናዝሬተ፤ ወኢትጎንድዪ በግብጽ ከመ ዘአልብኪ ቤተ፤ በላዕሌኪ አልቦ እንተ ያመጽእ ሁከተ፤ ለወልድኪ ዘየኃሥሦ ይእዜሰ ሞተ፤ በከመ ነገሮ መልአክ ለዮሴፍ ብሥራተ።

ወረብ
"ተመየጢ"/፪/ እግዝእትየ ማርያም ሀገረኪ/፪/
ወኢትጎንድዪ "በግብጽ"/፪/ ከመ ዘአልብኪ ቤተ/፪/

ዚቅ
ሃሌ ሉያ፤ ተመየጢ ተመየጢ ሰላመ ሰጣዊት፤ ወንርዓይ ብኪ ሰላመ፤ ምንተኑ ትኔጽሩ በእንተ ሰላመ ሰጣዊት፤ እንተ ትሔውጽ እምርኁቅ፤ ከመ መድብለ ማኅበር ሑረታቲሀ ዘበስን ለወለተ አሚናዳብ።

መዝሙር
በ፮: ክርስቶስ ሠርዓ ሰንበተ፤ ክርስቶስ ሠርዓ ሰንበት፤ ወጸገወነ ዕረፍተ ከመ ንትፈሣሕ ኅቡረ፤ አዕጻዳተ ወይን ጸገዩ፤ ቀንሞስ ፈረየ፤ ሰሎሞን ጥቀ ኢለብሰ ከመ ፩ እምእሉ።

ዓራራይ
በሰንበት እውራነ መርሐ፤ በሰንበት አጋንንተ አውጽአ፤ እለ ለምጽ አንጽሐ፤ ቃለ ማዕነቅ ተሰምዓ በምድርነ፤ ሠርዓ ሰንበተ ለዕረፍት።

ዕዝል
መንክር ግብሩ ለ፩ እግዚአብሔር አብ ዘላዕለ ኲሉ፤ መንክር ግብሩ ለዘሠርዓ ሰንበተ ለዕረፍት፤ መንክር ግብሩ ለዘአሠርገዋ ለምድር በጽጌያት፤ መንክር ግብሩ ለዘገብረ ብርሃናተ ዓበይተ ባሕቲቱ።

ሰላም
ተሣሐልከ እግዚኦ ምድረከ፤ ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሐረገ ወይን፤ እንተ በምድር ሥረዊሃ ወበሰማይ አዕፁቂሃ ሐረገ ወይን፤ እንተ በሥሉስ ትትገመድ፤ ወታፈሪ ለነ አስካለ በረከት ሐረገ ወይን፤ ሲሳዮሙ ለቅዱሳን ሐረገ ወይን፤ ሠርዓ ሰንበተ በቃሉ፤ ወጸገወ ሰላመ ለኵሉ።

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

✞ መድኃኔዓለም ✞

መድኃኔዓለም የለም የሚሳነው
አማኑኤል የለም የሚሳነው
እርሱ ቃል ሲናገር ተራራው ሜዳ ነው
መድኃኔዓለም የለም የሚሳነው

አላስብም ነበር አልፈዋለሁ ብዬ
ጉንጭ አልፎ ትራሴን እያጠበ እንባዬን
እየተፈጸመ ኃይሉ በድካሜ
ማእበሉን አለፍኩኝ ቀለለልኝ ሸክሜ

          /አዝ=====

የቤቴ እራስ ነው የእቅዴ መሪ
በክፉም በደጉም ነፍሴን አስተማሪ
ፈጥሮ የማይረሳኝ ቤዛዬ ደረሰ
ቤቴን ደስታ ሞላው እንባዬ ታበሰ

          /አዝ=====

ትናንት ባዶ ነበር የለኝ የሚሰፈር
አንዳች አልነበረኝ የሚታይ የሚቆጠር
ከርሱ የተነሳ ዛሬ ግን ሙሉ ነኝ
ክብር ለእርሱ ይሁን አለ የማይተወኝ

          /አዝ=====

እየከለከለ ለእኔ ማይጠቅመኝን
በጊዜ እየሰጠ ደግሞ የሚረባኝን
ሁሉ በእርሱ ሆኗል አልሆነም ያለ እርሱ
ውዳሴ ምስጋና ይድረስ ለንጉሱ


#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።

╔​✞═══●◉❖◉●═════✞╗
   ❖   @mezmuredawit     ❖
   ❖   @mezmuredawit     ❖
   ❖   @mezmuredawit     ❖  
╚✞═══●◉❖◉●═════​✞╝

✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

✞ ፀሀይ ወጣ ከሮሜ ✞

ፀሀይ ወጣ ከሮሜ ብርሀን ነው ለአለም
መርቆሬዎስ /2/ የአምላክ ባለሟል

በእግዚአብሔር መላክ አሮስ ከሞት ድኗል
በሮም ሀገር መርቆሬዎስ ተወልዷል
እንደእናት አባቱ ኖህና ታቦት
በምግባር የፀና ሆነ በእምነት /2/

           /አዝ=====

ከእግዚአብሔር መላክ ሰይፍን ተቀናጅቷል
በጠላቶቹ ላይ ግርማውም ያስፈራል
ዲያብሎስ ይርዳል ስሙ ሲጠራበት
መርቆሬዎስ ብሎ ለተማፀነበት/2/

           /አዝ=====

እንደ ባስልዮስ እና ጎርጎርዮስ
ጋሹ አምባ ላይ ያለው ቅዱስ መርቆሬዎስ
ስለቴ ተሰማ ዘምር ዘምር አለኝ
መርቆሬዎስ ደርሶልኝ ችግሬ ቀለለኝ/2/

           /አዝ=====

ደምህን እንደጎርፍ ዳኬዎስ ቢያፈሰው
ስጋህን በእሳት ላይ ደፍሮ ሊያቃጥለዉ
የእሳቱን ቶን ደምህ አጥፎቶታል
ስለቅድስናው ሶስት አክሊል አግኝቷል/2/

           /አዝ=====

አንገትህ ሲታረድ ቂሳርያ ታወከች
የተጋድሎ ፅናት ባይኖቿ ስላየች
ዝክርህን ዘክሮ ስምህን ለጠራ
በመንግስተ ሰማይ ይኖራል ካንተ ጋራ/2/


#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።

╔​✞═══●◉❖◉●═════✞╗
   ❖   @mezmuredawit     ❖
   ❖   @mezmuredawit     ❖
   ❖   @mezmuredawit     ❖  
╚✞═══●◉❖◉●═════​✞╝

✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

ለድንግል ይቤላ ✞

ለድንግል ይቤላ /*3/
ተፈስሒ ተፈስሒ ለድንግል ይቤላ
ወሪዶ ገብርኤል ምድረ ገሊላ

ሀርና ወርቅ እያስማማሽ
የአበውን ቃል እየሰማሽ
አደግሽ እና በመቅደሱ
እናት ሆንሽው ለንጉሱ
ተፈስሒ ተፈስሒ ለድንግል ይቤላ

       /አዝ=====

ገብርኤል ነው ያስተማረኝ
ምስጋናሽን የነገረኝ
ተፈስሒ ሰምቻለው
በፍስሐ ጠራሻለው
ተፈስሒ ተፈስሒ ለድንግል ይቤላ

       /አዝ=====

ወደ ናዝሬት ያኔ ሲላክ
ከአንቺ ዘንድ ደጉ መልአክ
ያለልሽን ያንን ሰላምታ
ተቀኘውት በእልልታ
ተፈስሒ ተፈስሒ ለድንግል ይቤላ

       /አዝ=====

ብርክት አንቲ በኤፍራታ
ያቀረብሽን ወደ ጌታ
ደስብሎሽ ደስ ብሎናል
ሞታችንን ተራምደናል
ተፈስሒ ተፈስሒ ለድንግል ይቤላ

ክንፉ ፀለላ/*3/ 
ተፈስሒ ተፈስሒ ለድንግል ይቤላ
ክንፉ ጋረዳት/*3/ 
ደስ ይበልሽ ድንግል ሆይ እያላት


#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።

╔​✞═══●◉❖◉●═════✞╗
   ❖   @mezmuredawit     ❖
   ❖   @mezmuredawit     ❖
   ❖   @mezmuredawit     ❖  
╚✞═══●◉❖◉●═════​✞╝

✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

✞ ማርያም ጎየይኪ ✞

ማርያም ጎየይኪ እምገጸ ሄሮድስ
ለአርእዮ(፬) ተአምረ ግፍዕኪ(፪)
   
ማርያም ሽሺ ከሄሮድስ ፊት
ለማሳየት(፬) የግፍ ተአምርሽን(፪)
    
           
የደብረ ገሊላ አማኑኤል ካቴድራል
እግዚአብሔር ምስሌነ ሰ/ት/ቤት

#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።

╔​✞═══●◉❖◉●════✞╗
   ❖   @mezmuredawit     ❖
   ❖   @mezmuredawit     ❖
   ❖   @mezmuredawit     ❖  
╚✞═══●◉❖◉●════​✞╝

✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

✞ አቡነ አረጋዊ ✞

አቡነ አረጋዊ
ጻድቁ ባሕታዊ
የወንጌል መምሕር
የሾመኽ እግዚአብሔር/2/

አቡነ አረጋዊ        ዘንዶውን ረግጠኽ
አቡነ አረጋዊ        እንደ አምደ ክርስቶስ
አቡነ አረጋዊ        ወጣኽ ተራራው ላይ
አቡነ አረጋዊ        ሥሙን ለመቀደስ
አቡነ አረጋዊ        ግሩም የአምላክ ሥራ
አቡነ አረጋዊ        እጹብ የእርሱ ነገር
አቡነ አረጋዊ        በአንተ ጽኑ ዕምነት
አቡነ አረጋዊ        በቃን ለመከበር

           /አዝ=====

አቡነ አረጋዊ        ዳሞም መሠከረች
አቡነ አረጋዊ        መምሕር ይኸው ብላ
አቡነ አረጋዊ        ሐይቅም አሞገሰች
አቡነ አረጋዊ        ጸጋን ተቀብላ
አቡነ አረጋዊ        እነ ኢየሱስ ሞዓ
አቡነ አረጋዊ        ከአንተ ሥለ ወጡ
አቡነ አረጋዊ        በኢትዮጵያ ምድር
አቡነ አረጋዊ       ትልቅ ለውጥ አመጡ

           /አዝ=====

አቡነ አረጋዊ        በዕምነት የጸናኽ
አቡነ አረጋዊ        የወንጌል ምሥክር
አቡነ አረጋዊ        የሠራዊት ጌታ
አቡነ አረጋዊ        የቃኘኽ በክብር
አቡነ አረጋዊ        አቡነ አቡነ
አቡነ አረጋዊ        ብዬ ሥጠራኽ
አቡነ አረጋዊ        ቶሎ ድረስል
ቡነ ጋዊ        ርዳኝ በምልጃኽ

#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።

         ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @enamsgn ❖  
❖ @enamsgn @enamsgn ❖   
        ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

🌹✞ አዘክሪ ድንግል አዘክሪ ✞🌹

አዘክሪ ድንግል አዘክሪ
ለልጅሽ አሳስቢ አዘክሪ
ለሐጥዓን አኮ ለጻድቃን /2/


ከአንቺ መወለዱን----------አዘክሪ
በቤተልሔም---------------አዘክሪ
በጨርቅ መጠቅለሉን------አዘክሪ
መኝታው ግርግም----------አዘክሪ
ለሐጥዓን አኮ ለጻድቃን

         /አዝ=====

በዚያ በብርድ ወራት------አዘክሪ
የገበሩለትን----------------አዘክሪ
የአድግ እና የላም----------አዘክሪ
እስትንፋሣቸውን-----------አዘክሪ
ለሐጥዓን አኮ ለጻድቃን

         /አዝ=====

በግብጽ በረሐ---------አዘክሪ
መሰደድሽን------------አዘክሪ
የአሸዋውን ግለት------አዘክሪ
ርሐቡ እና ጥሙን------አዘክሪ
ለሐጥዓን አኮ ለጻድቃን

           /አዝ=====

በመቃብሩ ዘንድ-------አዘክሪ
በዓነባሽው ዕንባ--------አዘክሪ
አሳስቢ ድንግል ሆይ----አዘክሪ
ገነት እንድገባ-----------አዘክሪ
ለሐጥዓን አኮ ለጻድቃን
                
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።

  ╔​✞═══●◉🌹◉●════✞╗
   🌹  @mezmuredawit  🌹
   🌹  @mezmuredawit  🌹
   🌹  @mezmuredawit  🌹  
  ╚✞═══●◉🌹◉●════​✞╝
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

✞ መዓዛ አፈዋት ✞

መዓዛ አፈዋት ማርያም/2/ ጽጌ መንግሥቱ ቡርክ/2/
ጽጌ/2/ ዘሰሎሞን ወዳዊት አብርሃ ወአጽብሐ/2/

ትርጉም:- በጎ መዓዛ ያለሽ ሽቱ /ቅመም/ የተባረክሽ የመንግሥት/የክብር/ አበባ ማርያም የሰሎሞን የዳዊት የአብርሃና የአጽብሃ ክብራቸው ነሽ።

#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።

  ╔​✞═══●◉🌹◉●════✞╗
   🌹  @mezmuredawit  🌹
   🌹  @mezmuredawit  🌹
   🌹  @mezmuredawit  🌹  
  ╚✞═══●◉🌹◉●════​✞╝
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

✞ አርሴማ ቅድስት ወሰማዕት ✞

አርሴማ ቅድስት/2/ ወሰማዕት
ወሰማዕት/5/ አርሴማ ቅድስት ኧኸ/3/

ከምድር ሙሽርነት ይበልጣል የሰማይ
በማለት ወሰነች ሰይፍ ስለቱን ሳታይ
የሰማዕትነቷ ፅኑ መከራዋ
ተቀበለችበት የክብርን ፅዋ

            /አዝ=====

የዚህችን ዓለም ጣዕም ፍፁም ያልበገራት
የንጉስ ግልምጫ ከእግዚአብሔር ያልለያት
አምላኯን መረጠች መክሊቷን አትርፋ
አክሊል ተቀዳጀች ለእምነት ተሰልፋ

            /አዝ=====

የማይታየውን ለመውረስ ተብሎ
በሚታየው ዓለም ይበዛል ተጋድሎ
የሰማዕታት ዋጋ  ይኸው ነው ውጤቱ
በዚህ ምድር ሳይሆን በሰማይ ነው ቤቱ

            /አዝ=====

ውበት ከንቱ ነው ደም ግባት ሀሰት
እንዲህ ብላ ፀናች አርሴማ ቅድስት
ያመነችው ጌታ በሰጣት ቃልኪዳን
ልዩ እናት ሆናለች ትውልዱን በማዳን


#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።

╔​✞═══●◉❖◉●═════✞╗
   ❖   @mezmuredawit     ❖
   ❖   @mezmuredawit     ❖
   ❖   @mezmuredawit     ❖  
╚✞═══●◉❖◉●═════​✞╝

✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

✞ መስቀል ክብሬ ነው ✞

ምልክቴ ነው ከገጽ ማምለጫዬ
መስቀል ክብሬ ነው ከክፉ መውጫዬ

የእባቡ እራስ ሚቀጠቀጥበት
በመስቀል ቤዛነት መርገም ተሻረበት
ሰው በዕፀ መስቀል ከእግዚአብሔር ታረቀ
የምሕረት ቀን ወጣ መከራው ራቀ
   ኦ በመስቀል ጠላት ተቸገረ
   " " " "    ጨለማው ተሻረ
   " " " "    ደሙን አፈሰሰ
   " " " "    ስጋውን ቆረሰ
      
         /አዝ=====

ፊቴን ሰውነቴን በእርሱ አማትባለው
በልቤ አትሜ በአንገቴ አስረዋለው
አይሁድ በሚክዱት እኔ ግን አምኜ
እግሩ ለቆመበት እሰግዳለሁ ድኜ
    ኦ በመስቀል እስረኛ ተፈታ
      " " " "    ከሳሹ ተረታ
      " " " "    ሞትን ገደለልን
      " " " "    በሩን ከፈተልን

         /አዝ=====

የቤዛ ክርስቶስ የክብሩ ዙፋን ነው
በዕምነት የሚያጸና በስሙ ላመነው
የቅድስና የሕይወት ማሕተም
መስቀል ትምክህት ነው እስከ ዘለዓለም
    ኦ በመስቀል ፍቅሩን ገለጸልን
      " " " "    ነብሱን ለኛ ሰጠን
      " " " "    እንባችን ታበሰ
      " " " "    ጸጋ ተለበሰ

         /አዝ=====

ፊቴን ሰውነቴን በእርሱ አማትባለው
በልቤ አትሜ በአንገቴ አስረዋለው
አይሁድ በሚክዱት እኔ ግን አምኜ
እግሩ ለቆመበት እሰግዳለሁ ድኜ
     ኦ በመስቀል እስረኛ ተፈታ
      " " " "    ከሳሹ ተረታ
      " " " "    ሞትን ገደለልን
      " " " "    በሩን ከፈተልን

👉ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ

#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።

╔​✞═══●◉❖◉●══✞╗
   ❖ @mezmuredawit ❖
   ❖ @mezmuredawit ❖
   ❖ @mezmuredawit ❖  
╚✞══●◉❖◉●═══​✞

✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

#መዝሙረ_ዳዊት_150_መዝሙር_እንዳለሁ ሁሉ
#መዝሙረ_ኤፍሬም_ሦርያዊ_በ150_መዝሙር_ቀርቦላችኋል
#በሊቀ_ሊቃውንት_ቀለመወርቅ_ቢራራ_ተተርጉሞ በማይታመን ዋጋ ወደ እናንተ ቀርቦላችኋል።

#መጽሐፉን_በመግዛት_ለእንህ_ሊቅ_ሊቃውንት_አባት_የበኩላችንን_ድርሻ_እንወጣ_ስንል_በእግዚአብሔር_ስም_እንጠይቃለን

#የአንዱ_ዋጋ_300_ብር_ብቻ

#መፅሐፍት_ለምትፈልጉ_እህት_ወንድሞቼ 📬_inbox @Slamanshdngl አናግሩኝ


ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጐድል ምን ይጠቅመዋል።
  ማቴዎስ ወንጌል  ፲፮ ፳፮


#ለበለጠ_መረጃ_በስልክ_ቁጥር  +251942219920 ይደውሉልን

እግዚአብሔር አምላካችን ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን!

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

✞ 🌼 እሰይ እልል በሉ  🌼✞

እሰይ እልል በሉ
ተገኘ መስቀሉ  /2/

የጥል ግድግዳ   አበባ
የፈረሰበት   አበባ
ሰው ከእግዚአብሔር ጋር  አበባ የታረቀበት   አበባ
የእግዚአብሔር ልጅ   አበባን የነገሰበት   አበባ
የሞት አበጋዝ   አበባ
የወደቀበት    አበባ

             /አዝ✞✞✞✞✞

አይሁድ በቅናት   አበባ
መስቀሉን ቀብረው   ጨአበባ
ቢከድኑት እንኳን   አበባ
በቆሻሻቸው    አበባ
ጌታን መቃወም    አበባ
ስለማይችሉ    አበባ
ይኸው ተገኘ    አበባ
ወጣ መስቀሉ    አበባ

             /አዝ✞✞✞✞✞

ደጉ ኪራኮስ    አበባ
ሽማግሌው   አበባ
እሌኒን መራ    አበባ 
በደመራው  አበባ
ጌታ በሱ ላይ   አበባ
በመሰቀሉ    አበባ
ጢሱ ሰገደ   አበባ 
ወደ መስቀሉ አበባ

              /አዝ✞✞✞✞✞

የእምነት ምልክት አበባ
መስቀል ነውና  አበባ
ተራራው ሜዳ አበባ
ሆነ እንደገና አበባ
እንደ ተነሳው አበባ
ጌታ እንደቃሉ   አበባ
ከጉድጓድ ወጣ አበባ
እፀ መስቀሉ  አበባ

               /አዝ✞✞✞✞✞

እኛም በመስቀል   አበባ
እንመካለን   አበባ
በእግዚአብሔር ጥበብ   አበባ መቼ እናፍራለን አበባ
ሞኝነት እንኳን  አበባ
ቢሆን ለዓለም  አበባ
ኃይል እፀ ወይን ነው አበባ ለዘላለም አበባ

               /አዝ✞✞✞✞✞

ግድግዳው ፈርሷል አበባ
የልዩነቱ   አበባ
ምድርና ሰማይ  አበባ
ሆኑ እንደ ጥንቱ  አበባ
ነብስና ስጋ   አበባ
በሱ ታርቀዋል  አበባ
ሕዝብና አሕዛብ አበባ
ወንድም ሆነዋል አበባ
       

╔​✞═══●◉🌼◉●═══✞╗
✞   @mezmuredawit   ✞
✞   @mezmuredawit   ✞
✞   @mezmuredawit   ✞  
╚✞═══●◉🌼◉●═══​✞╝

✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

✞ የመረረ ዕንባ ✞

የመረረ እንባ ከአይንሽ የፈሰሰ
ችግርና ስቃይ በአንቺ የደረሰ
ሊናገሩት ቀርቶ ሲያስቡት ይከፋል
ድንግል ሆይ መከራሽ እጅግ ያሳዝናል

በበረሃ በሀሩር በአሸዋ ስታልፊ
ከጨካኙ ሄሮድስ ልጅሽን ልታተርፊ
አየንሽ እመአምላክ በግብፅ ተሰደሽ
የዓለሙን መድህን በጀርባሽ አዝለሽ
     ነይ ሙሽራችን ተመለሽ አሁን
     ከገሊላ ግቢ እመብርሀን/2×/

        /አዝ=====

ለፍጥረቱ ሁሉ ውሀን የፈጠረ
ለአዳም ቃል ገብቶ ተጠምቶ ነበረ
የቅዱሳን ስደት እንዲባረክ በእሱ
ተሰደደ በግብፅ እየሱስ ቅዱሱ
     ነይ ሙሽራችን ተመለሽ አሁን
     ከገሊላ ግቢ እመብርሀን/2×/

        /አዝ=====

ድንግል ወላዲቱ የስኑዳን ተስፋ
አሳስቢ ከልጅሽ ፍጥረቱ እንዳይጠፋ
በመሪሩ እንባሽ በዝቶ በፈሰሰው
አማልጂን ድንግል ሆይ ለኛ ለደከምነው
     ነይ ሙሽራችን ተመለሽ አሁን
     ከገሊላ ግቢ እመብርሀን/2×/

👉በምዕራፈ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።

╔​✞═══●◉❖◉●═════✞╗
   ❖   @mezmuredawit     ❖
   ❖   @mezmuredawit     ❖
   ❖   @mezmuredawit     ❖  
╚✞═══●◉❖◉●═════​✞╝

✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

✞ ኦርቶዶክስ_ተዋሕዶ_ሀገር_ናት ✞

በውሀ ግድግዳ በደም መሰረት
ለክብሩ የመረጣት በስሙ የጠራት
ቤተክርስቲያን ተዋህዶ ናት

አትፈርስም ጉልላቷ እርሱ ነው
የቀደሳት የሰራት ደሙ ነው
ብትፈተን በእሳት በመከራ
ትኖራለች ሁሉንም ተሻግራ
     ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀገር ናት
     የሰጠች ክብር ነፃነት /2/

         /አዝ=====

የማጠ በእሳት የተራች
ከምድር ሆና ሰማይ የደረሰች
የእግዚአብሔር የፀጋው ግምጃ ቤት
ተዋህዶ ስንዱዋ እመቤት
     ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀገር ናት /2/
     የሰጠች ክብር ነፃነት /2/

         /አዝ=====

የፅድቅ ቤት የድህነት መርከብ
መጠሪያ ነች ለሀገር እና ሕዝብ
ሕይወት ያላት እውነት የምትገልጥ
የማታረጅ የማትለወጥ
     ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀገር ናት /2/
     የሰጠች ክብር ነፃነት /2/

         /አዝ=====

ተዋህዶ ያለች በቅድምና
ለኢትዮጵያ ሞገሷ ናት እና
ያለ እርሷ ትዮጵያ አትኖ
መለያየት ከቶ አይቻልም
     ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀገር ናት /2/
     የሰጠች ክብር ነፃነት /2/

👉ዘማሪት ሰብለወንጌል እሸቴ

#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።

╔​✞═══●◉❖◉●═════✞╗
   ❖   @mezmuredawit     ❖
   ❖   @mezmuredawit     ❖
   ❖   @mezmuredawit     ❖  
╚✞═══●◉❖◉●═════​✞╝

✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

✞ ተፈፀመ_ማኅሌተ_ጽጌ ✞

ንግሥተ ሰማያት ወምድር ማርያም ድንግል
ተፈፀመ (፭)ማኅሌተ ጽጌ

#ትርጉም
የሰማይና የምድር ንግሥት ድንግል ማርያም
ማኅሌተ ጽጌ ተፈፀመ

#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።

  ╔​✞═══●◉🌹◉●════✞╗
   🌹  @mezmuredawit  🌹
   🌹  @mezmuredawit  🌹
   🌹  @mezmuredawit  🌹  
  ╚✞═══●◉🌹◉●════​✞╝
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

​​✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡፡ አሜን✞✞✞

#ቅዱስ_ማርቆስ_ዘአንበሳ

✞✞✞ በዚሕች ዕለት ከ72ቱ አርድእት አንዱ የሆነ: ወንጌላዊ: ሐዋርያ: ሰማዕት: ዘአንበሳና ርዕሰ ሊቃነ ዻዻሳት የተባለ ቅዱስ ማርቆስ ተወልዷል ::

ቅዱስ ማርቆስ እናቱ ማርያም: አባቱ አርስጥቦሎስ ይባላሉ:: በልጅነቱ ኦሪትንና የዘመኑን ጥበብ ሥጋዊ በሚገባ ተምሮ ክርስቶስን ከቤተሰቦቹ ጋር ተከትሏል:: የመጀመሪያ ስሙ ዮሐንስ ሲሆን ከ120ው ቤተሰብ በእድሜ በጣም ትንሹ /20 ዓመት/ እርሱ ነበር::

ለ3 ዓመታት ከጌታ እግር ሥር ተምሮ: በበዓለ ሃምሳ ጸጋ መንፈስ ቅዱስን ተቀብሎ ለሐዋርያዊ አገልግሎት ብዙ ደክሟል:: በተለይ የግብፅና የኢትዮዽያ ቤተ ክርስቲያን አባት ነው:: ክህነትን ያገኘን ከርሱ ነውና::

ቅዱስ ማርቆስ 16 ምዕራፍ ያለውን ወንጌሉን ሲጽፍ ኪሩብ ገጸ አንበሳ በቀኙ: ሊቀ ሐዋርያት በግራው ሆነው ይራዱት ነበር:: ቅዱሱ ክቅዱስ ዻውሎስ: ከበርናባስና ዼጥሮስ ጋር ተጉዟል:: ከብዙ ስቃይና መከራ በኋላ ሰሜን አፍሪካ አካባቢ አረማውያን ገድለውታል:: ይህቺ ዕለት የልደቱ መታሠቢያ ናት::

ዳግመኛ በዚህ ቀን የቅዱስ ማርቆስን ወላጆችን እናስባቸው ዘንድ ይገባል:: ቅዱስ አርስጥቦሎስ (አባቱ) የጌታ ቅን አገልጋይ የነበረ: ቅድስት ማርያም (እናቱ) ከ36ቱ ቅዱሳት አንስት አንዷ: ጌታችንን ያገለገለች ቤቷን ለሐዋርያትና ለጌታ በስጦታ ያበረከተች ቅድስት ናት::

ቤቷም (ጽርሐ ጽዮን) የመጀመሪያዋ ቤተ ክርስቲያን ስትሆን ይህች ቤት መንፈስ ቅዱስ ወርዶባታል:: የእመቤታችን ግንዘትም ተከናውኖባታል::

እግዚአብሔር ከሐዋርያዊው ቅዱስ ቤተሰብ በረከትን ያድለን::

#ቅዱስ_ዮሐንስ_መጥምቅ

ቅዱስ ወንጌል ላይ ከእመቤታችን ቀጥሎ የነዘካርያስን ቤተሰብ ያህል ክብሩ የተገለጠለት ፍጡር ይኖራል ብሎ መናገሩ ይከብዳል:: ቅዱስ ሉቃስ ወንጌሉን የጀመረው በዚህ ቅዱስ ቤተሰብ ነውና መንፈስ ቅዱስ እንዲህ ሲል አጽፎታል:: "ዘካርያስ ካህኑና ቅድስት ኤልሳቤጥ በሰውና በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ የሚኖሩ ጻድቃን ነበሩ" ይላቸዋል:: (ሉቃ. 1:6)

የሰውን እንተወውና በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ መኖር ምን ይረቅ? ለዚህ አንክሮ (አድናቆት) ይገባል!
እሊህ ቅዱሳን ባልና ሚስት ግን መካኖች በመሆናቸው ልጅ ሳይወልዱ ዘመናቸው አልፎ ነበር:: እንደ ቤተ ክርስቲያን ትውፊት ዕድሜአቸው የኤልሳቤጥ 90 የዘካርያስ 100 ደግሞ ደርሶ ነበር::

ፍጹም መታገሳቸውን የተመለከተ ጌታ ግን በስተ እርጅናቸው ከሰው ሁሉ በላይ የሆነ: ትንቢት ለብቻው የተነገረለት (ኢሳ. 40:3, ሚል. 3:1) ታላቅ ነቢይን ይሰጣቸው ዘንድ መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤልን ላከላቸው::

ቅዱስ ዘካርያስ ሰው ነውና ከደስታ ብዛት በመከራከሩ ድዳ ሆነ:: ቅድስቲቷ ግን መስከረም 26 ቀን ታላቁን ሰው ጸንሳ ለ6 ወራት ራሷን ሠወረች:: በ6ኛው ወር የፍጥረት ሁሉ ጌታ በተጸነሰ ጊዜ የአርያም ንግሥት ድንግል እመቤታችን ደጋ ደጋውን ወደ ኤልሳቤጥ መጣች:: ሁለቱ ቅዱሳት የእህትማማች ልጆች ናቸው::

የአምላክ እናቱ ስትደርስና "ሰላም" ስትላቸው መንፈስ ቅዱስ በእናትና ልጅ ወርዶ ኤልሳቤጥ በምስጋና: ዮሐንስ ደግሞ ገና በማሕጸን ሳለ በደስታ ዘለለ (ሰገደ):: ከዚህ በኋላ በዚህች ቀን (ሰኔ 30) ተወልዶ: አባቱ ዘካርያስ "ዮሐንስ" ሲለው አንደበቱ ተፈትቶለታል::

ቅዱስ ዮሐንስ ከተወለደ 2 ዓመት ከ6 ወር በሆነው ጊዜ ሰብአ ሰገል በመምጣታቸው በእሥራኤል ምድር የሚገኙ ሕጻናትን ሔሮድስ ቁዝ አስፈጀ:: ትንሽ ቆይቶም አይሁድ ለሔሮድስ ስለ ቅዱሱ ሕጻን ነገሩት:: "ሲጸነስ የአባቱን አንደበት የዘጋ: ሲወለድ ደግሞ የከፈተ 'ዮሐንስ' የሚባል ሕጻን አለና እሱንም ግደል" አሉ::

እናቱ ቅድስት ኤልሳቤጥ ይዛው ስትሸሽ ካህኑን ዘካርያስን ግን በቤተ መቅደስ መካከል ገድለውታል:: አረጋይት ኤልሳቤጥም ሕጻኑን እያሳደገች በገዳመ ዚፋታ ለ3 (5) ዓመታት ቆይታለች:: ቅዱስ ዮሐንስ 5 (7) ዓመት ሲሞላው ግን እዚያው በበርሃ እናቱ ዐረፈች:: ከሰማይ ዘካርያስና ስምዖን ወርደው ቀበሯት::

ሕጻኑ ዮሐንስ ሲያለቅስ ድንግል ማርያም ስንት አገር አልፋ ሰማችው:: እርሷም ስደት ላይ ነበረችና:: ከጌታ ጋር በደመና ሒደው ድንግል አቅፋ አጽናናችው:: ጌታንም "እንውሰደው ይሆን?" አለችው:: ጌታችን ግን "ለአገልግሎት እስክጠራው እዚህ ይቆይ" አላት:: ባርካው: አጽናንታውም ተለያዩ::

ቅዱስ ዮሐንስ ከዚህ በኋላ በዚያ ቆላ የግመል ጠጉር ለብሶ: ጠፍር ታጥቆ ተባሕትዎውን ቀጠለ:: ለ25 (23) ዓመታትም በንጽሕና ሲኖር ከምድር አራዊትና ከሰማይ መላእክት በቀር ማንንም አላየም:: ይሕችን ዐመጸኛ ዓለምም አልቀመሳትም::

ከዚህ በኋላ 30 ዘመን ሲሞላው እግዚአብሔር ከሰማይ ተናገረው:: "ሒድ! የልጀን ጐዳና ጥረግ" አለው:: ነቢያት ስለዚህ ነገር ተናግረው ነበርና:: (ኢሳ. 40:3, ሚል. 3:1) አባቱ ዘካርያስም "ወአንተኒ ሕጻን ነቢየ ልዑል ትሰመይ: እስመ ተሐውር ቅድመ እግዚአብሔር ከመ ትጺሕ ፍኖቶ" (ሉቃ. 1:76) ብሎ መንገድ ጠራጊነቱን ተናግሮ ነበርና::

ቅዱስ ዮሐንስ በዚያ ጊዜ በኃይለ መንፈስ ቅዱስ እየገሰገሰ ከበርሃ ወደ ይሁዳ መጣ:: ያዩት ሁሉ ፈሩት: አከበሩት:: ቁመቱ ቀጥ ያለ: ጽሕሙ እንደ ተፈተለ ሐር የወረደ: ጸጉሩ የቁራ ያህል የጠቆረ: መልኩ የተሟላ: ግርማው የሚያስፈራ ገዳማዊ ነውና::

ፈጥኖም ሕዝቡን ለንስሃ ሰበከ: ለንስሃም በርካቶችን አጠመቃቸው:: በዚህ አገልግሎት ለ6 ወራት ቆይቶ ጌታችን ወደ እርሱ ዘንድ መጣ:: ዮሐንስ ሰማይን ከነግሱ: ምድርን ከነልብሱ የያዘ ፈጣሪ 'አጥምቀኝ' ብሎ ሲመጣ ደነገጠ:: የሚገባበትም ጠፋው::

"እንቢ ጌታየ! አንተ አጥምቀኝ" አለው:: ጌታ ግን "ፈቅጄልሃለሁ" አለው: አጠመቀው:: በዚህ ምክንያት ይሔው እስከ ዛሬም "መጥምቀ መለኮት" ሲባል ይኖራል:: ቅዱስ ዮሐንስ በመጨረሻ ሔሮድስን ገሰጸው:: ንጉሡም ተቀይሞ ለ7 ቀናት አሠረው::

በዚህች ቀንም ልደቱን ባከበረ ጊዜ ወለተ ሔሮድያዳ በዘፈን አጥምዳ አስማለችው:: እርሱም የታላቁን ነቢይ ራስ አስቆርጦ በወጪት አድርጐ ሰጣት:: አበው "እምሔሶ ለሔሮድስ ይብላዕ መሐላሁ - ሔሮድስ መሐላውን በበላ በተሻለው ነበር" ይላሉ:: የቅዱስ ዮሐንስ ራሱ በርራ ስትሔድ አካሉን ግን ደቀ መዛሙርቱ ቀብረውታል:: (ማቴ. 3:1, ማር. 6:14, ሉቃ. 3:1, ዮሐ. 1:6)

ርጉም ሔሮድስ አንገቱን ካስቆረጠው በኋላ የመጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ ራሱ የጸጋ ክንፍ ተሰጥቷት ጌታችን ወዳለበት ደብረ ዘይት ሔዳ በፊቱ ሰገደች:: ቅዱሳን ሐዋርያት በአዩት ነገር ተገርመው ራሱን እጅ ነሷት::

ከዚሕ በኋላ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቅዱስ ዮሐንስ ራስ የማስተማር ስልጣን ሰጥቶ አሰናበታት:: በመላው ዓለም ለ15 ዓመታት ስትሰብክ ኑራ ዓረቢያ ውስጥ ዓርፋለች::

👉 ይህች ዕለት ለቅዱሱ 'አስተርዕዮተ ርዕሱ' ወይም ቅድስት ራሱ ከተወረችበት የተገለጠችበት ነው::

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

✞ አዝላው ወረደች ✞

አዝላው ወረደች ወደ ግብፅ(፪)
ስደተኛዋ የአምላክ እናት
ይህ ዓለም ለእርሷ መች ተገባት

ዓለም በምኗ ታስተናግዳት
የፍቅር ምንጯ ተሟጦባት
እነ ኮቲባን እየላከች
የአምላክን እናት ተሳደበች
እነ ሄሮድስን እየላከች
ህፃኑን ልትገድል አሳደደች
       
       አዝ=====

የክብርን ጌታ ተሸክማ
ውርደት ለበሰች እንደ ሸማ
የሀብቱን ጌታ በጀርባ አዝላ
ሰው ተዘከራት ተቸግራ
      
       አዝ=====

በቃሉ ትዕዛዝ ምድርን ሠርቶ
ተንከራተተ ማደሪያ እጥቶ
ጌታ ሲወለድ የምሥራች
በረት ሰጠችው ዓለም ታካች
      
       አዝ=====

ግና መላእክት በሰማያት
ሃሌ ሉያ አሉ በፍርሃት
ወልድን በአብ ቀኝ ከላይ አይተው
ደግሞም በምድር ከድንግል ክንድ
ከላይም ሳይጎድል ተመልክተው{፪}
      
       አዝ=====

ዓለም በምኗ ታስተናግዳት
የፍቅር ምንጯ ተሟጦባት
እነ ኮቲባን እየላከች
የአምላክን እናት ተሳደበች
እነ ሄሮድስን እየላከች

       አዝ=====

ህፃኑን ልትገድል አሳደደች
በቃሉ ትዕዛዝ ምድርን ሠርቶ
ተንከራተተ ማደሪያ እጥቶ
ጌታ ሲወለድ የምሥራች
በረት ሰጠችው ዓለም ታካች

         
 👉ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ

#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።

╔​✞═══●◉❖◉●═════✞╗
   ❖   @mezmuredawit     ❖
   ❖   @mezmuredawit     ❖
   ❖   @mezmuredawit     ❖  
╚✞═══●◉❖◉●═════​✞╝

✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

✞ ተክለ ስላሴ ነህ ✞

ተክለ ስላሴ ነህ ጸድቀህ ያፈራህ
በታላቅ ተጋድሎህ ሃገር ያቀናህ
ትውልድ ይህን አውቆ ስምህን ይጠራል
        ተክለሃይማኖ  /2/
ተክለሃይማኖት ብሎ ዝክርህን ይዘክራል

አባ ሰላማ ሆይ ሰላምህን ስጠን
ጠብን እየጫረ ጠላት አይለያየን
እግዚአብሔር ተክሎሃል ፍሬ እንድታፈራ
ዛሬም አለምልመን በወንጌል አዝመራ /2/

           /አዝ=====

ፃድቃን የበዙለት ህዝብ ደስ ይለዋል
ሰላምና ፍቅር ተስፋ ይታየዋል
ሲሰለጥኑ ግን እኩያን ኃጥአን
ወገን ተቸግሮ ያጣል መጠለያን /2/

           /አዝ=====

ከስርሽ ተነቅለሽ ነይ በላት ዛፏን
ሰይጣን እያደረ ያሳተባትን
በአምልኮተ ጣኦት ህዝብህ ጠፍቷልና
በወንጌል ፈልገው በሀይማኖት ፋና /2/

           /አዝ=====

ባርከህ እንደቀየርከው ገብረ ዋኅድን
እኛንም ለውጠህ ጳውሎስ አድርገን
ሳውልነት ይብቃን ልጅህ እንሁን
በምግባር ትሩፋት አንተን እንምሰል /2/

#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።

╔​✞═══●◉❖◉●═════✞╗
   ❖   @mezmuredawit     ❖
   ❖   @mezmuredawit     ❖
   ❖   @mezmuredawit     ❖  
╚✞═══●◉❖◉●═════​✞╝

✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

✞ አባ ጽጌ ድንግል ✞

አባ ጽጌ ድንግል ፍቅርሽ አገብሮት
ምስጋናን አበዛ በስደትሽ ሰዓት
በተመስጦ ሆኖ ለአንቺ እየዘመረ
ምድርን ለቆ ሄደ ከፍ ከፍ እያለ

ይወድሻል ከልቡናው
አቤት ሲያዜም ስንሰማው
ማህሌትሽ ሲወረብ
ትመጫለሽ ከመ ርግብ
    
      /አዝ====

ስዕልሽን ታቅፈውት
በማዕጠንት ውስጥ ሲያዩት
ትታያለሽ እመ ብርሀን
ስትባርኪን በብርሃን
    
      /አዝ====

ካህናቱ ነጭ ለብሰው
ፅጌረዳ ሁሉም ይዘው
ሲወረቡ በሽብሸባ
አቤት ሲያምር ልቤ ገባ

      /አዝ====

የብርሃንሽ ፀዳል በዝቶ
በምስጋናሽ ሁሉ ፈክቶ
ሌሊቱ አጥሮ ነጋብን
ማርያም እያልን ስላደርን

👉 መልአከ ሰላም ቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ

#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።

    ╔​✞═══●◉❖◉●════✞╗
   ❖   @mezmuredawit     ❖
   ❖   @mezmuredawit     ❖
   ❖   @mezmuredawit     ❖  
    ╚✞═══●◉❖◉●════​✞╝

✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

✞ እንወድሻለን ኪዳነምሕረት ✞

ለእግዚአብሔር ታቦቱ መቅደሱ
ቀርበናል ባንቺ ወደ ንጉሡ
የክብራችን ጌጥ ሽልማት
እንወድሻለን ኪዳነምሕረት

በጨለማው ላለ ብርሀንን አየ
ለእርስቱ ተካፋይ እንዲሆን ተለየ
ወደ ቀድሞ ክብሩ ሊመለስ ዳግመኛ
አንቺ ነበርሽ ተስፋው ለአዳም መዳኛ

             /አዝ=====

ያን ሁሉ ዘመናት የፈሰሰው ደም
ዓለምን ከእስራት ሊፈታ አልቻለም
ወደ ሚሻል ኪዳን በደም ሊያሻግረን
ደምሽን ተዋህዶ መድኃኔዓለም ዋጀን

             /
አዝ=====

አለን ብዙ ምክንያት አንቺን ምንወድበት
ዓለም ያልተረዳው ያለወቀው እውነት
ያወቀ የተረዳ የመድኃኑን ምስጢር
አያፍርም ክብርሽን ቆሞ ለመናገር

             /አዝ=====

አውቃለው እግዚአብሔር የሰጠሽን ክብር
ላመስግንሽ እኔም ሳልቀንስ ሳልጨምር
ሚባርክሽ ቡሩክ ነው እና እናቴ
ኪዳነምሕረት ንገሽ እመቤቴ

👉
በዘማሪ ዲ/ን አቤል መክብብ

#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።

╔​✞═══●◉❖◉●═════✞╗
   ❖   @mezmuredawit     ❖
   ❖   @mezmuredawit     ❖
   ❖   @mezmuredawit     ❖  
╚✞═══●◉❖◉●═════​✞╝

✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

✞ ለኔ ያደረገው ሚካኤል ብዙ ነው ✞

ለኔ ያደረገው ሚካኤል ብዙ ነው (2)
ከእግዚአብሔር ተልኮ ድንቅ  አደረገልኝ
አፅናኝና እረዳት ሚካኤል ሆነልኝ

ታናሽ ብላቴና ስምክን የማይረሳ
ደግፈኝ ሚካኤል ስወድቅ እንድነሳ
ስምህን በልቤ ፅላት እፅፋለሁ
በክንፎችህ ጥላ ዛሬም ድረስ እላለሁ

          /አዝ=====

ውለታህ እንዳይጠፉ ሁሌም ከሀሳቤ
ሚካኤል ሳልልህ ፍቅርህን ከልቤ
አንተነህ የዋህ መልአክት የእርግብ አምሳል
የብርሃን አክሊል ነህ ሚካኤል ኃያል

          /አዝ=====

ለኔ ያለህን ፍቅር በዓይኔ አይቻለሁ
ውለታህን ሳስብ እጅግ አደንቃለሁ
በነፍስም በስጋም መታመኛዬ
የምትጥብቀኝ መከታ ጋሻዬ

          /አዝ=====

ስወጣ ስገባ ከሌሎች እንቅፋት
ሚካኤል ጠብቀኝ ከሚገጥመኝ ጥፋት
ደግ ነው ሚካኤል ፍቅሩ በዝቶልኛል
በዘመኔ ሁሉ እሱ ይረዳኛል

👉ሊቀ ልሳናት ዘማሪ ቸርነት ሰናይ

#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።

╔​✞═══●◉❖◉●═════✞╗
   ❖   @mezmuredawit     ❖
   ❖   @mezmuredawit     ❖
   ❖   @mezmuredawit     ❖  
╚✞═══●◉❖◉●═════​✞╝

✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

✞ ንዑድ ክቡር ✞

ንዑድ ክቡር የእግዚአብሔር ሰው ቅዱስ
ርዕሰ ባህታውያን ገብረ መንፈስ ቅዱስ
የገዳም መብራት ለቤተክርስቲያን ማህቶት
የተጋደልክ በጾም ወጸሎት በቀንና በሌሊት

በስራና በቃል ቅዱሳን መላእክት ሐዋርያትን መስለህ
አናብርቱ አናብስት መባርቅት ወነፋሳት የሚታዘዙልህ
    የአቅሌሲያ ፍሬ የስምዖን በረከት
    አስራት ሀገርህን ኢትዮጵያን ታደጋት በአማላጅነት

          /አዝ=====

የፈታኙን ውጊያ ፍላፃና ፆር መርዙን አጥፍተህ
ዓይንህን ቢነቁረው በትህትና ሆነህ ድል ተቀናኘህ
    በአንድነት ሶስትነት ስላሴን ያየ ሰው
    ፀጋ እንደ ሱራፌል እፁብ ገናና ነው

          /አዝ=====

ኢትዮጵያን አስምራት በአፀደ ነፍስ ሆነህ ዛሬም ለምንላት
ህዝቦቿን ከጥፋት ምድሪቱን ከቅጣት እባክህ አስምራት
   ዝቋላ እንዳየነው ከባህር ውስጥ ጠልቀህ
   በምድረከብድ ሰማይ ከፀሀይ ከፍ ብለህ እንደ ለመንክ


👉ዘማሪት ወይንሸት አለሙ

#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።

╔​✞═══●◉❖◉●═════✞╗
   ❖   @mezmuredawit     ❖
   ❖   @mezmuredawit     ❖
   ❖   @mezmuredawit     ❖  
╚✞═══●◉❖◉●═════​✞╝

✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

✞ አክሊለ ጽጌ

አክሊለ ጽጌ ማርያም ቀፀላ መንግሥቱ ለጊዮርጊስ/፪/
ክበበ ጌላ ወርቅ/፪/ አክሊለ ጽጌ

ትርጉም:- በአበባ የተሸለመ አክሊልን የወርቅ ዘውድንም የምታቀዳጂ ማርያም ሆይ የጊዮርጊስ የመንግሥቱ አክሊል/የነገሠብሽ አክሊል/ ነሽ

#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።

╔​✞═══●◉🌹◉●════✞╗
   🌹  @mezmuredawit  🌹
   🌹  @mezmuredawit  🌹
   🌹  @mezmuredawit  🌹  
╚✞═══●◉🌹◉●════​✞╝
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

ብፁዕ አቡነ ሰላማ ከዚህ ዓለም ድካም አረፉ።

ጸሎተኛው ፣ ደጉ ፣ ርህሩሁና ታጋሹ አረጋዊው አባት ብፁዕ አቡነ ሰላማ ዛሬ መስከረም ፲፰ቀን ፳፻ ፲ወ፮ዓ.ም ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል።ብፁዕ አባታችን ባደረባቸው ህመም ምክንያት በአዲስ አበባ ሃሌሉያ ሆስፒታል በህክምና ላይ እንዳሉ ነው ከዚህ ዓለም ድካም ያረፉት።የብፁዕነታቸውን ሽኝት መርሐ ግብር በተመለከተ በቋሚ ሲኖዶስ እንደተወሰነ ዝርዝሩን  የምናሳውቅ ይሆናል።

  የብፁዕነታቸው በረከት ይደርብን አሜን!!!

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

✞ ድል በቀራንዮ ✞

ድል በቀራንዮ ድል ጎልጎታ
በክርስቶስ መስቀል ጠላት ድል ተመታ (2)
ቤዛነ(2)    መስቀል ቤዛነ መስቀል
ለዕለ አመነ መስቀል ቤዛነ መስቀል
ጠላትን ድል መንሻ  መስቀል ቤዛነ መስቀል
ረስትን መውረሻ  መስቀል ቤዛነ መስቀል
ሞትን ማሸነፊያ  መስቀል ቤዛነ መስቀል
መከራን  ማለፍያ   መስቀል ቤዛነ መስቀል
ሰላምን   ማወጃ   መስቀል ቤዛነ መስቀል
የህይወት ማስረጃ   መስቀል ቤዛነ መስቀል

ቤዛነ (2)   መስቀል ቤዛነ መስቀል
ለዕለ አመነ  መስቀል  ቤዛነ መስቀል
ውበት ድመቀታችን መስቀል ቤዛነ መስቀል
ሀይል ትምክታችን መስቀል ቤዛነ መስቀል
ነገን መመልከቻ  መስቀል ቤዛነ መስቀል
አሳዳጁን መርቻ  መስቀል ቤዛነ መስቀል
የአለም መዳኛ  መስቀል ቤዛነ መስቀል
የሰላም መገኛ  መስቀል ቤዛነ መስቀል

ቤዛነ  (2)  መስቀል ቤዛነ መስቀል
ለዕለ አመነ  መስቀል ቤዛነ መስቀል
የድላይን አርማ  መስቀል ቤዛነ መስቀል
የነፍሳችን ግርማ መስቀል ቤዛነ መስቀል
በደም አሸብርቆ  መስቀል ቤዛነ መስቀል
በብርሃን ደምቆ  መስቀል  ቤዛነ መስቀል
ታየ በምድር ሁሉ መስቀል ቤዛነ መስቀል
ሳነጥፍ ፀዳሉ  መስቀል ቤዛነ መስቀል
 
ቤዛነ (2)  መስቀል ቤዛነ መስቀል
ለዕለ አመነ መስቀል ቤዛነ መስቀል
የፍቅር መግለጫ  መስቀል ቤዛነ መስቀል
የስቃይ መቋጫ  መስቀል ቤዛነ መስቀል
ለኛ ውበታችን  መስቀል ቤዛነ መስቀል
ሞት ለጠላታችን መስቀል ቤዛነ መስቀል
የመዳን ምልክት መስቀል ቤዛነ መስቀል
የአዳም ትምክህት  መስቀል ቤዛነ መስቀል


#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።

     ╔​✞══●◉❖◉●═✞╗
   ❖ @mezmuredawit  ❖
   ❖ @mezmuredawit  ❖
   ❖ @mezmuredawit  ❖  
     ╚✞══●◉❖◉●══​✞╝

✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

✞ 🌼 መስቀል አበባ  🌼 ✞

መስቀል አበባ     ነህ ውብ አበባ
አደይ አበባ ነሽ    ውብ አበባ/2/
      
መስቀል አበባ   ተቀብሮ ሲኖር
አደይ አበባ       ስነ ሥቅለቱ
መስቀል አበባ   ዕሌኒ አገኘች
አደይ አበባ       ደገኛይቱ

        /አዝ✞✞✞✞✞

መስቀል አበባ   ጥራጊ ሞልተው
አደይ አበባ       አይሁድ በክፋት
መስቀል አበባ   ጢሱ ሰገደ
አደይ አበባ       መስቀል ካለበት

         /አዝ✞✞✞✞✞

መስቀል አበባ   ወንዙ ጅረቱ
አደይ አበባ       ሸለቆው ዱሩ
መስቀል አበባ   አሸብርቀው ደምቀው
አደይ አበባ       ለአንተ መሰከሩ

  
╔​✞═══●◉🌼◉●═══✞╗
✞   @mezmuredawit   ✞
✞   @mezmuredawit   ✞
✞   @mezmuredawit   ✞  
╚✞═══●◉🌼◉●═══​✞╝

✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

✞ 🌼  ደስ ይበለን እልል በሉ 🌼 ✞

ደስ ይበለን እልል በሉ /2/
አልቀረም ተቀብሮ ተገኘ መስቀሉ /2/
በብርሃን መላት ዓለሙን በሙሉ /2/


ምን ቢተባበሩ ምንቀኞች ቢጥሩ /2/
ቅዱስ መስቀሉንም ሸሽገው ቢሰውሩ /2/
አልቻሉም ሊያጠፉት ምን ቢተባበሩ /2/

               /አዝ✞✞✞✞✞

በተራራ ተሰውሮ ለዘመናት /2/
ተጥሎ በተንኰል ተደብቆ ከኖረበት /2/
ተገለጠ እነሆ በደመራ እሳት /2/

               /አዝ✞✞✞✞✞

እሌኒ ናት ይህን ምስጢር ያስገኘችው /2/
ደመራን በጥበብ በቦታው ያስቆመችው /2/
የተነኰልን ተራራ ያስቆፈረችው /2/

               /አዝ✞✞✞✞✞

ታሪካዊ የክርስቶስ ሕያው መስቀል /2/
ይኸው ተገለጠ በክብር በግሩም ኃይል/2/
ምንጊዜም ሲያበራ እንዲህ ይኖራል /2/
   
    

╔​✞═══●◉🌼◉●═══✞╗
✞   @mezmuredawit   ✞
✞   @mezmuredawit   ✞
✞   @mezmuredawit   ✞  
╚✞═══●◉🌼◉●═══​✞╝

✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ

Читать полностью…
Subscribe to a channel