የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ የመዝሙር ግጥሞችን እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን" መዝ 150÷6 " አሕዛብ ሁላችሁ፥ እጆቻችሁን አጨብጭቡ፥ በደስታ ቃልም ለእግዚአብሔር እልል በሉ።" (መዝሙረ ዳዊት 47:1) ለማንኛውም ሀሣብ, ጥቆማ, አስተያየት @Kidusyared_comment_bot ላይ ቢያስቀምጡልን ይደርሰናል
መስቀል ተመርኲዘን
መስቀል ተመርኲዘን ወንጌል ተጫምተን
ሃይማኖትን ሰብከን በክርስቶስ አምነን
ማን ያሸንፈናል እኛ ክርስቲያንን
ክርስቶስ አለልን
ንግሥቲቷ ዕሌኒ በጣም የታደለች
በዕጣን ጢስ ተመርታ መስቀሉን አገኘች
መድኃኒት ስትፈልግ ኪራኮስን ይዛ
መስቀሉን አገኘች የዓለሙን ቤዛ
ንዑ ንወድሶ ለዕፀ መስቀል
የተሸከመውን የአምላክን ቃል
ንዑ ንወድሳ ለማርያም ድንግል
አክሊለ ምእመናን ምክሐ ደናግል
ሙታን ተነሥተው ያመሰገኑት
ዕፀ መስቀሉ ነው የእኛ መድኃኒት
መስቀል ምርኲዛችን ጎዳና ወንጌል
ወደ ገነት እንጂ አንሄድም ሲኦል
╔✞═══●◉🌼◉●═══✞╗
✞ @mezmuredawit ✞
✞ @mezmuredawit ✞
✞ @mezmuredawit ✞
╚✞═══●◉🌼◉●═══✞╝
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
አለው ሞገስ
አለው (2) ሞገስ ኧኸ አለው ሞገስ
የመስቀል በዓል ሲደርስ ኧኸ አለው ሞገስ
አለው (2) አበባ ኧኸ አለው አበባ
የመስቀል በዓል ሲገባ ኧኸ አለው አበባ
አለው (2) ደስታ ኧኸ አለው ደስታ
መስቀል ሲከብር በዕልልታ ኧኸ አለው ደስታ
አለው (2) ሰላም ኧኸ አለው ሰላም
መስቀል ሲታይ በዓለም ኧኸ አለው ሰላም
አለን (2) አለኝታ ዕፀ መስቀል መከታ
እዩት (2) ሲያበራ የመስቀል በዓል ደመራ
እዩት (2) ሲያምር መስቀል በዓለም ሲከበር
አለን (2) እምነት ተዋሕዶ ንጽሕት
╔✞═══●◉🌼◉●═══✞╗
✞ @mezmuredawit ✞
✞ @mezmuredawit ✞
✞ @mezmuredawit ✞
╚✞═══●◉🌼◉●═══✞╝
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
🌼🌼 የአዋጅ ነጋሪው ቃል 🌼🌼
የአዋጅ ነጋሪው ቃል በበረሃ አየለ
የእግዚአብሄርን መንገድ አስተካክሉ እያለ
ምስክርነቱን ዮሃንስ ካስረዳ ልባችን
ለጌታ መልካም መንገድ ይሁን
የደናግል መመኪያ የነቢያት ገዳም
አወደ አመቱን ባርኪልን ድንግል ማርያም/2/
ተራራው ዝቅ ይበል ጠማማውም ይቅና
ካልተስተካከለ መንገድ የለምና
የእግዚአብሄርን መንግስት እንመስክር ሁላችን
ማረፊያ እንዲሆነን ለመጪው ሀብታችን
የደናግል መመኪያ የነቢያት ገዳም
አወደ አመቱን ባርኪልን ድንግል ማርያም/2/
/አዝ🌼🌼🌼🌼
ክፋትና ተንኮል ከልባችን ይጥፋ
ጽድቅና ርህራሄ በእኛ ላይ ይስፋፋ
ስጋና ደምህን በክብር አግኝተናል
ህይወት እንዲሆነን አምላክ ተማጽነናል
የደናግል መመኪያ የነቢያት ገዳም
አወደ አመቱን ባርኪልን ድንግል ማርያም/2/
/አዝ🌼🌼🌼🌼
ሁለት ልብሶች ያሉት ከማብዛት ልብስን
ለሌለው ያድለው ሁለተኛውን
ከበደላችን አንጻን አደራህን
በክፋ እንዳንጠፋ እኛ ባሮችህ
የደናግል መመኪያ የነቢያት ገደማ
አወደ አመቱን ባርኪልን ድንግል ማርያም/2/
/አዝ🌼🌼🌼🌼
ክፋትና ተንኮል ከልባችን ይጥፋ
ጽድቅና ርህራሄ በእኛ ላይ ይስፋፋ
ስጋና ደምህን በክብር አግኝተናል
ህይወት እንዲሆነን አምላክ ተማጽነናል
የደናግል መመኪያ የነቢያት ገዳም
አወደ አመቱን ባርኪልን ድንግል ማርያም/2/
🌼 ዘማሪት ፀዳለ ጎበዜ
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔✞═══●◉🌼◉●════✞╗
🌼 @mezmuredawit 🌼
🌼 @mezmuredawit 🌼
🌼 @mezmuredawit 🌼
╚✞═══●◉🌼◉●════✞╝
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ🌼
✞ መልዐከ ጥዒና ✞
መልዐከ ጥዒና(ሰላም) ሩፋኤል
ነፍሴን ታደጋት ከሲኦል
ከመከራ ከሃዘን አድነኝ
በክንፈ ረድኤትህ እየሰወርከኝ
ነፍሴን እየጎዳው ለስጋዬ አድልቼ
እንዳልኖር በስቃይ ከአምላክ ተጣልቼ
ማደሪያው እንዳልሆን ለዛ ፈታኝ ከይሲ
ሃኪሜ አንተ ድረስ የነፍሴ ፈዋሲ
/አዝ=====
ሥልጣን ተሰጥቶሃል ቁስሌን ትፈውስ ዘንድ
ፈታሄ ማህጸን ድኅነት የምትወድ
በስምህ ስማጸን ትቆማለህ ለኔ
ከቶ አያገኘኝም ፍርድ እና ኩነኔ
/አዝ=====
እመካለሁ በአንተ እስከ ዕለተ ሞቴ
ሁሌም ከኔ ጋር ነህ ሩፋኤል ረዳቴ
ጠበልህ ፍቱን ነው እኔን ጎብኝቶኛል
ከእግረ ሙቀት ስርዓት ከሞት አድኖኛል
/አዝ=====
ውስጤን ታውቀዋለህ ድካም እንዳለብኝ
ስበድል ሳጠፋ በፍጹም አትራቀኝ
እምነቴን አጽናልኝ ልኑር ካንተ ጋራ
በተሰጠህ ሥልጣን ሩፋኤል አደራ
👉በዘማሪ ዳዊት ክብሩ
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔✞═══●◉❖◉●═════✞╗
❖ @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit ❖
╚✞═══●◉❖◉●═════✞╝
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ከፅንሰታቸው ጀምሮ በሐዋርያዊ ተግባራቸውና ተጋድሏቸው ውስጥ ፈቃደ እግዚአብሔርን ሲፈጽሙ ነውና የኖሩት፤ ስለ ዕረፍታቸው ጌታቸውን እንዲህ ሲሉ ጠይቀዋል ‹‹ጌታዬ ወደ ሰማዕትነት አደባባይ ሄጄ በስምህ እንድሞት እዘዘኝ››፡፡ ጌታችንም ‹‹መጋደልንስ ፈጸምህ፣ ከሞት በቀር ምንም ምን አልቀረህም፤ እነሆ በክፉ ሞት በሕማመ ብድብድ በሆድ ሕመም በጽኑ ደዌ በንዳድ ትሞታለህ፤ እሷንም እንደ ስቅላቴና ካንተ በፊት እንደነበሩ ሰማዕታት ደም እቆጥረዋለሁ፤ ነገር ግን ለብቻህ አይደለም፤ በዚህች ገዳም በዚህ ዓይነት ደዌ የሚሞቱትን ቁጥራቸውን ከሰማዕታት ጋር አደርገዋለሁ፤ በመንግሥተ ሰማይም ለአንተ እሰጣቸዋለሁ›› አላቸው፡፡ ልብ ልንለው የሚገባን ነገር መከራ ለቅዱሳን ክብራቸውን የሚያበዛላቸው ከተሰቀለው ክርስቶስ ጋር በግብር የሚያመሳስላቸው መሆኑን ነው፤ 1ኛ ጴጥ 4፥13፡፡ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተቀበላቸው ሕማማተ መስቀል ለቤዛ ዓለም ሲሆን የቅዱሳን ግን ስለ ክርስቶስ ክብር እስከ ደም ጠብታ ደርሶ መመስከርን የሚያጠይቅ ነው።
ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአቡነ ተክለ ሃይማኖት አስቀድሞ እንደ ነገራቸው ሦስት ደቀ መዛሙርቶቻቸው በሕማመ ብድብድ በሽታ ከሞቱ በኋላ ጻድቁ አባታችንም ለ10 ቀናት በሕመም ቆይተው ዕረፍታቸው ሲደርስ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናቱ ከቅድስት ድንግል ማርያምና ከቅዱሳን መላእክት ጋር ተገልጾላቸዋል፡፡ ‹‹ወዳጄ ተክለ ሃይማኖት ሆይ! ከብዙ ድካም ወደ ዕረፍት፣ ከመከራ ወደ ደስታ ላሳርፍህ መጥቻለሁ፤ ጾምና ጸሎትህን ተቀብዬልሃለሁ፤ ስምህን በቅን ሕሊና የሚጠራውን ሁሉ ከመከራው አድነዋለሁ፤ በስምህ ዝክር የሚዘክሩና መታሰቢያህን የሚያደርጉትን አንተ ከገባህበት ውሳጤ መንጦላዕት አስገባቸዋለሁ›› የሚል ቃል ኪዳንም ሰጥቷቸዋል፡፡ ‹‹ከአንተ በኋላ በመንበርህ ላይ ኤልሳዕ ይሾማል፤ ግን ብዙ ጊዜ አይቆይም ያርፋል›› አላቸው፡፡ የጻድቁ ተክለ ሃይማኖት ቅድስት ነፍስ ከክብርት ሥጋቸው ነሐሴ 24 ቀን በይባቤ መላእክት፣ በመዓዛ ገነት፣ በመዝሙረ ዳዊት ተለየች፡፡ አርድዕቱ ቅዱስ ሥጋቸውን እንደ ሥርዓቱ ገንዘው በስብሐተ እግዚአብሔር በማኅሌት ከቁመት ብዛት እግራቸው በተሰበረበት በትሩፋት ሥራ በስግደት ብዛት ወዛቸው በተንጠፈጠፈበት በደብረ አስቦ ዋሻ አሳረፉት፡፡
አቡነ ተክለ ሃይማኖት ባረፉ በ56ኛው ዓመት ሦስተኛው ዕጨጌ አቡነ ሕዝቅያስ አበምኔት በሆኑ ጊዜ አቡነ ተክለ ሃይማኖት በራእይ ለአቡነ ሕዝቅያስ ተገልጠው ዐፅማቸውን ወደ ቤተ ክርስቲያኑ እንዲያስገቡ ነገሯቸው፤ እርሳቸውም በየቦታው የነበሩትን ደቀ መዝሙሮቻቸውን ጠርተው ግንቦት 12 ቀን ዋሻውን ከፍተው ዐፅማቸውን በክብር አወጡት፤ ወደ ደብረ ሊባኖስ ቤተ ክርስቲያንም አስገቡት፡፡
የጻድቁ መላ ዕድሜያቸው 99 ዓመት ከዐሥር ወር ነው፡፡ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን በየዓመቱ የጻድቁን ፅንሰታቸውን መጋቢት 24 ቀን፣ልደታቸውን ታኅሣስ 24 ቀን፣ ስባረ ዐፅማቸውን ጥር 24 ቀን፣ ዕረፍታቸውን ነሐሴ 24 ቀን፣ ፍልሠተ ዐፅማቸውን ግንቦት 12 ቀን እግዚአብሔርን በማመስገን ጻድቁን በማክበር በመንፈሳዊ ሥነ ሥርዓት ታከብራለች፡፡ የጻድቁ በረከት ከሁላችን ጋር ትሁን አሜን!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!
ምንጭ፦ ገድለ ተክለ ሃይማኖት ፣ ስንክሳር ዘነሐሴ 24
- ሕይወቱ ወገድሉ ለብፁዓዊ ቅዱስ አቡነ ተክለሃይማኖት (አውሎግሶን)
በዚህም ተደስታ ልብሰ ምንኲስናዋን ይዛ፣ የመጨረሻውን የሦስት ዓመት ሕፃን ልጇን አዝላ ከሞት የተነሳችውን አገልጋይዋን አስከትላ ወደ ደብረ ሊባኖስ ገዳም ሄዳ አስቀድማ ያዘጋጀችውን ልብሰ ምንኲስና ለብሳ ከሴቶች ገዳም ገባች፡፡ ይዛው የተሰደደችው ሕፃን ግን ወንድ ስለሆነ ከገዳሙ ውጭ አስቀምጣው ስለገባች ሕፃኑ አምርሮ ማልቀሱን የተመለከተች ከመነኰሳቱ አንዲቷ ሲያለቅስ ከሚያድር ብላ ወደ በዓቷ ልታስገባው ስትል ቅዱስ ሚካኤል ነጥቆ ወስዶ በገነት አስቀመጠው፤ ታኅሣሥ 29 ቀን ተወልዶ በሦስት ዓመቱ ታኅሣሥ 12 ቀን ብሔረ ሕያዋን አስገብቶታል፡፡
ከዕለታት በአንደኛው ቀን ቅዱስ ሚካኤል ካለችበት በዓት አውጥቶ በክንፉ ወደ ጣና (ጓንጉት) ደሴት አደረሳት፤ በዚያም ሰውነቷ ተበሳስቶ ዓሣ ሰውነቷን መመላለሻ እስኪያደርጋት ድረስ ለ12 ዓመት በባሕሩ ውስጥ ቁማ ስትጸልይ ኖራለች፡፡ እግዚአብሔርም ከመከራዋ ብዛት ከገድሏ ጽናት የተነሣ 6 የጸጋ ክንፍ ሰጥቷታል፡፡ እግዚአብሔር ‹‹ወዳጄ ክርስቶስ ሠምራ ምን እንዳደርግልሽ ትፈልጊያለሽ?›› ብሎ በጠየቃት ጊዜ ‹‹ደቂቀ አዳምን እንዳያስታቸው ዲያብሎስን ማርልኝ›› አለችው፡፡ ‹‹እርሱ ምሕረት አይሻም እንጂ ከወደደ ጥሪው›› ብሎ ቅዱስ ሚካኤልን ረዳት አድርጎ ወደ ሲዖል ላካት፡፡ በዚያም ዲያብሎስን በስሙ ጠርታ ‹‹ፈጣሪ ምሮሃልና ና ውጣ›› አለችው፡፡ ዲብሎስም ‹‹አስቀድሜ ስፈልግሽ እኖር ነበር አሁን አጠገቤ መጣሽልኝ›› ብሎ ጎትቶ ወደ ሲዖል ጣላት፡፡ ከዚያም ቅዱስ ሚካኤል የብርሃን ሰይፉን መዞ ሲዖልን ቢመታት ታላቅ ንውጽውጽታ ሆነ፤ ሲዖልም ብርሃን ለበሰች፡፡ ወዲያው ቅዱስ ሚካኤል በክንፉ ነጥቆ ሲያወጣት በተሰጣት የጸጋ ክንፍ እጅግ የበዙ ነፍሳትን ማርካ ወጥታለች፡፡ ከዚህ በኋላ በጾም በጸሎት ተወስና ስትኖር እግዚአብሔር ‹‹ቅዱስ ሚካኤልን ባልደረባ ሰጥቼሻለሁ፤ ክብረ በዓልሽም በየወሩ ከሚካኤል ጋር ይታሰባል›› ብሎ ቃል ገብቶላታል፡፡ ከዚህም የተነሣ በየዓመቱ ግንቦት 12 ቀን በደማቅ ክብረ በዓል ትታሰባለች፡፡ የዕረፍቷ መታሰቢያ ነሐሴ 24 ቀን ነው፡፡ በረከቷ ለሁላችን ይድረሰን አሜን!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!
ምንጭ፦ መድበለ ታሪክ ፣ መዝገበ ቅዱሳን
✞ ሰላሜ ነሽ ድንግል ✞
ሰላሜ ነሽ ድንግል ዋስትናዬ
ውበቴ ነሽ ማርያም አለኝታዬ
የጭንቀቴ ደራሽ የህመሜ
ተፈታልኝ ባንቺ ፅኑ ህልሜ
ወገን ዘመድ ያልኩት ሁሉ ራቀኝ
ሃዘን ፅልመት ችግር ገዝፎ ታየኝ
ብራብ ምግቤ ሆነሽልኝ አይቻለው
ሰላም ባጣም ባንቺ እፅናናለው
ፍቅርን ወልደሽ ሰላምን አገኘው
ድንግል በምልጃሽ ተፈውሻለው
/አዝ=====
የሰላም ምንጭ የነፃነት አርማ
ክብር የምትሰጭ ሞገስ ታላቅ ግርማ
አንቺን ተስፋአድርጌ ወጥቻለው
ቀንና ለሊት ነይ እልሻለው
ላንቺ ልንበርከክ አይዛል ጉልበቴ
ውዳሴሽ ይብዛ ከአንደበቴ
/አዝ=====
ሱላማጢስ ስልሽ እረካለው
በህይወቴ ሰላም አግንቻለው
እንደ ሰው ልጅ ቀን እያየሽ የማትርቂኝ
የአማኑኤል እናት ዛሬም ባርኪኝ
ተባርኬዋለው ድንግል በፍቅርሽ
እሄሁ ቆሜያለው ልዘምርልሽ
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔✞═══●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
❖ @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit ❖
✥ ✢
╚✞═══●◉❖◉●═════✞╝
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
🕯 #ፍልሰተ_ሥጋሃ_ለእግዝእትነ_ማርያም
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በ64 ዓመቷ ጥር 21 ቀን ከዚህ ዓለም ድካም ማረፏን ‹ዕረፍታ ለእግዝእትነ ማርያም› በሚለው በጥር 21 የጽሑፍ ዝግጅታችን መጻሕፍትን ጠቅሰን ማቅረባችን ይታወሳል፡፡ ሐዋርያትም ሥጋዋን በክብር ለማሳረፍ ወደ ጌቴሴማኒ ይዘዋት ሲሄዱ አይሁድ በምቀኝነት ተነሳስተው ሥጋዋን ከሐዋርያት እጅ ነጥቀው ሊያቃጥሉት ሲሄዱ ታውፋንያ የተባለው መሪያቸው የአልጋውን ሸንኮር ቢይዘው የታዘዘ መልአክ ሁለቱን እጁን ቆርጦ የእመቤታችንን አስከሬን ከወንጌላዊው ዮሐንስ ጋር ነጥቆ ገነት ከዕፀ ሕይወት ሥር እንዳኖረው ‹ጸመ ፍልሰታ ለማርያም› በሚለው ጽሑፋችን ገልጸን ነበር፡፡ ከጥቂት ጊዜ በኋላም ቅዱስ ዮሐንስ ተመልሶ ሲመጣ በገነት ዕፀ ሕይወት ሥር መኖሯን ለሐዋርያት ነገራቸው፡፡ እነርሱም እንደ ዮሐንስ ባለማየታቸው ሲያዝኑ ዓመት ከተቀመጡ በኋላ ምን እናድርግ ብለው መክረው ከነሐሴ 1 ቀን ጀምረው ሁለት ሱባዔ ያዙ፤ በሁለተኛው ሱባኤ መጨረሻ (ነሐሴ 14 ቀን) መልአክ የእመቤታችንን ሥጋ ከገነት ዕፀ ሕይወት ሥር አምጥቶ ሰጣቸውና ወደ ጌቴሴማኒ ወስደው ቀበሯት፡፡ የእመቤታችንን ሥጋ በሚቀብሩበት ጊዜ ከ12ቱ ሐዋርያት አንዱ ቅዱስ ቶማስ በአገልግሎት ምክንያት ወደ ሀገረ ስብከቱ (ሕንድ) ሄዶ ነበር፡፡ እርሱ ከአገልግሎት በደመና ሲመለስ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስታርግ አገኛት፡፡ ቅዱስ ቶማስ ያን ጊዜ ሌሎች አይተው ለእርሱ የቀረበት መስሎት ‹‹ቀድሞ የልጅሽን ትንሣኤ ዛሬ ደግሞ ያንችን ትንሣኤ ሳላይ›› ብሎ ከደመናው ተወርውሮ ሊወድቅ ፈለገ፡፡ እመቤታችንም አጽናንታው እርሱ ብቻ እንዳያት አስረድታ ለምልክት የተገነዘችበትን ሰበን ሰጥታ ሰደደችው፡፡
ቅዱስ ቶማስ ከሐዋርያቱ ዘንድ በደረሰ ጊዜ ዐውቆ ነገሩን ደብቆ ‹‹የእመቤታችን ነገር እንዴት ሆነ?›› ብሎ ቢጠይቃቸው ‹‹አግኝተን ቀበርናት እኮ›› አሉት፤ ቶማስም ‹‹አይሆንም ሞት በጥር በነሐሴ መቃብር ለሰሚም አያምርም›› አላቸው፡፡ ከዚያ ‹‹ቀድሞ የጌታችንን ትንሣኤ ተጠራጠርክ፤ አሁን ደግሞ አታምንም›› ብለው በቅዱስ ጴጥሮስ መሪነት ወደ መካነ መቃብሯ ይዘውት ሄደው መቃብሩን ከፍተው ቢያጧት ደንግጠው ቆመው ሳለ ቶማስ ‹‹አታምኑኝም ብዬ ነው እንጅ ተነሥታ ዐርጋለች›› ብሎ የቀበሩበትን ሰበን አሳያቸው፤ እነርሱም ትንሣኤና ዕርገቷን አምነው ሰበኑን ለበረከት ተከፋፍለውታል፡፡
ከዚህ በኋላ በመንፈሳዊ ቅንዓት ‹‹ቶማስ አይቶ እኛ ትንሣኤዋን ዕርገቷን ለምን አናይም?›› ብለው ትንሳኤዋን ዕርገቷን እንዲያሳያቸው በዓመቱ ነሐሴ 1 ቀን ሱባዔ ገቡ፡፡ ሁለተኛው ሱባዔ ነሐሴ 14 ቀን ተጠናቅቆ ከሁለት ቀን በኋላ በተነሣችበት ነሐሴ 16 ቀን ሐዋርያትን ሰብስቦ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሠራዒ ካህን፣ ቅዱስ ጴጥሮስን ተራዳኢ ካህን፣ እስጢፋኖስን ደግሞ ሠራዒ ዲያቆን አድርጎ፣ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን መንበር አድርጎ ቀድሶ አቍርቧቸው ትንሣኤዋንና ዕርገቷን አሳይቷቸዋል፡፡ ለእመቤታችንም ‹‹በዚህች ቀን ሥጋዬንና ደሜን የሚቀበል፣ ለተቸገረ የሚሰጥ ኃጢአቱን ይቅር እልለታለሁ፤ መንግሥተ ሰማያትንም አወርሰዋለሁ›› ብሎ ቃል ኪዳን ሰጥቷታል፡፡
የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ምልጃና ጸሎት አይለየን አሜን!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!
ምንጭ፦ ነገረ ማርያም ፣ ስንክሳር ዘነሐሴ 16 ፣ መድበለ ታሪክ
#ሀሁ_ብዬ
#ዘማሪ_ዲ/ን_ታዴዎስ_ግርማ
#@mezmuredawit
#@mezmuredawit
ሃሌ-ሉያ አንተ ሰው ሆይ
ሃሌሉያ አንተ ሰው ሆይ (4)
ቡሄ መድረሱን ሰምተሃል ወይ
ሀሌሉያ አንተ ሰው ሆይ
መስማቱንማ ሰምቼ ነበር
ሀሌሉያ አንተ ሰው ሆይ
ከዚያ ቢያደርሰኝ ልዑል እግዚአብሔር
ሃሌሉያ አንተ ሰው ሆይ
እናቴ ሆይ.......... ሆ
ይህን ባየሻ ........ሆ
በቁርማ ዳቦ .......ሆ
ሲጥለኝ ውሻ........ሆ
ደጓ ጫማዋን ......ሆ
አውልቃዋለች.......ሆ
ውሃ ሲጠማ.........ሆ
አጠጥታዋለች......ሆ
የስዋ ውዳሴ .......ሆ
ሆኖኛል ውይን ......ሆ
ዘሬም ብዘምር ......ሆ
እኖራለሁኝ ...........ሆ
ዘምር በለው ተነሳ በገናን አንሳ (4)
በእምነት እንውጣ .ሆ
ከተራራው ላይ......ሆ
ይታይ ብርሃኑ........ሆ
ክብሩ ኤልሻዳይ....ሆ
ሙሴን እንጠይቅ...ሆ
የጥንቱን ነገር .......ሆ
ምን እንደሚለው ...ሆ
ጌታን ሲያናግር......ሆ
ድምጹን እንስማ ....ሆ
እንደ ትሁትነቱ.......ሆ
እንቀበለው ..........ሳ
እኛም በትሩን .......ሆ
ዘምር በለው ተነሳ በገናን አንሳ (2)
ተቁኙለት በልልታ ላዳኙ ጌታ(2)
ተራራውማ ..........ሆ
ነውና አምሳል.......ሆ
ለቤተ ክርስቲያን...ሆ
መንበረ ልዑል........ሆ
ወጥተን እንጠይቅ .....ሆ
ኤልያስን.............ሆ
እንድንዳስሰው.....ሆ
ጸጓራር ክንዱን....ሆ
ሰማይ በትለጉም...ሆ
ባህር ቢከፍል.......ሆ
እሳት ብታወርድ.....ሆ
ጠላትም ቢርድ......ሆ
በሰረገላ ..............ሆ
የተነጠከው...........ሆ
ይህ ሁሉ ክብር .....ሆ
በማን ስልጣን ነው....ሆ
ለሁላችን መልካም ነው በዚህ መኖር(4)
የእመብርሃን .........ሆ
የምዬ ልጅ............ሆ
ተጥሎ ላይቀር .....ሆ
ተረስቶ ደጅ...........ሆ
ሰአሊ ለነ .............ሆ
ባለበት አፉ...........ሆ
የጭንቁን እለት.....ሆ
ተሰብሮ ሰልፉ......ሆ
እንዳባቶቹ ............ሆ
ቅኔን ተቀኘ.............ሆ
ድንግል ስትረዳው....ሆ
አይኑ ስላየ..............ሆ
ተፈስሂ ደብረ ታቦር(2)
ተፈስሂ አርሙኒየም (2)
ባንቺ ላይ ታየ እግዚአብሔር
ተፈስሂ አርሙንየም
ሙሴ ስላለ ............ሆ
መና ያውርዳል........ሆ
ቅዱስ ኤልያስ.........ሆ
ስጋ ያመጣል..........ሆ
ዮሃንስንም............ሆ
ጌታ ይወዳል.........ሆ
መድኃኒታችን........ሆ
ፈውስ ይሆነናል.....ሆ
በዚህ እንድንኖር ...ሆ
ዳሱን ጥለናል .....ሆ
ዘምር በለው ተነሳ በገናን አንሳ (4)
አባቴም ቤት..........ሆ
አለኝ ለከት.............ሆ
እናቴም ቤት ...........ሆሆ
አለኝ ለከት...,..........ሆ
ፍልሰታ ስትሆን.......ሆ
የቆምኩባት............ሆ
በድብረ ታቦር .........ሆ
ያጌጥኩባት...........ሆ
ዘምር በለው ተነሳ በገናን አንሳ(2)
ተቀኙለት በልልታ ላዳኙ ጌታ(2)
አመት አውዳመት "ድገምና" አመት "ድገምና"
ያባብዬን ቤት "ድገምና" አመት "ድገምና"
ይግባ በረከት "ድገምና" አመት "ድገምና"
የማምዬ ቤት "ድገምና" አመት "ድገምና"
ይትረፍረፍ በእውነት "ድገምና" አመት "ድገምና"
ነሩ በሀይማኖት
ጽኑ በጸሎት
በተዋህዶ ቤት(4)
የሰማይ ሰራዊት "በእምነት" ያድርጋችሁ "አሜን"
አማኑኤል በጸጋ "በእምነት" ያኑራችሁ "አሜን"
ከስጋ ወደሙ "በእምነት"
ያድላችሁ "አሜን"
ዘርን እደ አብርሃም "በእምነት"
ያብዛላችሁ "አሜን"
ይባረክ በእግዚአብሔር በእምነት ዘመናችሁ "አሜን"/2/
እድሜና ጤናውን በእምነት ያድላችሁ "አሜን" (2)
ዘማሪ አርቲስት ይገረም ደጀኔ /አስቴር /
እና ዘማሪ አዱኛ ፍቃዱ
╔✞═══●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
❖ @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit ❖
✥ ✢
╚✞═══●◉❖◉●═════✞╝
✍ ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ
✞ ስድቤን አርቀሽ ✞
ስድቤን አርቀሽ ነውሬን ሸፈንሽው
እመ አምላክ በአንች መቸም አላፍርም
ስምሽን ጠርቸ እጽናናለሁ
ሀዘኔን በአንች እረሳለሁ
ነውር አለብኝ ብዙ ስድብ
አንጀት የሚልጥ ልብ የሚያቆስል
ስሜን ለውጠው ቢያንቋሽሹኝ
በሀዘን በለቅሶ ድንግል መጣሁኝ
እንደሀና ሁኜ በቤተ መቅደስ
በመረረ ሀዘን ነው እኔ እማለቅስ
ፍረጅልኝ እና ልመለስ ከቤቴ
ሀዘኔን በደስታ ለውጭው እናቴ
በግራም በቀኜ ጠላት ቢከበኝ
አብዝቸ እጮሀለሁ እናቴ ስሚኝ
/አዝ=====
መከራው በዝቶ ግራ ገብቶኛል
ድምጽሽን ልስማ ያረጋጋኛል
የሰው ህይወቱ ብርቱ ሰልፍ ነው
ደስታ እና ሀዘን የማይለየው
በእጃችን ወድቋል ሲሉ ጠላቶቸ
አመለጥኳቸው ስምሽን ጠርቸ
ሰው የዘራውን ያንኑ ያጭዳል
በቆፈረው ጉድጓድ እራሱ ይገባል
እናቴ እመቤቴ ብየ ስጠራሽ
ከመከራ ሁሉ ታወጭያለሽ
/አዝ=====
በምርኮ ሳለሁ በሰው ሀገር
ግፍ ውለውብኝ ስኖር በእስር
ምልጃሽ ደርሶልኝ ተፈትቻለሁ
በታምራትሽ እኔ ድኛለሁ
ቃልሽን ሰምቶ ፅንሱ ሰገደ
ብላለች ኤልሳቤጥ ነውሬ ተወገደ
የጌታየ እናት እኔን አሰበችኝ
ታሪኬን ቀይራ ይሄው ባረከችኝ
የእመቤቴ ከሆንኩ ማን ይቃወመኛል
ወጀቡም ማዕበሉም ይታዘዝልኛል
/አዝ=====
ወይን እኮ አልቋል የዶኪማስ ቤት
ድንግል አማልጅው ነይ የኛ እመቤት
ስምሽ ሲጠራ በየቦታው
ይሞላልናል የጎደለው
ግራ የገባው የቸገረው
ድንግልን ይጥራት እንድትረዳው
ሳዝን ስተክዝ የምታጽናና
እናት አለችኝ ርህርህተ ልቦና
እናቴ እመቤቴ ብየ ስጠራሽ
ከመከራ ሁሉ ታወጭኛለሽ
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @enamsgn ❖
❖ @enamsgn @enamsgn ❖ ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
🕯 #ዮሴፍ_አረጋዊ
አረጋዊው ዮሴፍ ትውልዱ ከነገደ ይሁዳ ከቤተ ዳዊት ሲሆን እግዚአብሔርን የሚፈራ፣ ለሰው የሚራራ ደግ ሰው ነበር፤ (ማቴ 1፥16-25 ፣ ሉቃ 1፥27)፡፡ ድግር ጠርቦ፣ ጥርብ አለዝቦ በመሸጥ ይተዳደር ነበር፤ ለዚህም ነው ኢየሱስ ክርስቶስን ‹‹የጠራቢው ልጅ አይደለምን?›› እያሉ የሚጠሩት፤ (ማቴ 13፥55-56)፡፡ ቅዱስ ዮሴፍ ማርያምን (የቅድስት ኤልሳቤጥና ቅድስት ሐና እመ ማርያም እኅት) አግብቶ ያዕቆብ፣ ዮሳ፣ ስምዖን፣ ይሁዳና ሰሎሜ የሚባሉ ልጆችን ወልዷል፡፡ ሚስቱ ከሞተችበት በኋላ አይሁዳውያን በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ላይ በጠላትነት ተነሥተው ከቤተ መቅደስ ትውጣልን ባሉ ጊዜ ወስዶ ከቤቱ አስቀምጧታል፡፡ ከዚህ በኋላ እስከ ዕለተ ሞቱ ድረስ በደስታዋም በኀዘኗም ጊዜ አልተለያትም፡፡ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በወለደች ጊዜም ዳስ ሠርቶ አገልግሏታል፡፡
ሄሮድስ ሕፃናትን በሰይፍ በአስፈጀ ጊዜ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ልጇን ለማዳን ወደ ግብፅና ኢትዮጵያ በተሰደደች ጊዜ ሦስት ዓመት ከመንፈቅ ረሃቡን፣ ጥሙን፣ የቀን ሐሩሩን፣ የሌሊት ቁሩን ታግሣ በረሀ ለበረሀ በተንከራተተችበት ወቅት አልተለያትም፤ (ማቴ ምዕራፍ 2)፡፡
ከስደት ከተመለሱ በኋላም ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ አባት ሆኖ አሳድጎታል፤ አይሁዳውያን ጌታን የዮሴፍ ልጅ የሚሉትም በዚህ ምክንያት ነው፡፡ ቅዱስ ዮሴፍ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ከኒቆዲሞስ ጋር ገንዞ በአዲስ መቃብር አኑረውታል፤ (ዮሐ 19፥38)፡፡ አረጋዊው ዮሴፍ በ104 ዓመቱ ሐምሌ 26 ቀን ዐርፏል፡፡ የአረጋዊው ቅዱስ ዮሴፍ ጸጋና በረከት ይደርብን አሜን!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!
ምንጭ፦ መጽሐፍ ቅዱስ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
#በዓለ_ቅዱስ_ገብርኤል (ሐምሌ 19)
ይህ ዕለት መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ቅድስት ኢየሉጣንና ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስን ከእቶን እሳት ያዳነበት ነው፡፡ ቅዱስ ቂርቆስ ሀገሩ ሮም ሲሆን አባቱ ቆዝሞስ እናቱ ኢየሉጣ ይባላሉ፡፡ እናቱ ቅድስት ኢየሉጣ በትውልዷ ከአዝማደ ነገሥት ወገን ናት፡፡ ዲዮቅልጥያኖስ በነገሠ በ20 ዓመት በአባ ባጋግዮስ ምክንያት ‹‹የጣዖታት ቤቶች ይከፈቱ አብያተ ክርስቲያናት ይዘጉ›› ብሎ አሳወጀ፤ በዚህ ጊዜ ግማሾቹ ተሰደዱ ቅድስት ኢየሉጣም ልጇ የ3 ዓመት ሕፃን ነበርና ለርሱ ብላ ወደ ኢቆንዮን ሸሸች፡፡
በዚያም ሀገረ ገዢው ‹‹ክርስቶስን ካጂ ለጣዖት ስገጂ›› ቢላት ‹‹ዓይን እያለው ለማያይ ጆሮ እያለው ለማይሰማ በቃልህ አዘህ በእጅህ ሠርተህ ላቆምከው ምስል አልሰግድም›› ብላ መለሰችለት፡፡ እርሱም መልሶ ‹‹እምቢ ካልሽ በሰይፍ እቀጣሻለሁ›› ብሎ ቢያስፈራራትም እርሷ ግን ‹‹ይህን ሕፃን ጠይቀው›› አለችው፡፡ ከዚያም ሕፃኑን ‹‹ወርቅ እሰጥሃለሁ ለዚህ ጣዖት ስገድ›› አለው፡፡ ሕፃኑ ቂርቆስ መንፈስ ቅዱስ አድሮበታልና ‹‹ራሳቸውን እንኳ ማዳን ለማይችሉ ጣዖታትህ አልሰግድም›› ብሎ በመለሰለት ጊዜ ንጉሡ ተበሳጭቶ ‹‹በብረት ጋን ውኃ አፍልታችሁ ከዚያ ውስጥ ጣሏቸው›› ብሎ አዘዘ፡፡ የውኃው ፍላት እንደ ክረምት ነጎድጓድ 42 ምዕራፍ ድረስ ይሰማ ነበር፡፡ የንጉሡ አገልጋዮች ሊከቷቸው ሲወስዷቸው የቅድስት ኢየሉጣ ልቧ በፍርሃት ታወከባት፤ ቅዱስ ቂርቆስ ግን የእናቱን ፍርሃት እንዲያርቅላት ይጸልይ ነበር፤ እርሷንም ሁለተኛ ሞት አያገኘንምና እናቴ ሆይ በርቺ ፣ ጨክኚ፤ አናንያ፣ አዛርያና ሚሳኤልን ያዳነ እኛንም ያድነናል›› በማለት እያጽናናት ልብሷን እየጎተተ ከእሳቱ ቀረቡ፡፡ ከዚህ በኋላ ቅድስት ኢየሉጣ ጨክና በፍጹም ልብ ሆነው ተያይዘው ከእሳቱ ገብተዋል፡፡ እግዚአብሔርም መልአኩ ቅዱስ ገብርኤልን ልኮ በበትረ መስቀሉ እሳቱን አጥፍቶ የፈላውን ውኃ አቀዝቅዞ አውጥቷቸዋል፡፡ ቅድስት ኢየሉጣ እና ቅዱስ ቂርቆስ በወጡም ጊዜ ልብሳቸውና ሰውነታቸው ሳይቃጠል ተመልክተው ከአሕዛብ ብዙዎቹ አምነው ሰማዕትነት ተቀብለዋል፡፡ ቅዱስ ገብርኤል ከሚፈላ ውኃ ያወጣቸው ሐምሌ 19 ቀን ሲሆን ሰማዕትነት የተቀበሉት ግን ጥር 15 ቀን ነው፤ (ስንክሳር ዘጥር 15 ይመልከቱ)፡፡ የቅድስት ኢየሉጣ እና የቅዱስ ቂርቆስ በረከታቸው ይደርብን አሜን!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!
ምንጭ፦ ስንክሳር ዘሐምሌ 19 ፣ መድበለ ታሪክ ፣ መዝገበ ታሪክ
✞ ኪዳነ ምሕረት የ ረፍቴ እናት ✞
ኪድነ ምሕረት የእረፍቴ እናት
ሠላም ሆነ በ አንቺ አማላጅነት
ንጽሕት ድንኳን በ ዕምነት የአጌጥሁብሽ
ሠላም ሆነ በ አማኑኤል ልጅሽ
ሠላም ሆነ በ አማኑኤል ልጅሽ/፪/
የ ብርሐን ዝናር በአይኖረኝም
በ ንጉሥ ፊት ተሸልሜ ብቆም
በ ልጅሽ ነው ውበቴ ማማሩ
በ ምልጃሽ ነው ሥሜ መቀየሩ
በ ልቤ ላይ ተነበበ ልጅሽ
አዎ ሥሜ ተጠርቷል በ ልጅሽ
ከ ታች በ ምድር እስከ ሠማያት ድረስ
ድርሻዬ ነው ሥምሽን ማወደስ
ድርሻዬ ነው ሥምሽን ማወደስ
/አዝ=====
የ ከበረ ሆነሽ ንግግሬ
ቅኔ አነሳሁ ለ ክብርሽ ዘምሬ
እንደ ዝግባ ከፍ ብዬ ብታይ
ወጥቶልኝ ነው በ ሠማይ ጸሐይ
ሥለ ምልጃሽ ዘይቱ ፈሠሠ
አንቺን ይዤ ሙሽራው ደረሠ
ቀንዲሌ ነሽ ድንግል አዛኝቱ
በ ልጅሽ ነው የ ነፍሴ ጽናቱ
በ ልጅሽ ነው የ ነፍሴ ጽናቱ
/አዝ=====
ከ ኤልያብ ቢደምቅ ደም ግባቴ
ማን ሊመርጠኝ ያለ አንቺ እናቴ
ተዋብሁብሽ ነፍሴ በ አንቺ አበራ
አንደበቴ ሥምሽን ሲጠራ
እንደ ሙሴ እንደ አሮን በትር
ማምለጫዬ ከ ፈርዖን ቀንበር
ከ እንግዲኽማ እኔ እንዴት አዝናለሁ
አማላጄ አንቺን ይዤሻለሁ
አማላጄ አንቺን ይዤሻለሁ
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔✞═══●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
❖ @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit ❖
✥ ✢
╚✞═══●◉❖◉●═════✞╝
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
✞ መስቀል ኃይላችን ✞
መስቀል መስቀል ኃይላችን
ጠላትን ማጥፊያችን /2×/
በመስቀል እንመካለን እንድንበታለን /2×/
የክርስቲያን ጋሻ መስቀል ኃይላችን
የክርስትያን ጦር መስቀል ኃይላችን
ዕፀ መስቀሉ ነው መስቀል ኃይላችን
የማያሳፍር መስቀል ኃይላችን
/አዝ✞✞✞✞✞
መድኃኒት የሚሆን መስቀል ኃይላችን
ደሙ ፈስሶበታል መስቀል ኃይላችን
መስቀሉን ጥግ አድርጉ መስቀል ኃይላችን
እርሱ ይፈውሳል መስቀል ኃይላችን
/አዝ✞✞✞✞✞
ክርስቶስ በደሙ መስቀል ኃይላችን
ስለቀደሰው መስቀል ኃይላችን
መስቀል ላመነበት መስቀል ኃይላችን
ድል ማድረጊያ ነው መስቀል ኃይላችን
/አዝ✞✞✞✞✞
የክርስቶስ ሥጋ መስቀል ኃይላችን
የተፈተተበት መስቀል ኃይላችን
መስቀል ኃይላችን ነው መስቀል ኃይላችን
የምንድንበት መስቀል ኃይላችን
/አዝ✞✞✞✞✞
ሕይወትን ለማግኘት መስቀል ኃይላችን
ከሞት ለመዳን መስቀል ኃይላችን
መመኪያ ኃይላችን መስቀል ኃይላችን
መስቀል አለልን መስቀል ኃይላችን
አምስቱ ዘማሪያን በሕብረት
╔✞═══●◉🌼◉●═══✞╗
✞ @mezmuredawit ✞
✞ @mezmuredawit ✞
✞ @mezmuredawit ✞
╚✞═══●◉🌼◉●═══✞╝
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
🌼🌼ዘመን ተሰጠን ለምስጋና🌼🌼
ዘመን ተሰጠን ለውዳሴ
ተመስገን ሥላሴ
ቸርነትን ሰጠን ዘመን ለፍስሐ
ይቺም እድሜ ለእርቅነች ለንስሀ
ጥበባችን መቼ ሆነ እውቀታችን
ምሕረትህ በዝቶልን ነው መቆማችን
ከሰጠኸን አዲስ ዓመት
ከሰጠኸን አዲስ እለት
እንዘምራለን በደስታ በአኮቴት
/አዝ🌼🌼🌼🌼
የለውም ጫፍ የለው ድንበር ያንተ ምህረት
በእድሜያችን ጨመርክልን ይህቺን እለት
ተደነቅን ተገረምን በአንተ ፀጋ
ቀንና ሌት ሲፈራረቅ ክረምት በጋ
ከሰጠኸን አዲስ ዓመት
ከሰጠኸን አዲስ እለት
እንዘምራለን በደስታ በአኮቴት
/አዝ🌼🌼🌼🌼
ምድር ረክታ በዝናቡ በሰማይ ጠል
በአበባ ደምቃ ታየች በሐመልማል
በእድሜያችን ላይ ከጨመርከው ይህን ዓመት
የንስሀ ይሁንልን የመጸጸት
ከሰጠኸን አዲስ ዓመት
ከሰጠኸን አዲስ እለት
እንዘምራለን በደስታ በአኮቴት
/አዝ🌼🌼🌼🌼
የእርቅ ይሁን ዘመናችን የይቅርታ
ሰላም ትሁን ሀገራችን ፍቅር ተመልታ
መለያየት መጠላላት የሌለበት
አድርግልን ጌታችን ሆይ ይህን ዓመት
ከሰጠኸን አዲስ ዓመት
ከሰጠኸን አዲስ እለት
እንዘምራለን በደስታ በአኮቴት
🌼ዘማሪ ዲ/ን አብኤል መክብብ
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔✞═══●◉🌼◉●════✞╗
🌼 @mezmuredawit 🌼
🌼 @mezmuredawit 🌼
🌼 @mezmuredawit 🌼
╚✞═══●◉🌼◉●════✞╝
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ🌼
🌼✞ አዲሱ አመት ባርክልን ✞🌼
አሮጊ አመት አልፎ አዲሱ ዘመን መጣ
ምድረ በዳው ሁሉ አበባን እንዲያወጣ
ጭጋጉ ዝናብ ዘመኑን ጨርሶ
ርዕሰ አውዳመት መጣ ተመልሶ/2/
በአድይ አበባ ምድሩ ተንቆጥቁጦ
ጨለማው በብርሃን ደምቆ ተለውጦ
በወርሃ መስከረም ቅዱስ ዮሐንስ
እንደ ምን ደስ ይላል ጌታ ሲወደስ
አበባ አየሽ ሆይ እንበል/4/
ኢዮሃ አበባ እንበል/4/መስከረም ጠባ
ባርክልን/4/ አዲሱ አመት ባርክልን
አውዳመቱን ባርክልን/2/
/አዝ🌼🌼🌼🌼
የጠራውን ሰማይ እንድናይፈቀደ
አዲስ ቀን ሊሰጠን እግዚአብሔር ወለደ
በዳዩን ሰውነት ጥለን እንድንመጣ
ለአዲስ ማንነት አዲስ አመት መጣ
አበባ አየሽ ሆይ /4/.......
/አዝ🌼🌼🌼🌼
በችቦ ብርሃን ስንሰንቅ ተስፋ
ችግርና ስደት ከኢትዮጵያ እንዲጠፋ
እንዲሰማን አምላክ ምህረት እንዲመጣ
ከወቀልና ግፍ ከቁጣም እንድንወጣ
አበባ አየሽ ሆይ /4/.......
/አዝ🌼🌼🌼🌼
በዙፋኑ ያለ በዘመን የሚኖር
አመትን ሊሰጠን ስለ ድንግል ብሎ
ልክ እንደ ዘመኑ ልባችን ይለወጥ
በቀኙ እንድንቆም ለፍርድ ሲቀመጥ
አበባ አየሽ ሆይ እንበል/4/
ኢዮሃ አበባ እንበል/4/መስከረም ጠባ
ባርኪልን/4/ አዲሱን አመት ባርኪልን
ድንግል ማርያም ባርኪልን/2/
/አዝ🌼🌼🌼🌼
በተሰጠሽ ኪዳን ባንቺ አማላጅነት
ለአስራት ሃገርሽ ይምጣላት ምህረት
የፍቅርን ሸማ ኢትዮጵያ ትልበስ
እርጋታን ያድላት የእግዚአብሔር መንፈስ
ባርኪልን/4/ አዲሱን አመት ባርኪልን
ድንግል ማርያም ባርኪልን
🌼 ዘማሪ ዲ/ን ሄኖክ ሞገስ
🌼 አርቲስት ዘማሪ ይገረም ደጀኔ
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🌼 @mezmuredawit 🌼
🌼 @mezmuredawit 🌼
🌼 @mezmuredawit 🌼
🌼🌼🌼🌼🌼🌼
✞ አየኋት ባይኔ አሻግሬ ✞
አየኋት ባይኔ አሻግሬ
የያሬድን ውብ ዝማሬ
ተቀኘው እንደ አባቶቼ
እጄን ለክብሯ ዘርገቼ/2/
ድካም እና እንቅልፍ እንደምን ሊረታኝ
ድንጋይ ብንተራስ ፍቅርሽ አያስተኛኝ
አይኔ ቢከደን አለሽ በምናቤ
አልተከለልሽም ነግሰሻል በልቤ/2/
/አዝ=====
መረማመጃ የሎዛ መሠላል
የዜማ ቤቴ የመቅደስ ጽናጽል
የሰማይ ንጉስ በበላይሽ አለ
ድንኳን አድርጎ አንቺን የተከለ/2/
/አዝ=====
ስምሽ በሁሉ ስለተወደደ
ድንግል ለክብርሽ ፍጥረት አረገደ
ካላመኑት ዘንድ ቢሆንም ዝምታ
ከገብርኤል ነው የስምሽ ሠላምታ/2/
/አዝ=====
ሳደርስ ውዳሴ መፃፋን ገልጬ
ተመለከትኩሽ አይኔ እምባ እየረጨ
በገናን ዳዊት መሰንቆንም እዝራ
ሰጡኝ ላነሳሽ በክብሩ ተራራ/2/
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔✞═══●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
❖ @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit ❖
✥ ✢
╚✞═══●◉❖◉●═════✞╝
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
🕯#ዕረፍቱ_ለቅዱስ_ተክለ_ሃይማኖት (ነሐሴ 24)
ስለ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ታሪክ ከዚ በፊት ሐዲስ ሐዋርያ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ዘደብረ ሊባኖስ ፅንሰታቸውና ልደታቸው እና ፍልሰተ ሥጋሁ ለአቡነ ተክለ ሃይማኖት በሚል ርዕስ በተዘጋጀው ጽሑፋችን ማቅረባችን ይታወሳል፡፡ በዚህ ጽሑፍ ደግሞ የቅዱስ ተክለ ሃይማኖትን ዕረፍት በአጭሩ እንዳስሳለን፡፡ ነቢየ እግዚአብሔር ዳዊት ‹‹ክቡር ሞቱ ለጻድቅ በቅድመ እግዚአብሔር - የጻድቅ ሞት በእግዚአብሔር ፊት የከበረ ነው›› መዝ 115፥6 እንዳለ፤ ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት የዕረፍታቸው ጊዜ ሲደርስ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቅድስት ድንግል ማርያምንና 12ቱን ሐዋርያት ይዞ ወደ አባታችን መጡ፡፡ በምን ዓይነት ሕማም ነፍሳቸው ከሥጋቸው እንደምትለይ አስቀድሞ ‹‹በሥራህ ሁሉ እነሆ እኔን ተከተልህ ወዳጄ ሆይ አሁንም በመንግሥተ ሰማያት መንገሥ ከእኔ ጋር እንድትተካከል በሞቴም ልትመስለኝ ይገባሃል›› ብሎ አስታውቋቸው ነበር፤ ጌታችን በመንግሥተ ሰማያት ከእኔ ጋር እንድትተካከል ሲል የእርሱ የባሕርይው ሲሆን ለቅዱሳኑ ግን የጸጋ ንግሥና እንደሚሰጣቸው ለማጠየቅ ነው፡፡
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
🕯 #ቅድስት_ክርስቶስ_ሠምራ
በኢትዮጵያ ቡልጋ አካባቢ ልዩ ስሙ ቅዱስ ጌዬ በሚባል ቦታ የተወለደችው ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ከአባቷ ደረሳኒ ከእናቷ ዕሌኒ ግንቦት 12 ቀን ተወለደች። ወላጆቿ የእግዚአብሔርን ሕግጋትና ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን በማስተማር አሳደጓት፤ ለዐቅመ ሔዋን በደረሰች ጊዜም ለሠምረ ጊዮርጊስ ዳሯት፤ ካገባትም በኋላ ካህን ሆነ፤ 12 ልጆችንም (ዐሥር ወንዶችና ሁለት ሴቶች) ወለዱ። ቅድስት ክርስቶሰ ሠምራ እግዚአብሔርን የምትፈራ፣ በጾምና በጸሎት ተወስና የምትኖር ደግ ሴት መሆኗን የሰማው በዘመኑ የነበረው ንጉሥ ዓፄ ይስሐቅ (የንግሥና ስሙ ንጉሥ ዓፄ ገብረ መስቀል) እንዲያገለግሏት 174 አገልጋዮችን ‹‹በጸሎትሽ አስቢኝ›› ብሎ ላከላት፡፡ ከአገልጋዮቿ መካከል አንዷ ምግባሯ አስቸጋሪ በመሆኑ ቅድስት ክርስቶስ ሠምራን በጣም ታበሳጫት ነበር። ይህችው አገልጋይ ከዕለታት አንድ ቀን ስታስቸግራት ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ የእሳት ትንታግ አንስታ በአገልጋይዋ አፍ አደረገችባትና ወዲው ሞተች፡፡ በዚህም ክርስቶስ ሠምራ ደነገጠችና ወደ ሰማይ አንጋጣ ‹‹እኔ ክርስቲያንና የካህን ሚስት ስሆን ነፍሰ ገዳይ ሆንኩ፤ ወዮልኝ ነፍሴን ምን እላታለሁ? ልሸከማት የማልችል ኃጢአት አገኘችኝ›› እያለች ፈጣሪዋን ትማጸን ጀመር፤ ዳግመኛም ‹‹ይህችን ነፍስ ከሥጋዋ አዋሕደህ ብታስነሣልኝ ልጆቼን፣ ቤቴን፣ ንብረቴንና ሀብቴን ትቼ አንተን እከተላለው›› ብላ ስዕለት ተሳለች፡፡ ‹‹አቤቱ ጸሎቴን ስማኝ ጩኸቴም ወደ አንተ ይድረስ በመከራዬ ቀን ፊትህን ከእኔ አትመልስ›› (መዝ 101፥1-2) እንዲል ቅዱስ ዳዊት በመዝሙሩ ክርስቶስ ሠምራም ይህንኑ መዝሙር ስትዘምር የሞተችዋን አገልጋይ አግዚአብሔር አስነሣላት።
✞ ዐረገች በስብሐት ✞
ዐረገች በስብሐት ዐረገች በእልልታ
በስብሐት በእልልታ
ዐረገች ዐረገች በእልልታ
የጻድቃን እመቤት የሀጥዐን ተስፋ
ዐረገች ዐረገች በእልልታ
የማይታበለው እንዲፈጸም ቃሉ
ብታርፍም እመአምላክ ብዛዊተ ኩሉ
ዐረገች ተነስታ ድንግል የእኛ እናት
እልል በሉላት እልል በሉላት
የጻድቃን እመቤት የሀጥዐን ተስፋ
ዐረገች ዐረገች በእልልታ
/አዝ=====
ሰማያት ተደንቀው በአዲሲቷ ሰማይ
ያልቻሉትን ጌታ ወስናው ብትታይ
ሊቀበሏት ወጡ በሐሴት በሙሉ
ንዒ ንዒ እያሉ ንዒ ንዒ እያሉ
የጻድቃን እመቤት የሀጥዐን ተስፋ
ዐረገች ዐረገች በእልልታ
/አዝ=====
ዘመኗን በሙሉ ስለ ልጇ አልቅሳ
የመከራ ሰይፍን አሳልፋ ነፍሷ
በቀኙ ልትቆም ንግስት እየተባለች
ይኸው ዐርጋለች ይኸው ዐርጋለች
የጻድቃን እመቤት የሀጥዐን ተስፋ
ዐረገች ዐረገች በእልልታ
/አዝ=====
በሐዋርያት አበው ትምህርት የጸናችው
የልጇ ምስክር ከዘሯ የቀራችው
ከሞት ተነስታለች ቅድስት እናታችሁ
እንኳን ደስ ያላችሁ እንኳን ደስ ያላችሁ
የጻድቃን እመቤት የሀጥዐን ተስፋ
ዐረገች ዐረገች በእልልታ
/አዝ=====
ልጅሽ በዳሰሰው በነካው ሰበን
እንደባረክሻቸው ሐዋርያቱን
ማርያም ማርያም ስንል ደጅሽ ላይ ቆመን
እኛንም ባርኪን እኛንም ባርኪን
የጻድቃን እመቤት የሀጥዐን ተስፋ
ዐረገች ዐረገች በእልልታ
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @enamsgn ❖
❖ @enamsgn @enamsgn ❖ ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
✞ ቡሄ_በሉ ✞
ቡሄ በሉ /2/ ሆ
ልጆች ሁሉ ሆ
የኛማ ጌታ ሆኦ የዓለም ፈጣሪ ሆ
የሰላም አምላክ ሆ ትሁት መሀሪ ሆ
በደብረ ታቦር ሆ የተገለጠው ሆ
ፊቱ እንደ ፀሐይ ሆ በርቶ የታየው ሆ
ልብሱ እንደብርሃን ሆ ያንፀባረቀው ሆ
ድምጽህን ሰማና በብህሩ ደመና/2/
የቡሄው ብርሃን ለኛ መጣልን/2/
ያዕቆብ ዮሐንስሆ እንዲሁም ጴጥሮስ ሆ
አምላክን አዩት ሆ ሙሴ ኤልያስ ሆ
አባቱም አለ ሆ ልጄን ስሙት ሆ
ቃሌ ነውና ሆ የወለድኩት ሆ
ድምጽህን ሰማና በብህሩ ደመና/2/
የቡሄው ብርሃን ለኛ መጣልን/2/
ታቦር አርሞንኤም ሆ ብርሃን ታየባቸው ሆ
ከቅዱስ ተራራ ሆ ስምህ ደስ አላቸው ሆ
ሰላም ሰላም ሆ የታቦር ተራራ ሆ
ብርሀነ መለኮት ሆ ባንቺ ላይ አበራ ሆ
ድምጽህን ሰማና በብህሩ ደመና/2/
የቡሄው ብርሃን ለኛ መጣልን/2/
በተዋህዶ ሆ ወልድ የከበረው ሆ
የእግዚአብሔር አብ ልጅ ሆ ወልደማርያም ነው ሆ
ቡሄ በሉ ሆ ቡሄ በሉ ሆ
የአዳም ልጆች ሆ ብርሃንን ሆ ተቀበሉ ሆ
ድምጽህን ሰማና በብህሩ ደመና/2/
የቡሄው ብርሃን ለኛ መጣልን/2/
አባቴ ቤት ሆ አለኝ ለከት ሆ
እናቴ ቤት ሆ አለኝ ለከት ሆ
ከአጎቴም ቤት ሆ አለኝ ለከት ሆ
አክስቴም ቤት ሆ አለኝ ለከት ሆ
ተከምሯል ሆ እንደ ኩበት ሆ
ድምጽህን ሰማና በብህሩ ደመና/2/
የቡሄው ብርሃን ለኛ መጣልን/2/
የዓመት ልምዳችን ሆ ከጥንት የመጣው ሆ
ከተከመረው ሆ ከመሶቡ ይውጣ ሆ
ከደብረ ታቦር ሆ ጌታ ሰለመጣ ሆ
የተጋገረው ሆ ሙልሙሉ ይምጣ ሆ
ድምጽህን ሰማና በብህሩ ደመና/2/
የቡሄው ብርሃን ለኛ መጣልን/2/
ኢትዮጵያውያን ሆ ታሪክ ያላችሁ ሆ
ባህላችሁን ሆ ያዙ አጥብቃችሁ ሆ
ችቦውን አብሩት ሆ እንዳባቶቻችሁ ሆ
ምስጢር ስላለው ሆ ደስ ይበላችሁ ሆ
ድምጽህን ሰማና በብህሩ ደመና/2/
የቡሄው ብርሃን ለኛ መጣልን/2/
አባቶቻችን ሆ ያወረሱን ሆ
የቡሄን ትርጉም ሆ ያሳወቁን ሆ
እንድንጠብቀው ሆ ለእኛ የሰጡን ሆ
ይህን ነውና ሆ ያስረከቡን ሆ
ድምጽህን ሰማና በብህሩ ደመና/2/
የቡሄው ብርሃን ለኛ መጣልን/2/
ለድንግል ማርያም ሆ አሥራት የሆንሽ ሆ
ቅዱሳን ጻድቃን ሆ የሞሉብሽ ሆ
በረከታቸው ሆ ያደረብሽ ሆ
ሁሌም እንግዶች ሆ የሚያርፉብሽ ሆ
ሀገረ እግዚአብሔር ሆ ኢትዮጵያ ነሽ ሆ
ድምጽህን ሰማና በብህሩ ደመና/2/
የቡሄው ብርሃን ለኛ መጣልን/2/
ለሐዋርያት ሆ የላከ መንፈስ ሆ
ዛሬም ለኢትዮጵያ ሆ ጸጋውን ያፍስስ ሆ
በበጎ ምግባር ሆ እንድንታነጽ ሆ
በቅን ልቦና ሆ በጥሩ መንፈስ ሆ
በረከተ ቡሄ ሆ ለሁላችንይድረስ ሆ
ዓመት ዓውዳመት ድገም እና ዓመት ድገም እና
በጋሽዬ ቤ ድገም እና ዓመት ድገም እና
ያውርድ በረከት ድገም እና ዓመት ድገም እና
ወርቅ ይፍሰስበት ድገም እና ዓመት ድገም እና
በእማምዬ ቤት ድገም እና ዓመት ድገም እና
ይግባ በረከት ድገም እና ዓመት ድገም እና
ማርና ወተት ድገም እና ዓመት ድገም እና
ይትረፍረፍ በእውነት ድገም እና ዓመት ድገም እና
እንዲሁ እንዳላችሁ በምነት አይለያችሁ በምነት
ላመቱ በሰላም በምነት ያድርሳችሁ በምነት
ክርስቶስ በቀኙ በምነት ያቁማችሁ በምነት
የመንግስቱ ወራሽ በምነት ያድርጋችሁ በምነት
እንዲሁ እንዳለን በምነት አይለየን በምነት
ለዓመቱ በሰላም በምነት ያድርሰን በምነት
አማኑኤል በቀኙ በምነት ያቁመን በምነት
የመንግስቱ ወራሽ በምነት ያድርገን በምነት
የቅዱሳን መላክት የፃድቃን ሰማዕታት
ረድኤት በረከት ይግባ በሁሉም ቤት
በሁሉም ቤት/2/ ይግባ በረከት/2/
እንቁም በሃይማኖት ፀንተን በትጋት
የአስራት አገር የአበው ቀደምት
የቅዱሳን አባቶች ትውፊት
ይገባልና ልንጠብቅ በእውነት
ባህላችንን የአባቶች ትውፊት 3
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔✞═══●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
❖ @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit ❖
✥ ✢
╚✞═══●◉❖◉●═════✞╝
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
✞ ደብረ ታቦር ✞
ደብረ ታቦር ተሞላ በግርማ
ብርሃን ከበበው
አሸብርቋል ረጅሙ ተራራ
ክብሩ ሲያበራ
ጴጥሮስና ያዕቆብ ደግሞም ዮሀንስ
ክብሩ ሲያበራ
ይዟቸው ተጓዘ የመረጣቸው
ከፊታቸው ሳለ ድንገት ተለወጠ
ኢየሱስ ሲያበራ ልባቸው ቀለጠ
/አዝ=====
ሙሴና ኤልያስ ከሱ ጋር ታያቸው
ጴጥሮስ በተመስጦ ዳስ እንስራ አላቸው
ልቡን የቀመሰ አይመችም ሌላ
ክርስቶስ ነውና እውነተኛ ተድላ
/አዝ=====
በእርሱ ደስ የሚለኝ ልጄ ይህ ነውና
ስለመዳናችው ስሙት በፅሞና
ሄዶ ሲመሰክር ከሰማይ ንጉሱ
ከእየሱስ በቀር አላዩም ሲነሱ
ተገለጠ በግርማ ሸሸ ጨለማ×፪
እንደ ፀሀይ ሲያበራ ማነው የማይፈራ×፪
ሆያ ሆዬ ሆ ሆያ ሆዬ ሆ×፪
የተሰቀለው ሆ በክብር ይመጣል ሆ
ሰማይና ምድር ሆ በቃሉ ያልፋል ሆ
በማድጋችን ሆ ይቀመጥ ወይኑ ሆ
ተግተን እንጠብቅ ሆ ቅርብ ነው ቀኑ ሆ
ድምፅህን ሰማና በብሩህ ደመና ×፪
የቡሄው ብርሀን ለኛ በራልን×፪
የቃሉን ሙልሙል ሆ እንመገበው ሆ
የዜማን ችቦ ሆ እንድንለኩሰው ሆ
የእምነት ደመራ ሆ ይደመርና ሆ
ከርሞ እንዲያደርሰን ሆ እናመስግና ሆ
ድምፅህን ሰማና በብሩ ህ ደመና ×፪
የቡሄው ብርሀን ለኛ በራልን ×፪
አመት አውደ አመት ድገምና አመት
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔✞═══●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
❖ @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit ❖
✥ ✢
╚✞═══●◉❖◉●═════✞╝
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
✞ ሀሁ ብዬ ✞
ሀሁ ብዬ ፊደል የቆጠርኩብሽ
ባቦጊዳ አፌን የፈታዉብሽ
በመልክተ መንፈሴ ተደሰተ
በዳዊቱ ብዙ ነው በረከቱ/2/
ተዋህዳ አህ ሀይማኖቴ እህ
የእውቀት ምንጭ አህ መሰረቴ እህ
አለኝ ትዝታ ከዛፉስር የኛ የኔታ ዱላ በትር/2/
ሀሁ ብዬ ስጮህ ሀ
ድምፄን እያሰማው ሁ
አንዶን ቃል ስገርፋት ሂ
የኔታን አስቆጣ ሃ
ሀ ማለት እግዚ ነው ሄ
እያሉ ሲቀኙ ህ
የኔታን አንደበት ሆ
ማር ይንጠፍጠፍበት ሆ
/አዝ=====
አቦጊዳ ብዬ መልክተን ሳልወጣ የኔታ ደከሙ እንቅልፋቸው መጣ/4/
ፊደል ገበታዬ ሀ ግዕዝ
ይያዝ ከመሬት ሁ ካብ
አቧራዬን ማቡነን ሂ ሳልስ
ያዝኩኝ መላፋት ሃ ሃራብ
ሲነቁ የኔታ ሄ ሀምስ
ወስደው ከግዱሙ ህ ሳድስ
ልምጯን አሰሙ ሆ ሳብ
ዱላ ቃል አሰሙ ሀ ግዕዝ
/አዝ=====
ተማሪና ውሻ ሁል ጊዜ አይስማሙ እስከ እድሜ ልካቸው አሉ እንደተዳሙ/4/
አቆፉዳ አንግቦ ሀ
ደበሎዉን ለብሶ ሁ
በእንተ ስሞ ሲል ሂ
ድምፁን አለስልሶ ሃ
አንዲት እፍኝ ጥሬ ሄ
ለቁራሽ እንጀራ ህ
ውሻ ሲያባርረው ሆ
አያለው መከራ ሀ
/አዝ=====
አለኝ ትዝታ ቅኔ ቤት በእንተ ስሟ ለ ማርያም ማለት/4/
የዜማው መለኪያ ህ
ጭረት ምልክቱ ሆ
እዝል እና ግዕዝ ህ
ቅናቱ ድፋቱ ሀ
ሳቢዘር ጥሬ ዘር ሄ
ደሞም ቅኔ ቤት ህ
አገባብ ሚስጢሩ ሆ
ሰባት ስምንት ቤት ሆ
/አዝ=====
አለኝ ትዝታ ከመቅደሱ ለሊቱን ሙሉ ማወደሱ/4/
መፃፉን ዘርግቶ ሀ
ለጉባዬ ዉሎ ሆ
ቅኔ ዜማ አጥንቶ ሄ
ስምአኒ ብሎ ሀ
ተፈስሂ እያልኩ ሄ
እሱን ስደረድር ህ
ሳዜመው ይነጋል ሆ
ቅኔ ስደረድር ሆ
/አዝ=====
አለኝ ትዝታ ከጎጀዬ ተሰቅላ ቆፋዳዬ/4/
ሀሁ ብዬ ፊደል የቆጠርኩብሽ
ባቦጊዳ አፌን የፈታዉብሽ
በመልክተ መንፈሴ ተደሰተ
በዳዊቱ ብዙ ነው በረከቱ/2/
👉ዘማሪ ዲ/ን ታዴዎስ ግርማ
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔✞═══●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
❖ @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit ❖
✥ ✢
╚✞═══●◉❖◉●═════✞╝
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
✞ በቤተ መቅደስህ ✞
በቤተ መቅደስህ ያሳደከኝ
ለአፌ ጥበብን ያስተማርከኝ
የልጅነት አምላክ ወዴት አልህ
በዚህ አለም አሳብ ክንዴ ዛለ
ያሸዋ ላይ ህንፃ ሆኗል ቤቴ
ያረገርጋል መሰረቴ
ጠላት ሰልጥኖብኝ ደክሚያለሁ
ዛሬ ብቻዬን ቀርቻለሁ
/አዝ=====
አባካኝ ሆኛለሁ አመፀኛ
ለዚህ አለም ሀጢያት የማልተኛ
ነብሴ ተንገላታች በመከራ
ማን ያገናኛት ካንተ ጋራ
/አዝ=====
ሰላሜ ነህ አንተ ትዝታዬ
ፅፌ ያኖርኩህ በእንባዬ
አለም ወስዳኛለች በዘፈኗ
እባክህ ስራኝ እንደገና
/አዝ=====
አመፀኞች ሁሉ ቤትህ ገቡ
ምህረት ፍቅርህን እያሰቡ
እጅህን ዘርግተህ አቀፍካቸው
ባንተ ገለጠ ልቦናቸው
👉ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔ ✞ ═════●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit @enamsgn ❖
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
✥ ✢
╚✞ ═════●◉❖◉●═════✞╝
✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
✞ መአዛህ ያዉዳል ✞
ደብረ ሊባኖስ ገዳም
መአዛህ ያዉዳል ለአለም /2/
ደብረ ሊባኖስ ላይ
ክብርህን አይተናል /2/
በጻዲቁ ፀሎት
እረፍት አግኝተናል
ቅዱስ ላሊበላ ገዳም
መአዛህ ያዉዳል ለአለም /2/
ቅዱስ ላሊባላ
የሰራህው ስራ /2/
ለእኛ መዳን ሆኖአል
ፅድቅን እንድንሰራ
ዝቋላዉ አቦ ገዳም
መአዛህ ያዉዳል ለአለም /2/
በረከትህን ናፍቀን
አምነን በምልጃህ /2/
ገብረ መንፈስ ቅዱስ
መጣን ከደጅህ
ሸንኮራዉ ዮሐንስ ገዳም
መአዛህ ያውዳል ለአለም /2/
ሽንኮራዉ ዮሐንስ
ስመ ገናና ነህ /2/
በአራቱም ማእዘን
ትመሰገናለህ
👉ዘማሪት ውዴ ታችበሌ
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @enamsgn ❖
❖ @enamsgn @enamsgn ❖ ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
✞ እኔስ በማርያም ✞
እኔስ በማርያም እፅናናለው እታመናለሁ
እኔስ በድንግል እመካለሁ እታመናለሁ
የሰላሜ ወደብ እታመናለው
የልቤ ደስታ እታመናለው
የአበው መፅናኛ እታመናለው
እናቱ የጌታ እታመናለው
የኩክየለሽ ማርያም እታመናለው
የበረሀ ስንቄ እታመናለው
ክብርን የተመላሽ እታመናለው
ዝናር እና ትጥቄ እታመናለው
/አዝ=====
ምስጋናሽ በልቤ እታመናለው
ሞልቶ እጠራሻለው እታመናለው
ጠዋትና ማታ እታመናለው
ፅዮን እልሻለው እታመናለው
የቤቴ ብርሀን እታመናለው
ድምቀቴ ሆነሻል እታመናለው
መሶብ ማድጋዬን እታመናለው
በፍቅር መልተሻል እታመናለው
/አዝ=====
ከእናትም በላይ እታመናለው
ክንድሽ ደግፎኛል እታመናለው
ከሀዘን ከመከራ እታመናለው
ልጅሽ ታድጎኛል እታመናለው
የፃድቃኔ ማርያም እታመናለው
የመንፈሴ እርካታ እታመናለው
ትውልድ ያከበረሽ እታመናለው
የጌታ ስጦታ እታመናለው
/አዝ=====
ምግብ መጠጤነሽ እታመናለው
ስምሽ ይማርካል እታመናለው
ወንድም እና እህቴ እታመናለው
ዘመዴ ሆነሻል እታመናለው
ብራብም ብጠማም እታመናለው
እርካታዬ ነሽ እታመናለው
ፍቅርሽ ሲበዛልኝ እታመናለው
አልኩሽ ኩክየለሽ እታመናለው
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔✞═══●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
❖ @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit ❖
✥ ✢
╚✞═══●◉❖◉●═════✞╝
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
✞ ኦ እንዳንተ ያለ ወዳጅ ✞
ኦ እንዳንተ ያለ ወዳጅ አላገኘሁም እኔ
ኦ ውለታህን ሳስበው በእንባ ይመላል አይኔ
ከእናቴም ልጆች በላይ አንተ ውድ ነህ ለእኔ
ወዳጅና ዘመዴ ጌታ የክፉ ቀኔ
ምን አለኝና ልስጥህ የሚነገር የሚወራ
እኔስ ተሸንፊያለሁ በእንባ ስምህን ልጥራ
/አዝ=====
ተሰድጄ ብወጣ ወጥተሃል ከእኔ ጋራ
ትላንትናን አለፍኩት ጠላቴን እያራራ
ደግሞ የነገውን ቀን አንተ ታውቃለህ ጌታ
ወጥመዴን ስበርና አፌን ሙላው በእልልታ
/አዝ=====
በእስረኞች መሀል ሁኜ ሰንሰለት ለብሻለሁ
አለም እውነት የላትም ፍትህ ካንተ እሻለሁ
መቼ ታጽናናኛለህ ወዳጅና ዘመዴ
አውጣኝ አውጣኝ ለሚልህ አንተ አታጣም ዘዴ
/አዝ=====
መመላለስ አይደክምህ እኔን ማስታመም አንተ
ደክመህ አልፈልህልኛል እጆቼን አበርትተ
ሁሌ በሬ ላይ ቁም ደጃፌን የምትመታ
ግባ የክብር ንጉስ ብያለሁ ማራናታ/5×/
👉ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @enamsgn ❖
❖ @enamsgn @enamsgn ❖ ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#እና_እባካችሁ_ለዚች_ቤተክርስቲያን_የተቻላችሁን_ሁሉ_በማድረግ_ተባበሩን
#በገንዘብ
#ጸሎት_በማድረግም
#ሼርም_share_በማድረግም_ተባበሩን🙏🙏🙏
👇👇👇👇👇👇
#አካውንት_ቁጥር
1000021309005
#ኩናፋ_ፈረስ_ጋማ_ቅዱስ_ገብርኤል_ቤተክርስቲያን
#ስልክ_ቁጥር 0910322023, 0994629494